የሰለፎች ግንዛቤ - nesihaa.com · ቁርአን መረጃ መሆኑን ማንም...

7
Page1 የሰለፎች ግንዛቤ ፈህሙ አስ-ሰለፍ ሰለፎች ስንል እኛን የተቀደሙ እና በመልካም ስራቸው አርአያ ሆነው ያለፉ አበው የሰሀባ እና እነርሱን በመልካም የተከተሉ ታቢዒዮች ለማለት ነው። የሰለፎችን ግንዛቤ መከተል ሁሉንም ሙስሊሞች ወደ አንድ ቀጥተኛ እና ስኬታማ መንገድ የሚያመጣ ንትርኮችን እና አለመግባባቶችን ሁሉ የሚፈታ ልዩ መርህ ነው። ቁርአናዊ መልዕክቶችን አስመልክቶ ብዙ ሰዎች የተለያየ ትንተና ይሰነዝራሉ፡፡ ቁርአን መረጃ መሆኑን ማንም አይጠራጠርም፡፡መሠረታዊ በሆነ መልኩ ሙስሊሞች ሁሉ ቁርአንን ይቀበላሉ፡፡ ነገር ግን የቁርአን መልዕክት ላይ የግንዛቤ ልዩነት ሲፈጠር ውዝግብም ሲከተል ማነው የሚዳኘን? የሚለው ወሳኝ ጥያቄ ነው። ምላሹም «ቁርአንና ሐዲሥን መገንዘብ እና መተግበር የሚጠበቅብን አላህ (ሱ.ወ) ቁርአንና ሐዲሥን በትክክል እንደተገነዘቡትና እንደተገበሩት በመሰከረላቸው ሰሀቦች እና እውነተኛ ተከታዮቻቸው ግንዛቤ ብቻ ነው» የሚለው ነው። የመልዕክተኛዉ ንግግርም በዚሁ መልኩ ይታያል። ለምሳሌ አንድ ሰው ብዙ መልዕክቶችን ቢያስተላልፍልን፣ እከሌ ልጄ ነው፣በጣም የሚገነዘብ ልጅ ነው፣ እኔ ያልኩትን በሚገባ ተገንዝቧል፣ ተግባራዊ በሆነ መልኩ ያልኩትን ፈጽሟል፣ ስለዚህም እርሱ የሚላችሁን ስሙ ካልገባችሁ ወደርሱ ተመለሱ ብሎ ቢለን፡፡ እኛ በሆነ ርዕስ ላይ ከተጨቃጭቀን «አባትህ እንዲህ ሲል ምን ለማለት ፈልጎ ነው?» በማለት ልጁን እንጠይቀዋለን። አባትህ ምን ለማለት ፈልገው ነው? እንለዋለን፡፡ እርሱም «እኔ እኮ ይህንን ትዕዛዙን በዚህ

Upload: others

Post on 16-Sep-2019

23 views

Category:

Documents


0 download

TRANSCRIPT

Page 1: የሰለፎች ግንዛቤ - nesihaa.com · ቁርአን መረጃ መሆኑን ማንም አይጠራጠርም፡፡መሠረታዊ በሆነ መልኩ ሙስሊሞች ሁሉ ቁርአንን

Page

1

የሰለፎች ግንዛቤ

ፈህሙ አስ-ሰለፍ

ሰለፎች ስንል እኛን የተቀደሙ እና በመልካም ስራቸው አርአያ ሆነው ያለፉ አበው የሰሀባ እና እነርሱን በመልካም የተከተሉ ታቢዒዮች ለማለት ነው። የሰለፎችን ግንዛቤ መከተል ሁሉንም ሙስሊሞች ወደ አንድ ቀጥተኛ እና ስኬታማ መንገድ የሚያመጣ ንትርኮችን እና አለመግባባቶችን ሁሉ የሚፈታ ልዩ መርህ ነው። ቁርአናዊ መልዕክቶችን አስመልክቶ ብዙ ሰዎች የተለያየ ትንተና ይሰነዝራሉ፡፡

ቁርአን መረጃ መሆኑን ማንም አይጠራጠርም፡፡መሠረታዊ በሆነ መልኩ ሙስሊሞች ሁሉ ቁርአንን ይቀበላሉ፡፡ ነገር ግን የቁርአን መልዕክት ላይ የግንዛቤ ልዩነት ሲፈጠር ውዝግብም ሲከተል ማነው የሚዳኘን? የሚለው ወሳኝ ጥያቄ ነው። ምላሹም «ቁርአንና ሐዲሥን መገንዘብ እና መተግበር የሚጠበቅብን አላህ (ሱ.ወ) ቁርአንና ሐዲሥን በትክክል እንደተገነዘቡትና እንደተገበሩት በመሰከረላቸው ሰሀቦች እና እውነተኛ ተከታዮቻቸው ግንዛቤ ብቻ ነው» የሚለው ነው። የመልዕክተኛዉ ንግግርም በዚሁ መልኩ ይታያል።

ለምሳሌ አንድ ሰው ብዙ መልዕክቶችን ቢያስተላልፍልን፣ እከሌ ልጄ ነው፣በጣም የሚገነዘብ ልጅ ነው፣ እኔ ያልኩትን በሚገባ ተገንዝቧል፣ ተግባራዊ በሆነ መልኩ ያልኩትን ፈጽሟል፣ ስለዚህም እርሱ የሚላችሁን ስሙ ካልገባችሁ ወደርሱ ተመለሱ ብሎ ቢለን፡፡ እኛ በሆነ ርዕስ ላይ ከተጨቃጭቀን «አባትህ እንዲህ ሲል ምን ለማለት ፈልጎ ነው?» በማለት ልጁን እንጠይቀዋለን። አባትህ ምን ለማለት ፈልገው ነው? እንለዋለን፡፡ እርሱም «እኔ እኮ ይህንን ትዕዛዙን በዚህ

Page 2: የሰለፎች ግንዛቤ - nesihaa.com · ቁርአን መረጃ መሆኑን ማንም አይጠራጠርም፡፡መሠረታዊ በሆነ መልኩ ሙስሊሞች ሁሉ ቁርአንን

Page

2

መልኩ ተገንዝቤ ፈጽሜዋለሁ፣ ሠርቼዋለሁ፣ ምንም አላወገዘኝም፤ እንደውም አጽድቆልኛል» ይለናል፡፡

የሰለፎችን ግንዛቤ ማስቀደምና መቀበል ግዴታ መሆኑን የሚገልጹ በርካታ መረጃዎች አሉ። ጥቂቶቹን እንዳስሳለን፦

1- አላህ (ሱ.ወ) ቁርአንን ከማንም ይበልጥ መልዕክቱን እንደ ተገነዘቡት፣ የአላህን ትዕዛዛት እንደፈጸሙ፣ ክልከላዎችንም እንደራቁ፣ የሚፈለገው ቦታ ላይ እንደደረሱ የመሰከረላቸው የነብዩ ባልደረቦች ናቸው፡፡ እነዚህ የመጀመሪያዎቹ ቀዳሚዎች ከሙሓጂሮችና ከአንሳር፣ እነርሱንም በመልካም የተከተሉአቸውን አላህ (ሱ.ወ) ጀነትን አዘጋጅቶላቸዋል፡፡ አላህ (ሱ.ወ) በዱንያ ላይ እያሉ ጀነት እንደሚገቡ መስክሮላቸዋል፣ ለሁሉም ሥራቸውን እንደወደደላቸው ጠቁሞናል፡-

ከስደተኞቹና ከረዳቶቹም የመጀመሪያዎቹ ቀዳሚዎች፤ እነዚያም በበጎ ሥራ የተከተሉአቸው፤ አላህ ከነርሱ ወዷል (ሥራቸውን ተቀብሏል)፤ ከእርሱም ወደዋል (በተሰጣቸው ምንዳ ተደስተዋል)፤ በሥሮቻቸውም ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶች በውስጣቸው ዘላለም ነዋሪ ሲሆኑ ለነርሱ አዘጋጅቶላቸዋል፤ ይህ ታላቅ ዕድል ነው፡፡ (ሱረህ አት-ተውባህ፡100)

በዱንያ ህይወታቸው ዲኑንም ሕግጋቱንም በውዴታ ተቀብለው እንደነበረው ሁሉ እንደዚሁ የአላህን ምንዳ በውዴታ ተቀብለዋል፡፡

Page 3: የሰለፎች ግንዛቤ - nesihaa.com · ቁርአን መረጃ መሆኑን ማንም አይጠራጠርም፡፡መሠረታዊ በሆነ መልኩ ሙስሊሞች ሁሉ ቁርአንን

Page

3

በዚህ መልኩ አላህ (ሱ.ወ) ቃል ኪዳኑን ሲገልጽላቸው ሙሓጂሮችና አንሳሮች ብቻ ሳይሆኑ የተጠቀሱት ከሙሓጂሮችና ከአንሳሮች ውጭ በመልካም የተከተሉአቸውም ተጠቅሰዋል፡፡ በበጎ ሥራ የተከተሉአቸው የሚለው ግን መስፈርት ነው።

ይህንን ደረጃ ለማግኘት ከነርሱ በኋላ መምጣት ብቻ ሳይሆን እነርሱን “ቢኢሕሳን” በመልካም ሥራ፣ በበጎ ተግባር መከተል የግድ ነው፡፡ ስለዚህ አል-ሙሓጂሩን ወል አንሳርን መከተል የግድ ይሆናል ማለት ነው፡፡ ማንኛዉም ሙስሊም ትልቁ የሚፈልገው ነገር ጀነት መግባት፣ የአላህን ውዴታ ማግኘት ነው፡፡ አላህ (ሱ.ወ) የሰሀቦች ጉዞ ለጀነት እንዳበቃቸው ከነገረን ይህ የተሞከረ መንገድ ትክክለኛ መንገድ ስለመሆኑ በፍጹም ሳንጠራጠር ግንዛቤያቸዉን ማስቀደም ይጠበቅብናል።

ይህ አንቀጽ ፈህሙ አስ-ሰለፍ፣ ከሁሉ አስቀድሞ ሶሓቦች ቁርአንና ሐዲሥን በተገነዘቡበት መልኩ መገንዘብ የግድ መሆኑን የሚገልጽ አንቀጽ ነው፡፡

2- በሌላ አንቀጽ ላይ ተከታዩን መልዕክት እናገኛለን፦

ቅኑም መንገድ ለርሱ ከተገለጸ በኋላ መልዕክተኛውን የሚጨቃጨቅና ከሙእሚኖቹ መንገድ ሌላ የሆነን የሚከተል ሰው (በዚህ ዓለም) በተሾመበት (ጥመት) ላይ እንሾመዋለን (በመረጠው ላይ እንተወዋለን)፤ ገሀነምንም እናገባዋለን፤ መመለሻይቱም ከፋች፡፡ (ሱረህ አን-ኒሳእ፡115)

Page 4: የሰለፎች ግንዛቤ - nesihaa.com · ቁርአን መረጃ መሆኑን ማንም አይጠራጠርም፡፡መሠረታዊ በሆነ መልኩ ሙስሊሞች ሁሉ ቁርአንን

Page

4

በዚህ አንቀጽ ላይ (ከሙእሚኖቹ መንገድ ሌላ የሆነን የሚከተል) ሲል ሙእሚኖች የሚለው ቃል መጀመሪያ የሚገባው ለሶሓቦች ነው ስለዚህ ከነርሱ መንገድ ውጭ መውጣት አደጋ ነው ማለት ነው፡፡ በተለይ አንቀጹ በነርሱ ዘመን የወረደ እንደመሆኑ መጠን የመጀመሪያዎቹ ተጠቃሾች እነርሱ ናቸው፡፡ ሌሎቹ በዚህ ውስጥ ሊካተቱ ይችላሉ፡፡ ይህም አንቀጽ ከሰሀቦች ግንዛቤና አካሄድ ያፈነገጠ ሁሉ የጥፋትን መንገድ እንደያዘ ያስረዳል።

3- በሌላ የቁርአን አንቀጽም አላህ(ሱ.ወ) እንዲህ ይላል፡-

በርሱ ባመናችሁበት ብጤ ቢያምኑ በርግጥ ተመሩ፤ ቢዞሩም እነርሱ በጭቅጭቅ ውስጥ ብቻ ናቸው፡፡ (ሱረህ አል-በቀራህ፡137)

ይህ አንቀጽ ግልጽ በሆነ መልኩ እንደሚያመለክተው የሰለፎች እምነትና ግንዛቤ ከእነርሱ በኋላ የሚመጡ ሰዎችን ሁሉ የሚዳኝ መመዘኛ ነው። እናንተ (ሶሓቦች) ባመናችሁበት ካመኑ ቀጥተኛዉን መንገድ ተመርተዋል እናንተ (ሶሓቦች) ባመናችሁበት ብጤ ካላመኑ ግን መንገድ ስተዋል፣ ጠመዋል ማለት ነው፡፡ ሰሀቦች በእውነተኛ ተከታይነታቸው እና በመልካም ግንዛቤያቸው ለሰው ልጆች ሁሉ ተምሳሌት ናቸው፡፡

4 - የአላህ መልዕክተኛ በትክክለኛ ሐዲሥ ላይ ሰሒሕ ነው ገይሪማ እንደሚናገሩት ቢሪዋየት ዒምራን እብን ሐሰን ይላሉ፡-

الذين مث يلوم الذين مث قرين الناس خري «: وسلم عليه اهللا صلىرسول اهللا قال رواه البخاري ومسلم » يلوم

Page 5: የሰለፎች ግንዛቤ - nesihaa.com · ቁርአን መረጃ መሆኑን ማንም አይጠራጠርም፡፡መሠረታዊ በሆነ መልኩ ሙስሊሞች ሁሉ ቁርአንን

Page

5

«ከሰዎች ሁሉ የተሻለው ትውልድ የኔ ትውልድ ነው፡ ቀጥሎም ተከታዮቻቸው፡ ቀጥሎም ተከታዮቸቸው» ይላሉ፡፡ ‹ቀርን› የሚለው ቃል በቁርአንና በሐዲሥ ክ/ዘመኑ (ጊዜው) ወይ ደግሞ በክ/ዘመን ውስጥ የሚኖሩት ትውልዶችን ሊያመለክት ይችላል፡፡ በቁርአን ዉስጥ በብዛት ትውልድ በሚለው ነው የሚተረጎመው፡፡

ከዚያም ከኋላቸው ሌሎችን ትውልዶች አስገኘን፡፡ (ሱረህ አል-ሙእሚኑን ፡ 31)

በዚህም ሀዲስ ላይ ‹ቀርን› የሚለው ቃል ዘመኑን ሳይሆን በክፍለዘመኑ የኖሩትን ምርጥ ትዉልዶች ይመለከታል። መልዕክተኛ “ቀጥሎም ተከታዮቸቸው” እነርሱን ተክተው የሚመጡ፣ ማለትም የታቢዒዮች ትውልድ ማለት ነው፡፡ አስከትለዉም “ቀጥሎም ተከታዮቸቸው” ናቸው አሉ፡፡ በዚህ መልኩ የአላህ መልዕክተኛ ሦስት ትውልዶችን አወድሰዋል፡፡ “ሰለፉ ሷሊሕ” ደጋግ አበው ትውልዶች (ሰለፎች) የሚባሉት እነርሱ ናቸው፡፡ ይህ ውዳሴ ያለ ምክንያት አይደለም፡፡

ዐብደሏህ ኢብን መስዑድ (ረ.ዐ) ስለሶሓቦች (ረ.ዐ) ሲናገር ምን ይላል፡-

قد مبن فليسنت مستنا منكم كان من( : عنه اهللا رضي مسعود بن اهللا عبد قال قلوبا األمة هذه أبر حممد أصحاب أولئك ، الفتنة عليه تؤمن ال احلي فإن ، مات

هلم فاعرفوا ، دينه وإقامة نبيه لصحبة اهللا اختارهم قوم ، تكلفا وأقلها علما وأعمقها ) املستقيم اهلدى على كانوا فإم ، ديهم ومتسكوا حقهم

Page 6: የሰለፎች ግንዛቤ - nesihaa.com · ቁርአን መረጃ መሆኑን ማንም አይጠራጠርም፡፡መሠረታዊ በሆነ መልኩ ሙስሊሞች ሁሉ ቁርአንን

Page

6

(የምትመሩበትና አርአያ አድርጋችሁ የምትይዙት ሰው ካስፈለገ በሀቅ ላይ እያለ የሞተው፣ ያለፈው ሰው ይሻላችኋል።በህይወት ያለ ፈተናን ይፈራለታል። እነዚያ የረሱል ባልደረቦች፤ የርሳቸው ሶሓቦች ናቸው፡፡ ከማንም ይበልጥ ቅን ልቦና ያላቸው ፤ ከማንም የበለጠ የጠለቀ ዒልም ያላቸው፣ ጥልቅ ዒልም የነበራቸው ናቸው፡፡ ከአቅም በላይ ይሆነ መፍጨርጨር የሌለባቸው ናቸው። የመልዕክተኛው ባልደረቦች እንዲሆኑና ዲኑንም እንዲያቋቁሙ የመረጣቸው ትውልዶች እነርሱ ናቸው፡፡ ለነርሱ የሚገባዉን ክብር እወቁላቸው። አካሄዳቸዉን አጥብቃችሁ ያዙ። በእርግጥም በቀጥተኛው ጎዳና ላይ ነበሩ።)

5 - ኢጅማዕ ወይም የዑለማዎች ስምምነት በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ በቁርአንና በሐዲሥ ላይ የተመረኮዘ ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ከኢጅማዕ ውስጥ የሚካተት አንድ የኢጅማዕ መገለጫ የሆነ ርዕስ ወይም ክፍል አለ፡፡ እርሱም ፈህሙ አስ-ሰለፍ የሰለፎች ግንዛቤ ነው። የሰለፎች ግንዛቤ ግዴታ መሆኑን ከሚጠቁሙ መረጃዎች መካከል ኢጅማዕ መረጃ ለመሆኑ ከቁርአንና ከሐዲሥ የሚጠቀሱ መረጃዎች የገኙበታል። የኢጅማዕ መረጃዎች ሁሉ ለፈህሙ አስ-ሰለፍም መረጃ ናቸው፡፡ ምክኒያቱም የሰለፎች ግንዛቤ የሚባለው የኢጅማዕ አንድ መገለጫ ክፍል ነው፡፡ ፈህሙ አስ-ሰለፍ ሲባል የሁሉም ሰለፎች የጋራ አቋም እንጂ የተወሰኑት ግለሰቦች ግንዛቤ ብቻ ለማለት አይደለም፡፡ የሰለፎችን ግንዛቤ እንከተል ሲባል የአብዱላህ ኢብኑ መስዑድን ወይም የአብዱላህ ኢብኑ ዓባስን አለያም የኢማም አሕመድ ኢብን ሐንበል ወይም የሻፊዒይን የግል ግንዛቤ እንከተል ለማለት አይደለም፡፡ የሁሉንም የጋራ ግንዛቤ እና አቋም ለማለት ነው። አላህ (ሱ.ወ) እነርሱን ያወደሰበት ላይ ከነርሱ ኋላ እንጓዝ ነው፡፡ ስለዚህ ቅድም የኢጅማዕ መረጃ ነው ብዬ የጠቀስኩት አንቀጽ ለፈህሙ አስ-ሰለፍም መረጃ ይሆነናል ማለት ነው፡፡ ስለዚህም የኢጅማዕ መረጃዎች ሁሉ ለፈህሙ አስ-ሰለፍም መረጃ ናቸው፡፡

Page 7: የሰለፎች ግንዛቤ - nesihaa.com · ቁርአን መረጃ መሆኑን ማንም አይጠራጠርም፡፡መሠረታዊ በሆነ መልኩ ሙስሊሞች ሁሉ ቁርአንን

Page

7

በመጨረሻዎቹ ዘመናት የኖሩ ብዙ ኡለማዎችም የሰለፎችን ክብር እና ደረጃ አብራርተዋል። ኢብኑ ረጀብ “በያን ፈድል ዒልሚ ሰለፍ ዐላ ዒልሚል ኸለፍ” «የሰለፎች እውቀት ከምትኮች(ኸለፍ) እውቀት መብለጡን መግለጫ» የሚል ጽሁፍ አላቸው፣ እብኑ ረጀብ በዚሁ መጽሀፍ ላይ እንደጠቀሱት «አንዳንድ ሰው ንግግሩ ከበዛ ዒልሙ የበዛ ይመስላል፡፡ ነገር ግን ሰለፎች ንግግራቸው ትንሽ ነበር፡፡» ሌሎችም ይህንን አባባል ጠቅሰዉታል። በብዛት ስናስተውል የሆነ ርዕስ ላይ ሲጠየቁ አንድ ቃል፣ ወይ ሁለት ቃል ይመልሳሳሉ፡፡ ንግግራቸው ትንሽ ነበር፡፡ ዒልማቸው ግን ብዙ ነበር፡፡ ነገር ግን ጊዜ እየገፋ ሲሄድ በተቃራኒው ንግግርና ወሬ እየበዛ መጣ፡፡ ዒልሙ ግን እያነሰ ሄደ፡፡

አላህ በእውነት ሰለፎችን ተከትለን በሰለፍያ ጎዳና ላይ እስከ ህይወት ፍጻሜ የምንጸና አላህ ያድርገን።

የአላህ ሰላም እና እዝነት በመልዕክተኛው በቤተሰቦቻቸዉና በባልደረቦቻቸው ላይ ይሁን። ምስጋናም ለአላህ የተገባ ነው።