የአካባቢ አየር ብክለት · 2015-03-12 · ማሞቂያ ምድጃ በቱቦው...

አድራሻ፦ ይሁዳ ሀሌቪ 48 ቴላቪቭ | ለማካቢም፦ ፓስታ ሳ.ቁ. 15 ቴላቪቭ 61000 | ቴሌፎን 03-5669939 ፋክስ 03-5669940 ኢንተርኔት፤ | adamteva.org.il | [email protected] | ሀሞኬድ ሃያሮክ (አረንጓዴው መእከል) የሚያስብልህ አካል አለ የሞኬድ ሃያሮክ - መረጃ ሰነዶች የአካባቢ አየር ብክለት በመኖሪያ ቤቴ አቅራቢያ የተቋቋሙ አየር የሚበክሉ አምራች ፋብሪካዎች በመቃወም ምን ምን ማድረግ እችላለሁ? ብከለት የሚፈጥሩ ጉዳዩችን እየተከታተሉ መረጀዎችን መሰብሰብ ያስፈልጋል። ለምሳሌ የጭስ ማውጫ ቱቡዎችን ፎቶ ግራፍ ማንሳት፤ ፋብሪካው ዘውትር የሚያመርትበትን ስዓታት መመዝገብና አየር የሚበከለው ምንጩ ወይም መነሻው የት እንደሆነ ማጋለጥ ያስፈልጋል። መረጃዎችን ከሰበሰቡ በኃላ ለከተማው ማዘጋጃ ቤት የአካባቢ አየር ጥበቃ ክፍል በማስታወቅ ለችግሩ መፍትሄ እንዲሻ ጠይቅ (በከተማው የአካባቢ አየር ንጽህና ጥበቃ ክፍል ካለ) የከተማ ማዘጋጃ ቤት ለችግሩ መፍትሄ የማይሰጥ ከሆነ በክልላችሁ በሚገኘው የአገር አቀፉ የአካባቢ አየር ጥበቃ መ/ቤት ክስ ተቀባይ ክፍል ማመልከቻ ማቅረብ ይቻላል። ይህን ጉዳይ በተመለከተ በሚመለከተው ገጽ በዝርዝር ቀርቧል። ችግሩ እንዲወገድ ከዚህ በላይ ለተጠቀሱት መ/ቤቶች ያቀረባችሁት ማመለከቻ መፍትሄ ካላገኘ «ሞኬድ ሃያሮክ» ለተባለው «አዳም ጤባ በዲን» ለተባለው ድርጅት ማመልከቻ በማቅረብ ለችግሩ መፍትሄ እንዲገኝለት እርዳታ መጠየቅ ትችላላችሁ። የአየር ብክለት ማለት ምን ማለት ነው? የአካባቢ ንጹህ አየር መበከል የእሥራኤል አገር ከባድ ችግሮች መካከል አንዱ ነው። በርካታ ጥናቶች እንዳረጋገጡት የአካባቢ ንጹህ አየር ብከለት ከሰው ልጆች ጤንነት ጋር በቀጥታ ግንኙነት ያለው ከመሆኑም ባሻገር ሰዎች በወጣትነት እድሚያቸው በሞት እንዲለዩ ዋና ምክንያት መሆኑን ጥናቶች አረጋግጠዋል። ንጹህ አየር ከሚበክሉት መካከል ከፊሎች የሚመነጩት ከተፈጥሮ ነው። ለምሳሌ በአትሞስፔር ወይም በአካባቢ አየር ብክለት ይፈጠራል፤ ከመሬት እሳተ ጎመራ ሲፈነዳ አቧራ ፤ አሽዋና ጭስ ወደ ላይ ወጥቶ አየሩን ይበክለዋል። ከዚሁም ጋር አብዛኛውን ጊዜ የአካቢን ንጹህ አየር የሚበክለው የሰው ልጆች በሚሰሯቸው ሥራዎች ምክንያት ሲሆን እነሱም የኃይል ማመንጫዎች ፤ ኢንዱስትሪዎችና የመጓጓዢያ ዘዴዎች ንጹህን አየር ይበክሉታል። ቦታን በየት እንደሚገን መረጃ ከየት አገኛለሁ? ለአካባቢ ጥበቃ መ/ቤት አገር አቀፉ ንጹህ አየር ጥበቃ ክፍል ዘንድ መረጃ መቀበል ይችላለሁ። እንዲሁም በአካባቢ ማዘጋጃ ቤቶች የከተማ አካባቢ የአየር ጥበቃ ድርጅቶች ኢንተርኔት ድረ ገጾች ላይ ጠቃሚ መረጃዎችን ያገኛሉ። በእሥራኤል አገር በዋናነት የሚጠቀሱ የአየር ብክለት መሰኤዎች ምንድን ናቸው በጤንነታችን ላይ ምን ዓይነት ተጽእኖ ያሳድራሉ? በእሥራኤል አገር የአር የሚበክሉ ሶስት ዋና ዋና ምንጮች መኪናዎች፤ ኢንዳስትሪዎችና የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫዎች ናቸው። የአየር ብክለት ሳንባን ይጎዳል ፤ የልብ ህመም ያስከትላል ፤ ለካንሰር ወይም ለነቀርሳ በሽታ መንስኤ ይሆናል። ይህን ጉዳይ በተመለከተ በዓለም የጤና ጥበቃ ድርጅት ኢንተርነት ድረ ገጽ ארגון הבריאות העולמיመረጃ ታገኛላችሁ። በእሥራኤል ሀገር በተለያዩ ቦታዎች የአካባቢው ንጽህና የተጠበቀለት ለኑሮ የሚመች ከተሽከርካሪ መኪናዎች የሚወጣ ጭስ ንጹህ አየር እንዳይበክሉ ምን ማድረግ አለብኝ? በከተማ አካባቢ 80% የሚሆነው ንጹህ አየር የሚበከሉት ከተሽከርካሪ መኪናዎች የሚወጣ የተበከለ ጭስ ሲሆን በተልይ ከቤት የግል መኪናዎች የሚወጣ ጭስ የአካባውን ንጽህ አይር ይበክላል። የቤት መኪናዎችን ለመጓጓዢያ መጠቀም በጎዳናዎች የትራፊክ መጭነቅነቅ ምክንያት ከመሆናቸው ባሻገር በሚገባ እንክብካቤ ያልተደረገላቸው መኪናዎች የነዳጅ ዘይት ስለሚበላሽ የከተማዎችን አካባቢ የአር እየበከሉ ታላቅ ችግር ያስክትላሉ። ወደ ስራ ቦታ

Upload: others

Post on 07-Jan-2020

11 views

Category:

Documents


0 download

TRANSCRIPT

Page 1: የአካባቢ አየር ብክለት · 2015-03-12 · ማሞቂያ ምድጃ በቱቦው ቀዳዳ ወደ ውጭ እወጣ የሚትጎለጎል ጭስ ስለሚረብሸኝ ምን

አድራሻ፦ ይሁዳ ሀሌቪ 48 ቴላቪቭ | ለማካቢም፦ ፓስታ ሳ.ቁ. 15 ቴላቪቭ 61000 | ቴሌፎን 03-5669939 ፋክስ 03-5669940 ኢንተርኔት፤ | adamteva.org.il | [email protected] |

ሀሞኬድ ሃያሮክ (አረንጓዴው መእከል) የሚያስብልህ አካል አለ

የሞኬድ ሃያሮክ - መረጃ ሰነዶች

የአካባቢ አየር ብክለትበመኖሪያ ቤቴ አቅራቢያ የተቋቋሙ አየር የሚበክሉ አምራች ፋብሪካዎች በመቃወም ምን ምን ማድረግ እችላለሁ?ብከለት የሚፈጥሩ ጉዳዩችን እየተከታተሉ መረጀዎችን መሰብሰብ ያስፈልጋል። ለምሳሌ የጭስ ማውጫ ቱቡዎችን ፎቶ ግራፍ ማንሳት፤ ፋብሪካው ዘውትር

የሚያመርትበትን ስዓታት መመዝገብና አየር የሚበከለው ምንጩ ወይም መነሻው የት እንደሆነ ማጋለጥ ያስፈልጋል። መረጃዎችን ከሰበሰቡ በኃላ ለከተማው

ማዘጋጃ ቤት የአካባቢ አየር ጥበቃ ክፍል በማስታወቅ ለችግሩ መፍትሄ እንዲሻ ጠይቅ (በከተማው የአካባቢ አየር ንጽህና ጥበቃ ክፍል ካለ) የከተማ ማዘጋጃ

ቤት ለችግሩ መፍትሄ የማይሰጥ ከሆነ በክልላችሁ በሚገኘው የአገር አቀፉ የአካባቢ አየር ጥበቃ መ/ቤት ክስ ተቀባይ ክፍል ማመልከቻ ማቅረብ ይቻላል።

ይህን ጉዳይ በተመለከተ በሚመለከተው ገጽ በዝርዝር ቀርቧል። ችግሩ እንዲወገድ ከዚህ በላይ ለተጠቀሱት መ/ቤቶች ያቀረባችሁት ማመለከቻ መፍትሄ ካላገኘ

«ሞኬድ ሃያሮክ» ለተባለው «አዳም ጤባ በዲን» ለተባለው ድርጅት ማመልከቻ በማቅረብ ለችግሩ መፍትሄ እንዲገኝለት እርዳታ መጠየቅ ትችላላችሁ።

የአየር ብክለት ማለት ምን ማለት ነው?የአካባቢ ንጹህ አየር መበከል የእሥራኤል አገር ከባድ ችግሮች መካከል አንዱ ነው። በርካታ

ጥናቶች እንዳረጋገጡት የአካባቢ ንጹህ አየር ብከለት ከሰው ልጆች ጤንነት ጋር በቀጥታ

ግንኙነት ያለው ከመሆኑም ባሻገር ሰዎች በወጣትነት እድሚያቸው በሞት እንዲለዩ ዋና

ምክንያት መሆኑን ጥናቶች አረጋግጠዋል።

ንጹህ አየር ከሚበክሉት መካከል ከፊሎች የሚመነጩት ከተፈጥሮ ነው። ለምሳሌ

በአትሞስፔር ወይም በአካባቢ አየር ብክለት ይፈጠራል፤ ከመሬት እሳተ ጎመራ ሲፈነዳ

አቧራ ፤ አሽዋና ጭስ ወደ ላይ ወጥቶ አየሩን ይበክለዋል። ከዚሁም ጋር አብዛኛውን ጊዜ

የአካቢን ንጹህ አየር የሚበክለው የሰው ልጆች በሚሰሯቸው ሥራዎች ምክንያት ሲሆን

እነሱም የኃይል ማመንጫዎች ፤ ኢንዱስትሪዎችና የመጓጓዢያ ዘዴዎች ንጹህን አየር

ይበክሉታል።

ቦታን በየት እንደሚገን መረጃ ከየት አገኛለሁ? ለአካባቢ ጥበቃ መ/ቤት አገር አቀፉ ንጹህ አየር ጥበቃ ክፍል ዘንድ መረጃ መቀበል

ይችላለሁ። እንዲሁም በአካባቢ ማዘጋጃ ቤቶች የከተማ አካባቢ የአየር ጥበቃ ድርጅቶች

ኢንተርኔት ድረ ገጾች ላይ ጠቃሚ መረጃዎችን ያገኛሉ።

በእሥራኤል አገር በዋናነት የሚጠቀሱ የአየር ብክለት መሰኤዎች ምንድን ናቸው በጤንነታችን ላይ ምን ዓይነት ተጽእኖ ያሳድራሉ?በእሥራኤል አገር የአር የሚበክሉ ሶስት ዋና ዋና ምንጮች መኪናዎች፤ ኢንዳስትሪዎችና

የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫዎች ናቸው። የአየር ብክለት ሳንባን ይጎዳል ፤ የልብ ህመም

ያስከትላል ፤ ለካንሰር ወይም ለነቀርሳ በሽታ መንስኤ ይሆናል። ይህን ጉዳይ በተመለከተ

በዓለም የጤና ጥበቃ ድርጅት ኢንተርነት ድረ ገጽ ארגון הבריאות העולמי መረጃ

ታገኛላችሁ።

በእሥራኤል ሀገር በተለያዩ ቦታዎች የአካባቢው ንጽህና የተጠበቀለት ለኑሮ የሚመች

ከተሽከርካሪ መኪናዎች የሚወጣ ጭስ ንጹህ አየር እንዳይበክሉ ምን ማድረግ አለብኝ?በከተማ አካባቢ 80% የሚሆነው ንጹህ አየር የሚበከሉት ከተሽከርካሪ መኪናዎች የሚወጣ

የተበከለ ጭስ ሲሆን በተልይ ከቤት የግል መኪናዎች የሚወጣ ጭስ የአካባውን ንጽህ አይር

ይበክላል።

የቤት መኪናዎችን ለመጓጓዢያ መጠቀም በጎዳናዎች የትራፊክ መጭነቅነቅ ምክንያት

ከመሆናቸው ባሻገር በሚገባ እንክብካቤ ያልተደረገላቸው መኪናዎች የነዳጅ ዘይት

ስለሚበላሽ የከተማዎችን አካባቢ የአር እየበከሉ ታላቅ ችግር ያስክትላሉ። ወደ ስራ ቦታ

Page 2: የአካባቢ አየር ብክለት · 2015-03-12 · ማሞቂያ ምድጃ በቱቦው ቀዳዳ ወደ ውጭ እወጣ የሚትጎለጎል ጭስ ስለሚረብሸኝ ምን

አድራሻ፦ ይሁዳ ሀሌቪ 48 ቴላቪቭ | ለማካቢም፦ ፓስታ ሳ.ቁ. 15 ቴላቪቭ 61000 | ቴሌፎን 03-5669939 ፋክስ 03-5669940 ኢንተርኔት፤ | adamteva.org.il | [email protected] |

ሀሞኬድ ሃያሮክ (አረንጓዴው መእከል) የሚያስብልህ አካል አለ

በእግር ወይም በሳይክል መሄድ የማይቻል ከሆነ ዋናው ተመራጭ መፍትሄ በህዝብ

ማጓጓዢያ አውቶቡሶች መጓዝ ነው። በተመሳሳይ ሁኔታም የመኪና ነዳጅ ዘይት ጥራት ያለው

መኪና መጠቀም ያስፈልጋል። ለምሳሌ ሀይብሪድ የሚባሉ ሞተራቸው በኤሌክትሪክ ኃይል

የሚሰሩ መኪናዎች የአካባቢን አየር ስለማይበከሉ በእነዚህ ዓይነቶች መኪናዎች መጠቀም

የአካባቢን አየር ንጽሕና መጠበቅ ይቻላል።

የአካባቢን ንጹህ አየር በጣም የሚበክል መኪና አይቻለሁ ታዲያ ምን ማድረግ አለብኝ?ከተለያዩ መኪናዎች የጭስ መውጫ ቱቦ የሚወጣው ጥቁር ጭስ የአካባቢን አየር ይበክላል።

ከመኪናው የጭስ መውጫ የሚወጣው ጭስ በጣም ጥቁር ከሆነ አየርን የሚበክሉ ጥቃቅን

ነገሮች በብዛት እየወጡ የአካባቢን አየር ይበክላሉ ወይም ያቋሽሻሉ ማለት ነው። የህዝብ

ማጓጓዢያ ዘዴዎችን በተመለከተ የአካባቢ ጥበቃ ሚኒስቴር ዜጎች የአካባቢን ንጹህ አየር

የሚበክሉ የህዝብ ማጓጓዢያ አውቶቡሶችን በሚመለከቱበት ስዓት ክስ እንዲያቀርቡ

ከሚያስችላቸው ትእዛዝ ሰንድ ላይ ፈርመዋል። ስለሆነም የህዝብ ማጓጓዢያ ድርጅት ንብረት

የሆነ አውቶቡስ ጥቁር ጭስ እያወጣ አየር የሚበክል ከሆነ ጉዳዩ ለሚመለከታቸው የህዝብ

ሮሮ ተቀባይ ክፍል ኃላፊዎች አቤቱታ የማቅረብ መብት አላችሁ። ወይም የአውቱቡሱ

ኃላፊ ለሆነው ድርጅት የህዝብ አቤቱታ ተቀባይ ክፍል ማመልከቻ ማቅረብ ትችላላችሁ።

የህዝብ መጓጓዢያ አውቱቡስ ድርጅቶች ሥም ዝርዝር የሚከተሉት ናቸው፦ ኤጌድ ፤ ዳን

፤ ሜትሮዳን ፤ ማርጋሊት፤ ኦቶቡሲም ምኡሀዲም ነጸሬት፤ ነቲብ ኤክስፕረስ እና ሱፐርቡስ

ናቸው።

የቤት ወይም የግል መኪናዎቸ - አካባቢን ንጹህ አየር በጣም የሚበክል መኪና ካያችሁ

ለአካባቢ ጥበቃ መ/ቤት መኪናዎች የሚፈጥሩትን የአየር ብክለት ለሚከላከለው ክፍል

ማስታወቅ አለባችሁ። በምታስተላልፉለት መረጃዎች ቀንና ስዓቱን ፤ አየር የሚበክለውን

መኪና ሰሌዳ ቁጥር ፤ የሚጓዝበትን አቅጣጭ ወዘተ… ማስታወቅ ይኖርባችኋል።

ነፍታሌ ኮሄን የህዝብን አቤቱታ ይቀባላል። ቴሌፎን ቁ. 03-6419503 ፋክስ ቁ. 03-

6426268 ኢሜል፡ [email protected]

የጎረበቴ የቤት ማሞቂያ ካሚን ወይም ታኑር ሀሳቃ የቤት ማሞቂያ ምድጃ በቱቦው ቀዳዳ ወደ ውጭ እወጣ የሚትጎለጎል ጭስ ስለሚረብሸኝ ምን ማድረግ እችላለሁ? ለዚህ ችግር መፍትሄ ለመሻት አንዱ መንገድ እርስዎ ለሚኖሩባት ከተማ ማዘጋጃ ቤት

ማመልከቻ ማቅርብ ነው። ማዘጋጃ ቤቱ እርስዎን ለመረዳት በሁለት መንገዶች ለችግሩ

መፍትሄ ያፈላልጋል። አንደኛው መንገድ በመዘጋጃ ቤቱ ለሰዎች ጉዳት የሚያደርሱ ነገሮች

ማስወገድ የሚያስችሉ እንዲሁም ጎረቤትን የሚረብሹ የቤት ማሞቂያ ምድጃዎች በተመለከተ

እርምጃ መውሰድ የሚያስችሉ ህጎች ካሉ በህጉ መሰረት ለችግሩ መፍትሄ ያፈላልግልዎታል።

ሁለተኛው መንገድ ደግሞ የከተማ ማዘጋጃ ቤት የሚከተለው ህግ ባይኖርም ለማናቸውም

ሰዎችን በሚጎዱና በሚረብሹ መጥፎ ሽታ ለማስወገድ እርምጃ ይወስዳል። መጥፎ ሽታን

በተመለከተ በመረጃ ሰነድ በቀረቡት ማብራሪያዎች መሰረት ማዘጋጃ ቤቱ ለችግሩ መፍትሄ

ይሰጣል።

መግለጽ የሚያስፈልግ ጠቃሚ ጉዳይ ቢኖር በአንድ ወቅት በርካታ ዜጎች ለማዘጋጃ

ቤትና ለሚመለከታቸው መ/ቤቶች ማመልከቻ ካቀረቡ ለችግሩ አስቸኳይ መፍትሄ

እንዲሰጠው ተጽእኖ ያሳድራል። በመሆኑም ችግሩ ጎረቤቶችን የሚያሰቃይ ከሆነ ተባብረው

ለሚመለከታቸው መ/ቤቶች ማመልከቻ እንዲያቀረቡ መገፋፋት ጠቃሚ ነው።

የንጹህ አየር ህግ ማለት ምን ማለት ነው?ምክር ቤቱ ወይም ክነሴቱ የንጹህ አየር ህግ እዲደነገግ ከፍተኛ ጥረት ያደረገው «አዳም ጤቫ

በዲን» የተሰኘው ድርጅት ሲሆን በ2008 ዓ.ም በክነሴት የጸደቀው ህግ በ2011 ዓ.ም ተግባር

ላይ ዋለ። ይህ ህግ የእሥራኤል መንግስት የካባቢን ንጹህ አየር ከብከሌት ለመታደግ ወይም

ለመከላከል ካጸደቃቸው እጅግ በጣም ጠቃሚ ከሆኑት ህጎች መካከል አንዱ ነው።

ይህ ህግ የተለያዩ ለአየር ብክለት ምክንያት የሆኑትን ነገሮች ሁሉ ለማስፈጸም ብሎም

አድርግ ወይም አታድርግ የሚሉትን ትእዛዝት ያካተተ ከመሆኑም ባሻገር ግልጽ በሆነ

መንገድ አካባቢው አየር ምን ያህል እንደተበከለ መረጃዎችን ለህዝብ ያቀርባል። ህጉ

ማዘጋጃ ቤቶች ብክለትን ለመዋጋት በሚያደርጉት እንቅስቃሴ ስልጣናቸውን ያስከብራል፤

አማራች ፍብሪካዎች የአር ብክለትን በሚመለከቱ ጉዳዩች ኃላፊነትና ግደታ እንዳለባቸው

ህጉ ያዛል። አየር የሚበክሉ ሰዎች እንዲቀጡ ህጉ ያዛል። መንግስት የአካባቢ አየር ብክልት

መቀነስ የሚያስችል የረጅም ዓመታት ፕሮግራም እንዲነድፍ ህጉ ያስገድደዋል። ይህን ጉዳይ

በተመለከተ «በአዳም ጤቫ ቨዲን» ድርጅት ኢንተርኔት ድረ ገጽ ላይ ተጨማሪ መረጃ

ስለሚገኝ አንብቡት።

አንድ ፍብሪካ በህግ በተፈቀደለት ወደ ውጭ በሚወጣው ጭስ መጠን ለመንደፍ በምን መንገድ ጣልቃ መግባት ይቻላል?በንጹህ አየር ህግ መሠረት ፍብሪካዎች የአካባቢን የአር በመበከል እረገድ ዋና ምክንያቶች

ስለሆኑ ፋብሪካዎች የሚያወጡትን የጭስ መጠን በተመለከተ ፍቃድ የመቀበል ግዴታ

አለባቸው። ፍቃድ ለመቀበል የሚቀረቡ እያንዳንዱ ማመለከቻ ይዘት ህዝቡ እንዲያውቅ

በአካባቢ ጥበቃ መ/ቤት ኢንተርኔት ድረ ገጽ ላይ ይለቀቃል። እያንዳንዱ ዜጋ መረጃውን

ካነበበ በኃላ የሚቃወም ከሆነ ወይም መታረም የሚገባው ጉዳይ ካለ መረጃው

ከተሰራጨበት ቀን ጀምሮ በ45 ቀናት ውስጥ አስተያዩቱን ማቅረብ ይችላል። መ/ቤቱ

ፋብሪካው ለሚያወጣው የጭስ መጠን ፍቃድ ከመስጠቱ

በፊት እያንዳንዱ ዜጋ ያቀረበለትን ማመልከቻ እንዲገመግም ህጉ ያስገድደዋል።

የአካባቢ ጥበቃ ሚኒስቴር ጽ/ቤት የተለያዩ ክፍለተ ሀገራት የህዝብ አቤቱታ ተቀባይ

ሰብሳቢዎች አድራሻ-

የሰሜን ክፍል ሀገር - ወ/ሮ ሪኪ ሻሎሽ

ቴሌፎን ቁ. 04-6059139 ፋክስ ቁ. 04-6020590

ኢሜል፡ [email protected]

የሀይፋ ክፍለ ሃገር - ወ/ሮ ኦሺራ ጎትሊብ

ቴሌፎን ቁ. 04-8632249 ፋክስ ቁ. 04-8632288

ኢሜል፡ [email protected]

መካከለኛው ክፍለ ሃገር - ወ/ሮ ሳሉዓ ዳዓስ

ቴሌፎን ቁ. 08-9788802 ፋክስ ቁ. 08-9229135

ኢሜል፡ [email protected]

የቴላቢቭ ክፍለ ሀገር - ወ/ሮ ካርሜላ ስቱሌር

ቴሌፎን ቁ. 03-7634452 ፋክስ ቁ. 03-7634401

ኢሜል፡ [email protected]

የእየሩሳሌም ክፍለ ሃገር - ወ/ሮ ጋሊት ነህሚያ -አሚር

ቴሌፎን ቁ. 02-5654414 ፋክስ ቁ. 02-5654455

ኢሜል፡ [email protected]

የደቡብ ክፍለ ሃገር - ወ/ሮ አየሊት በስኪንድ

ቴሌፎን ቁ. 08-6264001/2 ፋክስ ቁ. 08-6264111

ኢሜል፡ [email protected]

የይሁዳና ሰማሪያ ቀበሌዎች ክፍለ ሃገር - ወ/ሮ ሺራን ሻሀፍ

ቴሌፎን ቁ. 02-9977776