ሁለተኛው የዮሐንስ መልእክት - t.l.c.f .... 2 john.pdf · ሰለዚህም ይህ...

45
ሁለተኛው የዮሐንስ መልእክት 2014 0 www.tlcfan.org በመጋቢ ሊዮን ኢማኒኤል

Upload: trinhcong

Post on 14-Feb-2018

528 views

Category:

Documents


83 download

TRANSCRIPT

ሁለተኛው የዮሐንስ መልእክት 2014

0 www.tlcfan.org

በመጋቢ ሊዮን ኢማኒኤል

ሁለተኛው የዮሐንስ መልእክት 2014

1 www.tlcfan.org

የተመረጠች እመቤት 2ኛ የዮሐንስ መልእክት

የመጀመሪያ እትም

Copyright ©1998 የሁለተኛ እትም REVISED 2015

መብቱ የተጠበቀ ነው፦

All rights Reserved to: Bible Teacher Pastor Leon Emmanuel

FOUNDER OF

THE LION S CALL FOR ALL NATION INTERNATIONAL MINISTRY

Permission is granted to copy and quote freely

from this publication for non-commercial purposes.

ሁለተኛው የዮሐንስ መልእክት 2014

2 www.tlcfan.org

ማውጫ

1) ሐዋርያው ዮሐንስ ............................................................................... 3

2) በኛ ለዘላለም የሚኖር እውነት .............................................................. 8

3) እኔ ሽማግሌው ................................................................................... 14

4) እውነት በማወቅ መውደድ .................................................................... 17

5) የተመረጠች እመቤትና ልጆችዋ ............................................................ 21

6) ጸጋ፣ ምሕረት፣ ሰላምና እውነት በፍቅር ................................................ 23

7) በእውነት የሚሄዱ ልጆች ...................................................................... 25

8) ከመጀመሪያ የነበረች ትእዛዝ ................................................................. 27

9) ሙሉ ደሞዝ......................................................................................... 31

10) የክርስቶስ ትምሕርት ........................................................................... 41

Copyright ©1998

ሁለተኛው የዮሐንስ መልእክት 2014

3 www.tlcfan.org

ሐዋርያው ዮሐንስ

ዮሐንስ የጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን ሰማያዊ መልኩን ከነሙሉ ክብሩና ግርማዊነቱ በመንፈስ በፊጥሞ ደሴት ላይ በመከራ ውስጥ እያለ የተመለከተ ታላቅ ሐዋርያ ነው። ኢየሱስ ከሚወዳቸው ሐዋርያት መካከልም የመጀመሪያውን ስፍራ ይይዛል። በመድሐፍ ቅዱስ ውስጥ ኢየሱስ የሚወደው ዮሐንስ ተብሎ ተጽፎ ይገኛል።

ይህ በእግዚአብሔር ተወዳጅ የሆነ ዮሐንስ ኢየሱስ አብ ያዘጋጀለትን ጽዋ ሊጠጣ በቀረበ ጊዜ የፋሲካን ራት በተዘጋጀው ድርብ ቤት ውስጥ ሳሉ አሳልፎ ሰለሚሰጠው ሰው ማንነት ሁከት ሲፈጠር ወደ ጌታ ደረት ተጠግቶ መልስን ያገኘ የእግዚአብሔር ቃል የሚያስተውል የሚያደምጥ የተረጋጋ እግዚአብሔር ባሪያ ነው።

“የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ፦ ከመከራ ስጋት ያርፋል።” (ምሳሌ.1፥32)

የሚለው ቃል የተፈጸመበት ሰው ነው። ጴጥሮስ ከፍርሃቱ የተነሳ የማያደርገውን ነገር እንደሚያደርግ ሰው ሲፎክር ዮሐንስ ግን ከጌታ የወጣ ቃል በመስማቱ በእርጋታ የተቀመጠ አሰተዋይ ባርያ ነው። በደብረ ዘይት ተራራም ከጴጥሮስና ያቆብ ጋር በመሆን ከገናናው ክብር የወጣውን የአብ ጽምፅ፣ የኢየሱስን የክብር ነጸብራቅ የሙሴንና የኤልያስን መገለጥ ተመለከተ። ደግሞም ኢየሱስ በመስቀል ላይ በተስቀለ ጊዜ ሁሉ ርቆ ሲከተል እርሱ ግን በመስቀሉ አጠገብ በመገኘት የኢየሱስን ጭንቀት፣ የደምና የውሃ ከጎኑ መፍሰስ ከቅርብ በመሆን ያስተዋለ ነው። ሰለዚህም ይህ ምስክርነት በእርሱ ወንጌል ብቻ ተጽፎ እንዲገኝ አድርጎታል።

የኢየሱስ እናት ማርያምን እንደ እናቱ እርሱም እንደ ልጇ እንዲተያዩ በጌታ ትዕዛዝ የተነገረለት ተወዳጅ ሐዋርያ ነው። ይህ ብቻ ሳይሆን ከኢየሱስ ትእዛዝን እንደ ልማዱ ጠጋ ብሎ የተቀበለ ነው። በከፍታም ሆነ በዝቅታ ውስጥ የሚመጣውን ቃል የሚሰማ ባሪያ ነው። የቃል አስተማሪው ያለበትን ሁኔታ ተመልክቶ አይሰማም። በዚያን ወቅት በመስቀል ላይ የተሰቀለ በሃይማኖተኞች ሰዎች እርጉም ስህተት የተሞላ ከተባለ ከእንዲህ ከሚባል ሰው እየሞተ ካለ ሰው ትዕዛዝንና መልዕክትን መቀበሉ የሚያስደንቅ የማይለወጥና የማያመቻምች ማንነቱን የሚያሳይ ነው።

የዮሐንስ ወንጌል 1ኛ፣ 2ኛ ና 3ኛ የዮሐንስን መልዕክት የጻፈ የበሰለ ሐዋርያ ሲሆን በምድር ቆይታው ማጠቃለያ ዘመኑ ላይ የክርስቶስን ራዕይ ከመላአኩ ተመልክቶ የጻፈ ድንቅ የእግዚአብሔር ባርያ ነው። የመንፈስን ሃይልና ፍቅር የጠገበ፣ በሁሉ ነገር የተረጋጋ፣ ፍቅር የሚባለውን መለኮታዊ ቃል በሕይወቱ አካል ያበጀለት፣ እውነትንም እንደ ቀበቶ የታጠቀ የእውነትና የፍቅር ባልንጀራ ነው።

መክዕክቶቹ በአብዛኛው ሁለት ዋና መልዕክት የያዙ ሲሆኑ ማብራሪያዎቹም እነዚሁን ቃላት በተለያዩ መልኮች ሲገልጻቸው ይታያል። እነዚህም ፍቅር ና እውነት ናቸው። “እግዚአብሔር ፍቅር ነው።”… እኛ ደግሞ እርስ በእርሳችን ልዋደድ ይገባናል። በፍቅር የሚኖር በእግዚአብሔር ይኖራል። በፍርድ ቀን ድፍረት ይሆንልን ዘንድ ፍቅር በዚህ ከእኛ ጋር ተፈጽሟል።

ሁለተኛው የዮሐንስ መልእክት 2014

4 www.tlcfan.org

ፍጹም ፍቅር ፍርሃትን አውጥቶ ይጥላል። በፍቅር ፍርሃት የለም። እውነት በእኛ ለዘላለም ይኖራል። እውነት በውስጡ የሌለው ሰይጣን ነው። እውነት አርነት ያወጣል።… የሚሉ ተደጋጋሚ ቃላት በመልዕክቱ እናገኛለን። እውነትንም ሆነ ፍቅርን በተለያየ መልኩ እያጎላው በመጨረሻም አካል እንደ ሆነ አስረግጦ ያስቀምጣዋል። ይህ የእውነትና የፍቅር አካልም ክርስቶስ ኢየሱስ መሆኑንም በግልጽ ያስቀምጣል። “ልጆቼ በእውነት ሲሄዱ ከመስማት ይልቅ የሚበልጥ ደስታ የለኝም።” (3ኛ ዮሐንስ)

ለብዙ ዓመት በመንፈስ ሲመራ የኖረ ሰው ሰለ እውነት ደስ ይለዋል። “እውነተኛ በሆነው በእርሱ አለን። እርሱም ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እርሱ እውነተኛ አምላክና የዘላለም ሕይወት ነው።” (1.ዮሐ.5፥20-24) በማለት ደስታውን በጽሁፍ ይገልጣል።

ሐዋርያው ዮሐንስ በተለያዩ ዓመታት መንፈሳዊ እንቅስቃሴን ያከናወነ ስለ ፍቅርና እውነት ማስተማር ቀዳሚ ሲሆን ፍቅርንና እውነትን ካከኘ እነዚህ ነፍሱን ሓሴት ይሰጧታል። ለፍቅርና ለእውነት የኖረ የሞተም የመጀመሪያውን ትንሳኤ ወራሽ የሆነ ድል ነሺ የእግዚአብሔር ልጅ ነው።

ዮሐንስ በሽምግልናው ዘመን አንድ ትልቅ መለኮታዊ ሚስጥር በፍጥሞ ደሴት ላይ ተመለከተ። በዚህ ደሴት ላይ ተመልከቶ የጻፈው አንድ ራዕይ ቢሆንም እንኳ ለዘመናት ለብዙዎች እንቆቅልሽና አስደንጋጭ ሆኗል። ይሁን እንጂ እውነትና ፍቅር እንጂ በሐዋርያው በተመለከተው ራዕይ ውስጥ ድንጋጤና ፍርሃት የለበትም።

የዚህ ሐዋርያ የመጨረሻ መገለጥ ኢየሱስ ክርስቶስን በሙሉ ክብሩ መመልከት ነው። ዮሐንስ ኢየሱስን በተለያየ ክብሩ ተመልክቶታል። ከመሞቱ በፊት፣ በተራራው ላይ ሲያበራ፣ በመስቀል ላይ ሲሞት፣ ከትንሳኤው በኃላ በከበረው የትንሳኤ አካል፣ በሽምግልናው ደግሞ በቤተክስቲያን ውስጥ በሙሉ ክብሩ ቆሞ ተመለከት። እስጢፋኖስም የድንጋይ ውርጅቢኝ ውስጥ እያለ በመንፈስ ኢየሱስን የእግዚአብሔር ክብርን ቆሞ ተመለከተ። ነገር ግን እንደ ዮሐንስ ግልጽ አልነበረም ወይም ሊያብራራ ጊዜ አልነበረውም ገና አፉን ሲከፍት ሃይማኖተኞች በድንጋይ ወግረው ገደሉት። አሁንም እንዲህ ናቸው። በቃላት ድንጋይ የተገለጠላቸውን ሰዎች የሚወግሩ ቀናተኛ ነን ባይ ሃይማኖተኞች አሁንም ብዙ ናቸው። ነገር ግን እስጢፋኖስ ቢገደል ለዮሐንስ ደግሞ የሚገልጥ ጌታ አለ። ሰው ሊሞት ሊታገድ አፉ ሊዘጋ ይችላል። እውነት ግን መቼም አይታሰርም አይታገድም። እውነት ቢሞት እንዃ ይነሳል።

ዮሐንስ በሽምግልናው የተመለከተው ኢየሱስን በሙሉ ክብሩና ማንነቱ በመቅረዝ ወይም ፍጹም በሆነችው ቤተ ክርስቲያ ውስጥ መሆኑን ነው። ይህ ራዕይ ኢየሱስን ከዚህ በፊት ዮሐንስ ካየበትና ከተለማመደው ሁሉ ይልቅ የሚበልጥ ነበር። ያኔ አብሮ ቁጭ ይል የነበረ አሁን ግን በፊቱ ተደፋ።

ሁለተኛው የዮሐንስ መልእክት 2014

5 www.tlcfan.org

ይህን በመልክቱም ለቤተክርስቲያ ከጌታ መልዕክት ከመቀበል በላይ ወደ ላይ ወደ ሰማይ እንዲወጣ በተከፈተው በር ኢየሱስ ውጣ አለው። ሲያወጣውም ሊያሟሙቀው ሳይሆን ሊሆን የሚገባውን የሚያስፈልገውን ነገር ሊያሳየው ነበር። እንዳለውም ጌታ ለዮሐንስ ሁሉ በግልጽ አሳይቶታል። ወደ ሶስተኛ ስማይም ተወስዶ ሰው ሊሰማው የማይችለውን ነገር የሰማው ብዙዎች እንደሚሉት ጳውሎስ ሳይሆን ይህ ሐዋርያው ዮሐንስ ነው። ወደ ገነት የተወሰደውም በመንፈስ በመሆን ነው። ጳውሎስ ግን ራዕይ ገና ተጽፎ ስላልነበረ መወስዱን ብቻ ሰምቷል።

“1 ትምክህት የሚያስፈልግ ነው፤ አይጠቅምም ነገር ግን ከጌታ ወዳለው ራእይና መገለጥ እመጣለሁ፣ ( ዮሐንስ ወደ ተመለከተው ራዕይና መገለጥ ማለቱ ነው፣ ምክንያቱ ለዮሐንስ

ራዕዩና መገለጡ የመጣለት በጌታ በራሱ ነው፣) 2 ሰውን (ዮሐንስን) በክርስቶስ (ባለን በእምነት ጉዞ) አውቃለሁ፥ በሥጋ እንደ ሆነ አላውቅም ወይም ከሥጋ ውጭ እንደ ሆነ አላውቅም፥

እግዚአብሔር ያውቃል፤ እንዲህ ያለው ሰው (በጌታ ከመወደዱ የተነሳ በክርስቶስ የማውቀው ዮሐንስ) ከአሥራ አራት ዓመት በፊት እስከ ሦስተኛው ሰማይ ድረስ ተነጠቀ። 3 እንዲህ

ያለውንም ሰው (ዮሐንስን) አውቃለሁ፥ በሥጋ እንደ ሆነ ወይም ያለ ሥጋ እንደ ሆነ አላውቅም ( ወደ ገነት የተወሰደው ዮሐንስን ማለቱ ነው፣ ምክንያቱ የተወሰደው ጳውሎስ ቢሆን በመነፈስ ይሁን በስጋ በምን እንደተወሰደ ያውቅ ነበር)፥( ጳውሎስ ግን እንዲህ አለ እኔ አለውቅም) እግዚአብሔር ያውቃል፤ 4 ወደ ገነት ተነጠቀ (ዮሐንስ) ፥ ሰውም ሊናገር የማይገባውን

የማይነገረውን ቃል ሰማ። (የሰማውን በዚህ ጥቅስ ላይ ተመልከቱት (ራዕይ.10፦1-4) ነገር ግን ለሰው እንዳይጽፈው እንዲያትመው ታዘዘ ምክንያቱም ለሌላው የማይነገረውን እርሱ ብቻ

ሊሰማው የተፈቀደለት ሰማ) 5 እንደዚህ ስላለው እመካለሁ (ወደ እዚህ ድምዕ ደርሼ እራሴ እስከ ምሰማ በእምነቴ ጠነክራለሁ)፥ (አሁን ግን ማለት ይህን በጻፈበት ወቅት ብዙ የብሉይ ኪዳን የሕጉ

መገለጥ የበዛለት ቢሆንም እንኳ ሰለ ራሱ እንዲህ ይላል) ስለ ራሴ ግን ከድካሜ በቀር አልመካም። (ይህ ትጋቱን እንጂ ድካሙ ሃጢያት ማለቱ አይደለም) 6 ልመካ ብወድስ ሞኝ

አልሆንም፥ እውነትን እላለሁና፤ ነገር ግን ማንም ከሚያይ ከእኔም ከሚሰማ (ከዮሐንስ) የምበልጥ አድርጎ እንዳይቆጥረኝ ትቼአለሁ፣ ስለዚህም በመገለጥ ታላቅነት እንዳልታበይ የሥጋዬ መውጊያ፥ እርሱም የሚጎስመኝ የሰይጣን መልእክተኛ ተሰጠኝ፤ ይኸውም እንዳልታበይ ነው፣ 8 ስለዚህ ነገር ከእኔ እንዲለይ ሦስት ጊዜ ጌታን ለመንሁ።9 እርሱም። ጸጋዬ ይበቃሃል፥ ኃይሌ በድካም

ይፈጸማልና አለኝ። እንግዲህ የክርስቶስ ኃይል ያድርብኝ ዘንድ በብዙ ደስታ በድካሜ (መከራው ፤ትጋቱ ፤አገልግሎቱ) ልመካ እወዳለሁ።10 ስለዚህ ስለ ክርስቶስ በድካም በመንገላታትም

በችግርም በስደትም በጭንቀትም ደስ ይለኛል፤ ስደክም ያን ጊዜ ኃይለኛ ነኝና።11 በመመካቴ ሞኝ ሆኜአለሁ፤ እናንተ ግድ አላችሁኝ፤ እናንተ እኔን ልታመሰግኑ ይገባ ነበርና። እኔ ምንም

ባልሆን እንኳ፥ ከዋነኞቹ ሐዋርያት በምንም አልጎድልምና።….” (2.ቆሮ.12፥1-11)

ጳውሎስ የዮሐንስን የእምነት ፈለግ ተከትሏል። ሰለ ፍቅር ሰለ እውነት ከዮሐንስ ቀጥሎ ብዙ ያስተማረ ጳውሎስ ነው። ከዮሐንስንም ስለ ትምህርት ሳይማር አይቀርም። ለምሳሌ ያህልም ዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ ስምንትንና ገላትያ ምዕራፍ አምሰትን እንመልከት። ጳውሎስ ከመንፈስ በተሰጠው የመገለጥ መንፈስ የዮሐንስን ትምህርት መንፈሱን ገልጦ አስተምሯል።

ሁለተኛው የዮሐንስ መልእክት 2014

6 www.tlcfan.org

“… ሂጂ ደግመሽ ሃጢያትን አትስሪ።…34 ኢየሱስ መለሰ፥ እንዲህ ሲል። እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ኃጢአት የሚያደርግ ሁሉ የኃጢአት ባርያ ነው። 35 ባርያም ለዘላለም በቤት አይኖርም፤

ልጁ ለዘላለም ይኖራል። 36 እንግዲህ ልጁ አርነት ቢያወጣችሁ በእውነት አርነት ትወጣላችሁ።”

የሚለውን ቃል ጳውሎስ “ በነጻነት ልንኖር ክርስቶስ ነጻነት አወጣን እንግዲህ ጸንታችሁ ቁሙ በባርነት ቀንበር አትያዙ።” ብሎ በግልጽ ያስቀምጠዋል። ይህ ደግሞ ዮሐንስ የደረሰበት መድረስ ብቻ ሳይሆን ትምህርቱን ሕይወቱን ፈለግ አድርጎ ይከተለው እንደ ነበር በቀለሉ መመልከት እንችላለን።

ጳውሎስ ከዮሐንስ ብዙ ነገርን ከጌታ በተማረው ላይ ጨምሮ እንደ ተማረ የሁለቱን ሐዋርያት መጽሐፎች ጎን ለጎን በማድረግ በቀላሉ መመልከት መረዳት ይቻለል። ሐዋ.13፥13 መሰረት ጳውሎስ በመንፈስ ተለይቶ አገልግሎት ሲጀምር አገልግሎቱ በመንፈስ መሆኑን ለመመልከትና ለአገልግሎቱ የሚሆነውን እውነት ለማስያዝ ዮሐንስ አብሮት ከጳውሎስ ጋር ወጥቶ ነበር። ነገር ግን የጳውሎስ እጅ ጌታ እየፈጸመ ያለው ነገር ከጌታ መሆኑን ስላረጋገጠ ዮሐንስ ወደ ኢየሩሳሌም ተመልሶ መጥቷል። ጳውሎስ ለአገልግሎት የበቃ ማንነት ከጌታ መቀበሉን አብሮት በውጣት ያረጋገጠው ዮሐንስ ነበር።

ዮሐንስ በመንፈስ ከመሆኑ የተነሳ የራዕይ መጀመሪያውን ኢየሱስን በሙሉ ክብሩ በቤተክርስቲያ መካከል መመልከት ቻለ። ዮሐንስ ይህን ራዕይ ሲመለከት እንደ ሞተ ሰው ሆኖ ከግሩ በታች ወደቀ። ለ60 አመት መንፈስ ቅዱስን ተሸክሞ የኖረ ኢየሱስን በሙሉ ክብሩ ሲያይ ወደቀ። የጌታ መገኘት በሃይል ሲሆን ትልቅ ትንሽ አይልም ሁሉን ይጥላል። ነገር ግን ገፍትረውና ገፍተው የሚጥሉትን የዘመኑን አገልጋይ ነን ባይ ሰዎች አልልም። የጌታ መገኘት ያለ ሰው ግፊትና ግፍትሪያ ይጥላል።

እኛም የራዕይ ሁሉ መጀመሪያ ሊሆንልን የሚገባው የኢየሱስን የሕይወታችን ሆነ የቤተክርስቲያን መመልከለኛነትን ነው። ያላየ እርሱን መምሰል አይችልም። የጳውሎስም ምኞት ይህ ነበር። ለጳውሎስም ኢየሱስ ተገልጦለታል። ነገር ግን እንደ ዮሐንስ በግልጥ አይደለም። ጳውሎስ ብርሃን ብቻ ተመለከተ ዮሐንስ ግን ሁሉን በዝርዝር አየ። ዮሐንስ የቤተ ክርስቲያ ታሪክ እንደሚናገረው ሰለ እግዚአብሔር ቃልና ኢየሱስ ክርስቶስ ምስክር በፈላ ዘይት ውስጥ ተጥሎ ምንም ሊሞት ስላልቻለ በፍጥሞ ደሴት እንደታሰረ ያነገራል። ይህ ደግሞ ላመነበት ነገር ቆራጥነቱን ያሳያል። አባቱን የሚወድ በምድር ዕድሜን እንደሚጠግብ ሕጉ እንደሚናገር ከሐዋርያት ሁሉ መጨረሻ የቀረ እድሜን የጠገበ እርሱ ብቻ ነበር። ሁሉ ቀድመውት ሰማዕታት ሆኑ። ጌታን በመውደዱ ራሱን ገለጠለት። “ የሚወደኝ ቢኖር ራሴን እገልጥለታለሁ።” እንዳለ ማለት ነው።

ይህ ዮሐንስ ብዙዎች ሊያዩት የሚፈልጉትን የሚመኙትን ኢየሱስ ክርስቶስን በመንፈስ በመሆን በኃይለኛ መከራ ውስጥ ሆኖ ሳለ በጥራት በሙሉ ክብሩ ተመለከተው። ለኛም አስተላልፎልን የሄደው ነገር በቀላሉ የሚታይ አይደለም። ሕይወቱም ቢሆን ልንከተለው የሚገባ ታላላቅ ትምህርቶችን ያስተምሩናል።

ሁለተኛው የዮሐንስ መልእክት 2014

7 www.tlcfan.org

የሰማይን፣ የምድር፣ የሰይጣን፣ የጥልቁ፣ የእሳት ባሕር፣ አዲሲቱ እየሩሳሌም፣ የቤተክርስቲያን፣ የድል ነሺዎች ሕይወት፣ ነጩ ዙፋን፣ የእግዚአብሔር ፍርድ፣ የሞትና የሲኦል ፣ፍርድ፣ የባቢሎን አወዳደቅ፣ የሺው ዓመት መንግስት፣ ሙሽራይቱ፣ የክርስቶስ መገለጥ… የተለያዩ ድንቅ ሚስጥራት ተመለከተ። የተመለከተውን ጽፎ ለእኛ ያሰቀመጠልን በእግዚአብሔር ተወዳጀ የሆነ የእግዚአብሔር ባርያ ዮሐንስ ነው።

ከዮሐንስ ሕይወት የምንማረው ትልቁ ነገር ኢየሱስን ትግስት፣ ፍቅርና እዉነት ነው። ዮሐንስን ጌታ ያገኘው መረቡን ሲጠግን ነው። ይህም የተጠመደ አሳ ከመረቡ እንዳይወጣ ቀዳሚ የሆነ ጥንቃቄ ሲያደርግ ነው። ወደ ጌታም ከመጣ በኃላም የእግዚአብሔር መንግስት የሆነችው መረብ ውስጥ የገቡ አማኞች በስሕተት እንዳይወሰዱ የተበላሽን ትምሕርት በማስተካከል ዋነኛና ቀዳሚ ባሪያ ነው።

ሁለተኛው የዮሐንስ መልእክት 2014

8 www.tlcfan.org

በእኛ ለዘላለም የሚኖር እውነት

“1-2 . በእኛ ስለሚኖርና ከእኛ ጋር ለዘላለም ስለሚሆን እውነት፥ እኔ ሽማግሌው በእውነት ለምወዳቸውና እኔ ብቻ ሳልሆን እውነትን የሚያውቁ ሁሉ ደግሞ

ለሚወዱአቸው ለተመረጠች እመቤትና ለልጆችዋ፤”

በእኛ የሚኖረው ኢየሱስ ነው። የኢየሱስ ክርስቶስ መኖሪያ የሰው ልጆች ናቸው። ይህ ኢየሱስ ክርስቶስ እውነት ነው።

“ኢየሱስም። እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም።”

ዮሐ.14፥6

የእውነት መኖሪያው የሰው ልጆች ናቸው። ሰው በውስጡ እውነት በመኖሩ ሰውን ማታለለል በጣም ከባድ ነው። በሌላ መልኩ ደግሞ ሊታለል የሚችል ሰው እውነት በውስጡ እንዳለ የማያውቅና እውነትን የተቀማ የማያምን ብቻ ነው። ይህ እውነት በሰው ልጆች ውስጥ የሚኖረው ለዘላለም ነው። ይህ እውነት የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ ያለው በእውነት ውስጥ ያለው ነገር ሁሉ አለው።

ይህ እውነት በአማኞች ብቻ ሳይሆን ገና የምስራቹን ባልሰሙት ውስጥ እንኳን ይኖራል። ምክንያቱም የእውነት መኖሪያ የሰው ልጆች ናቸውና ነው። እውነት ራሱ የእግዚአብሔር ሕግ ነው። ሮሜ.2 ጳውሎስም ሰለ አማኞች ሲናገር እውነት በእናንተ እንዳለ ሰምታችኃል እውነትም በእናንተ እንዳለ ታውቃላችሁ አለ። ሰምታችኃል ማለቱ የምስራቹን ወንጌል መስማታችንን ለማሳየት ነው። በወንጌል የምስራች ኢየሱስ ክርስቶስን ያመናችሁ በውስጣችሁ እውነት አለ ማለት ነው። ይህ ደግሞ ለእኛ የሆነው በሞቱና ትንሳኤው ስራ በኩል ነው።

የአሕዛብ ክብር ተስፋ ኢየሱስ በእነርሱ ውስጥም መኖሩ ነው። ለአማኞች ግን ኢየሱስ በአማኞች ውስጥ የክብር ተስፋ ብቻ ሳይሆን ክብር ነው። ለአሕዛብ ግን ገና ኢየሱስ በውስጣቸው እንዳለ ሰለ ሞቱ ትንሳኤው ከዛም በኃላ በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት እርሱና አብ ወደ እነርሱ መጥተው ማደሪያ ማድረጋቸውን ገና አልሰሙም አላወቁም። ይሁን እንጂ እውነት የሆነው ብርሃን በልባቸው በርቷል። ይህ ብርሃን የሚበራው ለሰው ሁሉ ነው። ዘር ቋንቋና የተለያዩ ማሟያ መስፈርት የሚጠይቅ አይደለም። አብ ብርሃን ይሁን ስላለ ብርሃን ለሁሉ በሁሉ ሆኗል።

“ለሰው ሁሉ የሚያበራው እውነተኛው ብርሃን ወደ ዓለም ይመጣ ነበር።

በዓለም ነበረ፥ ዓለሙም በእርሱ ሆነ፥ ዓለሙም አላወቀውም።” ዮሐ.1፥9-10

ሁለተኛው የዮሐንስ መልእክት 2014

9 www.tlcfan.org

ኢየሱስ ሁሉን ይዞ ለሁሉ መሞቱና በትንሳኤው ደግሞ ፈጽሞ ሁላችንን ይዞ እንደ ተነሳ ብሎም በመንፈስ በእኛ ውስጥ መኖሪያውን እንዳደረገ ለአሕዛብ ሊነገር የሚገባ መልካም ዜናና የምስራች ነው። ለአሕዛብ የክብር ተስፋ አላቸው። ይህም አወቁም አላወቁም ኢየሱስ በእነርሱ ውስጥ በብርሃን መኖሩ ነው።

“19-20 እግዚአብሔር ሙላቱ ሁሉ በእርሱ እንዲኖር፥ በእርሱም በኩል

በመስቀሉ ደም ሰላም አድርጎ በምድር ወይም በሰማያት ያሉትን ሁሉ ለራሱ እንዲያስታርቅ ፈቅዶአልና። 21-22 እናንተንም ነውርና ነቀፋ የሌላችሁና ቅዱሳን አድርጎ በእርሱ ፊት ያቀርባችሁ ዘንድ፥ በፊት የተለያችሁትን ክፉ ሥራችሁንም በማድረግ በአሳባችሁ ጠላቶች የነበራችሁትን አሁን በሥጋው ሰውነት በሞቱ በኩል አስታረቃችሁ። 23 ይህም፥ ተመሥርታችሁና ተደላድላችሁ ከሰማችሁትም ከወንጌል ተስፋ ሳትናወጡ፥….

…..በሃይማኖት ጸንታችሁ ብትኖሩ ይሆናል። ያም ወንጌል ከሰማይ በታች ባለው

ፍጥረት ሁሉ ዘንድ የተሰበከ ነው፥ እኔም ጳውሎስ የእርሱ አገልጋይ ሆንሁ።

24 አሁን በመከራዬ ስለ እናንተ ደስ ይለኛል፥ ስለ አካሉም ማለት ስለ ቤተ ክርስቲያን በሥጋዬ በክርስቶስ መከራ የጐደለውን እፈጽማለሁ። 25 ስለ እናንተ እንደ ተሰጠኝ እንደ

እግዚአብሔር መጋቢነት፥ የእግዚአብሔርን ቃል ፈጽሜ እንድሰብክ እኔ የቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ሆንሁ። 26 ይህም ቃል ከዘላለምና ከትውልዶች ጀምሮ ተሰውሮ የነበረ ምሥጢር ነው፥ አሁን ግን ለቅዱሳኑ ተገልጦአል። 27 ለእነርሱም እግዚአብሔር በአሕዛብ ዘንድ ያለው የዚህ ምሥጢር ክብር ባለ ጠግነት ምን እንደ ሆነ ሊያስታውቅ ወደደ፥ ምሥጢሩም የክብር ተስፋ ያለው ክርስቶስ በእናንተ ዘንድ መሆኑ ነው። 28 እኛም በክርስቶስ

ፍጹም የሚሆን ሰውን ሁሉ እናቀርብ ዘንድ ሰውን ሁሉ እየገሠጽን

ሰውንም ሁሉ በጥበብ ሁሉ እያስተማርን የምንሰብከው እርሱ ነው።”

ቆላ.1፥19-28

ተሰፋ የሆነበት ምክንያት ገና መልካሙን ዜና ሰምተው ይህን እውነታ ስላልተመለከቱት ነው። ቢያዪት ግን ተስፋ ሊሆን አይችልም። “በተስፋ ድነናልና፤ ነገር ግን ተስፋ የሚደረግበቱ ነገር ቢታይ ተስፋ አይደለም። የሚያየውንማ ማን ተስፋ ያደርገዋል?” ሮሜ.8፥24 አማኞች ግን ይህን እውነት ስላዩት ተሰፋ ሳይሆን ኢየሱስ በአማኞች ውስጥ ክብር ነው።

ይህ እውነት የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ ከእኛ ከሰው ልጆች ጋር ለዘላለም ይኖራል። ይህ ሁሉ የሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀሉ ስራ ነው። ይህንንም ደግሞ ሞትን ድል አድርጐ በመነሳት ለእኛ ለሰው ልጆች ሁሉን ፈጽሟል። ማንኛውም የሰው ልጅ በራሱ የሚመካበት ነገር የለውም። ሁሉ በእርሱና ከእርሱ ለእርሱ ነው።

“1-2 በበደላችሁና በኃጢአታችሁ ሙታን ነበራችሁ፤ በእነርሱም፥ በዚህ ዓለም እንዳለው ኑሮ፥ በማይታዘዙትም ልጆች ላይ አሁን ለሚሠራው መንፈስ አለቃ እንደ ሆነው በአየር ላይ ሥልጣን እንዳለው አለቃ ፈቃድ፥ በፊት ተመላለሳችሁባቸው። 3 በእነዚህም ልጆች መካከል እኛ ሁላችን ደግሞ፥ የሥጋችንንና የልቡናችንን ፈቃድ እያደረግን፥

ሁለተኛው የዮሐንስ መልእክት 2014

10 www.tlcfan.org

በሥጋችን ምኞት በፊት እንኖር ነበርን እንደ ሌሎቹም ደግሞ ከፍጥረታችን የቁጣ ልጆች ነበርን።4 ነገር ግን እግዚአብሔር በምሕረቱ ባለ ጠጋ ስለ ሆነ፥ 5 ከወደደን ከትልቅ ፍቅሩ

የተነሣ በበደላችን ሙታን እንኳ በሆንን ጊዜ ከክርስቶስ ጋር ሕይወት ሰጠን፥ በጸጋ ድናችኋልና፥ 6-7 በሚመጡ ዘመናትም በክርስቶስ ኢየሱስ ለእኛ ባለው

ቸርነት ከሁሉ የሚበልጠውን የጸጋውን ባለ ጠግነት ያሳይ ዘንድ፥ ከእርሱ ጋር አስነሣን በክርስቶስ ኢየሱስም በሰማያዊ ስፍራ ከእርሱ ጋር አስቀመጠን። 8 ጸጋው በእምነት አድኖአችኋልና፤ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም፤

9 ማንም እንዳይመካ ከሥራ አይደለም።” ኤፌ.2፥1-9

ምሕረትንም ለወደደ ወይም ለሮጠ አይደለም። ከሚምር ከአንዱ ከእግዚአብሔር ነው። ዳግም መወለድም ቢሆን ከእግዚአብሔር ፈቃድ እንጂ ከሰው ፈቃድ አይደለም። የሰው ልጅ እግዚአብሔር ካልገለጠለት ወይም እንዲያምን እግዚአብሔር ካላሰማውና ካልጠራው በቀር ማንም ማመን ወይም ዳግም መወለድና ወደ እውነት ሊመጣ አይችልም።

“ለተቀበሉት ሁሉ ግን፥ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው፤ 13 እነርሱም ከእግዚአብሔር (ፈቃድ) ተወለዱ እንጂ

ከደም ወይም ከሥጋ ፈቃድ ወይም ከወንድ ፈቃድ አልተወለዱም።” ዮሐ.1፥12-13

ለተቀበሉት ሁሉ ብሎ ዮሐንስ ያስቀመጣቸው ያመኑበትን አይሁዶች ነው። ይሆኑ ዘንድ ግን ስልጣንና ሃይልን ሰጣቸው፣ ስልጣኑን ከተቀበሉት መካከል ሃዋርያቶቹ የመጀመሪያዎች ናቸው። ኢየሱስ ሞቶ ከተነሳ በኃላ ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ ሆነ ከአብ ሰምቶ የሚያምን ሁሉ ዳግም ተወልዷል። የእግዚአብሔር ልጅ ለመሆን ስልጣንን ተቀብሏል።

“ክርስቶስ ነው ብሎ በኢየሱስ የሚያምን ሁሉ ከእግዚአብሔር ተወልዶአል፥ ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው፣”

1.ዮሐ.5፥1

ዮሐንስ በመልክቱ ሰለዚህ አስረግጦ ሲናገር ከኢየሱስ ትንሳኤ በኃላ ሰለ ሆንነው ነገር፦

“1 የእግዚአብሔር ልጆች ተብለን ልንጠራ አብ እንዴት ያለውን ፍቅር እንደ ሰጠን እዩ፥ እንዲሁም ነን። ስለዚህ ምክንያት ዓለም እርሱን ስላላወቀው እኛን አያውቀንም። 2 ወዳጆች ሆይ፥ አሁን የእግዚአብሔር ልጆች ነን፥ ምንም እንደምንሆን ገና

አልተገለጠም። ዳሩ ግን ቢገለጥ እርሱ እንዳለ እናየዋለንና እርሱን እንድንመስል እናውቃለን፣”

1.ዮሐ.3፥1-2

እውነት በእኛ በሰው ልጆች መኖር የፈለገው በፈቃዱ እንጂ በፈቃዳችን አይደለም። ወዶ እንጂ ወደን አይደለም። አብ ካልጠራው በቀር ወደ ኢየሱስ መምጣት የሚችል የለም። ወደ እንደዚህ ያለ እውነት ለመምጣት የምንችለው አብን ሰምተንና ተምረን ብቻ ነው።

ሁለተኛው የዮሐንስ መልእክት 2014

11 www.tlcfan.org

አብ ካልተናገረን ደግሞ መስማትም ሆነ ማመንም አንችልም። ሰለዚህ ሰው በፈቃዱ እውነት በእነርሱ እንዲኖር ለማድረግ ፈጽሞ አንችልም። ማንም አገልጋይ ለአንድ ሰው እውነት በውስጡ እንዲኖር ማድረግ በራሱ ፈቃድ ፈጽሞ አይችልም። እነርሱም ከእግዚአብሔር (ፈቃድ) ተወለዱ እንጂ ከደም ወይም ከሥጋ ፈቃድ ወይም ከወንድ ፈቃድ አልተወለዱም። ይላልና ነው። ሰባኪም ያስፈለገው ለዚሁ ስራ መፈጸም ነው። ከእግዚአብሔር ተቀብሎ የእግዚአብሔር ነገር ተናግሮ ሰዋች እንዲያምኑ የእግዚአብሔር መልዕክተኛ መሆን ነው።

“37 አብ የሚሰጠኝ ሁሉ ወደ እኔ ይመጣል፥(አብ ደግሞ ለልጁ ሁሉን አሳልፎ ስጥቶታል) ወደ እኔም የሚመጣውን ከቶ ወደ ውጭ አላወጣውም፤ 38 ፈቃዴን ለማድረግ አይደለም እንጂ የላከኝን ፈቃድ ለማድረግ ከሰማይ ወርጃለሁና። 39 ከሰጠኝም ሁሉ አንድን ስንኳ እንዳላጠፋ በመጨረሻው ቀን እንዳስነሣው እንጂ የላከኝ የአብ ፈቃድ ይህ ነው። 40 ልጅንም አይቶ በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወትን እንዲያገኝ የአባቴ ፈቃድ ይህ ነው፥ እኔም

በመጨረሻው ቀን አስነሣዋለሁ። ….44 የላከኝ አብ ከሳበው በቀር ወደ እኔ ሊመጣ የሚችል

የለም፥ እኔም በመጨረሻው ቀን አስነሣዋለሁ። 45 ሁሉም ከእግዚአብሔር የተማሩ ይሆናሉ

ተብሎ በነቢያት ተጽፎአል፤ እንግዲህ ከአብ የሰማ የተማረም ሁሉ ወደ እኔ ይመጣል።”

ዮሐ.6፥37-45

ሁሉ ከተማሩ የሚመጡት ሁሉ ናቸው። ነገር ግን እያንዳንዱ በራሱ ተራ ይሆናል። የነቢያትም ትንቢት ተፈጽሟል። የአብ ፈቃድም እንዲህ ሆኗል አብ የወደደውን መቼም አጥቶ አያውቅም። ሰለዚህም፦

“3-4 ሰዎች ሁሉ ሊድኑና እውነቱን ወደ ማወቅ ሊደርሱ በሚወድ በእግዚአብሔር በመድኃኒታችን

ፊት መልካምና ደስ የሚያሰኝ ይህ ነው። 5 አንድ እግዚአብሔር አለና፥ በእግዚአብሔርና በሰውም መካከል ያለው መካከለኛው ደግሞ አንድ አለ፥ እርሱም ሰው የሆነ ክርስቶስ

ኢየሱስ ነው፤ ራሱንም ለሁሉ ቤዛ ሰጠ፥ ይህም በገዛ ዘመኑ ምስክርነቱ ነበረ።”

1.ጢሞ.2፥3-5

ጳውሎስ ይህን ሚስጥር ለጢሞቴዎስ አስረግጦ ሲነግር እንዲ ብሎ ይለዋል፦

“ይህ ቃል የታመነ ሁሉም እንዲቀበሉት የተገባ ነው፤ 10 ይህን ለማግኘት እንደክማለንና፥

ስለዚህም እንሰደባለን፤ ይህም ሰውን ሁሉ ይልቁንም የሚያምኑትን በሚያድን በሕያው

አምላክ ተስፋ ስለምናደርግ ነው። 11-12 ይህን እዘዝና አስተምር።…” 1.ጢሞ.3፥10-12

ጳውሎስ ይህን እውቀት ከራሱ ከኢየሱስ ተምሮታል እንጂ ከሰው አልተቀበለውም። ሰለዚህም አስረግጦ በተለያዩ ሰፍራዎች ይህን የእውነት እውቀት ያስተጋባል፡

“21 ሞት በሰው በኩል ስለ መጣ ትንሣኤ ሙታን በሰው በኩል ሆኖአልና።

22 ሁሉ በአዳም እንደሚሞቱ እንዲሁ ሁሉ በክርስቶስ ደግሞ ሕያዋን ይሆናሉና።

23 ነገር ግን እያንዳንዱ በራሱ ተራ ይሆናል።…..”1.ቆሮ.15፥21-23

ሁለተኛው የዮሐንስ መልእክት 2014

12 www.tlcfan.org

“እግዚአብሔር ሁሉን ይምር ዘንድ ሁሉን በአለመታዘዝ ዘግቶታልና።” ሮሜ.11፥32

ባጠቃላይ ሁሉ ኢየሱስ ጌታ ነው ይላል።

“9-10 መጽሐፉን ትወስድ ዘንድ ማኅተሞቹንም ትፈታ ዘንድ ይገባሃል፥ ታርደሃልና፥

በደምህም ለእግዚአብሔር ከነገድ ሁሉ ከቋንቋም ሁሉ ከወገንም ሁሉ ከሕዝብም ሁሉ

ሰዎችን ዋጅተህ ለአምላካችን መንግሥትና ካህናት ይሆኑ ዘንድ አደረግሃቸው፥ በምድርም ላይ ይነግሣሉ እያሉ አዲስን ቅኔ ይዘምራሉ። 11 አየሁም፥ በዙፋኑም በእንስሶቹም በሽማግሌዎቹም

ዙሪያ የብዙ መላእክትን ድምፅ ሰማሁ፤ ቍጥራቸውም አእላፋት ጊዜ አእላፋትና ሺህ ጊዜ ሺህ ነበር፥ 12 በታላቅም ድምፅ። የታረደው በግ ኃይልና ባለ ጠግነት ጥበብም

ብርታትም ክብርም ምስጋናም በረከትም ሊቀበል ይገባዋል አሉ። 13 በሰማይና በምድርም

ከምድርም በታች በባሕርም ላይ ያለ ፍጥረት ሁሉ በእነርሱም ውስጥ ያለ ሁሉ።

በረከትና ክብር ምስጋናም ኃይልም ከዘላለም እስከ ዘላለም በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው፥ ለበጉም ይሁን ሲሉ ሰማሁ። 14 አራቱም እንስሶች። አሜን አሉ፥

ሽማግሌዎቹም ወድቀው ሰገዱ፣” ራዕይ.5፥9-14

እውነት መኖሪያው የሰው ልጆች ናቸውና ሰው በውስጡ ባለው እውነት ግን እንዴት መኖር እንደሚችል ሊማር ይችላል። ለዚህም ደግሞ እግዚአብሔር ለአማኞች አስተማሪዎችን ሰጥቷል። እውነትን ሰዎች ካልነገርን መስማት አንድ አንዴ ከባድ ነው። ምክንያቱም እንደ ጳውሎስ መለኮታዊ የእግዚአብሔርን ጣልቃ ገብነት የሚጠይቅ ነው።

ስዎች እውነትን ብቻ እንዲናገሩ እግዚአብሔር ይፈልጋል። እግዚአብሔርም እውነትን ከሚናገሩ ጋር ከላይ በተዘረዘሩት የተስፋ ቃሎች መሰረት ይሰራል። እግዚአብሔር በእውነት ደስ ይሰኛል። እውነት ባለበትም ስፋራ በመገኘት መገኘቱን በስራው ያሳያል። ሰለዚህን እውነትን ለመናገርና ለመቀበል የቆረጥን ሰዎች እንሁን። ከውሽት ጋር አንተባበር። ከውሽት ጋር የሚተባበሩ እግዚአብሔርን ሳይሆን ሰይጣንን የሚያስደስቱ የሰይጣን ባሪያዎች ሃሰተኛ ነብያቶች ናቸው። ውሽታቸውን በየመድረኩ በማያውቁ ሰዎች መካከል በሚሰሩት ስራቸው እውነትን ሊያስመስሉ ይጥራሉ። እግዚአብሔር ግን ሁሉን ያያል ውሸትን በእሳቱ ያጠራዋል። እሳቱም የእግዚአብሔር ቃልና ሕግ ነው።

አገልጋዬች መጥተው ታማችሁ ሳለ አልታመማችሁም ሲሏችሁ አትቀበሉ። ኢየሱስም ታምሜ አልጠየቃችሁኝም ብሏልና። ደክማችሁ ሳለ ብርቱ ናችሁ ቢሏችሁ አትስሙ። በመንፈስ የወደቃችሁ ለማሰመሰል ሲጸልዮላችሁ ለሰዎች እይታ በጉባኤ መሃል እንድትወድቁላቸው አገልጋዬች ሲገፉችሁ አትውደቁ። ይህን ሁሉ ስል ግን በእምነት የምታደርጉትን ነገር የምነቅፍ አይደለም። በሕዝቡ መካከል ሰርገው የገቡትን የውሽት አገልጋዬችን ለማሳፈር ይህን አድርጉ እላለሁ።

ሁለተኛው የዮሐንስ መልእክት 2014

13 www.tlcfan.org

ጌታ በመስቀሉ ላይ የሰራውን ስራ እንጂ ሕመም እንዳለብን አለማመን ፈውስን አያመጣም። ድካም አይቶ ሃጢያትን ተናዞ በጽድቅ መኖር እንጂ ብርቱ ነህ ሰለተባልክ ብርቱ አትሆነም። የሰው ልጅ ብርታቱና ድፈረቱ በእግዚአብሔር በጽድቅና በቅድስና በእውነት መኖሩ ነው።

ሁለተኛው የዮሐንስ መልእክት 2014

14 www.tlcfan.org

እኔ ሽማገሌው

ሽማግሌ ማለት የኢየሱስን የእውነት ትምህርት ለማስተማር የበቃ የበሰለ አማኝ ማለት ነው፣ ሽማግሌ ስንል ቶሎ የሚታየን ጸጉሩ ነጭ የሆነ፣ በቤተክርሲያን ወይም በጌታ ብዙ አመታትን ያስቆጠረ ሰው ነው። ይህ ግን ከእውነት የራቀ ነው። እውነት ነው ይህ የሚታየው ሽበት የሰው የመሸምገል ምልክት ነው። ሰለ ሽማግሌ ምንነት ማንነት ምሳሌይዊ መረጃን ይጨምራል። ይህም ነጭ ጸጉር ክብርንና ንጹ አዕምሮን ያመለከታል። ሽማግሌዎች ማለት አዕምሮአቸው ንጹህ የሆነ እውነት የሞላበት ማለት ነው። ኢየሱስ በራዕይ አንድ ላይ ዮሐንስ ሲያየው ጸጉሩ ነጭ ነበር። ሽማግሌዎችም የኢየሱስ አይነት አዕምሮ ያላቸው ናቸው ማለት ነው። ሽማግሌዎች ይህ አዕምሮ የተሰጣቸው ከመጀመሪያ ያለውን እርሱን አልፋ የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስን በማወቅ ነው።

ስለዚህ ሽማግሌ ማለት በእግዚአብሔር ቃልና ሕግ እውቀት የበሰለ፣ የክርስቶስ አዕምሮ ያለው ከመጀመሪያ የነበረውን እግዚአብሔር የሚያውቅ ሰው ሁሉ ነው። ይህ እድሜ ጾታና በጌታ ቤት የዘመን ቆይታን የሚጠቅ አይደለም። ስለ ሽማግሌ ጥልቅ እውቀት የሚሰጠን ኢዮብ ሞራፍ 32 ነው።

“አባቶች (ሽማግሌዎች) ሆይ፥ ከመጀመሪያ የነበረውን አውቃችኋልና እጽፍላችኋለሁ።…” 1.ዮሐ.2፥14

“1. ኢዮብም ራሱን ጻድቅ አድርጎ ነበርና እነዚያ ሦስቱ ሰዎች መመለስን ተዉ። 2. ከራም ወገን የሆነ የቡዛዊው የባርክኤል ልጅ የኤሊሁ ቍጣ ነደደ፤ ከእግዚአብሔር ይልቅ ራሱን ጻድቅ አድርጎ ነበርና ኢዮብን ተቈጣው።( ይህ የስማግሌ ባሕሪ ነው፣ ቁጣ የሚለውን እብራይስጡ

ተገሳፅ ወይም ፍርድ ይለዋል) 3. ደግሞም በኢዮብ (ምድራዊ ፍርድ) ፈረዱበት እንጂ የሚገባ መልስ ስላላገኙ በሦስቱ ባልንጀሮቹ ላይ ተቈጣ። 4. ኤሊሁ ግን ከእርሱ ይልቅ (በምድራዊ እድሜ)

ሽማግሌዎች ነበሩና ከኢዮብ ጋር መናገርን ጠብቆ ነበር። (ይህ ለመናገር ሳይቸኩል የዘገየበት ትግስቱ መንፈሳዊ ሽምግልናውን ያሳያል) 5. ኤሊሁም በነዚህ በሦስቱ ሰዎች አፍ መልስ እንደሌለ ባየ ጊዜ ቍጣው ነደደ።(ምክንያቱም በእድሜ እንጂ በመንፈሳዊ ሽምግልና አልሸመገሉም፣) 6. የቡዛዊውም የባርክኤል ልጅ ኤሊሁ ተናገረ እንዲህም አለ። እኔ በዕድሜ ታናሽ ነኝ፥ እናንተ ግን ሽማግሌዎች ናችሁ (በእድሜ)፤ ስለዚህም ሰጋሁ፤ እውቀቴን እገልጥላችሁ ዘንድ ፈራሁ። (ያስፈራው አለመበሰላቸው በክርስቶስ አዕምሮ አለመኖራቸው ነው፣ ይህን ደግሞ ጌታ እራሱ

በምዕራፍ ኢዮብ 42፦7 ላይ አስረግጦ ያስቀምጠዋል፣ ከጌታ የሆነ ነገር አልተናገሩም፣) 7. እንደዚህም አልሁ። ዓመታት በተናገሩ ነበር፥ የዓመታትም ብዛት ጥበብን ባስተማረች ነበር።

(ማለት ጥበብ የሆነውን የኢየሱስ አዕምሮ የዓመታት ብዛት አያመጣውም ምድራዊ እድሜ መቁጠር በክርስቶስን አዕምሮ እንድንሄድ በፍጹም አያደርገንም) 8. ነገር ግን በሰው ውስጥ መንፈስ አለ፥

(ይህም ከላይ በቁጥር አንድ ላይ እንዳየነው እውነት የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ ነው) ሁሉንም የሚችል የአምላክ እስትንፋስ ማስተዋልን ይሰጣል። (ይህ ለሁሉ ነው፣ ደግሞም መንፈሳዊ

ሽምገልና የሚመጣው ሁሉን ከሚችል አምላክ ብቻ ነው፣) 9. (በምድራዊ ዕድሜ) በዕድሜ ያረጁ ጠቢባን አይደሉም፥ ሽማግሌዎችም (በምድራዊ እድሜ ያረጁ) ፍርድን

አያስተውሉም። 10. ስለዚህም። ስሙኝ፤(ስሙኝ የሚላቸው ኢዮብን ሊያጽናኑ የመጡትን ቴማናዊው ኤልፋዝ፥ ሹሐዊው በልዳዶስ፥ ነዕማታዊው ሶፋርን ነው፣ የሚናገርው ግን በመንፈሳዊ ነገር

የሽመገለው በእድሜ ግን ከሁሉ ታናሽ የሆነው የቡዛዊውም የባርክኤል ልጅ ብላቲናው ኤሊሁ ነው፣)

ሁለተኛው የዮሐንስ መልእክት 2014

15 www.tlcfan.org

እኔ ደግሞ እውቀቴን እገልጥላችኋለሁ አልሁ። (ይህም እውቀት ከውስጡ ካለው መንፈስ ከሆነው እውነት የመነጨ ነው፣) 11. እነሆ፥ ቃላችሁን በትዕግሥት ጠበቅሁ፤ የምትናገሩትን ነገር እስክትመረምሩ

ድረስ፤ ብልሃታችሁን (በምድራዊ እድሜ ብልሃት እንጂ ጥበብ የክርስቶስ አዕምሮ አይገኝም፣) አዳመጥሁ። 12. እንዲሁም ልብ አደረግሁ፤ እነሆም፥ በእናንተ መካከል ኢዮብን ያስረዳ፥

ወይም ለቃሉ የመለሰ የለም። 13. እናንተም። ጥበብን (ኢየሱስ ክርስቶስን) አግኝተናል፤ እግዚአብሔር ነው እንጂ ሰው አያሸንፈውም እንዳትሉ ተጠንቀቁ።

(ሰውም በመንፈሳዊ አዕምሮ ከሸመገለ በክርስቶስ አዕምሮ ሰውን ማሸነፍ ይችላልና ነው፣) 14. እርሱ(ኢዮብ) ግን ቃሉን በእኔ (በኤሊሁ) ላይ አልተናገረም፤(ኢዮብ በበላቴናው ኤሊሁ

ላይ ነቀፋና ተግሳጽ አልሰነዘረም፣ ኢዮብ ሽማግሌ የሆነውን አትገስጸው የሚለውን የጌታ ትዕዛዝ ያከብራል፣ 1.ጢሞ.5፦1 ይህ ደግሞ ኣኢዮብ ራሱ ሶስቱን እንደ ሽማገሌ እንዳልተቀበላቸው

ያሳያል ምክንያቱ ይገስጻቸው ይነቅፋቸው ነበር ጌታም ሳትቀር ይነቅፋቸዋል) እኔም (እንደነ እናንተ ባለ ንግግር ለኢዮብ ) በንግግራችሁ አልመልስለትም። …..

15. እነርሱ ደነገጡ፥ ዳግመኛም አልመለሱም፤ የሚናገሩትንም አጡ። (ምድራዊ እድሜ የሰጣቸው ብልሃት ተገለጠ) 16. እነርሱ አልተናገሩምና፥ ቆመው

ዳግመኛ አልመለሱምና እኔ በትዕግሥት እጠብቃለሁን? (ሁሉ ጸጥ አላዋቂዎችን ጸጥ ካደረገ በኃላ መናገር እንደሚገባው ውስጡን ጠይቆ መናገር ጀመር፣)17. እኔ ደግሞ ፈንታዬን

እመልሳለሁ፥ እውቀቴንም እገልጣለሁ፤ 18. እኔ ቃል ተሞልቻለሁና፥ (ሽማገሌ ቃሉን የተሞላ ኢየሱስን የተሞላ ነው፣) በውስጤም ያለ መንፈስ አስገድዶኛልና። ( ሽማገሌ በውስጡ ባለው የእውነት መንፈስ ምሪት የሚናገር ነው፣) 19. በተሐ ጠጅ እንደ ተሞላና ሊቀደድ እንደ ቀረበ አቁማዳ፥ ሊፈነዳ እንደማይችል እንደ ወይን ጠጅ አቁማዳ፥ እነሆ፥ አንጀቴ ሆነ። (በውስጡ የእውነት መንፈስ ሳይገፋው አይናገርም) 20. ጥቂት እንድተነፍስ እናገራለሁ፤

ከንፈሬን ገልጬ እመልሳለሁ።( የእውነትን እውቀት እገልጣለሁ፣) 21. ለሰው ፊት ግን አላደላም፤ ሰውንም አላቈላምጥም። (ይህ የሽማገሌ በሃሪ ነው፣) 22. በማቈላመጥ

እናገር ዘንድ አላውቅምና፤ ያለዚያስ ፈጣሪዬ ፈጥኖ ከሕይወቴ ይለየኝ ነበር፣ ( የምድር እድሜው የረዘመው እውነትን ለሰው ፊት ሳያደላና በማቆላመጥ

ሳይናገር መሆኑን የእውነት እውቀቱን ገለጠ፣” ኢዮብ.32፥6-22

በቤተ ክርስቲያን ይህ መረዳት ከመጉደሉ የተነሳ በእድሜ የበለጸጉ ነገር ግን መንፈሳዊ ሕጻናትን በመሪነትንና በአስተዳዳሪነት በሽማግሌነት ሲቀመጡ ይታያል። ይህ ደግሞ ጉዳቱ የከፋ ነው። እንደ እነዚህ አይነቶችን ሰዎች እየገስጹና እየተቆጡ ዝም ማሰኘት ማስቀመጥ ይገባል። አላዋቂዎችን ዝም ታሰኙ ዘንድ ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው ተብሎ በእግዚአብሔር ቃል ጽፎል። ለተገለጠ ፍቃድ ደግሞ ፍቃድህ ነው ወይ ብሎ መገለጥ መጠባበቅ አያስፈልግም።

ዮሐንስ ሽማግሌ ነበር። ይህም መንፈሳዊ ብሰለቱን ለማሳየት ነው። ይህም ብለቱ ስዎችን ሁሉ በእውነት እንዲወድድ አስችሎታል። “እኔ ሽማግሌው በእውነት ለምወዳቸው…” ይላል። ሰውን ሁሉ በክርስቶስ የመውደድ ብቃት የሚመጣው እውነትን በማወቅ ወደ መንፈሳዊ ሽምግልና በመምጣት ነው። እውነትን እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስን ያወቀ በክርስቶስ ሁሉን የሰው ልጆች መውደድ ይችላል። ሰው በክርስቶስ ሰውን ሁሉ ያለ ምክንያት መውደድ ጀመረ ማለት ሸምግሏል ማለት ነው።

ሁለተኛው የዮሐንስ መልእክት 2014

16 www.tlcfan.org

እንደ ጌታ አዕምሮ መመለለስ ጀምፘል ማለት ነው። ያመኑትንም ሆነ ያለመኑትን ሁሉ መውደድ አብረው ሕይወትን እንደሚወርሱ ማመን ታላቅ መንፈሳዊ ብስለትን ሽማግሌነትን የሚጠይቅ ነገር ነው። ይህ ፍቅር የታላቅ ሚስጥር ፍጻሜ ነው። የአመታት ብዛት ሚስጥርና ጥበብ የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስን አያሳውቅም። በጌታ ቤት ብዙ አመት ኖርክ ማለት ሸመገልክ ማለት አይደለም።

እውነትን የሚያውቁ ሁሉ የሚታወቁት በፍቅራቸው ነው። እውነትን ማለት ኢየሱስ ክርስቶስን የሚያውቁ ሁሉ ሰውን ሁሉና እውነትን ይወዳሉ። ፍቅራቸው የጌታ አይነት ፍቅር ነውና ልዩነት አያደርግም። ይህ ፍቅር በሁኔታ ላይ የተመሰረተ ሳይሆን በኢየሱስ ሰራ ላይ የእውነት መንፈስ መረዳት ላይ የተመሰረተ ነው። ጌታ ለሰው ልጆች ሁሉ ያለው ፍቅሩ ያሳየው ገና ሙታን ሳለን በሃጢያታችን የማንታዘ ሆነን ሳለ ነው። ሁሉን ከሃጢያት የሚያድነው ኢየሱስ ከመጣ በኃላማ እንዴት አብልጦ ሁሉን አይወድም። ያኔ ሃጢያተኞች እያለ ከወደደን ኢየሱስ በመስቀሉ ሃጢያታችንን ካስወገደልን አሁንማ እጅግ አብልጦ ይወደናል።

ሁሉን በጌታ አይነት ፍቅር እንደ ዮሐንስ በእውነት መውደድ እንድንችል ወደ መፈሳዊ ሽምግልና ሁላችንን ጌታ እንዲያሳድገን ፀሎቴ ነው። ዮሐንስ እውነትን የሚያውቁ ሁሉ ሰውን ሁሉ በእውነት መውደድ እንደሚችሉ አሰቀምጧል። “በእውነት ለምወዳቸውና እኔ ብቻ ሳልሆን እውነትን የሚያውቁ ሁሉ ደግሞ ለሚወዱአቸው።” 2.ዮሐ.1

ሁለተኛው የዮሐንስ መልእክት 2014

17 www.tlcfan.org

እውነት በማወቅ መውደድ

ዮሐንስ እኔ ሽማግሌው በእውነት ለምወዳቸውና እኔ ብቻ ሳልሆን እውነትን የሚያውቁ ሁሉ ደግሞ ለሚወዱአቸው ይላል። እውነትን በማወቅ የሚሆን ፍቅር ከሁሉ መውደድ የሚበልጥ ነው። መረዳት የሌለው ፍቅር በብዛት በሁኔታዎች ላይ የተመሰረተ ነው።

“በእውነት ለምወዳቸውና እኔ ብቻ ሳልሆን እውነትን የሚያውቁ ሁሉ ደግሞ ለሚወዱአቸው።” 2.ዮሐ.1

ሽማግሌዎች በመንፈስ የበሰሉ ሰዎች አንዱ መለያቸውም እውነትን በማወቅ በሆነ ፍቅር እግዚአብሔርን፣ ወንድሞችንና ጠላቶቻቸውን ማለት የሚቃወሟቸውን ሁሉ መውደዳቸው ነው። መውደድ ወይም ፍቅር ከእግዚአብሔር ዘንድ የተሰጠ ብቸኛ ሁሉን ትዕዛዛትንና ነብያትን የተሸከመ ትእዛዝ ነው። ሶስት የተለያዩ ልንወድ የሚገባ ነገሮች አሉ። እነርሱም፦

1. እግዚአብሔር መውደድ፦

“እግዚአብሔርንም ለሚወዱት እንደ አሳቡም ለተጠሩት ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን።” ሮሜ.8፥28

ጥቅሱ እንደሚናገረው እግዚአብሔርን ለሚወድ ነገር ሁሉ ለበጎ ይደረግለታል። ይህ ማለት እግዚአብሔርን የሚወዱ ሁሉ ነገር በጎ ነው አይልም። ነገር ግን በጎ ባይሆን እንኳ በእግዚአብሔር ለበጎ ይድረጋል ማለቱ ነው። እግዚአብሔር ለሚወዱ ስዎች ነገር ሁሉ ያማረና የተስተካከል አይደለም። ነገር ግን በእግዚአብሔር የተስተካከል ያማረ ይሆናል።

“ ብትወዱኝ ትእዛዜን ጠብቁ።…” ዮሐ.14፥15

መውደድ በአንደበት ብቻ የሚገለጥ ነገር አይደለም። እውነት በማወቅ መውደድ ስንል እውነት የሆነውን እየሱስን የእግዚአብሔርን ቃልና ሕግ አውቀን በመታዘዝ መኖር ነው። ዛሬ በበዙ የአምልኮ ስፍራዎች የምንመለከተው ግን ይህን በእውነት የሆነውን መውደድ አይደለም። እግዚአብሔርን እንደሚወዱ በአፋቸው ይናገራሉ በስራቸው ግን ይክዱታል። ከእውነት የመነጨ ፍቅር ግን ስራ አለው። የሚገለጥ የሚጨበጥ ተግባር አለው።

ኢየሱስም ለዚህ ነው ደቀመዛሙርቱን ብትወዱኝስ ትእዛዜን ጠብቁ አለቸው። ይህ መውደድ ተግባር እንደሚጠይቅ ያሳያል። ይህም ተግባር ትእዛዙን መፈጸም ነው። የኢየሱስ ፍቅር ለእኛ በስራ የተገለጠ እንጂ በአንደበት በአፍ ብቻ አይደለም። እኛም እርሱን መውደዳችንን የምንገልጠው እኛ ከእርሱ የተወለድን ወንድማማቾች እርስ በእርሳችን ብንዋደድ ሕጉንም ብንጠብቅ ብንታዘዝ ነው።

ሁለተኛው የዮሐንስ መልእክት 2014

18 www.tlcfan.org

2. ወንድምን መውደድ፦

ወንድሞችንና እህቶችን መውደድ ጌታን እንደምትወድ የሚታወቅበት መንገድ አንዱ ነው። ጌታን የሚወድ ከእርሱ የተወለደውን ሁሉ ይወዳል። ወንድሙን የሚወድ በሕግ አታደርግ የተባለውን ሁሉ በወንድሙ ላይ አያደርግም። እንድንዋድድ ከጌታ የመታዘዝ እዳ አለብን። ጌታን እወዳለሁ የሚል በዚህ ይገለጣል።

“9 አብ እንደ ወደደኝ እኔ ደግሞ ወደድኋችሁ፤ በፍቅሬ ኑሩ። 10 እኔ የአባቴን ትእዛዝ እንደ ጠበቅሁ በፍቅሩም እንደምኖር፥ ትእዛዜን ብትጠብቁ በፍቅሬ ትኖራላችሁ። 11 ደስታዬም

በእናንተ እንዲሆን ደስታችሁም እንዲፈጸም ይህን ነግሬአችኋለሁ። 12 እኔ እንደ ወደድኋችሁ እርስ በርሳችሁ ትዋደዱ ዘንድ ትእዛዜ ይህች ናት። 13 ነፍሱን ስለ ወዳጆቹ ከመስጠት ይልቅ

ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር ለማንም የለውም። 14 እኔ ያዘዝኋችሁን ሁሉ ብታደርጉ እናንተ ወዳጆቼ ናችሁ።”

ዮሐ.15፥9-14

“13 ወንድሞች ሆይ፥ እናንተ ለአርነት ተጠርታችኋልና፤ (ይህም አርነት ከሰዋዊ ሕግ እንጂ ከጌታ ሕግ አይደልም) ብቻ አርነታችሁ ለሥጋ

ምክንያትን አይስጥ፥ ነገር ግን በፍቅር እርስ በርሳችሁ እንደ ባሪያዎች ሁኑ። 14 ሕግ ሁሉ በአንድ ቃል ይፈጸማልና፥

እርሱም። ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ የሚል ነው።” ገላ.5፥13-14

ይህ ጥቅስ ትልቅ ሚስጥርን ይገልጻል። ሰው ባልንጀራውን መውደድ ያለበት ራሱን በሚወድበት መጠን ነው። ሰው ራሱን የማይወድ ከሆነ ሰውን ይወዳል ብሎ መገመት ፈጽሞ ስህተት ነው። ምክንያቱም ቃሉ እንደ ራስህ ወደድ ብሎ ያዛልና ነው። አንድ ሰው ራሱን ሊወድ ይገባል። ይህም ራስ መውደድ እውነትን ከማወቅ የሚመጣ መውደድ እንጂ ራስን በራስ ወዳድነት መውደድ አይደልም። ሰው ራሱን በራስ ወዳድነት ሲወድድና ሰው ራሱን በእውነት እውቀት ሲወድ የተለያየ ነገር ነው።

ከራስ ወዳድነት የሚወጣ ፍቅር እንካ በእንካ የሆነ የጅንጀሮ አይነት ፍቅር ነው። አንተ ጀርባዬን ልቀም እኔም ያንተን ጀርባ ለቅማለሁ አይነት ነው። ራሱን በራስ ወዳድነት የሚወድ ሌላውን ሰው ለመውደድ የተለያየ ምክንያትን ይፈልጋል። እቤቱ ስትመጣ እቤትህ ይመጣል። የሆነ ነገር ሰታደርግለት ይወድሃል ሳታደግለት ሰትቀር ደግሞ ያኮርፍሃል። ሰትሰጠው ይሰጥሃል…ወዘተ። ይህ ከራስ ወዳድነት የሚገለጥ በሃሪ ነው።

በራስ ወዳድነት ራሱን የሚወድ ወንድሙን ጌታ እንደሚለው አይነት መውደድ ፈጽሞ ሊወድ አይችልም። ስለዚህም እንዲህ አይነቱ ሰው የጌታን ትእዛዝ አይጠብቅም። ጌታንም አይወድም። ራስህን ጌታ እንደሚወድህ ለመውደድ ፈጽሞ አትፍራ። ምክንያቱም ሌሎችን የመውደድ ጉልበት ያለው ራስንህ ጌታ እንደሚወድህ በመውደድ ውስጥ ነው።

ሁለተኛው የዮሐንስ መልእክት 2014

19 www.tlcfan.org

“18 ፍጹም ፍቅር ፍርሃትን አውጥቶ ይጥላል እንጂ በፍቅር ፍርሃት የለም፥ ፍርሃት ቅጣት አለውና፤ የሚፈራም ሰው ፍቅሩ ፍጹም አይደለም።19 እርሱ አስቀድሞ ወዶናልና እኛ

እንወደዋለን።20 ማንም። እግዚአብሔርን እወዳለሁ እያለ ወንድሙን ቢጠላ ሐሰተኛ ነው፤ ያየውን ወንድሙን የማይወድ ያላየውን እግዚአብሔርን ሊወደው እንዴት ይችላል?

21 እግዚአብሔርንም የሚወድ ወንድሙን ደግሞ እንዲወድ ይህች ትእዛዝ ከእርሱ አለችን።” 1.ዮሐ.4፥18-21

“1 ክርስቶስ ነው ብሎ በኢየሱስ የሚያምን ሁሉ ከእግዚአብሔር ተወልዶአል፥ ወላጁንም የሚወድ ሁሉ ከእርሱ የተወለደውን ደግሞ ይወዳል።2 እግዚአብሔርን ስንወድ

ትእዛዛቱንም ስናደርግ የእግዚአብሔርን ልጆች እንድንወድ በዚህ እናውቃለን።” 1.ዮሐ.5፥1-2

ሰው ሰውን መውደድ የሚችለው መጀመሪያ በእግዚአብሔር እውነት ራሱን የወደደ እንደ ሆነ ነው። ለዚህም ነው ዮሐንስ “…በእውነት ለምወዳቸውና እኔ ብቻ ሳልሆን እውነትን የሚያውቁ ሁሉ ደግሞ ለሚወዱአቸው…” ብሎ ያስቀመጠልን። ይህ ሁሉ የሚለው እኔን፣ አንተንና አንቺን ይጨምራል። ስለዚህ እውነትን ካወቅን ራሳችንን ጌታ በሚወደንን መውደድ እንወዳለን። ይህ ደግሞ ሌሎችን ለመውደድ ትልቅ ጉልበታችን ይሆናል። ራሱን ጌታ እንደሚወደው ያህል ያልወደደ ሰው ሌላውንም ሊወድ ፍጽሞ አይችልም። ለሌሎች ፍቅር መስጠት ካቃተህ ራስህን በእውነት እንደማትወድ ልታውቅና ንስሃ ልትገባ ይገባሃል። ይህም ጌታ እንዴት እንደሚወድህ ማወቅና አዕምሮህን በዚህ የእውነት እውቀት በመቃኘት ራስህ መውደድ መጀመር ነው። ይህ ደግሞ ሌሎችን መውደድን በአንተ ውስጥ መውለድ ይጀምራል። ጌታ ሁሉን ወዳል።

“19 እነርሱም ደግሞ በእውነት የተቀደሱ እንዲሆኑ እኔ ራሴን ስለ እነርሱ እቀድሳለሁ። 20-21 ሁሉም አንድ ይሆኑ ዘንድ፥ ከቃላቸው የተነሣ በእኔ ስለሚያምኑ ደግሞ እንጂ ስለ እነዚህ ብቻ

አልለምንም፤ አንተ እንደ ላክኸኝ ዓለም ያምን ዘንድ፥ አንተ፥ አባት ሆይ፥ በእኔ እንዳለህ እኔም በአንተ፥ እነርሱ ደግሞ በእኛ አንድ ይሆኑ ዘንድ እለምናለሁ። 22-23 እኛም አንድ እንደ

ሆንን አንድ ይሆኑ ዘንድ፤ እኔም በእነርሱ አንተም በእኔ ስትሆን፥ በአንድ ፍጹማን እንዲሆኑ፥ የሰጠኸኝን ክብር እኔ ሰጥቻቸዋለሁ፤ እንዲሁም ዓለም አንተ

እንደ ላክኸኝ በወደድኸኝም መጠን እነርሱን እንደ ወደድሃቸው ያውቃል።” ዮሐ.17፥19-23

3. ጠላትን መውደድ፦

ጌታ እንድንወድ የሚፈልገው ወድሞቻችንን ብቻ አይደለም። ጠላቶቻችንን ጭምር እንድንወድ ከጌታ ትእዛዝ አለን። ጠላታችን ስንል የማይቀበሉን፣ የሚቃወሙን፣ በከንቱ ስማችንን የሚያጠፉ፣ በከንቱ የሚተቹን፣ የሚሰድቡን፣ የሚያሰቃዩን፣ በከንቱ የሚያለፉን…ወዘተ ናቸው። እነርሱን መውደድ ይጠበቅብናል። ምክንያቱም የበሰሉ ልጆች የምንባለው ጠላትን የሚወድ ማንነት ሲኖረን ነው።

ሁለተኛው የዮሐንስ መልእክት 2014

20 www.tlcfan.org

በልጅና በበሰለ ልጅ መካከል ትልቅ ልዩነት አለ። የተመረጠች ሴት ልጆችዋ የበሰሉ ድል ነሺዎች ናቸው። ይህ መብሰል ግን የሚመጣበትን ቁልፍ ኢየሱስ ሲያስቀምጥ ጠላታችሁን ብትወዱ የበሰሉ ልጆች ትሆናላችሁ ይለናል። ወንድሙን የሚወድ የወለደውን ጌታውንም ይወዳል። ነገር ግን ጠላቱን የማይወድ በሰማይ ላለ አባቱ የበሰለ ልጅ ሊሆን አይችልም። ወንድሙን በመውደዱ ጌታን የሚወድ ሕፃን ልጅ ሊሆን ይችላል። ሕፃን ስንል ያልበሰለ ገና ወተት የሚጋት የጠነከረ የእግዚአብሔር እውነት መመገብ የማይችል ልጅ ማለት ነው።

“43 ባልንጀራህን ውደድ ጠላትህንም ጥላ እንደ ተባለ ሰምታችኋል። 44-45 እኔ ግን እላችኋለሁ፥

በሰማያት ላለ አባታችሁ (የበሰሉ. υιος. uihos) ልጆች ትሆኑ ዘንድ ጠላቶቻችሁን ውደዱ፥

የሚረግሙአችሁንም መርቁ፥ ለሚጠሉአችሁም መልካም አድርጉ፥ ስለሚያሳድዱአችሁም ጸልዩ፤ እርሱ በክፎዎችና በበጎዎች ላይ ፀሐይን ያወጣልና፥ በጻድቃንና በኃጢአተኞችም ላይ ዝናቡን

ያዘንባልና። 46 የሚወዱአችሁን ብትወዱ ምን ዋጋ አላችሁ? ቀራጮችስ ያንኑ ያደርጉ የለምን? 47 ወንድሞቻችሁንም ብቻ እጅ ብትነሡ ምን ብልጫ ታደርጋላችሁ?

አሕዛብስ ያንኑ ያደርጉ የለምን?” ማቴ.5፥43-47

ሰለዚህ ጠላታችንን እንወደድ። እርሱ ለሁሉ እኩል ጸሃይንና ዝናብን እንደሚያዘንብ እኛም ለወዳጆቻችን የምንሰጠውን ፍቅር ለማይወዱንም በእኩል መልኩ ልንወድ ይጠበቅብናል። የበሰለ ልጅ ለመሆን ይህን ማድረግ ይጠበቅብናል። ይህ ብስለት ከጌታ የምንቀበለው ዋጋችንና ብልጫችን ነው።

ኢየሱስ ጠላትን መውደዱ በምስቀል ላይ ሆኖ እንኳ ስለእነርሱ በመለመን የተገለጠ ነው። የተፉበት፣ የመቱት፣ ያላገጡበት፣ ያለ ምክንያት የከሰሱትን ….. ሁሉ የሚሰሩትን አያውቁምና ይቅር በላቸው ሲል ወደ አባቱ በመጸለይ መውደዱንና ፍቅሩን ገለጠ። ፍቅር የሚገለጥበት አንዱ መንገድ ምሕረት ነው። ከኢየሱስ በኃላ ደግሞ የኢየሱስን ፈለግ በመከተል እስቲፋኖስ ይህንኑ ጸሎት በድንጋይ ለሚወግሩት ስጋዊ ሕይወቱን ለሚገድሉት ጠላቶቹ አደረገ። እኛም የኢየሱስን ፈለግ እንደ እስቲፋኖስ በመከተል ጠላታችንን በመውደድ ብሎም ሰለ እነርሱ በመፀለይና ምሕረት በማድረግ ፍቅራችንን እንድንገልጥ ይገባናል።

ሁለተኛው የዮሐንስ መልእክት 2014

21 www.tlcfan.org

የተመረጠች እመቤትና ልጆችዋ

የተመረጠች እመቤት ሲል ብዙ የተመረጡ እመቤቶች ወደ ልባችን ይመጣሉ። እናም የተመረጠችው እመቤት ማን እንደ ሆነች ለመለየት ግራ እንጋባለን። ምክንያቱ ማርያም እመቤታችን በመባል ስትጠራ ከልጅነታችን ጀምረን አድገንበታል። ነገር ግን የእግዚአብሔር ቃል “የተመረጠችው የእኅትሽ ልጆች ሰላምታ ያቀርቡልሻል” ብሎ በምጨረሻው ቁጥር ላይ ያስቀምጣል። ይህ ቃል ደግሞ የተመረጠችው እሷ ብቻ ሳትሆን እንደ እሷ ከአንድ አባትና እናት የተወለደችው እህቷም ጭምር ናት። ነገር ግን መፅሐፍ ቅዱስ የተመረጠች እመቤትና ልጆችዋ ማን እንደሆኑ በብሉይም ሆነ በአዲስ ኪዳን በግልጽ አስቀምጧል።

ለምሳሌ በሉይ ኪዳን ያሉ የተመረጡ እመቤቶችን እንመልከት ሄዋን ከብዙ አጥንቶች መካከል የተመረጠች አጥንት ነች። ስለዚህ የተመረጠች እመቤት ነች። ሳራ ከሌሎቹ ሚስቶቹ ሁሉ የተመረጠች እመቤት ነች። ርብቃ በታዛዥነቷ የተመረጠች እመቤት ነች። ራሄል ከልያና ከባሪያዎቹ ሁሉ የተመረጠች እመቤት ነች። ትዕማር በጥበብዋና አስተውላ በማድረጓ የተመረጠች እመቤት ነች። ሩት፣ ሃና፣ አስቴር…ወዘት። ሁሉን ልዘረዝር አልችልም። ነገር ግን ወደ አዲስ ኪዳን የተመረጡ እመቤቶች ስንመጣ በአንደኛ ደረጃ የምናገኛት ማርያም ነች። የኢየሱስ እናት ከሴቶች ሁሉ የተመረች እመቤት ናት። ከአስሩ ቆነጃጅት ጋር የሌለች ከሙሽራው ጋር አብራ የመጣችዋ ሙሽሪት ድል ነሺዋ ቤተክርስቲያን የተመረጠች እመቤት ናት። የበጉ ሚስት ከሰባቱ ቤተ ክርስቲያን ድል የነሳች የተመረጠች እመቤት ናት። እርሷ አብራው መጣች አስሩ ግን ርቀው ጠበቁ ስለዚህም ከአስሩ ይልቅ እርሷ ለእርሱ የተሻላለች የተመረጠች ነች።

ብዙ ልንል እንችላለን ሁሉን ግን ተመራጭ ያደረጋቸው የየራሳቸው የሆነ ባሕሪ አላቸው። ጌታ የመረጣት እመቤት ግን አንድ ናት። እርሷም ራሰዋን ያዘጋጀችው እመቤት ነች። ይችም ድል ነሺዋ የመጨረሻዋ ዘመን ቤተክርሲያን ናት።

“7 የበጉ ሰርግ ስለ ደረሰ ሚስቱም ራስዋን ስላዘጋጀች ደስ ይበለን ሐሤትም እናድርግ ክብርንም ለእርሱ እናቅርብ። 8 ያጌጠና የተጣራ ቀጭን የተልባ እግር ልብስ

እንድትጐናጸፍ ተሰጥቶአታል። ቀጭኑ የተልባ እግር የቅዱሳን ጽድቅ ሥራ ነውና።” ራዕይ.19፥7-8

ሁሉ እመቤቶች በዚህች እመቤት ይዋጣሉ። ማለት ሁሉ እመቤቶች ላይ የተገለጠው የተለያየ ባሕሪ በዚች እመቤት ላይ በሙላት ተንጸባርቆ ይታያል። አንተ ወይም አንቺ የተመረጥሽ እመቤት ልትሆኑ ትችላላችሁ። ነገር ግን ራስዋን ያዘጋጀችው እመቤት ላይ የተገለጠው ማንነት ሊገለጥብን ይገባል። ይች የተመረጠች እመቤት ልጅ ብቻ ሳይሆን ልጆች አሏት። ይህ ደግሞ የሚያሳየው በአምሳልዋ የመውለድ የማፍራት ብቃትዋን ነው። ደግሞም ማርያም ብቻ እንዳልሆነች የሚያሳይ ነው። ትልቁ የማፍራትዋ ቁልፍ ግን ይች የተመረጠች እመቤት ባል ያላት መሆንዋ ነው። ባልዋ በጉ የናዝሬቱ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ባልዋ በእርሱዋ እርሱዋም በባልዋ የምትኖር ነች። ይህ ትዳር ከሰጋዊ ትዳር ጋር ምንም መገናኘት የለውም። ይህ አይነቱ ማፍራትና መብዛት ነው። በዘፍጥረት. 1፥27-28 የምናገኘው ነው።

ሁለተኛው የዮሐንስ መልእክት 2014

22 www.tlcfan.org

“26፤ እግዚአብሔርም አለ። ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር፤ የባሕር ዓሦችንና የሰማይ ወፎችን፥ እንስሳትንና ምድርን ሁሉ፥ በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ይግዙ።

27፤ እግዚአብሔርም ሰውን በመልኩ ፈጠረ፤ በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው፤ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው።28፤ እግዚአብሔርም ባረካቸው፥ እንዲህም አላቸው። ብዙ፥

ተባዙ፥ ምድርንም ሙሉአት፥ ግዙአትም፤ የባሕርን ዓሦችና የሰማይን ወፎች በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ግዙአቸው።”

ዘፍ.1፥26-28

ይህ መብዛትና ማፍራት በስጋ አልነበረም። ምክንያቱም አዳም ሚስቱ ገና ከእርሱ አልወጣችም ነበርና ነው። ይህን ሚስጥር በዚህ መጽሐፍ ባለስቀምጠውም ይህ ማፍራት ግን በውስጣችን ካለው እውነት ጋር በመጋባት የሚወለድ ዘር የሚበዛ ፍሬ ነው። ዘፍጥረት 1፥27 ላይ ያለው ሰው ወንድም ሴትም ነበር። አሁንም አንቺም ሆንክ አንተ ወንድም ሴትም ናችሁ። የበለጠ ሰለዚህ ሚስጥር ለመረዳት (ዘፍጥረት በሸመገለው አይን) የሚለውን ቁጥር አንድ መጽሐፌን ያንብቡ።

ይህች እመቤት በጌታ የተመረጠች ነች። ለምን እንደ መረጣት ለዋወቅ ከፈለግን ከላይ የዘረዘርኳቸውን እመቤቶች አመራረጥ በመመልከት መገንዘብ እንዝላለን። ልጆችዋንም ለማወቅ እመቤቶቹን መመልከት ብቻ በቂ ነው። ማርያም ጸጋን ስላገኘች በዘመንዋ የተመረጠች እመቤት ነች።

ሁሉ ሰው ተጠርቷል ሁሉ ግን አልተመረጠም። ይህ ማለት ያልተመረጡት ሕይወትን ያጣሉ ማለት አይደለም። ነገር ግን በመንፈሳዊ ትዳር ውስጥ የሚገኘው በረከት ይጎድላሉ ወይም ከመንግስቱ ይጎድላሉ። የመጀመሪያውን ትንሳኤና ርስታችውን ያጣሉ። እንደ አስቴር የንጉሱ አልክሊል አይደረግላቸውም። ነገር ግብ በንጉሱ ቤት ለዘላለም ይኖራሉ።

እነዚህ ያልተመረጡት በምደረ በዳ እንደ ቀሩት እንደ ሙሴና የእስራኤል ሕዝብ ናቸው። በእረፍት ወደ ሚገኘው ደስታ በረከት አልገቡም። ነገር ግን በፋሲካው በግ በጌታ ኢየሱስ ግን ሁሉ እስራኤል የገባውም ሆነ ያልገባው መልካሙም ሆነ ክፉው ሳያደርግ በደሙ ድኗል። ደሕንነትን ባለመመረጥ ምክንያት አይጠፋም። አለመመረጥ ግን ብዙ በረከትንና ክብርን ያጎድላል።

ከላይ ከተዘረዘሩት እመቤቶች ጋር የነበሩ ያልተመረጡ እመቤቶችን ታሪክ በማንበብ ያለተመረጡበትን ምክንያት እናግኝ። ይህ በማድረግ የእኛም መመረጥ እንዲፀና መልካም ትምህርትንና ምክርን እንቀበል።

ሁለተኛው የዮሐንስ መልእክት 2014

23 www.tlcfan.org

ጸጋ፣ ምሕረት፣ ሰላምና እውነት በፍቅር

“3 ከእግዚአብሔር አብና ከአብ ልጅ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ምሕረት ሰላምም በእውነትና በፍቅር ከእኛ ጋር ይሆናሉ።” 2.ዮሐ

ከላይ ያየናቸው ጸጋ ምህረትና ፍቅር ሁሉ በአንዱ እውነት ውስጥ የሚጠቃለሉ ናቸው። እውነት በውስጣችን እንዳለ። ለዘላለምም እንደሚኖር። እውነትንም የሚያውቅ ሁሉ በእውነት ሁሉን መውደደ እንደሚችሉ፣ ከገባን ከእግዚአብሔር አብና ከአብ ልጅ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ምሕረት ሰላምም በእውነትና በፍቅር ከእኛ ጋር ይሆናሉ። ይህም ከኛ ጋር የመሆኑ ሚስጥር ለሰዎች ሁሉ ለመስጠት እንጂ ለእኛ ብቻ እንድንጠቀመው አይደለም።

ጸጋና ምሕረት ሰላምም በእውነትና በፍቅር ከእኛ ጋር ካሉ ለሰው ሁሉ የምናካፍለው ጸጋ የምንምርበት ምሕረት ፣ የምናረጋጋበት ሰላም የምንወድበት ፍጹም ፍቅር አለን ማለት ነው። ይህ ደግሞ ከእግዚአብሔር አብና ከአብ ልጅ ከኢየሱስ ክርስቶስ የመጣ በመሆኑ ፍጹምና ልዩ ይሆነ ነው።

“4 ትእዛዝን ከአብ እንደ ተቀበልን ከልጆችሽ በእውነት የሚሄዱ አንዳንዶችን ስለ አገኘኋቸው እጅግ ደስ ብሎኛል።’’ 2.ዮሐ

የአብ ትእዛዝ፦

የአብ ትእዛዝ ፍቅር ነው። ፍቅር ደግሞ የሕግ ሁሉ ፍፃሜ ነው። አብ ልጆቹ ሁሉ ከፍቅር ሌላ ምንም አይነት ሕግ እንድንሸከም አይፈቅድም። ከፍቅር ውጪ ሌላ አይነት ሕግ ሊጭኑ የሚወዱ ቢኖሩ እግዚአብሔርን ይፈታተናሉ። ጸጋ፣ ምሕረት፣ ሰላምና እውነት በፍቅር ነው። ያለ ፍቅር የሚሆን ምንም ነገር የለም። ፍቅር ራሱ እግዚአብሔር ነው። ከፍቅር ውጭ ምንም እዳና ቀንበር የለብንም።

“5 ከፈሪሳውያን ወገን ግን ያመኑት አንዳንዶቹ ተነሥተው። ትገርዙአቸው ዘንድና የሙሴን ሕግ እንዲጠብቁ ታዙአቸው ዘንድ ይገባል አሉ። 6 ሐዋርያትና ሽማግሌዎችም ስለዚህ ነገር ለመማከር

ተሰበሰቡ። 7 ከብዙ ክርክርም በኋላ ጴጥሮስ ተነሥቶ እንዲህ አላቸው ወንድሞች ሆይ፥ አሕዛብ ከአፌ የወንጌልን ቃል ሰምተው ያምኑ ዘንድ እግዚአብሔር በመጀመሪያው ዘመን ከእናንተ እኔን እንደ መረጠኝ እናንተ ታውቃላችሁ። 8 ልብንም የሚያውቅ አምላክ ለእኛ ደግሞ እንደ ሰጠን መንፈስ

ቅዱስን በመስጠት መሰከረላቸው፤ 9 ልባቸውንም በእምነት ሲያነጻ በእኛና በእነርሱ መካከል አንዳች አልለየም። 10 እንግዲህ አባቶቻችንና እኛ ልንሸከመው ያልቻልነውን ቀንበር በደቀ መዛሙርት ጫንቃ

ላይ በመጫን እግዚአብሔርን አሁን ስለ ምን ትፈታተናላችሁ? 11 ነገር ግን በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ እንደ እነርሱ ደግሞ እንድን ዘንድ እናምናለን።”

ሐዋ.ሥ.15፥5-11

ሁለተኛው የዮሐንስ መልእክት 2014

24 www.tlcfan.org

አብ ለኛ የሰጠን ትእዛዝ አንዲት ናት። ነገር ግን ሁሉን ጠቅልላ የምትይዝ የበለጠገች፣ የከበረች ትእዛዝ ነች። እርስዋም ትዕዛዝ ፍቅር ነች። አብ በሰዋዊ ሕግና ስርዓት ወግ እንድንመለለስ ፈጽሞ አይወድም። በወግና በሰዋዊ ሕግ እንድንሄድ የሚያደርጉንን ሁሉ ፈጽሞ ይገስፃል ደግሞም ወደ ፍርድም ያመጣቸዋል። አባታችን ሲናገረን እንዲህ አለ፦

“8 እርስ በርሳችሁ ከመዋደድ በቀር ለማንም ዕዳ አይኑርባችሁ፥ ሌላውን የሚወድ ሕግን ፈጽሞታልና። 9 አታመንዝር፥ አትግደል፥ አትስረቅ፥ በውሸት አትመስክር፥ አትመኝ የሚለው

ከሌላይቱ ትእዛዝ ሁሉ ጋር በዚህ። ባልንጀራህን እንደ ነፍስህ ውደድ በሚለው ቃል ተጠቅልሎአል። 10 ፍቅር ለባልንጀራው ክፉ አያደርግም፤ ስለዚህ ፍቅር የሕግ ፍጻሜ ነው፣”

ሮሜ.13፥8-10

“13 ወንድሞች ሆይ፥ እናንተ ለአርነት ተጠርታችኋልና፤ ብቻ አርነታችሁ ለሥጋ ምክንያትን አይስጥ፥ ነገር ግን በፍቅር እርስ በርሳችሁ እንደ ባሪያዎች ሁኑ። 14 ሕግ ሁሉ በአንድ ቃል ይፈጸማልና፥

እርሱም። ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ የሚል ነው። 15 ነገር ግን እርስ በርሳችሁ ብትነካከሱ ብትበላሉ እርስ በርሳችሁ እንዳትጠፋፉ ተጠንቀቁ፣”

ገላ.5፥13-15

ሰለ እግዚአብሔር ሕግ የበለጠ እውቀትን በገብየት ከፈለጉ (ሕይወት ያላቸው ቃሎች የሚለውን መጽሐፊን ያንብቡት)

ሁለተኛው የዮሐንስ መልእክት 2014

25 www.tlcfan.org

በእውነት የሚሄዱ ልጆች

“6 እንግዲህ ጌታን ክርስቶስ ኢየሱስን እንደ ተቀበላችሁት በእርሱ ተመላለሱ። 7 ሥር ሰዳችሁ በእርሱ ታነጹ፥ እንደ ተማራችሁም በሃይማኖት (በእምነት) ጽኑ፥

ምስጋናም ይብዛላችሁ። 8 እንደ ክርስቶስ ትምህርት ሳይሆን፥ እንደ ሰው ወግና እንደ ዓለማዊ እንደ መጀመሪያ ትምህርት ባለ በፍልስፍና በከንቱም

መታለል ማንም እንዳይማርካችሁ ተጠበቁ።” ቆላ.2፥6-8

እውነት የሆነው ኢየሱስ በውስጣችን እንዳለ መረዳት አንድ ነገር ሲሆን በውስጣችን ባለው እውነት ደግሞ መሄድ መመላለስ ሌላ ነው። እውነት በአፋቸው የሚናገሩ በእውነት የማይመላለሱ የማይኖሩ ብዙዎች ናቸው። በእውነት መመላለስና በእውነትም ስር ሰዶ ወደ መንፈሳዊ ብስለት መታነጽ፣ መገንባት አስፈላጊ ነው።

እውነት እንዳሰተማረንም በሰማነው የእውነት እውቀት መጽናት ይጠበቅብናል። ያልጸና መራመድ መሄድ አይችልም። ይህ ምስጋናን ከጌታ ሲያበዛልን የክርሰቶስ ትምህርት ካልሆኑ ወግና አለማዊ ፍልስፍና እንዳንከተል የምንጠበቅበትን ማንነት በላያችን ይፈጥራል። ፈሪሳዊና ሰዱቃዊያን ችግራችው ይህ ነው። እውነት ቢያውቁም በእውነት አይሄዱም። በእውነት ላይም ሰር አይሰዱም።

“1 በዚያን ጊዜ ኢየሱስ ለሕዝቡና ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ ብሎ ነገራቸው። 2 ጻፎችና ፈሪሳውያን በሙሴ ወንበር ተቀምጠዋል። 3 ስለዚህ ያዘዙአችሁን ሁሉ አድርጉ ጠብቁትም፥ ነገር ግን እየተናገሩ አያደርጉትምና እንደ ሥራቸው አታድርጉ። 4 ከባድና አስቸጋሪ ሸክም

ተብትበው በሰው ትከሻ ይጭናሉ፥ እነርሱ ግን በጣታቸው ስንኳ ሊነኩት አይወዱም። 5 ለሰውም እንዲታዩ ሥራቸውን ሁሉ ያደርጋሉ፤ ስለዚህ አሽንክታባቸውን ያሰፋሉ ዘርፉንም

ያስረዝማሉ፥ 6 በምሳም የከበሬታ ስፍራ፥ በምኵራብም የከበሬታ ወንበር፥ 7 በገበያም ሰላምታና። መምህር ሆይ መምህር ሆይ ተብለው እንዲጠሩ ይወዳሉ። 8 እናንተ ግን። መምህር

ተብላችሁ አትጠሩ፤ መምህራችሁ አንድ ስለ ሆነ እናንተም ሁላችሁ ወንድማማች ናችሁ። 9 አባታችሁ አንዱ እርሱም የሰማዩ ነውና በምድር ላይ ማንንም። አባት ብላችሁ አትጥሩ። 10 ሊቃችሁ አንድ እርሱም ክርስቶስ ነውና። ሊቃውንት ተብላችሁ አትጠሩ። 11 ከእናንተም የሚበልጠው አገልጋያችሁ ይሆናል። 12 ራሱን ከፍ የሚያደርግ ሁሉ ይዋረዳል፥ ራሱንም

የሚያዋርድ ሁሉ ከፍ ይላል። 13 እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን፥ መንግሥተ ሰማያትን በሰው ፊት ስለምትዘጉ፥ ወዮላችሁ እናንተ አትገቡም የሚገቡትንም እንዳይገቡ ትከለክላላችሁ።

14 እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን፥ በጸሎት ርዝመት እያመካኛችሁ የመበለቶችን ቤት ስለምትበሉ፥ ወዮላችሁ፤ ስለዚህ የባሰ ፍርድ ትቀበላላችሁ። 15 እናንተ ግብዞች ጻፎችና

ፈሪሳውያን፥ አንድ ሰው ልታሳምኑ በባሕርና በደረቅ ስለምትዞሩ፥ በሆነም ጊዜ ከእናንተ ይልቅ ሁለት እጥፍ የባሰ የገሃነም ልጅ ስለምታደርጉት፥ ወዮላችሁ።…”

ማቴ.23

ሁለተኛው የዮሐንስ መልእክት 2014

26 www.tlcfan.org

ይህ ባሕሪ በአሁን ዘመን ያሉ አንዳንድ አገልጋዬችንም መልክ በግልጽ ያሳያል። ብዙ ሰዎች የእውነት ነገር ይናገራሉ። ነገር ግን በሚናገሩት ነገር ውስጥ የሉበትም። ጌታ ግን እውነትን የምንናገር ብቻ ሳይሆን በእውነት የምንሄድ እንድንሆን ይፈልጋል። ዛሬም እግዚአብሔር ለማገልገል የምንፈልግ ብዙ እውቀት ማካበት ብቻ ሳይሆን የሚታይን የቅድስና ሕይወት እንኖር ዘንድ ይገባል።

የሚኖር ሰው ከማውራት ይልቅ ኑሮውን በአካኔዱና በስራው የሚያሳይ ነው። ከስራ የተለየ እምነት የሞተ ነው። ስራ የሌለው አገልግሎትም የሞተ አጋልግሎት ነው። ከምንናገረው ነገር ይልቅ ለምንኖረው ሕይወት አብልጠን ልንጠነቀቅ ይገባል። በእውነት የሚሄድ ሰው በዘመኑ ሁሉ ድል ነሺ ነው።

ሁለተኛው የዮሐንስ መልእክት 2014

27 www.tlcfan.org

ከመጀመሪያ የነበረች ትእዛዝ

“5 አሁንም፥ እመቤት ሆይ፥ እርስ በርሳችን እንድንዋደድ እለምንሻለሁ፤ ይህች ከመጀመሪያ በእኛ ዘንድ የነበረች ትእዛዝ ናት እንጂ አዲስ ትእዛዝን እንደምጽፍልሽ አይደለም።6 እንደ ትእዛዛቱም እንሄድ ዘንድ ይህ ፍቅር ነው፤ ከመጀመሪያ እንደ

ሰማችሁ፥ በእርስዋ ትሄዱ ዘንድ ትእዛዙ ይህች ናት።” 2.ዮሐ

ፍቅር ከመጀመሪያ የነበረች ለሙሴ ከተሰጠው ሕግ የቀደመች ትእዛዝ ነች። እግዚአብሔር ይህን ፍቅሩን በመጀመሪያ ለዳምና ለሄዋን መስጠት ብቻ ሳይሆን ለእነሱ ያለውን ፍቅሩን ባደረገላቸው፣ በሰጣቸው፣ ባስገዛላቸው ነገር ሁሉ ተገልጧል።

የመጀመሪያ ጋብቻ የተመሰረተውም በዚሁ ፍቅር ነው። አዳምም ሆነ ሄዋን ይዋደዱ ነበር። ይህን መዋደዳቸውን አዳም የሰጠችውን ፍሬ እንደሚገድለው እያወቀ መብላቱ ፍቅሩን ያሳያል። እርሱ በደሏንና መተላለፏን ተቀበለ። ይህ ተገባሩ የኢየሱስን በደላችንንና መከራችንን መቀበል መሸከም ትንቢታ ጥላ ነበር። ዛሬ የምንኖረው ለመጪው ትውልድ ትንቢታዊ ነገርን የሚይዘው እውነትንና ፍቅርን የተከተል ብቻ ከሆነ ነው።

በጥልቀት ልናውቀው የሚገባው ነገር ቢኖር በአዳም ውስጥ ሁላችንን ሰለ ነበርን ይህ የመጀመሪያ ትእዛዝ ሲሰጥ በአዳም ውስጥ ይህን ትእዛዝ ሁላችን ተቀብለናል። ይህ ድምፅ አሁንም በያንዳዳችን ውስጥ ያስተጋባል። በዚህ ትእዛዝ ለመሄድ ትበረቱ ዘንድ ይህ ትእዛዝ ዛሬም እንዳልተለወጠና ያዘዘን ጌታ መሆኑ ገብቶን በትህትና በአክብሮት ትእዛዙን ልንፈጽም ይገባል። የበሰሉ ሰዎች ልመናም ይህ ነው እርስ በእርሳችን እንዋደድ። ይህ ከእግዚአብሔር ሕግ ዋንኛ ከሚባሉት አንዱ ፍቅር ነው። ማቴ.23፥23

ሽማገሌው ዮሐንስ የተመረጠችውን እመቤት ይህን ትእዛዝ እንድትፈጽም ይለምናል። እኔም ይህን መጽሐፌን የምታነቡትን ሁሉ እርስ በእርሳችንን እንድንዋደድ እለምናችኃለሁ። ምክንያትም ብዙ ይህን ፍቅር የማይወዱ አሳቾች በዚህ ባለንበት ዘመን አሉና ነው።

“7 ብዙ አሳቾች ወደ ዓለም ገብተዋልና እነርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ እንደ መጣ የማያምኑ ናቸው፤ ይህ አሳቹና የክርስቶስ ተቃዋሚው ነው።” 2.ዮሐ

ወደ አለም የገቡ ብዙ አሳቾች ናቸው። በዚህ ባለንበት በመመጨረሻው ዘመን ብዙ አሳቾች በአለም ብቻ ሳይሆን በአምልኮ ስፍራዎች መድረኮች ሞልተው ሳያፍሩ የጌታችንን ሰም እየጠሩ ምዕመናንን ሲያስቱ መመልከት ለበሰሉ ክፉን መለየት በስራቸው ለለመዱ አማኞች የተለመደ ነገር ሆኗል። የጌታን ትዕዛዝ በኑሯቸው መጣስ ብቻ ሳይሆን በየመድረኩ እንደተሻረ ያስተምራሉ። ይህ ደግሞ ከኢየሱስ ክርስቶስና ከሐዋርያት ትምሕርት የራቀ ነው።

ሁለተኛው የዮሐንስ መልእክት 2014

28 www.tlcfan.org

ይህ ቃሉን በሚያገለግሉና በሚተነብዩ ሰዎች ብቻ ሳይሆን በሚዘምሩ ዘማሪዎችም ጀርባ ይህ የስህተት መንፈስ ሲገለጥ ይታያል። ለዘማሪዎች ዝማሬ ከጌታ ቃል ውጪ የወጣ ነገር ሲዘምሩ መስማት ያደጉበትና የበሉበትን ስህተት የተሞላ ገበታ ማንነት ይገልጠዋል።

ዛሬ በዚህ ዘመን ውሸትና ስህተት ያለ አንዳች ተቃውሞ በሰዎች ዘንድ ተቀባይ ሲያገኝ እውነት ግን ባባቶቻችን ዘመን እንደ ነበር ሲገፋ በግልጽ ይታያል። ይህ ጌታንና የጌታን ቃል ለሚያውቁ የሚያስደንቅ ነገር አይደለም። ለማያውቁ ደግሞ የከፋ ነው። ምክንያቱም ሰሚዎችን ማሳቱ ብቻ ሳይሆን ወደ እውነት እንዳይመጡ አዕምሮአቸውን ያደነዝዘዋል።

ሃዋርያው ጳውሎስ ለዚህ አይነቱ ስህተት ታላቁ ምሳሌያችን ነው። ከእንደዚህ አይነት ስህተት እንዴት እንደምናመልጥ መመሪያ ጥሎልን ያለፈ መልካም መጋቢ ነው። ጳውሎስ ጌታን ያገለገለ መስሎት በሃይማኖት ስቶ ፈሪሳዊ የዘመኑ ቴረሪስት ሆኖ ነበር። ለእግዚአብሔር ብሎ ቅዱሳንን ያሳድድ ያስገድል ነበር።

የስህተት ክፋቱ ይህን ያህል ነው። ዛሬም በስጋ የሚታይ መገዳደል ባይታይም በጥላቻ ጥይት ተመትተው የሞቱ ሃያሌ የጌታ ባሪያዎችና ልጆች ናቸው። እውነት ሲናገሩ እውነታቸው ወደ ስዎች እንዳይደርስ በሰዎች ዘንድ እንዲጠሉ እነዚህ በጌታ ቤት ያሉ አሳቾች የሃሰትን መንፈስ ምንም በማያውቁ ሰዎች ላይ ያስተለልፋሉ።

ወንድሙን የሚጠላ ነፍሰ ገዳይ ነው። የአሳቾች አንዱ መገለጫቸው ይህ ነው። አንዱ አንዱን ሲወደው አይወዱም። ጥላቻንም በሰዎች ጆሮ ይዘራሉ። መንግሥተ ሰማያትን በሰው ፊት ይዘጋሉ። እንደዚህ አይነት መሪዎች፣ እረኞች፣ አሰተማሪዎች፣ ወንጌላዊያን፣ ነብያት፣ ሃዋርያት፣ ዘማሪዎች ባሉበት ሰፍራ ሁሉ ከፍቅር ይልቅ የሚገለጠው ጥላቻ ጸብና ክርክር ነው። ልቡን መጠበቅ ያልቻለ ያልበሰለ አማኝ በስህተታቸው ተጠላልፎ አብፘቸው በፍርድ ይወድቃል። ባለማውቅ የሃጢያታቸው ተካፋይ ይሆናል። ነገር ግን ባያውቅም ከፍርድ አያመልጥም ጥቂትም ቢሆን መቀጣቱ አይቀርም። ሳያውቅ ስቶ በስራቸው የተካፈለ ሰላለማወቁ አውቀው ከሚያደርጉት ባነሰ ቅጣት ይቀጣል። ውጣትን መቀበሉ ግን አትቀርም። እውነትን አውቀው የማያደርጉና የማይታዘዙ ግን ቅጣታቸው የከፋ ነው፦

“47 የጌታውንም ፈቃድ አውቆ ያልተዘጋጀ እንደ ፈቃዱምያላደረገ ያ ባሪያ እጅግ ይገረፋል፤ 48 ያላወቀ ግን መገረፍ የሚገባውንም ያደረገ ጥቂት ይገረፋል። ብዙም ከተሰጠው ሰው ሁሉ ከእርሱ ብዙ ይፈለግበታል፥ ብዙ አደራም ከተሰጠው

ከእርሱ አብዝተው ይሹበታል።” ሉቃ.12

“13 እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን፥ መንግሥተ ሰማያትን በሰው ፊት ስለምትዘጉ፥ ወዮላችሁ እናንተ አትገቡም የሚገቡትንም እንዳይገቡ ትከለክላላችሁ። 14 እናንተ ግብዞች

ጻፎችና ፈሪሳውያን፥ በጸሎት ርዝመት እያመካኛችሁ የመበለቶችን ቤት ስለምትበሉ፥ ወዮላችሁ፤ ስለዚህ የባሰ ፍርድ ትቀበላላችሁ። 15 እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን፥ አንድ ሰው

ልታሳምኑ በባሕርና በደረቅ ስለምትዞሩ፥ በሆነም ጊዜ ከእናንተ ይልቅ ሁለት እጥፍ የባሰ የገሃነም ልጅ ስለምታደርጉት፥ ወዮላችሁ፣…” ማቴ.23

ሁለተኛው የዮሐንስ መልእክት 2014

29 www.tlcfan.org

የአሳቾች ባሕሪ ትልቁ ችግሩ አንዴ ካሳመኑ ከእነርሱ በእጥፍ የባሰ አሳች ነው የሚወልዱት። እነዚህ አሳቾች በቀለሉ ለማሳት የሚመርጡት ሰዎች መበለቶችን ነው። መበለት ማለት ባል የሞተባት ሴት ማለት ነው። ከክርስቶስ ጋር ያለው ጋብቻ መረዳት የሌላቸው ሰዎች ሁሉ አሳቾች ለመጠቃት የመጀመሪያውን ስፍራ ይይዛሉ። ጳውሎስ ሰለ መጨረሻው ዘመን ሲናገር እንዲህ ብሎ ተነበየ፦

“1-2 መንፈስ ግን በግልጥ። በኋለኞች ዘመናት አንዳንዶች የሚያስቱ መናፍስትንና በውሸተኞች ግብዝነት የተሰጠውን የአጋንንትን ትምህርት እያደመጡ፥ (እምነትን) ይክዳሉ ይላል፤ በገዛ ሕሊናቸው እንደሚቃጠሉ ደንዝዘው፥ 3 እነዚህ ውሸተኞች መጋባትን ይከለክላሉ፥ አምነውም እውነትን የሚያውቁ ከምስጋና ጋር ይቀበሉ ዘንድ እግዚአብሔር ከፈጠረው መብል(ከመንፈሳዊው መብልም ጭምር) እንዲርቁ ያዝዛሉ። 4 እግዚአብሔር የፈጠረው ሁሉ መልካም ነውና፥ ከምስጋናም ጋር ቢቀበሉት የሚጣል ምንም የለም (ከቃሉ አንዳች የሚጣል ክፍል የለውም) ፤ 5 በእግዚአብሔር ቃልና በጸሎት የተቀደሰ ነውና። 6

ስለዚህ ወንድሞችን ብታሳስብ፥ በእምነትና በተከተልኸው በመልካም ትምህርት ቃል የምትመገብ የኢየሱስ ክርስቶስ መልካም አገልጋይ ትሆናለህ። 7 ነገር ግን ለዚህ ዓለም ከሚመችና የአሮጊቶችን ሴቶች ጨዋታ ከሚመስለው ተረት ራቅ። እግዚአብሔርን ለመምሰል ግን ራስህን አስለምድ። 8 ሰውነትን ለሥጋዊ ነገር ማስለመድ ለጥቂት ይጠቅማልና፤ እግዚአብሔርን መምሰል ግን የአሁንና

የሚመጣው ሕይወት ተስፋ ስላለው፥ ለነገር ሁሉ ይጠቅማል። 9 ይህ ቃል የታመነ ሁሉም እንዲቀበሉት የተገባ ነው፤ 10 ይህን ለማግኘት እንደክማለንና፥ ስለዚህም እንሰደባለን፤ ይህም ሰውን ሁሉ ይልቁንም

የሚያምኑትን በሚያድን (ያመኑ የተሻለ ክብር አላቸው ነገር ግን እግዚአብሔር ሁሉን ያድናል) በሕያው አምላክ ተስፋ ስለምናደርግ ነው።”

2ጢሞ.4፥1-9

“1 ነገር ግን በመጨረሻው ቀን የሚያስጨንቅ ዘመን እንዲመጣ ይህን እወቅ። 2 ሰዎች ራሳቸውን የሚወዱ ይሆናሉና፥ ገንዘብን የሚወዱ፥ ትምክህተኞች፥ ትዕቢተኞች፥ ተሳዳቢዎች፥ ለወላጆቻቸው

የማይታዘዙ፥ የማያመሰግኑ፥ 3 ቅድስና የሌላቸው፥ ፍቅር የሌላቸው፥ ዕርቅን የማይሰሙ፥ ሐሜተኞች፥ ራሳቸውን የማይገዙ፥ ጨካኞች፥ መልካም የሆነውን የማይወዱ፥ 4 ከዳተኞች፥ ችኩሎች፥ በትዕቢት

የተነፉ፥ ከእግዚአብሔር ይልቅ ተድላን የሚወዱ ይሆናሉ፤ 5 የአምልኮት መልክ አላቸው ኃይሉን ግን ክደዋል፤ ከእነዚህ ደግሞ ራቅ። 6-7 ወደ ቤቶች ሾልከው እየገቡ፥ ኃጢአታቸው የተከመረባቸውን በልዩ ልዩ ምኞትንም የሚወሰዱትን ሁልጊዜም እየተማሩ እውነትን ወደ ማወቅ ሊደርሱ ከቶ የማይችሉትን

ሞኞችን ሴቶች የሚማርኩ፥ ከእነዚህ ዘንድ ናቸውና። 8 ኢያኔስና ኢያንበሬስም ሙሴን እንደ ተቃወሙት፥ እንዲሁ እነዚህ ደግሞ አእምሮአቸው የጠፋባቸው ስለ እምነትም የተጣሉ ሰዎች ሆነው፥ እውነትን ይቃወማሉ። 9 ዳሩ ግን የእነዚያ ሞኝነት ደግሞ ግልጥ እንደ ሆነ፥ ሞኝነታቸው ለሁሉ

ይገለጣልና ከፊት ይልቅ አይቀናላቸውም። 10 አንተ ግን ትምህርቴንና አካሄዴን አሳቤንም እምነቴንም ትዕግሥቴንም ፍቅሬንም መጽናቴንም ስደቴንም መከራዬንም ተከተልህ፤11 በአንጾኪያና በኢቆንዮን በልስጥራንም የሆነብኝን የታገሥሁትንም ስደት ታውቃለህ፤ ጌታም ከሁሉ አዳነኝ። 12 በእውነትም በክርስቶስ ኢየሱስ እግዚአብሔርን እየመሰሉ ሊኖሩ የሚወዱ ሁሉ ይሰደዳሉ። 13 ነገር ግን ክፉዎች

ሰዎችና አታላዮች፥ እያሳቱና እየሳቱ፥ በክፋት እየባሱ ይሄዳሉ። 14 አንተ ግን በተማርህበትና በተረዳህበት ነገር ጸንተህ ኑር፥ ከማን እንደ ተማርኸው ታውቃለህና፤ 15. ከሕፃንነትህም ጀምረህ ክርስቶስ ኢየሱስን በማመን፥ መዳን የሚገኝበትን ጥበብ ሊሰጡህ የሚችሉትን ቅዱሳን መጻሕፍትን

ሁለተኛው የዮሐንስ መልእክት 2014

30 www.tlcfan.org

አውቀሃል። 16-17 የእግዚአብሔር ሰው ፍጹምና ለበጎ ሥራ ሁሉ የተዘጋጀ ይሆን ዘንድ፥ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ ለትምህርትና ለተግሣጽ ልብንም

ለማቅናት በጽድቅም ላለው ምክር ደግሞ ይጠቅማል፣” 2 ጢሞ.3

ትልቁ ጳውሎስ ለጢሞቴዎስ ያስቀመጠለት የማምለጫ ቁልፍ በመጨረሻው ቁጥር ላይ ይገኛል። እነዚህም አንደኛው ጥበብን ሊሰጡ የሚችሉትን ቅዱሳን መጽሐፍትን ማወቅ። ሁለተኛ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ ለትምህርትና ለተግሳጽ ልብንም ለማቅናት በጽድቅ ላለው ምክር ሁሉ እንደሚጠቅም ማወቅ ነው። የእርሱ በረከት ተካፋይ መሆን ወይም በሕይወት ላይ መለማመድ ነው። ይህን ቃል ካገኘን ካነበብናችውና ከኖርናቸው በቀላሉ ከአሳቾች ወጥመድ እንተርፋለን።

ሁለተኛው የዮሐንስ መልእክት 2014

31 www.tlcfan.org

ሙሉ ደሞዝ

“8 ሙሉ ደመወዝን እንድትቀበሉ እንጂ የሠራችሁትን እንዳታጠፉ ለራሳችሁ ተጠንቀቁ።” 2.ዮሐ

ሙሉ ደሞዝ የምንቀበለው ከጌታ ነው። ጌታ አንድ ነገር እንድናደርግ ሲያዘን ስራውን ስንጨርስ ደሞዛችንን ሳያሳድር ይከፍለናል። በማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 20 ላይ ስለ አሰሪና ሰለ ሰራተኛ ደግሞም ሰለ ደሞዝ አከፋፈል የሚናገር ታልቅ የኢየሱስ ትምህርት እናገኛለን።

ማወቅ የሚገባን ግን ያልሰራ ደሞዝ አይቀበልምና ከጌታ ደሞዝ የሚጠብቅ ሁሉ በመንፈሳዊ ስራ በጌታ ሥራ የተጠመደ ሊሆን ይገባዋል። ይህም በቅድስናና በእውነት ከመኖር ይጀምራል። አሳቾች አንዱ መገለጫቸው ከስራ ማስተጓጎል ቅድስናንና እውነትን ማጥፋት፣ ማቅለል ነው። ሰራን ግን መስራት ይጠበቅበናል። ጌታን ማመን የመጀመሪያ ስራችን ሲሆን ካመንን በኃላ ደግሞ ሕጉ ልንጠብቅ ይገባል። ይህም ለመዳን ሳይሆን የምድርን በረከት ለመብላት እግዚአብሔርንና የእግዚአብሔር የሆነውን ነገር ሁሉ በሰው ሁሉ ፊት ለማስከበር እና መንግስቱን ለመውረስ ነው።

“27 ለሚጠፋ መብል አትሥሩ፤ ነገር ግን ለዘላለም ሕይወት ለሚኖር መብል የሰው ልጅ ለሚሰጣችሁ ሥሩ፤ እርሱን እግዚአብሔር አብ አትሞታልና። 28 እንግዲህ።

የእግዚአብሔርን ሥራ እንድንሠራ ምን እናድርግ? አሉት። 29 ኢየሱስ መልሶ። ይህ የእግዚአብሔር ሥራ እርሱ በላከው እንድታምኑ ነው አላቸው።”

(ዮሐ.6፥27-29)

ደግሞ ከላይ እንዳየነው ራሳችንን እግዚአብሔር መምሰል ማስለመድ ሌላው ልንሰራው የሚገባ ከጌታ የተሰጠን ስራ ነው። ነገር ግን የእግዚአብሔር ስራ ይህ ብቻ ነው ብለን ማጠቃለያ ልንሰጥ አይገባም። ነገር ግን ቀዳሚዎቹ እነዚህ ናቸው። እነዚህን ሥራዎች ሰርቶ የጨረሰ ብዙ ሌላ ሥራን እንዲ ስራ በጌታ ይደረጋል።

“1 መንግሥተ ሰማያት ለወይኑ አትክልት ሠራተኞችን ሊቀጥር ማልዶ የወጣ ባለቤት ሰውን ትመስላለችና። 2 ሠራተኞችንም በቀን አንድ ዲናር ተስማምቶ ወደ ወይኑ አትክልት ሰደዳቸው። 3

በሦስት ሰዓትም ወጥቶ ሥራ የፈቱ ሌሎችን በአደባባይ ቆመው አየ፥ 4 እነዚያንም። እናንተ ደግሞ ወደ ወይኔ አትክልት ሂዱ የሚገባውንም እሰጣችኋለሁ አላቸው። እነርሱም ሄዱ። 5 ደግሞም በስድስትና

በዘጠኝ ሰዓት ወጥቶ እንዲሁ አደረገ። 6 በአሥራ አንደኛውም ሰዓት ወጥቶ ሌሎችን ቆመው አገኘና። ሥራ ፈትታችሁ ቀኑን ሁሉ በዚህ ስለ ምን ትቆማላችሁ? አላቸው። 7 የሚቀጥረን ስለ አጣን ነው

አሉት። እርሱም። እናንተ ደግሞ ወደ ወይኔ አትክልት ሂዱ የሚገባውንም ትቀበላላችሁ አላቸው። 8 በመሸም ጊዜ የወይኑ አትክልት ጌታ አዛዡን። ሠራተኞችን ጥራና ከኋለኞች ጀምረህ እስከ ፊተኞች ድረስ ደመወዝ ስጣቸው አለው። 9 በአሥራ አንደኛው ሰዓትም የገቡ መጥተው እያንዳንዳቸው አንድ ዲናር ተቀበሉ። 10 ፊተኞችም በመጡ ጊዜ አብዝተው የሚቀበሉ መስሎአቸው ነበር፤ እነርሱም ደግሞ እያንዳንዳቸው አንድ ዲናር ተቀበሉ። 11-12 ተቀብለውም። እነዚህ ኋለኞች አንድ ሰዓት ሠሩ፥የቀኑንም ድካምና ትኩሳት ከተሸከምን ከእኛ ጋር አስተካከልሃቸው ብለው በባለቤቱ ላይ አንጐራጐሩ። 13 እርሱ

ግን መልሶ ከእነርሱ ለአንዱ እንዲህ አለው። ወዳጄ ሆይ፥ አልበደልሁህም በአንድ ዲናር

ሁለተኛው የዮሐንስ መልእክት 2014

32 www.tlcfan.org

አልተስማማኸኝምን? 14 ድርሻህን ውሰድና ሂድ፤ እኔ ለዚህ ለኋለኛው እንደ አንተ ልሰጠው እወዳለሁ፤ በገንዘቤ የወደድሁትን አደርግ ዘንድ መብት የለኝምን? 15 ወይስ እኔ መልካም ስለ ሆንሁ ዓይንህ ምቀኛ ናትን? 16 እንዲሁ ኋለኞች ፊተኞች፥ ፊተኞችም ኋለኞች ይሆናሉ፤

የተጠሩ ብዙዎች፥ የተመረጡ ግን ጥቂቶች ናቸውና።” ማቴ.20፥1-16

ይህ የወይኑ ባለቤት የሆነው ጌታችን ሰራተኞች ለመቅጠር ከቤት የወጣው በቀን አምስት ጊዜ ነበር። ማለዳ፣ በ3ሰዓት፣ በ6፣ በ9 እና በ11 ሰዓት ለመቅጠር ወጣ። ይወጣል ሰራተኞችን ይዞ ይመጣል። ይወጣል ሰራተኞችን ለወይን አትክልቱ ይቀጥራል። በመሆኑም ሰራተኛ እጅግ በማነሱ በ11ኛ ሰዓትም ጭምር ወጣ። የ11 ሰዓቱ ሰራተኞች ወደ ወይኑ ተላኩ። የወይኑን አትክልት የት እንዳለ ስለሚያዉ ስራም እንዴት እንደሚሰራ ስለሚያውቁ እርሱ ስፍራውን ማሳየት አላስፈለገውም።

አንድ ሰዓትም ቢሆን ቢሰራለት ለወይኑ አትክልት ባለቤት ትልቅ እርካታ ሥራው መሰራቱና ወደ ፍጻሜ ነው። ወይኑ ከሚበላሽ በ11 ሰዓትም ቢሆን ሰራተኛ ለመቅጠር ወደ ኃላ አይልም። ይህ ባለቤት ቀኑን ሙሉ ሰራተኛ በመቅጠር ሥራው እንዲ ሰራ እርሱ ደግሞ ያለ እረፍት የመቅጠር ሥራን ሰራ። መቅጠር የጌታ ብቸኛ መብት ነው። ማንም ራሱን መቅጠር ወይም ቀጣሪ ሊሆን አይችልም። ይህን ስል ለመንፈሳዊው ሥራ ማለቴ መሆኑ ግልጽ ይሁን። የማይሰራ ደግሞ ደሞዝን አይቀበልም። በእርሱ ስራ የተሰማራን ሁሉ ደሞዝን ከእርሱ መጠበቅ ትክክል ነው።

ሰራተኛ ለማግኘት ከማለዳ እስከ11 ሰዓት ተጓዘ። በሰው እጅ አምስት ጣቶች እንዳሉት ሁሉ አምስት ጊዜ ከቤት ወጥቶ ሰራተኞችን ሰበሰበ። ሥራው በሙሉ እጅ የሚሰራ እንጂ በከፊል የሚታገዝ አይደለምና ነው። ይህ ባለቤት ከቤት ሲወጣ ሲገባ የዋለ ባለቤት የመንግስተ ሰማያትም ምሳሌ ነው።

የወይን አትክልቱን በሰራተኛ ሲያጥለቀልቅ የዋለ ሰው መንግስተ ሰማይን ይመስላል። እርሱም ክርስቶስ ኢየሱስ ነው። የቁርስና የምሳ ሰዓት ላይ እንኳ ሰራተኞች ለመቅጠር ውጭ ስለ ነበረ ለዚህ የወይን አትክልት ሥራ መስዋዕትነትን ከፈለ። ቀጣሪው የጾታ ልዩነት አያደርግም።

“ይህም ሲሆን ሳለ ደቀመዛሙርቱ ብላ ብለው ለመኑት፣ እርሱ ግን እናንት የማታውቁት የምበላው መብል እኔ አለኝ አላቸው።”

(ዮሐ.4፥31-32)

ቀጣሪው ለሚያሰራው ስራ ራሱን የቻለ የወሰነው የሰራተኞች ሁሉ ደሞዝ በእጁ አለው። ለወይኑ አትክልት የወሰነው ዋጋ ነበር። አንድ ዲናር የደሞዝ ዋጋ ተምኖ ሊቀጥር ከቤቱ ወጣ ነገር ግን ለሰራተኞች ሁሉ ሊሰጠው ያሰበውን ደሞዝ አለነገራቸውም። የነገራቸው መጀመሪያ ላገኛቸው ሰራተኞች ብቻ ነው። ለአብርሃም የነገረው ደሞዝ የእኛም ደሞዝ ከእርሱ በኃላ የተቀጠርን ሰራተኞች ደሞዛችን ነው። ሙሉ ደሞዝ ማለት እንግዲህ ይህ ነው።

ሁለተኛው የዮሐንስ መልእክት 2014

33 www.tlcfan.org

የተነጋገረውና የተስማማው በማለዳ ወጥቶ ካገኛቸው ሰራተኞች ጋር ሲሆን ለሌሎቹ ሰራተኞች የደሞዙን ልክ አልገልጸላቸውም ነበር። ደሞዛችንን ለማቅወቅ መጀመሪያ ያገኛቸውን አባቶቻችን የገባላቸውም የደሞዝ ዋጋ ማየት ይገባል። የማለዳዎቹ በአንድ ዲናር ከተስማሙ ሌሎች በዚህ እንደሚስማሙ ቀጣሪው ጌታ ያውቃል። የቤተ መቅደስ ግብር ሁለት ዲናር ነበር። በመሆኑ አንድ ዲናር ያህል ክፍያ ለአንድ ቀን ውሎ ትልቅ ደሞዝ ነው። መምህራችሁ ሁለቱን ዲናር አይገብርምን... አሉት። (ማቴ.17፥24)

ይህ ቀጣሪ ጌታ የሚሰራለትን ሲፈልግ የሚቀጥራቸው ያጡ ሰዎች ቆመው ተገኙ “ሥራ ፈትታችሁ ቀኑን ሁሉ በዚህ ስለ ምን ቆማችኋል? አላቸው። የሚቀጥረን ስለ አጣን ነው አሉት። እሱም እናንተ ደግሞ ወደ ወይኔ አትክልት ሂዱ የሚገባውንም ትቀበላላችሁ አላቸው። በወይን አትክልት ዉስጥ ሥራ መስራት እየቻሉ ችሎታው እያላቸው የመቅጠር መብት የጌታ መሆኑ ሰለገባቸው የወይኑ ጌታ እሰከ ሚመጣና ወደ ወይኑ እሰከሚልካቸው ድረስ እስከ ቀኑ 11 ሰዓት ቆመው ጠበቁ። መስራት ይችላሉ የሚያሰራቸው ግን ገና አልመጣም ነበር። ቀኑን ሙሉ ባለመስራታቸው ቀኑ ሊያልቅ ቀርቦባቸው በሰው አይን ሲታዩ ስራ ያጡ ለስራ ያልተፈልጉ ተደርገው ሊቆጠሩ ይችላሉ።

ሁሉ ሰራተኞች የጌታውን ሥራ ሲሰሩ እነኝህ ግን በመንገዱ ቆመዋል። ሌሎች ደሞዛቸውን ለመቀበል ሰዓታቸውን ሲመለክቱ ከየት መጡ የማይባሉ ሰራተኞች የወይን ሥፍራውን አጥለቀለቁት። ይህ ለመጨረሻውም ዘመን ትንቢታዊ ነው። ይህ ባለቤት በወይኑ አትክልት ምን ያህል እንደተሰራ ሳይሆን ብዙ ሰዎች ገብተው መከሩን እንዲሰበስቡ፣ እንዲያነሱና ጎተራውን ወደ ሙላት እንዲያመጡ ማድረግ ግቡ ነበር።

ሰራተኞች እስከ 11 ሰዓት በመንገድ ቆመዋል። ባለቤት ግን እንደ እነዚህ ዓይነቱን ለመፈለግ ማለዳ ተነስቷል። በዚህም ዘመን በእግዚአብሔር የወይን ቦታ ለመስራት ብቃቱ እያላቸው የሚቀጥራቸው ያጡ የመሰሉ ጌታቸውን በትግስት የሚጠብቁ ሃያሌዎች ናቸው። ሌሎች ተቀጥረዋል። እነዚህ ግን በቀጣሪ ጌታ በመጠባበቅ መንፈስ ድል ነሺዎች ስራውን ወደ ፍጻሜ ለማምጣት ወደ ስራ የሚልካቸው የወይኑ ባለቤት ጌታን በመጠባበቅ ቆመዋል። እነርሱ ቀጣሪውን አላገኙትም እንጂ ቀጣሪው እነርሱ አልጠፉበትም። የት እንደ ቆሙ ያውቃል። እግዚአብሔር ግን ለወይን አትክልት ሰፍራ የሆነችው ቤተክርሲያን ሰራተኞችዋ የት እንዳሉ የሚያውቅ ቀጣሪ ጌታ ነው። ስለዚህ ነው ስራተኛ እንዲልክ ወደ እርሱ ጸልዮ የተባልነው።

ሰው ራሱን በሙል ጊዜ ለጌታ ሊሰጥ ወይም ሊቀጥር አይችልም። ጌታ ሊቀጥረው ሊጠራው ይገባል። እድሜያችንና ጊዜው ያለቀ ቢመስልም ሰራተኛ ፍለጋ የወጣው ጌታ በ11ኛ ሰዓት ያገኘናልና በትግሰት ጌታን እንጠብቅ። ከእርሱ ሳይታዘዙ መውጣት መስራት ፍሬ ቢስ ያደርጋል እንጂ ውጤት አይኖረውም። በትግስት የሚጠብቁትን ባልጠብቁት ስዓት መጥቶ ወደ ወይኑ አትክልትም ይልካቸዋል። በሁሉ ተስፋ ቢቆረጥም በአምላካችን ተስፋ አይቆረጥም።

ሁለተኛው የዮሐንስ መልእክት 2014

34 www.tlcfan.org

ብዙዎች በቤተክስቲያ በአሁን ወቅት በአገልገሎት በስራ ላይ ያሉት ስፍራ ካልለቀቁ መቀጠር የሚችሉ አይመስላቸም። ሰለዚህም ቀደመው የተቀጠሩትን ሲተቹ ይታያል። ይህ በጣም የተሳሳተ እንደሆነ ከዚህ ትምህርት በቀላሉ ልንማር እንችላለን። የዚህ ወይን አትክልት ጌታ በስራ ላይ ያሉትን ሰራተኞች ሌላ መቅጠር ሲፈልግ ስራቸውን አይነሳቸውም ወይም አያባራቸውም። ነገር ግን ሥራ ያጡትንና የቆሙትን በላያቸው ላይ ይቀጥራል። ሳዖልንና ዳዊትን መመልከት እንችላለን። ምንም እንኳ የሳዖልን ሰራውን ቢንቀውም ንግስናውን እስከሚሞት ድረስ ከእርሱ አልወሰደውም። እግዚአብሔር በመጥራቱና በስጦታው አይጸጸትም። በላዮ ላይ ግን ዳዊትን ቀባ።

በተመሳሳይም የመለኮት እውቀትና ችሎታ እያላቸው በወይን አትክልት መሳተፍ የሚችሉትን መንፈሳዊ ብቃት ያላቸው በሰው የተናቁ በጌታ የተመረጡትን አያሌዎች ይቀጥራል። ሐዋርያትን የሆኑትን ስንመለከት ከቤተመቅደስ ውጭ የራሳቸውን ሥራ እየሰሩ የወይኑን አክልትን ሥራ ግን አይሰሩም ነበር። በራሳቸው ሥራ እንጂ በመለኮታዊው ስራ ሥራ ፈት ሆነው ቆመው ነበር። በመሆኑም ከቤተመቅደስ ውጭ ሆነው በዓሳ አስጋሪነት፣ በግ ጠባቂነት፣ በቀራጪነት የተሰለፉትን በሙሉ ጌታ ለራሱ ሰራ ቀጥሮ ወሰዳቸው፣ በወይኑ እንዲሰሩ አደረጋቸው።

የወይን አትክልት ጌቶችና ሰራቶኞች ነን የሚሉ ፈሪሳዊያንና ሰዱዋዊያን ቃላተኞች በእግዚአብሔር ስራ ሲቀጠሩ አልታዩም። ይልቅም እኛ የሙሴ፣ የኤልያስ በማለት የራሳቸው ጌታ እንዳላቸው ገለፁለት። ሰው ለሰው ጌታ ሊሆን አይችልም። ሰለዚህ እኔ ከሁሉ ነገር ርቄ ያለሁትን ሰው የሚቀጥረኝ አጥቼ የምንከራተተውን ማን ይፈልገኛል ማለት አይቻለም። እግዚአብሔር ይፈልግሃል ይፈልግሻል። ተገቢውን ዋጋ ለመክፈል ያሰማራሃል ያሰማራሻል። በትግስት በቦታህ ጠብቀው ጠብቂው ቢዘገይ በእርግጥ ይመጣል። ዘው ብለን በወይኑ አትክልት ያለዋጋ ከመስራት ጌታ ይጠብቀን።

በመሸም ጊዜ ማትም ቀኑ ሲጠቀለል የወይኑ አትክልት ጌታ አዛዡን፦ ሰራተኞች ጥራና ከኋለኞች ጀምረህ እስከ ፊተኞች ድረስ ደሞዝ ስጣቸው አለው። በአስራ አንደኛው ሰዓትም የገቡ መጥትው እያንዳንዳቸው አንድ ዲናር ተቀበሉ።

ቀን ለስራ ሲመደብ ምሽት ደግሞ ለእረፍት ነው። ቀን ሳለ ብቻ በወይን አትክልት ይሰራል። በመሸ ጊዜ ግን ደመወዝን መቀበል ይከተላል እንጂ ስራ የለም። ወደ እረፍት የገባ እግዚአብሔር ከስራው እዳረፈ እርሱም ሊያርፍ ይገባዋል። የወይን አትክልቱ ጌታ የሰራተኞችን ደሞዝ አያሳድርም። በዚያኑ ቀን ለሁሉ ከፍሎ ወደ እረፍት ያሰናብታል። ሲቀጥራቸው ራሱ ወጥቶ ተነጋግሮ አመጣቸው። ደሞዝ ሲከፍል ግን በቤቱ አዛዡ ይከፍላል።

እግዚአብሔር የሰራተኛ ደመወዝ ሳያድር እንዲከፈል ያዛል። እንዲያውም ሰራተኛን ነገ ተነገ በስቲያ ማለት ሃጢያት ነው። “ድሀ ነውና፦ ነፍሱም ጠንክራ ትፈልገዋለችና ወደ እግዚአብሔር እንዳይጮህብህ ሃጢያትም እንዳይሆንብህ ደሞዙን ፀሐይ ሳይገባ በቀኑ ስጠው።“ (ዘዳ.24፥15) በሕይወያችን ሆነ በሌሎች ሰዎች ሕይወት ለሰራነው ስራ ጌታ ደሞዝ አለው።

ሁለተኛው የዮሐንስ መልእክት 2014

35 www.tlcfan.org

“እነሆ እርሻችሁን ያጨዱት የስራተኛ ደሞዝ በእናንተ ዘንድ ተቀምጦ ይጮኻል፣ የአጫጆች ድምፅ ወደ ጌታ ጸባኦት ገብቷል።”

ያቆ.5፥4…

ይህ ከላይ ያለው ጥቅስ ምን ማለቱ እንደሆነ በዝርዝ ማወቅ ከፍለጋዝሁ። እግዚአብሔር ገንዘብህን ይፈልጋልን? የሚለውን መጽሐፊን ያንብቡት። በአምስቱም ጊዜያት የተቀጠሩት ደሞዝ አንድ አይነት መሆኑ ስራው ሲጠናቀቅ ተገለጠ። ከሁሉም ብዙ ስራ የሰሩት ወይም በወይኑ አትክልት ላይ የቆዩት የማለዳዎቹ ነበሩ። እነርሱም አንድ ዲናር ብቻ ተቀበሉ። ሌሎቹ ግን በባለቤቱ ሙሉ ፍቃድ ከመጀመሪያዎቹ እኩል ተክፈላቸው። ብዙ መከራና የጸሃይ ትኩሳት አላገኛቸውም። መጨረሻ የተቀጠሩት ምን ያህል እንደ ሚከፈላቸው አያውቁም። የሚገባቸውን ግን እንደሚቀበሉ ያውቃሉ። ማለዳ የገቡትን ደሞዝ ሲያውቁ የእነርሱ ደሞዝ ጠዋት ከተቀጠሩት እንደሚያንስ ይገምታሉ። ምክንያቱም የማለዳዎቹ በአንድ ዲናር ተስማምተው እንደ ነበሩ የታወቀ በመሆኑ የአስራ አንድ ሰዓቱ ዝቅተኛ እንደሚሆን ይገመታል።

11 ሰዓቱ ስራ በማግኘታቸው ባለው በቀረው ሰዓት የባለቤቱን ስራ ሰሩ። ሌላው የሌላውን መመልከት እንደማይገባው ይህ ምሳሌያዊ የኢየሱስ ትምህርት ያስረዳናል። ፊተኞችም በመጡ ጊዜ አብዝተው የሚቀበሉ መሰሎአቸው ነበር። እነርሱም ደግሞ እያንዳንዳቸው አንድ ዲናር ተቀበሉ። ተቀብለውም እነዚህ ኋለኞች አንድ ሰዓት ሰሩ፤ የቀኑም ድካምና ትኩሳት ከተሸከምን ከእኛ ጋር አስተካከልሃቸው ብለው በባለቤቱ ላይ አንጎራጎሩ።” የነዚህ ሰራተኞች ችግር እነዚህ ነበሩ፦

ሀ/ ሌሎቹን ማየት፦

የፊተኞቹ በወይን አትክልት ሲሰሩ በነበሩ ወቅት በእርግጠኝነት ከወይኑ ፍሬ በልተዋል። የወይኑ ባለቤት ያን ያክል ተጨንቆ በቀን አምስት ጊዜያት ከቤት የወጣው ገና ለሚቆፈር ማሳ አይደለም። ይልቅም ወይኑ ተንዠርግጎ ሊወድቅበትና ወፎች ሊያጠፉት የደረሰ መሆኑን እንገነዘባለን። በተጨማሪም የወይኑ ጌታ የዚያኑ ቀን ክፍያ መክፈሉ የሁሉ ነገር ተስፋ በእጁ መኖሩን እናስተውላለን።

የወይኑን ባለቤት ከሰራተኞች አንድ ነገር የፈለገ ይመስላል። እንደ ሰው ስርዓት መክፈል የሚገባው አስቀድሞ በማለዳ ለተቀጠሩት መሆን ነበረበት። ነገር ግን አስቀድሞ ከኋለኞች ጀመረ። የፊተኞች በዚህ ጉዳይ እንደሚያዝኑ ያውቃል። ነገር ግን ማስተማር የፈለገው አንድ ነገር ሌሎችን መመልከት ሳይሆን የተስማሙበትን ተጠርተው የተቀጠሩበትን ውል ብቻ ማየት እንዲኖርባቸውን ነው።

ሲቀጠሩ የተስማሙት ከባለቤቱ ጋር ነው። የስምምነትም አንቀፅ ዋጋና አከፋፈል የሚል አለው ዋጋው አንድ ዲናር፣ የስራ ቀን ዛሬ፣ ክፍያ ሲመሽ፣ በቃ፣ ከዚህ ውጭ ያሉ ነገሮች በሙሉ ዋጋ ቢስ ናቸው። የራሳቸውን ዋጋ ለሰው የተከፈለውን በመመልከት ቀየሩት። ውሉን በሁኔታዎች ሻሩት። ባለቤቱ ጠዋት የተናገረውን ማታ አይደግመውም ብለው ቀየሩት።

ሁለተኛው የዮሐንስ መልእክት 2014

36 www.tlcfan.org

ሌሎችን በማየት ዋጋቸውን በራሳቸው ፈቃድ ለማስተካከል ወሰኑ። በአእምሮአቸው ውሉን ሻሩት። ጌታው ግን ፈጽሞ አይቀያየርም ደሞዙም አንድ ነው። የመንግስተ ሰማይን ምሳሌ የሆነውን የወይኑን ባለቤት ባለማወቃችን ከመንግስተ ሰማያት ጌታ ጋር ብዙ ሁከት ውስጥ እንገባለን። ሌሎቹን መመልከት ከወይኑ ጌታ ጋር የተዋዋልነውን ውል እንድንሽር ይገፋፋናል።

ማንኛውም ሰራተኛ ሰው ከመንግስተ ሰማይ ወይን ጌታ ጋር ውል ሊኖረን ይገባል። ከመንግስተ ሰማይ ወይን ጌታ ጋር ውላችሁ ምንድን ነው? በምን ተስማማን? ይህ ውል በደሞዝ ክፍያ ጊዜ ይምታታ ይሆን? አንድ ዲናር ተስማምተን የሌሎችን በማየት የኛን ዋጋ እንተምናለን? የዋጋችን ተመን የሌሎች ደሞዝ ነው? ወይስ በማለዳ የተዋዋልነው ውል? እግዚአብሔር በአዲስ ኪዳን የገባው ኪዳን ምንድ ነው? በብሉይስ ኪዳን የገባው ምንድን ነው? ኪዳን ካለ ውል አለ፣ ውል ሰጭ፤ ውል ተቀባይ ውል አስፈፃሚ አለ። እንግዲህ ይህን ውል በምን እንሻረው?

ከዝያ ወራት በኋላ ከእስራኤል ቤት ጋር የምገባው ቃል ኪዳን ይህ ነውና ይላል ጌታ ሕጌን በልቡናቸው አኖራለሁ በልባቸውም እፅፈዋለሁ። እኔም አምላክ እሆናቸዋለሁ እነርሱም ሕዝብ ይሆኑኛል። (ዕብ.8፥10) ውል ይህ ነው። ውሉ የእግዚአብሔር ሕግ በልቦናችን መፃፍ ነው። የሚፅፈው እግዚአብሔር ነው። የመፃፊያውም አውድማ ልብ ነው። ይህ ከሆነ ለዚህ ሕዝብ እግዚአብሔር አምላኩ ነው።

ይህ ሕዝብ የእግዚአብሔር ሕዝብ ነው። ነገር ግን በእግዚአብሔር ጣት የእግዚአብሔር ሕግ (ቃል) ያልተፃፈለት ሰው በመጨረሻ ቀን ቀርቦ ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ ቢለው የዚህ ሰው እንዲህ ብሎ መጥራት ውሉን አይሽርም። እዚህ ሰው ውስጥ የተፃፈ የእግዚአብሔር ቃል ከኖረ ይህ ሰው የእግዚአብሔር ሰው ነው። ዓርማ ያለው፣ ማህተም ያለው ይህ ነው። ብዙዋች ግን ይህን የእግዚአብሔርን ሕግ ሰዎችን በማየት ሊሽሩት ይሞክራሉ። ዉሉ የቃል ውል ሆኖ፥ ከቃል ውጭ ያለ ውልን ይሻሉ።

ለምሳሌ ለእገሌ ይህን በማድረግህ አሁን የምፈልገው ይህን ነው። ፓስተር እገሌ ይህን ያህል ይከፈለዋል፥ እኔ ግን ይህን ያህል ዓመት ሳገለግልህ በአንድ ዲናር ብቻ የሚሉ አሁንም አልታጡም። የአንተ ሕዝብ ያንተ አገልጋይ መሆኔ የሚታወቀው ይህንና ያንን ያደረክልኝ እንደ ሆነ ነው። የሚሉም አልታጡም......ወዘተ ሲሉ ይሰማል እነዚህ ከወይኑ ቁርስ ፣ምሳና መክሰስ መብላታቸውን የዘነጉ የወይኑን ስራን ወደ ፍፃሜ ማምጣት የተሳናቸው ሰራተኞች ድምጽ ነው። ይህ ሲባል ስምታችኋልን?

የመንግስተ ሰማይ ወይን ጌታ ቀድመው ወደ ማሳው ከገቡት አገልጋዬቹ ጋር የተስማማው ደሞዝ ዛሬ የእኛም ደሞዝ ነው። እንደውም ለመጨረሻው ዘመን ሰራተኛ እግዚአብሔር የሚበልጥን ነገር አይቶላቸዋል። (ዕብ.11፥39) ይህም ስራውን ወደ ፍፃሜ ስለሚጠቀለሉለት ሌሎችንም ስለማይመለከቱ ቀድመው እንዲከፈሉ አደረገ የሚበልጠውና ሙሉ ደሞዝ ማለት ይህ ነው። ደሞዝ ግን ከኖህ፣ ከአብርሃም.... ጋር የተዋዋለው የእኛም ደሞዝ ያው ነው።

ሁለተኛው የዮሐንስ መልእክት 2014

37 www.tlcfan.org

ሌሎችን መመልከት ካስፈለገ መልካም ስራ ለመማር፣ መልካም ባሕሪ ለመቅስም እንጂ ለምን እንደ እነርሱ አልሆንኩም የእነርሱን ዘመን አምጣልን፣ የሐዋርያትን ቅባት ስጠን ስንል ብንገኝ ከመንግስተ ሰማይ ወይን ጌታ ጋር እንጣላለን። ከእነርሱ ጋር የተዋዋለው ውል ያንተም ውል ነው።

ካንተና ካንቺ የሚጠበቀው በወይን ጌታ የተሰጠውን ስራና የስራውን ደምዝ አውቀህ የጌታህን ሥራ በጊዜው መፈጸም ነው። እርሱ ስራው ሳያልቅ አይከፍልህምና በሒወታችንም ሆነ በአገልግሎታችን ስራው ላይ ፍጻሜን እናምጣ። ቃል እንደ ገባልህ ዋጋህን ይህን ያህል አያገኝም በተባልክበት ስፍራ በአደባባይ ሁሉ እያየ በእጅህ ጌታህ ያስረክብሃል።

እውነተኛ የአገልግሎትም ሆነ የሕይወት ምሳሌ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ማድረግም ከሆነ ከእርሱ በላይ እንጂ ከሌሎች ስዎች በላይ አይደለም። ስለዚህ ወገኔ ሌሎችን አትመልከቱ። ይህ ከመንግስተ ሰማይ ወይን ጌታ የመጣ ንፁ የእውነት ትምህርት ነው።

ለ/ ማንጎራጎር፦

ከአምስቱ ሰዓት ሰራተኞች የመጨረሻው ሰዓት ተቀጣሪዎች በመጀመርያ ተቀበሉ። የዚህን የመጨረሻው ሰዓት ሰራተኛ ሰው ደሞዝ አራቱም ተመለከቱት። የመጨረሻው ተደሰተ ሌሎቹ አንጎራጎሩ። ይህ ሰው ትንሽ ቢሰጠው ሁሉ ደስ ይላቸው ይስማማቸውም ነበር። ይህ ሰው አንድ ዲናር ማግኘቱ የማንጎራጎሩ መነሻ ሆነ። በዚህ አንድ ዲናር ማግኘት የሁሉ ማጉረምረም መነሻ በማድረግ በጌታው ተነሱበት።

የወይኑን ጌታ ኢየሱስን አላዋቂ ሊያደርጉት ተነሱ። ከአምስቱ የአራቱ ሰዓት ሰራተኞች ቅር አላቸው። ቅሬታቸውንም በማስረጃ አቀረቡ። ማስረጃቸው ትክክል ቢመስልም መሰረት የሌለው ከቅንዓት የመነጨ ነበር። የ11ኛ ሰዓቱ ሰው የደሞዙን ልክ ባያሳያቸው ማንጎራጎር ባልተገኘባቸው ነበር። ነገር ግን የተሰጠው በግልጥ ነበርና በቅንዓት መንፈስ አንጎራጎሩ። ከአምስት አራቱ ሰማንያ በመቶው አንጎራጎረ። ዛሬም እንዲሁ ነው። የያቆብ ወንድም ይሁዳ ስለ ዕድላቸው የሚያንጎራጉሩትን በግልፅ አስቀመጣቸው።

“እነዚህ እንደ ምኞታቸው እየሄዱ የሚያንጎራጎርን ስለ ዕድላቸው የሚያጉረመርሙ ናቸው፣ እንዲረባቸው በሰው ፊት እያዳሉ አፋቸው ከመጠን ይልቅ ትላቅ ቃል ይናገራል፣” ይሁዳ(16)

የሚያንጎራጉር ሰው እንዲያውም የሚያዳላ እርሱ ነው። በማንጎራጎራቸው ምክንያት ከሚጠብቀው በላይ ታላቅና ክፉ ቃል ከአፋቸው በጌታ ላይ ይወጣል። የወይኑንም አትክልት ጌታ በታላቅ ቃል ተናገሩት። ስም ጠርተው ለምን ለ11ኛ ሰዓቱ እዲህ ሰጠኸው አሉ። የቀኑን ትኩሳት፣ ድካም ተሸክመን በማለት የማንጎራጎርያ ርዕስ አደረጉት።

ሁለተኛው የዮሐንስ መልእክት 2014

38 www.tlcfan.org

የቀኑ ትኩሳትና ድካም አውቀው ከገቡ በኋላ ይህን ጉዳይ ለባልቤቱ ገለፁለት። ድካሙና ትኩሳቱ ዋጋው አንድ ዲናር ነው። ካልሆነ ሲጀመሩ አያዋጣኝም ማለት ተገቢ ነበር። ዛሬም የእግዚአብሔርን ሥራ በማጉረምረምና በደሞዝ ምክንያት ቸል የሚሉ የወይን ባቤቱን ተግሳጽም ሆን ቅጣት ሳይቀበሉ አይቀሩም። “የእግዚአብሔርን ስራ በቸልተኝነት የሚያደርግ የተረገመ ይሁን።” ተብሎ ተፏልና ነው።

ባለንበት ዘመን ብዙዎች ስለ እምነት ብለው በእስርና በተለያየ ሁኔታ ከእኛ ቀድመው ዋጋ ስለ ከፈሉ ቀዳሚ አባቶች ሲተረክ በመድረክም ሆን በጋዜጦች መስማት የተለመደ ነው። እነዚህ የእግዚአብሔር ስዎች ቢኖሩም ካአምላካቸው ጋር ተስማምተው የገቡበት እንጂ በአሁን ዘመን ከመጡት አገልጋዬች የተለየ ነገርም ሆነ ደሞዝ የላቸውም። ራሳቸውን በአዲሱና በትኩሱ ትውልድ ላይ ማክበድም ሆነ ማኩራት አይገባቸውም። እንደውም አንዳዶቹ ቀደምት ሰራተኞች ዋጋ ከፍለናል ባዬች ከ11 ሰዓታት በፊት ከተቀጠሩት የተለየ ባሕሪና ጥያቄ የላቸውም።

ሐ/ ምቀኝነት፦

“እርሱ ግን መልሶ ከእነርሱ ለአንዱ እንዲህ አለው።፦ ወዳጄ ሆይ አልበደልሁም በአንድ ዲናር አልተስማማኸኝምን ድርሻህን ውሰድና ሂድ እኔ ለዚህ ለኋለኛው እንደ አንተ ልሰጠው እወዳለሁ በገንዘቤ የወደድሁትን አደርግ ዘንድ መብት የለኝምን ወይስ እኔ መልካም ስለ ሆንሁ ዓይንህ

ምቀኛ ናትን” አለው።

እንግዲህ መንግስተ ሰማይ ይህን የወይን ባለቤትን ከመሰለች የምቀኞች መድሐኒት ነች ማለት ነው። ከምቀኞች ጋር አብራ የምትቆም ሳትሆን ምቀኞችን ታሳፍራለች። ምቀኞች የሚያፍሩት በመንግስተ ሰማያት መልካምነት ነው። ምቀኞቹ ባለቤቱ የወደደውን እንዳያደርግ በዓይናቸው ቀኑ። በሌላው የሚመቀኝ ከመንግስተ ሰማያት በምቀኝነቱ የሚያተርፈው አንዳች የለም። አንዱን ዲናር ይዘህ ሂድ አለው እንጂ በማንጎራጎሩ የተጨመረ ሳንቲም የለም። መንግስተ ሰማያት የምትሰራው በዉሉ መሰረት ነው።

እንግዲህ ከመንግስተ ሰማይ ጋር ለመስማማት ምቀኝነትን ለማራቅ መፍትሔው የራስን ድርሻ ብቻ ተመልክቶ መጓዝ ነው። የመንግስተ ሰማይ ምሳሌ የሆነው ባለቤት ምቀኞችን መንጥሮ ለማውጣት የተጠቀመበት ዘዴ ደሞዝ አከፋፈል ላይ ነው። ይህ ባለቤት እያወቀ በመጀመርያ ለ11ኛ ሰዓቱ ሰው ደሞዙን ከፈለ። በዚህ ምክንያት ምቀኞች ከቅኖች ተለዩ። የምቀኞች ማንነት የተገለፀው በመንግስተ ሰማያት ቸርነትና በባልንጀራው አንድ ዲናር ነው። መንግስተ ሰማያት ውሉን ሳታፈርስ ለቅኖችና ለትጉ ሰራተኞች ጨምራ መስጠት ትችላለች። ምቀኛም ቢሆን ደምወዙ አያጣም። ለእያንዳንዱ እንደ ስራው ትከፍላለች። የመንግስተ ሰማያት ዋጋ አከፋፈል በአብዛኛው እኩል የሚያደርግ ነው። ለአምስቱም ሰራተኞች አንድ ዲናር ከፈለች። ይህ አሁን የመጣ ስለሆነ ተብሎ ደሞዝ ሲቀንስ ያኛው ብዙ ጊዜ ተጎዳ ደከመ በማለት ዋጋን ሲጨምር አልታየም። ይልቅም ለከፋይ እንዲቀል ሁሉን አሰልፎ አንድ ዲናር ከፈለ። ሁላችን የተመደበልንን ስራ እንስራ። እግዚአብሔር ለሰዎች የሰጠውን ፀጋ ከቻልን እናድንቅ ካልተቻለ ልባችንን በሰው ጉዳይ አንጣል። ልክ እንደ ትሁት ሙሴ እንሁን።

ሁለተኛው የዮሐንስ መልእክት 2014

39 www.tlcfan.org

”ከልጅነቱ ጀምሮ የሙሴ አገልጋይ የነበረው የነዌ ልጅ እያሱ።- ጌታዬ ሙሴ ሆይ፤ ከልክላቸው አለው፣ ሙሴም።- የእግዚአብሔር ሕዝብ ሁሉ ነቢያት ቢሆኑ እግዚአብሔርም

በእነርሱ ላይ መንፈሱን ቢያወርድ አንተ ስለ እኔ ትቀናለህን አለው።” (ዘሁልቁ.11፥28-29)

ከልጅነቱ ጀምሮ በሙሴ ስር ያደገ የነዌ ልጅ ይህን ፈተና ማለፍ ተሳነው። ብዙ ዘመን አገለገለ በዚህ ጉዳይ ግን ማንነቱ ተፈተነ። ሙሴ ግን እግዚአብሔር ሰው ሁሉ ነብያት ቢያደርግ ሁሉ ትንቢት ቢናገሩ ደስተኛ እንደ ሆነ ለኢያሱ በማስተማር ቅንነቱ ገለፀ። ይህም ብቻ አይደለም የእግዚአብሔር መንፈስ በሁሉ ላይ ቢወርድ ፣ ሁሉ የመንፈስ ተሸካሚ ቢሆኑ የሙሴ ታላቅ ደስታ ነበር። ኢያሱ ግን ከሙሴ በትሩን ከመቀበሉ በፊት ይህን ትምህርት መማር ተገባው። እኛም ከበትር በፊት ይህን እንማር። ከአግልግሎትና ከስራ በፊት ከቅናት መንፈስ ነፃ ልንወጣ ይገባል።

መ/ አንዱን ጠርቶ፦

በምቀኝነት ቀንበር የወደቁ ብዙ ስለ ነበሩ ረብሻውን ለማስቆም ባለቤቱ ለሁሉ አልተናገረም። በጩኸት ላይ ጩኸት እንዳይታከል ከእነዚህ ጯሂዎች መሃል አንዱን በመጥራት ውሉን ከመጀመርያ ጀምሮ አብራራለት። ለማለዳዎቹ አንድ ዲናር እንደ ተስማማ ለማታዎቹ ግን በሱ ፍቃድ እንዳደረገ ገለፀለት። ባለቤቱ ተጎዳ እንጂ የማለዳዎቹ አልተጎዱም ብሎ ገለጠለጥ።

ኢየሱስ ክርስቶስ በምድር ሲያስተምር ብዙውን ጊዜ አንዱን ጠርቶ ሲነጋገር ይስተዋላል። ይኸውም ጴጥሮስ ነበር። ”ጴጥሮስም እንዲህ አለው......” የሚሉ ሃረጎችን እንመለከታለን። ኢየሱስ አንድ ስለ ነበረ አንድን ጉዳይ ለማስረዳት አንድን ሰው ይጠራል። ኢየሱስ እግዚአብሔርን ሲወክል ጴጥሮስ ሐዋርያትን ይወክላል። ጩኸት፣ ረብሻ፣ ከአፍ ላይ ሲነጠቅ መታወክ ይወገዳል። አንድ ሰው ጠርቶ መናገር በዚህም አንድ ሰው ሌሎችን ሁሉ ይደርሳቸዋል። እግዚአብሔርም ከአንድ ሰው ጋር የሚሰራው ይበዛል። ለምሳሌ አዳም፣ አብርሃም፣ ኖኅ፣ ዳንኤል፣ ኢዮብ፣ ኤርሚያስ ....... በሌላም መልኩ በዓለም ላይ ከመቶ የሚበልጡ መንግስትታትና ነገስታት እያሉ ከአንድ መንግስትና ንጉስ ጋር ቃል ኪዳን አደረገ። ከእስራኤል ሃገር ጋር እና ከንጉስ ዳዊት ጋር።

የመንግስተ ሰማይ ባለቤት የሆነው ነገሩን የዘጋው የሚያንጎራጉርትን አፍ በመዝጋት ነው። ይህ ግን በቁጣ፣ በቅጣት ወይንም በሌላ ሳይሆን በማስተማር ነው። ምቀኞች የያዟት ነገር በቂ እንደ ሆነ በተለይም በውሉ መሰረት እንደ ተፈፀመ በማስገንዘብ ነው።

በዚህ ባለንበት ዘመን ግን የእግዚአብሔር ቤት መድረክ የማንም ሃሳብ መስጫ ሆኗል። ይህ የሆነበት ምክንያት ከላይ ያየነው የወይን ባለቤት አይነት ባሕሪ ያለው ሰው መጥፋቱ ነው። እግዚአብሔር በቤቱ ይሾማል ነገር ግን የበላዩን እግዚአብሔርን ያጣ የበታቹን የተሾመበትን ያጣል። ባጠቃላይ የበላይ የሌለው የበታች የለውም። አዳምን ተመልከቱ እግዚአብሔር የበላይ ባደረገበት ዘመን ሁሉ የበታች ነበረው። ያሚገዛው ነበረው የበላዩን ያጣ ጊዜ የበታቹ ያሳድደው ጀመር። ለምሳሌ አንበሳ፣ ቀበሮ፣ ጅብ...ወዘተ። ዛሬም ልተመራው የተሰጠህ ሕዝብ ካሳደደህ ጌታህ ከላይህ እንደጣልከው እወቅ። የበታች እንዲኖርህ የበላይ ይኑርህ ለበላይህም በስርዓት ተገዛ።

ሁለተኛው የዮሐንስ መልእክት 2014

40 www.tlcfan.org

ሠ/ ታማኝነት፦

ማልዶ የወጣ የወይን ባለቤት ቤቱ አርፎ የተቀመጠው የ11 ሰዓቱን ቀጥሮ ከተመለሰ በኃላ ነበር። ይህ ባለቤት ጊዜውን ሁሉ፣ አዕምሮውንና ጉልበቱን የሰጠው ሰራተኛ በማግኘት ላይ ነው። ይህ ሰው ቀኑን በሙሉ በውጭ ነው የዋለው። የተገኙትን ይዞ ለመግባት ብቻ ይገባል። አንዳዶቹንም ወደ ወይን አትክልቴ ሂዱ ይላቸዋል። የሚወጣው አደባባይ በመንገድ ነው። በዚህም ምክንያት በወይኑ ላይ የቀጠራቸው ሰራኞች የቀጣሪ ክትትል የለባቸውም። ይህ በመሆኑም መለገም ፣ ወሬን በማውራት ጊዜን ማቃጠል ይችላሉ። ቀጣሪው ሩቅ በመሆኑ ተቆጣጣሪያቸው የራሳቸው ህሊና፣ ለወይኑ ያላቸው ፍቅር፣ ታማኝነትና የባለቤቱ ጭንቀት ሽክም ነው።

ብዙ የዚህ ዘመን ሰራተኞች እግዚአብሔር ሲመሻሽ የማይመጣና የተሰራውን ስራ የማይመለክት መስሏቸው የእግዚአብሔርና የእግዚአብሔርን ህዝብ ጊዜና ዘመን በከንቱና ፍሬ ቢስ በሆነ የወይኑን አትክልት ስራ ወደ ፍፃሜ የማያመጣን ወሬ በሟሟቅ ያባክናሉ ያገላግላሉ። ከበታቻቸው ጌታ የሚልካቸውን ይደበድባሉ። ሉቃ.12

እግዚአብሔር ግን ሰራተኞችን በላይ በላዩ በመጨመር ስራውን ይፈጽማል። ይህ ብቻ አይደለም ሲመሻሽ እራሱ ተገልጦ ማንነታቸውን ባደባባይ ለሁሉ ይገልጠዋል። የእግዚአብሔር ቅጥረኞች ባለቤቱ ሩቅ ነው እስከ አሁን አልፈረደብኝም ብለን አንታበይ። ተመክሮ ተመክሮ ያልተመለስ ድንገት በእግዚአብሔር መገለጥ ይሰበራል መመለሻም የለውም። በውሰጡ የተደበቀው ክፉ ባሕሪ ይገለጣል። ስለዚህም ዛሬ ዮሐንስ በሁለተኛው መልዕክቱ እንዳስተማረን በእውነትን በፍቅር እንስራ። ይህም ከእግዚአብሔር ሙሉ ደሞዝ እንድንቀበል ያደርገናል።

ሁለተኛው የዮሐንስ መልእክት 2014

41 www.tlcfan.org

የክርስቶስ ትምህርት

“9 ለሚወጣ ሁሉ በክርስቶስም ትምህርት ለማይኖር ሰው አምላክ የለውም፤ በክርስቶስ ትምህርት ለሚኖር አብና ወልድ አሉት፣ 10 ማንም ወደ እናንተ ቢመጣ ይህንም ትምህርት ባያመጣ

በቤታችሁ አትቀበሉት ሰላምም አትበሉት፤ 11 ሰላም የሚለው ሰው በክፉ ሥራው ይካፈላልና።”

የክርሰቶስ ትምህርት በቁጥር አምስት ላይ እንደተመከትነው ፍቅር ነው። “አሁንም፥ እመቤት ሆይ፥ እርስ በርሳችን እንድንዋደድ እለምንሻለሁ፤ ይህች ከመጀመሪያ በእኛ ዘንድ የነበረች ትእዛዝ (ትምህርት) ናት እንጂ አዲስ ትእዛዝን(ትምህርት) እንደምጽፍልሽ አይደለም። 6 እንደ ትእዛዛቱም(ትምህርቱም) እንሄድ ዘንድ ይህ ፍቅር ነው፤ ከመጀመሪያ እንደ ሰማችሁ፥ በእርስዋ ትሄዱ ዘንድ ትእዛዙ (ትምህርቱ) ይህች ናት።

የክርስቶስ ትምህርት መነሻው ፍቅር ነው። ፍቅር በትምህርቱ የመጀመሪያውን ስፍራ ይይዛል። ደግሞም የዕብራውያን ጸሃፊ እንደ ሚያስተምረው ኢየሱስ በመጀመሪያ የሚያስተምራቸው የሚናገራቸው ቃሎች በቀደሙ አቢያተክርስቲያናት ዘንድ መሰረታዊ ትምህርት ተብለው የሚታውቁ ትምህርቶችም እንዳሉት አስቀምጣጧል፣

“1-2 ስለዚህ የክርስቶስን ነገር መጀመሪያ የሚናገረውን ቃል ትተን ወደ ፍጻሜ እንሂድ፤ መሠረትን ደግመን አንመሥርት፥ እርሱም ከሞተ ሥራ ንስሐና በእግዚአብሔር እምነት፥ ስለ ጥምቀቶችና እጆችንም ስለ መጫን ስለ

ሙታንም ትንሣኤ ስለ ዘላለም ፍርድም ትምህርት ነው፣” ዕብ.6፥1-2

እነዚህ የክርስቶስ ትምህርቶች ከአንድ ሰው ልብ በጠላት ሊወሰዱ የሚችሉ ሰለ ሆኑ በልባችን ከቃል ለቃሚ ልንጠብቅ ይገባል። እነዚህ ትምህርቶች የመንፈሳዊ ሕይወታችን እድገት መለኪያም ናቸው። የመሰረታችን ጥንካሬ ያህል እድገታችንም እንዲሁ ነው። መሰረታዊ ትምህርት የሌለው ሰው ጠንካራ ምግብ መመገብ አይችልም። ይህ መሰረታዊ ትምህርት ከልባችን ከተወሰደ ደግሞ ደግመን እነዚህን የክርሰቶስ ትህርቶች ልንመሰርታቸው ይገባል። በእውነት እነዚህን መሰረታዊ የክርስቶስ ትምሕርቶች ጠንቅቀህ ታውቃለህን?

የክርስቶስን ትምህርት የማያመጣውን አትቀበሉት ሰላምም አትበሉት አለን። ይህን ቃል በመንፈስ ተመርቶ የሚናገረን በመንፈሳዊ ሕይወቱ ብዙ መንፈሳዊ ልምድ ያካበተው ሽማግሌው ዮሐንስ ነው። ይህ ብቻ አይደለም ቃሉ እንደሚል ይህን አይነት ሰው ጋር የሚተባበር ሰው የሰውየውን አይነት ፍርድ ይቀበላል። ከክፉ ስራው ጋር ይተባበራል ብሎ እውነቱን ይነግረናል። ሰለዚህ ክርስቶስ ካሰተማረው ፍቅር ውጭ የወጣ ትምህርት የሚያመጣ ሰውን መስማትም ሆነ ህብረት ማድረግ አይገባም።

ብዙዎች በዚህ ዘመን የራሳቸው አገልገሎት በሚሰሙዋቸው ዘንድ ተቀባይነትን እንዲያገኝ በንግግራቸው ወይም በትምህርታቸው ውስጥ ሌሎች አገልጋዬች የሚያሰጠላ መንፈስን በመልከታቸው ጀርባ ያስተላልፋሉ። ጥላቻን የያዘና የተሸከመ ትምህርት ሁሉ ከጌታ አይደለም።

ሁለተኛው የዮሐንስ መልእክት 2014

42 www.tlcfan.org

እግዚአብሔር ፍቅር ነው። ወደ ፍቅር የማይጠጋ የማያስጠጋ ትምህርት በሙሉ ለሚሰማውም ሆነ ለሚያሰማው ቅጣትን ያከማቻል። የክርስቶስን ትምህርት የማያመጣ ቢኖር በመጀመሪያ ደረጃ በትዕቢት ተነፍትቷል አንዳችም አያውቅም። ሰለዚህ ከእንደዚህ አይነቱ ሰው መልካም እውቀት አይገኝም። ይህ አይነቱ ሰው ጊዜን ያባክናል አዕምሮንም ያበክታል። የራሱን የሃጢያት ቅጣት እንድንካፈል ያደርገናልና እንጠንቀቅ።

“3 እነዚህን አስተምርና ምከር። ማንም ልዩ ትምህርት የሚያስተምር ከጌታችንም ከኢየሱስ ክርስቶስ በሆነው ጤናማ ቃልና እግዚአብሔርን ለመምሰል በሚስማማ ትምህርት የማይጠጋ ቢሆን፥ 4-5 በትዕቢት ተነፍቶአል አንዳችም አያውቅም፥

ነገር ግን ምርመራን በቃልም መዋጋትን እንደ በሽተኛ ይናፍቃል፤ ከእነዚህም ቅንዓትና ክርክር ስድብም ክፉ አሳብም እርስ በርስ መናደድም ይወጣሉ፥ አእምሮአቸውም በጠፋባቸው እውነትንም በተቀሙ፥ እግዚአብሔርን መምሰል ማትረፊያ የሚሆን

በመሰላቸው ሰዎች ይገኛሉ። እንደነዚህ ካሉት ራቅ።” 1.ጢሞ.6፥3-6

ጳውሎስ ለጢሞቴዎስ ይህንን በደንብ አድርጎ አስተምሮታል። የክርስቶስ ትምህርት ጤናማ ትምህርት ሲሆን ከእርሱ ትምህርት የሚለየው ግን ትምህርቱ ራሱ በሽታና በሽተኛ የሚያደርግ ነው። የብዙ በሽታዎች ምንጭ የተሳሳተ የጌታ ቃል መሞላት ነው። እንደ እዚህ አይነቱ ሰው እውነተኛ የእግዚአብሔር ቃል ሲማር ይፈወሳል። ምሳሌ ሶስት ላይ የሚናገረውም ይህንን ነው። እውነተኛውን የክርስቶስን ትምህርት በልቡ የሚጠብቅ ሰው ለስጋው ፈውስ ለአጥንቱም ጠገን ይሆንለታል። በዚህ ብቻ ማጠቃለያ የማንሰጠው የኢየሱስ ክርስቶስ እውነተኛ ትምህርት በእኛ ላይና በሚሰሙት ሁሉ ላይ የተለያዩ መልካም ስራዎችን ይሰራል።

የኢየሱስ ክርስቶስ ጤናማ ትምህርት እግዚአብሔር ለመምሰል የተስማማ ነው። ይህን ሰንል እግዚአብሔር እንድንመስል አዕምሮአችንን ይለውጣል። አንዱም እግዚአብሔር የምንመስልበት ነገር ፍቅራችን ነው። ይህን የክርስቶስን ትምህርት የማያመጣ በትዕቢት የተነፋና አንዳች የማያውቅ ነው ብሎ የእግዚአብሔር ቃል ያስቀምጣል። አንዳች ከማያውቅና ከትዕቢተኛ ሰው አንዳች መልካም ነገር መጠበቅ ሞኝነትና ጥፋትን ለራስ ማከማቸ ነው።

እንደ እነዚህ አይነት ሰዎችን የምንለይበት ቁልፎችን የእግዚአብሔር ቃል ያሰቀምጥልናል። በቃሉ ለተገለጠ ነገር መታዘዝ እንጂ መገለጥ አያስፈልገውም። እነዚህ ሰዎች ላይ የሚገለጡ ባሕሪዎች ከንቱ የቃል ምርመራ፣ በቃል መዋጋት፣ ቅንዓት፣ ክርክር፣ ስድብ ፣ ክፉ ሃሳብና እርስ በእርስ መናደድ ናቸው። ይህ ባሕሪያቸ በቀላሉ እንደዚህ አይነቶችን ሰዎች እንድንመነጥር ያደርገናል። እንደዚህ አይነት ስዎች በዙሪያህ ካሉ እርምጃ ምን መሆን እንዳለበት የእግዚአብሔር ቃል ይናገራል፣ “እንዲህ ካሉት ራቅ”

እነዚህ ሰዎች አዕምሮቸው የጠፋባቸው እውነትንም የተነጠቁ ሰዎች ናቸውና እውነት ከእነርሱ ዘንድ አይገኝም። የተለያዩ ታምራትን ሊያደርጉ ቆንጆ ቃላቶችን ሊናገሩ ይችላሉ ነገር ግን በጌታ ዘንድ ቢቀርቡ አርሱ አላውቃቸው ይላቸዋል።

ሁለተኛው የዮሐንስ መልእክት 2014

43 www.tlcfan.org

ትልቁ ፍላጎታቸው ደግሞ እግዚአብሔር በመምሰል ሁሉ ከፈልጉ የሚፈልጉት ለማትረፍ ነው። ይህ ትርፍ ደግሞ ገነንዘብንና ዝናን የሚያጠቃልል ነው። ጳውሎስ ትምህርቱን በመቀጠል እንዲህ ይላል፦

“6 ኑሮዬ ይበቃኛል ለሚለው ግን እግዚአብሔርን መምሰል እጅግ ማትረፊያ ነው፤ 7 ወደ ዓለም ምንም እንኳ አላመጣንምና፥ 8 አንዳችንም ልንወስድ አይቻለንም፤

ምግብና ልብስ ከኖረን ግን፥ እርሱ ይበቃናል፣9 ዳሩ ግን ባለ ጠጎች ሊሆኑ የሚፈልጉ በጥፋትና በመፍረስ ሰዎችን በሚያሰጥምና በሚያሰንፍ በሚጎዳም በብዙ ምኞትና

በፈተና በወጥመድም ይወድቃሉ። 10 ገንዘብን መውደድ የክፋት ሁሉ ሥር ነውና፥ አንዳንዶች ይህን ሲመኙ፥ ከእምነት ተሳስተው በብዙ ሥቃይ ራሳቸውን ወጉ፣

11 አንተ ግን፥ የእግዚአብሔር ሰው ሆይ፥ ከዚህ ሽሽ፤ ጽድቅንና እግዚአብሔርን መምሰል እምነትንም ፍቅርንም መጽናትንም የዋህነትንም ተከታተል፣ 12 መልካሙን የእምነት ገድል ተጋደል፥ የተጠራህለትንም በብዙም ምስክሮች ፊት

በመልካም መታመን የታመንህለትን የዘላለምን ሕይወት ያዝ፣ 13 ሁሉን በሕይወት በሚጠብቅ በእግዚአብሔር ፊት፥ በጴንጤናዊውም በጲላጦስ ዘንድ መልካሙን መታመን በመሰከረ በክርስቶስ ኢየሱስ ፊት አዝሃለሁ፤ 14 ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እስኪገለጥ ድረስ

ያለ እድፍና ያለ ነቀፋ ሆነህ ትእዛዙን ጠብቅ።” 1.ጢሞ.6፥6-14

እኛ ግን ልንኖር የሚገባውና ልንከተለው የሚገባውን እውነተኛ ትምህርት እውነተኛ መንገድ እንዲህ ዘርዝሮ አስቀመጠልን። የክርስቶስን ትምህርት የማያመጡ ሰዎች ትምህርታቸው የሚያሳድፍ። የሚጎዳ፣ የሚሰሙት ሰዎች ወደ ታች ቁልቁል የሚያሰጥም፣ በብዙ ምኞትና ፈተና የሚያገባ በመጨረሻም ጥፋትና መፍረስን ሞትን የሚያመጣ ነው።

የእግዚአብሔር ቃል ደግሞ ደጋግሞ ከነዚህ ሰዎች ትምህርትና ከሚያስተምረው ሰው ሽሽ ይለናል። በመቀጠልም ልንከተለው የሚገባውን ነገር ያሳየናል። እርሱም ጽድቅንና እግዚአብሔርን መምሰል እምነትንም ፍቅርንም መጽናትንም የዋህነትንም መከታተል ማድረግ መለማመድ ነው። ከኛ የሚጠበቀው የታዘዝነው መልካም ምስክርን ብቻ በሚመሰክረውና በሚያስተምረው ጌታ ፊት መሆኑን አውቀንና ተገንዝበን መታዘዝ ማድረግ ነው። ይህን ትዕዛዙን ብናደር ክርስቶስ እስከ ሚገለጥ ድረስ ያለ እድፍና ያለ ነቀፋ ያደርጉናል።

ይህን ትዕዛዝ ማድረግ መልካም የእምነት ገድልን መጋደል ነው። ይህ ደግሞ ውጊያ እንዳለው ያሳያል። ድል ግን የእኛ ነው። ምክንያቱም ያዘዘን ጌታ ሊረዳን ከእኛ ጋር ነውና ነው። ደግሞም ትእዛዙን ማድረግ የተጠራንለትንም በብዙም ምስክሮች ፊት በመልካም መታመን የታመንለትን የዘላለምን ሕይወት የሆነውን እውነት የሆነው ኢየሱስን ማወቅና መያዝ ነው።

ጌታም በወንጌል ላይ “የሎጥን ሚስት አስቧት” ይለናል። ከእንደ እነዚህ አይነት ሰዎች መሸሽ ብቻ ሳይሆን ዞር ብለንም ልንመለከታቸው አይገባም። በእነርሱ ላይ የእግዚአብሔር ቁጣ ይገለጣል። የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ ተቀብሎ ወደ ፊት በፍርሃትና በጽድቅ የሚመላለስ ሰው ጋር ብቻ ሕብረት ልናደርግ ይገባል። ይህ ነገር ልክ እንደ ሎጥ ዋጋ የሚያስከፍል ጽናት ገድል ነው።

ሁለተኛው የዮሐንስ መልእክት 2014

44 www.tlcfan.org

“12 እንድጽፍላችሁ የምፈልገው ብዙ ነገር ሳለኝ በወረቀትና በቀለም ልጽፈው አልወድም፥ ዳሩ ግን ደስታችሁ ፍጹም እንዲሆን ወደ እናንተ ልመጣ አፍ ለአፍም ልናገራችሁ ተስፋ

አደርጋለሁ። 13 የተመረጠችው የእኅትሽ ልጆች ሰላምታ ያቀርቡልሻል።”

የእግዚአብሔር ቃል ጭምር ከወረቀትና ከቀለም ባለፈ ሁኔታ በግልጽ የሚደረግን ሕብረትንና አገልግሎትን ይደግፋል። ይህ ማለት ግን እግዚአብሔር መልክት እንዲጽፉ ስዎችን አያዝም ማለት አይደለም። ነገር ግን ከብዕርና ወረቀት የሚበልጠው ፊት ለፊት ሆኖ መነጋገርና መማማር ነው። ይህ ሲሆን ዮሐንስ በመልክቱ እንዳስቀመጠው ደስታችን ፍጹም ይሆናል። በጣም አስደሳች ይሆናል ማለት ነው።

እግዚአብሔር በብሉይ ኪዳን በብዕርና በወረቀት በባሪያዎቹ በማለፍ ብዙ ተናግሮን ነበር።

ነገር ግን በዘመን መጨረሻ ኢየሱስን ልኮ አፍ ለአፍ ተናገረን። ይህ ደግሞ የእግዚአብሔርና የሰው ሁሉ ደስታ እንዲፈጸም ታላቅን ስራ ስርቷል። አሁንም እርስ በእርስ መመካከር መጸለያችንን አንተው። ከጹሁፍ ባሻገር ሰዎችን በአካል ተገኝተን ማገልገልንም አንጠው ይህ በማድረግ የፍቅራችን ፍጹምነት እናጸናለን። እኔም የጌታ ጸጋ እንደረዳኝ ቅዱሳንን በጹሁፍ ሆነ በአካል በመገኘት አገልግላለሁ። ይህ ለእናንተም ይብዛ። ማራናታ!!!!!

ሌሎች መጽሐፎችን ለማግኘት ይህ ድረ ገጽ ይጫኑ።

www.tlcfan.org

.........................................................ተፈጸመ...........................................................