po s 6co²c Óf;j ú -...

36
1 °”l 6— ¯Sƒ lØ` 119 ግንቦት 2006 ዓ.ም

Upload: buiquynh

Post on 21-Apr-2018

310 views

Category:

Documents


8 download

TRANSCRIPT

1°”l 6— ¯Sƒ lØ` 119 ግንቦት 2006 ዓ.ም

2 °”l 6— ¯Sƒ lØ` 119 ግንቦት 2006 ዓ.ም

ግንቦት 30 /2006 ሰኔ 14 /2006 ሰኔ 28 /2006

ቁ 120 ቁ 121 ቁ 122

’Nc? 1999 ¯.U }SW[}

u›KT¾G< QƒSƒ“ Te�¨mÁ �/¾}/¾Ó/Tህበር በፖለቲካ፣ኪነ ጥበብና ማኀበራዊ Ñ<ÇÄ‹ በማተኮር በየ15 ቀኑ ለሕትመት

የምትበቃ መፅሔት

ማኔጂንግ ዳይሬክተር:- ፍቃዱ ማኅተመወርቅE-mail: [email protected]

ማኔጂንግ ኤዲተር

›Å=e ²Ñ¾

ª“ ›²ÒÏ:- አብዱ ሰይድአራዳ ¡õK Ÿ}T ቀበሌ 19 የu?ƒ lØ` 15/314

ከፍተኛ አዘጋጅ፡- በሪሁን አዳነ ሰሎሞን ለማ ብሩክ መኮንን አዘጋጆች፡- õp` ’Ò ƒ´� ›và አለምሸት ሞገስ ¢Uú¨<}` ፅሑፍ:- - ኃይማኖት ካሳዬ - Ièƒ H/Ñw`›?M›UÅ™‹ - ሠርፀ ፍሬ ስብሐት - ዶ/ር ቴዎድሮስ ኃ/ማርያም - Ñ@�†¨< ¨M¿ (ዩ.ኤስ.አሜሪካ)- Ê/` lUL†¨< ›v}- ነብዩ ሲራክ (ከሳዑዲ አረቢያ)- ሁሴን ከድር- ሄኖክ አክሊሉ- ፍቃዱ ልመንህ የዝግጅት ክፍሉ አድራሻከአዲስ አበባ ሬስቶራንት ፊት ለፊት በሱፍቃድ ሕንፃ ገባ ብሎ አራዳ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 05 የቤት ቁጥር 149ስልክ- 0930033879 0118951693 0911 22 76 61ፋክስ - 011-1562335

ኢሜይል፦ [email protected]@gmail.comFacebook- enkumag

ፖስታ- 676 ኮድ 1029›Ç=e ›uv ›=ƒÄåÁ

›�T>:- ፋኖስ ሰርቪስስ ኃ/የተ/የግ/ማኀበርአድራሻ፡-ቂርቆስ ክ/ከቀበሌ 04 የቤት ቁ. 304

ማውጫ

ግንቦት 30 /2006 ሰኔ 14 /2006 ሰኔ 28 /2006

ቁ 120 ቁ 121 ቁ 122

ዕንቁ ክፍል

6

9

10

4

15

18

17

16

12 13

20

22

1

የዞን ዘጠኙ በፍቃዱ፣ እንደሀገር ወዳድ ዜጋ…

ግንቦት 20 የወለደው የመለያየት አደጋ!

4ኛው መሠረታዊ ፍላጎት

ዛሬም!የብሔራዊ ዕርቅ ጥሪ እናሰማለን!

የአባይ ውሃ እና የግብፅ ኢኮኖሚያዊ ይዞታ በኢትዮጵያዊው ዲፕሎማት ዕይታ

‹‹ግንቦት 20 አንድን ፈላጭ ቆራጭ በሌላ ፈላጭ ቆራጭ አገዛዝ ነው የተካው››

‹‹ኢሕአዴግ የመለሰው አንድም ጥያቄ የለም››

‹‹የኑሮ ደረጃ አድጓል›› ማለት፤ የድህነትንና የጉስቁልናን መልክ

አይቀይርም

አባቴን ንጉሥ ሳላሰኝ ፈረሴን ከቀይ ባህር ዉሃ ሳላጠጣ ንጉሠ ነገሥት

ተብዬ ዘዉድ አልጭንም

የጎሳ ፖለቲካ አደጋ አለው!

ዛሬም እዛው ላይ ነን? ወደ ፊት መሔድን ማን ከለከለን?

‹‹ትላንት የኢትዮጵያ ሕዝብ ያከበረኝ አትሌት ነበርኩ››

የ፲አለቃ ገብሬ ጉርሙ

አቶ ገብሩ ገ/ማርያም

አቶ ሀብታሙ አያሌው

4 °”l 6— ¯Sƒ lØ` 119 ግንቦት 2006 ዓ.ም

በመጋቢት ወር 2005 ዓ.ም ከጋዜጠኛ እና ጦማሪ በፍቃዱ ኃይሉ ጋር በአካል ለመጀመሪያ ጊዜ የተገናኘነው በዚህቹ ዕንቁ መጽሔት ላይ ነበር፡፡ - እሱ ማኔጂንግ ኤዲተር እኔ ደግሞ ዋና አዘጋጅ ሆኜ፡፡ ከትውውቃችን ቀን ጀምሮ በፍቄ እንጂ በፍቃዱ ብየው እንኳን አላውቅም፡፡

በፍቃዱን ሳውቀው በጣም ረጋ ያለ፣ ትሁት፣ ሰውን በአክብሮት ብቻ የሚያናግር፣ አስተዋይ፣ ሰውን የሚረዳ፣ የራሱን ሀሳብ፣ አቋምና ዕምነት በቀላሉ የሚያስረዳ፣ የተለየ የሰዎችን ሀሳብ፣ አቋምና ዕምነት በጨዋ ደንብ የሚያከብር (ይሄን ዐይነት ባህሪ ብዙ ሰዎች ጋር መመልከት አልቻልኩም)፣ በሀሳቦች ላይ ውይይት የሚወድ፣ ጊዜውን በአግባቡ ከፋፍሎ ለሚወዳቸው ሥራዎቹ የሚሮጥ፣ ራሱን በዕውቀት፣ በወቅታዊ መረጃዎችና በተለያዩ ሥልጠናዎች ማበልጸግ የሚወድ እጅግ ቅን ልጅ ነው፡፡

በመጽሔቷ ላይ ለአምስት ወራት ያህል አብረን ሰርተን ነበር፡፡ በእነዚህ ጊዜያቶች ሀተታዊም ሆነ ግለ-ሃሳባዊ ጽሑፎችን ለማሰናዳት ጠቃሚ ወቅታዊ መረጃዎችን መሰብሰብ ይወድዳል፡፡ በመረጃዎቹ ላይ ከባልደረቦቹ ጋር መደበኛም ሆነ መደበኛ ባልሆኑ ስብሳባዎች ላይ ውይይት ከፍቶ ሐሳቦችን መለዋወጥም ልምዱ ነበር፡፡ ይህን ዓይነት ልምድ ለየትኛውም ነጻ ጋዜጠኛ ወሳኝ ነው የሚል ጠንካራ እምነት አለኝ፡፡ በቢሮ ጠረጴዛ ላይ ተጀምረው በቢሮ ጠረጴዛ ላይ የሚጠናቀቁ ጽሑፎችን የሚያሰናዱ፣ ለመስክ ሥራ መልፋት የማይወዱ "ጋዜጠኞች" እና ጸሐፊያን በሀገራችን መኖራቸውንም አውቃለሁ፡፡

በፍቃዱ እና …ጭንቀቱየትኛውም የህትመት ውጤት በውስጡ

ከሚይዛቸው የጽሑፍ ይዘቶች ባሻገር ለንባብ የሚሆን መስህብ ያለው የፊት ገጽ ግራፊክ ዲዛይን ማዘጋጀት ይጠበቅበታል፡፡ ግነት ባልበዛበት መልኩ የህትመቱን ወሳኝ ርዕሰ ጉዳይ እና ጉዳዮች የሚያሳይ ጥሩ የግራፊክ ዲዛይን በብዙ አንባቢያን ዘንድ ተወዳጅ መሆኑ አጠያያቂ አይመስለኝም፡፡

የሕትመት ውጤቶች የፊት ገጽ ግራፊክ ዲዛይን ከልብ ሲያስጨንቃቸው ከተመለከትኳቸው ጥቂት የሙያ አጋሮቼ መካከል አንዱ በፍቃዱ ነው፡፡ በተለያዩ የሥራ አጋጣሚዎች ከሀገር ውጭ ወጥቶ ሲመለስ፣ ሁሌ በጀርባው እና በትከሻው በሚያነግታት ቦርሳው ውስጥ የተለያዩ ሐገራትን መጽሔቶች እና ጋዜጦች ይይዝ ነበር - በፍቃዱ፡፡ እነዚህን የህትመት ውጤቶች ለእኛ ለባልደረቦቹ በኤዲቶሪያል ስብሰባ ወቅት እና መደበኛ ባልሆኑ ግንኙነቶች ወቅት ከቦርሳው አውጥቶ ስለጽሑፎች ይዘት፣ ስለሕትመት ጥራቶች፣ ስለፊት እና ውስጥ ገጾች ግራፊክ ዲዛይኖች የፈጠራ ጥበብ በተመሥጦ ለማስረዳት ሲሞክር ከልቡ ነው፡፡

ሰልፎች ላይ አጣሁትበ2006 ዓ.ም በመዲናችን አዲስ አበባ አና

በተለያዩ የክልል ከተሞች ከተመለከትናቸው ሁነቶች መካከል አንዱ ጥቂት ተቃዋሚ ፓርቲዎች ያደረጉት እና ለማድረግ እየተንቀሳቀሱ የሚገኙት ሰላማዊ ሰልፍ ነው፡፡

ይብዛም ይነስም በብዙ ውጣ ውረድ

ተቃዋሚዎች የሚያደርጓቸው ሰላማዊ ሠልፎች እና ሰልፎችን ለማድረግ የሚያደርጓቸው እንቅስቃሴዎች እንደ ዜጋ ጥሩ ነው ብዬ አምናለሁ፡፡ ነገር ግን፣ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የሚጠሯቸው ሰላማዊ ሰልፎች ሁሌም በሥርዓቱ ፈተና፣ ተግዳሮትና አፈና እንደገጠመው ነው፡፡ …

በፍቃዱን እንደኢትዮጵያዊ ዜጋ፣ ካከበርኩለት አቋሙ አንዱ የህዝብ ድምጾች በሚሰሙባቸው ሰላማዊ ሰልፎች ላይ በነቃ መንፈስ መገኘት መቻሉ፣ መታዘቡና ይህንንም በሕትመት እና በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ መዘገብ መቻሉ ነው፡፡ (አንዳንድ ጋዜጠኞች እና ጸሐፊያን ተምኔታዊ የአብዮት ናፍቆትን በብዕራቸው ይከትባሉ፣ በስንት ትግል በሚገኙ ሰላማዊ ሰልፎች ላይ ግን ድርሽ ሲሉ አይታይም፡፡ ይህ ለእኔ ግምት ላይ የሚጥል ትልቅ ተቃርኖ ነው፡፡)

በቅርቡም ሰማያዊ እና አንድነት ፓርቲ በአዲስ አበባ ህዝብን ያማረሩ የማኅበራዊ አገልግሎት ችግሮች እንዲስተካከኩ በማለም የጠሯቸው ሰላማዊ ሰልፎች ነበሩ፡፡ በሁለቱም ሰልፎች ላይ ተገኝቻለሁ፡፡ ቀዳሚው ሰልፍ የነበረው የሰማያዊ ፓርቲ ነበር፡፡ በዚህ ቀን ግን በፍቃዱን በጣም አሰብኩት፡፡ ሰልፉ ላይ የለም! እዝነት ተሰማኝ፡፡ በፍቃዱ በዚህ ሰልፍ ላይ ተገኝቶ መዘገብ ያልቻለው ከሌሎች የሙያ አጋሮቹ ጋር እስከአሁን ድረስ ጥርት ብሎ ባልታወቀ የወንጀል ጉዳይ በፖሊስ ተጠርጥሮ በማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ በመታሰሩ ምክንያት ነው፡፡

የፋሽስት ግራዚያኒ ሐውልት በጣሊያን መቆሙን ተከትሎ በባለዕራይ ወጣቶች ማኅበር አነሳሽነት እና በሳማያዊ ፓርቲ ድጋፍ በአምስት ኪሎ አደባባይ የሰማዕታት ሐውልት አካባቢ በተጠራው ሰልፍ ላይ ከተገኙት እና ለአንድ ቀን ያህል ለእስር ከተዳረጉት ሰዎች መካከል በፍቃዱ አንዱ ነበር፡፡ በፍቃዱ እንደሀገር ወዳድ ዜጋ፣ ጋዜጠኛና ጦማሪ ወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮችን በትኩረት እንደሚከታተል እና ስለሀገር ጉዳይ ያገባኛል ብሎ ስለሚያስብ ይመስለኛል እንደዚህ ዓይነት ጉዳዮች ላይ የሚገኘው፡፡

ነፍሱ ወደየት ታደላለች? በተፈጥሮ እያንዳንዳችን ለነፍሳችን ቅርብ

የሆኑ ነገሮች አሉን፡፡ ከዚህ አኳያ በፍቃዱን ሳስበው ወደውስጤ ወዲያው የሚመጣልኝ አንድ ጉዳይ አለ፡፡ መጽሔቷ ሥራ ላይ በነበረው ቆይታ አስተውዬ ስመለከተው ነፍሱ ለማኅበራዊ ሚዲያ በጣም ቅርብ ሆና አይቻታለሁ፡፡

ሁላችንም የሥራ ባልደረቦች መጽሔቷን ለመዘጋጀት ሥራዎችን ተከፋፍለን እንሰራ ነበር፡፡ በተለይ ማተሚያ ቤት ለመግባት ሁለት ቀናት ሲቀሩ የሥራው ውጥረት ከፍ ያለ ነው፡፡ በፈቃዱም ከሚጽፋቸው ጽሑፎች ባሻገር ሌሎች ጽሑፎች አርትዖት ሲያደርግ ሁሌም የሚገርመኝ ነገር አለ፡፡ ጽሑፎች እየጻፈም ሆነ አርትዖት ሲያደርግ ሞባይሉን በመክፈት ማኅበራዊ ድረ-ገጾችን ወዲያው ወዲያው መከታተሉ ነበር፡፡ ይሄን ልምዱን በተደጋጋሚ ማየቴ ለብቻዬ ፈገግታን ይጭርብኝ ነበር፡፡ ለመጽሔቷ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ፍቃዱ ማሕተመወርቅ እና ለአዘጋጁ በሪሁን አዳነ “የበፍቄ ነፍስ ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ነች” በማለት ፈገግታዬን አጋርቻቸው ነበር፡፡ እነሱም እየሳቁ ሃሳቤን መጋራታቸውን አስታውሳለሁ፡፡

የበፍቃዱን ብዕር በጥቂቱ ዕንቁ ቁጥር 89፣ መጋቢት 2005 ዓ.ም

ላይ ‹‹ግልጽ ደብዳቤ ለአቶ ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል እና አቶ በረከት ስምኦን›› በሚል ርዕስ የሀሳብን መግለጽ ነጻነት አደጋ ላይ መሆኑን በተመለከተ ጥሩ መጣጥፍ አስነብቦ ነበር፡፡ እንዲህ ቀነጨብኩት፡-

‹‹ከ20 ዓመታት በፊት ፓርቲዎቻችሁ ሕወሐትም ሆነ ብአዴን ብዙ የኢትዮጵያ ልጆች ሕይወታቸውን የገበሩለትን ጦርነት ያካሄዱት፣ ኢትዮጵያውያን ‹ጀርባቸውን ሳይመለከቱ› በነጻነት አመለካከታቸውን እና ሐሳባቸውን እንዲያንጸባርቁ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ይህ ብዙዎች ደማቸውን ያፈሰሱለት፣ በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ የተሰየመለት (አንቀጽ 29) ‹የአመለካከት እና ሐሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት› ከኢትዮጵያውያን እጅ ቀስ በቀስ አፈትልኮ እየወጣ መሆኑ ቢያሳሳስበኝ ይህንን ግልጽ ደብዳቤ ለመጻፍ ተገደድኩ፡፡

…ክቡራን ሚኒስትሮች፣ መንግሥት የዜጎችን ሐሳቦች፣ ጋዜጦችንና ጦማሮችን በተደራጀ መልኩ እያሰሰ እና እያነበበ የሕዝቦችን ብሶት እና ችግር ተረድቶ ለመፍትሔው መረባረብ ሲኖርበት፣ ዜጎች መረጃዎቹን እንዳያወጡ እንቅፋት መሆንን ከመረጠ በየት በኩል ኃላፊነት የሚሰማው ማኅበረሰብ መፍጠር ይቻለዋል? መንግሥት በምሳሌነት የሚሳየውን ሥርዓት ከሕዝብ እንዴት መጠበቅ ይቻለዋል? እንግዲህ እነዚህን ጥያቄዎቼን በቅን ልቦና ተረድታችሁ ለጥያቄዎቼ ሁሉ መልስ እንደምትሰጡኝ በማመን በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 29 (2) በመጥቀስ ደብዳቤዬን እቋጫለሁ››

ኬንያ ድርሶ ከተመለሰ በኋላ በቁጥር 94፣ ሰኔ 2005 ዓ.ም ላይ ደግሞ ‹‹ናይሮቢን በአዲስ አበባ አይን›› በሚል ርዕስ ስር እንዲህ ብሎ ነበር፡-

‹‹ …ስለአዲስ አበባ እና ናይሮቢ ብዙ ማለት ይቻላል፡፡ ነገር ግን ገጹ አይበቃም፡፡ …ናይሮቢ በሌቦች እና አልፎ አልፎ በሽብር የምትታወክ ከተማ ስትሆን አዲስ አበባ ግን በአብዛኛው የጨዋታዎች እና ሰላማዊ የመሆኗ ነገር አስደሳች ነው፡፡ ችግሩ አዲስ አበባ ገና ፍዝዝ፣ ድንግዝ ያለች እና መነቃቃት የሚቀራት መሆኑ ነው፡፡›› ከዚህ ጽሑፍ በግልጽ ለመረዳት የቻልኩት በፍቃዱ ሽብር ሳይሆን ሰላም ወዳድ ኢትዮጵያዊ መሆኑን ነው፡፡

በሰኔ 2005 ዓ.ም፣ ቁጥር 93 ላይ፣ ‹‹የልማታችን ጥፋቶች›› በሚል ርዕስ የልማት አካሄዶችን በምክንያታዊነት እንዲህ በማለት ተችቷል፡-

‹‹በቂ ጥናት ሳይደረግባቸው ወደተግባር የሚገባባቸው ሥራዎች የመንግሥትን ገንዘብ ሙሉ ለሙሉ ሊያከስሩ የሚችሉበት ዕድል አለ፡፡ …ግንባታዎችን ከማስጀመር እና ከማስጨረስ እኩል ለአገልግሎት የመዋላቸው ነገር ሊታሰብበት ይገባል፤ አለበለዚያ የልማት ሥራዎች ከላስቲክ ጀበናነት የበለጠ ትርጉም የሌላቸው ሊሆኑ ነው›› ይህንን የበፍቃዱን የሀሳብ ድምዳሜ በግሌ የምጋራው ሃቅ ነው፡፡

በፍቃዱ (በፍቄ) መታሰርህ ብቻ ሳይሆን እጆችህ በካቴና ታስረው አራዳ ፍ/ቤት ሳይህ ጥልቅ ሀዘን ቢሰማኝም ጠመንጃ በወደሩ ፖሊሶች መካከል ከአንተ ያየሁት የፈገግታ ብልጭታ መንፈሠ ጠንካራነትህን አሳይቶኛል፡፡ አይዞን! እውነት ታሸንፋለች፡፡

የዞን ዘጠኙ በፍቃዱ፣ እንደሀገር ወዳድ ዜጋ…በኤልያስ ገብሩ

አስተያየት

5°”l 6— ¯Sƒ lØ` 119 ግንቦት 2006 ዓ.ም

㙀㙀㙀ዜና㙀

በአፍሪካ ከፍተኛ የነዳጅ ሃብት ካላቸው ሃገራት ግንባር ቀደም በሆነችው ናይጄሪያ ባለፈው ረቡዕ በሁለት ቦታዎች በተከሰተው የቦንብ ፍንዳታ በትንሹ 118 ሠዎች ሲገደሉ ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ደግሞ የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸዋል፡፡

አደጋው የደረሰው በሰሜን ምሥራቅ ናይጄሪያ ጆስ በምትባል ከተማ ሲሆን ሁለቱ የቦንብ ፍንዳታ አደጋ የደረሱት በተጨናነቀው የገበያ ማዕከል እና በከተማ ባለው ትልቅ ሆስፒታል አጠገብ ነው፡፡

እስካሁን ሃላፊነቱን የወሠደ አካል ባይኖርም ሠሞኑን በትምህርት ላይ ያሉ ሴቶችን አፍኖ ከመውሰድ በተጨማሪ የተለያዩ ጥቃቶችን በሀገሪቱ ላይ ሲፈፀም የነበረው ቦኮሀራም የተባለው አማፂ ቡድን ከቦንብ ፍንዳታውን ጀርባ ስሙ እንዳለ የናይጄሪያ መንግሥት መግለፁን የሀገሪቱን ፖሊስ ጠቅሶ ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

በ‹‹ዩኤስ ዶክተርስ ፎር አፍሪካ›› እና ‹‹ፒፕል ቱ ፒፕል›› በተባሉ ሁለት ድርጅቶች አማካኝነት የተዘጋጀው የመላው አፍሪካ ሜዲካል ዶክተሮችና የጤና አጠባበቅ ጉባኤ ከግንቦት 13-14 ቀን 2006 ዓ.ም. ተካሄደ፡፡ በአፍሪካ ሕብረት አዳራሽ በተካሂያደው በዚሁ ጉባኤ የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ዶ/ር ደላሚኒ ዙማ፣ የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ፣ የኢፌዴሪ የውጪ ጉዳይ ሚኒስተር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድኃኖም እንዲሁም በውጪ የሚኖሩ ዶክተሮችን ጨምሮ ብዙ የጤና ባለሙያዎችና ዲፕሎማቶች ተገኝተዋል፡፡

የ‹‹ዩኤስ ዶክተርስ ፎር አፍሪካ›› መስራችና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ቴድ ዓለማየሁ እንዲሁም ‹‹ፒፕል ቱ ፒፕል›› የተሰኘው ድርጅት ሊቀመንበር ዶ/ር እናውጋው መሃሪ በዕለቱ እንደገለጹት የጉባኤው ዓላማ በዓለም

በተለያዩ ጊዜያት በሕገወጥ መንገድ ዝሆኖችን በማደን በሕገወጥ መንገድ ከሀገር ሊወጣ ሲል የተያዘ በቻይና በቤጂንግና በሻንጋይ ከተሞች በሚገኙ የዝሆን ጥርስ መሸጫ መደብሮች ቢሸጥ 18 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ወይንም 11 ሚሊዮን የእንግሊዝ ፓውንድ የሚያወጣ የዝሆን ጥርስ ከዝሆን ጥርስ የተሰሩ ልዩ ልዩ ጌጣጌጦችን ክምችትዋን ኢትዮጵያ ልታስወግድ በዝግጅት ላይ መሆንዋ ተሰማ፡፡

በሕገወጥ መንገድ የሚካሄድ የአራዊት አደን ለመከላከል በሚመክር በለንደን የተካሄደ ጉባኤ ላይ ነው፡፡ ኢትዮጵያም በአለም አቀፍ ደረጃ የዝሆን ጥርስ ዝውውርን ሕገወጥ ንግድን ለመግታት ያከማቹትን የዝሆን ጥርስ ለማስወገድ እርምጃ ከሚወስዱ ሀገራት ተርታ ለመመደብ ፍቃደኛ መሆንዋን የኢትዮጵያ መንግስት ከፍተኛ ባለስልጣን መንግስታቸው ፍላጐት እንዳለው ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት በተለያዩ ጊዜያት በሕገወጥ መንገድ ሲዘዋወር ያገኘውን በሕገወጥ አደን ምክንያት የተገኙ 6.3 ቶን የሚመዝን ወይንም ከ 600 ዝሆኖች ላይ የተወሰደ የዝሆን ጥርስ ክምችትዋን በጥብቅ ጥበቃ እንደተደረገለት በአንድ

በተለያዩ የኮንስትራክሽን ዘርፍ ላይ በመሰማራት በሪል ስቴት የመኖሪያ ቤቶችንና የመሸጫ ሱቆችን ገንብቶ ለተጠቃሚው በማስረከብ የሚታወቀው ፍሊንት ስቶን ሆምስ በቅርቡ ደግሞ በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ማለትም ለልብስ፣ ለቆዳና ለጫማ ማምረቻ ማከማቻና መሸጫ አገልግሎት የሚሆኑ ሱቆችን የያዘ ህንፃ መሸጥ መጀመሩን አስታውቋል፡፡

"ክላስተር ላይት እንዱስትሪ ቢዩልዲንግ የተባለው ፕሮጀክት ግንቦት 9/2006 በይፋ ተግባራዊ ሲሆን በጫማ ሰፊ፣ በልብስ፣ በቆዳና በህትመት ሰራዎች የተሰማሩ የኢንተርፕራይዞችን ለማስተሳሰር የማምረቻና የመሸጫ ሱቆችን ከእነ ሙሉ የማሽን መሣሪያዎቹ በመሸጥ ላይ መሆኑን የፍሊንትስቶን ኢንጂነሪንግ ድርጅት ስራ አስኪያጅ ለዕንቁ ተናግረዋል፡፡

የዓመቱ በጎ ሰው ሽልማት ሥነ-ሥርዓት ቅዳሜ ግንቦት 30 ቀን 2006 ዓ.ም በኢሊሊ ሆቴል ከአምስት መቶ በላይ ክቡራንና ክቡራት እንግዶች በተገኙበት እንደሚካሄድ የሽልማት ኮሚቴው ሰብሳቢ ዳንኤል ክብረት አስታውቋል፡፡ ታዋቂው ሰባኬ-ወንጌል ዳንኤል ክብረት ለዝግጅት ክፍላችን እንደገለጸው ከሆነ በሕዝብ ጥቆማ ለሽልማት ከታጩት 120 የበጎ ሥራ ባለሙያ ኢትዮጵያውያን መካከል ከሠላሳ በላይ የሚሆኑት ልቀው በመገኘታቸው ለመጨረሻው ዙር የተሸላሚነት ፍልሚያ ቀርበዋል፡፡

በሰባት መሥፈርቶች ተወዳዳሪዎቹን የሚለዩትና ዋናዎቹን ተሸላሚዎች አንጥረው የማውጣት ኃላፊነት የተሰጣቸው ዳኞችም ሽልማቱ

ዙሪያ ተበትነው የሚገኙትን አፍሪካውያን የጤና ባለሙያዎች ወደ አፍሪካ በአጭርና በረዥም ጊዜ አምጥቶ ለመጠቀም ወይም ባሉበት ሆነው ዩኒቨርሲቲዎችንና ሆስፒታሎችን የሚያግዙበትን መንገድ ለመቀየስ እንዲሁም አፍሪካውያን የጤና ባለሙያዎችና ሳይንቲስቶች እንዲቀራረቡና የእርስ በርስ የልምድ ልውውጥ እንዲያደርጉ ሁኔታዎችን ለማመቻቸት ነው፡፡

አዘጋጆቹ ጨምረው እንደገለጹት ጉባኤው በኢትዮጵያ የተካሄደው ኢትዮጵያ በጤናው መስክ ባስመዘገበችው ዕመርታ ነው፡፡ ጉባኤውን በንግግር የከፈቱት ፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመ በበኩላቸው ኢትዮጵያ በጤናው መስክ ብዙ ርቀት መጓዟን ጠቅሰው የምዕተ ዓመቱን የልማት ግብ ከሚያሳኩ ሀገሮች አንዷ እንደሆነችም አስገንዝበዋል፡፡ በጉባኤው ብዙ ጥናታዊ ጽሑፎች ቀርበው ሰፊ ውይይቶች ተካሂዶባቸዋል፡፡

የመላው አፍሪካ ሜዲካል ዶክተሮች ጉባኤ ተካሄደ

በጎ አድራጊ ኢትዮጵያውያን ይሸለማሉ

ፈሊንስቶን ሆምስ የመሸጫ ሱቆች

ፕሮጀክቱን በይፋ ጀመረ

በናይጄሪያ በፈነዳው ቦንብ ከ 46 በላይ ሠዎች ተገደሉ

በሚሰጥበት ቀን የተሸላሚዎቹን ስም ይፋ ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቀል፡፡ ባለፈው ዓመት በተከናወነው መሰል ሥነ-ሥርዓት ላይ በተሠማሩበት የሙያ ዘርፍ መልካም ተግባር ላከናወኑ አራት ኢትዮጵያውያን ሽልማት የሰጠው አሸላሚ ኮሚቴው በቀደመ ተግባሩ አድናቆት እንጂ ነቀፌታ እንዳልገጠመው ግልጽ አድርጓል፡፡ “የሽልማቱ ዋና ዓላማ በኢትዮጵያ ውስጥ በጎ ሰዎችን በማበረታታት ሌሎች መሰሎቻቸውን ማፍራትና አርዓያዎቻችንን በሕይወት ሳሉ መሸለምና ለመልካም ድርጊታቸው ዋጋ መስጠት ነው” ያለው ዳንኤል ክብረት፤ ወደፊትም በዚህን መሰሉ ተግባር እንደሚገፋበትና ሌሎችም ወገኖች ተሳትፎ ቢያደርጉበት ለሀገርም ይሁን ለወገን እንደሚበጅ አሳስቧል፡፡

ምድር ቤት ውስጥ በሚገኝ ክፍል ውስጥ ከወለሉ እስከ ጣሪያው ድረስ ተቆልሎ እንደሚገኝና በእጅግ ከባድ በሆነ ብረት በተሠራው በዚሁ የማካማቻ ክፍል ተቆልፎበት ቁልፉን በብቸኝነት የያዘው ተሬሳ በያታ የተባለ የመጋዘኑ ኃላፊ መሆኑን ቁልፉን እጅግ በጥንቃቄ እንደያዘውና ለሚስቱ እንኳን የሚያስቀምጥበትን እንደማያሳይ ቃለምልልስ ለአደረገው የዕንቁ ጋዜጠኛ ተናግሯል፡፡

ዘቴሌግራፍ የተሰኘው የእንግሊዝ ታዋቂ ጋዜጣ ዘጋቢ ባልተለመደ መልኩ የኢትየጵያ መንግስት በሕገወጥ አዳኞችና አዘዋዋሪዎች የወረሰውን የዝሆን ጥርስ ክምችን ለማየትና ፎቶ ለማንሳት ፈቃድ እንዳገኘ ዘግቦአል፡፡

በኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን መሰሪያ ቤት ስር የሚተዳደረው በዚሁ የዝሆን ጥርስ ማከማቻ መጋዘን ካሉ የዝሆን ጥርሶች ክብደቱ አንድ ሙሉ ሰው የሚያክል 116 ኪሎ የሚመዝን ጥርስ እንዳለ የዘገበው የቴሌግራፍ ጋዜጣ ዘጋቢ ከክምችቱ ውስጥ በእንጨት ሳጥን ውስጥ ታሽጐ ከላዩ ላይ መድኃኒት የሚል ታግ የተለጥፎለት ከሀገር ሊወጣ ሲል ተይዞ የተወረሰ በረካታ የዝሆን ጥርስ በኢትዮጵያ ጉምሩክ ፈታሾች ጥረት ተይዞ መወረሱን ኃላፊዎች መናገራቸውን ዘግቦአል፡፡

ኢትዮጵያ አስራ አንድ ሚሊዮን ፓውንድ የሚያወጣ የዝሆን ጥርስ ክምችት ልታወስግድ ነው

ከአዲስ አበባ በ47 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ቢሾፍቱ ከተማ በ 3200 ካሬ ሜትር ስፋት ላይ በአርባ ሚሊዮን ብር የተገነባው አሻም አፍሪካ ሆቴልና ሪዞርት አገልግሎት መስጠት ጀምሯል፡፡ 32 የአፍሪካ ሀገራትን ስያሜ የያዘ መኝታ ቤትን ጨምሮ የተለያዩ አለም አቀፍ ስታንዳርድ ያሟሉ አገልግሎቶችን የሚሠጠው አሻም አፍሪካ ሆቴልና ሪዞርት የአህጉሪቱ ታዋቂ የሥነ-ጥበብ ሠዓሊዎች አሻራ ያረፈባቸው የስዕልና ፎቶ ግራፍ ውጤቶችን የያዘ ጋለሪም በውሥጡ ይዟል፡፡

አሻም አፍሪካ ሆቴልና ሪዞርት የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር፣ የሀገራት አምባሳደሮች፣ ዲፕሎማቶች ታዋቂ ግለሠቦች እና ጥሪ

በ 40ሚሊዮን ብር በቢሾፍቱ ሀይቅ ላይ የተገነባው አሻም አፍሪካ ዓለም

አቀፍ ሆቴልና ሪዞርት ተመረቀ

6 °”l 6— ¯Sƒ lØ` 119 ግንቦት 2006 ዓ.ም

ፊቸር

የግንቦት ሃያ 23ኛ ዓመት በተለያዩ ዝግጅቶች በመከበር ላይ ነው፡፡ ኩነቱን ምክንያት በማድረግ የመንግሥት መገናኛ ብዙኃንና የድርጅቱ (ኢሕአዴግ) አመራሮች ግንቦት ሃያ ለሀገራችን “አስገኝቷቸዋል” የሚሏቸውን ትሩፋቶች እየዘረዘሩ የተለያዩ ዘገባዎችን በማቅረብ ላይ ናቸው፡፡ የዕንቁ ባልደረቦች በበኩላቸው ግንቦት ሃያ “መጣብን ወይስ መጣልን?” ሲሉ ይጠይቃሉ፡፡

ግንቦት ሃያን በሚመለከት፣ የመንግሥት መገናኛ ብዙኃንና የኢሕአዴግ አመራሮች የሚያስቀምጧቸው የተለመዱ ተረኮች አሉ፡፡ “ሀገራችን የዛሬ ሃያ ሶስት ዓመት መስቀለኛ መንገድ ላይ ነበረች፤ የብተና አደጋ ተጋርጦባት ነበር፤ ከዚህ ሁሉ አደጋ የታደጋት ኢሕአዴግ የሚመራው መንግሥት ነው” ወዘተ ይባላል፡፡ የኢሕአዴግ መሪዎች እንደሚሉት አሁንም ቢሆን ሀገራችንን ከአደጋ ሊታደጋት የሚችለው የኢሕአዴግ መስመር ብቻ ነው፡፡ ሕዝቡም ወይ የኢሕአዴግን ‹‹ልማታዊና ዴሞክራሲያዊ›› መስመር ወይ ደግሞ የተቃዋሚዎችን ‹‹ፀረ-ልማትና ፀረ-ዴሞክራሲያዊ›› መንገድ ሊመርጥ እንደሚችል፤ የተቃዋሚዎችን መስመር መከተል ግን ሀገሪቱን ወደ ጥፋት እንደሚወስዳት አበክረው ሲገልጹ ቆይተዋል፡፡ ለመሆኑ በአገዛዙ በኩል ሲነገሩ የቆዩትና በመነገር ላይ ያሉት ነጥቦች ምን ያህል ውሃ የሚቋጥሩ ናቸው? የተወሰኑትን እንመርምራቸው፡፡

የኢኮኖሚው ሁኔታ አገዛዙ በተለያዩ ሰነዶቹ እንደሚገልጸው

ከተሃድሶው በፊት ባሉት 10 ዓመታት ውስጥ ያለምንም የጠራ ርዕዮተ-ዓለምና ስትራቴጂ ሲንገዳገድ ቆይቶ በድርጅቱ በተለይ በሕወሓት ውስጥ የተከሰተው መከፋፈል (የተወሰኑትን አመራሮች ከአባልነት በማስወገድና የተወሰኑትን በማሰር) ከተወገደ በኋላ በተሃድሶው ወቅት የተለያዩ የልማት ስትራቴጂዎችን ቀርፆ መንቀሳቀስ በመጀመሩ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ማስመዝገብ ችሏል፡፡ በተለይ ላለፉት ስምንት ዓመታት በተከታታይ ሲመዘገብ የቆየው ዕድገት የስትራቴጂውን ትክክለኛነት ያረጋገጠ እንደሆነ በሰፊው ይነገራል፡፡

ኢትዮጵያ ውስጥ መንግሥት የሚለውን ያህል ባይሆንም ኢኮኖሚዊ ዕድገት መኖሩን ብዙ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች መስክረዋል፡፡ በቅርቡ ሙዲስና ፊችና ስታንደርድ ኤንድ ፑር የተባሉት የተባሉት ታዋቂ ዓለም አቀፍ ድርጅቶችም የሀገሪቱን የኢኮኖሚ ሁኔታና ብድር የማግኘት ዕድሏን ገምግመው ሁለቱም ድርጅቶች ቢ አንድ (B1) ሰጥተዋታል፡፡ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት መኖሩን ላለፉት አሥርት ዓመታት የተሠሩትን መንገዶችና፣ ግድቦችና ሌሎች መሠረተ ልማቶችን እንዲሁም በግሉ ዘርፍ የሚሠሩ ፕሮጀክቶችንና ሌሎች እንቅስቃሴዎችን በመመልከት ማንም ሊመሰክርለት ይችላል፡፡ መጠኑ ቢያከራክርም ዕድገት ስለመኖሩ

የብዙዎች ይስማማሉ፡፡ ጥያቄ የሚነሳው ዕድገቱ ምን ዓይነት ዕድገት ነው? ከዕድገቱ ተጠቃሚ የሆኑት ወገኖች እነማን ናቸው? ወዘተ በሚሉት ነጥቦች ላይ ነው፡፡

የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅትና ዓለም ባንክ በተደጋጋሚ እንደገለጹት የኢትዮጵያ መንግሥት በኢኮኖሚው ውስጥ ያለው ተሳትፎ እጅግ የተጋነነና አሳሳቢ ነው፡፡ የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት የኢትዮጵያ መንግሥት በኢኮኖሚው ውስጥ ያለው ተሳትፎ እጅግ የተጋነነ (በዓለም በኢኮኖሚ ውስጥ ከፍተኛ ተሳትፎ ከሚያደርጉ ሶስት መንግሥታት አንዱ ነው) በመሆኑ የግሉን ዘርፍ ዕድገት እያቀጨጨው ነው፤ ስለዚህም ተሳትፎውን መቀነስ እንዳለበት ሲያሳስብ ቆይቷል፡፡ ስለዚህ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ቢኖርም ዕድገቱ በግሉ ሴክተር እንቅስቃሴ የተመዘገበ አለመሆኑ ደግሞ ግልጽ ነው፡፡ ይህ አንዱ ችግር ነው፡፡

ሌላም ነጥብ አለ፡፡ የግል ዘርፍ የሚባለው አካልም በብዙ መልኩ ሊታይ የሚገባው ነው፡፡ በአንድ በኩል አቶ ክቡር ገና በአንድ ጽሑፋቸው እንዳሉት ከመንግሥትና ከመንግሥት ባለሥልጣናት ጋር አብረው በመሥራት በጣም በአጭር ጊዜ የከበሩ ‹‹ፓራሹት ነጋዴዎች›› አሉ፡፡ እነኝህ አካላት በጥቂት ዓመታት ውስጥ በሚያስገርም ፍጥነት የብዙ መቶ ሚሊዬን ባለንብረቶች የሆኑ ናቸው፡፡ ከዕድገቱ በከፍተኛ ደረጃ ተጠቃሚ የሆኑት እነኝህ አካላት ናቸው፡፡

በኢንዶውመንት ስም የሚንቀሳቀሱት ግዙፍ የፓርቲ ድርጅቶችም በግሉ ዘርፍ ሥር የሚጠቃለሉ ናቸው - በመንግሥትም በዓለም አቀፍ ድርጅቶችም፡፡ ይሁን እንጂ እነኝህን ግዙፍ ድርጅቶች በኃላፊነት የሚያንቀሳቅሷቸው የኢሕአዴግ መሪዎች መሆናቸው ደግሞ የታወቀ ነው፡፡ የአገዛዙ መሪዎች የሚመሯቸው ድርጅቶች ከሌላው የግል ዘርፍ አኩል ይንቀሳቀሳሉ፤ የበለጠ እንክብካቤ አይደረግላቸውም ማለት በጭራሽ አይቻልም፡፡ እንደሚታየውም በግል ጥረቱ የሚፍጨረጨረው ነጋዴ ከጊዜ ወደ ጊዜ ከገበያ ውጪ ሲሆን እነኝህ ድርጅቶች በአንጸሩ እየገነኑ በመሄድ ላይ ናቸው፡፡ አቶ ስብሃት ነጋ በአንድ ወቅት ለአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ እንደገለጹት ዛሬ በኢትዮጵያ ውስጥ የኤፈርትን ያህል ትልቅ ሀብት የሚያንቀሳቅስ ድርጅት የለም፡፡ ድርጅቱ ይህን ያህል ግዙፍ ሀብት ያፈራው ባለፉት ሃያ ሶስት ዓመታት ውስጥ ነው፡፡ እንዴት እንደዚህ ሊያድግ ቻለ? በኢኮኖሚው ውስጥ ያለ ያልተፈታ ጥያቄ ነው፡፡

ኢኮኖሚያው ዕድገቱ በጥረቱ የሚንቀሳቀሰው የግል ባለሀበት የተመዘገበ አለመሆኑ ዋናው የሀገሪቱ ራስ ምታት ነው፡፡ ዕድገቱ የተገኘው በአብዛኛው በመንግሥት እንቅስቃሴ ነው፡፡ መንግሥት ለተለያዩ የልማት ተግባራት የሚያወጣው አብዛኛው ገንዘብም በብድር የተገኘ መሆኑም ይታወቃል፡፡ ከዕድገቱ የሚጠቀሙት አካላት ደግሞ የመንግሥት አካላትና ከእነሱ ጋር አብረው የሚሠሩት ‹‹የፓራሹት ነጋዴዎች›› ናቸው፡፡ ሌላው ሁሉ የበይ ተመልካች ነው፡፡ በዚህ ዓይነት ግልጽነትና ተጠያቂነት በሌለበት የቢዝነስ ከባቢ ውስጥ ሕገ-ወጦች ሲያድጉ በጥረታቸው ለማደግ

የሚንቀሳቀሱት ከገበያ ውጪ ይሆናሉ፡፡ ብሔራዊ ከበርቴ መፍጠር አይቻልም፤ አልተፈጠረም፡፡

‹‹ግብርና መር የኢንዱስትሪ ልማት ስትራቴጂው በጣም ውጤታማ ነው፤ ሚሊየኖችን ሚሊየነር አድርጓል›› ሲባል የቆየ ቢሆንም አርሶ አደሩ አሁንም እንደድሮው (ወይም ከዚያ በባሰ ሁኔታ) ከእጅ ወደ አፍ የሆነ ሕይወት በመምራት ላይ ነው፡፡ የታየ መዋቅራዊ ለውጥ የለም፡፡ እንደታቀደው እንኳን ግብርናው አድግ ኢንዱስትሪውን ሊመራው ይቅርና ራሱን አርሶ አደሩንም መመገብ አልቻለም፡፡

በአጠቃላይ፣ አንደኛ ዕድገቱ በራስ ሀብት እና/ወይም ባለሀብት የተገኘ አይደለም፡፡ በዚህ ምክንያት በመንግሥትና በብድር ላይ የተንጠለጠለ በመሆኑ ቀጣይነቱ አጠራጣሪ ነው፡፡ ከሁሉ በላይ ደግሞ፣ ዕድገቱ ፍጹም ፍትሃዊ አይደለም፡፡ ከገዥው ኃይል ጋር ንክኪ ያለው ቡድን ፍጹም ባልተጠበቀ ፍጥነት ሲመነደግ አብዛኛው ሕዝብ አሁንም የበይ ተመልካች ነው፡፡ በሀገራችን ባለፉት ሃያ ሶስት ዓመታት ከታዩት አዳዲስ ጉዳዮች አንዱ የፖለቲካ ሥልጣኑን የያዘው ኃይል ራሱን በከፍተኛ ደረጃ በኢኮኖሚው እንቅስቃሴ ውስጥ ማስገባቱ ነው፡፡ በጣም የተደራጀ የፖለቲካ መደብ ተፈጥሯል፡፡ ዕድገቱ እንደሚባልለት አይደለም፡፡ እንዲያውም አደጋ ያረገዘ ነው ለማለት ነው፡፡

የፖለቲካው ሁኔታ በእርግጥም የአገዛዙ መሪዎች

እንደሚሉት ባይሆንም ሀገራችን የዛሬ ሃያ ሶስት ዓመት ችግር ላይ ነበረች፡፡ ሕዝቡ ለአሥርት ዓመታት ጨቁኖና አስጨንቆ ሲገዛው የነበረው የደርግ አገዛዝ በመውደቁ ቢደሰትም (መደሰቱን ተቃዋሚዎችን በመርዳትና ለአገዛዙ ድጋፉን በመንፈግ ገልጿል) ሽምቅ ተዋጊዎች በያዙት አቋም ላይም ከፍተኛ ጥርጣሬ ነበረው፡፡ በዚህ ምክንያት ብዙ ስጋቶች ነበሩ፡፡ ይህ እውነት ነው፡፡ መረጋጋት የተፈጠረው ግን አሸናፊ የሆነና የታጠቀ ብቸኛ ኃይል (ኢሕአዴግ) በመኖሩ እንጂ እንደሚባለው ሁሉንም ያሳተፈ የሽግግር መንግሥት በመፈጠሩ ቅሬታ ያለው አካል በመጥፋቱ አልነበረም፡፡

በኃይልም ቢሆን ግን ሠላም በመፈጠሩና ኢሕአዴግ ሥልጣን ከጨበጠ በኋላ የመድበለ ፓርቲ ሥርዓት ለመመስረት እንደሚሠራ፣ የመደራጀትና የመናገርና የመጻፍ ነጻነትን እንደሚያከብር ወዘተ በመግለጹ ብዙዎች ተስፋቸው ከፍተኛ ነበር፡፡ ይህን ተስፋ አንግበው ወደሀገራቸው የገቡ ብዙ ወገኖችም ነበሩ፡፡ ከእነኝህ ውስጥ አንዳንዶቹ ተመልሰው የአገዛዙ ጠንካራ ተቃዋሚዎች ለመሆን በቅተዋል፡፡ ይህ ሁሉ ያለ ምክንያት አይደለም፡፡

የኢሕአዴግ መሪዎች በዓለም አቀፍ ደረጃ በተከሰተው የርዕዮተ-ዓለም ለውጥ ምክንያት ጥርሳቸውን የነቀሉበትን የኮምኒስት (በተለይ “የአልባንያ ሲሻሊዝም”) ትተው ‹‹ነጭ ካፒታሊዝም›› ያሉትን ርዕዮትና ዴሞክራሲያዊ ሥርዓትን እንደሚከተሉ ቢያውጁም ሃቀኛ ለሆነ የመድበለ-ፓርቲ ሥርዓት ፍቅር እንደሌላቸው በብዙ ከመጀመሪያው ጀምሮ ታይቷል፡፡ በሽግግሩ ወቅት ሁሉም ድርጅቶች በፖለቲካ ሂደቱ እንዳይሳተፉ ከማድረግ ጀምሮ የተሳተፉትም ቢሆኑ በልዩ ልዩ

ግንቦት 20የወለደው የመለያየት አደጋ!

7°”l 6— ¯Sƒ lØ` 119 ግንቦት 2006 ዓ.ም

ጥላቻውና ቂም በቀሉም አለ፡፡ የተፈጠረውን የፌደራል አደረጃጀት ተጠቅመው በየክልሉ የከበሩ የመንግሥት ኃላፊዎች እና/ወይም ‹ኤሊቶች› ሕዝቡ እርስ በርሱ እንዲናከስ አበክረው ይሠራሉ፡፡ በዚህ ምክንያት ባልተለመደ መልኩ ብዙ የብሔረሰብ ግጭቶች ተከስተዋል፡፡ አሁንም በብዙ ቦታዎች በቋፍ ላይ ያሉ ግጭቶች አሉ፡፡ ሁሉም በየቤቱ ቂም በቀል እያረገዘ ‹‹እህህ›› ማለት ጀምሯል፡፡ አገዛዙ እንደሚለው ሳይሆን አሁንም ከዩጎዝላቪያ፣ ሩዋንዳ ወይም ሶማሊያ ሁኔታ ብዙም ፈቀቅ አላልንም፡፡ እንዲያውም አሁን ሁኔዎችን ይበልጥ ለመለያየት ምቹ አድርገናቸዋል ማለት ይቻላል፡፡ መለያየቱም በሠላም ሊፈጸም የሚችል አይሆንም፡፡

የቤት ሥራቸውን ያልሠሩ ሀገራት ምን ያህል ዕድገት ቢያስመዘግቡ፣ ምን ያህል የዜጎች የነፍስ ወከፍ ገቢ ቢያድግ፣ ግሩም ግሩም መሠረተ ልማቶችን ቢገነቡ፣ ምን ያህል ለረዥም ጊዜ የዘለቀ ሰላም (በጭቆና ውስጥ ያለ ሰላም ሰላም ከተባለ) ከብጥብጥ እንደማያመልጡ እነሊቢያ አሳይተውናል፡፡ ትልቅ አብነቶች ናቸው፡፡ ያች ዜጎቿን እየከፈለች ታስተምር የነበረችው ሊቢያ በጎሣ ከአምስት ስድስት ተከታትፋ፣ እነዚያ የሚያማምሩ ወደቦቿና ከተሞቿ ወድመው የጦር አበጋዞች መፈንጫ ሆናለች፡፡ ዜጎቿ በየጎሣው ተቧድነው መተጋተጉን ይዘውታል፡፡ የሶሪያም ሁኔታ ተመሳሳይ ነው፡፡ እኛስ ወዴት እያመራን ነው? አንዳንዶች ኢሕአዴግና ኢሕአዴግ የዘረጋው ብሔረሰብ-ተከል የፌደራል ሥርዓት ለሁለት አሥርት ዓመታት መዝለቁ በራሱ የተዘረጋው ሥርዓት ጥንካሬ እንደሆነ አድርገው ይገልጻሉ፡፡ ይህ ግን በጭራሽ ውሃ የሚቋጥር አመክንዮ አይደለም፡፡ ለመሆኑ ጋዳፊ የሚመሩት ሥርዓት ለስንት ዘመን ኖረ? የአሳድ ቤተሰቦች የሚመሩት ጨቋኝ ሥርዓት ለስንት ጊዜ ቆየ? ራሳችንን ካላሞኘን በስተቀር መንገዳችን እጅግ ፈታኝና ተስፋ አስቆራጭ እየሆነ ነው፡፡ ለዚህ ነው ግንቦት ሃያ መጣልን ወይስ መጣብን ብሎ መጠየቅ አስፈላጊና ወቅታዊ የሚሆነው፡፡

ከዋቢዎች1. ኢሕአዴግ፣ ዴሞክራሲና ዴሞክራሲያዊ

አንድነት በኢትዮጵያ (1997 ዓ.ም.)2. ኢሕአዴግ፣ አገራዊ ለውጦች ቀጣይ

ፈተናዎችና አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ መፍትሔዎች (2000 ዓ.ም.)

3. Oktay F. Tanrisever, why are Federal arrangements not a panacea for containing ethnic nationalism? Lessons from the post-soviet Russian experience (2009)

4. ገብሩ አስራት፣ የኢሕአዴግ አብዮታዊ ዴሞክራሲና ችግሮቹ (2002)

5. Samuel Huntington, political Development in Ethiopia: a peasant based dominant party democracy (1993)

ፊቸር

መንገድ ከሂደቱ እንዲወጡ ተደርጓል፡፡ ከቀዝቃዛው ጦርነት ማብቃት በኋላ ሊብራል ዴሞክራሲ አሸናፊ ሆኖ በመውጣቱና ምዕራባውያን ሀገራትና የገንዘብ ድርጅቶች ብድርና ዕርዳታን ከዴሞክራሲ/ዴሞክራታይዜሽን ጋር በማያያዛቸው ምክንያት ኢሕአዴግ ገንነው እስካልወጡ ድረስ የሌሎችን ድርጅቶች መኖር በተወሰነ ደረጃ ይፈልገው ነበር፡፡ የምርጫ- አምባገነን የሚባሉትን ሀገራት ፈለግ ሲከተል ቆይቷል፡፡

ኢትዮጵያ ባለችበት ሁኔታ ጠንካራ መንግሥት እንደሚያስፈልጋት እና ያንን ጠንካራ መንግሥት ሊመራ የሚችል ጠንካራ ድርጅት እንደሚያስፈልግ ለኢሕአዴግ መሪዎች ምክር ከለገሱ ምሁራን መካከል የታወቁት የሀርቨርድ ዩኒቨርሲቲ ምሁር ፕሮፌሰር ሳሙኤል ሃንቲንግተን ተጠቃሽ ናቸው፡፡ ይሁን እንጂ የፕ/ር ሃንቲንግተን ምክር በሃሳብና በተግባር ልዕልናን/የበላይነትን (hegemony) ስለመያዝ እንጂ በጠብ-መንጃ እያስፈራሩ ወይም አንድ ለአምስት እያደራጁ ወዘተ በሁሉም ምርጫ ማሸነፍን አያካትትም፡፡ ሌሎች የምርጫ አምባገነኖች እንደሚያደርጉት ሁሉ የኢሕአዴግ መሪዎች የመረጡት ጠንካራ ፓርቲዎችን በጠብ-መንጃ አፈሙዝ ማዳከምና ማጥፋት፣ ለሥልጣን የማያሰጉ ድንክየና የተዳከሙ ድርጅቶች እንዲኖሩ ሁኔታዎችን ማመቻቸትና ወቅቱን የጠበቀ ምርጫ እያደረጉ መመረጥን ነው፡፡

የምርጫ-አምባገነናዊ ሥርዓቱን በአብዮታዊ ዴሞክራሲ፣ በልማታዊ መንግሥት ወይም ደግሞ በአውራ ፓርቲ ወዘተ ሥርዓታት ስም ለመቀባባት ይሞከራል፡፡ አገዛዙ በ1997 ዓ.ም ከደረሰበት አስደንጋጭ ውድድር ወዲህ በርግጎ የወሰዳቸው እርምጃዎች እውነተኛ ማንነቱን የሚያስገነዝቡና የሃሳብ ብዝኃነትን ለማስተናገድ ፍላጎት የሌለው መሆኑን የሚያጋልጡ ናቸው ማለት ይቻላል፡፡ በግሉ መገናኛ ብዙኃንና በሲቪክ ማኅበራቱ ላይ የደረሱትና የሚደርሱት አሉታዊና ዴሞክራታይዜሽኑን የማያግዙ እርምጃዎች ሁኔታውን ይበልጥ ግልጽ ያደርጉታል፡፡ አገዛዙ በዚኸው አስተሳሰብ እየተመራ ዋና ዋና ተቃዋሚዎችን አዳክሞ (ከራሳቸው የውስጥ ችግር ጋር) በምርጫ 2002 ዓ.ም. ማንነቱን በሚያጋልጥ መልኩ 99.9 በመቶ አሸነፍኩ አለ፡፡ ብዙዎች ይህን የምርጫ ውጤት ከታዘቡ በኋላ ከምርጫ-አምባገነናዊ ሥርዓት ወደ ብቸኛ ፓርቲ ሥርዓት እየሄድን ነውን ሲሉ ጠይቀዋል፡፡

ስለዚህ ኢሕአዴግ ጨቋኙን አገዛዝ የታገለው ለሕዝብ ነጻነትና ሉዓላዊነት እንደሆነ አበክሮ ቢገልጽም ያለፉት ሃያ ሶስት ዓመታት ተመክሯችን እንደሚያስገነዝቡን ከግንቦት 20/1983 ዓ.ም. በኋላም ቢሆን ያው በአምባገነን አገዛዝ ሥር መሆናችን ከመቼውም ጊዜ በላይ ግልጽ እየሆነ መጥቷል፡፡ ከጊዜ ወደ ጊዜ ከመሻሻል ይልቅ የተለየ ሃሳብ ያላቸውን ወገኖች የማይታገስ፤ የሃሳብ ብዝኃነትን የማይታገስ ደርጅት እየሆነ ነው ማለት ይቻላል፡፡ አሁንም እንደ ድሮው በፖለቲካ አቋማቸው ምክንያት ወደ ሀገራቸው የማይገቡ ኢትዮጵያውያን በዓለም ዙሪያ ይገኛሉ፡፡ አሁንም እንደ ድሮው ጋዜጠኞችና የተቃዋሚ ድርጅት መሪዎች ይሰደዳሉ፤ ገለልተኛ ማኅበራት እንዲጠፉ ይደረጋል ወዘተ፡፡ ምናልባት የተቀየረው ጭቆናው ሳይሆን የጭቆናው መንገድ ሳይሆን አይቀርም፡፡ ችግሩ ‹‹ሠላም ሰፍኗል፤ ልማት ላይ ነን፤ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መሥርተናል፤ በትክክለኛው የህዳሴ ጎዳና ላይ ነን›› ወዘተ በሚባልበት በአሁኑ ወቅት ሀገራችን መስቀለኛ መንገድ ላይ መሆኗ ነው፡፡

ኢትዮጵያ ወዴት? ‹‹ኢሕአዴግ ወደ ሥልጣን በመምጣቱና

ትክክለኛ ስትራቴጂ በመከተሉ ምክንያት ኢትዮጵያ ብዙዎች እንደገመቱትና እንደጠበቁት እልቂት አልተከሰተም፡፡ ሀገሪቱም እንደነ ዩጎዝላቪያ፣ ሩዋንዳ ወይም ሶማሊያ አልሆነችም፡፡›› ይላሉ የኢሕአዴግ ሰዎች፡፡ ኢትዮጵያ ከግንቦት ሃያ 1983 ዓ.ም. ወዲህ በዘረጋችው የፌደራል ሥርዓት ምክንያት ሠላም እንዳገኘች፣ በሕዝቡ መካከል ዴሞክራሲያዊ

አንድነት እንደተፈጠረም ይነገራል፡፡ አሁን የአፈጻጸምና ዴሞክራሲው ታዳጊ በመሆኑ ምክንያት እዚህም እዚያም ከሚፈጠሩ ጥቃቅን ግጭቶች በስተቀር ችግር እንደሌለ፣ ሀገራችን በህዳሴ ጉዞ ላይ ስለመሆኗም በብዛት ይወራል፤ ይጻፋል፡፡

በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያን የገጠማት አደጋ ልክ እንደድሮው አንድ ጨቋኝ አምባገነናዊ አገዛዝን መሸከሟ አይደለም፡፡ የወቅቱ ችግር በእጅጉ ከዚያ ያልፋል፡፡ ሁሉንም ዜጋ ሊያሳስበው የሚገባም ነው፡፡ ግንቦት ሃያ ሕዝቡ ከአንድ አስከፊ አምባገነናዊ አገዛዝ ተላቅቆ ወደተሻለ አገዛዝ የተሸጋገረበት ወሳኝ ምዕራፍ ነው ለማለት አይቻልም፡፡ ባለፉት አሥርት ዓመታት የተከሰቱትና አሁንም በመከሰት ላይ ያሉት ሁኔታዎች ይህን አያሳዩም፡፡ ሕዝቡ የጠበቀውን ዴሞክራሲ አላገኘም፡፡ ሲካሄዱ የቆዩት ምርጫዎች በአብዛኛው የአገዛዙ የቅቡልነት ማግኛ ወይም የመግዣ መሣሪያዎች ናቸው፡፡ የተሻለ ነጻነትና ውድድር የነበረው የ1997ቱ ብሔራዊ ምርጫም እንደታየው በገዥው ኃይልና በራሳቸው በተቃዋሚዎች ችግር ምክንያት በአሳዛኝ ተደምድሟል፤ እንዲያውም የዚያ ምርጫ ጦስ እስካሁንም ብዙ ችግሮችን እየወለደ ቀጥሏል፡፡ ሕዝቡ የተገባለት በነጻነት የመደራጀትና ሃሳቡን በነጻነት የመግለጽ መብቱ አልተከበረም፡፡ አሁንም ጋዜጠኞቸ ይታሠራሉ፤ ይሰደዳሉ ወዘተ፡፡

ይህ ሁሉ ግን የችግሩ በጣም አነስተኛው ክፍል ነው፡፡ ሌላ ሁሉንም ዜጋ የሚያሳስብና ሊያሳስብም የሚገባ የሀገሪቱን በሀገርነት መቀጠል አለመቀጠል የሚመለከት ችግር አለ፡፡ እንደሚባለው ግንቦት ሃያ የዴሞክራሲያዊ አንድነት መገንባት የተጀመረበት ወሳኝ የታሪክ ምዕራፍ ቢሆን መልክም ነበር፡፡ ግን አይደለም፡፡ እንደሚባለው ሳይሆን በገቢር እንደሚታየው ከግንቦት ሃያ 1983 ዓ.ም. በኋላ በኢትዮጵያውያን መካከል መለያየት፣ ጥላቻና ቁርሾ ነግሷል፡፡ ዜጎች በኢትዮጵያዊነታቸው በሁሉም አካባቢዎች ተንቀሳቅሰው መሥራት የማይችሉበት ሁኔታ ተፈጥሯል፡፡ ሁሉም በየክልሉ ተጠርንፎና ታጥሮ እንዲቀመጥ ተፈርዶበታል፡፡ ከክልሉ ወጪ የሚሄድ ካለ ያለቦታው እንደተገኘ ይቆጠራል፡፡ ምን ያህል አካባቢውን ቋንቋ ጠንቅቆ ቢያውቅም የመንግሥት ሥራ አያገኝም፤ የቤት መሥሪያ ወይም የንግድ ቦታ አይሰጠውም፤ እንዲያውም ‹‹አካባቢህ አይደለምና ውጣ›› ይባላል፡፡ እንደነዚህ ያሉ እጅግ የበዙ አጋጣሚዎችን ታዝበናል፤ ሁኔታው አሁንም ቀጥሏል፡፡

ቀደም ሲል በናይጀሪያና በሌሎች የአፍሪካ ሀገሮች ስንሰማቸው የቆየናቸው ሁኔታዎች በሀገራችን እየታዩ ናቸው፡፡ ዛሬ በሚያሳዝን መልኩ ዴሞክራሲያዊ አንድነት ተፈጥሯል በሚባልባት ኢትዮጵያ፣ ከአንዱ ወደ ሌላው ክልል መንቀሳቀስ ልክ ወደሌላ ሀገር እንደመሄድ እየተቆጠረ ነው፡፡ እንዲያውም ወደ ሌላ ሉዓላዊ ሀገር የሚሄዱት ወገኖች መብታቸው የተጠበቀ ነው ማለት ይቻላል፡፡ አንዱ አስፈሪ እውነታ ይህ ነው፡፡

ከግንቦት ሃያ 1983 ዓ.ም. በኋላ በኢትዮጵያውያን መካከል

መለያየት፣ ጥላቻና ቁርሾ ነግሷል፡፡ ዜጎች በኢትዮጵያዊነታቸው

በሁሉም አካባቢዎች ተንቀሳቅሰው መሥራት የማይችሉበት ሁኔታ

ተፈጥሯል፡፡ ሁሉም በየክልሉ ተጠርንፎና ታጥሮ እንዲቀመጥ

ተፈርዶበታል፡፡ ከክልሉ ወጪ የሚሄድ ካለ ያለቦታው እንደተገኘ

ይቆጠራል፡፡ ምን ያህል አካባቢውን ቋንቋ ጠንቅቆ ቢያውቅም

የመንግሥት ሥራ አያገኝም፤ የቤት መሥሪያ ወይም የንግድ ቦታ

አይሰጠውም፤ እንዲያውም ‹‹አካባቢህ አይደለምና ውጣ›› ይባላል

8 °”l 6— ¯Sƒ lØ` 119 ግንቦት 2006 ዓ.ም

ይድረስ ለዕንቁ

የአዘጋጁ መልእክት

ኢትዮጵያንን እየገነባናት ወይስ እያፈረስናት?

የመጽሔታችሁ ታዳሚ ነኝ፡፡ በዝግጅታችሁ ላይ ያስተዋልኩት መሻሻል አለ፡፡ የምታነሷቸው ሀገራዊ ጉዳዮች የእኔንም ፍላጎትና ሐሳብ የሚመለከቱ በመሆናችሁ ብዙውን ጊዜ እርካታ ይሰማኛል፡፡ ያም ሆኖ ግን ሥራዎቻችሁ ሙሉ በሙሉ የተዋጣላቸው ናቸው ማለት አይደለም፡፡ ለምሣሌ በዕንቁ 6ኛ ዓመት ቁጥር 117 ሚያዚያ 2006 ዓ.ም ‹‹የሶሻሊስት ፓርቲ ወቅታዊነት›› በሚል ርዕስ የቀረበው ጽሑፍ አስፈላጊነቱ ጎልቶ አልታየኝም፡፡ በዚህ አያየዛችሁ አንዳንዴ ጊዜው ያለፈበትንና ዓለም ተግባራዊ ማድረግ አቅቶት የተወውን የሶሻሊዝም ማለት የኮሚኒዝምን ርዕዮተ-ዓለም አስፈላጊነት ለመስበክ ሙከራ ማድረጋችሁ የምትጽፉበትን ጭብጥ ያጣችሁ ያስመስልባችኋል፡፡ ‹‹ሶሻሊዝም ብሎም ኮሚኒዝም›› የሚባለው ነገር መቼም ይሁን መቼ ኢትዮጵያ ውስጥ ሊሠራ ይቅርና ከቶውንም ሊሞከር የማይገባው ርዕዮተ-ዓለም ነው፡፡

በይሆናል ስሜታዊ ግፊት ተሞክሮ ያመጣውን ምስቅልቅልና ቀውስ ደግሞ

ለርዕዮተ-ዓለሙ ስርጸት በልኩ ያልተሰፋው የኢትዮጵያው ማኅበረሰብ አሳምሮ ያየው በመሆኑ፤ ጽንሰ-ሐሳቡ የቱን ያህል ጥሩ ቢሆን፤ የሚተገብረውም ይሁን በቃል ደረጃ የሚቀበለው ዜጋ ይኖራል ተብሎ አይታሰብምና ይኸው ርዕሰ-ነገር እንደ ትልቅ አጀንዳ ተቆጥሮ ብዕር የተነሳበት መሆኑ ብዙም አልደላኝም፡፡

ሌላው አርዓያ በማለት የምታቀርቧቸው ‹‹ታዋቂ›› የሚባሉ የኢትዮጵያ ልጆች ጉዳይ ነው፡፡ በርግጥ አርዓያነታቸው የጎላና በሀገር ውስጥም ይሁን በባሕር ማዶ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ወይም ‹‹ትውልደ-ኢትዮጵያውያን›› የሚባሉ መኖራቸው ይታወቃል፡፡ ግን ማንም ሆነ ማን አርዓያነቱ የሚመዘነው አንድ ግለሰብ ባለው ግላዊ እውቀቱ ብቻ አይደለም፡፡ በገንዘቡም አይደለም፡፡ ዋናው ነገር በእውቀቱም ይሁን በገንዘቡ ለሀገሩና ለወገኖቹ የሚጠቅም ምን ተግባር አከናወነበት በሚለው ነው፡፡ በነጮች መንደር፣ ማጀትና አደባባይ አዋቂ የሆኑ፣ የምርምር ተግባር ያከናወኑ፣ በነጮቹ አስተሳሰብና ዘረኛ አመለካከት ተቀይደው

አይደለም ሀገራቸውን እህት ወንድሞቻቸውን፣ እናት አባቶቻቸውን በአግባቡ ማስተማር፣ማሳወቅና መደጎም ይቅርና ማስታወስ ያልሆነላቸው የመንፈስ ምርኮኞች፤ በምንም መመዘኛ ለመጪው ኢትዮጵያዊ ትውልድ የበጎ አስተሳሰብ፣ የትጋትና የስኬታማነት አርዓያ ሊሆኑ አይችሉም፡፡

እንደነዚህ ዓይነት የኢትዮጵያ ልጆች እንደጠፉ ሆነው የሚቆጠሩ ናቸው፡፡ ሌላው ቀርቶ በመወለዳቸውና በስማቸው ካልሆነ በቀር ኢትዮጵያዊ ናቸው ለማለትም የማይቻሉ በመሆናቸው ስለነሱ አርዓያነት ለአንባቢያን ከመሰናዳቱ በፊት የጠፉት የኢትዮጵያ ልጆች አርዓያነት ምንድን ነው? የሚለው ሊጤን ይገባዋል፡፡ አንድ ኢትዮጵያዊ በእውቀት፣በችሎታ፣በታታሪነቱ የቱን ያህል በአሜሪካና በአውሮፓ ስሙ የጎላ ሆኖ ቢገኝም አርዓያ ሆኖ ሊመዘን የሚችለው ለሀገሩና ለወገኖቹ ጥቂትም ቢሆን ምን አበርክቷል? በሚለው ጥያቄ አሳማኝ መልስ ማግኘት ብቻ ነው፡፡

መሠረት ድልነሳው ከአዲስ አበባ.

የጠፉት የኢትዮጵያ ልጆች አርዓያነት ምንድን ነው?

ኢሕአዴግ ‹‹ዴሞክራሲና ዴሞክራሲያዊ አንድነት በኢትዮጵያ›› በሚለው ሰነዱ “በኢትዮጵያ ሕዝብ ፊት የተደቀነው ምርጫ ግልጽና ቀላል ነው፡፡ አንድም በጥገኝነት መንገድ ተጉዞ ወደ ፀረ-ዴሞክራሲ፣ ወደ እልቂትና ብተና መጓዝ ነው፤ አሊያም ጥገኝነትን መክቶ በአብዮታዊ ዴሞክራሲ ጎዳና ወደ ሰላም፣ ልማትና ዴሞክራሲ መራመድ ነው፡፡ ሌላ ምርጫ የለም፡፡ ምርጫው የሕልውና ጉዳይ ነው፡፡ ስለሆነም ማንኛውም ኢትዮጵያዊ መሀል ሰፋሪና ታዛቢ ሆኖ ሊያልፈው የሚችል አይደለም፡፡ አንድም የሰላም የልማትና የዴሞክራሲ ወገን ሆኖ ይሰለፋል፣ አሊያም በማወቅም ሆነ ባለማወቅ የጥፋትና የጥገኝነት ሀይል ይሆናል፡፡ ወጣቱ በተለይም ወጣቱ ምሁር የሀገር ተረካቢና መሪም በመሆኑ የሚሻለውን መርጦ ሚናውን መለየት ይጠበቅበታል፡፡” ይለናል፡፡

አገዛዙ የኢትዮጵያን ሁኔታ የሚያየው በዚህ መነጽር ነው፡፡ ይህን ነጥብ ይዘን ብዙ ነገሮችን ማለት እንችላለን፡፡ ግንቦት ሃያን ምክንያት በማድረግ የተወሰኑትን እንያቸው፡፡ ከሁሉ አስቀድሞ፣ ኢሕአዴግ በተለይ ሕወሓት የትጥቅ ትግል እንዲያካሂድ ካስገደዱት ምክንያቶች መካከል የደርግ አገዛዝ የዜጎችን ነጻነት በማፈኑ እንደሆነ አበክሮ መግለጹ ይታወቃል፡፡ ድርጅቱ ደርግን አስወግዶ የሥልጣን መንበሩን ከጨበጠ በኋላም የሕዝቡን የመደራጀት፣ ሐሳቡን በነጻነት የመግለጽ ወዘተ መብቶች እንደሚያከብርና የመድበለ ፓርቲ ሥርዓትን እንደሚፈቅድ ቃል መግባቱ ይታወሳል፡፡ እነኚህ መብቶች መጀመሪያ በሽግግሩ ቻርተር ቀጥሎም በሕገ-መንግሥቱ ተቀምጠዋል፡፡

በነጻነት የመደራጀት መብትና የመድበለ-ፓርቲ ሥርዓት ተረጋግጧል ይባላል፡፡ ይሁን እንጂ፣ ኢሕአዴግ ከልቡ የመድበለ-ፓርቲ ሥርዓትን እንደማይቀበልና ለዚህም እንደማይሠራ ከላይ የቀረበው ሃሳብ ያረጋግጣል፡፡ በአንድ በኩል ፓርቲዎች በነጻነት እንዲንቀሳቀሱ ሕገ-መንግሥትን አክብሬ እሠራለሁ ይላል፡፡ ይሁን እንጂ ሕዝቡ ያለው ምርጫ ኢሕአዴግን ብቻ ነው፤ የቀረው የጥፋት መንገድ ነው ይላል፡፡ በእርግጥ አንድ የፖለቲካ ድርጅት ራሱን ከፍ ከፍ ቢያደርግና ሌሎች ደካሞችና የማይጠቅሙ እንደሆኑ ቢገልጽ ሊገርም አይችልም፡፡ በየትኛውም ሀገር የተለመደ ነውና፡፡ የኢሕአዴግ አቋም እጅግ አደገኛ የሚሆነው ድርጅቱ “ለኢትዮጵያ ሕዝብ ያለሁት ብቸኛ አማራጭ እኔ ብቻ ነኝ ከእኔ ውጪ ያለው አጥፊና ለኢትዮጵያ ሕልውና የማይጠቅም ነው” ማለቱ ነው፡፡

ከላይ የተጠቀሰው ሰነድ በግልጽ እንደሚያስረዳው ኢሕአዴግ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ድባብ በዴሞክራትና ፀረ-ዴሞክራት፣ በልማታዊና በጥገኛ/ኪራይ ሰብሳቢ …ወዘተ ድርጅቶች ትግል የተወጠረ ነው፡፡ በ1997ቱ ብሔራዊ ምርጫ ማግስት እንደታየው ኢሕአዴግ የሚገዳደሩትን ድርጅቶች በፀረ-ዴሞክራት፣ በጥገኛነትና በሀገር አጥፊነት ፈርጆ የሀገሪቱን ሕልውና በመጠበቅ ስም በጠበም-መንጃ አፈሙዝ ከመታገል አይመለስም፡፡ ለነገሩ አንድ ድርጅት ከመነሻው በፖለቲካ ተቀናቃኝነት ሳይሆን በጠላትነት ከተፈረጀ መጥፋቱ ሊገርም አይችልም፡፡ ይህ ድርጅቶችን ሁሉ በጠላትነት የሚፈርጅና ከሲቪል ፖለቲካዊ አስተሳሰብ ጋር የተጣላ አስተሳሰብ

አሁንም በሰፊው እየተሰራበት ይገኛል፡፡ ኢሕአዴግ አሁንም በሰነዶቹ ይህን አስተሳሰብ አጠንክሮ እያራመደው ይገኛል፡፡ አሁንም “ከእኔ ውጪ ያሉት ድርጅቶች ለኢትዮጵያ ሕልውና የማይጠቅሙ፣ ፀረ-ዴሞክራቶች፣ ጥገኞችና አጥፊዎች ናቸው፡፡” ይላል ኢሕአዴግ፡፡

ይህ አስተሳሰብ እስካልተቀየረ ድረስ በነጻነት ስለመደራጀትና ስለመድበለ-ፓርቲ ሥርዓት ቢነገር ዋጋ የለውም፡፡ አፋኣዊ ነው፡፡ ቀደም ሲል ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች ሥርዓቱን እስካልተገዳደሩ ድረስ አምስትም አስርም የፓርላማ ወንበር እያገኙ እንዲኖሩ ይፈቀድላቸው ነበር፡፡ ከምርጫ 19997 ዓ.ም ወዲህ ግን ይህም አደጋ ላይ ወድቋል፡፡ ከአንድ ወንበር በስተቀር ሁሉም የፓርላማ ወንበሮች በኢሕአዴጋውያን ተሞልተዋል፡፡ አሁንም ቢሆን በአንድ ለአምስትም ይሁን በልማት ሠራዊት ስም የሚሰራው ይህንኑ ሁኔታ ለማስቀጠል መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ ሥርዓቱ ብዝኃነትን ያከብራል ይባላል፡፡ ይሁን እንጂ፣ አሁንም ከአገዛዙ የተለየ ሃሳብ ያላቸው ዜጎች አይፈለጉም፡፡ በጠላትነት ይፈረጃሉ፣ ይታሰራሉ፣ ይሳደዳሉ፡፡ ችግሩ እጅግ ብዙ ነው፡፡

ሁኔታው ይኸው ነው፡፡ የሚያሳዝነው በዚህ የሚያሳዝን ሁኔታ ላይ ባለንበት በአሁኑ ወቅት ችግሩን ከመፍታት ይልቅ ችግሩን ይበልጥ እያባባስነው ነው፡፡ ኢሕአዴግ አሁንም ከሃያ ሶስት ዓመታት በኋላ ራሱን እንደ ነፃ አውጭ እንጂ እንደ ሲቪል ድርጅት አይቆጥርም፡፡ ከሃያ ሶስት ዓመታት በኋላ አሁንም በሽምቅ ጦርነት ሥነ-ልቦና እየተመራን ነው፡፡ አሁንም ቁምጣ የታጠቁ ሽምቅ ተዋጊዎችን፣ የተቃጠሉ ታንኮችን፣ የሞቱ ኢትዮጵያውያንን በቴሌቪዥን እያየን ነው፡፡ ድርጅቱ ከሃያ ሶስት ዓመታት በኋላ ራሱን ወደ ሲቪል ድርጅትነት አለመለወጡ እጅግ የሚያሳስብ ብቻ ሳይሆን በነጻ ምርጫ ቢሸነፍም ሥልጣን ሊያስረክብ እንደማይችል የሚያስገነዝብም ነው፡፡ ሽምቅ ተዋጊ ድርጅት ሁልጊዜም ጦርነት ላይ ነው፡፡ ጦርነት ላይ የሆነ ድርጅት ሥልጣን ያስረክባል ብሎ መጠበቅ ደግሞ የሚቻል አይደለም፡፡ ይህን ለማድረግ የግድ ወደሲቪል ድርጅትነት መቀየር አለበት፡፡ የሚያሳዝነው እያየን ያለነው እሱን አይደለም፡፡

የግንቦት 20 ሃያ ሶስተኛ ዓመት በሚከበርበት በአሁኑ ወቅት የመንግሥት ባለሥልጣናት እና የመንግሥት መገናኛ ብዙኃን አበክረው የሚያወሩት ባለፉት ዓመታት ስለተመዘገበው የኢኮኖሚ ዕድገት ነው፡፡ ይሁን እንጂ፣ ሀገራችን ምን ያህል ትልቅ የኢኮኖሚ ዕድገት ብታስመዘግብ የፖለቲካው ሁኔታ እንደሚታየው ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተዘጋ ከሄደ ተገኘ የተባለው ዕድገት ቀጣይነት ሊኖረው አይችልም፡፡ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ብቻ ሀገራቱን ከአመጽና ከብጥብጥ እንደማያድናቸው ብዙ ጊዜና በብዙ ሀገሮች ታይቷል፡፡ እጅግ በጣም ሊያሳስበን የሚገባው አሁንም ከሃያ ሶስት ዓመታት በኋላ ብሔረሰብ ተከሉ የፌዴራል ሥርዓት በፈጠረው መከፋፈል ምክንያት “ሀገራችን ትበተን ይሆን?” እያልን የምንጠይቅ መሆናችን ነው! ከሃያ ሶስት ዓመት በኋላ አሁንም ሀገራችን መንታ መንገድ ላይ ናት፡፡ ሊያሳስበን የሚገባው፣ ልንወያበት የሚገባው፣ መፍትሔ ልንሰጠው የሚገባን ወሳኝ ነጥብ ይህ ነው፡፡

ኢትዮጵያ በመንታ መንገድ ላይ

9°”l 6— ¯Sƒ lØ` 119 ግንቦት 2006 ዓ.ም

መሠረት ደሞዜ

ጣይቱ ገጽ

በአለም አቀፍ ደረጃ ለሰው ልጆች ሁሉ አስፈላጊ ናቸው ተብለው የተገለፁት መሰረታዊ ፍላጎቶች ወይም Basic needs መጠለያ፤ ምግብ እና ልብስ ናቸው፡፡ ማንኛውም የሰው ልጅ ከነዚህ ነገሮች ውጭ ሆኖ ኅልውናው አይጠበቅም፡፡ ለመኖሩ የሚያስፈልጉ ወሳኝ ነገሮች ናቸው፡፡ እንዴት ያለ መጠለያ፤ እንዴት ያለ ምግብ እንዲሁም እንዴት ያለ አልባሳት የሚለውን ጥያቄ በተመለከተ እንደ ኑሮው ደረጃውና የአኗኗር ዘይቤና ልምዱ ቢለያይም ሶስቱ ነገሮች አለምን ተጋፍጦ ለመኖር በግንባር ቀደምትነት የሚያስፈልጉ መሰረታዊ ፍላጎቶች ናቸው፡፡

እኔ ደግሞ ከእነዚህ መሰረታዊ ፍላጎቶች በተጨማሪ ለሰው ልጆች ሁሉ በቀደምትነት ያስፈልጋል ተብሎ ሊካተት የሚገባው ነገር አለ እላለሁ፡፡ ምን አላችሁ; ሐሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት! አዎ! የሰው ልጅ በውስጡ የሚመላለሰውን ሐሳብ፤ አመለካከት ለሌሎች የማካፈል፤ የመወያየት መብቱ በአለም አቀፍ ደረጃ በመሰረታዊ ፍላጎትነት ሊመዘገብ ይገባል፡፡ ለዚህ ምክንያትሽ ምንድነው; ካለችሁኝ “እስኪ የትኛው የሰው ልጅ በየትኛው የአለም ክፍል የሚገኝ የሰው ዝርያ ነው የራሱ የሆነ እሳቤ፤ እምነት ወይም አመለካከት የሌለው; ይህንንስ እሳቤውንና አመለካከቱን በአንድም በሌላም ምክንያት በሚደርስበት ወይም በሌሎች ላይ በሚደርሰው ተፅዕኖ ሸሽጎት እንጂ ለማካፈል የማይፈልግ ማን አለ;!” መልሴ ነው፡፡ ሁሉም የግሉ አመለካከት እሳቤ አለው፡፡ እንደምንኖርበት ማኅበረሰብ እንደ እውቀታችን መጠን ደረጃው ቢለያይም ሰው የሆነ ሁሉ የግሉ አመለካከት አለው፡፡

ሐሳብ (አመለካከት) ማለት ምን ማለት ነው;

ሐሳብ (አመለካከት) ማለት “የእሳቦትንና የኑባሬን ግንኙነት የሚገልፅ በፍቺና በስምምነት ሊተረጎም የሚችል የፍልስፍና ፈርጅ ነው” በሚል በይላቅ ኃ/ማርያም የተዘጋጀው “ሐበሻ” የአማርኛ መዝገበ ቃላት የሚፈታው ሲሆን ባህሩ ዘርጋው ግዛው ደግሞ “ዘርጋው ከፍተኛ አማርኛ መዝገበ ቃላት” በሚለው መፅሐፋቸው “አሳብ የእሳቦትንና የኑባሬን ግንኙነት የሚገልፅ፤ በፍቺና በስምምነት ሊተረጎም የሚችል፤ በአዕምሮ የሚወለድ፤ የሚያሳድገው፤ የስራ የነገር ትውልድ፤ ከሰውነት የሚታሰብ፤ የመልካም ሆነ የክፉ ሐሳብ ወይም በአዕምሮ ውስጥ የሚቀረፅ የሚታቀድ፤ የሚመላለስ ፅንስ፤ ነገረ ግንዛቤ (ስነቃል)” መሆኑን ይገልፃሉ፡፡

ማንኛውም አለም ላይ ተከስቶ ያለፈ፤ እየተከሰተ ያለ፤ ወደፊትም የሚከሰት ነገር ጥሩም መጥፎም መነሻው ሐሳብ ነው፡፡ አድጎ መሬት ላይ የሚወርደውና ተግባራዊ የሚሆነው መንገዱ ቢለያይም ለሌሎች መድረስ ሲችልና በውይይት

ሲዳብር ነው፡፡ አንድ ግለሰብ የያዘው ሐሳብ መጥፎ እንኳ ቢሆን እንደ ሐሳብ ተከብሮለት በውይይት እሳቤውን እንዲቀይር ማድረግ የሚቻለው ሀሳቡ መከበሩን አውቆ ለውይይት ይፋ ያደርገውና በተለያየ በጎ እሳቤ ልክ አለመሆኑን ስናመላክተው ነው፡፡ ለዚህ መሳካት ደግሞ ሐሳብን በነፃነት የመያዝ ለሌሎች የማካፈል መብት ከመብትነት ባለፈ ከመሰረታዊ ፍላጎቶች ጎራ ሊመደብ ይገባል፡፡

ሐሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት ስንል…

ሐሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት ማለት ካለምንም ጣልቃገብነት እና ገደብ እሳቤዎችን የመያዝ፤ ለሌሎች የማካፈል መብት ማለት ሲሆን ሐሳብን የምናካፍልበት መንገድ በማናቸውም የመገናኛ ብዙሃን ተቋማት፤ በጥበብ ስራዎች፤ በሕዝብ ተቃውሞችና ብሮድካስቲንግንም ጭምር ሆኖ በፅሁፍና በቃል ሊሆን ይችላል፡፡ ነገር ግን ይህ መብት ፍፁም አይደለም፡፡ መሰረታዊ ፍልስፍናዎችን ሳይለቅ የራሱ የሆነ ሃላፊነቶች ሊኖሩት ይችላሉ፡፡

ዓለምአቀፍ ብሎም ሐገራዊ ከለላው ምን ይመስላል;

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን የሲቪልና ፖለቲካዊ መብቶችን በተመለከተ በግሪጎሪያን ዘመን አቆጣጠር መጋቢት 23/1976 ዓ.ም ለፊርማ ክፍት ባደረገው አለም አቀፍ ስምምነት አንቀፅ (Article) 19(1) (2) ላይ በግልፅ ተቀምጧል፡፡ የድንጋጌው አንድምታ ማንኛውም ሰው ሐሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት ማለት ካለምንም ጣልቃገብነት እና ገደብ እሳቤዎችን የመያዝ፤ ለሌሎች የማካፈል መብት ማለት ሲሆን ሐሳብን የምናካፍልበት መንገድ በማናቸውም የመገናኛ ብዙሃን ተቋማት፤በጥበብ ስራዎች፤ በሕዝብ ተቃውሞችና ብሮድካስቲንግንም ጭምር ሆኖ በፅሁፍና በቃል ሊሆን እንደሚችል የሚያመላክት ነው፡፡

በዚህ ስምምነት የተጠቀሱት መብቶች የሰው ልጅ ሰው በመሆኑ ብቻ የሚኖረው ወይም ከሰው ልጅ ጋር ቁርኝት ያላቸው ተፈጥሯዊ እሴቶች መሆናቸውን ያስረዳል፡፡ ስምምነቱን አምኖ የፈረመ ሀገር እንደ ስምምነቱ የመተግበር ብሎም የማስፈፀም ግደታ አለበት፡፡

ወደ ሐገራዊ ከለላው ስንመጣ በቀደሙት ዘመናት ዜጎች በመገናኛ ብዙሃን ተጠቅመው ሃሳባቸውን ለሚመለከተው አካል የማስተላፉ ነገር በበቂ አልነበረም፡፡ የመጀመሪያው ጋዜጣ እንኳ ለህትመት የበቃው በዘመነ ዳግማዊ ምኒልክ ነው፡፡ ቢሆንም ቅሉ ማኅበረሰቡ ሃሳቡን ወደ ገዢዎቹ እሳቤውን ለማስተላለፍ የራሱ መንገዶች ነበሩት፡፡ ታሪክ ስናገላብጥ ገዢዎቹም የሕዝቡን የልብ ትርታ ለማወቅ “እረኞች ምን አሉ;” የማለት ልምድ እንደነበራቸው ያሳውቁናል፡፡ ይህም የሰዎችን ሃሳብ ዋጋ መስጠትን ያመላክተናል፡፡

አሁን ላይ የመገናኛ ብዙሃን፤ ብሮድካስቲንግ፤ እና መሰል ሃሳብን ማስተላፊያ መንገዶች አሉና “እረኛ ምን አለ;” ብሎ መጠየቅ አይጠበቅም፡፡ በሀገራችን የሲቪልና ፖለቲካዊ መብቶች ስምምነት ፈራሚ ናትና ለሰው ልጆች ሃሳብ ከለላ ትሰጣለች፡፡ ከዚህ አለም አቀፍ ስምምነት በተጨማሪ የህጎች ሁሉ የበላይ በሆነው ህገ መንግስታችን አንቀፅ 29 ላይ ይህንን መብት አጎናፅፎናል፡፡ ይህ ድንጋጌ ከአለም አቀፍ

4ኛው መሠረታዊ ፍላጎት ስምምነቱ ጋር በቀጥታ የተቀዳ በሚመስል መልኩ ተመሳሳይነት አለው ለማለት ይቻላል፡፡

“ማንኛውም ሰው ያለማንም ጣልቃ ገብነት የመሰለውን አመለካከት ለመያዝ ይችላል፡፡ ማንኛውም ሰው ያለምንም ጣልቃ ገብነት ሐሳቡን የመግለፅ ነፃነት አለው፡፡ ይህ ነፃነት በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጭ ወሰን ሳይደረግበት በቃልም ሆነ በፅሁፍ ወይም በህትመት፤ በስነ ጥበብ መልክ ወይም በመረጠው በማንኛውም የማሰራጫ ዘዴ ማንኛውንም ዓይነት መረጃና ሐሳብን የመሰብሰብ፤ የመቀበልና የማሰራጨት ነፃነቶችን ያካትታል፡፡” አንቀፅ 29 (1) እና (2)

እንግዲህ ሃሳብ ከሃሳብነቱ ልቆ በአለም አቀፍም ሆነ ሀገራዊ ከለላ የተደረገለት የሁሉ ነገር መነሻ በመሆኑ አይደል; ከመብትነቱ ባለፈ የላቀ ሚና ያለው ሀብት በመሆኑም አይደል; እውነት ነው! እንደ መብት እንኳ ባይሰጥ ሃሳብን በሃሳብነቱ ላለመያዝ መከላከል የማንችለው ሞገድ ነው፡፡ ይህም ሃሳብን የመግለፅ መብት በተከበረበትም ሆነ ባልተከበረበት በየትኛውም አለም ላይ ያለ ማኅበረሰብ ከተለመደው ሃሳብ ውጭ ወይም ሀገርን የሚያስተዳድረው መሪ መስማት ከሚፈልገው ሀገራዊ እሳቤዎች ልቆ ያለውን እምነት እና ፍልስፍና ዋጋ እንደሚያስከፍል እንኳ እየታወቀ ሃሳብን ከመያዝም ከመግለፅም ወደኋላ የማይባለው፡፡

ከመሰረቱም ሃሳብን ለማካፈል ለመወያየት ብሎም ለመተግበር የሚተጉ ሰዎች ይብዛም ይነስም ሃላፊነት የሚሰማቸው ናቸው፡፡ ለሰው ልጆች ክብር፤ ለሰው ልጆች እኩልነት፤ ለሀገር እድገት፤ለሀገር ሰላም ያገባናል የሚሉ ሰዎች ናቸው፡፡ ደረጃው ከፍ ሲል እነዚህ ሰዎች ናቸው ሀገር ብትወረር፤ ዳር ድንበሯ ቢደፈር፤ ጠላት ቢበዛባት የሀገሬ ጉዳይ ያገባኛል ብለው የተሻለ ሐሳብን ለማካፈል እንዳልቦዘኑት ሁሉ ደረታቸውን ለጥይት ስጋቸውን ለአሞራ ለመስጠት ወደኋላ የማይሉትና የሀገርን ክብር ህይወታቸውን ገብረው የሚያስጠብቁት፡፡

ይህ እሳቤን በነፃነት የመግለፅ መብት ግን ከመብትነት አልፎ (መብት ከሆነ በፍላጎት ነውና ሃሳብን ያለመግለፅም መብትም አብሮ ስለሚኖር) በመሰረታዊ ፍላጎት ደረጃ ከተቀመጠ ግን በመናገሬ እንገላታለሁ፤ በመናገሬ ዋጋ እከፍላለሁ ብሎ ከያገባኛል ይልቅ ምን አገባኝን መርጦ ታፍኖ ያለው የሰው ልጅ ሁሉ ሀገርን ጠቃሚ ሀገርን ጠባቂ ይሆናል፡፡ ከጥሩ እሳቤዎች ጎን መጥፎ እሳቤዎች ቢኖሩም በመሰረታዊ ፍላጎትነት ተፈርጇልና በውይይት በክርክር ስህተትነቱን አሳይቶ እሳቤውን ማስቀየር ይቻላል፡፡ (በመሰረቱ ሰው ልጅ መጥፎ እሳቤ ውስጥ የሚገባው የሚፈልገውን ነገር በመልካም መንገድ ማግኘት ሲያቅተው ነው የሚል እምነት አለኝ፡፡)

እናም ይህ መብት በመሰረታዊ ፍላጎትነት ተመድቦና ተግባር ላይ ውሎ ልክ እንደ ጋሽ ጥሌ

“ሁሉማ አውቆ እንዲኖር ሰብዓዊ መብቱን በፈጣሪ ፀጋ የተሰጠው ሐብቱን ነበረ ምኞቴ ሰመረ መሰለኝ ፍላጎቴ ደርሶ አይቼው ደስ አለኝ….”

እያልኩ የማንጎራጉርበት ጊዜ ሩቅ ባይን እያልኩ እናፍቃለሁ!!!

በስተመጨረሻም የሀገሬ ህልውናዋ ያገባኛልና እንዲህ እላለሁ

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር !!!

10 °”l 6— ¯Sƒ lØ` 119 ግንቦት 2006 ዓ.ም

ወቅታዊ ጉዳይ

ወቅታዊው ትኩሳት እንደ ግርሻ የሆነው የብሔሮች ግጭት ነው ማለት ይቻላል፡፡ አማራው በኦሮሞው ወገኑ ልጆች አማራ ሆኖ በመወለዱ ብቻ እየተጠቃ ወይም የዘር ጥላቻ ሰለባ እየሆነ ነው፡፡ ጥቃቱም እስከ ግድያ ድረስ በዘለቀ ርምጃ ጭምር እየተገለጸ ነው፡፡ በአንዳንድ ሥፍራዎችም ዜጎች የትግራይ ክልል ተወላጅ ወይም በብሔራቸው ትግሬ በመሆናቸው ብቻ የመሰል ጥቃት ሰለባ የመሆናቸው አዝማሚያ መታየቱ ቢያንስ እየተሰማ ነው፡፡ ‹‹ከክልሌ ውጣልኝ! ወደ መኖሪያ መንደርህና ወደ ትውልድ ቀዬህ ተመለስ! በእኛ ክልል ያፈራኸው ሀብትና ንብረት የአንተ አይደለምና እርቃንህን ቅር! ነፍስህን በጨርቅ ቋጥረህ የመውጣት መብት ብቻ ነው ያለህ…›› የሚለው ግፊትና ትንኮሳ እያሰለሰም ቢሆን ወዲያና ወዲህ እየተፈፀመ ለመሆኑ ሰሚ ያጡት የሰለባዎቹ ድምፆች በራሳቸው ማስረጃዎች ናቸው፡፡ እኛ ደግሞ እንዲህ ዓይነቱ ድርጊት በኢትዮጵያ ውስጥ ተፈጽሞ መገኘቱ ብቻ ሳይሆን መሰማቱ በራሱ እጅግ በጣም አሳሳቢ ነው እንላለን፡፡

ከፍ ሲል የገለጽነው ችግር እስከዛሬ ድረስ ወጥ የሆነና ተመልሶም እንዳያገረሽ የሚደረግበት ርምጃ ያለመወሰዱ ጉዳይ እንደተጠበቀ ሆኖ፤ ከድርጊቶቹ መደጋገምም ይሁን አሁን አሁን እየተባባሱ የመጡበትን ሁኔታዎች ከማስተዋላችን አኳያ የሚከተሉትን ጥያቄዎች መልሰን ማንሳት ተገቢ መስሎ ታይቶናል፡፡ እውን በአንዳንድ አክራሪ ብሔረተኛ በሆኑ የኦሮሞ ብሔር ተወላጆች ‹‹ መናጢ ደሀና አሮጌ ውራጅ ለባሽ እንኳን ቢሆን መንፈሰ ኩሩና ሌላውን በንቀት የሚመለከት ዘር ነው…›› ተብሎ የተፈረጀው አማራ፤ የኦሮሞው ወገኑ ጠላት ነው? በሌሎች ወገኖቹስ ላይ ‹‹ ጭቁን፣ቢሮክራት፣ነፍጠኛ…›› ተብሎ የሚፈረጀው አማራ፤ ከማንም እና ከምንም የበለጠ ባለጋራ ነው? ለመሆኑ አማራ የሚባለው ብሔረሰብ ተወላጅ የሆነው የኢትዮጵያ ሰው፤ አማርኛ ቋንቋን ከመናገር ውጪ ሌላ የመግባቢያ ቋንቋ ባለቤት ያልሆነው ኢትዮጵያዊ ጭምር፤ እንደ ‹‹ብሔር ብሔረሰብ ሕዝቦች መብት›› ሁነኛ ተጻጻሪ ሆኖ በአንዳንድ ጽንፈኛ ብሔረተኞች የሚፈረጀውና በዚህም አጓጉል ፍረጃ ምክንያትነት ዘወትር በጥርጣሬ የሚታየው ለምንድን ነው? መጽሔታችን ይህን የመሰለውን ጥያቄ መልሳ የምታነሳው፤ የጥላቻው ፖለቲካ የሁላችን ሀገር የሆነችውን ኢትዮጵያ ፍፁም ወደማንጠብቀውና በቀላሉም ወደማንቆጣጠረው ወይም መፍትኄ ወደማናገኝለት ቀውስ የሚመራን መሆኑን ግምት ውስጥ በማስገባት ብቻ ነው፡፡ ምናልባትም እንዲህ ብሎ ማለት ‹‹እሳት ማቀጣጠልና ነገር ማራገብ ላይ ያተኮረ የግሉ ፕሬስ ተግባር ነው…›› ተብሎ የሚያስተቸን እስካልሆነ ድረስ፡፡ ለሁሉም ከወዲሁ በብሔራዊ ዕርቅም ይሁን በሌሎች የቅድመ ችግር ማስወገጃ ማኅበራዊና ፖለቲካዊ ስልቶች፤ የገዥው ፓርቲ ተሳትፎ ባለበት ሁኔታ ነገ ወይም ዛሬ ሳይባል መድኃኒት የሚያስፈልገው ወቅታዊ ትኩሳት ነው አንደኛው ኢትዮጵያዊ ሰው ሌላውን ኢትዮጵያዊ ዜጋ በቋንቋውና በዘሩ… ምክንያት ለማጥቃት የሚነሳሳበትና የሚያደባበት አዝማሚያ ነው ብለናል፡፡

ስለሆነም በአገራችን ጥልቅና የማያዳግም መፍትኄ ከሚያስፈልገው ወቅታዊ ትኩሳት አኳያ በተሰማበት አካባቢ ተግባራዊውም ሆነ አልሆነ፤ በቅርቡ

ከወደ ሱዳን ካርቱም የተሰማው ደስ የሚያሰኝ ዜና ነው እንላለን፡፡ የተሰማው ዜና ዋንኛ ትኩረት ብሔራዊ ዕርቅን የሚጠይቅ መልዕክት ያቋተ እንደመሆኑ ‹‹በእኛም ሀገርና መንግሥት በሆነ›› ያስብላል፡፡ በድጋሚ አደረጉትም አላደረጉት፤ ዘግይተውም ቢሆን ፕሬዚዳንት ጄነራል አልበሽር ያሰሙት የብሔራዊ ዕርቅ ጥሪ፤ ለኢትዮጵያ በጎውን ነገር ለሚመኙ የሰው ዘሮች በሙሉ የመንፈሳዊ ቅናትን ክብሪት በአዕምሮ ውስጥ የሚያጭር ነው፡፡ መቼም ይሁን መቼ እስካልደረሱብን ድረስ፣ ካልተነኮሱን፣ ካልነካኩን፣ በኢትዮጵያ ውስጥ ከቤት እስከ አደባባይ የሚስተዋለውን የነገር ፍም፣ ቤኒዚንና ነፋስ እየሰጡት ዝንተ-ዓለም የሚቀጣጠል እሳት እንዲሆን የሤረኛነት ሥራ እስካልሠሩብን ድረስ፤ የጎረቤት ሀገሮቻችንን፣ የሕዝባቸውና የመንግሥታቸው ሁለንተናዊ ሰላም፤ የእኛም ሰላም ነው፡፡ መግባባታቸውና ፍቅራቸውም በእነሱው ሊወሰን የሚችል አይደለም፡፡ ቢያንስ የዕርቀ-ሰላማቸው ካፊያ እኛንም ያረሰርሰናል ብለን እናምናለን፡፡ ስለዚህም አሁን ካለንበት አሳሳቢ ሁኔታ አንፃር ከወደ ካርቱም የተሰማው ዜና አዲስ አበባም ላይ በእኛ ባለሥልጣኖች ቢደገም መልካምነቱ ለገዥዎችም ይሁን ለተገዥዎችም ነው፡፡

የሱዳን መንግሥትና የመንግሥቷም ወሳኝ ሰው የሆኑት የአልበሽር የብሔራዊ ዕርቅ ጥሪና የፖለቲካ እሥረኞችን ሁሉ ለመፍታት የመወሰን እርምጃ፤ የካርቱም ዕልቂትና ውድመት ጠሪ ፖለቲካዊ ግለት ማብረጃ ብቻ ሳይሆን፤ የመላው አፍሪካ ቀንድ በይበልጥም የኢትዮጵያ፣ የሶማሌያ፣ ችግሯን ለማመቅ የምትንደፋደፈው የኡጋንዳ፣ ከእናት ሀገሯ በ ‹‹ናጽነት›› ስም ተለይታ በፖለቲካዊ የነገር ማብለያ ምድጃ ላይ በመጣድ ለምትንጨረጨረው ኤርትራ ወቅታዊ ትኩሳት ማቅለያ የሚሆነውን መድኃኒት አመላካች ጭምር ነው የሚል ዕምነት አለን፡፡

በመሆኑም ይኼን ከወደ ካርቱም የተሰማን እና ሱዳንን የመሰለ ሀገር በሀገርነቷና በመንግሥትነቷ ሊያስቀጥል የሚያስችል፣ የሚጣሉት ዝሆኖች መፈንጫና የደም ጥማት ማርኪያ ሆኖ ለሚቀርበው ወንድም የሱዳን ሕዝብ ዘለቄታዊ ሰላምን ብቻ ሳይሆን ከዘለቄታዊ ሰላሙ ሊያገኝ የሚችለውን የዕድገትና የብልፅግና …ፍሬ ተቋዳሽ ሊያደርገው የሚያስችለውን የብሔራዊ ዕርቅ ጥሪንና የፖለቲካ እሥርኞችን በሙሉ ከእስራት ነፃ የማድረግን ያህል ዜና መስማት፤ ሌላው ቢቀር ‹‹እንደዚህ ዓይነቱን ይበል የሚያሰኝ ነገር ለእኛም ባደረገው…›› የሚል ቀና ስሜት፤ እናት ሀገራችን ኢትዮጵያ ከጦርነት፣ ከጥፋት፣ ከውድመትና እርስ በእርስ በነገር ከመቋሰል አዙሪት እንድትወጣ ሌት ተቀን ከልባቸው አጥብቀው በሚመኙ ዜጎች ዘንድ እንዲጎለብት የሚያደርግ፤ ወቅታዊ ጉዳይ፣ ወቅታዊ ትኩሳትም ብለን ማመናችን በራሱ ችግር ያለው ሆኖ አይሰማንም፡፡

ዓመታት ያልፈቱት ችግርያለፉትን ዓመታት ፖለቲካዊ ስንክሳሮች

ስንመረምራቸውም ሆነ የአሁኑን ሁኔታ እያስተዋልን ስለመፃኢው ጊዜ ስናሰላስል፤ ኢትዮጵያ ባለቤት ያጣች ሀገር ሆና የምትታየን መሆኑን አንክድም፡፡ ‹‹አገሪቱ የማን ነች?›› ተብሎ ሲጠየቅ በቃል ደረጃ በቅፅበት የሚከሰተው መልስ ‹‹የዜጎቿ ሁሉ›› የሚለው ነው፡፡ ከመኖር ከተገኘው እውነትም ይሁን በየዋህነትም ይባል በተላላነት… ፀንቶ ከኖረው ዕምነት አኳያ ‹‹ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያውያን ሁሉ›› የመሆኗ ሐቅ፤ አሁንም በቃል ደረጃ የሚያሻማ አይደለም፡፡

ከቅድመ 1983 ዓ.ም በፊት በነበረው ሁኔታ፤ ሀገሪቱ የኢትዮጵያውያን ዜጎች ሁሉ (የኦሮሞው፣ የአማራው፣ የትግሬው፣ የአፋሩ፣ የሱማሌው፣ የወላይታው፣ የጋምቤላው፣ የሸኰው፣ የመዠንገሩ፣ የኮንሶው፣ የከንባታው፣ የአደሬው፣ የአገው፣ የሺናሻው…) ‹‹ነች›› መባሉ፤ በማለት ደረጃ የሚያስማማ ነበር፡፡ በኑሮ ደረጃ፣ በኢትዮጵያ ሀብትና ፀጋ የበለጠ ተጠቃሚ፣ የበለጠ ተገልጋይ የበለጠ ወሳኝ፣ ሰጪና ነሺ፣ አድራጊና ፈጣሪ… በመሆን ደረጃ ግን በተግባር የሚታይ ዜግነታዊ ልዩነት ነበረ፡፡ ይህ ‹‹ነበረ›› የምንለው ልዩነት ከዚያም በቀደመው ጊዜ የነበረ እንደመሆኑ መጠን፤ ዛሬ ደግሞ ቅርፁንም ይሁን መልኩን ለውጦ በችግርነቱ ቀጥሏል፡፡ ይልቁንም ‹‹ኢትዮጵያዊነትን›› በራሱ ጥያቄ ምልክት ውስጥ ከማስገባት ተንደርድሮ፤ ጎሣን ወይም ነገድን፣ ብሔርን ወይም ብሔረሰብን በራሱ እንደዜግነት ወደ መቁጠሩ ወይም ወደ መውሰዱ የአክራሪነትም እንበለው የዘረኛ ጽዮናዊነት ጽንፍ እያመራ ይገኛል፡፡

ይህ እያመራ ያለው ሀገራዊ እውነት፣ ማንም ወደደው ወይም ጠላው በዛሬይቱ ‹‹ፌዴራላዊት ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ›› ከዳር ምድር እስከ መሀል መዲና በግልፅ የሚታይ ነው፡፡ የመታየቱም ምክንያት በኢትዮጵያ ለዓመታት ያልተፈቱት ፖለቲካዊ፣ አስተዳደራዊ፣ ምጣኔ ሀብታዊ፣ ሕጋዊና አስተሳሰባዊ ችግር ሰፍኖ መኖሩን ብቻ ሳይሆን ዛሬም ችግሩ ‹‹እየተቀረፈ ነው…›› ቢባልም እንኳ በይበልጥ መወሳሰቡንና ከናካቴውም ውሉ እንደጠፋበት ልቃቂት መሆኑን አመላካች ነው፡፡ በእንደዚህ መሰሉ መለኪያ የኢትዮጵያ አጠቃላይ ሁኔታ፤ ዓመታት ያልፈቱት፣ ይልቁንም ከመጥበሻው ወደ እሳቱ እያመራ የሚገኝ ችግር መሆኑ፤ ከመፃኢው የከፋና አይቀሬ የሚሆን አደጋ እናመልጥ ዘንድ ብሔራዊ ዕርቅን እንመኝ ዘንድ የማያስገድደን ነው ሊያሰኝ አይችልም፡፡

እንደሚስተዋለው በኢትዮጵያችን እጅግ በጣም ብዙ ፖለቲካዊ ጥያቄዎች ‹‹ነበረ›› የሚባለውን ‹‹ብሔራዊ ጭቆና›› ለማስወገድ ‹‹ያስችላሉ›› በሚል ተነስተዋል፡፡ መነሳት ብቻ አይደለም ‹‹በሕገ-መንግሥቱ እና በሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱ›› ቡራኬ፤ ለተነሱትና ‹‹መልካም አማራጭ ናቸው›› ለተባሉት ‹‹ዴሞክራሲያዊ›› ለተባሉ ጥያቄዎች ‹‹ዴሞክራሲያዊና ፍትሐዊ›› የተባለ መልስ ተሰጥቷል፡፡ መልሱን እንዲያስፈፅሙ ወይም ተግባራዊ እንዲያደርጉም፤ የነገው ሁነት በትላንቱ እና በመፃኢው ጥሩ መነፅር ለሚመለከቱ ሩቅ አሳቢዎች… ሳይሆን በሌላው ውድቀትና መዋረድ የራሳቸውን ማንሰራራትና ክብር ብቻ ለሚመዝኑ፣ ‹‹እኔ ከሞትኩ ሠርዶ አይብቀል›› ለሚሉ፤ ምርኮኛና በልቶ አደር ፖለቲከኞች ሥልጣንና ኃላፊነቱ ተሰጥቷል፡፡ እንደዚህም ስለተሰጠና የአፈፃፀሙንም ሁኔታ ለማረምና ለማስተካከል ‹‹ዓባይን በጭልፋ›› ወይም ‹‹ቁጭ ብለው የሰቀሉትን….›› እየሆነ አስቸግሯል፡፡ ስለአስቸገረም ‹‹ዴሞክራሲያዊና ሕገ-መንግሥታዊ መብታችንን እንዳሻን የመተርጎም ነፃነት ተጎናፅፈናል…›› በሚሉ ተላሎችና አውቆ አጥፊዎች ርምጃ፣ ጥቂት የማይባሉ የሀገሪቱ ዜጎች ‹‹የእኛም ናት…›› በሚሏት ኢትዮጵያ ውስጥ ‹‹የዚህ ወይም የዚያኛው ክልል ተወላጅ ናችሁ አይደላችሁም…›› በሚል ምክንያት፤ የገዛ አገራቸው ተፈናቃይ፣ ስደተኛና ‹‹አቤት…›› ቢሉም መልስ የማያገኙ ዜጎች ሆነዋል፡

ዛሬም!የብሔራዊ ዕርቅ ጥሪ እናሰማለን!

11°”l 6— ¯Sƒ lØ` 119 ግንቦት 2006 ዓ.ም

ወቅታዊ ጉዳይ

፡ የእንደዚህ ዓይነቱም ሁነት ግፊት የሀገሪቱ ‹‹ዳር አገር…›› ናቸው ከሚባሉት አካባቢዎች እየተነሳ አድማሱን በማስፋፋት ለአዲስ አበባ ከተማ እጅግ ቅርብ በሆኑትና እንደ አምቦ ባሉት የኢትዮጵያዊነት ማዕከሎች ሳይቀር በተግባር መታየት ጀምሯል፡፡

ይህ አሳሳቢና ፍፁም አስጊ ሊሆን የሚችል ‹‹የዴሞክራሲያዊ መብት›› አተገባበር በአምቦ ሲፈፀም ከታየ፣ እነ አቶ ፀጋይ ዳምጤን ከዳኖ ወረዳ …ካፈናቀለ፣ ለመደብደብ፣ ለእንግልት ካደረገ፤ ከዚህም አልፎ ተርፎ ለአንድ ሰውም ቢሆን በዘር የተነሳ ለሕይወት መጥፋት ሰበብ ከሆነ፤ በአምቦ የተፈፀመው ነውረኛ ድርጊት ነገ ወይም ዛሬ ‹‹ፊንፊኔ የኦሮሞ ነው!…›› በሚል ሰበብ በአዲስ አበባ ከተማ ተግባራዊ ላለመሆኑ ምን ዓይነት መተማመኛ ማግኘት ይቻላል? የስጋቱ ጉዳይ ከሆነ ምልክቱ እየታየ ነው፡፡ አንዳንድ ግለሰቦች፤ ነገር ግን ሊናቁ የማይገባቸው የኦሮሞ ልጆች ከወደ ዳር ሀገር ተቀምጠውም ይሁን በቅርብ ሆነው በውክልና የሚያስተዳድሩትንና የሚያዙበትን ቤትና ንብረት ‹‹ለምን ለአማራ አከራያችሁት? ለምንስ ነፍጠኛ እንዲገለገልበት ታደርጋላችሁ?…›› በማለት፤ ውክልናውን በሰጧቸው ወዳጆቻቸው ወይም የቤተሰቦቻቸው አባላት ላይ ተግሣጽና ቁጣ አዘል ማስጠንቀቂያ ሲሰጡም ‹‹ሆደ ሰፊው›› የአገራችን ዜጋ ሰምቶ እንዳልሰማ ሆኖ እያለፋቸው ነው፡፡ ታዲያ ይኼን የመሰለው ቀላል የሚመስል ግን ቀላል ያልሆነ፣ ብልጭ ድርግም ሲል… የሚስተዋል፤ ነገር ግን ውስጥ ውስጡን የሚፍምና የሚግም ከዘረኛው ፖለቲካ ማህፀን የሚቀፈቀፍና ዓመታት ያልፈቱት ችግር፤ በብሔራዊ ዕርቅ መውረድ አማካይነት ማርከሻ የማያስፈልገው ነው አይባልም፡፡

በበቀል መንገድ ላይያለ ጥርጥር ኢትዮጵያን እዚህ ያደረሰው መንገድ

ጤነኛ አልነበረም፡፡ ‹‹ኧረ ጤነኛም ነበር…›› ከተባለ፤ የኢትዮጵያ ታሪክ በአብዛኛው ‹‹የጦርነት ታሪክ ነው›› ባልተባለ ነበር፡፡ እዚህ ያደረሰን መንገድ ጤነኛ ባለመሆኑ የተነሳ፤ የመንግሥትነትና የአገር ገዥነት ሥልጣኑ በጉልበት እየተያዘ፣ በጦርነት የሚቀማና በነፍጥና በነፍጠኞች ብዛትና ኃይል እየተጠበቀ ለዝንተ ዓለም ፀንቶ የሚቆይ እየመሰለ ቀጥሏል፡፡ ኢትዮጵያ የሦስት ሺህም፣ የመቶ ዓመትም ይሁን የሉሲን …ያህል የመንግሥትነትና የሀገርነት ታሪክ ይኑራት፤ የተጓዝንባቸው መንገዶች በአያሌው ወደ ጦርነትና ወደ ውድመት የመሯት የበቀል መንገዶች ናቸው፡፡ እንዲህ ብሎ ማለት፤ በሀገሪቱ ታሪክ ውስጥ በአንደኛውም ወቅት ቢሆን ከበቀልና ከቂመኝነት አዚም የፀዳ የዕርቅና ከልብ ለመግባባት የመፈለግ፣ በወንድማማችነትና በእህትማማችነት የመተያየት፣ ተከባብሮና ተፋቅሮ የመኖር ስሜት የተንፀባረቀበት አንድም የታሪክ አጋጣሚ አልተፈጠረም ማለት አይደለም፡፡

የቅርብ ጊዜው የሀገርነትና የመንግሥትነት፣ የገባሪና የአስገባሪነት፣ የገዥና የተገዥነት ዶሴያችን እንደሚመሰክረው እውነት ከሆነ ግን፤ ዛሬ ላይ ያደረሰን የበቀል መንገድ ነው፡፡ ከቤተሰብ እስከ ማኅበረሰብ፣ ከማኅበረሰብ እስከ ላይኛው መንግሥታዊ ቅርፅ ድርስ፤ አመለካከቱ ‹‹ልኩን አሳየዋለሁ!…›› በሚለው ጉልበትንና ኃይልን በተከታዩ ላይ ከማሳየት ፍላጎት ወይም ከበቀል ዕንቁላል ከሚፈለፈልና አስተማሪ መሆን ከማይችል መርህ የሚመነጭ ነው፡፡

እኛ በአብዛኛው (ሰዋዊ ባሕሪ ነው ቢባልም) ትላንት አውቆም ይሁን ሳያውቅ… የጎዳንን፣ ‹‹በእንጀራችን ላይ ቆሞ ነበር…›› የምንለውን፣ የመሰከረብንን፣ የተኮሰብንን፣ ያስተኮሰብንን፣ አንድ ጥቅም ያሳጣንን ወይም ያጓደለብንን ብቻም ሳይሆን ‹‹እንደዚያ ለማድረግ አስቦ ነበር ወይም ከማድረግ የማይመለስ ሰው ነበር›› በማለት የምንገምተውን ወይም የምንጠረጥረውን ዜጋ፤ ገብቶትም ይሁን ሳይገባው… ያላጨበጨበልንን፣ ያልፈከረልንን፣ ያልሳቀልንን …ወገን፤ በጨዋነትና በትህትና፣ በአስተዋይነትና በብልሃት፣ በመተውና በመርሳት፣ ከዛሬው በጣም ጥሩ አጋጣሚ ለነገ እጅግ በጣም ብዙ ትርፍ ሊያስገኝ በሚችል ጥበብ ለማስተማር የምንፈልግ ወይም ተነሳሽነቱ ያለን አይደለንም፡፡

ዛሬ ደግሞ ልክ እንደትላንቱ ያለፈው እየተናፈቀ የአሁኑ የሚረገምበት ብቻ አይደለም፡፡ ዛሬ ባለወር ተራው ያለፈውን ሥርዓትና የሥርዓቱን አራማጆች ብቻ ሳይሆን ‹‹ተቀናቃኝ ናቸው›› የሚላቸውን ሁሉ፤ ከማውገዝ፣ ከማጥላላት፣ ከመወንጀልና ወህኒ ከማውረድ አልፎ ራሱንና ራሱን ብቻ የተቀደሰና ፍፁም የተሻለ አድርጎ በመስበኩ ተግባር ተጠምዶ የሚታይበትም ነው፡

፡ ዛሬ ‹‹ተቃዋሚ›› ወይም ‹‹የሥርዓት ለውጥ ናፋቂ›› የሚባለው የፖለቲካ ድርጅትም ቢሆን በውስጡ እርስ በእርስ፣ በውጪ አንደኛው ከሌላው፣ በጋራ ደግሞ ሁሉም ከገዥው ፓርቲና መንግሥት ጋር የሚናከስና ‹‹ጠብና ልዩነት›› አለኝ ባይ ነው፡፡ የዚህ ሁሉ ዛሬ መነሻው የበቀልተኝነት ዘር የሆነው ቂመኝነትና ከፍፁም በራስ ያለመተማመን ስሜት የሚመነጨው ተጠራጣሪነት ብሎም ራስን ከሌላው አልቆ በማክበር የመኮፈስ አዝማሚያ ሲሆን፤ መዳረሻው ደግሞ ጦርነት፣ ውድቀትና ትንሳዔ አልባው ሁለተናዊ ሞት ነው፡፡

ይሄን በመሰለው የበቀል መንገድ ላይም፤ ደርጎች ብቻ ሳይሆኑ ኢሕአፓዎች፣ መኢሶኖች፣ አንድነቶች፣ መኢአዶች፣ ሕብረቶች፣ ቅንጅቶች፣ ኦነጎች፣ ኢሕአዴጎች ….ብዙ ርቀት ተጉዘዋል፡፡ ዛሬም ከራሳቸውም ጋር ይሁን ከሌላው ወይም ከባላንጣዎቻቸው ጋር አልታረቁም፡፡ አንዳንዶቹ ታሪክ ራሱና ትውልድ ድብን አድርጎ እስኪታዘባቸው ድረስ፤ የጋራ በሚሆን ባላንጣቸው ተደምስሰው ባለፉበት ሁኔታ እንኳን፤ መካሰስና መወነጃጀላቸውን አላቆሙም፡፡ እስከደም መቃባት ደረጃ ካደረሳችው ፖለቲካዊ ሥልጣን ብዙ ሺህ ኪሎ ሜትር ርቀውና ‹‹እንሞትልሻለን…›› ያሏትን ሀገር በፉክክር አፍርሰው ካበቁም በኋላ፤ ህሊናቸው ልጣቸው መራሱን፣ ጉድጓዳቸው መማሱን እየነገራቸውም ቢሆን የመረጡት በበቀል መንገድ ላይ መረማመዱን ነው፡፡ የኢትዮጵያ አድባርና አውጋር ግን፤ ወደ ደም መፋሰሱና ወደ ርስ በርስ ዕልቂቱ… የሚያሳልፈው ከተንበሪ ( መዝጊያ ) ተዘግቶ የሚያይበትን ቀን በመናፈቅ፤ ካርቱም ላይ የተሰማው የብሔራዊ ዕርቅ ጥሪ፤ ከኢሕአዴጋዊው ቤተ-መንግሥትም እንዲመነጭ የሚማፀን ይመስላል፡፡

ምን ይሻለናል?የሚሻለን ዛሬም ብሔራዊ ዕርቅ ነው፡፡ የሚሻለን

ቂም የሚያርቅ፣ ደም የሚያደርቅ ብሔራዊ ዕርቅ በኢትዮጵያ እንዲወርድ መመኘት ብቻ አይደለም፡፡ ለተግባራዊነቱም ከልብ መትጋት ነው፡፡ ለዓመታት የዘለቁትንና ከድጡ ወደ ማጡ እያመሩ ያሉትን የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ችግር ለማስወገድ፤ የሚኖረው የተሻለና አማራጭ የማይኖረው ምርጫ ብሔራዊ ዕርቅ ለማውረድ ዝግጁ መሆን ነው፡፡ ዝግጁነቱም ያልተንዛዛ ሰበብንና ጊዜ ቀጠሮን ይሻል፡፡

በዚህ ገረድ የሚኖረውን የበለጠ ድርሻ ማንሳት የሚኖርበት ደግሞ፤ እንደ አልበሽር መንግሥት ሁሉ፤

በሕወሓት ኢሕአዴግ የሚዘወረው የአቶ ኃይለማርያም አስተዳደር ነው፡፡ አስተዳደሩ በክፉ ከሚነሳበት ‹‹የአገዛዝ ባሕሪው›› እና ዕርቅን ከሚጠየፈው መጥፎ አዚሙ ተላቆ በተጨባጭ የሀገርና የመንግሥት አስተዳዳሪ መሆኑን ለማሳየት፣ ለራሱም ይሁን ለኢትዮጵያ የሚበጀውን መስመር በቁርጠኝነት ለመከተል …በሆደ ሰፊነት የብሔራዊ ዕርቁን አይቀሬነት የሚያበስረውን የጥሪ ደወል ለመደወል፤ ነገ ሳይሆን ዛሬ ከነበረ ማንነቱ ጋር ተወያይቶ ከአንድ ውሳኔ ላይ መድረስ አለበት፡፡ የነፍጥ አምልኮ ሲያበቃ፣ የትምክህተኝነት ፖለቲካዊ ውርስ ሲያከትም፤ በይበልጥ የሚጠቀመውና ከበቀል መንገድ ጉዞው ኪሣራ ነፃ የሚሆነው መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ መሆኑን በመገንዝብ፤ የሕወሓት ኢሕአዴግ መንግሥት የፖለቲካ እሥርኞቹን ‹‹አሟጦ›› በመፍታትና የብሔራዊ ዕርቅ ጥሪ በማስተላለፍ አዲስና በኢትዮጵያ የትንሳዔ ዘመን የታሪክ መዝገብ ላይ ስሙን በደማቅ ቀለም የሚያፅፍ አስመስጋኝ ተግባር ማከናወን ይጠበቅበታል፡፡

ለኢትዮጵያው መንግሥት የሚሻለው ከፍ ሲል የተገለጸው ነው፡፡ እርስ በርሳቸው ለሚወነጃጀሉት፣ የሀገሪቱን እና የሕዝቧን የጣዕር ዘመን በመነካከሳቸው ብዛት ለሚያረዝሙት ስመ ተቃዋሚዎችም ቢሆን ለብሔራዊ ዕርቅም ይሁን ከየራሳቸው ጋር ለመታረቅ፤ ከዛሬ የተሻለ ቀን፣ ከዛሬ የተሻለ ሰዓት፣ ከዛሬ የተሻለ ዕድል የላቸውም፡፡ ለግራ ቀኙ ወገን የተሻለው ነገር ይኸውና ይኸው ብቻ ሲሆን ከዚህ ውጪ ያለው፣ ሊኖር የሚችለውና የሚታየው መንገድ ሁሉ ግን፤ እስከዛሬ ኢትዮጵያ ‹‹ይበጀኝ ይሆናል…›› እያለች ወይም ‹‹ልማታዊና ዴሞክራሲያዊ ለመሆን ያበቃታል…›› እየተባለላት ወደ አዘቅት የምትወርድበት የቁልቁለት መንገድ ነው፡፡

ልማትም ቢሆን ብዙኃኑ አብሮ በኑሮው መሻሻል፣ በተስፋው መለምለም፣ በአብሮነቱ ፍቅር ያለ አንዳች ስጋት ከነአዕምሮው መልማት ሲችል እንጂ በፎቅ ክምርና በጥቂቶች ማበጥ የሚመዘን ወይም የሚለካ አይደለም፡፡ ስለዚህ የሚሻለው አብሮ በጋራ በሁለንተናዊ መስክ መልማት ነው፡፡ ወደዚህ የሚያደርሰውም ለዓመታት ያልተፈቱትን ችግሮች የሚቀርፈው፣ በበቀል መንገድ ላይ ከምናደርገው አጥፊ ጉዞ ሊያቅበን የሚችለው፣ ኢትዮጵያን በሀገርነቷ የማስቀጠል ዋስትና የሚሆነው፣ አመንም አላመንም በሀገሪቱ አየር ላይ የሚያንዣብበውን የሕዝባዊ አመፅ ደመና በመግፈፍ ዳግመኛ ሠይፍ ከምንማዘዝበት ሜዳ እንዳንወርድ የሚገላግለን፤ ዛሬም በኢትዮጵያ ብሔራዊ ዕርቅ የመውረዱን አስፈላጊነት አምነን በመቀበል ተግባራዊ ስናደርገው ነው፡፡ እጅግ ለሚያስፈልገውና ለብሔራዊ ዕርቁ መውረድ መደላድል የሚሆነውም፤ የፖለቲካ እሥረኞችን መፍታት ነው፡፡ አዳዲስ የፖለቲካ እሥርኞችን ወደ ወህኒ ከማጋዝ መቆጠብ ነው፡፡ ሥልጣንን ለማጋራት፣ አገሪቱን የጋራ ቤት ለማድረግ መወሰን ነው፡፡ በጥሪ ደረጃ የተሰማውን ነገር ግን ከልብ እንዲሆን የሚፈለገውን የአልበሽርን አማራጭ መከተል ነው፡፡ የካርቱምን ጥሪ ‹‹ለእኔም…›› ብሎ መስማት ነው፡፡

አማራጩን ለመከተልና አስደሳቹን ጥሪ ለመስማትም፤ የግድ ኢትዮጵያ ሱዳን የገባችበት የፖለቲካ ማጥ ውስጥ በመግባት ሂሣቧን ካወራረደች በኋላ መሆን የለበትም፡፡ የደቡብ ሱዳን መገንጠልና ገና በጫጉላነት ዘመኗ ወደ ሌላ ዙር ጦርነት ያለፈችበት፣ የረሃብ፣የችጋር፣ የማይነጥፍ የሚመስለው የጠብ ቆስቋሽነት ሁኔታና እንደ ኤርትራ ዓይነቱ ጉዳይ ኢትዮጵያ ውስጥም ተደግሞ መታየት ይኖርበታል አይባልም፡፡ ይህም ክፉ ነገር በሃገራችን ይሆን ዘንድ ኢትዮጵያችን ‹‹የዕብድ ገላጋይ›› ያስፈልጋታል ተብሎ አይተሰብም፡፡ አሁን ላይ ሆኖ የዳርፉርና የአቢዬ ግዛት ውጥረትና ጡዘት ብቻውን አልበሽርን ለብሔራዊ ዕርቅ ጥሪ …ገፋፍቷል ብሎ ማሰብም ትንሽ የማይባል የአመለካከት ጉድለት አለው፡፡ ከእንግዲህ የኢትዮጵያ መንግሥት መሪዎች በጎረቤት ሀገራት ተፈጠረ የሚባለውን ቀውስ ለማስወገድ በሽምግልና ስም መሯሯጥ ብቻ አይደለም የሚጠበቅባቸው፡፡ በቤታቸውም ለነፋስ የተጋለጠ የነገር ፍም መኖሩን ተገንዝበው ሰደዱ ከመቀስቀሱ በፊት የአደጋው ተከላካይ ዳኛ ሆነው የመቆም ህሊናዊም፣ታሪካዊም ኃላፊነት አለባቸው፡፡ በአንቀፅ 39 ላይ የተዋደደው የመጠበቂያ ቀለበት ከተነቀለ የሚያስከትለው መዘዝ ‹‹ጦርነትን እንሠራዋለን…›› ለሚሉት ሰዎች የሚጠፋቸው አይመስለንምና ነው ዛሬም የብሔራዊ ዕርቅ ጥሪ እናሰማለን የምንለው ፡፡

...እኛ በአብዛኛው (ሰዋዊ

ባሕሪ ነው ቢባልም) ትላንት

አውቆም ይሁን ሳያውቅ…

የጎዳንን፣ ‹‹በእንጀራችን ላይ

ቆሞ ነበር…›› የምንለውን፣

የመሰከረብንን፣ የተኮሰብንን፣

ያስተኮሰብንን፣ አንድ ጥቅም

ያሳጣንን ወይም ያጓደለብንን

ብቻም ሳይሆን ‹‹እንደዚያ

ለማድረግ አስቦ ነበር ወይም

ከማድረግ የማይመለስ ሰው

ነበር›› በማለት የምንገምተውን

ወይም የምንጠረጥረውን ዜጋ፤

ገብቶትም ይሁን ሳይገባው…

12 °”l 6— ¯Sƒ lØ` 119 ግንቦት 2006 ዓ.ም

የዕንቁ እንግዳ

ዕንቁ፡- ከግንቦት 20 ቀን 1983 ዓ.ም በፊት ያልተመለሱት መሠረታዊ የፖለቲካ ጥያቄዎችን ባጭሩ ቢነግሩን?

አቶ ገብሩ ገ/ማርያም፡- ትልቁና ዋንኛው ጥያቄ የብሔር ብሔረሰቦች መብት ጉዳይ ትኩረት የተነፈገው ከመሆኑ አኳያ የነበረው ነው፡፡ ሌላው ዴሞክራሲያዊ መብቶች ያለመጠበቃቸው ነው፡፡ ብሔር ብሔረሰቦች ራሳቸውን በራሳቸው የማስተዳደር፣ባሕላቸውን ለማሳደግም ይሁን በቋንቋቸው በአግባቡ የመጠቀም መብትን አለማግኘታቸው ጉዳይ ያዋለዳቸው ጥያቄዎች ነበሩ፡፡

ዕንቁ፡- ኢሕአዴግ የኢትዮጵያን ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ጥያቄዎች መልስ እንዲያገኙና ዜጐች የነፃነት ባለቤት እንዲሆኑ ታግያለሁ ብሏል፡፡ ባለፉት 23 ዓመታት ኢሕአዴግ የታገለላቸው ጥያቄዎች ተመልሰዋል ወይ?

አቶ ገብሩ፡- አልተመለሱም፡፡ ኢሕአዴግ የመለሰው አንድም ጥያቄ የለም፡፡

ዕንቁ፡- የመድብለ-ፓርቲው ሥርዓት አስፈላጊነት ጉዳይ ሕገ መንግሥታዊ ድጋፍ ያለው ነበረ፡፡ ነገር ግን ባለፉት 23 ዓመታት ይኸው የመድብለ-ፓርቲ ሥርዓት ይሰፍን ዘንድ ግንቦት 20 ምን ያበረከተው ነገር አለ?

አቶ ገብሩ፡- የደርግ ሥርዓት በወደቀበት ጊዜ አብዛኛውም ባይሆን ከፊሉ የኢትየጵያ ሕዝብ ‹‹ፍትሕ፣ ዴሞክራሲ፣ እኩልነት በዚህች ሀገር ላይ ይሰፍናል ብሎ ተስፋ በማድረግና ስለዚህም ተስፋው እውን መሆን ደስታውን ለመግለጽ በኢሕአዴግ ታንኮችና የጦር ተሽከርካሪዎች ላይ የአበባ ጉንጉን አስቀምጦ ነበር፡፡ እንዲህም ሆኖ ኢሕአዴግ በገባበት ጊዜ የተደበላለቀ ስሜትም በአደባባይ ተስተውሏል፡፡ ሁሉም ሕዝብ የአበባ ጉንጉንና የዘንባባ ዝንጣፊ ይዞ አልተቀበለውም፡፡ ኢሕአዴጐች ወደ ሥልጣን ሲመጡ በመላው ኢትዮጵያ የነበረው ስሜት የተደበላለቀ ነበር፡፡ ‹‹የብሔር ብሔረሰቦችን እኩልነት አከብራለሁ! ዴሞክራሲን አሰፍናለሁ! የመድብለ-ፓርቲ ሥርዓትን እፈጥራለሁ!›› እያለ በመጀመሪያዎቹ ቀናት እንደዛሬው ሳይደላደል አንዳንድ ርምጃዎችን የወሰደውና ከሰባ በላይ የብሔር ብሔረሰብ ፓርቲዎች እንዲቋቋሙ የፈቀደው ኢሕአዴግ፤ ጥቂትም ሳይሰነብት ነበር ማንነቱን በውል ያሳወቀበትን ተግባሮች ማሳየት የጀመረው፡፡ የአብዮታዊ ዴሞክራሲ መፈክሮቹን ይዞ ቁጭ ያለው፡፡ ለምዕራባውያን ጭምር በአስመሳይነት ‹‹ዴሞክራሲን አሰፍናለሁ›› ብሎ ያታለላቸው መሆኑ በግልጽ የታየው፡፡

በነገራችን ላይ እነሱ አብዮታዊ ዴሞክራሲ የሚሉት፤ የአብዮቱ ወገን የሆኑ ሰዎች ማለትም ገበሬውን፣ ወዝ-አደሩን የዴሞክራሲ መብት ተጠቃሚ እንዲሆን፤ ሌሎችን ፊውዳል፣ ኢፔሪያሊስቶችና የእነሱም ደጋፊዎች ናቸው የሚሏቸውን፤ ይሄን ዴሞክራሲ ከልክሎ እነሱን መጨቆን፣….እንደማለት ነው፡፡ አሁን ኢሕአዴግ የማይፍልጋቸውን ሰዎች ለመጨቆንና እሱን የሚደግፉትን ለማገዝና ለማግዘፍ ካልሆነ በቀር አብዮታዊ ዴሞክራሲ ብሎ ነገር ያለ አይመስለኝም፡፡

ስለዚህ አብየታዊ ዴሞክራሲ የሚባለውን ነገር ብቅ አድርጐ፤ ዛሬ ብዙ የተባለለትና የተፎከረለት የመድብለ- ፓርቲ ሥርዓቱም ተቀልብሶ፣ ቀኝ ኋላ ዙር! ተብሎ የኢሕአዴግ የአውራ ፓርቲነት ዝማሬ ነው አሁንም በግንቦት 23ኛ ዓመት ዋዜማ ላይ ሆነን የምንሰማው፡፡ እኩለ ሌሊት ድረሰ ተቀምጬ ቴሌቪዥን እመለከታለሁ፤ አዲስ ነገር አላየሁም፡፡ ያው የነበረው የአብዮታዊ ዴሞክራሲ ቀረርቶ ብቻ ነው፡፡

እውነቱ ‹‹በቀን ሦስቴ ይበላል›› የሚባለው ነገር ቀርቶ ዘወትር እንደምናነሳው፤ ምሳ ከበላ ያው ለሁሉም በቂ ነው ብሎ የሚኖር ሕዝብ ነው የምናየው፡፡ የፖለቲካ ምህዳሩም ተዘግቷል ማለት ይቻላል፡፡ አብቦ የነበረው የፕሬስ ነፃነት ጉዳይ በአፍጢሙ ተደፍቷል፡፡ ለሐቅ በሐቅ የሚናገሩ ጋዜጠኞች በዝዋይና በቃሊቲ ታጉረዋል፡፡ ምርጫ በራሱ የማታለያና ሳጥን ገልብጦ ሰውን ለማስመሰያነት የመጠቀሚያ ብቻ የማድረግ ድራማ የሚሠራበት ሀገር ነውና እኔ በግንቦት 20 ምን መጣ ማለት እንደሚቻል አላውቅም፡፡

በርግጥ እነዚህ የሚታዩ የመንገድ፣ የድልድይና የባቡር መስመር ዝርጋታ ሥራዎች አንድ መንግሥት በመንግሥትነቱ የሚያከናውናቸው ተግባሮች ናቸው፡፡ ይሄን ያህል የሚያስፎክር አይደለም፡፡ ግን የተሠሩትም ቢሆኑ በብድር ገንዘብ ነው፡፡ የብድሩ ዕዳም ለልጅ ልጆቻችን የሚተላለፍ ነው፡፡ ማንም የራሱን ፍላጎት ወደ ጐን ብሎ ለሌላው የሚሠራ የለም፡፡ በአሁኑ ጊዜ ቻይናዎቹ በየትኛዎቹም መስኮች ኢትዮጵያ ውስጥ የሚሠሯቸው ሥራዎች በምፅዋት መልክ የቀረቡ ወይም ቅንጣት ዕዳ የሌለባቸው የበጎ አድራጐት ሥራዎች አይደሉም፡፡ የእኛው ቡና፣ ሰሊጥ፣ ኑግ፣ አበባውና ማንኛውም በዚች ሀገር ላይ የሚመረት ምርት ሁሉ ወደ ቤዥንግና ሻንጋይ በርካሽ ዋጋ እየሄደ ነው፡፡ ስለዚህ እነሱ የሚያደርጉትን ነገር

ሁሉ እንዲሁ በነፃ የሚሰጡን አድርጎ ማየት የፖለቲካውን ውስብስብነት ጠንቅቆ አለመረዳት ነው፡፡

ዕንቁ፡- የፌዴራል ሥርዓቱ መዋቅር በቋንቋቸውና በትውልድ አካባቢያቸው ምክንያት ለተፈናቀሉና ወደፊትም ይፈናቀላሉ ተብሎ ለሚታሰቡ ወገኖች ዋስትና መስጠቱን ያሳየ የግንቦት 20 ፍሬ ነውን?

አቶ ገብሩ፡- ይሄ ነው ችግሩ! ኢሕአዴግ ጋር ያለው ትልቁ ችግር ራሱ አስረቅቆ ያፀደቀውን ሕገ-መንግሥት እንኳ ያለ ማክበሩ ነው፡፡ ከፖለቲካው ምህዳርና ከመጋረጃው በስተጀርባ ከወጣሁበት ከ 1997 ዓ.ም ጀምሮ ደጋግሜ የምናገረው፤ እነ ዶክተር መረራም ከዚያ በፊት ደጋግመው የሚናገሩት፤ ኢሕአዴግ እኮ መስማት የማይችል ፓርቲ ሆኖ ለራሱ ሕገ-መንግሥት የማይገዛ ነው፡፡ ለሕገ-መንግሥቱ ላይ የተጻፉት እንኳ አልተከበሩም እኮ፡፡ የብሔር ብሔረሰቦች ነፃነት የምትለው እኮ አንዱን ክልል ታደርጋለህ፡፡ አንዳንዱን ደግሞ ትንሽ ሕዝብ በማለት ላንተ ፍላጐት እንዲመች ታደርጋለህ፡፡ ይሄ ይሄ ሕዝቦችን ለግጭት፣ ለጥላቻ በመዳረግ የራሱን ሥልጣን ለማራዘም የተፈጠረ ፓርቲ ነው፡፡ በቀለም በተዋቡ ቃላት ብዙ ማውራት ይቻላል፡፡ የፓርቲውን የተግቦር ዝርዝር ስትገባ ግን ብዙ ችግሮች፣ አሳፋሪ ቅሌቶች ታገኝበታለህ፡፡ ሰሞኑን እንኳን ብታይ፤ ራሳቸው ባለሥልጣኖቹ ‹‹የተማሪዎቹ ጥያቄ ትክክል ነው›› እያሉ በተቃራኒው ደግሞ ሕዝቡን በግዳጅ ሠላማዊ ሠልፍ እያስወጡ ተቃውሞው ትክክል እንዳልሆነ ያስነግራሉ፡፡ እንዲህ ዓይነት የተምታታ ነገር እስከመቼ እንደሚያዛልቅ እኔ አልገባኝም፡፡

ዕንቁ፡- ከፍ ሲል የገለፁትን የመሰሉ ችግሮች በሚስተዋሉበት ሀገር የሚገነቡት የመሰረተልማት አውታሮችና የኢንዱስትሪ ተቋማት ዘላቂ ዋስትና አላቸው ወይ?

አቶ ገብሩ፡- ዓይናችን እያየ ምን ዋስትና አለው ብለን እንመን፡፡ የኦሮሞ መሬት ተወስዶ ለባዕድ እየተሰጠ እኮ ነው፡፡ ክልል ከተከለለ በኋላ፤ ሕገ-መንግሥቱ ላይ ከተቀመጠ በኋላ፤ ይሄን ፌዴራሊዝም እነሱ የገነቡት ከታች ወደ ላይ እንደመረጡ እንዲወሰኑ ነበር፡፡ አሁን ያለው አፈፃፀም ግን ከላይ ወደታች በሕወሓት ፍላጐት ላይ ብቻ ያጠነጠነ አወቃቀር በመሆኑ ወደ ታች ወርዶ ነው የሚያስፈፅመው፡፡ ስለዚህ በዚህ መሠረት ክልሉ የተከለለ ስለሆነ የፌዴራል መንግሥት በዚህ ክልል በፈለገው ጊዜ ገብቶ ነው የሚሠራው እያልን እኮ ነው፡፡

ዕንቁ፡- የልማታዊ መንግሥትና የፌደራል ሥርዓት አብረው ሊሄዱ የሚችሉ ናቸው?

አቶ ገብሩ፡- እንግዲህ ልማታዊ መንግሥት የምንለው አስተሳሰብ በኋላ የመጣ ነው፡፡ ይሄ ከእንቅልፋቸው ሲነቁ ነው የሚፈጠረው፡፡ የፌዴራል ሥርዓት ገንብተህ ልማታዊ መንግሥት ልትል አትችልም፡፡ ሕዝቡ ምን ያህል አጥንጥኖ፣ አብላልቶ፣ በደንብ ሰልቆት እንደሚወሰደው ባላውቅም ኢሕአዴግ

የግንቦት 20ን ሃያ ሦስተኛ ዓመት በዓል ምክንያት በማድረግ ‹‹ ግንቦት 20 ለኢትዮጵያ ሕዝብ ያበረከተው ነገር ምን አንደሆነ…›› እንዲገልጹልን፤ የመድረክና የአንድነት ፓርቲ አመራር አባል የሆኑትን አቶ ገብሩ ገብረማርያምንና አቶ ሀብታሙ

አያሌውን አነጋገርናቸዋል፡፡ ፖለቲከኞቹ ለዕንቁ ዕንግዳ ዐምድ የሰጡትን ምላሽ እንደሚከተለው አቅርበነዋል፡፡

‹‹ኢሕአዴግ የመለሰው አንድም ጥያቄ የለም››

አቶ ገብሩ ገ/ማርያም

ወደ ገፅ14 ዞሯል

13°”l 6— ¯Sƒ lØ` 119 ግንቦት 2006 ዓ.ም

‹‹ግንቦት 20 አንድን ፈላጭ ቆራጭ በሌላ ፈላጭ ቆራጭ አገዛዝ ነው የተካው››

የዕንቁ እንግዳ

ዕንቁ፡- ከግንቦት 20 ቀን 1983 ዓ.ም በፊት ያልተመለሱት መሠረታዊ የፖለቲካ ጥያቄዎችን ባጭሩ ቢነግሩን?

አቶ ሀብታሙ፡- ከግንቦት 20፣ 1983ዓ.ም በፊት በነበረው ዘመን በፊውዳላዊ ሥርዓትና የደርግ ሥርዓት ውስጥ የነበረ የኢትዮጵያ ሕዝብ ጥያቄ አለ፡፡ አንዱና መሠረታዊው ጉዳይ ለዘመናት የዘለቀ የኢትዮጵያ ሕዝብ ጥያቄ ከድህነት የመውጣት ጥያቄ ነው፡፡ ከድህነት የመውጣት ጥያቄ ስንል ከሌላው ይቀድማል ማለቴ አይደለም፡፡ መሠረቱ የኢትዮጵያ ሕዝብ ለነፃነት ብሎ ነው፤ ዘመኑን ሁሉ የኖረው፡፡ ስለዚህ ከግፍ አገዛዝና ከፀረ-ዴሞክራሲያዊ አገዛዞች ነፃ የመሆን ጥያቄ ለረጅም ዘመን የቆየ ነው፡፡ ገዥዎች በራሳቸው ሕዝቡን ይጨቁኑት ነበረ፤ የውጭ ወራሪ ኃይሎች ገዥ ሆነው ጨቋኝ ሆነው ይመጡ ነበር፡፡ እንደ ሀገር ከውጭ ኃይሎች ሀገሪቷን እየተከላከለ ነፃነቱን ሲጠብቅ የነበረ ነው፡፡ ኢትዮጵያ በልዩ ሁኔታ የምትታወቀው በዓለም ላይ ነፃነታቸውን አስጠብቀው ከኖሩ ጥቂት ሀገራት ቀዳሚዋ በመሆን ነው፡፡ በቅኝ ያልተገዛች ነፃ ሀገር መሆኗ ነው፡፡

ስለዚህ የኢትዮጵያ ሕዝብ ነፃነቱን ሲጠብቅ የነበረ ኩሩ ሕዝብ ነው፡፡ በነፃነት ውስጥ የሚነሱት ዴሞክራሲያዊ እና ሰብዓዊ መብቶች ናቸው፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ ከሕዝቡ የወጡት ገዥዎች ዴሞክራሲና ሰብዓዊ መብቶችን አለማክበራቸውና ገዥዎች የፈለጉትን እርምጃ በፈለጉበት ጊዜ የሚወስዱበት ሥርዓት ነበር፡፡ የፍትህ ጥያቄ ገኖ

ይነሳ ነበር፡፡ የሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብት እጦትም አለ፡፡ ከነዚህም ጋር ተዳምሮ ከድህነት ነፃ የመሆን ጥያቄም በኢትዮጵያ ውስጥ ነበረ፡፡ እነዚህ አሁን የግንቦት ሃያ ፍሬዎች ነን ባሉ ኃይሎች ሲነሱ፣ በቡድን ተደራጅተው የቡድን ነፃነት እናመጣለን ብለው የተነሱ ናቸው፡፡ ሕዝቡ ለዘመናት ሲጠይቅ የነበረውን የነፃነት ጥያቄ እንቀርፋለን፣ ፍትህ እናመጣለን፤ ዴሞክራሲያዊና ሰብዓዊ መብቶች እንዲከበሩ በአጠቃላይ ኢትዮጵያ ለሕዝቦቿ የምትመች እንድትሆን እንፈልጋለን በሚል መርህ በቡድን ተደራጅተው ከደርግ የተገለለ ክልል መሠረት ነው፡፡

ለአብነት ያህል ነፃ ትግራይ ሪፐብሊክ መንግሥት ለመመስረት ሕወሓት፤ ከኢትዮጵያ የተገነጠለች የትግራይ ሪፐብሊክ ለመመስረት ሻዕብያ፤ ከኢትዮጵያ የተገነጠለ የኦሮሞ ሪፐብሊክ ለመመስረት ኦነግ፤ የኦጋዴን ነፃ አውጭን ለመፍጠር ኦብነግ ወዘተ እያሉ ከ19 የማያንሱ ነፃ አውጪዎች ለነፃነት፣ ለዴሞክራሲ፣ ለእኩልነት፣ ጥያቄ መልስ አላገኘንም፡፡ ሁሉንም በእኩል ዓይኗ የምትመለከት ኢትዮጵያ አልተፈጠረችም በሚል ስሜት፣ ነፃነት ሊገኝ የሚችለው ከኢትዮጵያ ስንገነጠል ብቻ ነው የሚል መፍትኼ ይዘው በየጫካ የሰፈሩ ናቸው፡፡ በመጨረሻው ሰዓት ደርግ ሲወድቅ ኢትዮጵያን የማስተዳደር ዕድል እንደተገኘ ሲረዱ ደግሞ አንድ ወደመሆን የመጡ ናቸው፡፡

አንድ ለመሆን ያልተስማሙት ደግሞ አሁንም በዱር በገደሉ ናቸው፡፡ የመጀመሪያ ፍላጎታቸው ይሄ ነበር፡፡ እንጂ ቀድሞውንም በኢትዮጵያ ውስጥ ዜጎች በአመለካከታቸው የማይታሰሩበት፤ ዲሞክራሲያዊና ሰብዓዊ መብቶች የተከበረበት፤ የፍትህ ሥርዓቱ ቀልጣፋና ለሁሉም ዜጋ በእኩል የሚያገለግልበት፤ ነፃ

የገበያ ሥርዓት ያለበት፤ በኢኮኖሚ ሁሉም እኩል ሊወዳደር የሚችልበት፤ የሁሉም ባሕል ቋንቋ፣ ሥርዓት፣ ወግ የመሳሰሉት እኩል የሚከበሩበት፤ ዜጎች በሃይማኖታቸው የማይበላለጡባት ሀገርን እንፈጥራለን ብለው የተነሱ፣ የተመሠረቱ ቡድኖች አይደሉም፡፡

ዕንቁ፡- ስለዚህ? አቶ ሀብታሙ፡- በዚህ አስተሳሰብ ከመጡ በኋላ

በድንገት ባልጠበቁት ሁኔታ ደርግ እየተፍረከረከ በመሄዱ ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር የመምራት ዕድሉን ሲያገኙ ያን የመገነጣጠል ዓላማ ቀየሩ አስቀድመው ግን የሕዝቡን ጥያቄ መመለስ የሚያስችል ቲዮሪ(እሳቤ) ያልሠሩ፤ ቀድሞም ለዚያ ያልተዘጋጁ፤ በመገነጣጠሉ ላይ ብቻ እምነት ይዘው የታገሉ መሆናቸው፤ ከዚያ በኋላም በሥልጣን እስካሁን ባሉበት ዘመን ሥልጣኑን ጠብቆ ለመቆየት የሚያስችላቸውን ሥርዓት ከመዘርጋት ባሻገር፤ የሕዝቡን የዘመናት ጥያቄ ለመመለስ አቅምም ፍላጐትም ያጡበት ሁኔታ ነው የሚታየኝ፡፡

ዕንቁ፡- ኢሕአዴግ የኢትዮጵያን ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ጥያቄዎች መልስ እንዲያገኙና ዜጐች የነፃነት ባለቤት እንዲሆኑ ታግያለሁ ብሏል፡፡ ለመሆኑ ግንቦት 20 ለኢትዮጵያ ሕዝብ ያበረከተው ነገር አለው ወይ?

አቶ ሀብታሙ፡- እኔ በአጠቃላይ ግንቦት 20 ለኢትዮጵያ ያበረከተው ነገር ሕወሓት የሚባል ጉልበታም ድርጅት ሌሎችን ድርጅቶች እንደ ትሮይ ፈረስ ጭኖ እየጋለበ ሀገሪቷን ለማያቋርጥ 23 የአበሳ ዓመታት መርቶ ለቀጣይ አርባ ዓመት ለመምራት ያቀደበትን ሥርዓት ነው ያሠፈነው ብዬ እወስደዋለሁ፡፡ ግንቦት 20 ያመጣልን ነገር ቢኖር ደርግ የሚባል ጉልበታም አስወግዶ ሕወሓት የሚባል ጉልበታም አምጥቶ አነገሰ፡፡ ቴዲ አፍሮ ‹‹አዲስ ንጉሥ እንጂ ለውጥ መቼ መጣ›› እንዳለው ትላንት ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ይጣሳሉ፤ ዛሬም ይጣሳሉ፤ እየተጣሱም ነው፡፡ የቅርፅና የስልት ካልሆነ በስተቀር በይዘት ደረጃ ትናንት ደርግ ሲያደርገው የነበረውን ነው ኢሕአዴግ እየሠራ ያለው፡፡ የተለየ ነገር አለ ማለት ይከብዳል፡፡ ግንቦት 20 አንድን ፈላጭ ቆራጭ በሌላ ፈላጭ ቆራጭ አገዛዝ ነው የተካው፡፡

በመሠረቱ ከደርግ በፊት የነበረው የረጅም ዘመናት የሕዝብ ጥያቄ 23 ዓመታት በቆየው የኢሕአዴግ ሥርዓት ውስጥ ሊመለስ አልቻለም፡፡ ይሄን ካነሳን የመድብለ-ፓርቲ ፖለቲካ ሥርዓት የሚባለው ቀድሞውንም የሚመነጨው ዴሞክራሲያዊ አስተሳሰብ ካለውና በአንድ ሀገር ዴሞክራሲያዊ ስርዓትን ለማስፈን ከሚፈልግ የአገዛዝ ስርዓት ነው፡፡ የመድብለ-ፓርቲ ፖለቲካ ሥርዓት በኢትዮጵያ እንዲያብብ በሰነድ ደረጃ በሕገ-መንግሥቱ የተጠቀሰ ቢሆንም ለሁሉም እኩል በሆነ መልኩ የፖለቲካ ምህዳሩ ክፍት ቢደረግ ይህ የሚጨቆነው ሕዝብ ኢሕአዴግን በሥልጣን ለማቆየት የሚያስችል የአንድ ደቂቃ ዕድል የለውም ነበር፡፡

ዕንቁ፡- የመድብለ-ፓርቲው ሥርዓት

አቶ ገብሩ ገ/ማርያም

እስከዛሬ ድረስ ስንቱ ጋዜጠኛ ካገሩ

እየተባረረ ተሰደደ፡፡ ስንቱ በእስር

ቤት ተወረወረ፡፡ ስንቱ ለሞት

በቃ፡፡ ስንቱ ወደ ድህነት ሄደ፤

የቱ ነው ነፃነት? ስለዚህ ነፃነት

ምላሽ አላገኘም፡፡ አንዲት ጥያቄ

ለኢትዮጵያ ሕዝብ ኢህአዴግ መጥቶ

ይህንን መልሷል የሚባል የለውም፡

፡ የብሔር ጥያቄ ራሱ አሁንም

ስላልተመለሰ በየቦታው እየተነሳ ነው

አቶ ሀብታሙ አያሌው

14 °”l 6— ¯Sƒ lØ` 119 ግንቦት 2006 ዓ.ም

የዕንቁ እንግዳ

የሚለው ነገር በፍፁም! በፍፁም! ከሕዝቡ ፍላጐት ጋር የማይሄድ ነው፡፡ ዴሞክራሲና ልማት ልዩነት የላቸውም፡፡ ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ ለሕዝቦች የማይበጅ ልማት፤ ልማት ሊባል አይችልም፡፡ ዞሮ ዞሮ ለሰው ልጆች የሚሠራው ማንኛውም ልማት ለሰው ልጅ ልማት ነው የሚሠራው፡፡ ልማት ከሌለ፣ ለሰው ልጅ የማይበጅ ከሆነ፣ የሰውን ልጅ ችግር መቅረፍ የማይችል ልማት ከሆነ፣ ለሰው ልጅ ፋይዳ የማያመጣ ከሆነ፣ የሰውን ልጅ ችግር መፍታት የማይችል ከሆነ፤ ‹‹ልማት መጥቷል›› የሚለው ትርጉሙ አይገባኝም፡፡ ይሄ በየቦታው የሚወራለት ልማት የሕዝባችን ኪስ ውስጥ ገብቶ ረሃቡን አስወግዷል ወይ? የሕክምና እጦቱን፣ የንፁህ መጠጥ ውሃ ችግሩን፣ ትምህርቱ ጥራት አለማግኘቱን፣ በርሃብ መቀጣትና ስደቱን፣ ሌሎች ሊነሱ የሚችሉ እጅግ በርካታ ችግሮችን ልማቱ አስወግዷል ወይ? ሕዝቡን በሰላም እንዲኖርስ አድርጐታል ወይ?

ስለዚህ እነዚህን የማይፈታ ልማት ለነማን አየለማ እንደሆነ አይገባኝም፡፡ በእርግጥ የነማን ልማት እንደሆነ ታሪክ ወደፊት ይፈታዋል፡፡ በሕዝብ ሀብት የሚበለጽጉት እነማን እንደሆኑ ታሪክ ያወጣዋል፡፡ ዴሞክራሲና ልማት የሚነጣጠሉና ሊነጣጠሉ የሚችሉ አይደሉም፡፡ የተሳሰሩ ናቸው፡፡ እንዲያውም የዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ለልማት በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ የሕዝቡን ተሳትፎ የሚያጠናክርና አለ የሚባለውንም ልማት ቀጣይነቱን የሚያጠናከር የሚሆነው፤ ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓቱ ሕገ-መንግሥታዊ ጥበቃ እግኝቶ፤ ዜጐች የመናገር የመጻፍ መብታቸው ሳይከበር ስለልማት ማውራት ካፕሮፖጋንዳ የዘለለ ትርጉም የለውም፡፡

ዕንቁ፡- በአሁኑ ወቅት በኦሮሚያ ክልል በሚኖሩ የሌሎች ብሔረሰብ አባላት ላይ ስለሚሰነዘርው ጥቃት የእርስዎ አስተያየት ምንድን ነው?

አቶ ገብሩ፡- በግሌ ማንም ሰው ላይ ጉዳት እንዲደርስ አልፈልግም፡፡ እንደ ፓርቲም ይህን የመሰለውን ነገር ፈጽሞ የማንቀበለው ነውና የምንቃወመው ነው፡፡ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች ተፋቅረውና ተዋደው በስምምነት ሲኖሩ፣ አብሮነታቸውን ሲያከብሩ የኖሩ ብሔረሰቦች ናቸው፡፡ ይሄ መከባበር፣ ይሄ መፈቃቀድ፣ ይሄ አብሮነት እንዲቀጥል ነው ሁሌም የምመኘው፡፡

በተቃራኒው ጥላቻንና አጥቂነትን የሚያራግቡ ሰዎች ካሉም፤ በእውነት ነው የምልህ ለማንም የሚጠቅም ተግባር አይደለም የሚያከናውኑት፡፡ ይሄን ግን ሆን ብለው የሚያደርጉ ኃይሎች በየትኛውም ክፍል እንዳሉ በጣም እርግጠኞች ነን፡፡ በየትኛውም ክልል የፖለቲካ ጥቅማቸውን ለማስጠበቅና በምርጫ ዋዜማ ሕዝቡን ደብድቦ ፀጥ ለማሰኘት የታሰበም ይመስላል፡፡ ስለዚህ ይሄ ነገር ለማንም አይበጅም፡፡ በአንዳንድ ክልሎች ደግሞ ከአመጣጣቸው፣ ከአፈጣጠራቸው ጀምሮ ይሄን ነገር ከማድረግ የሚቆጠቡ አይመስልም፡፡

ዕንቁ፡- ቀደም ሲል ላቀረብነው የልማቱና የኢንዱስትሪው መስፋፋት ዋስትና ጉዳይ ላይ አጥጋቢ ምላሽ የሰጡን አይመስለንም፡፡

አቶ ገብሩ፡- ነገርኩህ እኮ! አንድ መንግሥት በጀት አለው፡፡ አንድ መንግሥት እርዳታ ያገኛል፡፡ ብድር ይጠይቃል፡፡ ሌሎችም የታክስ፣ የግብር ገቢዎች አሉት፡፡ መሬት በሊዝ በመቸብቸብ የሚያገኘውም ገቢ አለ፡፡ በዚህ በኩል የሚቆጣጠራቸው አካል የለም፡፡ ‹‹የት አደረሳችሁት?›› የሚላቸው የለም፡፡ በጨረታ ተብሎ፤ ዓይናችን እያየ ከገበሬ ከ100 ብር ባነሰ መሬት እየተወሰደ በአስራ ሰባት ሺህ ይሸጣል፡፡ የሚሠራው እኮ በነዚህ አሁን ባልኳቸው ሁሉ ነው፡፡ የግንቦት 20 ቱርፋት አይደለም እኮ፡፡ የኢትዮጵያን ሕዝብ አንጡራ ሀብት እየዘረፉ ወስደው በተራረፈው ይሄን የሚታየውን ቁሳዊ ልማት ሠርተው የግንቦት 20 ቱርፋት ነው ማለት ቀልድ ነው፡፡

ከ ገፅ 12 የዞረኢሕአዴግ...

አስፈላጊነት ጉዳይ ሕገ-መንግሥታዊ ድጋፍ ያለው ነበረ፡፡ ነገር ግን ባለፉት 23 ዓመታት ይኸው የመድብለ-ፓርቲ ሥርዓት ይሰፍን ዘንድ ግንቦት 20 ምን ያበረከተው ነገር አለ?

አቶ ሀብታሙ፡- የመድብለ ፓርቲ የፖለቲካ ሥርዓት ሊያብብ የሚችለው ነፃና ገለልተኛ በሕዝብ የሚታመን ፍርድ ቤት ያለ እንደሆነ፣ ሁሉም ፓርቲዎች እምነት የሚጥሉበት ምርጫ ቦርድ ያለ እንደሆነ፣ የፀጥታ ኃይሉን የሚቆጣጠሩ የደህንነት፣ የፖሊስ፣ የመከላከያ አካላት ገለልተኛ ሆነው ሕዝቡን ብቻ ማገልገል የቻሉ እንደሆነ ነው፡፡ ይህ ግን አልሆነም፡፡ ይህን እኔ አይደለም የምለው፡፡ ኪሊማንጃሮ የሚባል መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት ባስጠናው ጥናት እንደተረጋገጠው በኢትዮጵያ እምነት ከማይጣልባቸው ተቋማት መካከል ምርጫ ቦርድ፣ የፀጥታ ኃይሉ፣ ፍርድ ቤት፣ ተጠቃሾች ናቸው፡፡ የነዚህ ተቋማት ነፃነት ባልተረጋገጠበት ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት የሚባል ነገር አይታሰብም!

ዕንቁ፡- የፌዴራል ሥርዓቱ መዋቅር በቋንቋቸውና በትውልድ አካባቢያቸው ምክንያት ለተፈናቀሉና ወደፊትም ይፈናቀላሉ ተብሎ ለሚታሰቡ ወገኖች ዋስትና መስጠቱን ያሳየ የግንቦት 20 ፍሬ ነውን?

አቶ ሀብታሙ፡- እንግዲህ ባለፉት 23 ዓመታት ኢሕአዴግ ሕገ-መንግሥት ደረጃ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች እኩልነት፣ ሉዓላዊነት አግኝተዋል እያለ ነው፡፡ ከየትኛውም ያለፉ ሥርዓቶች በባሰ ሁኔታ በኢትዮጵያ ውስጥ ዋነኛ የግጭት ምንጭ ብሔር ብሔረሰብ ሆኗል፡፡ በየትኛውም የሀገሪቷ ክፍል መረጋጋት የለም፡፡ ወደ ስሜኑ የሄድክ እንደሆነ ራያ አዘቦ፤ ራያ ቆቦ፣ የሚል ክፍፍል ተፈጥሮ አንዱ ራያ ነኝ ሲል እኔ ቆቦ ተብዬ ወሎ አዘቦ ተብዬ ትግራይ ልባል አይገባም በሚል ሙግት አንስተው ጉዳያቸው በፌዴሬሽን ምክር ቤት እየታየ ነው፡፡

ሌላው ወደ አፋር የሄድን እንደሆነ አፋር ክልል የሚኖሩ የትግራይ ብሔረሰብ አባላት ወይም የትግርኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች በሙሉ ይውጡልን ብለው አስወጥተው በቅርብ ጊዜ ፌዴሬሽን ምክር ቤት መጥተው አቤቱታ ሲያቀርቡ ነበር፡፡ አሁን ደግሞ ወደ ወለጋ ነቀምት፣ አምቦ መስመርን ይዞ አማርኛ እየተናገርክ እዚህ ክልል ላይ መኖር አትችልም የሚል ፅንፈኛ አስተሳሰብ እያደገ በብሔሮች መካከል የከረረ ግጭት የተፈጠረበት ሁኔታ እንዳለ ነው የምንረዳው፡፡ በደቡብ አካባቢ ቁጫ የሚባል የወላይታ ማኅበረሰብ ‹‹እኔ ወላይታ አይደለሁም ቁጫ ነኝ› የሚል ጥያቄ አቅርበው ከ 350 በላይ አባዋራዎች የማንነት ጥያቄ ስላነሱ እስር ቤት ናቸው ያሉት፡፡

እዚያው ከደቡብ ሳንወጣ ዶርዜን መውሠድ እንችላለን ጋሞናችሁ ተብለን በጥቅል ተፈርጀናል እኛ ዶርዜ እንጂ ጋሞ አይደለንም የሚል ጥያቄ አንስተው በዚህ ውዝግብ ውስጥ ይገኛሉ፡፡ ፌዴሬሽን ምክር ቤት በየዓመቱ ከስምንት ያላነሱ የብሔረሰብ የጐሣ ጥያቄዎች እየቀረቡ እነሱን መፍታትና አንድ ማድረግ አልተቻለም፡፣ በዚህ ሀገር ውስጥ በቋንቋቸው፣ በአነጋገር ዘይቤያቸው በትንንሽ የባሕል ቅርፃቸው ተለያይተው አንዱ ካንዱ በጋራ የማይኖሩበት ሥርዓት የተፈጠረው ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የቋንቋ ፌዴራሊዝም የፈጠረው የመለያየት፣ የመከፋፈል ፖለቲካ የፈጠረው አደጋ ነው፡፡ በዩኒቨርሲቲዎች በአሳፋሪ ሁኔታ ባለፉት ዘመናት ሁሉ የብሔረሰብ እኩልነት ጥያቄ አነሱ የሚባሉት የነዋለልኝ የአማራ ሳይንት ተወላጅ፤ እነ ጥላሁን የወሎ ልጆች ናቸው፡፡ ያኔ አማራ ሆኖ መወለድ፣ ኦሮሞ ሆኖ መወለድ፣ ጉራጌ ሆኖ መፈጠር ከየትኛውም ቤተሰብ መገኘት አያስፈልግም ነበር፡፡ የኦሮሞን ሕዝብ መብት ለማስከበር ኢትዮጵያዊነት ብቻ በቂ ነበር፡፡

ዕንቁ፡- ኢሕአዴግ ከታገለላቸው መሠረታዊ ጥያቄዎች በላይ በአሁኑ ጊዜ ተጨማሪ ጥያቄዎች እየቀረቡለት አይደለም ወይ?

አቶ ሀብታሙ፡- እውነት ነው፡፡ በየቀኑ የሚወለዱት ጥያቄዎች ለማመን በሚያስቸግር ሁኔታ ከዓቅም በላይ ሆነዋል፡፡ በቀን 3 ጊዜ የሚመገብ፣ ከድህነት የተላቀቀ ማኅበረሰብ

እንፈጥራልን ተብሎ በየመንግስት ሚዲያው ሲደሰኮር በድህነቱ ከሆነ በሱስና በርሃብ እየናወዘ መከራውን የሚያይ ትውልድ እየተፈጠረ እንደሆነ ሁሌም የምናየው ነው፡፡ ከአራቱ ጥያቄ የትኛው ነው የተመለሰው ፍትህ ከሆነ መቼም የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በአጠቃላይ እንዲሁም የኢትየጵያ ሕዝቦች በአጠቃላይ ራሳችንን ልንዋሽ አንችልም፡፡ ፍትህ የአንድ ፓርቲ ሥልጣንና ጥቅማጥቅም ማስከበሪያ ሆኗል፤ የፍትህ ስርዓቱ ፓርቲውን የተቃወመ፣ የተቸ ሁሉ ገደል የሚገባበት ሥርዓት ነው ያለው፡፡ የፍትህን ጥያቄ ኢትዮጵያ ውስጥ መመለስ አልተቻለም፡፡ አሁን ኢንተርቪው የምታደርገው መፅሔት ነገ ላለመዘጋቱ ዋስትና የለህም፡፡

እስከዛሬ ድረስ ስንቱ ጋዜጠኛ ካገሩ እየተባረረ ተሰደደ፡፡ ስንቱ በእስር ቤት ተወረወረ፡፡ ስንቱ ለሞት በቃ፡፡ ስንቱ ወደ ድህነት ሄደ፤ የቱ ነው ነፃነት? ስለዚህ ነፃነት ምላሽ አላገኘም፡፡ አንዲት ጥያቄ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ኢህአዴግ መጥቶ ይህንን መልሷል የሚባል የለውም፡፡ የብሔር ጥያቄ ራሱ አሁንም ስላልተመለሰ በየቦታው እየተነሳ ነው፡፡ በዓመት ሠባት ስምንት ውዝግቦች ይነሳሉ፡፡ ኢሕአዴግ እኮ ለሆድ ቁርጠት ታማሚ የራስ ምታት ኪኒን ወይም ሆዱን ላመመው መነፅር እያዘዘ ነው የተቸገረው፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ የነበረው ችግር በሀገሪቱ የአንድነት ጥላ ሥር የመዋል ሳለ አሁን ግን ከባህል አንፃር ጥያቄ ነው፤ የነፃነት መብት ጥያቄ ነው፤ እኩል አንሁን ጥያቄ ነው ሁልጊዜ የምትሰማው፡፡ እነዚህን ጥያቄዎች መንግስት መመለስ ሲገባው በብሔር አስምሮ፣ የልዩነት ወሰኑን አድምቆ ሕዝቦቹን በመለያየት ለትርምስ የዳረገ ሥርዓት ነው፡፡ ስለዚህ አንድም ጥያቄ አልተመለሰም፡፡

ዕንቁ፡- ከፍ ሲል የገለፁትን የመሰሉ ችግሮች በሚስተዋሉበት ሀገር የሚገነቡት የመሰረተልማት አውታሮችና የኢንዱስትሪ ተቋማት ዘላቂ ዋስትና አላቸው ወይ?

አቶ ሀብታሙ፡- የኢትዮጵያ ሕዝብ የዘመናት ጥያቄ ማኅበራዊ ልማት እንጂ ቁሳዊ ልማት አይደለም፡፡ ቁሳዊ ልማት በኋላ የሚከተል ነው፡፡ ጤናማ የሆነ በበጎ ስነምግባር የታነፀ፤ ራዕይ ያለው ትውልድ ከሌለ ቁሳዊ ልማቱ ለማነው? ትውልዱ በሱስ እየደከመ፣ ጥራት በሌለው ትምህርት እየሾቀ አገሩን ለቆ ለመሰደድ እየወሰነ፣ ጤናማ ማኅበረሰብ መፍጠር ሳይቻል መንገድ ብትሠራ፣ የእርዳታ እህል ከማመላለስ ውጭ ምንድነው የምታደርገው? በእውነት የሚሠሩትስ መንገዶችና ልማቶች በምሁራዊ ዓቅም ነው የተሰሩት? ለምሣሌ መንገዶቹ እና ህንፃዎቹ ስንት ዓመት እንዲቆዩ ሆነው ነው እየተሰሩ ያሉት? ሁለት ዓመት ሳይሞላቸው የሚቆፈሩ መንገዶች እኮ ናቸው፡፡ በዓመቱ የሚፈረካከስ ብሎኬት እኮ ነው ህንፃዎች እየቆሙ ያሉት፡፡ አንድ ሰው የስድስትና የሰባት ህንፃ ባለቤት ሆኖ በድንገት ይገኛል፡፡

በአዲስ አበባ ከ5ሚሊዮን ከሚገመተው ሕዝብ ውስጥ ስንቱ ሰው ነው ፎቅ የሠራው? የተማረ ማኅበረሰብ፣ ጤናማ ትውልድ በሌለበት እንዴት ነው ልማት ሊመጣ የሚችለው? በአጠቃላይ ከቁሳዊ እድገት ማህበራዊ እድገት በዋናነት ይቀድማል ብለን ብንሰማማ እንኳ ማኅበራዊ መግባባት በሌለበት፣ ማኅበራዊ ድቀት ባለበት ህዝብ ውስጥ ልማት እንዴት ነው ቀጣይነት ሊኖረው የሚችለው? እንዴትስ ዋስትና ሊሆን ይችላል? ባለሀብቱ ዋስትና የለኝም ብሎ የሚያስበው እኮ በሀገሪቱ ውስጥ የሶሻል (ማኅበራዊ) ቀውስ፤ የፖለቲካ ቀውስ ሲኖር ነው፡፡ እነዚህ ቀውሶች ካሉ (ልማት) የሚባል ነገር አይኖርም፡፡ ማኅበራዊ እድገት መረጋጋትን ይፈልጋል፡፡ ቀውስ ካለ ማኅበራዊ እድገት አይኖርም ማኅበራዊ እድገት ከሌለ ደግሞ ቁስ እድገት ሊሆን አይችልም፡፡ እነዚ ሁሉ ባሉበት ቀጣይነት ያለው ልማት የሚባል የሚታሰበብት አይደለም፡፡ ወቅታዊም ይሁን ለፕሮፖጋንዳም ይሁን ምርጫን ተንተርሰው የሚነሱ የቁስ ልማቶች ናቸው እየበዙ የሚታዩት፡፡ እነዚህ ደግሞ ከቀጣይነት አንፃር ብዙ ርቀት ሊሄዱ አይችሉም ነው የምለው፡፡

15°”l 6— ¯Sƒ lØ` 119 ግንቦት 2006 ዓ.ም

ፖለቲካ

ነሐሴ 12 ቀን 1977ዓ.ም በሕይወቴ የማትረሳኝ ቀን ናት፡፡ ለበርካታ ጊዜያት ወደ ተለያዩ የአውሮፓና የአፍሪካ ሀገራት የመጓዝ ዕድል የነበረኝ ቢሆንም በዚያች ቀን በግብፅ የኢትዮጵያ

ኤምባሲ በዲፕሎማትነት በመመደቤ ወደ ግብፅ ዋና ከተማ ካይሮ አቀናሁ፡፡ ለረዥም ጊዜያት ከሀገር ውጭ መኖር በእጅጉ ከሚያስጨንቃቸው ሰዎች አንዱ በመሆኔ ነው መሠል ካይሮ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ አውሮፕላኑ ሲያርፍ አስፈላጊውን ፎርማሊቲ አጠናቅቄ ሊቀበሉኝ የሚጠብቁኝ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ባልደረቦች ጋራ እስክገናኝ ድረስ መንፈሴ ታውኮ ነበር፤ በትካዜ ተውጬ ነበር፡፡ የኤምባሲው ባልደረቦች ጋራ ከተገናኘሁ በኋላ ብቸኝነቱና ድብርቱ ሲለቀኝ ተሰማኝ፡፡

በኤምባሲው መኪና ተሳፍሬ በካይሮ አውራጐዳና ግራና ቀኝ የቆሙትን ሕንፃዎች እያደነኩኝ፤ በአውራ ጐዳናው ስፋትና አሰራር በአግራሞት እየተመለከትኩ ከምጠብቃት በላይ ዘመናዊ ሆና ያገኘኋትን የካይሮ ከተማን ውበት እያጣጣምኩ፤ ኦክቶበር ስድስት በመባል በሚታወቀው ትልቅና ረዥም ድልድይ ላይ እያቋረጥን እያለ መኪና ውስጥ ከአጠገቤ ቁጭ ያለው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ባልደረባ “ይኼውልህ እንግዲህ አባይ ይህንን ይመስላል” ሲለኝ በውስጤ ከዚህ በፊት የማላውቀው ድንግርግር፣ ሽብር ሽብር የሚል ስሜት መላ ሰውነቴን አጥለቀለቀው፡፡ “በጣም ያምራል” የሚል ምላሽ ሰጠሁት፡፡

መኪናዋ ወደፊት እየገሰገሰች ቢሆንም የእኔ ስሜትና መንፈስ ግን ከወንዙ ላይ ቀርቶ ውሉን የማላውቀው ስሜት፤ የቁጭት ይሁን የሌላ ስሜት የተደበላለቀበት አንዳች ሃይል ውስጤን መናጥ ቀጥሎ ነበር፡፡ ይህ አይነቱ ስሜት አጋጣሚውን አግኝተው ካይሮን የጐበኙ ኢትዮጵያውያን ሁሉ ይሰማቸው ይሆን እያልኩ ማሰላሰል ጀመርኩ፡፡

በንዲህ ሁኔታ ላይ እያለሁ በእንግሊዝ ሀገር ኪንግስ ኮሌጅ ሎንዶን ውስጥ የፒኤች ዲ ዲግሪዋን ለማግኘት በናይል ወንዝ ላይ እየሠራች እንደሆነ የገለፀች ፖርቹጋላዊቷ ወደ ኤምባሲያችን መጥታ ኢትዮጵያን ለመጐብኘት የቪዛ ጥያቄ ካቀረበች በኋላ ፀሐፊዬን የኤምባሲውን ባለስልጣን ማናገር እፈልጋለሁ ስላለች ተዋወቅን፡፡ “አና እባላለሁ” ካለችኝ ሴት ጋር ባደረግሁት ቆይታ ስለ አባይ ወንዝ በርካታ የማላውቃቸውን ነገሮች ስትነግረኝ በመገረም ደንዝዤ ማዳመጥ ብቻ ነበር ምርጫዬ፡፡ ጽሁፎችን እንደምትልክልኝ ቃል ገብታልኝ የኢሜል አድራሻ ተለዋውጠን ተለያየን፡፡

ጥንታዊያኑ ግብፆች የአባይ ወንዝን የተፈጥሮ ፍሰት የሚገነዘቡት ከመለኮታዊ ኃይል ጋር በተያያዘ መንገድ ነበር፡፡ አባይ ወንዝ ለብዙ ሺህ ዓመታት ወደ ግብፅ ግዛት በመፍሰስ ዝናብ አጠር የሆነውን እና በረሃማውን የግብፅ ግዛት ለእርሻ ልማት ጥቅም እንዲሰጥ በማድረግ በአገሪቱ ኢኮኖሚ ውስጥ ጉልህ ድርሻ መጫወቱ ይታወቃል፡፡

በበርካታ ምሁራን እንደሚነገረው ግብፅ የአስዋን ግድብን በመገንባቷ በየዓመቱ በትነትና ወደ መሬት በማስረግ እስከ 10 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ውሃ እንደምታባክን የተረጋገጠ ነው፡፡ በመሆኑም በኢትዮጵያ ወይንም በሌሎቹ የላይኛው ተፋሰስ አገሮች የታላቁ ሕዳሴ ግድብ እና ሌሎች ተመሳሳይ ግድቦችን በመገንባት በአስዋን ላይ የሚባክነውን የውሃ መጠንን ማስወገድ ይቻላል፡፡ በዚህም የግብፅ ውሃ ፍላጐት ቢያንስ በዚህ መጠን በቋሚነት እንዲፈስ ማድረግ ለችግሩ እልባት መስጠት ይቻላል፡፡

ግብፅ ላለፉት ሃምሳ ዓመታት በተፋሰሱ ውስጥ አስጠብቃ የቆየችውን ብቸኛ ሃያል አገርነት፤ አዲስ በማቆጥቆጥ ላይ ባለው የኢትዮጵያ ሃይል

እየተፈታተነው ይገኛል፡፡ ኢትዮጵያ ከሶስት ዓመት በፊት በጀመረችው የታላቁ የሕዳሴ ግድብ ግንባታና የስድስት ሺህ ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግንባታ በቀጠናው በሃይድሮ ፖለቲካ ውስጥ አገሪቱ ተፅዕኖ ፈጣሪ እንድትሆን ከማድረጉ አንፃር ግብፆች ፍትሃዊ እና ወቅታዊ የውሃ አጠቃቀም ታሪካዊ መብት በማንሳት ለውዝግብ፣ ለፖለቲካ ውጥረት መፈጠር ምክንያት መሆናቸውን ቀጥለዋል፡፡ ግብፅ በናይል ተፋሰስ ብቸኛዋ ኃያል የነበረችው አስዋን ግድብን በመገንባቷ ነው፡፡

ይህን ብቸኛ ኃያልነትዋን አስከብራ የቆየችው ግብፅ ኢኮኖሚያዊ ይዞታዋ ከትላንት እስከ ዛሬ ምን ይመስላል?

ግብፅ በጋማል አብድል ናስር በመመራት ስርነቀላዊ መንግስት የሀገሪቱን ኢኮኖሚያዊ ሕይወት ለመለወጥ የአስዋን ግድብን ለመገንባት አስፈላጊነት ላይ ፅኑ አቋም በመያዝ በሙሉ አቅሙ ተንቀሳቅሶ በ 1960 ነበር የግድቡ ሥራ የተጀመረው፡፡

የአስዋን ግድብ 110 ሜትር ቁመት እንዲሁም 980 ሜትር ስፋት ከመሠረቱ ሲኖረው 43 ሚሊዮን ሜትር ኪዮብ ማቴሪያል ለግንባታው ውሏል፡፡ 11000 ሜትርኪዮብ ውሃን ከግድቡ በሰከንድ የማሳለፍ ብቃት ያለው ሲሆን ለአደጋ ጊዜ የሚሆን በሰኮንድ 5000 ሜትርኪዮብ ውሃ ማስተንፈሻ ተሰርቶለታል፡፡ ይህ ናስር ሃይቅ የተሰኘ ግድብ በዓለም ትልቁን ሠው ሠራሽ ሃይቅ በመፍጠር 550 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለውና ከዚህ ርዝመቱ 135 ኪሎ ሜትሩ በሱዳን ግዛት የሚገኝ ሃይቅ ፈጥሯል፡፡

በስር ነቀሉ የግብፅ አብዮት ከወሰዳቸው እርምጃዎች አንደኛው በጥቂት የመሬት ከበርቴዎች እጅ የነበረውን የመሬት ይዞታ ለአርሶ አደሮች በማከፋፈል የመሬት ላራሹን ጥያቄ በመፍታት የመሬት ባለቤትነት መብትን ማሪጋገጥ ግንባር ቀደሙ ነበር፡፡

ከዚህ በተጨማሪ አዲስ የእርሻ መሬቶቹ እየለሙ መሬት ለሌላቸው ትምህርታቸውን አጠናቀው የተመረቁ ሥራ አጥ ወጣቶችን እንዲከፋፈል አደረገ የሰፋፊ እርሻ ልማት በማስፋፋት የመንግስት እርሻዎች እንዲቋቋሙ አደረገ በዚህም የግብፅ የግብርና አብዮት አንድ እርምጃ እንዲራመድ ሆነ፡፡

የግብፅ ኢኮኖሚ በውጭ ከሚኖሩ ግብፃውያን ወደ ሀገር ቤት በሚልኩት ገንዘብ፤ የነዳጅ ዘይት ሽያጭ፤ የሲዊዝ ካናል ኪራይ ገቢ እና የቱሪዝም መስክ እንደ ቅደም ተከተላቸው ለኢኮኖሚው ዋና ዋና የገቢ ምንጭ ሆነው አገልግለዋል፡፡ የግብፅ መንግስት የአስዋን ግድብን ከገነባ በኋላ በ1986 ግዙፎችን የልማት ፕሮጀክቶች የግብርና የመሬት ይዞታ ሚኒስቴር በኩል (Land master plan) በተስማሚ የአፈር ይዞታና የውሃ ሀብት ላይ ጥናት በማካሄድ በዚህም ለግብርና ልማት አመቺ የሆነ የ 1.2ሚሊዮን ፌዳያን የእርሻ መሬት መኖሩን በጥናት አረጋገጠ፡፡ በዚህ ጥናት መሠረት በተነደፈው መሪ ዕቅድ በሲናይ 250,000 ፌዳየን ለግብርና ለማልማት ተስማሚ መሆኑ ቢታወቅም ከሶስት ዓመት በኋላ በተካሔደ ሌላ ጥናት 265,000 ፌዳያን የሚደርስ መሬት ሊለማ እንደሚችል ተረጋገጠ፡፡ የዚህ ፕሮጀክት አፈፃፀምና ፕላንን የመከታተል ኃላፊነት ከግብርና የመሬት ይዞታ ሚኒስቴር ወደ ሕዝብ የውሀ ሃብት ሚኒስቴር እንዲዘዋወር ተደርጐ የፕሮጀክቱ ዲዛይን ክፍል ተቋቋመ፡፡ የሜድትራንያን ባህር ዳርቻ ይዞ የሚገኝ የበረሃማ መሬት ለማልማት፤ የግብርና ምርትን ለማሳደግና ወደውጭ የሚላኩ ፍራፍሬዎችና የአትክልት ምርትን በመሰብሰብ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪን ሀገሪቱ እንድታገኝ አስችሏል፡፡

የአልሰላም ካናል “ዲኦሜታኦ” በመባል በሚታወቀው የናይል ወንዝ ቅርንጫፍ የሚፈሰው ወንዝ በመጥለፍ እና በሲዊስ ካናል ስር አሳልፎ ወደ ሲናይ

ልሳነምድር በማሸጋገር በ1997 እ.ኤ.አ ጥቅምት ወር ሥራውን በብሎክ አንድ በመጀመር 50,000 ፌዲያን መሬት አለሙ፡፡ ብሎክ ሁለት፣ ሶስት፣ አራት የተባሉ የሚታወቁትን የራባ ዞን ደቡባዊ ኢንታአራን እና ቤል አል አብድን አጠቃላይ አካባቢዎችን ለግብርና ልማት ማካሄጂያነት አዋለ፡፡

ብሎክ አምስት የተባለው ፕሮጀክት ዓላማ ውሃው የግብፅን ግዛት ክልል በማቋረጥ ፍልስጤምንና እስራኤልና ግዛቶች ጋራ በማገናኘት ነዋሪዎች የአባይ ወንዘ ውሃ ተጠቃሚ እንዲሁኑ እንደሚያደርግና የፕሮጀክቱ ድብቅ አላማም የናይል ተፋሰስ ሀገሮች የውሃ አጠቃቀም ዙሪያ ያለውን ችግር ከአፍሪካ ወደ መካከለኛው ምስራቅ በማዛመት ችግሩን ለማወሳሰብ የታለመ አካሔድ እንደሆነ ይነገራል፡፡

የግብፅ መንግስት በአባይ ወንዝ ላይ የተመሠረቱ የልማት ዕቅዶቹን ከ 2004 ጀምሮ ወደ ስርነቀል የኢኮኖሚ ዕድገት የሚያመጡ አድርጐ ወደ ትግበራ የገባበትና የፖሊሲ አቅጣጫ በማስቀመጥም በዋነኝነት አዳዲስ ከተሞችን እና የኢንዱስትሪ ዞኖችን ከናይል ወንዘ ሸለቆ ዴልታ ውጭ በመመስረት ላይ ያተኮረ እንቅስቃሴ በማካሄድ ላይ ነው፡፡ በዚህ መሰረት አስራ ስድስት አዳዲስ ከተሞች በመገንባት እስከ ሁለት ሺህ አስራ ሰባት ድረስ 8.8 ሚሊዮን ሕዝብ በነዚህ ከተሞች የማስፈር እቅድ ተዘርግቶ በመተግበር ላይ ይገኛል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ሌሎች አርባ አንድ ከተሞች ተመርጠው እስከ 2017 ድረስ 6.7 ሚሊዮን ሕዝቦች በማስፈርና በኢንዱስትሪ የማስፋፋትና የሥራ ዕድል የመፍጠር ሁኔታዎች የሚያመቻች ሥራ እየሰሩ ነው፡፡

ይህንን መሰሉን ግዙፉ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ በአባይ ወንዝ ውሃ ላይ የሚያካሄዱ ግብፆች በናይል ተፋሰስ ኢንሼቲቭ አማካይነት ከ 1999 ጀምሮ እያካሄዱት የነበረው ያለው ድርድር በአንድ መገን ፍትሐዊ ክፍፍልና ድርድር እያደረጉ በሌላ በኩል ደግሞ እጅግ ግዙፍ የልማት ዕቅዶችን በሥራ ላይ ለማዋል እየተንቀሳቀሱ በመሆኑ የወንዙ ውሃ ብቸኛ ተጠቃሚነታቸውን የሚያረጋግጡበት ሁኔታ በተግባር ላይ ካልዋለ በማለት ሌሎች የተፋሰሱ ሀገሮች የሚያቀርቡትን ፍትሃዊ የውሀ ክፍፍል አጠቃቀምን በሥራ ላይ እንዳይውል በሁሉም ዘርፍ ተፅዕኖ መሰናክል ለመፍጠር ከቶም አይቦዝኑም፡፡ ከዚህ በመነሳት ነው ታላቁ የታሪክ ሰው ሄሮዶዱተን ጽሁፍ በዋቢነት በመጥቀስ የናይልና ግብፅ ሕይወት የተሳሰረ ነው እየተባለ የሚገለፀውን አባባል ፖርቹጋላዊቷ አና ካስኮ ይህ ሁኔታ ከጊዜ ከእውቀት አንፃር ሲመረመር በአንድወቅት የነበረ እውነታ በሰው ልጅ የእድገትና የስልጣኔ ገፅታውን ሊቀይር እንደማይችል በሚያስገነዝብ መልኩ ናይል ዛሬ የግብፅ ብቸኛ ሕይወት ያለመሆኑን ግብፅ ያለናይልም መኖር እንደምትችል ለማየት ሞክራለች፡፡

እኔ አንድ አንድ ኢትዮጵያዊ በጉዳዩ ላይ በጥልቀት ማንበብና መረጃዎችን ማሰባሰብ ከጀመርኩ በኋላ በጉዳዩ ላይ ተጨባጭ ማስረጃዎችን በመንተራስ አንድ መለስተኛ መጣጥፍ ለማዘጋጀት ጥረት አላደርግም ከሚል እሳቤ በመነሳት ባለ አምስት ምዕራፍ 138 ገፅ ያለውን “ናይል እና የግብፅ ኢክኖሚያዊ ይዞታ ከትላንት እስከዛሬ በሚል ርዕስ መፅሐፍ አሳትሜ የበኩሌን አስተዋፅኦ “ሀ” ብዬ ጀምሬያለሁ፡፡

በቀጣይም “የኢትዮ ኢጅፕት ግለኝነትና የናይል ዶሴ ከጥንት እስከ አሁኑ ዘመን” የሚል ርዕስ የያዘ መፅሐፍ ለሕትመት ለማብቃት ዝግጅቴን በማጠናቀቅ ላይ ነኝ፡፡ በግብፅ ኢኮኖሚያዊ ይዞታና የአባይ ወንዝ ላይ ጥልቅ ጥናትና ምርምር ለሚያደርጉ ወገኖች እንደመነሻ ያገለግል ዘንድ ብቃት ያለው መፅሐፍ የፃፉት በግብፅ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ባልደረባ የነበሩት አቶ ግርማ ባልቻ ናቸው፡፡

የአባይ ውሃ እና የግብፅ ኢኮኖሚያዊ ይዞታ

በኢትዮጵያዊው ዲፕሎማት ዕይታ

ኢሕአዴግ...

16 °”l 6— ¯Sƒ lØ` 119 ግንቦት 2006 ዓ.ም

ኢኮኖሚ

ኢትዮጵያ ከዛሬ አሥርና አሥራ ሁለት ዓመታት ጀምሮ በተከታታይ ፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገት እያስመዘገበች ስለመሆንዋ የመንግሥት ባለሥልጣናትና ሚዲያዎች በተደጋጋሚ ነግረውናል፡፡ በ”ልማታዊ መንግሥት”፣ በ”ልማታዊ የኢኮኖሚ ፖሊሲ” በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያኖች ከተራ ገበሬነትና ከቦዘኔነት ተላቀው ‹‹ሚሊየነር ሆነዋል›› የተባሉ ሰዎችን በቴሌቪዥን መስኮት እንድንመለከታቸው ተደርጓል፡፡

ከቅርብ ጊዜ ወዲህም በጥቃቅንና በአነስተኛ የብድር ማኅበራት የተደራጁና ሥራ-አጥ የነበሩ ወጣቶች፤ በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠር ብር ባለቤት ስለመሆናቸውም የሚገልጹ ዘገባዎች እየቀረቡ ነው፡፡ አይሱዚውን፣ ቴሌቪዥኑን፣ ወፍጮ ቤቱን፣ ቪላውን ሁሉ በአያልቅበቱ ቴሌቪዥን መስኮት ተመልክተነዋል፡፡ ይህ በሙሉ ተአምር ሠሪው አብዮታዊ ዴሞክራሲ ያስገኘው ፈጣን የኢኮኖሚ ድል ስለመሆኑም፤ ባለሥልጣኖች ከሚያምረው ቢሮአቸው ውስጥ በቆዳ በተለበጠ መቀመጫዎቻቸው ላይ ተቀምጠው የሰጡትን ቃለ መጠይቅም ተከታትለናል፡፡…

ግን የሚደመጠውም ይሁን የሚታየው…”ኑሮው የሞላላት ሰው ሁሉም ቤት የሞላ ይመስለዋል” እንደሚባለው ዓይነት ወይም ዳቦ በጠፋበት ሃገር፣ የረሃብ መጋዝ የድሀውን አንጀት በሚቀረጥፍበት ከተማ የተቸገረው ዜጋ “ለምን ለስለስ ያለውንና የሚጣፍጠውን ኬክ አይበላም ነበር” እንደማለትም ይመስላል፡፡ የሆነው ሆኖ ዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ ዕድገት መመዘኛዎች ሳይፈተሹ ኪሱን በምዝበራና በማታለል ያደለበ ባለሥልጣንና ካድሬ፤ እንዲሁም እበላ ባይ ምሁር ተብዬ ሁሉ የራሱን የምቾት ኑሮ ለማስቀጠል በማሰብ ብቻ ‹‹የኢትዮጵያውያን የኑሮ ደረጃ አድጓል! ተመንድጓል!›› ቢል፤ በኢትዮጵያ ውስጥ በግልፅ የሚታየውን ድህነትና ጉስቁልና ሊቀይረው ይችላልን? በፍፁም አይቻለውም፡፡ እስቲ በሀገራችን ታይተዋል፣ ተደርሶባቸዋል የሚባሉትን ዕድገቶች፤ በኢኮኖሚያዊ የዕድገት መመዘኛዎች እንመልከታቸው?

የፈጣን ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ማመልከቻ ከሚባሉት አንኳር መመዘኛዎች መካከል አራቱ፤ አንደኛ፡- የሃገሪቱ ሕዝብ የኑሮ ሁኔታ ከነበረበት የኑሮ ደረጃ በተሻለ መልኩ ስለመሻሻሉ ወይም ስለማደጉ የታዩ መሠረታዊ ለውጦች፤ ሁለተኛ፡- በዜጎች መካከል የሚታየው የኑሮ ልዩነት እየጠበበ መምጣቱን የሚያሳዩ ሁኔታዎች፤ ሦስተኛ፡- የዜጎች ሥራ የማግኘት ዕድል መስፋትና አራተኛው፡- በሸማቾችና በነጋዴዎች መካከል የሚኖረው የንግድ ልውውጥ መረጋጋት ሁኔታዎች መኖር ናቸው፡፡ ከፍ ሲል የተገለጹት ፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገት ማመልከቻዎች፤ በምግብ አቅርቦት፣ በጤና አገልግሎት አሰጣጥ ምሉዕነት፣ በትምህርት መስፋፋት፤ እንዲሁም መሠረታዊ በሆኑት መጠለያ የማግኘት፣ በመንገድ፣ በውሃ፣ በመብራትና በስልክ አገልግሎቶች መስፋፋትና ምሉዕነት ባለው ጠቀሜታቸው ርግጠኝነት ላይ መሠረት የሚያደርጉ ናቸው፡፡

ለአባባሉ ርግጠኝነት በቅድሚያ የሚጠቀሰው ኢትዮጵያ በምግብ ሰብል አቅርቦት ዛሬም ራሷን አለመቻሏ ነው፡፡ እነሆ ዓለም አቀፍ መረጃዎች ባለፈው ሳምንት እንዳመለከቱት፤ በተለያዩ ሰበበ ምክንያቶች 6.5 ሚሊዮን የሚሆኑት ዜጎቿ የዕለት ምግብ ፈላጊ ወይም ተመጽዋች ናቸው፡፡ በሃገሪቱ የእህሉ አዝመራ ዘንድሮ “የሰመረ

ነው” ተብሎ በመንግሥት ሚዲያዎች ከበሮ የሚደለቅበት ቢሆንም፤ በዚሁ ከበሮውን በደለቀው ሬዲዮና ቴሌቪዥን…”ዘንድሮ 4 ሚሊዮን ለሚሆኑ የዕለት ደራሽ ምግብ ፈላጊ ኢትዮጵያዊያን እርዳታ እንዲለግሱ ለመጽዋች ሃገሮች የእርዳታ ጥያቄ ቀረበ” ተብሏል፡፡ ይህ በራሱ የዕድገቶቹ ውጤቶች የት ደረሱ? የሚያሰኝ ነው፡፡ በሐቅ የመነጋገርና የመግባባት ባሕል በዳበረበት ሃገር ቢሆን ኖሮ፤ እየተራበ፤ እየተቸገረ ያለን ሕዝብ ‹‹አልተራብክም፣ አልተቸገርክም፣ ኢኮኖሚህ 11 በመቶ አድጐልሃል፣ አንድ ለአምስት ከተጠረነፍክ ደግሞ ዕድገትህ ወደ 20 በመቶም ሊፈናጠር ይችላል›› ብሎ መለፈፍ በጣም የሚከብድ ጉዳይ በሆነ ነበር፡፡

የጤና አጠባበቅን ሁኔታን በተመለከተም ‹‹ለዜጐች የተሻለ ተደራሽነት ያለው አገልግሎት እየተሰጠ ነው›› ተብሎ በስፋት ይነገራል፡፡ አዎን አባባሉ ጭራሽ የእውነት መነሻ የሌለው ነው ሊባል አይችልም፡፡ በመስኩ የተወሰኑ መሻሻሎች ይታያሉ፡፡ የበለጸጉት ሃገራትና የዓለም የጤና ጥበቃ ማዕከላት የሚሰጡት ከፍተኛ የገንዘብ ድጋፍ መኖሩን ሳንዘነጋ ማለት ነው፡፡ እንደዛም ሆኖ ግን በሆስፒታል ደረጃ ያሉት ሐኪም ቤቶች በንጉሡ ዘመን ከተሠሩት ውጭ በአዲስ ሁኔታ የታነጹት በጣት የሚቆጠሩ ሆነው እናገኛቸዋለን፡፡ ለዚህም ማረጋገጫው በየቀኑ በየሆስፒታሉ የሚታየው የሕክምና እርዳታ ፈላጊው ቁጥር ብዛት፤ የአንድ ከተማ ሰው ለገበያ ነቅሎ የወጣ መስሎ መታየቱ ነው፡፡ የሆስፒታሎቹ ግቢ፣ ኮሪደሩና ውጩ ሳይቀር በአገልግሎት ፈላጊዎች ተጣቦ መገኘቱም ነው፡፡ ብቃት ያላቸውን ሐኪሞች ለማግኘት የስድስት ወርና የአንድ ዓመት የጊዜ ቀጠሮም የሚጠየቅበት ሁኔታም መኖሩ ነው፡፡ ተኝቶ ለመታከም ያለው ጠባብ ዕድል በሎተሪ የሚገኝ ዕጣ ዓይነት የመምሰሉም ሂደት፣ ሐኪም ተገኝቶ ለበሽታው መድኃኒት ቢታዘዝ እንኳን የታዘዘውን መድኃኒት የማግኘቱም ይሁን የዋጋው ነገር በድሀ አቅም የሚደፈር አለመሆኑ ሌላው አስረጅ ነው፡፡

በአንፃሩ የ”ፈጣን ኢኮኖሚ ዕድገት” ተጠቃሚ የሆኑት የጊዜው ባለሥልጣናትና ካድሬዎች “ታመዋል፣ አተኩሷቸዋል…” ሲባል፤ ወደ ታይላንድ፣ ቢልጂየም፣ እንግሊዝ እየሄዱ በከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ እንዲታከሙም ይሁን ናፈስ ናፈስ ብለው እንዲመለሱ የመደረጋቸው እውነት ሊካድ የሚችል አይደለም፡፡ ምንም እንኳን ባለሥልጣናቱ በጽኑ ታመው ከሆነና ህመማቸውም ፋታ የማይሰጥና በሀገር ውስጥ ሕክምና የማይፈወስ መሆኑ በተረጋገጠ ጊዜ ወደ ውጪ ተልከው መታከማቸው ነውር ባይሆንም እንደው በስመ ህመም ባለሥልጣናቱን ለማሳከም ተብሎ በየጊዜው በውጭ ምንዛሪ ፈሰስ የሚደረጉ ወጪዎች ከምዝበራና ከብኩንነት ነፃ እንዲሆኑ ቢደረግ፤ ስንትና ስንት ክሊንኮችንና ሆስፒታሎችን ለመገንባት ባስቻሉ ነበር፡፡ ‹‹የኑሮ ደረጃ አድጓል›› ብሎ ማለቱም ለብዙኃኑ ሕዝብ የሚዋጥለት እውነት የመሆኑ ነጥብ ባላነጋገረም ነበር፡፡

ከኢኮኖሚ ዕድገት ማመልከቻዎች አንዱ የሆነውን የትምህርት መስፋፋትን ጉዳይም እንቃኘው፡፡ ከመነሻው በኢትዮጵያ የትምህርት ተደራሽነት ምን መልክ አለው? የትምህርት መስፋፋት ስንል በየክልሉ ሲሚንቶ እያቦኩ ብሎኬት በመደርደር ‹‹ይህን ያህል ዩኒቨርስቲ ተገንብቷል…›› ማለት ነው ወይ? የሥርዓተ-ትምህርቱ አካዳሚያዊ ይዘትስ ምን ይመስላል? የተቀረፀው የትምህርት ካሪኩለም ኢኮኖሚውን የሚያደራጅና የሚያቀላጥፍ ይዘት አለው ወይንስ በሥልጣን ላይ ላለው መንግሥት የፖለቲካ መዘውርነት እንዲስማማ ተደርጎ የተሰናዳ

ነው? ግን ለእነዚህ ሁሉ ጥያቄዎች የሚሰጠው መልስ አሳማኝ አይደለም፡፡

የአንድን ሀገር ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ለማፈጠን በተለያዩ ሙያ የሠለጠኑ ወጣቶችን ከየትምህርት ተቋማቱ ማፍራት የግድ የሚል ጉዳይ ነበር፡፡ ኢሕአዴግ ግን ቅድሚያ የሰጠው የፖለቲካ ሥልጣኑን የሚያጠናክሩለትን ካድሬዎች ለመፈልፈል የሚያስችሉትን ማዕከላት ማደራጀት ነው፡፡ በዚህ ላይ ልዩ ትኩረት በማድረጉም ለኢኮኖሚው ዕድገት የሚያስፈልጉትን ባለሙያዎች በሚያስፈልገው መጠን ሲተካ አይታይም፡፡ ይልቁንም የትምህርት ቤቶችን ቁጥር ማደግ ጉዳይ፤ በደርግ ወይም በንጉሡ ሥርዓት ከነበሩ የትምህርት ቤቶች ቁጥር ጋር በማነፃፀር ‹‹የትምህርት ተደራሽነት በ 80 እና በ 90 በመቶ አድጓል›› በማለት በመረጃ ላይ መሠረት ባደረገ አሳማኝ ጉዳይ ሳይሆን በተራ የፕሮፓጋንዳ ትርፍ ላይ አትኩሯል፡፡ ይህም በራሱ ከቶውንም የትምህርት ጥራት ከዜሮ በታች በሆነበት በዚህ ወቅት፤ የትምህርት መስፋፋትን የሚያመላክት አሳማኝ ነጥብ አይሆንም፡፡

ሌላው የሥራ-አጥ ዜጎችን ቁጥር ለመቀነስ በሚደረገው እንቅስቃሴ በኩል ብዙ ክፍተቶች የመታየታቸው ሁኔታ ነው፡፡ በዚህም ዘርፍ የተሰጠው ትኩረት ኢኮኖሚያዊ ሳይሆን ፖለቲካዊ ሆኖ ይታያል፡፡ ነገር ግን ኢሕአዴግ እንደ ትልቅ ስኬት አድርጐ መላልሶ የሚጠቅሰው በጥቃቅንና በአነስተኛ ማህበራት የተደራጁ ወጣቶችን መሻሻልና ሚሊየነር የመሆናቸውን ጉዳይ ብቻ ነው፡፡ ይሁንና እነዚህ ማኅበራት፤ በውስጠ ታዋቂነትም ሆነ በግልጽ ‹‹የሥርዓቱ ታማኝ ምልምሎች የሚደራጁበት ማዕከላት ናቸው›› የሚሉ ስሞታዎችም የመስፋፋታቸው ጉዳይ የኢሕአዴግን አባልነት የግድ ይላል ከሚለው ዜና ጋር ተዳምረው የሚደመጡ ናቸው፡፡ ይሄም ብቻ ሳይሆን በአዲስ አበባ ከተማ ብቻ ለሥራ ከደረሱ ወጣቶች መካከል ከ 25-30 በመቶ የሚሆኑ ሥራ-አጥ ወጣቶች የመኖራቸውን እውነትም አንዳንድ ጥናታዊ መረጃዎች በግልጽ ያመለክታሉ፡፡

በአራተኛ ደረጃ የተቀመጠው የፈጣን ኢኮኖሚያዊ ዕድገት መመዘኛ “በሸማቾችና በነጋዴዎች መካከል የሚኖረው የንግድ ልውውጥ መረጋጋት ነው” ብለናል፡፡ ግን ባለፉት 23 ዓመታት በሸማቾችና በነጋዴዎች መካከል ጤናማ የንግድ ልውውጥ ነበረ ወይ? ብለን ብንጠይቅ፤ በርግጠኝነት መልሱ “የለም” ወይም “አልነበረም” የሚል ነው ፡፡ ባለፉት 23 ዓመታት አለመተማመን፣ መሸዋወድ በግልጽ ተስተውሏል፡፡ የሸቀጦች ዋጋም ሲጨምር እንጂ ሲቀንስ አልታየም፡፡ በአንፃሩ በንግዱ ዘርፍ ላይ የተሰማሩ ባለጊዜዎች ከብዙኃኑ የንግዱ ማኅበረሰብ በተለየ ከባንኮች ብድር በማግኘትም ይሁን ለንግድ አመቺ የሆኑትን ቦታዎች በመቆናጠጥ ልዩ ተጠቃሚ መሆን የቻሉበት ሁኔታ በሰፊው ታይቷል፡፡

በአጠቃላይ ከፍ ሲል በድርበቡ በተገለጹትም ይሁን በሌሎች መስፈርቶች ቢታይ ለብዙኃኑ ሁለንተናዊ ጥቅም ሰጥቷል ወይም አስገኝቷል የሚያሰኝ ብሔራዊ ዕድገት በሀገራችን አለመመዝገቡ አያሻማም፡፡ “የኢኮኖሚ ዕድገትን” በማስመልከት ታዋቂና ተሰሚነት ያላቸው ዓለም አቀፍ ተቋማት በየጊዜው የሚያወጧቸውን መግለጫዎች ብንመለከትም፤ ኢትዮጵያ አሁንም ቢሆን ከዓለም ድሀ ሃገራት የተመደበች ብቻ ሳይሆን በኢኮኖሚ ምርታማነት የደረጃ ሠንጠረዥ የዓለም ጭራ ሆና ነው የምትገኘው፡፡

‹‹የኑሮ ደረጃ አድጓል›› ማለት፤ የድህነትንና የጉስቁልናን መልክ አይቀይርም

ቀለመ ገብሬ

17°”l 6— ¯Sƒ lØ` 119 ግንቦት 2006 ዓ.ም

ታሪክ

የዛሬዉ ጽሁፌ ከመቶ ዓመት በፊት በግንቦት ወር 1906 ዓ.ም የተፈጸመ አንድ ታሪካዊ ክስተት ያስቃኘናል፡፡ በ1901 ዓ.ም አፄ ምኒልክ በጠና በመታመማቸው ምክንያት የመንግሥቱን ሥራ በሚገባ ለመከወን ባለመቻላቸው ሥልጣናቸውን ለወራሻቸው ለማስተላለፍ ወሰኑ፡፡ ወንድ ልጅ ስላልነበራቸው ከልጃቸው ከሸዋረጋ ምኒልክና ከወሎዉ ራስ ሚካኤል የተወለደው የ13 ዓመቱ የልጅ ልጃቸውን ልጅ ኢያሱን አልጋ ወራሽ ማድረጋቸውን ግንቦት 10 ቀን 1901 ዓ.ም በአዋጅ ለሕዝብ አስታወቁ፡፡ በዚያው ቀን የኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ አቡነ ማቴዎስ የዳግማዊ ምኒልክን ቃል የማይቀበሉትን ሰዎች ሁሉ አወገዙ፤ ረገሙ፡፡ የሚቀበሉትን ግን ባረኩ፣ መረቁ፡፡

በ1906 ዓ.ም አፄ ምኒልክ ማረፋቸዉን ተከትሎ የሚኒስትሮች ምክር ቤት አባላት መሣፍንትና መኳንንቱ ወደ ልጅ ኢያሱ ቀርበው ንጉሠ ነገሥት ተብለው በአያታቸው ዙፋን እንዲቀመጡ ጠየቋቸው፡፡ ልጅ ኢያሱም “አባቴን ንጉሥ ሳላሰኝ ፈረሴን ከቀይ ባሕር ውሃ ሳላጠጣ ዘውድ ጭኜ ንጉሠ ነገሥት አልባልም” በማለት መለሱላቸዉ፡፡ (ፈረሴን ከቀይ ባህር ዉሃ ሳላጠጣ የሚለዉ አነጋገር የኢትዮጵያ ተፈጥሮአዊ ድንበር የሆነዉን ቀይ ባህርን ሳላስመልስ፣ ለሀገሬ ወደብ ሳላመጣ የሚል አንድምታ ያለዉ ነዉ፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ ልጅ ኢያሱ ኤርትራን ከጣልያን ለማስመለስና ቀይ ባህርን የኢትዮጵያ አካል ለማድረግ ያደረጉትን ጥረት በሌላ ጽሁፍ የምንመለከተዉ ይሆናል፡፡)

በዚህ መሰረት ልጅ ኢያሱ ንጉሠ ነገሥት ከመሆናቸው በፊት አባታቸውን ንጉሥ ለማሠኘት ወሠኑ፡፡ እንደዜና መዋዕል ጸሐፊያቸው እንደ ኤልያስ ገብረ እግዚአብሔር ገለፃ ልጅ ኢያሱ ይህን ያሰቡበት ምክንያት የስልጣን መሰረታቸውን ለማጠናከር ነው፡፡ በእናታቸው የንጉሠ ነገሥት ልጅ የሆኑት ልጅ ኢያሱ አባታቸውን ንጉሥ በማሰኘት የሁለት ነገሥታት ልጅ ለመባል ስለፈለጉ ነው፡፡

በዚህ መሰረት ልጅ ኢያሱ አባታቸዉን ራስ ሚካኤልን ግንቦት 23 ቀን 1906 ዓ.ም ንጉሥ አሰኙ፡፡ በዚህ ዕለት በተካሄደ ሥነ ሥርዓት በግብፃዊው ጳጳስ አቡነ ጴጥሮስ እጅ ተቀብተዉ “ሚካኤል ንጉሠ ወሎ ወትግሬ” ተብለው ዘውድ ጫኑ፡፡ “ራስ ሚካኤል ርዕሰ መሳፍንት” የሚለው ማኅተማቸው ተቀይሮ “ዘስልጣኑ ጽሑፍ ዲበ መትከፍቱ ሚካኤል ንጉሠ ጽዮን ንጉሠ ወሎ ወትግሬ” (ስልጣኑ በትከሻዉ ላይ የተጻፈ ሚካኤል የወሎና የትግራይ ንጉሥ) በሚል ተተካ፡፡ ሹመቱ በወሎና በትግራይ ላይ በመሆኑ የትግራይ ነገሥታት በተለይም አፄ ዮሐንስ ይጠቀሙበት የነበረዉን ስም ንጉሠ ፅዮን የሚለውን ቀፅለውታል፡፡

ደሴ ከተማ ላይ ሆጤ በተባለው ሜዳ የተፈፀመው ይህ የንግሥና ሥነ-ሥርዓት እጅግ ደማቅ እንደነበር ሥነ-ሥርዓቱን የተከታተሉት የሀገር ውስጥም ሆነ የውጭ ሀገር ፀሐፊዎች ዘግበዉታል፡፡ በንግሥና ሥነ-ሥርዓቱ ላይ በርካታ የሀገሪቱ መሣፍንትና መኳንንት ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ሲታደሙ የሃይማኖት መሪዎች፣ የውጭ ሀገር ዜጎች እና ከሃምሣ ሺ ህዝብ በላይ ተገኝቷል፡

፡ ለሥርዓተ ንግሡ ድምቀት ሲባል ከምኒልክ ቤተመንግሥት ዘውድና ሌሎች አልባሳት እንዲሁም ቁጥሩ በርከት ያለ ለበን ጠመንጃ ወደ ደሴ ተልኮ ነበር፡፡ ይህ ለበን ጠመንጃ አፄ ምኒልክ ለክፉ ቀን ይሆነኛል ለጠላት መከላከያ ያገለግለኛል ብለው ከፈረንሳይ አገር ያስመጡት መሳሪያ ነበር፡፡ እነዚህ አልባሳትና መሳሪያዎች በልጅ ኢያሱ ትዕዛዝ ወደ ወሎ መላካቸዉ በሸዋ መኳንንት ዘንድ ቅሬታ አሳድሮ እንደነበር መርስዔ ኃዘን ወልደ ቂርቆስ ጠቁመዋል፡፡

ሥርዓተ ንግሡን ከታደሙት የውጭ ሀገር ዜጎች አንዱ ጀርመናዊው ናክላስ ጀንሰን ሥርዓቱ ደማቅ የነበረ መሆኑን ከመዘገቡም በላይ ከዚህ ቀጥሎ የምንመለከተውን ፎቶ ግራፍ በክብር ልብሣቸው አንስቷቸዋል፡፡

ንጉሥ ሚካኤል ከነገሡ ከአንድ ዓመት በኋላ

ጎንደርና ጎጃም በግዛትነት ተጨምረውላቸዋል፡፡ ይህንንም በፅሁፍ መረጃዎች፣ በማህተማቸውና ለአንዳንድ አብያተ ክርስቲያናት በሠጧቸው የብራና መጻሕፍት ላይ ተመዝግቦ እናገኘዋለን፡፡ በብዙዎቹ የብራና መጻሕፍት ላይ “. . . ዝ መጽሐፍ ዘወሐቦ ሚካኤል ንጉሠ ወሎ ወትግሬ ወጎንደር ወጎጃም . . .” ማለትም ይህ መጽሐፍ የወሎ የትግራይ የጎንደርና የጎጃም ንጉሥ ሚካኤል የሰጠዉ ነዉ የሚሉ ፅሁፎችን እናገኛለን፡፡ ይህ ሹመት ሚካኤልን ግማሽ በሚሆነው የኢትዮጵያ ክፍል ላይ ንጉሥ እንዲሆኑ አስችሏቸዋል፡፡ በተጨማሪም የንጉሥ ሚካኤል ሹመት ወሎን ከተራ ክፍለ ሃገርነት ወደ ስልጣን ማዕከልነት አሸጋግሮታል፡፡ ልጅ ኢያሱ በንጉሠ ነገሥት ሥልጣን ላይ ከተቀመጡና ሚካኤልም ንጉሥ ከሆኑ በኋላ ተፅዕኖ ፈጣሪነታቸው ጨምሯል፡፡ በሀገሪቱ በርካታ የፖለቲካ ጉዳዮች ላይ ቁልፍ ቦታ የነበራቸው መሆኑና ብዙዎቹም የልጅ ኢያሱ ውሣኔዎች በአባቱ ምክር የተቃኙ እንደነበር ይነገራል፡፡ ይህንንም ከሚከተሉት ነጥቦች መረዳት እንችላለን፡፡

የመጀመሪያዉ ነጥብ የጣሊያን፣ የእንግሊዝና የፈረንሣይ አምባሳደሮች ለንጉሥ ሚካኤል የነበራቸው አመለካከትና ከፍተኛ ግምት ነዉ፡፡ በ1906 ዓ.ም የጣሊያኑ አምባሳደር ለእንግሊዝና ፈረንሳይ አቻዎቹ በኢትዮጵያ የወደፊት ሁኔታ ላይ ከንጉሥ ሚካኤል ጋር ለመወያየት ሥምምነት ላይ ከደረሱ በኋላ ይህንን ማድረጉ ሌሎቹን መሳፍንት ማስቆጣት ይሆንብናል በሚል ሥጋት ሃሳባቸውን ሠርዘውታል፡፡ ሆኖም ግን ከዚህ ሁኔታ ንጉሥ ሚካኤል በውጭ ዲፕሎማቶች ዘንድ የነበራቸውን ቦታና በሃገሪቱም ፖለቲካ ላይ የነበራቸዉን ሁነኛ ቦታ መገንዘብ እንችላለን፡፡

የልጅ ኢያሱ እንደራሴ ራስ ቢትወድድ ተሰማ ናደው ሚያዝያ 3 ቀን 1903 ዓ.ም በሞት ሲለዩ ከአንጋፋዎቹ መሣፍንት እነ ራስ አባተ፣ እነ ፊታውራሪ ኃብተ ጊዮርጊስ ልጅ ኢያሱ ዛሬ ራሱን ችሎ ለመግዛት ገና አልደረሰም የሚል ሀሳብ አደረባቸዉ፡፡ ለአካለ መጠን እስኪደርስ በራስ ተሠማ ምትክ ሌላ ሞግዚት እንሹምለት በማለት ተመካከሩ፡፡ ወደ ልጅ ኢያሱም ገብተው “እርስዎ ለሥራው እስኪደርሱ በራስ ቢትወድድ ፈንታ ሰው መርጠን ልናደርግልዎ ፈቅደናልና የርስዎም ፈቃድዎ እንዲሆን እናመለክታን፡፡” የሚል ሀሳብ አቀረቡላቸዉ፡፡ ልጅ ኢያሱ ሀሳቡን በመቃወም እንዲህ ሲሉ መለሱለቸዉ “ለሥራዉ ደርሰናል፡፡

አንዳንድ ሹም ያልተደረገበት ቦታ ቢኖር ልናደርግበት ይቻላል፡፡ ይልቅስ ግቢዉን ለቃችሁ ወደቤታችሁ ተመለሱ፡፡” ልጅ ኢያሱ ሞግዚት እንዳይሾምላቸዉ የፈለጉበት ዋናዉ ምክንያት ከሌላ ሰዉ ይልቅ አባታቸዉን አማካሪ ማድረግ ስለፈለጉ ነዉ፡፡ ልጅ ኢያሱ የመራኄ መንግሥትነቱን ስልጣን ከጨበጡ በኋላ በክፉ በበጎው ከአባታቸው ጋር ለመመካከር በተደጋጋሚ ወደ ደሴ ይመላለሱ ነበር፡፡

ሌላው የንጉሥ ሚካኤልን ተፅዕኖ ፈጣሪነት የምንመለከትበት ሁኔታ የቀኛዝማች በየነ ሹመት ነው፡፡ ቀኝ አዝማች በየነ በታህሳስ ወር 1907 ዓ.ም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሆነው ሲሾሙ የሹመት ማረጋገጫ ደብዳቤ (Letter of Approval) የደረሳቸው ከንጉሥ ሚካኤል ነው፡፡ ቀኝ አዝማችም ለልጅ ኢያሱና ለውጭ ዲፕሎማቶች ሪፖርት ሲጽፉ ለንጉሥ ሚካኤልም ይጽፉ ነበር፡፡ እንዲህ አይነት ደብዳቤ የሚጻፍለት ሌላ መስፍን (ባለሥልጣን) አልነበረም፡፡

በተጨማሪም ንጉሥ ሚካኤል ከአውሮፓ ሀገሮች በተለይም ከጀርመን ጋር ግንኙነት መፍጠር ችለው ነበር፡፡ ወቅቱ የመጀመሪያው የዓለም ጦርነት የተጀመረበት ጊዜ ስለነበር በምስራቅ አፍሪካ ቅኝ ግዛት ያልነበራት ጀርመን የኢትዮጵያን ወዳጅነት ትፈልግ ነበር፡፡ በወቅቱም የጀርመኑ ዲፕሎማት ሎሬንዝ ጀንሰን መቀመጫውን ደሴ ላይ አድርጎ ነበር፡፡ በጀርመን ኤምባሲ በአስተርጓሚነት ሲያገለግሉ የነበሩት ከንቲባ ገብሩም በንጉሥ ሚካኤል ትዕዛዝ ከአዲስ አበባ ወደ ደሴ በመዛወር የንጉሡ አማካሪና አስተርጓሚ ሆነው እንዲያገልግሉ ተመድበው ነበር፡፡

በዚሁ ጊዜ ፍሬዴሪክ ሀስ የተባለ ዲፕሎማት ከጀርመን መንግሥት የተላከ ደብዳቤና ገንዘብ ለኢትዮጵያ መንግሥት ለማድረስ ይላካል፡፡ ጊዜው የመጀመሪያው የዓለም ጦርነት የተጀመረበት ወቅት ስለነበር የመልዕክቱ ዋና ዓላማ የኢትዮጵያን ድጋፍና ወዳጅነት ለማግኘት የታሰበ ነበር፡፡ ዲፕሎማት ሀስ አስመራ ሲደርስ ጣልያኖች በቁጥጥር ሥር አውለው አሰሩት፡፡ ምንም እንኳን ሀስ ኤርትራ ውስጥ በእስር ቢቆይም ለኢትዮጵያ መንግሥት እንዲደርስለት የፈለገው ደብዳቤና ገንዘብ ለንጉሥ ሚካኤል እንዲደርስ ነበር ያደረገው፡፡ ሚካኤል ግን የሰሜኑ ክፍለ ሀገራት ንጉሥ እንጂ የኢትዮጵያ መንግሥት ንጉሠ ነገሥት አልነበሩም ፡፡ ከላይ የተጠቀሱት ሁኔታዎች የንጉሥ ሚካኤል የፖለቲካ ስልጣንና ተፅዕኖ ፈጣሪነት ምን ያህል ከፍተኛ እንደነበር ያስገነዝቡናል፡፡ ይህ ሁኔታ ደግሞ በልጅ ኢያሱም ይሁን በራሣቸው በሚካኤል ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ፈጥሮ አልፏል፡፡

የአባትና የልጅ ሥልጣን መፈርጠም በሌሎች አካባቢዎች መሳፍንት በተለይም በሸዋ መሣፍንቶች ዘንድ በበጎ አልተተረጎመም፡፡ የሥልጣኑ ወደ ወሎ መሄድ፤ የኃይል ሚዛኑም ወደንጉሥ ሚካኤል ማጋደል ስጋት ጫረባቸው፡፡ በመሆኑም የልጅ ኢያሱን መንበር ለማነቃነቅ ምክንያትና ምቹ አጋጣሚን መጠባበቅ ጀመሩ፡፡ በመጨረሻም ልጅ ኢያሱን በሰሩትም ባልሰሩትም ምክንያት ከዙፋናቸዉ አስወግደዉ ስልጣኑን በእጃቸዉ ለማቆየት ችለዋል፡፡ ለሰገሌ ጦርነት ምክንያት የሆነዉም ይኸዉ የልጅ ኢያሱ ከስልጣን መወገድ ነዉ፡፡

“አባቴን ንጉሥ ሳላሰኝ ፈረሴን ከቀይ ባሕር ውሃ ሳላጠጣ ዘውድ ጭኜ ንጉሠ ነገሥት አልባልም”

አባቴን ንጉሥ ሳላሰኝ ፈረሴን ከቀይ ባህር ዉሃ ሳላጠጣ ንጉሠ ነገሥት ተብዬ ዘዉድ አልጭንምምስጋናው ታደሰ

18 °”l 6— ¯Sƒ lØ` 119 ግንቦት 2006 ዓ.ም

የጎሳ ፖለቲካ አደጋ አለው!ዶ/ር ቴዎድሮስ ኃ/ማርያም

ግለ-ሃሳብ

መንደርደሪያዜትላው ጄስማን የተባለ ሰው በ1961

ዓ.ም “ኢትዮጵያ የዘር ውህደት መፈተኛ” በሚል ርዕስ ባቀረበው መጣጥፍ ላይ፣ አገሪቱ ‹የዘር› ልዩነትን በሚደንቅ ሁኔታ በማሰተናገድ ላይ ያለች፣ ለአፍሪቃውያን ቀርቶ ለምዕራባውያን እንኳን ተምሳሌታዊ ልትሆን የምትችል ናት ብሎ አሞካሽቷት ነበር፡፡ በተቃራኒው ይህ ዓመት ዋለልኝ መኮንን “ለአዋጁ አዋጅ” በሚል “የኢትዮጵያ ህዝብ ማለት አድስጌና ሞጃ ብቻ መሆኑ ነውን?” እያለ የጠየቀበት፣ ጥቂት ወራት ቆይቶም “የብሄረሰቦች ጥያቄ በኢትዮጵያ” የሚለውን መጣጥፍ ይዞ የወጣበት ነበር፡፡ ተማሪው ክፍል የአገሪቱን ፖለቲካዊ፣ ኤኮኖሚያዊና ማኅበራዊ አቋሞች ለመረዳትና የራሱንም ሚና ለመወሰን የሚጥርበት ጊዜ ነበር፡፡ ማርክሲዝም በመሪ ርዕዮተ ዓለምነት ገሃድ የወጣበት ዘመን፡፡ በከተማ ቀመሱ ኢትዮጵያዊ ዘንድ የጎሳ ንቃት እያንሰራራ የመጣበት ዘመን፡፡ ተሜ በያቅጣጫው ንቃቃቱ እየሰፋ የመጣውን አፄያዊውን ሥርዓት ለማፍረስ ያቆበቆበበት ነበር፡፡

ለመሆኑ ሞጃ የትነው? አዲስጌስ ምንድነው? እነዚህ በኢትዮጵያ ካርታ ላይ እንኳን ያልተነቆጡ ቦታዎች የአዲሱ ምሁራዊ መደብ በማንነት የተቃኘ ፖለቲካ መነሻዎች ሆነው በታሪክ ሰፍረዋል፡፡ ከዚህ በኋላ በተማሪው ንቅናቄ ውስጥ የተፀነሰው የብሄረሰቦች ጥያቄ ጉዳይ ብቸኛ መታገያ መሆኑ አይቀሬ ነበር፡፡ ከመደባዊ ወደብሄራዊ ትንታኔዎች የተደረገው ሽግግር አጭርና በወጉም ያልተመከረበት ነበር፡፡ ለመሆኑ አንድ ሰፊ ማህበረሰብን በጅምላ ጨቋኝ ወይም ተጨቋኝ፣ ተራማጅ ወይም አድሃሪ ብሎ መፈረጅ እንዴት ይቻላል? በታሪካዊውና ነባራዊው ጭቆና መካከል ምን አይነት ግንኙነትና ልዩነት አለ? አገሪቱስ ለአብነት እንኳን የሚወሳ ባህላዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ማኅበራዊ እሴቶች የላትምን? የሚሉ ጥያቄዎች እንደቅንጦት ተቆጠሩ፡፡ በጊዜው በተማሪ መጣጥፎች ውስጥ ተወዳጅ ከነበሩ ጥቅሶች አንዱ “ኢትዮጵያ ዓለምን ረስታ ዓለምም ረስቷት ለሺህ ዓመታት አንቀላፋች” የሚለው ኤድዋርድ ጊበን ነበር፡፡ ጄስማን ይህንን ጨለምተኝነት ሲተች “የዘመኑ የኢትዮጵያ ምሁር የአገሪቱን ኅብራዊ ተሰጥኦ ከቁብ የማይገባ፣ እንዲያውም አሳፋሪና የማያስመካ “አጤያዊ ቅሪት” አድርጎ ለማጣጣል ዝግጁ ነበር” ይለዋል፡፡

ለመሆኑ ታላቁን የኢትዮጵያን አብዮት መስመር ያሳተውና፣ አገሪቱን ለግማሽ ምዕት ያህል ደም ያቃባው ‹የብሄረሰቦች ጉዳይ› ምንድነው? ዛሬ ላይ አንጋፋዎቹ አብዮተኞች ይህን ጥያቄ የሚመልሱት መሬት በአይናቸው እየቆረቆሩ ነው፡፡ ለያኔው ደቀመዝሙር ለፕሮፊሰር አንድሪያስ እሸቴ የብሄረሰቦች ጥያቄ “ከስልጣን መወጣጫ ብልሃትነት ያለፈ አልነበረም”(ባህሩ ዘውዴ 2010):: ማለትም ጥያቄው ከአነሳሱም በጥንቃቄና በታማኝነት

አልተያዘም፡፡ በዚህም የተነሳ ለጎሰኞች፣ ለሥልጣን ጥመኞችና ለኢትዮጵያ ጠላቶች ተስማሚ ሽፋን በመስጠት ከፍተኛ ዋጋ አስከፍሏል በማስከፈልም ላይ ይገኛል፡፡

የዛሬ 23 ዓመት በወርሃ ግንቦት ኢህአዴግ ቤተ መንግሥት ሲገባ ለኢትዮጵያ ህዝቦች ይዠላችሁ መጣሁ ያለው ትልቁ ስጦታው ‹የብሄሮች ጉዳይን› የሚመለከት ነበር፡፡ በወቅቱ በጎሰኝነት መለዮ ሲዋጋ ለኖረ ድርጅት በቀላሉ ተጠምዝዞ አገራዊ አንድነትን ማቀንቀን ትልቀ አቀበት መሆኑ አይካድም፡፡ በዚህ ላይ የማንነት ፖለቲካ በዓለም አቀፍ ደረጃ ቀን እየወጣለት ነበር፡፡ ስለዚህም አዲሱ መንግሥት ራሱን እንደተማሪው ትግል ወራሽ በመቁጠር ለብሄር ብሄረሰቦች ጥያቄ የማያዳግም መልስ ለመስጠት በቋንቋና በማንነት ላይ የተመሰረቱ የጎሳ ክልሎችን ፈጠረ፡፡ ይህንንም ህገ-መንግሥታዊ ይሁንታ አቀዳጀው፡፡ አብሮ መኖር ያለፈለገ ቢኖር ከማህበራችን መውጣት ይችላል ብሎም ደነገገ፡፡ ሁልህም በየጎሳህ ተቆጠር፡፡ በጎሳህ ከተገዛህ፣ በጎሳህ ምድር ከኖርህ፣ በጎሳህ አንደበት ከተናገርክ፣ ከተማርክ፣ ከዘፈንክ ችግርህ ይቃለላል አለ፡፡ ነገር ግን ይህ ጉዳይ ነፋስ በወጥመድ እንደመያዝ የቀለለ ነበር፡፡

በተለይም የኢህአዴግ የጎሳ ፖሊሲ ፅንፈኝነት ደጋፊዎቹን እንኳን ያሸማቀቀ፤ በአገራችን ጉዳይ ያገባናል የሚሉ ቅን ዜጎች ሁሉ ላለፉት ሁለት አሥርታት ሳያሰልሱ የሞገቱበት ጉዳይ ነበር፡፡ የማንነት ፖለቲካ አደገኛ ነው፤ የጎሳ ፌዴሬሽን ደግሞ በአብዛኛው ዓለም ሊሰራ አልቻለም ተባለ፡፡ ኢህአዴግም እኔ አሰራዋለሁ በዚህ ጉዳይ አትምጡብኝ አለ፡፡ ውሎ ሲያድር ይህ ነገር አያያዙ ትክክል አይደለም፣ አቅጣጫውን የሳተ ይመስላል የሚሉትን ሁሉ “ሟርተኞች የፌዴራል ሥርዓቱን ለመቀልበስ አስባችሁ ነው፣ አዲሱን አስተሳሰብ የሚረከብ ትውልድ እየቀረፅሁ ነው” እያለ ዘለቀ፡፡ ታዲያ ሰሞኑን በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች በተከሰቱት አሳዛኝ ውድመቶች በግንባር ቀደምትነት የተሰለፉት በዚሁ ዘመንና አስተሳሰብ ያደጉ ወጣቶች መሆናቸው የፖለቲካ ሥርዓቱ የያዘውን አቅጣጫ በድጋሚ መመርመር እንደሚያስፈልግ የሚያሳይ ነው፡፡ የዚህ አጭር ፅሁፍ ዓላማም ችግሩን ከጎሰኝነት ባህሪያትና ከመንግሥት አያያዝ አኳያ በመቃኘት ጥቂት የመፍትሄ ሃሳቦችን ለመሰንዘር ነው፡፡

የብሄርተኝነት- ጎሰኝነት ባህሪያት

እውነቱን እንነጋገር ከተባለ ጎሰኝነት በከበረበት ሀገር “ብሄርተኝነት” ተብሎ ይሞካሻል፡፡ ለእኩልነት፣ ለነጻነትና ለማኅበራዊ ፍትህ አማራጭ የሌለው ነው ይባላል፡፡ ማንነቱንም ለመደበቅ “የራስን እድል በራስ መወሰን” በሚል ማደናገሪያ ይመራል፡፡ ነገር ግን ታዋቂው ምሁር ኤሊ ኬዱሬ እንደሚለው “ጎሰኝነት ከበታችነት ሥነ-ልቡና የሚመነጭ ርዕዮተ ዓለማዊ ልክፍት ነው፡፡” እንኳንስ ህጋዊ የበላይነት ተሰጥቶትና ጎሰኝነት ሌሎች ጉዳዮችን የመዋጥና የመግነን ዝንባሌ አለው፡፡ የራሴ ለሚሉት ማኅበረሰብ ጥቅሞች፣ እምነቶችና ባህሎች ከመቆርቆርና ከመመካት ላይ አይቆምም፡፡ ሌላውን እንደ ባላንጣ

አልፎም እንደ ጠላት የማየትና ይህንንም ጥላቻ ወይም ፍራቻ ለማስወገድ ማንኛውንም መንገድ እስከመጠቀም ይሄዳል፡፡ የዘር ማጽዳት፣ ጅምላ ጭፍጨፋ፣ መድልኦና ኤኮኖሚያዊ በደል፣ ወዘተ ‹ህጋዊ› የፖለቲካ ትግል መሳሪያዎቹ ናቸው፡፡ ጎሰኝነት ሆብሳዊውን የብላ ተባላ ዓለም የሚመኝ በመሆኑ አደጋ አለው፡፡

የጎሳ ማንነት ብቸኛና ሊያመልጡት የማይቻል የሰብአዊነት መገለጫ በሆነበት ሥርዓት ውስጥ ታሪካዊ፣ ባህላዊና ማኅበራዊ መሰረቱን ለቅቆ ሥነ-ተፈጥሮአዊ ይሆናል፡፡ ይህ የማይለወጥ ጎሰኝነት ለዘረኝነት ይቀርባል፡፡ ምክንያቱም የተለያዩ ማኅበረሰቦችን እንደተለያዩ ሰብአዊ ዝርያዎች ስለሚወስድ፡፡ ጎሰኝነት ወደፊት ሳይሆን ወደኋላ ተመልካች በመሆኑ የአንድን ህዝብና አገር ታሪክ ለመከለስ ሳይታክት ይማስናል፡፡ የሚያራምደውም ወገንተኛ ታሪክ ተቃርኖአዊ ይዘት ይኖረዋል፡፡ ከማገናኘት ይልቅ ማለያየት፣ ከስምምነት ይልቅ ጠላትነትን ያበረታታል፡፡ ማኅበረሰቦች በረዥም ዘመናት ሂደት የመሰረቷቸውን ድልድዮች ሁሉ ለማፍረስ ይሰራል፡፡

ጎሰኝነት በአስተዳደራዊ መዋቅርነት ሲተገበር አንዳንዶችን በክልላቸው ውስጥ አንደኛና ብቸኛ ባለቤቶች፣ ሌሎችን ደግሞ ያልተፈለጉ እንግዶች አድርገው እንዲያስቡ ይገፋፋል፡፡ የዚህ ክልላዊ አስተሳሰብ ዋነኛ ማጠንጠኛ የሆነው ‹ተወላጅነት› በአንዲት አገር ዜጎች መካከል ወንድማማችነትን ያጠፋል፡፡ በእኩልነት የመዘዋወር፣ የመስራት፣ የመኖር፣ የመዳኘት ወዘተ መብቶችን ይሸረሽራል፡፡ በገዛ አገራቸው ህጋዊ መብቶቻቸው ተገፍፈው እንደ ሁለተኛና ሶስተኛ ዜጎች የሚቆጠሩ የህብረተሰብ ክፍሎችን ይፈጥራል፡፡ ይህ ደግሞ እንደ ሀረሪ፣ ጋምቤላ፣ ቤንሻንጉል ጉሙዝ ባሉ ትናንሽ ክልሎች ብቻ ሳይሆን እንደ ኦሮምያና ደቡብ ህዝቦች ውስጥ ያሉ በአማካይ እስከ 20 በመቶ የሚደርሱ ኢትዮጵያውያንን ይመለከታል፡፡

የማንነት ፖለቲካ ለዲሞክራሲ አጋዥ ሳይሆን አፍራሽ ነው፡፡ በእንዲህ ያለው የፖለቲካ ሥርዓት ፓርቲዎች እንኳን አማራጭ አቋም እንዳያራምዱ ማነቆ ይሆንባቸዋል፡፡ ህብረ-ብሄራዊ ነኝ ወይም አልቦ-ብሄራዊ ነኝ ቢሉም ካንዱ ወይም ከሌላው ብሄረሰብ ጋር መፈረጃቸው አይቀሬ ይሆናል፡፡ ሰዎች በብሄረሰባቸው እንዲያስቡ፣ እንዲደራጁና እንዲመርጡ ማስገደድ ዲሞክራሲን የፍላጎት መግለጫ ሳይሆን የተወላጅነት ማረጋገጫ ያደርገዋል፡፡ በእንደዚህ ያለ ህብረተሰብ ውስጥ የሚደረግ ምርጫ ከህዝብ ቆጠራ የማይለይ ይሆናል፡፡ ዶናልድ ሆሮዊዝ እንደሚለው በአፍሪቃ፣ በእስያና በካሪቢያን ለዴሞክራሲ ማቆልቆል ዋነኛ ምክንያቶች እንዲህ ያሉ የይስሙላ ምርጫዎች ናቸው፡፡

እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ጥልቅ ክፍፍል ባላቸው ማኅበረሰቦች ውስጥ ደግሞ ጎሰኝነት በሁሉም ጉዳዮች ውስጥ መንፀባረቁ አይቀሬ ነው፡፡ በማኅበራዊ ተቋማት፣ በልማት እቅዶች፣ የትምህርት፣ የንግድ፣ የግብር፣ የመሬት ፖሊሲዎች ወዘተ፡፡ በተለምዶ በተራ አስተዳደራዊ መስክ የሚመደቡ ጉዳዮች እንኳን በጎሳ በተከፋፈሉ ማኅበረሰቦች የፖለቲካ አጀንዳ ውስጥ አማካይ ቦታ ይይዛሉ፡፡ ጎሰኝነት በባህሪው ተካራሪና ዜሮ ድምራዊ በመሆኑ ከፖለቲካ

የጎሳ ፖለቲካ አደጋ አለው!

19°”l 6— ¯Sƒ lØ` 119 ግንቦት 2006 ዓ.ም

የጎሳ ፖለቲካ አደጋ አለው!ግለ-ሃሳብ

ሂደት ውስጥ ሚዛናዊነትን፣ መቻቻልንና ሰጥቶ መቀበልን ያጠፋል፡፡ በምትካቸውም ግልፍተኝነትን፣ አኩራፊነትንና ስሜታዊነትን ያሰፍናል፡፡ ከአምባገነናዊነቱና ሁሉን ጠቀስነቱና የተነሳ የጎሳ ግጭት የፖለቲካው ሁሉ ማጠንጠኛ ይሆናል፡፡

መሰረታዊ መንሥኤዎችና አያያዛቸው

ነገር ግን የጎሰኝነትና በዚህ የተነሳ የሚከተሉ አደጋዎች መንስኤ በፖለቲካ ባህሪው ብቻ የተወሰነ አይደለም፡፡ እንዲያውም ጎሰኝነት የሌሎች መሰረታዊና ነባራዊ ችግሮች ነጸብራቅ ነው ሊባል ይችላል፡፡ ተደጋጋሚ የሆኑት የግጭት ምክንያቶች በመሬት ይዞታ ወይም አጠቃቀም ላይ የሚነሱ አለመግባባቶች፣ በውሃ ሃብቶች፣ በየአካባቢው ባሉ የስራ እድሎች፣ የባህል ፖሊሲዎች፣ መለዮዎችና የክብር ጉዳዮች፣ የሰፈራ ወይም የኢንቨስትመንት ፈቃዶች፣ በትምህርትና ሥራ ቋንቋ ፖሊሲ፣ ወይም ኤኮኖሚያዊ በደሎች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ለምሳሌ ማኅበረሰቦች ትላልቅ መንግሥታዊ የልማት ክንውኖች ከጥቅማቸው ይልቅ ሸክማቸው የበዛ ሊመስላቸው ይችላል፡፡ ሌላው የአገሪቱ ክፍል በኛ ትከሻ ነው ያለው ብለው ሊያስቡ ይችላሉ፡፡ “የኢትዮጵያ ኤኮኖሚ አፏን ወደኛ ግቷን ወደእነኛ ያደረገች ጥገት ናት” እስከማለት ይደርሳሉ፡፡

የቀድሞው የአፍሪቃ ኤኮኖሚ ኮሚሽን ሊቀመንበር የነበሩት አደባየ አዴዴጂ የአህጉሪቱ ምሁር ወይም ልሂቅ ንቃሪ ይሉኝታ የሌለውና ራስ ወዳድ በመሆኑ ጎሰኝነትን በማራገብ ላደረሰው ማኅበራዊ ቀውስ ተጠያቂ ነው ይላሉ፡፡ የሚገርመው ነገር አፍሪካውያን ፖሊሲ አውጭዎች የችግሩን ምንጭ በቅጡ የተረዱት አይመስሉም፡፡ የግጭቶች ዋነኛ ምክንያት የባህል ልዮነቶች ናቸው ብለው የሚያስቡ ይመስላሉ፡፡ ሰለዚህም የጎሳ ፌዴሬሽኖችና ራስ ገዞችን መፍትሄ አድርገው ያቀርባሉ፡፡ ሆኖም ችግሩ ሰፋ ባሉ የፖለቲካና ማኅበረ-ኤኮኖሚያዊ ፍትሃዊነት ላይ የተመረኮዘ በመሆኑ የጎሳ ፌዴሬሽን መመስረት በራሱ ሰላምና ብልጽግናን ሊያረጋግጥ አይችልም፡፡

የአፍሪቃ ቀንድ የዓለማችን ዋነኛው የጦርነትና ያለመረጋጋት ቀጠና የሆነበት ምክንያት ብዝሃነት ሳይሆን የዲሞክራሲና የመልካም አስተዳደር እጦት ነው፡፡ በተለይ ደግሞ በኢትዮጵያ የሰላምና የልማት ነቀርሳ የሆነው ዘውጌ ፖለቲካ መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ የዜጎችን የመማር፣ የመዘዋወር፣ የመነገድ፣ በተለያዩ ማኅበራዊና ፖለቲካዊ ዘርፎች የመሳተፍ መብቶች ስለሚገድብ ለልማት ዋልታ የሆነውን ግለሰባዊ ተነሳሽነትን ያኮላሻል፡፡ የጎሳ ፌዴራሊዝም ለብክነትና ለድግግሞሽ የተጋለጠ ሥርዓት በመሆኑ ለልማት ቀና አይደለም፡፡ የዚህም ምክንያት በማዕከልም ሆነ በክልል መንግሥታት የሚደረጉ አንኳር የሆኑ ውሳኔዎች የሚመሩት በጎሳዊ መነጽር በመሆኑ ነው፡፡ በዚህ ሂደት ኤኮኖሚያዊ አዋጭነት ሁል ጊዜ አንደኛ ታሳቢ ላይሆን ይችላል፡፡ ሰሞኑን እንደታዘብነው የአዲስ አበባና ዙሪያዋ ከተሞች የተቀናጀ የልማት እቅድ የቱንም ያህል ብሄራዊ ጥቅም ቢኖረው በአንዳንድ ወገኖች ዘንድ ሰፊ ጥርጣሬና ተቃውሞ ማስነሳቱ የዚህ ውጤት ነው፡፡

መንግሥታችን ሙጥኝ ያለው ጽንፈኛ

የጎሳ ፖለቲካ ለያካባቢው ልሂቃን የጥቅም ተፎካካሪዎቻቸውን የሚያስወግዱበት ምቹ መስፈርት ስለሰጣቸው በማኅበረሰቦች መካከል ልዩነቶችንና ተቀናቃኝነቶችን፣ ጥርጣሬንና ፍራቻን፣ መናናቅንና መፏተትን ሲኮተኩቱና ተወረርክ፣ ተቀማህ፣ ተናቅህ፣ ተዋጥህ ሲሉ ኖረዋል፡፡ ኢህአዴግ ደግሞ በአቶ መለስ አባባል ‹ሂሳብ ማወራረድን› እንደ ሥርዓቱ ባህሪ የሚቆጥር በመሆኑ በተወላጅነት መብት ስም ዜጎች ሲሳደዱ፣ ደም ሲፈስስ፣ ንብረት ሲወድም አይቶ እንዳላየ አልፏል፡፡ በየደረጃው ለእንደዚህ ያሉ ችግሮች መፍቻ ባለማደራጀቱ ዜጎች እንዲበደሉ፣ እንዲሳደዱና በመንግሥታቸው ላይ እምነት እንዲያጡ አድርጓል፡፡ ስለዚህም እያደር እየጎለበቱ የመጡት ግጭቶች አላማ ተቀናቃኞችን ማኮላሸት፣ መጉዳት ወይም ከናካቴው ማጥፋት መሆኑ አይቀሬ ነበር፡፡ በዛየር፣ በናይጄርያ፣ በሩዋንዳ፣ በብሩንዲ፣ በሱዳን፣ ወዘተ የተከሰቱና የሚከሰቱ የዘር ጥቃቶች የረዥም ጊዜ መድልዎና መገፋት ውጤቶች እንጂ በአንድ ጀምበር የተፈጠሩ አይደሉም፡፡ በኢትዮጵያም እንደዚሁ፡፡

በሰላሙ ረገድ ኢህአዴግ የተሳካለት ጉዳይ ቢኖር ችግሩን ‹ዲሴንትራላይዝ› አድርጎ ከማእከል ወደታች ማውረዱ ይመስላል፡፡ ለጊዜው መንግሥትን ለመጣል የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች መዳከማቸው የግጭቶች ምንጭ ያለው በያካባቢው እንጂ እኔ ዘንድ አይደለም ለማለት አስችሎታል፡፡ በየክልሉ ባሉ የቋንቋና ባህል ማኅበረሰቦች መካከል ለሚነሱና ለሚስፋፉ ግጭቶች ደግሞ ቀዳሚ ሃላፊነት የለብኝም ይላል፡፡ ስለዚህም ኢህአዴግ ችግሮቹን በሙሉ ከራሱ አውርዶ በእሳት አጥፊነት ተግባር ከተሰማራ ቆይቷል፡፡ ውሎ አድሮ ሥልጣኑን እስካልነቀነቀው ድረስ መሆኑ ነው፡፡ ስለዚህ የጎሳ ፖለቲካ መጣላችሁ የተባሉትንም መጣባችሁ የተባሉትንም ካላስደሰተ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ በጠመንጃ ተጭኖ በጠመንጃ የሚጠበቅ ርዕዮተ ዓለም መሆኑ ነው፡፡ የጉልበት ፖለቲካ እስከየት ያዘልቃል?

አሁንም አቶ መለስ ከጥቂት ዓመታት በፊት በአሜሪካ መሰረቱን ላደረገው ‹ኢትዮጵያ ትቅደም› ለተባለው የሃበሻ ቴሌቪዥን ያለወትሮአቸው በሰጡት ቃለ መጠይቅ ላይ “የህዝብ አንድነት ሊመጣ የሚችለው ከምንም በላይ በጥቅም መተሳሰር ሲፈጠር ነው” ማለታቸውን እናስታውሳለን፡፡ በእርግጥም ይህ አስተሳሰብ ከፊል እውነትነት አለው፡፡ ሆኖም ጥቅማጥቅሞችን ብቸኛ የብሄራዊ አንድነት ማስጠበቂያ ማድረግ ማኅበረሰቦችን በአጥንት እንደሚጣሉ ውሾች ከመቁጠር አይተናነስም፡፡ ለኤኮኖሚያዊ ትስስር ማጥበቂያ የሚሆን የጋራ ባህል፣ የጋራ እሴቶች፣ የጋራ እምነቶች፣ የጋራ ተቋማት፣ የጋራ አስተሳሰብና የጋራ ራዕይ የሌለው አገር በድቡሽት ላይ እንደተሰራ ቤት ይቆጠራል፡፡ እንደምናየው በጠመንጃ ኃይል ካልተጠረነፈ በስተቀር አብሮ መቆም አይችልም፡፡

አገራዊ ወይም ዜግነታዊ ብሄርተኝነት አካታች፣ አደላዳይ ሲሆን፣ ዘውጋዊ ወይም ጎሳዊ ብሄርተኝነት ደግሞ አግላይ ባህሪ አለው፡፡ ዘውጋዊነት በአግባቡ ከተያዘ ገንቢ ማኅበራዊ ኃይል፣ ቅጥ ያጣ ጎሰኝነት ግን የማኅበረሰብ ጠንቅ ነው፡፡ ስለዚህም በዚህ ተግባር ላይ ሚዛናዊነት መሪ ቃል ነው፡፡ እንደተቀሩት የአፍሪቃ መንግሥታት ሁሉ ወታደራዊው ደርግ ጎሰኝነትን ለኢትዮጵያዊነት

ግንባታ እንቅፋት አድርጎ ድምጥማጡን ለማጥፋት ያደረገው ትግል አልተሳካም፡፡ ሊሳካም የማይችል ነበር፡፡ ሆኖም ቢያንስ በማኅበረሰቦች ደረጃ ድልድዮችን በመዘርጋት፣ መቻቻልና አብሮ መኖርን ለማስፈን፣ ግጭቶችን ለመቆጣጠርና በአገራዊ ዜግነት የሚመራ አመለካከት ለመፍጠር ያደረገው ጥረት ጥሩ ጎኖች እንደነበሩትም መካድ አይቻልም፡፡

ኢህአዴግ በበኩሉ የቡድን መብቶች ተገቢውን ትኩረት እንዲያገኙ ማድረጉ ይበል የሚሰኝ ሆኖ፣ በጎሳ ማንነትና በብሄራዊ ማንነት መካከል ቅጥ ያጣ ባላንጣነት እንዲኖር መጣጣሩ አፍራሽ ነው፡፡ “ትግራይ መንነትና ኢትዮጵያ ዜግነትና” የሚለው ግንዛቤ ብሄራዊ ውዥንብር የሚፈጥር ይመስለኛል፡፡ ሰዎች በርካታ የማንነት መገለጫዎች (ማኅበራዊ፣ ጾታዊ፣ ሞያዊ...) እንዳሏቸው ሁሉ ጎሳዊና አገራዊ ማንነታቸውን ሳይጠፋፉ እንደያግባቡ ማስተናገድ ይችላሉ፡፡ በየትም አገር እንዳለው በኛም ዘንድ በጋራ ማንነትና ታሪክ ላይ ያለመግባባት ሊኖር ይችላል፡፡ ይህ ግን ብሄራዊ ማንነትን ለመገንባት ከመጣጣር የሚያስቀር ምክንያት ሊሆን አይችልም፡፡ ያንዲት አገር ህዝቦችን በደባልነት እንዲኖሩ ማድረግ ሊጠቅም የሚችለው ሥልጣናቸውን በከፋፍለህ ግዛው ለማቆየት ለሚፈልጉ ወገኖች ብቻ መሆኑን ሁላችንም ልብ እንበል፡፡

በማኅበረሰቦች መካከል ልዪነት መኖሩ ግጭትን አይቀሬ አያደርገውም፡፡ ግጭቶች ደግሞ እንዲሁ በዘፈቀደ የሚከሰቱ ሳይሆን በእቅድ፣ በመሪና በተከታይ የሚደረጉ መሆናቸውን መረዳት ያሻል፡፡ አማራጭ ማኅበራዊና ፖለቲካዊ ተቋማት በተዳከሙበት አገር ዋነኛው ሃላፊነት የሚወድቀው መንግሥት ትከሻ ላይ በመሆኑ፣ የግጭቶችን ተጨባጭ መንስኤዎች ለማስወገድ መንግሥት ዙሪያ ገብ ጥረት ማድረግ አለበት፡፡ የችግሩ ሳይሆን የመፍትሄው ሃይል መሆን አለበት፡፡ ይህ ደግሞ በመጀመሪያ ከመልካም ፈቃደኝነት ይነሳል፡፡ ሃብትንና እውቀትንም መጠቀም ይፈልጋል፡፡ ሁሉንም ባለድርሻ አካላት ያማከለም ሊሆን ይገባል፡፡ ለአጭር ጊዜ መተንፈሻ ሳይሆን ለዘላቂነት የታቀደ፤ ከላይ የሚወርድ ሳይሆን ከመሰረት የሚገነባ መሆን አለበት፡፡ ባህላዊን ከዘመናዊ በወጉ ያቃየጠ መሆንም አለበት፡፡ በዚህ ረገድ ማንኛችንም የአገራችን ጉዳይ ይመለከተናል የምንል ዜጎችም አጠቃላዩን አገራዊ ሰላም፣ መቻቻልና ወንድማማችነት ለመገንባት የየራሳችንን ድርሻ መፈለግ ይኖርብናል፡፡

ከሁሉም በላይ ግን በሥልጣን ላይ ያለው መንግሥት የአስተዳደር ወኪሎች አስተማማኝና ሁሉን አቀፍ የእርቅ ማእቀፍና በማንነት ላይ ሳይሆን በአንገብጋቢ ጉዳዮች ላይ የተመሰረተ የድርድር ስርዓት ለመዘርጋት መቻል አለባቸው፡፡ በአገሪቱ የህግና የአስተዳደር ሥርዓት ውስጥ በብሄረሰቦች መብቶችና በግለሰቦች መብቶች መካከል የሚከሰተውን ተቃርኖ የሚያለዝብ መፍትሄ መበጀት አለበት፡፡ በኢትዮጵያዊነትም ሆነ በብሄረሰቦች ስም የሚነሱ ጥያቄዎችን በአግባቡ ማስተናገድ እንጂ ከተቃዋሚዎች ወይም ከተወሰኑ ቡድኖችና ማኅበረሰቦች ጋር ለማቆራኘት መሞከር አያዋጣም፡፡ እንደተለመደው ሁሉንም ዜጎች በየአቅጣጫው እያጎሩ “ህዝባዊ ንቅናቄ” በሚሉ ሽወዳዎች፣ ትዕይንቶችና ዶክመንተሪዎች መግደርደር ብዙ ሊያስከፍለን ይችላልና፡፡

የጎሳ ፖለቲካ አደጋ አለው!

20 °”l 6— ¯Sƒ lØ` 119 ግንቦት 2006 ዓ.ም

lUL†¨< ›v} (T@Ç=. Ê¡}`)

ከ23 ዓመት በፊት የነበርንበት የውጥረት፣ የመበታተን ስጋት አሁንም አብሮን እየተጓዘ ነው፡፡ የግንቦት ሃያው የመንግስት ለውጥ፤ የኢህድሪ መንግስት ሕልውና ማክተም በኋላ ታንኮቻችን ወደ ትራክተርነት ጠመንጃዎቻችን ወደ ማረሻና ዶማነት እንቀይራለን ብለን ከነታንኮቻችን ጋር እየረገጥን አለን፡፡ በየዓመቱ በረሃብ ቸነፈር ለመገረፍ ግድ ያላቸውን ወገኖቻችንን ለመቀለብ የእርዳታ እህል የመለመን ታሪካችንንም አልቀየርንም፡፡

ኢትዮጵያን ከብሔረሰቦች እስር ቤትነት አውጥተን ሁሉም ብሔር ብሔረሰቦች በመፈቃቀድ ላይ የተመሠረተች አንዲት ኅብራዊት ኢትዮጵያን ለመመስረት የታቀደው ወደተግባር ግን ሲቀየር አላየነውም፤ ለምን ይሆን? ከሰሞኑ በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ስር በሚገኙ የክልሉ ከተሞች ተፈጥሮ የነበረው ብጥብጥና በጥቂት ግለሰቦች አነሳሺነት ተፋፍሞ የነበረው የጐሳ ግጭት መንስኤው ምንድን ነው? ምንስ ድረስ ይዘልቃል? ከጥይት የተሸለ መፍትሔስ ይኖረውን? በእርግጥ በአዲስ አበባና በዙሪያዋ ባሉ የኦሮሚያ ልዩ ዞን ስር ያሉ ከተሞችን በልማት ያስተሳስራል ተብሎ ለውይይት የቀረበው የጋራ ማስተር ፕላን መፅደቅና በሥራ ማዋል ጋራ የተያያዘ ብቻ ነውን? ወይንስ ሌላ የታመቀ ሕዝባዊ ተቃውሞን መቆስቆሻ አጋጣሚ ነው ተብሎ ይታለፋል? ለእነዚህ ሁሉ ችግሮች መፍትሔው ምንድን ነው? በሚሉ አሳቦች ዙሪያ የዕንቁ ባለደረቦች ያጠናከሩት ዘገባ በሚከተለው መልኩ ተቀናብሮ ቀርቧል፡፡

በ1983 የደርግ መንግስት ከስልጣኑ ተወግዶ ለ17 ዓመታት ሲፋለሙት የነበሩ አማፂያን ተቃዋሚዎች ከሞላ ጐደል የተሳተፉበት የሽግግር መንግስት መተዳደሪያ ቻርተር ዋና ጉዳዩ ያደረገው፤ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊት ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገመንግስት ያለ አንዳች መሸራረፍ ተከብሮ በሥራ ላይ ቢውል ቢያንስ እኒህ ጥያቄዎች በአእምሮ እንኳ ሊታሰቡ ባልቻሉ ነበር፡፡ ነገር ግን ይህ ሳይሆን ቀረ፤ ግልጽነትና ተጠያቂነትን የምር፣ የምር፣ የምር መርሁ ያደረገ ስርዓት በመላው አገሪቱ ተፈፃሚ ቢሆን ኖሮ እነዚህ ለአርባ ዓመትና ከዚያም በላይ ሕዝቡ ያነገባቸው መልስ የሚሻላቸው ጥያቄዎቹ ምላሽ አግኝተው ዛሬ በትዝታ እያወጋነው ስለወደፊቱ ብሩህ ጊዜ ራዕያችን ማሰብ ብቻ እንችል ነበር፡፡

ከዛሬ አርባ ዓመት በፊት አንስቶ ያልታደሉት አብዛኛዎቹ የአገሪቱ ባለስልጣናት፣ ፖለቲከኞችና ምሁራን በብሔር ብሔረሰቦች መብትና ጥያቄዎች አፋቸውን ፈቱ፡፡ ለዚያን ጊዜዎቹ ኢትዮጵያውያን “ልሂቃን” በዚያን ወቅት ጥያቄው ውስብስብ፣ አወዛጋቢ፣ አገር በታኝ ወይም አሸባሪ አልነበረም፡፡

የዘውዳዊውን ስርዓት ገርስሶ የተደራጀና የነቃ ሕዝብ እና የፖለቲካ ፓርቲ የለም በሚል ሐሳብ የስልጣን እርካቡን ማንም እንዳይወጣ የወጣውም እንዳይወርድ አድረጎ ጊዜያዊው ወታደራዊው

የደርግ መንግስት መንበሩን ተቆናጠጠበት፡፡ በቅብብል የመጣውን የብሔር ብሔረሰቦች የራስን ዕድል በራስ የመምረጥና የመወሰን መብታቸውን በመርህ ደረጃ ተቀበልኩ አለ፡፡ ነገር ግን ሕዝቦች ራሳቸውን በራሳቸው ያስተዳድሩ የሚለውን አቋም ለማራመድና ለመተግበር ግን፣ ስልጣንን እንደ ዳቦ ቆራርሶ ማከፋፈል ተገቢ አይደለም በሚል ግትር አቋም በሥራ ላይ ሳያውል ለግብአተ መሬት አዋለው፡፡

ኢህአዴግ ፌዴራላዊ፣ ያልተማከለ አስተዳደርን መስርቼያለሁ እንዲሁም ሕዝቦች ራሳቸውን በራሳቸው የማስተዳደር፤ የመወሰን መብት ሳይሸራረፍ እንዲኖራቸው አድርጌያለሁ ብሎም ለአለፉት 23 ዓመታት ለብሔርና ብሔረሰቦች ጥያቄዎች ምላሽ የተለያዩ እርምጃዎችን ወስዷል፡፡ ለዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ዋነኛው መሰረት የሕዝብ ተወካዮች የሚመሯቸው ምክር ቤቶች ማጠናከር ተልዕኳቸውን በአግባቡ እንዲወጡ የሚያስችላቸውን ደልዳላ መድረክ ለመፍጠር ይረዳ ዘንድ ሕዝቡ ወኪሎቹን በነፃና ያለምንም ጣልቃ ገብነት በመምረጥ ወኪሎቹ ሆነው እንዲመሩት ማድረግ እንዲቻል ሰርቻለሁም ብሏል፤ ቢያንስ ተልዕኮውን በሚፈጽሙለት ሚዲያዎቹ ነው፡፡ ይህን የሚያበቃ ነፃና ዴሞክራሲያዊ ስርዓት አስፈላጊ የሆኑ መሰረታዊ ዴሞክራሲያዊና ሰብዓዊ መብቶች

የተከበሩበት ከሕዝብ ለሕዝብ የሆነ ስርዓትን ለመገንባት ቃል የገባውን ያህል ግን አልሰራም፡፡ ከዚህ ይልቅ ዴሞክራሲያዊ ስርዓትን አሰፍናለሁ፤ ብሔር ብሔረሰቦች የራሳቸውን እድል በራሳቸው እንዲወስኑ የሚያስችላቸውን መብት አጐናጽፌያለሁ የሚለውን ልፈፋ ግን እንኳን ወደታች አውርዶ ሊተገብረው ሳይሻ ለይስሙላ ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ፍጆታ እንዲውል ያመቻቸውና ድጎማ ለመቃረሚያ ያቀረበው ማመልከቻ ነው የሚል ክስ በተደጋጋሚ ሲቀርብበት ይታያል፤ ይደመጣልም፡፡

“መንግስት ከሕዝብ እየተቆነጠረ፤ በሚሰጥ ስልጣን የተቋቋመ አካል ቢሆንም በመሠረቱ የሕዝብ ጠላት ነው” ሲል ለመጀመራያ ጊዜ የተናገረው ሩሶ የተባለው የአለማችን ፈላስማ ነበር፡፡ በሕዝቡ ስም በሕዝቡ ድምፅ ወደስልጣን የሚወጡ ፖለቲከኞችና ባለስልጣናት ከሕዝብ ፊት ቀርበው ከሕዝብ ለሚነሱ ጉዳዮች ላይ ማብሪሪያ እንዲሰጡና በማወቅና ባለማወቅ የተፈጸሙ ስህተቶችን ተረድተው እንዲያስተካክሉ የሚያስችላቸውን ዕድል ከመጠቀም ወደኋላ የሚሉበት ምክንያት ምን ይሆን?

ገዢው ፓርቲ በየጊዜው የሚገጥሙትን የሕዝብ ቅሬታዎችና ሮሮዎችን መሠረት ያደረጉ ተቃውሞዎችን እንዲሁም ውግዘቶች ሲበረክቱበትና ለሕልውናውም አደገኛ መሆኑን ሲገነዘብ ብቻ ነው ራሱን መልስ ለመስጠት የሚባንንነው፡፡ ወደሕዝብ

ዛሬም እዛው ላይ ነን? ወደ ፊት መሔድን ማን ከለከለን?ልዩ ዘገባ

21°”l 6— ¯Sƒ lØ` 119 ግንቦት 2006 ዓ.ም

ወርዶ ምንድን ነው ያስቀየምናችሁ ቅሬታችሁን ጥያቄያችሁን ለመመለስ እንጥራለን የአሁኑን ብቻ እሺ በሉ የሚል መለማመጫ በሚድያው ሲለፍፍ የኔድርጊት ትክክል ነው ለማለት ከኋላ በጥይት ከፊት ለፊት በባለስልጣናቱ አንደበት ያፏጫል፡፡

ገዢው ፓርቲ ለልማት ዴሞክራሲና ሠላም ሲባል በየበረሃውና ዱር ገደሉ የወደቁ የተሰው አባሎቹን ዘላለማዊ ክብር ይቀዳጁ ዘንድ ቁርጠኛነቱ ካለው ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ሳይሸራርፍ የሚረጋገጡበትን ግልፅኝነት ተጠያቂነት የሠፈነበት ስርአትን በሀገሪቱ ማስፈን ዋናው ታሪካዊ ተልዕኮ መሆኑን ሊያውቅና ሊሰራ በተገባው ነበር፡፡

ኢህአዴግ አውቆም ይሁን ሳያውቅ ሁሌም ራሱን ለፈተና የሚዳርግ፣ ፈተናዎችን እያሸነፈ በድል አድራጊነት የሚረማመድ፣ ከወደቀበትም ተነስቶም ተወዳድሮ የሚያሸንፍ፣ ወዘተ “ሁሉን ቻያዊ” ባህርይ እንዳለው ከባለስልጣናቱ አንደበት መስማት የተለመደ ነው፡፡ ይህ የተሳሳተ የራስ ምስል ወይም ድምጽ ተደጋግሞ ሲታይም ይሁን እንደገደል ማሚቶ ተደጋግሞ ሲሰማ ሕዝብ ድረስ ዓላማቸው/ምኞታቸው

የደረሰላቸው አድርገው እንዲያስቡ ሳያደርጋቸው አልቀረም፡፡

ሰሞኑን በኦሮሚያ ክልል ባሉ ዩንቨርሲቲዎች በአዲስአበባ ዙሪያ ባሉ የፊንፊኔ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን አስተዳደሮች የጋራ ልማት ማስተር ፕላን ትግበራን በብርቱ በመቃወም በርካታ ሰዎች ለሕልፈት የተዳረጉበት የድሃዋ አገር ጥሪት በከፍተኛ መጠን ሲወድም ታይቷል፤ ተዘግቧልም፡፡ የክልሉ አጠቃላይ ገፅታ ላይ ጥፋት እንዲደርስ ያስቻለው ዋነኛ ጉዳይም ኢህአዲግ መራሹ የክልሉ ገዢ ፓርቲ የኦህዴድ ባለስልጣናት መካከል ከ1988ዓ.ም ጀምሮ አንዳንድ አባላቱ የሚየቀነቅኑለትን ዴሞክራሲያዊ ብሔርተኝነትን ወደጎን በመተው ጎጠኝነትን ለማራመድ በሚያስችል ብሔርተኛ አስተሳሰቦች የመለከፍ አባዜ ነው፡፡

በእርግጥ በኦህዴድ ውስጥ ተንበርካኪ በሚል የሚፈረጁ የድርጅት አባላትና ካድሬዎች አሉን? በማስተር ፕላኑ ሳቢያ ሕዝቡ ያሳየው የተቃውሞ እንቅስቃሴና እንዲብራራለት ያቀረበው ጥያቄ፣ የመጠየቅ ዴሞክራሲያዊ መብቱ ያጎናጸፈው መሆኑን ማንም ሊክደው ወይም ሊሽረው ባልተገባ ነበር፡፡

የተቃውሞው ግርግርን በመጠቀም እኩይ አላማቸውን ለማስፈፀም የተንቀሳቀሱ ኃይሎች አሉ ተብሎአል፤ ሊኖሩ ይችሉ ይሆናልም፡

፡ ነገር ግን የተቃውሞ እንቅስቃሴውን ተከትሎ ለተቃውሞውና ለሕዝባዊ ቁጣው ምክንያቱ የሆነውን የሚመለከተውን ሕዝብ ያላሳተፈና ያላማከረ የባለስልጣናቱ “የምን አገባኛዊ” አካሄድ እንደመንስኤነት ማየቱ ተገቢ ነው፡፡

ይሁን እንጂ በተለይም በኦሮሚያ ክልል ባሉ ዋና ዋና ከተሞች ባሉ ዩንቨርሲቲዎች በዚሁ ሰበብ በተቀሰቀሰው ተቃውሞና መንግስትም ለተቃውሞው ምላሽ በሰጠው ወታደራዊ ርምጃ ተገቢነትን ለማስመስከር የሚቀርቡ ማስተባበያዎች አሉ፡፡ የወታደራዊ ርምጃውን ተገቢነት ለማስገንዘብ ለተፈጠረው የሕይወት መጥፋትና የንብረት ውድመት የፌዴራል መንግስቱና የክልሉ መንግስት ባወጡት መግለጫ የማስተር ፕላኑን ወደስራ አለመግባት በተመለከተ ከሕዝቡ ጋራ የተለያዩ የውይይት መድረኮችን በማዘጋጀት ምክክር ሲደረግ ማብሪሪያ ሲሰጥ ነበር እየተባለለት ነው፡፡

እነዚህ ሐረጐች በመግለጫው ውስጥ የተካተቱበት ምክንያት ምናልባት በክልሉ ገዢ ፓርቲ በሆነው በኦህዴድ ብቻ ሳይሆን በኢህአዴግ ውስጥ ሥራው ሳይሰራ የውሸት ሪፖርት የማቅረብ ችግር እንደተንሰራፋ የሚያስጠረጥር ነው የሚሉ ወገኖች አሉ፡፡ ይሔን ያህል ሕዝብ አወያየን የሚል ሪፖርት በዞን፣ በወረዳ፣ በጐጥ፣ በከተማ ደረጃ ባሉ ካድሬዎችና የፖለቲካ አመራሮች ለአለቆቻቸው አቅርበው ይሆንን? ብለው የሚጠይቁ በርካቶች ናቸው፡፡

ብዙ ጊዜ ሚሊዮኖች ተስፋ ያደረጉበት የአዲስ ስርአት ጅማሮ፣ የዴሞክራሲያዊ ስርአት ምሉዕነት የተረጋገጠበት የፖለቲካ ሥርአት ግንባታን ላለማየት መንስኤ የሚሆነው ተስፋውም የሚጨነግፈው የሕዝብን ሉአላዊነትን ወደጎን በሚተው የግዴለሽነት አካሄዶች ናቸው፡፡ ለዚህም ማስረጃችን አሁንም ቀደም ሲል የጠቀስነውን ፈረንሣዊ ፈላስፋና አስላሰይ ዣን ዣክ ሩሶ ማኅበራዊ ውል (social contract) በተሰኘ ሥራው ባሰፈረው የፍልስፍና መጣጥፍ “ስልጣንም ሆነ ሉአላዊነት የሚመነጨው ከመለኮት ሳይሆን ከሕዝብ ነው፡፡ ለሉአላዊነት የሚበቃ ሕዝባዊ መሪ የሕዝቡን አጠቃላይ ፍላጐት ወይንም ይሁንታ በተግባር ላይ የሚያውል ከሆነ ነው!” ይላል፡፡

ሉአላዊነትም የሚገለፀው በንጉሳዊው ዘውዳዊ አገዛዝ ስርዓት ሳይሆን በሕዝባዊ መንግስት ነው! መሪው ሕዝባዊ ይሁንታውን በተግባር ላይ ያላዋለው እንደሆነ ህዝባዊ አመፅ እንዲካሄድበት ያስፈልጋል ብሎ ባስተማረው መሠረት የፈረንሣይ ሕዝብ በንጉስ ሉዊ 16ኛ የፊውዳል መንግስት ላይ ፀረ-ንጉሳዊ አገዛዝ አብዮት አካሂዶ ድል ተቀዳጀ፡፡ ልክ እንደዚያው ከዛሬ አርባ አመት በፊት በኢትዮጵያችን የዘውድ አገዛዝን በሕዝባዊ አመጽ ታቃውሞ ከገረሰስን አንስቶ እስከዛሬ የብሔረሰቦች መብት የራስን በራስ የማስተዳደር ጥያቄ አወዛጋቢ ችግራችን ሆኖ መቀጠሉ ለምንድን ነው?

ዛሬ የኦሮሞ ሕዝብን እንወክላለን የሚሉ የኦሮሞ ልሂቃን በኢትዮጵያ በተፈጠረው አንድነት ተጠቃሚ ናቸውና ሊጫወቱት የሚገባቸውን

ዛሬም እዛው ላይ ነን? ወደ ፊት መሔድን ማን ከለከለን?የአውራነት ሚና ከመጫወት ይልቅ የመለያየትና የመገነጣጠል መብት ላይ የሙጥኝ ብለው በኢትዮጵያ አንድነት ላይ ያንዣበበ አደጋ እንዳለ ያመላከቱበት ይመስላል፤ ይህን አካሄድ አዘውትረው ሲጠቀሙበትም ታይቷል ለምሳሌ የኦሮሚያ ዋና ከተማ አዲስ አበባ እንጂ አዳማ አትሆንም በሚል ተቃውሞ በየዩኒቨርስቲዎቻችን ተቀስቅሶ ገሚሱ ሞቶ፣ ገሚሱ ታስሮ፣ ገሚሱ ተሰዶ ሲያልቅ የቅርብ ጊዜ ትዝታችን ነበር፤ ባለስልጣናቱም፣ ያለቀው አልቆ፣ የሞተው ሞቶ፣ የተሰደደው ተሰዶ፣ ያው በድርጅታቸው ስር ከነስልጣናቸው ወደ ህዝቡ ግን ሳይወርዱ አሉ፡፡ በተቃውሞ አገር ከፈራረሰች በኋላ እሳቱን እንዲያጠፉለት መንግስት ህዝቡ ያምንባቸዋል የተባለላቸውን ባለስልጣናት ተአኔሪካም ድረስ ቢሆን አስመጥቶ በገጠር እያንገላታ የአዳራሽና የቀበሌ ስብሰባዎችን እንዲመሩ እያዘዘና እያናዘዘ መሄድን መርጧል፡፡

ዛሬ ከ 23 አመት በኋላ በግንቦት 20 ዋዜማ ላይ ሆነን ሕዝቦች በአንድነት፣ በብሔራዊ መግባባት በአንድ ዴሞክራሲያዊ መሰረት ላይ ያረፉ ጠንካራና ዘላቂ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ማኅበረሰብ ለመመስረት ያለመቻላችን ምክንያቱ ምንድን ነው? ብሎ መጠየቅ፣ መጠየቅ፣ መጠየቅ ያሻል፡፡

እስከዛሬም በገዢው ፓርቲና በተቃዋሚ ኃይሎች መካከል ዕልባት ያላገኙ የፖለቲካ ልዩነቶችና ችግሮች እየተንከባለሉ የዴሞክራሲ ስርአት ግንባታውን ወደ ኋላ የሚጐትቱ ሲጎትቱ ይታያል፡፡ ያልተመለሱ ግን መልስ የሚያሻቸው የመብት ጥያቄዎችን ምላሽ ሳይሰጥ “በጠመንጃ የወጣን በጠመንጃ አወርዳለሁ” የሚል ቅኝት ያለውን ኃይል ለመፍጠር የሚያበቃ አካሄድ ስጋት አለው፡፡

ኢህአዴግም ሆነ በሀገሪቱ ያሉ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በውስጣቸው ያልፈጠሩት ወይንም ቀደም ሲል የነበራቸውን አሁን ያጡትን ዴሞክራሲያዊ ባህልና አሰራር በሀገር ደረጃ ለማስፈን ብቃቱና ፍላጐቱ ሲጠፋባቸው ወይም ሲያንስባቸው ማየት የተለመደ ሆኗል፡፡

ለዚህም ነው ዛሬም እዛው ላይ ነን! ከቅድመ 1983 በፊት ባለ አስተዳደርም ሆነ ድኅረ 1983ዓም የስልጣን እርፉን የያዙ መሪዎቻችን ላይ ለሕዘብ ኖሮ ለሕዝብ ማለፍ የሚያስችልን ጐዳና እንዳይመርጡ ማን ከአእምሮአቸው አጠፋባቸው? ምላሽ ሊሰጠው የሚገባ ወቅታዊ ጥያቄ ነው፡፡ የእኛን አገር ፖለቲከኞች/ገዥዎች በሚገባ ይገልጻቸዋል በሚል የሚከተለውን ከሩሲያዊ ደራሲ አይዛክ ዶቸር እንጥቀስ "አንዳንድ አብዮተኞች ለሚያቃጥሉት አብዮት የሚሠግዱ፣ ሌሎች ደግሞ አብዮተኞችን አቃጥለው የሚሠግዱ ናቸው” ይላቸዋል፡፡ በእርግጥም ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ያለገደብ ተፈጻሚነታቸው ይረጋገጥ ዘንድ ደማቸውን ያፈሰሱ፣ አጥንታቸውን የከሰከሱ፣ ሕይወታቸውን የገበሩ በሺዎች የሚቆጠሩ ወንድም እህቶቻችን የከፈሉት መስዋዕትነት ምንዳን ለመቀበልና በእነርሱ ክቡር መስዋዕትነት ላይ የተመሠረተ ሁሉን አቀፍ ዴሞክራሲያዊ ስርአት ባለቤት መሆንን ለምን አልመረጥንም?

ልዩ ዘገባ

22 °”l 6— ¯Sƒ lØ` 119 ግንቦት 2006 ዓ.ም

ኢትዮጵያ በማራቶን ውድድር አሸናፊነቷን ካስመሰከረችበት የሮም ኦሎምፒክ ጀምሮ በአትሌትክሱ ዓለም በስመ-ገናናነቷ እንደቀጠለች ነው፡፡ አበበ ቢቂላ እና ማሞ ወልዴ የልዕልቷ ማራቶን ‹‹ባለቤት›› መሆናቸው ከተነገረበት ጊዜ ወዲህም በርካታ አይበገሬ ሯጮች ብቅ ብለው ሀገራችን የስመ-ጥሩ ስፖርተኞች መፍለቂያ ምድር መሆኗን አስመስክረዋል፡፡ ይሄን የመሰለው ሂደት ቀጥሎ ኢትዮጵያ ከአትሌቲክስ ፌዴሬሽኗ ጋር ዛሬ የደረሰችበት ደረጃ ላይ ብትደርስም፤ የቀድሞ ባለውለታዎቿን አይደለም በአግባቡ ለመካስ ይቅርና በአንድና በሁለት አሥር ዓመታት አንድ ጊዜ እንኳን በክብር ለማሰብ አልታደለችም፡፡ ይኼን የመሰለውም ነገር በየዘርፉ የሚስተዋል የሀገሪቱና የዜጎቿ ዕጣ-ፈንታ በመሆኑ ጥቂት የማይባሉ የትላንት የስፖርት ዓለም ጀግኖች፤ በስተርጅና እና በደካማነት ዕድሜያቸው አንገታቸውን ደፍተው በተብሰልስሎት የሚኖሩ ሆነዋል፡፡ በዚህ መልኩ ኑሯቸውን ኑሮ ብለው ከሚኖሩት የስፖርት ጀግኖቻችን መካከል የዛሬው የመንገድ ዐምድ እንግዳችን፤ አትሌት ገብሬ ጉርሙ አንዱ ነው፡፡ የአሥር አለቃ ገበሬ ጉርሙ የእነ አበበ ቢቂላን፣ ማሞ ወልዴን፣ ዋሚ ቢራቱንና የእነ ባሻዬ ፈለቀን …ፈለግ በመከተል ወደ ሩጫው ስፖርት የመጣና በማራቶን ውድድር መስክ በጥንካሬውና በአሸናፊነቱ ስሙን ለማፃፍ የበቃ ነው፡፡ በ1935 ዓ.ም በቀድሞው ሸዋ ክፍለ ሀገር በአዲስ አበባ ዙሪያ ልዩ ስሙ ‹‹ቦሌ ገላን›› በተባለ አካባቢ የተወለደው ገብሬ ጉርሙ፤ በአገር፣ በአህጉርና በዓለም አቀፍ ደረጃ በተካሄዱ የማራቶን ውድድሮች በወጣትነት ዘመኑ ተሳትፎ በማድረግ ለውጤት የበቃ፣ ለሀገሩ ኢትዮጵያ ዋንጫና ሜዳሊያ ማስገኘት የቻለ፣ ባንዲራችን ከፍ ብሎ እንዲውለበለብ ምክንያት የሆነ ድንቅ አትሌት ነበር፡፡ ይህንን አትሌት ሰሎሞን ለማ በቅርቡ አነጋግሮታል፡፡ዛሬ የሰባ አንድ ዓመት አዛውንት ለሆነውና የማይረሳ ሥራ ሠርቶ እንዳልነበር፤ ተረስቶ በጉስቁልና ለሚኖረው ገብሬ ጉርሙ፤ የትላንት ድል አድራጊነቱ፣ የትላንት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ መሠረት ጣይነቱ፣ የትላንት ውጣ ውረዱና ድካሙ …አሁን አሁን ባለመታወሱ መስታወት ውስጥ የሚታየው ‹‹ነበር›› የሚባል የሕይወቱ መራር አይሉት ጣፋጭ …ዓይነት ትዝታ ነው፡፡ ያን ትዝታውን ሲያስበውም፤ ወገን አልባ፣ አስታዋሽ የለሽ መሆኑ ጎልቶ ይታየውና ዕንባው ያለፈ ታሪኩን ከመተረኩ እየቀደመ ይፈሳል፡፡ በርግጥ ዕንባ በመረሳት እድፍ የታጀለ ማንነትን የማጠብም ሆነ የማጥራት አቅምና ጉልበት የለውም፡፡ ባይኖረውም ለሀገር ሠርቶ፤ በሀገር ባዕድ ሆኖ የመታየትን የተብሰልስሎት ህመም ትኩሳት ያበርዳል ተብሎ ስለሚታሰብ፤ ተፈጥሯዊ በሆነ መንገድ በራሱ ጊዜ ሲመጣ እንደ አመጣጡ መስተንግዶ ተደርጎለት ይሸኛል፡፡ ገብሬ በእንደዚህ ዓይነቱ ሁኔታ ውስጥ ሆኖ ያለፈ ትዝታውን፣ የዛሬ አኗኗሩን … ‹‹የሚያስታውሰኝም ወገን አለ እንዴ?›› በሚለው የአግራሞት ስሜት ታጅቦ እንደሚከተለው አጫወተን፡- ‹‹በ1960 ዓ.ም ጅጅጋ ላይ ተካሂዶ በነበረው የ42 ኪሎ ሜትር ማራቶን፤ የአንደኛ ክፍለ ጦር አካል የሆነውን 19ኛ ሻለቃን በመወከል

ተወዳደርኩ፡፡ በዚያ የመጀመሪያ ተሳትፎዬም አንደኛ ወጣሁ፡፡ ሌላ ውድድር በዚያው ዓመት ሲደረግም የሚቀድመኝ አልተገኘም፡፡ በዚህ መነሻ ኮሎኔል ሙሉጌታ ናትናኤል ይመሩት ለነበረው 1ኛ ብርጌድ የስፖርት ቡድን አባል እንድሆን አደረጉ፡፡ በ1963 ዓ.ም የተዛወርኩበትን ክፍል በመወከል በመላው የጦር ኃይሎች ውድድር ላይ ተሳታፊ በመሆን በ42 ኪሎ ሜትር ማራቶን 3ኛ ወጣሁ፡፡ በጊዜው በሥፍራው የተገኙት ቀዳማዊ ኃይለሥላሴም የአንድ መቶ ብር ሽልማት አበረከቱልኝ፡፡ ከዚያ ውድድር በኋላ በአህጉርና በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳድሬ የዋንጫና ሜዳይ ተሸላሚ መሆን ብችልም፤ ይኸው እስከ ዛሬ በአሸናፊነቴ ምክንያት አገኘሁት የምለው ገንዘብ፤ ከኃይለሥላሴ እጅ የተቀበልኩት አንድ መቶ ብር ብቻ መሆኑ ሲገርመኝ ኖሯል…›› ‹‹ገና ከማለዳው የነበረው አጋጣሚ ያንን ቢመስልም፤ እኔና በዚያን ጊዜ ቀዳሚዎቹ የእነ አበበ ቢቂላ ፈለግ ተከታይ የነበርነው እነ ደረጀ ነዲ፣ ወልዴ ሮበሌ፣ ሌንጪሳ በዳኔ፣ ጌታቸው ከበደ፣ ታደሠ ወልደመድህን፣ ታደሠ ሰጥአርጋቸው፣ ምሩፅ ይፍጠር፣ መሐመድ ከድር፣ ከበደ ባልቻ፣ ዮሐንስ መሐመድ፣ እሸቱ ቱራና ሌሎችም አትሌቶች፤ በሲዊዲናዊው ሜጀር ኦን ስካን፣ እንደዚሁም በእነ ነጉሤ ሮባና ወልደ መስቀል ኮስትሬ …እየሰለጠንን፤ በአህጉርና ዓለም አቀፍ ውድድሮች በመሳተፍ የኢትዮጵያን ስም በተደጋጋሚ አስጠርተናል›› ‹‹በበኩሌ በኅዳር ወር 1967 ዓ.ም ጂቡቲ ላይ በተካሄደ የ21 ኪሎ ሜትር የግማሽ ማራቶን ውድድር ተሳታፊ በነበርኩበት ጊዜ፤ አምስተኛ ወጥቻለሁ፡፡ በወቅቱ አንደኛ በመውጣት አሸናፊ የነበረው ምሩፅ ይፍጠር ነበር፡፡ ይሁንና ከጂቡቲ መልስ በ1968 ዓ.ም በአገራችን በተካሄደው የ42 ኪ.ሜ ማጣሪያ አንደኛ መውጣት በመቻሌ ኢትዮጵያን ወክለው በመላው አፍሪካ ጨዋታዎች እንዲሳተፉ ከተመረጡት አትሌቶች መካከል የመጀመሪያው መሆን ቻልኩ፡፡ በታንዛኒያ ዛንዚባር በተደረገው ውድድርም በ42 ኪ.ሜትር አንደኛ

ወጥቼ ለአገሬ ዋንጫ አስገኘሁ፡፡ በዚያው ዓመት በሞንትሪያል ካናዳ በተካሄደው የኦሎምፒክ ውድድር ተሳታፊ ለመሆን ወደ ሥፍራው ከቡደኑ አባላት ጋር ያመራሁ ቢሆንም የኢትዮጵያ መንግሥት በወሰደው ደቡብ አፍሪካን የሚመለከት የፖለቲካ አቋም ምክንያት ተሳታፊ ሳንሆን ተመልሰናል›› ‹‹ከካናዳ መልስ በ1969 ዓ.ም ወደ አልጄሪያ አልጀርስ በማምራት በማራቶን ተወዳደርን፡፡ በዚያ ውድድርም ኢትዮጵያ በቡድን አሸናፊ መሆን ችላለች፡፡ ነገር ግን በግል አሸናፊ የሆነው የሌላ አገር ዜጋ ሲሆን፤ ደረጀ ነዲ የሁለተኛ፣ እኔ የሶስተኛ ደረጃን አግኝተናል፡፡ በ1972 ዓ.ም ደግሞ ወደ ኩባ በመጓዝ፤ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በየተመደብንበት ምድብ ሁላችንም አንደኛ፣ አንደኛ በመውጣት የሃገራችንን ስም አስጠርተናል፡፡ በ1967 ዓ.ም በአሜሪካ ኒውዮርክ ተካሂዶ በነበረው የ21 ኪ.ሜ ሩጫም ተሳትፌ ነበር፡፡ ያኔ አምስተኛ በመሆን ውድድሩን ስፈጽም የገባሁበት ሰዓት ጥሩ እንደነበር አስታውሳለሁ፡፡ በዚያ ውድድር ላይም አንደኛ እና ሁለተኛ ሆነው የገቡት ሻምበል ምሩፅ ይፍጠር እና መሐመድ ከድር ነበሩ፡፡ ዳግመኛ በአሜሪካ ፖርቶሪኮ በ1968 ዓ.ም በተካሄደው መሰል ውድድርም ተሳታፊ ሆኜ አሥረኛ ወጥቻለሁ፡፡ በጥቅሉ በአገር ውስጥም ይሁን ከአገራችን ውጪ ያኔ እናደርግ የነበረው ስፖርታዊ ውድድር የክፍላችንንና የኢትዮጵያን ስም ከማስጠራት ያለፈ ግብ አልነበረውም››‹‹በ1984 ዓ.ም በጡረታ እስከተሰናበትኩበት ጊዜ ድረስ የአገሪቱን የአትሌቲክስ ስፖርት የተሻለ ደረጃ ላይ ለማድረስ የበኩሌን ጥረት ከማድረግ ባለፈ የገንዘብ ጥቅም ለማግኘት ሲባል ያከናወንኩት ሙያዊ ተግባር አልነበረም፡፡ ዛሬ ዘመኑ ሌላ ነው፡፡ የበረታ አትሌት ተወዳድሮ በሚያገኘው ውጤት፤ የአገሩን ስም ከማስጠራቱ ባሻገር የራሱን፣ የቤተሰቡንና የዘመድ አዝማዶቹን ሕይወት መለወጥ የሚችልበት ገቢ ባለቤት የሚሆንበት ዕድል አለው፡፡ ይሄ ደስ የሚያሰኝ ነገር ነው፡፡ ቢሆንም የዛሬው ትውልድ ዕድል የተመቻቸው በቀድሞው የሀገር ባለውለታዎች ጥረት መሆኑ ቢታሰብ፣ እንደ እኔ ያሉትንም ለማስታወስ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን መሥራት የሚገባውን የሚያስከብር ሥራ ቢሠራ ጥሩ ይሆን ነበረ››‹‹ይኼ ሲሆን ግን አልታየም፡፡ አስተውሎቱና ለወገን አሳቢነቱ ካለ፤ ፌዴሬሽናችን እኔን የመሰሉትን አትሌቶች ቢያንስ በጥበቃ የሥራ ዘርፍ እንኳን እንድንሠማራ በማድረግ ሊረዳን ይችል ነበር፡፡ ሆኖም የቀድሞ የሀገር ባለውለታዎችን ‹የት ነው ያሉት? …እስቲ እንደግፋቸው..›› የሚል ወገን አለ ወይ? የሚለው በራሱ ያጠራጥረኛል፡፡ ይኸው አርባ ሁለት ዓመታት ባስቆጠረው ትዳሬ ሰባት ልጆችን አፍርቼ፤ ከጡረታ በማገኛት 280 ብርና በስተርጅና ዕድሜዬ ባገኘሁት የጥበቃ ሥራ አማካይነት በማገኘው መጠነኛ ገቢ እተዳደራለሁ፡፡ በጦፈው የኑሮ ውደነት፤ ይኼን በመሰለ ገቢ ልጆችን ማሳደግ፣ ማስተማር …እንዴት ነው የሚቻለው? የሚለውን እንቆቅልሽ የሚያውቅ ያውቀዋል፡፡ ትላንት ጎበዝና ትንፋሼ በቀላሉ የማይቋረጥ ስፖርተኛ ነበርኩ፡፡ ትላንት የኢትዮጵያ ሕዝብ ያከበረኝ፣ ያጨበጨበልኝ፣ በሀገሬ ባንዲራ ፊት በአሸናፊነት ግርማ ሞገስ የቆምኩ አትሌት ነበርኩ፡፡ ዛሬ አስታዋሽ የሌለኝ አዛውንት ነኝ…››

‹‹ትላንት የኢትዮጵያ ሕዝብ ያከበረኝ አትሌት ነበርኩ››

የ፲አለቃ ገብሬ ጉርሙ

23°”l 6— ¯Sƒ lØ` 119 ግንቦት 2006 ዓ.ም

2የአ

ዘጋ

ጁ መል ክትዕ

28

29

33

35

36

26

31

24

30

ዕንቁ ክፍል

‹‹ከእንጨት መርጦ ለታቦት ከሰው መርጦ ለሹመት›› ይሉ ብሂል አለን፡፡ በማናቸውም የሕይወት ዘርፎቻችን መርጦ፣ ነቅሶና መርምሮ የሚበጅ የሚበጀውን ለአገልግሎት ማዋል፤ የማይበጀውንም አንጓልሎ መጣል ይገባል፤ ምክንያቱም ሀብቶች የተትረፈረፉባት ሀገር የለችንምና፡፡ ኢትዮጵያዊው ከተሜ ዜጋ ለውጭ ሀገር የስፖርት ውድድሮች እንጂ የሀገሩን እንዲያስብና እንዲያደንቅ ሚዲያውም አልሰራም፤ የሀገርን የሚያስመርጥ ሥርዓትም አልተዘረጋለትም፡፡ የኢትዮጵያው የስፖርት ውሎም ከድጥ ወደማጡ አካሄድን ሲመርጥ የሚመልሰው ትችት ወይም ቅን አሰራር አልቃኘውም፡፡ ከክለቦቻችን ወጥተው በዓለማቀፍ ደረጃ ፕሮፌሽናል ተጫዋች የመሆን ዕድልን ሲያገኙ ‹‹እሰየው….ዕልልልል››…..እንዳላልን፣ እኒያው የሀገራችን ክለቦች ከውጭ ሀገራት ሚዛን የማይደፉ ተጫዋቾችን አስመጥተው ክለቡ ውጤት ሲርቀው አሰራሩን ዳግም ቃኝቶና ገምግሞ የማሻሻያ ርምጃ ለመውሰድ አለመቻል እየተለመደ ነው፡፡ ፌዴሬሽኑ እንኳ ለሀገሬው ስፖርትና ታዳጊዎች በመቆርቆር ሥርዓት ሲያበጅ አልታየም ፡፡በየመስኩ ከውጭ ሀገራት በርካታ የማይጠቅሙ ሰዎች በባለሙያነት ሥም መጥተው ሥራና ውጤትን ሲያበላሹም ላበላሹበትም ሒሳባቸውን ቆጥረው ኪሳቸው ሲከቱ ጠያቂም ተጠያቂም የሌለ ያስመስላል፡፡ ሰሪውም ሆነ ሥርዓቱ ከውጭ ሀገር የሚመጡልንን ኮንትሮባንዶች የመቆጣጠሪያና የሀገሬውን ነጋዴ የመንከባከቢያ/የመጠበቂያ ሥርዓት አበጅቷል፡፡ ምነው ሰውስ ወደሀገር ውስጥ ሲገባ የሚጠቅምና የማይጠቅመውን ለይቶ መምረጥ የሚበጀውን መሳብ የማይበጀውን መተው አልቻለን አለ? የሀገሬው የትምህርት ሥርዓት አንዳንዴ አደጋ ላይ እንዳለ ምስክር የሚሆኑ የዩኒቨርስቲ መምህራንን ከህንድ፣ ከአፍሪካ ሀገራትና ከሌሎች ሀገራት አስመጥቶ የተማሪና የአስተማሪ ግንኙነት እንዳይሳለጥ መምህሩም ዝም መጽሐፉም ዝም ብለው ተፋጥጠው እንዲተያዩ አድርጓል፤ በሌሎች ዘርፎችም የተሰማሩ የቻይና ዜጎችን ውጤት ቤቱ ይቁጠረው ግን ደሞዝ በዶላር ይከፈላቸዋል፡፡ የእግር ኳሱ ሰሪም ሆነ ሥርዓት የተጓዘበት ታሪክ አኩሪ የነበረ ቢሆንም አሁን አሁን የሚጠቅምና የማይጠቅመውን የሚለይ አካሄድን እየተከተለ አይደለም፡፡ መቼም እንደፊፋ ካለፈ በኋላ ‹‹የተሳሳትነው ነገር ነበረን›› የሚል ድፍረት እንዳይኖረው አበሻዊ ይሉኝታና ድፍረት የያዘው ነው፡፡ ሚድያው የሀገርን ኳስ በባዕዳኑ እንዲተካ ጉልህ ሥራ ሰርቷል፣ የሥራውን ውጤትም እየሰበሰበ ነው፤ ምክንያቱም የመንግስትን የሥራ ሰዓት በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ጉንጭ አልፋ ክርክር ማባከን ተለምዷልና፤ ሥራ የሌላቸው ወጣቶች ሥራ የሚፈጥሩበትን አሳብ፣ ተማሪው አኩሪ ውጤት እንዲያስመዘግብ የሚረዳውን የማንበበቢያና የመወያያ ጊዜ በሩቅ አስተሳሰቦች ሞልተው በዚህ እየቆዘሙ እንዲውሉ አስችሏልና፡፡ እኛ ምንም አያውቁም የምንላቸው አባቶቻችን ከጎረቤት አስተሳሰቦችን፣ አመለካከቶችን፣ ይትበሃሎችን ሲወርሱና ሲዋሱ የሚጠቅምና የማይጠቅመውን እየለዩ ነበር፡፡ ሰውማ ሲዋሱ እጅግ መርጠው፣ ቀምሰውና አጣጥመው እንደሆነ ታሪክን የኋሊት መቃኘት ያሻል፡፡ አሁን ደግሞ ባደገው በተሻሻለው የስልጣኔ ዘመን ሰውን ለመምረጥ እንዳይቻል የሚያደርግ ሥርዓትና ሰሪ በማወቅም ባለማወቅም እየተከወነ ይገኛል፡፡ የአየር ንብረት ብክለትን ለመቋቋምና ለመመከት ቀን ከሌት የሚተጋ አሰራር ተዘርግቷል፤

የአሰራር ዘዬአችን ትርፍና ውጤትን የሚለካና የሚዳኝ እንዲሆን ያሻል

“በቆሻሻ መኪና ሄደን መንግስቱ ኃ/ማርያም በሸለመን አውቶብስ ተመለስን”

ሥነ-ጥበብ…ለሃያ ሦስት…ሦስት ጉዳይ፤

ከዛሬ 8400 ቀናት በፊት...

የመገጣጠሚያ አካላት የህመም ስሜቶችና መፍትሄዎቻቸው

“መብራት ባይኖርም የመብራት እከፍላለሁ”

መታወቂያዬን ሳየው

32 ኢትዮ-አሜሪካዊ ማንነቴን መሠረት ያደረገ አልበም ሠርቻለሁ

የውጭ ተጫዋቾች በኢትዮጵያ

አስገራሚው ‹‹ኤልሻማ ድንጋይ››

ድምፃዊ መሀመድ ይመር

ጌታቸው አበራ

“በአዲሱ ትውልድ ተስፋ አደርጋለሁ” ዶ/ር ሰለሞን አሠፋ

24 °”l 6— ¯Sƒ lØ` 119 ግንቦት 2006 ዓ.ም

በቀድሞው አብዮት አፍላ ዞን በየክፍለ ሀገራቱ ከተቋቋሙት አኩሪ የኪነጥበብ ክዋክብት መካከል የጐንደሩ “ፋሲለደስ” የጐጃሙ “ግሼ አባይ” እና የወሎው “ላሊበላ” የኪነት ቡድኖች አስተዋፅኦ ዘመን ተሻግሮ ዛሬም የደረሰ ነው፡፡ በእነዚህ ኪነት ቡድኖች ለባህል ሙዚቃችን ጌጥ የሆኑ ድምፃውያንና መሳሪያ ተጫዋቾች ቢኖሩም አብዮቱ ሲፈርስ በአዲሱ መንግሥት “ከኑግ የተገኘህ ሰሊጥ አብረህ ተወቀጥ” እንዲሉ ከያንያኑም እንደ አብዮቱ ሁሉ በከፉ ዓይን ታይተው አብረው ተወቅጠዋል፡፡ ከሀገር የወጡት ወጥተው፣ የዳኑት ድነው፣ የሞቱት ሞተው ቀሪዎቹም በሕይወትና በሞት መሀል ሆነው እዚህ ደርሰዋል፡፡ “ከመከም ጐፈሬ” በሚል ባህላዊ ሙዚቃ የምናውቀው የወሎ ላሊበላ ኪነት አባል የሆነው ድምፃዊ መሀመድ ይመር ከእነሱ አንዱ ነው፡፡ በቅርቡ “ሶሎ ራዮ ኮሙዩኒኬሽን ኤንድ ኤቨንት” ባዘጋጀው ፕሮግራም ወደ ውጫሌ ስንሔድ ደሴ ከተማ ላይ የቡድኑን አንጋፋ ድምፃዊ መሐመድ ይመርን የዕንቁ ባልደረባ ተክሉ አረጋዊ አግኝቶ አነጋግሮታል፡፡ ዕንቁ፡- ድምፃዊ መሀመድ ይመር በቅድሚያ ስላገኘሁህ ደስ ብሎኛል፡፡መሀመድ፡- እንግዲህ ስንት ህይወት አልፎ ነው የተገናኘነው፡፡ ያ ሁሉ ክፉ ቀን አልፎ ቀና ስንል ስለተገናኘን እኔም ደስ ብሎኛል፡፡ዕንቁ፡- የት ነው ውልደትና እድገትህ?መሀመድ፡- እዚሁ ደሴ አካባቢ ነው፡፡ ደሴ 16 ወረዳዎች፣ 12አውራጃዎች የነበሩት ከተማ ነው፡፡ እኔ እንግዲህ በወረዳ ደረጃ መቼላ ወይም ሲቂ ይባላል ሀገሩ፤ የተወለድኩበት፡፡ዕንቁ፡- ስንት ዓመተምህረት ደሴ ገባህ?መሀመድ፡- 1962 ገብቻለሁ፡፡ዕንቁ፡- የዛሬ 43 ዓመት ማለት ነው፡፡ እድሜህ ስንት መሆኑ ነው በዚህ አይነት?መሀመድ፡- ደሴ ስገባ ትንሽ ነኝ፡፡ ሱሪ አልታጠኩም፡፡ የ13 ዓመት ልጅ እሆናለሁ፡፡ ሁለቱን መደመር ነው እንግዲህ እድሜዬ ላይ ለመድረስ፡፡ 56 ላይ ትይዘዋለህ፡፡ዕንቁ፡- የድምፃዊነት መነሻህ ምንድነው? መሀመድ፡- ልጅ ሆኜም እዘፍናለሁ፡፡ ሰብል ውስጥ ነው ውዬ የማድረው፡፡ ደሞ አዝማሪዎች አሉልህ ሰርግ ሲኖር እየዞሩ የሚያዘምሩ፡፡ እነሱን ሳይ ይሔን ሙዚቃ መጨመር አለብኝ ብዬ ለመጀመሪያ ጊዜ ልጅ ሆኜ ሰርግ ላይ በምዘፍነው ካገኘሁት በአራት ብሩ መሰንቆ ገዛሁ፤ እንደ አዝማሪዎቹ ለመሆን፡፡ዕንቁ፡- በልጅነትህ ሬዲዮ ሰምተህ ታውቃለህ?መሀመድ፡- የለም በጭራሽ፡፡ ከየት ይመጣል? በሬዲዮ የተቀረፀ ዘፈን ሰምቼም አላውቅ፡፡ እና ሰርግ ላይ “ለፍጀሌ” የሚባል አለ፡፡ዕንቁ፡- ለፍጀሌ?መሀመድ፡- አዎን፡፡ ሙሽራይቱ ተድራ ከቤት እስክትወጣ ድረስ የሚዘፈን ነው፡፡ እዚያ ላይ በጣም ዘፋኝ ነኝ፡፡ዕንቁ፡- በስንት ዓመትህ ለመጀመሪያ ጊዜ ዘፈንን በሬዲዮ ሰማህ?መሀመድ፡- የዘፈን ምርጫ አልነበረም፡፡ ከ1964 ጀምሮ ትዝ አይልህም? እሁድ ከሰዓት እንዳለ ዘፈን ምርጫ ነው፡፡ ያኔ ትንሽ ሬዲዮ ገዛሁ ደሴ እንደገባሁ፡፡ዕንቁ፡- በምንህ ገዛህ?መሀመድ፡- ማሲንቆ ገዝቼ እሰራ ነበር ማታ ማታ፡፡ ቀን ደግሞ አልቃት ጮራ የሚባል ት/ቤት አለ፤ እዚያ ሦስተኛ ክፍል ገብቼ ነበረ፡፡ ጠጅ ቤት እየሰራሁ የማገኛትን አጠራቅሜ ሬዲዮ ከ 25 እስከ 40 ብር ነው፤ ገዛሁ፡፡ዕንቁ፡- ያም ሆኖ እንዴት ከሌላው ነገር ሬዲዮ መግዛትን አስቀድመክ?መሀመድ፡- ሌላ ምን የሚቀረኝ አለ? የከተማ ልጅ ለመሆን ከተማ ገብቼ ልብስ ለብሻለሁ፤ ት/ቤት ገብቻለሁ፡፡ ሬዲዮ ነበር የቀረኝ፡፡ ደሞ ሬዲዮ ውስጥ የእነ መሀሙድ አህመድ፣ የነጥላሁን ገሠሠ፣ የነብዙነሽ በቀለ፣ የነዓለማየሁ እሸቴ፣ የነታምራት ሞላ ታዳምጣለህ፡፡ በኋላ ላሊበላ

“በቆሻሻ መኪና ሄደን መንግስቱ ኃ/ማርያም በሸለመን አውቶብስ ተመለስን”

ኪነት ገብቼም ከእነሱ ጋር አብሬያቸው ሰርቻለሁ፡፡ ብዙ ህይወት አሳልፈናል፤ ይወዱኛል፡፡ የእነሱ ዘፈን ይጥም ነበር፡፡ ልክ 8፡00 ሰዓት ሲሆን ከሰዓት ሬዲዮኔን ይዤ፣ መጽሐፍ ነገር ሀሁ የምትባል የ5ሳንቲም ፊደል ነበረች፡፡ እሷን ይዤ እሄዳለሁ፡፡ ለትምህርቴ እንዲቀናኝ እያነበብኩ ዘፈን እሰማለሁ፡፡ አንጐራጉራለሁ፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ (እያንጐራጐረ)…“አልማዝ ምን እዳ ነው ጉልቻው ስሙኒ ምጣዱ ብር ነው አልማዝ ምን እዳ ነው፡፡”የሚባል ዘፈን ነበር፡፡ በማሲንቆዬ ያቼን ዘፈን አጠና ነበር፡፡ዕንቁ፡- አልማዝ ምን እዳ ነውን ለይተህ በምን ወደድከው?መሀመድ፡- ዘፈኑን ሳዳምጠው እንግዲህ ከምን ጋር እንዳያያዝኩት አላውቅም፡፡ ዜማውን ነው የወደድኩት፡፡ዕንቁ፡- እንጂ አልማዝ የምትባል በቅርበት የምታውቃት ሴት የለችም?መሀመድ፡- አልማዝ ምናልባት እዚያው የምኖርበት ሰፈር ጠጅ ቤት የምትሰራ አልማዝ የምትባል ልጅ ነበረች፡፡ የሚገርምህ ነገር….ዕንቁ፡- ይኸውልህ ቀስቀስ እያለች እውነቷ እየወጣች ነው፡፡?መሀመድ፡- የሚገርም ነው፡፡ ነገሩ ብዙ ጊዜ ሆኖት ነው እንጂ መቼም አንድ ነገር ያለ ምክንያት አይወደድም፡፡ ለመጥላትም ምክንያት አለ፡፡ እና ይቺ አልማዝ ያኔ ገና ልጅ ነኝ፤ ወደሴት አልሄድም፤ጠጅ ትቀዳለች፡፡ ትንሽ ናት እሷም፡፡ እኔ እሷን ለመድፈር እፈራለሁ፡፡ እሷም ትፈራለች፡፡ ከዚያ ያንን ዘፈን ሰምቼ ስመጣ እሷን አገኘኋት፡፡ አልሚዬ ዛሬ ሬዲዮን ስላንቺ ሲዘፍን ዋለ፡፡ እኔም ልዝፈንልሽ ብዬ ዘፈንኩላት፡፡ “አልሚ ምን እዳ ነው” እያልኩ ሳንጐራጉርላት በቃ ትምርክ (ተማረከች እንደ ማለት) አለችና ተግባብተን በእሷ ነው ሴት የጀመርኩት፡፡ዕ ን ቁ ፡ - ወደቀደመው የወሎ ላሊበላ ኪነት የመግባት

ምክንያትህ ምንድነው?መሀመድ፡- ቀደም ሲል ጀምሮ እዚህ ደሴ

ከተማ በየጠጅ ቤቱ እየዞሩ የሚያዘምሩ አሉ፡፡ ቅድም መድረክ ላይ ያየኸው ሸበቶው ሰውዬ አራጌ ይማም ይባላል፡፡ እሱ የማሪቱ ወንድም አሰፋ ለገሠና ራሷ ማሪቱ ለገሠ፣ እነ ዙሪያሽ ብዙ አዝማሪዎች ነበሩ እዚህ ከተማ ውስጥ፡፡ ከእነሱ ጋር ወደ 60 የምንሆን አዝማሪዎች ተሰብስበን የባህል ተጫዎቾች ማህበር መሰረትን፡፡ ስለ ኪነጥበብ ወሬ አልነበረም፡፡

ቆይታ

ድምፃዊ መሀመድ ይመር

25°”l 6— ¯Sƒ lØ` 119 ግንቦት 2006 ዓ.ም

“በቆሻሻ መኪና ሄደን መንግስቱ ኃ/ማርያም በሸለመን አውቶብስ ተመለስን”

በ1969 ካራማራ ተለቆ ጂጂጋ ላይ ትልቅ ባዛር ነበረ፡፡ እንጃ እንግዲህ ደርሰህበት ታውቀው እንደሆን?ዕንቁ፡- ታሪኩን አውቃለሁ፡፡መሀመድ፡- እዚያ እንድንገናኝ ተብለን ራሳችን ባሰፋነው የባህል ልብስ ተገኘን፡፡ ጥሩ ትርዒት አሳይተን ተመለስን፡፡ 1970 ላይ ወሎ ባህል አምባ በእርግጥ በፊት ይህ ስያሜ ሳይሰጠው አንዲት ጣሊያናዊት ሲኒማ ታሳይበት ነበረ፡፡ የባህል ቡድን ማህበሩ እንዳለ ወሎ ባህል ገባ፡፡ዕንቁ፡- የወሎ ላሊበላ የተባለው እሱ ነው?መሀመድ፡- መሰረቱ እሱ ነው፡፡ ከእሱ በኋላ ኪነት መቋቋም አለበት ተባለ፡፡ ናደው ዘካርያስ የሚባሉ የወሎ ክፍለ ሀገር አስተዳዳሪ ነበሩ፡፡ በጣም ግሩም የባህል ፍቅር የነበራቸው ናቸው፡፡ ቀለመ ወርቅ ሲመጣ ያገኘው በማህበር የተደራጀነውን እኛን ነው፡፡ እንዳለ ይዞን አዳራሽ ገባና ሸምገል ሸምገል ያሉትን ወደ ኋላ አድርጐ እኛን አቅፎ ያዘን፡፡ ኪነቱ በወጣቶች ተገነባ፡፡ ከመስከረም 2 መዘምራንነት ከመጡት ውስጥ ደግሞ እነ ዙሪያሽ አብዮ፤ ፀሐይ ካሳ፣ ዚነት ሙሀባ ተገኙ፡፡ ትልልቆቹም ግን አልተጣሉም፡፡ በጥበቃ፣ በጽዳት፣ በአስተዳደር እንደየ አቅማቸው ተመርጠዋል፡፡ዕንቁ፡- ደመወዝ ይቆረጥላችሁ ጀመር?መሀመድ፡- የለም፡፡ ከ1970 እስከ 1971 ለዓመት ያህል በነፃ ሰርተን ነው ከዚያ ወደ ደመወዝ የገባነው፡፡ዕንቁ፡- በኪነቱ ውስጥ አንተ በምን ተጫዋችነት ነው የተያዝከው?መሀመድ፡- በድምፃዊነት ነበር፡፡ በኋላ ላይ ሁለገብ የሚል ስያሜ ተሰጠን፡፡ ቴአትር እሰራ ነበር፡፡ በወንዶች በኩል መሪ ተወዛዋዥ ነበርኩ፡፡ዕንቁ፡- ምን ምን ቴአትሮች ላይ ተውነሃል?መሀመድ፡- ብዙ ነው፡፡ “ድላችን” የሚባል ታላቅ ቴአትር ላይ በመሪ ተዋናይነት ተጫውቻለሁ፡፡ ቴአትሩ የቀለመወርቅ ደበበ ነው፡፡ ፍሰሃ በላይ ይማም ታውቀዋለህ? ፍስሃ በላይ እንዴት ያለ ትንታግ ደራሲ ነበር፡፡ዕንቁ፡- አዎን በጣም አውቀዋለሁ፡፡መሀመድ፡- ምን ያደርጋል ሞት ክፉ ነው፡፡ ስንቱን ወሰደብን፡፡ የእሱን፤ “ስመኝ ስንታየሁ” “አልቃሽና ዘፋኝ” የሚሉ ቴአትሮች ላይ በከፍተኛ ደረጃ ሰርቻለሁ፡፡ዕንቁ፡- የት የት ዞራችሁ አሳያችሁ?መሀመድ፡- የት ነው ያልሄድነው እንጂ፡፡ ምን ቀረ ያልደረስንበት ቦታ፤ እግራችን ያልረገጠበት ቦታ ምን አለ? መላው ሀገሪቱ፣ 14ቱም ክ/ሀገር ዞረናል፡፡ አስመራን እስከ መጨረሻ፤ ቃሮራ፣ አፋቤት፣ አልጌና፣ ሳህል ጠረፍ ጫፍ ድረስ ሄደናል፡፡ አንድም ቦታ ላይቀር እስከ ቀበሌ ድረስ ወርደን ሰርተናል፡፡ ጦር ሜዳ ድረስ፣ ጦሩ ባለበት ሁሉ አሳይተናል፡፡ የምንበላው፣ የምንጠጣው እንደልብ በማይገኝበት ስፍራ፣ መኪናም ባይኖር በተገኘው ላይ ተጭነን እየሄድን ሰርተናል፡፡ ብዙ ክፉ ደግ አይተናል፡፡ዕንቁ፡- ቤተ-መንግሥት አሳይታችኋል?መሀመድ፡- እንዴ በደንብ ነዋ፡፡ ኮ/መንግሥቱ ፊት አሳይተናል፡፡ እንዲያውም አንድ ታሪክ ብነግርህ የኤፌዲሪ ምስረታ የሚባል ታላቅ ጉባዔ በአዲስ አበባ አልተካሔደም? ለዚያ መዝጊያ የ14ቱም ክፍለ ሀገር ኪነቶች ሦስት ሦስት ዘፈን እንዲያቀርቡ ታዞ ሁላችንም አዲስ አበባ ሄድን፡፡ ሙዚቃውን ያቀረብነው በብሔራዊ ቴአትር ነው፡፡ዕንቁ፡- ኮ/መንግሥቱም ብሔራዊ ቴአትር ሄደው አዩ?መሀመድ፡- አዎን እንጂ፡፡ ብሔራዊ ቴአትር ገብቶ ነው ያየው፡፡ እዚያ ልንሰራ ስንሔድ በቂ ዝግጅት አላደረግንም፡፡ ወሎ ባህል አምባ ሦስት ቀን እዚያው እያደርን ተለማምደን፡፡ “ፈጣን ነው ባቡሩ”ን አጠናን እና ወደ አዲስ አበባ ስንሄድ መኪና ስለሌለ ማዘጋጃ ቤት ቆሻሻ መጣያ መኪና ሰጥቶን ነው ከላይ ተጭነን የሔድነው፡፡ ሦስቱን ሙዚቃዎች እንደ ሰራን ግን መንግሥቱ ኃ/ማርያም በሥራችን በጣም ስለተደሰተ ሰዓት ተጨምሮልን ስድስት ሥራ አቀረብን፡፡ ከዚያም “ምንድነው ችግራችሁ?” ተብለን የምንመላለስበት መኪና ስንል አንበሳ አውቶቡስ ካስመጣቸው መሀል 61 ሰው ሊጭን አውቶቡስ በስጦታ ተሰጥቶን በእሱ ደሴ ገባን፡፡ በቆሻሻ መኪና ተጭነን ሄደን በተሸለምነው አውቶቡስ ተመለስን፡፡ዕንቁ፡- እስቲ ወሎ ላሊበላ ኪነት መቼ እና እንዴት እንደ ፈረሰ ደግሞ ንገረኝ?መሀመድ፡- 1983 ለውጥ እንደመጣ እኛ ሥራችንን ቀጠልን፡፡ አዳራሽ ውስጥ ልምምድ እያደረግን ማን እንደፃፈው የማይታወቅ አንድ ደብዳቤ ተለጥፎ ወጥታችሁ አንብቡ ተባልን፡፡ዕንቁ፡- ምን የሚል?መሀመድ፡- “ለወሎ ላሊበላ ኪነት ቡድን አባላት፡፡ ከሥራም ሆነ ከደመወዝ የታገዳችሁ በመሆኑ በየትውልድ ሀገራችሁ እንድትገቡ” የሚል ነው፡፡ አንብበን ወደሚመለከተው ክፍል ሄደን ጠየቅን፡፡ “ምን አጥፍተን ነው ይህ የሆነው?” ስንል “መታሰር ነበረባችሁ ግን የምትታሰሩ ሆናችሁ ስላላገኘናችሁ ነው እንጂ እስካሁን ወህኒ ነበራችሁ” የሚል መልስ ሲሰጠን በትክክልም ታስቦበት የተደረገ ነው ብለን በቃ በየቤታችን ገባን፡፡ ነገሩን ካለመገንዘብ አድርገውት ይሆናል የምንል ሰዎችም ነበርን፡፡ ኋላ ተስፋ ስንቆርጥ ሁላችንም በየሙያችን እንስራ እንጂ ሌላ መላ የለውም አልን፡፡ ዕንቁ፡- አንተ ከድምፃዊነትህ ሌላ ምን ሙያ ነበረህ?መሀመድ፡- ማሲንቆ እችላለሁ አሁንም፡፡ በዚያ ሰዓት ግን ሙዚቃ የሚባለው ነገር አስጠላኝ፡፡ አልሰራም ብዬ አሰመርኩበት፡፡ ሙዚቃ የደከምኩበት ስለነበረ፤ የተንገላታሁበት ስለነበረ፤ እንዲሁ እንደ አሮጌ ቁና በመወርወራችን አለቅስ ነበረ፡፡ ሙዚቃ የሞትኩበት ነበር ማለትም ይቻላል፡፡ በረሀ ላይ አሸዋ ተጭኖን ነው የኢትዮጵያን ባህል ያስተዋወቅነው፡፡ዕንቁ፡- ታዲያ ምን ሰራህ በወቅቱ?

መሀመድ፡- ቤቴ መንገድ ዳር ስለነበረ አፀዳድቼ ሻይ ቤት ከፈትኩባት፡፡ ከየበረሀው ስመጣ ያገኘኋትን እቋጥር ነበር፡፡ አጥፊ አልነበርኩም፡፡ዕንቁ፡- ሱሳ ሱስ ነገርስ የለብህም ሌላው ቢቀር መጠጥ?መሀመድ፡- ምንም የለብኝም፡፡ አልጠጣም፣ አላጨስም፣ አልቅምም፤ ከተበተንን በኋላ መቃም ጀመርኩ፤ ማጨስም ጀመርኩ፡፡ ሻይ ቤቴን ከፍቼ መስራት ጀምሬ 1992 ላይ ባለቤቴ ሞተችብኝ፡፡ ችግሩ ተደራረበኝ፡፡ዕንቁ፡- ስንት ልጆች ነው የወለዳችሁት?መሀመድ፡- ሁለት ልጆች አሉን፡፡ እሷ ስትሞት ልጆቹ የሁለትና የሦስት ዓመት እድሜ ነው ያላቸው፡፡ እነሱን ይዤ ብቻዬን ልጆቹን ማሳደግ ጀመርኩ፡፡ ቤቱ ተሟሙቆ ጥሩ ሥራ እየተሰራ እያለ ላሊበላ ከማገኘው በላይ ብር አገኝ ነበር፡፡ ብዙዎቹ ወዳድቀዋል፡፡ ማሪቱ ወደ አዲስ አበባ ሄደች፡፡ ብዙዎቹም ሞቱ፡፡ዕንቁ፡- ታመው ነው?መሀመድ፡- በብስጭትና በኑሮ ጉዳት ነው እንጂ፡፡ ለሀገራቸው የበረሀ አውሬ ሳይፈሩ፣ በቆሻሻ መኪና እየተጫኑ እምቢ ላይሉ፣ በውሀጥም እየተቃጠሉ ለሀገሬ ስለሆነ ይሁን ብለው ስንት ስቃይ ያዩ ኪነቶች፤ በእጅ በተፃፈ ብጣሽ ወረቀት ከሥራና ከደመወዝ ታግዳችኋል ሲባል የሚመጣውን ስቃይ፣ ተስፋ መቁረጥ፣ ብስጭቱን አስበው፡፡ ልጅ የወለዱ አሉ፡፡ እኔ እንኳን ያኔ አልወለድኩም፡፡ በነገራችን ላይ እንዲህ እንዳንተ ከሥሩ ጀምሮ የሚጠይቅ ሲመጣ ይቺን ወረቀት ማን ጽፏት እንደተበተንን የሚናገር ጠፋ፡፡ እኔ ነኝ የሚል አልነበረም፡፡ እውነት ለመናገር ደሞ የምንሰራው ፖለቲካ ሳይሆን የሀገር ባህልን ማንፀባረቅ ነው፡፡ ፖለቲካም ቢኖር ደግሞ በዚያ በመንግስቱ ዘመን ሥራ ተብለህ እምቢኝ ብትል የሚመጣው ምንድነው? ይሔ ተግምት ውስጥ መግባት ነበረበት፡፡ ቀድሞ ብዙ ሕይወት አልፎ ተገናኘን አላልኩህም? ስንት ችግር ነበር፤ በእኔም በሌላውም የደረሰ፡፡ ስንት የወሎ ላሊበላ ኪነት አባላት (ትክዝ ብሎ) ቀና ሳይሉ በዚየው የተደፉ፤ ስንት የሀገር ባለውለታዎች፡፡ የፈጣሪ ነገር ሆኖ እኔና ጥቂቶች አለን”፡ ተመስገን እንጂ ሌላ ምን ይባላል?ዕንቁ፡- ከመከም ግጥምና ዜማው የማን ነው?መሀመድ፡- የራሴ ነው፡፡ ብዙ ግጥምና ዜማ አለኝ፡፡ ሌላው ደሞ ብዙ ችግር ያልኩህ ከ1992-1994 ለ2 ዓመት ያህል ታመምኩ፡፡ 9 ወር ሆስፒታል ተኝቼ ነበር፡፡ ብቻ አንድ አራት ዓመት ይሆናል፤ በጠቅላላው የታመምኩት፡፡ዕንቁ፡- የአዕምሮ ጭንቀት ነበር ያመመህ?መሀመድ፡- በኋላ እንደተነገረኝ ጭንቀት ነበር፡፡ ሳንባዬን ታምሜም 120 መርፌ ወስጃለሁ፡፡ ሻይ ቤቷን እየሰራሁም የቋጠርኩት ስለነበረችኝ በእሷ ነው የታከምኩት፡፡ዕንቁ፡- ልጆቼን አሳደኩ ስትል እንጀራ ገዝተህም አስጋግረህም ታመጣለህ? ወሎ ደሞ ቸር ነው ፍቅር አይቸግረውም፡፡ ወጡን ምኑን እንዴት ታደርገዋለህ?መሀመድ፡- ራሴ እሰራለሁ፡፡ ልጆቼ አይደሉ? እነሱን ለማሳደግ የማልሰራው ምንም የለም፡፡ ተመስገን ነው፡፡ እነሱም አደጉልኝ፤ እኔም ኖርኩ፡፡ ደግሞ የወንድሞቼ ልጆች የማሳድጋቸው ስለነበሩ እኔ ስታመም ልጆቹን እነሱ ያዙልኝ፡፡ዕንቁ፡- ባለቤትህ ካረፈች በኋላ አላገባህም?መሀመድ፡- አ…ይ በጭራሽ፡፡ እስታሁን በሀሳቤም አልመጣ፡፡ዕንቁ፡- ለምን?መሀመድ፡- ምን መሰለህ? ተባለቤቴ ጋር 25 ዓመት ኖረን ነው ሞት የወሰደብኝ፡፡ ጥሩ ኑሮ ደስ የሚል ሕይወት አሳልፈናል፡፡ ፍቅር ነበረን፤ ተከባብረን ነው፡፡ ያንን ጊዜ መቼም አገኘዋለሁ ብዬ አላምንም፡፡ ደሞ ብዙ ባልና ሚስቶች ወልድውና ንብረት አፍርተው በፍርድ ቤት ሲጨቃጨቁ ነው የማያቸው፡፡ እነሱን ሳይ ካሁን በኋላ የማላውቃትን ሴት ከማገባ የበፊቱን ጥሩ ጊዜየን ደስታ ያጋኘሁበትን ትዳሬን እንዲሁ እያሰብኩት ብኖር ይሻለኛል እላለሁ፡፡ዕንቁ፡- ትናንት ማታ (ቃለ መጠይቁ ከተደረገበት ዕለት) እዚህ አልማ አዳራሽ ሥራችሁን ስታቀርቡ ሳይ “ከመከም” የሚለው ዘፈንህን በበፊት ለዛና ውበቱ አንድም ገርገጭ ሳያደርግህ ነበር የምታቀርበው፡፡ ዘፈኑ ከተሰራ ከ 33ዓመት በላይ ሆኖታል፡፡ ይህ ዘፈን ሲሰራ የተወለዱ ልጆች አድገው ሙዚቃ ጀምረው፤ ዝነኛ ሆነው፤ ሀብትም አፍርተው መልሰው ከሙዚቃው ወርደዋል፡፡ ያንን ዘፈናቸውን እንኳ ደግመው መዝፈን አይችሉም፡፡ አንተ ግን እዚያው ስፍራ ላይ አለህ፡፡ ምሥጢሩ ምንድነው?መሀመድ፡- የሚያስገርመው ይሔ ነው፡፡ ደግሞ ኪነቱ ከፈረሰ በኋላ 20 ዓመት ገደማ አልዘፍንም ነበር፡፡ አንዳንድ ጊዜ ለሠርግ ኮንትራት ይጠሩኛል፡፡ ከዚያ ውጭ አልዘፍንም፡፡ ኑሮዬ እንጂ ድምፄ አልወደቀም፡፡ዕንቁ፡- በአዲስ መልክ የተቋቋመው ወሎ ላሊበላ ኪነት ከተመሠረተ 1ዓመቱ ነው፡፡ እንዴት ጠሩህ?መሀመድ፡- ትፈለጋህ አሉኝና መጣሁ፡፡ አሁን በደመወዝ ነው የምሰራው፡፡ ሻይ ቤቷም እንደ ነገሩ ትሰራለች፡፡ አሰልጣኛችን ዳምጤ (ባቢ) ቅድም እዚያ መድረክ ፊት ያየኸው …እሱ ከእናት ከአባት ይበልጣል፡፡እውቀቱም፣ መልካምነቱም የተሟላ ወንድማችን ነው፡፡ዕንቁ፡- አንተ ከመከምን ስትሰራ ካልተወለዱ ልጆች ጋር ነው አሁን አብረህ የምትሰራው፡፡ ምን ትመክራቸዋለህ ለልጆቹ?መሀመድ፡- ከሁሉ በላይ ዲሲፒሊን ነው፡፡ ደሞ ሱሰኛና አባካኝ እንዳይሆኑ እነግራቸዋለሁ፡፡ እኔ ገንዘብ ስለያዝኩ ነው ታምሜ የዳንኩት፡፡ ከሁሉም በላይ ደግሞ ዳምጤ አለ የቡድኑ መሪ፡፡ እሱ ይመክራቸዋል፡፡ዕንቁ፡- ባሳለፍከው የጥበብና የሕይወት ዘመን ውስጥ “እንዲህ ባደረኩ ኖሮ” ብለህ የሚቆጭህ አለ? ወይም ባላደረኩት የምትለው?መሀመድ፡- አይ አይ የለም፡፡ የሚቆጨኝም የምፀፀትበትም ነገር የለም፡፡ ያለፈው ተመልሶ አይመጣም፡፡

ቆይታ

26 °”l 6— ¯Sƒ lØ` 119 ግንቦት 2006 ዓ.ም

ፍቃዱ ልመንህ

ከአራት ቀናት በኋላ፤ ወደ ሥልጣን የመጣበትን የሃያ ሦስተኛ ዓመት የሚያከብረው የኢሕአዴግ መንግሥት፤ ካለፉት ሥርዓቶች ጋር ተነጻጽሮ፤ “ይሄንን ከውኗል፣ ይሄኛውን ጭራሽ ተረት እስኪመስል ድረስ አስረስቶታል፣ ይሄኛው ደግሞ በመንግስት ልዩ ቁጥጥር ውስጥ እንዲወድቅ አድርጓል ወ.ዘ.ተ.” እያልን፤ እንደ ዜጋ የምንተነትናቸውና የምንተቻቸው ተግባራት እንደሚኖሩት እሙን ነው፡፡ ምንጊዜም ቢሆን፤ የመንግሥትና የዜጎች ተዋስዖ፤ ከዚህ የተለየ መልክ ይኖረዋል ተብሎ የሚጠበቅ አይመስለኝም፡፡ በተለይ እንደ ኢሕአዴግ ከሁለት አሥርት ዓመታት በላይ እየዘለቀ ላለ ሥርዓት፤ ይህ ዓይነቱ የዜጎች ትችትና ትንተና፤ ከምንምና ከማንም በላይ፤ ተገቢ፣ ጤናማና ወሳኝ ይመስለኛል፡፡ የዕይታ ጥልቀቱና የእውነታ ምርኮዛው ላይ ጥያቄ ይኖረው ይሆናል እንጂ፤ ሥርዓቱም ይህንን ዓይነቱን የዜጎች በጎ ሥርዓታዊ ምልከታ የሚጠላው አይመስለኝም፡፡ ከጠላውም “ጨው ለራስህ ስትል ጣፍጥ፤” ነው እንጂ ሌላ ምንም ሊባል አይቻልም፡፡

ብዙውን ጊዜ፤ ሥርዓቱን ፊት ለፊት ለመውቀስም ሆነ ለማወደስ ወይም ለትችት ባህላችን ቅርብ የሆኑት ጉዳዮች፤ “በፖለቲካ ምኅዳሩ ሥፋትና ጥበት”፣ “በሰብዓዊ መብት አያያዙ”፣ “በፍትሕ ሥርዓቱ አተገባበር”፣ “በምጣኔ ሀብት ውጥኑ” እና በመሳሰሉት ላይ ያተኮሩ ናቸው፡፡ የፖለቲካዊ ትችት ወጋችን፤ ሥርዓቶቻችን በሥነ-ጥበብ ዙሪያ ምን እንደሚያስቡ የምንገመግምበት የተዋስዖ አቅጣጫ የፈጠረልን አይመስለኝም፡፡ ማንኛውም የሀገራችንን ሁኔታ ከሥርዓቱ ይዞታ አንጻር የሚተች ተቋም ወይም ግለሰብ፤ የትንታኔ ምህዋሮቹ፤ ቀደም ሲል በዘረዘርኳቸው የትኩረት ‘ዒላማዎች’ ላይ በመሆኑ፤ ዛሬ እኔ ድንገት ተነስቼ፤ “የሥርዓቱ ሥነ-ጥበባዊ ፍልስፍናና ይዞታም ይፈተሸልኝ፤” ብል ያልተለመደ ጥያቄ ነውና ብዙዎችን ግር ማሰኘቱ አይቀርም፡፡ ከረር አድርጎ የተናደደብኝ ካለም፤ “ሥነ-ጥበብን ከፈጠራው እስከ ክወናው ጠቢቡ ይጨነቅበት እንጂ፤ መንግሥትን ደግሞ ምን ያገባዋል?” ብሎ ሊሞግተኝ ይችላል፡፡ የዛሬ ሦስት ዓመት ከቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ጋር የሥነ-ጥበብ ባለሙያዎች ውይይት ባደረጉበት ጊዜ፤ የገጠመውም ይህንን የመሰለ ሁኔታ ነበር፡፡ መድረኩ በአፈጻጸሙ ዘብረቅረቅ ብሎ ስለነበር ለበርካታ ሽሙጦች በር የከፈተ እንደነበር ማንም አይዘነጋውም፡፡ ከተሰሙት ሽሙጦች አንዱ፤ “አርቲስቶቹ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ‘ዜማና ግጥም ይድረሱልን፤’ ሊሏቸው ምንም አልቀራቸው!” የሚል ነበር፡፡ የሥነ-ጥበብ ጉዳይ፤ ፖለቲካዊ ሥርዓቱ እንደሰጠው የትኩረት ደረጃ፤ ሊያብብ ወይም ሊከስም እንደሚችል ለማስረዳት መሞከር፤ ከተለመደው ፖለቲካዊ ወጋችን እጅግ የወጣና አለቦታው የቀረበ ሙግት ስለሚመስል፤ እንዲህ ላለ ሽሙጥ ቢዳርግ ብዙም አይደንቅም፡፡

ሥን

ሠርፀ ፍሬ ስብሐት

አንዳንድ ጊዜ መንግሥት ራሱም ትልልቅ ሀገራዊ ዕቅዶቹን፤ በአምስትና በአሥር ዓመት ርዕይ ደረጃ ተልሞ በሚያቀርብባቸው ሰነዶች ላይ ሳይቀር የሥነ-ጥበብ ጉዳይ ተረስቶ ይገኛል፡፡ የኢሕአዴግ መንግሥት የአምስት ዓመታት መርኀ-ግብሩ ምን ሊሆን እንደሆነ ባሳወቀበትና፤ ተደጋግሞ በመሰበኩ ከትዝታችን ባልወጣው “የትራንስፎርሜሽን እቅዱ” ውስጥ ተዘንግተው ከነበሩት ነገሮች አንዱ፤ የሥነ-ጥበብ ጉዳይ እንደሆነ ምን ያህሎቻችን እናውቃለን? የኢሕአዴግ አንዳንድ ባለሥልጣናት በማይክዱትና በአንዳንድ መድረኮች ላይ ባመኑት ልክ፤ የሥነ-ጥበብ ጉዳይ ፍፁም የተዘነጋና ከሃያ ዓመታት በላይ ከመንግሥት ሥርዓታዊ ዕቅዶች ውጪ እንደነበረስ ምን ያህሎቻችን እናውቃለን? መንግሥት ስለ ሥነ-ጥበብ ያሰበበት ጊዜና “የታላቁ የሕዳሴ ግድብ” ሥራ የተጀመረበት ጊዜ፤ በዕድሜ አኩዮች መሆናቸውን ብነግርዎስ ያምኑኝ ይሆን?

ቀደም ሲል በርካታ አንጋፋ የሥነ-ጥበብ ባለሙያዎች፤ “የኢሕአዴግ መንግስት የዛሬ ሃያ ሦስት ዓመት ግንቦት 20 ቀን 1983 ዓ.ም. ሥልጣን ከያዘበት ጊዜ ጀምሮ፤ ተመልሰው እንዳያንሰራሩ አድርጎ ያፈረሳቸውን” የሥነ-ጥበብ ተቋማት(በተለይም የወታደራዊ የሙዚቃ ክፍሎቹን) በመጥቀስ፤ ጠንካራ ትችታቸውን ሲሰነዝሩ መቆየታቸው ይታወሳል፡፡ እነዚህ ትችቶችና “የሀገሪቱ አዳዲስ የልማት አቅዶች” ተደማምረው፤ መንግሥት ከሥነ-ጥበብ ጋር የነበረውን ‘ሆድና ጀርባ’ የመሰለ ግንኙነት ለማስተካከል አስቦ ይመስላል፤ በቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር በአቶ መለስ ዜናዊ (ነፍስ ኄር) አማካኝነት፤ ከሥነ-ጥበብ ባለሙያዎች ጋር፤ ግንቦት 29 ቀን 2003 ዓ.ም. (ዘንድሮ ላይ ሆነን ስንቆጥረው፤ ጊዜውን “ለሃያ ሦስት፤ ሦሰት ጉዳይ” እለዋለሁ፤) “የሥነ-ጥበቡን ችግሮች ለመቅረፍ” ሲባል በተያዘ አጀንዳ፤ ከሥርዓቱ የሃያ ዓመታት ዕድሜ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ውይይት አካሂዶ ነበር፡፡

የመድረኩ ሁኔታና የሥነ-ጥበብ ባለሙያው የጥያቄ አቀራረብ የበርካቶችን የትችት ትኩረት የሳበ ስለነበር፤ በጠቅላይ ሚኒስትሩ በኩል የቀረቡት የመንግስት ሥነ-ጥበባዊ አስተሳሰቦች ከቶውንም ለውይይት አልቀረቡም ነበር፡፡ ጥያቄውን ያቀረቡትም ሆኑ “ደንቀፍቀፍ” አሉ የተባሉት፤ ሀገር ያወቃቸው የሥነ-ጥበብ ባለሙዎች ስለነበሩ፤ የትችት ዱላው እነሱ ላይ አረፈ እንጂ፤ “መንግሥት ስለ ሥነ-ጥበብ ምን አለ?” አልተባለም፡፡ ምንም ያልተተቸው የመንግሥት ሥነ-ጥበባዊ ግንዛቤና የወደፊት ዕቅድ (እስካሁን ተግባራዊ ሆኖ ያላየነው) ምን ይመስል እንደነበር ብንመረምረው ብዬ አሰብኩና፤ የአቶ መለስን የመድረክ ንግግር ለጽሑፍ ሥርዓት እንዲሆን ከማድረግ በቀር፤ ያለ ምንም መቆራረጥና አርትዖት፤ እንደሚከተው ላቀርብላችሁ ወደድኩ፡፡ የግንቦት 20ው ድል ሃያ ሦስተኛ ዓመት በመንግሥት ደረጃ በሚከበርበት ሰሙን፤ ይሄንን ብዙም ያልተባለለትን የኢሕአዴግ የሥነ-ጥበብ “አስተምኅሮ”፤ በሕልፈት ካጣናቸው የሥርዓቱ ዋና ሰው ከአቶ መለስ ዜናዊ ጋር ለማስታወስ፤ “የግንቦቱ ዐውድ” የሚፈቅድልን ይመስለኛል፡፡ በአካዳሚያው በኩል ስለ ሥነ-ጥበብ በሚቀርበው ተዋስዖ ላይ የሚያተኩረውን ቀጣዩን መጣጥፌን ለማቅረብ፤ የዚህ መድረክ ምልከታ ጥሩ መሠረት የሚሆነኝ ይመስለኛል፡፡

I.በአጠቃላይ የመንግሥትን የሥነ-ጥበብ ግንዛቤና የሚከተለውን ፍልስፍና በተመለከተ አቶ መለስ የሰጡት ማብራሪያ፤

“በተደጋጋሚ እንዳነሳችሁት፤ “ሥነ-ጥበብ” ካለ መንግሥት ድጋፍ የሚጓዝበት ርቀት የራሱ ውሱንነት አለው፡፡ ከታሪካዊ አመጣጡም ሆነ፤ አሁን በ19ኛው፤ በ20ኛውና በ21ኛው ክፍለ ዘመን የሚታየው እውነታ ይኸንኑ የሚያመለክት ነው፡፡ ስለዚህ ‘መንግሥት ሥነ-ጥበብን መደገፍ አለበት’ የሚለው ላይ እንስማማለን፡፡ የሚደግፍበት መንገድ የተለያየ ሊሆን ይችላል፡፡

አንደኛ፡- ሥነ-ጥበብ ሊያብብ የሚችልበት ምቹ መደላድል (enabling environment) መፍጠር ይቻላል፡፡ ይህ አንዱ ትልቁ ጉዳይ

ሥነ-ጥበብ…ለሃያ ሦስት…ሦስት ጉዳይ፤

አንደኛ፡- ከፍተኛ የሆነ የሰለጠነ የሰው ኃይል ችግር ስላለ፤ ጥራቱን የጠበቀ

ትምህርት ለመሥጠት፤ በቂ መምህራን ላይኖሩን ይችላሉ፡፡ ሁለተኛ፡- በተለይ

በአንዳንዶቹ መስኮች፤ ተጨማሪ ኢንቨስትመንት ይጠይቃል፡፡ ስለዚህ የገንዘብ

አቅሙም ሊገድበን ይችላል፡፡ እነዚህን ገደቦች ግምት ውስጥ ከተን ባለን

የሰው ኃይል፣ ባሉን የትምህርት ተቋማት ጀምረን፤ ደረጃ በደረጃ ጥራቱን

የተጠበቀ አድማሳዊ ይዘት ያለው፣ በአድማሳዊ ይዘቱ ላይ ስፔሽያላይዝድ

የሆነ ትምህርት በየደረጃው የሚሰጥበትና ዓለም አቀፋዊ ደረጃውን የጠበቀ

ትምህርት እንዲሆን (አገራዊ ባህርዩ እንደተጠበቀ ሆኖ፤) መሥራት የምንችል

ይመስለኛል፡፡ መጀመሪያ ባሉን ተቋማት መጀመር እንችላለን

27°”l 6— ¯Sƒ lØ` 119 ግንቦት 2006 ዓ.ም

ሥን

ነው፡፡ ሁለተኛው፡- የተመቻቸ ሁኔታ ከመፍጠርም ባሻገር በአጋርነት መሰለፍ ይችላል፡፡ ሊሰለፍም ይገባዋል፡፡ መንግሥት እንደ መንግሥት፣ (በመንግሥት ውስጥ ያሉ ግለሰቦች የሚኖራቸው አመለካከትና ፍላጎት እንደተጠበቀ ሆኖ)፤ ሥነ-ጥበብ ላይ ያለው ጥቅም (interest) ግልጽ ነው፡፡ መንግሥት እንደ መንግሥት ከሥነ-ጥበብ የሚጠብቀው ነገር አለ፡፡ ከሥነ-ጥበብ የሚጠብቀው ነገር፤ ለሁለንተናዊ ልማት፤ ማለትም ለሰው ኃይል ልማት ባለው አስተዋጽዖው ነው፡፡ የሰው ኃይል ልማት ማለት፤ በአስተሳሰቡ፣ በሥነ-ምግባሩ፣ በእውቀቱ፣ በክህሎቱ የዳበረ ግለሰብ እና የዳበረ ሕብረተሰብ መፍጠር ማለት ነው፡፡ ከሁሉም ነገር በላይ፤ ልማት ማለት የሰው ጭንቅላት ልማት ማለት ነው፡፡ መንገድ አይደለም፣ ግድብ አይደለም፡፡ እነዚህ የጭንቅላት ውጤቶች ናቸው፡፡ ስለዚህ የመጨረሻው የልማት መመዘኛውና ውጤቱ የሰው ኃይል ልማት ነው፡፡ በዚህ በሰው ኃይል ልማት ውስጥ ሥነ-ጥበብ የማይተካ ሚና አለው፡፡ ‘መንግስት በአጋርነት መሥራትና ማስቻያ ሁኔታዎችን መፍጠር አለበት’ ሲባል፤ ጥቅም ስላለው ነው፡፡ የሰው ኃይል ልማት አጀንዳውን ለማሳካት ፍላጎት ስላለውም ነው፡፡

በሌላ በኩል፤ የሥነ-ጥበብ ሰዎች ከዚህ ከጋራ ዓላማ ባሻገር ሥነ-ጥበብን የሚመለከቱበት የራሳቸው ምክንያት አላቸው፡፡ ራሳቸውን የሚገልጹበት ነው፡፡ (የself- expression ወይም የself- fulfillment ጉዳይ ሊሆን ይችላል)፡፡ የገቢ ምንጭም ሊሆን ይችላል፡፡ የተለያዩ ጥቅሞች ይኖሯቸዋል፡፡ ነገር ግን አሁን እያነሳን ያለነው፤ መንግሥት እንደ መንግሥት ወይም እንደ ኢንስቲትዩሽን፤ ከሥነ-ጥበብ ሰዎች ጋር የሚኖረው መደጋገፍና አጋርነት፤ በአንድ የጋራ ዓላማና በሚያስማማን የጋራ ጉዳይ ላይ ነው፡፡

የሥነ-ጥበብ መስፋፋት የዜጎቻችንን የአመለካከት አድማስ በማስፋፋት የሰው ኃይል ልማትን ያፋጥናል፡፡ ስለዚህም የመጨረሻውን ልማታችንን ያረጋግጥልናል፡፡ በዚህ ደረጃ አብረን መሥራት ይኖርብናል፡፡ አብረን ሥንሠራ መንግሥት የማስቻያውን ሁኔታ ሊፈጥር ይችላል፡፡ መንግሥት በተወሰነ ደረጃ አጋር ሆኖ ዘርፉን ማገዝ ይኖርበታል፤ የሚለው ላይ እንስማማለን፡፡ መንግሥት ተክቶ ሊሠራ አይችልም፣ መንግስት ተክቶ ለመሥራትም መሞከር የለበትም፣ መንግሥት ተቆጣጣሪ አይደለም፣ መንግሥት በፊት የነበረው የአርት ፔትሮን ተብሎ የሚታወቀው ዓይነት ድጋፍ ሊሰጥ አይችልም፡፡ በፊት የነበረው “Patron Relationship” በይዘቱ ኢ- ዴሞክራሲያዊ ገጽታዎች አሉት፡፡ ያንን ማስተናገድ መንግሥት በአሁኑ ሰዓት አይችልም፡፡”

II.የሥነ-ጥበብ ትምህርትን በሥርዓተ ትምህርት ውስጥ በስፋት ለሁሉም ዜጎች፣ በልዩ ትኩረት ደግሞ ለሥነ-ጥበቡ ሰው

ስለመስጠት ተጠይቀው የሰጡት ምላሽ፤“የሥነ-ጥበብ ትምህርት መሠረታዊ የሚሆነው፤ ሥነ-ጥበብ የሥነ-

ጥበብ ሰዎች የሚያመርቱት ቢሆንም፤ ተጠቃሚው ሕብረተሰቡ በጠቅላላ ነው፡፡ ሕብረተሰቡ ተጠቃሚ ካልሆነ ሥነ-ጥበብ ሊያድግ አይችልም፡፡ ስለዚህ ሕብረተሰቡ በሥነ-ጥበብ ውጤቶች ለመጠቀም፣ የሥነ-ጥበብ ውጤቶችን ለማድነቅ፣ በሥነ-ጥበብ ውጤቶች ለመደሰት እንዲችል፤ መሠረታዊ የሥነ-ጥበብ እውቀት እንዲገበይ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ ከዚያም ባሻገር፤ በእነዚህ የሥነ-ጥበብ አስተሳሰቦች የአመለካከት አድማሱን እንዲሰፋ ለማድረግ፤ ዜጋውን በጠቅላላ በመነሻ ደረጃ የሚያገለግል የሥነ-ጥበብ ትምህርት ያስፈልገዋል፡፡ የሥነ-ጥበብ ትምህርት ለሁሉም ዜጋ ሲዳረስ፤ ከዚያ ውስጥ ተሰጥዖ ያላቸው ሰዎች ጥቂቶቹ በዘርፉ ይገፉበታል፡፡ ሌላው (የተቀረው ብዙኃኑ) የአምራቾቹ ተጠቃሚ ይሆናል፡፡ በአቅሙ በልኩ ደግሞ የአስተሳሰብ አድማሱን ለማስፋትም ይችላል፡፡ ስለዚህ ልዩ የሥነ-ጥበብ ትምህርትን ጨምሮ፤ አድማሳዊ (Universal) የሆነ ትምህርት፤ የሥነ-ጥበብ ልማት መሠረቱ ነው፡፡ በአቅማችን ልንሠራቸው ከምንችል፣ ብንሠራቸው መሠረታዊ ለውጥ ሊያመጡ ከሚችሉ ሥራዎች አንዱ፣

በእኔ ግምት ዋናው፤ በሥነ-ጥበብ ትምህርት ዙሪያ ሊሠራ የሚገባው ጉዳይ ነው፡፡

ይህንን ነገር አስፋፍተን እንሥራ ካልን ችግሮች ይኖራሉ፡፡ አንደኛ፡- ከፍተኛ የሆነ የሰለጠነ የሰው ኃይል ችግር ስላለ፤ ጥራቱን የጠበቀ ትምህርት ለመሥጠት፤ በቂ መምህራን ላይኖሩን ይችላሉ፡፡ ሁለተኛ፡- በተለይ በአንዳንዶቹ መስኮች፤ ተጨማሪ ኢንቨስትመንት ይጠይቃል፡፡ ስለዚህ የገንዘብ አቅሙም ሊገድበን ይችላል፡፡ እነዚህን ገደቦች ግምት ውስጥ ከተን ባለን የሰው ኃይል፣ ባሉን የትምህርት ተቋማት ጀምረን፤ ደረጃ በደረጃ ጥራቱን የተጠበቀ አድማሳዊ ይዘት ያለው፣ በአድማሳዊ ይዘቱ ላይ ስፔሽያላይዝድ የሆነ ትምህርት በየደረጃው የሚሰጥበትና ዓለም አቀፋዊ ደረጃውን የጠበቀ ትምህርት እንዲሆን (አገራዊ ባህርዩ እንደተጠበቀ ሆኖ፤) መሥራት የምንችል ይመስለኛል፡፡ መጀመሪያ ባሉን ተቋማት መጀመር እንችላለን፡፡ እነዚህን በይበልጥ ውጤታማ በሆነ መልኩ በመጠቀም ልንጀምር እንችላለን፡፡

በዩኒቨርሲቲ ደረጃ 70 በመቶ በተፈጥሮ ሳይንስ ትምህርቶች ላይ እንዲያተኩሩ አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡ ይህ ማለት ግን፤ ለሥነ-ጥበብ ወይም “ለሊብራል አርትስ” ትኩረት አልተሰጠም ማለት አይደለም፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ በተፈጥሮ ሳይንስና በምህንድስና ዘርፍ የሚሰማሩ ሰዎች ከሥነ-ጥበብ ትምህርት ነጻ እንዲሆኑ የተቀመጠ አቅጣጫ የለም፡፡ ልዩ ትኩረታቸው (ስፔሽያላይዜሽናቸው) በሳይንስ፣ በኢንጂነሪንግ እንዲሆኑ ነው እንጂ ምንም የሥነ-ጥበብ እውቀትና ግንዛቤ እንዳይኖራቸው የሚል ሀሳብም የለም፡፡ እንዲያውም በዚህ ጉዳይ የተወሰነ እውቀት ወይም ግንዛቤ እንዲኖራቸው ማድረግ ጥሩ መሐንዲስ፣ ጥሩ ሳይንቲስት ለመሆንም ተጨማሪ ግብአት ነው፡፡ ስለዚህ ሳይንስ፣ ሂሳብ ወይም ምህንድስና ብቻ አይደለም እንዲማሩ የሚፈለገው፡፡ ከአንደኛ ደረጃ ትምህርት ጀምሮ፤ ሁለተኛ ደረጃም ሆነ ዩኒቨርሲቲም ቢሆን በሳይንስ ውስጥ ስፔሽያላይዝ የሚያደርገው ሰው የተወሰኑ የሥነ-ጥበብ ኮርሶችምንም አብሮ የሚወስድባቸው ዕድሎችም አሉ፡፡ ከዚያም በላይ 30 በመቶ የሚሆነው፣ ከሳይንስና ከምህንድስና ውጪ ነው ያለው፡፡ ስለዚህ ለሊብራል አርትስ የተሰጠው ትኩረት አነስተኛ በመሆኑ አይደለም፡፡ የግንዛቤ ጉዳይ ነው የሚመስለኝ፡፡ እንደሚታወቀው፤ መሐንዲስ ላይ የጥራቱን ያህል የቁጥር ብዛት ያስፈልጋል፡፡ ሥነ-ጥበብ ላይ፤ ከቁጥሩ በላይ የሰውየው ጥራት ትልቅ ቦታኖረዋል፡፡ ስለዚህ 30 በመቶ አንሷል በሚል ሊወሰድ አይችልም፡፡”

III.የአእምሯዊ ንብረት መብት አከባበርና የፍትሕ ሥርዓቱን ግንዛቤ በተመለከተ ለቀረቡት ጥያቄዎች የሰጡት ምላሽ፤ “የሰው ኃይሉን ከፈጠርን በኋላ፤ የሥነ-ጥበብ ሰውን እየፈጠርን

ባለንበት ሁኔታ፤ የሥነ-ጥበቡ ሰው ተግቶ ሊቀጥል የሚችለው፤ በሥራ ውጤቱ ተጠቃሚ የሆነ እንደሆነ ብቻ ነው፡፡ ስለዚህም የአእምሯዊ ንብረት ጉዳይ በጣም መሠረታዊ ይሆናል፡፡ ከዚያም ባሻገር ባለን አቅም ለመፈጸም አስቸጋሪም ላይሆን ይችላል፡፡ ጥረት ይጠይቃል፤ ነገር ግን ከፍተኛ ገንዘብ የሚጠይቅ አይደለም፡፡ ‘የሕግ ክፍተት አለ’ ተብሏል፡፡ በአዋጁ ላይ ተመሥርቶ መውጣት የነበረባቸው ደምቦችና መመሪዎች ወ.ዘ.ተ. ተሟልተው አልወጡም፤ ይህ ትክክል ነው፡፡ ‘በሕጉ መሠረት ወደ ተግባር በሚገባበት ወቅት፤ በፖሊስ፣ በዐቃቤ-ሕግ፣ በዳኞች አካባቢ የአተረጓጎምና የክትትል ችግር አለ’ ተብሏል፡፡ የዳኞችን ጉዳይ እዚህ መድረክ ላይ መወያየት አንችልም፡፡ በፖሊስና በዐቃቤ-ሕግ ላይ ግን መወያየት እንችላለን፡፡ እዚህ አካባቢ ችግር የለም አልልም፡፡ ችግር የለም የማልልበት ምክንያት፤ በሌሎች መንግሥት ሊያስፈጽማቸው በሚፈልጋቸው ሕጎች ላይም ተመሳሳይ ችግር ስላለ ነው፡፡ ኮንትሮባንዲስቶች ከአንድ ዓመት እስከ አስከ አስራ አምስት ዓመት በሚለያይ ርቀት እየተቀጡ ነው፡፡ በሙስና ወንጀል የተከሰሱ

ሥነ-ጥበብ…ለሃያ ሦስት…ሦስት ጉዳይ፤

ወደ ገጽ 34 ዞሯል

28 °”l 6— ¯Sƒ lØ` 119 ግንቦት 2006 ዓ.ም

ታሪክ

ወደ ምዕራብ አድማስ በምታሽቆለቁለው ፀሐይ ዙሪያ ባልተለመደ ቀይ ቀለበት ተከባለች፡፡ የዚያን ቀን አመሻሽ በመላው ኢትዮጵያ ሁሉም ወደየእምነቱ በማምራት ፈጣሪውን ምህረትን እንዲልክ መማፀኑን ተያይዞታል፡፡ በአገሪቱ ያንዣበበው አደጋ በማንኛውም ሰዓት ሁሉም ነገር ሊቆጣጠሩት ወደማይቻል አስጊ ደረጃ በመሸጋገር ላይ ይገኝ ነበር፡፡

የአዲስ አበባ ሒልተን ሆቴል ግን እንደ ወትሮው በተገልጋዮች እንደ ተሞላ ነው፡፡ በርካታ ኢትዮጵያውያንና የተለያዩ ሀገር ዜጐች ሞልተውታል፡፡ ገሚሶቹ በሆቴሉ መዋኛ ስፍራ ራሳቸውን ዘና ለማድረግ ይዋኛሉ፡፡ ገሚሶቹ ደግሞ በሆቴሉ አዳራሽ በየሕንፃዎቹ በረንዳ ላይ በየመናፈሻዎቹ ውስጥ ቁጭ ብለው መጠጥ እየጠጡ ምግብ እየቀማመሱ ይውካካሉ፡፡

በሆቴሉ አንደኛው ሕንፃ ላይ ከሚገኝ የእንግዶች ማረፊያ ክፍሎች በአንዱ ውስጥ ለሕሙማን ማጓጓዣ ጋሪ መሳይ ስትሬቸር ከፊት ለፊታቸው ሰድረው፤ በቀጣይ ስለሚያደርጉት እርምጃ የሚመካከሩ፤ ከአጠገባቸው ካለው ጠረጴዛ ላይ እያገባደዱ ያሉትን የሼቫዝሮጋል ውስኪ ጠርሙስ ወዲያው ወዲያው ወደየብርጭቋቸው የሚያንቆረቁሩ ሁለት ደልደል ያለ ተክለ ሰውነት ያላቸው ሰዎች ከባለረዥም መስታወት መስኰት በኩል ወደ ሆቴሉ መዋኛ ዞር እያሉ እያዩ ያወራሉ፡፡

የእስራኤል ኢታማዦር ሹም ኢሁድ ባራክ “ወደ አዲስ አበባ የምታመሩት ወታደራዊ ግዳጅ ልትወጡ ነው፡፡ ይህ ወታደራዊ ግዳጅ ከዚህ ቀደሞቹ ግዳጆች የሚለየው ግዳጁ እንዲከናወን የተፈለገው ያለምንም የተኩስ ልውውጥ ነው፡፡ ተኩስ የምትከፍቱበት አጋጣሚ ቢኖር እንኳን ለኅልውናችሁ አደገኛ የሆነ ክስተት ካጋጣማችሁ ብቻ ነው፡፡” ሲሉ መመሪያ የሰጠዋቸው ሁለት መቶ የእስራኤል ልዩ ኮማንዶዎች ናቸው፡፡

ለአስራ ሰባት ዓመታት የኢትዮጵያ ርዕሰ ብሔር የነበሩት ኮሎኔል መንግስቱ ኃይለማርያም ከሶስት ቀናት በፊት ነበር ሀገራቸውን ለቀው በስደት ወደ ዙምባብዌ ያመሩት፡፡ የእስራኤል መንግስት በኢትዮጵያ ያሉ ቤተ-እስራኤላውያን ወደ እስራኤል ለማጓጓዝ የሚያደርገውን እንቅስቃሴ ለማሳካት ከኢትዮጵያ መንግስት በኩል ሆኖ ጉልህ ድርሻ የሚጫወተው የሚስጥራዊው ካሣ ከበደ ተሰማ ቡድን፤ መንግስቱ ኃይለማርያም ሀገር ጥሎ መሰደዱ ከተሰማ በኋላ የሚጫወተውን ሚና ለማሳደግ ካሳ ከበደ ቢሞክርም ተጠባባቂ ፕሬዚዳንቱ ጄኔራል ተስፋዬ ገ/ኪዳንና የደኅንነት ሚኒስትሩ ተስፋዬ ወልደስላሴ ቦታ ስላልሰጡትና ከቁብ ስላልቆጠሩት ተበሳጭቶ ውስኪ ሲጨልጥ አድሮ እንደሰከረ ከእስራኤላውያን ዲፕሎማቶች ጋራ ተገናኝቶ ለመወያየት ያደረገው ጥረት ሁሉም ነገር ከእጁ እንደወጣ ያሳወቀበት ነበር፡፡

መንግስቱ ኃ/ማርያም ቤተ እስራኤላውያን ወደ እስራኤል እንዲጓጓዙ ለመፍቀድ ለኢትዮጵያ መንግስት የመቶ ሚሊዮን ዶላር ክፍያ እንዲከፍል

እንደሚፈልግ በካሣ ከበደ በኩል ጠይቆ ነበር፡፡ ከብዙ ድርድር በኋላ በ35ሚሊዮን ዶላር ክፍያ እንዲሰጠው በመስማማቱ እስራኤሎች ይህንኑ ገንዘብ ወደ ኢትዮጵያ መንግስት የባንክ አካውንት ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት ባለሥልጣናት 35 ሚሊዮን ዶላር ኒውዮርክ በሚገኘው የኢትዮጵያ መንግስት አካውንት ውስጥ እንዲያስገቡ እስራኤላውያኑን እየወተወቱ ነበር፡፡ ካሣ ከበደ የኢትዮጵያ መንግስትን የባንክ አካውንት ነው ብሎ ያመጣው ቁጥር የተሳሳተ ሌላ መሆኑን ያረጋገጡት እስራኤሎች ትክክለኛው የኢትዮጵያ መንግስትን የባንክ አካውንት ለማግኘት ባደረጉት ጥረት ወሌ ቸኮል ለአሜሪካ ኤምባሲ ጉዳይ ፈፃሚ በስልክ ትክክለኛውን ቁጥር በመስጠቱ ችግሩ ለጊዜው ተቃሏል፡፡

ካሣ ከበደ ግን እኔ የሰጣኋችሁ ቁጥር ልክ አይደለም እያላችሁ ነው፡፡ መቼም በዓለም ታዋቂ ሰላዮች አሏችሁ አይደል? እነርሱን ለምንድን ነው የማትጠይቋቸው? እያለ ማፌዙን ቀጥሏል፡፡ የእስራኤል አምባሣደር አሸር ነአም የባንክ አካውንት ቁጥሩን ኒውዮርክ ወደሚገኘው የአይሁዳዊያን ኤጄንሲ በመደወል አስተላልፈዋል፡፡

ይህ እየሆነ እያለ ግን በእስራኤል ኤምባሲ ቅጥር ግቢና በቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ቤተ-እስራኤላውያንን ወደ እስራኤል ለማጓጓዝ የተዘረጋው የሰማይ የባቡር መስመር ሥራ ጀምሮ ነበር፡፡ እስከዚያች የአርብ ምሽት ድረስ ስምንት ሺህ ኢትዮጵያውያን ወደ እስራኤል ተጓጉዘው ሶስት ሺህ ቤተ-እስራኤላውያን ደሞ ለመጓዝ ተራቸውን እየጠበቁ ነበር፡፡

በቦሌ አየር ማረፊያ በእስራኤል አየር ኃይል አብራሪዎች የሚያበሯቸው አውሮኘላኖች እየተከታተሉ በአየር ማረፊያው ሜዳ ላይ ያርፋሉ፡፡ ስምንት ግዙፍ ሔርኩለስ አውሮፕላኖች የአየር ማሪፊያውን የአውሮፕላን መንደርደሪያ ስፍራ ጭምር አርፈው መንገደኞችን እያሳፈሩ ነው፡፡

በጨለማው ሰማይ ላይ የወጣችው ጨረቃ እንደቀኑ ፀሐይ ሁሉ ደም በሚመስል የደመና ቀለበት ታጅባ ነበር የምትታየው፡፡ ከአየር ማሪፊያው መንገደኞችን አሣፍረው ወደ እስራኤል የሚያቀኑ አውሮፕላኖችና ከእስራኤል ወደ አዲስ አበባ ያመሩ አውሮፕላን ክንፎቻቸው ሊነካኩ የተቀራረቡ ያህል ተጠጋግተው ሲተላለፉ ማየት እጅግ አስገራሚ ትዕይንት ነበር፡፡ በዚያ ምሽት እንኳን 28 ሔርኩለስ አውሮፕላኖች ተጓዦችን አሳፍረው ወደ እስራኤል በረዋል፡፡፡፡

የአሜሪካ ኤምባሲ ጉዳይ ፈፃሚ ቦብ ሆዴክ ወደ አዲስ አበባ ለመግባት ዙሪያውን የከበቡት አማፅያን አስቀድመው የላኩት ቃኚ ኃይል በቅርብ ርቀት በቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ እየተካሄደ ያለውን ሚስጥራዊ ተልዕኮን እየተመለከቱና እየተቆጣጠሩ መሆኑን መረጃ ማግኘቱን ለእስራኤላውያኑ ወዳጆቹ ነገራቸው፡፡

ኦፕሬሽን ሰለሞን የተባለው ከ14ሺህ በላይ ቤተ-እስራኤላዉያን ኢትዮጵያውያን ወደ እስራኤል የማጓጓዙ ተልዕኮ ለ36 ሰዓታት ቀጥሎ ሊጠናቀቅ ነው፡፡ በአዲስ አበባ ሒልተን ሆቴል ሆነው ኦፕሬሺኑን ሲከታተሉ የነበሩት ኡሪ ሉባራኑ፣

አሊ አባባሪ፣ ዲቮንያጋር፣ ሚኪ ፍልድ፣ ማን ፍራይድ፣ ማን በርግማን፣ የእስራኤሉ አምባሣደር አሸር ነአም፣ ጄኔራል ሚሞን፣ የአሜሪካ ኤምባሲ ጉዳይ ፈፃሚው ቦብ ሆዴክ ወደ ቦሌ አየር ማረፊያ በሁለት መኪናዎች ታጭቀው ጉዞ ከመጀመራቸው በፊት ሁለት የዲፕሎማቲክ ኮር ታርጋ የለጠፉ መኪናዎች ላይ ሁለት የሒልተን ሆቴል ብርድ ልብስ የለበሱ (ከስትሬቸሩ ጋራ በሚገባ የታሰሩ) ሕሙማን የተኙበት ቃፊላዎችን (የህመምተኛ ማመላለሻ አልጋ በተለምዶ ስትሬቸር የሚባለውን) ጫኑ፡፡

ሕሙማኑን የያዙ ቃሬዛዎች ወደ መኪናዎች ሲጫኑ ሲያዩ የነበሩ የሞሳድ አባላት ኡሪ ሉባራኒንን “እንዲህ በጠና ከታመሙ ለምን እናጓጉዛቸዋለን? ከሕመምቸው ድነው ሲያገግሙ ቢመጡ አይሻልምን?” ብለው ጠይቀውት ነበር፡፡ ኡሪ ሉባራኒ በግድየለሽነት “እዚህ ልተዋቸው መጨከን የሚያስችል አንጀትም ሆነ ወኔ የለኝም፡፡ ማን ያውቃል ከሞት ተርፈው እነርሱም በቃሬዛ እስራኤል ገባን ብለው ሊያወሩ ይችላሉ፡፡ በከፍተኛ ጥበቃና ጥንቃቄ እንዲጓጓዙ ማድረግ ብቻ ነው የእናንተ ኃላፊነት” አላቸው ቃሬዛዎቹን አተኩሮ እያየ፡፡

ቅዳሜ ሊነጋጋ ሲል የመጨረሻዎቹ ሔርኩለስ ሲ 130 አውሮፕላኖች ከቦሌ አየር ማረፊያ ሜዳ ላይ ቆመው ለኦፕሬሽኑ የመሳካት በአዲስ አበባ ለቀናት በግዳጅ ላይ የነበሩ የእስራኤል አየር ኃይል ባልደረቦችን፣ ወታደሮችን፣ ልዩ ኃይል አባላት በመሉ ወደ እስራኤል ለማጓጓዝ እያሳፈሩ ነው፡፡

አሜሪካውያኑን ዲፕሎማቶች እና እስራኤላውያኑን ባለስልጣናት ያያዙ ሁለቱን ሕሙማን የተኙባቸው ቃሬዛዎች የጫኑ አራት መኪናዎች ተከታትለው አየር ማረፊያው ሜዳ ላይ ደረሱ፡፡ እዚያው ቦሌ አየር ማሪፊያ በእስራኤላውያን ጥገና የተደረገለት አውሮፕላን ላይ ሁለቱ ከስትሬቸሩ ጋር የታሰሩ ሕሙማን እንዲጭን ለአብራሪው ኡሪ ላቦራኒ አዘዘ፡፡

በእርግጥም በትዕዛዙ መሠረት በሁለት ቃሬዛ የተኙት ኢትዮጵያውያን ሕሙማን በእስራኤል የፀጥታ ሠራተኞች በጥንቃቄ በተቀነባበረ መንግድ ወደ አውሮፕላኑ ተሣፍረው አውሮፕላኑ ለመብረር ማኮብኮብ ሲጀምር እስራኤላውያኑ ዲፕሎማቶች ተያይተው ተሣሣቁ፡፡

ሁለቱ ሕሙማን በሒልተን ሆቴል አንድ ክፍል ውስጥ አቅላቸውን እስኪስቱ ድረስ ሺቫክ ሬጋል ውስኪ ሲጨልጡ ያነጉት አምባሣደር ካሣ ከበደና የሀገር ውስጥ ደህንነት ምክትል ሚኒስትሩ ኮሎኔል መርሻ ቀፀላ ነበሩ፡፡

ኦፕሬሽን ሰለሞን ከተጀመረበት ከ34 ሰዓታት በኋላ ከአዲስ አበባ የመጨረሻው አውሮፕላን ቦይንግ 757 አውሮፕላን ወደ ቴልአቪቭ ማምራቱን ያረጋገጡት ዲፕሎማቶች ልክ እንደ ሕፃን ልጅ በደስታ ሰክረው ሲዘሉ “አሣካነው አሣካነው” እያሉ በደስታ ሲተቃቀፉ በምስራቁ አድማስ ላይ የንጋት ፀሐይ ለመውጣት ጐህ እየቀደደች ነበር፡፡ ከንጋቱ 11፡30 ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ላይ የተፈፀመ ታሪካዊ ክስተት ነበር፡፡ ከዛሬ 8400 ቀናት በፊት እነሆ እንደ አዲስ በታሪክ አምድ ላይ ዘከርነው፡፡

ከዛሬ 8400 ቀናት በፊት...

ብሩክ መኮንን

29°”l 6— ¯Sƒ lØ` 119 ግንቦት 2006 ዓ.ም

ዋናው ጤና

ከመቶ በላይ የሚሆኑ የመገጣጠሚያ ህመሞች አሉ፡፡ የመገጣጠሚያ ህመም ሲባል በጥቅሉ በሰውነት የሚገኙ ትናንሽም ይሁኑ ትላልቅ መገጣጠሚያዎችን ያማከለ በዋነኝነት እብጠትና የመጠዝጠዝ ስሜት የሚያስከትል ህመም ሲሆን መጠኑ፣ ዓይነቱን ተከትሎ የሚከሰተው ችግር ይለያይ እንጂ ልጅ አዋቂ ሳይል በማንኛውም እድሜ ክልል ፆታና ዘርን ሳይለይ ይከሰታል፡፡ በመሰረቱ የመገጣጠሚያ ህመም ሲባል የግድ መነሻው መገጣጠሚያ ነው ማለት አይደለም፡፡ ማንኛውም በሽታ የመገጣጠሚያ ህመም አያስከትልም ባይባልም አብዛኛውን ጊዜ የአጥንት፣ የጡንቻና የመገጣጠሚያ ህመሞች መገለጫ ሊባል ግን ይችላል፡፡ ቀላል ወይም ከባድ የጤና ችግር የሚያስከትሉ የመገጣጠሚያ ህመሞች ባጀማመራቸው ተመሳሳይ ምልክቶችን ሊያሳዩ ይችላሉ፡፡ ለመገጣጠሚያ ህመሞች የሚደረግ ምርመራ አፋጣኝ ምላሽ ማግኘት የሚገባቸውን፤ በጊዜ ሂደት ሊፈቱ ከሚችሉት ለመለየት ያስችላል፡፡

የመገጣጠሚያ ህመም መነሻ ምንድን? የሚለውን ለመመለስ ሙሉ የጤና ምርመራ ማድረግ አስፈላጊነቱ አያጠራጥርም፡፡ ለባለሙያ በሚነገረው የምልክት ይዘት፣ ሂደት፣ ተከታታይ ስሜቶች ወዘተርፈ የህመሙን ክብደት መገመት ይቻላል፡፡ ቀጥሎ ሊከወን የሚገባውንም የአካል ምርመራ እንዲሁም ትኩረት የሚሹ የላቦራቶሪና ተያያዥ ምርመራዎች ለመምረጥ አቅጣጫ መተለሚያ ነው፡፡

አንድ ታማሚ ሊገልፃቸው የሚገቡ ምልክቶች የሚከተሉትን ሊያካትት ይገባል፡፡

የመገጣጠሚያ አካላት አካባቢ ያሉ ማናቸውም የህመም ስሜቶችን (ለምሳሌ መጠዝጠዝ)፣ የታመሙ መገጣጠሚያዎች ቁጥር፣ የህመሙ አስከፊነት፣ድግግሞሽ፣ ቆይታ እንድሁም ጠቅላላ ይዘት (አልፎም መዘርዘር የሚገባቸው እውነታዎች ቢኖሩትም) መገለፅ ይገባዋል፡፡ የእብጠቱም እንዲሁ ሂደቱ፣ ቆይታው፣ የእብጠቱ ሙቀት፣ እብጠቱን የሸፈነው ቆዳ መልክ ለውጥና የመሳሰሉትም በተመሳሳይ መገለፅ ይኖርባቸዋል፡፡

• ህመም፣ እብጠት በዚህም የተነሳ መገጣጠሚያን ማጠፍ መዘርጋት አለመቻል፡፡ እብጠትን እንጂ የህመምን ልክ በወጉ ለመግለፅ ሊከብድ ይችላል፡፡ የሆነው ሆኖ አስቀድሜ ከጠቀስኳቸው ምልክቶች ባሻገር የታመመው መገጣጠሚያ፣ የህመሙ ክስተት ፍጥነት እንዲሁም አጠቃላይ ህመሙን የሚያባብሱ ወይም የሚያሻሽሉ ነገሮች መገለፅ ይገባቸዋል፡፡

• የህመሙን የክፋት ልክ በወጉ መግለፅ ከባድ እንደሆነ ግልፅ ነው፡፡ ህፃናት (በተለይ በለጋ ዕድሜ ያሉት ህመማቸውን በወጉ መግለፅ ስለማይችሉ) የበለጠ ሊያስቸግር ይችላል፡፡ ለማንኛውም የመገጣጠሚያ ህመሙ ምንም ዓይነት ስራ ለማከናወን የማይቻልበትን ሁኔታ ካስከተለ አሳሳቢ እንደሆነ መረዳቱ ፈጣን ምላሽም እንደሚያሻው አያጠራጥርም፡፡ ለእንዲህ ዓይነት

መገጣጠሚያዎች እብጠት፣ ቃንዣ፣ ማጠፍ፣ መዘርጋት አለመቻል መነሻዎች አጥንት ወይም መገጣጠሚያ በባክቴሪያ ወይም በካንሰር ህመም ተይዞ መሆኑን ጠቋሚዎች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ መስራት አለመቻል፣ የታመመውን የአካል ክፍል ጨርሶውኑ አለማንቀሳቀስ፣ እንቅልፍን ማጣጣም አለመቻል ወዘተ የህመሙን ክብደት ማሳያዎች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡

• የታመሙትን መገጣጠሚያዎች ማወቅ (የትኛውን መገጣጠሚያ ነው የሚያመኝ? ምን ያህል መገጣጠሚያዎችን?….ለሚሉት ጥያቄዎች መልስ ማግኘት፣ በቀጣይነት መወሰድ የሚገባቸውን ምርመራዎች እንዲሁም ሊሰጥ የሚገባውን ህክምና ፈር ማስያዣ ናቸው፡፡ አብዛኛውን ጊዜ አንድ መገጣጠሚያ ሲታመም ፈጣን ምላሽ ሊያሻው እንደሚችል መገመት መልካም ነው፡፡

• የህመሙ ተከታታይነት፣ አልፎ አልፎ መከሰት፤ አለበለዚያም ካንድ መገጣጠሚያ ወደ ሌላ መዛወሩ መነሻ ምክንያቱን ጠቋሚ በመሆኑ አፋጣኝ ህክምና ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ ያመላክታል፡፡ ለምሳሌ ፋታ የማይሰጥ፤ ተከታታይ ህመም ባንፃሩ አሳሳቢ መነሻዎች አሉት፡፡ ህመሙ የሚባባስበት ሰዓትም እንዲሁ የህመሙን አስከፊነት መገመቻ ነው፡፡ አንዳንድ የመገጣጠሚያ ህመሞች ጧት ሰላም ሆነው ቀኑ እየገፋ ሲሄድ የሚባባሱ አሉ፡፡ ሌሎች ደግሞ በተቃራኒው ቀን ምንም ሳይሉ ሌሊት አያስተኙም፡፡ ህመሙ የተስተዋለበት ፍጥነትም በተመሳሳይ ሁኔታ ለህመሙ መሰጠት የሚገባውን ትኩረት ያመላክታል፡፡

የሚያባብሱ ሁኔታዎች በእርግጥ በአካል ላይ የሚደርሱ አደጋዎች

የመገጣጠሚያ ህመሞች ብቸኛ መነሻ ምክንያቶች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ በሌላ የሰውነት ክፍል ላይ የተስተዋሉ ቁስለቶች፣ ህመሞች ወዘተ፤ ከህመሙ በፊት የነበረው ያጠቃላይ የሰውነት እንቅስቃሴ ይሄን ለመገመት ያስችላል፡፡ በዘር የሚተላለፉ የመገጣጠሚያ ህመም መነሻዎችም እንዳሉ ማስታወሱ የግድ ነው፡፡ በእህት፣ ወንድም ብቻ ሳይሆን በብዙ ዘመዶችም የሚስተዋል ሊሆን ይችላል፡፡

አጠቃላይ የአካል ክፍሎችን መመርመር ለምሳሌ ትኩሳት፣ ቁስለት፣ የቆዳ ሽፍታ፣ የሰውነት ክብደት መቀነስ፣ የሆድ ቁርጠት፣ እንዲሁም የዓይን ህመም መኖር አለመኖሩን መርምሮ ማወቅ መሰረታዊ ነው፡፡ መገጣጠሚያዎች ሊያብጡ፣ሊቀሉ፣ ሲነኩ የህመም ስሜት ሊያስከትሉ ይችላሉ፡፡ የመገጣጠሚያ አካላቱ ከትንሽ ጀምሮ አስከ መካከለኛ ከዚያም ሲብስ ባጠቃላይ አካላትን ማንቀሳቀስ ሊያቅት ይችላል፡፡

የመገጣጠሚያ እብጠት ወይም ህመም መነሻ የሆኑ ብዙ የሰውነት ክፍል ህመሞች ስላሉ አነዚህን የአካል ክፍሎች ያማከለ ምርመራ ማድረግ ይገባል፡፡ (ለምሳሌ የሳንባ፣ የልብ፣ የአንጀት ወዘተ)

በባለሙያ በሚታዘዙ ምርመራዎች በመገጣጠሚያዎች ላይ የደረሰውን ጉዳት መጠን ወይም ዓይነት ማወቅ ይቻላል፡፡ የራጅ ምርመራ እንዲሁም የተለያዩ የደም ምርመራዎች ሊደረጉ ይችላሉ፡፡ ከመገጣጠሚያ እባጮችም ፈሳሽ ተቀድቶ

የላቦራቶሪ ምርመራ ይደረጋል፡፡

ህክምና እንግዲህ ታማሚው በሚናገረው፣ በአካላዊም

ይሁን በሌላ ምርመራ በሚገኘው ውጤት መሰረት የተለያዩ ህክምናዎች ሊደረጉ ይችላሉ፡፡ በመሰረቱ ለመገጣጠሚያ ህመም የሚደረግ ህክምና ዓላማዎች ህመም(ቃንዣ) ለመቀነስ፣ የተጎዳውን መገጣጠሚያ ስራ ለማሻሻል እንዲሁም የመገጣጠሚያ ህመም የጎንዮሽ ጉዳትን ለመቀነስ ነው፡፡ በአብዛኛው (ለማስታወስ ያህል ከመቶ ያላነሱ ምክንያቶች ስላሉት) መነሻ ምክንያቱን ማዳን ይከብዳል፡፡

ያኗኗር ዘይቤን ማሻሻል /መለወጥ/ እርስዎ መገጣጠሚያዎትን ካመመዎት

ከህክምና ባለሙያ ጋር በሚያደርጉት ግንኙነት አጥንት እና መገጣጠሚያ ላይ የደረሰውን ጉዳት ለማስታገስ ብዙ መፍትሄዎችን መውሰድ ይችላሉ፡፡ ለማጠፍ ለመዘርጋት ያስቸገረ መገጣጠሚያን፣የህመም እና የድካም ስሜቱን ለማስታገስ የጡንቻን እና የአጥንትን ጥንካሬ ለማሻሻል እንቅስቃሴ ትልቅ አስተዋፅኦ ያበረክታል፡፡ ሊደረግ የሚገባው የእንቅስቃሴ ዓይነት እንደ ተጎዳው አካል ይለያያል፡፡ ለማጠፍ ለመዘርጋት፣ለጥንካሬ ወዘተ፡፡ ሙቀት ወይም ቅዝቃዜ እንደ ህመሙ አይነት ሊመከሩ የሚችሉበት አጋጣሚም ይኖራል፡፡ በቂ እንቅልፍ ማግኘት፣ የተጎዳውን መገጣጠሚያ አንድ ቦታ ላይ ለረዥም ጊዜ አለማቆየት ፣ በእንቅስቃሴም ይሁን በሌላ አጋጣሚ የተጎዳው መገጣጠሚያ ላይ ጫና አለማሳረፍ እና የመሳሰሉት ለህመሙ በጊዜ መሻር የራሳቸውን አስተዋፅኦ ያበረክታሉ፡፡

ለፈውስ ወይም ጊዜያዊ መፍትሄ ለመስጠት የተለያዩ መድሃኒቶች ይታዘዛሉ፡፡ አንድ ጊዜ የታዘዙ መድሃኒቶችን በራስ ተነሳሽነት እየገዙ ከታቀደለት ጊዜ በላይ መጠቀም መጥፎ ነው፡፡ እንደሚታወቀውም ያለ ባለሙያ ትዕዛዝ የሚወሰዱ ብዙ የዕውነትም ጥሩ መድሃኒቶች ቢኖሩም ሊያስከትሏቸው የሚችሏቸው ብዙ ችግሮች ስላሉ ከመውሰድዎ በፊት ባለሙያ ያማክሩ፡፡ ለማንኛውም መድሃኒትዎትን ባለሙያ ባዘዘው ልክ ላዘዘው የጊዜ ርዝማኔ ያህል ብቻ ይውሰዱ፡፡ ሌሎች የሚወስዷቸው መድሃኒቶችም ካሉ ለሚከታተለዎት ባለሙያ ያሳውቁ፡፡ ለአንዳንድ የመገጣጠሚያ ህመሞች ሌሎች የህክምና አማራጮች ካልተሳኩ ቀዶ ጥገና የሚያስፈልግበት አጋጣሚም አለ ፡፡

በመገጣጠሚያዎች ላይ የሚደርስ ጉዳትን ለመቀነስ ሳይዘገዩ ምርመራ ማድረግ ተገቢ ነው፡፡ ስለሆነም ከሚከተሉት የህመም ስሜቶች አንዱን ካስተዋሉ ባለሙያ ከማማከር አይቦዝኑ፡-

• የመገጣጠሚያ ህመምዎ ከ3 ቀናት በላይ ከቆየብዎት

• ሊገልፁት የማይችሉት ህመም ካለብዎት• መገጣጠሚያዎትን ማንቀሳቀስ ካልቻሉ• የታመመው መገጣጠሚያ ቆዳ ከቀላ፣

ከሞቀ • ትኩሳት ካለብዎት እንዲሁም ክብደት

ከቀነሱ ወዘተርፈ ባለሙያ ያማክሩ፡፡በቸር እንሰንብት!!!

lUL†¨< ›v} (T@Ç=. Ê¡}`)

የመገጣጠሚያ አካላት የህመም ስሜቶችና መፍትሄዎቻቸው

30 °”l 6— ¯Sƒ lØ` 119 ግንቦት 2006 ዓ.ም

መንገድ

ዕንቁ፡- ሠርተው ያደረጉትን ስታይ ምን ይሰማሃል? ከትንሽ ተነስተው … የሚባል ነገር አለና፡፡

ጌታቸው፡- ይባላል፡፡ እኔም እሰማለሁ፡፡ እኔ ግን ጥሎ ማለፉን አልቻልኩበትም፡፡ ሆኖም ይኸው እየሰራሁ አለሁ፡፡

ዕንቁ፡- በዚህ ስራ ላይ ከ 20 ዓመት በላይ ቆይተሃል፡፡ መቼም እንደፀጉር አስተካካይ ብዙ ሰው የሚገጥመው የለምና ከአንዳንድ ሰው ምን ትታዘባለህ?

ጌታቸው፡- አንዳንዱ ጺሙን ብቻ ተስተካክሎ መሄድ ይፈልጋል፡፡ እኛ ጠጉሩንም ነካካ..ነካ..ነካ አድርገን ትንሽ የክፍያ ጭማሪ እንዲያደርግ እንሰራለን፡፡

ዕንቁ፡- ዋጋቸው ተወደደ ብሎ የሚነጫነጭ አይገጥምም?

ጌታቸው፡- ሊኖር ይችላል፡፡ እኛ ግን ለክፍያ አትከራከሩ እንላቸዋለን፡፡ ከጠበቁት በላይ ቆንጆ ሆነው ባማሩ ግዜ የተሻለ እንደሚከፍሉ እናውቃለን፡፡ በርግጥ እንዲህ አሳምረህ ቲፕ የምታገኘው በስንት አንዴ ነው፡፡

ዕንቁ፡- አስቸጋሪ የምትለው የደንበኛ አይነት አለ መቼም?

ጌታቸው፡- ያው የህፃናት ረባሾች አሉ፡፡ ይቅበጠበጣሉ፣ የሚያለቅሱም ያጋጥማሉ፡፡ በዘዴ እያባበልክ ታስተካክላቸዋለህ፡፡ መቼም ምን ታረገዋለህ ተረት ምናምንም መዋራት ግድ የሚልበት ጊዜ አለ፡፡ ለማባበል ማለት ነው፡፡

ዕንቁ፡- በአዋቂ በኩልስ አበላሸብኝ ብሎ የሚሳደብ ይኖራል?

ጌታቸው፡- አንድ ሰውዬ ፀጉሩን ቆርጬ ከጨረስኩ በኋላ ድንገት ማሸኑ ዘሎ ከኋላው መላጣ አደረገው፡፡ ይኼኔም በኋላው መስተዋት አየና ከወንበሩ ብድግ አለ፡፡ "አ…..ብ….ሽር ይሄ እንደገና ይስተካከላል” ብዬ በዩቲ ቁርጥ አድርጌ ላክሁት…

ዕንቁ፡- ይሄ የስራ ላይ ያጋጣሚ ችግር መሆኑ ነው፡፡ ችግሩን የምታልፍበት ዘዴም አሪፍ ነው ባክህ?

ጌታቸው፡- ሙያችን ዕኮ ነው፡፡ዕንቁ፡- ሙያችሁን የሚፈታተን ችግር የለም

ማለት ነዋ?ጌታቸው፡- እንዴ….! እንዴ….! አለ እንጅ

ለምሳሌ የመብራት ችግር ትልቅ ፈተና ነው፡፡ በምን ትመክተዋለህ፡፡ አቅም የለን ጀኔሬተር አንገዛ፤ እጅ ሰጥተን ቁጭ ነው፡፡

ዕንቁ፡- ቁጭ ብቻ?ጌታቸው፡- ያው ቁጭ ብለን መንግስትን

እናማርራለና፡፡ 21ዓመት እናለቅሳለን ያው የደሃ ለቅሶ፡፡

ዕንቁ፡- ከደንበኛስ ለምሳሌ የፀጉራቸው ዓይነት አስቸጋሪ የሆነ ሰዎች ይገጥማሉ?

ጌታቸው፡- ለስራ ሲሆን ሁሉም ይመቻል ባክህ፡፡ ፀጉሩ በዛ፣ አነሰ ሳይሆን እኛ የምንፈልግው መጥቶ ተስተካክሎ የሚከፍል ደንበኛ ነው፡፡

ዕንቁ፡- በአጠቃላይ ሳይህ ብዙ ችግር የሚገጥምህ ሰው አይደለህም ልበል?

ጌታቸው፡- ኸረ በጣም ብዙ ችግር አለ፡፡ ያሳለፍኩት ብዙ ውጣ ውረድ ቢከብድም በውስጣችን አፍነን ነው የምንኖረው፡፡ ገባህ? ፀጥ!

ዕንቁ፡- በወንዶች ፀጉር ቤት ዕኮ የመዋብያ ዕቃዎች ይሸጣሉ፡፡ አንተስ ለምን አታቀርብም?

“መብራት ባይኖርም የመብራት እከፍላለሁ”ጌታቸው አበራ

ጌታቸው፡- አቅርቤ ነበር፡፡ ገበያው ቀዝቃዛ ስለሆነ እራሴ ተጠቅሜ ጨረስኩት፡፡

ዕንቁ፡- ካፒታልህ እንዴት ነው፡፡ እንዲያው በምን ያህል መጠን ይለካል?

ጌታቸው፡- ወይ ካፒታል…!! (በረጅሙ እየተነፈሰ) ገንዘብ እንደሰማይ ርቆኝ ስለ ካፒታል ምናምን ትጠይቀናለህ ዛሬ የሰራኋትን ለዛሬ ውሎ ነው የማደርጋት፡፡ ከእጅ ወደ አፍ ነው፡፡ የልጆች አባት ነኝ፡፡ የመንግስት ግብር ከፋይ ነኝ፡፡ የመብራት ከፋይ ነኝ፡፡ መብራት ሲጠፋ ስራ አቆማለሁ፡፡ ወጭዬ ግን አይቀንስም፡፡ ልጆቼ መብራት ጠፍቷል ብለው ሳይበሉ አያድሩም፡፡ መንግስት መብራት ተቆራርጧል ብሎ ግብር አይምርህም፡፡ እንዴ….ምን ይላል?

ዕንቁ፡- ለካፒታል የምትሆንህ መቶ ምናምን ሺህ ብታገኝ ምን ይልሃል?

ጌታቸው፡- ምን ምን እንደሚለኝ ሲደርሰኝ ብነግርህ አይሻልም?

ዕንቁ፡- የስራና የወደፊት ዕቅድህስ?ጌታቸው፡- ነገርኩህ ዕኮ ገንዘብ ሳይኖርህ ማቀድ

ማለት መሳቀቅ ማለት ነው፡፡ ምናልባት ባታሳቅቀኝ?ዕንቁ፡- ተወው በቃ እሺጌታቸው፡- ችግር የለም ቀጥል፡፡ ግን ስለገንዘብና

ዕቅድ…ዕንቁ፡- መቼም ፀጉሩን አይቶ የሚደሰት

እንዳለ ሁሉ አንዳነዲ ሊበሳጭ ሊናደድ የሚችልበት አጋጣሚዋ አይጠፋም፡፡

ጌታቸው፡- ይናደዳ ታዲያ!! ዕድሉ ነው፡፡ ሰካራም ይመጣል፤ የተናደደ ይመጣል፤ የተደሰተም ይመጣል፡፡ ይሄ ቦታ ቀበሌው መዝናኛ ፊት ለፊት ስለሆነ አንዳንዱ ጠጥቶ ሹልክ ብሎ ይመጣል፡፡ እኔ ግን ሁሉንም እኩል የማሰተናግደው ለስራዬ ክፍያ እስካገኘሁ ድረስ ነው፡፡ ደግሞም የስራ ባህሪያችን ሆኖ ሁሉንም እንደ አመጣጡ ማስተናገድ አለብን ዕኮ፡፡ ሰውን እንደ አመጣጡ እና እንደ ፀባዩ ይዘህ ከመለስከው ነገ ደንበኛህ ይሆናል፡፡

ዕንቁ፡- ስራውን ስትጀምርና አሁን ከብዙ ጊዜ በኋላ ስታየው ምን ለውጥ አገኘህበት?

ጌታቸው፡- እንዴ አሁን ደህና ነኝ፡፡ ወንበሬን ለውጨዋለሁ ቢያንስ ቢያንስ፡፡ በፊቱ ዕኮ እንደ ኩሽኔታ የሚሽከረከር ወንበር ስለነበር ተደግፌው ነው የምቆርጥ የነበረው፡፡ እነዚያን ወንበሮች እኔና ደንበኞቼ አንረሳቸውም፡፡

ዕንቁ፡- ለስራህ መስተካከል ምንምን ትመኛለህ? ጌታቸው፡- ምኞት በለው …ምኞቴማ ለምሳሌ

ወንበሮቼ ሞደርን ቢሆኑ፣ አሪፍ ካፒታል ቢኖረኝ ኸረ በናትህ ብዙ ነገር አለ፡፡ እራስህን ከፍ ባለ ደረጃ ለማድረስና ስራህን ለማሳደግ የግድ ጥሩ ካፒታል ያስፈልጋል፡፡ ፈልግልኝ እስቲ….?

ዕንቁ፡- ኸረ ባክህ አንተው ራስህ በቂ ያለህ ይመስላል ለምሳሌ ጠጉር ቤትህ ውስጥ ቀኑን ሙሉ የማይዘጋው ቴሌቬዥን….

ጌታቸው፡- ፐ….! ዛሬ የትም ቦታ ብትሄድ ዲሽ አለ፤ ጣብያዎችን ይለዋውጣሉ እኔ ግን የለኝም፡፡ የኔ ምንም የሌለው ቤት ነው፡፡ አንዳንዱ ዕኮ የሻይና የቡና መስተንግዶ ሁሉ አለው እኔ ግን ብዙ ያልተሟላልኝ ነገር እያለ ስራዬን ስራ ብዬ ነው የተያያዝኩት፡፡ ወጭዬም ቅድም እንደነገርኩህ ነው፡፡ በቃ ዝም ብዬ ለመኖር ስል እሰራለሁ፡፡

ዕንቁ፡- ድሮ ጆሮዬን እንዳትቆርጥ እያሉ የሚሰጉ ደንበኞቼ ነበሩ አሉ?

ጌታቸው፡- አሉ እንጅ እኔ አስተካክየው እስከምጨርስ ድረስ ሁለቱንም ጆሮውን ለአስይዤው ያስተካከልኩት ሰው አለ፡፡ በበኩሌ ስራዬን ስለማውቅ እንዴት ጆሮ እቆርጣለሁ፡፡ የፈለገውን ያህል ከዓይኔን ብጨፍን እንኳ አልቆርጠውም፡፡

ዕንቁ፡- የፀጉር ስራ በተለይ ለደንበኛ የሚደረግ ጥንቃቄን ይጠይቃል፡፡ በተለይ በተለይ በንፅህና በኩል፡፡ አይደለም?

ጌታቸው፡- ታዲያ አታይም እንዴ? የእኔ ቤት ቆንጆ አይደለም? 1ኛ ደረኛ ነው ዕኮ! ይህ የውበት ሳሎን የፀጉር ማቃጠያ ማሽን አለኝ (ጨረር) የተሟላ ሆኖ የጐደለኝ ትንንሽ ነገሮች ናቸው፡፡

ዕንቁ፡- ትንንሽ ስትል? ጌታቸው፡- እጅግ በጣም ትንንሽ ግን እጅግ

በጣም ብዙ፡፡ ዕንቁ፡- እኒህ የጐደሉህን ነገሮች የሚረዳህ አካል

ቢኖርስ እንዴት ነው?ጌታቸው፡- በቃኝ ጨረስኩ፡፡ የሚረዳ አካል

ትለኛለህ እንዴ፡፡ ካለ ይርዳኝ እንዲረዳኝ ፈልጋሁ፡፡ ዕንቁ፡- ተበሳጨህ እንዴ?ጌታቸው፡- ታድያ ያዘጋጀከው ካፒታል ያለ

ይመስላል ዕኮ አጠያየቅህ፡፡ዕንቁ፡- በኑሮህ ደስተኛ ነህ ወይስ እንዴት ነው

ጌቾ?ጌታቸው፡- እየሰራሁ እያየኸኝ ነው አይደለም

እንዴ? እና እየሰራሁ እይለቃቀምኩ ነው ያለሁትና የምኖረው፡፡ ሌላ ገቢ የለኝም፡፡ የልጆቼን የቤቴን ወጭ ሸፍናለሁ፡፡ ምንም እንኳ ኑሮ የሊማሊሞ ዳገት ቢሆንብኝም፡፡

ዕንቁ፡- የሊማሊሞ ዳገት?ጌታቸው፡- አዎና ሁሉ ነገር ጨመረ ነው፡፡

ቀነሰ ሲባል ሰምተህ ታውቃለህ? በየሱቁ በየቀበሌው ጨመረ ጨመረ ሲሉ ኑሮ ይሰቀጥጥሃል፡፡ ሌላ ነገር ዕኮ አትሰማም ወደፊት በዚህ መልኩ መኖር የሚቻል አይመስለኝም፡፡

ዕንቁ፡- ጌች የውበት ሳሎን ምን ያህል ሰራተኞች አሉህ?

ጌታቸው፡- ለግዜው ሁለት ነን፡፡ ቅዳሜና እሁድ አብሮ የሚሰራ አንድ ወንድም አለኝ፡፡ በቃ ሙያውን ለማሳደግ አንዳንዶችን አቆራረጥ እያሳያሁ አግዛቸዋለሁ፡፡ ከዚህ የበለጠ ምን ያስፈልጋል?

ዕንቁ፡- የፀጉር መዋብያ የተባሉት እነ ጄል የተሰኙትን አትጠቀምም ልበል?

ጌታቸው፡- ሁሉም ነበረኝ፡፡ ማንንም ስለማይጠቅም ትቸዋለሁ፡፡ አንድ ግዜ ቀብተኸው በሌላ ቀን በነፃ ሊቀባ የሚፈልግ አለ፡፡ ታዲያ ይሄ አዋጭ ነው ወይ? ቢኖረኝም ትቼዋለሁ፡፡ እንኳንም ተውኩት፡፡ ምነው ለራስህ ፈልገህ ነው?

የአዲስ አበባ ነዋሪ ነው፡፡ በሩፋዔል አካባቢ ከ20 ዓመት በላይ ፀጉር ሲያስተካክል ቆይቷል፡፡ “ኑሮና ስራ እንዴት ነው?” ብለን ስንጠይቀው፤ “ከእጅ ወደ አፍ” ይለናል፡፡ ስለ ዕድገት ለማውራት በማይክሮ የመደራጀትን ሁኔታ ስናነሳለት "በኮሚቴ የተዋቀረ ስራ አይመቸኝም" አለ፡፡ "ተደራጅቼም አላውቅም፣

መደራጀትም አልወድም፣ ፍላጉቴም አይደለም፣ አዋጭም አይደለም…" ብሎ ቁርጥ ነገረን፡፡"እኛኮ ልናደራጅህ አልመጣንም” በሚለው ተግባብተን አብረን ቆየን

መታወቂያዬን ሳየውመታወቂያዬን ሳየው

31°”l 6— ¯Sƒ lØ` 119 ግንቦት 2006 ዓ.ም

ሰሎሞን ለማ ገመቹ

የብዕር አሳንሰር

ብቻዬን ሆኜ ቀበሌ የሰጠኝን የነዋሪነት መታወቂያ እመለከተዋለሁ፡፡ ልክ እንደ ሎሬት ጸጋዬ ገብረመድህን ቀዌሳ የግጥም ሰው ‹‹አጠንቅሬ አስተውለዋለሁ›› የማያውቀኝ የማላውቀው ይመስለኛል፡፡ ምንድነው ይህ የመታወቂያ ታሪክ ብዬ ራሴን እጠይቀዋለሁ፡፡ መልስ ሳጣለት ከአባቴ ጋር በጉዳዩ ዙሪያ ስብሰባ እቀመጣለሁ፡፡ ከአንደኛ ደረጃ መምህሬ ጋር፣ ከቀድሞ የቀበሌያችን የአብዮት ጠባቂዎች ሊቀመንበር ጋር፣ ከባለቤቴ የንስሃ አባት ጋር፣ የቀበሌያችን የእግር ኳስ ክለብ ኃላፊ ከነበሩት አዛውንት ጋር በተናጠል ጉባዔ አካሂዳለሁ፡፡ አልጥመኝና አልዋጥልኝ ሲል የድራፍት ብርጭቆ ከሚጨብጡትና በጂን መለኪያ ከሚጫወቱት ታርቲመኞቼ ጋር አተካራ እገጥማለሁ፡፡

በዚህ ሁሉ ሂደት ውስጥ ለመታወቂያዬ ትርጓሜ ርግጠኛና ተስማሚ የሚሆን ምላሽ አጣና መታወቂያውን ራሱን ከዓይኔ ስር አስቀምጬ ከራሴው ጋር አተካራ እገጥማለሁ፡፡ ቀበሌያችን ቀበሌ ከመሆኑ በፊት፣ቀበሌም ከሆነ በኋላ ያልነበሩ ሰዎች፤አይደለም የእናትና የአባቴን የእኔን ማንነት በአግባቡ ለማወቅ ፈቃደኛ ያልሆኑ ሰዎች በቀበሌያችን ውስጥ ተመስገው ካየኋቸው ከስንት ዓመት ቆይታ ወዲህ ነው፤ የነዋሪነት መታወቂያዬ ላይ የብሔሬን ማንነት የሚገልጸውን ቃል ያስተዋልኩት፡፡

የእኔ ብሔር፣የአባቴና የእናቴ ብሔር፣የአያት የቅድም አያቶቼ ብሔር ኢትዮጵያዊ የሚለው ነበረ፡፡ አሁን ትግሬ ሆነ፡፡ አማራ ተባለ፡፡ አፋር ሆነ፡፡ ጉራጌ፣ኦሮሞ፣ጌዲኦ፣አገው፣ከፍቾ፣ሐረሪ…ተብሎ ተጻፈልኝ፡፡ ምነው? ብዬ ብል፤ ‹‹ሕገ-መንግሥታዊ መብትህ ነው ተቀበለው…›› ይሉኛል፡፡ ‹‹ታዲያ ሕገ-መንግሥቱ የነበረኝ መብት ተስማምቶኝ ሳለ ሌላ መብት አጎናጽፌአለሁ የሚለኝ ለምንድነው?...›› ብዬ ስል፤ ባለዋስትና የሚያደርገኝን መልስ የሚሰጠኝ ሰው ፈልጌ ከዙሪያዬ አጣለሁ፡፡

በዚህን ጊዜ ‹‹ይህን ሁሉ ነገር ያመጣብኝ ቀበሌ ነው! ቀበሌ ነው! ቀበሌ ነው!...ቀበሌ መጥቶ የቀበሌ መታወቂያ ባይከተል ኖሮ ለኢትዮጵያ ሰው ኢትዮጵያዊነቱና ሰው መሆኑ ብቻ ከመልካም አመሉ ጋር በመታወቂያነቱ እያገለገለው ይኖር ነበር፡፡ መታወቂያ ያስፈልገዋል ከተባለም ለሙያው መግለጫ፣ ለአንዳንድ ማኅበራዊ ጥቅማ ጥቅሞቹ ማስከበሪያና ማሳለጫ ይሆነው ዘንድ ብቻም ነበር…›› እልና በራሴ ላይ እራሴ እጮኻለሁ፡፡ ተሳስቼአለሁ ጎበዝ? አይመስለኝም፡፡ በዛሬይቱ ኢትዮጵያ እኮ፤ አንድ ሰው የሌላውን ሰው መላጣ እስካልነካ ድረስ አይደለም እራሱ ላይ መጮኽ ይቅርና ‹‹እገሌ እኮ መላጣ ነው…›› ብሎ ማለት ይችል የለም እንዴ?

ጮኼ ግን አላበቃም፡፡ የሆነ ነገር ትዝ ይለኝና ከራሴው ጋር የመጽናኛ ዓይነት ወግ እገጥማለሁ፡፡ ‹‹ ቀበሌ የሚባለው ነገር ሳይቋቋም በፊት…›› እልና ወጌን እጀምራለሁ፡፡ ደግሞ መታወቂያዬን አየዋለሁ፡፡ እሱ ነው የሚያጫውተኝ፡፡ እሱ ነው የሚያነጋግረኝ፡፡ ‹‹ውሃን ምን ያናግረዋል? ብለው ቢሉ፤ ድንጋይ›› አሉ፡፡ ክቡራንና ክቡራት አንባቢያን! ለማንኛውም እኔ ውሃ ነኝ፡፡ የሚያናግረኝ መታወቂያዬ ነው፡፡ እሱን ግን ‹‹ድንጋይ ነው›› ለማለት አልደፈርኩም፡፡ በቃ ‹‹ለምን? እንዴት?…›› እያላችሁ አትጠይቁኝ፡፡ እንደዛ ብሎ ለማለት ሕገ-መንግሥታዊ መብቴ አይደለም፡፡ አብዮታዊ መብቴ አይደለም፡፡ ንጉሠ-ነገሥታዊ መብቴም አይደለም፡፡ ራሴን ውሃ ማለትና ከውሃም ድንጋይ የሚያናግረው ውሃ ነኝ ማለት ግን ሰው የመሆኔ መብት ነው፡፡

ግን ድንጋይ ነው ለማለት የማልደፍረው መታወቂያዬ እያናገረኝ ነው፡፡ ጥሎብኝ ሳየው እፈረዋለሁ፡፡ መታወቂያዬ የስጋቴ ምንጭ ነው፡፡ በእሱ ላይ ሁቱ ወይም ቱትሲ መሆኔ ተጽፏል፡፡ እኔ ግን ሁቱም ቱትሲም አይደለሁም፡፡ ቱትሲዎች እየፈለጉኝ ነው ብዬ ሳስብ፤ ምናለ እዚህ መታወቂያ ላይ የተቀለመውና ‹‹ሁቱ ነህ›› የሚለው ቃል ባልሰፈረ? እላለሁ፡፡ መቼም ቱትሲዎች ለሹመትና ለሽልማት አይፈልጉኝ፡፡ ‹‹ዛሬ ሁቱዎች ተቆጥተው! ቱትሲዎችን አያሳየን ብለው…ተነስተዋል›› ብለው ሲሉኝ፤ አሁንም መታወቂያዬን አጠንቅሬ እመለከተዋለሁ፡፡

በመታወቂያዬ ገጽ ላይ ከብሔሬ ማንነት መገለጫ አንፃር የሰፈረው ቃል ‹‹ቱትሲ›› ይላል፡፡ መታወቂያዬን ሳልይዝ ወይም ሳላሳይ ሁቱዎች በተቆጡበት ጎዳና ስንዝር መራመድ አልችልም፡፡ ሁቱ ብሆን እንኳ ቋንቋቸውን መናገር አይሆንልኝምና በእንዴት ያለ ዘዴ ሰለባቸው ከመሆን አለመልጣለሁ? ምናለ በመታወቂያ ገጽ ላይ ‹‹ሩዋንዳዊ›› የሚለው ቃል ብቻ ቢሰፍር? ብዬ መታወቂያዬን በለሆሳሳ እጠይቀዋለሁ፡፡ መልስ አይሰጠኝም፡፡ ግን ‹‹በቃ ቱትሲ ነህ! ሁቱ መሆንስ ያሳፍርሃል እንዴ?…›› እያለ የሚሳለቅብኝ ይመስለኛል፡፡ ‹‹አሁን አንተ ሰርቭ፣ክሩዋት፣መቄዶንያ፣አልባኒያ፣ቱርክ…ብትሆን ዩጎዝላቪያዊ ሆኖ ለመኖር የሚከለክልህ ማነው?...›› እያለ በመታወቂያዬ ላይ ያደረው መንፈስ ሊያጨዋውተኝ ይሞክራል፡፡…

እንዲህ ብሎ ሲለኝ እናደዳለሁ፡፡ እንዴት ነው መናደዴ የሚያናድደው ይኖር ይሆን? ካለ ጤናማነቱን ሳልጠራጠረው አላልፍም፡፡ ለምን ብትሉኝ በዚህ ዘመን በራስ ጉዳይ ካልሆነ በቀር በሌላው ስሜት ውስጥ ሆኖ መበሰጫጨት የስኒ ማዕበል የማስነሳት ያህል ጠቀሜታ እንደሌለው በተጨባጭም ይሁን በጨባጭ ተረጋግጧል፡፡ ስለዚህ አደራ የምለው ማንም ሰው በእኔ መናደድ እንዳይናደድ ወይም እንዳይበሳጭ ነው፡፡ ደግሞ ተናዳጁና ተበሳጩ ሲበዛ የሚያመጣውን ነገር አለመጠርጠር የዋህነት ነው፡፡ ‹‹ያልጠረጠረ ተመነጠረ›› እንደሚለው ሲጠረጠር የኖረው የአበሻ የነገር መዝገብ ማለቴ ነው፡፡

እና መታወቂያዬ እያናደደኝ ያለፈውን ሁነት ከመታወቂያ ታሪካዊ ሂደት አንፃር አሰላስላለሁ፡፡ በ1969 ዓ.ም አካባቢ ይመስለኛል መታወቂያ በየመንደር ሠፈሩ ለሚኖረው ለአቅመ አዳምና ሔዋን የደረሰ ሰው መታደል የጀመረው፡፡ ምክንያቱ አስተዳደራዊ ብቻ አልነበርም፡፡ በተጨባጭ ፖለቲካዊ ወይም የአብዮቱና የፀረ-አብዮት ትግሉ ተረፈ እሴት ነው፡፡ ‹‹እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የነዋሪነት መታወቂያ ያስፈልገዋልና ወደየቀበሌውና ወደየቀበሌ ገበሬ ማኅበሩ ጽ/ቤት እያመራ መታወቂያውን ይውሰድ…›› ተባለ፡፡ ለሰለጠነ መንግሥታዊና አብዮታዊ ክትትልና ቁጥጥር የሚኖረውን ግንባር ቀደም ድርሻ የተገነዘበውም ያልተገነዘበውም ሁሉ ‹‹መንግሥት ያለው እግዚአብሔር የፈቀደው ነው…›› እያለ ወደየቀበሌው ሄደ፡፡ ‹‹ማን ነህ? ከየት ነህ? እንዴት ነህ?…›› የሚሉትን ቅድመ ጥያቄዎች እየመለሰ መታወቂያ በመታወቂያ ሆነ፡፡

ግን ይህ በሆነ ማግስት አስተዳደራዊ ሥራው መልክ መያዝ ቢጀምርም መታወቂያው ለቁጥጥርና ለክትትል መሣሪያነትም በማገልገሉ ቡልቲካውን አወሳሰበው፡፡ የተወሳሰበውን ቡልቲካ ለማፍታታት ተብሎ ደግሞ ‹‹መሸኛ! መልቀቂያ! መዛወሪያ ወረቀት ያስፈልግሃል፣ያስፈልግሻል…›› የሚል ነገር ተከተለ፡፡ እንዲህም ሆኖ ግንቦት 20 ሰማንያ ሦስት እስኪብት፤ በመታወቂያው ላይ ብሔር ተኮር ነገር አልነበርም፡፡ ሌላው ግን ከነጓዙ ወዲህም እንዲህም ተሸጋግሯል፡

፡ የማውቀው ይሄንን ነው፡፡ አባቴም የነገሩኝ፣አያቴም ያጫወቱኝ ከዚህ የተለየ አልነበርም፡፡ የዛሬ መታወቂያዬ የሚያወራኝ ግን ሌላ ነው፡፡ አላውቅህም እያልኩት ‹‹ተው ባክህ አውቅሃለሁ›› ይለኛል፡፡ እንደው ዝም ብሎ የአህያ ባል ዓይነት ሆኖብኛል፡፡ አንዳንዴም ‹‹ሆቴል ሩዋንዳ…››የሚባለውን ፊልም በመታወቂያዬ ወስጥ የማየው ይመስለኝና እሸበራለሁ፡፡

ለዚህ ሁሉ ስጋቴና ፍርሃቴ መጽናኛ የሚሆነኝ አጎቴ ትዝታውን ክራሩን እየገረፈ፡- ‹‹ በፊት መታወቂያ ብሎ ነገር አልነበረኝም፡፡ አባቴም አልነበረውም፡፡ ጓደኞቹም አልነበራቸውም፡፡ አያቴም ቢሆን አልነበረውም፡፡ ባልንጀሮቹም መታወቂያ የሚባል ነገር አያውቁም፡፡ ከአሥመራ ይነሱና እግራቸው በመራቸው ተጉዘው ሐረር፣ደሴ፣ከፋ፣ቦንጋ፣አርባ ምንጭ…ይገኛሉ፡፡ ከዚያም ተነስተው ወደ ትውልድ ቀዬአቸው ይመለሳሉ፡፡ መንገዱ አማን ነው፡፡ ሰው ሁሉ የራሱም የሌላውም ሰው ጠባቂና ከለላ ነው፡፡ ብቻውን አይባለም፣ብቻውን አይጠጣም ነበር የእኔ ልጅ፡፡ ለነገሩ መጠጣቱን ዛሬም አብራችሁ እንደምትጠጡ አስተውዬአለሁ፡፡ ዳሩ መጠጣቷን ብቻ ወርሳችሁ በእጥፍና በጥራት አሳደጋችኋት! የማሪቱንም ጠጅ አጠፋችኋት፡፡ ግን ብትኖር በምን አቅማችሁ ትጠጡት ነበር?

‹‹ዛሬ የውስጣችሁ ሰላም ታውኮ ልቦናችሁ ሲያውቀው፤ ‹ሰላም ነው?!...›› እየተባባላችሁ እንደምትጠቃቀሱት መሰለህ? አይደለም! ያኔ ለኢትዮጵያ ልጆች መታወቂያቸው ጨዋነታቸውና ሰው አክባሪነታቸው፣ ከምንም በላይ ኢትዮጵያዊነታቸው ብቻ ነበር፡፡ ደርሼ የነበረውን ነገር ሁሉ ለመውቀስ ሳይሆን፤ ስልሳ ዘጠኝ መጣና እኔም፣አባቴም፣አያቴም፤ ያለ ጾታ፣ ያለ ሃይማኖትና ያለ ብሔር ልዩነት ባለመታወቂያ ሆንን፡፡ ስንሆን ጊዜና ጠርጣራው አያቴ ከመታወቂያው ባሻገር ያለው መጪው ነገር፤ ማለት አሁን አንተ ከመታወቂያ ደፍተርህ ጋር እየተፋጠጥክ የምትተክንበት ነገር ታይቶት ነው መሰለኝ ‹ዛሬማ በሰውነት መሆኑ ቀርቶ በወረቀት ሆነ የምንወዳጅና የምንተማመን…› እያለ ሲያጥላላና ሲነቅፍ ኖሮ አለፈ፡፡

‹‹እናልህ በኛ ጊዜና! የቀበሌ መታወቂያ ብሎ ነገር አልነበረም፡፡ በመልክህ፣በደም ግባትህ፣በአለባበስ አረማመድህ፣በጨዋነትህ ወይም በአጨዋወት ስልትህ፤ የአገር ሰው፣የእናት ሀገር ኢትዮጵያ ልጅ በመሆንህ ትታወቃለህ፡፡ ትከበራለህ፡፡ ታልፋለህ፣ታገድማለህ፡፡ ማተብ ስለነበር ‹አሳድሩኝ…› ያልክ እንደሁ ፈጣሪውን ያለ ሰው ‹አይ ወንድሜን! አወይ እህቴን!…›› ብሎ ያሳድርሃል፡፡ ዛሬ ግን መታወቂያህ ራሱ እንደሚያናድድህ፣ ባየኸው ቁጥር ‹ይመጣብኝ ይሆን?!…›› እያልክ ለምትሰጋበት ችግር ዋስትና እንደማይሰጥህ የምትነግረኝን ያህል እኔም ጠንቅቄ አውቀዋለሁ…›› እያለ ከተስፋ ሰጪ ቃላት ጋር ሲተርክልኝ ነው፡፡

እሱ ያለፈው ጊዜ ዞሮ የሚመጣ ይመስለዋል፡፡ እኔ ደግሞ መታወቂያዬን አጠንቅሬ እያየሁ ‹‹እሱ የሚለው የሚሆን ይመስልሃል እንዴ?...›› እያልኩ እጠይቀዋለሁ፡፡ መታወቂያዬ መልስ የለውም፡፡ ስለዚህ እፈራለሁ፡፡ መታወቂያዬ ደርሶ ያስፈራኛል፡፡ ‹‹ሲሰማ የሞተን ሲያይ ቅበረው›› አይደል የሚባል? እነዛ በዩጎዝላቪያ አባቶቻቸው፣ወንድሞቻቸውና ባሎቻቸው ከተገደሉባቸው በኋላ እነሱም በተራቸው ተገደው በተደፈሩ ማግስት የሚረሸኑት ሴቶች በዓይነ ህሊናዬ ይመላለሳሉ፡፡… ታዲያ ምነው አልፈራ? መታወቂያዬን ሳየው እፈራለሁ፡፡

/ ለተሬሳ ይማሙ፤ ማክሰኞ ግንቦት 5-2006 ዓ.ም ጊምቢ/

መታወቂያዬን ሳየውመታወቂያዬን ሳየው

32 °”l 6— ¯Sƒ lØ` 119 ግንቦት 2006 ዓ.ም

“ኢትዮ አሜሪካዊቷ ድምፃዊና የግጥምና ዜማ ደራሲ የ24 ዓመቷ ማርያ መረባ በዓለም አቀፍ የመዚቃ መድረክ ውስጥ የራስዋ ቦታ እንዲኖራት የሚያስችላት አዲስ ሥራዋን እነሆ በረከት ለማለት እያሟሟቀች ነው” ሲል ታዋቂው አፍሮ አሜሪካውያን የኪነጥበብና መዝናኛ ጉዳይ ላይ የሚያተኩረው ኢቦኒ መፅሔት ከትላንት በስቲያ ከዚህችው ተስፋ ከተጣለባት ኢትዮጵያዊት ድምፃዊና የግጥም ደራሲ ጋራ ባደረገው ቃለምልልስ አስነብቦናል፡፡

የኢቦኒ መፅሔት ዘጋቢ በቅርቡ ገበያ ላይ የሚውለው የማርያ መረባ የሙዚቃ ሥራዎች አዳዲስና ባልተለመደ አቅጣጫ ዓለምን ፍቅርን፣ ውበትን፣ ተፈጥሮን የቃኘችበት ድንቅ ግጥምና ዜማ ቅንብር የተጣመሩበት እንደሆነና እኒህ ሥራዎቿን በቅርቡ ለዓለም እንደምታሰማ ተዘግቧል፡፡ ከስመጥሩ ምዕራባውያን አቀንቃኞች ከእነ ሎረን ሒል፣ ዊትኒ ሒውስተን ጋራ የሚወዳደር ኮርኳሪና መሳጭ ቅላፄዎች አጣምራ የያዘች ባለልዩ ተሰጥዖ አቀንቃኝ መሆንዋን ማስመስከር የሚያስችል ብቃት አላት፡፡

የኢቦኒ መፅሔትና ድረገፅ ዘጋቢ ከማርያ መረባ ጋር ያደረገችው ቃለ ምልልስ እንደሚከተለው አቅርበነዋል፡፡

እንዴትና መቼ ነው ሕይወትሽን ከሙዚቃ ጋራ እንዲቆራኝ ያደረገ ወሳኝ አጋጣሚ የተፈጠረልሽ?

ማርያ መረባ፡- ምናልባት ገና የአራት ዓመት ልጅ ሆኜ እናቴ ዘቦዲጋርድ የተሰኘ ፊልም ኬቨንኮትነር፣ ዊትኒ ሒውስተን በመሪ ተዋናይነት የሠሩበት ፊልም ላይ የነበረ ዘፈኖችና የፊልሙ ማጀበያ ሙዚቃ፣ የተቀረፀበት ካሴት ወደቤት ይዛ መጥታ ስታዳምጥ በነበረበት ከዚያ የሕፃንነት እድሜዬ ጀምሮ ይመስለኛል፡፡ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ነው የዊትኒ ሒውስተንን ዘፈን በማዳምጥበት ወቅት በውል የማላውቀው ኃይል ነፍስያዬን እያንሳፈፈ ወደ አንድ ያልታወቀ ተአምረኛ ደሴት ይዞኝ የሚጓዝ የሚመስል ድባብ ውስጥ ይከተኛል፡፡ እነዚያ የዊትኒ ሁስተንን ድንቅ ሥራዎች የያዙ አልበሞች ላይ ያሉ ዘፈኖችን አንድ ሳላስቀር በቃሌ ይዤ ለዓመታት ሳንጐራጉራቸው ስለነበር ከዚህ የጀመረኝ ይመስለኛል፡፡

እውነትሺን ነው እነዚያ በፊልሙ ላይ የነበሩ የዊትኒ ዘፈኖችን የያዙ አልበሞች ድንቅ ሥራዎች ናቸውና፡፡ ራስሺን በሮሊንግ ስቶን አይነት የዜማ ስልት እንድትወስኝ ያደረገሺና ለአሁኑ ማንነትሽ ያደረሰሽ ልዩ አጋጣሚስ ምን ነበር?

ማርያ መረባ፡- የሮሊንግ ስቶን ስልት ተከታይ የሆንኩት እንደምገምተው ወላጆቼም የዚህ ስልት አቀንቃኞች እንዲሁም የስልቱ አፍቃሪና አድናቂ በመሆናቸው በደሜ ዘልቆ የገባ ይመስለኛል፡፡ ኢትዮጵያዊት ጥቁር መሆኔም በውስጤ ጎልቶ ስለሚታየኝና ስለሚሰማኝ ሊሆን ይችላል፡፡ አባቴ በ1960ዎቹ መጀመሪያ ላይ ከዩኒቨርሲቲ አይደህዋ የነፃ የትምህርት ዕድል አግኝቶ ከኢትዮጵያ ወደ አሜሪካ የመጣ ሲሆን እናቴ አሁን ድረስ አብዛኛዎቹ ዘመዶቻችን ከሚኖሩበት ዊስኮንሲ ከሚዋኪያ ውስጥ የተወለደች አሜሪካዊት ናት፡፡

ወላጆቼ የዩነቨርሲቲ መምህራን ናቸው፡፡ ሁለቱም በተለያዩ ስቴቶች የሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች ውስጥ በመዘዋወር ስለሚያስተምሩ እነርሱ በሥራ ምክንያት ወደ ግዛቶች ሲዛዋወሩ አብሬያቸው እዞር ስለነበር የተለያዩ ማኅበረሰቦችን ባህልና ወግ እንዲሁም የሙዚቃ ሥራዎች ለማወቅ ከመቻሌ ጋራ የሚገናኝ

ይመስለኛል፡፡ስለ ዩኒቨርሲቲ ካነሳሽ ዘንዳ የሁለተኛ ደረጃ

ትምህርትሽን ከካርኔንጅ እና ሚሎን ኮሌጆችና በስፔልማን ዩኒቨርሲቲ የከፍተኛ ትምህርትሽን መከታተልሽን ተረድቼያለሁ፡፡ የመጀመሪያ ዲግሪሽን በምንድን ዘርፍ ነው ያገኝሺው? ብዙዎች በሙዚቃው ላይ ሲያተኩሩ የከፍተኛ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ ስለማይታዩ እንዴት በትምህርትሽስ ልትገፊበት ቻልሽ?

ማርያ መረባ፡- ዲግሪዬን ያገኘሁት በእንግሊዘኛ ቋንቋ ስነጽሁፍ በንኡስ የሙያ ዘርፍም (ማይነሬ ደግሞ) በሙዚቃ ላይ ነው፡፡ እንዳልሺው የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቴን እንዳጠናቀኩኝ ወደ ሙዚቃው ነበር ፊቴን ላዞር የነበረው፡፡ ነገር ግን አባቴ ይሔንን ሓሳቤን እንድቀይር ባደረገው ያላሰለሰ ጥረት ተደግፌ ዩኒቨርስቲ ለመግባት ቆረጥሁ፡፡

አባቴ ይህቺን ዓለም ያለ ትምህርት የሚኖርባት አይመስለውም፤ ዓለም ካለ ትምህርት ጎደሎ ናት ብሎ ያምናል፡፡ አባቴ ስለትምህርት ያለው አመለካከት እጅግ ድንቅ ነው፡፡ ለዚህም ማሳያው ራሱንና በትምህርት ዓለምን ያሸነፉ ሰዎችን ምስክር አድርጎ ያቀርባል፡፡ ለእርሱ ትምህርት ግለሰባዊ ነፃነቱን የሚቀዳጅበት የነጻነቱ የመክፈቻ ቁልፍ እና የመግቢያ ትኬቱ አድርጐ ነው የሚያየው፤ ሁሉንም በሮቹን በትምህርት ቁልፍ ለመክፈት ነው የሚሻው፡፡ “ያልተማረ ሰው አይሆንም” የሚል አቋምን ያራምዳል፡፡ የአባቴ ፍላጐት በመገንዘብ ምኞቱን አክብሬ ተቀብዬ ወደዩኒቨርሲቲ በመግባት ትምህርቴን ተከታትዬ አጠናቅቄያለሁ፤ የርሱ መርህ መንገድ ሆኖኛል፡፡ ትምህርት ወደ አንድ የዕድገት ደረጃ የሚያደርስ መሰላል እንደሆነ አድርጌ ነው የማስበው፡፡ ሕይወት ራስዋ ትምህርት ቤት አይደለች እንዴ?

ልትይ የፈለግሺው ገብቶኛል፡፡ በሙዚቃ ሕይወትሽ አሁን ለደረስሽበት የስኬት ማማ እንድትቆናጠጭ በማድረግ ረገድ የሕይወት ፍልስፍናሽና የኑሮ ዘይቤሽ ምን አይነት ተፅዕኖ ፈጥሮብሻል?

ማርያ ማረባ፡- እንደማስበው ሁልጊዜ የእያንዳንዱ እንቅስቃሴዎቼን ውጤቶች በጥልቀት እመረምራለሁ፤ በአጠቃላይ የሕይወቴ ጉዞዎችም የታዛቢነት ሚና ነው ያለኝ የሚመስለኝ፡፡ አንዳንድ ጊዜ ከመጋረጃ በስተጀርባ ሆኜ ዓለም እንዴት እንደምትንቀሳቀስ እንደምትሰራ አያለሁ፡፡ በዚህ ነው የሰውን ልጆች ባንድ ሊያስማማ የሚችል ሁሉን አቀፍ (ዩንቨርሳል የሆነ) እውነታ እንዳለ ለመገንዘብ የቻልኩት፡፡

እንደ ደራሲነቴ ከበርካታ የማኅበረሰብ ክፍሎች ጋራ በተለያዩ አጋጣሚዎች የአኗኗር ዘይቤዎቻቸውን/ስልቶቻቸውን፣ ርእዮተዓለማዊ አስተሳሰቦቻቸውን፣ ባህል፣ ወግና ልማዶቻቸውን አጠናለሁ፡፡ ስለዚህም በስራዎቼ ታሪክ ተተራኪና ተናጋሪ እንዲሆኑ እቀርጻቸዋለሁ፡፡ ስለዚህም ሙዚቃ ማለት ለእኔ የምደበቅበት ጎጆዬ፤ የምሰደድበት የስደት ጓደኛዬ፤ የቅርብ አጫዋቼ፣ የልብ ወዳጄ፣ ብሶቴን ተጋሪዬ አድርጌ ማየት ጀምሬያለሁ፡፡

ለበርካታ ሰዓታት ብቻዬን ክፍሌን ቆልፌ ተቀምጬ ግጥም እየገጠምኩ፤ እየፃፍኩ፣ ጊታሬን እየገረፍሁ፤ እየዘፈንኩ፣ እያንጎራጎርኩ አሣልፋለሁ፡፡ በዚያው አጋጣሚም የመጪውን ጊዜ የህይወት እንቅስቃሴ በተመስጦ በምናቤ አሰላስላለሁ፡፡ በዚህም መቼም ቢሆን ራሴን ነፍሴን ከተቆራኘኝ ልዩ ተአምራዊ የተሰጥዖ ደሴት ርቄ ሄጄ አላውቅም፡፡

ከዚሁ ጋራ በአሜሪካ ኑሮውን የመሠረተው የመጀመሪያው ኢትዮ-አሜሪካዊ ትውልድ ውስጥ የምንገኝ እንደመሆናችን፤ ኢትዮ-አሜሪካዊ ድብልቅ ብዝኀ ባህልና ማንነትን መሰረት አድርጌ ነው ሕይወትንም ዓለምንም የማየው፡፡ በዚሁ ነው የሥራዎቼ ቅኝት ያስተካከልኩት፡፡

እንደ አንቺ በ 20ዎቹ አመት ዕድሜ ክልል ውስጥ ላሉ ታዳጊ ወጣቶች በተለይም በመልክ ለሚመስሉሽ ጥቁር ወጣቶች ምን ታስተላልፊላቸዋለሽ?

ማርያ መረባ፡- ልል የምችለው ዓለም የእናንተ ናት፤ የዓለምና የህይወት መንገዶቻችሁን በራሳችሁ ወስኑ እንጂ አንዳንዶች በተለሙት የራሳቸው ትልም እንድትጓዙላቸው በነርሱ አንጻር ሊመሯችሁ ሲሞክሩ ቦታ አትስጧቸው፡፡ ለራሳችሁ ራሳችሁ ብቻ ናችሁ ወሳኞቹ፡፡ በማኅበረሱቡ ውስጥ ያላችሁን ወሳኝ ድርሻ ለማረጋገጥ መስራት ይኖርባችኋል፡፡ እናንተ የተፈጠራችሁት ገደብ፣ ድንበርና ወሰን ባልተበጀለት በፈጣሪያችሁ አምሳል ነውና የለውጥ ኃይሎች መሆናችሁን አምናችሁ ክህሎትና ዝንባሌያችሁን በማጣመር ለሕይወት ጥሪያችሁ ምላሽ ስጡ ማለትን እሻለሁ፡፡

እስቲ ቀጥሎስ ከጥቁሯ አንስት ወደፊት ምን እንጠብቅ?

ማርያ መረባ፡- የመጀመሪያውን አልበሜን ሰርቼ አጠናቅቄ በገበያ ላይ የሚውልበትን ጊዜ በናፍቆት እየጠበኩ ነው፡፡ THE RADIO FIYER በሚል ርዕስ የሚጠራው አልበሜ ወደዓለም የሙዚቃ አፍቃሪዎች ወገኖቼ ለማድረስ ዝግጅቴን በማጠናቀቅ ላይ ነኝ፡፡

ብዙዎች ተስፋ የጣሉባት የታዋቂዋ ኢትዮ-አሜሪካዊት አቀንቃኝ የማሪያ መረባ አዲስ አልበም ጁላይ 29 ቀን 2014 ቀን በገበያ ላይ የሚውል ሲሆን በዚሁ አልበም ላይ የሚገኘው “ሰፕቴምበር” የተሰኘው ነጠላ ዘፈን ከሰኞ ሜይ 27 ቀን 2014 ጀምሮ ይለቃቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ኢትዮ-አሜሪካዊ ማንነቴን መሠረት ያደረገ አልበም ሠርቻለሁ

ማርያ መረባ

ሙዚቃ

33°”l 6— ¯Sƒ lØ` 119 ግንቦት 2006 ዓ.ም

ዕንቁ ስፖርት

በገነነ መኩሪያ (ሊብሮ)

አላን ኮል የተባለ ጃማይካዊ በ1969 ዓ.ም ለአየር መንገድ ሲጫወት በኢትዮጵያ እግር ኳስ ታሪክ ውስጥ ፌዴሬሽኑ በሚያዘጋጀው ውድድር የተጫወተ የመጀመሪያው የውጭ ተጨዋች ነው፡፡ አላን መልኩ ቀይ ሆኖ ቁመቱ ረጅም ሲሆን በኳስ ቴክኒክ ችሎታው የተደነቀ ኳስን እንደፈለገ የሚያደርግ ነበር፡፡ ከምድር ጦር ጋር በተደረገ ጨዋታ ሪጎሬ እግሩን አቆላልፎ ሲመታ ተመልካቹ በጣም ተደንቆ ነበር፡፡ አላን ኮል የታዋቂው የሬጌ አቀንቃኝ የቦብ ማርሊ ፕሮሞተር ነበር፡፡ ከቦብ ጋር አብሮ አደግ ሲሆን ወደ ኢትዮጵያ ያስመጣውም በ1971 ዓ.ም እርሱ ነበር (በአዲስ አበባ ስታዲየም ለማቅረብ ያሰቡት ዝግጅት ባይሳካም) አላን አሁን በእንግሊዝ ሀገር ይገኛል ፡፡ በተጫዋችነት ዘመኑ ለአርጀንቲና እና ለብራዚል ክለቦች ተጫውቷል ፡፡ ናውቲካ፤ አጀኖቲካና ሳንቶስን የመሳሰሉ ክለቦች አዳርሷል፡፡ አየርመንገድ አላንን ከውጭ አስመጥቶት እንደ ፕሮፌሽናል ተጫዋች ኮንትራት ተፈራርሞ ሳይሆን በሌላ ጉዳይ ኢትዮጵያ ውስጥ ስለመጣ እንዲጫትላቸው ጠይቀውት ነው፡፡ ወደ ሀገሩ ለእረፍት ሲሄድ ትራንስፖርት በነጻ ነው፤ከአላን በኋላ የውጭ ተጨዋቾች መምጣት የጀመሩት ከ18 አመት በኋላ ነበር በ1987 ከኬንያ አንድ ናይጀሪያዊ አጥቂ ጊዮርጊስ አስመጣ፡፡ አመት ቆይቶ ሄደ፡፡ ከዚያ በኋላ ለተወሰኑ አመታት የመጣ ሰው አልነበረም ካለፉት 12 አመታት በኋላ ግን እየተበራከቱ ከበረኛ እስከ አጥቂ በመጉረፍ ላይ ይገኛሉ፤...በእኔ እይታና ምደባ ከውጭ የሚመጡ ተጫዋቾች በአምስት ይከፈላሉ፡፡ በተለይ ከናይጀሪያ፣ ጋና፣ ካሜሩን የመጡ፡፡ ለምሳሌ ከናይጀሪያ የሚመጡትን ስናይ 1ኛ ደረጃ፡- አውሮፓ በተለይ ትላልቅ ሊጎች እንግሊዝ፣ ስፔይን፣ ጣሊያን የሚጫወቱ2ኛ ደረጃ፡- ምስራቅ አውሮፓ እንደ ሩማንያ፣ ቡልጌርያ የሚጫወቱ3ኛ ደረጃ፡- በኤሽያ የሚጫወቱ4ኛ ደረጃ፡- በአፍሪካ ሰሜን አካባቢ ቱኒዝያ፤ግብጽ፤ሞሮኮ የሚጫወቱ5ኛ ደረጃ፡- ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡ ናቸው፡፡

እዚህ የሚጫወቱት ምራጭና አራቱ ደረጃዎች ጋር እድል ያላገኙ በሰሜን አፍሪካም ለመጫወት ሞክረው ሳይሳካላቸው የሚመጡ ናቸው፡፡ ስድስተኛ ደረጃ ስለሌለ የመጨረሻቸው እዚህ ነው፡፡በሀገራቸው ምናልባት ቀበሌ ካለ ከዚያ ወይም በዚያ አቻ ከሆነ ቦታ ወይም ሰፈር ከሚባለው ሜዳ የመጡ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ እዚህ የሚመጡት የናይጀሪያና የካሜሩን ተጫዋቾች አንድም ቀን ለሀገራቸው ብሄራዊ ቡድን ያልተጫወቱ፡፡ መጫወት ብቻ ሳይሆን ለምርጫ የመጠራት አድል የማያገኙ ናቸው፡፡ ፊፋ ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉትን እነዚህን ተጫዋቾች የሀገራቸው ብሄራዊ ቡድን ሲጫወት የኢትዮጵያን ክለቦች ቶሎ እንዲለቋቸው አያስገድድም፤ (ስለማይጠሩ) ክለባቸውም ለብሄራዊ ቡድን ለመጫወት ስለማይሄዱ የተጨዋች እጥረት ይገጥመኛል የሚል ሀሳብ የለበትም፡፡ እስካሁን በብዛት ተጫዋቾችን በግንባር ቀደምትነት ያስመጣ ጊዮርጊስ ነው፡፡ካሜሩን፣ ኬንያ፣ ሩዋንዳ፣ ናይጀሪያ፣ ታንዛንያ፣ ኡጋንዳ፣ ጋና... ጊዮርጊስ ከ1987 ጀምሮ ሲያስመጣ አስካሁን 19 አመት ሆኖታል፡፡ በእነዚህ አመታት ጊዮርጊስ ምን ተጠቀመ? ጊዮርጊስ እነዚህን የውጭ ተጫዋቾች ከማምጣቱ በፊት በርካታ ዋንጫዎች አግኝቷል፡፡ እነርሱም ከመጡ በኋላ ሻምፒዮና ሆኗል፡፡ ስለዚህ ከእነርሱ የተለየ ነገር አላገኘም፡፡ ጊዮርጊስ በኢንተርናሽናል ውድድር እነርሱ ከመምጣታቸው በፊት ደካማ ነው፡፡ የውጭ ተጨዋቾች ይሄን ይቀርፋሉ እንዳይባል በፊትም የነበረውን ውጤት ነው አሁንም ያስመዘገበው፡፡ በኒህ 12 አመታት ውስጥ በርካታ የውጭ ተጫዋቾች ወደ ክለቡ መጥተው የምስራቅ አፍሪካ (ሴካፋ) ዋንጫን እንኳን አላገኙም፡፡ ታዲያ የውጭ ተጫዋቾች በጊዮርጊስ ክለብ ውስጥ ምን የተለየ ነገር አሳዩ? በኢንተርናሽናል ውድድሮች ለውጥ ካልመጣ ለሀገር ውስጥ ዋንጫ ድሮውንም በኢትዮጵያውን ተጫዋቾች ውጤት እያመጣ ነበር፡፡ እኒህ ከቁጥር የማይገቡ ተጫዋቾች መጥተው ካገራችን ዶላር ይወስዳሉ በተጨማሪም የአንድን ሀበሻ የመጫዋቻ ቦታ/ዕድል ይይዛሉ/ይዘጋሉ..... መብራት ሃይል ካሁን ፊት በሚያሳድጋቸው ተጫዋቾች ጥሩ ቡድን በተደጋጋሚ ሰርቷል፡፡ ማሳደጉ የተጀመረው በ1958 ጀምሮ ነው፤ (ከፍቃደ ሙለታ-እስከነ መስኡድ ድረስ) ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በብዛት ከታችኛው ቡድን ያወጣል፡፡ በ1993 ደብል ዊነር (መንቶ አቸናፊ ቢባልስ) ሲሆን በአብዛኛው ባሳደጋቸው ተጨዋቾች ነበር፡፡ ካለፉት አራት አመታት ወዲህ ግን ከውጭ በግዢ በሚያስመጣቸው ተጫዋች እየተጠቀመ ነው፡፡ በቡድን ብቃት፣ በተጫዋች ጥራትና በውጤት ያሁኑ ቡድን ከበፊቱ ያነሰ ብቻ ሳይሆን የወረደ ነው፡፡ ከጨዋታም ከውጤትም የለበትም፡፡በማሳደግ ጥሩ ተጨዋች እያገኘና ይሄን የቡድን ባህል የሆነውን አሰራር አፍርሶ ምንም ለውጥ ወዳላሳዩ የውጭ ተጫዋቾች መሄድ ለምን አስፈለገ? 1ኛ ከገንዘብ አንጻር2ኛ በብዛት ከማሳደግ አንጻር

የተሻለው የበፊቱ ነው፡፡ በተለይበ2004 ከበረኛ ጀምሮ እስከ

አጥቂ በውጭ ተጫዋች ተደራጅቶ ነበር፡፡ አስታውሳለሁ ደጋፊው የናይጄሪያን ባንድራ ይዞ እስከማውለብለብ ደርሶ ነበር፡፡ ቡድኑ የኢትዮጵያ መብራት ሳይሆን የናይጄሪያ መብራት ሃይል ይመስል ነበር፡፡ እነዚህ ከውጭ በብዛት ተጨዋች የሚያስመጡ ለወደፊቱ ደጋፊ ከናይጄሪያና ከካሜሩን ሊያስመጡ ይችላሉ የሚል ድምዳሜ ላይ እንድደርስ እየገፋፉኝ ነው፡፡

በአገራችን እስካሁን የተጫወቱ እኒህ የውጭ አገር ተጫዋቾች (በመጫወት ላይ ያሉ) በሁሉም ክለቦች ሲታዩ ወሳኝ ተጨዋቾች አይደሉም፤(እንደ ናይጀሪያዊነታቸው) ለምሳሌ በረዥም አመት ቆይታቸው ኮከብ ተጨዋች የተባለ አጥቂ ወይም አማካይ ሰምቼ አላውቅም፡፡እሺ!! ይሄ እንኳን መራጮቹ ለአገራቸው አድልተው ነው ሊባል ይችላል፤ ኮከብ ግብ አግቢ ግን በምርጫ አይደለም በብቃት ነው የሚፈጠረው፤ ባገባው ጎልነው የሚወስነው፤ አንድ ጊዜ እንኳ ኮከብ ግብ አግቢ ተብሎ ውድድሩን የጨረሰ የውጭ ተጨዋች አላየሁም፡፡

ይህ የውጭዎችን የማግበስበስ አባዜ በአዲስ አበባ ክለቦች ብቻ ሳይሆን ክፍለ ሃገር ባሉ ክለቦች ድረስ እየሄደ ነው፡፡ በሃገራችን እግር ኳስ ዕድገት ላይ ምንም ጠቀሜታ ከሌላቸው ምን ያደርጉልናል? እነርሱን በክለባችን አካተንና ሳናካትት በዓለማቀፍ የክለቦች ውድድር ውጤት ካላገኘን የነርሱ መኖር ምን ጠቀሜታ አለው? የውጭ ተጫዋች ብርቃችም ነው እንዴ? ከአንድ አመት በፊት ድሬደዋ ከነማ ሶሰት ያህል የውጭ ተጫዋቾች ነበሩት፤ ድሬደዋ አሸዋ ሜዳ ባፈራቸው ድንቅ ተጨዋቾቹ ከራሱ አልፎ ለአዲስ አበባ ክለቦች በርካታ ተጨዋቾች አፍርቷል ያንን አኩሪ ልማድና ባህል ትተው ከናይጀሪያ ተጨዋች አሰመጡ፤ድሬዳዋ ከነማ ሳይሆን ናይጀሪያ ከነማ ለመባል ምን ቀራቸው? ለነገሩማ ድሬዳዋን አነሳሁ እንጅ አዳማ ከነማንም አጥለቅልቀውታል፤ የሚገርመው ከከነማ አልፈው ክፍለ ከተማ ድረስ ሄደዋል፤ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አንድ የውጭ ተጫዋች አስፈርሞ ነበር፡፡ ክፍለ ከተሞች በስራቸው ብዙ ቀበሌዎች አላቸው፡፡ ዓላማቸውም በየቀበሌው ያሉ ተጨዋቾችን አወዳድሮ ጥሩ የተባሉትን ወደ ዋናው ቡድን ማሳደግ ነው/ነበር ቢባል ይሻላል መሰለኝ፡፡ ነገር ግን ይሄ ቀርቶ ከነማዎች ከውጭ ሲያስመጡ ከአላማቸው ከአሰራሩም ወጡ ማለት ነው፡፡ ወደ ዋናው ቡድን እንገባለን ያሉ የቀበሌ ተስፈኞች ከነማው ፊቱን ወደ ናይጀሪያ ሲያዞር ከታች ያሰፈሰፉት የስራ ዘርፋቸውን ለመቀየር ይገደዳሉ፡፡... ባለፈው ጊዜ ፌዴሬሽን በጠራው ውይይት የተነሳው አንዱ ጉዳይ የበረኞቻችን ብቃት ማነስ ችግር ተብሎ ቀረበ፤ ለዚህም ምክንያቱ በክለቦች አብዛኛውን ጊዜ የመሰለፍ እድል የሚያገኙት ከውጭ የመጡት በመሆናቸው የኛዎቹ የመሰለፍ እድሉን ስለማያገኙ ብቃታቸው ወርዷል ተባለ፤ እንዲያውም ክለቦች ከውጭ በረኛ እንዳያስመጡ የሚል መመሪያ ለማውጣት እየተዘጋጁ እንዳሉ አውቃለሁ፡፡ በርግጥ ይሄ ሲታይ እውነት ሊመስል ይችላል፡፡ የኛዎቹ ቦታቸው በውጭ በረኞች በመያዙ አልነበረም ብሄራዊ ቡድን ውስጥ ችግር የተፈጠረው፡፡ እነዚህ የውጭ በረኞች በብዛት የመጡት ከስምንት አመት ወዲህ ነው፡፡ ከዚያ በፊትም ቡድናችን ላይ በብዛት ግብ እየተቆጠረ የበረኛ ችግር አለ ሲባል ነበር፡፡አሁንም በበረኞቻችንም ላይ ያለው ችግር ከአጨዋወት ጋር የሚያያዝ እንጅ የውጭ በረኞች ቦታ ስለያዙ አይደለም፡፡ እንደአጠቃላይ ሲታይ የውጭ በረኛ አሰለፍንም አላሰለፍም ምንም ለውጥ አላመጣንም፡፡ መነጋገር ያለብን ጉዳይም የውጭ ተጫዋቾች በአገራቸን እግር ኳስ ላይ ምን ለውጥ አመጡ? የሚለውን ነው.... በመንግስት/በህዝብ ሃብት የሚደገፉ ክለቦች ዓላማቸው ስፖርቱን መደገፍና ማሳደግ ለአገራቸው ዜጎች ቅድሚያ መስጠትና ማብቃት ወዘተ “የሃገሩን ሰርዶ ለሃገሩ በሬ ነው ወይስ በሃገሩ በሬ?”… ነው/ነበር፡፡ የአገርን ገንዘብ የውጭ ሰው ቀጥረን ለርሱ ማጉረስ፤ የአገራችንን ተጫዋቾች የስራ ዕድል ነጥቀን ለነርሱ መስጠቱ ምንይባላል? ክለቦቻችን በዓለማቀፍ ውድድሮች ውጤት ቢኖራቸው የአገርን ስም ስለሚያስጠራ ማጫወቱ አይከፋም እንል ነበር፤ ምንም ለውጥ ለሌለው ውጤት ግን ለምን ከውጭ ስድስተኛ ደረጃ ተጫዋች እናስመጣለን? ያውም በዶላር ለምንከፍላቸው፤ አሁኑኑ ይሄ አካሄድ በውይይት አንድ እልባት ማግኘት አለበት፡፡ ደግሞም እኮ ዝውውሩ የአንድ ወገን ነው፡፡ በእኛ አገር በተለያዩ ጊዜ ከ30 አስከ 40 የሚሆኑ ናይጀሪያውያን መጥተዋል፤ ነገር ግን አንድም ኢትዮጵያዊ ናይጀሪያ ክለብ የመጫወት ቀርቶ የሙከራ እድልም አላገኘም፡፡ እኛ በእርግጥም ስለማንመጥን ወይም ለእግር ኳስ አስፈላጊ ከሚባሉት አገራት ከነናይጀሪያ ስለማንሻል ከእኛ አልወሰዱም፡፡ ሆኖም እኛም ስናመጣ እዚህ ካሉት የተሻሉ ሊሆኑ ይገባል፡፡ ግን እስካሁን ሲሻሉም ሆነ ወሳኝ ሆነው ሲቀርቡ አላየንም፡፡ እናም አሁን ቆም ብለን እናስብና እንወስን፡፡ ስላልጠቀሙን ገንዘባችንንና ከእኛ ልጆች ነጥቀው የወሰዱብንን የመሰለፍ ቦታ እናስመልስ፤ ኳሱ የራሱን አገር ጉርሻ ነጥቆ ለሌሎች ባጎረሰው ሲጎለምስና ሲያድግ አልታየምና፡፡

የውጭ ተጫዋቾች በኢትዮጵያ

ከአፍሪካ የሰፈር ሜዳዎች የሚገዙ ተጫዋቾች ለክለቦቻችን ምን ፈየዱ?

34 °”l 6— ¯Sƒ lØ` 119 ግንቦት 2006 ዓ.ም

ሥን

ከገጽ 25 የዞረ

ሰዎችም ቅጣታቸው ‘አራምባና ቆቦ’ የሚሆንበት ሁኔታ አለ፡፡ ክትትሉም እንዲሁ ደከም የሚልበት ሁኔታ እንዳለ ይታወቃል፡፡ ስለዚህ አእምሯዊ ንብረት ማስከበር ላይ በመንግሥት ሕግ አስከባሪዎች ረገድ ችግር ቢኖር አይገርመኝም፡፡ እንደሚኖርም መገመት እችላለሁ፡፡ ከዳኞች ጋር የሚኖረውን መስተጋብር ግን፤ በሌላ መድረክ፣ በሌላ አኳኋን ልትከታተሉት ትችላላችሁ፡፡ ከመንግሥት አስፈጻሚ አካላት ጋር የሚኖረውን መነጋገር ይቻላል፡፡ እዚህም ላይ ሁለት ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ሥራ አብረን ብንሠራ፤ አንደኛው የሕግ ክፍተት የሚባሉትን ለይተን የሕግ ክፍተቶቹን ለመሙላት የሚያስችለን የጋራ እነቅስቃሴ ብናደርግ ጥሩ ነው፡፡

ሁለተኛው በፖሊስና በዐቃቤ-ሕግ አካባቢ አሉ የተባሉት ችግሮች ከምን እንደሚመነጩ በጋራ ለይተን፤ በጋራ የመፍትሄ አቅጣጫ ብናስቀምጥ፣ የጋራ ስትራቴጂና መርኀ-ግብር ብንነድፍ፣ አፈጻጸሙ ላይ በጋራ የምንከታተልበት ሁኔታ ቢፈጠር መልካም ይመስለኛል፡፡ ‘ቁጥጥሩ ላይ በንግድ ሚኒስቴርም በጉምሩክም በሌላም… ሕገ ወጦችን መቆጣጠር ላይ ትልቅ ችግር አለ’ ተብሏል፡፡ ‘መንግሥት ፈቃድ የሰጣቸው ሰዎች በሕገ ወጥ ንግድ ውስጥ ተሰማርተዋልም’ ተብሏል፡፡ ይሄ ትክክል ነው፡፡ እስካሁን ድረስ የነበረው የፈቃድ አሰጣጥ ሥርዓት ለቁጥጥር በምንም መልኩ የሚያመች አልነበረም፡፡ በዚህም ምክንያት ብዙ በሕገ ወጥ መንገድ መሥራት የሚፈልጉ ነጋዴዎች በር ተከፍቶላቸው ቆይቷል፡፡ ለምሳሌ፡- በመንግሥት አሠራር በተደጋጋሚ የሚያጋጥመን ችግር፤ አንድ ነጋዴ በኪሱ ውስጥ ሰባትም፣ ስምንትም የንግድ ፈቃድ ይኖረዋል፡፡ አንዳንዱ በራሱ ውሻ ወይም ድመት ሥም ሳይቀር ፈቃድ ያወጣል፡፡ የቁጥጥሩ መላላት ምን ያህል አስገራሚ ደረጃ ላይ እንደደረሰ በዚህ መገንዘብ ይቻላል፡፡ ስለዚህ ሦስት አራት ዓመታት በአንደኛው የንግድ ፈቃድ ይሠራል፣ ሦስት አራት ዓመታት የታክስ አፎይታ አለኝ ይላል፣ የታክስ እፎይታ ጊዜው ሲያልቅ ደግሞ፤ የመጀመሪያውን ፈቃድ ያወልቅና ቀጥሎ ያለውን ፈቃድ ይጠቀምበታል፡፡ በየጊዜውም አዳዲስ ፈቃድ እየመነዘረ፣ ታክስ ሳይከፍል የሚኖርበት ሁኔታ ነበር የነበረው፡፡ ይህንን ለማስተካከል እያንዳንዱ ባለፈቃድ በርግጠኝነት እንዲታወቅ ለማድረግ ነው በጣት አሻራ ላይ የተመሠረተ የታክስ መለያ ቁጥር እያንዳንዱ ግብር ከፋይ እንዲይዝ ሙከራ ያደረግነው፡፡ ይህንን ሙከራ በምናደርግበት ወቅት፤ ሁላችሁም እንደምታውቁት ሁለት ችግሮች ናቸው ያጋጠሙን፡፡ አንደኛው ችግር፡- ጫካ ሲመነጠር፤ ሽፍታ መደበቅ አይችልም፡፡ ስለዚህ ሽፍታ ማድረግ ያለበት የመጀመሪያው ሥራ፤ ጫካው እንዳይመነጠር መከላከል ነው፡፡ በዚህ ጫካ ውስጥ የነበሩት ሽፍቶችም፤ ጫካው እንዳይመነጠር ከግራም ከቀኝም ከፍተኛ ተቃውሞና ጩኸት ነበር ያሰሙት፡፡

ሁለተኛው ችግራችን፡- ጫካውን ለመመንጠር የሚንቀሳቀሰው ኃይላችን የተልፈሰፈሰ መሆኑ ነው፡፡ ዓላማቸው ምን እንደሆነ፣ በዚህ ተጎጂ ማን እንደሆነ፣ በትክክል ማስጨበጥ አልቻልንም፡፡ የአእምሯዊ ንብረት ውጤቶች የሆኑትን ዘርፎች ብቻ ለይተን ከኪራይ ሰብሳቢነት ነጻ ልናወጣቸው አንችልም፡፡ ጫካው ነው መመንጠር ያለበት፡፡ በጥቅሉ ጫካው ሲመነጠር ማን ምን እየሠራ እንደሆነ፣ ማን በምን የንግድ መስክ እንደተሰማራ በርግጠኝነት ለማወቅ የምንችልበት የመረጃ ሥርዓት ከፈጠርን በኋላ፤ (ብርሃን ሲሆን፣ ገለጥለጥ ሲል ሌባ

ሊደበቅ ስለማይችል) በዚህ ዓይነት መቆጣጠር እንችላለን፡፡ የንግድ ሥርዓቱን በጠቅላላ ግልጽነት የተላበሰ እንዲሆን ለማድረግ እንጂ፤ ዋናው አጀንዳችን ግብር መሰብሰብ አልነበረም፡፡ ነገር ግን ‘ይሄንን ያህል ግብር ይቆለልባችኋል፣ ይሄንን ያህል ትከፍላላችሁ፤’ የሚሉት ጫካውን የሚያስጠብቁ ሽፍቶች በነዙት ውዥንብር እና የራሳችን መልፈስፈስ ተደማምሮ፤ ሕብረተሰቡ ውስጥ በዚህ ጉዳይ ላይ ትክክለኛ ግንዛቤ ሳይያዝ ሥራው የሚስተጓጎልበት ሁኔታ ተፈጥሯል፡፡

አሁን የባዶ ሲዲ ጉዳይ መጥቷል፡፡ በብዙ መስኮች የሚያጋጥሙን ይህንን የመሳሰሉ ችግሮች ናቸው፡፡ ባዶ ሲዲ በሙሉ የኮንትሮባንድ መሣሪያ ነው ማለት ያስቸግራል፡፡ ነገር ግን፤ በተጠቀሰው ልክ ለሕጋዊ ዓላማ ይውላል ለማለት ደግሞ በጣም አስቸጋሪ ነው የሚሆነው፡፡ ለሕጋዊ ዓላማ የሚውለውንና ለሕገወጥ የሚውለውን መለየት ላይ ነው እየተቸገርን ያለነው፡፡ ‘ማባዣ መሣሪያዎች ሕገ ወጥ በሆነ መንገድ እየገቡ ነው፤’ ተብሏል፡፡ የቁጥጥር ችግር ነው፡፡ እንደዚህ ዓይነቱን የቁጥጥር ድክመት፤ ቅድም ባነሳነው መልኩ እናየዋለን፡፡ ዋናው ጉዳይ ሕጋዊ የንብረት መብታችሁ ቢከበር አብዛኛው የኢኮኖሚ ጥያቄ ይመለሳል የሚለው ነው፡፡”

IV.የሥነ-ጥበብ መሠረተ ልማት ላይ መንግሥት ቢሰማራ፤ በሚል የቀረበው

ሀሳብ ላይ ሲተቹ፤“የመሠረተ ልማት ጉዳይን በተመለከተ፤

‘ቴአትር ቤቶች በአገር አቀፍ ደረጃ ያሉት አምስት ናቸው፡፡ አምስቱም ደግሞ በአዲስ አበባ የሚገኙ ናቸው፤’ በሚል የተነሳ ጉዳይ አለ፡፡ የቴአትር ቤቶች ጉዳይ፣ የማሰልጠኛ ተቋሞች ጉዳይ፣ የአርት ጋለሪዎች ጉዳይና የመሳሰሉት የሥነ-ጥበብ መሠረተ ልማት ጉዳዮች ተነስተዋል፡፡ ነገሩ ከአዲስ አበባም በላይ ወጣ ብሎ በየክልሎቹ መስፋፋት አለበት፡፡ በአዲስ አበባ ብቻ ሊታጠር አይችልም፡፡ እዚህ ላይ ግንዛቤ ሊወሰድ የሚገባው፤ በተቻለ መጠን መንግሥት የግሉ ዘርፍ ሊሠራው ከሚችለውና ሊሠራው ከሚገባው ሥራ መውጣት አለበት፡፡ የሲኒማ ቤቶችና የቴአትር ቤቶች ባለቤት ሆኖ፤ ይህንን በዘላቂነት እያስፋፋ መኖር የለበትም፡፡ በርግጥ የተወሰኑ ምርጥ አገራዊ ፋይዳ ያላቸው ቴአትር ቤቶች በመንግሥት አስተዳደር ሥር የሚተዳደሩ መኖር አለለባቸው፡፡ ይሄ በሌሎችም አገሮች የተለመደ ጉዳይ ነው፡፡ ነገር ግን፤ ዘላቂው መፍትሄ መንግሥት ሁሉንም መሠረተ ልማቶች እያሟላ እንዲሄድ ማድረግ አይደለም፡፡ ከትምህርት ተቋሞች እና ከተወሰኑ የተመረጡ የሥነ-ጥበብ መሠረተ ልማቶች ውጪ የተቀረው የዘርፉ ተዋንያንና የግሉ ዘርፍ ሊሰሯቸው የሚገቡ ተግባራት ናቸው፡፡ ስለዚህ መንግሥት የሚሠራውን ለይተን፤ መንግሥት አሁን ካለው አቅም በመነሳት፤ ምን ምን ሊሠራ ይችላል? በመንግሥት ሊሠራ የማይችለውን ደግሞ በምን መልኩ ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት እንዲሠሩት ማድረግ ይቻላል? ብለን በጋራ ዘርዝረን ብናወጣውና ወደ ተግባር ብንገባ የተሻለ ይሆናል፤ የሚል ሀሳብ አለኝ፡፡”

V. የሥነ-ጥበቡ እንቅስቃሴ፤ የኢንቨስትመንት ማበረታቻ አያስፈልገው ይሆን? ወይስ ‘በማይበረታቱት ዘርፎች’ ውስጥ የተያዘ ይሆን? ለሚለው የጥበብ

ሰዎች ጥያቄ የሰጡት ምላሽ፤ “ከማትጊያዎች ወይም “ኢንሴንቲቭዝ”

ጋር የተነሳው ጉዳይ፤ በእኔ ግምት ዋና ጉዳይ አይደለም፡፡ ‘የወረቀት ዋጋ ሰማይ ተሰቅሏልና

ሥነ-ጥበብ ወገቡ ላይ ተመቷል፤’ ሊባል የሚችል አይመስለኝም፡፡ በተመሳሳይ መልኩ፤ በኢንቨስትመንት ማበረታቻ ውስጥ ከገቡት ውስጥ አልገባም፣ የኢንቨስትመንት ማትጊያ ተጠቃሚ አይደለም፤ ተብሏል፡፡ ማበረታቻ የሚሰጠው ለሁሉም ኢንቨስትመንቶች አይደለም፡፡ በጣም አስፈላጊ ተብሎ ለሚወሰድ ኢንቨስትመንትም አይደለም፡፡ የኢንቨስትመንት ማበረታቻ የሚሰጠው፤ አስፈላጊ ሆኖ ሳለ፤ የግሉ ዘርፍ ሊገባበት የማይፈልግ ሲሆን፣ ገበያው በቂ ምላሽ ያልሰጠውን ዘርፍ ለማበረታታት የኢንቨስትመንት ማበረታቻ ይሰጥ ነበር፡፡ አሁን ግን፤ የውርስ ንብረት ይመስል፤ ዘመድ አዝማድ በሙሉ ተካፍሎታል፡፡ የገበያ ጉድለት ያለውም የሌለውም የኢንሴንቲቭ ተጠቃሚ ሆኗል፡፡

ይህ የሆነው መንግሥትም ቢያንስ በተወሰነ ደረጃ ዓላማውን በሳተ መልኩ ስለተረጎመው ነው፡፡ በሌላ መልኩ ደግሞ፤ ሕብረተሰቡም በአግባቡ ስላልተገነዘበው ነው፡፡ በዚህ ምክንያት፤ የሆቴል ማንኪያና ሹካ በኢንሴንቲቭ ሊስት ውስጥ ገብቶ፤ ከታክስ ነፃ ይገባል፡፡ በተመሳሳይ ቴሌቪዥን፣ በተመሳሳይ መልኩ ስሚንቶ… ያልገባ ነገር የለም፡፡ መጨረሻ ላይ ሁሉም የሚገኙት ግን መርካቶ ነው፡፡ በዚህ አቅጣጫ መሄድ ስለማንችል አሁን ዘርፎቹን እያጠበብንና እየቀነስን አንጂ እያስፋፋን አንሄድም፡፡ በገበያው የሚመለሱ ነገሮች በገበያው ይመለሳሉ፡፡ በገበያ የማይመለሱ ሆነው ሲገኙ ብቻ ነው ማትጊያው ሊሰጣቸው የሚገባው፡፡

‘ለሥነ-ጥበብ ውጤቶች፤ የኢንሹራንስና የባንክ ብድር አገልግሎት እንዲሰጥ በሚለው ላይ፤’ ቴክኒካሊ የሚከለክል ሕግ የለም፡፡ ነገር ግን፤ የባንኮቻችን ፕሮጀክት የማጥናትና የመገምገም ብቃት ውሱንነት አለው፡፡ ስለዚህ “ጨርቃጨርቅ ፋብሪካ አቋቁሜ ማትረፍ እችላለሁ፤” ብሎ የቀረበ ፕሮጀክት መገምገም ካስቸገራቸው፤ “ፊልም ሠርቼ ማትረፍ አችላለሁ፤” የሚለውን ፕሮጀክት ለመገምገም በይበልጥ ሊቸገሩ እንደሚችሉ ምንም ጥርጥር የለውም፡፡ የሚሸከሙትም ኃላፊነት(Risk) ይለያያል፡፡ ጨርቃጨርቅ ፋብሪካ ቢከስር፤ ቢያንስ ሕንፃውን ያገኛሉ፡፡ የፊልም ፕሮጀክቱ ከከሰረ ግን የሚያዝ ቋሚ ንብረት ያለ አይመስለኝም፡፡ ስለዚህ ዘርፉ ኢኮኖሚው እያደገ (Complex)፤ እየሆነ ሲሄድ አብሮ የሚመጣ ነገር ነው እንጂ፤ ዘለን ለመግባት የምንሞክርበት አይደለም፡፡ ዘለን ከገባንበት ደግሞ፤ ‘ያለወቅቱ የተወለደ ሕፃን’ ይሆንና ይሞትብናል፡፡ ሀሳቡ ግን፤ በሌሎች ሀገሮች የተሠራበት ነው፤ ጥሩ ሀሳብም ነው፡፡ ዘርፉን በደንብ የሚያውቁ፣ በዘርፉ የተሻለ እውቀት ያላቸው፣ ጥሩ ተስፋ ያለውን የጥበብ ሥራ ተስፋ ከሌለው ሥራ፤ ከቢዝነስም ከሙያም አንጻር መለየት የሚችሉ ናቸው በዚህ ዘርፍ ቢሰማሩ በይበልጥ ውጤታማ የሚሆኑት፡፡ በሥነ-ጥበብ መስክ ስኬታማ የሆናችሁ፣ ገንዘብ ያገኛችሁ (ጥቂቶች ልትሆኑ ትችላላቸሁ)፤ እናንተ ናችሁ ዘርፉን ይዛችሁ ልትወጡ የምትችሉት፡፡ ሌላው ዘርፉን በሚገባ ያልተገነዘበ፤ እንኳን መንግሥት ባለሀብትም ቢሆን ኃላፊነት ይውሰድ ቢባል፤ ከአቅም በላይና አስቸጋሪ ይሆናል፡፡”

በማለት ነበር አቶ መለስ የመንግሥትን አቋም ያብራሩት፡፡ ከዚህ ውይይት የሥነ-ጥበቡ ማኅበረሰብም ሆነ ሕብረተሰቡ ምን ተገነዘበ? እነደ ሌሎች የመንግሥት አስተሳሰቦች በሦስተኛ ወገን ምን ያህል ተተቸ?... እስከ ዛሬ ያልተነሳ ጉዳይ ነው፡፡ ቀጣዩ መጣጥፌ፤ ደርጀት ያለውን የዚህን ውይይት ትችት የያዘ ይሆናል፡፡

ሥነ-ጥበብ...

ይቆየን!

35°”l 6— ¯Sƒ lØ` 119 ግንቦት 2006 ዓ.ም

ኤልሻማ ድንጋይ

ቅርስ

አስገራሚ ሠው ሁሌም አለ፡፡ አስገራሚ የእንስሳ ወይም የሠው አፈጣጠርም አለ፡፡ ድንጋይ ግን ድንጋይ ነው፡፡ ግን ድንጋይ ከድንጋይነቱ በዘለለ አስገራሚ አፈጣጠር ይዞ መገኘቱ ትንሽ ሣያነጋግር አይቀርም፡፡ በተለይ የኮንስትራክሽን ቤተሠቦች ይሄን ድንጋይ ሲያዩት ምራቃቸውን ዋጥ፤ ዓይናቸውን በመጎምዠት ፈጠጥ ማድረጋቸው አያጠራጥርም፡፡

አንድ ግንበኛ ወይም የቤት ግንባታ ባለሙያ የሚፈልግበት ቦታ ላይ ተገቢውን ቅርፅ የያዘ ድንጋይ "ስክት" ብሎ ሲገባለት ይደሰታል፡፡ ታዲያ ይሄን ደስታውን ለማግኘት ይለፋል፣ እጅግ ብዙ አስፈላጊ ጉልበት ይባክናል፡፡ ላቡን ያንጠፈጥፋል፡፡ "ለምን?፣ እንዴት?" ቢሉ መጀመሪያ ለግንባታው የተቆለለው ድንጋይ ቅርፅ አልባና ግራ የሚያጋባ ቋጥኝ ድንጋይ ነው፡፡ ለምሣሌ፣ "ላዳ ታክሲን" የሚያክል ድንጋይም ሊሆን ይችላል፡፡ ታዲያ ይሄን የሚያህል ድንጋይ ቅርፅ ሣናወጣለት እንዲሁ እንዳለ ለግንባታ በቀጥታ አናውለውም፡፡ መቀጥቀጥ አለበት፡፡ ቅርፅ ያላቸው ብዙ የግንባታ ድንጋዩች እስኪወጣው ድረስ በሠው ጉልበት ሲቀጠቀጥ ይውላል፡፡ በዚህ ጊዜ ብዙ ጉልበትና ጊዜ እንዲሁም ገንዘብ ይባክናል፡፡ ብዙ ወጣቶችም ከመንግሥት ቦታ በመረከብ ከመሬት ውስጥ ቅርፅ አልባ ቋጥኝ ድንጋይ በብዙ ድካም በማውጣት ቅርፅ እያበጁ ለቤት ግንባታ አቅርቦት በመስጠት ላይ ናቸው፡፡ የሚያገኙት ክፍያና የሚያባክኑት ጉልበትና ጊዜ ባይመጣጠንም ስራውን ግን ተያይዘውታል፡፡ የስራ ዘርፉም "ድንጋይ ፈለጣ" ይባላል፡፡ (ጥቃቅንና አነስተኛ ወጣቶችን ሲያደራጅ ዳቦ ሳይቆርስ ያወጣላቸው ስያሜ መሆኑ ነው፡፡)

የድንጋዩ ቀለም ቢጫ ነው፡፡ በመሬት ውስጥ ያለው ክምችት እጅግ ብዙ፤ የጥልቀቱ መጨረሻ የማይታወቅ እና እንደተለመደው ቋጥኝ ድንጋይ አይደለም፡፡ አራት ማዕዘን፣ ሶስት ማዕዘን፣ ሞላላ፣ ክብ፣ ጠፍጣፋ የመሣሰሉት ልዩ ልዩ ቅርፆች የያዘ ድርብርብ ድንጋይ ነው፡፡ ሠው ያስቀመጠው፣ የደረደረው ይመስል ከመሬት ውስጥ ተከማችቶ ይገኛል፡፡ (ፎቶውን ይመልከቱ) ይህን ሀብት አውጥቶ ለመጠቀም እንደ አዲስ አበባዎቹ የድንጋይ ፈለጣ ወጣቶች ቡድን መሮ፣ መራጃና ድጅኖ ወይም ሌሎች ቁሶች አያስፈልጉም፤ ላብ አይንጠፈጠፍም፣ ለቀናት ቅርፅ ለማውጣት ሲቀጠቅጡ መዋል አያሻም፡፡ የሚያስፈልገው ነገር ቢኖር ከበላዩ ያለውን ለም አፈር አነስ ባለች ዶማ ቆፈር አድርጐ ሲፈልጉ በእንጨት ወይም በአንዲት የብረት ዱላ ይህን የተደረደረ ባለ ቅርፅ ድንጋይ ፈንቀል፣ ፈንቀል እያደረጉ እያንዳንዱን ቅርጹ ያለቀለት ድንጋይ መኪና ላይ መጫን፡፡ ከዚያም ለግንበኛው ባለሙያ መስጠት፡፡

የድንጋዩ መገኛ ቦታ ስያሜ እና ይዘት፡- ድንጋዩ የሚገኘው በአማራ ክልል በደቡብ ወሎ

ዞን ካሉት 23 የገጠር ወረዳዎች ውስጥ ጃማ ወረዳ በተባለው ቦታ ይገኛል፡፡

"ኤልሻማ ድንጋይ" ከስምንት በላይ ቅርፆች ያሉት በተፈጥሮው ተደርድሮ ያለ ሲሆን ካስፈለገም ድንጋዩን በማድቀቅ ለአርማታ ሙሊትና ለመሣሠሉት መጠቀም ይቻላል፡፡ ኤልሻማ ድንጋይ ከትንንሽ እስከ ትላልቅ መጠን ያላቸው ቢኖሩም የትልቁ ቅርፅ ድንጋይ ክብደት ከፍተኛ በመሆኑ በአንድ ሠው አይነሳም፡፡ ለምሣሌ አራት ማዕዘኑን ብንመለከት ስፋቱ በግምት አንድ ክንድ በአንድ ክንድ ሲሆን ክብደቱ ከ10-15 ኪሎግራም ይመዝናል፡፡ (ከዚህም ስፋት የሚያንሱ አራት ማዕዘን ድንጋዮች አሉ)፡፡ ድንጋዩ በተፈጥሮው ጠንካራና ብረት መሠል

ድንጋይ ከመሆኑ በተጨማሪ እጅግ ውብ ነው፡፡ በኤልሻማ ድንጋይ የተገነባ ቤት ከ150 ዓመት በላይ ያለ እድሳት፤ 60 ዓመት ደግሞ ከእድሣት በኋላ መቆየት እንደሚችል አንዳንድ ምሁራን ይናገራሉ፡፡ ድንጋዩ በኤልሻማ ቀበሌ መሬት ላይ ከ4-5 ኪሎ ሜትር ስፋት ተከማችቶ ይገኛል፡፡ በመሬት ውስጥ ያለው ሃብትም እጅግ ግዙፍ የድንጋይ ክምችት እንደሆነ ተገምቷል፡፡

በሃገራችን ሚዛን የሚደፉና የማይደፉም በርካታ ጥናቶች ተደርገዋል፤ የሃገሪቱን ሃብቶች ጥቅም ላይ ለማዋል የተደረገ አመርቂ ጥናት መኖሩ ግን ያጠራጥራል፡፡ በቲያትሪካል አርት ተመርቆ በወረዳው ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት ሲሰራ የነበረው ወጣት ኢሳያስ ገላው ደግሞ “የፈረሰ የግንብ ከተማ ነው ማለትም ይከብዳል፤ አምላክ በተዓምሩ የሠራው ነው ብሎ እርግጠኛ መሆንም አይቻልም” በሚል በሁለት ተቃራኒ ሃሣቦች ይገልጸዋል፡፡ እንደ ኢሳያስ አባባል “የኤልሽማን ድንጋይ አመጣጥና አፈጣጠር ለማወቅ ሳይንሣዊ መፍትሔ ያሻዋል፡፡ የወረዳው አስተዳደር በሃገሪቱ ውስጥ ካሉት ከፍተኛ የምርምር ተቋማት ጋር ግንኙነት በመፍጠር ቦታውን የማስጠናት ሃላፊነቱን ሊወጣ ይገባል” ይላል፡፡ አንዳንድ ጥናቶች የኤልሻማ ድንጋይ ሠው የደረደረው መስሎ ውበቱን ጠብቆ ከከርሰ ምድር ውስጥ መገኘቱ የሆነ ሚስጥር እንዳለው ያስገምታል ይላሉ፡፡ የግምታቸው መነሻ ቀበሌው በ1914 ዓ.ም "አሮጌ ከተማ" ይባል እንደነበርና በአፄ ምንሊክ ጊዜ የወሎ ንጉስ የነበሩት ንጉስ ሚካኤል "ራስ ወሌ" የተባሉ ገዢ ሾመውበት ቦታውን ያስተዳድሩት እንደነበር መረጃ ስላገኙበት ነው፡፡ ከዚህ በመነሳት ከክፍለ ዘመናት በፊት በዚህ አካባቢ ግዙፍ ከተማ ተገንብቶ ፈርሷል ወይም ወደ መሬት ሰምጧል የሚል ግምት ሰጥተዋል፡፡ ከ1914ዓ.ም በፊት "አሮጌ ከተማ" በሚል በንጉሥ ሚካኤል ስር በነበሩት በራስ ወሌ (የምንሊክ የዝምድና ሀረግ ያላቸው) ይተዳደር እንደነበርም ይነገራል፡፡ ስለዚህ የፈረሰች ከተማ ካለች ማን? እንዴት? መቼ? የሚሉት ጥያቄዎች ለመመለስ የየዘርፉ ባለሙያዎች ጥናት ቢያካሄዱበት መልካም ነው፡፡

ከብዙ ዓመታት በፊት የነበረ የግንብ ከተማ ወደ መሬት ሰምጦ ነው የሚል የጥናት ውጤት ካለም፤ የወረዳው አስተዳደር እና ህዝቡ ቦታውን ታሪካዊ የቱሪስት መስህብ ማድረግ ስለሚችል

ድንጋዩን ከመሸጥ ያድነዋል፡፡ ቅርስ ይጐበኛል እንጂ አይቸበቸብምና፡፡ ከግለሰቦችና አንዳንድ በቡድን ከተደራጁ ድንጋይ ፈላጮች በተጨማሪ የወረዳው አስተዳደር ለከተማው የመንገድ ዝርጋታ ስራ እየተጠቀመበት ይገኛል፡፡ አጥኚዎች “ይህ ቦታ ጥንታዊ ከተማ ነው” ካሉ ወረዳው በግዴለሽነት ቅርስ እያጠፋ ይገኛል እንደማለት ነው፡፡ በተማራማሪዎች ጥናት ተደርጎበት ቁርጡ እስኪታወቅ ድረስ ይህ አስገራሚ ውብ ድንጋይ ከሠዎች ንኪኪና ከመሸጥ መጠበቅ አለበት፡፡ ወረዳው የድንጋይ ችግር ስለሌለበት ከሌሎች አማራጭ ቦታዎች (ለምሣሌ ኩታዬ አፋፍ) ለተለያዩ የመሰረተ ልማት አገልግሎቶች ሆነ ለሌላ ግንባታ መጠቀም አለባቸው፡፡

የፈረሰ ከተማ ሣይሆን ራሷ ተፈጥሮ በግርምት የሠራችው ውብ ድንቅ ድንጋይ ነው የሚል ከሆነም ደግሞ፤ አሁንም የወረዳው አስተዳደር ቦታውን በመከለል ወረዳው ከፍተኛ ገቢ የሚያገኝበትን አሠራር ቀይሶና ከሚገኘው ገቢ የወረዳው ህዝብ ተጠቃሚ እንዲሆን ማድረግም ኃላፊነቱ ነው፡፡ አንድም በአስገራሚነቱ የቱሪስት መስህብ ይሆናል፡፡

ይህ በኤልሻማ ቀበሌ የሚገኘው ድንጋይ በደንብ መታወቅ ከጀመረ ከ10 ዓመታት በላይ ሆኖታል፡፡ ባለፉት ዓመታት ያለማቋረጥ በአርሶ አደሮች ቁጥጥር ስር ሆኖ ለተለያዩ አገልግሎቶች ሲውል ቆይቷል፡፡ የወረዳው አስተዳደርም በማወቅ ይሁን ባለማወቅ ለተለያዩ የአገልግሎት መስጫ ዘርፎች ግንባታ ተጠቅሞበታል፡፡ እንደ አሁኑ ትውልድ ማንነቱ፣ ምንነቱና ከየትነቱ በደንብ ተለይቶ ያልታወቀውን የወረዳውን ትልቅ ሀብት በተለያዩ አካላት ለጥፋት እየተዳረገ ይገኛል፡፡ "ያሉንን ሃብቶች ለልማት ልናውላቸው ይገባል" የሚል ልማታዊ አካሄድን መንግስት እያከናወነና እየከወነ እንዳለ በየዕለቱ ይሰማል፡፡ የጃማ ወረዳ አስተዳደር አፍንጫው ስር ስላለው የራሱ አስገራሚ የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃን ተላልፎ እያሣየ ያለው ደንታቢስነት ሊቀንስና እንደአስፈላጊነቱ በባለሙያዎች አስጠንቶ የቱሪስት መስህብነቱን እንዲያስጠብቅለት ያሻል፡፡ ስለዚህ ይህ ከተመራማሪዎች ዕይታ የተሸሸገውን ድንጋይ ለግንባታ በሚል ተሽጦ እንዳያልቅ ወደ አለመኖር እንዳይደርስ ከወዲሁ ሊታሰብበት ያሻል፡፡ አስፈላጊውን ጥበቃ እንዲያደርግለት ግድ ይለዋል እላለሁ፡፡

‹‹ኤልሻማ ድንጋይ›› በአብዱሠይድ ይማም

አስገራሚው

36 °”l 6— ¯Sƒ lØ` 119 ግንቦት 2006 ዓ.ም

አርአያ

በእርግጥ “ትልቅ ነበርን ትልቅ እንሆናለን” የሚለው መፈክር ወይንም መሪ ቃል እውን ሆኖ የምናይበት የሽግግር ዘመን ላይ እንገኛለን ብለው ተስፋ የሚያደርጉ ኢትዮጵያውያን አሉ፡፡ ይህን ለማለታቸው ደግሞ አልፎ አልፎ በዓለማቀፉ መድረክ በብርቱ ተፎካክረው እያሸነፉ ያሉ፣ የተስፋ ጭላንጭል የሚያሳዩ ኢትዮጵያውያንን ለምስክርነት ይቆጥራሉ፡፡

በዓለም አቀፍ ደረጃ ታዊቂ ከሆኑ ግዙፍ የምርምር ተቋማት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እያበረከቱ ያሉና የነበሩ በሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፎች የበለጠጉ ውጤታማ ኢትዮጵያውያን ተመራማሪዎችና የሥራ ኃላፊዎችን በስፋት እያየን ስማቸው ሲነሳ እያደመጥን ነው፡፡

ከነዚህ በርካታ ኢትዮጵያዉያን ምሁራን ተመራማሪዎች ውስጥ እድሜው አርባ ለመሙላት ሁለት ደመራ የቀረው ወጣቱ ተመራማሪ ዶክተር ሰለሞን አሠፋን እነሆ፡፡

ኢትዮጵያዊው ሳይንቲስት ዶ/ር ሰለሞን አሠፋ በዓለማችን በተለያዩ ዘርፎች በሚያደርገው እንቅስቃሴ ስመጥር በሆነው በግዙፉ አይ ቢ ኤም የተባለ ኩባንያ ውስጥ ተቀጥሮ ነው የሚሠራው፡፡ በተሰማራበት የሥራ ዘርፍ ከፍተኛ የምርምር ሥራ ያከናወነው ኢትዮጵያዊው ዶክተር ሰለሞን አሠፋ በዚህ ያላሰለሰ ጥረቱ በመስኩ ከፍተኛ እውቅና የተሰጠው ባለሙያዎች ተርታ መቀመጥና መጠራት ችሏል፡፡

“ከልጅነቴ ጀምሮ የአንድን ነገር አሠራር እንዲሁም አፈጣጠር ምንነትና እንዴትነት፣ የሚሰጠውን ጠቀሜታ በተመለከተ በጥልቀት ለማወቅ እተጋ ነበር፤ ይህንን ዝንባሌዬን የተረዱ ቤተሰቦቼ በዚሁ እንድገፋ የበኩላቸውን እገዛ አድርገውልኛል፡፡ ለዛሬው እኔነቴ ለደርስኩበት ስኬት የወላጆቼ ሚና ከፍተኛ ነው፡፡ እቤታችን ውስጥ ያለው ራዲዮ ድምፅ እንዴት ሊያስተላልፍ ይችላል? እኛ ሳናያቸው ተናጋሪዎቹ ራዲዮ ውስጥ ገብተው የሚሠሩ እንደሆነ እንዴት ለእኛ ሳይታይ ራዲዮኑ ውስጥ ገብተው ያወራሉ? በሚል ጥያቄ ታዳጊው አእምሮዬ ያለማቋረጥ ያሰላስል ነበር፡፡ አንድ ቀን ያንን እንቆቅልሽ ለማወቅ አባቴ እንደውድ እቃው የሚያያትን ራዲዮኑን ደብቄ ወደ ጓሮ ወስጄ በመፍታታት ሰዎቹን ለማግኘት ያደረኩት ሙከራ ፈፅሞ አይረሳኝም፡፡” ይላል ዶክተር ሰለሞን አሠፋ፡፡

የአንደኛና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ከአጠናቀቀ በኋላ ወደ ዩኒቨርሲቲ ለመግባት የሚያስችለውን ውጤት ካገኘ በኋላ የመረጠው የፊዚክስ ትምህርትን ነበር፤ በዚሁም የመጀመሪያውን ዲግሪ ከትምህርት ክፍሉ በማዕረግ አጠናቀቀ፡፡

ወደ ዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ ለማቅናት ዕድል ያገኘው ወጣቱ ሰለሞን አሠፋ በአሜሪካ የከፍተኛ ትምህርቱን በመቀጠል በዓለም አቀፍ ደረጃ በታዋቂው የማሳቹስቴት ኢንስቲትዩት ኦፍ ቴክኖሎጂ (ኤም አይ ቲ) በተባለ ተቋም በመግባት የሁለተኛ ዲግሪውን ያገኛል፡፡ የማስተርስ ዲግሪውን ለማግኘት በተቋሙ የመመረቂያ ጥናቱን በአደረገበት መስከ ተስፋ ሰጭ ውጤት ቀጣይ የምርምር አቅጣጫ ያሣየ ነበር፡፡ የዩንቨርሲቲው ሴኔት የኢንስቲትዮቱ አካዳሚክ ኮሚሽን ዶክትሬት ዲግሪውን እንዲያገኝ ነፃ የትምህርት ዕድልን ለወጣቱ ተመራማሪ ለሰለሞን አሠፋ በመስጠት በዩንቨርሲቲው የምርምርና ሥርዓት ክፍል ውስጥ እንደ ብልጭታ ያሣያቸውን የተመራማሪነት ክህሎቱን እንዲሁም በምርምር ማዕከል ውስጥ መስራትን እንዲለማመድ ሁኔታዎችን አመቻቹለት፡፡

በተቋሙ የሚሰጠውን የድህረ ምረቃ ትምህርቱን በማዕረግ አጠናቆ ዶክትሬት ዲግሪውን ካገኘ በኋላ ተቀማጭነቱ በአሜሪካ በሆነው ዓለም አቀፍ ዕውቅና ባለው የ አይ ቢ ኤም ኩባንያ ተቀጥሮ መስራት ጀመረ፡፡

ከሥራው ጋራ በተያያዘ በምርምርና ጥናት ላይ በማተኮሩ በአጭር ጊዜ ውስጥ የታዋቂዎቹ የአሜሪካ

“በአዲሱ ትውልድ ተስፋ አደርጋለሁ” ዶ/ር ሰለሞን አሠፋ

የምርምርና ጥናት ሥራዎች ላይ በግንባር ቀደምትነት ተሳትፈዋል፡፡ ኢትዮጵያዊው ሳይንቲስት ሰለሞን አሠፋ በፎቶ ቴክኖሎጂ ዙሪያ ባደረገው ለዓመታት የዘለቀ ምርምር በስኬት በማጠናቀቅ-ሲ ኤም ኦ ኤስ የሲልካን ፎቶ ቶኒክ ክርስቲያል ዲቨይሰን-ፎቶ ቶኒክ አንቲካል ኢንተርኮኔክት-በኳንተም ኮምኒኬሽን የኢንፎርሜሽን ፕሮሰሲንግ መረጃ ማስተላለፊያ አዲስ ቁስ ለመፈብረክ በመቻል በመስኩ በዓለማችን የመጀመሪያ አዲስ የሆነ የምርምር ውጤትን ይፋ አደረጓል፡፡

በምርምር ያገኛቸውን ሶስት ግኝቶችን በሥራ ላይ እንዲውሉ መላው ዓለም ከምርምር ሥራዎቹ ተጠቃሚ እንዲሆን በመሻት የፓተንት መብት እንዲያገኙ ከተደረጉ በኋላ የሚሠራበት የአይ ቢ ኤም ኩባንያ በዓለም አቀፍ ደረጃ በሚገኙ ተቋማቶቹ አማካይነት ዶክተር ሰሎሞን አሰፋን የናኖ ፎቶ ቶኒክ ኢንቴግሬሺን ቴክኖሎጂ የኮሜርሻል ሲኤም ኦሲ ማደራጃና ማዘጋጃ ተቋምን በኃላፊነት እንዲመራ ሾመው፡፡

ኢትየጵያዊው ሳይንቲስት ዶክተር ሰለሞን አሠፋ በዓለም ዙሪያ በሚገኙ ሀገሮች የሚገኙ የአይ ቢኤም ቅርንጫፍ ኩባንያዎችና ቢሮዎች እያዘጋጁ በሚያካሂዷቸው ዓለም አቀፍ የእውቀት ሽግግርና በዘመኑ የመረጃ ማስተላለፊያ ሂደትን የተቀላጠፈ ለማድረግ ያስቻሉ የኦፕቲካል ፋይበር የሌዘር ኤሌክትሮ አንቲካል ግኝቶችን አጠቃቀምና ያላቸውን ፋይዳ በተመለከተ ሰፊ ስልጠና የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮችን ከሌሎች የሥራ ባልደረቦቹ በአባልነት ባቀፈ ግብረሃይል መሪ በመሆን ስልጠናዎችን ሰጥቷል፡፡

ኢትዮጵያዊ ሳይንቲስት ሰለሞን አሠፋ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ መቀመጫውን በናይሮቢ ኬኒያ ባደረገው በአፍሪካ የመጀመሪያውንና ግዙፉን ቤተሙከራ አይ ቢ ኤም ሲያቋቁም ቤተሙከራውን በማደራጀት ሥራውን በኃላፊነት በመምራት የተሰለፈበትን ኃላፊነት በአግባቡ ከመወጣቱ ጐን ለጐን የምርምርና ጥናት ሥራውን በትጋት እያከናወነ ይገኛል፡፡

በዚህ በግሎባላይዜሽን ዘመንም የሕይወትን ውጣውረዶች ለማቅለል የሚረዳ በኢንተርኔትና በድምፅ ወምስል ከብዙ ሺህ ኪሎሜትር ርቀት ካለ ወዳጅ ጋር መገናኘት የሚያስችለውን ሳይንሳዊ ግኝት ለዓለሙ መድረክ አበርክቷል፡፡

አንቲካል ሶሳይቲና የዓለም የስነፈለክ ተመራማሪዎች ማኅበር እንዲሁም የኤለክትሪካልና የኤለክትሮኒክስ ምሕንድስና ባለሙያዎች ማኅበር አባል ንቁ ተሣታፊ ሆነ፡፡

ኢትዮጵያዊው ወጣት ዶክትር ሰለሞን አሠፋ ለምርምር ሥርዓት እንቅስቃሴዎች ላይ ሲያከናውነው በነበረው ተግባሩ በዋትሰን የምርምር ተቋም በተመራማሪነት መሥራት ጀመረ፡፡ በዚህም በዓለም አቀፍ ደረጃ ለሚካሄዱ የምርምር ሥራዎች ስኬታማነት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያደረጉ ተመራማሪ ወጣት ሳይንቲስቶችን ለማበረታታት የሚሰጥ ሽልማት ተሸላሚ ለመሆን ያስቻለውን ስኬት ተቀዳጀ፡፡

በዓለም አቀፍ ደረጃ ውጤታማ ምርምር ካከናወኑ ወጣት ሳይንቲስቶች አንዱ በመሆን በ 35 ዓመቱ በ 2011 ከፍተኛ እውቅና ያለውን የ “ቲ አር 35 የተሰኘውን በማሳቹሴትስ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዮት አዘጋጅነት” የሚለውን ሽልማት አግኝቷል፡፡ በመቀጠልም በግዙፍ ዓለም አቀፋዊ ተቋም በአይ ቢ ኤም ዳይሬክተሮች ቦርድ አዘጋጅነት የሚሰጡትን “የቴክኒካል አኮምንሊሽመንት አዋርድ፤ ኮርንፊት ሪኮርዴሺን አዋርድ የተሰኙ አለም አቀፍ ሽልማቶችን ለማግኘት የበቃበትን የምርምር ሥራ አከናውኗል፡፡

በዋትሰን የምርምር ተቋም ከሚሠሩ ከፍተኛ ዕውቅና ያላቸው ተመራማሪዎች ጋራ በመሆን በተለያዩ