ˆ - 3rd all ethiopia · pdf fileየጥንቱ የግሪክ ኦሊምፒክ መጫወቻ

56
መልዕክቶች ....................................... 3 ኦሊምፒዝም ...................................... 9 ቆይታ .............................................. 14 ዐብይ ርዕስ ...................................... 18 ኦሮሚያ ........................................... 23 የእኛ ጀግኖች ................................... 32 የካሜራው ማስታወሻ ................... 36 ከመሰንበቻው ................................... 38 ስፖርትና ልማት ............................ 41 የመላ አፍሪካ ጨዋታዎች ............. 48 ልዩ ልዩ ........................................... 51 አዘጋጆች የ3 ኛው መላ ኢትዮጵያ ጨዋታዎች የህዝብ ግንኙነትና ዶክመንቴሽን ንዑስ ኮሚቴ ናስር ለገሰ እንየው ዓሊ አስቻለው ሽፈራው ዳንኤል ሀይለ ለሜሳ ወዩማ ሆሳዕና ደሳለኝ አርታኢ አስቻለው ሽፈራው እንየው ዓሊ ተያቢ ማሚት ወ/ገብርኤል ፎቶ ብርሃነ በዛብህ ፀጋዬ ሀይሉ ተፈሪ ጣሰው ዲዛይነር ፍቃድ ኪሮስ አታሚ ሜጋ ማተሚያ ማውጫ

Upload: dokiet

Post on 20-Mar-2018

298 views

Category:

Documents


50 download

TRANSCRIPT

Page 1: ˆ - 3rd All Ethiopia  · PDF fileየጥንቱ የግሪክ ኦሊምፒክ መጫወቻ

መልዕክቶች ....................................... 3ኦሊምፒዝም ...................................... 9ቆይታ .............................................. 14ዐብይ ርዕስ ...................................... 18ኦሮሚያ ........................................... 23የእኛ ጀግኖች ................................... 32የካሜራው ማስታወሻ ................... 36ከመሰንበቻው ................................... 38ስፖርትና ልማት ............................ 41የመላ አፍሪካ ጨዋታዎች ............. 48ልዩ ልዩ ........................................... 51

አዘጋጆች የ3ኛው መላ ኢትዮጵያ ጨዋታዎች የህዝብ ግንኙነትና ዶክመንቴሽን ንዑስ ኮሚቴ

ናስር ለገሰ እንየው ዓሊአስቻለው ሽፈራው ዳንኤል ሀይለለሜሳ ወዩማ ሆሳዕና ደሳለኝ

አርታኢ አስቻለው ሽፈራውእንየው ዓሊ

ተያቢማሚት ወ/ገብርኤል

ፎቶብርሃነ በዛብህ ፀጋዬ ሀይሉተፈሪ ጣሰው

ዲዛይነር

ፍቃድ ኪሮስ

አታሚሜጋ ማተሚያ

ማውጫ

Page 2: ˆ - 3rd All Ethiopia  · PDF fileየጥንቱ የግሪክ ኦሊምፒክ መጫወቻ

2

ሦስተኛው የመላ ኢትዮጵያ ጨዋታዎች

Page 3: ˆ - 3rd All Ethiopia  · PDF fileየጥንቱ የግሪክ ኦሊምፒክ መጫወቻ

3

በቅድሚያ ከአራቱም የሀገሪቱ ማዕዘናት ተወጣጥታችሁ በኦሮሚያ ክልል አስተናጋጅነት በሚካሄደው የመላዉ ኢትዮጵያ ስፖርቶች ውድድር ላይ የምትሳተፉ ወጣቶችን እንኳን ደህና መጣችሁ እላለሁ።

ሀገራችን ኢትዮጵያ በ2003 ዓ.ም በህዝብ ውይይትና ቀጥተኛ ተሳትፎ የዳበረውን የአምስት ዓመት የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ አዘጋጅታ ወደ ትግበራ ከገባች ወዲህ እነሆ ተስፋ ሰጪ ውጤት

የተገኘበት አንድኛ ዓመት ተጠናቆ ሁለተኛውም እየተገባደደ ይገኛል።

ፈጣን፣ ቀጣይነት ያለውና ህዝባችንን በየደረጃው ተጠቃሚ የሚያደርግ ልማት ማስመዝገብ የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ዋንኛ ምሰሶ መሆኑ ይታወቃል። ይህን ልማት ለማረጋገጥ መልካም ተሞክሮን በማስፋት ስትራቴጂ በርካቶችን ተጠቃሚ ለማድረግ የተቀየሰው አቅጣጫ ውጤት በማስመዝገብ ላይ ይገኛል።

በክልላችንና በአጠቃላይ በሀገራችን ባለው

መልዕክቶች

ክቡር አቶ ዓለማየሁ አቶምሳየኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ፕሬዝዳንት መልዕክት

Page 4: ˆ - 3rd All Ethiopia  · PDF fileየጥንቱ የግሪክ ኦሊምፒክ መጫወቻ

4

አስተማማኝ ሰላምና መንግስት በፈጠረው ምቹ ሁኔታ ወደ ክልላችን የሚደረገው ኢንቨስትመንት ፍሰት ከመቼውም ጊዜ በበለጠ እየጨመረ መጥቷል። በገጠርና በከተማ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት፣ በትምህርትና በጤና አገልግሎት መስክም በክልሉ የማይናቅ ውጤት ተመዝግቧል።

በሁሉም የመንግስት መስሪያ ቤቶች ግልጽነትና ተጠያቂነት የሰፈነበት አሰራርን ለመዘርጋት ለህዝቡ ቀልጣፋና ፈጣን አገልግሎት ለመስጠት እንዲቻል በክልሉ የተለያዩ የሪፎርም ሥራዎች በመተግበር ላይ ናቸው።

ቀደም ባሉት አመታት መንግስት ወጣቱን ተጠቃሚ የሚያደርግ የትምህርትና ሥልጠና ፕሮግራም ቀርጾ በሥራ ላይ ላይ ከማዋሉም በተጨማሪ የወጣቱን ማህበራዊና ኦኮኖሚያዊ ችግሮች ለመቅረፍ የሚያስችል የወጣቶች ፓኬጅ ነድፎ ተግባራዊ ማድረጉ ይታወቃል።

ወጣቱ በእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅዱ ዋንኛ የትኩረት አቅጣጫ ሲሆን የተነደፈው ብሔራዊ የወጣቶች ፖሊሲም ወጣቱ በሀገሪቱ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ንቁ ተሳትፎ እንዲኖረው ከልማቱም ተጠቃሚ እንዲሆን ማብቃት ነው።

በዚህ ረገድ መንግስት ወጣቱን በማህበራት በማደራጀት፣ የቴክኒክና የማቴሪያል እንዲሁም የተሻለ አመራረት ዘዴና የአከባቢ ሥልጠናዎችን በመስጠት፣ አዲስ የምርት ቦታዎችን አጥንቶ በማዘጋጀት፣ የወጣቱን ሥራ የመፍጠር አመለካከት በማሳደግና በማበረታታት የፖሊሲውን ስትራቴጂያዊ አቅጣጫ በታቀደው መሠረት በመተግበር ላይ ይገኛል።

በተለይ የመልካም አስተዳደርና የዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ በማፋጠንና ግልጽነትና ተጠያቂነትን በማስፈን ረገድ ወጣቱ ለሚያደርገው አስተዋጽኦ መንግስት ልዩ ትኩረት የሚሰጠው ይሆናል።

በጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ፣ በጌጠኛ ድንጋይ (ኮብልስቶን) ሥራና ከዚህም አልፎ በገጠር መንገድ ግንባታ ሰፊ እድል በመፍጠር ወጣቱን

ተጠቃሚ ለማድረግ መንግስት የበኩሉን ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል።

ከግብርና መሩ ኢኮኖሚ ወደ ኢንዱስትሪ በሚደረገው ሽግግር በጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ደረጃ ያሉትን አደረጃጀቶች ወደ መካከለኛ ኢንዱስትሪ ለማሸጋገር በሚደረገው ጥረት ውስጥ የወጣቱ ሚና ወሳኝ መሆኑ የሚያጠያይቅ አይደለም። ይህንን እቅድ ተግባራዊ ለማድረግ በቅድሚያ ወጣቱ ከኪራይ ሰብሳቢነት የፀዳ አመለካከት ሊኖረው ይገባል።

ከዛም አለፍ ሲል ምንም አይነት እሴት ሳይጨምሩና ለኢኮኖሚው እድገት አንዳችም አስተዋጽኦ ሳያበረክቱ በአቋራጭ ለመበልጸግ የሚደረግን ህገ-ወጥ እንቅስቃሴ ወጣቱ ማውገዝና ማጋለጥ ይጠበቅበታል።

በአጠቃላይ በንድፈ ኃሳባዊና በተግባራዊ ሥልጠና በመታገዝ በሰፊው የግንዛቤ ማስጨበጫና የቅድመ ዝግጅት ሥራ አንጻር ሲታይ ወደፊት በዘርፉ ከፍተኛ ውጤት እንደሚመዘገብ ተስፋ ተደርጓል።

መንግስት የወጣቱ መንፈሳዊና አካላዊ ብቃት እንዲዳብር የተለያዩ የወጣቶች ስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎችና መዝናኛ ማዕከላትን ከማስፋፋቱም በላይ በርካታ ክለቦችን በማደራጀት ለባለሙያዎችና ለስፖርተኞችም ተከታታይ ስልጠና በመስጠት ለዘርፉ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል።

የስፖርቱ ዘርፍ በመንግስት ድጋፍ ብቻ ሊያድግ እንደማይቻል ይታወቃል፡፡ ስፖርት ህዝባዊ መሠረት ሊኖረው ስለሚገባ በዚሁ መስክ ህዝቡ ለስፖርቱ እድገት እያደረገ ያለውን ድጋፍ አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት በዚህ አጋጣሚ መግለጽ እፈልጋለሁ።

በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት አስተናጋጅነት የሚካሄደው ይህ የመላዉ ኢትዮጵያ ስፖርቶች ውድድር ከውድድርነት አልፎ የሀገራችንን ብሔር ብሔረሰቦችን ወክለው የመጡ ወጣቶች እርስ በርስ የሚተዋወቁበት የባህልና የልምድ ልውውጥም የሚያደርጉበት መድረክ እንደሚሆን ይጠበቃል።

ከዚህም ባሻገር መድረኩ ክልሉ ትልልቅ ውድድሮችን ማዘጋጀት እንዲችል አቅም ከመፍጠሩም በላይ በክልሉ ላለው ስፖርታዊ እንቅስቃሴ መነቃቃትም የራሱን ድርሻ እንደሚያበረክት ይታመናል።

በመጨረሻም የመላዉ ኢትዮጵያ ስፖርቶች ውድድር ሠላማዊ የፉክክርና የወዳጅነት ማጎልበቻ መድረክ መሆኑ ታውቆ ሁሉንም የስፖርት መርሆዎች በማክበር በተሟላ ስፖርታዊ ጨዋነት ውድድሩን ማጠናቀቅ ከወጣቶች እንደሚጠበቅ እየገለጽኩ ለሁሉም መልካም ውጤትና ቆይታን እመኛለሁ።

አመስግናለሁ!

ስፖርት ህዝባዊ መሠረት ሊኖረው ስለሚገባ በዚሁ መስክ ህዝቡ ለስፖርቱ እድገት እያደረገ ያለውን ድጋፍ አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት በዚህ አጋጣሚ መግለጽ እፈልጋለሁ።

Page 5: ˆ - 3rd All Ethiopia  · PDF fileየጥንቱ የግሪክ ኦሊምፒክ መጫወቻ

5

ስፖርት በማህበራዊ ዘርፍ የህዝቦችና የአገሮች መተዋወቂያ፣ የግንኙትና የትስስር መፍጠሪያ፣ ማጠናከሪያና የአካልና የአዕምሮ ጤንነትና ደህንነት

መጠበቂያ ነው። በኢኮኖሚው ረገድ የሀብት ምንጭ፣ ሥራና የሥራ ዕድል ሲሆን በፖለቲካው ደግሞ የመቻቻልና የሠላም መገለጫ እንዲሁም የዓለም አቀፍ የልማትና የሰላም አጀንዳዎች ማራመጃ መሣሪያ መሆኑ ገሀድ ነው፡፡

በመሆኑም የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ

ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት በስፖርት ልማት አገራችንና ሕዝቧን ተሳታፊና ተጠቃሚ ማድረግ የሚያስችል ብሔራዊ የስፖርት ፖሊሲ ቀርፆ ወደ ትግበራ ገብቷል። ይህን መሠረት በማድረግ ህዝባዊ መሠረት ያለው ስፖርት በመላው ሀገራችን እንዲስፋፋ በማድረግ የዜጎችን የስፖርት ተሳትፎና ተጠቃሚነት፣ ለማረጋገጥ እና በዓለም የስፖርት አውደ ውድድሮች አገራቸውን ወክለው በመሰለፍ በሚያስመዘግቡት አንጸባራቂ ድል የአገራቸውንና የህዝቦቻቸውን መልካም ገጽታ ማስተዋወቅ የሚችሉ አትሌቶች ለማበርከት በሕዝብ ተሳትፎና ባለቤትነት ሰፊ የልማት ሥራ ላይ እንገኛለን፡፡

ክቡር አቶ አብዲሣ ያደታየፌዴራል ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር መልዕክት

Page 6: ˆ - 3rd All Ethiopia  · PDF fileየጥንቱ የግሪክ ኦሊምፒክ መጫወቻ

6

ሁላችንም እንደምናውቀው ልማታዊና ዴሞክራሲያዊ መንግስታችን በሚቀጥሉት አመታት ሀገራችንን ካለችበት ኋላቀርነትና ድህነት ተላቃ መካከለኛ ገቢ ካላቸው አገራት ተርታ ለማሰለፍ ፈጣን የልማት ዕቅድ ዘርግቶ ለተግባራዊነቱ ሰፊ ርብርብ በማድረግ ላይ እንገኛለን፡፡ በተለይ ደግሞ ይህን ከማሳካት አኳያ የአምስት ዓመት ሀገራዊ የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ቁልፍ ሚና አለው።

በዚሁ መሠረት በዕቅድ ዘመኑ በስፖርቱ ሴክተር የስፖርት ማህበራትንና ኮሚቴዎችን ቁጥር በማሳደግ፤ ለስፖርት ማህበራትና ኮሚቴዎች የፋይናንስ፣ የቴክኒክና የማቴሪያል ድጋፍ ማድረግ አንዱ ተግባር ነው። የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎችን ቁጥር በማሳደግ፤ የስፖርት ማሰልጠኛ ማዕከላትን በማስፋፋት፤ በስፖርት ኢንቨስትመንት የሚሰማሩ ባለሀብቶችን ቁጥር ከፍ ማድረግ ሌላኛው የዕቅዱ ግብ ነው። የሕብረተሰቡን ተሳትፎ ከፍ በማድረግ፤ የስፖርት ፌስቲቫሎችን፣ ውድድሮችንና መድረኮችን ቁጥር በስፋት በማበራከት፤ የስፖርት ባለሙያዎችን በብዛት በማፍራት፣ የታዳጊ ወጣቶች ሰልጣኞችን ፣ የሰፖርት አይነቶች እና በዘርፉ የጥናትና ምርምር ስራዎችን በስፋት በማካሄድ በአገራችን ስፖርት የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ የሚያስችሉ ግቦች በዕቅዱ ተካተው ትግበራው ተጀምሯል፡፡

የስፖርት ውድድሮችና ጨዋታዎች መካሄድ መነሻው በዋናነት በነዚህ ሁነቶች አማካኝነት የአገራችን ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ተወካዮች በአንድ መድረክ ተገናኝተው ከጨዋታዎችና ከውድድሮች ጎን ለጎን እርስ በእርስ እንዲተዋወቁ፣ ግንኙነት እንዲመሠርቱና እንዲያጠናክሩ በሰላም፣ በመቻቻል፣ በመከባበርና በፍቅር የአብሮ መኖር ተምሳሌት እንዲሆኑ ማድረግ ነው። በአጠቃላይ ደግሞ የስፖርትን ዓለም አቀፋዊ የልማትና የሰላም መሣሪያነቱንና መድረክነቱን በተግባር እንዲያስመሰክሩ ለማስቻል ነው፡፡ ከዚህ አኳያ በአገራችን ከሚካሄዱት አገር አቀፍ የስፖርት ጨዋታዎችና ፌስቲቫሎች መካከል አንዱ የሆነው የመላ ኢትዮጵያ ጨዋታዎች ዓላማም ከላይ ያነሳኋቸው ዓለማዎች መተግበሪያ አንዱ መድረክ ነው፡፡

በ1999 ዓ.ም. የተጀመረውና ለሦስተኛ ጊዜ በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት አስተናጋጅነት “የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅዱን ተግባራዊ በማድረግ በስፖርት የህብረተሰቡን ተሳትፎና ተጠቃሚነትን እናረጋግጣለን” በሚል መሪ ቃል ከመጋቢት 2 እስከ 18/2004 ዓ.ም የሚካሄደው የመላው ኢትዮጵያ ጨዋታዎች የመላው አፍሪካ ጨዋታዎችንና የዓለም ኦሊምፒክ ጨዋታዎችን መርህ የተከተለና በእነዚህም መንፈስ ተገርቶ የስፖርቱን

ዓላማዎች ለማሳካት የሚከናወን ነው፡፡ በየክልሉና ከተማ አስተዳደሩ ባለፉት ሣምንታት ሲካሄዱ የነበሩት ክልላዊና ከተማ አቀፍ ጨዋታዎች በስፖርት ወዳድ ኅብረተሰብ ዘንድ ከፍተኛ መነቃቃትን የፈጠሩ ከመሆኑም በላይ የ3ኛ መላው ኢትዮጵያ ጨዋታዎች ተሣታፊ ምርጥ ቡድንን ለመምረጥ ያስቻሉ ጠቃሚ የውድድር መድረክ ሆነው አልፈዋል፡፡

የመላ ኢትዮጵያ ጨዋታዎች ከአምስት አመቱ የስፖርት ሴክተር የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ግቦች አኳያ የህዝብ ተሳትፎና የተተኪ ስፖርተኞች መገኛ መድረክነታቸውና በዚህም ያላቸው አስተዋጽኦ ጉልህ እንደሆነ ይታመናል፡፡ በመሆኑም የመላው ኢትዮጵያ ጨዋታዎች ዝግጅትና አፈጻጸም ለአገራዊው የስፖርት ልማት የራሱን ሚና መጫወት እንዲችል የፌዴራል ስፖርት ኮሚሽን አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል፡፡

በዚህ መልካም አጋጣሚ ለጨዋታው ታዳሚዎችና ለመላው የሀገራችን ህዝቦችና የስፖርት ቤተሰቦች ማስተላለፍ የምፈልገው ፤ የአምስት አመቱ የስፖርት ሴክተር የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድና ቀጣይ የልማት ስራዎች በተፈለገው ደረጃ ተፈጽመው ለውጤት የምንበቃው የህዝባችን ሁለንተናዊ ተሳትፎና ድጋፍ ሲታከልበት በመሆኑ፤ ለዚህ ሁላችንም በአዲስ መንፈስና ቁርጠኝነት ተነሳስተን ለአገራችን ስፖርት ልማት የሚጠበቅብንን አስተዋጽኦ እንድናበረክት ጥሪዬን አቀርባለሁ፡፡

በመጨረሻም ሦስተኛው የመላ ኢትዮጵያ ጨዋታዎች በተሳካ ሁኔታ እያስተናገደ ላለው ለኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት እና ለዝግጅቱ አስፈላጊውን ድጋፍ ላደረጉ አካላት በሙሉ ልባዊ ምስጋናዬን በራሴና በፌዴራል ስፖርት ኮሚሽን ስም እያቀረብኩ ጨዋታው በጥሩ ስፖርታዊ ጨዋነትና ሥነ ምግባር ታጅቦ በስኬት እንዲጠናቀቅ ልባዊ ምኞቴን እገልጻለሁ፡፡

አመስግናለሁ !

የመላው ኢትዮጵያ ጨዋታዎች ከአምስት አመቱ የስፖርት ሴክተር የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ግቦች አኳያ የህዝብ ተሳትፎና የተተኪ ስፖርተኞች መገኛ መድረክነታቸውና በዚህም ያላቸው አስተዋጽኦ ጉልህ እንደሆነ ይታመናል፡፡

Page 7: ˆ - 3rd All Ethiopia  · PDF fileየጥንቱ የግሪክ ኦሊምፒክ መጫወቻ

7

ሀገራችን በኦሊምፒክ ጌምስ ከ1956 ዓ.ም ጀምሮ በመሳተፍ ዓለምአቀፍ የወጤታማነት ታሪክ እያስመዘገበች እንደመቀጠሏ በሌላ ወገን ህዝቦቿን በጋራ ሊያገናኝና ሊያሰባስብ የሚችል ብሔራዊ

የኦሊምፒክ ጨዋታ ግን በአንጻራዊነት ረጅም ለሚባሉ ዓመታት ሳታዘጋጅ ቆይታለች። የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ የኦሊምፒክ ፍልስፍናና መርህን መሠረት

አቶ ብርሃነ ኪዳነማርያምየኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት መልዕክት

Page 8: ˆ - 3rd All Ethiopia  · PDF fileየጥንቱ የግሪክ ኦሊምፒክ መጫወቻ

8

በማድረግ የኢትዮጵያ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች በአንድ መደበኛ የኦሊምፒክ ስፖርቶች መድረክ እንዲገናኙ እንቅስቃሴዎች ሲያደርግ ቆይቶ በ1999 ዓ.ም የመጀመሪያውን ‹የመላው ኢትዮጵያ ጨዋታዎች› ከፌደራል ስፖርት ኮሚሽንና ሌሎች አካላት ጋር በመሆን ማካሄድ መቻሉ ተቋሙ የቆመላቸውን ዓላማዎች በማሳካት ረገድ ተጨማሪ ዕርምጃ መጓዙን ያመላከተ ነበር።

ከኦሊምፒዝም መገለጫ አኳያም በአዲስ አበባ ከተማ የተጀመረው የመላ ኢትዮጵያ ጨዋታዎች በመዲናችን ሳይወሰን ዛሬ ሁሉም ክልሎች በየተራ ለማስተናገድ በተዘጋጁበት ጊዜ ላይ ደርሰናል ። በዚህ ረገድ የ3ኛው የመላ ኢትዮጵያ ጨዋታዎች አስተናጋጅ የሆነው የኦሮሚያ ክልል በቀዳሚነት ይህን ብሔራዊ የኦሊምፒክ መድረክ ለማስተናገድ ላሳየው ፍላጎትና ጨዋታው በሚካሄድባቸው ከተሞችም አስፈላጊ የሆኑ አቅርቦቶችን ለማሟላት ላከናወናቸው ተግባራት የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ከፍተኛ አድናቆት አለው።

ከኦሊምፒክና የመላው አፍሪካ ጨዋታዎች ጋር በተቃኘ መልኩ የሚካሄደው የመላ ኢትዮጵያ ጨዋታዎች የኢትዮጵያን ህዝቦች ወዳጅነትና አንድነት ከማጎልበት ባሻገር በዓለም አቀፍ መድረኮች የሀገራችንን መልካም ስምና ክብር ከፍ አድረገው የሚያሳዩ ወጣትና ተተኪ ስፖርተኞችን ለማፍራት እንደሚያግዝ ይጠበቃል። መድረኩ የተሳካ እንዲሆን የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ቀደም ብሎ ለአትሌቶች፣ ለአሰልጣኞችና ሌሎች ባለሙያዎች ስልጠናዎች አዘጋጅቶ የሰጠ ሲሆን በተጨማሪም የ2 ሚሊየን ብር የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል። በተቋሙ በኩል ኦሊምፒዝም በኢትዮጵያ ህዝቦች የአብሮነት ህይወትና በባህላዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እንቅስቃሴዎቻቸው ውስጥ የሚኖረው አዎንታዊ ሚና እንዲሰፋ የማድረግ መሰል ድጋፎች ወደፊትም ይበልጥ ተጠናክረው የሚቀጥሉ ይሆናሉ።

በመሆኑም መላው የስፖርቱ ቤተሰቦች በነዚህ የኦሊምፒክ እንቅስቃሴዎች ውስጥ ተሳታፊና ተጠቃሚ እንድትሆኑ ጥሪዬን ሳስተላልፍ ታላቅ ክብር ይሰማኛል።

ይህ ዓመት በማፑቱ በተካሄደው 10ኛው

የመላ አፍሪካ ጨዋታዎች የተካፈለው ብሔራዊ ቡድናችን ከምንጊዜውም የተሻለ /የሜዳሊያዎች/ ውጤት አስመዝግቦ የተመለሰበትና በተጨማሪም ሀገራችን በለንደን 2012 ኦሊምፒክ ጌምስ ለመካፈል እየተዘጋጀች ያለችበት ልዩ ወቅት ነው። የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ሀገራችን በኦሊምፒክ ያላት ደማቅ ታሪክ ዘንድሮም በለንደን 2012 ኦሊምፒክ ጌምስ የበለጠ ደምቆ እንዲደገም በከፍተኛ ትጋትና የኃላፊነት መንፈስ እየሰራ ይገኛል። ከተለያዩ ተቋማት የተወከሉ ኢትዮጵያውያንን ጭምር በማሳተፍ እየተደረገ ያለው ዝግጅት የሀገራችን ልዑክ በተሟላና ብቃት ባለው መልኩ በኦሊምፒክ እንዲካፈል የሚያስችለው በመሆኑ ለስኬቱ ሁሉም ዜጎች ሀገራዊ ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪዬን አቀርባለሁ።

በሌላ በኩል የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ የኦሊምፒክ ተቋማትን ለማስፋፋት ከያዛቸው የልማት ዕቅዶች መካከል በአዲስ አበባ የኦሊምፒክ አካዳሚና በቢሾፍቱ የኦሊምፕአፍሪካ ግንባታዎች የዲዛይን ስራ በመጠናቀቁ ፈጥኖ ወደ ተግባር ለመለወጥ ቅድመ ስራዎችን እያከናወነ ነው። ከነዚህም በአዲስ አበባ

ከተማ የሚገነባውና በ120,000 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ የሚያርፈው የኦሊምፒክ አካዳሚ፣ እንዲሁም በቢሾፍቱ ከተማ የሚገነባው የኦሊምፕአፍሪካ አካዳሚ ሰፊ የሀብት ወጪን የሚጠይቁ በመሆናቸው በአጭር ጊዜ ውስጥ እውን እንዲሆኑ ከተቋማችን ውጭ ያሉ አካላትንም ርብርብ ይጠይቃሉ። አካዳሚዎቹ በኦሊምፒዝም እንቅስቃሴ ውስጥ በየስፖርት ዓይነቱ ለሚሳተፉ ስፖርተኞችና በአጠቃላይም ለህዝባችን ከሚኖራቸው የላቀ ጠቀሜታ አንጻር ሁሉም ወገኖች ግንባታውን በማገዝ እንዲሳተፉ በዚህ አጋጣሚ መልዕክቴን አስተላልፋለሁ።

ኦሊምፒዝም በኢትዮጵያ ሰፊ መሰረት እንዲኖረው የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ በልዩ ልዩ ፕሮግራሞችና ፕሮጀክቶች የሚያከናውናቸውን ስራዎች አጠናክሮ ይቀጥላል። የዚሁ አካል የሆነው የመላው ኢትዮጵያ ጨዋታም በቀጣይ በስፖርት ዓይነትና በተሳታፊዎች ቁጥር ይበልጥ እንዲጐለብት ይደረጋል።

በመጨረሻም ዘንድሮ ለ3ኛ ጊዜ የሚካሄደው የመላው ኢትዮጵያ ጨዋታዎች ያማረና የደመቀ እንዲሆን ጥረት ላደረጋችሁ በሙሉ በኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴና በራሴ ስም ምስጋና አቀርባለሁ።

በተቋሙ በኩል ኦሊምፒዝም በኢትዮጵያ ህዝቦች የአብሮነት ህይወትና በባህላዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እንቅስቃሴዎቻቸው ውስጥ የሚኖረው አዎንታዊ ሚና እንዲሰፋ የማድረግ መሰል ድጋፎች ወደፊትም ይበልጥ ተጠናክረው የሚቀጥሉ ይሆናሉ።

Page 9: ˆ - 3rd All Ethiopia  · PDF fileየጥንቱ የግሪክ ኦሊምፒክ መጫወቻ

9

ግሪክ ለጥንት ኦሊምፒክ ጨዋታ ዕድገትና በአሁኑ ዘመን በየአራት ዓመቱ አንድ ጊዜ ለሚከናወነው የኦሊምፒክ ጨዋታ መሠረት ነች። ፍልስፍናው ዘመን ተሻግሮ አሁን የምናውቀውን ኦሊምፒክ

እንደፈጠረ ሁሉ ከዚያም ባለፈ ወደ አህጉርና ሀገር (ብሔራዊ) ደረጃ ዘልቆ ወርዶ የመላው አፍሪካ ጨዋታንና የመላው ኢትዮጵያ ጨዋታን ወልዷል። በዚህም ከመጀመሪያው የኦሊምፒክ ስፖርት መሰረታዊ አስተሳሰቦችን በመውሰድ በዘመናችን ህብረተሰብ ዘንድ ስፖርት ዐብይ የሰብዓዊነትና አለምአቀፋዊ ግንኙነት መሳሪያ ሆኖ ጥቅም ላይ እየዋለ ይገኛል።

ታሪክን የኋሊት … የዚህን ዘመን የኦሊምፒክ አስተሳሰብና መንገድ

ለመረዳት እጅግ ወደ ኋላ ተጉዞ እንደ ውቅያኖስ ከሰፋው የጥንታዊት ግሪክ የኦሊምፒክ ጨዋታ ፍልስፍና እና ታሪክ መሀከል ጥቂቱን እንኳ ጨለፍ አድርጎ ተመልሶ ማወቅና መገንዘብ ግድ ይላል።

የጥንቶቹ ግሪኮች በጦርነት፣ በሰላም፣

ታላቁ መንገድበአስቻለው ሽፈራው

በሀይማኖትና በሌላው ጉዳያቸው ሁሉ የህይወት መንገዳቸውን የሚመራ፣ የሚያምኑበት፣ የሚታመኑለትና መስዋትነት የሚከፍሉለት ከየአይነቱ የጣኦት አማልክት ነበራቸው። የእመነታቸውን ልክና ለአማልክቱ የሚሰጡትን ክብር ለማሳየት ሲሉም ልዩ ልዩ በዓላትን ያዘጋጁ ነበር። በዚህ ወቅት የጅምናስቲክ ስፖርት፣ የግጥም፣ የቅርጻ ቅርጽ፣ የሥዕልና የሙዚቃ ውድድሮች ይከናወናሉ።

ለአማልክቶቹ በየደረጃቸው ለክብራቸው ሲባል በዓል የሚዘጋጅ ቢሆንም በኦሊምፒያ ከተማ ለአማልክቶች አምላክ ለዚውስ ክብር ይደረግ የነበረው ክብረ በዓል ግን ከማንኛቸውም የላቀና ከፍተኛ ነበር። ይህም ለኦሊምፒክ መከሰት ምክንያት ሆነ። የዚያን ዘመን ግሪኮች በኦሊምፒያ ከተማ የሚያዘጋጁት ክብረ በዓል በየአራት (4) ዓመቱ አንዴ እጅግ ደማቅ በሆነ መልኩ የሚከናወን ሆኖ ከ776 ቅድመ ክርስቶስ (ዓ.ዓ) እስከ 394 ድህረ ክርስቶስ (ዓ.ም) ወይም በድምሩ ለ1170 ዓመታት ያህል እንደዘለቀ ተጽፏል።

የኦሊምፒክ ጨዋታዎች በሚካሄዱበት አምስት ቀናት ወቅትም “የተቀደሰ ሰላም“ በሚል መርሆ ማናቸውም ጦርነቶች እንዲቆሙ ይደረጋል። ምናልባት በተግባር ያልተረጎመው ወገን ቢገኝ ደግሞ ከፍተኛ

ኦሊምፒዝም

Page 10: ˆ - 3rd All Ethiopia  · PDF fileየጥንቱ የግሪክ ኦሊምፒክ መጫወቻ

10

ቅጣት ያገኘው እንደነበር የታሪክ አዋቂዎች በተለያዩ ጽሁፎቻቸው አስፍረዋል። በዚያን ዘመን የኦሊምፒክ ጨዋታዎች ከመካሄዳቸው አንድ ሳምንት ቀደም ብሎ በሁሉም የግሪክ ግዛቶች የሚገኙ መኳንንትና መሳፍንቶች፣ የፖለቲካ ሰዎች፣ ገበሬዎች፣ አትሌቶች ወዘተ ወደ ኦሊምፒያ ይጎርፋሉ። በኦሊምፒያ መንደሮችም ድንኳናቸውን ተክለው ይከትማሉ። በእንዲህ መልኩ በመሰባሰባቸውም ለመነጋገር፣ ለመቀራረብ፣ ሀሳብ ለመለዋወጥና የወንድማማችነት ቅርበት ለማጎልበት ዕድል ያገኛሉ።

በወቅቱ እንደዛሬው ዘመን ትላልቅ ስታዲየሞችና ጂምናዚየሞች ባይኖሩም እስከ 40000 ህዝብ የሚያስተናግዱ የነበሩ የኦሊምፒያ ተፈጥሯዊ ሜዳዎች ተከልለው ለውድድር አገልግለዋል። ይሁንና ለዓመታት ሲከበር የቆየው የኦሊምፒክ ጨዋታ እንዳይቀጥል ብዙ መሰናክሎች ገጠሙት። የግዛት ክፍፍልና የንጉሳዊ አስተዳደር መውደቅና መነሳት፣ ለጨዋታው ዝቅተኛ ግምት እየተሰጠው መሄድና ኋላም የተጣለበት ክልከላ እያከሰመው ሄዶ ጭርሱኑ አጠፋው።

ሰወኛው መሰናክል በተፈጥሮአዊ ቅጣት ተጠናቀቀ። ኦሊምፒያ በመሬት መናወጥ ተደበላለቀች። የግሪክ የባህል ማዕከል፣ ለዘመናት የተጓዘችበት ታላቅ መንገድ ኦሊምፒዝምና፣ የፍልስፍናው አራማጅ የነበሩት ህዝቦቿም ተዋጡ።

የኦሊምፒክ ጨዋታዎች በሚካሄዱበት አምስት ቀናት ወቅትም “የተቀደሰ ሰላም“ በሚል መርሆ ማናቸውም ጦርነቶች እንዲቆሙ ይደረጋል።

የጥንቱ የግሪክ ኦሊምፒክ መጫወቻ መግቢያ

የጥንቱ የግሪክ ኦሊምፒክ መጫወቻ ሜዳ

Page 11: ˆ - 3rd All Ethiopia  · PDF fileየጥንቱ የግሪክ ኦሊምፒክ መጫወቻ

11

የኦሊምፒዝም ትንሳዔኦሊምፒዝም ከተቀበረበት ወጥቶ በዘመናዊ

መልክ ዳግም ለሰው ልጆች እንዲጠቅም ለማድረግ በርካቶች ጥረዋል። እ.ኤ.አ ከ1450 እስከ 1604 በአውሮፓ በተለያዩ ሀገራት የኦሊምፒክን ጽንሰ ሀሳብ መለስ ብለው የሚጠቁሙ ጹሁፎች፣ የመድረክ ትዕይንቶች፣ አዳዲስና የጥንቱን የኦሊምፒክ ጨዋታ የተከተሉ ጌምስ ጭምር ታዩ። እንደ የዓለም ቀይ መስቀል ማህበርና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ያሉ የየሀገራት ህዝቦች የሚተዋወቁባቸውና በጋራ የሚገናኙባቸው ተቋማት መመስረትም የኦሊምፒዝምን መንፈስ እንዲያንሰራራ አደረገው። ከዚሁ ጋር በጎረቤት ሀገራት ዩኒቨርስቲዎች መካከል የሚካሄዱ የጂምናስቲክ

ስፖርት ውድድሮች ደግሞ ይበልጥ አጠነከረው። ከዚሁ ጋር በ19ኛው ክ.ዘ መጨረሻ ላይ

ፈረንሳዊው ፒየር ዲ.ኩበርቲን የሀገሩ ወጣቶች ጠንካራና ጤናማ እንዲሁም በእምነትና ስነ ምግባር የጠነከሩ እንዲሆኑ ካለው ፍላጎት የተነሳ ያደረጋቸው እንቅስቃሴዎች ለዘመናዊ ኦሊምፒክ መፈጠር ትልቅ ምክንያት ሆኗል። በተያያዘ ኩበርቲን በአስተሳሰቡ ሁሉም ብሔሮች በዓለም ላይ አብሮ የመኖርና የመስራት ነፃነት ሊኖራቸው ይገባል የሚለውን እምነት አራማጅ ነበር። በወቅቱ በአውሮፓ ይታይ የነበረው የማንአህሎኝነት ስሜትም ዕረፍት አሳጥቶታል። ለዚህ ሁሉ ደግሞ የሰውነት ማጎልማሻ ስፖርት በጨዋታ መልክ ጥቅም ላይ ቢውል አጋዥ

Page 12: ˆ - 3rd All Ethiopia  · PDF fileየጥንቱ የግሪክ ኦሊምፒክ መጫወቻ

12

እንደሚሆን በማመኑም አንድ ቡድንና ተከትሎም አጋዥ ኮሚቴ አቋቋመ። ስራውን የቀጠለው ኮሚቴው በሂደት በአትሌቲክስ ስፖርት የጥንት ኦሊምፒክ ጨዋታዎችን ወደማዘጋጀት ሀሳብ ተሸጋገረ። ሀሳቡ በአሜሪካ ፣ በስዊዲን ፣ በሀንጋሪና ሌችም ዘንድ ድጋፍና ተቀባይነት እያገኘ ሄደ።

በዚህ መልኩ ለዘመናዊ ኦሊምፒክ መጀመር መንገዱን ያሰፋው ኩበርቲን የአለም አቀፍ ስፖርት እንቅስቃሴ በንጹህ ወንድማማችነት፣ የእርስ በእርስ መግባባትና መተዋወቅ ላይ የተመሰረተ መሆን አለበት የሚል አቋም ነበረው። በተጨማሪም ዓላማው መሳተፍ እንጂ ማሸነፍ ብቻ መሆን እንዳልነበረበትና ይህንንም ተግባራዊ ለማድረግ ማናቸውም ድርጅቶች የሚችለውን ያህል አስተዋጽኦ እንዲያደርግ አስፈላጊ መሆኑን ያምናል።

እነዚህንና እነዚህን የመሳሰሉትን ለሰው ልጆች መቀራረብ ብሩህ ተስፋ የሚያጎናጽፉ ትክክለኛ አስተሳሰቦችን በማጠናከር ፒየር ዲ-ኩበርቲን ለኦሊምፒክ ጨዋታ ዕድሳት መሰረት አኖረ። ኩበርቲን እኤአ በ1894 በጻፈው ማስታወሻም “በ4 ዓመት አንድ ጊዜ በሚካሄደው የኦሊምፒክ ጨዋታ የዓለም ብሔሮች

የመላው ኢትዮጵያ ጨዋታዎች ጨዋታ የኦሊምፒክና የመላ አፍሪካ ጨዋታዎችን መርሆች ተከትሎ በሀገራችን በየሁለት ዓመቱ የሚካሄድ ከፍተኛ የስፖርት ውድድር ነው።

Page 13: ˆ - 3rd All Ethiopia  · PDF fileየጥንቱ የግሪክ ኦሊምፒክ መጫወቻ

13

ተወካዮች ስለሚገናኙ የተሟሉና ሰላማዊ ውድድሮችን በማካሄድ እጅግ በጣም የተሻለ ዓለም አቀፋዊነትን እንደሚፈጥሩ እምነት ሊኖረን ይችላል” ብሎ ነበር።

በዚያው ዓመት የመጀሪያው ኦሊምፒክ ጨዋታም እንዲከናወን ውሳኔ ተላለፈ። ሰኔ 16/ 1894 እንግሊዝ፣ አሜሪካ፣ ስዊዲን፣ ስፔን፣ ጣሊያን፣ ቤልጂየም፣ ሩሲያ፣ ሀንጋሪና፣ ግሪክ በተወካዮቻቸው እንዲሁም አውስትራሊያና ጃፓን በጽሁፍ በሰጡት ድጋፍ ዓለም አቀፍ የኦሊምፒክ ኮሚቴ እንዲቋቋም ተወሰነ። ለዚህም ትግበራ በግሪክና በሌሎች ሀገራት ብዛት ያላቸው ኮሚቴዎች እንዲቋቋሙ ተደረጉ።

የኦሊምፒክ ደንቦች የመጀመሪያ ገጾች ….

አንቀጽ 1- በኦሊምፒክ ጨዋታዎች ….የሀገር ፣ ብሔር ፣ ሀይማኖት፣ የሀላፊና የሰው ልዩነት ማድረግ ፍጹም አይቻልም

አንቀጽ 3- የኦሊምፒክ እንቅስቃሴ ዓላማ ወጣቶች ለአካል ጥንካሬ ያላቸውን ስሜት ማሳደግና ለአማተር ስፖርት መሠረት በሆነው ጥሩ ስነምግባር …. የታነጹ አንዲሆኑ መንከባከብ ነው ።

ከላይ የተጠቀሱተት ተጨባጭ ሁኔታዎች በሙሉ ኩበርቲንና የዓለም አቀፍ ኦሊምፒክ ኮሚቴ መሠረታዊ ዓላማ በስፖርት ፍላጎት አማካይነት ብሔሮችን በዘር፣ በሀይማኖት፣ በርዕዮተዓለም አመለካከታቸው ሳይለያዩ ጥሩ የእህትማማችነት፣ የወንድማማችነትና የአብሮነት መንፈስ እንዲተግብሩ የሚቻልበትን መንገድ ያሳየናል። ከዚህም በመነሳት በዚህ አስተሳሰብ ተመስርቶ በኦሊምፒክ ጨዋታዎች ላይ የሚገኘው የስፖርትና የስፖርተኛው ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መጥቷል ።

ኦሊምፒዝም እና የመላኢትዮጵያ ጨዋታዎች ትስስር

የመላው ኢትዮጵያ ጨዋታዎች ጨዋታ የኦሊምፒክና የመላ አፍሪካ ጨዋታዎችን መርሆች ተከትሎ በሀገራችን በየሁለት ዓመቱ የሚካሄድ ከፍተኛ የስፖርት ውድድር ነው። ጨዋታው በዋናነት ቀጥሎ ያሉትን ዓላማዎች መሰረት ያደርጋል፡-

- የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በማቀራረብ የባህልና የቋንቋ ትውውቅ፣

የልምድ ልውውጥ እና የአንድነትና የወዳጅነት ስሜት በመካከላቸው እንዲኖር ምቹ መድረክ መፍጠር

- በስፖርቱ ውድድር አማካኝነት በሁሉም ክልሎች የሚገኙ የሀገራችን ዜጎች የእርስ በእርስ መተዋወቅና መግባባትን በመፍጠር ስለአካባቢያቸው መረጃዎችንና ተሞክሮዎችን እንዲለዋወጡ ማድረግ

- ሀገራችን በተለያየ ጊዜና ደረጃ በምትሳተፍባቸው አህጉራዊና አለም አቀፋዊ የስፖርት ውድድሮች የሚወክሏትን ምርጥ ስፖርተኞች ለማግኘት፣ ተተኪ ወጣቶች የሚፈሩበትን መድረክ ለመፍጠር

- በሚከናወነው ስፖርታዊ ውድድር አማካኝነት ወጣቶች የሚሳተፉበትን ከፍተኛ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ መፍጠር

የመጀመሪያውን የመላ ኢትዮጵያ ጨዋታ አዲስ አበባ ከመጋቢት 2-15 ቀን 1999 ዓ.ም አስተናገደች። 2ኛው የመላ ኢትዮጵያ ጨዋታም እንዲሁ የተካሄደው በመዲናችን ሲሆን ወቅቱ 2002 ዓ.ም ነበር። ዘንድሮ ይኸው ብሔራዊ የኦሊምፒክ መድረክ ከአዲስ አበባ ወጥቶ ወደ ክልል ተጉዟል። በኦሮሚያ ክልል አስተናጋጅነት የአዳማ፣ የአሰላና የደብረ ዘይት ከተሞች የጨዋታው መድመቂያ ይሆናሉ።

Page 14: ˆ - 3rd All Ethiopia  · PDF fileየጥንቱ የግሪክ ኦሊምፒክ መጫወቻ

14

ቆይታ

መላ ኢትዮጵያ፡- የመላ ኢትዮጵያ ጨዋታዎች በየጊዜው መካሄድ አጠቃላይ ዓላማው ምንድን ነው?አቶ አምበሳው፡- አጠቃላይ ዓላማው

የኢትዮጵያ ብሔራዊ የስፖርት ፖሊሲ ዋና ዓላማ ነው።

እንደሚታወቀው ህብረተሰቡ በስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች የሚያደርገውን ተሳትፎ በማስፋትና በማሳደግ፣ ከሰፊው የህዝብ ተሳትፎ ምርጥ

ስፖርተኞችን በማፍራት ሀገራችን በአህጉርና ዓለም አቀፍ ውድድሮች ተገቢውን ደረጃ እና ዝና ማስጠበቅ የስፖርት ፖሊሲው አጠቃላይ ዓላማ ነው።

በመሆኑም ይህንን ዓላማ ተግባራዊ ለማድረግ በየደረጃው ከቀበሌ እስከ ሀገር አቀፍ ደረጃ ጨዋታዎችንና ውድድሮችን በብዛትና በጥራት በማካሄድ መላውን ህብረተሰብ ማሳተፍና ማነቃነቅ ነው። እንዲሁም ከእነዚህ ውድድሮች በአህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ውድድሮች ሀገርን የሚወክሉ ብሔራዊ

በኦሮሚያ ክልል አስተናጋጅነት የሚካሄደው 3ኛው መላ ኢትዮጵያ ጨዋታዎች የተሳካ ይሆን ዘንድ የተለያዩ አደረጃጀቶች ተፈጥረው ቅድመ ዝግጅቶች ሲደረጉ ቆይተዋል። ለፕሮግራሙ ስኬት የተከናወኑ ስራዎችን በተመለከተ ከዝግጅቱ ዐብይ ኮሚቴ ሰብሳቢና የፌደራል ስፖርት ም/ኮሚሽነር ክቡር አቶ አምበሳው እንየው ጋር እንየው ዓሊ ቆይታ አድርጓል።

Page 15: ˆ - 3rd All Ethiopia  · PDF fileየጥንቱ የግሪክ ኦሊምፒክ መጫወቻ

15

ቡድኖችን ለማዘጋጀትና ተተኪዎችን በብዛትና በጥራት ለማፍራት ታስቦ የሚዘጋጅ ነው።

ከዚህ ባሻገር ስፖርታዊ ውድድሮች ከላይ ከተጠቀሱት ዓላማዎች ባለፈ መቀራረብን፣መቻቻልን፣ እንዲሁም ማህበራዊ ግንኙነቶችን በማጠናከር ረገድ ሁነኛ መሣሪያ ናቸው። ስለሆነም ይህ በየጊዜው የሚካሄደው የመላ ኢትዮጵያ ጨዋታዎች በሀገራችን የሚገኙ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦችን በማቀራረብ ፣ የአንድነትና የወዳጅነት ስሜት በመካከላቸው እንዲኖር የማድረግ ዓላማ አለው።

መላ ኢትዮጵያ፡- እርስዎ የ3ኛው መላ ኢትዮጵያ ጨዋታዎች ዝግጅትና ክትትል አብይ ኮሚቴ ስብሳቢ እንደመሆንዎ ዝግጅቱ ምን እንደሚመስል ቢገልጹልን?አቶ አምበሳው፡- የዘንድሮ መላ ኢትዮጵያ

ጨዋታዎች የሚካሄደው “የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅዱን ተግባራዊ በማድረግ የህብረተሰቡን በስፖርት ተሳትፎና ተጠቃሚነት እናረጋግጣለን” በሚል መሪ ቃል ይካሄዳል።

የሀገራችንን የስፖርት ፖሊሲ ተግባራዊ ለማድረግና የኦሊምፒክ ፍልስፍናን ለማስፋፋት በ1999 ዓ.ም. እና በ2002 ዓ.ም. ሁለት የመላ ኢትዮጵያ ጨዋታዎች በ17 የስፖርት ዓይነቶች በሁሉም ክልሎችና ከተማ መስተዳድሮች መካከል በተከታታይ በአዲስ አበባ ከተማ በደመቀ ሁኔታ መካሄዱ ይታወቃል። ከእነዚህ ጨዋታዎች በርካታ ልምዶችን አግኝተናል። ስለዚህ የ3ኛው መላ ኢትዮጵያ ጨዋታዎች ዝግጅት የተጀመረው ከአለፉት ሁለት ጨዋታዎች

አፈፃፀም ልምድና ተሞክሮ በመነሳት ነው። በመሆኑም ይህን ጨዋታ ቀደም ካሉት

ጊዜያት በተሻለ ሁኔታ ለመምራት የሚያስችል አደረጃጀት ፈጥረን ለዚሁ ማስፈፀሚያ የሚሆን ዕቅድ በማዘጋጀት ወደ ሥራ ገብተናል። በተለይ ውድድሩ ከአዲስ አበባ ውጭ በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልል የሚካሄድ በመሆኑ በየስፖርት ዓይነቱ በቂ የመወዳደሪያ ቦታዎች እንዲኖሩ አስፈላጊው ሥራ ተሠርቷል። ከሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳድሮች ለሚመጡ ልዑካን ቡድኖች የማደሪያና መመገቢያ ሥፍሪዎች ተመቻችተዋል።

በጐ ፍቃደኞችን በማሰልጠን በእያንዳንዱ የስፖርት ዓይነት ድጋፍ እንዲሰጡ የስምሪት ሥራ ሠርተናል።

በሌላ በኩል ሁሉም ክልሎችና ከተማ መስተዳደሮች ለ3ኛው መላ ኢትዮጵያ ጨዋታዎች ዝግጅት የውስጥ ውድድራቸውን በጥሩ ሁኔታ አካሂደዋል። በተመሳሳይ ሁኔታ እኛም ጨዋታው እጅግ ባማረና በደመቀ ሁኔታ ለማካሄድ ዝግጅታችንን አጠናቀን ለመክፈቻው ደርሰናል። ይህም በስፖርት ቤተሰቡ እና በመላው ህብረተሰብ ተሳትፎ እውን ይሆናል ብዬ አስባለሁ።

መላው ኢትዮጵያ፡- የዘንድሮው ጨዋታ ከአለፉት ጨዋታዎች ለየት የሚያደርገው ነገር ይኖራል?አቶ አምበሳው እንየው፡- በትክክል! 3ኛው

መላ ኢትዮጵያ ጨዋታዎች ዝግጅት ከሌላ ጊዜ ልዩ የሚያደርገው አንደኛ መንግሥት ለስፖርቱ በሰጠው

ም/ል ኮሚሽነር ቅድመ ዝግጅቶችን ሲጎበኙ - አዳማ ፣ አሰላ

Page 16: ˆ - 3rd All Ethiopia  · PDF fileየጥንቱ የግሪክ ኦሊምፒክ መጫወቻ

16

ትኩረት የስፖርት ሴክተር በኮሚሽን ደረጃ እንዲደራጅ በአዋጅ ቁጥር 692/2003 የተደነገገበት ወቅት መሆኑ ልዩ ያደርገዋል።

በዚህ መሠረት ኮሚሽ ስፖርትን በማስፋፋት መላውን ህብረተሰብ ተሳታፊና ተጠቃሚ ለማድረግና የተጣለበትን ህጋዊ ኃላፊነት ለመወጣት በርካታ ሥራዎችን በማከናወን ላይ ይገኛል።

እንዲሁም ቀደም ሲል የተቀረፀውን የስፖርት ፖሊሲና ስትራቴጂ መሠረት በማድረግ ስፖርታዊ አደረጃጀቱና አመራሩ ህዝባዊ መሠረት እንዲኖረውና ሰፊ የተሳትፎ መድረክ እንዲፈጠር ለማድረግ የሚያስችል በሀገር አቀፍ ደረጃ ከተነደፈው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ የመነጨ የሴክተሩን የቀጣይ አምስት ዓመት የልማት ዕቅድ አዘጋጅቶ ለባለድርሻ አካላት አከፋፍሎ በመስጠት ተግባራዊ ለማድረግ ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ ባለበት ወቅት መሆኑና፤ የ3ኛው መላ ኢትዮጵያ ጨዋታዎች ዝግጅትም የዚሁ ዕቅድ አካል መሆኑ ነው። ሌላው ለሀገራችን የኢኮኖሚ ዕድገት ወሳኝ የሆነው የህዳሴው ግድብ ግንባታ የተጀመረበት ወቅት ላይ መሆኑ ልዩ ያደርገዋል።

በተጨማሪም ቀደም ብዬ እንደጠቀስኩት ያለፉት ሁለት የመላው ኢትዮጵያ ጨዋታዎች የተካሄዱት በአዲስ አበባ ከተማ ነበር፤ የ3ኛው መላ ኢትዮጵያ ጨዋታዎች ክልሎች በተለይ አስተናጋጁ ኦሮሚያ ክልል በውድድር ሥፍራዎች፤ በማደሪያና መመገቢያ ቦታዎች እንዲሁም በሌሎች ሎጅስቲክ ጉዳዮች ላይ አቅም ፈጥሮው ከሁሉም ክልሎች የሚመጡ ልዑካን ቡድኖችን በበቂ ሁኔታ ማስተናገዳቸው ከሌላው ጊዜ ልዩ ያደርገዋል።

መላ ኢትዮጵያ፡- ከ1ኛው እና 2ተኛው መላ ኢትዮጵያ ጨዋታዎች የተወሰዱ ጠንካራና ደካማ ጐኖች ካሉ?አቶ አምበሳው፡- ቀደም ሲል እንደገለፅኩት

የ3ኛው መላ ኢትዮጵያ ጨዋታዎች ዝግጅት መነሻችን የአንደኛው እና የሁለተኛው የመላ ኢትዮጵያ ጨዋታዎች አፈፃፀም በሚመለከት በተካሄደው ግምገማ እና በተገኘው ልምድና ተሞክሮ ውጤት መሠረት በማድረግ ነው።

በመሆኑም የነበሩንን አበረታች የሆኑ ጠንካራ አፈፃፀሞችን ይበልጥ በማጠናከር መሻሻል የሚገባቸውን ደግሞ ለማሻሻል ተሞክሯል።

ለምሳሌ፡- አጠቃላይ ጨዋታውን በተሳካ ሁኔታ ሊመራና ሊያስተባብር የሚችል አደረጃጀት ከመፍጠር ጀምሮ በሚፈለገው መጠን እና ዓይነት የመወዳደሪያ ሥፍራዎች መዘጋጀታቸው፣ የኦሊምፒክ ፍልስፍናን የተከተለ የውድድር ደንብ እና የሽልማት

ሥርዓት ተዘጋጅቶ ተግባራዊ መደረጉ በጥንካሬ ከተወሰዱት መካከል መጥቀስ ይቻላል።

በሌላ በኩል በተዘጋጀው የውድድር ደንብ ዙሪያ በሰፊው ግንዛቤ በማስጨበጥ ረገድ፣ በደንቡ መሠረት ውድድሩን በመምራት በተለይ ከተጨዋች ተገቢነት አኳያ ክፍተቶች እንደነበሩ ለማየት ተችሏል። በዘንድሮው ጨዋታ እነዚህ የታዩ ክፍተቶች እንዳይደገሙ የማድረግ ሰፊ ሥራ ተሠርቷል።

መላ ኢትዮጵያ፡- ይህ ጨዋታ በየጊዜው መካሄዱ ለስፖርቱ ዕድገት ምን ፋይዳዎች ይኖሩታል? አቶ አምበሳው፡- ጥሩ፤ የመላው ኢትዮጵያ

ጨዋታዎች በየጊዜው መካሄዱ ለሀገራችን የስፖርት ዕድገት በርካታ ፋይዳዎች አሉት። እነዚህን ፋይዳዎች በኢኮኖሚ፣በማህበራዊ፣ በፖለቲካ ብሎ ተንትኖ ማስቀመጥ ይቻላል። ነገር ግን ጠቅለል አድርገን ስናየው ይህ ውድድር ከቀበሌ ጀምሮ የሚካሄድና መላው ህብረተሰብ ተሳታፊና ተጠቃሚ የሚሆንበት በመሆኑ ለሀገሪቱ ስፖርት ዕድገትም ይሁን ለተጀመረው ልማታዊና ዲሞክራሲያዊ ጉዞ ስኬት ሚናው የጐላ ነው።

ለአብነት ብንወስድ በሀገራችን የሚገኙትን ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች በማቀራረብ የባህል እና የቋንቋ ትውውቅ፣ የልምድ ልውውጥ፣ አብሮ የመኖር፣ የአንድነትና የወዳጅነት ስሜት ለመፍጠር የመላው ኢትዮጵያ ጨዋታዎች ትልቅ መድረክና ድልድይ ሆኖ ያገለግላል።

የዘንድሮ መላ ኢትዮጵያ ጨዋታዎች የሚካሄደው “የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅዱን ተግባራዊ በማድረግ የህብረተሰቡን በስፖርት ተሳትፎና ተጠቃሚነት እናረጋግጣለን” በሚል መሪ ቃል ይካሄዳል።

Page 17: ˆ - 3rd All Ethiopia  · PDF fileየጥንቱ የግሪክ ኦሊምፒክ መጫወቻ

17

የአዳማ ስታዲየም ትሪቡን ግንባታ በከፊል

ከዚህ በፊት የሚዘወተሩ ስፖርቶችን የበለጠ በሀገሪቱ ለማስፋፋት፣ የማዘውተሪያ ሥፍሪዎች እንዲገነቡ ለምሳሌ አንድ የውድድር አስተናጋጅ ሀገር ወይም ከተማ ውድድሩን ለማስተናገድ በቂ የማወዳደሪያ ሥፍራ መገንባት ይጠበቅበታል። የኦሮሚያ ክልልም የ3ኛው መላ ኢትዮጵያን ለማስተናገድ በርካታ የስፖርት ማዘውተሪያ ሥፍሪዎች የግንባታ እና የጥገና ሥራ ሠርቷል። ስለዚህ ይህ ዝግጅት ለክልሉም ይሁን ለሀገሪቱ ስፖርት ዕድገት ትልቅ አቅም ነው።

በሌላ በኩል የመላ ኢትዮጵያ ጨዋታዎች የኦሊምፒክ መርህን መሠረት በማድረግ የሚዘጋጅ በመሆኑ አህጉራዊና አለም አቀፋዊ ውድድሮችን የማዘጋጀት እና የመምራት ልምድን ያዳብራል። የኦሊምፒዝምን አጠቃላይ ፍልስፍና በሀገራችን በስፋት ለማስረፅ ዝግጅቱ ጠቀሜታ ይኖረዋል። ከዚህ ባሻገር በኢትዮጵያ ብሔራዊ ስፖርት ፖሊሲ ላይ የተቀመጠውን ዓላማ ተግባራዊ ከማድረግ አኳያ በተለይ ከመላው የህብረተሰብ ተሳትፎ የሀገራችንን ስም እና ዝና በዓለም የስፖርት አደባባዮች የሚያስጠሩ ተተኪ ስፖርተኞችን የሚፈጠሩበት መድረክ በመሆኑ እንዲሁም የሴቶችና የአካል ጉዳተኞች ተሳትፎና ተጠቃሚነት የሚረጋገጥበት

በመሆኑ የመላው ኢትዮጵያ ጨዋታዎች ዝግጅት ፋይዳው ላቅ ያለ ነው።

መላ ኢትዮጵያ፡- ጨዋታውን አስመልክተው የሚያስተላልፉት መልዕክት ካለ?አቶ አምበሳው፡- በሀገር አቀፍ ደረጃ ለ3ኛ

ጊዜ የሚካሄደው የመላ ኢትዮጵያ ጨዋታዎች በተሳካ ሁኔታ እንዲካሄድና የታሰበለትን ግብ እንዲመታ እንደ ከዚህ ቀደሙ ሁሉ የስፖርት ቤተሰቡ እና የመላው ህብረተሰብ ተሳታፎና ድጋፍ ወሳኝ በመሆኑ ይህን ድጋፋቸውን አጠናከረው እንዲቀጥሉ አደራ እላለሁ። በመቀጠል የኦሮሚያ ክልል በተለይ የአዳማ፣ የአሰላና የቢሾፍቱ ከተማ ነዋሪ ሕዝብ የጨዋታው አስተናጋጅ እንደመሆናቸው መጠን ለተሳታፊ እንግዶች አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ በማድረግ የተለመደውን የእንግዳ ተቀባይነት ልምዳቸውን ለዚህም ዝግጅት እንደሚያጋሩ ዕምነቴ ከፍ ያለ ነው።

በመጨረሻም ለሁሉም የጨዋታው ተሳታፊ አካላት መልካም የጨዋታ እና የቆይታ ጊዜ እንዲሆንላቸው ልባዊ ምኞቴን እገልፃለሁ። አመሰግናለሁ!!

Page 18: ˆ - 3rd All Ethiopia  · PDF fileየጥንቱ የግሪክ ኦሊምፒክ መጫወቻ

18

ከ 0 ወደ 3በአስቻለው ሽፈራው

የሚሊኒየሙ ስጦታ 1999 ዓ.ም ኢትዮጵያውያን ሺዎች

ዓመታትን አጠናቀው ሌሎች ሺዎችን በተለየ አስተሳሰብና መንገድ ለመቀበል የተጠመዱበት ወቅት ነበር ። በቅርብም በሩቅም ያሉ ወገኖች ፣ አዲሱ ሚሊኒየም የሀገራቸውን ዕድገትና ለውጥ የሚያበስር ፣አንድነታቸውን ይበልጥ የሚያጠናክር ፣ የህዝባቸውን መጪ ዘመን የሚያሳምር እንዲሆን የመረጡና የቆረጡ መሆናቸውን በየፈርጁ የሚታየው አንቅስቃሴያቸው ሁሉ ያመለክት ነበር።

ህዳሴ ! ህዳሴ ! ህዳሴ ! የዓመቱ አጋማሽ በስፖርቱ መስክ አዲስ ነገር

የታየበትም ሆነ። በአለም አቀፍ የኦሊምፒክ መድረኮች በጀግኖች አትሌቶቿ ደማቅ ታሪክ የተጻፈላት ሀገር ህዝቦቿ መሠረታዊ ፍልስፍናና መርሁን ጠብቆ በተዘጋጀ ብሔራዊ የኦሊምፒክ ጨዋታ በጋራ የሚሳተፉበትን መደበኛ ፕሮግራም እውን አደረገች። በመሆኑም በየማዕዘኑ ያሉ ዜጎቿ በታሪካቸው ለመጀመሪያ ጊዜ በአንድ የኦሊምፒክ መድረክ ተገናኙ። ይህ “የመላው ኢትዮጵያ ጨዋታዎች” የሚል ስያሜ

ዐብይ ርዕስ

ይዞ የሀገሪቱን ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች በስፖርት ያሰባሰበና በወዳጅነት ስሜት ያቀራረበ መድረክ ይበልጥ እያደገም ሄደ።

በእርግጥ በሀገራችን ቀደም ባሉት ዓመታት በተለያዩ ጊዜያት በስፓርታኪያድ፣ በትምህርት ቤቶች፣ በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት፣ በመከላከያና በፖሊስ ሰራዊት ወዘተ ልዩ ልዩ የስፖርት ውድድሮችና ፌስቲቫሎች ይካሄዱ ነበር። ይሁንና እስከ 1999 ዓ.ም ድረስ የኦሊምፒክ መርህና ፍልስፍናን በተከተለ መልኩ በኦሊምፒክ ስፖርቶች የመላ ኢትዮጵያ ጨዋታዎች ፕሮግራም ጨርሶ ተካሂዶ አያውቅም። በመሆኑም ጨዋታው በሚሊኒየሙ መግቢያ ላይ ሲጀመር እንደ ዘመኑ አዲስና ለወቅቱ የተበረከተ ስጦታ ነበር ማለት ይቻላል።

የጨዋታው ምሰሶዎችየመላው ኢትዮጵያ ጨዋታዎች የኦሊምፒክ

ፍልስፍና እና መርህን መሠረት አድርጎ ሲዘጋጅ ማረፊያ የሆኑት ሁለት ምሰሶዎች አሉ። እነርሱም ህገ መንግስታችንና የሀገሪቱ የስፖርት ፖሊሲ ናቸው።

Page 19: ˆ - 3rd All Ethiopia  · PDF fileየጥንቱ የግሪክ ኦሊምፒክ መጫወቻ

19

የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ህገ መንግስት አንቀፅ 88 ንዑስ ቁጥር 2. መንግስት የብሔር፣ ብሔረሰቦችንና ህዝቦችን ማንነት የማክበርና በዚሁ ላይ በመመርኮዝ በመካከላቸው እኩልነት፣ አንድነትና ወንድማማችነት የማጠናከር ግዴታ አለበት ሲል ደንግጓል። በተያያዘም የኢፌዲሪ የስፖርት ፖሊሲ ዓላማው የህብረተሰቡን የስፖርት ተሳትፎ በማጎልበትና ምርጥ ስፖርተኞችን በማፍራት በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ውጤት ማስመዘገብ እንደሆነ በግልጽ አስቀምጧል።

እነዚህ ዐብይ መነሻዎች ከኦሊምፒዝም ፍልስፍናና መርህ ጋር የተጣጣሙ ሲሆኑ የመላው ኢትዮጵያ ጨዋታም ይህን መሰረት አድርጎ ሰፊ ዓላማዎችን ያሳካል። ፕሮግራሙ በየ 2 ዓመቱ 9 ብሔራዊ ክልሎችና 2 ከተማ አስተዳደሮቸ ወኪሎቻቸውን እየላኩ በተመረጡ ከተሞች አስተናጋጅነት ይከናወናል። በጨዋታው ከሁሉም የሀገሪቱ አቅጣጫ የሚሰባሰቡ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች የሚካፈሉ እንደመሆኑ ከስፖርታዊ ክንውንነቱ ባሻገር ለኢትዮጵያውያን የጋራ ግንኙነትና መቀራረብ ፋይዳው ትልቅ ነው። እነዚህ የብዙ ባህልና ዕሴቶች ባለቤት የሆኑ ህዝቦች በአንድ መድረክ ሲገናኙ ይበልጥ እንዲተዋወቁ ብሎም ልምዶቻቸውንና ችሎታቸውን ለሌሎች እንዲያሳዩ ያስችላቸዋል። በተጨማሪም ለወጣት አትሌቶች፣ ለስፖርት አመራሮችና ባለሙያዎችም ለዓለም አቀፍ መድረኮች ራሳቸውን ማዘጋጃና እርስ በርስ የመወዳደሪያ አጋጣሚ ይፈጥርላቸዋል።

የከፍታ ጉዞ …. የመጀመሪያው የመላው ኢትዮጵያ

ጨዋታዎች መካሄድ ከጀመረበት ከ1999 ዓ.ም ጀምሮ ፕሮግራሙ ዓላማውን እንዲያሳካ የፌደራል ስፖርት ኮሚሽንና የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ከሌሎች መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ጋር በመሆን ትልቅ ጥረት አድርገዋል። በጨዋታዎቹ ከታች ከቀበሌ ጀምሮ ያሉ ስፖርተኞች እንዲሳተፉ በማድረግ ከሌሎች ስፖርተኞች የሚገናኙበትንና ልምድ የሚለዋወጡበትን መድረክ መፍጠር ብቻ ሳይሆን ለከፍተኛ ውድድሮችም መንገዱ እንዲመቻችላቸው ተሰርቷል። አንጻር በአንጻር ደካማና ጠንካራ ጎኖች በሂደት እየታዩና እየታረሙ፣ አዲስ የጨዋታ ዓመት ሲመጣም ተጫማሪ ለውጦች እየተመዘገቡ ዘንድሮ

ለ3ኛው የመላው ኢትዮጵያ ጨዋታ ደርሰናል።ወደ ኋላ መለስ ብለንም የተከናወኑ ተግባራትና

የነበሩ እውነታዎችን ስንፈትሽ ጨዋታው ዓላማውን ጠብቆ ይበልጥ እየተጠናከረ እንዲሄድ ከፍተኛ ትኩረት እንደተሰጠው ያረጋግጥልናል። በመጋቢት 2002 ዓ.ም 2ኛው የመላው ኢትዮጵያ ጨዋታዎች ሊካሄድ ዝግጅት በቀጠለበት ወቅት ክቡር የኢፌዲሪ ስፖርት ኮሚሽን

Page 20: ˆ - 3rd All Ethiopia  · PDF fileየጥንቱ የግሪክ ኦሊምፒክ መጫወቻ

20

ኮሚሽነር አቶ አብዲሳ ያደታ የመጀመሪያው የመላው ኢትዮጵያ ጨዋታዎችን አስመልክቶ የገለጹት ለዚህ አንዱ ማሳያ ነው።

“በአንደኛው የመላ ኢትዮጵያ ጨዋታዎች ሁሉም የክልልና የከተማ አስተዳደሮች ለመወዳደር በመረጡት ስፖርታዊ ውድድርና ጨዋታዎች ተሳትፈዋል። በመሆኑም በስፖርተኞች፣ በተመልካቾችና በተሳታፊዎች መካከል የተወዳዳሪነትና የማሸነፍ ስሜት እንዲጨምር በማድረግ ተተኪ ስፖርተኞች ወደ ስፖርት መድረክ እንዲቀላቀሉ አነሳስቷል። ጨዋታው የሀገራችን ስፖርት ያለበትን

ተካፋዮች የሜዳሊያዎች ድምር

አ.አ 142ኦሮሚያ 115አማራ 55ደቡብ 29ትግራይ 15ድሬዳዋ 36ሐረሪ 15ቤንሻንጉል 8ጋምቤላ 13ሶማሌ 5አፋር -

የ1ኛው የመላው ኢትዮጵያ ጨዋታዎች ተካፋዮች ያገኙት የሜዳሊያዎች ድምር ውጤት

የመላው ኢትዮጵያ ጨዋታየስፖርት ዓይነቶች

- አትሌቲክስ፣ እግር ኳስ፣ ቮሊቦል፣ቅርጫት ኳስ፣ ጠረጴዛ ቴኒስ፣ ባድሜንተን፣ ብስክሌት፣ ቦክስ፣ ቼስ፣ ክብደት ማንሳት፣ ጅምናስቲክ፣ ቴኒስ፣ ቴኳንዶ፣ ካራቴ፣ እጅ ኳስ እና ውሀ ዋና ናቸው።

ሁኔታ እንዲታይ በማድረግ ጠንካራና ደካማ ጎኖቻችንን በመገምገም ውስንነታችንን በመሙላት በየደረጃው ተተኪ ስፖርተኞችን በማፍራት ረገድ፣ የአሰልጣኞችና የዳኞች አቅምን በመገንባት የስፖርት አደረጃጀቶችን በማጠናከር ህዝባዊ መሠረት እንዲኖረው ለማድረግ ለቀጣይ ስራዎች ግብዓት አድርገን ለመተግበር እንድንችል መልካም አጋጣሚ ፈጥሯል” ሲሉ ነበር የገለፁት።

በዚህ መልኩ የተጀመረው የመላ ኢትዮጵያ ጨዋታዎች ከመነሻውም የሀገራችን ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦችን በአንድ መድረክ አገናኝቶ በስፖርት እንደችሎታቸውና ፍላጎታቸው እንዲወዳደሩና እንዲጫወቱ በማድረግ የተቀመጡለትን ዓላማዎች በአብዛኛው ማሳካት የቻለ ነበር። በመዲናችን አስተናጋጅነት በ17 የስፖርት ዓይነቶች የተከናወነው ተሳትፎ ሲጠናቀቅ አዲስ አበባ 142 ሜዳሊያ፣ ኦሮሚያ 115 ሜዳሊያ እንዲሁም የአማራ ክልል 55 ሜዳሊያዎችን በማግኘት ከ1 እስከ 3 ያለውን ደረጃ አስመዝግበዋል።

ሁለተኛው የመላ ኢትዮጵያ ጨዋታዎች በ2002 ዓ.ም ዳግም በአዲስ አበባ ከተማ አስተናጋጅነት ሲካሄድ አንደኛውን የመላ ኢትዮጵያ ጨዋታዎች መነሻ በማድረግ የነበሩ ጠንካራና ሊታረሙ የሚገቡ ችግሮችን በጥልቀት ተመልክቷል። “ህዝባዊ መሠረት ያለው የስፖርት እንቅስቃሴ የተተኪ ስፖርተኞች ምንጭ ነው” በሚል መሪ ቃል የተከናወነው ይኸው ፕሮግራም የኦሊምፒክን መርህ ጠብቆ በመካሄዱ ዓላማዎችን ቢያሳካም ፍፁማዊ ግን አልነበረም። ፕሮግራሙ ዓመት ቆጥሮ ዘንድሮ ለሦስተኛ ጊዜ ሊካሄድ ዝግጅቱ ሲጀመር ደግሞ የጨዋታው መሪ አካላት በወቅቱ የታዩትን መልካምና ሊሻሻሉ የሚገባቸውን ጉዳዮች መለስ ብለው ፈትሸዋል።

ለዘንድሮው ጨዋታ የተዘጋጀው ሰነድ ከሁለት ዓመት በፊት የተከናወነውን የመላው ኢትዮጵያ ጨዋታዎች አስመልክቶ በሁለት መልክ የታዩ ጉዳዮችን ዘርዝሯል። ሰነዱ በወቅቱ ከመላው የሀገሪቱ ክፍሎች ወደ ወደ ጨዋታው አስተናጋጅ መዲናችን የመጡ የልዑካን ቡድን አባላት በፕሮግራሙ ከመካፈል ባሻገር በከተማዋ ውስጥ ያሉ የመሰረተ ልማት ተቋማትን፣ የስፖርት አካዳሚዎችን፣ ታሪካዊ ቦታዎችንና ሌሎችንም ስፍራዎች እንዲጎበኙ ፕሮግራም መመቻቸቱን በመልካምነቱ ይጠቀሳል። በቁጥር ከ350 በላይ የሚሆኑ በጎ ፍቃደኞች ጊዜያቸውንና ዕውቀታቸውን ከመስጠታቸው በተጨማሪ የሽልማት ስርዓቱ ኦሊምፒካዊ ደንብ እንዲጠብቅ መደረጉ በወቅቱ የታየ ሌሎች ጠንካራ ጎኖች ነበሩ ይላል።

Page 21: ˆ - 3rd All Ethiopia  · PDF fileየጥንቱ የግሪክ ኦሊምፒክ መጫወቻ

21

ሰነዱ በሌላ በኩል የስፖርታዊ ጨዋነት ችግርና የውድድር ሥነ ስርዓትን በተመለከተ አፋጣኝ ውሳኔ አለመስጠት ዘንድሮ መደገም የሌለባቸው እንደሆኑም አስቀምጧል።

ኦሮሚያ - ቀዳሚዋ የመላ ኢትዮጵያ ጨዋታዎች አስተናጋጅ ክልል

የቀደሙትን ሁለት ጨዋታዎች መዲናችን አስተናግዳ እነሆ ዘንድሮ ከአዲስ አበባ ወጥቷል። በክልል ደረጃ የማስተናገዱን ሀላፊነትም የኦሮሚያ ክልል ወስዷል። ጨዋታው የሚካሄድባቸው የአዳማ፣ ቢሾፍቱና አሰላ ከተሞች አስተዳደር እንዲሁም የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት አስፈላጊ ቅደመ ስራዎችን አጠናቀዋል። የየከተሞቹ ነዋሪዎች እንግዶችን

ተወዳዳሪ አትሌቶች 3084

አሰልጣኞች 277

አካል ጉዳተኞች 250

ዳኞች 353

የማዘወተሪያ 30

ተመልካች 40000

በጎ ፍቃደኞች 354

በ2ኛው የመላው ኢትዮጵያ ጨዋታዎች የተመዘገቡ የተሳታፊ ቁጥሮች

Page 22: ˆ - 3rd All Ethiopia  · PDF fileየጥንቱ የግሪክ ኦሊምፒክ መጫወቻ

22

ክልል/የከተማ አስተዳደር

የተሳታፊዎች ድምር

ትግራይ 392ሐረሪ 310ቤንሻንጉል 209አማራ 453ደቡብ 455ሶማሌ 205ኦሮሚያ 693ጋምቤላ 208አፋር 89ድሬደዋ 353አ.አ 557

ኦሮሚያ ላይ በ3ኛው የመላው ኢትዮጵያ ጨዋታዎች የሚሳተፉ ስፖርተኞች፣ አሰልጣኞችና

የቡድን መሪዎች ቁጥር ድምር

ለመቀበል፣ በጨዋታው ለመታደምና በክልሉ ያሉትን መልካም ዕሴቶች ለዕንግዶች ለማሳየት ተዘጋጅዋል።

ዘንድሮ 3ኛው የመላው ኢትዮጵያ ጨዋታዎች ሲካሄድ በስፖርቱ ሴክተር የተያዘውን የዓመቱን መሪ ቃል መሠረት አድርጎ ነው።

መሪ ቃሉ - “የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅዱን ተግባራዊ በማድረግ የህብረተሰቡን በስፖርት ተሳትፎና ተጠቃሚነት እናረጋግጣለን” - የሚል ነው።

ውድድሩ ከሁለተኛው የመላው ኢትዮጵያ ጨዋታዎች አንጻር ሲመዘን የተሻለ እንቅስቃሴ እንዲካሄድበት የታቀደ ሲሆን ይህንንም ለማየት በዝግጅት ሰነዱ ላይ በስፋት ከተቀመጠው በጥቂቱ ወስደን እንመልከት። ሰነዱ በዚህ ዓመት የተወዳዳሪ አትሌቶች ተሳትፎ በ15%፣ የሴቶች ተሳትፎ በ13.5%፣ የተመልካቾች ቁጥር በ100%፣ የአካል ጉዳተኞች ተሳትፎ በ60% እንደሚያድግ ይጠበቃል ሲል ይዘረዝራል። ታዲያ ለዚህ ሰፊ ዕድገት መመዝገብ አጋዥ የሆኑ ውስጣዊና ውጫዊ ምክንያቶችንም ተንትኗል።

የስፖርት ፖሊሲው መኖር፣ በጨዋታው የሚካፈሉ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስታት ያሳዩት ቁርጠኛ ወሳኔ፣ በሀገሪቱ በሚገኙ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች መካከል ጤናማ ግንኙነት መኖሩ፣ እንዲሁም ኢትዮጵያ ለተከታታይ የኢኮኖሚ ዕድገት ማስመዝገቧ ለዕድገቱ ጠቃሚ ፖለቲካዊ፣ ኦኮኖሚያዊና ማህበራዊ ምክንያቶች ከሚባሉት ጥቂቶቹ ናቸው።

በቁጥር ምንም ወይም የለም በሚባል ሁኔታ የነበረው ብሔራዊ የኦሊምፒክ መድረክ አሁን ለ3ኛው ዘመን በቅቷል። ብዙ የጨዋታ መድረኮች፣ አያሌ የመሰባሰቢ አውዶች ደግሞ ገና ከፊታችን አሉ።

በ3ኛው የመላው ኢትዮጵያ ጨዋታዎች የሚጠበቁ መሰረታዊ ቁጥሮች

• ተወዳዳሪ አትሌቶች - 4,000• የማስ ስፖርተኞች - 1,776• የሚጠበቁ የቀጥታ ተመላካቾች - 100,000• በጎ ፍቃደኞች - 500• የመወዳደሪያ ስፖርት ዓይነቶች - 17

Page 23: ˆ - 3rd All Ethiopia  · PDF fileየጥንቱ የግሪክ ኦሊምፒክ መጫወቻ

23

ወደ ኦሮሚያ እንኳን ደህና መጣችሁ

ከኦሮሚያ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ

ኦሮሚያ

በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት አስተናጋጅነት የሚካሔደዉን የ3ኛው መላ ኢትዮጵያ ጨዋታዎች በስኬት ለማጠናቀቅ የክልሉ መንግሰት አስፈላጊዉን ዝግጅት በማድረግ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ ሲሰራ ቆይቷል። በዚህም

መሰረት በክልሉ በየደረጃዉ የተለያዩ ኮሚቴዎች ተዋቅረው የመስተንግዶ፣ የመወዳደሪያ ቦታ ዝግጅትና ሎሎች ስራዎችን አከናውነዋል።

ክልሉ ውድድሩ በሚካሄድባቸዉ ከተሞች የማዘውተሪያ ስፍራዎች እድሳትን ጨምሮ ልዩ ልዩ ግንባታዎችን አካሂዷል። ለአብነትም 2000 መቀመጫዎችን የሚይዘው የአዳማ ስታዲዮም ትሪቡንና የቤት ውስጥ ጨዋታዎች ማካሄድ የሚያስችል የጅምናዚየም ግንባታ ተከናውኗል።

በተጨማሪም የአሰላ አረንጓዴ ስታዲየም ደረጃውን የጠበቀ ትራክ (Truck) እንዲኖረው ለማስቻል በውጭ ባለሙያዎች ግንባታ ተካሂዷል። በአጠቃላይ በዙሪያው ለሚያስፈልጉ ስራዎች ጨምሮ የ27 ሚሊዮን ብር ወጪ ተደርጓል። ትራኩ በቀጣይ ለአትሌቲክስ ውድድርና ለፓራሎምፒክ ውድድሮች ጭምር የሚያገለግል ይሆናል።

በሌላ በኩል በቢሾፍቱ ከተማ የሚደረጉት

የውሃ ስፖርትና እና የሜዳ ቴኒስ ውድድሮች ስኬታማ እንዲሆኑ አስፈላጊውን ሁሉ ያከናወነ ሲሆን በአጠቃላይ ለ3ኛው የመላው ኢትዮጵያ ጨዋታዎች ዝግጅት የኦሮሚያ ክልል 47 ሚሊዮን ብር ወጪ አድርጓል።

የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የመላዉ ኢትዮጵያ ጫወታዎች በማስተናገድ የመጀመሪያዉ ክልላዊ መንግስት ነዉ። ክልሉ ይህንን ታላቅ ዝግጅት በማስተናገዱ ዘርፈ-ብዙ ጠቀሜታዎችን እንደሚያገኝ ያምናል።• ወደ ክልሉ የሚመጡ እንግዶች በቆይታቸዉ

ወቅት ዉድድሩ በሚካሄድባቸዉ ከተሞች ተጠቃሚ ሲሆኑ የየከተሞቹ የንግዱ ማህበረሰብ ተጠቃሚ ናቸዉ።

• የስፖርት ስፍራዎች እንዲስፋፉ ሰፊ ዕድሎችን ፈጥሯል፤

• አጠቃላይ ለስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ዕድገትና መስፋፋት የበኩሉን ድርሻ ያበረክታል።

• የሁሉም ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች የተወከሉ ልዑካን በዉድድሩ ላይ ስለሚሳተፉ ዝግጅቱ ከስፖርታዊ ዉድድሩ ባለፈም የባህል፣ ወግና ልምድ ልዉዉጥ መድረክ ሆኖ ያገለግላል፤ ክልሉ ከሌሎች ክልሎች ጋር ያለዉን ማህበራዊ

Page 24: ˆ - 3rd All Ethiopia  · PDF fileየጥንቱ የግሪክ ኦሊምፒክ መጫወቻ

24

መሰረትያጠናክራል።• ጠንካራና ተተኪ ስፖርተኞችን ለማፍራት

ጉልህ ስፍራ አለዉ፣• የሀገራችን የስፖርት ዕድገት ከአምስት አመቱ

የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ለስፖርቱ

የቢሾፍቱ ዉሃ ስፖርቶች መወዳደሪያ

በአሰላ ስታዲየም በመሰራት ላይ ያለው ዲዛይን

ጉልህ ስፈራ የሰጠ መሆኑ ያሳያልበመሆኑም የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልል

የመጀመሪያዉ የመላ አትዮጵያ ጨዋታዎች አስተናጋጅ እንደመሆኑ አስተዳደሩ ከሁሉም የስፖርት ቤተሰቦች ጋር በመሆን ዝግጅቱን አጠናቋል።

Page 25: ˆ - 3rd All Ethiopia  · PDF fileየጥንቱ የግሪክ ኦሊምፒክ መጫወቻ

25

የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ሉዓላዊነትና የራስን ዕድል በራስ የመወሰን መብት የተረጋገጠበት፣ ለግለሰብና ለቡድን መብቶች እንዲሁም ለሃይማኖቶችና ለፆታ እኩልነት ወዘተ ልዩ ትኩረት

የተሰጠበት የሀገራችን ህገ መንግሥት ከፀደቀ እነሆ 17 ዓመታት ተቆጥረዋል። በህገ መንግሥቱ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ዲሞክራሲያዊና ሰብዓዊ መብቶቻቸውን ተጎናፅፈዋል። በዲሞክራሲያዊ አንድነት ላይ ለተመሠረተችው ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ ግንባታም መሠረት ተጥሏል።

የሀገራችን ህዝቦች ለብዙ ዓመታት ሲታገሉለት የቆዩትን መብቶች በትክክል ያጎናፀፈውና ህዳር 29/1987 ዓ. ም በፀደቀው ህገ-መንግሰት መሰረት በኢትዮጵያ ውስጥ ከተመሰረቱ ዘጠኝ ክልሎች መካከል የኦሮሚያ ክልል አንዱ ነው። ይህም በአዋጅ ቁጥር 7/1992 በ1985 ዓ.ም የተመሠረተ ሲሆን ይህም ከደርግ ውድቀት በኋላ አዲሱ ህገ መንግሥት ያስገኘው ውጤት ነው።

ክልሉ የራሱ የህግ አውጪ፣ ህግ አስፈፃሚና ህግ ተርጓሚ አካላት አሉት። ህግ አውጪው አካል “ጨፌ” ተብሎ ይጠራል። የጨፌ ኦሮሚያ 537 መቀመጫ ያሉት ሲሆን ክልሉን በበላይነት የሚመራ ፓርቲ የኦሮሞ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ድርጅት/ኦ.ህ.ዴ.ድ/ ነዉ። የክልሉ አስፈፃሚ አካላት በአራት ደረጃዎች የተዋቀሩ ናቸው። እነዚህም የክልሉ መንግሥትና የመስተዳደሩ ምክር ቤት፣ 18 የዞን መስተዳድሮች፣ 304 የወረዳና የከተማ መስተዳድሮችና

የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልል አጠቃላይ ገፅታ

ም/ቤቶች እንደዚሁም 6343 የቀበሌ መስተዳድሮችና ምክር ቤቶች 423 ከተሞች ናቸው።

የህግ ተርጓሚው አካልም በተመሳሳይ መልኩ አራት የአወቃቀር ደረጃዎች አሉት። እነሱም የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት፣ የዞን ከፍተኛ ፍ/ቤቶች፣ የወረዳ ፍ/ቤቶችና የቀበሌ ማህበራዊ ፍርድ ቤቶች ናቸው።

የክልሉ መልክአ ምድራዊ ገፅታታላቁ የምሥራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ

የኦሮሚያን ክልል ለሁለት ከፍሎ ያልፋል። በመሆኑም ክልሉ የተለያዩ መልክዓ ምድራዊ ገፅታዎች እንዲኖሩት አድርጓል። ሰማንያ ስምንት በመቶ የሚሆነው የክልሉ የቆዳ ስፋት ከባህር ወለል በላይ ከ500-4377 ሜትር ማዕከላዊ ከፍታ ውስጥ ይጠቃለላል። ካለው አጠቃላይ የቆዳ ስፋት ውስጥም 26.98% ለግብርና ልማት የዋለ ሲሆን 7% በደን የተሸፈነ፣ 12% ለግጦሽ የዋለ፣ 50% ደግሞ በዛፍና በቁጥቋጦ የተሸፈነ መሬት ነው። በከተማ ልማት የተያዘ 0.02% ሲሆን 4%ቱ ደግሞ ድንጋያማና ለግብርና የማይውል መሬት ነው። የኦሮሚያ የመሬት አቀማመጥ ከቦታ ቦታ የተለያየ ሆኖ ሰሜኑና ማዕከላዊ ክፍሉ ተራራማ ሲሆን ምዕራብ፤ ምሥራቁና ደቡቡ ክፍል ደግሞ ሜዳማ ነው። በአጠቃላይም ኦሮሚያ በተፈጥሮ ሀብት የበለፀገች በታላላቅ ተራራዎችና ኮረብታዎች የተዋበች፣ በሸለቆዎች የተከፋፈለች በሐይቆችና ወንዞች እንዲሁም በተፈጥሮ ፍል ውሃዎች የታደለች ክልል ነች።

በኦሮሚያ ክልል 423 ከተሞች የከተማነት ህጋዊ ዕዉቅና አግኝተዋል። ከነዚህ መካከል ስድስት/6/ ከተሞች ቡራዩ፣ ቢሾፍቱ፣ ጅማ፣ ሻሻመኔ፣አዳማና

Page 26: ˆ - 3rd All Ethiopia  · PDF fileየጥንቱ የግሪክ ኦሊምፒክ መጫወቻ

26

ሰበታ የአንደኛ ደረጃ ከተሞች ናቸው።ክልሉ በሁለት ዋና ዋና የዝናብ ወቅቶች

ይታወቃል። እነዚህም አንደኛው የበልግ ዝናብ ወቅት

ሲሆን ከመጋቢት እስከ ሚያዝያ ወር መጨረሻ እና ሁለተኛው የመኸር የዝናብ ወቅት፣ ከሰኔ እስከ ሐምሌ ወር መጨረሻ ድረስ የሚዘልቀው ነው። ክልሉ አዝናብ የሚያገኘው በዚህ ወቅት ነው። በሚኖረው የአየር ፀባይ ላይ በመመሥረት ማዕከላዊ የዝናብ መጠን ከምዕራብ ወደ ምሥራቅ የክልሉ ክፍል እየቀነሰ ይሄዳል። ምዕራባዊው ክፍል በዓመት እስከ 2600 ሚ.ሜ ዝናብ የሚያገኝ ሲሆን ምሥራቃዊው ክፍል ግን በአማካይ 500 ሚ.ሜ ያገኛል።

ኦሮሚያ የተለያዩ የአየር ንብረቶች ያላት ሲሆን ከክልሉ የቆዳ ስፋት 43% ቆላማ፣ 42.3% ወይና ደጋ፣ 14.5% ደጋማና 0.2% ደግሞ ውርጫማ ነው።

የቦታ አቀማመጥ ከፍታን ተከትሎ በክልሉ የሙቀት መጠን ሥርጭት በከፍተኛ ቦታዎች ከ140C-200C, ሲሆን በረባዳማ ቦታዎች ደግሞ በአማካይ ከ200c-250c, የሙቀት መጠን አላቸው።

ሀይማኖትኦሮሚያ የተለያዩ ሃይማኖት ተከታዮች

አብረው ተስማምተው የሚኖሩባት ክልል ነው። የተለያዩ የክርስትና ዘርፎች (ኦርቶዶክስ፣ ፕሮቴስታንት፣ ካቶሊክ) እስላም እና እንደ ዋቄፈና ያሉ ባህላዊ እምነቶች ይዘወተራሉ። የክርስትናና የእስልምና ሃይማኖቶች ከመምጣታቸው በፊት ዋና የኦሮሞ ህዝብ ሃይማኖት ዋቄፈና ነበር። ዋቄፈና ሁሉን በፈጠረ አንድ “ዋቃ” ወይም አምላክ ማመን ነው። ዋቃ የሚለው ቃል በእንግሊዝኛ “GOD” የሚለውን ይተካል።

ቋንቋ የኦሮምኛ ቋንቋ ከምሥራቃዊ የኩሽ ቋንቋ

ቤተሰብ ይመደባል። ከሰሜን ኢትዮጵያ በስተቀር በሌሎች የአገሪቱ ክፍሎችም ይነገራል። ባለው የተናጋሪ ብዛትና በሚሸፍነው መልክዓ ምድራዊ ስፋት አፋን ኦሮሞ በአፍሪካ ውስጥ ከሱዋህሊ፣ አውሳ፣ዓረብኛና ዩርባ ቋንቋዎች ቀጥሎ በሰፊው የሚነገር ቋንቋ እንደሆነም ጥናቶች ያመለክታሉ።

በአሁኑ ወቅት አፋን ኦሮሞ የክልሉ የሥራ ቋንቋ ነው፡ አማርኛ እንግሊዝኛና አረብኛም ይነገራሉ። የላቲን ፊደላት የተወሰኑ ማሻሻያዎች ተደርገውላቸው አፋን ኦሮሞን ለመፃፍ አገልግሎት ላይ ውለው ይገኛሉ።

አፋን ኦሮሞ ከደርግ መወገድ በኋላ በክልሉ ባሉ የተለያዩ የትምህርት ተቋማት የማስተማሪያ ቋንቋ ሆኖ እያገለገለ ይገኛል። በከፍተኛ የትምህርት ተቋማትም በዲፕሎማ፣ በመጀመሪያ ድግሪና በማስተርስ ድግሪ ደረጃ በመሰጠት ላይ ይገኛል። ለተለያዩ የሥነ ፅሁፍ ዘርፎች፣ በሚዲያዎችም በሰፊው አገልግሎት እየዋለ ይገኛል።

ኢኮኖሚ ግብርና

ግብርናው የአገሪቱ የኢኮኖሚ የጀርባ አጥንት እንደሆነ ሁሉ ለክልሉም ዋናው የኢኮኖሚ ዘርፍ

ነው። በዚህም መሠረት የክልሉ አጠቃላይ የገቢ ምርት (GDP) 65% ይሸፍናል። ሰማኒያ አምስት ከመቶ የሚሆነው የክልሉ ነዋሪ ህዝብ ኑሮው የተመሠረተው በግብርና ላይ ነው፡ ፡ ከክልሉ የቆዳ ስፋት 50 ከመቶው ለግብርና ተስማሚ እንደሆነም ይገለፃል። ለተለያዩ የግብርና ዘርፎችም ተስማሚ በመሆኑ የተለያዩ የእህል ዓይነቶች ማለትም እንደ

Page 27: ˆ - 3rd All Ethiopia  · PDF fileየጥንቱ የግሪክ ኦሊምፒክ መጫወቻ

27

ጥራጥሬ፣ የአገዳ እህሎች፣ አትክልትና ፍራፍሬዎች፣ የቅባት እህሎች ወዘተ ያሉት በስፋት ይመረታሉ።

ቡና፣ አበባ፣ ጫት፣ ቆዳና የቆዳ ውጤቶች፣ የቁም እንስሳት፣ የቅባት እህሎች ለሃገሪቱ የውጭ ምንዛሪ የሚያስገኙ ዋና ዋና የግብርና ምርቶች ናቸው።

የእንስሳት ሀብት የእንስሳት ሀብት ልማት በክልሉ ከሚካሄዱ

የግብርና ዘርፎች አንዱ ነው። በደጋማው ክፍልና በአርብቶ አደርና ከፊል አርብቶ አደር በሆኑ አካባቢዎችም ትልቅ የኢኮኖሚ ዘርፍ ነው። ሀገሪቷ ካላት የእንስሳት ሀብት 44.9% የላም፣ 43.3% የጋማ ከብቶች፣ 36.6% የበግና ፍየል፣ 35.81% የዶሮ፣ 53.2% የግመል ሀብት በዚህ ክልል ይገኛሉ።

የውሃ ሀብት በክልሉ ከዓመት እስከ ዓመት ሳያቋርጡ

የሚፈሱ በርዝመታቸውና በጠመዝማዛ ጉዞአቸው የሚደነቁ የአዋሽ፣ የጊቤ፣ የገናሌ፣ የዲዴሳ እና ሌሎችም ወንዞች ይገኛሉ።ኦሮሚያ የብዙ ሐይቆች ባለቤትም ነች።ላንጋኖ፣ አብጃታና ሻላ፣ ደምበል፣ አርሰዲ፣ ባቦጋያ እና ሌሎችም በኦሮሚያ ክልል ይገኛሉ፡ እንደ ሶር፣ በሬዳ፣ አዋሽ እና የመሳሰሉት ፏፏቴዎችም ታይተው የማይጠገቡ ፀጋዎች ናቸው።

ክልሉ ለሀይል ማመንጫና ለመስኖ ልማት ሊውል የሚችል ሰፊ የውሃ ሀብት አለው፡ በክልሉ የሚገኘው የገፀ ምድርና ከርሰ ምድር ውሃም ሰፊ የልማት ዕድል ይከፍታል።

በአጠቃላይ የውሃ ሀብትን በተመለከተ በኦሮሚያ ክልል 8 ተፋሰሶች ይገኛሉ። 68 ትላልቅ ወንዞችና 688 ገባሮቻቸው ሳያቋርጡ ይፈሳሉ። በነዚህ ወንዞች በዓመት 58 ቢሊየን ክዩቢክ ሜትር ውሃ ይፈሳል። በክልሉ 3135 km2 ቦታ የሚሸፍኑ 12 ትላልቅ ሐይቆችም ይገኛሉ።

ዋና ዋና የቱሪስት መስህቦች ከላይ እንደተጠቀሰው ኦሮሚያ የተለያየ

መልክዓምድራዊ አቀማመጥና የአየር ንብረት ያላት

መሆኗ ሰፊ የብዝሃ ህይወት ሀብት እንዲኖራት አድርጓል። ብዙ የዱር እንስሳትና የዕፅዋት ዝሪያዎች በክልሉ ይገኛሉ። በኢትዮጵያ ከ 861 በላይ የአዕዋፍና 277 የትላልቅ አጥቢ እንስሳት ዝሪያዎች ይገኛሉ። ከ861 የአእዋፍ ዝሪያዎች 281ዱ፣ ከ277ቱ ትላልቅ አጥቢ እንስሳት ደግሞ ሠላሣ አንዱ በኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ እንደሚገኙ አጥኚዎች ይገልጻሉ። ከነዚህ ውብ የተፈጥሮ ፀጋዎች ፍላሚነጎና ፐሊካኖችን ጨምሮ ሃያ ስምንቱም የአዕዋፍ ዝሪያዎች እንደዚሁም ከአጥቢዎቹ ደግሞ ሀያዎቹ የሚገኙት በኦሮሚያ ውስጥ ብቻ ነው። በክልሉ ውስጥ የሚገኙ እንደ ደምበል አብጃታ፣ ሻላ፣ ላንጋኖ ያሉ የስምጥ ሸለቆ ሐይቆች በኢትዮጵያ ውስጥ ለሚገኙ ለአብዛኞቹ የአዕዋፍ ዝርያች መኖሪያ ናቸው።

ኦሮሚያን ለመጀመሪያ ጊዜ የሚጎበኝ ሰው ባላት ተፈጥሮአዊ ውበትና ፀጋ በእጅጉ ሳይደነቅ አይቀርም፡ በኦሮሚያ ውስጥ ከሚገኙ ውብ የተፈጥሮ መስህቦች አንዱ የባሌ ተራራዎች ብሔራዊ ፓርክ ሲሆን 23 ሺህ Km2 ስፋት አለው። ከባህር ወለል በላይ ከ 1500ሜ - 4377ሜ ከፍታ ላይ ይገኛል።

በአፍሪካ ውስጥ ከታላላቆቹ የአፍሮ አልፓይን ተራራዎች አንዱ የሆነው የባሌ ተራራዎች ብሔራዊ ፓርክ ለ46 ዓይነት አጥቢ እንስሳትና ከ200 በላይ ለሚሆኑ የአዕዋፍ ዝሪያዎች መኖሪያ ነው። በፓርኩ ውስጥ ከሚገኙ ብርቅዬ እንስሳት መካከል የኢትዮጵያ ብቸኛ ሀብት የሆኑ ማለትም ቀይ ቀበሮ፣ የምንሊክ ድኩላ እና የደጋ አጋዘን (ኒያላ) በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታወቁና ለአብነት የሚጠቀሱ ናቸው። የብርቅዬ ዕፅዋት መብቀያ ሥፍራም ነው። አብዛኞቹ የኢትዮጵያ ብቸኛ ዕፅዋትም በዚህ ብሔራዊ ፓርክ ውስጥ እንደሚገኙ ጥናቶች ያመለክታሉ።

የአዋሽ ፏፏቴ ደንጓጅ ፏፏቴየሶር ፏፏቴ

Page 28: ˆ - 3rd All Ethiopia  · PDF fileየጥንቱ የግሪክ ኦሊምፒክ መጫወቻ

28

በደቡብ ምሥራቅ አቅጣጫ ከፊንፊኔ 225 ኪ. ሜትር ርቆ ሐረር መንገድ ላይ የሚገኘው የአዋሽ ብሔራዊ ፓርክም የቆየና የለማ የዱር እንስሳት መኖሪያ ነው። በፓርኩ 46 የአጥቢ እንስሳትና 453 የወፍ ዝሪያች እንደሚኖሩበት ጥናቶች ያመለክታሉ። ፓርኩ ከምሥራቅ አፍሪካ ፓርኮች ሁሉ የበለጠ የሳላ መንጋ፣ ፍል ውሃ (Palm springs) የአዋሽ ፏፏቴና የፈንታሌ ተራራ ውብ የተፈጥሮ መስህቦች ያሉበት ነው።

የአብጃታ ሻላ ብሔራዊ ፓርክም ሌላው በክልሉ የሚገኝ የተፈጥሮ መስህብ ነው። በሁለት መንትያ ሐይቆች የተፈጠረው የአብጀታ ሻላ ብሔራዊ ፓርክ 887 km2 ስፋት ሲኖረው 31 የአጥቢ እንስሳትና 367 የአገር በቀልና የውጪ የወፍ ዝሪያዎች ይኖሩበታል፡ በተለይም በሺዎች የሚቆጠሩ ፍላሚንጎዎችን፣ ነጭ

ፐሊካኖችን ማየት የተለመደ ነው። ሰንቀሌ ዲዴሣ ጥብቅ የዱር እንስሳት መኖሪያ ደኖችም ጥሩ መስህቦች ናቸው።

የጋራ ሙለታ ተራራዎች ዕይታ፣ የፈፈምና የባቢሌ የዱር አራዊት ክልል፣ የዳከታ ንብብር ድንጋይና የቁንድዶ ተራራ የዱር ፈረሶች ሊጎበኙ የሚገባቸው ተደናቂ የተፈጥሮ መስህቦች ናቸው።

ከፊንፊኔ በስተምዕራብ በኩል የሚገኘው የመናገሻ ተራራ ጥብቅ ብሔራዊ ክልል (የሱባ ደን) አራዊትና አዕዋፋት፣ የሚኖሩበት፣ በእሳተ ጎሞራ ክስተት የተፈጠረውና የራሱ የሆነ ውበት ያለው የወንጪ ሐይቅና የአካባቢው መልክዓ ምድር ትዕይንት፣ የጊቤ ሸለቆ ውበትና በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን የሚገኘው የአባይ ጮመን ሐይቅና በውስጡ የሚታዩ በሕብረ ቀለም የተዋቡ አዕዋፋት፣ በተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ የተፈጥሮ ፍል ውሃዎች ማለትም የአምቦ፣ የወሊሶና የሶደሬ ፍል ውሃዎች በፈዋሽነታቸው የታወቁ ከመሆናቸውም በላይ እንከን የማይወጣላቸው የመዝናኛ ሥፍራዎች ናቸው።

የኦሮሞ ባህልና ታሪክ ሲወሳ የገዳ ሥርዓት

ገልመ አባ ገዳ/አዳማ/

ከኦሮሚያ የዱርአራዊቶች መካከል

የቁንድዶ ተራራ የዱር ፈረሶች

የባቢሌ ንብብር ድንጋይ /ምስራቅ ሀረርጌ/

Page 29: ˆ - 3rd All Ethiopia  · PDF fileየጥንቱ የግሪክ ኦሊምፒክ መጫወቻ

29

አይዘነጋም። የገዳ ሥርዓት፣ የኦሮሞ ህዝብ ኢኮኖሚያዊ ማህበራዊና ፓለቲካዊ ህይወቱን የሚመራበት ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ነው።

ኦሮሚያ ታዋቂና የሚያኮሩ ጥንታውያን ሐውልቶች፣ የጥንታዊ ሰው መኖሪያና የተለያዩ የአምልኮ ሥፍራዎች፣ ኪነጥበባዊ ቅርሶችና የዕደ ጥበብ ውጤቶች አሏት። ከፊንፊኔ በስተደቡብ ምዕራብ የሚገኘው የመጀመሪያው የሰው ፍጡር ቅሪት አፅም የተገኘበት የመልካ ቁንጡሬ የአርኪዮሎጂ ሥፍራ ነው። በዚህ አካባቢ ከቋጥኝ ተፈልፍሎ መሠራቱ የሚነገርለት የአዳዲ ማርያም ቤተክርስቲያንም ሊጠቀስ የሚገባው የታሪክ ቅርስ ነው።

በምዕራብ ኦሮሚያ ከፍተኛ የንግድ እንቅስቃሴ በሚካሄድባት በጅማ ከተማ የሚገኘው 130 ዓመታት በላይ ዕድሜ ያለው የአባ ጅፋር ቤተመንግሥትና በነቀምቴ ከተማ የኦሮሞን የባህልና የታሪክ ቅርሶችን አካቶ የያዘው የወለጋ ሙዚየም እና የኩምሳ ሞሮዳ ቤተመንግስት ሳይጠቀሱ የማይታለፉ የታሪክ መዘክሮች ናቸው።

በየዓመቱ ታህሣሥና ሐምሌ 19 ቀን በብዙ ኢትዮጵያውያንና የውጭ ዜጎች የሚጎበኘው የቁልቢ ገብርኤል ቤተክርስቲያንም ለብዙ አገር ጎብኝዎች ጥሩ መስህብ የሚሆን ነው።

በባሌ ዞን የሚገኘውና በዓመት ሁለት ጊዜ የሚከበረው የድሬ ሼክ ሁሴን በዓል አከባበር አንዱ የቱርስት መስህበ ነዉ።

የኦሮሞ ባህላዊ አለባበስኦሮሚያ የተለያዩ ዞኖች ያለዉ ክልል

የገዳ ስርዓት በጉጂና ቦረና

እንደማሆኑ ሕዝቡ በተለያዩ ባህላዊ አለባበሶች ይታወቃል።

መልካ ቁንጡሬ የአርኪዮሎጂ ሥፍራ

የኦሮሚያ የተለያዩ ዞኖች ባህላዊ አለባበስ

በፊንፊኔ ግንባታዉ እየተጠናቀቀ የሚገኝ የኦሮሞ ባህል ማዕከል ገጽታ /በስታዲየም አከባቢ/

Page 30: ˆ - 3rd All Ethiopia  · PDF fileየጥንቱ የግሪክ ኦሊምፒክ መጫወቻ

30

መሠረተ ልማትና ማሕበራዊ አገልግሎቶች መንገድ

በኦሮሚያ በአሁኑ ወቅት 58,193.76 ኪሎ ሜትር መንገድ እንደተሠራ ጥናቶች ያመለክታሉ፡ ከዚህ ውስጥ የአስፋልት 2,653.88 ኪ.ሜ፣ የጠጠር 8,503.7 ኪ.ሜ፣ መጋቢ የገጠር መንገዶች 8,702.65 ኪ.ሜ በህዝብ ጉልበት የተሰራ 25,000 ኪ.ሜ፣ ሲሆን 13,033.53 ኪ.ሜ በጋ ከክረምት አገልግሎት የሚሰጡ ናቸው፡አብዛኞቹ መንገዶች ከፊንፊኔ ተነስተው ወደ ዞን ከተሞች የሚወስዱ ናቸው። የክልሉን ህዝብ የመንገድ ተጠቃሚነት ለማሳደግም ወረዳዎችን ከዞኖች ጋር የሚያገናኙ የገጠር መንገዶች እየተሠሩ ናቸው፡ በአምስት ዓመቱ የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ በክልሉ 42 ሺ ኪ. ሜትር በጋና ክረምት የሚያገለግል መንገድ ለመሥራት ታቅዶ ለተግባራዊነቱ እንቅስቃሴ በመደረግ ላይ ይገኛል።

ቴሌኮሙኒኬሽን የፌደራል መንግሥት የክልሉን ህዝብ

ተጠቃሚ ለማድረግ ከፍተኛ ኢንቨስትመንት ከሚያካሂድባቸው የመሠረተ ልማት ዘርፎች አንዱ የቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎት ነው። ህዝቡም በከፍተኛ ደረጃ ተጠቃሚ መሆን ችሏል። የኢትዮጵያ ቴሌኮሙኒኬሽን ኮርፖሬሽን በክልሉ የመደበኛ ስልክ፣ የሞባይል፣ የኢንተርኔት‹ የመልቲ ሚዲያ፣ ስኩልኔት እና የወረዳ ኔት አገልግሎቶችን እያቀረበ ይገኛል።

ትምህርት አዲስ የተቀረፀው የትምህርትና ሥልጠና

ፖሊሲ በክልሉ ከፍተኛ ውጤት አስገኝቷል። በሥራ የሚያምን ብቁ ዜጋ ለማፍራትም እያስቻለ ነው። ዕድሜአቸው ለትምህርት የደረሱ ህፃናት ትምህርት የማግኘትና በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው የመማር መብታቸው ተረጋግጧል።

በዚሁ መሠረት በክልሉ የተማሪዎች ብዛት - በአንደኛ ደረጃ (1-8) 6,286426 - በሁለተኛ ደረጃ (9-10) 536,886 - በመሰናዶ (11 -12) 55,540 - በቴክኒክና ሙያ ሥልጠና (TVET)

250,267 ሲሆን የክልሉ 1ኛ ደረጃ (1-8)የትምህርት ሽፋን 95.4% ላይ ደርሷል።

ጤናመንግሥት በሽታን በመከላከል ላይ ያተኮረ

የጤና ፖሊሲ አውጥቶ በመተግበሩ በክልሉ በርካታ ውጤቶች ተገኝተዋል። በመሆኑም የክልሉ የጤና አገልግሎት ሽፋን 90% ደርሷል። በክልሉ ያሉ የጤና ተቋማት (ሆስፒታሎች፣ ጤና ጣቢያዎች፣ ክሊኒኮች፣

የጤና ኬላዎች) ብዛትም 7047 ደርሷል። በሥራ ላይ ያሉ የጤና ኤክስተንሽን ሠራተኞች ብዛት 12,875 ናቸው።

የንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት የክልሉ የንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ሽፋን

54% ደርሷል።

ኢንቨስትመንት ግብርና፣ አግሮ ኢንዱስትሪ፣ ሆቴልና

ቱሪዝም፣ ሪልእስቴት፣ ኮንስትራክሽን፣ ትምህርት፣ ጤና፣ ንግድና ትራንስፖርት ወዘተየኢንቨስትመንት አማራጭ ዕድሎች ናቸዉ። በክልሉ ባለፉት ጥቂት ዐመታት በተሰሩ ስራዎች አበረታች ዉጤቶች ተመዝግበዋል።

- የተመዘገበ ጠቅላላ ካፒታል እስከ 2003 በጀት ዐመት 249 ቢሊየን ብር ያስመዘገቡ ባለ ሀብቶች ሲሆኑ

- ፍቃድ የተሰጣቸው የፕሮጀክቶች ብዛት 14,380

- የአገር ውስጥ ኢንቨስተሮች ብዛት 866 - የውጭ ኢንቨስተሮች ብዛት 1604 - ሙሉ በሙሉ ሥራ ሲጀምሩ ለ 684,643

ቋሚና ለ1,268,920 ጊዜያዊ ሠራተኞች የሥራ ዕድል ይፈጥራሉ።

ሚዲያ የቴሌቪዥን ፕሮግራም፤ የኦሮሚያ

ቴሌቪዥን፣በአሁኑ በሳምንት ለ72 ሰዓታትለውጭና ሀገር ዉስጥ አድማጮች ያሠራጫል።

የኦሮሚያ ራዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት (አዳማ)

Page 31: ˆ - 3rd All Ethiopia  · PDF fileየጥንቱ የግሪክ ኦሊምፒክ መጫወቻ

31

የራዲዮ ፕሮግራም፤ የኦሮሚያ ራዲዮ ኤ.ኤም በሳምንት ለ71 ሰዓታት የኦሮሚያ ኤፍ. ኤም በሳምንት ለ50 ሰዓታት ያሰራጫሉ።

በአሁኑ ወቅት የኦሮሚያ ራድዮ የክልሉን 90% ቴሌቪዥን ደግሞ 70% ይሸፍናሉ። የኦሮሚያ ቴሌቪዥን ዜና ከሁለት ቦታዎች ማለትም ከፊንፊኔና አዳማ ከተሞች በቀጥታ የሚተላለፍ ሲሆን ዋና ስቱዲዮ አደማ ይገኛል። የኢትዮጵያ ራዲዮ አፋን ኦሮሞ ፕሮግራም፣ ፋና ብሮድካስት ኮርፖሬት አፋን ኦሮሞ ፕሮግራም ጋዜጦች “ከለቻ ኦሮሚያ”፣ “በሪሣ” ሳምንታዊ ጋዜጦች፡ ሲሆኑ ኦሮሚያ በየሁለት ሳምንት አንዴ ይታተማል።

ስፖርትሀገራችን በረጅም ርቀት ሩጫዉድድር የምርጥ

አትሌቶች ማፍለቂያ ናት። ሀገራችን በተላላቅ የስፖርት ዉድድሮች መሳተፍ ከጀመረች ወዲህ አትሌቶቻችን ህዝቦቿን ወክለዉ አስደናቂ ዉጤቶችን በማስመዝገብ ሰንደቅአላማችን በአለም የክብር አደባባይ ከፍ ብሎ እንደዲዉለበለብ ወደር የሌለዉ ጀግንነት ፈፅመዋል።

እነዚህ የሀገር መኩሪያ ጀገኖች በአብዛኛዉ የፈለቁት ከኦሮሚያ ክልል ነዉ። ይህንንም ሀቅ በተለያዩ ተላላቅ የአለም የዉድድር መድረኮች የተመዘገቡ ዉጤቶች ያመለክታሉ። ለአብነትም በኦሎምፒክ፣ የመላው አፍርካ ጫወታዎች፣ የአለም አቲሌቲክስ

ጫወታዎችና የሀገር አቋራጭ ሻሚፒዮና ላይ የተገኙ ዉጤቶችን ለአብነት ማንሳት ይቻላል።

የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሀገራችን እነዚህ አኩሪ ድሎች ቀጣይ እንዲሆኑና ተተኪ ስፖረተኞችን በሁሉም የስፖርት ዘርፎች ለማፍራት በርከታ ተገበራትን እያከናወነ ይገኛል። በክልሉ ከተሰሩት ስራዎች መካከል 20 የአቲሌቲክስ ክለቦች ተዋቅሮ በዉስጡ 2000 የሚሆኑ ወጣቶች እንዲካተቱ ተደርጓል።

የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በክልሉ ስፖርት ሕዝባዊ መሰረት እንዲኖረዉና የስፖርት መሰረተ ልማቶች እንዲስፋፉ በርካታ ተግባራትን በመከናወን ላይ ይገኛል። በክልሉ በርካታ ደረጃቸውን የጠበቁ ስተ ዲየሞች በመገንባት ላይ ይገኛሉ። የወለጋ ስተዲየምና ወጣቶች ማዕከል፣ የሻሻመኔ ስታድየም፣ የሰበታ ስታዲየምና የሁሩታ ስታዲየም ዋናዋናዎቹ ናቸዉ።

የወለጋ ስተዲያም ይህ ስታዲየም በምስራቅ ወለጋ ዞን ነቀ

ምቴ ከተማ የሚገኝና የFIFAን ደረጃ ጠብቆ የተሰራ ሲሆን ስታዲየሙ በአንድ ጊዜ 22000 ተመልካቾችን ማስተናገድ ይችላ ል። ደረጃዉን የጠበቀ የሩጫትራክ፣ የእግር ኳስሜዳ፣ ዉሃዋና፣ የመረብኳስ ሜዳ፣ የእግር ኳስ ሜዳ፣ ቴንስ እንዲሁም አስፋላጊ አገልግሎቶችን የሚሰጡ ቢሮዎችን አካቷል።

በግንባታ ላይ የሚገኘዉ የወለጋ ስታዲየም ዲዛይን

Page 32: ˆ - 3rd All Ethiopia  · PDF fileየጥንቱ የግሪክ ኦሊምፒክ መጫወቻ

32

የመላው ኢትዮጵያ ጨዋታ በረከቶች

በአስቻለው ሽፈራው

የእኛ ጀግኖች

በቃና እና ያኔት ከተለያየ የኢትዮጵያ ማዕዘኖች የፈለቁ ወጣቶች ናቸው። በቃና ከምዕራብ ኢትዮጵያ ሲገኝ ያኔት ከሰሜን ኢትዮጵያ ብቅ ብላለች። ያኔት በዋና ስፖርት በቃና ደግሞ በሩጫ ስማቸው እየተጠራ

ይገኛል። ወጣቶቹ ከዛሬ አምስትና ስድስት ዓመት በፊት እምብዛም የጋዜጠኞች የወሬ አጀንዳ አልነበሩም። አሁን ለደረሱበት ደረጃ እንዲበቁ መነሻ የሆናቸው የመላው ኢትዮጵያ ጨዋታዎች ነው። ከዚህም ባለፈ ወጣቶቹ በዓለም የስፖርት መዲረኮች ላይ ጭምር መታየት ችለዋል።

በቃና በረጅም ርቀት በተለያዩ ዓለም አቀፍ ውድድሮች ለሀገሩና ለራሱ ድሎችን ማስመዝገብ የቻለ ሲሆን ያኔት ደግሞ በፊታችን የለንደን 2012 ኦሊምፒክ ጌምስ በውሀ ዋና ስፖርት ሀገሯን ወክላ ለመሳተፍ እየተዘጋጀች ትገኛለች። በዚህም ያኔት በውሀ ዋና ስፖርት በኦሊምፒክ ሀገሯን የወከለች የመጀሪያዋ ኢትዮጵያዊት በመሆን በታሪክ መዝገብ ስሟ ይሰፍራል።

ከመላ ኢትዮጵያ ጨዋታዎች ተነስተው በስኬት ከፍ እያሉ ከሚገኙ ስፖርተኞቻችን መሀከል

እነሆ ሁለቱ የዚህ እትማችን ምርጫ ሆነዋል - ተዋወቋቸው።

የበቃና የ7 ዓመታት ጉዞ

የፕሮፌሽናልነት ሀሁ በ1997 የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቴን ጨርሼ

ወደ አዲስ አበባ መጣሁ። አማርኛም ብዙ አላውቅም። ቅዳሜ ላይ ሆኜ “የኢትዮጵያ ባንኮች የፊታችን መክሰኞ የማጣሪያ ውድድር ያደርጋል “የሚል ወሬ ሰማሁና ሳመነታ ቆይቼ በአንድ ጓደኛዬ ገፋፊነት ጥየቃ ሄድኩኝ። ሁኔታው ትንሽ ተስፋ የሚያስቆርጥ ዓይነት ነበር። ሦስቱንም አሰልጣኞች ጠይቄ የለም ተባልኩኝ። አንዱ ግን ደግ ሆነልኝ -ግድየለም ና አለኝ። ከዚያ ለሚቀጥሉት 3 ቀናት እንቅልፍ አልወስድህ ብሎኝ ተቸገርኩ።

ለዝግጅት ከጨርቆስ ገበያ የስፖርት ልብስ (ፎዴ ቁምጣ) ገዛሁና ሲያበረታኝ በቆየው ጓደኛዬ መሪነት ቤተ መንግስት አካባቢ ወደ ተዘጋጀው የውድድር ስፍራ ሄድኩኝ። ለአካባቢውም ሆነ በዚያ ቦታ ላለው ስፖርተኛ አዲስ ነኝ። ማንም ሰው አያውቀኝም። እውነት ለመናገር እስከ 50ኛ እንኳ

Page 33: ˆ - 3rd All Ethiopia  · PDF fileየጥንቱ የግሪክ ኦሊምፒክ መጫወቻ

33

ለመውጣቴ እርግጠኛ አልነበርኩም። ሲጀመር ከፊት ቀድሜ ተፈተለኩኝ- በረርኩ። እነርሱም ‘ ይሄ ጀማሪ ?’ ብለው ነው መሰል እስከ 100 ሜትር ድረስ ለቀቁኝ። ማንም የተከተለኝ የለም።

ውድድሩ ስምንት ዙር ሆኖ ዳገትና ቁልቁለት ይበዛበታል። በጣም ፈታኝ ነው። ልዩነቴን ከ100 ሜትር ገደማ ወደ 400 ሜትር አሰፋሁትና ይበልጥ ራቅኩ። ቁልቁለቱን ስያያዘው ፊቴን አዞርኩና ቃኘኋቸው - ከኋላ አይታዩም። ባሰብኝ። ፍጥነቴን ይበልጥ ጨመርኩኝ ። በሁኔታዬ አሰልጣኞቹ እንኳ ይስቃሉ።

እንደራቁኝ አልቀሩም ….። ሁለት ዙር ሲቀር በጣም ፈጠኑና ደረሱብኝ። እኔም እንደጅምሬ ለማጠናቀቅ ቆረጥኩ። ትንፋሼን … ጉልበቴን ሰብስቤ ሮጥኩ። እግሬ ተላላጠ። ግን … እንደምንም አሸነፍኩኝ።

የክለብ ህይወት ያ በሁኔታዬ የተሳቀበት፣ እኔም ከጅምሩ

እስከፍጻሜው በሩጫ የጋለብኩበት የማጣሪያ ውድድር በህይወቴ የተሻለ ቀን ይዞልኝ መጣ። በኢትዮጵያ ባንክ ትቀጠራለህ ተባልኩኝና ከቅርቤ የማይጠፋው አበረታኝ ጓደኛዬ ወደዚህም ይዞኝ ሄደ- ስሜ ተለጥፏል። ግን እንደተባለው አልተቀጠርኩም። ባይሆን ሰርቪስና ምግብ እንችልሀለን አሉኝ። መጀመሪያ በአዲስ አበባ ኑሮ ፈተና ሆኖብኝ ስለነበር ‘እሺ እንዳላችሁት ይሁን’ አልኩኝ።

መጀመሪያ ላይ አዲስ አበባ ውስጥ ብቻ 11 ውድድር ተወዳደርኩኝ - ሀገር አቋራጭ፣ ታላቁ ሩጫ …። መሀል ላይ ሀገር አቋራጭ 6ኛ ስወጣ ቀጠሩኝ። ድካም አለ፣ ዘመድ የለኝም፣ በብዙ መከራ ተስፋ ባለመቁረጥ አሁን ለምታውቁኝ “በቃና” በቃሁ።

• ዕድሜ 24 • በኦሮሚያ ክልል ወለጋ ሲቀላ ተወለደ• በ1999 አዲስ አበባ፣ በመላው ኢትዮጵያ ጨዋታ፣ በ5000ሜ (1ኛ)• በ1999፣ በዓለም ሻምፒዮና (በ5000ሜ) የኢትዮጵያ ቡድን አባል፣ • በ2001 ካርልስባንድ በ5000 ሜ (1ኛ)• በ2001 ሮክ ኤን ሮል ላስ ቬጋስ፣ በግማሽ ማራቶን (1ኛ)

ስለ በቃና ዳባ አንኳር እውነታዎች

Page 34: ˆ - 3rd All Ethiopia  · PDF fileየጥንቱ የግሪክ ኦሊምፒክ መጫወቻ

34

“ልጅ ቢሮጥ አባቱን ይቀድማል” ዛሬ ላይ ሆኜ እንደማስታወሰው ልጅ እያለሁ

ከትምህርት ቤት መልስ ለቤተሰቦቼ ከብት እጠብቅ ነበር። አንዳንዴ ታዲያ አባቴ ስራዬን እያከናወንኩ መቀጠሌን ወይ ደግሞ ተዘናግቼ እንደሁ ለማረጋገጥ ሲል በሹሉክታ ብቅ እያለ ያየኛል። ድንገት ከቦታዬ ሲያጣኝ ካለሁበት ይደርስና “አባሮሽ” ይጀመራል። እርሱ ያሳድዳል እኔ አመልጣለሁ። አባቴ በቀያችን ከማንም በላይ ፈጣን ሯጭ ነበር። በእርግጥ “አባሮሹ” በተፈጠረ ቁጥር አንዳንዴ እየደረሰ ቢይዘኝም የማይደርስብኝም ወቅት ነበር። እንዲህ ዓይነቱ በአባቴ ያለመያዝ አጋጣሚ ሲደጋገም በውስጤ ሌላ ነገር ፈጠረ። ሁኔታው ለሩጫ ተሰጥኦ እንዳለኝ እንድረዳ አደረገኝ።

ህልምን ፍለጋ ቤተሰቦቼ ትኩረቴ ትምህርት ላይ እንዲሆን

ብርቱ ፍላጎት ነበራቸው። እኔ ደግሞ ሀሳቤ ከዚህ እየወጣ ነው ። ወደ ዩኒቨርሲቲ ለመግባት የሚያስችለኝ ነጥብ ሳይሟላ ሲቀር ከራሴ ጋር ተማከርኩ። ከቤተሰቦቼ ርቄ መሄድ እንዳለብኝ ወሰንኩና ዘመድ ወደሌለበት አዲስ አበባ አመራሁ። ህይወት በአዲስ አበባ ለኔ እጅግ ፈታኝ ነበር። በኦክቶበር 2005 የተካሄደውን የባንኮች ክለብ የማጣሪያ ውድድር ባልተገመተ ሁኔታ ማሸነፌ በክለብ እንድታቀፍ መንገድ ከፈተልኝ። ቀጥዬም በ2006 መጀመሪያ ላይ በኢትዮጵያ ሀገር አቋራጭ ውድድርና በብሔራዊ የትራክ ውድድር በተመሳሳይ ሁኔታ 9ኛ መውጣቴ ለብሔራዊ ቡድን እንድመረጥ አደረገኝ ። ከሀገር ውጭ የመጀመሪያ ውድድሬንም በ Brasschaat በተካሄደው የዓለም ሻምፒዮና ላይ ለማድረግ በቃሁ።

የመላ ኢትዮጵያ ጨዋታ ለኔ 1999 ዓ.ም እንጀራዬን ያገኘሁበት ጊዜ ነው።

ሚሊኒየሙን በማስመልከት በተዘጋጀው በ1ኛው የመላ ኢትዮጵያ ጨዋታዎች በ5000 ሜትር ውድድር አሸነፍኩ። ከዚያ በፊት የሀገር አቋራጭና ሌሎችም ውድድሮች የነበሩ ቢሆንም በህመም ምክንያት አላለፍኩም፣ ሀገሬንም አልወከልኩም። መሀል ላይ በዚህ ውድድር ተካፈልኩና አሸነፍኩ፣ ከማናጀርም አስተዋወቁኝ። ማናጀር ሳገኝ ውጪ ሄድኩ፣ ሚኒማ አሟላሁ፣ ሀገሬንም ወከልኩ። ወጣቶችን በመወከልና በሌሎችም እንድሳተፍም ዕድል አገኘሁ።

ይህ ውድድር በጣም አስፈላጊ ነው። ወጣት አትሌቶች በዚህ ውድድር ላይ ጠንክረው አልፈው እንደ ዝነኞቹ አትሌቶች ሚኒማ አምጥተው ታዋቂ እንዲሆኑ እመኛለው።

ሩጫና ትህግስትአዲስ አበባ የሚጨበጥ ነገር ሳልይዝ

መምጣቴን ነግሬያችኋለው። ታውቃላችሁ የሩጫ ውድድር በጣም አሰልቺ ነው። ብዙ መሰናክሎች ይበዛሉ ። ውድድር ተቃርቦ ህመምና ሌላም ያልታሰበ ችግር ያጋጥማል። ቢሆንም አንዴ ካልተሳካ ሌላ ጊዜ ሊሳካ ይችላል። ዋናው ተስፋ አለመቁረጥ ነው ። አንድ አትሌት በርትቶ ከሰራና በራሱ ጠንካራ ከሆነ የተቀረው ከዚያ በኋላ የሚመጣ ነው። መጀመሪያ መጎበዝ ያስፈልጋል። ለምሳሌ ወደ ክለብ ስገባ ደሞዜ 350 ብር ነበር። ከዚያ በፊት ደግሞ ጭራሽ ምንም አልነበረኝም። አንዳንድ ልጆች “ፋሲሊቲ” የለም፣ ሌላም ሌላም ይሉና ሞራላቸው ቶሎ ይነካል። ይህንን ተግተው ካላለፉ ውጤት የለም።

አሁን በኑሮዩ ጥሩ ተለውጫለሁ። ወንድሞቼን በኒቨርስቲ ጭምር እየከፈልኩ ማስተማር ችያለው። እንደኔው ሯጭ ለመሆን እየሰሩ ያሉ ወንድሞችም አሉኝ። በእኔም ሆነ በቤተሰቤ ለታየው ለዚህ ሁሉ ለውጥ መሰረቱ የኔ ተስፋ ሳይቆርጡ መስራት ነው። ዋናው ነገር … በጽናት ሁሉም ይሳካል።

ያኔት ስዩም - ከምቦልቻ እስከ ለንደን

ለኢትዮጵያ በኦሊምፒክ በውሀ ዋና ስፖርት የመጀመሪያዋ ተሰላፊ

ያኔት ስዩም ገብረ መድህን እባላለሁ። የኢትዮጵያ ውሀ ዋና ስፖርት ብሔራዊ ቡድን አባል ነኝ። ከስፖርቱ ውጭ ባለው ህይወቴ ደግሞ በአዲስ አበባ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ፋኩልቲ የኢንጂነሪንግ ትምህርት እያጠናሁ ነው።

የተወለድኩት በደቡብ ወሎ ዞን ኮምቦልቻ ከተማ ሀምሌ 3 ቀን 1986 ዓ.ም ነው። ዋና የጀመርኩት እንዲሁ በቃ አለ አይደል ብዙዎች እንደሚያደርጉት ለመዝናናት በሚል አይነት ነበር ማለት ይቻላል፡ ዋና እጅግ የሚወዱትና የሚያዘወትሩት ቤተሰቦቼ በከተማችን ወደሚገኘው የኮምቦልቻ ጨርቃጨርቅ ፋብሪካ መዋኛ ሲያመሩ እኔም አብሬያቸው እሄድ ነበር።

በአንድ ወቅት ‹ የወባ ቀን › ን በማስመልከት በተዘጋጀው ውድድር ላይ ተካፍዬ የብር ሜዳሊያ አገኘሁኝ። ዕለቱ ለኔ ትልቁን መንገድ እንድጀምር የተነሳሁበትም ሆነ። ከዚያ በኋላ ኢትዮጵያ ውስጥና በውጭ ሀገር በተዘጋጁ በርካታ ውድድሮች ላይ መካፈል ችያለሁ። አዲስ አበባ፣ ሀዋሳ፣ ድሬዳዋ፣ ደብረዘይት

Page 35: ˆ - 3rd All Ethiopia  · PDF fileየጥንቱ የግሪክ ኦሊምፒክ መጫወቻ

35

ከውጭ ኢጣሊያ(ሮም)፣ ሲንጋፖር፣ ቻይና (ሻንጋይ)፣ ዱባይ፣ ሞዛምፒክ (ማፑቶ)፣ ሞሮኮ ሀገሬን በመወከል ተሰልፌያሁ። በነዚህ ውድድሮች በአጠቃላይም 40 የወርቅ፣ 5 የብር እና 2 የነሐስ ሜዳሊያዎች አግኝቻለሁ።

እስካሁን በተካሄዱት የመላ ኢትዮጵያ ጨዋታዎች (በ1ኛው እና 2ኛው ) የተካፈልኩ ሲሆን በሁለቱም ውጤታማ ሆኛለሁ ማለት እችላለሁ። ምክንያቱም የመጀመሪያው የመላ ኢትዮጵያ ጨዋታዎች ለእኔ ከዚያ በፊት ከተሳተፍኩባቸው ውድድሮች ሁሉ ትልቁና የበለጠ የሚባለው ብቻ ሳይሆን በውጤት ደረጃም 3 የወርቅ እና 1 የነሐስ ሜዳሊያ የተቀዳጀሁበት ጭምር ነበር። በዚህ ጨዋታ ልምድ በመቅሰሜና ህጎቹንም በማወቄ በሁለተኛው የመላ ኢትዮጵያ ጨዋታዎች የበለጠ ውጤማ ለመሆን ቻልኩ። በመሆኑም 12 የወርቅ ፣ 1 የብርና 1 የነሐስ ሜዳሊያ ተሸላሚ ለመሆን ቻልኩ።

የባለታሪክነት ጉዞ በቀደሙት ዓመታት ህልሜ ሁሉ በውሀ ዋና

ኮከብ ኢትዮጵያዊት ሆኖ የመገኘት ራዕይ ነበር። ይህንን ማሳካት ችያለሁ። አሁን ደግሞ ፍላጎቴና ኢላማዬ ከዚህም ሰፍቷል። ምኞቴ በሰው ልጅ የስኬት መንገድ ላይ ሁሌም እንዲከተል የሚጠበቅ ተፈጥሮ እንደሆነ እናንተም እይጠፋችሁም። በስፖርቱ የእስካሁን መንገዴን እያነበባችሁ ባላችሁበት በዚህች ደቂቃም ትኩረቴን በአዲሱ ራዕዬ ላይ አድርጌ ቀጥያለሁ።

አሁን ባለሁበት ደረጃና ብቃት ሀገሬን ወክዬ በኦሊምፒክ ከምሳተፍበት ጊዜ ላይ ደርሻለሁ። ስለዚህም ሀሳቤን ለንደን 2012 ኦሊምፒክ ላይ አድርጌ ተወዳዳሪዎቼን በተሻለ ብቃት ለመወዳደር ዝግጅቴን ቀጥያለሁ። ከምንም በላይ ደግሞ በኦሊምፒክ በሚኖረኝ ተሳትፎ የራሴን ምርጥ ሰዓት ማስመዝገብ እፈልጋለሁ።

በአሁኑ ወቅት ልምምዴን በጥሩ ሁኔታ እያካሄድኩ ነው። በሌላ በኩል ደግሞ ቀደም ሲል እንዳልኳችሁ በአዲስ አበባ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የኢንጂነሪንግ ተማሪ በመሆኔ ከትምህርቴ ጋር የሚኖረው መደራረብ ሁለቱን አጣጥሞ ለመሄድ ከባድ ያደርገዋል። ይሁንና ሁለቱም ዕጣ ፈንታዬ በመሆናቸው ተመጣጥነው እንዲጓዙና እንዲሳኩ ለማደረግ የሚቻለኝን ሁሉ እየሰራሁ ነው።

ታዲያ በዚህ ሁሉ መልካምና መጥፎ ጭምር በኖረበት መንገዴ ከኔው ጋር የተጓዙ ሰዎች አሉ።

እነርሱም ቤተሰቦቼ ናቸው። በየውድድሩ የወርቅ፣ የብር አለያም የነሐስ ሜዳሊያ ይዤ ብመለስ እኔ ለነርሱ ሁሌም መመኪያና ኩራታቸው ነኝ። በኔ ደስተኞች ናቸው። ሁሌም ቢሆን የሚቻለኝን እስከሞከርኩ የማይሆን ምንም እንደሌለ ሲመክሩኝና ሲያበረታቱኝ ኖረዋል። በነርሱ ድጋፍ የዕጣ ፋንታዬን ግማሽ መንገድ መጓዝ በመቻሌም ዛሬ በዚህ አጋጣሚ ላመሰግናቸው እፈልጋለሁ ።

የመላ ኢትዮጵያ ጨዋታዎች ለእኔ

ይህ ጨዋታ በስፖርት ህይወቴ ብዙ መልኮች አሉት። በተለይም በስፖርት ውስጥ ብቻ ሳይሆን ከዚያም ውጭ ካሉት ጋር ለመተዋወቅና የየራሳችንን ነገሮች ለመለዋወጥ ትልቅ አጋጣሚ ሆኖ አግኝቸዋለሁ። ትንሽም ይሁን ትልቅ በህይወት ውስጥ የሚያጋጥሙ ነገሮችን እንዴት መቋቋም እንዳለብኝና በራስ የመተማመን ስሜቴንም እንዳዳብር ረድቶኛል። በሌላ በኩል በየውድድሩ የሚኖረው ተፎካካሪዬ ጠንካራም ሆነ ደካማ ‹አሸንፋለሁ› የሚል ስሜት በውስጥ ማኖር ለአሸናፊነት ለመብቃት ወሳኝ እንደሆነ እንድገነዘብ አድርጎኛል።

በዋና ስፖርት ታሪኬ የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳሊያ ያገኘሁት በመላው ኢትዮጵያ ጨዋታዎች ነው። በ1999 ዓ.ም በተዘጋጀው 1ኛው የመላ ኢትዮጵያ ጨዋታዎች በተለያዩ ውድድሮች 3 የወርቅን 1 የብር ሜዳሊያ ተሸለምኩ። በቀጠሉት ሌሎች ውድድሮችም ይበልጥ እየጠነከርኩ ሄድኩ።

በመጨረሻም ለ3ኛው የመላ ኢትዮጵያ ጨዋታዎች ተካፋይ ስፖርተኞች አንድ ነገር ማለት እፈልጋለው። የምትሳተፉበት የውድድር ዓይነት የቱንም ያህል ፈታኝ ቢሆን የምትችሉትን ያህል ብታደርጉ አሸናፊ ትሆናላችሁ። እንደኔ በትምህርት፣ በስራ አለያም በሌሎች ሁለት ምርጫዎች ውስጥ ብትወድቁ እንኳ የምትችሉትን ብታደርጉ ይሳካል።

Page 36: ˆ - 3rd All Ethiopia  · PDF fileየጥንቱ የግሪክ ኦሊምፒክ መጫወቻ

36

የካሜራው ማስታወሻ

Page 37: ˆ - 3rd All Ethiopia  · PDF fileየጥንቱ የግሪክ ኦሊምፒክ መጫወቻ

37

Page 38: ˆ - 3rd All Ethiopia  · PDF fileየጥንቱ የግሪክ ኦሊምፒክ መጫወቻ

38

የስፖርት ሴክተር የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ አፈጻጸም

ናስር ለገሠ

ከመሰንበቻው

ስፖርት ማንኛውም ግለሰብ ጤንነቱን ለመጠበቅ አካሉንና አእምሮውን ለመገንባት ካለው ጠቀሜታ ባለፈ በራስ መተማመንን፣ መቻቻልን፣ ማህበራዊ ግንኙነት በማጠናከር እንዲሁም ለሰው ልጆች መግባቢያ

ቋንቋ በመሆን የአለምን ህዝብ የሚያገናኝ ትልቅ መሳሪያ ነው። ስፖርት በአሁኑ ሰዓት እንደ መዝናኛ ብቻ የሚታይ ሳይሆን ለሀገራት የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የማህበራዊ ልማት መነሻና መድረሻ በመሆን ለሁለንተናዊ ዕድገት የላቀ ድርሻ እያበረከተ ይገኛል።

ሀገራችንም የስፖርትን ፋይዳ በመገንዘብ ለዘርፉ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥታ በመንቀሳቀስ ላይ ትገኛለች። በተለይም የኢትዮጵያን ስፖርት ደረጃ በማሻሻል እና ሰፊውን የህብረተሰብ ተሳትፎና ተጠቃሚነት መሠረት ያደረገ የስፖርት እንቅስቃሴ ለማስፋፋት እንዲሁም ከሰፊው ህዝብ ተሳትፎ ምርጥ ስፖርተኞችን በማፍራት ሀገራችን በአህጉርና በአለም አቀፍ ውድድሮች ተገቢውን ደረጃ እንድታገኝ ለማድረግ የሚያስችሉ ሥራዎች በመሠራት ላይ ናቸው።

የስፖርት ኮሚሽን ከ2ዐዐ3 ዓ.ም ጀምሮ በአዋጅ ቁጥር 692/2ዐዐ3 ህጋዊ ሰውነት በማግኘት ራሱን

ችሎ የፌዴራል መሥሪያ ቤት ሆኖ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ ራሱን በአዲስ መልክ እያደራጀ የለውጥ ስራ ጥናቶችን እየከለሰ በሴክተሩ የተያዘውን የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ግቡን እንዲመታ የሚያስችሉ ተግባራትን በማከናወን ላይ ነው።

የኮሚሽኑ አንድ አካል ሆኖ በአዋጅ እንዲቋቋም ከተደረገው አንዱ የስፖርት ምክር ቤት ነው። ይህ ብሔራዊ ስፖርት ምክር ቤት ህብረተሰቡን በሚወክሉ የተለያዩ ተቋማት ተወካዮች ስብስብ ያለው ሲሆን ጉባኤውን ለመጀመሪያ ጊዜ ታህሳሳ 26/ 2ዐዐ3 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ አካሂዷል።

ምክር ቤቱ በውሎው የራሱን መተዳደሪያ ደንብ፣ የስፖርት ማህበራት ስለሚቋቋሙበት ሁኔታ ለመወሰን የወጣ መመሪያ፣ የማርሻል አርት ስፖርቶች አሠራር ማኑዋልና በሌሎች ጉዳዮች ላይ በመወያየት ሥራዉን ጀምሯል። በማስከትል በብሔራዊ ስፖርት ፖሊሲ የስፖርት ዋና ችግር ሆኖ የተለዩ ጉዳዮች ምላሽ እንዲያገኙ በመደረጉ በየደረጃው ያለውን የአደረጃጀትና የአሠራር ችግሮችን በመቅረፍ የተቀናጀ ህዝባዊ ተሳትፎ ከቀበሌ እስከ ሀገር አቀፍ ደረጃ እንዲቀጣጠል አስችሏል።

በተጨማሪም ምክር ቤቱ ከሐምሌ 29 እና 3ዐ/ 2ዐዐ3 ዓ.ም ባካሄደው 2ኛ መደበኛ ጉባኤው

Page 39: ˆ - 3rd All Ethiopia  · PDF fileየጥንቱ የግሪክ ኦሊምፒክ መጫወቻ

39

የአንደኛ መደበኛ ስብሰባ ቃለጉኤ፣ የስፖርት ምክር ቤት ንቅናቄና ተሳትፎ ዕቅድ አፈፃጸም ሪፖርት መርምሮ በማፅደቅ የተሰጠውን ኃላፊነት በየጊዜው መወጣት ችሏል። በሌላ በኩልም የታወቁ የስፖርት ድርጅቶች የስፖርት አደረጃጀትና የአሠራር ማኑዋል ረቂቆች፣የስፖርት ሴክተር የ2ዐዐ4 ዓ.ም ዕቅድ ዋና ዋና ግቦችና አፈፃፀም አቅጣጫዎች፣ የሲቪል ሰርቪስ የልማት ሠራዊት ግንባታ ስትራቴጂክ ዕቅድ እና በሌሎችም ጉዳዩች ላይ በመምከር በአገራችን ስፖርት ማደግ በቅርበት ሆኖ ከኮሚሽኑ ጋር ሰርቷል።

ሌላው በሴክተሩ የተያዘውን የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ግቦች ለማሳካት የሲቪል ሰርቪስ የልማት ሠራዊት መፍጠርና ተቋማዊ ለውጥን እውን የማድረግ ተግባር ነው ።

ይሄን ቁልፍ ተግባር ተፈጻሚ ለማድረግ በመሠረታዊ የሥራ ሂደት ለውጥና በውጤት ተኮር ዕቅድ ዝግጅት ረገድ ሰፊ ሥራዎች ተከናውነዋል።

በመንግስታዊ መዋቅር ፈጻሚው ለዘመናት ያካበታቸው የአሠራር ባህሎች እና አደናቃፊ አሠራሮችን የመቀየር ተግባር በተቋሙ ትኩረት ተሰጥቶባቸዋል። ከተግባራቶቹም ያለፉ ሠነዶቹን በማዳበር እና በየደረጃው የውይይት መድረኮች በመፍጠር የአመራሮችንና

የህበረተሰቡን ግንዛቤ የማሣደግ ሥራዎች በመከናወናቸው በአገሪቱ ከቀበሌ ጀምሮ እስከ ሀገር አቀፍ ደረጃ በስፖርት ዘርፍ መሻሻሎች እየታዩ መቷል።

የመሠረታዊ የስራ ሂደት ጥናት መከናወን ተከትሎ ለስፖርት ሴክተር የልማት ዕቅድ ዝግጅት እና ውጤት ተኮር ጥናትን በማከናወን ከታህሳስ 01/2ዐዐ4 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ግባር የተገባ ሲሆን በየጊዜው ክትትል እና ድጋፍ እየተደረገ መሬት የማውረድ ሥራ እየተከናወነ ይገኛል።

በለውጥ ሂደቱ የሴክተሩ ዕቅድ ግቦችን ለማሳካትና መልካም

አስተዳደርን ማስፈን የሚያስችሉ የስፖርት ማህበራት ስለሚቋቋሙበትና ስለሚደራጁበት ሁኔታ ለመወሰን የወጣ መመሪያ፣ የማርሻል አርት ስፖርቶች የአሠራር ማንዋል፣ የታዋቂ ስፖርት ድርጅቶች የአሠራር ማኑዋል፣ የታዳጊ ወጣቶች የስልጠና ኘሮጀክቶች የአሠራር ማኑዋልና ወዘተ. ተዘጋጅቷል። የእነዚህ የአሠራር ሥርዓቶች መዘርጋት በሴክተሩ ግልፅና ተጠያቂነት ያለው የአሰራር ስርአት እንዲፈጠር አስችሏል።

የስፖርቱን ችግር በየደረጃው ይፈታል ተብሎ የሚጠበቀው ሌላው የስፖርት ማዘውተሪያ ሥፍራዎች አስተዳደር ረቂቅ አዋጅ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቦ ታህሳሳ 2ዐዐ4 ዓ.ም ፀድቋል። ይህ ደግሞ በዕቅድ ዘመኑ የተያዘውን የማዘውተሪያ ሥፍራዎች ግንባታ እና የማስፋፋት ተግባር በተሻለ መልኩ ስኬታማ እንዲሆን ትልቅ ድርሻ አለው።

በሴክተሩ ከተከናወኑት ተግባራት ሌላዉ ብቁና ጥራት ያላቸውን ተወዳዳሪዎች ማፍራት የሚያስችል የማበልፀጊያ ማዕከላት ግንባታና አስተዳደርን በተመለከተም የኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚ የአስተዳደር አዋጅ በኮሚሽኑ ተዘጋጅቶ ለሚኒስትሮች

የፌዴራል ስፖርት ምክር ቤት 1ኛ ጉባኤ

ከባለድርሻ ኣካላት ጋር በ2ዐዐ3 ዓ.ም የተደረጉ የምክክር መድረኮች

Page 40: ˆ - 3rd All Ethiopia  · PDF fileየጥንቱ የግሪክ ኦሊምፒክ መጫወቻ

40

በሀገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ ፀድቆ ተግባራዊ እየሆነ ያለው የብሔራዊ ስፖርት ፖሊሲ ዓላማዎች ህብረተሰቡ በባህላዊ ስፖርቶችና በስፖርት ለሁሉምና መዝናኛ አቅሙ በፈቀደ መጠን እንደፍላጐቱ ተሳታፊና ተጠቃሚ የማድረግና በተለይ የወጣቱ ትውልድ ግንዛቤና ተሳትፎን በማጠናከር የላቀ ችሎታ ያላቸውን ምርጥ ስፖርተኞች በማፍራት በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገብ እንዲችሉ ሁኔታዎችን የማመቻቸት ተግባራት በኮሚሽኑ በመከናወን ላይ ይገኛል።

ከተከናወኑት ተግባራት ጥቂቶቹ በአገሪቱ ተመዝግበው ዕውቅና ያገኙ ሀገር አቀፍ ማህበራት፣ ታዋቂ የስፖርት ድርጅቶች፣ አርሶ አደሩ፣ ሴቶች እና አካል ጉዳተኞች በስፖርት ለሁሉም ውድድሮች፣ በባህል ስፖርት ፌስቲቫሎች፣ የትምህርት ቤቶችና የታዳጊዎች ውድድር እንዲሁም በሀገር አቀፍ፣ በአህጉር እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ተሳትፎን በማሳደግ ህብረተሰቡን ተጠቃሚ የማድረግ ተግባራት ተከናውነዋል።

ለአብነት በ2ዐዐ3 ዓ.ም አገራችን የአህጉር እና አለም አቀፍ ውድድሮች በሲንጋፖር፣ በስፔን ፑንታ፣ በሱዳን፣ በሞሮኮ እና በሌሎችም ላይ በመሳተፍ አበረታች ውጤቶች ማስመዝገብ ተችሏል።

በአጠቃላይ ኮሚሽኑ የአገሪቱን ስፖርት በመምራትና በማስተባበር ሂደት የተሰጠውን ተልዕኮ እና ኃላፊነቶችን መሠረት በማድረግ ህብረተሰቡ በሚኖርበት፣ በሚሠራበት፣ በሚማርበት ሁሉ በስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችና መዝናኛዎች ተሳታፊና ተጠቃሚ የሚሆንበትን ተግባር አከናውኗል። ከዚህ በተጨማሪ የአሠራር እና የህግ ማዕቀፍ ዝግጅቶችን እያዘጋጀ ባለድርሻ አካላትም ግንዛቤ እያገኙ ወደ ተግባር ለመግባት የሚያስችል አያሌ መድረኮች ተፈጥረዋል። ከዚህም ባሻገር በስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ላይ ህብረተሰቡ በየደረጃው ተሳታፊ እንዲሆን፣ የሚያስችሉ ጨዋታዎች፣ ውድድሮችና ፌስቲቫሎች ተካሂደዋል። በመካሄድ ላይም ናቸው። በኮተቤ እና በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ከተካሄዱ ስልጠናዎች በከፊል

ምክር ቤት ቀርቦ የፀደቀ በመሆኑ አካዳሚውን ሥራ ለማስጀመር ምቹ ሁኔታ እንዲፈጠር ከማድረጉም ባሻገር በአገሪቱ የስፖርት ማበልፀጊያ ማዕከላትን ለማስፋፋት የሕግ ማዕቀፍ እንዲኖር ተደርጓል። ።

በአሁኑ ጊዜ በሀገር አቀፍ ስፖርት ማህበራት ፣ በክልሎች/ከተማ አስተዳደሮች የታዳጊ ወጣቶች ኘሮጀክት የማስፋፋት ተግባራት እየተከናወኑ ይገኛል። በዚህ መሠረት በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በኦሮሚያ ክልል በቆጂ ከተማ፣ በትግራይ ክልል ማይጨው፣ በአማራ ደብረብርሃንና በደቡብ ብ/ብ/ህ/ ክልል በሀገረ ሰላም ከተማ የስልጠና ማዕከላት ተከፍተው ስልጠናው ተግባራዊ እየሆነ ይገኛል። እንዲሁም የእግር ኳስ እና የቮሊቦል ስፖርቶችን ጨምሮ በ13 የስፖርት ዓይነቶች በሁሉም ክልሎችና ከተሞች የታዳጊ ወጣቶች ስልጠና ትኩረት ተሰጥቷቸው ወደ ሥራ ተገብቷል።

በመሆኑም በቀጣይ የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ግቦችን ለማሳካት የስፖርት ባለሙያዎችን በብዛትና በጥራት በማፍራት በዕውቀት ላይ ተመስርተው ሳይንሳዊ እና ዘመናዊ የሆነ የሥልጠና አሠራር እንዲኖር በመደረጉ የአትሌቶችን አቅም በመገንባት ሀገራዊ ተሳትፎአቸውን በብቃትና በጥራት መወጣት እንዲችሉ ተከታታይነት ያለው ስልጠና ተግባራዊ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።

በአጠቃላይ በስፖርት ሴክተር የልማት ዕቅድን ለማሳካት ሃያ ሺ የስፖርት ባለሙያዎች እና ሃያ ሺህ ታዳጊ ወጣቶች በአስራ ሶስት የስፖርት ዓይነቶች ስልጠና የመስጠት ተግባር በመጀመሩ በስፖርት ሳይንስ የመጀመሪያ ዲግሪ ተመራቂዎች በስድስት ከፍተኛ የትምህር ተቋማት በስድስት የስፖርት ዓይነቶች ስልጠና ተሰጥቷል።

በተጨማሪም ከሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ለተውጣጡ በሀረር፣ በደሴ፣ በአዲስ አበባ እና ጅማ ከተማ በተዘጋጀው የታዳጊ ወጣቶች የማሰልጠኛ ማኑዋል ላይ ከ 900 በላይ ለሆኑ መምህራን የአሰልጣኝነት ስልጠና እንዲያገኙ ተደርገዋል።

በደብረ ማርቆስ የተካሄደ የባህል ስፖርት ፌስቲቫል

Page 41: ˆ - 3rd All Ethiopia  · PDF fileየጥንቱ የግሪክ ኦሊምፒክ መጫወቻ

41

ስፖርት ሌላኛው ጭስ አልባ ኢንዱስትሪ

እንየው ዓሊ

ሰፖርትና ልማት

የሰው ልጆችን ያህል ዕድሜ እንዳስቆጠረ የሚነገርለት እና የዕለት ተዕለት ፍላጐትን ለማሟላት ይደረግ በነረበረው እንቅስቃሴ ላይ ተመስርቶ እያደገ የመጣው ስፖርት፤ በተደራጀና በውድድር መልኩ በሰፊው መዘውተር

የጀመረው እ.ኤ.አ. በ776 ከክርስቶስ ልደት በፊት ነበር። ይህ ስፖርትም የኦሊምፒክ ጌምስ በመባል በጥንታዊቷ ግሪክ ይከናወን እንደነበር ታሪክ ያስረዳል።

ከፍራፍሬ መልቀም ወደ አዳኝነት በመሸጋገር የሰው ልጅ ህልውናውን ለማቆየት ሲያካሂደው የነበረው እንቅስቃሴ በሂደት ራስን የማኖር ትግሉን ከማሸነፍ ባሻገር እንቅስቃሴው ወደ ባህላዊ ቱርፋት ተለውጦ እነሆ ዛሬ ዳር ድንበር ሳይገድበው አብዛኛውን የዓለም ህብረተሰብ ቀልብና ስሜት በከፍተኛ ደረጃ በመሳብ እና በማቀራረብ እንዲሁም የወንድማማችነት መንፈስ በመፍጠርና በማደበር ረገድ ስፖርት ታላቅ መድረክ ሆኖ በማገልገል ላይ ይገኛል።

ስፖርት ጤናማና ምርታማ ህብረተሰብን በመገንባት ድህነትንና ረሀብን ለመዋጋት፣ የልማት ዕድሎችን በመክፈት፣ የሥራ ዕድልን በመፍጠር፣ የቱሪዝም ምንጭ በመሆን የሀገርን ገቢና ዕድገት በማፋጠን፤ የልማት አቀጣጣይ ከሚባሉት ዘርፎች

Page 42: ˆ - 3rd All Ethiopia  · PDF fileየጥንቱ የግሪክ ኦሊምፒክ መጫወቻ

ውስጥ አንዱ በመሆን በአሁኑ ሰዓት ስፖርት እንደ ቱሪዝም ሁሉ ጭስ አልባው ኢንደስትሪ የሚል ስያሜን ለመጐናፀፍ በቅቷል።

በተለይ አለም አቀፉዊ፣ አህጉራዊና ብሔራዊ የስፖርት ውድድሮችን የሚያስተናገዱ ሀገራትና ከተሞች የቱሪዝም ኢንደስትሪያቸው በከፍተኛ ሁኔታ እንዲያድግ አስተዋጽኦው የጐላ ከመሆኑም በላይ ውድድሮችን ለማስተናገድ የሚያስችላቸው የአዳዲስ ሆቴሎች፣ መንገዶች፣ ሰታዲየሞች የስፖርት መንደሮች፣ … ወዘተ ግንባታ እንዲሁም ዘመናዊ የመሠረተ ልማት አውታሮች እንዲዘረጉ በማድረግ ለሀገራት የኢኮኖሚ ልማት ዕድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረክታል።

ለአብነትም የ2010 የአለም ዋንጫ አስተናጋጅ የነበረችውን ደቡብ አፍሪካ ብንወስድ ለዚህ ትልቅ ማሳያ ናት። ዝግጅቱን የተሳካ ለማድረግ 5 ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ አዲስ ስታዲየሞች የገነባች ሲሆን 5 ነባር ስታዲየሞችን የማሳደግ ሥራ ሰርታለች።

በከተሞች የተሻለ የትራንስፖርት አቅርቦት እንዲኖር የሚያስችሉ ደረጃቸውን የጠበቁ የመንገድና የባቡር ሀዲድ ግንባታዎችን ጨምሮ ፈጣን የሕዝብ ማመላለሻ ባቡሮችንና አውቶቡሶችን በከፍተኛ ወጪ በመግዛት ለአገልግሎት አቅርባለች። በተጨማሪም ዘመናዊ የቴሌኮሙኒኬሽን መሠረተ ልማት ዝርጋታ እና የእንገዶች ማረፊያ ተጨማሪ የሆቴሎች ግንባታ አከናውናለች። ለዚህ ስኬት በሀገሪቱ የሚገኙ ባለሀብቶች ሚና ከፍተኛ ነበር ይህም ስፖርት ልማትን ለማፋጠን ያለውን ሚና በቀላሉ ለመመልከት ያስችለናል።

በሌላ በኩል ኘሮፌሽናል ስፖርተኞች ከታዋቂነት አልፈው በሙያቸው ከፍተኛ ገንዘብ ተከፋይ በመሆን ትላልቅ ባለሀብቶች መሆን ችለዋል። በተለይ ከወር ደመወዛቸው ባሻገር በውድድር እና በሚያሸንፉበት ወቅት እንዲሁም የታዋቂ የስፖርት ቁሳቁሶች አምራች ኩባንያዎች ምርቶችን በማስተዋወቅ በሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ የሚያገኙ ስፖርተኞች ቁጥር ቀላለ አይደለም። ለዚህ ደግሞ ወደ እንግሊዝና

ስፔን ሳንጓዝ እንደ ኃይሌ ገ/ስላሴ፣ ቀነኒሳ በቀለ፣ መሠረት ደፋር የመሳሰሉ የሀገራችን አትሌቶች ትልቅ ማሳያዎች ናቸው። ዛሬ እነዚህ ግለሰቦች ከስፖርተኛነት ወደ ትላልቅ ባለሀብትነት እና ኢንቨስተርነት በመሸጋገር በሀገራቸውና በአካባቢያቸው ልማት ላይ ከፍተኛ አስተዋጽኦ በማበርከት ላይ ይገኛሉ።

በሌላ በኩል በአሁኑ ሰዓት በሀገራችን በስፋት እየተዘወተሩ እና እየተለመዱ የመጡት የማርሻል አርት ስፖርትቶች እና ጅምናዝየሞች ትልቅ የሀብት ምንጭ በመሆን ላይ ይገኛሉ። ባለሀብቶችም በዘርፉ በስፋት በመሠማራት ላይ ናቸው።

በአጠቃላይ በስፖርት የማያቋርጥ የኢኮኖሚ የገቢ ምንጭ ፈጣሪ በመሆኑ በርካታ የንግድና የሥራ ዕድሎችን በመፍጠር፣ ዘመናዊ የመሠረተ ልማት አውታሮች እንዲዘረጉ ዕድል በመክፈት፣ የሀገሮችና የከተሞች የቱሪዝም ኢንዱስትሪ እንዲስፋፋ በማድረግ በተለይ የሀገርን መልካም ገጽታ ለዓለም ሕዝብ በማስተዋወቅ ረገድ ስፖርት የማይናቅ ድርሻ በማበርከት ላይ ነው። ለዚህ ደግሞ በሀገራችን በየአመቱ የሚካሄድው ታላቁ ሩጫ አንዱ ምሳሌ ነው። የሀገራችንን መልካም ስምና ዝና ለዓለም በማስተዋወቅ የቱሪስት ፍሰት እንዲጨምር በማድረግ እና የውጭ ምንዛሬ ምንጭ በመሆን፣ ስፖርት ለሀገራት የኢኮኖሚ ልማት ዕድገት የራሱን ሚና በመጫወት ላይ ያለ በመሆኑ ዛሬ ዛሬ ስሙ ተቀይሮ ጭስ አልባው ኢንደስትሪ በመባል ይታወቃል።

በሀገራችን የስፖርት ፖሊሲ አቅጣጫ ላይ በግልፅ እንደተቀመጠው የስፖርቱ አጠቃላይ እንቅስቃሴ አደረጃጀትና አመራር ህዝባዊ መሠረት በማስያዝ ደረጃ በደረጃ ከመንግሥት በጀትና ድጐማ የሚላቀቅበትና ራሱን የሚችልበት ምቹ ሁኔታ ተመላክቷል።

በዚሁ መሠረት ፖሊሲው ተግባራዊ ይሆን ዘንድ እንዲሁም ስፖርት ልማትን ለማፋጠን ያለው ሚና መንግሥት በመገንዘብ አልሚ ባለሀብቱ በሀገሪቱ የስፖርት ልማት ውስጥ ሙሉ ተሳታፊና ተጠቃሚ የሚሆንበትን ዕድል አመቻችቷል። በተለይም በሌሎች የልማት መስኮች ኢንቨስት ለሚያደርጉ ባለሀብቶች

42

Page 43: ˆ - 3rd All Ethiopia  · PDF fileየጥንቱ የግሪክ ኦሊምፒክ መጫወቻ

43

ዕቃዎች ማምረቻ ኢንዱስትሪዎች እንዲሁም የስፖርት ትምህርት ተቋማትና የህክምና አገልግሎት ተቋማት የመሳሰሉት ተጠቃሽ ናቸው።

በመተሳሳይ በእነዚህ የማምረቻ ኢንዱስትሪዎች እና ተቋማት ለሚሰማሩ ባለሀብቶች ለካፒታል ዕቃዎችና መለዋወጫዎች የቀረጥ ነፃ መብት ከመስጠት ጀምሮ ለ5 ዓመት የሚቆይ የገቢ ግብር ነፃ መብት፣ የመሬት አሰጣጥ ማበረታቻ (ነፃ መሬት፣ የመሬት ሊዝ ዋጋ ቅናሽና የመሬት ሊዝ ዘመን ማራዘም) እና ሌሎች መሰል ማበረታቻዎች እንደሚደረግላቸው በግልፅ ተቀምጧል።

በተጨማሪም መንግሥት ባለሀብቶች በስፖርቱ ዘርፍ ኢንቨስት እንዲያደርጉ ከማበረታታት ባለፈ የተለያዩ አማራጮችን እና አቅጣጫዎችን በመንደፍ ግልፅና ቀልጣፋ አሠራሮችን በመዘርጋት የአልሚ ባለሀብቱን ተሳትፎ በማጐልበት ላይ ይገኛል።

ስለሆነም ባለሀብቶች ከላይ የተጠቀሱትን እና መሰል ማበረታቻዎችን በመጠቀም እንዲሁም ስፖርት በአሁኑ ሰዓት በዓለማችን ያለውን ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና ማህበራዊ ፋይዳውን በመገንዘብ በዘርፉ መዋለ ንዋያቸው ሊያፈሱ ይገባል።

የተለያዩ ማበረታቻዎች እንደሚደረግ ሁሉ በስፖርት ኢንቨስትመንት የሚሰማሩ ባለሀብቶችን የማነቃቂያና የማበረታቻ ሥራዎች በመሠራት ላይ ናቸው።

በርካታ ባለሀብቶችም ለስፖርት ኢንዱስትሪው የተቀመጡ ምቹ ሁኔታዎችን ብሎም፣ በሀገራችን ያለውን ተፈጥሮአዊ እና ወቅታዊ ምቹ ሁኔታዎች በመጠቀም እንዲሁም በሀገሪቱ ያለው የህዝብ ብዛትና የገበያ ፍላጐት እያደገ መምጣት በመገንዘብ በዘርፉ ከፍተኛ መዋለ ንዋያቸውን በማፍሰስ ላይ ናቸው። ይህም ለሀገሪቱ ስፖርት ዕድገት ከሚኖረው ሚና ባለፈ ለበርካታ ወጣቶች የሥራ ዕድል በመፍጠር እና የሀገሪቱን የውጭ ምንዛሬ በማዳን ፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገት በማረጋገጥ ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ በማበርከት ላይ ይገኛሉ።

በመሆኑም መንግሥት የሀገራችንን የስፖርት ኢንቨስትመንት አማራጮች በመለየት ለሀገር ውስጥና ለውጭ ባለሀብቶች ሰፊ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራ እየሠራ ሲሆን በግልፅ ከተለዩት የኢንቨስትመንት አማራጮች መካከል የስፖርት ትጥቆች፣ ማቴሪያሎችና ቁሳቁሶች ፣ የአካል ብቃት መሣሪያዎች፣ የማዘውተሪያ ግንባታ ማቴሪያሎች፣ የስፖርት የስጦታና የሽልማት

ታላቁ ሩጫ

Page 44: ˆ - 3rd All Ethiopia  · PDF fileየጥንቱ የግሪክ ኦሊምፒክ መጫወቻ

44

ስፖርት ዛሬ ዛሬ በተወዳዳሪዎች መካከል በሚደረግ ፉክክር ተመልካቾችን ከማዝናናትና የአለምን ህዝብ በማቀራረብ ትልቅ የመገናኛ መድረክ ሆኖ ከማገልገሉ ባሻገር ለአንድ ሀገር የኢኮኖሚ ዕድገት

አቀጣጣይ ከሚባሉት ዘርፎች (pillars) መካከል አንዱ

በመሆን ላይ ይገኛል። ይህ የምዕራቡ ዓለም ባህል የሆነው ዘመናዊ

ስፖርት በግሪክ ከተሞች መካከል ሲጀመር በኦሊምፒያ ተራሮች ከቤተ - ጣዖታቱና ከሀውልቶቻቸው በታች የመሬቱን ቅርፅ በማስተካከል የዛሬውን ዘመናዊ ስታዲየም መሰል ባለደረጃ የተመልካች መቀመጫ እና የመጨዋቻ ሜዳ አስተካክለው በማዘጋጀት ነበር። በዚህም በወጣቶችና በጐልማሶች መካከል በአትሌቲክስ ፣ጦር ውርወራ፣ ቀስት ኢላማ፣በፈረስ ስፖርት እና በሌሎች ስፖርቶች ፉክክር ይካሄድ እንደነበር የተለያዩ ፅሑፎች ያስረዳሉ።

አስቀድሞ ኦሊምፒክ በኦሊምፒያ በኋላም በሮማ ኮሎሲየም የተደረገው ጨዋታ እና የመጫወቻ ሜዳ ዝግጅት በአሁኑ ሰዓት እያደገና እየተስፋፋ መጥቶ በመላው ዓለም ስፖርትና ህይወት

የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች ልማት

የማይነጣጠሉበት ደረጃ ላይ ደርሷል። በተለይ ለኦሊምፒክ ዝግጅትም ይሁን ለተለያዩ ዓለም አቀፍ እና አህጉራዊ ውድድሮች ዝግጅት የሚገነቡት የማዘውተሪያ ሥፍራዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ እጅግ ዘመናዊ በሆነ መልኩ በመገንባት ላይ ናቸው። ለዚህ ደግሞ የ2008 የቤጂንግ ኦሊምፒክ ትልቅ ማሳያ ነው።

ቻይና በ2001 29ኛውን የኦሊምፒክ ጨዋታዎች እንድታስተናግድ ዕድሉ ከተሰጣት ጀምሮ በ7 ዓመታት ውስጥ በኦሊምፒክ ታሪክ ታይቶና ተሰምቶ የማይታወቅ ዝግጅት ያካሄደች ሲሆን ከዝግጅቶችም መካከል 37 አዳዲስ ስታዲየሞችን የመገንባትና የነባሮችን ደረጃ የማሻሻል ሥራ ሠርታለች። 63 የመለማመጃ ስታዲየሞችንም ገንብታ አቅርባለች። ሌላው ለየት የሚያደርገው እጅግ በረቀቀ ጥበብና ቴክኖሎጂ የተሰራው 91,000 መቀመጫ ያለው እና “ የወፍ ጐጆ” የሚል መጠሪያ የተሰጠው ብሔራዊ የኦሊምፒክ ሰታዲየም ግንባታ ነው። ይህም የዘመናዊ ስፖርት እና መጫወቻ ሜዳዎች ውልደት በግሪክ ኦሊምፒያ ተራሮች ዕድገቱ ደግሞ በቻይና ቤጂንግ መሆኑን ያሳየናል። ወደፊት ደግሞ ከዚህ የተሻለ ጥበብና ቴክኖሎጂ የምናይበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም።

እንየው ዓሊ

Page 45: ˆ - 3rd All Ethiopia  · PDF fileየጥንቱ የግሪክ ኦሊምፒክ መጫወቻ

45

የስፖርት ማዘውተሪያ ሥፍራዎች በኢትዮጵያ

የስፖርት ማዘውተሪያ ሥፍራዎች በተለያየ ደረጃ ህብረተሰቡን ማገልገል በሚችሉበት ሁኔታ ማደራጀት ለሰው ልጅ ዕድገትና ብልፅግና ካላቸው አስተዋጽኦ አኳያ ከፍተኛ ግምትና ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገባ ከመሆኑም በላይ፤ የአንድን ሀገር የስፖርት መሠረት ሊያዳብሩ ወይም ሊያቀጭጩ ከሚችሉ መሥፈርቶች መካከል የመጀመሪያውን ረድፍ ይዘው የሚገኙ ናቸው።

የአንድ ሀገር የስፖርት ዕድገት የሚለካውም ሆነ የሚታወቀው የስፖርት ማዘውተሪያ ሥፍራዎች በጥራትና በብቃት ከህብረተሰቡ ቁጥርና ፍላጐት፣ የአኗኗር ሁኔታ፣ ህብረተሰቡ በብዛት ከሚያዘውትረው የስፖርት ዓይነት፣ በአጠቃላይ ከተፈጥሯዊ አየር ሁኔታዎች አኳያ ተገንብተው ሲገኙ እንደሆነ

ጥናቶች ያመለክታሉ ። ሀገራችን በዚህ በኩል ያላት ዕድገት አዝጋሚ

ከመሆኑም በላይ ያሉን የስፖርት ማዘውተሪያ ሥፍራዎች ከሀገሪቱ አቅም ጋር ያልተዛመደ በመሆኑ በቁጥርም ሆነ በዘመናዊነታቸው እምብዛም ትልቅ ቦታ የምንሰጣቸው ሆነው አናገኛቸውም። ለዚህም ዛሬ ሀገሪቱ በአለም አቀፍ ደረጃ ለውድድር አገልግሎት ያስመዘገበቻቸው ስታዲየሞች ሁለት ብቻ ከመሆናቸውም በላይ መለስተኛ ስታዲየሞች ያሏቸው የክልል ከተሞች ጥቂት ናቸው። አብዛኞቹ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች በተፈጥሯዊ ሜዳ እና በጥርጊያ ሜዳ በመገልገል ላይ ይገኛሉ።

በሀገራችን ዘመናዊ ስፖርት የተጀመረው በ1916 ዓ.ም. አካባቢ ቢሆንም ጣሊያን ከመውረሩ በፊት በት/ቤቶች ከሚገኙ የመጫወቻ ሜዳዎች በስተቀር ስታዲየሞች አልነበሩም። ከጣሊያን ወረራ በኋላ በአንድ አንድ ቦታዎች ነጮች ብቻ የሚገለገሉባቸውና የሚወዳደሩባቸው የኳስ ሜዳዎች ከመገንባታቸው በስተቀር ሌሎች ሥፍራዎች አልነበሩም። ከዚያ በኋላም በደጃች ነሲቡ ሰፈር፣ በጃን ሜዳና መድፈኛ ግቢ እየተባለ በሚጠራው ሜዳ ላይ እንጨቶች እየተተከሉ ጨዋታዎች ይደረጉ እንደነበር በተለያዩ ጽሑፎች ላይ ለታሪክ ተፅፎ ይገኛል።

በ1940 ዓ.ም. የአዲስ አበባ ስታዲየም የመሠረት ድንጋይ ተጥሎ ሥራው በአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት አማካኝነት የስታዲየሙ ዙሪያ አጥር ታጥሮ 5000 ተመልካች ሊያስተናግድ የሚችል መቀመጫ ተሠራለት። በ1947 ዓ.ም. ማዘጋጃ ቤቱ ይህንኑ ስታዲየም በማሻሻል ለ25,000 ህዝብ የሚሆን የሲሚንቶ መቀመጫና ባለ 400 ሜትር የመሮጫ መም ከአፈር እንዲሰራ ተደረገ። ከዚያም የስፖርት ማዘውተሪያ ሥፍራዎች እድገታቸውን እየጠበቁ በሌሎችም አካባቢዎች ማለትም በወታደራዊ ካምፖች፣ በፖሊስ ሠራዊት፣ በዩንቨርስቲና በት/ቤቶች ቁጥራቸው በርካታ የሆኑ የማዘውተሪያ ስፍራዎች ተሠሩ ።

በመቀጠልም የስፖርት ማዘውተሪያ ሥፍራዎች ዕድገታቸው እየቀጠለ በመሄድ በሌሎችም አካባቢዎች ማለትም በድሬዳዋ፣ በሐረር እንዲሁም በወቅቱ የጠቅላይ ግዛት ዋና ከተሞች

በነበሩ እና በአውራጃዎች ለመወዳደሪያና ለልዩ ልዩ አገልግሎት መዋል የሚችሉ በማዘጋጀ ቤቶችና በህዝብ የተሳትፎ መለስተኛ ስታዲየሞች ተገንብተዋል።

በወቅቱ የስፖርት ማዘውተሪያ ሥፍራዎች ግንባታ በሁሉም ከተሞች ለማዳረስ የታሰበና የተጀመረ ቢሆንም የሀገሪቱ ህዝብ ፍላጐትና ዕድገት ጋር የተጣጣመ እና አለም አቀፋዊና አህጉራዊ ውድድሮችን በብቃት የሚያስተናግዱ ማዘውተሪያ ሥፍራዎች ተገንብተዋል ለማለት አያስደፍርም። የቻይና የወፍ ጎጆ ሰታዲየም

Page 46: ˆ - 3rd All Ethiopia  · PDF fileየጥንቱ የግሪክ ኦሊምፒክ መጫወቻ

46

ብዙዎቹ የተለያዩ ችግሮች ያሉባቸውና በጅምር የቀሩ ናቸው።

ከላይ ለመግለጽ እንደተሞከረው ዘመናዊ ስፖርት ወደ ሀገራችን የገባው የረጅም ጊዜ ታሪክ ያለውና በርካታ የስፖርት ዓይነቶች ቢዘወተሩም በሚፈለገው ፍጥነት በማደግ ረገድ እና በተለያዩ የውድድር መድረኮች የሚገኘው ውጤት እዚህ ግባ የሚባል አይደለም። ለዚህ ደግሞ ትልቁ ችግር ከሰለጠነ የሰው ሀይል አለመኖርባሻገር በቂና ዘመናዊ የስፖርት ማዘውተሪያ ሥፍራዎች አለመኖር በዋነኝነት ተጠቃሽ ነው።

ይሁን እንጂ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ስፖርቱ በህዝባዊና መንግሥታዊ አደረ ጃጀት መመራት ከጀመረ ጊዜ አንስቶ በየስፖርቱ ዓይነት ዕድገት ለማምጣት እና የማዘውተሪያ ስፍራዎችን ለማስፋፋት እንዲሁም የኢትዮጵያን ስፖርት ደረጃ ለማሻሻል እየተደረገ ያለው ጥረት በቀላሉ የሚታይ አይደለም።

በአሁኑ ሰዓት መንግሥት ልክ እንደ ሌላው ልማት ሁሉ ስፖርትን እንደ አንድ ቁልፍ የልማት አጀንዳ በመያዝ የስፖርት ፖሊሲ ከመቅረፅ ጀምሮ የተለያዩ ደረጃቸውን የጠበቁ የስፖርት ማዘውተሪያ ሥፍሪዎች በመገንባት እንዲሁም፣ ለውድድሮች እና ለሌሎች ጉዳዮች አስፈላጊውን በጀት በመመደብ ከፍተኛ ሥራ በማከናወን ላይ ይገኛል።

በዚህ ረገድ በለቀምት ከ280 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ በመገንባት ላይ የሚገኘው የወለጋ ሁለገብ ስታዲየም ተጠቃሽ ነው። ይህ ስታዲየም አለም አቀፍ ደረጃውን ጠብቆ እየተገነባ ሲሆን

22 ሺ ተመልካችን ይይዛል ተብሎ ይታሰባል። ግንባታውን ለመጨረስም ህዝብና መንግሥት ከፍተኛ ርብርብ በማድረግ ላይ ናቸው።

ሌላው በአማራ ክልል ባህር ዳር ከተማ እየተገነባ ያለው እና ግንባታውም በመፋጠን ላይ የሚገኘው የባህር ዳር ብሔራዊ ሁለገብ ስታዲየም ይገኝበታል። ስታዲየሙ ከ400 ሚሊየን ብር በላይ ይጨርሳል ተብሎ የሚታሰብ ሲሆን በአንድ ጊዜ 50 ሺ ተመልካች ማስተናገድ የሚችል ነው። ስታዲየሙ በተመረጠ ፋይበር ግላስ ዙሪያውን ጥላ ያለው ሲሆን በምስራቅ አፍሪካ በዓይነቱ የመጀመሪያ እንደሆነም ይታመናል።

በትግራይ ክልል በመቀሌ ከተማ በ1999 ዓ.ም. የተጀመረው እና በአሁኑ ሰዓት የመጀመሪያው

ፌዝ የተጠናቀቀው የመቀሌ ብሔራዊ ሁለገብ ስታዲየም ሌላው የሀገራችን የስፖርት ማዘውተሪያ ሥፍራዎች ዕድገት የሚያመላክት ነው። ይህ ስታዲየም ከ35 እስከ 40 ሺ ተመልካቾችን የመያዝ አቅም ያለው ሲሆን ከ450 ሚሊየን ብር በላይ ይጨርሳል ተብሎ ይታሰባል።

እስካሁንም ከ160 ሚሊየን ብር በላይ ለግንባታ ውሏል። ስታዲየሙ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ በመሆኑ ሲጠናቀቅ መላው አፍሪካን ጨምሮ ሌሎች አህጉራዊ እና ዓለም አቀፍ ውድድሮችን የሚያስተናግድ አቅም አለው፡

ከዚህ ባሻገር በቅርቡ ይገነባል ተብሎ የሚታሰበው እና የዲዛይን ጥናት እየተደረገለት የሚገኘው ብሔራዊ ሰታዲየምን ጨምሮ በሌሎች የክልል ዋና ከተሞችና አነስተኛ ከተሞች እንዲሁም በትምህርት ተቋማት ፣በፖሊስ ሠራዊት እና በወታደራዊ ካምፖች የተለያዩ መጠን ያላቸው ስታዲየሞችና የማዘውተሪያ ሥፍሪዎች በመገንባት ላይ ናቸው።

በተለይ በመንግሥት ከፍተኛ ተቋሟት መካከል በየዓመቱ የሚካሄደውን ውድድር መሠረት በማድረግ

የመቀሌ ሰታዲየም የተመልካች መቀመጫ

አንጋፋው የአዲስ አበባ ስታዲየም

Page 47: ˆ - 3rd All Ethiopia  · PDF fileየጥንቱ የግሪክ ኦሊምፒክ መጫወቻ

47

በዩንቨርስቲዎች (በባህርዳር፣ጐንደር፣ሀዋሳ፣አምቦ)እየተገነቡ የሚገኙ የስፖርት ማዘውተሪያ ሥፍራዎች ለሀገራችን የስፖርት ዕድገት ከፍተኛ ድርሻ አላቸው። ይህም በአምስት ዓመቱ የተቀመጠውን የስፖርት መሠረተ ልማት እና ማዘውተሪያ ሥፍራዎች ማስፋፋት ዕቅድ የተሳካ ያደርገዋል ተብሎ ይታሰባል።

በሌላ በኩል በዘርፉ ያለውን የተማረ የሰው ሀይል ችግር ለመቅረፍ እና የስፖርት ባለሙያዎችን በብዛትና በጥራት የሚፈሩበትን ሁኔታ ለማመቻቸት፣ እንዲሁም በሳይንሳዊ ዘዴ የተደገፈ ትምህርትና ስልጠና በመስጠት ውጤታማ ስፖርተኞችን በማፍራት ረገድ ወሳኝ ሚና ሊጫወት የሚችለው የብሔራዊ የስፖርት አካዳሚ ግንባታ በመጠናቀቅ ላይ ሲሆን አፈፃፀሙም 90% በላይ ደርሷል።

የብሔራዊ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚ ግንባታ ሙሉ ወጭ የተሸፈነው በመንግሥት ሲሆን ለግንባታውም ከ200 ሚሊዮን ብር በላይ ተመድቦለታል። ይህም መንግሥት ለዘርፉ የሰጠውን ትኩረት የሚያመላክት ነው።

አካዳሚው በእግር ኳስ፣ በአትሌቲክስ እና በቮሊቦል ስፖርተቶች ሥራ ለማስጀመር የሚያስችሉ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች የተጠናቀቁ ሲሆን በተለይ የአትሌቶች፣ የአሠልጣኞች፣

የዳኞችና የወጌሻዎች የሙያ ደረጃ ማረጋገጫ (Occupational standard) በኮሚሽኑ እና በትምህርት ሚኒስቴር የጋራ ትብብር ተዘጋጅቷል። እንዲሁም የአንደኛ ደረጃ የአትሌቶች ማሠልጠኛ ካሪኩለም (curriculum) ዜሮ ድራፍት ተጠናቋል።

በተመሳሳይ የአካዳሚው የሰው ሀይል ፍላጐትና መዋቅር፣ የፈርኒቸርና የቁሳቁስ ጥናቶች ተጠናቀው ለሚመለከተው አካል የቀረቡ ሲሆን

በተያዘለት የጊዜ ገደብም ሥራውን ይጀምራል ተብሎ ይታሰባል።

በአጠቃላይ በአንድ ሀገር የስፖርት ዕድገት ለማምጣትና ለማስፋፋት የመወዳደሪያም ሆነ የመለማመጃ የሚሆን ዘመናዊ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች በበቂ መጠን እና ዓይነት መገንባት መሠረታዊ ጉዳይ በመሆኑ እና መንግሥትም ይህንኑ በመገንዘብ ከሀገሪቱ የህዝብ ቁጥርና የስፖርት ፍላጐት አኳያ ከላይ የተጠቀሱትን የስፖርት ማዘውተሪያዎች ጨምሮ በየጊዜው የደረጃ ማሻሻያ የግንባታ ሥራ በማከናወን ላይ ይገኛል።

በተለይ በመጪዎቹ ሦስትና አራት ዓመታት የስፖርት ማዘውተሪያ ችግሮችን በመጠኑም ቢሆን ለመቀነስና የስፖርቱንም ህብረተሰብ ፍላጐት በዘላቂነትና በአስተማማኝ ሁኔታ ለማሟላት የሚያስችል ዕቅድ ተዘጋጅቶ በሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ተግባራዊ በመደረግ ላይ ነው።

በየክልሉ በመገንባት ላይ ካሉት ዘመናዊ ስታዲየሞች በከፊል (መቀሌ)

በቅርቡ ስራ የሚጀምረው የስፖርት አካዳሚ ገጽታ በከፊል

Page 48: ˆ - 3rd All Ethiopia  · PDF fileየጥንቱ የግሪክ ኦሊምፒክ መጫወቻ

48

የመላ አፍሪካ ጨዋታዎች እና የኢትዮጵያ ተሳትፎ

ዳንኤል ኃይለ

የመላ አፍሪካ ጨዋታዎች

እ.ኤ.አ በ1963 በአዲስ አበባ የተሰበሰቡ ሰላሳ የሚሆኑ የአፍሪካ መሪዎች የመላው አፍሪካ ጨዋታዎች እንዲካሄድ ተስማሙ፡፡ ይህንኑ ተግባራዊ ለማድረግ በስብሰባው ማብቂያ ላይ በሁለት አመት ጊዜ

ውስጥ ውድድር የሚያዘጋጅ አንድ ኮሚቴ ተሰየመ፡፡ በዚህ መሰረት እ.ኤ.አ ሐምሌ 18/1965 የመጀመሪያው መላ አፍሪካ ጨዋታዎች በኮንጎ ብራዛቪል ከተማ ተካሄደ፡፡

ይህ የአፍሪካ ኦሊምፒክ የሆነው የመላ አፍሪካ ጨዋታዎች በአፍሪካ ከፍተኛ የስፖርት ምክር ቤት (SCSA) መሪነት በየአራት አመቱ ይከናወናል፡፡ በዚህ ውድድር ላይ የተለያዩ አገሮችን ወክለው የሚመጡ የስፖርት ልዑካኖች የሚገኙበት መድረክ በመሆኑ ለህዝቦች የርስ በርስ ግንኙነት፣ ለሠላማዊ ፉክክር ፣ለአንድነት፡ ለመቻቻልና ለመከባበር እንዲሁም ባህላቸውን ለማስተዋወቅ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው፡፡ጨዋታዉ በአንዳንድ ምክንያቶች ከመስተጓጎሉ በስተቀር እስከ አሁን ዲረስ አስር ጊዜ ተካሂዷል፡፡ በእነዚህ ጊዜያትም የተሳታፊ አገሮች ፣ስፖርተኞችና

ውድድር የሚካሄድባቸው የስፖርት ዓይነቶች ብዛት እየጨመረ መጥቷል፡፡

ኢትዮጵያ ከሐምሌ 18-25/1965 በኮንጎ ብራዛቢል የተካሄደውን አንደኛ መላ አፍሪካ ጨዋታዎች በአትሌቲክስና ብስክሌት የተሳተፈች ስትሆን በ10,000 ሜትር በአትሌት ማሞ ወልዴ የነሐስ ሜዳሊያ በማግኘት ከአፍሪካ 3ኛ ደረጃ በመያዝ ውድድሯን አጠናቃለች፡፡

እ.ኤ.አ. ከመስከረም 1-18/2011 በሞዛምፒክ ዋና ከተማ ማፑቶ የተካሄደውን 10ኛው የመላው አፍሪካ ጨዋታዎች ኢትዮጵያ በ11 የስፖርት ዓይነቶች (በአትሌቲክስ፣ ፓራ ሊምፒክ፣ ጠረጴዛ ቴኒስ፣ቴኒስ፣ ቦክስ፣ ባድሜንተን፣ ብስክሌት፣ ቼስ፣ ካራቴ፣ ወርልድ ቴኳንዶ ፣ውሃ ዋና ስፖርቶች) በመሳተፍ በአጠቃላይ ውጤት ከአፍሪካ ዘጠነኛ ደረጃ በማግኘት ውድድሯን አጠናቃለች፡፡

በ10ኛው የመላ አፍሪካ ጨዋታዎች የአገራችን የተሳተፈችባቸው የስፖርት ዓይነቶች ብዛት ካለፉት ዘጠኝ የመላ አፍሪካ ጨዋታዎች የላቀ ነበር፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ከመቼውም ጊዜ በተሻለ ሁኔታ በማፑቶ የተገኘው የሜዳሊያ ብዛት ከፍተኛ ቁጥር የያዘ ሲሆን

Page 49: ˆ - 3rd All Ethiopia  · PDF fileየጥንቱ የግሪክ ኦሊምፒክ መጫወቻ

49

አገራችን በ11 የስፖርት ዓይነቶች ተሳትፋ በአራት የስፖርት ዓይነቶች ማለትም በአትሌቲክስ ፣በወርልድ ቴኳንዶ፣ፓራሊምፒክና ቦክስ ሜዳሊያዎችን አግኝተናል፡፡ በአጠቃላይ 26 ሜዳሊያዎችን በማግኘት አበራታች ውጤት ተመዝግቧል፡፡

በዚህ ውድድር ላይ የተመዘገበው ውጤት የላቀ አስተዋጽኦ ከነበረባቸው የስፖርት ዓይነቶች መካከል አትሌቲክስ ከፍተኛውን ድርሻ ይወስዳል፡፡ አጠቃላይ ከተገኙት 6 የወርቅ ሜዳሊያዎች በሙሉ የተገኙት በአትሌቲክስ የስፖርት ዓይነት ነው፡፡ አትሌት ኢብራሂም ጀላን በ2011 በዳጉ የተካሄደውን የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በ10 ሺ ሜትር አስደናቂ

ውጤት ባስመዘገበበት ማግስት በማፑቶ በ10 ሺ ሜትር የዳጉ ድሉን ደግሟል፡፡ የወርቅ ሜዳሊያ በማስገኘት ለውጤቱ ማማር ከፍተኛ አስተዋጽኦ ካደረጉ አትሌቶች አንዱም ሆኗል፡፡ በተመሳሳይም አትሌት ሱሌ ኡትራ በ5000 ሜትርና በ10 ሺ ሜትር፣ አትሌት ብርሃኑ ጌታሁን በ3000 ሜትር ፣ለሊሳ ዲሳሳ እና ማሬ ዲባባ በግማሽ ማራቶን የወርቅ ሜዳሊያ በማግኘት አገራችን ከዚህ በፊት ያገኘችውን የሜዳሊያ ብዛት ከፍ እንዲል አስተዋጽኦ አድርገዋል፡፡

በአጠቃላይ ኢትዮጵያ በ10ኛው የመላው አፍሪካ ጨዋታዎች በጥቂት ስፖርተኞችና የስፖርት ዓይነቶች አመርቂ ውጤት አስመዝግባለች፡፡

በ10ኛው መላው አፋሪካ ጨዋታዎች ወርቅ ካስገኙ አትሌቶች መካከል አትሌት ኢብራሒም ጄይላን እና ሱሌ ኡቱራ

አብነቶች

Page 50: ˆ - 3rd All Ethiopia  · PDF fileየጥንቱ የግሪክ ኦሊምፒክ መጫወቻ

50

ተ.ቁ.

ውድድር የተካሄደበት

አገር

ውድድር የተካሄደበት ጊዜ

(እ.ኤ.አ.)

ሜዳሊያ ያገኘችበት የስፖርት ዓይነት

ሜ ዳ ሊ ያ

ደረጃ

ጠቅላላ የተሳተፈችበት

የስፖርት ዓይነት

ወርቅ ብር ነሐስ ድምር

1 ኮንጎ ብራዛቪል

ከሐምሌ18-25/1965

አትሌቲክስ፣ ብስክሌት -- -- 1 1 3ኛ 2

2 ናይጄሪያ ሌጎስ

ከጥር 7-18/1973 አትሌቲክስ፣ ቦክስ፣ ብስክሌት፣ ጠረጴዛ ቴኒስ

4 3 6 13 8ኛ 5

3 አልጀሪያ አልጀርስ

ከሐምሌ 13-28/2004

አትሌትክስ፣ቦክስ 1 3 3 7 14ኛ 4

4 ኬንያ ናይሮቢ

ከነሐሴ 1-12/1987

አትሌቲክስ፣ ቦክስ፣ብስክሌት

3 5 3 11 8ኛ 7

5 ግብፅ ካይሮ ከመስከረም 20 እስከ ጥቅምት 1/1991

አትሌቲክስና ቦክስ 4 3 5 12 9ኛ 8

6 ዚምባቡዌ ሐራሪ

ከመስከረም13-23/1995

አትሌቲክስ፣ ጠረጴዛ ቴኒስ፣ክብደት ማንሳት

1 5 6 12 13ኛ 6

7 ደቡብ አፍሪካ ጁሀንስበርግ

ከመስከረም 10-19/1999

አትሌቲክስ፣ ቦክስ፣ ብስክሌት፣ ጠረጴዛ ቴኒስ፣ ክብደት ማንሳት

6 4 4 14 9ኛ 6

8 ናይጀሪያ አቡጃ

ከጥቅምት 4-18/2003

አትሌቲክስ ቦክስ፣ ወርልድ ቴኳንዶ

6 8 7 20 8ኛ 3

9 አልጀሪያ አልጀርስ

ከሐምሌ 11- 23/2007

አትሌቲክስ፣ ወርልድ ቴኳንዶ ቼስ፣ፓራሊምፒክ

4 5 10 19 11ኛ 4

10 ሞዛምፒክ ማፑቶ

መስከረም 1- 18/2011

አትሌቲክስ፣ ወርልድ ቴኳንዶ፣ፓራሊምፒክ፣ ቦክስ

6 9 11 26 9ኛ 11

ኢትዮጵያ በመላ አፍሪካ ጨዋታዎች

Page 51: ˆ - 3rd All Ethiopia  · PDF fileየጥንቱ የግሪክ ኦሊምፒክ መጫወቻ

መ ንግስት የአምስት አመት የዕድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ውስጥ የሀገሪቱን የኃይል አቅርቦት በአምስትእጥፍ ለማሳደግ የተቀመጠውን

ግብ ለማሳካት ታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ የተጀመረ ሲሆን እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ባለው አቅም የመንግስት ቦንድ በመግዛትና ድጋፎችን በማድረግ በተፈጥሮአዊ ሀብታችን በአግባቡ ለመጠቀም የተነደፈው ለታሪክ የመጀመሪያ የሆነውን የሀገሪቱን በዜጎች ከዳር እስከ ዳር የነቀነቀው ይህ ታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ የተለያዩ ተሳትፎና ድጋፎች ተደርጓል በመደረግ ላይ ይገኛል።

ስፖርት እና የሰው ልጅ፣ ስፖርት እና ሀገር የማይነጣጠሉ በመሆኑ ከዳር እስከ ዳር ሕዝቡ የነቀነቀው ለታላቁ የህዳሴ ግድብ ያሳየውን መነቃነቅ በስፖርት ሴክተር በመድገም የስፖርት ኮሚሽን ሰራተኞች የስፖርት ማህበራት፣ የኦሎምፒክ ኮሚቴ፣ ብሔራዊ አሰልጣኞች እና ታዋቂ አትሌቶች በድጋፍ እና በቦንድ ግዥ ከ2ዐ,911,ዐ46/ ከሃያ ሚሊዮን ዘጠኝ

መቶ አስራ አንድ ሺህ አርባ ስድስት ብር/ ለዕዳሴው ግድብ ድጋፋቸውን አድርገዋል።

ከላይ ከተጠቀሱት ድጋፎች በተጨማሪም ስፖርቱን ከማሳደግ እና ከማስፋፋት ጐን ለጐን ለህዳሴው ግድብ ግንባታ የሚሆን ገንዘብ ለማሰባሰብ

የ4 አመት መርሃ ግብር በማውጣት የስፖርት ንቅናቄዎችን በመፍጠር የግንዛቤ ማስጨበጥ ሥራዎችና የገቢ ማሰባሰቡ ተግባር በሴክተሩ እየተከናወነ ይገኛል። ።

የፌዴራል ስፖርት ኮሚሽን በሁሉም የአስተዳደር እርከን የሚገኝ የስፖርት ሴክተርን ማስተባበር እና በመደገፍ በስፖርቱ ተሳትፎ እና ንቅናቄ በማድረግ ሀገራችን በምታከናውነው የልማት እቅዶች ውስጥ ጉልህ አስተዋፅኦ በማድረግ ላይ መሆኑን መረዳት ይቻላል።

ልዩ ልዩ

የስፖርት ሴክተር እና የህዳሴው ግድብ ተሳትፎ

ለሜሳ ወዩማ

Page 52: ˆ - 3rd All Ethiopia  · PDF fileየጥንቱ የግሪክ ኦሊምፒክ መጫወቻ

52

ሆሳዕና ደሳለኝ

ስፖርታዊ ጨዋነት"ማለት በስፖርታዊ ውድድሮች ላይ ተሳታፊ የሆኑት አካላት ተወዳዳሪዎች፣ አሰልጣኞች፣ ዳኞች፣ ተመልካቾች፣ አመራሮች ወዘተ የጨዋነት መንፈስን መሠረት በማድረግ ጨዋታዎችን

ማካሄድ ማለት ነው። በዚህም መሠረት ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ተጀምረው እሰኪፈፀሙ ድረስ መንግሥታዊም ሆነ መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት፣ መገናኛ ብዙኋን፣ የስፖርታዊ አደረጃጀት አመራሮች ተወዳዳሪዎች፣ ዳኞች፣ ተመልካቾች ወዘተ. ለስፖርታዊ ጨዋነት መስፈን የየራሳቸው የሆነ ድርሻ አላቸው። ድርሻቸውን በጨዋነት መንፈስ መወጣት ደግሞ በመወዳዳሪያ ሥፍራዎች የህግ የበላይነት እንዲሰፍን ያደርጋል። የህግ የበላይነት ሲባል ለስፖርት ሥርዓትና ደንቦች መገዛት፣ መቻቻል፣ መረዳዳት መስማማት፣ የዘለፋ እና የትንኮሳ ቃላቶችን ያለመጠቀም ወዘተ. ያጠቃልላል።

የማዘውተሪያ ሥፍራዎች በርካታ ስፖርተኞች የሚፈልቁበት፣ ህፃናት፣ ወጣት፣ አዛውንት ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን በማየት የሚዝናኑበት ተመራጭ

ሥፍራ ነው። በዚህ ተወዳጅ ቦታ ከስፖርታዊ ጨዋነት ውጭ የሆኑና ያልተፈለጉ ቃላቶች በዳኛ፣ በግለሰቦች፣ በቡድን ወዘተ. ላይ መሳደብ (ማስደመጥ)፣ ለዘለቄታዊ የምንገለገልባቸውን ወንበሮችና ሌሎች ቁሳቁሶች መስበር ከስፖርታዊ ጨዋነት ውጭ የሆነ ተግባሮች ናቸው። እነዚህ አሉታዊ ተግባሮች ደግሞ የሰላም መደፍረስን፣ የሀብት (ንብረት) ብክነትን፣ ህፃናት፣ ሴቶች፣ አካል ጉዳተኞች፣ ነፃ ተመልካቾች ወዘተ. በማዘውተሪያ ሥፍራ በመገኘት የሚያገኙትን ደስታ ያሳጣሉ። ስለዚህ ስፖርታዊ ጨዋነት በውድድር ሥፍራዎች እንዲሰፍን ሁሉም ባለድርሻ አካል የበኩሉን መወጣት አለበት። በተለይም ተቋማት፣ አሰልጣኞች፣ ዳኞች፣ ተወዳዳሪዎችና ደጋፊዎች ከፍተኛ ኃላፊነት አለባቸው።

በአደረጃጀት ሂደት ውስጥ ክለቦች ወይም ድርጅቶች ለስፖርታዊ ክንውኖች ጉልህ ሚና አላቸው። አስተዋጽኦቸውም መዋዕለ ንዋይ በማፍሰስና የሰው ኃይልን በመጠቀም ለስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች እምርታ የበኩላቸውን ማድረግ ላይ የተመሠረተ ነው። ከዚህ በተጨማሪም ለሀገራችን ስፖርት ዕድገት ያላሰለሰ ጥረት ያደርጋሉ። እነዚህን ጥረቶችና ትጋቶች እውን ለማድረግ፡-

ስፖርታዊ ጨዋነት

Page 53: ˆ - 3rd All Ethiopia  · PDF fileየጥንቱ የግሪክ ኦሊምፒክ መጫወቻ

53

1. ውድድሮች በስፖርታዊ ጨዋነት ለመከናወናቸው የቅርብ ክትትል ማድረግ ፣

2. በማንኛውም የማስተማሪያ መድረክ በመጠቀም የስፖርታዊ ጨዋነትን ፅንሰ ሃሳብ ማስተማር፣ ማንኛውንም ዓይነት ፀብ አጫሪነትን በቁርጠኝነት መዋጋት ወዘተ. ናቸው፡፡

አሰልጣኝ መሪና የሙያ አባት ነው። ከተወዳዳሪ ስፖርተኞች ጋር ቅርበት ያለው፣ ጠንካራ ጎኖች እንዲጐለብቱ፣ ደካማ ጐኖች እንዲቀነሱ ክትትል የሚያደርግና ኃላፊነት የተጣለበት ባለሙያ ነው። ለስፖርታዊ ጨዋነት መርህ ራሱን በማነፅና ለተወዳዳሪዎቹ ትምህርት በመስጠት ቀዳሚ ነው። ስለዚህ ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ነጥቦች እንዲተገበር ይመከራል።

1. በስፖርታዊ ጨዋነት ራስን ማነፅ፣ ለሌሎች አርአያ መሆን፣

2. ተወዳዳሪዎችን በስፖርታዊ ጨዋነት ማነፅ፣ ማስተካከል፣

3. ከስፖርታዊ ጨዋነት ውጭ ተግባራትን የሚፈፅሙ ተወዳዳሪዎችን በቅርብ መከታተል፣ እርምት እንዲያደርጉ መምከር፣ ርምጃ መውሰድ፣

4. በውድድር ሜዳ ለሚከሰቱ ማናቸውም ጉዳዮች ተረጋግቶ፣ በማረጋጋት ነገሮችን በተገቢው መንገድ ማየት፣

5. የጨዋታ ደንቦች ማንበብ፣ ለተወዳዳሪዎች ስለደንቦች ግንዛቤ መስጠት የመሳሰሉት ናቸው።

ስለዚህ አሰልጣኝ ለስፖርታዊ ጨዋነት መስፈን የበኩሉን ድርሻ የሚወጣ ባለአደራ ነው ማለት ይቻላል።

ለስፖርታዊ ጨዋነት መኖር ጉልህ ሚና ከሚጫወቱት አካላት ዳኞች ይጠቀሳሉ። ዳኞች የውድድሩን ሂደት የሚቆጣጠሩ፣ ተገቢውን ውሳኔ የሚወሰኑ፣ አዎንታዊና አሉታዊ አተያዮችን በፀጋ የሚቀበሉ የሜዳው ላይ ንጉሶች ናቸው። (ንጉስነታቸው የመወዳደሪያ ህግን ከማስፈፀም አኳያ መሆኑ ሳይዘነጋ ነው) ከዚህ በተጨማሪም ትልቅ ኃላፊነት የተጣለባቸው አካላት ናቸው። ለስፖርታዊ ጨዋነት መስፈንም የበኩላቸው ድርሻ የሚወጡ ሲሆኑ፣ የሚከተሉትን ነጥቦችን ይተገብራሉ።

1. ያለአንዳች አድልዎና ተጽዕኖ የዳኝነት ህጉ ተከብሮ ውድድሩ እንዲፈፀም ማድረግ፣

2. የዳኝነቱን ተግባር ለህጉ ተገዢ በመሆን በጥንቃቄ ማስፈፀም፣

3. ዳኛና የዳኛ ምስክር እርሱ ብቻ መሆኑን በመገንዘብ ዳኝነቱን በህጉ መሠረት መምራት፣

4. ስህተት ሲፈፅሙ ፈጥኖ የማያወላውልና የማያጠያይቅ ውሳኔ መስጠት፣

5. የዳኝነት ህግና ደንቦችን ጠንቅቆ በዝርዝር ማወቅና በተግባር መተርጎም፣

6. ድፍረት፣ ጥሩ ሥነ ምግባር፣ በራስ መተማመን፣ በስብዕናው ውስጥ እንዲሰፍን ማድረግ፣ በሚያጫውቱበት ጊዜ ከሜዳ ውጭ አለማሰብና አለማሰላሰል ናቸው፡፡

ከዚህ በተጨማሪ በማዘውተሪያ ሥፍራዎች

Page 54: ˆ - 3rd All Ethiopia  · PDF fileየጥንቱ የግሪክ ኦሊምፒክ መጫወቻ

54

ዋና ተዋንያን የሚሆኑት ተወዳዳሪዎች ተዋናይነታቸው በስፖርታዊ እንቅስቃሴ ያዳብሩትን ክህሎት ለለበሱት መለያ ዋጋ የሚሰጡበት፣ በማዘውተሪያ ሥፍራ ለተገኘው ተመልካችም መዝናናት የሚፈጥሩበትና ለስፖርቱ ዕድገት የበኩላቸውን ድርሻ የሚወጡበት መሆኑ ነው። ስለዚህ ይህን አስተዋጽኦዎቻቸውን ከግብ ለማድረስ ከዚህ በታች ስለ ስፖርታዊ ጨዋነት መስፈን የተጠቀሱትን ነጥቦች እንዲተገበሩ ይመከራል።

1. ከውድድሩ በፊት የውድድር ደንብንና መመሪያውን ጠንቅቆ ማወቅ፣

2. የዳኛን ውሳኔ መቀበልና ማክበር፣ ከዚህ በተጨማሪም ለቡድን ባልደረቦች ፣ለተቃራኒ ተወዳዳሪዎችና ለተመልካቾች ተገቢውን አክብሮት መስጠት፣ የስፖርታዊ ጨዋነት አስተማሪ መሆን፣

3. ለማሸነፍ ሲባል አለማታለል፣ የጨዋታ ህጐችንና መመሪያዎችን አለመጣስ፣

4. የዳኛን ውሳኔ በጭቅጭቅና አግባብ ባልሆነ መንገድ ለማሻርና የራስን ፍላጐት ለማርካት መሞከርን ማስወገድ፣

5. ማሸነፍንም ሆነ መሸነፍን በፀጋ መቀበል፣ እራስን ማዘጋጀት፣

6. በተመልካቾችና በአሰልጣኝ እንዲሁም በመሪዎች ተፅእኖ ህገ ወጥ ጨዋታን ለማከናወን አለመሞከር ናቸው፡፡

ስፖርታዊ ጨዋነትን ለማስፈን ደጋፊዎች፣ ታዛቢዎች፣ አዘጋጆች የላቀ ድርሻ አላቸዉ። ምልከታቸውም የአንድ ወገን፣ የተገላቢጦሽ፣ ሁሉን አቀፍ ወይም ነፃ ተመልካቾች ይሆናሉ። በእነዚህ የአተያይ ሂደት ተመስርተውና በውድድር ማዘውተሪያ ሥፍራዎች ተገኝተው የድርሻቸውን ይወጣሉ። ለሚደግፉአቸው ቡድን፣ ክለብ፣ ሀገር ወዘተ. ያዜማሉ፣ ያሞግሳሉ፣ ብሎም ደስታቸውን ይገልፃሉ። የማዘውተሪያ ሥፍራ ውበቱና ድምቀቱ የተመልካች ድጋፍ አሰጣጥ፣ሆሆታ ወዘተ. ነውና። ስለዚህ እነዚህ የስፖርታዊ ጨዋነት መንፈስን የተከተሉ ቅዱስ አላማዎች ፀንተው እንዲኖሩ ያስፈልጋል።

ተመልካቾች የማዘውተሪያ ሥፍራዎች ውበቶችና ድምቀቶች እንደሆኑ ሁሉ በታቃራኒው መንገድ ላልተገባ ፀባይ የሚዳረጉ አይታጡም። እነዚህ ያልተፈለጉ ተግባራትን ለማስወገድ ደግሞ ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ነጥቦች መተግበር ያሻል።

1. ለጥሎችና ለጥፋቶች አበረታችና ደጋፊ

አለመሆን፣2. ማሸነፍና መሸነፍን በጨዋነት መንፈስ

መቀበል፣3. ተጫዋቾች ለስፖርታዊ ጨዋነት እራሳቸውን

እንዳያስገዙ መገፋፋትና በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ትምህርት መስጠት፣

4. ጥሩ ለተጫወተ በአግባቡ ድጋፍ መስጠት፣ 5. የራስን የግልፍተኝነት የውስጥ ስሜት

መቆጣጠር 6. በተሰጠ ፍርድና ውሳኔዎች ላይ ሕግንና

ደንብን ሳያውቁ፣ ሳያገናዝቡ ለመተቸት አለመሞከር፣

7. ጠባብነትና፣ ትምክህትን ማስወገድና ለዚህም መንስኤ የሚሆኑትን ሁሉ ከራስ ማስወገድ፣ ከዚሁ ሁሉ ነፃ የሆነና ጥሩ አርአያነት ያለው ተመልካች ለመሆን እራስን ማዘጋጀት ናቸው።

በአጠቃላይ “ስፖርታዊ ጨዋነትን ለማስፈን ሁሉም የባለድርሻ አካላት ተያይዞና ተደጋግፎ በመሥራት የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅዱን እናሳካለን” መልዕክታችን ነው!

Page 55: ˆ - 3rd All Ethiopia  · PDF fileየጥንቱ የግሪክ ኦሊምፒክ መጫወቻ

55

c?ƒ ›ƒK?„‹ KSËS]Á Ñ>²? u*K=Uú¡ ¨<ÉÉ` ¾}d}ñuƒ

እ.›?.›. u1928 û]e u}ŸH@Ũ< ¾*K=Uú¡ Ñ@Ue Là ’u`::

- ›=ƒÄåÁ u*K=Uú¡! 1995! Ñê 129

T@¡c=¢ c=+ u}ŸH@Ũ< ¾*K=Uú¡ እÓ` Ÿÿe ¨<ÉÉ` ŸS\ƒ

Ç™‹ ¨<eØ ›=”}`“i“M Ç— Y¿U ታ[k˜ ’u\:: ¾S\ƒ

¨<ÉÉa‹U “ÃÎ]Á“ w^²=M”! ð[”dÔ“ Íû”” እ”Ç=G<U

KÓTi õéT@ ÁKñƒ” T@¡c=¢”“ u<MÒ]Á” c=J”! u¨p~U

›É“qƒ” ›Ó˜}ªM::

- ›=ƒÄåÁ u*K=Uú¡!1995! Ñê 129

K[»U Ñ>²? ¨<ጤታT

KSJ” ¾¯LT ꓃! ¾ÓM

Ø[ƒ! ƒ°Óeƒ! ^e”

G<MÑ>²? T²Ò˃! ኃLò’ƒ

SgŸU ÁeðMÒM::

›Ñ_ KT^„” \Ý ¨Å

T@¡c=¢ ¾LŸ‹˜ ËU_

እ”Çg`Ø dÃJ” እ”ÅÚ`e

uSJ’< ÓÈታÀ” KS¨×ƒ

እ¾}cn¾G< Ú[eŸ<::

ከአትሌቶች አንደበት

ለግንዛቤ

Å^`~ ~K<

Д eቴó” ¡Iª]

Page 56: ˆ - 3rd All Ethiopia  · PDF fileየጥንቱ የግሪክ ኦሊምፒክ መጫወቻ

56

ትብብርንግንኙነትንለሕግ ተገዥነትንችግር አፈታትንመግባባትን መተዋወቅንአመራርን ጓደኛ ማክበርንፅዳትንአሸናፊነትንተሸናፊነትን

ውድድር መምራትንመረዳዳትንእምነትንታማኝነትንእራስ መግዛትን ቻይነትንጥቃት መቋቋምንየቡድን ሥራን ሥነ ሥርዓትበራስ መተማመን

ለሜሳ ወዩማ ምንጭ፡- ስፖርት ለልማትና ለሰላም (የተባበሩት መንግሥታት 2005)

ስፖርት ውስጥ የምንማረው ክህሎትና የምናገኘው ጥቅም