የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵ - ጥር 2007 ዓ.ም

13
የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ www.etsugar.gov.et || www.facebook.com/etsugar

Upload: meresaf

Post on 17-Jul-2015

452 views

Category:

Documents


14 download

TRANSCRIPT

Page 1: የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵ - ጥር 2007 ዓ.ም

የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ

www.etsugar.gov.et || www.facebook.com/etsugar

Page 2: የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵ - ጥር 2007 ዓ.ም

የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ

ዘመናዊ የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ በግል የውጭ ባለሃብቶችና በመንግሥት ሽርክና በኩባንያ መልክ የተጀመረው በ1946ዓ.ም. ከአዲስ አበባ 110 ኪሎ ሜትር ርቃ በምትገኘው ወንጂ ከተማ ላይ ሲሆን፣ በወቅቱ በሽርክና ወደ ስራ የገባው ኤች.ቪ.ኤ. የተሰኘ የሆላንድ ኩባንያ ነበር፡፡ ኩባንያው 5 ሺህ ሄክታር የሸንኮራ አገዳ ማልሚያ መሬት ተረክቦ ሰኔ 18 ቀን 1943ዓ.ም. ስራ ጀመረ፡፡ የፋብሪካ ግንባታው መጋቢት 11 ቀን 1946ዓ.ም. ተጠናቆ ስኳር ማምረት ሲጀምር 1 ሺህ 400 ኩንታል ስኳር እያመረተ ምዕዙን ስኳር እና ባለ አስር ሳንቲም እሽግ ስኳር ለገበያ ያቀርብ ነበር፡፡

በወቅቱ የወንጂ አካባቢ በዓለማችን ከፍተኛ ምርት ከሚያስመዘግቡና ለስኳር ምቹ ከሆኑ አካባቢዎች አንዱ ስለነበር ከወንጂ ስኳር ፋብሪካ ምስረታ ጋር ተያይዞ የወንጂ ከረሜላ ፋብሪካ ሰኔ 1953ዓ.ም. ተቋቁሞ ደስታ ከረሜላ እያመረተ ለገበያ ማቅረብ ጀመረ፡፡ የወንጂ ስኳር ፋብሪካ ሥራ ከጀመረ ከዘጠኝ ዓመት በኋላ በ1955ዓ.ም

እዛው ወንጂ ላይ የተቋቋመው የሸዋ ስኳር ፋብሪካ በወቅቱ በቀን 1 ሺህ 700 ኩንታል ስኳር ያመርት ነበር፡፡ ወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ በሚል የጋራ መጠሪያ በአንድ አስተዳደራዊ መዋቅር ስር ይተዳደሩ የነበሩት ሁለቱ አንጋፋ ፋብሪካዎች አንድ ላይ በዓመት 750 ሺህ ኩንታል ስኳር ገደማ ያመርቱ ነበር፡፡ የወንጂ እና ሸዋ ስኳር ፋብሪካዎች ከግማሽ ምዕተ ዓመት በላይ ካገለገሉ በኋላ በእርጅና ምክንያት እንደቅደም ተከተላቸው በ2004ዓ.ም እና በ2005ዓ.ም መጨረሻ የተዘጉ ሲሆን፣ በምትካቸው አዲስ ዘመናዊ ፋብሪካ ተገንብቶ ከ2006 ዓ.ም ጀምሮ ስኳር እያመረተ ይገኛል። በተመሳሳይ በኢትዮጵያ መንግሥትና የሆላንድ ኩባንያ በሆነው ኤች.ቪ.ኤ. መካከል በተደረሰው ስምምነት የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ሰኔ 26 ቀን 1957ዓ.ም. በአክሲዮን መልክ ተመሰረተ፡፡ ከዓመታት በኋላም ፋብሪካው በ1962ዓ.ም. ከአዲስ አበባ 200 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ

በምትገኘውና መርቲ ተብላ በምትታወቀው ቦታ ላይ ሥራ ጀመረ፡፡ በ10 ሺህ ሄክታር ላይ የሚለማ የሸንኮራ አገዳን በግብዓትነት የሚጠቀመው ይህ ፋብሪካ አማካይ በአሁኑ ወቅት ዓመታዊ ስኳር የማምረት አቅሙ 1 ሚሊዮን 300 ሺህ ኩንታል እንዲሁም ኤታኖል 12.5 ሚሊዮን ሊትር ገደማ ነው::

በ1967 ዓ.ም. በተደረገው የመንግሥት ለውጥ ምክንያት ስኳር ፋብሪካዎቹ በመንግሥት ይዞታ ስር ሆኑ:: ይህን ተከትሎ በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሕግ ክፍል ማስታወቂያ ቁጥር 58/1970 የተቋቋመው የኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽን ወንጂ ሸዋ እና መተሐራ ስኳር ፋብሪካዎችን ጨምሮ አዲስ ከተማ እና አስመራ ከረሜላ ፋብሪካን እንዲያስተዳድር ተደረገ፡፡

ለአገሪቱ ሶስተኛ የሆነውን የፊንጫአ ስኳር ፋብሪካ ለመገንባት በ1967 ዓ.ም. የመጀመሪያ ደረጃ ጥናት ተካሄዶ የፊንጫአ ሸለቆ ለስኳር ምርት አዋጭ ሆኖ ተገኘ፡፡ ጠለቅ ያለ ጥናት እንዲካሄድብትም ቡከርስ አግሪካልቸራል ኢንተርናሽናል ሊሚትድ በተባለ ኩባንያ

አማካይነት ከ1970 ዓ.ም. ጀምሮ ስለፕሮጀክቱ ዝርዝር ጥናት ተካሄደ፡፡ በፋይናንስ ዕጥረት ሳቢያ ለተወሰነ ጊዜ የተጓተተው የፋብሪካው ግንባታም የአፍሪካ ልማት ባንክና የልማት ፈንድ፣ የአውስትራሊያና የስፔን መንግስታት እንዲሁም የሀገር ውስጥ ባንኮች የፋይናንስ ምንጮች መሆናቸው ተረጋግጦ የፕሮጀክቱ የግንባታ ሂደት ጥር ወር 1981ዓ.ም. እንዲሁም የሸንኮራ አገዳ ተከላ ስራው በ1984ዓ.ም. ተጀመረ፡፡

የወንጂ ሸዋ እና የመተሐራ ስኳር ፋብሪካዎችን እንዲሁም የአዲስ ከተማንና የአስመራ ከረሜላን ያስተዳድር የነበረው የኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽን በ1984ዓ.ም. በሕግ ሲፈርስ በምትኩ በደንብ ቁጥር 88/85 መተሐራ ስኳር ፋብሪካ፣ በደንብ ቁጥር 88/85 ወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ እና በደንብ ቁጥር 199/86 ፊንጫአ ስኳር ፋብሪካ (በወቅቱ አዲስ የተጀመረ የስኳር ልማት ፕሮጀክት ነበር) እራሣቸውን የቻሉ የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ሆነው እንዲቋቋሙ ተደረገ፡፡

የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ

32 የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽን

Page 3: የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵ - ጥር 2007 ዓ.ም

የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ (የቀጠለ)

ከቀደምቶቹ ስኳር ፋብሪካዎች በተሻለ ዘመናዊ የሆነውን የፊንጫአ ስኳር ልማት ፕሮጀክት የፋብሪካና ኤታኖል ግንባታ ያከናወኑት ኤፍ.ሲ.ሼፈርና አሶሽየትስ የተባለ የአሜሪካ ኩባንያ እና በእርሱ ስር የፋብሪካውን ተከላ ያካሄደው ድዌቶ ኢንተርናሽናል የተባለ የደች ኩባንያ ሲሆኑ በርካታ የአገር በቀል ድርጅቶችም በግንባታው ተሳትፈዋል፡፡

ፊንጫአ ስኳር ፋብሪካ ግንባታው ተጠናቆ የሙከራ ምርት የጀመረው የካቲት ወር 1990ዓ.ም. ቢሆንም መደበኛ ስራውን የጀመረው በ1991ዓ.ም. ነው፡፡ በዚሁ ዓመት ያስመዘገበው ዓመታዊ ምርት 500,000 ኩንታል ስኳር ነበር፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ

ለስኳር ፋብሪካዎቹ የጋራ አገልግሎት እንዲሰጥ «የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ድጋፍ ሰጪ ማዕከል አክስዮን ማህበር» በሶስቱ ስኳር ፋብሪካዎች፣ በልማት ባንክ እና በመድን ድርጅት በአክስዮን መልክ ህዳር 1990 ተቋቋመ፡፡

በመቀጠልም አራተኛውና በአፋር ብሔራዊ ክልል የሚገኘው የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ በደንብ ቁጥር 122/98 እንዲቋቋም ተደረገ፡፡ ፋብሪካው በ50 ሺህ ሄክታር ላይ የሚለማ የሸንኮራ አገዳ መሬት እንዲኖረው እና ዓመታዊ የስኳር ምርት መጠኑ 619,000 ቶን እንዲሁም ዓመታዊ የኤታኖል ምርቱ 63 ሚሊዮን ሊትር እንዲሆን ታቅዶ የተጀመረ ፕሮጀክት ነው፡፡

በኋላም ድጋፍ ሰጪ ማዕከሉን በማፍረስ “የኢትዮጵያ ስኳር ልማት ኤጀንሲ” በአዋጅ ቁጥር 504/98 ተቋቁሞ የስኳር ፋብሪካዎቹን በመቆጣጠር፣ በፕሮጀክት ልማት፣ በምርምር፣ በስልጠናና በግብይት ረገድ ድጋፍ ሲሰጥ ቆየ፡፡ ይሁንና ከጥቅምት 19 ቀን 2003ዓ.ም. ጀምሮ ኤጀንሲው እንዲፈርስ ተደርጎ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 192/2003 የአሁኑ ስኳር ኮርፖሬሽን ተቋቋመ፡፡ ኮርፖሬሽኑ የስኳር ልማትን በአገራችን በስፋት ለማካሄድ በሚያስችለው መልኩ ተደራጅቶ ተግባራዊ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡

የስኳር ልማት ንኡስ ዘርፍ ስትራተጂያዊ ማዕቀፍ

የአገራችን ኢኮኖሚ ባለፉት 11 ተከታታይ አመታት በየአመቱ የሁለት አሀዝ ዕድገት የተመዘገበበት ነው፡፡ ይህንን ፈጣን እና መሰረተ ሰፊ የኢኮኖሚ ዕድገት በማስቀጠል መንግሥት የምዕተ አመቱን የልማት ግቦች ከማሳካት ባሻገር እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር ከ2012-2015 ባሉት አመታት ሀገሪቱን መካከለኛ ገቢ ካላቸው አገሮች ተርታ ለማሰለፍ አገራዊ ራዕይ አስቀምጦ ለስኬቱ በጽናት በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል፡፡ ለዚህ ተልዕኮ ስኬት ባለፉት አመታት የተካሄዱ የልማት ስራዎች የተመዘገቡ ውጤቶችን፣መልካም ተሞክሮዎችንና የአገሪቱን ራዕይ መሰረት በማድረግ ህዝቡ

በየደረጃው በስፋት የተሳተፈበት የአምስት አመት የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ተተግብሮ በማጠናቀቂያ ምዕራፍ ላይ ይገኛል፡፡

በእቅድ ዘመኑ ከፍተኛ ትኩረት ከተሰጣቸው የኢኮኖሚ መስኮች መካከል አንዱ የገቢ ምርቶችን ለሚተካው የኢንዱስትሪ ዘርፍ ነው፡፡ በዚህ ረገድ በኢንዱስትሪ ልማት ስትራተጂው መሰረት ከማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪዎች ውስጥ በተለይ በአግሮ ፕሮሰሲንግ ኢንዱስትሪዎች ስር የሚመደበው የስኳር ልማት ንኡስ ዘርፍ በዋናነት ይጠቀሳል፡፡

54 የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽን

Page 4: የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵ - ጥር 2007 ዓ.ም

ይህም የሆነው በብዙዎቹ ቆላማ የአገራችን አካባቢዎች ስኳር ለማምረት የሚቻል በመሆኑና በተለይም በእነዚህ አካባቢዎች ለመስኖ ልማት የተመቸና ሊለማ የሚችል ሰፊ መሬት ያለ ከመሆኑ አንጻር ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ከሕዝቡ የኑሮ እድገት ጋር ተያይዞ የአገር ውስጥ የስኳር ፍላጎት እየጨመረ በመሄዱና የስኳር ምርት ሰፊ የውጭ ገበያ ያለው በመሆኑ በአሁኑ ወቅት የስኳር ልማት ዘርፉን ማስፋፋት አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል፡፡

የአገራችን ነባር የስኳር ፋብሪካዎች የሚያመርቱት የስኳር ምርት እያደገ የመጣውን የአገር ውስጥ ፍላጎት ማርካት ባለመቻሉ ይህንኑ እጥረት ለመቅረፍ መንግሥት በየአመቱ ከፍተኛ ድጎማ እያደረገ በውጭ ምንዛሪ ስኳር ከውጪ አገር አስገብቶ በተመጣጣኝ ዋጋ ለህብረተሰቡ ሲያቀርብ መቆየቱ የሚታወቅ ነው፡፡ ይህንን ሁኔታ ለመለወጥ መንግሥት ባለፉት አመታት ባደረገው ርብርብ የወንጂ ሸዋና የፊንጫአ ነባር ስኳር ፋብሪካዎች የማስፋፊያ ፕሮጀክቶች ተጠናቀው ፋብሪካዎቹ በከፍተኛ የማምረት አቅም እየሰሩ ይገኛሉ፡፡ ከዚህ ባሻገር የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታ ተጠናቆ ፋብሪካው ማምረት የጀመረ ሲሆን የአዳዲስ የስኳር ልማት ፕሮጀክቶች ግንባታም በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡ በሌላ በኩል የስኳር ፋብሪካዎቹን በአለም ገበያ በዋጋና በጥራት ተወዳዳሪ ለማድረግ በአውሮፓ ገበያ ለስኳር አምራች የአፍሪካ አገሮች የተሰጠውን ልዩ እድል ለመጠቀም እንዲሁም ከዘርፉ የብዙኃኑን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ለዘርፉ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው፡፡

ከላይ የተጠቀሱትን ነባራዊ ሁኔታዎች እና የመንግሥትን የትኩረት አቅጣጫ መሰረት በማድረግ የዘርፉን የልማት እንቅስቃሴ ለመምራትና ለማስፈጸም በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 192/2003 ስኳር ኮርፖሬሽን ተቋቁሞ ኃላፊነቱን በመወጣት ላይ ይገኛል፡፡

የስኳር

ልማት ን

ኡስ ዘ

ርፍ

ስትራተጂያዊ ማ

ዕቀፍ-የቀ

ጠለ

በማቋቋሚያ አዋጁ የተቀመጠ የስኳር ኮርፖሬሽን ዓላማ

• የሸንኮራ አገዳና ስኳር የሚያስገኙ ሌሎች ሰብሎች ማልማት፣

• ስኳር፣ የስኳር ውጤቶችን፣ የስኳር ተረፈ ምርቶችን እና የስኳር ተረፈ ምርት ውጤቶችን

በፋብሪካ ማዘጋጀትና ማምረት፣

• ምርቶቹንና ተረፈ ምርቶቹን ለአገር ውስጥ እና ለውጭ ገበያ ማቅረብ፣

• አዳዲስና የማስፋፊያ የስኳር ልማት ፕሮጀክቶች የአዋጭነት ጥናት፣ የዲዛይን ዝግጅት፣

የቴክኖሎጂ መረጣና ድርድር፣ የተከላና ኮሚሽኒንግ ስራዎች እንዲካሄዱ ማድረግ፣

• ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር በሸንኮራ አገዳና በስኳር አመራረት ቴክኖሎጂ

ጥናትና ምርምር ማካሄድና ጠቃሚ ውጤቶችን በስራ ላይ ማዋል፣

• አቅሙ ካላቸው የሀገር ውስጥ ድርጅቶች ጋር በመተባበር ለመንግሥት የስኳር ፋብሪካዎች

የሚያስፈልጉ የማምረቻ መሳሪያዎችና መለዋወጫዎች ዲዛይንና ፋብሪኬሽን ሥራዎች

በሀገር ውስጥ እንዲከናወኑ ማድረግ፣

• በሕግ መሰረት ለስራው የሚያስፈልገው መሬት ባለይዞታ መሆንና ማልማት፣

• የአገዳ ምርታቸውን ለመንግሥት የስኳር ፋብሪካዎች የሚያቀርቡ አገዳ አብቃዮችን

ማበረታታትና መደገፍ፣

• ለስኳር ኢንዱስትሪ የሚፈለገውን የሰለጠነ የሰው ሃይል በሚፈለገው አይነት፣ መጠንና

ጥራት ለማፍራት እንዲቻል ከሚመለከታቸው የትምህርት ተቋማት ጋር መተባበር፣

• የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የሚያወጣውን መመሪያና የፖሊሲ አቅጣጫ

መሰረት በማድረግ ቦንድ መሸጥና በዋስትና ማስያዝ እና ከአገር ውስጥና ከውጭ የገንዘብ

ምንጮች ጋር የብድር ውል መደራደርና መፈራረም፣

• አላማውን ከግብ ለማድረስ የሚረዱ ሌሎች ተዛማጅ ሥራዎችን መስራት ናቸው፡፡

76 የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽን

Page 5: የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵ - ጥር 2007 ዓ.ም

የስኳር ኮርፖሬሽን ተልዕኮ፣ ራዕይ እና እሴቶች

ተልዕኮበአገሪቱ ያለውን እምቅ ሃብት ለማልማት የሚያስችል ዘመናዊ ቴክኖሎጂና የሰው ሀይል አቅም በማፍራት ስኳር፣ የስኳር ተረፈ ምርትና ተጓዳኝ ምርቶችን በማምረት የአገር ውስጥ ፍላጎት ከማርካት ባሻገር የጎላ የኤክስፖርት ድርሻ በመያዝ የአገሪቱን ኢኮኖሚ መደገፍ፡፡

ራዕይበቀጣይ እድገት ላይ በመመስረት በ2016 ዓ.ም. በዓለም ተወዳዳሪ ከሆኑ 10 ግንባር ቀደም የስኳር ኢንዱስትሪዎች ተርታ መሰለፍ፣

እሴቶች• የማያቋርጥ ለውጥና ቀጣይ ተወዳዳሪነት • መልካም ስነ ምግባር• ምርታማነት የህልውናችን መሠረት ነው• ህዝባዊነት መለያችን ነው • መማር አናቋርጥም• ፈጠራንና የላቀ ሥራን እናበረታታለን• በቡድን መንፈስ መስራት መለያችን ነው• አካባቢ ጥበቃ ለልማታችን መሠረት ነው• የሰው ሃብት ልማት ለስኬታማነታችን ወሳኝ ነው

ስኳር ፋብሪካዎች

በአገራችን የስኳር ፋብሪካ ታሪክ ፋና ወጊ የሆነው የወንጂ ስኳር ፋብሪካ በ1946ዓ.ም. ግንባታው ተጠናቆ ማምረት የጀመረ ሲሆን፣ የሸዋ ስኳር ፋብሪካ ደግሞ እዛው ወንጂ ላይ በ1955ዓ.ም. ተመርቆ ስራ የጀመረ ሌላው ስኳር ፋብሪካ ነው፡፡ ሁለቱ አንጋፋ ፋብሪካዎች በአንድ አስተዳደር እየተዳደሩ ያመርቱ የነበረ ሲሆን በእርጅና ምክንያት ስራቸውን እስካቆሙበት ማለትም ወንጂ እስከ 2004 እንዲሁም ሸዋ እስከ 2005 በጀት ዓመት መጨረሻ ድረስ የነበራቸው የማምረት አቅም በአማካይ በአመት 75,000 ቶን ስኳር ነው፡፡ ሁለቱም ስኳር ፋብሪካዎች ኤች ቪ ኤ በተባለ የሆላንድ ኩባንያ የተገነቡና በኩባንያውና በመንግሥት የጋራ ባለቤትነት በሽርክና የተቋቋሙ ናቸው፡፡ የወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ ነባር አጠቃላይ የሸንኮራ አገዳ መሬት 7ሺ ሄክታር ሲሆን ከዚህ መካከል 1ሺ ሄክታሩ የሚለማው በአካባቢው በሚገኙ አገዳ አብቃይና አቅራቢ አርሶ አደሮች አማካይነት ነው፡፡ ነባሩን የወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ በአዲስና ዘመናዊ ፋብሪካ ለመተካት የማስፋፊያ ፕሮጀክት በፋብሪካ እና በእርሻ

ዘርፍ ተከናውኖ የፋብሪካ ማስፋፊያ ስራው 2005 በጀት ዓመት መጨረሻ ላይ ተጠናቋል፡፡

አዲሱ የወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ የተቋቋመው እዚያው ኦሮሚያ ክልል ምስራቅ አርሲ ዞን ዶዶታ ወረዳ ቢሾላ ቀበሌ ገበሬ ማህበር ነው፡፡ ፋብሪካው አሁን ባለበት ደረጃ በቀን 6250 ቶን አገዳ በመፍጨት በዓመት ከ174ሺ ቶን በላይ ስኳር የማምረት አቅም አለው፡፡ ወደፊት የማምረት አቅሙን በማሳደግ በቀን ወደ 12ሺ 500 ቶን አገዳ እየፈጨ ዓመታዊ የስኳር ምርት መጠኑን እስከ 222ሺ 700 ቶን እንደሚያሳድግ ታሳቢ ተደርጎ የተገነባ ነው፡፡

ከዚህ ዘመናዊ የስኳር ፋብሪካ ተረፈ ምርት በዓመት እስከ 12ሺ 800 ሜትር ኩብ የሚደርስ ኤታኖል ለማምረት የሚያስችል የኤታኖል ፋብሪካ ለመገንባት ታቅዷል፡፡ የኤሌክትሪክ ኃይል በማመንጨት ረገድም ፋብሪካው በሙሉ አቅሙ ስራ ሲጀምር 31.15 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል በማመንጨት 10 ሜጋ ዋቱን ለራሱ ተጠቅሞ ቀሪውን

I. ወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ

98 የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽን

Page 6: የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵ - ጥር 2007 ዓ.ም

II. መተሐራ ስኳር ፋብሪካ III. ፊንጫአ ስኳር ፋብሪካ

1110 የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽን

21.15 ሜጋ ዋት ለአገሪቱ ማዕከላዊ የኃይል ማከማቻ ያበረክታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የፋብሪካውን የአገዳ እርሻ ማስፋፊያ ፕሮጀክት በተመለከተ የነባሩ የወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ የሸንኮራ አገዳ እርሻ መሬት የማስፋፋት ስራ ዋቄ ጢዮ፣ ሰሜን ዶዶታ እና ወለንጪቲ ተብለው በሚታወቁ አካባቢዎች እየተካሄደ ይገኛል፡፡ በ9ሺ ሄክታር መሬት ላይ የሚካሄደው የእርሻ ማስፋፊያ ፕሮጀክት ሙሉ በሙሉ ሲጠናቀቅ ከዚህ በፊት በነባሩ ፋብሪካ የለማውን 7ሺ ሄክታር መሬት ጨምሮ አዲሱ ፋብሪካ በአጠቃላይ 16,000 ሄክታር የሸንኮራ አገዳ መሬት የሚኖረው ሲሆን እስከ ታህሳስ 2007ዓ.ም ድረስ 11ሺ 26 ሄክታር መሬት በአገዳ ተሸፍኗል፡፡ የፋብሪካው አጠቃላይ የሸንኮራ አገዳ እርሻ ማስፋፊያ ስራ በአካባቢው በሚገኙ አገዳ አብቃይ ገበሬዎች የሚለማ ነው፡፡

የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ለአገራችን ሁለተኛው የስኳር ፋብሪካ ሲሆን ግንባታው ተጠናቆ ስኳር ማምረት የጀመረው በ1962 ዓ.ም. ነበር፡፡ ከአዲስ አበባ በ200 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የሚገኘው ይህ ፋብሪካ በአክስዮን መልክ በኢትዮጵያ መንግሥትና ወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካን በገነባው የሆላንዱ ኤች ቪ ኤ ኩባንያ አማካይነት የተቋቋመና በአሁኑ ወቅት 10,000 ሄክታር በሸንኮራ አገዳ የተሸፈነ መሬት ያለው ነው፡፡

ፋብሪካው ባካሄደው የማስፋፊያ ፕሮጀክት የኤታኖል ማምረቻ ፕላንት ገንብቶ ከ2003 ዓ.ም. አጋማሽ ጀምሮ ኤታኖል በማምረት ላይ ይገኛል፡፡ የፋብሪካው አማካይ ስኳር የማምረት አቅም በዓመት 136,692 ቶን ስኳር ሲሆን፣ ኤታኖል የማምረት አቅሙም በዓመት እስከ 12.5 ሚሊዮን ሊትር ይደርሳል፡፡

የፊንጫአ ስኳር ፋብሪካ ከአዲስ አበባ በስተሰሜን ምዕራብ 350 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በኦሮሚያ ክልል በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን በአባይ ጮመን ወረዳ በፊንጫአ ሸለቆ ውስጥ ልዩ ስሙ አገምሳ ተብሎ በሚጠራ ቦታ ላይ ይገኛል፡፡

የፋብሪካው ግንባታ በ1990 ዓ.ም. የተጠናቀቀ ቢሆንም ወደ ምርት የገባው ግን በ1991ዓ.ም.ነው፡፡ ፋብሪካው የማስፋፊያ ስራ ከማከናወኑ በፊት በዓመት 110,000 ቶን ስኳር እና እስከ 8 ሚሊዮን ሊትር የሚደርስ ኤታኖል ያመርት ነበር፡፡ እስከ 2003ዓ.ም. አጋማሽ ድረስም ብቸኛው ኤታኖል የሚያመርት ፋብሪካ ሆኖ ቆይቷል፡፡

ፊንጫአ ስኳር ፋብሪካ ለማከናወን ካቀደው የፋብሪካ እና የእርሻ ማስፋፊያ ስራ መካከል የፋብሪካ ማስፋፊያ ስራውን በ2005 በጀት ዓመት አጠናቋል፡፡ የእርሻ ማስፋፊያ ስራው ከፊንጫአ ወንዝ በስተምሥራቅ እና ነሼ ተብለው በሚጠሩ አካባቢዎች እንዲሁም በፊንጫአ ወንዝ በስተምዕራብ በለማው የአገዳ መሬት አጠገብ በሚገኙ ክፍት ቦታዎች ላይ በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡ ፋብሪካው እያካሄደ ባለው የእርሻ ማስፋፊያ ፕሮጀክት አማካይነት የሸንኮራ አገዳ መሬቱን 21,000 ሄክታር ለማድረስ በእንቅስቃሴ ላይ የሚገኝ ሲሆን እስከ ታህሳስ 2007 ዓ.ም. ድረስ በሸንኮራ አገዳ የተሸፈነ መሬቱን 18,750 ሄክታር አድርሷል፡፡

በፋብሪካ ማስፋፊያ ረገድም እስከ 2005 በጀት ዓመት በቀን 5,000 ቶን አገዳ ይፈጭ የነበረውን ፋብሪካ ወደ 12,000 ቶን የማሳደግ እንዲሁም ኤታኖል ፋብሪካውን የማስፋፋት ስራ ለማጠናቀቅ ተይዞ የነበረውን ግብ ለማሣካት ተችሏል፡: በዚህ የማስፋፊያ ስራ አማካይነትም ፋብሪካው በአመት 270,000 ቶን ስኳር እና 20,000 ሜትር ኩብ ኤታኖል ማምረት ወደሚችልበት ሙሉ አቅም ይሸጋገራል፡፡

Page 7: የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵ - ጥር 2007 ዓ.ም

IV. ተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ

1312 የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽን

በአዋሽ ተፋሰስ ዝቅተኛው አካባቢ በአፋር ብሔራዊ ክልል በ50ሺህ ሄክታር መሬት ላይ የሚለማ የሸንኮራ አገዳን በግብዓትነት የሚጠቀመው የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ ከአዲስ አበባ በ670 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ በግዙፍነቱ እና በተሻለ ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ተጠቃሚነቱ ጭምር ከሌሎቹ ነባር ስኳር ፋብሪካዎች የሚለየው ይህ ፋብሪካ ከአገሪቱ መዲና በስተምስራቅ ወደ ጅቡቲ የሚወስደውን መንገድ ተከትሎ ከጅቡቲ ወደብ በ300 ኪ.ሜ ርቅት ላይ ይገኛል፡፡ ይህ ምቹ ሁኔታም ወደፊት የፋብሪካውን ምርት ወደ ውጭ ለመላክ ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖረዋል፡፡

በ1998ዓ.ም. የፕሮጀክት ሥራው የተጀመረው የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ ይዞታ በሚሌ፣ በዱብቲ፣ በአሳኢታ እና በአፋምቦ ወረዳዎች ውስጥ ይገኛል፡፡ የግንባታ ምዕራፉ በሁለት ተከፍሎ የሚካሄደው የዚህ ፋብሪካ የመጀመሪያው ምዕራፍ ግንባታ ተጠናቆ ከጥቅምት 2007ዓ.ም ጀምሮ ተንዳሆ አንድ ወደ ማምረት የተሸጋገረ ሲሆን፣ በሙሉ አቅሙ ማምረት ሲጀምር በቀን 13ሺህ ቶን አገዳ ይፈጫል፡፡ የምርት መጠኑም ደረጃ በደረጃ እያደገ በአመት ከ300ሺህ ቶን ወይም ከ3ሚሊዮን ኩንታል ስኳር በላይ እንደሚደርስ ይጠበቃል፡፡ በተመሳሳይ በሁለተኛ ምዕራፍ የሚገነባው የተንዳሆ ቁጥር ሁለት ፋብሪካ በቀን 13ሺህ ቶን አገዳ እየፈጨ በአመት ከ3ሚሊዮን ኩንታል ስኳር በላይ የማምረት አቅም ይኖረዋል፡፡ በአጠቃላይ ተንዳሆ

አንድና ሁለት በጋራ በቀን 26ሺህ ቶን አገዳ የመፍጨትና በዓመት ከ6ሚሊዮን ኩንታል ስኳር በላይ የማምረት አቅም አላቸው፡፡

በተጨማሪም ከስኳር ተረፈ ምርት ማመንጨት ይችላሉ ተብሎ ከሚገመተው 120 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ሃይል ውስጥ ለአገሪቱ ማዕከላዊ የኤሌክትሪክ ሃይል ማከማቻ 76 ሜጋ ዋቱን በማስገባት ዘርፈ ብዙ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታቸውን ያረጋግጣሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ እንዲሁም በጋራ 63 ሚሊዮን ሊትር ኤታኖል ለማምረት ያላቸው አቅምም ይጠቀሳል፡፡

ለፋብሪካው ከሚያስፈልገው 50ሺህ ሄክታር መሬት ላይ ከሚለማ የሸንኮራ አገዳ ውስጥ 25ሺህ ሄክታሩ የሚለማው በአካባቢው በሚገኙ አገዳ አብቃይና አቅራቢ አርብቶ አደሮች ሲሆን፣ ማምረት ለጀመረው ተንዳሆ

አንድ ከሚያስፈልገው 25ሺህ ሄክታር መሬት ውስጥ በፋብሪካው አማካኝነት እስከ ህዳር 30/2007ዓ.ም ድረስ ከ19ሺህ ሄክታር መሬት በላይ ለምቷል፡፡

የአገዳ ልማቱ የሚከናወነው በአዋሽ ወንዝ ላይ በተሰራው የተንዳሆ ግድብ አማካኝነት ነው፡፡ ከ1.86 ቢሊዮን ሜትር ኩብ ውሃ በላይ የመያዝ አቅም ያለው ይህ ግድብ ከ60 ሺህ ሄክታር መሬት በላይ ማልማት ይችላል፡፡

ፋብሪካው በመስኖ የሚለማ መሬት ለአካባቢው አርብቶ አደሮች በማመቻቸቱም አርብቶ አደሩ ወደ ከፊል አርሶ አደርነት መሸጋገር የቻለበት ምቹ ሁኔታ ተፈጥሮ ተጠቃሚ መሆን ጀምሯል፡፡ ፋብካው ወደ ሙሉ አቅሙ ማምረት ሲገባ 50 ሺህ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ ዕድል ይፈጥራል፡፡

Page 8: የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵ - ጥር 2007 ዓ.ም

1514 የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽን

አንድ ሚሊዮን ሔክታር መሬት በላይ ከሚሸፍኑ የውኃ ገብ እና የመስኖ ልማት ቦታዎች ውስጥ

ከ500,000 ሺህ ሔክታር የሚበልጥ የአገሪቷን መሬት ለሸንኮራ አገዳ ልማት ማዋል እንደሚቻል በአገር አቀፍ ደረጃ በተካሄደ ጥናት ታውቋል፡፡ በዚሁ መሰረት በግንባር ቀደምትነት ለስኳር ልማት እንደሚሆኑ የተፈተሹት ቦታዎች የላይኛውና ታችኛው በለስ አካባቢዎች፣ከጣና ሐይቅ በስተደቡብ ምዕራብ የሚገኘው የላይኛው ዲንደር፣ የተከዜን ወንዝና ገባሮችን ተከትሎ በወልቃይትና ሁመራ፣ በአንገር ወንዝ ሸለቆ በነጌሶ፣በመካከለኛው ገናሌ ወንዝ እና

በጋምቤላ አካባቢ የባሮና ጊሎ ወንዞችን ተከትለው የሚገኙት አካባቢዎች ናቸው፡፡ በአምስት ዓመቱ የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመን ጥናት ከተካሄደባቸው ከላይ ከተጠቀሱት ቦታዎች መካከል በአማራና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በጣና በለስ በ75,000 ሄክታር መሬት ላይ የሚለማን የሸንኮራ አገዳ መሬት የሚጠቀሙ እያንዳንዳቸው በቀን 12ሺ ቶን አገዳ መፍጨት የሚችሉ ሦስት የስኳር ፋብሪካዎች በመገንባት ላይ ይገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል በደቡብ ኦሞ፣ቤንች ማጂ እና ካፋ ዞኖች

(ኦሞ-ኩራዝ ስኳር ልማት ፕሮጀክት) በ175,000 ሄክታር የሸንኮራ አገዳ መሬት ላይ የሚለማን ሸንኮራ አገዳ በግብዓትነት የሚጠቀሙ እያንዳንዳቸው በቀን 24 ሺህ ቶን አገዳ መፍጨት የሚችሉ ሁለት ፋብሪካዎችን እንዲሁም እያንዳንዳቸው በቀን 12 ሺህ ቶን አገዳ የመፍጨት አቅም ያላቸውን ሦስት ፋብሪካዎች በጠቅላላው አምስት የስኳር ፋብሪካዎችን ለመገንባት ታቅዷል፡፡

በትግራይ ክልል በወልቃይት (ወልቃይት ስኳር ልማት ፕሮጀክት) በ50,000 ሄክታር መሬት ላይ የሚለማ የሸንኮራ አገዳ መሬትን ተጠቅሞ በቀን 24ሺ ቶን አገዳ መፍጨት የሚችል አንድ የስኳር ፋብሪካ እንዲሁም በአፋር ክልል በከሰም

አዳዲስ የስኳር ልማት ፕሮጀክቶች

ስኳር ልማት ፕሮጀክት አማካኝነት በ20,000 ሄክታር ላይ የሚለማ የሸንኮራ አገዳ መሬትን ተጠቅሞ በቀን 10ሺ ቶን አገዳ መፍጨት የሚችል አንድ ስኳር ፋብሪካ በአጠቃላይ 10 አዳዲስ ስኳር ፋብሪካዎችን ለመገንባት የሚያስችል ሰፊ ሥራ በመከናወን ላይ ይገኛል፡፡

በሌላ በኩል በኦሮሚያ ክልል በምስራቅ ወለጋ እና በኢሉ አባቦራ ዞኖች አልሀበሻ በሚል መጠሪያ በአንድ የፓኪስታን የግል ኩባንያ የተቋቋመውንና ግንባታው ከዘጠና በመቶ በላይ የተጠናቀቀ ስኳር ፋብሪካን ኩባንያው ስራውን መቀጠል ባለመፈለጉ ወደ ስኳር ኮርፖሬሽን ንብረትነት በ2005 ዓ.ም እንዲዛወር ተደርጓል፡፡የፋብሪካ ግንባታውን የማጠናቀቅ እና በኩባንያው ብዙም ያልተገፋበት የሸንኮራ አገዳ ልማት ስራ በስፋት በመከናወን ላይ ይገኛል፡፡

ይህ በኮርፖሬሽኑ ይዞታ ስር የሆነው የአርጆ ዲዴሳ ስኳር ልማት ፕሮጀክት በ50ሺ ሄክታር መሬት ላይ የሚለማን የሸንኮራ አገዳ የሚጠቀም ሲሆን፣ የስኳር ፋብሪካው በሙሉ አቅሙ ወደ ምርት ሲገባ በቀን 12 ሺህ ቶን አገዳ የመፍጨት አቅም እንዲኖረው ተደርጎ ዲዛይን የተደረገ ነው፡፡

Page 9: የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵ - ጥር 2007 ዓ.ም

1716 የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽን

1.የከሰም ስኳር ልማት ፕሮጀክት

ሮጀክቱ በአፋር ብሔራዊ ክልል በዞን አምስት አዋሽ ፈንታሌ እና ዱለቻ ወረዳዎች ውስጥ የሚገኝ

ሲሆን ከመተሐራ ስኳር ፋብሪካ 50 ኪ.ሜ. ያህል ይርቃል፡፡ ፕሮጀክቱ 500 ሚሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ውሃ የመያዝ አቅም ባለው የከሰም ግድብ አማካኝነት በ20,000 ሄክታር መሬት ላይ የሸንኮራ አገዳ ያለማል፡፡ የአገዳ ልማቱ ከሰም ከተባለው አካባቢ በተጨማሪ ቦልሀሞን በተሰኘ አካባቢም ይከናወናል፡፡

የከሰም ሰኳር ልማት ፕሮጀክት የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ የማስፋፊያ ፕሮጀክት አካል ሆኖ የተጀመረ ቢሆንም ስኳር ኮርፖሬሽን ከተቋቋመ ወዲህ ቦታው ከመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ካለው ርቀት አንፃር ተመዝኖና ተጠንቶ እራሱን ችሎ እንደ አንድ የስኳር ፋብሪካ እንዲንቀሳቀስ ተደርጓል፡፡

በ2007ዓ.ም ስኳር ማምረት እንደሚጀምር የሚጠበቀው የከሰም ስኳር ፋብሪካ በመጀመሪያ 6,000 ቶን ከዚያም ደረጃ በደረጃ ወደ 10,000 ቶን ሸንኮራ አገዳ በቀን ወደሚፈጭበት ደረጃ እያደገ የሚሄድ ሲሆን የኤታኖል ፋብሪካና የኮጀነሬሽን ፋሲሊቲም ይኖረዋል፡፡

ፋብሪካው በመጀመሪያ ወደ ምርት ሲገባ እስከ 153,000 ቶን ስኳር እና እስከ 12,500 ሜትር ኩብ የሚደርስ አታኖል በዓመት የማምረት አቅም የሚኖረው ሲሆን በሙሉ አቅሙ ላይ ማምረት ሲጀምር ደግሞ በዓመት 260,000 ቶን ስኳር እና 30,000 ሜትር ኩብ ኤታኖል ማምረት ይችላል፡፡ ከዚህ ባሻገር 26 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል በማመንጨት 15 ሜጋ ዋቱን ለብሔራዊ የኤሌክትሪክ ኃይል ቋት እንደሚያበረክት ይጠበቃል፡፡

ፕ ህ የስኳር ልማት ፕሮጀክት በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል በደቡብ ኦሞ ዞን የሰላማጎ

እና የኛንጋቶም ወረዳዎች፣ በቤንች ማጂ ዞን የሱርማ እና የሜኢኒትሻሻ ወረዳዎች እንዲሁም በካፋ ዞን የዴቻ ወረዳ የተመረጡ አካባቢዎች የሚካሄድ ነው፡፡ በዚህ ፕሮጀክት በ1.75 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ የሚለማ የሸንኮራ አገዳ የሚጠቅሙ አምስት ስኳር ፋብሪካዎች የሚገነቡ ሲሆን ሶስቱ በቀን እያንዳንዳቸው 12 ሺህ ቶን አገዳ በመፍጨት በዓመት 278 ሺህ ቶን ስኳር እንዲሁም 26,162 ሜትር ኩብ ኤታኖል ማምረት የሚችሉ ናቸው፡፡

ቀሪዎቹ ሁለቱ ፋብሪካዎች በቀን እያንዳንዳቸው 24 ሺህ ቶን አገዳ በመፍጨት በዓመት 556 ሺህ ቶን

ስኳር እንዲሁም 52,324 ሜትር ኩብ ኤታኖል ማምረት የሚችሉ ናቸው፡፡ በዚህ ፕሮጀክት በአጠቃላይ በ175,000 ሄክተር መሬት ላይ የሸንኮራ አገዳ ልማት ይከናወናል፡፡ ለሸንኮራ አገዳ ልማቱ የሚያስፈልገው ውኃ ኦሞ ወንዝ ላይ በሚገነባና 381 ሜትር ስፋት እና 22.4 ሜትር ከፍታ ባለው የውኃ መቀልበሻ ዊር አማካይነት የሚገኝ ነው፡፡

በፕሮጀክቱ የሚገነቡት አምስቱ ስኳር ፋብሪካዎች ሙሉ የማምረት አቅማቸው ላይ ሲደርሱ በአጠቃላይ በዓመት እስከ 1,946,000 ቶን ስኳር እና 183,134 ሜትር ኩብ ኤታኖል ማምረት ይችላሉ፡፡ በተጨማሪም 415 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል በማምረት 275 ሜጋ ዋቱን ለብሔራዊ ኤሌክትሪክ ቋት ያበረክታሉ፡፡

2. ኩራዝ ስኳር ልማት ፕሮጀክት

Page 10: የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵ - ጥር 2007 ዓ.ም

1918 የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽን

3.ወልቃይት ስኳር ልማት ፕሮጀክት

ፕሮጀክቱ ከአዲስ አበባ በ1,200 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በትግራይ ብሔራዊ ክልል በምዕራባዊ ዞን ወልቃይት ወረዳ ይገኛል፡፡ በዚህ ፕሮጀክት በቀን 24ሺ ቶን አገዳ የመፍጨት አቅም ያለው የስኳር ፋብሪካ ይገነባል፡፡ ፋብሪካው ሙሉ የማምረት አቅሙ ላይ ሲደርስ በዓመት 484 ሺህ ቶን ስኳር እና 41,654 ሜትር ኩብ ኤታኖል ማምረት የሚችል ነው፡፡ ፋብሪካው 50,000 ሄክታር መሬት ላይ የሚለማ የሸንኮራ አገዳ

መሬት ይኖረዋል፡፡ ለሸንኮራ አገዳ ልማቱ የሚያስፈልገው የውኃ አቅርቦት የሚገኘው ዛሬማ ወንዝ ላይ ከሚገነባው የሜይ-ዴይ ግድብ ሲሆን ግድቡ 840 ሜትር ስፋት እና 135.5 ሜትር ቁመት እንዲኖረው ተደርጎ እየተገነባ ነው፡፡ የግድቡ ግንባታ ሲጠናቀቅ 3 ቢሊዮን 497 ሚሊዮን ሜትር ኩብ ውኃ የመያዝ አቅም ሲኖረው የግድቡ ግንባታ እስከ ህዳር 30/2007 ዓ.ም ድረስ 33 በመቶ ደርሷል ፡፡

4. በለስ ስኳር ልማት ፕሮጀክት

ይህ ስኳር ልማት ፕሮጀክት በዋናነት የሚገኘው በአማራ ብሔራዊ ክልል ሲሆን የተወሰነ የአገዳ እርሻ ልማቱ ሥራ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ብሔራዊ ክልል ውስጥ ይካሄዳል፡፡ ፕሮጀክቱ ከአዲስ አበባ 576 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ በዚህ ፕሮጀክት እያንዳንዳቸው በቀን 12ሺ ቶን አገዳ የመፍጨት አቅም ያላቸው ሦስት ስኳር ፋብሪካዎች የሚገነቡ ሲሆን፣ በ75,000 ሄክታር መሬት ላይ የሚለማን የሸንኮራ አገዳ

በግብዓትነት ይጠቀማሉ፡፡ ለሸንኮራ አገዳ ልማት የሚውለው ውኃ የሚገኘው በበለስ ወንዝ ላይ በተገነባ የውኃ መቀልበሻ ዊር አማካይነት ነው፡፡

ሦስቱም ስኳር ፋብሪካዎች ሙሉ የማምረት አቅማቸው ላይ ሲደርሱ እያንዳንዳቸው በዓመት 242,000 ቶን ስኳር እና 20,827 ሜትር ኩብ ኤታኖል የማምረት አቅም ይኖራቸዋል፡፡

5. አርጆ ዲዴሳ ስኳር ልማት ፕሮጀክት

ፕሮጀክቱ በምዕራብ ኢትዮጵያ በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በምስራቅ ወለጋ እና በኢሉ አባቦራ ዞኖች በዲዴሳ ሸለቆ ውስጥ ከአዲስ አበባ - ጅማ - በደሌ - ነቀምት መስመር በ540 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ ፋብሪካው እ.አ.አ በ2009 አል-ሐበሻ ስኳር ፋብሪካ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ በሚል መጠሪያ ተቋቁሞ የነበረ ቢሆንም ኩባንያው ፕሮጀክቱን ማስቀጠል ባለመቻሉ ከስኳር ኮርፖሬሽን ጋር የሽያጭ ውል በመፈጸም ፕሮጀክቱ እ.አ.አ ከ2012 ነሐሴ ወር ጀምሮ ወደ ስኳር ኮርፖሬሽን ንብረትነት ተዘዋውሯል፡፡

ፋብሪካው ወደ ኮርፖሬሽኑ በተዘዋወረበት ወቅት የፋብሪካው ግንባታ ስራ ከ90

በመቶ በላይ የተጠናቀቀ ሲሆን ከ2005 በጀት ዓመት ጀምሮ የሥራ አመራር አባላት ተመድቦለትና በየደረጃው የሰው ኃይል ተሟልቶለት ተልዕኮውን ለማሣካት እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡

በሂደት በ50ሺ ሄክታር መሬት ላይ የሚለማ የሸንኮራ አገዳን የሚጠይቀው ይህ ፋብሪካ በ2007 በጀት ዓመት ወደ ሥራ እንደሚገባ የሚጠበቀው ይህ ፋብሪካ በመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታው በቀን 8ሺ ቶን አገዳ የመፍጨት አቅም የሚኖረው ሲሆን፣ የፋብሪካው ዲዛይን ወደፊት በቀን 12ሺ ቶን አገዳ የመፍጨት አቅም እንዲኖረው ተደርጎ የተሰራ ነው፡፡

Page 11: የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵ - ጥር 2007 ዓ.ም

ማጠቃለያስኳር ኮርፖሬሽን በአዳዲስ ስኳር ልማት ፕሮጀክቶች የተያዘውን ዕቅድ ለማሳካት የስኳር ልማቱን የሚደግፉ የውኃ ግድብ፣ የመስኖ አውታር፣ የመሬት ዝግጅት፣ የመንገድ፣ የመብራት፣ የውኃና የስልክ አገልግሎት እንዲሁም መኖሪያና መኖሪያ ያልሆኑ አገልግሎት ሰጪ ቤቶች ግንባታ ሥራዎች ደረጃ በደረጃ እያከናወነ ይገኛል፡፡

ተልዕኮውን ለማሣካትም በራሱ ከሚያከናውናቸው ተግባራት በተጨማሪ ልማቱ ከሚካሄድባቸው ክልሎች ጋር በቅንጅት በመስራት ውጤት እያስመዘገበ ነው፡፡ እንዲሁም ከተለያዩ የግል፣ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት ጋር የስራ ውል በመግባት በዘርፉ ልዩ ልዩ ተግባራትን እንዲያከናውኑ እያደረገ ይገኛል፡፡

ኮርፖሬሽኑ በሚገነባቸው በሁሉም አዳዲስ የስኳር ፋብሪካዎች የሚሰሩ መኖሪያና መኖሪያ ያልሆኑ ቤቶች ሙሉ በሙሉ ከአግሮስቶን ምርት የሚገነቡና ወጪ እና ጊዜን በመቆጠብ ረገድ እጅግ አዋጭ የሆኑ ናቸው፡፡ ይህም ኮርፖሬሽኑ ከከተማ ልማት፣ ቤቶችና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴርና

ከሚኒስቴር መ/ቤቱ አማካሪ ድርጅት ጋር በጋራ በመስራት ከአካባቢዎቹ ሁኔታ ጋር ተስማሚ ዲዛይን ያላቸው ቤቶች ግንባታ ለማከናወን የቻለበት ውጤታማ ተግባር ነው፡፡ በተጨማሪም ከዚህ በፊት ለመሰል ግንባታዎች ይወጣ የነበረውን ከፍተኛ ወጪ እና ይባክን የነበረውን የግንባታ ጊዜ በእጅጉ መቀነስ ተችሏል፡፡

አዳዲስ የስኳር ልማት ፕሮጀክቶች የአገር ውስጥ የስኳር ፍላጎትን ከማሟላትና ምርቱን ወደ ውጭ ልኮ የውጭ ምንዛሬ ከማስገኘት በተጨማሪ በእርሻ፣ በፋብሪካ፣ በቤቶችና መስኖ ልማት ስራ ለሚሰማሩ ቁጥራቸው ከ500,000 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች በቀጥታ እና በተዘዋዋሪ ተጨማሪ የስራ ዕድል ይፈጥራሉ፡፡

በተጨማሪም የስኳር ልማቱ በሚካሄድባቸው አካባቢዎች የሚገኙ ሕዝቦች የልማቱ ተጠቃሚ እንዲሆኑ እና የተሻለ ኑሮ እንዲመሩ ለማስቻል በመስኖ ሊለማ የሚችል መሬት ከማቅረብ ጀምሮ በአካባቢያቸው የማህበራዊ አገልግሎት መስጫ ተቋማትና የመሰረተ ልማት አውታሮች የመገንባት ሥራ በመከናወን ላይ ነው፡፡

የስኳር ስርጭት

በመላ አገሪቱ የስኳር ሥርጭት የሚከናወነው መንግሥት ባስቀመጠው የስኳር መጠን (ኮታ) የሥርጭት አሠራር ሥርዓት መሰረት ሲሆን፣ የሚከናወነውም በሚከተሉት ሦስት መንገዶች ነው፡፡

በአሁኑ ወቅት ስኳር ለአዲስ አበባ ተጠቃሚዎች የሚሰራጨው የአዲስ አበባ ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ ኮታ በመደበላቸው የሸማቾች የሕብረት ሥራ ማኅበራት አማካኝነት በራሳቸው ሱቅና ለቸርቻሪ ነጋዴዎች በማሰራጨት ነው፡፡ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ስኳር የሚያገኙት በኢትፍሩት አማካይነት ነው፡፡

የስኳር ስርጭት በአዲስ አበባ

በክልሎች ስኳር ለተጠቃሚዎች የሚሰራጨው በጅንአድ አማካይነት ወደተመረጡት ማሰራጫ ከተሞች ከተጓጓዘ በኋላ የየክልሉ ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮዎች መርጠው በሚያቀርቧቸው ጅምላ ነጋዴዎች በኩል ለቸርቻሪ ነጋዴዎች በማሰራጨት ነው፣

የስኳር ስርጭት በክልሎች

ስኳርን በግብዓትነት የሚጠቀሙ ልዩ ልዩ ኢንዱስትሪዎች ስኳር የሚያገኙት ደግሞ ንግድ ሚኒስቴርና ኮርፖሬሽኑ በኮሚቴ በጥናት የመደቡላቸውን የስኳር መጠን (ኮታ) ነው፡፡ ሁሉም በስርጭቱ የሚሳተፉ አካላት ስኳር የሚያከፋፍሉት ከኮርፖሬሽኑ የስኳር መጋዝኖች በመረከብ ነው፡፡

የስኳር ስርጭት ለኢንዱስትሪዎች

2120 የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽን

Page 12: የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵ - ጥር 2007 ዓ.ም

2322 የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽን

የስኳር ኮርፖሬሽን ወቅታዊ አደረጃጀት

ስኳር ኮርፖሬሽን በዋና ዳይሬክተር የሚመራ በርካታ የሥራ ዘርፎች አሉት፡፡ ኮርፖሬሽኑ በአገሪቱ የሚገኙ ስኳር ፋብሪካዎችን እና አዳዲስ የስኳር ልማት ፕሮጀክቶችን የሚመራ ተቋም ነው፡፡ የዋና መስሪያ ቤቱን አደረጃጀት በተመለከተ በ2004 ዓ.ም. መጋቢት ወር ላይ ተጠናቆ ተግባራዊ በተደረገው የመሰረታዊ የሥራ ሂደት ለውጥ (BPR) መሠረት በምክትል ዋና ዳይሬክተሮች የሚመሩ አንድ የዋና ዳይሬክተር ጽ/ቤት፣ አንድ ማዕከልና 12 ዘርፎች አሉት፡፡ የጽሕፈት ቤትና የዘርፎቹ ተግባራትና ኃላፊነትም የሚከተሉት ናቸው፡፡

1.የዋና ዳይሬክተር ጽ/ቤትበዋና ዳይሬክተሩ ተለይተው የሚሰጡ ልዩ ክትትል የሚያስፈልጋቸውን ስራዎች (ስፔሻል አሳይመንትስ) መከታተልና ማስፈጸም፣የሥራ አመራር ስብሰባዎችን ማቀድ፣ማስተባበርና ማስፈጸም፣ለዘርፎች በጋራ የተሰጡና ልዩ ትኩረት የሚያስፈልጋቸውን ሥራዎች መከታተል፣ማስተባበርና ስለአፈጻጸማቸው ሪፖርት ማቅረብ፣

2.የመስኖና ቤቶች ግንባታ ዘርፍ በነባርና አዳዲስ ስኳር ፋብሪካዎችና ፕሮጀክቶች ኮርፖሬሽኑ የሚያካሄደውን የመስኖ እና የቤቶች ግንባታ ማከናወን፣የጥገና አገልግሎት መስጠትና የአካባቢ ጥበቃ ስራ ማከናወን እና መምራት፣

3.የኦፕሬሽን ዘርፍበነባርና አዳዲስ ስኳር ፋብሪካዎች እና ፕሮጀክቶች የእርሻ እና የፋብሪካ ኦፕሬሽን ስራዎች ላይ ክትትል፣ድጋፍና ቁጥጥር ማድረግና መምራት፣

4.የሕዝብ አደረጃጀት ዘርፍበስኳር ፋብሪካዎች እና በስኳር ልማት ፕሮጀክቶች የሚገኙ የሸንኮራ አገዳ አብቃዮችና አነስተኛ ተቋማትን ማደራጀት፣ ማስተባበር፣ መከታተልና ማረጋጋጥ፤ ልማት በሚካሄድባቸው አካባቢዎች የሕዝብ ግንኙነት ፣የካሳ ክፍያ ፣የመልሶ ማቋቋም እና የመሬት ርክክብ ስራዎችን መምራትና ማስፈጸም፣

5.የግብይት ዘርፍበስኳርና ተጓዳኝ ምርቶች ላይ የገበያ ጥናትና የፕሮሞሽን ስራ ማከናወን፤የሀገር ውስጥ ስርጭትን መምራትና ማከናወን ፤የውጭ ግብይትና የሎጅስቲክ ማኔጅመንት ስራ

ማከናወን፣ 6.የምርምርና ስልጠና ዘርፍ

በሸንኮራ አገዳ አመራረት ተያያዥ ስራዎች ላይ ምርምር ማካሄድ፤ለሸንኮራ አገዳ ዝርያ ዴቨሎፕመንት የምርምር ስራዎችን ማከናወንና መምራት፤በስኳር ቴክኖሎጂ ዙሪያ የምርምር ስራዎችን መምራትና ማከናወን፤የስልጠና እና ስርጸት ስራዎችን መምራትና ማስፈጸም፣

7.የዕቅድና ፕሮጀክት ዘርፍየኮርፖሬት ፖሊሲዎችን እና ስትራተጂክ ዕቅዶችን ማዘጋጀት፤የኦፕሬሽን ዕቅድ፣ ክትትልና ቁጥጥር ስራዎችን መምራትና ማስፈጸም፤የጥናትና ፕሮጀክት ዕቅድ፣ ክትትልና ግምገማ ማከናወን፣

8.የሰው ሀብት ልማትና አመራር ዘርፍ

የሰው ሀብት አመራርና አስተዳደር ስራዎችን መምራትና መፈጸም፤የሠራተኛና ኢንዱስትሪ ግንኙነትን የሚያጠናክሩ ተግባራትን መምራትና ማከናወን፤የሰው ሀብት ልማትና አሰራር ሥርዓት መዘርጋት፣መምራትና ማስፈጸም፣

9.የፋይናንስ ዘርፍየፋይናንስ እና ተያያዥ ስራዎችን ማከናወን፤የፋይናንስ ቁጥጥር ስራዎችን ማከናወን እና የፈንድ አስተዳደር ስራዎችን መምራትና መፈጸም፤የትሬዠሪ ማኔጅመንት ስራዎችን መምራትና መፈጸም፣

10.የአገዳ ተክል ልማት እና ፋብሪካ ግንባታ ዘርፍ

በስኳር ፋብሪካዎች እና በስኳር ልማት ፕሮጀክቶች የሚካሄዱ የአገዳ ተክል ልማት እና የፋብሪካ ግንባታ ስራዎችን መምራት እና ማስፈጸም፣

11.የኮርፖሬት ካይዘንና የለውጥ ሥራ አመራር ዘርፍ

የትራንስፎርሜሽን ሥራ የትራንስፎርሜሽን ሥራ አመራር ለውጥ ሥርዓት በመዘርጋት መምራትና ማስፈጸም፤ የካይዘን ትግበራን በመከታተል፣ በመቆጣጠርና በማረጋገጥ ማስፈጸም፤ የለውጥ ፕሮግራም ዲዛይን

ማድረግና ማስተዋወቅ፤ የለውጥ ፕሮግራም ፍኖተ ካርታ ማዘጋጀትና እንዲተገበር ማድረግ፤ በለውጥ ፕሮግራም የአሰራር ሥርዓት በመዘርጋት ማስፈጸም፣

12.የግዢና ንብረት አስተዳደር ዘርፍ የግዢ፣ የንብረትና የፋሲሊቲ አስተዳደር ስራዎችን መምራትና ማከናወን፣

13.የተጓዳኝ ምርቶችና አግሮፕሮሰሲንግ ዘርፍ

የስኳር ተረፈ ምርቶችን ከሌሎች ተጨማሪ ውህዶች ጋር በማደባለቅ የእንስሳት መኖ ማዘጋጀት፤ ከስኳር እና ከኢታኖል ዝቃጮች የተፈጥሮ ማዳበሪያ ማዘጋጀት፤ ከሸንኮራ አገዳ ጋር በማሰባጠር በማሳዎች ላይ ተጓዳኝ ሰብሎችን ማልማት፤ ከብት ማድለብ፣ የወተት ላሞችን ማርባትና የወተት ተዋጽኦዎች ማቀነባበሪያ ፋብሪካ ማቋቋም፤ ፍራፍሬ ማልማትና በፋብሪካ ማቀነባበር፣

14.የማሽነሪ መለዋወጫ እና ጥገና አገልግሎት ኢንዱስትሪ ማዕከል

የማሽነሪ፣ የእርሻ መሳሪያዎች፣ የቀላልና ከባድ ተሸከርካሪዎች፣ የሞተር ሳይክሎች፣ የመስኖ ዲዝል ፓምፖች፣ የጀነሬተሮች፣ የጋራዥ የመገልገለያ መሳሪያዎች እና የመለዋወጫ አቅርቦት እንዲሟላ ማድረግ፤ የእርሻ፣ የኮንስትራክሽን፣ ቀላልና ከባድ ተሸከርካሪዎች፣ የመስኖ ዲዝል ፓምፖች፣ ተቀጥላ መሳሪያዎችና የሞተር ሳይክሎች አስተማማኝ የጥገና አገልግሎት በማዕከል፣ በፋብሪካዎች እና ፕሮጀክቶች መስጠት፣

የዝግጅት ክፍሉ አድራሻ- የስኳር ኮርፖሬሽን የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬትየኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር - ዘመድኩን ተክሌስልክ ቁጥር፡ ሞባይል- 0913-53 96 94 ቢሮ - 011 552 74 75 የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ኢ-ሜይል- [email protected]

Page 13: የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵ - ጥር 2007 ዓ.ም

ስኳር ኮርፖሬሽን:+251-(0)11-552-7475/6322 : +251-(0)11-515-1283 : 20034 Code 1000 A.A [email protected]

www.etsugar.gov.et || www.facebook.com/etsugar

የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ