2 3 - phe ethiopiaphe-ethiopia.org/pdf/toolkit_semien_amharic.pdf · 2 3 2006 ዓ/ ም አዲስ...

52

Upload: dodieu

Post on 20-Feb-2018

264 views

Category:

Documents


22 download

TRANSCRIPT

Page 1: 2 3 - PHE Ethiopiaphe-ethiopia.org/pdf/Toolkit_Semien_amharic.pdf · 2 3 2006 ዓ/ ም አዲስ ... ፈንድ ሲሆን ለተደረገው ድጋፍ የኢትዮጵያ ሥነ-ህዝብ&
Page 2: 2 3 - PHE Ethiopiaphe-ethiopia.org/pdf/Toolkit_Semien_amharic.pdf · 2 3 2006 ዓ/ ም አዲስ ... ፈንድ ሲሆን ለተደረገው ድጋፍ የኢትዮጵያ ሥነ-ህዝብ&

2 3

2006 ዓ/ምአዲስ አበባ፤ ኢትዮጵያ

አሳታሚ

የኢትዮጵያ ሥነ-ህዝብ& ጤናና አካባቢ ጥምረትስልክ፡ +251 -11-663 0833/ +251-11-860 8190ፋክስ፡ 251-11-663 8127የመ.ሣ.ቁ፡ 4408አዲስ አበባ፤ ኢትዮጵያ

አርታኢ

ነጋሽ ተክሉታደሰ ኃይሉኃይለ ልዑል ነጋሽ

ምሥጋና

ይህ ፅሁፍ ሰፋ ያለ ተደራሽነት እንዲኖረው በማሰብ ለሕትመት የሚያስፈልገውን ወጪ በገንዘብ የደገፈው ሥልታዊ የአየር ንብረት ተቋማት መርሃግብር (SCIP) ፈንድ ሲሆን ለተደረገው ድጋፍ የኢትዮጵያ ሥነ-ህዝብ& ጤናና አካባቢ ጥምረት (PHE EC) ልባዊ ምስጋና ያቀርባል፡፡

የዚህን ፅሁፍ የኤሌክትሮኒክስ ቅጂ ከሚከተለው ድህረ ገጽ ማግኘት ይቻላል፡፡www.phe-ethiopia.org

Page 3: 2 3 - PHE Ethiopiaphe-ethiopia.org/pdf/Toolkit_Semien_amharic.pdf · 2 3 2006 ዓ/ ም አዲስ ... ፈንድ ሲሆን ለተደረገው ድጋፍ የኢትዮጵያ ሥነ-ህዝብ&

2 3

ማውጫ1. የዓለም ሙቀት መጨመር---- 7

1.1. የዓለም የሙቀት መጨመር ማለት ምን ማለት ነው?---- 7 1.2. የሙቀት መጠን እንዲጨምር የሚያደርግ ተፈጥሯዊ የአየር ንብረት ለውጥ---- 91.3. የከባቢ አየር ይዘትን የሚለውጡ የሰዎች ተግባራት---- 101.4. የሙቀት መጨመር ተፅዕኖ የሚያስከትል የከባቢ አየር ይዘት መለዋወጥ---- 11

2. የአየር ንብረት ለውጥ---- 14

2.1. የአየር ንብረት ለውጥ ማለት ምን ማለት ነው?---- 142.2. የአየር ንብረት ለውጥ አመጣጥ---- 14 2.3. ለአየር ንብረት ለውጥ ያለው የተጋላጭነት ሁኔታ---- 152.3.1. የመቋቋም አቅም---- 16 2.3.2. የማገገም አቅም---- 172.3.3. አደገኛ ሁኔታ---- 172.3.4. ሥጋት---- 182.3.5. አደጋ---- 182.3.6. የአደጋና ሥጋት ቁጥጥር---- 182.4. የአየር ንብረት ለውጥ ተፅእኖዎች----19 2.5. የአየር ንብረት ለውጥን መቀነስ---- 23 2.6. የአየር ንብረት ለውጥን መቋቋም----26

3. የካርበን ዑደት እና የግሪንሀውስ ተጽእኖ---- 27

3.1. ደንና የአየር ንብረት ለውጥ---- 273.2. ደንና የካርበን ዑደት---- 273.3. የደኖች ካርበን አምቆ የመያዝ ሁኔታ---- 283.4. የካርበን ዑደት---- 283.5. የግሪንሀውስ ጋዝ ተፅዕኖ---- 28

4. የአየር ንብረት ለውጥ እና ብዝሃ ህይወት---- 31 4.1. የአየር ንብረት ለውጥ በብዝሃ ህይወት ላይ የሚኖሩት ተፅዕኖዎች----314.2. በብዝሃ ሕይወት ሥርጭት ላይ ተፅዕኖ ያላቸው ሌሎች ሁኔታዎች----334.3. የአየር ንብረት ለውጥ የመቋቋም ጥረቶች ለብዝሃ ህይወት ጥበቃና እንክብካቤ---- 33

Page 4: 2 3 - PHE Ethiopiaphe-ethiopia.org/pdf/Toolkit_Semien_amharic.pdf · 2 3 2006 ዓ/ ም አዲስ ... ፈንድ ሲሆን ለተደረገው ድጋፍ የኢትዮጵያ ሥነ-ህዝብ&

4 5

5. የኢትዮጵያ ጥበቃ ቦታዎች---- 35

5.1. የጥበቃ ቦታዎች መግለጫ---- 355.1.1. የጥበቃ ቦታዎች ጠቀሜታ---- 355.1.2. የጥበቃ ቦታዎችን በተመለከተ ያሉ ዋና ዋና ስጋቶች---- 365.2. የዱር እንስሳት ጥበቃ ቦታዎች ዓይነትና ሥርጭት---- 375.3. የጥበቃ ቦታዎች የአየር ንብረት ለውጥን በመቋቋም ለአረንጓዴው ልማት ያላቸው አስተዋጽኦ---- 415.3.1. የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋም የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ስትራቴጂ---- 425.3.2. በደን ልማት ዘርፍ የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ዋነኛ ትኩረት---- 435.3.3. በደን ልማት ዘርፍ ለ2002 የተያዙ የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ልማት---- 44

ማጣቀሻዎች---- 46

Page 5: 2 3 - PHE Ethiopiaphe-ethiopia.org/pdf/Toolkit_Semien_amharic.pdf · 2 3 2006 ዓ/ ም አዲስ ... ፈንድ ሲሆን ለተደረገው ድጋፍ የኢትዮጵያ ሥነ-ህዝብ&

4 5

LIST OF ACRONYMS

ADB Asian Development BankASEAN Association of South East Asian NationsASFN ASEAN Social Forestry NetworkCBD Convention on Biological DiversityCRGE Climate Resilient Green EconomyDRR Disaster Risk ReductionEPA Environmental Protection AuthorityEWCA Ethiopian Wildlife Conservation AuthorityMDGs Millennium Development GoalsGHG Green House GasGtCO2e Giga tones of carbon dioxide equivalentGt Giga tones(equivalent to billion metric tones)GTP Growth and Transformation PlanIPCC Intergovernmental Panel for Climate ChangeMtCO2e Mega tones of carbon dioxide equivalentMt Mega tones(equivalent to million metric tones)NAPA National Adaptation Programme for Action° C Degree CelsiusOECD Organization for Economic Co-operation and DevelopmentPHE EC Population , Health and Environment Ethiopia ConsortiumREDD Reducing emissions from deforestation and degradationSNNPR Southern Ethiopia Nations, Nationalities, and Peoples Regional StateUNEP United nations Environmental ProgrammeUNFCC United Nations Framework Convention on Climate ChangeWMO World Meteorological OrganizationWTO World Trade Organization

Page 6: 2 3 - PHE Ethiopiaphe-ethiopia.org/pdf/Toolkit_Semien_amharic.pdf · 2 3 2006 ዓ/ ም አዲስ ... ፈንድ ሲሆን ለተደረገው ድጋፍ የኢትዮጵያ ሥነ-ህዝብ&

6 7

Page 7: 2 3 - PHE Ethiopiaphe-ethiopia.org/pdf/Toolkit_Semien_amharic.pdf · 2 3 2006 ዓ/ ም አዲስ ... ፈንድ ሲሆን ለተደረገው ድጋፍ የኢትዮጵያ ሥነ-ህዝብ&

6 7

1. የዓለም የሙቀት መጨመር

1.1. የዓለም የሙቀት መጨመር ምንድር ነው?

የዓለማችን ሙቀት እየጨመረ ይገኛል፤ አየር ንብረቱም እየተለወጠ ነው፡፡ የሙቀት መጠን በሁሉም ወቅቶች በየብስም ሆነ በባህር ላይ እየጨመረ ነው፡፡ ከባድ ዝናብ

የመጣል ክስተት ከወትሮ የጨመረ ሲሆን ይህ ደግሞ የጎርፍ መጥለቅለቅን በማባባስ ላይ ይገኛል፡፡ ከፍተኛ የሆነ የሙቀት መጠኑም ትነት እንዲጨምር እና የአፈር እርጥበት እንዲሟጠጥ በማድረግ ድርቅን እያባባሠ ይገኛል፡፡ የባህር በረዶ ከአርክቲክ ዙሪያ ጠረፍ እየሸሸ ሲሆን፣ በአልፕስ፣ በአላስካ እና በግሪንላንድ እንዲሁም በዓለም ዙሪያ በሚገኙ ዝቅተኛ ላቲትዩድ የተራራ ሰንሰለቶች የሚገኘው የበረዶ ግግርም በፍጥነት እየቀለጠ ይገኛል፡፡ የባህር ወለል ከፍ እያለ ሲሆን የመጨመር ሁኔታውም እየፈጠነ እንደሆነ ይታመናል፡፡ የአየር ንብረት ትንበያዎች እንዲሚጠቁሙት ዓለማችንን ወደፊት የከፋ የአየር ንብረት ለውጥ ይጠብቃታል፡፡

እየተለወጠ ያለው የአየር ንብረት በአካባቢ እና በህብረተሰብ ላይ የሚያስከትላቸው ተፅዕኖዎች እየጠነከሩና ውስብስብ እየሆኑ ይሄዳሉ፡፡ የሙቀት መጨመርን ተከትሎ የእንስሳትና የዕፅዋት ዝሪያዎች በምድር ዋልታዎች አቅጣጫ በመሸሽ ላይ ይገኛሉ፤ ከፍታ ባላቸው ቦታዎችም መታየት ጀምረዋል፡፡ በባህር ዳርቻዎች ላይ በሚገኙ ከተሞች የህዝብ ቁጥር መብዛት እና የልማት ሥራዎች መስፋፋት እነዚህን ህዝቦች ለባህር ወለል መጨመር እና ለማዕበል ተጋላጭነት እንዲጨምር አድርጓል፡፡ እንዲሁም የዓለም ሙቀት መጨመር ከባድ ማዕበሎች እንዲከሠቱ እያደረገ ነው፡፡ የአየር ንብረት ለውጥ እያየለ ሲመጣ የህብረተሰብ የኑሮ መሠረት የሆኑ የተፈጥሮ እና የሥነምህዳር ስርጭት በከፍተኛ ሁኔታ እንዲታወክ ያደርጋል፡፡ የምግብ ሠብሎችን በቀጣይነት የማምረት ሁኔታ የሚወሠነው የተመቻቸ ሁኔታ የሚፈጠርላቸውን አረሞች እና ፀረ ሠብል ተባዮችን ለመቆጣጠር የሚያስፈልገው አቅም ባለመኖሩ ለግብርና ሥራ የሚሆኑ ቦታዎች እና የምግብ ሰብሎችን የማምረት ሁኔታ እየተለወጡ ይሄዳሉ፡፡ በብዙ የዓለማችን አካባቢዎች መጠኑን እና ወቅቱን የጠበቀ የውሃ ሀብት የማግኘት ሁኔታ እጥረትን በሚያባብስ መልኩ የሚለዋወጥ ይሆናል፡፡ የባህር ወለል ከፍታ የመጨመር ክስተት የባህር ዳርቻዎችን በቀጣይነት የሚሸረሽር እና በዝቅተኛ ቦታዎች ለሚገኙ ደሴቶች ትልቅ ሥጋት ይሆናል፡፡

የአየር ንብረት ለውጥ ተጋላጭነትን በመቀነስ ረገድ አስፈላጊ እርምጃዎች ካልተወሠዱ በስተቀር በተደጋጋሚና ረዘም ላለ ጊዜ የሚከሠተው ጠንከር ያለ የሙቀት ሁኔታ የብዙ ሰዎችን ህይወት ለህልፈት የሚዳርግ ይሆናል፡፡ በብዙ አካባቢዎች ለወባ ትንኝ እና ለሌሎች በሽታ አስተላላፊ ነፍሣት አመቺ የሆኑ ሁኔታዎች መፈጠራቸው የተላላፊ በሽታዎች ስርጭት እንዲባባስ በማድረግ ከፍተኛ የሆነ ሥጋት የሚፈጥሩ ስለሚሆኑ የተጠናከረ የዕጽዋት የህይወት ዑደቶች፣ የፍልሰት ወቅቶች፣ የብዝሃ ህይወት ዝርያዎችና መጠለያዎቻቸው ላይ ለውጦች ሲከሠቱ ከተፈጥሯዊ የህይወት መረብ ወቅቶችና ቅደም ተከተሎች ጋር የተቆራኙት ሀገር በቀል ባህሎችና ሥርዓቶች የሚዛቡ ይሆናል፡፡

የአየር ንብረት ለውጥ በአካባቢ ላይ የሚያሣድራቸው ተፅእኖዎች የምዕተ ዓመቱን ግቦች ማሣካትን ጨምሮ የሰው ልጆችን የአኗኗር ሁኔታ ለማሻሻል በሚደረጉ ጥረቶች ውስጥ የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶች እንዲጨምሩ ያደርጋል፡፡ በሚቀጥሉት

Page 8: 2 3 - PHE Ethiopiaphe-ethiopia.org/pdf/Toolkit_Semien_amharic.pdf · 2 3 2006 ዓ/ ም አዲስ ... ፈንድ ሲሆን ለተደረገው ድጋፍ የኢትዮጵያ ሥነ-ህዝብ&

8 9

አሥርተ-ዓመታት ውስጥ ከፍተኛ የሆነ የአካባቢ አየር ሙቀት፣ የትነት ሁኔታ መዛባት እና ከፍተኛ የሆነ የአፈር እርጥበት መቀነስ መጠነ ሰፊ የሆነ መልክዓ ምድራዊ ለውጥ የሚያስከትሉ እና በብዙ አካባቢዎች የግብርና ሥራዎችን ለማካሄድ በጣም አስቸጋሪ የሆኑ ሁኔታዎች እንዲከሰቱ እና በውሃ ሀብት እጥረት ከፍተኛ የሆነ ውጥረት እንዲፈጠር ምክንያት የሚሆኑ ናቸው፡፡ ከፍተኛ የሆነ የትነት ሁኔታ መኖር እና የማዕበል ክስተቶች ከፍ ያለ የትነት ሁኔታ መኖር እና የማዕበል ክስተቶች ከፍ ባሉ ኮረብታማ አካባቢዎች፣ በሸለቆአማ ሥፍራዎች እና በባህር ዳርቻዎች አካባቢ በሚኖሩ ማህበረሰቦች ላይ ተደጋጋሚ ተፅዕኖዎችን የሚፈጥር እና አንዳንዴ ድህነትን ለማሸነፍ በዘመናት ጥረቶች የተገኙ ውጤቶችን ይጎዳቸዋል፡፡ ለሠደድ እሳት መከሰት አመቺ የሆኑ ሁኔታዎች በስፋት መፈጠራቸው ብዙ ሰዎች ከመኖሪያቸው እንዲፈናቀሉ፣ የመሠረተ ልማቶች እንዲወድሙ፣ እንዲሁም የህብረተሰቡ የህልውና መሠረት የሆኑ የተፈጥሮ ሀብቶች እንዲያልቁ ያደርጋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም የአየር ንብረት ለውጥ የአየር ብክለትን በማባባስ የሰውን ልጅ የጤና ሁኔታ ይጎዳል፣ ለሠብሎች ውድመትም መጨመር ምክንያት ይሆናል፡፡ የውሃ ትነት፣ የካርቦንዳይ ኦክሣይድ ልቀት፣ የሚቴን ልቀት፣ የኡዞን መሳሳት እና ናይትረስ ኦክሣይድ በተፈጥሮ የሚከሠት ኃይል ወደ ህዋ እንዳይመለስ እንቅፋት በመፍጠር የዓለም ሙቀት እንዲጨምር የሚያደርጉ ናቸው፡፡

እነዚህ ጋዞች በተፈጥሮ በሚገኙበት ደረጃ ላይ በመሆናቸው የሚፈጠረው የሙቀት ሁኔታ ተፈጥሯዊ የግሪንሀውስ ተፅዕኖ ተብሎ ይታወቃል፡፡ ይህ ተፅዕኖ አብዛኛው የዓለማችን ውሃ በፈሣሽ መልክ እንዲገኝ በማድረግ ህይወት ከምድር ወገብ እስከ ዋልታዎቿ ድረስ ለመኖር እንዲችል ያደርጋል፡፡ የባለፉት ዘመናት የጂኦሎጂ እና ፓሌዎክላይማቲክ (ቀደምት የአየር ንብረት መረጃዎች) መረጃዎች በግልፅ እንደሚያመለክቱት የእነዚህ ጋዞች የመጠራቀም ሁኔታ ላይ የተከሠቱት ለውጦች በዓለም ታሪክ ውስጥ ለተከሠቱት ተፈጥሯዊ የአየርን ንብረት ለውጦች ምክንያት ከሆኑት ዋና ዋና ነገሮች ውስጥ አንዱ ነው፡፡ በተፈጥሮ ከሚከሠተው ይልቅ በሰው ልጅ አማካኝነት የሚከሠተው የከባቢ አየር ይዘት ለውጥ ባለፉት ዘመናት ውስጥ ከተከሠቱት እጅግ ትላልቅ የአየር ንብረት ለውጦች የማይተናነሱ ለውጦች በአየር ንብረት ላይ እንዲከሠት ያደርጋል፡፡

ግብርና፣ የደን ልማት፣ የዓሣ ምርት ወዘተ ካሉት የአየር ንብረት ሁኔታዎች ጋር የተቆራኙ በመሆናቸው፤ በመላው ዓለም በጣም ብዙ ህዝብ የሚኖረው እና ከፍተኛ የመሠረተ ልማት ኢንቨስትመንቶች የሚደረጉት በወንዞች እና በባህር ዳርቻዎች ላይ ወይም አቅራቢያ በመሆኑ በአየር ንብረት ላይ የሚከሠት ማንኛውም ከፍተኛ የሆነ ለውጥ በተለይ የዝናብ ሥርጭት፣ የአፈር እርጥበት ሁኔታ፣ የወንዞች መሙላት፣ በተለያዩ ወቅቶች የሚነሡ ማዕበሎች፣ በባህር ጠለል ከፍ ማለት ጋር በተያያዘ የሚከሰቱ ለውጦች በጣም አስከፊ የሆኑ ተፅዕኖዎችን ሊያስከትሉ ይችላሉ፡፡ ከአየር ንብረት መለዋወጥ ጋር በተያያዘ የሚከሠቱ ተፅዕኖዎች ጠባይና ደረጃ የሚወሰነው በለውጦቹ ላይ ብቻ ሣይሆን ለተፅዕኖዎቹ ባለው የተጋላጭነት ሁኔታ ላይም በመመስረት ነው፡፡ እነዚህ አሉታዊ ተፅዕኖዎች አደጋ የሚሆኑትና ውድመት የሚያስከትሉት ሰፊ አከባቢን የሸፈኑ ውድመት በማስከተል የተለያዩ ማህረሰቦችና ህዝቦችን የዕለት ተዕለት ሁኔታዎች ላይ ከፍተኛ ለውጥ ሲያመጡ ነው፡፡ ከፍተኛ የሆነ የአየር ንብረት የመለዋወጥ ሁኔታዎች፣ ከእነዚህ ሁኔታዎች ጋር በተያያዘ ለሚከሠቱ ተፅዕኖዎች ያለው የተጋላጭነት ሁኔታ በተለያዩ መንስኤዎች የሚወሰኑ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥም ከሰው ልጅ ተግባራት ጋር የተያያዘ የአየር ንብረት ለውጥ፣ ተፈጥሯዊ የአየር ንብረት መለዋወጥ እንዲሁም ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ የልማት

Page 9: 2 3 - PHE Ethiopiaphe-ethiopia.org/pdf/Toolkit_Semien_amharic.pdf · 2 3 2006 ዓ/ ም አዲስ ... ፈንድ ሲሆን ለተደረገው ድጋፍ የኢትዮጵያ ሥነ-ህዝብ&

8 9

እንቅስቃሴዎች ይካተታሉ፡፡ ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር በተያያዘ የአደጋና ሥጋት ቁጥጥር ወይም ዝግጁነት ስራዎች የሚያተኩሩት ተጋላጭነትን በመቀነስ ላይ እና ሊደርሱ የሚችሉ አሉታዊ ተፅእኖዎችን ለመቋቋም የሚያስችል አቅም በመፍጠር ላይ ነው፡፡ በመሆኑም ከሁኔታዎች ጋር ለመጣጣም ጥረት ማድረግ እና ተፅእኖዎችን መቀነስ ተደጋጋፊ ነገሮች ሲሆኑ በአንድነት ከዚህ በታች የተመለከቱትን የአየር ንብረት ለውጥ ሥጋቶች በጣም ለመቀነስ ያስችላሉ፡፡

ምስል 1፤ የአየር ንብረት ለውጥ ተጋላጭነት እና የአደጋና ሥጋት ቁጥጥር

ከዚህ በላይ በተመለከተው ምስል ላይ ለአየር ጠባይና አየር ንብረት ክስተቶች ያለው ተጋላጭነት፣ከክስተቶቹ ጋር በተያያዘ የሚፈጠሩ ተፅዕኖዎች እና አደጋ የመከሰት ሁኔታ እንዴት እንደሚወስን ተመልክቷል፡፡ በተጨማሪም ተጋላጭነትን በሚመለከት የሚኖረው የልማት ሂደት ሚና፣ አደጋና ሥጋት በተመለከተ የሚኖረው እንድምታ፣ እና በአደጋዎችና በልማት መካከል ያሉ ትስስሮች ተመልክተዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የአደጋና ሥጋት ቁጥጥር እና ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር የተጣጣመ አኗኗር መከተል ለአየር ጠባይና አየር ንብረት ክስተቶች የሚኖረውን ተጋላጭነት እንዴት እንደሚቀንሱና ለማስቀረት የማይቻሉ አደጋዎችን የመቋቋም አቅም እንደሚጨምሩ ያሣያል፡፡ ሌሎች ዋና ዋና ሂደቶች እንደ ልማት በግሪንሀውስ ጋዝ ልቀት ላይ የሚያሣድረው ተፅዕኖ፣ ከሠው ልጅ ተግባራት ጋር በተያያዘ የሚፈጠሩ የአየር ንብረት ለውጦች፣ እንዲሁም እነዚህን ለውጦች ለመቀነስ የሚኖረው አቅም ተመልክተዋል፡፡

1.2. የሙቀት መጠን እዲጨምር የሚያደርግ ተፈጥሯዊ የአየር ንብረት ለውጥ

የውሃ ትነት፣ ካርቦንዳይኦክሳይድ፣ ኦዞን፣ እና ናይትሬስ ኦክሳይድ በሙሉ በተፈጥሮ የሚገኙ የግሪን ሀውስ ጋዞች ሲሆኑ ሙቀት ወደ ከባቢ አየር እንዲተላለፍ በማድረግ የአለም ሙቀት እንዲጨምር ያደርጋሉ፡፡ በነዚህ ግሪን ሀውስ ጋዞች አማካኝነት የሚከሰት ተፈጥሯዊ የአለም ሙቀት መጨመር ሁኔታ ‘’ተፈጥሮአዊ የግሪን ሀውስ ውጤት’’ ተብሎ ይጠራል፡፡ እነዚህ የግሪን ሀውስ ውጤትና ተጽእኖዎች ውሃ በፈሳሽ መልኩ እንዲኖር በማድረግ ህይወት እንዲቀጥል ያደርጋሉ፡፡ ያለፉት የጂኦሎጂካል

Page 10: 2 3 - PHE Ethiopiaphe-ethiopia.org/pdf/Toolkit_Semien_amharic.pdf · 2 3 2006 ዓ/ ም አዲስ ... ፈንድ ሲሆን ለተደረገው ድጋፍ የኢትዮጵያ ሥነ-ህዝብ&

10 11

እና ፓሊውክላማቲክ ማህደሮች እንደሚያሳዩት በእነዚህ የግሪን ሀውስ ጋዞች ፍሰት፣ የሚከሰት ለውጥ የሚታየው የአካባቢ ንብረት ለውጥ ዋና ምክንያት እንደሆኑ አሳማኝ መረጃዎች አቅርቧል፡፡ በቅርብ የተደረጉ ጥናቶችም ያለውን የአየር ንብረት ከተፈጥሯዊ ምክንያቶች ይልቅ በሰው ሰራሽ ወይም ሰዎች በሚፈጥሩት ምክንያት የሚደርስ እንደሆነ ጥናቶቹ ያሳያሉ፤ ምክንያቱም በተፈጥሮ የሚደረጉ ለውጦች ብዙ ጊዜ የሚፈጁ እና ዝግመታዊ ሂደት ያላቸው ሲሆን በሰው ሰራሽ ከፍተኛ ለውጦች አሳይቷል፡፡ እርሻ፣ ደን፣ የስነ ዓሣ ልማት በአሁኑ ጊዜ ባለው የአካባቢ ንብረት ለውጥ በከፍተኛ ደረጃ ተጎድተዋል፡፡ በወንዞች እና በዳርቻዎች የሚገኙት መዋዕለ ንዋይና ኢንቨስትመንትም በአየር ንብረት ለውጡ በከፍተኛ ደረጃ ተጎድቷል፡፡በእነዚህ አካባቢ የሚከሰት ማንኛውም የአየር ንብረት ከፍተኛ ለውጥ የነበረው መደበኛ የዝናብ፣ የአፈር እጥበት፣ የወንዝ ፍሰት፣ ወቅታዊ የአየር ለውጦች፣ በባህር ላይ በከፍተኛ ደረጃ ጉዳት እና ተጽእኖ ያደርሳሉ፡፡

1.3. የከባቢ አየር ይዘትን የሚለውጡ የሰዎች ተግባራት

ለግብርና ሥራ ሠዎች የሚያከናውኗቸው ተግባራት ለግሪንሀውስ ጋዞች መከማቸት ለብዙ ዘመናት ተፅዕኖ የነበራቸው ቢሆንም በ1750ዎቹ አካባቢ የተጀመረው የኢንዱስትሪ አብዮት አዲስ እና ከፍተኛ የሆነ ምዕራፍ የከፈተ እንደ ከሠል፣ ነዳጅና የተፈጥሮ ጋዝ ያሉ የቅሪት ነዳጆች በማቃጠል ካርንዳይ ኦክሳይድ ወደ አየር በመልቀቅ ተፅዕኖዎቹ መጠነ ሰፊ እንዲሆኑ አደርጓል፡፡

በአሁኑ ወቅት እነዚህን ነዳጆች በማቃጠል የሚገኘው ኃይል ሰዎች ለኢንዱስትሪ፣ ለግብርና፣ ለመኖሪያ አካባቢዎች እና ለንግድ ማዕከላት ከሚጠቀሙት ኃይል 80 በመቶ ያህሉ ሲሆን በየአሥርተ ዓመቱ የኢንዱስትሪ አብዮት መጀመሪያ ወቅት የነበረው ካርቦንዳይኦክሳይድ 10 በመቶ እንዲጨምር መንስኤ ሆኗል፡፡ በተመሣሣይ መልኩ ደን መጨፍጨፍና መሬት ማረስ ቀደም ብሎ በዕፅዋት ውስጥ፣ በሥራሥሮች፣ በሞቱ ወይም በበሠበሱ ነገሮች ውስጥ ተይዞ የነበረውን ካርቦን ወደ ከባቢ አየር በመልቀቅ የካርቦን ክምችት እንዲፈጠር ያደርጋሉ፡፡ ከ1750ዎቹ ጀምሮ በሚቃጠል ነዳጅና በደን መጨፍጨፍ እንዲሁም መሬት በማረስ ምክንያት የካርቦንዳይኦክሣይድ ከምችት በ35 በመቶ ጨምሯል፡፡ በከባቢ አየር ውስጥ ያለውን የካርቦንዳይኦክሣይድ ክምችት ከመጨመር በተጨማሪ ከሠው ልጆች ተግባራት የተነሣ ከካርንዳይኦክሣይድ የሚበልጠው ሚቴን (ሲ.ኤች.ፎር) የተባለው ጋዝ ክምችት በከባቢ አየር ውስጥ እንዲጨምር ሆኗል፡፡ ሠብሎችን በማምረት፣ የቤት እንስሣትን በማርባት፣ የቆሻሻና ፍሣሽ ክምችት በመጨመር፣ የድንጋይ ከሠልና የተፈጥሮ ጋዝ በማቃጠል ወዘተ የሚቴን ክምችት ከኢንዱስትሪ አብዮት በፊት ከነበረው መጠን በ150 በመቶ ያህል እንዲጨምር ሆኗል፡፡ በተመሣሣይ ከኢንዱስትሪና ከግብርና ጋር የተያያዙ ተግባራት ኒትረስ ኦክሣይድ ከኢንዱስትሪ አብዮት በፊት ከነበረው መጠን በ17 በመቶ ያህል እንዲጨምር አድርገዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ድንገት ወይም ሣይታሰቡ እና በዕቅድ ከሚደረጉ ልቀቶች የተነሣ ግሪንሀውስ ጋዞች የሆኑ የተለያዩ የፍሎሮካርቦን ዓይነቶች በከባቢ አየር ውስጥ በከፍተኛ ሁኔታ እየተከማቹ ይገኛሉ፡፡ ከሠው ልጆች ተግባራት ጋር በተያያዘ በእነዚህ የግሪንሀውስ ጋዞች የክምችት ሁኔታ ላይ የሚፈጠረው ተፅዕኖ አነስተኛ መስሎ ቢታይም የተፈጥሯዊ ግሪንሀውስ ተፅዕኖን በማባባስ በከባቢ አየር ኃይል ላይ የሚፈጠረው ለውጥ ከፍተኛ ነው፡፡

በሌላ በኩልም የሠዎች ተግባራት በከባቢ አየር ውስጥ የሚገኙና የፀሐይ ብርሃንን በማንፀባረቅና በመሠብሠብ በአየር ንብረት ላይ ተፅዕኖ የሚፈጥሩ ብናኞች ወይም

Page 11: 2 3 - PHE Ethiopiaphe-ethiopia.org/pdf/Toolkit_Semien_amharic.pdf · 2 3 2006 ዓ/ ም አዲስ ... ፈንድ ሲሆን ለተደረገው ድጋፍ የኢትዮጵያ ሥነ-ህዝብ&

10 11

ረቂቅ አካላት በመጠንና በባህሪይ እንዲለውጡ አድርገዋል፡፡ በከባቢ አየር ውስጥ የሚገኙትን ብናኞች በመጨመር ረገድ ጋዝማ ሰልፈር ዳይኦክሣይድ እንዲለቀቅ በማድረግ ከፍተኛ ድርሻ ካሉት የሠዎች ተግባራት ዋነኛው ከሠልና ከፍተኛ የሰልፈር ክምችት ያለው ነዳጅ የማቀጣጠል ተግባር ነው፡፡ ከዚህ በላይ እንደተጠቀሠው በከባቢ አየር ውስጥ የሚካሄዱ የተፈጥሮ ሂደቶች ሠልፈር ዳይኦክሳይድን (S02) ወደ ሠልፌት ብናኞች ይቀይሩታል፡፡ እነዚህ ብናኞች በዓለማችን ከፍተኛ የሆነ የከተማ መስፋፋት በሚታይባቸው አካባቢዎች የሚታየውን ጭጋግ በመቀነስ እና ወደ ምድር ከሚደርሱ የፀሐይ ብርሃን ጨረሮች የተወሠኑት ወደ ህዋ እንዲመለሱ በማንፀባረቅ የማቀዝቀዝ ተፅዕኖ ይፈጥራሉ፡፡ በሃያኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ ላይ ጊዜያዊ የሆነና በግሪንሀውስ ጋዝ ክምችት መጨመር የተከሠተው የሙቀት ሁኔታ ለውጥ ወይም ክስተት እንዲታይ ያደረገው የእነዚህ ብናኞች ከቁጥጥር ውጪ የሆነ የክምችት መጨመር ነበር፡፡ ከዚህ የተነሣም የልቀት ቁጥጥር ተግባራዊ መደረግ ባይጀምር ኖሮ ዝቅተኛ የሆነና ረዘም ላለ ጊዜ ምድርን የማቀዝቀዝ ሁኔታ እንዲፈጠር ሊያደርግ ይችል ነበር፡፡ እነዚህ የሰልፌት ብናኞች ከተፈጠሩ በኋላ በጥቂት ሣምንታት ውስጥ ተፈጥሯዊ በሆኑ ሂደቶች ከከባቢ አየር ውስጥ የማስወገድ ሁኔታም የአሲድ መጠን በእርጥበት ውስጥ እንዲበዛ በማድረግ አሲድ ዝናብ የተሰኘው እንዲዘንብ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ከሚያደርጉ ሁኔታዎች ቀዳሚው ነው፡፡ ይህ የአሲድ ዝናብም የአፈር ለምነት እዲቀንስ ያደርጋል፣ ዕፅዋትንና ህንፃዎችን ይጎዳል፣ ለሰዎች ጤናም ከፍተኛ የሆነ ሥጋት ይፈጠራል፡፡ ከሠልና ባዮማስ ወይም ብስባሽ ማቃጠል እና ብቃት የሌላቸው ሞተሮችም ጥቁር ካርበን የተባሉ የጥላሸት ብናኞችን በሂደት ወደ ብናኝት የሚለወጡ ኦርጋኒክ ጋዞችን ወደ ከባቢ አየር እንዲለቀቁ ያደርጋል፡፡ እነዚህ የጥላሸት ብናኞች የሚያርፍባቸውን የፀሐይ ኃይል በመሰብሠብ የሚያስቀሩ ስለሆኑ የእነዚህ ብናኞች ወደ ከባቢ አየር መለቀቅ የሙቀት መጠን ከፍ እንዲል ያደርጋል፡፡ ዕፅዋትን የመመንጠር ሥራ በከባቢ አየር ውስጥ ያለው የካርበን ዳይኦክሳይድ እና የሌሎች ጋዞች ክምችት እንዲጨምር ከማድረግ በተጨማሪ ልክ እንደ ሠልፌት ብናኞች ሁሉ የፀሐይ ብርሃንን በማንጸባረቅ ቅዝቃዜ እንዲፈጠር የሚያደርጉ ብናኞች ክምችት እንዲጨምሩ ያደርጋል፡፡ ደን መጨፍጨፍም በአጠቃላይ የምድራችን ገፅታ የፀሐይ ብርሃን የማንፀባረቅ ሁኔታ እንዲጨምር በማድረግ ተጨማሪ የቅዝቃዜ ክስተት እንዲኖር ያደርጋል፡፡ ዋነኞቹ የአየር ንብረት ለውጥ ምክንያቶች ከ1750 እስከ 2000 ባለው ጊዜ (የኢንዱስትሪ አብዮት እስከተጀመረበት ጊዜ ድረስ) ተፈጥሯዊና ሠው-ሠራሽ ናቸው፡፡ ከእነዚህ ሁለቱ ምክንያቶች ውስጥ ደግሞ ቀዳሚው ሠው-ሠራሽ ምክንያቶች ናቸው፡፡ የውሃ ትነት ተፈጥሯዊ የሆነና ከፍተኛ ግምት የሚሠጠው የግሪንሀውስ ጋዝ ቢሆንም በአየር ንብረት ላይ ያን ያህል ተፅዕኖ የሚፈጥር ሁኔታ ተደርጎ አይወሠድም፡፡ በሌላ በኩል ግን ከሠዎች ተግባራት ጋር በተያያዘ በከባቢ አየር ውስጥ የሚገኘው የካርቦንዳይኦክሣይድ ክምችት እንዲጨምር በማድረግ የዓለም የሙቀት መጠን እንዲጨምር የማድረግ ሁኔታ ግን ከፍተኛ የሆነ የውሃ ትነት መጠን በከባቢ አየር ውስጥ እንዲኖር በማድረግ በግሪንሀውስ ጋዞች የሚፈጠረው ሙቀት የመጨመር ሁኔታ እንዲባባስ ያደርጋሉ፡፡

1.4. የሙቀት መጨመር ተፅዕኖ የሚያስከትል የከባቢ አየር ይዘት መለዋወጥ የአብዛኞቹ ግሪንሀውስ ጋዞች ዕድሜ በዓመታት እና ከዚያ በላይ የሚቆጠር በመሆኑ የሚደረጉ ልቀቶች በዓለማቀፍ ደረጃ ውህደት በመፍጠር የሚያስከትሉ የሙቀት ሁኔታ ተፅዕኖ ዓለማቀፋዊ ይዘት ያለው ይሆናል፡፡ ብዛት ያላቸው የግብረ-መልስ አሠራሮች ይህንን ዓለማቀፋዊ ተፅዕኖ ያጠናክራሉ፡፡ ከዚህ በላይ ከተገለፀው የውሃ ትነት ግብረ-መልስ በተጨማሪ ከሙቀት መጨመር ጋር በተያያዘ በከፍተኛ ላቲትዩድ

Page 12: 2 3 - PHE Ethiopiaphe-ethiopia.org/pdf/Toolkit_Semien_amharic.pdf · 2 3 2006 ዓ/ ም አዲስ ... ፈንድ ሲሆን ለተደረገው ድጋፍ የኢትዮጵያ ሥነ-ህዝብ&

12 13

አካባቢዎች የሚገኘው የበረዶ መቅለጥ የምድርን የፀሐይ ብርሃን የማንፀባረቅ ችሎታ በመቀነስ በአጠቃላይ የሙቀት መጨመር እንዲኖር ያደርጋል፡፡ በውሃ ትነት፣ በከባቢ አየር የሙቀት መጠንና ዝውውር መለዋወጥ ጋር ተያይዞ የሚኖረው የደመና ሽፋን የመለዋወጥ ሁኔታ የሙቀት መጠን እንዲጨምር ወይም እንዲቀንስ ሊያደርግ ይችላል፡፡ ይህም የከፍተኛ ደመና ሽፋን ከጨመረ የሙቀት መጠን ይጨምራል፣ የዝቅተኛ ደመና ሽፋን ሲጨምር ደግሞ የሙቀት መጠን ይቀንሣል፡፡ ከተለያዩ ምክንያቶች የተነሣ የሚፈጠረው የደመና ሽፋን የመለዋወጥ ሁኔታ የሚያደርሰው ተፅዕኖ በውል ተለይቶ አልታወቀም፡፡ በመሆኑም ይህ ሁኔታ ከግሪንሀውስ ጋዞች ክምችት ጋር በተያያዘ የሚፈጠረውን የሙቀት መጠን በግልጽ ለማወቅ አስቸጋሪ ሁኔታ ከሚፈጥሩ ጉዳዮች ውስጥ ዋነኛው ነው፡፡

የቅርብ ዘመናት የዓለማችን የሙቀት ሁኔታ ታሪክ መንስኤ የሆኑት ውስብስብ ሁኔታዎች ከሠዎች ተግባራት ጋር በተያያዘ የሚፈጠሩት የሙቀት መጨመርና መቀነስ ተፅዕኖዎች እና ከእሣተ-ገሞራ ፍንዳታዎች፣ ከፀሀይ መሬት ላይ የሚያርፈው የኃይል መጠን መለዋወጥ፣ እንዲሁም በከባቢ አየር፣ በውቅያሶች እና በበረዶ መካል ከሚደረገው የኃይል ሽግግሮች ጋር ተያይዞ የሚከሠተው የአየር ንብረት ሥርዓት የውስጥ መለዋወጥ ያካትታል፡፡ የእነዚህ ውስብስብ ሁኔዎች ተፅዕኖ እንዳለ ሆኖ ከ1970ዎቹ ጀምሮ ለዓለም የሙቀት መጠን መጨመር ከፍተኛ ድርሻ ያለው የግሪንሀውስ ጋዞች ከምችት በተለይም የካርቦንዳይ ኦክሳይድ ክምችት በከፍተኛ ሁኔታ በከባቢ አየር ውስጥ መጨመር ነው፡፡ የዓለም የሙቀት መጠን አማካይ ለማወቅ በዓለማቀፍ ደረጃ ሠፊ ቦታን የሸፈነ የሙቀት ልኬት ምዝገባ መካሄድ የመጀመረው ከ1860ዎቹ ጀምሮ ሲሆን ከዚህ የተገኘው መረጃ እንደሚያሳየው ከ1860 እስከ 2000 ባለው ጊዜ ውስጥ በአማካይ 0.75 ድግሪ ሴልሽየስ ከፍ ብሏል፡፡

ሥዕል 2፡ የአየር ንብረት ሞዴል

ምንጭ፡ የአሜሪካ ብሔራዊ የጥናትና ምርምር ካውንስል (2012 እ.ኤ.አ)

Page 13: 2 3 - PHE Ethiopiaphe-ethiopia.org/pdf/Toolkit_Semien_amharic.pdf · 2 3 2006 ዓ/ ም አዲስ ... ፈንድ ሲሆን ለተደረገው ድጋፍ የኢትዮጵያ ሥነ-ህዝብ&

12 13

የአየር ንብረት ሞዴሎች ማለት ምን ማለት ነው?

ለብዙ አሥርተ-ዓመታት ሣይንቲስቶች የዓለም የአየር ንብረት ሁኔታን ለማጥናት እጅግ የላቁ ኮምፕዩተሮችን በመጠቀም በአየር ንብረት ውስጥ የሚካሄዱትን ውስብስብ ሂደቶች አስመስለው እንዲታዩ አድርገዋል፡፡ እነዚህ ሞዴሎች የከባቢ አየር፣ የመሬትና የሌሎች የአየር ንብረት ሞዴሎች የባለፉት ጊዜያት የአሁንና የወደፊት የአየር ንብረት ለውጦችን ለማጥናት ጠቃሚ መሣሪያዎች ናቸው፡፡ የአየር ንብረት ሞዴሎቹን በተጨባጭ በምልከታ ከተገኙት መረጃዎች ጋር በማስተያየትና በመፈተሽ ሣይንቲስቶቹ ሞዴሎቹን በመጠቀም ባለፉት ዘመናት ውስጥ በአየር ንብረት ላይ የተከሠቱ ክስተቶችን ለማወቅ ይገለገሉባቸዋል፡፡

Page 14: 2 3 - PHE Ethiopiaphe-ethiopia.org/pdf/Toolkit_Semien_amharic.pdf · 2 3 2006 ዓ/ ም አዲስ ... ፈንድ ሲሆን ለተደረገው ድጋፍ የኢትዮጵያ ሥነ-ህዝብ&

14 15

2. የአየር ንብረት ለውጥ

2.1. የአየር ንብረት ለውጥ ማለት ምን ማለት ነው?

የአየር ንብረት ለውጥ ማለት ከተፈጥሮ የሁኔታዎች መለዋወጥ ወይም ከሰዎች ተግባራት የተነሣ በሂደት በአየር ንብረት ላይ የሚከሠት ማንኛውም ለውጥ ማለት ነው፡፡ የአየር ንብረት ለውጥ ስንል በምልከታ የታወቁ እና በትንበያ የተገመቱ አማካይ የዓለም ሙቀት መጠን የመጨመር ሁኔታዎች እና ተያያዥ ተፅዕኖዎች (ለምሣሌ፡- የአየር ጠባይ ፅንፎች የድግግሞሽ ወይም የመጠን መጨመር፣ የግግር በረዶ መቅለጥ፣ የባህር ጠለል ከፍ ማለት፣ እና የዝናብ ወቅት ወይም መጠን መለዋወጥ ማለታችን ነው፡፡

የአየር ንብረት ለውጥ በዓለም ኢኮኖሚና በኢኮሎጂ እንዲሁም በሠው ልጆች ጤና እና ኑሮ ላይ ከባድ ሥጋት ሊያሣድር የሚችል ከፍተኛ የሆነ ዓለማቀፋዊ የአካባቢ ችግር መሆኑ በሥፋት ተቀባይነት እያገኘ ነው፡፡ የአየር ንብረት ለውጥ በተጨባጭ እየተከሠተ ያለ እና በአብዛኛው የግሪንሀውስ ጋዞች ክምችት በከባቢ አየር ውስጥ እንዲጨምር ከሚያደርጉ የሠዎች ተግባራት የተነሣ የሚከሠት ሁኔታ ነው፡፡

የአየር ንብረት ለውጥ የሙቀት መጠን እንዲጨምር፣ የባህር ጠለል ከፍ እንዲል፣ የአየር ጠባይ እንዲለዋወጥ፣ እንዲሁም ለመተንበይ አዳጋች የሆኑ ሌሎች ከባድ የአየር ጠባይ የመለዋወጥ ሁኔታዎች እንዲከሠቱ ያደርጋል ተብሎ ይገመታል፡፡ በተጨማሪም የዝናብ ሥርጭት ለውጦች፣ የጎርፍ ክስተቶች፣ የድርቅ ወቅቶች፣ ተደጋጋሚ የሠደድ እሣት አደጋዎች፣ የውሃ አቅርቦት መመናመን፣ ወዘተ እንዲፈጠሩ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ የእነዚህ የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖዎች ድምር ውጤትም የሠዎች ተጋላጭነት መጨመር፣ የግብርና ምርቶች መቀነስ፣ የምግብ ዋስትና አለመኖር፣ የውሃ አቅርቦት ችግር መባባስ፣ የሥነምህዳር መጎዳት እና የጤና ችግሮች መስፋፋት ይሆናል፡፡

2.2. የአየር ንብረት ለውጥ አመጣጥ

የአየር ንብረት ለውጥ በዓለማቀፍ ማህበረሰብ ላይ ከተጋረጡ እጅግ ከባድ ተግዳሮቶች ውስጥ አንዱ ነው፡፡ የዓለም ሙቀት መጨመርን ለመቀነስ እና ተያይዘው የሚከሠቱ ተፅዕኖዎችን ለመቋቋም ከፍተኛ የሆነ የኢኮኖሚ ኢንቨስተመንት የሚጠይቅ ከሁሉም በላይ ደግሞ የፖሊሲ አውጪዎች የጋራ ቁርጠኝነት የሚሻ ጉዳይ ነው፡፡ ለነዚህ መጠነ-ሰፊ ተግዳሮቶች የብዙ ባለድርሻ አካላት ትብብር ወሳኝ ሲሆን እየተካሄዱ ያሉ የአየር ንብረት ለውጥ አለማቀፍ የአየር ንብረት ድርድሮች በስኬት መጠናቀቅም ለወደፊት ትውልድ ዘላቂነት ያለውን ልማት ለማረጋገጥ የመጀመሪያው እርምጃ ይሆናል፡፡

በአየር ንብረት ለውጥ ላይ የተገኙ ሣይንሳዊ መረጃዎች ከአሣማኝ በላይ ናቸው፡፡ ከሣይንስ-ነክ የህትመት ውጤቶች የተገኙ መረጃዎችን መሠረት በማድረግ በአየር ንብረት ላይ የመንግሥታት ፓኔል (Intergovernmental Panel on Climate Change- IPCC) በሠጠው ማጠቃለያ የዓለማችን የአየር ንብረት ሥርዓት ሙቀት መጨመር የማያሻማ ክስተት እንደሆነና ለዚህ የሙቀት መጨመር በዋናነት ምክንያት የሆኑትም የሠዎች ተግባራት መሆናቸውን አረጋግጧል፡፡ ባለፈው ክፍለ ዘመን አማካይ የዓለም የሙቀት መጠን በ0.74 ዲግሪ ሴልሽየስ እንደጨመረ

Page 15: 2 3 - PHE Ethiopiaphe-ethiopia.org/pdf/Toolkit_Semien_amharic.pdf · 2 3 2006 ዓ/ ም አዲስ ... ፈንድ ሲሆን ለተደረገው ድጋፍ የኢትዮጵያ ሥነ-ህዝብ&

14 15

ይገመታል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ብዙ የግሪንሀውስ ጋዞች ረዘም ላለ ጊዜ በከባቢ አየር ውስጥ ከመቆየታቸው ጋር ተያይዞ የሚከሠተው የዓለም ሙቀት መጨመር አሁን ልቀቶች በከፍተኛ መጠን ቢቀንሱ እን ኳን ለሚመጡት በመቶዎች ለሚቆጠሩ ዓመታት የምድራችን የተፈጥሮ ሥርዓቶች ላይ ተፅዕኖ የማሳደሩ ሁኔታ የሚቀጥል ይሆናል፡፡ ባለፉት ዘመናት ተደርገው የነበሩ የግሪንሀውስ ጋዞች ልቀቶች በስሌቱ ውስጥ ቢካተቱ የዓለም ሙቀት መጠን ከ1.8 እስከ 2.0 ዲግሪ ሴልሽየስ የሚደርስ ጭማሪ ያሳያል፡፡

ከሁሉም የበለጠ ሥጋት የሚፈጥረው ግን ከፍተኛ የሆነ ልቀት አሁንም ያለ መሆኑና ፖሊሲዎችና ተግባራት ላይ ሥር ነቀል ለውጥ ካልተደረገ በቀር የግሪንሀውስ ጋዞች ልቀቱ ከፍተኛ እንደሆነ ለወደፊቱም የሚቀጥል መሆኑ ነው፡፡ የዓለማቀፍ ኢነርጂ ኤጀንሲ በሪፖርቱ እንዳመለከተው የግሪንሀውስ ጋዞች ልቀት ከኢንዱሰትሪ አብዮት መጀመሪያ ዘመን ወይም ከ1750ዎቹ ጀምሮ በእጥፍ አድጓል፡፡ በአሁኑ ጊዜ ባለው ትንበያም የእነዚህ ጋዞች ልቀት ከ2000 እስከ 2030 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ ከ25 እስከ 90 በመቶ በሚደርስ ሊጨምሩ ይችላሉ፡፡ ይህም በሚቀጥሉት አሥርተ-ዓመታት በታዳጊ ሀገራት የሚደረገው የግሪንሀውስ ጋዞች ልቀት ድርሻ ከፍ እያለ የሚሄድ መሆኑ ከግምት ውስጥ ገብቶ ነው፡፡ ባለፈው ግማሽ ክፍለ ዘመን ውስጥ በኢንዱሰትሪ በበለፀጉ ሀገራት የአንድ ሰው የግሪንሀውስ ጋዞች ልቀት ድርሻ በታዳጊ ሀገራት ከነበረው የአንድ ሰው የግሪንሀውስ ጋዞች ልቀት ድርሻ በአራት እጥፍ ይበልጣል፡፡ የኢኮኖሚና የልማት ትብብር ድርጅት (OECD) አባል ሀገራት ማለትም በዓለማችን በኢንዱሰትሪ እድገት በእጅጉ ያደጉ ሀገራት እስካሁን በነበረው የግሪንሀውስ ጋዞች ልቀት የ77 በመቶ ድርሻ አላቸው፡፡ ሆኖም ግን በታዳጊ ሀገራት የሚደረገው የግሪንሀውስ ጋዞች ልቀት ከፍተኛ እየሆነ የመጣ ሲሆን ወደ ከባቢ አየር እየተደረጉ ካሉት ልቀቶች ሁለት-ሶስተኛው የኢኮኖሚና ልማት ትብብር ድርጅት አባል ባልሆኑ ሀገራት እንደሆነ ይገመታል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ከ2005 እስከ 2030 ባለው ጊዜ ውስጥ የኢኮኖሚና ልማት ትብብር ድርጅት አባል ባልሆኑ ሀገራት የሚኖረው የግሪንሀውስ ጋዞች ልቀት በየዓመቱ በአማካይ በ2.5 በመቶ ያድጋል ተብሎ ይጠበቃል፤ በአንፃራዊነትም የድርጅቱ አባል ሀገራት የልቀት መጠን 0.5 በመቶ የሆነ ዓመታዊ ዕድገት ያሣያል ተብሎ ይገመታል፡፡ ይህ የልቀት መጨመር ደግሞ የዓለም የሙቀት መጠን በመጨመሩ እንዲቀጥል ያደርገዋል፡፡ በአሁኑ ጊዜ ያለውን የአየር ንብረት ለውጥ በተመለከተ የሣይንቲስቶች ግምት እንደሚገልፀው ከ1990 እስከ 2100 ዓ.ም ድረስ የዓለማችን አማካይ የሙቀት መጠን ከ1.4 እስከ 6.4 ዲግሪ ሴልሽየስ የሚደርስ ጭማሪ ሊያሣይ ይችላል፡፡ ይህ ደግሞ የሙቀት መጠን መጨመርን በተመለከተ ብዙ ጊዜ ከ2 እስከ 3 ዲግሪ ሴልሽየስ የሚደርስ ጭማሪ እንደ የመጨረሻ ጣሪያ የሚጠቀስ ከመሆኑ አንፃር እጅግ ከፍተኛና ሊቀለበስ የማይቻል የዓለም አየር ንብረት አደገኛ የሆነ የመዛባትን ሁኔታ ሊያስከትል የሚችል ይሆናል፡፡

2.3. ለአየር ንብረት ለውጥ ያለው ተጋላጭነት

ለአየር ንብረት ለውጥ ተጋላጭ መሆን ማለት በተፈጥሮም ሆነ በሠው ልጆች ምክንያት ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር በተያያዘ የሚከሠቱ አሉታዊ ተፅእኖዎች በመቋቋም ለመቀጠል የማይችልበት ወይም ተጋላጭ የሚሆንበት መጠንን የሚያሣይ ነው፡፡ ተጋላጭነት የአየር ንብረት ጠባይ፣ መጠን፣ እና የድግግሞሽ ሁኔታዎች ድምር ተፅዕኖዎች እና አንድ ስርዓት እነዚህን ለመቋቋም የሚኖረው አቅምና ከእነዚህ የተነሣ የሚደርስበት ለውጥ ሁኔታን የሚመለከት ነው፡፡ ከእነዚህ ሥርዓቶች ውስጥ

Page 16: 2 3 - PHE Ethiopiaphe-ethiopia.org/pdf/Toolkit_Semien_amharic.pdf · 2 3 2006 ዓ/ ም አዲስ ... ፈንድ ሲሆን ለተደረገው ድጋፍ የኢትዮጵያ ሥነ-ህዝብ&

16 17

ደግሞ ዋነኞቹ ተጋላጭ የሆኑ ማህበረሰቦች፣ ቤተሰቦችና ግለሰቦች ሲሆኑ እነዚህ ሁሉ የተለያየ የተጋላጭነት ሁኔታና ደረጃ ያላቸው ናቸው፡፡

ለአየር ንብረት ለውጥ ተጋላጭ የመሆን ሁኔታ በዋናነት የሚወሠነው በጂኦግራፊያዊ ቦታዎች ነው፡፡ ለምሣሌ ያህል በባህር ዳርቻዎች የሚኖሩ ማህረሰቦች ለባህር ጠለል ከፍ የማለትና ለማዕበሎች ክስተት የበለጠ ተጋላጭነት ይኖራቸዋል፡፡ በሌላ በኩል ቆላማ በሆኑ አካባቢዎች የሚኖሩ ማህበረሰቦች ደግሞ ለድርቅ ከፍተኛ ተጋላጭ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ የተጠቂነት መጠን ደግሞ የሚያሳየው ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር በተያያዘ በአንድ ማህበረሰብ ወይም ሥርዓት ላይ የሚደርሰውን የተፅዕኖ መጠንን ነው፡፡ ለምሣሌ በዝናብ ላይ በተመሠረተ ግብርና የሚኖሩ ማህበረሰቦች ማዕድናትን በማምረት ከሚኖሩት የበለጠ በዝናብ ሥርጭት ላይ በሚከሠት ለውጥ ይጠቃሉ፡፡

ለአየር ንብረት ለውጥ የሚኖረው የተጋላጭነት መጠን በሀገራት፣ በማኀበረሰቦች እና በቤተሰሠቦች ደረጃ ጭምር የተለያየ ነው፡፡ በተመሳሳይ መልኩ ተፅዕኖ የመቋቋም አቅሙ አነስተኛ የሆነና በቆላማ አካባቢ የሚኖረው ሥነምህዳር በምድር ወገብ አካባቢ ከሚኖረው የበለጠ በዝናብ መጠን የመቀነስ ሁኔታ ተጠቂ ይሆናል፡፡

ለአየር ንብረት ለውጥ የሚኖረው የተጋላጭነት ሁኔታ ወይም መጠን በሀገራት ውስጥ በማህበረሰቦች እና በቤተሰብ ደረጃ ጭምር የተለያየ ነው፡፡ በመሆኑም ማን ተጋላጭ እንደሆነና ለምን ተጋላጭነት እንደጨመረ ለመረዳት ነባራዊ ሁኔታን መሠረት ያደረገ የባዮፊዚካል፣ የማህበራዊ እና የኢኮኖሚያዊ እንዲሁም ፖለቲካዊ ትንታኔ ይፈልጋል፡፡ ከዚህ ቀጥሎ የተመለከቱት የማኀበረሰብ ክፍሎች ለአየር ንብረት ለውጥ በእጅጉ ተጋላጭ የሆኑ ናቸው፣

በተፈጥሮ ሀብቶች ላይ የተመሠረተ ኑሮ የሚመሩ ማህበረሰቦች (ግብርና በተለይም በዝናብ ላይ የተመሠረተ ግብርና፣ የዓሣ ምርት፣ የደን ምርት፣ አርብቶ አደሮች ወዘተ)

ድሀ ሴቶች፣ ሕጻናት፣ አረጋዊያንና ሌሎች ትኩረት ያላገኙ የማህበረሰብ አባላት፣ መሬት አልባና ሥራ-አጥ የማህበረሰብ አባላት ፣

የመንቀሳቀስ ችሎታቸው የተገደበ ሠዎች/የአካል ጉዳተኞች ስደተኞች እና ከመኖሪያ አካባቢዎቻቸው ወይም ከሀገራቸው የተፈናቀሉ ሰዎች

2.3.1. የመቋቋም አቅም

የመቋቋም አቅም ማለት የአየር ንብረት ለውጥ እና ተያያዥ ተፅዕኖዎችን በተመለከተ የተፈጥሮ ወይም የሰው ልጅ ሥርአት ሊደርስበት የሚችለውን ጉዳት ለመቀነስ የሚፈጠሩ እድሎችን ለመጠቀም ወይም ተፅዕኖዎቹን ለመቋቋም የሚኖረው አቅም ማለት ነው፡፡ የግለሰቦችን፣ የቤተሰቦችን እና የማህበረሰቦችን የመቋቋም አቅም ከሚወስኑ ዋና ዋና ጉዳዮች ውስጥ አንዱ ለተፈጥሮ፣ ለሰው ኃይል፣ ለማህበራዊ፣ ለፊዚካል እና ለፋይናንስ ሀብቶች ያሏቸው ተደራሽነት እና እነዚህን ሀብቶች የመቆጣጠር አቅም ነው፡፡ የመቋቋም አቅምን ከሚወስኑ ሁኔታዎች ውስጥ በምሳሌነት ለመጥቀስም ከአየር ንብረት ጋር የተያያዙ ሥጋቶች በተመለከተ ያለው

Page 17: 2 3 - PHE Ethiopiaphe-ethiopia.org/pdf/Toolkit_Semien_amharic.pdf · 2 3 2006 ዓ/ ም አዲስ ... ፈንድ ሲሆን ለተደረገው ድጋፍ የኢትዮጵያ ሥነ-ህዝብ&

16 17

ዕውቀት፣ መልካም የሆነ የጤንነት ሁኔታ፣ የሴቶች የቁጠባና የብድር ማህበራት፣ ገበሬዎችን ማዕከል ያደረጉ ድርጅቶች ባህላዊ መረዳጃ ተቋማት፣ ወዘተ ናቸው፡፡ በአጠቃላይ በዓለማችን ያሉ እጅግ ድሀ የሆኑ ሕዝቦች እነዚህን የመቋቋም አቅም ለሚጨምሩ ሀብቶች ዝቅተኛ የሆነ ተደራሽነት አላቸው፡፡ ለእነዚህ ሀብቶች ያለው ተደራሸነትም በሀገራት ውስጥ በማህበረሰቦች እና በግለሰቦች ደረጃ የተለያየ ነው፡፡ እንደ ፖሊሲዎች፣ ተቋማት እና የሥልጣን መዋቅሮች ባሉ ውጫዊ ሁኔታዎችም የሚወሰን ነው፡፡ ለምሳሌ ያህልም ሴቶች ለመረጃ፣ ለተለያዩ ሀብቶችና አገልግሎቶች ያላቸው ተደራሽነት የተገደበ ከመሆኑ የተነሣ ለአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖዎችም በተለይ ተጋላጭ ናቸው፡፡

2.3.2. የማገገም አቅም

የማገገም አቅም ማለት አንድ ሰው/ማህበረሰብ በተፈጥሯዊ ወይም በሰው ሰራሽ ሁኔታ ከደረሰበት አደጋ የተነሳ ያጋጠሙትን ተፅዕኖዎች ወይም ሁኔታዎች ለመቋቋም፣ ለመቻል፣ እና ውጤታማ በሆነ ሁኔታ በማገገም መሰረታዊ የሆኑ አሰራሮቹን፣ ባህሪያቱንና አገልግሎቶቹን ለማቆየት ወይም መልሶ ለመያዝ ያለው አቅም ማለት ነው፡፡ አደጋና ስጋቶችን በመቀነስ ጥረቶች ውሰጥ የመቋቋም አቅም የሚለው ፅንሰ-ሃሳብ የሚታወቅ ሲሆን ከሁኔታዎች ጋር ተጣጥሞ የመኖር ሂደት ውስጥም በሰፊው የውይይት ነጥብ እየሆነ የመጣ ነው፡፡ ከፍተኛ የሆነ የመቋቋም አቅም ያለው ማህበረሰብ የሚደርስበትን አደጋዎች ለመቆጣጠር፣ ተፅዕኖዎቹን ለመቀነስ ወይም/እና ከማንኛውም አሉታዊ ተፅዕኖ በፍጥነት ለማገገም እና አደጋው ከደረሰበት በፊት ወደነበረበት ሁኔታ ወይም ወደ ተሻለው ለማድረስ የተሻለ አቅም ይኖረዋል፡፡ የመቋቋም አቅም እና ከሁኔታ ጋር ተጣጥሞ ለመኖር ያለው ችሎታ ጠንካራ ቁርኝት ያላቸው ጉዳዮች እንደመሆናቸው መጠን በማህበረሰብ ውስጥ በመቋቋም አቅማቸው በሰፊው የሚለያዩ የማህበረሰቡ አካላት ይኖራሉ፡፡

2.3.3. አደጋ

አደጋና ስጋትን ከመቀነስ ጋር በተያያዘ አደጋ ማለት የህይወት መጥፋት ወይም የአካል ጉዳት፣ የንብረት ውድመት፣ የኑሮ መናጋት፣ የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ወይም አካባቢያዊ ሁኔታዎች መቃወስ ሊያስከትል የሚችል ሁኔታ ወይም የሰዎች ተግባር ማለት ነው፡፡ የተፈጥሮ አደጋዎች በጂኦሎጂካል (የመሬት መንቀጥቀጥ፣ የሱናሚ ክስተቶች፣ የእሳተ-ገሞራ ክስተቶች) ወይም በባዮሎጂካል (የበሽታ ወረርሽኝ) ወይም በሃይድሮ-ሜትዎሮሎጂካል (የጐርፍ መጥለቅለቅ፣ አውሎ ነፋስ፣ ድርቅ ወ.ዘ.ተ) መንስኤዎቻቸው መሰረት ሊከፋፈሉ ይችላሉ፡፡ አደጋዎች በሰው ልጆች ምክንያት (የአየር ንብረት ለውጥ፣ እሳት፣ የማይተኩ ሃብቶችን አሟጦ መጠቀም፣ ከቴክኖሎጂ ጋር የተያያዙ) ሊከሰቱ ይችላሉ፡፡

አደጋዎች በመንስኤዎቻቸውና በሚያደርሷቸው ተፅዕኖዎቻቸው የአንድ ጊዜ ክስተት (ነጠላ) ወይም ተከታታይነት ያላቸው ወይም ጥምረት ያላቸው ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ አደጋን (ለምሳሌ ጐርፍ) አደጋው ከሚያስከትላቸው ተፅዕኖዎች (ለምሳሌ የከብቶች እልቂት) ለይቶ ማየት ያስፈልጋል፡፡ አንዳንድ ተፅዕኖዎች ለምሳሌ እንደ የምግብ እጥረት ያሉት የሚከሰቱት እንደ የአየር ንብረት ለውጥ፣ የአፈር ለምነት መቀነስ፣ የገበያ ተደራሽነት ማነስ፣ ወዘተ ያሉት ተጣምረው የሚያደርሷቸው ይሆናሉ፡፡ የተጋላጭነትን ሁኔታ በተገቢው ለመተንተን የአደጋዎችን ተቀያያሪ ተፈጥሯዊ ባህሪያት እንዲሁም መንስኤዎቻቸውን በሚገባ መረዳት ያስፈልጋል፡፡ በምስል 3

Page 18: 2 3 - PHE Ethiopiaphe-ethiopia.org/pdf/Toolkit_Semien_amharic.pdf · 2 3 2006 ዓ/ ም አዲስ ... ፈንድ ሲሆን ለተደረገው ድጋፍ የኢትዮጵያ ሥነ-ህዝብ&

18 19

ውስጥ የተጋላጭነት ሁኔታ ከመረሰታዊ መንስኤዎች በመነሳት ከዚያም አደጋዎች እንዲከሰቱ የሚያደርጉ ሁኔታዎች ድረስ ያለውን ሂደት ለማሳየት ተሞክሯል፡

2.3.4. ስጋት

ስጋት ማለት በተፈጥሯዊ ወይም በሰው ሰራሽ አደጋዎች እና የተጋላጭነት ሁኔታዎች መካከል ካለው ግንኙነት የተነሳ ጐጂ የሆኑ ክስተቶች ወይም አደጋዎች (የህይወት መጥፋት፣ ጉዳት፣ የንብረት ውድመት፣ የኢኮኖሚ መናጋት፣ የአካባቢ መጐዳት) የመከሰት እድልን የሚያመለክት ነው፡፡

2.3.5. በአደጋ የሚደርስ ውድመት

ውድመት የሚለው የማህበረሰብ ወይም የህብረተሰብ ሁኔታ በከፍተኛ ደረጃ በመናጋት መጠነ-ሰፊ የሆነ የሰው፣ የቁሳቁስ፣ የኢኮኖሚ ወይም የአካባቢ ጉዳት መድረስን የሚያመለክት ሲሆን ይህም ተጐጂው ማህበረሰብ ወይም ህብረተሰብ ያሉትን ሀብቶች በመጠቀም ለመቋቋም ከሚችልበት ደረጃ የበለጠ የከፋ ነው፡፡ በአደጋ የሚያደርስ ውድመት የስጋት ሂደቶች ድምር ውጤት ሆኖ የአደጋ ክስተቶች ተጋላጭ የመሆን ሁኔታዎች፣ ሊከሰቱ የሚችሉ አሉታዊ ተፅዕኖዎችን ለመቀነስ የአቅም አለመኖር በጋራ የሚያስከትሉት ሁኔታ ነው፡፡

ምስል-3 ለአደጋ ተጋላጭ የመሆን ሁኔታ

ምንጭ፡ ዓለምአቀፍ የቀይ መስቀልና የቀይ ጨረቃ ማኀበራት (1999 እ.ኤ.አ)

2.3.6. የአደጋ ሥጋት ቁጥጥር (Disaster Risk Management)

የአደጋ ሥጋት ቁጥጥር ማለት የአደጋ ክስተቶችንና ተፅዕኖዎችን ለመከላከል፣ ለማሣለፍ እና ለመቀነስ የሚደረግ ስትራቴጂያዊ ተግባራት ወይም ሂደትን የሚመለከት ነው፡፡ በዚህ የመቆጣጠር ሂደት ውስጥም ብዙ ጊዜ እንደ አንድ ዑደት የሚታዩ ተግባራት የሚካተቱበት ሲሆን እነዚህም መከላከል/መቀነስ፣ ዝግጁነት፣ ምላሽ መስጠት እና ማገገም ናቸው፡፡

Page 19: 2 3 - PHE Ethiopiaphe-ethiopia.org/pdf/Toolkit_Semien_amharic.pdf · 2 3 2006 ዓ/ ም አዲስ ... ፈንድ ሲሆን ለተደረገው ድጋፍ የኢትዮጵያ ሥነ-ህዝብ&

18 19

2.4. የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖዎች

የዓለም የሙቀት መጠን መጨመር እና ተያያዥ የዓለም አየር ንብረት ለውጦች በተለያዩ መንገዶች ትኩረት ይሰጣቸዋል፡፡ በዓለማቀፍ ደረጃ የአየር ንብረት ለውጦች መገለጫ የሚባሉት የሚከተሉትን ያካትታሉ፡-

በዓለምአቀፍ ደረጃ በድርቅ የሚጠቃ አካባቢ መጨመር በብዙ ቦታዎች የየብስ ላይ የአየር ሞገድ በተደጋጋሚ መከሰት ከባድ ዝናብ የመከሰት ሁኔታ ወይም/እና ወቅቱን ያልጠበቀ ወይም አነስተኛ የሆነ የዝናብ መጠን

በዓለምአቀፍ ደረጃ የበረዶ መቅለጥ እና የባህር ጠለል መጨመር

የዓለም የሙቀት መጠን እየጨመረ ከመምጣቱ ጋር ተያይዞ ተፅዕኖዎቹም እየተጠናከሩ ይሄዳሉ፡፡ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች በተለይም ድሆች በከፍተኛ ሁኔታ ለድርቅ፣ ለጐርፍ አደጋ፣ ለውሃና ምግብ እጥረት፣ ለበሽታ ተጋላጭ እየሆኑ ከኑሮአቸውና ከመኖሪያቸው እየተፈናቀሉ ይሄዳሉ፡፡ በተለይም በማደግ ላይ ያሉ ሀገራት በአብዛኛው በአየር ንብረት ሁኔታዎች ላይ የተመረኮዙ የኢኮኖሚ ዘርፎች (ለምሳሌ ግብርና) ላይ በከፍተኛ ደረጃ የተመሠረቱ በመሆናቸው በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት ለሚደርሱ ተፅዕኖዎች እጅግ ተጋላጭ የሆኑ ናቸው፡፡ በመሆኑም በሁሉም ሴክተሮች የተጠናከረ ጥረት በማድረግ፡-

የልቀት መጠንን የሚያባብሱ ዕቃዎችና አገልግሎቶች ፍላጐት እንዲቀንስ ማድረግ፣

የኃይል አጠቃቀም እንዲሻሻል ማድረግ

ለኃይል ምንጭነት ዝቅተኛ የሆነ የካርበን ልቀት ያላቸው ቴክኖሎጂዎችን መጠቀም የደን መጨፍጨፍ በከፍተኛ ሁኔታ እንዲቀንስ ማድረግ ይገባል፡፡

የግሪንሀውስ ጋዞች ልቀት እና የሙቀት መጠን እየጨመረ በሄደ ቁጥር ከአየር ንብረት ለውጥ የተነሣ የሚከሰቱ ተፅዕኖዎች መጠነ-ሰፊ እና ከባድ እየሆኑ ይሄዳሉ፡፡ ለምሳሌ ያህል አማካይ የሙቀት መጠን አነስተኛ የሆነ የመጨመር ሁኔታ በማሣየቱ እንደ ማዕበል፣ አውሎ ንፋስ፣ ድርቅ፣ ከባድ ዝናብ ወዘተ ያሉ ክስተቶች በመጠንም ሆነ በድግግሞሽ ብዛት በጣም ይጨምራሉ፡፡ ሆኖም ግን የእነዚህ የአየር ጠባይ ክስተቶች ሥርጭት ከቦታ ቦታ ይለያያል፡፡ በዓለምአቀፍ ደረጀ ገና በማደግ ላይ ያሉ ሀገራት በተለይም በከባድ ድህነት ውስጥ የሚኖሩ የኀብረተሰብ ክፍሎች ለወደፊቱ በሚከሰቱ የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖዎች በእጅጉ ተጋላጭ የሆኑና በከፍተኛ ሁኔታ የሚጐዱ ይሆናሉ፡፡ ከዚህ በተጨማሪም የአየር ንብረት ለውጥን ተከትሎ የሚመጡት ተፅዕኖዎች አሁንም በእነዚህ የዓለም ክፍሎች ከፍተኛ ተግዳሮት ሆነው ያው እንደ ድህነት፣ የጤና አገልግሎት ማነስ፣ የምግብ ዋስትና አለመረጋገጥ፣ የኃይል ምንጭ ተደራሽነት አለመኖር ወዘተ እንዲባባሱ ያደርጋሉ፡፡ ለምሣሌ የአየር ንብረት ለውጥ በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ሕዝቦች የውሃ አቅርቦት እጥረት ወይም

Page 20: 2 3 - PHE Ethiopiaphe-ethiopia.org/pdf/Toolkit_Semien_amharic.pdf · 2 3 2006 ዓ/ ም አዲስ ... ፈንድ ሲሆን ለተደረገው ድጋፍ የኢትዮጵያ ሥነ-ህዝብ&

20 21

የሚቀርበው ውሃ ጥራቱን የጠበቀ አለመሆን ችግሮች ያጋጥሟቸዋል፡፡ ይህ ደግሞ ለበለጠ የጤና ችግር እንዲደርስባቸው ያደርጋል፡፡ የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖዎች ከቦታ ቦታ እና በልማት ደረጃ ሁኔታ የተለያዩ ቢሆኑም አብዛኞቹ በዓለም ኢኮኖሚ ዘርፎች ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር በተያያዘ በሚከሰቱ ተፅዕኖዎች የሚጠቁ ይሆናሉ፡፡ እነዚህ ሁኔታዎች ደግሞ በዓለምአቀፍ የንግድ ልውውጥ ላይ የራሣቸው የሆነ አሉታዊ ተፅዕኖ ይኖራቸዋል፡፡ ቀጥሎ የተዘረዘሩት የኢኮኖሚ ሴክተሮች በተለይ ለአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖ ተጋላጭ የሆኑ ናቸው፡፡

ግብርና፡ ግብርና ለአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖ በእጅጉ ተጋላጭ ከሆኑ ሴክተሮች ውስጥ አንዱ ሲሆን በዓለምአቀፍ የንግድ ልውውጥ ውስጥም ቁልፍ ሚና ያለው ነው፡፡ በዝቅተኛ ላቲትዩድ በሚገኙ የዓለም ክፍሎች ማለትም አብዛኞቹ በማደግ ላይ ያሉ ሀገራት በሚገኙባቸው አካባቢዎች አነስተኛ የሚባል እስከ 1 ዲግሪ ሴልሽየስ የሚደርስ የሙቀት መጠን መጨመር ከ5 እስከ 10 በመቶ የሚደርስ የዋና ዋና ሰብሎች ምርት ቅናሽ እንዲከሰት ያደርጋል፡፡ በመካከለኛ እና ከፍተኛ ላቲትዩድ አካባቢዎች ከ1 እስከ 3 ዲግሪ ሴልሽየስ የሚደርስ የሙቀት መጠን መጨመር ጠቀሜታ ይኖረዋል ተብሎ የሚጠበቅ ቢሆንም ከእነዚህ አካባቢዎች ባሻገር ላሉት ግን ከፍተኛ የሆነ አሉታዊ ተፅዕኖ ያስከትላል፡፡ በቅርቡ የተካሄዱ ጥናቶች እንደሚያሳዩት በ2020 ዓ.ም እ.ኤ.አ በአንዳንድ የአፍሪካ ሀገራት የሰብል ምርት እስከ 50 በመቶ በሚደርስ መጠን ይቀንሣል፣ በ2010 እ.ኤ.አ ከሰብሎች ምርት የሚገኘው የተጣራ ገቢ በ90 በመቶ እንደሚቀንስ ነው፡፡ ሀገራት በሚገኙባቸው የቦታዎች አቀማመጥ መሠረትም በረዶ በመቅለጡ በሚከሰት የውሃ መጥለቅለቅ እና በዝናብ እጥረት የተነሳ ስለሚከሰት ድርቅ የግብርናው ዘርፍ ከባድ የሚባል ችግር የሚገጥመው ይሆናል፡፡

ቱሪዝም፡ የቱሪዝም ሴክተር ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር በተያያዘ ለሚደርሱ ተፅዕኖዎች በከፍተኛ ሁኔታ ተጋላጭ የሆነ ሌላኛው ዘርፍ ነው፡፡ ይህም በበረዶ ሽፋንና በባህር ዳርቻዎች ላይ በሚከሰቱ ለውጦችና በአየር ጠባይ ተለዋዋጭነት ምክንያት የሚከሰት ለውጥ በቱርስት መስህቦች ላይ የሚያደርሰው ጉዳት ነው፡፡

የዓሣና የደን ልማት፡- የዓሣ ምርትና የደን ልማትም ለአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት ለሥጋት የተጋለጡ ሴክተሮች ናቸው፡፡ በባህር ዳርቻዎች በሚገኙ ሥነምህዳሮች ላይ እና በባህር ውስጥ በሚገኘው ብዝሀ ሕይወት ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ ይደርሣል ተብሎ ይገመታል፡፡

ንግድ፣ መሠረተ ልማት እና ትራንስፖርት ፡- በመጨረሻም በግልፅ ሊታይ የሚችል ከፍተኛ ተፅዕኖ የሚደርሰው በንግድ፣ በመሠረተ ልማት አውታሮች እና በትራንስፖርት ላይ ነው፡፡ ከባህር ጠለል ከፍታ መጨመር እና እንደ ጐርፍና ማዕበል ካሉ የአየር ጠባይ ለውጦች የተነሣ በህንጻዎች፣ በባቡር መንገዶች፣ በአየር መንገዶች፣ በድልድዮች ወዘተ ላይ ከፍተኛ የሆነ የውድመት ሥጋት እንደሚከሰት ይጠበቃል፡፡ በተጨማሪም ከባህር ውስጥ በረዶ ለውጥ ጋር ተያይዞ በተለይ በአርክቲክ አካባቢዎች አዳዲስ የመርከብ መስመሮች እንዲፈጠሩ ያደርጋል፡፡

Page 21: 2 3 - PHE Ethiopiaphe-ethiopia.org/pdf/Toolkit_Semien_amharic.pdf · 2 3 2006 ዓ/ ም አዲስ ... ፈንድ ሲሆን ለተደረገው ድጋፍ የኢትዮጵያ ሥነ-ህዝብ&

20 21

እርምጃዎች

የአየር ንብረት ለውጥ

ሴክተር ተፅዕኖ መወሰድ የሚገቡ እርምጃዎች

የሙቀት መጠን መጨመር

ግብርና •የሰብሎች ምርት ሥርጭትና ወቅቶች ላይ የሚከሰት ለውጥ፣ የሰብሎች ምርት መቀነስ

•የትነት መጠን መጨመር፣ በሰብሎችና በከብቶች ላይ የሚደርስ ከፍተኛ የሆነ የሙቀት ችግር

•ለመስኖ ሥራ የሚፈለገው የውሃ መጠን መጨመር

•የከብቶች ሞት መጨመር •የምግብ ዋስትና አለመኖር እና የኑሮ መናጋት

•በሀብቶች አጠቃቀምና ክፍፍል የግጭት መስፋፋት

• በአጭር ጊዜ የሚደርሱ የሰብል ዝርያዎችን ማስተዋወቅ

• የተለያዩ የሰብል ዝርያዎችን ማምረት

•ድርቅን መቋቋም የሚችሉ የሰብል ዝርያዎችን መጠቀም

• የአፈር የኦርጋኒክ ይዘት እንዲጨምር ማድረግ

•እርጥበት እንዲቆይ ለማድረግ የሚችሉ የሰብል ዓይነቶች መጠቀም

• ለከብቶች መኖ ሊሆኑ የሚችሉና ለጥላነት የሚያገለግሉ የዛፍ ዝርያዎችን መትከል

• የተለያዩ የከብት ዝርያዎችን ማርባት

•መስኖ መጠቀም• የሀብት አጠቃቀም መመሪያና ፖሊሲዎችን ማዘጋጀት

የውሃ ሀብት

• በወንዞች ፍሰት ላይ ተፅዕኖ የሚፈጥር የበረዶ መቅለጥ መጨመር

•የውሃ ፍላጐት መጨመር እና የውሃ አቅርቦት መቀነስ

•በበረዶ መቅለጥ የሐይቆች መፈጠርና በሂደት የማጥለቅለቅ ሁኔታ መከሰት

•የውሃ አቅርቦት እጥረት መባባስ •በውሃ ሀብት ላይ የሚነሱ ግጭቶች

•የውሀ መበከል

•ውሃ የማቆር ዘዴዎችን ማስተዋወቅ

•ውሃን የመንከባከብ ዘዴዎችን ማስተዋወቅ

• የመጥለቅለቅ ሥጋት በተመለከተ የቅድሚያ ማስጠንቀቂያና መከላከያ ሥርዓት መዘርጋትና መሥራት

• በባህር ዳርቻዎች የሚገኙ ዕፅዋትን መንከባከብ

• የውሃ ማጣሪያ ዘዴ መጠቀም

Page 22: 2 3 - PHE Ethiopiaphe-ethiopia.org/pdf/Toolkit_Semien_amharic.pdf · 2 3 2006 ዓ/ ም አዲስ ... ፈንድ ሲሆን ለተደረገው ድጋፍ የኢትዮጵያ ሥነ-ህዝብ&

22 23

ምንጭ ፡- የዓለም የንግድ ድርጅትና የተባበሩት መንግሥታት የአካባቢ ጥበቃ (2009)

የሰዎች የጤና ሁኔታ

•በከፍተኛ ሙቀት የሚከሰት የጤና ጠንቅ (ስትሮክ)

•እንደ የወባ በሽታ ያሉ በሽታዎች መስፋፋት

•የሰው ኃይል ምርታማነት መቀነስ

•የምግብ እጥረት

• የወባ ትንኞች በሚገኙባቸው አካባቢዎች የአልጋ አጐበር ማስተዋወቅ

• ከሙቀት ጋር የተያያዙ የጤና ጠንቆች ላይ የህብረተሰብ ግንዛቤ ማሣደግ

• የሥራ ባህልን ማዳበርና የጓሮ አትክልትና የገቢ ማስገኛ ሰብሎችን ማምረት

የዝናብ ሥርጭትና ወቅት ላይ የሚከሰት ለውጥ

ግብርና •የአፈር መሸርሸር መጨመር •የግብርና ሥራዎችን ለማከናወን ወቅቶችን ለመገመት አለመቻል

•ወቅቱን ባልጠበቀ ዝናብ በሰብሎች ላይ የሚደርስ ጉዳት/ውድመት

•የግብርና ወቅቶች መዛባት

•ትክክለኛ፣ ተደራሽና አስተማማኝ የሆነ የአየር ጠባይ ትንበያ እንዲኖር ማድረግ

• የተለያዩ የሰብል ዝርያዎችን በመቀላቀል ማምረት

• የተለያዩ ገቢ ማስገኛ ሥራዎችን መሥራትና አቅም መገንባት

• የሰብሎች መድን/ኢንሹራንስ

• የጐርፍ ማጥለቅለቅ አደጋ ሲከሰት መልሶ የማቋቋም ሥራዎች ማከናወን

የባህር ጠለል ከፍታ መጨመር

በባህር ዳርቻዎች የሚገኙ ሀብቶችና የማህበረሰቦች የኑሮ ሁኔታ

•የጨዋማ ውሃ ማስፋፋት •የጐርፍና የማዕበል ክስተት መጨመር

•የመሬት በውሃ መሸፈን/የአፈር መሸርሸር

•የአውሎ ንፋስ ክስተት መጨመር

•ጨው መቋቋም የሚችሉ የሰብል ዝርያዎች ማስተዋወቅ

• የተለያዩ የገቢ ማስገኛ ሥራዎችን መሥራት

• ለአውሎ ንፋስና ማዕበል የቅድሚያ ማስጠንቀቂያ ሥርአት መዘርጋት

• የውሃ መከላከያ ግድቦችን መገንባት

• ከውሃ ጋር ተያያዥ የሆኑ የመንከባከብ ሥራዎችን ማከናወን

Page 23: 2 3 - PHE Ethiopiaphe-ethiopia.org/pdf/Toolkit_Semien_amharic.pdf · 2 3 2006 ዓ/ ም አዲስ ... ፈንድ ሲሆን ለተደረገው ድጋፍ የኢትዮጵያ ሥነ-ህዝብ&

22 23

2.5. የአየር ንብረት ለውጥን መቀነስ/መግታት

የአየር ንብረት ለውጥ ለመግታት የሚሠሩ ሥራዎች የግሪንሀውስ ጋዞች ልቀት በመቀነስ ወይም ከከባቢ አየር ውስጥ ካርበን እና ካርበንዳይኦክሳይድን በመሣብ የክምችታቸው መጠን እንዲቀንስ በማድረግ ላይ ያነጣጠሩ ናቸው፡፡ በመሆኑም በዓለም የሙቀት መጨመር ሁኔታ ላይ ተፅዕኖ ለመፍጠር የሚከናወኑ ሥራዎች ናቸው፡፡ ከእነዚህ ተግባራት ውስጥ የተወሰኑት፣ ከቅሪት-አካል የሚገኝ ነዳጅ መጠቀምን መቀነስ፣ ዘላቂነት ያላቸው የኃይል ምንጮችን መፍጠርና ማስፋፋት፣ የደን መጨፍጨፍ መቀነስ፣ የደን ሽፋን እንዲጨምር ማድረግን ወዘተ ያካትታሉ፡፡ የአየር ንብረት ለውጥን ለመግታት በሚደረጉት ጥረቶች ውስጥ የደኖች ሚና በተለይም በምድር ወገብ አካባቢዎች የሚገኙ ትሮፒካል ደኖች ወሣኝ ናቸው፡፡ እነዚህ ደኖች ከፍተኛ የሆነን የካርበን ጋዝ በግንዳቸው ውስጥ እና በአፈር ውስጥ ተይዞ እንዲቀር ያደርጋሉ፡፡ በመሆኑም የደን መጨፍጨፍ በከባቢ አየር ውስጥ የካርቦንዳይኦክሣይድ ክምችት እንዲጨምርና ተያያዥ የአየር ንብረት ለውጦች እንዲከሰቱ ከሚያደርጉ ምክንያቶች ዋነኛው ነው፡፡ በዓለም አቀፍ ደረጃ ሣይንቲስቶች ባካሄዱት ጥናት መሠረት እነዚህ ደኖች እስከ 4.8 ቢሊዮን ቶን የሚደርስ ካርበንዳይኦክሣይድ በየዓመቱ ተይዞ እንዲቀር የሚያደርጉ ሲሆን ይህም በየዓመቱ ከሚቀጣጠለው ነዳጅ ጋር በተያያዘ የሚኖር የካርበን ልቀት 18 በመቶ ያህሉ ነው፡፡

በመሆኑም ከደን መጨፍጨፍ ጋር በተያያዘ የሚከሰቱ ተፅዕኖዎች ሁለት እጥፍ ናቸው፡፡ የመጀመሪያው የደን መጨፍጨፍ በዛፎች ግንዶች ውስጥ ተይዞ የነበረው ካርበን ወደ ከባቢ አየር እንዲለቀቅ በማድረግ ከፍተኛ የሆነ የካርበንዳይኦክሣይድ ክምችት እንዲኖር ያደርጋል፡፡ ሁለተኛው ይህ ድርጊት ለወደፊቱ በከባቢ አየር ውስጥ ያለውን ካርበን በመሣብ የሚጠቅሙ የደኖች ሽፋን እንዲመናመን ያደርጋል፡፡ የደን መጨፍጨፍን በመቀነስ የአየር ንብረት ለውጥን የመግታት ዘዴ ወጪ ቆጣቢ እንደሆነ በኢኮኖሚ ዘርፍ የተካሄዱ ጥናቶች ያሣያሉ፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ሥነምህዳርን በመንከባከብ ብዙ አዎንታዊ ተፅዕኖዎች ያሏቸው ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ፡-

በአካባቢ ደረጃ የአየር ንብረት ማረጋጋት

የብዝሀ ሕይወት ጥበቃ/እንክብካቤ

የአፈርና የውሃ ጥበቃ/እንክብካቤ

የተፋሰስ ሁኔታ መሻሻል እና

ለገቢ ማስገኛነት ለባህላዊ ቅርስነት እና ለመገናኛነት የሚውሉ የደን ውጤቶች ይጠቀሳሉ፡፡

ከደኖች ጋር በተያያዘ የአየር ንብረት ለውጥ ለመግታት የሚጠቅሙ ስትራቴጂዎች የሚከተሉትን ያካትታሉ፡፡ ከደን መጨፍጨፍ ጋር በተያያዘ የሚከሰተው የካርቦንዳይኦክሣይድ ልቀት መቀነስ፣ የደኖች ልማትና እንክብካቤ ሥራዎችን ማከናወን፣ ዛፎችን በመትከል የደን ሽፋን እንዲጨምር በማድረግ የካርበን ልቀት እንዲቀንስ ማድረግ ናቸው፡፡

Page 24: 2 3 - PHE Ethiopiaphe-ethiopia.org/pdf/Toolkit_Semien_amharic.pdf · 2 3 2006 ዓ/ ም አዲስ ... ፈንድ ሲሆን ለተደረገው ድጋፍ የኢትዮጵያ ሥነ-ህዝብ&

24 25

በአጠቃላይ የአየር ንብረት ለውጥን ለመግታት የሚኖር የገንዘብ አቅርቦት በሚከተሉት የመፍትሄ ሥራዎች ላይ ያነጣጠረ ነው፡፡ እነዚህም ፡-

1. ታዳሽ ኃይል የመጠቀም ሁኔታ እንዲጨምር ማድረግ

2. ኃይል ቆጣቢ እና/ወይም አነስተኛ ካርበን ያላቸው ዕቃዎች እና ቴክኖሎጂዎች ማስፋፋትና መጠቀም

3. ካርበን ለመቀነስ የሚያስችሉ ቴክኖሎጂዎችን መፍጠርና መጠቀም

ሠንጠረዥ 2፡- የአየር ንብረት ለውጥ በመግታት ውስጥ ሚና ያላቸው ልቀት የሚቀንሱ ቴክኖሎጂዎችና አሠራሮች

ሴክተር በአሁኑ ወቅት በገበያ ላይ የሚገኙ ልቀት የሚቀንሱ ቴክኖሎጂዎችና

አሠራሮች

በቅርቡ ለገበያ ይቀርባሉ ተብለው የሚጠበቁ ልቀት የሚቀንሱ ቴክኖሎጂዎችና አሠራሮች

የኃይል አቅርቦት

• የተሻሻሉና ኃይል ቆጣቢ የሆኑ ቴክኖሎጂዎች (ምድጃ፣ የቤት ቁሳቁሶች አቅርቦትና ሥርጭት)

• ለኃይል ምንጭነት ከከሰል ወደ ጋዝ መሸጋገር

• የኑክሌር ኃይል • ታዳሽ የሙቀትና የኃይል

ምንጮች (የሃይድሮ ኃይል፣ የሶላር፣ የንፋስ፣ ጂኦቴርማል፣ ባዮኢነርጂ)

• ድብልቅ ኃይልና ሙቀት • በወቅቱ ካርበንን በመሰብሰብና

ከተፈጥሮ በማስወገድ በካርበን ዳይኦክሣይድ መልክ እንዲከማች ማድረግ

• ካርበን የማስወገድ አሠራር ለባዩማስ እና በከሠል ኤሌክትሪክ የሚያመነጩ መሣሪያዎች ተግባራዊ ማድረግ

• የላቀ የኑክሌር ኃይል • ላቅ ያሉ ታዳሽ የኃይል ምንጮች

(እንደ ጨረር፣ ዌቭ፣ ወዘተ ያሉ)

ትራንስፖርት

• ነዳጅ ቆጣቢ የሆኑ ተሽከርካሪዎች

• ሃይብሪድ ተሽከርካሪዎች • አነስተኛ ጭስ የሚያወጡ

ተሽከርካሪዎች • የባዮ-ነዳጅ • ከመንገድ ትራንስፖርት ወደ

ባቡር ትራንስፖርት እና ወደ የሕዝብ ትራንስፖርት መሸጋገር

• ሞተር አልባ የትራንስፖርት ዘዴዎች (ብስክሌት፣የእግር ጉዞ)

• በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ተሸከርካሪዎች

• የመሬት አጠቃቀምና የትራንስፖርት እቅድ

• ሁለተኛ ደረጃ የሆኑ ባዮ-ነዳጆች • የተሻሻሉ አውሮኘላኖች • በኤሌክትሪክ የሚሰሩ የላቀ

ኃይል ያለው ባትሪ ያላቸው ተሽከርካሪዎች

Page 25: 2 3 - PHE Ethiopiaphe-ethiopia.org/pdf/Toolkit_Semien_amharic.pdf · 2 3 2006 ዓ/ ም አዲስ ... ፈንድ ሲሆን ለተደረገው ድጋፍ የኢትዮጵያ ሥነ-ህዝብ&

24 25

ሕንጻዎች

• ኃይል ቆጣቢ የመብራት መሣሪያዎች መጠቀም

• ኃይል ቆጣቢና የተሻሻሉ በኤሌክትሪክ የሚሠሩ የቤት ውስጥ መገልገያዎች

• የተሻሻሉ ምድጃዎች • የተሻሻሉ ኢንሱሌሽን • ለማሞቅና ለማቀዝቀዝ ከፀሐይ

ብርሃን የሚገኝ ኃይል • አማራጭ የማቀዝቀዣ ፊሳሾች

• የንግድ ማዕከላት የሆኑ ሕንጻዎች የተቀናጀ ዲዛይን (መረጃ የሚሰጡ የመላከያ መሣሪያዎች እና ሌሎች)

• ከፀሐይ ብርሃን የሚገኝ ኃይል መስመር ከህንጻዎች ጋር ተያይዞ እንዲሰራ ማድረግ

ኢንዱስትሪ

• ኃይል ቆጣቢ የሆኑ የኤሌክተሪክ እቃዎች

• ካርበንዳይኦክሣይድ ያልሆኑ ልቀት ቁጥጥር

• ለተወሰኑ ተግባራት አገልግሎት የሚሰጡ መሣሪያዎች

• ቁሳቁሶችን መልሶ ጥቅም ላይ ማዋልና መተካት

• የሙቀትና የኃይል ሪከቨሪ

• የላቀ ኃይል ቆጣቢነት • በሲሚንቶ፣ አሞኒያ እና ብረት

ማምረቻ ሂደት ውስጥ ካርበን የማስወድ አሠራር

• ለአሉሚኒየም ኢነርት ኤሌክትሮድ የመጠቀም አሠራር

ግብርና • የአፈር ካርበን የመጠራቀም አቅም ለመጨመር የሚያስችል የተሻሻለ የሰብልና የግጦሽ መሬት አያያዝና አጠቃቀም

• ለምነቱን ያጣ መሬት እንዲያገግም የማድረግ ዘዴ

• የሚቴን ጋዝ ልቀት ለመቀነስ የተሻሻለ የሰብል አመራረት እና የከብቶች ፍግ አያያዝ

• የተሻሻሉ የናይትሮጂን ማዳበሪያ አጠቃቀም ዘዴዎች /ኒትረስ ኦክሣይድ ለመቀነስ

• ምርጥ ዘር መጠቀም

• የሰብል ምርታማነት መሻሻል

የደን ሀብት ልማት

• ዛፎችን መትከል • የተራቆቱ ቦታዎችን በደን

መሸፈን • የደን ሀብት ጥበቃ/እንክብካቤ • የደን መጨፍጨፍ መቀነስ • የእንጨት ምርቶች ቁጥጥር

• የተሻሻሉ የዛፎች ዝርያዎች በመጠቀም የካርበን ልቀት የመቀነስ አሠራር

• “ሪሞት ሴንሲንግ” ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም የዕፅዋትና የአፈር ካርበን የማስቀረት/የመያዝ ሁኔታ ክትትል

የቆሻሻ አወጋገድ

• በአፈር መልሶ በመሙላት ከሚቴን ጋዝ ጉዳት ማገገም እንዲችል የማድረግ አሠራር

• ኮምፖስት በማዘጋጀት የኃይል ምንጭ እንዲሆን ማድረግ

• የተሻለ የፍሳሽ አወጋገድ• ቆሻሻ ነገሮችን መልሶ ጥቅም

ላይ የማዋል አሠራር

• የሚቴን ጋዝ ከኦክጂን ጋር የመዋሃድ ሁኔታ ለመጨመር (ኦክሲዴሽን) ባዮ-ከቨር እና ባዮ-ፊልተር መጠቀም

Page 26: 2 3 - PHE Ethiopiaphe-ethiopia.org/pdf/Toolkit_Semien_amharic.pdf · 2 3 2006 ዓ/ ም አዲስ ... ፈንድ ሲሆን ለተደረገው ድጋፍ የኢትዮጵያ ሥነ-ህዝብ&

26 27

ምንጭ፡- የዓለም የንግድ ድርጅትና የተባበሩት መንግሥታት የአካባቢ ኘሮግራም (2009 እ.ኤ.አ)

2.6. ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር የተላመደ አኗኗር

ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር የተላመደ ወይም የተገናዘበ የአኗኗር ሁኔታ በአንድ በኩል አሉታዊ ተፅዕኖዎችን በመቀነስ በሌላ በኩል የሚፈጠሩ ዕድሎችን በመጠቀም ለመቀጠል የሚደረግ ጥረት ነው፡፡ በሌላ አገላለጽ ለውጡን የመግታት ጥረት ከአየር ንብረት ለውጥ በመጠን እንዲቀንስ ከማድረግ ጋር የተያያዘ ሲሆን ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር የተገናዘበ የአኗኗር ሁኔታ ደግሞ የሰዎችንና የሥነምህዳር ለውጡን የመቋቋም አቅም በማሣደግ ለውጡን ተከትሎ ሊደርስ የሚችልን ጉዳት መቀነስ ነው፡፡ ይህ ሂደት ተጋላጭነትን በመቀነስ ላይ ያተኮረና በተለይ የድሆችን የመቋቋም አቅም የማጠናከር ሂደት ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር በተያያዘ ለሚከሰቱ ተፅዕኖዎች ያለውን የተጋላጭነት ሁኔታ መቀነስን ያካትታል፡፡ በእርግጥም ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር የተገናዘበ የአኗኗር ሁኔታ ተጋላጭነትን ከመቀነስም በላይ ነው፡፡ ይህም ተጋላጭነትን መቀነስ ተጣጥሞ የመኖር ሂደት መሠረት ስለሆነ ማን እና እንዴት ተጋላጭ እንደሆኑ በዝርዝር መረዳትን የሚጠይቅ ጉዳይ ነው፡፡ በዚህ መረጃ ላይ በመመርኮዝ አግባብነት ያላቸው ስትራቴጂዎችን ለመንደፍና ተግባራዊ ለማድረግ ይቻላል፡፡ የተግባራትን ውጤታማነት መከታተልና መገምገም እንዲሁም ተሞክሮዎችን መለወጥ በዚህ ሂደት ውስጥ ወሣኝነት ያላቸው ሥራዎች ናቸው፡፡ ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር የመላመድ ሁኔታ ማለት የሰው ሠራሽ ወይም የተፈጥሮ የሆነ ሥርዓት በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት የሚከሰቱ ተፅዕኖዎችን ለማቋቋም እንዲችል አቅም የመገንባት ሥራዎችን የሚያካትት ነው፡፡ ለዚህ ሂደት ጠቃሚ ከሆኑት ስትራቴጂዎች መካከል የተወሰኑት፡- ድርቅን ለመቋቋም የሚችሉ የዕፅዋት ዝርያዎች ማስተዋወቅ፣ በወንዞችና በባህር ዳርቻዎች አካባቢ የውሃ መከላከያ እርከኖችን መገንባትና ሌላ አካባቢ ማስፈር ናቸው፡፡

Page 27: 2 3 - PHE Ethiopiaphe-ethiopia.org/pdf/Toolkit_Semien_amharic.pdf · 2 3 2006 ዓ/ ም አዲስ ... ፈንድ ሲሆን ለተደረገው ድጋፍ የኢትዮጵያ ሥነ-ህዝብ&

26 27

3. የካርበን ዑደትና የግሪንሀውስ ተፅዕኖ

3.1. ደኖችና የአየር ንብረት ለውጥ

የደን ዘርፍ የአየር ንብረት ለውጥ በመግታት ሂደት ውስጥ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል፡፡ የደን ልማት በዓለማቀፍ ደረጃ 17 በመቶ ያህል የሚሆን የግሪንሀውስ ጋዝ ልቀት የሚፈጥር ሲሆን ከኢንዱስትሪ እና ከኃይል አቅርቦት ቀጥሎ ሦስተኛው ከሰዎች ተግባራት ጋር በተያያዘ ከፍተኛ የልቀት መንስኤ/ምክንያት ነው፡፡ በደን የሚደረገው የልቀት መጠን አሜሪካን ወይም ቻይና ከሚያደርሱት ዓመታዊ የልቀት መጠን ጋር ተመጣጣኝ ነው፡፡ ልቀቱን ለመግታት የሚደረግ ጥረት በሌለበት ሁኔታ በደን ብቻ የሚደረገው የካርበን ልቀት በከባቢ አየር ውስጥ ያለውን የካርበን መጠን የሚጨምር ይሆናል፡፡ በመሆኑም ደኖች የአየር ንብረት ለውጥን በተመለከተ በሚደረጉ ውይይቶች ወይም ስምምነቶች ውስጥ ዋነኛ ሥፍራ ይኖራቸዋል፡፡

የደን መጨፍጨፍ እና የደን ሽፋን መቀነስ ካርበን በካርቦን ዳይኦክሳይድ መልክ ወደ ከባቢ አየር እንዲለቀቅ ያደርጋል፡፡ በአሁኑ ወቅት ያለው ከፍተኛ የሆነ የደን መመናመንን ተከትሎ በደን መጨፍጨፍና በደን ሽፋን መመናመን ምክንያት የሚፈጠረውን ልቀት መቀነስ የታለመውን ግብ ለማሣካት በሚደረገው ጥረት ውስጥ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል፡፡ ደኖች የዓለማችን የአየር ንብረት የተረጋጋ እንዲሆን በማድረግ ረገድ ከፍተኛ ሚና ይጫወታሉ፡፡ ይህም በካርቦን ዑደት አማካኝነት ካርቦንን ከመሬት በላይና ከመሬት በታች በማከማቸት ከከባቢ አየር ውስጥ እንዲወገድ በማድረግ ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት የዓለማችን የደን ሽፋን 30 በመቶ የሚሆን የየብስ ክፍል የሚሸፍን ሲሆን 77 በመቶ የሚሆን ካርቦን በዕፅዋት ውስጥ 39 በመቶ ያህሉ ደግሞ በአፈር ውስጥ ተከማችቷል፡፡ የተፈጥሮ ደኖች የካርቦን ክምችት እንዲቀጥል እያደረጉ እና ካርቦን በመሰብሰብ እና ከከባቢ አየር በማስወገድ ከፍተኛ አስተዋፅኦ በማድረግ ላይ ይገኛሉ፡፡

3.2. ደኖችና የካርቦን ዑደት

ደኖች የዓለም አየር ንብረትን በማረጋጋት ረገድ ወሣኝ ሚና የሚጫወቱ ሲሆን ይህም በካርቦን ዑደት አማካኝነት የካርቦን ጋዝ ተሰብስቦ ከመሬት በላይና በመሬት ውስጥ እንዲከማች ያደርጋሉ፡፡ በአሁኑ ጊዜ የዓለም የደን ሽፋን 30 በመቶ ያህል ሲሆን 77 በመቶ የሚደርስ ካርበን በዕፅዋት ውስጥ ተከማችቶ ይገኛል፡፡ 39 በመቶ ያህሉ ደግሞ በአፈር ውስጥ ተይዞ የሚገኝ ነው፡፡ ደኖች ከሌሎች የዕፅዋት ሽፋኖች በበለጠ ሁኔታ በሔክታር ብዙ ካርበን ተይዞ እንዲከማች ያደርጋሉ፡፡ ካርበን በተከታታይ በውቅያኖስ፣ በየብስና በከባቢ አየር ውስጥ ዑደት ያደርጋል፡፡ በዚህ ዑደት ውስጥ ሕይወት ያላቸው ነገሮች፣ አፈርና ብስባሾች ወሣኝ ሚና የሚጫወቱ ሲሆን ይህም ካርበን ከከባቢ አየር ውስጥ እንዲወገድ እና በካርበንዳይ ኦክሣይድ መልክ ተመልሶ ወደ ከባቢ አየር እንዲለቀቅ በማድረግ ነው፡፡ ሕይወት ባላቸው እና በሞቱት ዕፅዋት ውስጥ የሚገኘው የካርበን ክምችት እነዚህ ዕፅዋት በሚቃጠሉበት ወይም በሚበሰብሱበት ወቅት ወደ ካርበንዳይኦክሣይድ በመለወጥ ወደ ከባቢ አየር ይለቀቃል፡፡ በዕፅዋት ቅሪት ውስጥ የሚከማቸው የካርበን መጠን አብዛኛውን ጊዜ ከመሬት በላይ ባለው ባዮማስ ውስጥ ከሚከማቸው የካርበን ክምችት ጋር ተቀራራቢ ወይም የሚበልጥ ይሆናል፡፡

Page 28: 2 3 - PHE Ethiopiaphe-ethiopia.org/pdf/Toolkit_Semien_amharic.pdf · 2 3 2006 ዓ/ ም አዲስ ... ፈንድ ሲሆን ለተደረገው ድጋፍ የኢትዮጵያ ሥነ-ህዝብ&

28 29

ከደን መጐዳት ጋር በተያያዘ ሌሎች እንደ ኒትረስ ኦክሣይድና ሚቴን ያሉ የግሪንሀውስ ጋዞችም ሊፈጠሩ ይችላሉ፡፡ ከደን መጨፍጨፍ የተነሣ የሚከሰት የልቀት መጨመር የተመነጠረው መሬት እንዲሰጥ በሚደረገው አገልግሎት ይወሰናል፡፡ መሬቱ ለእርሻ ማሣ የሚውል ከሆነ ተጨማሪ ልቀት በሚቴን እና በኒትረስ ኦክሣይድ መልክ በከብቶች በማረስ እና ማዳበሪያ በመጠቀም የተነሣ የሚፈጠር ይሆናል፡፡

3.3. የደኖች ካርበን የመሣብ ሁኔታ

ደኖች በተለይም በትሮፒክ አካባቢ የሚገኙት በተፈጥሮ ካርበንን ከከባቢ አየር ውስጥ በፎቶሲንቴሲስ የሚሰበስቡ ሲሆን፣ ይህም ከሚተነፍሱት ወይም በ”ረስፖይሬሽን” ወደ ከባቢ አየር ከሚለቁት የበለጠ ነው፡፡ ካርበንን የሚሰበስቡ ነገሮች በሰው ሠራሽ ምክንያቶች ወደ ከባቢ አየር የሚደረገውን የካርቦን ዳይኦክሣይድ ልቀት በመግታት ረገድ ከፍተኛ ሚና ይጫወታሉ፡፡ በአሁኑ ጊዜ በየዓመቱ በከባቢ አየር ውስጥ ያለው የካርቦንዳይኦክሣይድ ክምችት መጨመር ይህ በፎቶሲነቴሲስ የመሰብሰብ ሁኔታ ባይኖር ኖሮ ከነዳጅ መቀጣጠል የተነሳ ከሚፈጠረው ልቀት በ75 በመቶ የሚበልጥ ይሆን ነበር፡፡

ይህ የሚያመለክተው ደኖች ካርበንን በመሣብ አምቀው የማያስቀሩ ባይሆን ኖሮ በሰው ሠራሽ ምክንያቶች ወደ ከባቢ አየር የሚለቀቀው የካርቦንዳይኦክሣይድ መጠን በእጅጉ የበለጠ ይሆን ነበር፡፡

የሕዝብ ብዛት መጨመርና የሀብት ክምችት ለግብርና ምርቶችና ለጣውላ ፍላጐት መጨመር ምክንያቶች ናቸው፡፡ በአሁኑ ጊዜ ይህንን ፍላጐት ለማሟላት ደኖችን የመጨፍጨፍ ተግባር እየተከናወነ ይገኛል፡፡ በመሆኑም የመሬት ምርታማነት ለመጨመር እና የአካባቢን ዘላቂነት ለማረጋገጥ ዘላቂነትን መሠረት ያደረገ የመሬት አያያዝ እና ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን መጠቀሙ እጅግ ወሣኝ ነው፡፡

3.4. የካርበን ዑደት

ካርበን ተከታታይነት ባለው ሁኔታ በከባቢ አየር፣ በውቅያኖስ፣ በመሬት እና በዕፅዋት መካከል ይቀያየራል፡፡ በአጭር ጊዜ ውስጥ ካርቦንዳይኦክሣይድ በዕፅዋት መካከል፣ በዛፎች፣ በእንስሳት እና በአየር መካከል የሚቀያየር ሲሆን በውቅያኖስና በከባቢ አየር መካከልም በጋዝ ልውውጥ መልክ ይቀያየራል፡፡ ከአለት፣ በአየር ጠባይ መለዋወጥ እና ከነዳጅ መፈጠር ጋር በተያያዘ የሚኖረው የካርበን ዑደት እጅግ ዘገምተኛ በመሆኑ ብዙ ክፍለ-ዘመናትን የሚወስድ ሂደት ነው፡፡ ለምሳሌ ያህል አብዛኛው የዓለማችን የነዳጅ ክምችት የተፈጠረው ከብዙ ሚሊዮን ዓመታት በፊት የዕፅዋትና የእንስሳት ቅሪቶች ከውቅያኖስ በታች በአሸዋ ሥር በተቀበሩ ጊዜ ነው፡፡ ከዚህ ካርበን ውስጥ ጥቂት ብቻ በየዓመቱ የካርበን ዑደት በማጠናቀቅ ከእሣተ ገሞራ አማካኝነት ወደ ከባቢ አየር ይለቀቃል፡፡ እንደ ከሰል፣ ነዳጅ፣ የተፈጥሮ ጋዝ የማውጣትና በማቃጠል ተግባራት ላይ ያሉ ሰዎች በአጭር ጊዜ ውስጥ ብዙ ካርበን እንዲለቀቅ በማድረግ የተፈጥሮው የካርበን ዑደት እንዲዛባ ያደርጋሉ፡፡ ከዚህ በታች በምስል-4 በከባቢ አየር በመሬትና በውቅያኖስ መካከል ያለው የካርበን ዑደት ተመልክቷል፡፡

Page 29: 2 3 - PHE Ethiopiaphe-ethiopia.org/pdf/Toolkit_Semien_amharic.pdf · 2 3 2006 ዓ/ ም አዲስ ... ፈንድ ሲሆን ለተደረገው ድጋፍ የኢትዮጵያ ሥነ-ህዝብ&

28 29

ምስል-4 የካርበን ዑደት

ምንጭ፡- የአሜሪካ ብሔራዊ የጥናትና ምርምር ካውንስል

3.5. የግሪንሀውስ ጋዝ ተፅዕኖ

የኢንዱስትሪ አብዮት ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ በሰው ሠራሽ ምክንያቶች የግሪንሀውስ ጋዝ ልቀት በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መጥቷል፡፡ በመሆኑም በከባቢ አየር ውስጥ ያለው ክምችትም ጨምሯል፡፡ በከባቢ አየር ውስጥ ከፍተኛ የሆነ የግሪንሀውስ ጋዝ ክምችት መኖር ወደ ህዋ ተንፀባርቆ ይመለስ የነበረው የፀሐይ ብርሃን ሙቀት በምድር ከባቢ አየር ውስጥ እንዲቀር ያደርጋል፡፡ ይህ ሁኔታ ደግሞ የዓለም የሙቀት መጠን እንዲጨምርና የአየር ንብረት ለውጥ እንዲከሰት ያደርጋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ብዙ የግሪንሀውስ ጋዞች ለረጅም ጊዜ በከባቢ አየር ውስጥ የሚቆዩ በመሆናቸው ከአሁኑ ጊዜ ጀምሮ የግሪንሀውስ ጋዞች ልቀት በከፍተኛ ደረጃ ቢቀንስ ወይም ሙሉ በሙሉ ቢቆም እንኳን ከልቀት ጊዜው ጀምሮ የአየር ንብረት የክምችት ሁኔታውን የማመጣጠን ሂደት እስኪያከናውን ድረስ ሰፊ የጊዜ ክፍተት በመኖሩ የዓለም ሙቀት የመጨመሩ ሁኔታ የሚቀጥል ይሆናል፡፡ የግሪንሀውስ ተፅዕኖ ዓለማችን ሙቀት እንዲኖራት ለማድረግ አስፈላጊ የሆነ የተፈጥሮ ክስተት ነው፡፡ ልክ እንደ የቤት መስኮት ግሪንሀውስ ጋዞችም የፀሐይ ብርሃን ወደ ከባቢ አየር እንዲገባና እንዲቀር ያደርጋሉ፡፡ እነዚህ ጋዞችም ካርቦንዳይኦክሳይድ፣ ሚቴን፣ ኒትረስ ኦክሣይድ እና የውሃ ትነት ናቸው፡፡ እንደ የነዳጅ ማቀጣጠል ያሉ የሰዎች ተግባራት የብዙ ግሪንሀውስ ጋዞች ክምችት እንዲጨምር ያደርጋሉ፡፡

ከፀሐይ ኃይል ውስጥ ግማሽ ያህሉ በከባቢ አየር ውስጥ በማለፍ በምድር ገጽ ይሰበሰባል፡፡ ከዚያም የምድር ገጽ የሙቀት ኃይሉን መልሶ ወደ ህዋ ያንፀባርቀዋል፡፡ በዚህ ሂደት ውስጥ የሙቀት ኃይሉ በአብዛኛው በከባቢ አየር ውስጥ በሚገኙ የግሪንሀውስ ጋዞች ሞሎክዮሎች ይሰበሰባል፡፡ የዚህ ሂደት ውጤትም የምድር ገጽ ሙቀት እንዲኖረውና የሙቀቱም መጠን ሕይወት በምድር ላይ ለመኖር በሚያስችል ደረጃ ብቻ እንዲገደብ ያደርጋል፡፡ ወደ ከባቢ አየር ከፍተኛ የሆነ የካርቦን ልቀት የሚኖር ከሆነ ይህ ከባቢ አየርን የሸፈነው የግሪንሀውስ ጋዞች ክምችት ከሚፈለገው

Page 30: 2 3 - PHE Ethiopiaphe-ethiopia.org/pdf/Toolkit_Semien_amharic.pdf · 2 3 2006 ዓ/ ም አዲስ ... ፈንድ ሲሆን ለተደረገው ድጋፍ የኢትዮጵያ ሥነ-ህዝብ&

30 31

መጠን በላይ እንዲሆን በማድረግ ከሚፈለገው በላይ የሆነ የፀሐይ ሙቀት እንዲቀር ያደርጋል፡፡ የዓለማችን አማካይ የሙቀት መጠን መጨመር በዓለም የተፈጥሮ ሥርዓቶች ላይ ብዙ አሉታዊ ተፅዕኖዎችን ያስከትላል፡፡

ምስል-5 የግሪንሀውስ ጋዝ ተፅዕኖ

ምንጭ፡- የፖርትላንድ ከተማና መልቲኖማ ካውንቲ (2009)

Page 31: 2 3 - PHE Ethiopiaphe-ethiopia.org/pdf/Toolkit_Semien_amharic.pdf · 2 3 2006 ዓ/ ም አዲስ ... ፈንድ ሲሆን ለተደረገው ድጋፍ የኢትዮጵያ ሥነ-ህዝብ&

30 31

4. ብዝሀ ሕይወትና የአየር ንብረት ለውጥ

4.1. የአየር ንብረት ለውጥ በብዝሀ ሕይወት ሥርጭት ላይ የሚያስከትላቸው ተፅዕኖዎች

በሰፊው እንደሚታወቀው ብዝሀ ሕይወት ማለት ዕፅዋት፣ እንስሳት፣ ረቂት ሕዋሣት፣ ሥነምህዳር እና በዝሪያዎች ዘረመል፣ በቴክቶኒክ፣ በሰው-ሠራሽ በባዮሎጂካል፣ ወዘተ ምክንያቶች የሚወሰን ነው፡፡

ብዝሀ ሕይወት የተለያዩ ሕይወት ያላቸው ነገሮች መጠሪያ ነው፡፡ የአየር ንብረት ለውጥ በመቋቋም የመኖር ሂደት ሰው-ሰራሽና ተፈጥሯዊ የሆኑ ሥርዓቶች ለአየር ንብረት ለውጥ ያላቸውን ተጋላጭነት ለመቀነስ የሚረዱ ተግባራትን ያካተተ ነው፡፡ ብዝሀ ሕይወት የሚወሰነው በአየር ንብረት የመለዋወጥ ሁኔታ የቦታው የምርታማነት ሁኔታ፣ ቀደም ብሎ የነበረው የብዝሀ ሕይወት ሁኔታ፣ ሕይወት ያላቸው ነገሮች እርስ በራሣቸው የሚኖራቸው ግንኙነቶች መጠንና ተያያዥ የመሆን ሁኔታ ወዘተ ላይ ነው፡፡ ብዙ ጥናቶች እንደሚያስረዱት ባለፉት ዘመናት በአየር ንብረት ላይ የደረሰው ለውጥ በዝሪያዎች ሥፋት ላይ ትልቅ የሚባል ለውጥ አስከትሏል፡፡ በየዓመቱ 3.2 ጊጋ ቶን ያህል የከባቢ አየር ካርበን የሚለቀቅ ሲሆን ይህም በመሬትና በውቅያኖስ ተወግዶ የሚቀረውን ሣይጨምር ነው፡፡ ከአስራ አምስት ዓመታት በፊት ብዝሀ ሕይወት ማለት አየር፣ መሬት፣ የመሬት ላይ ውሃ፣ ደኖች፣ የባህር ዳርቻና የውሃ ውስጥ ሀብቶች እንደሆነ ተደርጐ ይወሰድ ነበር፡፡ ከሥነምህዳር አንጻር ሲስተም ውስብስብና ተለዋዋጭነት ያለው የተፈጥሮ መጠለያ እንዲሁም ሕይወት ያላቸውና ሌሎች ሀብቶች በሰፊው እርስ በራሣቸው ላይ ተፅዕኖ የሚፈጥሩበት እንደሆነ ነው፡፡ ከብዙ ሚሊዮን ዓመታት በፊት በዓለም የአየር ንብረት ላይ የተከሰተው ለውጥ ከፍተኛ የሆነ የብዝሀ ሕይወት ዝርያዎች፣ የመሬት አቀማመጥ፣ የዝርያዎቹ የሥርጭት ሁኔታ ለውጥ እንዲፈጠር አድርጓል፡፡ በ21ኛው ክፍለ ዘመን ይኖራል ተብሎ የሚጠበቀው የአየር ንብረት ለውጥ ግን ባለፉት 1.8 ሚሊዮን ዓመታት ከተከሰቱት ለውጦች አንጻር ታይቶ የማይታወቅና እጅግ ከፍተኛ ይሆናል ተብሎ ይገመታል፡፡ የሰው ልጅ ምድርን በስፋት ከመቆጣጠሩ ጋር ተያይዞ ዝርያዎች በአሁኑ ዘመን ከተለዋዋጭ ሁኔታዎች ጋር እራሣቸውን አጣጥመው የመቀጠላቸው ሁኔታም አጠያያቂ እየሆነ መጥቷል፡፡ ትርፋማ የሆኑ ተግባራት ለሥነምህዳር ውድመት ጉልህ አስተዋጽኦ እያደረጉ ቢሆንም የብዝሃ ሕይወት እንክብካቤና ዘላቂነትን መሠረት ያደረገ አጠቃቀም ወሣኝ ሚና የሚጫወቱበት ሁኔታ አለ፡፡ የተሻለ ለውጥ ሊመጣ የሚችለው የብዝሃ ሕይወት ጥበቃና እንክብካቤን ከዋናው የልማትና የድህነት ቅነሣ ስትራቴጂ ጋር በማቀናጀት ነው፡፡ በሴክተሮች ውስጥ የሚካሄዱ ተግባራትን በተቀናጀ መንገድ ማካሄድና ከሥነምህዳር የሚገኙ አገልግሎቶች ጥቅሞችንና ጉዳቶችን ባገናዘበ አኳኋን እንዲሁም ፍትሐዊ በሆነ መንገድ ለሁሉም ሊደርሱ በሚችሉበት መንገድ ማከናወን ይገባል፡፡

የሥነምህዳር አገልግሎቶች

በጣም ወሣኝ የሆኑ የሥነምህዳር አገልግሎቶች የሚከተሉት ናቸው፡፡

አጋዥ አገልግሎቶች (ሕይወት በዓለም ላይ ለመቀጠል እንዲችል አመቺ ሁኔታዎችን በመፍጠር) የአፈር መፈጠርና ተይዞ መቆየት፣ የኒውትረንት ዑደት፣ ዋነኛ ምርት፣ ፖሊኔሽን፣ የካርበንዳይኦክሣይድ መመረት፣ በመጠለያነት ማገልገል

Page 32: 2 3 - PHE Ethiopiaphe-ethiopia.org/pdf/Toolkit_Semien_amharic.pdf · 2 3 2006 ዓ/ ም አዲስ ... ፈንድ ሲሆን ለተደረገው ድጋፍ የኢትዮጵያ ሥነ-ህዝብ&

32 33

የማረጋጋት አገልግሎቶች (ማለትም የሥነምህዳር ሂደቶችን ከማረጋጋት የሚገኙ ጥቅሞች) የአየር ጥራት በመጠበቅ፣ የአየር ንብረት እና የውሃ ሁኔታዎችን ማረጋጋት፣ ጐርፍ መከላከል፣ ውሃ ማጥራት፣ ቆሻሻ ማስወገድ፣ መርዛማ ነገሮችን ማስወገድ፣ የሰዎች በሽታዎችን መቆጣጠር፣ በሥነ-ሕይወት የከብቶችና የሰብሎች ተባዮችን መቆጣጠር፣ አውሎ ንፋስን መከላከል፤

ምርቶችን የመስጠት አገልግሎት (ከሥነምህዳር የሚገኙ ውጤቶች) ምግብ፣ ማገዶ፣ ቃጫ፣ ባዮ ኬሚካል፣ መድሃኒቶች፣ የዘረመል ሀብቶች፣ የመዋቢያ ነገሮች፣ የመጠጥ ውሃ፣ ማዕድናት፣ አሸዋና ሌሎች ሕይወት የሌላቸው ሀብቶች

ባሕላዊ አገልግሎቶች (ከሥነምህዳር የሚገኙ ቁሣዊ ያልሆኑ ጥቅሞች) የባሕል ማንነት መንፈሳዊና ሃይማኖታዊ እሴቶች፣ የዕውቀት ሥርዓት ትምህርታዊ እና ስነ ውበታዊ እሴቶች፣ ማኀበራዊ ግንኙነቶች የባህል ቅርስ፣ መዝናኛና ኢኮቱሪዝም፣ ተምሳሌታዊ ጥቅሞች ናቸው፡፡

ምስል 6፡ በብዝሃ ሕይወት፣ በሥነምህዳር አገልግሎቶች እና በሰዎች ደህንነት መካከል ያለ ግንኙነት

ምንጭ፡- ዊንሮክ ኢንተርናሽናል (ህንድ 2006 እ.ኤ.አ)

ከዚህ በላይ የተመለከተው ዲያግራም ብዝሃ ሕይወት እንዳይጐዳ ለማድረግ ከግምት ውስጥ መግባት ያለባቸውን ጉዳዮች ነው፡፡ በገበያ የሚሸጡና የሚገዙት ብቻ ሣይሆን ሁሉም የሥነምህዳር አገልግሎቶች ዋጋ ከግምት ውስጥ በማካተት መወሰንና በዋናው የልማትና የድህነት ቅነሳ ስትራቴጂ ውስጥ ማካተት ይገባል፡፡ በመሆኑም ጥበቃና እንክብካቤ ለማድረግም ሆነ ዘላቂነት ባለው ሁኔታ ለመጠቀም የሚደረጉ የተቀናጁ ጥረቶች ለብዝሃ ሕይወት እና ለሥነምህዳር አስፈላጊ የሆኑ የማብቃት ሁኔታዎችን የሚፈጥሩ አካላትን የማጠናከር ሁኔታ አስፈላጊ ይሆናል፡፡ በተለያዩ ኮንቬንሽኖች ወይም ስምምነቶች መካከል ማለትም የብዝሃ ሕይወት ኮንቬንሽኖች መካከል ግንኙነቶችን ለማጠናከር ዕድሉ ያለ ሲሆን በዚህም ግልፅነት የሰፈነበትና አሣታፊ በሆነ የሥነምህዳር አስተዳደር ወይም ቁጥጥርና የብዝሃ ሕይወት ጥበቃና

Page 33: 2 3 - PHE Ethiopiaphe-ethiopia.org/pdf/Toolkit_Semien_amharic.pdf · 2 3 2006 ዓ/ ም አዲስ ... ፈንድ ሲሆን ለተደረገው ድጋፍ የኢትዮጵያ ሥነ-ህዝብ&

32 33

እንክብካቤ ከሁኔታዎች ጋር ተጣጥሞ የመኖር ስትራቴጂ የተሣካ እንዲሆን ከፍተኛ ጠቀሜታ ያለው ከመሆኑ በተጨማሪ ውሣኔዎችንም ለመስጠት የሚያገለግሉ አሠራሮችን በሚገባ መጠቀም ያስችላል፡፡

4.2. ሌሎች የብዝሃ ሕይወት ስርጭት ላይ ተፅዕኖ የሚያስከትሉ ጉዳዮች

ከአየር ንብረት ለውጥ በተጨማሪ በብዝሃ ሕይወት ላይ ተፅዕኖ የሚፈጥሩ ዋና ዋና ሁኔታዎች ወይም ጉዳዮች የሚከተሉትን ያካትታል፡-

የዘረመል መሸርሸርና የዝርያዎች መጥፋት የሚያስከትል የመኖሪያ አካባቢ (ሃቢታት) መጐዳትና መበታተን፡፡

ከግብርና ሥራዎች ከኢንዱስትሪ ልማት ወዘተ ጋር በተያያዘ የዕፅዋት ሽፋን መመናመን፣ የመሬት ቁፋሮ ሲካሄድ የሚከሰተው የመጠለያ (ሃቢታት) መጐዳት

ከፍተኛ የሆነ የዕፅዋትና የእንስሳት ዝርያዎችን የማዳቀል ሥራ ከማከናወን ጋር ተያይዞ የዘረመል አቅም የመዳከም ሁኔታ

ሕይወታዊ ሀብቶችን ከሚገባው በላይ በመጠቀም ምክንያት የሥነምህዳር እና የዝርያዎች የማገገም አቅም መሟጠጥ

ብክለት፣ በተለይ ጨዋማ ባልሆነ ውሃና በባህር ዳርቻዎች የሚገኙ መጠለያዎች ወይም የመኖሪያ አካባቢዎች

በሰዎችና በዱር እንስሳት መካከል ከግብርና ማሣ መስፋፋትና ከሠፈራ ጋር በተያያዘ የሚከሰቱ ግጭቶች

ለአንድ አካባቢ ባዳ የሆኑ ዝርያዎች በደኖች የውሃ አካላት የግብርና ሥርዓቶች ወዘተ የወረራ ሁኔታ መፍጠር

ከህዝብ ቁጥር መጨመር ጋር በተያያዘ በሥነምህዳርና በዝርያዎች ላይ የሚፈጠር ግፊትን ያካትታል፡፡

4.3. ለብዝሃ ሕይወት እንክብካቤ ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር ለመጣጣም የሚደረጉ ጥረቶች ብዝሃ ሕይወትን ለመጠበቅና ለመንከባከብ የአየር ንብረት ለውጥን ያገናዘበ የአኗኗር ሁኔታ ሂደቶች የሚከተሉትን ተግባራት ያካትታሉ፡፡

የአካባቢው ቀደምት የሆነ ሥነምህዳርን መንከባከብና መጠበቅ፣ የመጥፋት ሥጋት የተጋረጠባቸው ዝርያዎችን መንከባከብ፣

ከመጠን በለይ በሆነ የግብርና ሥራ መካሄድ፣ በብክለትና ባዕድ በሆኑ ዝርያዎች መወረር የተነሳ በብዝሃ ሕይወት ላይ የሚፈጠረውን ግፊት ወይም ጫና መቀነስ

የጥበቃ ቦታዎችን መረብ በመዘርጋትና በመካከላቸው የብዝሃ ሕይወት ኮሪደሮችን በመፍጠር ለጥፋት ተጋላጭነታቸውን መቀነስ፤

Page 34: 2 3 - PHE Ethiopiaphe-ethiopia.org/pdf/Toolkit_Semien_amharic.pdf · 2 3 2006 ዓ/ ም አዲስ ... ፈንድ ሲሆን ለተደረገው ድጋፍ የኢትዮጵያ ሥነ-ህዝብ&

34 35

ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር በተያያዘ የጥበቃ ቦታዎችን ተፅዕኖ የመቋቋም አቅም ማጠናከር፤

የዕፅዋትና የእንስሳት መኖሪያ አከባቢዎች ወይም መጠለያዎች ከሌሎች ለእንስሳቱ ወይም ለዕፅዋቱ አመቺ የሆኑና በመጠባበቂያነት ከተከለሉ ቦታዎች ጋር የሚገናኙበት መተላለፊያዎችን በመፍጠር አስፈላጊ በሆኑ ጊዜያት እንስሳቱ መተላለፍ እንዲችሉ ማድረግ፡፡

Page 35: 2 3 - PHE Ethiopiaphe-ethiopia.org/pdf/Toolkit_Semien_amharic.pdf · 2 3 2006 ዓ/ ም አዲስ ... ፈንድ ሲሆን ለተደረገው ድጋፍ የኢትዮጵያ ሥነ-ህዝብ&

34 35

5. በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ የጥበቃ ቦታዎች የሚደረግላቸው እንክብካቤ

5.1. የጥበቃ ቦታዎች አጠቃላይ መግለጫ

የአየር ንብረት ለውጥ በሥነምህዳር ላይም ተፅዕኖ የሚፈጥር ሲሆን በተፈጥሮ ሀብቶች ላይ ጫና ይፈጥራል፡፡ የአየር ንብረት ለውጥን አሳሳቢነት በመረዳት የኢትዮጵያ መንግስት በዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ፣ በኤን.ኤ.ፒ.ኤ፣ እንዲሁም የአየር ንብረትን የሚቋቋም አረንጓዴ ኢኮኖሚ ስትራቴጂዎች የችግሩን ተፅዕኖ ለመግታት ወሳኝነት ይኖራቸዋል፡፡ “የተከለሉ ወይም ጥበቃ የሚደረግላቸው ቦታዎች” የሚለው ሐረግ በብዝሃ ሕይወት ስምምነት/ኮንቬንሽን አንቀጽ 2 ዉስጥ እንደተገለፀው የጥበቃና እንክብካቤ ዓለማዎችን ለማሳካት የተከለሉ ወይም የሚጠበቁ አካባቢዎች ናቸው፡፡ ሆኖም ግን በኢትዮጵያ ውስጥ አብዛኞቹ የተከለሱ ቦታዎች በከፍተኛ ሁኔታ እየተሸረሸሩ ሲሆን ይህም ለግብርና ሥራ፣ ለማገዶና ለግንባታ ሥራ በሚደረግ የደን መጨፍጨፍ፣ ለከብት ግጦሽ ለመጠቀም በሚደረጉ ጉዳት እጨመረ ባለው የሕዝብ ቁጥር ዘላቂነትን መሠረት ያላደረገ የተፈጥሮ ሀብት አጠቃቀም፣ የወጡ ደንቦችና መመሪያዎችን ተፈጻሚ በማድረግ ረገድ ባለው ድክመት፣ እንዲሁም የአየር ንብረት ለውጥን በተመለከተ የማህበረሰብ ግንዛቤ አነስተኛ መሆን ችግሩን በማባባስ ረገድ ከፍተኛ ሚና አላቸው፡፡ ስለዚህ የኢትዮጵያን የብዝሃ ሕይወት ዝሪያዎች እና ሥነምህዳርን የመጠበቅና የመንከባከብ ተግባራት ዘላቂነት ያለው ልማት ለማጠናከር፣ የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖዎችን ለመግታት እና ሕይወት እንዲቀጥል የሚያደርጉ ሥርዓቶችን ለመጠበቅና ለመንከባከብ እጅግ ወሳኝ ነው፡፡

5.1.1. የጥበቃ ቦታዎች ጠቀሜታ

የተከለሉ ወይም ጥበቃ የሚደረግላቸው ቦታዎች ለሰዎችና ለሰው ልጅ ደህንነት ጠቃሚ የሆኑ ብዙ አገልግሎቶች አሏቸው፡፡ የጥበቃ ቦታዎች ዋና ዋና ጥቅሞች የሚከተሉት ናቸው፡፡

የብዝሃ ሕይወት እንክበካቤ፡- የዘረመል ሀብቶችና ሕይወታዊ ብዝሃነትን መንከባከብ፤

የተፋሰስ ጥበቃ/ እንክብካቤ፡- ለሃይድሮ ኤሌክትሪክ፣ ለመስኖ፣ እና ለውሃ አቅርቦት ሥራዎች የሚውሉ አካባቢዎች የተፋሰስ አከባቢን መጠበቅ፤ ከባድ ንፋስ መከላከል፡- የባሕር ዳርቻዎች በማዕበልና በአውሎ ንፋስ እንዳይጐዱ መከላከል፤

ቱሪዝም፡- ተፈጥሯዊ የሆኑ የቱሪዝም መዳረሻ ቦታዎች እና መዝናኛዎች በመሆን አገልግሎት መስጠት፤

የአንድ አከባቢ የአየር ንብረትን በማረጋጋት የአካባቢን የአየር ንብረት ሁኔታዎች እንክብካቤ እንዲያገኙ ማስቻልና ለአካባቢ ማህበረሰቦች አገልግሎት መስጠት፤

የደን ውጤቶች የጣውላ ምርትን ጨምሮ ሌሎች የተለያዩ ውጤቶች አቅርቦት ማዋል፤

Page 36: 2 3 - PHE Ethiopiaphe-ethiopia.org/pdf/Toolkit_Semien_amharic.pdf · 2 3 2006 ዓ/ ም አዲስ ... ፈንድ ሲሆን ለተደረገው ድጋፍ የኢትዮጵያ ሥነ-ህዝብ&

36 37

ካርቦን መሰብሰብ በከባቢ አየር ውስጥ ያለውን ካርቦን በመሰበሰብ በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት ሊመጡ የሚችሉ ተፅዕኖዎችን በመቀነስ ረገድ አስተዋጽኦ ማድረግ፤ ለትምህርት፣ ለጥናትና ምርመር፣ ለሳይንሳዊ ጥናትና ምርምሮች የሚሆኑ ቦታዎች፣ የኢኮሎጂ፣ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ትምህርት መስጠት፤

ባህላዊ እሴቶች - ባህላዊ ጠቀሜታ ያላቸው አካባቢዎችና ሀብቶች እንዲጠበቁ ማድረግ እና የአንድን ሀገር የተፈጥሮ ቅርሶች ማሣየትን ያካትታል፡፡

5.1.2 የጥበቃ ቦታዎች ዋና ዋና ሥጋቶች

የጥበቃ ቦታዎች ዋና ዋና ሥጋቶች የሚከተሉት ናቸው፡፡

እንደ ዕፅዋትና እንስሳት ያሉ ወይም በውሃ አካላት የሚኖሩ ሕይወት ያላቸው ነገሮች በአጠቃላይ ከጥበቃ ቦታዎች መጥፋት፣

በጥበቃ ቦታዎች ውስጥ የብዝሃህይወት በግብርና፣ በግጦሽ፣ በብክለት፣ በደን መጨፍጨፍ ወዘተ መመናመን የዕፅዋት ሽፋን መራቆት፣ በመንገድ ግንባታ፣ በሠፈራ መስፋፋት፣ በማዕድን ሥራ ወዘተ መጐዳት በአጠቃላይ ከአካባቢው የመነጠል ወይም የመለየት ሁኔታ

በመጤ ዝሪያዎች መወረር ናቸው፡፡

የሀገሪቱ ሥነ-ሕይወታዊ ጂኦግራፊያዊ ሁኔታ ሁለት ዋና ዋና መገለጫዎች ያሉት ሲሆን የመጀመሪያው ጥንታዊ የሆነና የአፍሪካ ቀንድ በረሃማ ሥፍራዎች ለየት ያሉ መገለጫ ከሆኑት ውስጥ አንዱ ማለትም ኦጋዴን በኢትዮጵያ የሚገኝ መሆኑ ነው፡፡ ሁለተኛው ደግሞ የከፍተኛ ቦታ ኘላቶዎቿ ናቸው፡፡ ኢትዮጵያ በከፍተኛ ሥፍራ ላይ በመገኘቷ ከአካባቢዎቿ ለየት ማለቷ በሀገሪቱ ብቻ የሚገኙ የብዝሀ ህይወት ሀብት እንዲበራከት አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡ ስለዚህ በረሃማው የሀገሪቱ ምሥራቃዊ ጫፍ እና ከፍተኛ ቦታዎቿ በአንጻራዊነት በዝሪያዎች ብዛት አነስተኛ ቢሆኑም በሀገሪቱ ብቻ የሚገኙት ብርቅዬ እጽዋትና እንስሳት ብዙ ናቸው፡፡ በመሆኑም ኢትዮጵያ ከ7ሺህ በላይ የሚሆኑ የዕፅዋት ዝሪያዎች፣ 861 የአዕዋፋት ዝርያዎች፣ 279 የአጥቢ እንስሳት ዝርያዎች፣ 201 የተሣቢ እንስሳት ዝርያዎች፣ 23 ባህር ውስጥ የሚኖሩ የዓሣ ዝርያዎች አሏት፡፡ በሀገሪቱ የሚገኙ ዕፅዋት በአምስት ዋና ዋና ባዮሞች ይከፈላሉ፡፡ ሱዳንያን፣ ኮንጐ-ጊኒያን፣ የሣህል ቆላማ ዞን፣ ሶማሊ-ማሣይ፣ እንዲሁም አፍሮ-ትሮፒካል እና ሞንቴን ናቸው፡፡ እነዚህ ደግሞ በአሥር ትላልቅ ሥነምህዳሮች ሊከፈሉ ይችላሉ፡፡

1. አፍሮ-አልፖይን እና ሰብ-አልፖይን 2. ደረቅና ለምለም የሞንቴን ደን እና በሣር የተሸፈነ መሬት 3. እርጥብና ለምለም የሞንቴን ደን 4. እርጥብና ለምለም የዝቅተኛ አካባቢ ደን 5. የኮንጐ-ጊኒያን ደን

Page 37: 2 3 - PHE Ethiopiaphe-ethiopia.org/pdf/Toolkit_Semien_amharic.pdf · 2 3 2006 ዓ/ ም አዲስ ... ፈንድ ሲሆን ለተደረገው ድጋፍ የኢትዮጵያ ሥነ-ህዝብ&

36 37

6. ግብርና ቁጥቋጦ የበዛባቸው አካባቢዎች 7. አኬዢያ-ኮሚፎራ አካባቢዎች 8. ኮምብሬተም- ተርሚናሊያ አካባቢዎች 9. ሐይቆች፣ ረግረጋማ ቦታዎች እና ወንዞች 10. በረሃማ ሥፍራዎች

የእነዚህ ሥነምህዳሮች ዓለማቀፋዊ ጠቀሜታ በዓለማቀፍ የብዝሃ ሕይወት ጥበቃና እንክብካቤ ተቋም እውቅና የተሰጠው ነው፡፡ ሀገሪቱ ሁለት የብዝሃ ሕይወት ዋነኛ ሥፍራዎች ወይም አካባቢዎች የያዘች ስትሆን እነርሱም የአፍሪካ ቀንድና የኢትዮጵያ ከፍተኛ ቦታዎች (በምስራቃዊ አፍሮ-ሞንቴን ውስጥ የሚጠቃለሉ) ናቸው፡፡ የብዝሃ ሕይወት ዋነኛ ማዕከል ተደርገው የሚወሰዱ አካባቢዎች በአብዛኛው በሀገሪቱ ውስጥ የሚገኙ ሲሆኑ በእነዚህ ውስጥም ከባህር ጠለል በላይ ከ1100 ሜትር በታች የሆነው ምስራቃዊ ክፍል እና ከባህር ጠልል በላይ ከ1100 ሜትር በላይ የሆኑ ከፍተኛ ሥፍራዎች ይጠቃለላሉ፡፡

5.2. የጥበቃ ቦታዎች ስርጭትና ዓይነት

ዋና ዋና የጥበቃ ሥፍራዎች ክልላዊ ሥርጭት፣ የተመሠረቱበት ዘመን እና የቆዳ ስፋት እንዲሁም በዓይነታቸው ብሔራዊ ፖርኮችን፣ የዱር እንስሳት መጠለያዎችን፣ የዱር እንስሳት ጥብቅ ሥፍራዎችን፣ የማኀበረሰብ የጥበቃ ሥፍራዎችን፣ የዱር እንስሳት የነፍስ-አድን ማዕከላትን፣ የቁጥጥር አደን ቀበሌዎችን እና ባዮስፌር ሪዘርቮችን ያካተቱ ሲሆን ከዚህ በታች በቀረበው ሠንጠረዥ ውስጥ ተመልክተዋል፡፡

Page 38: 2 3 - PHE Ethiopiaphe-ethiopia.org/pdf/Toolkit_Semien_amharic.pdf · 2 3 2006 ዓ/ ም አዲስ ... ፈንድ ሲሆን ለተደረገው ድጋፍ የኢትዮጵያ ሥነ-ህዝብ&

38 39

ሠንጠረዥ-3፡- የጥበቃ ቦታዎች ሥርጭት

ተ.ቁ የተከለለው ሥፍራ መጠሪያ

ክልላዊ ሥርጭት

የተመሠረተበት ዘመን

(እ.ኤ.አ)

የቆዳ ስፋት በኪ/ሜ2

1. ብሔራዊ ፖርኮች

1 ቃፍታ ሺራሮ ትግራይ 2007 2117

2 የሰሜን ተራሮች አማራ 1966 412

3 አላጥሽ አማራ 2005 2666

4 ባህር ዳር የጥቁር አባይ ወንዝ ሚሊኒየም

አማራ 2008 4729

5 ቦረና ሣይንት አማራ 2008 43256 ያንጉዲ-ራሣ አፋር 1977 47317 አዋሽ ኤሮሚያና

አፋር 1966 756

8 ዳቲ ወለል ኦሮሚያ 2010 10359 የባሌ ተራሮች ኦሮሚያ 1970 220010 ቦረና ኦሮሚያ 2013 100011 አብያታ ሻላ ኦሮሚያ 1970 887

12 የአርሲ ተራሮች ኦሮሚያ 2011 938

13 ገራሌ ሱማሌ 2006 385814 ጋምቤላ ጋምቤላ 1974 5061

15 ነጭሣር የ ደ ቡ ብ ብ / ብ / ሕ /ክልል

1974 514

16 ኦሞ የ ደ ቡ ብ ብ / ብ / ሕ /ክልል

1976 3566

17 ማጐ የ ደ ቡ ብ ብ / ብ / ሕ /ክልል

1974 1942

18 ማዜ የ ደ ቡ ብ ብ / ብ / ሕ /ክልል

2005 225

19 ጊቤ ሸለቆ የ ደ ቡ ብ ብ / ብ / ሕ /ክልል

2009 248

20 ሎቃ አባያ የ ደ ቡ ብ ብ / ብ / ሕ /ክልል

2009 500

21 ጨበራ ጩርጩራ የ ደ ቡ ብ ብ / ብ / ሕ /ክልል

1997 1190

Page 39: 2 3 - PHE Ethiopiaphe-ethiopia.org/pdf/Toolkit_Semien_amharic.pdf · 2 3 2006 ዓ/ ም አዲስ ... ፈንድ ሲሆን ለተደረገው ድጋፍ የኢትዮጵያ ሥነ-ህዝብ&

38 39

2. የዱር እንስሳት መጠለያዎች

1 የባቢሌ የዝሆኖች መጠለያ ኦ ሮ ሚ ያ ና አፋር

1969 6982

2 የስንቅሌ የቆርኬዎች መጠለያ

ኦ ሮ ሚ ያ ና ደቡብ

1972 54

3. የዱር እንስሳት ጥብቅ ክልል 1 ጨልቢ ደቡብ ክልል - 42122 አሊዳጌ (ሃላይዳጌ) አፋር -- -3 ሚሌ ሰርዶ አፋር4 ገዋኔ አፋር3 ሊማ ሊሞ አማራ - -

4. የማኀበረሰብ ጥበቃ ሥፍራዎች1 ታማ ደቡብ ክልል - 16652 ሰሜን ጊቤ ደቡብ ክልል 2001 493 ጋራሜባ ደቡብ ክልል 2001 254 መንዝ ጉዋሣ አማራ - 1005 አቡነ ዮሴፍ (ላሊበላ

አቅራቢያ )አማራ - 50

6 ዝዋይ ኦሮሚያ 20037 ምሥራቅ ላንጋኖ ኦሮሚያ 20038 ሌፒስ ኦሮሚያ 20039 ኮንሶ ደቡብ ክልል 200310 ዶርዜ ደቡብ ክልል 200311 ማዜ ደቡብ ክልል 2003

5. የዱር እንስሳት የነፍስ አድን ማዕከላት

1 የእንሰሳ ኮቴ የዱር እንስሳት መንከባከቢያና የትምህርት ማዕከል (ሆለታ)

ኦሮሚያ 2009 0.78

2 ጣራ የዱር እንስሳት (ዝንጅሮና ጦጣ ) ማዕከል

አማራ - -

6. የቁጥጥር የአደን ቀበሌዎች 1 አስባህሬ አፋር 2012 1742 ብሌን ሄርታሌ አፋር - 10903 ጭፍራ አፋር 1998 5104 መልካ ሰዲ አፋር 2012 1225 ተላላክ-ዳዌ አፋር - 5806 አባሸባ ደመሮ ኦሮሚያ 1994 1667 አሉቶ ኦሮሚያ - 280

Page 40: 2 3 - PHE Ethiopiaphe-ethiopia.org/pdf/Toolkit_Semien_amharic.pdf · 2 3 2006 ዓ/ ም አዲስ ... ፈንድ ሲሆን ለተደረገው ድጋፍ የኢትዮጵያ ሥነ-ህዝብ&

40 41

ምንጭ፡- ጀምስ ያንግ (2012 እ.ኤ.አ)

8 አርባጉጉ ኦሮሚያ 1995 3389 በስመና-ኦዶቡሉ ኦሮሚያ 1993 35010 ዲንዲን ኦሮሚያ - 28511 ሃንቶ ኦሮሚያ 1991 20612 ሃሮ አባዲኮ ኦሮሚያ 2000 24413 ሁርፋ ሶማ ኦሮሚያ 2000 23114 ሙኔሣ-ኩኬ ኦሮሚያ 1993 11115 ሸደም በርበሬ ኦሮሚያ 1988 17016 ዑርጋን ቡላ ኦሮሚያ 2000 7817 ሙሩሌ የደቡብ ክልል - 69018 ወልሼት ሣላ የደቡብ ክልል 2000 28819 ደምበል-አይሾ-አዲገላ ሱማሌ 2012 91020 ሽንሌ ሜጦ ሱማሌ 2012 484

7. የባዮሰፌር ሪዘርቦች 1 ያዩ ኦሮሚያ 2010 4672 የከፋ የቡና ደን አካባቢ ደቡብ ክልል 2010 4673 ሸካ (በጋምቤላና በጐደሬ

አቅራቢያ)ደቡብ ክልል - -

4 የጣና ሐይቅ አማራ - -

Page 41: 2 3 - PHE Ethiopiaphe-ethiopia.org/pdf/Toolkit_Semien_amharic.pdf · 2 3 2006 ዓ/ ም አዲስ ... ፈንድ ሲሆን ለተደረገው ድጋፍ የኢትዮጵያ ሥነ-ህዝብ&

40 41

ምስል 7፡ በኢትዮጵያ ውስጥ የጥበቃ ቦታዎች ሥርጭት ዓይነት

5.3. የጥበቃ ቦታዎችና የአየር ንብረት ለውጥን በመቋቋም ለአረንጓዴ ኢኮኖሚው ልማት ያላቸው አስተዋጽኦ

በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ የጥበቃ ቦታዎች እጅግ ብዙ የሆነ የእንስሳትና የዕፅዋት ዝርያዎች ያሏቸው ሲሆኑ፣ ከፍተኛ የሆነ የእልቂት ወይም የመጥፋት ሥጋት የተጋረጠባቸው ወሣኝ የሆኑ የብዝሃ ሕይወት ጥበቃና እንክብካቤ ቦታዎች ናቸው፡፡ በአሁኑ ወቅት እነዚህን አካባቢዎች በመንከባከብ ረገድ ከፍተኛ የሆነ ሥጋት በመፍጠር ላይ ካሉ ጉዳዮች መካከል ዋና ዋናዎቹ፡- የሕዝብ ብዛትና ተያያዥ የሠፈራ መስፋፋት ሂደት፣ የግብርና ማሣ የማስፋፋት ሥራ፣ እየጨመረ ያለ የኃይል ፍላጐት፣ ድህነትና የምግብ ዋስትና አለመረጋገጥ፣ በሰዎችና በዱር እንስሳት መካከል የሚነሱ ግጭቶች በእነዚህ አካባቢዎች የአካባቢ መጐዳት እንዲባባስ እና ከአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖዎች ጋር ተዳምሮ የብዝሃ ሕይወት መመናመን እንዲፈጠር አድርገዋል፡፡ በመሆኑም እነዚህን የጥበቃ ሥፍራዎችን የመንከባከብና

መክፈቻ ፡ 1. ቃፍታ ሽራሮ 2. የሰሜን ተራሮች 3. አላጥሽ 4. ባህር ዳር የጥቁር አባይ ሚሊኒየም 5. ቦረና ሣይንት 6. ያንጉዲ-ራሣ 7. አዋሽ 8. ዳቲ-ወለል 9. የባሌ ተራሮች 10. ያቤሎ 11. አብያታ ሻላ 12. የአርሲ ተራሮች 13. ገራሌ 14. ጋምቤላ 15. ነጭሣር 16. ኦሞ 17. ማጐ 18.ማዜ 19.ጊቤ ሸለቆ 20. ሎቃ አባያ 21. ጨበራ ጩርጩራ

Page 42: 2 3 - PHE Ethiopiaphe-ethiopia.org/pdf/Toolkit_Semien_amharic.pdf · 2 3 2006 ዓ/ ም አዲስ ... ፈንድ ሲሆን ለተደረገው ድጋፍ የኢትዮጵያ ሥነ-ህዝብ&

42 43

የመጠበቅ ተግባራት ለብዝሃ ሕይወት እና አካባቢ ጥበቃ ዘላቂነት እንዲሁም ከቱሪዝምና ከተለያዩ የሥነምህዳሮች ውጤቶችና አገልግሎቶች በሚገኙ ገቢዎች ለሀገር ኢኮኖሚ ትልቅ ፋይዳ ይኖራቸዋል፡፡

5.3.1. የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋም የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ስትራቴጂ

የኢትዮጵያ አረንጓዴ ኢኮኖሚ ስትራቴጂ በሀገሪቱ መንግሥት በ2003 የተዘጋጀ ሲሆን እንደ ራዕይ የያዘውም ሀገሪቱ በ2017 ዓ.ም (2025 እ.ኤ.አ) መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሀገራት ጐራ ለመቀላቀል ትችል ዘንድ የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋም አረንጓዴ ኢኮኖሚ የልማት ስትራቴጂን መተግበር ነው፡፡ እንዲሁም የሀገሪቱን የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ማሣካት፣ የምዕተ-ዓመቱን ግቦች ማሣካት፣ ከካርበን ልቀት የነጻ እና ኃይል ቆጣቢ ወደሆነ ኢኮኖሚ መሸጋገር፣ በአካባቢ ላይ ተፅዕኖ የማያስከትል ዘላቂነት ያለው የኢኮኖሚ ዕድገትና የአካባቢ ዘላቂነትን ማረጋገጥ የስትራቴጂው ዓላማዎች ናቸው፡፡ የአረንጓዴ ኢኮኖሚው ስትራቴጂ አራት ዋና ዋና መሠረቶች ያሉት ሲሆን እነርሱም፡-

የሰብሎች ምርትና የከብቶች እርባታን በማሻሻል የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥና የአርሶ አደሮች ገቢ እንዲጨምር ማድረግ እንዲሁም በግብርና ዘርፍ ያለውን የልቀት መጠን መቀነስ፤

ከኢኮኖሚና ከሥነምህዳር ግልጋሎቶቻቸው አንጻር ደኖችን መጠበቅና መንከባከብ፤ በኃይል አቅርቦት ዘርፍ የታዳሽ ኃይል በማስፋፋት ኤሌክትሪክ ማመንጨትና ለሀገር ውስጥ እና ለጎረቤት ሀገር ገበያ ማቅረብ፤

በትራንስፖርት፣ በኢንዱስትሪ እና በግንባታ/ኮንስትራክሽን ዘርፎች እየተደረገ ያለውን ጥረት በማጠናከር ወደ ዘመናዊና ኃይል ቆጣቢ ቴክኖሎጂዎች በማሸጋገር የግሪንሀውስ ጋዞች ልቀትን ሙሉ በሙሉ መግታት ናቸው፡፡

አረንጓዴ ኢኮኖሚ የሚለው ፅንሰ-ሃሣብ የሚያመለክተው በአካባቢ ላይ ተፅዕኖ የማያስከትል፣ የተፈጥሮ ሀብቶችን በመንከባከብ ላይ የተመሠረተ፣ አረንጓዴ ኃይልና የሥራ ዕድሎች ለመፍጠር የሚችል የኢንቨስትመንት አቅም፣ ብክለትና ልቀቶች እንዲቀንሱ በማድረግ፣ በማምረት ሂደት አገልግሎቶችን በማቅረብ ረገድ እና እነዚህን በመጠቀም ረገድ በአካባቢ ላይ ጉዳት የማያስከትል የኢኮኖሚ ሥርዓት ነው፡፡

በመሆኑም የአረንጓዴ ኢኮኖሚ መርሆች የተመሠረቱት፡-

ዘላቂነት ያለው ልማት አስተሣሰቦች፤

ፍትሐዊነትና የድህነት ቅነሳ፤

ተፅዕኖዎችን የመቋቋም አቅም፤

ሁሉ-ዓቀፍነት እና

ዘላቂነት ያለው አካባቢ በመፍጠር ላይ የተመሠረቱ ናቸው፡፡

Page 43: 2 3 - PHE Ethiopiaphe-ethiopia.org/pdf/Toolkit_Semien_amharic.pdf · 2 3 2006 ዓ/ ም አዲስ ... ፈንድ ሲሆን ለተደረገው ድጋፍ የኢትዮጵያ ሥነ-ህዝብ&

42 43

ይህንን ለማሳካት በሚደረጉት ጥረቶች ውስጥ የጥበቃ ቦታዎች በተለያየ መንገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያላቸው ሲሆን ለምሳሌ ያህል የካርበን ልቀትን በመቀነስ ወይም በከባቢ አየር ውስጥ ያለውን ካርቦን በመሰብሰብ ከካርበን ልቀት ነጻ የሆነ የኢኮኖሚ ዕድገት እንዲኖር ብሎም የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም የሚችል አረንጓዴ ኢኮኖሚን ለመገንባት ወሣኝነት ይኖራቸዋል፡፡ በስትራቴጂው ውስጥ እንደተገለጸው የተከለሉ ወይም የጥበቃ ቦታዎችን መልሶ የማቋቋም ተግባር በሀገሪቱ ውስጥ የአየር ንብረት ለውጥ ለመቋቋም የሚችል አካባቢና የኑሮ ሁኔታ መፍጠር አንዱና ዋነኛው የትኩረት አቅጣጫ ነው፡፡

5.3.2. በደን ልማት ዘርፍ የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ዋነኛ ትኩረት የኢኮኖሚ ልማቱንና የሥነምህዳር አገልግሎቶችን በማጠናከር የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅዱ እንዲሣካ ለማድረግ የደን መጨፍጨፍና የአካባቢ መራቆት እንዲቆም ማድረግ ይገባል፡፡ በአሁኑ ወቅት በተለይ በሀገሪቱ የገጠር አካባቢዎች ደኖች 80 በመቶ የኃይል ምንጭ ወይም የማገዶ እንጨት ምንጭ በመሆን የሚያገለግሉ ናቸው፡፡ በተጨማሪም የደን ሴክተር በሀገሪቱ አጠቃላይ ዓመታዊ የምርት መጠን ውስጥ 4 በመቶ ያህል አስተዋጽኦ የሚያደርግ ሲሆን ይህም በማር ምርት፣ በጫካ ቡና፣ ጣውላ እና በሌሎች ምርቶች አማካኝነት የሚገኝ ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ደኖች በአፈርና ውሃ ጥበቃ፣ በብዝሃ ሕይወት ጥበቃ፣ ካርቦን በመቀነስ፣ የአካባቢ አየር እንዲጠራና ለጤንነት ተስማሚ እንዲሆን በማድረግ የአፈር ለምነትን በማሻሻል፣ የመሬትን ምርታማነት በመጨመር ወዘተ ከፍተኛ ጥቅም ይሰጣሉ፡፡

በኢትዮጵያ ውስጥ ደኖች ዘርፈ-ብዙ ጥቅሞች እየሰጡ ቢሆንም እንኳን ከሕዝብ ቁጥር መጨመር ጋራ በተያያዘ ለኃይል ምንጭ እና ለግብርና ቦታ ያለው ፍላጐት በከፍተኛ ሁኔታ እያደገ በመምጣቱ እና እነዚህን ፍላጐቶች ለማሟላት ደኖች በመጨፍጨፋቸው ቀላል የማይባል ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡ በስትራቴጂው ውስጥ እንደተገለፀው አሁን ያለው ደን የመጨፍጨፍ ድርጊት የሚቀጥል ከሆነ ከ2002 እስከ 2022 (ከ2010-2030 እ.እ.አ) ባለው ጊዜ ውስጥ 9 ሚሊዮን ሄክታር የሚሆን መሬት ይራቆታል፡፡ ከዚህም አሀዝ ይጨምራል ተብሎም ይገመታል፡፡ ይህ ሁኔታ ደግሞ 22 ሚሊዮን ቶን ያህል የሚሆን ደን እንዲጨፈጨፍ ያደርጋል፡፡

በደኖች ላይ እየተከሰተ ያለውን ጫና ለመቀነስ በግብርና ዘርፍ መወሰድ ካለባቸው እርምጃዎች ጐን ለጐን በአረንጓዴ ኢኮኖሚ ውስጥ ዘላቂነት ያለው የደኖች እንክብካቤና ጥበቃ እንዲኖር ትኩረት የተሰጣቸው ሶስት ስትራቴጂያዊ ጉዳዮች አሉ፡፡ እነርሱም፡- ኃይል ቆጣቢና ዘመናዊ ምድጃዎችን በማቅረብና በማስራጨት እንዲሁም ሌሎች አማራጮችን በማስተዋወቅ (እንደ አሌክትሪክ፣ የተደባለቀ ነዳጅ የባዮጋዝ ምድጃ ወዘተ ያሉትን) ለማገዶ እንጨት ያለውን ፍላጐት መቀነስ፤

የደን ሽፋን ማስፋፋት፣ የተራቆቱ አከባቢዎችን መልሶ በደን መሸፈን እና የደን ልማትና ቁጥጥር በማጠናከር ዘላቂነት ያለው የደን ልማት በሀገሪቱ ውስጥ እንዲስፋፋ ማድረግ፤

የተራቆቱ የግብርናና የግጦሽ ቦታዎችን በመከለል የመልሶ ማቋቋም ተግባራት በማከናወን እንዲያገግሙ ማድረግ ናቸው፡፡

Page 44: 2 3 - PHE Ethiopiaphe-ethiopia.org/pdf/Toolkit_Semien_amharic.pdf · 2 3 2006 ዓ/ ም አዲስ ... ፈንድ ሲሆን ለተደረገው ድጋፍ የኢትዮጵያ ሥነ-ህዝብ&

44 45

5.3.3 በደን ልማት ዘርፍ ለ2022 የተያዙ የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ግቦች

አምስት ሚሊዮን ሔክታር የሚሆን የደን ሽፋንና 2 ሚሊዮን ሔክታር በሳርና በቁጥቋጦ የተሸፈነ መሬት በደን ልማት ዘርፍ 50 በመቶ የሚሆን የሀገሪቱን ካርቦንዳይኦክሳይድ የመቀነስ አቅም አለው (130 ሜጋ ቶን ካርቦንዳይኦክሳይድ)፡፡ዘርፈ ብዙ በሀገሪቱ የሚኖር አጠቃላይ ልቀት ሙሉ በሙሉ ከአካባቢ አየር ተወግዶ በዛፎች ግንድና በተለያዩ የዕፅዋት ክፍሎች እንዲከማች የማድረግ አቅም አለው፡፡ ይህንን እውን ለማድረግ ደግሞ ወሳኝ ሚና ሊጫወት የሚችለው አንዱ ስትራቴጂ ኃይል ቆጣቢ ምድጃዎችን በማቅረብና በማሰራጨት ለማገዶ እንጨት ያለውን ፍላጐት መቀነስ ነው፡፡ ይህንን ስትራቴጂ በተገቢው ተግባራዊ ማድረግ ብቻውን እስከ 35 ሜጋ ቶን የሚደርስ ካርቦንዳ ኦክሳይድ ወደ ከባቢ አየር ሳይለቀቅ እንዲቀር ለማድረግ ያስችላል፡፡ ይህንን አቅም ለመጠቀምም የሚከተሉት ተግባራት መከናወን ይኖርባቸዋል፡፡ 20 ሚሊዮን አባራዎች ኃይል ቆጣቢ ምድጃዎችን ወደ መጠቀም እንዲሸጋገሩ ማድረግ፤ አሁን ያለውን የደን ሽፋን በ2 ሚሊዮን ሔክታር ማሳደግ፤

1 ሚሊዮን ሔክታር የሚሆን የተራቆተን መሬት መልሶ በደን መሸፈን፤ 2 ሚሊዮን ሔክታር በደን የተሸፈነ መሬትና 2 ሚሊዮን ሔክታር በሳርና በቁጥቋጦ የተሸፈነ መሬት የመንከባከብና የመጠበቅ ሥራ ማከናወን፡፡

ከግብርና ዘርፍ ጋር በተያያዘ በደኖች ላይ የሚደርሰውን ጫና ለመቀነስ፣ ያለውን የግብርና መሬት ምርታማነት ለመጨመርና ቴክኖሎጂዎችን በሥፋት በመጠቀም ወይም የተራቆቱ አካባቢዎች እንዲያገግሙ በማድረግ እስከ 2022 (2030 እ.ኤ.አ) 40 ሜጋ ቶን የሚሆን የካርባንዳይኦክሳድ ልቀት ለማስቀረት ይቻላል፡፡

Page 45: 2 3 - PHE Ethiopiaphe-ethiopia.org/pdf/Toolkit_Semien_amharic.pdf · 2 3 2006 ዓ/ ም አዲስ ... ፈንድ ሲሆን ለተደረገው ድጋፍ የኢትዮጵያ ሥነ-ህዝብ&

44 45

ሰንጠረዥ-4፡- በደን ዘርፍ የልቀት መጠን ለመቀነስ የተለዩ የትኩረት አቅጣዎችና ተግባራት

ምንጭ- የኢትዮጵያ መንግስት፣ የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ስትራቴጂ (2011 እ.ኤ.አ)

ልቀት ለመቀነስ የሚተኮርባቸው ዋና ዋና

አቅጣዎች

ዝርዝር ተግባራት ተፅዕኖ የሚፈጠርበት ዘርፍ

ከግብርና ሴክተር ጋር በተያያዘ በደን ላይ የሚደርስ ጫና መቀነስ

- ባለው መሬት ላይ የግብርና ሥራ ማጠናከር

- ምርታማነትን በመጨመር ለአዲስ የግብርና መሬት ያለውን ፍላጐት መቀነስ

- በመካከለኛና ከፍተኛ የመስኖ ሥራ አዳዲስ መሬቶችን ለግብርና ዝግጁ ማድረግ

- በመስኖና በማዳባሪያ ለምነት ያገኘ መሬትን በመጠቀም የደን መሬት የመጠቀም ሁኔታ መግታት

- በአነስተኛ የመስኖ ሥራ አዳዲስ መሬቶችን ለግብርና ሥራ ዝግጁ ማድረግ

- በመስኖና በማዳባሪያ ለምነት ያገኘ መሬትን በመጠቀም የደን መሬት የመጠቀም ሁኔታ መግታት

የማገዶ እንጨት ፍላጐት ማቀነስ

- ማገዶ ቆጣቢ ምድጃዎች

- ማገዶ ቆጣቢ ምድጃዎችን በተለይ በገጠርማ አካባቢዎች በመጠቀም ደን የሚጐዳ ፍላጐት መቀነስ

- የኤሌክትሪክ ምድጃዎች

- በተለይ በከተማ አካባቢዎች የኤሌክትሪክ ምድጃን ወደ መጠቀም መሸጋገር

- ኤልፒጂ ምድጃዎች - ኤል.ፒ.ጂ ምድጃዎችን ወደ መጠቀም መሸጋገር

- የባዮጋዝ ምድጃ - የባዩጋዝ ምድጃን ወደ መጠቀም መሸጋገር

ካርቦንን ከከባቢ አየር ውስጥ የሚያስወግድ ሂደት ማጠናከር

- የደን ሽፋን መጨመር፣ የተራቆቱ አካባቢዎችን በደን መሸፈን

- የደን ልማትና እንክብካቤ

- መጠነ-ሰፊ ምድጃን የተራቆቱ አካባቢዎችን በደን የመሸፈንና የደን ሽፋንን የመጨመር ተግባር ማከናወን

- መጠነ-ሰፊ የሆነ የደን ልማትና እንክብካቤ መርሀ-ግብሮችን ማካሄድ

Page 46: 2 3 - PHE Ethiopiaphe-ethiopia.org/pdf/Toolkit_Semien_amharic.pdf · 2 3 2006 ዓ/ ም አዲስ ... ፈንድ ሲሆን ለተደረገው ድጋፍ የኢትዮጵያ ሥነ-ህዝብ&

46 47

References: (ማጣቀሻዎች)ADB (2010). Sector Vulnerability Profile: Biodiversity and Ecosystem Services, Strengthening Capacity for Climate Change Adaptation, climate change secretariat SRI LANKA.

ኤ.ዲ.ቢ (2010) የዘርፉ ተጋላጭነት ኘሮፋይል፡ የብዝሃ ሕይወት እና ሥነ ሕይወት አገልግሎቶች፣ የአየር ንብረት ተለዋዋጭነትን የማላመድ አቅምን ማጠናከር፣ የአየር ንብረት ለውጥ ፀሐፊ ሲሪላንካ

ADB (2010). ADB Climate Change Programs: Facilitating Integrated Solutions in Asia and the Pacific, Manila, Philippines.

ኤ.ዲ.ቢ (2010) ኤ.ዲ.ቢ የአየር ንብረት ለውጥ ኘሮግራሞች፡ በኢስያ እና በፖስፊክ ማኔላ ፊሊፒንስ ውስጥ የተጠናከሩ መፍትሄዎችን ማፋጠን

American National Research Council (2012). Climate Change evidences, impacts, and choices: answers to common questions about the science of climate change, National Research Council of the National Academies, USA.

የአሜሪካ ብሔራዊ የምርምር ማዕከል (2012). የአየር ንብረት ለውጥ ማስረጃዎች ፣ እንደምታዎች እና ምርጫዎች ፡ የአየር ንብረት ለውጥ ሳይንስ ላይ የተነሱ አንዳንድ የተለመዱ ጥያቄዎችን መመለስ፣ የብሔራዊ ትምህርት ምክር ቤት ምርምር ማዕከል አሜሪካ

ASEAN Social Forestry Network (ASFN)( 2008). Malaysia Report to Second Meeting of the ASFN, Bangkok, 27-29 August 2008.

የኢሲያ የማኀበራዊ ደን ጥበቃ ጥምረት (2008) ለኤስኤፍኤን ባንኮክ 27-29 ነሐሴ 2008 2ኛ ስብሰባ የቀረበ የማሊዥያ ሪፖርት

CARE (2010). Toolkit for Integrating Climate Change Adaptation into Development Projects

ኬር (2010) በልማት ኘሮጀክቶች ድጅታል መመሪያ - ክፍል 1.10 ከዘለቄታማ ልማት አለምአቀፍ ተቋም ጋር በመተባበር የተዘጋጀ የተጠናከረ የአየር ንብረት ለውጥ ማላመጃ መመሪያ ሐምሌ 2010 አሜሪካ

Digital Toolkit – Version 1.0 produced in collaboration with the International Institute for Sustainable Development (IISD)– July 2010, USA.

CITY OF PORTLAND AND MULTNOMAH COUNTY (2009). CLIMATE ACTION PLAN 2009. WWW.PORTLANDONLINE.COM/BPS/CLIMATE.

የፖርት ላንድ ከተማ እና መልቲ ኖማህ ካውንቲ (2009) የአየር ንብረት ለውጥ ድርጊት መርሃ ግብር 2009

Charlotte Sterrett (2011). Review of Climate Change Adaptation Practices in South Asia: Oxfam Research Reports, Climate Concern, Melbourne, Australia.

ቻርሎቴ እስትሬት (2011) የአየር ንብረት ለውጥ በደቡብ ኢስያ የኦክስፋም ምርምር ሪፖርቶች፣ የአየር ንብረት ለውጥ አሳሰቢነት ሜልቦርን አውስትራልያ የአየር ንብረት

Page 47: 2 3 - PHE Ethiopiaphe-ethiopia.org/pdf/Toolkit_Semien_amharic.pdf · 2 3 2006 ዓ/ ም አዲስ ... ፈንድ ሲሆን ለተደረገው ድጋፍ የኢትዮጵያ ሥነ-ህዝብ&

46 47

ለውጥ ማላመጃ አሠራሮችን መከለስ

EWCA(2013). Distribution of National Parks, Wildlife Sanctuaries, Wildlife Reserves, Community Conservation Areas, Wildlife Rescue Centers, Controlled Hunting Areas, and Biosphere Reserves in Ethiopia, unpublished data, Addis Ababa, Ethiopia.

ኢ.ደብሊው.ሲ.ኤ (2013)፡ በኢትዮጵያ ውስጥ የብሔራዊ ፖርኮች፣ የዱር እንስሳት መጠለያዎች፣ የዱር እንስሳት ጥበቅ ቦታዎች፣ የማኀበረሰብ ጥበቃ አካባቢዎች፣ የዱር እንስሳት ነብስ አድን ማዕከላት የቁጥጥር የአደን ቀበሌዎች እና በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ የሥነ ሕይወት ጥበቃ ቦታዎች ያልታተመ ዳታ አ.አ ኢትዮጱያ

Eliasch (2008). The Eliasch Review 2008. Climate change: Financing global forests, UK, London.

ኤልያሽ (2008) የ2008 ክለሳ የአየር ንብረት ለውጥ ላይ በእንግሊዝ ለንደን የዓለም ደኖች ፋይናንስ

EPA (2009). EPA Initiatives and Programs to Address Climate Change, U.S. EPA Region 2, New York Energy Forum, New York, USA.

ኢ.ፒ.ኤ(2009) በአሜሪካ ኒውዮርክ የኢነርጂ ፎረም ኢ.ፒ.ኤ ክልል 2 የአየር ንብረት ለውጥን አስመልክቶ የኢ.ፒ.ኤ ጅማሮዎች እና ኘሮግራሞች

FAO(2008). DISASTER RISK MANAGEMENT SYSTEMS ANALYSIS: A guide book for DRM system analysis, ENVIRONMENT, CLIMATE CHANGE AND BIOENERGY DIVISION, Rome, Italy.

ፋኦ (2008)፡ የአደጋ ምዘና አስተዳደር ሥርአት ትንተና ለአካባቢ፣ ለአየር ንብረት ለውጥ እና ለሥነ ሕይወት ኢነርጂ መምሪያ ጣሊያን ሮም የቀረበ የዲ.አር.ኤም ሥርዓት ትንተና መመሪያ መጽሐፍ

Global Leadership for Climate Action(2009). Facilitating an International Agreement on Climate Change: Adaptation to Climate Change, A proposal for Global Leadership for Climate Action, June 2009.

የአየር ንብረት ለውጥ አለም አቀፍ አመራር (2009) በሰኔ 2009 የአየር ንብረት ለውጥ መርሃ ግብር ላይ የቀረበ የአለም አቀፍ አመራር ኘሮፖዛል - በአየር ንብረት ለውጥ ማላመጃ

GoE (2011). Ethiopia’s Climate-Resilient Green Economy (CRGE) strategy, Addis Ababa, Ethiopia.

ጂ.ኦ.ኢ(2011) በአ.አ ኢትዮጵያ፤ የኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥ የመቋቋም አቅም፣ የአረንጓዴው ኢኮኖሚ እስትራቴጂ

International Federation of Red Cross and Red Crescent Societies (1999). A guide to vulnerability and capacity assessment produced with the financial support of the Britain’s Department for International Development (DFID), Disaster and Risk Reduction Progremme Forum, Geneva, July 1999.

የቀይ መስቀል እና የቀይ ጨረቃ ማእከላት አለም አቀፍ ፌዴሬሽን 1999፡ በእንግሊዝ

Page 48: 2 3 - PHE Ethiopiaphe-ethiopia.org/pdf/Toolkit_Semien_amharic.pdf · 2 3 2006 ዓ/ ም አዲስ ... ፈንድ ሲሆን ለተደረገው ድጋፍ የኢትዮጵያ ሥነ-ህዝብ&

48 49

የአለም አቀፍ ልማት፣ የአደጋ እና የአደጋ ተጋላጭነት ቅነሳ ኘሮግራም መመሪያ፤ ጄኔቨ ሐምሌ 1999

International Research Institute for Climate and Society/IRI(2011). A Better Climate for Disaster Risk Management. International Research Institute for Clim ate and Society (IRI), Climate and Society No. 3, Columbia University, New York, USA.

የአየር ንብረት ለውጥ አለም አቀፍ ምርምር ተቋም እና ማኀበር 2011፡ የተሻለ የአደጋ ተጋላጭነት አስተዳደር እቅድ፤ የአለም አቀፍ ምርምር ተቋም ለአየር ንብረት ለውጥ እና ለማኀበሩ ቁጥር 3 ኮሎምቢያ ዩኒቨርስቲ ኒውዮርክ አሜሪካ

IPCC (2007c). “Summary for Policymakers”, Climate Change 2007: The Physical Science Basis. Contribution of Working Group I to the Fourth Assessment Report of the Intergovernmental Panel on Climate Change, Cambridge University Press, Cambridge and New York, NY.

አይ.ፒ.ሲ.ሲ(2007ሲ) “የፖሊሲ አውጪዎች ማጠቃለያ” የአየር ንብረት ለውጥ 2007 የፊሲካል ሳይንስ መሠረት በአየር ንብረት ለውጥ የተለያዩ መንግስታት ጉባኤ 4ኛ የምዘና ሪፖርት ለሥራ አካሄድ ቡድን 1 ያለው አስተዋጽኦ

James Young (2012). Ethiopian Protected Areas, A ‘Snapshot’: A REFERENCE GUIDE FOR FUTURE STRATEGIC PLANNING AND PROJECT FUNDING, Addis Ababa, Ethiopia.

ጀምስ ያንግ(2012) የኢትዮጵያ የተጠበቁ አካባቢዎች ማሳያ የወደፊት ስልታዊ እቅድ እና የኘሮጀክት ፈንድ ማጣቀሻ መመሪያ አ.አ ኢትዮጵያ

Lewis, S. et al. (2009). Increasing carbon storage in intact African tropical forests. Nature, 19 February 2009.

ሊዊስ ኤስ. ኤታል (2009) ባልተነኩ የአፍሪካ የትሮፒክ ደኖች ውስጥ የካርበን መጠራቀምን መጨመር፤ ኔቸር 19 የካቲት 2009

Martin Khor (2011). RISKS AND USES OF THE GREEN ECONOMY CONCEPT IN THE CONTEXT OF SUSTAINABLE DEVELOPMENT, POVERTY AND EQUITY, Research paper, 40, Geneva, Switzerland.

ማርቲን ኮሆር(2011) በዘለቄታማ ልማት ድህነትና ፍትሃዊ ድርሻ ላይ የቀረበ የምርምር ወረቀት፤ 40 ጄኔቫ ሲውዘርላንድ

Secretariat of the Convention on Biological Diversity (2004). BIODIVERSITY ISSUES FOR CONSIDERATION IN THE PLANNING, ESTABLISHMENT AND MANAGEMENT OF PROTECTED AREA SITES AND NETWORKS, CBD Technical Series No 15, Montreal, Quebec, Canada.

የብዝሃ ሕይወት ስምምነት ፀሐፊ 2004፡ በተጠበቁ የአካባቢ ሥፍራዎች እና ጥምረቶች እቅድ አወጣጥ መቋቋም እና አስተዳደር ላይ የብዝሃ ሕይወት ጉዳዮችን ስለመድረስ

PHE EC(2013). Building Institutional Capacity and Participatory Leadership in Awash and Simien Mountains National Parks for Resilience, Mitigation and

Page 49: 2 3 - PHE Ethiopiaphe-ethiopia.org/pdf/Toolkit_Semien_amharic.pdf · 2 3 2006 ዓ/ ም አዲስ ... ፈንድ ሲሆን ለተደረገው ድጋፍ የኢትዮጵያ ሥነ-ህዝብ&

48 49

Adaptation to Climate Change (BICAS-RMACC) project proposal submitted to SCIP for funding, Addis Ababa, Ethiopia.

ፒ.ኤች.ኢ. ኢ.ሲ (2013) የአዋሽ እና የሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፖርኮች የአየር ንብረት ለውጥ መቋቋም አቅምን ማለሳለስ እና ማላመድ

Sierra Nevada Alliance( 2007 ). Sierra Climate Change Toolkit: Planning ahead to protect Sierra natural resources and rural communities, 2nd edition, 2007, South Lake Tahoe.

ሴራኔቫዳ አሊያንስ (2007)፡ የሴራ የአየር ንብረት ለውጥ መመሪያ 2ኛ እትም 2007 ሳውዝ ሌክ ታሆ

Stern, N. (2006). Stern Review: The Economics of Climate Change. Cambridge University Press, Cambridge, UK.

እስተርን ኤን (2006) በእንግሊዝ ካምኘሪጅ ዩኒቨርስቲ የአየር ንብረት ለውጥ የተደረገ ክለሳ

Scientific Expert Group on Climate Change (2007): CONFRONTING CLIMATE CHANGE: AVOIDING THE UNMANAGEABLE AND MANAGING THE UNAVOIDABLE, Xi, Research Triangle Park, NC, and the United Nations Foundation, Washington, DC, USA.

የአየር ንብረት ለውጥ ሳይንሳዊ ሙያ ቡድን 2007፡ ለማስወገድ እና ለማስተዳደር የማይቻለውን አይቀሬ የአየር ንብረት ለውጥ አደጋን መጋፈጥ በተመ ፋውንዴችን ዋሽንግተን ዲሲ አሜሪካ

Turner, et al (2003). A framework for vulnerability analysis in sustainability science. PNAS, 100(14).

ተርነር (2003) የዘለቄታማ ሳይንስ ተጋላጭነት ትንተና መዋቅር

UNEP (2008). Towards a Green Economy, United Nations Environmental Programme, Geneva, Switzerland.

ዩ.ኤን.ኢ.ፒ (2008) በተመ የአካባቢያዊ ኘሮግራም ለግሪን ኢኮኖሚ የተዘጋጀ ጄኔቫ ሲዊዘር ላንድ

UNEP(2009). A Preliminary Stocktaking: Organizations and Projects focused on Climate Change Adaptation in Africa, United Nations Environmental Programme, Nairobi, Kenya.

ዩ.ኤን.ኢ.ፒ (2009) በመጀመሪያ ደረጃ ክምችት አወሳሰድ በናይሮቢ ኬኒያ የተመ አካባቢያዊ ኘሮግራም በአየር ንብረት ለውጥ ያተኮሩ ድርጅቶችና ኘሮጀክቶች

UNEP et al( 2011). Green economy: Why a Green Economy Matters for the Least Developed Countries, Nairobi, Kenya.

ዩ.ኤን.ኢ.ፒ (2011) በጣም በዝቅተኛ የእድገት ደረጃ ላይ የሚገኙ ሃገራት የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ሥርአት ምን ይፈይድላቸዋል፡፡ ናይሮቢ ኬኒያ

UNEP et al (2012). Green Economy in a Blue World: Synthesis Report,

Page 50: 2 3 - PHE Ethiopiaphe-ethiopia.org/pdf/Toolkit_Semien_amharic.pdf · 2 3 2006 ዓ/ ም አዲስ ... ፈንድ ሲሆን ለተደረገው ድጋፍ የኢትዮጵያ ሥነ-ህዝብ&

50 51

Geneva, Switzerland.

ዩ.ኤን.ኢ.ፒ (2012) አረንጓዴ ኢኮኖሚ በብሉ ወርልድ በጄኔቫ ሲዊዘርላንድ የቀረበ የምርምር ሪፖርት

U.S. Environmental Protection Agency(2007). Climate Change Technologies and Programs: World Environment Day, Washington, DC, USA.

የአሜሪካ ለአካባቢያዊ ጥበቃ መ/ቤት 2007፡ በዋሽንግተን ዲሲ አሜሪካ የአየር ንብረት ለውጥ ቴክኖሎጂዎች እና ኘሮግራሞች የአለም አካባቢ ቀን

WINROCK INTERNATIONAL INDIA(2006). Proceedings of the International Workshop on Vulnerability and Adaptation to Climate Change: From Practice to Policy, May 11-12, 2006, Hotel Metropolitan Nikko Bangla Sahib Road, New Delhi 110001, India

ዊንሮክ ኢንተርናሽናል ኢንድያ 2006፡ በአየር ንብረት ለውጥ ተጋላጭነት እና መላመድ ላይ የአለም አቀፍ ወርክሾኘ ኒውደልሂ ሕንድ

WMO and UNEP( 2012). MANAGING THE RISKS OF EXTREME EVENTS AND DISASTERS TO ADVANCE CLIMATE CHANGE ADAPTATION: SPECIAL REPORT OF THE ERGOVERNMENTAL PANEL ON CLIMATE CHANGE (IPCC), USA.

ደብሊው.ኤም.ኦ. እና ዩ.ኤን.ኢ.ፒ 2012፡ የአየር ንብረት ለውጥ መላመድን ወደፊት በማስኬድ አስከፊ ክስተቶች እና አደጋዎችን ማስወገድ በአየር ንብረት ለውጥ ላይ የተዘጋጀ ልዩ ሪፖርት

World Bank (2008a), Development and Climate Change. A Strategic Framework for the World Bank Group, Consultation Draft, August 2008.

የአለም ባንክ 2008፡ የአለም ባንክ ቡድን የምክክር ረቅቂቅ 2008 ነሐሴ ወር ስልታዊ መዋቅር

WTO and UNEP (2009). Trade and Climate Change: A report by the United Nations Environment Programme and the World Trade Organization, Geneva, Switzerland.

የአለም ንግድ ድርጅት እና ዩ.ኤን.ኢ.ፒ (2009) የንግድ እና የአየር ንብረት ለውጥ በተመ የአካባቢ ኘሮግራም እና የአለም ንግድ ድርጅት ጄኔቫ ሲዊዘርላንድ የቀረበ ሪፖርት

Page 51: 2 3 - PHE Ethiopiaphe-ethiopia.org/pdf/Toolkit_Semien_amharic.pdf · 2 3 2006 ዓ/ ም አዲስ ... ፈንድ ሲሆን ለተደረገው ድጋፍ የኢትዮጵያ ሥነ-ህዝብ&

50 51

Page 52: 2 3 - PHE Ethiopiaphe-ethiopia.org/pdf/Toolkit_Semien_amharic.pdf · 2 3 2006 ዓ/ ም አዲስ ... ፈንድ ሲሆን ለተደረገው ድጋፍ የኢትዮጵያ ሥነ-ህዝብ&

52 PB

Design+Print: PH

ILMO

N PR

ESS