ከባንክ ውጭ ከ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር በላይ ማስቀመጥ...

16
79ኛ ዓመት ቁጥር 343 ነሐሴ 13 ቀን 2012 ዓ.ም ዋጋ 5:75 ተጠየቅ 8 ፍረዱኝ 10 ከባንክ ... ወደ ገጽ 4 ዞሯል የአመጽ ... ወደ ገጽ 2 ዞሯል ማስታወቂያ - ኮሚሽነር ጄኔራል አራርሳ መርዳሳ የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን የአመጽ ጥሪ አቅራቢዎች ቅጥረኛና ከሀዲዎች በመሆናቸው ህዝቡ ጆሮ ነስቷቸዋልከባንክ ውጭ ከ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር በላይ ማስቀመጥ ተከለከለ በጋዜጣው ሪፖርተር አዲስ አበባ፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በትናንትናው እለት 10 ሹመቶችን መስጠታቸው ተገለጸ። ጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው ዶ/ር ቀንዓ ያደታ የመከላከያ ሚኒስትር ዶ/ር ጌድዮን ጢሞቴዎስ፤ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዶ/ር ሳሙኤል ሁርካቶ፤ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ኢ/ር ታከለ ኡማ፤ የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስትር አቶ ተስፋዬ ዳባ፤ ምክትል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ አቶ ዮሐንስ ቧያለው፤ የኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት ስትራቴጂክ ጥናት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ንጉሡ ጥላሁን፤ የሥራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን ኮሚሽነር ኢ/ር እንዳወቅ አብቴ፤ የብረታ ብረት ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ፍቃዱ ጸጋ፤ ምክትል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ፕሮፌሰር ኂሩት ወልደ ማርያም፤ በሚኒስትር ማዕረግ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማኅበራዊ ዘርፍ አማካሪ ሆነው ተሹመዋል ። በተያያዘ ዜና ወ/ሮ አዳነች አቤቤን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ም/ከንቲባ አድርጎ ሾሟል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ሹመት ሰጡ • አስተዳደሩ ወ/ሮ አዳነች አቤቤን ም/ከንቲባ አድርጎ ሾመ በጋዜጣው ሪፖርተር አዲስ አበባ፦ በኢትዮጵያ በግለሰቦች ወይንም በኩባንያዎች ከባንክ ውጭ ከ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር በላይ ማስቀመጥ እንደማይቻል የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ አስታወቀ። የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ገዥ ዶክተር ይናገር ደሴ ትናንት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፣ ባንኩ ባለፉት 2 አመታት የተለያዩ የማሻሻያ ስራዎችን ሲሰራ እንደነበረ አስታውቀው፤ የሀገሪቱን የፋይናንስ ስርዓት ዘመናዊ እና ተደራሽ የሚያደርጉ የማሻሻያ ስራዎችን እየሰራ መሆኑን አመልክተዋል ፡፡ በእለቱ ይፋ የተደረጉት የማሻሻያ መመሪያዎች በአምስት ዋና ዋና ነጥቦች ላይ ያተኮሩ እንደሆነ የተናገሩት አቶ ይናገር ደሴ፣ ከብር አያያዝ አንፃር የሚታየውን ችግር ለመቅረፍ ባንኩ አስገዳጅ መመሪያዎችን ማውጣቱን አስታውቀዋል ፡፡ ዶክተር ይናገር በኢትዮጵያ ግለሰቦች ወይንም ኩባንያዎች ከ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር በላይ ከባንክ ውጭ ማስቀመጥ መከልከሉን ጠቅሰው፤ የመንግስትም ሆኑ የግል ባንኮች ከውጭ አበዳሪ ተቋማት በዶላር መበደር ‹‹ኢትዮጵያን የሚጎበኝ ቢኖርም አስተናጋጅ የለም፤ አስጎብኝ የለም መባል የለብንም›› - አቶ ገዛኸኝ አባተ የሆቴልና ቱሪዝም ሥራ ማሰልጠኛ ማዕከል ምክትል ዋና ዳይሬክተር በጋዜጣው ሪፖርተር አዲስ አበባ:- የአመጽ ጥሪ አቅራቢዎች ቅጥረኛ እና ከሀዲዎች መሆናቸው ስለሚታወቅ ህዝቡ በተደጋጋሚ ጆሮ እንደነሳቸው የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄኔራል አስታወቁ። ህዝቡ በተለይም ወጣቱ ለጸረ ሰላም ሃይሎች ጥሪ ጆሮ ባለመስጠት ላሳየው የሰላም አጋርነት ምስጋና አቅርበዋል ። ኮሚሽነር ጄኔራል አራርሳ መርዳሳ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ በሰጡት መግለጫ እንደተናገሩት፤ ለትናንት ተላልፎ የነበረው አይነት ተመሳሳይ የአመጽ ጥሪዎች በተደጋጋሚ አልተሳኩም ፣ ያልተሳኩት ደግሞ የአመጹ ጥሪ አቅራቢዎች ቅጥረኛ እና ከሀዲዎች መሆናቸው ህዝቡ ስለሚያውቅ እንደሆነ አስታውቀዋል እንደ ኮሚሽነር አራርሳ ገለጻ፤ ህዝቡ ትላንት ሲታገል ለምን አደባባይ ይወጣ እንደነበር በደንብ ስለሚያውቅና ዛሬ የሚተላለፈው ተመሳሳይ ጥሪ የፍትህ ያለህ ባዮቹ

Upload: others

Post on 20-Nov-2020

14 views

Category:

Documents


0 download

TRANSCRIPT

Page 1: ከባንክ ውጭ ከ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር በላይ ማስቀመጥ ተከለከለሕግ • ዶ/ር ሳሙኤል ሁርካቶ፤ የሳይንስና ከፍተኛ

79ኛ ዓመት ቁጥር 343 ነሐሴ 13 ቀን 2012 ዓ.ም ዋጋ 5:75

ተጠ

የቅ

8

ፍረ

ዱኝ

10

ከባንክ ... ወደ ገጽ 4 ዞሯል

“ የአመጽ ... ወደ ገጽ 2 ዞሯል

ማስታ

ወቂ

- ኮሚሽነር ጄኔራል አራርሳ መርዳሳ የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን

“የአመጽ ጥሪ አቅራቢዎች ቅጥረኛና ከሀዲዎች በመሆናቸው ህዝቡ

ጆሮ ነስቷቸዋል”

ከባንክ ውጭ ከ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር በላይ ማስቀመጥ ተከለከለ

በጋዜጣው ሪፖርተር

አዲስ አበባ፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በትናንትናው እለት 10 ሹመቶችን መስጠታቸው ተገለጸ። ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው

• ዶ/ር ቀንዓ ያደታ የመከላከያ ሚኒስትር• ዶ/ር ጌድዮን ጢሞቴዎስ፤ ጠቅላይ ዐቃቤ

ሕግ• ዶ/ር ሳሙኤል ሁርካቶ፤ የሳይንስና ከፍተኛ

ትምህርት ሚኒስትር• ኢ/ር ታከለ ኡማ፤ የማዕድንና ነዳጅ

ሚኒስትር• አቶ ተስፋዬ ዳባ፤ ምክትል ጠቅላይ አቃቤ

ሕግ• አቶ ዮሐንስ ቧያለው፤ የኢትዮጵያ የውጭ

ግንኙነት ስትራቴጂክ ጥናት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር

• አቶ ንጉሡ ጥላሁን፤ የሥራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን ኮሚሽነር

• ኢ/ር እንዳወቅ አብቴ፤ የብረታ ብረት ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን ምክትል ዋና ዳይሬክተር

• አቶ ፍቃዱ ጸጋ፤ ምክትል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ

• ፕሮፌሰር ኂሩት ወልደ ማርያም፤ በሚኒስትር ማዕረግ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማኅበራዊ ዘርፍ አማካሪ ሆነው ተሹመዋል ።

በተያያዘ ዜና ወ/ሮ አዳነች አቤቤን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ም/ከንቲባ አድርጎ ሾሟል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ

ሹመት ሰጡ• አስተዳደሩ ወ/ሮ አዳነች አቤቤን ም/ከንቲባ አድርጎ ሾመ

በጋዜጣው ሪፖርተር

አዲስ አበባ፦ በኢትዮጵያ በግለሰቦች ወይንም በኩባንያዎች ከባንክ ውጭ ከ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር በላይ ማስቀመጥ እንደማይቻል የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ አስታወቀ።

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ገዥ ዶክተር ይናገር ደሴ ትናንት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፣ ባንኩ ባለፉት 2 አመታት የተለያዩ የማሻሻያ ስራዎችን ሲሰራ እንደነበረ አስታውቀው፤ የሀገሪቱን የፋይናንስ ስርዓት ዘመናዊ እና ተደራሽ የሚያደርጉ የማሻሻያ ስራዎችን እየሰራ መሆኑን

አመልክተዋል ፡፡በእለቱ ይፋ የተደረጉት የማሻሻያ መመሪያዎች

በአምስት ዋና ዋና ነጥቦች ላይ ያተኮሩ እንደሆነ የተናገሩት አቶ ይናገር ደሴ፣ ከብር አያያዝ አንፃር የሚታየውን ችግር ለመቅረፍ ባንኩ አስገዳጅ መመሪያዎችን ማውጣቱን አስታውቀዋል ፡፡

ዶክተር ይናገር በኢትዮጵያ ግለሰቦች ወይንም ኩባንያዎች ከ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር በላይ ከባንክ ውጭ ማስቀመጥ መከልከሉን ጠቅሰው፤ የመንግስትም ሆኑ የግል ባንኮች ከውጭ አበዳሪ ተቋማት በዶላር መበደር

‹‹ኢትዮጵያን የሚጎበኝ ቢኖርም አስተናጋጅ የለም፤ አስጎብኝ የለም መባል የለብንም››- አቶ ገዛኸኝ አባተ የሆቴልና ቱሪዝም ሥራ ማሰልጠኛ ማዕከል ምክትል ዋና ዳይሬክተር

በጋዜጣው ሪፖርተር

አዲስ አበባ:- የአመጽ ጥሪ አቅራቢዎች ቅጥረኛ እና ከሀዲዎች መሆናቸው ስለሚታወቅ ህዝቡ በተደጋጋሚ ጆሮ እንደነሳቸው የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄኔራል አስታወቁ። ህዝቡ በተለይም ወጣቱ ለጸረ ሰላም ሃይሎች ጥሪ ጆሮ ባለመስጠት ላሳየው የሰላም አጋርነት ምስጋና አቅርበዋል ።

ኮሚሽነር ጄኔራል አራርሳ መርዳሳ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ በሰጡት መግለጫ እንደተናገሩት፤ ለትናንት ተላልፎ የነበረው አይነት ተመሳሳይ የአመጽ ጥሪዎች በተደጋጋሚ አልተሳኩም ፣ ያልተሳኩት ደግሞ የአመጹ ጥሪ አቅራቢዎች ቅጥረኛ እና ከሀዲዎች መሆናቸው ህዝቡ ስለሚያውቅ እንደሆነ አስታውቀዋል ።

እንደ ኮሚሽነር አራርሳ ገለጻ፤ ህዝቡ ትላንት ሲታገል ለምን አደባባይ ይወጣ እንደነበር በደንብ ስለሚያውቅና ዛሬ የሚተላለፈው ተመሳሳይ ጥሪ

የፍትህ ያለህ ባዮቹ

Page 2: ከባንክ ውጭ ከ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር በላይ ማስቀመጥ ተከለከለሕግ • ዶ/ር ሳሙኤል ሁርካቶ፤ የሳይንስና ከፍተኛ

ረቡዕ ነሐሴ 13 ቀን 2012 ዓ.ም

ገጽ 2 ዜና

ደግሞ ለምንና ለማን ፍጆታ እንደሆነ ይረዳል። በመሆኑም ትናንት በኦሮሚያ ክልል የተጠራው የአመጽ ጥሪ ከሽፎ ህዝቡ በተለመደው የእለት ተእለት ስራው ላይ ውሏል።

“በጸጥታው መዋቅር ላይ እየተወሰደ ያለው እርምጃ ለውጥ አምጥቷል፡፡ በገንዘብ ድጋፍ የአመጽ ጥሪን ለማስፈጸም የሚጥሩ የጸጥታ ኃይል አካላት ነበሩ። እነዚህ ወገኖች ከስልጣን በተባረረው ከጥፋት ኃይል ጋር ሆነው ችግር ሲፈጽሙ ቢቆዩም ተለይተውና ተጣርቶ እርምጃ በመወሰዱ አሁን እየታየ ላለው የሰላምና የጸጥታ ለውጥ የራሱን አስተዋጾ አበርክቷል። ለትናንቱ ጥሪ አለመሳካትም የተወሰደው እርምጃ ትልቅ አስተዋጾ አድርጓል”ብለዋል ፡፡

ሰኞ እለት በምዕራብ አርሲ እና በምዕራብ ሀረርጌ አካባቢ የተወሰኑ እንቅስቃሴዎች ቢኖሩም የጸጥታ አካላትና ህብረተሰቡ ባደረጉት የተቀናጀ ጥረት ወዲያውኑ መቆጣጠር ተችሏል ያሉት ኮሚሽነሩ፤ አመጹ በተጠራበት እለት ትናንት ግን በሁሉም የክልሉ ዞኖችና ከተሞች

“የአመጽ ጥሪ አቅራቢዎች ቅጥረኛና ከሀዲዎች...ከ1ኛው ገጽ የዞረ ምንም አይነት የጸጥታ ችግር አልታየባቸውም፤ በአንጻሩ

መደበኛ ሥራ ሲከናወን መዋሉን አመልክተዋል። በማህበራዊ ሚዲያዎች ሲደረግ የነበረው የአመጽ ጥሪ

የወደቀ ሃሳብ በመሆኑ በህዝቡ ዘንድ ተቀባይነት አላገኘም ያሉት ኮሚሽነሩ፤ በተደጋጋሚ በማህበራዊ ሚዲያዎች የሚደረጉ ጥሪዎች ተቀባይነት እያገኙ አይደለም፤ ይህም ህዝቡ “ለሽፍታ እና ለተላላኪ እጅ አንሰጥም” የማለቱ አብይ ማሳያ ነው ሲሉም ተናግረዋል።

“እነዚህ ሃይሎች ጥሪውን ለምን እንደሚያደርጉት በግልጽ ይታወቃል፡፡ ከስልጣን የተባረረው ኃይል በሚሰጠው ገንዘብ የሚከናወን ሥራ ነው፤ ጥሪውን የሚያደርጉት አካላት ገንዘቡን ተቀብለው ሂሳቡን ለማወራረድ የሚሰሩ ተቀጣሪዎች ናቸው” ብለዋል።

ከሰኞ እለት ማታ ጀምሮ በኦሮሚያ ክልል ተቃውሞ እንደተነሳ ግጭት እንደተፈጠረ በማስመስል ከዚህ በፊት የነበሩ የተቃውሞ ምስሎችን በመጠቀም ቅስቀሳ ለማድረግ መሞከሩን የጠቀሱት ኮሚሽነሩ፤ ነገር ግን በክልሉ ትናንት ምንም አይነት ግጭት እንዳልነበረና

የተጎዳ ሰውም እንደሌለ ገልፀዋል።ችግር ቢኖር ኖሮ የክልሉ መንግስት ከዚህ በፊት

በአርቲስት ሀጫሉ ግድያ ወቅት የተፈጠረውን ሳይደብቅ በሙሉ እንዳሳወቀው ሁሉ ያሳውቅ ነበር ያሉት ኮሚሽነሩ፤ ዛሬም ሆነ ወደፊት ችግር ከተፈጠረ የምንደብቅበት ምንም አይነት ምክንያት የለም፤ ከተፈጠረም ወንጀለኞችን ፈልገን ለህግ እናቀርባለን እንጂ የምንደብቀው ጉዳይ አይኖርም ብለዋል።

የአመጽ ጥሪ በተደረገበት እለት በተቃራኒው በአምቦ፣ በጎባ እና በሌሎች ከተሞች ላይ ወጣቶች በጽዳትና መሰል የልማት ስራዎች ላይ ተሰማርተው መዋላቸውን ጠቁመዋል።

ህዝቡ በተለይም ወጣቱ ለጸረ ሰላም ሃይሎች ጥሪ ጆሮ ባለመስጠት ላሳየው የሰላም አጋርነት ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን፤ በቀጣይም በተመሳሳይ ለሰላምና ለልማት ያለውን አቋምና ጽኑ ፍላጎት አጠናክሮ እንዲቀጥል ፤ ከጸጥታ ሃይሉ ጋርም ተባብሮ እንዲሰራ ጥሪ አቅርበዋል ።

ይበል ካሳ

አዲስ አበባ፡- የዘንድሮው የበጎ ሰው ሽልማት ከታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታና ከኮሮና ወረርሽኝ መከላከል ሥራ ጋር ለሕዝብ አርዓያነት ያለው ተግባር ላይ ያተኮረ ሆኖ በልዩ ሁኔታ እንደሚካሄድ ተገለጸ፡፡

ዘንድሮ ለስምንተኛ ጊዜ የሚካሄደውን የበጎ ሰው ሽልማት መርሃ ግብር አስመልክቶ ትናንትና ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡት የበጎ ሰው የሽልማት በጎ አድራጎት ድርጅት የቦርድ ሰብሳቢ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት፤ ወቅታዊ ሁኔታውን ታሳቢ ባደረገ መልኩ የዘንድሮው የበጎ ሰው ሽልማት በዘርፎች ላይ ሳይሆን በሁለት ወቅታዊና ሃገራዊ አንኳር ጉዳዮች ላይ ልዩ አስተዋፅኦ ላበረከቱ ኢትዮጵያውያን የሚሰጥ ይሆናል ብለዋል፡፡

እንደ እርሳቸው ማብራሪያ፤ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት በዓለም ላይም ሆነ በሃገሪቱ ባለው ወቅታዊ ሁኔታ የተነሳ ሽልማቱን በተለመደው መንገድ ለመስጠት አይቻልም፤ በመሆኑም የዘንድሮውን መርሃ ግብር በተለየ መንገድ ለማከናወን ተወስኗል፤ በበሽታው ምክንያት ከሰዎች ንክኪና ግንኙነት ነጻ በሆነ መንገድ ማካሄድ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ሽልማቱ ከዚህ ቀደም ከተለመደው በተለየ ሁኔታ ይካሄዳል።

የበጎ ሰው ሽልማት በጎ አድራጎት ድርጅት የቦርድ ጸሐፊ አቶ ቀለመወርቅ ሚዴቅሳ በበኩላቸው ድርጅቱ በየዓመቱ በአስር ዘርፎች በየሙያቸው ለሃገራቸው የላቀ ተግባር ላከናወኑ ኢትዮጵያውያን በሕዝብ ፊት ዕውቅና ሲሰጥ መቆየቱን አስታውሰው፤ “በጎ ሰዎችን በማክበርና ዕውቅና በመስጠት ሌሎች በጎ ሰዎችን እናፍራ” በሚል መሪ ሃሳብ ባለፉት ሰባት ዓመታት ሽልማቱ ሲከናወን መቆየቱን ጠቁመዋል፡፡

የዘንድሮውን ሽልማት ለማከናወንም ከየካቲት 1 እስከ መጋቢት 15 ቀን 2012 ዓ.ም ከሁለት መቶ በላይ ዕጩዎችን በመቀበል ታሪካቸውንና አበርክቷቸውን የማጥናት ሥራ መሰራቱንም አመልክተው፤ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በዓለም አቀፍ ደረጃ በመቀስቀሱና በሃገሪቱም ከጊዜ ወደ ጊዜ ስርጭቱ እየተባባሰ በመምጣቱ በዕቅዱ መሰረት እንደ ልብ ተንቀሳቅሶ መሥራት ባለመቻሉ የዘንድሮው ሽልማት በልዩ ተሸላሚ ሥነ ሥርዓት እንዲካሄድ በቦርዱ አባላት በተወሰነው መሰረት የሚከናወን መሆኑን አቶ ቀለመወርቅ አስታውቀዋል፡፡

አቶ ቀለመወርቅ ሁለት ወቅታዊና አንኳር ሃገራዊ ጉዳዮች መመረጣቸውንና ከታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ እና በኮሮና ወረርሽኝ መከላከል ሥራ ለሕዝብ አርዓያነት ያለውና የላቀ ተግባር ላከናወኑ ግለሰቦችና ተቋማት በልዩ ሁኔታ የዘንድሮው በጎ ሰው ሽልማት እንደሚበረከትላቸው ተናግረዋል፡፡

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ እንዲሳካ፣ ለመጀመሪያው ዙር ውሃ ሙሌት እንዲበቃና በሕዝቡ ዘንድ ብሔራዊ ኩራት እንዲፈጠር ምክንያት የሆኑ በጎ ሰዎችና ድርጅቶች የዘንድሮው የበጎ ሰው ተሸላሚ ይሆናሉ ብለዋል፡፡

የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በሃገሪቱ ከተከሰተበት ጊዜ ጀምሮ በሕዝብ ላይ የሚደርሰውን የጤና ችግር ለመከላከል፣ በበሽታው መስፋፋት የተነሳም በሃገሪቱ ምጣኔ ሃብት ላይ ሊደርስ የሚችለውን ጉዳት ለመቀነስና በተለያዩ መንገዶች ለተጎጂ ወገኖች ድጋፍ በማድረግ የተጉና አርዓያነት ያለው ተግባር የፈጸሙ ኢትዮጵያውያን የሚመሰገኑበት እንደሚሆንም አክለዋል፡፡

በሁለቱ ጉዳዮች ዙሪያ ለሃገራቸው የላቀ አስተዋፅኦ ያበረከቱ ስምንት ኢትዮጵውያን ግለሰቦችና ድርጅቶች የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁንና የጤና ተቋማት ደንብን ባከበረ መንገድ በተመጠኑ ታዳሚያንና በቀጥታ የሚዲያ ስርጭት በመታገዝ ጳጉሜ 1 ቀን 2012 ዓ.ም በአዲስ አበባ በሚካሄድ መርሃ ግብር የዘንድሮው የበጎ ሰው ሽልማት የሚከናወን ይሆናል፡፡

የዘንድሮው የበጎ ሰው ሽልማት በልዩ

ሁኔታ እንደሚካሄድ ተገለጸ

ተቋማዊ ቅንጅት ለላቀ ውጤትሙሉቀን ታደገ

ሙስና በወንጀል የተገኘን ገንዘብ ወይም ንብረትን ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብ፣ ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳት፣ ህገ ወጥ የገንዘብና የሰዎች ዝውውር እና የመሳሰሉ ወንጀሎች የአለምን ኢኮኖሚ፣ ሰላምና ደህንነት እየተፈታተኑ ከሚገኙ ኢኮኖሚያዊ ወንጀሎች በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀስ ነው፡፡

ሃገራት እነዚህን ወንጀሎች ለመከላከል የተለያዩ ጥረቶችን በማድረግ ላይ ይገኛሉ፡፡ ከእነዚህ መካከልም ዓለም አቀፍ ስምምነቶችን ፈርሞ በማፅደቅና ሃገራዊ የህግ ማዕቀፍ ማዘጋጀት ተጠቃሽ ናቸው፡፡ አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችን በመተንተን ወንጀሉን የሚከላከሉ፣ የሚያጣሩና ለህግ የሚቀርቡ ተቋማትን በማቋቋም ወንጀሎቹ የሚያደርሱትን ሁለንተናዊ ተፅዕኖ ለመቀነስ ጥረት ያደርጋሉ፡፡

በኢትዮጵያም እነዚህን ወንጀሎች ለመከላከልና ተፈፅመው ሲገኙ ለህግ ለማቅረብ ይበጃል የተባለ ተግባር እየተከናወነ ይገኛል፡፡ የፋይናንስ ደህንነት መረጃ ማዕከልና የፌዴራል የስነ ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ትናንት በጋራ በሰጡት መግለጫ በአምስት ዋና ዋና ጉዳዮች ለመተባበር መስማማታቸውን ይፋ አድርገዋል፡፡

ተቋማቱ በጥናትና ምርምር፣ በአቅም ግንባታ፣ በመረጃ ልውውጥ፣ ስራን በቴክኖሎጂ ለመደገፍና የፀረሙስና ግምገማ በጋራ ለማድረግ የሚያስችላቸው ስምምነት ላይ መድረሳቸውን አስታውቀዋል፡፡

የፌዴራል የስነ ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ፀጋ አራጌ እንደሚሉት፤ ተቋማቸው ከፋይናንስ ደህንነት መረጃ ማዕከል ጋር በትብብር ለመስራት ስምምነት ላይ መድረሱ ለኢትዮጵያ ዘርፈ ብዙ

ፋይዳ ይኖረዋል፡፡ ኢትዮጵያ ብዙ አለም አቀፋዊና አህጉራዊ ሃላፊነት

ያለባት፣ ከፍተኛ ግምትና ሚዛን የሚሰጣት እንደመሆኗ የተጣለውን ሃላፊነት በብቃት ለመወጣት ተቋማት በግልፅ ከተደነገገ ተቋማዊ ሃላፊነት ባሻገር በተናጥልና በጋራ የሚተገበሩ ስራዎች አሉ ሲሉም ይናገራሉ፡፡

የተጀመረውን የብልፅግና ጉዞ ሂደቶች መሻገር የሚቻለው ከተናጥላዊ እንቅስቃሴዎች በተጨማሪ የሚመለከታቸው ተቋማት ለአንድ ግብ አላማ በጥምረት የጋራ ውጤት ማስመዝገብ ሲችሉ ብቻ ነው ሲሉም ያመለክታሉ፡፡ የሁለቱ ተቋማት ስምምነት ሃገሪቱን ወደተሻለ ለውጥ እንደሚያሸጋግርም ያክላሉ፡፡

የፋይናንስ ደህንነት መረጃ ማዕከል ዋና ዳይሬክተር አቶ ቴዎድሮስ በቀለ በበኩላቸው ማዕከሉ በህገወጥ የተገኘን ገንዘብ ህጋዊ አስመስሎ በሚንቀሳቀሱ አካላት መረጃን በመሰብሰብ፣ መረጃውን በመተንተንና መረጃውን ለሚመለከታቸው አካላት በማሰራጨት ወንጀሎችን የሚከላከል ተቋም መሆኑን ይናገራሉ፡፡

ማዕከሉ አለም አቀፋዊ ተፈጥሮ ስላለው በአለም አቀፍ መድረክ ሃገሪቱን ጉልህ ችግር ካለባቸው ሃገራት መካከል አስገብቷት እንደነበር ያስታውሳሉ፡፡ ከችግሩ ለመውጣት ባለፉት ሁለት አመታት ከብሄራዊ ባንክና ከሰላም ሚኒስቴር ጋር በመሆን በተሰሩ ስራዎች ጉልህ ችግር ካሉባቸው ሃገራት ማውጣት ተችሏል ብለዋል፡፡

በተመሳሳይ የአውሮፓ ህብረትም በኢትዮጵያ ጥሩ መሻሻል እንዳለ ገልጿል ሲሉም ነው ዋና ዳይሬክተሩ የሚናገሩት፡፡ ተቋሙ በርካታ ስራዎችን ቢያከናውንም የሚጠበቅበትን ስራ ፈፅሟል ማለት አይቻልም ባይ ናቸው፡፡

ከለውጥ አንጻር መንግስት በሰጠው አቅጣጫ

በመነሳት ሁለቱ ተቋማት ግንኙነት መፍጠር መጀመራቸውን ነው የጠቆሙት፡፡ ትግበራው ማዕከሉ ሃላፊነቱን ለመወጣት ጉልህ ሚና እንደሚኖረውን ነው ዋና ዳይሬክተሩ የሚያክሉት፡፡

የፌዴራል ስነ ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አቶ ወዶ አጦ በበኩላቸው፤ በሃገር አቀፍ ደረጃ ለሚደረገው የፀረ-ሙስና ትግል ውጤታማነት ኮሚሽኑ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅትና በትብብር ይሰራል ይላሉ፡፡

የፀረ-ሙስና ትግሉ በሃገር አቀፍ ደረጃ ወደ ተሟላ ደረጃ ደርሶ ትግሉ ውጤታማ እንዲሆን ሰፊ ዝግጅት እየተደረገ እንደሚገኝም ያመለክታሉ፡፡

ተቋማት በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ ህገ ወጥነትን የሚከላከሉና የሚታገሉ ናቸው፡፡ የስራ ክፍፍል ቢኖርም የልምድ ልውውጥ ለማድረግ ጠቃሚ እንደሚሆንም ነው የሚያብራሩት፡፡ ተቀራራቢና ተዛማጅ ስራ ያላቸው ተቋማት በአንድ አይነት ማዕቀፍ ውስጥ ሆነው ቅንጅቱን በሚገባ በማጠናከር ትርጉም ያለው ስራ መስራት ይኖርባቸዋል ሲሉም አመላክተዋል፡፡

የፋይናንስ ደህንነት መረጃ ማዕከል ምክትል ዳይሬክተር አቶ ብሌን ግዜወርቅም ኢትዮጵያ ትልቅ የብልፅግና ጉዞ መጀመሯን አስታውሰዋል፡፡ ጉዞውን ለማሳካት ደግሞ በርካታ ስራዎች እና ሃላፊነቶች እንዳሉም ነው የተናገሩት፡፡

በተለይም ሁለቱ መስሪያ ቤቶች በህግ የተሰጡ ሃላፊነቶች በአግባቡ መወጣት ይገባናል፤ በተናጠል የምንወጣው ሃላፊነት እንደመኖሩ መጠን በጋራ መቀናጀት ካልቻልን ውጤቱ ያነሰ ስለሚሆን ለላቀ ውጤት ሃገራዊ ቅንጅትና ተቀራርቦ መስራት ያስፈልጋል ሲሉ ገልጸዋል፡፡

Page 3: ከባንክ ውጭ ከ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር በላይ ማስቀመጥ ተከለከለሕግ • ዶ/ር ሳሙኤል ሁርካቶ፤ የሳይንስና ከፍተኛ

ረቡዕ ነሐሴ 13 ቀን 2012 ዓ.ም

ገጽ 3 ዜና

የትናየት ፈሩ

እየተጠናቀቀ ባለው 2012 ዓ.ም 264 ተጨማሪ ወረዳዎች የጤና መድህን ዋስትና ተጠቃሚ መሆናቸውን የጤና መድህን ኤጀንሲ አስታወቀ።

የጤና መድህን የኤጀንሲ የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዘመድኩን አበበ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት ፣ 2011 ዓ.ም ሲጠናቀቅ በአገር አቀፍ ደረጃ 600 አካባቢ ወረዳዎች የጤና መድህን ዋስትና ተጠቃሚ የነበሩ ሲሆን ፤ በ2012 ዓ.ም መጨረሻ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ የሆኑ ወረዳዎች ቁጥር 862 ደርሷል።

ዳይሬክተሩ እንደተናገሩት፣ የጤና መድህን ሽፋን ተጠቃሚ አባላት ቁጥር በየአመቱ እየጨመረ አዳዲስ ወረዳዎች አገልግሎት ማግኘት ጀምረዋል፤ ኮቪድ 19 በመከሰቱና በአንዳንድ ክልሎች የሰላም መደፍረስ በማጋጠሙ ስራዎች በታሰቡትና በታቀዱት ልክ ባለመከናወናቸው እንጂ ከተጠቀሰው ቁጥር የሚልቁ ወረዳዎች የጤና መድህን ሽፋን አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረግ ይቻል ነበር።

የጤና መድህኑ በሁለት መንገድ ለህዝብ አገልግሎት ይቀርባል የሚሉት ዳይሬክተሩ፣ በተለይም መደበኛ ገቢ የሌላቸውና ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው በዓመት አንድና ሁለት ጊዜ አምርተው ሸጠው የሚተዳደሩ እንዲሁም አርብቶ አደር አካባቢ የሚገኙ ማህበረሰቦች አባል እንዲሆኑ ታስቦ በገጠራማ አካባቢዎች በስፋት መተግበሩን ገልጸዋል።

እንደ ዳይሬክተሩ ማብራሪያ ፤ በሁለተኛው መንገድ አገልግሎት የሚያገኘው መጀመሪያ ብዙም ፍላጎት ያልነበረው መደበኛ ገቢ ያለው የመንግስት ሰራተኛና የግል ድርጅት ተቀጣሪው ጥቅሙን እያየ ጥያቄ እያቀረበ በመሆኑ ምላሽ ለመስጠት ዝግጅት ተደርጓል። በቅርቡ የጤና ሚንስትሯ ይፋ ባደረጉት ዕቅድ እንደተገለጸው በቀጣዩ አስር ዓመት ውስጥ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ የጤና መድህን ዋስትና ያገኛል።

እንደ አቶ ዘመድኩን ገለጻ የመንግስት ሰራተኞችና የግል ድርጅት ተቀጣሪዎች እስካሁን የጤና መድህን

ዋስትና ተጠቃሚ ያልሆኑት ቀደም ሲል በአዋጅ ጸድቆ ለሰራተኛው እንዲወርድ ተወስኖ ተግባራዊ ሲደረግ የተሄደበት አካሄድ ችግር ስለነበረው ሰራተኛው ባለመቀበሉ ነው። በወቅቱ ምርጫና ወቅታዊ ሁኔታዎች ስለነበሩ ወዲያውኑ መረጋጋትና ሰላም እንዲኖር ሲባል የሰራተኛው የጤና መድህን ዋስትና እንዲቆም ተወስኗል። አሁን ሰራተኛውን የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ለማድረግ ኤጀንሲው በመጀመሪያው አዋጅ ላይ ያሉትን እንከኖች ነቅሶ ብዙ ማሻሻያዎች በማድረግ እንደገና አዲስ አዋጅ አዘጋጅቶ ዓቃቢ ህግ እንዲያየው በማድረግ በ2011 ዓ.ም መጨረሻ እንዲጸድቅ ለሚንስትሮች ምክር ቤት ተልኳል።

አቶ ዘመድኩን ሰራተኛው ጥያቄ እያቀረበ ኤጀንሲውም አገልግሎት እንዲጀመር ግፊት እያደረገ መሆኑን፤ ነገር ግን ህግና ደንብን ተከትሎ መሄድ ስላለበት በሚንስትሮች ምክር ቤት መጽደቅ እንዳለበት፤ እንደ አገር አሁን ያለንበት ሁኔታ የሽግግር ወቅት ስለሆነ ተግዳሮቶችም ስላሉ ኮቪድ 19 በመከሰቱ ምክንያት እንጂ ማሻሻያ የተደረገበት አዋጅ ውሳኔ አግኝቶ እስካሁን ተግባራዊ ይደረግ እንደነበር አስረድተዋል።

የአገልግሎት ማዕቀፉ መጀመሪያ አካባቢ ለጉንፋንና ኮሶ መድሃኒት አይነት እንደሆነ ተደርጎ ለሰራተኛው ሲቀርብ ነበር ያሉት ዳይሬክተሩ፤ « አሁን ማዕቀፉ ለጌጥ የህክምና አይነቶች ካልሆነ በስተቀር የማንኛውንም ህክምና ወጪን ሸፍኖ ያሳክማል። ጥርስ አናስተክልም ፤ መነጽር አንገዛም በተጨማሪም የውበት ቀዶ ጥገናዎች አናደረግም። እነዚህን የመሳሰሉትን ካለማካተቱ በስተቀር ተቋሙ የትኛውንም አይነት ህክምና ለአባላቱ ይሰጣል። ስለ ማዕቀፉም ሰፋ ባለ ትንታኔ ለህዝብ ግልጽ የሆነ መረጃ እንዲቀርብና ሰራተኛው ተወያይቶ የተስማማበትና ያጸደቀው እንዲሆን ዝግጅቶች ተደርጓል። አገልግሎቱ ከመንግስት የጤና ተቋማት ተጨማሪ በግል የህክምና ተቋማት እንዲሰጥ ለማድረግም ከተቋማችን ጋር ውል ገብተው መመሪያንና ደንብን ተከትለው በውሉ መሰረት በመንግስት አቅጣጫ የሚሄዱ የግል የህክምና ተቋሙት ወደፊት አብረውን እንዲሰሩ የማድረግ ዕቅድና ሀሳብ አለን » ብለዋል።

264 ተጨማሪ ወረዳዎች የጤና መድህን ዋስትና ተጠቃሚ ሆኑ

አንተነህ ቸሬ

አዲስ አበባ፡- በአሸንድዬ በዓል ተሳታፊ የሚሆኑ ልጃገረዶች ለኮሮና ቫይረስ ተጋላጭ እንዳይሆኑ በጥንቃቄ እየተሰራ መሆኑን የላሊበላ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ።

የከተማ አስተዳደሩ የባሕል፣ ቱሪዝምና ስፖርት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ መሪጌታ መልካሙ ዓለሙ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት፤ ልጃገረዶች ተሰባስበው በዓሉን በሚያከብሩበት ወቅት ለኮሮና ቫይረስ ተጋላጭ እንዳይሆኑ ቁጥራቸውን የመመጠን ሥራ እየተሰራ ነው። ከዚህ ቀደም ከነበረው የልጃገረዶች ቁጥር ከግማሽ በታች በመቀነስ ተራርቀው ለመጫወት የሚያስላቸውን ልምምድ እያደረጉ ነው። በበዓሉ ተሳታፊ የሚሆኑ የባህል ቡድኖች አባላትም የኮሮና ቫይረስ ምርመራ አድርገዋል። የልብስ አጠባና ጸጉር መሰራትን ጨምሮ የበዓሉ አከባበር አካል የሆኑ የሌሎች ክዋኔዎች ዝግጅት እየተካሄደ ይገኛል። የቀበሌ የባሕል ቡድኖችም በጥሩ የዝግጅት መንፈስ ላይ ናቸው።

እንደ መሪጌታ መልካሙ ገለፃ፤ ከዚህ ቀደም ሲደረግ የነበረው በአንድ ላይ ተሰብስቦ በዓሉን በጎዳናዎች ላይና በስቴዲየም ውስጥ የማክበር ልምድ ዘንድሮ አይኖርም። ልጃገረዶች ጥንቃቄ በማድረግ በየመንደሮቻቸው የተለመደውን ባሕላዊ ክዋኔ ያካሂዳሉ።

ከበዓሉ አከባበር ጋር ተያይዞ ነሐሴ 17 ቀን 2012 ዓ.ም ወልዲያ ዩኒቨርሲቲ ላሊበላ ከተማ ላይ ለሚከፍተው ቅርንጫፍ የመሠረት ድንጋይ እንደሚቀመጥና በዕለቱም የመንግሥት የሥራ

ኃላፊዎችን ጨምሮ ሌሎች እንግዶች ይገኛሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ፣ በዕለቱ የፓናል ውይይት እንደሚኖርና ነሐሴ 18 ቀን 2012 ዓ.ም ደግሞ ለአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር እቅድ እንደተያዘ መሪጌታ መልካሙ ገልፀዋል።

በክረምት ወቅት የቱሪስቶች ፍሰት የሚቀንስ ቢሆንም በአሸንድዬ በዓል ምክንያት ብዙ ቱሪስቶች ወደ ላሊበላ ይመጡ እንደነበር የጠቆሙት መሪጌታ መልካሙ፤ ‹‹አሸንድዬንና ሆያ ሆዬን በዩኔስኮ ለማስመዝገብ እንቅስቃሴ እየተደረገ ነው። ዘንድሮ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ደመቅ ባለ ሁኔታ ሰርተን ምዝገባውን እውን ለማድረግ አቅደን ነበር። ይሁን እንጂ ጥረታችን በኮሮና ምክንያት ተስተጓጉሏል። ወረርሽኙ በዓሉን በዩኔስኮ ለማስመዝገብ በሚደረገው ጥረት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ይኖረዋል ብለን እናስባለን። ድባቡን ወደ ኋላ እንዳይመልሰውና እንደገና እንደአዲስ የምንጀምርበት ሁኔታ እንዳይፈጠርም እንሰጋለን›› ብለዋል።

በሌላ በኩል በላሊበላ ከተማ ያለውን ወቅታዊ የቱሪዝም እንቅስቃሴ አስመልክቶ መሪጌታ መልካሙ ‹‹ለወትሮው ከአካባቢው ነዋሪ የበለጠ የቱሪስት ቁጥር የነበራት ላሊበላ ዘንድሮ ከመጋቢት ወዲህ ቱሪስት የማይታይባት ከተማ ሆናለች። ላሊበላ ውስጥ በአሁኑ ወቅት ቱሪስት የሚባል የለም። የአውሮፕላን በረራም አልነበረም፤ከነሐሴ አንድ ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ በሳምንት አንድ ቀን እሁድ፣ በረራ የተጀመረ ቢሆንም የአካባቢው ተወላጆችና ዳያስፖራዎች እንጂ ለጉብኝት የሚመጣ ቱሪስት የለም። የቱሪስት እንቅስቃሴ ተብሎ የሚፈረጅ ምንም ነገር የለም›› በማለት ተናግረዋል።

የበዓሉ ተሳታፊ ልጃገረዶች ለኮሮና ቫይረስ ተጋላጭ እንዳይሆኑ በጥንቃቄ

እየተሰራ መሆኑ ተጠቆመ

የአምነስቲ ኢንተርናሽናል በኢትዮጵያ ላይ ያቀረበው ሪፖርት አሉታዊ ተጽዕኖ ያሳደረ ፤ ወቅታዊውን የተወሳሰበ የአገሪቱን የፖለቲካ ሂደት ያላጤነ መሆኑን በመገንዘቡ ለተፈጠረው ስህተት ይቅርታ መጠየቁን በይፋ ድረ ገጹ አስታውቋል፡፡

ድርጅቱ በትዊተር ገጹ እንዳመለከተው ምን ጊዜም ቢሆን የኢትዮጵያውያን ሰብአዊ መብት መከበርን እንደሚደግፍ በመግለጽ በአሁኑ ወቅት በአገሪቱ ያለውን ውስብስብ የፖለቲካ ሁኔታ በመገንዘብ በስህተት በድረ ገጹ የለጠፈውን ዘገባ አንስቷል።

በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር አቶ ፍጹም አረጋ በትዊተር ገጻቸው «አለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ከሆነው ተቋም ሙያዊና ደረጃውን የጠበቀ ሪፖርት መስማት እንጠብቃለን፤ ዘግይቶም ቢሆን ተቋሙ ስህተቱን መገንዘቡ ትምህርት የሚወስድበት ወቅት እንደሆነ ፣ለወደፊቱም በኢትዮጵያ ላይ ገለልተኛ፣ ፍትሀዊ፣ ነጻና አድልዎ የሌለበት ሪፖርት እንደሚያቀርብ እምነቴ ነው »ሲሉ አስፍረዋል።

ባለፈው ግንቦት ወር አምነስቲ ኢንተርናሽናል በአማራ እና በኦሮሚያ ክልሎች አካሄድኩት ባለው ጥናት በተወሰኑ አካባቢዎች የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት አባላት፣ የክልል ልዩ ኃይሎች እና የታጠቁ ወጣት ሚሊሽያዎች ከባድ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ፈጽመዋል ሲል መክሰሱ ይታወሳል።

ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በበኩሉ በራሱ መሪነት ከፌዴራልና ከክልል መንግስታት፣ ከፖሊስና ከትምህርት

አምነስቲ ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያን አስመልክቶ ላሰራጨው የሀሰት ሪፖርት

ይቅርታ ጠየቀ

ተቋማት ከተውጣጡ አጥኚ የቡድን አባላት ጋር በተካሄደ የማጣራት ሥራ የአምነስቲ ኢንተርናሽናል ሪፖርት “መንግሥት ሕግ ለማስከበር የሚወስዳቸውን እርምጃዎች ሁሉ የሰብዓዊ መብት ጥሰት አድርጎ የማጠልሸት ዝንባሌ የሚስተዋልበት፣ በአብዛኛው ገለልተኛነት የጎደለው፣ የማስረጃ ምዘና ችግር ያለበት፣ የአገሪቱን ነባራዊ ሁኔታና

አውድ ያላገናዘበ እንዲሁም መሠረታዊ ግድፈቶች ያሉበት እንደሆነ ተረጋግጧል” ሲል ምላሽ ሰጥቶ ነበር።

ጠቅላይ አቃቤ ህግ መግለጫው በተጨማሪም ሪፖርቱ ገለልተኛነትና ተዓማኒነት የጎደላቸው የሆኑ ምስክርነቶችን በመያዝ እጅግ ውስብስብ በሆኑ ግጭቶችና የፀጥታ ችግሮች ዙሪያ የተሳሳቱ መደምደሚያዎች ላይ

መድረሱን አመልክቶ፤ በሕግ ማስከበር ሂደት በመንግሥት

የሚወሰዱ እርምጃዎችን የመብት ጥሰት አድርጎ

ማቅረቡንና “የሌሉ ጉዳዮች እንዳሉ በማስመሰል ያቀረበ

መሆኑ በአዘጋጆቹ ዘንድ ያለውን የፖለቲካ ወገንተኛነት

ያሳያል” ማለቱ ይታወሳል።

Page 4: ከባንክ ውጭ ከ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር በላይ ማስቀመጥ ተከለከለሕግ • ዶ/ር ሳሙኤል ሁርካቶ፤ የሳይንስና ከፍተኛ

ረቡዕ ነሐሴ 13 ቀን 2012 ዓ.ም

ገጽ 4 ዜናከ9ኛው ገጽ የዞረ

የሚችሉበት አሰራር መፈቀዱን፣ አሰራሩም በአገሪቱ የሚስተዋለውን የውጭ ምንዛሬ እጥረት ለማቃለል እንደሚረዳ አመልክተዋል ።

ዶክተር ይናገር የማይክሮ ፋይናንስ ተቋማትም ወደ ባንክነት ማደግ የሚችሉበት መመሪያ መውጣቱን ይፋ አድርገው፤ የኤሌክትሮኒክስ ግብይት ስርዓትን ለማሳለጥ ሲባል ከባንኮች በተጨማሪ ሌሎች ፋይናንሻል ያልሆኑ

አዲስ ዘመን፡- የ2013 የትኩረት አቅጣጫዎች ምን ምን ናቸው?

አቶ ገዛኸኝ፡- የተቋሙ ማሻሻያ እንዲጸድቅልን ጥረት ማድረግ ነው። ሁለተኛው በተቋማችን ምቹ የሆኑ የስልጠናና የማማከር መንገዶችን ማመቻቸት ነው።

የስልጠና መስኮቻችን አሁን ካለው ወደ 5 ማሳደግ ነው፤ የመደበኛ አጫጭር የማታና ቅዳሜና እሁድ ስልጠናዎች ከዲግሪ መርሃ ግብር በተጨማሪ የኦን ላይን ስልጠና በመጨመር የተቋሙን ስልጠና በየክልሎቹ ላሉ ፈላጊዎች ተደራሽ ማድረግ ነው፤ ለዚህም ቅድመ ዝግጅት እያደረግን ነው።

ሌላው በማማከር አገልግሎት ከኮቪድ 19 ጋር ተያይዞ ተቋሞቻችን ደረጃቸውን ጠብቀው ነገ ወደ አገሪቱ ይመጣል ተብሎ የተተነበየውን ቱሪስት ማስተናገድ እንዲቻል እንዴት ነው በኮቪድ ወቅት አገልግሎት መስጠት ያለባቸው ከኮቪድ በኋላስ እንዴት መቀጠል አለባቸው የሚለውን የስልጠናና የማማከር ሥራ ኢንዱስትሪውን መደገፍ ነው። ሌላው ከክልሎችና ከተለያዩ ተቋማት ጋር ሳተላይት በመፍጠር ምልመላችንንም በዚያ ቦታ ያሉ ሰልጣኞቻችን የሚበቁበትና ወደ ሥራ የሚገቡበትን መንገድ መፍጠር ነው።

ሌላው በኢኮ ቱሪዝም ላይ ሰፊ የሥራ ዕድል መፍጠሪያ አድርገን የማማከሩንና የስልጠናውን ሥራ ከባህልና ቱሪዝምና ከክልሎችና ከሌሎች መንግሥታዊ ካልሆኑ ተቋማት ጋር በመቀናጀት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ያቀደውን እቅድ እውን ማድረግ ነው።

ሌላ የትኩረት አቅጣጫ ብለን የያዝነው ዘርፉ ካለው ባህላዊ እይታ ወጥቶ ዘርፉ ያለው ጠቀሜታና የሚፈጥረው የሥራ ዕድል የሚል ሃሳብ ወስደን ፕሮፖዛል ተዘጋጅቶ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ሆነን ትምህርት ቤቶች ላይ ክበባት እንዲስፋፉ ማድረግ የአገር ውስጥ ቱሪዝም ባህል እንዲዳብር ከሆቴልና ቱሪዝም ጋር የተያያዙ ሙያዎች ተማሪዎች በሥራ ዕድል እንዲጠቀሙ የማድረግ እቅዶች በትኩረት እየተንቀሳቀስን ነው ያለነው።

አዲስ ዘመን፡- የሞሰብ ፕሮጀክት ምንድ ነው ያለው ?

አቶ ገዛኸኝ፡- የሞሰብ ፕሮጀክት በአጋጣሚ ባህልና ቱሪዝም እያለሁ የመጣ ፕሮጀክት ነው፤ አሁንም ክብርት ሚኒስትሯ ጉዳዩን ይዘውት በከፍተኛ የመንግሥት አካላት ጉዳዩ እየታየነው ያለው የሞሰብ ፕሮጀክት ያለው ትልቅ አስተዋጽኦ ምናልባት መንግሥት ያልቻለውን መንግሥትም ያለበትን የበጀት ውስንነት በማመን ማህበረሰብ አቀፍ ድጋፎች እንዲጎላ ይደረጋል፤ ተደራጅተው የመጡ የአክሲዮን ማህበር የሞሰብ ሕንፃ ዲዛይን ነው ይዘው የመጡት፤ ስለዚህ ይሄ ተቋም ችግር ስላለበት ገነት ሆቴል ቦታ ስላለው ትንሽ የማስፋፊያ ሥራዎችን በመስራት እዚያ ላይ ቢገነባ የተቋሙን የማሰልጠን ችግር ይፈታል።

በዚህም ሞዴል ሆቴል ይገነባሉ፣ ለተማሪዎች የማደሪያ ክፍሎች ዶርሚተሪ የሚሆን ይገነባሉ፣ ተቋሙ ምንም ዓይነት ወጪ አያወጣም ዲዛይን ይዘው ይመጣሉ፣ እነርሱ ትልቅ ሞሰብ ታወር ሲገነቡ በዚያ ልክ ለብቻው ለተቋሙ በሚሰጣቸው ሞዳሊቲ ባለ20 እና 25 ወለል ፎቅ እራሱን የቻለ አንድ ተቋም ሊገነቡልን ነው፤ ከሚኒስትሯ ጋር ሞሰብ ታወር ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ነው የተፈራረሙት።

ስለዚህ ለተቋሙ ትልቅ እድል የምንወስደው መንግሥት ይሄንን ተቋም መቼ ይገነባልናል? እንዲሁም ሞሰብ ታወሩ እዚህ ቢገነባ ሁለት ጥቅም አለው ለኛ የተቋሙ ተማሪዎች የማደሪያ ክፍሎች የሞዴል ሆቴል ማሰልጠኛ ተቋም የተለያዩ ላቦራቶሪዎች ከተማሪዎች የመኝታ ክፍል ጨምሮ የሚሰራልን ከሆነ የመንግሥትንና የአገርን ጫና የሚያቃልል ይሆናል። ደረጃውን የጠበቀ ስልጠና እንድንሰጥ ምቹ ሁኔታ ይፈጠርልናል። አንዱ በግንባታ ላይ ቅድም ያነሳነውን የመንግሥትን ችግር የሚቀርፍ ነው። ስለዚህ 70 ወለል ያለው ሲባል አንድ ትልቅ የቱሪስት መስህብ ነው፤ ዘርፉ ብዙ ስልጠናዎችን እንዲያገኙ ያስችላል ኮርፖሬት ትሬኒንግ እዚያው በአቅራቢያው አገኘን ማለት ነው፤ የኛው ግቢ በሆነ ቦታላይ ተማሪዎችን እናሰለጥናለን ማለት ነው።

የሕግ ማዕቀፉ ዝግጅት አጠቃላይ ወደታች ወደሠራተኞቹ ወርዶ መወያየት ያስፈልጋል። ተጨማሪ ማስፋፊያ የሚያስፈልጉ አሉ በዕርግጥ አሁን ባለው ቦታ መገንባት ይቻላል እንደዚያ ዓይነት ሃሳብ አላቸው ግን ዲዛይኑ በትክክል ለተባለው አላማ እንዲውል መጠነኛ ማስፋፊያ ይፈልጋል።

የገንዘብ አቅሙን አሰባስበው መስራት የሚችሉበት ደረጃ መሆኑ ተረጋግጦ ሲታመንበት ወደ ሥራ የሚገባ ይሆናል። አንዳንድ ፕሮጀክቶች ይሯሯጡና ታጥሮ ቁጭ ይላል ይህንን ዓይነት ሁኔታ ለአንድም ቀን አንፈቅድም፤ ምክንያቱም ስልጠናችን ሳይቋረጥ የሆቴል አገልግሎት

«ኢትዮጵያን የሚጎበኝ ቢኖርም...የሚሰጡ ሠራተኞች ሥራቸውና ጥቅማጥቅማቸው ሳይቆም ተሰርቶ በሰላም ሽግግሩ እንዲከናወን ነው የምንፈልገው፤ ያንን ለማድረግ በመደበኛም መደበኛ ባልሆነ አመራሮች ባሉበት የተቋሙ የተወሰኑ ሠራተኞች ባሉበት ውይይት ተደርጓል። የተቋሙ ሥራ ሳይስተጓጎል ተሰርቶ እውን የሚሆን ከሆነ ለአገርም ለተቋማችንም ለአካባቢውም ከፍተኛ አስተዋጽዖ ያበረክታል። የስልጠና ችግራችን የሚፈታልን ነው ብለን ነው የምናስበው።

በሚቀጥሉት 10 ዓመታት 7 ሚሊዮን ቱሪስት ነው ለማምጣት ዕቅድ የተያዘው። ይሄንን የሰው ኃይል ሊያስተናግድ የሚችል የተማረ የሰው ኃይል ሊያስተናግድ የሚችል፤ እንደ እስከዛሬው ለወሬ ማጣፈጫ ሳይሆን ቱሪዝም ለአገር ኢኮኖሚ የጀርባ አጥንት መሆኑ በተግባር የሚፈተሽበት ወቅት ላይ ደርሰናል። በተግባር ቅርሶቻችንና ኢንዱስትሪ ፓርኮቻችን ወደ ተግባር ለመግባት በመንገድ ላይ ናቸው።

አዲስ ዘመን፡- የሞሰብ ታወር ፕሮጀክት ዕውን ካልሆነ የሞዴል ሆቴል ግንባታ በምን መልኩ ይሰራል?

አቶ ገዛኸኝ፡- የሞሰብ ታወር ፕሮጀክት እንደ አማራጭ የመጣ መልካም አጋጣሚ ነው። የመጣውን መልካም አጋጣሚ ለመጠቀም ጥሩ አማራጭ ነው። ይሄ የሚሆን ከሆነ እናያለን፤ ይሄ ካልሆነ ብለን ዝም አላልንም በ10 ዓመቱ እቅዳችን ላይ ለሞዴል ሆቴልና ተቋሙን ለማዘመን እስከ መምህራን መኖሪያቤት ግንባታ የሚደርስ እቅድ ይዘናል። ይሄንን እቅድ መንግሥት አይቶ ያጸድቅልናል ብለን እናስባለን። ወደ 3 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በጀት ይዘናል በ10 ዓመት ውስጥ። የአገራችን የመንግሥት የበጀት አቅም እየታየ ይገነባል ብለን እናስባለን። እስከዚያው ድረስ ግን የገነት ሆቴልን ኪችኑን ማዘመን፣ አስጎብኝ ድርጅት እንዲከፈት በማድረግ በመምህራኖቻችን እንዲደራጅ በማድረግ ሥልጠናውን ለማዘመን ነው የሚሰራው። በራሳችን አማራጭና በመንግሥት በጀትም የመስራት እቅድ አለን። መደበኛ ሥራችን በመንግሥት በጀት የሚከናወን ነው።

አዲስ ዘመን፡- የስልጠና ጥራትን ከማስጠበቅ አንፃርስ ምን እየተሰራ ነው?

አቶ ገዛኸኝ፡- በትምህርት ጥራት ተቋማችን ችግር የለበትም ከተቋማችን ሲወጡ የትብብር ስልጠና ሆቴሎች አካባቢ ያለውን አለማምዶ መዝኖ የማምጣት ሲስተም ላይ አንድ ትልቅ እንቅፋት ተፈጥሮብን አሁን እሱ ላይ ማንዋል አዘጋጅተናል፤ የትብብር ስልጠና መተግበሪያ ማንዋልን ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት እናደርግበታለን። ይሄ መምህሩ ወይም አሰልጣኙ ሆቴል ተማሪዎቹን ልኮ የትበብር ስልጠና ወስደዋል ብሎ መመለስ ሳይሆን ማነው የትኛው ሆቴል ሂዶ በትክክለኛው መንገድ እየሰለጠነ ያለው በሚል እዚህ በቀረቡት መመዘኛ ሰልጣኛችን ሂዶ የሚያይበት ነው።

ሁለተኛ ግብዓትና አቅርቦት ጋር ከፋይናንስ ግዢዎች ጋር ተያይዞ ተማሪዎቻችን እራሳቸው ቅሬታ ያቀርቡ ነበር፤ ለምሳሌ የምንጠቀመው የመንግሥት በጀት ነው፤ አንዳንድ ጊዜ ግዥ ሲፈፀም የተጋነነ ዋጋ መጣ ብለህ ስታየው ደግሞ ተማሪው ለስልጠና ሰዓት የማይደርስበት ተግባራዊ ልምምድ ሳያደርግ የሚሄድበት አንዳንድ ሁኔታዎች ተንጸባርቀው ነበር።

ከግዢ ኤጀንሲው ጋር በመነጋገር ከተራ ለቀማ ጀምሮ ለተለያዩ ወንጀሎች እንዳይዳረግ ብክነትም እንዳይኖር ተማሪዎች ግን በስልጠና ጊዜ የሚያስፈልጋቸው ዘመናዊ የስልጠና ቁሳቁሶች ላቦራቶሪና ሙዚየም እስከማደራጀት ድረስ እየሄድን ነው ያለነው። አዳዲስ 16 የሚሆኑ ላቦራቶሪዎች አሉ። በሁሉም አገሪቱ ክፍሎች ያሉ መዳረሻ ቦታዎችን ታሪካዊ ስፍራዎችን ሂደው አይተው የስልጠናቸው አካል አድርገው ተለማምደው የሚመጡበት ፕሮግራም አለን። የከተማ ውስጥ የተግባር ላይ ልምምድ አላቸው። የሆቴሉም እንደዚያው ስለዚህ ተግባርና ንድፈ ሃሳቡ ተመጣጥኖ ተማሪው የትኛውም ቦታ ሂዶ ፊት ሊያደርግ የሚችልበት የስልጠና ሥርዓት ወቅቱ የሚያስፈልገውን ነገር እያየን ግብዓት እያሟላን ለመሄድ ነው እየጣርን ያለነው።

አዲስ ዘመን፡- ተማሪዎች ትምህርታቸውን በአግባቡ እንዲከታተሉ ግብዓቶችን የማሟላት ነገርስ?

አቶ ገዛኸኝ፡- ተማሪዎች ከመጡ በኋላ ምን እናድርግ ብለን ብዙ ነገር ተነጋግረናል። ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደብዳቤ ጻፍን። የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ዶርም እንዲተባበረን ሁሉ ጠይቀናል። ኪራይ ፈልገን ቤት ተከራይተን ወደዚያ ብናስገባቸው ብለን አስበናል። እኛ ከመጣን በኋላ ሜክሲኮ ያለውን ካምፓስ ዶርሚተሪ ብናደርግ ብለን አስበናል፤ ነገርግን ተማሪን በአንድ ላይ አድርገን የዕርስ በዕርስ ግጭት ቢያስነሱ ሌሎች ችግሮች ቢከሰቱ እያልን እናስባለን።

ገንዘብ ሚኒስቴርን ሁሉ ጠየቅን። እርሱም ምንም ማድረግ እንደማይችል እንደማንኛውም ነው እየመደበ ያለው የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ነው እንደማንኛው ተማሪ የሚመድበው የአገራችንን ተጨባጭ ሁኔታ እያየህ ለይስሙላ የምትጠይቀው ነገር ነው የሚሆነው።

ስለዚህ ችግሩ ይፈታል ተብሎ የምናስበው መንግሥት የግንባታ በጀት ቢፈቅድልን ቀድመን የተማሪዎች ዶርሚተሪ በመገንባት ችግሩን መቅረፍ እንችላለን። ቁጥር ቢበዛብን እንኳን ትምህርት ቤት ተከራይተን ማስተማር እንችላለን። ጥናትም እናስጠናለን ውይይትም እናደርጋለን ሴት እህቶቻችን ለብዙ ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ ችግሮች እየተጋለጡ ነው። የቀድሞ ተማሪዎችን እያስተባበርን የተለያዩ የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶች እንዲወስዱ እናደርጋለን፤ ክሊኒክ አለ፤ ችግሩ ሊፈታ የሚችለው ሕንፃ ኖሮ ዶርሚተሪ ሲኖር ነው። የአንበሳ የከተማ አውቶቡስ እንዲፈቀድላቸው ለክቡር ከንቲባው ጽፈናል፤ ክበብ በመምህራንና በድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች እየተሸፈነ ለተማሪዎች በአነስተኛ ዋጋ አገልግሎት እንዲያገኙ የማድረግ ሥራ ተሰርቷል።

ለወደፊት ደንቡ ጸድቆ የዲግሪ መርሃ ግብር የምንጀምር ከሆነ የላይኛውን ካምፓስ ዶርሚተሪ አድርገን ወደፊት ተቋሙ ሊስፋፋ የሚችልበት አቅም አለው።

አዲስ ዘመን፡ አፍሪካዊ ይዘት ያላቸው የምግብ አሠራሮች ላይ ከማሰልጠን አንፃርስ ምን ዓይነት እንቅስቃሴ አለ?

አቶ ገዛኸኝ፡- አንድ የምግብ ዝግጅት ባለሙያ

እስከመቼ ነው የውጭ ምግብ ዝግጅት ብቻ ተምሮ የሚወጣው ከዘመናዊው ባሻገር ባህላዊ ድባብ እንዲኖረው ደረጃውን የጠበቀ ዓለም አቀፍ ካሪኩለም ነው የምንሰጠው የትም ቦታ ሂደው እንዲሰሩ ዓለምአቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ሆቴሎች ላይ ሊያገለግሉ የሚችሉ የሆቴል ባለሙያ አስጎብኚዎችን ነው የምናፈራው።

የሆቴልና የቱሪዝም ኢንዱስትሪ በመንግሥትና በተወሰኑ አካላት ላይ የተንጠለጠለ የሥራ ዘርፍ አይደለም ድንበር ተሻጋሪ ነው። ሥራ ዕድል ለመፍጠር ጥራት ያለው አገልግሎት ለመስጠት የደንበኛን ለማርካት መንግሥት የሚሰራው ሥራ አለ ባለሀብቱ የበኩሉን መወጣት አለበት የአካባቢው ማህበረሰብ የሚወጣው የራሱ ኃላፊነት አለበት።

አዲስ ዘመን፡- በስተመጨረሻ የሚያስተላልፉት መልዕክት ካለ ?

አቶ ገዛኸኝ፡- ተቋሙ ይሄንን ያህል ዕድሜ አስቆጥሯል ማለት ሳይሆን የቀድሞ የተቋሙ ተማሪዎች ባላቸው እውቀትና ክህሎት በገንዘብም በቁሳቁስም ባላቸው አቅም ተቋሙ የተሻለ ደረጃ እንዲሄድ አብረውን እንዲሰሩ ¬ጥሪ ማስተላለፍ እወዳለሁ። ተቋሙ ከዕድሜውና ታሪኩ ጋር የተመጣጠነ ስልጠና እንዲሰጥ አገሪቱ ወደፊት በኢንዱስትሪው የምትሸከመውን የሰው ኃይል በብቃትና በጥራት እንዲሁም በብዛት ለማፍራት ደንቡን የሚያጸድቁ አመራሮች በአስቸኳይ እንዲያጸድቁልንና እኛም የተጣለብንን ኃላፊነት በብቃት እንድንወጣ ተማሪዎቻችን ኅብረተሰቡ እንዲሁም መንግሥት ተጠቃሚ እንዲሆን ዘርፉ የሚጠበቅበትን ኃላፊነት እንዲወጣ ጥሪ ማቅረብ እንወዳለን።

ከባንክ ውጭ ከ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር...ከ1ኛው ገጽ የዞረ ተቋማትም በክፍያ ስርዓት ላይ መሳተፍ እንደሚችሉ

ጠቁመዋል ።ተቋማቱ ከብሄራዊ ባንክ ፈቃድ በመውሰድ

በኤቲኤም፣ በፖስ ማሽን እንዲሁም ሌሎች አማራጮች የክፍያ ስርዓት ላይ መሳተፍ እንደሚችሉ፤ በኢትዮጵያ የብር ኖቶች ላይ መፃፍም ሆነ ስዕል መሳል የተከለከለ ስለመሆኑም ዶክተር ይናገር ገልጸዋል።

Page 5: ከባንክ ውጭ ከ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር በላይ ማስቀመጥ ተከለከለሕግ • ዶ/ር ሳሙኤል ሁርካቶ፤ የሳይንስና ከፍተኛ

ዋለልኝ አየለ

ዛሬ ቡሄ ነው። ‹‹እዚያ ማዶ ጭስ ይጨሳል…›› የሚለው የልጆች የሆያ ሆዬ ዘፈን ይዘፈናል። በነገራችን ላይ ይሄ የልጆች የሆያ ሆዬ ጭፈራ ውስጠ ወይራ ነው አሉ። እንዲያውም ሰሞኑን በአንድ መጽሔት ላይ ትንታኔ ተሰርቶበት አንብቤያለሁ። ‹‹አጋፋሪ ይደግሳል….. ያቺ ድንክ አልጋ አመለኛ ያለ አንድ ሰው አታስተኛ…›› ፖለቲካዊ መልዕክት የያዙ ናቸው። በሰኔ ወር ውስጥ ‹‹እረኛ ምን አለ?›› በሚል ርዕስ ፖለቲካዊ መልዕክት ያላቸው የእረኞችን እንጉርጉሮ በዚሁ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ አስነብበናችኋል። በዘመኑ የመገናኛ ብዙኃን አማራጭ ስለሌለ የነፃ ሀሳብ መንሸራሸሪያ የእረኛና የገበሬ እንጉርጉሮ ነበር።

ዛሬ ቡሄ ነው። ‹‹እዚያ ማዶ ጭስ ይጨሳል…›› የሚባልበት ማለት ነው። የአበው ልጆች ጭስ የድግስ ጭስ ሲሆን የኛ ጭስ ግን የሲጋራ እና የጎማ ማቃጠል ጭስ ሆኗል። እዚህ ማዶ ያለ ሰው ወዲያ ማዶ የሚታየው የሕንፃ ጭስ ነው። አሁን ላይ ያሉ ሕፃናት ይሄን ጭፈራ ቢሰሙ እዚያ ማዶ ሲቃጠል የሚያዩትን ቤት ጭስ ሊመስላቸው ይችላል። አይፈረድባቸውም! ልክ እንደ ድግስ ጭስ ወጣቶች ሆያ ሆዬ ነዋ የተቃጠለው። በቤት ቃጠሎው ጭስ ‹‹ሰልፊ›› ፎቶ ሲነሱ አይተዋል።

የዘንድሮን ‹‹እዚያ ማዶ ጭስ ይጨሳል…›› ከፈለግን ደግሞ ከባህር ማዶ መሻገርም እንችላለን። ከባህር ማዶ ጭስ ይጨሳል። አሜሪካ በእሳት ስትጋይ ቆይታለች፤ የሊባኖስ ጭስ አሁንም አልጠፋም። ሩሲያ ውስጥ ገና ክብሪት ሲፈልጉ ‹‹የኮሮና መድኃኒት አገኘሁ›› ብላ አጀንዳ አስቀየረች። ብቻ ምን አለፋችሁ በብዙ የዓለም አገራት አሁንም ጭስ አለ። እኛም የአንዱ አመድ ሳይከስም ሌላ ስናጨስ ከርመናል። እዚያ ማዶም እዚህ ማዶም ጭስ ይጨሳል!

እነሆ ኮሮና ደግሞ ሌላ ጭስ ሆኖብናል። እዚያ ማዶም እዚህ ማዶም ሳይሆን ‹‹ዙሪያውን ጭስ ይጨሳል›› ያሰኛል። ብዙ ገቢ የሚያስገኙ ጭስ አልባ የቱሪዝም ዘርፎችን በጭስ ሸፍኖ አስቀርቷቸዋል። በአደባባይ የሚከበሩ በዓላትን ጥላሸት ቀብቷቸዋል።

ዛሬ ቡሄ ነው። ልጆች በየመንደሩ እየዞሩ የሚጨፍሩበት። በስንኞቻቸው ያስደሰታቸውን የሚያወድሱበት፤ ያስከፋቸውን ሸንቆጥ የሚያደርጉበት። እንዲህ ዓይነት ክስተቶች የዘመን ምስክር ናቸው። ያ ዘመን ምን ይመስል እንደነበር፤ ፖለቲካዊና ማህበራዊ ሁኔታዎችን ያሳያሉ። ከልጆች የሚሰሙ ስንኞች የድሮ ቃል ግጥሞች ብቻ አይደሉም፤ በዘመኑ ዓውድ ቀይረው የሚጠቀሟቸው አሉ። መንግሥት በተደጋጋሚ ‹‹ኪራይ ሰብሳቢ›› ሲል ይሰማሉ። ይሄው ክስተት በልጆች ሆያ ሆዬ ውስጥ ተካቷል። ‹‹እረኛ ምን አለ?» ማለት ይሄ ነው።

ዛሬ ቡሄ ነው። የዛሬው ቡሄ ግን ከዚህ በፊት ከነበሩት ይለያል። ልጆች ተሰባስበው በየመንደሩ እየዞሩ አይሉም (ካሉም እንደ እስከዛሬው አይሆንም)። ይሄን ዕለት ግን በመገናኛ ብዙሃን ማስታወስ ይቻላል (ኮሮናን ደስ አይበለው!) እስኪ በቡሄ የሚባሉ የልጆች የሆያ ሆዬ ጭፈራ ስንኞችን እንያቸው።

ቡሄ መጣያ መላጣ

ቅቤ ቀቡት እንዳይነጣይሄ ከቃሉ ትርጉም ጋር የሚሄድ ነው። ‹‹ቡሄ›› ማለት ቡሃ ከሚለው

ቃል የመጣ ነው፤ ቡሃ ማለት ገላጣ ማለት መሆኑን የሃይማኖት አባቶችና የቋንቋ ሰዎች በየዓመቱ ይናገሩታል።

የእኔማ ጌታ የሰጠኝ ሙክትከግንባሩ ላይ አለው ምልክትመስከረም ጠባ እሱን ሳነክት

ይሄ የውደሳ ግጥም ነው። በድሮው ጊዜ ለሆያ ሆዬ ልጆች ሙክት (ፍየል) ይሰጥ ነበር ማለት ነው። በነገራችን ላይ በገጠር አካባቢ ልጆች ከሆያ ሆዬ የሚያገኙትን ብር ሙክት ገዝተው ነው የሚበሉበት። የቅጠል ድንኳን (ዳስ) ይሰራል። ከአካባቢው ሰዎች ይገባቸዋል ያሏቸውን (ሽማግሌና የሃይማኖት አባት) ይጠራሉ። ከዚያ ውጭ የመጣ ግን ቀላዋጭ ነውና የሚጠብቀው የልጆች ግልምጫና ውረፋ ነው።

ሆያ ሆዬ ሲሉ ብር የሚቀበሉት እንደየሰዎች አቅም ነው። የአካባቢው ልጆች ስለሆኑ የየሰውን አቅም ያውቁታል። ሀብታም ከሆነ

በቀላል አይላቀቁም። ‹‹ከአንተ ይሄን አንቀበልም›› ብለው ሆያ ሆዬውን ይደጋግሙታል። ከእንዲህ ዓይነቱ ሀብታም ነው ሙክት የተበረከተላቸው ማለት ነው። ‹‹መስከረም ጠባ እሱን ሳነክት›› ማለት ከቀናት በኋላ የሚገባውን መስከረም ሳይሆን በዓመቱ የሚመጣውን ነው።

የእኔማ እመቤት የፈተለችውየሸረሪት ድር አስመሰለችው

ሸማኔ አቅቶት ማርያም ሰራችውይሄም ውደሳ ነው። ይሄኛው ውደሳ ለእመቤቷ ነው። በዘመኑ የሴት ሙያ የሚለካው በፈታይነትና በባልትና ብቃት ነው። ከድሮው የቃል ግጥም እንውጣና በዘመኑ የሚባሉትን እንያቸው። በዘመኑ የሚታየውን፣ የሚባለውን፣ የሚሆነውን የሚናገሩ ናቸው። ያም ሆኖ ግን መነሻ ስንኞቻቸው የቀደምቶቹ ናቸው።

ወዲያ ማዶ አንድ ጋቢወዲህ ማዶ አንድ ጋቢ

የኔማ እንትና ኪራይ ሰብሳቢ!ምናልባት ይሄ በተባለበት ጊዜ ጭስ አልነበረም መሰለኝ በጋቢ ቀይረውታል። ኪራይ ሰብሳቢ የሚለውን ለመግለጽ ቤት እንዲመታላቸው ነው፤ በሌላ በኩል ደግሞ ‹‹ጭስ›› ካሉ ሙሉ በሙሉ የድሮው ሊሆን ነው። ያስከፋቸውን ሰው ኪራይ ሰብሳቢ ብለው ሲሰድቡት ያስደሰታቸውን ደግሞ እንዲህ ብለዋል።

እዛ ማዶ አንድ በረኪናእዚህ ማዶ አንድ በረኪናየኔማ አባብዬ ባለመኪና

እዚህ ጋ የተቀየረው ሌላው ነገር ‹‹ጌታ›› የሚለው ነው። በድሮው ጊዜ ጌታ እና እመቤት የሚሉ ቃላት ነበሩ፤ አሁን አባዬ እና እማዬ በሚል መሆኑ ነው። ለዚህም ነው ለሴቷ እንዲህ የተባለው።

እዛ ማዶ አሮጌ ትሪእዚህ ማዶ አሮጌ ትሪ

የእኔማ እማምዬ ማሪያ ኬሪግን ‹‹አዲስ ትሪ›› ቢሉት ምን ችግር ነበረው? ወይስ አሮጌው ትሪ

ያልገባኝ መልዕክት ይኖረው ይሆን? እንዲያውም ከማሪያ ኬሪ ጋር የሚሄድ አዲስ ትሪ ቢሆን ነበር (ለነገሩ ማሪያ ኬሪም እያረጀች ነው)። ችግሩ ዘፋኝም ተዋናይም የራሳችን እያሉን የውጭዋን ማስበለጣቸው ነው።

ተው ስጠኝና ልሂድልህእንደ አሮጌ ጅብ አልጩህብህ

ይሄ የልጆች ስንኝ ግን በቅርብ ጊዜ የተባለ ቢሆን ኖሮ ህወሃት ‹‹ዶክተር አብይ ነው የጻፈላቸው›› አይልም ነበር ትላላችሁ? ደግሞ እኮ ዶክተር አብይ ሰሞኑን ግጥም እየጻፉ ነው። በአንድ ወቅት ‹‹የቀን ጅብ›› ብለው ተናግረው ህወሃት ቶሎ ብሎ ‹‹እኔን ነው›› ብሏል። ሰዎችም ‹‹የአቦን ፍየል የበላ ይለፈልፋል›› በሚል ‹‹አዎ! አንተን ነው›› ብለውታል። ለማንኛውም ይሄ የልጆች የቡሄ ቃል ግጥም የድሮው ነው። ማን ያውቃል ያኔስ ቢሆን ለፖለቲካ መልዕክት ተጠቅመውት ቢሆን?

የልጆችና የእረኞች ቃል ግጥሞች የአዋቂዎች እጅ ያለበት ይመስላል። እርግጥ ነው ሲወርድ ሲወራረድ የመጣ ነው፤ ግን ጨዋታው የልጆች ብቻ ስለሆነ ከልጅ ወደ ልጅ እንጂ ከአዋቂዎች ወደ ልጅ ይተላለፋል? ወይስ ነገር ስለምናጣምም እነርሱ ያላሰቡትን ትርጉም እየሰጠነው ይሆን? አይመስለኝም! ‹‹ያለአንድ ሰው አታስተኛ›› የተባለው መቼም የሆያ ሆዬ ጎረምሳ ከአባወራ ቤት አልጋ ላይ ይተኛል ተብሎ አይደለም። የጌቶች ወንበር በቀላሉ አይገኝም ለማለት ነው።

የዚያ ማዶው ጭስ የአጋፋሪ ድግስ ይሁን እያልን በዚሁ ጨዋታ እንሰናበታችሁ፤ መልካም ቡሄ!

እዚያ ማዶ ጭስ ይጨሳልአጋፋሪ ይደግሳል

ይሄን ድግስ ውጬ ውጬከድንክ አልጋ ተገልብጬያቺ ድንክ አልጋ ነገረኛያለአንድ ሰው አታስተኛ!

Website - www.press.et Email - [email protected] Facebook - Ethiopian Press Agency

ርዕሰ አንቀፅ

ግንቦት 30 ቀን 1933 ዓ.ም ተቋቋመ

አዲስ ዘመን

የዝግጅት ክፍል ፋክስ - 251-011-1-56-98-62

ምክትል ዋና አዘጋጅአያሌው ንጉሴስልክ ቁጥር - 011-1-26-43-26አዘጋጆችሶሎሞን በየነእፀገነት አክሊሉየትናየት ፈሩዘላለም ግዛውፍዮሪ ተወልደአንተነህ ቸሬይበል ካሳ

አምደኞችጌታቸው በለጠ/ዳግላስ ጴጥሮስፍሬው አበበ

የገበያ ልማትና ፕሮሞሽን ዘርፍኢሜይል - [email protected] ስልክ - 011-156-98-73ፋክስ - 011-156-98-62

የማስታወቂያ መቀበያ ክፍልስልክ - 011-156-98-65

የማስታወቂያ ሽያጭ ማስተባበሪያስልክ - 011-1-26-43-39

ማከፋፈያስልክ - 011-157-02-70

ረቡዕ ነሐሴ 13 ቀን 2012 ዓ.ም

ገጽ 5 / ጎሜ

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዋና ስራ አስኪያጅ

ስልክ ቁጥር - 011-126-42-22ዋና አዘጋጅ

አንተነህ ኃ/ብርሃን ወ/መድህንአድራሻ

ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከወረዳ 06የቤት ቁጥር 319ኢሜይል - [email protected]ስልክ ቁጥር - 011-1-26-42-40

እዚያ ማዶ ጭስ ይጨሳል ...

ሚዛናዊነት ተቀባይነትን ያስገኛል እንጂ ነቀፋን አያስከትልም!

አምነስቲ ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያን የተመለከተ ወቅታዊ የአገሪቱን ሁኔታ ከግምት ያላስገባ ሪፖርት በማውጣቱ ሪፖርቱን እንደ ትክክለኛ መረጃ በመጠቀም ወትሮም የአገሪቱን በጎ ስም የማይፈልጉ አካላት የመጫወቻ ካርታቸው አድርገውት መሰንበታቸው ይታወሳል፡፡

ከትናንት በስቲያ ደግሞ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያን አስመልክቶ ላሰራጨው የሀሰት ሪፖርት ይቅርታ የጠየቀበት ሁኔታ መከሰቱን አድምጠናል፡፡ የአምነስቲ ኢንተርናሽናል አጥኚ ቡድን በቅርብ ጊዜ በኢትዮጵያ ላይ ያቀረበው የሀሰት ሪፖርት አሉታዊ ተጽዕኖ ያሳደረ፤ ወቅታዊውን የተወሳሰበ የአገሪቱን የፖለቲካ ሂደት ያላጤነ እንደነበር በመገንዘቡ ለተፈጠረው ስህተት ይቅርታ መጠየቁን በይፋ ድረገጹ ተጠቅሷል፡፡

ድርጅቱ በትዊተር ገጹ እንዳመለከተው ምንጊዜም ቢሆን የኢትዮጵያውያን ሰብአዊ መብት መከበርን እንደሚደግፍ ፤ በአሁኑ ወቅት በአገሪቱ ያለውን ውስብስብ የፖለቲካ ሁኔታ በመገንዘብ በስህተት በድረገጹ የለጠፈውን ዘገባ አንስቷል።

በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር አቶ ፍጹም አረጋ በትዊተር ገጻቸው «ዓለምአቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ከሆነው ተቋም ሙያዊና ደረጃውን የጠበቀ ሪፖርት መስማት እንጠብቃለን፤ ዘግይቶም ቢሆን ተቋሙ ስህተቱን መገንዘቡ ትምህርት የሚወስድበት ወቅት እንደሆነ፣ ለወደፊቱም በኢትዮጵያ ላይ ገለልተኛ፣ ፍትሀዊ፣ ነፃና አድልዎ የሌለበት ሪፖርት እንደሚያቀርብ እምነቴ ነው» ሲሉ አስፍረዋል።

ባለፈው ግንቦት ወር አምነስቲ ኢንተርናሽናል በአማራ እና በኦሮሚያ ክልሎች አካሄድኩት ባለው ጥናት በተወሰኑ አካባቢዎች የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት አባላት፣ የክልል ልዩ ኃይሎች እና የታጠቁ ወጣት ሚሊሽያዎች ከባድ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ፈጽመዋል ሲል መክሰሱ ይታወሳል።

ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በበኩሉ በራሱ መሪነት ከፌዴራልና ከክልል መንግሥታት፣ ከፖሊስና ከትምህርት ተቋማት ከተውጣጡ አጥኚ የቡድን አባላት ጋር በተካሄደ የማጣራት ሥራ የአምነስቲ ኢንተርናሽናል ሪፖርት «መንግሥት ሕግ ለማስከበር የሚወስዳቸውን እርምጃዎች ሁሉ የሰብዓዊ መብት ጥሰት አድርጎ የማጠልሸት ዝንባሌ የሚስተዋልበት፣ በአብዛኛው ገለልተኝነት የጎደለው፣ የማስረጃ ምዘና ችግር ያለበት፣ የአገሪቱን ነባራዊ ሁኔታና ዐውድ ያላገናዘበ እንዲሁም መሠረታዊ ግድፈቶች ያሉበት እንደሆነ ተረጋግጧል» ሲል ምላሽ ሰጥቶ ነበር።

ነገር ግን መግለጫው የድርጅቱን ሪፖርት ሙሉ ለሙሉ ውድቅ አላደረገውም በዚህም መሠረት በዘገባው ውስጥ ከተካተቱት የመብት ጥሰት ወቀሳዎች የተወሰኑት በከፊልም ቢሆን ተዓማኒነት ያላቸው ሆነው መገኘታቸውን ገልጾ፤ «ከእነዚህ በከፊል ተዐማኒነት ካላቸው ጉዳዮች መካከል በርካቶቹ በመንግሥት ታውቀው ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ የምርመራ ሥራ ሲከናወንባቸው የነበሩ ናቸው» ብሏል።

ጠቅላይ አቃቤ ሕግ በወቅቱ ስለተሰራጨው የሀሰት ሪፖርት በመግለጫው ሪፖርቱ ገለልተኛነትና ተዓማኒነት የጎደላቸው ምስክርነቶችን በመያዝ እጅግ ውስብስብ በሆኑ ግጭቶችና የፀጥታ ችግሮች ዙሪያ የተሳሳቱ መደምደሚያዎች ላይ መድረሱን አመልክቶ፤ በሕግ ማስከበር ሂደት በመንግሥት የሚወሰዱ እርምጃዎችን የመብት ጥሰት አድርጎ ማቅረቡንና «የሌሉ ጉዳዮች እንዳሉ በማስመሰል ማቅረቡ በሪፖርቱ አዘጋጆች ዘንድ ያለውን የፖለቲካ ወገንተኛነት ያሳያል» ማለቱ ይታወሳል።

መቼውንም ቢሆን አንድ ሪፖርት ሲቀርብ በእውነት ላይ የተመሰረተ ሲሆን ተአማኒነቱና ተቀባይነቱ በብዙዎች ዘንድ ይሁንታን ያስገኝለታል እንጂ እምነቱን አያቀልበትም፡፡ በተለይም ዓለም አቀፉ ኅብረተሰብ ስለራሱ የመብት ጥሰት ቋሚ ጠበቃ ይሆንልኛል ብሎ ከሚጠብቀው ዓለም አቀፍ ተቋም እውነትን እንጂ አድልዎ ያለበትና ገለልተኛነት የራቀው ሪፖርት ሲያደምጥ ነግ በእኔ ማለቱ የማይቀር ነው፡፡

አምነስቲ ኢንተርናሽናል እንደቀደመው ዓይነቱ የሀሰት ሪፖርቱን ከማሰራጨት ተቆጥቦና ካከናወነው ድርጊት ስህተቱን ተገንዝቦ ራሱን ለማረም መነሳቱ የሚደገፍ ሲሆን ለወደፊቱ በተቋሙና በኢትዮጵያ በኩል ለሚኖረው በእውነት ላይ ለተመሰረተ ግንኙነት መልካም መንገድን የሚከፍት እንደሚሆን ይገመታል፡፡ ሚዛናዊነት ተቀባይነትን ያስገኛል እንጂ ነቀፋን አያስከትልምና ከነቀፋ ለመዳን ሁሌም ለዕውነት መቆም ይገባል፡፡

Page 6: ከባንክ ውጭ ከ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር በላይ ማስቀመጥ ተከለከለሕግ • ዶ/ር ሳሙኤል ሁርካቶ፤ የሳይንስና ከፍተኛ

ረቡዕ ነሐሴ 13 ቀን 2012 ዓ.ም

ገጽ 6 ነፃ ሀሳብ

ይህ ዓምድ በተለያዩ ፖለቲካዊ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ዜጎች ነፃ አስተያየታቸውን የሚሰጡበት ነው። በዓምዱ ላይ የሚወጡ ጽሑፎች የዝግጅት ክፍሉን አቋም አያመለክቱም።

በቁምላቸው አበበ ይማም ( ሞሼ ዳያን )[email protected]

«አልማዝ በደጅ ፣ አልማዝ በጓሮ...!?

ተአምረኛ፣ ትንግርተኛ እና ከአእምሮ በላይ የሆነውን ሸገርን የማስዋብ ፕሮጀክት አካል የሆኑትን የአንድነት ፓርክ፣ የኢዮቤልዩ ቤተመንግሥት፣ የእንጦጦ መዝናኛ ፓርክና የአዲስ አበባ የወንዝ ዳር ልማት ዘጋቢ ፊልም ስመለከት በስነ አእምሮ፣ በስነ ልቦና፣ በሰባኪያንና በወንጌላውያን በማጣቀሻነት ተደጋግሞ የሚነሳውንና ብዙ የተጻፈለትንና የተነገረለትን ዘመን ተሻጋሪ የሩሶል ኮንዌልን “Acres of Diamonds” (አልማዝ በደጅ፣ አልማዝ በጓሮ)ን አስታወሰኝ። ኮንዌል እ.አ.አ በ1870 ከባልጀሮቹ ጋር በመሆን የጢግሪስ ወንዝን እና ባቢሎንን ለመጎብኘት ወደ ኢራቅ ባግዳድ ያመራል። ጉበኝቱን ምሉዕና ቀላል ለማድረግ ደግሞ ስለአካባቢው በቂ እውቀት ያለው አስጎብኝና አስተርጓሚም አፈላልጎ ያገኛል። ሆኖም ጉብኝቱ፣ ጉዞው አድካሚና አሰልቺ ስለነበር ከቀን ወደቀን የአስጎብኛቸው ገለጻና ማብራሪያ እንዲሁም ጎብኝዎችን ዘና ለማድረግ የሚያወጋቸው አፈ ታሪኮችና ሐተታ ተፈጥሮዎች እጅ እጅ ማለታቸው አልቀረም። በተለይ ኮንዌል የአስጎብኝው ወግ እንቶ ፈንቶ ስለሆነበት ጆሮም ትኩረትም እስከመንፈግ ደርሶ ነበር። አስጎብኝውም የዋዛ አይደለምና ይሄን ስለተረዳ በተለያየ አስቂኝ ትዕይንት ፈታ ለማድረግ ሞከረ እሱም ያሰበውን ያህል አልተሳካለትም።

ሆኖም አስጎብኝው በዚህ ተስፋ አልቆረጠም። ወደ ኮንዌል ዘወር ይልና እንደ እናንተ ላሉ ልዩ እንግዶቼ ያስቀመጥሁትን ወግ ላጫውታችሁ ይልና ይሁንታቸውን ሳያገኝ ይቀጥላል። በጥንታዊቷ ፋርስ በኢንደስ ወንዝ አቅራቢያ የሚኖር አል ሀፊድ የሚባል የመሬት ከበርቴና ባለፀጋ ነበር። በአንድ ጦሰኛ ምሽት በአቅራቢያው የሚኖር የቡድሀ ቄስ ወደ ቤቱ ጎራ ይላል። ሻይ ይዘው የእሳት ዳር ወግ ያወጋሉ። ቄሱም በዓለማችን ውድ ስለሆነውና ስለከበረው ድንጋይ ስለ አልማዝ ያጫውተዋል። አልማዝ ካለ በሰማይ መንገድ እንዳለ፤ በአንድ ጀምበር ባለጠጋ እንደሚሆንና ዓለምን በመዳፉ እንደሚጨብጣት ያጫውተዋል። ከበርቴውም አልማዝ አግኝቶ በተድላና በፍስሐ ማማ ላይ ሲቀማጠልና ሲዘባነን በዓይነ ህሊናው ውል ይለውና። ቄሱን ለመሆኑ ይህ የከበረ ማዕድን የት ነው የሚገኘው ሲል ይጠይቃል። ቄሱም በሁለት ተራሮች መካከል በነጭ አሸዋ ላይ በሚፈስ ወንዝ ይለዋል። አል ሀፊድም አልማዝ አግኝቶ ሕይወቱ በአንድ ጊዜ ሲቀየር ታየውና ሀሴት ውስጡን ሞላው። ጉጉት የሚይዝ የሚጨብጠውን አሳጣው። ሌሊቱ አልነጋ አለው። አልማዙን አግኝቶ ጌታ ሲሆን ታየው። በበነጋው መሬቱን፣ ቤት ንብረቱን ሁሉ ሸጦ አልማዝ ፍለጋ ወጣ። ከቀናት በኋላ ያ የቡድሀ ቄስ የአል ሀፊድን መሬት የገዛውን ሰው ሊጠይቅ ይመጣል። ቤቱ እንደገባም ከምድጃው ራስጌ ከሚገኝ መደርደሪያ ላይ ዓይኑ የሚያበራና የሚያንጸባርቅ ማራኪ ነገር ላይ ያርፋል። ፈጥኖም ይሄን አልማዝ ከየት አገኘኸው ብሎ ይጠይቀዋል። እሱም ቀለል አድርጎ ኧረ አልማዝ አይደለም ደጅ ካለው መሬቴ ሳርስ ነው ያገኘሁት ይለዋል። አልማዝ ነው። ና የአገኘህበትን ቦታ አሳየኝ ይለዋል። ወጥተው ሲያሳየው ቤት የተመለከተውን ዓይነት አልማዝ በነጭ አሸዋማ መሬት ላይ እዚህም እዚያም በብዛት ሲያንጸባርቅ ይመለከታል። ለቃቅሞ ሲመለከቱት አልማዝ መሆኑን ያረጋግጣሉ። አስጎብኝውም እንግዲህ በዓለማችን በሰው ልጅ ታሪክ ትልቁ ከሚባለው የደቡብ አፍሪካው ኪምበርሊ በዋጋ የሚበልጠው የጎልኮንዳ የአልማዝ ማዕድን ማምረቻ የሆነው ያ አል ሀፊድ አልማዝ አሰሳ ሸጦት የሄደው የአልማዝ እርሻ ነው ሲል አስጎብኝው አፈ ታሪኩን ይቋጫል። የእንግሊዝ ንግስት እና የራሽያ ዛር ንጉሳዊ ቤተሰብ እጅግ ውድ የሆኑት ዘውዶች የተሰሩት

ከዚህ የአልማዝ እርሻ ከተገኘ አልማዝ ነው። አል ሀፊድ የአልማዝ እርሻውን ሸጦ አልማዝ ፍለጋ በዓለም ሲባዝን ኖሮ አልማዙንም ሳያገኝ ፤ እርሻው የአልማዝ እርሻ ፤ ደጁና ጓሮው ፍለጋ የወጣለት አልማዝ መገኛ እንደነበር ሳያውቅ እንደወጣ ቀረ።

“Acres of Diamonds” ወይም «አልማዝ በደጅ፣ አልማዝ በጓሮ» በሚል ወደ አማርኛ ለመመለስ የሞከርሁት ፅንሰ ሐሳብ ሁላችንም በአእምሮአችን ጓዳ ያለውን ሀሳብ፣ በጓሯችንና በደጃችን፣ በማህበረሰባችን፣ በከተማችን ከፍ ሲልም በሀገራችን ያለውን እምቅ ሀብት ዓይናችንን ከፍተን ማየት ባለመቻላችን እንደ ሀገርም ሆነ ሕዝብ መክሊታችንን ሳናገኝ በምድረ በዳና በበረሀ ስንባዝን መኖራችንን ያመለክታል። በአንጻሩ በደጃችን፣ በጓሮአችንና በአካባቢያችን የፈሰሰውን አልማዝ መመልከት ብንችል ምን ያህል ልንበለፅግና ልንለማ እንደምንችል ያሳያል። ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር በ«ሸገርን ማስዋብ» ፕሮጀክት ማለትም በአንድነት ፓርክ፣ በኢዮበልዩ ቤተመንግሥት፣ በእንጦጦ መዝናኛ ፓርክና በአዲስ አበባ የወንዝ ዳር ልማት በአጭር ጊዜ ዓይናችንን ከፍተው በደጃችንና በጓሮአችን የተትረፈረፈውን አልማዝ አሳይተውናል። ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዙሪያ ገባችን እንቁ እንደሆነ በይቻላል መንፈስ፤ «ትልቅ እናልማለን በትንሽ እንጀምራለን፤ በተግባር ሰርተን እናሳያለን፤ ከብልፅግና የሚያቆመን ኃይል የለም። ኢትዮጵያን ወደ ቀደመው ታላቅነቷ እንመልሳለን፤ ወዘተረፈ» ባሉት መሠረት ግርዶሹን ገፈው፣ መጋረጃውን ቀደው፣ ሀሳብ አፍልቀው፣ ሀብት አፈላልገው፣ የአካባቢ ግብዓት፣ የሀገር ቤት ባለሙያ ከያለበት ጠርተው፣ አቀናጅተው እየመሩ፤ ለዚያውም በደባ ፖለቲካ ሀገር እየታመሰች፣ ጽንፍና ጽንፍ በረገጠ ዘውጌያዊነት ሀገር እየተላጋች፤ ሌት ተቀን፣ ከቀኝ ከግራ ቀውስ ጎናቸውን ቀስፎ ይዟቸው እያለ፣ የጦርነት ነጋሪት አንድ ጊዜ ከሰሜን ሌላ ጊዜ ከምዕራብ አሁን ደግሞ ከውጭ በግብፅ እየተጎሰመ፤ እንደ ሀገር ጥሩ ዜና ብርቅ በሆነበት፣ ተስፋ በመነመነበት በአድናቆት እጅን በአፍ የሚያስጭን፣ ዓይናችንን ማመን እስኪቸግረን ታምር አሳይተውናል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተስፋችንን አለምልመውታል። ትክክለኛ አመራር ካለና ከተሰራ ብልፅግና ላም አለኝ በሰማይ ሳይሆን የሚደረስበት፣ የሚዳሰስ፣ የሚቀመስና የሚጨበጥ መሆኑን ዓይናችንን ከፍተው አስመልክተውናል። ታሪካችን፣ የተፈጥሮ ሀብታችንና ዜጋችን ወደ አልማዝ እንደሚቀየር አሳይተውናል።

እንጦጦና የአዲስ አበባ ወንዞች ለዘመናት ነበሩ። የኢዮበልዩ ቤተ መንግሥትም ሆነ በስሩ ያሉ ቅርሶች ለዓመታት ነበሩ። አልማዝና ጸጋ መሆናቸውን ግን እስከዛሬ ያሳየን ማንም አልነበረም። እንዲያውም የ«ኢትኦጵ» የቀድሞው ጋዜጠኛ ዓርአያ ተስፋማርያም በዚያ ሰሞን በፋና ቴሌቪዥን ቀርቦ እንደነገረን በዘመነ ትህነግ አገዛዝ የእንጦጦ ጋራና ጫካ እንደ ማዕከላዊ ዜጎች የሚሰቃዩበት የሚገደሉበት ስፍራ ነበር። እናቶች ጀርባቸውን የሚልጥና ትክሻቸውን የሚያጎብጥ እንጨት የሚለቅሙበት ጫካ ነበር። ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ምስጋና ይግባቸውና ዛሬ እንጦጦ አልማዝ የሚለቀምበት እና ህሊና ዘና የሚልበት አድርገውታል። ከዚህ በላይ ማለም፣ ማቀድና መተግበር እንደሚቻል በተግባርና በምሳሌ ሌት ተቀን ሰርተው አሳይተውናል። ለእኔ ሸገርን የማስዋብ ፕሮጀክት ከፕሮጀክትም በላይ የብልፅግና ራዕይ የተገለጠበት፤ የብልፅግና ፍኖተ ካርታ የተነደፈበት፤ ቃል የእምነት እንጂ የአባት ዕዳ ካለመሆኑ በላይ ስጋ ለብሶ ግዘፍ ነስቶ የተገለጠበት አሻራ ነው። ሀገራችን ሰላምና ፍቅር ብትሆን፤ ዜጎቿ አንድ መሆን ብንችል፤ የሴራ ፖለቲካ ባይኖር፤ ጥላቻና መጠራጠር፤ ምቀኝነትና መጠላለፍ፤ ሌብነትና ስግብግብነት፤ ወዘተረፈ ቢወገድ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዴት ያለ ተአምር ሊያሳዩን እንደሚችል የተረጋገጠ ፍንጭ የሚሰጥ ነው። ከሁሉም በላይ የልቦና የአስተዳደር ውቅራችንን በአዲስ የበየነ ክስተት ነው። ዘጋቢ ፊልሙ ለሕዝብ ከመለቀቁ አንድ ቀን በፊት የማየት ዕድሉን ያገኙት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲው የአደባባይ ምሁር፤ ዶ/ር ሲሣይ መንግስቴ ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በእርግጥም ለዚች አገር አስደናቂ የሆነ ራዕይና ብሩህ ተስፋ ያላቸው መሪ መሆናቸውን በተግባር አሳይተውናል። ራዕይ ካለና የይቻላል መንፈስ ከተያዘ ታዕምር መስራት እንደሚቻል የሚያሳይ አስደናቂ ውጤት በአጭር ጊዜ ውስጥ ማምጣት እንደሚቻል መመልከታችንን መመስከር ተገቢ ነው ይላሉ። ዶ/ር ሲሳይ በማከልም በትብብር ከተሰራም ተስፋ ሰጪ ውጤት ማምጣት እንደሚቻል ያመላክታል ብለዋል።

እግረ መንገድ ከእሳቸው በፊትም ዛሬም ያሉ፣ የነበሩ ገዥዎችና ልሒቃን አል ሐፊድን እንዳሰደደው የቡድሀ ቄስ ዓይነት እንደነበሩ አስታውሰውናል። ሀገር በተፈጥሮ ሀብት፣ በታሪክና በባህል በደለበ ሀብት አልማዝ ተቀምጣ እያለ ደጅ ደጁን የሚቀላውጡ፣ እጁን አጣምሮ እርዳታ የሚለምኑ፣ የሕዝብን ዓይን ከፍተው ከአፍንጫቸው ስር ያለውን አልማዝ ከማሳየት

ይልቅ የስደት መንገድ ጠራጊ፣ መሪ፤ ተስፋ አስቆራጭ፣ የጎረቤት ቀላዋጭ እና የህልም፣ የርእይ ቡዳ ነበሩ ማለት ይቻላል። በደጃቸውና በጓሮአቸው ያለን የአስተዳደር፣ የአመራር መላ፣ ባህላዊ ወረት፣ የደለበ ሀገረ መንግሥት፣ ጥንታዊ ሀገር፣ ወዘተረፈ ችላ ብለው፤ የራሳቸውን አቃለው ከውጭ ሲኮርጁና ሲገለብጡ መኖራቸው ዛሬ ለምንገኝበት መውጫ ለሌለው አጣብቂኝ ዳርጎናል። በገዳማትና በአብያተ ክርስቲያናት ይሰጥ የነበረው ትምህርት ላይ ደምሮና ቀንሶ ዘመናዊ ትምህርትን ማስፋፋት ሲቻል፤ ሙሉ በሙሉ የአውሮፓን ሥርዓተ ትምህርት መገልበጣችን ዛሬ ለምንገኝበት ሁለንተናዊ ክሽፈት ዳርጎናል። ዛሬ በዓለማችን አንቱታን ያተረፉ እንደ ሀርቫርድና የል ያሉ ዩኒቨርሲቲዎች ገዳማትና አብያተ ክርስቲያናት ነበሩ። በዚህ እርሾ አብሲት ጥለው ነው ዛሬ የሚያጠግብና የሚያረካ የእውቀት እንጀራ የሚጋግሩት። ዛሬ ዋሸራና ዲማ እዚያው ባሉበት እንዲያውም ከነበሩበት ቁልቁል ወርደው ነው የምናገኛቸው። እንደ ገዳ ያሉ የአስተዳደር ዘይቤዎችን አልምቶና አጎልብቶ ሥራ ላይ ከማዋል ይልቅ የእነ ሌኒንና ስታሊን የማንነት ፖለቲካ እንዳለ ገልብጠን በመተግበራችን ሀሞት እያስተፋን ይገኛል። ሀገር በቀል እውቀቶቻችንን ትተን ደጅ ደጅ መመልከታችን ዛሬ ለምንገኝበት ህልቁ መሳፍርት ለሌለው ቀውስ ጥዶናል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሸገርን ማስዋብ ፕሮጀክት ከዚህ እኩይ አዙሪት ሰብረን የምንወጣበትን ጠባብ የማርያም መንገድ አመላክተውናል። የአረንጓዴ አሻራ፣ መደመር፣ በበረሀና ቆላማ አካባቢ ስንዴና ግጦሽን ማምረት እና የምግብ ዘይትና ስንዴን በአጭር ጊዜ ውስጥ በሀገር ውስጥ ለማምረት የተጣለው ግብ ደጃችን በአልማዝ የተሞላ መሆኑን ጠንቅቆ ከመገንዘብ የመነጨ ነው።

ከመሪነት መገለጫ አንዱ በቃል መገኘት ነውና፤ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የኢህአዴግን ውህደት በኢህአዴግ ምክር ቤት መፅደቅን እና የአዲሱ ውህድ ፓርቲ ስያሜ «የብልፅግና ፓርቲ መሰኘቱን በነገሩን ወቅት ... ብልፅግና ለኢትዮጵያ በቁስ ብቻ ሳይሆን በክብርም በነፃነትም በሁለንተናዊ መልክ ማረጋገጥ ነው። ... » ብለው ነበር። ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር በሸገርን የማስዋብ ፕሮጀክት፤ ብልፅግና ለኢትዮጵያ በቁስ ብቻ ሳይሆን በክብርም በነፃነትም በሁለንተናዊ መልክ ማረጋገጥ መሆኑን በተግባር አሳይተውናል። በሌላ መድረክ ደግሞ፤ «...ነገን እንመን፤ ተስፋን እንሰንቅ። ነገን የምንጠራጠር ከሆነ ሌሊቱ አይነጋም። ብልፅግና ጨለማው እንደሚነጋ በማመን የሚሰራ ድርጅት ነው። በርካታ ሀገራት ነጋቸውን በማመናቸው ዛሬአቸውን ሰርተዋል። ትናንት « ነገን እንመን ! » ባሉን መሠረት የእምነታችንን አስታቅፈውናል። እንደገና ነገን እንድናምንም ተስፋ አሰንቀውናል።

የፕሬዚዳንታዊ ታሪክ አጥኝዎችና የሕይወት ታሪክ ጸሐፍት ዶሪዝ ከርነስ እና ጆን ሜቻም አንድ መሪ ሊያሟላቸው ከሚገቡ ዋና ዋና ባህሪያት አንዱ የሕዝብን ችግር እንደ ራስ ማየት፣ መረዳት እና ለተከታዮቹ ተደራሽ መሆን ነው እንዳሉት፤ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር በሸገርን የማስዋብ ፕሮጀክት፤ የመንፈስና የቁስ ድህነታችንን ተረድተው በማዘን የመንፈስና የቁስ ብልፅግና ምሳሌ የሆነውን ፕሮጀክት አበርክተውልናል። ዘጋቢ ፊልሙ ላይ በመተረክም የተለመደውን ተደራሽነታቸው አረጋግጠውልናል። በዚህ ፕሮጀከት እግረ መንገዳችንን ዶ/ር ዐቢይ የሀሳብ ባህር፣ የተሰጥኦ ባለቤት፣ የተዋጣላቸው የፕሮጀክት አስተዳዳሪ፣ ሰርተው የሚያሰሩና ምሳሌ መሆን የሚችሉ መሪ ብቻ ሳይሆኑ ባለብዙ ሙያ፣ ክህሎትና እውቀት ባለቤት መሆናቸውንና የተሳካላቸው የዘጋቢ ፊልም አዘጋጅ ፣ ዳይሬክተርና ጥሩ ተራኪም እንደሆኑ ተረድተናል።

አብቹ ገለቱማ !ሀገራችን ኢትዮጵያን እና ሕዝቧን ፈጣሪ ይጠብቅ !አሜን !

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተስፋችንን

አለምልመውታል፡፡ ትክክለኛ

አመራር ካለና ከተሰራ ብልፅግና ላም

አለኝ በሰማይ ሳይሆን የሚደረስበት፣

የሚዳሰስ፣ የሚቀመስና የሚጨበጥ

መሆኑን ዓይናችንን ከፍተው

አስመልክተውናል፡፡

Page 7: ከባንክ ውጭ ከ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር በላይ ማስቀመጥ ተከለከለሕግ • ዶ/ር ሳሙኤል ሁርካቶ፤ የሳይንስና ከፍተኛ

ይህ ዓምድ በተለያዩ ፖለቲካዊ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ዜጎች ነፃ አስተያየታቸውን የሚሰጡበት ነው። በዓምዱ ላይ የሚወጡ ጽሑፎች የዝግጅት ክፍሉን አቋም አያመለክቱም።

በጌታቸው በለጠ/ዳግላስ ጴጥሮስ)

አዲስ ዘመን ረቡዕ ነሐሴ 13 ቀን 2012 ዓ.ምገጽ 7

ነፃ ሀሳብልጆቿን ከብሔራዊ ፈተናዎች አዘግይታራሷ በብሔራዊ ፈተናዎች እየተፈተነች ያለች ሀገር

ማጣቆሚያ፤ የሀገራችን ተማሪዎች የትምህርት ቤታቸው

ቅጥረ ግቢ ተዘግቶ በራሳቸው ግቢ ታጥረው እንዳሉ ይታወቃል። ምክንያቱ ደግሞ ኮቪድ መሆኑ ግልጽ ነው። ይሄም ቢሆን ግን የስምንተኛና የአሥራ ሁለተኛ ክፍሎችን መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተናዎችን እንደሚፈተኑ የሚጠበቁት ልጆቻችን ልባቸው በተስፋ ተንጠልጥሎ በመጻሕፍቶቻቸውና በደብተሮቻቸው ላይ ዓይኖቻቸውን ተክልው፤ በልባቸው ደግሞ የመከራ ቀናቱ እንዲያጥሩ በጸሎት እየቃተቱ እንደየእምነታቸው ፈጣሪያቸውን ሲማጸኑ እያስተዋልንም እየሰማንም ነው። ከፈተና የዘገዩት ተማሪዎቻችን ጥሪ እስኪደረግላቸው ድረስ በማሕበራዊና በተፈጥሮ ሳይንስ ትምህርቶች ጥናት ላይ በአሸናፊነት ለመውጣት ዝግጅት እያደረጉ መሆናቸው እንደተጠበቀ ሆኖ በአንጻሩ ሀገራቸው ኢትዮጵያ በወቅት ወለድ «የአብቲትዩድ ፈተና» ተቀስፋ እያቃሰተች እንዳለች የሚጠፋቸው አይመስለም። እየተጋፈጠችው ያለውን የፈተናዋን ዝርዝርና ዓይነት ዝቅ ብዬ አብራራለሁ።

ማዝገሚያ፤የዓለማችንን መሠረቶች ያናጋው ኮቪድ እንደ ሌሎቹ

አህጉራትና ሀገራት ሁሉ እኛንም ከመናጥ ቸል አላለም። ልዩነቱ መሠረታቸውን በዓለት ላይ ያነፁ ሀገራት ከፋም ለማም ለጊዜው ይንገዳገዱ ካልሆነ በስተቀር ጨርሶውኑ ተንኮታኩተው ላይወድቁ ይችላሉ። ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ መሠረታቸውም ሆነ ማሕበራዊ ቅኝታቸው ጠንካራ ስለሆነ ፈጥነው ለማገገም አይሳናቸውምና። ችግሩ ጎልቶ የሚታየው በተፈጥሮ ሀብት በልጽገው፣ ከአስተሳሰብ ድህነት ጋር በመናቆር ከጠብመንጃ ጨዋታ መላቀቅ በተሳናቸው አፍሪካን መሰል «ያልታደልሽ እንዴት አደርሽ» አህጉራትና ሀገራት ላይ ነው። እነዚህ ሀገራት ፖለቲካቸው፣ ኢኮኖሚያቸውና ማሕበራዊ መዋቅራቸው የታነፀው በድቡሽት ላይ ስለሆነ ኮቪድ ሙሉ ለሙሉ በቁጥጥር ሥር እስካልዋለ ድረስ ንፋሱንና ጎርፉን ተቋቁሞ ለማለፍ አቅማቸው ልፍስፍስ ስለሚሆን አወዳደቃቸው ሊከፋ እንደሚችል መገመቱ ከሃሳዊ መሲህነት አያስቆጥርም።

ሀገሬ እየተፈተነችባቸው ያሉትን መልከ ብዙ የፈተና ዓይነቶች ሳስብ ለጊዜው መንፈሴ ኮምጠጥ ቢልም ተስፋችን ግን የለመለመ ስለሆነ እጅግም የእምነቴ ጉልበት አይርድም። እርግጥ ነው የሀገሪቱ ኢኮኖሚ በጸና መሠረት ላይ የቆመ ባለመሆኑና የኑሮው ውድነት «ርእደ መሬት» ከዕለት ወደ ዕለት እየጠነከረ በመሄድ ላይ ስለሆነ እንቅጥቃጤው ከጓዳችን ድረስ ዘልቆ መሰማት ከጀመረ ሰነባብቷል። የኮሮናው ምት ከመሻሻል ይልቅ እየጠነከረ በመሄድ ላይ ስለመሆኑም ዕለት በዕለት በምናደምጠው ሪፖርቶች እንደተሳቀቅን አለን። በብዙ ጉዳዮች የታቀብንበት የማሕበራዊ ምሰሷችንም ቢሆን ነውጡ የበረታበት መሆኑን ባንክድም ጎብጦ ካልሆነ በስተቀር ጭራሹኑ የሚሰበር ደረጃ ላይ ደርሷል ማለት አይቻልም። ከኢኮኖሚያዊና ከማሕበራዊው አእማድ ይልቅ በዋነኛነትና በከፍተኛ ንዝረት እየተጠቃ ያለው የፖለቲካው አምድ ይመስላል።

ሀገሬ እየተፈተነችበት ያለው «የአብቲትዩድ ቴስት» ይዘት በእነዚህ ሦስት ብሔራዊ ጉዳዮቻችን ዙሪያ የሚያጠነጥን ነው። ለመሆኑ «አብቲትዩድ ቴስት» ምንድን

ነው? ለምንስ የሀገሬ ፈተናዋ በአብቲትዩድ ሊመሰል ቻለ? ምልከታዬንና ማነጻጸሪያውን በጥቂቱ ላብራራ። አብቲትዩድ ቴስት የሚመዝነው በተፈጥሮና በትምህርት ወይንም በተሞክሮ የተከማችን ዘርፈ ብዙ እምቅ እውቀት እንጂ የተሸመደደን የትምህርት ዓይነቶች ብቻ አይደልም። ፈተናው ጥበብን፣ ማስተዋልን፣ ማሰላሰልን፣ ማገናዘብን ወደፊትና ወደኋላ መመልከትን፣ በርካታ «ጠቢባን አማካሪዎችን» ከጎን ማሰለፍን ይጠይቃል። በአብቲትዩድ ቴስት የሚገመትም ሆነ የማይገመት ተግዳሮት ቢያጋጥም ለምን ያልተማርኩት ጥያቄ ሊመጣ ቻለ ተብሎ አይጠየቅም።

ሀገሬንም የተጋረጣት ይህንን መሰል ዝንጉርጉር የፈተና ዓይነት ነው። በኮቪድ ምክንያት ልጆቿን ከትምህርት ቤት ውጭ በማድረግ በብብቷ ውስጥ ሸሽጋቸው ብሔራዊ ፈተናዎቻቸውን ብታራዝምላቸውም እርሷ ግን ከላይ በዘረዘርኳቸው መሠረታዊ የብሔራዊ ፈተናዎቿ ስትጨነቅ ማየት «ጎሽ ለልጇ ስትል ተወጋችን» ብሂል ያስታውሰናል።

ከፊቷ ተጋርጠው እየፈተኗት ያሉት «የአብቲትዩድ ቴስት» ጋሬጣዎች በአንጻራዊ መልኩም ቢሆን ከአሁን በፊት ተፈትና ካለፈችባቸው ፈተናዎች ሁሉ በእጅጉ የሚለይ ባህርይ እንዳላቸው ቢገባኝም ለማሳያነት ግን ማነጻጸሪያ ምሳሌዬ በደብዛዛነቱም ቢሆን ሥዕሉን ሊያሳየን የሚችል ይመስለኛል።

እርግጥ ነው የውጥር ይዞ የቀሰፈን ሀገራዊ ፈተናችን ውስብስብና ዝንጉርጉር ቢመስልም በጨለማው ብርታት ተረትተን እንሸነፋለን ማለት ግን አይደለም። በፍጹም። ከኮቪድ ወረርሽኙ ጎን ለጎን ከውስጥ የሚያምሷት፣ ከውጭ ሆነውም የጦርነት ከበሮ እየደለቁ «እንደ አዶ ከበሬ» በማጓራት የሚገዳደሯት ቀስተኞች ከመቼውም ጊዜ ይልቅ ዛሬ እጅና ጓንት ሆነው በመተቃቀፍ ለጥፋት መሰለፋቸው እያረርን እንድንስቅ አድርጎናል። ከየአቅጣጫቸው ጡጫቸውን በመሰንዘርም ከመፋለሚያው መድረክ (ሪንግ) ላይ ገፍትረው ሊጥሏት ቢሞክሩም «ሞክረን ነበር» ከማለትና ከመሸነፍ ውጪ በምንም ሁኔታ የድል በለስ ቀንቷቸው እንደማያቅራሩ አስረግጦ መናገሩ አያሸማቅቅም።

የአፕቲትዩድ ቴስቱን እየተፈተነ ያለው ጠቅላላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ቢሆንም ለፈተናው የሚቀመጠውና በአሸናፊነት የሚወጣው ግን በዋነኛነት የሕዝብን ውክልና የተቀበለውና በሥልጣን ላይ ያለው መንግሥት ነው። በጸሐፊው የአመለካከት ዐውድ መንግሥት ስል ፖለቲካዊ ሥርዓቱን የሚዘውረውን ሉዓላዊ መዋቅር ማለቴ እንደተጠበቀ ሆኖ የማተኩረው ግን የመንግሥት ሥርዓቱን በተቀዳሚነት እየመሩ ያሉትን ጠቅላይ ሚኒስትሩን ይሆናልና ትኩረቴን በእርሳቸው ላይ አድርጌ ምልከታዬን እቀጥላለሁ።

በወጅብ መካከል ጸንተው የቆሙት ሰውዬ፤ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ መንበረ ሥልጣኑን

የያዙበትን ጊዜ መነሻ አድርገን በቀናት ቁጥር እናመላክት ካልን እስከ ዛሬዋ ቀን ድረስ ያስቆጠሩት 870 ቀናትን ብቻ ነው። የበርካታ ሀገራት መንግሥታት ወደ ሥልጣን ሲወጡ የሚገመገሙበትን አንድ ሺህ ቀናት እንኳን ገና አልደፈኑም። በእነዚህ ውሱን ቀናት ውስጥ በፈተናና በወጀብ ታጅበው ያከናወኗቸው ሀገራዊ ስኬቶችን እንዘርዝር ብንል በርካታ ማስረጃዎችን ማቅረብ ይቻላል። ሰውዬው የሌት እንቅልፍም ሆነ የቀን እረፍት እንደሌላቸው የምናረጋግጠው በቃላቸው ስለነገሩን ብቻ ሳይሆን በህዋ፣ በውሃ እና በየብስ ላይ ባስመዘገቧቸው ውጤቶችና ተግባሮቻቸው ጭምር ነው። እውነታውን በማሳያ አብነቶች ላመላክት። በህዋ ላይ (ETRSS-1 የሳተላይታችንን መምጠቅ)፣ በውሃ ላይ (ከታላቁ

የህዳሴ ግድባችን ጋር የሚጠቀሰውን ድል)፣ እና በየብስ ላይ (የቢሊዮኖች ችግኝ ተከላ ስኬትና የሪፎርምና የግንባታ ውጤቶችን) ብቻ ማስታወሱ በቂ ይሆናል። በእነዚህ ክስተቶች ላይ ያሳረፉትን ደማቅ አሻራ አክብሮ አለማመስገን ንፉግነት ተብሎ ብቻ የሚታለፍ ሳይሆን ከዚያ ከፍ ያለ መግለጫ ቢሰጠውም ሲያንስበት ነው።

በቅዱስ መጽሐፍ ውስጥ ለየትኛውም እምነት ተከታይ ወገን የሚበጁ የመልካም ሰብእና መመዘኛ አምስት አእማድን ላስታውስ። አምስቱ አእማድ ብዬ የሰየምኳቸው ትዕዛዛት በጢሞቴዎስ መጽሐፍ ውስጥ እንደሚከተለው ተዘርዝረዋል። «በቃል፣ በኑሮ፣ በፍቅር፣ በእምነት፣ በንጽሕና ምሳሌ ሁን» (1ጢሞ. 4፡11-12) ጠቅላይ ሚኒስትሩ በእስካሁኑ የሥልጣን ጉዟቸው እነዚህን የሕይወት መርሆዎች በተግባር እየተረጎሙ ተልዕኳቸውን እየተወጡ ስለሆነ «አሹ!» ብሎ ማበረታታት አስተዋይነት ነው። በግል ሕይወታቸው ብቻም ሳይሆን በመደመር መጽሐፋቸው ይዘት እና በሚያምኑበት የፖለቲካ ፍልስፍና ጭምር እነዚህን አንኳር መርሆዎች በአስኳልነት እያጎሉ ሲጠቅሷቸው ደጋግመን ሳናደምጥና ሳናስተውል የቀረን አይመስለኝም።

ሰውዬው በገቡልን ተስፋ ምሳሌነታቸውን አላጓደሉም ስንል ለሕዝብ የሚገቡትን ቃል በተሻለ ውጤት ሲፈጽሙ ስለምናስተውል ነው። የሰሞኑን አስገራሚ ክስተት ብቻ ማስታወስ በቂ ይመስለኛል። «እንደ አንድ የቱሪስት ጋይድ» ራሳቸው አስጎብኚ ሆነው በዩኒቲ ፓርክ፣ በኢዮቤልዩ ቤተመንግሥት፣ የሸገር ወንዝ ዳርዎች አካል በሆነው የሸራተን አካባቢና በእንጦጦ ደን ውስጥ የተሰሩትን መናፈሻዎች ስንመለከት መቼ ታቅደው መቼ እንደተከናወኑ ለመገመት እስኪያስቸግር ድረስ በግሌ «አጃኢብ!» አሰኝቶ እጄን በአፌ ላይ አስጭኖኛል።

ይህንን ስኬት ያለማመስገን ክፋት እንጂ በጽድቅነት የሚያስቆጥር አይሆንም። ይህ ውጤት አልዋጥ ብሎ የጎፈነናቸው ግለሰቦችና ቡድኖች ወቅታዊ ሀገራዊ ችግሮቻችንን እየዘረዘሩ «ቅድሚያ ለማይሰጠው ጉዳይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሀብት እያባከኑ ነው!» እያሉ ቢያብጠለጥሏቸውም የሚያስለፈልፋቸውና የተጠናወ ታቸው እኩይ ጂኒ እንጂ ሌላ ስለማይሆን ንቆ ማለፉ ጥበብ ነው። እርግጥ ነው በአፕቲትዩድ ቴስት የመሰልነው ሀገራዊ ፈተናችን መልኩ የተለያየ ብቻ ሳይሆን እያስከተላቸው ያሉት ውጤቶችም መፃኢው ትውልድን ሳይቀር የሚያሸማቅቁ ናቸው። ቢሆንስ በችግሮቹ ጉዝጓዝ ላይ አንጥፎ በመቀመጥ ማላዘን ይሻላል ወይንስ ችግሮቹን በሰከነ አመራር እየፈቱ በልማት ላይ መረባረብ ይበጃል? ጥያቄውን እንዲመልሱ ዕድል የምሰጠው ለጨለምተኞቹ ተቺዎች ለራሳቸው ይሆናል።

ሰውዬው ቃላቸው ብቻ ሳይሆን አኗኗራቸውም በራሱ ምሳሌነት ያለው ነው። ዝቅ ማለት አይከብዳቸውም። መገልገል ብቻ ሳይሆን ማገልገልም ዳገት አይሆንባቸውም። ሥራንም ሆነ ሠራተኛን ትንሽ ትልቅ ብለው አይነቁም። እጃቸውም አፈር አይጠየፍም። ቀድመው አርአያ ለመሆንም ትጉህ ናቸው። በቃልና በኑሮም ብቻ ሳይሆን ለፍቅርም ቢሆን በርካታ የጎሉ ምሳሌነትን አሳይተውናል። በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል ያበዱ ፖለቲከኞች ለዓመታት የገነቡትን የጥል ግድግዳ አፍርሰው ሁለት ወንድማማች ሕዝቦች በፍቅርና በይቅርታ እንዲተቃቀፉ ማድረጋቸውን ማስታወሱ ብቻ በቂ ነው። የዓለም የሰላም ሎሬት ተብለው መሸለማቸውም በዚሁ የፍቅር ተምሳሌትነታቸው መሆኑ የሚዘነጋ አይደለም።

የማረሚያ ቤቶችን በሮች ወለል አድርገው በመክፈት የፖለቲካና የህሊና እስረኞችን የሰንሰለት ካቴና ከእጃቸው ላይ በመቁረጥ ነፃ መልቀቃቸው፣ ለግድያ የሚፈላለጉ ጠበኞችን አስታርቀው ማስተቃቀፋቸውና ማጨባበጣቸው፣ ስደተኛ ወገኖችን በራሳቸው ጎን አስቀምጠው በማጓጓዝ ለሀገራቸው አፈር ማብቃታቸው፣ ከፖለቲካ ወደረኞቻቸው ጋር በአንድ ወንበር ተቀምጠው መወያየታቸው፣ ለእምነት ቀኖናቸውና አስተምህሯቸው ብቻ ሳይሆን ከፈጣሪያቸው ጋር ጭምር ላለመታረቅ አሻፈረኝ ብለው ሙግት የገጠሙ የየቤተ እምነትን መራሄ ሃይማኖት አባቶች አቀራርበው ማስታረቃቸው ወዘተ. ለፍቅር ሰውነታቸው ጥሩ ማሳያዎችና መገለጫዎች ናቸው።

ሀገራቸው በአጭር ዓመታት በልጽጋ ፊት ቀደም እንድትሆንና ሕዝባቸውም ተባርኮ የድህነትን ትቢያ ከራሱ ላይ በማራገፍ ሰጪ እንጂ ተቀባይ እንዳይሆን መጨከናቸውም ከንግግር ያለፈና በተግባር እየተረጋገጠ

ስለመሆኑ የአደባባይ ምሥጢር ነው። በቃል፣ በኑሮ፣ በፍቅር ብቻም ሳይሆን በንጽህናም አይታሙም። እንኳንስ እጃቸውን በመንግሥት ካዝና ውስጥ ከተው እንደ ቀዳሚ ጓደኞቻቸው የሀገሪቱን የድህነት መክሊት ሊቦጠቡጡ ቀርቶ በስሜት እንኳን እንደማይፈተኑ ብንመሰክር «በምን አረጋገጣችሁ!» ተብሎ የሚያስጠይቅ አይሆንም። እኛ የምናውቀው ቀደምት መሪዎች ከሀገሪቱ መቀነት ላይ አዋዩዋን ያለርህራሄ ቦጥቡጠውና አራግፈው በስማቸው የውጭ ሀገራትን ባንኮች ሲያደልቡና ለራሳቸውና ለቤተሰቦቻቸው መቀናጫ ሲያደርጉ ነው።

እርሳቸው ግን ዓለም ከአድናቆት ጋር አጨብጭቦ የሸለማቸውን ማትጊያ ሳይቀር ሳይሰስቱና ሳይፈተኑበት ለሀገራቸው ልማት ሲያውሉ እያስተዋልን ነው። ከዚህ በላይ ልግስናና ንጽህና ከየት ይመጣል። የውስጥ ማንነታቸው ንጽህና የህሊናቸው ንጽህና መገለጫ እንደሆነ በሚገባ ተግባራቸው እያወጀላቸው ነው። አካባቢንና የሥራ ቦታን አስቀድሞ በማጽዳት ተግባርን መጀመር በራሱ ሥነ ልቦናዊ ትርጉሙ ላቅ ያለ ነው። እርሳቸው በጣታቸው ለመንካት የሚጠየፉትን ሸክም ሕዝቡ እንዲሸከም ስለማይፈልጉ ቀድመው በአርአያነት ትከሻቸውን ጎንበስ በማድረግ ሠርተው ያሳያሉ። ቃላቸው፣ ኑሯቸው፣ ፍቅራቸውና ንጽህናቸው ብቻ ሳይሆን በሀገራቸው ብልጽግናና መለወጥ ላይ ያላቸው እምነትም እንደ በሃ ድንጋይ የሚፍረከረክ ሳይሆን እንደ ባልጩት ድንጋይ የጠነከረ ነው። በአሥር ዓመታት ውስጥ ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ሀገራት መካከል ዋነኛ ተጽእኖ ፈጣሪ መሆኗን የሚያረጋግጡልን ልብን በሚያሞቅ እምነታቸው የሕዝባቸውንም ስሜት እያጋሉ ነው። ጅምር ሥራዎቻቸው ፅኑ እምነታቸውን አሜን ብለን እንድንቀበል ማረጋገጫውን ሰጥተውናል።

የሰውየው የውስጥና የውጭ መልክ ይህ ነው። ስለዚህም ነው የሀገራችንን መልከ ብዙ «የአብቲትዩድ ፈተና» ተፈትነው ሕዝባቸውን ወደ ታላቅ ከፍታ እንደሚያሸጋግሩ ቅንጣት ያህል ጥርጣሬ የማይገባን። ሀገሬን የውጥር ይዞ ጫን ጫን የሚያስተነፍሳትን ብሔራዊ ፈተና በአሸናፊነት ከፍ ማድረጋቸው እንደተጠበቀ ሆኖ በማዲያት የተበላሸውን መልኳን እንደ ወርቅ አንጥረው ያስውቧት ካልሆነ በስተቀር ብዙዎቹ ንግርተኞች እንደሚጮኹት እንደ በረዶ አሟሟተው አያቀልጧትም።

መቼም ባህላችንና አስተዳደጋችን የቃኘን የተሰራውንና የተሞከረውን መልካም ውጤት ፈጥኖ ከማመስገን ይልቅ ተሽቀዳድሞ መንቀፍን እንድናስቀድም ስለሚያስገድደን የውስጣችን ጨለማ ለበጎ ነገሮች ሁሉ ግርዶሽ እንደሆነብን ዘልቋል። ከዚሁ የአስተዳደግ ውርሳችን ጎን ለጎን በክፉ ቅንዓት ጥቁር ቱቢት ህሊናችንን ጋረደን ቢጫውን ጥቁር፣ ነጩን ቀይ እያልን ለመሟረት አይከብደንም። ክፉ መርገምት ይሏል ይህንን ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሥልጣን ላይ ከወጡ ጊዜ ጀምሮ ያከናወኗቸውን መልካም ተግባራት ነቅፎ ለማስነቀፍ ታጥቀው የተነሱ፣ ተማምለው የተወዳጁ ብዙዎች ናቸው። ለካንስ ከሀገር ማህጸን ውስጥ የሚወለደው ልጅ ብቻ ሳይሆን በደመ ነፍስ የሚንቀሳቀሱ የእንግዴ ልጆችም አብረው ይወለዳሉ?

እርግጥ ነው መሪዎች ስህተት ሲሰሩ የዜጎች ዓይኖችም ሆኑ ሕጉ ሊከታተላቸው የሚገባቸው በአትኩሮት ነው። መልካም ሥራዎች ሲተገበሩም የታጠፉ እጆች ተዘርግተው ሊያጨበጭቡ ግድ ይሏል። ያለበለዚያ መሪዎች በቀኝ እየተራመዱ ተግባራቸው ላይ ደፋ ቀና ሲሉ፤ የመሰናክል ድንጋይ ተሸክሞ በግራ በኩል በመታጠፍ ከፊታቸው ለመኮልኮል መሞከር በሰይጣናዊ ተግባር ከመፈረጅ በዘለለ ለበረከት ሆኖ የሚመረቁበት ጉዳይ አይሆንም። ለማንኛውም ፈተናው ቢያይልም ሀገሬ «የአብቲትዩድ ቴስቷን» በአሸናፊነት ተወጥታ ዓለም እንደሚያጨበጭብላት በፍጹም ጥርጥር አይገባንም። ከአሁን ቀደም በተውሶ ያገኘኋትንና ጥቂት ማሻሻያ በማድረግ በዚሁ ገጼ ላይ ያስነበብኳትን አንዲት ባለ ሁለት ስንኝ ግጥም ደግሜ በማስታስ ማሳረጊያ ላድርጋት።

«እነርሱን ተዋቸው ሥራህን ይናቁ፣አንተ ባጋጋምከው በወይራ ፍልጥ እሳት ምራቅ እየተፉ።»ሰላም ይሁን!

ሀገሬ እየተፈተነችባቸው

ያሉትን መልከ ብዙ

የፈተና ዓይነቶች ሳስብ ለጊዜው

መንፈሴ ኮምጠጥ ቢልም

ተስፋችን ግን የለመለመ ስለሆነ

እጅግም የእምነቴ ጉልበት

አይርድም፡፡

Page 8: ከባንክ ውጭ ከ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር በላይ ማስቀመጥ ተከለከለሕግ • ዶ/ር ሳሙኤል ሁርካቶ፤ የሳይንስና ከፍተኛ

ረቡዕ ነሐሴ 13 ቀን 2012 ዓ.ም

ገጽ 8ተጠየቅ

ሶሎሞን በየነ

«ኢትዮጵያን የሚጎበኝ ቢኖርም አስተናጋጅ የለም፤ አስጎብኝ የለም መባል የለብንም»

አቶ ገዛኸኝ አባተ

የሆቴልና ቱሪዝም ሥራ ማሰልጠኛ ማዕከል ምክትል ዋና ዳይሬክተር

አዲስ ዘመን፡- ተቋሙ ሲመሰረት ዓላማው ምን ነበር?

አቶ ገዛኸኝ፡- ለሆቴልና ቱሪዝም ኢንዱስትሪው አገልግሎት የሚሰጥ ባለሙያ የሰው ኃይል ማፍራት ነው።

አዲስ ዘመን፡- በ51 ዓመታት ጉዞው ያበረከተው አስተዋጽኦ ምን ይመስላል?

አቶ ገዛኸኝ፡- የዚህ ተቋም አስተዋጽኦ በጣም ከፍተኛ ነው። ፋናወጊ የሆነ ተቋም ነው። በኢንዱስትሪው ከከፍተኛ ባለሙያነት እስከ ባለሀብትነት አንቱ የተባሉ የሰው ኃይል ከማፍራት አንጻር ከፍተኛ የሆነ አስተዋጽፆ ያበረከተ ብቸኛና አንጋፋ ተቋም ነው ብሎ መውሰድ ይቻላል። ለምሳሌ አሁን ባሉ ትላልቅ ሆቴሎችና በአስጎብኝ ተቋማት በባለቤትነት፣ በማህበር መስራችነት፣ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ውስጥ በመምህርነትና በአሰልጣኝነት ወዘተ… ያሉ ትላልቅ ሰዎች የዚህ ተቋም ውጤቶች ናቸው። የመጀመሪያዎቹ ተማሪዎች እዚህ ተምረው የውጭ የትምህርት ዕድል ያገኙም ናቸው። እነርሱ አሁን የሆቴል ባለቤት፣ ሥራ አስኪያጆች፣ ሱፐርቫይዘሮች፣ አማካሪዎች ናቸው። በቱሪዝሙም በሆቴሉም ዘርፍ በሁለት ክፍል የጀመረው የማሰልጠኛ ተቋም ከ20ሺ ያላነሰ ሙያተኛ ለኢንዱስትሪው አበርክቷል።

ከዚህ ጎን ለጎን ለሌሎች ተቋማት መመስረት ትልቅ አስተዋጽፆ አለው። የትኛውም አካባቢ ቢኬድ የሆቴልና ቱሪዝም ተቋማት ሲከፈቱ በመንግሥትም ይሁን በግል ደረጃ ልምድና የማጣቀሻ መጽሐፎችን ጭምር የሚወስዱት ከዚህ ነው፤ ለዘርፉ አስተዋጽፆ ሊያበረክቱ የሚችሉ ለስልጠና፣ ለምርምርና ለትምህርት የሚሆኑ ወቅታዊ የሆኑ ማጣቀሻዎችን ማግኘት የሚቻለው ከዚህ ተቋም ነው።

በአሁኑ ወቅት ቁጥራቸው 14 የሚደርሱ ዩኒቨርሲቲዎች በሆቴልና ቱሪዝም ማኔጅመንት ዘርፍ ትምህርትና ስልጠና ይሰጣሉ። ለምሳሌ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ የትምህርት ክፍሉን ለማደራጀት ብዙ ግብዓቶችን ከዚህ ተቋም ተጠቅሟል። ከዚህ በተጨማሪ ኤምባሲዎች ከተቋሙ ጋር ግንኙነት ሲኖራቸው የእኛን ተማሪዎች በማሰልጠን የልምድ ልውውጥ እናደርጋለን። ተቋሙ የሰለጠነ የሰው ኃይል በማፍራት ኢንዱስትሪው አሁን ያለበት ደረጃ እንዲደርስና የማኔጅመንት ኢንስቲትዩት በማደራጀት ከፍተኛ አስተዋጽዖ አበርክቷል።

ይህ ተቋም ሌሎች የመንግሥት ተቋማትን በተለይ የምግብ ዝግጅትና የመኝታ መስተንግዶ የሚሰጡ ድርጅቶችን የማማከርና የማደራጀት ሥራ በስፋት ይሰራል። ስለዚህ ከመደበኛው ሥልጠና ጎን ለጎን በጥናትና በማማከር ከፍተኛ አስተዋጽዖ እያበረከተ ያለ ተቋም ነው።

አዲስ ዘመን፡- ባለፉት 51 ዓመታት ያጋጠሙት ተግዳሮቶች ምንድን ናቸው?

አቶ ገዛኸኝ፡- ይሄ ተቋም ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ የሆቴልና ቱሪዝም ዘርፉ መሪዎች ለንግግር ማጣፈጫ ካልሆነ በስተቀር በተለይ ከለውጡ በፊት የነበሩት ‹‹አገራችን እንግዳ ተቀባይ ናት›› ከማለትና ከወሬ ማጣፈጫ ባሻገር ወደ ትክክለኛው ትግበራ መጥቶ ይሄንን ሰራሁ የሚል መሪ አልነበረም።

አሁን ላይ የሚታዩ ተስፋዎች ቢኖሩም የዚህ ተቋም አንዱ ችግር የትኩረት ማጣት ችግር ነው። ይሄ ተቋም በከፍተኛ ትምህርትና በኮሌጆች የሚሰጡ ስልጠናዎች የሚተኩት ተቋም አይደለም። እያንዳንዱ ሚኒስቴር መስሪያቤት ወይም በመንግሥት ደረጃ የሚቋቋም ትልቅ የመንግሥት አካል ከዘርፉ ፍላጎት የመነጨ የሰው ኃይል ማፍራት ይኖርበታል።

ተቋሙ በሆቴልና በቱሪዝም ዘርፍ ከፍተኛ የሆነ የሰው ኃይል ፍላጎት ለማምጣት የተቋቋመ ተቋም ነው። በከፍተኛ ወይም በሌላ ስር ያልሆነበት ትልቁ ምክንያት የኢንዱስትሪውን ችግር በቅርበት ሊፈታ የሚችል የሰው ኃይል የማፍራት ኃላፊነት እንዲወጣ ነው። አንደኛ የአጭርና የረጅም ጊዜ ስልጠናዎችን ይሰጣል። ሁለተኛው

ማማከር ነው፤ ሦስተኛው ጥናትና ምርምር ነው። ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ከባለድርሻ አካላት

ጋር ከውጭ የሚያገኛቸውን ተሞክሮዎችን ለዘርፉ የሚቀርጻቸውን ፖሊሲና ስትራቴጂዎች ለማስፈጸም በዘርፉ የአቅም ግንባታ ሥራ ያስፈልጋል። ይሄ የአቅም ግንባታ ሥራ በዩኒቨርሲቲ የተለያዩ ዲግሪና ዲፕሎማዎች ስልጠና የሚሸፈን ይኖራል፤ በጥናትና ምርምር የሚፈታም ይኖራል።

የሆቴል ኢንዱስትሪው ካልሰፋ፤ አስጎብኝ ካላገኘን፤ ማናጀሮችን ማፍራት ካልቻልን ቱሪስቱ ‹‹ኢትዮጵያ ውስጥ ሄደን የሚጎበኝ ቢኖርም አስተናጋጅ የለም ፤ አስጎብኝ የለም›› መባል የለብንም።

ኢንዱስትሪው ትኩረት በማጣቱ ይሄ ተቋም ባለበት ደረጃ ከኢንስቲትዩት ደረጃ ወደ ማዕከልነት ነው የወረደው። የተቋሙ አመራሮች ብቻ ሳይሆን በወቅቱ የነበሩ ካቢኔዎች ከኢንስቲትዩት ወደ ማዕከልነት አጽድቀው ነው የወጡት። ‹‹ሴንተር ኦፍ ኤክሰለንስ›› ይሁን ብለው ሰነድ ሲልኩ ‹‹ኤክሰለንስ›› የሚለውን አጥፍተው ‹‹ሴንተር›› ብለው አመጡት። ስለዚህ ከኢንስቲትዩትነት ወደ ማዕከል አወረዱት። በአሁኑ ጊዜ ሆቴልና ቱሪዝም ማሰልጠኛ ማዕከል ነው የሆነው። መጀመሪያ የነበረው ኢንስቲትዩት ነበር። በዲፕሎማና በተለያዩ ደረጃዎች ያሰለጥን ነበር። አሁን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የገባው ሰነድ የነበረው እንዲመለስ የሚጠይቅ ነው። አሁን ያለው ማዕከል ማለት ከኢንስቲትዩት በታች ነው። በነበሩ አመራሮች በተፈጠረ ክፍተት ተቋሙ ወደታች እንዲወርድ አድርገውታል። ስለዚህ አንዱ ያጋጠመው ችግር የትኩረት ማጣት ችግር ነው።

ከሁሉም የአገሪቱ ክፍሎች ነው ተማሪዎችን የምናሰለጥነው። በሁሉም የቴክኒክና ሙያ ደረጃ ተማሪዎችን እናሰለጥናለን። ትምህርት ቤቱ ዶርም የለውም። እንደ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ የሚመደብለት 510 ብር ነው። በ39 ጣቢያዎች ላይ በምናደርገው ምልመላ ከቅድመ ገለፃ ጀምሮ በሁሉም ክልሎች 39 የክልልና የዞን ከተማዎች በአቅራቢያ ኮታ እንሰጥና በየአካባቢዎቹ ለየዘርፎቹ ተማሪዎችን ከለየን በኋላ ተማሪዎች እንዲመጡ እናደርጋለን። ከመምጣታቸው በፊት ገለፃ እንሰጣለን። ‹‹ከጓደኛ ጋር ቤት ተከራይታችሁ፤ ለምግብ ወላጆች ድጎማ አድርገው ነው የምትማሩት›› ብለን ስለምንነግራቸው እነዚህ ተማሪዎች ለተለያዩ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ይጋለጣሉ። በኮቪድ ምክንያትም የማስተማሪያ ክፍሎችን ለማመቻቸት አልቻልንም።

ልምድ ያላቸው በትልልቅ ሆቴሎች የሰሩ፤ በጥናትና ምርምር በተለያዩ ደረጃዎች እስከ ዶክትሬት ዲግሪ የተማሩ ብቃት ያላቸው መምህራን በዘርፉ አሉ። ይሄ ተቋም ነው ሌሎቹን የመሰረተው። ተቋሙ ወደከፍተኛ ትምህርት ያላደገበት ምክንያት ጥናት የሚያስፈልገው ቢሆንም በእኔ አስተያየት ምክንያቱ የዕይታ (የአመለካከት) ችግር ነው ብዬ ነው የምወስደው። ኢንዱስትሪው ታሪኩ ሊወራለት ይችላል፤ ነገርግን የሚያስፈልጉ ነገሮች አልተሟሉለትም።

የትልልቅ ሆቴል ማናጀሮች ከኬንያ ይመጣሉ። የእኛ አገር ደግሞ ዲግሪና ማስተርስ ይዘው በየሥራ ማስታወቂያው ቦርድ ሲሰለፉ ይውላሉ። ይሄ ተቋም ኢንዱስትሪው እያደገ ሲሄድ በማስተርስና በዲግሪ ደረጃ ያሉትን ዕድሎች ለኅብረተሰቡ በማሳወቅ አሰልጥኖ ወደ ኢንዱስትሪው ለማቀላቀል ትክክለኛውና ብቸኛው ተቋም ነው። አሁን ከሸገር ማስዋብ ፕሮጀክት ጋር በጋራ ስለምንሰራበት ጉዳይ በስፋት እየተነጋገርን ነው።

አዲስ ዘመን፡- ተቋሙ ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋምነት እንዲያድግ ያቀረባችሁት ጥያቄ እንዲተገበር በምን መልኩ ግፊት እያደረጋችሁ ነው?

አቶ ገዛኸኝ፡- ጥያቄው የቀረበው አሁን ካሉት ሚኒስትር በፊት ባሉት ሚኒስትሮች ጊዜ፣ ከለውጡ በፊት ነው። ከለውጡም በኋላ ቀርቧል። በመካከል የኮሮና ጉዳይ መጣ። አሁን ያሉት ሚኒስትርም ሥራዬ ብለው እንደሚከታተሉት ተስፋ አለን። እኛ እንደተቋም ችግር

ላይ እንዳለን ገልጸናል። በኃላፊነት ወደዚህ ተቋም ከመጣሁ ጀምሮ ተቋሙ በአደረጃጀቱ ምክንያት ከፍተኛ ችግር ውስጥ ነው ያለው። በሚፈለገው ደረጃ የማሰልጠን ከፍተኛ ችግር አለበት።

በታሪክም በረጅም ጊዜ ልምድ ያለው በአደረጃጀትም በሰው ኃይል ብቃትም ይሄንን ተቋም እበልጠዋለሁ የሚል በኢንዱስትሪው ይመጣል የሚል ዕምነት የለኝም።

የተለያዩ የትምህርት ፍላጎቶችን እያየ ማስፋት አልቻለም። ኢንዱስትሪው የሚፈልገውን የሰው ኃይል ማፍራት አልቻለም። ዲግሪ ፕሮግራም የምንሰጠው ከኢትዮ-ቻይና፣ አሁን ከፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ኢንስቲትዩት ጋር ተፈራርመን ነው። ኢንስቲትዩት ቢሆንና ትክክለኛውን አቅም እንድንጠቀም እውቅና ቢሰጠን ግን ገበያው ላይ ምንድነው የሚያስፈልገው በምን ዘርፍ እንስራ የትኛው ዘርፍ በዲግሪ መርሃ ግብር መቀጠል አለበት የሚለውን መለየት ይቻላል።

ሌላ በውስጥ አሠራር ከፍተኛ ችግሮች አሉት። በፋይናንስ አስተዳደር ላይ ከፍተኛ ችግር አለው። ምክንያቱም ዲግሪ ማስተማር የሚችል ማስተርስና ከዚያ በላይ የትምህርት ዝግጅት ያለው ሠራተኛ አለ። ብቃት ያላቸውን ባለሙያዎች በአግባቡ እንዳንጠቀም አድርጎናል። ሚኒስቴር መስሪያቤቱ ቀንም ማታም በሰነዶቻችን የ10 ዓመት ዕቅድ የማሻሻያ ደንቡ ሳይጸድቅ በከፍተኛ ትምህርት ተቋም መተዳደር ወይም መመራት አልቻለም። በዚህ ምክንያት ሀብትም የክህሎትና የዕውቀት ሁኔታን በአግባቡ መጠቀም ያልቻልንበት ሁኔታ ነው ያለው።

ወጥ የሆነ አሠራር እንዳይኖር ሆኗል። መንግሥት ኃላፊነት ሰጥቶን ከሰራን ችግራችን ተፈትቶ ለአገር አስተዋጽዖ ልናበረክት የምንችልበትና የምንፈተንበትም ጭምር ሁኔታ የሚፈጠረው በዚህ ደንብ ምክንያት ነው በሚል በቅርብ ጊዜ መልስ እናገኛለን ብለን ተስፋ እናደርጋለን።

የ10 ዓመት ዕቅዱን ያቀድነው ይሄንን ታሳቢ አድርገን ነው። የለውጥ ኃይሉ ከመጣ በኋላ አንድ ጊዜ የሳይንስና ከፍተኛና ትምህርት ሚኒስቴር አስተያየት እንዲሰጥበት ተጠይቆ አስተያየቱን ሰጥቶ በባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ተጠሪ ሆኖ ቢያገለግል ለኢንዱስትሪው አስፈላጊና ወሳኝ መሆኑ ታምኖበት ለሁሉም ሚኒስትሮች አጀንዳው ይታያል ተብሎ ሰነድ ተባዝቶ ወደ ሚኒስትሮች ምክርቤት ሂዷል። ስለዚህ አጀንዳውን አቅርቦ ማጸደቅ ነው። ይሄ ከሆነ ሴንተር ኦፍ ኤክሰለንስ ሆነን መስራት እንችላለን። ስናቅድም ዕድሜውን ሊመጥን የሚችል የሌሎችን አቅም ሊገነባ የሚችል ሥራ እንሰራለን ብለን ነው የምናስበው።

አዲስ ዘመን፡- ወደ ተቋምነት ቢያድግ ምንድነው የሚያበረክተው?

አቶ ገዛኸኝ፡- ተቋሙ ወደ ኢንስቲትዩትነት ቢያድግ በሆቴልና በቱሪዝም በአጠቃላይ በእንግዳ አቀባበል ኢንዱስትሪው ያለውን ከፍተኛ የሆነ የሰለጠነ የሰው ኃይል ዕጥረት ችግር ይፈታል:: ለምሳሌ ቴክኒክና ሙያዎችን ብንወስድ በሁሉም ክልሎች ከ100 በላይ አሉ። በአዲስ አበባ ብዙ ተቋማት አሉ። እንደ ንፋስ ስልክ እንጦጦ የተመረጡ ቴክኒክና ሙያ ተቋማት በሆቴልና በቱሪዝም ባለሙያዎችን ያሰለጥናሉ። ክልሎችም እንደዚያ። ይሄ ተቋም ያሉትን መምህራን በሆቴልና በቱሪዝም ዘርፍ እያሰለጠን ያለነው ኢንዱስትሪው ከኬንያ ማናጀር፣ ከሌላ አገር ሼፍ የሚሆነው እየመጣ በዶላር የሚከፈለውን የውጭ ምንዛሬ ለማስቀረት የሚያስችል ደረጃውን የጠበቀ ስልጠና እንሰጣለን። ከኢንዱስትሪው ጋር በመተሳሰር የልኅቀት ማዕከል ብንሆን ብለው ቀድሞ የነበሩ አመራሮች ሲያስቡ በእሳቤ አልተሳሳቱም፤ ሰነድ ላይ ነው የተሳሳቱት ምንም ሳያስፈልገው ኢንስቲትዩት ሆኖ የልኅቀት ማዕከል

መሆን ይችላል። ዩኒቨርሲቲ፣ ቴክኒክና ሙያ ተቋም ሆኖ የልኅቀት ማዕከል መሆን ይችላል። የሚሰራው ሥራ ነው የልኅቀት ማዕከልነትን የሚያመጣው። ስለዚህ ተቋሙ የልኅቀት ማዕከል እንዲሆን ነው የምንፈልገው እንጂ የሆነ ቴክኒክና ሙያ ተቋም የሚሰራውን ስልጠና ደረጃ አንድና ሁለት እያለ ከክልል ሰዎችን እያሰባሰበ ዕድሜ ልኩን ያስተምራል ማለት አይደለም። እነዚያን የሚያበቁ ሰዎች ኢንዱስትሪው ላይ በተለያየ ደረጃ የማብቃት ሥራዎች፣ የማማከርና የጥናትና ምርምር ሥራዎችን ከፍ ባለ ደረጃ እንሰራለን፤ ከአገር ውስጥ አልፎ ለውጭ አገር ኤክስፖርት የሚደረጉ ባለሙያዎችን የማፍራት ሥራ እንሰራለን። በግል ፈቃድ ወስደው የሚሰሩ ሰዎችን የማብቃት ሥራዎችን አንሰራለን ሆቴሎችን የማብቃት የመመዘን ሥራዎችን እንሰራለን የመስራት አቅም ያለው ተቋም ነው። ለምሳሌ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ብቃት ማረጋገጥ ዲፓርትመንት አለው ብቃት የሚያረጋግጥበት ዲፓርትመንት ተከፍቷል። ለባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር አንዱ ተጠሪ ተቋም ይሄ ነው ስለዚህ የሬጉላቶሪውን ሥራ አብሮ በቅንጅት ከባህልና ከቱሪዝም ሚኒስቴር ጋር መስራት የሚችል አቅም አለው፣ የማማከርም የማሰልጠንም አቅም አለው፤ ስለዚህ ይሄ ተቋም ወደ ከፍተኛ ተቋም ማደጉ ገበያውን መሰረት ያደረገ ፍላጎትን ያገናዘበ ስልጠና በተለያዩ ደረጃዎች እንሰጣለን።

በዋናነት ባለን አቅም አንዳንጠቀም ከፍተኛ ማነቆ ሆኗል። ችግሩ ከተፈታ ግን በዚህ መሰረት የኢንዱስትሪውን ችግር ለመፍታት ትልቅ አስተዋጽዖ ያበረክታል። ከፍተኛ ሀብት ቢኖረውም መመሪያና ደንብ

አቶ ገዛኸኝ አባተ የሆቴልና ቱሪዝም ሥራ ማሰልጠኛ ማዕከል ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሲሆኑ፤ ማዕከሉ እስካሁን ያከናወናቸውን፣ ያጋጠሙትን ተግዳሮቶችና ስኬቶቹን እንዲሁም የወደፊት ዕቅዱን በተመለከተ ከጋዜጣው ሪፖርተር ጋር ቃለ ምልልስ አድርገዋል እንደሚከተለው አቅርበናል፡-

ፎቶ

: በኢ

ዮብ

ተፈ

Page 9: ከባንክ ውጭ ከ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር በላይ ማስቀመጥ ተከለከለሕግ • ዶ/ር ሳሙኤል ሁርካቶ፤ የሳይንስና ከፍተኛ

ረቡዕ ነሐሴ 13 ቀን 2012 ዓ.ም

ገጽ 9 ተጠየቅካልደገፈው በሚፈለገው ደረጃ አቅሙን ልንጠቀም አንችልም። ከቴክኒክና ሙያ ጋር ትብብር ባንፈራረም ተቋሙ ዲግሪ መስጠት አይችልም ማለት ነው። ስለዚህ ተቋሙን እየተጠቀምንበት አንሄድም፤ እንደ አመራር ተቋሙ ማበርከት ያለበት ይሄነው ወይ ብለህ ስትጠይቅ በቂ አይደለም።

አዲስ ዘመን፡- ቱሪስቱ የሚማረርባቸው ነገሮች ምንድናቸው?

አቶ ገዛኸኝ፡- ቱሪስቱ የሚማረርባቸው ነገሮች ሁለት ናቸው። አንዱ የሚሰጠው አገልግሎት፤ በተለይ ሆቴል ላይ በጣም ደረጃውን የጠበቀ አይደለም። ከባህል አንጻር አስረው የያዙ መስተንግዶ ጋር የተያያዙ ችግሮች አሉ። የዕውነት እንግዳ ተቀባዮች ነን የሚባለው መፈተሽ ያለበት በተቋም ነው፤ ችግሩ መፈታት ያለበት ደግሞ በእንደዚህ ዓይነት ተቋም ነው። ስለዚህ ያንን ጥናት ካጠናህ በኋላ ያንን ችግር ሊፈታ የሚችል ተቋም ከሌለ ይሄን ያህል ዕድሜ ጠገብ ተቋም ይዞ በስም መፎከር አይገባም።

ሌሎች ጎረቤት አገሮች እኛ ዘንድ ለመሰልጠን ይፈልጋሉ። መጥተው ሲያዩ ቤት ተከራይተን ነው፤ ሌላ ቦታ ደግሞ ስልጠናዎች የሚሰጡበት አግባብ የተለየ መንገድ ነው። እንዲሁም የምንሰጠው የምስክር ወረቀት ሲታይ ደግሞ አይመጥነንም በሚል ወደሌሎች አገሮች ይሄዳሉ።

ሌላው ቀርቶ ከአቻ ተቋማት ጋር የልምድ ልውውጥ ለማድረግ ደረጃ ይጠየቃል። ምክንያቱም ትክክለኛው የተቋሙ ስም ማዕከል ነው። ስለዚህ አንድ ማዕከል ከአንድ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ወይም ኢንስቲትዩት ጋር አቻ ስለማይሆን የሚፈለገውን የልምድ ልውውጥ ማድረግ አይቻልም። ስለዚህ እነዚህን ሁሉ ችግሮች ማነቆ ስለሆኑ ችግሩን የሚፈታ ውሳኔ ያስፈልጋል። መንግሥት ውሳኔዎችን እየሰጠ ስለሆነ ሰሚ ካለ ለኢኮኖሚ ዘርፍ አንዱ መሰረት አድርጎ ስለሚታይ የቱሪዝሙን ትንሳኤ የምናይበት ወቅት ነው።

የተቋማት ችግር የሚፈታ ከሆነ በዚህ ተቋም ላይ ትልቅ ኃላፊነት መጣል አለበት። በዚያው ልክ እንዲሰራ መጠየቅ አለበት። ወደ ኢንስቲትዩት ሲያድግ ይፈተንበታል። የዘርፉን ችግር ሊፈታ የሚችል አቅም ፈጥረህለት ከዚያ በኋላ የሚጠበቅበትን ካልተወጣ አስፈላጊውን እርምጃ መውሰድ ይቻላል።

አዲስ ዘመን፡- በሆቴልና ቱሪዝም ዘርፉ የተሰማሩ አካላት ዘርፉ ከሚጠይቀው ተገቢ ሙያዊ ብቃት አንፃር ሲመዘኑ ያሉት ችግሮች እንዴት ይገለፃሉ?

አቶ ገዛኸኝ፡- ያለውን ችግር በተመለከተ ተቋማችን ጥናት አጥንቷል። በኢንዱስትሪው ውስጥ በተለይ ባለኮከብ ሆቴሎች ላይ በተጠና ጥናት ኢንዱስትሪው ውስጥ በሙያው የሰለጠነው 32 በመቶ ነው። ከዚህ ውስጥ 15 በመቶው በዚህ ተቋም የሰለጠኑ ናቸው። በክልልም በከተማም በቴክኒክና ሙያ ተቋማት ደረጃውን የጠበቁ ሰልጣኞችን እንዲያወጡ እነርሱን ሊያወጡ የሚችሉ አሰልጣኞችን የማብቃት፤ ሰልጣኞች የሚጎላቸውን ነገር በመለየት በዘርፉ ያለውን የሙያ መመዘኛ ብቃቱን የሚያዘጋጀው ይሄ ነው።

ቦርዱ ውስጥ የሆቴል ባለቤቶች ማህበር ፕሬዚዳንት፣ የአስጎብኝ ድርጅቶች ማህበር ፕሬዚዳንት እንዲሁም የሆቴልና የልዩ ልዩ አሰሪዎች ፌዴሬሽን የተካተቱበት ቦርድ ነው ያለው። ከነዚህ ጋር መሆናችን ምንድነው የሚጠቅመን በሥራ ላይ ስልጠና እንዲሰለጥኑ፤ የኛ ደግሞ የሚጠበቀው ከነርሱ ልምድ ከኛ ደግሞ አጫጭር ስልጠናዎች በመስጠት ማብቃት ነው አዳዲስ ሰልጣኞች እንዲገቡ ማድረግ፤ የነርሱንም ሰልጣኞች እንዲሰለጥኑ ማድረግ ነው። የነርሱን ባለሙያዎች ጭምር ይጠቅማል የኢንዱስትሪውን ችግር ማጥናት አንዲሁም የተለያዩ መንገዶችን በመጠቀም የሰው ኃይሉን የማብቃት ሥራ በመስራት ኃላፊነቱን ይወጣል።

ባለፈው ዓመት ከ10 በላይ ከተሞች የኛ ተቋም ባለሙያዎች የማማከር ሥራዎች ሰርተዋል፤ ከሆቴል ባለቤቶች ማኔጀሮች ጋር ቁጭ ብለው ተነጋግረው የማማከር ሥራ ሰርተው ምንድነው የሚጎድላቸው የሚለውን ፍላጎት ለይተው ከ6 ወር ግምገማችን በኋላ ወደ ስልጠና ልንገባ በዝግጅት ላይ እያለን ኮቪድ መጣ። በማማከር ወቅት ያገኘነውን ክፍተት መሰረት አድርገን ክልሎችና አዲስ አበባ ላይ ያሉትን የሆቴል ሠራተኞችና ባለቤቶች ለማብቃት ተሰርቷል።

የደረጃ ምደባ ከመጣ በኋላ በዘመድ በምናምን የሚባለው እየቀነሰ የሚሄድበት ሁኔታ አለ አንዳንዱ ለመምራትም ሲል ሙያውን እየተማረ ነው። ስለኢንዱስትሪው ግንዛቤ ያለበት ቦታ ሠራተኞቹን በማሰልጠን ቢያንስ በሙያው መሰረታዊ ነገር

እንዲኖራቸው ይፈልጋሉ። ይሄንን የሚፈታ የሰው ኃይል ማፍራት የኛ ኃላፊነት

ነው። ያሉትን የማብቃት፤ ችግሩን የመለየት፤ በስልጠና የመደገፍ፤ አዳዲስ ኃይሎችን የማፍራት የኛ ኃላፊነት ነው። በዚህ መልክ ችግሮቹ ይፈታሉ። ባህልና ቱሪዝም የያዘውን አቋም ማጠንከር አለበት። ባለሀብቶችም ይህንን እንዲያውቁ ማድረግ ያስፈልጋል።

የኮቪድ 19 አገራዊ ጥናት አጥንተናል። በሚቀጥሉት ቀናት የምናሳውቀው ይሆናል። አስተያየት ተሰጥቶ የመጨረሻ ሥራው ላይ ነው ያለው። እኛ እንደተቋም ኮቪድ 19ን መሠረት አድርገን ሆቴሎች እንዴት ነው አገልግሎት የሚሰጡት፤ ነገን እንዴት ይጠብቁት፤ ዛሬን እንዴት ይለፉት የሚል እስትራቴጂ መንደፍ፤ የስልጠና ይዘቶችን ማዘጋጀት ሆቴሎችንና አስጎብኝ ተቋማትን የማብቃትና ነገ ከሚመጣው ሁኔታ ጋር እራሳቸውን አዋህደው እንዲሄዱ ሥራዎችን እየሰራን ነው ያለው። ስለዚህ ከተቋሙ የሚጠበቁት እንደዚህ ዓይነት ሥራዎች ናቸው።

አዲስ ዘመን፡- ባሕልና ቱሪዝም ሚኒስቴር እየሰጠው ያለው ትኩረት ምንድን ነው?

አቶ ገዛኸኝ፡- ደንቡን ያፀደቀውና አጠቃላይ አገሪቱን የሚመራው የሚኒስትሮች ምክርቤት ነው። በእርግጥ እዚህ የነበረው የተቋሙ ኃላፊ አንዱን ድርሻ ይይዛል። ከታች እስከ ላይ የነበረው አመራር የፈጠረው ክፍተት ነው።

አሁን ያለው አመራር ያለው አመለካከት ጥሩ ቢሆንም ድጋፉ ወጥ አይደለም። ያለውን የደንብ ችግር ለመቅረፍ ሚኒስትሯ እራሳቸው ናቸው እያዩት ያሉት። በካቢኔ ሪፖርት ቀርቧል፤ እንደችግር ተብሎ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት የቀረበው የዚህ ተቋም ችግር ነው። የሞዴል ግንባታ ሥራው በመንግሥት በጀት እንዲፈቀድ ካልሆነ ደግሞ በግል በመንግሥትና በኅብረተሰብ ተሳትፎ ሊሰሩ የሚችሉ ፕሮጀክቶችን በማፈላለግ የተቋሙን ችግር ለመፍታት ድጋፍ አለ። ከመንግሥታቱ ድርጅት የልማት መርሃ ግብር የኪችን ዕቃዎችን በስፋት አግኝተናል፤ ለስልጠናና ልምድ ልውውጥ እየተንቀሳቀስን ነው። ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ፕሮጀክት ያገኘው አሁን ነው። ስለዚህ አሁን ያለው የለውጡ አመራር ደንቡን እንዲያጸድቅልን ድጋፉ ወጥ ከመሆን አንጻር ክፍተት አለበት። ከዚያ ውጪ ግን ከአደረጃጀት ጋር ከመመሪያና ደንቡ መሻሻል ጋር በተያያዘ

ክብርት ሚኒስትሯ ጉዳዩን በኃላፊነት ይዘው እየሰሩ እንደሆነ አውቃለሁ።

በበጀት ደረጃ በዚህ ዓመት መንግሥትን የጠየቅነውን ነው ያጸደቀልን። በጥሩ ሁኔታ ሊያሰራ የሚችልና ስልጠናዎችን በተሳካ ሁኔታ ለመስጠት የሚያስችል በጀት አለን፤ አመራሩ ድጋፉ ጥሩ ነው።

አዲስ ዘመን፡- የሥራ ዕድል ከመፍጠር አንፃር ተቋሙ ምን እየሰራ ነውአቶ ገዛኸኝ?

አቶ ገዛኸኝ፡- የስራ ዕድል ከመፍጠር አንጻር የኛ ያሰለጠንናቸው ሰልጣኞች ከኢንዱስትሪው ጋር በሚደረግ ትስስር ከሆቴል አሶሴሽን ጋር በሚፈጠር የሥራ ዕድል ፈጠራ ትስስር በየዓመቱ በተቋማችን የሚከበር የሆስፒታሊቲ ሳምንት አሰሪና ሠራተኛ የሚገናኝበት የአዲስ አበባ ሆቴሎች ማህበር ባህልና ቱሪዝም እንዲሁም ከእኛ ጋር በጋራ ያዘጋጀነው የሥራ አውደርዕይ አለ፤ የሆቴልና የአስጎብኝ ተቋማት ባለቤቶች ቁጭ ብለው ሲቪ እያዩ ኢንተርቪው እያደረጉ ስልጠና ጭምር አየተሰጠ ሰዎች እንዲገቡ ይደረጋል። የዚህ ዓይነት ሚና በመጫወት ተመራቂ ተማሪዎች የሥራ ዕድል እንዲያገኙ የምንሰራው ሥራ አለ፤ ሌላው ደግሞ በቅርብ አሁንም እንደፕሮጀክት ይዘነው እየተንቀሳቀስን ያለነው ሚኒስቴር መስሪያቤቱ ያስገባነው ኢኮ ቱሪዝም ብዙ አልተሰራበትም ተራራዎች ጥብቅ ደኖች ወዘተ… የመሳሰሉ ማህበረሰብ አቀፍ ልማት ያሉበት አለ እዚያ አካባቢ ላይ በዘርፉ የሰለጠኑትን ሰዎች በሆቴል በቱሪዝሙ በተለያዩ ዘርፎች የምናሰለጥናቸው ተማሪዎች ተደራጅተው ቦታ ወስደው እያለሙ እየሰሩ የሚጠቀሙበት ለአካባቢው ነዋሪም ለአገር ውስጥና ለውጪም ቱሪዝም ሙሉ ሎጅ (ጮቄ ተራራ ያለውን ተሞክሮ በመቀመር ወደሌሎች አካባቢዎች እንዲሰፋ) ፕሮጀክት ቀርጸን እየሰራን ነው ያለነው። እዚህም ያሉትን ተቋማት የማማከር ሥራ አለ። የማታና የአጫጭር ስልጠና ቡድን አለን ይሄ ቡድን መንግሥታዊ ካልሆኑ ተቋማት ጋር አጫጭር ስልጠናዎችን ይፈራረማል። እነዚህን ሰልጣኞች ካሰለጠነ በኋላ ከድርጅቶች ጋር በመሆን የሥራ ዕድል የሚያገኙበትን መንገድ ይፈጥራል። የማደራጀት፣ የማማከር፣ በስምሪታቸው ደግሞ ውጤታማ የማድረግ ሥራ ይሰራል፤ ስለዚህ ከሚሰለጥኑት ሰልጣኞች ባሻገር ሴቶችን በመስተንግዶ፣ በቤት አያያዝ፣ በምግብ ዝግጅት የሰለጠኑ በተለያዩ ሆቴሎችና ሆስፒታሎች ጭምር እንዲቀጠሩ የማደረግ ሥራ ተሰርቷል።

አዲስ ዘመን፡- በአገሪቱ የቱሪስት ፍሰት እንዲጨምር ተቋሙ ምን ምን ሥራዎችን አቅዶ እየሰራ ነው?

አቶ ገዛኸኝ፡- የማሰልጠን፣ የማማከርና የጥናትና ምርምር ሥራዎች ተልኮ ያሉት ሲሆን ከዚህ በፊትም የተቋሙ ባለሙያዎች ቦታውን አይተው መጥተዋል። በቀጣይ 10 ዓመታት እንደ ትልቅ ዕድል የሚታይ ቦታ ነው። መንግሥት የሰጠው ትኩረት ይሄንን ተቋም ካንቀላፋበት እንዲነቃ የሚያደርግ ደወል ነው። ይሄ ማለት የሰው ኃይል ለማፍራት በመንግሥትም በባለሀብትም የሚሰሩ ተቋማት ምን መሆን አለባቸው የሚል ጥናት ያስፈልጋል፤ የሌላ አገሮችንም ተሞክሮ ማምጣት ያስፈልጋል ከእኛ አገር ተጨባጭ ሁኔታ አንጻር በማማከር የማብቃት ሥራ እንሰራለን፤ ስለዚህ ወደፊት አገራችን የምትደርስበት ደረጃ ምንድነው? ሚኒስቴር መስሪያቤቱ ይሄንን ያህል ሚሊዮን ቱሪስት አስባለሁ ብሎ ሲያቅድ የሰለጠነውን የሰው ኃይል 59 በመቶ ለማድረስ ባህልና ቱሪዝም ሲያቅድ ይሄንን 59 በመቶ የሰለጠነ የሰው ኃይል ተቋሙ ብቻውን አይደለም የሚያበቃው። ስለዚህ ይሄ ተቋም የልህቀት ማዕከል ከሆነ ዩኒቨርሲቲዎችን ቴክኒክና ሙያ ተቋማትን እንዲሁም የተለያዩ ረጃጅምና አጫጭር ስልጠና የሚሰጡ ተቋማትን መንግሥታዊና መንግሥታዊ ካልሆኑ ተቋማት ጋር በቅንጅት መስራት አለበት። ስለዚህ የነገውን የቱሪስት ፍሰት ሊያስተናግድ የሚችል በብዛትም በጥራትም የሰው ኃይል እንዲያፈራ የማድረግ ኃላፊነት ያለበት ይሄ ተቋም ነው።

በአጭር ጊዜ ውስጥ ከክልሎች ጋር ትስስር እንፈጥራለን፤ ለምሳሌ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ላይ እስከዛሬ ድረስ ያለው የቱሪስት እንቅስቃሴና ኢንቨስትመንቱ ውስን ስለሆነ ሄዶ መልምሎ በማምጣት የተወሰኑ አጫጭር ስልጠናና ማማከር ካልሰራን በስተቀር በልዩ ትኩረት አቅደን የምንሰራበት አካባቢ አልነበረም። መጪው ጊዜ ግን እዚያ ቦታ አቅደን የምንሰራበት ነው የሚሆነው። በአካባቢው ካለ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ፣ ዩኒቨርሲቲ ከመሳሰሉ ተቋማት ጋር ትስስር እንፈጥራለን። ይሄንን ሊያደርግ የሚችል የቅድመ ዝግጅት ሥራ እንሰራለን። በቀጣይ ባለሙያዎቻችን ይሄን ዓይነት ስልጠና ያፈልጋቸዋል እያልን ግብዓት እየሰጠን የምንሰራበትን ሁኔታ እንፈጥራለን፤ በዕቅድ ደረጃ ያለንን አቅም የማደራጀት ሁኔታዎች እየሰራን ነው።

አዲስ ዘመን፡- የስልጠና አቅምን ከማሳደግ አንፃርስ?

አቶ ገዛኸኝ፡- አሁን እየሰጠን ያለነው በሆቴል በቱሪዝም፣ በቤት አያያዝ በተለያዩ ደረጃዎች የቴክኒክና ሙያ ኤጀንሲ ባስቀመጠው የስልጠና አግባብ በማሰልጠን እናስመርቃለን። በትብብሩ ደግሞ በዲግሪ መርሃ ግብር በሆቴልና በቱሪዝም ማኔጅመንት አስመርቀናል። 17 ዓይነት ስልጠናዎችን የምንሰጥ ይሆናል።

ከነዚህ በተጨማሪ አዳዲስ ስልጠናዎችን የምናመጣበት ሁኔታ ይፈጠራል። በቱሪዝሙና በሆቴል ዘርፍ እንዲሁም አዳዲስ አዋጭ የሆኑ ከማስጎብኘትና ፓርኮች አካባቢ የሚያስፈልገውን የሰው ኃይል በማጥናት አዳዲስ የስልጠና ዘርፎችን የምንከፍት ይሆናል።

አሁን ካለው የዲግሪ መርሃ ግብር ባሻገር በርካታ ዘርፎችን በዲግሪ መርሃ ግብር የምንሰጥ ይሆናል። ስለዚህ የካሪኩለም ክለሳ እናደርጋለን። ደንቡ እንደጸደቀ አዳዲስ ካሪኩለሞችን መቅረጽና ያሉትን ማሻሻል አለብን ብለን ነው ያቀድነው።

ቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን ቅርሶችን የሚጠግኑ ሰዎች እንድናፈራላቸው ይፈልጋሉ። ሙያው እንዲከፈትና ደረጃው ከወጣ በተመረጡ ሙያዎች የመተካካት ሥራዎች ይሰራል። ያሉትን ፍላጎቶች ይዘን የምናሰፋቸው በርካታ ዘርፎች ይኖሩናል ማለት ነው። አሰልጥነን ሥራ አጥ ሆነው ቁጭ እንዳይሉም እንሰራለን።

በከፍተኛ ደረጃ ስልጠናዎችን መስጠት የሚችል ተቋም መገንባት ነው። ደንቡ ጸድቆ ሲመጣ በተፈቀደው ልክ ገበያው የሚፈልገውን ባለሙያ የማፍራት ሥራ ይሰራል።

አዲስ ዘመን፡- በ2012 ዓ.ም የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት ምን ምን ናቸው ?

አቶ ገዛኸኝ፡- በስልጠናው ረገድ በእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅዱ ያልተሳኩ እቅዶችን ለማሳካት ነበር ያቀድነው። ጥናትና ምርምርን በተመለከተ ባለፉት አምስት ዓመታት ሳይገመገም 40 ጥናት እንዲያጠና ይጠበቅ ነበር። አፈፃፀሙ ግን የሚጠበቀውን ያህል አልነበረም። ከስልጠናና ማማከር አንፃርም በኮቪድ ምክንያት እንደታሰበው መሆን አልቻለም። 40 የስልጠና ጣቢያዎች አቅደን 39ኙ ላይ ስልጠና ለመስጠት ችለናል። ወደ 5 ሚሊዮን ብር ገቢ ለማሰባሰብ ታቅዶ ሰብስበናል።

ወደ 4ኛው ገጽ ዞሯል...

ፎቶ

: በኢ

ዮብ

ተፈ

Page 10: ከባንክ ውጭ ከ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር በላይ ማስቀመጥ ተከለከለሕግ • ዶ/ር ሳሙኤል ሁርካቶ፤ የሳይንስና ከፍተኛ

ረቡዕ ነሐሴ 13 ቀን 2012 ዓ.ም

ገጽ 10ፍረዱኝ

በጄኢጂ (የስራ ምዘና እና ደረጃ አወሳሰን) የተሰራው ጥናት ከመጀመሪያውም ክፍተት አለበት።ሲጀመርም በክፍለ ከተሞች እና ወረዳዎች ላይ ብቻ ነው።ማእከል ላይ ስለምደባ የሚታወቅ ነገር አልነበረም።ይህ እንዳለም በጄኢጂ ሌሎች ዘርፎች ደመወዝ መክፈል ወይም ተግባራዊ ማድረግ ሲጀምሩ የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ ውድቅ መሆኑ ተነገረን።

ጊዜ ፈጅቶ ሌላ ጥናት እንዲሰራ ተደረገ እና በኮርፖሬሽን ደረጃ ጥናት ተሰርቶ መጣ።በኋላም አሰራሩ ትክክል አይደለም የሚል እና ተመሳሳይ አስተያየቶች መቅረብ ጀመሩ።ከዛሬ ነገ ምደባ ተሰጥቶን ጥቅም እናገኛለን፣ ኑሯችን ይሻሻላል የሚለው የኤጀንሲው ሰራተኞችም ጭላንጭል ተስፋ ጨልሞ፣ ጊዜ መቁጠሩን ቀጥሏል ይላሉ የዛሬ የፍረዱኝ አምድ ቅሬታ አቅራቢዎች።

ዝርዝር ጉዳዩ ለደህንነታቸው በመስጋት ማንነታቸውን እንዳንገልጽ

የጠየቁን በአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ ሰራተኞች ቅሬታ ፈጥሮብናል ያሉትን ጉዳይ ይዘው ወደ ዝግጅት ክፍላችን ቀርበው አቤት ብለዋል።ቅሬታቸውም በአዲስ አበባ ከተማ ደረጃ ሰራተኞችን ለመመደብ በጄኢጂ (የስራ ምዘና እና ደረጃ አወሳሰን) ከሐምሌ ወር 2011 ዓ.ም ጀምሮ ለሁሉም ዘርፎች አዲስ መዋቅር መሰራቱን ያስታውሳሉ።በመዋቅሩም የቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ በጄኢጂ እንደ ሌሎቹ ዘርፎች በመዋቅር ተመድበው መቆየታቸውንም ነው የሚጠቁሙት።በሌሎቹ ዘርፎች የሚሰሩ ሰራተኞች ከተመደቡበት ጊዜ አንስቶ የተጠራቀመው የወራት ክፍያ ተከፍሏቸዋል።ሆኖም የዛሬዎቹ ቅሬታ አቅራቢዎች የቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ ሰራተኞች ግን እስካሁን እንዳልተከፈላቸው በመጥቀስ አቤት ይላሉ።

እንዲከፈላቸው በተደጋጋሚና በየደረጃው

በስራ ላይ ከፍተኛ ተጽእኖ ያሳድራል ሲሉ የሚያብራሩት ቅሬታ አቅራቢዎቹ፤ ‹‹በፊት ከነበረን የሥራ ሞራል አንጻር አሁን ሲታይ ስራ ባንገባ ሁሉ ደስ ይለናል፤ የስራ ሞራላችንን ገድሎታል፤ሌሎች ጽህፈት ቤቶች የሚሰሩ ጓደኞቻችን ተመድበው አነሰም በዛ የተሻለ ገንዘብ እያገኙ ስናይ የሞራል ውድቀት ደርሶብናል፤ መጠቋቆሚያም ሆነናል›› ይላሉ።የኑሮ ሁኔታው ከእለት እለት እየጨመረ ባለበት ሁኔታና የኮሮና ወረርሽኝ ተከስቶ የትራንስፖርት ክፍያ ሳይቀር እጥፍ ክፍያ እየተጠየቀ ባለበት ወቅትም ቢሆን ችግራችን ግንዛቤ ውስጥ አልገባልንም ነው የሚሉት።

የአከፋፈል ስርዓቱም ቢሆን በየክፍለ ከተሞችም የሰው ሃይል መልካም ፍቃደኝነት የሚለያይ ነው።ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ አራት ላይ ምደባ ከተሰራ በኋላ ባለሙያዎች እንዳይጎዱና ሞራላቸው እንዲጠበቅ በማሰብ መጀመሪያ በጄኢጂ በተጠናው መሰረት ደመወዛቸው እንዲከፈላቸው መደረጉን ይጠቁማሉ።የስራ ሂደት ላይ አንዳንድ ቦታዎች በአምስት ዓመት ልምድ አትመድቡ ተብሎ ሲታገድ በዚህ ወረዳ ግን በአምስት ዓመት ልምድ የስራ ሂደት ኃላፊ ተደርጎ የተሰጣቸው መኖራቸውንም ይናገራሉ።የሰው ሃይል አመዳደቡ ተናብቦ የተፈጸመ አይደለም ሲሉም ቅሬታቸውን ያሰማሉ፡፡

ፐብሊክ ሰርቪስ ቢሮ እኛ ደንበኞቹን ባግባቡ አያስተናግድም።ለምነን ገብተን እንኳን ይገፉናል።ይህ ሁኔታ ሊቀየር ይገባዋል።‹‹ቅሬታችንንም የሚሰማን እንፈልጋለን፣ ታፍነናል፣ የት ሄደን እንጩህ ? የሚመለከታቸው አካላት ተናብበው መብታችንን ሊያስከብሩልን እና ምላሽ ሊሰጡን ይገባል›› ካሉ በኋላ በአጠቃላይ ችግራቸው ታይቶ ፈጣን ምላሽ እንዲሰጣቸው ይጠይቃሉ፡፡

እንደቅሬታ አቅራቢዎቹ ማብራሪያ፤ መመሪያ እና ደንብን የጣሰ አካሄድ ተፈጻሚ አይሆንም።በምደባ በመመሪያው የተቀመጠው የስራ ልምድ እና የትምህርት ዝግጅትን መሰረት በማድረግ የሚፈጸም እንጂ ወጥ የሆነ

ለሚገኙ አካላት ጥያቄ ማቅረባቸውን የሚጠቅሱት ቅሬታ አቅራቢዎቹ ‹‹የእናንተ ገና ነው።ጥናት አልተጠናም።ቤቶች ልማት ኤጀንሲ ኮርፖሬሽን ስለሆነ አዲስ ጥናት ያስፈልገዋል፤ ስለዚህ ጠብቁ›› ተብለናል ይላሉ።ይህንንም ተቀብለው በመጠባበቅ ሰባት ወራት ማስቆጠራቸውን ያክላሉ።

ይህንን ያህል ጊዜ በትዕግስት ሲጠብቁ ቢቆዩም እንደገና አዲስ ነገር መምጣቱን ነው የሚያነሱት።ቤቶች ኮርፖሬሽን ሆኖ ጥናት ማስጠናቱን ይጠቅሱና፤ 20/80 ፣ 40/60 እና ቤቶች ኤጀንሲ የሚባሉት በአንድ ላይ ተዋህደው የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ የሚል ስያሜ መያዙን ይናገራሉ።ከዚሁ ጋር ተያይዞም ግንቦት 2012 ዓ.ም እንደ አዲስ ምደባ መሰራቱንም ቅሬታ አቅራቢዎቹ ይናገራሉ።ምደባው ከተካሄደ በኋላ ግን የተጠራቀመ ክፍያ አልተከፈለንም ጥቅሙን አላገኘንም ባይ ናቸው።

አሁንም አጥጋቢ ባልሆነ እና የማይረባ ምክንያት በመደርደር ሊከፈለን የሚገባው እንዲሁም ማግኘት ያለብን ጥቅም እና መብት አልተሰጠንም ሲሉ ነው አቤት የሚሉት።‹‹በእዚህም ችግራችን አልፈታ ሲለን የድጋፍ ፊርማ በማሰባሰብ ለአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ አቤቱታ አቅርበናል›› በምደባ ከአንድ ሺ በላይ ሰራተኞች ተንሳፍፈዋል (አልተመደቡም)።የተንሳፈፉት ሰራተኞች አሁንም ምላሽ አላገኙም።ምላሽ እስኪሰጥ ታገሱን የሚል ምላሽ ነው አሁንም ያለው ነው የሚሉት።

የሚመለከታቸውን አካላት ማለትም፤ ለአዲስ አበባ ቤቶች ልማት አስተዳደር ኤጀንሲ፣ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ኃይል ልማት ቢሮ ቢጠይቁም ተመሳሳይ ምላሽ ከመስጠት ባሻገር ጠብ የሚል ነገር እንዳላገኙም ነው የሚናገሩት።ሁለቱ ተቋማት እንዳልተግባቡ ነው የሚገልጹልን የሚሉት ሰራተኞቹ እነሱ ባለመግባባታቸው ምክንያት ደግሞ እኛ እየተጎዳን እንገኛለን ይላሉ።

የፍትህ ያለህ ባዮቹ ያለመግባባቱን የሚያስረዱት ቅሬታ አቅራቢዎች

ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ በአከፋፈሉ ዙሪያ እንደ 40/60 ስኬል ደመወዝ ለመክፈል ጥናት ሰርቶ ማቅረቡን፤ በአንጻሩ ፐብሊክ ሰርቪስ ሁሉም ተመሳሳይ ክፍያ እንዲከፈለው በጄኢጂ ያስጠናውን ጥናት በመጥቀስ በ40/60 እንጂ በጄኢጂ አልከፍላችሁም መባሉን ነው የሚጠቁሙት።ይህንን እንደ ምክንያት በማቅረብ አንዱ ሌላው ላይ ጣት ከመቀሰር ውጪ መፍትሄ ማግኘት እንዳልተቻለም አክለው ይገልጻሉ፡፡

ቅሬታቸውን ይዘው ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ ሲሄዱም ኤጀንሲው ያጠናሁትን ጥናት ፐብሊክ ሰርቪስ አልቀበለኝ አለ በሚል ወደ ፐብሊክ ሰርቪስ ሂዱ እንደሚባሉ፤ ፐብሊክ ሰርቪስ ሲሄዱ ደግሞ ‹‹መስሪያ ቤታችሁ ያስጨርስላችሁ እንጂ የምናውቀው ታሪክ የለም፣ እኛ ጥናት ተጠንቶ ሲቀርብልን መክፈል ነው እንጂ አጥና አታጥና፣ ክፈል አትክፈል ብለን አንጨቃጨቅም›› በማለት እንደሚገፋፉም ነው የሚናገሩት።ተቋማቱ ባለመግባባታቸው ምክንያት ደግሞ ጥቅም እና መብታቸው ሊከበርላቸው አለመቻሉንም ይጠቁማሉ፡፡

የአመራሮቹ ደመወዝ የሚጸድቀው በካቢኔ በመሆኑ ጉዳያችንን እንደ ጉዳያቸው ይዘው ሊያስፈጽሙልን አልቻሉም፤ የስራ ሸክሙ ባለሙያው ላይ ተጭኖ የሚረዳን እና የሚያግዘን አመራር ባለመኖሩ አዝነናል ሲሉም ያክላሉ ቅሬታ አቅራቢዎች።አሁን በወቅታዊ ሁኔታ የሥራ ዕድል በመጥበቡ እና በቅጥር የሚዘዋወሩበት ተቋም በማጣታቸው እንጂ ለቅቀው ቢወጡ ደስ እንደሚላቸውም ይናገራሉ።

ከመጀመሪያው ምደባ አንስቶ እስካሁን ድረስ አንድ ሰራተኛ ከአንድ ደረጃ ወደ ሌላ ደረጃ (በአንድ ደረጃ ብቻ) ቢያድግ እንኳን ቢያንስ በወር አንድ ሺ 500 ብር ያገኝ ነበር።ይህ ማለት 14 ወራት ያህል አንድ ሰራተኛ በትንሹ ማግኘት የሚገባውን 21 ሺ ብር (ሃያ አንድ ሺ ብር) አሳጥቶቷል ሲሉም ቅሬታ አቅራቢዎቹ ያማርራሉ።

እንዲህ አይነት አሰራር በማህበራዊ ህይወት እና

ዘላለም ግዛው

ፎቶ

፡ በፀ

ሐይ

ንጉ

የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች

Page 11: ከባንክ ውጭ ከ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር በላይ ማስቀመጥ ተከለከለሕግ • ዶ/ር ሳሙኤል ሁርካቶ፤ የሳይንስና ከፍተኛ

ረቡዕ ነሐሴ 13 ቀን 2012 ዓ.ም

ገጽ 11 ፍረዱኝ አሰራር ተግባራዊ አይደረግም።

የእኛን መብት እና ጥቅም ያላስከበረው አካል አረፈዳችሁ የሚል ስሞታ ያቀርብብናል።በእርግጥ የስራ ሰዓት መከበር፣ ስራ ባግባቡ መሰራቱም ቢሆን መረጋገጥ ይኖርበታል።ነገር ግን ፐብሊክ ሰርቪስ መብታችንን ማስከበር ቀዳሚ ተግባሩ መሆን ነበረበት።አሁን ግን መብታችንን እያስከበረ አይደለም፣ የስራ ሞራላችንንም እየነካ ይገኛል ይላሉ፡፡

ቅሬታ አቅራቢዎቹ የሚጠይቁት ፍትህእንደቅሬታ አቅራቢዎቹ ገለጻ፤ በ20/80፣ 40/

60 እና በቤቶች ኤጀንሲ አከፋፈል መሰረት የቀረበው ተመዝኖ በ40/ 60 እንዲከፈል የሚል ውሳኔ ተላልፏል።ነገር ግን ፐብሊክ ሰርቪስ ከሌሎች ዘርፎች መብለጥ የለበትም በሚል ይህንን ውሳኔ ሊቀበለው አልቻለም።ይህ አለመግባባት ግን ሰራተኛውን ለእንግልት ዳርጎታል።ሁለቱ ተቋማት ተናብበው አንድ ውሳኔ ላይ መደረስ ይኖርበታል።የ40/60 ሰራተኞች ከፍተኛ ክፍያ የሚያገኙ ሲሆን፤ ለምሳሌ ደረጃ 11 የሆነ ሰው 11 ሺ ብር ሲከፈለው 20/80 በተመሳሳይ ደረጃ ላይ የሚገኝ ስምንት ሺህ ያገኛል፤ መሬት ኤጀንሲ ደግሞ በተመሳሳይ ደረጃ ሶስት ሺህ ብር ነበር የሚከፈለው።

አሁን ሶስቱ ተቋማት ተጨፍልቀው አንድ ላይ ኮርፖሬሽን ሆነዋል።ተመሳሳይ ስራ የምንሰራ እና በአንድ ተቋም ስር የምንተዳደር ከሆነ በጥናቱ መሰረት ተመሳሳይ ክፍያ ሊከፈለን ይገባል።ለዚህም ተግባራዊነት በ40/60 እንዲሰራ የጸደቀ በመሆኑ ፐብሊክ ሰርቪስ የተደረገውን ጥናት ሊቀበለው ይገባል የሚል ሃሳብ ያቀርባሉ።

ከሐምሌ አንድ 2011 ዓ.ም ጀምሮ በተጠናው የ40/60 መሰረት ሊከፈለን ይገባል።አሁን ባለው ወቅታዊ ሁኔታ ይህ አይሆንም ቢባል እንኳን የአንድ ዓመቱ የኋላ ክፍያ ተጠንቶ በነበረው በጄኢጂ መሰረት እንዲከፈል ሊደረግ ይገባል ነው የሚሉት፡፡

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ ምላሽ

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ኃላፊ አቶ ሰለሞን ዲባባ፤ በሁለቱ ተቋማት መካከል ምንም አይነት ክፍተት አለመኖሩን ይናገራሉ።ተቋማቱን የሚያገናኘው የስራ ግንኙነት በመሆኑ በአሰራር እና ደንብ መሰረት እኛ ፍላጎታችንን እናቀርባለን፤ እነርሱ ደግሞ ህግና ደንብን ተከትለው ያጸድቃሉ፤ በተግባቦት ስራው ይተገበራል ይላሉ።

የተንሳፈፉ ሰራተኞችን አስመልክቶ ምን ያህል እንደሆኑ በቁጥር ለይቶ ለመናገር አስቸጋሪ መሆኑንም አቶ ሰለሞን ይናገራሉ።ምክንያቱ ደግሞ ሙሉ ለሙሉ ስራው ስላልተጠናቀቀ እና ጉዳያቸው በቅሬታ ሰሚ እየታየ የሚገኝ በመሆኑ ጭምር ነው።የአዲስ አበባ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስ ቢሮ በመመሪያ እና በአዋጅ መብት የተሰጠው በመሆኑ የመጨረሻ ውሳኔ የሚያገኘው በቢሮው በኩል መሆኑንም ነው የተናገሩት።ከደመወዝ ስኬል እና ከስራው አጠቃላይ ሁኔታ ጋር በተያያዘ ከቢሮው ጋር በቅንጅት የሚሰራ መሆኑንም ነው የሚያክሉት።

በአዲሱ ምደባ ተመድበው ‹‹ልትነሱ ትችላላችሁ›› በሚል በሰራተኞች እየተነሳ ያለውን ስጋት አስመልክተው ምላሽ የሰጡን ኃላፊው፤ በአሰራሩ መሰረት በመመሪያ፣ በደንብ እና አሰራሩን ጠብቆ ሰራተኞች ከተመደቡ በኋላ የሚነሱበት ምክንያት የሌለ መሆኑን ነው የሚናገሩት።ሁሉም ተግባር መመሪያና ደንብን ተከትሎ የሚሰራ በመሆኑም የሚወራው ምናልባት ተራ አሉባልታ ሊሆን ይችላል ባይ ናቸው።

ምደባው ከመመሪያ ውጪ የሚተገበርበት መንገድ እንደሌለ በመጥቀስም፤ ለአሰራር በሚመች መልኩ መዳቢ ኮሚቴ ተቋቁሞ ከሰራተኞች ተወክለው በኮሚቴው ተሳትፎ የሚደረግበት ነው ሲሉም ነው አቶ ሰለሞን የሚናገሩት።ትግበራው የሰው ልጅ የሚሰራው በመሆኑ ሙሉ በሙሉ ትክክል ነው ባይባልም አጠቃላይ አሰራሩ ህግን፣ ደንብን እና መመሪያን የተከተለ መሆኑን ነው የተናገሩት።

በ40/60 የደመወዝ ስኬል መሰረት ሊከፈለን ሲገባ አድሏዊ በሆነ መልኩ እስካሁን መብትና ጥቅማችን አልተከበረም የሚለውን ቅሬታ አስመልክተው የሚናገሩት አቶ ሰሎሞን፤ በ20/80 ፣ በ10/90 ፣ 40/60 እና በሌሎቹም ዘንድ የደመወዝ ልዩነት እንደነበር ነው የሚያስታውሱት።የ40/ 60 ቤቶች በልማት ድርጅት ይተዳደር ስለነበር በከተማው አስተዳደር ስር ካሉ ዘርፎች ሁሉ የተለየ አከፋፈል ይተገበር እንደነበር ይናገራሉ።አሁን ግን አደረጃጀቱ እንደአዲስ ተዋቅሮ በአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ ስር እንዲካተት መደረጉን ያነሳሉ።ከዚህም ጋር ተያይዞ አሁንም በአከፋፈል ሁኔታ ልዩነት መኖሩንም ያክላሉ።

ልዩነቱን ለማጥበብ በአዲሱ መዋቅር የደመወዝ ስኬል ሲሰራ በመጀመሪያ የተሰራው በ40/60 የደመወዝ እስኬልም መሰረት በማድረግ ነበር ይላሉ።ይህ ደግሞ የመጨረሻ ውሳኔ የሚያገኘው በአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ አማካኝነት አይደለም።እንዲህ አይነት ሁኔታዎች ውሳኔ የሚያገኙት በፐብሊክ ሰርቪስ ቢሮ እና በከተማው ምክር ቤት አማካኝነት ነው።

በመሆኑም በ40/ 60 ቤቶች መሰረት የተሰራው የደመወዝ ስኬል ውድቅ ሆኗል።አሁን አማካኝ፣ ሁሉንም የሚያግባባ እና ሚዛናዊ ይሆናል በሚል እሳቤ በ20/80 ቤቶች ሰራተኞች የደመወዝ ስኬል መሰረት ለመክፈል እና በሰራተኞቹ መካከል ያለውን ልዩነት ለማጥበብ እየተሞከረ ነው።ይህ የ20/80 ቤቶች ሰራተኞች የደመወዝ እስኬል ሚዛናዊ፣ ፍትሃዊ እና ተቀባይነት የሚያገኝ ይሆናል ብለንም እንጠብቃለን።

ቀደም ሲል ለደመወዝ ክፍያ በዓመት ይወጣ የነበረው ወደ 35 ሚሊዮን ብር ነበር።አሁን ስኬሉን ለማሻሻል ስናስብ በእጥፍ አድጎ ወደ 90 ሚሊዮን ብር ጠይቆናል።ይህንን አንችልም በሚል ነው ያልተቀበለው። ቀደም ሲል የልማት ድርጅት የነበረ ስለሆነ የክፍያው ወጪ አስቸጋሪ አልነበረም።አሁን ህግና መመሪያ በሚፈቅደው በመንግስት ሰራተኞች የደመወዝ እስኬል መሰረት ነው የምንችለው ተብለናል።

ተጠቃልለው በአንድ አስተዳደር ስር በሚተዳደሩ ሰራተኞች መካከል ምናልባትም ተመሳሳይ መደብ ተመድበው በሚተገብሩ ለአንድ ዓላማ በቆሙ ሰራተኞች መካከል የአከፋፈል ስርዓቱ መለያየቱ ቅሬታ ሊፈጥር ይችላል ይላሉ አቶ ሰለሞን።ከዚህ በፊት የነበረው አሰራር የ40/60 ከፍተኛ ገቢ ላላቸው እና አሰራሩም ጥራት ያለው እንዲሆን ታስቦ በልማት ድርጅት እንዲሆን በሚል ታቅዶ ሲተገበር መቆየቱን እና ትርፋማ እንደነበረም ይናገራሉ።አሁን ወደ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ ሲቀላቀልም በፊት ሰራተኞች ከነበራቸው ጥቅም አንጻር ሊለያዩ ይችላሉ።ግን ክፍያውን መተግበር የምንችለውም በመንግስት አቅም እና ችሎታ በመሆኑ ከእዚህ ሌላ መፍትሄ ማምጣት አንችልም ይላሉ ኃላፊው።

መንግስት አሁን እንዲደረግ የሚፈልገው በአቅሙ ልክ ነው።‹‹ውሳኔው ያለው በፐብሊክ ሰርቪስ እና በምክር ቤቱ እጅ በመሆኑ ምንም ማድረግ አይቻልም።ይህ ውሳኔ ከቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ አቅም በላይ ነው።ተግባራዊ ማድረግ የምንችለው በሚፈቀድልን መሰረት ነው›› ሲሉም ያክላሉ።

አቶ ሰለሞን ከሐምሌ ወር 2011 ዓ.ም ጀምሮ በጄኢጂ ምደባ መደረጉን ያምናሉ።በጀት በየአመቱ የሚያዝ በመሆኑ እና የኋለኛውንና ከተመደቡበት ጊዜ አንስቶ የተጠራቀመውን ለመክፈል ውይይት ባለመደረጉ በዚህ ዙሪያ ከሰራተኞች የተነሳውን ጥያቄ ለመመለስ በልዩ ሁኔታ የሚታይ ይሆናል።

ከኑሮ ውድነት እና አጠቃላይ ካለው ተጨባጭ

ሁኔታ አንጻር ችግር ሊኖር ይችላል።ሰራተኞቻችንን ደስተኛ ማድረግ ካልቻልን ወደ ተቋማችን የሚመጡ ደንበኞችን በደስታ ማስተናገድ እንደማንችል እንገነዘባለን።የውጭ ደንበኞችን በአግባቡ ለማስተናገድ የውስጥ ደንበኞቻችንን (ሰራተኞችን) ቅሬታ መቀነስ እንደሚኖርብን እናውቃለን።ግን ካለው ተጨባጭ እና ወቅታዊ ሁኔታ የተነሳ ነው ሙሉ ለሙሉ የሰራተኞቻችንን ፍላጎት ማሟላት ያልቻልነው ይላሉ ኃላፊው።

አቶ ሰለሞን በአዲሱ ዓመት ሰራተኞች እንዲበረታቱ በተሻለ ራዕይ እና ተነሳሽነት ስራ እንዲተገበር ቢሮው የአቅሙን ያደርጋል።ሰራተኞች ተገቢውን ጥቅም እንዲያገኙ ለማድረግ፣ በመመሪያው እና በደንቡ መሰረት ተገቢውን ጥቅምና መብት ለማስጠበቅ እየሰራን እንገኛለን።ቢሮው የተጣለበትን ተልዕኮ ከግብ ለማድረስ የሰራተኞችን ፍላጎት ለማሟላት ጥረት እናደርጋለን።ስለሆነም ሰራተኞች በትዕግስት ሊጠብቁን ይገባል የሚል መልእክት አስተላልፈዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስ ቢሮ ምላሽ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስ ቢሮ ኃላፊ አቶ ሃይሉ ልኡል፤ የሚኒስትሮች ምክር ቤት በመደበኛ ስብሰባው ከሐምሌ 1 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ ማንኛውም በኢትዮጵያ ክልል የሚገኝ የመንግስት ሰራተኛ የሚያገኘው ደመወዝ በጄኢጂ መሰረት የተቀመጠ መሆኑን አመልክቷል ባይ ናቸው።ነገር ግን ይህ አሰራር ከመምጣቱ በፊት በተለያየ አግባብ አነስተኛ ከሆነ ቦታ ከፍ ወደ አለ ቦታ ተወዳድረውና ተዘዋውረው የዚያን ደመወዝ የያዙ ሰራተኞች እንዳሉ ይናገራሉ።እነዚህ ሰዎች አዲስ የተወዳደሩበትን መደብ ሳያገኙ የሚኒስትሮች ምክር ቤት መመሪያ ሲመጣ ጄኢጂ ተግባራዊ መደረጉን ያነሳሉ።

ጄኢጂ ባስቀመጠው መስፈርት መሰረት ለምሳሌ X የተባለው ወደ Y አድጓል፤ Y ተሰፍሮ የተቀመጠለት መደብ እና ለመደቡም የተፈቀደለት ደመወዝ አለ።ከእዚህ ደመወዝ ውጪ መጠየቅ አይችሉም።እነርሱ ግን ድሮ በልዩ እስኬል የተፈቀደው ስኬል እንዲሰጣቸው ነው እየጠየቁ የሚገኙት።ጄኢጂ እሳቤው ደመወዝ የመቀነስ ስላልሆነ ከፍ ያለ ደመወዝ ይዞ የነበረው ሰው ደመወዙን ይዞ ዝቅ ያለ መደብ ላይ ተቀምጦ ሊሆን ይችላል።ነገር ግን ከሐምሌ 1 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ በጄኢጂ መስፈርት በወጣው እና ለእርሱ በተቀመጠው መስፈርት ውጪ መክፈል ስለማይቻል የደመወዝ ልዩነቶች አሉ።

ተመሳሳይ ደረጃ ላይ ሆነው፣ ተመሳሳይ የትምህርት ዝግጅት ኖሯቸው የደመወዝ ልዩነት ተፈጥሯል።ይህንን ልዩነት የፈጠረውም ስርዓቱ ነው።ይህ በረጅም ሂደትም ቢሆን እየተስተካከለ ይሄዳል።ለምሳሌ ሰዎች ሲለቁ ምደባ የሚደረገው በአዲሱ ደመወዝ፤ ለደረጃው በተፈቀደው መስፈርት ይሆናል፣ ሰዎች በጡረታ ሲወጡም ተመሳሳይ እየሆነ ወጥነት ይኖረዋል።በኢትዮጵያ ደረጃ

አንድ የስራ መደብ ተመሳሳይ ደመወዝ ይኖረዋል።ይህ ሲሆንም ሰራተኞች ወደ ሌላ ተቋም ለመዘዋወር አይኳትኑም።ምክንያቱም ወደ ሌላ መስሪያ ቤት ብዘዋወር የተሻለ ደመወዝ አገኛለሁ የሚል እሳቤ አይኖርምና።ምናልባት የስራ ሁኔታ ካልተመቸ ብቻ ነው ክፍተት ሊፈጥር የሚችለው ይላሉ አቶ ኃይሉ ልዑል፡፡

ጥያቄውን ከሐምሌ 1 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ ያደጉ ሰራተኞች ከሆኑ እየጠየቁ ያሉት የሚኒስትሮች ምክር ቤት በመደበኛ ስብሰባ የወሰነውን ማናችንም መሻር ስለማንችል ተግባራዊ ይደረጋል።ምናልባት አከፋፈሉ ሊለያይ ይችል ይሆናል እንጂ ያደጉት በጄኢጂው ከሆነ ደረጃው እና ጄኢጂው ለደረጃው የፈቀደው ደመወዝ ይከፈላቸዋል።ጭማሪው እስከ አንድ ሺ 500 ብር ጭማሪ ደመወዝ የሚያስገኝ ከሆነ በአንድ አመት ያገኛሉ።ክፍያቸው ከአንድ ሺ 500 ብር በላይ የሚጨምር ከሆነ እና ሁለት ሺ፣ ሶስት ሺ እና አራት ሺህ እያለ የሚጨምር ከሆነ በጄኢጂ ያገኙት ከሐምሌ 2012 ዓ.ም ጀምሮ ሙሉ ደመወዛቸውን እንዲያገኙ ተደርጓል።አሁን በአዲስ አበባ ከተማ ስር በጄኢጂ ሙሉውን እየከፈልን እንገኛለን ነው አቶ ኃይሉ ልዑል የሚሉት።

እንደ እርሳቸው ማብራሪያ፤ የልማት ድርጅት ወይም በጎ አድራጎት ድርጅት ካልሆነ በስተቀር ከአሁን በኋላ የልዩ ደመወዝ እስኬል ክፍያ የሚባል አይኖርም።ሁሉም ተቋም በአገር ደረጃ በተቀመጠው እና ወጥነት ባለው የደመወዝ እስኬል መሰረት ይስተናገዳል። መቀጠል ያለበትም ይህ አዲስ ስርዓት ነው።የትኛውም ተቋም ይዞ የሚመጣው መስፈርት ጄኢጂው ይጠናል፣ ስራው የሚመዘንበት የራሱ ሥርዓት ያለው ሲሆን፤ የሚመዘነውም በፌዴራል ደረጃ ነው።ከተመዘነ በኋላ ደረጃ ይቀመጥለታል።በመቀጠልም የደረጃው ደመወዝ ይከፈለዋል።ዛሬ፣ ነገም ሆነ ከነገ ወዲያ የሚቋቋም ተቋም ቢሆንም፣ ወጥነት ባለው እና በአገሪቱ መሰረት በተቀመጠው የደመወዝ እስኬል መሰረት ይስተናገዳል።

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ የመንግስት ነው።በፊት በቢሮው ስር የነበረ አንድ ድርጅት አሁን ፈርሷል።ቢሮውን እንደ አዲስ አደራጅተን ምደባ ተሰርቶ እና ቅሬታም ታይቶ ተጠናቅቋል።የተንሳፈፉ ሰራተኞች በክፍለ ከተማው ስር በሚገኙ ክፍት መደቦች ላይ እንዲመደቡ ውሳኔ ተላልፎ እየተመደቡ ይገኛል።ባላቸው የትምህርት ዝግጅት እና የስራ ልምድ የያዙትን ደመወዝ ይዘው በከተማው ስር ባሉ በሚመጥናቸው ክፍት መደቦች ላይ ይመደባሉ።

በጄኢጂ የሚተገበረው አሰራር ሰውን አያይም። የሚታየው የስራው ክብደት፣ የስራው ልፋት፣ የፈጠራ ሁኔታ፣ ተጋላጭነቱን እና መሰል ወሳኝ መስፈርቶች ናቸው።ስራውን አይቶ ባግባቡ ያስመዘነ አካል ተገቢውን ደረጃ እና ጥቅም ያገኛል።ሲሉም ሃሳባቸውን አጠቃለዋል።

የ20/80 የጋራ መኖሪያ ቤቶች

Page 12: ከባንክ ውጭ ከ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር በላይ ማስቀመጥ ተከለከለሕግ • ዶ/ር ሳሙኤል ሁርካቶ፤ የሳይንስና ከፍተኛ

ረቡዕ ነሐሴ 13 ቀን 2012 ዓ.ም

ገጽ 12 የዘመን ችሎት

«ጋብቻ በሁኔታ ፈርሷል» የሚባለው እንዴት ነው? በገብረክርስቶስ

እንደምን ሰነበታችሁ! እንኳን በጤና ተገናኘን!ሰው በዚህ ዓለም ሲኖር የደስተኝነቱ ጥግ፤ የመኖር

ጣዕሙ ልኬት የሚታወቀው በትዳርና በፍሬዎቹ ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም።

ምን ቢያጌጡ፤ የቱንም ያክል በሀብት ሰገነት ላይ ቢሞናደሉ ፈጣሪ የባረከው ቤተሰብን የመመስረት ያክል የሚያስደስት ነገር የለም።

ፍቅርና ሰላም በሞላበት ትዳር ውስጥ እንኳን የላመ የጣመ በልተው፤ የጣፈጠ ጠጥተው ይቅርና እፍኝ ጥሬ ቆርጥመው ቢያድሩ ደስታ ይገኛል።

በመተሳሰብና በመዋደድ በተሰናሰለ ቤተሰብ ውስጥ ባል መኩሪያና ሞገስ ይሆናል። ሚስትም በቤት እልፍኝ ውስጥ ጊዜውን ሳይስት እንደሚያፈራ የወይን ተክል ናት። ልጆችም በማዕድ ዙሪያ እንደ አዲስ የወይራ ችግኝ ይሆናሉ።

እንዲህ ያለ ቤተሰብ መስርቶ ኖሮ ማለፍ ዓለም ነው። ይሁንና ህይወት መልከ-ብዙ ናትና ሁልጊዜ እንዳማሩ መኖር አይገኝም። ይህኔ ታዲያ ትዳር ይናጋል፤ ቤተሰብም ይበተናል።

እንዲህ ያለው “አያድርስ” የሚያሰኝ አጋጣሚ ሲመጣ ታዲያ በብልህነት ጉዳዮችን ፈር ማስያዝ ቀሪ የሕይወትን ተስፋ ለመጠባበቅ በር ይከፍታል።

እናም ጋብቻ በሕግ የሚመሰረት፤ ቤተሰብም ሕጋዊ ጥበቃና ዕውቅና ያለው ማሕበራዊ መዋቅር ነውና ሕጉ ምን ይላል የሚለውን መገንዘብ ያስፈልጋል።

ለዚህም ነው ጋብቻ ከሚፈርስባቸው ምክንያቶች ውስጥ አንዱ የሆነውን የሁኔታ ምክንያት እንደሰበዝ መዝዘን ዛሬ ልናስቃኛችሁ የወደድነው።

ጋብቻና ቤተሰብ ቤተሰብ የማህበረሰብም ሆነ የአገር መሰረት ነው።

በአንድ ቤተሰብ ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች በስጋና በደም የተሳሰሩ በመሆናቸው ከየትኛውም የማህበረሰብ መዋቅር በላቀ ሁኔታ የጠነከረ ማህበራዊ ትስስር ያዳብራሉ።

የግለሰቦች የመጀመሪያ ትምህርት ቤት ቤተሰብ ነው። የማንነት መሰረት የሚታነጸው በቤተሰብ ውስጥ ነው። በቤተሰብ ውስጥ የግለሰብ ባህርይ ይቀረጻል።

የቤተሰብ ጠንካራም ሆነ ደካማ አስተዋጽኦ ከግለሰቦች ሕይወት አልፎ በማህበረሰቡ ውስጥም የራሱ ሚና አለው። በዚህ መነሻ መንግስታት ቤተሰብ እንዴት ይመሰረታል፤ የባልና የሚስት እንዲሁም የልጆች ግንኙነት ምን መምሰል ይገባዋል፤ የቤተሰብና የንብረት ጉዳይ እንዴት ይመራል፤ ፍቺስ እንዴት ይፈጸማል ወዘተ የሚሉ የቤተሰብ ጉዳዮችን በተመለከተ ሕግ በማውጣት በቤተሰብ ጉዳይ ላይ ጣልቃ ይገባሉ።

በተሻሻለው የፌዴራል የቤተሰብ ሕግ መሰረት ቤተሰብ አንድም በስጋ ዝምድና ማለትም አያት፣ አባትና እናት እንዲሁም ልጆች እየተባለ በተወላጅነት ይመሰረታል። በሌላ በኩል በጋብቻ ይመሰረታል ቤተሰብ። በጉዲፈቻም እንዲሁ።

ከእነዚህ ሁሉ ታዲያ ቤተሰብ የሚመሰረትበት ዓይነተኛ መሳሪያ ጋብቻ ነው። ባልና ሚስት በትዳር ሲተሳሰሩ ሚስት የባሏ ወላጆችም ልጅ ወይም ምራት (Daughter in law) ትሆናለች፤ ባልም እንዲሁ የሚስቱ ወላጆች ልጅ ወይም አማች (Son in law) ይሆናል።

በመሆኑም ባልና ሚስት በሚጋቡበት ወቅት ከራሳቸው አልፈው ቤተሰቦቻቸውንም ጭምር በማጋባት የጋብቻ ዝምድና ስለሚፈጥሩ ሰፊ ማህበራዊ ትስስር ያለበት ግንኙነትን ይፈጥራሉ ማለት ነው።

ጋብቻ በሶስት ዓይነት መልኩ ከተከናወነ የጸና እና በሕግም ፊት ዋጋ ያለው ይሆናል። ጋብቻ በክብር መዝገብ ሹም ፊት ይፈጸማል። ይህም በአሁኑ ወቅት እንደ ልደት፣ ጋብቻ፣ ፍቺ እና ሞት ያሉትን ወሳኝ ኩነቶች በሚመዘግብ መስሪያ ቤት ውስጥ በባለሙያው ፊት ምስክሮች ባሉበት የሚፈጸም ጋብቻ ነው። ጋብቻ በምድር ላይ ከከበሩ ነገሮችም በላይ ክቡር ነገር ነውና በክብር መዝገብ ላይ በክብር ይመዘገባል።

ከዚህ ሌላ ተጋቢዎቹ በሐይማኖታቸው ወይም ከሁለቱ በአንዳቸው ሐይማኖት መሰረት የሚጸና ጋብቻ ለማቋቋም የሚያስፈልገውን ስርዓት በመፈጸም

የሐይማኖታዊ ስርዓት ጋብቻ ይፈጽማሉ። ኢትዮጵያ የብዙ ብሔር ብሔር ብሔረሰቦች አገር

ናትና አንድ ሴትና አንድ ወንድ በሚኖሩበት አካባቢ ባህል መሰረት በሕግ የሚጸና ጋብቻ መመስረትም ይችላሉ። እነዚህ ሶስቱም የጋብቻ አፈጻጸም ስርዓቶች በኢትዮጵያ ሕግ እኩል የሆነ እውቅናና ጥበቃ የተደረገላቸው ናቸው።

በየትኛውም ዓይነት መንገድ የተመሰረተ ጋብቻ እስከ ህይወት ፍጻሜ ድረስ ጸንቶ እንደሚቆይና ባልና ሚስትን ከሞት በስተቀር ሌላ የሚለያቸው እንደማይኖር ይታሰባል።

ይሁንና በተለያዩ ምክንያቶች ጋብቻ እድሜው አጥሮ ባልና ሚስቱም አይንህን ላፈር፣ አይንሽን ላፈር መባባላቸው

አይቀርም። በዚህ መነሻም የባልና ሚስት የእህል ውሃ ገመድ ይበጠሳል፤ ባልና ሚስት መሆናቸውም ቀርቶ እንደ ሌላ ባዕድ (ሶስተኛ ወገን) ይተያያሉ።

እናም ጋብቻ ሲፈርስ የራሱ ውጤቶች ስላሉት ሲፈርስም ሆነ መፍረሱን ተከትሎ የሚከናወኑት ነገሮች በአግባቡ እንዲፈጸሙ ህግ የራሱን መፍትሄዎች አስቀምጧል።

በሕግ ጋብቻ የሚፈርስባቸው ምክንያቶችጋብቻ በሁለት መልኩ ነው የሚፈርሰው - ህግ

በሚያስቀምጣቸው ምክንያቶች እና በባልና ሚስቱ ምክንያት።

ጋብቻ በሕግ የሚፈርስበት የመጀመሪያው ምክንያት ከተጋቢዎቹ የአንዱ መሞት ወይም በፍርድ ቤት የመጥፋት ውሳኔ መሰጠት ነው።

ባል ወይም ሚስት በህይወት ከሌለ/ች አብሮ መኖር የሚባለው ጉዳይ በመሰረቱ ስለማይኖር ጋብቻ በህግ ይፈርሳል ማለት ነው። በሌላ በኩል ባል ወይም ሚስት ጠፍቶ/ታ ወሬው/ዋ ለሁለት ዓመታት ያልተሰማ እንደሆነ ማንኛውም ሰው ቢሆን የመጥፋት ውሳኔ በፍርድ ቤት እንዲሰጥበት ያስደርጋል።

ፍርድ ቤቱ የመጥፋት ውሳኔውን በሰጠበት ቀን ጋብቻው እንደሚፈርስ ስለ ሰዎች የተመለከተው የፍትሐብሔር ሕጋችን ይደንግጋል። የመጥፋት ውሳኔ የተሰጠበት ተጋቢ ተመልሶ ቢመጣ እንኳን ቀደም ሲል የነበረውና በመጥፋቱ ምክንያት የፈረሰው ጋብቻ ተመልሶ በመምጣቱ ምክንያት ዳግም ነፍስ አይዘራም።

ለጋብቻ መፍረስ ሕጉ ራሱ ከሚያስቀምጣቸው ከሞትና ከመጥፋት ምክንያቶች በተጨማሪ ጋብቻ ለመፈጸም መሟላት ካለባቸው ሁኔታዎች ውስጥ አንዱ ከተጣሰም የጋብቻን መፍረስ ያስከትላል።

ይህም ማለት ተጋቢዎቹ ለመጋባት ነጻና ሙሉ ፈቃዳቸውን ሳይሰጡ ወደ ትዳር ውስጥ ገብተው ከሆነ፤ 18 ዓመት ሳይሞላቸው የተጋቡ ከሆነ፤ ተጋቢዎቹ ወላጆችና ተወላጆች አልያም እህትና ወንድም ወይም አክስት አጎት ከሆኑ ጋብቻውን ህጉ ራሱ ፈራሽ ነው ይለዋል።

ለዚህ ጽሁፍ መነሻ የሆነውና ጋብቻ በሁኔታ የሚፈርስበትን ምክንያት የሚመለከተው ጉዳይ ደግሞ ጋብቻ በሕግ የሚፈርስበት ምክንያት ነው።

ጋብቻ በተጋቢዎች የሚፈርስበት አግባብከላይ ከተብራሩት የሕግ ምክንያቶች ሌላ ራሳቸው

ተጋቢዎቹ በሚወስዱት ርምጃ ጋብቻ ይፈርሳል። ይኸውም ፍቺ መፈጸም ነው። አንድም ባልና ሚስት ጋብቻቸውን ለማፍረስ ሊስማሙ ይችላሉ፤ አልያም በተናጠል ጋብቻቸውን በፍቺ ማፍረስ ይችላሉ።

ባልና ሚስት በስምምነት ለመፋታት ሲወስኑ ይህንኑ ለፍርድ ቤት አቅርበው ውሳኔያቸው ተቀባይነት ካገኘ እንዲሁም ከተጋቢዎቹ አንዱ ወይም ሁለቱም በአንድነት ጋብቻቸው በፍቺ እንዲፈርስ ለፍርድ ቤት ካመለከቱ ጋብቻ ይፈርሳል። ጋብቻ ባልና ሚስት በራሳቸው የሚፈጽሙት ጥብቅ የሆነ ሕጋዊ ድርጊት በመሆኑ ፍቺንም ቢሆን በራሳቸው እንጂ በውክልና ሊፈጽሙ አይገባም።

በዚሁ መሰረት ባልና ሚስት በስምምነት ለመፋታት የወሰኑ እንደሆነ የፍቺ ስምምነታቸውንና ፍቺው የሚያስከትለውን ውጤት (ከንብረት ክፍፍል አልያም ከልጆች አያያዝ ወዘተ በተገናኘ) በጽሑፍ ለፍርድ ቤት በማቅረብ ፍቺው እንዲጸድቅላቸው መጠየቅ እንደሚችሉ ህጉ ደንግጓል።

ባልና ሚስቱ ታዲያ ለፍርድ ቤቱ በሚያቀርቡት የፍቺ ማመልከቻ ላይ ለመፋታት የወሰኑበትን ምክንያት እንዲገልጹ አይገደዱም።

እዚህ ላይ ልብ ሊባል የሚገባው ቁም ነገር ተጋብተው ስድስት ወር ያልሞላቸው ባልና ሚስት በስምምነት ለመፋታት እንደማይፈቀድላቸው ነው።

በባልና ሚስት የጋራ ስምምነት ከሚቀርብ የፍቺ ጥያቄ በተጨማሪ ከተጋቢዎቹ አንዱ ወይም ሁለቱም ተጋቢዎች በአንድነት በመሆን ጋብቻቸው በፍቺ እንዲፈርስ ለፍርድ ቤት ካመለከቱ ጋብቻ ይፈርሳል።

በእንዲህ ዓይነት ሁኔታ ጥያቄያቸውን ሲያቀርቡ ታዲያ ፍቺ ለመጠየቅ ምክንያት የሆናቸውን ጉዳይ ለመግለጽ ይችላሉ፤ ነገር ግን እንዲገልጹ አይገደዱም።

እዚህ ላይ ግንዛቤ ሊያዝገበት የሚገባው ጉዳይ ተጋብተው ስድስት ወር ያልሞላቸው ባልና ሚስት በስምምነት ለመፋታት የተከለከሉ ቢሆንም ቅሉ፤ በተናጠል የፍቺ ማመልከቻ በማቅረብ ጋብቻ እንዲፈርስ ከመጠየቅ የሚያግዳቸው ህግ ግን አለመኖሩ ነው።

በዚሁ መሰረት ፍርድ ቤት የፍቺ አቤቱታው እንደቀረበለት ወዲያውኑ ባልና ሚስቱ ስለሚተዳደሩበትና ስለሚኖሩበት ሁኔታ፤ ስለልጆቻቸው አጠባበቅ፤ ስለሚኖሩበት ስፍራና ስለአኗኗራቸው እንዲሁም ስለንብረታቸው አስተዳደር ተገቢ መስሎ የታየውን ትዕዛዝ ይሰጣል።

ባልና ሚስት ጋብቻቸውን በፍቺ ለማፍረስ ከተስማሙ ለፍርድ ቤት የሚያቀርቡት የጽሑፍ የፍቺ ስምምነታቸውን ብቻ ሳይሆን ፍቺው የሚያስከትለውን ውጤትም በተመለከተ የተስማሙበትንም ጽሑፍ ጭምር ነው።

የፍቺ ጥያቄ በተናጠል በሚቀርብበት ወቅት ግን ፍቺው የሚያስከትለውን ውጤት በተመለከተ ፍቺ ጠያቂው ወገን እንዲያቀርብ አይገደድም።

ምክንያቱም በስምምነት የተደረገ የፍቺ ጥያቄ ባለመሆኑ እንኳንስ በውጤቱ በመሰረቱ እንኳን በፍቺው ላይ ስምምነት ሳይኖር በተናጠል የተወሰደ ርምጃ በመሆኑ “ጋብቻው ሊፈርስብኝ አይገባም” የሚል ክርክር ከሌላው ተጋቢ መቅረቡ አይቀሬ ነው።

በዚሁ መሰረት የፍቺ ውሳኔ ከሰጠ በኋላ ፍቺው ስለሚያስከትለው ውጤት እንዲስማሙ ባልና ሚስቱን ይጠይቃቸዋል። ከተስማሙ ፍርድ ቤት አቅርበው ይሁንታውን ያሰጣሉ።

ለመስማማት ካልፈለጉ ወይም ለመስማማት ሞክረው ስምምነት ላይ መድረስ ያልቻሉ እንደሆነ ደግሞ ፍርድ ቤቱ በራሱ ወይም በሽማግሌዎች ወይም ራሱ

በሚሾማቸው ባለሙያዎች አማካይነት ወይም አመቺ መስሎ በታየው ዘዴ የፍቺውን ውጤት ይወስናል።

በተናጠል ከሚቀርብ የፍቺ ጥያቄ ጋር በተያያዘ ሌላው በህጋችን የተመለከተው ጉዳይ ካሳን የተመለከተው ነው። ከባልና ከሚስት አንዱ ለፍቺው ምክንያት የሆነውን በደል (ጥፋት) ፈጽሞ የተገኘ እንደሆነና ፍርድ ቤቱም ለፍትህ አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው በሌላው ተጋቢ ላይ ለደረሰው ጉዳት በዳዩ ተመጣጣኝ የሆነ ካሳ እንዲከፍል ሊወስንበት እንደሚችል ህጉ አስቀምጧል።

እርግጥ ነው በሕጋችን የፍቺ ጥያቄ አቅራቢው በሌላኛው ተጋቢ የተፈጸመ በደል (ጥፋት) ስለመኖሩ እንዲገልጽ

አይገደድም። የካሳ ጉዳይ የሚነሳ ከሆነ ግን ጥፋት ስለመኖሩ መረጋገጥ አለበት።

ጋብቻ በሁኔታ ፈርሷል የሚባለው መቼ ነው?

የተጋቢዎቹ የአንዱ መሞት ወይም የመጥፋት ውሳኔ እንዲሁም የጋብቻ ቅድመ-ሁኔታዎች አለመሟት ጋብቻ በሕግ የሚፈርስባቸው ምክንያቶች መሆናቸውን ከላይ ተረድተናል።

ጋብቻን በሁኔታ ማፍረስ ደግሞ ሌላው የሕግ ምክንያት ነው። ይህ ጉዳይ እንደ ሞት አልያም መጥፋት ወይንም ደግሞ እንደ ጋብቻ ቅድመ-ሁኔታዎች አለመሟላት ቀላል ያለ ምክንያት አይደለም።

ይልቁንም በየጊዜው የተለያዩ ክርክሮችን እያስነሳ እስከ ፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ድረስ የሚያሟት ቁልፍ ጉዳይ ነው።

የተጋቢዎች ተለያይቶ ለረዥም ጊዜ መኖር ወይም በዚህ ረዥም ጊዜ ውስጥ ሌላ ትዳር መስርቶ መገኘት የቀደመውን ጋብቻ ፈራሽ ያደርገዋል።

ጋብቻው በሞት፣ በመጥፋት ወይም በፍርድ ቤት በተሰጠ ውሳኔ ፈርሷል ባይባልም ጋብቻ በተጋቢዎች መካከል የመተጋገዝ፣ የመደጋገፍና የመከባበር እንዲሁም አብሮ የመኖር ግዴታን የሚጥል ሆኖ ሳለ ባልና ሚስቱ በተለያየ ምክንያት ተለያይተው ለረዥም ጊዜ መኖራቸው ጋብቻውን ያፈርሰዋል።

ጉዳዩን በቀላሉ ለመረዳት እንዲረዳ ከጥቂት ጊዜያት በፊት በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት እልባት ካገኘ አንድ የቤተሰብ ጉዳይ ክርክር ይህንን እናካፍላቸሁ።

አቶ በቀለ በላቸው እና ወይዘሮ አልማዝ ለሼ ይባላሉ። በደብረብርሃን ነው ነዋሪነታቸው። ጥንዶቹ በባህላዊ ሥነስርዓት ተጋብተው ለበርካታ አስርት ዓመታት በትዳር ጥላ ኖረዋል፤ የየአብራክ ክፋይ የማህጸን ፍሬም አግኝተዋል።

ይሁንና በአንድ ጣሪያ ሥር አብሮ መኖራቸውን አቁመው በራሳቸው ጊዜ ተለያይተው ለ19 ዓመታት ይቆያሉ። በመጨረሻ ወይዘሮ አልማዝ ከጥቂት ዓመታት በፊት ጀምሮ ተስማምተው አብረው መኖር ባለመቻላቸውና ከመካከላቸውም ሰላም መጥፋቱን በመግለጽ ጋብቻው ፈርሶ የጋራ ንብረታቸውን እንዲካፈሉ የፍቺ አቤቱታ ለወረዳው ፍርድ ቤት ያቀርባሉ።

ፍርድ ቤቱም የግራቀኙን ክርክር አድምጦ እና ማስረጃዎቻቸውንም መዝኖ ጥንዶቹ ከአስር ለሚልቁ ዓመታት በትዳር ጥላ ሥር አብረው መኖር ባለመቻላቸው ምክንያት ጋብቻቸውም በሁኔታ ፈርሷል በሚል የአማራ ክልል የቤተሰብ ሕግን መሰረት በማድረግ ወስኗል።

ወይዘሮዋም ጉዳዩን በየደረጃው ለሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ከዚያም ለክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቅርበው የሥር ፍርድ ቤት ውሳኔ ጸንቶባቸዋል። በመጨረሻም ለፌዴራሉ ሰበር ሰሚ ችሎት አቤት ብለዋል።

ይሁንና በአገሪቱ የመጨረሻ ውሳኔ የመስጠት ሥልጣን ያለው የሰበር ችሎቱም በመሰረቱ ጋበቻ በተጋቢዎች ላይ የመተጋገዝ፣ የመደጋገፍና አብሮ የመኖር እንዲሁም ቤተሰባዊ ግዴታን በጋራ የመወጣት ኃላፊነትን ስለሚጥል ሁለቱ ግለሰቦች ደግሞ ከዚህ በተቃራኒው ከ1987 ዓ.ም. ጀምሮ በራሳቸው ምክንያት በአንድ ጣሪያ ሥር መኖራቸውን በማቆማቸው ምክንያት ጋብቻቸው በሁኔታ መፍረሱን ነው የደመደመው።

በደህና እንሰንብት!

በየትኛውም ዓይነት መንገድ የተመሰረተ ጋብቻ እስከ ህይወት ፍጻሜ ድረስ ጸንቶ እንደሚቆይና ባልና ሚስትን ከሞት በስተቀር ሌላ የሚለያቸው እንደማይኖር ይታሰባል። ይሁንና በተለያዩ ምክንያቶች ጋብቻ እድሜው አጥሮ ባልና ሚስቱም አይንህን ላፈር፣ አይንሽን ላፈር መባባላቸው አይቀርም፡፡ በዚህ መነሻም የባልና ሚስት የእህል ውሃ ገመድ ይበጠሳል፤ ባልና ሚስት መሆናቸውም ቀርቶ እንደ ሌላ ባዕድ (ሶስተኛ ወገን) ይተያያሉ፡፡ እናም ጋብቻ ሲፈርስ የራሱ ውጤቶች ስላሉት ሲፈርስም ሆነ መፍረሱን ተከትሎ

የሚከናወኑት ነገሮች በአግባቡ እንዲፈጸሙ ህግ የራሱን መፍትሄዎች አስቀምጧል፡፡

Page 13: ከባንክ ውጭ ከ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር በላይ ማስቀመጥ ተከለከለሕግ • ዶ/ር ሳሙኤል ሁርካቶ፤ የሳይንስና ከፍተኛ

ረቡዕ ነሐሴ 13 ቀን 2012 ዓ.ም

ገጽ 13

አዲስ ዘመን

ድሮ የትናየት ፈሩ

የትናየት ፈሩ

ሳምንቱ በታሪክ

ጥቅምት 20 ቀን 1958 ዓ.ም የታተመው አዲስ ዘመን ጋዜጣ የብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት ሰራተኛ የሆኑ ሴቶች ታኮ ጫማ አድርገው እንዳይመጡ መከልከላቸውን የሚገልጽ ዘገባ አስነብቦ ነበር።

ሴቶች ተረከዘ ረዥም ጫማ እንዳያደርጉ ተከለከለ

በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት ውስጥ ተቀጥረው የሚያገለግሉ ሴቶች በስራ ጊዜ ተረከዝ ያለው ባለታኮ ጫማ እንዳያደርጉ ተከልክለዋል። ከብረት የተሰራው ሹል የሴቶች ጫማ ሰራተኞቹን እንደፍላጎታቸው ከወዲያ ወዲህ ሊያራምዳቸውና ሊያሰራቸው ስለማይችል በስራ ሰዓት ልጥፍ ጫማ ብቻ እንዲያደርጉ የተፈቀደ መሆኑን የማተሚያ ቤቱ ስራ አስኪያጅ ትናንት ከሰጡት ወሬ ለመረዳት ተችሏል። ጫማው ለሥራ ፍጥነት አዋኪ ከመሆኑም በላይ ከፕላስቲክ የተሰራውን የማተሚያ ቤት ወለል እየሰረጎደ አበላሽቶታል ሲሉ አቶ ለማ የተጠቆመውንና የተበሳሳውን ወለል አሳይ ተውናል። ሴቶቹ ታኮ ጫማ ለማድረግ ፍላጎት ካላቸው ልጥፉን ጫማ ይዘው በመምጣት ከማተሚያ ቤቱ ሲደርሱ ቀይረው ወደ ስራ ለመሰማራት እንደሚችሉ ተናግረዋል። ተቀያሪውን ታኮ ጫማ የስራ ሰዓት እስኪደርስ በተሰጣቸውና በተወሰነላቸው ቁም ሣጥን ውስጥ ሊያስቀምጡት እንደሚችሉ ተገልጧል። የተከለከለውን ጫማ አድርጎ የተገኘ የማተሚያ ቤቱ ባልደረባ ቅጣት ሊደርስበት እንደሚችል በትናንትናው ቀን ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷል በማለት ሥራ አስኪያጁ በተጨማሪ አስረድተዋል። ******** ******** ********ህዳር 20 ቀን 1958 ዓ.ም የታተመው አዲስ ዘመን ጋዜጣ የአይን ብሌናቸውን ለአይነ ስውራን እንዲሰጥ በመናዘዝ የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ ናቸው ያላቸውን የመቶ አለቃ ተደናቂ ተግባር የሚገልጽ ዘገባ አስነብቦ ነበር።

የመቶ አለቃ ፋንታሁን ዓይናቸውን ለበጎ አድራጎት ተናዘዙ

የመቶ አለቃ ፋንታሁን ካሳ የተባሉ የወንጀለኛ ምርመራ ባልደረባ ህይወታቸው ከዚህ ዓለም ሲያልፍ ሁለቱ አይኖቻቸው ለአይነ ስውራን እንዲያገለግሉ የተናዘዙ መሆናቸውን የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ በጎ አድራጎት ድርጅት በሰጠው ወሬ አስረድቷል። መቶ አለቃ ፋንታሁን ይህን ልግስና ሊያደርጉ የተገደዱበት ዋናው ምክንያት አይነ ስውራንን በማከም ላይ በሚገኙት በሁለቱ እንግሊዛውያን የዓይን ሊቃውንት ስራ በመደሰት እንደሆነ ታውቋል። መቶ አለቃው የዓይን ስጦታቸውን የሚያረጋግጥ ፊርማ ለቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ በጎ አድራጎት ድርጅት ፈርመዋል። ስለዚሁ ጉዳይ መቶ አለቃ ፋንታሁን ሲያስረዱ "ከጥሩ ጥቅም ላይ እንዲውል ከምፈልገው አንዱ አይኖቼን ስለሆነ ብርሃን እንዲያዩ ከሚሹቱ አይነ ስውራን ለአንዱ እንኳን ቢያገለግል በጣም ደስ ይለኛል" ብለዋል። መቶ አለቃ ፋንታሁን ባለፈው ዓመት ስለሕክምና ለሚያጠኑ የፖሊስ ተማሪዎች ሰውነታቸውን ለአካል ምርመራ ፈቅደው እንደ ነበር የሚታወስ ነው። አሁንም ቢሆን አይነ ስውራንን ለመርዳት ያደረጉት ጥረት የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ አሰኝቷቸዋል። እንግሊዛውያኑ የዓይን ሊቆች የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ በጎ አድራጎት ድርጅት እንግዳ በመሆን ለአይነ ስውራን የሚተካ ሃያ ዓይኖች ይዘው መጥተው አይነ ስውራኑን ኦፕራሲዮን አድርገው ብርሀናቸውን ለመመለስ በተስፋ የሚጠባበቁ መሆናቸውን ወሬው በተጨማሪ አስረድቷል።

በፋሺስት ኢጣሊያ ወረራ ወቅት ከጠላት ጋር በተለያዩ የጦር ግንባሮች የተዋጉትና የፋሽስት ጣሊያንን አውሮፕላን መተው የጣሉት ዝነኛው አርበኛ ሌተና ጀኔራል ራስ አበበ አረጋይ (በፈረስ ስማቸው አባ ገስጥ) የተወለዱት በዚህ ሳምንት ነሐሴ 14 ቀን 1896 ዓ.ም ነበር፡፡

አበበ አረጋይ ከአባታቸው አረጋይ ቢቸሬ እና ከእናታቸው ወይዘሮ አስካለማርያም ጎበና በተጉለትና ቡልጋ አውራጃ ጅሩ ውስጥ ተወለዱ። አባታቸው በአፈንጉሥነት አገልግለዋል። ኋላም የአክሱም ጽዮን ንቡረ እድ ለመባል በቅተዋል። እናታቸው ደግሞ የዳግማዊ አፄ ምኒልክ የጦር አበጋዝ የነበሩት የራስ ጎበና ዳጬ ልጅ ናቸው።

በልጅነታቸው በቤታቸው ውስጥ መምህር ተቀጥሮላቸው የግዕዝና ባህላዊውን ትምህርት ተምረዋል። ከዚያም ተፈሪ መኮንን ትምህርት ቤት ገብተው በፈረንሳይኛ ቋንቋ ዘመናዊ ትምህርት ተከታትለዋል። ሲጎለምሱም በክብር ዘበኛ በውትድርና ሙያ ሰልጥነው የመቶ አለቅነትን፣ ብሎም የሻምበልነትን ማዕረግ አግኝተዋል።

አበበ በክብር ዘበኛ ሰራዊት በመኮንንነት ካገለገሉ በኋላ በ1926 ዓ.ም በባላምባራስ ማዕረግ ለግማሹ የአዲስ አበባ ከተማ ጥበቃ በአራዳ ዘበኛ አለቃነት ወደ አዲስ አበባ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ተዛወሩ። በፋሺስት ኢጣሊያ ወረራ ወቅት የአዲስ አበባን ሰላምና ጸጥታ የማስከበሩና ከወራሪው ኃይል የመከላከሉ ግዳጅ የተሰጠው ለአራዳ ዘበኞች ነበር። በ1928 ዓ.ም ደግሞ ንጉሰ ነገሥት ቀዳማዊ አፄ ኃይለሥላሴ ወደ ሰሜን የጦር ግንባር ሲዘምቱ ባላምባራስ አበበ አረጋይ የአራዳ ዘበኛ ጠቅላይ አዛዥ ሆነው ተሾሙ።

የፋሺስት ኢጣሊያ ጦር ወረራውን እያሰፋ ቀጥሎ ወደ አዲስ አበባ ከተማ ሲቃረብ የወቅቱ የአዲስ አበባ ተጠባባቂ ከንቲባ ብላታ ታከለ ወልደሐዋርያት የከተማውን ሹማምንት ሰብስበው ተወያዩ። በውይይቱም ወራሪውን ኃይል ከተማ ውስጥ ለመከላከል መሞከር ሕዝቡን ማስጨረስ እንደሚሆን ስምምነት ላይ በመደረሱ አዲስ አበባን ለቆ በመውጣት በዱር በገደል የፋኖ ውጊያ ለመቀጠል ተወሰነ። አበበም ውሳኔውን ለሰራዊቱ ሹማምንት ካሳወቁ በኋላ ቤተሰቦቻቸውንና ጥቂት ሰዎችን አስከትለው ለአርበኝነት ተጋድሎ ወደ ሰሜን ሸዋ አመሩ። የፋሽስት ጠላት ጦር ጣርማ በርን አልፎ ወደ አዲስ አበባ እየተጠጋ ስለነበር ለፋሺስት ጦር ጥቃት ፈጽሞ አይመችም በሚል በሰሜን ሸዋ ገደላገደልና ሸንተረር ውስጥ በመመሸግ አዲስ አበባ ውስጥ የሚከማቸውን የጠላት ጦር ሰላም በመንሳት ሌት ከቀን እንዲባንን አደርጋለሁ ያሉት አበበ አዲስ አበባን በለቀቁ ማግሥት ጣሊያን ወደ ከተማዋ ገባ፡፡

አባ ገስጥ ግንቦት 6 ቀን 1928 ዓ.ም ሰሜን ሸዋ ጅሩ ከደረሱ በኋላ ፋሺስት ኢጣሊያ በኢትዮጵያ ላይ እያደረገ ስላለው ነገር ሁሉ ለአካባቢው ሕዝብ ገለፁ። ሕዝቡም እርስ በእርሱ እየተገናኘ ከተወያየና ስንቅና መሳሪያውን ካዘጋጀ በኋላ ለአገር ነፃነት ለመዋጋት ወስኖ ከአባ ገስጥ ጋር ተቀላቀለ። አበበም አብሯቸው ለመታገል ከወሰነው አርበኛ መካከል በወታደርነትና በማስተባበር ልምድ ያላቸውን እየመረጡ አርበኛውን በአለቆች አደራጁት።

አበበ የፀረ-ፋሺስት ትግል ለመጀመር ዝግጅት እያደረጉ መሆናቸውን የሰማው የጠላት ጦር በበኩሉ በእርሳቸውና በተዋጊዎቻቸው ላይ አደጋ ለመጣል ዝግጅት አደረገ። አበበም ስለጉዳዩ ሰምተው አርበኞቻቸው ሁሉ በአንድ ቦታ እንዲሰባሰቡ አደረጉ። የፋሺስት ጦር በቀኛዝማች ቁምቢ ከምሲ እየተመራ ለፍልሚያ ጉዞ ጀመረ። ግንቦት 24 ቀን 1928 ዓ.ም ደነባ ላይ ሙሉ ቀን የፈጀ ውጊያ ተካሄደ። አባ ገስጥም ከወዲያ ወዲህ እየተሯሯጡ ሲተኩሱና ሲያስተኩሱ ዋሉ፤ አርበኛውም በኃይለኛ ወኔ ተዋጋ። በመሳሪያው ጥራት ተማምኖ የነበረው የፋሺስት ጦርም የማሸነፍ እርግጠኛነቱ ከዳው። ከአባገስጥ አርበኞች የተረፈው የጠላት ጦር ከነአዛዡ ሸሽቶ ደብረ ብርሃን ገባ።

በጦርነቱ ማግሥት አባ ገስጥ ከአርበኞቻቸው መሪዎች ጋር በሌሎች የሰሜን ሸዋ አካባቢዎች የፀረ-ፋሺስት ትግል ከጀመሩ አርበኞች ጋር መተባበር እንደሚገባ ተወያዩ።

በሃሳቡ ላይ በመስማማታቸው አባ ገስጥ ከደጃዝማች አበራ ካሳ ጋር ለመነጋገር ወደ ፍቼ ተጓዙ። እግረመንገዳቸውንም ከፊታውራሪ ዘውዱ አባ ኮራን ጋር ተገናኝተው ተወያዩ። ሰኔ 25 ቀን 1928 ዓ.ም ደጃዝማች አበራ ካሳ፣ ወንድማቸው ደጃዝማች አስፋወሰን ካሳ፣ ፊታውራሪ ዘውዱ አባ ኮራን የሐይማኖት አባቶችን፣ መኳንንትንና ወታደሮችን ይዘው ከአባገስጥና የጦር አበጋዞቻቸው ጋር ተገናኝተው ጠላትን በትብብር ለመከላከል ተስማሙ።

በፋሺስት ወረራ ወቅት የጠላት ኃይል ሲበረታ ከጠላት መሰወርና ቦታ እየቀያየሩ ጠላትን መፋለም የአርበኛው ሁሉ ተግባር ስለነበር አበበም አዳኝም ታዳኝም ስለነበሩ በአንድ ስፍራ ላይ ለረጅም ጊዜ አይቆዩም ነበር። በዚህም ምክንያት በሰኔ 1929 ዓ.ም ከመርሃቤቴ ወደ ግንደበረት እየተጓዙ ሳለ መንከራተት የበዛባቸው ባለቤታቸው ወይዘሮ ቆንጂት አብነት በድንገት ምጥ ያዛቸው። ሰኔ 17 ቀን 1929 ዓ.ም ግንደ በረት በረሃ ላይ ወንድ ልጅ ተገላገሉ። ቀደም ሲል ገና በአስረኛ ወሩ በአንቀልባ ታዝሎ በጅሩ በረሃ ውስጥ ሕይወቱ ባለፈው ልጃቸው ምትክ ሌላ ወንድ ልጅ አገኙ። አበበ ባለቤታቸውን ከሌሎች ሴቶችና ከጠባቂዎቻቸው ጋር ትተው ጉዟቸውን ቀጠሉ። ይሁን እንጂ የፋሺስት ጦር በባንዳዎች ጥቆማ እነወይዘሮ ቆንጂት ያሉበትን ቦታ በማወቁ ወይዘሮ ቆንጂትንና ልጃቸውን ማርኮ ወሰደ። አባገስጥም የባለቤታቸውንና ልጃቸውን መማረክ ባወቁ ጊዜ ክፉኛ አዘኑ። ወይዘሮ ቆንጂት መጀመሪያ ወደ አዲስ አበባ ከዚያም ወደ ደብረ ብርሃን ተወስደው ታሰሩ። ደብረ ብርሃን ለጥቂት ጊዜያት ያህል ከቆዩ በኋላ እንደገና ወደ አዲስ አበባ ተመልሰው ለአምስት ወራት ያህል ታሰሩ፤ በመጨረሻም ወደ ሸኖ ተልከው በእስር እንዲቆዩ ተደረገ። በዚያ ሳሉም ልጃቸውን ይዘው ለማምለጥ ሲሞክሩ ተይዘዋል።

ገና በ15 ዓመቱ ውጊያ ላይ የተሰለፈው የአበበ የበኩር ልጅ ዳንኤል ቆስሎ ተማርኮ ነበር። ታዳጊው ዳንኤል ሕክምና እንዳያገኝ ተከልክሎ በቀጥታ ወደ እስር ቤት ተወስዶ ተቆለፈበት። የአበበ ፈተና በዚህ ብቻ ሳያበቃ በውጊያ ላይ ሳሉ ቆስለው የነበሩት እናታቸው ወይዘሮ አስካለማርያም ጎበናም ተማረኩ። አበበ ግን ይህ ሁሉ መከራ ቢደርስባቸውም ጠላትን ከመፋለም ወደ ኋላ አላሉም። ፋሺስቶች የግንደበረት አገረ ገዢ አድርገው የሾሙትንና ሕዝብን ሲያሰቃይ የነበረውን ሰው ሰኔ 21 ቀን 1929 ዓ.ም ውጊያ ገጥመው ድል በማድረግ መቀጣጫ አደረጉት።

የቡልጋ አርበኞች በየአካባቢው ያለውን የአርበኞች እንቅስቃሴ በአገር ደረጃ ለማስተባበር ንጉሥ ማንገስ አስፈላጊ መሆኑን በማመን ከሌሎች የአካባቢው አርበኞች ጋር ደብዳቤ ተፃፅፈው እንግዳእሸት የተባለውንና በአብዩ ገዳም የነበረውን የልጅ ኢያሱ ሚካኤልን ልጅ

‹‹መልዐከፀሐይ›› በሚል ስም አነገሱ። አባ ገስጥም እንደራሴ ሆነው ተመርጠው የራስነት ማዕረግ ተሰጣቸው። ራስ አበበም በአርበኞች ቁጥጥር ስር ያለውን አገር ሲያስተዳድሩና ንግሥናውም በመላ ኢትዮጵያ ተቀባይነት እንዲያገኝ ጥረት በማድረግ ላይ ሳሉ ወጣቱ ንጉሥ መልዐከፀሐይ በድንገት አረፈ። መልዐከፀሐይ ቢያርፍም ራስ አበበ ግን ሕዝቡን የማስተዳደሩን ስራ ያከናውኑና ሚዛናዊ ፍርድ ይሰጡ ነበር።

የአርበኞችና የጠላት ፍልሚያ ቀጥሎ የራስ አበበና የፋሺስት ጦር ደንገዜ ተራራ አካባቢ ተፋጠጠ። የፋሺስት ጦር አዛዥ ኮሎኔል ማሌቲ አካባቢውን በመድፍና በአውሮፕላን ቢደበድበውም የራስ አበበ ጦር ከጠላት መሐል ገብቶ የፋሺስትን ጦር በታተነው። ያ የጦር ሜዳ ውሎና የጀግንነት ወኔ፣ የዓላማ ቆራጥነትና የውጊያ ስልት ከመሳሪያ ጥራትና ብዛት የበለጠ ፋይዳ እንዳላቸው የታየበት ሆነ። የፋሺስት ወታደሮች

አስክሬንም የሚያነሳው ጠፍቶ አውሬ በየሜዳው ጎተተው።

ራስ አበበ ጠላትን የሚቀጡት በውጊያ ሜዳ ብቻ ሳይሆን በመኖሪያ ቤቱም ጭምር ነበር። ቁምቢ ከምሲ የተባለ የባንዳ አለቃ በተሾመበት አካባቢ የሚኖረውን ሕዝብ ያሰቃይ ስለነበር ወደ ሰፈሩ ሄደው ድል በማድረግ ጀግንነታቸውን አስመስክረዋል። ፋሺስት ኢጣሊያ ከራስ አበበ ጋር ተደጋጋሚ ውጊያዎችን ቢያደርግም ራስ አበበን መማረክ አልቻለም። ጣሊያኖች ከራስ አበበ ጋር መታረቅ ብቸኛ አማራጭ መሆኑን በማመን የእርቅ ጥያቄ አቀረቡ። ይሁን እንጂ ለራስ አበበ ጋር የቀረቡት ተደጋጋሚ የእርቅ ጥያቄዎች ውድቅ ተደረጉ።

በ1931 ዓ.ም ‹‹የጥንታዊት ኢትዮጵያ የጀግኖች ማኅበር›› ሲቋቋም ራስ አበበ አረጋይ የማኅበሩ የክብር ፕሬዚዳንት ሆነው ተመረጡ። በ1933 ዓ.ም ማኅበሩን የሚመሩ አመራሮች በድጋሚ ሲመረጡ ራስ አበበ አረጋይ የማኅበሩ ፕሬዚዳንት ሆነው ተመርጠው ነበር። ንጉሰ ነገሥት ቀዳማዊ አፄ ኃይለሥላሴ ከእንግሊዝ ወታደሮች ጋር በመሆን በሱዳን በኩል አድርገው ወደ ኢትዮጵያ ሲገቡ ሚያዝያ 27 ቀን 1933 ዓ.ም ራስ አበበ 10ሺ ጦራቸውን ይዘው እንጦጦ አካባቢ ለንጉሰ ነገሥቱ አቀባበል አደረጉ። ወዲያውኑም ራስ አበበ አረጋይ የሜጀር ጀኔራልነት ማዕረግና የአዲስ አበባ ገዢነት ተሰጣቸው። ተማርከው ከነበሩት ቤተሰቦቻቸው ጋርም ተገናኙ። በነሐሴ 1933 ዓ.ም የሲዳሞ፣ የቦረናና የወላይታ አገረ ገዢ ሆነው ተሾሙ። የካቲት 16 ቀን 1934 ዓ.ም የጦር ሚኒስትር ሆነው ተሾሙ። በዚህ ኃላፊነታቸውም በተለያዩ አካባቢዎች እየተዘዋወሩ ሰላምና ጸጥታን አስከብረዋል። በ1941 ዓ.ም ደግሞ የአገር ግዛት ሚኒስትርነትን ተሹመው ውስብስብ የነበረውን የአገር አስተዳደር መልክ ለማስያዝ ደፋ ቀና ሲሉ በ1947 ዓ.ም በሌተናንት ጀኔራል ማዕረግ የመከላከያ ሚኒስትር ሆነው ተሾሙ።

በመጨረሻም በወንድማማቾቹ ብርጋዴር ጀኔራል መንግሥቱ ንዋይ እና ገርማሜ ነዋይ በታኅሣሥ 1953 ዓ.ም በንጉሰ ነገሥት ቀዳማዊ አፄ ኃይለሥላሴ መንግሥት ላይ የተሞከረው የመፈንቅለ መንግሥት እንቅስቃሴ ለራስ አበበ አረጋይ ሕይወት ማለፍ ምክንያት ሆነ። የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራው ጠንሳሾች ታኅሥሥ 7 ቀን 1953 ዓ.ም በግፍ ከረሸኗቸው የንጉሰ ነገሥቱ መንግሥት ሹማምንት መካከል አንዱ ራስ አበበ አረጋይ ነበሩ።

ራስ አበበ አረጋይ ለጀግንነታቸው እንዲህ ተገጥሞላ ቸዋል፡-

« ጠላት በአውሮፕላን በአየር ሲንደረደር፣የአርበኞቹ መሪ ደባለቀው ከአፈር፣አንተ አበበ አረጋይ ፈረስህን ገስጥ፣የፋሺስትን አንጎል የሚበጠብጥ።»

ፋሽስት አስጨናቂው አርበኛ - ራስ አበበ አረጋይ

Page 14: ከባንክ ውጭ ከ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር በላይ ማስቀመጥ ተከለከለሕግ • ዶ/ር ሳሙኤል ሁርካቶ፤ የሳይንስና ከፍተኛ

ባለውለታዎቻችን ረቡዕ ነሐሴ 13 ቀን 2012 ዓ.ም

ገጽ 14

አንተነህ ቸሬ

‹‹ … ሰው ከሙሉ የሰውነት ደረጃ የሚደርሠው በትምህርት ነው። ትምህርት ቀላል ነገር አይደለም። ስለትምህርት ያለን አስተያየት ትክክለኛ ከሆነ ማንኛውም የሕይወት ችግር ሊፈታ ይችላል … ስለትምህርት የሚናገር ሠው ሁሉ ሶስት ጥያቄዎችን ለመመለስ አስቀድሞ መዘጋጀት አለበት። ያለዚያ ነገሩ ፍሬቢስ እንደሚሆንበት ያስፈራዋል። እነዚህ ሶስት መሠረታውያን ጥያቄዎች የሚቀጥሉት ናቸው፤ ምን፣ ለምንና እንዴት። የመጀመሪያዎቹ ሁለቱ በመካከላቸው ግንኙነት ያላቸው ናቸው። ትምህርት ሲባል ምንድነው፣ ለምን ወይስ ምን ዓላማ ማገልገል ይገባዋል። እኒህ ሁለቱ ጥያቄዎች ሠው ምን መሆን እንደሚገባው እንመራመር ዘንድ ስለሚያሳስቡን በቀጥታ ወደ ስነምግባር ፍልስፍና ሠፈር ይመሩናል። ስለዚህ የትምህርትን ባሕሪና ዓላማ በትክክል አይቶ ለመወሠን በፍልስፍና ሲስተሞች ውስጥ ገብቶ ማሠብ ግድ ያስፈልጋል። ይህ ካልሆነ ነገሩን እንደምንበድለው አያጠራጥርም …››

ይህ ሃሳብ ‹‹የከፍተኛ ትምህርት ዘይቤ›› ከተባለው የፍልስፍና፣ የሕግና የስነ-ጽሑፍ ሊቁ የዶክተር እጓለ ገብረ ዮሐንስ መጽሐፍ ላይ የሰፈረና የትምህርትን ኃያልነትና ወሳኝነት የሚያመለክት ዘመን ተሻጋሪ ዕሳቤ ነው። የሐሳቡ ባለቤት ዶክተር እጓለ ገብረዮሐንስ ረቂቅ በሆነው በጥንታዊው የኢትዮጵያ ሐይማኖታዊ ትምህርት ጀምረው፤ ወደ ግሪክ፣ ጀርመንና እንግሊዝ ተሻግረው ዘመናዊውን ፍልስፍናና ስነ-ጽሑፍ አጥንተውና ፍልስፍናን ከሐይማኖትና ከነባር አገራዊ እውቀት ጋር በማጣመር በሁለቱ ዕሳቤዎች መካከል ድልድይ የሆኑ አስደናቂ ሃሳቦችን ቀምረው ምክንያታዊ ማኅበረሰብ እንዲፈጠር የተጉ ሊቅ ናቸው።

እጓለ የካቲት 6 ቀን 1924 ዓ.ም አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ (መስቀል አደባባይ፣ ደብረሰላም ቅዱስ እስጢፋኖስ አጥቢያ) ተወለደ። አባቱ መምሬ ገብረዮሐንስ ተሰማ በአካባቢያቸው የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ክርስትና እምነት ተከታዮች ‹‹ጻድቁ ዮሐንስ›› ተብለው የሚታወቁ ሊቅ ነበሩ። እናቱ ወይዘሮ አመለወርቅ ሀብተወልድ ይባላሉ። ከወንድሞቹ መካከል አንዱ፣ ኃይሉ ገብረዮሐንስ (ገሞራው)፣ በኢትዮጵያ ተማሪዎች ትግል ከፍተኛ ተሳትፎና አስተዋፅኦ (አበርክቶ) የነበረው የዘመኑ አብዮተኛ ነበር።

እጓለ እድሜው ለትምህርት ሲደርስ በደብረሰላም ቅዱስ እስጢፋኖስ ገዳም ፊደል መቁጠር ጀመረ። በዚህ ስፍራ ከፊደል ቆጠራ እስከ ዳዊት መድገም ድረስ ከተማረ በኋላ በመንበረ መንግሥት ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ወንበር ዘርግተው ያስተምሩ ወደነበሩት ሊቀ-ጠበብት ኃይለ ጊዮርጊስ ዘንድ ሄዶ የዜማ ትምህርትን፣ እስከ ጾመ ድጓ ድረስ ተምሯል። በወቅቱ ከየደብሩ የተመረጡ ሁለት ሁለት ተማሪዎች ወደ ቅድስት ሥላሴ ትምህርት ቤት እንዲገቡ ይደረግ ነበር፤ በትምህርት አቀባበሉ አስደናቂ የነበረው እጓለ ከተመራጮቹ መካከል አንዱ ሆኖ ወደ ትምህርት ቤቱ ገባ። በዚያም እስከ ስምንተኛ ክፍል ድረስ ከተማረ በኋላ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ወደ ግሪክ ሄዶ አጠናቀቀ።

ሶቅራጥስን፣ ፕላቶንና አርስቶትልን ያፈራችው የፍልስፍናዋ ምድር ግሪክ፣ ኢትዮጵያዊው ወጣት እጓለ ወደ ፍልስፍና የትምህርት መስክ እንዲያተኩር ቀልቡን ገዛችው። ዝንባሌው ግልፅ እየሆነ ሄዶ የፍልስፍናን መጽሐፍት በብዛት እየገዛ ማንበቡን ቀጠለ። ለፍልስፍና የነበረው የጋለ ፍቅር እስከሕይወቱ ፍፃሜ ድረስም አልከሰመም ነበር።

እጓለ በቆሮንጦስ ትምህርት ቤት የነበረውን የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ሲጨርስ ንግግር እንዲያደርግ የተወሰነው እርሱ ነበር:: ቅደም ተከተሉ የሠመረና ጥልቅ የፍልስፍና ሐሳብን ያዘለ ንግግር አደረገ። በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የአቴንስ ዩኒቨርሲቲ መምህራንም በወጣቱ እጓለ ንግግርና እሳቤ እጅግ ተደንቀው ስለነበር አመሰገኑት።

አቴንስ ዩኒቨርሲቲ ገባ። በዚያም መንፈሳዊ ትምህርትን ከፍልስፍና ጋር አዛምዶ አእምሮውን ያንጽ ጀመር። ለትምህርት የነበረው ፍቅር በአርአያነት የሚጠቀስ ነበር። በዩኒቨርሲቲው ከ1946 እስከ 1949 ዓ.ም የኦርቶዶክስ ነገረ መለኮትን እንዲሁም በአውሮፓም ሆነ በሌላው ዓለም እጅግ ተደናቂ የሆነውን የግሪክ ስነ-ጽሑፍንና ፍልስፍናን አጥንቶ በማዕረግ ተመረቀ።

ፍልስፍናን በጥልቀት የማጥናት ፍላጎቱ ከፍተኛ ስለነበር ከግሪክ ወደ ጀርመን ተሻገረ። የስመ ጥሮቹ ፈላስፎች የኢማኑኤል ካንትና የሄግል አገር ጀርመንም የእጓለን የፍልስፍና ጥም ለማርካት በቦን ዩኒቨርሲቲ በኩል በሯን ከፈተችለት። እጓለም በፍልስፍና ትምህርት ክፍል ተመዝግቦ ሲጓጓለት የነበረውን የፍልስፍና ባህር ይዋኝበት ጀመር።

በወቅቱ በቦን ዩኒቨርሲቲ የሚያስተምሩት መምህራን በዓለም አቀፍ ደረጃ የታወቁ ሊቃውንት ነበሩ። በእነዚህ መምህራን የመማር እድል ያገኘው እጓለ፤ ትምህርታቸውን

የስነ ምግባር መሰረቶች እንደሆኑ በደንብ አድርገው ጽፈዋል። የኅሊናን ገዢነት በእሳቤዎቻቸው በጥልቀት ተመልክተዋቸዋል። ትምህርታቸውን ከራሳቸው ስብዕና ጋር በሚገባ አዋህደው ጠቃሚው የትኛው እንደሆነ አንጥረው አውጥተዋል … ›› ይላሉ።

‹‹የከፍተኛ ትምህርት ዘይቤ›› (1956 ዓ.ም) እና ‹‹ብፁዓን ንጹሐነ ልብ - ስለ ክርስቲያን ሥነ-ምግባር መሠረት›› (1983 ዓ.ም) የተሰኙት ሁለቱም የዶክተር እጓለ መጻሕፍት በዓላማ የተለያዩ ቢመስሉም በይዘታቸው ግን ተመሳሳይነት አላቸው። ይኸውም ሥነ-ምግባራዊ በጎነት ላይ ያተኮሩ መሆናቸው ነው። ‹‹የዶክተር እጓለ እሳቤዎች›› በሚል ርዕስ ስለሊቁ ስራዎች ትንታኔ ያቀረቡት እያሱ ባሬንቶ ‹‹ … የዶክተር እጓለ መጻሕፍት በይዘታቸው ተመሳሳይነት አላቸው። አንደኛው ሥነ ምግባራዊ በጎነትን ከትምህርት እና ከስልጣኔ ፍልስፍና ጋር አዋህዶ ሲያቀርብ ሌላኛው ደግሞ ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባርን ከካንት ፍልስፍና ጋር አዋህዶ ያቀርብልናል።

የሁለቱም መዳረሻ፣ እንዲሁም ማዕከላዊ ትኩረት ግን አንድ ነው። ማዕከላዊው ባለ ጉዳይ ሰውነት ነው፤ ‹‹ሰውን ወደ ሰውነት ክብሩ ከፍ ማድረግ›› ሲሆን፣ መዳረሻቸው ደግሞ የሰለጠነ እና ምክንያታዊ ማኅበረሰብ ግንባታ ላይ ያተኩራል። የሊቁም ምኞት በጥበብና በሥነ ምግባር እንዲሁም በማኅበራዊ እሴቱ ያልተረበሸ፣ የተስተካከለ እና በምክንያታዊነት የሚያምን ማኅበረሰባዊ ውቅር መገንባት ነው። ይህንንም በሚወዳት አገሩ በኢትዮጵያ እውን ሆኖ ማየት ነው። ምናልባትም በበርካታ የአውሮፓ ስፍራዎች ተዟዙሮ ያየውን ማህበራዊ ምክንያታዊነት በፖለቲካዊ፣ ማህበረ ኢኮኖሚያዊ፣ ባህላዊ እና ሃይማኖታዊ እሴቶች እንዲሁም አስተሳሰባዊ ዝብርቅርቅ ውስጥ ለሚገኘው ኢትዮጵያዊ ህብረተሰብ የሚመራበትን የዘመናዊ አስተሳሰብ መንገድ ለመጠቆም በማሰብ ያዘጋጃቸው ይመስላሉ። እርሱ በነበረበት ዘመን የነበረው ስጋት እና ተምኔት የእኛንም ዘመን የሚመለከት ነው … ›› ብለዋል።

በ17 ንዑሳን ርዕሶች ተከፋፍሎ የቀረበውና ‹‹የከፍተኛ ትምህርት ዘይቤ›› የተሰኘው መጽሐፋቸው ‹‹ትምህርት›› እና ‹‹ስልጣኔ›› የሚሉ ቃላትን በተደጋጋሚ ያነሳል። ሁሉም ንግግሮች በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ከትምህርት ፍልስፍና ጋር ግንኙነት ያላቸው እንደሆኑ ተጠቅሷል። ዶክተር እጓለ በንግግሮቻቸው ትኩረት የሰጡት ስለትምህርት አስፈላጊነትና ስለስልጣኔ አመራር ነው። የኢትዮጵያ ስልጣኔና ትምህርት ከምን ዓይነት ነባራዊ እውነታዎች ጋር እንደተጋጠመና እንዴትስ መሻገር እንደሚችል በዝርዝር አብራርተዋል። የፍልስፍና ትምህርትን ከሐይማኖትና ከነባሩ አገራዊ እውቀት ጋር በማጣመር ምክንያታዊ የሆነ ጠንካራ ትውልድ ስለመገንባት በተደጋጋሚ አስረድተዋል።

በ1983 ዓ.ም የታተመውና ‹‹ብፁዓን ንጹሐነ ልብ - ስለ ክርስቲያን ሥነ-ምግባር መሠረት›› የተሰኘው መጽሐፋቸውም የፍልስፍና፣ የሃይማኖት (የሥነ-መለኮት)፣ የታሪክ፣ የትምህርት፣ የቋንቋና የማህበራዊ ሳይንስ ይዘት ያለው ስራ ነው።

ሰለሞን ተሰማ ጂ. መጽሐፉን በገመገሙበት ሂሳዊ ጽሑፋቸው …

ይህም መጽሐፍ እንደ ቀዳሚው(ታላቅ ወንድሙ) ‹‹የከፍተኛ ትምህርት ዘይቤ››፣ በአዳዲስ ሃተታ የታጨቀ መጽሐፍ ነው … የደራሲው ዋናው የትምህርት ጥናታቸው ፍልስፍናና ሥነ-መለኮት በመሆኑ፣ የመጽሐፋቸው ይዘት ምንም ያህል አያስደንቅም። ፍልስፍናን (ሕሊናን)ና ሃይማኖትን ለማስታረቅም ያደረጉት ጥረት የሚደነቅ ነው። ‹‹ሃይማኖት ጸረ-ሕሊና ወይም ህየንተ ሕሊና ሆኖ የሚቆይ ነገር አይደለም። መልዕልተ ሕሊና ነው እንጂ። ግንኙነታቸው የላይና የታች ነው። የሕሊና ላዕላይ ደረጃ ሃይማኖት ይባላል›› (ገጽ 50)።

መጽሐፋቸው በኢትዮጵያ የሥነ-ጽሑፍ ታሪክ ውስጥ ጉልህ ስፈራንና የተለየ ቦታን የያዘ ለመሆኑ ጥርጥር የለኝም። እኔ እስከማውቀው ድረስ፣ በይዘቱ እስካሁንም ድረስ ተወዳዳሪ የለውም። ቃላት የሚፈለጉበትን ዘይቤና ሃሳብ በዕምቅ ጥልቀት እንዲገልጡ ሆነው ተደክሞባቸዋል።

በአስተሳሰባቸውና በአቀራረባቸውም የገለልተኛነት ስፍራን ለመውሰድ ጥረዋል። የአንድ ፍልስፍና ትምህርት ቤት

በጥንቃቄ ከመከታተል በተጨማሪ በግልም እያነጋገረ ስለ ፍልስፍና ትምህርት አጠናንና አቀራረብ መመሪያ ይቀበል ነበር። ይህም አልበቃ ብሎት ወደ ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች በመሄድ በተቋማቱ ውስጥ የሚያስተምሩ መምህራንን ትምህርት ተከታትሏል። ከእነዚህ መካከልም የፍራይቡርግ ዩኒቨርሲቲው ማርቲን ሃይድገር እና የሐይደልበርግ ዩኒቨርሲቲው ካርል ጃስፐርስ ተጠቃሽ ናቸው።

ስለዶክተር እጓለ የሕይወት ታሪክ የሚያወሳ ጽሑፍ የጻፉት ዶክተር ሥርግው ሐብለሥላሴ ስለጉዳዩ ሲያብራሩ ‹‹ … በሌላ ዩኒቨርስቲ አንቱ የተባሉና በዓለም መድረክ ያንጸባረቁ ለምሳሌ ፍራይቡርግ ዩኒቨርስቲ ማርቲን ሃይድገር፤ ሀይደልበርግ ዩኒቨርስቲ ደግሞ ካርል ጃስፐርስ ያስተምሩ ስለነበር እዚያ ያሉበት ድረስ እየሄደ ትምህርታቸውን አዳምጧል። ሁለቱም እንደሚታወቀው (Existentialist Philosophers) ናቸው:: የማርቲን ሃይድገር የታወቀው ሥራ ‹‹ጊዜና መሆን (Time and Be-ing)›› የሚለው ምን ያህሉንም እጓለን ያረካ አልመሰለኝም። የጃስፐርስን ‹‹ከእውነት (Von der Wahrheit)›› የሚለውን ግን ከአንደበቱ አይለየውም ነበር። ሁሉንም ባይሆንም እንኳ አብዛኛዎቹን የዚህን ፈላስፋ ድርሰቶች ገዝቶ ከግል ቤተ መጻሕፍቱ አከማችቷል። ምናልባት መንፈሱ ወደዚህ ፈላስፋ ያጋደለው ሚዛናዊና ኃላፊነት የተሞላ አስተሳሰብ ስላለው ሳይሆን አልቀረም›› በማለት ጽፈዋል።

በቦን ዩኒቨርሲቲ የነበረውን የአራት ዓመታት ቆይታ አጠናቆ በዶክትሬት ዲግሪ ተመረቀ። በከፍተኛ የትምህርት ተቋም የማስተማር ፍላጎት ስለነበረው ለዚሁ ተግባር ስኬት ይረዳው ዘንድ እንዲሁም የእንግሊዝኛ ቋንቋና ስነ-ጽሑፍ ችሎታውን ለማበልፀግ ወደ እንግሊዝ ሄደ። እውቀት ለማግኘት የማይታክተው የስነ-ጽሑፍ፣ የነገረ መለኮትና የፍልስፍናው ሊቅ ዶክተር እጓለ በርሚንግሃም ዩኒቨርሲቲ ገብቶ የእንግሊዝኛ ቋንቋና ስነ-ጽሑፍ አጠና።

እውቀት የመሸመት ጽኑ ፍላጎታቸው ከግሪክ ወደ ጀርመን፤ ከጀርመን ወደ እንግሊዝ ያዘዋወራቸው ዶክተር እጓለ በ1953 ዓ.ም ወደ ኢትዮጵያ ተመለሱ። በቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ የፍልስፍና አስተማሪ ሆነው የማስተማር ስራቸውን ጀመሩ። በወቅቱም ፍልስፍና ለበስ ንግግሮችን በተከታታይ በሬዲዮ ለሕዝብ ያሰሙ ነበር። የእነዚህ ንግግሮቻቸው ስብስብ በ1956 ዓ.ም ‹‹የከፍተኛ ትምህርት ዘይቤ›› በሚል ርዕስ በመጽሐፍ መልክ በአዲስ አበባ ታትመዋል። ንግግሮቻቸውንና እሳቤዎቻቸውን አሰባስቦ የያዘው ይህ መጽሐፍም እስከዛሬ ድረስ እጅግ ተወዳጅ ሆኖ ዘልቋል። የነገረ መለኮትና የፍልስፍና መምህራን እንደሚናገሩት የዶክተር እጓለ ሃሳቦች በኢትዮጵያ አስተሳሰብና በምዕራብ አስተሳሰብ መካከል ድልድይ ሠርተዋል።

የነገረ መለኮት አስተማሪው መምህር ዳንኤል ሰይፈሚካኤል ‹‹ … ዶክተር እጓለ ጥንታዊውንም ዘመናዊውንም ትምህርት የመማር እድል አግኝተዋል። ወደአገራቸው መጥተው ከነባሩ እውቀት፣ ስልጣኔ፣ ማኅበራዊ ሕይወት ጋር ለማዋሃድ ያደረጉት ጥረት አስገራሚ ነው። የራስን የሆነን ነገር ላለመተውም ትኩረት ይሰጡ ነበር። እውቀት ብቻውን ለውጥ እንደማያመጣና አዋቂዎችን ጥሩ ስብዕና እንዲኖራቸው የሚያደርጋቸው

ጥገኛ ለመሆን አልፈለጉም … በግዕዝ ሥነ-ጽሑፋችን ውስጥ እዚያና እዚህ የተሰራጩትን ድንቅ ሃሳቦች አደራጅተውና አስፋፍተው በመፃፍ አንድ ጉልህ ፈር ቀደዋል። የሥነ ምግባርና የክርስቲያናዊ አርዓያነትን የአስተሳሰብ ጅረቶች እንዴት ለማገናኘት እንደሚቻል አውጠንጥነው ሲያበቁ፣ የኢትዮጵያውያንን የባህል፣ ሃይማኖታዊና ማኅበራዊ ሁለንተና ‹‹የሚያሻሽል ምግባረ ሠናይነት›› እንዴት ሊገኝ ይችላል ሲሉ በጥልቅ መርምረዋል። የሚቻልበትንም መላና ዘዴ ገልጠዋል። ተፈላጊውም ሥነ ምግባር፣ ለሃገሪቱና ለህዝቧ በእጅጉ አስፈላጊና ዘላቂም ሊሆን እንደሚገባው አትተዋል … በአጠቃላይ መጽሐፉ የረቀቀን ሀሳብና ፈላሰፋዊ በሆነ መልኩ መግለጥ መቻሉን እንገነዘባለን … ›› ብለዋል።

ዶክተር ስርግው እንደፃፉት፤ ዶክተር እጓለ ቀደም ካሉት ፈላስፋዎች መካከል የሚያደንቋቸው አፍላጦንን (ፕሌቶንና) ኢማኑኤል ካንትን ነበር። የዶክተር እጓለ አስተሳሰብ የተመሠረተው በሶቅራጥስ የጥያቄና ምላሽ ዘዴ ላይ ነበር። ዘዴውም ስለእውነት ሲባል የአንድን ሐሳብ ደካማና ጠንካራ ጐን እየገመገሙ እስከ መጨረሻው ሂደት ማድረስ ነበር። በሚከራከሩበት ወቅት በምንም ዓይነት መልኩ አይቆጡም። የሚቆጣ ሰው እንኳን ቢያጋጥማቸው አለሳልሰው ወደ ጤናማ ክርክር ይመልሱታል።

‹‹ … ከባለቅኔዎች መካከል ደግሞ አሊጌሪ ዳንቴን፣ ፍሬድሪክ ዊልሔምን፣ ጆሴፍ ቮን ሽለርንና ዮሐንቮልፍጋንግ ቮንጌቴን ይወዳል። እንደ ባለቅኔዎቹ ቅደም ተከተል በዚያኑ መጠን ፍቅሩ እያየለ ይሄዳል። ጌቴ ላይ ሲደርስ ፍቅሩ ይጠናል። ከፊተኞቹ ሁለቱ ላይ ቀንጨብ እያደረገ በስንኝ ወደ አማርኛ ተርጉሟል። ከዳንቴ ስራዎች አንዱን ‹‹መካነ ንስሐ›› ብሎ ከመግቢያው ተርጉሞ በመጀመሪያው መጽሐፉ ውስጥ ጨምሮ አሳትሞታል። እንዲሁም ከሽለር ደግሞ ‹‹ዋስትና›› የሚለውን ተርጉሟል። ይበልጥ ያተኮረው ግን ጌቴ ላይ ነበር። ‹‹ፋውስት››ን በሙሉ በስንኝ ለመተርጐም አቅዶ ጀምሮ አካሂዶታል። ነገር ግን ዳር ሳያደርሰው በሞት ተቀደመ። እንደዚሁ በጅምር የቀሩ ‹‹ከተረት ወደ ኅሊና›› የሚል የፍልስፍና ድርሰትና ‹‹መዝሙረ ኢትዮጵያዊ›› የሚል የግጥም ሰብስብ ይገኝበታል። ቀደም ሲል የካንትን ሥነ ምግባር ለማስተማሪያ እንዲያገለግል ገና ከትምህርት ቤት እንዳለ ተርጉሞታል። እጓለ የግጥም ተሰጥዖም ነበረው። የግጥሙ ስልት የሚከተለው ከፍ ብለው በተጠሩት ባለቅኔዎች ፈር ነበር። ሌላው ተዘጋጅቶ አልቆለት ሳይታተም የቀረ በአንቀጸ ብጹዓን ላይ የተመሰረተ የአባቱን ምግባረ ሠናይ የሚገልጽ በመንፈሳዊና በፍልስፍና ሐሳብ የተጠናከረ ሰፋ ያለ ጽሑፍ ነው። የዚህን መጽሐፍ ታትሞ መውጣት ለማየት በጣም ይጓጓ ነበር።››

ዶክተር እጓለ ከ1953 እስከ 1956 ዓ.ም በቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ውስጥ ከነበራቸው የማስተማር ኃላፊነት ባሻገር በማስታወቂያ ሚኒስቴር የፕሮግራም አማካሪ ሆነውም አገልግለዋል። በአስተማሪነቱ ለረጅም ጊዜያት በኢትዮጵያ ሬዲዮ የታወቀውንና ‹‹መምህር አብራራው›› በመባል የሚታወቀውን ፕሮግራም ስያሜውን የሰጡትና ፕሮግራሙንም የጀመሩት ዶክተር እጓለ ናቸው።

በ1956 ዓ.ም ወደ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተዛወሩ። በቦን፣ ጀርመን የኢትዮጵያ ኤምባሲ አንደኛ ጸሐፊ ሆነው ተመድበው ለስድስት ዓመታት ያህል አገለገሉ። ከስራቸው ጎን ለጎን የሕግ ትምህርት አጠኑ። በ1962 ዓ.ም አጋማሽ ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰው በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በምስራቅ አውሮፓ ክፍል የፖለቲካና የባሕል ጉዳይ አማካሪ ሆነው ሲሰሩ ቆዩ። በኋላም እስከ 1965 ዓ.ም የክፍሉ ኃላፊ ሆነው ሰርተዋል።

ዶክተር እጓለ በሚያዝያ 1964 ዓ.ም ከወይዘሪት እታፈራሁ ተስፋዬ ጋር በተክሊል ስርዓት ጋብቻ ፈፅመው ሦስት ልጆችን አፍርተዋል።

ከኅዳር እስከ ሰኔ ወር 1970 ዓ.ም በድጋሜ ወደ ጀርመን ተልከው በበርሊን የኢትዮጵያ ኤምባሲ አማካሪ ሆነው አገልግለዋል። ከዚያም ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰው ጡረታ እስከወጡበት ጥር 1972 ዓ.ም ድረስ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በምስራቅ አውሮፓ ክፍል የፖለቲካ ጉዳይ ዋና ኃላፊ ሆነው ሰርተዋል። ጡረታ ከወጡ በኋላ በኢትዮጵያ የመጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር አማካኝነት የግዕዙን ሐዲስ ኪዳን ለማሻሻል በተቋቋመው ቡድን ውስጥ የጎላ አስተዋፅኦ አበርክተዋል።

በምክንያታዊ አስተሳሰብ የተገነባ ማኅበረሰብ ባለቤት የሆነች ኢትዮጵያን ለማየት ሲሉ አህጉራትን አቆራርጠው ተምረው በትምህርት፣ በፍልስፍና፣ በሕግ፣ በዲፕሎማሲና በስነ-ጽሑፍ መስኮች ለአገራቸው የደከሙት ሊቁ ዶክተር እጓለ ገብረዮሐንስ፤ የጤና እክል አጋጥሟቸው መጋቢት 23 ቀን 1983 ዓ.ም አርፈው ስርዓተ ቀብራቸው መጋቢት 26 ቀን 1983 ዓ.ም በአዲስ አበባ ቀራንዮ መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ተፈፅሟል።

ለትምህርትና ለምክንያታዊነት የተጉት የፍልስፍና ሊቅ

Page 15: ከባንክ ውጭ ከ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር በላይ ማስቀመጥ ተከለከለሕግ • ዶ/ር ሳሙኤል ሁርካቶ፤ የሳይንስና ከፍተኛ

ረቡዕ ነሐሴ 13 ቀን 2012 ዓ.ም

ገጽ 31 ከታዘብነው

ከሰኔ 23ቱ የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ጋር ተያይዞ ለማድረግ ይቅርና ለማሰብ የሚዘገንኑ፣ ሰው ሆኖ መፈጠርን የሚያስጠሉ እጅግ የሚከብዱ የጭካኔ ድርጊቶች በሰው ልጆች ላይ መፈጸማቸውን የሚያሳዩ መረጃዎችና ማስረጃዎች እየወጡ ነው። በሊቢያ የሜዲትራኒያን ባህር ዳርቻ አይ.ኤስ.አይ.ኤስ በተባለ ወንጀለኛ ቡድን በኢትዮጵያውያን ወንድሞቻችን ላይ የተፈጸመው እጅግ የሚዘገንነው አረመኔያዊ ድርጊት እዚሁ በራሳችን ወገኖች ላይ ተፈጽሟል። ለመውለድ ቀናት የቀሯት ዘጠኝ ወር የደፈነች ነፍሰ ጡር እናት………………..ኧረ ምኑን ላውራው……….መንቀሳቀስ ያቃታቸው በሰው የሚወጡ የሚገቡ የሰማንያ ዓመት አሮጊት እናት………………ብቻ ብዙ አሰቃቂ ለሰሚው የሚከብድ ጉድ ተፈጽሟል። ለመሆኑ ይህ እንዴት ሊሆን ቻለ? እንዲህ ዓይነቱ ከሰው ልጅ አዕምሮ በላይ የሆነ እንግዳ ጭካኔስ ከየት መጣ? እንዲህ ዓይነቱ ድርጊት ስለ ሰው ልጆች ምን ይናገራል?

የሰው ልጆች ጭካኔ ከየት መጣ?በእኔ ዕምነት ምናልባትም ሰው እንዲህ ዓይነቱን

ክፉ የጭካኔ ባህሪይውን ያመጣው “አቡሃ ለሃሰት” ከተባለው የክፋትና የሃሰት አባት ከሆነው ሰይጣን ሊሆን ይችላል። የጥንቱ ሳጥናኤል የአሁኑ ሰይጣን የእግዚአብሔር መላእክነትን ከአለቅነት ጋር አጣምሮ ለመልካም ዓላማ ተፈጥሮ ሳለ በሃሰት ታብዮ ከራሱ ልብ ክፋትን አብቅሎ፤ በራሱ ምርጫ የክፋትና የጥፋት ሁሉ ምንጭ ሆኗልና ሰውም ከራሱ ልብ አለያም ከሰይጣን ሊሆን ይችላል ክፋትን የወረሰው! “ሰይጣን እንዲህ ክፉ የሆነው እግዚአብሔር ስለረገመው ነው” ሊባል ይችላል። ሆኖም ይህም የተሳሳተ አስተሳሰብ ነው። ምክንያቱም ሰይጣን የተረገመው በራሱ ፍላጎት በፈጠረው ክፋት እንጂ እግዚአብሔርማ ማንንም ሊረግም አይፈጥርም፤ እግዚአብሔርማ መልካም አድርጎ፣ መልዓክ አድርጎ፣ አለቃ አድርጎ ፈጥሮት!

ሰይጣን ከእግዚአብሔር ቀጥሎ ያለው ትልቅ ስልጣን ለእርሱ ተሰጥቶት ሳለ “የለም ይሄ አይበቃኝም እኔ ራሴ እግዚአብሔር መሆን አለብኝ” የሚለው የአልጠግብ ባይነት ፍላጎቱ፣ ትዕቢቱ ፣ፍጡር መሆኑን ረስቶ ፈጣሪ ነኝ ማለቱ ሳያንሰው ከአንዴም ሁለት ሦስቴ በደሉንና ጥፋቱን ይቅር ሲባል ከክፋቱ አለመመለሱና ይቅርታንና ምህረትን ንቆ በክፉ ሥራው መቀጠሉ አዋርዶታል። ራሱ የፈጠረው መጥፎ ሃሳብ ርግማን ሆኖታል። ሰውም ጨካኝና ክፉ የሚሆነው ክፋትና ጭካኔ ከእግዚአብሔር ያገኘው ተፈጥሯዊ ባህርይው ሆኖ ሳይሆን ልክ እንደ ሳጥናኤል ክፋትንና ሃሰትን ከገዛ ከልቡ በሚያመነጭበት ወቅት ነው። እንጂ በተፈጥሮውማ ሰው በፍጹም ክፉ ሊሆን አይችልም! ምክንያቱም ሰው ከሳጥናኤልም በላይ ለሆነ ታላቅ መልካም ዓላማ “የእግዚአብሔር መልአክ” ሳይሆን “የእግዚአብሔር አምሳል” ሆኖ ነውና የተፈጠረው! እናም ለዚህ ታላቅ ዓላማ ተፈጥሮ ከራስ በሚመነጭ ክፉ ሃሳብ እንደ ሰይጣን በትዕቢትና በአልጠግብ ባይነት በጥፋት ላይ ጥፋት በበደል ላይ በደል መጨመር ከሰይጣንም በላይ ለክፉ ውድቀትና ውርደት ይዳርጋል!

የቅርብ መንስኤውበሰው ልጆች ላይ ለሚፈጠረው ጭካኔ መሰረታዊ

መንስኤውን ከላይ ለማሳየት እንደሞከርኩት ራስን ብቻ ወዳድነት፣ ስግብግብነት፣ አልጠግብ ባይነትና ትዕቢትን የመሳሰሉ ሰይጣናዊ ባህሪያት ሊሆኑ ይችላሉ። ይህ እንዳለ ሆኖ ግን ከአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ጋር ተያይዞ አሁን ላይ በአገሪቱ እየተፈጸሙ ለሚገኙ፤ ቅድስት ሃገር በምትባለው በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በዓለም ዓለም ታይተውና ተሰምተው ለማይታወቁ እጅጉን የሚዘገንኑ የጭካኔ ድርጊቶች የቅርብ መንስኤው ጥላቻ ነው። ይኸውም ኅወሓት/ኢህአዴግ ወደ ጫካ ከገባበትና ስልጣን ላይ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ባለፉት 17+27 ዓመታት በሃገሪቱ ሲነዛ የቆየው እጅግ አደገኛ የሃሰት የጥላቻ ትርክት ፍሬ ማፍራቱ ነው።

ለብዙ ሺህ ዘመናት አብሮ በኖረ ወንድማማች ህዝብ መካከል በክፋት ፈላስፎች የተፈበረከ ሃሰተኛ የጥፋት ታሪክን የሚያስተምሩ፣ ጥላቻን የሚሰብኩ፣ ወንድም ወንድሙን እንዲያፈናቅልና እንዲገድል አመራር የሚሰጡ ከአውሬም ከሰይጣንም የሚብስ የክፋት፣ የጭካኔና የጥፋት ስብዕና የተላበሱ ታህተ-ሰብዕ ሰዎች ብዙሃን መገናኛን ተጠቅመው በሕዝብ ላይ ያሰረጹት መርዝ ነው ለዚህ ዘግናኝ የጭካኔ ድርጊት የቅርብ ገፊ መንስኤው!

ጭካኔ - ታላቁ የሰው ልጆች ውርደትይበል ካሳ

ያስፋፉት በመብዛታቸው ወቅትና ሁኔታውን የሚዋጅ የአመራር ዘይቤ ሊኖረን ይገባል። የሚገርመው ነገር ጥላቻ አስተማሪዎቹ ከክፋታቸውና ከርኩሰታቸው መብዛት የተነሳ ትምህርታቸው በሕዝብ ልብ ውስጥ ሰርጾ እንዲገባ በርካታ ሚሊዮኖችን አውጥተው ጥላቻን የሚሰብክ ሃውልትም ቀርጸው አቁመዋል። ከእነርሱ አልፈው ይህንኑ የክፋትና የጥፋት አስተሳሰባቸውን ምንም በማያውቀው(የማያውቀው ክፋትን ብቻ ነው) በየዋሁ ህዝብ ውስጥ ለማስረጽና “አንድ የፖለቲካል ኢኮኖሚ ማህበረሰብ” ለመገንባት ህገ መንግስት አርቅቀው፣ ፖሊሲ ቀርጸው ሌት ተቀን ያለ እረፍት ሰርተዋል፤ አሁንም እየሰሩ ይገኛሉ።

ይህንን ገዳይ ህልማቸውን ለማሳካትም ማንኛውንም ዓይነት ወንጀልና ርኩሰት በሰው ላይ የሚፈጽሙ፤ ይኸው አስተሳሰባቸውም “በመቃብራቸው ላይ ካልሆነ

በቀር” እንዲቀየርባቸው የማይፈልጉ፤ በክፉ ሥራቸው የሚፎክሩ፣ ራሳቸውን ብቻ ፍጹም ትክክለኛ አድርገው የሚቆጥሩ፣ ርዝራዥ ትህትና ያልፈጠረባቸው፣ ሰውን በጣም የሚንቁ፣ ትዕቢተኞችና ባለጌዎች አሁን ላይ ክፉ ዘራቸው ባየነው መንገድ ጭካኔ ሆኖ በቅሏል። መነሻው ምንም ይሁን ምን አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ እየታየ እንዳለው ዓይነት ዘግናኝ የጭካኔ ድርጊት ሊፈጸም ይገባዋልን? ስለ ሰው ልጆች እና ስለ ሰውነትስ ምን የሚናገረው ነገር አለ? በመጀመሪያ ሰው ከአውሬም እንዳነሰ ያሳያል

ሰው ከሰውነት ባህሪ የወጣ የጭካኔ ድርጊቶችን ሲፈጸም “ምን ዓይነት አውሬ ነው” እያሉ ከእንስሳት ወይም ከአውሬ ጋር ማወዳደር የተለመደ ነው። ይሁን እንጂ ይህ ፍጹም ስህተት ነው፤ ምክንያቱም አውሬው እኮ “የጭካኔ” ድርጊቱን የሚፈፅመው ተፈጥሯዊ ባህሪው ስለሆነ ነው። አዳኝ ታዳኝን አሳድዶ ሲገድል ጠልቶት አይደለም፤ እንዲህ አድርጎ እንዲኖር ስለተፈጠረ ነው። ይህም ስህተት አይደለም፣ በቃ የሆነውን ነው የሆነው። ሰው ግን በፍፁም እንዲህ ዓይነት ጨካኝ ድርጊቶችን እንዲፈፅም የሚያደርግ አረመኔያዊ ባህሪይን ይዞ አልተፈጠረም! ሰው እንዲህ ዓይነት ክፉ ባህርያትን ያበቀለው ከራሱ ነው። ስለሆነም በተፈጥሮው መልካም ሆኖ የተፈጠረው ሰው በራሱ ክፋት የሚያመነጨውን ክፋትና ጭካኔ በተፈጥሮ ከመጣው የአውሬ ጭካኔ ጋር ማነጻጸር ፍጹም ስህተት ነው።

ሰው በፈጣሪው አምሳል ተፈጠረ ከሚለው ሃሳብ በተቃራኒ “ሰው ከጦጣ መሰል ፍጡር ነው የተገኘው” ብለው በዝግመተ ለውጥ የሚያምኑ አንዳንድ ዘገምተኞች ሰው የመገዳደል ባህሪን የወረሰው ከዝንጀሮ መሰል አራዊቶች መሆኑን ቢናገሩም የሥነ አዕምሮ ሊቁ ኤሪክ ፍሮም እንዳሉት ደስታ ለማግኘት መሰሉን ሆን ብሎ በክፉ እሳቤ የሚገድል ፍጡር ግን ሰው ብቻ ነው። የስግብግብነትና የአልጠግብ ባይነት ተምሳሌት ተደርጎ የሚወሰደው ጅብ እንኳን ከመሰሎቹ በልጦ ለመገኘት ሲል እርስ በእርሱ አይጠፋፋም፤ ፉክክሩ ከሌሎች ሥጋ በል እንስሳት ጋር እንጂ ከጅቦች ጋር አይደለም፤ ተሰባስቦ በሕብረት ያጠቃል እንጂ ተከፋፍሎና ተቧድኖ እርስ በእርስ አይጠቃቃም።

ሁሉንም ፍጥረታት ይገለገልባቸውና ይገዛቸው ዘንድ ከፈጣሪው ስልጣን ተሰጥቶት ሳለ ሁሉን መግዛት አልበቃ ብሎት አንዱ አንዱን ለማሸነፍና ወንድም ወንድሙን በበላይነት ለመግዛት ሌላውን የውጭ ጠላቱን ትቶ እርስ በእርሱ በጠላትነት እየተያየ እርስ በእርስ የሚጨካከነው የሰው ልጅ ከአውሬም እንዲያንስ ያደርገዋል።

እናም ክፉና አረመኔ ሰው “አውሬ” ተብሎ ሊሰደብ አይገባም፤ ከተፈጥሮው የሌለውን ክፋትና አረመኔነት ፈልጎ ያመጣው ሰው “አውሬ” ተብሎ ሲጠራ ሙገሳ ይሆንበታልና!

ሰው ከሰይጣንም በላይ ያረክሳል በእግዚአብሔር አምሳል ከተፈጠረው ሰው

የሚወጣው ክፋት በዚህም ምክንያት የሚፈጸመው ኢ-ሰብዓዊ ጭካኔ፣ ጥፋትና በደል ከሰይጣን ክፋትም ይገዝፋል! ለምን ቢሉ ቢያንስ ሰይጣን ክፉ የሆነውና በደል የፈጸመው “ለምን በአምሳልህ አልፈጠርከኝም” በሚል በእግዚአብሔር አኩርፎና ተቀይሞ ሊሆን ይችላል! ሰው ግን በምን ያመካኛል፤ ከእርሱ በቀር በእግዚአብሔር አምሳል የተፈጠረ(ቅዱሳን ትጉሃን መላዕክትም ቢሆኑ) ሌላ ፍጡር የለምና! በታላቁ በእግዚአብሔር አምሳል ከመፈጠር የበለጠ ትልቅ ነገርስ ምን ሊኖር ይችላል። እናም በገዛ ፈቃዱ ክፉና አረመኔ የሆነን ሰው “ሰይጣን” ብሎ መስደብም ትክክል አይደለም። ምክንያቱም በመልካሙ እና በርህሩሁ እግዚአብሄር አምሳል ተፈጥሮ በተፈጥሮው የሌለበትን ከክፋት ሁሉ የሚበልጥ ክፋት፣ ከበደል ሁሉ የሚከፋ የጭካኔ በደልን በራሱ ፍጥረት ላይ የሚፈጽም፤ ወንድሙን አሰቃይቶ በጭካኔ የሚገድል ክፉና አረመኔ ሰው ከአውሬም ብቻ ሳይሆን ከራሱ “ከመጀመሪያው ክፉ” ከሴጣንም የሚያንስ ወራዳ ፍጥረት ነውና!

ለሰው ልጆች ታላቅ ውርደት ነውሰው የተፈጠረው ከእርሱ ውጭ ያሉ በምድር

ላይ የሚኖሩ ሌሎች ፍጥረታትን ሁሉ “ይገዛ” ዘንድ ታላቅነትን ብቻ ሳይሆን አለቅነትንም ጭምር ይዞ ሁሉን በሚችለው ፈጣሪ የዚህች ምድር ታላቅ ፍጡር ሆኖ መፈጠሩን በመንፈሳዊው የሥነ ፍጥረት እሳቤ ዘንድ ዋነኛ ማጣቀሻ ሆኖ የሚያገለግለው መጽሃፍ ቅዱስ በማያሻማ ቋንቋ በግልጽ መዝግቦት ይገኛል። ሆኖም ታላቅ ሲባል አንሶ፣ ክቡር ሲባል ወርዶ፣ መአምር ሲባል መሃይም ሆኖ የተገኘው ክፉውና ስግብግቡ የሰው ልጅ ላለመበለጥና

ለመብለጥ፣ ከሆነለትም አሸናፊና የበላይ ሆኖ ለመገኘት ከእርሱ ውጭ ያሉ ሌሎች የህልውና ስጋቶችንና የሕይወት ጠላቶችን ሁሉ ትቶ፣ በራሱ ፍጥረት ላይ በጭካኔ የሚነሳና የሚያጠፋ ከሆነ ይህ ለሰው ልጆች ታላቅ ውርደት ነው። የሰው ልጅ ከፍጡር ሁሉ በልጦ የተሰጠውን ይህን ሁሉ ዕውቀቱንና ኃይሉን ሁሉ ከፈጣሪው ጥበቃ በታች ከራሱ ሳይሆን ከሌሎች ፀረ ሰውና ፀረ ህይወት ፍጡራን ሊደርስበት የሚችለውን ጥቃት ለመከላከል እና መልካም ነገርን ለማድረግ ሊጠቀምበት ሲገባው ከፍጥረቱ በተቃራኒ መቆጣጠር የሚችለውን አዕምሮውን በጭካኔ ተሰልቦ ለዘግናኝ ጥፋትና ወንጀል ከተጠቀመበት ይህ አስፀያፊ ነው።

እናም ይህን ያህል ታላቅ ተፈጥሮውን፣ ኃያል ማንነቱን ማወቅ ተስኖት የሰው ልጅ ከሰውነት ወርዶ ሰው መሆን አቅቶት በአስከፊ ጭካኔ ውስጥ ተዘፍቆ ሲገኝ ታላቁን ውርደት ይረዳል። ለእርሱ ብቻ ተዳልቶ በተሰጠው በታላቁ አዕምሮው ምክንያት የምድራችን ታላቁ ፍጡር መሆን የቻለው ሰው ስጦታውን ማወቅ ሳይችል ቀርቶ ሰው መሆን ባልቻለ ጊዜ ሰው ከሁሉም የከፋውን ጥፋት አጥፍቷልና ከምድር ፍጥረታት ሁሉ የሚያንስ ወራዳ ፍጥረት ይሆናል። ክፉና በጎን፣ ስህተትና ትክክልን፣ እውነትና ሃሰትን፣ ልማትና ጥፋትን፣ ሞትና ህይወትን የተሻለውን አመዛዝኖ እንዲመርጥበት ከፍጥረት ሁሉ ተዳልቶ “አዕምሮ” የተባለ ውድ ስጦታ የተሰጠው የሰው ልጅ ይህንን ታላቅ ስጦታውን ማወቅ የተሳነው(ወይም ማወቅ ባልፈለገ ጊዜ) ጭካኔን ይሞላል፣ ርህራሄ ያጣል፣ ከሰውነት በታች ሆኖ ከሁሉም አንሶ ይዋረዳል። ሰው ምንም እንኳን ስጋዊ ጠባይ ቢኖረውም በእግዚአብሔር አምሳል የተፈጠረ በመሆኑ አምላካዊም፣ መለኮታዊም ሆኖ ሳለ ይህንን ታላቅ ስጦታውን ረስቶ ያለተፈጥሮው በጭካኔ እና በአረመኔያዊ ባህሪይ ተመልቶ መኖር ከጀመረ፣ በራሱ ስህተት ከታላቁ የሰውነት ባህሪው ይጎድላል፣ ከሁሉም የከፋ ታላቅ ውርደትን ይከናነባል። ከሰውነት ባህሪይው በራሱ ጊዜ ከጎደለ፣ ሰው ሆኖ ያለ አግባብ ሰውን ከበደለ፣ በፍቅር ፋንታ ጥላቻን ከመረጠ፣ በበጎነት ፋንታ ክፋትን ካስበለጠ፣ ከሰላም ይልቅ ጦርነትን ከናፈቀ ያኔ ሰው ከሰውነቱ ብቻ ሳይሆን ታናሽ ከሚባሉ ፍጥረታትም በታች አንሶ ተዋርዷል። ማሰብ መሰላሰል ማመዛዘን ከማይችለው፣ አንጎል እንጂ አዕምሮ ከሌለው ከእንስሳም በታች እንስሳ ሆኗል። በተለይም ደግሞ ሰው በገዛ ወገኑ ላይ በተቃራኒው ከቆመ፣ ሰው በሰው ላይ በጭካኔ ከተነሳ፣ ከሰሞኑ እንዳየነውና እንደሰማነው ሰው ሰውን እንደ እባብ በዱላ ቀጥቅጦ ከገደለ፣ ሰው ሆኖ ሰውን እንደ በግ በአንገቱ ላይ ቢላዋ የሚጥልበት “አቅም” ካገኘ ያኔ ሰው አይደለምና ከታላቁ ፍጡር ከሰውነት ይቅርና ህይወት ከሌለው ከያዘው ገጀራና ዱላም ማነሱን ሊያውቅ ይገባል።

ወንጀልና ኃጢአትም ነው፤ ያስጠይቃልም ይህ ሰው ሆኖ ሰውነቱን አለማወቅ ለሰው ልጆች እና

ለሰውነት ውርደት ብቻ አይደለም፤ ስህተት፣ ከስህተቶች ሁሉ የከፋ ስህተትም ነው። ስህተት ብቻ ሳይሆን ጥፋት፣ ወንጀል፣ ከሁሉም በላይ ደግሞ ሃይማኖቱ ምንም ይሁን ምን በፈጠረው አካል የሚያስጠይቅ ምህረት የሌለው ክፉ ኃጢአትም ነው። ሰው ሰው መሆኑን ባለማወቁ ምክንያት ለሚፈጽመው ለዚህ ክቡድ ስህተቱም ከራሱ ውጭ ማንንም ተወቃሽ ሊያደርግ አይችልም። ለዚህ ዓይነት ወንጀል መፈጸም መንግስትም ቢሆን ተጠያቂ ሊሆን አይገባውም። ምክንያቱም ሰው መሆንን፣ ሰውነትን ለማወቅና ይህንንም ለማክበርና ለማስከበር ህግም አስፈላጊ አይደለምና።

ሰው መሆንን ለማሳወቅ ፖሊስ አይሰማራም። ሰው መሆንን ለማወቅ በዚህም ሰው ባለመሆን ምክንያት ለሚፈጠር ከሰሞኑ በሃገራችን እንዳየነው ዓይነት ጥፋትና ወንጀል ለመዳን ሰው ሆኖ መፈጠር ብቻ በቂ ነውና! አሁን ላይ በአገራችን እየተፈጠረ ያለው አሳዛኝ ክስተትም የዚሁ ሰው ሰውነቱን ያለማወቅ ጥፋትና ያስከተለው ውጤት ነው። እናም ሰው ሰው መሆኑን ማወቅ አቅቶት ለፈጸመው ለእንዲህ ዓይነት ዘግናኝ አረመኔያዊ ድርጊት ተጠያቂው ራሱ ፈጻሚው አረመኔው እና ጨካኙ ነው። የሚጠየቀውም በምድር ብቻ አይደለም እንደየ ሃይማኖቱ በሰማይ ቤት በፈጠረው በአምላኩም ነው የሚጠየቀው። ወንጀሉም የታላቁን የሰውነትን ክብርና ህግ የሻረ፣ ከባድና ምንም ዓይነት አመክኖአዊ ትክክለኛነት ሊቀርብለት የማይችል ፍጹም ስሁት በመሆኑ ይቅርታና ምህረት ሊደረግለት አይገባም። ምድር ላይ ከዚህ የበለጠ ጥፋት ሊኖር አይችልምና!

ኃያል ማንነቱን ማወቅ ተስኖት

የሰው ልጅ ከሰውነት ወርዶ

ሰው መሆን አቅቶት በአስከፊ

ጭካኔ ውስጥ ተዘፍቆ ሲገኝ

ታላቁን ውርደት ይረዳል፡፡

ለእርሱ ብቻ ተዳልቶ በተሰጠው

በታላቁ አዕምሮው ምክንያት

የምድራችን ታላቁ ፍጡር

መሆን የቻለው ሰው ስጦታውን

ማወቅ ሳይችል ቀርቶ ሰው

መሆን ባልቻለ ጊዜ ሰው

ከሁሉም የከፋውን ጥፋት

አጥፍቷልና ከምድር ፍጥረታት

ሁሉ የሚያንስ ወራዳ ፍጥረት

ይሆናል፡፡

Page 16: ከባንክ ውጭ ከ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር በላይ ማስቀመጥ ተከለከለሕግ • ዶ/ር ሳሙኤል ሁርካቶ፤ የሳይንስና ከፍተኛ

በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ታተመ

ስፖርት

ገጽ 32 ረቡዕ ነሐሴ 13 ቀን 2012 ዓ.ም

ስልክ ቁጥር፡- 011-1-11-98-58/011-1-11-97-77/011-1-11-11-57

-011-1-57-51-07ነጻ ስልክ ቁጥር ፡- 888/1/2/7

ፋክስ +251 11 1 55 03 69

ድረ ገጽ፡- www.poessa.gov.etኢ. ሜይል፡- [email protected]

ማኅበራዊ ድረ-ገጽ፡- www.Facebook.com/poessaፖ.ሳ.ቁ፡- 33921

አዲስ አበባ- ኢትዮጵያ

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የግል ድርጅቶች ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ

አድራሻ

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር

ለግል ድርጅቶች ሠራተኞች አገልግሎት ጡረታ ፈንድ በሠራተኛው ደመወዝ ላይ ተመስርቶ የሚደረገው መዋጮ 1. በግል ድርጅቱ 11 በመቶ2. በግል ድርጅት ሠራተኛው ሰባት በመቶ ይሆናል፡፡የጡረታ መዋጮ ክፍያ1. እያንዳንዱ የግል ድርጅት የሠራተኞቹን የጡ ረታ መዋጮ

ከደመወዛቸው ቀንሶና የራሱን መዋጮ ጨምሮ ለጡረታ ፈንዱ በየወሩ የመክፈል ግዴታ አለበት፡፡

2. ከላይ በቁጥር አንድ የተገለጸው የጡረታ መዋጮ ለሠራተኞች የወር ደመወዝ ከተከፈለበት ወር መጨረሻ ቀን አንስቶ በ” ቀናት ውስጥ ለጡረታ ፈንዱ ገቢ መደረግ አለበት፡፡

3. ከሠራተኞቹ ደመወዝ ሊቀነስ የሚገባውን መዋጮ ሳይቀንስ የቀረ የግል ድርጅት ክፍያውን ራሱ ለመፈጸም ኃላፊ ይሆናል፡፡

4. ከግል ድርጅቶችና ከግል ድርጅት ሠራተኞች የሚሰበሰበው የጡረታ መዋጮ ኤጀንሲው በሚወክላቸው አካላት አማካኝነት ተሰብስቦ ከላይ በቁጥር ሁለት በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ተሰብስቦ በቀጣዩ ወር የመጀመሪያዎቹ የስራ ቀናት ለጡረታ ፈንዱ ገቢ ይደረጋል፡፡

5. ኤጀንሲው በዚህ አንቀጽ መሠረት የሚሰበሰበው የጡረታ መዋጮ በትክክል ገቢ ስለ መደረጉ የመቆጣጠር ሥልጣን ይኖረዋል፡፡

6. ኤጀንሲው ወይም ውክልና የተሰጠው አካል ተገቢውን የጡረታ መዋጮ ለጡረታ ፈንዱ ገቢ ሳያደርግ ከ3 ወር በላይ የቆየ የግል ድርጅትን በባንክ ካለው ሂሣብ ላይ ተቀንሶ ገቢ እንዲሆን የማስደረግ ሥልጣን ይኖረዋል፡፡

7. ማንኛውም ባንክ በኤጀንሲው ወይም ውክልና በተሰጠው አካል ሲጠየቅ የሚሰበሰበውን የጡረታ መዋጮ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከግል ድርጅቱ ሂሣብ ላይ ቀንሶ ለኤጀንሲው ወይም ውክልና ለተሰጠው አካል ገቢ የማድረግ ግዴታ አለበት፡፡

8. በግል ድርጅቶች ጡረታ ዐቅድ ለተሸፈኑ ሠራተኞች ደመወዝ

የግል ድርጅቶች ሠራተኞች የጡረታ መዋጮ አሰባሰብየሚከፍል አሠሪ ገንዘቡ የሚገኝበትን የባንክ ቅርንጫፍና የሂሣብ ቁጥሩን ለኤጀንሲው በጽሁፍ የማሳወቅ፣ የባንኩ አድራሻና የሂሣብ ቁጥሩ ሲለወጥም ለውጡ ከተከሰተበት ቀን አንስቶ በ5 ቀናት ውስጥ ለኤጀንሲው በጽሁፍ የመግለጽ ግዴታ አለበት፡፡

9. ኤጀንሲው ወይም ውክልና የተሰጠው አካል በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (7) መሠረት ሊሰበሰብ ያልቻለን ውዝፍ የጡረታ መዋጮ ግብር የመክፈል ግዴታቸውን ያልተወጡ ግብር ከፋዮች ሀብት በመያዝና በመሸጥ የግብር አሰባሰብ የሚከናወንበትን ስርዓት ለመወሰን የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ያወጣውን መመሪያ በመከተልና በቀጥታ የግል ድርጅቱን ንብረት በጨረታ በመሸጥ ገቢ የማስደረግ ሥልጣን ይኖረዋል፡፡

10. ከጡረታ መዋጮ ገንዘብ ላይ ቀንሶ ለአገልግሎት ክፍያ፣ ለገንዘብ ማስተላለፊያ፣ ለዕዳ ወይም ለማንኛውም አገልግሎት መጠቀም የተከለከለ ነው፡፡

11. ኤጀንሲው የጡረታ መዋጮ ገቢን ከመሰብሰብና ከማስፈፀም ጋር የተያያዙ ማናቸውንም ስራዎች ለሌሎች አካላት ውክልና በመስጠት ማሰራት ይችላል፡፡12. የጡረታ መዋጮ ክፍያ ከማንኛውም ዕዳ ክፍያ

ቅድሚያ ይኖረዋል፡፡የጡረታ ፈንድ አስተዳደርና አጠቃቀምበአዋጅ ቁጥር 715/2003 መሠረት የተቋቋመውን የጡረታ ፈንድ የሚያስተዳድረው ኤጀንሲው ሲሆን፤ የጡረታ ፈንዱ ጥቅም ላይ የሚውለው፡- ሀ) በዚህ አዋጅ የተመለከቱትን የጡረታ አበል ክፍያዎች

ለመፈጸም፤ ለ) ለትሬዠሪ ቦንድ መግዣና የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት

ሚኒስቴር በሚያወጣው መመሪያ ለሚወሰኑ ሌሎች አትራፊና አስተማማኝ ኢንቨስትመንቶች፤ እና

ሐ) ለኤጀንሲው አስተዳደራዊ ወጪዎች ብቻ ይሆናል፤ በተጨማሪም የጡረታ ፈንዱ በማናቸውም የዕዳ ክፍያ ምክንያት ሊከበር ወይም ሊያዝ አይችልም፡፡

በሀገራት የዕድገት ጉዞና የልማት ሂደቶች ውስጥ ከተሳታፊነትና ተጠቃሚነት አንጻር በሰው ሰራሽና በተፈጥሮ ምክንያቶች የሚገለሉና ለማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች የሚጋለጡ የሕብረተሰብ ክፍሎች አሉ። ከእነዚህ የህብረተሰብ ክፍሎች መካከል ከአካል ጉዳት ጋር የሚኖሩ ዜጎች ለዘመናት በህብረተሰቡ ውስጥ በኖረው የተዛባና ስር የሰደደ አመለካከት የተነሳ ለአድሎና መገለል በቀዳሚነት ተጋላጭ ናቸው። የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎቶች ተጠቃሚ ሳይሆኑ ለዓመታት ኖረዋል።

አድሎና መገለል ለአካል ጉዳተኞች የዕለት ተዕለት የኑሮ እንቅስቃሴ አካል እንደሆነ ለሁሉም ግልጽ ነው። መገለል ሲባል ደግሞ ከትምህርት፣ ከስራ፣ ከመረጃ፣ ከመሰረታዊ ልማት፣ ከጤና አገልግሎት፣ ከልማት ፕሮግራሞች፣ ከኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራሞች፣ ትራንስፖርት አገልግሎቶችንና ሌሎች መሰል ችግሮችን ያጠቃልላል። አብዛኞቹ አካል ጉዳተኞች መረጃ በአግባቡ ባለማግኘታቸው ምክንያት አካል ጉዳት ከሌላቸው በበለጠ ሁኔታ የችግሮቹ ተጠቂ እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል።

የአካል ጉዳተኞች ፍላጎት ዘርፈ ብዙ እንደመሆኑ መጠን ተጠቃሚነታቸውንና ተሳትፎአቸውን ለማረጋገጥ የብዙ ሴክተሮች ድርሻ ነው። የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤትም የእነዚህን የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት የሚያሳድጉ ጉዳዮች ላይ ከፍተኛ ቁጥር ያለውን የህብረተሰብ ክፍል ያገለለ ለውጥ ውጤቱ ዝቅተኛ መሆኑን በመገንዘብ በ2011 የአካል ጉዳተኞች ጉዳይ ራሱን ችሎ በዳይሬክቶሬት ደረጃ እንዲቋቋም አድርጓል። ዳይሬክቶሬቱም የሚከተሉትን ዋና ዋና ተግባራት ያከናውናል።

በአካል ጉዳተኞች ዙሪያ ችግር ፈቺ ጥናቶችን በማካሄድ ለሕግ፣ ደንብ፣ መመሪያና ለፖሊሲ ቀረጻና ፕሮግራም ዝግጅት በግብአትነት እንዲውሉ ያደርጋል፤ ተሳታፊነታቸውንና ተጠቃሚነታቸውን ለማሳደግ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ተገቢ ሚናቸውን እንዲወጡ የግንዛቤ መስጫ ስራዎችን ያከናውናል።

የአካል ጉዳተኞችን ሁለንተናዊ ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የወጡ አህጉራዊና ዓለም አቀፍ ስምምነቶች

ተግባራዊ እንዲደረጉ የሚመለከታቸውን መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ አካላትን የማስተባበር፣ የመከታተልና የመደገፍ ስራዎችን ያከናውናል። በሀገሪቱ የሚገኙ የሰው ሰራሽ የአካልና የአካል ድጋፍ አገልግሎት የሚሰጡ ማዕከላትን ጥራት ለማስጠበቅ ተከታታይነት ያለው ክትትልና ድጋፍ በማድረግ ግብረ መልስ በመስጠት አገልግሎቱን እንዲሻሻል ያደርጋል።

በሰው ሰራሽ አካልና አካል ድጋፍ አገልግሎት አሰጣጥ ረገድ ያለውን የጥራት ደረጃ ለማሳደግ የሚያስችል የስታንዳርድ ሰነድን ወደ ተግባር በማሻገር በየጊዜው እየፈተሹ በማሻሻል ተፈጻሚነቱን ያጎለብታል። የተለያየ ጉዳት ያለባቸው አካል ጉዳተኞች በገቢ ማስገኛ ስራዎች ተደራጅተው የተዘዋዋሪ ብድር ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሚያስችል የአሰራር ማኑዋል በማዘጋጀት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር የማህበራዊና ኢኮኖሚ ተጠቃሚነታቸውን ያረጋግጣል። በየአስር ዓመቱ በሚካሄደው የሕዝብና ቤት ቆጠራ ወቅት አካል ጉዳተኞች በተገቢው እንዲቆጠሩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር ይሰራል። በአገር አቀፍ ደረጃ የሚወጡ ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች አካል ጉዳተኞችን ያካተቱ መሆናቸውን ያረጋግጣል። እንደ አስፈላጊነቱም ግብአት ይሰጣል።

የአካል ጉዳተኞችን መብት ወጥ በሆነ መንገድ ለማስከበር የሚያስችል የተጠቃለለ ሕግ እንዲወጣና ተግባራዊ እንዲሆን ያደርጋል። ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተሳትፎኣቸውን ለማሳደግና ተጠቃሚነታቸውን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ መቋቋምና ዲስአብሊቱ ፈንድ እንዲሁም በብሔራዊና በክልል ደረጃ ምክር ቤት እንዲቋቋም ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር ይሰራል።

በአጠቃላይ የአካል ጉዳተኞች ጉዳይ የሁሉም ዜጋ ጉዳይ መሆኑን በመገንዘብ እያንዳንዱ ዜጋ የአካል ጉዳተኞች የእኩል ዕድል ተሳታፊነትና ተጠቃሚነትን ማሳደግ የግድ ይላል። ለዚህም ሁሉም መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እና ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን ሚና ሊጫወቱ ይገባል።

ምንጭ: በሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የአካል ጉዳተኞች ጉዳይ መከታተያ ዳይሬክቶሬት

የአካል ጉዳተኞች የእኩል ዕድል ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት

ብርሃን ፈይሳ

በኮቪድ 19 ምክንያት ክፉኛ የተጎዳው የዓለም አትሌቲክስ ታላላቅ ዓለም አቀፍ ውድድሮችን ለመመለስ በእንቅስቃሴ ላይ እንደሚገኝ ይታወቃል። ውድድሮች መቋረጣቸውን ተከትሎም ከወራት በኋላ የመጀመሪያው የአትሌቲክስ ውድድር ባለፈው ሳምንት መጨረሻ መካሄዱ የሚታወስ ነው። የውድድሮች መመለስ ለአትሌቶችና ለስፖርት ቤተሰቡ መልካም ዜና ቢሆንም፤ ውድድሮች ተመልካቾች በሌሉበት በዝግ ስታዲየም መከናወናቸው ያልተለመደና አዲስ የውድድር ድባብ የፈጠረ ሆኗል።

በወረርሽኙ ምክንያት የሌሎች ስፖርቶችም ሆነ የአትሌቲክስ ውድድር በታቀደላቸው መርሃ ግብር ምክንያት ሊካሄድ አልቻለም። የውድድር አዘጋጅ ሃገራትም ካለባቸው የቫይረሱ ስርጭት ስጋት ጋር በማመዛዘን የውድድሩ መካሄድና አለመካሄድ ላይ ምላሻቸውን ይሰጣሉ። በመሆኑም የዓለም አትሌቲክስ የተዘበራረቀውን መርሃ ግብር በማስተካከልና በማካካስ ላይ ይገኛል። በሞናኮ በተካሄደው የዳይመንድ ሊግ ውድድር ላይም በዓለም ላይ ጥቁር ጥላውን ባጠላው ወረርሽኝ ምክንያት ከአትሌቶች በቀር ደጋፊዎችና የስፖርት ቤተሰቡ ስታድየም መታደም አልተቻለም። በዚህም የዓለም አትሌቲክስ የቀድሞውን የስታዲየም ድባብ በከፊል ለመመለስ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን የሚጠቀም መሆኑን ስፖርት ቢዝነስ በድረገጹ አስነብቧል።

እንደሚታወቀው በስፖርታዊ ውድድሮች ውጤታማ ለመሆን ከሚያግዙ መሰረታዊ ጉዳዮች መካከል አንዱ የደጋፊዎች ማበረታቻ ነው። ጽናትንና ብርቱ ተፎካካሪነትን በሚጠይቀው እንደ አትሌቲክስ ባሉ ስፖርቶች ደግሞ ለአትሌቱ ተጨማሪ አቅም የሚሆኑትና በሚያስመዘግበው ሰዓትና ውጤት ላይ ሚና የሚኖራቸው በስታዲየም አልያም በጎዳና የመሮጫ አቅጣጫን ተከትለው የሚያበረታቱ የስፖርቱ ወዳጆች ናቸው። ይህ ወቅት ደግሞ ዓለም አቀፉ ወረርሽኝ ሰዎችን በአንድ ለማሰባሰብ የማያስችል እንደመሆኑ እንደ እግር ኳስ ሁሉ

የስታድየሞች ድባብ በቴክኖሎጂዎች እየታገዙ ነው

አትሌቲክስንም ያለ ተመልካች በአትሌቶች መካከል ብቻ እንዲካሄድ አድርጓል። ለስፖርቱ የጀርባ አጥንት የሆኑት ደጋፊዎች በቴሌቪዥን መስኮቶቻቸው ውድድሮችን በቀጥታ መከታተል ችለዋል። አትሌቶች በበኩላቸው ከለመዱት በተቃራኒው በባዶ ስታዲየም መሮጣቸው ተጽእኖ እንዳያደርስባቸው የዓለም አትሌቲክስ የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችን መጠቀም የግድ ሆኖበታል።

ስፖርቱን በበላይነት የሚመራው ተቋም መቀመጫውን በአውስትራሊያ ካደረገ የቴክኖሎጂ ድርጅት ጋር እየሰራ ሲሆን፤ በሞናኮ ውድድር በተግባር ላይ አውሎታል። ቴክኖሎጂው ከዚህ ቀደም በተካሄዱ የዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና እንዲሁም ዳይመንድ ሊግ ውድድሮች ላይ የተወሰዱ የድጋፍ ድምጾች ላይ ጥቂት ማስተካከያ በማድረግ በስታዲየም ለአትሌቶች አየር ላይ የሚውል እንዲሁም በቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭቱም ላይ የሚሰማ ነው። ይህም እንደቀደመው ጊዜም ባይሆን የስታዲየምና ውድድር ድባቡን በከፊል ለመመለስ የሚችል ነው።

የቴክኖሎጂውን በስራ ላይ መዋል ተከትሎም በዓለም አትሌቲክስ የውድድር ማናጀር ፍሎሪያን ዌበር፤ ለአትሌቶች ምቹ መድረክን ማዘጋጀት ከስራዎቻቸው መካከል አንዱ መሆኑን ጠቁመዋል። አክለውም ‹‹ውድድሩ በምርጥነትና ተመራጭነት እንዲቀጥል አዳዲስ ነገሮችን መፍጠርና የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም ያለ ደጋፊ ውድድራቸውን እንዲያካሂዱ ማድረግ አለብን። ውድድርን በጸጥታ ማድረግ መልካም ባለመሆኑ ተፎካካሪ እንዲሆኑና የቴሌቪዥን ተመልካቾችን ጥሩ ድባብ ለመፍጠር ቴክኖሎጂውን ተጠቅመናል›› ብለዋል።

ለወራት ተቋርጦ የቆየው የአትሌቲክስ ውድድር ዳይመንድ ሊግን ተከትለው እንደሚካሄዱ የውድድር አዘጋጆች እያስታወቁ ነው። በከፍተኛ ጉጉት ይጠበቅ የነበረውና ተራዝሞ የቆየው የለንደን ማራቶን ከሁለት ወራት በኋላ ጥቂት አትሌቶችን ብቻ በማሳተፍ እንደሚደረግ ታውቋል። የአቴንስ፣ የፓሪስ፣ የሮተርዳም እንዲሁም አህጉር አቀፎቹ የዙር ውድድሮችም በቅርቡ የሚካሄዱበትን ጊዜ ያስታውቃሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የስታድየሞችን ድባብ እንደቀድሞው ለማድረግ የተለያዩ ቴክኖሎጂዎች ተግባራዊ እየተደረጉ ነው፤