3 web viewየምርምርና ስርፀት . አሰራር መመሪያ ማንዋል....

98
LOGO ኮኮኮኮኮ ኮኮኮኮኮኮ ኮኮኮኮኮ ኮኮኮኮ KOMBOLCHA TEXTILE SHARE COMPANY Form No.: OP/KTSC/044 ኮኮኮኮ Issue No . 1 Page No.: Page 1 of 1 ኮኮኮኮኮኮ ኮኮኮኮ ኮኮኮኮ ኮኮኮኮ ኮኮኮኮ ኮኮኮኮኮ ኮኮኮ ኮኮኮ ኮኮኮ ኮኮኮ ኮኮኮኮ ኮኮኮ ኮኮኮኮ ኮኮኮ

Upload: ledan

Post on 07-Feb-2018

242 views

Category:

Documents


7 download

TRANSCRIPT

Page 1: 3  Web viewየምርምርና ስርፀት . አሰራር መመሪያ ማንዋል. አዘጋጆች. ንጉሴ ሙላት. ከድር ዘዉዱ. መሰረት ገነቱ

LOGO ኮምቦልቻጨርቃጨርቅ አክሲዮን ማህበርKOMBOLCHA TEXTILE SHARE COMPANY

Form No.:

OP/KTSC/044

ማንዋል Issue No .

1Page No.:

Page 1 of 1

የምርምርና ስርፀት

አሰራር መመሪያ ማንዋል አዘጋጆች

ንጉሴ ሙላት

ከድር ዘዉዱ

መሰረት ገነቱ

ሕይወት ይመር

ህዳር 2005 ዓ. ም

Page 2: 3  Web viewየምርምርና ስርፀት . አሰራር መመሪያ ማንዋል. አዘጋጆች. ንጉሴ ሙላት. ከድር ዘዉዱ. መሰረት ገነቱ

LOGO ኮምቦልቻጨርቃጨርቅ አክሲዮን ማህበርKOMBOLCHA TEXTILE SHARE COMPANY

Form No.:

OP/KTSC/044

ማንዋል Issue No .

1Page No.:

Page 1of 2

ክፍል 1i. መግቢያ--------------------------------------------------------------------------------------------

1

1. የትናት ፕሮፖዛል (Research Proposal)--------------------------------------------------------3

1.1 የጥናት ፕሮፖዛል ጥቅም (Importance of Research proposal)----------------------3

1.2 የጥናት ፕሮፖዛል ትርጉም (Definition)------------------------------------------------------3

1.3 የጥናት ፕሮፖዛል መነሻ (initiative of research proposal)-----------------------------4

1.4 በጥናት ፕሮፖዛል መካተት ያለባቸው(Requirement of Research Proposal)-------4

2. ጥናትና የጥናት አወቃቀር ዘዴ(Research & Research Approach)----------------------8

2.1 የጥናት ትርጉም(Definition)---------------------------------------------------------------------8

2.2 በጥናት ስራ ላይ መሟላት የሚገባቸዉ (Requirements of research)------------------8 2.2.1 ከንድፍ በፊት መታወቅ የሚገባቸዉ(prerequisite)-----------------------------------------8 2.2.2 በጥናቱ የሚፈቱ ችግሮችን አመራረጥ (problems Identification)-------------------------9

2.2.3 ከጥናቱ ግኝቶች አጠቃላይ ግንዛቤ መውሰድ (internalization)------------------------10

2.3 የጥናት አወቃቀር ዘዴ (The Research approach)----------------------------------------10

2.3.1 መላምት (Hypothesis)-------------------------------------------------------------------------10

2.3.1.1 በመላምት አቀራረፅ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች-----------------------------------------------11

2.3.2 የጥናት ርዕስ አመራረጥ-------------------------------------------------------------------------11

2.3.3 የጥናት ርዕስ አገላለፅ ---------------------------------------------------------------------------12

3. የናሙና አወሳሰድ ዘዴዎች (sampling techniques)-------------------------------------------12

3.1 እኩል እድል የማይሰጥ ናሙና (Non-probability sampling)-------------------------------12

3.2 እኩል እድለ ሰጭ ናሙና (probability sampling)--------------------------------------------13

4. የመረጃ ማሰባሰብ ስልቶች (Data collection tools)---------------------------------------------14

Page 3: 3  Web viewየምርምርና ስርፀት . አሰራር መመሪያ ማንዋል. አዘጋጆች. ንጉሴ ሙላት. ከድር ዘዉዱ. መሰረት ገነቱ

LOGO ኮምቦልቻጨርቃጨርቅ አክሲዮን ማህበርKOMBOLCHA TEXTILE SHARE COMPANY

Form No.:

OP/KTSC/044

ማንዋል Issue No .

1Page No.:

Page 2 of 2

4.1 የጥናት መረጃ ማጠናቀሪያ ስልት አይነቶች-----------------------------------------------------14

4.1.1 የመጠይቅ አዘገጃጀት-----------------------------------------------------------------------------15

4.1.2 የቃለ መጠይቅ አዘገጃጀት------------------------------------------------------------------------16

4.2. የጥናቱ ፅሁፍ ሲዘጋጅ መካተት የሚገባቸው---------------------------------------------------17

ክፍል 21. ፕሮጀክት እና ፅንሰ ሃሳቦቹ----------------------------------------------------------------------------24

1.1 ትርጉም---------------------------------------------------------------------------------------------24

1.2. የፕሮጀክት ዕቅድ ዝግጅት (Project planning)-----------------------------------------------24

2. የፕረሮጀክት ዑደት /Project cycle/----------------------------------------------------------------24

2.1. ፕሮጀክት ልየታ (project Identification)---------------------------------------------26

2.2. ፕሮጀክት ዝግጅት / project preparation or formulation/-------------------------------26

2.2.1 ቅድመ ዝርዝር ጥናት/pre-feasiblity study/----------------------------------------------26

2.2.2 የፕሮጀክት ዝርዝር/feasibility study/------------------------------------------------------26

2.3 ፕሮጀከት ምዘና / የፕሮጀክት ብቃት ግምገማ/ (project appraisal)-------------------------30

2.4. የፕሮጀክት ትግበራ /Implementation/----------------------------------------------------------31

2.5. ክትትልና ግምገማ (Monitoring and Evaluation)------------------------------------------32

3. የፕሮጀክት ቀረፃና ሪፖረት ፎርማት---------------------------------------------------------39

3.1. አንድ ፕሮጀክት ቀረፃ(propozal) ሊያካትታቸው የሚገባቸው ዋና ዋና ርእሶች--39

3.2 ፕሮጀክት ሪፖርት(Project Report)-------------------------------------------------------------41

ክፍል 3

Page 4: 3  Web viewየምርምርና ስርፀት . አሰራር መመሪያ ማንዋል. አዘጋጆች. ንጉሴ ሙላት. ከድር ዘዉዱ. መሰረት ገነቱ

1. ሪፖረት አቀራረብ-----------------------------------------------------------------------------------------44

1.1 የጥናትና የፕሮጀክት አቀራረብ---------------------------------------------------------------------44LOGO ኮምቦልቻጨርቃጨርቅ አክሲዮን ማህበር

KOMBOLCHA TEXTILE SHARE COMPANY

Form No.:

OP/KTSC/044

ማንዋል Issue No .

1Page No.:

Page 1 of 47

i. መግቢያ

ምርምርና ስርፀት በአንድ ድርጅት ዉስት ወጭቆጣቢና ዉጤታማ አሰራር እንዲኖር ፤ ዉጤታማ ያልሆኑ አሰራሮች

እንዲቀየሩ፤አዳዲስና ከዘምኑ ቴክኖሎጂ ጋር አብረዉ ሊሄዱ የሚችሉ አሰራሮች በድርጅቱ እንዲተገበሩና አዳዲስ

የፈጠራ ሃሳቦችና፤ችግሮችንመፍታት የሚያስችሉጥናቶችና ፕሮጀክቶችን በመስራት ድርጅቱን ወደተሻለ ምእራፍ

ለማሸጋገር ወሳኝሚና ይጫወታል፡፡ በኮምቦልቻጨርቃጨርቅ አክሲዮን ማህበርምምርምርና ስርፀት

በአገልግሎትና አሰራር ማሻሻያ አገልግሎት ስር በዋና ክፍልነት ተዋቅሮ እየሰራ የሚገኝ ሲሆን ፡፡ የምርምርና ስርፅት

ወሳኝ ተግባራትን ለማከናወን የምርምርና ስርፀት አሰራርመመሪያ ማንዋልመኖሩ ለአሰራር አስፈላጊ በመሆኑ የህ

ማንዋል ተዘጋጅቷል፡፡ አንድን ፕሮጀክት ወይም ጥናት ለመስራት ጥናቱ ወይም ፕሮጀክት ፡-

ሲሰራ በምን መልኩ መስራት እንዳለበት

ዶክመንቱ ሲዘጋጅ መካተት ያለባቸዉን ዋና ዋና ርእሶችና በየአንዳንዱ ርእስ ስር መካተት ያለባቸዉ ፍሬ

ሃሳቦች ምን እንደሆኑ

የሚሰራዉ አካል ሊያዉቅ ይገባል፡፡በተጨማሪም አንድ ድርጅት ዉስጥ የሚሰሩ ጥናቶችና ፕሮጀክቶች

ተመሳሳይ የአቀራረብ ፎርማት ይዘዉ እንዲሰሩ የአቀራረብ ፎርማት ማዘጋጀት ያስፈልጋል ፡፡ከላይ

ያየናቸዉን ሁለት መሰረታዊ ነገሮች ለመመለስ ይህ የምርምርና ስርፀት አሰራርመመሪያ ማንዋል

የሚሰጠዉ ጥቅም አስፈላጊነት ታምኖበት ቀርቧል፡፡ ማንዋሉ ሦሥት ክፍል ያለዉ ሲሆን በመጀመሪያዉ

ክፍል ዉስጥ ጥናት ምን እንደሆነ፤የጥናት ንድፈ ሃሳብ(proposal) እንዴት መቅረብ እንዳለበት፤ጥናት እንዴት መሰራት እንዳለበት፤ በዉስጡ ስላሉ መሰረታዊ ነገሮችና የጥናት ጽሁፍ ማካተት ሰለሚገባዉ

ዋናዋና ርእሶችና በርእሶቹ መካተት ስላለባቸዉ ፍሬ ሃሳቦች ጥልቅ የሆነ ማብራሪያ ይሰጣል፡፡በሁለተኛዉ ክፍል ደግሞ ፕሮጀክት ምን እንደሆነ፤የፕሮጀክት ንድፈ ሃሳብ(proposal) እንዴት መቅረብ

እንዳለበት፤ፕሮጀክት እንዴት መሰራት እንዳለበት፤ በዉስጡ ስላሉ መሰረታዊ ነገሮችና ፕሮጀክት ንድፈ

ሃሳብ(proposal) እና ሪፖርት ጽሁፍ ማካተት ሰለሚገባዉ ዋናዋና ርእሶችና በርእሶቹ መካተት

ስላለባቸዉ ፍሬ ሃሳቦች በጥልቀት ያብራራል፡፡ ሦሥተኛዉ ክፍል ደግሞ ስለጥናትና ፕሮጀክት አተገባበር

ያትታል፡፡

Page 5: 3  Web viewየምርምርና ስርፀት . አሰራር መመሪያ ማንዋል. አዘጋጆች. ንጉሴ ሙላት. ከድር ዘዉዱ. መሰረት ገነቱ

LOGO ኮምቦልቻጨርቃጨርቅ አክሲዮን ማህበርKOMBOLCHA TEXTILE SHARE COMPANY

Form No.:

OP/KTSC/044

ማንዋል Issue No .

1Page No.:

Page 2 of 47

ክፍል አንድ

ጥናት (reaserch)

Page 6: 3  Web viewየምርምርና ስርፀት . አሰራር መመሪያ ማንዋል. አዘጋጆች. ንጉሴ ሙላት. ከድር ዘዉዱ. መሰረት ገነቱ

LOGO ኮምቦልቻጨርቃጨርቅ አክሲዮን ማህበርKOMBOLCHA TEXTILE SHARE COMPANY

Form No.:

OP/KTSC/044

ማንዋል Issue No .

1Page No.:

Page 3 of 47

ምእራፍ 1

1. የትናት ፕሮፖዛል (Research Proposal)

1.1 የጥናት ፕሮፖዛል ትርጉም (Definition)

የጥናት ፕሮፖዛል ማለት አንድ አጥኚ ለመስራት ላቀደው ስራ የሚያቀርበው ሰነድ ሲሆን፤ ጥናቱ/ስራው/ ምን እንደሆነ፤ለምን፤ እንዴት፡ የት፤ መቸ፤ እና ለማን እንደሚሰራ የሚገልፅ ነው፡፡

1.2 የጥናት ፕሮፖዛል ጥቅም (Importance of Research proposal)

የጥናት ፕሮፓዛል መፃፍ በርካታ የተለያዩ ጠቀሜታዎች ይሰጣል፡፡ ጥቂቶቹ የሚከተሉት ናቸው፡፡

ተመራማሪዎች፤ ለምርምር ስራ የገንዘብ ድጋፍ የሚያደርጉ ተቋማትን፤ ድርጅቶችንና የበላይ አመራሮችን/ ስለሚሰራው ምርምር ጠቀሜታ በመረዳት ለዚህ ስራም አስፈላጊው ትኩረት

እንዲሰጥበት ለማድረግ፤

በአንድ ጥናት ስራ ላይ የሚሰሩ ባለሙያዎች በጥናቱ ዙሪያ/ በቂ ግንዛቤ/ እንዳላቸዉ ለማሳየት ይህንንም ለማድረግ ከጥናቱ ርዕስ ጋር ተዛማጅ የሆኑ ቲዎሪዎችን በማነፃፀር፤ በማቀናጀትና

በማጠቃለል ይቀርባል፤

ወደ እውነታ የተቃረቡ የጥናት ስራ አሰራሮችን/ አካሄዶችን በመግለፅ በአንድ ጥናት ዙሪያ አጥኚው ብቁና ተወዳዳሪ ክህሎት ያለው መሆኑን ያሳያል፡፡

የጥናት ፕሮፖዛል በአጥኚውና ስራውን በሚያፀድቀው መካከል እንደ ውል የሚያገለግል ፅሁፍ ነው፡፡ ፕሮፖዛሉ እያንዳንዱ ተዋዋይ ምን እንደሚጠበቅበት በግልፅ ያስቀምጣል፡፡ለምሳሌ የሃብት/የገንዘብ

አጠቃቀምና ጥናቱ መቸ ተጀምሮ መቸ ማለቅ እንዳለበት፤ የሚጠበቁ ውጤትን፤ የጥናት አላማና ግብ፤ ወዘተ

ፕሮፖዛል እንደ እቅድ መሳሪያ ያገለግላል፡፡ በርካታ ጥናቶች/ ፕሮጀክቶች በትክክል ባለመታቀዳቸው ምክንያት ከፍፃሜ ሳይደርሱ ይታያሉ፡፡ ግልፅ የሆነ የድርጊት መርሃ ግብር ከመጀመሪያ አንስቶ የተቀመጠ ከሆነ የጥናት ሥርዓት በአጥጋቢ ሁኔታ ይከናወናል፡፡

LOGO ኮምቦልቻጨርቃጨርቅ አክሲዮን ማህበርKOMBOLCHA TEXTILE SHARE COMPANY

Form No.:

OP/KTSC/044

ማንዋል Issue No .

1Page No.:

Page 4 of 47

Page 7: 3  Web viewየምርምርና ስርፀት . አሰራር መመሪያ ማንዋል. አዘጋጆች. ንጉሴ ሙላት. ከድር ዘዉዱ. መሰረት ገነቱ

1.3 የጥናት ፕሮፖዛል መነሻ (initiative of research proposal)

አንድ የጥናት ፕሮፖዛል ከመቀረፁ በፊት ግልፅ የሆነ የጥናት መነሻ ያስፈልጋል ፡፡ አንድ አጥኝ እነዚህን ጥያቄዎች ከተለያዩ ቦታዎች ሊያገኝ ይችላል፡፡ ለምሳሌ

i. ከአካባቢ ምልከታ(observation)

አጥኝዎቹ ብዙዉን ጊዜ አካባቢን አትኩረዉ ስለሚመለከቱ በዙሪያ ያለዉን ችግር በቀላሉ መለየት ይችላሉ፡፡

ii. ከንድፈ ሃሳብ(theory) አብዛኛዉን ጊዜ ተመሳሳይ ክስተቶችን በተለያየ መንገድ የሚገልፁ ንድፈ ሃሳቦች አሉ፡፡እነዚህን ንድፈ

ሃሳቦች በጥያቄ መልክ በማገናዘብ የትኛው ንድፈ ሃሳብ በይበልጥ ትክክል መሆኑን ሊያስረዳ የሚችል የምርምር ጥያቄ ማውጣት ይቻላል፡፡

iii. ቀድሞ የተሰሩ የጥናት ስራዎች(Privious studies) አንድን ጉዳይ ለመዳሰስ የሚሰራ ጥናት ሙሉ ለሙሉ ለምንፈልገው ጥያቄ መልስ አይሰጠንም አዳዲስ

የምርምር ግኝቶች ሁልጊዜ አዳዲስ የምርምር ጥያቄዎችን የሚያነሳሱ ናቸው፡፡

iv. ከሥራ አካባቢዎች ልምድ(Experience) አጥኝዎቹ ከህይወት ልምዳቸው ከሚያጋጥሟቸው ክስተቶች በመነሳት ማህበረሰቡ ያለበትን ችግር ይገነዘባሉ፡፡ ለእነዚህም ችግሮች ምላሽ ለመስጠት የሚያስችሉ ምርምሮችን ይሰራሉ፡፡

v. ፍላጎት(Interest) አጥኚዎች በአንዳንድ መስኮች የራሳቸው የሆነ ፍላጎት አሏቸዉ፤ እነዚህም ፍላጎቶች የጥናት ርዕስ

ሊያስገኙ ይችላሉ፡፡

1.4 በጥናት ፕሮፖዛል መካተት ያለባቸው(Requirement of Research Proposal)

የጥናት ፕሮፖዛል በሚቀረፅበት ወቅት የሚከተሉትን ርእሶች ማካተት ይኖርባቸዋል፡፡

I. የጥናቱ ርዕስ(Topic)፡- በርዕስ ገፅ ላይ የሚኖሩ ቃላት በጥንቃቄ መመረጥና ቃላቱም የተመጠኑ እና ጥናቱን በደንብ የሚገልጹ መሆን አለባቸዉ፡፡

በርእስ ገጽ ላይ መካተት ያለባቸዉ፡- የጥናቱ ርዕስ

የአጥኝዎቹ ስምና አድራሻ

ጥናቱ የሚቀርብለት ድርጅት

የጥናቱ ፕሮፖዛል የሚቀርብበት ቀንና አመት

LOGO ኮምቦልቻጨርቃጨርቅ አክሲዮን ማህበርKOMBOLCHA TEXTILE SHARE COMPANY

Form No.:

OP/KTSC/044

ማንዋል Issue No .

1Page No.:

Page 5 of 47

Page 8: 3  Web viewየምርምርና ስርፀት . አሰራር መመሪያ ማንዋል. አዘጋጆች. ንጉሴ ሙላት. ከድር ዘዉዱ. መሰረት ገነቱ

II. ማውጫ(Table of content) ማውጫ አንባቢዎች ማንበብ የሚፈልጉትን ክፍል በቀላሉ እንዲያገኙት የሚረዳ ክፍል ነው፡፡በዚህ ርእስ ስር

ሁሉ ም ርዕሶችና ንዕስ ርዕሶች እስከሚኙበት ገፅ ጭምር መገለጽ ይኖርባቸዋል፡፡

III. መግቢያ(Introduction) መግቢያ ለአንባቢዎች የጥናቱን መነሻ መረጃ የሚሰጥ ነው፡፡ የመግቢያ ፅሁፍ ስፋት እንደ ጥናቱ ቢወሰንም ከአንድ ገፅ መብለጥ ለበትም፡፡

መግቢያ፡- የአንባቢውን ፍላጎት የሚያነሳሳ

የጥናቱን ወሰንና አቅጣጫ የሚያመላክት

ለአንባቢው ጥናቱእንዴት እንደሚሰራ የሚያሳይ

የጥናቱን ጭብጥ የሚያሳይ

የጥናቱን የትኩረት አቅጣጫና ማጠቃለያ የሚያመላክት መሆን ይኖርበታል፡፡

IV. የጥናቱ ዓላማ(Objective) የጥናቱ ዓላማ ጥናቱ ሲጠናቀቅ የሚሰጠውን ጥቅም የሚያሳይ ነው፡፡

የጥናት ዓላማ፡- የመጨረሻ የጥናቱን ውጤት ማሳየት አለበት

በአጭርና ግልፅ በሆነ መንገድ የተገለፀ መሆን አለበት፡፡

V. ጥናቱ የሚመልሳቸው ችግሮች(statement of problem):- ጥናቱ የሚመልሳቸው ችግሮች ለአንባቢው ስለችግሩ ግልፅ የሆነ መረጃ የሚሰጥ ሲሆን ከአንድ ወይም ከሁለት ገፅ መብለጥ የለበትም፡፡

በውስጡ መካተት እና መግለጽ ያለበት፡- ችግሩን ችግር ያሰኘውን ምክንያት

ችግሩ በጥናቱ ሊፈታ የሚችል መሆኑን

ችግሩ ከድርጅቱ ግብ ጋር ያለውን ትስስር እና

ለድርጅቱ ከሚያስገኘው ጥቅም አንፃር የጥናቱ የመጨረሻ ውጤት ባካተተ መልኩ መቅረብ ይኖርበታል፡፡

VI. የጥናቱ አስፈላጊነት( Significance of the study)፡- በዚህ ርዕስ ውስጥ ጥናቱ የሚያስፈልግበትን ምክንያትና ጥናቱ ለድርጅቱ የሚያበረክተው አስተዋፅኦ ገላጭ በሆነ መልኩ መቀመጥ አለበት፡፡

VII.LOGO ኮምቦልቻጨርቃጨርቅ አክሲዮን ማህበር

KOMBOLCHA TEXTILE SHARE COMPANY

Form No.:

OP/KTSC/044

ማንዋል Issue No .

1Page No.:

Page 6 of 47

VIII. የጥናቱ ወሰን (Scope of the study):- በዚህ ክፍል ውስጥ፡-

በጥናቱ ምን ምን እንደሚሰራ

የጥናቱ ዳራ ከምን እስከምን ድረስ እንደሆነ እና ጥናቱ የሚጠናቀቅበትን ጊዜ ማመላከት ይኖርበታል፡፡

IX. ጥናቱን ለማካሄድ ታሳቢ ችግሮች(Limitation)

Page 9: 3  Web viewየምርምርና ስርፀት . አሰራር መመሪያ ማንዋል. አዘጋጆች. ንጉሴ ሙላት. ከድር ዘዉዱ. መሰረት ገነቱ

በዚህ ርዕስ ውስጥ ጥናቱን በሚሰራበት ጊዜ ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮች አስቀድመዉ መገለፅ ይኖርባቸዋል፡፡ የሚያጋጥሙ ችግሮችን አስቀድሞ መግለፁ ጥናቱን ለመምራት ይህ ነው የማይባል

አስተዋፅኦ አለው፡፡

X. የተዛማጅ ፅሁፍ ምልከታ(Litrature Review)፡- የተዛማጅ ፅሁፍ ምልከታ በሚጠናው ጥናት ዙሪያ ከዚህ በፊት በተጠኑ ጥናቶችን፤ ስምምነቶችን የተቀመጡ ንድፈ ሃሳቦችን በጥልቀት የምናይበት ቦታ ነው፡፡

ይህ ክፍል ጥናት በሚደረግበት ርእስ ዉስጥ የሚገኙትን ቁልፍ ቃላትን በመያዝ የተለያዩ የመረጃ መረቦችን በማሰስ በጥናቱ ዙሪያ የተጻፉ መረጃዎችን በመፈለግ ዋቢ መረጃ ማዘጋጀት አለበት፡፡

በተቻለ መጠን አጥኝዉ ከተዛማጅ ጽሁፍ ፍሬ ነገሩን በማስታወሻ በሚያሠፍርበት ጊዜ በራሱ ቃላት /ቋንቋ/ ቢጠቀም ይመረጣል ፡፡ነገር ግን በአንድ ተዛማጅ ጽሁፍ ዉስጥ አጥኝዉ የሚያገኘዉ ፍሬ ነገር አገላለጹ በጣም

ማራኪ ከሆነበትና በራሱ ቃላት/ቋንቋ/ ቢያስቀምጠዉ ፍሬ ነገሩ ለዛዉን የሚጣ ከሆነ እንዳለ ወስዶ ሊጠቀምበት ይችላል ፡፡

የተዛማጅ ፅሁፍ ምልከታ የሚከተሉትን ነጥቦች ይመልሳል፡-

በጥናቱ ርዕስ ዙሪያ ከአሁን በፊት የተሰራ ስራ ካለ፤ የነበሩት ቁልፍ ፅንሰ ሃሳቦች ምን እንደሆኑ፤ በርዕሱ ዙሪያ ሙህራኖች የተስማሙበት ንድፈ ሃሳብ ምን እንደሆነ፤ በየትኛው የርዕሱ ፅንሰ ሃሳብ ላይ ትኩረት እንደተደረገ፤

ጥናቱ ሲካሄድ የተከተሉት ዘዴ ወይም ስልት ምን እንደነበር፤ በተሰሩት ጥናቶች ልዮነቶች መኖራቸውንና አለመኖራቸውን በተጨማሪም የትኛው የተሻለ እንደሆነ፤ የቅርብ ጊዜ የተሻለ ጥናት መኖሩን፤ አሁን እየተጠና

ያለው ጥናት ከበፊተኞቹና አሁን ካሉ ሌሎች ጥናቶች የሚለየው ምን እንደሆነ መመለስ አለበት፡፡

LOGO ኮምቦልቻጨርቃጨርቅ አክሲዮን ማህበርKOMBOLCHA TEXTILE SHARE COMPANY

Form No.:

OP/KTSC/044

ማንዋል Issue No .

1Page No.:

Page 7 of 47

በአጠቃላይ የተዛማጅ ፅሁፍ ምልከታ ስፋት በጥናቱ ርዕስና በአጥኝዎቹ የሚወሰን ቢሆንም የፅሁፉ ምዕራፍ እስከ 20 ገፅ ሊደርስ ይችላል፡፡ ነገርግን ለትንንሽ ስራዎች በተወሰኑ ገፆች ሊገለጽ ይችላል፡፡

XI. የጥናቱ ዘዴና አካሄድ (Methodology of the study):- በዚህ ርእስ ስር ሶስት መሰረታዊ ጥያቄዎች “ሊመለሱ ይገባል፡፡ እነሱም እንዴት?” “መቼ?” “እና ለምን?” ‘’ ’’ የሚሉት ናቸዉ፡፡ እንዴት የሚለውን ለመመለስ በምን መልኩ ጥናቱ እንደሚካሄድ ጥልቅ የሆነ ማብራሪያ መስጠት ይኖርበታል፡

‘’ ’’መቼ ለሚለዉ ደግሞ የሚሰሩት ስራዎች የአሰራር ዘዴያቸውንና የሚያስፈልጋቸውን የጊዜ ገደብ በተጨባጭ መግለፅ ይሆናል፡፡

‘’ ’’ለምን የሚለውን ለመመለስ የተጠቀምንባቸውን መንገዶች የተለዮ ወይም አዲስ መሆናቸውንና መንገዶቹ የተመረጡበት ምክንያት ምን እንደሆነ ማረጋገጥ አለበት፡፡

XII. የስራ ዕቅድ(work plan)

Page 10: 3  Web viewየምርምርና ስርፀት . አሰራር መመሪያ ማንዋል. አዘጋጆች. ንጉሴ ሙላት. ከድር ዘዉዱ. መሰረት ገነቱ

1. የጊዜ ሰሌዳ (Time scheduele) ጥናቱ መቼ ተጀምሮ መቼ እንደሚጠናቀቅ እና ዝርዝር የስራ ክንውኖቹን ከሚፈፀሙ ጊዜ ጋር ያመለክታል ይህም በሰንጠረዥ ቢገለፅ የተሻለ ግልፅና የጥናቱ ንድፍ ለሚቀርብበት አካል ግልፅ የሆነ መረጃ

ይሰጣል፡፡

2. የሃብት ክፍፍል(Budget scheduele) ለጥናቱ ከሚያስፈልጉት ነገሮች ውስጥ በእጅ ያለውን፤ መገዛት ያለበትን እና ጥናቱ ከቦታ ቦታ ተንቀሳቅሶ የሚሰራ ከሆነ ወጪው መካተት አለበት፡፡በአጠቃላይ በዚህ ርዕስ ስር ለጥናቱ የሚያስፈልገዉ ወጭ በግልጽ መቅረብ አለበት፡፡ ይህም በሰጠረዥ ቢቀርብ የተሻለ ግልፅና የጥናቱ ንድፍ ለሚቀርብለት አካል

ግልፅ የሆነ መረጃ ይሰጣል፡፡

XIII. ማጣቀሻ(Reference) ይህ ርዕስ የጥናቱን እውነተኛነት ያመላክታል፡፡የተጠቀምንባቸዉን የመረጃ ምንጮች፤ በማን እንደተፃፈ፤ መቼ እንደፃፈ የመረጃ መረቡ ስም በግልፅ መቀመጥ አለበት፡፡

LOGO ኮምቦልቻጨርቃጨርቅ አክሲዮን ማህበርKOMBOLCHA TEXTILE SHARE COMPANY

Form No.:

OP/KTSC/044

ማንዋል Issue No .

1Page No.:

Page 8 of 47

ምዕራፍ 2

2. ጥናትና የጥናት አወቃቀር ዘዴ(Research & Research Approach)

2.1 የጥናት ትርጉም(Definition)

ጥናት ለችግሮች መፍትሄ በማመንጨት ላይ የሚያተኩር ስራ ነው፡፡ በማንኛውም የሥራ ሂደት የተለያዮ ችግሮች ሊያጋጥሙ ይችላሉ፡፡ እነዚህንም በአግባቡ በሳይንሳዊ መንገድ በመለየትና በመተንተንለችግሮች አስተማማኝ

መፍተሄ ማበጀት የጥናት ዋና ተግባር ነው፡፡ ስለዚህ ጥናት ሳይንሳዊ ሂደትን የሚከተልና በምልከታና ሙከራ ሊረጋገጡ የሚችሉ ጉዳዮች ብቻ የሚዳስስ ነው፡፡

ማንኛውም ጥናት ሳይንሳዊ ለመባል የሚከተሉትን ማሟላት ይኖርበታል፡፡

የሚጠናው ጉዳይ በሚገባ ማጤን ወይም መረዳት ፤

Page 11: 3  Web viewየምርምርና ስርፀት . አሰራር መመሪያ ማንዋል. አዘጋጆች. ንጉሴ ሙላት. ከድር ዘዉዱ. መሰረት ገነቱ

የጥናቱ መሰረታዊ/ ቁልፍ ጥያቄዎች መለየት፤

አስተማማኝ መረጃ መሰብሰብ፤

የተገኘውን መረጃ መተንተን፤

የተገኘውን መረጃ መተርጎም ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡

የማንኛውም ጥናት ውጤት ሌሎች በሙያው ያሉ ወይም የተሰሩ ሰዎች ሊፈትሹትና ሊመረምሩት የሚችሉበት ሁኔታ ግልፅ ሆኖ መቅረብ አለበት፡፡

በአጠቃላይ ጥናት በምልከታዊ ወይም ተግባራዊ ልምድ በሚመነጩ መረጃዎች ላይ በመመስረት የተሰበሰበውን መረጃ አሃዛዊ ወይም ገላጭ መንገድ በመከተል ከስሜታዊነት ነፃ በሆነ መንገድ ተንትኖ ወደ

አንድ ሳይንሳዊ ድምዳሜ ለመድረስ የሚከናወን ተግባር ነው፡፡

2.2 በጥናት ስራ ላይ መሟላት የሚገባቸዉ (Requirements of research)

የአንድ ጥናት ሥራ ከመጀመሩ በፊት ጥናቱ ለምን፤ እንዴት፤ መቼ፤ ለማን እንደሚሰራ በጥናቱ ፕሮፖዛል ላይ መነደፍ ይኖርበታል፡፡ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት በቅድሚያ በጥናቱ ፕሮፖዛል ላይ የሚታዮ ቢሆንም ጥናታዊ ፅሁፉ

ሲዘጋጅም አብረው መካተትይኖርባቸዋል፡፡

2.2.1 ከንድፍ በፊት መታወቅ የሚገባቸው (prerequiste)

በአንድ ሁኔታ ወይም ችግር ላይ ጥናት ማካሄድ የሚያስፈልገው ሁኔታው ወይም ችግሩ በሚከተለው አኳኋን ሲገኝ ነው፡፡

LOGO ኮምቦልቻጨርቃጨርቅ አክሲዮን ማህበርKOMBOLCHA TEXTILE SHARE COMPANY

Form No.:

OP/KTSC/044

ማንዋል Issue No .

1Page No.:

Page 9 of 47

ሀ. ስለ ሁኔታው/ ችግሩ እስከ አሁን ድረስ ምንም አይነት ጥናት ካልተካሄደበት፤

ለ. ስለ ሁኔታው/ ችግሩ በከፊል ጥናት ተደርጎበት ነገር ግን የተደረገው ጥናት ሙሉ በሙሉ ሁኔታን ወይም ችግሩ በመጠኑ ብቻ የተመረመረ ከሆነ፤

ሐ. ስለ ሆኔታው ወይም ስለ ችግሩ የተደረገው ጥናት ጠቋሚ እንጅ በጥልቀትና በስፋት ያልተጠና ከሆነ፤

መ. ስለ ሁኔታው/ ችግሩ እስከ አሁን የተደረገው ጥናት ስህተት ያለው ከሆነ በአጠቃላይ በጥናት ሂደት በመጀመሪያ ችግሩን ለይቶ ማወቅ ያስፈልጋል፡፡ችግሩን ከለዮ በኃላ መንሰኤውን በጥናት ማግኘት ተገቢ

ይሆናል፡፡

2.2.2 በጥናቱ የሚፈቱ ችግሮችን አመራረጥ (problems Identification)

አንድ አጥኚ በአንድ ችግር ወይም ሁኔታ ላይ ጥናት ለማካሄድ በሚያስብበት ጊዜ ውሳኔ ላይ ለመድረስ የሚከተሉትን ነጥቦች ማጤን ይኖርበታል፡፡

ጥናት ሊካሄድበት የታሰበበት ችግር አዲስ ነው ወይስ አይደለም ካልሆነስ ምን ያህል ጥናት ተደርጎበታል የተደረገውስ ጥናት ምን ያህል ስፋትና ጥልቀት አለው?

ጥናት ሊካሄድበት የታሰበበት ችግር በሳይንሳዊ የጥናት ሥልትና በተጨባጭ ሊጠና የሚችል ነው ወይሰ አይደለም?

Page 12: 3  Web viewየምርምርና ስርፀት . አሰራር መመሪያ ማንዋል. አዘጋጆች. ንጉሴ ሙላት. ከድር ዘዉዱ. መሰረት ገነቱ

ጥናት ሊካሄድበት የታሰበበት ችግር ወይም ሁኔታ ምን ያህል ተፈላጊ ነው? ማለትም ጥናቱ ምን ችግርን ለመፍታት ይጠቅማል? የሚለው በጣም ቁልፍ ጥያቄ ነው፡፡ ምክንያቱም የጥናት አንድ ዋና

አላማ ለጥናቱ ብቻ ሳይሆን የሚደረገው ጥናት አንድ ችግር ወይም እንቆቅልሽ የሚፈታ ሊሆን ይገበዋል፡፡

ጥናት ሊካሄድበት የታሰበበት ችግር ላይ አጥኚው ምን ያህል ለማወቅ ፍላጎት አለው? ምክንያቱም አጥኚው በሚያደርገው ጥናት ላይ ፍላጎት ከሌለው ጥናቱ የሚጠይቀውን መስዋዕትነት ለመክፈል

ዝግጁ ሊሆን አይችልም፡፡ ጥናት ብዙ መስዋዕትነት የሚጠይቅ ነው፡፡በተለይ የጊዜ፤ የትግስት እነዲሁም ሌሎች፤

ጥናት ሊካሄድበት የታሰበበት ጉዳይን በሚመለከት አጥኚው ጥናቱን ለማካሄድ ተፈላጊውን በቂ እውቀት እዳለው ከመጀመሪያ እርግጠኛ መሆን ይገባዋል፤

ከዚህ በተጨማሪ ጥናት ሊካሄድበት የታሰበበት ጉዳይ ወይም ችግር ላይ መረጃ ለመሰብሰብ የሚያስችል ሁኔታ መኖሩንና እንዲሁም ለጥናቱ የሚያስፈልጉት መሳሪያወች እንደሚገኙ ማረጋገጥ፤

ጥናቱ ሊካሄድት በታሰበበት ችግር ወይም ሁኔታ ላይ ጥናት እንዲካሄድበት በሃሳብና በገንዘብ የሚደግፍ ድርጅት መኖሩን ማወቅ ይበጃል፤

LOGO ኮምቦልቻጨርቃጨርቅ አክሲዮን ማህበርKOMBOLCHA TEXTILE SHARE COMPANY

Form No.:

OP/KTSC/044

ማንዋል Issue No .

1Page No.:

Page 10 of 47

ከዚህም በላይ ጥናቱን ለማካሄድ የሚያስፈልገውን ገንዘብ፤ የቁሳቁስ፤ የሰው ሃይልና ጊዜ ምን ያህል መሆኑን መተመን ያስፈልጋል፤

በመጨረሻም ጥናቱ ሊያስከትል የሚችለው ውጣ ውረድ፤ አደጋ እና መሰናክል ከመጀመሪያው መገመትና መዘጋጀት ተገቢ ይሆናል፡፡

2.2.3 ከጥናቱ ግኝቶች አጠቃላይ ግንዛቤ መውሰድ (internalization)

በአንድ ርዕስ ላይ ጥናት የሚካሄደው በርዕሱ ላይ ጥናት ከተካሄደ በኃላ የተከሰቱት ግኝቶች በርዕሱ ላይ አጠቃላይ ግንዛቤ ለመውሰድ እንዲያስችል ነው፡፡ እንደሚታወቀው ጥናት የሚካሄደው ለናሙና በተመረጡ

መላሾች ሲሆን እነዚህም ለናሙና የተመረጡ መላሾች ሁሉን ይወክላሉ ተብሎ ታምኖበት ቢሆንም የተገኘውም የጥናት ውጤት ሁሉን አስከምን ድረስ እንደሚመለከት አጠቃላይ ግንዛቤ ከጥናቱ የስፋትና ጥልቀት ወሰን

የዘለለ መሆን የለበትም፡፡

በተጨማሪም አጠቃላይ ግንዛቤው በጥናቱ የተሰበሰበው መረጃ ከሚደግፈው ውጭ እንዳይሆን መጠንቀቅ ያስፈልጋል፡፡ በጥናቱ ስለተገኙት ግኝቶች አጠቃላይ ግንዛቤ ሲሰጥ የሚከተሉትን ነጥቦች ማጤን ይገባዋል፡፡

ስለ ግኝቶች የሚሰጠው አጠቃላይ ግንዛቤ በጥናቱ አላማና በሚገኘው መረጃ ላይ ብቻ መሆን አለበት እንጂ ከዚህ ውጭ መሆን የለበትም፤

ስለ ግኝቶች የሚሰጠው አጠቃላይ ግንዛቤ በጠንካራ ማስረጃ ላይ የተመሰረተ እንጂ በትንሽ ፍንጭ ላይ የተመሰረተ መሆን አይገባውም፤

Page 13: 3  Web viewየምርምርና ስርፀት . አሰራር መመሪያ ማንዋል. አዘጋጆች. ንጉሴ ሙላት. ከድር ዘዉዱ. መሰረት ገነቱ

በጥናቱ ውስጥ ባልነበሩ አዲስ መረጃ ላይ የተመሰረተ አጠቃላይ ግንዛቤ ማቅረብ ተገቢ አይደለም፤

በስህተት ላይ የተመሰረተ ትንታኔና አተረጓጎም እንዳይኖር ጥንቃቄ ሊደረግ ይገባል፤

እንዲሁም አጠቃላይ ግንዛቤው የአጥኚውን የግል አስተሳሰብ ወይም የተሳሳተ አስተሳሰብ የሚያንፀባርቅ መሆን አይገባውም፡፡

2.3 የጥናት አወቃቀር ዘዴ (The Research approach

2.3.1 መላምት (Hypothesis)

መላምት፡-

የአንድ ጥናት መሰረታዊ ጥያቄ ጊዜያዊ መልስ የሚሰጥ ፤ አንድ አጥኚ ጥናት ሊያደርግ ሲነሳ በአእምሮ ውስጥ “ ለሚመላለሱ ጥያቄዎች ወይም እንዲህ ይሆን?” ለሚለው ጥርጣሬ የሚሰጠው ጊዛዊ ምላሽ ፤ በጥናት

ተግባራዊ ሂደት ውስጥ የሚፈተሽና የሚረጋገጥ ሲሆን ይህም

LOGO ኮምቦልቻጨርቃጨርቅ አክሲዮን ማህበርKOMBOLCHA TEXTILE SHARE COMPANY

Form No.:

OP/KTSC/044

ማንዋል Issue No .

1Page No.:

Page 11 of 47

ያስፈለገበት ምክንያት ለጥናት ተግባር ሂደት የተፈተሸና የተረጋገጠ እውነታ በማፍለቅ የሰዎችን የእውቀት አድማስ በማስፋትና በማጠናከር የጥናቱ ተጠቃሚ ለማድረግ ነው፡፡ መላምት ከንድፍ ሃሳብ፤ ከምልከታ ወይም ከእነዚህ

ከሁለቱም በጋራ ጥምረት ሊፈልቅ ይችላል፡፡

2.3.1.1 በመላምት አቀራረፅ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች

መላምቱ ግልፅ ሁኖ መስፈር አለበት፤ በጥናት ተግባራዊ ሂደት ውስጥ መላምቱን ለመፈተሽና ለማረጋገጥ አንዲቻል በመላምቱ ውስጥ ሊጠቃለሉ የሚችሉትን ተለዋዋጭ ሁኔታዎች በግልፅ ማስቀመጥ አስፈላጊ ነው፡፡

መላምት በፍተሻ ሊረጋገጥና ሊጣራ የሚችል ሁኖ መቅረብ ይኖርበታል፡፡ የአንድን መላምት ተጨባጭ መረጃዎች አሰባስበን በሚደረገው ትንታኔ ትክክለኛነቱን ለመፈተሽ ወይም ለማረጋገጥ ይቻላል፡፡ መላምቱን መሰረት ያደረገ መረጃ መሰብሰብና የመተንተን ሂደት ተግባራዊ ማድረግ ላይ ችግር ከገጠመን

ግን መላምቱ ሊፈተሽ ወይም ሊረጋገጥ የማይችል ነው፡፡ ይህን አይነቱን መላምት መተው ያስፈልጋል፡፡

መላምቱ የተንዛዛ ሆኖ መቅረብ የለበትም ከመላምቱ ጋር አብረው ተያይዘው ሊታዮ የሚገባቸው በጥናቱ ውስጥ መረጃ በማሰባሰብ፤ ልንመልሳቸው ያቀድናቸው መሰረታዊ ጥያቄዎች ናቸው፡፡ በጥናቱ ወይም

በምርምሩ ሂደት ውስጥ የሚመለሱት እነዚህ መሰረታዊ ጥያቄዎች አስቀድመን ያሰፈርነውን መላምት እውነት መሆን ወይም አለመሆን የሚያረጋግጡ መሆን አለባቸው፡፡

2.3.2 የጥናት ርዕስ አመራረጥ

የጥናት ርዕሶችን በመፈለግ፤ በመምረጥ፤ ለይቶ በማስቀመጥ ሂደት አስፈላጊ ጥንቃቄዎች መደረግ ይኖርባቸዋል፡፡ይኸውም፡-

Page 14: 3  Web viewየምርምርና ስርፀት . አሰራር መመሪያ ማንዋል. አዘጋጆች. ንጉሴ ሙላት. ከድር ዘዉዱ. መሰረት ገነቱ

I. የምርምር ርዕስ ሲመረጥ በቅድሚያ በጉዳዮ በቂ እውቀትና ስለጉዳዩም አወንታዊ ፍላጎት ስለመኖሩ መረጋገጥ አለበት፤ ከአጥኚው ልምድ፤ እውቀትና ፍላጎት ውጭ እንዳይሆን፡፡

II. ርዕሰ ጉዳዩን በሚመለከት ጥናቶች ተሰርተው ከሆነ የተለየ ነገር እናሳያለን ብለን ካመን በጉዳዮ ልንገፋ እንችላለን፡፡

III. መረጃዎች እየተጠናቀሩ በራሳቸው ተፋሰስ እንዲሄዱ የሚያስችል ርዕስ መምረጥ

IV. የጥናት ርዕስ ስንመርጥ ከስሜታዊነት ነፃ ሆነን በነፃ አዕምሮ ልንሰራው የምንችለውን መምረጥ፤

V. የጥናት ርዕስ ስንመርጥ ጥናታችን ሊመልሰው የሚገባ ጥያቄ ወይም ሊፈታ የሚገባ ችግር መኖሩን ማረጋገጥ አለብን፡፡

VI.LOGO ኮምቦልቻጨርቃጨርቅ አክሲዮን ማህበር

KOMBOLCHA TEXTILE SHARE COMPANY

Form No.:

OP/KTSC/044

ማንዋል Issue No .

1Page No.:

Page 12 of 47

2.3.3 የጥናት ርዕስ አገላለፅ

የጥናት ርዕስ በምናሰፍርበት ጊዜ ልናተኮርባቸው የሚገቡ ነጥቦች

የርዕሱን ሃሳብ ሳያንዛዙ በጥቂት ቃላት ማስፈር፤

ርዕሱ የሚገለፅበትን ሃረግ በተቻለ መጠን አጭር ማድረግ፤

የማያስፈልጉ ቃላትን ማስወገድ ይቻል ዘንድ እያንዳዱ ቃል በትክክል ተፈላጊውን መልዕክት ማስተላለፍ መቻሉን ማረጋገጥ፤

ቃላትና ሃረጎች ሰዋሰዋዊ በሆነ መንገድ ተክተው መቀመጣቸውን ማረጋገጥ

ከዚህ በተጨማሪ አንድ አጥኚ የጥናት ርዕሱን ለመግለፅ በሚሞክርበት ጊዜ አስቀድሞ የነደፈውን መላምትና መሰረታዊ ጥያቄ በአእምሮው መያዝ ይኖርበታል፡፡ይህንን ዘንግቶ የጥናት ርዕስ ላይ መሰማራት የሚፈለገውን

ውጤት እንዳይገኝ እንቅፋት ሊሆነ ይችላል፡፡

ምእራፍ 3

3. የናሙና አወሳሰድ ዘዴዎች (sampling techniques)

መረጃ በሚሰበሰብበት ወቅት ጥናቱ የሚመለከታቸውን ማንኛውንም ሰው ወይም ነገር ሁሉ ለመረጃ ሰጭነት መጠቀም ብዙውን ጊዜ አስቸጋሪ ይሆናል፡፡ ይህ አይነቱ አሰራር የማያመችና አንዳንዴም የማይቻል ከመሆኑም

በላይ ብዙ ገንዘብ፤ ጊዜና ጉልበት ይጠይቃል፡፡ አማራጩ ከጠቅላላው ጥናቱ ከሚመለከታቸው ሰዎች መካከል ጥቂቶቹን መርጦ ለጥናቱ የሚያስፈልገውን መረጃ ከነሱ መሰብሰብ ነው፤ ይህም ናሙና ይባላል፡፡

በዚህ መልክ የሚወሰደው ናሙና ጥናቱ የሚመለከታቸውን ሰዎች ወይም ነግሮች ሁሉ የሚወክል መሆን ይኖርበታል፡፡ ናሙናው ወካይ ከሆነ የጥናቱ ውጤት መረጃው ከሁሉም ሰዎች ወይም ነገሮች ተሰብስቦ ትንተናው

ቢካሄድ ኑሮ ከሚገኘው ውጤት ወይም መንደርደሪያ ጋር ተመሳሳይ ይሆናል፡፡

የናሙና አወሳሰድ ዘዴዎችን በሁለት መልክ ከፋፍሎ መመልከት ይቻላል፡-

Page 15: 3  Web viewየምርምርና ስርፀት . አሰራር መመሪያ ማንዋል. አዘጋጆች. ንጉሴ ሙላት. ከድር ዘዉዱ. መሰረት ገነቱ

3.1 እኩል እድል የማይሰጥ ናሙና (Non-probability sampling)

ጥናቱ ለሚመለከተው ለዕያንዳዱ አባል በናሙናነት የመወሰድ እድል ያለው መሆኑን አለማረጋገጡ ነው፡፡

LOGO ኮምቦልቻጨርቃጨርቅ አክሲዮን ማህበርKOMBOLCHA TEXTILE SHARE COMPANY

Form No.:

OP/KTSC/044

ማንዋል Issue No .

1Page No.:

Page 13 of 47

እኩል እድል ከማይሰጡ የናሙና አይነቶች ዉስጥ የሚከተሉትን በምሳሌነት መመልከት ይቻላል፡-

ያጋጣሚ ናሙና(Accidental sampling) ተመራማሪው የሚፈልገውን የናሙና ብዛት እስኪሞላለት ድረስ ከፊቱ ወይም ከአጠገቡ ያገኘውን ሁሉ በናሙናነት ይወስዳል፡፡ ይህ ዘዴ የአጋጣሚ የሚያስገኘው

ለናሙናነት የሚወሰዱ ሰዎች ተመራማሪው የሚመርጣቸው ወይም ፈልጎ የሚያገኛቸው ሳይሆኑ ቦታና ግዜ የሚያጋጥማቸው ነው፡፡

የግኝት ናሙና(Snowball sampling) በናሙና እጦት ጥቅም ላይ የሚውል ነው፡፡

የኢላማ ናሙና(Purposive sampling) ሆን ብሎ በመምረጥ የሚከናወን ነው፡፡ ተመራማሪው በናሙናነት የሚወስደው ያጋጠመውን ወይም ያገኘውን ሁሉ ሳይሆን ከጠቅላላ ጥናቱ ከሚመለከታቸው

መካከል ለሚፈለገው አላማ ይጠቅማሉ ብሎ የሚገምታቸውን በጥንቃቄ በመምረጥ ነው፡፡

የኮታ ናሙና(Quota sampling) ይህ ዘዴ ጥናቱ የሚመለከታቸው የተለያዮ ቡድኖች በብዛታቸው መጠን በናሙና ውስጥ መታቀፋቸውን የሚያረጋግጥ ነው፡፡ የዚህ ናሙና አወሳሰድ ዘዴ ዋነኛ ድክመቱ ከአንድ ክፍል ምን ያህል ናሙና እንደሚወሰድ እንጅ እነማን እንደሚወሰዱ ማመልከት አለመቻሉ ነው፡፡

3.2 እኩል እድለ ሰጭ ናሙና (probability sampling)

በተለያየ መልኩ ሊከናወን ይችላል፡፡ የዚህ ዘዴ ዋና ባህሪ ደግሞ ለእያንዳዱ አባል በናሙናነት የመወሰድ ተመሳሳይ እድል መሰጠቱ ነው፡፡ ይህም በመሆኑ በዚህ ዘዴ የሚወሰድ ናሙና ጥናቱ የሚመለከታቸውን ሁሉ የመወከል ሃይሉ እኩል እድል ከማይስጥ ናሙና በጣም የተሻለ ነው፡፡

ከእኩል እድል ሰጭ ናሙና አይነቶች ዉስጥ የሚከተሉትን በምሳሌነት መመልከት ይቻላል፡-

ተራ የእጣ ናሙና(simple Random sampling) የዚህ ዘዴ የመጀመሪያ ተግባር የሚሆነው ጥናቱ የሚመለከታቸውን ሰዎች ወይም ነገሮች በሙሉ የያዘ ዝርዝር ማዘጋጀትና ተራ ቁጥር መስጠት ነው፡፡ ለናሙናነት የሚወሰደው ምን ያህል ሰው ወይም ነገር እንደሆነ መወሰኑ ሁለተኛው ተግባር ነው፡፡ ከተዘጋጀው ዝርዝር ውስጥ በናሙናነት የሚወሰዱት ወይም የሚመረጡት በእጣ ሲሆን የእጣ

አጣጣሉ ዘዴ እንዳስፈላጊነቱ የተለያዮ መንገዶች ሊከተል ይችላል፡፡

ምድብ የእጣ ናሙና(Cluster sampling) በጥናቱ ውስጥ የሚካተቱ በእድሚያቸው፤ በፆታቸው፤ በሀይማኖታቸው የተለያዮ ሁነው ሲገኝ ናሙናው ከሁሉም አይነት ምድብ

Page 16: 3  Web viewየምርምርና ስርፀት . አሰራር መመሪያ ማንዋል. አዘጋጆች. ንጉሴ ሙላት. ከድር ዘዉዱ. መሰረት ገነቱ

LOGO ኮምቦልቻጨርቃጨርቅ አክሲዮን ማህበርKOMBOLCHA TEXTILE SHARE COMPANY

Form No.:

OP/KTSC/044

ማንዋል Issue No .

1Page No.:

Page 14 of 47

የተመጣጠነ ቁጥር የያዘ መሆን ስላለበት የምድብ እጣ ናሙና ዘዴ ለመጠቀም እንገደዳለን ማለት ነው፡፡

ቡድን/ክልል/ ናሙና(Area sampling) በናሙናነት የሚመረጡት ግለሰቦች/ነገሮች/ ሰፋ ባለ ቦታ የሚመረጡ ተበታትነው የሚገኙና በጣም ብዙ ሲሆን ከአንድ የእጣ ናሙና አወሳሰድ ዘዴ

ለመጠቀም አስቸጋሪ ስለሚሆን ጥናቱ የሚመለከታቸው ሰዎች በቡድን ናሙና መጠቀሙ ጊዜ፤ ጉልበትና ገንዘብ ከመቆጠብ ባሻገር የበለጠ ምቹ ይሆናል፡፡

ምእራፍ 4

4. የመረጃ ማሰባሰብ ስልቶች (Data collection tools) እና የጥናት ፎርማት

ጥናት ለማካሄደድ አስተማማኝ መረጃዎችን ማሰባሰብ አስፈላጊ ነው፡፡ በተለይ የጥናቱ ዋና አላማ አሁን በጊዜው በተጨባጭ የተከሰተ ሁኔታን ወይም ችግርን ለማጥናት ከሆነ መረጃው ወቅታዊ ቢሆን ይመረጣል፡፡ ምክንያቱም

ጊዜ ያለፈበት መረጃ ከሆነ ያሁኑን ሁኔታ ወይም ችግር ለማጥናት አይጠቅምም፡፡

4.1 የጥናት መረጃ ማጠናቀሪያ ስልት አይነቶች

የፅሁፍ መጠይቅ(Questionnaries) በተለይ ሰዎችን በግንባር ለማግኘት በማይችልበት ሁኔታ ይህን ዘዴ መጠቀም ያስፈልጋል፡፡

ቃለ- መጠይቅ(Interview) በተለይ ማንበብና መፃፍ ከማይችሉ ሰዎች መረጃ ለመሰብሰብ ያስችላል፡፡

ምልከታ(observation) በቂ ጊዜ ወስዶ በፕሮግራም በተወሰነ ጊዜ ነገሩን ወይም ሁኔታውን መመልከትና የተመለከቱትንም ወዲያውኑ ሳይረሳ መመዝገብ ይጠይቃል፡፡

የቡድን ውይይት(focus group or group discussion) ይህ ዘዴ ተመራጭ የሚሆነው ለጥናቱ አስተማማኝ መረጃ የሚገኘው ተተኳሪዎች ወይም መረጃ ሰጭዎችን በቡድን በማወያየት ነው ብለን

ካመንን ነው፡፡

ሙከራ(Experiment) ለጥናቱ አላማ ሲባል የተለያዮ ሙከራዎች በማድረግ መረጃን የምናሰባስበትና በከፍተኛ ደረጃ ለሚደረጉ ጥናቶች መረጃን ለማሰባሰብ የሚውል ነው፡፡ ማለትም ሙከራዎች ሲደረጉ

ተለዋዋጮዎችን በጥንቃቄ መቆጣጠር ሲቻል ሊፈጠር የሚችለውን ሁኔታ በመዳሰስ መረጃን ለማሰባሰብ የሚያስችል ነው፡፡ የሙከራው ሂደት ተለዋዋጮች በሚኖራቸው የርስበርስ ግንኙት ላይ

ያነጣጥራል፡፡

ከሰነድ ግምገማ (Document Analysis) የተለያየ አይነት ያላቸው ሰነዶች ለልዬ ልዬ ጥናቶች በመረጃ ምንጭነት ጥቅም ላይ ይውላሉ ይኸውም ከሌሎች የመረጃ ዘዴዎች ጋር በመቀናጀት ወይም ራሳቸውን ችለው ሊሆን ይችላል፡፡ ሰነድ ስንል የተለያዮ ተቋማት መዛግብት፤ ደብዳቢዎች፤ አስተዳደራዊ

ሰነዶች/ ለምሳሌ ሪፖርቶች፤ አጀንዳዎች፤ ቃለ- ጉባኤ ወዘተ.. የመሳሰሉትን ያጠቃልላል፡፡

LOGO ኮምቦልቻጨርቃጨርቅ አክሲዮን ማህበርKOMBOLCHA TEXTILE SHARE COMPANY

Form No.:

OP/KTSC/044

ማንዋል Issue No .

1Page No.:

Page 15 of 47

Page 17: 3  Web viewየምርምርና ስርፀት . አሰራር መመሪያ ማንዋል. አዘጋጆች. ንጉሴ ሙላት. ከድር ዘዉዱ. መሰረት ገነቱ

4.1.1 የመጠቅ አዘገጃጀት

መጠይቅ ከመውጣቱ በፊት ጥናት ስለሚደረግበት ርዕስ ብዙ ማወቅ ማለትም በርዕሱ ላይ ቀደም ብለው የተፃፉ ፅኁፎችን ማንበብ እንዲሁም የጥናቱን አላማ መወሰን ለምንስ አይነት ጥያቄዎችና መፍተሄዎች ምላሽ

እንዲያስገኝ እንደሚፈልግ አጥኚው መወሰን ይገበዋል፡፡ መጠይቅ ለማውጣት ሲታሰብ የአጠያየቁን ዓይነት መወሰን ያስፈልጋል፡፡

ሀ/ ነፃ ምላሽ የሚያሰጡ፡ ጥያቄው ክፍት ሆኖ መላሹም እንደልቡ ሃሳቡን የሚሰጥበት ነው፡፡ መላሹ በአመላለሱ አይገታም፤ አጥኚውም ያላሰበውን አንዳንድ አዳዲስ ሃሳቦች ከመላሾች እንዲያገኝ ያስችላል፡፡

ለ/ ዝግ የሆነ ምላሽ የሚያሰጥ፡ ዓይነቱ አጠያየቅ የሚያስገኘው መልስ ውስን ነው፡፡

አንድ አጥኚ መጠይቅ በሚያዘጋጅበት ጊዜ ማስታወስ የሚገባቸው ነጥቦች፡

ጥያቄዎች ሁሉ ጥናት በሚደረግበት ርዕስ ላይ ብቻ የተመሰረቱ መሆናቸውን፤

ጥያቄዎቹ ሁሉ ለጥናቱ ዓላማና ግብ መምታት ሚረዱ መሆናቸው፤

ጥያቄዎቹ ሃሳብ ግልፅ በሆነ መንገድ መንፀባረቁን፤

ጥያቄዎቹ ሁሉ ቋንቋቸው ግልፅ እንጅ አሻሚ አለመሆኑ፤

እያንዳዱ ጥያቄ ራሱን የቻለ አንድ ጥያቄ እንጅ የተደራረበ ጥያቄ ወይም ሃሳብ ያልያዘ መሆኑን ፤

የጥናቱን አላማ በሚገባ የሚሸፈኑ ጥያቄዎች መጠየቃቸውን፤

የጥያቄዎቹ አጠያየቅና የቃላትም አገባብ መላሾችን የማያስቀይም፤ የማያስፈራና የማያናድድ መሆኑን፤

የጥያቆዎች አጠያየቅና የቃላትም አገባብ አጥኝው የሚወደውን ወይም የሚጠላውን ሃሳብ የማያንፀባርቅ አለመሆኑን፤

ጥያቄዎች ሁሉ ያልሆነ ወይም ልዮ ትርጉም የሚሰጣቸው አለመሆናቸው፤

ለተጠየቁት ጥቄዎች ሁሉ ምላሾች መልስ ሊሰጡባቸዉ የሚችሉ መሆኑን፤

ጥያቆዎች አለመጠን የተንዛዙ አለመሆናቸውንና ጥያቄዎቹ የመላሾችን ጊዜ ከመጠን በላይ የሚወስዱ አለመሆናቸውን፤

LOGO ኮምቦልቻጨርቃጨርቅ አክሲዮን ማህበርKOMBOLCHA TEXTILE SHARE COMPANY

Form No.:

OP/KTSC/044

ማንዋል Issue No .

1Page No.:

Page 16 of 47

በመጠይቁ መስፈር ያለባቸው

Page 18: 3  Web viewየምርምርና ስርፀት . አሰራር መመሪያ ማንዋል. አዘጋጆች. ንጉሴ ሙላት. ከድር ዘዉዱ. መሰረት ገነቱ

በመጠይቁ መጀመሪያ ላይ አጥኘው የስራ ቦታ፤ አድራሻና እንዲሁም የጥናቱ አላማ ምን እንደሆነ በግልፅ መፃፍ አለበት፤

መላሾች መጠይቁን ሲሞሉ ስማቸው መፃፍ የማይገባቸው መሆኑን መጠቀስ አለበት፤

የመጠይቁ አስፈላጊነት ( የጥናቱ ዋና አላማ) በግልፅ መጠይቁ እንዴት መሞላት እንደሚገባው በመጠይቁ መጀመሪያ ላይ ግልፅ እና አጠር ያለ መመሪያ መስጠት ያስፈልጋል፤

መጠይቁን እንዲሞሉ የተጠየቁ ሰዎች በጎ ፈቃድና የጥናትን ጥቅም በመገንዘብ እንጅ በግዴታ ስላልሆነ ለሚያሳዮት በጎ ፍቃድና ትብብር እንዲሁም መጠይቁን ለመሙላት ለሚያጠፉት ጊዜ ማመስገን ተቢ

መሆኑን አጠር ያለ ምስጋና በቃለ- መጠይቁ ላይ ቢታከልበት አይከፋም፤

4.1.2 የቃለ መጠይቅ አዘገጃጀት

ጠያቂና መላሽ ግንባር ለግንባር በመገናኘት መረጃ የሚሰበስቡበት ስልት ነው፡፡ በተለይም ማንበብና መፃፍ ከማይችሉና ከህፃናት መረጃ ለመሰብሰብ ይጠቅማል፡፡ ቃለ- መጠይቅን ልክ እንደ ፅሁፍ መጠይቅ በጥንቃቄ

ማዘጋጀት ያስፈልጋል፡፡ ቃለ መጠይቅ በሚገባ ከተዘጋጀ በኃላ የሚከተሉትን ማድረግ አስፈላጊ ነው፡፡

ቃለ- መጠይቁ ምን ያህል ጊዜ እንደሚወስድ፤

ስለ ቃለ መጠይቁ ዓላማ ለመላሾች ማስረዳት፤

መላሹ ፍቃደኛ ከሆነ ለራሱ እንደሚመቸው ቀጠሮ መውሰድ፤

በቀጠሮው ግን ሰዓቱን አክብሮ መገኘት፤

መላሹን አክብሮት በተሞላበት ሁኔታ መያዝ፤

ጥያቄዎችን በሚገባ መጠየቅ፤ መላሹን በጥሞና ማዳመጥ አለአግባብ ጣልቃ ገብቶ አለመናገር፤

መላሹ የሚሰጠውን መልስ ፍሬ ነገሩን ብቻ መፃፍ፤

መላሹ ጥያቄው በደንብ ሳይገባው ወይም ጥያቄው ላለመመለስ ብሎ ከጥያቄው ውጭ ያልሆነ ነገር ሲናገር ቀስ ብሎ በትህትና ጥያቄውን እንዲመልስ ማድረግ፤

መላሹ የሰጠው መልስ ማብራሪያ ካስፈለገ በትህትና መጠየቅ፤

መላሹ የሚሰጠው መልስ በቴፕ ለመቅረፅ የሚያስፈልግ ከሆነ ከቀጠሮው በፊት የመላሹን ፈቃድ ማግኘት ተገቢ ነው፤

LOGO ኮምቦልቻጨርቃጨርቅ አክሲዮን ማህበርKOMBOLCHA TEXTILE SHARE COMPANY

Form No.:

OP/KTSC/044

ማንዋል Issue No .

1Page No.:

Page 17 of 47

መላሹ ከተወሰነው ጊዜ በላይ መልስ መስጠቱን ለመቀበል ከፈለገ የቃለ መጠይቁን ጊዜ ማራዘም ይቻላል፡፡

ምቹ ቦታና ጊዜ መምረጥ ያስፈልጋል፤ 4.2. የጥናቱ ፅሁፍ ሲዘጋጅ መካተት የሚገባቸው

I. የጥናቱ ርዕስ(Topic) በርዕስ ገፅ ላይ የሚኖሩ ቃላት በጥንቃቄ መመረጥና ቃላቱም የተመጠኑ እና ጥናቱን በደንብ የሚገልፁ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡

Page 19: 3  Web viewየምርምርና ስርፀት . አሰራር መመሪያ ማንዋል. አዘጋጆች. ንጉሴ ሙላት. ከድር ዘዉዱ. መሰረት ገነቱ

በርእስ ገፅ ላይ መካተት የሚገባቸው ነገሮች፡- የጥናቱ ርዕስ የአጥኝዎቹ ሰምና አድራሻ ጥናቱ የሚቀርብለት ድርጅት የጥናቱ ፕሮፖዛል የሚቀርብበት ቀንና አመት

II. ምስጋና(Acknolodgement) ጥናቱ ሲካሄድ ለአጥነው በገንዘብ፤ በማማከር፤ አጥኒውን በማበረታታት እና የተለያዮ ድጋፍ በማድረግ ጥናቱ እንዲሳካ ለተባበሩ ሁሉ ስማቸውን በመግለፅ ምስጋና የሚገለፅበት ክፍል ነው፡፡

III. ማውጫ(Table of content)

ማውጫ አንባቢዎች ማንበብ የሚፈልጉትን ክፍል በቀላሉ እንዲያገኝት የሚረዳ ነው፡፡ማውጫ ሁሉንም ርዕሶችና ንዕስ ርዕሶች እስከሚኙበት ገፅ ጭምር ማስቀመጥ ይኖርበታል፡፡

IV.ምስልና ሰንጠረዥ ማውጫ(Lists of figure and tables)

ይህ በአማርጭነት የሚያዝ ነው ጥናቱ በዛ ያሉ ስዕላዊ መግለጫና ሰጠረዥ ከያዘ ብቻ የምንጠቀምበት ነው፡፡ በዚህ ውስጥ የተጠቀምንባቸውን መግለጫዎችና ሰንጠረዦች ስማቸውንና የሚገኙበትን ገፅ ጭምር በግልፅ መቀመጥ አለበት፡፡

V. ሙያ ነክ ቃላትን ወይም ሃረጎችን መግለጽ(Putting key & phrases)

ጥናቱ በሚካሄድበት ርዕስ ላይ የሚያጋጥሙት ሙያ ነክ ቃላትን ወይም ሀረጎችን በጥናቱ ውስጥ እንደተሰጣቸው አተረጓጎም ወይም አነባበብ መግለፅ ይኖርባቸዋል፡፡በተጨማሪም ምህፃረ ቃሎችን ከተጠቀምን ምህፃረ ቃሎቹንና

ትርጉማቸውን ማስቀመጥ ያስፈልጋል፡፡

VI. መግቢያ(Introduction)

መግቢያ ለአንባቢዎች የጥናቱን መነሻ መረጃ የሚሰጥ ነው፡፡ የመግቢያ ፅሁፍ ስፋት እንደ ጥናቱ ቢወሰንም ከአንድ ገፅ በላይ መብለጥ ለበትም፡፡

መግቢያ፡-LOGO ኮምቦልቻጨርቃጨርቅ አክሲዮን ማህበር

KOMBOLCHA TEXTILE SHARE COMPANY

Form No.:

OP/KTSC/044

ማንዋል Issue No .

1Page No.:

Page 18 of 47

የአንባቢውን ፍላጎት የሚያነሳ

የጥናቱን ወሰንና አቅጣጫ የሚያመላክት

ለአንባቢው ጥናቱን እንዴት እንደሚሰራ የሚያሳይ

የጥናቱን ጭብጥ የሚያሳይ

የጥናቱን የትኩረት አቅጣጫና ማጠቃለያ የሚያመላክት መሆን ይኖርበታል፡፡

VII. የጥናቱ ዓላማ(Objective) አጥኚው ሊያጠናው የፈለገውን የጥናት ርዕሰ ጉዳይ ከመረጠና ከዚያም በኃላ እስከ አሁን ስለችግሮቹ ያሉን መረጃዎች ካነበበ በኃላ የጥናት አላማ መዘጋጀት ይኖርበታል፡፡ የጥናቱ ዓላማ በግልፅ ከተቀመጠ በኃላ

ጥናቱ መልስ የሚያስገኝላቸው አበይት ወይም ቁልፍ ጥያቄዎች ወይም መላምቶችን ማንሳት ተገቢ ነው፡፡

Page 20: 3  Web viewየምርምርና ስርፀት . አሰራር መመሪያ ማንዋል. አዘጋጆች. ንጉሴ ሙላት. ከድር ዘዉዱ. መሰረት ገነቱ

የጥናቱም መሰረታዊ አላማ ለነዘህ ጥያቄዎች መልስ ማስገኘት ነው፡፡የጥናቱ ዓላማ ጥናቱ ሲጠናቀቅ የሚሰጠውን ጥቅም የሚያሳይ ነው፡፡

የጥናት ዓላማ፡- የመጨረሻ የጥናቱን ውጤት ማሳየት አለበት

በአጭርና ግልፅ በሆነ መንገድ የተገለፀ መሆን አለበት፡፡

VIII. የጥናቱ አስፈላጊነት( Significance of the study)፡-

በዚህ ርዕስ ውስጥ ጥናቱ የሚያስፈልግበትን ምክንያትና ጥናቱ ለድርጅቱ የሚያበረክተው አስተዋፅኦ ገላጭ በሆነ መልኩ መቀመጥ አለበት፡፡

በአንድ ርዕስ ላይ ጥናት የሚካሄደው አስፈላጊነት ሲኖረው እንጂ እንደዚሁ ለጥናትነቱ ብቻ አይደለም፡፡ ስለዚህ አንድ ጥናት ሲካሄድ ለአስፈላጊነቱ የሚከተሉትን ማየት ይገባል፡፡

ሀ. ጥናቱ ሊካሄድበት የታሰበው ርዕስ ጥናት ቢካሄድበት ስለችግሩ ወይም ሁኔታው የበለጠ ማወቅ ስለሚያስችል፡

ለ. በጥናት ርዕሱ ላይ ጥናት ቢካሄድ ለችግሩ መፍተሄ ለማግኘት ስለሚረዳ፤

ሐ. በጥናት ርዕሱ ላይ ጥናት ቢካሄድበት ሌሎች አጥኒዎች ወደፊት ይህን ፈለግ በመከተል በርዕሱ ላይ በስፋትና በጥልቀት ጥናት እንዲያደርጉ ሊያበረታታ ስለሚችል፤

መ. በዚህ ርዕስ ላይ ጥናት ቢካሄድ እስካሁን የነበረውን የእውቀት አድማስ ለማስፋት ስለሚያስችል፡፡

ስለዚህ አንድ የጥናት ርዕስ ከላይ ከተጠቀሱት ምክንያቶች መካከል በሁሉም እንኳን ባይሆን በጥቂቱ የተነሳዉ አስፈላጊነት ወይም ጥቅም እንዳለው መግለፅ ተገቢ ይሆናል፡፡

IX. የጥናቱን ወሰን ማመላከት(Scope of the study):-

የጥናቱ ወሰን ሲባል ጥናት የሚካሄድበት ርዕሰ ጉዳይ ስፋቱና ጥልቀቱ እስከ ምን ያህል እንደሚሆንና የጊዜውን ሁኔታ በግልፅ መለየት ማለት ነው፡፡

LOGO ኮምቦልቻጨርቃጨርቅ አክሲዮን ማህበርKOMBOLCHA TEXTILE SHARE COMPANY

Form No.:

OP/KTSC/044

ማንዋል Issue No .

1Page No.:

Page 19 of 47

በዚህ ክፍል ውስጥ፡-

በጥናቱ ምን ምን እንደሚሰራ

የጥናቱ ዳራ እስከምን ድረስ እንደሆነ እና ጥናቱ የሚጠናቀቅበትን ጊዜ ማመላከት ይኖርበታል፡፡

X. ጥናቱን ለማካሄድ ታሳቢ ችግሮች(Limitation)

አንድ ጥናት እንደተፈለገው በሚገባ ለማካሄድ ብዙውን ጊዜ አይቻልም፡፡ ምክንያቱም ለጥናቱ አስፈላጊ ሆነው የሚገኙ ነገሮች ሁሉ ሙሉ በሙሉ ላይሟሉ ስለሚችሉ ነው፡፡ አንዳንዶቹ ከቁጥጥር ውጭ

በመሆናቸው ሌሎች ደግሞ ሊገኙ ባለመቻላቸው ይሆናሉ፡፡ ስለሆነም አጥኚው እነዚህን ነገሮች ለይቶ በማወቅ ጥናትን እንደተፈለገውና በሚገባ ለማካሄድ ችግር ፈጥረውበት እንደሆነ መግለፅ ያስፈልጋል፡፡

XI. የጥናቱ ዘዴና አካሄድ(Methodology of the study):-

Page 21: 3  Web viewየምርምርና ስርፀት . አሰራር መመሪያ ማንዋል. አዘጋጆች. ንጉሴ ሙላት. ከድር ዘዉዱ. መሰረት ገነቱ

እንደ ርዕሱ ጠባይና እንደዚሁም እንደጥናቱ አላማ የጥናቱ ዘዴ የተለያየ ሊሆን ይችላል፡፡ ለምሳሌ ገላጭ ጥናት (Descriptive research) ፤ የፕሮጀክት ጥናት (project Research)፤

ታሪካዊ(Historical Research) ጥናት ወይም በሙከራ የታገዘ ጥናት(Experimental research) ሊሆን ይችላል፡፡

ከዚህ በኃላ መረጃ ለመሰብሰብ ሊጠቀሙበት የታሰበውን የመረጃ መሰብሰቢያ ዘዴ መጠቆም አለበት፡፡ የመረጃውም መሰብሰቢያ ዘዴ እንዴት አንደተዘጋጀ፤ ምን አይነት ሙከራ እንደተካሄደበት፤ እንዴት እንደተሰራጨ እና እንደተሰበሰበ መጥቀስ ያስፈልጋል፡፡ በሙከራ የታገዘ ጥናት (Experimental

Research) ከሆነ ምን አይነት የላብራቶሪ ወይም መስክ ሙከራ እንደተካሄደ ለምን ያህል ጊዜና በምን አይነት አኳኋን እነደተካሄደ በዝርዝር መግለጽ ይኖርበታል፡፡

በተጨማሪም ለጥናቱ ምን የናሙና አይነት እንደተመረጠ ለምንስ እንደተመረጠ መግለፅ ይኖርበታል፡፡ የናሙናውም ይዘትና አመራረጡም እንዴት እንደሆነና ለምንስ እንደዛ እንደሆነ ማብራራት ተገቢ ይሆናል፡፡

LOGO ኮምቦልቻጨርቃጨርቅ አክሲዮን ማህበርKOMBOLCHA TEXTILE SHARE COMPANY

Form No.:

OP/KTSC/044

ማንዋል Issue No .

1Page No.:

Page 20 of 47

እንዲሁም የተሰበሰበው መረጃ በምን አይነት ስታትስቲካዊ ስልት እንደሚተነተንና ለምንስ በምን አይነት ስልት እንደሚተነተን፤ በተጨማሪም የተመረጠውን ስልት አስተማማኝነት መገለፅ ያስፈልገዋል፡፡

XII. የተዛማጅ ፅሁፍ ምልከታ(Litrature Review)፡- የተዛማጅ ፅሁፍ ምልከታ በሚጠናዉ ጥናት ዙሪያ ከዚህ በፊት የተደረጉ ጥናቶችንና ስምምነቶችን የተቀመጡ ንድፈሃሳቦችን በጥልቀት የምናይበት ክፍል ነዉ፡፡

ይህ ክፍል ጥናት በሚደረግበት ርእስ ዉስጥ የሚገኙትን ቁልፍ ቃላት በመያዝ የተለያዩ የመረጃ መረቦችን በማሰስ በጥናቱ ዙሪያ የተጻፉ መረጃዎችን መፈለግና ዋቢ መረጃ ማዘጋጀት አለበት

በተቻለ መጠን አጥኝዉ ከተዛማጅ ጽሁፍ ፍሬ ነገሩን በማስታወሻ በሚያሠፍርበት ጊዜ በራሱ ቃላት /ቋንቋ/ ቢጠቀም ይመረጣል ፡፡ነገር ግን በአንድ ተዛማጅ ጽሁፍ ዉስጥ አጥኝዉ የሚያገኘዉ ፍሬ ነገር

አገላለጹ በጣም ማራኪ ከሆነበትና በራሱ ቃላት/ቋንቋ/ ቢያስቀምጠዉ ፍሬ ነገሩ ለዛዉን የሚጣ ከሁነ እንዳለ ወስዶ ሊጠቀምበት ይችላል ፡፡

የተዛማጅ ፅሁፍ ምልከታ የሚከተሉትን ነጥቦች ይመልሳል፡- በጥናቱ ርዕስ ዙሪያ ከአሁን በፊት የተሰራ ስራ ካለ፤ የነበሩት ቁልፍ ፅንሰ ሃሳብ ምን እንደሆነ፤ በርዕሱ

ዙሪያ ሙህራኖች የተስማሙበትን ንድፈ ሃሳብ ምን እንደሆነ፤ በየትኛው የርዕሱ ፅንሰ ሃሳብ ላይ ትኩረት

Page 22: 3  Web viewየምርምርና ስርፀት . አሰራር መመሪያ ማንዋል. አዘጋጆች. ንጉሴ ሙላት. ከድር ዘዉዱ. መሰረት ገነቱ

እንደተደረገ፤ ጥናቱ ሲካሄድ የተከተሉት ዘዴ ወይም ስልት ምን እንደሆነ፤ በተሰሩት ጥናቶች ልዮነቶች መኖራቸውንና አለመኖራቸውን በተጨማሪም የትኛው የተሻለ እንደሆነ፤ የቅርብ ጊዜ የተሻለ ጥናት

መኖሩን፤ አሁን እየተጠና ያለው ጥናት ከበፊተኞቹና አሁን ካሉ ሌሎች ጥናቶች የሚለየው ምን እንደሆነ መመለስ አለበት፡፡

በአጠቃላይ የተዛማጅ ፅሁፍ ምልከታ ስፋት በጥናቱ ርዕስና በአጥኝዎቹ የሚወሰን ቢሆንም የፅሁፉ ምዕራፍ አስከ 20 ገፅ ሊደርስ ይችላል፡፡ ነገርግን ለትንንሽ ስራዎች የተወሰኑ ገፆች ሊኖሩት ይችላል፡፡

XIII. የጥናት ውጤቶች አቀራረብ ትንተናና ትርጉም (Data analysis)

የተገኙ የጥናት ውጤቶች በአብዛኛው በሰንጠረዥ በተደገፈ ትንተና መቅረብ ይገባቸዋል፡፡ እያንዳዱ ሠንጠረዥ ርዕስ ሊኖረው ይገባል፡፡ በሠንጠረዡም ውስጥ የሚቀርቡት ግኝቶች በአኃዝ ከመቅረባቸውም በላይ ለአንባቢ ግልጽ በሆነ ሁኔታ መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ የጥናት ውጤቶች የሚቀርብበት በሠንጠረዥ ብቻ ሳይሆን በተለይ የዋና ግኝቶች መተንተንና መተረጎምም በጣም ተገቢ ይሆናል፡፡ አንድን ጥናት ጥናት የሚያሰኘው አጥኚው የሳይንስና

የሎጂክን ስልት በመከተል በግኝቶቹ ላይ የሚደረገው ትንታኔና ትርጉም እንጂ ጥሩ የሆኑ መረጃ በማቅረብ ብቻ አይደለም፡፡

LOGO ኮምቦልቻጨርቃጨርቅ አክሲዮን ማህበርKOMBOLCHA TEXTILE SHARE COMPANY

Form No.:

OP/KTSC/044

ማንዋል Issue No .

1Page No.:

Page 21 of 47

የአንድን ጥናት ደረጃ ከፍተኛነቱ ወይም ዝቅተኛነቱ የሚለካው በዚሁ ነው፡፡ስለሆነም የምርምርን ግኝቶች በጥንቃቄ ለመተንተንና ለመተርጎም የሚከተሉትን መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡

ሀ. በተቻለ መጠን አስተያየትን ከተጨባጭ ሁኔታ መለየትና አንዱን ከሌላው ጋር አለማጋጨት፤

ለ. የጥናቱን ወሰን አለመዘንጋትና ከጥናቱ ወሰን ዘሎ የሚሄድትንታኔ ወይም ትርጉም ውስጥ አለመግባቱ፤

ሐ. የተሳሳተ ትንታኔና ትርጉም አለመስጠት በተለይም በሎጂክ ላይ ያልተመሰረተ ወይም ከሎጅክ ጋር የሚቃረን ትንታኔ ወይም ትርጉም አለመስጠት እንዲሁም እስካሁን በሳይሳዊ ጥናት ከተደረሰባቸው ትክክለኛ ቲወሪዎችና ህጎች ጋር የሚቃረን ትንታኔና ትርጉም አለመስጠት፤

መ. የጥናቱን ግኝት ለመተንተን ለጥናት የማይሆን የስታትስቲክስ ስልቶች አለመጠቀም፤

ሠ. ከአጥኚው አስተሳሰብ ጋር የሚቃረን ግኝት ካለ ያንን አለማስቀረት ወይም ግኝቱ ከአጥኒው አስተሳሰብ ጋር እንዲጣጣም ለውጥ ያለማድረግ እንዲሁም ከዘመኑ የተሳሳተ አስተሳሰብ ጋር የሚቃረን ግኘት ካለ ያን

አለማስቀረት ወይም ግኝቱ ከዘመኑ አስተሳሰብ ጋር እንዲጣጣም በግኝቱ ላይ ለውጥ ያለማድረግ፡፡

XIV.ማጠቃለያ(Conclusion)

እንደሚታወቀው አንድ የጥናት ሥራ እንደሁኔታው ስፋትና ጥልቀት አለው ስለሆነም ጥናቱን ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው አንብቦ ለመረዳት ጊዜ የሚጠይቅ ጉዳይ ይሆናል፡፡ ብዙ አንባቢያን ባላቸዉ ጥቂት ጊዜ ውስጥ

የጥናቱን ፍሬ ነገር በቀላሉ እንዲረዱት አሳጥሮ ማቅረብ አስፈላጊ ነው፡፡ በተቻለ መጠን የጥናቱን አላማ ባጭሩ ማስቀመጥ እንዲሁም አበይት የሆኑትን ግኝቶች ባጭሩ ማስፈር ተገቢ ይሆናል፡፡ በዚህ ርዕስ የሚቀመጠዉ

ማጠቃለያ ሀሳብ አሁንን የሚገልፅ መሆን አለበት፡፡

XV. የመፍተሄ ሃሳብ(Recommendation)

Page 23: 3  Web viewየምርምርና ስርፀት . አሰራር መመሪያ ማንዋል. አዘጋጆች. ንጉሴ ሙላት. ከድር ዘዉዱ. መሰረት ገነቱ

የመፍተሄ ሃሳቦች ሊመነጩ የሚችሉት በመጀመሪያ ደረጃ የችግሩ መንሰኤዎች በጥናት በውል ከታወቁ በኃላ ነው፡፡የመፍተሄ ሀሳቦች በመጀመሪያ ሊቀርቡ የሚችሉት የችግሩን መንሰዔዎች በጥናት

ከተረዳው ከተመራማሪው ሊሆን ይችላል፡፡ ሆኖም ግን አጥኚዉ በመጠይቁ ውስጥ ምላሾቹን ስለችግሩ የመፍተሄ ሀሳብ እንዲሰጡ በማድረግ

LOGO ኮምቦልቻጨርቃጨርቅ አክሲዮን ማህበርKOMBOLCHA TEXTILE SHARE COMPANY

Form No.:

OP/KTSC/044

ማንዋል Issue No .

1Page No.:

Page 22 of 47

ከተጠቆሙት የመፍተሄ ሃሳቦች ሊጠቅሙ የሚችሉትን በመምረጥ በመፍትሄ ሃሳቦቹ ውሰጥ ሊያካትታቸው ይችላል፡፡

የመፍተሄ ሃሳቦች በሚሰጡበት ጊዜ ግንዛቤ የሚያስፈልገዉ የሚሰነዘሩት የሚፈትሄ ሃሳቦች ባለው ተጨባጭ ሁኔታ ተግባራዊ ሊሆን የሚችሉ መሆናቸውን ነው፡፡ ምክንያቱም በተግባር ሊተረጎሙ የማይችሉ የመፍተሄ ሃሳቦች ማቅረብ ዋጋ የለውም፡፡

XVI. አባሪ(Appendices):- ጥናቱ ለማካሄድ የተጠቀምናቸውን መረጃዎች ማለትም መጠይይቆች፤ የተለያዮ ፕሮግራሞች እና ሌሎች

ፎርማቶች ከጥናቱ ጋር ተያይዘው የሚቀርቡበት ነው፡፡

XVII. ማጣቀሻ(Reference) በዚህ ክፍል የጥናቱ እውነተኛነት ይመለከትበታል፤ የተቀምናቸው የመረጃ ምንጫቸው በማን እንደተፃፈ፤

መቼ እንደፃፈ የመረጃ መረቡ ስም በግልፅ መቀመጥ አለበት፡፡

Page 24: 3  Web viewየምርምርና ስርፀት . አሰራር መመሪያ ማንዋል. አዘጋጆች. ንጉሴ ሙላት. ከድር ዘዉዱ. መሰረት ገነቱ

LOGO ኮምቦልቻጨርቃጨርቅ አክሲዮን ማህበርKOMBOLCHA TEXTILE SHARE COMPANY

Form No.:

OP/KTSC/044

ማንዋል Issue No .

1Page No.:

Page 23 of 47

ክፍል ሁለት

ፕሮጀክት

Page 25: 3  Web viewየምርምርና ስርፀት . አሰራር መመሪያ ማንዋል. አዘጋጆች. ንጉሴ ሙላት. ከድር ዘዉዱ. መሰረት ገነቱ

LOGO ኮምቦልቻጨርቃጨርቅ አክሲዮን ማህበርKOMBOLCHA TEXTILE SHARE COMPANY

Form No.:

OP/KTSC/044

ማንዋል Issue No .

1Page No.:

Page 24 of 47

ምእራፍ 1

1. ፕሮጀክት እና ፅንሰ ሃሳቦቹ

1.1 ትርጉም

ፕሮጅክት ውስን የሆነ ውስን በሆነ ጊዜና ቦታኢንቨስት በማድረግ አንድ አላማን የምታስፈፅምበት ድርጊት ነው፡፡

በሀብት አጠቃቀም/ በጀት/ ደረጃም በውስን ተመድቦለት የሚፈፀም ተግባር ነው፡፡ በሌላ መንገድ ፕሮግራም የተለያዮ ፕሮጀክቶችን ለመደገፍ የተቀመረ ሰፊ የፕሮጀክቶች ስብስብ ነው፡፡ በጊዜ፤ በበጀትና በውጤት ደረጃም

በጣም ሰፊ የሚሆን ነው፡፡

1.2.( የፕሮጀክት ዕቅድ ዝግጅት)Project planning

የፕሮጀክት ፅነሰ ሃሳብና አስፈላጊነት

በፅንሰ ሃሳብ ደረጃ ሳይንሳዊ የሆነ ዐቅድ አሰራር የሃብት ብክነትና ጉድለት በማስቀረት ቀልጣፋና ውጤታማ በሆነ መንገድ የተቀመጡ ግቦችንና ዓላማዎችን ከዳር ለማድረስ የሚያስችል ሂደት ነው፡፡

ፕሮጀክት ማለት ወደፊት ጥቅም ያስገኛል ብሎ በማሰብ የተወሰነ ሃብትን ስራ ላይ በማዋል ማንኛውም የኢንቨስትመንት እቅድ ነው፡፡ ዓላማውም ውስን ሆነውን እምቅ ሃብት ይበልጥ ጠቀሜታ ሊያገኝ የሚችል የልማት

እንቅስቃሴ ላይ በማዋል ከወጪው የበለጠ ወይም እኩል የሆነ ጥቅም ማስገኘት ነው፡፡

ፕሮጀክት መስራት ለምን አስፈለገ?/Why project is undertaken?/

ለዕድገትና ውጤታማነት

ውጤታማነት፤ በጥራት፤ በብዛት፤ ተደራሽነት እና ድንገተኛ ችግሮችን ለመቀነስ

ሃብትን በቁጥባ ለመጠቀም፤ ጊዜን በአግባቡ ለመጠቀም፤ ወጪን ለመቀነስና የሰው ሀይልን መጥኖ ለመጠቀም ይረዳል፡፡

የአገልግሎት ስርጭትን በእኩል ለማዳረስ

የአደጋ ተጋላጭነትን ለመቀነስ

Page 26: 3  Web viewየምርምርና ስርፀት . አሰራር መመሪያ ማንዋል. አዘጋጆች. ንጉሴ ሙላት. ከድር ዘዉዱ. መሰረት ገነቱ

ምዕራፍ ሁለት

2. የፕረሮጀክት ዑደት/Project cycle/

በፕሮጀክት ዑደት ተተንትነው ያለፉ ፕሮጀክቶች በተግባር ተፈፃሚ የመሆን እድላችው ከፍተኛ ከመሆኑ በላይ የታለመላቸውን ዓላማ በመምታት ለዕድገት የጎላ አስተዋፅኦ አላቸው፡፡

LOGO ኮምቦልቻጨርቃጨርቅ አክሲዮን ማህበርKOMBOLCHA TEXTILE SHARE COMPANY

Form No.:

OP/KTSC/044

ማንዋል Issue No .

1Page No.:

Page 25 of 47

የፕረሮጀክት ዑደት/Project cycle/ እንደሚከተሉት ናቸው

I. ፕሮጀክት ልየታ(project Identification)II. ፕሮጀክት ዝግጅት/ project preparation or formulation/III. ፕሮጀከት ምዘና(project appraisal & decesion)IV. ፕሮጀክት ትግበራ(project implementation)V. ክትትልና ግምገማ(Monitoring and Evaluation)

2.1. ፕሮጀክት ልየታ(project Identification)

የተለያዮ የፕሮጀክት ሃሳቦች በብዛት ስለሚመነጭ ለፕሮጀክቶች ምርጫ እንድናወጣ እንገደዳለን፡፡

የፕሮጀክቶች መረጣ በአብዘሃኛው በሦስት ነገሮች ላይ መሰረት ያደረገ ነው፡፡

ፍላጎትን መሰረት ያደርጋል/demand based/ ሲሆን ይህም የተጠቃሚውን ህዝብ ፍላጎት የሚያበረታታ የውጭ ገበያ እንዲሁም ከፍተኛ የጥሬ ዕቃ ፍላጎት ወዘተ በሚኖር ወቅት

የመሰረታዊ ሃብቶች መኖር መሰረት ያደረገ /resource based/ ሲሆን ፤ የጥሬ ዕቃ …መኖር፤ጥቅም ላይ ያልዋሉ የማሽን መለዋወጫ ዕቃና ኬሚካል፣

መሰረታዊ ፍላጎቶች ሁኔት /need based/ መሰረት ያደረገ ለምሳሌ፡- ደረጃዉን የጠበቀ የጥሬ …ጥጥ ፍላጎት፣

ፕሮጀክት መረጣ ሂደት

ሀ. የፕሮጀክት ዋነኛ ችግሮች ልየታ/problem identification/

አንድ ድርጅት በፕሮጀክት ልየታ ወቅት የመጀመሪያ ስራው ፕሮጀክት የሚሰራበትን የድርጅቱን ዋነኛ ችግር ማወቅ ይሆናል፡፡ ይህን ችግር ያገባኛል ባዮች/stakeholders/ ያካተተ ስለድርጅቱ ዋነኛ ችግር የሃሳብ ማሰባሰቢያ የውይይት መድረክ ሊያዘጋጅ ይገባል፡፡ በውይይቱ ወቅት የሚቀርቡት ችግሮች ብዙ ሊሆኑ ቢችሉም የችግሮችን

ስፋትና ጥልቀት በመረዳት በደረጃ አስቀምጦ ዋነኛ ችግሩን/core problem/ መለየት ይጠይቃል፡፡ ከዚህ ለመድረስ የችግሩን ዘርፈ ብዙ ቅርንጫፍ/problem tree/ ማስቀመጥ መተንተን ያስፈልጋል፡፡የችግሩ መኖር ያስከተለው ተፅዕኖ/Impact or effect/ በዝርዝር ማውጣትና ለዚህ ችግር መንሰኤ የሆኑ ምክንያቶችን

/cause/ መለየት ይኖርባቸዋል፡፡ የዚህ ችግር ተፅዕኖ ከምክንያቶቹ ጋር ያለው ግንኙነትና ተያያዥነት በመተንተን ማስረዳት ያስፈልጋል፡፡ ከዚህ ትንተና በመነሳት የፕሮጀክቱን ግብና ዓላማ ማስቀመጥ ይቻላል፡፡ችግሩ በድርጅቱ

ለምን እንደተፈጠረ፤ መቸ እንደተፈጠረ፤ በየትኛው የድርጅቱ ክፍል ላይ ችግሩ እንደሚያጠነጥን ማሳየትና ችግሩ ያስከተለውን ውጤት ማወቅ ተገቢ

Page 27: 3  Web viewየምርምርና ስርፀት . አሰራር መመሪያ ማንዋል. አዘጋጆች. ንጉሴ ሙላት. ከድር ዘዉዱ. መሰረት ገነቱ

LOGO ኮምቦልቻጨርቃጨርቅ አክሲዮን ማህበርKOMBOLCHA TEXTILE SHARE COMPANY

Form No.:

OP/KTSC/044

ማንዋል Issue No .

1Page No.:

Page 26 of 47

ይሆናል፡፡ የዚህን ችግር ዋነኛነትን አጉልተው የሚያሳዮ ሌሎች አሀዛዊ መረጃዎችን በማሰባሰብ ትክክለኛነቱን ማስረገጥ ያስፈልጋል፡፡ ስለዚህ አንድን ችግር ስናጠና የማን፤ ምን አይነት፤ የት፤ ለምንና መቸ የሚሉ ጥያቄዎችን የሚመልስና በዝርዝር የሚያስረዳ መሆን ይኖርበታል፡፡

ለ. የፕሮጀክቱን ግብና ዓላማ ማስቀመጥ

ግብ ሰፊ የሆነና አንድና ከአንድ በላይ የሆኑ ፕሮጀክቶች በመጨረሻ ሊደርሱ የታሰበበት በለውጥ ሂደት የሚመጣ ውጤት ነው፡፡ ዓላማ ከአስቀመጥነው ግብ የሚመነጭ በመጠን፤ በጥራት፤ በወጭና በጊዜ የሚለካ ከግብ የጠበበ የፕሮጀክቱን ችግር ለማቃለል የሚችል የአጭር ጊዜ ውጥን ነው፡፡

2.2 ፕሮጀክት ዝግጅት/ project preparation or formulation/

በፕሮጀክት ዝግጅት ወቅት የፕሮጀክት ሃሳቦች ከተሰበሰቡ በኃላ ወደ ፕሮጀክት ዝግጅት ተግባር የሚያልፉና ብቁ የሆኑ ሃሳቦችን ለመምረጥ በመጀመሪያ የድርጅቱን ሁኔታ፤ የድርጅቱን ሃብት እና የሰው ሃይል ግንዛቤ ውስጥ

በማስገባት ተግባራዊ ሊሆን የሚችለውን የመምረጥ ተግባር ነው፡፡

የፕሮጀክት ዝግጅት ከ 7-10% የፕሮጀክት አጠቃላይ ዋጋ ያወጣል ተብሎ ስለሚገመት በጥንቃቄ መስራት ያስፈልጋል፡፡ ስለሆነም በፕሮጀክት ዝግጅት ወቅት የቅድመ ዝርዝር ጥናትና የዝርዝር ጥናት እንደአስፈላጊነቱ

ማየትና ማጥናት ተገቢ ነው፡፡

2.2.1 ቅድመ ዝርዝር ጥናት/pre-feasiblity study/

ይህ ጥናት በቅድሚያ ከፍተኛ ወጭ በማውጣት ዝርዝር ጥናት አጥንቶ የማያዋጣ መሆኑን ከማረጋገጥ በአነስተኛ ወጭ የመጀመሪያ ጥናት በማካሄድ የፕሮጀክቱን ተስፋ ሰጭነት ለማረጋገጥ ይረዳል፡፡

2.2.2 የፕሮጀክት ዝርዝር/feasibility study/

በቅድመ ዝርዝር ጥናትና በዝርዝር ጥናት መካከል የሚካሄደው የጥናት ሂደት ተመሳሳይነት ያለው ሲሆን ልዮነቱ የሚከሰተው በትንተናው የስፋት ደረጃና በሚሰበሰበው መረጃ ብዛትና ጥራት ነው፡፡ በዚህ ጥናት እንደሌሎቹ

ጥናቶች ፕሮጀክቱ ተቀባይነት እንዲኖረው ወይም ውድቅ እንዲሆን ለመወሰን የሚያስችለውን ሃሳብ ለማግኘት እንዲቻል እስከ መጨረሻው ጥቃቅን ጉዳዮች ድረስ በዝርዝር የሚታይበት የፕሮጀክት ዑደት አካል ነው፡፡ በደንብ የተዘጋጀ የፊዚቢሊቲ ጥናት በመጀመሪያ የፕሮጀክት ጥናት የታዮ ጉዳዮችን ሁሉ በመመርመር እንደገና

በትክክለኛው መንገድ ያስተካክላል፡፡ የፕሮጀክቱ ግብና ዓላማ በትክክል ከፕሮጀክቱ ጋር ተያያዥነት ያላቸው መሆኑን ያረጋግጣል፡፡

LOGO ኮምቦልቻጨርቃጨርቅ አክሲዮን ማህበርKOMBOLCHA TEXTILE SHARE COMPANY

Form No.:

OP/KTSC/044

ማንዋል Issue No .

1Page No.:

Page 27 of 47

Page 28: 3  Web viewየምርምርና ስርፀት . አሰራር መመሪያ ማንዋል. አዘጋጆች. ንጉሴ ሙላት. ከድር ዘዉዱ. መሰረት ገነቱ

ፕሮጀክቱ ተፈፃሚ በሚሆንበት ወቅት ሊያስከትላቸው የሚችሉ ችግሮች ወይም አመቺ ሁኔታዎች በዚህ ውስጥ ይተነተናሉ፡፡ ለችግሮቹም መፍተሄ ሊሆኑ የሚችሉ አማራጮች ይቀመጣሉ ስለፕሮጀክት ስናስብ ግንዛቤ ውስጥ

ማስገባት ያለብን ሁሉም ፕሮጀክቶች አንድ አይነት የጥናት ወይም የአሰራር ዘዴ አይኖራቸውም፡፡ ስለሆነም በአንዱ ፕሮጀክት ላይ ሁሉም ነገር በዝርዝር ሲታይ በሌላው አላስፈላጊ ሆኖ የሚታለፍ የጥናት ዓይነት ሊኖር ይችላል፡፡

በዚህ ስር የሚተነተኑት የገበያ ጥናት ማካሄድ፤የፕሮጀክት ቴክኒካዊ ሃሳቦች ማጎልበት፤ ስለ ፕሮጀክቱ አመራርና ድርጅታዊ መዋቅር ሃሳብ ማቅረብ፤ ስለ አካባቢው ተፅዕኖ ማጥናት፤ ስለ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ሁኔታ ማጥናት፤ እንዲሁም የፕሮጀክቱን ወጪና የሚያስከኘውን ጥቅም መተንተን ይሆናል፡፡

ሀ. የፕሮጀክት አካባቢ ጥናት/Back ground information/

የዚህ ጥናት ዋና ዓላማ ፕሮጀክቱ ለድርጅቱና ለአካባቢዉ ለያስገኝ የሚችለዉን ጥቅምና የሚያስከትለዉን ተፅእኖ ለይቶ ማስቀመጥ ይሆናል፡፡ ፕሮጀክቱን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የሚመለከቱ ሁኔታዎች በሙሉ ማለትም ኢኮኖሚያዊ፤ ማህበራዊ፤ አስተዳደራዊ ፖለቲካዊና ጂኦግራፊያዊ ሁኔታዎችን መዳሰስ ያስፈልጋል፡፡

ለ. ገበያ ጥናት ማካሄድ/Market assesment/

የፕሮጀክቱ ምርት በሚቀርብበት የገበያ ሁኔታ በቀጠና እና ተጠቃሚ ተለይቶ መጠናት ይኖርበታል፡፡ ለፕሮጀክቱ ምርት በቂ ገበያ በሃገር ውስጥ ወይመ በውጭ አገር መኖሩ ወይም አለመኖሩ መረጋገጥና ምርት የሃገር ውስጥ ገበያን ፍላጎት በምን ያህል እንደሚያረካ መገምገም ያስፈልጋል፡፡ አስካሁን ድረስ ድርጅቱ ተመሳሳይ

ምርቶችን ከየት ሲያገኝ እንደነበር መብራራት ይኖርበታል፡፡ለምርት የተተመነው ዋጋ አሁን በገበያ ላይ ከሚሸጠው ወይም ከሚቀርቡት ተመሳሳይ ምርቶች ጋር እንደሚነፃፀር መግለፅ ያስፈልጋል፡፡ ስለሆነም

የተለያዮ አመታት የፍጆታ መረጃዎችን /consumption coeficcient/ በመጠቀም፤ ጥቅም ላይ የዋሉ የምርትና የግብዓት መረጃዎችን /input-out put model/ መጠቀም በወቅቱ አመች የሆነውን ዘዴ

በመምረጥ ሳይንሳዊ የሆነውን መንገድ ተንትኖ የገበያውን አጠቃላይ ሁኔታ መረዳት ያስፈልጋል፡፡

ይህን የትንበያ ጥናት ማካሄድ በፕሮጀክቱ አገልግሎት እድሜ ውስት ሊገኝ የሚችለውን የገበያ አዋጭነት ለማጤን ይረዳል፡፡ በመጪዎቹ አመታት ውስጥ ምርቱን በተመለከተ ሊኖር የሚችለውን የገበያ ፍላጎት አውቆ መጠኑን ለመተንበይና ለመወሰን ያስችለናል፡፡ ከጥናቱ በመነሳት የምርት ተጠቃሚ እንዲጨምር ምን መሰራት

እንደሚኖርበት ይጠቁመናል፡፡

LOGO ኮምቦልቻጨርቃጨርቅ አክሲዮን ማህበርKOMBOLCHA TEXTILE SHARE COMPANY

Form No.:

OP/KTSC/044

ማንዋል Issue No .

1Page No.:

Page 28 of 47

ሐ. ስለፕሮጀክቱ ቴክኒካዊ ሃሳቦች

ፕሮጀክቱ ሊያመርት ላቀዳቸው ምርቶች የቀረበው የአመራረት ዘዴ እንዴት እንደተመረጠ ሌሎች አማራጮች የአመራረት ዘዴዎች አብራርቶ በማስቀመጥ ተመራጭነቱን በግልፅ ማሳየት ያስፈልጋል፡፡

Page 29: 3  Web viewየምርምርና ስርፀት . አሰራር መመሪያ ማንዋል. አዘጋጆች. ንጉሴ ሙላት. ከድር ዘዉዱ. መሰረት ገነቱ

የቴክኖሎጂ አማራጮችን በማወዳደር ብቃት ያለውን ለመምረጥ ይቻል ዘንድ 1 ኛ/ አዲስ መሳሪያ መትከል ወይስ ያለውን ማሻሻል 2 ኛ/ ቴክኒዎሎጂው በአመዛኙ የሰው ሃይል ወይስ ካፒታል የሚጠቀም ስለመሆኑ 3 ኛ/ ጥቅም ላይ የሚውለው ቴክኒዎሎጂ የሚጠቀመው ጥሬ እቃ የሃገር ውስጥ ወይስ የውጪ 4 ኛ/ተመራጭ

ቴክኖሎጂ በምርምር ያለፈ መሆኑንና በተግባር የተፈተነ ስለመሆኑ ማረጋገጥ 5 ኛ/ የቀረበው ቴክኖሎጂ ዋጋና የሚሰጠው ጥቅም 6 ኛ/ ለሚሰራበት አካባቢ አየር ፀባይ ተስማሚ መሆኑን ማረጋገጥ 7 ኛ/ቴክኖሎጂውን ለመጠቀም የሚያስፈልገው የስልጠና ፍላጎትና በዚያው አቅም መጠገን ስለመቻሉ 8 ኛ/ ጊዜው

ያላለፈበት/obsolete/ ላለመሆኑ ከአማራጭ ቴክኖዎሎጂ ጋር በማወዳደር ተመራጭነቱን ማረጋገጥና፡፡ በተጨማሪም የቴክኒዎሎጂው የማምረት አቅም በቀን፤ በወርና በአመት ገምቶ አዋጭነቱን በመረጃ አስደግፎ

ማቅረብና ለወደፊት ያለውን የመስፋፋት ዕድል በማብራራት የአካባቢውን የገበያ ጥናት መሰረት በማድረግ ወደ ምርጫ መሄድ ይቻላል፡፡

መ. የፕሮጀክቱ ወጪና የሚያስገኘው ጥቅም

አንድ ፕሮጀክት ሊያካትታቸው የሚችላቸው ወጪዎች

ጠቅላላ የመዋዕለ ነዋይ ወጭ/ Invetment cost/ የቋሚ መዋለ ነዋይ/fixed cost/ የመተኪያ ወጨዎች /maintenance or repair cost/ / ለመኪና ለቢሮ ዕቃዎች/ የቅድመ ምርት ወጪዎች/pre operating cost/ ለስልጠና፤ ለማምረቻ መሳሪያ ሙከራ፤

ለጥናት

የስራ ማስኬጃ ወጭዎች/ ለጥሬ ዕቃ መለዋወጫ ክምችት፤ ለድንገተኛ ክፍያ ወዘተ

የማምረቻ ወጪዎች/production cost/ የዕለት ተዕለት ወጪዎች / ለጥሬ ዕዋ መግዣ፤ ለሰራተኛ ደመወዝ፤ ለመብራትና ውሃ፤

ለጽህፈት መሳሪያ ወዘተ

የእልቀት ወጪዎች /Depreciation cost/ የህንፃ፤ የማምረቻ መሳሪያ፤ የመኪና ወዘተ

የወለድ የታክስ ክፍያ ወጪዎች ሌሎችንም ጨምሮ በወጪ ደረጃ ፕሮጀክቱ አዋጪ መሆኑን መመርመር ያስፈልገዋል፡፡

LOGO ኮምቦልቻጨርቃጨርቅ አክሲዮን ማህበርKOMBOLCHA TEXTILE SHARE COMPANY

Form No.:

OP/KTSC/044

ማንዋል Issue No .

1Page No.:

Page 29 of 47

እንደዚሁም አንድ ፕሮጀክት ሊያስገኝ ከሚችላቸው በርካታ ጥቅሞች ቢኖሩም ለአብነት ያህል ትርፋማነት፤ የስራ ዕድል መፍጠር፤ የውጭ ምንዛሬ ማዳን ወይም ማስገኘት፤ የህዝቡን መሰረታዊ ፍላጎት ማርካት ወዘተ፡፡ ስለዚህ

ፕሮጀክቱ እንዲቀጥል ከተፈለገ ስለእያንዳዱ የፕሮጀክት አካሎች ስለሚያስከትሉት ወጪም ሆነ ገቢ ሳይንሳዊ በሆነ ዘዴ ተሰልተው አዋጭነታቸው ሊታይ ይገባል፡፡

ሠ. ስለ ፕሮጀክቱ አደረጃጀት ምርጫ

ስለዚህ ዓላማና ግብ ያለው የተቆጠረ ተግባራትን ያስቀመጠና የክትትልና ቁጥጥር ሥልት በማውጣት ፕሮጀክቱን መምራት የሚችል አወቃቀር ስልት መከተል ያስፈልጋል፡፡

Page 30: 3  Web viewየምርምርና ስርፀት . አሰራር መመሪያ ማንዋል. አዘጋጆች. ንጉሴ ሙላት. ከድር ዘዉዱ. መሰረት ገነቱ

አንድን ፕሮጀክት በማዋቀር ደረጃ በአብዘሃኛው ሁለት አማራጮች ሊኖሩት ይችላል፡፡ ፕሮጀክቱ በድርጅቱ /functional organization/ ውሰጥ እንዲመራ ማድረግና ስራዎቹን ማስፈፀም ወይም እራሱን ችሎ አዲስ በሚቋቋም/pur project organization/ የፕሮጀክት መዋቅርና አመራር እንዲተዳደር ማድረግ ይቻላል፡፡

በአንድ ፕሮጀክት ውስጥ ሊኖሩ የሚችሉትን የስራ መደብ

የሚከናወነው ተግባር ለይቶ ማስቀመጥና እያንዳዱ ክፍል ከሌላው ጋር ሊኖረው ስለሚችል ቅንጅት ትርጉም በሚሰጥ መልክ ተብራርቶ ሊቀመጥ ይገባል፡፡

ረ. ሥነ አካባቢያዊ ጥናት/Environmental feasibility/

በፕሮጀክት አፈፃፀም ወቅት በአካባቢ የሚከሰቱ በጎና በጎ ያልሆኑ ሁኔታዎች ስለሚኖሩ አንድ ፕሮጀክት ወደ ተግባር ከመለወጡ በፊት በቅድሚያ በአካባቢ የሚፈጠረውን ተፅዕኖ እንድናጠና እንገደዳለን፡፡

አንድ ፕሮጀክት ጥሬ ዕቃን በመጠቀምም ሆነ ተረፈ ምርት በማስወጣት በኩል አካባቢን መልሶ የሚጎዳ እንዳይሆን ጉዳቱን ለመቀነስና ለማጥፋት የሚቻልበት ሁኔታ ማመቻቸት ተገቢ ይሆናል፡፡

ጉዳቱ የማይካካስ ወይም የማይቀረፍ ሆኖ በትውልድ ላይ መጥፎ ሁኔታ የሚፈጥር ወይም የሚያስከትል ከሆነ አማራጭ የፕሮጀክት ሃሳቦችን እስከማየት መሄድ ይኖርብናል፡፡ በፕሮጀክቱ ሂደትና ውጤት በበጉ ሁኔታ የሚታይ

ከሆነም ጠቀሜታውን በሚገባ ማብራራትና ማሳወቅ ያስፈልጋል፡፡

ቀ. ማህበራዊና ፖለቲካዊ ጥናት /Social & political study/

LOGO ኮምቦልቻጨርቃጨርቅ አክሲዮን ማህበርKOMBOLCHA TEXTILE SHARE COMPANY

Form No.:

OP/KTSC/044

ማንዋል Issue No .

1Page No.:

Page 30 of 47

የዚህ ጥናት የመጀመሪያ ሥራ በህብረተሰቡ ማህበራዊ ሂደት ላይ ያተኮረ መሰረታዊ መረጃ በማሰባሰብና ሰፊ ጥናት ማካሄድ ነው፡፡ ስለሆነም በዚህ ጥናት 4 ጉዳዮችን መመለስ መቻል አለብም፤

ይህ ፕሮጀክት በተግባር ሲፈፀም የሚያስከትለው ማህበራዊ ተፅዕኖ/Impact/ ምን ሊሆን ይችላል? ይህ ፕሮጀክት በተግባር ሲፈፀም የሚያስከትለው ፖለቲካዊ ተፅዕኖ/Impact/ ምን ሊሆን ይችላል? ለፕሮጀክቱ ግብ መሳካት ወይም አለመሳካት አስተዋፅኦ የሚያደርጉ ማህበራዊ ጉዳዮች አሉን? ለፕሮጀክቱ ግብ መሳካት ወይም አለመሳካት አስተዋፅኦ የሚያደርጉ ፖለቲካዊ ጉዳዮች አሉን? ብሎ

መጠየቅና አሉታዊና አወንታዊ ተፅዕኖችን ማወቅ ያስፈልጋል፡፡

መእራፍ ሁለት

2.3. ፕሮጀከት ምዘና / የፕሮጀክት ብቃት ግምገማ/ (project appraisal)

ምዘና በአመዛኙ አስፈላጊ ሁኖ የሚገኘው በባለንብረትነት ያስተዳድራል የተባለው አካል ወይም ለፕሮጀክቱ መመስረት ድጋፍ የሚሆነውን አብዘሃኘውን የገንዘብ መጠን የሚያቀርቡ አካሎች ነው፡፡ የፕሮጀክት

Page 31: 3  Web viewየምርምርና ስርፀት . አሰራር መመሪያ ማንዋል. አዘጋጆች. ንጉሴ ሙላት. ከድር ዘዉዱ. መሰረት ገነቱ

ምዘና/Appraisal/ ማለት ተዘጋጅቶ የቀረበውን ፕሮጀክት ዝርዝር ሁኔታ በመመርመር በተግባር ሊተረጎም የሚችል መሆኑን አስፈላጊውን መመዘኛ ማሟላቱን ማረጋገጥና ለቀጣይ ተግባር ማሳለፍ ነው፡፡ ይህም ሲባል

የፕሮጀክት ዝግጅት ሰፊ ጥናት ከተደረገበት በኋላ በአቅራቢው አካል በሰነድ ተዘጋጅቶ ለውሳኔ ሰጭ ክፍል ይቀርባል፡፡

የፕሮጀክቱ ሰነድ የቀረበለትም አካልም የፕሮጀክት ብቃት ግምገማ/Appraisal/ በሚያካሂድበት ወቅት ግምተ ውሥጥ ሊያስገባ ከሚገቡ ጉዳዮች መካከል ዋነኞቹ የሚከተሉት ናው፡፡

የፕሮጀክቱ ይዘት ከአገሪቱ አጠቃላይ የልማት አቅጣጫ ጋር የሚጣጣምና የዘርፉ ፖሊሶዎችንና መመሪያዎችን ያገናዘበ መሆኑን;

ተዘጋጅቶ የቀረበው ፕሮጀክት ለድርጅቱ አስፈላጊ መሆኑን

ፕሮጀክቱ በዝቅተኛ ወጭ አንገብጋቢ የድርጅቱን ችግሮች ለመፍታት ሌሎች አማራጮችን ማካተቱ፤

ፕሮጀክቱ የድርጅቱን ሃብት ጥቅም ላይ የማዋል ችሎታው

የፕሮጀክቱ ስፋትና መጠን ለማስተዳደር አመችነት ያለውና ከማስተዳደር አቅም ጋር መጣጣሙ

ፕሮጀክቱ በአካባቢ ስለሚኖረው ተፅዕኖ

LOGO ኮምቦልቻጨርቃጨርቅ አክሲዮን ማህበርKOMBOLCHA TEXTILE SHARE COMPANY

Form No.:

OP/KTSC/044

ማንዋል Issue No .

1Page No.:

Page 31 of 47

የፕሮጀክቱ ወጭ በትክክል መታወቁንና ለድርጅቱ የሚያስገኘው ጥቅም ከወጭ አንፃር ሲመዘን የበለጠ መሆኑን

ፕሮጀክቱ በጊዜ የመጣና ወቅታዊ መሆኑን የመሳሰሉት ናቸው፡፡

በፕሮጀክት ብቃት ግምገማ/Appraisal/ ወቅት ሌላው ትኩረት ሊሰጠው የሚገባው ጉዳይ የፋይናንስ ግምገማ ነው፡፡ በዚህ ወቅት መታየት የሚገባቸው ጉዳዮች

ፕሮጀክቱን ወደ ተግባር ለማሸጋገር በጥናቱ የተጠቀሰው የገንዘብ መጠን መኖሩን ማረጋገጥ

የፋይናንስ ምንጩን በግልፅ ማመላከቱን ነው

ፕሮጀክቱ ተጠናቆ መደበኛ አገልግሎቱነ ሲጀምር በመደበኛ በጀት ላይ ሊኖረው የሚችለው ተፅዕኖ

በተጨማሪም የፕሮጀክት ምዘና በሚካሄድበት ወቅት ተዘጋጅቶ የቀረበው ፕሮጀክት በተለያዮ ሌሎች መስፈርቶች ማለትም

1. ቴክኒካዊ ሁኔታው/Technical aspect/2. የገበያ ሁኔታ/Commercial aspect/3. የአስተዳደር ድርጅታዊ ሁኔታዎች/Managerial& organizational aspect/ ሊተነተኑ ይገባል፡፡

በፕሮጀክት ቴክኒካዊ ሁኔታ የተለያዮ አማራጮችን ማለትም የፕሮጀክቱ መጠን፤ የስራ ቦታ ተስማሚነት፤ የመተግበሪያ ጊዜ እንዲሁም የቴክኖሎጂ ጥንቅር በመውሰድ የተመረጠው ፕሮጀክት ብቁ መሆኑን

ማየትም ተገቢ ነው፡፡

Page 32: 3  Web viewየምርምርና ስርፀት . አሰራር መመሪያ ማንዋል. አዘጋጆች. ንጉሴ ሙላት. ከድር ዘዉዱ. መሰረት ገነቱ

2.4. የፕሮጀክት ትግበራ/Implementation/

የፕሮጀክት ተፈፃሚነት ደረጃ ተብሎ የሚታወቀው ክፍል ከፕሮጀክቱ የግምባታ ስራ ጀምሮ ፕሮጀክቱ በታለመለት መሰረት ሙሉ በሙሉ የምርት ሂደት ወይም አገልግሎት የማቅረብ ደረጃ መድረስ እስከተቻለበት ድረስ ያለውን

የሚያጠቃልል ነው፡፡

የፕሮጀክት አፈፃፀም ደረጃ ላይ

የፕሮጀክት አፈፃፀም ዲዛይንና የስራ ዝርዝር ግምት

የጨረታ ዶክመንቶች ማዘጋጀት

ለፕሮጀክቱ የሚያስፈልጉ ማተሪያሎች ማዘጋጀት

ለፕሮጀክቱ አስፈላጊ የሆኑ ስምምነቶችናና ኮንትራቶችን መፈራረም

ለፕሮጀክቱ አስፈላጊ የሆኑ ሠራተኞችን መቅጠር ወዘተ የሚከናወኑበት ደረጃ ነው፡፡

አንድ ፕሮጀክት ተግባራዊ ለማድረግ ከታለመለት ግብ ለመድረስ እንዲቻል ዝርዝር የስራ መርሃ ግብር/action plan/ ሊነደፍ ይገባል፡፡ የፕሮጀክቱ የስራ መርሃ ግብር/action plan/

LOGO ኮምቦልቻጨርቃጨርቅ አክሲዮን ማህበርKOMBOLCHA TEXTILE SHARE COMPANY

Form No.:

OP/KTSC/044

ማንዋል Issue No .

1Page No.:

Page 32 of 47

የሚከናወነውን ሥራ ዓይነት፤ አስፈፃሚው አካል፤ ስራው የሚጠይቀው ጊዜ፤ ለስራው የሚያስፈልግ ወጭ፤ ስራው የሚካሄድበትን ቦታና ጊዜ ወዘተ ሊያካትት ይችላል፡፡ ለምሳሌ፤

ተቁ

የስራ ዝርዝር

መለኪያ

ፈፃሚውአካል

አመታዊእቅድ

የሚፈፀምበት ጊዜ(በወር) ጠቅላላ በጀት

የሚያስፈልግ ወጭ(በ 0000)

መ ጥ ህ ታ ጥ የ መ ሚ ግ ሰ መ ጥ ህ ታ ጥ የ መ ሚ ግ ሰ1 ጥሬ ዕቃ

አቅርቦት-

2 - -3 - -4 - -

የስራ መርሃ ግብር የልማትና የአገልግሎት ፕሮጀክቶች ወይም ፕሮግራሞች መቼ? በማን? የት? እንዴት? እንደሚሰሩ የሚጠቁም የስራ መመሪያ ሲሆን በአፈፃፀም ወቅትም ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮችን የሚዳስስና

የተለያዮ አማራጭ የአፈፃፀም፤ የክትትልና ግምገማ ስልተችን የሚያካትት ነው፡፡

2.5. ክትትልና ግምገማ(Monitoring and Evaluation)

አሳታፊ ክትትልና ግምገማ የፕሮጀክቱን ተጠቃሚዎችና ሌሎች ተሳታፊዎች(stakeholders) ባሳተፈ መልኩ አንድን ፕሮጀክት ወይም ፕሮግራም ውቴታማነትና ተፅዕኖ ለመለካት የሚያስችል መረጃ የመሰብሰብና የመተንተን

ሂደት ነው፡፡

Page 33: 3  Web viewየምርምርና ስርፀት . አሰራር መመሪያ ማንዋል. አዘጋጆች. ንጉሴ ሙላት. ከድር ዘዉዱ. መሰረት ገነቱ

ክትትልና ግምገማ የተሳሰሩ ሃሳቦች ቢሆንም የየራሳቸው ስልትና የትኩረት ነጥብ አላቸው፡፡ ክትትል/monitoring/ ተጨማሪ ውድቀት ሳይከተል ችግሮችን በወቅቱ ለማመልከት እና ለማስተካከል

የሚያስችል መሳሪያ ነው፡፡ በሌላ መልኩ ግምገማ/Evaluation/ አሁን እውን የሆነው ፕሮጀክት ቀደም ሲል በዝርዝር ጥናትና በሃሳብ ደረጃ በነበረበት ወቅት ታልሞለት ነበረውን ዓላማና ግብ አሳክቷል ወይስ አላሳካም

የሚል ነው፡፡ ይህም በአንድ ፕሮጀክት ተግባራዊ ሂደት(process) ፤ ውጤታማነትና አስተዋፅኦ ስልታዊ/systematic/ በሆነ አቀራረብ በተወሰነ ጊዜ ቆይታ የሚታይበት መንገድ ነው፡፡

ግምገማ/Evaluation/ አንድ ፕሮጀክት ግምገማው ዓላማ በሂደት ላይ እያለ ወይም ከተጠናቀቀ በኃላ ሊሄድ የሚችል ሲሆን ትኩረት የሚሰጠው ለፕሮጀክት ውጤት/ result or output/ ፤ እሴት /value/ እና ላስገኘው ተጨባጭ ለውጥ/Impact/ ነው፡፡

LOGO ኮምቦልቻጨርቃጨርቅ አክሲዮን ማህበርKOMBOLCHA TEXTILE SHARE COMPANY

Form No.:

OP/KTSC/044

ማንዋል Issue No .

1Page No.:

Page 33 of 47

አሳታፊ የግምገማ ዘዴ ለልማት ፕሮጀክቶች ዉጤታማነት ዋነኛ መሳሪያ መሆኑን እዉቅና በማግኘቱ በአሁኑ መቅት በስፋት እየተሰራበት ይገኛል፡፡ በፕሮጀክት ክትትል ግምገማና ሪፖርት ዝግጅት ወቅት ተጠቃሚው ክፍሎችና ሌሎች ተሳታፊ አካላት ሚና እንዲኖራቸው ማድረግ ለፕሮጀክቶች ስኬትና ዘላቄታውነት እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡

ሀ. የክትትልና ግምገማ ዓላማ

የአንድን ፕሮጀክት ዓላማ፤ ግብና ስትራቴጂን ለማመልከት፤

የፕሮጅትቱን ተግባራት ለመረዳት ለመጠቀምና በሁኔታዎች ውሳኔ ለመስጠት፤

ስራዎች በወጣላቸው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት እየተካሄዱ መሆኑን ማረጋገጥ

የስራዎችን የክንውን ደረጃ ለማወቅ

የፕሮጀክት ተሳታፊዎችን ለማንቀሳቀስ፤ ትጋትና የሃላፊነት ስሜት/commitment/ ለማሳደር እና የቡድን ስራን በማበረታታት አቅም ለመገንባት

ግልፀኝነት/Transparency/ እና ተጠያቂነት /accountability/ ለማጎልበት ይረዳል

የጥራት ቁጥጥርና አስተዳደርን ለማረጋገጥ /Ensure quality management/ የስራ አፈፃፀም ለመተንበይ

ለለውጥና መሻሻል የሚረዱ ተሞክሮዎችን ለማግኘት

የፕሮጀክቱ ተጠቃሚ አካል ጠቃሚ መሆኑን ለማረጋገጥ

የፕሮጀክቱ ምርት ወይም ዘላቂነት ለመዳሰስ

ለ. የክትትልና ግምገማ ውጤት

የክትትል ግምገማ ሪፖርት አዘጋጅቶ ጉዳዮ እንዲታወቅ ማድረግ

የፕሮጀክት አፈፃፀም ማሻሻል

አዲስ የፕሮጀክት ሃሳብ ማፍለቅ፤ ፖሊሲን በአዲስ ሃሳብ ማዳበር

በፕሮጀክት ስራዎች የምክር አገልግሎት ለመስጠት ይረዳል

ሐ. የክትትልና ግምገማ ዓይነቶች

Page 34: 3  Web viewየምርምርና ስርፀት . አሰራር መመሪያ ማንዋል. አዘጋጆች. ንጉሴ ሙላት. ከድር ዘዉዱ. መሰረት ገነቱ

I. የስራ ክንውን ክትትል/Activity or physical progress monitoring/ የሚመለከት ሲሆን ይህም የስራውን መቀላጠፍና መዘግየት ለማወቅና የማስተካከያ እርምጃዎችን ለመጠቆም ያግዛል፡፡

II. የፋይናንስ ስራ ክትትል/financial progress monitoring/ ይህ የክትትል ዓይነት የሚያተኩረው በወጭና፤ የተከናወነ የፊዚካል ስራ መጠን ላይ ሲሆን ከእቅድ አንፃር የተሰራውን ስራ ርቀትና መወሰድ

የሚገባቸውን እርምጃዎች ያመላክታል፡፡

III. ልዮ የማሻሻያ ጥናት /special diagnostic study/ የአንድን ፕሮጀክት የአፃፀም ደረጃ ለይቶ የሚያሳይና የሚተነትን ሲሆን የማሻሻያ ሃሳቦችን የማመንጨት ተልዕኮ አለው፡፡

LOGO ኮምቦልቻጨርቃጨርቅ አክሲዮን ማህበርKOMBOLCHA TEXTILE SHARE COMPANY

Form No.:

OP/KTSC/044

ማንዋል Issue No .

1Page No.:

Page 34 of 47

IV. የተጠቃሚዎች ተሳትፎና ግንኙነት ክትትል/beneficiary participation & contact Monitoring/ የተጠቃሚው ክፍል ተሳትፎ ደረጃ የሚጠበቀውን ያክል መሆኑን ለማረጋገጥና የተሻለ

ተሳትፎ እንዲኖር እርምጃ ለመውሰድ የሚረዳ ክትትል ዓይነት ሲሆን ይህም በቃል ጥያቄና በሌሎች ዘዴዎች የተጠቃሚዎች ናሙና ወስዶ የሚጠና የክትትል አይነት ነው፡፡

መ. የግምገማ አይነቶች

I. የጅማሮ ግምገማ /start- up evaluation or Ex-ante evaluation/ በፕሮጀክቱ መነሻ ወቅት የሚደረግ የመረጃ ማሰባሰብ ስራን ይመለከታለ፡፡

II. ሒደታዊ ግምገማ /Ongoing evaluation or formative progress evaluation/ የዋና ዋና ውሳኔ ሰጪ አካላት የመረጃ ፍላጎት ላይ ያተኩራል፡፡ ምሳሌ የፕሮጀክቱን እድገት ያጠናል፤ በእቅድ ላይ የተደረገ ማሻሻያ ወይም ለውጥን ያመለክታል፤

III. የአጋማሽ ዘመን ግምገማ/Mid term evaluation/ ይህ ግምገማ ዓይነት የፕሮጀክቱን የመካከለኛ ዕድሜ ውጤት ለመፈተሽ የሚረዳ ነው፡፡

IV. የማጠናቀቂያ ግምገማ/summative evaluation or Terminal, end, Impact evaluation/ ይህ የግምገማ አይነት በፕሮጀክቱ መጠናቀቂያ ወቅት የሚካሄድ ሲሆን የፕሮጀክቱን

አጠቃላይ ውጤትና አስተዋፅኦ ለማመልከት ያስችላል፡፡ የፕሮጀክት የማጠናቀቂያ ግምገማ አጭር ዕድሜ ላላቸው

V. ፕሮጀክቶች ከተጠናቀቁ በኃላ የሚካሄድ ግምገማ /Ex-post evaluation/ ይህ ግምገማ ዓይነት የሚከናወነው ፕሮጀክት ከተጠናቀቁ ጥቂት አመታት/5-10 ዓመት/ ቆይታ በኃላ በተለይም የፕሮጀክቱ

ውጤት / አስተዋፅኦ ሙሉ በሙሉ በተጠቃሚዎች ላይ ይታያል ተብሎ የሚጠበቅበት ወቅት ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ይህ ግምገማ ዓይነት አጠቃላይ ውጤቶችን በመዳሰስ ለወደፊት ፕሮጀክቶች ግብዓት

የሚሆን ሃሳብ ለማመንጨት ይረዳል፡፡

የግምገማ ዲዛይኑም የሚከተሉትን መሰረት በማድረግ የሚዘጋጅ ሊሆን ይገባል፡፡

የፕሮጀክቱ አላማ ትክክለኛነት

የፕሮጀክቱ ቀጣይነትና ጠቀሜታ

የፕሮጀክት አፈጻጸሙ ዉጤታማነት

የፕሮጀክቱን አላማ ለማሳካት የሚረዱ አማራጮች አይነት

Page 35: 3  Web viewየምርምርና ስርፀት . አሰራር መመሪያ ማንዋል. አዘጋጆች. ንጉሴ ሙላት. ከድር ዘዉዱ. መሰረት ገነቱ

ፕሪጀክቱ ለተጠቃሚዎቹ ያበረከተዉ አስተዋጽኦ ናቸዉ፡፡

LOGO ኮምቦልቻጨርቃጨርቅ አክሲዮን ማህበርKOMBOLCHA TEXTILE SHARE COMPANY

Form No.:

OP/KTSC/044

ማንዋል Issue No .

1Page No.:

Page 35 of 47

ሰንጠረዥ 1. የክትትልና ግምገማ ተያያዥነት፤

ከትትል/monitoring/ ግምገማ /evaluation/ በፕሮጀክት አፈጻጸም ላይ ያተኩራል በፖሊሲ ጉዳዮች ላይ ያተኩራል

ለዉጤት መንገድ ይጠርጋል ዉጤትን ያብራራል /ይገልጻል/ የመካከለኛ ወቅት ዉጤቶችን ይዳስሳል በአፈጻጸም የታዩ ጠቃሚ

ጉዳዮችን፤ጥራት፤ስጋትና ለወደፊትየሚታዩ ሁኔታዎችን ይዳስሳል

በየደረጃዉ የተገኙ ዉጤቶች ላይ ያተኩራል ለመጨረሻ ዉጤት ትኩረት ይሰጣል ለፕሮጀክት ተግባራዊነትና መሻሻል ወሳኝ ነዉ የልማት ስትራቴጅዉን ለማዉጣት ወሳኝ ነዉ

ዝርዝር መረጃን ሊጠቀም ይችላል /disagrigate/

የተጠቃለለ መረጃ ሊያሥፈልግ ይችላል/agrigate/

ሠንጠረዥ 2 የክትትልና ግምገማ ልዩነት

መለያ ምክንያት ክትትል ግምገማትኩረት/focus/ የፕሮጀክቱን ግብአት ተግባርና ዉጤት ወይም

ምርት ለመወሰንና ሂደትን ለማሻሻል ያስከተለዉን ለዉጥ ወይም ያስገኘዉን

ለመወሰንዓላማ/objectiveor purpose/

የስራ ጊዜ ሰሌዳ በጀትን የስራ ቅደም ተከተልን ለማስተካከል የስራ ብቃትን ለማሻሻል

የስራ ጊዜ ሰሌዳ በጀትን የስራ ቅደም ተከተልን ለማስተካከል የስራ ብቃትን

ለማሻሻል የሚሰበሰበዉ መረጃ ዓይነት በቀዳሚነት የመጠን መረጃ /quantitave

data/ በቀዳሚነት የዓነት መረጃ /Qualitative

data/ የመረጃማሰባሰቢያ መሳሪያዎች ጉብኝት፤ በእይታ፤ ከሪፖርት እና በፈጣን ዳሰሳ እይታ፤ በሪፖርት፤ ረጅም የጽሁፍና የቃል

መጠይቆች፤ በጥናት እና በሰርቬይ የመረጃ ማሰባሰቢያ ወቅት ፕሮጀክቱ በሂደት ላይ እያለ በመደበኛና በፕሮግራም በዋናነትፕሮጀክቱከተጠናቀቀ በኃላ የመረጃ ማሰባሰብ ሂደት በየጊዜውና በመደበኛነት ወቅታዊ

ፈፃሚዎች የፕሮጀክቱ ሰራተኞች እና የፕሮጀክቱ ተጠቃሚዎች፤ተሳታፊዎች/stakeholder/

የፕሮጀክቱ ሰራተኞችና ተሳታፊዎች በተጨማሪ ገለልተኛ ሰዎችንም ያካተተ

የመረጃ አጠቃቀም በፕሮጀክቱ የተግባር እንቅስቃሴ ወቅት ለሚሰጥ ውሳኔ ሌሎች ፕሮጀክቶችን ለማቀድ በተሞክሮነት ይጠቅማል፤

የሚነሱ ጥያቄዎች የትኛው ተሳካ የቱስ ሳይሳካ ቀረ? የቱ ወደ ኃላ ቀረ? የትኛው ነው መሻሻል? ያለበት እንዴት ሊሻሻል ይችላል?

ምን ውጤት ተገኘ? ማን ተጠቃሚ ሆነ? በምን ዓይነት ሀብት /resource/?ውጤት/Result/

Page 36: 3  Web viewየምርምርና ስርፀት . አሰራር መመሪያ ማንዋል. አዘጋጆች. ንጉሴ ሙላት. ከድር ዘዉዱ. መሰረት ገነቱ

LOGO ኮምቦልቻጨርቃጨርቅ አክሲዮን ማህበርKOMBOLCHA TEXTILE SHARE COMPANY

Form No.:

OP/KTSC/044

ማንዋል Issue No .

1Page No.:

Page 36 of 47

ክትትልና ግምገማ ምን ላይና መቼ ይካሄዳል? የሚገመገመው ምንድን ነው?

ፕሮጀክቱን ተገቢነት/ Relevance/ አዋጭነትና ወጤታማነት/feasibility & efficiency/ የመካከለኛ ወቅት ውጤቶች/Intermediate results/ እውን መሆናቸውን የዘላቄታዊነት ጉዳዮች የሚጠበቀው ጥቅምና ለውጥ እውን መሆኑን ለወደፊት የሚጠቅሙ ተሞክሮዎች መገኘታቸውን

ግምገማ መቼ ያስፈልጋል? በክትትል ወቅት ያልተጠበቁ አሉታዊ / በጎ ውጤቶች መኖራቸውን የሚያመለክቱ ወይም የሚጠቁሙ

ሁኔታዎች ሲታዮ የፕሮጀክቱ የበላይ አመራር ሰጪ አካል ለውሳኔ የሚረዱ መረጃዎችን በሚፈለግበት ወቅት በክትትል ወቅት መፈታት የሚገባቸው ቁልፍ ጥያቄዎችና ችግሮች መኖራቸው ሲጠቆም አስቀድሞ በተወሰዱ ዋና ዋና ታሳቢዎች ላይ ወሳኝ የሆኑ ለውጦች ሲከሰቱ ቁልፍ የሆኑ ተሞክሮዎችን ማውጣት አስፈላጊ በሚሆንበት ወቅት

ግምገማው ላይ የሚሳተፉ አካለት

በፕሮጀክት ተጠቃሚዎች/Beneficiaries/ የበላይ አመራር አካላት በፕሮጀክቱ አስፈፃሚ አካላት በፕሮጀክቱ ፈፃሚ ቡድን ወዘተ

ሠ. ክትትልና ግምገማ የሪፖርት ዝግጅትና አቀራረብ

ሪፖርት በክትትልና ግምገማ ስራ ስለተገኘው ውጤት ግንዛቤ ማግኛ መሳሪያ ነው፡፡

የሪፖረት ባህሪያት

ክትትልን ወይም አንድን ክንውን ይገልፃል፤ መደበኛ የሆነ አቀራረብ ያለውና የግንኙነት መስመርን/Format/ ተከትሎ የሚቀርብ ነው፡፡ ለአንድ ለተወሰነ ተጠቃሚ ወይም አዳማጭ/Audience/ ክፍል የሚቀርብ ነው፡፡ መረጃው እንዴት እንደተሰበሰበና ምን ያህል ጠቃሚ እንደሆነ ይጠቁማል፡ የተረሰበትን መደምደሚያ ሊያካትት ይችላል በተጨማሪም እንደ አስፈላጊነቱ የመፍተሄ ሃሳብ ሊያጠቃልል ይችላል

Page 37: 3  Web viewየምርምርና ስርፀት . አሰራር መመሪያ ማንዋል. አዘጋጆች. ንጉሴ ሙላት. ከድር ዘዉዱ. መሰረት ገነቱ

LOGO ኮምቦልቻጨርቃጨርቅ አክሲዮን ማህበርKOMBOLCHA TEXTILE SHARE COMPANY

Form No.:

OP/KTSC/044

ማንዋል Issue No .

1Page No.:

Page 37 of 47

የክትትልና ግምገማና ሪፖርት ሲዘጋጅ የሚከተሉትን ነጥቦች ከግምት ውስጥ ማስገባት አስፈላጊ ነው፡፡

የሪፖርቱን ዓላማ በሚገባ ማወቅ የሪፖርቱ ተጠቃሚዎች/ ሪፖረቱ የሚቀርብባቸው ክፍሎች/ እነማን እንደሆኑ መለየት፤ ተጠቃሚዎች ሊያውቁት የሚፈልጉትን ጉዳይ መረዳት የሪፖርቱን ማቅረቢያ ጊዜ መወሰን ተገቢ የሆነ መረጃ ጊዜ መወሰን፤ ተገቢ የሆነ መረጃ ማሰባሰቢያ መሳሪያ መቅረፅ ብቁ የሆኑ የሪፖርት ቅፆችን መጠቀም ለተጠቃሚዎቹ የሚየስፈልገውን መረጃ በጥንቃቄ መምረጥ፤ እንደ አስፈላነቱ መደምደሚያና የመፍተሄ ሃሳቦችን ማካተት፤ ሪፖርቱ ጥቅም ላይ ከመዋሉ በፊት ረቂቅን ለሚመለከታቸው ለአስተያየት ማቅረብ፤ ሪፖርቱ ሰፋ ያለ ከሆነ ሪፖርቱን እንደገና መፈተሽና የዋና ዋና ግኝቶች፤ መደምደሚያና የመፍተሄ ሃሳቦች

ማጠቃለያ ማዘጋጀት፤ በመጨረሻም ሪፖርቱን ለሚመለከታቸው ማሰራጨት

በክትትልና ግምገማ ስራዎች አካባቢ የሚታዮ ችግሮች፡- በበቂ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች አለመታገዝ፤ ስለክትትልና ግምገማ አስፈላጊነት በተወሰነ ደረጃም ቢሆን የግንዛቤ እጥረት መኖርና ለዚህ ስራ

የሚሰጠው ትኩረት በቂ አለመሆን፤ የተዘጋጀም ቢኖር ያለ በቂ ምክንያት ለምዘና የሚያስፈልጉ የፕሮጀክቱ ዓላማዎችና ግቦች በየጊዜው

መለዋወጥ፤ የክትትል ግምገማ ስራዎች ልዮ ልዮ ስልቶችን መሰረት አድርጉ ወደ ተግባር ለመግባት ወጥነት ያለው

አሰራሮችና አመለካከቶች (common formats, major indicator and variables) አለመኖር፤

የክትትልና ግምገማ ስራዎች ተከታታይነትና ወጥነት ባለው መንገድ አለማከናወንና በየትኛውም መንገድ የሚከናወነው ስራ በፕሮግራም ተይዞ እንዲከናወን ቅድመ ዝግጅት አለማድረግ፤

የክትትልና ግምገማ ስራዎች በደጋፊ መረጃዎች ላይ አለመመስረትና በውጤት መነሻነት ውሳኔ ሰጪው አካል ለፕሮጀክቱ ተገቢውን ድጋፍ በወቅቱ ማድረግ አለመቻል(poor feed back system)

በተለያየ ምክንያት የሚጠቀስ የአቅምና ልምድ ማነስ፤ ለክትትልና ግምገማ ስራዎች ተገቢውም ትኩረት ካለመስጠት የሚዘጋጁ ሪፖርቶች ወቅታዊ አለመሆኑን

ለዝግጅቱ በቂ ትኩረት አለመስጠት፤ የክትትልና ግምገማ ስራዎችን በታቀደው መሰረትና ጊዜ ለማከናወን የሰው ሃይል እጥረት መኖር ሚሉት

በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀሱ ሲሆን፤

LOGO ኮምቦልቻጨርቃጨርቅ አክሲዮን ማህበርKOMBOLCHA TEXTILE SHARE COMPANY

Form No.:

OP/KTSC/044

Page 38: 3  Web viewየምርምርና ስርፀት . አሰራር መመሪያ ማንዋል. አዘጋጆች. ንጉሴ ሙላት. ከድር ዘዉዱ. መሰረት ገነቱ

ተጠቃሎ ሲታይ

ለፕሮጀክቶች ወደ ተግባር መሸጋገሪያ ወሳኝ የሆኑ ቅድመ ዝግጅቶች በበቂ ደረጃ አለመከናወናቸው፤

የፕሮጀክቶች የተግባር መርሃ-ግብር(plan action) ከማስፈፀም ጋር በሚገባ ተገናዝበው በአፈፃፀም ሂደት ሊከሰቱ የሚችሉ የአቅም ክፍተቶችን ለማስወገድ በሚያስችል መልኩ አለመዘጋጀት የተነሳ

በፕሮጀክቶች አፈፃፀም ላይ የራሳቸው የሆነ አሉታዊ ተፅዕኖ ሲያሳድሩ ይታያል፡፡

በመፍተሄነት የሚቀርቡ ሀሳቦች

የክትትልና ግምገማ ሂደት ውስጥ ተሳትፎ የሚኖራቸው ክፍሎች በአጠቃላይ ስለ ክትትልና ግምገማ አስፈላጊነትና አካሄድ ተገቢው ግንዛቤ እንዲኖራቸው ማድረግ፤

የክትትልና ግምገማ ሂደት ውስጥ አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችን የማሰባሰብ፤ የማከማቸት፤ መተንተን፤ የማሰራጨትና ወጥነት እንዲኖረው የማድረግ ባህልን ማሳደግ፤

የክትትንና ግምገማ ሂደት ውስጥ ለሚከናወኑ መረጃን የማሰባሰብ፤ የማከማቸት፤

የመተንተንና የማሰራጨት ተግባራት የሚውሉ ዘዴዎች ወጥነትና ተከታታይነት እንዲኖራቸዉ ማድረግ፤

ለክትትልና ግምገማ መነሻ የሚሆነውን የፕሮጀክቱ ዓላማና ግብ፤ ይህንኑ ከዳር ለማድረስ የተዘጋጀውን የድርጊት መርሃ ግብር መሰረት አድርጎ መነሳትና የክትትልና ግምገማውን ስራ በመረጃ ማስደገፍ፤

ክትትልና ግምገማ የሚካሄዱበትን ጊዜያት መወሰንና ከዚህ አንፃር መታየት የሚገባቸውን ጉዳዮች መለየት፤ በየወቅቱ የሚከናወኑ የክትትልና ግምገማ ስራዎችን የሚጠበቀውን ውጤት መወሰንና ይህንኑ በግልፅ በማስቀመጥ፤ ስለዚህም ፕሮግራም አውጥቶ ለተግባራዊነቱ የተቻለውን እንቅስቃሴ ሁሉ

ማድረግ፤

የክትትልና ግምገማ ትልቁ ጠቀሜታ የሚለካው ወቅታዊ በመሆኑና ተገቢውን ደረጃ ጠብቆ ሲገኝ ሲሆን በዚህ ረገድ የሚመለከተውን ድጋፍ ለማግኘት እንዲቻል (feed back) ከጊዜና መታየት ከሚገባቸው

ጉዳዮች አንፃር እንዲሄዱ ማድረግ፤

በማጠቃለያ የግምገማ ስራ ውስጥ በአፈፃፀም ሂደት አዳዲስ አሰራር ስልቶች ምን ያህል የማስፈፀም አቅምን እንዳሻሻሉ መቃኘትና ለዚህም በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀሱትን ሁሉ ማበረታታት፤

በማጠቃለያው የግምገማ ስርዓት ውስጥ በአፈፃፀም ሂደት የተገኙ አዳዲስ አሰራሮች በተመክሮነት ለመጠቀም የሚያስችል የአሰራር ስርዓት መዘርጋተ፤

LOGO ኮምቦልቻጨርቃጨርቅ አክሲዮን ማህበርKOMBOLCHA TEXTILE SHARE COMPANY

Form No.:

OP/KTSC/044

ማንዋል Issue No .

1Page No.:

Page 39 of 47

ምዕራፍ ሦስት3. የፕሮጀክት ቀረፃና ሪፖረት ፎርማት

3.1. አንድ ፕሮጀክት ቀረፃ(propozal) ሊያካትታቸው የሚገባቸው ዋና ዋና ነጥቦች፡-I. ማውጫ(Table of content) ገፁ ከሦስት ከበለጠ ማውጫ ሊዘጋጅለት ይገበዋል፡፡ ማውጫ ሁሉንም ምራፎችና ንዑስ ምዕራፎች

ያሉበትን ገፅ ባመላከተ መልኩ መዘጋጀት ይኖርበታል፡፡II. አጭር መግለጫ(Excutive Summary)

Page 39: 3  Web viewየምርምርና ስርፀት . አሰራር መመሪያ ማንዋል. አዘጋጆች. ንጉሴ ሙላት. ከድር ዘዉዱ. መሰረት ገነቱ

ከግማሽ ገፅ ያልበለጠ ሆኖ ለያካትታቸው የሚገባቸው ሃሳቦች፡- ፕሮጀክቱ እንዲሰራ ያስገደደው ዋና ችግር ፕሮጀክቱ የሚያመጣው ተፅዕኖ ለችግሩ የተቀመጠ መፍተሄ የፕሮጀክት አዋጭነት የሚያመላክት ግምገማ ፕሮጀክቱ የሚያስገኘው ጥቅም ፕሮጀክቱ የሚያስፈልገው የገንዘብ መጠንና የሚወስደው ጊዜ መካተት አለባቸው፡፡

III. መግቢያ(Back Ground) ከአንድ ገፅ ባልበለጠ መገለፅ ሲገባው የሚያካትታቸው ነጥቦች፡-

ፕሮጀክቱ የሚፈታው ችግር ምን እንደሆነ ችግሩን ለምን መፍታት እንዳስፈለገው ስለፕሮጀክቱ አጠር ያለ ማብራሪያ የሚሉትን ይይዛል፡፡

IV. ፕሮጀክቱ የሚመልሳቸው ችግሮች(Rationale) ፕሮጀክቱ እንዲሰራ ምክንያት የሆኑ ነገሮች ተሰርተው መገለፅ አለባቸው በተጨማሪም የፕሮጀክቱ

አጠቃላይ ግብ ለአንባቢው ግልፅ በሆነ መንገድ መስፈር አለበት፡፡V. የፕሮጀክቱ ዓላማ(project objective)

ፕሮጀክቱ ሊሰራበት የሚችሉ ዋናውንና ዝርዝር ዓላማዎች ለይቶ ማቅረብ አለበት፡፡ ይህም ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ ሊያስገኘው ይችላል ተብሎ የታሰበውን ወጤት መግለፅ ያስፈልጋል፡፡

VI. የፕሮጀክቱ መግለጫ(project Description):- የፕሮጀክቱ ስያሜና ዓላማ ጉዳዮን የሚያስረዳ ገለፃ የፕሮጀክቱ ቀጣይነት የፕሮጀክተ የሚተገበርበት ስልት ለፕሮጀክቱ የሚያስፈልጉ ግብዓቶችና የፕሮጀክቱን የግዜ ሰሌዳ ከአስር ገፅ ባልበለጠ

መገለፅ አለበት፡፡VII. የፕሮጀክቱ አመራርና አደረጃጀት(project management and

organization):- ፕሮጀክቱን የሚመሩቱና የሚሳተፉ የባለሙያዎችን ኃላፊነትና ተግባር

LOGO ኮምቦልቻጨርቃጨርቅ አክሲዮን ማህበርKOMBOLCHA TEXTILE SHARE COMPANY

Form No.:

OP/KTSC/044

ማንዋል Issue No .

1Page No.:

Page 40 of 47

የፕሮጀክቱን ውስጣዊ አሰራር አደረጃጀት አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘም መግለፅ አለበት፡፡

VIII. የፕሮጀክቱ ያገባኛል ባዮችና ተጠቃሚዎች(stakeholders and Beneficiaries):-

ተጠቃሚዎች(Beneficiaries) ማለት በፕሮጀክቱ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ተጠቃሚ የሚሆኑትን ይገልፃል፡፡

ያገባኛል ባዮች(stakeholders):- የመጀመሪያ ደረጃ ያገባኛል ባዮች(Primary stake holders)፡- በፕሮጀክቱ በቀጥታም ሆነ

በተዘዋዋሪ በአሉታዊም ሆነ በአወንታዊ ተፅዕኖ የሚደርስባቸው ወይም በፕሮጀክቱ ላይ የሚያደርሱትን ያካትታል፡፡

Page 40: 3  Web viewየምርምርና ስርፀት . አሰራር መመሪያ ማንዋል. አዘጋጆች. ንጉሴ ሙላት. ከድር ዘዉዱ. መሰረት ገነቱ

የሁለተኛ ደረጃ ያገባኛል ባዮች(secondary stake holders)፡- ለፕሮጀክቱ መሰራት የራሳቸው ድርሻና ተፅዕኖ ያላቸው ግለሰቦች፤ ቡድኖችና ተቋማት ተለይተው መዘርዘር አለባቸው፡፡

IX. 5.9 የፕሮጀክቱ ትግበራ(project implementation):- የፕሮጀክት ዕቅድ ማለት የሚሰሩት ስራዎች፤ ስራውን ለመስራት የሚያስፈልጉ የሀብት ድልድል፤ ስራው

በማን፤ እንዴት፤ መቸና የት እንደሚፈፀም መገለፅ አለበት፡፡

X. ሊያጋጥሙ የሚችሉ ስጋትና በጎ ጎኖች(Risk and Assumption):- ፕሮጀክቱ ተግባራዊ ሲሆን ሊያጋጥሙ ይችላሉ ተብሎ የሚታሰቡ ስጋቶች ይገለፁበታል፡፡

ለፕሮጀክቱን ተፈፃሚነት የሚያፋጥኑ፤ የሚረዱ በጎ ጎን ያላቸው ነገሮች አብራርቶ በሰንጠረዥ መገለፅ አለበት፡፡

XI. ክትትና ግምገማ(Monitoring and Evaluation):

ይህ ርዕስ የሚይዛቸው፡- የስብሰባ ቃለ ጉባኤ፤ የስራ ጉብኝት፤ የማማከር ስራ መቸ እንደሚደረግና በስንት ጊዜ ልዮነት

እንደሚቀርብ

የክትትል ስራ የሚሰራበት ስልት

የግምገማ ዕቅድን

ፕሮጀክት እንዴት ለሚመለከታቸው ሪፖርት እንደሚደረግ

XIV. የፕሮጀክቱ ቀጣይነት(sustainability): ፕሮጀክቱ የሚሰጠውን ጥቅም ዘላቂነት መገለፅ አለበት፡፡

LOGO ኮምቦልቻጨርቃጨርቅ አክሲዮን ማህበርKOMBOLCHA TEXTILE SHARE COMPANY

Form No.:

OP/KTSC/044

ማንዋል Issue No .

1Page No.:

Page 41 of 47

3.2 ፕሮጀክት ሪፖርት(Project Report)

ፕሮጅት በትግበራ ላይ ያለበትንና ያመጣውን ለውጥ የምናሳውቅበት መንገድ ነው፡፡

ይህም የሚያካትታቸው፡-I. የጥናቱ ርዕስ(Topic)

በርዕስ ገፅ ላይ የሚኖሩ ቃላት በጥንቃቄ መመረጥና ቃላቱም የተመጠኑ እና ጥናቱን በደንብ የሚገልፁ መሆን አለባቸዉ፡፡ በዚህ ክፍል ዉስጥ መካተት የሚገባቸው ነገሮች፡-

የጥናቱ ርዕስ የአጥኝዎቹ ሰምና አድራሻ ጥናቱ የሚቀርብለት ድርጅት የጥናቱ ፕሮፖዛል የሚቀርብበት ቀንና አመት

Page 41: 3  Web viewየምርምርና ስርፀት . አሰራር መመሪያ ማንዋል. አዘጋጆች. ንጉሴ ሙላት. ከድር ዘዉዱ. መሰረት ገነቱ

II. ምስጋና(Acknolodgement) ጥናቱ ሲካሄድ ለአጥነው በገንዘብ፤ በማማከር፤ አጥኒውን በማበረታታት እና የተለያዮ ድጋፍ በማድረግ ጥናቱ እንዲሳካ ለተባበሩን ሁሉ ስማቸውን በመግለፅ ምስጋና የሚገለፅበት ነው፡፡

III. ማውጫ(Table of content) ማውጫ አንባቢዎች ማንበብ የሚፈልፉትን ክፍል በቀላሉ እንዲያገኝት የሚረዳ ክፍል ነው፡፡ማውጫ

ሁሉንም ርዕሶችና ንዕስ ርዕሶች እስከሚኙበት ገፅ ጭምር ማስቀመጥ ይኖርበታል፡፡IV. ምስልና ሰንጠረዥ ማውጫ(Lists of figure and tables)

ይህ በአማርጭነት የሚያዝ ነው ጥናቱ በዛ ያሉ ስዕላዊ መግለጫና ሰጠረዥ ከያዘ ብቻ የምንጠቀምበት ነው፡፡ በዚህ ውስጥ የተጠቀምንባቸውን ስእላዊ መግለጫዎችና ሰንጠረዞችን ስማቸውንና የሚገኙበትን

ገፅ ጭምር በግልፅ መቀመጥ አለበት፡፡V. ሙዳየ ቃል(Nominiclature)

ይህ እንደ አስፈላጊነቱ የሚገባ ሲሆን ብዙ ምፃረ ቃሎች ከተጠቀምን ምህፃረ ቃሎቻቸውና ትርጉማቸውን ማስቀመጥ ያስፈልጋል፡፡

VI. አጭር መግለጫ(Abstract) ይህ ክፍል ውስጥ ስለፕሮጀክቱ አጠቃላይ የሚገለፅበት ነው፡፡ ይህም ከአንድ መቶ እስከ ሁለት መቶ ቃላት ሊይዝ ይችላል፡፡ በዚህ ክፍል ውስጥ መካተት ያለባቸው፡-

የፕሮጀክቱ መነሻ ሃሳብ፤ ችግርና የሚያስገኘው ጥቅም በአጭርና በግልፅ ፕሮጀክቱ ለመስራት የተጠቀምንበት መንገድ ዋና ዋና የፕሮጀክቱን ውጤቶችና ግኝቶች የፕሮጀክቱ ማጠቃለያ

LOGO ኮምቦልቻጨርቃጨርቅ አክሲዮን ማህበርKOMBOLCHA TEXTILE SHARE COMPANY

Form No.:

OP/KTSC/044

ማንዋል Issue No .

1Page No.:

Page 42 of 47

VII. የፕሮጀክቱ ሪፖርት አካል(Project Report Body)

ይህ ክፍል በፕሮጀክቱ ውስጥ የተሰሩትን ስራዎች፤ የፕሮጀክቱ የተጠቀመባቸው ቁሳቁሶችና አጠቃላይ የፕሮጀክቱ የሚገለፅበት ነው፡፡ በዚህ ርዕስ ውስጥ መካተት የሚገባቸው ርዕሶች እንደ ሪፖርቱና አይነት የሚለያይ ቢሆንም በመሰረታዊነት የሚከተሉትን ማካተት አለባቸው፡፡

አጠቃላይ የፕሮጀክቱን ፅንስ ሃሳብና ናሙና

የፕሮጀክቱን ትንታኔና አጠቃላይ ማብራሪያ

VIII. ማጠቃለያ(Conclusion)

በዚህ ርዕስ ከፕሮጀክቱ ጋር የሚገናኙ ማጠቃለያዎች አሁንን በሚገልፅ መልኩ ይቀመጣሉ

IX. የመፍተሄ ሃሳብ(Recommendation)

Page 42: 3  Web viewየምርምርና ስርፀት . አሰራር መመሪያ ማንዋል. አዘጋጆች. ንጉሴ ሙላት. ከድር ዘዉዱ. መሰረት ገነቱ

ይህ ርዕስ ከማጠቃለያው ጋር በቀጥታ መገናኘት አለበት በተጨማሪም ለተጨማሪ ስራ የሚሆኑ ሃሳቦችን ማካተት አለበት፡፡ በአጠቃላይ ይህ ርዕስ በጥናቱ ግኝቶች ላይ የራሳቸውን ተፅእኖ ለሚያሳድሩ አካላት ትልቅ የሆነ ድርሻ

አለው፡፡

X. አባሪ(Appendices)

ፕሮጀክቱን ለማካሄድ የተጠቀምናቸውን መረጃዎች ማለትም መጠይቆች፤ የተለያዮ ፕሮግራሞች እና ሌሎች ፎርማቶች ከጥናቱ ጋር ተያይዘው የሚቀርቡበት ነው፡፡

XI. ማጣቀሻ(Reference)

በዚህ ክፍል የጥናቱን እውነተኛነት ይመለከትበታል፤ የተጠቀምናቸው የመረጃ ምንጮች በማን ፤ መቼ እንደፃፉና የመረጃ መረቡ ስም በግልፅ መቀመጥ አለበት፡፡

LOGO ኮምቦልቻጨርቃጨርቅ አክሲዮን ማህበርKOMBOLCHA TEXTILE SHARE COMPANY

Form No.:

OP/KTSC/044

ማንዋል Issue No .

1Page No.:

Page 43 of 47

ክፍል 3

Page 43: 3  Web viewየምርምርና ስርፀት . አሰራር መመሪያ ማንዋል. አዘጋጆች. ንጉሴ ሙላት. ከድር ዘዉዱ. መሰረት ገነቱ

የጥናትና የፕሮጀክት አተገባበር

LOGO ኮምቦልቻጨርቃጨርቅ አክሲዮን ማህበርKOMBOLCHA TEXTILE SHARE COMPANY

Form No.:

OP/KTSC/044

ማንዋል Issue No .

1Page No.:

Page 44 of 47

ምዕራፍ 1

1. የጥናትና የፕሮጀክት አቀራረብ.1. ሪፖረት አቀራረብ

የተሰሩ ስራዎችን የሚገልፅ፤ የሚሰሩ ስራዎችን የሚያመላክቱ ሪፖርቶች፤ የሚቀረፁ ፕሮፖዛሎች በሚመለከታቸው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

I. ፕሮፖዛልን በተመለከተ የሚቀርብ ሪፖርት

Page 44: 3  Web viewየምርምርና ስርፀት . አሰራር መመሪያ ማንዋል. አዘጋጆች. ንጉሴ ሙላት. ከድር ዘዉዱ. መሰረት ገነቱ

በምርምርና ስርፀት ባለሙያዎችም ሆነ በሌሎች አካሎች ተሰርቶ የሚቀርብ ፕሮፖዛል በመስፈርቱ መሰረት በምርምርና ስርፀት ተገምግሞ ካለቀ በኃላ ለሲስተምና ደንበኞች አገልግሎት ማሻሻያ አገልግሎት ለአስተያየትና ለማስፀደቅ ይቀርባል፡፡ ምን አልባት በቀረበው ፕሮፖዛል ላይ አስተያየት ከተሰጠበት

በተሰጠው አስተያየት መሰረት ማስተካከያ በማድረግ በድጋሜ ለሲስተምና ደንበኞች አገልግሎት ማሻሻያ አገልግሎት ይቀርባል፡፡

የስራ ክፍሎች በሚፈልጉት ቦታዎች ላይ ጥናት/ ፕሮጀክት እንዲሰራላቸው ሲፈልጉ ለምርምርና ስርፀት መነሻ ሃሳብ ያቀርባሉ፡፡ በቀረበው መነሻ ሃሳብ መሰረት በምርምርና ስርፀት ባለሙያዎች አስተያየት

ከተሰጠበት በኋላ ተግባራዊ(feasibile) የሚሆን ከሆነ ፕሮፖዛል ይቀረፃል፡፡ በመጨረሻም ለሲስተምና ደንበኞች አገልግሎት ማሻሻያ አገልግሎት ለአስተያየትና ለማስፀደቅ ይቀርባል፡፡ምን አልባት በቀረበው ፕሮፖዛል ላይ አስተያየት ከተሰጠበት በኋላ በተሰጠው አሰተያየት መሰረት ማስተካከያ በማድረግ በድጋሜ

ለሲስተምና ደንበኞች አገልግሎት ማሻሻያ አገልግሎት ይቀርባል፡፡

ከድርጅቱ ውጭ የሆኑ አካሎች ጥናት/ ፕሮጀክት እንዲሰራላቸው ሲፈልጉ መነሻ ሃሳብ (TOR) በማዘጋጀት ከማመልከቻ ጋር በመዝገብ ቤት በኩል ለዋና ስራ አስኪያጅ በኩል ያቀርባሉ፡፡ተቀባይነት ካገኘ በሲስተምና

ደንበኞች አገልግሎት ማሻሻያ አገልግሎት በኩል ወደ ምርምርና ስርፀት ይመራል፡፡ በቀረበው መነሻ ሃሳብ መሰረት በምርምርና ሰርፀት ባለሙያዎች አሰተያየት ከተሰጠበት በኋላ ተግባራዊ የሚሆን ከሆነ

ፕሮፖዛል ይቀረፅለታል፡፡ ምን አልባት በቀረበው ፕሮፖዛል ላይ አስተያየት ከተሰጠበት በተሰጠው አስተያየት መሰረት ማስተካከያ በማድረግ በድጋሜ ለሲስተምና ደንበኞች አገልግሎት ማሻሻያ አገልግሎት

ይቀርባል፡፡

II. የጥናት/ ፕሮጀክት ስራን በተመለከተ የሚቀርብ ሪፖርት

እንደ ጥናትና ፕሮጀክት ስራው ስፋት አንፃር በመከፋፈል ፕሮግረስ ርፖርት በየደረጃው ለሲስተምና ደንበኞች አገልግሎት ማሻሻያ አገልግሎት ለአስተያየት ይቀርባል፡፡ በተሰጠው አስተያየት መሰረት ማስተካከያ

በማድረግ በቀጣይ በሚደረገው ፕሮግረስ ሪፖርት ወይም

LOGO ኮምቦልቻጨርቃጨርቅ አክሲዮን ማህበርKOMBOLCHA TEXTILE SHARE COMPANY

Form No.:

OP/KTSC/044

ማንዋል Issue No .

1Page No.:

Page 45 of 47

የመጨረሻ ሪፖረት በማቅረብ በአጠቃላይ ስራው ላይ በተሰጠው አስተያየት ማስተካከያ በማድረግ የመጨረሻውን የጥናት/ ፕሮጀክት ስራ ውጤት ይቀርባል፡፡

III. የተሰራ ስራን ወይም ፕሮጀክትን ወደ ተግባር መለወጥን በተመለከተ

አንድ የፀደቀ የጥናት/ የፕሮጀክት ስራ በሚከተለው መንገድ ወደ ተግባር ይለወጣል

ለመተግበር በሚያስፈልገው ጊዜ፤ በጀት፤ የሰው ሃይልና የመሳሰሉት ላይ ንድፍ ላይ ይዘጋጃል፤

የተዘጋጀው ዝርዝር ንድፍ ለሲስተምና ደንበኞች አገልግሎት ማሻሻያ አገልግሎት ይቀርባል፤ የተዘጋጀው ንድፍ ከፀደቀ በኋላ ወደ ስራ ይገባል

ለጥናት / ለፕሮጀክት ውጤቱ የመጨረሻ ተጠቃሚዎች በየደረጃው ስልጠና ይሰጣል፤ በተጨማሪም የአጠቃቀም ማንዋል ይዘጋጃል

የመጨረሻ ተጠቃሚዎች ምን ያክል የተሰራውን ስራ እንደተጠቀሙበት ግምገማ በማካሄድ እንደ አስፈላጊነቱ የማሻሻያ ስልጠና ይሰጣል

Page 45: 3  Web viewየምርምርና ስርፀት . አሰራር መመሪያ ማንዋል. አዘጋጆች. ንጉሴ ሙላት. ከድር ዘዉዱ. መሰረት ገነቱ

የስራው አተገባበር ሂደት ውጤት ሪፖርት ለሲስተምና ደንበኞች አገልግሎት ማሻሻያ አገልግሎት ይቀርባል፡፡

IV. ወደ ተግባር በተለወጠ የጥናት/ ፕሮጀክት ስራ ላይ ማሻሻያ ማድረግን በተመለከተ

አንድ ጥናት/ ፕሮጀክት ወደ ተግባር ተለውጦ እያገለገለ ባለበት ሁኔታ ማሻሻል ቢያስፈልግ በሚከተለው መንገድ መከናወን ይኖርበታል፡፡

ጥናቱ/ ፕሮጀክቱ ለምን መሻሻል እንዳለበት የሚያመላክት ዝርዝር መረጃ ከስራው የመጨረሻ ተጠቃሚዎች፤ ወይም ጥናቱን ወይም ፕሮጀክቱን ከሰራው/ ከሰሩት ይቀርባል፤

መሻሻሉ አሳማኝ ሁኖ ሲገኝ የማሻሻያ ፕሮፖዛል ለሲስተምና ደንበኞች አገልግሎት ማሻሻያ አገልግሎት ይቀርባል፡፡

የማሻሻያ ስራው ቀደም ሲል የጥናቱ/ ፕሮጀክቱን በሰራው/ በሰሩት በተጨማሪም ስለፕሮጀክቱ ጥሩ ግንዛቤ ባላቸው ሰዎች ይከናወናል፡፡

በማሻሻው ስራው ላይ እንደአስፈላጊነቱ ስልጠናና የአጠቃቀም ማንዋል ይዘጋጃል፤

የማሻሻው ስራው አጠቃላ ውጤት ለሲስተምና ደንበኞች አገልግሎት ማሻሻያ አገልግሎት ይቀርባል፡፡

V. ወደ ተግባረ በተለወጠ ጥናት/ ፕሮጀክት የሚያጋጥም ችግር/Failure/ መፍታትን በተመለከት

አንድ ጥናት/ ፕሮጀክት ወደ ተግባር ተለውጦ እያገለገለ እያለ ችግር ቢያጋጥመው በሚከተለው መንገድ ሊፈታ ይችላል፡፡

LOGO ኮምቦልቻጨርቃጨርቅ አክሲዮን ማህበርKOMBOLCHA TEXTILE SHARE COMPANY

Form No.:

OP/KTSC/044

ማንዋል Issue No .

1Page No.:

Page 46 of 47

በጥናቱ/ ፕሮጀክቱ የመጨረሻ ተጠቃሚዎች የQMS አሰራርን መሰረት በማድረግ ነን ኮነፎርማንስ በመምላት ችግሩን ለምርምርና ስርፀት ቀርባል፤

የምርምርና ስርፀት የቀረበውን ችግር እንደ አስፈላጊነቱ ለሲስተምና ደንበኞች አገልግሎት ማሻሻያ አገልግሎት ያሳውቃል፤ችግሩን ለመፍታት የሚያስችል ዝርዝር እቅድ ያዘጋጃል ያፀድቃል፡

ስራው ከዚህ በፊት ጥናት/ ፕሮጀክት ስራውን ባከናወነው/ ባከናወኑት እና እንደ አስፈላጊነታቸው በሌሎች ተጨማሪ ባለሙያዎች ይከናወናል፡

የስራው ውጤት የያዘ ሪፖርት ለሲስተምና ደንበኞች አገልግሎት ማሻሻያ አገልግሎት ይቀርባል፡፡

VI. የፀደቁ የጥናትና ፕሮጀክት ሰነዶች አቀማመጥን በተመለከተ

ለሰነዱ የመጨረሻ ተጠቃሚዎች፤ ለዋና ስራ ስራ አስኪያጅ፤ ለም/ ዋና ስራ አስኪያጅ፤ ለመምሪያዎችና አገልግሎቶች፤ ለምርምርና ስርፀት ለኩባንያው ላይብራሪ አንድ አንድ ኮፒ እንዲጠቀሙበት

ይሰጣቸዋል፡፡በተጨማሪም እንዳስፈላጊነቱም ለሚመለከታቸው የመንግስት አካሎችና ሌሎች አጋሮች ሰነዱ ሊሰጥ ይችላል፡፡

Page 46: 3  Web viewየምርምርና ስርፀት . አሰራር መመሪያ ማንዋል. አዘጋጆች. ንጉሴ ሙላት. ከድር ዘዉዱ. መሰረት ገነቱ

LOGO ኮምቦልቻጨርቃጨርቅ አክሲዮን ማህበርKOMBOLCHA TEXTILE SHARE COMPANY

Form No.:

OP/KTSC/044

ማንዋል Issue No .

1Page No.:

Page 47of 47

ማጣቀሻ ( Refrence)

1. የፕሮጀክት ዕቅድ አዘገጃጀት ክትትልና ግምገማ አሰራር, በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ, ባህርዳር, ሰኔ 1999 ዓ. ም .

2. Research proposal   - Wikipedia, the free encyclopedia

en.wikipedia.org/wiki/Research_proposal3. What is   research proposal ? definition and meaning www.businessdictionary.com/definition/ research - proposal .html 4. Writing a   Research Paper   - Purdue OWL https://owl.english.purdue.edu/owl/owlprint/658/ 5. What Is a   Project Proposal? www.wisegeek.com/what-is-a-project-proposal.htm6. steps to writing a successful   project proposal   - University of Lethbridge www.uleth.ca/education/sites/.../files/Steps_to_Project_Proposal.pdf7. Format   for   project reports carmaux.cs.gsu.edu/~mweeks/project.html 8.format   for preparation of   project report   - Anna University www.annauniv.edu/academic/ug_format.doc

Page 47: 3  Web viewየምርምርና ስርፀት . አሰራር መመሪያ ማንዋል. አዘጋጆች. ንጉሴ ሙላት. ከድር ዘዉዱ. መሰረት ገነቱ

LOGO ኮምቦልቻጨርቃጨርቅ አክሲዮን ማህበርKOMBOLCHA TEXTILE SHARE COMPANY

Form No.:

OP/KTSC/044

Annex A (document writing templet) Issue No .

1Page No.:

Page 1 of 1

ISSUE HISTORYIssue Discription of

ChangeOriginator Effective Date

1 Initial Realease Negusie mulatMeseret genetu

Keder zeweduHiwot yimer

REFERENCE DOCUMENTDocument Number Document Title

FOR DOCUMENT CONTROLUSE ONLY

Page 48: 3  Web viewየምርምርና ስርፀት . አሰራር መመሪያ ማንዋል. አዘጋጆች. ንጉሴ ሙላት. ከድር ዘዉዱ. መሰረት ገነቱ

APPROVAL Name: Signature: Date:

LOGO ኮምቦልቻጨርቃጨርቅ አክሲዮን ማህበርKOMBOLCHA TEXTILE SHARE COMPANY

Form No.:

OP/KTSC/200

Issue No .

1Page No.:

Page 1 of 1

……………ቁጥር . ………………ቀን .

ለአሰራርና አገልግሎት ማሻሻያ አገልግሎት ከምርምርና ስርፀት ዋና ክፍል ጉዳዮ፡- ፡ የምርምርና ስርፀት አሰራር መመሪያ ማንዋል ስለማቅረብ

በ 2005 በጀት ዓመት በሁለተኛ ሩብ ዓመት በያዝነው መርሃ-ግብር መሰረት የምርምርና ስርፀት አሰራር መመሪያ ማንዋል አዘጋጅተን የላክን መሆኑን እየገለፅን ታይቶ እንዲፀድቅልን እንጠይቃለን፡፡

ከሠላምታ ጋር