* p hß ß0 16 1//6 Á÷ - ethiopia media...

16
ነፃነት አራተኛ ዓመት ቁ.87 ቅዳሜ ህዳር 27 /2007 ዓ.ም የኢትዮጵያ ህዝብ የሉዓላዊ ስልጣኑ ባለቤት እንዲሆን እንታገል! ዋጋው 8 ብር Visit us :- www.fnotenetsanet.com, www.andinet.org በነፃነት የማሰብ ሰለባው ተመስገን ደሳለኝ 12 7 4 13 5 5 የምርጫ ስትራቴጂ እንዴት ይሁን? ሕገ-መንግስቱ ባለቤት አልባ ነው ለምርጫ 2007 ከህዝቡ ምን ይጠበቃል? ህገመንግስት የፀደቀበትን ቀን ከማክበር፣ህገመንግስትን ማክበርን ሊያስቀድም ይገባል! የጉልበተኞች “ቀይ መስመር” የምንታገለው፣ ምን ዓይነት ስርዓት ለማምጣት ነው? አቶ ተማም አባቡልጉ (የህግ ጠበቃ) ህጉን ቅቡል ለማድረግ ይሄን አይነት አገላለፅ በመንግስት ባለስልጣናት መቅረቡ በራሱ የኢትዮጵያን ነፃነትና ሉዓላዊነት የሚዳፈር ነው ብዬ የማምነው፡፡ የእነ አንዷለም አራጌ አቤቱታ ውድቅ ተደረገ ሰማያዊ ፓርቲ፣ ዛሬ የአዳር ሰልፍ እንደሚያደርግ ይጠበቃል ኢህአዴግ ካድሬዎቹን ወደ ትምህርት ቤቶች እያሰረገ ነው መድረክ፣ የጠራው የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ እውቅና አገኘ “ውሳኔው በሀገራችን ነፃ የፍትህ ስርአት እንደሌለ አመላካች ነው” አንድነት ፓርቲ በሽብርተኝነት ወንጀል ተጠርጥረው በጠቅላይ ፍርድ ቤት ውሳኔ ጥፋተኛ የተባሉት የአንድነት ለፍትህና ለዴሞክራሲ (አንድነት) አመራሮች እንዲሁም የመኢዴፓ አመራር ያቀረቡት አቤቱታ ውድቅ መደረጉን የተከሳሾቹ ጠበቃ ለፍኖተ ነፃነት ገለፁ፡፡ የአንድነት አመራር የሆኑት አቶ አንዷለም አራጌ ፣ አቶ ናትናኤል መኮንን ፣ የመኢዴፓ አመራር ፣ አቶ ክንፈሚካኤል አበበ (አበበ ቀስቶ) ለፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ያቀረቡት አቤቱታ ውድቅ ተደርጎ የስር ሠማያዊ ፓርቲ፣ በዛሬው ዕለት ከጠዋቱ 3፡00 ጀምሮ "ነፃነት ለፍትሐዊ ምርጫ" በሚል ርዕስ እስከ እሁድ ስድስት ሰዓት ድረስ የሚዘልቅ የአዳር ሠላማዊ ሠልፍ እንደሚያደርግ አስታወቀ፡፡ ፓርቲው በተለያዩ የከተማዋ ክፍሎች እየተዘዋወረ የተለያዩ በራሪ ወረቀቶችን እና የመኪና ላይ ቅስቀሳዎችን ያደረገ ሲሆን በማህበራዊ ድረ-ገፁ እንዳሰፈረውም “ . . . የህዝብን ፍርድ ቤቱ ውሳኔ እንዲፀናባቸው ተደርጓል፡፡ ፍርድ ቤቱ ፣ ዓቃቤ ሕግ በሰውና በሰነድ ማስረጃ ድርጊቱን አረጋግጧል በማለት የመከላከያ ማስረጃቸውን ውድቅ በማድረግ ጥፋተኛ ብሎአቸው አቶ አንዷለም አራጌ ላይ የእድሜ ልክ ፅኑ እስራት ፣ አቶ ናትናኤል መኮንን ላይ የ18 ዓመታት ፅኑ እስራትና አቶ ክንፈ ሚካኤል ደበበ ላይ የ 25 ዓመታት ፅኑ እስራት መበየኑ ይታወሳል፡፡ ሰበር ሰሚ ችሎቱ የአቶ ክንፈ ሚካኤል ደበበን (አበበ ቀስቶ) የ25 ዓመታት ፅኑ እስራት ወደ 16 ዓመታት ዝቅ ያደረገ ሲሆን ፣ በአቶ አንዷለም እና አቶ ናትናኤል ላይ የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ እንዲፀና አድርጓል፡፡ የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የህግ ስህተት ተፈፅሟል ማለት እንደማይቻል በመግለፅ አቤቱታውን ውድቅ እንዳደረገው ለማወቅ ተችሏል፡፡ የአንድነት ፓርቲ ተ/የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አስራት አብርሃ የፍርድ ቤቱን ውሳኔ አስመልክተው ለፍኖተ ነፃነት በሰጡት አስተያየት “አመራሮቻችን የተከሰሱት አላግባብ ነው፤ ሽብርተኞች እንዳልሆኑም ይታወቃል፡፡ ከስር እስከ ሰበር ፍ/ቤት የተሰጠው ውሳኔ የፍትህ ስርዓቱን በመንግስት መጠለፍ ያሳያል፡፡” ብለዋል፡፡ ድምፅ በማፈን እና አማራጭ የዴሞክራሲ ሀይሎችን በማሠርና በማሳደድና በመግደል ዳግም የይምሰል ምርጫ ለማካሄድ ሽር ጉድ እያለ ነው፡፡ . . . በዚህ ታሪካዊ ቀን ሁላችንም አደባባይ በመውጣት ለነፃነታችን እና ለለውጥ በጋራ ድምፃችንን እናሠማ . . .” የሚል ጥሪን አስተላልፏል፡፡ በአራዳ ክፍለ ከተማ ፒያሳ አካባቢ ለአዳር ሰልፉ ሲቀሰቅሱ ከነበሩት መካከል የሰማያዊ ፓርቲ አባላት የሆኑት ሜሮን አለማየሁ፣ ወይንሸት ንጉሴ፣ ባህረን እሸቱ፣ ማቲያስ መኩሪያ እንዲሁም ጉለሌ ክፍለ ከተማ ውስጥ ሲቀሰቅስ የነበረው ሲሳይ በፖሊስ ተይዘው መታሰራቸው ተገልጿል፡፡ የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ ዮናታን ተስፋዬ ፣ ስለጉዳዩ በሰጡን አስተያየት “ማዘጋጃ ቤት እስከ አሁን እውቅና እንዳልሰጣቸውና በፖሊሶች ከፍተኛ ጫና እያደረሰባቸው መሆኑን ገልጸው ሰልፉን ከማድረግ ወደኋላ እንደማይሉ አስታውቀዋል፡፡ " " " " 8

Upload: others

Post on 08-Sep-2020

1 views

Category:

Documents


0 download

TRANSCRIPT

Page 1: * p Hß ß0 16 1//6 Á÷ - Ethiopia Media Forumethioforum.org/amharic/wp-content/uploads/2014/12/finote-netsanet … · እንዲቀየር በፖለቲካው ጨዋታ ሜዳ አስገድዶታል፡፡

ነፃነትአራተኛ ዓመት ቁ.87ቅዳሜ ህዳር 27 /2007 ዓ.ም የኢትዮጵያ ህዝብ የሉዓላዊ ስልጣኑ ባለቤት እንዲሆን እንታገል! ዋጋው 8 ብር

Visit us :- www.fnotenetsanet.com, www.andinet.org

በነፃነት የማሰብ ሰለባው ተመስገን ደሳለኝ12

7

4

13

55

የምርጫ ስትራቴጂ እንዴት ይሁን?

ሕገ-መንግስቱ ባለቤት አልባ ነው

ለምርጫ 2007 ከህዝቡ

ምን ይጠበቃል?

ህገመንግስት የፀደቀበትን ቀን ከማክበር፣ህገመንግስትን ማክበርን ሊያስቀድም ይገባል!

የጉልበተኞች “ቀይ መስመር”የምንታገለው፣ ምን

ዓይነት ስርዓት ለማምጣት ነው?

አቶ ተማም አባቡልጉ (የህግ ጠበቃ)

ህጉን ቅቡል ለማድረግ ይሄን አይነት አገላለፅ በመንግስት ባለስልጣናት መቅረቡ

በራሱ የኢትዮጵያን ነፃነትና ሉዓላዊነት የሚዳፈር ነው ብዬ የማምነው፡፡

የእነ አንዷለም አራጌ አቤቱታ ውድቅ ተደረገ

ሰማያዊ ፓርቲ፣ ዛሬ የአዳር ሰልፍ እንደሚያደርግ ይጠበቃል

ኢህአዴግ ካድሬዎቹን ወደ ትምህርት ቤቶች እያሰረገ ነው

መድረክ፣ የጠራው የተቃውሞ

ሰላማዊ ሰልፍ እውቅና አገኘ

“ውሳኔው በሀገራችን ነፃ የፍትህ ስርአት እንደሌለ አመላካች ነው” አንድነት ፓርቲ በሽብርተኝነት ወንጀል

ተጠርጥረው በጠቅላይ ፍርድ ቤት ውሳኔ ጥፋተኛ የተባሉት የአንድነት ለፍትህና ለዴሞክራሲ (አንድነት) አመራሮች እንዲሁም የመኢዴፓ አመራር ፣ ያቀረቡት አቤቱታ ውድቅ መደረጉን የተከሳሾቹ ጠበቃ ለፍኖተ ነፃነት ገለፁ፡፡

የአንድነት አመራር የሆኑት አቶ

አንዷለም አራጌ ፣ አቶ ናትናኤል መኮንን ፣ የመኢዴፓ አመራር ፣ አቶ ክንፈሚካኤል አበበ (አበበ ቀስቶ) ፣ ለፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ያቀረቡት አቤቱታ ውድቅ ተደርጎ የስር

ሠማያዊ ፓርቲ፣ በዛሬው ዕለት ከጠዋቱ 3፡00 ጀምሮ "ነፃነት ለፍትሐዊ ምርጫ" በሚል ርዕስ እስከ እሁድ ስድስት ሰዓት ድረስ የሚዘልቅ የአዳር ሠላማዊ ሠልፍ እንደሚያደርግ አስታወቀ፡፡

ፓርቲው በተለያዩ የከተማዋ ክፍሎች እየተዘዋወረ የተለያዩ በራሪ ወረቀቶችን እና የመኪና ላይ ቅስቀሳዎችን ያደረገ ሲሆን በማህበራዊ ድረ-ገፁ እንዳሰፈረውም “ . . . የህዝብን

ፍርድ ቤቱ ውሳኔ እንዲፀናባቸው ተደርጓል፡፡

ፍርድ ቤቱ ፣ ዓቃቤ ሕግ በሰውና በሰነድ ማስረጃ ድርጊቱን አረጋግጧል በማለት የመከላከያ ማስረጃቸውን ውድቅ በማድረግ ጥፋተኛ ብሎአቸው አቶ አንዷለም አራጌ ላይ የእድሜ ልክ ፅኑ እስራት ፣ አቶ ናትናኤል መኮንን ላይ የ18 ዓመታት ፅኑ እስራትና አቶ ክንፈ ሚካኤል ደበበ ላይ የ 25 ዓመታት ፅኑ እስራት መበየኑ ይታወሳል፡፡

ሰበር ሰሚ ችሎቱ የአቶ ክንፈ ሚካኤል ደበበን (አበበ ቀስቶ) የ25 ዓመታት

ፅኑ እስራት ወደ 16 ዓመታት ዝቅ ያደረገ ሲሆን ፣ በአቶ አንዷለም እና አቶ ናትናኤል ላይ የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ እንዲፀና አድርጓል፡፡ የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የህግ ስህተት ተፈፅሟል ማለት እንደማይቻል በመግለፅ አቤቱታውን ውድቅ እንዳደረገው ለማወቅ ተችሏል፡፡

የአንድነት ፓርቲ ተ/የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አስራት አብርሃ የፍርድ ቤቱን ውሳኔ አስመልክተው ለፍኖተ ነፃነት በሰጡት አስተያየት “አመራሮቻችን የተከሰሱት አላግባብ ነው፤ ሽብርተኞች እንዳልሆኑም ይታወቃል፡፡ ከስር እስከ ሰበር ፍ/ቤት የተሰጠው ውሳኔ የፍትህ ስርዓቱን በመንግስት መጠለፍ ያሳያል፡፡” ብለዋል፡፡

ድምፅ በማፈን እና አማራጭ የዴሞክራሲ ሀይሎችን በማሠርና በማሳደድና በመግደል ዳግም የይምሰል ምርጫ ለማካሄድ ሽር ጉድ እያለ ነው፡፡ . . . በዚህ ታሪካዊ ቀን ሁላችንም አደባባይ በመውጣት ለነፃነታችን እና ለለውጥ በጋራ ድምፃችንን እናሠማ . . .” የሚል ጥሪን አስተላልፏል፡፡

በአራዳ ክፍለ ከተማ ፒያሳ አካባቢ ለአዳር ሰልፉ ሲቀሰቅሱ ከነበሩት መካከል የሰማያዊ ፓርቲ አባላት የሆኑት ሜሮን

አለማየሁ፣ ወይንሸት ንጉሴ፣ ባህረን እሸቱ፣ ማቲያስ መኩሪያ እንዲሁም ጉለሌ ክፍለ ከተማ ውስጥ ሲቀሰቅስ የነበረው ሲሳይ በፖሊስ ተይዘው መታሰራቸው ተገልጿል፡፡

የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ ዮናታን ተስፋዬ ፣ ስለጉዳዩ በሰጡን አስተያየት “ማዘጋጃ ቤት እስከ አሁን እውቅና እንዳልሰጣቸውና በፖሊሶች ከፍተኛ ጫና እያደረሰባቸው መሆኑን ገልጸው ሰልፉን ከማድረግ ወደኋላ እንደማይሉ አስታውቀዋል፡፡

"

"

"

"8

Page 2: * p Hß ß0 16 1//6 Á÷ - Ethiopia Media Forumethioforum.org/amharic/wp-content/uploads/2014/12/finote-netsanet … · እንዲቀየር በፖለቲካው ጨዋታ ሜዳ አስገድዶታል፡፡

የኢትዮጵያ ህዝብ የሉዓላዊ ስልጣኑ ባለቤት እንዲሆን እንታገል!

ፍኖተ ነፃነት

Visit us :- www.fnotenetsanet.com, www.andinet.org

አራተኛ ዓመት ቅፅ 4 ቁ 872 ቅዳሜ ህዳር 27 2007 ዓ.ም

“ግዜው 1998 ዓ.ም ነው፡፡ የስምጥ ሸለቆዋ ሐዋሳ የኢህአዴግን ጠቅላላ ጉባኤ እያዘጋጀች ነው፡፡ ጉባኤው ከሌሎች ግዜያት በተለየ ከፍ ያለ የሀሳብ ሙቀት

የተስተዋለበትም ነበር፡፡ ከስብሰባው ቀደም ብሎ ሰላሳ ሺህ ሰዎችን “መደራጀት የምትፈልጉት በምን መልኩ ነው?” ብሎ መጠይቅ በትኖ 92 በመቶ የሚሆኑትን “የብሔር አደረጃጀት አንፈልግም!” የሚል ግብረ መልስ የያዘው ቡድን፤ ኢህአዴግን ወደ ወጥ-ፓርቲ ቅርጽ በሚለውጥ መልኩ ሙግቱን ገፍቶበታል፡፡ በአንጻሩ ከፍተኛ የብሔር ድጋፍ አለን የሚለውን ህወሓት የሚወክሉት ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ “ይህን ጉዳይ ለስራ አስፈጻሚው ውክልና ይሰጥ” በማለት ጉባኤውን ጠየቁ ፡፡ ኢህአዴግ ወጥ ፓርቲ መሆን አለበት ብለው ሲገፉ የነበሩት ተፈራ ዋልዋ ቆመው ጭምር በመናገር ጉባኤው ታሪካዊ ውሳኔ ወስኖ እንዲሄድ ተማጸኑ፡፡የጉባኤው አባላት ግርታ ላይ የወደቁ መሰሉ፡፡ በዚህ መሀል ነበር፡- “አላማችንን ለማሳካት የትኛው አደረጃጀት ይሻለናል የሚለውን በጉባኤ ከምንወስን ዝርዝር ጥናት ሰርተን በሌላ ግዜ ብንመለከትው ይሻለል” በማለት አቶ በረከት ስምኦን ሀሳብ ያቀረቡት፡፡ በዚህ የአቶ በረከት ሀሳብ ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስተር ድምጽ እንዲሰጥበት አድርገው ሀሳቡን ዘጉት፡፡” ይህንን የሚነግረን የቀድሞ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ሚኒስትር ደኤታ ኤርሚያስ ለገሰ በ‹‹መለስ ትሩፋቶች›› መጸሀፉ ነው፡፡ ይህ የመጸሐፉ ክፍል፡- የግንባሩ መሪዎች የብሄር ጥያቄን እንዴት እንደሚያዩትና በአራቱ መሰረታዊ ድርጅቶች መሀከል በብሄር ጥያቄ ዙሪያ ያለውን ልዩነት ፍንትው አድርጎ ያሳየ ነበር፡፡

የህወሓት ስጋት

ህወሓት በአራቱ አባል ድርጅቶች መሀል ያለው ተደማጭነት ከፍ ያለና እንወክለዋለን በሚሉት ህብረተሰብ ክፍል ዘንድ በቂ የድጋፍ መሰረት በአንጻራዊነት አለኝ ብሎ የሚያምን ድርጅት ነው፡፡ የዚህ ድርጅት ዋንኛ የስጋት ምንጭ ሊሆን የሚችለው ግን፡- ‹‹የብሄር-ተኮር ቅርጽ ቢጠፋ ወይም ቢፈርስ ህወሓት ይሟሟል›› የሚል ስጋት ነው፡፡ ትልቁን ውቅያኖስ ስንቀላቀል ትንሿ ወንዛችን ትደርቃለች ዓይነት ብሂል፡፡ በተለይም ምስለኔዎችን በየክልሉ ሾሞ አጀንዳ ወደታች ማውረድ ለለመደው፣ የደህንነትና የመከላከያ ሀይልን ለሚዘውረው ህወሓት በአባላቶቹ ላይ የሚታየው የብቃት ችግር እና በሀሳብ

ተቸንክሮ መቅረት ለድርጅቱ የብሄር ፖለቲካን ከፍተኛ የድጋፍ መሰረትና በዘር የመሰባሰቢያ ማዕከል አድርጎ ከመያዝ ውጭ አማራጭ ያለው አይመስልም፡፡

ከአራቱ ግንባር ከመሰረቱት ድርጅቶች አንዱ የሆነው ኦህዴድ ችግር ደግሞ የኦሮሞ ብሄርተኝነት ሳይሆን እንወክለዋለን በሚሉት ህብረተሰብ ክፍል ዘንድ ያለው የተኣማኒነት ችግር ነው፡፡ከአፈጣጠሩ ጀምሮ የብሄሩን ተወላጆች ቅቡልነት ለማግኘት ዳገት የሆነበት ኦህዴድ የብሄር መዋቅርን ለሙሰኝነት መደበቂያ አድርጎታል፡፡ ይህም ድርጅቶቹ ወደ ወጥነት ቢቀየሩ ‹‹በክልሉ ላገኘው የምችለው ዘርፈ ብዙ ጥቅሜን አጣለው›› የሚል ከፍተኛ ሥጋት አለበት፡፡ በተለይም በባለስልጣናቱ የሀብት ማጋበሻ የሆነው የመሬት ንግድ ወደ ወጥነት ብንቀየር ልናጣው እንችላለን የሚለው ስጋት ብሄርተኝነትን ለጥጦ እንዲገፋበት አድርጎታል፡፡

የሀሳብ ተቃርኖና ብዥታው በግልጽ የሚታየው ግን ብአዴንና ደህዴን ላይ ሲሆን፤ ለወከሉት ህዝብ ሊያስተላልፉት ቀርቶ ለራሳቸው እንኳ በቅጡ ያልገባቸውንና ግልጽ ያልሆነላቸውን የብሄር ፖለቲካ ያራምዳሉ፡፡ የቀድሞው ኢህዴን የአሁኑ ብአዴን ቀደም ብሎ በኢትዮጵያዊ ብሄርተኝነት የተዋቀረና ህብረ ብሄራዊ መልክ የያዘ ማዕቀፍ ውስጥ ሲንቀሳቀስ ከቆየ በኃላ፤ ከትጥቅ ትግሉ መልስ ግን ወደ አማራ ማንነት እንዲሰበሰብ ግድ ሆነበት፡፡ ይህም የሆነበት ምክንያት፡- በግንባሩ

እየጋለ በመጣው የብሄር ፖለቲካ ሳቢያ ከጨዋታው ሜዳ ላለመገለል በተለይ በክልሉ እያደገ የመጣው የመአህድ ተቀባይነትን የፈራው ህውሓት፤ ኢህዴንን ወደ ብአዴንነት እንዲቀየር በፖለቲካው ጨዋታ ሜዳ አስገድዶታል፡፡

ሌላኛው የውስጠ-ተቃርኖ ተጠቂ ደግሞ ደኢህዴን ነው፡፡ በአንድ ግዜ ከሃምሳ በላይ የብሄር ማንነቶችን እንዲወክል ተደርጎ የተሰራውና የጋራ ክልላዊ ቋንቋው ሳይቀር ብዥታ ውስጥ ከቶት መቆየቱ ሳያንስ፤ በአብዛኛው አባላቱ ዘንድ ቅሬታ የሚቀርብበት “የሲዳማ ተወላጆች ተጽዕኖ በርትቶአል፤ ጥርት ያለ የብሄር አጀንዳ አልያዝንም” የሚሉ ድምጾች የላቸው የሚያሳየው የተለያዩ ማንነቶችን ወደ ወጥነት ከመለወጥ ውጭ የብሄር መብታቸው አለመከበሩን ያሳያል፡፡በተለይም በግንባሩ ሊሂቃን ዘንድ እንደ ስጋት የሚቆጠረው ወደ ወጥ ፓርቲነት ብንቀየር በሎሎች የብሄር ድርጅቶች እንዋጣለን ስጋት የትብትቡ መሀልን ብሄር ላይ እንዲተክል አድርጎታል፡፡

የትግራይ ብሄር (Tigray ethno-nationalism) በማቀንቀን የጀመረው ህውሓት፤ ይህንኑ ብሄርተኝነት፣ ከግራው የማርክሲዝምና ሌኒኒዝም አመለካከቶች ጋር ለማስታረቅ የሞከረ ቢመስልም፤ ብዙም ርቀት ሳይጓዝ የቀዝቃዛው ጦርነትን ማብቃት ተከትሎ ‹‹አብዮታዊ ዲሞክራት ነኝ›› ቢልም ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር የነጭ ካፒታሊዝም ተከታይ መሆናቸውን ቆይተውም ቢሆን በገደምዳሜ ተናገሩ፡፡ ይህን የድርጅቱን የርዕዮተ-አለም ዥዋዥዌ ለተመለከተ ሊሰጠው የሚችለው ምስል እውነተኛ ማንነቱ የትግራይ ብሄርተኝነት ሆኖ ሎሎች የብሔር ድርጅቶች ከመጡ ልሂቃንን በመጠቀም ርዕዮታዊ ጥራት እና ወጥ-መስመር (ideological conviction) ያለው በማስመሰል የኢኮኖሚ ጥቅምን ብቻ መሰረት ያደረገ፤ ዘላቂነት(consistency) የሌለው ግዜያዊ ጥቅምን ብቻ ትኩረት የሰጠ (Pragmaic and Opportunist) የሆነ መሬትን፤ ሹመትን ፤የኢኮኖሚ ጥቅምን ብቻ መሰረት ያደረገ ድርጅት ነው፡፡ ይህን አይነት ድርጅት ይህ ነው ብሎ ለመፈረጅ እጅግ አዳጋች ያደርገዋል፡፡

በተለይም ቀደም ቀደም ያሉ ተጻራሪ ርዕዮታዊና ፖለቲካዊ አመለካከቶችን፤ በአጭር ርቀት ፖለቲካዊ ፕሮግራሞች ለማስታረቅ ሲመክሩ የነበሩት ጠቅላይ ሚኒስትርን ካጣ ወዲህ ርዕዮተ አለማዊ እርቃኑ የተጋለጠ ይመስላል ፡፡ ቀጣይ የፓርቲው ስጋትም እያደገ የመጣውን የወጣቶች ቁጥር ንረት (youth bulge) ጥያቄዎችን ለመመለስ በተለይም የቀድሞወቅን ስርአት የማያውቅና ከህዝብ ቁጥር ብዛት 64.3 በመቶ የሚሆነው በዚህ ስርአት ያደገ እንደመሆኑ ቆሞ ቀሩንና ያለተቃርኖ መቆም ለከበደው ድርጅት ስጋት መሆኑ የማይቀር ያደርገዋል፡፡

ታላቁ የባስክ ብሄርተኝነት አባት የሆነው Sabino de Arana y Goiri በሀገሩ ስላለው እውነታ ሲናገር እንዲህ ነበር ያለው “All the maketos, aristocratic and plebeian, middle-class and proletarian, learned and ignorant, good and bad, all are enemies of our fatherland.” በኛ ሁናቴም ስንመልሰው ደኢህዴን ሆነ ብአዴን፣ ኦህዴድ ሆነ ህውሓት፣ ገሀዴን ሆነ ሶህዴፓ እነዚህ ሁሉ በብሄር ስም ተቧድነው የተለያየ ጭንብል በማጥለቅ ጭቆናን አፈናን ብዝበዛን በህዝብ ላይ ለማጽናት የሚተጉ አስመሳይ የብሄር ነጋዴዎች መሆናቸውን አንስተውም፡፡

የብሔር ፖለቲካና ኢህአዴግ፤ ከተቃርኖ እስከ ቅርቃር!

ዳግማዊ ተሰማ

Page 3: * p Hß ß0 16 1//6 Á÷ - Ethiopia Media Forumethioforum.org/amharic/wp-content/uploads/2014/12/finote-netsanet … · እንዲቀየር በፖለቲካው ጨዋታ ሜዳ አስገድዶታል፡፡

ፍኖተ ነፃነት

Visit us :- www.fnotenetsanet.com, www.andinet.org

3የኢትዮጵያ ህዝብ የሉዓላዊ ስልጣኑ ባለቤት እንዲሆን እንታገል! አራተኛ ዓመት ቅፅ 4 ቁ 87ቅዳሜ ህዳር 27 2007 ዓ.ም

ሰለሞን ስዩም

የአለም ታሪክ ዋነኛው አንጓ ግዛት ማስፋት ነው፡፡ ታላቁ እስክንድር፣ በአንድ ወቅት ዓለምን በሙሉ ለመጠቅለል በሚመስል ሁኔታ የመስፋፋት ፖሊሲ ይከተል ነበር፡፡ ግዛቶችን ሁሉ እያንበረከከ መሬቱን አስፋፋ፡፡ በምድርም ከጥግ እስከ ጥግ ገናና ሆነ፡፡ ከጊዜያት በኋላ ግን የባህር ንግዱን የሚያሸብር የባህር ሽፍታ ተነሳበት፡፡በዚህን ጊዜ ያለ የሌለ አቅሙን ተጠቅሞ እንዲታደን ያደርገዋል፡፡ ተይዞም እስክንድር ፊት ቀረበ፡፡ ንጉሱም ጠየቁ፡-

“ለመሆኑ ምን አይነት መንፈስ ነው ባህሩን እንድታካልል የሰፈረብህ?”

ሽፍታውም ፡- “እርሶ የብሱን እንዲያካልሉ የሰፈረብዎ መንፈስ” ሲል መለሰ ይባላል፡፡

መሬት እጅግ ወሳኝ ሀብት ነው፡፡ ብዙዎች ከመሬት የሚያስቀድሙት ነገር የላቸውም፡፡

በመግቢያችን ላይ እንዳነሳነው ሁሉ የኢትዮጵያ ነገስታትም በዚህ የግዛት ማስፋፋትና አንድነት ጥበቃ ረገድ እጅጉን አኩሪ ታሪክ ያላቸው ነበሩ፡፡ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ኢትዮጵያዊ ሁሉ ሞቱን ሲያስብ “የሀገሬ አፈር ይብላኝ” በማለት ለመሬቱ ያለውን ፍቅር ይገልፃል፡፡ እትብቱንም ከመሬት ጋር በማስተሳሰር “እትብቴ የተቀበረበት” ሲል ጥምረቱን ያሳያል፡፡ ይህ የተለየ ትስስሮሽ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ የነበረ ቢሆንም አሁን በተቃራኒው የእፍረት ምንጭ እየሆነው ነው፡፡ የአሁኑ መሪዎቻችን ደግሞ መሀሉን ሀገር፣ ዳር እያደረጉት ችግር ላይ ወድቀናል፡፡ በቀየአችንም መሬታችንን የሚቀሙ ባዕዳን ይጠሩብናል፡፡ ስለመሬት ስናነሳ የመጀመሪያው ጥያቄያችን የሞኝ መሆን አለበት፡- “እኔ ሀገሬ የምላት፣ ጎኔን የማሳርፍበት የቤት መስሪያ ቦታ በሊዝ ግዛ የምትለኝን ነው?”፤ “`ያ አድማስ ይታያችኋል? እስከዚያ ድረስ የሰፈሩትን አንሷቸውና ውሰዱ` ስትል ባዕዳንን የምትጠራብኝን ነው?”

ዜግነት፣ የዚህ መሬት ባለቤትነት መገለጫ ነው፡፡ ዜግነት በዚህ መሬት ላይ ለሁሉም ኢትዮጵያዊ በእኩልነት የባለመብትነት ድርሻን ህጋዊ አድርጎ የሚደለድል ነው፡፡ በዚህ መሬት ላይ መኖር፣ መክበርና መከበር፣ ለዚህ መሬት ከመሞት ጋር የተያያዘ መብትና ግዴታ ነው፡፡ መብቱ ከሌለ ግዴታው የለም፤ ግዴታ ከሌለ መብትም የለም፡፡

እንግዲህ በመሬት ዙሪያ የተለያዩ ዓይነት ስሪቶች አሉ፡፡ ነገር ግን በትክክለኛ ትርጉማቸው ለዚህ ትውልድ አልደረሱም፡፡በትክክል እየታዩ አይደለም፡፡ “አፅመ-ርስት” የሚለው የይዞታ ዓይነት፣ ለመሬት የሞተውን ወገን ሲወክል “ርስት” ደግሞ የተረፈው በቀዳሚዎቹ አፅም ከስካሽነት የሚወርሰው ነው፡፡ በመሆኑም ለኢትዮጵያዊያን መሬት ከመስዋዕትነት ጋር የተቆራኘ ነው፡፡ አሁን አሁን “ገባር” የሚባሉት የህብረተሰብ ክፍሎች በመሬት ላይ ያላቸው መብት እንደሌለ ይታሰብ ነበር፡፡ ነገር ግን ባለመሬትና ለያዘው መሬት ግብር ከፋይ ማለት ነው፡፡ ባለጉልቶች በበኩላቸው ለያዙት የአስተዳደር ቦታ በምርት ላይ የሚሰጣቸው መብት በዛሬው ቋንቋ ደመወዝ ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ርስት ይወረሳል፤ ጉልት ግን አይወረስም፡፡ እንግዲህ ኢሕአዴግ ሰዎችን ከመደብ ላይ እንደማንሳት እንኳ ሳይቆጥር የሚያፈናቅለው

አስፍሯል፡፡ አብዛኛዎቹ የመሬት ይዞታ የሚያጠኑ ቡድኖች በበኩላቸው ዋናው ችግር ዋስትና ማጣት እና የመሬት እያነሰና እየተበጫጨቀ መምጣት (Fragmented and diminution) መሆኑን በየጥናት ሰነዶቻቸው አረጋግጠዋል፡፡ ዞሮ ዞሮ ታላቅ መስዋዕትነት የተከፈለለት መሬት የግል ንብረትነት የመሆኑ ጉዳይ ሣይሣካ ሳይሳካ ቀረ፡፡

የኢፌዴሪ ሕገ-መንግስትና መሬት

የኢሕአዴግ የመሬት ስሪት በሁለት ጎኑ ይቃኛል፡፡ አንድም መሬትን ለፖለቲካዊ ስልጣን ማስጠበቂያ ማዋል፣ አሊያም ለሰዎች ዴሞክራሲያዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ እና ሰብአዊ መብቶች ተገዢ በመሆን ከሚመነጭ ሃሳብ በመነሳት ተግባራዊ ማድረግ፡፡ መሬት ቁሳዊ ብቻ ሳይሆን መንፈሳዊ ልዕልናን ጭምር የሚጠቀልል የተለየ የተፈጥሮ ስጦታ ነው፡፡ አንዳንዴ ከውጭ ሀገር መልስ ሰው “ለመሆኑ ለምን መሬት ይስማል?” ብለን መጠየቅ አለብን፡፡ ልዩ መንፈሳዊ ቁርኝት ቢኖረው ነው፡፡ በጅምላ ፍረጃ ደርግ በ1980ዎቹ መጀመሪያ ላይ ያወጣው የማሻሻያ አዋጅ ከዛሬው የመሬት አዋጅ ጋር ተመሳሳይ ነው ለማለት ያስደፍራል፡፡

የኢሕአዴግ መንግስት ሕገ-መንግስት አንቀጽ 40(3) “መሬት የማይሸጥና የማይለወጥ የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች የጋራ ንብረት ነው” ሲል ይቆይና “የገጠሩም ሆነ የከተማ መሬትና የተፈጥሮ ሀብት ባለቤትነት መብት የመንግሥትና የሕዝብ ብቻ ነው፡፡” ሲል ያወዛግባል፡፡ ችግሩ እና ያልጠራው ሀሳብ በሕገ-መንግስቱ አንቀፆች 40(3)፣ 40(4)፣ 40(5)ና 40(6) የተካተቱት ናቸው፡፡

አንቀጽ 40(3) “መሬት የማይሸጥና የማይለወጥ የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች የጋራ ንብረት ነው፡፡”

አንቀጽ 40(4)፣ “የኢትዮጵያ አርሶ አደሮች መሬት በነፃ የማግኘትና ከመሬታቸው ያለመነቀል መብታቸው የተከበረ ነው፡፡” ይላል፡፡

አንቀጽ 40(5) “የኢትዮጵያ ዘላኖች ለግጦሽም ሆነ ለእርሻ የሚጠቀሙበት መሬት በነፃ የማግኘት፣ የመጠቀምና ከመሬታቸው ያለመፈናቀል መብት አላቸው፡፡” ይህንን ሁሉ ሲል የከረመው ሕገ-መንግስት መልሶ መብታቸውን ሲገፍ የሚከተለውን በቆረጣ ያስገባል፡፡

አንቀጽ 40(6) “መሬት የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ መንግስት ለግል ባለሀብቶች በህግ በሚወሰን ክፍያ በመሬት የመጠቀም መብታቸውን ያስከብርላቸዋል፡፡”ይላል፡፡ እዚህ ውስጥ ባለሀብቱ በሕገ-መንግስት የተጠበቀለት የመሬት ባለድርሻነት መብት አለው ማለት ነው፡፡

አሊያም “ከመሬት ያለመፈናቀል መብት” ከሚከተሉት ሕገ-መንግስቱ ውስጥ ከተካተቱት ሀሳቦች ጋር ተፈጥሯዊ ቅራኔ አለው፡-

1.ለግል ባለሀብቱ በህግ በሚወሰን ክፍያ የሚሰጠው መሬት ከየት የመጣ ነው?

2.ከማን ድርሻ? በየትኛው ህግ? ህዝቡ አውቋል?

3.ድርሻ ውስጥ ባለሀብቶች (መብት ውስጥ) ካሉ ቀድሞ ነገር ስሪቱ በመንግስት፣ በህዝብና በግል ይዞታነት መሰራት ነበረበት፡፡

ስርዓቱ፣ ገበሬውን እያፈናቀለ መሬት መቀማቱ ብቻ ሳይሆን ከአካባቢ ጥበቃ አንፃርም ምንም ጥንቃቄ የማያደርግ መሆኑ ነው፡፡ የቀድሞው ፕሬዚዳንት አቶ

መሬት፣ መሬት፣ መሬትግርማ ወልደጊዮርጊስ (ግርማ ወልጊዮርጊስ በአካባቢ ተቀርቋሪነታቸው የሚታወቁ ሲሆን በአካባቢ ጥበቃ ላይ የሚሰራው መልካ ማህበር የበላይ ጠባቂም ነበሩ፡፡)፣ ታህሳስ 2003 ዓ.ም ለግብርና ሚኒስትሩ አቶ ተፈራ ደርበው በጻፉት ደብዳቤ፣ “በምንም ምክንያት የደን መሬት ለእርሻ መሰጠት ስለሌለበት ደኑን ማልማት ለሚፈልጉ ሰዎች፣ ወይም በሕዝብ ተሳትፎ እንዲለማ ተገቢው እንዲፈጸም እጠይቃለሁ፤” ሲሉ ማሳሰባቸው ይታወሳል፡፡

ሌላው አሻሚ ነገር “የመንግሥትና የህዝብ ብቻ /exclusively vested in the state and the peoples of Ethiopia /” የሚለው ነው፡፡ አምታች ነው፡፡የሕገ-መንግስቱ የሀሳብ ጥራት ጉድለቱ በብዙዎቹ የሚወቀስ ነው፡፡የደርግ ሕግ-መንግሥት የሃሳብ ጥራትን ከኢህአዴጉ ሕገ-መንግስት በተቃራኒው መሆኑን ለመመስከር “ያልተጣሩና ያልተመከረባቸው፣ የተምታቱና የሚቃረኑ ነገሮችን መሸከሙ”ን በማየት መመስከር እንደሚቻል ብዙዎች ይመሰክራሉ፡፡

በዚህ እሳቤ መሰረት መንግስት፣ “state” ከሚለው የኢንግሊዘኛ ቃል ጋር አቻ ነው፡፡ ከዚህ የተነሳ ይህንን ተምኔት የሆነ “መንግስት” የተባለ አካል የደርግ ሕገ-መንግስት አንቀጽ 13 “የመንግስት ባለቤትነት የሕዝብ ነው” ወይም “State ownership in public ownership” ሲል በግልፅ አስቀምጦታል፡፡

ኢሕአዴግ በሕገ-መንግስቱ ከአንቀጽ 50 በቀር የመሬትን ጉዳይ ባነሳባቸው የተለያዩ ቦታዎች መንግስትን እና ህዝብን የተለያዩ ራሳቸውን የቻሉ አካላት (entities) ያደርጋቸዋል፡፡ የሕገ-መንግስቱን የማርቀቅ ሂደት የተከታተሉ አንዳንድ ምሁራን የሀሳብ ጥራቱ ችግር መንስኤ በአርቃቂነት የነበሩት የነፕ/ር እንድሪያስ እሸቴ፣ ዶ/ር ሳሙኤል አሰፋና አቶ ክፍሌ ወዳጆ እውቀት ማጣት የተነሳ ሳይሆን ከፖለቲካ አስተሳሰብ አንፃር የሚሰማቸው ጠፍቶ ነው ይላሉ፡፡

መሬት የማይሸጥ የማይለወጥ የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች የጋራ ንብረት ከሆነ፡- “ህዝቡ” ማን ነው? ምክንያቱም በሁለተኛው “ብሔረሰቦች …” ይላቸዋልና፡፡

መንግስት፣ የመሬት ባለቤትነት መብት ያገኘበት አስተሳሰብ ከየት የመጣ ነው?ፕሮፌሰር መስፍን “ከሕዝብ ውጭና ልዩ ሆኖ የመሬት ባለቤት የሚሆነው የት ሆኖና እምን ላይ ቆሞ ነው?” ይላሉ፤ በአንድ በኩል የመንግሥትና የህዝብ ብቻ ነው የተባለው መሬት በሌላ በኩል የብሔረሰብ የጋራ ንብረት የሚሆነውስ እንዴት ነው? አንዱ ለመሬት እንዲሞት ሲገደድ ሌላው ያንኑ መሬት ያውም ለውጭ ሰዎች እየቸበቸበ የሚከብርበት ምንም የተፈጥሮም ሆነ የህግ መሰረት የለውም፡፡

የሆነ ሆኖ የኢትዮጵያ ህዝብ መንግስትን ሲያምን አልኖረም፡፡መንግስታቱም ለህዝብ አልታመኑም፡፡የመንግስት አንዱ መታመኛ ደግሞ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት መዘርጋት ነው፡፡ ይህ የለም፡፡ ስለዚህ ለማያምነው ስርዓት አደራ አይሰጥም፡፡ ደግሞም ግለሰቡ ባለመብት መሆን አለበት፡፡

ኢሕአዴግ፣ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ (certification) በመስጠት ገበሬውን ለማረጋጋት ይሞክራል፡፡ እስካፈናቅልህ ተጠቀም ከማለት በዘለለ እውነተኛ ባለቤት አይደለም፡፡ እውነተኛ ባለቤትነት እንዳይኖርና እንዳይሰጥ ኢሕአዴግ ድርሻውን ለመንግስት ሰጥቷል፡፡ ለዚያውም በሕገ-መንግስት፡፡መሬትን የመንግስት ማድረግ አንድ አካባቢ ለኢንቨስትመንት የማይፈለግ ከሆነ ነዋሪዎቹን መሬት ላይ

ከዚህ አይነቱ የተለየ መብት ነው፡፡

ይህን ሁኔታ አንዳንዶች “መሬት ላለማጣት ሞትን፣ ከዚያመ አሞራና ጅብ በላን፡፡ እንኳን ለመኖሪያ ለመቀበሪያ መሬት አጣን፡፡ በመሆኑም መሰዋቱ ለራስም ለልጆችም ለቤተሰብም አይደለም-ለገዥዎች ነው፡፡” ሲሉ ያስቀምጡታል፡፡

ማንም ሰው ለመሞት በቆረጠበት ጊዜ “የምሞተው ለምን አላማ? ለማን አላማ ነው? የሚለው ጥያቄ መሰረታዊ ነው ይላሉ” ፕሮፌሰር መስፍን፡፡ ማንኛውም ሰው ለመሞት በቆረጠበት ጊዜ “የምሞተው ለምን አላማ ነው?” ብሎ መጠየቅና እውነተኛ መልሱን ማግኘት አለበት፡፡ አለዚያ አፅሙ የሌላ፣ ርስቱ የሌላ፣ ወይም … አፅሙ የአርበኛ፣ ርስቱ የባንዳ እየሆነ ይቀጥላል፡፡

ቅድመ አብዮቱ

የቅድመ-አብዮቱ የመሬት ስሪት እና ያስከተላቸው ችግሮች በደንብ የተጠኑ እንዳልሆነ ብዙ ምሁራን ይናገራሉ፡፡ ለነበሩት የተለያዩ የመሬት ስሪቶች የሀገሪቷን መልክዓ-ምድር፣ ዘውግ፣ ባህልና ብዝሃነት እንዲሁም ታሪካዊ ዳራዎችን በምክንያትነት ማስቀመጥ ይችላል፡፡ ቆይቶ ለመጣው የይዞታ ምስቅልቅል ግን የስሪት ለውጥ ማድረጋችን ዋናው ምክንያት ይሆናል፡፡

በወቅቱ የነበረው የይዞታ ዓይነት ርስት (kinship)፣ የወል (communal)፣ ቀየ / አጥብያ /diessa/village/ የግል ይዞታ፣ የመንግስትና የቤተ-ክርስቲያን የሚሉ ነበሩ፡፡ከሁሉም ግን ርስት፤ የግል፣ የቤተ-ክርስቲያን እና የመንግስት ይዞታዎች በጣም የሚሰራባቸው ነበሩ፡፡ ርስት በሰሜን የሀገሪቷ አካባቢ፣ የመንግስት ይዞታ በበኩሉ በቆላማውና በአርብቶ-አደሩ ክፍል ይበዛ ነበር፡፡

ችግሮች

ርስት፣ የይዞታ መመናመን፣ የመሬት መቆራረስ እና መቋጫ የሌለው የመሬት ክርክር ያስነሳል፡፡ ጉልት በበኩሉ ስርዓታት ህዝቡን የሚቆጣጠሩባት ስልት ናት፡፡ የግል ይዞታ 60% የሀገሪቱን ገበሬና 65% የሀገሪቱን ህዝብ ጎድቶ እንደነበር ጥቂቶች አስቀምጠዋል፡፡ በአፄው የመጨረሻ ዘመን በተለይ ደቡቡ የሀገሪቷ ክፍል መሬት በጥቂት ሰዎች እጅ ገብቶ እንደነበር ይታወሳል፡፡

የደርግ አዋጅ ዓላማዎች

የደርግ የመሬት አዋጅ፣ አዋጅ ቁ.31/1975 ተብሎ ይጠራል፡፡ የጭሰኛና የመሬት ከበርቴውን ግንኙነት ማጥፋት፣ መሬቱን የሚያርሱት የመሬቱ ባለቤት እንዲሆኑ ማስቻል፣ የመሬት ምርታማነትን መጨመር፣ የግብርና ኤክስቴንሽን ማስፋፋት፣ የሥራ እድል መፍጠር፣ መሬት ማከፋፈልና የገጠር ገቢን መጨመር የሚሉ ዋና ዋና ሀሳቦችን ይዟል፡፡

ሁሉም የገጠር መሬት የህዝብ አንዲሆን፣ የግል መሬትን ለአራሹ ማከፋፈል፣ ሽያጭ፣ ልዋጭ፣ ውርስ፣ የብድር መያዣ ማድረግ የተከለከለ እንዲሆን አድርጓል፡፡ በተጨማሪ የወል ይዞታ በሚሰሩበት ጊዜ ብቻ የነሱ መሆኑ እና 10 ሄክታር የመጨረሻው የመሬት ይዞታ ጣሪያ መሆኑን የሚደነግግ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ ባለሙያዎች ማህበር፣ “current land policy issues in Ethiopia” በሚል ባሰራው የጥናት ሰነድ የተለያዩ ሰዎችን በማነጋገር እንዳስቀመጠው የቀድሞው የመሬት ስሪት ችግር “በዝባዥ፣ መሬትን በአንድ ሰው እጅ ማከማቸት፣ ለያዙት መሬት ዋስትና ማጣት፣ የይዞታ እያነሰና እየተበጫጨቀ መምጣት” እንደሆነ

ወደ ገፅ 6 ይዞራል

Page 4: * p Hß ß0 16 1//6 Á÷ - Ethiopia Media Forumethioforum.org/amharic/wp-content/uploads/2014/12/finote-netsanet … · እንዲቀየር በፖለቲካው ጨዋታ ሜዳ አስገድዶታል፡፡

ርዕሰ አንቀፅፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ ሐምሌ 2003 ዓ.ም ተመሰረተ፡፡

ፍኖተ ነፃነት በአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ

(አንድነት) ስር የሚታተም በፖለቲካዊ፣በማህበራዊ፣

ወቅታዊ ጉዳዮችና በመዝናኛ ላይየሚያተኩር ጋዜጣ ነው፡፡

ጋዜጣችን ሚዛናዊና ነፃ ጋዜጣ ሆኖ ማገልገል መርሁ ነው፡፡ ማንኛውም ሀሳብና አመለካከት የሚስተናገድበትና የሚንሸራሸርበት እንዲሆን እንሻለን፡፡ ሰፊ የሚዲያ ሽፋን ያለው የሚባለውኢህአዴግም በዚህ ሚዲያ አቋሙንናፖሊሲዉን ለማግለፅ ቢፈልግ መድረኩ ክፍት ነዉ፡፡

ዋና አዘጋጅ፡-ነብዩ ኃይሉአድራሻ፡-ልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 10የቤት ቁ.320ስልክ ሞባይል፡- [email protected]

አምደኞች፡-ግርማ ሰይፉ ዳንኤል ተፈራመምህር አበበ አካሉአስራት አብርሃምሰለሞን ስዩምዳግማዊ ተሰማበለጠ ጎሹደረጀ መላኩ

ዜና ክፍል ወንድወሰን ክንፈ 0911654669

አሳታሚ፡-አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት)አድራሻ፡-አራዳ ክ/ ከተማ ወረዳ 07 የቤት ቁ. አዲስአታሚ፡- አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት)

የዝግጅት ክፍሉ ስልክ፡-01 11249659ፖ.ሳ. ቁ. 4222ኢሜይል ፡[email protected]@gmail.comandinet@ andinet.orgፋክስ ቁጥር ፡-+251-111226288

ፍኖተ ነፃነት

Visit us :- www.fnotenetsanet.com, www.andinet.org

4

ዲዛይን እና ሌይአውት አብነት ረጋሳ 0913366064

ኮምፒዩተር ጽሁፍ ብርቱካን መንገሻ

ሪፖርተር ኢዮኤል ፍሰሐ

የኢትዮጵያ ህዝብ የሉዓላዊ ስልጣኑ ባለቤት እንዲሆን እንታገል! አራተኛ ዓመት ቅፅ 4 ቁ 87ቅዳሜ ህዳር 27 2007 ዓ.ም

ሕገ-መንግስት በአንዲት ሀገር ሊኖሩ ከሚችሉ በርካታ ህጐች ሁሉ የበላይ የሆነ ህግ ነው፡፡ ሁሉም ሕጐች ሕገ-መንግስትን ተደግፈውና ተመስርተው ይወጣሉ፡፡ ኢትዮጵያም በተለያዩ የአገዛዝ ስርዓቶች አራት ያህል ሕገ-መንግስቶችን አጽድቃለች፡፡ አሁንም ሀገራችን የምትተዳደርበት ሕገ-መንግስት ተግባር ላይ ከዋለ 20 ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡ በእነዚህ ሁለት አስርታት ግን ሕገ-መንግስታዊ ስርዓት በኢትዮጵያ ሊመሠረት አልተቻለም፡፡ በሕገ-መንግስቱ ላይ የተካተቱት “አማላይ” አንቀፆች የወረቀት ላይ ነብር ከመሆን እንዳያልፉ ያደረገው ቅጥ ባጣ ሁኔታ በስልጣን ጥም የታወረው ገዢው ፓርቲ፣ ስለ ህገ-መንግስቱ ከርቀት የሚሰማ የአድናቆት ከበሮ ቢያስደልቅም፤ እለት ከለት ህገ-መንግስቱን በመናድ ተግባር ላይ መሰማራቱ ነው፡፡

ገዢው ቡድን ሕገ-መንግስቱን ከዜጐች ነጥቆ የህግ ሰውነት ለሌላቸው “ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች” በማለት ለሰየማቸው መስጠቱ፣ ሕገ-መንግስቱ የወጣበትንም ቀን አበርክቶ «የብሔሮችና ብሔረሰቦች በዓል» ሲል መሰየሙ እና በጭፈራ ማክበሩ በኢትዮጵያ ብሔረሰቦችና በሕገ-መንግስቱ ከጭፈራ በላይ ሚና እንደሌላቸው ማመኑን ያስገነዝባል፡፡

ኢህአዴግ፣ ሕገ-መንግስቱን ከብሔረሰቦች ጋር ማስተሳሰሩ የራሱ ፖለቲካዊ ተቃርኖ እንዲፈጥር የሚያደርገው፣ ለሕገ-መንግስቱም ሆነ ለኢትዮጵያ ህዝብ ክብር የማይሰጥ መሆኑ ነው፡፡ ሕገ-መንግስቱን ባለማክበር የሚያደርጋቸው እንቅስቃሴዎች፤ የአገዛዝ ስርዓቱን እድሜ ለመቀጠል ታስበው የሚከወኑ የመሆናቸውን ያክል፤ ህዝብን ከህዝብ በማጋጨት እድሜውን ለማራዘም ሲተጋም ይስተዋላል፡፡

በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሕገ-መንግስት በብዙ ረገዶች ጠቃሚ አንቀፆችን የያዙ መሆናቸው አያከራክርም፡፡ በተለይም የህዝብን ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች የሚያስጠብቁ፣ በአለም-አቀፍ ስምምነቶች የተሸፈኑ አንቀፆችን መያዛቸው እንደጠቃሚ ጐን የሚያዙ ናቸው፡፡ ከዛው ጐን ለጐን የገዢውን ቡድን ስልጣን ለማራዘም ተብሎ በሕገ-መንግስቱ ውስጥ የተሰገሰጉ አንቀፆችም እንደሚገኙ አይካድም፡፡ በተለይም ለመንግስት ስልጣን ገደብ ያለመበጀቱ እንዲሁም ሕገ-መንግስቱ በቀላሉ እንዳይሻሻል ተብለው የገቡት አንቀፆች በዋነኝነት ይጠቀሳሉ፡፡

የሕገ-መንግስት ፍርድ ቤት እንዲኖር አለመደረጉ ሌላኛው የሕገ-መንግስቱ ክፍተት ነው፡፡ አገዛዙ በተለያዩ ጊዜያት ለሚደርታቸው ቀፍዳጅ ህጎች፣ ቅቡልነት እንዲያገኙ ይረዳው ዘንድ በዴሞክራሲ ትግበራ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ከደረሱ አገሮች፤ “ኮማ” ሳይቀር እንደተቀዳ እንደሚነግረን ሁሉ፣ ለአገሪቱ መልከ-ብዙ ክንውኖች በመለኪያነት ለሚያገለግለው ሕገ-መንግስት፣ መልካም ተሞክሮዎችን ቢዋስ መልካም ነበር። በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሕገ-መንግስት፣ ሕገ-መንግስቱን እንዲተረጉም ስልጣን የተሰጠው የፌዴሬሽን ምክር ቤት፤ የኢትዮጵያ ብሔረሰቦች “ወኪል” እንደሆነ ኢህአዴግ በድፍረት ይናገራል፡፡ ሆኖም ግን ፌዴሬሽን ምክር ቤት በገዢው ቡድን መዳፍ ስር መሆኑ፣ ሕገ-መንግስቱም በኢህአዴግ ቁጥጥር ስር መውደቁ የአደባባይ ምስጢር ነው፡፡ በመሆኑም ሕገ-መንግስት የፀደቀበትን ቀን ከማክበር፣ሕገ-መንግስትን ማክበርን ሊያስቀድም ይገባል፡፡ ሕገ-መንግስቱን በተለያዩ ህጎችና አሰራሮች በመናድ የሚታወቀው ገዢው ቡድን ራሱን የሕገ-መንግስቱ ጠባቂ አድርጎ መቁጠሩ በየትኛውም መለኪያ የህግ የበላይነት ማስፈኑን አያመላክትም፡፡

ሕገመንግስት የፀደቀበትን ቀን ከማክበር፣ሕገመንግስትን

ማክበርን ሊያስቀድም ይገባል!

Page 5: * p Hß ß0 16 1//6 Á÷ - Ethiopia Media Forumethioforum.org/amharic/wp-content/uploads/2014/12/finote-netsanet … · እንዲቀየር በፖለቲካው ጨዋታ ሜዳ አስገድዶታል፡፡

ፍኖተ ነፃነት

Visit us :- www.fnotenetsanet.com, www.andinet.org

5የኢትዮጵያ ህዝብ የሉዓላዊ ስልጣኑ ባለቤት እንዲሆን እንታገል! አራተኛ ዓመት ቅፅ 4 ቁ 87ቅዳሜ ህዳር 27 2007 ዓ.ም

የምንታገለው፣ ምን ዓይነት ስርዓት ለማምጣት ነው?

አስራት አብርሃ

አንድ ፖለቲካዊ ድርጅት ወይም ፓርቲ፤ በስልጣን ላይ ያለን ስርዓት ለመቀየር ለትግል ከመነሳቱ በፊት ምን ዓይነት ስርዓት ለማምጣት ነው የምታገለው? የሚለውን ጥያቄ በአግባቡ መመለስ መቻል አለበት። በዚህ መሰረታዊ ጉዳይ ላይ ግልፅነትና መስማማት ከሌለ፣ ትግሉም ውጤታማ ሊሆን አይችልም። በመጀመሪያ ስርዓቱ ይውደቅ እንጂ ከዚያ በኋላ ይታሰብበታል የሚለው የደመ-ነፍስ ትግል ውጤቱ የከፋ ሊሆን እንደማይችል ዋስትና የለንም።

ለዚህ ጥሩ ምሳሌ የሚሆኑን ኤርትራውያን ናቸው። ኤርትራውያን፣ ለነፃነት ብለው ሰላሳ ዓመት ተዋጉ፤ እጅግ በጣም ደም ያፋሰሰ ትግልም አደረጉ፤ በውጤቱ ግን የግለሰብና የቋንቋ እንጂ መሰረታዊ የሆነ የስርዓት ለውጥን አላመጡም። ጥቁረትና ቅላት ራሱን የቻለ ለውጥ ነው ካልተባለ በስተቀር፣ መንግስቱ ኃይለማርያምን በኢሳይያስ አፈወርቂ ነው የቀየሩት። መንግስቱ ኃይለማርያም ጥቁርና

ጥላሁን ጉልበተኛ ነው፤ የራሱን ቀይ መስመር በኪሱ በሚይዘው ጠመኔ በመጫር ያንን የተላለፈውን ሁሉ በጡንቻው የሚዳኝ ስመ-ጥር ፀበኛ፡፡ ታዋቂው ደራሲ ስብሀት ገ/እግዚአብሔር፣ በሚያዝያ ወር 1993 ዓ.ም “ሌቱም አይነጋልኝ” በሚል ርዕስ ባሳተመው ልብ-ወለድ ላይ ጉልበተኝነቱ በጉልህ የተተረከው ጥላሁን፣ ሁሉም ሰው ሊዝናና በሚታደምበት መሸታ ቤት ውስጥ በኪሱ የሚይዘውን ጠመኔ እየመዠረጠ “ወንድ ከሆንክ ይቺን መስመር ተሻገር” በማለት የራሱን ህግ ያወጣል፡፡ እንደውቤ በረሃው ጥላሁን፣ የደደቢት በረሃ ጉልበተኞችም ያላሸረገደላቸውን ሁሉ በጡንቻቸው ለመዳኘት ይታትራሉ፡፡

ህጎችን በሶስት ዋና ዋና መደቦች ለይቶ መተንተን እንደሚቻል የዘርፉ ባለሙያዎች ያስረዳሉ ፡፡ ምድቦቹንም ማርክሳዊ፣ ማኪያቬሊያዊና ሊበራል ወይም ዴሞክራሲያዊ የህግ እሳቤ በማለት ይደለድሏቸዋል፡፡ ማርክሳዊ የህግ እሳቤ፣ «ህጐች የገዢው መደብ የመጨቆኛ መሳሪያ ናቸው» ይላል፡፡ ማኪያቬሊያዊው በበኩሉ፤ “ህግ በጉልበት ያገኘኸውን ስልጣን ማስጠበቂያ መሣሪያ ነው” ይላል፡፡ ከላይ የቀረቡት ሁለቱም “በህግ መግዛት” (Rule by law) የሚለውን የህግ መነሻ የያዙ ናቸው፡፡

አጭር እንዲሁም ወፍራም ከንፈር ያለው ሰው ሲሆን፤ ኢሳይያስ አፈወርቂ ቀይ፣ ረጅም መልከ-መልካም የሚባል ዓይነት ሰው ነው፤ በሁለቱ መሪዎች መካከል ያለው ልዩነት ከዚህ አይዘልም፡፡ መንግስቱ በአማርኛ የሚደነፋውን፣ ኢሳይያስ በትግርኛ ይለዋል። ትላንት ገራፊዎቹና ገዳዮች አማርኛ ይናገሩ ነበር፤ ዛሬ ደግሞ ገራፊዎችና ገዳዮች ትግርኛ ይናገራሉ፤ በኤርትራ ግድያው፣ እስሩና ስደቱ ዛሬም አልቆመም። በኤርትራ የነፃነትና የፍትህ እጦት አሁንም አለ። ይሄ ስለምን ሆነ? የሚል ጠያቂ ካለ መልሱ ‹ኤርትራውያን የነፃነት ትርጉም ሳይገባቸው አሊያም በቅጡ ሳያስቡበት በመዋጋታቸው ነው፡፡› የሚል ይሆናል፡፡

የፍልስፍና መምህሬ ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ፣ ቦስተን (አሜሪካ) ነዋሪ ሳለ ከኤርትራውያን ጓደኞቹ ጋር ሲገናኝ “አሁን ለነፃነት እየታገላችሁ ነው፤ ነፃ ስትወጡ ምን ዓይነት ስርዓት ነው የምትመሰርቱት?”” የሚል ጥያቄ ያቀርባል፤ እነርሱ ለዚህ ጥያቄ የነበራቸው መልስ “በመጀመርያ ነፃ እንውጣ እንጂ ስለእሱ ሲደረስ ይታሰብበታል” የሚል ነበር፡፡ በእኛ አገርም እንዲህ የሚሉ ጠፍተው አያውቁም፤ ብቻ ጃንሆይ ይውረዱ እንጂ ከዚያ በኋላስ የፈለገው ይሁን ተባለ፤ ደርግ መጣ የፈለገው ሁሉ ሆነ! ከዚያ ደግሞ ደርግ ይጥፋ እንጂ ከዚያ በኋላስ የፈለገው ይሁን ተባለ፤ ኢህአዴግ አህያ እየነዳ፣ በባዶ እግሩ ሰተት ብሎ መጣ፤ እናም እንደገና የፈለገው ሆነ! አሁንም ደግሞ ኢህአዴግ ይውደቅ እንጂ የፈለገው ይሁን የሚሉ ሞልተዋል። ከእንግዲህ በኋላ የፈለገው እንዲሆን መመኘት የለብንም፤ መሆን ያለበትን በትክክል አውቀን፣ ለአላማችን መሣካት ትግል ማድረግ ይኖርብናል፡፡

በመሰረቱ የጨዋታው መጨረሻ ምን እንደሚሆን የማናውቀውን የፖለቲካ ጨዋታ መጫወት የለብንም። በሚወድቀው

ስርዓት ምትክ፣ ምን ዓይነት ስርዓት ነው የምንተክለው? የሚለው ጥያቄ መመለስ ያለበት! አሁን ነው፡፡ ኢሕአዴግ ከወደቀ በኋላ የሚታሰብበት ነገር አይደለም። አሁን ያለውን ስርዓት እየታገልነው ያለነው ኢ-ፍትሐዊ፣ አምባገነንና ወገንተኛ በመሆኑ ነው። የምንታገለው፣ እንዲህ ዓይነቱ ፖለቲካዊ ባህል ለማንም ስለማይጠቅም ነው፡፡ ነገር ግን በትግሉ እየተሳተፈ የሚገኘው ሁሉ፤ የትግሉን ዓላማ በዚህ ልክ ተረድቶትና ገብቶት ነው ለማለት ይቸግራል፡፡አንዳንዱ ከሆነ ክልል ወደሌላ ክልል ተወሰደብኝ የሚለውን መሬት ለማስመለስ ወደ ትግል የመጣ አለ፤ አንዳንዱ ደግሞ የሆነ ብሔረሰብ ስለተበደለ ብድር ለመመለስ ብሎ ቂሙን ቋጥሮ ወደፖለቲካ ክበቡ የመጣ አለ። ከሁሉም የተሻለ የሚሆነው ግን ለሁሉም የሚስማማ ስርዓት ለማምጣት፣ ለነፃነትና ለዴሞክራሲ ብሎ መታገል ነው። በህግ የበላይነትና በዴሞክራሲ የሚያምን ሰው፤ ማንኛውንም ችግር በዴሞክራሲያዊ መንገድ፣ በህዝባዊ ውሳኔ መፍትሄ ያገኛል ብሎ ያስባል፤ ለዚህ ዓይነቱ መርህም በፅናት ይቆማል። በደልን በበደል፤ መጥፎ ተግባርን በሌላ መጥፎ ድርጊት ለመካስ መሞከር ጊዜያዊ ደስታ ይሰጥ እንደሆነ እንጂ ዘላቂ መፍትሄ አያመጣም። ሕወሓቶችም ባለፉት ስርዓታት በደል ደረሰብን፤ ብለው ጫካ ገብተው አሸንፈው ሲመጡ ካለፉት ስርዓታት ተሽለው አልተገኙም፤

ለነፃነትና ለተሻለ ስርዓት የሚታገል ሰው፤ በመጨረሻ የእውነትም በነፃነት እንደሚኖር አውርደውታል፡፡ ዋስትና ይፈልጋል፡፡ አለበለዚያ ህይወቱን በሙሉ ከአንድ ትግል ወደ ሌላ ትግል ሲገላበጥ ሊመሽበት ነው እኮ!! ፖለቲካዊ ትግል የባህል ለውጥ የማምጣት ትግል ነው፤ የባህል ለውጥ የሚመጣው ደግሞ በየጊዜው ቀስ-በቀስ በሚገነባ ዴሞክራሲያዊ ሂደት እንጂ በአንዲት ጀምበር አይደለም። ምክንያቱም ነፃ ማህበረሰብና ነፃ ተቋማት በሌሉበት ዴሞክራሲያዊ

ስርዓት የሚታሰብ ነገር አይደለምና።

ዛሬ በከፍታው ያለው ስርዓት ወደ ስልጣን እንዲመጣ ምክንያት የሆኑት ችግሮችና አስተሳሰቦች አሁንም አሉ፤ ችግሩ ውስብስብ ነውና በቀላሉ የሚፈታ አይሆንም። ለምሳሌ አሁን ያለውን ነባራዊ ሁኔታ ያየን እንደሆነ በምንም አይነት ሁኔታ ኢትዮጵያን ወደ አሃዳዊ ስርአት መመለስ የሚቻል አይደለም። አሁን ያለው የክልሎች አወቃቀር ቢቀየር እንኳ ሊሆን የሚችለው በሌላ የተሻለ መልክ ነው፡፡ በአገዛዞች ፍርርቅ ሲሰፉና ሲጠቡ የነበሩና አጨቃጫቂ የሆኑ አካባቢዎችም አሁን በቦታው በሚገኙ ነዋሪዎች ህዝበ-ውሳኔ መሠረት ዳግም የማካለል ስራ ከመስራት የተሻለ ሌላ አማራጭ ይኖር አይመስለኝም፡፡ በመሆኑም መሆን ያለበት የተለያዩ ቋንቋዎችን የሚናገሩ ህዝቦች ያሉባት አገር እንደመሆኗ ለእነዚህ ሁሉ ስጋት የማይሆን፣ ማንንም የማያገልል ሳይንሳዊ ስርዓት መፍጠር ነው።

በተለይ ደግሞ አንድን ህዝቦች በጅምላ ተጠያቂ የሚያደርግ ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ምናልባትም በሆነ አጋጣሚ የዘር ማጥፋት ወንጀል ለመፈፀም ምክንያት ሊሆን ይችላል፡፡ በዚህ የአስተሳሰብ መንገድ የተደላደለ ስርዓት ለመመስረት ፈጽሞ አይቻልም። እንዲያውም ባንፃሩ ሁኔታዎች ሲረጋጉ ሊከተል የሚችለው የህግ ተጠያቂነት ነው። አግባብ ባለውና በሰከነ ሁኔታ ትግሉን መምራት ያስፈልጋል የምንለውም ለዚህ ነው፡፡ እየታገልን ያለነው ስርዓቱ ስለማይመጥነን ከሆነ ከዚህ ያነሰ ስርዓት ለወደፊቱም ቢሆን አይገባንም ማለት ነው። የህግ የበላይነት፤ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት፤ የግለሰብንና የቡድን መብቶች ሙሉ ለሙሉ የሚያከብር ስርዓት ለማምጣት መታገል ይኖርብናል፡፡ በዚህ መግባባት ላይ የቆመ ፖለቲካዊ ትግል፤ ምንም ጥርጥር የለውም በመጨረሻ ላይ አሸናፊ ሆኖ ይወጣል።

ነብዩ ኃይሉ

የጉልበተኞች “ቀይ መስመር”የሊበራል የህግ እሳቤ (ዴሞክራሲያዊው የህግ አስተሳሰብ) ግን “የህግ የበላይነት” Rule of law የሚባለውን እሳቤ መነሻ የሚያደርግ ነው፡፡

የጉልበተኞች ቀይ መስመር በህግ የሚበጀው፣ በጉልበት የተገኘ ስልጣንን የሚያስጠብቅ መሣሪያ እንዲሆን ተደርጎ ነው፡፡ በአሜሪካን የነበረውና በጥቁሮች ላይ መድሎ የሚፈፅመው ህግም ሆነ በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ በተግባር ላይ የሚገኘው የፀረ-ሽብር ህግና መሰል አፋኝ ህጎች፤ የህግ የበላይነት መርሆዎች የሆኑትን “ገለልተኝነት” እና “አጠቃላይነት” የያዙ አለመሆናቸው ያመሳስላቸዋል፡፡

በአሁኑ ሰዓት የዴሞክራሲ ምሳሌ ተደርጋ በምትወሰደው አሜሪካ፣ ከጥቂት አስርት ዓመታት በፊት የጥቁሮችን መብት የሚደፈጥጥ ቀይ መስመር “በህግ” ተሰምሮ እንደነበር ታሪክ ዘግቧል፡፡ ህጉ፣ ጥቁሮች ከነጮች እኩል በህዝብ መጓጓዣዎች እንዳይገለገሉ የሚያግድ መሆኑን ሁሉም ጥቁሮች ቢረዱትም፤ ቀዩን መስመር በተቀናጀ ሁኔታ ለመተላለፍ የሚያስችል ዘዴ አልቀመሩም ነበር፡፡ በተናጥል የሚያደረጉትን የመብት ማስከበር እንቅስቃሴዎች ወደተቀናጀ ንቅናቄ የመራው ክስተት እ.ኤ.አ በህዳር 1955 ዓ.ም በሮዛ ፓርክስ ፈር-ቀዳጅነት ተጀመረ፡፡ ሮዛ በአሜሪካዋ ሞንቴኔግሮ ከተማ ለነጮች ብቻ ተለይቶ በተከለለው የአውቶብስ መቀመጫ ላይ ተቀምጣ የጉልበተኞቹን ህግ ጣሰች፤ በዚሁ ሰበብም ለእስር ተዳረገች፡፡ የሮዛ ፓርክስን የቀዩን መስመር የመጣስ ውሳኔ እንደተራ ጀብደኝነት የቆጠሩት ባይጠፉም፣ የአሜሪካ ጥቁሮችን ወደ ተቀናጀ የመብት ማስከበር ንቅናቄ ቀየረው፡፡ ጥቁሮቹም የሞንቴኔግሮን በአውቶብስ

ያለመጠቀም አመፅ በዚሁ ቀን ጀመሩት፡፡

የሞንቴኔግሮን በአውቶብስ ያለመጠቀም አመፅም በዓለም-ዓቀፍ ደረጃ፣ በሰላማዊ ትግል እንቅስቃሴ እንደ አዕማድ ከሚቆጠሩት ጀግኖች መካከል በቀዳሚነት የሚጠቀሰውን የአሜሪካ ጥቁሮች የመብት እንቅስቃሴ አባት ማርቲን ሉተር ኪንግ ጁኒየርን አበረከተ፡፡

ማርቲን ሉተር የጥቁሮችን መብት ለማስከበር ባደረገው እንቅስቃሴ ሰበብ በግፍ ከታሰረበት የበርሚንግሀም እስር ቤት፤ “Letter from Birmingham jail” በሚል በላከው ደብዳቤ፤ “ሂትለር ያደረገው ሁሉ ህግን የተደገፈ’ እንደነበር አንረሳም፤ የሀንጋሪ የነፃነት ታጋዮች እንቅስቃሴም ‘ህገ-ወጥ’ ተብሏል፡፡በሂትለር ስቃይን የተቀበሉ ይሁዲዎችን መርዳትም ‘ህገ-ወጥ’ ነበር፡፡ ምንም እንኳን ህገ-ወጥ ቢሆን፣ እኔ በዚያን ጊዜ ጀርመን ብኖር ያለጥርጥር ይሁዲ ወንድሞቼን እደግፍ ነበር፡፡ ክርስትና በሚረገጥባቸው የአሁኖቹ ኮሚኒስት ሀገሮች ውስጥ ብኖርም፣ በይፋ ፀረ-ሃይማኖት ለሆኑት ህጎች ህዝብ እንዳይገዛ እቀሰቅስ ነበር፡፡” በማለት መልእክቱን አስተላልፎ ነበር፡፡የጉልበተኞችን ቀይ መስመር በመጣስ፣ ጨቋኞች የሚያወጧቸውን ህጎች ተንተርሰው የትግል እንቅስቃሴን “ህገ-ወጥ” ማድረግ እንደማይችሉ አሳይቷል፡፡

ኢትዮጵያውያንን አፍኖ በመግዛት ላይ የሚገኘው ገዢ ቡድንም በተለያዩ ሀገራት እንደነበሩትና አሁንም እንዳሉት የአገዛዝ ስርዐቶች ሁሉ የህግ የበላይነትን ተከትለው ባልፀደቁ አፋኝ ህጎች ጠፍሮ ሊገዛን ይፈልጋል፡፡ በህገ-ወጥ ህጎች የነፃነት ትግሉን ለማኮላሸት ታጋዮችን በሰበብ አስባቡ ያስራል፡፡ ለመብቶች ገደብ እያበጁ፣ ቀይ መስመር

ያሰምራሉ፤ የገዛ ህጋቸውን ጠቅሰውም ያስራሉ፡፡

ሀሳብን የመግለፅ መብት እና የፕሬስ ነፃነት በህገ-መንግስቱ ዋስትና ቢሰጣቸውም፤ በፕሬስና በፀረ-ሽብር ህጎች አማካኝነት፣ ገዢው ቡድን ባሰመረው ቀይ መስመር ተገድበዋል፡፡የመደራጀት መብቶችም በሲቪክና የበጎ አድራጎት ህግ ተደፍጥጠዋል፡፡

ይህ አመት አምስተኛው አገር-አቀፍ ምርጫ የሚካሄድበት ነው፡፡ ምርጫ በማጭበርበር የሚታወቀው ኢህአዴግ፣ ለወጉ በሚደረጉ ምርጫዎች እድሜውን ለማራዘም እንደለመደው ተዘጋጅቷል፡፡ ይህንን የሚያረጋግጠው ለካድሬዎቹ በሚሰጣቸው ስልጠናዎች ላይ “የ2007 ምርጫን ከ2002ቱ

የተሻለ ውጤት ማምጣት አለብን” የሚል መመሪያ መስጠቱ ነው፡፡

ገዢው ቡድን፣ ሀቀኛ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የሚያደርጉትን የነፃነት ትግል ለማምከን የሚጠቀምባቸውን ቀይ መስመሮች በመጣስ፣ የነፃነት ትግሉን አንድ እርምጃ ማራመድ ይገባቸዋል፡፡ ከላይ ለማሳያነት የጠቀስናት ሮዛ ፓርክስ፣ በአሜሪካ ጥቁሮች ታሪክ ውስጥ ህገ-ወጥ “ህግን” በመተላለፍ ቀዳሚ አልነበረችም፡፡ ከሷ በፊት በሚደረጉ የተናጥል ዕምቢ-ባይነቶች በርካታ ጥቁሮች ለእስር ተዳርገዋል፡፡ የሮዛ ዕምቢ-ባይነት ግን የተናጥል እንቅስቃሴዎችን ወደ አንድ ያመጣ ነው፡፡ በዚህ ረገድ በኢትዮጵያ ገዢው ቡድን ያስቀመጠውን ቀይ መስመር ለመጣስ፣ በተናጥል ፓርቲዎች የሚወስዷቸውን እርምጃዎችን እስከዛሬ ተመልክተናል፡፡ ጊዜው የሚጠይቀው የትግል ስልት፣ የተናጥል እንቅስቃሴዎችን በማቀናጀ ንቅናቄዎችን ማስኬድ ነው፡፡

Page 6: * p Hß ß0 16 1//6 Á÷ - Ethiopia Media Forumethioforum.org/amharic/wp-content/uploads/2014/12/finote-netsanet … · እንዲቀየር በፖለቲካው ጨዋታ ሜዳ አስገድዶታል፡፡

ፍኖተ ነፃነት

Visit us :- www.fnotenetsanet.com, www.andinet.org

6 የኢትዮጵያ ህዝብ የሉዓላዊ ስልጣኑ ባለቤት እንዲሆን እንታገል! አራተኛ ዓመት ቅፅ 4 ቁ 87ቅዳሜ ህዳር 27 2007 ዓ.ም

የአሥራሰባት አመት ወጣት ነው። ጥይት የጎረሰ ሽጉጥ በእጁ ይዟል። እጅግ በጣም ብዙ ሕዝብ በተሰበሰበበት አደባባይ፣ ንግግር አድርገው ወደጨረሱ አንድ የእድሜ ባለጸጋ ሰው ቀስ በቀስ መጠጋት ያዘ። በቂ ርቀት ላይ እንደደረሰም ሰውየውን ተኩሶ ጣላቸው፡፡ አካባቢው በጩኽት ተናወጠ። አምቡላንስ በአፋጣኝ በስፍራው ደረሰ። የወደቁትን ሰው ይዘዋቸው በፍጥነት ወደሆስፒታል ጉዞ ጀመሩ። ሆስፒታል ሳይደርሱ በመንገድ ላይ የሠውየው ሕይወት አለፈች። ተኳሹ፣ ይጋል አሚር ይባላል። ሟቹ ደግሞ የቀድሞ የእሥራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ይሳቅ ራቢን ነበሩ።

ይሳቅ ራቢን፣ እድሜ ዘመናቸውን በሙሉ የጥይትና የመድፍ ድምጽ በመስማት ያሳለፉ ጦረኛ ወታደር ነበሩ። በፈረንጆች አቆጣጠር በ1941 ዓ.ም ከታዋቂው ሞሼ ዳያን ጋር የፓልማክ ግብረ-ኃይል አባል ሆነው፣ ያኔ በፈረሳንዮች ቅኝ ግዛት ስር በነበረችው ሊባኖስ፤ የናዚ ጀርመን ደጋፊ ከነበረው የፈረንሳይ ቪቺ መንግስት ወታደሮች ጋር ተዋግተዋል። ሰውየው፣ ከአረቦች ጋር በተደረጉት ተከታታይ ጦርነቶች ትልቅ ጀግንነትና የውትድርና ብቃት ያሳዩ፣ በእሥራኤል ታሪክ አሉ ይባሉ ከነበሩት ታላላቅ የጦር መሪዎች አንዱ ነበሩ። የእሥራኤል የመከላከያ ሚኒስቴር፣ የጦሩ የኢታ ማጆር ሹም ሆነውም አገልግለዋል።

ይሳቅ ራቢን፣ «እኔ ሰላም ሳላይ እድሜዬን ጨርሻለሁ። ለልጆቻችን ሰላም ማምጣት አለብን» በሚል እምነት፣ ድፍረት የተሞላበት የሰላም እርምጃ ወሰዱ። የእሥራኤል ጠላቶች ከሚባሉት ጋርም መነጋገር ጀመሩ። ከመገደላቸው ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ያደረጉት ንግግር፣ ለእኛ ለኢትዮጵያውያንና ለመሪዎቻችን ትልቅ ትምህርት የሚሰጥ አስደናቂ አባባል ነበር፤ «የሰላም መንገድ ከጦርነት ይሻላል። ይሄን የምለው እንደ አንድ ወታደር ነው። መከላከያ ሚኒስቴር ሆኜ የእስራኤል ወታደሮች ቤተሰቦች ስቃይ ይሰማኛል። ለነርሱ፣ ለልጆቻችን፣ ለልጅ ልጆቻችን ስንል መንግስታችን ዘላቂ ሰላም እስኪያገኝ ድረስ ማንኛውንም ቀዳዳና ማንኛውንም እድል መጠቀም አለበት» ነበር ያሉት።

የጦርነትን ፣ የጥላቻና የእልህ ፖለቲካ አደገኛነትን ያውቁታልና፣ አብረዋቸው የነበሩ ጓደኞቻቸው ሲረግፉ፣ አካለ-ስንኩል ሲሆኑ፣ ንብረት ሲወድም ፣ ሰው በሰው ላይ ሲጨክንና አውሬ ሲሆን አይተዋልና፣ እርሳቸው የኖሩበትን በጦርነት የተበከለን አየር ለልጅ ልጆቻቸዉ ማውረስን አልፈለጉም። እርሳቸው ይመኙትና ይናፍቁት የነበረውን

ታላቁ እስክንድር!ለመማር አልረፈደም

ሰላም፣ ባያገኙትም እንኳን፣ የልጅ ልጆቻቸው እንዲያገኙ፣ መደረግ ያለበትን ሁሉ ማድረግ እንዳለባቸው ተገነዘቡ። «ለልጅ ልጆቻችን ስንል ሰላም እንዲመጣ የተገኘችዋን ቀዳዳ ሁሉ መጠቀም አለብን» በሚል ጽኑ አምነት፣ በጦርነት ያልሆነ፣ የውስጥና የልብ ጀግንነት ለማሳየት ተንቀሳቀሱ። የእሥራኤል ጠላት ከተባሉት ከነያሲር አራፋት ጋር መነጋገር ጀመሩ። ብዙ ተቃውሞ መጣባቸው። ግትር ፖለቲካ የሚያራምዱ፣ በጭንቅላት ሳይሆን በጠብ-መንጃ የሚያምኑ፣ እነርሱ ብቻ ከሌላው እንደተሻሉ በመቁጠር በትእቢት የተወጠሩ፣ ሰዎች ማንጎራጎር ጀመሩ።

ኢሳቅ ራቢን ግን ወደ ኋላ አላሉም። «የሰላም ጠላቶች አሉ። ሊጎዱን፣ የሰላሙን መንገድ ሊያጨናግፉ የሚፈልጉ። በድፍረት እናገራለሁ። ከፍልስጤማውያን መካከል የወጣውና፣ በፊት ጠላታችን የነበረው የፍልስጤም ነጻ አውጭ ግንባር አሁን የሰላም አጋራችን ሆኗል» ሲሉ ከቀድሞ ጠላቶቻቸው መካከል ወዳጆችን እንዳፈሩ ተናገሩ። ከያሲር አራፋት ጋር በአንድ ላይ ለሰላም ቆሙ። ኢሳቅ ራቢን በጦርነት ሊያጠፉት ያልቻሉትን የያሲር አራፋትን ቡድን በሰላም አሸነፉት።

ለዘመናት በጦር ሜዳ ሲዋጉ በጥይት ያልተመቱት እኝህ ታላቅ ሰው፣ በሰላሙ ሜዳ በቴላቪቭ ከተማ ጥይት አገኘቻቸው። ለሰላም፣ ለፍቅርና ለወንድማማችነት ሲሉ ወደቁ።

የይሳቅ ራቢንን ታሪክ ያለምክንያት አላመጣሁትም። አምባገነኖች፣ ተቃዋሚዎችን መጨፍለቅ ጀግንነት ይመስለናል። ኃይላችንን የምንመዝነው በያዝነው ብረትና በዘረጋነው የሥለላ አውታር መጠን ነው። መነጋገር፣ መወያየት፣ ፍቅርና መግባባት፣ በጦርነትም ሆነ በጉልበት ከሚገኝ ግዜያዊ መፍትሄ የበለጠ ዘለቄታ ያለው ጥቅም ሊያመጣ እንዲሚችል አናስብም። የሩቁን፣እኛ ካለፍን በኋላ በልጆቻችንና በልጅ ልጆቻችን ዘመን ሊፈጠር የሚችለውን፣ መልካም ግዜ አንመለከትም። ግዜያዊ ጥቅማችንንና ስልጣናችን ላይ ብቻ በማተኮር ግትር ፖለቲካን እናራምዳለን።

እንደ ኢሳቅ ራቢን ሁሉ አሁን በሥልጣን ላይ ያሉት የኢሕአዴግ ባለሥልጣናት ከወጣትነታቸው ጀምሮ ጦርነትን ያዩ፣ በጦርነት የኖሩ ሰዎች ናቸው። በታሪክ ስለሚኖራቸው ቦታ፣ ስለ ልጆቻቸውና የልጅ ልጆቻቸው ማሰብ አለባቸው እላለሁኝ። ምንም እንኳን እንደ “ጠቅላይ ሚኒስትር” ኃይለማርያም ደሳለኝ እና ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሀኖም ያሉ ሰዎች በፊት ገጽ ላይ ቢሠየሙም፣ ከጀርባ ሆነው የሚገዙት ጦረኞቹ እንደሆኑ እናውቃለን እናም ጦረኝነት ሠላምን ከማፋቀር እንደማያግድ ሊለስተውሉ ይገባል፡፡

ሽብርተኝነትን ለመቋቋም ተብሎ በወጣው፣ ሕገ-መንግስቱን በሚቃረን አዋጅ መሰረት፣ ለሰላማዊና ሕጋዊ ትግል ጠንካራ አቋም ያላቸው እንደ እስክንድር ነጋ፣ ተመስገን ደሳለኝ፣ አንዱዓለም አራጌ፣ ዞን ዘጠኖች፣ ሃብታሙ አያሌው፣ አብርሃ ደስታ፣ ርዕዮት አለሙን የመሳሰሉ ጀግኖች ወደ ወህኒ መውረዳቸው፣ ከጊዜ ወደ ጊዜ በተቃዋሚዎች ላይ በየወረዳውና በየክልሉ የሚደርሰው ወከባ … ኢሕአዴግን ከሕዝብ ጋር የሚያቆራርጡ፣ ጥላቻ እንዲሰፋ የሚያደርጉ፣ ዜጎች የበለጠ ወደ ከረረ አቋም እንዲሄዱ የሚገፋፉ እንጂ የመግባባትን መንፈስ የሚያመጡ አይደለም።

ንጹሀን የኃይል እርምጃ መውሰድ፣ በበቀል መነሳሳት፣ ሰውን ማዋረድ፣ መስደብ፣ መክሰስ፣ ዜጎችን ያለ ክስ ለወራት ማሰር፣ በማእከላዊ እንደሚደረገው በጨለማ ቤት ውስጥ እስረኞችን ማሰቃየት እንደ እንስሳ መሆን ነው። በአይናችን ላይ ትልቅ ምሰሶ እያለ፣ የሌላውን

ጉድፍ ማየት፣ የተገነባውን ማፍረስ፣ አገርን ከድህነት ወደ ድህነት ማውረድ፣ ጠላቶችን ማፍራት፣ ሕዝብን ከሕዝብ መከፋፈል፣ ወንድምን ከወንድም ማጣላት ቀላል ነው።

ይሳቅ ራቢን እንዳደረጉት ጠላት የነበሩትን ወዳጅ ማድረግ፣ የፈረሰውን መገንባት፣ አገርን ከድህነት ማውጣትችግሮችን በውይይት መፍታት፣ የተጣሉትን ማስታረቅ፣ የተበተኑትን መሰብሰብ፣ ትችትና ወቀሳን በትህትና ተቀብሎ፣ ስድብና አሉባልታን ንቆ ነገሮችን በትእግስት ማለፍ ላጠፋ ምህረት ማድረግ እጅግ በጣም ከባድ ነገር ነው። በመሆኑም እንደ አንድ አገር ወዳድ ዜጋ፣ መንግስት ቀናውን መንገድ እንዲይዝና መጪውን ምርጫ በታማኝነት እንዲካሂድ፣ ከዚህም ሌላ ከተለያየ አቅጣጫ ስለብሔራዊ መግባባት ለሚጮኹ ድምፆች ጆሮውን ይሠጥ ዘንድ እጠይቃለው፡፡

መንግስት፣ ነፃና ፍትሐዊ ምርጫ ለማካሄድ፣ በተለያዩ አዋጆችና የስውር ደባዎች በጋሬጣ የሞላውን የፖለቲካ ምህዳር በማስፋት ከፍተኛውን ሀላፊነት መውሰድ ይኖርበታል፡፡ በአገሪቱ ካሉት ትላልቅ ፓርቲዎች ማለትም እንደ አንድነት እና መድረክ ከመሣሠሉት ጋር በሀቀኛ የተፎካካሪነት ስሜት ከምርጫው በፊት መመካከርና መወያየት ይኖርበታል፡፡

ፍቅርን ከፈራን፣ በግትርነት ከፀናን፣ እውነተኛ ፉክክርን ከጠላን… በእድላችን እየተጫወትን ነው፡፡ በዳዩንም ተበዳዩንም ነፃ የሚያወጣውና የሚፈውሰው የይቅርታ ጠበል ነው፡፡ ለመማርና ከጥፋት ጎዳና ለመመለስ ዛሬም አልረፈደም፡፡ እውነተኛ ትምህርትና ፀፀትም፣ ጉልበት ሳይከዳና መንገዶች ሣይጠብቡ በፊት የሚገለፅ ነው፡፡

ግርማ ካሳ

ባለቤትነት እንዳይኖርና እንዳይሰጥ ኢሕአዴግ ድርሻውን ለመንግስት ሰጥቷል፡፡ ለዚያውም በሕገ-መንግስት፡፡መሬትን የመንግስት ማድረግ አንድ አካባቢ ለኢንቨስትመንት የማይፈለግ ከሆነ ነዋሪዎቹን መሬት ላይ የተሰፉ እንዲሆኑ ያደርጋል፡፡ ይህ ሁኔታ ደግሞ አየጠበበ በሚመጣ መሬት ላይ የግብርና እስረኝነትን ያስከትላል፡፡ በዚህ ቢቆም መልካም በነገር፤ ነገር ግን የጉልበት ብክነትም ጭምር አለበት፡፡ አንድ ሰው በሙሉ ኃይሉ የማያሰራውን መሬት (Uneconomic) ለመያዝ ይገደዳል ማለት ነው፡፡

ምሳሌ፡- በቅርቡ በወጣ ጥናት ሁለት ሰዎች ማሳ ላይ ቢሰማሩ በትክክል የሚሰራው 0.8 ሰው (ከአንድ በታች) ነው፡፡ እንግዲህ አንደኛው ስለሌላው ጭምር ይለፋል ማለት ነው፡፡ ይህ ባለበት የሚረግጠው ኢንዱስትሪው ብዙ ሰዎችን እንዲቀጥር ተደርጎ የተቀረፀ ፖሊሲ የለም፡፡

ቀጥሎ ያለው ከአንድነት የስትራቴጂ ሰነድ ገፅ 153 ላይ የተገኘ ነው፡-

“…አንድነት ወደ አርሶ አደሩ ይዞት የሚገባው የማትጊያ አጀንዳ ገበሬውን ባለመሬት፣ የማሳው ባለቤት ማድረግ ሲሆን ለዚህም ዝርዝርና የተሟላ የግብርና ፖሊሲ ያዘጋጃል፡፡አንድነት መሬትን ከፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና

መሬት.. ከገፅ 3 የዞረማሕበራዊ ፋይዳው በመነጠል ከፍተኛ ዋጋ መክፈል የቻለ ሁሉ እንዲወስድ ፈፅሞ የማይፈቅድና አርሶ አደሩን ገንዘብ ላላቸው መሬት ወራሪዎች አጋልጦ የማይሰጥ ፖሊሲ ይዞ ይቀርባል፡፡

የአንድነት የግብርናና የመሬት ፖሊሲ የግብርናው ዘርፍ አዋጪ ለሆነለት የአርሶ አደሩ ክፍል እንዲለቀቅ (እንዲተው) የሚያደርግና ይህንን የአርሶ አደር ክፍል ከዘመናዊ ቴክኖሎጂና ገበያ ጋር በማገናኘት ዘመናዊ እንዲሆን የሚያደርግ ይሆናል፡፡ በዚሁ ሂደት ከግብርናው ስራ ውጪ የሚሆነው ትርፍ ጉልበት በዘመናዊ እርሻ፣ በኢንዱስትሪ፣ በማዕድን ልማት ወ.ዘ.ተ የተሻለ አማራጭ መተዳደርያ እንዲያገኝ ምቹ ሁኔታ የሚፈጥርለት ፖሊሲ ይቀመጣል፡፡”

እንዲህ ስንል እንደመድማለን፤ በመግቢያችን ላይ ያነሳነው ታላቁ እስክንድር ከመሞቱ በፊት አንድ ነገር ተናዞ ነበር፡፡ ሞቶ ሲቀበር አንድ እጁ ከመቃብር ውጪ ወደ ላይ እንዲደረግ፡፡ ይህን ያለው ያን ሁሉ ግዛት ቢያስፋፋም አንዲት ነገር ለግሉ በማድረግ እንዳልወሰደና ባዶ እጁን እንደነበር ለማሳየት፡፡ ግዛት ከማስፋፋት ይልቅ ሲያተቡ የነበሩ የሀገሬ ገዥዎች እጃቸው ከመቃብር በላይ መሆን የማይችለው ያን ሁሉ የዘረፉትን ጋሻ መሬት መሸከም ስለማይችሉ ነው፡፡

ይቀጥላል፡፡

Page 7: * p Hß ß0 16 1//6 Á÷ - Ethiopia Media Forumethioforum.org/amharic/wp-content/uploads/2014/12/finote-netsanet … · እንዲቀየር በፖለቲካው ጨዋታ ሜዳ አስገድዶታል፡፡

ፍኖተ ነፃነት

Visit us :- www.fnotenetsanet.com, www.andinet.org

7የኢትዮጵያ ህዝብ የሉዓላዊ ስልጣኑ ባለቤት እንዲሆን እንታገል! አራተኛ ዓመት ቅፅ 4 ቁ 87ቅዳሜ ህዳር 27 2007 ዓ.ም

የምርጫ ስትራቴጂ እንዴት ይሁን?

በስትራቴጂካዊ ዕቅድ ዝግጅት ወቅት ከተለመዱት የአካባቢ ሁኔታ መተንተኛ መሳሪያዎች አንዱ የውጭ እና የውስጥ ሁኔታን አገናዝበን የምንተነትንበት በእንግሊዘኛ ስዎት/ (SWOT/SLOT Analysis) የሚባለው ይገኝበታል፡፡ ወደ ውስጣችን ተመልክተን ጥንካሬያችን የቱ ጋር ነው? የሚለውን ጥያቄ መመለስ ሲሆን፤ በተመሣሣይ መልኩ ደግሞ ያሉብን ድክመቶች ወይም ውሱንነቶች የትኞቹ ናቸው የሚለውን አጥርቶ መመልከት ነው፡፡ ወደውጭ ስንመለከት ደግሞ ለዕቅዳችን ምን ምቹ ሁኔታ አለ የሚለው አንደኛው ሲሆን ሌላኛው ደግሞ የተግዳሮቶቹን መልክና መጠን መገንዘብ ነው፡፡ እነዚህን በዝርዝር ማየት ይኖርብናል፡፡

አንድ የስትራቴጂክ ዕቅድ የውስጥና የውጭ ትንተና ተሰርቶ ሲያበቃ . . .

•በውስጣዊ ጥንካሬ ላይ የተመሠረቱ እና በውጭ ያሉትን ምቹ ሁኔታዎች በመጠቀም ላይ ያተኮረ፣

• በውጭ ያሉ መልካም አጋጣሚዎችን በመጠቀም እና የውስጥ ድክመቶችን በማስወገድ ላይ ያተኮረ፤

•የውስጥ ጥንካሬዎችን በመጠቀም፣ የውጭ ተግዳሮቶችን በማሸነፍ ላይ ያተኮረ እና

•የውስጥ ድክመቶች እና የውጭ ተግዳሮቶች የሚያደርሱትን ጉዳቶች በመቀነስ ላይ ያተኮሩ ስልቶችን መንደፍ የግድ ይላል፡፡

•እነዚህን በዝርዝር ከሰላማዊና ህጋዊ የትግል ስልት፣ በተለይም ከምርጫ ዝግጅት አንፃር እንዴት ማየት እንዳለብን መረዳት ተገቢ ነው፡፡ ስልቶቹን በምሳሌ እያስደገፍን ማየቱ እስከ ዛሬ የመጣንበትን ከመፈተሽ በዘለለ፤ ወደፊት እንዴት መሄድ እንዳለብን ለውይይት ጥርጊያ መንገድ ይከፍታል የሚል እምነት አለኝ፡፡ ከላይ የተቀመጡትን ስልቶች የተገኙት በዚህ መልክ ከተቀመጠ ሰንጠረዥ ውስጥ ነው፡፡

ውስጣዊ ሁኔታዎችጥንካሬ ድክመት/ውሱንነት

መ ል ካ ም አጋጣሚዎች/ዕድሎች

በውስጣዊ ጥንካሬ ላይ ያተኮሩ እና በውጭ ያሉትን ምቹ ሁኔታዎችን በመጠቀም ላይ ያተኮረ

በ ው ጭ ያ ሉ መ ል ካ ም አ ጋ ጣ ሚ ዎ ች ለ መ ጠ ቀ ም እ ና የ ው ስ ጥ ድ ከ መ ቶ ች ን በማስወገድ ላይ ያተኮረ

ተግዳሮቶችበውስጥ ጥንካሬዎችን በመጠቀም የውጭ ተግዳሮቶችን በማሸነፍ ላይ ያተኮረ

የውስጥ ድክመቶች እና የውጭ ተግዳሮቶች የሚያደርሱትን ጉዳቶች በመቀነስ ላይ ያተኮሩ

ከላይ የተዘረዘሩትን ስልቶች ከታች ወደላይ እንመልከታቸው፡፡

እንደሚታወቀው በተቃዋሚ ጎራ የምንገኝ ስብስቦች ትኩረት ሰጥተን ስንሰራ የባጀነው፤ የውስጥ ድክመቶቻችንን እና የውጭ

ተግዳሮቶች የሚያደርሱብንን ጫናዎችና ጉዳቶች በማጉላት ላይ ነበር፡፡እርግጥ፣ ከውስጥም ሆነ ከውጭ ያሉትን ችግሮች ማወቁ ተገቢ ቢሆንም፤ እነርሱኑ ደጋግሞ ማንሳት መፍትሔ ሊያመጣ እንደማይችል ግን አልተረዳንም፡፡ በስትራቴጂክ እቅድ ዝግጅት ወቅት እነዚህ ጉዳት የሚያደርሱ ውስጣዊና ውጫዊ ሁኔታዎች እንዳሉ ተረድቶ፣ እነርሱን ለመቀነስ የሚወሰዱ እርምጃዎች ቅድሚያ ማግኘት ይኖርባቸዋል፡በተለይ ደግሞ መከላከል ማድረግ ለማንችልባቸው ውጫዊ ጫናዎች ትኩረት ሰጥቶ እነርሱን ማግዘፉ፣ ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል፡፡ ከዚህ አንፃር ከምርጫ ጋር የተገናኙ ውስጣዊ ችግሮች ከምንላቸው አንዱ ለምርጫ ለመወዳደር ያለብን የፋይናንስ ችግር አንዱ ምናልባትም ዋነኛው ነው፡፡ይህን ችግር ማስወገድ ባይቻል እንኳ ለመቀነስ ስልት ነድፈን ከመንቀሳቀስ ይልቅ የገዢው ፓርቲ ድጋፍን እንደ አማራጭ እንወስደዋለን፡፡ አገዛዙ ከሚፈጥርብን ጫና ራሳችንን ለማላቀቅ ከሚረዱን ነገሮች አንዱ ምንም እንኳ መብት ቢሆን ለምርጫ ዘመቻ የሚያደርገውን ድጎማ በዋነኛ ግብዐትነት ከመመልከት ይልቅ ሌሎች የራሳችንን የገቢ ማግኛ መንገዶች ማፈላለግ ነው፡፡

ከፋይናንስ አንፃር ባነሳነው ምሳሌ ብንቀጥል የተቃዋሚ ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች፣ በአምስት መቶ አርባ ሰባት የምርጫ ክልል ለማሸነፍ የሚያስችል የፋይናንሲንግ ስትራቴጂ ልንጠቀም እንችላለን፡፡ ይህም ለእያንዳንዱ ዕጩ የገንዘብ ሽፋን የሚያደርግ አንድ ደጋፊ መመልመል ሲሆን፤ ድጋፉ ለአንድ ሰው ይበዛል ከተባለ ለአስር ማካፈል ይቻላል፡፡ አንድ ዕጩ ተወዳዳሪ፣ አሸናፊ ሆኖ እንዲወጣ አስር ደጋፊዎች የገንዘብ ሽፋን ሊሰጡት ይችላሉ፡፡ በዚህ ስሌት መሠረት አንድ ፓርቲ አምስት ሺ ደጋፊዎች ያስፈልጉታል ማለት ነው፡፡ ከዚህ በተጓዳኝ ተቃዋሚ ፓርቲዎች፤ የሚያገኟትን ገንዘብን በቁጠባ ከመጠቀም ጎን ለጎን፤ በነፃ የሚያገለግሉ ስፍር ቁጥር የሌላቸው ወጣት አባላቶች በውስጣቸው መኖራቸው ትልቅ ካፒታል መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡ይህንን አጠንክሮ መቀጠል ያለብንን የገንዘብ እጥረት ለመፍታት ይረዳናል፡፡

በአሁኑ ሰዓት ከተቃዋሚ ፓርቲዎች ውጭ ያሉ አመቺ ሁኔታዎች እጅግ ብዙ ናቸው፡፡ ለምሳሌ መንግስት በሚቀርፃቸው የተሳሳቱ ፖሊሲዎች እና አፈፃፀም ዙሪያ ያሉትን ችግሮች በሚያስከትልበት ምስቅልቅል

የተነሳ ህዝቡ ተቃዋሚ ፓርቲዎችን ለመደገፍ ዝግጅቱን እያሳየ ይገኛል፡፡ ይህን ዝግጁነት ወደተግባር ለመለወጥ በውስጥ ያሉብንንወደህዝብ የመቅረብ ችግር አስወግደን ለውጤት ማብቃት ይኖርብናል፡፡ እኛ ወደህዝቡ በመቅረብ ያሉንን አማራጮች ካላቀረብንለት

እና ከእርሱ ምን እንደምንጠብቅ ካላስረዳነው፣ ማዶ ለማዶ እየተያየን መቀጠላችን ነው፡፡

ገዢው ፓርቲ በተለያየ መልኩ የሚሰራቸው ስህተቶች ለተቃዋሚዎች የተዘጋጁ ዕድሎች ሲሆኑ፣ ተቃዋሚዎች ደግሞ ወደ ህዝቡ ለመቅረብ ያለባቸውን ችግር በማስወገድ ለድል የሚያበቃ ሰልት መንደፍ የግድ ይላቸዋል፡፡ እዚህ ነጥብ ላይ ‹ወደ ህዝብ መቅረቢያውን መንገድ ኢህአዴግ ዘግቶታል› የሚል ሀሳብ ሊነሣ እንደሚችል እገምታለሁ፡፡ ደግሞም ትክክል ነው፡፡ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች ህዝቡን ማግኘት ያለብን በአዳራሽና በአደባባይ ብቻ ነው ከሚለው አቋም ወጥተን የአንድ ለአንድ፣ የሰው ለሰው ግንኙነት በየሰፈራችን መጀመር ይኖርብናል፡፡ (ማህበራዊ ሚዲያዎች እንደተጠበቁ ሆነው ማለቴ ነው፡፡)

ዋነኛው ስትራቴጂ መሆን ያለበት ግን ጥንካሬዎቻችን ላይ መሰረት ማድረግና በውጭ ያሉ ምቹ ሁኔታዎችን አሟጦ መጠቀሙ ላይ መሆኑ መዘንጋት የለበትም፡፡ላለፉት 23 ዓመታት ስለ ጫናዎች እና ተግዳሮቶች ከበቂ በላይ ተናግረናል፡፡ እነርሱ የሚያደርሱትን ጉዳት ለመቀነስ ከመስራት ይልቅም፣ መኖራቸው እንዲታወቅ ጩኽናል፡፡ አሁን የአተያይ አቅጣጫው ተለውጦ ያሉትን እድሎች ያለ አንዳች ማመንታት ለመጠቀም ቆርጦ የመነሳት መሆን ይኖርበታል፡፡ ምንም ትንሽ ቢመስሉ በውስጣችን የሚገኙትን ጥንካሬዎች መፈተሽ እና ከውጭ የሚገኙ የመዘናጋት ዕድሎችን መጠቀም ይኖርብናል፡፡ለምሳሌ አሁን በሀገራችን ያሉት ወጣቶች ከሞላ ጎደል ፊደል የቆጠሩ ናቸው እነዚህ ወጣቶች በእውቀት ላይ የተመሰረተ አማራጭ ከቀረበላቸው ያለምንም ፍርሃት በመራጭነት ለመሳተፍ አያቅማሙም፡፡ይህ ትልቅ ዕድል ነው፡፡ ተቃዋሚዎች፣ የበለጠ የስራ እድል ለመፍጠር የሚያስችሉ የፖሊሲ አማራጮች፣ ወጣቶችን ከመንግስት ጥገኝነት የሚያላቅቅ የመኖሪያ ቤት ፖሊሲ፣ ወጣቶችን የመሬት ባለቤት ሊያደርግ የሚችል የመሬት ፖሊሲዎች እንዳሉን ግልፅ ነው፡፡ ይህ ወጣቱን ከፍተኛ የምርጫ ሀይል ሊያደርግ የሚችል በውጭ ያለ ዕድል እና በፓርቲዎች ውስጥ ያለ ጥንካሬ ነው፡፡

ኢሕአዴግ፤ የገጠሩን ህዝብ በእርሻ መሬቱ እንደያዘው ሁሉ ከተሜውን ደግሞ በኮንዶሚኒየሙ ጠርንፎታል፡፡የኮንዶሚንየም ቤቱን ለአምስት ዓመት እንዳይሸጥ እንዳይለውጥ፤ በባንክ እንዳያሲዝ የሚያደርግ ፖሊሲ አለው፡፡ የአንድነት ዓይነት ፓርቲ ስልጣን ቢይዝ፤ በእርግጠኝነት በወራት ውስጥ አሰራሩን ቀይሮ ሁሉንም የቤቱ ባለቤት እንደሚያደርግ ነው፡፡ የዚህ ዓይነት የሚታዩና የሚጨበጡ እርምጃዎችን የሚያሳዩ እንቅስቃሴዎች ማድረግ ይኖርብናል፡፡አንድነት፣ ከዩኒቨርሲቲ ስትመረቁ ኮብል ስቶን /ድንጋይ ፈለጣ/ ትገባላችሁ አይልም፡፡ ድንጋይ ለመፍለጥ አራት ዓመት በዩኒቨርሲቲ መቆየት አያስፈልግም፡፡ እንደ አማራጭ የስራ መስክ ሆኖ ለሌሎች ይቆያል፡፡ የተማሩ ዜጎች ስራ እንዲይዙ ምቹ ሁኔታ የሚፈጥሩ የግል ባለሀብቶች ግልፅ በሆነ አሰራር እንዲስፋፉ ድጋፍ ማድረግ ነው፡፡ ሀገር ማለት ህዝብ ነው ስንል ዜጎች ለዜጎች የስራ እድል የሚፈጥሩበት ማለታችን ጭምር ነው፡፡

ቸር ይግጠመን!!!!

ግርማ ሴይፉ ማሩ[email protected]

ገዢው ፓርቲ በተለያየ መልኩ

የሚሰራቸው ስህተቶች ለተቃዋሚዎች

የተዘጋጁ ዕድሎች ሲሆኑ፣ ተቃዋሚዎች

ደግሞ ወደ ህዝቡ ለመቅረብ ያለባቸውን

ችግር በማስወገድ ለድል የሚያበቃ

ሰልት መንደፍ የግድ ይላቸዋል፡፡

"

"

Page 8: * p Hß ß0 16 1//6 Á÷ - Ethiopia Media Forumethioforum.org/amharic/wp-content/uploads/2014/12/finote-netsanet … · እንዲቀየር በፖለቲካው ጨዋታ ሜዳ አስገድዶታል፡፡

ፍኖተ ነፃነት

Visit us :- www.fnotenetsanet.com, www.andinet.org

8 የኢትዮጵያ ህዝብ የሉዓላዊ ስልጣኑ ባለቤት እንዲሆን እንታገል! አራተኛ ዓመት ቅፅ 4 ቁ 87ቅዳሜ ህዳር 27 2007 ዓ.ም

ፍኖተ ነፃነት፡- የህግ የበላይነት መገለጫዎች ምን ምን ናቸው?

አቶ ተማም፡- የህግ በላይነት መገለጫዎች ማለት ቀደም ብሎ ለወጡ ህጎችና ደንቦች መንግስትም ሆነ ሌሎች አካሎች ከህግ በታች የሚሆኑበት ማለት ነው፡፡ ሁለተኛው የትኛውም አካል የዘፈቀደ አሰራር (arbitrary act) የማይኖርበት ሁኔታ ማለት ነው፡፡ ሶስተኛው ህግን የተከተለ አሰራርን (due process of law) የግድ ማለት፣ በየትኛውም ሁኔታ የትም ፍጪው ዱቄቱን አምጪው የሚባለው ግብታዊ አሰራር የማይኖርበት ማለት ነው፡፡ ህግ እንጂ የሰዎች ስልጣን ቦታ የማይሰጥበት

ነው፡፡ሁሉም ሰዎች ከህግ በታች ሆነው በህግ የሚመሩበትና የዘፈቀደ አሰራር የማይኖርበት ነው፡፡ እንዲሁም እያንዳንዱ ውጤት ህግ ብቻ የበላይ የሚሆንበትና ህግ የሚገዛበት ማለት ነው፡፡

ፍኖተ ነፃነት፡- በህግ መግዛት (Rule by law) ምን ማለትስ?

አቶ ተማም፡- “ህግ ገለልተኛ ነው፤ መንግስትም ገለልተኛ ነው” ከሚለው የሊበራሊዝምና የዴሞክራሲ መርህ ሲወጣ “በህግ መግዛት” የሚባለው ነገር መጣ፡፡ቻይና በ1950ዎቹ የወንጀለኛ መቅጫ ህጋቸውን አግደው፣ “የመንጋ ፈራጅነት” (mob justice) የሚባለውን አሰራር ተከተሉ፡

፡ይህ የሆነው ህግ መደባዊ ነው የሚል አስተሳሰብ ግዘፍ በመንሳቱ ነው፡፡ በመሆኑም ህዝብ ጉዳይህን መርምሮ ይፈርድብሃል፣ ይገድልሃል፡፡ ይህ ብዙ አሉታዊ ነገሮችን ፈጠረ፡፡ መረጋጋትን ሊፈጥር የሚችለው ህግ ነው አሉና ህገ-መንግስትና ወንጀለኛ መቅጫ ህግን መልሰው አረቀቁ፡፡ በህግ መግዛት ማለት ከህገ-መንግስቱ ውጪ ለሆነ አላማ ህግን መጠቀም ማለት ነው፡፡ ይህ ደግሞ በኮሚኒስት ሀገሮች ያለ አሰራር ማለት ነው፡፡

ፍኖተ ነፃነት፡- ከህግ የበላይነት መለከያዎች አንፃር ሲታይ ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉት ነባራዊ ሁኔታዎች “የህግ የበላይነት” ሰፍኗል ማለት እንችላለን?፤

አቶ ተማም፡- አይቻልም፤ የህግ የበላይነት ሰፍኗል ማለት እኮ የመንግስታዊ መስሪያ ቤቶች አሰራር ህግና ህግን መሰረት ያደረገ ሲሆን ብቻ ነው፡፡ ለምሳሌ አንድ ፖሊስ ጣቢያ ሄደህ የሚያጋጥምህ ህጋዊ አሰራር ሌላ ፖሊስ ጣቢያ በእርግጠኝነት የሚያጋጥምህ ሲሆን ነው፡፡ የፀሃይ መግቢያና መውጫ የታወቀ እንደሆነ ሁሉ ሀገሪቱ ላይ ያለው አሰራር ህጋዊ መሆኑን እርግጠኛ ስትሆን የህግ የበላይነት አለ ለማለት ነው፡፡ከመሰረታዊ ልዩነቶችህ ውጪ መብትህን ታውቃለህ፡፡በሁሉም ቦታ ላይ “ይሄ መብት አለኝ፤ ይሄ መብት አይነካብኝም” ስትል ነው የህግ የበላይነት አለ ማለት የሚቻለው፡፡ የሆነ ቦታ ሄደህ መብትህን የማታገኝ ከሆነና አንድ ሰው በዘፈቀደ የአንተን መብት ሊጥስ ሲሞክርና

መብትህን ተወው የሚባልበት ሁኔታ ካለ፣ የህግ የበላይነት አለ ለማለት አይቻልም፡፡

ፍኖተ ነፃነት፡- የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ህገ-መንግት የፀደቀበት ቀን 20ኛ አመት ከነገ በስቲያ በመንግስት ይከበራል፡፡ ከህግ መሰረታዊ አላባዊያን አንፃር የህገ-መንግስቱ ጠንካራ ጎኖች ምንድን ናቸው? መሻሻል ያለባቸው ነገሮችስ?

አቶ ተማም፡- የህገ-መንግስቱ ጠንካራ ጎን ብዬ የምወስደው ከዓለም-አቀፍ የሰብአዊ መብት ስምምነቶች የተወሰዱ ድንጋጌዎችን ማካተቱን ነው፡፡ ከአንቀፅ 13፣14 ጀምሮ እስከ አንቀፅ 28 ፣29 ፣ 30 ያሉት ከዓለም-ዓቀፍ

ስምምነቶች የተወሰዱ አንቀፆች ናቸው፡፡ እነዚህ የህገ-መንግስቱ ጠንካራ ጎኖች ናቸው፡፡

መሻሻል አለባቸው ብዬ የማስበው የመብት አጠባበቅን በተመለከተ፣ የመንግስት ስልጣን አያያዝንና የመንግስት የመቋቋም አላማ እነዚህን መብቶች ለማስከበር ነው ተብሎ በግልፅ መቀመጥ አለበት፡፡ ህገ-መንግስቱ ላይ ይህ በግልፅ አለመፃፉ፣ መሻሻል ካለባቸው ነገሮች ውስጥ የምመድበው ነው፡፡ ሁለተኛው የህገ-መንግስቱ ባለቤት ማን ነው የሚለው ነው? ህገ-መንግስቱ መላውን የኢትዮጵያ ህዝብ ባለቤት ባለማድረጉ “ህገ-መንግስቱ ባለቤት አልባ ነው” ማለት ያስችላል ፡፡ ለምሳሌ ብሔር፣ብሔረሰቦችና ህዝቦች በህግ “ህጋዊ ሰውነት” ስለሌላቸውና

ሊኖራቸው ስለማይችል እንደ ህግ ባለሙያ ትርጉም አይኖራቸውም፡፡ የፖለቲካ ትርጓሜ ሊኖረው ይችላል፡፡ ህግ ደግሞ የሚያውቀው የተፈጥሮ ሰውን አልያም በህግ “ህጋዊ ሰውነት” ተሰጥቶት የተቋቋመ አካልን ብቻ ነው፡፡ ብሔር ብሔረሰቦች ደግሞ በየትኛውም መለኪያ የህግ ሰውነት ሊኖራቸው አይችልም፡፡ እንደ ህግ ባለሙያ ሳየው ይህ ትልቅ ስህተት ነው፡፡ ስህተቱ በቅንነት የተደረገ ሊሆን ይችላል፤ ለስህተቱ ምንም ምክንያት ቢሰጠው ግን ይህ የህግ ክፍተቱ መሻሻል አለበት፡፡

ፍኖተ ነፃነት፡- በፀረ-ሽብር ህጉ

ለተከሰሱ በርካታ ግለሰቦች ጥብቅና እንደመቆምዎ መጠን የኢትዮጵያ የፀረ-ሽብር ህጉ፣ ከህገ-መንግስቱ አንፃር ያሉት ተፋልሶዎች ምን ምን ናቸው?

አቶ ተማም፡- የአፄ ኃይለስላሴን ህገ-መንግስት አንቀፅ 3 አይተህ እንደሆነ ከወንጀለኛ መቅጫ ህግ ውጪ ሊኖሩ የሚችሉትን ጥፋቶች ሁሉ የደንብ መተላለፍ ጉዳዮች ናቸው ይላል፡፡ አዲሱ የወንጀለኛ መቅጫ ህግ አንቀፅ 3 ላይ ግን ይህ ነገር የለም፡፡ የወንጀል ህግ የህዝብን ሰላምና ደህንነት መጠበቂያ ነው፡፡ ህጎች የሚወጡት ህገ-መንግስቱን ለመጠበቅ ነው፡፡የህግ የበላይነት የምንለው ነገር እኮ ህጉን የማብራራት ነገር ነው፡፡ የሚወጡት ህጎች ከህገ-መንግስቱ ሊቃረኑ

“ህገ-መንግስቱ ባለቤት አልባ ነው”የዚህ ሳምንት እንግዳችን ታዋቂው የህግ ባለሙያ አቶ ተማም አባቡልጉ ናቸው፡፡ በህግ ጠበቃነት ከ15 በላይ አመታትን ያሳለፉት አቶ ተማም፣ በተለይ በፀረሽብር ህጉ ለተከሰሱ ዜጎች የጥብቅና አገልግሎት በመስጠትና ህጉ ከኢ.ፌ.ዴ.ሪ ህገ-መንግስት ጋር ያለውን ተፋልሶ በመተንተተን ይታወቃሉ፡፡ አቶ ተማም በተለያዩ ህግ ነክ ጉዳዮች ዙሪያ ከፍኖተ ነፃነት ጋር ያደረጉትን ቆይታ ተከታተሉን፤ መልካም ንባብ፡፡

Page 9: * p Hß ß0 16 1//6 Á÷ - Ethiopia Media Forumethioforum.org/amharic/wp-content/uploads/2014/12/finote-netsanet … · እንዲቀየር በፖለቲካው ጨዋታ ሜዳ አስገድዶታል፡፡

ፍኖተ ነፃነት

Visit us :- www.fnotenetsanet.com, www.andinet.org

9የኢትዮጵያ ህዝብ የሉዓላዊ ስልጣኑ ባለቤት እንዲሆን እንታገል! አራተኛ ዓመት ቅፅ 4 ቁ 87ቅዳሜ ህዳር 27 2007 ዓ.ም

አይገባም፡፡ ህግን የሚቃረን ነገር አለመቀበል አለብህ፡፡ ህጎች የሚወጡት መብቶችን ለመገደብ ነው፡፡ ህገ-መንግስቱን የሚቃረን ነገር አያስኬድም ብለህ መቃወም አለብህ፡፡አዋጁ ለኢትዮጵያውን መውጣት አለበት ብዬ አላምንም፡፡ የትኛውም ሀገር ዜጋ በሽብር ህግ አይገዛም፤ የሚገዛው በወንጀለኛ መቅጫ ህግ ነው፡፡ በወንጀለኛ መቅጫ ህግ ሊያስቀጣ የሚችልን ነገር ቅጣት ለማክበድ ተብሎ በሽብር ህጉ የመዳኘት ነገር አለ፡፡ ለምሳሌ አንተ ሰው ብትገድል ሊታይ የሚገባው ነገር ሰው መግደልህ እንጂ ለፖለቲካ አላማ ብለህ ሰው ብትገድል፣ ለአይዲዮሎጂ ብለህ ብትገድል፣ ከገደልክ ገደልክ ነው፡፡ በወንጀለኛ መቅጫ ህጉ መሰረት ትጠየቃለህ፡፡

ሁለተኛው ነገር ደግሞ የፀረ-ሽብር ህጉ ቅጣት የማክበድ ነገር አለው፡፡ የፀረ-ሽብርተኝነት አዋጁን ከአሜሪካ አንፃር ስንወስደው፤ እ.ኤ.አ በ2001 በኒውዮርክ በደረሰ የሽብር ጥቃት አሜሪካ የተፈጠረውን አዲስ ሁኔታ ለመከላከል በዜጎች ላይ የማይተገበር፣ ሀገርን ለመከላከል ሌሎች ሰዎች የሚቀጡበት የጦር ፍርድ ቤት ነው ያቋቋሙት፡፡ ይህ ህግ ዜጎች ላይ የማይተገበር ሀገርን ለመጠበቅ የወጣ ህግ ነው፡፡ በመንግስት ባለስልጣናት “የፀረ ሽብር ህጉ ከሌሎች ሀገራት የተቀዳ ነው” ሲባል እንሰማለን፤ ሌሎች ሀገራት ግን ህጉን በዜጎቻቸው ላይ አይተገብሩትም፡፡ህጉ የወጣው የሀገርን ደህንነት ለመጠበቅ ከሆነ የሀገርን ደህንነት የምትጠብቀው ከዜጋ አይደለም፡፡ በወንጀለኛ መቅጫ ህግ ሊዳኙ የሚችሉ ነገሮችን ያካተተ ነው፡፡ ከዚህ በመነሳት ህጉ ህገ-ወጥ ነው እላለሁ፡፡

ፍኖተ ነፃነት፡- በእነ ሀብታሙ አያሌው መዝገብ ስር ካሉ የህሊና እስረኞች መካከል አብዛኞቹ ድብደባ እንደተፈፀመባቸው ተናግረዋል፤ በእናንተ (በጠበቆቻቸው) እንዳይጎበኙም ተደርገው ነበር፡፡

አቶ ተማም፡- በህገ-መንግስቱ አንቀፅ 19 ንዑስ አንቀፅ አምስት መሰረት አንድ ሰው የትኛውንም ማስረጃ ለማመን አይገደድም፡በእኔ ደምበኞች ላይ የቀረበው ማስረጃ ስልካቸውን በመጥለፍ የተገኘ ነው፡፡ በወንጀለኛ መቅጫ ህግ አንቀፅ 6 ንዑስ አንቀፅ 6 ላይ ስልክ መጥለፍ ክልክል መሆኑን ይደንግጋል፡፡በደምበኞቼ ላይ የተፈፀመ የመብት ጥሰት አለ፡፡እንደነገሩኝ ከሆነ ቃላቸውን ሲሰጡ፤ መንግስት ጠረጠርኳቸው ካለበት ጉዳይ ጋር በማይገናኝ መልኩ ስለፓርቲያቸው ጭምር ተጠይቀዋል፡፡ይሄ አግባብነት የለውም፡በህጋዊነት የተቋቋመ ፓርቲ ስራው መንግስትን መተቸት ነው፡በስልጣን ላይ የሚገኘውን መንግስት ደካማ ጎኖች አሳይተህ እኔ የተሻልኩ ነኝ ብለህ ስልጣን መያዝ ነው፣ ፓርቲዎች የሚመሰረቱት፡፡ ያንን ለማድረግ የመናገር ነፃነት፣ የመፃፍና ሀሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት ሊከበር ይገባል፡፡ የሽብር አዋጁ እነዚህን ሁሉ ይከለክላል፡፡ የፀረብር አዋጁ አንቀፅ 5፣ 6 እና 7ትን አይተህ እንደሆነ፣ ሁሉንም ሰው ተጠያቂ ለማድረግ የወጡ ናቸው፡፡ ማንም ከዚህ ሊያመልጥ አይችልም፡እነዚህ አንቀፆች በህገ-መንግስቱ እውቅና የተሰጣቸውን የመደራጀት፣ ሀሳብን በነፃነት የመግለፅ መብቶችን ሁሉ የሚያጠፉ ናቸው፡ይሄን ያወጣው ደግሞ መንግስት ነው፡፡መንግስት ይሄን ማውጣት አይችልም፡፡ “አጠቃላይነት” አለው፣ ገለልተኝነት አለው ብዬ አላምንም፡፡ ገለልተኝነት ሊኖረው የሚችለው፣ ኢትዮጵያውያን ላይ የማይተገበር ቢሆን ነበር፡፡ አሜሪካኖችን ለምሳሌ ብንወስድ

የፀረ-ሽብር አዋጁን ያወጡት አዲስ ክስተት ተፈጥሮብናል ብለው ነው፡፡ የሽብር ስጋት አለብን ብለው ነው፡፡ ኢትዮጵያ ሽብር ያሰጋታል ወይ? የሚለው ነገር ራሱ አጠያያቂ ነው፡፡ አለባት ተብሎ ቢታሰብ እንኳ እኛ ነን መጠበቅ ያለብን፤ እኛ ደግሞ የምንጠበቀው ዴሞክራሲያዊ መብታችን ሲከበር ነው፡፡

ፍኖተ ነፃነት፡- በምርመራ ጊዜ የህሊና እስረኞች ላይ የሚፈፀም ስቃይ እና ድብደባ እንዳለ ይታወቃል፡፡ ህገ-መንግስቱ ለዜጎች የሚሰጠውን ዋስትና በመተላለፍ

በድብደባ ቃል የማሰጠት እና ታሳሪው ራሱ ላይ በመመስከር ራሱን ተጠያቂ የማስደረግ እርምጃም ይወሰዳል፡፡ በጠበቆችና የሀይማኖት አባቶች እንዳይጎበኙም ይደረጋል፡፡ ይህን እንደ አንድ የህግ ባለሙያ እንዴት ያዩታል?

አቶ ተማም፡- በርካታ ደምበኞቼ እንደዚህ ያሉ ድርጊቶች እንደሚፈፀሙባቸው በፍርድ ቤት ጭምር ተናግረዋል፡፡ ቶርቸር ወይም ድብደባ ከሌሎች በተለየ ሁኔታ ሰውን የማሳነሻ መንገድ ነው፡፡ ሰውየውን ከሰውነቱ የምታወጣበት መንገድ ነው፡፡ አንድ ሰውን አዋርደህ በራስ መተማመኑን እንዲያጣ አድርገህ ሰብዕናውን እንዲያጠፋ ነው የምታደርገው፡፡ ገራፊውም፣ ተገራፊውም

ሰብዕናቸውን የሚያጡበት ነው፡፡ ምን ትርጉም እንዳለው ያለማወቅም ነው፡፡ ሁሉ ነገር ሰውን መሰረት ያደረገ መሆን አለበት፡፡ ከህገ-መንግስቱ አንፃር ብቻም ሳይሆን ከዚህ አንፃር ነው የማየው፡፡

ፍኖተ ነፃነት፡- በማእከላዊ የሚፈፀሙ ጥቃቶችን በሚመለከት ለፍርድ ቤት በተደጋጋሚ አቤቱታዎችን ለማቅረብ ሞክራችኋል፡፡ ምን አይነት ምላሽ ተሰጣችሁ? ይህ ድርጊት የመሻሻል ሁኔታ አሳይቷል?

አቶ ተማም፡- የመሻሻል ሳይሆን የመባባስ ሁኔታ ነው ያለው፡፡ በፍርድ ቤት በኩልም ያለው ሁኔታ ተመሳሳይ ነው፡፡ ለምሳሌ በእነ አብቡከር የክስ መዝገብ፣ ቃል አሰጣጥን በሚመለከት በጣም ነው የተቃወምነው፤ ቃል አሰጣጡ ህገ-ወጥ እንደሆነ አስረድተናል፡፡ በዚህ መልኩ የሚሰጡ ቃሎች ተቀባይነት ሊኖራቸው አይገባም በማለት ተቃውመናል፡፡ህገ-መንግስታዊ ጥያቄ አቅርበን ፌዴሬሽን ምክር-ቤት ድረስ ሄደናል፡፡ ያ ትርጉም አልነበረውም፡፡ አብዛኞቹ ተከላከሉ የተባሉት፣ ተገደው በሰጡት ቃል ነው፡፡ የእነ ሀብታሙን የክስ መዝገብ በምናይበት ጊዜም “ደምበኞቼ ዋስትና ሊከለከሉ አይገባም” ብዬ ህገ-መንግስታዊ ጥያቄ አቅርቤያለሁ፡፡ ፍርድ ቤቱ ይህን መመርመር ይችላል? አይችልም? ለሚለው ይችላል ነው መልሱ። ፍርድ ቤት ህግ የመተርጎም ስልጣን አለው፡፡ ህጉ፣ በእኛ ላይ ተፈፃሚነት ለምን እንደሌለው ጠቅሼ ነው የተከራከርኩት ዝርዝሩን አሁን ይግባኝ ልንልበት ጠይቀናል፡፡ በችሎት እንደተነገረን ከሆነ ግን ዝርዝሩ ተቀባይነት አላገኘም፡፡ በአጠቀላይ በፀረ-ሽብር አዋጁ የተከሰሱ ደንበኞቼን ሁኔታ ስመለከት ግን የሚፈፀምባቸው የመብት ጥሰት የመሻሻል አዝማሚያ አለማሳየቱን ነው የምገነዘበው፡፡

ፍኖተ ነፃነት፡- በተከሳሾች ላይ የሚቀርቡ ማስረጃዎች የሚያስገርሙ ናቸው፡እኔ የተመለከትኳቸው ክሶች ላይ ከኢሳት ጋር ተነጋግረሃል የሚል ክስ ሁሉ አለ፡፡ ኢሳት በሽብርተኝነት አልተፈረጀም፤ ከህግ አንፃር ይሄ እንዴት ይታያል?

አቶ ተማም፡- ሚዲያ ሀሳብን የምትገልፅበት መድረክ ነው፡፡ ከእከሌ ጋር ተነጋገርክ፤ ከእከሌ ጋር አወራህ የሚለው የማንም ራስ ምታት ሊሆን አይገባም፡፡መብትህን አትጠቀም እንደ ማለት ነው፡፡ የፀረ-ሽብር ህጉ፣ ህገ-መንግስታዊ መብቶች እንዲጣሱ በመሳሪያነት የሚያገለግልና የህዝብን አብሮነት የሚያናጋ ነው፡፡ አንድን ሰው እንድትጠራጠር የሚያደርግ ስሜት መፍጠሩ፣ የህጉን የአፋኝነት ባህሪ ያሳያል፡ህጉን ያወጡት ሰዎች፤ “ከውጪ ነው ያመጣነው” በማለት ሲገልፁ ይደመጣሉ። እንደዚህ አይነት አፋኝ ህግ ለምንድነው ከውጪ የሚመጣው? “ይሄ ህግ ከውጪ ነው የመጣውና መቀበል አለባችሁ” ከተባልን ኢትዮጵያ የራሷ ሉዓላዊነት የሌላት፤ የራሷ ህግ ከሌላ አገር ህግ አንፃር የሚተረጎምባት ሀገር ናት ማለት ነው፡፡ ህጉን ቅቡል ለማድረግ ይሄን አይነት አገላለፅ በመንግስት ባለስልጣናት መቅረቡ በራሱ የኢትዮጵያን ነፃነትና ሉዓላዊነት የሚዳፈር ነው ብዬ የማምነው፡፡

ፍኖተ ነፃነት፡- ስለነበረን ቆይታ አመሰግናለሁ

ተማም፡- እኔም አመሰግናለሁ

“ህገ-መንግስቱ ባለቤት አልባ ነው”አቶ ተማም አባቡልጉ (የህግ ጠበቃ)

"

"ለምሳሌ በእነ አብቡከር የክስ

መዝገብ፣ ቃል አሰጣጥን በሚመለከት

በጣም ነው የተቃወምነው፤

ቃል አሰጣጡ ህገ-ወጥ እንደሆነ

አስረድተናል፡፡ በዚህ መልኩ የሚሰጡ

ቃሎች ተቀባይነት ሊኖራቸው

አይገባም በማለት ተቃውመናል፡፡ ህገ-

መንግስታዊ ጥያቄ አቅርበን ፌዴሬሽን

ምክር-ቤት ድረስ ሄደናል፡፡ ያ ትርጉም

አልነበረውም፡፡ አብዛኞቹ ተከላከሉ

የተባሉት፣ ተገደው በሰጡት ቃል ነው፡፡

Page 10: * p Hß ß0 16 1//6 Á÷ - Ethiopia Media Forumethioforum.org/amharic/wp-content/uploads/2014/12/finote-netsanet … · እንዲቀየር በፖለቲካው ጨዋታ ሜዳ አስገድዶታል፡፡

ፍኖተ ነፃነት

Visit us :- www.fnotenetsanet.com, www.andinet.org

10 የኢትዮጵያ ህዝብ የሉዓላዊ ስልጣኑ ባለቤት እንዲሆን እንታገል! አራተኛ ዓመት ቅፅ 4 ቁ 87ቅዳሜ ህዳር 27 2007 ዓ.ም

ሀገራችን ኢትዮጵያ የሰው ድሃ አይደለችም። በየጊዜው ሰው ይወጣላታል። በእሷ ፍቅር የከነፉ ልጆችን ሁሌም ቢሆን አታጣም። እማማ እንደዚህ አይነት ልጆቿን አምጣ ትወልዳቸዋለች። በእርግጥ ሁላችንም ተምጠን ብንወለድም ፣ ለእሷ ራሳቸውን አሳልፈው ሊሰጧት የተዘጋጁትን ግን ከሁላችንም በከፋ ምጥ ውስጥ ትወልዳችዋለች። ለዛሬ ከእነዚህ እማማ ኢትዮጲያ በከፋ ምጥ ውስጥ ከወለደቻቸው ጀግኖች መሃል የሚመደበውን ታላቁ እስክንድር እንቃኛለን።

እስክንድር ነጋ ፤ ከራሱ ይልቅ የሀገሩን ጥቅም የሚያስቀድም ፣ በሀገሩ ጉዳይ ባይተዋርነት የማያጠቃው ፣ ለግለሰብ ልዕልና የሚታገል ፣ ነጻነትን አጥብቆ የሚፈልግና ለዛም ዋጋ እየከፈለ የሚገኝ ታጋይ ነው። እስክንድር ፣ ላመነበት ነገር ዋጋ እንደሚከፍል በተግባር ያሳየ ሰው ነው። ‹‹ለውጥ ያለመስዋዕትነት አይገኝም። ነጻነታችንን የምንፈልገው ከሆነ ደግሞ እያንዳንዳችን ዋጋ ልንከፍል ይገባል›› ይላል። ይህ ሰው ለነጻነቱ ሲሟገት ሚስቱና ልጆቹን በስደት ተነጥቆ ስጋውን ደግሞ ቃሊቲ አድርጎ ነው። ቃሊቲ ውስጥ ሆኖም ስጋው እንጂ መንፈሱ እንዳልታሰረ በሚገባ ያስታውቃል። አርቆ አሳቢነቱ ፣ አስተዋይነቱና ከአሉታዊ ነገሮች ውስጥ እንኳ አዎንታዊ ነገሮችን የማውጣት ብቃቱ ልዩ ነው። ሰውንም በሰውነቱ ያስተናግዳል። ሁሉንም ሰው በእኩል አይን ማየት ይችላል። እስክንድር ዘንድ ዶክተር ፣ ኢንጅነር ፣ አርቲስት ፣ ጋዜጠኛ ፣ አትሌት ወዘተ…… ሁሉም እኩል ናቸው። ለራሱ መቼም ቢሆን ከፍተኛ ግምት አይሰጥም። እኔ ምን ሰራሁ? ይህ ሁላ ሙገሳ አይገባኝም የሚል ሰው ነው። የፔን አዋርድ ተሸላሚ የሆነ ጊዜ ከወዳጆቼ ጋር በመሆን «እንኳን ደስ አለህ» ለማለት ቃሊቲ በተገኘንበት ጊዜ እንኳን እንዲህ ማለቱን አስታውሳለሁ፤

‹‹እኔ ምን ሰራሁ? ይህ ሽልማት እኮ የእኔ አይደለም። በኢትዮጵያ ውስጥ ዴሞክራሲያዊ ስርአት እንዲሰፍን እየታገሉ የሚገኙት ውጤት ነው። እኔ ብቻዬን ምንም አላደረኩም። ስለዚህ እንደራሴ ሽልማት አድርጌ አልቆጥረውም።›› ይህን ሲለን እጅግ ተገረምኩ።

እሱ እየከፈለ የሚገኘውን ዋጋ እያየሁ እኔ ምን አደረኩ? ሲልም ተደመምኩ። ይህን ሲለን የታሰረ ሰው እንኳ አይመስልም። የመንፈስ ጥንካሬው አስገራሚ ነው። መንፈሱ ከቃሊቲ ውጪ እንደሚገኝ እስክንድርን ቃሊቲ ተገኝቶ የጠየቀው ሁሉ ይመሰክራል። ስጋውም ቢሆን አልተጎዳም። እስኬው ፤ ከጥሩ ተነጋሪነቱ ባሻገር ጥሩ አድማጭም ጭምር ነው። የሰውን ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ መብትንም ያከብራል። ትህትናው ደግሞ ልዩ ነው።

‹‹እስክንድር ማለት ቤተ-መጻሕፍት ነው።›› ስትል ባለቤቱ ሠርካለም ፋሲል የተናገረችው እውነት እንደሆነም መመስከር እችላለሁ። አዎ! እስክንድር ቤተ-መጻሕፍት

ነው። ምን ያህል እውቀት እንዳለው ጠጋ ብላችሁ ስታናግሩት ታውቃላችሁ። እውቀቱን ለማካፈል ባለመሳሳቱ ደግሞ እውነተኛ ምሁር ብዬ እንድጠራው እገደዳለሁ። በአጭር ደቂቃዎች እንኳ ከእስክንድር አንደበት ብዙ ቁም ነገሮችን ቀስሞ መመለስ ይቻላል። ይህ ደግሞ የእስኬውን የእውቀት መጠን በሚገባ ያሳያል። እስኬው ቃሊቲ መሆኑ ክፉኛ

ያበሳጫል። ከቃሊቲ ውጪ ቢሆን ኖሮ ብዙ ነገሮችን መስራት ይችላል። ገዢዎቻችንም ይህን ስለተረዱ ክስ መስርተውበት 18 አመት ፅኑ እስራት በይነውበታል። ይህን በሚመለከት ከአንድ ወዳጄ ጋር ስናወጋ ‹‹የእስክንድርን እስር የአንድ ግለሰብ እስር አድርጌ ለመቀበል ይከብደኛል። እስክንድር እኮ የኢትዮጲያ ሪሶርስ ነው። ኢትዮጲያ አንድ ትልቅ ሪሶርስ አታለች። ይህ ሪሶርስ ቃሊቲ መቀመጥ የለበትም። ከቃሊቲ መውጣት አለበት።›› ነበር ያለኝ፡፡ ስለ እስክንድር ይህን ሁላ ብዬ ስለ ጽናቱ ሳላነሳ ባልፍ የእስክንድርን ትልቁንና ዋናውን ጠንካራ ጎን መሳት ይሆናል። እስክንድር ጽናቱ እጅግ ያስደምማል። ጽናቱ የት ድረስ እንደሆነ የሚገልጹ አንድ ሁለት ነገሮችን ላንሳላችሁ።

እስክንድር ፣ ናፍቆት የሚባል

ብቸኛ ልጅ አለው። ናፍቆት የተወለደው ምርጫ 97ትን ተከትሎ እሱና ባለቤቱ ለእስር በተዳረጉበት 1998 ዓ.ም ላይ ነው። የናፍቆት የትውልድ ቦታ ደግሞ ቃሊቲ እስር ቤት ነው። ባለቤቱ ሠርካለም ናፍቆትን የተገላገለችው በቃሊቲ እስር ቤት ውስጥ በሚገኝ ክሊኒክ ነው። እስክንድር ከእስር አስኪፈታ ማለትም እስከ 1999 ዓ.ም ድረስ

ልጁን አላየውም። ከዚህ በመነሳትም ልጁን ናፍቆት ሲል ሰየመው። እስክንድር እንዲህ የሚወደውን ልጁን ለስምንተኛ ጊዜ ለእስር በበቃበት ማለትም በ መስከረም 3 ቀን 2004 ዓ.ም ላይ በድጋሚ ተለየው። በወቅቱ ናፍቆትን ከትምህርት ቤት በማውጣት ላይ የነበረው እስክንድር ፣ በፖሊሶች ቁጥጥር ስር ሲውል ልጁ ናፍቆት አብሮት ነበረ። ፖሊሶቹ ናፍቆትን ከአባቱ በመለየት አባቱን ይዘውት ሄዱ። ይህን ሲያስተውል የነበረው ናፍቆት ክፉኛ ተረብሾ ነበር።

እስክንድር በእንዲህ መልኩ ከልጁ ከተነጠለ በኋላ ልጁን የሚያገኘው በቃሊቲ ወህኒ ቤት ውስጥ ነው። ናፍቆት ከጊዜ ወደ ጊዜ ስነልቦናው በጣም እየተጎዳ ሲመጣ እስክንድርና ባለቤቱ ሠርካለም በአንድ ነገር ላይ መከሩ። ይህም ልጃቸው አዲስ ከባቢ

ኢዮኤል ፍሰሐ

እንደሚያስፈልገው ነው። በዚህ መሠረትም ሠርካለምና ናፍቆት እስክንድርን በመሰናበት ወደ አሜሪካ አቀኑ። ይህ ውሳኔያቸው ምንኛ ከባድ እንደነበር ሠርካለም ለስደት በተዳረጉበት ጊዜ ፤ በአንድ መጽሄት ላይ እዚህ ውሳኔ ላይ ለመድረስ ያለፈችባቸውን ውጣ ውረዶች ጽፋ ለንባብ ማብቃቷን አስታውሳለሁ። ይህን ጽሁፍ ካነበብኩ በኋላ ቃሊቲ በማምራት

እስክንድርን አገኘሁት። እሱና ሠርካለም ስላሳለፉት ውሳኔ ስጠይቀውም እንዲህ አለኝ፡-

‹‹ለናፍቆት በማሰብ ያደረግነው ነው። እዚህ ሲመጣ የመረበሽ ስሜት አስተውልበት ነበር። ከዛም በተጨማሪ በትምህርት ቤት ውስጥ ከሌሎች ልጆች የመነጠልና የብቸኝነት ስሜት ይታይበት ስለነበር ከባቢ መቀየር የተሻለ ሆኖ ስላገኘነው በጋራ መክረን የደረስንበት ውሳኔ ነው።››‹‹ባለቤትህንና ልጅህን አንተ እዚህ ሆነህ በስደት መነጠቅህ አይከብድም ወይ?›› አልኩት

እሱም ፡ - ‹ ‹ ባ ለቤቴንና ልጆቼን በእጅጉ እናፍቃቸዋለሁ። ከእነሱ መነጠሌ ክፉኛ ጎድቶኛል። ግን ይህ መስዋትነት መከፈል ያለበት መስዋዕትነት ነው። እነ ናፍቆት ዴሞክራሲያዊ ስርአት በተገነባባት ኢትዮጵያ ውስጥ መኖር አለባቸው። ለእዚህ ደግሞ መስዋትነቱን መክፈል ያለብኝ እኔ ነኝ።›› ሲል መለሰልኝ፡፡

የተናገረው ንግግሩ የእስክንድር ጽናት ምን ደረጃ እንደሆነ ፍንትው አድርጎ ያሳያል። እንዲህ አይነቱ ጽናት ያላቸው ሰዎች ፣ እጅግ በጣም ጥቂቶች ናቸው። ከእነዛ ጥቂቶች መሀል ደግሞ አንዱ ታላቁ እስክንድር ነው።

የእስክንድርና ጽናት የሚያሳይ አንድ ሌላ ነገር ጨምሬ ጽሁፌን ልቋጭ። በአንድ ወቅት እስክንድርን እየፈራሁና እየተባሁ እንዲህ የሚል ጥያቄ አነሳሁለት። ‹‹እስክንድር ፣ይቅርታ ጠይቀህ የመውጣት ሀሳብ የለህም ወይ?›› (ይህን ጥያቄ ያነሳሁለት የእስክንድር ምላሽ ጠፍቶኝ ሳይሆን የእስክንድር እዛ መሆን ስለሚያበሳጨኝ ነው።)

እንዲህ በማለት ለጥያቄዬ ምላሹን አስከተለ፡- ‹‹የኢህአዴግን መንግስት አይደለም ይቅርታ ይቅርና አመክሮ አልጠይቀውም። 18 አመት አይደል የፈረደብኝ እሷኑ 18 አመት ጠጥቼያት እወጣለሁ እንጂ እንዲህ አይነት ነገርን በጭራሽ አላስብም።››

ይህ ምላሹ የእስክንድር የአእምሮ ጥንካሬና ጽናት ምን ድረስ እንደሆነ እንድገነዘብ አድርጎኛል። እንዲህ አይነት ጽናት ከየት እንደሚገኝ ግን አላውቅም። እንደ ታላቁ እስክንድር ለመሆን እንዲህ አይነት ጽናትና የአእምሮ ጥንካሬ ግድ ይላል። ኢትዮጵያ ብዙ ታላቁ እስክንድሮችን ትሻለች። እስከዛው ግን በአንዱና ቃሊቲ በሚገኘው ታላቁ እስክንድሯ አንገቷን አትደፋም!

ታላቁ እስክንድር!

Page 11: * p Hß ß0 16 1//6 Á÷ - Ethiopia Media Forumethioforum.org/amharic/wp-content/uploads/2014/12/finote-netsanet … · እንዲቀየር በፖለቲካው ጨዋታ ሜዳ አስገድዶታል፡፡

ፍኖተ ነፃነት

Visit us :- www.fnotenetsanet.com, www.andinet.org

11የኢትዮጵያ ህዝብ የሉዓላዊ ስልጣኑ ባለቤት እንዲሆን እንታገል! አራተኛ ዓመት ቅፅ 4 ቁ 87ቅዳሜ ህዳር 27 2007 ዓ.ም

በስንቱ አንደኛ እንውጣ ሰለቸን ለለውጥ ያህል ሁለተኛ!

አሁን በኢሕአዴግ ዘመን ባስመዘገበቻቸው ድሎች ከዲጂት ዲጂት የምታደርገውን እመርታ በክፉ የሚያዩ ሁሉ ሰሞኑን በወጣው የአለም እስረኞች ቁጥር እንደሚያዝኑ እናም የሀገራችንን ደረጃ ያለአግባብ ለደቡብ አፍሪካ የሰጡብን መሆኑን አይስተውም፡፡ እኛስ ይብላኝ ለእነሱ ደግሞ ወላድ በድባብ ትሂድ እንጂ ለመታሰር የማይፈሩ ዜጎቿ እስካሉ ድረስ የሚጠበቅብንን ቁጥር ለመሙላት መጪው ምርጫ በቂያችን ነው፡፡ ቁጥሩ ሞልቶ ከዓለም አንደኛ ካልሆንን ካድሬውንም ቢሆን አስረን እናሟላለን፡፡

በዓለም ላይ 10 ሚሊየን ገደማ እስረኞች እንዳሉ ሰማን፡፡ ከነዚህም አብዛኞቹ አፍሪካውያን መሆናቸውንና ከደቡብ አፍሪካ ቀጥሎ ኢትዮጵያ በሁለተኛነት ደረጃ ላይ የምትገኝ መሆኑንም ተረዳን፡፡ ኢትዮጵያችን በስንቱ ጉዳይ አንደኛ ወጥታ ትችለው ይሆን፤ችግር የለም፡፡ እነሆ ደግሞ በእስረኛ ብዛት ከአፍሪካ ሁለተኛ ሆነች፡፡ መቼም አድሏዊነቱን ወደፊት በህግ የምንፋረደው ይሁንና በአንድ ነገር ግን ያው አንደኛ መሆናችንን ማረጋገጥ እንችላለን፡፡ በታሳሪዎቹ ብዛት ሳይሆን ጥራት፣ወይም ብቃትና እውቀት ላይ ማንም አይደርስብንም፡፡

‹‹ነገርየው መንገድ የለም እንጂ መኪና ቢኖረን እንነዳ ነበር ነው›› ብለን እንዳንል ሕጋዊ የሆነ የመንጃ ፈቃድ ራሱ የለንም፡፡ አሃ ለመጀመሪያ መንጃ ፈቃድ 5000 ብር ቅድሚያ ለመክፈል የኢሕአዴግዬ አሽከር መሆን ያሻላ፡፡ ደግሞ መንዳትና መግዛት አፍሪካ ውስጥ እንደመምራት መቆጠር ከተጀመረ እነሆ ሶስተኛው ሚሊኒየም ገባ አደል፡፡

ኧረ በቃ በቃ አትሉም! የባጃጅ ሾፌር ለመሆን 5ሺ ብር !... ይሁን የሶስት ሰው ህይወት ይዞ ለመንቀሳቀስ መንጃ ፈቃድ ያስፈልጋል፡፡ እረ ለራሴም ቢሆን ባወጣ ባልከፋኝ፡፡ ግን አንድ የአንድ ቀበሌን ነዋሪ ለማሽከርከር ግን በመሃይምነት ምስክር ወረቀት ሊያውም 3000ብር ተከፍሎት መንዳት የሚቻልባት ሱፐርዲሞክራቲክ ሃገር እኮ ነው ያለን!ባለም አንደኛ! የታላቁ መሪያችን ራዕይ ውጤት ነዋ!

እኔምለው ያ መንጃ የሚሰጠው የት ነው…፡፡ 5ሺ ከፍዬ እሱን ቢሰጡኝ ሣይሻል አይቀርም!... ያዋጣኛላ! ‹‹ማን ፉል አለ በተወደደ ባቄላ››፣ ይባል ነበር ድሮ በኛ ጊዜ፡፡ ለማንኛውም ማንም ሳይቀድመኝ ሔጄ አንደኛ ልሰለፍ እና ልከድር፡፡…ካድሬ ልሁን ማለቴ ነው፡፡ ‹‹አ..ን..ደ…..ኛ!....አ..ን..ደ…..ኛ!..›› የሚል ዘለግ ያለ ድምፅ የሚያወጣ ዘፋኝ አለን ልበል? ይህ ጥዑም ዜማ፣ በየቀኑ እንደ ኢኮኖሚ ዋልታችን መሰማት ያለበት ይመስለኛል፡፡ በሁሉም ስርዓት -በተመሳሳይ ሰዓት፡፡ አዎ! ከፊት ብቻ ሳይሆን ከኋላም ቢሆን አንደኛ መውጣት መቻል አለብን! እኛ የአፍሪካ ነፃ አውጪዎች ! ራሳችንን ከድህነትም ሆነ ከጭቆና ነፃ ባናወጣም …የአፍሪካ መዲና ነን ብለን እንኮፈስ የለ! ማንም አይቅደመን! አሁን አንደኝነታችን እንደ ድሮው በረሓብ አደለም በጥጋብ ነው እንጂ፡፡ ዲሞክራሲያዊነትን በማፈን አንደኛ ሆነናል፡፡ ሰልፈኛን በመረሸን ከቻይና ጡት አባታችን ቀጥለን አንደኛ ሆነናል፡፡ ከሁሉ ከሁሉ የመድብለፓርቲ ስርዓትን በማስፋፋት እና በተቃዋሚ ፓርቲዎች ብዛት ከአፍሪካ አንደኛ ነን ወይም ሳንሆን አንቀርም፡፡ ባለ ሶስት ዲጂት የተቃዋሚ ፓርቲዎችን የማበረታታት እድገት እንዳሳየን ተመስክሮልናል፡፡ 100 ፓርቲዎች አሉንና፡፡ ሆኖም አንዳንድ አደናጋሪ የሆኑና በብእር ስም የሚንቀሳቀሱ ባለ አንድ ቢሮ ፓርቲዎች መኖራቸው ስለሚታወቅ ጉዳዩን መንግስት እንደመንግስት በትዕግስት የሚከታተለው ይመስለኛል፡፡ ምክንያቱም በፓርቲዎች ብዛት አንደኛ ለመውጣት ለሚደረገው ትግል እንቅፋት ይሆንብናል፡፡ ባለፈው አንድነት የሚሉት 10 ፓርቲዎችን አንድ አላደረገም?

የእነዚህ ፓርቲዎች ዋና ቢሮ፣ በራሱ በመንግስት ድጎማ የሚደረግለት መሆኑም ከአፍሪካ ልዩ ያደርገዋል፡፡ ብዙ ጊዜ ፓርቲዎች በፕሮግራሞቻቸው መለያየት የተነሳ የማይስማሙና የሚወነጃጀሉ ቢሆንም፤ በመንግስት አርቆ አሳቢነት ዞሮ ዞሮ የሀገር ልጆች ስለሆኑ የጋራ ቢሮአቸውን ሙሉ ወጪ በመሸፈን በአንድነት እንዲወያዩና የሙሉ ጊዜ ፖለቲከኛ እንዲሆኑ ለማድረግ በከፍተኛ በጀት በቃሊቲና በቂሊንጦ፤ በልዩ ጥበቃ የህይወት ዘመን ስልጠና እየሰጠ ለቀጣዩ ዘመን መሪዎችን እያዘጋጀ ይገኛል፡፡ ይህም ሰናይ ምግባር በአምነስቲ ሳይቀር ታላቅ ከበሬታ ያገኘ ሲሆን፤ በአፍሪካ ብቸኛ እና አንደኛ እንድንሆን ያደረገበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡ መንግስታችን ለሚያደርገው ለዚህ ሰናይ ሀገራዊ ራዕይ ህዝቡ ከፍተኛ ድጋፉን በዝምታ እየገለጸ ሲሆን፤ ጥቂት አማፂያን ግን እስረኞችን ፍርድ ቤት ሲቀርቡ እየተከታተሉ በጭብጨባ እያጀቡ አስቸግረውናል፡፡ በተለይም በምርጫ 97 የተደረገውን ታላቅ ጥረት ያልተረዱ ተቃዋሚ አካላት ራሳቸው አንድ ላይ ወደ ስልጠና መግባት ሲገባቸው ባለመስማማታቸው ሁለት ቦታ ተሰነጠቁ፡፡ለየዋሁ ኢሕአዴግዬ የተመኙት መሰንጠቅ ሳይደፈን የነሱ ብሶ ቁጭ አለላቸዋ፡፡ይኸው ከዚያ ጊዜ ጀምሮ እነሱም ላይገባቸው፣ ኢሃዴግም ላያርመው፣ ስልጠናውን በዝዋይ በቃሊቲና ቂሊንጦ እየሰጠ ይገኛል፡፡ አሁን እንደውም የቀጣዩን ትውልድ መሪዎች በትክክል ማፍራት ተችሏል፡፡ ምክንያቱም ወያኔ ራሷ ኢህአዴግ ሳትሆን በፊት፣ ገና ጨቅላ ህጻናት የነበሩ፤ በእሷው ሥርዓተ-ትምህርት ያደጉ ጎረምሶች፣ ፖለቲካ ካልተማርን ብለው አስቸግረው ዞን ዘጠኝ ነን የሚሉ ዘጠኝ ወጣቶች እንደፍላጎታቸው በማስተናገድና በተጨማሪ በጀት ስምንት የነበረውን ዞን በቃሊቲ ወደ ዘጠኝ አሳድጎታል፡፡ ጃንሆይ፣ ለህዝቡ ከረሃብ እስከ ጥጋብ አቀረቡለት፡፡ ያባታቸውን ግቢ ለተማሪ ቤትነት ሰጡ፡፡ ቾምቤ በበኩሉ “መሬት ላራሹ” ያለውን ወጣት ጥያቄውን መልሶ ተሜን ረሸነ፡፡ ከምስራቅ ወደ ሰሜን እየነዳም የጦርነት ስልት አስተማረ፡፡ ድልንም ሽንፈትንም ያለስስት አቃመሰ፡፡ታዲያ ኢሕአዴግዬ ከዚህ የባሰ ምን አጠፋ? ዲሞክራሲ ያለዳቦ ምን ያደርግላችኋል? መጀመሪያ ድህነትን ተረት እናርግ አለ እንጂ፡፡ በምርኮ ሰበብ ብዙ ማሽኖችን ወደ ትግራይ ቢልክም፣ ራሱን ግን ከአዲሳ’ባ ቆነጃጅት መነጠል ተሳነው፡፡ ይህም ህብረብሄራዊነቱ የወለደው ወገንተኝነቱ፣ በአንዳንድ ጠባብ የወያኔ አባላት አስወነጀለው፡፡በዚህም ምክንያት “በሰበሰ” ተባለ፡፡

አሁን በጣም ያስቸገሩን በተቃዋሚ ስም የኢሃዴግን ማሊያ የለበሱ እና በደጋፊ ስም ሜዳ ገብተው እየተጫወቱ ያሉ ተለዋዋጭ መልክ ያላቸው ካድሬ + ታቃዋሚ የሆኑ፣ ሰው መሳይ ዝንጀሮዎች ናቸው፡፡ ሰላማዊ ትግል ሲባል እነዚህን ጋንዲም ሆነ ኪንግ ያልደረሱባቸውን ሰው መሳይ ዝንጀሮ ፖለቲከኞች፤ በስመ ሰርጎገብ ብቻ ማለፍ የሚቻል አልመሰለኝም፡፡ ሯጭ ናቸው ብላችሁ ስትከተሉአቸው አሯሩጠውና ፊያቶ አስጨርሰው ውልቅ ይላሉ፡፡ ሜዳውም ያው ብላችሁ ስትተዉላቸው ደግሞ ወደራሳቸው ጎል ኳስ ሲጠልዙ ታገኟቸዋላችሁ፡፡ታዲያ እኒህን ለመያዝ የተቋቋመ ልዩ ፖሊስ እና ፖሊሲ ያሻቸዋል፡፡ ሃሳብ ነው ፤ ተቀባይ ካለ፡፡ ጊዜው እኒህን መሰል ስውዝሮዎች ፈርጥጠው የሚወጡበት ወቅት መድረሱን ይጠቁማል፡፡ እንደ አንድ የሰላማዊ ትግሉ አራማጅ አገላለፅ፤ ስውዝሮዎች አፋዳሾች ናቸው፡፡ ለውጥንና ተቃውሞን በተለይ የማፋደስ ልዩ ክህሎታቸው፤ ገዢው ፓርቲ ምንም ነገር ቢሸልማቸው እንኳን የማያረካው ባለውለታዎቹ ሆነው ይገኛሉ፡፡ እሳት አደጋ ናቸው ስትሉ፣ እነሱ ግን ቀድመው እንደአትክልተኛ የችግር ችግኞችን ውሃ በማጠጣት የሚያፈሉ ዋነኛ አቀጣጣይ ሲሆኑ ታገኟቸዋላችሁ፡፡ እረ ከስውዝሮዎች ይሰውረን! … የስውዝሮዎች ጥቅም ይቅርብን! እኒህን ማርገፍ አለብንና!... እኒህ ሲረግፉ ነው ታዲያ ውጤታማ የምንሆነውና ፍሬ የምናፈራው፡፡ ማርገፍ ማለት ታዲያ እንዲሞት መቅበር ሳይሆን፣ ከቅርንጫፉ ሳለ ማድረቅ ነው፡፡ ግድያን አጥብቆ ይቃወማልና ኢሃዴግ ኋላ ወስዶ ፍርድ ቤት ቢገትረንስ፡፡ በ97 እኮ 199 ሰው የገደሉ አግአዚዎች በቁም እስር ውስጥ እኮ ነው ያሉት፡፡ ውስጥ አዋቂዎች እንደነገሩን በወታደራዊ ፍርድ ቤት ቀርበው ‘ከእንግዲህ ሰው ቀርቶ ትንኝ አንገድልም’ ብለው በይቅርታ ተፈተዋል ይባላል፡፡

እኔም የዘመኑ ተማሪ ስለሆንኩ የራሴን አዲስና ኦርጅናሌ ነገር ማፍረጥ ባልችልም፣ እድሜ ለአቤ ቶኪቻው በተማርኩት የኩረጃ ዘዴ አተኳኮሱን ችዬበታለሁ ! ምናአገባኝ! እሱ ለሽብርተኝነት ማእረግ ባይበቃም፤ እኔ ግን ከምላሴ ጸጉር ብእሬ ጠላቶቼን በብዕር እሩምታ ቅንድብ ቅንድባቸውን ማለቱ አይቀርም፡፡ ይህን የምናገረው ለናንተ ለተጠራጣሪዎቹ ነው፡፡ኢሕአዴግን እየሰደብኩም አታምኑኝ ይሆናል ብዬ እኮ ነው፡፡ እመኑኝ! ኢሕአዴግ ከምሆን ብሞት ይሻለኛል፡፡ በዕርግጥ ለሃያ ሶስት ዓመታት ኢሕአዴግዬን ሳልቃወም መኖሬን አልክድም፡፡

አርቲ-ቡርቲዎቻችን ከ “ሁሉም ዜሮ ዜሮ” እስከ “81 ዜሮ ዜሮ!”

ዛሬ ዛሬ ለወንድ ቅንድብ የሚዘፍኑ ወንድ ቅልቦች እየተበራከቱ መጥተዋል፡፡ በጋጋኖ ጉሮሮአቸው ትናንት ያበሻቀጡትን ዛሬ ሊያሽቃብጡለት ጭራቸውን እንደነቦቢ የሚቆሉ “አርቲ-ስት” ተብዬዎች! ኪነ-ጥበብን የገዢ-መደብ ካዳሚ ለማድረግ ቀሚሳቸውን አጥልቀው፣ አፋቸውን እያሞጠሞጡ፣ ከገበታው ሊቀላውጡ ቋምጠዋልና ያለአንዳች ይሉኝታ በየቤታችን የቴሌቭዥን መስኮት ብቅ ብለዋል፡፡ የጫካ-ኩታራ ከመንደር-ኩታራ ጋር ኩታ ገጥሞ፤ ከያንዳንዳችን ጉሮሮ ተነጥቆ ለሚሠራ ሥራ ለገዥው ጨቋኝ “ዝማሬ መወድስ” እንድናቀርብና እንደነሱው እንድንካድም እየጎተጎቱን ይገኛሉ፡፡

ኦ - ያ - ያ . . .ኦያ-ህያ . . . አያ-ሆዬ አያያ-ሆዬ

እያናፉ እንዳ’ህያ

. . .ሆድዬ፤ አልጠግብም ሸቅዬ

ህሊናየን ጥዬ

እንደ-ንዋይዬ

ልዝፈን ለነአብዬ….

እያልኩ በትርዬ

ሙሴዬ መልዬ

ከካድሬ-አካዳሚ ስልጠና ያገኙ ካዳሚዎች የዘራፊ-ቡድኖች አንሶላ ውስጥ ገብተው የሀብት መንገዱን በተጋደሙበት አልጋ ላይ እየፈለፈሉ ያዜማሉ-ፍልፈሎች!

“ይህ ጽሁፍ የተያቢዋን እንጂ የፀሐፊውን አቋም አያንፀባርቅም”

እናንተዬ -“ዘጋቢ” (ትርጉም-በስለሺ) የሚለውን ጋዜጣ ግን ታነቡታላችሁ? ከግማሽ በላይ የሚሆን የማስታወቂያ ገፁን ማለቴ አይደለም! ከግማሽ በታች የሆኑትን በተለያዩ ዓምደኞች (ምንደኞች) የሚጣፉ ጥሁፎችን ማለቴ እንጂ! ሁሉም ከግርጌያቸው፡- “ጽሑፉ የጸሐፊውን አመለካከት ብቻ የሚያንፀባርቅ መሆኑን እንገልፃለን፡፡” እያሉ አዘጋጆቹ ከኃላፊነት የመሸሽ ሩጫቸውን ይኽው ለ20 ዓመታት ገፍተውበታል! ወቸው ጉድ! “ከመዘጋት መሰንበት” ያለው ይህ ጋዜጣ በአጠቃቀስኩ ዘይቤው ሰበር -ሰካ እያለ፤ ሳይሄስም ሳያወድስም ይኽው እንደ-አማረ’በት ሽክ ብሎ ከኛው ጋር አለ፡፡ “አለሁ ከናንተው ጋር!” አለ ጃሉድ¡ “ፕሬስን ከስቅላት አድኑ!” እያለ የሚማጠነው ይህ ጋዜጣ፣ ከዘመነ-ጋቤጣ እስከ ዘመነ-ቡጥቦጣ ከትጥቅ-ታጋዮቹ ጋር በዘለቀ ግለሰብ የተቋቋመ ነውና አትፍረዱበት! የጓዶቹ ነገር አልሆንለት ቢለው ነው፡፡

በዚህ አካሄዱ ከገፋበት እኮ . . . ይህ “ዘጋቢ” ጋዜጣ ርዕሰ-አንቀፁ ስር፤ “ርዕሰ-አንቀፁ የተያቢዋን እና የጋዜጣ አዟሪዎችን አመለካከት ብቻ የሚያንፀባርቅ መሆኑን በጓዳዊ ትህትና እንገልጻለን! ከምስጋና ጋር -የናንተው የገዢዎቼ!” የሚለን

ኢትዮጵያዊነት

ኢትዮጵያዊነት ዕዳዬ ኢትዮጵያዊነት ፀጋዬ

ኢትዮጵያዊነት ስቃዬ ኢትዮጵያዊነት ደስታዬ

ኢትዮጵያዊነት ጉድለቴ ኢትዮጵያዊነት ሙላቴ

ኢትዮጵያዊነት ሹመቴ ኢትዮጵያዊነት ቅጣቴ

ኢትዮጵያዊነት ጭነቴ ኢትዮጵያዊነት እረፍቴ

ኢትዮጵያዊነት ሕይወቴ ኢትዮጵያዊነት እረፍቴ

ኢትዮጵያዊነት ለቅሶዬ ኢትዮጵያዊነት ተስፋዬ

ሰለሞን ሞገስ(ፋሲል) ጽሞና እና ጩኸት ጥር 2006፤ ገጽ 16

‹‹አብዮት ጠሪዎችን››፤ ራሱን ‘መንግስት’ ብሎ የሚጠራው ቡድን ሃይ ይበላቸው እንጂ…..!!!

ማመልከቻ፡-

4ኪሎ አካባቢ ያሉ በጣት የሚቆጠሩ ‹‹ጥቂት›› የታክሲ ወያላዎች ባለማቋረጥና ለነውጥ በሚያነሳሳ አስገምጋሚ ነጎድጓዳማ ድምፀት፤ ‹‹አብዮት …. አብዮት …… አብዮት፡- አንድ የቀረው! አብዮት…፣

1 የቀረው…፣የሞላ አብዮት…..! …›› በማለት አብዮት እየጠሩ ነውና ጠሃዩ-መንግስታችን ፈጣን እርምጃ ይውሰድልን፡፡

‹‹አብዮት ጠሪዎችን››፤

****************************************************************************

****************************************************************************

***************************************************************************

****************************************************************************

“የጉድ አገር ገንፎ . . .”

አንድ ወዳጄ በራድዮ የቆዳ ጃኬቴ ተሰነጣጠቀብኝ የሚል ግለሰብ፣ በጣቢያው ተገኝቶ ለችግሮቹ ምላሽ ከሚሠጥ ባለሙያ ጋር ሲወያይ ሠምቶ ክፉኛ ማዘኑንን አጫወተኝ፡፡ ብስጭቱ፣ በኢቦላ ፍጥነት ተጋባብኝ፡፡ በተለያየ የችግር ውርጭ ጃኬቱ ሳይሆን አከላቱ በተሰነጣጠቀ ህዝብ መሀል፤ ወደ አንድ ባለሙያ ሄዶ በቀላሉ የሚፈታን ጉዳይ እንደ ብሔራዊ ችግር በሚዲያ ማስታመም በደሀው ቀጭ ማላገጥ እንጂ ሌላ ምን ይባላል?

ትላንት ስለቆዳ በሽታ አድምጠን ስናካብድ፣ ዛሬ ስለቆዳ ጃኬት መስማት ጀመርን… ነገ ደግሞ . . . ይሄን የሠማች አያቴ የሚዲያ እና የሜዳ ወሬ ቢቀላቀልባት፤ “የጉድ አገር ገንፎ . . .” ስትል ተረተች። እሷ አንጠልጥላ ብትተወውም እኔ ጨረስኩት፤ “ሱፐር ማርኬት ይገኛል”

ታላቁ እስክንድር!

Page 12: * p Hß ß0 16 1//6 Á÷ - Ethiopia Media Forumethioforum.org/amharic/wp-content/uploads/2014/12/finote-netsanet … · እንዲቀየር በፖለቲካው ጨዋታ ሜዳ አስገድዶታል፡፡

ፍኖተ ነፃነት

Visit us :- www.fnotenetsanet.com, www.andinet.org

12 የኢትዮጵያ ህዝብ የሉዓላዊ ስልጣኑ ባለቤት እንዲሆን እንታገል! አራተኛ ዓመት ቅፅ 4 ቁ 87ቅዳሜ ህዳር 27 2007 ዓ.ም

ሕዝብ ይሾማል፣ ሕዝብ ይሽራል፤ ዲሞክራሲያዊ ምርጫ ሲሰፍን በድምጽ መስጫ ካርዱ፣ አምባገነናዊ አገዛዝ እንደመርግ ሲጫነው ደግሞ በእምቢተኝነት! በሰላማዊ አብዮትም ሕዝብ መሪዎችን ይሾማል፣ ይሽራል፡፡ ይህ ፀሐይ የሞቀው ሃቅ ቢሆንም፤ አገራችን ኢትዮጵያ በዲሞክራሲያዊ ምርጫ መሪዎች ነግሰውባት አያውቁም፡፡ በዚህ ጽሁፌ እንደ ኢሕአዴግ ሹማምንት ያለፉትን መንግስታት ለመኮነን አይዳዳኝም፡፡ መውቀስ የማልሻው የእነሱን መልካም ምግባር አድንቀን ከስህተታቸው ደግሞ በመማር የነገን ጉብጠት ማቅናት እንደሚገባ ስለማምን ነው ፡፡

ለዘመናት በህዝብ ጫንቃ ላይ የተንሰራፋውን የአፄውን “የንጉስ አይከሰስ” ዘመን አሽቀንጥሮ የጣለው ሕዝባዊ አብዮት፤ በወታደራዊ ጁንታ መጨንገፉ ትልቁ የታሪክ ማፈሪያችን ነው፡፡ ሕዝባዊ አብዮቱ የቀደደውን ጐህ፣ ወታደራዊው ደርግ በጽልመት ጋረደውና አገሪቱን ለሌላ አብዮት አሳልፎ ሰጣት፡፡ ለ17 ዓመታት የመከራን ገፈት ሲጨልጥ የነበረው የኢትዮጵያ ህዝብም፤ የሥርዓቱ አገዛዝ ጎፍንኖት የዛሬዎቹን መሪዎቻችንን ከደደቢት በረሃና ከአሲምባ ተራራ የሽፍትነት ዘመን ጀምሮ እያገዘ ለአራት ኪሎው ቤተ-መንግስት ቢያበቃቸውም፤ የዜጎች ውድ በህይወት የተገበረለት የነፃነት ትግል፣ ለጥቂት ግለሰቦች ንግስና ተጠምዝዞ አረፈው፡፡በተለይም በ1987 ዓ.ም ሕገ-መንግስቱ በህዝብ ይሁንታ ሳይሆን በሥርዓቱ ዘዋሪዎች ፍላጎት በመጽደቁ፣ ነጋሪት የተጎሰመለት የዲሞክራሲ ስፍነት ከወረቀት ላይ ፉከራና ቀረርቶ የዘለለ አልሆነም፡፡

በተለይም ከምርጫ 97 በኋላ ኢሕአዴግ የለየለት አምባገነን ሆኖ ብቅ አለ፡፡ ድርጅታዊ መዋቅሩን እንደ ኢሠፓ አደረጃጀት በየመንግስት መሥሪያ ቤቱ አስርጎ በማስገባት ፈላጭ ቆራጭ ሆነ፡፡ የፓርቲና የመንግስት አሰራር ፍፁም በተቀላቀለበት አካሄድ አገሪቱ የእውር ድንብሯን መዳከር ያዘች፤ አልፎ ተርፎ ግንባሩን ያዋቀሩት ዘውጌ ድርጅቶች፣ የአገሪቱን ግዙፍ የገቢ ምንጮች በመቆጣጠር፣ የለየላቸው ነጋዴዎች ሆነው አረፉት፡፡ሹማምንቱም ወንበራቸውን ተተግነው የአገርን ሃብት እየዘረፉ የታላላቅ አክሲዮኖች ባለቤት ሲሆኑ፤ ህዝቡ እጁን አጣጥፎ በበይ ተመልካችነት እየታዘባቸው ነው፡፡ እነሱ በህዝብ ሃብት ሲቀናጡ፣ ዜጎችን ከቀዬአቸው እያፈናቀሉ መሬቱን ሲቸበችቡ፣ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮችና ሀቅ ዘካሪ ጋዜጠኞችን በየቀኑ እያፈኑ ዘብጥያ ሲወረውሩ፣ ወጣቱ ትውልድ በአገዛዙ ተንገሽግሾ ለባዕድ አገር ስደት ሲዳረግ፣ ድህነት ለዜጎች ህልውና

ለምርጫ 2007 ከህዝቡ ምን ይጠበቃል?

ፈተና ሲሆን፣ የህዝብ ዝምታ ለምንድን ነው? እያንዳንዱ ዜጋ በአገሩ ጉዳይ ከጠቅላይ ሚ/ሩ ወይም ከሹማምንቱ እኩል ያገባኛል በሚል ስሜት ሊነሳ ይገባዋል፡፡ ህዝቡ፤ የዘር፣ የሃይማኖት ልዩነቱን አጥብቦና አቻችሎ፣ የሥርዓቱን አምባገነናዊ አገዛዝ በጋራ ሊታገል በየሚገደድበት ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ በ1997 ዓ.ም የተነጠቀውን የመሾም የመሻር መብቱን የሚያስመልስበትና ሥልጣን የህዝብ መሆኑን የሚያስመክርበት ወቅት ቢኖር አሁን ነው፡፡ በምርጫ 2007 ዓ.ም አኩሪ ታሪክ መሠራት ይኖርበታል፡፡

ከዚህ አንፃር ከባለፉት የምርጫ ተመክሮዎች በመነሳት ከህዝቡ ምን ይጠበቃል? የሚለው ጉዳይ ምላሽ የሚሻ ጥያቄ ነው፡፡ ኢሕአዴግ፣ የተቃውሞውን ጐራ እንቅስቃሴ ለማዳፈንና የመድብለ-ፓርቲ ሥርዓቱን ሙሉ ለሙሉ ለመናድ የማይፈነቅለው ድንጋይ እንደማይኖር ግልጽ ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት ተቃዋሚ ፓርቲዎች ተራ የአዳራሽ ውስጥ ስብሰባ አድርገው እንኳ ከሕዝብ ጋር እንዳይገናኙ በሩ ተከርችሟል፡፡ ነገር ግን በሰላማዊ ትግል ጥላ ስር የተጠለሉና የዜግነት ግዴታቸውን ለመወጣት የሚፍጨረጨሩ ታጋዮችን በአሸባሪነት እየፈረጀ ሲያስር ተመልክተን ተስፋ መቁረጥ የለብንም፡፡ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች ሲታሰሩ፣ በሌላ መሪ መተካት ወቅቱ የሚጠይቀው የትግል ስልት ነው፡፡ በአንድ ሰው ቦታ አስር ሰዎችን ለመተካት ህዝባዊ ንቅናቄዎች መቀጣጠል አለባቸው፡፡ እንደ ሰንሰለት የተሰናሰለ ህዝባዊ እምቢተኝነት ማለትም ይሄ ነው፡፡

ባለንበት የምርጫ ዋዜማ ከምንግዜውም በተሻለ ሁኔታ ህዝቡ እምቢተኝነቱን በአደባባይ እየገለፀ በመሆኑ ጅማሬው እጅግ አበረታች ነው፡፡ ኢሕአዴግ፣ በምርጫ 2002 ወቅት 96.6% ያህሉን የፓርላማ ወንበር የተቆናጠጠው በህዝብ ይሁንታ እንዳልሆነ ስለሚያውቅ፣ መቼም ቢሆን የሚመራውን ህዝብ አያምንም፡፡ ሕዝቡም የኢሕአዴግ ባዶ ተስፋ አንገሽግሾታል፡፡ የኢሕአዴግን ዲስኩር አምኖ መቀበል ጉም እንደመዝገን ሆኖበታል፡፡

በአሁኑ ወቅት የኢህአዴግ ቱባ ሹማምንት ወደ ሕዝብ እየወረዱ ባደረጉት ውይይት የገጠሟቸው ፈተናዎች እጅግ አስደንጋጭ ሆነውባቸዋል፡፡ ሹማምንቱ፣ ከሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች ጀምሮ ለሚሰነዝሯቸው የተቃውሞ ሃሳቦችና ለሚያነሷቸው ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት አቅም ሲያጥራቸው ተስተውሏል፡፡ በተለይም በኢህአዴግ የአገዛዝ ዘመን ለአቅመ-አዳምና ለአቅመ-ሄዋን የደረሱ ወጣቶች ሥርዓቱን ፊት ለፊት እየተጋፈጡት ይገኛሉ፡፡ ሌላው ቀርቶ ድርጅቱ በግዴታም ሆነ በውዴታ “ፎርም” እያስሞላ አባል ያደረጋቸው ካድሬዎቹ ሣይቀሩ ፈታኝ የሆኑ ጥያቄዎችን በማንሳት እየሞገቱት ነው፡፡ አብዛኛዎቹም ራሳቸውን ከአባልነት እያገለሉ ይገኛሉ፡፡ ይሄ ህዝባዊ እምቢተኝነት ሳይቀዛቀዝ መቀጠል ይኖርበታል፡፡ የተገኘውን ጭላንጭል ቀዳዳ በመጠቀም ህዝብን ማንቀሳቀስ ይገባል፡፡

በዚህ ረገድ ከምርጫ 97 ክሽፈትና ከቅንጅት መፈራረስ ማግስት፤ የቅንጅትን መንፈስ ተላብሶ የተመሠረተው አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ፤ ከገዢው ፓርቲ የተሻለ እቅድ ቀምሮና ኢሕአዴግ ከሚከተለው ከአብዮታዊ ዲሞክራሲ ፍልስፍና

ይልቅ ሊበራሊዝም የተሻለ ብቻ ሣይሆን የዘመኑ ቀዳሚ ምርጫ መሆኑን አምኖ ህዝብ ውስጥ ገብቷል፡፡ አንድነት ፓርቲ፣ ባለፉት ስድስት የትግል አመታት የተቃውሞውን ጎራ ቢቻል በውህደት ካልሆነም በግንባር ለማሰባሰብና ኢህአዴግን በብርቱ የሚፈታተን አውራ ተቃዋሚ ፓርቲ ለመፍጠር በብርቱ ጥሯል፡፡ በተለያዩ መሠናክሎች ሳቢያ ጥረቱ ባይሳካም የራሱን መዋቅር በመላ አገሪቱ ዘርግቶ፣ በ2007 ዓ.ም ምርጫ ህዝብን የሥልጣን ባለቤት ለማድረግ ከወዲሁ እየተዘጋጀ ነው፡፡ በተለይም ከሐምሌ 2005 ዓ.ም ጀምሮ “የሚሊዮኖች ድምጽ ለነፃነትና ለመሬት ባለቤትነት” በሚል መርህ በመላ አገሪቱ ባደረጋቸው ሰላማዊ ሰልፎችን እና የአዳራሽ ስብሰባዎች /ከገዢው ፓርቲ ጋር አንገት ላንገት በመተናነቅ ማሳካት የተቻለ መሆኑ ሊጤን ይገባዋል፡፡/ የህዝቡን የልብ ትርታ በሚገባ አዳምጧል፡፡ ህዝቡ፣ የሥርዓት ለውጥ ፍላጐት እንደ ቋያ በውስጡ የሚንቀለቀልበት ወቅት ላይ ስለመሆኑ አያጠራጥርም፡፡

ይህን ህዝባዊ እምቢተኝነት በውል የተረዳው አንድነት ፓርቲ፣ በዚህ በተጠናቀቀው የህዳር ወር በ2007ዓ.ም ምርጫ እንደሚሳተፍ በአደባባይ መግለጫ ሰጥቷል፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ ለተነሱ አሉታዊም ሆነ አዎንታዊ ማጉረምረሞች የተከበሩ አቶ ግርማ ሠይፉ፤ “በምርጫ መሳተፍ መርህ ላይ የተመሠረተ ውሳኔ ወይስ ኢህአዴግን ማጀብ?” በሚል ርዕስ የፓርቲው ልሳን በሆነችው ፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ ላይ ያስነበቡን መጣጥፍ በቂ ነው የሚል እምነት ስላለኝ ወደዚያ ሃሳብ አልገባም፡፡

የዚህ ጽሁፍ ትኩረቱ፣ የ2007 ዓ.ም ምርጫ በህዝባዊ ድል እንዲደመደም ህዝብ ማድረግ የሚገባውን ማሳየት ነው፡፡ከዚህ አንፃር በቅድሚያ መሆን ያለበት ህዝቡ በምርጫ ካርዱ መንግስትን መቀየር አንደሚችል አምኖ እንዲቀበል፤ ከግለሰብ ጀምሮ የማሳመን ሥራ መስራት ነው፡፡ከዚሁ ጋር በማያያዝ ህዝቡ ድምጽ ሊያሰጠው የሚያስችለውን ቅድመ-ሁኔታ ያለምንም ማመንታት ማከናወን ይኖርበታል፡፡ የምርጫ ጣቢያዎችን እያጣበበ፣ የምርጫ ቦርድ ባወጣው ፕሮግራም መሠረት መመዝገብና የምርጫ ካርዱን መውሰድ ይኖርበታል፡፡ የወቅቱን ወሳኝነት በማጤን፣ ህዝቡ በየቀኑ ከምርጫ ጋር የተያያዙና ከተለያዩ ወገኖች ማለትም ከገዢውም ሆነ ከተቃዋሚ ፓርቲዎች የሚሰነዘሩትን ሃሳቦችና የሚተላለፉትን መልዕክቶች በሚገባ መከታተል ጠቀሜታው የጎላ ነው፡፡ ህዝቡ በሚገናኝባቸው ማህበራዊ ትስስሮቹ ማለትም በሰንበቴ፣ በእድር፣ በእቁብ፣ በሥራ ቦታ፣ በልቅሶ ቤት፣ በሠርግ ቤት፣ ራሱ ኢህአዴግ በሚጠራቸው ስብሰባዎች እና ስልጠናዎች፤ እንደዚሁም በ1 ለ5 አደረጃጀቶች ላይ በዋነኛነት ምርጫን የተመለከቱ ሃሳቦችን በማንሳት፣ መረጃ መለዋወጥና መመካከር ህዝባዊ እምቢተኝነቱን ያጎለብተዋል፡፡ ሀሳብን በነፃነት የመግለፅ ሕገ-መንግስታዊ መብትን በመጠቀም በተለያዩ የስብሰባ መድረኮች ላይ የገዢውን ፓርቲ ህፀፆች በመንቀስ ማጋለጥ ተገቢነቱ አያጠያይቅም፡፡በተለይም ኢሕአዴግ አማራጭ የፖለቲካ ፓርቲዎች ወደህዝቡ እንዳይደርሱ የሚተገብራቸውን ስውር ሴራዎች ማጋለጡ እጅግ ጠቃሚ ነው፡፡ በዚህ ረገድ ከመስከረም 5 እስከ 11/2007 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ መምህራን ከኢሕአዴግ ሹማምንት

ጋር በነበራቸው ቆይታ የገዢውን ፓርቲ አምባገነንነት ያገዘፉና በብርቱ የኮነኑ ነበሩ፡፡

ሌላው ከህዝቡ የሚጠበቀው ጉዳይ በተቃውሞው ጐራ የተሰለፉ ፓርቲዎችን ተአማኒነት መመርመር ነው፡፡ ምርጫ ሲመጣ እንደ አይጥ ከተሰወሩበት ጎሬ ብቅ ብለው የምርጫ ምልክት የሚወልዱና በሁለትና በሦስት ሰዎች የተዋቀሩ አጃቢ-ኢሕአዴግ ፓርቲዎችን መለየት ከህዝብ ይጠበቃል፡፡ ህዝባዊ መሰረት ያላቸውና የተሻለ ፕሮግራምና ስትራቴጂ የማቅረብ አቅሙ ያላቸው ፓርቲዎች፤ የተለያዩ የመገናኛ ብዙሃንን ተጠቅመው በየጊዜው የሚያስተላልፉትን መልእክት በንቃት መከታተልና ለጥሪያቸው ተገቢውን ምላሽ መስጠት ያስፈልጋል፡፡

በ1997 ዓ.ም ምርጫ የሕዝቡ ዱብ-እዳ ውሳኔ ያስደነገጣቸው የቀድሞው ጠቅላይ ሚ/ር አቶ መለስ ዜናዊ፣ በቴሌቪዥናችን መስኮት ቀርበው፤ “የአዲስ አበባ ህዝብ ኢህአዴግን ለመጣል እኩለ ሌሊት ወጥቶ ተሰለፈ፡፡” ሲሉ ተደምጠው ነበር፡፡ ይሄ አኩሪ ህዝባዊ እምቢተኝነት በምርጫ 2007 ዓ.ም መደገም ይኖርበታል፡፡ ኢህአዴግ፣ ‹እኔ ከሌለው አገሪቱ አትኖርም፣ ትፈርሳለች፣ እኔ ካልነገስኩኝ አገር አትለማም፣ እኔ ካልተሾምኩኝ የዕለት ጉርስ አታገኙም› በሚለው የቅዠት አዙሪት ሳንታለል፤ በኢትዮጵያዊ ጨዋነት ድምጽ በመንፈግ ልናስተምረው ይገባል፡፡ ከኢህአዴግ አገዛዝ ማክተም በኋላ ኢትዮጵያም እንደ አገር፣ ህዝብም በኢትዮጵያዊነቱ አምኖ እንደሚዘልቅ የማሳያው ሰዓት አሁን ነው፡፡

ዛሬ እንደ መርፌ ቀዳዳ የጠበበውን የአገራችንን የፖለቲካ ምህዳር ለማስፋት የተቃዋሚ ፓርቲዎች አባላትና መሪዎች፣ የቁርጥ ቀን ልጅ የሆኑት እንደ እነ እስክንድር፣ ርዕዮትን እና ተመስገን ደሳለኝን የመሳሰሉ ለሆዳቸው ያላደሩ በጣት የሚቆጠሩ ጋዜጠኞች ተጋድሎ ብቻ ውጤት ያመጣል ተብሎ አይጠበቅም፡፡ ከእነዚህ ውድ የኢትዮጵያ ልጆች ጐን መቆም የወቅቱ ጥያቄ መሆኑን መላው የአገራችን ህዝብ መገንዘብ አለበት፡፡ በተለይም የቤተ-መንግስቱ አፍንጫ ስር ከከተመው የአዲስ አበባ ህዝብ ብዙ-ብዙ ይጠበቃል፡፡

ሌላው ከምርጫ 97፣ ከ2002 እና ከ2005ቱ የማሟያ ምርጫ መማር የሚገባን ነገር ቢኖር የድምጽ ቆጠራውን ሂደት በንቃት የመከታተሉ ጉዳይ ነው፡፡ የተቃዋሚ ፓርቲ እጩ ተወዳዳሪ ታዛቢዎች ፍጹም ሀቀኛ ሆነው የግንባር ሥጋ ሊሆኑ ይገባል፡፡ የአንድም ኢትዮጵያዊ ዜጋ ድምጽ እንዳይጭበረበር መታገል ያስፈልጋል፡፡ ኢሕአዴግ በለመደ እጁ የምርጫ ኮሮጆውን እንዳይገለብጥ መረባረብ ከህዝቡ ይጠበቃል፡፡ በተለይም የተማረው ማህበረሰብ ለዚህ ቅዱስ ተግባር ዋጋ ሊከፍልና ህዝባዊ ወገናዊነቱን ሊያስመሰክር ይገባል፡፡ ኢህአዴግ የኑሮ ውድነቱ በደቆሰውና ፊደል ባልቆጠረው ህዝብ እየነገደ እስከመቼ ይዘልቃል? የሚለው ጥያቄ በምሁራን አዕምሮ ውስጥ ማቃጨል አለበት፡፡ በቀጣይ ከምርጫ ውጤት በኋላ ከህዝቡ የሚጠበቀውን ተጋድሎ ለማሳየት እሞክራለሁ፡፡

ቸር እንሰንብት

አበበ አካሉ ክብረት

Page 13: * p Hß ß0 16 1//6 Á÷ - Ethiopia Media Forumethioforum.org/amharic/wp-content/uploads/2014/12/finote-netsanet … · እንዲቀየር በፖለቲካው ጨዋታ ሜዳ አስገድዶታል፡፡

ፍኖተ ነፃነት

Visit us :- www.fnotenetsanet.com, www.andinet.org

13የኢትዮጵያ ህዝብ የሉዓላዊ ስልጣኑ ባለቤት እንዲሆን እንታገል! አራተኛ ዓመት ቅፅ 4 ቁ 87ቅዳሜ ህዳር 27 2007 ዓ.ም

ከጥቅምት ወር አጋማሽ ጀምሮ በእስር ላይ የሚገኙት የአንድነት ፓርቲ የክልል አመራሮች በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ቀረቡ፡፡ አቶ አለባቸው ማሞ ፣ አቶ አንጋው ተገኝ ፣ አቶ እንግዳ ዋኘውና አቶ በላይነህ ሲሳይ ፣ ረቡዕ ህዳር 23 ቀን 2007 ዓ.ም በፌደራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ቀረቡ፡፡

በተከሳሾቹ ላይ የግንቦት ሰባትን ተልዕኮ በመቀበል፤ ከአማራ ክልል ለግንቦት ሰባት አባል በመመልመል ወደ ኤርትራ በመላክና የሽብር ወንጀል ለመፈፀም ሲንቀሳቀሱ በቁጥጥር ስል መዋላቸውን ፖሊስ ገልጿል፡፡ፖሊስ በበኩሉ ተጠርጣሪዎቹ ግንኙነት ሲያካሂዱ የነበሩት በኤሌክትሮኒክስ መሳሪያ መሆኑን ፤ የሰነድ ማስረጃዎችን ሰብስቦ አለመጨረሱንና ያልተያዙ ግብረ-አበሮቻቸው መኖራቸው ገልፆ ይሄን አጣርቶ ለመቅረብ የጊዜ ቀጠሮ እንዲሰጠው ጠይቋል፡፡

የተከሳሾቹ ጠበቃ የሆኑት አቶ ገበየሁ ይርዳው ፣ በበኩላቸው ደምበኞቻቸው ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ቆይተው የጊዜ ቀጠሮ የሚሰጥበት አንድም የህግ አግባብ አለመኖሩን ገልፀው ፤ ደምበኞቻቸው ለፍርድ ቤት ቃላቸውን ሳይሰጡ ፣ ለፖሊስ የጊዜ

በምስራቅ ኢትዮጵያ የተንቀሳቀሰው የአንድነት አደራጅ ቡድን ፤ በምዕራብ ሀረርጌ ፣ በምስራቅ ሀረርጌና ድሬዳዋ ተንቀሳቅሶ ድርጅታዊ መዋቅሩን በማጠናከር ስኬታማ ስራዎችን አከናውኖ በአሰብ ተፈሪ ፣ ጭሮ ከተማ የምዕራብ ሀረርጌ ዞን ፅህፈት ቤት ከፈተ፡፡

የምርጫ ግብረ-ሀይልና የድርጅት ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ፣ በቀጣዩ ሳምንት በ10 የማስተባበሪያ ፅህፈት ቤቶች ለድርጅታዊ ተልዕኮ በመላ ኢትዮጲያ እንደሚንቀሳቀሱ ከድርጅት ጉዳይ ፅ/ቤት የደረሱን መረጃዎች ያመለክታሉ።

አንድነት ባሳለፍነው ሳምንት በሀዋሳ ፣ መቱና ባህርዳር አዳዲስ ፅህፈት ቤቶችን መክፈቱን ለማወቅ ተችሏል።

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ፣ ለሙስሊም ተወካዮች ምስክርነቱን ሰጠየአንድነት ፓርቲ የክልል አመራሮች ፍርድ ቤት ቀረቡ

በጦማርያኑና ጋዜጠኞቹ ላይ የተሻሻለው ክስ ቀረበ

መድረክ፣ የጠራው የተቃውሞ ሰላማዊ

ሰልፍ እውቅና አገኘ

አንድነት ፓርቲ በተለያዩ የክልል ከተሞች ፅህፈት ቤት ከፈተ

ኢህአዴግ ካድሬዎቹን ወደ ትምህርት ቤቶች እያሰረገ ነው

ቀጠሮ መፈቀዱን ተቃውመዋል፡፡ አቶ ገበየሁ ፣ የደምበኞቻቸው አያያዝ ህገ-ወጥ መሆኑንና አንድ ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር ሊውል የሚችለው ተጠርጣሪው ለመያዝ የሚያበቃው በቂ ማስረጃ ሲኖር መሆኑን ተናግረው ፤ ተከሳሾቹን ለመያዝ የሚያስችል በቂ የሰውና የሰነድ ማስረጃ ሳይቀርብ በቁጥጥር ስል መዋላቸው ህገ-ወጥ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ አንድ ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር ሊውል የሚችለው ተጠርጣሪው ለመያዝ የሚያበቃው በቂ ምክንያት ሲኖር ነው፡፡ “ደምበኞቼ በተጠረጠሩበት ወንጀል ለመያዝ የሚያበቃ በቂ ምስክርና ሰነድ ሳይኖር እንደተያዙ ያመላክታል” በማለት ተናግረዋል፡፡

ተከሳሾቹ ከፍተኛ የሆነ ኢ-ሰብአዊ ድርጊት እንደተፈፀመባቸው የገለፁ ሲሆን ፣ የተያዙትም የፖለቲካ ፓርቲ አባል በመሆናቸውና መጪው የምርጫ ጊዜ እንደመሆኑ መጠን ፓርቲያችን በሰጠን ተልዕኮ መሰረት ህዝቡን በመቀስቀሳችን ነው እንጂ አንድም የሰራነው ወንጀል የለም ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

የፌደራሉ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ፖሊስ የጠየቀውን የ28 ቀን ቀጠሮ በመፍቀድ ቀጣይ ቀጠሮውን ለጥር 21 ቀን 2007 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

ህዝበ-ሙስሊሙ ህገ-መንግስታዊ የሀይማኖት ነፃነት ጥያቄ አስይዞ ውክልና የሰጣቸው የህዝበ ሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎች ፣ ህዳር 25 ቀን 2007 ዓ.ም በዋለው ችሎት የመከላከያ ምስክራቸውን አስደመጡ፡፡ የችሎቱ ቀዳሚ ምስክር የነበረው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ፣ ከዚህ ቀደም ሳይቀርብ የቀረ ቢሆንም የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ለመጨረሻ ጊዜ በሰጠው ትእዛዝ መሰረት ሀሙስ ሕዳር 25 ቀን 2007 ዓ.ም በዋለው ችሎት ታስሮ ከሚገኝበት ዝዋይ ማረሚያ ቤት በመምጣት ፣ ታስረው ለሚገኙት የህዝበ ሙስሊሙ መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴዎች የመከላከያ ምስክርነቱን ሰቷል፡፡ጋዜጠኛ ተመስገን ፣ መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴዎቹ በተከሰሱበት ጭብጥ አራት ላይ ምስክርነቱን እንደሰጠም ለማወቅ ተችሏል፡፡ በዚህ ጭብጥ ላይ ምስክርነቱን

በእነ ሶልያና ሽመልስ የክስ መዝገብ የሽብር ክስ ተመስርቶባቸው ጉዳያቸው እየታየ ያሉት ጦማርያንና ጋዜጠኞች ላይ በዓቃቤ ህግ በኩል ተሻሽሎ ቀርቧል የተባለው የክስ ዝርዝር ረቡዕ ሕዳር 24 ቀን 2007 ዓ.ም በልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተሰምቷል፡፡“ክሱን አሻሽዬ መጥቻለሁ” ያለው ዓቃቤ ህግም በክሱ ውስጥ ፤ ቡድን ድርጅትና የመሳሰሉት እያለ የሚገልፀው ከየትኛው ቡድን ጋር እንደሆነ ከዚህ በፊት በነበረው ክስ ላይ በግልፅ ያላስቀመጠው ቢሆንም ፤ በተሻሻለው ክስ ላይ ድርጅት/ቡድን/ ተብሎ የተጠቀሰው ግንቦት ሰባት እንደሆነ አቅርቧል፡፡ተከሳሾቹ የስራ ክፍፍል አድርገው ለሽብር እንደተንቀሳቀሱ ከዚህ በፊት በክሱ ላይ ያካተተው ዓቃቤ ህግ ፣የስራ ክፍፍላቸውን በመጠኑም ቢሆን ለማቅረብ ሞክሯል፡፡በዚህም መሰረት አንደኛ ተከሳሽ ሶልያና ሽመልስ ፣ የቡድኑ አስተባባሪ ነች ስትባል፤ ሁለተኛ ተከሳሽ በፍቃዱ ኃይሉ ፣የቡድኑ ፀሓፊ እንዲሁም ሶስተኛ ተከሳሽ ናትናኤል ፈለቀ የቡድኑ የሀገር ውስጥ አስተባባሪ ናቸው ብሏል፡፡የተቀሩት ተከሳሾች የቡድኑ

የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ (መድረክ) በአዲስ አበባ ከተማ ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚያደርግ የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ሃላፊው አቶ ጥላሁን እንደሻው ለፍኖተ- ነጻነት ገለጹ፡፡

ሰልፉ ታህሳስ 5 ቀን 2007 ዓ.ም ከጥዋቱ 3፡00 ጀምሮ እስከ ከቀኑ 7፡00 የሚዘልቅ ሲሆን፤ መነሻውን ግንፍሌ ድልድይ አድርጎ መዳረሻውን በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ታቦት ማደርያ ያደርጋል፡፡ በሰልፉ ከሚነሱት ዋና ዋና አጀንዳዎችም መካከል በ2007 ዓ.ም የብሄራዊ ምርጫ ጉዳይን በተመለከተ ኢህአዴግ የያዘውን ግትር አቋም አለዝቦ፣ ለድርድር ዝግጁ እንዲሆን መጠየቅ፤ የ2007 ብሄራዊ ምርጫ ፍትሃዊ እና ዲሞክራሲያዊ ይሆን ዘንድ በገለልተኛ የምርጫ ቦርድ አስፈፃሚዎች እንዲፈፀም፣ ምርጫ ቦርድ ከገዢው ፓርቲ ተላላኪነት ነፃ እንዲሆን፤ ኢህኣዴግ በምርጫ ዋዜማ የተቃዋሚ ፓርቲ አባላትን ማሳደድና ማሰር እንዲሁም ምርጫውም ማወኩን እንዲያቆም፣ የፖለቲካ እና የህሊና እስረኞች እንዲፈቱ. ኢህአዴግ ነፃ ፕሬስን ማፈንና ጋዜጦኞችንና ጦማርያንን ማሳደድና ማሰር እንዲያቆም፣ ኢህኣዴግ ላፀደቀው ህገ-መንግስት ተገዢ እንዲሆንና እንዲያከብረው እንዲሁም የአዲስ አበባ ከተማ ህዝብ የትራንስፖርት እና የውሃ እጥረት እንዲፈታና የከተማው የቴሌኮሚኒኬሽን እና የመብራት መቆራረጥን የመሳሰሉ ጥያቄዎች እንደሚነሱ መድረክ አስታውቋል፡፡ መላው የአዲስ አበባ ከተማ ህዝብ፤ ፍትህና ነፃነት የጠማቸው ኢትዮጵያውያን፤ በኑሮ ውድነት ተማረው ከሰው በታች የሚኖሩ ዜጎች፤ በመብራትና በውሃ መቆራረጥ የተሰቃየው ነጋዴ፤ በአጠቃላይም መላው የከተማው ነዋሪ ለዚህ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ስኬት እንዲረባረብ መድረክ ለፍኖተ ነፃነት በላከው መልዕክት ጥሪውን አስተላልፏል፡፡

ሰላማዊ ሰልፉ በአዲስ አበባ መስተዳድር እውቅና እንዳገኘም ለማወቅ ተችሏል፡፡

የሰጠው ተመስገን ፣ ኮሚቴዎቹ የህዝብ ወኪል መሆናቸውንና ይዘውትም የተንቀሳቀሱት የህዝብ ጥያቄ እንደሆነ ለፍርድ ቤቱ አስረድቷል፡፡ የህዝበ ሙስሊሙ ጥያቄ ከተነሳበት ጥር 11 ቀን 2007 ጨምሮ ጥር 18 ፣ የካቲት 26 ፣ መጋቢት 9ና 30 በአወሊያ መገኘቱን የገለፀው ተመስገን ፣ በእነዚህ ቀናት የህዝቡም ሆነ የመሪዎቹ እንቅስቃሴ ከመሪዎች አመራረጥ ጀምሮ ፍፁም ሰላማዊ እንደነበረም ገልጿል። የካቲት 26 የፌደራል ጉዳዮችና የህዝበ ሙስሊሙ መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴዎች አድርገውት የነበረውን ውይይት ሪፓርት የካቲት 30 አወሊያ በመገኘት ከህዝብ ሙስሊሙ ተወካዮች አንደበት መስማቱንም ለፍርድ ቤቱ ተናግሯል፡፡የሙስሊሙ መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት መንግስት በሀይማኖት ጉዳይ ላይ የሚያደርገውን ጣልቃ- ገብነት በመቃወማቸው የተነሳ ለእስር መዳረጋቸው ይታወሳል፡፡

መስራችና አባላት መሆናቸውን ገልጿል፡፡ ህዳር 24 ቀን 2007 ዓ.ም ጠዋት በዋለው ችሎት፣ በጦማርያኑና ጋዜጠኞቹ ላይ ተሻሽሎ የቀረበው የክስ ዝርዝር በንባብ የተሰማ ሲሆን ፤ በክስ ወረቀቱ ላይ ከተመለከቱት ነጥቦች መካከል ግልጽ ያልሆኑ ነጥቦችን አካትቶ እንዲያቀርብ ለዓቃቤ ህግ ትዕዛዝ ተሰጥቶታል፡፡

በጠበቆቹ በኩል ክሱ ቀደም ብሎ ፍርድ ቤቱ በሰጠው ትዕዛዝ መሰረት መሻሻሉን ለማረጋገጥ ያለፈው የፍርድ ቤቱ ብይን ግልባጭ እስካሁን እንዳልደረሳቸው በመግለጽ፣ በአጭር ጊዜ ውስጥ እንዲደርሳቸው ጠይቀዋል፡፡ በዚህም የተነሳ የብይኑ ግልባጭ ሳይደርሰን ፣ ተሻሻለ የተባለው ክስ መሰማት የለበትም ቢሉም ፤ክሱን አይታችሁ መቃወሚያ ካላችሁ አስተያየት እንድትሰጡበት እድል እንሰጣለን ያለው ፍርድ ቤቱ ክሱ እንዲሰማ አድርጓል፡፡

ፍርድ ቤቱ ጠበቆቹ ያላቸውን አስተያየት ይዘው እንዲቀርቡ ለታህሳስ 7 ቀን 2007 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱ ታውቋል፡፡

በአዲስ አበባ ትምህርት ቤቶች ለፖለቲካ ስራ የታጩ ምክትል ርዕሰ መምህራን እየተመደቡ መሆኑን የፍኖተ ነፃነት ምንጮች ገለጹ፡፡

ምንጮቹ እንደገለፁት ቀደም ሲል የመማር ማስተማር እንቅስቃሴዎችን የሚከታተሉ እና የመምህራንን የእድገት ደረጃ የሚወሰኑ ሁሉት፣ም/ርዕሰ መምህራን ሲመደቡ ቆይተዋል፡፡ በቅርቡ ከመንግስት በተላለፈ መመሪያ ከመጀመሪያ ደረጃ እስከ

ፕሪፓራቶሪ ትምህርት በሚሰጥባቸው ትምህርት ቤቶች ሶስተኛ ርዕሰ መምህራን እየተመደቡ ነው፡፡ የፍኖተ ነፃነት ምንጮች ጨምረው እንደገለፁት የአንድ ለአምስት አደረጃጀቶችን፣ የኢህአዴግ ህዋሶችን፣ የተማሪ ፓርላማ በሚል የተመሠረቱ አደረጃጀቶችን እና የተማሪ ክበባትን እንደሚከታተሉና እንደሚቆጣጠሩ ታውቋል፡፡በአዲስ አበባ በመምህራን የተጀመረው ይህ አሰራር ኢህአዴግ ምርጫውን ለመጠቅለል ካለው እቅድ አንፃር ተግባራዊ የተደረገ እንደሆነ ታውቋል፡፡

Page 14: * p Hß ß0 16 1//6 Á÷ - Ethiopia Media Forumethioforum.org/amharic/wp-content/uploads/2014/12/finote-netsanet … · እንዲቀየር በፖለቲካው ጨዋታ ሜዳ አስገድዶታል፡፡

ፍኖተ ነፃነት

Visit us :- www.fnotenetsanet.com, www.andinet.org

14 የኢትዮጵያ ህዝብ የሉዓላዊ ስልጣኑ ባለቤት እንዲሆን እንታገል! አራተኛ ዓመት ቅፅ 4 ቁ 87ቅዳሜ ህዳር 27 2007 ዓ.ም

በለጠ ጎሹ

ቅዳሜ ህዳር 20/2007 ዓ.ም ወንድሜ ሰለሞን ስዩም “የኢትዮጵያ አንድነት ቅርቃሮች” በሚል ርእስ ያቀረበው ጽሁፍ፣ እጅግ ትምህርት ሰጪ ሆኖ አግኝቼዋለሁ፡፡ እግረመንገዱንም፣ ስለ እኔ የፃፋቸው መልካም ቃላት ልብ የሚነኩና የሚያበረታቱ ስለሆኑ፣ ሰለሞንን አመሰግናለሁ፤ እግዚአብሔር ያክብርልኝ እላለሁ!

ለግዛት የአንድነት ህልውና ተፃራሪው የግዛት ብሔርተኝነት ነው፡፡ በኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ አደገኛው ነገር ኦሮሞነት አይደለም! ኦሮሚያዊነት እንጂ! አደገኛው የማኅበረሰቡ ቋንቋ ኦሮምኛ ሳይሆን፣ ግዛታዊ ክልሉ ኦሮሚያ ነው! ኦሮሚያ፣ የአገር አፍራሽ ብሔርተኝነት ውጤት ነው፡፡ምክንያቱም ኦሮሚያ የኢትዮጵያ ተፃራሪ መልክዓ-ምድራዊ ክልል ነውና፡፡ ኦሮሚያ ሌላ አዲስ ሀገር፣ አዲስ ዜግነት፣ አዲስ ሉዓላዊ ሕዝብ ለመፍጠር ታልሞ፤ በፀረ ኢትዮጵያ የውስጥና የውጭ ኃይሎች ሴራ የተፈጠረ፣ በረጅሙ የኢትዮጵያ ታሪክ ያልነበረ የምኞት ክልል ነው፡፡ እናም ወንድሜ ሰለሞን፣ የአንድነት ኃይሎች የሚጠሉት ኦሮሞነትን ሳይሆን ኦሮሚያዊነትን ነው፡፡

ሰለሞን እንዲህ ይላል፤ “እኔ ግን እላለሁ፣ ግማሽ መንገድ የመጣውን ኦሮሚያዊነት፣ የአንድነት ሀይሎችም ግማሽ መንገድ ሄደው ይቀበሉት፤ ያኔ ጥርጣሬአችን ይከስማል፡፡” የአንድነት ኃይሎች አሉታዊ ብሔርተኝነትን እንዲቀበሉ እየተገደዱ ነው፡፡ይህን የግማሽ መንገድ ጉዞ ካደረጉ እኮ የሚሟገቱለት ኢትዮጵያዊነት አይኖርም፡፡

ለአንድነት ሀይሎች ግማሽ መንገድ መሄድ ማለት ኦሮሚያን መቀበል ሊሆን አይችልም፡፡ ሀገር አፍራሹንና አሉታዊውን ብሔርተኝነት መቀበል ማለት ሊሆን አይችልም! ይህን መቀበል ማለት ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያዊነትን መካድ ማለት ነው፡፡ይህ የአንድነት ኃይሎች ቀይ መስመር ነው! ለአንድነት ሀይሎች የኦሮሞን ብሔር በተመለከተ ግማሽ መንገድ መሄድ ማለት የሚከተሉትን ነጥቦች በዋነኝነት ያካትታል፡፡

1ኛ. ኦሮምኛን ከአማርኛ ጐን ለጐን የመላ ኢትዮጵያ የስራ ቋንቋ ማድረግ፣

2ኛ. በኢትዮጵያ ፓርላማ ኦሮምኛ ተናጋሪው ሕዝብ የብዛቱን ያህል ውክልና እንዲኖረው ማድረግ፣

3ኛ. በኦሮምኛ ተናጋሪ ክፍለ-አገራት ሕዝቡ የራሱን አስተዳዳሪዎች እንዲመርጥ ማስቻል፣

4ኛ. ከብሔራዊ በጀቱ ኦሮምኛ ተናጋሪ ክፍለ-አገራት የሕዝብ ብዛታቸውን የሚመጥን

በጀት እንዲመደብላቸው ማድረግ

5ኛ. በብሔሩ የባህል ሂደት እና ክንውኖች ላይ ምንም አይነት ገደብም ሆነ ክልከላ አለማድረግ ናቸው፡፡

ፀሀፊ ሰለሞን፣ “ኦሮሞ ሳትሆን ኢትዮጵያዊ ነህ ማለት የበላይ የነበረውን ባህል ተቀበል ለማለት ስለሚያስችል ነው፡፡” ይለናል፡፡

“የበላይ የነበረውን ባህል” የተባለው የአማራ ባህልን እንደሆነ ይሰማኛል፡፡በታሪክ ውስጥ ኢትዮጵያዊነት የኦሮሞን አለባበስ፣ ምግብ፣ ሙዚቃ፣ ክብረ-በዓላት፣ አምልኮ ወዘተ ከልክሎ ያውቃል? እኔ እንደሚመስለኝ፣ ኢትዮጵያዊነት በአማራዊነት የሚከሰሰው፣ አማርኛ የሁሉም ማኅበረሰቦች የመግባቢያ ቋንቋ በመሆኑ ነው፡፡ ይሄ ደግሞ በየግዜው የነበሩ ገዥዎች በውድም በግድ የተገበሩት ነው፡፡ በመሆኑም አግባብ ያለው ጥያቄ የሚሆነው፣ ‹ኦሮምኛ በጣም ብዙ ሕዝብ የሚናገረው ቋንቋ ስለሆነ፣ እንደ አማርኛ የመላ ኢትዮጵያ መግባቢያ መሆን የለበትም ወይ?› የሚለው ይመስለኛል፡፡

በስታሊን እና በሌኒን ትርጉም መሠረት በኢትዮጵያ ብሔር የለም ማለቴንም ፀሀፊው አልወደደልኝም፡፡ በበኩሌ፣ “ብሔር” የሚባለውም ቃል አይጥመኝም፤ ምክንያቱም አገር ማለትም ነው፤ ርእሰ-ብሔር እንዲሉ! ከብሔር ይልቅ ማኅበረሰብ ይስማማኛል፡፡ኢሕአዴግ፣ እስከአሁን ድረስ በብሔር-ብሔረሰብ እና በሕዝብ መካከል ያለውን አንድነትና ልዩነት ሊነግረን አልቻለም፡፡ እንዲያውም፣ የኢሕአዴግ ሕገ-መንግሥት ለሶስቱም ቃላት የሚሰጠው ትርጉም አንድ አይነት ነው፡፡ ስታሊን እና ሌኒን ግን ለብሔር የጋራ ግዛት ይሰጡታል፡፡ ታዲያ፣ በኢትዮጵያ ውስጥ በአራቱም ማዕዘናት ፈልሶ የሠፈረው ኦሮሞ ግዛቱ የቱ ነው? በእኔ አመለካከት የኦሮሞ ግዛት፣ ራሷ ኢትዮጵያ ነች!

ሰለሞን በመቀጠል “ገዳን የመሰለ ሥርዓት እንደ ታሪክ እርከን ሳይታይ ስለምን ቀረ?” ሲል ይጠይቀናል፡፡ የገዳ ሥርዓት በኢትዮጵያ ታሪክ ጐልቶ አለመታየቱ የታሪክ ፀሓፊዎች ግድፈት ነው፡፡ እንደሚታወቀው፣ ባህላዊ ታሪክ ፀሓፊዎች አጉልተውና አግንነው የሚዘግቡት የነገሥታቱን ገድልና ስኬቶችን ነው፡፡ ይሁንና ዘመናዊው ዲሞክራሲ እያለ በጥንታዊው እንጠቀም ማለት፣ በቶዮታ መኪና ፈንታ ጋሪ እንጠቀም እንደማለት ነው፡፡

ፀሐፊው በሙግቱ በመግፋት፡- “ራሱን ሲከላከል የነበረውን ንጉስ ጦና ስለምን በወራሪው ንጉሥ ምኒልክ ቦታ አድርገን እንድናስብ ተፈለገ?” ይለናል። እንደሚታወቀው በፊውዳልና በቅድመ-ፊውዳል ሥርዓት አገር የተገነባው ጠንካራው ደካማውን አስገብሮ ነው፡፡ በዚህ አመክንዮ ንጉሥ ጦና ጠንካራ ቢሆኑ ኖሮ፣ ምኒልክን እንደሚወጉና ግዛታቸውን እንደሚያሰፉ ግልፅ ነው፡፡ በታሪክ አጋጣሚ ምኒልክ የተሻለ ጦር ስለነበራቸው አሸነፉ፡፡በመሆኑም ለምን በዲሞክራሲያዊ ውይይትና ድርድር ችግሩን አልፈቱትም ብለን ለመከራከር አንችልም፡፡ አይሮፕላን ከመፈልሰሙ በፊት መብረር እንደማንችለው ሁሉ፣ ዲሞክራሲ ከመፈልሰሙ በፊት ስለ ዲሞክራሲያዊ መብቶች ማውራት አንችልም!

የፀሐፊውን ዓለም-አቀፋዊ አመለካከት ከታዘብኩባቸው አገላለፆች፤ “መሠረታዊው

ነገር ዘር የሚባል ነገር ያለመኖሩ ነው፡፡ የሰው ዘሩ ሰው ነው”፤ የሚለው ይገኝበታል፡፡ ከዘረ-መል (DNA) አኳያ የሰው ዘር ምንጩ አንድ ነው። የሰው ልጅ እርስ በርሱ ይቅርና ከጦጣ ዝርያዎች ጋር እንኳ ከዘጠና ስድስት በመቶ በላይ ተመሳሳይነት አለው! ይሁንና በተለያዩ ምክንያቶች ሳቢያ የቆዳ ቀለም፣ የዓይን ቀለም፣ የፀጉር ዓይነት፣ ቁመትና ክብደት ልዩነት ይኖራል፡፡ በተራ ቋንቋ ዘር ሲባል ይህን ለማመልከት ይመስለኛል፡፡ እኛ ኢትዮጵያውያን እርስ በእርሳችን የተካለስን ስለሆንን በቆዳ ቀለምም፣ በዓይን ቀለምም፣ በፀጉር ዓይነትም ተመሳሳይነት አለን፤ ይህም መመሳሰል እየጨመረ በመሄድ ላይ ነው፡፡

ሌላው አቶ ሰለሞን ያነሳው ነጥብ “የመዳቀሉን ነገር ካመንን የድቅሉን ጭቆና ማመን ለምን ይክበደን? አንድ ብሔር እጅጉን አንድ ከሚሆንባቸው አንጓዎች አንዱ የጋራ የበደል ታሪክ መሆኑን እንዴት እንዘነጋለን” የሚል ነው፡፡

‹በባሪያ ሥርዓት ጭቆና ነበር፤ በቅድመ-ፊውዳል ሥርዓት ጭቆና ነበር . . .› ወዘተ. እያሉ ማውራት የአዋጁን በጆሮ እንደ ማለት ነው፡፡ ይህ የሕብረተሰብ ዕድገት ታሪክ ነው፡፡ ማንም ተጠያቂ ሊሆን አይችልም፡፡ የግድ ይጠየቅ ከተባለም፣ ተጠያቂ የሚሆነው የባሪያ እና የፊውዳል ሥርዓት እንጂ በዛሬው ዘመን ያለነው ልንሆን አንችልም፡፡ ያ ትውልድ እኮ የኢትዮጵያን ፊውዳሊዝም ጐሳ ሳይለይ እኩል ነው የተፋለመው! የኢሕአፓና የመኢሶን አባላት እኮ ከሁሉም የቋንቋ ማኅበረሰቦች የተውጣጡ ነበሩ፤ እኔ ባለኝ መረጃ መሠረት ከኢሕአፓ አባላት ከሰባ በመቶ ያላነሱት አፍ-መፍቻ ቋንቋቸው አማርኛ ነበር! በብዛት የቀይ ሽብር ሰለባም የሆኑት እነሱው ናቸው! እናም፣ ፊውዳሊዝም ለፈፀመው በደል ተጠያቂው ሥርዓቱ እንጂ እንዴት ኦሮሞ ወይም አማራ ይሆናል? ደግሞም ፊውዳሊዝም የሕብረተሰብ ዕድገት እርከን በመሆኑ ሥርዓቱ ራሱ እንኳ ተጠያቂ ላይሆን ይችላል! ፊውዳሊዝም በዲሞክራሲ፣ ጋሪ በመኪና ተተካ፡፡ ጋሪ መወቀስ አይችልም፤ ምክንያቱም የዕድገት መሸጋገሪያ ድልድይ ሆኖ አገልግሏልና!

ፀሀፊው፣ መነሻ ሃሳቦቼ የተሳሳቱ መሆናቸውን ቢነግረኝም፤ እኔ ግን አልተሳሳትኩም እላለሁ፡፡ የአንድነት ሀይሎች ኦሮሞነትን አይቃወሙም፣ የሚቃወሙት ግዛታዊ ብሔርተኝነትን ነው፤ በተለይም የኦሮሞ ግዛታዊ ብሔርተኝነትን! የአማራ ግዛታዊ ብሔርተኝነት፣ በፀረ-ኢትዮጵያው ህወሓት/ኢሕአዴግ አማካኝነት በአማራ ማኅበረሰብ ላይ በጉልበት የተጫነበት በመሆኑ፤ ጊዜው ሲፈቅድ ራሱ የአማራ ማኅበረሰብ ያፈርሰዋል! ሰለሞን ሆይ! አማራ የሚባል ክልልን የአማራ ማህበረሰብ እንደማይፈልገው ላረጋግጥልህ እወዳለሁ፡፡የአንተ አቋም ምንድን ነው? አሉታዊ ብሔርተኝነት ታምናለህን? የአሉታዊ ብሔርተኝነት ተምሳሌት የሆነው አማራ ክልል ይፈርሳል፤ ኦሮሚያስ? የችግሩ ቋጠሮ ይኼ ነው! የሌሎቹ ማኅበረሰቦች (የቋንቋ ማኅበረሰቦች) ጉዳይ እንዴት እንደሚታይ መነጋገር እንችላለን፤ ግን በመጀመሪያ የኦሮሞና የአማራ ጥያቄ ምን እንደሆነ እንወቅና፣ ግማሽ መንገድ ሄደን ችግሩን ለመፍታት እንሞክር!

የምቃወመው አሉታዊ ብሔርተኝነትን ነው!

Page 15: * p Hß ß0 16 1//6 Á÷ - Ethiopia Media Forumethioforum.org/amharic/wp-content/uploads/2014/12/finote-netsanet … · እንዲቀየር በፖለቲካው ጨዋታ ሜዳ አስገድዶታል፡፡

ፍኖተ ነፃነት

Visit us :- www.fnotenetsanet.com, www.andinet.org

15የኢትዮጵያ ህዝብ የሉዓላዊ ስልጣኑ ባለቤት እንዲሆን እንታገል! አራተኛ ዓመት ቅፅ 4 ቁ 87ቅዳሜ ህዳር 27 2007 ዓ.ም

ይህ ገፅ የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ አቋሞች የሚስተናገዱበት ነው

የአገርን ጥቅምና ህልውና የሚመለከቱ ጉዳዮች

አገራችን ኢትዮጵያ በሰው ዘር መገኛነቷ የምትታወቅ ሀገር ናት፡፡ በአካባቢያችንም በስልጣኔ ማእከልነት ታሪክ ከሚያውቃቸው ጥቂት አገሮችም አንዷ ነች፡፡ ኩሩና አገር ወዳድ ዜጎች፣ ነጻነትን ጠብቀው ያወረሱን ጀግኖች አባቶችን ያበቀለች፣ በነጻነቷ፣ በመንፈሳዊ ሃብቷና ስልጣኔዋ የምትታወቅ፣ ልጆችዋ የሚኮሩባትና እሷን ላለማስደፍር የሚሞቱላት አገር ነች፡፡

የቅርቡ የአገራችን ገጽታ ግን ከዚህ በእጅጉ ይለያል፡፡ ያለፉት ሰላሳና አርባ ዓመታት ታሪካችን ረሃብና ጦርነት የነገሱበት ነው፡፡ አገራችን አሁን ድረስ በዜጎችዋ ሰቆቃና የመብት ጥሰት በተደጋጋሚ የምትወሳ አገር ሆናለች፡፡ ድህነቱና የመብት ጥሰቱ ተጣምረው አገራችንን “ዜጎቿ ሊኖሩባት የማይመርጡዋት” አገር እያሰኛት ነው፡፡የተማሩት ዜጎች ካገር ለመውጣት አጋጣሚውን ባገኙ ቁጥር በየደረሱበት የውሃ ሽታ ሆነው ለመቅረት ይፈልጋሉ፡፡የኮሌጅ ተማሪዎች ሳይቀሩ ከዲግሪያቸው ይልቅ ከኢትዮጵያ የሚወጡበትን አጋጣሚ የሚመርጡበት ሁኔታ ተከስቷል፡፡ ኢትዮጵያ ከፍተኛ የሕዝብ እድገት ካለባቸው አገራት አንዷ መሆኗ ቢታወቅም በቅርቡ የወጣ ዘገባ እንደሚያመለክተው ዜጎችዋ እንደፈለጉት አገራቸውን መልቀቅ ቢችሉና ወደፈለጉት አገር ለመግባት እድል ቢሰጣቸው ሀገራችን ከፍተኛ የሕዝብ ፍልሰት ሊያጋጥማት እንደሚችል አመላክቷል፡፡ የሕዝብ ብዛቷም በ 46% ሊቀንስ እንደሚችል ተገምቷል (AP Aug.23/2010: Gallop) ፡፡ አገሩን የሚለቀው የተማረውና አምራቹ ትኩስ ሃይል መሆኑ ሲታሰብ፣ በኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ችግሮቻችን ምክንያት የሰው ዘር መገኛ የሆነችው አገራችን ሰው የሚሸሻት አገር ትሆናለች ሲባል ዘራችንና ማንነታችን ሊጠፋ እንደሚችል አመልካች ሊሆን ይችላል፡፡

አገራችን ኢትዮጵያ በግዙፍ ብዝሃ-ሕይወት ባለቤትነትዋ ትታወቃለች፡፡ ይህም ሆኖ አካባቢያችን ከፍተኛ የአየር ንብረት መዛባት የሚታይበትና ውሃ የጠማውና ፈጣን የበረሃነት መስፋፋት የሚታይበት መሆኑ ሌላው ኢትዮጵያውንን ሊያሳስበን የሚገባ ጉዳይ ነው፡፡ ውሃችን እየቀነሰ፣ ጫካዎቻችን እያነሱ፣ አፈራችን እየተከላ፣ አካባብያችን ህይወትን ለመሸከምና ለማቆየት ያለው እድል እየተመናመነ ሲሄድና አገራችን የብዝሃ ሕይወት ጸጋዋን እያጣችና በዚያውም ሰውንም የማኖር ችሎታዋ እየተመናመነ እንደሚሄድ ግንዛቤ ሊወሰድ ይገባዋል፡፡

አገራችን ኢትዮጵያ ውሃ በተጠማ በረሃማ አካባቢ የምትገኝ ብትሆንም በዚህ አካባቢ ብቸኛ የበርካታ ትላልቅ ወንዞች መነሻ/አመንጪዋ አገር ናት፡፡ ይህ ዕውነታ በአንድ በኩል ለመኖርና ለማደግ እድል ያለን መሆኑን ሲያመለክት በሌላ በኩል ደግሞ በዚህ ሳብያ ከጎረቤትና የአካባቢ አገራት ጋራ ትልቅ ፍጥጫ ውስጥ ሊያስገባን የሚችል መሆኑን መገንዘብ ይኖርብናል፡፡ ከዚህ በመነሳት የአገራችን የመሬት ገጽታ፣ የአየር ንብረትና አንደምታውን መመለከቱ ለሀገራችን ፖለቲካ ትንተና አስፈላጊ ይሆናል፡፡

ወንዞቻችን የሚፈልቁት ከከፍተኛውና ደጋማው የአገሪቱ አካባቢ ነው፡፡ ይህ አካባቢ እጅጉን በተጣበበ ሁኔታ አብዛኛው የአገሪቱ ሕዝብ የሚኖርበት፣ በብዝሃ ህይወት ተሸካሚነቱም ከፍተኛ ድርሻ ያለው ነው፡፡ወንዞቹ ደጋውን ለቀው ሜዳማውና ቆላማውን የአገራችን አካባቢ አቆራርጠው አብዛኛዎቹ ድንበር ይሻገራሉ፡፡ ቆላማው የአገራችን አካባቢ ውሃ የተጠማ ቢሆንም በጣም ለም አፈር ያለውና ለዘመናዊ ሰፋፊ እርሻ ምቹ ነው፡፡ ይህም ሆኖ በአሁኑ ወቅት ለኑሮ አስቸጋሪ በመሆኑ በእንስሳት እርባታ የሚተዳደር አነስተኛ ሕዝብ የሚኖርበት አካባቢም ነው፡፡ ውሃውን በደጋው በመያዝ ለመለስተኛ መሰኖዎችና ለሃይድሮ አሌክትሪክ ሃይል አመንጪነት መጠቀም የምንችልበት ዕድል አለን፡፡ በቆላው አከባቢም እንደዚሁ

የአንድነት እስትራቴጂ በአጠቃላይ የኢትዮጵያ ሁኔታ ግምገማ ላይ ለሃይድሮ አሌክትሪክ ሃይል፤ ለሰፋፊ የመስኖ እርሻዎችና አግሮ ኢንዱስትሪ የማዋል ተስፋውና እድሉ ያለን ቢሆንም የአገራችን የውስጥ የፖለቲካዊ ችግሮችና ከውሃ ጋር የተያያዘው የአካባቢ አታካራ ትልቅ ፈተና እንደሚሆኑብን መገንዘብ ይገባል፡፡

እኛ በምንገኝበት ከአፍሪቃ ቀንድ ማዶ የባሕረ ሰላጤ (የጋልፍ) አገሮች ይገኛሉ፡፡ በመካከላችን የቀይ ባሕርና የባብኤል መንደብ መተላለፍያ ውሃዎች ይገኛሉ፡፡

የጋልፍ አካባቢ ትልቁ የነዳጅ አመንጪ አካባቢ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ከዚህ አካባቢ የሚቀዳው ነዳጅ፤ ከአውሮፓ ወደ ምስራቅ አፍሪቃና ኤስያም ሆነ ከምስራቅ አፍሪካና ኤስያ ወደ አውሮፓ የሚደረገው የመርከብ ምልልስ በቀይ ባሕርና በባብአል መንደብ ውሃዎች ያልፋሉ፡፡ ይህ አካባቢ የዓለም ኢኮኖሚና ህይወት የሚያቆም አካባቢ እንደመሆኑ የዓለም ሃያላን ጥቅም ያለበትና እጅጉን የእነሱን ትኩረት የሚስብ አካባቢ ነው፡፡በዚህ አካባቢ ከፍተኛ የሕዝብ ብዛት ያለን ግን ደግሞ የባሕር በር የሌለን ብቸኛ አገር ነን፡፡ እነዚህ ዕውነታዎች ስለ እኛ ህልውናና ደህንነት የሚሉት ብዙ ነገር አላቸው፡፡ በዚህ አካባቢ በርካታ ትናንሽ አገሮች ባለ ወደብ የሆኑበት፣ ኢትዮጵያ ደግሞ ወደብ አልባ የሆነችበት ሁኔታ መኖሩ አጅግ የተወሳሰበ ሁኔታ የመፍጠር አደጋ አለው፡፡ በዚህ አካባቢ የሚከሰት የአገሮች የጥቅም ግጭት የሚቀሰቅሰው አምባጓሮ እኛንም ጎትቶ ችግር ውስጥ የማስገባት አደጋ አለው፡፡ ስለሆነም ሌሎች ጭረውት በሚነድ ሰደድ ውስጥ እንዳንገባ ጥንቃቄ ማድረግ አስፈላጊ የመሆኑን ያክል ጥቅማችን እንዳይነካብንም በትኩረትና በጥንቃቄ መከታተል ይጠበቅብናል፡፡

የምንገኝበት የአፍሪቃ ቀንድ አካባቢ በድህነት፣ በበረሃማነትና በደፈረሰ ጸጥታው የሚታወቅ ቢሆንም ትልቅ የነዳጅና የማዕድን ይዞታ አለው ተብሎ የሚገመት አካባቢ ነው፡፡ከላይ እንደተገለጸው በርካታ ወንዞችና እጅግ ለም አፈር ባለበት በዚህ አካባቢ አገራችን ኢትዮጵያ ቁልፍ ስፍራ ያላት መሆኑም አንድና ሁለት የለውም፡፡ ምክንያቱም ሌላውን እምቅ ሃብትዋን አቆይተን ለም መሬትዋንና የውሃ ሃብትዋን ብቻ ለማቀናጀት ብንችል ትልቅ ኢኮኖሚ የመሆን ዕድል አላት፡፡ በሌላ በኩል ይህ እውን እንዳይሆን የሚፈልጉ ወገኖች መኖቸው ይታወቃል፡፡ በዚህ ሁኔታ እነዚህ ትናንሽ ባለወደብ አገሮች የሚኖራቸው ሚና እጅግ አሳሳቢ ነው፡፡ አማራጮቹን ስንመለከት እነዚህ አገሮች አንድም የኢትዮጵያ እሴቶች የመጀመርያ ደረጃ ባለመብት ነን በማለት ከኢትዮጵያ ጎን በመቆም ኢትዮጵያ ሰላምና ልማት እንድታገኝ፤ እነሱም ከዚህ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ይሰራሉ፡፡ አልያም ጊዚያዊ ጥቅሞችን በማገትና ኢትዮጵያን መተንፈሻ በማሳጣት፤ እድገትዋን በማገትና ሰላምዋን በማወክ የበለጠ እንጠቀማለን ከሚሉ ሃይሎች ጋር ይሰለፉና በኢትዮጵያ ላይ ችግር መፍጠርን እንደዋነኛ ተልእኮ ይወስዳሉ፡፡ የኢትዮጵያ የባህር በር መብት ጥያቄ እና የአካባቢው ልማትና መረጋጋት እጅግ የተሳሰሩ እንዲሆኑ የሚያደርጋቸውም ይኸው ሃቅ ነው፡፡

አገራችን ኢትዮጵያ የበርካታ ብሄር ብሄረሰቦች አገር የመሆንዋን ያክል የተለያዩ የሃይማኖት እምነት ተከታዮች የሚኖሩባት ሃገር ነች፡፡ ፖለቲካችን እነዚህ እውነታዎች የሚገነዘብ እና መቻቻልና እኩልነትን የሚቀበል እንዲሆን ማድረጉ እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡ በሌላ ወገን መረን የለቀቀ የብሄርና የሃይማኖት አክራሪነት የአገራችንን ፖለቲካ እንዳያናጋብን በጥንቃቄና በብስለት መጓዝ ግድ ይለናል፡፡ ከፍ ብሎ ከተገለጸው የውሃ ፖለቲካና በአካባቢያችን እየታየ ካለው ሴኩላሪዝምን የመጋፋት አዝማሚያ አንፃር ሲታይ ብዙሃነታችን የሚፈጥራቸው አንዳንድ ቅራኔዎች የሚስተናገዱበት ሁኔታ ልዩ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ይሆናል፡፡

በዚህ የተወሳሰበ ከባቢ ውስጥ መገኘታችን ሳያንስ የአገራችን የውስጥ ፖለቲካም እጅጉን የተወሳሰበ ነው፡፡ በስልጣን

ላይ ያለው መንግሥት (ፓርቲ) የውሃ ሃብት፣ የባሕር በር፣ የአገር ዳር ድንበር፣ የአገርና የሕዝቧ ደህንነትና በመሳሰሉት መሰረታዊ የአገር ጥቅም ጥያቄዎች ላይ የተአማኒነት ችግር ያለበት መሆኑ ይታወቃል፡፡ በመላው ኢትየጵያውያን ዘንድ ዕምነትና ተቀባይነት ያጣ ጠባብ ሕዝባዊ መሰረት ያለው አገዛዝ ነው፡፡ ሕዝባዊ መሰረቱ ደካማ መሆኑን በመገንዘብ ስጋትና ጭንቀት ውስጥ የሚኖር እና ለዚህ መዳኛው ጉልበትና አፈና ብቻ ነው ብሎ የተሳሳተ አቋም የወሰደ አገዛዝ ነው ያለን፡፡ በመሆኑም ኢትዮጵያ በዓለም በአምባገነናዊ አገዛዝ መዳፍ ስር በመገዛት ከሚገኙ አገሮች ውስጥ 9ኛ� ደረጃን በመያዝ በአምባገነንነት የምትገዛ አገር ናት፡፡ በዚህ የደረጃ ሰንጠረዥ የአንደኝነት ደረጃውን የወሰደው የሰሜን ኮርያው ኪም ጆንግ ኢል ሲሆን የኤርትራው አምባገነን ደግሞ አምስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡

ስለሆነም እኛ ኢትዮጵያውያን የአገራችን እምቅ አቅም ወደ ተጨባጭ/ግልጽ ሀብትነት እንዲለወጥ ማድረግ ይጠበቅብናል፡፡ይህንን ለማሳካት መጀመርያ የአገራችንን ውስጣዊ ሁኔታ ማስተካከል ፈፅሞ ጊዜ የሚሰጠው ጉዳይ አይደለም፡፡

የአገራችን አጠቃላይ ፖለቲካ

የአካባቢያንችን እውነታዎች ውስጣዊ ችግሮቻችንን መፍታትና ማስከን እንዳለብን ቢያመለክቱም አገራችንን እምቅ አቅሟን አውጥታ ተገቢው ስፍራዋን እንድትይዝ የውስጥ ችግሮቻችንን መፍታት ምን ያህል አስፈላጊና ወሳኝ ሀገራዊ አጀንዳ እንደሆነ እሙን ነው፡፡ ነገር ግን በአፍራሽነቱ የሚታወቀው ፖለቲካ ልዩነቶች አፈታት ባህላችን ግን ይህንን እንዳናደርግ ትልቅ ሳንካ ሲፈጥሮብን ቆይቶአል፡፡ ሥራው አሁንም የኛን -የፖለቲከኞቹን- ስክነትና ጥበብ የተሞላበት እርምጃ ይጠይቃል፡፡

ፖለቲካችን መደራደርና መቻቻል የሌለው የእልህ ፖለቲካ ነው ማለት ይቻላል፡፡ለዚህ እውነታ ባህልና ታሪካችን ትልቅ አሻራ እንዳሳረፈ መገመት ይቻላል፡፡ገዥዎች አንዱ ሌላውን በሃይል ካላስገበሩ ወይም ካላጠፉ በጀ የማይሉ፣ ተቀናቃኞቹ ቀን ሲወጣላቻቸው አይምረኝም በሚል ለጦርነትና ለሴራ እየተዘጋጁ መኖርን በአገራችን ነገስታት ታሪክ ገኖ የሚታይ ዕውነታ ነው፡፡ በባህላችን በከማናንሼነት ነጋሹን ጥሎ ለመንገስ መሸፈትና ማመጽ የተለመደ ነበር፡፡ ይህ አስተሳሰብ ዘመኑ ካመጣቸው አዳዲስ አስተሳሰቦችና ርእዮተ ዓለም ጋር እየተዳቀለ መልኩ ቢቀያየርም አሁን ድረስ የዘለቀ ችግራችን ነው፡፡በስድሳዎቹ የአገራችን ፖለቲካ ታሪክ የበላይነትን ይዞ የነበረው ግራ ዘመም ፖለቲካ በአገራችን እጅግ ዘግናኝ የሆነ የርስበርስ ፍጅት/ጦርነት ማስከተሉ ችግሩ ከርእዮተ-ዓለሙ ብቻ ሳይሆን ከቆየ ታሪካችንም ጋር ተያያዥነት እንደነበረው ያመለክታል፡፡ ያ ታልፎአል በተባለበትና በተወገዘበት በአሁኑ ወቅትም ሁሉም በሊበራል ዴሞክራሲ ስም ቢምሉም ለመሰባሰብ፣ አንድነት ለመፍጠርና ለመስማማት አለመቻሉ የሚያመለክተው ገና ከታሪክና ባህል እስር ጨርሰን አለመላቀቃችንን ነው፡፡ የአገራችን ፖለቲካ አሁን ድረስ ብሄረተኝነትን ከኢትዮጵያውነት በሚገባ ለማስታረቅ አለተቻለውም፡፡ አንዱ ሌላውን የመካድ እንጂ ሁለቱም አብረው ኗሪ መሆናቸውን ተቀብሎ እኩልነት በሰፈነባት አንዲት ኢትዮጵያ ግንባታ ላይ መሬት የያዘና የሰከነ መግባባት አለ ለማለት አይቻልም፡፡ በሕገ-መንግስት ዙርያ ያለው አለመግባባት በዚህ ጉዳይ ለጠፋው ብሄራዊ መግባባት አንድ ትልቅ ምሳሌ ነው፡፡

ፖለቲካችን ጠቅልሎ ወደ ሰላማዊ የልዩነት መፍቻ ዘዴ ያልገባና አሁንም የጉልበትና የጦር መሳርያ ትግል የተጠናወተው ነው፡፡ የሰላማዊ የትግል ስልትንና ፋይዳን የሚገባውን ያህል የማያውቅና የማይገነዘብ ፖለቲካ ያለን በመሆኑ ትንሽ ጠጠር ያለ ሁኔታ ባጋጠመ ቁጥር እሳትን በእሳት ማለት እንጂ የኃላ ኋላ የዚህም ውጤት ያው እሳት መሆኑ ያለማየት ችግር አለብን፡፡

የደርግ ኢሠፓ አገዛዝ ወድቆ በኢትዮጵያ የዴሞክራሲና የፍትሕ ስርዓት ይመጣል ተብሎ ሲጠበቅ ኢህአዴግ ራሱ ሌላ አምባገነናዊ አገዛዝ ሆኖ አረፈው፡፡ አብዮታዊ ዴሞክራሲ በሚባለው የፖለቲካ ቀመር የሚመራው የኢህአዴግ አገዛዝ ከደርግ የኢሰፓ አገዛዝ ብዙም ያልተለየ ጠቅላይና አፋኝ አገዛዝን ፈጥሮአል፡፡ የብሔር ብሔረሰብ መብት በማስከበር ላይ የተመሰረተ ፌዴራላዊ ስርዓት እገነባለሁ ቢልም እጅግ የተማከለ አገዛዝ ፈጥሮአል፡፡ በሕግ አውጪ፣ ሕግ አስፈጻሚና ሕግ ተርጓሚ አካላት ዘንድ ይኖራል የተባለው የስልጣን ክፍፍልም ጠፍቶ ሁሉም በአንድ ፓርቲና በተወሰነ ግለሰቦች ቁጥጥር ስር እንዲገቡ ተደርጓል፡፡ነፃና ገለልተኛ ዳኝነት፣ ገልልተኛና ነጻ የምርጫ ተቋምና ከፓርቲ ወገንተኝነት የወጡ ሕዝቡ የሚተማመንባቸው የጸጥታ ተቋማት የሉንም፡፡ የዜጎችና የብሔር ብሔረሰብ መብት የተከበረባት ኢትዮጵያን ለመገንባት ቃል እንዳልተገባ ሁሉ አገራችን ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት የዜጎቿ መብት የሚረገጥባት አገር ሆናለች፡፡ ነጻና ገለልተኛ የሕዝብ መገናኛ ተቋማት የሉንም፤ ሕዝቡ ሃሳቡን በነፃ የመግለጽና መረጃን በነፃነት የማግኘትና የመለዋወጥ መብቱን ተነፍጎአል፡፡ ሕዝቡ የራሱ ነጻ የሲቪክ ማሕበራት እንዳይኖሩት ገደብ ተጥሎበታል፡፡ በዜጎች መሃከል አንድነትና ፍቅር እንዳይጠናከር ሆን ተብሎ የጥላቻና የአለመተማመን መርዝ እየተረጨበት ነው፡፡

በአጠቃላይ በአሁን ወቅት በአንድ በኩል ጠቅላይ የሆነ የአንድ ግለሰብና አንድ ፓርቲ አገዛዝ የሰፈነበት በሌላ በኩል ደግሞ እጅግ ደካማና የተከፋፈለ ተቃዋሚ ያለበት አስቸጋሪ የፖለቲካ ምሕዳር ውስጥ እንገኛለን፡፡አብዛኛዎቹ የአገራችን ልሂቃን በሁኔታው እጅግ አሳሳቢነት ላይ ስምምነት ቢኖራቸውም ይህንን ለማስተካከል የሚያስችል መሰባሰብ መፍጠር አልተቻላቸውም ማለት ይቻላል፡፡

በአገራችን የተመዘገቡ ብዙ ተቃዋሚ ፓርቲዎች አሉ፡፡ ነገር ግን ያለፉት ሃያ ዓመታት የተቃዋሚ ፓርቲዎች ጉዞ የሚያመለክተው የመብዛትና የመከፋፈል እንጂ የመሰባሰብና ጥቂት ጠንካራ ማእከሎችን የመፍጠር አይደለም፡፡ የመሰባሰብ ሙከራዎች ቢኖሩም መልሶ የመበተንና ውጥን ያለመጨረስ አባዜ ጎልቶ ይታያል፡፡ በዚህም ምክንያት ተቃዋሚ ፖለቲከኞች አሁን ድረስ በአገራችን አንድ ጠንካራ ስብስብ/ፓርቲ ሊወጣቸው አልቻሉም፡፡

አፋኝ አገዛዙ በሚወስዳቸው እርምጃዎችና በተቃዋሚው ሰፈር ውስጥ ባሉ ችግሮች ምክንያት ሕዝቡ በተቃውሞ ፖለቲካው ጎራ በግልጽ መታየትን አደገኛና ውጤት የማያመጣ ከንቱ መላላጥ አድርጎ እንዲመለከተው አድርጎታል፡፡ ለውጥ ቢፈልግም ለውጥ ይመጣል የሚል ተስፋው ከጊዜ ወደ ጊዜ እንዲደበዝዝ እያደረገው ይገኛል፡፡

በአሁን ወቅት በአገራችን ስራቸውን በገለልተኝነት የሚያከናውኑ መንግስታዊ/የህዝብ ጠንካራ ተቋማት የሉም፡፡ አሉ ከተባለም የገዢው ፓርቲ አቋምና ፍላጎት ማስፈጸምያ ናቸው፡፡ አልያም በገዢው ፓርቲና እርሱ በሚመራው መንግስት በዓይነ ቁራኛ የሚጠበቁና ከፍተኛ ችግር ላይ የወደቁ ናቸው፡፡ በአገራችን በጠንካራና ገለልተኛ ተቋማት ምትክ ገኖ እየወጣ ያለው የአንድ ፓርቲ እና የአንድ ግለሰብ ፍጹም ቁጥጥር የሰፈነበት አፋኝ አገዛዝ ነው፡፡ እነዚህ እውነታዎች ተደማምረው ኢትዮጵያን በከሸፉ መንግስታት ተርታ ውስጥ በአስራ ስድስተኛነት (Failed States Index (FSI) 2010)

እንድትቀመጥ አድርገዋታል፡፡በመጀመርያ ደረጃ የተቀመጠችው ሶማልያ ናት፡፡ ኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ ሶማልያ ባለችበት ሁኔታ ላይ ባትሆንም ከላይ በተገለጹት እውነታዎች ምክንያት ሊደቀኑባት የሚችሉትን ችግሮች ተቋቁማ ለመዝለቅ ያላት እድል አጠራጣሪ እንዲሆን አድርጐታል፡፡

Page 16: * p Hß ß0 16 1//6 Á÷ - Ethiopia Media Forumethioforum.org/amharic/wp-content/uploads/2014/12/finote-netsanet … · እንዲቀየር በፖለቲካው ጨዋታ ሜዳ አስገድዶታል፡፡

ፍኖተ ነፃነት

Visit us :- www.fnotenetsanet.com, www.andinet.org

16የኢትዮጵያ ህዝብ የሉዓላዊ ስልጣኑ ባለቤት እንዲሆን እንታገል! አራተኛ ዓመት ቅፅ 4 ቁ 87ቅዳሜ ህዳር 27 2007 ዓ.ም

ፋይናንሺያል ታይምስ የተባለው ታዋቂ ጋዜጣ፣ የኢሕአዴግ መንግሥት ከምዕራብያውያን አበዳሪ ድርጅቶች በ “ሶቭሬን ቦንድ” መልክ ብድር ካላገኘ፣ ኢትዮጵያ የሽብርተኝነት፣ የጦርነትና የረሀብ አውድማ ልትሆን እንደምትችልና የአካባቢውም ሰላም ሊናጋ እንደሚችል ለእነዚሁ አበዳሪዎችና የፋይናንስ ኢንቬስተሮች ማስጠንቀቂያ መስጠቱን አስታውቆአል፡፡ አክሎም፣ ከኤርትራ ጋር ጦርነት ሊቀሰቀስ እንደሚችል፣ በግንኙነት መሻከር ምክንያት የጅቡቲ ወደብ አገልግሎት ቢቋረጥ፣ በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ ችግር እንደሚደርስና በ2007ዓ.ም ምርጫ ውዝግብና ትርምስ ሊከሰት እንደሚችል የኢህአዴግ መንግሥት ማስታወቁን ዘግቧአል፡፡ ኢሕአዴግ፣ ለአለፉት አሥራ ሁለት ዓመታት የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በአሥራ አንድ በመቶ አድጐአል፤ ተመንድጎአል እንዳላለ፣ አሁን ይህን አስደንጋጭና አስገራሚ ማስጠንቀቂያ መስጠቱ ከምን ጭንቀትና ሥጋት የተነሳ ይሆን?

እሁድ ህዳር 28/ 2007 ዓ.ም ጠዋት ከ3:00 ጀምሮ

የመድረክ ክርክር በወጣት እንግዳ ወልደፃዲቅ እና

ጋዜጠኛ ስለሺ ሀጎስ መካከል “የ2007 ምርጫ ለኢህአዴግ

የመጨረሻው ወይስ የመጨረሻው መጀመሪያ ምርጫ?”

በሚል ጥልቅና ሰፊ ክርክር ያደርጋሉ በመሆኑም እርስዎም

በቦታው በመገኘት ክርክሩን እንዲታደሙ ተጋብዘዋል፡፡

ቦታ፡- ቀበና መድሀኒአለም ቤ/ክ ፊት ለፊት በሚገኘው

የአንድነት ፓርቲ ጽ/ቤት

አዘጋጅ ፡-የአንድነት ወጣቶች ቋሚ ኮሚቴ

አስደንጋጩ የፋይናንሺያል ታይምስ ዘገባ

መንግሥታዊ ሽብርተኝነት?

የኢሕአዴግ መንግሥት፣ ምዕራብያውያን ጭምር በሚረዱት ሠራዊቱ ተጠቅሞ፣ ኢትዮጵያን ወደብ-አልባ አድርጐአታል፤ ሕዝቡን በጐሣ ከፋፍሎ አናክሶታል፣ ኢኮኖሚዋን ያለ-ገደብ መዝብሮታል፤ ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶችን በገሀድ እየረገጠ ዜጐቿን ደብድቦአል፤ አሥሯል፤ ገድሏል፡፡ ይህን ሁሉ ግፍና በደል እየፈፀመም፣ እነዚሁ ምዕራብያውያን መንግሥታትና እነሱ የሚቆጣጠሯቸው ዓለም-አቀፍ የገንዘብ ድርጅቶች፣ እንዲሁም በተለይ የቻይና መንግሥት ለኢህአዴግ በዓመት ወደ አራት ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ ብድርና ዕርዳታ ሰጥቷል፤ አሁንም እየሰጡት ነው፡፡ ገንዘቡ ግን አልበቃውም፡፡ ኢህአዴግ ያለው አማራጭ እንደ መንግስታዊ አሸባሪ ምዕራብያውያኑን ማስፈራራት ነው፤ አለበለዚያ ተጨማሪ ብድርና ዕርዳታ ላይሰጡት ይችላሉና፡፡

አሁን ያላቸው አንደኛው አማራጭ

ለኢህአዴግ ካሣውን መክፈል ነው፡፡አለበለዚያ፣ ኢሕአዴግ እንደፎከረው ኢትዮጵያን የሽብርተኝነት አውድማ ሊያደርጋት ይችላል፡፡ ሠራዊቱን ከነትጥቁ በየጐሣው በትኖ፣ ከሩዋንዳው የማይተናነስ የጐሣ ጦርነትና እልቂት ሊቀሰቅስ ይችላል፡፡ኢሕአዴጋያውያን የዘረፉትን ገንዘብ ወደአስቀመጡባቸው ሀገሮች (ማሌዥያ፣ ቻይና) ሊፈረጥጡ ይችላሉ፡፡ ኢህአዴግያውያን ለኢትዮጵያ ቢያስቡ ኖሮ፣ በትሪሊዮን ብር የሚቆጠረው የዘረፉት ገንዘብ አሁን ከገቡበት የኢኮኖሚ ቀውስ ሊያወጣቸው ይችል ነበር፡፡ የአባይ ግድብ የሚያስፈልገው ገንዘብ እኮ አምስት ቢሊዮን ዶላር ገደማ ነው፡፡ እነሱ ዘርፈው ከሀገር በዶላር ያስወጡት ገንዘብ ብቻ ሃያ አምስት ቢሊዮን ዶላር ደርሶአል፡፡

የምዕራብያውያኑ ሌላው አማራጭ

ለምዕራብያውያኑ ቀላሉ አማራጭ ኢሕአዴግ የጠየቀውን ማለትም በጠቅላላው ከአምስት ቢሊዮን ዶላር ያልበለጠ ገንዘብ ሰጥተውት መገላገል ነው፡፡ ግን ሌላ የተሻለ አማራጭም አላቸው፡፡ ኢሕአዴግን

ለማስታገሥና ጊዜ ለመግዛት ትንሽ ገንዘብ ወርውረውለት፣ ጐን ለጐን በሐቀኛ ተቃዋሚዎች በኩል ሰላማዊ ሕዝባዊ ንቅናቄ እንዲቀሰቀስ አመቺ ሁኔታ መፍጠር ይችላሉ፡፡ ሠራዊቱን በተመለከተ ከሻለቃ በታች ያለው ሁሉ ከሕዝብ ጐን እንዲሰለፍ ማድረግ ይቻላል፡፡ በመንግሥታዊ አሸባሪዎች ተገድዶ ካሣ ከመክፈል፣ ይኼኛው አማራጭ ሳይሻል አይቀርም፡፡

ማጠቃለያ

ለሃያ ሶስት ዓመታት ሀገር ሲያፈርስና ሲመዘብር የኖረ ሥርዓት፣ ወደ መንግሥታዊ አሸባሪነት እንደሚቀየር ለማወቅ ነብይነትን አይጠይቅም፡፡ ይልቅስ በራሳችን ማፈር ያለብን ይመስለኛል! በሃያ አንደኛው ክፍለ-ዘመን በባርነት ቀንበር ሥር ወድቀን እያለን፣ እንደ ሀገርና እንደ ሕዝብ ሕብረት መፍጠር አቅቶን፣ በዚህ ሰው በላ ሥርዓት ለሃያ አራት ዓመታት እንደ እባብ ራስ ራሳችንን ተቀጠቀጥን! ተደበድብን፣ ታሠርን፤ ተገደልን! እረ፣ ዛሬ እንኳን በቃን እንበል!