ከሊቀመንበሩ ማኀደር -...

16
1 Addis Ababa, Ethiopia ሼህ አብደላ ሁሴን አሊ አል-አሙዲ ከዶ/ር አረጋ ይርዳውና ከኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ተወካይ ጋር ሱፐርማርኬቱን መርቀው ሲከፍቱ ከሊቀመንበሩ ማኀደር Volume 17, Issue No. 94 August 2019 u¨<eØ Ñ뉋” 4 4 A BI-MONTHLY PUBLICATION OF THE OFFICE OF THE CHIEF EXECUTIVE OFFICER This Newsletter provides customers, employees, suppliers, shareholders and the community at large with current information on major performance and other activities of the companies under the leadership of the CEO ዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ የ36ኛ ዙር ተማሪዎቹን አስመረቀ...............................11 መልዕክት፣ ከቺፍ ኤግዚኪዩቲቭ ኦፊሰር ..........................................16 የክብር ዶ/ር ሼህ ሙሐመድ ሁሴን አሊ አል-አሙዲ አደራን መወጣት ሰ∁묀눀阀꼀츁㠀켁뤁됀愁阀Щ呪 የዛሬ መልዕክቴ መነሻ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የክብር ዶክትሬት ሸልማት የተበረከተልኝ ቀን ትውስታ ነው:: ዩኒቨርሲቲው በወቅቱ “በሀገራችን የልማት እድገት በወሰዷቸው ፈር ቀዳጅ እርምጃዎችና ዘርፈ ብዙ ተሳትፎ” በሚል ለእኔ የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ሲያበረክትልኝ እጅግ አስደስቶኛል:: ወደ ገጽ 3 ዞሯል u¨<eØ Ñ뉋” የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በስድስት ኪሎ ካምፓስ የተገነባውን ቤተ-መጻሕፍት ሕንፃ ተረከበ ኩዊንስ ሱፐርማርኬት ዘመናዊ የሆነውን የኮልፌ ቀራኒዮ ፕላዛ ቅርንጫፍ ሱፐር ማርኬቱን አስመረቀ ሚድሮክ ወርቅ ማዕድን ግብርን በመክፈሉ በወርቅ ደረጃ ተሸላሚ ሆነ ወደ ገጽ 7 ዞሯል ወደ ገጽ 2 ዞሯል ወደ ገጽ 4 ዞሯል

Upload: others

Post on 25-Aug-2020

20 views

Category:

Documents


0 download

TRANSCRIPT

Page 1: ከሊቀመንበሩ ማኀደር - MIDROCmidroc-ethiotechgroup.com/sites/default/files/Newsletters/R_issue_9… · ሼህ አብደላ ሁሴን አሊ አል-አሙዲ ከዶ/ር

1Addis Ababa, Ethiopia

ሼህ አብደላ ሁሴን አሊ አል-አሙዲ ከዶ/ር አረጋ ይርዳውና ከኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ተወካይ ጋር ሱፐርማርኬቱን መርቀው ሲከፍቱ

ከሊቀመንበሩ ማኀደርVolume 17, Issue No. 94 August 2019

u¨<eØ Ñ뉋” 44

A BI-MONTHLY PUBLICATION OF THE Office Of the chief executive OfficerThis Newsletter provides customers, employees, suppliers, shareholders and the community at large with current information

on major performance and other activities of the companies under the leadership of the CEO

ዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ የ36ኛ ዙር ተማሪዎቹን አስመረቀ...............................11 መልዕክት፣ ከቺፍ ኤግዚኪዩቲቭ ኦፊሰር ..........................................16

የክብር ዶ/ር ሼህ ሙሐመድ ሁሴን አሊ አል-አሙዲ

አደራን መወጣት ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባ ጉዳይ ነው!

94

የዛሬ መልዕክቴ መነሻ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የክብር ዶክትሬት ሸልማት የተበረከተልኝ ቀን ትውስታ ነው:: ዩኒቨርሲቲው በወቅቱ “በሀገራችን የልማት እድገት በወሰዷቸው ፈር ቀዳጅ እርምጃዎችና ዘርፈ ብዙ ተሳትፎ” በሚል ለእኔ የክብር ዶክትሬት ዲግሪ

ሲያበረክትልኝ እጅግ አስደስቶኛል:: ወደ ገጽ 3 ዞሯል

u¨<eØ Ñ뉋”

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በስድስት ኪሎ ካምፓስ የተገነባውን ቤተ-መጻሕፍት ሕንፃ ተረከበ

ኩዊንስ ሱፐርማርኬት ዘመናዊ የሆነውን የኮልፌ ቀራኒዮ ፕላዛ ቅርንጫፍ ሱፐር ማርኬቱን አስመረቀ

ሚድሮክ ወርቅ ማዕድን ግብርን በመክፈሉ በወርቅ ደረጃ ተሸላሚ ሆነ

ወደ ገጽ 7 ዞሯል

ወደ ገጽ 2 ዞሯል

ወደ ገጽ 4 ዞሯል

Page 2: ከሊቀመንበሩ ማኀደር - MIDROCmidroc-ethiotechgroup.com/sites/default/files/Newsletters/R_issue_9… · ሼህ አብደላ ሁሴን አሊ አል-አሙዲ ከዶ/ር

2

MIDROC NewsletterVolume 17, Issue # 94 August 2019

Addis Ababa, Ethiopia

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በስድስት ኪሎ ካምፓስ የተገነባው ሕንፃ ...በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ስድስት ኪሎ ካምፓስ የተጠናቀቀው ሕንፃ የርክክብ ሥነ ሥርዓት የተካሄደው ሐሙስ ሐምሌ 4 ቀን 2011 ዓ.ም ክብርት ፕሮፌሰር

ሒሩት ወልደ ማርያም የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር በክብር እንግድነት በተገኙበት ከተመረቀ በኋላ፤ ክቡር ዶ/ር አረጋ ይርዳው፣

የሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ቺፍ ኤግዚኪዩቲቭ ኦፊሰር እና የዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት የክብር ዶ/ር ሼህ ሙሐመድ ሁሴን አሊ አል-አሙዲን በመወከል

ሕንፃውን ለፕሮፌሰር ጣሰው ወልደ ሐና የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት አስረክበዋል፡፡

ክቡር ዶ/ር አረጋ ይርዳው፣ የሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ቺፍ ኤግዚኪዩቲቭ ኦፊሰር እና የዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ሕንፃውን ለፕሮፌሰር ጣሰው ወልደ ሐና የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ሲያስረክቡ

በሥነ ሥርዓቱ ላይ ክቡር ዶ/ር አረጋ ይርዳው ባደረጉት ንግግር፤ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ

የክብር ዶ/ር ሼህ ሙሐመድ ሁሴን አሊ አል-አሙዲ ክብርና አርያነት ያለውን ከፍተኛ

አስተዋጽኦ ከግምት ውስጥ በማስገባት ርክክቡ የተከናወነውን ይህንን የኢትዮጵያ ጥናትና

ምርምር ተቋም ዘመናዊ ቤተ መጻሕፍት ሕንጻ፤ በሼህ ሙሐመድ ሁሴን አሊ አል-አሙዲ

ስም እንዲሰየም በማድረጉ እና በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ታሪክ ውስጥ አገራዊ ከበሬታንና

የታሪክ ባለ አደራነትን የመወጣት ተግባር ሆኖ መመዝገቡ አሰደስቶኛል፡፡

“ሼህ ሙሐመድ በአብዛኛው የኢትዮጵያ ሕዝብ ዘንድ አገር ወዳድ፣ አዛኝ እና ለጋስ ባለሀብት

እንደሆኑ ይታወቃሉ፡፡ እሳቸው ከሚመኙዋቸው ነገሮች አንዱ በሕይወታቸው እያሉ ኢትዮጵያ

“ደሀ ሀገር” የሚለው ስሟ ተለውጦ በስልጣኔ ጎልብታ “ራሳቸውን ችለዋል” ከሚባሉት ተርታ

ተሰልፋ ማየት ሲሆን ለዚህም ምኞት እውን መሆን ትምህርት ዋነኛ መሣሪያ እንደሆነ

ያምናሉ፡፡” በማለት ዶ/ር አረጋ ተናግረዋል፡፡

የኢፌዲሪ ሳይንስና የከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ፕሮፌሰር ሒሩት ወ/ማርያም

በበኩላቸው ባደረጉት ንግግር ሀገር ወዳድና ለጋሱ ባለሀብት የክብር ዶ/ር ሼህ ሙሐመድ

ሁሴን አሊ አል-አሙዲ ከዚህ ቀደም በትምህርት ዘርፍ ካደረጓቸው በርካታ ድጋፎች በተጨማሪ

ይህንን ሕንጻ ከፍተኛ ገንዘብ በማውጣት ሙሉ ወጪውን ሸፍነው በማበርከታቸው በራሴና

በኢትዮጵያ መንግሥት ስም ምሥጋናዬን አቀርባለሁ ብለዋል፡፡

ሚኒስትሯ አያይዘውም ኢትዮጵያ ዘመን ተሻጋሪ ባህል አላት በመሆኑም ሌሎች የሀገራችን

ባለሀብቶች የሼህ ሙሐመድ ሁሴን አሊ አል-አሙዲ አርኣያነት እንዲከተሉና ለከፍተኛ

ትምህርት ተቋሟት ተመሳሳይ ድጋፍ በማድረግ ቋሚ የሆኑ አሻራቸውን በማስተላለፍ ድጋፍ

እንዲያደርጉ አሳስበዋል፡፡

የዚህ ህንፃ ዓላማ ከሌሎች የመማሪያና ምርምር ተቋም ከማድረጊያ የተለየ እንደሆነ ማስታወስ

ይቻላል ያሉት ሚኒስትሯ፤ ስለ ጥንታዊቷና ታሪካዊቷ ኢትዮጵያ ታሪካችን ማወቅ ለዛሬ

እኛነታችን ትልቅ ፋይዳ አለው ብለዋል፡፡

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደሃና በበኩላቸው ባደረጉት ንግግር

ይህ ሕንፃ ለኢትዮጵያ ጥናት ብሎም ለአገራችን የምርምር መስክ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንደአለው

በማመን የክብር ዶ/ር ሼህ ሙሐመድ ሁሴን አሊ አል-አሙዲ ያደረጉት እገዛ ከፍተኛ በመሆኑ

ላመሰግናቸው እወዳለሁ፡፡

ክብርት ፕሮፌሰር ሒሩት ወልደ ማርያም የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር

የሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ቺፍ ኤግዚኪዩቲቭ ኦፊሰርና የዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር አረጋ ይርዳው

የሕንፃ ርክክብ፣ከገጽ1 የዞረ

Page 3: ከሊቀመንበሩ ማኀደር - MIDROCmidroc-ethiotechgroup.com/sites/default/files/Newsletters/R_issue_9… · ሼህ አብደላ ሁሴን አሊ አል-አሙዲ ከዶ/ር

3

MIDROC NewsletterVolume 17, Issue # 94 August 2019

Addis Ababa, Ethiopia

ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደ ሐና የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት

እስከ ዛሬ ለሀገሬ ላበረከትኳቸውና እያበረከትኳቸው ላሉ አስተዋጽዖዎች

ፈጣሪን አመሰግናለሁ::

እንደ እውነቱ ከሆነ በሀገሬ ላይ ለማፈሰው መዋዕለ ነዋይ ወሳኞቹ እኔ

በሀገሬ ላይ እንድሠራ የፈቀደልኝ መንግሥት፣ ለሀገራቸው እድገት ሌት

ከቀን የሚሠሩ ምሁራንና ቤተሰቦቼ፣ በተለይ ደግሞ ሥራዬን የሚደግፉ

የኢትዮጵያ ልጆች በመሆናቸው ዛሬ ላይ 74ቱ ኩባንያዎች ለበርካታ

ኢትዮጵያውያን ከፍተኛ የሥራ እድል በመፍጠር፣ በአገሪቱ የኢኮኖሚ

እድገት የበኩላቸውን በመወጣ ት ላይ ስለሚገኙ ተደስቻለሁ::

በተለይ ደግሞ ለስኬቴ ሁሌም ከጎኔ ከማይለዩት እና ፈጣሪ አደራ የመወጣት

ጸጋን ከሰጣቸው ቤተሰቦቼ መካከል አንዱ የሆነው ወንድሜ ዶ/ር አረጋ

ይርዳውን ላመሰግነው እወዳለሁ:: ዶ/ር አረጋ ከብዙ በጥቂቱ አምስት

ኩባንያዎችን ተረክቦ፣ሀገራችን ላይ ለመገንባት ያሰብኩዋቸውን ፋብሪካዎች

ቁጥር 26 በማድረስ፤ ወልድያ ስታድየም ደረጃውን ጠብቆ እንዲገነባ

በማድረግ፣ ከምንም በላይ ደግሞ በኦሮሚያ ክልል ከቤት ንብረታቸው

ለተፈናቀሉ ወገኖች ቢሾፍቱ ላይ በአጭር ጊዜ ቤት ገንብቶ በማስረከብ፣

ዩኒቲ ዩኒቨርሲቲን ከነበረበት የመዘጋት አደጋ በመታደግ የሚድሮክ

ኢንቬስትመንት አካል እንዲሆን በማድረግ እና በማጠናክር ሀገራችን በግሉ

ዘርፍ አንድ ስመ ጥር አማራጭ ዩኒቨርሲቲ እንዲኖራት እና ዩኒቨርሲቲው

በአዲስ አበባ፣ በአዳማ፣ በቡራዩና በደሴ ካምፓሶች ከKG እስከ PhD

የተቀናጀ ትምህርት የማስፋፋት ሥራ እንዲሠራ በማቀድና በመምራት

ጉልህ የመሪነት ተግባር አከናውኗል:: ወንድሜ ዶ/ር አረጋ ከሌሎች

አጋሮቹ ጋር በመሆን ለዛሬ መልዕክቴ ምክንያት ለሆነኝ የኢትዮጵያ

የጥናትና ምርምር ተቋም ቤተ መጻሕፍት ሕንፃ መጠናቀቅ፣ በብቁ

አመራር አደራውን መወጣቱንና፤ እየተወጣ መሆኑን መናገር ለቀባሪው

እንደ ማርዳት ይሆንብኛል::

በተለይ ማህበራዊ ኃላፊነትን ለመወጣት ባሉኝ እቅዶች እኔ በግሌ

ብቻዬን እሠራለሁ የምለው ምንም ነገር የለም፤ ነገር ግን ቀደም ሲል

እንደገለጽኩት ሀሳቤንና ፍላጎቴን የሚረዱ ሰዎችን ፈጣሪ ስለሠጠኝ ሁል

ጊዜም አመሰግነዋለሁ:: በተለይ ለልቤ ደስታ ከሰጡኝ ማኅበራዊ ተሳትፎዎች

መካከል፤ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አካል በሆነው በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል

ግቢ ውስጥ ለህጻናት የልብ ህሙማን እንዲያገለግል ሙሉ ህንጻ አሰርቼ

ማስረከቤ ነው:: በተለያየ ጊዜ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን በውጭ አገር

እውቀት ቀስመው ሀገራቸውን እንዲጠቅሙ ለማድረግ ያደረኩትንና

የተሳካልኝን ሁኔታ ወደ ኋላ መለስ ብዬ ሳስበው ያስደስተኛል:: በምግብ

እጦት ለተቸገሩ በሺዎች ለሚቆጠሩ የአዲስ አበባ ህጻናት ተማሪዎች ብዙ

ሚሊዮን ብሮች በዓመት በመመደብ የታዳጊ ህጻናቱ የወደፊት እጣ ፈንታ

መልካም እንዲሆን የበኩሌን ለማድረግ ሞክሬያለሁ::

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በጉጂ ዞን የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ኮሌጅ

እንዲሁም የሁለተኛ ደረጃና የመሰናዶ ት/ቤቶች ግንባታ እንዲስፋፋና

ተዛማጅ የውስጥ ቁሳቁሶች እንዲሟሉ፤ በዞኑ ለሚገኙ ት/ቤቶችም የገንዘብ

እርዳታ በማድረግ የበኩሌን አስተዋጽዖ አበርክቻለሁ::

በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች በብዙ መቶ ሚሊዮን ብሮች መዋዕለ ንዋይ

ፍሰት ከተደረገባቸው መሀከል በቀዳሚነት ለሚገኘው የአባይ ግድብ የበኩሌን

ድርሻ ተወጥቻለሁ:: በህዋ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዘርፍ እንዲሁም የሀገሬ

የተፈጥሮ መስህብ ከሆኑት ቦታዎች መካከል በእንጦጦና በላሊበላም

ህንጻዎች እንዲገነቡ መደረጉን አስታውሳለሁ::

ለዛሬ መልዕክቴ መንደርደሪያ እንዲሆነኝ ከላይ ከገለጽኩት ሀሳብ ባሻገር

ትዝ እንደሚለኝ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የክብር ዶክትሬት ሲያበረክትልኝ

እጅግ አስደስቶኛል:: ለኔ ሽልማት አዲስ አይደለም ቢሆንም ይኼኛው

ተለይቶብኛል:: ደሰታዬ ወደር አልነበረውም:: በወቅቱም ከቀድሞው

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ከፕሮፌሰር እንድሪያስ እሸቴ በኢትዮጵያ

የጥናትና ምርምር ተቋም ቤተ መጻሕፍት ሕንፃ ግንባታ ለቀረበልኝ ጥያቄ

አፋጣኝ ምላሽ በመስጠት ሙሉ ወጪውን ሸፍኜ አዲስ የቤተ መፃሕፍት

ሕንጻ ለመገንባት ቃል ገባሁ እንደተለመደው አደራዬን ለወንድሜ ለዶ/ር

አረጋ ይርዳው፣ የሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ቺፍ ኤግዚኪዩቲቭ ኦፊሰርና

የዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት አስተላለፍኩ በቃሌ መሠረትም የሕንፃው

ግንባታ ሙሉ በሙሉ ተጠናቅቆ የርክክብ ሥነ-ሥርዓት ተደርጓል:: ዛሬም

ካለሁበት ቦታ ሆኜ በሀገሬ ቃል ወደ ተግባር ተለውጦ ስመለከት ደስታዬ

ወደር የለውም::

የሕንፃው ግንባታ ሙሉ በሙሉ መጠናቀቅ በኢትዮጵያ የጥናትና ምርምር

ተቋም ቤተ መጻሕፍት ሕንፃ ውስጥ የሚገለገሉ ተጠቃሚዎች በጥናትና

ምርምር ውጤቶቻቸው ጭምር እንዲዳብሩ አጋዥ ኃይል ሊሆን እንደሚችል

እገምታለሁ:: ፈጣሪ ኢትዮጵያና ህዝቦቿን ይባርክ!!

የማስተማር፣ የምርምርና የማህበረሰብ አገልግሎት ከፍተኛ እገዛን ለሚያደረገው ለዚህ ሕንፃ

እውን መሆን የቀድሞ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ምሩቅ የሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ኩባንያዎች

ቺፍ ኤግዚኪዩቲቭ ኦፊሰር የዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር አረጋ ይርዳው ላደረጉት

ከፍተኛ አስተዋጽኦ ምስጋና አቀርባለሁ ብለዋል፡፡ በመጨረሻም ይህ የተጠናቀቀው ሕንፃ

በኢትዮጵያ፤ ጥናትና ምርምር ለሚያደርጉ ሁሉ የሚያገለግል በመሆኑ ውድ እንግዶች

ሌላ ቦታ የማይገኙ ዶክሜንቶችን በማንበብም ሆነ ምርምር ለመሥራት ብትፈልጉ በራችን

ሁልጊዜም ክፍት ነው በማለት አሰታውቀዋል፡፡

የሼህ ሙሐመድ ሁሴን አሊ አል-አሙዲ ሕንፃ ግንባታ ሂደት የተመራውና የተጠናቀቀው

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የምህንድስና ዘርፍ ምሩቅ በሆኑት በዶ/ር አረጋ ይርዳው የዩኒቲ

ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳትና የሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ቺፍ ኤግዚኪዩቲቭ ኦፊሰር የቅርብ

ክትትልና ተሳትፎ ሲሆን በሚድሮክ ኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ግሩፕ አባል በሚፓ

ኮንትራክቲንግ እና ማኔጅመንት አገልግሎት ዋና ኮንትራክተርነት የሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ

ኩባንያዎች በተለይም የዘመናዊ ሕንፃ ኢንዱስትሪ፣ ዋንዛ ፈርኒሺንግስ ኢንዱስትሪ፣ ቪዥን

አሉሚነም ማኒፋክቸሪንግ እና ሌሎችም የየበኩላቸውን አስተዋጽኦ በስፋት አበርክተውበታል፡፡

ይህ ዘመናዊ የቤተ መጻሕፍት ሕንጻ ከተሟሉለት ቁሳቁሶች ጋር 116,000,000 (አንድ መቶ

አስራ ስድስት ሚሊዮን) ብር ወጪ እንደተደረገበት ታውቋል፡፡

አደራን መወጣት ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባ ጉዳይ ...ከሊቀመንበሩ፣ከገጽ1 የዞረ

Page 4: ከሊቀመንበሩ ማኀደር - MIDROCmidroc-ethiotechgroup.com/sites/default/files/Newsletters/R_issue_9… · ሼህ አብደላ ሁሴን አሊ አል-አሙዲ ከዶ/ር

4

MIDROC NewsletterVolume 17, Issue # 94 August 2019

Addis Ababa, Ethiopia

ኩዊንስ ሱፐርማርኬት ...

የሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ኩባንያዎች አባል ኩዊንስ ሱፐርማርኬት እጅግ ዘመናዊ የሆነውን የቀራኒዮ ፕላዛ ቅርንጫፍ ሱፐርማርኬቱን አስፈላጊዎቹን

ህጋዊ መስፈርቶች አሟልቶ በማደራጀት ማክሰኞ ሐምሌ 16 ቀን 2011 ዓ.ም ሁሉን በአንድ ባቀፈውና ማራኪ በሆነው በኮልፌ ቀራኒዮ ፕላዛ ቅጥር ግቢው

አስመረቀ፡፡

በዚሁ የምረቃ ሥነ ስርዓት ላይ ዶ/ር አረጋ ይርዳው የሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ቺፍ ኤግዚኪዩቲቭ ኦፊሰር እና የዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ባደረጉት

ንግግር፤ በዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያላቸው ደንቦችን መሠረት ባደረገ ዲዛይን የተሠራው፤ ኩዊንስ ሱፐርማርኬት አካሄዱም ለደምበኞች ቀላልና ምቹ

የግብይት ሁኔታ ለማስፈን ትኩረት የሠጠ ነው ብለዋል፡፡

ሱፐርማርኬቱ በሚገኝበት በቀራንዮ ፕላዛ፣ የዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ አካዳሚ፣ በዓይነቱ ልዩ የሆነ የነዳጅ ጣቢያ/ማደያና የተሽከርካሪ እጥበትና መለስተኛ ጥገና

አገልግሎት መስጫ እና በትንሹ ከ150 በላይ መኪኖች ማቆሚያ፣ የእርሻ ምርቶች መሸጫ፣ ካፌና ሱቅ፣ ባንክ፣ እና ሁለገብ አዳራሽ መኖሩን የገለጹት ዶ/ር

አረጋ፤ እነዚህ በአንድ አካባቢ መደራጀታቸው፤ ደንበኞቹን በአንድ የንግድ ማዕከል በርካታ አገልግሎቶች እንዲያገኙ የሚያስችል በመሆኑ፣ሱፐርማርኬቱን

ልዩ ያደርገዋል ብለዋል፡፡

የሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ቺፍ ኤግዚኪዩቲቭ ኦፊሰርና የዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር አረጋ ይርዳው ንግግር ሲያደርጉ

ኩዊንስ፣ከገጽ 1 የዞረ

Page 5: ከሊቀመንበሩ ማኀደር - MIDROCmidroc-ethiotechgroup.com/sites/default/files/Newsletters/R_issue_9… · ሼህ አብደላ ሁሴን አሊ አል-አሙዲ ከዶ/ር

5

MIDROC NewsletterVolume 17, Issue # 94 August 2019

Addis Ababa, Ethiopia

ለኩዊንስ ኩባንያ መቋቋምና በዚህ ደረጃ መስፋፋት ምክኒያት ለሆኑት ለሚድሮክ ኢትዮጵያ ሊቀመንበርና ባለሀብት ለሼህ ሙሐመድ ሁሴን አሊ አል-አሙዲ

በቅድሚያ ምስጋና ያቀረቡት ዶ/ር አረጋ፤ በዛሬው ቀን በመካከላችን ለተገኙት ወንድማቸው ለሼህ አብደላ ሁሴን አሊ አል-አሙዲ ምስጋና አቀርባለሁ ብለዋል፡፡

እንዲሁም፣ የቀራኒዮ ቅርንጫፍ ፕሮጀክት በዚህ ለገበያ አመቺ በሆነ ቦታ እንዲገነባ ለረዱን የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር አመራሮች እና የሚመለከታቸው ሠራተኞች፣ በአካባቢው የሚገኙ ነዋሪዎች፣ መብራት ኃይል፣ የቴሌፎንና የውሃ ተቋማት፣ የአ.አ. የመንገድ ሥራዎች ተቋም፣ የአካባቢው

የፖሊስ እና የፀጥታ ኃላፊዎች እና ሌሎችም ላደረጉልን መተባበር ከፍተኛ ምስጋና አቀርባለሁ ብለዋል፡፡

ዶ/ር አረጋ በዚሁ ንግግራቸው፤የኩዊንስ ቀራኒዮ ቅርንጫፍ ፕሮጀክት ለቅድመ መደበኛ አገልግሎት ፕሮጀክት ማስፈጸሚያ፣ ለሥራ ማስኬጃ እና ለሽያጭ

የሚያገለግሉ ዕቃዎች (መደርደሪያዎች፣ ማቀዝቀዣዎች፣…) ግዢ፣ የሲስተም ዝርጋታ ወጪን ጨምሮ፤ ለሸቀጣ ሸቀጥ አቅርቦት ጠቅላላ ወጪ 59.3

ሚሊዮን ብር መሆኑን አስረድተው፤ ሕንፃው በ37.7 ሚሊዮን ብር ወጪ መገንባቱንና የኤልፎራ አግሮ ኢንዱስትሪ ንብረት በመሆኑ፣ ኩዊንስ በኪራይ

እንደሚገለገልበት አስታውቀዋል ፡፡

የሪቴል ግሩፕ ፕሪንሰፓል ኦፕሬሽን ኦፊሰር ወ/ሮ ታህሳሥ ወንድምነህ በበኩላቸው ባደረጉት ንግግር ኩዊንስ ሱፐርማርኬት ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኀበር

ሰኔ 25 ቀን 2002 ዓ.ም 46 ቋሚ እና 5 ኮንትራት፣ በድምሩ 51 ሠራተኞች በመያዝ የተቋቋመ መሆኑን አስታውሰው፣ ኩባንያው የአግሮ ኢንዱስትሪ

ውጤቶችን (የዶሮ፣ የወተት እና የሥጋ ተዋጽዖዎችን)፣ የእርሻ ምርቶችን (ሰብሎች፣ አትክልት፣ ፍራፍሬ እና አበባዎች)፣ የባሕር ምግቦች (ዓሣ)፣ የንጽህና

መጠበቂያ ምርቶች (ሣሙና….) የታሸጉ ምርቶች፣ መጠጦች እና ሌሎች የፋብሪካ ውጤቶችን (የጽሕፈት መሣሪያዎችን፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን እና

የቤት ውስጥ የመገልገያ ዕቃዎች) በችርቻሮ እና በጅምላ በመሸጥ እና በማከፋፈል ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡

የሪቴል ግሩፕ ፕሪንሰፓል ኦፕሬሽን ኦፊሰር ወ/ሮ ታህሳሥ ወንድምነህ

ዶ/ር አረጋ ይርዳው ሱፐርማርኬቱን ሲያስጎበኙ

Page 6: ከሊቀመንበሩ ማኀደር - MIDROCmidroc-ethiotechgroup.com/sites/default/files/Newsletters/R_issue_9… · ሼህ አብደላ ሁሴን አሊ አል-አሙዲ ከዶ/ር

6

MIDROC NewsletterVolume 17, Issue # 94 August 2019

Addis Ababa, Ethiopia

በዚሁ የምረቃ ሥነ-ሥርዓት ላይ ለፕሮጀክቱ መሳካት አሰተዋጽኦ ያበረከቱ ድርጅቶችና ግለሰቦች፤ የተዘጋጀላቸውን ሠርቲፊኬት ከዕለቱ የክብር እንግዳ ከሼህ አብደላ ሁሴን አሊ አል-አሙዲ እጅ ተቀብለዋል፡፡

የምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ፤ የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ሥራ አስፈጻሚ ተወካይና ሌሎች ከፍተኛ የሥራ አመራሮች፣ የሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ከፍተኛ

የሥራ ኃላፊዎች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እና ደንበኞች በተገኙበት ተካሂዷል፡፡

ወ/ሮ ታህሳሥ በዚሁ ንግግራቸው፤ ኩባንያው በአሁኑ ጊዜ የካፒታል መጠኑ ወደ ብር 23,786,000፣ የሠራተኞቹ ብዛት ወደ 142 (132 ቋሚ እና 10

ኮንትራት) ማደጉን አመልክተው፤ ዓመታዊ ሽያጩም ሥራ ሲጀምር ከነበረው ከብር 12,192,000 ወደ ብር 157,000,000 ማደጉን አስታውቀዋል፡፡

አያይዘውም ኩባንያው ቅርንጫፎቹን ወደ ሰባት በማሳደግ ጥራት ያላቸውን ምርቶች በበቂ ሁኔታ በማቅረብ ላይ እንደሚገኝ እና ተጨማሪም አንድ የዳቦ

ማምረቻና መሸጫ በመቻሬ ቅርንጫፍ በማቋቋም ለሠራተኞችና ለኀብረተሰቡ አገልግሎት በመስጠት ላይ መሆኑን አስረድተው፤ ሱፐርማርኬቱ ለ50 ተጨማሪ

ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠሩንና ዓመታዊ ሽያጩም ብር 75,000,000 እንደሚሆን፤ የኩባንያውን ዓመታዊ የሽያጭ መጠንንም በግማሽ በማሳደግ አስተዋጽዖ

እንደሚያደርግ አሰታውቀዋል፡፡

ወ/ሮ ታህሳሥ ለኩዊንስ ኩባንያ መቋቋምና በዚህ ደረጃ መስፋፋት ምክንያት ለሆኑት ለሚድሮክ ኢትዮጵያ ሊቀመንበርና ባለሀብት ለክብር ዶ/ር ሼህ ሙሐመድ

ሁሴን አሊ አል-አሙዲ፣እንዲሁም፣ የቀራኒዮ ቅርንጫፍ ፕሮጀክት በዚህ ለገበያ አመቺ በሆነ ቦታ እንዲገነባ የፕሮጀክት ሀሳብ በማቅረብ፣ አስፈላጊውን በጀት

በመመደብ፣ በፕሮጀክቱ ሂደትም ያልተቋረጠ የዕለት ተዕለት ክትትል በማድረግ፣ የቅርብ አመራር በመስጠት እና አቅጣጫ በማስያዝ ፕሮጀክቱ በአጥጋቢ

ሁኔታ እንዲጠናቀቅ ላበቁት ለዶ/ር አረጋ ይርዳው የሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ቺፍ ኤግዚኪዩቲቭ ኦፊሰር እና ፕሬዚዳንት፤ ከፍተኛ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ዶ/ር አረጋ ይርዳው ሱፐርማርኬቱን ሲያስጎበኙ

Page 7: ከሊቀመንበሩ ማኀደር - MIDROCmidroc-ethiotechgroup.com/sites/default/files/Newsletters/R_issue_9… · ሼህ አብደላ ሁሴን አሊ አል-አሙዲ ከዶ/ር

7

MIDROC NewsletterVolume 17, Issue # 94 August 2019

Addis Ababa, Ethiopia

ሚድሮክ ወርቅ ማዕድን ...

የገቢዎች ሚኒስቴር ግብር ከፋዮች እንደ አፈጻጸማቸው ለማመስገንና

ለመሸለም በፕላቲኒየም፣ በወርቅና፣ በብር፣ ደረጃ ከመደባቸው 165 ግብር

ከፋዮች መካከል ሚድሮክ ወርቅ ማዕድን ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር

የወርቅ ደረጃ ተሸላሚ ሆነ፡፡

ሚድሮክ ወርቅ ማዕድን ሐምሌ 20 ቀን 2011 ዓ.ም በብሔራዊ ቤተ

መንግሥት በተካሄደው ሥነ-ሥርዓት የወርቅ ደረጃ ተሸላሚ ለመሆን

የቻለው እ.ኤ.አ ለ2017 የግብር አፈጻጸሙ ታማኝ ግብር ከፋይ መሆኑ

በገቢዎች ሚኒስቴር በመረጋገጡ ነው፡፡

በዚሁ ሥነ-ሥርዓት ላይ ኩባንያው የተሸለመውን የወርቅ ደረጃ ሽልማት

የሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ቺፍ ኤግዚኩዩቲቭ ኦፊሰር/ፕሬዚዳንትና

የሚድሮክ ወርቅ ማዕድን ዋና ሥራ አስኪያጅ ዶ/ር አረጋ ይርዳው

ከኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ እጅ ተቀብለዋል ፡፡

ሚድሮክ ወርቅ ማዕድን የወርቅ ደረጃ ተሸላሚ በመሆን እውቅናና

ምስጋና ሊያገኝ የቻለው እ.ኤ.አ በ2017 በጀት ዓመት ንግድ ትርፍ ግብር

ለመንግሥት ብር 471,565,369,63 ለከፍተኛ ግብር ከፋዮች ጽ/ቤት

በወቅቱ በታማኝነት ክፍያ በመፈጸሙ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ሚድሮክ ወርቅ ማዕድን ከማርች 29,1998 እስከ

ማርች 28,2018 ድረስ በነበረው የሥራ እንቀስቃሴ በተሻሻለው የገቢ ግብር

ህግ መሠረት ላለፉት 19 ዓመታት የከፈለውን ስንመለከት፤

• የማዕድን ሥራዎች ገቢ ግብር (ለፌዴራል መንግሥት የተከፈለ) ብር 4,324,669,756፣

• የሮያሊቲ ክፍያ በየሩብ ዓመቱ በተመረተ የማዕድን ዓይነትና መጠን ላይ የሚጣል (ለፌደራል መንግሥት የተከፈለ) ብር 1,332,287,712፣

• የደመወዝ ገቢ ግብር፣ በየወሩ በሚገኝ የደመወዝ ገቢ ላይ የሚጣል (ለአዶ ሻኪሶ ወረዳ ገቢዎች ቢሮ የተከፈለ) ብር257,583,604፣

• የማምረቻ እና የከተማ ቦታ ኪራይ ግብር፣ፌዴራል እና በክል ታሪፍ መሠረት በየዓመቱ የሚከፈል (ለአዶ ሻኪሶ ወረዳ ገቢዎች ቢሮ የተከፈለ) ብር 15,658,235፣

• የአክሲዮን ድርሻ ትርፍ ግብር፤በዓመታዊ የ98% የአክሲዮን ባለድርሻዎች ላይ የሚጣል (ለከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ ቤት የተከፈለ) ብር 746,435,960፤

• የመንግሥት የአክሲዮን ድርሻ ትርፍ፤ በዓመታዊ የተጣራ ትርፍ ላይ የሚከፈል (ለፌዴራል መንግሥት የተከፈለ)ብር 248,012,134

• የደመወዝ ገቢ ግብር፣በየወሩ በሚገኝ የደመወዝ ገቢ ላይ የሚጣል (ለከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ ቤት የተከፈለ) ብር 58,749,801 ሲሆን

• የዚህ ሁሉ ክፍያ ጠቅላላ ድምር 6,983,397,202 ብር መሆኑን የድርጅቱ የፋይናንስ አፈፃፀም ያስረዳል፡፡

ሚድሮክ ወርቅ ማዕድን በታማኝነት በግብር ከፋይነቱ የወርቅ ደረጃ ተሸላሚ

መሆኑ የሚያኮራ ነው፡፡ ግብር የመክፈል ግዴታን በታማኝነት መወጣት

አገርን፣ ወገንን እና ትውልድን የሚጠቅም መሆኑ ግልጽ ነው፡፡

ሚድሮክ ወርቅ ማዕድን 1200 ሠራተኞች የሚያሰተዳድር ሲሆን ማኅበራዊ

ኃላፊነትን በመወጣት ረገድ ለአካባቢው ህብረተሰብ ለመሠረተ ልማት

ዝርጋታ ማለትም፤ለመንገድ፣ ለንጹህ መጠጥ ውሃ፣ ለጤና እና ለሚድሮክ

ወርቅ መንደር ግንባታ፣ በአጠቃላይ የህብረተሰብ አቀፍ የልማት አጋርነት

ለበጎ ሥራዎች ከብር 311.6 ሚለዮን በላይ በማውጣት የበኩሉን አስተዋጽኦ

ያበረከተ ግዙፍ ኩባንያ መሆኑ የሚታወቅ ነው፡፡

ሚድሮክ ወርቅ ማዕድን ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኀበር /ኩባንያ/ ለማዕድን

አውጪው ኢንዱስትሪና ባጠቃላይ ለአገሪቱ ያደረገውን አስተዋጽኦ ከላይ

ከተገለጸው የወርቅ ደረጃ የሽልማት ዜና ጋር በማያያዝ ስለ ኩባንያው

ከኢትዮጵያ የማዕድን አውጪ ኢንዱስትሪዎች ግልጽነት ኢኒሼቲቭን እውን

ለማድረግ በተመሰረተ ተቋም የተገለጸውንና እ.ኤ.አ. ለ2013/2014 በጀት

ዓመት ከተዘጋጀው ዓመታዊ ዘገባ የተገኘውን መረጃ እናሰቃኛችሁ፡-

ከዚህ በታች የሚገኙት የፋይናንስ ትንተናዎች ሚድሮክ ወርቅ ማዕድን

ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኀበር /ኩባንያ/ ለማዕድን አውጪው ኢንዱስትሪና

ባጠቃላይ ለአገሪቱ ያደረገውን አስተዋጽኦ በተመለከተ ከኢትዮጵያ የማዕድን

አውጪ ኢንዱስትሪዎች ግልጽነት ኢኒሼቲቭን እውን ለማድረግ የተመሰረተ

ተቋም እ.ኤ.አ. ለ2013/2014 በጀት ዓመት ካዘጋጀው ዓመታዊ ዘገባ የተገኘ

መረጃነው፡፡ በደንቡ መሰረት ለባለቤትነት እውቅና ክፍያ፣ ለማዕድን የገቢ

ታክስ፣ ለስኬጁል ሲ (ማዕድን ቁፈራ) ለተጨማሪ እሴት ታክስ፣ ለተከፋይ

ድርሻ ክፍያ፣ ለሰራተኞች የገቢ ግብር፣ ለጡረታ መዋጮ እና እንዲሁም

የነጻ ተሳትፎ ወለድ (ፍሪኤኩቲ) ክፍያዎችን ተግባራዊ አድርገናል፡፡

ሚድሮክ ወርቅ፣ ከገጽ 1 የዞረ

Page 8: ከሊቀመንበሩ ማኀደር - MIDROCmidroc-ethiotechgroup.com/sites/default/files/Newsletters/R_issue_9… · ሼህ አብደላ ሁሴን አሊ አል-አሙዲ ከዶ/ር

8

MIDROC NewsletterVolume 17, Issue # 94 August 2019

Addis Ababa, Ethiopia

1. በሴክተሮች የሚደረግ አስተዋጽኦ የክፍያ ትንተና

በማዕድናት አውጪ የኢኮኖሚ ዘርፍ የተደረጉ የመንግስት ክፍያዎች እንደሚያመለክቱት እነኚህ በሶስት ንዑሳን ዘርፎች የተከፋፈሉ ማለትም (ወርቅና

የተዛማጅ ማዕድናት፣ ሲሚንቶ፣ ነዳጅና ጋዝ) የማዕድናት አውጪ ኩባንያዎች ከጁላይ 8 ቀን 2013 እ.ኤ.አ. እስከ ጁላይ 7 ቀን 2014 እ.ኤ.አ ድረስ

ያለውን አጠቃላዩን የመንግሥት ዓመታዊ ገቢ 89.4በመቶ አካባቢ አስተዋጽኦ አድርገዋል፡፡

በዚሁ ወርቅ ከወርቅና ተዛማጅ ማዕድናት ኩባንያዎች የተገኘው ገቢ ከጠቅላላው የማዕድን አውጪው የቁፋሮው ኢንዱስትሪ ከተገኘው ገቢ 40.7 በመቶ

ነው፡፡

ሰንጠረዥ – 1: በየሴክተሩ የተደረገ አስተዋጽኦ

2. የሚድሮክ ወርቅ ኩባንያ በዘርፉ ያደረገው አስተዋጽኦ

የወርቅና የተዛማጅ ማዕድናት ኩባንያዎች ለመንግሥት ያደረጉትን ገቢ በተመለከተ የተደረገው ትንተና እንደሚያሳየው የኢትዮጵያ የበጀት ዓመት 8

ጁላይ 2013 እ.ኤ.አ እስከ 7 ጁላይ 2014 እ.ኤ.አ ሁለት (2) ኩባንያዎች የኢትዮጵያን ዓመታዊ ገቢ 40.7 በመቶ ለመንግሥት ገቢ አድርገዋል፡፡ በዚያ

ዓመት በጠቅላላው አገሪትዋ ካስገባችው ከማዕድን ዘርፉ ኢኮኖሚ ገቢ 99% ከሚድሮክ ወርቅ ማዕድን ኩባንያ የተገኘ ነው፡፡

ሰንጠረዥ – 2: የሚድሮክ ወርቅ ኩባንያ ለሴክተሩ ያደረገው አስተዋጽኦ

Page 9: ከሊቀመንበሩ ማኀደር - MIDROCmidroc-ethiotechgroup.com/sites/default/files/Newsletters/R_issue_9… · ሼህ አብደላ ሁሴን አሊ አል-አሙዲ ከዶ/ር

9

MIDROC NewsletterVolume 17, Issue # 94 August 2019

Addis Ababa, Ethiopia

3. የክፍያው ዝርዝር ትንተና ከኩባንያዎች አስተዋጽኦ አንጻር

የማዕድን ኩባንያዎች ለመንግሥት ገቢ ያደረጉት አስተዋጽኦ ሲታይ ከ8 ጁላይ 2014 እ.ኤ.አእስከ 7 ጁላይ 2014 እ.ኤ.አ ባለው በጀት ዓመት ከጠቅላላው

የመንግሥት ገቢ ድርሻ 16 ኩባንያዎች 89%ገደማ ገቢ አድርገዋል፡፡ ከዚህ ጠቅላላ የማዕድን አውጪ ኢንዱስትሪ ገቢ ሚድሮክ ወርቅ ማዕድን ኃላፊነቱ

የተወሰነ የግል ማኅበር ገቢ ያደረገው40.4%ነው፡፡በሰንጠረዥ3 ዝርዝር ትንተና እንደሚታየው ከጠቅላላው ለመንግሥት ገቢ ከተደረገው በሲሚንቶ

ምርት የተሰማሩ 9 ኩባንያዎች ወደ 39.8% የሚጠጋ አስተዋጽኦ ሲያደርጉ 6 በነዳጅና በጋዝ ምርት የተሰማሩ ኩባንያዎችም በዚህ በተጠቀሰው የበጀት

ዓመት 8.9%ገቢ እንዳደረጉ መገንዘብ ተችሏል፡፡ እንዲሁም በዚያ በተጠቀሰው ዓመት በማዕድን ማውጣት ተግባር የመንግሥት ድርሻ 10.9%ገደማ

ገቢ አስገኝተዋል፡፡

ሰንጠረዥ – 3: ሚድሮክ ወርቅ ማዕድን ኩባንያ ለአገሪቷ ያደረገው አስተዋጽኦ

4. የማዕድን ገቢ ታክስ፣ ስኬጁል ሲ (ማዕድን ቁፈራ)

እንደገለልተኛው አስተዳዳሪ ዘገባ መንግሥት ከማዕድን ከሚያገኘው ጠቅላላ የተገናዘበ ሂሣብ ገቢ 29%ቱ ከማዕድን የገቢ ታክስ ስኬጁል ሲ የሚገኝ

ነው፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ በተጠቀሰው ዓመት ከተደረገው ክፍያ ውስጥ 98%የማዕድን የገቢ ታክስ የስኬጁል ሲ የተገኘው ከሚድሮክ ወርቅ ማዕድን

ኩባንያ ነው፡፡

ሰንጠረዥ – 4: የሚድሮክ ወርቅ ኩባንያ ለማዕድን የገቢ ታክስ ስኬጁል ሲ ያደረገው አስተዋጽኦ

Page 10: ከሊቀመንበሩ ማኀደር - MIDROCmidroc-ethiotechgroup.com/sites/default/files/Newsletters/R_issue_9… · ሼህ አብደላ ሁሴን አሊ አል-አሙዲ ከዶ/ር

10

MIDROC NewsletterVolume 17, Issue # 94 August 2019

Addis Ababa, Ethiopia

5. የባለቤትነት እውቅና ክፍያ

በማዕድን አውጪ ኢንዱስትሪ የተሰማሩ 169 የግል ድርጅቶች በኢትዮጵያ የበጀት ዓመት (8 ከጁላይ 2013 እ.ኤ.አ.) ለመንግሥት የሚያስገኙት

የባለቤትነት እውቅና ክፍያ ገቢ ከጠቅላላው ከሚሰበሰበው ዓመታዊ የታክስ ገቢ 5%ቱን ይሸፍናል፡፡

በተጠቀሰው የበጀት ዓመት በዚህ የክፍያ ሥርዓት የሚድሮክ ወርቅ ማዕድን ኃ.የተ.የግ.ማ ኩባንያ ለመንግሥት የከፈለው ከጠቅላላው የአገሪቱ የማዕድን

አውጪ ኢንዱስትሪ የባለቤትነት እውቅና (ሮያሊቲ) ክፍያ 92%ነው፡፡

ሰንጠረዥ – 5: በባለሌትነት እውቅና ክፍያ ሚድሮክ ወርቅ ኩባንያ አስተዋጽኦ

6. የትርፍ ክፍፍል ታክስና ካፒታል (ኤኩዩቲ)

በተጠቀሰው የበጀት ዓመት 4 ኩባንያዎች 120,286,275 ብር የትርፍ ክፍፍል ታክስ ለመንግሥት የከፈሉ ሲሆን፣ ከዚህም ክፍያ ውስጥ 98%ቱ

የሚድሮክ ወርቅ ማዕድን ኩባንያ ድርሻ ነው፡፡

ሰንጠረዥ – 6: የትርፍ ክፍፍል ታክስ የሚድሮክ ወርቅ ኩባንያ አስተዋጽኦ

Page 11: ከሊቀመንበሩ ማኀደር - MIDROCmidroc-ethiotechgroup.com/sites/default/files/Newsletters/R_issue_9… · ሼህ አብደላ ሁሴን አሊ አል-አሙዲ ከዶ/ር

11

MIDROC NewsletterVolume 17, Issue # 94 August 2019

Addis Ababa, Ethiopia

ዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ የ36ኛ ዙር ተማሪዎቹን አስመረቀ

ዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ በመጀመሪያና በሁለተኛ ዲግሪ መርሀ ግብሮች

ያሰለጠናቸውን የ36ኛ ዙር ተማሪዎቹን ሐምሌ 20 ቀን 2011 ዓ.ም

በሚሊኒየም አዳራሽ ፕሮፌሰር ሂሩት ወ/ማርያም፣ የሳይንስና ከፍተኛ

ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር፣ የተመራቂ ወላጆች፣ ጥሪ የተደረገላቸው

እንግዶች በተገኙበት አስመርቋል፡፡

በ36ኛው ዙር የዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች የምረቃ ሥነ-ሥርዓት ላይ

ፕሮፌሰር ሂሩት ወ/ማርያም፣ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር

ሚኒስትር ባደረጉት ንግግር በሀገራችን የመጀመሪያው የግል ዪኒቨርሲቲ

በመሆን በመንግስት እውቅና የተሰጠው ዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ ላለፉት ሶስት

አስርት ዓመታት በተለያዩ የትምህርት ደረጃዎች ተደራሽነቱን ለማስፋት

ባደረገው ጥረት ስርዓት ለመጠበቅና ለማሻሻል እንዲሁም ፍትሀዊነትን

ለማረጋገጥ መንግሥት ለሚያደርገው እንቅስቃሴ ላበረከተው ጉልህ

አስተዋጽዖ ልዩ ቦታ ሊሰጠው ይገባል ብለዋል፡፡

የአዲስ አበባ ተመራቂ ተማሪዎች በከፊል

የዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ ሴኔት ከፕሮፌሰር ሂሩት ወ/ማርያም፣ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ጋር

Page 12: ከሊቀመንበሩ ማኀደር - MIDROCmidroc-ethiotechgroup.com/sites/default/files/Newsletters/R_issue_9… · ሼህ አብደላ ሁሴን አሊ አል-አሙዲ ከዶ/ር

12

MIDROC NewsletterVolume 17, Issue # 94 August 2019

Addis Ababa, Ethiopia

ሚኒስትሯ አያይዘውም ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ የሀገሪቱ

ኢኮኖሚ እያደገ በሄደ ቁጥር የሚፈለገው የሰው ኃይል

በቁጥርም በጥራትም እየጨመረ ስለሚመጣ የየወቅቱን

የእድገት እርምጃና የሥራ ገበያ ፍላጎት የሚመጥን

የማስተማር የምርምርና ሕብረተሰብ አገልግሎት ሥራ

መሥራት የሚጠበቅበት መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ተገንዝቦ

የፕሮግራም አድማሱን ከደንበኞችና ከሀገራችን ፍላጎት ጋር

በማገናዘብ እና የአገልግሎት ጥራቱን በማሻሻል አጋርነቱን

አጠናክሮ እንዲቀጥልበት በዚህ አጋጣሚ አደራ ለማለት

እወዳለሁ በማለት ገልጸዋል::

በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንት

ዶ/ር አረጋ ይርዳው በበኩላቸው ባደረጉት ንግግር፤ ትምህርት

ለአንድ ሀገር ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ እድገት

ዋንኛውን ሚና እንደሚጫወት ለሁላችንም ግልጽ ነው::

ይህም ማለት አንድ ሕብረተሰብ ብቁና ምርታማ የሰለጠነ

የሰው ኃይል ካለው ለሁለንተናዊ እድገትም ሆነ በዓለም

ተወዳዳሪ የመሆን ዕድሉ እጅግ ከፍተኛ ነው:: በመሆኑም

በትምህርት ዘርፍ የሚሳተፉ ተቋማት ለትምህርት ጥራት

መረጋገጥ የሚሰጡት ትኩረትና የሚያደርጉት ተግባራዊ

እንቅስቃሴ ለአንድ ሀገር ህልውና ወሳኙን ድርሻ ይወስዳል

በማለት አስገንዝበዋል::

ዶ/ር አረጋ አያይዘውም ዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ እንደ አንድ

የከፍተኛ ትምህርት ተቋም ይህንን ትልቅ ሀገራዊ ኃላፊነት

ለመወጣት ላለፉት በርካታ ዓመታት ከተደራሽነት ባሻገር

በትምህርት ጥራት ላይ ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት

የሚቻለውን ሁሉ ሲያደርግ መቆየቱን አስታውሰው፤

በአሁኑ ወቅትም ይህንኑ በማጠናከር ትኩረት ሰጥቶ

እየሠራ ይገኛል ብለዋል::

ፕሮፌሰር ሂሩት ወ/ማርያም ንግግር ሲያደርጉ

የዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር አረጋ ይርዳው ንግግር ሲያደርጉ

በዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ተወካይ ንግግር ሲያደርግ

Page 13: ከሊቀመንበሩ ማኀደር - MIDROCmidroc-ethiotechgroup.com/sites/default/files/Newsletters/R_issue_9… · ሼህ አብደላ ሁሴን አሊ አል-አሙዲ ከዶ/ር

13

MIDROC NewsletterVolume 17, Issue # 94 August 2019

Addis Ababa, Ethiopia

የከፍተኛ ትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ ከታች ከጅምሩ ሕጻናት ላይ

በትኩረት መሥራት አስፈላጊ መሆኑን የገለጹት ዶ/ር አረጋ፣ ይህንንም

የዩኒቨርሲቲው ማኔጅመንት ስለተገነዘበ፤ ካለፉት ዓመታት ጀምሮ ከአፀደ

ሕጻናት እስከ 12ኛ ክፍል ተማሪዎችን ተቀብሎ በማስተማር ላይ እንደሚገኝ

አስታውቀዋል:: ይህ አሰራርም የከፍተኛ ትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅና

ለማሳለጥ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያደርግ አሰገንዘበው በቀጣይም

ዩኒቨርሲቲያችን የዶክትሬት ዲግሪ ፕሮግራም ለመጀመር እየሠራ ይገኛል::

ይህ ደግሞ ተቋማችንን በትምህርት ዘርፍ ከቅድመ መደበኛ (KG) እስከ

ዶክትሬት ድረስ ተሳታፊ ያደርገዋል በማለት ተናግረዋል::

የዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ ተመራቂ ተማሪዎች ኮሚቴ ሰብሳቢ ሄኖክ ተስፋዓለም

ጸጋዬ በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ባደረገው ንግግር፤ በግንባር ቀደምትነት

ደግሞ በተመረቅንበት የትምህርት ዘርፍ የበኩላችንን ጠንካራ አስተዋጽኦ

ለአገርና ለወገን በመደመር፣ በአንድነትና በሰላም እሳቤ እንድናበረክት እና

የዩኒቨርሲቲያችን ኩሩና ብቁ አምባሳደሮችም እንድንሆን ዘወትር ራሳችንን

እያበቃን፣ የዓለማችንና የሀገራችን የሥራ ገበያ የሚፈልገውን ሁሉ

ለመመለስ እንድንችል ሀገራዊና ተቋማዊ አደራ እንደተጣለብን በድጋሚ

አበክሬ ላሳስባችሁ እወዳለሁ ብሏል::

በማያያዝም ለዚህም ተጨማሪ አቅም ይፈጥርልንና ድጋፍም ይሆነን

ዘንድ ዩኒቨርሲቲያችን እያጠናከረ ባለው የድህረ ምረቃ ፕሮግራም እና

የቀድሞ ተማሪዎች ማህበር ምስረታ መርሐ ግብሮች ላይ በመሳተፍ

በቀጣይነት እራሳችንን ይበልጥ እያሻሻልን እና ትስስራችንም እያጠናከርን

እንደምንቀጥልና ለሌሎችም አርአያ እንደምንሆን እተማመናለሁ በማለት

ተናግሯል::

በዘሁ የምረቃ ሥነ- ስርዓት ላይ የዓመቱን የላቀ ውጤት ያመጡ

ተመራቂዎች የወርቅ ሜዳልያ፣ የሊቀመንበሩንና የፕሬዚዳንቱን ዋንጫ

ከክብር እንግዳዋ እጅ ተቀብለዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ ላለፉት ሰባት ዓመታት፣ በየምርቃት

ሥነ-ሥርዓቱ፣ በሊቀመንበራችን በክብር ዶ/ር ሼህ ሙሐመድ ሁሴን አሊ

አል-አሙዲ ስም የተሰየመውን የሜዳሊያ ሽልማት በተለያዩ የሙያ መስኮች

ለተሰማሩ 26 ሰዎች መስጠቱ ይታወሳል፡፡ ዘንድሮም በ36ኛው የዩኒቲ

ዩኒቨርሲቲ የምርቃ ሥነ-ሥርዓት ላይ ለረጅም ዘመን የላቀ አገልግሎት

የሚሰጠውን፣ ይህንኑ የሜዳሊያ ሽልማት ለአራት ሰዎች ሰጥቷል፡፡

በተያያዘ ዜና ዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ በዩኒቲ አዳማ ካምፓስ በ36ኛ ዙር

በመጀመሪያና በሁለተኛ ዲግሪ መርሀ ግብር ያስተማራቸውን 225

ተማሪዎች አስመረቀ፡፡ በካምፓሱ ታሪክ በሁለተኛ ዲግሪ በማስተርስ ኦፍ

ቢዝነስ አድሚኒስትሬሽን ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ ተማሪዎች የተመረቁት

ለመጀመሪያ ጊዜ ነው፡፡

በዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ አዳማ ካምፓስ ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ ምሩቃን፡

የአዳማ ከተማ ከንቲባ ተወካይ አቶ ደረሰ ፈይሳ በክብር እንግድነት

በተገኙበት በመጀመሪያና በሁለተኛ ዲግሪ ተመርቀዋል፡፡

በዚህ የምረቃ ሥነ ስርዓት ላይ የሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ቺፍ

ኤግዚኪዩቲቭ ኦፊሰርና የዩኒቲ ዪኒቨርሲቲ ፕሬዚደንት ዶ/ር አረጋ ይርዳው

ባደረጉት ገለፃ የዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ አዳማ ካምፓስ የዛሬዎቹ ተመራቂዎቸ

እንኳን ለዚህ ቀን አደረሳችሁ፣ ቀጣዩን የሥራ ምዕራፍ የምትገናኙበት

የመጀመሪያው ቀን በመሆኑ ልዩ ቀን ነው ብለዋል።

የዓመቱን የላቀ ውጤት ያመጡ ተመራቂዎች የወርቅ ሜዳልያ፣

የሊቀመንበሩንና የፕሬዚዳንቱን ዋንጫ ከክብር እንግዳው እጅ ተቀብለዋል።

ወ/ሮ መሰንበት ሸንቁጤ የአዲስ አበባ ንግድ ምክር ቤት የመጀመሪያዋ ሴት ፕሬዚዳንት

አቶ ታደለ ይመር የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ አሠሪዎች ኮንፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት

ዶ/ር ቡቴ ጎቱ የፕሬዚደንቱ ከፍተኛ አማካሪ (Senior Advisor)

አቶ ካሳሁን ፎሎ የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት

Page 14: ከሊቀመንበሩ ማኀደር - MIDROCmidroc-ethiotechgroup.com/sites/default/files/Newsletters/R_issue_9… · ሼህ አብደላ ሁሴን አሊ አል-አሙዲ ከዶ/ር

14

MIDROC NewsletterVolume 17, Issue # 94 August 2019

Addis Ababa, Ethiopia

ከአዳማ ካምፓስ የምረቃ ሥነ-ሥርዓት በከፊል

Page 15: ከሊቀመንበሩ ማኀደር - MIDROCmidroc-ethiotechgroup.com/sites/default/files/Newsletters/R_issue_9… · ሼህ አብደላ ሁሴን አሊ አል-አሙዲ ከዶ/ር

15

MIDROC NewsletterVolume 17, Issue # 94 August 2019

Addis Ababa, Ethiopia

ድጋፍ ይሰጣል፣ ያበረታታልም:: በተለይም ተመራማሪዎች ችግር ፈች

በሆኑ ጉዳዮች ላይ ትኩረት እንዲሰጡ በየጊዜው ድጋፍ ያደርጋል::

ዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ በየዓመቱ በርካታ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች

ዓቅሙ በፈቀደ መሠረት የነፃ ትምህርት ዕድል ሰጥቷል አሁንም

እያስተማረ ይገኛል:: ለሚድሮክ ኢንቬስትመንት ግሩፕ ኩባንያ

ሠራተኞችና ቤተሰቦቻቸው ልዩ የትምህርት ክፍያ ቅናሽ በማድረግ

የማህበራዊ አገልግሎት አስተዋጾ ያደርጋል::

ዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ በ26ቱ የሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ የተካተተ

እንደመሆኑ፤ በዩኒቨርሲቲውና አምራችና አገልግሎት ሰጭ በሆኑት

ኩባንያዎች መካል ማለትም በአካዳሚክሱና በኢንዱስትሪው መካከል

ቁርኝት (Synergy) በመፍጠር ውጤታማ ተግባር ሠርቷል፣ ይሰራም::

ዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ የዩኒቨርሲቲውን ማህበረሰብ ተሳታፊ ከማድረግ አኳያ፣

የቀድሞ ተማሪዎች ስብስብ (Alumni) እንዲኖር ከፍተኛ ትኩረት

በመስጠት በዳይሬክተር የሚመራ የአሉምናይ ክፍል አቋቁሟል::

በዚህ ተግባርም በሀገራችን በከፍተኛ ደረጃ በሥራ ላይ የሚገኙ የቀድሞ

የዩኒቨርሲቲው ምሩቃንን በማሰባሰብ የዩኒቨርሲቲውን የአካዳሚ ተግባር

ለሥራ ዓለሙ ተደራሽ ለማድረግና የአሉምናይ አባላቱንም ቤቴሴቦች

የዩኒቨርሲቲውን ማህበረሰብ እንዲቀላቀሉ በማድረግ ተጠቃሚ እንዲሆኑ

የማድረግ ዕቅዱን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅቱን አጠናቋል::

የዘንድሮ ተመራዎችም የዚህ የአሉምናይ አባልነት የውዴታ መብታችሁ

ስለሆነ እንድትጠቀሙበት ከወዲሁ ጥሪዬን አቀርባለሁ::

ዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ በአሁኑ ወቅት በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ማለትም

በቢዝነስ፣ በኢኮኖሚክስ፣ በኢንጂነሪንግ፣ በቴክኖሎጂ፣ በጠየናና በእርሻ

መርሃግብሮ በመጀመሪያና እንዲሁም በቢዝነስ፣ በኢኮኖሚክስና

ሊደርሺፕ መርሃ ግብሮች በሁለተኛ ዲግሪ በአዲስ አበባ፣ በአዳማ፣

በቡራዩና በደሴ ትምህርት እየሰጠ ሲሆን፣ በርቀት ትምህርት ደግሞ

በተለያዩ የክልል ከተሞች ማዕከላትን በመከፈት የመጀመሪያ ዲግሪ

ትምህርት እየሰጠ ይገኛል::

ዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ የጤናውን ኮሌጅ ወደ ሜዲካል ኮሌጅ ለማሳደግ

የትምህርት ሚኒስቴርንና የጤና ጥበቃ ሚኒስቴርን መስፈርት

ለማሟላት፣ ጠንክሮ እየሰራ መሆኑን ስገልጽ ተቋማችን በጤናው

ዘርፍ ላይም በትኩረት እየሠራ መሆኑን ለመጥቀስ ያህል ነው::

ዩኒቨርሲቲያችን ለተለያዩ ተቋማት ሰራተኞች የአጫጭር ጊዜ

ስልጠናዎችንም “Executive Classes” በመስጠት የታወቀ ሲሆን

በተለይ ደግሞ በሊደርሽፕና በማኔጅመንት ለኩባንያዎችና ለተለያዩ

መሥሪያ ቤት ኃላፊዎች ሥልጠና እየሰጠ ይገኛል::

ውድ የእለቱ የእጩ ተመራቂዎች፣ ቤተሰቦችና መምህራን

ትምህርት የማይሰረቅ፣ የሚያስከብር፣ ከብዙ ነገር ነጻ የሚያደርግ፣

ለሚፈልጉ ደግነትን የሚያሰርጽ፣ እና ከችግር የሚታደግ ከፍተኛ ሀብት

ነው:: ይህን መሳይ ትልቅ እሴት በስጦታ ለእነዚህ እጩ ተመራቂዎች

መምህራንና ቤተሰቦች በታላቅ መስዋዕትነት ስላበረከታችሁላቸው እጅግ

በጣም ልትመሰገኑ ይገባል:: ፈጣሪ ውለታችሁን ይክፈላችሁ::

እጩ ተመራቂዎች ለዚህ ቀን ለመድረስ ያደረጋችሁት ጥረት

በትምህርቱ ዓለም ውጤታማ እንድትሆነ አብቅቷችኋል:: ለፍቶ፣

ጥሮ፣ ግሮ ውጤት ማግኘት ያስደስታል:: ያረካልም::

በአሁኑ ጊዜ ወይም ወቅት ቀጣዩን የሥራ ዓለም ለመቀላቀልና

ውጤታማ ለመሆን የምታደርጉት ጥረት አልጋ ባልጋ ሳይሆን እጅግ

አልህ አስጨረሽ እንደሚሆንባችሁ ሀቁን ልነግራችሁ እወዳለሁ::

ይህም አባባል ወቅታዊውን የሀገራችንን የሥራ ፈላጊና የሥራ አቅራቢ

ከፍተኛ ክፍተትን ከግንዛቤ በማስገባት ነው:: ስለዚህ ሥራ የማግኘትም

ሆነ የመፍጠር ጥረታችሁን ተስፋ ባለመቁረጥ ሁሉንም ዓይነት ሥራ

በማክበር እና በሥራው ዓለም ከተደባለቃችሁ በኋላ ማደግንም ከግንዛቤ

በማስገባት ውጤታማ ለመሆን ከፍተኛ ጥረት ማድረግ ይጠበቅባችኋል::

በሥራ ላይ እያላችሁ የዕውቀት አድማሳችሁን ለማሻሻል ትምህርት

ስትከታተሉ ቆይታችሁ በዛሬው እለት የምትመረቁት ደግሞ

በተሠማራችሁበት የሥራ ዘርፍ ካለፈው የሥራ አፈጻጸማችሁ

የተሻለ ሆኖ ለመገኘት የተማራችሁትን በሥራ ዓለም ላይ ማዋል

ይጠበቅባችኋል:: ዲግሪ ማግኘትን ለደመወዝ ጭማሪ ብቻ ሳይሆን

ለአፈጻጸም ምጥቀትም መጠቀም በአሠሪዎቻችሁ እንደሚጠበቅባችሁ

ከወዲሁ ላስገነዝባችሁ እወዳለሁ::

በሌላ በኩል ትምህርታችሁን መቀጠል የምትሹም ይህንኑ ፍላጎታችሁን

ጊዜ ሳትሰጡ መቀጠሉ በብዙ መልኩ በአሁኑ ጊዜ የሚመረጥ አካሄድ

መሆኑን መገንዘቡ እጅግ ይጠቅማል::

በመጨረሻ መማር፣ እኔ አውቃለሁ፣ የእኔ ሃሳብ ብቻ ተቀባይነት

ሊያገኝ ይገባል፣ ለዛሬው ጥቅም ካስገኘልን ለነገው የነገው ትውልድ

ገዳይ ነው፣ እራስን ከሀገርና ወገን በላይ ተጠቃሚ ለማድረግ መጣር፣

ሰላምን የማደፍረስ፣ ፍልስፍናንና አሉታዊ ትረካን ሙጥኝ የማለት

አባዜ፣ የምዕራቡን፣ የምሥራቁን ወይም ሌላውን መጤ ባህልና ፈሊጥ

የማሞካሸት የራስን የማጠልሸት (ወዘተ) ሥራ በመሥራት አዋቂ

ለመምሰል መጣር ልንጸየፈው የሚገባ ተግባር ነው::

መማር ለበጎ ተግባር፣

ለራስ ለቤተሰብና ለሀገር፣

እንጂ

መማር የችግር ምክንያት፣

ለሀገር ውድቀትና ጥፋት፣

አይገባም ሊሆን፣ እንስጠው ትኩረት::

ይህን ተገንዝባችሁ ከፍተኛ ችግር ላይ ያለችን እናት ሀገር ጥሪዋን

ሰምታችሁ፣ በፖለቲካ ዓለም ብቻ ሳይሆን በተለያዩ የሥራ መስችም

በመሳተፍ፣ ከጥፋት፣ ከመከራ እንድትታደጓት ጥሪዬን እያቀረብኩ፣

መልካሙን ሁሉ በመመኘት በድጋሚ እንኳን ደስ አላችሁ እላለሁ::

ፈጣሪ ኢትዮጵያን ይባርክ!!

አመሰግናለሁ::

አረጋ ይርዳው (ዶ/ር)

የ36ኛው የምረቃ ሥነ-ሥርዓት ...mL:KT½ ከገጽ15 የዞረ

Page 16: ከሊቀመንበሩ ማኀደር - MIDROCmidroc-ethiotechgroup.com/sites/default/files/Newsletters/R_issue_9… · ሼህ አብደላ ሁሴን አሊ አል-አሙዲ ከዶ/ር

16

MIDROC NewsletterVolume 17, Issue # 94 August 2019

Addis Ababa, Ethiopia

አረጋ ይርዳው (ዶ/ር)ግሩፕ ቺፍ ኤግዚኪዩቲቭ ኦፊሰር፣ ሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ

ፕሬዚዳንት - ዩኒቲ ዩኒቨርሲቲArega Yirdaw (Phd.)

Group CEO - MIDROC Technology GroupPresident - Unity University

u’í ¾T>�ÅM (Distributed at no Cost)

Address: MIDROC Technology GroupOffice of the Chief Executive Officer, Fax: +251-11-371-5988 / 372-4977P.O. Box: 5787, Addis Ababa EthiopiaE-mail: [email protected]: www.midroc-ethiotechgroup.com

mL:KT½ kcEF x@Gz!k!†tEV åðsR

የ36ኛው የምረቃ ሥነ-ሥርዓት የፕሬዝዳንቱ የመክፈቻ ንግግር

ክብርት፡ ፕሮፌሰር ሂሩት ወ/ማርያም፣ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት

ሚኒስቴር ሚኒስትር፣

የተከበራችሁ፤ የዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ የሴኔት አባላትና የዩኒቨርሲቲው

ማህበረሰብ፣

የተከበራችሁ፣ ጥሪ የተደረገላችሁ እንግዶች፣ የእጩ ተመራቂ

ቤተሰቦች እና ውድ የዓመቱ እጩ ተመራቂዎች

እንደምን አረፈዳችሁ

ዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ ለ36ኛ ጊዜ የሚያከብረውን የምረቃ በዓል ምክንያት

በማድረግ የደስታችን ተካፋይ ለመሆን በመሀከላችን በመገኘታችሁ

እንኳን ደህና መጣችሁ እያልኩ የአክብሮት ምስጋናዬን አቀርባለሁ::

በተለይም የኢትዮጵያ የሳይንስና የከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትራችን

ክብርት ፕሮፌሰር ሂሩት ወ/ማርያም የክብር እንግዳ በመሆን ፍቃደኛ

ሆነው በመካከላችን በመገኘታቸው እንደተለመደው በመካከላችን

ሊገኙልን እየፈለጉ ሊመቻቸው ባለመቻሉ በመካከላችን ባልተገኙት፣

በዩኒቨርሲቲያችን ሊቀመንበር በሼህ ሙሐመድ ሁሴን አሊ አል-አሙዲ

እና በራሴ ስም ከፍተኛ ምስጋና ማቅረብ እወዳለሁ::

ትምህርት ለአንድ ሀገር ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊና ፖለቲካዊ እድገት

ዋንኛውን ሚና እንደሚጫወት ለሁላችንም ግልጽ ነው:: ይህም

ማለት አንድ ህብረተሰብ ብቁና ምርታማ የሰለጠነ የሰው ኃይል ካው

ለሁለንተናዊ እድገትም ሆነ በዓለም ተወዳዳሪ የመሆን ዕድ እጅግ

ከፍተኛ ነው:: በመሆኑም በትምህርት ዘርፍ የሚሳተፉ ተቋማት

ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ የሚሰጡት ትኩረትና የሚያደርጉት

ተግባራዊ እንቅስቃሴ ለአንድ ሀገር ህልውና ወሳኙን ድርሻ ይወስዳል::

ዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ እንደ አንድ ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ይህንን ትልቅ

አገራዊ ኃላፊነት ለመወጣት ላለፉት በርካታ ዓመታት ከተደራሽነት

ባሻገር በትምህርት ጥራት ላይ ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት የሚቻለውን

ሁሉ ሲያደርግ ቆይቷል:: በአሁኑ ወቅትም ይህንኑ በማጠናከር ትኩረት

ሰጥቶ እየሠራ ይገኛል:: በዚህም ረገድ በሰው ኃይል ልማት ዘርፍ

ብቁ ባለሙያ ለማፍራትና የትምህርቱነህም የጥራት ደረጃ ለማስጠበቅ

ዩኒቨርሲቲያችን በሚከተሉት ዋና ዋና ተግባራት ላይ ባለማሰለስ እየሰራ

ይገኛል::

የከፍተኛ ትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ ከታች ከጅምሩ ሕጻናት ላይ

በትኩረት መስራት አስፈላጊ በመሆኑና፣ ይህንንም የዩኒቨርሲቲው

ማኔጅመንት ስለተገነዘበ፤ ካለፉት ዓመታት ጀምሮ ከአፀደ ሕጻናት

እስከ 12ኛ ክፍል ተማሪዎን ተቀብሎ በማስተማር ላይ ይገኛል::

ይህምየከፍተኛ ትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅና የተሳለጠ እንዲሆን

ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደርጋል:: በቀጣይም ዩኒቨርሲቲያችን የዶክትሬት

ዲግሪ ፕሮግራም ለመጀመር እየሠራ ይገኛል:: ይህ ደግሞ ተቋማችንን

በትምህርት ዘርፍ ከቅድመ መደበኛ (KG) እስከ ዶክትሬት ድረስ

ተሳታፊ ያደርገዋል::

ዩኒቨርሲቲው ጥራትን ለማስጠበቅ የጥራት ቤት ወይም

“Quality House” የሚለውን መርህ በመከተል በየጊዜው

የየፕሮግራሞቹን ሥርዓተ ትምህርት ይፈትሻል ይከልሳል:: እንዲሁም

አዳዲስ ፕሮግራሞችንም ቀርጾ በሥራ ላይ ያውላል:: ባለ ሙያዎችን

ይቀጥራል:: ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር ጥራትን በሚመለከት በልዩ

ሁኔታ አትኩሮት በመስጠት እጅና ጓንት ሆኖ ይሠራል::

የዩኒቨርሲቲያችንን አቅም ከማሳደግና እንዲሁም የትምህርቱን ጥራት

ከማስጠበቅ ረገድ የዩኒቨርሲቲው ማኔጅመንት በየጊዜው ላቦራቶሪዎችን

ዎርክሾፖችንን ሌሎች ግብዓቶችን ለማዘመን ጥረት እያደረገ ይገኛል::

ለምሳሌ በዚህ በያዝነው ዓመት እጅግ ዘመናዊ የሆነ ቤተመፃህፍት

ገርጂ በሚገኘው የአል-አሙዲ ፓምፓስ ገንብቶ የጨረሰ ሲሆን ለቀጣዩ

የትምህርት ዘመን አገልግሎት ይሰጣል::

ለመማር ማስተማር ሂደቱም ሆነ ለጥናትና ምርምር የሚያግዙ

ግብዓቶችን በየጊዜው እንዲሟሉ ያላሰለሰ ጥረት እያደረገ ይገኛል::

ዩኒቨርሲቲው የቴክኖሎጂ፣ የሰው ኃይል፣ የምርምርና የልምድ

ልውውጥ ለመፍጠር ከተለያዩ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር የጋራ

ስምምነት በመፍጠር እየሠራ ይገኛል:: ለምሳሌ ያህል አዲስ አበባ

ዩኒቨርስቲቲ፣ አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ፣ ኦሮሚያ

ስቴት ዩኒቨርሲቲ እና ሌሎች ተቋማትን መጥቀስ ይቻላል::

የመማር ማስተማሩን ሂደት ከመደገፍ አንጻር ዩኒቨርስቲው

ለመምህራንም ሆነ ለተማሪዎ ጥናትና ምርምር እንዲሳተፉ አስፈላጊውን

ወደ ገጽ 15 ዞሯል