title of presentation - ርስቶስ_ክፍል_3...1.pdf · pdf fileየስርየት...

21

Upload: vuongthu

Post on 14-Feb-2018

273 views

Category:

Documents


9 download

TRANSCRIPT

Page 1: Title of Presentation - ርስቶስ_ክፍል_3...1.pdf · PDF fileየስርየት መንሥኤ፣ የእግዚአብሔር ፍቅር፥ የዮሐንስ ወንጌል 3:16 የእግዚአብሔር
Page 2: Title of Presentation - ርስቶስ_ክፍል_3...1.pdf · PDF fileየስርየት መንሥኤ፣ የእግዚአብሔር ፍቅር፥ የዮሐንስ ወንጌል 3:16 የእግዚአብሔር

ትምህርተ ክርስቶስ

ስርየት፤

የትምህርተ ግብረ ክርስቶስ ዐውድ፤

የግብረ ክርስቶስ ልዩ ልዩ ጥቅልል ምሳሌዎች፣

ክርስቶስ፥ ነብይ፣ ካህንና ንጉሥ መሆኑ፣

ክርስቶስ እንደ ነብይ፤

ክርስቶስ እንደ ካህን፤

ክርስቶስ እንደ ንጉሥ፤

ትምህርተ ግብረ ክርስቶስ፤

Page 3: Title of Presentation - ርስቶስ_ክፍል_3...1.pdf · PDF fileየስርየት መንሥኤ፣ የእግዚአብሔር ፍቅር፥ የዮሐንስ ወንጌል 3:16 የእግዚአብሔር

ትምህርተ ክርስቶስ

ስርየት፤

ትምህርተ ግብረ ክርስቶስ፤

Page 4: Title of Presentation - ርስቶስ_ክፍል_3...1.pdf · PDF fileየስርየት መንሥኤ፣ የእግዚአብሔር ፍቅር፥ የዮሐንስ ወንጌል 3:16 የእግዚአብሔር

ትምህርተ ክርስቶስ

ስርየት፤

ስርየት፥ ማለት ክርስቶስ ድነታችንን ለማስገኘት በሕይወቱና በሞቱ የሠራው ሥራ ነው።

የስርየት መንሥኤ፣

የስርየት አስፈላጊነት፣

የስርየት ባሕርይ፣

ትምህርተ ግብረ ክርስቶስ፤

Page 5: Title of Presentation - ርስቶስ_ክፍል_3...1.pdf · PDF fileየስርየት መንሥኤ፣ የእግዚአብሔር ፍቅር፥ የዮሐንስ ወንጌል 3:16 የእግዚአብሔር

የስርየት መንሥኤ፣

የእግዚአብሔር ፍቅር፥

የዮሐንስ ወንጌል 3:16

የእግዚአብሔር ትክክለኛ ፍርድ፥

ወደ ሮሜ ሰዎች 3:25

የስርየት አስፈላጊነት፣

“የማንኛውም ሰው ማዳን ለእግዚአብሔር በፍጹም አስፈላጊ ወይንም ግዴታ አይደለም”

2ኛ የጴጥሮስ መልእክት 2:4

“ነገር ግን እግዚአብሔር ሰውን ማዳን ከፈለገ ከልጁ ሞት በቀር ሌላ መንገድ አልነበረም”

የማቴዎስ ወንጌል 26:39፣ የሉቃስ ወንጌል 24:25-26፣ ወደ ሮሜ ሰዎች 3:25-26፣ ወደ ዕብራውያን 2:17

Page 6: Title of Presentation - ርስቶስ_ክፍል_3...1.pdf · PDF fileየስርየት መንሥኤ፣ የእግዚአብሔር ፍቅር፥ የዮሐንስ ወንጌል 3:16 የእግዚአብሔር

የስርየት ባሕርይ፣

ገቢራዊ ታዛዥነት (የክርስቶስ ስለ እኛ መታዘዝ)፣

በአርምሞ መታዘዝ (ክርስቶስ ስለ እኛ መከራ መቀበሉ)፣

በመላ ሕይወቱ መከራ መቀበሉ፣

የመስቀል ሥቃይ፣

ሥጋዊ ሥቃይና ሞት፣

ኀጢአትን የመሸከም ሥቃይ፣

ብቻውን መተው፣

የእግዚአብሔርን ቍጣ መሸከም፣

Page 7: Title of Presentation - ርስቶስ_ክፍል_3...1.pdf · PDF fileየስርየት መንሥኤ፣ የእግዚአብሔር ፍቅር፥ የዮሐንስ ወንጌል 3:16 የእግዚአብሔር

የስርየት ባሕርይ፣

ገቢራዊ ታዛዥነት (የክርስቶስ ስለ እኛ መታዘዝ)፣

ክርስቶስ የኖረው ኑሮ ለእግዚአብሔር በፍጹም መታዘዝ እኛን በመወከል ነው፣

የማቴዎስ ወንጌል 3:15፣ የዮሐንስ ወንጌል 8:29፣ ወደ ሮሜ ሰዎች 5:19፣ 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 1:30-31፣ ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 3:8-9

Page 8: Title of Presentation - ርስቶስ_ክፍል_3...1.pdf · PDF fileየስርየት መንሥኤ፣ የእግዚአብሔር ፍቅር፥ የዮሐንስ ወንጌል 3:16 የእግዚአብሔር

የስርየት ባሕርይ፣በአርምሞ መታዘዝ (ክርስቶስ ስለ እኛ መከራ መቀበሉ)፣

በመላ ሕይወቱ መከራ መቀበሉ፣የማቴዎስ ወንጌል 4:1-11፣ ወደ ዕብራውያን 5:8፣ ትንቢተ ኢሳይያስ 53:3፣ 1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 1:20-21

የመስቀል ሥቃይ፣ “ነፍሴ እስከ ሞት ድረስ እጅግ አዘነች፤ በዚህ ቆዩ ከእኔም ጋር ትጉ አላቸው።” የማቴዎስ ወንጌል 26:38

ሥጋዊ ሥቃይና ሞት፣የማርቆስ ወንጌል 15:24

ኀጢአትን የመሸከም ሥቃይ፣የብሉይ ኪዳን ዳራ፥

• ኦሪት ዘሌዋውያን 4:1-4፣ 16:15-22፣ ትንቢተ ኢሳይያስ 53:6

2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 5:21፣ ወደ ገላትያ ሰዎች 3:13፣ ወደ ዕብራውያን 9:28፣ 1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 2:24

ብቻውን መተው፣የማርቆስ ወንጌል 14:34፣ የማቴዎስ ወንጌል 26:56፣ የማቴዎስ ወንጌል 27:46

የእግዚአብሔርን ቍጣ መሸከም፣ἱλαστήριον - hilastērion (ሂላ-አስ-ቴ-ሪ-ኦን)- ስርየት፤

• ወደ ሮሜ ሰዎች 3:25፣ ወደ ዕብራውያን 2:17፣ 1ኛ የዮሐንስ መልእክት 2:2፣ 1ኛ የዮሐንስ መልእክት 4:10

መተው፣• የማቴዎስ ወንጌል 27:46፣ መዝሙረ ዳዊት 22:1-2

ፍጻሜ፣• የዮሐንስ ወንጌል 19:30፣ የዮሐንስ ወንጌል 10:17-18፣ የሉቃስ ወንጌል 23:46፣ ትንቢተ

ኢሳይያስ 53:11-12

Page 9: Title of Presentation - ርስቶስ_ክፍል_3...1.pdf · PDF fileየስርየት መንሥኤ፣ የእግዚአብሔር ፍቅር፥ የዮሐንስ ወንጌል 3:16 የእግዚአብሔር

ትምህርተ ክርስቶስ

የትምህርተ ግብረ ክርስቶስ ዐውድ፤

የግብረ ክርስቶስ ልዩ ልዩ ጥቅልል ምሳሌዎች፣

ትምህርተ ግብረ ክርስቶስ፤

Page 10: Title of Presentation - ርስቶስ_ክፍል_3...1.pdf · PDF fileየስርየት መንሥኤ፣ የእግዚአብሔር ፍቅር፥ የዮሐንስ ወንጌል 3:16 የእግዚአብሔር

የትምህርተ ግብረ ክርስቶስ ዐውድ፤

“. . . ክርስቶስ ስለ ኃጢአታችን ሞተ፥ . . .” 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15:3

የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ሥራ ከፍ ያለና መሠረታዊ የክርስትና ሃይማኖት ትምህርት ነው።

ሰዎች ወደ ክርስቶስ ሲሄዱ፥ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ በእነርሱ ፈንታ ኀጢአታቸውን እንደተሸከመ እስኪያስተውሉ ድረስ፤

የይቅርታን፥

የሰላምን፥

የደስታንና፥

የነጻነትን ሕይወት አያውቁም።

ትምህርተ ግብረ ክርስቶስ፥ ክርስቶስ በምድር ሳለ ምን እንደፈጸመና አሁን በሰማይ ምን እንደሚሠራ የሚያስተምር ትምህርት ነው።

Page 11: Title of Presentation - ርስቶስ_ክፍል_3...1.pdf · PDF fileየስርየት መንሥኤ፣ የእግዚአብሔር ፍቅር፥ የዮሐንስ ወንጌል 3:16 የእግዚአብሔር

የትምህርተ ግብረ ክርስቶስ ዐውድ፤ . . .

ትምህርተ ግብረ ክርስቶስን እንደሚገባ ለመረዳት፥

ዘመናትን ዘልቆ የታየውን የቤተ ክርስቲያንን ታሪክ እንደሚጋባ ማጥናትና መረዳትን ይጠይቃል፣

ትምህርተ ሥጋዌና ትምህርተ ግብረ ክርስቶስ የተያያዙ መሆናቸውን ማጤን ያስፈልጋል፣

ግብረ ክርስቶስ ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ያለውን ግንኙነት ማወቅ ይጠይቃል፣

የግብረ ክርስቶስ ትርጕም እጅግ ሰፊ መሆኑን መገንዘብ ያሻል፣

Page 12: Title of Presentation - ርስቶስ_ክፍል_3...1.pdf · PDF fileየስርየት መንሥኤ፣ የእግዚአብሔር ፍቅር፥ የዮሐንስ ወንጌል 3:16 የእግዚአብሔር

የትምህርተ ግብረ ክርስቶስ ዐውድ፤ . . .

ትምህርተ ግብረ ክርስቶስን እንደሚገባ ለመረዳት፥ . . .

ዘመናትን ዘልቆ የታየውን የቤተ ክርስቲያንን ታሪክ እንደሚጋባ ማጥናትና መረዳትን ይጠይቃል፣

የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ስለ ትምህርተ ግብረ ክርስቶስ ምን ያስተምረናል?

በሐዋሪያት ዘመን፣ (የአዲስ ኪዳን መጸሐፍት)

በቤተ ክርስቲያን አባቶች ዘመን (ከ1ኛው - 5ኛው መቶ ክፍለ ዘመን)

የቤተ ክርሲትያን ታሪክ (ከ6ኛው - 14ኛው መቶ ክፍለ ዘመን)

የቤተ ክርሲትያን ታሪክ (ከ15ኛው - 18ኛው መቶ ክፍለ ዘመን)

የቤተ ክርሲትያን ታሪክ (ከ19ኛው - 21ኛው መቶ ክፍለ ዘመን)

Page 13: Title of Presentation - ርስቶስ_ክፍል_3...1.pdf · PDF fileየስርየት መንሥኤ፣ የእግዚአብሔር ፍቅር፥ የዮሐንስ ወንጌል 3:16 የእግዚአብሔር

የትምህርተ ግብረ ክርስቶስ ዐውድ፤ . . .

ትምህርተ ግብረ ክርስቶስን እንደሚገባ ለመረዳት፥ . . .

ትምህርተ ሥጋዌና ትምህርተ ግብረ ክርስቶስ የተያያዙ መሆናቸውን ማጤን ያስፈልጋል፣

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በማንነቱ ላይ እጅግ አተኩሮ ሲናገር በወንጌላት እናነባለን፤

“ለቀደሙት፦ ... እንደ ተባለ ሰምታችኋል፤ . . . እኔ ግን እላችኋለሁ፥ ...” ((የተራራው ስብከት) የማቴዎስ ወንጌል 5:21-22፣ 27-28፣ 31-32፣ 33-34፣ 38-39፣ 43-44)

ሰባት ጊዜም የስራውን ምሳሌ ከሰጠ በኋላ “እኔ ነኝ” ብሎ አሳቡን በመደምደም በማንነቱ ላይ አተኩሯል፤

• “የሕይወት እንጀራ እኔ ነኝ”፤ “እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ”፤ “እኔ የበጎች በር

ነኝ”፤ “መልካም እረኛ እኔ ነኝ”፤ “ትንሣኤና ሕይወት እኔ ነኝ”፤ “እኔ

መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ”፤ “እውነተኛ የወይን ግንድ እኔ ነኝ”

(የዮሐንስ ወንጌል 6:35፣ 8:12፣ 10:7,11፣ 11:25፣ 14:6፣ 15:1)

Page 14: Title of Presentation - ርስቶስ_ክፍል_3...1.pdf · PDF fileየስርየት መንሥኤ፣ የእግዚአብሔር ፍቅር፥ የዮሐንስ ወንጌል 3:16 የእግዚአብሔር

የትምህርተ ግብረ ክርስቶስ ዐውድ፤ . . .ትምህርተ ግብረ ክርስቶስን እንደሚገባ ለመረዳት፥ . . .

ትምህርተ ሥጋዌና ትምህርተ ግብረ ክርስቶስ የተያያዙ መሆናቸውን ማጤን ያስፈልጋል፣ . . .

“የሕይወት እንጀራ እኔ ነኝ” – “ወደ እኔ የሚመጣ ከቶ አይራብም በእኔ የሚያምንም ሁልጊዜ ከቶ አይጠማም”

“እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ” – “የሚከተለኝ የሕይወት ብርሃን ይሆንለታል እንጂ በጨለማ አይመላለስም”

“እኔ የበጎች በር ነኝ” – “በሩ እኔ ነኝ፤ በእኔ የሚገባ ቢኖር ይድናል፥ ይገባልም ይወጣልም መሰማርያም ያገኛል”

“መልካም እረኛ እኔ ነኝ” – “መልካም እረኛ ነፍሱን ስለ በጎቹ ያኖራል”

“ትንሣኤና ሕይወት እኔ ነኝ” – “የሚያምንብኝ ቢሞት እንኳ ሕያው ይሆናል”

“እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ” – “በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም።”

“እውነተኛ የወይን ግንድ እኔ ነኝ” – “በእኔ ኑሩ እኔም በእናንተ”

(የዮሐንስ ወንጌል 6:35፣ 8:12፣ 10:7,11፣ 11:25፣ 14:6፣ 15:1)

Page 15: Title of Presentation - ርስቶስ_ክፍል_3...1.pdf · PDF fileየስርየት መንሥኤ፣ የእግዚአብሔር ፍቅር፥ የዮሐንስ ወንጌል 3:16 የእግዚአብሔር

የትምህርተ ግብረ ክርስቶስ ዐውድ፤ . . .ትምህርተ ግብረ ክርስቶስን እንደሚገባ ለመረዳት፥ . . .

ትምህርተ ሥጋዌና ትምህርተ ግብረ ክርስቶስ የተያያዙ መሆናቸውን ማጤን ያስፈልጋል፣ . . .

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፍጹም አምላክ ፍጹም ሰውም ሲሆን አንድ ክርስቶስ ነው። ሰውን ላማዳን መሲሑ ፍጹም አምላክ ፍጹም ሰውም መሆን ነበረበት።

“አምላክ ብቻ ቢሆን ኖሮ የሞት ጉዳይ ሊሰማው አይችልም ነበር፤ እግዚአብሔር አይሞትምና፤ ሰው ብቻ ቢሆን ኖሮ ሞትን ሊያሸንፍ አይችልም ነበር።” (ጆን ካልቪን)

የእግዚአብሔር ፍትሕ፥ የሰውን ዕዳ የሚከፍልና ኀጢአትን ያልሠራ ሰውን ይጠይቃል።

ፍጹም አምላክነት የሌለው ክርስቶስ እግዚአብሔርን ለመግለጥ እንደማይችል ሁሉ፥ ፍጹም ትስብእት የሌለው ክርስቶስም ሰውን ለማዳን አይችልም፤

ክርስቶስ በእግዚአብሔር ፊት ይወክለን ዘንድ ፍጹም ሰው መሆን እንደነበረበት ሁሉ፥ እግዚአብሔርን እንዲገልጥልንም ፍጹም አምላክ መሆን ነበረበት።

Page 16: Title of Presentation - ርስቶስ_ክፍል_3...1.pdf · PDF fileየስርየት መንሥኤ፣ የእግዚአብሔር ፍቅር፥ የዮሐንስ ወንጌል 3:16 የእግዚአብሔር

የትምህርተ ግብረ ክርስቶስ ዐውድ፤ . . .ትምህርተ ግብረ ክርስቶስን እንደሚገባ ለመረዳት፥ . . .

ግብረ ክርስቶስ ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ያለውን ግንኙነት ማወቅ ይጠይቃል፣አብ ዐቃጅ፥ ወልድ አደራጅና መንፈስ ቅዱስ ፈጻሚ (ግብራቸውን (ሥራቸውን) እና የግብራቸውን አፈጻጸም ለመለየትና ላማብራራት)የሦስቱም አካላት ፈቃድ አንድ በመሆኑ፥ አንዱ ያለ ሌሎቹ አይሰራምና እንደ አሠራራቸው ከሌሎቹ ጋር አብረው በሥራ ይሳተፋሉ። (ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በተመለከተ፥) . . .

በትሥጉቱ፤ (ወልድ ከአብ ተላከ፤ መንፈስ ቅዱስ የኢየሱስን እናት ማርያምን ጸለላት) “መልአኩም መልሶ እንዲህ አላት፦ መንፈስ ቅዱስ በአንቺ ላይ ይመጣል፥ የልዑልም ኃይል ይጸልልሻል ስለዚህ ደግሞ ከአንቺ የሚወለደው ቅዱስ የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል።” የሉቃስ ወንጌል 1:35በጥምቀቱ፤ (አብ፥ “የምወድህ ልጄ አንተ ነህ፥ በአንተ ደስ ይለኛል”፤ መንፈስ ቅዱስ፥ “በአካል መልክ እንደ ርግብ በእርሱ ላይ ወረደ”) “መንፈስ ቅዱስም በአካል መልክ እንደ ርግብ በእርሱ ላይ ወረደ፤ የምወድህ ልጄ አንተ ነህ፥ በአንተ ደስ ይለኛል የሚል ድምፅም ከሰማይ መጣ።” የሉቃስ ወንጌል 3:22በአገልግሎቱ፤ ኢየሱስ የአብን ፈቃድና ተእዛዝ እየጠበቀና እያከበረ አስተማረ ሰራም፤ (የሉቃስ ወንጌል 2:49፤ የዮሐንስ ወንጌል 5:36፤ 9:4፤ 10:25-27፤ 14:24) በመንፈስ ቅዱስ ኃይል አገልግሏል፤ (የማቴዎስ ወንጌል 12:28፤ የሐዋርያት ሥራ 10:38-39)በሞቱ፤ በህይወቱ ሁሉና በመስቀል ላይም የመስዎዕትነት አገልግሎቱን ሲፈጽም መንፈስ ቅዱስ አልተለየውም፤ አብም ይርሱን እየተመለከተው ነበር፤ (ወደ ዕብራውያን 9:14፤ የማቴዎስ ወንጌል 27:46፤ የሉቃስ ወንጌል 23:34,46)በትንሣኤው፤ በትንሳኤ የአብ ሥራ፥ (የሐዋርያት ሥራ 2:24,32፤ 3:15) መንፈስ ቅዱስ፥ (ወደ ሮሜ ሰዎች 8:11)

Page 17: Title of Presentation - ርስቶስ_ክፍል_3...1.pdf · PDF fileየስርየት መንሥኤ፣ የእግዚአብሔር ፍቅር፥ የዮሐንስ ወንጌል 3:16 የእግዚአብሔር

የትምህርተ ግብረ ክርስቶስ ዐውድ፤ . . .

ትምህርተ ግብረ ክርስቶስን እንደሚገባ ለመረዳት፥ . . .

የግብረ ክርስቶስ ትርጕም እጅግ ሰፊ መሆኑን መገንዘብ ያሻል፣

የብሉይ ኪዳን ጥላ፥

በብሉይ ኪዳን ያሉ መሥዋዕቶች፤

በብሉይ ኪዳን ልዩ ልዩ ታሪኮች፤

የመገናኛው ድንኳን በብሉይ ኪዳን፤

የብሉይ ኪዳን ትንቢቶች፤

Page 18: Title of Presentation - ርስቶስ_ክፍል_3...1.pdf · PDF fileየስርየት መንሥኤ፣ የእግዚአብሔር ፍቅር፥ የዮሐንስ ወንጌል 3:16 የእግዚአብሔር

የትምህርተ ግብረ ክርስቶስ ዐውድ፤ . . .

የግብረ ክርስቶስ ልዩ ልዩ ጥቅልል ምሳሌዎች፣

የክርስቶስ ስሞች፤

ክርስቶስ፥ የቃል ኪዳን ጌታ፤

Page 19: Title of Presentation - ርስቶስ_ክፍል_3...1.pdf · PDF fileየስርየት መንሥኤ፣ የእግዚአብሔር ፍቅር፥ የዮሐንስ ወንጌል 3:16 የእግዚአብሔር

የትምህርተ ግብረ ክርስቶስ ዐውድ፤ . . .የግብረ ክርስቶስ ልዩ ልዩ ጥቅልል ምሳሌዎች፣

የክርስቶስ ስሞች፤ጌታ፤ ይህ ስም እርሱ በዓለም ሁሉና በምእመናን ሕይወት ከሁሉ በላይ፥ አዛዥና ኀላፊ መሆኑን ያሳያል፤ (የዮሐንስ ወንጌል 1:23፤ 6:68፤ 9:38፤ 13:13-14፤ 20:28፤ 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 2:8፤ የዮሐንስ ራእይ 19:16፤ 22:20-21)ኢየሱስ (እግዚአብሔር ያድናል)፤ ይህ ስም ሕዝቡን ከኀጢአታቸው የሚያድን መሆኑን ያሳያል፤ (የማቴዎስ ወንጌል 1:21፣ የሉቃስ ወንጌል 1:31፣ የሐዋርያት ሥራ 8:35፣ 9:17፣ 17:3,18፣ ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4:21፣ ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 2:10፣ 1ኛ ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች 1:9-10፣ ወደ ዕብራውያን 2:9፣ 12:2,24፣ 13:12፣ የዮሐንስ ራእይ 14:12፣ 22:16)ክርስቶስ (መሲሕ)፤ የተቀባ ማለት ነው፤ (የማቴዎስ ወንጌል 16:16፣ የሉቃስ ወንጌል 2:11፣ የዮሐንስ ወንጌል 4:25፣ 20:31፤ የሐዋርያት ሥራ 2:31,36፣ 4:26፣ 10:38፣ 17:3፣ ወደ ሮሜ ሰዎች 5:6,8፣ 8:17,35፣ 9:5፣ 10:4፣ 12:5፣ 14:10፣ 15:7፣ ወደ ገላትያ ሰዎች 4:7፣ 5:1፣ ወደ ኤፌሶን ሰዎች 1:1-14,19-23፣ ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 1:21፣ 4:13፣ ወደ ቆላስይስ ሰዎች 1:27፣ 1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 1:19፣ 2:21-24፣ 3:18፣ የዮሐንስ ራእይ 12:10፣ 20:4)የሰው ልጅ፤ ብሉይ ኪዳን ይህንን ስም ለልዩ አገልግሎት በፈቃዱ ከእግዚአብሔር እንደተላከ ይገልጣል፤ (ትንቢተ ዳንኤል 7:13-14፣ የሉቃስ ወንጌል 9:26-27፣ 21:27)የዳዊት ልጅ፤ ይህ ስም ለዳዊት የተሰጠው ተስፋ በኢየሱስ እንደሚፈጸም ያሳያል፤ (የማቴዎስ ወንጌል 21:9፣ 22:43-45፣ የሐዋርያት ሥራ 13:22,34-39፣ የዮሐንስ ራእይ 22:16)የእግዚአብሔር ልጅ፤ ይህ ስም ኢየሱስ የእግዚአብሔር የባሕርይ ልጅ መሆኑን፣ (የዮሐንስ ወንጌል 20:17,31) የአባቱን ክብር እንደሚገልጥ፣ (የማቴዎስ ወንጌል 11:27፣ የዮሐንስ ወንጌል 1:18) የአባቱን ፈቃድ እንደሚፈጽም ያሳያል፤ (የማቴዎስ ወንጌል 11:27-30፣ የዮሐንስ ወንጌል 6:37-40)አማኑኤል (እግዚአብሔር ከእኛ ጋር)፤ እርሱ የሚኖርበት ሕዝብ ሁሉ የእግዚአብሔርን በረከት በእርሱ አማካኝነት መቀበሉን ያሳያል፤ (ትንቢተ ኢሳይያስ 7:14፣ 8:8፣ የማቴዎስ ወንጌል 1:23)

Page 20: Title of Presentation - ርስቶስ_ክፍል_3...1.pdf · PDF fileየስርየት መንሥኤ፣ የእግዚአብሔር ፍቅር፥ የዮሐንስ ወንጌል 3:16 የእግዚአብሔር

የትምህርተ ግብረ ክርስቶስ ዐውድ፤ . . .

የግብረ ክርስቶስ ልዩ ልዩ ጥቅልል ምሳሌዎች፣ . . .

ክርስቶስ፥ የቃል ኪዳን ጌታ፤

ክርስቶስ “የሚሻል ኪዳን”፣ “የሚሻል አገልግሎት”፣ “የአዲስ ኪዳን መካከለኛ” . . . ነው፤

“አሁን ግን በሚሻል ተስፋ ቃል በተመሠረተ በሚሻል ኪዳን ደግሞ መካከለኛ እንደሚሆን በዚያ ልክ እጅግ የሚሻል አገልግሎት አግኝቶአል።” ወደ ዕብራውያን 8:6

“ስለዚህም የፊተኛው ኪዳን ሲጸና ሕግን የተላለፉትን የሚቤዥ ሞት ስለ ሆነ፥ የተጠሩት የዘላለምን ርስት የተስፋ ቃል እንዲቀበሉ እርሱ የአዲስ ኪዳን መካከለኛ ነው።” ወደ ዕብራውያን 9:15

“የአዲስም ኪዳን መካከለኛ ወደሚሆን ወደ ኢየሱስ፥ ከአቤልም ደም ይልቅ የሚሻለውን ወደሚናገር ወደ መርጨት ደም ደርሳችኋል።” ወደ ዕብራውያን 12:24

Page 21: Title of Presentation - ርስቶስ_ክፍል_3...1.pdf · PDF fileየስርየት መንሥኤ፣ የእግዚአብሔር ፍቅር፥ የዮሐንስ ወንጌል 3:16 የእግዚአብሔር

የትምህርተ ግብረ ክርስቶስ ዐውድ፤ . . .የግብረ ክርስቶስ ልዩ ልዩ ጥቅልል ምሳሌዎች፣ . . .

ክርስቶስ፥ የቃል ኪዳን ጌታ፤ . . .

ክርስቶስ፥

ለኖኅ በተሰጠው ቃል ኪዳን መሠረት ለፍጥረት ሁሉ የበረከት ፍጻሜ፣ (ኦሪት ዘፍጥረት 9:15፣ ወደ ሮሜ ሰዎች 8:19-22፣ ወደ ኤፌሶን ሰዎች 1:10፣ ወደ ቆላስይስ ሰዎች 1:19-20)

ለአብርሃም በተሰጠው ቃል ኪዳን መሠረት የሥጋዊ ዘሩ ብቻ ሳይሆን፥ የምድር ነገዶች ሁሉ አንድነትና በረከት ፍጻሜ፣ (ኦሪት ዘፍጥረት 12:3፣ 22:16-18፣ ወደ ገላትያ ሰዎች 3:28-29፣ 1ኛ የዮሐንስ መልእክት 2:2)

ለሙሴ በተሰጠው ቃል ኪዳን መሠረት እንደ እርሱ ያለውን (ቃል ኪዳንን የሚሰጥ) የሚያስነሳ የተስፋ ቃል ፍጻሜ፣ (ኦሪት ዘዳግም 18:15-16፣ የሐዋርያት ሥራ 3:18-22)

የኀጢአት መሥዋዕቶች ሁሉ ፍጻሜ፣ (ኦሪት ዘሌዋውያን 1-6፤ የሐዋርያት ሥራ 13:38-39፣ ወደ ዕብራውያን 9:26-28፤ 10:11-18)

ለዳዊት በተሰጠው ቃል ኪዳን መሠረት ከዳዊት ዘር ለዘለዓለም የሚገዛው የሕዝቡ ንጉሥ ፍጻሜ፤ (መጽሐፈ ሳሙኤል ካልዕ 7:16፣ መዝሙረ ዳዊት 89:3-4፣ የሐዋርያት ሥራ 13:22,34፣ የዮሐንስ ራእይ 5:5)