awramba times issue 161 megabit 24

24
- አዶኒስ የወንጀል ክስ እንዲመሰረት አቤቱታ አቅርቧል - የኢትዮጵያ ቴሌቪዥንም ድራማውን በማስተላለፉ ተከሷል - የሞራል ካሳና የስፖንሰር ገቢ እንዲከፈለው ደራሲው ጠይቋል ገመና ቁጥር 2 የዕግድ ጥያቄ ቀረበበት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ ከትናንት በስትያ ‹አምባገነኑ ሥርዓት በሕዝብና በሀገር ላይ የሚያደርሰው የከፋ ግፍ ፅዋው ሞልቶ እየፈሰሰ ነው› በሚል ርዕስ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጠ፡፡ ኢሕአዴግና አቶ መለስ እስካሁን በሥልጣን ላይ መቆየታቸውን በጠቆመው መግለጫ መንግስት በዚህ ጊዜ ውስጥ ስህተቶችን አርሞና አስተካክሎ አገሪቷን ሌሎች የዓለም አገራት ወደደረሱበት የዕድገት ደረጃ ሊያደርሳት የሚያስችላትን ዕድልና አጋጣሚ ሁሉ ሆን ብሎና አውቆ እንደተሰራ በሚያስመስል መልኩ ማበላሸቱንና እያበላሸም እንደሚገኝ ተጠቅሷል፡፡ በመግለጫው ውስጥ ከተዘረዘሩት ጉዳዮች የተወሰኑት ሥርዓቱ ኢትዮጵያን የምታክል ሰፊ አገር ወደብ አልባ እንዳደረጋትና ‹ወደብ ሸቀጥ ነው› ብሎ ማፌዙን፣ በኢትዮ-ኤርትራ ድንበር ጉዳይ በጦርነት ምክንያት የፈሰሰውን የብዙ አስር ሺህዎች ኢትዮጵያውያንን ደም ከንቱ ባደረገ መልኩ እንዲደመደም የአልጀርስ ስምምነት መፈረሙ፣ ከኢህአዴግ ጋር ግንኙነት ያላቸው የንግድና ኢንቨስትመንት ተቋማት በነፃ የገበያ ኢኮኖሚ መጎልበት ላይ ተፅዕኖ እንዲፈጥሩ መፈቀዱ ተገልጿል፡፡ ‹‹በሕዝብ ላይ የሚደርሰው ግፍ ፅዋው ሞልቶ እየፈሰሰ ነው›› የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ ‹‹ዶ/ር ብርሀኑን ማግኘት መብቴ ነው የሻቢያን ሰዎች ግን አላገኘሁም›› ዶ/ር መረራ ጉዲና ‹‹ማሰር ሰለቸን›› እኔ የማውቀው ጋዳፊ በመስፍን ወልደ ማርያም (ፕሮፌሰር) በዮዌሪ ሙሰቪኒ ሰዓት እላፊው ይነሳ! 3 3 ወደ ገፅ 19 ዞሯል

Upload: ambachew201421

Post on 06-Mar-2015

246 views

Category:

Documents


5 download

TRANSCRIPT

Page 1: Awramba Times Issue 161 Megabit 24

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 161 ቅዳሜ መጋቢት 24 2003

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

- አዶኒስ የወንጀል ክስ እንዲመሰረት አቤቱታ አቅርቧል

- የኢትዮጵያ ቴሌቪዥንም ድራማውን በማስተላለፉ ተከሷል

- የሞራል ካሳና የስፖንሰር ገቢ እንዲከፈለው ደራሲው ጠይቋል

ገመና ቁጥር 2 የዕግድ ጥያቄ ቀረበበት

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ ከትናንት በስትያ ‹አምባገነኑ ሥርዓት በሕዝብና በሀገር ላይ የሚያደርሰው የከፋ ግፍ ፅዋው ሞልቶ እየፈሰሰ ነው› በሚል ርዕስ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጠ፡፡ ኢሕአዴግና አቶ መለስ እስካሁን በሥልጣን ላይ መቆየታቸውን በጠቆመው መግለጫ መንግስት በዚህ ጊዜ ውስጥ ስህተቶችን አርሞና አስተካክሎ አገሪቷን ሌሎች የዓለም አገራት ወደደረሱበት የዕድገት ደረጃ ሊያደርሳት የሚያስችላትን ዕድልና አጋጣሚ ሁሉ ሆን ብሎና አውቆ እንደተሰራ በሚያስመስል መልኩ ማበላሸቱንና እያበላሸም እንደሚገኝ ተጠቅሷል፡፡ በመግለጫው ውስጥ ከተዘረዘሩት ጉዳዮች የተወሰኑት ሥርዓቱ ኢትዮጵያን የምታክል ሰፊ አገር ወደብ አልባ እንዳደረጋትና ‹ወደብ ሸቀጥ ነው› ብሎ ማፌዙን፣ በኢትዮ-ኤርትራ ድንበር ጉዳይ በጦርነት ምክንያት የፈሰሰውን የብዙ አስር ሺህዎች ኢትዮጵያውያንን ደም ከንቱ ባደረገ መልኩ እንዲደመደም የአልጀርስ ስምምነት መፈረሙ፣ ከኢህአዴግ ጋር ግንኙነት ያላቸው የንግድና ኢንቨስትመንት ተቋማት በነፃ የገበያ ኢኮኖሚ መጎልበት ላይ ተፅዕኖ እንዲፈጥሩ መፈቀዱ ተገልጿል፡፡

‹‹በሕዝብ ላይ የሚደርሰው ግፍ ፅዋው ሞልቶ እየፈሰሰ ነው››

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ

‹‹ዶ/ር ብርሀኑን ማግኘት መብቴ ነው የሻቢያን ሰዎች ግን አላገኘሁም››ዶ/ር መረራ ጉዲና

‹‹ማሰር ሰለቸን›› እኔ የማውቀው ጋዳፊበመስፍን ወልደ ማርያም (ፕሮፌሰር) በዮዌሪ ሙሰቪኒ

ሰዓት እላፊው ይነሳ!

3 3

ወደ ገፅ 19 ዞሯል

Page 2: Awramba Times Issue 161 Megabit 24

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 161 ቅዳሜ መጋቢት 24 2003

T’@Í=”Ó ›?Ç=}` Ç©ƒ ŸuÅ

ª“ ›²ÒÏõì<U TV

(›É^h ¾” ¡/Ÿ kuK? 03/04 ¾u?.l 1540)

U/ª“ ›²ÒЋ Ó³¨< KÑW¨<wgƒ �Â

Ÿõ}— ›²ÒÏ ›u?M ¯KT¾G<

›²ÒϨc”cÑÉ Ñ/Ÿ=Ç”

Ÿõ}— ]þ`}a‹

›?MÁe Ñw\c<^õ›?M Ó`T

¯UÅ™‹ ›uu „L

cKV” VÑeƒ°Óeƒ ¨”ÉS<

iÁß“ Te�¨mÁ }hK cÃñ}hK ¨ÇÏ

¢Uú¨<}` îG<õ SpÅe õeN

Ó^ò¡e ›?Ç=}` ’w¿ Seõ”

(0911 18 09 33)E-Mail:[email protected]

¾´Óσ ¡õK< eM¡eM¡:- ®911 62 92 78 ®911 62 92 82 0911 15 62 48

þ.X.l [email protected]://www.awramba.com

›d�T>¨<ብሉ ኤርዝ ጀነራል ቢዝነስ

ኃላ/የተ/የግል/ማህበር

ር ዕ ሰ አ ንቀፅ

ማን ምን አ ለ

2

ዕውቁ እንግሊዛዊ ፀሐፊ በርናንድ ሾው በአንድ ወቅት የተናገረው ንግግር በአስተማሪነቱ ተደጋግሞ ይጠቀሳል፡፡ ‹‹ስታጠቃው በዝምታ ከሚመለከትህ ወይም መልሶ የማጥቃት ሙከራ ከማይፈፅምብህ ሰው እጅጉን ተጠንቀቅ...›› ይላል የዚህ ጸሐፊ ምክር፡፡ ምክንያቱን ሲያስቀምጥ ደግሞ ‹‹...የዚህ ዓይነቱ ሰው የምታደርስበትን በደል በቸልታ እየተመለከተ ሳይሆን ቂም እየቋጠረብህ በመሆኑ ምላሹ ሊጠነክር የሚችል ከመሆኑም በላይ በቸልታ የሚያልፍበት አጋጣሚ ቢፈጠር እንኳን በፈፀምክበት ጥቃት በፀፀት እየተለበለብክ እንድትኖር ስለሚያደርግህ ነው፡፡››

እንዲህ ዓይነቱን በሳል አባባል በጥንቃቄ ሊያስተውሉትና ተገቢውን ትምህርት ሊወስዱበት የሚገባው ነው፡፡ በአገራችንም መሰል አባባሎች፣ ቅኔያዊ መልዕክቶችና አስጠንቃቂ አስተምህሮዎች አሉ፡፡ መስማት እንዳለበት ለሚገነዘብ፣ የሰማቸውን ምክሮች አድምጦ የእርምት እርምጃ ለሚወስድና በተሳሳተው መስመር ዳግመኛ ለማይሄድ ሰው የሕይወት ዘመን መመሪያ፣ ለመሪዎች ደግሞ የመልካም አስተዳደር ቁልፍ ምስጢር ሊሆን ይችላል ብለን እናምናለን፡፡

በአገራችን ነባራዊ ሁኔታ የስርዓት ለውጥ ተደረገ ከተባለባቸው ሁለት አስርት ዓመታት ወዲህ ብቻ እንኳ በርካታ የማስጠንቀቂያ መልዕክቶች ተላልፈዋል፡፡ መልዕክቱ የሚተላለፍላቸው ወገኖች ግን የመልዕክቱን ፍሬ ሃሳብ በቅንነትና በኃላፊነት ስሜት መርምሮ ተገቢውን የመፍትሔ እርምጃ ከመውሰድ ይልቅ ያላስፈላጊ ስሌቶች ውስጥ እየገቡ የችግሩን ገፈት በሕዝቡ ላይ ሲያሳርፉ ኖረዋል፡፡ የሚያሳዝነው

አሁንም ማስጠንቀቂያዎች ሲቀርቡ የተለመደው የተዛባ ስሌት ተግባራዊ እየተደረገ መሆኑ ነው፡፡

ምን ማስጠንቀቂያዎች ቀረቡ? ማስጠንቀቂያዎቹ ለምን ተገቢው ምላሽ ተነፈጋቸው? ምን ጉዳትስ አስከተሉ? ብለን ብንጠይቅ በርካታ መድብሎች የተከፋፈሉና ሰፋፊ ትንታኔዎችን የያዙ እውነታዎች ማዥጎድጎድ ይቻላል፡፡ ማዳመጥ እንዳለበት የሚገነዘብ፣ ያደመጣቸውን ምክሮች መሰረት አድርጎ የእርምት እርምጃ ለሚወስድ እና በተሳሳተው መስመር ዳግመኛ ለማይሄድ ቢሆን ኖሮ አዎን ሲደርሱ የኖሩትም እነዚሁ ማስጠንቀቂያዎችን አስቀድሞ የመስጠት የዜግነት ኃላፊነቶች ነበሩ፡፡

ብዙ ማስጠንቀቂያዎች ቀርበዋል፡፡ የተወሰኑትን ለዋቢነት መጥቀስ ይቻላል፡፡ ኤርትራ ከኢትዮጵያ ስትለይ ተሽቀዳድሞ ዕውቅና ከመስጠት ይልቅ ሕጋዊ መብታችን የሆነችው አሰብ እና 70 ሚሊዮን ያህል ሕዝብ ሊኖረው የሚገባው የባሕር በር የማግኘት መብት ጉዳይ የዓለም አቀፍ ሕግና በሁለትዮሽ የመጠቃቀም መርሕ ይታሰብበት ሲባል ነበር፡፡ ይህ ካልሆነ እርዳታም ሆነ የንግድ ሸቀጦቿ ከውጭ ወደ ውስጥ ለሆነባት አገራችን ውሎ አድሮ ሊያስከትልባት የሚችለው ጉዳት ከፍተኛ ነው ተብሎ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷል፡፡ የሰማ የለም፡፡ ለመስማት የፈለገም አልነበረም፡፡ በዚህም ሕዝቡ በሁለንተናዊ ችግሮች ተቀጠቀጠ፡፡

በእንደነዚህ ያሉ ጊዜያት ሁሉ በመግቢያችን ላይ ያለው ማስጠንቀቂያ ይሰራል፡፡ ጉዳቶች ከመድረሳቸው በፊት እና በመድረስ ላይ እያሉ ለመንግስት ስርዓቶች ማስጠንቀቂያዎች ይሰጣሉ፡፡ ሰሚ

ሲጠፋ ሕዝቡ ዝም ሊል ይችላል፡፡ ችግሮቹን አሜን ብሎ ተቀብሏቸዋል ማለት ግን አይደለም፡፡ ሲሆን የኖረውና እየሆነ ያለውም ይኸው ነው፡፡ - ሊካድ የማይችል ጉዳት ደርሶብናል እየደረሰብንም ነው ብለን እናምናለን፡፡

ጉዳቶቹ ቀስ እያሉ የአንድን አገር የኢኮኖሚ መዋቅር ማናጋት ይጀምራሉ፡፡ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሻቀበ የመጣው በጅቡቲ ወደብ አጠቃቀም ላይ የሚታየው አከርካሪ የሚሰብር የታሪፍ ጭማሪና ያልታሰቡ ያለመረጋጋት ቀውሶች እያጋጠሙ ነው፡፡ ንብረቶቻችን ከወደብ ተነስተው ሲመጡ ጥቃት እየተሰነዘረባቸው ነው፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚ/ር ከሳምንት በፊት በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ችግሩን ለመቅረፍ ጥረት እያደረገ እንዳለ ቢገልፅም መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ግን ስጋቱን የሚያንሩ ሁኔታዎች በስፋት አሉ፡፡

መ ረ ጃ ዎ ች እንደሚያመለክቱት ሕጋዊ መብታችንን ለመጠየቅ ተነሳሽነት በመጥፋቱ ኃይላችንን ከእጃችን እንዳወጣው ይገለጻል፡፡ ማስጠንቀቂያዎች ሲቀርቡ ባለመስማት የደረሰብን ኪሳራ ነው፡፡ በእርግጥ የችግሩ ገፈት ቀማሽ አሁንም የኢትዮጵያ ሕዝብ እንጂ በስልጣን ማማ ላይ የሚገኙ መሪዎች እንዳልሆኑ እንረዳለን፡፡

የገንዘብ አጠቃቀም ስርዓታችንን አስመልክቶም ኤርትራ ሉአላዊት አገር ከተባለች በኋላ በመሰል ክስተት ወቅት ተግባራዊ ከሚደረገው ፈፅሞ በተለየ ኢ-ፍትሃዊ መንገድ ኢትዮጵያችን እየደማች ኤርትራ እየለማች የሄደችበት ለዓመታት በገንዘባችን የመገልገሏ መዘዝ ማስጠንቀቂያ ሲቀርብበት ነበር፡፡ መስማት አልተፈለገም፤

ስለዚህም ምሁራን የሚበጀውን ሲመክሩ ያልተሰማላት አገር ኃብት ያለ ሕግ አግባብ እንዲበዘበዝ ሲደረግ ከኖረ በኋላ በመጨረሻ የአዞ እንባ ሲነባም እየተመለከትን ነው፡፡

አሁንም የውጭ ጉዳይ ሚ/ር ቀደም ሲል በተጠቀሰው ዕለት በሰጠው መግለጫ ከሕግ ስርዓት ውጭ ኢኮኖሚዋን ስትገነባ የኖረችው ኤርትራ መሪዎች ጥቅማቸው ሲቋረጥ የከፈቱት ጦርነት ነበር አለ፡፡ ይህ ማስጠንቀቂያውን መስማት ሊሆን አይችልም፡፡ ከጉዳቱ በኋላ የሚቀርብ ሪፖርት ነውና፡፡

ማስጠንቀቂያ ሰጩዎቹ ዜጎችና የዘርፉ ምሁራን በወቅቱ ተሰምተው ቢሆን ኖሮ ወራሪዋ በራሳችን ኃብት ያለአግባብ በልጽጋ ጥቅሜ ለምን ተቋረጠ? በሚል ጦር ባልሰበቀች በዚህም ሕይወት፣ አካልና ከፍተኛ መጠን ያለው ኃብት ባልጠፋብን ነበር፡፡ እነዚህንና መሰል ጉዳዮች የምናነሳው ዛሬም ከዚህችው አገር ጋር የተጀመረ የአንድ ከባድ አደጋ ዋዜማ እሰጥ አገባ ላይ በመሆናችን ነው፡፡ ዜጎች፣ ወዳጅ አገራትና፣ የዘርፉ ምሁራን ይበጃል ያሉትን እየመከሩ ነው፤- እያስጠነቀቁ ነው!

ማ ስ ጠ ን ቀ ቂ ያ ዎ ች ን ና ምክሮችን ያለማዳመጥና ያለመተግበር ከማይወጡት አዘቅት ውስጥ እንደሚነክር ይስተዋል፡፡ እኛን በእጅጉ የሚያሣስበን ነገር አለ፡፡ የችግሩ ገፈት ቀማሽ የስልጣን ማማ ላይ የተቆናጠጡት ሳይሆኑ ሕዝባችን መሆኑ! እናም ሕዝባችንን አድምጡ፣ ባለሙያዎችን አድምጡ፣ ወዳጅ አገራት የሚሉትን አድምጡ እንላለን፡፡

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!!

የካቲት 2000 ዓ.ም ተመሠረተ

አውራምባ ታይምስ፡- በብሉ ኤርዝ ጀነራል ቢዝነስ ኃላ/የተ/የግል/ማህበር ስር የሚታተም፤ በፖለቲካዊና ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩር፤ በንግድ ሚኒስቴር በቁጥር 020/2/6572/2001 የተመዘገበ ሳምንታዊ ጋዜጣ ነው፡፡

አድራሻ አራዳ ክ/ከተማ ቀበሌ 09

የቤት ቁጥር 191

ከአራት ኪሎ ወደ ፒያሳ በሚወስደው መንገድ ፣ ከራስ መኮንን ድልድይ አለፍ ብሎ ወደ ሀገር ፍቅር ቲያትር መገንጠያ አስፋልት ላይ በሚገኘው ባህረ ነጋሽ ሕንፃ ግቢ ውስጥ፡፡

አታሚ፡-

ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ክ/ከተማ፡- አራዳቀበሌ፡- 17የቤት ቁጥር፡- 984

‹‹መንግስት ምን ያህል ከእውቀት ጋር እንደተጣላ

ያሳያል››ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም

ሰሞኑን የተደረገውን የህትመት ጭማሪ በማስመልከት

ከሪፖርተር ጋዜጣ ለቀረበላቸው ጥያቄ የሰጡት ምላሽ፡፡

‹አንድን ሰው ጆሮው እንዳይሰማ፣ አይኑ እንዳያይ፣

አፉ እንዳይናገር አድርጎ ማቆየት ይቻላል ወይ?››አቶ በቀለ ነጋ

የኦፌዲን ዋና ፀሐፊ በቅርቡ ተቃዋሚዎች በጀርመን ራዲዮ መግለጫ ይሰጣሉ ተብሎ ሲጠበቅ መታፈኑን አስመልክቶ

ለፍትሕ ጋዜጣ ከሰጡት አስተያየት የተወሰደ፡፡

ሕዝባችንን አድምጡ! ባለሙያዎችን አድምጡ! ወዳጅ አገራት የሚሉትን አድምጡ!

‹‹በእኔ ላይ በደል ስላደረሱብኝ ብዬ በአጠቃላይ ስለ ፕሬስ ሙያ መጥፎ የሆነ አመለካከት ሊኖረኝ አይችልም፡፡››

አቶ ልደቱ አያሌው የቀድሞው የኢዴፓ ሊቀ-መንበር

‹‹በአንድ ወቅት በሰጡት መግለጫ ጋዜጦች አሳውቀውኛልም ገድለውኛልም ብለው ነበር፡፡ አፋኝ በተባለው የመረጃ ነፃነት ሕግ ረቂቅ ላይ ተሳታፊ ነበሩ፡፡ አሁን ላይ ሆነው ስለ ጋዜጦች የመረጃ ነፃነት ሕግ የሚሉት ነገር አለ?›› በሚል ከሪፖርተር ጋዜጣ ለቀረበላቸው ጥያቄ ከሰጡት ምላሽ የተወሰደ፡፡

Page 3: Awramba Times Issue 161 Megabit 24

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 161 ቅዳሜ መጋቢት 24 2003

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

ኮሜንተሪ

ሰዎች መጠን የአንድ ማኅበረሰብ ወይም አገር የማምረትና ምርቱን የመሸጥ አቅም ይቀንሳል፤ እድገት በዚያው መጠን ያዘግማል፤ ደሀነት በዚያው መጠን ይስፋፋል፤ ስለዚህም ጉልበት አለኝ ብሎ ማሰር ለአንድ ሰው ወይም ለጥቂት ሰዎች ከማሰልቸቱ በላይ የአገርን እድገት በእግር ብረት ይጠፍራል፤ እንደዚህም መጥፎ ሆኖ ለአገርና ለሕዝብ ደኅንነት ሲባል ማሰር ሥራ ነው፤ ስለዚህም ስድስት ሺህ አራት መቶ ብር እየበሉ ሥራ ሰለቸኝ ማለት አያዋጣም፤ የሚሰለቸውን ሥራ መተው ትክክለኛው አማራጭ ነው፡፡

ማሰር ሰለቸን የሚያሰኘው እንደእስክንድር ነጋ ያለውን ሰላማዊ ሰው ከሆነ ማሰር ሕጋዊ ሥራ መሆኑ ይቀርና ጉልበት ያለው የሚፈጽመው ግፍ ይሆናል፤ የሰለቸው ግፍ መሥራት ከሆነ ኅሊና ከእንቅልፉ ነቅቷል ማለት ነውና ይማርህ፣ ያበርታህ ማለት ይገባል፤ ነገር ግን ነገሩ የጤና አይመስልም፤ ለእስክንድር ነጋ ‹‹ረብሻ ቢነሳ... አንተ ላይ ነው እርምጃ የምንወስደው›› ያለው ሰው የሕክምና እርዳታ የሚያስፈልገው ነው፤ ማሰብ የሚችል ባለሥልጣን ቢሆን የቱኒዚያና የግብፅ የፖለቲካ አውሎ ነፋስ በኢትዮጵያም ያልፋል ብሎ ለሚተነብይ ሰው ለማስጠንቀቂያው ሽልማት ባይሰጠውም አመስግኖ ለመፍትሔው መዘጋጀት ነው እንጂ ‹ረብሻ ቢነሳ በአንተ ላይ እርምጃ እንወስዳለን› ማለትን ምን አመጣው? ገና ባልተሰራ ‹‹ወንጀል›› ገና ባልተያዘ ‹‹ወንጀለኛ›› ገና ባልተደረገ ‹‹ምርመራ››

3

ለአል-ኢትሀድ ከሚነገረው መመሪያ በምን ይለያል? ይህ የማሰብ ችግርን አያሳይም?

ማሰር ምን ማለት ነው? አእምሮን፣ ዓይንን፣ ጆሮን፣ አንደበትን መጋረድና ማፈን ነው፤ እጅንና እግርን ሽባ ማድረግ ነው፤ ሰውን ከአምራችነት ተራ ማውጣት ነው፤ ከገበያ ውስጥ ማስወጣት ነው፤ ስለዚህም በታሰሩት

በቅርቡ አንድ አስቀያሚ ቀልድ ሰማሁ፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ ለሦስት ይከፈላል ብሎ ይጀምርና አንደኛ የታሰሩ፣ ሁለተኛ ታስረው የተፈቱ፣ ሦስተኛ ወደፊት የሚታሰሩ ይላል፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ ከሦስቱ የማይወጣ ከሆነና ኢጣልያ ተመልሶ ካልመጣ አሳሪው ማን ሊሆን ነው? ሌላም ታሪክ ያስታውሰኛል፤ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት በሩስያ ግንባር የጀርመን ጦር በጣም አይሎ ነበር፤ ጀርመኖች በምዕራብ ሩስያ ቀድመው ቦታ ይዘውና ጠንካራ ምሽግ ሰርተው ስለነበረ፤ የሩስያ ጦር እየተጋለጠ ሲመጣ በመትረየስ ያጭዷቸው ነበር፤ ከኋላ ያለው በሬሳው ላይ እየተራመደ መጥቶ ሲወድቅ ሌላው እየመጣ የሬሳ ተራራ ተፈጠራ፤ በዚህን ጊዜ ብዙ የጀርመን ወታደሮች መግደል እያቅለሸለሻቸው ያስመልሳቸው ጀመር፤ መግደልም ይሰለቻል፤ እንዲያውም ያንገሸግሻል፡፡ አሁን ደግሞ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ማሰር ሰለቸን ሲለን በመጀመሪያ ሲሰሙት ያስደነግጣል፤ ዓላማውም ማስደንገጥ ሳይሆን አይቀርም፤ ብዙ ጊዜ ብዙ ሰዎች ኢትዮጵያ የእስር ቤት ነች እያሉ ተናግረዋል፤ ጽፈዋልም፤ የጠቅላይ ሚኒስትሩ አነጋገር ኢትዮጵያ እስር ቤት ነች የሚለውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ይመስላል፤ ገበሬው እስር ቤት፣ ነጋዴው እስር ቤት፣ የመንግሥት ሠራተኛው እስር ቤት፣ ፖለቲከኛው እስር ቤት፣ ተማሪው እስር ቤት፣ ጋዜጠኛው እስር ቤት፣ ለተመቸውና ለሆነለት የእስር ቤት አማራጩ ስደት እየሆነ እዚህ ደርሰን

ነበረ፤ በኢትዮጵያ የሚታሰረው ሰው ብቻ አይደለም፤ ዘፈንም ይታሰራል፤ ማኅበርም ይታሰራል፤ ገንዘብም ይታሰራል፤ ምን የማይታሰር ነገር አለ? ታዲያ ማሰር እንዴት አይሰለችም! አሁን ደግሞ የስደቱ መንገድ በበረሀ ወይም በውሃ የሚጠፉበት ሲሆን ማሰር ሰለቸን ሲል ምን ሊያደርገን አሰቦ ነው? ብለን እንድንሰጋ ተመኝቶ ይሆናል፤ የግንዛቤ ችግር ነው እንጂ እስር ቤት ውስጥ ያለ ሰው መታሰር ለምን ይፈራል? ዝናብ ላይ ቆሞ መርጠብ የሚፈራ አለ? በጣም የሚያስደንቀው አንድ ድርጅት ሃያ ዓመታት ሙሉ በአንድ ስልት ብቻ፣ በማሰር ብቻ እየተጠቀመ መቆየቱ በዚያ ቤት የማሰብ ችግር እንዳለ ማስረጃ ነው፤ ለእስክንድር ነጋ የተነገረው መመሪያ ለሻዕቢያ ከሚነገረው መመሪያ፣ ወደ ገፅ 23 ዞሯል

በመስፍን ወልደ ማርያም (ፕሮፌሰር)

‹‹ማሰር ሰለቸን››‹‹ማሰር ሰለቸን››

ጉልበት አለኝ ብሎ ማሰር ለአንድ ሰው ወይም ለጥቂት ሰዎች

ከማሰልቸቱ በላይ የአገርን እድገት በእግር ብረት ይጠፍራል፤ እንደዚህም

መጥፎ ሆኖ ለአገርና ለሕዝብ ደኅንነት ሲባል ማሰር ሥራ ነው፤ ስለዚህም

ስድስት ሺህ አራት መቶ ብር እየበሉ ሥራ ሰለቸኝ ማለት አያዋጣም፤

የሚሰለቸውን ሥራ መተው ትክክለኛው አማራጭ ነው፡፡

ኮሎኔል ሙአመር ጋዳፊ በ1969 ሥልጣን በያዙበት ወቅት፣ እኔ በዳሬስ-ሳላም ታንዛኒያ የሶስተኛ ዓመት የዩኒቨርስቲ ተማሪ ነበርኩ፡፡ ጋዳፊ ብሔርተኛና ፓን-አረባዊ አቋም የነበራቸውን የግብፁን ኮሎኔል ጋማል አብዱል ናስርን ዱካ የተከተሉ መሪ ነበሩና ሥልጣን መያዛቸውን በደስታ ተቀበልነው፡፡ ሆኖም ብዙም ሳይቆይ ዩጋንዳ ድረስ የዘለቁ ችግሮች ከጋዳፊ ጋር አብረው አቆጠቆጡ፣ ጥቁር አፍሪካም ስጋት ገባው፡፡ የሚከተሉት ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡-

ድጋፍ ለኢዲ አሚን ኢዲ አሚን በ1971 ሥልጣን የጨበጡት በእንግሊዝና በእስራኤል ድጋፍ ነበር፤ ሁለቱም ሀገራት ኢዲ አሚን ለእነርሱ መጠቀሚያነት የሚስቸግር እውቀት የላቸውም ብለው አስበው ነበር፡፡ ግና አሚን ታንዛኒያን ለመውጋት የጦር መሳሪያ ግዢ ጥያቄ ለእንግሊዝና ለእስራኤል አቅርበው ጥያቄያቸው ውድቅ በመደረጉ በደጋፊዎቻቸው ላይ ተነሱባቸው፡፡ እንደአለመታደል፣ ጋዳፊ አስቀድመው ስለዩጋንዳ በቂ መረጃ ሳያሰባስቡ ዘለው ለአሚን ድጋፍ ማድረግ ጀመሩ፡፡ ይህንንም ያደረጉበት ምክንያት አሚን ‹‹ሙስሊም›› ስለነበሩ እና ዩጋንዳም ሙስሊሞች በክርስቲያኖች ‹‹ይጨቆኑባት›› የነበረች ‹‹ሙስሊም ሀገር›› በመሆኗ ነበር፡፡ ኢዲ አሚን ከሕግ አግባብ ውጭ አያሌ ሰዎችን ገድለዋል፤ ጋዳፊም በእነዚህ ስህተቶች እጃቸው አለበት ተብለው አብረው መነሳታቸው አልቀረም፡፡ በ1972ና 79፣ እኛ - የዩጋንዳ ብሔራዊ ነፃ አውጪ ግንባር - ኢዲ አሚንን ባጠቃንበት ወቅት፣ ጋዳፊ ለአሚን ድጋፍ ለመስጠት የሊቢያ ወታደሮችን ላኩ፡፡ ይታወሰኛል - በ1979 በምባራራ ሳለን የሊቢያ ቦምብ ጣይ አውሮፕላን (‹‹Tupolev Tu-22››) ሊያጋየን ሙከራ ሲያደርግ፡፡ አብራሪዎቹ የታቀደላቸውን ኢላማ በትክክል ለመምታት በሚያስችላቸው ቅርበት መብረር ባለመቻላቸው እና ፈርተውም ስለነበር የተሸከሙት ቦምብ የኋላ ኋላ በቡሩንዲ ኒያሩባንጋ ወደቀ፡፡ ከመሬት ወደ አየር ተወንጮፊ ሚሳየሎችን በመጠቀም ከዚያም በፊት በርካታ የአሚንን ሚጎች ጥለን ነበር፡፡ አብዛኛውን ውጊያ የተፋለሙት የእኛዎቹ ታንዛኒያውያን ወንድሞችና እህቶች ነበሩ፡

፡ ብዙ ሊቢያውያን ታጣቂዎች ተማርከው በታንዛኒያ ለሊቢያ ተላልፈው ተሰጥተዋል፡፡ ይህ ትልቁ የጋዳፊ ስህተት የነበርና በዩጋንዳና በምስራቅ አፍሪካ ላይ የተቃጣ ግልፅ ወረራ ነበር፡፡ የአፍሪካ አንድነት መንግስት ይመስረት የሚል አቋም በጋዳፊ የተፈፀመው ሁለተኛው ትልቅ ስህተት ከአፍሪካ ሕብረት የተለየ አቋም በመያዝ፣ ‹‹አሁኑኑ›› አሕጉራዊ መንግሰት ይቋቋም ሲሉ ጥሪ ማቅረባቸው ነበር፡፡ ከ1999 አንስቶ ይህን አቋማቸውን አጠናክረው ገፍተውበታል፡፡ ጥቁር ሕዝቦች ሁሌም ትሁት ናቸው፡፡ ሌሎች ሰዎችን ማስቀየም አይሆንላቸውም፡፡ ይህ በራንያንኮሬ ቋንቋ ኦቡፉራ፣ ወይም በሉዎ ምዎሎ ይባላል፤ በተለይ እንግዶችን በእንክብካቤና በአክብሮት መያዝ እንደማለት፡፡ አንዳንድ አፍሪካዊ ያልሆኑ ባሕሎች ኦቡፉራ ያላቸው አይመስልም፡፡ የሆነ ሰው ሁለት ፀጉር ያበቀለ መሰሉን፣ ልክ የመዋዕለ-ሕፃናት ልጅ እንደሚያናግር አይነት ሲያወራ/ሲያወራት ሊመለከቱ ይችላሉ፡፡ ‹‹ይህን ማድረግ አለብህ፤ ያን ማድረግ አለብህ፣ ወዘተ፡፡›› በአጭርና በመካከለኛ ግዜ ውስጥ አሕጉራዊ መንግስት ማቋቋም አስቸጋሪ ስለመሆኑና ከዚያ ይልቅ በአፍሪካ ኢኮኖሚ ማሕበረሰብ፣ እና ከተቻለም በክልላዊ ፌዴሬሽኖች ምስረታ ላይ ማተኮር እንዳለብን ለጋዳፊ በትህትና

ለመጠቆም ሞክረን ነበር፡፡ ፡፡ ሆኖም ጋዳፊ የሚለሳለሱ አልነበሩም፡፡ የአፍሪካ ሕብረትን ሕግ ለመቀበል አሻፈረኝ አሉ፡፡ በፊት በተካሄዱ ስብሰባዎች የታዩ ርዕሶችን ወይም ውይይቶችን በጋዳፊ ዳግም ይነሱ ነበር፡፡ በሁሉም የአፍሪካ ርዕሰ-መስተዳድርች ድጋፍ ያገኙ ውሳኔዎችን ‹‹ይሽራሉ››፡፡ አንዳንዶቻችን በግልፅ የተሳሳተውን አቋማቸውን መቃወም ነበረብን፡፡ ከሌሎችም ጋር በመተባበር ምክንያት አልባውን አቋማቸውን በተደጋጋሚ ውድቅ አድርገንም ነበር፡፡ ራሳቸውን ንጉሰ ነገስት ብለው መሾማቸውሶስተኛው የጋዳፊ ስህተት በበርካታ የአፍሪካ ሀገራት የውስጥ ጉዳዮች ውስጥ ጣልቃ የመግባት አዝማሚያቸው ነው፤ ያንንም የሚያደርጉት ከእነዚያ ሀገራት አንፃር ሊቢያ ያላትን መጠነኛ ገንዘብ በመጠቀም ነበር፡፡ አንዱ ጉልህ ምሳሌ ከጥቁር አፍሪካ ባሕላዊ መሪዎች - ንጉሶች፣ የበላይ አለቆች ወዘተ - ጋር የነበራቸው ቁርኝት ነው፡፡ የአፍሪና አንድነት መንግስት እቅዳቸውን የአሕጉሪቱ የፖለቲካ መሪዎች ውድቅ በማድረጋቸው፣ የፖለቲካ መሪዎቹን አልፈው ከእነዚህ ንጉሶች ጋር ለመስራትና ምኞታቸውንም እውን ለማድረግ አብረው ለመስራት አስበው ነበር፡፡ በፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ውስጥ ተሳትፎ በሚያደርግ በማንኛውም የዩጋንዳ ንጉስ ላይ እርምጃ

ሊወሰድ እንደሚችል ጋዳፊን በአዲስ አበባ አሳስቤያቸው ነበር፤ ለዚያም ምክንያቱ የንጉሶቹ ፖለቲካዊ ተሳትፎ ከሕገ መንግስታችን ጋር የሚቃረን ስለነበር ነው፡፡ በተጨማሪ፣ በሕብረቱ በነበሩን ስብሰባዎቻችን ላይ ንግግር ያደረጉ ንጉሶችን (ባሕላዊ መሪዎችን) የሚያጣቅሱ ሁሉም የአፍሪካ ሕብረት መዝገቦች እንዲወገዱ በአዲስ አበባ ሀሳብ አቅርቤ ነበር ምክንያቱም መሪዎቹ በመድረኮቹ የተገኙት ትክክለኛውን መንገድ ሳይከተሉ በጋዳፊ ጋባዥነት ነበርና፡፡የደቡብ ሱዳን ስቃይ በቸልታ መመልከትአራተኛውና ለተራዘመ ግዜ በስቃይ ካሳለፈው የደቡብ ሱዳን ሕዝብ ጋር የተያያዘው ትልቁ ስህተት የተፈፀመው በአብዛኞቹ የአረብ መሪዎች ነው፤ በከፊልም በኮሎኔል ጋዳፊ፡፡ የዚያች ሀገርን ጥቁር ሕዝብ ስቃይ በርካታዎቹ የአረብ ሀገራት በዝምታ አልፈውታል ወይም ደግፈውታል፡፡ ይህ ርትዕ-አልባነት በእኛ እና በአረቦች መካከል ሁሌም ውጥረትና ፍጭት ይፈጥር ነበር፡፡ ያም ሆኖ ግን፣ ጋዳፋና ፕሬዝዳንት ሆስኒ ሙባረክ የሱዳን ሕዝበ-ውሳኔ ከመካሄድ ጥቂት አስቀድመው ወደዚያው በመጓዛቸውና በቆይታቸውም የሪፈረንደሙን ውጤት ፕሬዝዳንት ኦማር አል-ባሽር እንዲያከብሩ ምክራቸውን በመለገሳቸው አክብሮቴን

እገልፅላቸዋለሁ፡፡ሽብርተኝነት፡- አንዳንዴ ጋዳፊና የተቀሩት የመካከለኛው ምስራቃዊ አክራሪዎች፣ የሚዋጉት ለትክክለኛ ጥያቄ ሆኖ ሳለ እንኳን፣ ራሳቸውን በበቂ መልኩ ከሽብርተኝነት አያርቁም፡፡ ሽብርተኝነት ወታደራዊና ወታደራዊ ያልሆኑ ኢላማዎችን ሳይለዩ የጅምላ ጥቃት መሰንዘር ነው፡፡ ከጥቁር አፍሪካ አብዮተኞች በጣም የሚለዩት የመካከለኛው ምስራቃዊ አክራሪዎች፣ ጠላትን እየተዋጋህ እስከሆነ ድረስ ማንኛውም የትል መንገድ ተቀባይነት አለው ብለው የሚያምኑ ይመስላሉ፡፡ ለዚያም ነው አውሮፕላኖችን የሚጠልፉት፤ በመጠጥ ቤቶች ውስጥ ፈንጂ የሚጠምዱት ወዘተ፡፡ ስለምን ፈንጂ በመጠጥ ቤቶች ውስጥ ይጠምዳሉ?በፀረ-ቅኝ-አገዛዝ ትግል ከአረቦች ጋር አብረን ነበርን፡፡ ሆኖም፣ የጥቁር አፍሪካ የነፃነት ንቅናቄዎች የተጓዙት ከአረቡ በተለየ መንገድ ነበር፡፡ የጦር መሳሪያዎቻችንን ተጠቅመን የተዋጋነው ወታደሮችን ነበር፤ በመሰረተ-ልማቶች ላይ ጥቃት እንሰነዝር ነበር፡፡ የጅምላ ዘዴዎች የመካከለኛው ምስራቅንና የአረቡን ዓለም የመነጠል አዝማሚያ አላቸው፡፡ በእነዚህ አካባቢዎች ያሉ አክራሪዎች፣ የጅምላ ጥቃት ስንዘራ ዘዴያቸውን ቢያጤኑት መልካም ይሆን ነበር፡፡እነዚህ ናቸው የተወሰኑት ከጋዳፊ ጋር የተያያዙ አሉታዊ የሆኑ ነጥቦች፡፡ በጋዳፊ የተወሰዱት እያንዳንዳቸው እነዚህ ነጥቦች አሳዛኝና አላስፈላጊ ነበሩ፡፡ ያም ሆኖ ጋዳፊ በርካታ አዎንታዊ ነጥቦች ነበሯቸው - ለሊቢያ፣ አፍሪካና ለሶስተኛው ዓለም መልካምነት የተደረጉ፡፡ አንድ በአንድ እዳስሳቸዋለሁ፡፡ጋዳፊ ብሔርተኛ ናቸውጋዳፊ ከተፅዕኖ የተላቀቀ የውጭ ፖሊሲ ተግባራዊ አድርገዋል፣ እንዲሁም የውስጥ ፖሊሲዎችን፡፡ ነፃ አስተሳሰብ የሚያራምዱ መሪዎችንና አሻንጉሊቶችን የሚመርጡ የሚመስሉትን የምዕራቡን ሀገራት አቋም ልገነዘብ አልቻልኩም፡፡ ለማንኛውም ሀገር አሻንጉሊቶች ጥሩ አይደሉም፡፡ ከ1945 አንስቶ ከሶስተኛው ዓለም ወደ አንደኛው ዓለም ሽግግር ያደረጉ አብዛኞቹ ሀገራት ነፃ አስተሳሰብ ያራመዱ መሪዎች የነበሯቸውና ያሏቸው ናቸው፡- ደቡብ ኮርያ (ፓርክ ቹንግ-ሂ)፣ ሲንጋፖር (ሊ ኩዋን ይው)፣ ሕዝባዊት

በዮዌሪ ሙሰቪኒ (ፕሬዝዳንት)

እኔ የማውቀው ጋዳፊ

ወደ ገፅ 18 ዞሯል

ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም፣

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን

መስራች ናቸው

ዩቬሪ ሙሴቪኒ፣የኡጋንዳ

ፕሬዚዳንት ናቸው

Page 4: Awramba Times Issue 161 Megabit 24

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 161 ቅዳሜ መጋቢት 24 2003ፊ ቸ ር4

በአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንት የዓለም አቀፍ መረጃ ፕሮግራሞች ቢሮ በቅርቡ ባሰራጨው የሜዲያ ሕግጋትን የሚያብራራ አንድ መድብል የፕሬስ ነፃነት

ምንነትን አስመልክቶ በመግቢያው ላይ ቀጥሎ ያለውን አስፍሯል፡፡ “Freedom of the press” is not just a slogan. Nor it it is only for journalists. The right to receive and Impart information is a universal one.” ወደአገርኛው ቋንቋ ስንመልሰው፡- ‹‹የፕሬስ ነፃነት›› እንዲሁ ባዶ መፈክር ወይም የጋዜጠኞች ጉዳይ ብቻም አይደለም፡፡ መረጃን የመቀበልና የመስጠት ሁሉን አቀፍ መብት እንጂ›› የሚል ትርጉም ይሰጠናል፡፡ ከተቋቋመ የሶስት ትውልድ ዕድሜ ሊደፍን በጣት የሚቆጠሩ ዓመታት የቀሩት ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት በታሪኩ ለመጀመያ ጊዜ በሕትመት ዋጋ ላይ ያደረገው ከፍተኛ የሕትመት ዋጋ ጭማሪ አንድምታ ግን በፈታኝ ሁኔታዎች ውስጥ አልፈው ለአንባቢው ሲደርሱ ለቆዩት የግል ጋዜጦች ‹‹የፕሬስ ነፃነት ባዶ መፈክር ብቻ አይደለም›› የሚለው አጽንኦት ምጸት እንደሆነባቸው እየገለጹ

ይገኛል፡፡ ድርጅቱ የሁልጊዜ ደንበኞቹ የሆኑት አሳታሚዎች እስከ አምሳ በመቶ ስለሚደርሰው የዋጋ ጭማሪው ሰበር በሆነ ማስታወቂያው በገለጸበት ወቅት በአሳታሚዎች በኩል ቀርቦ የነበረው ‹‹የዋጋ ጭማሪው ከፍተኛ በመሆኑ አንዳንድ ሁኔታዎች እስኪስተካከሉ የሶስት ወር ጊዜ ይሰጠን›› ጥያቄ ውድቅ ተደርጓል፡፡ እንዲያውም የአታሚ ድርጅቱ አመላለስ ድማሜን እንደፈጠረባቸው ገልጸዋል፡፡ ብርሃንና ሰላም ‹በጠየቃችሁት መሰረት የእናንተን የደንበኞቼን ችግር ከግምት ውስጥ በማስገባት ጭማሪውን በአንድ ሳምንት አራዝመነዋል፡፡...›› ካለ በኋላ በዓለም ገበያ ላይ የጋዜጣ ማተሚያ ወረቀት ዋጋ መጨመርን፣ የብር የውጭ ገንዘብ ግዥ ዋጋ ቅናሽ መደረጉንና የመሳሰሉትን በምክንያትነት ዘርዝሯል፡፡ በአሳታሚዎቹ በኩል የቀረበውን ለጭማሪው ሰበብ የሆኑ ጉዳዮች እና ተያያዥ ሁነቶች ለማስተካከል ይሰጠን የተባለ የጊዜ መራዘም ጥናቱ ከአንድ ሰዓት የዘለለ ጊዜ እንደማይወስድ በመግለጽ ውሳኔው ይገባኝ የማይጠየቅበት (extra Judiciary) መሆኑን በገደምዳሜ አስታውቋል፡፡ ውሳኔው በዓለም ላይ እጅግ

ዝቅተኛ የሆነ መጠን የጋዜጣ ስርጭት ካላቸው አገራት አንዷ በሆነችው ኢትዮጵያ ውስጥ አደገኛ እንደሆነ ማስጠንቀቂያዎች እየተሰጡ ቢሆንም በመንግስት በኩል ሁኔታውን ለማስተካከል ስልቶችን ከመንደፍ ይልቅ ጨምዳጅ ሕጎችንና ስልታዊ ጫናዎችን እያሳረፉ የመቀጠሉ አካሄድ ሊሻሻል አልቻለም ለሚለው መከራከርያ ዓይነተኛ ማሳያ ተደርጎ ተወስዷል፡፡ ካለው ሁለንተናዊ ችግርና ከዜጎች የመግዛት አቅም ጋር ሲነጻጸር የጭማሪው ከፍተኛነት ሁሉንም ወገን ሊያሳስብ የሚገባ ቢሆንም በመንግስት በኩል የዳር ተመልካች የመሆን አዝማሚያ በግልጽ እየታየ እንዳለ ይገለጻል፡፡ በተለይ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትር ዴኤታ የሆኑት አቶ ሽመልስ ከማል በጉዳዩ ዙርያ አንድ የግል ጋዜጣ ላቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ የሰቱበት መንገድ ከላይ የቀረበውን መከራከርያ የሚያጎላ ሆኗል፡፡ ‹‹ከ60 እስከ 70 በመቶ የማስታወቂያ ገቢ ያላቸው ጋዜጦች አይጎዱም፡፡ ስለዚህ ሁሉም ሰው የሚያነበው ጋዜጣ ማሳተም ያስፈልጋል፡፡›› ካሉ በኋላ በአገሪቱ የሚታተሙት ጋዜጦች ለአንድ የተወሰነ የፖለቲካ አመለካከት ያለው ወገን ብቻ ያነጣጠሩ በመሆናቸው ብዙ ሰው እንዲያነባቸወ ከፈለጉ ሚዛናዊነት ይጠበቅባቸዋል...››

ሲሉ ደመደሙ፡፡ ሚኒስትር ዴኤታው ባነሱት ሃሳብ ውስጥ የተጠቀሱት የማስታወቂያ ተጠቃሚነት፣ ለሁሉም ሰው ተደራሽ የሆኑ ጋዜጦች መኖርና ‘የፖለቲካ ወገንተኝነት’ ጉዳይ ከነባራዊው እውነታ ጋር ፈጽሞ የማይጣጣም አባባል ተደርጎ ተወስዷል፡፡ እንዲያውም የዋጋ ጭማሪውን ከስልታዊ የፕሬስ አፈና ጋር የሚያያይዙ ወገኖች የተለያዩ ስነ አመክንዮዎችን በመደርደር ‹‹...ሳታመኻኝ ብላኝ›› ይሉትን ብሂል አስታውሰዋል፡፡ ድርጅቶች ለግል ፕሬሶች ማስታወቂያ ለመስጠትም ሆነ ፕሬሶቹ የሕትመት ቅጂያቸውን መጠን ለማሳደግ የሚያደርጉት ጥረት የሚመክነው በመንግስት በኩል የግሉን ፕሬስ ጠላት አድርጎ ከመፈረጅ እንደሆነ የሚገልጹት የነጋድራስ ጋዜጣ ስራ አስኪያጅ የሆኑት ጋዜጠኛ አያሌው አስረስ ናቸው፡፡ ‹‹በመንግስት ሜዲያዎች በኩል ሲካሄድ የቆየውና አሁንም በስፋት የሚስተዋለው ለአንድ አገር እድገት መሰረት የሆነውን የዕውቀት መዋቅር የሚመሰርቱ የነፃ ፕሬስ ውጤቶችን ሳያሰልሱ የመርገም የተሳሳተ አስተሳሰብ ነው፡፡›› የሚሉት አያሌው ችግሩ ከጋዜጣ ስራዎች ውጭ እንደ መጽሐፍት ባሉ የዕውቀት

በውብሸት ታዬ

በውብሸት ታዬ

ይግባኝ የሌለው ቅጣት

የ1985ቱ የፕሬስ ሕግ ከወጣ በኋላ በነበሩት ጥቂት ዓመታት ከ380 በላይ ጋዜጦችና መጽሔቶች የሕትመት ፈቃድ ወስደው የነበረ ቢሆንም በፈታኝ ምዕራፎች የተከፋፈለው ጉዟቸው ብዙዎቹን ከዘርፉ ውጭ አድርጓቸዋል፡፡ ቁጥራቸው ቀላል የማይባል ባለሙያዎች ተሰደዋል፡፡ ስልታዊ ጫናዎች፣ የሕገ መንግስቱን ድንጋጌዎች የሚጣረሱ አዋጆችና ተከታታይ የዋጋ ጭማሪዎች፤

ጭልጭል የሚለውን የኢትዮጵያ ነፃ ፕሬስ ህልውና ወደማሕደሩ እየከተቱት ነው!

Page 5: Awramba Times Issue 161 Megabit 24

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 161 ቅዳሜ መጋቢት 24 2003

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

ፊ ቸ ር 5

ማስተላለፊያዎች ላይ ሳይቀር በመጫኑ የዜጎች የዕውቀት ምንጭ እየነጠፈ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ መንግስት የግሉ ፕሬስ የተጋረጠበትን ከፍተኛ ዋጋ ለመቋቋም የማይችለው ሁሉም ሰው ሊያነበው የሚችለው ዓይነት የሕትመት ውጤት ማቅረብ ባለመቻሉ ነው የሚለው አቋሙ ግን የአገራችን ተጨባጭ ሁኔታ በዓለም አቀፉ መድረክም ሆነ ከጎረቤት የአፍሪካ አገራት ጋር ሲነጻጸር የሚያሸማቅቅ ልዩነት እንዳሉበት የዘነጋ መሆኑን የሚያሳብቅበት ነው፡፡ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት የኤሌክትሮኒክስ ሜዲያዎች እጅግ በተስፋፉበት በአሁኑ ወቅት በዓለማችን ላይ አንድ ቢሊዮን ያህል ሰዎች /ከስድት ሰዎች አንዱ አከባቢ መሆኑ ነው፡፡/ ዕለታዊ ጋዜጣ ያገኛሉ፡፡ ወደ ኢትዮጵያ ስንመጣ ግን ከመንግስ ጋዜጦች ውጪ በየዕለቱ የሚታተሙ ጋዜጦች የሌሉ ከመሆኑም በተጨማሪ የአንድ ጋዜጣ ተደራሽነት ለ14 ሺሕ ያሕል ሕዝብ /1=14,000/ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ አንጋፋው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ለሰሞኑ የማተሚያ ዋጋ መናር የቀረቡት ሰበቦች ካልተዋጠላቸው ሰዎች አንዱ ነው፡፡ ጋዜጠኛው የተያዘው አካሄድ ጭል ጭል የሚለውን ዘርፍ እስከወዲያኛው እንዳያጨልመው ያስጠነቅቃል፡፡ ‹‹ዕውቀት የመንፈስ ምግብ ነው፡፡›› የሚለው ባለሙያው የሕዝብ ቁጥራቸው ከእኛ ጋር ሊነጻጸር የማይችሉት እንደአልጄሪያ ያሉ የአፍሪካ አገራት እንኳ እስከ 150 ጋዜጦችን እንደሚያሳትሙ በማስታወስ በዚሁ ችግር ላይ የሚደረገውን ማባባስ ነቅፎታል፡፡

የወገንተኝነት ክሶችና የፕሬስ ነጻነት መርሆች

የፕሬስ ነጻነት ዕድገት የተመሰረተው የተለያዩ አመለካከቶችን በመያዝና ያለገደብ በማሰራጨት የማይገሰስ መብት ላይ ነው፡፡ የኢፌዴሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 29 ቁጥር 4 ለዴሞክራሲያዊ ስርዓት አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎች፣ ኃሳቦችና አመለካከቶች በነፃ መንሸራሸራቸውን ለማረጋገጥ ሲባል ፕሬስ በተቋምነቱ የአሰራር ነፃነትና የተለያዩ አስተያየቶች የማስተናገድ ችሎታ እንዲኖረው የሕግ ጥበቃ ይደረግለታል ይላል፡፡ ቁጥር 6 ደግሞ ይህ መብት ገደብ ሊጣልበት ስለሚችልበት ሁኔታ የሚገልፀው እጅጉን ትኩረት በሚስብ መንገድ ነው፡፡ ‹‹...የሃሳብና መረጃ የማግኘት ነፃነት በአስተሳሰባዊ ይዘቱና ሊያስከትል በሚችለው አስተሳሰባዊ ውጤት ሊገታ አይገባውም በሚል መርሕ ተመስርቶ በሚወጣ ሕግ ብቻ ...›› /ሰረዝ የተጨመረ/ ይላል፡፡ ይህ ድንጋጌ ለፕሬስ ነፃነቱ ዋስትና ሆኗል?፣ በተከታታይ የወጡት ሕጎች ይህንን የሚያጠናክሩ ነበሩ ወይስ አደጋ ላይ የሚጥሉ? የሚሉ የሕግ ባለሙያዎች ዛሬ ለተደነቀረው አደጋ መሰረቱ መጣል የጀመረው ቀስ በቀስና ከሕገ መንግስቱ ድንጋጌዎች ጋር የሚጣረሱ አዋጆችን አከታትሎ በማውጣት እንደሆነ ይጠቁማሉ፡፡ ወደተጣራሽ ሕጎቹ ዝርዝሮች ከመገባቱ በፊት የፕሬስ ነጻነት በጎለበተባቸው አገራት ያሉ ታላላቅ ሚዲያዎች ተሞክሮ ሊፈተሽ እንደሚገባው ይመከራል፡፡ በምዕራቡ ዓለም ትልቁ የመነጋገሪያ አጀንዳ የሚዲያ ወገንተኝነት ነው፡፡ ሚዲያው ወገንተኛ አለመሆኑ ትክክለኛና ያልተዛባ መረጃ ለአንባቢ/አድማጭ ለማቅረብ ወሳኝ ቢሆንም የተወሰነ ወገን ላይ ትኩረት አድርገው የሚሰሩ ሜዲያዎች በመንግስት በኩል የሚታዩት ለዴሞክራሲያዊ ስርዓት ማበብ እንደ ግብአትነት ነው፡፡ አሜሪካንን በምሳሌነት ከሚጠቀሱት አገራት አንዷ አሜሪካ ናት፡፡ ሲ.ኤን.ኤን፣ ዘ ዎል ስትሪት ጆርናል፣ ቺካጎ ትሪቢዩንና አሶሺየትድ ፕሬስ ለዓመታት የሪፐብሊካን ፓርቲ ልሳኖች ተርገው ይታያሉ፡፡ እነዚህ የሚዲያ ተቋማት አቋማቸውን በግልፅ ይፋ አድርገው በሚሊዮን ለሚቆጠሩ ተደራሾቻቸው መረጃዎችን ያቀብላሉ፡፡ ምርትና አገልግሎታቸውን የሚያስተዋውቁት ከፍተኛ አቅም ያላቸው ኩባንያዎችም ለእነዚህ ሚዲያዎች ማስታወቂያዎቻቸውን በመስጠት በተዘዋዋሪ ለሚደግፏቸው ፓርቲዎች አጋርነታቸውን ያሳያሉ፡፡ ሚዲያዎቹም ፕሮግራማቸውን ሲቀርጹ ተደራሽ የሚሆኑለትን የሕብረተሰብ ክፍል/Targeted Audience/ አስቀድመው ያጠናሉ፡፡ ይህ በሚሆንበት ጊዜ ሁሉ ግን የሙያውን የስነ ምግባር መርሆች በጥብቅ እንደሚከተሉ ይገለጻል፡፡ ከአቋማቸው እንዳፈነገጡ ሲታወቅም የማስታወቂያ

ውል ያላቸው ድርጅቶች ውላቸውን ያቋጣሉ፡፡ ለዚህ ዋነኛ ምሳሌ ሆኖ የሚጠቀሰው የ‹‹ABC›› እህት ሚዲያ የሆነው ‹‹ኤር አሜሪካ›› ነው፡፡ ይህ የሚዲያ ተቋም ተደራሽ የሆነለትን የሕብረተሰብ ክፍል አስተሳሰብ የሚቃረን ፕሮግራም አስተላልፏል ተብሎ በመታመኑ ከጥቂት ዓመታት በፊት በአሜሪካ ትልልቅ ኩባንያዎች ጋር ቅራኔ ውስጥ መግባቱ አልቀረም፡፡ በዚህም መሰረት wall-mark, Exxon Mobile, Microsoft, Bank of America, Fed-Ex, MC Donald’s, SONY, Johnson & Johnson የመሳሰሉ ድርጅቶችን ጨምሮ ከ90 በላይ ኩባንያዎች የማስታወቁያ ውላቸውን መሰረዛቸው ይታወሳል፡፡ የእነዚህ ታላላቅ ሚዲያ ተዋናዮች የሚዲያ ተቋሙ ከሚደግፈው የፖለቲካ ፓርቲ ጋር የጠበቀ ቁርኝት አላቸው፡፡ በሚዲያዎቹ የሚዘጋጁ የቶክ-ሾው ዝግጅቶች ላይ ከፓርቲው በስተጀርባ ያሉ ወሳኝ ተቋማትን የሚመሩ ባለሙያዎችን በመጋበዝ ሰፊ ሽፋን ሰጥተው ያስተናግዷቸዋል፡፡ Fox News በተደጋጋሚ የUSA Next ተቋም ኃላፊዎችና መስራቾችን የዕለት ተዕለት እንቀስቃሴ ሲያስተዋውቅ ነበር፡፡ USA Next የፖለቲካ ወትዋቾች (lobbyists) ቡድን ነው፡፡ ይህ ቡድን የሪፐብሊካን ፓርቲ የፖለቲካ ስትራቴጂዎችና ተመራማሪዎች እ.ኤ.አ ከ1991-2004 እንዲሁም ከ1985-2004 በታተሙ 389 የአሜሪካ ጋዜጦች ላይ ባደረጉት ጥናት፤ ከቀረቡት ዘገባዎች ውስጥ 9.6% እና 14.7% በመቶ ብቻ በሪፐብሊካን እጩ ፕሬዚዳንቶች ላይ አዎንታዊ ዘገባዎች ተገኝተውባቸዋል፡፡ በሌላ በኩል ሪካርዶ ፑግሊሲ የተባለ (የማሳቹሴት ኢንስቲትዩት ቴክኖሎጂ) ተመራማሪ) እ.ኤ.አ ከ1946 እስከ 1997 በታተመ የኒውዮርክ ታይምስ ርዕሰ አንቀጾች ላይ ባደረገው ጥናት ጋዜጣው የዴሞክራት ፓርቲ ወገንተኛ ሆኖ አግኝቶታል፡፡ በምዕራቡ ዓለም የሚገኙ ታላላቅ ሚዲያዎች የፖለቲካ ወገንተኝነት በምርጫ ወቅት ጎልቶ እንደሚወጣ ይነገራል፡፡ በ2008 በተደረገው የአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ወቅት ከ240 በላይ የአሜሪካ ታዋቂ ጋዜጦች ኦባማን እንደሚደግፉ በግልፅ አቋማቸውን አራምደዋል፡፡ ወደ አገራችን ተጨባጭ ሁኔታ ስንመለስ በአሜሪካ ያሉ ትልልቅ ኩባንያዎች በሚዲያው ላይ የሚያሳድሩት ዓይነት ተጽዕኖ ጨርሶ እንደሌለ በዘርፉ ባለሙያዎች የሚገለጽ ሲሆን ድርጅቶች ምርትና አገልግሎታቸውን በግል ጋዜጦች ላይ እንዳያስተዋውቁ ጫና የሚያሳድሩ ቅስቀሳዎች በመንግስት መገናኛ ብዙኃን በሰፊው ይስተናገዳሉ፡፡ የአንድን ወገን ፖለቲካዊ አስተሳሰብ ማራመድ ነጻ ፕሬስ ጠንካራ መሰረት ተጥሎባታል በምትባለው እንግሊዝ ሳይቀር በስፋት እንደሚታይ የሚገልጹት ደግሞ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነትና ኮሙኒኬሽን መምሕር የሆኑት ረ/ፕሮፌሰር መኩርያ መካሻ ናቸው፡፡ እነዚህ ጋዜጦች የሌበር ወይም ኮንሰርቫቲቭ ፓርቲ ደጋፊ ሆነው እንደሚጽፉ ካስታወሱ በኋላ የሙያው ስነ ምግባር እስከተጠበቀ ድረስ የዚህ ዓይነቱ ወገንተኝነት በመርሕ ደረጃ ችግር እንደሌለበት ይገልጻሉ፡፡ ‹‹ይሁንና...›› ይላሉ ፕ/ር መኩርያ ‹‹...በአገራችን ከ1985ቱ የፕሬስ ሕግ መውጣት በኋላ ብዙ የሕትመት ውጤቶች ለንባብ መብቃታቸው ትልቅ ጅምር ቢሆንም የግሉና የመንግስት ፕሬሶች በየፊናቸው የፖለቲካ ፕሮፓጋንዳ የማጫፈር አዝማሚያ ውስጥ ገቡ፡፡ ይህ ደግሞ መስመሩን በመሳት ከሙያው ስነ ምግባር ጋር የሚጣረሱ አስተሳሰቦችን ለማራመድ መንገድ ይከፍታል፡፡

ከ 1985 - 2003 ዓ.ም የብርሃንና ሰላም ሰበር መግለጫ ለደንበኞቹ ሲነገር ትግበራው የሚያስከትለው ውጤት ድርጅቱ የሚሰጠው አገልግሎት ዕውቀትን ከማንሸራሸር ጋር የተያያዘ መሆኑን ታሳቢ ያደረገ አይመስልም ተብሏል፡፡ ለዘርፉ ባለሙያዎች ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ይህን ያህል የሕትመት ዋጋ ጨምሬያለሁ፤ አራት ነጥብ የሚል ዓይነት መሆኑ የተከታታይ ዓመታቱን ሁለንተናዊ ጫናዎች በዚህ መንገድ ለመቋጨት ያለመ አድርገው እንዲያስቡ አድርጓቸዋል፡፡ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት በ1985 ዓ.ም የወጣውን የፕሬስ አዋጅ ተከትሎ በተከታታይ በነበሩት አምስት ዓመታት ብቻ ከ380 በላይ የሚሆኑ የግል

ጋዜጦችና መጽሔቶች የሕትመት ፈቃድ ተሰጥቷቸዋል፡፡ በየጊዜውም አዳዲስ ሕትመቶችን መመልከት የተለመደ ሆነ፡፡ የሆነ ሆኖ ግን መጠነ ሰፊ የማንገላታት ዘመቻው የጀመረው ወዲያው እንደነበር በወቅቱ በጋዜጦች ላይ ይሰሩ የነበሩ ጋዜጠኞች ያስታውሱታል፡፡ ከጊዜ በኋላ ግን በመንግስት በኩል የሚወሰደው እርምጃ ሕገ መንግስታዊ ድንጋጌዎችን በሚጣረሱ አዋጆች በመተካት እንደተቀየረ ይገለጻል፡፡ የአሁኑ ስልት ደግሞ መንግስት እነዚህ ሁሉ ጫናዎች ያላረኩት መሆኑን ያመላክታል ተብሏል፡፡ የፕሬስ አሰራርን ይጎዱታል ከሚባሉት አዋጆች አንዳንዶቹ እጅግ የተለጠጡና ለትርጉም በመጋለጥ ፈጽሞ የማያሰሩ ተብለው ይነቀፋሉ፡፡ የ2001ዱ የፀረ ሽብርተኝነት አዋጅ በአንቀጽ 6 ሽብርተኝነትን ስለማበረታታት በሚል ከዘረዘራቸው ሁኔታዎች ተደራሲዎቹ/አንባቢቹ/ የሚያነቡት ነገር ‹‹... ድርጊቱን እንዲፈጽሙ ወይም ለመፈፀም እንዲዘጋጁ ወይም እንዲነሳሱ በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ መንገድ የሚያበረታታቸው ወይም በማናቸውም ሌላ ሁኔታ የሚገፋፋቸው እንደሆነ አድርገው ይረዱታል ተብሎ ሊገመት የሚችል መልዕክት ... ከ10-20 ዓመት ፅኑ እስራት ...፡፡›› / ሰረዝ የተጨመረ/ ይላል፡፡ ‹‹በማናቸውም ሌላ ሁኔታ፣ የሚገፋፋቸው አድርገው ይረዱታል፣ እንዲሁም ተብሎ ሊገመት የሚችል›› የሚሉትን ሶስት ሐረጎች የሚያነቡ ሰዎች ‹‹ማናቸውም ሌላ ሁኔታዎች ምንድናቸው? አንባቢዎቹ የሚገፋፋቸው አድርገው መረዳታቸው ከግላዊ እምነታቸውና የፖለቲካ አስተሳሰባቸው የሚመነጭ ከመሆኑ አንፃር ይህ ሃሳብን የመረዳት መጠን ሌላኛውን ወገን እስከ 20 ዓመት የሚያስቀጣው በምን ስነ አመክንዮ ነው? ሊገመት የሚችል የሚለውስ በአንድ የወንጀል ድርጊት ውስጥ በርካታ ተገማች ሁኔታዎች መኖራቸው ወደውጤት ያመራሉ እንጂ ሊገመቱ መቻላቸው በራሱ (ደግሞ ገማቹስ ማነው?) እንዴት ጥፋተኛ ያደርጋል?...›› ብለው መጠየቃቸው አልቀረም፡፡ የዚህን ሕግ ፍሬ ነጥቦች ‹‹በአስተሳሰባዊ ይዘቱና ሊያስከትለው በሚችለው አስተሳሰባዊ ውጤት ሊገታ አይገባውም›› ከሚለው የሃሳብና መረጃ የማግኘት ነፃነት መርሕ ተነስቶ የተደረገ ገደብ ነው ሊባል አይችልም የሚሉ ወገኖች የ2002ቱን የመገናኛ ብዙኃን የአዘጋገብ ስነምግባር እና በሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አማካይነት የመገናኛ ብዙኃንን አስመልክቶ በ2000 ዓ.ም የወጣውን የመገናኛ ብዙሃንና የመረጃ ነፃነት አዋጅን በማስታከክ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ሲቀርቡበት ከነበሩት ቅሬታዎች ሁለቱ ብቻ እንኳ ለሂደቱ ማሽቆልቆል እንደምሳሌነት ይጠቀሳሉ፡፡ ባለስልጣን መ/ቤቱ በየጊዜው የሚወጣ የህትመት ሥራ ወይም የዜና አገልግሎት ሥራ ለመሥራት የምዝገባ የምስክር ወረቀት እንዲሰጥ በአዋጅ የተሰጠውን ስልጣን በመጠቀም ባዘጋጀው የማመልከቻ ቅጽ ተራ ቁጥር 6 ላይ የፕሬስ ሕጉን አንቀጽ 6 (ዋና አዘጋጅ ስላለው ስልጣን፣ ሊኖረው ስለሚገባ ችሎታና የሕግ ተጠያቂነት) በማጣቀስ የሕትመት ባለቤቶች ዋና አዘጋጅና ም/ዋና አዘጋጅ መሆን አይችሉም ይላል፡፡ በማመልከቻ ቅጽ ቁጥር 9 ላይ ደግሞ የፕሬስ አዋጅ አንቀጽ 7/3/ን (በየጊዜው የሚወጣ የሕትመት ሥራን የሚሰራ ኩባንያ በተመሳሳይ ዘርፍ ካለ ሌላ ኩባንያ ውጤታማ ቁጥጥር ሊኖረው እንደማይገባ የሚደነግገውን) በማጣቀስ አመልካቹ ድርጅት መስራት ያለበት

በመጽሔት ወይም በጋዜጣ ላይ ብቻ መሆኑን በመግለጽ ቀደም ሲል የነበረውን በአንድ ስያሜ መጽሔትና ጋዜጣ የማሳተም መብት ይቀለብሰዋል፡፡ የመገናኛ ብዙኃንና የጋዜጠኞች የምርጫ አዘጋገብ የሥነ ምግባር ደንብ ሲወጣ ግን በአንፃራዊ ሁኔታም እንኳ የተሻሉ ሊባሉ ከሚችሉት የባሰና ጉዞው የኋልዮሽ እንደሆነ ያመለከተ እንደሆነ የአንቀጾቹን የተወሰኑ ክፍሎች በማየት ብቻ ማረጋገጥ እንደሚቻል ይነገርላቸዋል፡፡ አንቀጽ 7 ቁጥር 2 ‹‹የሕዝብ መገናኛ ብዙሃን በርዕሰ አንቀጾቻቸው ላይ ማንኛውንም የፖለቲካ ፓርቲ የሚደግፍ ወይም የሚቃወም ሃሳብ ወይም አስተያየት ማቅረብ የለባቸውም፡፡›› ይላል፡፡ እዚህ ላይ የሕገ-መንግስቱ አንቀጽ 29 ቁጥር 4 ለዴሞክራሲያዊ ስርዓት አስፈላጊ የሆኑ ሃሳቦችና አመለካከቶች በነፃ እንዲንሸራሸሩ የሚደነግግ ሲሆን ፕሬስ በተቋምነቱ የተለያዩ አስተያየቶች የማስተናግድ ችሎታ እንዲኖረው ስለሚደረግለት የሕግ ጥበቃ ይገልፃል፡፡ እዚህ ላይ አንድ የሕግ ባለሙያ ሁኔታውን በንጽጽር ሲያቀርቡ እንደሚከተለው ብለዋል፡፡ ‹‹አንድ የፖለቲካ ፓርቲ ፍትሐዊ የኃብት ክፍፍል እንዲፈጠር የሚያስችል የኢኮኖሚ ፖሊሲ ይቀርጻል፡፡ የመገናኛ ብዙሃኑም ይህ ፖሊሲ ለዴሞክራሲያዊ ስርዓቱና ለአገር ይጠቅማል ብሎ በማመን በርዕሰ አንቀጹ ‹ይህ የፖሊሲ ሃሳብ ሊዳብር ይገባል፣ ለአገር ይጠቅማል› የሚል አስተየየት ሊሰነዝር ይችላል፡፡ በሌላ በኩል አንዱ ፓርቲ በአንድ ጉዳይ ላይ አሉታዊ ውጤት ሊያስከትል የሚችል አስተሳሰብ ሲያራምድ መገናኛ ብዙሃኑ ‹ይህ የፖለቲካ አካሄድ አገር ስለሚጎዳ ሊታረም ይገባዋል፡፡› ሊሉ ይችላሉ፡፡ ሚዲያ መረጃ መስጠት፣ ማስተማርና ማዝናናት የሚሉ ተልዕኮች ያሉት ሲሆን የፕሬስ ሕጉ መግቢያ ደግሞ አጋላጭ መረጃዎችን ሳይቀር እንዲያሰራጩ ያበረታታቸዋል፡፡ አንቀጽ 4 -ንዑስ አንቀጽ 3/ሐ ‹ማንኛቸውም የመንግስት አካላት መገናኛ ብዙሃኑ የሕዝብን አስተያየት በመቅረፅ ሂደት የመሳተፍ መብታቸውን ሊያከብሩላቸው ይገባል፡፡›› ይላል፡፡ የስነ ምግባር ደንቡ በአንቀጽ 9 ቁጥር 1 የምርጫ አስፈፃሚ አካላት የኤዲቶሪያል ነፃነትን ጨምሮ የሜዲያ ተቋማትን ነፃነትና የፖለቲካዊ ወገንተኛነትን የመግለጽ መብት ማክበር ይኖርባቸዋል›› /ሰረዝ የተጨመረ/ ይላል፡፡ በአንድ በኩል የፖለቲካ ወገንተኝነት እንኳ መከበር አለበት ሲል ይሞግታል በሌላ በኩል የፖለቲካ ፓርቲን የሚደግፍ ወይም የሚቃወም ሃሳብ ወይም አስተያየት በርዕሰ አንቀጽ መቅረብ የለበትም ይላል፡፡ አንቀጽ 7 ቁጥር 6 የመገናኛ ብዙሃን ተቋማት ለሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ዕጩ ተወዳዳሪዎችና መድረኮቻቸው ፍትሐዊና ቋሚ የዘገባ ሽፋን መስጠት እንዳለባቸው ይደነግጋል፡፡ አውራምባ ታይምስ ከብሮድካስት ባለስልጣን ኃላፊዎች ገጥሟት ከነበረው ውዝግብ አንዱ ለተወሰኑ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሰፊ ሽፋን ትሰጣላችሁ (በተለይ የስምንት ፓርቲች ስብስብ ለነበረው (፣መድረክ፣) የሚል እንደነበር ይታወሳል፡፡ የጋዜጣዋ ዝግጅት ክፍል በወቅቱ ይዞት የነበረው በስነ አመክንዮ ላይ የተመሰረተ አሰራር ‹‹በእርግጥ ፍትሐዊ ሽፍን መሰጠት አለበት፤ ፍትሐዊ ማለት ግን ‹‹ለሚገባው የሚገባውን ያህል መስጠት›› ማለት እንጂ የፖለቲካ ፓርቲነት ሰርተፍኬት ስለያዘ ብቻ አንድና እኩል ሽፋን መስጠት የ‹‹ፍትሕ››ን መርሕ ማፋለስ ነው የሚል ነበር፡፡ እነዚህና መሰል

ጫናዎችን ተቋቁሞ የዘለቀው የግል ፕሬስ ግን ማንንም ያላሳመነና የተጠየቀውን የጥናት ጊዜ በገፋ መልኩ የዋጋ ጭማሪ መመርያውን ተግባራዊ አድርጓል፡፡ ይህ ደግሞ የፕሬሱን ዕጣ ፈንታ አደጋ ላይ እንደሚጥለው ብዙዎች እያሳሰቡ ይገኛሉ፡፡

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ ከትናንት በስቲያ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የኢህአዴግ መንግስት በነፃ ጋዜጦች ላይ እያደረሰ ያለውን ጫና አስመልክቶ የገለፀውም ይህንኑ ስጋት የሚያረጋግጥ ነው ተብሏል፡፡ መግለጫው ‹‹በነፃ ጋዜጦች ላይ ተገቢ ያልሆነ ክስ በመመስረት፣ራሳቸውን በራሳቸው ሳንሱር እንዲያደርጉ፣ የሕትመት ዋጋን ሆን ብሎ በማናር ገበያ ላይ ተወዳዳሪ እንዳይሆኑና እንዲከስሙ እያደረገ ነው፡፡...›› የሚል ነው፡፡ በሌላ በኩል ነፃ ራዲዮኖችና ቴሌቭዥኖች እንዲኖሩ በድረግ ፋንታ የውጭ ፕሮግራችን በመሸበብና በመሳሰሉት የዜጎችን መረጃ የማግኘት መብት እየጣሰ እንደሆነ ገልጿል፡፡ የዚህ ዓይነቶቹ መግለጫዎችና ሪፖርቶች በዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተማጋቾች በተደጋጋሚ የሚሰጡ ሲሆን በመንግስት በኩል ለእያንዳንዱ አጋላጭ ሪፖርት ማስተባበያ እየሰጡ ከመሄድ ውጪ የእምነት እርምጃ ሲወሰድ አይታይም በሚል ይነቀፋል፡፡ ‘ሂውማን ራይትስ ዎች’ የተሰኘው ዓለም አቀፍ ተቋም ከሁለት ወር በፊት ይፋ ባደረገው የዓመታዊ ሪፖርቱ ገለልተኛ ድምጾችና ተቋማት እንዲዳከሙ በማድረግ የዜጎችን መረጃ የማግኘት መብት የመገደቡ ዘመቻ እየተጠናከረ መምጣቱን አውስቷል፡፡ የዴሞክራሲ ተቋማት የሆኑት ነፃ ፕሬሶች፣ መንግስታዊ ያልሆኑ የሲቪክ ማሕበራትና የመሳሰሉት በጫና እንዲዳከሙ ከተደረገ በኋላ ተግባራዊ ገለልተኝነት የሌላቸው ተቋማትን የማደራጀት ተግባር ላይ መሰማራቱንም ጠቅሷል፡፡

የመጨረሻው ደወል? ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ከፍተኛውን የዋጋ ጭማሪ ማድረጉን ተከትሎ የመንግስት ባለስልጣናት ለስሱው ጉዳይ ያሳዩት ግዴለሽነት አሁን ያሉትን የግል ፕሬሶች ከጨዋታ ውጭ የሚያደርግ፣ ወደዘርፉ መግባት የሚፈልጉትንም ባሉበት እንዲቆሙ የሚያስገድዳቸው እንደሆነ እየተገለጸ ነው፡፡ የፍትሕ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ የሆነው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ የግል ማተሚያ ቤቶች ያደረጉትን ከ15 እስከ 20 በመቶ ጭማሪ በመጥቀስ በአንጻራዊ ደረጃ የተሻለ ቅናሽ ማድረግ የሚጠበቅበት የመንግስት ድርጅት የዚህን ያህል ጭማሪ ማድረጉ ግርምትን እንደፈጠረበት ይገልጻል፡፡ ‹‹ግድ የለም የጭማሪው አንድምታ ፖለቲካዊ አይደለም እንበል...›› ይላል ተመስገን ‹‹... እሺ ምንድነው ታዲያ?›› ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ በበኩሉ መንግስት የሰሜን አፍሪካ አገሮች ሕዝባዊ አብዮት እንቅስቃሴ በፈጠረበት ስጋት የግሉን ሚዲያ በስልት ከአንባቢው ለማለያየት ያለመ አቅጣጫ መሆኑን ይጠረጥራል፡፡አንድ ማንነታቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ ደራሲ ግን በሕጋዊ መንገድ የሚንቀሳቀሱ ጋዜጦችን በተለያዩ ጫናዎች ከገበያ ውጭ ማድረግ ቢቻልም የመረጃ ፍሰቱን ለመተካት የሚፈጠረው አዲስ ስልት ግን ‹‹የወረወርኩት አንካሴ ተመልሶ ለራሴ›› እንደሚባለው ራሱን የኃሳቡን አመንጪ እንደሚጎዳው ይናገራሉ፡፡ ‹‹በዓለም ታሪክ ውስጥ የፕሬስ አፈና በተደረገባቸው ጊዜያት ሁሉ ሰዎች ኃሳባቸውን ለመግለጽ የውስጥ ለውስጥ ጽሁፎችን ሲለዋወጡ ታይተዋል፡፡ በኢትዮጵያ አብዮት ማግስት ለሊቱን ሲበተኑ የሚያድሩ ጽሑፎች መንስኤ፣ ይዘትና ዓላማም ይኸው ነበር፡፡›› በኢትዮጵያ የነጻ ፕሬስ ታሪክ ውስጥ ዘርፉ ቁልቁል እንዲጓዝ ቢገደድም በሌሎች አገራት ግን ተገቢው ጥበቃ ስለሚደረግለት የዕድገት ሂደቱ ‹ተንገራግጮ› አያውቅም፡፡ በዓለም የነፃ ፕሬስ ታሪክ ውስጥ የማያቋርጥ እድገት ካሳዩ ዘርፎች አንዱ የሕትመት ሚዲያ እንደሆነ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ በካምብሪጅ ዩኒቨርሲቲ የዓለም አቀፍ ግንኙነትና የሶሽዮሎጂ መምህር የሆኑት ፕ/ር ጃሹዋ አላን ስለዚሁ ጉዳይ ባቀረቡት አንድ ጥናታዊ ፅሁፍ በረዥም የክ/ዘናት ፍሰት ውሰጥ ዘርፉ እየደገ ከመሄዱ በተጨማሪ እንደአውሮፓ ያሉ አገራት ደግሞ ለሶስት መቶ ዓመታት ያካሄዱትን ህዳሴ ማረጋገጥ የቻሉት የህትመቱ ሜዲያ ቁልፍ ሚና እንደነበር አስምረውበታል፡፡

በኢትዮጵያ የነጻ ፕሬስ ታሪክ ውስጥ ዘርፉ ቁልቁል

እንዲጓዝ ቢገደድም በሌሎች አገራት ግን ተገቢው

ጥበቃ ስለሚደረግለት የዕድገት ሂደቱ ‹ተንገራግጮ›

አያውቅም፡፡ በዓለም የነፃ ፕሬስ ታሪክ ውስጥ

የማያቋርጥ እድገት ካሳዩ ዘርፎች አንዱ የሕትመት

ሚዲያ እንደሆነ መረጃዎች ያመለክታሉ፡

Page 6: Awramba Times Issue 161 Megabit 24

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 161 ቅዳሜ መጋቢት 24 2003

‹የጠነከረ ህይወቱን አኗረ›/survival of the fittest/

6

ኸርበርት ሰፔንሰር የተለየ አቋም ከነበረው መምህር አባቱ ኢንግላንድ፣ ደርቢ ውስጥ ነው የተወለደው፡፡ ከዘጠኝ ልጆች ውስጥ ለጉልምስና ዕድሜ የበቃው (የተረፈው) እርሱ ብቻ ነው፡፡ ቤት ውስጥ በአባቱ አማካኝነት ነው ትምህርቱን የተማረው፤ የአጎቱ ሬቨረንድ ቶማስ ስፔንሰር እገዛም ታክሎበታል፡፡ ላይ ላዩን ሲታይ የልጅነት ዘመኑ ከጆን ስትዋርት ሚል ጋር ይመሳሰላል፤ የስፔንሰር ትምርት በይበልጥ ማቲማቲክስ እና የቴክኒክ ትምህርት ቢሆንም፡፡ ኬምብሪጅ ገብቶ የመማር ሀሳብ ነበረው፣ ነገር ግን የገንዘብ እና የሃይማኖት ስንክሳሮች ገድበውታል (የአንግሊካን ቤተክርስቲያን አባል ካልሆነ በቀር ማንም ሰው ከኦክስፎርድም ሆነ ከኬምብሪጅ ዩኒቨርስቲዎች ዲግሪ ማግኘት የማይችልበት ዘመን ነበር፡፡)

ስፔንሰር ከ1837 እስከ 1848 የባቡር ትራንስፖርት መሀንዲስ ሆኖ በቅድሚያ በለንደን እና በበርሚንግሃም፣ ቀጥሎም ለበርሚንግሃም እና ለግሎሴስተር የሬልዌይ ካምፓኒዎች ሰርቷል፡፡ ከ1848 እስከ 1853 ባሉት ዓመታት ውስጥ በጋዜጠኝነት ሙያ ቆይቷል፤ በታዋቂው የልቦለድ ድራሲ ጆርጅ ኤልየት አማካኝነት በሚዘጋጀው ‹ዌስት ሚኒስተር ሪቪው› ላይ ይፅፍ ነበር፤ ‹‹ዘ ኢኮኖሚስት›› ላይም ረዳት አዘጋጅ ሆኖ ሰርቷል፡፡

በ1853 አጎቱ ቶማስ ስፔንሰር ሲሞት ጠርቀም ያለ ሀብቱን ትቶለት ያልፋል፤ ይህም ያለምንም መዘናጋት ወደ ሥነ-ፅሁፍ ሙያ እንዲያተኩር አስችሎታል፡፡ ስፔንሰር ህልም ያለው እና ብዙ ሥራዎችን ማምረት የቻለ ፀሐፊ ነበር፡፡ ግለ-ታሪኩ እንኳን ሁለት ጥራዞችን እና ተጨማሪ 400 ሺህ ቃላቶችን የፈጀ ነበር፡፡ በ1850ዎቹ መጀመሪያ ባዮሎጂን፣ ሶሺዮሎጂን፣ ሳይኮሎጂን፣ ኤቲክስ እና ፖለተካን ወደ አንድ ጥቅልነት የማዋሃድ አስደናቂ ሀሳብ አፍልቆም ነበር፡፡ ይህ “System of Synthetic philosophy” የተሰኘ ሥራው በሰላሳ ዓመታት ውስጥ በአስር ጥራዞች ሆኖ ታትሟል፡፡ ከእኛ እያታ አንፃር፣ ዋነኛ ሥራዎቹ “Social Statics(1850)”፣ “The Man versus the State(1884)”፣ እና “The Principles of Ethics(1892-3)” የተሰኙት ናቸው፡፡ የጭንቀት ችግር ሲያጠቃው የቆየ የሚመስለው ስፔንሰር በመጨረሻ ዓመታቶቹ ለጤናው መዳከም ምክንያት የሆኑ አስቸጋሪ ጊዜትን አሳልፏል፡፡

በጥቅሉና ከፖለቲካዊ እና ማህበራዊ አስተምህሮቶቹ ጋር በተያያዘ፣ የስፔንሰር ፍልስፍና መነሻ መርሆ የአዝጋሚ ለውጥ ወይም የኢቮሉሽን እሳቤ ነው፡- እንደርሱ አጠራር ‹የቀጣይነት መርህ› ወይም ‹principle of continuity›፡፡ በባቡር መንገድ ዋሻዎች ጉፋሮ የዘመናት ቅሪት አካላት መገኘታቸው ነበር ለአዝጋሚ ለውጥ የነበረውን ፍላጎት በቀዳሚነት ያነሳሳበት፡- “the survival of the fittest” ወይም ‹‹የጠነከረ ህይወቱን አኗረ›› የሚለውን ሀረግ የቀመረው (የፈጠረው) ዳርዊን ሳይሆን እርሱ ነበር፡፡

ስፔንሰር የዳርዊንን የተፈጥሮ ምርጦሽ (natural selection) እሳቤ ይቃወም ነበር፤ በምትኩ ህይወታን (Organisms) ከሚኖሩበት አካባቢ ጋር የመላመድ ጠባዮችን በመያዝ ተከታይ ትውልዳቸው ደግሞ እነዚያን ጠባዮች

የሚወርስበትን የላማርኪያን መላምትን (በፈረንሳያዊው ዢን ባፕቲስቴ ደ ላማርክ የተጠነሰሰውን የአዝጋሚ ለውጥ ፅንሰ-ሀሳብ) ይመርጣል፡፡ ከተመሳሳይነት ወይም ቀላል ከሆነ ሁኔታ ወደ ስብጥርነት እና ውስብስብ ወደሆነ ሁኔታ መሸጋገር የሁሉም ህይወታን ተፈጥሮ እንደሆነ ስፔንሰር ያምናል፡፡ ይህ እንቅስቃሴ ወይም ሽግግር በአጠቃላይ የተፈጥሮ ጠባይ ነው፤ እናም ህብረተሰቦችም ሆነ ግለቦች በዚህ መንገድ (በአዝግሞት) ይለወጣሉ፡፡ ማህበራዊ አዝጋሚ ለውጥ እየጨመረ የሚመጣ የተወሳሰበ የትግበራ ልዩነትን በመታዘብ ከተመሳሳይ (homogeneous) ኃላ ቀር ህብረተሰቦች ወደ ውስብሰብ ስብጥሮሽ (heterogeneous) የሚደረግ የጉልብትና ወይም የእድገት ሂደት ነው፡፡

ህብረተሰቦች ከንጉሳዊ እና ወታደራዊ ወደ ኢንዱስትሪያዊ እና ትብብራዊ የመደራጀት ቅርጾች (በአዝግሞት) የመለወጥ ተፈጥሯዊ አዝማሚያ እንዳላቸው ስፔንሰር ያምናል፡፡ ነገር ግን ህብረተሰቦች፣ ወይም በውስን አግባብ ‹ህይወታን›፣ ደስታን የሚሹ - ይህም ከህመም ወይም ከስቃይ ይልቅ የተትረፈረፈ እርካታን ወይም ደስተኝነትን ለማግኘት የሚጣጣሩ (ከዚህ አንፃር ስፔንሰር ዩቲሊታሪያን ነው) - እና ይህንንም እውን ለማድረግ እርስ በርሳቸው የሚተባሩ ግለሰቦች ስብስብ እንጂ ሌለ አይደሉም፡፡ ግለሰቦች የብጥብጥ እና የጦርነት ስጋቶችን ለማስወገድ ሲሉ መተባበር ይጀምራሉ፡፡ ከመተባበር የሚገኘው ጥቅም ከጊዜ ወደ ጊዜ ይበልጥ እየተገለጠላቸው ሲመጣ የሌሎች ልዩ ግለሰባዊ ማንነትም እንዲሁ ይገለጥላቸዋል፡፡ ይህ መገለጥ ስፔንሰር ሰብዓዊ ፍጡራን አንዳቸው ለአንዳቸው አላቸው ብሎ በሚያስበው ተፈጥሯዊ የመተዛዘን ስሜት እየታገዘ ‹‹የእኩል ነፃነት ሕግ›› ወይም “Law of equal freedom” ለተሰኘው መሠረታዊ ሕግ እውቅና እንዲሰጡ ይመራቸዋል፡፡ (ምንም እንኳን ይህ ሕግ የሞራል ሕግ ወይም የጥንቃቄ ምሳሌያዊ ገለፃ አልያም ገላጨ-ተፈጥሮ ሕግ ስለመሆኑ ስፔንሰር ሙሉ ለሙሉ ግልፅ ባይሆንም)፡፡ ሁሉም ሰው የሌን ሰው ተመሳሳዩን የማድረግ እኩል ነፃነት አስካልጣሰ ድረስ የፈቀደውን የማድረግ ነፃነት እዳለው ይህ ሕግ ያስቀምል፡፡ የስፔንስር የአዝጋሚ ለውጥ ፅንሰ-ሀሳብ የሰው ልጅን የመደራጀት እድገት ለመግለፅ የቀረበ ቢመስልም የታሪክ ፍልስፍና ጭምር ሆኖ መስራቱ የሚሰመርበት ነው፡፡ ህብረተሰቦች ከወታደራዊ ወደ ኢንዱስትሪ፣ ከኋላቀር ወደተሻለ፣ ከአረመኔያዊነት (barbarism) ወደ ሥልጣኔ ያድጋሉ፡፡

የእያንዳንዱ ግለሰብ የእኩል ነፃነት ሕግን መሠረት ያደረገ እድገት ቀስ በቀስ ሰብዓዊ ህይወት ከአካባቢው ጋር ሙሉ ለሙሉ እንዲላመድ ያደርጋል፤ በዚህም የተነሳ የሁሉም ደስተኝነትን ያመጣል፡፡ ታሪክ የመሻሻል ሂደት ነው፤ ነገር ግን የአዝጋሚ ለውጡ ሂደት ተፈጥሯዊ ስለሆነ ጣልቃ ልንገባበት ወይም ልንቆጣጠረው መሞከር አይገባንም፡፡ የሰብዓዊ ነፃነትን ትግበራ ተፈጥሯዊ ባልሆነ መንገድ የሚያሰናክል ማንኛውም ነገር ሰብዓዊ እድገትን የሚገድብ መሆኑ የግድ ነው፡፡ ይህም ከፖለቲካ አንፃር አነስተኛ ወይም (በእንቅስቃሴው) ዝቅተኛ የሆነ መንግስትን ያመለክታል፡፡ ከኢኮኖሚክስ አንፃር ደግሞ “laissez-faire” የተሰኘውን አስተምህሮት

ያመለክታል፡፡ - መንግስታት የጥበቃ እና ከጥቃት የመከላከል ትግበራዎችን ብቻ በመከወን ግለሰቦች ጣልቃ ሳይገባባቸው ወይም ቁጥጥር ሳይደረግባቸው የተቻለውን ያህል ከፍተኛ ነፃነት እንዲኖራቸው ሊተውዋቸው ይገባል፡፡

ስፔንሰር እንደሚያስበው፣ የግለሰቦች ነፃነት መለካት ያለበት እየኖሩ ባሉበት የመንግስት አደረጃጀት ፀባይ ወይም ተፈጥሮ ሳይሆን እነርሱ ላይ በሚጭነው የግደባ መጠን ነው፡፡ ነፃነቱ በመንግስት ድርጊት የተጣሰበት ማንኛውም ሰው መንግስትን ችላ የማለት ወይም እንደሌለ የመቁጠር መብት አለው፡፡ ሕግ የግለሰቦችን የፈቀዱትን ሁሉ የማድረግ ነፃነት ሸርሻሪነቱ የማይካድ በመሆኑ በተቻለ መጠን ትንሽ ወይም አነስተኛ ሕግ መኖር አለበት፡፡ ለሰው ልጆች የመተባበር እና የፈጠራ ችሎታዎች ሙሉ ለሙሉ መውጣት ምስጋና ይግባና፣ ከጊዜ በኋላ ሕጎች ከነጭራሹ አስፈላጊ የማይሆኑበት ሁኔታ ላይ ይደረሳል፡፡ ሆኖም በዚህ ጊዜ ውስጥ ሥራ አጡን መደገፍ ስንፍናን እንደማበረታታት ነው፤ ትምርት፣ ኢኮኖሚያዊ ቁጥጥር እና ህሙማንን እና ችግረኞችን መንከባከብ በመንግስት የሚተገበሩ አይሆኑም፤ በፋብሪካ ውስጥ የንፅህና ቁጥጥርም ሆነ የደህንነት መጠበቂያ ቁሶችን ጥቅም ላይ የማዋል የመሳሰሉ ነገሮችን በተመለከተም ቢሆን በኢንዱስትሪው ላይ መንግስታዊ ቁጥጥር ሊኖር አይገባም፡፡ ብቃት የለሹን እና ሰነፉን ከብቃት መጓደል እና ከስንፍና የተነሳ ከሚደርሱበት ነገሮች ለመጠበቅ የሚደረግ ተግባር ሊኖር አይገባም፡፡ ትጉህ እና ስኬታማዎቹ በራሳቸው ጥረት የሚገባቸውን ያገኛሉ፤ ደካማው የተፈጥሮ ነገር ነውና ወድቆ ይቀራል፡፡

ስፔንሰር መጀመሪያ አካባቢ መሬት በመንግስት ባለቤትነት መያዝን

ማ ስ ታ ወ ቂ ያ

የጫጩት ማስፈልፈያ ማሽኖችን

ኢንኩቤተሮችን

የፖለቲካ ፈ ላ ስፎች

መጠናቸው ከትንሽ እስከ ትላልቅ •ማለትም ባለ 50፣100፣200፣300፣400፣500... •ወዘተ እንቁላል በመያዝ ጫጩቶችን ማስፈልፈል የሚችሉ የክልል ደንበኞች ሙሉ ክፍያ •በአድራሻችን ከላኩ ወይም በአካል ከከፈሉ በሚኖሩበት ከተማ ሆነው ማሽኑን የሚረከቡበትን ሁኔታ እናመቻቻለን፡፡ በብዛት ለሚያዙ የዋጋ ቅናሽ አለን•

ሻያ ኤሌክትሮ መካኒካል ቴክኖሎጂ ኃ/የተ/የግ/ማህበር

በተመጣጣኝ ዋጋ በነጠላና በብዛት እናቀርባለን ይጠይቁን መጠናቸው ከትንሽ እስከ ትላልቅ ማለትም

ስልክ 0911 69 31 02/0913 54 87 21/

ኢያን አዳምስ እና አር. ደብሊው. ዴይሰን በጋራ ባሰናዱት “FIFTY MAJOR POLITICAL THINKERS” መፅሐፋቸው

ከቀደምት አንስቶ እስከ ቅርብ ጊዜ ካሉት ውስጥ አምሳ የፖለቲካ ፈላስፎችን በመምረጥ ለዓለም አስረክበው ያለፏቸውን

ፖለቲካዊ እሳቤዎች በዝርዝር አዋቅረው አቅርበዋቸዋል፡፡ እኛም ለአንባቢ በሚያመች መልኩ እንዲህ አቅርበናቸዋል፡፡

በግዛው ለገሠ

ኸርበርት ስፔንሰር (1820-1903)ሲሆን እነዚህን አስተምህሮቶች ትቷቸዋል፡፡ የእርሱ ‹ማህበራዊ ዳርዊኒዝም› በ19ኛው ክፍለዘመን መጨረሻ ለተነሳውና ቲ.ኤች. ግሪን ይበልጥ አቀንቃኙ በመሆን ለሚታወቅበት ‹አዲስ› ሊበራሊዝም ዋነኛ ቀስቃሽ ከነበሩት ውስጥ ነው፡፡

ስፔንሰር በዘመኑ በኢንግላድ፣ በአውሮፓ እና በአሜሪካ እጅግ ታዋቂ ፀሐፊ ነበር፡፡ እራሱ ዳርዊን፣ ጆርጅ ኤልየት፣ ቶማስ ካርላይል እና ቲ.ኤች. ሀግዝሌይ በመሳሰሉ አስተያየታቸው በሚከበርላቸው አያሌ ሰዎች ከፍተኛ ቦታ የተሰጠው ነበር፡፡ ሆኖም ህልመኛ የፍልስፍና አካሄዶቹ ወጥነት የጎደላቸውና አንዳንዴም በተራ ስህተት የተሞሉ ስለመሆናቸው መካድ የማይቻል ነው፡፡ ፍልስፍናው ከጠቅላላ እውቀት እና ከልክ ባለፈ በራስ መተማመን አማካኝነት የመጣ እንደሆነ ቢገለፅ ኢ-ፍትሃዊ አይሆንም፡፡ ወደ ኢንዱስትሪያዊነት እየተለወጠች በነበረችው ደርቢ መወለዱና በቴክኖሎጂ መማሩ በደካማው ላይ ለሚደረግ የጠንካራው ያልተገደበ ብዝበዛ ፅንሰ-ሀሳባዊ አክብሮት ወይም ተቀባይነት የመስጠት ፕሮጀክት የነበረው የኢንዱስትሪ አብዮቱ ልጅ ተደርጎ እንዲታይ ያደርገዋል፡፡ (የእርሱ በድን በሃይጌት መካነ መቃብር ከካርል ማርክስ መቃብር ፊት ለፊት መቀበሩ የሚያስገርም ነው፡፡)

የተወሰኑ የሊበርታሪያን (በዜጎች ህይወት ላይ የመንግስት ጣልቃ ገብነት እጅግ ዝቅተኛ ይሁን የሚለው የሊበርታሪያኒዝም ተከታዮች) ወይም ‹ኒው ራይት› እሳቤዎች ተጠቃሾች - በተለይም ሮበርት ኖዚክ - እጅጉን ያነሱት ነበር፡፡ ሆኖም በአጠቃላይ ስፔንሰር ከታሪክ አንፃር ትኩረት የሚሰጣቸው ቢሆኑም ሥራዎቹ ፋሽን ያለፈባቸው ጉልህ የቪክቶሪያ ዘመን ሰው ነው፡፡

“nationalisation” እና ሁል-አቀፍ ተሳታፊነትን ይደግፍ ነበር፤ ነገር ግን ወደኋላ ዓመታቱ ወጣት ለውጥ ናፋቂነት እየጨመረ ለመጣው መራር እና ጨለምተኛ ወግ አጥባቂነት ቦታ ሲለቅና ተግባራዊነታቸው የማይሆን

Page 7: Awramba Times Issue 161 Megabit 24

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 161 ቅዳሜ መጋቢት 24 2003

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

7

የ1997 ዓ.ም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ የሀገራችንን የፖለቲካ አየር በውጥረት የሞላ ነበር፡፡ በከተማውም ሆነ በገጠሩ ድብልቅልቅ ያለ ሁኔታ ይታያል፡፡ ተስፋና ፍርሀት፣ ሕልምና ቅዥት፣ ድርድርና ውዝግብ፣ ጉጉትና ሰቀቀን፣ ፅናትና መልመጥመጥ (አድር ባይነት)፣ ብቻ በጥቅሉ ምን የማይታይ፣ ምን የማይሰማ ጉድ ነበር? በዚሁ ወቅት ለቃለ-ምልልስ በተያዘልኝ ቀጠሮ መሠረት የማስታወሻ ደብተርና የድምፅ መቅጃ መሣሪያዬን አንግቤ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ፣ በኢኮኖሚክስ ዲፓርትመንት መምህር ከሆኑት ዶ/ር ጌትነት አለሙ ቢሮ ተገኝቻለሁ፡፡ ዶ/ር ጌትነት ላነሳሁላቸው ኢኮኖሚ-ነክ ጥያቄዎች ተራ በተራ ምላሽ ከሰጡ በኋላ ከወቅቱ የሀገሪቱ የፖለቲካ ትኩሳት ጋር በማያያዝ ላቀረብኩት ጥያቄ ሲመልሱ ‹‹ወይ ወደመልካም አስተዳደር ወይ ወደመጥፊያችን የምንሄድበት መንታ መንገድ ላይ ቆመናል›› ነበር ያሉት፡፡

በእርግጥ መምህሩ እንደጠቆሙት ወደየትኛው አቅጣጫ እያመራን መሆናችንን ለመገንዘብ ከዚያ በኋላ የተከተሉት ጥቂት ወራት ብቻ በቂ ነበሩ፡፡ እለት ከእለት የኢትዮጵያ ሰማይ ጠቆረ፡፡ ፍርሀት፣ ሽብርና ሀዘን ነገሰ፡፡ የተስፋው ጀምበር ከሰመ፡፡ የእኚህ መምህር አባባል ግን አሁን ደረስ በሕሊናዬ ያቃጭላል፡፡ ከዚያን ጊዜ ወዲህ በሀገራችን የሚካሄዱትን ድርጊቶች ስታዘብም ይኸው ቃል ይታሰበኛል፡፡ ‹‹ወይ ወደመልካም አስተዳደር ወይ ወደመጥፊያችን የምንሄደበት መንታ መንገድ ላይ ቆመናል፡፡›› የመምህሩን ምላሽ ምሁራዊ አስተያየት ብቻ ሳይሆን ፖለቲካዊ ትንቢት ሆኖ አየዋለሁ፡፡

በምርጫው መምከን ሳቢያ ተስፋዎቻችን ተሰናክለዋል፤ ህልሞቻችን ጨንግፈዋል፡፡ የዲሞክራሲ ተስፋችንን አርቀን ቀብረነዋል፡፡ በድህረ ምርጫው ገዥው ግንባር ኢህአዴግ በውድድሩ የተሸነፈበትን ምክንያት በመገንዘብ በአፀፋው በሶስት አካላት ላይ ግልፅና ስውር ጫናውን አሳርፏል፡፡ በምርጫው

እንድሸነፍ ያደረጉኝ ናቸው ያላቸውን አካላት አበጥሮ ለይቷል፡፡ ከለየ በኋላም በዝምታ ሊያልፋቸው አልፈቀደም፡፡ በእነዚህ አካላት ላይ ጠንካራ በትርና ክንዱን አሳርፏል፡፡ እነዚህ ሶስት ኃይሎች የተቀናጁ የቃዋሚ ፓርቲዎች፣ የሙያና የሲቪል ማህበራት፣ እንዲሁም ነፃ ፕሬሶች ናቸው፡፡ ከእነዚህ ሶስት አላት ፍፁም መዳከም በኋላ ነው ‹‹አውራ ፓርቲ›› የሚለው አዲስ ዜማ የተለቀቀው፡፡

ተቃዋሚ ፓርቲዎች ምንም እንኳ የራሳቸው ችግር የነበራቸው መሆኑ ባይካድም ከውስጥና ከውጭ በተለያየ መልኩ እንዲመቱና እንዲበተኑ ተደርጓል፡፡ የዶ/ር መረራን አባባል ልዋስና፣ የተቃዋሚው ስብስብ ሲቻል ‹‹ባሞሌ›› ሳይቻል ‹‹በዱላ›› ተፈትኗል፡፡ የገዥው ግንባር ኢህአዴግ ስትራቴጂ እራሱን በማጠናከር ብቻ ሳይሆን ሌሎችን በማዳከም ላይ እንደነበር ባለፉት ዓመታት የታዘብናቸው በርካታ ሂደቶች አረጋግጠዋል፡፡ የተቃዋሚው ጎራ ጉልበቱን እንዲያጣና አቅሙ እንዲዳከም አያሌ እሾህ እና ጋሬጣዎችን በመደርደር ሰፊው ጎዳና ለእራሱ ለገዥው ግንባር፣ አቀበትና ቁልቁለቱ ደግሞ ለተቃዋሚዎች እንዲሆን አድርጓል፡፡

በሌላ በከል በምርጫው ተሳትፎ ሕዝቡን በማንቃትና በማስተማር ጠቃሚ ድርሻ የነበራቸው የሙያ ማህበራት፣ እንዲሁም የሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብት ተቋማት ቀጣዩን በትር አስተናግደዋል፡፡ ‹‹ዜጎችን ስለዲሞክራሲያዊ መብቶቻቸው ማስተማር የመንግስት ሚና ነው›› በሚል መርህ እነዚህ አካላት ከውጭ የሚያገኙትን የፋይናንስ ድጋፍ በማገድ እጅና እግራቸው ተሸብቧል፡፡ ተጠናክረው ሊጓዙና ለዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ሊያበረክቱ ይችሉ የነበሩ ተቋማት ፈፅሞ እንዲሽመደመዱና ከጨዋታ ውጪ እንዲሆኑ ተደርጓል፡፡ ብዙዎቹም ከዲሞክራሲ ተቋምነት ወደ ስንዴ ሰፋሪነት ተሸጋግረዋል፡፡

በግንቦት 97 ድህረ ምርጫ ነፃው ፕሬስ ወደበለጠ ጨለማ ገብቷል፡፡ ኢህአዴግ በነፃው ፕሬስ ላይ ቂም

ቋጥሮ እንደቆየ ይታወቃል፡፡ የጋዜጠኞች መታሰር፣ መሰደድና ከሥራ መፈናቀል በሰፊው የታየ ክስተት ነበር፡፡ የነፃው ፕሬስ አባላት በምርጫው ማግስት አበባ እናያለን፣ ማርና ወተት እንጠጣለን ስንል ጠብቀን እሬት የተጋትንበት ዘመን ነው፡፡

ከሰሞኑ በማተሚያ ቤት ላይ የታየው ጣሪያ የነካ (45 በመቶ በላይ) የማተሚያ ቤት ጭማሪ የዚሁ ጫና ቀጣይ ሂደት ሆኖ ይታያል፡፡ ነፃውን ፕሬስ ከስሩ ነቅሎ ለመጣል የተደረገ ስልት ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም፡፡ ቀድሞም ቢሆን ጋዜጦቹ የሚንቀሳቀሱት በውስን የገንዘብ አቅም ነው፡፡ ጋዜጠኞች የአነስተኛ ደመወዝ ተከፋይ ናቸው፡፡ በሽያጭና ስርጭት ችግሮች፣ እንዲሁም በማስታወቂያ እጦት ምክንያት የጋዜጠኞች ደመወዝ ሳይከፈል የሚዘገይባቸው በርካታ ሁኔታዎች ይታያል፡፡ የሀገራችን ጋዜጠኞች ይህን ሁሉ ፈተና ተሸክመው ነው ሙያዊ ግዴታቸውን ለመወጣት የሚሞክሩት፡፡ ይህ የ45 ከመቶ የህትመት ጭማሪ ግን ነፃውን ፕሬስ ወደመጨረሻው ግብዓተ መሬቱ የሚሸኝ እርምጃ ነው፡፡

የሕትመት ዋጋ ጭማሪው የጋዜጠኞችን ሰርቶ የመኖር መብት የሚጋፋ ብቻ አይደለም፡፡ የሕትመት ዋጋ ጭማሪው የሕገመንግስቱን አንቀፅ 29 ‹የአመለካከትና ሀሳብን በነፃ የመያዝና የመግለፅ መብት› ሙሉ ለሙሉ የሚገድብ ጭምር ነው፡፡ በሕገመንግስቱ አንቀጽ 29 ንዑስ ቁጥር (3) ላይ ‹‹የፕሬስና የሌሎች መገናኛ ብዙሃን እንዲሁም የሥነ-ጥበብ ፈጠራ ነፃነት ተረጋግጧል›› የሚል ቢሆንም ሕገመንግስቱ የሰጠው ነፃነትና መብት ተግባራዊ ሊሆን የሚችልበት መንገድ እየተዘጋ ሄዷል፡፡

ገዥውን ግንባር ኢህአዴግን የምንወቅሰው በያዛቸው ዓላማና ፕሮግራሞች ብቻ አይደለም፡፡ ኢህአዴግን የምንወቅሰው አቋሜ ናቸው ሲል ያስቀመጣቸውን ፕሮግራሞች መፈፀም ባለመቻሉም ጭምር ነው፡፡ ለምሳሌ በኢትዮጵያ የዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ጉዳዮች በሚል ሰነዱ የሚዲያውን

ሚና አስመልክቶ የሚከተለውን ሀሳብ አስፍሯል፡፡

‹‹በሚዲያ መቅረብ ያለበት መረጃ አገሪቱ በምትከተላቸው መሠረታዊ አቅጣጫዎች ዙሪያ የሚፈፀሙትን ተግባራት የሚመለከት ብቻ መሆን የለበትም፡፡ በእርግጥ ዋናው ጉዳይ ሕዝቡ የራሱን ሕይወት ለመምራት፣ በአገሩ ጉዳይ ላይ በብቃት ለመሳተፍ የሚያስችለው መረጃ የማግኘቱ ጉዳይ ነው፡፡ በመሆኑም ዋናው ለሕዝብ መቅረብ ያለበት መረጃ የአገሪቱንና የሕዝቡን እድል በሚወሰኑት የልማትና የዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ እንቅስቃሴዎች ላይ ያተኮረ መሆን አለበት፡፡ ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ ህይወቱን በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ መንገድ የሚነኩ የውጭ ዜናዎችን፣ መረጃዎችንና ሌሎችንም መረጃዎች ማግኘት መቻል አለበት፡፡ ወቅታዊና ትክክለኛ መረጃ ያለው ዜጋ የዲሞክራሲ ትልቅ እሴት ነውና ሚዲያ እንደዚህ ዓይነት ዜጋ እንዲኖር በማድረግ ረገድ የላቀ ሚና መጫወት ይገባዋል፡፡›› (ገፅ 111-112)

ከላይ እንደተጠቀሰው መንግስት በሚዲያው ላይ አለኝ የሚለው አቋም ብዙም የሚያጣላ አይደለም፡፡ ነገር ግን ይህን ሀሳብ ያሰፈረው ቪ.ኦ.ኤን የሚያፍን፣ ዶቸ ዌሌን በአየር ሞገድ የሚዘጋ፣ ድረ-ገጾች በሀገር ውስጥ እንዳይታዩ የሚያግድ፣ በጋዜጠኞች ላይ ቀጥተኛና ተዘዋዋሪ ጫናዎችን የሚያሳድር መሆኑ በሚባለውና በሚሰራው መካከል ምን ያህል ልዩነትና ቅራኔ ያለ መሆኑን የሚያንፀባርቅ ነው፡፡

በሰሞኑ የህትመት ዋጋ ጭማሪ 24 ያህል አሳታሚዎች ተሰባስበው በችግራቸው ላይ እየመከሩ መሆናቸው ተገልጿል፡፡ ዛሬ እነሆ የሀገራችን ፕሬስ በገደል አፋፍ ላይ ቆሞ ይገኛል፡፡ ‹‹ፕሬስ ከሌለው አገር እና መንግስት ከሌለው አገር የሚለውን ሳነፃፅር የኋለኛውን እመርጣለሁ›› ያለው ማን ነበር? ለመሆኑ የሀገሪቱ የጋዜጠኞች ማህበራትስ ምነው ድምፃቸው ጠፋ?

የመጋቢት ወር ካቀፋቸው ሰላሳ ቀናት ውስጥ በአንዱ፣ የቀትር አጋንንት ለክፎኝ ይሁን ሌላ፣ ብቻ እስከዛሬ ድረስ ስውር በሆነብኝ ምክንያት አንድ የቀን ጨለማ ቤት ውስጥ ዘልዬ ገባሁ፡፡ አገባቤ ቅጥ አምባር የተለየው በመሆኑ ጨለማዊ ስህተት ፈፀምኩኝ፡፡ ሳላውቅ ገበር ምጣድ የሚያክለው እግሯን የረገጥኩባት ሴት “ከብት” ብላ ሰደበቺኝ፡፡ እናደደቺኝ፡፡ ስድቡ አልነበረም ያናደደኝ፡፡ ቃሉ ነው፡፡ ቃሉ በተለያየ መንገድ ሊተረጎም ይችላል፡፡ “የጋማ ከብት ነኝ ወይስ የቀንድ ከብት?” ብዬ አቧራ ላጨስ ባይዳዳኝም፣ የስድቡ አለመብራራት ቅሬታ ፈጥሮብኝ ነበር፡፡

ሁልጊዜ አንድ አውሮፕላን ከሰማይ እየምዘገዘገ መጥቶ ምድር ላይ ሲከሰከስና ዱቄት ሲሆን፣ ፈጣሪ ምን ዓይነት ‹‹ስሜት›› ይሰማው ይሆን? ያለቅሳል? ዝናል?... እያለኩ ማንም የማይመልሰውን ጥያቄ እጠይቃለሁ፡፡

አሁንም፣ መንግስት በጨለማ ሳይሆን በድፍረትና በጠራራ ፀሐይ የሚፈፅማቸው ጉድፎች አማካኝነት ዜጋው ሲሰቃይ ምን ይሰማው ይሆን? እውነት ግን እረፍት ይሰጣል? ጥሩ እንቅልፍ ያስተኛል? በአሁን ሰዓት የተለያየ መጠንና መልክ ይዞ በየአውራጃው የሚስተጋባው መራራ ጩኸት፣ ሙታኖች እንኳን የሚሰሙት ነው፤ አይደለም አውቆ የተኛ መንግስት ቀርቶ፡፡

መንግስት የሚለው ቃል ‹‹አያገባኝም፣ አልሰማም፣ ያልኩትን ብቻ ተቀበሉ...›› ተብሎ የተተረጎመ እስኪመስል ድረስ የሚታየውና የሚሰማው ነገር ሁሉ አላምር፣ አልስብ እያለ መጥቷል፡፡

እኔ በበኩሌ የህትመት ዋጋ ከሚንር ይልቅ የኮንዶም ዋጋ ቢጨምር ይሻለኛል፡፡ ማንበብና ማወቅ ግን ከጤናም በላይ ነው፡፡ ኤድስ ቢያጠቃኝ ያን ያህል ሳልደናበር መኖር እችል ይሆናል፡፡ አንዱም በሽታውን ሳልፈራ እንድኖር የሚያደርገኝ ነገር ከጋዜጣና ከመፅሔት፣ እንዱሁም ከመፅሐፍ የሚገኘው የጥንቃቄ ስልት ነው፡፡

የማያነብ ህብረተሰብ ባለማንበብ ከሚያድርበት የፀና በሽታ የሚድነው በሃይማኖት ኃይል ሳይሆን በማንበብ ‹‹ብቻ›› ነው፡፡ በባቢሎን ወንዞች አጠገብ እንዳቆጠቆጠች የወይራ ዛፍ ከዓመት ዓመት ለምልሞ መኖር የሚቻለውም

በማንበብ ብቻ ነው፡፡ መንግስት ‹‹ሊያብራራው››

የሚገባው ጉዳይም ይኼ ነው፡፡ እንዲሁ በደፈናው ከብት ብሎ እንደሴቲቱ ያልተብራራ ስድብ መለጠፍ ከንቱነትን ነው የሚያሳየው፡፡ በህትመት ውጤቶች ላይ የወረደው ‹‹መዓት›› ሲብራራ የሚሰጠው ትርጉም ምንድነው? መንግስት የጋዜጦቹ ትችትና ነቀፌታ እየወጋው ስለተቸገረ ነው ቁጣ ያዘነበባቸው? በርግጥም ጎርፉ የተለያዩ ጋዜጦችን ጠራርጎ አባይ ወንዝ ውስጥ (ስደት ውስጥ) እንደሚከታቸው፣ የትኛውም የንባብ ትንበያ ባለሙያ ያውቀዋል፡፡

በርግጥም እንደ ቀንድ ከብት፣ በትችታቸው የሚዋጉ ጋዜጦች አሉ፡፡ ጋዜጦቹ ቀንድ እንዲያበቅሉ ያደረጋቸው መንግስት እንደሚለው፣ ውስጣቸው አምቀው የያዙት የተለየ አጀንዳ ሳይሆን፣ የራሱ የመንግስት ያለተገባ አካሄድ ነው፡፡

የዜጎችን መራራ ጩኸት የሚያስነብብ ጋዜጣ ለመንግስት የተሞረደ ቀንድ ሆኖ ሊገኝ ይችላል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ የህብረተሰቡን ጩኸት የማይዘግብ ጋዜጣ ለህብረተሰቡ ሁነኛ ቀንድ ነው፡፡ በመሐል የሚፈጠረውን አጣብቂኝ ለማስታረቅ ደግሞ ጋዜጦቹ ወደ ህብረተሰቡ መወገናቸው አይቀርም፡፡ በዚያ ላይ ደግሞ መንግስትን የመወገን ግዴታ ሳይሆን የማጋለጥ፣ የመተቸትና አካሄዱን እንዲያስተካክል የማድረግ ግደታ ነው በጫንቃቸው ላይ የተጫነው - ጋዜጦቹ፡፡

ከሁሉም በፊት አንድ ጋዜጣ

የሚቋቋምበትን መሠረታዊ ሁነቶች ማጥናት ያስፈልጋል፡፡ በትክክለኛው ኤዲቶሪያል ፖሊሲ የሚመሩ ጋዜጦች የመንግስትን የካቢኔ አወቃቀር፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ አቀማመጡን ሌት ተቀን እያወደሱ ይኖራሉ ማለት የ21ኛው ክፍለ ዘመን የዋህነት ነው፡፡ ስለዚህ መንግስት በሚሰራው መልካም ሥራ እንደሚመሰገነው ሁሉ ካጠፋም ‹‹ተው ዜጋውን አታስለቅስ›› ማለት የማይቀር ዕዳ ነው፡፡

በጣም የሚያሳዝንና ‹‹ዋስትና›› የሌለበት መጥፎ ዘመን ነው - አሁን የቆምንበት ዓመት፡፡ በ1927 ቤታችንን ባነፅንበት መዶሻ፣ በ1928 የካቲት 12 ቋቅ እስኪለን ተጨፍጭፈንበታል፡፡ የራሴ የሆነ ነገር አንድ ቀን እንደሚነሳብኝና ሊያጠፋኝ እንደሚችል ያወቅሁበት አጋጣሚ ነው - የካቲት 12/1928፡፡

ወደድኩም ጠላሁም፣ አስነጠሰኝም አሳለኝም አሁን መቀመጫውን አራት ኪሎ ያደረገው የኢህአዴግ መንግስት የኔ መንግስት ነው፡፡ የኔ ያልኩት መንግስት ሁልጊዜ ጥሩ እንደማይሆን ይገባኛል፡፡ ትላንት በፃፍኩበትና ‹‹የኔ›› ባልኩት ጋዜጣ እንደምጠፋ አምናለሁ - ልክ እንደመዶሻው!

አንድ ጋዜጣ ሲዘጋ አብሮ ተዳፍኖ የሚቀረው የጋዜጣው አምድ ብቻ አይደለም፡፡ በጋዜጣው አማካኝነት በልተው የሚያድሩ ሰዎች አሉኮ! የእነሱ ህይወት ከንቱ ሆኖ መቅረት አለበት? በዚያ ላይ ጋዜጦቹ የመንግስትን ‹‹ሸክም››

እንዳቃለሉ ኢህአዴግ መዘንጋት የለበትም፡፡ ወይስ ሁሉም ሰው የመንግስት መሥሪያ ቤቶች ደጅ ላይ መኮልኮል አለበት? በሌላ በኩል ደግሞ አንድ ጋዜጣ ሲዘጋ መንግስት በማተሚያ ቤቱ በኩል የሚደርስበት የኢኮኖሚ ክስረት እንዳለ መዘንጋት የለበትም፡፡ ወይስ ጋዜጦቹ በህትመት ህይወት ኖረው ‹‹ከሚተቹኝ›› ይልቅ በነሱ መሞት ምክንያት የሚደርስብኝ ኪሳራ ይሻለኛል ብሎ አስቦ ይሆን?... ‹‹መብራራት›› አለበት፡፡ የጋማ ከብት ነው የቀንድ ከብት?

‹‹ሕገ-ልቦና›› ማለት ማንኛውም ዓይነት የሃይማኖትም ሆነ ሌሎች ሕጎች ሳይረቀቁ በፊት ሰዎች ልቦናቸው በሚያዛቸው ሕግ የሚመሩበት ነው፡፡ በሕገ-ልቦና እንኳን ኢትዮጵያውያን ቅን ሰዎች ነበሩ፡፡ አስቡት፤ የዛኔ መግደልና መዝረፍ እንኳን ሐጢያት ናቸው ተብሎ በሕግ አለተደነገጉም ነበር፡፡ ማንም የልቦናውን ፈቃድ ተከትሎ የፈለገውን የማድረግ መብት ነበረው፡፡ በጊዜው ምንም ዓይነት የሚያስርም ሆነ የሚፈታ ሕግ ሳይኖር ኢትዮጵያውያን ‹‹ጨዋ›› መሆናቸው ያስገርማል፡፡ ሕግ የለም ብለው አያስፈራሩም፤ አይፈሩም፤ አንዱ አንዱን አያስለቅስም ነበር፡፡

ቅንነትና ጨዋነት በሕገ-ልናቦ የሚፈርስ በ21ኛው ክፍለ ዘመን የሚገነባ ካብ አይደለም ለካ! የሰው ልጅ ቅን መሆን ከፈለገ የተፃፈ ሕግ እንደማያስፈልገው፣ የባዕዳን ታሪክ ሳይሆን የራሳችን ታሪክ ይነግረናል፡፡ ያለፈው የኢትዮጵያዊነት ባህልና ወግ ሙሉ ለሙሉ ባይሆንም በግርድፉ ሊቆነጥጠንና ስርዓት ሊያሲዘን ይገባል፡፡

መጓጓዣዋን አህያ አድርጋ በነበረችው የያኔዋ ኢትዮጵያ እና መመላለሻዋን አውሮፕላን ባደረገችው የዛሬዋ ኢትዮጵያ መሐል ትልቅ ክፍተት አለ፡፡ አሜሪካ አሊያም አውሮፓ በሮ ስለተሄደ ብቻ ቅን መሆን እንደማይቻል የሚታዩት ነገሮች ይመሰክራሉ፡፡ እነዚያ ግን ‹‹ደደብ›› ከምትባለው አህያ ጋር እየኖሩ ቅን ሆነው አልፈዋል፡፡

በስውር አጀንዳ ጋዜጣ በመዝጋት ከጋዜጠኛው ትችት መራቅ ይቻል ይሆናል፡፡ የዕውቀት ‹‹ሰዓት እላፊ››

በሰሎሞን ሞገስ

[email protected]

የነፃው ፕሬስ ሥርዓተ-ቀብር

ወደ ገፅ 23 ዞሯል

ኮሜንተሪ

በታዲዎስ ጌታሁን

ሰዓት እላፊው ይነሳ!በትክክለኛው ኤዲቶሪያል ፖሊሲ የሚመሩ ጋዜጦች

የመንግስትን የካቢኔ አወቃቀር፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ

አቀማመጡን ሌት ተቀን እያወደሱ ይኖራሉ ማለት የ21ኛው

ክፍለ ዘመን የዋህነት ነው፡፡ ስለዚህ መንግስት በሚሰራው

መልካም ሥራ እንደሚመሰገነው ሁሉ ካጠፋም ‹‹ተው ዜጋውን

አታስለቅስ›› ማለት የማይቀር ዕዳ ነው፡፡

Page 8: Awramba Times Issue 161 Megabit 24

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 161 ቅዳሜ መጋቢት 24 2003የ አቤቶ ወግ8

ወዳጄ እንዴት አሉልኝ ኑሮ እንዴት ይዞታል እኔማ ምን እሆናለሁ ጥጋቡ ሀገር ላይ ተቀምጬ፤በቀን በማታው እንደ ባውዛ የሚያበራ፣ ሌት ተቀን ከእሳት በላይ የሚሞቅ ፀሀይ መንግስት ይዤ ምን እሆናለሁ ብለሁ ነው!? ወዳጄ… እንግዲህ በፕሬስ ውጤቶች ላይ የሚደረገው ጭማሪ ዛሬ እውን ሆኗል፡፡ በእውነቱ ሌላው ሌላው ጉዳይ ሁሉ ‹ይቅርብኝ› ብሎ ሰባት ብር አውጥቶ ይህንን ጋዜጣ ለማንበብ የደፈረ ሰው እርሱ ወደፊት ጥሩው ቀን ሲመጣ ‹ብሔራዊ ጀግና› ተብሎ ኒሻን ሳይሸለም አይቀርም የሚል ጥርጣሬ በልቤ ውስጥ እየተጎማለለ ነው፡፡ ብቸኛው እና አንድ ለእናቱ የሆነው አንጋፋው… ውይ አሳነስኩት መሰል ‹አዛውንቱ› ብለው ያስተካክሉልኝ፤ (ወይ ደግሞ በጥቅሉ የእድሜ እና የማሽን ሀብታም የሆነው ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ማለትም እንችላለን) የሆነ ሆኖ የመንግስት የብቻ ልጅ ነውና ከልካይም የለበትምና ከየት ያመጣሉ ብሎ ሳይጨነቅ በጋዜጦች ላይ ወዳጅ ጠላትን ያስደነገጠ ጭማሪ አድርጓል፡፡ እውነቱን ለመናገር ጭማሪው በርካታ ደጓሚ አልባ የግል ጋዜጦችን የገንዘብ አቅም ባዶ የሚያስቀር ቢሆንም፤ ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅትን ደግሞ በብልፅግና ተወዳዳሪ የሌለው ያደርገዋል፡፡ (‹ብልፅግና› ከሚለው ውስጥ ‹ፅ› ን እንዳትገድፉ አደራ እላለሁ፡፡ ኋላ ከሰዎቼ ጠብ እንዳይመጣብኝ፡፡) በነገራችን ላይ የህትመት ዋጋ ጭማሪውን እስከዛሬ ድረስ አላመንኩትም ነበር፡፡ ትላንት የፈረንጆቹ አፕሪል አንድ ስለነበር የአውራምባ ታይምስ አሳታሚዎች ከነጭማሪው ለመክፈል ሲሄዱ የብርሃንና ሰላም ገንዘብ ተቀባዮች ‹‹አፕሪል ዘፉል›› ሊሏቸው ይችላሉ… የሚል ሚጢጢ ተስፋ ሰንቄ ነበር፡፡ ነገር ግን የማተሚያ ቤቱ ሰዎች ያለ አንዳች ርህራሄ በሁሉም ጋዜጦች ላይ ወደ ሃምሳ በመቶ የሚጠጋ ጭማሪ አድርገው ተቀብለዋቸዋል፡፡ እናም አፕሪል ዘፉል አለመሆኑን አረጋግጫለሁ!እኔ የምለው ይቺ አፕሪል ዘፉል የምትባል ነገር በቃ በኛ ሀገርም ቄጤማ ተጎዝጉዞ ከሚከበሩ በዓላት ተርታ ልትመደብ አይደለም እንዴ…? የሀገሬ ሰው መጣች አልመጣች ብሎ ወዳጁን ማስደንገጫ ተንኮል ሸርቦ እኮ ነው የሚጠባበቃት፡፡ በእውኑ በየጊዜው ኑሮ ለሚያስደነግጠው ህዝብ ይህ አይነቱ የወዳጅ አይሉት ጠላት ማስደንገጫ ደግሞ ሲጨመር ‹‹በወባ ላይ ታይፎይድ›› አይሆንበትም ትላላችሁ? ከሁሉ ግን ያሳሰበኝ፤ ከውጪ የምናስገባቸው ባህሎችም ሆኑ ምርቶች ላይ ጥንቃቄ አለማድረጋችን ነው፡፡ እናም እንደሚከተለው እመክራለሁከውጪ ባህል አታስገቡ ትምህርትም አትቅሰሙ አልልም፡፡ ነገር ግን እላለሁ… ቅኝቱን ወደ ሀገረሰብ መቀየር ተገቢ ነው፡፡ ‹ወፍ እንደ ሀገሯ ትጮሀለችና!› ኧረ ወዳጄ ከቱኒዚያ የቀሰሙትን ግብጾች ተግባራዊ እንዳደረጉት ሁሉ በርካታ የአምባገነን

‹‹እየዬን›› የምታነቡ‹‹ሀ…ሁ›› ን አታንብቡ! ተባለ… አሉ

አገራት ህዝቦች ሊተገብሩት በተለያየ ብልሀት እየተንቀሳቀሱ ነው የሚባለው ነገር እንዴት ይመለከቱታል? እንኳንም አምባገነን መሪ አልኖረን እንጂ እኛም አይቀርልንም ነበር! (ምን ያስቅዎታል?) በነገራችን ላይ ሰሞኑን የአፍሪካ ወጣቶች በሀገራቸው ጉዳይ ላይ ለመምከር የአፍሪካ ህብረት መዲና በሆነችው አዲስ አበባ ላይ አንድ የውይይት መድረክ አዘጋጅተዋል፡፡ በምክክራቸው ከሚያነሱዋቸው ጉዳዮች አንዱ ወጣቶች ወደ

አመራር ስለሚመጡበት ሁኔታ መወያየት ነው፡፡ ተብሏል፡፡ ይህንን ዜና አብሮኝ ሲሰማ የነበረ አንድ ወዳጄ ምን እንዳለኝ ያውቃሉ? ‹‹ይሄማ ምን ምክክር ያስፈልገዋል?›› አለና ጀመረ… እና ያለምክክር የሚሆን ምን ነገር አለ? ብዬ ብጠይቀው ‹‹የአፍሪካ ወጣቶች ወደ መሪነት እንዲመጡ ከፈለጉ ምንም መመካከር ሳያስፈልግ አዛውንት መሪዎቻቸውን እግዜር በጊዜ እንዲሰበስብላቸው መለመን ብቻ ነው፡፡ እንጂ የአፍሪካ መሪ ምን ቢያረጅ ምን ቢያፈጅ ስልጣን መልቀቅ ይሉትን ጨዋታ መጫወት አይፈልግምና!›› አለኝ፡፡ እውነት ግን ይኽው ጋዳፊ እንኳ አንዳች እንደነከሰ ጉንዳን ጭንቅላቴን ካልቆረጣችሁኝ ንቅንቅ አልልም ብሎ አይደለም እንዴ? ደግነቱ ባለስልጣናቱ እርሱን ለሰይጣኑ ትተውት አንድ በአንድ ውልቅ እያሉ ይገኛሉ፡፡ በዚህም አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች ‹‹የጋዳፊ አስተዳደር እንደ አፋፍ መሬት ተሸርሽሮ አለቀ›› እያሉት ይገኛሉ፡፡ ኧረ ወዳጄ ከዛሬ ነገ አነሳዋለሁ እያልኩ ርስት አድርጌው በዛ ሰሞን የፌደራል ፖሊስ ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ የሆኑት ኮማንደር ደምሳሽ ሀይሉ ወደ እንግሊዝ ሄደው መቅረታቸውን አንድ ጋዜጣ ዘግቦ ነበር፡፡ ሰሞኑን ደግሞ ሌላ ባለስልጣን እንዲሁ ምነው ከአይኔ ጠፉብኝ ብዬ ብል ወደ ጀርመን ነው ወዴት… ብቻ ሄደው አልተመለሱም የሚል አሉባልታ ሰምቻለሁ የጋዳፊ ባለስልጣናትስ የሰውየው ነገረ ስራ አልጥም ቢላቸው ‹አሁንስ አበዛኽው!› እያሉ ነው የሚኮበልሉት፡፡ የኛዎቹ ጉዶች ደግሞ ምን ሆንኩኝ ብለው ነው ስልጣናቸውን እየተዉ እብስ የሚሉት? ወደ ቀደመው ነገራችን ስንመለስ ብርሃንና ሰላም ያደረገው ጭማሪ አፕሪል ዘፉል አለመሆኑ ተረጋገጠ እና አሳታሚዎች በሙሉ የዋጋ ጭማሪ ተደረገባቸው፡፡ ይኽው እርስዎም እንግዲህ የነዳጅ ጭማሪው አነስዎትና (ነጠላ ሰረዝ) የስኳር ዋጋ ጭማሪው አነስዎትና (ነጠላ ሰረዝ) የዘይት ዋጋ ጭማሪው አነስዎትና (ነጠላ ሰረዝ) የቡና ዋጋ ጭማሪው አነስዎትና (ነጠላ ሰረዝ) የወዘተ. ጭማሪው አነስዎትና ዛሬ ደግሞ ጋዜጣ ለማንበብ ጭማሪ መጣብዎ! አይዞን ቆፍጠን ማለት ነው፡፡ ከሌሎች አፍሪካ ሀገራት ጋር ሲነጻፀር እኮ አሁንም የኛ አኗኗር ጥጋብ እና ተድላ የተሞላበት ነው፡፡ (ይህ አይነቱን ንግግር ከኢትዮጵያ ሬድዮ ወይም ቴሌቪዥን ሰምተው ከነበረ አቅራቢው እኔ ነበርኩ ማለት ነው፡፡) አንዳንዶች ምን እያሉ እንደሆነ ሰምተዋል…? (አንዳንዶች ምን የማይሉት አለና የቱን ሰምቼ የቱን አስታውሰዋለሁ አሉኝ እንዴ?) ለማንኛውም አንዳንድ ወገኖች ‹‹መንግስት በተለያየ ጊዜ በተለያዩ ነገሮች ላይ ጭማሪ እያደረገብን ጥረታችንንም ሆነ ጥሪታችንን ባዶ እያስቀረብን ነው!›› እያሉ ይገኛሉ፡፡ መቼም እርስዎ በዚህ አሳብ እንደማይስማሙ አምንብዎታለሁ፡፡ ምን ያድርግ እርሱም እኮ ችግር ብሎት ነው! ዘንድሮ አበዳሪዎቻችን ራሱ ‹‹ቋጣሪ›› ሆነዋል፡፡ይኽው የአባይ ወንዝን ለሀይል ማመንጫ ልንጠቀም አስበን አንድ እንኳ አበዳሪ አልጠፋም እንዴ?! ለነገሩ ይብላኝ ለነርሱ እንጂ እኛው ራሳችን ተባብረን እንገነባዋለን! ይኽው

መንግስት ቦንድ ሽያጭ ለህብረተሰቡ አዘጋጅቶ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል በቦንድ ግዢ የሀይል ማመንጫ ግንባታው ላይ አስተዋፅኦ እንዲያደርግ ጥሪ አስተላልፏል፡፡ እኔ በበኩሌ ይህ መልካም አጋጣሚ እንዲያልፈኝ አልፈልግም ለመንግስቴ እና ለአገሬ ያለኝን ቀና አመለካከት የማሳይበት ጊዜው አሁን ነው፡፡ ለአንድ ወዳጄ ይህንን አቋሜን ነገርኩትና የርሱን አቋም ለመገምገም ብዬ የምን ያህል ብር ቦንድ ለመግዛት እንዳሰበ ጠየቅሁት፡፡ ወዳጄም ትክ ብሎ እያየኝ ‹‹ቆይ

ኑሮውን ከእለት እለት እንዴት እያናራችሁት እንደሆነ አልታየህም?›› አለኝ ቆጣ ብሎ፡፡ በርግጥ ኑሮ ተወዷል… ይሄ ግን በአለም አቀፍ ደረጃ የተከሰተ ችግር እንጂ የኛ ብቻ አይደለም፡፡ አልኩት ፈርጠም ብዬ! (እነ ኢቲቪ እንዲህ ነው አይደል የሚባለው?) ‹‹ተወኝ… ክፉ ደግ አታናግረኝ… ኑሮን እንደ ቦንብ እየተኮሳችሁ ምንም እንዳላደረገ ሰው ቦንድ ግዛ አትበሉኝ… የለኝም… እንደሌለኝም ታውቃላችሁ!›› ሲል ክፉ ደግ አታናግረኝ ብሎ ጀምሮ ክፉ ደግ ተናገሮ ጨረሰ፡፡ እና ወዳጄ ሰዉ ከኑሮው የተነሳ እየዬ እያለ ማንባት ስራው ሆኗል፡፡ አሁን ደግሞ የፕሬስ ዋጋ ጭማሪው ሰማይ ነክቷል፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ ታድያ አንዳንዶች ‹እየዬን› የሚያነባ ሰው ‹ሀ..ሁ›ን እንዳያነብ ተከለከለ እያሉ ነው አሉ፡፡ እውነት ግን እኮ የፈለገ ኑሮ ውድነት ቢኖር የህትመት ዋጋው እንኳ ቀነስ ቢያደርግ ሰዉም መተከዣም መተንፈሻም ስለሚያገኝ ጥሩ ነበር አሁን ግን የተደረገው እየገረፉ አትጭሁ እንደማለት ነው የዚህ ውጤት ደግሞ….. እያሉ ክፉ ትንቢት የሚናገሩም አልጠፉም፡፡ ወዳጄ የዛሬው ወጋችን ሊጠናቀቅ የቀረው ‹‹በመጨረሻም›› ብቻ ነውበመጨረሻምገበና 2ታታሪው የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ‹የአድማጭ ተመልካቹን› ፍላጎት ለማርካት ዘወትር በመታተር ላይ ይገኛል፡፡ እኛም ይህንን ትትርና ስናደንቅ ይኽው አመታት ተቆጥረዋል፡፡ ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ባለፈው ጊዜ ልጅ ከአዋቂ ሳይለይ ከእንግሊዝ ፕሪምር ሊግ ቀጥሎ በአትኩሮት የተከታተልነውን ‹ገበና› የተሰኘ ድራማ አቅርቦ ነበር፡፡ ማቅረብ ብቻም አይደል ከዚህ በፊት በአገሪቱ ውስጥ ድራማ ተሰርቶ የማያውቅ ይመስል የድራማው ተዋናዮች ደራሲ እና አዘጋጆችን ደግሶ ሸልሟል፡፡ በእውነቱ ይህ መልካም ነው ምክንያቱም አርቲስቶቻችንን ያበረታታልና! (ይኸው ከሽልማቱ በኋላ ማስታወቂያ ሰራተኛው ሁላ ፊቱን ወደ ድራማ አዙሮ የለም እንዴ!)የሆነ ሆኖ ገበና ድራማ ተጠናቆ ዛሬ ደግሞ ቴሌቪዥናችን ሌላ ድራማ ‹ገበና 2› በሚል ርዕስ እያሳየን ይገኛል፡፡ የገበና ድራማ ደራሲ ከአሰሪዎቹ ጋር ባለመስማማቱ ድርሰቱን አልሰጥም ብሏል፡፡ ይበላ! እነ ኢቲቪ ጣጣ አላቸው እንዴ!? በደህናው ጊዜ ‹ባለጊዜ› ሆነዋል፡፡ ማን ከልካይ ማንስ ተናጋሪ አላቸው? ማንም፡፡ በእውነቱ ኢቲቪንም ሆነ የድራማውን አቅራቢ ጉልቤነት ሳናደንቅ አናልፍም፡፡ ከሁሉ ግን እኔ ግራ የገባኝ በቴሌቪዥናችን የሚቀርብ ድራማ ‹ገበና› ካልተባለ አናይም ብለናል እንዴ? ወይስ አንዳች ያልታሰረ አዋቂ ‹‹ማንኛውንም ድራማ ‹ገበና› ካላላችሁት ዋጋ የለውም›› ብሏችኋል፡፡ ሁልግዜ በእሁድ መዝናኛ ቴሌቪዥን ፕሮግራም የሚቀርቡ ድራማዎችን ‹ገበና› እያላችሁ ህፃናት ‹ገበና› ማለት ምን ማለት ነው ሲባሉ ‹የቴሌቪዥን ድራማ› በሚል ትርጉም እንዲስቱ ስለምን ታደርጋላችሁ? ኧረ ተዉ ጎበዝ!ወዳጄ ይበሉ ያሰናብቱኝአማን ያሰንብተን!

[email protected]

አነጋጋሪው መፅሀፍ በገበያ ላይ ዋለ

የሰዶም ነፍሳት

ትንፋሽ የሚቆርጥና አስገራሚ እውነት የያዘውን የሰዶም ነፍሳት መፅሀፍ እያነበቡ፡-

‹‹እኔ የት ሄጄ ነው ይሄ ሁሉ ታሪክ ከተማው ውስጥ የሚከናወነው?›› ሲሉ ይገረማሉ፡፡

የታፈነና የተሸፋፈነውን እውነት ዛሬውኑ ያንብቡ፡፡

የሰዶም ነፍሳት መፅሀፍን በየመፅሀፍት መደብሩ ያገኙታል፡፡

ሙሉ በሙሉ እውነተኛ ታሪክ

ይኽው እርስዎም እንግዲህ የነዳጅ ጭማሪው አነስዎትና (ነጠላ ሰረዝ)

የስኳር ዋጋ ጭማሪው አነስዎትና (ነጠላ ሰረዝ) የዘይት ዋጋ ጭማሪው

አነስዎትና (ነጠላ ሰረዝ) የቡና ዋጋ ጭማሪው አነስዎትና (ነጠላ ሰረዝ)

የወዘተ. ጭማሪው አነስዎትና ዛሬ ደግሞ ጋዜጣ ለማንበብ ጭማሪ

መጣብዎ! አይዞን ቆፍጠን ማለት ነው፡፡ ከሌሎች አፍሪካ ሀገራት ጋር

ሲነጻፀር እኮ አሁንም የኛ አኗኗር ጥጋብ እና ተድላ የተሞላበት ነው

Page 9: Awramba Times Issue 161 Megabit 24

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 161 ቅዳሜ መጋቢት 24 2003

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

ማ ስ ታ ወ ቂ ያ

9ኮሜንተሪ

95 በመቶው ህይወትዎ የሚመራውና የስኬታማነት አድማስዎ የሚወሰነው በሳብኮንሼስ ማይንድዎ መሆኑን ያውቃሉ? ብዙዎች መድረስ የሚፈልጉበት ደረጃ መድረስ እየፈለጉና እየተመኙ፣ እቅድ እያወጡና አላስፈላጊ ባህሪን ለመተው እየወሰኑ የማይሆንላቸው የሳብኮንሼስ ማይንዳቸውን ሀያል ጥበብ ባለማወቃቸውና 95 በመቶው ፍላጐታቸውና እቅዳቸው በዚሁ አዕምሯቸው የሚቀለበስ በመሆኑ ነው፡፡ዘማይንድ - 4 የተባለውና ሰሞኑን ታትሞ ለንባብ የበቃው የዶ/ር አቡሽ አያሌው መፅሐፍ በሳብከንሼስ ማይንድ ምንነትና አጠቃቀም ዙሪያ ሰፋ ያለ ሙያዊ ትንታኔ የያዘ ሲሆን በሰሚናሩ ወቅት የሚመረቅ ይሆናል፡፡ በዕለቱ፡-

1. 97 በመቶው ህዝብ በትክክል እንደማይጠቀምበት በሚነገርለት የሳብኮንሼስ ማይንድ ምንነትና አጠቃቀም ዙሪያ በደራሲውና ሞቲቬሽናል ስፒከሩ ዶ/ር አቡሽ አያሌው ትምህርት ይሰጣል!!2. በዘርፉ ከፍተኛ ልምድና እውቀቱ ባላቸው ሞቲቬሽናል ስፒከር የሆኑት ህንዳዊው አሳይ ዱራይ በሰብኮንሼስ ማይንድ ዙሪያ ጥናታዊ ፅሁፋቸውን ያቀርባሉ!!3. በሳብኮንሼስ ማይንድ አጠቃቀምና አስተሳሰብ ህይወታቸው የተለወጡ ሰዎች የህይወት ተሞክሯቸውን ያካፍላሉ!!4. በሳብኮንሼስ ማይንድ ዙሪያ በቪዲዮ የታገዘ ትምህርት ይሰጣል5. ስለ ሳብኮንሼስ ማይንድ ከታዳሚዎች በሚነሱ የተለያዩ ጥያቄዎች ዙሪያ ውይይት ይደረጋል፡፡

6. በሳብኮንሼስ ማይንድ ዙሪያ የተቀናበሩ አዝናኝ የኪነ-ጥበብ ዝግጅቶች ይቀርባሉ

ነፃ ሰሚናር በሳብኮንሼስ ማይንድ ምንነትና አጠቅቀም ዙሪያዘማይንድ 4 መፅሐፍ በገበያ ላይ ውሏል፤ ይመረቃል!!

ቦታ፡- ሀገር ፍቅር ቲያትር አዳራሽ ሚያዚያ 2/2003 (እሁድ ከጧቱ 2፡00-6፡00)

የመግቢያ ዋጋ፡- ካሁን ቀደም ካነበቧቸው የዶ/ር አቡሽ አያሌው መፅሐፍት አንዱን ይዘው ከመጡ በነፃ ይካፈላሉ፤ ወይም በዕለቱ ሰሚናሩ በሚሰጥበት

ቦታ አንድ መፅሐፍ ብቻ ገዝተው ሰሚናሩን በነፃ መካፈል ይችላሉ፡፡

ተጨማሪ ምርቃት፡- አንድ መፅሐፍ ይዞ የመጣ ሌሎች 3 ሰዎችን በነፃ እንዲካፈሉ መጋበዝ ይችላል!!

በሰ ሞ ነ ኛ ው አጀንዳ ዙሪያ-ገባ የኢትዮጵያና ኤርትራ እሰጥ አገባ ቅኝት በአውራምባ ታይምሱ ውብሸት ታዬ የቀረበውን፣ የብርሃኑ ደቦጭ “ አ ደ ህ ይ ቶ ና አደንቁሮ መግዛት...”

መጣጥፎች እንዲሁም ከጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ጋር የተደረገውን ቃለ ምልልስ በጥሞና ተመልክቸዋለሁ/ሁሉም ባለፈው ሳምንት ዕትም ላይ የቀረቡ ናቸው/፡፡ ከላይ የተጠቀሱት ጭብጦች ማጠንጠኛ ወቅታዊው የአገሪቱ ተጨባጭ እውነታ መሆኑ አያከራክርም፡፡

የአገሪቱ ወቅታዊ ነባራዊ ተጨባጭ ሁኔታን በተመለከተ አንዳንድ ነጥቦችን መሰንዘር ለአድባሩም ለአውጋሩም ለቆሌውም/እንዲሉ/ የተገባ ሳይሆን አይቀርም፡፡ በየዕለቱ ስለ ወ/ሮ ስኳሬና ዘይቴ ስናስብ መምሸት መንጋቱ፣ ዛሬ ደግሞ የትኛው አስቤዛ ዋጋ ጨምሮ ይሆን? የሕፃናት አሳዳጊ ሞግዚት ወላጆች ጭንቀት የፍጆታ እቃ እጦት በምርት እጥረት መነገድ ለምግብ መሰለፍ (አሁን በኢትፍሩት ሱቆች ደርቷል) የኮሙኒዝም ሥርዓት አስተሳሰብ ፍልስፍና ማጠንጠኛ ነው፡፡

ይህ ጉባኤ የገባው የለሆሳስ ኮሙኒዝም አሁን እያንሰራራ ያለ ይመስላል፡፡ ሰዎችን አደንቁሮና አደህይቶ መግዛት የኮሙኒዝም መሰረታዊ መርህ ነው፡፡ ኦሽ የተባለው ሕንዳዊ ፀረ ሐይማኖት አስተሳሰብ አራማጅ ግለሰብ ሰዎች ሀሳቡን እንዲቀበሉት ለማስገደድ በረሀብና በሥራ ብዛት አዳክሞ ሰውን ተከታይ ለማድረግ ታክቲክ እንደሚጠቀም መረጃዎች ያስረዳሉ፡፡

በዚህኛው ዓመት (2003) የተደረገው የብርና ዋጋ የማውረድ ብቻም ሳይሆን አገራዊ ገንዘብን የማዋረድ ውሳኔ የዋጋ ግሽበት እያናረና እያናጠረ ነው፡

፡ በመሆኑም ሰው ለሌላ ሌላው ጉዳይ ሳይሆን ስለዋጋ ጭመራ ብቻ እንደሚያስብ በቀንበር የተጠመደ አራሽ በሬ ያህል በማነቆ ተሰንጎ ተይዟል፡፡

አሁን በከተማችንና በአገሪቱ እየካሄደ ያለው ጨዋታ ከዛሬ 66 ዓመታት በፊት በእንግሊዛዊው ጋዜጠኛ/በፖለቲካዊ ጉዳዮች ለይ አተኩሮ የሚሰራ ነበር/ ጆርጅ ኦርዌል (ኤሪክ ብሌር) የተደረገው አሥራ ዘጠኝ ሰማንያ አራት (1984) የተባለው መጽሐፍ የሳይኮ ድራማውን ጭብጥ በነጥብ ብነጥብ ያስቀምጠዋል፡፡

ለምሳሌ “የጥላቻ መድረክ” በተባለው ጭብጥ አካሄድ በየዕለቱ የፓርቲው ወጣት አባላት ጥላቻቸውን / ብሶታቸውን ከራሳቸው አውጥተው በሌሎች የመላላክ ጠላት ያሉትን ወገንን የማወገዝ... የመራገም መፈክሮችን ሁሉ እንዲያስተጋቡ የተወሰነ ደቂቃ ይሰጣቸዋል፡፡ በዚህ ሂደት የራሳቸውን የግል ኑሮ ውጣ ውረድ እንዲረሱ ይደረጋሉ፡፡ በጥቃቅን ጥቅማጥቅሞች የመሻኮትና መራኮት፣ መጠላለፍና መሰነካከል በድራማው ውስጥ የሚታዩ ገፅታዎች ናቸው፡፡ የጦስ ዶሮ መፈለግ፣ ለተፈጠረው ችግር ሁሉ ዘላቂ መፍትሔ ከመፈለግ ይልቅ ሰበብ መደርደር፣ ጭራቅ ፈልጎ መውቀስ ችግሩ ዞሮ ተሽከርክሮ እንዲመጣ ከችግር ሽክርክሪት የማያስወጣ የአዙሪት ድራማ መጫወት የኦርዌል፣ ስንክሳር፣ በኢትዮጵያ በሚገባ እየተተገበረ ያለ ይመስላል፡፡

ወደ አገራችን ተጨባጭ ሁኔታ እንመለስ፡፡ የኮሙኒዝም ልክፍት አባዜ ባለፉት ሃያና ሰላሳ ዓመታት በሺዎች የሚቆጠሩ ት/ቤቶች ተገንብተዋል፡፡ በየዓመቱ ቁጥራቸው ከ10 ሚሊዮን የሚበልጡ ሕፃናት አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ይታደማሉ፡፡ ደብተሮችና መጻህፍትን በብዛት ይፈልጋሉ፡፡ ለአገሪቱ ዓመታዊ ፍጆታ አይደለም፡፡ ለውጭ አገር ገበያ ንግድ የሚበቃ ለወረቀት ማምረቻ አስፈላጊው የግብአት ጥሬ ዕቃ መኖሩን ደግሞ አይካድም፡፡ ለምንድነው ታዲያ

አንድ እንኳን የወረቀት ፋብሪካ ሊገነባ ያልተቻለው ይሆን?

የፕሬስ ነጻነት ከታወጀበት 1985 ዓ.ም ጀምሮ ወረቀት ችግር ሆኖ ያልተነሳበት አንዳችም ጊዜም የለም፡፡ የፕሬስን ነፃነት በወረቀት ዋጋ ጭመራ ለመቆጣጠር የሚረግበት ጨዋታ ዓላማና ግብ ምን ይሆን? የዕቃ እጥረትን አብዝቶ በማምረት መቆጣጠር እየተቻለ ረሀብ፣ ድንቁርናና ድህነት የመቆጣጠሪያና የአምባገነን መሳሪያ መሆናቸው የሚያበቃው መቼ ይሆን? ሰዎችን በሚበላ ነገር የመቆጣጠር ዘይቤ የኋላቀር ማሕበረሰብ አስተሳሰብ መግለጫ ነው፡፡ ‹‹አንተን ማሰር ሰልችቶናል፣ እርምጃ ...›› ያሉት ባለስልጣን እውነታቸውን ነው፡፡

የአንድ ፓርቲ ወታደራዊ አገዛዝ ባለበት አገር ውስጥ የተለመደው ነፃ እርምጃ ነው፡፡ የአንድ ፓርቲ ሥርዓት መስፈን ወደ ንጉሰ ነገስትነት ያመራል ... ተጠያቂነት የለም፡፡ በቀድሞው የደርግ ኢሠፓ አገዛዝ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዘመን እንኳን ያልነበረ ... ቁጥሩ በብዙ ሺዎች የሚቆጠር የፌዴ/ፓሊስ ደንብ ልብስ ዩኒፎርም የለበሰ የጦር ሰራዊት በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ይገኛል፡፡ በጦርነት ቀጣና ውስጥ ያሉ ይመስል የተለያዩ ተተኳሽ የቡድን መሳሪያ የታጠቀ የፖሊስ ሰራዊት አባል በሲቪሉ ሕብረተሰብ መካከል ተሰማርቶ የታየበት በዓለም ላይ በየትም አገር አይገኝም፡፡

ይህ በሲቪሉ ህዝብ መካከል የሚተራመሰው የጦር ሰራዊት የወታደራዊ አገዛዝ መገለጫ ከመሆን አያልፍም፡፡ በዚህ የሚከራከር ወገን ይኖር ይሆን? የትራፊክ መብራት ማቋረጫ መስመር ላይ የጦር ሰራዊት ሰው በተጨናነቀበት ሁሉ በመሳሪያ ያስፈራራሉ፡፡ ለነገሩማ ሕገ መንገስቱስ በጦር ሰራዊት ይጠበቃል ተብሎ የለም እንዴ?

አሁን ያለው የአንድ ፓርቲ አገዛዝ ወታደራዊ ኃይሉን ለማጠናከር፣ በጀት ለማስጨመር እና አምባገነንነት እንዲጎለብት ‹‹የማርያም ጠላት››/.witch-

hunt/ የማሳደድ ዘመቻ ማካሄድ የግድ ይላል፡፡ እንዲህ የዳበረ “ጭራቅ” መጣብኝ ካልተባለ ለበጀት ማስጨመር አጀንዳ መጫወት አይመችም፡፡ ነገር ግን የጭራቅ ጦርነት ዘመቻ እስከመቼ? ኑሮ ራሱ ጥይት በሆነበት አዲስ አበባ ‹የፈላ ዘይት› ያህል የሚያቃጥል የእለት ጉርስ ፍለጋ ውጣ ውረድ ባለበት አዲስ አበባ የወታደራዊ በጀት ለማስጨመር የሚባለው ደፋ ቀና ዓላማና ግብ ምንድነው?

እዚህ ላይ አንድ ነገር ትዝ አለኝ ... ለካስ ረስቼው ነበር ... የዋጋ ጨመራው የጭንቅላት ጫወታው ለልጅ ሞግዚት አባ ወራዎች /ጎረምሦች/ የተሰጠ የየዕለቱ የቤት ሥራ ነው አይደል? የተቀናቃኞችን አስተሳሰብ /አእምሮ ግራ እያጎባህ ተቆጣጠረው ያለው የየትኛው ሀገር ጥንታዊ የጦርነት ሊቅ / ጦረኛ ጠቢብ ማን ነበር? እናም ጫወታው የሰወችን የተራበ ጭንቅላት ... በየዕለቱና በየሳምንቱ የዋጋ ጭመራውን አቀባብሎ ማጉረስና በተሌ ማድረግ የተዋጣለት የስነ ልቡና ጦርነት ዘዴ አይደለም? ሌላ ሌላውን አማራጭ ለማሰብ ጊዜ የለውማ?

በነገራችን ላይ 80 ሚሊዮን ሕዝብ ከ60 ሚሊዮን ሕዝብ አገር ጋር ጦርነት መግጠም አንድ ትልቅ ገለጀጅ (ጅላንፎ ልጅ ከአንድ ትንሽ ሚጢጢዬ ልጅ ጋር ጠብ የመግጠም የጅል ጠብ አይመስልም? ይህ በሌሎች ዘንድ አያስወቅስም? አያዋርድም? መሸነፍም ሊያመጣ ይችላል፡፡ በድሮ ዘመን “ጭሰኛ ሲሰነብት ባለርስት ይሆናል” እንደተባለው በስልጣን ኮርቻ ላይ ከአምስት ዓመት በላይ የሰነበቱ ባለስልጣናት ንጉሰ ነገሥት የመሆን ጉጉትና ፍላጎት እንደሚጠናወቻው፣ ስልጣንን በዘር ለማስተላለፍ ሲውተረተሩ በግብ፣ በየመን፣ በሊቢያና በሌሎችም ሀገራት ለማስተላለፍ ሲወተረተረ በግብፅ፣ በየመን፣ በሊ|ቢያና በሌሎች ሀገራት ውሰጥ ለማስተዋልና ለመታዘብ በቅተናል፡፡

ስለሆነም የአንድ ፓርቲ ሥርዓት እየከፋ ሲመጣ ምን የሚያስደንቅ ነገር አለው? በመሆኑም ጧትና ማታ ሰው በዘፈቀደ እንደጥጃ ማሰርና መፍታት አልበቃ ብሎ “ማሰር” ሰልችቶኛል መባሉ፣ ማንአለብኝነቱ ዳር ድንበር የለውም ማለት ነው፡፡ ለማንኛውም አገር እስከመቼ አምባገነኖችን ለማጠናከር ሰው በረሀብ እየተጠበሰ “የማርያም ጠላት” የማሳደድ ዘመቻ ጦርነት ውስጥ ትገባለች?

“የማርያም ጠላት!” - የማሳደድ ዘመቻው እስከ መቼ?

በአበራ ፋኖሴ

Page 10: Awramba Times Issue 161 Megabit 24

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 161 ቅዳሜ መጋቢት 24 2003እ ን ግ ዳ10

p Ç T@ S ´ “ —

በንፍታሌም

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ፣ ከወትሮው በተለየ መልኩ ረዥም ልብ ወለድ ሥራዎች ለአንባቢያን እየቀረቡ ይገኛሉ፡፡ ይሁን እንጂ ለአንባቢያን ከሚቀርቡ የልብ ወለድ ሥራዎች ከፊሎቹ ልብ ወለድ ተብሎ የሚታወቀውን የሥነ-ፅሁፍ ዘርፍ መስፈርቶች ገሚሱን እንኳ የሚያሟሉ አለመሆናቸው በህሊናችን አንዳንድ መጠይቆችን እናነሳ ዘንድ ግድ የሚሉ ናቸው፡፡ ምነው ቢሉ? ልብ ወለድ ከደራሲው ምናባዊ ፈጠራ የሚመነጭ ነው፤ ጥበብ ነው፡፡ ልብ ወለድ ፈጠራ ነው ስንል ግን፣ በእውኑ ዓለም የሚንቀሳቀሱ ሰዎችን አጠቃላይ ሰዋዊ ባህርያትና ክንዋኔዎች ሁሉ እውነት አስመስሎ የሚያቀርብ የሥነ-ፅሁፍ ዘርፍ መሆኑን መዘንጋት እንደሌለብን የዘርፉ ባለሙያዎች በአፅንኦት ያሰምሩበታል፡፡ ረዳት ፕሮፌሰር ዘሪሁን አስፋው ‹‹የሥነ-ፅሁፍ መሠረታዊያን›› በሚል ርዕስ ባሳተሙት መፅሐፍ “ልቦለድ በእውኑ ዓለም በሰዎች የህይወት ገጠመኝ ከተፈፀመውና ሊፈፀም ከሚችለው በመነሳት በከያኒው ግንዛቤና አመለካከት ተቀምሮ የሚቀርብ፣ የማህበረሰቡ ቁሳዊና ህሊናዊ ገፅታ የሚታይበት ኪነታዊ ሥራ መሆኑን መገንዘብ” እንደሚኖርብን በአፅንኦት ይገልፃሉ (ገፅ 153)፡፡ የልብ ወለድ ፍሬ ነገሮች ወይም አላባውያን ተብለው የሚታወቁት ታሪክ፣ ትልም፣ ገፀ-ባህሪይ፣ ግጭት፣ መቼት፣ ጭብጥ እና አንፃር መሆናቸውንም ያስረዳሉ፡፡ ከእነዚህ መሠረታዊ አላባውያን አንፃር ነው የአሰፋ በቀለ ድርሰት የሆነውን “ያልታበሱ ዕንባዎች” በመጠኑ የምንዳስሰው፡፡ ከልብ ወለድ መሠረታዊ ገፅታዎች መካከል አንዱና ዋነኛው አንድ ዓይነት ታሪክ መተረኩ እንደሆነ የአደባባይ ምስጢር ነው፡፡ የ”ያልታበሱ ዕንባዎች” ደራሲ አሰፋ በቀለም በቀረፃቸው ገፀ-ባህርያት አማካኝነት ሰዎች የተለየ የፖለቲካ አመለካከት በመያዛቸው ብቻ ለአላስፈላጊ ችግርና መከራ መዳረጋቸውን ነው በዋነኛነት የሚተርክልና፡፡ ለዚህ አባባላችን አብነት ይሆነን ዘንድ ከልብ ወለዱ ውስጥ የሚከተለውን ክፍል መንቀስ ይበቃል፡፡ “የሀገራችን አምባገነኖች ከየትም ይነሱ፣ በየትም ይምጡ፣ መቸም ይድረሱ፣ አንድ የጋራ ባህርይ አላቸው፡፡ ይህም በፊት ለፊት በሕዝባቸው ስም እየማሉ በስውር ግን የገዛ ሕዝባቸውን በጠላትነት የመፈረጅ መሰሪነታቸው ነው፡፡ መሠረታዊ ምክንያቱ ደግሞ ሥልጣን ላይ የሚወጡት በኃይል እንጂ የሕዝብ ይሁንታ አግኝተው እንዳልሆነ ራሳቸው ስለሚያውቁት ነው፡፡ ግን ደግሞ ሥልጣኑን ይፈልጉታል፡፡ በድሀ ሀገር ሥልጣን የሀብት ምንጭ ነውና ከያዙም በኋላ ሙጭጭ ይሉበታል፡፡ ይቆዩበት ዘንድ ሕዝብን ያተረማምሱበታል፡፡ ቢያንስ በሁለት፣ አንዳንዴም ከዚያ በላይ ይከፍሉታል፡፡ አንዱን ወገን ወዳጅ አድርገው ሌላውን ወገን በጠላትነት ይፈርጁታል፡፡ የጠሉትን ወገን የተለያየ

ስም እየለጠፉ ይበልጥ እንዲጠላ አውርተው ያስወሩበታል፡፡ በዚህም የእርስ በእርስ ጠላትነት ይፈጥራሉ፡፡ ሕዝብና መንግስት በጠላትነት እንዲተያዩ ያደርጉና ጥላቻና ጥርጣሬን ያነግሱበታል፡፡ በዚህ ጊዜ የራሳቸውን የሥልጣን ኮርቻ ያደላድላሉ፡፡ የችሎታ ሳይሆን የብልጠት አካሄድ!” (ገፅ 119)ይህ ከላይ ለአስረጅነት የጠቀስነው አንቀፅ በአገሪቷ በሰፈነው ብልሹ የፖለቲካ ሥርዓት የተነሳ ሙያዊ ተግባሩንና ግላዊ ህይወቱን መምራት ባለመቻሉ የተነሳ ለስደት የተዳረገ ሰው (የሕክምና ዶክተር) ከተፃፈ ረዥም ደብዳቤ መሀል የተቀነጨበ ነው፡፡ ተሰዳጁ ደብዳቤውን (ከገፅ 117-124) የፃፈው ከወቅቱ የፖለቲካ ሹመኞች ጋር ተቃርኖ ውስጥ ለገባውና በልብ ወለዱ ውስጥ በዋና ገፀ-ባህሪይነት ለተቀረፀው አስቻለው ፍስሐ ለተባለው ሰው ነው፡፡ በአጭሩ “ያልታበሱ ዕንባዎች” የአገራዊ ፖለቲካዊ እሳቤ ተቃርኖ፣ ከግለሰቦች የዕለት ተዕለት ህይወት ጋር የተዳወረበት፣ ፍቅርና ማህበራዊ ህይወት የተወሳሰቡበት ነው ብሎ መደምደም ይቻላል፡፡ ልብ ወለዱ ጠንከር ጠንከር ያሉ ሀሳቦች የተገለፁበት ይሁን እንጂ የልብ ወለድን የሥነ-ፅሁፍ ዘርፍ መስፈርቶች ከፊሉን እንኳ ያሟላል ብሎ አፍን ሞልቶ መናገር የሚያስችል አይደለም፡፡ በሌላ አገላለፅ ከልብ ወለድ የአፃፃፍ ዘይቤ አንፃር በርካታ ችግሮች ወይም ህፀጾች የሚስተዋሉበት ነው፡፡ የ”ያልታበሱ እንባዎች” ልብ ወለድን በርካታ ህፀጾች አንድ በአንድ ለመዘርዘር ጊዜና ቦታ የማይበቃን ቢሆንም ጥቂቶቹን አለፍ አለፍ ብለን ለማየት እንሞክራለን፡፡

አንድበልብ ወለድ ሥራ ውስጥ የደራሲ ተግባር አንድን ታሪክ መተረክ ከሆነ፣ ቀጣዩ ጉዳይ የገፀ-ባህርያቱ ቀረፃ እንደሆነ የዘርፉ ባለሙያዎች ያሰምሩበታል፡፡ “ታሪክ የተወሰነ የጊዜ ቅደም ተከተል የተቀናጁ ሁነቶች ውጤት ነውና፡፡ ስለዚህ ደራሲው የተለያዩ ሁነቶችን ያበጃል፤ በሁነቶቹም ሰንሰለታዊ ጉዞ ታሪኩን ከአንድ ደረጃ ወደሌላ ደረጃ ለማሸጋገር ገፀ-ባህርያቶችን በአግባቡ መቅረፅ ያስፈልጋል” ይላሉ፡፡ ከዚህ አንፃር ደራሲ በርካታ ገፀ-ባህርያትን የመቅረፅና የመገንባት ሚና ይጠበቅበታል፡፡ ገፀ-ባህርያት የየራሳቸው አመለካከትና አስተሳሰብ እንዲኖራቸው በተለያየ መንገድ ገደብ ሊያበጅላቸው ግድ ነው፡፡ አንድ ደራሲ በገፀ-ባህርያት ቀረፃ ወይም ግንባታ ረገድ የተለያዩ ዘዴዎችን ሊጠቀም ይችላል፡፡ ድርሰቱ በገፀ-ባህርያቱ አማካኝነት በተገቢው መጠንና ቅደም ተከተል ተዋህደውና ተሳስረው የተአማኒነት ውጤትን የሚያስገኙት ደግሞ በምልልስ፣ በገለፃ፣ በምልሰትና በንግግር የአተራረክ ዘዴዎች ነው፡፡ በእነዚህ ዘዴዎች ዋና ገፀ-ባህርያትን እንዲሁም አስተኔ ወይም ታይተው የሚጠፉ ገፀ-ባህርያትን... ወዘተ አንባቢያን በሚገባ እንዲያውቁ ማድረግ ይችላል፡፡ ደራሲያን ታሪክን ወደፊት ለማስኬድና ገፀ-ባህርያትን ለመገንባት የምልሰት ዘዴን መጠቀም ይችላሉ ሲባል፣ ሁሉን

ነገር አንድ ቦታ ይዘረግፉታል ወይም ይዘከዝኩታል ማለት አይደለም፡፡ ምነው ቢሉ፣ ምልሰት ደራሲው በመተረክ ላይ ካለው ጉዳይ ወይም ድርጊት አስቀድሞ የተደረገን ሁኔታ በማስገባት የሚቀርብ የአተራረክ ዘዴ ነው፡፡ በሌላ አባባል በልብ ወለዱ ውስጥ ያሉ ገፀ-ባህርያትን የያዙት ስብዕና ወይም አጠቃላይ ባህሪይ ምን እንደሆነ በቅንጭቡ የኋሊት ተጉዞ ማሳያ ዘዴ ነው፡፡ ይህ ዘዴ በረዥም ልብ ወለድ ትረካ መሀል አልፎ አልፎ እንደቅመም ጣል የሚደረግ እንጂ ሁሉም ነገር በአንዴ የሚዘረገፍ አይደለም፡፡ መሆንም የለበትም፡፡ የ”ያልታበሱ ዕንባዎች” ደራሲ አሰፋ በቀለ ባቀረበልን የሥነ-ፅሑፍ ሥራ ውስጥ ይህንን ተግባር መፈፀም አልቻለም፡፡ ምክንያቱም በመጀመሪያው ምዕራፍ ብቻ (ከገፅ 1 አስከ 26) ከሦስት በላይ ሁነቶችን በምልሰት ዘዴ ይተርክልናል፡፡ ዋናው ገፀ-ባህሪይ አስቻለው ከፈቅረኛው እህት ሸዋዬ ጋር የተዋወቀበት አጋጣሚ (ገፅ 5-7)፣ ዋናው ገፀ-ባህሪይ አስቻለው ከፍቅረኛው ሔዋን ጋር የተዋወቀበት አጋጣሚ (ከገፅ 7-9)፣ የፍቅር ጓደኛው ሔዋንን ለፍቅር ጓደኝነት የጠየቀበት ትውስታ (ገፅ 9) ወዘተ፡፡ እነዚህ የምልሰት ትረካዎች መደራረባቸው አንባቢያንን እንደሚያታክቱ ደራሲው አለመገንዘቡ ደግሞ አንዳች ጥያቄ የሚያጭር ነው፡፡

ሁለትይህም ብቻ አይደለም፡፡ ደራሲያን ለአንባቢያን በሚያበረክቱት ታሪክ ውስጥ የሚቀርጿቸውን ገፀ-ባህርያት የሚኖራቸውን ሚና ይወስናሉ ሲባል ገፀ-ባህርያቶቹ የሚኖራቸውን ወይም ያላቸውን ልዩነት የማሳየት ክህሎት ሊኖራቸው ይገባል፡፡ ምክንያቱም ልብ ወለድ የገሀዱ

ዓለም ነፀብራቅ ነው፡፡ በገሀዱ ዓለም የሚኖሩ ሰዎች ደግሞ በስብዕና መልካቸው ፍፁምና አንድ ወጥ አይደሉም፡፡ በመልክ መመሳሰል ቢኖር እንኳ በአስተሳሰባቸው፣ በአመለካከታቸው፣ በድርጊታቸው፣ ቢያንስ ቢያንስ በቋንቋ አጠቃቀም ዘይቤአቸው ... ወዘተ ይለያያሉ፡፡ ከዚህ አንፃር “ያልታበሱ ዕንባዎች” በቀላሉ ሊታረሙ የሚችሉ በርካታ ግድፈቶች የሚታዩበት ነው፡፡ ለአብነት ያህል በምዕራፍ አንድ ውስጥ ዋና ገፀ-ባህሪይው አስቻለው የወደዳትን ልጅ “እስቲ አንዴ ቆም በይ” ብሎ (ገፅ 10) የፍቅር ጥያቄ

እንዳቀረበላት ደራሲው ያሳየናል፡፡ ይኸው ገፀ-ባህሪይ በገፅ 13 ላይ “እስቲ ቆም በይ” ብሎ ከጋብቻ በፊት ወሲብ እንደማይፈፅም ቃል ይገባላታል፡፡ ይሁን እንጂ “ያልታበሱ ዕንባዎችን” ታሪክ እያነበብን ወደፊት ከተጓዝን በኋላ የዋና ገፀ-ባህሪይውን የአነጋገር ዘይቤና ተግባር ማንደፍሮ የተባለው ገፀ-ባህሪይ ቃል በቃል ሲናገረውና ተግባሩንም ሲፈፅመው እናስተውላለን፡፡ ማንደፍሮ የዋናውን ገፀ-ባህሪይ ፍቅረኛ የሌላ ሰው እንድትሆን ለማግባባት የአንገት ሀብል በስጦታ መልክ ይዞ መጥቶ “እስቲ አንዴ ብድግ በይ” (ገፅ 192) ብሎ ሲያጠልቅላት ይታያል፡፡ “ያልታበሱ ዕንባዎች” እንዲህ ዓይነት ተራና በርካታ ግድፈቶች የሚስተዋልበት ልብ ወለድ ሥራ ነው፡፡

ሦስትከላይ እንደጠቀስነው ከልብ ወለድ ገፅታዎች መሀል አንዱና ዋንኛው አንዳች ታሪክ የያዘ መሆኑ ነው፡፡ ታሪኩ ደግሞ በገፀ-ባህሪያቶች አማካኝነት ወደፊት ይራመዳል፡፡ ታሪክ መጀመሪያ እንዳለው ሁሉ መጨረሻ አለው፡፡ ደራሲው ትረካውን በምንም ዓይነት መልኩ ያጠናቅቀው መጨነቅ ያለበት ለዋና ገፀ-ባህርያቱ የመጨረሻ ዕጣ ፈንታ እንጂ፣ በልብ ወለዱ ውስጥ ላካተታቸው ሁሉ ገፀ-ባህርያት የመጨረሻ ዕጣ አይደለም፡፡ ሊሆንም አይገባም፡፡ የ”ያልታበሱ ዕንባዎች” ደራሲ አሰፋ በቀለ ግን የሳላቸውን ገፀ-ባህርያት የመጨረሻ ዕጣ ፈንታ ለአንባቢያን ካልነገርክ የተባለ ይመስል “እከሌ እንዲህ ሆነ፤ እከሌ ደግሞ እንደዚህ፤ እከሌ ደግሞ እንደዚያ ሆነ” እያለ ፍፃሜአቸውን በአጓጉል መልኩ ይተርካል፡፡ ትርፌ ሞተች (ገፅ 286)፡፡ አስቻለው ፍስሐ ሞተ (ገፅ 287)፡፡ የሔዋን እናት በድንጋጤ ዱዳ ሆኑ (ገፅ..290)፡፡ በልሁ ከቀብር መልስ ሸዋዬን አንቆ ገደለ፤ የዛኑ ቀን ተይዞ 15 ዓመት ተፈረደበት (ገፅ 293)፡፡ ታፈሱ በሃዘን ብዛት ታማ ሆስፒታል ገባች (ገፅ 294)፡፡ ወዘተደራሲው አሰፋ በቀለ በዚህ መልኩ የቀረፃቸውን ገፀ-ባህርያት የመጨረሻ ዕጣ ፈንታ ለመተረክ ሲል አላስፈላጊ ጥድፊያ ውስጥ እንደገባ በቀላሉ መረዳት ይቻላል፡፡ አላስፈላጊ ጥድፊያ ውስጥ መግባቱ ደግሞ ትረካው ተአማኒነት እንዲያጣ ምክንያት ሆኗል፡፡ ይህም ብቻ አይደለም፤ ደራሲው አላስፈላጊ ትንታኔ ውስጥ ገብቶ ለአንባቢያን ሁሉን ነገር ለማስረዳት ሲባዝንም ይታያል፡፡ “እከሌ የተባለው ወይም የተባለችው ገፀ ባህሪይ እንዲህ ብላ የተናገረችው፣ እንዲህ ለማለት ወይም ይህንን ጉዳይ ለመግለፅ ነው” ዓይነት ትንታኔ በመደንቀር የአንባቢን ስሜት ያነጥባል፡፡ ሌላም... ሌላም... ሌላም...

በመጨረሻበ”ያልታበሱ ዕንባዎች” ረዥም ልብ ወለድ ውስጥ የታዩት ኪናዊ ግድፈቶች ብዙ፣ እጅግ ብዙ ሊባልባቸው የሚችሉ ናቸው፡፡ እነዚህ ግድፈቶች ወይም ህፀጾች በሌላ መልኩ ስናያቸው የሌላ ወገንንም ድክመት የሚያሳዩ ይመስላሉ - የሃያስያንን፡፡ ምነው ቢሉ፣ ሃያስያን የሥነ-ፅሁፍ ሥራዎችን እግር በእግር ተከታትለው ተግባራቸውን በትክክል ለመወጣት ቢተጉ ኖሮ፣ ደራሲዎቻችን ሥራዎቻቸውን ለህትመት ከማብቃታቸው በፊት መለስ ብለው ራሳቸውንና ሥራቸውን መፈተሽ ይችሉ ነበር ብዬ አስባለሁ፡፡ እንዲያ ከሆነ ደግሞ ችግሩ የደራሲያን ብቻ ሳይሆን የሃያሲያንም ጭምር ነው ብንል ስህተት አይሆንም፡፡ ቀሪውን ለአንባቢያን ትቼ በዚሁ ብሰነባበትስ?

የመፅሐፉ ርዕሥ፡- ያልታበሱ ዕንባዎች

የመፅሐፉ ዓይነት፡- ልብ ወለድ

የመፅሐፉ ደራሲ፡- አሰፋ በቀለ

የመፅሐፉ ዋጋ፡- 32 ብር

የገፅ ብዛት፡- 297

የታተመበት ዘመን፡- ሚያዚያ 2002 ዓ.ም

ህፀጾችና ያልታበሱ ዕንባዎችዳ ሰ ሳ

ደራሲያን ለአንባቢያን

በሚያበረክቱት ታሪክ

ውስጥ የሚቀርጿቸውን ገፀ-

ባህርያት የሚኖራቸውን ሚና

ይወስናሉ ሲባል ገፀ-ባህርያቶቹ

የሚኖራቸውን ወይም

ያላቸውን ልዩነት የማሳየት

ክህሎት ሊኖራቸው ይገባል፡፡

ምክንያቱም ልብ ወለድ የገሀዱ

ዓለም ነፀብራቅ ነው፡፡ በገሀዱ

ዓለም የሚኖሩ ሰዎች ደግሞ

በስብዕና መልካቸው ፍፁምና

አንድ ወጥ አይደሉም፡፡

Page 11: Awramba Times Issue 161 Megabit 24

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 161 ቅዳሜ መጋቢት 24 2003

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

11እ ን ግ ዳ

p Ç T@ S ´ “ —

አ ፍታ1

ውጪ የምለው ነገር አይኖረኝም፡፡

የማስታወቂያ ኢንዱስትሪው የማስተዋወቅ ዘዴው ምንም እድገት አላሳየም የሚሉ አሉ፡፡ ምናልባትም በዘርፉ የተሰማራችሁ ተመሳሳይ ሶፍትዌሮችንና አቀራረቦችን ትጠቀሙ ይሆናል፡፡ ማስታወቂያ የማስተላለፊያ ዘዴዎቻችሁም ተመሳሳይ ናቸው፡፡

ማስታወቂያው አላደገም... አላደገም እውነት ነው፡፡ ምክንያቱም ስለዚህ ጉዳይ ብዙ ሩቅ መሄድ አያስፈልግም፡፡ ዛሬ በዲሽ የሚተላለፉትን ማስታወቂያዎች ብዙዎች የሚያዩ ይመስለኛል፡፡ የማስታወቂያ ደረጃ በውጭው ዓለም ምን ደረጃ ላይ ነው? የሚለውን ስናይ ትንሽ ረቀቅ እያለ እየሄደ ነው፡፡ የሶፍትዌርም ጉዳይ ብቻ ሳይሆን እኔን ጨምሮ በፈጠራው ሥራ ላይ ድግግሞሽ ይታያል፡፡ አለ፡፡ አንዳንዴ በኢንዱስትሪው ጀማሪ እንደመሆናችን መጠን እድገቱ ጥሩ ነው የሚባል ነገር አለ፡፡ ሊበረታታ ይገባል ከሚለው አኳያ ስንመለከተው ጥሩ ነው እንላለን፡፡ ሆኖም አንድ መረሳት የሌለበት ነገር ግሎባላይዜሽን ዓለምን አንድ አድርጓታል፡፡ ሌላው ዓለም የሚሆነው ነገር በኢትዮጵያ ውስጥ ሊሆን የማይችልበት ነገር የለም፡፡ ለምሳሌ ቦይንግ አውሮፕላን ገና እንደተጀመረ ወደ ኢትዮጵያ አልገባም፡፡ አሁን አሁን ስንመለከት በዓለም ላይ ያልዋለው ቦይንግ 787 የሚባለው አውሮፕላን በበለፀጉት አገሮችና ኢትዮጵያ ውስጥ ሥራ ላይ የሚውልበት ጊዜ በጣም በተቀራረበ ጊዜ ላይ ነው፡፡ በሞባይል ስልክ ቴክኖሎጂም አዲስ የሚወጣውን ወዲያው በኢትዮጵያ

አለህ? ሞተሃል ሲባል ነበር፡፡አዎን፡፡ ወሬው ብዙ ቦታ

ደርሷል፡፡ የተዛመተው በአንድ ጊዜ ነው፡፡ የዛን ዕለት ዜናው የተላለፈው በሸገር ኤፍ.ኤም ጠዋት 12፡30 ሰዓት ላይ ይመስለኛል፡፡ ከዚያን ጀምሮ ከአዲስ አበባና ከመላው ኢትዮጵያ አርብ፣ ቅዳሜና እሁድ የነበሩት የስልክ ጥሪዎች በጣም በርካታና አስቸጋሪዎች ነበሩ፡፡ በእኔ ስልክ ብቻ ሳይሆን የእኔን ስልክ የሚያውቁ፣ ነገር ግን በስም እንኳን ከማንተዋወቅ አንዳንድ ሰዎች ጋር በጣም ብዙ ስልክ ተደውሎ እንዳስቸገራቸው ይነግሩኝ ነበር፡፡ እኔን ለማግኘት በስልክ የሞከሩም አግኝተውኛል፡፡ ከዚያ በኋላ ደግሞ ከእሁድ ጠዋት ጀምሮ እስከ ትናንት ማክሰኞ ድረስ [ቃለ-ምልልሱ ረቡዕ ነበር] ከውጭ አገራት ከአሜሪካ፣ አውሮፓና ከተለያዩ ቦታዎች የሚደወሉ ስልኮች ናቸው፡፡ የነበረው ይኼ ሲሆን ትንሽ አጨናንቆን ነበር፡፡

አንተን ሞቷል ብለው ላሰቡ ምን ትላቸዋለህ?

በአቶ ጥላሁን ጉግሳ አለሙ [ባለፈው ሳምንት ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩና የቲያትር ደራሲና አዘጋጅ የነበሩ] ከዚህ ዓለም በሞት መለየት በጣም አዝኛለሁ፡፡ በአንድ ወቅት የአለቆቼ አለቃና ባሕል ሚኒስቴር የመምሪያ ኃላፊ ነበሩ፡፡ ያን ጊዜ አውቃቸው ነበር፡፡ ለቤተሰቦቻቸው መፅናናትን እመኛለሁ፡፡ በዚህ አጋጣሚ ግን የሞትኩት እኔ አይደለሁም፡፡ እኔ እንደሆንኩ ላሰቡ፣ ለገመቱና ላዘኑ ሰዎች እኔ እንዳልሆንኩ ከመግለፅ

አግኝተነዋል፡፡ ማስታወቂያ ላይ ስንመጣ ገና ታዳጊዎች ነን ብለን ገና ምክንያት የምንፈጥር ከሆነ ስህተት ነው፡፡ ስህተቱም ያለው እኛው ሠራተኞቹ ጋር ነው፡፡ የውጭዎቹ የሰሩትን የማንሰራበት ምክንያት ሊኖረንና ልናበጅ አይገባንም፡፡ ከዚህ አኳያ ካየነው ትንሽ ሳይሆን በደንብ ቀርቶናል፡፡ ስለዚህ ራሳችንን ማየትና መፈተሽ ያስፈልገናል ባይ ነኝ፡፡ ተገናኝተን እንዳንወያይ ደግሞ ልምዱ የለንም፡፡ በሌሎች የሙያ ዘርፎች ላይ ማሕበራት አሏቸው፡፡

‹አንተ የምትሰራቸው ማስታወቂያዎች ደረቅ ያሉ ናቸው› ለሚባለውስ?

እ... ደረቅ ያሉ ስትለኝ ምን ለማለት ነው? [ኮስተር ባለ ዕይታ]

የመለሳለስ ነገር የማይታይበት ‹ጠንከር ያለ ነው› ለማለት ፈልጌ ነው፡፡

እ... ደረቅ ያሉ የሚባሉ አይደሉም፡፡ እንደየደንበኛው ፍላጎት የሚሰሩ ናቸው፡፡ በነገራችን ላይ ትወናን በማድረግ በማስታወቂያ ዙሪያ እንደ ድርጅት ቅድሚያውን የያዝኩት እኔ ነበርኩ፡፡ ብዙዎች ማስታወቂያዎቼ ትወና ያለባቸው ናቸው፡፡ እኔ የምሄደው እንደደንበኞች ፍላጎት እና እንደማስታወቂያው ባህሪይ ነው፡፡ ለስለስ ተደርጎ የሚባለው ትወና ሲደረግ ከሆነ ትወና የማይፈልጉ ማስታወቂያዎች ላይ ገብቼ ትወና አላደርግም፡፡ በመጀመሪያ ስለማስታወቂያው ልሰራው የሚገባኝን ነገር አየዋለሁ፡፡ የእኔን ጣልቃ ገብነት ይፈልጋል ወይስ አይፈልግም? ተብሎ የሚወሰን ነው፡፡ ይኼንን የማደርገው ደግሞ ከማንም ጋር ተማክሬ ሳይሆን በራሴ ነው፡፡ ማስታወቂያው በራሱ ተሰርቶ ከእኔ የሚጠበቀው ድምፅ ብቻ ከሆነ ድምፄን አስገባበታለሁ፡፡ መተወን የሚገባኝ ከሆነ የማስታወቂያውን ባህሪይ አይቼ እተውናለሁ፡፡ ይኼም በመጀመሪያ የሚሆነው ማስታወቂያውን ልሰራው ስዘጋጅና ማስታወቂያውን በምን መልኩ ልስራ ብዬ ሀሳብ ሳወጣና ሳወርድ የሚወሰን ነው፡፡

በሕይወትህ በጣም መስዋዕትነት ከፍዬበታለሁ የምትለው ነገር አለ?

በነገራችን ላይ ለምንም ነገር መስዋዕትነት ከፍያለሁ ብዬ አልልም፡፡ መስዋዕትነት መክፈል እጅግ ሩቅና ከባድ የሆነ ነገር ነው፡፡ ያንን ሩቅና ከባድ ነገር ‹እኔ ከፍዬበት ነው› ማለት በጣም ይቸግረኛል፡፡ በሕይወት ውስጥ የተለያዩ ነገሮች ያጋጥማሉ፡፡ የተለያዩ ችግሮች ሊከሰቱ ይችላሉ፡፡ እነዚህን ችግሮች እንደችግርነታቸው ተቀብሎ የመፍትሔ ሀሳብ መፈለግ ነው፡፡ መፍትሔዎቹ አንዳንድ ጊዜ

ወደ ገፅ 16 ዞሯል

‹‹አልሞትኩም››ጥላሁን ጉግሳ (አርቲስት)

ለረዥም ዓመታት በበርካታ ቲያትሮች ላይ በመሪ ተዋናይነት ተሳትፏል፡፡ የተለያዩ ቲያትሮችንም በደራሲነትና በዳይሬክተርነት ለመድረክ ዕይታ አብቅቷል፡፡ ስድስት በሚሆኑ የቴሌቪዥን ድራማዎችም ተውኗል፡፡ በስሙ የሰየመውን የማስታወቂያና ኪነ-ጥበባት ድርጅት አቋቁሞ በባለቤትነትና በሥራ አስኪያጅነት እየመራ ይገኛል፡፡ ኤልያስ ገብሩ ‹ለምንም ነገር መስዋዕትነት ከፍያለሁ ብዬ አልልም› ከሚለው አርቲስት ጥላሁን ጉግሳ ጋር አንዳፍታ ቆይታ አድርጓል፡፡

ገመና ቁጥር 2 የዕግድ ጥያቄ ቀረበበት

በወሰንሰገድ ገ/ኪዳንየገመና ቁጥር አንድ ደራሲ አቶ አድነው ወንድይራድ (አዶኒስ) በጠበቃና ጋዜጠኛ ጳውሎስ ተሰማ አማካኝነት በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ክስ መሠረተ፡፡ የአቶ አድነው ተወካይና ጠበቃ የመሠረቱት ክስ ካለፈው ሳምንት እሁድ ጀምሮ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን መተላለፍ የጀመረው “ገመና ቁጥር ሁለት” እንዲታገድ የሚጠይቅ እንደሆነም ለማወቅ ተችሏል፡፡ ክሱ የተመሰረተባቸው የሜጋ ኪነ-ጥበባት ማዕከል ሥራ አስኪያጅ በነበሩት አቶ ዕቁባይ በርሄ፣ የዳዕማት መልቲ ሚዲያ ፕሮዳክሽን ሥራ አስኪያጅ አቶ ሀብታሙ በርሄ፣ እንዲሁም የኢትዮጵያ ሬድዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ናቸው፡፡ በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ ቤት 8ኛ የፍታብሔር ችሎት፣ ተከሳሾች በቀረበው የዕግድ ክስ ላይ ያላቸውን ምላሽ ይዘው የፊታችን ማክሰኞ መጋቢት 27 ቀን 2003 እንዲቀርቡ ትዕዛዝ መስጠቱን ለማወቅ ተችሏል፡፡ አቶ አድነው የመሠረቱት ክስ ይዘት፣ የቅጅና ተዛማጅ መብቶች ጥበቃ አዋጅ ቁጥር 41ዐ/96 መሰረት የፈጠራ መብት ባለቤትነት እንዲከበርና ላደረሱባቸው የሞራል ጉዳት ሦስቱም ተከሳሾች በአንድነትና በነጠላ ጠቀም ያለ የገንዘብ ካሳ እንዲከፍሏቸው የሚጠይቅ መሆኑ የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡ የቀረበው ክስ ዝርዝር እንደሚያሳየው፣ አንደኛና ሁለተኛ ተከሳሾች የቁጥር አንድ ገመና ደራሲ ክፍል ሁለት ድራማን በማቅረብ የጠየቀውን የገንዘብ መጠን የማይፈፅሙ ከሆነ፣ በእያንዳንዱ ሳምንት ለሚተላለፈው የገመና ቁጥር ሁለት የቴሌቭዥን ፕሮግራም ብር 50 ሺህ፣ እንዲሁም በዚህ ድራማ ከስፖንሰር የሚገኘውን ገንዘብ ሙሉ በሙሉ ለደራሲው እንዲከፍሉ ይጠይቃል፡፡ የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ታህሳስ 10 ቀን 2003 ዓ.ም በተካሄደው የገመና ቁጥር አንድ ገመና ድራማ የመዝጊያ ሥነ-ሥርዓት ላይ ለከሳሽ የምስጋና ምስክር ወረቀት በይፋ የሰጠ መሆኑን ያስታወሱት ጠበቃና ጋዜጠኛ ጳውሎስ ተሠማ፣ ገመና ቁጥር ሁለት የቴሌቪዥን ድራማ የደራሲው እውቅና (ፈቃድ) የሌለው መሆኑ ተጠቅሶ ለአንደኛ ተከሳሽ ድራማው እንዳይተላለፍ መጋቢት 16 ቀን 2003 የተሰጠው የሕግ ማስጠንቀቂያ ግልባጭ ደርሶት ሳለ፣ በቸልተኝነት ድራማውን በማስተላለፉ በ3ኛ ተከሳሽነት እንዲከሰስ መደረጉን ገልፀዋል፡፡ የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ከአንደኛና ሁለተኛ ተከሳሾች ጋር በመሆን በደንበኛቸው ላይ ለደረሰው የሞራል ጉዳት ክፍያ፣ ከስፖንሰሮች የተገኘውን ገንዘብ በሙሉ፣ እንዲሁም የዳኝነት፣ የጠበቃ አበልና ልዩ ልዩ ወጪዎችን ከቁርጥ ኪሣራ ጋር እንዲከፍሉ መጠየቃቸውንም አብራርተዋል፡፡ አቶ አድነው ከዚህ በተጨማሪ አንደኛና ሁለተኛ ተከሳሾች በአዋጅ ቁጥር 410/96 መሠረት የወንጀል ኃላፊነት ስላለባቸው የወንጀል ምርመራ እንዲጣራባቸው በፍትሕ ሚኒስቴር አራዳ ፖሊስ መምሪያ ዐቃቤ ሕግ ፅ/ቤት የግል አቤቱታ ማቅረባቸውንም ለማወቅ ተችሏል፡፡ የወንጀል ክስ ጉዳይ የመንግስት ስለሆነ የክስ አቤቱታውንም ፍርድ ቤት የሚያቀርበው ዐቃቤ ሕግ መሆኑን የገለፁት ጠበቃና ጋዜጠኛ ጰውሎስ፣ ደንበኛቸው የደረሰባቸውን የፈጠራ መብት መገሰስ ከማስረጃዎቻቸው ጋር በማያያዝ ማቅረባቸውን ጠቁመዋል፡፡ የቀረበው የወንጀል አቤቱታ ጉዳዩ ተጣርቶና ወደ ፍርድ ቤት ቀርቦ ተከሳሾች ጥፋተኛ የሚባሉ ከሆነ በቅጅና ተዛማጅ መብቶች ጥበቃ አዋጅ ቁጥር 410/96 አንቀፅ 36 መሠረት ከአንድ ዓመት እስከ አምስት ዓመት የሚደርስ የእስር ቅጣት ሊጠብቃቸው ይችላል ብለዋል፡፡

በአውራ አምባ ማህበረሰብ ላይ የሚያጠነጥን መጽሐፍ ታተመ

በደቡብ ጎንደር ፎገራ ወረዳ ውስጥ የሚገኙትን የአውራ አምባ ማህበረሰብ አባላት የሥራ ፍልስፍናና የአኗኗር ሁኔታ የሚዳስሰው መፅሐፍ የተፃፈው በአቶ ሰዒድ መሐመድ ሲሆን ርዕሱ “Unique Social Paradigm in Awra-amba Community” የተሰኘ ነው፡፡ የተፃፈበት ቋንቋ ደግሞ እንግሊዘኛ ነው፡፡ አቶ ሰዒድ ለአውራምባ ታይምስ እንደገለፁት፣ መጽሐፉን ለማሳተም ያነሳሳቸው በማሕበረሰቡ ላይ ያካሄዱት ጥናት የማሕበረሰቡን አጠቃላይ ገፅታ ስላሳወቃቸው፣ የተለያዩ ምሁራንና የፖለቲካ ሰዎች በሰጧቸው አስተያየቶች መሠረት የማሕበረሰቡ ፍልስፍናና የሥራ ባሕል ለአገሪቱ ሞዴል ሆኖ ልማትን ለማምጣት ትልቅ መሣሪያ ሊሆን እንደሚችል በማመናቸው ነው፡፡ ጀርመን በሚገኝ አሳታሚ ድርጅት ለሕትመት የበቃው መፅሐፍ ጠቀሜታው የማህበረሰቡን መልካም ፍልስፍና ለመላው ዓለም ማስተዋወቁና በአውራ አምባ ማሕበረሰብ ዙሪያ ለሚካሄዱ ሌሎች ጥናቶች በር ከፋችና መነሻ ሊሆን መቻሉ እንደሆነ የመፅሐፉ አዘጋጅ ለዝግጅት ክፍላችን አስታውቀዋል፡፡ መፅሐፉን በአማርኛ ቋንቋ ለማሳተም በእንቅስቃሴ ላይ መሆናቸውንና አንዳንድ የአርትኦት ሥራዎች ተከናውነው ከተጠናቀቁ በኋላ በቅርቡ እንደሚታተም አቶ ሰዒድ ገልፀዋል፡፡

የሕፃናት ኤግዚቢሽንና ባዛር ሊዘጋጅ ነውበታሪክ ፒክቸርስ አዘጋጅነት ‹‹ትኩረት ለሕፃናት›› በሚል መሪ ቃል የሕፃናት ኤግዚብሽንና ባዛር ከግንቦት 6-8 2003 ዓ.ም በቦራ አሚዩዝመንት ፓርክ ሊቀርብ ነው፡፡ ባሳለፍነው ረቡዕ በቦራ አሚዩዝመንት ፓርክ የታሪክ ፒክቸርስ ሥራ አስኪያጅ አቶ ስምዖን ወርቁ፣ ምክትል ሥራ አስኪያጅ ወ/ሮ ሊዲያ ጎርፉ እና የፓርኩ አስተዳዳሪ በተገኙበት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ በኤግዚቢሽኑ የተለያዩ የሕፃናት አዝናኝና ትምህርታዊ ዝግጅቶች፣ ውድድሮች እና ትርዒቶች መካተታቸው የተገለፀ ሲሆን ኤግዚቢሽኑና ባዛሩ ከ6000 በላይ ሕፃናትና ወላጆች እንደሚጎበኝና በመክፈቻው፣ ዕለትም የሚመለከታቸው የመንግስት አካላትና ተጋባዥ እንግዶች እንደሚገኙ ተገልጿል፡፡

የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞችን የጭቆናና የትግል ታሪክ የሚሳይ መፅሐፍ ተመረቀ

“ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ከ615-1700 የጭቆናና የትግል ታሪክ” በሚል ርዕስ በአሕመዲን ጀበል የተፃፈው ቅፅ አንድ መፅሐፍ ባሳለፍነው ሳምንት እሁድ መጋቢት 18 ቀን 2003 ዓ.ም ተመረቀ፡፡ በታሪክ ዙሪያ ለሚደረግ የጥናትና ምርምር ሥራ ትልቅ አስተዋፅኦ እንዳለው የተገለፀለት መፅሐፍ 80 ሺህ ብር ያህል ወጪ ተደርጐበት ከአምስት ሺህ ኮፒ በላይ መታተሙ ተገልጿል፡፡ በመፅሐፉም ላይ 12 ያህል ምሁራን አስተያየት የሰጡበት ሲሆን በምርቃቱ ዕለትም ፕሮፌሰር ላጲሶ ዴሌቦ ተገኝተዋል፡፡ መፅሐፉ 272 የገፅ ብዛት ያለው ሲሆን በ45 ብር በመሸጥ ላይ ይገኛል፡፡

አርቲስት ሸዋፈራሁ ደሳለኝ ቅሬታ ቀረበበትበሐዋሳ ከተማ የሚገኘው ስልሳ ሻማ የኪነ-ጥበብ ማህበር እሁድ መጋቢት 18 ቀን 2003 ዓ.ም አርቲስት ሸዋፈራሁ ደሳለኝን የወሩ እንግዳ በማድረግ ለአንድ ወር ያህል ሲያደርግ የነበረውን ዝግጅቱን አጠናቆ አርቲስቱን ቢጠብቅም አርቲስቱ “የውሃ ሽታ” እንደሆነባቸው ከሐዋሳ የማህበሩ አባላት ገለፁ፡፡ አባላቱ ለዝግጅት ክፍላችን “በጣም የሚሳዝነው መቅረቱ ብቻ ሳይሆን ስልክ በተደጋጋሚ ሲደወልለት ያለማንሳቱ ነበር፡፡ ቢያንስ ዕለቱ ካለፈ በኋላ እንኳን ደውሎ ይቅርታ ያለመጠየቁ ምን ይባላል? ይህ የሚያሳየው የጥበብ አፍቃሪያንን ብቻ ሳይሆን የሐዋሳ ከተማ ህዝብንም ጭምር የናቀው ያስመስላል” ብለዋል፡፡ የማህበሩ አባላት በአርቲስቱ አለመኖር ሳይረበሹ ለዕለቱ የተያዙትን የኪነ-ጥበብ ሥራዎች ለታዳሚያን ማቅረባቸውን ገልጸው “እኛ የጥበብ አፍቃሪዎች ከእንዲህ አይነት አርቲስት ምንድነው የምንማረው?” ሲሉ በአርቲስት ሸዋፈራሁ ደሣለኝ ላይ ቅሬታቸውን አቅርበዋል፡፡

Page 12: Awramba Times Issue 161 Megabit 24

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 161 ቅዳሜ መጋቢት 24 200312

በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ሆነው በተሾሙበት ወቅት በአሜሪካ ሴኔት ተገኝተው ንግግር ሲያደርጉ ቅድሚያ የሚሰጧቸው አገሮች እንዳሉ ገልፀው ነበር፡፡ እንደሚታወሰው እዚህ ከመጡ በኋላ ኢህአዴግ 99.6 ከመቶ ድምፅ ማግኘቱ ቢገለጽም የምርጫው ሂደት በአውሮፓ ሕብረት ታዛቢዎች ሳይቀር ዓለም አቀፍ መስፈርቶችን እንደማያሟላ መግለጫ ተሰጥቶበታል፡፡ በቅርቡ እንኳን ዕውቋ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ አገራቸውን ጥለው ወደ አሜሪካ ለመሄድ የተገደዱበት ሁኔታ አለ፡፡ እነዚህ ነባራዊ ሁኔታዎች በተሾሙበት ወቅት በሴኔት ካደረጉት ንግግር አንፃር ሲያዩት አያሳስብዎትም?

የ2002ቱን ምርጫ በተመለከተ በወቅቱ መግለጫ የሰጠንበት ጉዳይ ስለሆነ በይበልጥ ለወደፊት ሁለቱንም አገሮች ሊጠቅሙ በሚችሉ ዋነኛ የአጋርነት አጀንዳዎች ዙሪያ ማተኮሩ ይሻላል፡፡ በሌሎች ጉዳዮች ላይ ያሉ ነገሮችን

ለማሻሻል ሲባል ቅራኔ በሚፈጥሩ ነገሮች ላይ ትኩረት ማድረግ ጠቀሜታ ያለው አይመስለኝም፡

፡ ዋናው ጉዳይ አሁንም ቢሆን በአዎንታዊ መንገድ

በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር የሆኑት ዶናልድ

ቡዝ ቀደም ሲል በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ

ቤት የውጭ ድርጅቶች ጉዳይ ጽ/ቤት የቴክኒክና

ስፔሻላይዝድ ቢሮ ዳይሬክተር ሆነው አገልግለዋል፡፡ ወደ

ኢትዮጵያ ከመምጣታቸው በፊትም በላይቤሪያና ዛምቢያ

በአምባሳደርነት አገልግለዋል፡፡

ባለትዳርና የሦስት ልጆት አባት የሆኑት አምባሳደር ቡዝ

የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ከጆርጅ ታውን ዩኒቨርሲቲ

በ‹‹ውጭ አገልግሎት››፣ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ደግሞ

ከቦስተን ዩኒቨርሲቲ በ ‹‹ቢዝነስ አድሚኒስትሬሽን››

እንዲሁም ተጨማሪ ሁለተኛ ዲግሪ በ‹‹ብሔራዊ

ደህንነት›› ከብሔራዊ ጦር ኮሌጅ አግኝተዋል፡፡ ኢትዮጵያ

ውስጥ አምባሳደር ሆነው ከተሾሙበት ከመጋቢት 03 ቀን

2002 ዓ.ም ጀምሮ ለአንድ ዓመት ያህል ቃለ-ምልልስም

ሆነ ጋዜጣዊ መግለጫ ከመስጠት ተቆጥበው የቆዩት

ዶናልድ ቡዝ ለመጀመሪያ ጊዜ ከትናንት በስቲያ በፅህፈት

ቤታቸው ከጋዜጠኞች ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይቱ ላይ የተሳተፈው ባልደረባችን ዳዊት

ከበደ ግን ጋዜጠኞቹ በአምባሳደሩ ምላሽና ለዘብተኛ

አቋም ብዙም አልተደሰቱም ይላል፡፡ በተለይ አንዳንዶቹ

‹‹የኢሕአዴግን መንግስት አስመልክቶ በሚቀርቡላቸው

ጥያቄዎች ላይ በአብዛኛው ያንጸባረቋቸው ኃሳቦች ሽፋን

የመስጠት ጥረት አስመስሎባቸዋል›› ሲሉ አስተያየት

ለመስጠት የተገደዱበት ሁኔታ መታዘቡንም ይገልጻል፡

፡ ከአምባሳደር ቡዝ ጋር የተደረገው ውይይት ለጋዜጣችን

አንባቢያን በሚመች መልኩ እንዲህ አቅርቦታል፡፡

‹‹ጭቆና የፈጠረው ብሶት … የየአገራቱ ሕዝቦች ለለውጥ እንዲነሳሱ ምክንያት ሆኗል››

ዶናልድ ቡዝ /በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር/

Page 13: Awramba Times Issue 161 Megabit 24

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 161 ቅዳሜ መጋቢት 24 2003

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

13

ያጠነጠነ ነው፡፡ በአካባቢ አገሮች ፀጥታና እንዲሁም ዘላቂ ሰላም እንዲኖር በመስራት ረገድም፣ መንግስት በሰብአዊ መብት አያያዝ ላይ ያለው ሁኔታ እንዲያሻሽል መመካከርን ጨምሮ በበርካታ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ሰጥተን እንሰራለን፡፡ ስለዚህ በእኔ የስራ ዘመን ዋናዎቹ የትኩረት አቅጣጫዎቻችን ለሁለቱ አገሮች ጠቃሚ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ያጠነጠኑ ናቸው፡፡ የግል ሴክተር እንቅስቃሴን በተመለከተ፣ የአሜሪካ ንግድ ማህበረሰብ አባላት እዚህ ካሉት ጋር ጠንካራ ግንኙነት መስርተው ውጤታማ በመሆን ላይ ናቸው፡፡ እንደሚታወቀው በአገሪቱ ያለውን ምቹ የንግድና የኢንቨስትመንት ዕድል ለመጠቀም በርካታ የአሜሪካ ኩባንያዎች እዚህ ገብተው በመስራት ላይ ይገኛሉ፡፡ ስለዚህ አንዱ ዋነኛ የአጋርነታችን ትኩረት እሱ ነው፡፡ ማለትም ኢኮኖሚያዊ ግንኙነትን ይበልጥ ማጠናከር፡፡ በኢኮኖሚው ላይ ያለንን እንቅስቃሴ ምን ያህል ጠንካራ እንደሆነ በየጊዜው ከአሜሪካ ለኢትዮጵያ የሚሰጠው እርዳታና ድጋፍ አስረጂ ነው፡፡ ይህንን ስል በኢኮኖሚው በኩል ያለው ግንኙነት የግድ መለካት ያለበት በምንሰጠው የእርዳታ መጠን ነው ማለት አይደለም፡፡ እርዳታው በልማት እርዳታና በሰብአዊ እርዳታ ላይ ያተኩራል፡፡ የሰብአዊ እርዳታው በዋናነት በምግብ እርዳታ ላይ ትኩረት ያደርጋል፡፡ ከእርዳታው ባሻገር ግን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በይበልጥ ትኩረት እየሰጠን ያለነው ከምግብ ተረጅነት ይልቅ ዘላቂ የሆነ የምግብ ዋስትና እንዲረጋገጥ ብሎም የግብርና ምርታማነት እንዲጨምር በማድረግ በኩል እገዛ እያደረግን ነው፡፡... ሌላው በርካታ መጠን ያለው እርዳታና ድጋፍ የምንሰጠው ለጤናው ሴክተር ነው፡፡ በአሜሪካ ፕሬዝዳንት ኢኒሽየቲቭ ስር የተቋቋመውና በኤች አይ ቪ ኤድስ፣ በወባ፣ በሕፃናት እና እናቶች ጤና ዙሪያ ድጋፍ የሚያደርገው ፕሮጀክት በአንድ በኩል፣ በሌላ በኩል ደግሞ በዩ.ኤስ.ኤይድ ሀላፊነት የሚከናወነው የቤተሰብ ምጣኔ ፕሮግራም አለ፡፡ እናም በጤና በኩል ብዙ ስራዎች ተሰርተዋል፡፡ ዞሮ ዞሮ ይህ ማለት በዓለም አቀፍ ደረጃ የተነደፈውን ዓለም አቀፍ የጤና ኢኒሽየቲቭ አካል እንደመሆኑ እሱን ውጤታማ ለማድረግ ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ጋር በቅርብ እየሰራን ነው፡፡ ከጤና ጥበቃ ጋር በመቀናጀት መስራታችን እርዳታውና ድጋፉ ከአገሪቱ የአምስት ዓመቱ ዕድገትና የጤና ስትራተጂ ጋር በተጣጣመ ሁኔታ ስራ ላይ እንዲውል አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡...ትምህርትን በተመለከተም ድጋፍ እንሰጣለን፡፡ በተለይ እንግሊዝኛ ቋንቋ በካሪኩለም ደረጃ ተቀርጾ በመጀመሪያ ደረጃ ለሚማሩ ተማሪዎች እንዲቀርብ በማድረግ ረገድ ድጋፍ አድርገናል፡፡ ይህም ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች የእንግሊዝኛ ክህሎታቸውን አዳብረው ወደ ሁለተኛ ደረጃ ብሎም ወደ ዩኒቨርሲቲ እንዲዘልቁ በማድረግ ረገድ ጠቀሜታ አለው፡፡ ስለዚህ የሁለቱ አገሮች ግንኙነት በእርዳታ ላይ ከመመስረት ይልቅ ወደ ቢዝነስና ኢኮኖሚያዊ አጋርነት እንዲያድግ ነው

እየሰራን ያለነው፡፡ ስለዚህ እርዳታውና ድጋፉ የሁለቱ አገር ሕዝቦችን በሚጠቅም መልኩ በጠንካራ መሰረት ላይ የተጣለ የአጋርነት ድጋፍ ነው፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት በ80 ቢሊዮን ብር ወጪ ትልቅ ግድብ ለማስገንባት በዝግጅት ላይ እንዳለ ገልጿል፡፡ በዚህ ዙሪያ የአሜሪካ መንግስት አቋም ምንድነው?

የግድብ ግንባታ እቅዱን በተመለከተ፣ በኢትዮጵያ መንግስት የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ውስጥ በጉልህ ከሚታዩ ትልልቅ እቅዶች አንዱ ነው፡፡ ቀደም ብዬ እንደገለጽኩት የአሜሪካ መንግስት የሚሰጣቸው ድጋፎች ከኢትዮጵያ መንግስት የልማት ዕቅዶች ጋር የተጣጣሙ ናቸው፡፡ ለምሳሌ በጤናው ዘርፍ የምናደርገው ድጋፍ የኢትዮጵያ መንግስት ካወጣው የጤና ዕቅድ (ከእድገትና ትራንስፎርማሽን ዕቅድ) ጋር የተጣጣመ ነው፡፡ ... በግብርናው ዘርፍ፣ በኢንቨስትንትም ሆነ በትምህርቱ ሴክተር የምናደርገው ድጋፍ በጠቅላላ ማለት ይቻላል መንግስት ካወጣው የልማት ዕቅድ መርሃ ግብር ጋር የተስማማ ነው፡፡ በተለይ እዚህ ላይ አፅንኦት ሰጥቼ መግለፅ የምፈልገው ሁሌም የምግብ እርዳታ እየለገሱ ከመኖር ይልቅ ኢትዮጵያውያን እስከወዲያኛው በምግብ እህል ራሳቸውን እንዲችሉ በማድረግ ረገድ መስራቱ ይበልጥ ጠቀሜታ አለው፡፡ ለዚህም ነው በይበልጥ ለሴፍትኔት ፕሮግራሞች ድጋፍ እየሰጠን የምንገኘው፡፡ ... ስለዚህ መንግስት ያወጣውን የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ስኬታማ እንዲሆን ገንዘብ በመለገስ ብቻ ሳይሆን የግሉ ሴክተር ገብቶ ለእቅዱ ስኬታማነት እንዲረባረብም ጭምር ድጋፍ እንሰጣለን፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት በኤርትራ መንግስት ላይ አዲስ የስትራቴጂ ለውጥ ማድረጉን ይፋ አድርጓል፡፡ ይህንን የኢትዮጵያ መንግስት አቋም የአሜሪካ መንግስት እንዴት ይመለከተዋል?

የኤርትራን ጉዳይ በተመለከተ እኛ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በአካባቢያዊ ፀጥታና ሰላም ዙሪያ በቅርበት እየሰራን ነው፡፡ በአካባቢው ሰላም እንዲሰፍን የኢትዮጵያን መንግስት ከማማከር አንስቶ በበርካታ ጉዳዮች ላይ በአጋርነት እየሰራን ነው፡፡ በዚህ ረገድ የሚያስማሙ የጋራ ፍላጎቶችም አሉን፡፡ በኤርትራ ብቻ ሳይሆን በሶማሊያም ሆነ በአካባቢው የሽብርተኝነት አደጋን ለመቅረፍ በጋራ እንደምንሰራ ይታወቃል፡፡ ስለዚህ የአካባቢውን ሰላም ሊያውኩ የሚችሉ ስጋቶችን በመከላከል ረገድ በጥምረት እና በመቀናጀት እየሰራን ነው፡፡

የአሜሪካ መንግስት በአካባቢ ፀጥታና መረጋጋት ዙሪያ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በጋራ እየሰራ እንደሆነ ቀደም ብለው

ገልፀውልናል፡፡ ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ደግሞ አሜሪካ ለፀረ ሽብር አጋርነት ብቻ ቅድሚያ በመስጠት አምባገነኖችን ትደግፋለች ታበረታታለች ሲሉ ይተቿታል፡፡ ከዚህ አንፃር መንግስትዎ ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን የፀረ ሽብር አጋርነት እንዴት ይገመግሙታል?

ሁላችንም በአንድ ጉዳይ ላይ እንስማማለን፡፡ የየትኛውም አገር ዜጎች የሽብርተኞች ሰለባ ሲሆኑ ሚሊዮኖችን የሚመለከት ጉዳይ ይመስለኛል፡፡ ስለዚህ መንግስታት በዚህ ጉዳይ ላይ አንድ አይነት አቋም ሲኖራቸው የአሜሪካና የኢትዮጵያ መንግስታትም ጉዳዩ ያሳስባቸዋል፡፡ ዜጎቻቸውን ከአሸባሪ ቡድኖች የመጠበቅና የመከላከል ኃላፊነትም አለባቸው፡፡ እናም ጉዳዩ የጋራ አቋምና ፍላጎት ይሆናል ማለት ነው፡፡ ለዚህ ነው ሁለቱም አገሮች በዚህ ዙሪያ የሚተባበሩት፡፡ ሁለት አገራት ለዜጎቻቸው ህልውና ሲሉ በአንድ ጉዳይ ላይ መስማታቸው ከብሔራዊ ጥቅም አንጻር ተፈጥሯዊ ነው፡፡ ደግሞም ሁለቱም አገሮች በዚህ ትብብራቸው ተጠቅመዋል እንጂ አልተጎዱም፡፡

የኢትዮጵያ ሕዝብ (እንደ ሰሜን አፍሪካ) ስልጣን ላይ ባለው መንግስት ላይ የሚያምፅ ይመስልዎታል?

በሰሜን አፍሪካም ሆነ በመካከለኛው ምስራቅ እየተደረገ ያለው ሕዝባዊ አመጽን በተመለከተ ለምሳሌ በሊቢያ ያለው አይነት የሰብአዊ መብት ረገጣ በሌላው ዓለምም አለ ብሎ ለማለት አያስደፍርም፡፡ በእኔ እምነት በሰሜን አፍሪካና በአንዳንድ አገሮች የምንመለከተው ሕዝባዊ ተቃውሞ ከእነዛ አገሮች የጭቆና ታሪክ ጋር የተቆራኘ ምክንያት አለው፡፡ ፍርሀት፣ ተስፋ መቁረጥ እና ጭቆና የፈጠረው ብሶት የየአገራቱ ሕዝቦች ለለውጥ እንዲነሳሱ ምክንያት ሆኗል፡፡ እናም መንግስታት ለዜጎቻቸው ጥቅምና ፍላጎት ሊሰሩ ይገባል፡፡ ኢንቨስትመንትን በማስፋፋት ለዜጎች የስራ እድል መክፈት አለባቸው፤ ለልጆቻቸው የትምህርት ዕድል ማመቻቸት ይገባቸዋል፡፡ እነዚህን ነገሮች በሰሜን አፍሪካ ያሉ ሕዝቦች ከመንግስቶቻቸው ማግኘት ያልቻሏቸው ነገሮች ናቸው፡፡ ይህ ደግሞ በሌላው የአለም ክፍል ካለው ሁኔታ ፍፁም የተለየ ነው፡፡

ቀደም ሲል ከኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት ጋር በምትወያዩ ሰዓት የማትስማሙባቸው ጉዳዮችም እንዳሉ ገልፀውልን ነበር፡፡ እነዛ ነገሮች ምን ምን እንደሆኑ ሊነግሩን ይችላሉ? በአንዳንድ ጉዳዮች ላይ እንስማማለን፡፡ የተወሰኑት ደግሞ የበለጠ ሰፊ ውይይት የሚጠይቁ ሆነው ይገኛሉ፡፡ በአጠቃላይ

ከልማት ጋር የተያያዙ፣ የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ሊያሳድጉ በሚችሉ ጉዳዮች ላይ እንስማማለን በፀጥታና ተያያዥ ጉዳዮችም ላይ ተመሳሳይ አቋም አለን፡፡ ተስማምተንም አብረን እየሰራን ነው፡፡ ስለዚህ ብዙ የሚያስማሙን ነገሮች የመኖራቸውን ያህል ተጨማሪ ውይይት የሚጠይቁ ጉዳዮች እንዳሉ ይታወቃል፡፡ ከእነዚህ ጉዳዮች አንዱ ሰብአዊ መብትን የሚመለከቱ ነጥቦች ናቸው፡፡ እነሱም ቢሆኑ እየተሻሻሉ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ሁኔታ በሚገባ እንረዳለን እናም ያልተሻሻሉ ነገሮች እንዲሻሻሉ በውይይትና በመግባባት ጥረት እናደርጋለን፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት በኤርትራ ላይ የስትራቴጂና የአቋም ለውጥ ሲያደርግ በተለይ ወታደራዊ አማራጭን የሚከተል ከሆነ ይህንን እንዴት ትመለከቱታላችሁ?

የኢትዮጵያ ባለስልጣናትም እሱን አማራጭ እንደሚጠቀሙ ነግረውኛል፡፡ የጦርነት አማራጭ ብዙ ዋጋ ያስከፍላል፡፡ ከአስር ዓመት በፊት በሁለቱም አገሮች መካከል የተቀሰቀሰውን ጦርነት ብንመለከት እንኳን ወደ መቶ ሺህ የሚጠጋ ሕዝብ መስዋዕትነት ከፍሎበታል፡፡ ያንን ደግሞ ማንም ማየት አይፈልግም፡፡ ነገር ግን አገሮች ራሳቸውን የመከላከል መብት አላቸው፡፡ ያንን እኛም እንደግፋለን፡፡

አሁንም ብዙ ወራት ወደኋላ ልመልስዎትና ለመጀመሪያ ጊዜ ከጋዜጠኞች ጋር የተገናኙት ዛሬ በመሆኑ በ2002ቱ ምርጫ ኢሕአዴግ 99.6% ማሸነፉ በቀጣይነት በኢትዮጵያ ሊኖር ከሚገባው የዴሞክራሲ ግንባታ አንፃር ውጤቱን እንዴት አገኙት?

ምርጫውን በተመለከተ በወቅቱ መግለጫ ሰጥተናል፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ የምርጫውን ውጤት ተቀብሏል፡፡ እሱን መፈታተን የእኛ ኃላፊነት አይደለም፡፡ ከመንግስት ጋር በሰብአዊ መብት፣ በዴሞክራሲ በመልካም አስተዳዳር ጉዳይ ላይ አብረን እየሰራን ነው፡፡ በሚያስማሙን ጉዳዮች ላይ አብረን እየሰራን በማያስማሙን ጉዳዮች ላይ ደግሞ ቀጣይ ውይይት በማድረግ ላይ እንገኛለን፡፡ ስለዚህ አስር ወር ወደኋላ ከመመለስ ይልቅ የወደፊቱን እያስተካከሉ መሄድ የኢትዮጵያን ሕዝብ የበለጠ ይጠቅማል፡፡... ቀደም ብዬ እንደገለፅኩት በአንድ ጉዳይ ላይ ብቻ ትኩረት አድርጎ ሌሎች የአጋርነት ሴክተሮችን ከማስተጓጎል ይልቅ ኢትዮጵያ መካከለኛ ገቢ ወዳላቸው አገሮች የምታደርገውን ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ብንደግፍ ይሻላል፡፡ ኢትዮጵያ እዚያ ደረጃ ላይ ስትደርስ ዕድገቱ በራሱ አሜሪካ ወደምትደግፈው ዴሞክራሲና የመድብለ ፓርቲ ስርዓት እንድታመራ ያግዛታል፡፡

‹‹ጭቆና የፈጠረው ብሶት … የየአገራቱ ሕዝቦች ለለውጥ እንዲነሳሱ ምክንያት ሆኗል››

እየተወያየን የምናሻሽላቸው ነገሮች እንዳሉ ይታወቃል፡፡ በሰብአዊ መብት አያያዝ፣ በመልካም አስተዳዳር እንዲሁም በልማትና ዕድገት፣ እንዲሁም በአካባቢያዊ ሰላምና ፀጥታ ዙሪያ ሁሌም ነገሮች እንዲሻሻሉ እንወያያለን፡፡ በአንዳንዶቹ ላይ ሳንግባባ እንለያያለን፡፡ በአንዳንዶቹ ላይ እንግባባለን፡፡ ... ዳኛ ብርቱካንን በተመለከተ አገሯን ጥላ ወደ አሜሪካ ለመሸሽ እንደተገደደች ገልጸሀል፡፡ እኔ ግን የጉዞዋን ምክንያት እንደዛ አድርጌ አልተረዳሁትም፡፡ እስር ቤት ከመቆየቷ ጋር ተያይዞ ከደረሰባት ችግር ለማገገም ወደ አሜሪካ እንደተጓዘች ነው የገባኝ፡፡ አገሯን ጥላ እንደምትሄድ ስላልነገረችኝ እንደዛ ነው ብዬ ለመውሰድ እቸገራለሁ፡፡

የግሉ ሚዲያ እንዲጠናከር ፍላጎት እንዳላችሁ በተለያየ አጋጣሚ ስትገልፁ ይሰማል፡፡ ከዚህ አንፃር በጋዜጦች የማተሚያ ዋጋ ላይ በቅርቡ የተደረገውን ከፍተኛ ጭማሪ እንዴት ታዩታላችሁ?

የሕትመት ዋጋ ጭማሪውን በተመለከተ የህትመት ሚዲያዎች ፈተና እንደገጠማቸው፤ እንደውም አሳታሚዎች የዋጋ ጭማሪው ለሦስት ወር እንዲራዝምላቸው ያቀረቡት ጥያቄም ውድቅ እንደተደረገባቸው ሰምቼአለሁ፡፡ እንግዲህ ለሕትመት ዋጋ ጭማሪው ዋነኛው መንስኤ በዓለም አቀፍ ደረጃ እየተስተዋለ ያለው የወረቀት ዋጋ መወደድ ችግር ነው፡፡ የአሜሪካ ሚዲያዎችም ተመሳሳይ ችግር እንደገጠማቸው ይታወቃል፡፡ የሕትመት ሚዲያው ችግር እየገጠመው ያለው በዓለም አቀፍ ደረጃ ወረቀት በመወደዱ ብቻ ሳይሆን የኤሌክትሮኒክስ ሚዲዎች በዘመናዊ መልኩ በማደጋቸው ዘርፉ በፍትሀዊ መንገድ ተወዳዳሪ ሆኖ እንዳይዘልቅ ችግር ስለተጋረጠበትም ጭምር ነው፡፡ እና በአሁኑ ሰአት የአሜሪካ ሕትመት ሚዲያዎች ችግሩን ለመቋቋም እየሞከሩ ነው፡፡ እንደውም አንዳንዶቹ ወደ ኤሌክትሮኒክስ ሚዲያ ለመሸጋገር ሙከራ እያደረጉ ነው፡፡ አንዳንዶቹ ደግሞ መጠኑን በመቀነስና የተለያዩ ስትራተጂዎችን በመንደፍ በተመጣጣኝ ዋጋ ለአንባቢ ለማቅረብ እየሞከሩ ነው፡፡ ስለዚህ በእኔ እምነት እዚህ ያለው ሚዲያም በተለይ በአሜሪካ ያሉ ሚዲያዎች የተከተሏቸው አይነት አማራጭ ስትራተጂዎችን መከተል ያለበት ይመስለኛል፡፡ ...የአሜሪካ መንግስት በሕገ-መንግስቱ ላይ በግልፅ ካስቀመጣቸው መርሆዎች አንዱ የፕሬስ ነፃነት ነው፡፡ እናም የነፃና ገለልተኛ ሚዲያ መኖር አሜሪካ በፅኑ የምትደግፈው ነው፡፡ ኢትዮጵያም ውስጥ ጠንካራ ፕሬሶች (ፕሬስ ስንል የግሉ ፕሬስ ብቻ ሳይሆን ሁሉንም ለማለት ነው) እንዲኖሩ እንፈልጋለን፡፡ ይህ ማለት የአሜሪካ መንግስት የሕትመት ጭማሪውን በመደጎም እገዛ ያደርጋል ማለት ሳይሆን ሚዲያው ሌሎች አማራጭ የቢዝነስ ዘዴዎችን እንዲከተል በሚያስችል ሁኔታ (ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በመተባበር) ስልጠና በማመቻቸት እገዛ ልናደርግ እንችላለን፡፡ ምክንያቱም በሌሎች አገሮችም ይህ አይነቱ ቴክኒካዊ ስልጠና ሚዲያዎች ሕልውናቸውን ጠብቀው እንዲቀጥሉ ያስችላቸዋልና፡፡

በእርስዎ የአምባሳደርነት ዘመን ያለው የሁለቱ አገሮች የግንኙነት እንቅስቃሴ ካልተሳሳትኩ በአብዛኛው በትምህርትና በባሕል ጉዳዮች ላይ ይበልጥ ትኩረት ያደረገ ይመስለኛል ለምንድነው?

እንግዲህ በፕሬስ መግለጫው ላይ ትኩረት ለመስጠት እንደተሞከረው የሁለቱ አገሮች ግንኙነት ከንግድና ኢንቨስትመንት ባሻገር ሚዛናዊ በሆኑ በርካታ ጉዳዮችም ላይ

የኢትዮጵያ ባለስልጣናትም እሱን አማራጭ እንደሚጠቀሙ ነግረውኛል፡፡ የጦርነት አማራጭ ብዙ ዋጋ

ያስከፍላል፡፡ ከአስር ዓመት በፊት በሁለቱም አገሮች መካከል የተቀሰቀሰውን ጦርነት ብንመለከት እንኳን

ወደ መቶ ሺህ የሚጠጋ ሕዝብ መስዋዕትነት ከፍሎበታል፡፡ ያንን ደግሞ ማንም ማየት አይፈልግም፡፡

ነገር ግን አገሮች ራሳቸውን የመከላከል መብት አላቸው፡፡ ያንን እኛም እንደግፋለን፡፡

Page 14: Awramba Times Issue 161 Megabit 24

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 161 ቅዳሜ መጋቢት 24 200314

ሕብር ስኳር አክሲዮን ማህበር Hiber Sugar Share Company

ሕብር ስኳር አ.ማ ከ5,280 በላይ የሚሆኑ አባላቱን በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ጽ/ቤት ማስፈረም ጀምሯል፡፡ ቀዳሚዎቹ ፈራሚዎች የቦርድ አባላትና 32ቱ ዋና መስራቾች ሆነዋል፡፡

ስለሆነም እስከ ጥር 25/2003 ዓ.ም አክሲዮን የገዛችሁ የተከበራችሁ የሕብር ስኳር አ.ማ ቀሪ መሥራች አባላትና ባለአክሲዮኖች በሚከተለው ሠንጠረዥ መሠረት በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ቢሮ ቀርባችሁ እስከ መጋቢት 30 ቀን

2003 ቀን ድረስ እንድትፈርሙ የአክብሮት ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡

ስማችሁ የሚጀምርበት ፊደልና ተራ ቁ. የመፈረሚያ ቦታ(A)የ አ ዝርያ(ከተራ ቁ. 1-913)

ዋናው መስሪያ ቤትሜክሲኮ አደባባይ አጠገብ ጨለለቅ አልሣም ታወር 2ኛ እና 3ኛ ፎቅ

(B, C, D, E)በ፣ ቸ፣ ጨ፣ ደ፣ ኢ፣ ኤ፣ እ ዝርያ(ከተራ ቁ. 914-1789)

ቅርንጫፍ 4 ጽ/ቤትአምስት ኪሎ አ.አ.ዩ ቴክኖሎጂ ፋኩልቲ ፊት ለፊት

(F, G, H, I, J, K) ፈ፣ ገ፣ ሀ፣ ሐ፣ኀ፣ ኸ፣ ጀ፣ከ፣ቀ ዝርያ(ከተራ ቁ. 1790-2731)

ቅርንጫፍ 1 ጽ/ቤትደብረ ዘይት መንገድ ተሻለ ገራዥ አጎና ሲኒማ ቤት አጠገብ ባለኬር ሕንፃ 1ኛ ፎቅ

(L, M, N, O, P, Q, R) ለ፣ መ፣ ነ፣ ኦ፣ ጰ፣ ረ ዝርያ(ከተራ ቁ. 2732-3613)

ቅርንጫፍ 3 ጽ/ቤት መገናኛ መንገድ ትራንስፖርት ሕንፃ ጀርባ ራሒም ሕንፃ 1ኛ ፎቅ

(S, T) ሰ፣ ሠ፣ ሸ፣ ተ፣ ጠ፣ ፀ፣ ጸ ዝርያ(ከተራ ቁ. 3614-4656)

ቅርንጫፍ 5 ጽ/ቤትሰሜን ማዘጋጃ ሸገር መናፈሻ አካባቢ ብርሃን ሕንፃ 1ኛ ፎቅ

(U, V, W, Y, Z)ኡ፣ ቪ፣ ወ፣ የ፣ ዘ፣ ዝርያ (ከተራ ቁ. 4657-5280)

ቅርንጫፍ 2 ጽ/ቤትመርካቶ ክፈለ ሀገር አውቶቢስ ተራን አለፍ ብሎ ሸዋ ፀጋ ሕንፃ 2ኛ ፎቅ

ወደ ሰነዶች ምዝገባና ጽ/ቤት ለፊርማ በምትመጡበት ጊዜ

የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ ወይም መንጃ ፍቃድ ወይንም ፓስፖርት 1. አክሲዮን የገዛችሁበትን የምዝገባ ቅጽ2. ገንዘብ የከፈላችሁበትን የባንክ ደረሰኝ3. ሕጋዊ ውክልና ማስረጃ4. ለሕፃናት የገዛችሁ (የልደት ሰርተፍኬት)5. በጋራ የገዙ ባለትዳሮች የጋብቻ ሰርተፍኬት (አንዳቸው እንዲፈርሙ)6. በማህበር የገዛችሁ (የተወከላችሁበትን ቃለ-ጉባዔ፣ መተዳደሪያና መመስረቻ ጽሁፎች ወይም የምዝገባ ሰርተፍኬት)

ይዛችሁ እንድትቀርቡ እያሳሰብን ሰነድ ላይ ፊርማችሁን ያላኖራችሁ አባላት የሕብር ስኳርን የአክሲዮን ባለቤትነት ሰርተፍኬት ማግኘት የማትችሉ መሆናችሁን ከወዲሁ እናስታውቃለን፡፡

ለስራ ቅልጥፍና ሲባል የምዝገባ ተራ ቁጥራችሁን በስልክም ሆነ ዋናው መ/ቤት በመምጣት ለማወቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ የሕብር ስኳር አክሲዮን ሽያጭ በሰነዶች ማረጋገጫ እና ምዛገባ ፅ/ቤት ፊርማው እስኪጠናቀቅ ድረስ ስለሚቀጥል አክሲዮናችሁን እንድታሳድጉና ሌሎች ፍላጎት ያላችሁ ሁሉ አክሲዮን በመግዛት የመጨረሻው ዕድል ተጠቃሚ እንድትሆኑ ጥሪ እናቀርባለን፡፡

የአንድ አክስዮን ዋጋ • = 1000ዝቅተኛው የአክሲዮን መጠን 1ዐ አክሲዮኖች • = 10,000የአገልግሎት ክፍያ 7• %

አክስዮን መግዛት የምትፈልጉ ሁሉ በኢትዮጵያ ፖስታ ድርጅት መላው ቅርንጫፎች እና በዋናው መስሪያ ቤት እንዲሁም በሽያጭ ወኪሎች አማካይነት መጠቀም የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

አድራሻ፡- ሕብር ስኳር አ.ማ ሜክሲኮ ከዲ’አፍሪክ ሆቴል ፊት ለፊት ታደሰ ተፈራ ሕንፃ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁ. 105ስልክ ቢሮ 0118501357/58 E-mail - [email protected] web - www.hibirsugarethiopia.com

ስማችሁ የሚጀምርበት ፊደልና ተራ ቁ. የመፈረሚያ ቦታ

(A)የ አ ዝርያ(ከተራ ቁ. 1-913)

ዋናው መስሪያ ቤትሜክሲኮ አደባባይ አጠገብ ጨለለቅ አልሣም ታወር 2ኛ እና 3ኛ ፎቅ

(B, C, D, E)በ፣ ቸ፣ ጨ፣ ደ፣ ኢ፣ ኤ፣ እ ዝርያ(ከተራ ቁ. 914-1789)

ቅርንጫፍ 4 ጽ/ቤትአምስት ኪሎ አ.አ.ዩ ቴክኖሎጂ ፋኩልቲ ፊት ለፊት

(F, G, H, I, J, K) ፈ፣ ገ፣ ሀ፣ ሐ፣ኀ፣ ኸ፣ ጀ፣ከ፣ቀ ዝርያ(ከተራ ቁ. 1790-2731)

ቅርንጫፍ 1 ጽ/ቤትደብረ ዘይት መንገድ ተሻለ ገራዥ አጎና ሲኒማ ቤት አጠገብ ባለኬር ሕንፃ 1ኛ ፎቅ

(L, M, N, O, P, Q, R) ለ፣ መ፣ ነ፣ ኦ፣ ጰ፣ ረ ዝርያ(ከተራ ቁ. 2732-3613)

ቅርንጫፍ 3 ጽ/ቤት መገናኛ መንገድ ትራንስፖርት ሕንፃ ጀርባ ራሒም ሕንፃ 1ኛ ፎቅ

(S, T) ሰ፣ ሠ፣ ሸ፣ ተ፣ ጠ፣ ፀ፣ ጸ ዝርያ(ከተራ ቁ. 3614-4656)

ቅርንጫፍ 5 ጽ/ቤትሰሜን ማዘጋጃ ሸገር መናፈሻ አካባቢ ብርሃን ሕንፃ 1ኛ ፎቅ

(U, V, W, Y, Z)ኡ፣ ቪ፣ ወ፣ የ፣ ዘ፣ ዝርያ (ከተራ ቁ. 4657-5280)

ቅርንጫፍ 2 ጽ/ቤትመርካቶ ክፈለ ሀገር አውቶቢስ ተራን አለፍ ብሎ ሸዋ ፀጋ ሕንፃ 2ኛ ፎቅ

ማስታወቂያ

Page 15: Awramba Times Issue 161 Megabit 24

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 161 ቅዳሜ መጋቢት 24 2003

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

15

ደሳለኝ ሥዩም [email protected]

ድንግል ሀገሬ ሆይ ጥንተ ተደንግሎየሕፃናቱን ደም አዘክሪ ኩሎሕፃናቱ ታርደው ያንችም ልብ ቆስሎልጅሽ ተሰደደ አንችን ተከትሎአስጨነቀኝ ስደትሽእመቤቴ ተመለሽ ተመለሽ/ዬፍታሔ ንጉሤ እና ሰይፉ መታፈሪያ ፍሬው/

ዓይን አያሳየው የለ ከሚሉት አባቶቻችን ይችኑ ቃል እንውረሳ፡፡ የጋዜጣ ሕትመት ባንዴ ዋጋው ሽቅብ ተሰቀለ አሉ፡፡እነሆ ኅሊናዬ ከነገር ብዛት በብሶት መደረት ተረበሸና እንዲህ ነው እንዲያ ነው ሳልል ዘው አልኩ፡፡ ዛሬም ብሶት አመጣኝ፡፡ እስቲ ይህችው ጉሮሮአችን እስክትዘጋ እንወጋወግባት፡፡ መልካም ወግ ከማር ይልቅ እንደሚጣፍጥ መክረውበት አዲስን የፈጠሩበት አባቶቻችን ምስክሮች ናቸው፡፡የሕፃናት መታረድ፣ የአዋቂዎች መታገት፣ የወጣቶች መጨቆንን ማሰብ አሰከረኝና ገጣሚ ሰይፉ መታፈሪያ ፍሬው የተጓጎጠ ልብ ባለው የግጥም መጽሐፉ መግቢያ ላይ የራሱን ስንኝ ቀላቅሎ ያሰፈረውን የዮፍታሔ ንጉሤን ግጥም አስቀደምኩ፡፡ ቃሉ ራሱ ይከብዳል ያስጨንቃል፡፡ ‹ሕፃናቱ ታርደው ያንችም ልብ ቆስሎ› ይላል አንዱ የግጥም ዘለላ፡፡ ልጆቿ ሲፈጁ፣ ልጆቿ በጨለማ እንዲኖሩ ሲበየን ልቧ የማይደማ እናት፣ ውስጧ የማያለቅስ ሀገር የትኛዋ ናት? በዚህ ዘመን ብረት ተጠፍጥፎ የሚሰራ ቢላ ይዞ ልጅሽን ላርድ ነው የሚል እየጠበቅን ከሆነ ይበልጡንም ለመታረድ የዋሆች ነን፡፡ ከዕለት ዕለት እየተንገዳገደ የነበረውን የጋዜጣ ሕትመት ይበልጡን ለማቀዛቀዝ ወይም ጨርሶ ለማውደም ይመስላል ሃምሳ ፐርሰንት ዋጋ ጨመሩበት አሉ፡፡እንዲያው ለነገሩ ስለምን እንደምንናገር የማይገባው ነው ወይስ እንዲገባው የማይፈልግ ነው ያለው? የቢራን ዋጋ ቀንሱ ብለን ሳንተነፍስ ዋጋ ተመን አወጣን እና ኑሮን አረጋጋንላችሁ እንባላለን፡፡ ሰው በሳምንት ሰባት ቀን ቢራ የሚመገብ ይመስል፡፡እስቲ ያለውን እንችለዋለን፣ ይህንንም ቀን እናልፈዋለን ብለን ስንቀመጥ ደግሞ ቁልቁል ካልቀበርናችሁ አንረካም ለማለት በሚመስል አኳኋን መብታችን እንዲደፈጠጥ የእንቅፋት መዓት ይከመርብናል፡፡ የመናገር እና የመፃፍን መብት ማፈን፤ ለዚያውም በዚህ ዘመን፡፡ አንድ የኮምፒዩተር ኢንጅነር ወዳጄን ይህንን ሰሞን አንድ የቸገረኝን ነገር ነገርኩት፡፡ ‹‹ኮምፒዩተሬ ላይ የማስቀምጣቸው ፋይሎች ይጠፉብኛል ... ለነገሩ ከእኔ ውጭም በኮምፒዩተሩ የሚጠቀሙ ሰዎች አሉ፡፡ እና አውቀው በድፍረት ሳያውቁ በስህተት እየደለቱብኘ ስለተቸገርኩ ምን መፍትሔ ትሰጠኛለህ? ... እንዲያው የሆነ ቴክኖሎጂ ይኖር ይሆን?›› አልኩት ፡፡ኢንጅነሩ ወዳጄ እንዲህ አለኝ፣ ‹‹በዚህ ዘመን አእምሮ ከማጥፋት በላይ ቅንነትን ማሰብ እንዳለበት ስለታመነ ይህን የሚቆጣጠር ቴክኖሎጂ የለኝም፡፡›› ታዲያ እነዚህ ከዘመናችን ምን ያክል ቢርቁ ነው ጥፋት እና ሰውን ማስጨነቅ ብቻ የሚታያቸው?ገና ለገና ሀሳቦች ይንሸራሸራሉ፣ እውነታዎች ይፃፋሉ፣ ሰው ከሰው ይገናኛል ተብሎ የወረቀትን ዋጋ ከዕለት ዕለት ማናር በሕዝቡ ላይ መፍረድ ነው፡፡ የማይታይ ግን የሚያብለጨልጭ ቢላ ይዞ መቅረብ ነው፡፡ እስከዛሬ ከዚህ በተለየ ዓይን እያየን እውነትም ተቸግረዋል እያልን ታግሰን ኖረን አልነበር? እነሱም ታዲያ ትዕግስታችንን ተረድተውልን የቢራን ዋጋ አስቀነስንላችሁ አሉ፡፡ ...ነገ ከነገ ወዲያ ደግሞ የሲጋራ እና የጫት ዋጋ ያስቀንሱልን ይሆናል፡፡ እንዲያው ለመሆኑ ሕዝብ ቢሰለጥን ማን ወይ ምናችን ይጎዳል? ዜጎች ቢማሩ፣ ሰዎች ቢያውቁ፣ መረጃ ፈጣን ቢሆን ማን ይሞታል? ቢራ ፋብሪካ ላይ ተፅዕኖ መፍጠር የቻለ መንግስት የወረቀት ቀረጥ ላይ መወሰን የቸገረው ለምንድን ነው? እያስተማርናቸው ያሉ ተማሪዎቻችን ብለን የምንጠራቸው ቁጥሮች እስቲ እውን ይሁኑ፡፡ ቁጥርም ብቻ ሳይሆን የአእምሮ እድገትም እውን ይሁን እስቲ፡፡ ፊደል የቆጠረ ያንብብ፤ ያነበበ ይፃፍ፤ የተፃፈ ይስፋፋ፤ ሰው ከእውቀት፣ ከጥበብ፣ ከቴክኖሎጂ ጋር ይገናኝ፡፡ እንደፈለገ አንብቦ እንደልቡ ይፃፍ፡፡ለሆነው ሁሉ ምክንያቱ ምንድን ነው እያልኩ አንዳንዴ አስባለሁ፡፡ ዘጠና እጅ የሚሆኑት ጋዜጦች የሚታተሙበት አንድ ማተሚያ ቤት በድንገት ሃምሳ ፐርሰንት የዋጋ ጭማሪ ሲያደርግ በሺዎች የሚቆጠሩ ቤተሰቦችን ህይወት እንደሚያተረማምስ ማሰብ የነበረበት ይመስለኛል፡፡ ግና ማሰብ በነሱ ዘንድ ከባድ ሆኖ አየሁት፡፡ የምር ዳገት የመውጣት ያክል ሆኖባቸው አየሁት፡፡ እንጅማ ፀሐፊዎች፣ አሳታሚዎች፣ ጋዜጠኞች፣ አከፋፋዮች፣ አዟሪዎች እና ተሳታፊዎች የሚተራመስ ህይወት እንዳላቸው አጥተውት አይደለም፡፡ ሕዝባችን ዘመንን እየተከተለ፣ መረጃን እየፈለገ፣ ይህንንም ልማዱን ዕለት ዕለት እያዳበረ በመጣበት በዚህ ወቅት የመረጃ ሰጭንና ተቀባይን ሞራል የሚነካ እንቅፋት ድንገት ተምዘግዝጎ ይወርዳል? ተገቢ ነበር? እስቲ ይሁንላቸው፤ የአረብ ሀገራት የመተራመስ ወሬ ሀገራችን ውስጥ እንዳይወራ ይፈልጉ፡፡ ግን ቢወራ እዚህ ሀገር ብጥብጡ ይከሰታል ብሎ ማሰቡ ለእኔ ቀልድ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ ራሱን ያውቃል፡፡ የአረብ ነገስታት ይቀየሩልን ብሎ ሕዝባቸው ስላመፀ የኢትዮጵያ ሕዝብ ተነስቶ በመንግስት ላይ ድንጋይ ይወረውራል ብሎ ማሰብ ሞኝነት ያጀበው ንቀት ነው - ለእኔ፡፡ እና ያረቦችን ውሎ ሕዝቡ በጋዜጣ እንዳይደርስበት (የሀገር ውስጥ አጀንዳዎች እንደተጠበቁ ሆነው) አስበው የደረሱበት ዘዴ የጋዜጣ ወረቀት ተወደደ ብሎ በአንዴ ሃምሳ እጅ ዋጋ መጨመር ነው፡፡ እንዳላዝን ለማን? እንዳላፍር ያልፈጠረብኝን! እንዳልጮህ ለማን? እንዳላለቅስ እንዴት? እኒህን ሁሉ ስሜቶች ደበላልቄ እስቃለሁ፡፡ የማተሚያ ቤቱ (የብርሃንና ሰላም) የሥራ ኃላፊ ለአንድ ጋዜጣ የሰጡትን ቃል አስተዋልኩት፤ ‹‹የዋጋ መጨመር እና የፕሬስ ነፃነት መታፈንን የሚያገናኛቸው ነገር የለም›› የሚል ቃል አለበት ፡፡ እንግዲህ በእሳቸው እሳቤ ይህን ያክል ወደኋላ ቀርተናል ማለት ነዋ፡፡ እሳቸው እንዲህ ያስቡናል፡፡ እኛ ማለት የፕሬስ ነፃነት መብታችን የተከበረልን፣ መብታችን ተገድቧል ለማለት የሚያስችል ምንም ምክንያት የሌለን፣ ቢኖረንም እንኳ በየአደባባዩ ትላልቅ ታፔላዎች የፕሬስ መብት የለም ብለው እስካላወጁ ድረስ እንደተጨቆን አገሩ ሰላም ነው ብለን የምናስብና የምንኖርም ነን - ለእሳቸው፡፡

እርግጥ ያረጀ ወሬ መርጦ አንዳንዴም አዛብቶ የሚያቀርበውን የመንግስት ሚዲያ ብቻ እንደጤፍ እንጀራ በየዕለቱ እየተቋደስን! ... እንደዚች ሀገርም የፕሬስ ነፃነት አላየን (ከትከት ብሎ መሣቅ ጥርስ ያነቃንቃል ያሉት አያቴ ወይስ ጎረቤቴ?)የፕሬስ ነፃነት ማለት ‹‹አዲስ አበባ ከመጣሁ ሁለት ሳምንት ሆነኝ›› ብሎ መግለጫ የሰጠን ፈረንጅ ንግግር አዲስ አበባ ውስጥ ሁለት ሳምንት እቆያለሁ አለ እየተባለ የሚተረጎምበት የመንግስት ቴሌቪዥን መከታተል ነው፡፡

ትውልድ እናስብ፡፡ ነገ እንደምንኖርበት እርግጠኛ በማንሆነው ወንበር ላይ ተቀምጠን ሰውን ደስ የማያሳኝ፣ ሀገርን ኡኡ የሚያሰኝ፣ ወገንን የማያኮራ ተግባር አናከናውን፡፡ ወዴት ነው መሄዳችን? ወደምንድን ነው መጓዛችን? ከማን ነው መሰወራችን? ማንን ነው መዋሸታችን? ማንን ነው መጉዳታችን? ለመፃፍ ስሜታዊ መሆንን የሚመክር የለም፡፡ እኔ ግን እንደዚያ ሆንኩ፡፡ እና መቀበጣጠሬን በአንድ ሀገርኛ ተረት ልጠቅልል፡፡አንድ ጅብ ነበር፡፡ ጅብ፡፡ ሆዳም ጅብ፡፡ በልቶ የማይጠግብ ከእሱ ውጭ መሠሪ የሌለ የሚመስለው፡፡ ሁሉን መሸወድ እና መብለጥ እንደሚችል የሚያስብ ጅብ፡፡በአሳቻ ሰዓት እየጠበቀ የገበሬዎችን የቤት እንስሳት በመብላቱ ይኩራራል፡፡ ምንም ሊፈጥሩ እንደማይችሉ ያምናል፡፡ አንድ ቀን ግን ጉድ ሆነ፡፡ አንድ ገበሬ ታላቅ ጉድጓድ ቆፍሮ በውስጡ የሞተ እንስሳ አስቀመጠ፡፡ የጉድጓዱን አፍም በቅጥል ሸፈነው፡፡ ብልጡና የማይሸወደው ታላቁ ጅብ የሞተውን እንስሳ እያሸተተ እየተንጎማለለ በቅጠሉ ላይ መራመድ ጀመረ፡፡ ቅጠሉ ከዳውና ጉድጓዱ ውስጥ ገባ፡፡ ገበሬውም ፈጥኖ ደርሶ እልሁን ሊወጣ ደጋሞ በጦር ይወጋውና ሳይሞት ጥሎት ይሄዳል፡፡ ታላቁ ጅብ ታዲያ ቆስሎ ሳይሞት በጉድጓድ ውስጥ ቀናትን በማሳለፉ ተራበ፡፡ ርሀቡ ሲጠናበት ከምርጥ አእምሮው ዘንድ ዘዴ አፈለቀ፡፡ በገበሬው ጦር ሲወጋ የተዘረገፈ የገዛ አንጀቱን መብላት ጀመረ፡፡ የታላቁ ጅብ ፍፃሜ ራሱን በራሱ በልቶ መጨረስ ነበር፡፡

ቸሩ ያሰንብተን!

Private Hospitals AssociationVacancy Announcement

1. Position Title: Manager of the Association a. Place of work: Addis Ababab. Educational Qualification: B.A, B.Sc. Or LLB or MA in Management, Economics, Health Science Law or any other social science and related fields c. Work Experience: 2-3 Years relevant work experience d. G.P.A: 2.8 and above e. Age: Below 40 years f. Salary: Negotiable g. Terms of employment: On contract h. Other requirement skill: Computer proficiency is mandatory i. Work Schedule Full time

2. Position Title: Administrative Assistant a. Place of work: Addis Ababab. Educational Qualification: Diploma in Secretarial Science or B.A. in Management c. Work Experience: 2 years relevant work experience d. G.P.A: 2.8 and above e. Age: Below 35 years f. Salary: Negotiable g. Terms of Employment: On contract h. Other requirement skill: Computer Proficiency is mandatory i. Work Schedule: Full time

3. Position Title: Accounting Assistant place of work: Addis Ababa a. Educational Qualification: Diploma or B.A in Accounting b. Work experience: 2 years relevant work experience c. G.P.A: 2.8 and above d. Age: Below 35 years e. Salary: Negotiable f. Terms of Employment: Permanent g. Other required skill: Computer proficiency is mandatory h. Work Schedule: Full time i.

Interested and qualified applicants are invited to submit their application, CV and other testimonials to Dr. Asmamaw Kelemu at the CURE Hospital, near Hamle 19 Park, within 7 days after the announcement. The Association has full right to reject or take any other option in this regard.

for more information please contact 0911 60 12 96

‹‹ሰሞኑን የሚንስትሮች ስብሰባ ነበር ... ምን መረጃ ትሰጡኛላችሁ?›› ተብሎ ሲጠየቅ ስብሰባ ነበራቸው እንዴ? የሚል የመንግስት የሬዲዮ ጣቢያ መከታተል ለመብታችን መከበር ታላቁ ማሳያ ነው፡፡በእርግጥ ስለ መንግስት ድጎማ ቀመር ስሌት የማውቀው ጉዳይ የለም፡፡ ለሕዝቡ መሠረታዊ የሆኑ ነገሮችን ዋጋ ለማመጣጠንና በተገቢው ብዛት እንዲሰራጩ ሲባል በአንዳንድ ነገሮች ዋጋ ላይ ድጎማ እንደሚደረግ እሰማለሁ፡፡ በዚች ሀገር በዚህ ጊዜ (እነሱ ራሳቸው የእድገት እና የልውጠት ጊዜ ብለውታል) ለዚህ ሕዝብ የሚያስብ እውነተኛ መንግስት ከሆነ ሲጀመር ወረቀት አልተወደደም፣ ቢወደድ እንኳ ድጎማ ማድረግ ያለበት ይመስለኛል፡፡ እንጅ ባልተወደደ ወረቀት ሁለት ወገን ፍላጎት (የገንዘብ እና የአፈና) ለማሟላት መፈለግ ተገቢ አይመስለኝም፡፡ አንድ ኢትዮጵያዊ ያለበትን የመረጃ ስስት ለማርካት በሳምንት በሳምንት ሦስት ጋዜጦችን ቢገዛ በወር ምን ያህል ወጭ ሊያወጣ እንደሚችል ይታሰብና ይህም እንደመሠረታዊ ፍጆታ የሚቻል ወጭ ነው? ይባስ ተብሎ ደግሞ ዋጋ ይጨመራል፡፡ አንድ የሚደንቀኝ ጉዳይ አለ፡፡ ዕለት ዕለት ብሶታችንን ስንናገር የሚሰማን (የሚያነበን) የመንግስት አካል የለም፡፡ ቻይና ወይም ጣሊያን ውስጥ አንድ የሰፈር ጋዜጣ የቦሌ መንገድ ያምራል ብሎ ቢፅፍ (እንደሚያምር እያወቅነውም) በቴሌቪዥን ሰፊ ሰዓት ተሰጥቶት እንደገና ይነበብልናል፡፡እስቲ ይችን ሀገር፣ ይኼን ሕዝብ፣ በተለይ ነገ ይመጣል የምንለውን

የታላቁ ጅብ ውድቀት

Page 16: Awramba Times Issue 161 Megabit 24

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 161 ቅዳሜ መጋቢት 24 2003

መፍትሄው ለሕዝብ ጥያቄ ቀና መልስ መስጠት ነው

16

ከጥቂት ወራት በፊት በተቀሰቀሰዉ ሕዝባዊ ንቅናቄ፣ ቢያንስ ቢያንስ አራት መቶ ሰዎች በግብጽ፣ ሁለት መቶ በቱኒዚያ፣ ሰባት በባህሬን ሕይወታቸውን አጥተዋል። የቱኒዚያዉ ቤን አሊ፣ የግብጹ ኦስኒ ሙባረክ ለአሥር አመታት ከተቆናጠጡበት የስልጣን ወንበር የተወገዱ ሲሆን የሊቢያዉ ጋዳፊ፣ የሶሪያዉ ባሺር አላሳድና የየመኑ ሳሌህ የሕዝብ ቁጣ በለኮሰዉ እሳት ችግር ዉስጥ እንዳሉ በገሃድ እያየን ነዉ።

እርግጠኛ ነኝ በአብዛኛዉ ኢትዮጵያዊ አይምሮ ዉስጥ አንድ ጥያቄ እንደሚመላለስ። እርሱም «በአረብ አገሮች የታየዉ እንቅስቃሴ መች ይሆን በኢትዮጵያ የሚታየዉ?» የሚለዉ ጥያቄ ነዉ።

አቶ በረከት ስምኦን በግብጽ የታየዉ አይነት ሕዝባዊ ንቅናቄ በኢትዮጵያ ሊታይ እንደማይችል ይናግራሉ። ለዚህም የሚሰጡት ምክንያት በኢትዮጵያ «እየታየ ነዉ» የሚሉትን የኢኮኖሚ እድገት ነዉ። «ኢትዮጵያ እያደገች የመጣች አገር ናት። ድህነት እየቀነሰ ነዉ። በመሆኑም ህዝቡ ለሰልፍና ለተቃዉሞ የሚወጣበት ምክንያት አይኖረዉም» ይላሉ አቶ በረከት። የእኝህን ሰዉ አባባል በሌላ መልኩ ሳስቀምጠዉ «ግብጽና ቱኒዚያ እንደ ኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ልማት ላይ ቢያተኩሩ ኖሮ አሁን የታየዉ ክስተት አይታይም ነበር» ማለታቸዉ ይመስለኛል።

ለአቶ በረከት አስተያየት ቀጥተኛ ምላሽ ከመስጠት ይልቅ፣ በመላ ምትና በስሜት ላይ የተመረኮዘ ሳይሆን በመረጃ የተደገፈ አንዳንድ ነጥቦችን ለማስቀመጥ እሞክራለሁ።

የሲ.አይ.ኤ መረጃ እንደሚዘግበዉ በኢኮኖሚ አንጻር የኢትዮጵያ ሕዝብ ከግብጽና ከቱኒዚያ ሕዝብ ጋር ሲነጻጽር በከፋና በመራራ ድህነት ላይ ነዉ የሚገኘዉ። ብዙ ጊዜ ስለኢኮኖሚ ስናወራ ጂዲፒ (GDP) የሚለዉን ቃል እንጠቀማለን። የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር «በአሥራ አንድ በመቶ አደግን» በሚሉበት ጊዜ የሚያወሩት ስለ ጂዲፒ ነዉ። ነገር ግን ኢኮኖሚስቶች የአንድን አገር የኢኮኖሚ እድገት ለማወቅ የሚጠቀሙት ጂዲፒን ሳይሆን ጂዲፒ ፐር ካፒታ (GPD Per Capita) የሚሉትን ነዉ። ጠቅላላ ጂዲፒዉ፣ አገሪቷ ባላት የሕዝብ ብዛት ሲካፈል ጂዲፒ ፐር ካፒታን ይሰጠናል።

የግብጽ ጂዲፒ ፐር ካፒታ 6200 ዶላር ሲሆን የቱኒዚያ ደግሞ ወደ 9500 ይደርሳል። የኢትዮጵያ ከ1000 ያነሰ ነዉ። ይህ ምን ያህል ኢትዮጵያ ከግብጽና ከቱኒዚያ ጋር ስትነጻጸር እታች የምትገኝ አገር እንደሆነች ያሳያል።

በግብጽ የሥራ አጡ ቁጥር ሃያ በመቶ ሲሆን በቱኒዚያ 3.5 በመቶ አካባቢ ነዉ። በኢትዮጵያ ምን ያህል እንደሆነ አይታወቅም። ቁጥሩ በጣም ትልቅ ከመሆኑ የተነሳ፣ ጊዜ ወስዶ የሥራ አጡን ቁጥር የቆጠረ አካል ወይንም ድርጅት አናገኝም።

እርግጥ ነዉ በተለያዩ መስክ በተለይም የኢሕአዴግ አባል ለሆኑ የሥራ እድል እየተከፈተ ነዉ። ነገር ግን አሁን አብዛኛዉ ሕዝባችን ምናልባትም ከስባ በመቶ በላይ የሚሆነዉ፣ ሥራ አጥ ነዉ። ዜጎች የስራ እድል የማይከፈትላቸዉ ከሆነ፣ አገሪቷ ትልቅ የኢኮኖሚ ችግር ላይ እንዳለች መገመት አያስቸግርም። ዜጎች ተምረዉ ሥራ ካላገኙ፣ ለአመታት በቤተሰቦቻቸዉ ላይ ጥገኛ ሆነዉ ይቆያሉ አሊያም ከአገር ይሰዳዳሉ።

ሶስተኛዉ የኢኮኖሚ እድገት መለኪያ አገሪቷ ያላት የዉጭ ምንዛሪ ተቀማጭ ነዉ። በአገር ዉስጥ ለመገበያያ ብርን መጠቀም ይቻላል። ነገር ግን ከዉጭ አስፈላጊ እቃዎችን ለማስገባት ከተፈለገ በቂ የዉጭ ምንዛሪ ያስፈልጋል። ግብጽ በአመት 26 ቢሊዮን፣ ቱኒዚያ ደግሞ 17 ቢሊዮን ዶላር በኤክስፖርት ሲያስገቡ ኢትዮጵያ 1.7 ቢሊዮን ዶላር ብቻ ነዉ የምታስገባዉ። ምን ያህል ግብጽ/ቱኒዝያ በአንድ በኩል ኢትዮጵያ በሌላ በኩል የተለያዩ የኢኮኖሚ ደረጃ ላይ እንዳሉ በድጋሚ እናያለን።

እንግዲህ በጣም በኢኮኖሚ የተሻሉ ግብጻዉያንና ቱኒዚያዉያን የመብት ጥያቄ አንስተዉ በመንግስቶቻቸዉ ላይ ከተነሱ «ኢትዮጵያዉያን በኢኮኖሚ ተሻሽለዋልና አይነሱም» ማለት «አንድ ሲደመር አንድ ሶስት ነዉ» እንደማለት ነዉ። ሕዝቡ «አለ ፣ ተገኝቷል» የሚባለዉ የኢኮኖሚ እድገት ተካፋይ ካልሆነ፣ የአገሪቷን ሃብት ጥቂቶች ብቻ መቆጣጠራቸዉን ከቀጠሉ፣ ጥቂቶች የኢሕአዴግ አባል በመሆናቸዉ ወይንም ከባለስልጣናቱ ጋር ባላችዉ ዝምድና በአጭር ጊዜዉስጥ ሚሊየነር ከሆኑ ፣ አንድ ዜጋ ተምሮ፣ ደክሞ ጥሮና ግሮ ኑሮን ማሸነፍ ካልቻለ፣ በአገር ዉስጥ የሚመረቱ እቃዎች ዋጋቸዉ ከቁጥጥር ዉጭ ከሆነ፣ በሰሜን አፍሪካ አገሮች የታየዉ በኢትዮጵያ የማይደገምበት ምንም ምክንያት የለም። ግብታዊ ይሁን የተደራጀ ሕዝባዊ ንቅናቄ መነሳቱ አይቀርም።

ሕዝባዊ ንቅናቄን ካነሳን አይቀር መልስ የሚያስፈልጋቸዉ አበይት ጥያቄዎች አሉ። እነርሱም «የሚነሳዉ የሕዝብ ንቅናቄ ምን መልክ ይኖረዋል? ምን ዉጤትስ ያመጣል ?» የሚሉት ናቸው። በነዚህ ጥያቄዎች ዙሪያ አንዳንድ ሃሳቦችን ለመተንተን ሶስት አገሮችን እንደ ምሳሌ ማየት እፈልጋለሁ።

የመጀመሪያዉ ምሳሌ በሞሮኮ የታየዉ ሰላማዊ ለዉጥ (peaceful reform) ነዉ። ሁለተኛዉ በግብጽ ያየነዉ ሰላማዊ አብዮት (Peaceful Revolution) ሲሆን ሶስተኛዉ በሊቢያ የታየዉ፣ ወደ እርስ በርስ መተላለቅ የወሰደዉ የአምጽ ትግል (Violent Insurrection) ነዉ።

ከላይ በተጠቀሱት ሶስቱም አገራት ህዝባዊ ንቅናቄዎች ተነስቷል። ነገር ግን ባለስልጣናቱና የመከላከያ ሰራዊቱ የሕዝብን ጥያቄ ያስተናገዱበት መንገድ የተለያየ በመሆኑ የተለያዩ ሁኔታዎች ሊፈጠሩ ችለዋል።

በሞሮኮ የዘዉድ አገዛዝ ነዉ ያለዉ። ሕዝቡ መብቱ እንዲከበርለት የፖለቲካና የኢኮኖሚ ለዉጦች እንዲመጡ በሰላማዊ ሰልፎች ጥያቄዉን አቀረበ። ንጉሱ እንዲነሳ

ወይንም የዘዉድ አገዛዙ እንዲያከትም ህሕዝቡ አልጠየቀም። «ንጉሴን እወደዋለሁ። ለዉጥ ሊያመጣ ይችላል ብዬ ነዉ የማምነዉ» ስትል ነበር ሙስታክባል መዲና የምትባል የሰብዓዊ ተሟጋች ድርጅት መሪ የሆነች ሴት፣ ሕዝቡ ከንጉሱ ጋር ጸብ እንደሌዉ ያስረዳችዉ። ዩኔስ ዴራዝ የሚባል ሌላ ወጣት የተቃዋሚ ሰልፈኛ ደግሞ «እንደ ስፔን፣ እንግሊዝ፣ ኖርዌይ ዘዉዱ ስልጣኑን ለፓርላማዉ በስፋት ካካፈለ በሞሮኮዉ ያለዉ የዘዉድ አገዛዝ እንዲቀጥል ማድረግ ይቻላል» ሲልም ሕዝቡ ተስፋ ሰጪ ለዉጦችን ካየ ስርነቀል የስርዓት ግርሰሳ ላያስፈልግ እንደሚችል ይገልጻል። �

ለሕዝቡ የመብት ጥያቄ ንጉሱ ተገቢዉን ምላሽ በጊዜዉ እንደሰጠም በሰፊዉ ተዘግቧል። በሕገ መንግስቱ መሰረታዊ ለዉጦች እንደሚደረጉ፣ ክልሎች የበለጠ ስልጣን እንደሚኖራቸዉና የፖለቲካ ሲስተሙ እንደገና ተጠንቶ እንደሚሻሻል በአስገራሚ ሁኔታ ነበር ንጉስ ማህመድ ወዲያዉ ለሕዝብ ያስታወቁት። ይህም የሚያሳየዉ የሞሮኮ ሕዝብ የዘዉድ አገዛዙን ሳይገረስስ የተጨበጡ ለዉጦች ሊመጡ የሚችሉበት ሁኔታ ማረጋገጡን ነዉ።

በግብጽ እንደ ሞሮኮ ሪፎርም ሳይሆን አብዮት ነዉ የተከሰተዉ። የግብጽ ሰላማዊ አብዮት ዉጤት እንዲያመጣ፣ ሰልፈኞቹ ለመብታቸዉ በተነሱ ጊዜ የተጠቀሙት አንድ ትልቅና ቁልፍ ስትራቴጂ ነበር። እርሱም ጦር ሰራዊቱ ለግለሰቦች ሳይሆን ለሕዝብ እንዲቆም ማድረጋቸዉ ነዉ። ከጅምሩ ለወታደሩ ከበሬታ እንዳላቸዉ ሰልፈኞቹ ይገልጹ ነበር ። በዚህም ምክንያት ጦር ሰራዊቱ በቀላሉ ከሕዝቡ ጎን ሊቆም ቻለ። ሙባረክም ከስልጣናቸዉ በቀላሉ ተወገዱ። ሙባረክ «እኔ ከሌለዉ አገር ትበጠበጣለች» ነበር የሚሉት። ነገር ግን ጦር ሰራዊቱ ሃላፊነቱን ተረክቦ ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ የስልጣን ሽግግር እንኪደረግ ድረስ በአደራ መልክ አገሪቷን ማስተዳደር ጀመረ።

በሊቢያ እያየን ያለነዉ በሁሉም መስፈርት ፍጹም ከሞሮኮና ከግብጽ የተለየ ነዉ። ሕዝባዊዉ ንቅናቄ ከሰላማዊነት ወደ አመጽ የተሸጋገረበት ሁኔታ ነዉ ያለዉ። አገሪቷ አሳዛኝ በሆነ መልኩ የእርስ በርስ ጦርነት ዉስጥ ተዘፍቃለች። ሊቢያናዉያን እርስ በርስ እየተላለቁ ነዉ። አገር እየፈራረሰች ነዉ። መልካም ነገር ተጠብቆ ነበር። ነገር ግን የከፋ ነገር ተከሰተ። የጋዳፊ ግትርነት፣ የተቃዋሚዎችም ድክመት የሊቢያን ብሄራዊ አንድነት አጠያያቂ አድርጎታል። አሁን ባለዉ ሁኔታ ከተቀጠለ በቤንጋዚና በትሪፖሊ ሁለት መንግስታት ሊኖሩ ይችላሉ ተብሎም ይጠበቃል።

በአገራችን ኢትዮጵያ ሕዝባዊ ንቅናቄ ከተነሳ በኢትዮጵያ ምን ሊፈጠር እንደሚችል ለመተንበይ ይከብዳል። አቶ መለስ ዜናዊ እንደ ሞሮኮዉ ንጉስ በአስቸኳይ ለሕዝብ የኢኮኖሚና የፖለቲካ ጥያቄ ምላሽ መስጠት አለባቸዉ ባይ ነኝ። የአምስት አመት እቅዱ አስደሳች ቢሆንም፣ ስለ አምስት አመት እቅድ ነጋ ጠባ በማዉራት የሕዝብን መሰረታዊ የመብት ጥያቄዎች ማፈን አይቻልም። የሰዉ ልጅ እንደ እንስሳ ምግብ እየተወረወረለት፣ አንገቱ በገመድ ታስሮ እንዲኖር የተፈጠረ አይደለም። የሰዉ ልጅ በባህሪዉ በነጻነት እንዲኖር የተፈጠረ ፍጡር ነዉ። ይህንን አቶ መለስ ተገንዝበዉ ለኢትዮጵያዉያን በሙሉ ከበሬታቸዉን እንዲገልጹ ያስፈልጋል። አገር የምትለማዉ በመከባበር ነዉ። የአገር አንድነት የሚጠበቀዉ በመከባበር ነዉ። የአምስቱ አመት እቅድ ተግባራዊ የሚሆነዉ ኢትዮጵያዉን ሲያያዙ ሲከባበሩ ነዉ። አገር ከዉጭ ወራሪዎች የምትመከተዉ ኢትዮጵያዉያን አንድ ሲሆን ሲከባበሩ ነዉ።

በግብጽ የሕዝብ ጥያቄ ምላሽ ያገኘዉ መለዮ ለባሹ ከሕዝብ ጎን በመቆሙ ነበር። በሊቢያ መለዩ ለባሹ በብዛት ከጋዳፊ ጋር በመሰለፉ፣ ጋዳፊ አሁንም በስልጣን ላይ ነዉ ያሉት። «የኢትዮጵያ የመከላከያ ኃይል ምን አይነት ሁኔታ ላይ ነዉ ያለዉ ? እንደ ሊቢያ ሰራዊት በሕዝብ ላይ ይተኩሳል ወይንስ እንደ ግብጽ ሕዝብን ይጠበቃል ?» የሚሉት ጥያቄዎች ሊነሱ የሚገባ ጥያቄዎች ናቸዉ።

አቶ መለስ ለሕዝብ ጥያቄ ምላሽ የማይሰጡ ከሆነ፣ የዲሞክራሲያዊ ሂደቱ እንዲቀጥል ካልተደረገ፣ የዲሞክራሲ ተቋማት ነጻና ገለልተኛ ሆነዉ ካልተዋቀሩ፣ ተደራጅቶ መታገል ያስፈልጋል። አንድ የፖለቲካ ፓርቲ መጣ፣ ሄደ ፣ የጦር ኃይሉ የአንድ የፖለቲካ ድርጅት የቦዲ ጋርድ ስብስብ ሳይሆን፣ የአገርና የሕዝብ ሕልዉናን በእጁ የያዘ፣ የተከበረ አካል እንደሆነ ማረጋገጡ የግድ ነዉ። ይህ ከሆነ፣ በቀላሉ መለዮ ለባሹን ከሕዝብ ጎን እንዲሰልፍ ማድረግ ይቻላል። ሕዝቡም በቀላሉ ድል ሊያስመዘግብ ይችላል።

አቶ መለስ ለሕዝብ ጥያቄ አልገዛም ብለዉ፣ የጦሩም መኮንኖች እገርን ሳይሆን አቶ መለስን ብቻ ለማገልገል ከወሰኑ፣ በሊቢያ የታየዉ እንደዉም በእጅጉ በባሰ ሁኔታ በኢትዮጵያ መከሰቱ አይቀሬ ነዉ። አገራችን ኢትዮጵያ በከፋ የእርስ በርስ ጦርነት ዉስጥ በቀላሉ ልትዘፈቅ ትችላለች። ሁሉም በየቦታዉ በግባታዊነት ፣ በጥላቻና በበቀል መንፈስ ተሞልቶ መንቀሳቀስ ከጀመረ ምናልባትም ኢትዮጵያ የምትባል አገር ላትኖርም ትችላለች።

በሊቢያ የታየዉ በኢትዮጵያ እንዳይደገም የኢሕአዴግ ባለስልጣናትም ሆነ የተቃዋሚ መሪዎች አስፈላጊዉን እርምጃ በዚህ አጋጣሚ እማጸናለሁ።በጠርሙስ ያለን ዉሃ ጠርሙሱን ሰብሮ ማፍሰሰ ቀላል ነዉ። ዉሃዉን መልሶ በተሰበረዉ ጠርሙስ መክተት ሌላ ነገር ነዉ። ጠርሙሱ ከመሰበሩ በፊት ጥንቃቄ እናድርግ እላለሁ።

አቶ መለስ ዜናዊ ከአራት አመት በኋላ ስልጣናቸዉን እንደሚለቁ ተናግረዋል። ሕገ መንግስቱ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፈለጉበት ጊዜ ፓርላማዉን ሊበትኑና አዲስ ምርጫም ሊጠሩ እንደሚችሉ ይደነግጋል። በመሆኑም አራት አመት ከመጠበቅ፣ ከሁለት አመት በኋላ አዲስ ምርጫ የሚደረግበትን ሁኔታ ከተቃዋሚዎች ጋር መነጋገሩ የሚበጅ ይመስለኛል። በቅንነት፣ በወንድማማችነት ብንነጋገር፣ ብንግባባ የአምስቱን አመት እቅድ፣ በኤርትራም በኩል ያለዉን ችግር በመፍታት ዙሪያ ሊሰሩ የሚገባቸዉን ሥራዎችን ከግብ እናደርስ ነበር። እነ አቶ መለስ ዜናዊ እንደ ሞሮኮዉ ንጉስ አስተዋይ ከሆኑ፣ የግድ የግብጽ አይነት አብዮት አያስፈልገንም።

በግርማ ካሳ ከቺካጎ ([email protected])

በመሆኑም አራት አመት ከመጠበቅ፣ ከሁለት አመት በኋላ

አዲስ ምርጫ የሚደረግበትን ሁኔታ ከተቃዋሚዎች ጋር መነጋገሩ

የሚበጅ ይመስለኛል።

Page 17: Awramba Times Issue 161 Megabit 24

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 161 ቅዳሜ መጋቢት 24 2003

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

‹‹ሳማ ሰምበት››በዐቢይ ጾም እኩሌታ የሚከብረው

ል ዩ ቅ ኝ ት 17

ክፍላተ አገራት የሚከበር ቢሆንም በታላቅ ድምቀት የሚከበረው በ‹‹ሳማ ሰንበት›› ነው፡፡

ሰንበትሰንበት በዕብራይስጥ ቋንቋ ‹‹ማቆም›› ወይም ‹‹መተው›› ማለት ነው፣ ዲያቆን ቴዎድሮስ ‹‹እረፍት›› ማለት ነው ሲል አቻ ትርጉሙን ይበልጥ ይገልፀዋል፡፡ በመፅሐፍ ቅዱስ በኦሪት ዘፍጥረት ምዕራፍ 2÷2-5 ላይ ‹‹እግዚአብሔርም የሰራውን ስራ በሰባተኛው ቀን ፈፀመ፤ በሰባተኛውም ቀን ከሰራው ስራ ሁሉ ዐረፈ፡፡ ሰባተኛውን ቀን ባረከው ቀደሰውም ሊያደርገው ከፈጠረው ስራ ሁሉ አልፎአልና›› ይላል፡፡ እንደ መንግስተ ሰማያት ምሳሌም ተደርጎ የሚታየው ሰንበት በግዕዝ ቋንቋ የዕለት ስም ሆኖ ሰባተኛው ቀንን ይወክላል፡፡ ‹‹ሙሴም- የእግዚአብሔር ሰንበት ዛሬ ነውና ብሉት፤ ዛሬ በሜዳ አታገኙትም፡፡ ስድስት ቀን ልቀሙት ሰባተኛው ቀን ግን ሰንበት በእርሱ አይገኝም አለ፡፡ በሰባተኛውም ቀን እንዲህ ሆነ ከህዝቡ አንዳንድ ሰዎች ሊለቅሙ ወጡ ምንም አላገኙም›› ኦሪት ዘጸአት 16÷ 25-28፡፡ ጌታቸው በቀለ በሐመር መፅሔት 17ኛ ዓመት ቁጥር አንድ የሚያዚያ 2001 ዓ.ም እትም ላይ ‹‹ሳማ ሰንበት›› በሚል ርዕስ ያሰፈሩት ፅሁፍ ላይ ‹‹ሰንበት በብሉይ (በኦሪት) ቀዳሚት ሰንበት፣ ሰንበት አይሁድ ሲባል በዘመነ ሐዲስ ሰንበተ ክርስቲያን (እሁድ ሰንበት) በመባል ሁለቱ ሰንበታት ይታወቃሉ፡፡ ቀዳሚት ሰንበት አከባበሩም የጠበቀና ከባድ ነበር፡፡ በፍትሐ

ነገሥት- ፍትሕ መንፈሳዊ አንቀጽ 19 ‹ለክርስቲያን ልጆች በሰንበት እንደ አይሁድ ሥራ መፍታት አይገባቸውም፡፡ ነገር ግን እንደ ክርስቲያን ሥርዓት መልካም እንጂ፣ እንደ አይሁድ ሰንበትን አትጠንቀቁ› ተብሎ መደንገጉ የሁለቱ ዘመናት የሰንበት አከባበር ሥርዓት የተለያየ እንደ ሆነ መረዳት ይቻላል›› ሲሉ ልዩነቶች በሐዲስ እና በብሉይ እንደነበሩ አሳይተዋል፡፡ ግሪኮች ሰንበትን ኩራኬ (kyriake) እያሉ ይጠሩታል፤ ‹‹የጌታ ቀን›› የሚለውን አቻ አማርኛ ቃል ይተካል፡፡ እንደ ጌታቸው በቀለ ገለፃ በመፅሐፍ ቅዱስ በዮሐንስ ራእይ ምዕራፍ 1÷10 ‹‹በጌታ ቀን በመንፈስ ነበርኩ...›› የሚለው ይህንኑ ቀን ነው፡፡በተለያዩ የእምነት እና ዓለማዊ መፅሐፍ ላይ እሁድ እንደ ሳምንቱ መጀመሪያ ቀን ይጠቀሳል፡፡ በአዲስ ኪዳን በማቴዎስ ወንጌል 28÷1 ላይ ‹‹በሰንበትም መጨረሻ የመጀመሪያው ቀን ሲነጋ...›› በማለት ስለ ጌታ ትራሳኤ ሰፍሯል፡፡ በአዲስ ኪዳን ‹‹ሰንበተ ክርስቲያን›› በመባል የምትታወቀው እለት እሁድ የጌታ ቀን ትባላለች፡፡ ያሰኛትም ‹‹ዓለምን መፍጠር የጀመረበት፣ አላካዊ ቃል በማህፀን ማርያም ያደረበት (የተፀነሰበት)፣ ከሞት የተነሳበት፣ እና ጰራቅሊጦስ መንፈስ ቅዱስን የላከበት (መንፈስ ቅዱስ የወረደበት) እለት በመሆኗ ነው፡፡ በአምስተኝነትም ዳግመኛ እንደሚመጣ የሚታመንበት ቀን ነው›› በማለት ዲያቆን ቴዎድሮስ አሰፋ ያብራራል፤ ስለ እለቱ

‹‹ክቡር›› መሆን በማስገንዘብ፡፡

‹‹ሳማ ሰንበት››‹‹ሳማ›› በአማራ ከልል፣ ሰሜን ሸዋ ዞን፣ ምንጃር ሸንኮራ ወረዳ ውስጥ የሚገኝ ቦታ ስም ነው፡፡ ቦታው አስቀድሞ ‹‹መምህር አገር›› ይባል እንደነበር ምክንያቱም በወቅቱ ቦታው የበርካታ ሊቃውንት መገኛ ስለነበር መሆኑን ጌታቸው በቀለ በፃፉት ፅሁፍ ላይ ሊቀ ካህናት ቀዲስ አደበብ የተባሉ ሰውን ጠቅሰው አስፍረዋል፡፡ ቦታው ‹‹ሳማ›› የተባለበት በአፈ-ታሪክ የሚወሩ መሬዎች አሉ፡፡ ከእነዚህም ውስጥ አንዱ እኔም ከቦታው ነዋሪዎች እንደሰማሁት ጌታቸውም ሰማሁ ብለው እንደፃፉት ሁለት ጓደኛሞች በአሉባልታ ወሬ ተጣልተው አንዱ አንዱን እያማ ይኖሩ ነበር፡፡ ቀድሞ እውነታው የተገለፀለት ሰው ጓደኛውን ‹‹ለካ እውነቱ እንዲህ ነበር? እኔ እንዲያው ሳማ›› ብሎ ይቅርታ በመጠየቅ ‹‹ይቅር›› በመባባላቸው ቦታው ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ‹‹ሳማ›› መባሉ ይነገራል፤ ከ1802 ጀምሮም በዚህ ስም መጠራት እንደጀመረ ጭምር፡፡ በዚህ ስፍራ ‹‹እግዚኣ ለሰንበት መድሀኒዓለም ክርስቶስ›› ፅላት ያለበት ‹‹ሳማ እግዚኣ ለሰንበት›› (ሳማ ጌታዋ ለሰንበት) ገዳም በተለምዶ ‹‹ሳማ ሰንበት›› ገዳም ተብሎ ይጠራል፡፡ ሞጆ ደርሰው በስተ ግራ በኩል ያለውን አቧራማ መንገድ ይዘው ረዥም መንገድ ይዘው ሲዘልቁ ከአዲስ አበባ 116 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ የተሰራው የሸዋ ንጉስ በነበሩት ሳህለ

ሥላሴ ዘመነ መንግስት ሲሆን መስራቹ አባ ገ/ሕይወት የተባሉ የበቁ አባት መሆናቸውን ጌታቸው በቀለ በሐመር መፅሔት ላይ አስፍረዋል፡፡ ህይወታቸው እስኪያልፍ ድረስም የደብሩ አስተዳዳሪ ነበሩ፡፡ በአንድ ወቅት ደብሩ የመቃጠል አደጋ ደርሶበት እንደነበር የሚገልፁ አሉ፡፡ ጥቅምት 14 1980 ዓ.ም. ባማረ ሁኔታ የታነፀበት የመሰረት ድንጋይ ያረፈበት ቀን መሆኑን ገላጭ ፅሁፍ ያሳያል፡፡በዚህ ሰፊ ቅጥረ ጊቢ ያለው ያማረ ገዳም በዐቢይ ጾም እኩሌታ በሚውለው እሁድ (ደብረ ዘይት) ከተለያዩ ቦታዎች በተሰባሰቡ ምዕመኖች በድምቀት ይከበራል፡፡ የምዕመኑ ቁጥር በርካታ በመሆኑ ሳቢያ ለማደር ከጊቢው አልፎ በዙሪያው በሚገኝ አፈራማ መሬት ላይ ጎኑን ለማሳረፍ የሚገደደው በርካታ ነው፡፡ የመጸዳጃ ቤት በቦታው ባለመኖሩ ቁልቁል ተንደርድሮ ሰው በየሜዳው ላይ ይፀዳዳ ነበር፡፡ ምግብና መጠጥ ከማቅረብ በዘለለ ከሀይማኖታዊ ስፍራው ጋር የሚፃረሩ የአልኮል መጠጦችን ለመቸርቸር በደብሩ አቅራቢያ የደኮኑ ‹‹ነጋዴዎች›› አዲስ መንደር ፈጥረው ነበር፡፡

ጊዜያዊ መንደርሳማ ሰንበት ቀበሌ እንደ ሌሎች የገጠር ቀበሌዎች ሁሉ ጭርታ ይነግስባታል፡፡ በቦታው በኩታ ገጠም የሚኖሩ ነዋሪዎች በዓመት አንዴ የጭርታውን መጋረጃ ገፍፎ የሚጥለውን በሳማ እግዚኣ ለሰንበት ገዳም በዐቢይ ጾም እኩሌታ የሚከበረውን የደብረ ዘይት በዓል በጉጉት ይጠብቁታል፡፡ እንደ ክብረ በዓሉ ዓመታዊ ተሳታፊዎች እና የአካባቢው ነዋሪዎች ገለፃ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በዓሉ ሲከበር ‹‹አዲስ መንደር›› እየተፈጠረ መሆኑ በጉልህ እየታየ ነው፡፡ ክስተቱም በአዲስ መንደር ፈጣሪዎቹ ከበዓሉ ሁለት ቀን አስቀድሞ (አርብ ከሰዓት በኋላ አንስቶ) ይጀመራል፡፡ የጨዋታዬን ሰምና ወርቅ ለማግኘት ሳይዋትቱ ነገሩ እንዲህ ነው ልበልዎት፡፡ በሳማ ሰንበት ደብር መግቢያ በር አቅራቢያ እና ፊት ለፊት ከዋዜማው እስከ በዓሉ ፍፃሜ ድረስ በርካታ ሰው የመትመሙን አጋጣሚ በመጠቀም ኪሳቸውን ለማሳበጥ በሚንቀለቀሉ የመንገድ ላይ ነጋዴዎች ይሞላል፡፡ በላስቲክ ዳስ በመስራት 24 ሰዓት መጠጥ ሲቸረችሩ ውለው ያደሩ

‹‹ሳማ ሰምበት››በዐቢይ ጾም እኩሌታ የሚከብረው

አቤል ዓለማየሁ ባለፈው ቅዳሜ ወደ ሳማ ተጓዘ፣ የደብረ ዘይት ክብረ በዓል የሚከብርበትን ‹‹ሳማ ሰንበት››ን ቃኘና ተመለሰ፡፡ በበዓሉ ዙሪያ የተፃፉ ረጂ ሰነዶችን

አገላበጠናም ተከታዩን ፅሁፍ አሰናዳ፡፡ መልካም ንባብ!!!

ለማምለክ ወይስ ለመዝናናት• ?

ጾም- ጾዊም ከሚለው የግእዝ ጥሬ ዘር፤ ጾም ከሚለው ግስ የተገኘ ቃል ሲሆን ትረጓሜውም ‹‹መከልከል›› ማለት ነው፡፡ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ዘንድ ሰባት ዓመታዊ አጽዋማት አሉ፣ አንዱም ዐቢይ ጾም ነው፡፡ ጾሙ ኢየሱስ ክርስቶስ ከተጠመቀ በኋላ የመጣበትን የማስተማርና የማዳን ተልዕኮውን ከመጀመሩ በፊት አርባ ቀንና አርባ ሌሊት የጾመው በመሆኑ እና ከአጽዋማት ሁሉ ረጅም በመሆኑ - ዐቢይ ፆም ይባላል፡፡ ‹‹የጌታ ጾም›› ሌላኛው መጠሪያው ነው፤ ኢየሱስ ክርስቶስ የጾመው መሆኑን ለማመላከት ነው፡፡ ዐቢይ ጾም- ‹‹ጾመ ሁዳዴ››ም ይባላል፡፡ ‹‹‘ሁዳድ’ ማለት የመንግስት መሬት፣ የመንግስት ርዕት ማለት ሲሆን የመንግስት ሁዳድ ሲታረስ አዝመራው ሲሰበሰብ ዜጋ ሁሉ በስራው ይሳተፋል፡፡ ጾሙንም በክርስትና ክርስቲያን የተባልን ምዕመናን ሁሉ እርሱን እያሰብን የምንፆመው በመሆኑ ጾመ ሁዳዴ ይባላል፡፡›› ይላል ከሰረገው ሀብተ ስላሴ [ዶ/ር] እና በምዕራብ ጀርመን በከፍተኛ መንፈሳዊ ት/ቤት በሚማሩ ኢትዮጵያውያን በ1981 ዓ.ም. ሃይድልበርግ ውስጥ የተዘጋጀ የአማርኛ የቤተ-ክርስቲያን መዝገብ ቃላት፡፡‹‹ኢየሱስ ክርስቶስ የጾመው 40 ቀን ሆኖ ለምን 55 ቀን ይጾማል?›› የሚል ጥያቄ ያነሳሁለት በቅድስት ስላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ የአምስተኛ (የመጨረሻ) ዓመት ተማሪ የሆነው ዲያቆን ቴዎድሮስ አሰፋ የመጀመሪያው ሳምንት ‹‹ጾመ ሠርቃን›› እንደሚባል ያስረዳል፡፡ ‹‹ህርቃሉስ የሚባል የሮም ንጉስ ከጠላቶቹ ጋር በሚዋጋበት ወቅት ክርስቲያኖች አንተ ተዋጋልን እኛ ጾሙን እንጾምልሀለን ብለው የጾሙት ነው፡፡ የአርባ ቀን ጾም ከመጀመሩ በፊት እንደመዘጋጃ ተደርጎ አባቶች እንዲጾም አድርገዋል›› ይላል፡፡ ‹‹አርባው ቀን እንደተጠናቀቀ የሚገኘው የመጨረሻው የጾም ሳምንት ‹‹ጾመ ህማማት›› ተብሎ ይታወቃል፡፡ እየሱስ ክርስቶስ የተቀበለውን ህመም፣ መከራና ስቅላት እየታሰበ፣ እየተሰገደ፣ የሚፆምበት ሳምንት ነው፡፡››

ደብረ ዘይትበዐቢይ ፆም ሁሉም ሳምንታት የመታሰቢያ መጠሪያ ስያሜ አላቸው፡፡ የመጀመሪያው ሳምንት ‹‹ዘወረደ›› ይባላል፤ ቅድስት፣ ምኩራብ፣ መፃጉዕ - ከሁለተኛ እስከ አራተኛ ሳምንት ድረስ ያሉ ሳምንታት መጠሪያዎች ናቸው፡፡ ጾመ እኩሌታው የሚውልበት አምስተኛ ሳምንት ደግሞ በታላቅ ድምቀት የሚከበረው ደብረ ዘይት ነው፡፡ ደብረ ዘይት የተራራ ስያሜ ሲሆን የዘይት ተራራ ማለት ነው፡፡ ‹‹ደብረ ዘይት የወይራ ዘይት ያለበት ተራራ ነው፡፡ በዚህ ተራራ ላይ ደቀ-መዛሙርቱ ‹‹ጌታ ሆይ ዳግመኛ የመምጣትህና የዓለም መጨረሻ ምልክቱ ምንድን ነው?›› ሲሉ ጠይቀውት በአራት አይነት መንገድ ያሉትን ምልክቶች ነግሯቸዋል፡፡ ይህ ይታሰብበታል›› በማለት የሚገልፀው ዲያቆን ቴዎድሮስ አራቱ ምልክቶች ያላቸው ሃይማኖታዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ተፈጥሯዊና ማህበራዊ ምልክቶች ሲሆኑ ሃሰተኛ ነብያተኞች እና ‹ክርስቶስ ነን› ባዮች እና ወንጌልን እያጣመሙ የሚተረጉሙ እንደሚነሱ መናገሩ- ሃይማኖታዊ፣ ህዝብ በህዝብ፤ በመንግስት በመንግስት ላይ እንደሚነሳ መናገሩ ፖለቲካዊ፣ በየቦታው የምድር መናወጥ እንደሚኖር መጠቆሙ ተፈጥሯዊ፣ ከአመፅ የተነሳ የብዙዎች ፍቅር ትቀዘቅዛለች ማለቱ ማህበራዊ ምልክቶች ናቸው፡፡ [እነዚህ የምጥ ጣር መጀመሪያ እንጂ መጨረሻ አለመሆናቸው በማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 24 ላይ ሙሉ ታሪኩ ይገኛል፡፡] የደብረ ዘይት በዓል በተለያዩ ውስን ወደ ገፅ 23 ዞሯል

ሁለት ጓደኛሞች በአሉባልታ ወሬ ተጣልተው አንዱ

አንዱን እያማ ይኖሩ ነበር፡፡ ቀድሞ እውነታው የተገለፀለት

ሰው ጓደኛውን ‹‹ለካ እውነቱ እንዲህ ነበር? እኔ እንዲያው

ሳማ›› ብሎ ይቅርታ በመጠየቅ ‹‹ይቅር›› በመባባላቸው

ቦታው ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ‹‹ሳማ›› መባሉ ይነገራል

Page 18: Awramba Times Issue 161 Megabit 24

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 161 ቅዳሜ መጋቢት 24 200318

ለራስ ለባለቤቱ ብዙ አሉታዊና ቀና ተፅዕኖ ይኖራቸዋል፡፡ መፍትሔዎቹን በመፈለግ ጊዜ ብዙ የሚጎረብጡ ነገሮች ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ ቢሆንም እንደ ሁኔታው ተቀብሎ ማስተናገድ ነው፡፡ እኔም ያለሁት በእንደዚህ ዓይነት ነገር ውስጥ ነው፡፡ ያን ያህል መስዋዕትነት ያስከፈለኝ ነገር ያለ አይመስለኝም - በሕይወቴ፡፡

የ‹ባህር በር› የሚል ፊልም መስራትህ ይታወቃል፡፡ በአንተ ግምት ኢትዮጵያ የባህር በር መቼ ይኖራታል ብለህ ታስባለህ?

[አሰብ አድርጎ] በእኔ ግምት የሚሆን ነገር የለም፡፡ እንደሀሳቤ፣ በእኔ ግምት ቢሆን ኖሮ አሁን የባህር በር ነበረን ማለት ነው፡፡ ለዚህም የአገሪቱ ተጨባጭ ሁኔታና ሌሎች ሌሎች ነገሮችም ይታያሉ፡፡ ከዚህ አኳያ በመሆኑ በዚህ ጊዜ ኢትዮጵያ ወደብ ይኖራታል ብሎ ለማለት በጣም አስቸጋሪ ነው፤ ከብዙ ነገሮች ጋር ስለሚያያዝ፡፡ ይኼ የጊዜ ገደብ የሚሰጠው አይደለም፡፡ እኔ በፊልም ያቀረብኩት የፈጠራ ሥራ ነው፡፡ ያም በውስጡ ሳይንሳዊ መረጃዎች አሉት፡፡ ...ነገ ጠዋት ቢሆን ግን እመኛለሁ፤ ደስ ይለኛል፡፡

ወደግል ሕይወትህ እንመለስና ባለቤትህ በአሜሪካን አገር ትገኛለች፡፡ ጥገኝነት እንደጠየቀች የሚነገረው እውነት ነው?

[ዝምታ]

ከአንተስ ጋር ተለያይታችኋል?አልተለያየንም፡፡ በፈረንጆች

ገና ጥር ወር ላይ እዚያ ነበርኩኝ፡፡ ካናዳ ፕሮግራም ነበረኝ፡፡ ያንን እንደጨረስኩኝም ካናዳ የጋበዙኝ ሰዎች ናቸው ወደ አሜሪካን ትኬት ቆርጠው የላኩኝ፡፡ በእዛም ብዙ አልቆየሁም እንጂ ባለቤቴንና ልጆቼን አይቼ መጥቻለሁ፡፡ ወደ አሜሪካን እየሄድኩኝ እመጣለሁ፡፡ ችግር የለብኝም፡፡

በሕይወትህ መቋቋም አቅቶህ የተውከው?መቋቋም አቅቶኝ የተውኩት

ነገር የለም፡፡ ነገር ግን፣ የፊልም ጉዳይ አንዳንዴ ያደክምሃል ትተወዋለህ፡፡ ምን መስራት አለብኝ? ብዬ ሳስብ በሌላ መስመር ሌላ ነገር ነው መስራት ያለብኝ ብዬ እላለሁ፡፡ ለምሳሌ የ‹ባህር በር› ፊልሜን ብንወስድ ኪሳራው ቀላል አይደለም፡፡ ከባድ ነው፡፡

በሁሉም ነገር ደግሞ ምቾትን አልሰጠኝም፡፡ ስለዚህ መቋቋም ያቃተኝ ነገር የለም፡፡ ነገር ግን እንደዚሁ ትመለከትና እነዚህን ‹‹ባልሰራስ›› የምትላቸው አሉ፡፡

የመንግስትና የግል ጋዜጦችን ታነባለህ?

አዎ፤ አነባለሁ፡፡

ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት በጋዜጦች ህትመት ዋጋ ላይ 45 በመቶ እና ከዚያ በላይ ጭማሪ አድርጓል፡፡ ይኼን እንደ አንድ አንባቢ እንዴት ትመለከተዋለህ?

ይኼንን የማየው በሁለት መልኩ ነው፡፡ የመጀመሪያው ነገር ይታተም የነበረው የጋዜጣ/ የመፅሔት ቁጥር ወደታች በመውረዱ የተባለውን የዋጋ ጭማሪ መቋቋም ያስችላል ወይ? ለምሳሌ 40 ሺህ ኮፒ ይታተም የነበረውን 20 ሺህ ኮፒ በማሳተም የተደረገውን ጭማሪ ‹መቋቋም እንችላለን› ከሆነ ይኼ ሌላ ነገር ነው፡፡ ሁለተኛው ነገር የዋጋ ጭማሪው ተገቢ ነው ወይስ አይደለም? ለማለት እንደዚሁ ዝም ብሎ ያላዋቂ ንግግር ይሆንብኛል፡፡ አለበለዚያ መሠረታዊ የሆኑ ነገሮችን ማወቅና ማጥናት ከእንደኔ ዓይነት ሰው ይጠበቃል፡፡ አንድ ጋዜጣ ታትሞ አንባቢ እጅ እስኪገባ ያሉትን ሂደቶችና በሂደቶች ውስጥ በየደረጀው እስከ አሳታሚው ድርጅት ድረስ ምን ያህል ያተርፉ ነበር? የሚሉትን ማየት የግድ ነው፡፡ አለበለዚያ የተጨመረው ጭማሪ ተገቢ አይደለም ብሎ ለመናገር መሠረት የሌለው ይሆንብኛል፡፡

በዶላር ምንዛሪ መጨመር ሳቢያ የወረቀት ዋጋ መናሩን ማተሚያ ቤቱ በምክንያትነት አቅርቧል፡፡

45 በመቶ ጨመረብን ሲባል ሲታይ በሁለት መንገድ የማየው ለዚህ ነው፡፡ ምክንያቱም ከማሳተሚያው ዋጋ 60 በመቶ ያተርፍ የነበረው አንድ ጋዜጣ ከዚህ በፊት 45 በመቶውን ማተሚያ ቤቱ ቢወስደው ምንም ላይሆን ይችላል፡፡ ትርፉን ሊቀንስበት ይችላል፡፡ ነገር ግን በፊት ያተርፍ የነበረው 20 በመቶ ከነበረ አሁን የተጨመረው 45 በመቶ ተገቢ አይደለም፡፡ ምክንያቱም የመንግስት ጋዜጦች የበጀት ድጎማ አላቸው፡፡ ከኪስ የሚወጣ ነገር የላቸውም፡፡ መረጃ ለሕብረተሰቡ እንዲደርስ ብቻ ስለሆነና በበጀት ስለሚተዳደሩ አያስቸግራቸውም፡፡

የግል ጋዜጦች የሚተዳደሩት ግን በግል ነው፡፡ አንዳንድ ጊዜ የግል የሚባለው ነገር ዝም ብሎ የግል ተብሎ የሚታለፍ አይደለም፡፡ ብዙ ነገሩ የመንግስት ነው፡፡ የግል ፕሬሱ በሥሩ ብዙ ሠራተኞች አሉት፡፡ የቤት ኪራይ ይከፍላል፡፡ ከሚከፍለውም የቤት ኪራይ ግብር ይከፍላል፡፡ ሠራተኛው እንደዜጋ ሥራ ላይ ነው ያለው፡፡ ስለዚህ የመንግስትን ነገር እየተካፈለ ነው ማለት ነው፡፡ እነዚህ ሁሉ አብረው መታሰብ አለባቸው እንጂ ዝም ብሎ ወደግለሰብ ኪስ የሚገባ ነው ማለት አይደለም፡፡ ሌላው ደግሞ ሕጋዊ ፈቃድ አውጥተው መንግስት በነፃው ፕሬስ አማካኝነት የሚያስፈልገውን መረጃ እንዲያገኝ፣ በተጨማሪም ዴሞክራሲንም ለመለማመድ እያደረግን ነውና ሕዝቡ ምን ያህል የዴሞክራሲ መብቱ ተጠቃሚ ነው? እነዚህ ፕሬሶች ለዴሞክራሲ ማበብ ምን ያህል አስተዋፅኦ አላቸው? እነዚህ ሁሉ ነገሮች አብረው ተጣምረው የሚሄዱ ናቸው፡፡

ዴሞክራሲን የማሳደግ፣ የማስዋብ፣ የማጎልበት ኃላፊነት የመንግስትም ጭምር ነው፡፡ ስለዚህ በዚህ መስመር ታይቶ የግል ጋዜጦች መታተማቸው በራሱ ትልቅ ነገር አለው፡፡ የማይደክሙበትና የማይሽመደመዱበት መንገድ ቢፈለግ መልካም ይመስለኛል፡፡ እነሱንም መንግስት ቢደጉም እላለሁ፡፡ ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት ወረቀት ከውጭ በውድ ዋጋ ነው የምገዛው ካለ ዋጋ ጨምሮበት ሊሆን ስለሚችል ምንም ማድረግ አይቻል ይሆናል፡፡ ማቻቻል የሚቻልበት ነገር ካለና የግል ጋዜጦችን በእርግጥ አክሳሪ ከሆነ መንግስት እንዲያየው ማድረግ ነው፡፡ ብዙ ወጪዎች ስላሉባቸው ከስረው ዝም ብለው (ድርጅታቸውን) ዘግተው የሚቀመጡ ከሆነ መልካም አይሆንም፡፡ ለያዝነውና እያራመድነው ላለው የዴሞክራሲ ማበብና መጎልበት እንቅፋት ይፈጥራልና መንግስት ነገሩን አይቶ መፍትሔ የሚያገኝበትን ሁኔታ ይቃኝ ከማለት ውጪ የምለው የለኝም፡፡

የልምዣት መፅሐፍ ደራሲ ማን እንደሆኑ ንገረኝና እናብቃ?

አዲስ አለማየሁ መሰሉኝ፤ ክቡር ዶክተር ሃዲስ አለማየሁ ናቸው፡፡

‹‹አልሞትኩም›› . . .

ሪፑብሊክ ቻይና (ማኦ ዜ ዱንግ፣ ቾ ኢንሌይ፣ ዴንግ ዢያኦፒንግ፣ ማርሻል ያንግ ሻንግኩን፣ ሊ ፔንግ፣ ጂያንግ ዝሚን፣ ሁ ጂንታኦ)፣ ማሌዢያ (ዶ/ር ማህታይር ሞሐመድ)፣ ብራዚል (ሉዊስ ኢናቺዮ ዳ ሲልቫ)፣ ኢራን (አያቶላዎቹ ኮሚኒ እና ካሚኒ)፣ ወዘተ በመጀመሪያውና በሁለተኛው የዓለም ጦርነቶች መካከል ሶቭየት ሕብረት በአምባገነናዊው፣ ሆኖም ግን ነፃ አስተሳሰብ በነበራቸው ጆሴፍ ስታሊን አመራር ወደ ኢንዱስትሪያዊ ሀገርነት ሽግግር አድርጋለች፡፡ እኛም ከበርካታ ነፃ አስተሳሰብ ካራመዱ መሪዎች ተጠቃሚ ሆነናል፤ የግብፁ ኮሎኔል ናስር፤ የታንዛኒያው ምዋሊሙ ኔይሬሬ፣ የሞዛምቢኩ ሳሞራ ሚቼልና ሌሎች፡፡ በዚህ መንገድ ነው ደቡባዊ አፍሪካ ነፃ የወጣችው፡፡ በዚህ መልኩ ነው ኢዲ አሚንን ያስወገድነው፡፡ የሩዋንዳ የዘር ጭፍጨፋ መቆም እና የዴሞክራቲክ ሪፑብሊክ ኮንጎ ሞቡቱ ሴሴ-ሴኮ መወገድ የአፍሪካ ነፃ አስተሳሰብ አራማጅ መሪዎች ጥረት ውጤቶች ናቸው፡፡ጥፋቶቻቸው የፈለገ ቢሆን እንኳ፣ ጋዳፊ እውነተኛ ብሔርተኛ ናቸው፡፡ ለውጭ ጥቅሞች አሻንጉሊቶች ከሆኑት ይልቅ ብሔርተኞችን እመርጣለሁ፡፡ የት ነው አሻንጉሊቶች የሀገራትን ዕድገት ያሳኩት? ከአሻንጉሊትነት ጋር ትውውቅ ያላቸው ይህን በተመለከተ መረጃ ቢሰጡኝ ምነኛ ደስ ባለኝ፡፡ በአንፃሩ፣ ከተፅዕኖ የተላቀቀ አስተሳሰብ አራማጁ ጋዳፊ አንዳንድ አዎንታዊ አስተዋጽኦዎችን ለሊቢያ፣ እንዲሁም እንደእኔ እምነት ለአፍሪካ እና ለሶስተኛው ዓለም አበርክተዋል፡፡ አንድ ምሳሌ ብቻ ይውሰዱ፤ እዚህ ዩጋንዳ ውስጥ ወንጀለኛ አምባገነኖችን እየተዋጋን በነበረበት ወቅት፣ በየካቲት 6/1981 በካባምባ በቂ የጦር መሳሪያዎችን በቁጥጥራችን ስር ለማዋል ባለመቻላችን ምክንያት በተፈጠረ ውስብስብነት አንድ ችግር አጋጥሞን ነበር፡፡ በወቅቱ ጋዳፊ በጣም ጠቃሚ የሆኑ 96 ጠብ-መንጃዎችን፣ 100 ፀረ-ታንክ ፈንጂዎችን፣ ወዘተ ጭነት ሰጡን፡፡ ይህንን ከማድረጋቸው አስቀድሞ ዋሽንግተንን

ወይም ሞስኮን አላማከሩም፡ ይህ ለሊቢያ፣ ለአፍሪካ፣ እና ለመካከለኛው ምስራቅ መልካም ነገር ነበር፡፡ የዚያ ነፃ አስተሳሰብ አካል የሆነው የእንግሊዝንና የአሜሪካንን ወታደራዊ ዕዞች ከሊቢያ የማስወጣታቸው እውነታ እንዲሁ የሚዘነጋ አይደለም፡፡

የነዳጅ ዘይት ዋጋ ጭማሪበ1969 ውስጥ ጋዳፊ ሥልጣን ከመያዛቸው አስቀድሞ፣ የአንድ በርሜል የነዳጅ ዘይት የመሸጫ ዋጋ 40 (የአሜሪካ) ሳንቲም ነበር፡፡ ምዕራቡ ለነዳጅ ዘይት ከፍ ያላ ዋጋ ካልከፈለ በስተቀር የአረብ ነዳጅ ዘይት አቅርቦትን ለመግታት ዘመቻ ጀመሩ፡፡ ከዚያ በኋላ የአንድ በርሜል ዋጋ ወደ 20 የአሜሪካ ዶላር የጨመረ ይመስለኛል፡፡ የ1973ቱ የአረብ እስራኤል ጦርነት በፈነዳበት ወቅት፣ አንድ በርሜል ዋጋ ወደ 40 የአሜሪካ ዶላር አሻቀበ፡፡ እናም የገልፍ ሀገራትን ጨምሮ፣ ብዙዎቹ የዓለም ነዳጅ አምራች ሀገራት በዚህ ጉዳይ ላይ ጋዳፊ የተጫወቱትን ታሪካዊ ሚና የማያሰምሩበት መሆኑ ይገርመኛል፡፡ ቢያንስ በከፊል፣ አብዛኞቹ እነዚህ ዘይት አምራች ሀገራት ያገኙ የነበረው የነበረው ከፍተኛ የኃብት መጠን በጋዳፊ ጥረት የተገኘ ነው፡፡ የምዕራቡ ሀገራት ለነዳጅ ዘይት የበለጠ ዋጋ ቢከፍሉም፣ እድገታቸው አልተገታም፡፡ ስለዚህም ከጋዳፊ አስተዋፅኦ በፊት የነበረው የነዳጅ ዘይት ሁኔታ፣ የዘይት አምራች ሀገራት በምዕራብያውያን እጅግ ይበዘበዙበት እደነበር ቁልጭ ያለ እውነታ ነው፡፡

የሊቢያ ግንባታበሊቢያ ያለውን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታዎች ለመመርመር ከነጭራሹ ግዜ ወስጄ አስቤው አላውቅም፡፡ ለመጨረሻ ግዜ ሊቢያ በነበርኩበት ወቅት፣ በአየር ላይ ሆኜ እንኳን ጥሩ መንገዶችን መመልከት ችዬ ነበር፡፡ በምዕራብያውያኑ ጋዜጠኞች የታጀቡ አማፂዎች፣ እጅግ በግሩም መልኩ በተሰሩ መንገዶች ላይ በፒክአፕ መኪናዎቻቸው ውስጥ ሆነው በጣም በፍጥነት ሲጓዙ በቴሌቪዥን ምስሎች ውስጥ መመልከት ይቻላል፡፡

እነዚህን መንገዶች ማነው ያስገነባቸው? እነዚህ መገልገያዎች የተገነቡት በንጉሱና የንጉሱ አጋሮች በነበሩት አሜሪካውያንና እንግሊዝያውያን የአገዛዝ ወቅት ነበርን? ወይስ በጋዳፊ? በቱኒዚያና ግብፅ የተወሰኑ ወጣቶች ሥራ ለማግኘት ባለመቻላቸው ምክንያት ራሳቸውን በእሳት አያይዘው ሕይወታቸውን አጥፍተዋል፡፡ እናስ፣ ሊቢያውያን በተመሳሳይ ሥራ አጦች ናቸውን? ታድያ ከሆኑ እነዚያ በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ የውጭ ሀገራ ሰራተኞች ስለምን በሊቢያ ተገኙ? ለሶስተኛው ዓለም ሰራተኞች እጅግ በርካታ ሥራዎችን በማቅረቡ፣ ሊቢያ የተገበረችው ፖሊሲ ትክክለኛ አልነበረም ማለት ነው? በሊቢያ ሕፃናቱ ወደ ት/ቤት ይሄዳሉ? በፊት እውነታው እንደዛ ነበር - ከጋዳፊ በፊት? በሊቢያ ያለው ግጭት ኢኮኖሚያዊ፣ ወይስ ፍንትው ያለ ፖለቲካዊ? ምናልባት የግሉን ሴክተር የበለጠ ቢያበረታቱ ኖሮ ሊቢያ በበለጠ ማደግ ትችል ነበር፡፡ ሆኖም ይህን ራሳቸው ሊቢያውያን በተሻለ የሚዳኙት ነው፤ አሁን ባለው ሁኔታ ሊቢያ የመካከለኛ ገቢ ሀገር ስትሆን አጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርቷ 62 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር ነው፡፡ለዘብተኝነትበአረቡ ዓለም ካሉ ጥቂት ዓለማዊ መሪዎች ውስጥ ጋዳፊ አንዱ ናቸው፡፡ በእስላማዊ አክራሪነት አያምኑም፤ ለዚያም ነው የሊቢያ ሴቶች ት/ቤት መሄድ፣ በሠራዊቱ ውስጥ አባል መሆን፣ እና እዲሁም በሌሎች መስኮች መሳተፍ የቻሉት፡፡

ወቅታዊው የሊቢያ ቀውስ በመጀመርያ፣ በሰላማዊ ተቃውሞዎችና የኃይል ጥቃት ባካተቱ ተቃውሞዎች መካከል ያለው ልዩነት ሊጤን ይገባል፡፡ በሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ ገዳይ ጥይቶችን መተኮስ አግባብ አይደለም፡፡ እርግጥ፣ ሰላማዊ ተቃውሞ ራሱ ከሌሎች ዜጎች መብቶች ጋር እንዳይጋጭ ከፖሊስ ጋር በተቀናጀ መልኩ ሊካሄድ ይገባል፡፡ ሆኖም፣ ሥልጣን የመያዝ ግብ አንግበው፣ ኃይል የተቀላቀለበት ተቃውሞ የሚያካሂዱ

የፖሊስ ጣቢያዎችንና የጦር ዕዞችን ሲያጠቁ፣ ሰላማዊ ሰልፈኞች መሆናቸው ያከትማል፤ አማፂዎች ሆነዋልና፡፡ ምላሽ ሊሰጣቸውም የሚገባው እንደአማፂነታቸው ነው፡፡ ኃላፊነት የሚሰማው መንግስትም ትጥቅ ለማስፈታት ተመጣጣኝ ኃይል ይጠቀማል፡፡ እርግጥ ነው ኃላፊነት የሚሰማው መንግስት በየወቅቱ በሚደረጉ ምርጫዎች የሕዝብን ይሁንታ ያገኘ መሆን አለበት፡፡ የመንግስቱን ሕጋዊነት በተመለከተ ጥርጣሬ ካለና ሕዝቡ የኃይል ትግል ለማወጅ ከወሰነ፣ ያ ውሳኔ የውስጥ ኃይሎች መሆን አለበት፡፡ የውጭ ኃይሎች ያን ድርሻ አግባብነት በሌለው መንገድ ራቸው ሊወስኑት አይገባም ምክንያቱም ብዙ ግዜ በትክክል ለመወሰን በቂ እውቀት የላቸውምና፡፡ከመጠን ያለፈ የውጭ ኃይል ጣልቃ-ገብነት ሁሌም አስከፊ መጣረሶችን ማስከተሉ የማይቀር ነው፡፡ ስለምን የውጭ ኃይሎች በሌሎች ሀገራት የውስጥ ጉዳዮች ራሳቸውን ይዶላሉ? ሕጋዊ የውስጥ የትጥቅ ትግል፣ ጥረቱን በሚያደርጉ መሪዎች ተመራጭ ሥትራቴጂ የሆነ ከሆነ ስኬታማ ይሆናል፡፡ የኢራኑ ሻ የተገረሰሱት በውስጥ የኃይል ሕዝባዊ ተቃውሞ ነው፤ የ1917ቱ የሩሲያ አብዮት፣ በ1964 የተካሄደው የዛንዚባር አብዮት፣ በዩክሬይን፣ ጆርጂያና የሌሎች ሀገራት በጠቅላላ የውስጥ አመጾች ውጤቶች ናቸው፡፡ በአንዲት ሀገር ውስጥ የሚንቀሳቀሱ መሪዎች ስትራቴጂያቸውን ራሳቸው እንዲወስኑበት ሊተዉ ይገባል፡፡ በሉዓላዊ ሀገራት ውስጥ የሚደግ የውጭ ፖለቲካዊና ወታደራዊ ጣልቃ-ገብነት በፍፁም አይዋጥልኝም፣ በተይ በአፍሪካ ሀገራት ውስጥ የሚደረጉ ጣልቃ-ገብነቶች፡፡ የውጭ-ጣልቃ ገብነት መልካም ከሆነ የአፍሪካ ሀገራት ከሁሉም በበለጠ ስኬታማ መሆን በተገባቸው ነበር ምክንያቱም በርካታ መሰል ተሞክሮዎች አሉንና፤ የባሪያ ንግድ፣ ቅኝ አገዛዝ፣ ኒዎ-ኮሎኒያሊዝም፣ ኢምፔሪያሊዝም ወዘተ፡፡ ያም ሆኖ ግን ሁሉም በውጭ ሀገራት የተጫኑት ሁነቶች እጅግ አንኮታኳች መሆናቸው ታይቷል፡፡ ገና አሁን በቅርቡ ነው አፍሪካ ቀና ማለት የጀመረችው፤ ከፊል ምክንያቱም የውጭ ጣልቃ-ገብነትን አንቀበልም ማለታችን ነው፡፡ የውጭ ጣልቃ-ገብነት እና ጣልቃ-ገብነቱን የአፍሪካውያን መቀበላቸው ለአህጉራችን ባለችበት መርገጥ ምክንያቶቹ ናቸው፡፡ በአብዛኛው በብዙ የአፍሪካ ሀገራት ውስጥ ያለው የተሳሳተ ቅድሚያ የሚሰጣቸው ነገሮች በውጭ ቡድኖች የተጫኑ ናቸው፡፡ ለምሳሌ መሰረተ-ልማትን ቅድሚያ አለመስጠት - በተለይ የኃይል አቅርቦት - በከፊል የእነዚህ ግፊቶች ውጤት ነው፡፡ ከዚያ ይልቅ የምርት ተጠቃሚነት ነው የሚበረታታው፡፡ በዩጋንዳ እንኳን ይህን ታዝቤያለሁ፡፡ ካለኃይል እንዴት ነው ኢኮኖሚ ሊደረግ የሚችለው? ባንዳዎችና የውጭ ኃይሎች ደጋፊዎች ይህ ሁላ አያሳስባቸውም፡፡ እንደሊቢያ ባሉ ትናንሽ ሀገራት ውስጥ የውጭ ኃይሎች አማፂዎችን የሚደግፉ ከሆነ፣ ከምዕራቡ ሥርዓት የተለየ ሥርዓት ያላትን ቻይናን ምን ሊደርጉ ነው? ድንገት አመፅ ይቀሰቀሳል በሚል ከበረራ ነፃ ቀጠና በቻይና ላይ ሊጣል ነው? ልክ በቲቤት፣ ቲያናንሜን አደባባይ ወይም ኡሩምኪ እንደሆነው? የምዕራቡ ሀገራት ሁሌም አንድ አይነት መመዘኛዎችን አይጠቀሙም፡፡ በሊቢያ ውስጥ ከበረራ ነፃ ቀጠና ለመጣል በጣም ነበር የጓጉት፡፡ ግና፣ አፍቃሬ-ምዕራብያውያን አገዛዞች ባሉባቸው ባህሬንና በሌሎች አካባቢዎች አይናቸው ዞር ብሎ ሊመለከት አልቻሉም፣ ምንም እንኳን በሀገራቱ ውስጥ ያለው ሁኔታ ከሊቢያ ተመሳሳይ ወይም የባሳ ቢሆንም፡፡ ከአል-ቃኢዳ ጋር ግንኙነት ያላቸውንና፣ በመስከረም 11/2001 አሜሪካውያንን፣ ባለፈው ሀምሌ ዩጋንዳውያንን የገደሉትን እና በሶማሊያውያን ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያደረሱ አሸባሪዎችን እንቅስቃሴ ለመግታት በሶማሊያ ላይ ከበረራ ነፃ ቀጠና እንዲጣል ለተ.መ.ድ አቤት ስንል ነበር፡፡ ሆኖም ጥያቄያችን የሚሰማ ጆሮና የሚያይ አይን ሳያገኝ ቀረ፡፡ ለምን? በቤንጋዚ እንዳሉት በሶማሊያ ሰብዓዊ ፍጡራን የሉም እንዴ?የምዕራቡ ሀገራት በሶስተኛው ዓለም በሚከሰት በእያንዳንዱ ችግር አስተያየታቸውን ለመስጠት ጥድፊያቸው፤ ለምሳሌ ቱኒዚያን፣ ግብፅን፣ ሊቢያን ወዘተ መመልከት ይቻላል፡፡ ያም ሆኖ እነዚሁ ሀገራት ናቸው የእነዚያን ሀገራት እድገት ሲያደናቅፉ የቆዩት፡፡ በ1952 በሂደት ወደ አብዮትነት የተለወጠ መፈንቅለ መንግስት ተካሂዶ ነበር - ኋላ ቀር በነበረችው ግብፅ፡፡ አዲሱ መሪ - ናስር - የሊቢያን ለውጥ እውን የማድረግ ራዕይ ነበራቸው፡፡ የኤሌክትሪክ ኃይል ለማመንጨት ብቻ ሳይሆን ጥንታዊውን የግብፅ የመስኖ ሥርዓት ለመደገፍ ግድብ ለመገንባት ፍላጎት ነበራቸው፡፡ ግብፃውያን የኤሌክትሪክ ኃይል ያስፈልጋቸዋል ብለው አላመኑም ነበርና ምዕራብያውኑ፣ ለግንባታው የሚያስፈልገውን ገንዘብ

ከለከሏቸው፡፡ ከዚያም ናስር ሱዊዝ ካናልን በመንግስት ቁጥጥር ስር በማድረግ ገለግባታው ንዘብ ለማግኘት ወሰኑ፡፡ ውሳኔያቸውን ተከትሎ በእስራኤል፣ ፈረንሳይና እንግሊዝ ጥቃት ተሰነዘረባቸው፡፡ በወቅቱ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት የነበሩት አይዘንሀወር ጥቃቱን ተቃውመውት ነበር፡፡ እርግጥ ነው በሶቭየት ሕብረትም በኩል ጠንካራ አቋም ተይዞ ነበር፡፡ የናስር የግድ ግንባታ ዕቅድ ምን ያህል የኤሌክትሪክ ኃይል ያመነጫል ተብሎ ነበር የታሰበው? 2000 ሜጋዋት ብቻ - ግብፅን ለምታህል ሀገር! በእነዚህ ሀገራት ጉዳዮች ውስጥ ራሳቸውን በመዶል አስተያየት ለመ፣ስጠት እነዚህ ሰዎች ምን አይነት የሞራል መብት አላቸው ታዲያ?ሁሉም እንደተጠበቁ ሆነው፣ በአፍሪካ ሕብረት አማካኝነት ከተቃዋሚዎች፣ እና በደንብ የምናውቃቸውና የተለያዩ ግለሰቦች ከተሰባሰቡባቸው በርካታ ቡድኖች ጋር ለሚደረግ ሰላም የማምጫ የእርቅ ውይይት፣ ኮሎኔል ጋዳፊ ዝግጁ መሆን አለባቸው፡፡ ጋዳፊ የራሳቸው የተመራጭ ኮሚቴዎች ስብስብ የሆነ ብሄራዊ ሕዝባዊ ሸንጎ ሥርዓት እንዳላቸው አውቃለሁ፡፡ ጋዳፊ፣ ይ ሸንጎ ከእኛ መድብለ ፓርቲ ሥርዓት የላቀ ነው ብለው እንደሚያስቡ አያጠራጥርም፡፡ እርግጥ ነው ይህ የእርሳቸው ሥርዓት ከእኛው ጋር ምን ያህል በትክክል ሊፎካከር እንደሚችል ግዜ ወስጄ አጥንቼው አላውቅም፡፡ ያም ሆነ ይህ፣ ሊፎካከር የሚችል ቢሆን እንኳን፣ በአገራቸው የመንግስት አስተዳደር ውስጥ ችግር አለ ብለው የሚያስቡ እጅግ በርካታ ሊቢያውያን በአሁኑ ወቅት መኖራቸው ግልፅ ነው፡፡ አይደለም ሌሎች ዓለም አቀፍ ታዛቢዎች፣ የአፍሪካ ሕብረት እንኳን የተገኘባቸው ምርጫዎች በሊቢያ ተካሂደው አያውቁምና፣ የትኛው ነው ስህተት፣ የትኛው ነው ትክክል ልንል አንችልም፡፡ ስለዚህም፣ ትክክለኛው አማራጭ መንገድ ውይይት ነው፡፡የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ወደሊቢያ ለመግባት አልተቻለውም፤ ምክንያቱም ተልዕኮው ሊቢያ መግባት ከነበረበት አንድ ቀን በፊት ምዕራብያውያኑ ሀገሪቱን በቦምብ መደብደብ ጀምረው ነበርና፡፡ ያም ሆኖ ተልዕኮው በጥረቱ ይገፋበታል፡፡ እንደእኔ አመለካከት፣ የአፍሪካ ሕብረት ተልዕኮ እያደረገ ካለው ጥረት በተጓዳኝ፣ ይህን እጅግ አንገብጋቢ የሆነን ጉዳይ ለማጤን ሕብረቱ በአዲስ አበባ አስቸኳይ ጉባዔ እንዲያደር ጥሪ ማቅረብ አስፈላጊ ሊሆን ይችላል፡፡የሊቢያን ተቃዋሚዎች በተመለከተ፣ በምዕራብያውያኑ የጦር አውሮፕላኖች ብደገፍ ኖሮ ጥሩ ስሜት አይሰማኝም ነበር፡፡ የውጭ ኃይሎች ጥቅሞች አገልጋይ ባዳዎች አፍሪካን መቼም ጠቅመዋት አያውቁም፡፡ ባለፉት 50 ዓመታት ውስጥ እጅግ በርካታ መሰል ባንዳዎችን አይተናል፤ ሞቡቱ ሴሴ-ሴኮ፣ ሆፎት ባይግኒ፣ ካሙዙ ባንዳ፣ ወዘተ ምሳሌዎች ሊሆኑን ይችላሉ፡፡ ባለፊት ግዜያት፣ ምዕራቡ በአፍሪካ እና በመካከለኛው ምስራቅ ውስጥ በርካታ ስህተቶችን ፈፅመዋል፡፡ ከባርያ ንግድና ከቅኝ አገዛዝ በተጓዳኝ፣ እስከቅርብ ግዜ ድረስ ብቸኛው የዴሞክራቲክ ሪፑብሊክ ኮንጎ ተመራጭ መሪ በነበሩት ፓትሪስ ሉሙምባ ግድያ፣ በካሜሩንያዊ የፖለቲካ መሪ ፌሊክስ ሞሚይ መመረዝ፣ የማዕከላዊ አፍሪካ ሪፑብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር በነበሩት ባርቶሎሚው ቦጋንዳ ግድያ ምዕራብያውያኑ ተሳትፎ አድርገዋል፡፡ የአንጎላውን ‹‹ዩኒታ››፣ በዩጋዳ ውስጥ ደግሞ፣ በአገዛዛቸው መጀመርያ ወቅት፣ ኢዲ አሚንን፣ እና በ1953 ውስጥ ደግሞ በኢራን ፀረ-አብዮተኞችን ምዕራቡ ደግፏል፡፡ በቅርቡ ግን የምዕራብያውያኑ የማን አለብኝነት አመለካከት ላይ መሻሻሎች ታይተዋል፡፡የሊቢያ ተቃዋሚዎች አርበኞች ከሆኑ፣ ጦርነታቸውን ራሳቸው በራሳቸው መዋጋት አለባቸው፤ ጉዳያቸውንም ራሳቸው ማስፈፀም አለባቸው፡፡ ከሊቢያ መንግስት ወታደራዊ ሠራዊት እኮ እጅግ በርካታ መሳሪያዎችን በቁጥጥራቸው ስር ለማድረግ ችለዋ፤ ታድያ ስለምን የውጭ ወታደራዊ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል? እኔ 27 ጠብ-ምንጃዎች ብቻ ነበሩኝ፡፡ አሻንጉሊት መሆን ጥሩ አይደለም፡፡ዓለም አቀፉን ማሕበረሰብ በተመለከተ፣ የፀጥታው ምክር ቤት የአፍሪካ አባላት በሊቢያ ላይ የተላለፈውን ውሳኔ ደግፈው ድምፃቸውን ሰጥተዋል፡፡ ይህ የአፍሪካ የሰላምና የፀጥታ ምክር ቤት በቅርቡ በአዲስ አበባ ከወሰነው ውሳኔ ጋር የተጣጣመ አይደለም፡፡ ይህ የሕብረቱ አስቸኳይ ስብሰባ ብቻ መፍትሄ የሚሰጠው ጉዳይ ነው፡፡ በፀጥታው ም/ቤት ውስጥ ያሉ አንዳንድ ትላልቅ አባላት - ሩሰሲያ፣ ቻይና፣ ብራዚል፣ እና ሕንድ - በዚህ ውሳኔ ድምፀ ተአቅቦ ማድረጋቸው መልካም ነበር፡፡ ይህም የሚያሳየው፣ የበለጠ ውይይቶች ከተደረጉ የበለጠ ትክክለኛ የሆነ ውሳኔ የሚያመኘጩ ሚዛናዊ ኃይሎች በዓለም መኖራቸውን ነው፡፡/ሁሉም አቆጣጠሮች እ.አ. ናቸው፡፡/

ከላይ የቀረበው ፅሁፍ የዩጋንዳው ፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሰቪኒ፣ ስለሊቢያው መሪ ኮሎኔል

ሙአመር ጋዳፊ፣ በጋዳፊ መንግስት ላይ እየተወሰዱ ስላሉ እርምጃዎች፣ ስለእርምጃዎቹ

አግባብነት፣ የኮሎኔሉ አሉታዊና አዎንታዊ ስላሏቸው ገፅታዎች፣ እና ስለሌሎች አሕጉራዊና

ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች አንድ መጣጥፍ መጋቢት 19/2003 ላይ ለንባብ አብቅተው ነበር፡፡ እኛም

‹‹ፎሬይን ፖሊሲ›› ከተባለ ድረ-ገጽ አግኝተን ወደ አማርኛ የመለስነው ነው

እኔ የማውቀው . . .

Page 19: Awramba Times Issue 161 Megabit 24

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 161 ቅዳሜ መጋቢት 24 2003

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

ኢትዮ ቴሌኮም የታሪፍ ለውጥ አደረገዜ ና ዎ ች 19

በወሰንሰገድ ገብረኪዳን

ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ላይ ግዙፍ የኤሌትሪክ ኃይል ማመንጫ ለመገንባት አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቋ ተገለፀ፡፡ ባለፈው ረቡዕ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ አለማየሁ ተገኑ እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች በሸራተን አዲስ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንደገለፁት፣ ኢትዮጵያ ልትገነባ ያቀደችው ግዙፍ የኃይል ማመንጫ ግድብ 5ሺህ 25ዐ ሜጋዋት የኤሌክትሪክ ኃይል የማመንጨት አቅም ይኖረዋል፡፡ ‹‹ታላቁ የሚሊኒየም ግድብ›› ወይም፣ ‹‹የአባይ ግድብ›› የሚል ስያሜ የተሰጠው ይህ ፕሮጀክት ግንባታው ሲጠናቀቅ፣ አሁን ያለውን የሀገሪቱን ኃይል አቅርቦት ከሶስት ዕጥፍ በላይ

እንዲሁም በ1997 ዓ.ም ሀገር አቀፍ ምርጫ ሙሉ በሙሉ በሚያሰኝ መልኩ በምርጫ ካርድ ሕዝብ ከሥልጣን ቢያወርደውም፣ በምርጫው ምሽት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በማወጅና የፖሊስ ኃይሉን በመጠቀም በሰላማዊ መንገድ ‹‹ድምፃችን ይከበር›› ባሉ ንፁሃን ዜጎች ላይ ጥይት በመተኮስ 193 ሰዎች መገደላቸው፣ ሌሎች እንዲቆስሉና እንዲታሰሩ ማድረጉ፣ መሬትና የተፈጥሮ ደን የሕዝቡን ጥቅም ባላስከበረ መልኩ ለኢንቨስተሮች እስከ 99 ዓመታት ለሚደርስ ጊዜ ነፃ ሊባል በሚችል ሁኔታ እያስረከበ መሆኑ ተብራርቷል፡፡በነፃ ጋዜጦች ላይ ተገቢ ያልሆነ ክስ በመመስረት ራሳቸውን በራሳቸው ሳንሱር እንዲያደርጉ፣ የህትመት ዋጋን ሆን ብሎ በማናር ገበያ ላይ ተወዳዳሪ እንዳይሆኑና እንዲከስሙ እያደገ መሆኑን ሬዲዮኖችና ቴሌቪዥኖች እንዲኖሩ በማድረግ ፈንታ ከፍተኛ ወጪ በማውጣት ከውጪ ሀገር የሚተላለፉ ፕሮግራሞችን እያፈነ እንደሚገኝና በዚህም የፕሬስ ነፃነትን በማፈንና የዜጎችን መረጃ የማግኘት መብት እየጣሰ እንደሚገኝ በመግለጫው ተዘርዝሯል፡፡ በምርጫ 2002ም 99.6 በመቶ መቀመጫ ኢህአዴግ ያገኘው በዘረፋና በስርቆት መሆኑን ተቃዋሚዎችም ሆነ ሕዝብ ጠንቅቀው እንደሚያውቁት፤ የዋጋ ግሽበትና የኑሮ ውድነቱ ሲባባስ መንግስት የዋጋ ተመን ካወጣ በኋላ የገበያ ትርምስ እየፈጠረ እንደሚገኝ፤ የገዥው ፓርቲና የመንግስት አካላት በኦሮሚያ 12 ዞኖች

በተለይም በምዕራብ ሸዋ፣ በምስራቅ ወለጋ፣ በሆሮጉድሩ ወለጋ፣ በኢሉባቦር በጅማ፣ በቦረና፣ በጉጂ፣ በፊንፊኔ ዙሪያና በሌሎችም ዞኖች ውስጥ በሚገኙ 27 ወረዳዎች ከየካቲት 22/2003 ዓ.ም ጀምሮ በንፁሃን ዜጎች ላይ የማዋከብ፣ የእስራትና የሰብዓዊ መብት ረገጣ እየፈፀሙ እንደሚገኙ ተገልጿል፡፡ በሌላ በኩል መግለጫው በሰሜን አፍሪካና በመካከለኛው ምስራቅ ጨቋኝ ሥርዓቶች ላይ የነደደው የሕዝብ ቁጣ ያስደነገጠው ይህ መንግስት በርካታ ተማሪዎችንና መምህራንን በገፍ እያሰረ እንደሚገኝ፣ መድረክ ከሕዝብ አመፅ ተጠቃሚና አትራፊ ለመሆን ባይፈልግም የሕዝብ ምሬት ወደ አመፅ ከመለወጡ በፊት መንግስት ተገቢውን እርምጃ እንዲወስድ አሳስቧል፡፡ በዚህም መሠረት መንግስት ያሰራቸውን ንፁሃን ዜጎች እንዲፈታና ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ ያቀረባቸውን የድርድር አጀንዳዎች ጨምሮ ሌሎች ባለድርሻ አካላት የሚያቀርቧቸውን ተጨማሪ አጀንዳዎች አካትቶ ብሔራዊ የውይይት መድረክ በአስቸኳይ ተጠርቶ በከፍተኛ የኃላፊነት ስሜት መሠረታዊ ለውጦች በኢትዮጵያ እንዲመጡ ጥሪውን በድጋሚ ለኢህአዴግ ማስተላለፉን መድረክ ገልጿል፡፡በተጨማሪም በኢንቨስትመንት ሽፋን የሕዝብንና የሀገርን ጥቅም በማያስከብር መልኩ መሬትንና የተፈጥሮ ሀብትን ነፃ ሊባል በሚችል ሁኔታ ለረዥም ዓመታት ለኢንቨስተሮች ማስረከቡን በአስቸኳይ

አቁሞ ጉዳዩን ለሕዝብ ነፃ ውይይት ክፍት እንዲያደርግና የኑሮ ውድነትና ሥራ አጥነትን ለመቅረፍ አስቸኳይ እርምጃ እንዲወሰድ መድረኩ በአፅንኦት ጠይቋል፡፡ በዕለቱ ለነበሩት የመድረክ አመራሮች ከጋዜጠኞች ጥያቄ ቀርቦላቸው ምላሽ ሰጥተውበታል፡፡ ኢትዮጵያና ኤርትራ ዳግም ወደ ጦርነት ሊገቡ ይችላሉ ስለሚባለው ስጋት አቶ ገብሩ አስራት ሲመልሱ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ‹‹ሻዕቢያ አዲስ አበባን ወደ ባግዳድነት ሊለውጣት ነው›› ማለታቸውን ሰው በፍርሃትና በስጋት እንዲዋጥ የሀሳብ ማስቀየሻ ስልት ነው ብለውታል፡፡ አያይዘውም፣ ‹‹በእርግጥ ሻዕቢያ የፀጥታ ችግር እየፈጠረ ነው፡፡ አገርን ለማተራመስ የሚችል እንቅስቃሴ ግን አላየንም፡፡ ኢህአዴግ እኔ ከሌለሁ አትኖሩም እያለ ነው›› ካሉ በኋላ በዚህ ጉዳይ ወደ ጦርነት የሚገባ ከሆነ መድረክ የሚኖረው አቋም የሚወሰነው በወቅቱ እንደሆነ አስረድተዋል፡፡ ከዋጋ ቁጥጥሩ ጋር በተያያዘ ለቀረበው ጥያቄም፣ በአገሪቱ ብዙ ሸቀጦች እየጠፉ ስለሆነ ችግሩ በአዋጅ እንደማይፈታ ምላሽ ተሰጥቶበታል፡፡ በቅርቡ መንግስት በአባይ ተፋሰስ ላይ ግድብ ለመስራት ማቀዱን አሰመልክቶ ለተነሳው ጥያቄ፣ ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ‹‹በልማቱ ላይ ጥል ባይኖረንም በዓለም አቀፍ ደረጃ በዲፕሎማሲያዊና ፖለቲካዊ ማዕቀፎች ዙሪያ በቂ ዝግጅት ተደርጓል ወይ?›› ብለው በመጠየቅ የጥንቃቄ እርምጃ እንደሚያሻው ጠቁመዋል፡፡ተባባሪ ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና በበኩላቸው ‹‹የራበው ሕዝብ መሪዎቹን ይበላል›› ብለው በአንድ ወቅት በፓርላማ የተናገሩት እየደረሰ ነው ወይ? ተብለው

ለተጠየቁት ‹‹ያ አነጋገሬ እንደትንቢት ቢወሰድልኝ ጥሩ ነው፡፡ ያኔ ኢህአዴግን መክሬ ነበር፡፡ አልረፈደም፡፡ ቢቀበል ጥሩ ነው፡፡ ኢህአዴግ ብዙ አማራጮች የሉትም፡፡ ካድሬዎቹን ማብላት ብዙም አይጠቅመውም›› ብለዋል፡፡ በቅርቡ በጀርመን አገር ከዶ/ር ብርሃኑ ነጋ እና ከኤርትራው ባለስልጣን አቶ የማነ ጋር ተገናኝተዋል ተብሎ መዘገቡን አስመልክቶ ‹‹ይህ እውነት ነው ወይ?›› ተብሎ ከአውራምባ ታይምስ ጋዜጣ ለቀረበላቸው ጥያቄ ረዳት ፕሮፌሰር መረራ ሲመልሱ፣ ‹‹ከጀርመን ፓርላማ ስለኢትዮጵያ ታውቃለህ? ተብዬ በፓርላማ ላይ ስለሰብዓዊ መብት ጉዳይ ዕውቀቴን ለማካፈል ተጋብዤ ነው የሄድኩት፡፡ ዶ/ር ብርሃኑም ተጋባዥ ነበር፡፡ ኢህአዴግ በአባሎቻችን ላይ እስራት እየፈፀመ ባይሆን ኖሮ ግብዣውን አልሳተፍም ብዬ ነበር፡፡ ዶ/ር ብርሃኑን ማግኘት ደግሞ መብቴ ነው፡፡ ከሻዕቢያ መሪ ጋር እንዴት እንዳገናኘኝ አላውቅም፡፡ በየትኛውም ሚዛን ወደ ኤርትራ አልቀርብም›› ብለዋል፡፡ የሰሜን አፍሪካ አገራት ሕዝባዊ ቀውስ በኢትዮጵያም ይከሰታል ብላችሁ ታስባላችሁ? ለሚለው የአውራምባ ታይምስ ሁለተኛ ጥያቄ መልስ የሰጡት ደግሞ ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ናቸው፡፡ ዶ/ር ነጋሶ የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ እና ማህበራዊ ችግር ከአረብ አገራት የባሰ መሆኑን ጠቅሰው በማን፣ እንዴት እና መቼ የሚለው ነገር ባይታወቅም የሕዝብ እንቅስቃሴ ሊጀመር እንደሚችል ያላቸውን ዕምነት ገልጸዋል፡፡ አያይዘውም ሰው የነማንችስተርን ጨዋታ ትቶ አልጀዚራና ቢቢሲን እየተመለከተ በመሆኑ ይኼ በሰው አዕምሮ ውስጥ እንደሚመላለስ አመልክተዋል፡፡

እንደሚያሳድግ በጋዜጣዊው መግለጫ ተመልክቷል፡፡ የታላቁ ሚሊኒየም ግድብ ግንባታ የሚከናወነው በቤኒሻንጉል/ጉሙዝ ክልል፣ ከሱዳን ድንበር ከ20 እስከ 40 ኪ.ሜ ወደ ኢትዮጵያ ድንበር ገባ ብሎ በሚገኝ ቦታ ላይ ሲሆን፣ 145 ሜትር ከፍታ እና 63 ቢሊዮን ሜትር ኪዩብ ውሃ የመያዝ አቅም እንደሚኖረው ሚኒስትር አለማየሁ ተገኑ አብራርተዋል፡፡ የሚገነባው ግድብ አሁን ካለው የጣና ሐይቅ የውሃ መጠን ከሁለት ዕጥፍ የሚልቅ ውሃ ሊይዝ እንደሚችል የገለፁት ሚኒስትሩ፣ ግንባታው ከ70 እስከ 80 ቢሊዮን ብር ወጪ እንደሚጠይቅ አትተዋል፡፡ ኢትዮጵያ ካሏት በርካታ የልማት ፕሮጀክቶች ወጪ አንፃር ለግድቡ ግንባታ የሚያስፈልጋትን ገንዘብ ማውጣት

ከባድ ቢሆንም፣ የማይቻል አለመሆኑን የገለፁት ሚኒስትር አለማየሁ፣ መንግሥት በራሱ ወጪ የአባይን ወንዝ ለማልማት በቁርጠኝነት መወሰኑን አብራርተዋል፡፡ የግብፅ መሪዎች በአባይ ላይ የሚካሄድ ልማት በሙሉ የሀገራቸውን ጥቅም የሚፃረር በማስመሰል፣ በዓለም ዓቀፍ አበዳሪ ተቋማት እና ሀገራት ዘንድ ያላቸውን ተሰሚነት ተጠቅመው፣ ኢትዮጵያ ወንዞቿን ለማልማት የሚያስፈልጋትን እርዳታና ብድር እንዳታገኝ ጫና ሲፈጥሩ እንደቆዩ ያሰታወሱት አቶ አለማየሁ ተገኑ፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ዓለም ዓቀፍ ትብብሮችን ለማግኘት ያላሰለሰ ጥረት ከማድረግ ሳይቆጠብ፣ እርዳታና ብድር ቢገኝም ባይገኝም በራሱ ወጪ የአባይን ወንዝ ለማልማት ዝግጅቱን ማጠናቀቁን በአፅንኦት ገልፀዋል፡፡ በሀገር ውስጥ እና በውጭ

የሚገኙ ሁሉም የሀገሪቱ ዜጎች፣ የግሉ ሴክተር እና የልማት አጋሮች በተቻላቸው መጠን ከተረባረቡ፣ ከዚህም በላይ መስራት እንደሚቻል መንግሥት ፅኑ ዕምነት እንዳለውም በመግለጫው ተመልክቷል፡፡ ‹‹ከዚህ መሠረታዊ ዕምነት በመነሳት መንግሥት ለግድቡ ግንባታ የሚያስፈልገውን የገንዘብ አቅም ለመፍጠር የሚያስችል የቦንድ ሽያጭ›› ማዘጋጀቱን የገለፁት ሚኒስትር አለማየሁ፣ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ባለው አቅም ይህንን ቦንድ በመግዛት የሀገሪቱን የተፈጥሮ ሀብት በአግባቡ ጥቅም ላይ ለማዋል እንዲረባረብ ጠይቀዋል፡፡

በ1997 ዓ.ም የተካሄደውን ሕዝባዊ ምርጫ ተከትሎ በተከሰተው ቀውስ ለእስር ተዳርገው ከነበሩት የቀድሞ ቅንጅት አመራሮች መካከል አንዱ የነበሩት አቶ አንተነህ ሙሉጌታ በቅንጅት አመራሮች፣ በጋዜጠኞች፣ በሲቪክ ማህበራት አባላት እና በቅንጅት ደጋፊዎች ላይ የተመሠረተውን ክስና የፍርድ ሂደት የሚተነትን መፅሐፍ አሳተሙ፡፡ መፅሐፉ “የሁለት ዓለም ሰዎች” የሚል ርዕስ ያለው ሲሆን ከዋናው ርዕስ ግርጌ “የተዋረደው ፍርድ ቤት” የሚል ንዑስ ርዕስም ሰጥተውታል፡፡ አቶ አንተነህ ሙሉጌታ በ1997 ምርጫ ቅንጅትን ወክለው በአዲስ አበባ ምክር ቤት የተመረጡ፤ ፓርቲው በአዲስ አበባ ሥልጣንን ሲይዝ በዋና ፀሐፊነት እንዲያገለግሎ ታጭተው እንደነበር

በሱራፍኤል ግርማ

ኢትዮ ቴሌኮም የታሪፍ ለውጥ እና ሌሎች ማሻሻያዎችን ማድረጉን አስታወቀ፡፡ ባለፈው ረቡዕ በሸራተን አዲስ በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈፃሚ የሆኑት ሚስተር ዦን ሚሼል፣ በሞባይል ስልክ የጥሪ ዋጋ ተመን፣ በሞባይል ስልክ ሲም ካርድ ዋጋ፣ በምትክ ሲም ካርድ ዋጋ፣ በኤ.ዲ.ኤስ.ኤል እና በኢ.ቪ.ዲ.ኦ አገልግሎት የዋጋ ተመን ላይ ከመጋቢት 23 ቀን 2003 ዓ.ም ጀምሮ ሥራ ላይ የሚውል የዋጋ ማሻሻያ መደረጉን አስታውቀዋል፡፡ በሀገር ውስጥ ለሚደረጉ የሞባይል ስልክ የድምፅ ጥሪ አገልግሎት አንድ ወጥ የዋጋ ታሪፍ እንዲኖር የተደረገ ሲሆን፣ በዚህም መሠረት በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች በመደበኛ ጊዜ ለሚደረግ የሞባይል ስልክ ጥሪ አዲሱ ዋጋ 0.72 ብር ሆኗል፡፡ በቅናሽ ግዜ ደግሞ 0.30 ብር ሆኗል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ቀድሞ የነበረውና ከክልል ክልል (ከአንዱ ታሪፍ ዞን ወደሌላው ዞን) ይለያይ የነበረውን ታሪፍ ሙሉ በሙሉ በማስቀረት፣ አንድ ወጥ የታሪፍ ተመን ሥራ ላይ እንዲውል በመደረጉ በመላ ሀገሪቱ ከሞባይል ወደ ሞባይል፣ ከሞባይል ወደ መደኛ ስልክ እና ከመደበኛ ስልክ ወደ ሞባይል የሚደረጉ ጥሪዎች ዋጋ 0.72 ብር እንዲሆን መደረጉን ዋና ሥራ አስፈፃሚው ገልፀዋል፡፡ ቀድሞ 85 ብር ይሸጥ የነበረው የሞባይል ሲም ካርድ ዋጋ የተጨማሪ እሴት ታክስንና የ15 ብር የአየር ሰዓትን ጨምሮ ወደ ብር 60 ዝቅ እንዲል ቢደረግም፣ ቀድሞ በ15 ብር ይሸጥ የነበረው ምትክ ሲም ካርድ ወደ 45 ብር ከፍ እንዲል ሆኗል፡፡ ለዚህም በምክንያትነት የተቀመጠው

“ፕሮጀስት” ለጋዜጠኞች

የሚሰጠውን ስልጠና እንደሚቀጥል ገለጸ

ፕሮጀስት የሥልጠናና የምርምር ማዕከል የአውራምባ ታይምስ ጋዜጣ ዝግጅት ክፍል ሦስት ባልደረቦችን ጨምሮ ለተለያዩ ጋዜጠኞች ከጥር 7 እስከ መጋቢት 3 ቀን 2003 ዓ.ም ድረስ የመሠረታዊ ሕግ ስልጠና ሲሰጥ የቆየ ሲሆን፣ ስልጠናው ወደፊትም እንደሚቀጥል አስታወቀ፡፡ ስልጣናው የተሰጠው በሰብዓዊ መብት፣ በኢትዮጵያ የሕግ ሥርዓት፣ በኢትዮጵያ የወንጀል እና የሥነ-ሥርዓት ሕግ፣ በችሎት ዘገባና በመገናኛ ብዙሃን፣ እንዲሁም በመረጃ ነፃነት ዙሪያ ነበር፡፡ የማዕከሉ ዋና ሥራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ደበበ ኃይለ ገብርኤል፣ ጋዜጠኞች መሠረታዊ የሕግ ጉዳዮችን እንዲገነዘቡ የሚያስችል ስልጠና ለመስጠት የመነሻ ምክንያት የሆነው ከተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን ተቋማት እና ጋዜጠኞች ጋር በሥራ ምክንያት በሚገናኙበት ወቅት የአብዛኞቹ ጋዜጠኞች የሕግ ዕውቀት ሊዳብር እንደሚገባ መገንዘባቸው መሆኑን ገልጸዋል፡፡ዋና ሥራ አስኪያጁ፣ መሰል ስልጠናዎች መገናኛ ብዙሃን ከሰብዓዊ መብቶች መከብር፣ ከዴሞክራሲ መስፈን እና የሕግ የበላይነትን ከማስከበር አኳያ የሚያበረክቱትን አስተዋጽኦ እንደሚያጎለብት ከገለጹ በኋላ ማዕከሉ እስካሁን ድረስ በሁለት ዙሮች ከግልና ከመንግስት የሚዲያ ተቋማት ለተውጣጡ 85 ጋዜጠኞች በአጠቃላይ የ60 ሰዓታት ስልጠና መስጠቱንና ሶስተኛውን ዙር ለመጀመር በእንቅስቃሴ ላይ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡ “በ32 ሰዓታት እና በ28 ሰዓታት ስልጠና በቂ የሆነ የሕግ ዕውቀት አስጨብጠናል ብለን ለመናገር አንደፍርም” የሚሉት አቶ ደበበ፣ ጋዜጠኞች ከስልጠናው ያገኙትን መጠነኛ ዕውቀት በራሳቸው ጥረት በማሳደግ ህብረተሰቡን ማሳወቅ እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል፡፡ በስልጠናው ተካፋይ ከነበሩት የሚዲያ ባለሙያዎች ውስጥ አብዛኞቹ ሕግን ለማወቅ ያላቸው ፍላጎት ከፍ ያለ ሆኖ የተስተዋለ ሲሆን ይነሱ የነበሩ ጥያቄዎችም በአመዛኙ ከጋዜጠኞቹ የዕለት ተለት ገጠመኝ ጋር የተያያዙ ሆነው “ይኼ ለምን ሆነ?” ለምን እንዲህ አይሆንም?” የሚል ይዘት ያላቸው የመብት ጥያቄዎች ነበሩ፡፡ ከጥር 7 እስከ መጋቢት 3 ድረስ የተሰጠው የሁለተኛው ዙር ስልጠና በተጠናቀቀበት ወቅት፣ “በዚህኛው ዙር ላይ ያየሁትና ደስ ያለኝ ነገር የጋዜጠኝነት ሙያን አክብረውና ወደው የሚሰሩ ወጣቶች እየተበራከቱ መምጣታቸው ነው” ያሉት የማዕከሉ ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ አሁን ባለው ሁኔታ ችሎቶች እና የፍርድ ቤት አሰራሮች በሚፈለገው መጠን እየተተቹ አለመሆናቸውን አልሸሸጉም፡፡ ስልጠናውን ከአዲስ አበባ ውጪ ለሚገኙ ጋዜጠኞችም የማዳረስ ዕቅድ እንዳለ ከተቋሙ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ሲም ካርዶች በውጭ ምንዛሪ ተገዝተው የሚገቡ መሆናቸውና ዋጋቸው ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ በመሄዱ፣ ኩባንያው ለከፍተኛ ወጪ መዳረጉ ነው፡፡የኢ.ቪ.ዲ.ኦ አገልግሎትን በተመለከተ ኢትዮ ቴሌኮም ቀደም ሲል ይሰጥ ከነበረው የ2 ጊጋ ባይት በተጨማሪ የ1 ጊጋ ባይት እና የ4 ጊጋ ባይት አገልግሎቶችን እንደየቅደም ተከተላቸው በብር 300 እና 700 ለደንበኞቹ የሚያቀርብ መሆኑን እና

በመፅሐፋቸው መግቢያ አስታውሰዋል፡፡ በኢ/ር ኃይሉ ሻውል የክስ መዝገብ ተከሰው ለእስር ተዳርገው የነበሩት አቶ አንተነህ ሙሉጌታ በዚሁ መፅሐፍ መግቢያ “የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በእነ ኢ/ር ኃይሉ ሻውል ላይ የፈረደውን ፍርድ እንደወረደ አሳትሞ ለሕዝብ እንዲደርስ አድርጓል፡፡ እኔም በበኩሌ በምርጫ 97 ሰፊና ውስብስብ ሂደት ውስጥ ክሱንና የፍርድ ሂደቱን በባለሙያ ዓይን ገምግሜ ለማቅረብ ሞክሬያለሁ” ሲሉ አትተዋል፡፡ አቶ አንተነህ ሙሉጌታ የሕግ ባለሙያ ሲሆኑ ከምርጫ 97 በፊት በዳኝነት ያገለገሉ መሆናቸው ይታወሳል፡፡ መፅሐፉ በዘጠኝ ምዕራፍ የተከፋፈለ ሲሆን ከምዕራፍ አንድ እሰከ ሶስት የዐቃቤ ሕግን የክስ አቀራረብና የክሶችን ይዘትና

ሕጋዊነት፣ ከምዕራፍ አራት እስከ ስድስት ዐቃቤ ሕግ ክሶቹን ያስረዱልኛል ብሎ ያቀረባቸውን ማስረጃዎችና ዳኞቹ በተለያየ ጊዜ የሰጡትን ብይን፣ በምዕራፍ ስምንት ከቪዲዮ ውጪ በቀረቡና ፀሐፊው አስቂኝና አስገራሚ ያሏቸው የሰነድ ማስረጃዎችና የምስክሮችን ቃል፣ በምዕራፍ ዘጠኝ ደግሞ በተመረጡ የዳኞች ብይኖች ላይ የሕግ ትንተና የቀረበበት ነው፡፡ ከገፅ 9 እስከ 38 ባሰፈሩት መቅድም ውስጥ ተቃዋሚ ፓርቲዎች እና አመራሮች ላይ የሰላ ሂስ ሰንዝረዋል፡፡ መፅሐፉ 296 ገፅ ያለው ሲሆን በብር 50 ለገበያ ቀርቧል፡፡

ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ላይ ግዙፍ የኤሌትሪክ ኃይል ማመንጫ ልትገነባ ነው

የኢ.ቪ.ዲ.ኦ አገልግሎት የደንበኝነት ዋጋ ላይ ቅናሽ መደረጉን ሚስተር ዦን ሚሼል ተናግረዋል፡፡ በጋዜጣዊ መግለጫው ወቅት፣ ‹‹በሌሎች ሀገራት እንደሚደረገው ለምን ሲም ካርድ በነፃ መስጠት አትጀምሩም? የመደበኛ ስልክ ታሪፍስ ለምን አይቀንስም?›› የሚሉ ጥያቄዎች ከአውራምባ ታይምስ ቀርበው ነበር፡፡ ለተነሱት ጥያቄዎች ምላሽ የሰጡት የኩባንያው የውጭ ግንኙነት ሥራ

አስኪያጅ አቶ አብዱራሂም አህመድ፣ ኢትዮ ቴሌኮም ከሚገለገልባቸው መሳሪያዎች ውስጥ አብዛኞቹ በውጪ ምንዛሪ የሚገዙ መሆኑን በማስታወስ፣ ሲም ካርድ በነፃ ማቅረብ አክሳሪ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡ የመደበኛ ስልክ ታሪፍን በተለከተ ደግሞ፣ ‹‹ኢትዮ ቴሌኮም የመደበኛ ስልክን ታሪፍ የመወሰን ሥልጣን የለውም፤ እሱ የሚወሰነው በሚኒስትሮች ምክር ቤት ነው›› ብለዋል፡፡

በቀድሞ የቅንጅት አመራሮች ላይ የቀረበውን ክስና ፍርድየሚተነትን መፅሐፍ ታተመ

‹‹በሕዝብ ላይ የሚደርሰው ግፍ...

Page 20: Awramba Times Issue 161 Megabit 24

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 161 ቅዳሜ መጋቢት 24 2003ጤ ና20

ሰብዓዊ ፍጥረታት በሙሉ ውስጣዊ የኃይል አወቃቀር እንዳለን መረጃዎች ያስረዳሉ፡፡ ልክ እንደኮምፒውተር ሁሉ የሰዎች የኃይል ስርዓት የተለያየ ደረጃ ኃይል፣ ፍጥነትና አንድን ነገር የማድረግ ብቃት አለው፡፡ ይኼንን ኃይል ይበልጥ ባወቁት ቁጥር ብዙ ነገር ማድረግ ያስችላል፡፡ እንዲሁም በደመ-ነፍስ የማወቅና የመረዳት ችሎታዎች፣ በአዕምሮ ይበልጥ የመጠቀም ብቃትና ነገሮችን በቀላሉ የመግለፅ አቅም፣ ዕጣ ፈንታን መለወጥ መቻልና ፈውስን ማምጣት እና ሌሎች አስገራሚና አስደሳች ነገሮች በማንነት ላይ እንዲጨምሩ ለማድረግ የላቀ አስተዋፅዎ አለው፡፡ የሰብዓዊ ኃይል መገኛ ስፍራ /Human Energy Field (HEF)/ አንዳንዴ ኦራ ተብሎ በእንግሊዘኛ ይገለፃል፡፡ ይኼም ውስብስብ ሆኖ አንዱ በአንድ ላይ በመነባበር ሕብረት የፈጠረ ተደጋጋሚ የኃይል አካሄድ በመሆን የእያንዳንዱን ሰው የተለየ መንፈሳዊ፣ አዕምሯዊ፣ ስሜታዊ እና አካላዊ አሰራር የሚገልፅ ነው፡፡ የግለሰቦች ሰብዓዊ የኃይል ስፍራ የመላው ሕዋ የኃይል መገኛ ስፍራ /universal Energy Field (UEF)/ አንዱ አካል ሲሆን እያንዳንድ ግለሰብ በራሱ ከሕዋ ጋር ሕብረት ይፈጥራል፡፡ ሰብዓዊ የኃይል መገኛ ስፍራን ለመግለፅ ሦስት መሠረታዊ መንገዶች አሉ፡፡ እነዚህም የኃይል ሀሳብ መስመሮች (ሜሪዲያንስ)፣ ቻክራስ እና የኃይል አካላቶች ተብለው ይጠራሉ፡፡ እነዚህም ኃይልን መሠረት ላደረጉ የፈውስ ዘዴዎች ትልቅ ግልጋሎት አላቸው፡፡

የኃይል የሀሳብ መስመሮችእነዚህ በሰዎች መላ አካላት ውስጥ ውስጣዊ የኃይል መተላለፊያ መስመሮች ሲሆኑ ውስጣዊ ዋና ዋና የሰውነት ክፍሎችንና የእነሱን ብዙ ንዑስ ስርዓቶችን በኃይል ተሞልተው ያገናኟቸዋል፡፡ በምሳሌነት የደም፣ የሆርሞን አምራችና አስተላለፊ (ኢንዶክራይን)፣ የነርቭና የምግብ ልመት/አፈጫጭ (ዳይጀሽን)... ወዘተ ስርዓቶች ይጠቀሳሉ፡፡ የኃይል ሀሳብ መስመሮች እና በመስመሮቹ ላይ የሚገኙ ውስን ነጥቦችን እንደ አኩፓንቸር (ሕመምና በሽታን ለማከም ልዩ የነርቭ ማዕከሎችን በመርፌ መውጋት)ና አኩፕሬዥር (በተለየ የግፊት ምት የሚሰራ) ተብለው በሚጠሩት መደበኛ ያልሆኑ ሕክምናዎች በመጠቀም ፈውስ ማምጣት ይቻላል፡፡ የእነዚህን ዕውቀት መቅሰም የፈውስ ዘዴዎችን ለመረዳት ብቻ ሳይሆን በሰዎች አካል ውስጥ ሕይወትን የሚያንቀሳቅስ ውስጣዊ የኃይል ማስተላለፊያ ስርዓት መኖሩን ይበልጥ ለመገንዘብ ይረዳል፡፡

ሰብዓዊ የ‹ቻክራ› ስርዓት በሕንድ ጥንታዊ ቋንቋ በነበረው ሳንስክሪት መሠረት ‹ቻክራ›ን ‹እንደእንዝርት የሚሾር ጎማ› ሲል ይገልፀዋል፡፡ በሰዎች አካል ውስጥ ያለው የቻክራ ስርዓት ሰባት ዋና ዋና እና ብዙ አነስተኛ ቻክራዎች አሉት፡፡ የኃይል መገኛ ስፍራዎችን በቀጥታ መመልከት የሚችሉ ሰዎች ወይም የዘርፉ የሕክምና ባለሙያዎች ዋነኛውን ቻክራ እንደእንዝርት ከሚሾር ጎማ ጋር ያመሳስሉታል፡፡ ይሁንና ይኼንን ከውስጥ ሲመለከቱት በፍጥነት እየተሽከረከረ ነገሮችን ወደ ራሱ መሀል የሚስብ ዕምቅ ክብደት አዘል ኃይልን እንደሚመስል ከዊኪፒዲያ ድረ-ገፅ ያገኘነው መረጃ ይገልፃል፡፡ እንዲሁም በመሬት ላይ ሲያልፍ እንደእንዝርት በመሾር ከፍና ዝቅ እያለ ሕንፃዎችን እንደሚያወድመው አይነት ጠንካራና አደገኛ የንፋስ ቅርፅ (tornado) ጋር በተወሰነ ደረጃ ተመሳሳይነት አለው፡፡

በኤልያስ ገብሩ

የቻክራ መገኛዎችየሰብዓዊ ቻክራ ስርዓት ዋነኛ አላማና ተግባር በዙሪያችን ካለው ከአጠቃላይ ሕዋ ከፍተኛ ርዝመትና ጥልቀት ያለው ኃይልን በመውሰድ የኃይሉን ሞገድና ንዝረት በመቀየርና ዝቅ በማድረግ በሰውነት አካል ለመጠቀም ነው፡፡ ክራውን ቻክራ የላይኛው የአዕምሮ ክፍልና የቀኝ አይንን፣ ብሮው ቻክራ ጆሮ፣ አፍንጫ፣ አነስተኛው የአዕምሮ ክፍል፣ የነርቭ ስርዓትና የግራ አይንን፣ የጉሮሮ (ስሮት ቻክራ) ሳንባዎችን፣ በአፍንጫና በሳንባ መካከል ያለ ክፍት ቦታና ድምፅን ለመፍጠር የሚረዳ ሕብረሕዋስ የያዘ አካል (larynax)፣ በስርዓተ ልመት ጊዜ ምግብ ከአፍ ጀምሮ እስከ ሰገራ መውጫ ድረስ ለሚያካሂደው ሂደት የመተላለፊያ መንገድ የሆነው (alimentary canal) ይገኙበታል፡፡የልብ ቻክራ ደግሞ በልብ፣ በደም፣ ቬገስ ነርቭና የደም ዝውውር ስርዓትን ይይዛል፡፡ ሶላር ፕሌክሰስ ቻክራ ሆድ፣ የሽንት ፊኛ እና ጉበትን፣ ሳክራል ቻክራ ደግሞ በመራባት ስርዓት የወንድና የሴት የዘር ፍሬ እንዲሁም የመጨረሻው ሩት ቻክራ የሕብለሰረሰር አምድንና ኩላሊቶችን አካትተዋል፡፡ በተጨማሪም ብዙ አነስተኛ ቻክራዎች በሰውነት አካሎች ውስጥ ይገኛሉ፡፡ እነዚህ በብዛት ከጉልበት፣ ከትከሻና ከቁርጭምጭሚት መገጣጠሚያዎች ጋር የሚያያዙ ናቸው፡፡ እንዲሁም በእጆች መዳፍ እና በውስጥ እግሮች፣ በጣቶችና በተረከዞች መጨረሻ ላይ ይገኛሉ፡፡ አነስተኛ ቻክራዎች መርፌ አካልን ሲወጋ “ጠቅ” እንደሚያደርገው አይነት የስሜት ኃይልን ከሰውነት ውስጥ ማስወጣትና ማስገባት እንጂ እንደ ዋነኞቹ ቻክራዎች በዕምቅ ኃይል ተሞልተው እንደእንዝርት አይሾሩም፡፡ የእነዚህ አንደኛና ዋነኛ የፈውስ ተግባራቸው በመንካት መፈወስ ሲሆን በጥፍር ጫፎች ውስጥ በማለፍ የሚወጡት የኃይል ፍንጣቂዎች የሰውነትን ተፈጥሯዊ የመፈውስ ሂደት ከማነቃቃት ባለፈ ያፋጥናሉ፡፡

የኃይል አካላትየሰብዓዊ ኃይል መገኛ ስፍራ መገለጫ ሦስተኛው መንገድ አምስት ደረጃ ያለው የኃይል አካላት ስርዓት ነው፡፡ የሚነካውና የሚታየው ሰውነት እንደኃይል አካል ይቆጠራል፡፡ ምክንያት ማንኛውም ቁስ አካል በአንድነት የተሰራው ከኃይል በመሆኑ ነው፡፡ ሌላው ወሳኙ እውነት ደግሞ ከፍተኛ የሆኑ፣ ነገር ግን በግልፅ የማይታዩ የኃይል አካላት በመላው ሰውነት ላይ ተደራርበውና አንዳቸው በአንዳቸው ውስጥ ሰርገው የገቡ መሆናቸው ይገለፃል፡፡ በጣም በተመሳሳይ መልኩ ለዚህ ምሳሌ የሚሆነው በርካታ የተለያዩ የቴሌቭዥን ጣቢያ ስርጭቶችን መፈለጊያ አንቴናዎች በአንድ ቦታና ጊዜ ላይ ሆነው በዙሪያችን ቢገኙም እያንዳንዳቸው የራሳቸው በሆኑ የተለያዩ ሞገዶች መለያየታቸው ነው፡፡ የኃይል ስርዓትን የሚያጠና/ የምታጠና ወይም በዘርፉ ባለሙያ የሆኑ ሰዎች እጆቻቸውን በታካሚ ደንበኞቻቸው ላይ በሚያስቀምጡበት ጊዜ ፈዋሽ ኃይላት ወደ ሰውነት አካል ላይ ብቻ ሳይሆን ወደእያንዳንዱ ከፍተኛ ኃይልን ወደሚፈጥሩ አካሎች ይላካሉ፡፡ ፈውሱም አካላዊ ደረጃን በመሻገር ከሰውነት አካል ውጪ ባሉት አራት ክፍሎች ላይ ይከናወናል፡፡ እነዚህም ኢተሪክ (ከሰውነት ውጫዊ አካል አንድ ኢንች ያህል ወጣ ያለ)፣ ስሜታዊ፣ አዕምሯዊና መንፈሳዊ ኃይላት ተብለው ይገለፃሉ፡፡ [ተከታዩ ፅሁፍ በሚቀጥለው ሳምንት ይቀርባል]

ኃይል የሚያልፍበት መስመር ለቆዳ አካል በጣም ቅርብ ሲሆን ጠንካራና በጣም የተጠባበቀ ይሆናል፡፡ ሆኖም በሂደት ከአካላዊ የሰውነት ክፍል ውጪ እየረዘመ በመሄድበት ጊዜ መስመሩ ሰፍቶ የውጫዊው የኦራ ጠርዝ ድረስ ይዘልቃል፡፡ እያንዳንዱ ዋነኛ “ቻክራ” ከፆታዊ ብልቶች አከባቢ (Root) ጀምሮ እስከ ቅንድብ (Brow) ድረስ አራት ዕምቅ ክብደት አዘል ኃይሎችን ይዟል፡፡ አንደኛው ወደ ላይ፣ ሁለተኛው ወደ ታችኛው ወደመሬት፣ ሦስተኛውና አራተኛው በአካል የፊተኛውና የኋለኛው ክፍል በኩል ይገኛሉ፡፡ ወደላይ የሚሄደው የዕምቅ ክብደት አዘል ኃይል አንዱ ቻክራ ወደ ታች ከሚወርደው ቻክራ ጋር ይገናኙና የኃይል አምድ በመፍጠር በቀጥታ ወደ ላይኛው የአካላዊ የሰውነት ክፍል አቅጣጫን በመያዝ ከታችኛው የፆታዊ ብልቶች አከባቢ (ሩት ቻክራ) ተነስተው እስከ ላይኛው የራስ አናት (ክራውን ቻክራ) ድረስ ይሄዳሉ፡፡ ክራውን ቻክራም ሁለት የዕምቅ ክብደት ኃይል እሽክርክሮሾች አሉት፡፡ አንደኛው ወደ ላይ ወደመንግስተ ሰማያት የሚከፈት ሲሆን ሌላኛው ደግሞ በኃይል አምድ አማካኝነት በሰውነት ውስጥ ወደታች የሚወርድ ነው፡፡ ቻክራው ጤነኛና የተመጣጠነ ከሆነ የፊት ለፊቱና የኋለኛው ዕምቅ ኃይል ይዘት እንደእንዝርት የሚዞረው ክብ በሆነ እንቅስቃሴ አማካኝነት ነው፡፡ ሆኖም የተረበሸ ነገር ካለ ወይም የኃይል ፍሰቱ በቻክራው መካከል መዘጋት ሲያጋጥመው እሽክርክሪቱ ትንሽ ሞለል ያለ ይሆናል፡፡ በጣም ከባድ ያለ ችግር ካለ ደግሞ በጎኑ በኩል በኃይል የተዘበራረቀ ይሆናል፡፡ የመዛባቱ ችግር የሰብዓዊ ኃይል መገኛ ስፍራን በማየትና ስሜቱን መረዳት በሚችሉ ሰዎች ስሜት ሊታወቅ ይችላል፡፡ ቀጥተኛ ባልሆነ መንገድም በፔንዱለም አማካኝነት ስሜቱን ለማወቅ እንደሚቻል መረጃዎች ያስረዳሉ፡፡ እያንዳንዱ ቻክራ የራሱ የሆነ የተለየ የእሽክርክሪት መጠንና ሞገድ አለው፡፡ የዚህ መጠን በፆታዊ ብልቶች አካባቢ በሚገኘው ሩት ቻክራ ላይ ዝቅተኛ ሲሆን ከፍተኛ የእሽክርክሪቶች ደረጃ የሚገኘው በጭንቅላት አናት፣ ክራውን ቻክራ ላይ ነው፡፡

ሰብዓዊ ኃይል

ብዙ አነስተኛ ቻክራዎች በሰውነት አካሎች

ውስጥ ይገኛሉ፡፡ እነዚህ በብዛት ከጉልበት፣

ከትከሻና ከቁርጭምጭሚት መገጣጠሚያዎች

ጋር የሚያያዙ ናቸው፡፡ እንዲሁም በእጆች

መዳፍ እና በውስጥ እግሮች፣ በጣቶችና

በተረከዞች መጨረሻ ላይ ይገኛሉ፡፡ አነስተኛ

ቻክራዎች መርፌ አካልን ሲወጋ “ጠቅ”

እንደሚያደርገው አይነት የስሜት ኃይልን

ከሰውነት ውስጥ ማስወጣትና ማስገባት እንጂ

እንደ ዋነኞቹ ቻክራዎች በዕምቅ ኃይል

ተሞልተው እንደእንዝርት አይሾሩም፡፡

Page 21: Awramba Times Issue 161 Megabit 24

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 161 ቅዳሜ መጋቢት 24 2003

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

ተ ጠ የ ቅ 21

በሱራፍኤል ግርማ

በእቴጌ ጣይቱ ብጡል ሀሳብ አመንጪነት፣ በአፄ ምኒልክ “ይሁን ባይነት” ከ124 ዓመታት በፊት የተቆረቆረችው አዲስ አበባ፣ ከምስረታዋ ጊዜ አንስቶ የተከናወኑባትን ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ኹነቶች የሚያስታውሱ አያሌ የሚንቀሳቀሱና የማይንቀሳቀሱ ቅርሶችን በውስጧ ይዛ ትገኛለች፡፡ ሐውልቶችን፣ ዋሻዎችን፣ የሃይማኖት ተቋማትንና ዕድሜ ጠገብ ቤቶችን ጨምሮ 173 የማይንቀሳቀሱ ቅርሶች በከተማዋ ውስጥ እንዳሉ ከአዲስ አበባ ባሕልና ቱሪዝም ቢሮ የተገኙ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ ይሁንና በመዲናይቱ የሚገኙት ተንቀሳቃሽም ሆነ የማይንቀሳቀሱ ቅርሶች አስታዋሽ አጥተው ለአደጋ ተጋልጠዋል፤ በተለይም ዕድሜ ጠገብ ቤቶች፡፡ የዘመን አሻራን የያዙ በርካታ ታሪካዊ ቤቶች በሚያሳዝን መልኩ የሞት ፍርድ ተወስኖባቸው ከመኖር ወደ አለመኖር የተቀየሩ ሲሆን ሌሎችም ለመፍረስ ቅርብ ሆነው ከታሪክ ማህደር ላይ የሚፋቁበትን ቀን እየተጠባበቁ ናቸው፡፡ የአውራምባ ታይምስ የዝግጅት ክፍል በከተማዋ ውስጥ የሚገኙትና የቅርስነት ማዕረግ ከተሰጣቸው 99 ዕድሜ ጠገብ ቤቶች ውስጥ አብዛኞቹ በአደጋ ውስጥ መሆናቸውን በመገንዘብ የቤቶቹን ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክቶ ለሚመለከተው የመንግስት አካል ጥያቄ አቅርቦ ነበር፡፡ ለአዲስ አበባ ባሕልና ቱሪዝም ቢሮ ያቀረብነው የመጀመሪያ ጥያቄ “አንድ ቤት ‹ቅርስ ነው› የሚባለው መቼ ነው?” የሚል ነበር፡፡ በቢሮው የቅርስ ጥናትና ልማት ኦፊሰር የሆኑት አቶ ኤርሚያስ ንማኒ፣ አንድ ቤት በቅርስነት የሚመዘገበው ፡- 1). የቤቱ ኪነ-ሕንፃዊ ውበት ሚዛን ሲደፋ፣ 2). ከከተማዋ ምስረታና ዕድገት ጋር የቤቱ ታሪክ እጅጉን የተቆራኘ ከሆነ፣ 3). ቤቱን አስመስሎም ቢሆን አሁን ለመስራት የማይቻል ከሆነ፣ 4). የቤቱ ባለቤት ታሪክ፣ እና 5). ቤቱ የተሰራባቸው ግብዓቶች ከግምት ውስጥ ገብተው መሆኑን አስረድተዋል፡፡ ነገር ግን እዚህ ጋር ለአቶ ኤርሚያስ ቤቶች በጥንታዊ ቅርስነት ሲመዘገቡ ያስቆጠሩት ዕድሜ ቢያንስ ስንት መሆን እንዳለበት በጠየቅናቸው ጊዜ “አይ ቁርጥ ያለ የዕድሜ ወሰን የለም” ማለታቸው ቢሮው ያዘጋጀው መስፈርት ትልቅ ክፍተት እንዳለበት አመላካች ሆኗል፡፡ አብዛኞቹ ዕድሜ ጠገብ (በቅርስነት የተመዘገቡ) ቤቶች በአሁኑ ሰዓት የመኖሪያ ቤትነት አገልግሎት እየሰጡ በመሆናቸው የተነሳ የሚገኙበት አስከፊ ይዞታ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ ነው፡፡ በተለይ ነዋሪዎቹ የሚያከናውኑት መለስተኛም ሆነ ስር ነቀል “ዕድሳት” የቤቶቹን ታሪካዊ አሻራ ሲያደበዝዘው ይስተዋላል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በቅርሶቹ ውስጥ ከአንድ በላይ ቤተሰቦች መኖራቸው የሚደርስባቸው የጥፋት መጠን እንዲባባስ የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ከፍ ያለ ነው፡፡ ለአብነት ያክል፡- - በተለምዶ “ሸጎሌ” ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የሚገኘው የቤኒሻንጉል አስተዳዳሪ የነበሩት የሼህ ሆጀሌ ቤት 39 አባወራዎች ይኖሩበታል፤ - በአራዳ ክ/ከ ቀበሌ 10 የሚገኘው፣ ከአፄ ምኒልክ የመጀመሪያ ሚኒስትሮች መካከል አንዱ የነበሩት የአፈንጉስ ነሲቡ ወ/መስቀል ቤት አምስት አባወራዎች ይኖሩበታል፤ - ሽሮ ሜዳ መንገድ የሚገኘው፣ የመጀመሪያው የአዲስ አበባ ከንቲባ የሆኑት የቢት ወደድ ወ/ጻድቅ ጎሹን ቤት ደግሞ ሶስት አባወራዎች ተጋርተውታል፡፡ በቅርሶቹ ውስጥ ለሚኖሩት ቤተሰቦች ተለዋጭ ቤት እንዲሰጥ ተደርጎ አስፈላጊው እንክብካቤ ለምን እንደማይደረግ ላቀረብነው ጥያቄ አቶ ኤርሚያስ ንማኒ ምላሽ ሲሰጡ “ቤቶቹን ለማስለቀቅ ሲፈለግ ብዙ የሚመለከታቸው አካላት ጋር መነካካታችን አይቀርም፤ ከእነሱ ጋር ስምምነት ላይ መድረስ ካልቻልን ቤቶቹን

ማስለቀቅ እጅግ ይከብዳል” ነበር ያሉት፡፡ በመሥሪያ ቤታቸው ጥረት እስካሁን ሁለት ዕድሜ ጠገብ ቤቶችን ብቻ ከነዋሪዎች ማስለቀቅ መቻሉን በከተማዋ ባሕልና ቱሪዝም ቢሮ የቅርስ ጥናትና ልማት ኦፊሰር እንደሚገልፁት ከሆነ፣ ቢሮው በቅርስነት የተመዘገቡ ቤቶችንና ሌሎች ሀብቶችን በደንብ እንዳይንከባከብ እና እንዳያድስ የሚያግደው የቅርስ ጥበቃ ሥራ በአብዛኛው ለፌዴራል መንግስት ብቻ የተፈቀደ በመሆኑ ነው፡፡ እኛም የአዲስ አበባ ባሕልና ቱሪዝም ቢሮ ‹‹ችግር እየፈጠረብኝ ነው›› ሲል ወቀሳ ወደሰነዘረበት የባሕልና ቱሪዝም ሚኒስቴር አምርተን የነበረ ሲሆን፣ በሚኒስቴር መ/ቤቱ ያገኘናቸው የሥራ ኃላፊዎች ደግሞ ጉዳዩን ወደ ቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን መርተውታል፡፡ ሆኖም ከተጠቀሰው ባለስልጣን መ/ቤት ተፈላጊውን መረጃ ልናገኝ አልቻልንም፡፡ ቤቶቹ በተጎሳቆለ ሁኔታ ላይ ከመገኘታቸው ባሻገር የተወሰኑት የምዝገባ ስማቸው ከታሪካቸው ጋር ምንም ግንኙነት የሌለው መሆኑ ጥያቄ ያጭራል፡፡ በከተማዋ ውስጥ ላሉት ቅርሶች ተገቢውን ጥበቃና እንክብካቤ እየተከናወነላቸው እንዳልሆነ የሚያምኑት አቶ ኤርሚያስን፣ ከቅርሶቹ ምዝገባ ጋር በተያያዘ ‹‹አንዳንዶቹ ዕድሜ ጠገብ ቤቶች በቅርስነት ሲመዘገቡ የቀድሞ ታሪካቸውን በማያሳይ መልኩ ስማቸው ተቀይሮ ነው፡፡ በቀድሞ ስማቸው (በባለቤቶቻቸው ስም) ለምን አልተመዘገቡም?” ስንል ጠይቀናቸው የሰጡን መልስ ግን ለትዝብት የሚዳርግ ነበር - “በመረጃ ዕጥረት የተነሳ ነው”፡፡ይህንን ፅሁፍ እያዘጋጀን ሳለ የኢትዮጵያ ቅርስ ባለአደራ ማኅበር ለአውራምባ ታይምስና ለሌሎች መገናኛ ብዙሃን የላከው ጥቆማ በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ ታሪካዊ ቤቶች “በልማት ስም” እየፈረሱ መሆኑን ያሳያል፡፡በማኅበሩ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ጌታቸው ታዬ ተፈርሞ የተላከው ጥቆማ፣ “በመዲናችን በአዲስ አበባ የራስ ናደው፣ የሻቃ በልሁ፣ የደጅ አዝማች ብሩ ኃይለማርያም፣ የወ/ሮ ስንዱ ገብሩና

ነገር ግን የአዲስ አበባ ባሕልና ቱሪዝም ቢሮ የተቋቋመው በ2000 ዓ.ም መሆኑን የሚገልፁት በቢሮው የቅርስ ጥናትና ልማት ኦፊሰር አቶ ኤርሚያሰ ንማኒ፣ ከቢሮው መቋቋም ወዲህ በቅርስነት የተመዘገበ ዕድሜ ጠገብ ቤት አለመፍረሱን ይናገራሉ፡፡ ቢሮው እንደ ቅርስ ቆጥሮ የሚከታተላቸው ቤቶች በከተማዋ ማስተርፕላን ላይ በቅርስነት የተመለከቱትን ብቻ መሆኑን የሚያስገነዝቡት ባለሙያው የኢትዮጵያ ቅርስ ባለአደራ ማሕበርን ጥቆማ ውድቅ አድርገዋል፡፡ በማኅበሩ ጥቆማ “ፈርሰዋል” ከተባሉት ውስጥ፤ የራስ ናደው እና የደጅ አዝማች ብሩ ኃ/ማርያም ቤቶች አለመፍረሳቸውን እና መክሲያዙናል መድኃኔዓለም ቤተ-ክርስቲያን ግቢ ውስጥ ይገኝ የነበረው የሻቃ በልሁ ቤት የፈረሰው ቢሮው ከመቋቋሙ በፊት መሆኑን ከተናገሩ በኋላ በፀሐፊ ትዕዛዝ ገ/ሥላሴ ረዲ ስም የተመዘገበ ቤት አለመኖሩን የገለጹ ሲሆን፣ የወ/ሮ ስንዱ ገብሩ እና የዲሚትሪ ጴጥሮስ ቤቶች ደግሞ በቅርስነት ያልተመዘገቡ መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡ ከባሕልና ቱሪዝም ቢሮ ባገኘነው መልስ

ላይ አስተያየት እንዲሰጡን፣ እንዲሁም “አንድን ቤት ‹ቅርስ› ለማለት መስፈርታችሁ ምንድን ነው? እንደፈረሱ የገለፃችኋቸውን ቤቶች በእርግጥ መፍረሳቸውን አይታችኋል ወይ? ለሚመለከተው የመንግስት አካል አመልክታችኋል ወይ?” ለሚሉት ጥያቄዎቻችን የኢትዮጵያ ቅርስ ባለአደራ ማኅበር ዋና ሥራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ጌታቸው ታዬ እና ሌሎች የሥራ ኃላፊዎች ምላሽ እንዲሰጡባቸው ያደረግነው ተደጋጋሚ ሙከራ ሳይሳካ ቀርቷል፡፡ ወደኋላ መለስ ብለን “በከተማዋ ማስተር ፕላን ላይ በቅርስነት ያልተመዘገቡ ግን የቅርስነት መስፈርቱን የሚያሟሉ ቤቶች እንክብካቤ የሚያገኙበት ሁኔታ የለም?” ስንል አቶ ኤርሚያስን ጠይቀናቸዋል፡፡ የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን እየተከለሰ በመሆኑ በአዲሱ ማስተር ፕላን ላይ በጣሊያን ወረራ ጊዜ የተገነቡ ቤቶችን ጨምሮ ሌሎች ዕድሜ ጠገብ ቤቶች በቅርስነት እንዲመዘገቡ ቢሮው ጥያቄ ማቅረቡን አስታውቀዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በአሁኑ ሰዓት የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የአራዳ ምድብ ችሎት እየተገለገለበት የሚገኘውን፣ በአፄ ምኒልክ ዘመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የነበሩት የቢትወደድ ኃይለ ጊዮርጊስ ወ/ሚካኤል ቤትን ለማስለቀቅ እንቅስቃሴ መጀመሩን ከአዲስ አበባ ባሕልና ቱሪዝም ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡ የቢሮው ም/ኃላፊና የቱሪዝም ልማትና የቅርስ አስተዳደር ዋና የሥራ ሂደት መሪ በሆኑት አቶ መሳይ ደምሴ ተፈርሞ በ23 ጥር 2003 ዓ.ም ለፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት የተላከው ደብዳቤ ‹‹በ1897 ዓ.ም የተገነባው መኖሪያ ቤትና የመጀመሪያው የከተማዋ ማዘጋጃ ቤት በመሆን ያገለገለው ሕንፃ በአሁኑ ሰዓት እጅግ በጣም የተጎዳና አደጋ ላይ የሚገኝ ታሪካዊ ሕንፃ ነው ... ስለሆነም የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤቱ የጉዳዩን አሳሳቢነት በመገንዘብ ግቢውንና ሕንፃውን ለዕድሳት ዝግጁ ለማድረግ እንድንችል የአራዳ ምድብ ችሎት እየተገለገለባቸው የሚገኙትን የሕንፃውን ክፍሎች እንዲያስረክበን በአክብሮት እንጠይቃለን›› ይላል፡፡ ይሁንና እስካሁን ድረስ ርክክቡ አልተፈፀመም፡፡ ዞሮ ዞሮ ቅርሶች የሀገራትን ታሪክ ይነግራሉ፡፡ የዜጎችን ማንነት ያሳያሉ፡፡ የሰው ልጅ ቀደምት ድርጊቶችና እንቅስቃሴዎችም ምን ይመስሉ እንደነበር ያመለክታሉ፡፡ ስለዚህ እነሱን የመጠበቅና የመንከባከብ ሥራ ዛሬውኑ ሊከወን የሚገባ እንጂ ለነገ ቀጠሮ የሚያዝለት ሊሆን አይገባም፡፡

የመዲናችን ታሪካዊ ቤቶች

ቅርሶች ወይስ መኖሪያዎች?

39 አባወራዎች

የሚኖሩበት

የሼህ ሆጀሌ ቤት

የሌሎችም መኖሪያ ቤቶች ፈርሰዋል... የኢትዮጵያ ቅርስ ባለአደራ ማኅበር ባምቢስ ድልድይ አካባቢ (በቂርቆስ ክ/ከተማ በወረዳ 01 በቤት ቁጥር 035 ተመዝግቦ የሚገኘውን) የ135 ዓመት ዕድሜ ያለውን የፀሐፊ ትዕዛዝ ገ/ሥላሴ ረዲ መኖሪያ ቤት በአደራ ለመረከብ በወረዳው ከሚገኙ የባሕልና ቱሪዝም ባለሙያዎች ጋር ተነጋግሮ፣ ቤቱን ጎብኝቶ ለመረከብ የሚያስችል ደብዳቤ የካቲት 7/2003 ዓ.ም ለወረዳ 01 አስተዳደር ጽፎ ለመረከብ በመጠባበቅ ላይ ነበር፡፡ ነገር ግን የካቲት 26/2003 ዓ.ም ቤቱ እንዲፈርስ መደረጉን ከወረዳው መረጃ ደረሶናል” ይላል፡፡ በመቀጠልም፣ እስከ ቅርብ ቀናት ድረስ የላየን ኢትዮጵያ የቱሪዝምና ሆቴል ማሰልጠኛ የነበረው (አራት ኪሎ 2ኛ ፖሊስ ጣብያ ጎን) በአርመናዊው ዲሚትሪ ጴጥሮስ የተሰራው ቤት እንዲፈርስ መደረጉን በማስታወስ፣ “ዘመናዊ ቤቶችን በመገንባት ሀገር ለማሳደግ እየሰራ ያለው መንግስታዊ አካል አዲስ ለመገንባት ከሚጨነቀው በላይ ጥንታዊዎቹ እንዳይፈርሱ ለማድረግ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ በእጅጉ ይጠበቅበታል” ይላል ጥቆማው፡፡

ቢሮው እንደ ቅርስ ቆጥሮ የሚከታተላቸው

ቤቶች በከተማዋ ማስተርፕላን ላይ በቅርስነት

የተመለከቱትን ብቻ መሆኑን የሚያስገነዝቡት

ባለሙያው የኢትዮጵያ ቅርስ ባለአደራ

ማሕበርን ጥቆማ ውድቅ አድርገዋል፡፡

Page 22: Awramba Times Issue 161 Megabit 24

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 161 ቅዳሜ መጋቢት 24 2003ስ ፖ ር ት22

የኢትጵያ ወጣት ብሔራዊ ቡድን በ1989 ዓ.ም. ወደ ካይሮ አቅንቶ ከግብፅ አቻውጋ ባደረገው ጨዋታ 5-0 ተሸነፈ፡፡ በመስመር እና በመሀል ሜዳ እንቅስቃሴው አዕምሮ ሊረሳው የማይችለው ፋሲል ተካልኝ የቡድኑ አምበል ነበር፡፡ ስለ ጨዋታው ሲያስታውስ ‹‹ምንም እንኳን እነሱ ከእኛ የተሻሉ ቢሆኑም በጨዋታ ላይ ተፅዕኖ ነበረብን፡፡ ሁለት ተጨቸቾቻችን በቀይ ወጥተው ሁለት የፍፁም ቅጣት ምት ተሰጥቶብን ነበር›› ይላል፡፡

በንጉሴ ገብሬ ይሰለጥን የነበረው የዚህ ቡድን አካላት ወደ አገራቸው ተመልሰው ዝግጅት ሲያደርጉ አምስት እና ከዚህ በላይ አግብተን እናሸንፋለን የሚል ስሜት ውስጣቸው አልነበረም፡፡ የጨዋታው ጊዜ ደረሰ፡፡ ቡድኖቹ አዲስ አበባ ስታዲየም ተገናኙ፡፡ ዘነበ ፍሰሀ ሁለት፣ ፈለቀ ሞሼ፣ ዘላለም አልጣህና የግብፁ ተጨዋች በራሱ ጎል ባገቡት ጎል ያልተጠበቀ የ5-0 ድል ኢትዮጵያ አስመዘገበች፡፡ ተፅዕኖ ስላልነበረባቸው በነፃነት በመጫወታቸው አምስት አግብተው ማሸነፋቸውን ፋሲል ያስታውሳል፡፡

በደርሶ መልስ በአቻ ውጤት ጨዋታው ተጠናቋልና ወደ መለያ ምት አመሩ፡፡ ግብጾች የመጀመሪያውዎቹን ሁለት ምቶች ቢያመክኑም ኢትዮጵያ ‹‹አላለላትም››፤ 3-1 በመለያ ምት ተሸንፋ ጉዞዋ ከመገታቱ በላይ አምስት ማግባቷ አነጋጋሪ ነበር፡፡

በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ካፕ ውድድር ከፖለቲካ ቀውስ ገና ያላገገመችው የግብፅ ክለብ የሆነው ሃራስ ኤል-ሁደድ (በድሮ ስሙ ሳዋህል) መቀመጫውን ባደረገበት አሌክሳንደሪያ ደደቢትን ገጥሞ አራት ጎል አስመዝቦ ወደ ሸገር መሸኘቱ እድሉ ተጣበበ እንጂ ተሟጠጠ ብሎ መደምደም እንደማይቻል የ1989 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ወጣት ቡድን ውጤት ጠቃሚ ሊሆን እንደሚችል የሚያምኑ አሉ፡፡

ሀራስ ኤል-ሁደድ ውጤታማ ፕሮፌሽናል አጨዋወት ያላቸው መሆኑን የሚገልፀው አሰልጣኝ ገ/መድኅን ኃይሌ የቡድን እንጂ የግል ጨዋታ ላይ ትኩረት እንደማይሰጡ ገልጾ በግል ሲመጡ ግን አቅሙ ስላላቸው ብልጫ ይወስዱባቸው እንደነበር አልደበቀም፡፡ የደደቢት የኳስ ቅብብል ላይ መሰረት አድርጎ የነበረው አጨዋወት 22 ሺህ ህዝብ በሚይዘው የሃራስ ኤል ሁደድ ስታዲየም ላይ መድገም እንዳይችሉ በጉልበት ተጭነው በመጫወት

በአቤል ዓለማየሁ

ሜዳውን ለደቂቃዎች ለውጠውታል፡፡ የክሪኬት እንጂ የእግር ኳስ ተጨዋቾች ልምምድ አይመስልም፡፡ ይህ ለፍጥነትና ፈጥኖ ለማሰብ የሚረዳው ለየት ያለ ልምምድ በቦታው ያገኘኋቸው አሰልጣኞችና ተጨዋቾች በህይወት ዘመናቸው አጋጥሟቸው የሚያውቅ አይደለም፡፡ የክሪኬት ተጨዋቾች የሜዳ ላይ እንቅስቃሴን በጭንቅላታችሁ ክተቱ፡፡ የኢትዮጵያ ብ/ቡድን አሰልጣኝ ኢፊ ኦኑራ ልምምዱን ቀጥለዋል፡፡ አምስት አምስት ለሁለት ቡድን ከፍለው የመረብ ኳስ አይነት ጨዋታን በእግር ብቻ ሁሉም ተጨዋች ተቀባብሎ ወደ ተቃራኒ ክልል ማሳለፍን ተጨዋቾች እየተዝናኑ ይከውኑታል፡፡ አንዱ ተጨዋችም ኦኑራ ናቸው፡፡ ይህ ሁሉ ሲሆን አሰልጣኙ ይስቃሉ፣ ተጨዋቾቻቸውን ያበረታታሉ፣ እየጮኹ ያስቆጠሩትንና የተቆጠረባቸውን ነጥብ ያደንቃሉ፡፡ አሰልጣኙ የሀበሻ ቀጠሮ ብለው ችላ ማለት ካልጀመሩ በስተቀር ከጋዜጠኞች ጋር ያላቸው የ9፡30 ቀጠሮ አስር ደቂቃ አልፎታል፡፡ ልምምዱ ሲጠናቀቅ ከሚሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ 15 ደቃቃ መዘግየታቸው ቢነገራቸውም ተረጋግተው ቀሪ ስራቸውን ቀጠሉ፡፡ ጫላ ድሪባና ዘነበ ከበደን ከረዳታቸው ጋር ሆነው በመቀነሳቸው እንዳያዝኑ አረጋግተው ወደ ጋዜጣዊ መግለጫው መስጫው አዳራሽ ገቡ፡፡ ከዚህ በኋላ አሰልጣኙ በሙሉ የራስ መተማመን ናይጄሪያን እንደማይፈሩ፣ ስላላቸው ፕሮፌሽናል ተጨዋቾች እንደማይጨነቁ፣ የእግር ኳስ ደረጃዋ ከኢትዮጵያ ርቋል ብለው ሀሳብ እንደማይገባቸው ገለፁ፡፡ ይህ የሆነው መጋቢት 13 ቀን ሲሆን በማግስቱ አቡጃ የተጓዘው ቡድን አራት ጎል አስተናግዶ መረብ መድፈር አቅቶት ተመለሰ፡፡

ቡድኑ ለምን ተሸነፈ? መሰረታዊ ችግሩ ምንድን ነው? እንዴት መታረም አለበት ለሚሉ ጥያቄዎች በላይ ግን ለexpress.co.uk ድረ ገፅ ላይ የሰጡት ቃለ-ምልልስ መነጋገሪያ መሆኑ በግሌ አስገርሞኛል፡፡

ደግሞ ለከብት!አርቲስቲክ በሆነ መልኩ ዘገባዎችን ማቅረብ የሚቀናው የድረ ገፁ ባልደረባ ቶኒ ባንክስ አሰልጣኙ ነግረውኝ ፃፍኩት ያለው ዘገባ ‹‹እንዴት?›› ባዮች መብዛታቸው ሳቅ ጫሪ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ብ/ቡድንን በማለዳ ከከተማ ይዘው ሲወጡ የወጡበት ሜዳ ላይ ከብቶች ለጋጣ ተሰማርተው እንደነበር ገልፀው ልምምድ የቀጠሉት ከብቶቹን ካሶጡ በኋላ እንደነበር አስረዱ፡፡ በተለይ በአንዳንድ የህትመትና የኤክትሮኒክስ ሚዲያዎች ትርጓሜውን ጠመም ለማድረግ በመሞከር ‹‹ልምምድ የምሰራው ከብቶች ጋር እየተጋፋሁ ነው...›› መሰል ቃላት በመደርደር አሰልጣኙ የኢትዮጵያን መልካም ገፅታ ለማበላሸት መትጋታቸውን በመግለፅ ወቅሰዋቸዋል፡፡ ከአያት ሆስፒታል ፊት ለፊት የሚገኘው በተለምዶ ‹‹ቫርኔሮ›› ተብሎ የሚጠራው ሜዳ አንጋፋው ቅ/ጊዮርጊስን ጨምሮ የተለያዩ ቡድኖች ልምምድ ይሰሩበት ነበር፡፡ በዙሪያው ደግሞ በርካታ ከብቶት ለግጦሽ ይንቀሳቀሳሉ፡፡ በሜዳው ላይ የከብቶች እዳሪ ማየት ብርቅ አይደለም፡፡ ሜዳውን አቋርጬ ካልሄድኩ ብለውም የሚያስቸግሩ ከብቶች አሉ፡፡ ሱሉልታ፣ ለቡ እና በሌሎች ብዙም ምቹ ባልሆኑ ሜዳዎች ላይ ይኼው ክስተት እንግዳ አይደለም፡፡ ኦኑራ ይህ ክስተት ገጥሟቸዋል ብሎ ሙሉ በሙሉ ርግጠኛ መሆን ባይቻልም በአዲስ አበባና በዙሪያዋ እንዲሁም በክልል ከተሞች በግልፅ ከሚታየው የሜዳ ችግርና ከብቶችን እያባረሩ ልምምድ የመቀጠል

የዕለት ተዕለት ተግባር አንፃር ‹‹በልምምድ ሜደ ላይ ከብቶች ተመለከትኩ›› ቢሉ ስህተቱ ምንድን ነው? ለምን እውነት አወሩ ወይም ያዩትን እንዳላዩ አድርገው መናገር አለባቸው የሚባለው የትኛው የእግር ኳስ ‹‹መልካም ገፅታ›› እንዳይበላሽ ነው፡፡ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ውስጥ ከዚህ የባሰ የተወሳሰቡ ችግሮች የሉምን? አፍ ሞልቶ ሊወራለት የሚችል እግር ኳስ ሳይኖረን ተንጠራርቶ ስለ ‹‹መልካም ገፅታ›› ከመደስኮር ይልቅ ዋና ተግባራት ላይ ማተኮር መልካም ነው፤ አሰልጣኙን ማን አይቶ መረጣቸው፣ መስፈርቱ ምንድን ነበር? ስለ አሰልጣኙ መምጣት የተነጋገረው ትክክለኛ የሚመለከተው ባለሙያ ነውን፣ የቅጥር ሁኔታቸው ስር መሰረቱ ምንድን ነው? ብሎ ጠይቆ መወያየትና እውነታውን ማስጨበጥ መልካም ነው፡፡ መጀመሪያም የኢትዮጵያን እግር ኳስ ደረጃና አወቃቀር የወረደ መሆኑን ያልተረዳ አሰልጣኝ ለቦታው መመደብ የስህተቶች ሁሉ መጀመሪያ ነው፡፡

የመርዳት እና መግዛት ልዩነትዘንድሮ በታንዛኒያ በተካሄደው የምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ ሻምፒዮና ላይ የኢትዮጵያ ብ/ቡድን ሲያመራ በመዘግየቱ በሌላ አይሮፕላን ለመጓዝ የ22 ሺህ ብር ቅጣት ከሚጓዝበት አየር መንገድ ተጣለበት፡፡ በኋላ ላይ አየር መንገዱ ‹‹ የኢትዮጵያ ብ/ቡድንንማ አንቀጣም›› በማለቱ 22 ሺህ ብሩ ነፃ ይወጣል፡፡ እንደ ምንጮቻችን ገለፃ አንዴ ወጥቷልና ወደ ካዝናው ከሚመለስ ለተጨዋቾች ተጨማሪ የመጫወቻ ጫማ እንዲገዛላቸው ይወሰናል፡፡ ብሩ ለሁሉም ለማዳረስ በቂ ስላልነበር ኦኑራ ከኪሳቸው በሺህዎች የሚገመት ብር ወጪ አድርገው ጫማው ይገዛል፡፡ አኑራ ግን እሳቸው ለቡድኑ

ጫማ ገዝተው ከውርደት እንደታደጉት ገልፀዋል፡፡ እዚህጋ በመርዳትና ሙሉ ለሙሉ በመግዛት መሀከል ሰፊ ልዩነት ይታያል፡፡ የዘር ሀረጋቸው ከናይጄሪያ የሚመዘዘው አሰልጣኝ ‹‹አጋነዋል›› ሊባል ይችላል እንጂ ነጭ ውሸት ዋሽተዋል ማለት አይቻልም፡፡ ይህ ከሆነ ሊገሰፁ ይገባል ነገር ግን ፌዴሬሽን የኦኑራ ዕዳ እንዳለበትም ያሳያልና ሊታረም እንደሚባው መልካም አጋጣሚ መውሰድ ይገባል፡፡ ‹‹መጥፎ›› ብለን በምናስባቸው ነገሮች ውስጥ ያለውን ጭላንጭል በጥሩ ተርጉሞ ለእርምት መውሰድ ይገባል እንጂ ‹‹ተነካሁ!›› ብሎ ቡራ ከረዩ የሚያስብል እግር ኳስ ገና መቼ ኖረንና!

መሰረታዊውን ማጥበቅ

የኢፊ ኦኑራ የስልጠና ዘይቤ ወይ ያላቸው ስብዕና ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ‹‹አዳኝ ›› ብሎ ማመን ስህተት አይሆንም፡፡ በግል ህይወተቸው ‹‹ዘው›› እያሉ መዘላበድ ግን አግባብነት የጎደለው ነው፡፡ አሰልጣኙ ፊልም ቤት ይታያሉ፣ ይዞራሉ፣ ሳቅ ጨዋታ ያበዛሉ እያሉ ጉንጭ አልፋ ወሬ መደስኮር ማውራት የሚያገባን እስከምን ድረስ አለመሆኑን ካለማወቅ የሚመጣ ነው፡፡ ጋዜጠኛ ሁሉ ከሚፅፈው ወይ ከሚያወራው ጀርባ ዓላማ የለውም ወይም ማንም የለም ብሎ እርግጠኛ መሆን አይቻልም፡፡ ኦኑራ ከኃላፊነታቸው ተነስተው እነሱ ያሰቡትና የፈለጉት ሰው አሊያም አጨዋወት እንዲተገብር የሚፈልጉ የሉም ማለት አይቻልም፡፡ እንደ ጋዜጠኛ ግን ሀሳብን በነፃነት ማንሸራሸርን ተገን አድርጎ ለዓላማ ከመትጋት መቆጠብ ያስፈልጋል ብዬ አስባለሁ፡፡

የእግር ኳሱ ‹‹መልካም ገፅታ›› የቱ ነው?

በ2012 በለንደን በሚካሄደው ኦሎምፒክ ለማሳተፍ ሁለተኛ የማጣሪያ ጨዋታውን የሚያደርገው የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ከጋና አቻው ጋር ነገ በአስር ሰዓት በአዲስ አበባ ስታዲየም ጨዋታውን ያደርጋል፡፡ አሰልጣኙ ሙሉ ዝግጅት አድርገው ያለፉ ስህተቶቻቸውን በተለይም የጎል ማግባት ችግርን አርመው ወደ ሜዳ እንደሚገቡ በትላንትናው ዕለት በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የመሰብሰቢያ አዳራሽ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ገልፀዋል፡፡

በአሰልጣኝ አብርሃም ተ/ሃይማኖት ዋና አሰልጣኝነት የሚመራው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በብሔራዊ ሆቴል ተቀምጦ ልምምዱን ማድረግ ከጀመረ ዛሬ 48ኛ ቀኑን የደፈነ ሲሆን በጉዳት ከቡድኑ ተለይታ የነበረችው ድንቋ የግራ እግር ተጨዋች ብርቱካን ገ/ክርስቶስ እና በትርፍ አንጀት ህመም የቀዶ ጥገና ህክምና ያደረገችው የቡድኑ አምበል ዘይቱና ያሲን አገግመው ልምምድ ላይ የሰነበቱ ሲሆን በነገው ጨዋታ ላይ

የመጀመሪያ ተሰላፊ ይሆናሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ለአውራምባ ታይምስ አስተያየቷን የገለፀችው የሉሲ አምበል ዘይቱና ያሲን ‹‹ጋና ጠንካራ ቡድን ነው፡፡ እኛም ጠንካራ ነን፡፡ ይፈሯቸዋል ብላችሁ እንዳታስቡ አሸንፈናቸው ለማለፍ ተዘጋጅተናል›› ብላለች፡፡ በቡድኑ ውስጥ ያለውን የመተሳሰብና የመከባበር መንፈስ ጠንካራ መሆን ሜዳ ላይ ለሚተገበሩት እግር ኳስ ትልቅ ጠቀሜታ እንዳለውም ተናግራለች፡፡

እ.ኤ.አ. በ1999፣ 2003 እና 2007 በዓለም ዋንጫ ላይ ተካፍለው ከአንደኛው ምድብ መሻገር ያልቻሉት ጥቁሮቹ ንግስቶች (ጋናዎች) በአፍሪካ ትልቅ ከሚባሉት ቡድኖች ተርታ የሚመደቡ ሲሆን ፊፋ በሚያወጣው ወርሃዊ የእግር ኳስ ደረጃ መሰረት ወቅታዊ ደረጃቸው 49ኛ ይገኛል፤ ኢትዮጵያ ደግሞ 110ኛ፡፡ የተመዘገቡ አገራት ቁጥር 126 ነው፡፡ አውራምባ ታይምስ መልካም ውጤት ለብሔራዊ ቡድናችን ትመኛለች፡፡

አውከዋቸዋል፤ እንደ አሰልጣኙ ገለፃ፡፡ከመስመር የሚነሱ ኳሶችን

ወደ ጎል ሜዳ ማሻገር ግብጾች የሚተገብሩት አጨዋወት ነው፡፡ አሰልጣኝ ገብረ መድህንም ይህንን አስቀድሞ በማወቁ ኳሶች የሚሻገሩበት ምንጭ መዝጋት አላማው አድርጎ ቢገባም (እንደ ዳሬ ሳለሙ) ‹‹አልተሳካልንም›› ይላል፡፡ ክፍተቶቹንም ለመድፈን እሱ ባሰበው ደረጃም ባይሆን እየሰሩ መሆናቸውን ይገልፃል፡፡ በተለይ ወጥቶ ተሻምቶ ኳሶችን የማምከን የኢትዮጵያ በረኞች ችግር በደደቢቱ ጀማል ጣሰው ላይም ታይቷል፡፡ ‹‹ትልቁ ችግራችንም ይህ ነበር›› ይላል ገብረ መድህን ሀሳቡን ሲያጠናክር፡፡

በግብፅ በተፈጠረው ያለመረጋጋት የተነሳ ለሁለት ወር ያህል ኤል-ሁደድ ከጨዋታ (ውድድር መራቁ) እንደ ጥሩ አጋጣሚ ሊሆን እንደሚችል

ደደቢቶች ቢያስቡም አልተሳካላቸውም፡፡ ገብረ መድህን ‹‹ቁጭ ብለው ያለ ልምምድ ይጠብቁናል ማለት አይደለም፡፡ ከውድድር መራቃቸው በራሱ የሚያሳጣቸው ነገር በመኖሩ ተስፋ አድርገን ነበር›› በማለት ከእነሱ ቀውስ አለማትረፉን ጠቁሟል፡፡ ‹‹ጨዋታው አልቋል ብለን ተስፋ አንቆርጥም፡፡ በእግር ኳስ አይቻልም የምትለው ነገር የለም፡፡ አራት እንዳገቡብን አራት ማግባት ሊያጋጥም የሚችል ነገር ነው፡፡ ሜዳ ውስጥ ብዙ ነገር ይፈጠራሉና›› ሲል ተስፋቸው እንዳልተሟጠጠ ገልጿል፡፡ ‹‹ግብጾች አየሩ ስለሚከብዳቸው በሦስት አጥቂ በመጠቀም በጣም በማስሮጥ ደክሟቸው እንዲቆሙ ለማድረግ አንዱ የገብረ መድህን ዘዴ ነው፡፡ የሚፈልገውን ያህል ተጨዋቾች እንዳልሰሩለት የጠቆመው አሰልጣኙ ቢሆንም ግን በማጥቃት ላይ ተጫውተው በክለቡ አዲስ ታሪክ መፃፍ መቻላቸው እድሉ እንዳላበቃ

ይስማማል፡፡ እ.ኤ.አ በ1950 የተመሰረተውና

ሁለት የኢጂፕት ካፕ፣ አንድ የሱፐር ካፕ ዋንጫ ያነሳው ሀራስ ኤል-ሁደድ 16 ቡድኖች በሚወዳደሩበት በዘንድሮው የኢጅፕት ፕሪምየር ሊግ በ15 ጨዋታ 17 ነጥብ በመሰብሰብ 11ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡ በአገሪቱ ቀውስ ከመፈጠሩ በፊት ባደረጋቸው ሁለት የሊግ ጨዋታዎች በኢኤንፒፒአይ እና በእስማኤሊ 3-2 በሆነ ተመሳሳይ ውጤት ተሸንፏል፡፡

ሁለቱ ቡድኖች ዛሬ በሚያደርጉት ጨዋታ ከቀኑ 11 ሰዓት ላይ በአዲስ አበባ ስታዲየም ይደረጋል፡፡

ሀራስ ኤል-ሁደድ ባንክን ባለፈው ዓመት በሁለተኛ የማጣሪያ ጨዋታ ከኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ያስወጣ ቡድን ነው፡፡ አውራምባ ታይምስ መልካም ውጤት ለደደቢት ትመኛለች፡፡

ያልተሟጠጠ እድል ያለው ደደቢት ሀራስ ኤል-ሁደድን ለዛሬ ቀጥሯልታሪክ ይደገም ይሆን?

ታላቅ ዓለም አቀፍ ጨዋታ በአዲስ አበባ ስታዲየምሉሲ VS ጥቁሮቹ ንግስቶች

“ተስፋ አንቆርጥም”- ገብረ መድህን ኃይሌ

“ስህተቶቻችንን አርመናል”- አብርሃም ተ/ሃይማኖት

በአቤል ዓለማየሁ

Page 23: Awramba Times Issue 161 Megabit 24

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 161 ቅዳሜ መጋቢት 24 2003

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

23

ካወጃችሁበት ሕዝብ ጩኸት ልታመልጡ አይቻላችሁም፡፡ ለሕዝብ ትልቅ አክብሮት አለኝ የሚል መንግስት የሚያሳያቸው አዎንታዊ ምልክቶች አሉ፡፡ ለሕዝብ ክብር እንደሌለው ከሚያሳይባቸው መንገዶች ውስጥ አንዱና ዋነኛው የንባብ ባህልን ከሕዝብ አፍ መንጠቅ ይገኝበታል፡፡

የአንዲት ሀገር ዕድገት የሚለካው ሰሊጥ በጆንያ ስለጠቀጠቀች ብቻ አይደለም፡፡ ከዚያ ይልቅ የጨለማ ህይወት ድል መንሻ የሆነውን የንባብ ባህል በእያንዳንዱ ጓዳ ስታዳርስ ነው ለሚያስተዳድራት መንግስት ምስጋና የሚሰጠው፡፡ አንድ ፓርቲ መንግስት ሆኖ ሲቀመጥ ‹‹የፈለገውን›› ነገር ሁሉ የማድረግ መብት እንዳለው የሚያስብ ከሆነ ትልቅ ስህተት እየሰራ መሆኑን ሊያውቀው ይገባል፡፡

አንዲት አገር በመንግስት ብቻ ሳይሆን በሕዝብ ፍላጎት ጭምር ልትተዳደርና ልትመራ ይገባል፡፡ በዚያ ላይ መንግስት የሚወስዳቸው እርምጃዎች ሁልጊዜ ‹‹ፍፁም›› ናቸው ተብሎ አይታመንም፡

፡ መንግስት ማለት እንደተቀረው ሕዝብ ሰው ነው፡፡ ስለዚህ ሊያጠፋ ይችላል፡፡ ጥፋቱን እንዲያስተካክል ሲጠየቅ ደግሞ ቢቻል ይቅርታ ጠይቆ አሊያም መሳሳቱን አምኖ ይፋዊ እርምት ሊወስድ ይገባል?

ማን ይሙት፣ ጋዜጣ ቢዘጋ ደስ የሚለው ሰው አለ? ጋዜጣን እንደ ጦር ከሚፈሩና መንግስታዊ ሰው ከሆኑ ሰዎች ውጪ ማለቴ ነው፡፡ ማንም ደስ አይለውም፡፡ ስንት ጎጂ ባህል በሞላበት ሀገር ውስጥ የንባብ ባህልን ለመደምሰስ ታጥቆ መነሳት ‹‹ጀግና›› አያስብልም፡፡ ምንም ዓይነት የክብር ስም አያሰጥም፡፡ ለማያውቁ ሰዎች ፋሺስትን ለማጥፋት የምትሯሯጡ ይመስለዋል እንጂ ታሪክም ሆነ ትውልድ የማይረሳውንና ይቅረታ የማያሰጠውን በደል ለመፈፀም የምትሯሯጡ አይመስልም፡፡

በሌላው ዕለታዊ ውጣ ውረድ ቁም ስቅሉን የሚያየውን ህብረተሰብ መካስ ሲገባችሁ ሌላ ጨለማ መደንቀራችሁ ለሕዝቡ ያላችሁን የወረደ አመለካከት ያመላክታል፡፡

አንድ መንግስት የራሱን ስሜት ተከትሎ መሄድ

}SdeK¨< Ÿ}c\ ð×” ¾h¨` ¨<H TVmÁ U`„‹ ÃÖ”kl ƒ¡¡K—¨<” ¾w^²=M

¾h¨` ¨<H TVmÁ ÃÖkS<

Brazmart International General Trading Plc. Address!- •Urail Alem Brehan Plaza 1st Floor #106 1. ›<^›?M u?} ¡`e+Á” ›”vu= ¯KU w`H” ýL³ 1— öp u=a lØ` 1062. Ku< ›Åvvà òƒ Kòƒ dS<›?M I”íuT”—¨<U ¾vD”vD“ ¾h¨` u?ƒ n ‹ SgÝ“ ”Ç=G<U u¾I”í SX]Á SÅwa‹ ÁÑ–< M::

c=Ѳ< ƒ¡¡K— ¾w^²=M U`ƒ SJ’<” Á[ÒÓÖ<! Tel. 251-11 552 -6011 /12 Fax 251-11-5526012

የያዘው ደብር ዲያቆን የሆነው ሲሳይ ግርማ ‹‹ሁኔታው አሳሳቢ በመሆኑ ቤተ-ክርስቲያን ከወረዳው ኃላፊዎች ጋር በመምከር ልትሰራበት የሚገባ ጉዳይ ነው›› በማለት ይገልፃል፡፡ሸንኮራ ‹‹የሚግጡ›› ህፃናትን ከሌሊቱ አስር ሰዓት ከአሰራ አምስት ደቂቃ ላይ ብታገኙ ምን ትላላችሁ? ሁለት ሰዓት የእግር ጉዞ አድርገው ‹‹ብርቄ›› ከተባለ አጎራባች ቀበሌ ሳማ የደረሱት ታደለ ድንቅነው እና ጓደኞቹ ይህን ሲያደርጉ ነበር፡፡ እየነጋ ሲሄድ የጀመረው ሰውነትን የሚያንጠረጥረው ብርድ የልጅነት ትከሻቸው ሳይከብዳቸው ከወዲህ ወዲያ ይቦርቁ ነበር፡፡ የድምፅ ብክለት ሌላው የቦታው ችግር! የመዝሙር ካሴት፣ ሲዲ፣ ቪሲዲ፣ መፅሐፍ፣ እና የእርዳታ (ርጠቡኝ) ጥያቄው በትልቅ ስፒከር ይስተጋባ ስለነበር ይረብሽ ነበር፡፡ ‹‹ኧረ እነዚህ ሌሊትም ጋብ አይልላቸውም እንዴ?›› በማለት የትዝብት ቃል የሚወረውሩም ነበሩ፡፡ ‹‹ድንገተኛ›› ለመሸጥም ድምፅ ማጉያ ያስፈለገው ‹‹መለኛ›› ሳይፎርሽ ‹‹ከሌላ አካባቢ የመጣችሁ አየሩ ሲቀየር ሊያማችሁ ስለሚችል መድኃኒት፤ ይህን ማኘክ ግድ ነው›› እያለ ለትንሿ ‹‹እስር›› አንድ ብር ያስከፍል ነበር፡፡

‹‹የቀረ መኪና አለን?››ቅዳሜ አመሻሹ ሳማ የደረሱ ምዕመናን የአገር አቋራጭ መኪኖች አውደ ርዕይ መሀከል የተገኙ አይነት ስሜት አድሮባቸዋል፡

የለበትም፡፡ መንግስት የሆነው ሕዝብ ለማስተዳደር እስከሆነ ድረስ የሕዝቡን የልብ ትርታ እየተከተለ የራሱን ፍላጎት መገደብ ይኖርበታል፡፡ ከኔ በላይ ላሳር የሚለው የማን አለብኝነት አባባል ጊዜው ያለፈበት መሆኑን ከእህት ሀገሮች ማየት በቂ ነው፡፡

ደርግ ሕዝቡን ተቃውሞውን ሰግቶ ሰዓት እላፊ በማወጅ በፈለጉበት ሰዓት የመንቀሳቀስ ነፃነትንና መብትን አገደ፡፡ ሰዓት እላፊው ቢታወጅም ደርግን የሚቃወሙ ኃይሎች ንቅናቄ መፍጠራቸውን አላቆሙም ነበር፡፡

ኢህአዴግ ደግሞ የጋዜጣ ትችቶችን ፈርቶ በንባብ ባህል ላይ እና በዕውቀት ብርሃን ላይ ሰዓት እላፊ አወጀ፡፡ በሰዓት እላፊው አማካኝነት የመፃፍ ነፃነትንና የማወቅ መብትን ገደባቸው፡፡ አዋጁ የማንንም ይሁንታ ማግኘት አልቻለምና ውሳኔው ደግሞ ደጋግሞ ቢሰላ መልካምነቱ ያመዝናል፡፡ ‹‹ለሌላው ያዘጋጁት ወጥመድ ለራስ ጠንቅ የሚሆንበት ጊዜ ይመጣል፡፡››

እስክንድር ነጋ ግንኙነት አለው ብሎ አሁኑኑ ፍርድ ለመስጠት የተዘጋጀ ሰው በሥልጣን ላይ መገኘቱ ለአገሪቱ አደጋው የከፋ ነው፤ ጥያቄም ያስነሳል፤ በእውነት ይህ ባለሥልጣን ፍላጎቱ አውሎ ነፋሱን ለማስቀረት ነው? ወይስ ለመጋበዝ? እስክንድር ነጋ ዱላ አልያዘ፤ ወያኔ በሥልጣን ላይ ከወጣ ጀምሮ እንደጥጃ ሲታሰር፣ ሲፈታ ቆይቷል፤ የሚታሰርበት ዋናው ምክንያት በሕገመንግስቱ አንቀጽ 29 በተደነገገው መብቱ በመጠቀሙ ነው፤ ማስፈራሪያውን ለሰጠው ባለሥልጣን አንድ ቀን ዕረፍት

ሰጥቶ የሕገመንግስቱን አንቀጽ 29 እንዲያነብና እንዲያጠናው ማድረግ ያስፈልጋል፤ አንድ በከፍተኛ ባለሥልጣኖቹ በተለይም በጠቅላይ ሚኒስትሩ እየተለመደ የሄደ አደገኛ ልማድ አለ፤ አፍ እንዳመጣ መናገር (ለምሳሌ ማሰር ሰልችቶናል)፤ ልቡ ለሹመት የቋመጠውን ሎሌ ወደተግባር ንግግሩ እንዲለውጥ ይገፋፋውና የሚመሰገን እየመሰለው ጥፋት ይሰራል፡፡ መማር የሚችሉ ጉዳዩ የሚነካቸው ባለሥልጣኖች የጆን ስቲዋርት ማል ስለነጻነት (On Liberty) በሚል የጻፈውን እንደምንም ተጨንቀው ያንብቡት፤

እስከዚያው ድረስ የኔ አስተዋጽኦ የሚከተለው ቅንጫቢ ይሁን፡-

‹‹አንድ ሰው ብቻ ተነጥሎ ሲቀር ሌሎቹ የሰው ልጆች ሁሉ በአንድ ላይ አንድ አስተያየትን ይዘው ቢቆሙና የተነጠለው አንድ ሰው ተቃራኒ አስተያየት ቢኖረው፣ የሰው ልጆች ሁሉ ያንን አንድ ሰው ጭጭ ለማሰኘት መብት የሌላቸውን ያህል ያም አንድ ሰው ጉልበት ቢኖረው የሰው ልጆችን በሙሉ ጭጭ ለማሰኘት መብት የለውም፡፡ አንድ አስተያየት የግል ንብረት ቢሆንና ከባለቤቱ በቀር ለማንም ለሌላ ሰው ዋጋ የሌለው ቢሆን፣ ያንን አስተያየት ማስተጓጎል ጉዳቱ ለጥቂቶች ወይም ለብዙዎች ስለሚሆን ትንሽ ልዩነት ያመጣ ነበር፤ ነገር ግን አስተያየትን ማፈን ወደባሰ እኩይነት የሚያወርደው የሰውን ልጆች በሙሉ መበደሉ ነው፤ አሁን ያለውንም ትውልድ ሆነ የሚቀጥሉትን ትውልዶት ይበድላል፣ አስተያየቱን የሚቃወሙትንም ሆነ የሚደግፉትን ይጎዳል፤ አስተያየቱ ትክክል ከሆነ አፋኞቹ ስህተትን (ጥፋትን) ወደእውነት ለመለወጥ ያላቸውን ዕድል ያጣሉ፤ አስተያየቱ ትክክል ካልሆነም እውነትና ስህተት ሲጋጩ የእውነት ግልጽና ሕያው ገጽታ የሚያስገኘውን ግንዛቤ ያጣሉ፡፡››

ለተለየ ሀሳብ ወይም አስተያየት ተገቢውን መልስ መስጠት የሚችል ሰው በመጥፋቱ ማሰር ቀላል መፍትሔ ሆኖላቸዋል፤ ሰውየውን ማሰር ቀርቶ መግደልም ቢሆን ሀሳቡን እንደማያስረው ክርስትና ጉልህ ማስረጃ ነው፤ ሀሳብ የሚሸነፈው በተሻለ ሀሳብ ብቻ ነው፤ ሀሳብን ማሰርም ሆነ መግደል ስለማይቻል ሀሳብን በእስር ወይም በግድያ ለማሸነፍ አይቻልም፤ መሞከሩም ቂልነት ነው፤ እስክንድር ነጋም ሆነ ሌላ የሀሳብ ነፃነት ታጋይ ያለበት የመንፈስ ልዕልና ደረጃ አሳሪዎችና አሳሳሪዎች በሀሳባቸውም የማይደርሱበት ነው፤ በኋላም ታሪክ የሚመዘግባቸው አልሚና አጥፊ አድርጎ ነው፤ የብርሃን መልእክተኛና የጨለማ መልእክትኛ ሆነው ነው፤ የማኅበራዊ እድገት አራማጆችና የማኅብራዊ እድገት እንቅፋቶች ሆነው ነው፤ በሁለቱም ተቃራኒ ሥራዎች ውጤት የየአንዳንዳቸው ልጆች ክብርን ይጎናጸፋሉ፣ ወይም ሐፍረትን ይከናነባሉ፤ ይህ የማይሻር የታሪክ ቃል-ኪዳን ነው፡፡

‹‹ማሰር ሰለቸን...

ሰዓት እላፊው..

ነበሩ፡፡ ምግብ አቅራቢዎችም አሉ፡፡ በአዲስ አበባም ሆነ በሌሎች የክልል ከተሞች በዓለ ንግስ ሲኖር አካባቢዋን የሚሞሉ ሸቀጦች ሁሉም ሳማንም አጣበዋት ነበር፡፡ ጊዜያዊ ቅርፅ ሰርተው አዲስ መንደር ገንብተው ነበር፡፡ ሻጮች የአካባቢው ነዋሪዎች ብቻ አይምሰሎት ብዙ ኪሎ ሜትሮችን አቆራርጠው የመጡ በርካቶች ይገኙበታል፡፡በዳስዎቹ ዙሪያ ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ ምሽት፣ ሌሊትና በእለተ ሰንበት እስከ ቀኑ አጋማሽ ድረስ ተዟዙሬ እንደቃኘሁት ከሆነ የእምነት ስርዓቱ የሚፃረሩ ድርጊቶች በርክተው ተመልክቻለሁ፡፡ ‹‹ለትሪፕ ነው የመጡት?›› የሚል ጥያቄ ለማጫር የሚያስገድዱ ግለሰብዎችን ለመታዘብ አይንን ወደ ዳስዎቹ ‹‹ጣል›› አድርጎ ‹‹ማንሳት›› በቂ ነበር፡፡ ጠላ፣ ጠጅ፣ አረቄና ቢራን በዳስዎቹ ውስጥ ‹‹የሚግፉ›› በርካታ ወጣት፣ ጎልማሳና አዛውንት ተባዕታት ነበሩ፡፡ እኔ አላየሁም እንጂ ጫትም የሚሸጡና የሚቅሙ በዙሪያው ነበሩ ብለውኛል፡፡አንድ ‹‹ብልጧ›› (ካቲካላ) ብቻ ያለማቆም ለተጠቃሚዎቹ በሚቸረችር ‹‹ዳስ›› ውስጥ አንድ መለኪያ አረቄ በአንድ ብር ከሃምሳ፣ የሻይ ብርጭቆ (በእነሱ አጠራር ጃንባ) አራት ብር ይሸጣል፡፡ ስራዋን በደንብ የተወጣችው ፈሳሽም ማንነታቸውን ቀይራ የምታለፋድዳቸው ብቻ ሳይሆን ‹‹ለብርድ ጠቅማናለች›› ሲሉ ትርፋማ መሆናቸውን

የሚናገሩላትም መስካሪዎች ነበሯት፤ ብልጧ፡፡ በሞቅታ ማሲንቆ ጭፈራውን የሚያደሩትም ነበሩ፡፡ በሁለት ብር አንድ ኩባያ ጠላ ይሸጥ በነበረበት ዳስ ውስጥ ደጋግመው ለግተው ‹‹ጥምብዝ›› ብለው ሰክረው ጭፈራ ብቻ የሚላቸው ነበሩ፤ ዓላማዊ ዘፈን በማቀንቀን፡፡ ይህ ‹‹መዝናናት›› ከተባለ ሰው የሚመጣው የሚጠጣበትን ቦታ ለመቀየር ያስመስለዋል፡፡ይህ ሁሉ እየሆነ ያለው ቅዳሜ ሌሊት በፋኖስ፣ በባትሪና ጄኔሬተር በሚያመነጨው መብራት በመታገዝ መሆኑን ልብ ይበሉ፡፡ እናም እሎታለሁ የስንዴ ማሳ ታጭዶ የቀረው ግፍጫ (ሳር መሰል ነገር) ብቻ የቀረው መሬት ላይ በህብረት አማርኛ፣ ጉራጊኛና ኦሮሚኛ ዘፈን እየታገዙ ሲጨፍሩ አቧራ ማጨሳቸውን ለተመለከተ ቦታው ሀይማኖታዊ ስፍራ አይመስልም ነበር፡፡ ሁሉም የመሸታ ቤት ደንበኞች ኮፍያ እና ጋቢ ማድረጋቸውን ላየ [ከቀን ጀምሮ ማለት ነው] የድንኳኖቹ ‹‹የግዴታ አለባበስ ነውን?›› ብሎ ሊጠይቅ ይችላል፡፡ እሁድ በማለዳ በቅዳሴ ሰዓት በምዕመናን ተከብበው ይሰብኩ የነበሩ ባህታዊ ‹‹ጠላ፣ አረቄ ጠጥታችሁ የመጣችሁ ወደዚያ ሂዱ ዓላማችሁን አትሳቱ›› እያሉ ይገስፁ ነበር፡፡ ትኩረታቸው እምነት ስርዓቱ ላይ ብቻ የሆኑ በርካቶች ‹‹ሊታረም የሚገባው›› ያሉትን ይህንን ተግባር ኮንነዋል፡፡ ከሀገረ ማርያም ከሰማ ወረዳ የሚገኝ ሰባት ደጅ መድኃኒያለም እና የውላት መሶቢትን አካቶ

፡ አይን ቆጥሮ ሊጨርሳቸው የማይችል ‹‹አንድ አገር›› መኪና ተደርድሮ ማየት ከዚህ ስሜት ውስጥ ከመነከር የዘለለ እድል አይሰጥም፡፡ ክብረት ግርማ ሳማ ሰንበት ሲጓዝ የመጀመሪያው ነው፡፡ በርካታ ምዕመናን ወደ ደብሩ ስለሚያመሩ የመኪኖች ብዛት አያሌ መሆኑን ቢሰማም ይህን ያህል ይበረክታል ብሎ አልጠረጠረም ነበር፡፡ የአገር አቋራጭ መኪኖቹ ‹‹ብፌ›› በአግራሞት ሲገለፅ የሰሙት የቦታው ደንበኞች ግን ‹‹ዛሬ እንዲህ ካልክ ነገ ምን ልትል ነው?›› በማለት እሁድ ማልደው የሚደርሱ መኪኖች ቁጥሩን እንዲያሻቅብ እንደሚያደርጉ ጥያቄያዊ መልስ ሰጡት፡፡ ክብረት እሁድ ረፋድ (አምስት ሰዓት አካባቢ) ከታቦተ ንግስ በኋላ ከሸገር አምጥቶ ወደሚመልሰው መኪና በመመለስ ላይ ሳለ አይኑን አሻግሮ ወደመጣበት ፒስታ መንገድ ሲመለከት አይኑ መጨረሻውን ሊደርስበት ያልቻለው የመኪና ሰንሰለት ‹‹አጀብ›› አሰኝቶታል፡፡ ሁኔታው ክብረትን ብቻ ሳይሆን ብዙዎችን በግርምት ከማወያየቱም በላይ ወደ ሌሎች ስፍራዎች የሚጓዙ አውቶብሶች እጥረት እንደሚያስከትል ፍንጭ የሰጠ ነበር፡፡ ወደ መጡበት በመመለስ ላይ የነበሩ መኪኖች የ‹‹እንፉቅቅ›› ጉዟቸው ተስፋ የዘራው ቢዘገዩም የትራፊክ ፖሊሶች ደርሰው በውስን ክፍተት እንዲንቀሳቀሱ ካደረጉት በኋላ ነበር፡፡ ይህ ባይሆን በ‹‹እኔ ልቅደም›› የተደበላለቀው

እስርስሮሽ አይፈታም ነበር፡፡ ‹‹በመኪና ላይ በረዳትነት መስራት ከጀመርኩበት ከ1992 ዓ.ም. ጀምሮ ‹‹ሳማ ሰንበት›› እመጣለሁ የሰው ቁጥር እያሸቀበ ነው›› በማለት በየዓመቱ ደብረ ዘይት ወደ ሚከበርበት ሳማ ሰንበት ደብር የሚመጣው ህዝብ እየበረከተ መሄዱን የገለፀልን ነጋሽ ጥላሁን የተባለ የአውቶብስ ረዳት ባለፈው ዓመት የመኪና እስርስሮሹ ሊፈታ ባለመቻሉ ስድስት ሰዓት ተነስተው ሞጆ የደረሱት ከምሽቱ ሦስት ሰዓት እንደነበር ያስታውሳል፡፡

ሳያልቅ መናፈቅየእግዚኣ ለሰንበት መድሀኒዓለም ታቦት ወጥቶ የደመቀው ሥነ ስርዓት ገና ሳይከናወን እንኳን የቀጣዩን ዓመት በዓል በጉጉት የሚጠብቁት አሉ፡፡ ‹‹ከሃይማኖታዊ ዳራው ሌላ ከወረዳችን አልፎ በመላው አገሪቱ ያሉ ምዕመናን በዓሉን ለማክበር ስለሚሰበሰቡ የምንገናኝበት ስለሆነም እንናፍቀዋለን›› ብሏል የሳማ ነዋሪው፤ አርሶ አደሩ አጥላባቸው ሺበሺ፡፡ ሃያ ኪሎ ሜትር (አራት ሰዓት) በእግር፣ ሃያ ኪሎ ሜትር በመኪና ተጉዞ በየዓመቱ ‹‹ሳማ ሰንበት›› የማይቀረው ዲያቆን ሲሳይ ግርማ ‹‹ዛሬ ላይ ሆኜ እንኳን ዓመቱ ይናፍቀኛል›› ሲል 365 ቀናት ተሻግሮ ሲያይ፤ ዓላማቸውን አውቀው ከአልባሌ ነገሮች ታቅበው ከሚመጡ ምዕመናን ጋር ለከርሞ በዓሉን ለማክበር በመመኘት ነው፡፡

በዐቢይ ጾም እኩሌታ . . .

Page 24: Awramba Times Issue 161 Megabit 24

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 161 ቅዳሜ መጋቢት 24 200324 ማስታወቂያ