የ2010 ዓ.ም ትምህርት ዘመን ሶስተኛው ትዉልድ ... · 2020-01-06 ·...

31
2010 .ትምህርት ዘመን ሶስተኛው ትዉልድ ዩኒቨርሲቲዎች የትግበራ ምዕራፍ የድጋፍና ክትትል ሥራ ሪፖርት 0 2010 .ትምህርት ዘመን ሶስተኛው ትዉልድ ዩኒቨርሲቲዎች የትግበራ ምዕራፍ የድጋፍና ክትትል ሥራ ሪፖርት ግንቦት 2010 .

Upload: others

Post on 13-Mar-2020

42 views

Category:

Documents


0 download

TRANSCRIPT

የ2010 ዓ.ም ትምህርት ዘመን ሶስተኛው ትዉልድ ዩኒቨርሲቲዎች የትግበራ ምዕራፍ የድጋፍና ክትትል ሥራ ሪፖርት

0

የ2010 ዓ.ም ትምህርት ዘመን ሶስተኛው ትዉልድ ዩኒቨርሲቲዎች የትግበራ ምዕራፍ የድጋፍና ክትትል ሥራ

ሪፖርት

ግንቦት 2010 ዓ.ም

የ2010 ዓ.ም ትምህርት ዘመን ሶስተኛው ትዉልድ ዩኒቨርሲቲዎች የትግበራ ምዕራፍ የድጋፍና ክትትል ሥራ ሪፖርት

1

1. ቁልፍ ተግባርን በተመለከተ

1.1 የትምህርትና ቴክኖሎጂ ልማት ሠራዊት አደረጃጀትና አሠራር

በጥንካሬ የታዩ ጉዳዮች፡-

በሁሉም ተቋማት የትምህርትና ቴክኖሎጂ ልማት ሰራዊት አደረጃጀት ተፈጥሮ

በየስራ ክፍሉ የሚያጋጥሙ ችግሮችን እየፈቱ ወደ ተቀራረበ የመፈጸም ደረጃ

ለማምጣት በተለይም በሁለተኛዉ ወሰነ ትምህርት በአዲስ መልክ በመከለስ መሰራቱ፣

በሁሉም ተቋማት በየደረጃው ያለው አደረጃጀት የከፍተኛ አመራር፣የመካከለኛ

አመራር፣ የታችኛው አመራር፣ የመምህራን፣ የአስተዳደር ሰራተኞችና የተማሪዎች

አደረጃጀት በመፍጠር በመማር ማስተማር፣ በጥናትና ምርምርና በማህበረሰብ

አገልግሎት የትኩረት መስኮች ድጋፍ በመስጠት ወደ ላቀ የመፈጸም ደረጃ የተሸጋገረ

አመራር ለመፍጠር እየተሰራ መሆኑና የላቀ አስተዋጽኦ ለማበርከት በሚያስችል

መነሳሳት ዉስጥ የተገባ መሆኑ

የተማሪዎች የትምህርትና የቴክኖሎጂ ልማት ሠራዊት አደረጃጀት /cooperative

learning/ የተፈጠረ ሲሆን በትምህርት ክፍሎች ላይ ውይይት በማድረግ እርስ በርስ

የሚገነባቡበት ሁኔታዎች መኖራቸውና የክትትል ሥርዓት ተዘርግቶ እየተሰራ ያለ

መሆኑ፤ (አዲግራት፣ዋቸሞ ፣ወልዲያ ፣ደበረታቦር እና አሶሳ ዩኒቨርሲቲዎች)

የህዝብ ክንፉን በመለየትና በጋራ እቅድ በማዘጋጀት ቋሚ የግንኙነት መድረኮች

በመተግበር በተቋሙ ዉጤታማ አፈጻጸሞች ላይ የህዝብ ክንፉ የላቀ ሚናዉን

መጫወት መቻሉ እንዲሁም በየደረጃው ያሉ ሃላፊዎች ክትትልና ድጋፍ በማድረግ

እየተሰራ ያለ መሆኑ (ቡሌሆራ ፣ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲዎች)

በዉሱንነት የታዩና መሻሻል የሚገባቸዉ ጉዳዮች

በሁሉም ተቋማት የየደረጃው ሰራዊት አደረጃጀት የከፍተኛ፣ የመካከለኛ እና

የታችኛው አመራር እንዲሁም የመምህራን፣ የአስተዳደር ሰራተኞችና የተማሪዎች

አደረጃጀት በመፈጠሩ ያመጣው ተቋማዊ ለውጥ በተጨባጭ ክትትልና ድጋፍ

እየተደረገ ፋይዳውን በመገምገም የተመዘገበውን ውጤት ከመለካት አንጻር እየተሰራ

አለመሆኑ፣

የ2010 ዓ.ም ትምህርት ዘመን ሶስተኛው ትዉልድ ዩኒቨርሲቲዎች የትግበራ ምዕራፍ የድጋፍና ክትትል ሥራ ሪፖርት

2

በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች የትምህርትና ቴክኖሎጂ ልማት ሰራዊት በሁሉም ስራ

ክፍሎች ወጥነት ባለዉ መንገድ ተከታታይነት ያለዉን ግንኙነት እያደረጉ

የአመለካከት የክህሎትና የግብዓት ችግሮችን እየፈቱ ከመሄድ አንፃር ዉስንነቶች

ያሉ መሆኑ

1.2 ልማታዊ የመልካም አስተዳደር ስራዎች ትግበራና አፈጻጸምን በተመለከተ

በጥንካሬ የታዩ ጉዳዮች፡-

በየደረጃው ያለውን የዩኒቨርስቲውን ማህበረሰብ በማወያየትና የመልካም አስተዳደር

ችግሮችን በመለየት ዕቅድ በማዘጋጀት ችግሮቹን ማን ሊፈታቸው እንደሚገባ ሰነድ

አዘጋጅቶ በማውረድ ወደ ተግባር የተገባ መሆኑንና በበላይ አመራሩ የዘወትር አጀንዳ

እየተደረገ እንደሚሰራ ከነበሩ የውይይት መድረኮችና ከሰነድ ምልከታ ለማረጋገጥ

ተችሏል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በየደረጃው ያለው አመራር እስከ ታች ድረስ በአካል

በመገኘት ክትትል የሚያደርግበትና ተለይተው ሊፈቱ የታቀዱ የመልካም አስተዳደር

ችግሮችን የሚፈተሽበት ሁኔታ አበረታች እንደሆነ ለማየት ተችሏል፡፡

(አዲግራት፣ዋቸሞ፣ደበረ ታቦር፣ መቱ እና ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲዎች)

በተቋሙ የቅሬታ ማቅረቢያ ስርዓት (የሀሳብ መስጫ ሳጥን ፣መዝገብ…) ተዘርግቶ

ተገልጋዮች በተሰጣቸዉ አገልግሎት ያላቸዉን እርካታና ቅሬታ የሚገልጹበት እድል

ከመመቻቸቱ ባሻገር በትምህርት ዘመኑ ቅሬታዎች ተለይተው በየደረጃው ባሉ

አመራሮች የቅርብ ክትትል እየተደረገ ምላሽ እንደሚሰጥ ማረጋገጥ ተችሏል፡፡

(ቡሌሆራ፣ደበረታቦር እና ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲዎች)

ተጠያቂነትንና ኃላፊነትን በግልፅ ሊያሣዩና ሊያሠፍኑ የሚችሉ ደንቦች፣ፖሊሲዎች

የአሠራር ሥልቶች፣ የተግባራት ስታንዳርድ መስፍርቶች ወዘተ እንደተቋም

ተዘጋጅተውና ጸድቀው ተገቢ የሆነ ኦረንቴሽን ተሠጥቶ በተግባር እንዲውሉ

መደረጉ፤ (አዲግራት፣ ቡሌሆራ፣ ወልዲያ፣ዋቸሞ እና ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲዎች)

በተቋሙ ለመምህራንና ለአስተዳደር ሰራተኞች የትምህርትና የስልጠና እድል

አሰጣጥ ፍትሃዊ ፣ ግልፀኝነት አሰራርን የተከተለና የመልካም አስተዳደር ጥያቄ

ሊያስነሳ በማይችል መልኩ በመመሪያ መሰረት እየተሰራ መሆኑ። (አዲግራት፣

ቡሌሆራ፣ ደብረ ታቦር፣ዋቸሞ፣ ወልቂጤ እና አሶሳ ዩኒቨርሲቲዎች)

የ2010 ዓ.ም ትምህርት ዘመን ሶስተኛው ትዉልድ ዩኒቨርሲቲዎች የትግበራ ምዕራፍ የድጋፍና ክትትል ሥራ ሪፖርት

3

የኪራይ ሰብሳቢነት ምንጮች አሳታፊ በሆነ መንገድ በስራ ክፍልና በተቋም ደረጃ

በመለየት እና የማክሰሚያ ስልቶች ተቀርጸዉ ወደ ተግባር ከመገባቱም በላይ

የፈጻሚዎች የመገምገሚያ መስፈርት ዉስጥ ጉልህ ክብደት ተሰጥቶት እንዲተገበር

ክትትል በማድረግ እንዲሁም ግንዛቤ በማስጨበጥ እየተሰራ መሆኑ (አዲግራት፣

ቡሌሆራ፣ ደብረ ታቦር፣ ዋቸሞና ወልዲያ እና ወልቂጤ ዩኒቨርሲተዎች)

በተቋሙ ያለውን የአገልግሎት አሰጣጥ የተገልጋዮች የእርካታ ደረጃን ለመለየት

በሚያስችል መልኩ በስራ ክፍሎችና እንደተቋም የዳሰሳ ጥናት ማድረግ መቻሉ ፡፡

/ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ-በስራ ክፍሎች፤ ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ እንደ ተቋም/

በዉሱንነት የታዩና መሻሻል የሚገባቸዉ ጉዳዮች፡-

እንደ ተቋምም ሆነ በስራ ክፍል ደረጃ የተገልጋዮች የአገልግሎት አሰጣጥ የእርካታ

ደረጃ ዳሰሳ ጥናት አለመደረጉና ከአገልግሎት አሰጣጥ የተገኘዉን ለውጥ በመለካት

መሻሻል ለሚገባቸው ጉዳዮች የቀጣይ አቅጣጫ እያስቀመጡ በመተግበር በኩል

እየተሰራ አለመሆኑ (አዲግራት፣ ቡሌሆራ፣ ደብረታቦር፣ መቱ፣ ወልዲያ እና አሶሳ

ዩኒቨርሲቲዎች)፡፡

የJEG /የሥራ ምዘና ስርዓትን ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችሉ የመመሪያ

ትዉዉቅ አስፈላጊ ቅድመ ዝግጅት በማድረግ በምደባ ወቅት ቅሬታዎች እንዳይነሱ

ለሰራተኞች ተገቢውን ግንዛቤ በማስጨበጥ ስራ እየተሰራ ያለ ቢሆንም የምደባ ስራ

ከመስራት አንጻር በሚፈለገው ጊዜ ለማጠቃለል በሚያስችል ሁኔታ እየተሰራ

አለመሆኑ በሁሉም ዩኒቨትሲቲዎች የሚታይ ሲሆን በአዲግራት ዩኒቨርሲቲ

ኮሚቴዎች ተሰይመው ወደ ስራም እንዳልተገባ ማረጋገጥ ተችሏል፡፡

በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ የሚጠቀሙ ነባር የተቋሙን

ማህብረሰብ አባላት ማለትም የአመራሩን፣ የመምህራንና የሰራተኞችን የትምህርት

ማስረጃ ህጋዊነት ለማረጋገጥ የተለያዩ ስልቶችን ነደፎ በመስራት ረገድ የሚታይ

ዉጤት ማስመዝገብ አለመቻል

በየደረጃዉ ያለዉ የአመራር ምደባ ብቃትን ተጠያቂነትንና እና ፍትሀዊነትነ መሰረት

ያደረገ የዉድድር ሥርዓት ከመዘርጋት አኳያ ግልጽ የሆነ መመሪያ ያለመኖርና

የዉድድር መስፈርቶች በየጊዜዉ የሚለዋወጡ ከመሆኑ ጋር ተያይዘዉ በፈጻሚዎች

በኩል ቅሬታ የሚታይበት መሆኑ፣ /ቡሌሆራ፣ወልቂጤ፣ መቱ እና ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ/

የ2010 ዓ.ም ትምህርት ዘመን ሶስተኛው ትዉልድ ዩኒቨርሲቲዎች የትግበራ ምዕራፍ የድጋፍና ክትትል ሥራ ሪፖርት

4

1.3 ተቋማዊ የለዉጥ ስራዎች ትግበራና አፈጻጸም

በጥንካሬ የታዩ ጉዳዮች፡-

የለውጥ ፕሮግራሞች በመተግበራቸዉ (በተማሪው በመምህራን በአመራሩ

በአስተዳደር ሰራተኞችና በሌሎች ባለድርሻ አካላት) በአመለካከት ፣ በክህሎትና

በስነ-ምግባር ለዉጥ ለማስመዝገብ ተገቢው ንቅናቄ ተፈጥሮ ክትትል በማድረግ

እየተሰራ ያለ መሆኑን ማረጋገጥ ተችሏል (ቡሌ ሆራ፣አዲግራት፣ ደብረ ታቦር፣ዋቸሞ

እና ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲዎች /

የውጤታማነት ስርዓት /Delivelorogy / ክፍል ራሱን ችሎ በሰው ሀይልና በግብዓት

ተሟልቶ መደራጀት መቻሉ፤ በስሩ የኬረር ሰርቪስ በማቋቋም ስራ መጀመሩ እና

ከትምህርት ሚኒስቴር ደሊቨሪ ዩኒት ጋር ተከታታይነት ያለዉ ሳምንታዊ የመረጃ

ልዉዉጥ ስርዓትን በተገቢዉ መንገድ ማስኬድ መቻሉ /አዲግራት፣ቡሌ ሆራ፣ ዋቸሞ፣

ደብረ ታቦር፣፣ ወልቂጤ እና አሶሳ ዩኒቨርሲቲዎች/

በዉሱንነት የታዩና መሻሻል የሚገባቸዉ ጉዳዮች፡-

በፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ሀብት ልማት ሚኒስቴር በትምህርት ዘመኑ በተዘጋጁ

ስምንት /8/ የስልጠና ርዕሶች ላይ የአሰልጣኞች ስልጠና ተወስዶ ከወልቂጤ

ዩኒቨርሲቲ በስተቀር ለሚመለከታቸው የተቋሙ ሰራተኞች ማድረስ አለመቻሉ

በየተቋማቱ በሚገኙ በርካታ የሥራ ክፍሎች እቅድን በBSC በማቀድ እስከ ግለሰብ

ፈጻሚ ድረስ ማውረድ አለመቻልና የፈጻሚዎች የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርት

አለመኖር፤ / ወልዲያ አዲግራት እና መቱ ዩኒቨርሲቲዎች /

በሁሉም ተቋማት የለውጥ ፕሮግራሞች በመተግበራቸዉ የተገኘዉ ተጨባጭ ዉጤት

በየደረጃዉ በጥልቀት እየተገመገመና የቀጣይ አቅጣጫ እየተቀመጠ ስለመሰራቱ

የሚያመላክት መረጃ አለመኖር፤

የ2010 ዓ.ም ትምህርት ዘመን ሶስተኛው ትዉልድ ዩኒቨርሲቲዎች የትግበራ ምዕራፍ የድጋፍና ክትትል ሥራ ሪፖርት

5

2. ዓበይት ተግባራት

2.1 የትምህርት ጥራትና አግባብነትን ማረጋገጥ

ሀ. የመምህራን ልማትን ማጠናከር

በጥንካሬ የታዩ ጉዳዮች፡-

ከዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ በስተቀር በሌሎቹ ዩኒቨርሲቲዎች የመምህራንን የትምህርት

ደረጃ ስብጥር ለማሻሻል የመምህራን ልማት ስራዉ የ0፡70፡30 ሀገራዊ ግብን ለማሳካት

በአገር ውስጥና ከአገር ውጭ የሚገኙ ለሁለተኛና ሶስተኛ ዲግሪ ትምህርት እድሎችን

አሟጦ ከመጠቀም ባሻገር ለትምህርት የተላኩ መምህራንን መረጃ በትክክል ተለይቶና

ተደራጅቶ ተይዞ የሰው ሀይልን በአግባቡ ከማስተዳደር አንጻር በጥሩ ጎን ሊወሰድ

የሚችል መሆኑንና ክትትል እየተደረገ ውል በገቡበት ወቅት እንዲመለሱ መደረጉ፡፡

በሁሉም ተቋማት ከአጋር አካላት ጋር የተጠናከረ ግንኙነት በመፍጠር በተለይም

በሳይንስና ቴክኖሎጂ መስክ የ2ኛና 3ኛ ዲግሪ ትምህርት ሥልጠና የሴት መምህራንን

ተሳትፎ ለማሳደግ ለሴቶች ከ5% እስከ 10% የማበረታቻ ነጥብ በቅጥርና በትምህርት

ዉድድር ላይ እንዲያገኙ ተደርጎ እየተሰራ መሆኑ፤

በሁሉም ተቋማት የመምህር ተማሪ ጥምርታ በየኮሌጁ በስታንዳርዱ መሰረት እና

በአማካኝ(1:19) ለማድረግ መምህራንን የትምህርት ዕድል በመስጠት፣ በዝውውርና

ቅጥር በመፈፀም ለማሟላት ጥረት እየተደረገ መሆኑ

በሁሉም ተቋማት የመምህራን የክፍለ ጊዜ ድልድልን ወደ ስታንዳርዱ ለማስጠጋት

በማለም የመምህራን ልማት ስራዉን ተጠናክሮ በመቀጠሉ ለመምህራን የሚሰጥ

ኦቨርሎድ ለመቀነስ የሚያስችል ተቋማዊ ስልትን ቀይሶ መተግበር መቻሉ

በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች የተከታታይ ሙያ ማሻሻያ ማዕከልን በማቋቋም የመምህራንን

የማስተማር አቅም ለማጎልበት የሚያስችል ስልጠናዎችን ለመስጠት ታቅዶ ለአዲስ

ቅጥር መምህራን የሙያ መተዋወቂያ ስልጠና (induction training)፤ የከፍተኛ

ዲፐሎማ ስልጠና (HDP) እንዲሁም የእንግሊዝኛ ቋንቋ ማሻሻያ ስልጠና እንዲያገኙ

መደረጉ

በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች የመምህራን የመልቀቅ ምጣኔ ለመቀነስ በየካምፓሱ ለሚገኙ

መምህራን ኮንዶሚኒየም ቤት በማቅረብ በየተቋማቱ እንዲቆዩ እና ፍልሰትን

የ2010 ዓ.ም ትምህርት ዘመን ሶስተኛው ትዉልድ ዩኒቨርሲቲዎች የትግበራ ምዕራፍ የድጋፍና ክትትል ሥራ ሪፖርት

6

ለመከላከል ጥረት እየተደረገ ሲሆን አንዳንድ ተቋማት (ወልቂጤ ፤ አሶሳ

ዩኒቨርሲቲዎች) ተጨማሪ የመምህራን መኖሪያ ቤት በማስገንባት ላይ መሆናቸዉ

በዉሱንነት የታዩና መሻሻል የሚገባቸዉ ጉዳዮች፡-

በሁሉም ተቋማት ሊባል በሚችል ደረጃ የመምህራን የትምህርት ደረጃ ስብጥር በ2012

ዓ. ም እንደሀገር ይደረስበታል ተብሎ ከተቀመጠዉ የ0፡70፡30 ሀገራዊ ግብ የራቀ

መሆኑ

ለመምህራንን ምቹ የስራ አካበቢ ከመፍጠር እና ብሎም የመልቀቅ ምጣኔን ከመቀነስ

አኳያ መምህራን ተረጋግተዉ እንዳይሰሩ የሚያደርጓቸዉን ዉስጣዊና ዉጫዊ

ምክንያቶች በመለየት በሰነድ የተደገፈ ስልት ቀይሶ ከመስራት ጎን ለጎን የግል መኖሪያ

ቤት እንዲገነቡ የሚያስችላቸዉን ምቹ ሁኔታ ከአካባቢው መስተዳድር ጋር በመነጋገር

መፍጠር አለመቻሉ፤ (ዓዲግራት፣ ቡሌሆራ፣ ደብረ ታቦር ፣መቱ ፣ዋቸሞ

ዩኒቨርሲቲዎች)፡፡

ከትምህርት ሚኒስቴር የሚላኩ የ2ኛና 3ኛ ዲግሪ የትምህርት ዕድሎች በወቅቱ ኮሌጆች

አወዳድረው ባለማቅረባቸው ምክንያት የትምህርት ዕድሎች መባከናቸዉ፤ እንዲሁም

ለመምህራን፣ ለሰራተኞችና ለቴክኒክ ሠራተኞች የአቅም ማጎልበቻ ሥልጠናዎች

መስጠት ላይ ዉሱንነቶች መኖራቸው (ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ)፡፡

ለ. ብቁ የአካዳሚክ ፕሮግራሞችንና ስርዓተ ትምህርቶችን መተግበር

በጥንካሬ የታዩ ጉዳዮች፡-

በሁሉም ሶስተኛ ትውልድ የኒቨርሲቲዎች አዳዲስ ፕሮግራሞችን በገበያው ተፈላጊና

የአገሪቱን የልማት አቅጣጫ የተከተሉ መሆናቸውን በማረጋገጥ ለፕሮግራሞች አከፋፈት

የሚረዳ መመሪያ በማዘጋጀት ሁሉንም የትግበራ ሂደቶች በመመሪያዉ መሰረት

በመተግበር በትምህርት ሚኒስቴር ይሁንታ ሲያገኝ ወደ ስራ መግባት መቻሉ፡፡

የስርዓተ ትምህርት አተገባበር ላይ ክትትል በማድረግ በየጊዜው ግብረ መልስ

መሰጠቱ እና በተሰጠ ግብረ መልስ አማካኝነት መስተካከሉን ክትትል በመደረጉ

የተሻለ አተገባበር እያከናወኑ መሆኑ በሰነድ ምልከታ ማረጋገጥ ተችሏል (ደብረ

ታቦር፣ወልዲያ፣አሶሳ፣ ዋቸሞና ውልቂጤ ዩኒቨርሲቲ)።

የ2010 ዓ.ም ትምህርት ዘመን ሶስተኛው ትዉልድ ዩኒቨርሲቲዎች የትግበራ ምዕራፍ የድጋፍና ክትትል ሥራ ሪፖርት

7

ለአንደኛ ዓመት ተማሪዎች ቅድሚያ በመስጠት በትምህርታቸዉ ጥሩ ዉጤት

እንዲያስመዘግቡ ስልት በመንደፍ የማጠናከሪያ ትምህርት ለሴቶች ቅድሚያ በመስጠት

መተግበር መቻሉ (ዋቸሞ፣ መቱ፣ ቡሌሆራ እና ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲዎች)

በተመረጡ ፕሮግራሞች ላይ የልህቀት ማዕከል እንዲሆን ለማስቻል የፕሮግራም

መረጣና የተቋሙን ማህበረሰብ ግንዛቤ በማስያዝ ወደ ስራ ለመገባት ጅምር ስራ መኖሩ

(ዓዲግራት፣ወልዲያ፣ ቡሌ ሆራ ፣ መቱ፣ አሶሳ)

የስርዓተ ትምህርት ተገቢነት ለማረጋገጥ የውስጥ ጥራት ኦዲት በእያንዳንዱ

ፕሮግራም በማካሄድ የተለዩ መልካም ተሞክሮዎችን ለማስፋትና የተለዩ ክፍተቶችን

ለማረም የውስጥ ሱፐርቪዥን ቡድን በማቋቋም በየሩብ ዓመቱ ሱፐርቪዥን በማካሄድና

ግብረ-መልስ በመስጠት በትምህርት ክፍሎችና በኮሌጆች ተቋቁሞ በመካካለቸው ጤናማ

ውድድር በመፍጠር ክፍተቶችን ለማረምና የተሻሉ አፈጻጸሞችን ለማስፋት በትኩረት

እየተሰራ መሆኑ፣ (ወልቂጤ፣አሶሳ፣ወልዲያ፣ ደብረ ታቦር፣ ዋቸሞ፣ ዓዲግራት

ዩኒቨርሲቲዎች)፡፡

ከወልዲያና ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲዎች በስተቀር በሁሉም ተቋማት በሥርዓተ ትምህርት

ዝግጅትና validation ላይ የውጭ ልምድ በመጠቀም ተግባራዊ ለማድረግ ጥረት

መደረጉ

የ2008 እና የ2009 ዓ.ም ምሩቃን በሰለጠኑበት ሙያ በ12 ወራት ውስጥ ወደ ስራ

ስለመግባታቸውና በተሰማሩበት የስራ መስክ ውጤታማ ስለመሆናቸው የዳሰሳ ጥናት

(Tracer study) ለማድረግ የየአመቱ ተመራቂዎች መረጃ የማሰባሰብና የማደራጀት ስራ

የጀመሩ ዋቸሞ፣ደብረታቦር፣ ወልዲያና ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲዎች ሲሆኑ መቱ

ዩኒቨርሲቲ የዳሰሳ ጥናቱን (Tracer study) አጠናቆ 75.6% የሚሆኑ ተመራቂዎች ስራ

መያዛቸዉን አረጋግጧል፡፡

በዉሱንነት የታዩና መሻሻል የሚገባቸዉ ጉዳዮች፡-

አዳዲስ የትምህርት መስኮች ( ጂኦሎጂ፣ቱሪዝም፣ፋርማሲ/ ሲከፈቱ ቤተ-ሙከራ

ሳይደራጅ፣ የማስተማሪያ መሳሪያ አቅርቦት ዉሱን በሆነበት ፣የማጠቃሻ መጽሀፍት

አቅርቦት በሌለበት በአጠቃላይ በቂ ዝግጅት አለመደረጉ፡፡ (ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ)

የስርዓተ ትምህርት አተገባበር ላይ ክትትል በማድረግ በየጊዜው ግብረ መልስ

የመስጠት ዉሱንነት መኖሩ (መቱ፣ ቡሌ ሆራ፣ ዓዲግራት፣ዩኒቨርሲቲዎች)፡፡

የ2010 ዓ.ም ትምህርት ዘመን ሶስተኛው ትዉልድ ዩኒቨርሲቲዎች የትግበራ ምዕራፍ የድጋፍና ክትትል ሥራ ሪፖርት

8

ለአንደኛ ዓመት ተማሪዎች ቅድሚያ በመስጠት ከአካባቢ ጋር እንዲላመዱና

በትምህርታቸው ጥሩ ውጤት እንዲያስመዘግቡ ስልት ነድፎ መተግበር የተጠናከረ

ማጠናከሪያ ትምህርት/ቲቶሪያል/ና የሥነ ልቦና የምክር አገልግሎት በአብዛኛዉ

ኮሌጆች በተጨባጭ ተግባራዊ ስለመደረጉ መረጃ አለመኖሩ፤ (አሶሳ፣ዓዲግራት፣

ወልቂጤና ወልዲያ ዩኒቨርሲቲዎች)፡፡

በዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ በኤሌክትሪካል ኢንጂኔሪንግ ፕሮግራም ላይ ለተመሳሳይ

ኮርሶች የተለያየ ኮድ ያላቸው መሆኑና ለተለያዩ ኮርሶች ተመሳሳይ ኮድ መኖሩ

በወልዲያ ዩኒቨርሲቲ በሒሳብ ትምህርት ክፍል ውስጥ በትይዩ መሰጠት

የሚገባቸው ኮርሶች በብሎክ እየተሰጡ መሆኑ (Calculus 1&2፣ Geometry)፡፡

የ2008 እና የ2009 ዓ.ም ምሩቃን በሰለጠኑበት ሙያ በ12 ወራት ውስጥ ወደ ስራ

ስለመግባታቸውና በስራ ገበያው ውጤታማ ስለመሆናቸው ተቋሙ የተመራቂ

ተማሪዎችን መዳረሻ የዳሰሳ ጥናት (Tracer study) አለመሰራቱ፣ (አሶሳና ቡሌ ሆራ

ዩኒቨርሲቲዎች)፡፡

ሐ. የመማር ማስተማር

በጥንካሬ የታዩ ጉዳዮች፡-

በሁሉም ሶስተኛ ትውልድ ዩኒቨርሲቲዎች በ2010 ዓ.ም. በሁለተኛው ሴሚስተር

ተማሪዎች በተቀመጠው 1st day 1st class የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ተመዝግበው

በአብዛኛው ትምህርት መጀመራቸውና ኮርሶች ባልተቆራረጠ ሁኔታ እንዲቀጥሉ ፤

ትምህርት እንደጀመሩ ከተለያዩ መድረኮች ለማረጋገጥ የተቻለ ሲሆን መምህራን

ለመማር ማስተማሩ ስራ አስፈላጊ የሆኑ (course outline, Teaching materials,

module) አዘጋጅተዉ ለተማሪዎች በወቅቱ ተደራሽ መደረጉና ጠንካራ ክትትልና

ድጋፍ እየተደረገ፣ ስራው ባግባቡ እየሄደ መሆኑ በምልከታ እና በውይይት

ለመረዳት መቻሉ፡፡

በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚማሩ ተማሪዎች 2.00 እና በላይ ውጤት

እንዲያመጡና ስነምግባራቸውን ለማሻሻል ተገቢዉ ክትትል እየተደረገ የቲቶሪያል

ስርዓት ተዘርግቶ፣በአካደሚክ ማህበራት በኩል የተለያዩ ሶፍትዌር ሥልጠና

መስጠት፣ ሳምንታዊ መልእክቶችን ፖስት ማድረግ፣ በክበባት ዙሪያ ስለስነ-ተዋልዶ

የ2010 ዓ.ም ትምህርት ዘመን ሶስተኛው ትዉልድ ዩኒቨርሲቲዎች የትግበራ ምዕራፍ የድጋፍና ክትትል ሥራ ሪፖርት

9

ሥልጠናዎችን መስጠትና በጸረ-ሙስና ግንዛቤ ማስጨበጥ ሥራ መከናወኑን

ከተለያዩ መድረክ ዉይይቶች ለማረጋገጥ መቻሉ፣ (ወልቂጤ፣ ቡሌ ሆራ፣

ደብረታቦር፣ ዋቸሞ፣ አሶሳና መቱ ዩኒቨርሲቲዎች)፡፡

በ2011ዓ.ም በቅድመ ምረቃና በድህረ ምረቃ የመቀበል አቅም/Intake Capacity /

ለማሳደግ የተለያዩ የማስፋፊያ ግንባታዎች በማከናወን ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ

(ዓዲግራት ፣ወልዲያና ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲዎች)

የመማር ማሰተማር ሂደቱ ተማሪዉን ለመመራመር፤ ለመጠየቅ የሚጋብዝ ተማሪ

ተኮር መማር ማስተማር ሂደት እንዳለና የተማሪዎች የማስተማር ስነ-ዘዴው ተማሪ-

ተኮር እንዲሆን ለመምህራን የአሳታፊና ተማሪ ተኮር የማስተማር ስነ-ዘዴ

ስልጠናዎችን በመስጠት እየተሰራ መሆኑ፣ (ደብረታቦርና ወልቂጤ

ዩኒቨርሲቲዎች)፡፡

ተማሪዎች በንድፈ ሀሳብ የተማሩትን ተጨባጭ ለማድረግ በተቋም ደረጃ በቂ

የተግባር ልምምድ የማድረጊያ ስርዓት ተዘርግቶ በመተግበሩ ተማሪዎች

በተቋማቸዉም ሆነ ከተቋሙ ዉጭ ላቦራቶሪ የተግባር ትምህርት ሳይታለፍ

ማከናወን መቻሉ፤ (ደብረታቦር፣ቡሌ ሆራ፣ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲዎች)፡፡

በ2011 ዓ.ም ለተመራቂ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና / Exit Exam / የሚሰጥ

መሆኑን በቂ የግንዛቤ ማስጨበጫ የሰጡ፤ (አሶሳ፣ወልዲያ፣ዓዲግራትና ቡሌ ሆራ

ዩኒቨርሲቲዎች)፡፡

በዉሱንነት የታዩና መሻሻል የሚገባቸዉ ጉዳዮች፡-

በ2010 ዓ.ም. ተማሪዎችን ከጠራ በኋላ day one class one/ first day first

class የማይከበርበት ለአንድ ሳምንት ያህል የትምህርት ጊዜ ማባከን የተለመደ

መሆኑና በአንዳንድ የትምህርት መስኮች ተማሪው ባለመገኘቱ በወቅቱ ትምህርት

አለመጀመርና በበዓላት ወቅት አልፎ አልፎ የመማር ማስተማር ሂደቱ መቆራረጥ

እንዳለ በተማሪዎች በስፋት መነሳቱ ( ወልቂጤ፣ ዋቸሞ፣ ወልዲያ፣ ደብረታቦር

ዩኒቨርሲቲዎች)

የመማር ማሰተማር ሂደቱ ተማሪዉን ለመመራመር፤ ለመጠየቅ የሚጋብዝ

ስለመሆኑና የተማሪዎችን ተነሳሽነት ከማሳደግ አንጻር ተግባራት መከናወናቸዉ

የ2010 ዓ.ም ትምህርት ዘመን ሶስተኛው ትዉልድ ዩኒቨርሲቲዎች የትግበራ ምዕራፍ የድጋፍና ክትትል ሥራ ሪፖርት

10

እንደተጠበቀ ሆኖ አሁንም የቅርብ ክትትል የማድረግ ውሱንነት መኖሩ፣ (ቡሌ

ሆራ፣ዓዲግራትና ወልዲያ ዩኒቨርሲቲዎች)፡፡

በቤተ መጽሀፍት የአካል ጉዳተኛ ተማሪዎችን ተደራሽ ያደረገ የዲጅታል ላይብረሪ

አገልግሎት አለመኖር፣ ካለባቸዉ ጉዳት አንጻር ተስማሚ የሆነ የማንበቢያ ስፍራ

አለመመቻቸት፤ (ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ)፡፡

በትምህርት አቀባበላቸዉ ዝቅተኛ ለሆኑ ተማሪዎች የማጠናከሪያ ትምህርት

አሰጣጥ ስርአት የተዘረጋ ቢሆንም የአተገባበር ሂደቱንና ያስገኘዉን ፋይዳ

እየተከታተሉ የመገምገም ዉሱንነት መኖሩ (ወልዲያ፣ ቡሌ ሆራ፣

ዓዲግራት፣ደብረታቦር ዩኒቨርሲቲዎች)፡፡

የንድፈ ሀሳብ ትምህርት በተግባር ልምምድ ተጨባጭ እንዲሆን ከማድረግ አንጻር

በአንድንድ የትምህርት ፕሮግራሞች በአብዛኛው በወርክሾፖችና በቤተ- ሙከራዎች

ላይ ተማሪዎች በቂ ልምምድ እያደረጉ እንዳልሆነና በቤተሙከራዎች የማይሰሩ

መሳሪያዎች መኖራቸው፤ (አሶሳና ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲዎች)፡፡

በወልዲያ ዩኒቨርሲቲ የመስክ ልምምድ በሚያስፈልጋቸው አንዳንድ ኮርሶች ላይ

ለመውጣት መምህራን ጥያቄ ቢያቀርቡም ምላሽ ከማግኘት አንጻር ውሱንነት

መኖሩና በአንዳንድ የተደራጁ ወርክሾፖችና ቤተ ሙከራዎች ውስጥ የመሥሪያ

ቁሳቁሶችን ማቅረብ ባለመቻሉ በአግባቡ አገልግሎት እየሰጡ አለመሆኑና አንዳንድ

መምህራን የሚያማክሩበትን ሠዓት አለማሳወቅና በፕሮግራምም አለመገኘት።

በአገር አቀፍ ደረጃ በ2011 ዓ.ም ለተመራቂ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና /Exit

Exam/ የሚሰጥ መሆኑን የግንዛቤ ማስጨበጫ በቂ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ

ያለመሠራቱ፣ (ወልቂጤ፣ መቱና ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲዎች)፡፡

በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ከህንድ የመጡ መምህራን ከቋንቋ የጀመረ ከፍተኛ

የብቃት ችግር የሚሰተዋልባቸዉ መሆኑ በስፋት መነሳቱ

መ. የተከታታይ ምዘና፣ ማብቃትና የፈተና አስተዳደር ሥርዓትን በተመለከተ፡-

በጥንካሬ የታዩ ጉዳዮች፡-

በሁሉም ሶስተኛ ትውልድ ዩኒቨርሲቲዎች የተከታታይ ምዘና አተገባበር ስርዓት

ከየትምህርት ክፍሉ ኮርስ ባህሪ ጋር የተጣጣመና የተማሪዉን ብቃት ለማረጋገጥ

በሚያስችል ሁኔታ ላይ ተመስርቶ እየተሰራ መሆኑ

የ2010 ዓ.ም ትምህርት ዘመን ሶስተኛው ትዉልድ ዩኒቨርሲቲዎች የትግበራ ምዕራፍ የድጋፍና ክትትል ሥራ ሪፖርት

11

ኮሌጆች/ በዲፓርትሜንቶች ደረጃ አስተማማኝ የፈተና ባንኪንክ ስርአት

በመዘርጋትና የፈተና ኮሚቴ ተደራጅቶ ለተማሪዎች የሚሰጡ ፈተናዎች በኮሚቴ

ተገምግሞ እንዲፈተኑ መሆኑ፣ (መቱ፣ ደብረታቦር፣ ዓዲግራት፣ አሶሳ፣ ዋቸሞና

ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲዎች)፡፡

በዉሱንነት የታዩና መሻሻል የሚገባቸዉ ጉዳዮች፡-

ተማሪዉ በተለይ የማጠቃለያ የፈተና ውጤቱን የሚያይበት ሁኔታ ጠንካራ

እንዳልሆነ ለማየት ተችሏል፤ አሶሳ ወልቂጤና ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲዎች፡፡

በተከታታይ ምዘና አተገባበር ሂደት የአመለካከትና የክህሎት ዉሱንነቶች

መታየታቸዉ (ቡሌ ሆራና ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ)፡፡

ከቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ በስተቀር በሌሎቹ ተቋማት የFX አተገባበር አላማዉን

በሳተ መንገድ እንዳይከናወን በተማሪዎችና መምህራን ላይ ተገቢዉን ክትትል

በማድረግ በሰሚስተር ከአንድ ኮርስ በላይ በቆይታቸዉ ተማሪዎች ከሦስት ጊዜ

በላይ FX ዉስጥ እንዳይገቡ ግንዛቤ የመፍጠርና ተከታትሎ የማስፈጸም

ዉሱንነት መኖሩ

በትምህርት ክፍል ደረጃ የተማሪዎችን ውጤትና ስነባህሪ ትንተና /Analysis/

በማድረግ በየጊዜዉ የሚመዘገቡ መልካም ዉጤቶች አጠናክሮ ማስቀጠልና

የሚታዩ ዉሱንነቶችን ለማረም የሚያስችሉ አሰራሮችን መተግበር ላይ

ዉሱንነት መኖሩ፤ (አሶሳ፣ቡሌ ሆራ፣ወልዲያና ወልቂጤ ዩቨርሲቲዎች)፡፡

ሠ. የትምህርት ግብአትና ፋሲሊቲ አቅርቦትን በተመለከተ

በጥንካሬ የታዩ ጉዳዮች፡-

የትምህርት መርጃ መሳሪያዎች (ቤተ መጽሐፍት፣ ወርክሾፖች፣ ቤተ-

ሙከራዎች፣) አዳጊ በሆነ መንገድ ተደራጅተዉ ግብዓት ተሟልቶላቸዉ

አገልግሎት በመስጠት ተማሪዎች በንድፍ ሀሳብ የተማሩትን ትምህርት

የተግባር ልምምድ በማድረግ የተሻለ ውጤት እንዲያስመዘግቡ ለማስቻል ጥረት

መኖሩ (ቡሌ ሆራ፣ በዓዲግራት፣ በአሶሳ፣ ወልቂጤ፣በደ/ታቦር፣ መቱ፣ ወልቂጤ

ዩኒቨርሲቲ)፡፡

የ2010 ዓ.ም ትምህርት ዘመን ሶስተኛው ትዉልድ ዩኒቨርሲቲዎች የትግበራ ምዕራፍ የድጋፍና ክትትል ሥራ ሪፖርት

12

ለአካል ጉዳተኛና ልዩ ፍላጎት ላላቸው ተማሪዎች የመረጡትን ትምህርት ክፍል

ቅድሚያ እንዲያገኙ ከማድረግ ጀምሮ በመማሪያና በማደሪያ ክፍሎቻቸዉ አቅም

በፈቀደ መጠን ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠር ጥረት መደረጉ (በዋቸሞና ወልቂጤ

ዩኒቨርሲቲዎች)

በአብዛኞቹ ተቋማት የዶርሚተሪ አገልግሎት ከሚ/ር መ/ቤቱ በተላከው የስም

ዝርዝር በኮሌጅ ተመድቦ በሚላከው መሰረት በስም ቅደም ተከተላቸው መሰረት

ህብረ-ብሔራዊነትን፣መቻቻልን በሚያጎለብት መልኩ ተመድበዉ፤ በቂ የመጸዳጃ

ቤቶች፤ የውሀና ሻወር የመብራት አቅርቦት እንዲኖር በማድረግ እየተሠራ መሆኑ

በዉሱንነት የታዩና መሻሻል የሚገባቸዉ ጉዳዮች፡-

በአብዛኞቹ ተቋማት ለአንዳንድ ኮርሶች የማጣቀሻ መጻህፍት እጥረት መኖር፣

በቤተ ሙከራዎችም የኬሚካልና ሪኤጀንት እጥረት መኖር፣

በቤተ መፃህፍት የ24 ሰዓት አገልግሎት አለመኖሩ፤ የሰለጠነ ባለሙያ ባለመኖሩ

በወርክሾፖች ማሽኖች ሳይገጣጠሙ ታሽገው የተቀመጡ መሆኑና በተጨማሪም

ለቤተ-ሙከራና ወርክሾፕ የቴክኒክ ረዳቶች የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና

አለመሰጠቱ እንዲሁም የደህንነት መጠበቂያ ቁሳቁሶች Glaves, Eye Goggles

የመሳሰሉት ግብአቶች እንዲሟሉ አለመደረጉ (ዓዲግራት፣ወልዲያ፣አሶሳ

ዩኒቨርሲቲ)፡፡

የዶርሚተሪ አገልግሎት አመቻች እና ተቆጣጣሪዎች ክትትል ባለማድረጋቸው

የጽዳት ሁኔታ ለተማሪዎች ጤና አሳሳቢ መሆኑ፤የትኋን ችግር መኖሩ፤የወንዶች

ልብስ ማጠቢያ እና ማስጫ ቦታ በአረንጓዴ ልማት ምክንያት የተነሳ ቢሆንም

በአቅራቢያው ምትክ አለመዘጋጀቱ (መቱ፣ ወልዲያ ዩኒቨርሲቲ)፡፡

በተማሪዎች መመገቢያ አዳራሽ ዙሪያ ንጽህናቸው የተጠበቀ አለመሆኑና

የመሰለፊያ መጠለያ (ሼድ) አለመኖሩ፤ (ወልዲያ፣ ቡሌ ሆራ፣ ዓዲግራትና መቱ

ዩኒቨርሲቲ)

በተማሪዎች ማደሪያ እና ቤተ መጻህፍት አካባቢ የሚገኙ መጸዳጃና መታጠቢያ

ቤቶች ንጽህና የጎደላቸው መሆኑ (ወልዲያ፣ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ)

የ2010 ዓ.ም ትምህርት ዘመን ሶስተኛው ትዉልድ ዩኒቨርሲቲዎች የትግበራ ምዕራፍ የድጋፍና ክትትል ሥራ ሪፖርት

13

የመምህራንና የተማሪዎች መዝናኛ (የላዉንጅ አገልግሎት፣ DSTV፣ TV room…)

በተሟላ ሁኔታ አለመቅረቡና አርኪ አገልግሎት ማግኘት አለመቻሉ (ቡሌ

ሆራ፣መቱና ወልዲያ ዩኒቨርሲቲዎች)

የአካል ጉዳተኞችንና ልዩ ፍላጎት ያላቸው ተማሪዎችን ታሳቢ ያደረጉ

የመማሪያ ክፍሎች አደረጃጀት በበቂ ግብዓት ለማሟላት የተደረገ ጥረት አናሳ

እንደሆነ ለማየት ተችሏል፤ (ደብረታቦርና ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲዎች)፡፡

አንዳንድ ማሽን ቀጥታ ኃይል /Direct Power/ ቢፈልጉም ምቹ የሆነ ሶኬት

በግድግዳ ላይ ባለመሰራቱ ማሸኑ አገልግሎት እየሰጠ አለመሆኑ።ባለሙያዎቹ

የክፍሉም ሆነ የራሳቸው ዕቅድ የሌላቸው መሆኑና ለቤተ ሙከራው ከሚያስፈልጉ

6 ማኑዋሎች አንድ ብቻ የተዘጋጀ ሲሆን በቤተ ሙከራ የሚሰሩ ሥራዎች መረጃ

ያለመያዝ (አቴንዳንስ፣ ማኑዋል፣በተጨማሪም በቤተሙከራ ውስጥ የካይዘን መርህ

ተግባራዊ አለመደረጉ። ከ2015-2017 (በፈረንጆቹ አቆጣጠር) ጊዜያቸው

ያለፉባቸው /Expired/ የሆኑ ኬሚካሎች ያልተወገዱ መኖራቸዉን ለማየት

ተችሏል። (አሶሳ ዩኒቨርሲቲ)

ረ. ተቋማዊ ፋይዳው የጎለበተ የ ICT አገልግሎትን ማጠናከር

በጥንካሬ የታዩ ጉዳዮች፡-

በአይሲቲ የዩኒቨርሲቲ ኢንደስቲሪ ትስስርን ለማጠናከር ከት/ሚር ስምምነት

ተደርጎባቸዉ የወረዱ Cisco & Huawei academies ተከፍተዉ ለተቋማቱ

ማህበረሰብ አገልግሎት እየሰጡ መሆኑ (ቡሌ ሆራ፣ መቱ፣ ዋቸሞ ዓዲግራት፣

ወልቂጤና አሶሳ ዩኒቨርሲቲዎች)

በተቋማቱ ደረጃዉን የጠበቀ የካምፓስ ኔትዎርክ ለመዘርጋት በተደረገዉ ጥረት ዳታ

ማእከል መገንባቱ፣ ሁሉም ኦፊሶች፣ የኮምፒዉተር ላብራቶሪዎች፣ ኢንተርኔት

ተደራሽ ማድረግ መቻሉ (ዓዲግራት፣ ወልዲያ፣ ቡሌ ሆራ፣ ዋቸሞ፣ ወልቂጤ ፣

አሶሳና ደብረታቦር ዩኒቨርሲቲዎች)

ቡሌ ሆራ፣ ዋቸሞ፣ ወልቂጤ፣ ዓዲግራትና ደብረታቦር ዩኒቨርሲቲዎች ያለዉን

የአይሲቲ መሰረተ ልማት አገልግሎት በመጠቀም ከተማሪዉ ቁጥር ጋር የተቀራረበ

የ Digital Library አገልግሎትና Wi Fi internet access ተደራሽ ማድረግ የቻሉ

ሲሆን አሶሳ ዩኒቨርሲቲ ተግባሩን ለማስጀመር የሚችልበትን ዝግጅት አጠናቋል፡፡

የ2010 ዓ.ም ትምህርት ዘመን ሶስተኛው ትዉልድ ዩኒቨርሲቲዎች የትግበራ ምዕራፍ የድጋፍና ክትትል ሥራ ሪፖርት

14

የዩኒቨርሲቲዉ ሰራተኞች (መምህራን፣ተመራማሪዎች፣ የአስተዳደር ሰራተኞችና

ሁሉም ተማሪዎች) የዩኒቨርሲቲዉን ኢ-ሜል እየተጠቀሙ መሆናቸዉ፣

(ወልቂጤ፣ዋቸሞ፣ዓዲግራት፣ወልዲያ ዩኒቨርሲቲዎች)።

በሁሉም ተቋማት IBEX (ICT) የተደገፈ በፋይናንስ አስተዳደር ስርዓት ተግባራዊ

መደረጉ

በዉሱንነት የታዩና መሻሻል የሚገባቸዉ ጉዳዮች፡-

በእጥረት የታ ጉዳዮች፡-

ከወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ በስተቀር በሁሉም የት/ት ደረጃዎችና ፕሮግራሞች የምርምርና

መመረቂያ ጥናቶች አገልግሎት ተጠቃሚዎች ተደራሽ መሆን እንዲችሉ የዲጂታል

መረጃ ቋት (Institutional repository) አለመደራጀቱ

በሁሉም ሶስተኛ ትውልድ ዩኒቨርሲቲዎች የአይሲቲ አቅም ግንባታ ስልጠና ፍሎጎትን

መሰረት ያደረገ መረጃ ከየክፍሎች በማሰባሰብ ለአመራሮች፣ መምህራኖች፣

ለሠራተኞችና በየደረጃው ላሉ ተጠቃሚዎች በሚፈለገው መጠን ስልጠናዎችን

እንዲያገኙ ከማደረግ አኳያ ክፍተት መኖሩ።

በICT የተደገፈ የሀብት አስተዳደር ስርዓት ተግባራዊ ለማድረግ በሰው ሀብት ልማት

አስተዳደር፤ በቤተ-መፃህፍት፣ በግዥና፣ በሪጅስትራር፣ የተማሪዎች አገልግሎትና

በሌሎችም የስራ ክፍሎች መረጃዎችን አውቶሜንት(Automate) ማድረግ፣ ዘመናዊና

ተደራሽ በማድረግ ስራዎች ትኩረት ተሰጥቷቸዉ ያልተሰሩ መሆኑና በሁለተኛዉ

የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ማጠናቀቂያ በሁሉም ተቋማት ዲጂታል ቤተ

መጻህፍት ተደራሽ ለማድረግ የታሰበዉን ሀገራዊ ግብን ለማሳካት በተጨባጭ እቅድ

የመተግበር ዉሱንነት መኖር (ደብረታቦር፣ቡሌሆራ፣ ወልዲያ ዩኒቨርሲቲዎች)፡፡

እንዲሁም በዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ በICT የተደገፈ የሀብት አስተዳደር ስርዓት

ተግባራዊ ለማድረግ የተዘረጋው የአይቤክስ ሲስተም በተደጋጋሚ መቋረጥና ፈጣን

ጥገና አለመደረጉ የሀብት አስተዳደር ስራውን ማከናወን አለመቻሉ፡፡

የ2010 ዓ.ም ትምህርት ዘመን ሶስተኛው ትዉልድ ዩኒቨርሲቲዎች የትግበራ ምዕራፍ የድጋፍና ክትትል ሥራ ሪፖርት

15

መማሪያ ክፍሎችን በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ በማዘመን smart class rooms

በማደረጃት አገልግሎት ላይ ከማዋል አኳያ በሁሉም የሶስተኛዉ ትዉልድ

ዩኒቨርሲቲዎች ዉሱንነት መኖሩ

መምህራን ፣ ተመራማሪዎች ፣ የአስተዳደር ሰራተኞችና ሁሉም ተማሪዎች

የዩኒቨርሲቲዉን የኢንስቲትዮሽናል ኢሜል በነጻ እንዲጠቀሙ ከማድረግ አኳያ

አብዛኛዉ የዩኒቨርሲቲዉ ማህበረሰብ አለመጠቀሙ፤ (ቡሌሆራ ፣ መቱ ፣ ወልዲያና

ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲዎች)።

በተከፈቱት ICT አካዳሚዎች የመምህራንና የአስተዳደር ሰራተኞች ተሳትፎ አነስተኛ

መሆንና የICT መሰረተ ልማት ዝርጋታዉ የመምህራንን መኖሪያና የተማሪዎችን

ማደሪያ አከባቢዎች ተደራሽ ማድረግ አለመቻሉ Wifi internet access ለተማሪዎች

በቀላሉ ተደራሽ የሚሆኑበት አከባቢን ለይቶ ተደራሽ ማድረግ በሚቻልበት ስፍራ

በማመቻቸት በኩል ውሱንነት ያለ መሆኑ፣ (ቡሌሆራ ዩኒቨርሲቲ)።

ያለዉን የአይ.ሲ.ቲ መሰረተ ልማት (የካምፓስ ኔትዎርክ) በመጠቀም በተቋም ደረጃ

እየተሰጠ ያለዉ (Digital Library, Wi Fi internet access….) አገልግሎት ከፍተኛ

ብክነት የሚታይበት ተጠቃሚዎችን ያላረካ መሆኑ፡-

በዲጅታል ላይብራሪ ከ20ሺ ያላነሱ soft copy መጻህፍት ተጭነዉ በ offline

access ማድረግ ይቻላል ቢባልም ተግባር ላይ ያልዋለ መሆኑ በአስጠቃሚ

ሰራተኞችም እዉቅና የሌለዉ መሆኑ፣

በዲጅታል ላይብራሪ በትንንሽ እንከን ከአገልግሎት መስጠት እየቻሉ

አገልግሎት ሳይሰጡ ለረጅም ጊዜ የተቀመጡ ኮምፒዉተሮች(39) መኖራቸዉ

በአንዳንድ ትምህርት ክፍሎች (ጂኦሎጂ) የተደራጀዉ የኮምፒዉተር

ላብራቶሪ በጥቃቅን ችግሮች 51 ኮምፒዉተሮች ከአንድ አመት በላይ ከስራ

ዉጪ መደረጋቸዉ፤ (ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ)።

የኤሌክትሪክ ኃይል ሲቋረጥ ለአይሲቲ፣ ለቤተ መጻህፍት፣ ለላቦራቶሪዎች፣

ወርክሾፖችና ወዘተ ክፍሎች ጄኔሬተር ባለመኖሩ ለተማሪዎች የሚሰጠውን

አገልግሎት ቀልጣፋና ምቹ ለማድረግ በተማሪዎች መመገቢያ፣ ቤተ መጻህፍትና

ወዘተ one card system ሥርዓት በመዘርጋት ተግባራዊ አለመደረጉ፤በተቋሙ

የተዘረጋው (በገመድ አልባና በባለገመድ) ኔትወርክ ተገቢውን አገልግሎት

መስጠት አለመቻሉ፤ (ወልዲያ ዩኒቨርሲቲ)።

የ2010 ዓ.ም ትምህርት ዘመን ሶስተኛው ትዉልድ ዩኒቨርሲቲዎች የትግበራ ምዕራፍ የድጋፍና ክትትል ሥራ ሪፖርት

16

ሰ. ሰላማዊ መማር ማስተማርን በዩኒቨርስቲዎች ስለማስፈን

በጥንካሬ የታዩ ጉዳዮች፡-

ተማሪዎች በተለያዩ መድረኮች ያነሷቸው ጉዳዮችና ለሰላማዊ መማር ማስተማር

እንቅፋት ሊሆኑ የሚችሉ ነጥቦች ተለይተው በሚመለከታቸው ክፍሎች እንዲፈቱ

የሚያስችል ስራ መሰራቱ (ወልቂጤ፣ አሶሳ፣ ቡሌሆራና ዓዲግራት

ዩኒቨርሲቲዎች)።

ከአካባቢው መስተዳድር ጋር በቅንጅት መሰራቱ፤በተማሪዎች የሚፈጠሩ

አደረጃጀቶች በሰላማዊ መማር ማስተማር ላይ በቅንጅትና በህብረት መስራት

መቻሉ፤ተማሪዎችና ሰራተኞች መካከል መልካም ግንኙነት መኖሩ፤ (አሶሳና

ወልዲያ ዩኒቨርሲቲ)።

ሰላማዊ መማር ማስተማር መስተጓጎል መንስኤ ሊሆኑ የሚችሉ ርዕሰ ጉዳዮችን

አስቀድሞ በመለየት ከህዝብ ክንፉ፣ ከተቋሙና ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር በጋራ

በመስራቱ በተቋሙ ሰላማዊ መማር ማስተማርን በሚያስመሰግን ደረጃ ማስፈን

መቻሉ። የሚፈጠሩ አደረጃጀቶች በሰላማዊ መማር ማስተማር ላይ በቅንጅትና

በህብረት መስራት እንዲችሉ የሰላም ፎረም እና የተማሪዎች ህብረት ተወካዮችን

በማደራጀት እየሰራ መሆኑ፤ (ዋቸሞ፣ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ)፡፡

በተቋሙ ተማሪዎችና ሰራተኞች መካከል መልካም ግንኙነት እንዲኖር የአቅም

ግንባታ ስልጠናዎች ለጥበቃ ሰራተኞች፣ለፕሮክተሮች፣ለምግብ ቤት ሰራተኞች፣ ቤተ

መፃህፍት ሰራተኞችስለመሰጠቱ ፤ ለክሊኒክ የህክምና ባለሙያዎች ከአጋር አካላት

በመቀናጀት ወቅታዊ የሆነ የሙያ ማሻሻያ ስልጠና መሰጠቱንና የሥልጠናወን ፋይዳ

የዳሰሳ ጥናት መደረጉን ከሰነድና ከዉይይት መድረኮች ለማረጋገጥ መቻሉ (ወልቂጤ

ዩኒቨርሲቲ)

የተማሪዎችን ስነ ምግባር ለማሻሻል በተቋሙ እየተከናወኑ ያሉ ተግባሮችና

በተጨባጭ የመጣው ለውጥ፤ (ከተማሪዎች አለባበስ፣ ከጸጉር ስታይል፣ የብሄር

ብሄረሰቦችን ብዝሃነት ከማክበር፣ ከአደንዛዥ እጽ ከመራቅ፣ የተቋሙን ንብረት

ከመጠበቅና ከመከባከብ እና ኩረጃን ከመፀየፍ አንፃር) እንዲሁምየተማሪዎችን code

of condact አተገባበር በተመለከተ በተለይም አደንዛዥ ዕጽን ከመከላከል አንጻር

የ2010 ዓ.ም ትምህርት ዘመን ሶስተኛው ትዉልድ ዩኒቨርሲቲዎች የትግበራ ምዕራፍ የድጋፍና ክትትል ሥራ ሪፖርት

17

ከመቀሌ ዩኒቨርሲቲ መቋሚያ ከተባለ ማህበር ጋር በመተባበር ለተማሪዎች የ4 ቀን

ሥልጠና መሰጠቱ፣ (ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ)፡፡

በዉሱንነት የታዩና መሻሻል የሚገባቸዉ ጉዳዮች፡-

በአካባቢ የሚፈጸሙ ስርቆትና አልፎ አልፎ ሚከሰቱ ድብደባዎች እንዳሉ በነበሩ

በሁሉም መድረኮች ስለተነሳና ስጋት ስላለ ትኩረት ተጥቶ ቢሰራ፣ ለመማር ማስተማሩ

ሥራ እንቅፋት እንዳይሆኑ ችግሮችን አስቀድሞ በመለየት ምላሽ ለመስጠት ጥረት

አለመደረጉ፤ (ደብረ ታቦር ዩኒቨርስቲ)፡፡

የተማሪው ሥነ ምግባር እንዲሻሻል ከማድረግ አንጻር የተሰሩ ሥራዎች ውስን መሆኑና

ተማሪዎች ከግቢ ወጪ ተከራይተው መኖራቸው፣ (ወልዲያ፣ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲዎች)።

ኩረጃን እንዲጸየፉ ከማድረግ አንጻር ክፍተት መኖሩ፣ የመምህራንና ተማሪዎች

አለባበስና ጸጉር ስታይል ላይ ጠንከር ያለ ስራ ባለመሰራቱ ክፍተት መታየቱ፤

( ወልቂጤና ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲዎች)።

በተማሪዎችና ሰራተኞች መካከል መልካም ግንኙነት እንዲኖር የአቅም ግንባታ

ስልጠናዎች ለጥበቃ ሰራተኞች ፣ ለፕሮክተሮች፣ ለምግብ ቤት ሰራተኞች፣ ቤተ

መፃህፍት ሰራተኞች የተሰጡ ስልጠናዎች በቂ ካለመሆናቸዉም በላይ ስልጠናዎቹ

ያስገኙት ፋይዳ እየተለካ ለላቀ አፈጻጸም ለማብቃት የሚያስችል አሰራርን አጠናክሮ

መቀጠል አለመቻል፤ በተማሪዎች ክሊኒክ የህክምና ባለሙያዎችን ከአጋር አካላት ጋር

በመተባበር ወቅታዊ የሆነ የሙያ ማሻሻያ ስልጠና እንዲያገኙ ከማድረግ አንጻር

ውሱንነት ያለ መሆኑ እንዲሁም አገራዊ ኩነቶችን መሰረት በማድረግ ተማሪዎች

የሀገር ፍቅር ስሜትን እንዲያጎለብቱና ችግሮችን በሰለጠነ መንገድ የመፍታት

ልምድን እንዲያዳብሩ ግንዛቤ ከመፍጠር አኳያ እጥረት ያለ መሆኑ

፤(ዓዲግራት፣ወልዲያ፣ ቡሌሆራ ዩኒቨርሲቲዎች)።

ተማሪዎች በተለያዩ መድረኮች የሚያነሷቸው ጉዳዮችና ለሰላማዊ መማር ማስተማር

እንቅፋት ሊሆኑ የሚችሉ ነጥቦች ተለይተው ቢታወቁም ከትምህርት ክፍል ጀምሮ

ባሉት አንዳንድ አመራሮች የውሳኔዎች መዘግየት እየታየ እና ፈጣን ምላሽ

እየተሰጣቸው አለመሆኑ ተማሪዎች በምሬት ማንሳታቸው እንዲሁም ተቋሙ ዙሪያ

አጥር ስራ ባለመጠናቀቁ የተማሪዎችን ስነ ምግባር ለማሻሻል በተቋሙ እየተከናወኑ

ያሉ ተግባሮችና በተጨባጭ የመጣው ለውጥ በተለይም ከተማሪዎች ስነምግባር

የ2010 ዓ.ም ትምህርት ዘመን ሶስተኛው ትዉልድ ዩኒቨርሲቲዎች የትግበራ ምዕራፍ የድጋፍና ክትትል ሥራ ሪፖርት

18

ጉዳዮች እና ከአደንዛዥ ዕጽ ከመራቅ አንጻር እየተሰሩ ያሉ ስራዎች አጥጋቢ

አለመሆን፤(አሶሳ ዩኒቨረሲቲ)።

2.2 የጥናትና ምርምር አተገባበርን በተመለከተ

በጥንካሬ የታዩ ጉዳዮች፡-

በሁሉም ሶስተኛ ትውልድ ዩኒቨረሲቲዎች በአገራዊ ፍላጐት ላይ የተመሰረተ ጥናትና

ምርምር ለማድረግ የአሠራር ሥርዓት በመዘርጋት የአፈጻጸም መመሪያና እቅድ

ተዘጋጅቶና ትኩረት የሚደረግባቸው የጥናትና ምርምር መስኮች /thematic areas/

በግልጽ መለየቱ፣ ለጥናትና ምርምር ተግባር ግልጽና ፍትሃዊ የበጀት ድልድል አሰራር

ሥርዓት መተግበሩና የበጀት አጠቃቀም ክትትል ለማድረግ ያመች ዘንድ የአፈጻጸም

ሪፖርቶችን በመገምገም የሚለቀቅ መሆኑ፤ የተለያዩ የትምህርት ክፍሎች፣ ጀማሪና

ነባር ተመራማሪዎች በቅንጅት ጥናትና ምርምር እንዲያካሂዱ በማድረግ ልምድ

እንዲለዋወጡና በቡድን የመስራት ስሜትን እንዲያዳብሩ መደረጉ፡፡

የሀገሪቱን የልማት አጀንዳዎች መሰረት በማድረግ ከሌሎች የምርምር ተቋማት፣ ሀገር

ውስጥና ከውጭ ሀገር ካሉ አቻ የምርምር ተቋማት ጋር ትስስር በመፍጠርና

በመቀናጀት የተለያዩ የምርምር ፕሮጀክቶችን አቅም በፈቀደ መጠን ለማካሄድ

ጅምር ሥራዎች መኖራቸው በተጨማሪም ሴት ተመራማሪዎች በጥናትና ምርምር ላይ

እንዲሳተፉ ለማድረግ ሥርዓት በመዘርጋት መተግበሩ።

በወልዲያ ዩኒቨርሲቲ በግቢ ውስጥ በሚገኘው የሀገር በቀል እፅዋት ጥበቃና ክብካቤ

የምርምር ማዕከል የተቋቋመ ሲሆን ይህንን ሂደት ከኢትዮጵያ ብዝሃ ህይወት

ኢንስቲትዩት ጋር በመነጋገር የማሰልጠኛ ማዕከል ለማድረግ ስምምነት ላይ

መደረሱ፡፡

ለምርምር ስራዉ አስፈላጊ የሆነ ሀብት ከአጠቃላይ የስራ ማስኬጃ የተቋሙ በጀት

እንደየተቋማቱ ሁኔታ መመደብ የተቻለ ሲሆን

ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ 5% (13ሚሊየን) ድርሻ ያለዉ በጀት መመደቡ

መቱ ዩኒቨርሲቲ 9% (23ሚሊየን) ድርሻ ያለዉ በጀት መመደቡ

በሁሉም የሶስተኛ ትዉልድ ተቋማት የጥናትና ምርምር ሥራውን ለማበረታታት

የክትትልና ድጋፍ ሥርዓት ተዘርግቶ የምርምር ፕሮጀክቶች እያሳዩት ያለዉን

እድገት በአካልና በጽሁፍ ሪፖርት በመከታተልና ድጋፍ ኤየተደረገ መሆኑ

የ2010 ዓ.ም ትምህርት ዘመን ሶስተኛው ትዉልድ ዩኒቨርሲቲዎች የትግበራ ምዕራፍ የድጋፍና ክትትል ሥራ ሪፖርት

19

በታዋቂ ዓለምአቀፍ ጆርናሎች ላይ በ2009 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የታተሙ

የምርምር ዉጤቶች መኖራቸዉና ለሚያሳትሙ መምህራን የማሳተሚያ ወጪን

በመደጎም ማበረታቻ እየተደረገ መሆኑ፤ (መቱ፣ቡሌሆራ፣አሶሳ ዩኒቨርሲቲ)፡፡

ከኢንዳስትሪና ከአለም አቀፍ የምርምር ገንዘብ ምንጮች /ከውጭ አገር አቻ

ዩኒቨርሲቲዎችና ሌሎች ድርጅቶች/ በፈጠረው ትስስር ፤ ለምርምር የሚሆን በአይነት

በጥሬ ገንዝብና በእውቀት ሀብት ከማሰባሰብ አኳያ

ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ 16 ሚሊየን ብርና 20ሺ ዩሮ ማግኘት መቻሉ

መቱ ዩኒቨርሲቲ ከ1.2 ሚሊዮን ብር ማግኘት መቻሉ

በዉሱንነት የታዩና መሻሻል የሚገባቸዉ ጉዳዮች፡-

ከኢንዳስትሪና ከዓለም አቀፍ አቻ ዩኒቨርሲቲዎች እና ሌሎች ድርጅቶች ትስስር

በመፍጠር የእውቀት ሽግግር፣ የቁሳቁስ አቅርቦት በዓይነትና በጥሬ የገንዘብ ድጋፍ

ከማግኘት አንጻር የሚደረግበትን አሰራር አጠናክሮ ማስቀጠል አለመቻሉ፡፡

(ቡሌሆራ፣አዲግራትና አሶሳ ዩኒቨርሲቲዎች)

የምርምርና ከዚሁ ተግባር ጋር የሚያያዙ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን በማዘጋጀት

ለመምህራንና ለተመራማሪዎች ያልተሰጠ በመሆኑና በተለይ የሴት ተመራማሪዎች

በመሪ ተመራማሪነት ተሳትፎ አናሳ በመሆኑ (መቱ፣ዓዲግራትና አሶሳ

ዩኒቨርሲቲዎች)፡፡

የጥናትና ምርምር አሰራር ሂደት በአብዛኛው Small Scale Research ላይ ያተኮረ

መሆኑ (Medium and Large Scale ጥናቶች አለመጀመራቸው)፤የጥናት እና ምርምር

ስራዎችን በታዋቂ ጆርናሎች ላይ መምህራን ያሳተሙ ቢሆንም አሃዛዊ መረጃ ማቅረብ

አለመቻሉና የእውቅና ምስክር ወረቀት አለመሰጠቱ፤ (ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ)፡፡

የምርምር በጀት ማነስ ጋር በተያያዘ ቅሬታዎች እየሰፉ መምጣታቸውን ና ለምርምር

ስራው የሚያስፈልጉ ግብአቶች በወቅቱ ተገዝተው አለመምጣት፣ (ደ/ታቦር

ዩኒቨርሲቲ)፡፡

የጥናትና ምርምር መስኮችን /thematic areas/ ለአካባቢዉ ማህበረሰብ፣

ለተመራማሪዎችና ለምርምር ተቋማት፤ የምርምር ዉጤትን ለሚጠቀሙ አምራቾችና

አልሚዎች፤ መንግስታዊና መንግስታዊ ላልሆኑ ተቋማት፤ የምርምር ወጪ መሸፈን

የ2010 ዓ.ም ትምህርት ዘመን ሶስተኛው ትዉልድ ዩኒቨርሲቲዎች የትግበራ ምዕራፍ የድጋፍና ክትትል ሥራ ሪፖርት

20

ለሚችሉ የፋይናንስ ተቋማት፤ እና መሰል አጋሮች እዉቅና የሚፈጠርባቸዉን ሁሉንም

የሚዲያ አማራጮች ማለትም ቢል ቦርድ፣ በራሪ ወረቀቶች፣ መጽሄቶች፣ ድረ ገጽ…

በመመጠቀም ረገድና የሴት ተመራማሪዎች ተሳትፎ ካለፉት አመታት አንጻር ያለዉን

ዕድገት የሚያመላክት ክትትል እየተደረገ ስለመተግበሩ መረጃ ማግኘት አለመቻል፤

(ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ)፡፡

ተቋሙ ከኢንዱስትሪ እና አለም አቀፍ ምንጮች በፈጠረዉ ትስስር በአይነት ፤በገንዘብ

፤በእዉቀት ሽግግር ምርምርን ለማሳደግ 50%እና ከዚያ በላይ ሀብት ለመሰብሰብ

የተደረገ ጥረት ዉስንናነት መኖሩ፣ የጥናትና ምርምር ውጤቶችን ለተጠቃሚዎችን

ለመድረስ የሚጠቀሙባቸው ስትራቴጂዎች በግልጽ ከማስቀመጥ አንጻር ክፍተት

መኖሩ እና የሴት ተመራቂዎች ተሳትፎ ለማሳደግ የማትጊያ ሥርዓት

በመዘርጋት(ስልጠና መሪ ተመራማሪዎችና በጀት) የተለዩ ከትትልና ድጋፍ

ያለማደረግ፤ (ወልቂጤና አሶሳ ዩኒቨርሲቲዎች)፡፡ እንዲሁም በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ

ለምርምር የሚመደበው በጀት ከተቋሙ መደበኛ በጀት ጋር ሲነጸጻር ከ5% በታች

በመሆኑ የሚያስፈልጉ የግብዓት እጥረት መኖሩ።

2.3 ማህበረሰብ አገልግሎትን በተመለከተ

በጥንካሬ የታዩ ጉዳዮች፡-

በሁሉም ሶስተኛ ትውልድ ዩኒቨረሲቲዎች አገራዊውን ፍላጎት መሰረት ያደረገ

ለማህበረሰብ አገልግሎት የሚውል የአጠቃቀም መመሪያን በማዘጋጀት ወደ ሥራ

መገባቱ።

የተለያዩ የምርምርና የቴክኖሎጂ ውጤቶች ወደ ፕሮጀክትነት ተለውጠው እንዲሰርጹና

እንዲሸጋገሩ ከማድረግ አንፃር የበለስ ትል የመከላከል፣ የዘር ብዜት በዓዲግራት

ዩኒቨርሲቲ ጅምር ሥራዎች ሲኖሩ በደብረታ ቦርና ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲዎች የተለያዩ

የምርምርና የቴክኖሎጂ ውጤቶችን ወደ ፕሮጀክትነት በመለወጥ ወደ ህብረተሰቡ

እንዲሸጋገሩ በማድረግ የአከባቢውን ህብረተሰብ የኑሮ ደረጃ ለማሻሻል የቴክኖሎጅ

ሽግግር ላይ እየተደረገ እንደሆነና በቡለሆራ ዩኒቨርሲቲ /በንብ ማነብ፣ ካዛቫ ተክል/

የማሸጋገር ሂደት መኖሩ። በወልዲያ ዩኒቨርሲቲ የተለያዩ የምርምርና የቴክኖሎጂ

ውጤቶች ወደ ፕሮጀክትነት ተለውጠው እንዲሰርጹና እንዲሸጋገሩ ከማድረግ አንፃር በ6

ዘርፎች ላይ ሥራዎች የተከናወኑ መሆኑ ለአብነት ያህል የሞላሰስ ኬክ ለከብቶች

የ2010 ዓ.ም ትምህርት ዘመን ሶስተኛው ትዉልድ ዩኒቨርሲቲዎች የትግበራ ምዕራፍ የድጋፍና ክትትል ሥራ ሪፖርት

21

መኖነት እንዲውል መደረጉ፣ የከብቶች መኖ ዘር ብዜት፣ የተሻሻሉ የማሽላና የጤፍ ዘር

ተግባራትን በማከናወን ማህበረሰቡን ለመደገፍ ጥረት መደረጉ።

ከአካባቢው ካሉ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ጋር በመገናኘት በክረምት ተማሪዎችን

ተቀብሎ የማሰልጠን፣ደረጃውን የጠበቀ ዘመናዊ ቤተመፃህፍት በመገንባት ግብአት

እንድሟላ በማድረግና ሙያዊ እገዛ በመስጠት ሞዴል ማድረግ መቻሉ (ደ/ታቦር

ዩኒቨርሲቲ)፡፡

ለ2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች ለሚገኙ ተማሪዎች የማጠናከሪያ ትምህርትና የቤተ ሙከራ

ቁሳቁስ ጥገና፣ ክረምት ስቲም ፕሮግራም በመተግበር ድጋፍ መደረጉ፤ እንዲሁም ነፃ

የህግ አገልግሎት መስጠት፣ ከጤና ተቋማት ጋር ኢንተርንሺፕ አገልግሎትና ስልጠና፣

በከተማ ሆስፒታሎች የሙያ አገልግሎት መሰጠቱ እና ለማህበረሰብ አገልግሎት

የሚውል ሀብት ከማመንጨት ጋር በተገናኘ ከማማከር ገቢ መገኘቱ፤30 የ2ኛ ደረጃ

ተማሪዎችን መርጦ በማስተማር ወደ ተሻለ ደረጃ እንዲደርሱ በቅንጅት የተሰራመሆኑና

ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ ስፖርት ቡድንን በመደገፍ ተሳትፎ ማድረግ መቻሉ

እንዲሁም የቱሪዝም ሥራዎችን በማስተዋወቅ ረገድ ባህላዊና ማኅበራዊ እሴቶችን

እንዲዳብሩ ለማድረግ መሠራቱ፤ (ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ)፡፡

በተቋሙ እየተተገበሩ ያሉ የማህበረሰብ አገልግሎት ተግባራትንና የምርምር ዉጤቶችን

ለህብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግ ለአከባቢዉ ማህበረሰብ የተሻሻሉ እንስሳትና የሰብል

ዝርዎች ማስፋፋት እየተሰራ ሲሆን ከኦሮሚያ ማዕድን ቢሮ ጋር በመተባበር ሙያዊ

ድጋፍ በማድረግ ለ11 ግለሰቦች ባዮ ጋዝ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረግ መቻሉ

እንዲሁም 13 ግለሰቦች የሚጠበቅባቸውን ቅድሚያ እንዲያሟሉና እንዲሰራላቸው

ፕሮግራም የተያዘላቸው ሲሆን በአካባቢዉ ካሉ ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማት ፣

2ኛ ደረጃ ት/ቤቶችን፣ የጤና ተቋማት፣ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች፣የፍትህ

ተቋማትን በልዩ ልዩ አግባብ በመደገፍ ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉ፤(ቡሌ

ሆራ ዩኒቨርሲቲ)፡፡

በምርምርና ማኀበረሰብ አገልግሎት የአካባቢውን ፍላጎትና ችግር በመለየት

ማኀበረሰቡን ተጠቃሚ ያደረጉ ሥራዎችና ስልጠናዎች በትምህርት፣በግብርና

በጤና፣ በህግ ፣ እየተሰሩና እየተሰጡ መሆናቸው፤ለመሳያ፡-

50 ለሚሆኑ የህግ ታራሚዎችና የህግ አስከባሪዎች Disability በሚል ርዕስ

የ2010 ዓ.ም ትምህርት ዘመን ሶስተኛው ትዉልድ ዩኒቨርሲቲዎች የትግበራ ምዕራፍ የድጋፍና ክትትል ሥራ ሪፖርት

22

ለ60 ሴት ሞዴል አርሶ አደሮች ለ5 ተከታታይ ቀናት Saving and

Improvement በሚል ርዕስ

ለ25 የቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ አሰልጣኞች ለ8 ተከታታይ ቀናት AutoCAD

and Solid work በሚል ርዕስ

ለ10 የገጠር ወጣቶች የ15 ቀን ስልጠና በፈሳሽና በደረቅ ሳሙና አዘገጃጀት

ስልጠና በመስጠት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ተደርጓል፤

ከመቱ ወረዳ ጤና፣ ግብርና ፣ትምህርትና የቀበሌ አመራር ለመጡ 60

ሰልጣኞች Adult Education በሚል ርዕስ

በኢሊባቡርና በቡኖ በደሌ ዞን ለሚገኙ የ2ኛ ደ/ት/ቤት ለ600 የሳይንስ

ተማሪዎች በ STEM እና English language በክረምት ወራት ማጠናከሪያ

ትምህርት የተሰጣቸው መሆኑ

ለ192 ሰዎች ነፃ የህግ አገልግሎት እንዲያገኙ በማድረግ ተጠቃሚ እንዲሆኑ

ተደርጎ። እየተተገበሩ ያሉ የማህበረሰብ አገልግሎት ተግባራትንና የምርምር

ዉጤቶችን ለህብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግ በዩኒቨርስቲዉ FM 95.6 የሚል

የማህበረሰብ ሬዲዮ ጣቢያ በመክፈት ከቀኑ 5 ሰዓት እስከ ምሽቱ 12 ሰዓት

በማሰራጨት አገልግሎት እየሰጠ ሲሆን በንብ፣በአሳ እና በዶሮ እርባታዎች

የተገኙ ጥናትና ምርምር ውጤቶች ፕሮጀክት በመቅረፅ 60 የሚሆኑ

የአካባቢው አርሶ አደሮች በዘመናዊ የአመራረት ዘዴ እንዲጠቀሙ

መደረጋቸው፣ (መቱ ዩኒቨርሲቲ)፡፡

እየተተገበሩ ያሉ የማህበረሰብ አገልግሎት ተግባራትንና የምርምር ዉጤቶችን

ለህብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግ በአከባቢዉ ካለ FM ሬዲዮ ጣቢያ የአየር ሰዓት

በመግዛት ተደራሽ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑና በተደራጁ የምርምር ጣቢያዎች

የተሻሻሉ ዝርያዎችን ማለትም በአፕል፣ በቡና፣ በእንሰት፣ በስንዴና በቆሎ ለማሰራጨት

እየተሰራ ከመሆኑም በላይ መሰራች ዘሮችን ለማባዛት የሚያስችል ፈቃድ ያገኘመሆኑ።

በአካባቢዉ ካሉ ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማት ፣ 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶችን፣ የጤና

ተቋማት፣ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች፣ የፍትህ ተቋማትን በልዩ ልዩ አግባብ

በመደገፍ ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉ፤ (ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ)፡፡

ለ2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች ለሚገኙ ተማሪዎች የማጠናከሪያ ትምህርትና የቤተ ሙከራ

ቁሳቁስ ጥገና፣ ክረምት ስቲም ፕሮግራም በመተግበር ድጋፍ መደረጉና ከፍትህ እና

የ2010 ዓ.ም ትምህርት ዘመን ሶስተኛው ትዉልድ ዩኒቨርሲቲዎች የትግበራ ምዕራፍ የድጋፍና ክትትል ሥራ ሪፖርት

23

ፖሊስ ጋር በመተባበር የህገ ወጥ የሰዎች ዝውውርና የሴቶችን ህፃናት ጥቃትን

በተመለከተ የግንዛቤ መስጫ ሥራ መከናወኑ እንዲሁም በምስርና በላስታና ሰቆጣ ማር

ብራንድ ለማሰጠት እየተሰራ ሲሆን ከሴቶችና ህፃናት ፅ/ቤት ጋር በመቀናጀት አንድ ሺ

ለሚጠጉ የኢኮኖሚ ተጋላጭ ለሆኑ ወላጆች የግብዓት ድጋፍ በማድረግና

ቤተሰቦቻቸውን ወደ ቁጠባ ሥርዓት እንዲገቡ ተደርጎ ሥራ እንዲጀምሩ በተጨማሪም

ዩኒቨርሲቲው ለማህበረሰብ አገልግሎት የሚውል ሀብት ከማመንጨት ጋር በተገናኘ

በማማከር እና የመኖሪያ ቤት ፕላን በማዘጋጀት ገቢ መገኘቱ፤ (ወልዲያ ዩኒቨርሲቲ)፡፡

የተለያዩ የምርምርና የቴክኖሎጂ ውጤቶች ወደ ፕሮጀክትነት ተለዉጠዉ እንዲሰርጹና

እንዲሸጋገሩ በማድረግ የአከባቢውን ህብረተሰብ የኑሮ ደረጃ ለማሻሻል ተደራሽ የሆኑ

የቴክኖሎጂዎች ከማስረጽ አንጻር ዩኒቨርስቲ ከሆለታ የግብርና ባዮቴክኖሎጂ እና

የጉራጌ ዞን እንስሳትና የአሳ ሃብት ቢሮ በጋራ በመሆን በጉራጌዞን በሚገኙ ጉመርና

እዣ ወረዳ የወተት ውጤት ለማሻሻል የሚያስችል ስራ በተሻሻሉ ከብቶች ሰው ሰራሽ

የማዳቀል ስራ መከናወኑ፤ በዩኒቨርስቲው አካባቢ ከቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማት

አብሮ ከመሥራት አንጻር በዩኒቨርሲቲው ለየቴ/ሙያ ስልጣኞች የተግበር ትብብር

ስልጠና አገልገሎት ለመስጠት Value chain analysiscc, በቴክኒካል

ድሮዊንግ፣በዲዛይን ኘሮሲጀር፣በdyeing operation እና Knittingoperation፣ በአውቶካድ

ሶፍት ዌር አጠቃቀም፣በሶሊድ መርክ ሶፍት ዌር አጠቃቀም፣በካቲያ ሶፍት

ዌር፣በዲጅታል ኢምብሮደሪ ላይ ስልጠና ለመስጠት የማንዋል ዝግጅት ተጠናቆ

በዝግጀት ላይ መሆኑ ፣ የፍትህ ተቋማት ጋር በጋራ ከመሥራት አንጻር ከ2006 ዓ.ም

ጀምሮ ነጻ የህግ ምክር መስጫ ማእከል በመክፈት አቅም ለሌላቸው የህ/ሰብ ክፍሎች

የማማከር፤ የክስና የአቤቱታ፣ የመልስ፣የይግባይ፣የአፈፃፀም እንዲሁም የጥብቅና

አገልግሎት በተመለከተ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች አገልግሎት

የሚያገኙበት ሁኔታ በማመቻቸት የበኩሉን ሃላፊነት እየተወጣ ይገኛል፡፡. ከዚህ አካያ

ዩኒቨርስቲው አስካሁን 123 የማማከር፤ 127 የክስ ማዘጋጀት፤ መልስ፤የመልስ መልስ

፤ይግባኝ እና 75 የፍርድ ቤት ውክልና በመውሰድ እነዲሁም 17 ጉዳዮችን በድርድር

እንዲያልቁ በማድረግ በድምሩ 342 ጉዳዮች በነጻ የህግ መስጫ ማእከሉን

እንዲሰተናገዱ መደረጉ፣ እና የማምረቻ ተቋማት ጋር በመቀናጀት በልዩ ልዩ አግባብ

ከመደገፍና በጋራ ከመሥራት አንጻር ለአብነት የካቲት የወረቀት ፋብሪካ፣ Tabor

cermic factory, EBC, STVR,INSA,METCH, Avon PLC,Abyssinia tannery

የ2010 ዓ.ም ትምህርት ዘመን ሶስተኛው ትዉልድ ዩኒቨርሲቲዎች የትግበራ ምዕራፍ የድጋፍና ክትትል ሥራ ሪፖርት

24

LIT,EEPC, Awash Tannery LIT, Kality food complex, Ethio-leather industry

P.L.C,Haile garment, GMM garment, የተቋሙ ተማሪዎች የትራንስፖርት

እየተከፈላቸው፣ የኢንዱስትሪውን ችግር በመለየት እንዲሰሩ እድል የፈጠረ መሆኑ፣

(ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ)፡፡

በእጥረት የታዩ ጉዳዮች፡-

የማህበረሰብ አገልግሎትን በስፋት መስራት ይቻል ዘንድ ለተግባራት ማስፈጸሚያ የሚሆን ሀብት የማመንጨት ስራዎች ላይ በቀሪ ጊዜያት እንዲጠናከሩ ርብርብ ቢደረግና የራሱ አየር ሰዓት በመጠቀም ለማህበረሰቡ ግንዛቤ መስጠት ላይ ትኩረት አድርጎ ቢሰራበት፤( ዩኒቨርሲቲዎች)፡፡

ሙያዊ የሆኑና የምርምር ውጤቶችን በቀጥታ ለህበረተሰቡና ለባለ ድርሻ አካላት

ተደራሽ የሚያደርግበት የማህበረሰብ ሬድዮና የራሱ ጋዜጣ ማቋቋማ ላይ ትኩረት

ተሰጥቶ መስራት ላይ ውሱንነት ያለ መሆኑ (ዓዲግራት፣ቡሌሆራ፣መቱ ፣ደ/ታቦርና

ወልዲያ ዩኒቨርሲቲዎች)፡፡

የማህበረሰብ አገልግሎት ስራዎች ፣ቴክኖሎጂን አዳዲስ አሰራሮችን ወደ ማህበረሰቡ

በማስረጽ የህብረተሰቡን ኑሮ ማሻሻል እንጂ የእርዳታ ሰጪነት አመለካከትንም

ተግባርንም ለመከላከል አልሞ መስራትና እየተሰጡ ያሉ የማህበረሰብ አቀፍ

አገልግሎቶች ተደራሽነትና አግባብነት በህብረተሰቡ ያለውን የአመለካከት ለውጥ፣

የሚሰጡት አገልግሎቶች ያመጡትን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ለውጥ እና ፋይዳ

በመገምገምና ከሚገኘው ውጤት በመነሳት የአሰራር ስርአቶችን ማሸሻልና ማዘመን ላይ

አሁንም መስራት የሚጠይቅ መሆኑ /በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች/

በተቋሙ አከባቢ ከሚገኙ 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶችን፣ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች

ከመደገፍና በጋራ ከመሥራት አንጻር ከፍተት መኖሩ፤ (ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ)፡፡

2.4 የዩኒቨርሲቲ ኢንዱስትሪ ትስስር

በጥንካሬ የታዩ ጉዳዮች፡-

የ2010 ዓ.ም ትምህርት ዘመን ሶስተኛው ትዉልድ ዩኒቨርሲቲዎች የትግበራ ምዕራፍ የድጋፍና ክትትል ሥራ ሪፖርት

25

በአብዛኞቹ የሶስተኛ ትውልድ ዩኒቨርሲቲዎች የዩኒቨርሲቲ ኢንደስትሪ ትስስርን

በበላይነት የሚመራ አደረጃጀት ተፈጥሮ በተገቢዉ የሰዉ ኃይልና ግብዓት

ተደራጅቶ ወደ ስራ መግባት መቻሉ፤

እንደተቋማቱ ነባራዊ ሁኔታ የኢንዱስትሪ ተቋማትን በመለየት የመግባቢያ

የስምምነት ሰነድ በመፈራረም በስምምነታቸዉ መሰረት ወደ ተግባር መግባት

መቻሉ

የተቋቋሙ የስራ ፈጠራ ማዕከላት (business incubation center) ከማደራጀት

አኳያ የICT Incubation Center በማቋቋም የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ተሰጥቶ

ወደ ስራ ለመግባት እየተሰራ መሆኑ/ (ዋቸሞ፣ ወልዲያ፣ ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ)፡፡

በተቋሙ የፈጠራ ውጤቶች መኖራቸው (በቀርከሃ ቴክኖሎጂ፣ የሌዘር ማቅለጫ

ቴክኖሎጂ፣ ጉድጓድ መቆፈሪያ ማሽንና የአማርኛ ቃላትን በድምጽ የሚያሰማ

ሶፍትዌር ቴክኖሎጂን) የፈጠራ ውጤት መኖሩ፤(ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ)፡፡

ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ ባይሆንም ተማሪዎች በንድፈ ሀሳብ የተማሩትን

በተገባር እንዲማሩት ለማድረግ ጥረቶች እየተደረጉ እንደሆነ ከነበሩ የውይይት

መድረኮች ለመረዳት ተችሏል፣ተማሪዎች ወደ ተግባር ትምህርት ትምህርት ሲላኩ

ጠንካራ ክትትል እየተደረገ እንደሚከናወን ከነበሩ የውይይት መድረኮች ለመረዳት

ተችሏል፣ (ደ/ታቦር ዩኒቨርሲቲ)፡፡

በዉሱንነት የታዩና ሊሻሻሉ የሚገባቸዉ ጉዳዮች፡-

በሁሉም የሶስተኛ ትዉልድ ዩኒቨርሲቲዎች ትስስር የፈጠሩ ኢንዱስትሪዎች ከተቋሙ

ለተግባር ትምህርት የሚላኩ ተማሪዎችን በቅንነት ተቀብሎ በማስተማር/በማለማመድ

በኩል የሚታዩ ዉስንነቶች ለመፍታት በስፋት መስራት ቢቻልና እየተሰጡ ያሉ ሁሉም

ፕሮግራሞች የየራሳቸዉን ኢንዱስትሪ በመለየት ትስስር ፈጥሮ ከመሄድ አንጻር በሙሉ

አቅም መስራት አለመቻል

በክፍሉ ኢንተርንሺፕ፣ ኢንዱስትሪ ዩኒቨርሲቲ ትስስር እና ቴክኖሎጂ ሽግግር የሚመራ

ባለሙያዎች ባለመኖራቸው ሥራዎች በአግባቡ እየተከናወኑ አለመሆኑና የስራ ፈጠራ

ማዕከላት (Business Incubation Center) አለመደራጀቱና ለኢንዱስትሪዎች

የሚያደርገው አስተዋጽኦ ዝቅተኛ በመሆኑ ከኢንዱስትሪዎች ጋር የተፈጠረ ትስስር

ቢኖርም በተደረገው የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ መሰረት ወደ ተግባር አለመገባቱና

የ2010 ዓ.ም ትምህርት ዘመን ሶስተኛው ትዉልድ ዩኒቨርሲቲዎች የትግበራ ምዕራፍ የድጋፍና ክትትል ሥራ ሪፖርት

26

ተማሪዎችን ከየኢንዳስትሪዎች ሚገኘውን የተግባር ትምህርት እንዲያገኙ የሚደረግበት

አሰራር አለመኖር፤ (ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ)፡፡

በወልዲያና ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲዎች የቴክኖሎጂ የፈጠራ ውጤቶችን ወደ ማህበረሰቡ

በማሸጋገር ተደራሽ አለመሆኑ፤

በተማሪዎችም ሆነ በመምህራን በግቢ ውስጥ እና በአቅራቢያው ያሉ ተቋማትን

ተጠቅሞ ከመስራት ይልቅ ራቅ ወዳሉ ቦታዎች ለመሄድ የመፈለግ ችግር እንዳለ

ለመገምገም ተችሏል፤(ደ/ብረታቦር ዩኒቨርሲቲ)፡፡

የዩኒቨርስቲ ኢንዱስትሪ ትስስር በማጠናከር በዩኒቨርስቲው የተደረጉ የቴክኖሎጂ

ሸግግር ክፍተት መኖር፣ ዩኒቨርስቲውና ኢንዱስትሪዎች የጋራ የጥናት ማዕከላት

በማቋቋም የፈጠራ ስራዎችን ለማህበረሰቡ ማበራከት አለመቻል፤ (ወልቂጤ

ዩኒቨርሲቲ)፡፡

ዳይሬክተሩና ባለሙያው ባለመገኘታቸው ምክንያት የስራ ክፍሉን ምልከታ ማድረግ

ባለመቻሉ ሪፖርትም ማዘጋጀት ካለመቻሉም በላይ በዩኒቨርሲቲ ኢንደስትሪ ትስስር

ዙሪያ ስላሉ አፈጻጸሞች በበላይ አመራሩ እዉቅና ያለዉ መረጃ ማግኘት አልተቻለም

(አሶሳ ዩኒቨርሲቲ)፡፡

2.5 ስለ ሀብት አጠቃቀምና ንብረት አስተዳደር

በጥንካሬ የታዩ ጉዳዮች፡-

በሁሉም የሶስተኛ ትዉልድ ዩኒቨርሲቲዎች፡-

ጠንካራ የፋይናንስና የንብረት አስተዳደር ስርዓት እንዲኖር የውስጥ ኦዲትን

በማደረጀት የውስጥ ቁጥጥር ሥራ እየተሰራ ያለ መሆኑ፣ ንብረቶች በአላቂና

በቋሚ ዕቃ ተለይተው ለቁጥጥርና ለኦዲት በሚያመች መልኩ መደራጀታቸው፣

ከዋና ኦዲተር፣ ከግዥ ኤጀንሲና ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተሰጡ ግብረ

መልሶችን ወደ ተግባር በመለወጥ የተስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት እየተሰራ

መሆኑ፣እንዲሁም የውስጥ ገቢን ከማሳደግ አንጻር የተለያዩ የገቢ ማስገኛ

ስራዎችን እየተከናወኑ መሆኑን ማረጋገጥ ተችሏል፡፡

የተመደበላቸውን ሃብት ለታለመለት ዓላማ ለማዋል የሚያስችል ህጋዊ አሰራር

ስርዓት ዘርግቶ ከመተግበር ባሻገር ከመንግስትና ከተለያዩ አካላት የተገኘዉን

የ2010 ዓ.ም ትምህርት ዘመን ሶስተኛው ትዉልድ ዩኒቨርሲቲዎች የትግበራ ምዕራፍ የድጋፍና ክትትል ሥራ ሪፖርት

27

ሀብት ለስራ ክፍሎችና ለፕሮግራሞች በወቅቱና በፍትሀዊነት ላይ ተመስርቶ

የማሰራጨት ስራ እንየተሰራ እንደሆነ ማረጋገጥ ተችሏል

በዉሱንነት የታዩና ሊሻሻሉ የሚገባቸዉ ጉዳዮች፡-

የግዥ ስርዓቱ ፈጣንነትን የሚፈታተኑ አገራዊና ዓለም አቀፋዊ ኩነቶች

እንደተጠበቁ ሆነዉ የስራ ክፍሎች የሚፈልጉትን ግብዓት በተሟላ ሁኔታ

ባለማቀዳቸዉ አልፎ አልፎም ቢሆን ተቋሙን ላላስፈላጊ የቁጥ ቁጥ ግዥ

መዳረጋቸዉ እንዲሁም ከማእቀፍ ግዥ ሥርዓት ጋር በተያያዘ ሂደቱ

የተጓተተና በወቅቱ መገዛት የሚገባቸው አስፈላጊ ግብዓቶች ተገዝተው ጥቅም

ላይ እንዲውሉ ከማድረግ እና የተገዙትም ንብረቶች ጥራት በተመለከተ ችግር

ያለ መሆኑ /በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች/

በፋይናንስ፣ በግዥና ንብረት አስተዳደር ክፍሎች ላይ እንዲሁም በኦዲት

ክፍል የሰው ኃይል በማሟላት ከመስራት አንጻር እጥረት እንዳለ ታይቷል

(በአዲግራት፣ ቡሌ ሆራ እና ወልዲያ ዩኒቨርሲቲዎች)

መጠገንና መወገድ የሚገባቸውን ንብረቶች ከሚመለከታቸው አካላት ጋር

በመመካከር ወቅታዊ መፍትሄ ከመስጠት አንጻር እጥረት እንዳለ ለማየት

ተችሏል፡፡ /አዲግራት፣ቡሌሆራ፣ዋቸሞ፣ወልዲያ እና አሶሳ ዩኒቨርሲቲዎች/

3 ባለዘርፈ ብዙ ተግባራትን ማከናወን

3.1 በሴቶችና ወንዶች መካከል ያሉ የትምህርት ተስትፎና የተጠቃሚነት ልዩነትን

ለማጥበብ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት

በጥንካሬ የታዩ ጉዳዮች፡-

በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች በሚባል ደረጃ ፡-

የሴቶችን በትምህርት የመዝለቅ ምጣኔ ከፍ ለማድረግ በትምህርት መስክ

ምርጫ ለሴቶች ቅድሚያ የሚታይበት አሰራር ስርዓት መኖሩ፣

የኢኮኖሚያዊ ችግር ላለባቸው ሴት ተማሪዎች የተለያዩ የበጀት ድጋፍ

አማራጮችን በማመቻቸት/ ከተለያዩ መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ

ድርጅቶች የገንዘብ፣ ቁሳቁስና የሥነ ልቦና ድጋፍ መደረጉ፤ እንዲሁም

የ2010 ዓ.ም ትምህርት ዘመን ሶስተኛው ትዉልድ ዩኒቨርሲቲዎች የትግበራ ምዕራፍ የድጋፍና ክትትል ሥራ ሪፖርት

28

ሴቶችን በአካዳሚክና በአስተዳደር ዘርፍ ወደ አመራርነት እንዲመጡ የሚደረጉ

ድጋፎች እንዳሉ ማረጋገጥ ተችሏል

ሴቶችን ከማንኛውም ጾታዊ ጥቃትና ትንኮሳ ለመከላከል ይቻል ዘንድ የተለያዩ

ግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎች ከመስራት ባሻገር በተለያዩ አደረጃጀቶች የሚደረጉ

የክትትል ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ማረጋገጥ ተችሏል፡፡

በዉሱንነት የታዩና ሊሻሻሉ የሚገባቸዉ ጉዳዮች፡-

ደረጃው የተለያየ ቢሆንም በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች በሚባል ደረጃ የሴቶችን

በትምህርት የመዝለቅና የመመረቅ ምጣኔን ከፍ ለማድረግ በትምህርታቸው

ዝቅተኛ ውጤት ያመጡ ሴት ተማሪዎችን በመለየት ድጋፍ የሚያገኙባቸውን

የትምህርት ዓይነቶች እንዲመርጡ በማድረግ እና በመረጧቸው የትምህርት

ዓይነቶች የማጠናከሪያ ትምህርት አተገባበሩ ላይ የክትትል ክፍተት መኖሩ፡-

እየተሰጠ ያለዉ የማጠናከሪያ ትምህርት ለምን ያህል ሰዓት፤ በምን በምን

ኮርሶች እንደተተገበረ የተጠናከረ መረጃ ተይዞ ዉጤታማነቱ እየተገመገመ

የሚኬድበት አሰራር ስርዓት የተጠናከረ አለመሆን

ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ሴት ተማሪዎችን በማበረታታት ለሌሎችም ምሳሌ

እንዲሆኑ በሚያስችል ሁኔታ የተለያዩ አማራጮችን በመጠቀም የማበረታቻ

ስርዓት ዘርግቶ በመተግበር በኩል አሁንም ውሱንነቶች ያሉ መሆኑ / በሁሉም

ዩኒቨርሲቲዎች/

3.2 ልዩ ድጋፍ ለሚሹ እና ለታዳጊ ክልል ተማሪዎች ስለሚደረግ ድጋፍ

በጥንካሬ የታዩ ጉዳዮች፡-

በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች የኢኮኖሚ ችግር ላለባቸው ተማሪዎች፣ ሴቶች፣ ከታዳጊ

እና አርብቶ አደር ክልሎች ለመጡ እና ለአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች

የፋይናንስ፣ የትምህርት ግብዓት አቅርቦት፣ የሥልጠናና የስነ ልቦና ድጋፍ

እንዲያገኙ በማድረግ የመመረቅ ምጣኔያቸውን ለማሳደግ እየተሰራ ያለ መሆኑ

በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች የአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች በመረጡትና አቅማቸው

በሚፈቅደው የትምህርት ዘርፍ እንዲመደቡ መደረጉ እንዲሁም የማደሪያ

ክፍሎችና በመመገቢያ አዳራሾች አገልግሎት ቅድሚያ የሚያገኙበት ሁኔታዎች

በማመቻቸት ድጋፍ እንደሚደረግላቸው ተረጋግጧል

የ2010 ዓ.ም ትምህርት ዘመን ሶስተኛው ትዉልድ ዩኒቨርሲቲዎች የትግበራ ምዕራፍ የድጋፍና ክትትል ሥራ ሪፖርት

29

በዉሱንነት የታዩና ሊሻሻሉ የሚገባቸዉ ጉዳዮች፡-

ከታዳጊ ክልል የመጡና የአርብቶ አደር ተወላጅ ተማሪዎችን ለይቶ መረጃ

በመያዝ የማጠናከሪያም ትምህርት ሆነ ሌሎች ድጋፎች ስለመደረጋቸዉ

የሚያሳይ መረጃ አለመገኘቱ / መቱ እና ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲዎች/

በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች፡-

የዲጂታል ላይበራሪ አገልግሎት፣ የመማሪያ ክፍሎች፣ የመጸዳጃ እና

ሻወር ቤት፣ ቤተ-ሙከራ/ የላብ አገልግሎት ክፍሎች ለአካል ጉዳተኛ

ተማሪዎች ተደራሽ ከማድረግ አንጻር እጥረት ያለ መሆኑ

ለልዩ ፍላጎትና አካቶ ትምህርት ክፍል አስፈላጊ ግብዓቶች እጥረት

መኖሩ፡- ለዓይነ ስውራን ተማሪዎች የጃውስ ሶፍትዌር፣ የኮምፒዉተር፣

መጻሕፍትና የመሳሰሉት ግብአት በማሟላት መስራት ላይ የሚቀር

መሆኑ፣

3.3 የአከባቢ ጥበቃ፣ ኤች.አይ.ቪ እና አደንዛዥ ዕጽን በተመለከተ

በጥንካሬ የታዩ ጉዳዮች፡-

ኤች. አይ. ቪ/ ኤድስን ሌሎች የአባለዘር በሽታዎችን ከመከላከል አኳያ

በተማሪዎች እና በተቋሙ ማህበረሰብ ላይ ተጨባጭ የባህሪ ለዉጥ ለማምጣት

የህይወት ክህሎት/Life skills/ ስልጠናዎችና የምክር አገልግሎት እየተሰጠ

መሆኑ እንዲሁም ቅንጅታዊ አሰራር በመዘርጋት የተማሪዎች ክሊኒክ ከሌሎች

ክፍሎች ጋር በመሆን የምግብ ቤት ሰራተኞች የጤና ምርመራ እንዲያደርጉ

ክትትል በማድረግ እየተሰራ መሆኑ /በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች/

በሁሉም ተቋማት ምድረ ግቢዉን ለተማሪዎች ለመምህራንና ለሰራተኞች ምቹ

ውብና ማራኪ ለማድረግ አረንጓዴ ልማትን በመተግበር ጽዳቱ የተጠበቀ ምቹ

ተቋም በመፍጠር በኩል በፍላጎቱ ልክም ባይሆን አዳጊ ስራዎች ያሉ መሆኑ

በዉሱንነት የታዩና ሊሻሻሉ የሚገባቸዉ ጉዳዮች፡-

በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ደረጃው የተለያየ ቢሆንም፡-

የተማሪዎች ክሊኒክ ለደረጃዉ በሚመጥን ሁኔታ አገልግሎት ከመስጠት ጋር

በተያያዘ የባለሙያ፣ የላብራቶሪ ግብዓትና የመድሃኒት ውስንነት ያለው

መሆኑን በተማሪዎች በስፋት የሚነሳ ሲሆን እነዚህን ችግሮች በማጥናት

የ2010 ዓ.ም ትምህርት ዘመን ሶስተኛው ትዉልድ ዩኒቨርሲቲዎች የትግበራ ምዕራፍ የድጋፍና ክትትል ሥራ ሪፖርት

30

አገልግሎት አሰጣጡን ቅሬታ በማያስነሳ አሰራር በመተግበር በኩል እጥረት

እንዳለ ማየት ተችሏል

በተቋሙ ሱስ አምጪ ዕፆችን ለመከላከል የሚያስችል አደረጃጀት

በመፍጠርና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመስራት የተቋሙን ማህበረሰብ

ከአደንዛዥ ዕፅ ተጋላጭነት መከላከል አንጻር ችግሩን በአስተማማኝ እና

በተሻለ ደረጃ ሊፈታ የሚያስችል ስራ እየተሰራ አለመሆኑ፤

ኤች. አይ. ቪ/ ኤድስን ከመከላከል አኳያ በተማሪዎች ላይ ተጨባጭ የባህሪ

ለዉጥ በማምጣት ወይም የማታ አቴንዳንስ ቁጥጥር በጥብቅ ዲስፕሊን

እንዲመራ በማድረግ ተማሪዎች ያለ ተቋሙ ፈቃድ ከግቢ ውጪ በማምሸት/

በማደር ራሳቸውን ለኤች.አይቪ ኤድስና ለሌሎች የአባለዘር በሽታዎች

እንዳይጋለጡ ከመጠበቅ አንጻር መስራት ላይ አሁንም የሚቀር መሆኑ፣

4 የክትትልና ድጋፍ ስራን በተመለከተ

በጥንካሬ የታዩ ጉዳዮች፡-

የዩኒቨርስቲው አመራር አካላት በየደረጃው ባሉ አደረጃጀቶች የዕቅድ አፈጻጸምን

በመገምገም እንዲሁም የተቋሙ የ2010 ዓ.ም ዕቅድ ከእ.ት.ዕ (GTP II) 20% ተወስዶ

የተዘጋጀ ሲሆን የሶስት ወርና የስድስት ወር ዕቅድ አፈጻጸም መድረክ በማዘጋጀት

መገምገም ስራ በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች እንዳለ ማየት ተችሏል

በዉሱንነት የታዩና ሊሻሻሉ የሚገባቸዉ ጉዳዮች፡-

በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች መልካም ተሞክሮዎችን በመለየት በማደራጀትና በመቀመር

የማስፋት፣ የማላመድና የማዝለቅ ስራዎች በቀጣይ ትኩረት ሰጥቶ መሰራት

የሚገባቸው ክፍተቶች እንደሆኑ ለማየት ተችሏል፡፡

2.4