awramba times issue 179

24
ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ የውስጥ ዜናዎች ኢትዮጵያዊ የመሆን ፈተና ከቀጫጫ ኑሮ የደለበ ሞት ይሻላል። የወፍራም ወይም የተደላደለ ኑሮ ፍቺው ሰንጋ ማጋደምና የገነት አምሳል ለመሆን በሚቃጣቸው ውብ ቤቶች ውስጥ መኖር ብቻ አይደለም። ከዛ በላይ የሆነ ረቂቅና ምስጢራዊ ትርጉም አለው - የተደላደለ ኑሮ። በውስጥ ገፅ በውስጥ ገፅ በውስጥ ገፅ ከኢትዮጵያ የተመዘበረ 8.4 ቢሊዮን ዶላር በውጪ ባንክ መገኘቱን መ/ቤታችሁ ያውቃል? ተጠሪነታችሁ ለፓርላማ መሆን ሲገባው ለጠ/ሚኒስትሩ መሆኑ ገለልተኛ ያስብላችኋል? “መንግሥታችን ፍላጎትን የማያነሳሳ ሕግ ያርቅቅልን” የኔ ጎረቤት ባሻዬ፣ ‘እንደው ይህን ያህል ግብር የጫኑባት እንዴት ነው?’ እያሉ ሲገረሙ፣ ‘በግምት ነው’ አላቸው አንዱ … ‘እኮ እኔ ጠርጥሬያለሁ እነኝህን ሰዎች የያዛቸው ሰይጣን አስገማቹ ነውንዴ? በዚህ አይነትኮ አገራችን በሁለት ዲጂት አደገች የሚሉትም ለካ በግምት ነው’ አሉ ‹‹ወደ ቤተ-ክርስቲያን የምንሄደው እግዚአብሔርን ለማገልገል ሳይሆን በእርሱ ለመገልገል ነው›› ሸዋፈራው ደሳለኝ አርቲስት በ ገፅ 11 በ ገፅ 7 ሸገር ኤፍ.ኤም ታዲያስ አዲስ vs በሱራፍኤል ግርማ በሸገር ኤፍ.ኤም 102.1 ይተላለፍ የነበረውና ባለፈው ሳምንት ተቋርጦ የነበረው ‹‹ታዲያስ አዲስ›› ፕሮግራም በድጋሚ ጀመረ። በሳምንት ለአምስት ቀናት የሚተላለፈው ይህ ፕሮግራም ለተወሰኑ ቀናት የተቋረጠው ሳያት ደምሴ በአሜሪካ ባቀረበችው ኮንሰርት ላይ በመዝፈን ፋንታ ‹‹ማይም›› ማድረጓ በመዘገቡ ነው። በዋሽንግተን ዲሲ በሰራችው ኮንሰርት ላይ በቅርቡ ባወጣችው አልበሟ ያቀነቀነችውን ዘፈን በሲዲ ማጫወቻ ከመድረክ ጀርባ እንዲለቀቅ በማድረግ እሷ ድምፅ አልባ የአፍ እንቅሰቃሴ ብቻ ማከናወኗን የተገነዘበው ታዳሚ ከፍተኛ ተቃውሞ ማሰማቱን አቶ ዓሊ ሱሌይማን /የፌዴራል የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር/ ተቋማችሁ በጠ/ሚኒስትሩ ላይ ክስ የመመስረት ድፍረት አለው ? ትልልቅ ሻርኮችን ትታችሁ ትንንሽ አሳዎችን ነው የምታጠምዱት ይባላል 4ኛ ዓመት ቁጥር 179 ቅዳሜ ሐምሌ 30 2003 ዋጋ 7፡00 ብር ኮሎኔል መንግስቱ ይናገራሉ በ ገፅ 9 ‹‹ዛሬ 64 ሺህ ካሬ ኪ.ሜ የቆዳ ስፋት ካለው ግዛታችን እና ከወገናችን ተነጥለናል፡፡ እንዲሁም ወደባችንን አጥተናል፡፡ በአጠቃላይ የኤርትራ መገንጠልና ከወገናችን መነጠላችን የሚያሳዝንና አጥንት ድረስ ዘልቆ የሚሰማ ሕመም ነው፡፡ በአሁኑ ሰዓት ኢትዮጵያ በምን ዓይነት ሁኔታ ላይ እንዳለች ለማንም ኢትዮጵያዊ ግልፅ ነው፡፡ … ስለዚህ ኢትዮጵያ አሁን ካለው አገዛዝ ነፃ መውጣት አለባት፡፡ ይህ ካልሆነ ትውልድ አስወቃሽ እና በጣም አሳፋሪ የታሪክ ቡሉኮ ለብሰን ነው ለዘለዓለም የምንኖረው፡፡›› ኮሎኔል መንግስቱ ኃይለማርያም በ ገፅ 8 ‹‹ለሳያት የሚሆን የባከነ ይቅርታ የለም›› ተቦርነ በሶማሊያ ዕርዳታ ለማድረስ የአፍሪካ ሕብረት ሰላም አስከባሪ ጦርን ማገዝ መፍትሔ መሆኑ ተነገረ 77 ሺህ ብር ያጭበረበረች ግለሰብ ተፈረደባት የ“ገመና” ጉዳይ ለ2004 ተቀጠረ በ ገፅ 19 በ ገፅ 12

Upload: balemlayl

Post on 02-Mar-2015

273 views

Category:

Documents


5 download

TRANSCRIPT

Page 1: Awramba Times Issue 179

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 179 ቅዳሜ ሐምሌ 30/ 2003

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

የውስጥ ዜናዎች

ኢትዮጵያዊ የመሆን ፈተናከቀጫጫ ኑሮ የደለበ ሞት ይሻላል። የወፍራም ወይም የተደላደለ

ኑሮ ፍቺው ሰንጋ ማጋደምና የገነት አምሳል ለመሆን በሚቃጣቸው

ውብ ቤቶች ውስጥ መኖር ብቻ አይደለም። ከዛ በላይ የሆነ ረቂቅና

ምስጢራዊ ትርጉም አለው - የተደላደለ ኑሮ።

በውስጥ ገፅ በውስጥ ገፅ በውስጥ ገፅ

ከኢትዮጵያ የተመዘበረ 8.4 ቢሊዮን ዶላር በውጪ ባንክ መገኘቱን መ/ቤታችሁ ያውቃል?

ተጠሪነታችሁ ለፓርላማ መሆን ሲገባው ለጠ/ሚኒስትሩ መሆኑ ገለልተኛ ያስብላችኋል?

“መንግሥታችን ፍላጎትን የማያነሳሳ ሕግ ያርቅቅልን”የኔ ጎረቤት ባሻዬ፣ ‘እንደው ይህን ያህል ግብር የጫኑባት እንዴት ነው?’

እያሉ ሲገረሙ፣ ‘በግምት ነው’ አላቸው አንዱ … ‘እኮ እኔ ጠርጥሬያለሁ

እነኝህን ሰዎች የያዛቸው ሰይጣን አስገማቹ ነውንዴ? በዚህ አይነትኮ አገራችን

በሁለት ዲጂት አደገች የሚሉትም ለካ በግምት ነው’ አሉ

‹‹ወደ ቤተ-ክርስቲያን

የምንሄደው እግዚአብሔርን ለማገልገል ሳይሆን በእርሱ

ለመገልገል ነው››ሸዋፈራው ደሳለኝ

አርቲስት

በ ገፅ 11 በ ገፅ 7

ሸገር ኤፍ.ኤም ታዲያስ አዲስvsበሱራፍኤል ግርማ

በሸገር ኤፍ.ኤም 102.1 ይተላለፍ የነበረውና ባለፈው ሳምንት ተቋርጦ የነበረው ‹‹ታዲያስ አዲስ›› ፕሮግራም በድጋሚ ጀመረ።በሳምንት ለአምስት ቀናት የሚተላለፈው ይህ ፕሮግራም ለተወሰኑ

ቀናት የተቋረጠው ሳያት ደምሴ በአሜሪካ ባቀረበችው ኮንሰርት ላይ በመዝፈን ፋንታ ‹‹ማይም›› ማድረጓ በመዘገቡ ነው።

በዋሽንግተን ዲሲ በሰራችው ኮንሰርት ላይ በቅርቡ ባወጣችው አልበሟ ያቀነቀነችውን ዘፈን በሲዲ ማጫወቻ ከመድረክ ጀርባ እንዲለቀቅ በማድረግ እሷ ድምፅ አልባ የአፍ እንቅሰቃሴ ብቻ ማከናወኗን የተገነዘበው ታዳሚ ከፍተኛ ተቃውሞ ማሰማቱን

አቶ ዓሊ ሱሌይማን /የፌዴራል የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር/

ተቋማችሁ በጠ/ሚኒስትሩ ላይ ክስ የመመስረት ድፍረት አለው?

ትልልቅ ሻርኮችን ትታችሁ ትንንሽ አሳዎችን ነው የምታጠምዱት ይባላል

4ኛ ዓመት ቁጥር 179 ቅዳሜ ሐምሌ 30 2003 ዋጋ 7፡00 ብር

ኮሎኔል መንግስቱ

ይናገራሉ

በ ገፅ 9

‹‹ዛሬ 64 ሺህ ካሬ ኪ.ሜ የቆዳ ስፋት ካለው ግዛታችን እና ከወገናችን ተነጥለናል፡፡ እንዲሁም ወደባችንን አጥተናል፡፡ በአጠቃላይ የኤርትራ መገንጠልና

ከወገናችን መነጠላችን የሚያሳዝንና አጥንት ድረስ ዘልቆ የሚሰማ ሕመም ነው፡፡ በአሁኑ ሰዓት ኢትዮጵያ በምን ዓይነት ሁኔታ ላይ እንዳለች ለማንም ኢትዮጵያዊ ግልፅ

ነው፡፡ … ስለዚህ ኢትዮጵያ አሁን ካለው አገዛዝ ነፃ መውጣት አለባት፡፡ ይህ ካልሆነ ትውልድ አስወቃሽ እና በጣም አሳፋሪ የታሪክ ቡሉኮ ለብሰን ነው ለዘለዓለም የምንኖረው፡፡››

ኮሎኔል መንግስቱ ኃይለማርያም

በ ገፅ 8

‹‹ለሳያት የሚሆን የባከነ ይቅርታ የለም›› ተቦርነበሶማሊያ ዕርዳታ ለማድረስ የአፍሪካ

ሕብረት ሰላም አስከባሪ ጦርን ማገዝ

መፍትሔ መሆኑ ተነገረ

77 ሺህ ብር ያጭበረበረች

ግለሰብ ተፈረደባት

የ“ገመና” ጉዳይ

ለ2004 ተቀጠረ

በ ገፅ 19

በ ገፅ 12

Page 2: Awramba Times Issue 179

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 179 ቅዳሜ ሐምሌ 30/ 2003

ግብር፣ ዜጐች በገቢያቸው መጠን በውዴታ የሚከፍሉት ወይስ በጉልበት የሚጋቱት?

T’@Í=”Ó ›?Ç=}` Ç©ƒ ŸuÅ

ª“ ›²ÒÏõì<U TV

(›É^h ¾ካ ¡/Ÿ kuK? 03/04 ¾u?.l 1540)

U/ª“ ›²ÒЋ Ó³¨< KÑW¨<wgƒ �Â

Ÿõ}— ›²ÒÏ ›u?M ¯KT¾G<

Ÿõ}— ]þ`}a‹ ›?MÁe Ñw\

c<^õ›?M Ó`T�ናፍቆት ዮሴፍ

ኮፒ ኤዲተርƒ°Óeƒ ¨”ÉS<

¯UÅ™‹ታዲዎስ ጌታሁን SpÅe õeNደሳለኝ ስዩም

iÁß“ Te�¨mÁ }hK cÃñ

Ó^ò¡e ›?Ç=}` ’w¿ Seõ”

(0911 18 09 33)E-Mail:[email protected]

የማስታወቂያ ክፍሉ ስልክ0911629281

¾´Óσ ¡õK< eM¡eM¡:- ®911 62 92 78 0923 02 88 91 ®911 62 92 82 0911 15 62 48 þ.X.l [email protected]://www.awramba.com

›d�T>¨<ብሉ ኤርዝ ጀነራል ቢዝነስ

ኃላ/የተ/የግል/ማህበር

ር ዕ ሰ አ ንቀፅ

ማን ምን አ ለ

2

ግብር ለአንድ አ ገ ር ሁ ለ ን ተ ና ዊ ዕድገት ወሳኝ ከ ሚ ባ ሉ ግ ብ አ ቶ ች መ ካ ከ ል

የሚጠቀስ፤ ዜጐች በሚያገኙት የገቢ መጠን ልክ ብቻ ተሰልቶ የሚከፈልና በውጤቱም አንዲት አገር መሠረታዊ ልማቶቿን የምታስፋፋበት፤ የአመታዊ በጀት አካል ሆኖ እቅዶቿን የምታሳካበት፣ ዜጎችን በሃላፊነት ለሚያገለግሉ የመንግስት ሠራተኞች ደመወዝ የምትከፍልበት፤ በአጠቃላይ ለአንዲት አገር መተዳደሪያ የሚውል በመሆኑ አስፈላጊነቱ አያጠያይቅም።

ምንም እንኳን እንደ ኢትዮጵያ ያሉ አገሮች የብድርና እርዳታ ጥገኛ በመሆናቸው ከዜጎች የሚሰበሰብ ግብር ከላይ ለጠቀስናቸው መሰረታዊ ጉዳዮች ይህ ነው የሚባል አስተዋጽኦ ባይኖረውም፤ ዜጎች በገቢያቸው መጠን ግብር ሊከፍሉ እንደሚገባ አያጠያይቅም፡፡

ይህ አይነቱ አሠራር በተለይ በሰለጠኑ አገሮች በሳይንሳዊ መንገድ የተለያዩ ጥናቶች ተደርጎበት፤ ዜጎች በአግባቡ እና በሰለጠነ ቀመር ብቻ ስለሚከናወን ማንም ዜጋ ‹‹አላግባብ ግብር ተጠየቅኩ›› ብሎ የሚያማርርበት ብሎም ‹‹የፍትሕ ያለህ›› እያለ

መሄጃ የሚያጣበት ሁኔታ ብዙም አልተለመደም። ምክንያቱም ከላይ እንደጠቀስነው በሳይንሳዊ መንገድ፣ በሰለጠኑና ስለ ሙያው በቂ ግንዛቤ ባላቸው ሙያተኞች አማካኝነት በተጠና ዘመናዊ አሰራር ስለሚከናወን።

ወደ አገራችን ስንመለስ ግን በየአመቱ በተለይ በክረምት ወቅት ለዜጎች በተለይ ደግሞ በአነስተኛ ንግድ ላይ ለተሰማሩ ነጋዴዎች የመርዶ ያህል ዱብ ዕዳ የሚሆንበት ነባራዊ ሁኔታ እንመለከታለን፡፡ ሰሞኑን በአዲስ አበባ ከተማ አነስተኛ ንግድ ባለቤቶች ላይ የምንመለከተው እሮሮና ጭንቀት ዋነኛ ምንጩ፤ ይህንን ኃላፊነት እንዲወጣ አደራ የተጣለበት አካል ዘመናዊ አሰራርን ባለመከተሉ፤ ከበለጸጉ አገሮች ልምድ በመቅሰም በጥናት ላይ የተመሰረተ አሰራርን ባለመከተሉና በየንግድ ተቋማቱ ተገኝተው የግብር መጠንን የሚገምቱ ሰራተኞችም በዘልማድና በልበ ብርሀን ስለሚገምቱ የተፈጠረ ችግር መሆኑን አውራምባ ታይምስ ለመገንዘብ ችላለች።

በርካታ ነጋዴዎች እንደሚሉት ‹‹አንድ አነስተኛ የንግድ ተቋም በአምስት እና በአስር አመት ውስጥ ማግኘት የማይችለውን አጠቃላይ ገቢ የአንድ አመት ግብር ተብሎ እንዴት ይጫንበታል፤ በተለይ ደግሞ የዚህ አመት የግብር ተመን በምን አይነት ስሌት እንደሚሰራ ግራ

ገብቶናል›› ሲሉ በምሬት እየገለጹ ይገኛሉ፡፡ ለመሆኑ እንደዚህ አይነቱ ስህተት እንዴት ሊፈጠር ቻለ? የሚል ጥያቄ ከተነሳ አንድም ግብር ሰብሳቢው መስሪያ ቤት የነጋዴዎቹን ገቢ የሚቆጣጠርበት አስተማማኝ ሲስተም ባለመዘርጋቱ የተፈጠረ አሊያም መስሪያ ቤቱ የሚያሰማራቸውና በየደረጃው ያሉ የተቋሙ አስፈፃሚዎች ስለ ገቢ አሰባሰብና ስለ ግብርና ታስክ መሰረታዊ ትርጓሜ ባለመገንዘባቸው የተፈጠረ ሊሆን እንደሚችል አያጠያይቅም።

ግልፅነትና ተጠያቂነት ያሰፈኑ መንግስታት ባሉባቸው አገሮች ዜጎች ግብር በመክፈላቸው አይቆጩም፡፡ ምክንያቱም በዜጎች ፈቃድ የመጡና ለህዝቦቹ ሁለንተናዊ ጥቅም የሚቆረቆሩ መንግስታት ባሉባቸው አገሮች ግብር መክፈል አገርን ከመውደድ ጋር የተቆራኘ በመሆኑ ያለምንም ቅሬታ መክፈል የሚገባቸውን በውዴታ ይከፍላሉ። ደግሞም መክፈል የሚገባቸውን መጠን እነሱም አስቀድመው ስለሚያውቁ እና ይህንኑ ተልዕኮ የሚያስፈፅሙ ተቋማትም ግብርን የሚሰበስቡት ዜጎችን ሳያስጨንቁ በመሆኑና ዜጎችም የሚከፍሉት ግብር ምን ላይ እንደዋለ የሚያጣሩበት ግልፅ አሰራር በመስፈኑ ያለምንም ማመንታት ይከፍላሉ። ይህ አይነት መንግስታዊ ተጠያቂነት በአገራችን ስለ መኖሩ ግን ጥርጣሬ አለን። ምክንያቱም

የካቲት 2000 ዓ.ም ተመሠረተ

አውራምባ ታይምስ፡- በብሉ ኤርዝ ጀነራል ቢዝነስ ኃላ/የተ/የግል/ማህበር ስር የሚታተም፤ በፖለቲካዊና ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩር፤ በንግድ ሚኒስቴር በቁጥር 020/2/6572/2001 የተመዘገበ ሳምንታዊ ጋዜጣ ነው፡፡

አድራሻ አራዳ ክፍለከተማቀበሌ 13/14

የቤት ቁጥር 467ከአራት ኪሎ ወደ መገናኛ በሚወደው መንገድ

ከራስ አምባ ሆቴል አለፍ ብሎ በሚገኘው

አቤኔዘር እንግዳ ማረፊያ ግቢ ውስጥ

አታሚ፡-

ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ክ/ከተማ፡- አራዳቀበሌ፡- 17የቤት ቁጥር፡- 984

‹‹የቻይናን ጉዳይ በተመለከተ ዓለም የሚያውቀው በመሆኑ ብዙም አስተያየት አልሰጥበትም። ነገር ግን እንግሊዝ መቼም ቢሆን የማታደርገው ነገር ቢኖር

ንግድን ከሰብዓዊ መብት ማስቀደም ነው።››

ሄንሪ ቤሊንግሃም የእንግሊዝ የአፍሪካ ጉዳዮች ሚኒስትር

ቻይና ለመልካም አስተዳደር እና ለሰብዓዊ መብት ምንም ቦታ ሳትሰጥ ከአገሮች ጋር በመነገዷ

ትወቀሳለች … በቻይናና በእንግሊዝ የንግድ መርህ መካከል መሠረታዊ ልዩነት አለ? በሚል ከሪፖርተር

ጋዜጣ ለቀረበላቸው ጥያቄ የሰጡት ምላሽ።

‹‹አቦይ አንዳንድ ጊዜም ጽሁፋቸው የማስፈራራት ቃላት ያዘለ ነው። ታዲያ የአገሬው ህዝብ አሁንም

ይፈራ እንደሆነ ለመፈተን አስበው ይሆን?››

አቶ አስገደ ገብረስላለሴየህወሓት መስራችና የአረና አመራር አባል

አቦይ ስብሀት ወደ ግል ጋዜጦች ብቅ ማለታቸው ለምን ይሆን? በሚል ርዕስ በፍትህ ጋዜጣ ላይ

ካሰፈሩት ፅሁፍ የተወሰደ

ማን ምን አ ለ

ዜጎች ‹‹የከፈልነው ግብር ምን ላይ ዋለ›› ብለው ሊጠይቁ ይቅርና ‹‹ከአቅማችን በላይ አላግባብ ከፍተኛ መጠን ያለው ግብር ተጥሎብናል ይጣራልን›› ብለው ለሚያቀርቡት ጥያቄ እንኳን ተገቢ ምላሽ አላገኙም ‹‹የተጠየቅከውን መጠን ክፈልና እንዳስፈላጊነቱ ሊጣራ ይችላል›› ነው እየተባሉ ያሉት፡፡ ይህ መፍትሄ አይደለም፡፡ ከዜጎች ግብር እንዲሰበስብ በአዋጅ ስልጣን የተሰጠው የአስፈፃሚ መስሪያ ቤት ኃላፊዎች እና ሰራተኞች ‹የተጠየቅነው የግብር መጠን ከአቅማችን በላይ ነው›› የሚል ጥያቄ ሲቀርብላቸው ስርዓት ባለው መንገድ መመርመርና ተገቢውን መፈትሄ መስጠት አለባቸው።

ግብር ለአንድ አገር ሁለንተናዊ ጠቀሜታ ምን ያህል ሚና እንዳለው ለዜጎች በማስረዳት ዜጎች ደግሞ በባለቤትነት ስሜት የሚጠበቅባቸውን በውዴታ እንዲከፍሉ ተገቢ ስራ መሠራት አለበት፤ ተገቢ ጥናትና ማህበረሰቡን ያሳተፈ ምክክር መደረግ አለበት፡፡ መንግስት ግብርን መሰብሰብ ያለበት በዛቻና በጉልበት ሳይሆን ግልጽነት በሰፈነበር ዘመናዊ አሰራር ነው። አላግባብ ግብር እንድንከፍል ተደርገናል ብለው ጥያቄ የሚያቀርቡ ዜጎችን ድምጽ በጥሞና ሊደመጥ ይገባል። አገር የጋራ እንጂ የጥቂቶች አይደለችም።

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!

|‹‹ማንሃወም ሃይማኖት የሰላም አባት መሆን አይችልም። ሰላምን በአቋራጭ ማምጣት አይቻልም።

ሰላም የሚመጣው ሰላማዊ፣ ልማታዊና ዴሞክራሲያዊ ሲኮን ነው››

አቶ ስብሃት ነጋየኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ የሰላምና የልማት ተቋም

ዳይሬክተር

‹‹በሰላም ጋዜጠኝነት›› ዙሪያ በአምቦ ከተማ በተዘጋጀ ስልጠና ተገኝተው ያደረጉትን ንግግር አስመልክቶ

ሰንደቅ ጋዜጣ ካሰፈረው የተወሰደ

Page 3: Awramba Times Issue 179

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 179 ቅዳሜ ሐምሌ 30/ 2003

ኢትዮጵያውያንን ያስደመመው የዓረብ “መነቃቃት”

3

ሥራ አጥነት፣ ድህነት፣ በውጭ እርዳታ መደገፍ፣ የምግብ ዋጋ ንረት እና እጥረቶች፤ እና ስለህዝቡ ፍላጎቶች አንዳች መረጃው የሌለው መንግሥት ናቸው።

በዳያስፖራ ያሉ አብዛኞቹ ኢትዮጵያውያን በኢትዮጵያ፣ እና በቱኒዚያና ግብፅ መካከለ ሰፊ ልዩነቶች መኖራቸውን ቢገነዘቡም፣ የሚመሳሰሉባቸው ነገሮችም አሉ የሚል ስሜት አላቸው፡፡ የግብፃውያን ሕዝባዊ አመፅ ቢያንስ ለሶሰት አስርት ዓመታት ሲብላላ ቆይቷል፤ የኢትዮጵያ ደግሞ ለ20 ዓመታት፡፡ እንደ ኢትዮጵያ ምሁራን የቱኒዚያና ግብፅ አመጾች ከኢትዮጵያ የተለዩ ልዩ ውስጣዊ ሁኔታዎች አግዘዋቸዋል ይላሉ፡፡ ከኢትዮጵያ የተለዩ ናቸው የሚሏቸውን እና የሁለቱም ሀገራት አብዮቶች መነሻ ያሏቸውን ስድስት

ውሳኝ መገለጫዎችንም ነቅሰው አስቀምጠዋል፡፡

አንደኛ፡- የየሀገራቱ ሕዝቦች የጋራ ትስስር ነው፡፡ ዛሬ ከ85 ሚሊየን በላይ የሚገመተው የኢትዮጵያ ሕዝብ የተለያዩ 80 የብሔር ቡድኖችን ያቀፈ ነው፡፡

ሁለተኛ፡- ያላቸው የመከላከያ ተቋም ነው፡፡ የኢትዮጵያ መከላከያ ሙሉ በሙሉ ማለት በሚያስችል መልኩ የሚመራው የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር - ኢህአዴግ - በበላይነት በተቆጣጠሩ ከሀገሪቱ በሕዝብ ብዛት አነስተኛ በሆኑ የአንድ ብሔር ቡድን ተወካዮች ነው፡፡ አብዛኞቹ ኢትዮጵያውያን በአንድ ብሔር የበላይነት የተያዘው ኮማንድ የሀገሪቱን ብሔራዊ መገለጫ ያኮስሳል የሚል ስሜት አላቸው፡፡

ኢትዮጵያውን፣ የግብጽ መከላከያ ተቋም የሀገሪቱን ሕዝብ አንድ አድርጎ የሚወክል እና በብሄር አልያም በርዕዮተ-ዓለም ችግሮች ያልታመሰ የመሆኑን እውነታ ያውቁታል፡፡ ግብፃውያንና ቱኒዚያውያን የሀገራቸው ዜጎች ሆነው መታገላቸውን ኢትዮጵያውያን ያደንቁታል። ኢትዮጵያውያን በብሔር የተከፋፈሉ ናቸው፡፡ ይህ ሰው-ሰራሽ ክፍፍል ወደሃይማኖትም እንደማያመራ ተስፋ አላቸው፡፡ ለዘመናት ሙስሊሞችና ክርስቲያኖች ሰላማዊ በሆነ መልኩ አብረው ተቻችለው ኖረዋል፤ ይህም በዓለም እምብዛም የሌለ ታላቅ ባህል ነው፡፡

ሶስተኛ፡- የቱኒዚያና የግብፅ ህዝብ ለራሱ ብሔራዊ ተቋማት ከፍተኛ አክብሮት አለው፡፡ ኢትዮጵያውያን በሁሉም ጊዜያት እና በሁሉም ጉዳዮች አንድ የሆኑ አርበኞችና ለራሳቸው ተቋማትና ባህሎች አንድ አይነት ብሔራዊ ስሜትና አክብሮት አላቸው የሚለውን በተመለከተ ብዙዎች እርግጠኞች አይደሉም፡፡ አራተኛ፡- ግብፅና ቱኒዚያ ከኢትዮጵያ በበለጠ አንድነት ያላቸውና ቁጥሩ ከፍተኛ የመካከለኛ

ገቢ ማህበረሰብ እና የተማረ የሰው ኃይል አሏቸው፡፡ ከሕዝባዊ አብዮቶች አንፃር ይህ ልዩነት እጅግ አስፈላጊ ከሆኑት መካከል አንዱ ነው፡፡ እዚህ ግቡ የማይባሉ ጥቃቅን ምቀኝነቶች እና ጥላቻዎች ከኢትዮጵያ ጋር ሲነፃፀሩ በእነዚህ ሀገራት ውስጥ የሉም ማለት ይቻላል፡፡ ይህም ሌላኛው ወሳኝ ልዩነት ነው፡፡

ዛሬ ኢትዮጵያ በዓለም በጣም ዝቅተኛ የቴክኖሎጂ ትስስር ካለባቸው ሀገራት መካከል ትመደባለች፡፡ ይህ ግን የሆነው በምርጫ ሳይሆን በመንግስት ገደቦች ነው፡፡ ከኢትዮጵያውያን በበለጠ የሚያስፈልጓቸው የቴክኖሎጂ መገልገያዎች - ኢንተርኔት፣ ተንቀሳቃሽ ስልኮች፣ ‹‹Facebook››፣ ‹‹You Tube››፣ ‹‹Twitter›› እና ጋዜጦች በጣም በቅርበት የሚያገኙአቸው ናቸው፡፡ ስድስተኛ፡- የሚጠቀሟቸው እንደ ባንዲራና መዝሙር ያሉ ባነሮች ሀገራዊ ናቸው፡፡ ‹‹እኛ ቱኒዚያውያን እና ግብፃውያን ነን!›› ገዥው ፓርቲ ሀገሪቱን ለመግዛት በብሄር ክፍፍልን ይጠቀማል የሚል ስሜት ያደረባቸው ኢትዮጵያውያን የሚስማሙባቸው አስተሳሰቦች ናቸው፡፡ ህዝብ እንደ አንድ ሲዋሃድ የትኛውም ኃይል አያቆመውም የሚለው አጠቃላይ መግባባት ላይ የተደረሰበት አመለካከት ነው፡፡ እንግዲህ ከላይ ከአንድ እስከ ስድስት የተዘረዘሩት ናቸው ኢትዮጵያውያን በግብፅና ቱኒዚያ የሚደነቁባቸው መገለጫዎች፡፡

በአባይ፣ እንዲሁም ሙስሊሞችና ክርስቲያኖች በሁለቱም ሀገራት አብረው የሚኖሩ

በአክሎግ ቢራራ/ፒኤች.ዲ/

በመሆናቸውና ግንኙነታቸው ከሺህዎች ዓመታት በፊትም የነበረ በመሆኑ ግብፅ ለኢትዮጵያ የተለየ ቦታ አላት፡፡ በየካቲት 1/2011 ላይ የተለያየ መሰረት ያላቸው ሁለት ሚሊየን የሚጠጉ ግብፃውያን ለተመሳሳይ ዓላማ ተሰባስበው እየፀለዩ በህብረት ተቃውሞአቸውን ባሰሙበት ወቅት ኢትዮጵያውያን ትኩረታቸውን በተለያዩ የሚዲያ አውታሮች ላይ አድርገው ነበር፡፡

ሚዲያ ለማግኘት የቻሉ ኢትዮጵያውያን የግብፀውያንን ሥልጡንነት፣ ብሄራዊ ኩራት እና አንድነት ያደነቁት እውነታ ነው፡፡ ግብፃውያን በርዕዩተ-ዓለም፣ ፖለቲካ፣ ሃይማኖት፣ ጾታ፣ በዴሞግራፊያዊና ማህበራዊ ልዩነቶች አለመመሰቃቀላቸው በወቅቱ ታይቷል፡፡ ለነፃነት፣ የሕግ የበላይነትና ፖለቲካዊ ብዝሃነት ከፍተኛ ስፍራን ይሰጣሉ። የግብፅ ባንዲራ የብሔራዊ አንድነት እና ማንነት ምልክት ሆኖ አገልግሏል፡፡ አብላጫው ሰልፈኛ ከየትኛውም ሀገር ጋር የማይነፃፀር ዲሲፒሊንና አንድነት አሳይቷል፡፡ በተለይ ዜጎቹ ላይ ለመተኮስ ፍቃደኛ ያለሆነውን የግብፅ መከላከያ ኢትዮጵያውያን የተደመሙበት ነው፡፡ ይህ በድህረ-ምርጫ 1997 በመቶዎች የሞቱበትና 40 ሺህ ገደማ ሰዎች ለእስር ከተዳረጉባት ኢትዮጵያ ጋር የማይጣጣም እውነታ ነው፡፡ ከግብፅ ጋር ተመሳሳይነት ያላቸው የሚመስሉት በ1970ዎች በኢትዮጵያ የታደረገውና ንጉሣዊውን ሥርዓት

እንደ ባንዲራና መዝሙር ያሉ ባነሮች ሀገራዊ ናቸው፡፡ ‹‹እኛ

ቱኒዚያውያን እና ግብፃውያን ነን!›› ገዥው ፓርቲ ሀገሪቱን

ለመግዛት በብሄር ክፍፍልን ይጠቀማል የሚል ስሜት ያደረባቸው

ኢትዮጵያውያን የሚስማሙባቸው አስተሳሰቦች ናቸው

በአራዳ ክ/ከተማ በሆቴል እና ቱሪዝም ዘርፍ በተደረገው ውድድር ንጉሴ ልዩ ክትፎ እና አሳ ቤት 1ኛ በመውጣት የዋንጫ ተሸላሚ ሆነ ልዩ መለያችን የሆነው፡-

የተለያዩ የአሳ ምግቦች •የፆም ምግቦች ተመራጭ ክትፎአችን •ንፁህ የመኝታ ክፍሎች•

አድራሻ፡- ቁጥር 1. ቅ/ማርያም ቤ/ክ ፊት ለፊት 5 ኪሎ

ቁጥር 2. ፒያሳ አፍሪካ ወርቅ ቤት ፊት ለፊት

ቁጥር 3. 5 ኪሎ ከጠቅላይ ቤተክህነት መግቢያ በር ፊት ለፊት

በቁጥር 2 እና 3 ምቹና ዘመናዊ መኝታ ክፍሎች ከበቂ የመኪና ማቆሚያ ጋር ይምጡ ማየት ማመን ነው!

011 156 61 75 8910Addis Ababa, Ethiopia

ጥራት ላለው የክትፎና የአሳ

ምግቦች የከተማችን

ቁጥር 1 ሆቴል

ንጉሴ ልዩ ክትፎ እና አሣ ቤት

በ ቱ ኒ ዚ ያ ው ያ ን ና ግብፃውያን ሕዝባዊ ተቃውሞዎች ምክንያት የኢትዮጵያውያንን ያህል መደመመ የሚስተካከል አንድም የሰሃራ በታች ሀገር የለም ብዬ አስባለሁ። ይህም አድናቆት ተመሳሳይ ለውጦችን በሀገራቸው ለመመልከት ጥልቅ ፍላጎትና መሻት ካላቸው ኢትዮጵያውያን ወጣቶች እና በመካከለኛ ገቢ ላይ ካሉ ኢትዮጵያውያን የመነጨ ነው፡፡

በአንድ በኩል መካከለኛ ገቢ ባላቸው እና በወጣቶች በተመሩት የቱኒዚያው ጃዝሚን እና የግብፀ ታህሪር አደባባይ፣ እና የተቀረው የመካከለኛው ምሥራቅና ሰሜን አፍሪካ ሕዝባዊ ተቃውሞዎች፣ እና በኢትዮጵያ ውስጥ ባሉ ሁኔታዎች መካከል ንፀፀሮሽ ለመስጠት ጊዜው በጣም ገና ቢሆንም፣ ለሕዝባዊ

ተቃውሞዎቹ መንስዔ የሆኑት ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ግን አንድ አይነት ናቸው። እነዚህም አፋኝ አስተዳደር፣ ርትዕ-አልባ ገቢ፣ የተንሰራፋ ሙስና፣ ኃብቶችን በሕገወጥ መንገድ ከሀገር ማስወጣት፣ እጅግ ከፍተኛ የወጣቱ በ ገፅ 23

Page 4: Awramba Times Issue 179

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 179 ቅዳሜ ሐምሌ 30/ 2003

የተ.መ.ድ ሪፖርቶች እና የሃያላኑ ጨዋታ በአፍሪካ ቀንድፊ ቸ ር4

የሰው ዘር መነሻና ጅማሮ የሆነው የአፍሪካ ቀንድ በአሁኑ ጊዜ የሰው ልጅ መጥፊያና የህይወቱ ማብቂያ አንደኛ ስፍራ

ሆኗል። የጥንት ታሪክ ስልጣኔ እና ትውፊት ያለው ይህ አካበቢ የመልካም እሴቶች ሁሉቋያ ሆኖ ባህሎቹን፣ ህዝቦቹን፣ ብሎም ተፈጥሯዊ አካባቢውን አብሮ እየበላ ይገኛል። ለዚህም አብነት ፡- ህያው ምስክር የሆነን የምንታዘበው? የረሃብና ድርቅ፣ የጦርነትና አመፅ፣ ወቅታዊን ክስተት አብይ ማስረጃ ነው። ምን ዓይነት እርግማን ተከትሎት ይሆን?በግምት በዚህ አካባቢ አንድ መቶ ሚሊዬን

እና ከዚያ በላይ የሚሆን ህዝብ ይኖራል። በኢትዮጵያ ወደ 85 ሚሊዮን፣ በሶማሊያ ወደ አስር ሚሊዮን፣ በኤርትራ ወደ ሦስት ሚሊዮን፣ በጅቡቲ 864 ሺህ፣ በሱዳን 42 ሚሊዮን እንዲሁም የሌሎችንም መጥቀስ ይቻላል። ታዲያ ይህ አካባቢ ባለፉት የአንድ መቶ አመታት ውስጥ ያረፈበት የቅኝ ግዛትና የጭቆና አስከፊ ዘመናት ከተፈጥሯዊና አካባቢያዊ አዘቅቶች ጋር ተዳምረው እንደቅጠል እያረገፉት ይገኛሉ።

የሰሞኑ የተ.መ.ድ ሪፖርቶች አንደምታ

የተባበሩት መንግስታት የቁጥጥር ቡድን በሶማሊያ እና ኤርትራ ሪፖርት እንዳስታወቀው በእርዳታ ሰጭ አካላት ላይ የሚደርስ ከፍተኛ ወከባ እና ማስፈራራት መኖሩን ነው። ታዲያ ይህ ሪፖርት ሰሞኑን በከፍተኛ ደረጃ እና መጠን በምስራቅ አፍሪካ አገራት የተከሰተውን ድርቅና ረሃብ ተከትሎ የተፈጠረውን ፍጥጫ በማስመልከት የተሰጠ ነው። እንደ የዓለም የምግብ ድርጅት (WFP) አመታዊ ዘገባ በኢትዮጵያ ብቻ ወደ ስድስት ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች በረሀብ አለንጋ ሊቀጡ አፋፍ ላይ ነበሩ። የተቀጡም ነበሩ ታዲያ። በያዝነው የ2011 ዓመትም በኬንያ፣ ጅቡቲ፣ ሶማሊያ እና ኢትዮጵያ ወደ 12 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች ለከፍተኛ ረሃብ ተዳርገዋል። በ13 ዓመታት ለመጀመሪያ ጊዜም በደቡባዊ ሶማሊያ የባኮል እና ታችኛው ሸበሌ አካባቢዎች ላይ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (UN) ረሃብ እንደተከሰተ አውጇል። ከነዚህ የተራቡ ህዝቦች ውስጥ ደግሞ ኢትዮጵያ ወደ 4.5 ሚሊዮን የሚያህሉትን ትወክላለች። በሶማሊያ ብቻ የሚገኙትን ረሃብተኞች ለመታደግ የተመድ ሊቀ መንበር ባን ኪ ሙን 1.6 ቢሊዮን ዶላር ከለጋሾች ጠይቀዋል። ሌላው የተመድ ሪፖርት ደግሞ ኤርትራን

የተመለከተ ነበር ‹‹ኤርትራ በኢትዮጵያ ሊካሄድ ተጠንስሶ በነበረው የቦንብ ጥቃት ሴራ ጀርባ የቆመች ኃይል ናት። ለሶማልያ የአል ሸባብ አማፅያንም የገንዘብ ድጋፍ እንደምታደርግ ተደርሶባታል።›› ሲል ነበር መረጃውን

ያሰራጨው። ሪፖርቱ ሲያብራራ፡- በመስከረም 2010 ኢትዮጵያ ውስጥ የተያዙት የኦጋዴን ነፃ አውጪ ግንባር ተዋጊዎች ሲጠቀሙበት የነበረው የጦር መሳሪያ ከኤርትራ የተሰጠ እና በቡልጋሪያ የተገጣጠመ እንደሆነ፤ በተጨማሪም የተማረኩት የኦጋዴን ነፃ አውጪ ግንባር አባላት በኤርትራ ስልጠና ሲሰጣቸው እንደቆየና በሶማሊ ላንድ በኩል ወደኢትዮጵያ ሰርገው እንደገቡ ለተመድ አጣሪዎች የምርመራ ቡድን ቃላቸውን ከሰጡት አማፅያን ተረጋግጧል።›› ብሏል። ይህ የረሃብና የሽኩቻ ሪፖርት ከሚያነሳው ርዕሰ ጉዳይም በላይ የሚያመለክተው ማባሪያ ያጣው የአካባቢውን ሰው ሰራሽና ተፈጥሯዊ ቀውስ ነው።

የቀንዱ አጭር ፖለቲካዊ ዳራይህ የምስራቅ አፍሪካ ቀጠና በታሪኩ ብዙ

የ ሩ ቅ ና የ ቅ ር ብ

ኃ ያ ላ ን መንግስታትን፣

ባህሎችን ብሎም ሰዎችን ሲያስተናብር

የኖረ ልዩ ስፍራ ነው። በነበረው ስትራቴጂካዊ እና

ጂኦፖለቲካዊ ወሳኝ አቅማመጥ ሳቢያ ለወታደራዊ፣ ንግድ እና

ዲፕሎማሲያዊ አመቺነቱ ሲባል አያሌ ዕቅዶች ተነድፈውለት ሲገነባ፣ ሲፈርስና

ሲታመስ የኖረ ነው። አሁንም በዚሁ የለውጥ ሂደት ውስጥ እያለፈ የሚገኝ አስገራሚ እና አወዛጋቢ ቀጠና እንደሆነ ቀጥሏል። በአውሮፓውያን ቅኝ ግዛት ታሪክ ውስጥ

የባዕድ አገዛዝ ስልታዊ ተንኮል ሰለባና የውጭ ወረራ ግንባር ቀደም መካች (አድዋን ልብ ይሏል)፣ የዘመናዊ ህዝበ-መንግስት (ዴሞክራሲ) መሠረት-ጣይ (የገዳ ስርዓት) እና የአስከፊ ጭቆናና ጨለማዊ አገዛዝ መገለጫ ሆኖ የህይወት ተቃርኖአዊ ውህደቶችን በውስጡ አቅፎ ይገኛል። ይህንን የቅኝ አገዛዝ ተከትሎም በባርነት ለመጋዝ፣ በብዝበዛ ለመደቆስ፣ በርሃብ ለመቀጣት ተዳርጓል። ለጥሬ ሀብቱ፣ለጉልበቱ፣ እና ለሸቀጥ ማራገፊያነቱ ሲባል እንደ እንግሊዝ፣ ፈረንሳይ፣ እና ጣልያን ለመሳሰሉ ባለጊዜ ሃያላን ጭዳ ሆኖ ቀርቧል። የቅኝ አገዛዝ ታሪክ ባልተሟላ ሁናቴ ከተደመደመም በኋላ ቢሆን በነበረው የቀዝቃዛው ጦርነት ባለሁለት ዋልታ የዓለም አሰላለፍ (bi-polar world order) ምክንያት የአሜሪካና፣ የሶቪየት ራሺያ መራኮቻ ሆኖ ቀርቷል። በነዚህም ሁሉ ጊዜያት ይህ አካባቢ ራሱን ቀና

አድርጎ በሁለት እግሩ ሊቆም ያልቻለ የሃያላን ተውሳክ ሆኖ በነፈሰበት ሲነፍስ አሁን ላይ ደርሷል። አሁን ደርሶበታል! ማለቱ ሳይሻል አይቀርም። አሁን ደግሞ የአሜሪካ ፍፁም የበላይነት (hegemony) የነገሰበት ይመስላል።

በአናንያ ሶሪ [email protected]

በቅርቡ ሂላሪ ክሊንተን በአፍሪካ ህብረት ስብሰባ ላይ ተገኝተው የተናገሩትን ንግግር

ሰምና ወርቅ ላስተዋለ ቅኔው ብዙም ምስጢር እንደማይሆን ያትታሉ። ነገር ግን

ይህም ከመሆኑ በፊት ‹‹ኢትዮጵያ ፊቷን ወደ ምስራቅ (ቻይና) በማዞር እጆቿን

ወደ ምዕራብ (አሜሪካ) መዘርጋቱን አለማቆሟ የመንግስቷን ጥንቁቅ አካሄድ

አስረጅ ነው›› ሲሉ ተንታኞች ያስጠነቅቃሉ።

Page 5: Awramba Times Issue 179

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 179 ቅዳሜ ሐምሌ 30/ 2003

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

የተ.መ.ድ ሪፖርቶች እና የሃያላኑ ጨዋታ በአፍሪካ ቀንድ5

ማስታወቂያ

በ ገፅ 15

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

ከዓለም ሲኒማ ተመልካቾች የተሰበሰበ

በጣም የተዋጣለት ፊልም ነው 1. ግሩም ኤርሚያስ የተዋጣለት 2. አማላይ ነው በተለይ ለእንደእኔ ትውልደ 3. ኢትዮጵያዊ ይመቻል በጥራት ስለሰራችሁት 4. አመሰግናለሁ ፊልም ማለት እንደዚህ ነው 5. ሁለት የተለያዩ ስቶሪዎች በፍቅር 6. አይቻለሁ ግሩም እኔን በጣም ነው ያማለለኝ 7. አስተዋውቁኝ እኔና ጓደኞቼ የእውነት ማለናል፡፡ 8.

ምስጋና ለዓለም ሲኒማ

ከባለሙያዎች የተሰጠ አርቲስት መርዓዊ ስጦት - ዘመኑን የዋጀ ፊልም አርቲስት ሠይፉ አርአያ - የወጣቶችን ልብ የሚማርክ ዘመናዊ ፊልም አርቲስት ጌትነት እንየው - በጣም የሚጣፍጥ ቀለል ያለ ታሪክ አርቲስት ቢኒያም ወርቁ - በሁሉም መስክ የተዋጣለት ፊልም ደራሲ እንዳለጌታ ከበደ - በባለሙያዎች የተሰራ ምርጥ ፊልም የሜዳሊያ ደራሲ አማኑኤል መሀሪ - ምርጥ ፕሮዳክሽን ሊያዩት የሚገባ

የአማላዩ ፊልም እውነታዎች በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር የተቀረፀ - በCanon 5D እና 7D የተቀረፀ- በከፍተኛ በጀት የተዘጋጀ፣ 7 ወራትን የፈጀ - በየጊዜው መረጃዎችን በጋዜጣዊ መግለጫ ያበሰረ - ለቀለም እርማት ሥራ ወደ ለንደን የተጓዘ - ከተመረቀ ጀምሮ ሳምንቱን ሙሉ በ21 እይታ የታየ- ተመልካቾችንና ባለሙያዎችን ያስማማ ምርጥ ፊልም - አማላዩ-

በእምቢልታ ሲኒማ፣ በኤድና ሞል፣ በአለም ሲኒማ፣

በዩፍታሄ ሲኒማ፣ በፓናሮሚክ ሳምንቱን ሁሉ ይገኛል

‹‹አማላዩ›› ከካም ግሎባል ፒክቸርስ አማላዩ ሮማንቲክ ኮሜዲ

ስለ ‹‹አማላዩ›› ፊልም ተመልካቾች ምን ይላሉ

አለም ሲኒማ ሰኞ ምሽት በ2፡30 ማክሰኞ 8፡00ረቡዕ 12፡30አርብ 10፡00

ዮፍታሔ እሁድ 12 ሰዓት እሮብ 10 እና 12 ሰዓት

እምቢልታ ሲኒማ ማክሰኞ ማታ 2 ሰዓትሀሙስ 12 ሰዓት ቅዳሜ 8 ሰዓት እሁድ 10 ሰዓት

ኤድናሞል ሰኞ 12 ሰዓት

አጎና ቅዳሜ 8 ሰዓት እሮብ 8 ሰዓት

ታዲያ የሃያላንን ጭራ መከተልና ሎሌነት ማደር ያልሰለቻቸው የቀንዱ ገዢዎች ከአሜሪካ ጋር መክነፉን ተያይዘውታል - እሷንም የሚያስረሳ እስኪያገኙ።

የሃያላኑ ጥቅምና ፍላጎት በቀንዱአንድ የኦሮምኛ ተረት አለ፡- ‹‹ዮካን ጋራ ተኢ፣

ዮካን ጋራ ኢርከዱ››፤ ‹‹ወይ ተራራ ሁን ወይ ተራራውን ተደገፍ›› እንደማለት ነው ትርጉሙ፡፡ በዚህ አካባቢ ላይ ዋነኛ ኮከብ ተዋናይ ሆና እስካሁን የቀጠለችው አሜሪካ የደህንነት እና የኢኮኖሚ ጥቅሞቿን በበላይነት ለማስጠበቅ የማትፈነቅለው ድንጋይ የለም። ከመስከረም 11ዱ የሽብር ጥቃት በኋላ ባወጀችው ‹‹የፀረ ሽብር ዘመቻ›› አማካይነት የብሔራዊ ጥቅም ማስከበር ስራውን ከወታደራዊ እርምጃ ጋር አጣምራ እየገፋችበት ነው። ለዚህም ገና ሳትጠራቸው አቤት ያሉ ብዙ የአካባቢው አጋር መሪዎች አሏት። ኢትዮጵያ ዋናዋ ስትሆን ሚጢጢዋ ጅቡቲም 1700 የአሜሪካ ወታደሮችን በወታደራዊ ጣቢያ በማስጠለል ተከታይዋ ናት። በአፍሪካ ላይ አፍሪኮም የተባለ ወታደራዊ ጣቢያ ለማቋቋም ለያዘችው ዕቅድ የሚረዳ የመጀመሪያው እርምጃ ሳይሆን አይቀርም። የሶማልያ ባህር ጠረፍ የባህር ላይ ውንብድና መባባስ ደግሞ አሜሪካ በምስራቅ አፍሪካ ልትዘረጋው ላሰበችው ወጥመድ መልካም አጋጣሚ ፈጥሮላታል። ከዚሁም ጋር ተያይዞ በቀጠናው ላይ የእስራኤል አስተማማኝ የልብ ወዳጅ ሆና የአካባቢውን አክራሪ- እስላሚዊ ፀረ እስራኤል ኃይል በቅርብ ርቀት በአይነ ቁራኛ የሚጠብቅ የታመነ አጋር ለማኖር እንደምትፈልግ የብዙዎች ጥርጣሬ ነው። እነዚህ ሁሉ እንግዲህ የደህንነት እና የበላይነት ፍላጎቶችዋ ማስፈፀሚያ ሲሆኑ ለኢኮኖሚና ንግድ ጥቅሞቿ ደግሞ እጅግም እንዳትደክም የሚረዷት በተለምዶ ‹የዋሽንግተን መግባባት› (The Washington consensus) በመባል የሚታወቁትን መርህዎች የሚያስፈፅሙ እንደ የዓለም ባንክ እና ዓለም ዓቀፉ የገንዘብ ተቋም የመሳሰሉ አሉላት። በዚህም የማይቋረጥ የግብርና ውጤቶች እና ማዕድናት መዳረሻ ሆና መቀጠል ትችላለች። በምላሹም የሰብዓዊና የልማት እርጥባን እየሰጠች የማይገፋ ነገር ግን የሚደገፉበት ታላቅ ተራራ የመሆን ዕቅዷን አጠናክራለች። ግን ይሄ ተራራ በቻይና ፊት ምን ይሆን? ደልዳላ ሜዳ የመሆንስ ዕድል አለው?በእስያ የማትነቃነቅ ግዙፍ ኃይል ሆና

የወጣችው ቻይና በበኩሏ ወደ አፍሪካ ቀንድ ጎራ እንድትል ያደረጋት ጉዳይ ደግሞ የሃይል እና ማዕድን ፍላጎቶችዋ በከፍተኛ መጠን መጨመር ነው። ከጠቅላላው የነዳጅ ዘይት ፍላጎቶቿ 25 በመቶው (25%) የሚሸፈኑት ከአፍሪካ በምታስገባው ነዳጅ ነው። ታዲያ ይሄን ወሳኝ ምርት ለማግኘት ቻይና የምትጠቀመው ስልት ከምዕራባውያን አገራት የተለየና ብዙ ቅድመ ሁኔታዎችን ያልደረደረ የተሻለና አዋጪ መንገድ ነው። ከግዙፍ የመሠረተ-ልማት ግንባታዎች እስከ ጨርቃ ጨርቅ ንግድ ድረስ ቻይና የምስራቅ አፍሪካ ደንበኞቿን በተመጣጣኝ ዋጋ የምታገለግል ወዳጅ አገር ለመሆን በቅታለች። ከዚህም በላይ በአነስተኛ ወለድ በማበደር፣ ሲላትም ዕዳን በመሰረዝ፣ በክፉ ቀንም የጦር መሳሪያ ሽያጭ በማቅረብ የአፍሪካን መሪዎች በአዲስ ፍቅር ጠምዳ ይዛቸዋለች። በዚህም አሜሪካ ክፉኛ ቂም ይዛባታለች።ህንድም ብትሆን ሌላኛዋ የቻይና አቻ እና

ተፎካካሪ ሆና በአፍሪካ ቀንድ ላይ እየተረባረበች ነው። ባብዛኛው በሰፋፊ እርሻ እና የንግድ ጉዳዮች ላይ በሰፊው እየተሳተፈች ነው። በቅርቡም ያደረገችው የህንድ-አፍሪካ ስብሰባ ከቻይና - አፍሪካ ጉባዔ በመከተል የአፍሪካን ወሳኝነት ካጎሉ ጉዳዮች ሁለተኛው ነው።

የአካባቢው ኃያላንበዚህ ክልል ተገዳዳሪ አቅም ይዘው የበላይነቱን

ለመቆናጠጥ እና የማይገሰስ ስልጣን ለማፅናት የሚራኮቱት ደግሞ ኢትዮጵያና ኤርትራ እንደሆኑ የሚገልጹት ጥቂት አይባሉም። አሁን አሁን ሱዳንም ሰልፍዋን አስተካክላ ከአሜሪካ ጋር ባደረገችው ይቅር- ለእግዜር አማካይነት የዓለም-ዓቀፍ የፖለቲካና የዲፕሎማሲ ተፅዕኖውን በማለዘብ በአዲስ መልክ ወደ ክልላዊ የበላይነት ፉክክር። ኢትዮጵያ ባላት የነፃነት ታሪክና የዲፕሎማቲክ ልዕልና የተነሳ በክልሉ ጉዳዮች የመሪነት ሚናውን እንደያዘች ይታሰባል። ከአሜሪካ እና ከቻይና

ጋር ያላት ያልተጣረሰ እና ጥንቃቄ የተሞላበት ግንኙነት፣ የጠ/ሚኒስትሯ የዓለም-አቀፍ ንድፈ-ሃሳባዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ብልጠታዊ ግንዛቤ፣ የአፍሪካን የተባበረ አንድ ድምፅ በማሰማት ረገድ ያላቸው የማስተባበርና የመምራት ችሎታ፣ ‹በሰላም ማስከበር› እንቅስቃሴ፣ እና ‹በፀረ ሽብር ዘመቻው› ታማኝ አጋርነት የተነሳ ኢትዮጵያ ከቀጠናው አገራት ጎላ ብላ እንድትታይ አድርጓታል። ከአካባቢው አገራት አብዛኛው ህዝብ የእስልምና

ኃይማኖት ተከታይነት እና ፀረ አሜሪካ ስሜት (anti-American Sentiment) አንፃር ሲታሰብ ደግሞ ሱዳንና ኤርትራ ተጨባጭ ኃያላን ባይሆኑም እምቅ (potential) ኃያላን መሆናቸው ግን መረሳት የለበትም። የሃይማኖታዊ ርዕዮተ-ዓለም ጥንካሬ ያላቸው ብዙ ህዝባዊ (popular) የኃይል አሰላለፎችን በውስጣቸው ይዘዋልና። ለዚህም እንደአስረጅ እና መከራከሪያ ነጥብ በቅርቡ እየተካሄደ ያለውን የሰሜን አፍሪካና የመካለኛው ምስራቅ አብዮትን በእማኝነት ይጠቅሳሉ። እነዚህ የክልሉ አገራት ባላቸው የታሪክና የፖለቲካ ጠባሳ ምክንያት ግን በርስ በርስ የማዳከምና የመጠፋፋት ፖለቲካ ተጠልፈው ወደባሰ አዘቅት እንዳይወድቁም የሚሰጉላቸው ብዙ ናቸው። ያም ሆነ ይህ ይሄንን ፍርድ ታሪክ እና ዘመን ስለሚያሳየን አሁን ብዙ አለማለቱ ይመረጣል። እንደውም አሁን በኃያላኑ የተያዘው የጠ/ሚ/ር

መለስ አስተዳደርን የማስደሰት (Appeasement) ፖሊሲ ያዩ ኢትዮጵያ ከሃያል የአካባቢው ተፅዕኖ ፈጣሪነትም አልፋ ወደማይናቅ አህጉራዊ ሃይልነት እየተንደረደረች መሆኗን ይገልፃሉ። ለዚህም እንደማሳያ የቪኦኤውን እቀባ፣ መጠኑ እየጨመረ የሚሄደውን እርዳታ፣ እና በዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ አፍሪካን እንድትወክል የሚደረገውን የማግባባት ስራ በአስረጂነት ያቀርባሉ።

የአካባቢው ሃያላን እና የዓለም ሃያላን ገመድ ጉተታ

ይህም ቢሆን ግን አሜሪካ እንደሁልጊዜው ሁሉ የሃይል ሚዛኑን አመዛዝና ድጋፍ መስጠቷን እንደማትተው እና የለውጥ ፈላጊነት በህዝቡ ዘንድ ከጎለበተ ግን ድጋፍ ለመስጠት ወደኋላ እንደማትል የግብፁን ክስተት በማስታወስ ይገልፃሉ። ከዚህም በላይ በቅርቡ ሂላሪ ክሊንተን በአፍሪካ ህብረት ስብሰባ ላይ ተገኝተው የተናገሩትን ንግግር ሰምና ወርቅ ላስተዋለ ቅኔው ብዙም ምስጢር እንደማይሆን ያትታሉ። ነገር ግን ይህም ከመሆኑ በፊት ‹‹ኢትዮጵያ ፊቷን ወደ ምስራቅ (ቻይና) በማዞር እጆቿን ወደ ምዕራብ (አሜሪካ) መዘርጋቱን አለማቆሟ የመንግስቷን ጥንቁቅ አካሄድ አስረጅ ነው›› ሲሉ ተንታኞች ያስጠነቅቃሉ። ድንገት ያላየችው እንቅፋት ሳይታሰብ

ካልጣላትም ወደምስራቅ እያዩ ወደምዕራብ ደጅ መጥናት ጥሩ ስልት መሆኑን ያነሳሉ። እስካሁን እንደታየው በምስራቅ አፍሪካ ላይ ዋነኛው የዓለም አቀፍ ኃያላን እና የአካባቢው ኃይለኞች መፋለሚያ ሜዳ ሆኖ የገነነው ራሱን በተለያዩ የጎሳ እና የኃይማኖት ክንፎች አክራሪ አሰላለፍ ወደውስብስብ ወጥመድ እየከተተ የሚገኘው የሶማሊያ አካባቢ ነው። የበላይነት ኃይሉም በአሜሪካ በሚደገፈው የጠ/ሚኒስትር መለስ አስተዳደር እና በኤርትራ በሚጋለበው የእስላማዊ ፍ/ቤቶች አንድነት (UIC) - በፊት አሁን አልሸባብ በሚባለው ይዋዥቃል። ለማንኛውም በዚህ ግንባር ያሉ የትኛውም ጎራ አስተማማኝ የበላይነት እና አሸናፊነት ያላገኙበት

ሁኔታ ይስተዋላል። ይበልጡን ትኩረት ሳቢ እና አጓጊ የሆነው

አዲሱ የፍልሚያ ግንባር ደግሞ ደቡብ ሱዳን ይመስላል።የመጀመያው በሰሜኑ እና ደቡብ ሱዳን መካከል ያለው የአቢዬን ግዛት የተመለከተው ፍጥጫ ነው። ይህንንም ተከትሎ ወደ 4200 ‹‹የሰላም አስከባሪ›› ኃይል ኢትዮጵያ ማሰማራቷ ይታወሳል። በራሱ በደቡቡ ግዛት ውስጥ ደግሞ የጎሳ እና ሥልጣን ጥማት ሽኩቻዎች በምን መልኩ እንደሚቀጥሉ አልታወቀም። ከዚህ ሁሉ በላይ ግን የአሜሪካ እና ቻይና ፍጥጫ በደቡብ ሱዳን የሚጓዝበት ጠመዝማዛማ መንገድ ከወዲሁ የብዙዎችን ቀልብ ስቧል።

በአፍሪካ ቀንድ ውስጥ ባሉ ውስጣዊ ሁነቶች ግን ኢትዮጵያ በሶማልያ በኩል የሚመጣባትን የኦጋዴን ነፃነት ጥያቄንና የኤርትራን ተዘዋዋሪ ጥቃት ለመመከት ከአሜሪካ ምዕራባውያን ጋር ስታብር፤ በልማቱና ዕድገቱ ግንባር ግን ከቻይና፣ ህንድ፣ ቱርክና ብራዚል ጋር ጐን ለጐን መሰለፉን መርጣለች። በዚህም አሁን እየተከሰተ ያለው የዓለም ኢኮኖሚ መናጋት፣ የዋጋ ግሽበትና የኑሮ መወደድ ብሎም ርሃብ መንስኤ የኒዎ ሊበራል ፍልስፍና ውስጣዊ ተቃርኖ (Internal contradiction) የፈጠረውና ራሱን በገበያ ጉድለት (Market failure) አማካኝነት የሚገልፅ ሁኔታ መሆኑን ለማስረዳት ከልቧ ትጥራለች። በመፍትሄነትም የደቡብ ኮሪያንና የታይዋንን የልማታዊ መንግስት ዘይቤ እንደአማራጭ ወስዳ እየተንቀሳቀሰች ነው። አሁን የሚታየው የልማት ችግር እና ድህነት በዋናነት የኒዎ ሊበራል አለመስራት የፈጠረው ቀውስ ነው ስትልም ትደመጣለች። ለምሳሌም፡- ‹‹ለእያንዳንዱ በዕርዳታ ለተሰጠ 1 ዶላር፣ አፍሪካ በኢ-ፍትሃዊ የንግድ ገደቦች ሳቢያ በአፀፋው 2 ዶላር እንደምትከስር›› የOxfam የጥናት ውጤትን ጠቅሰው የሚያስረዱ የኢህአዴግ ልማታዊ ምሁራን ቁጥር ቀላል አይደለም። ይህ እውነት እንዳለ ሆኖ ‹‹የአፍሪካ ችግር በዋናነት የውስጣዊ አምባገነን ሥርዓት ችግር ነው፤ አሁን ለምናየውም ሁለንተናዊ ቀውስ መፍትሄው ዴሞክራሲ እና መልካም አስተዳደር ነው›› ሲሉ የሚደመጡ ተንታኞች ቁጥርም ቀላል አይደለም።በዚያም አለ በዚህ፣ በረሃብም ሆነ በጦርነት፣

በኒዎ ሊበራልም ሆነ በልማታዊ መንግስት አማራጭ፡- ተጨባጬ እውነታ በአፍሪካ ቀንድ ላይ ህዝቦች እየሞቱና እየተጋደሉ የመሆኑ ጥሬ ሀቅ ነው። ከብዙ ሐተታና ዲስኩርም ይልቅ ህዝቦች ተግባራዊና አፋጣኝ ምላሽ በመጠየቅ ላይ ናቸው። የአካባቢውና የዓለም አቀፍ ሃያላን ተባብረው ቢያንስ ቢያንስ ህዝቦች እንዳይራቡ (ላልቶ የሚነበብ) እና በሰንካላ ምክንያት እንዳይሞቱ ለማድረግ መረባረብ ይገባቸዋል። ጥቅሞቻቸው እና ሥርዓቶቻቸው በዘላቂነት የሚፀኑት ህዝቦች እስካልራባቸው እና ተስፋ እስከታያቸው ድረስ ብቻ ነውና። አለበለዚያ ግን …

የደህንነት እና የበላይነት ፍላጎቶችዋ ማስፈፀሚያ ሲሆኑ ለኢኮኖሚና ንግድ ጥቅሞቿ ደግሞ እጅግም እንዳትደክም የሚረዷት በተለምዶ ‹የዋሽንግተን መግባባት› (The Washington consensus) በመባል የሚታወቁትን መርህዎች የሚያስፈፅሙ እንደ የዓለም

ባንክ እና ዓለም ዓቀፉ የገንዘብ ተቋም የመሳሰሉ አሉላት። በዚህም የማይቋረጥ የግብርና ውጤቶች እና ማዕድናት መዳረሻ ሆና መቀጠል ትችላለች። በምላሹም የሰብዓዊና የልማት እርጥባን እየሰጠች የማይገፋ ነገር ግን የሚደገፉበት ታላቅ ተራራ የመሆን ዕቅዷን

አጠናክራለች። ግን ይሄ ተራራ በቻይና ፊት ምን ይሆን? ደልዳላ ሜዳ የመሆንስ ዕድል አለው?

Page 6: Awramba Times Issue 179

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 179 ቅዳሜ ሐምሌ 30/ 20036 የፖ ለቲካ ፈ ላ ስፎችበግዛው ለገሠ

ኢያን አዳምስ እና አር. ደብሊው. ዴይሰን በጋራ ባሰናዱት “FIFTY MAJOR POLITICAL THINKERS” መፅሐፋቸው

ከቀደምት አንስቶ እስከ ቅርብ ጊዜ ካሉት ውስጥ አምሳ የፖለቲካ ፈላስፎችን በመምረጥ ለዓለም አስረክበው ያለፏቸውን

ፖለቲካዊ እሳቤዎች በዝርዝር አዋቅረው አቅርበዋቸዋል፡፡ እኛም ለአንባቢ በሚያመች መልኩ እንዲህ አቅርበናቸዋል፡፡

ይሁንና ግን ችግሩ ጥቅላዊ ድምዳሜ ላይ በመድረሳችን ስህተት ልንሰራ መቻላችን እንዳልሆነ መገንዘብ ያስፈልጋል፤ ይልቁንም እራሱ የጥቅላዊ ድምዳሜ ሂደት ነው እኛ ስለድምዳሜው ካለን እምነት ውጪ ዋስትና የሌለው። እስከዛሬ ድረስ የደረስንባቸው እጅግ ወሳኝ ድምዳሜዎች ሁሌም ቢሆን ጥሩ ነበሩ በማለትም የጥቅላዊ ድምዳሜን ችግር መፍታት የሚያስኬድ አይሆንም።

ታዲያ ሳይንስ ብዙ ሰዎች ነው ብለው በሚያስቡት መንገድ እንዴት ‹እውነት› ሊሆን ይችላል? ፖፐር ይንን ጥያቄ ኢንደክሽን ትክክለኛው የሳይንሳዊ መመዘኛ ዘዴ መሆኑን ባለመቀበል ለመመለስ ይሞክራል። ሳይንስ ‹‹ሕጎችን›› አያመነጭም፤ ‹‹ሕጎች›› ሲባል አውንታዊ፣ አሳማኝ እና ሁል-አቀፍ ማረጋገጫዎች ማለት ከሆነ። የቬና ክበብ ምንም ቢያስብ፣ የትኛውንም ነገር ‹‹ማረጋገጥ›› አንችልም። ምክንያቱም አሁን ስለምናምነው ነገር ያለ ማረጋገጫ እምነቶቻችን ለወደፊትም እውነት ሆነው እንደሚቀጥሉ ማሳየት አይችልም። ነገር ግን ውሸት ስለመሆኑ ማሳየት እንችላለን። አንዲት የተቃርኖ ምሳሌ እንኳን የአንድን ጥቅላዊ ድምዳሜ ውሸትነት ታሳያለች፤ ወይም ማሻሻያ እንደሚያስፈልገው ትጠቁማለች። ስለዚህም ሳይንሳዊ ምርምር ጥቅላዊ ድምዳሜዎችን የሚደግፉ ማስረጃዎችን የመሰብሰብ

ነፃ ህብረተሰብ ምን ዓይነት ነው?ሰር ካርል ፖፐር /1902-94/

ሂደት አይደለም። ‹‹የመገመት እና ውድቅ የማድረግ›› ተግባር ነው፡- ማስረጃ ላይ የተመረኮዘ ምናብን በመጠቀም መላምቶችን መቀመርና ከዚያ እነሱን ውሸት የማድረግ ተግባር መፈፀም ወይም ማሻሻል።

ሁሉም ሳይንሳዊ እምነቶች ጊዜያዊ ናቸው። እንደእምነት እንድንይዛቸው ብቸኛው ምክንያታችን ማንም ሰው እነሱን ውሸት የማድረግ ምርምር እስካሁን ባለማድረጉ ስለሆነ ጊዜያዊ ናቸው። እንዲህ ያለው ምርመራ ወይም እይታ ከተደረገ መላምቱ ሊቀረ፣ አልያም ቢያንስ ሊከለስ ግድ ነው። ክለሳ ከተደረገበት ደግሞ ሌላ የተቃርኖ ምሳሌ መጥቶ እስኪያስቀረው ወይም የበለጠ ክለሳ እስኪያደረግበት ጊዜ ድረስ እንደእምነት እንይዘዋለን። እነሱ ያቀረቡትን ቀመር የሚቃረን ማንኛውንም ማስረጃ ለመቀበል በር ባለመክፈታቸው ምክንያት በቀላሉ ውሸት የማይደረጉ እንድ ፍሩዲያን ሳይኮሎጂ ወይም የማርክሲስት ማህበራዊ ሳይንስ ዓይነት ምሁራዊ አወቃቀሮችን ነው ፖፐር ‹‹ዚዩዶ-ሳይንስስ›› በማለት የሚጠራቸው።

የፖፐር የፖለቲካ እሳቤ ውሸትነትን ከማሳየት (falsifiability) ጭብጠ ግንዛቤው የፈለቀ ነው። የእርሱ የፖለቲካ እሳቤዎች በሁለት መፅሐፎቹ ዳብረው የታዩ ናቸው፡- በ1945 ‹‹The Open Society and Its Enemies›› እና በ1957 ‹‹The Poverty of Historicism››። ሁለቱም በጥልቅ ተመስጦ የተፃፉ ናቸው። ፖፐር በማንኛውም እሴተ-ነፃ በሆነ የፖለቲካ ፅንሰ-ሀሳብ ዓይነት ላይ ማተኮሩን አይገልፅም፤ እንዲሁም የተማረው መደበኛ ሰው በሚረዳው መንገድ ነው የሚፅፈው። ‹‹Historicism›› ወይም ‹‹ታሪካዊነት›› ሲል የታሪካዊ እድገት ‹‹ሕጎችን›› ማግኘት (ማወቅ) እና እነዚህ ሕጎች ይጠቁማሉ ተብሎ በሚተሰበው የመጪው ጊዜ እውቀት ላይ መሠረት በማድረግ መጠነ ሰፊ የማህበራዊ እና የፖለቲካዊ እቅድ ማዘጋጀት ይቻላል የሚል እምነት ማለቱ ነው። የእንደዚህ ዓይነት እቅዶች ተፈፃሚነት ቡድናዊ (Holistic) ወይም አብዮታዊ ወይም ዩቶፒያን የህብረተሰብ አወቃቀር ይባላል። ነገር ግን ከልላይ የሆኑ የታሪክ ‹‹ሕጎች›› አሉ የሚለው እምነት የተሳሳተ ነው። መጪው ዘመን ምን እንደሚመስል ማወቅ አንችልም። ወደፊት ምን ዓይነት ግኝቶች እንደሚመጡና በታሪክ ሂደት ላይ ምን ዓይነት ተፅዕኖ እንደሚኖራቸው አናውቅም። መጪውን ጊዜ መተንበይ በራሱ ሰዎች ሊሆን ይችላል ከተባለው በተቃራኒ ባህሪያቸውን እንዲለውጡ በማድረግ በመጪው ጊዜ ላይ ተፅዕኖ ሊያሳድር ይችላል። ስለዚህም አስቀድሞ በተቀመጠ የወደፊት ዘመን ራዕይ ላይ መሠረት ያደረገ ማንኛውም የረጅም ጊዜ ፖሊሲ ያልታቀዱ እና ያልተገመቱ ውጤቶችን ሊያስከትል ይችላል። ማህበራዊ ሕጎች የሚመስሉት ሁሉ ግፋ ቢል አቅጣጫዎች ናቸው፤ እናም አቅጣጫዎች ላይ መሠረት ያደረገ አስተማማኝ ትንበያ ሊሰጥ አይችልም። ይህ የታሪካዊነት (Historicism) ሂስ ታሪካዊነት አናሳዎች ከሁሉም

ካርል ሬመንድ ፖፐር ከአይሁድ ቤተሰብ በቬና ነው የተወለደው። አባቱ የተሳካለት ጠበቃ ነበር፤ ነገር ግን

በመጀመሪያው የዓለም ጦርነት እና ተከትለው በነበሩ ክስተቶች ሳቢያ የቤተሰቡ ህይወት ተናጋ። ፖፐር በአስራ ስድስት ዓመቱ ትምህርቱን አቋርጦ የጉልበት ሥራ መስራት ጀመረ፤ በእንጨት ሥራ ውስጥም በተለማማጅነት ሰርቷል። በወጣትነት ዘመኑ ለኮሚኒዝም የነበረው ትኩረት የወቅቱን የኮሚኒስት አቀንቃኞች አመፅአዊ እንቅስቃሴ በታዘበ ጊዜ ሊገታ ችሏል። በኋላም በ1928 ቬና ዩኒቨርስቲ ገብቶ ፒኤች.ዲውን አግኝቷል። በ1930 ትዳር መስርቶም በመምህርነት መስራት ጀመረ። እየጨመረ የመጣውን ብጥብጥ እና የፀረ-ሴሚቲዝም እንቅስቃሴ የተመለከቱት ፖፐር እና ባለቤቱ በ1937፣ ልክ ጀርመን ኦስትሪያን ከመውረሯ አስቀድሞ ቬናን ጥለው ተሰደዱ። ከ1937-1945 ድረስ ፖፐር በኒው ዚላንድ ካንተርቡሪ ዩኒቨርስቲ ፍልስፍና ሲያስተምር ቆይቷል። ከዚያም ለቀጣይ ሶስት ዓመታት ትኩረቱን በንባብ ላይ ያደረገ ሲሆን ከ1948-69 በለንደን የኢኮኖሚክስ ትምህርት ቤት በፕፎፌሰርነት አስተምሯል። በ1945 እንግሊዛዊ ዜግነት የተሰጠው ካርል ፖፐር ‹‹ሰር›› የሚለውን ማዕረግ ያገኘው በ1965 ነበር። ቶሎ የመቆጣትና ተነጫናጭ ባህሪይ ይኑረው እንጂ በሥራ ባልደረቦቹና በተማሪዎቹ እጅጉን የተወደደ ነበር።

ፖፐር በትምህርት ቤት ሳለ እና ከዚያም በኋላ ከሩዶልፍ ካርናፕ፣ ሞርቴዝ ሽሊክ፣ ኩርት ጎዴል እና ከሌሎች የቬና ክበብ በመባል ከሚታወቀው የፓዘቲቪስት ፈላስፎች ቡድን አባላት ጋር መገናኘት ችሎ ነበር። ከነዚህ ፈላስፎች ጋር የነበረው ግንኙነት ኢማኑኤል ካንትን ከማንበቡ ጋር ተደምሮ ፖፐር ለሳይንስ ፍልስፍና የነበረውን የህይወት ዘመን ፍላጎት እንዲያሳድር አድርጎታል። በተለይ በሁለት ጥያቄዎች ላይ ያተኩራል፡- (1) ሳይንስ እንደ ሜታፊዚክስ፣ ሎጂክ፣ ማቲማቲክስ እና ፖፐር ‹‹ዚዩዶ-ሳይንስ›› በማለት ከሚጠራው ዘርፎች ድንበር የሚበጅለት እንዴት ነው፤ እንዲሁም (2) የትኛውንም ሳይንሳዊ ፅንሰ-ሀሳብ እውነት ነው ብለን ለማስቀመጥ ምን ምክንያት አለን? በ1934 ‹‹Logik der Forschung›› በተሰኘ መፅሐፍ እሳቤዎቹን አሳትሟል፤ በ1959 ‹‹The Logic of Scientific Discovery›› ተብሎ ተተርጉሟል። መፅሐፉ ሲታተም የፖፐር ጓደኞች ለአርበርት አንስታይን ቅጂውን ልከውለት የነበረ ሲሆን፣ እርሱም መልካም አስተያየቱን ሰጥቶበታል። (የአንስታይን አስተያየቶች ‹‹The Logic of Scientific Discovery›› መፅሐፉ በስተጀርባ ተያይዘው ታትመዋል።)

የፖፐር የሳይንስ ፍልስፍና ብዙውን ጊዜ ‹‹falsificationism›› ተብሉ ይጠራል። ይህንንም ለመገንዘብ ቀላሉ መንገድ ከረጅም ጊዜ በፊት በዴቪድ ሂዩም የተጠቀሰውን የኢንደክሽን (induction) ወይም ከተወሰኑ እውነታዎች በመነሳት ጥቅላዊ ድምዳሜ የመስጠት

‹ችግር› ላይ ትኩረት ማድረግ ነው። ሳይንስ ብዙ ነገሮችን በመመልከት ጥቅላዊ ድምዳሜዎችን የመቀመር ተግባር ነው። ይህ የመመልከት እና የጥቅላዊ ድምዳሜ ተግባር (በቀላሉ ስናስቀምጠው) ኢንደክሽን ማለታችን ነው። ብዙ ቁጥር ያላቸውን ያለፈ ጊዜ ሁነቶች ምልከታን ወይም እይታን መሠረት ያደረገ ድምዳሜን ወደፊት ምን እንደሚከሰት ለመተንበይ እንደሚያግዘን ‹‹ሕግ›› አድርገን እንቀበለዋለን። ስለዚህም በኢንደክሽን ሂደት ተፈጥሮ ወጥነት አለው (uniform) የሚል መላምታዊ ቅድመ ግምት ይቀመጣል፤ ይኸውም መጪው ጊዜ ካለፈው ጊዜ ጋር ተመሳሳይነት ይኖረዋል፣ እንዲያውም የግድ ይመሳሰላል የሚል። የኢንደክሽን ‹‹ችግር›› ይህ ቅድመ ግምት ዋስትና የሌለው በመሆኑ ላይ የተመረኮዘ ነው። ከዚህ ቀደም ፀሐይ የቱንም ያህል ጊዜ ብትወጣ ነገም በድጋሚ ስለመውጣቷ ልናውቅ አንችልም።

በ ር ት ራ ን ድ ራሴል ‹‹The Problems of Philosophy›› በተሰኘች አነስተኛ መፅሐፉ ስለዶሮዋ እና ስለአርቢዋ በማንሳት ጉዳዩን ያብራራዋል። ዶሮዋ ሁልጊዜ ጠዋት ጠዋት በአርቢዋ ጥሬ ይሰጣት ነበር፤ ለእርድ እስከበቃችበት ቀን ድረስ። ሁልጊዜ ጥሬ ይሰጠኛል የሚለው የዶሮዋ የኢንደክሽን እምነት በመጨረሻ ስህተት ሆኖ ተገኘ።

የበለጠ እውቀታቸውን ተጠቅመው በሌሎች ላይ የራሳቸውን ፈቃድ እንዲጭኑ ስለሚያስችላቸው ታሪካዊነት የጨቋኝ ሥርዓት አንድ አካል ነው ከሚለው እምነት የታገዘና በይበልጥም በዚሁ እምነት አማካኝነት የተነሳ ነው። ‹‹The Poverty of Historicism›› መፅሐፉ መተሰቢያነቱ የፋሺስት እና የኮሚኒስት እምነት ተጎጂ ለሆኑ በሁሉመ ዓይነት እምነት ወይም ሀገራት ወይም የዘር ግንድ ለሚገኙ አያሌ ወንዶች እና ሴቶች›› ነው።

ከ ማ ይ ታ ወ ቅ ና ስለዚህም ከማይገመት የመጪው ጊዜ ተፈጥሮ አንፃር ማህበራዊ ለውጥ - ‹ማህበራዊ አወቃቀር› - ጅምላ በሆነ መንገድ ሳይሆን ቀስ በቀስ እና ጊዜ እየጠበቀ ሊሆን ይገባል። በዚህ ሁኔታም የለውጥ ውጤቶች ክትትል ሊደረግባቸውና ያልተገመቱ እና የማይፈለጉ ውጤቶችም እራሳቸውን መግለጥ በጀመሩበት ጊዜ መፍትሔ ሊሰጥበቸው ይችላል። ሆኖም ይህንን የክትትል እና የቁጥጥር ሂደት ተግባራዊ የማድረጉ ሂደት በነዚያ ለውጦቹ ተፅዕና ባሳደሩባቸው ወገኖች የሚሰነዘረውን ትችት እና ሂስ በማድመጥ የሚፈፀም ነው። በግንዛቤ ላይ ማንም ሰው የብቸኝነት ቁጥጥር የለውም፤ እያንዳንዱ ግለሰብ የትክክለኛ ሂስ ምንጭነት አቅም አለው።

ስለዚህም ለዘላቂ መልካም አስተዳደር ሁለት ቅድመ ሁኔተዎች አሉ። የመጀመሪያው፣ ሕዝቦች ትችቶቻቸውን ውጤታማ በሆነ መንገድ የመግለፅ እድል ሊኖራቸው ይገባል። ሁለተኛው፣ እነሱን የሚጎዳ ድርጊት የፈፀመን መንግስት ሰላማዊ በሆነ መንገድ የመለወጥ እድል ሊኖራቸው ይገባል። እነዚህ እድሎች የተመቻቹለት ህብረተሰብን ነው ፖፐር ነፃ ወይም ግልፅ ህብርተሰብ (open society) በማለት የሚጠራው ህብረተሰብ በአንድ ልሂቅ እውቀት አማካኝነት በሚወጡ ማዕከላዊ እቅዶች መተዳደር ይችላል የሚሉትን ወገኖች ፖፐር ‹‹የነፃ ህብረተሰብ ጠላቶች›› ይላቸዋል። በተለይ ፕሌቶ፣ ሄግል (በሄግል ላይ ቅዋሜው ገደብ የለውም) እናማ ማርክስ ከነዚህ ወገኖች ይመደቡ ዘንድ በሀሳቡ የያዛቸው ናቸው።

የፖፐር የፖለቲካ እሳቤ ጆን ስትዋርት ሚል በዋናነት የሚያቀነቅነውን የሊበራሊዝም ዓይነት ከኤድመንድ በርክ ጋር ተያያዥነት ያለውን ጥንቃቄ የተሞላበት የለውጥ እሳቤ ጋር የሚያጣምር ነው። የመጀመሪያ ምንጭ የሆነ የፖለቲካ ፈላስፋ አይደለም፤ እርሱም ቢሆን ነኝ አይልም። ከፍተኛ ቦታ የሚሰጠው ፍልስፍናዊ ሥራው በሳይንስ ፍልስፍና ላይ ያቀረበው ነው። የፖለቲካ ፅሁፉ ሁለቱንም የዓለም ጦርነቶች የታዘበና ይህ ተሞክሮው ለብጥብጥ እና ለአምባገነናዊ መንግስት ጥላቻ እንዲያድርበት ያደረገው ሰው ትንፈሳዎች ናቸው። የፖፐር የፖለቲካ ፈላስፋነት ስም (ዝና) ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ የአውሮፓን ትምህርታዊ ህይወት መልሶ የመገንባት ተልዕኮን ላነገቡ የምሁርን ትውልዶች እሳቤዎቹ በተጫወቱት ሚና ላይ በይበልጥ የሚመረኮዝ ነው።

በርትራንድ ራሴል ‹‹The Problems of Philosophy››

በተሰኘች አነስተኛ መፅሐፉ ስለዶሮዋ እና

ስለአርቢዋ በማንሳት ጉዳዩን ያብራራዋል። ዶሮዋ ሁልጊዜ

ጠዋት ጠዋት በአርቢዋ ጥሬ ይሰጣት ነበር፤ ለእርድ እስከበቃችበት ቀን ድረስ። ሁልጊዜ ጥሬ ይሰጠኛል

የሚለው የዶሮዋ የኢንደክሽን እምነት በመጨረሻ ስህተት

ሆኖ ተገኘ።

Page 7: Awramba Times Issue 179

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 179 ቅዳሜ ሐምሌ 30/ 2003

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

7

የ አቤቶ ወግአቤ ቶክቻው[email protected]

ምርጥ የእውነተኛ ታሪክ መጽሐፍ በገበያ ላይ በታክሎ ተሾመ /ከአውስትራሊያ /

የእውነተኛ

ታሪክ

አንድ የአማርኛ መዝገበ ቃላት ‹‹ሰሞንኛ›› የሚለውን ቃል፣ ‹‹ከዕሁድ እስከ ዕሁድ የሚያገለግል ሰው›› ሲል ይተረጉመዋል። እኔም የሰማሁትን ላሰማዎ፣ ያየሁትን ላሳይዎ፣ ትጉ ሰሞነኛ አገልጋይዎ መሆንን ወደድሁ።

ሰ ሞ ነ ኛ

በወጋየሁ ታምራት

እኔ ሰሞንኛ አገልጋያችሁ ከሰላምታ በላይ ምንም ወሳኝ ነገር እንደሌለ አውቃለሁና ግምባሬ መሬት አስኪነካ ድረስ አጎንብሼ እጅ ነስቻለሁ። ዛሬ የማጫውታችሁ ከሴት ሊግ አባሏና ከድሮው ሥርዓት ናፋቂ ወዳጃችን በሥራ ምክንያት ያለሁት ርቄ ነውና ከአዲሱ ጓደኛዬ ባሻዬ ጋር አብሬያችሁ አዘግማለሁ። አቦ! መንግስት ልጅ ይውጣለት!

ለምን ቢሉ ለማናለብኝ ባዮች የሚሆን ሕግ ያወጣላ! ግን ፍራቻ አለን … የወረቀቱ ላይ ሕግ ቆሞ መሄድ ይሳነዋል። ይህንንም ሹክ እንላለን። መንግስትም ይሰማል። እንዴት ቢሉ ትልቅ ጆሮ አለዋ! የርዕዮተ-ዓለምና ሕግ ኃብታም እየሆንን የትግበራ አቅማችን ቁልቁል የሚሄደው ለመንድን ነው? ይገርመኝ ይገርመኝና መልሶ ይገርመኛል። አሁን በዛን ሰሞን የወጣው የታክሲ የጉዞ ምድብ የሚሰራበት የማይሰራበት ይበልጣል። ልክ ነኛ! ኧረ አንዳንዴስ ቦሌ መሄድ የፈለገውን ሸጎሌ ይወስዳሉ አሉ (ልብ በሉ አሉ ነው ያልኩት)እንደው ወፋፌ አትበሉኝና ከዚህ

በፊት ለሥራ ከዋሉት ኮረንቲ ማመንጫዎች ወደ ውጪ አገርም ለመላክ እየታሰበ ነው። ታዲያ ከአዲስ አበባ እየተቆነጠረ ነውንዴ ወደዛ የሚሄደው? ግራ ገባና! እውነቴን ነው እንደሰማሁት ከሆነ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥንም ሀቀኛ ጋዜጠኛ አጥቶ ነው’ንጂ … ‹‹የሰሞኑ የመብራት ሁኔታ መግለጫ… በቦሌ ሲኤምሲ እና ገርጂ (አራት ኪሎን ጨምሮ) ብርሃናማ፤ በዳትሰን ሰፈር ቺቺኒያና ካዛንቺስ ደብዛዛማ ሲሆን በሜክሲኮ ሽሮ ሜዳና ጨው በረንዳ ኩራዛማ ይሆናሉ›› ተብሎ በግልፅ ይነገረን ነበራ!ለነገሩ የመብራቱን መጥፋት

የሚመኙም አሉ’ኮ … አሁን በዛን ሰሞን አምስት ኪሎ ካለ ካፌ ተቀምጠን ሁለት ጥንዶች ሲተሻሹ አዬን። ቀጥለው ወደጥልቅ መሳሳም አመሩ። ቀጥለው ምን

ሊያረጉ እንደሚችሉ አለማሰብ ነው የሚሻለው … ብንናገራቸው ‹‹ቅናት›› የሚል ታርጋ ይለጥፉልናል ብለን ዋስ እንዳጣ ጋዜጠኛ አንገታችንን ደፍተን ወጣን … ግን’ኮ እኛም እንደነሱ የመሆን ፍላጎታችንን በእጥፍ ስላነሳሱት በቃ! አ’ደለም … ፍላጎትን በማነሳሳት ምናምን የሚል ሕግ ሊረቀቅልን ይገባል። ሕግ ለማውጣት ደሞ መንግስታችን የካበተ ልምድ አለዋ! ... ባሻ ወልዴ ችሎት ዘራፍ የምፈራ መስሎት! ... ዘራፍ አይጥ ሙታለች ከበራፍ!ፊት ነው አሉ ድሮ ድሮ …

ጥንቸልና ጅብ ድንበር ተካላው ተጎራብተው ይኖሩ ነበር ይላል ያልተተረተው ተረት … ኋላም በጅቦች ቤት ርሃብ ነገሰ። ለዚህም ተጠያቂዎቹን ጥንቸሎችን አደረጉ። እነሱ ስራስር ስለሚበጥሱ በዚህ ሰበብ ከላይ የመጣ ቁጣ ነው ተባለና በጅቦች ቤት ርሃቡ እንዲጠፋ ጥንቸሎቹን ከምድረ-ገፅ ማጥፋት። ፍርዱም ተወሰነ። ፋራጅና ዳኛው ጉልበተኛ ራሱ በራሱ። ያለንበት ጊዜም ከተረቱ ያለተለዬ ነው። ኤፍ.ኤሞች ሳታማሀኝ ብላኝ የሚለውን የጎሳዬን ለቻዩ መንግስት ጋብዙልኝማ! … ልክ ነኛ! ያይናችን ቀለም አላምራቸው ባለ ጊዜ ሲፈልጉ ኪራይ ሰብሳቢ … ሲፈልጉ ሽብረተኛ የሚል ታርጋ እየለጠፉልን ተቸገርን’ኮ!ሰዉ ዘና ብሎ የመሰለውን ማውራት

እየፈራ’ኮ መጣ! ኧረ ጋዜጠኞቹም ቢሆኑ ስጋት ውስጣቸው ገብቷል። እንኳን ፅፈው ልትፅፉ አስባችኋል ተብለው በአዲሱ ሕግ ሳይጠየቁ ይቀራሉ? ይች ናት ዴሞክራሲ! ቀደም ሲል አሉ፤ በየዋሆቹ ዘመን ስለመንግስት መጥፎ እንዳይወራ፣ ሴራ እንዳይጠነሰስ የሚከታተሉ እንደ አሁኖቹ ደህንነቶች የሚከታተሉ ፊርማቶሪ ይባላሉ። የሚገርማችሁ በመለዮአቸው ላይ ፊርማቶሪ የሚለው ፅሁፍ ስላለ ሰው በቀላሉ ያውቃቸዋል። እነሱ ባሉበት ወሬ ደህና ሰንብቺ ነው። አንድ ጊዜ አሉ፣ ንጉሱ በቴሌቪዥን

ንግግር ሲያደረጉ አንዱ ተናዶ፣ ‘አሁን እኒህ ሰው ናቸው?’ ሲል ከኋላው ፊርማቶሪው ሰማው። ‹‹እና ምንድን ናቸው?›› ‘መላዕክ እንጂ!’ ብሎ መለሰ። ቆዩኝማ፣ ሳልረሳው። የፊርማቶሪውን ልጨምርላችሁ።አንዱ መጠጥ ቀማምሶ ወደ ቤቱ

ሲገባ፣ ‹‹ቻዩ መንግስት ሺህ ዓመት ይኑር›› እያለ ሲሄድ ፊርማቶሪው ሰማው። ያዘውና እስር ቤት ዶለው። ሰውዬው፣ ‘ጌታዬ! ምን አጠፋሁ? ሺህ ዓመት ይኑሩ’ኮ ነው ያለኩት!?’ ቢለው፣ ‘እንዴት ሺህ ዓመት ይኑሩ ትላለህ? ለዘላለም ይኑሩ አትልም!?’ ብሎ እርፍ … መቼም ጨዋታ ነው። የአሁኖቹ ፊርማቶሪዎች ተመሳስለው ነው አሉ የሚሰልሉት። ሠይጣንን መሰለል ሲፈልጉ አንዱ ሰይጣን ይሆል እንደማለት’ኮ ነው! በነሱ የተማረረ ወፈፌ ወዳጄ ለምን መፃፍ አቆምክ ብለው በግጥም ነው የመለሰልኝ። አሃ! እነሱ ግጥምና ቅኔ አያርፉም ብሎ ይሆናላ! እንዲህ ነው ያለኝ … እንግዲህ ነገሬን ከከንፈሬ

አለቅም፣ አለ የሰው ዶሮ ከአፍ ካፍ

የሚለቅም።

ወላዲቴን! ከጋዜጠኝነቱ ገጣሚነቱ ነበር የሚሻለው … በቃ አስር ጊዜ ግጥሙን እየደጋገመ በዜማ ቢጫወተው አለቀ!... ከስሙ በፊት ድምፃዊ የሚለው ማዕረግ ይገጠምለት ነበራ! … እውነቴን ነው አሁን አሁን’ኮ መዝፈንና ክፉ መናገር የሚጠፋው የለም። ለዚህ’ኮ ነው አንዱ እንዲህ የዘፈነው፡-

መገን ሰሜን ጎንደር መገን ጃን አሞራ፣ አህል ዘርቶ ላውሬ ሰው ገሎ

ላሞራ።

አያችሁ ክፋቱን? … እህል ዘርቶ ላውሬ የሚሰጥ ሰነፍ ነው፤ ሰው

ገሎ ላሞራ መስጠትም የሽፍትነት ተግባር ነው (በየሰበቡ ማሰርም)። ግጥሙን እኔ ወፈፌው እንዲህ አቃናዋለሁ፡-

መገን ሰሜን ጎንደር መገን ጃን አሞራ፣ለጠገበው ጥይት ለራበው

እንጀራ።

አያችሁልኝ? ጥጋበኛ ካለ መድኃኒት፣ የተራበ ካለም አዛኝ ነው እንደማለት ይቆጥራል። ለማንኛውም የተጣመመ ግጥም እናስተካክላለን! የተጣመመ መንግስትን ግን …ቶማስ ጀፋርሰን የሚባሉት የቀድሞ

የዩ.ኤስ አሜሪካ ፕሬዝዳንት እንዲህ ብለው ነበር፡- ‹‹መንግሥት እያለ ነፃ ፕሬስ የሌለበት አገር ከሚኖር፣ ነፃ ፕሬስ ኖሮ መንግሥት የሌለበት አገር መኖር እመርጣለሁ››። የኛዎቹን አይመለከትም። ልክ ነዋ! ኪሎ እየጨመሩ ግን … አንዱ ወዳጄ ሹክ እንዳለኝ ከሆነ ሃምሳ በመቶ የሚሆኑት ባለስልጣናት በደም ማነስ፣ ቀሪዎቹ ደግሞ በእውቀት ማነስ እየተሰቃዩ ነው አሉ … አሃ!

ግብርን በግምት የመጣል ሳይንስ ከየት መጣ!? የስኒ ቡና ሽጣ ምሳና ራቷን በበላች፣ ልማታዊ ነሽ ተብላ ቆጥራ የማታውቀውን ብር ሲጥሉባት ታማ የማታውቀው ልጅ ታመመች … ነገ ደሞ ሀገር ትታመማለች። ህመሟን የሚፈውስላት ሃኪም ግን የላትም … ኤጭ! ያሉትን ተዋቸው፤ ውሃ እንደኪኒን የሚያዝ ዶክተር ነው ያለው። (ግን ውሃ እንደኪኒን ቢታዘዝልን በምን ልንውጠው ነው?)አውደ-ምህረቱን ፈልጋ ደጀ ሰላም

የገባችውን ውሻ ቅድስና የለሽም ብለን እንዳባረርናት፣ አራት ኪሎን ተገን አርጎ የነገሰ የጨለማ ንጉስ ካለ በብርሃን ይመላለስ ዘንድ የብርሃን አምላክ ይዘዝበት! አሜን ነው የሚባለው! ልክ ነኛ! የግብር ከፋይ ሀመሩህን ያዬ፣ ነገ ደሞ ሁመርሁ፣ ሂመርሂ … እያሉ፣ ከሰው ጋር ባወራንባቸው ቃላት ግምት ያወጡልናል … የሞቅናትንም ፀሀይ ታሳቢ አርገው … (በጃንጥላ ቢሆን አንሄዳለና!) ሆሆይ! መንግስት ሆይ! “ወይ ውረድ፣ ወይ ፍረድ” ለማለት አሰብኩና ወፈፌም ብሆን መፍራቴ የት ይቀራል? ተውኩት።እኒህ የኔ ጎረቤት ባሻዬ፣ ‘እንደው

ይህን ያህል ግብር የጫኑባት እንዴት ነው?’ እያሉ ሲገረሙ፣ ‘በግምት ነው’ አላቸው አንዱ … ‘እኮ እኔ ጠርጥሬያለሁ እነኝህን ሰዎች የያዛቸው ሰይጣን አስገማቹ ነውንዴ? በዚህ አይነትኮ አገራችን በሁለት ዲጂት አደገች የሚሉትም ለካ በግምት ነው’ አሉ ተናደው። ሆሆይ! ወደው አይስቁ። የታባቴ ሁኜ ልሳቀው?ነገ ዝናብ ይጥላል ወይም አይጥልም

እንደሚለው ሜቲዎሮሎጂያችን፣ ሕግና ደንቦች አንዳንዴ ይሰራሉ፣ አንዳንዴ አይሰሩም። ስለምን ቢባል፣ አባል የሆነ ሰው ቤት ከፈለገ ያገኛል … እዚህ ላይ ሕጉ ይሰራል። አባል ያልሆነ ተነስቶ ቤት ቢፈልግ ሕጉ አይሰራም። ዘራፍ! ባሻ ወልዴ ችሎት ዘራፍ! የምፈራ መሰሎት … የአገሯ

ልጆች የሆነው እኛ ምን የማይደርስብን ግፍ አለ። ይግረማችሁና ከ20 ዓመት በላይ የተኖረበትን ቤት በአንድ ጦማር አስለቀቋቸው። እንደዛ የሚል መመሪያ ግን የለም! አቤት የሚባልበትም የለም! የለም ብቻ ያለበት አገር ነዋ!

በእንዲህ ያለ ዘመን ሲመሽ ተወልጄጅቡን ጋሽ እላለሁ ውሻውን

ወድጄ

ግጥሙ ከብሶተኛ ህሊና አፈትልኮ የወጣ ይመስላል። ‘የኢህአዴግ ፖለቲካ ይገርመኝ ይገርመኝና መልሶ ይገርመኛል’ ያለው ማ ነበር? በቃ እኔ ልሁን። የጋራችን ሁና ስታበቃ የትምህርት እድልና የስራ ላይ እድገት ላይ ግን አባልነት እንደመስፈርት ሲቀመጥ ያስተዋሉት ባሻዬ፣ ‹‹ይሄ ነገር እኛ ሳናውቅ ከሕግ መንግስቱ ላይ ዱላውት ይሆን’ዴ?›› ብለውኛል። አባል ባንሆንም አትሊስት ለተባባሪ አባልነት ዱብ ዱብ ማለት ነዋ! ልክ ነኛ! ኋላ አባል ያልሆነ የኮቴ ምናምን እያሉ እዳ እንዳንገባ እና የአሲንባን በረሃ መንገድ ከመጠየቅም ያድናል።መቸም ውሸትና ትምህርት

አያልቅም የሚሉት የአራት ኪሎዎቹ ውሸት መስፈሪያው እራሱ ካቅሜ በላይ ነው ብሏል አሉ … ባድመ ለኛ ተወሰነ፣ ባንዲራውን ጨርቅ አላልንም፣ በቀን ሶስቴ ትበላላችሁ ወዘተን አስቀምጠን እንለፈው። ይህን የታዘቡት በሻዬ ትናንት ማታ ከባለቤታቸው ጋር ሲጨቃጨቁ ሰማሁ። ባለቤታቸው ‘አትዋሽ!’ ነው የሚሉት። ባሻዬም፣ ‘እንኳን እኔ፣ መንግስትም ይዋሻል’ ብለው አረፉታ!መንግስት ለካድሬዎቹም ውሸት

ነውን’ዴ የሚያስተምረው? ሲመረቁ ደሞ እየዋሹ ይኖራሉ። ወይኔ ጉዴ! የምፅፍበት እስክርቢቶ ማቋረጡ ነው፤ ትርፍ እስክርቢቶ ያለው?

ቸር እንሰንብት!

“መንግሥታችን ፍላጎትን የማያነሳሳ ሕግ ያርቅቅልን”የኔ ጎረቤት ባሻዬ፣ ‘እንደው ይህን ያህል

ግብር የጫኑባት እንዴት ነው?’ እያሉ

ሲገረሙ፣ ‘በግምት ነው’ አላቸው አንዱ

… ‘እኮ እኔ ጠርጥሬያለሁ እነኝህን ሰዎች

የያዛቸው ሰይጣን አስገማቹ ነውንዴ? በዚህ

አይነትኮ አገራችን በሁለት ዲጂት አደገች

የሚሉትም ለካ በግምት ነው’ አሉ

Page 8: Awramba Times Issue 179

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 179 ቅዳሜ ሐምሌ 30/ 20038

ምነው ስቀላው ቤት ጉልላት ያለበት

ከዚህ ሁሉ ዕድገት ከአገር ሙሉ ልማት

አልደርስህ እያለው ቀጣና ሞላበት

/ዶ/ር ኃ/ኢየሱስ ጌታሁን/

በአንድ መጽሐፍ መግቢያ ላይ ከዚህ በታች የሰፈረውን አነበብኩ። ከአገሩ ውጭ ለሚኖር ሰው ምንጩንና አገሩን መጠያየቅ የየዕለቱ ገጠመኝ ነው። ከየት ነህ? ነሽ? ሲባል ደፍሮ ኢትዮጵያዊ ነኝ ላለ ሰው ጠያቂው መልሱን ከሰማ በኋላ ‹‹እ…ኢትዮጵያ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ እንደገና አሁንም ድርቅ ገባ ይባላል?››

ሐ ሳ ባ ቸ ው የሚሽከረከረው በአንድ ጉዳይ ዙሪያ ለመሆኑ ጠንቋይ መጠየቅ አያስፈልግም። ድህነትና ችግር፣ ስለየሀገሩ ብዙ ይወራል። ስለሀገራችን የሚወራው ደግሞ እልቅ መሳፍርት የለውም የሚፃፈውም አያሌ ነው።

የምዕራቡ ዓለም የመረጃ ምንጭ በብዙኃን መገናኛ

ግቢው የባለስልጣናት ግቢ ያህል ያስፈራል። ሁለት መሳሪያ የታጠቁ ሰዎች ግቢው ውስጥ በተጠንቀቅ

ቆመዋል። ከሁለቱ ጥበቃዎች አልፎ ወደ ቤት በመግባት፣ የቤቱን ባለቤቶች ኑሮ የሚበጠብጥ ደፋር አጥቂ ጠላት የለም።

ቤቱ የተገነባው ምድራዊ በሆነ እብነበረድ ቢሆንም፣ ግርማ ሞገሱ ግን ሰማያዊ ነው። የሳሎን ቤቱ ግብዓተ ዕቃዎች እያንዳንዳቸው ቢመነዘሩ አንዳንድ መካከለኛ ቤት መገንባታቸው አያጠራጥርም። የቤቱ ግርግዳ ወርቅ ቅብ መሆኑ ባለቤቶቹ ቤታቸውን ለመገንባት በእሳት እንደተፈተኑ ያረጋግጣል።

ቤቱ ካቀፋቸው አራት መኝታ ቤቶች አንዱ እንኳን የወረደ አቋም የለውም። የአልጋው መልክዓ መኝታ ቤታዊ አቀማመጥ ይማርካል። የንጉሳውያን ቤተሰቦችን የአልጋ ግርማ ሞገስ የተበደረ የሚመስለው አልጋ፣ ሳይተኙበት እንኳን የተጨበጨበላቸው ህልሞችን ያመላክታል።

ባለቤቶቹ ድንገት ተጣልተው ቢፈነካከቱ የመጀመሪያ እርዳታ ለማድረግ የሚቃጣው ብርድ ልብስ

ኮሜንተሪ

ሳይለብሱት ይሞቃል። ይመቻል። ቡትቶ ለብሶ ከማደር ይልቅ እሱን እያዩና እሱን ከተነጠፈበት አልጋ አጠገብ በራቁት ቢተኙ በእጅጉ ይመረጣል።

ትራሶቹም ቢሆኑ ለማጅራት ገትርና ተመሳሳይ በአንገትና አካባቢው ለሚከሰቱ በሽታዎች አሳልፈው የማይሰጡ ታማኝ እና ለስላሳ ናቸው። የቤቱና ግብዓቱ ዝርዝር ሁኔታ ተፅፎ የማያልቅና ለብዙዎች የሚተርፍ ቢሆንም፣ ባለቤቶቹ የሚኖሩት ግን ለራሳቸውና ለራሳቸው ብቻ ነው። በራቸው የሚከፈተው ሲወጡና ሲገቡ ብቻ ነው። መሶባቸውም የነሱን የምሳ፣ እራት፣ ቁርጥ፣ ሰዓት ተከትሎ ይከፈታል እንጂ ስለሌላው ግድ የለውም። …

…የሰው ልጅ ደስታ የሚያገኝበት መንገድ በፀባዩ፣ በአስተሳሰቡና በነፍሱ ስጋዊ አቀማመጥ ልክ እና መጠን ነው። አንዱ ዝሆንን በመዳሰስ ሲደሰት፣ ሌላው ደግሞ የዝሆን ጥርስ ሸጦ በሚያገኘው ገንዘብ ሊደሰት ይችላል። አንድ አባት ልጁ ሌባ ባለመሆኑ ሲደሰት፣ ሌላው ደግሞ ልጁ ሰርቆ ባመጣው ቴሌቪዠን የፖሊስ ፕሮግራም እየተመለከተ፣ ሌቦች ላይ በተፈረደው ፍርድ ሊደሰት ይችላል።

አንድ ሰው ‹ኢትዮጵያዊ› ነው የሚባለው አዲስ አበባ ላይ ወይም ሌሎች ክፍላተ ሀገሮች ላይ ስለተወለደ አይደለም። የኢትዮጵያዊነት መስፈርቱ ኢትዮጵያ ውስጥ መወለድ ብቻ ይመስላል እንጂ አይደለም። መኖር ያስፈልጋል። መኖር ሲባል ደግሞ ቤት ሰርቶ ወይም ተከራይቶ እና በር ዘግቶ አይደለም።

የህዝብን ህመም መታመም፣ መታረዙን መሸፈን፣ ቀዳዳውን መድፈን፣ ጨምዳዳውን ማቃናት… ነው መኖር ማለትና

ኢትዮጵያዊ መሆን። አንድ ሰው ለተራበ ግለሰብ እንጀራ መስጠት ባይችል እንኳን፣ የግለሰቡ መራብ ሊያስቆጨው ይገባል። ለወገን ወይም ለሀገር ልጅ መኖር ማለት የግድ እንጀራና ውሃ መስጠት ብቻ አይደለም።

ፀሐይ ያጠወለገውን ሰው የዛፍ ጥላ ስር ማሳረፍ የሌላውን ድካም መካፈል ማለት ነው። ለሀገር እና ለወገን መኖር ሲባል፣ የግድ የራስን ኑሮ እርግፍ አድርጎ መተው ማለት አይደለም።

‹ሴሌን ዲዮን ትላንት ማታ እንቅልፍ አልወሰዳትም› የሚል ዜና የሚያነቡበትን ደቂቃ፣ በሀገር ውስጥ እንቅልፍ ለሚነሱ አንገብጋቢ ጉዳዮች ማዋል ለሀገር መኖር ማለት ነው› ሌዲ ጋጋ ቡትስ ጫማ ገዛች› ከሚል ዘገባ ይልቅ፣ ‹አንዲት ኢትዮጵያዊ እግሯ ተቆረጠ› ለሚል ዜና ትኩረት ሰጥቶ ህመሟን መታመም ለወገን መኖር ማለት ነው። እንጂ ለሃገር መኖር ማለት የራስን ቤት አፍርሶ የሌላውን መገንባት አይደለም። ሰኞ ጥቃቅንና ደቃቅ የሚመስሉ ሰከንዶች ለሌላው የህይወት መቀየሪያ ወርቅ ሊሆኑ ይችላሉ።

ከቀጫጫ ኑሮ የደለበ ሞት ይሻላል። የወፍራም ወይም የተደላደለ ኑሮ ፍቺው ሰንጋ ማጋደምና የገነት አምሳል ለመሆን በሚቃጣቸው ውብ ቤቶች ውስጥ መኖር ብቻ አይደለም። ከዛ በላይ የሆነ ረቂቅና ምስጢራዊ ትርጉም አለው - የተደላደለ ኑሮ።

በርግጥ ድህነትን ማሸነፍና ራስን እንዲሁም ቤተሰብን ጠቅልሎ ለልመና አለመውጣት የሚያስከብር ተግባር ቢሆንም፣ በሰበሰቡት ጥሪት መመካትና ለሌላው መከታ አለመሆን ግን ነውር ነው። ሌላው ላይ በር እና መሶብ በመዝጋት የሚደሰቱ ሰዎች፣ ጥርሳቸው ስለሳቀላቸው

ኑሯቸው ምሉዕ ሊመስላቸው የችላል፤ ግን አይደለም።

የአንድ ሰው የምድር ኑሮ ‹ምሉዕ› የሚሆነው ለቤተሰቡ ብቻ ሲኖር ሳይሆን ለማኅበረሰቡም ጭምር ሲኖር ነው። ግለሰቡ ቤተሰቡን የሚያኖርበትን / የሚያስደስትበትን ገንዘብ የሚያገኘው ከማኅበረሰቡ በሚሰበሰበው ግብር ነው። ይህ ሰው ለማኅበረሰቡ የማይኖር ከሆነ ወይም የማኅበረሰቡን ህመም ታሞ ችግሩን ለማስወገድ የማይንቀሳቀስ ከሆነ፣ ማኅበረሰቡ ግብር መክፈል አይችልም። አሊያም ግብር የሚከፍልበትን ስራ ሊያቆም ይችላል።

ግብር ሲቋረጥ ደግሞ የግለሰቡም ደሞዝ አብሮ ይቋረጣል። የደሞዙ መቋረጥ ደግሞ ቀድሞ ደስተኛ የነበውን ቤተሰቡን ወደ ሐዘን ይወስደዋል። ስለዚህ አንድ ሰው ለማኅበረሰቡ በኖረ ቁጥር የራሱን ቤት እያስደሰተ/እየኖረ፣ ልጅን እያሳደገ፣ ለመኪናው ነዳጅ እየሞላ መሆኑን … ሊያውቀው ይገባል።

… መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ውስጥ የሚሰራ ግለሰብ የግብር አለመሰብሰብ ደሞዙን ሊያደናቅፈው ይችላል። ነገር ግን ደሞዙን ተማምኖ ለማኅበሰቡ መኖርን እንዳይዘነጋ ይጠንቀቅ። ደሞዙን ከውጭ ድርጅት ቢቀበልም፣ ቀለቡን የሚገዛው ግን ከሀገር ውስጥ ድርጅትና ሱቅ ነው። ጠዋት ከቤት ሲወጣ የነጋዴው ሱቅ አላግባብ መታሸጉን ቸል ብሎ ቢሔድ፣ ከሰዓት ሲመጣ ግን ምሳውን እንደማይበላ ማወቅ አለበት። አለመራብ የሚቻለው የማኅበረሰቡ ሱቅ እና ዳቦ ቤት ክፍት ሲሆን ብቻ ነው። ከዚህ አንፃር ለሀገር፣ ለወገን፣ ለማኅበረሰብ መኖር ውዴታ ብቻ ሳይሆን ግዴታም ሊሆን ይችላል።

አንተ ከትልቅና ከውድ ቡቲክ የአንድ ሺህ ብር ጫማ

ልትገዛ ትችላለህ። ጫማህን የምታስጠርገው ግን ትንሽ ወንበር ላይ ቁጭ ብለህ በትንሽ ሊስትሮ ነው። ያንተ ትልቁ የአንድ ሺ ብር ጫማ ያለ ትንሹ ሊስትሮ ከንቱ ነው። ስለዚህ ለማኅበረሰቡ ክፋይ ለሊስትሮው መኖር ይጠበቅብኃል።

የአንድ ሀገር መሪ ብቻውን ትልቅ መሆን አይችልም። መሪውን ትልቅ የሚያደርገው የትንሹ ወይም የተራው ህዝብ ድምፅ ነው። ድምፅ ያላገኘ መሪ ቤተ መንግስት ገብቶ ትልቅ መሆን አይችልም። መሪው የማኅበረሰቡን፣ የሀገሩንና የህዝቡን ችግር ሲያስወግድ እና ህመሙን ሲታመም ብቻ ነው የተመኘውን ትልቅነት የሚያገኘው። ግን አንዳንድ መሪዎች ትልቅ የሚያርጋቸን የህዝብ ድምፅ፣ በጥይት ወይ በመጥፎ ፖሊሲ ሲያፍኑት ይታያል።

አንድ ኢትዮጵያዊ ኢትዮጵያ ውስጥ እየኖረ፣ የኢትዮጵያን ውሃ እየጠጣ፣ ምግቧን እየበላ፣ ታክሊዋን እንተሳፈረ ነገር ግን የአሜካውያንን አስተሳሰብ ብቻ ተቀብሎ የሀገሩን ካጣጣለ ምኑን ኢትዮጵያዊ ሆነ? የሚባለው የኢትዮጵያን ምግብ የሚተፋው /የሚያወራው ደግሞ የአሜሪካንን የበላይነት። በማን ነዳጅ/ምግብ የማን ሀገር ታሪክና ዝና ወደፊት ይጓዛል? ገኖ ይወጣል?

በርግጥ አንድ ሀበሻ ኢትዮጵያን ይበልጥ በኖረበት እና ለማኅበረሰቡ በተሟገተ ቁጥር አጣብቂኝ ውስጥ እየገባ መምጣቱ አይቀርም። ማኅበረሰቡ ለምን ስራ አጥ ሆነ? ለምን መብቱ አይከበርም፣ ለምን የሚጠይቀውን አያገኝም? የሚል ሰው የመንግስት አይን ውስጥ ይገባል። ይህ ሰው ለመንግስት ዓይን ጉድፍ ይሆንበታል።

ብቻ የተመሰረተ አይደለም። ነጮች በተለያዩ ምክንያቶች ወደ ኢትዮጵያ መጥተዋል። በሃይማኖት ስብከት ለታሪክ ጥናት ለንግድ ታሪካዊ ቅርሳ ቅርሶችን ከአገር ለማሸሽ ቅኝ ለመግዛት ለመሰለል ለእፅዋት ስለጫትም ሳይቀር ጥናት ለእንስሳ ጥናት ወዘተ ብለው ሀገራችንን ማየታቸው አልቀረም። ይሁን እንጅ ልናደርግ መጣን ባሉበት ተግባር ላይ ብቻ ተወስነው አያውቁም።

እግረ መንገዳቸውን የእኛን ማንነት ጓዳ ጎድጓዳችንን አካለው በገባቸው መንገድ የእኛን ገፅታ ‹‹ሰልለው›› ይመለሳሉ ለእርሻም ጉዳይ ሆነ አባይን ለማየት የመጣው ሁሉ ሀገሩ ሲመለስ ስለኛ መጽሐፍ ይጽፋል።

‹‹የችግር መናኸሪያ የህይወት አጣብቂኝ፤ የሰው ልጅ መንገላቻ ምድር፤ ብቻ የዓለማችን የጉስቁልና መድረክ አድርገው አገራችንን የሚቆጥሩ ጥቂት አይደሉም።

/ የ ኢ ት ዮ ጵ ያ ዊ ያ ን ማንነት በባዕዳን ቅኝት/

እንዲህ ክረምት ሲመጣ ከላይ ዝናብ ከታች ጎርፍ የሚያጠናግራትን አዲስ አበባን የሚያዩ ደግሞ ምን ብለው ሊሳለቁብን ይችሉ ይሆን? በነገራችን ላይ በአንዳንድ ነገር የሚያጣጥሙ ‹ግለሰቦች› ከላይ ዝናብ ስል ‹በላ ደግሞ ተፈጥሮን አላገዱም ብለህ ክሰሰን› ሊሉ ይችላሉ። ዳሩ ይህን ቢሉ ማሞ ሌላ መታወቂያ ሌላ ይሆንባቸውና በነሱ ይብሳል።

አሁን ስለ አንድ ዜጋ ብቻ አይደለም ማውራት የፈለግሁት። ወይም ስለ ተወሰኑ ዜጎች። በእርግጥ አንድ ሀገር ባለሁለት አሀዝ እድገት እያስመዘገበች ነው ከተባለ እያንዳንዱ ዜጋ /ከትንሽ እስከ ትልቅ/ በኑሮው በህይወቱ

በቁሳቁሶቹ ላይ የእድገት ለውጦች እንደታዩበት ይጠበቃል።

አሁን በተግባር እያየን ያለነው ግን የቁልቁለት ለውጥ ነው። ሁለት ልብስ የነበረው በአንድ ተወስኗል። አንድ ንፁህ ልብስ የነበረው ወደ አንድ የነተበ ልብስ ተቀይሮበታል። በሳምንት አንድ ቀን ከቤተሰቦቹ ጋር ወጣ ብሎ ሻይ የሚጠጣ ከአመት አንድ ጊዜ እየናፈቀው ነው። የአመት በዓል በግ የለመደ ወደ በግን በቅርጫ ተሸጋግሯል። ወዘተ ወዘተ

እንግዲህ ይህ ባለሁለት አሀዝ የሀገሪቱ አመታዊ እድገት የት ነው ያለው? የት እየገባ ለማን እየደረሰው የት ላይ እየተደመረ እነማን እየተቋደሱት ነው? ውኃ ቅዳ ውኃ መልስ የሚመስል ነገር እያየሁ መሆኑን የመገመት መብቴን ልጠቀምና የዘንድሮው የሀገሪቱ መቶ ምናምን ቢሊዮን ብር አመታዊ በጀት በቁጥር ከአምናው የገዘፉ ሲመስለን ውሀ ቀዳን እንበል። ውሀችን ስንመልስ ደግሞ የዘንድሮውን በጀታችን ለዶላር ምንዛሬአችን ስናካፍለው ከአምናው በጀት ብዙም ፈቀቅ እንዳላልን እናየዋለን።

እንግዲህ እድገቱ ምኑ ነው? የቱ ነው? ከምንለብሰው ልብስ ከምንመገበው ምግብ ከተጠለልንበት ጎጆ ከምንጠቀምበት ትራንስፖርት አገልግሎት ወዘተ ወዘተ እድገታችንን በየትኛው ተለውጠን አሳየን?

አሁን ከዚህ እንለፍና የአፍሪካ መዲና ስለሆነችው ከተማችን እናውራ። ዕድገት ስልጣኔ ሲነሳ መንገድ ተሰርቷል ህንፃ በዝቷል ወዘተ የሚሉ አታካች ንግግሮችን እሰማለሁ። እኔም ህንፃው የወሰን ሰዎች ነው ብዬ አሰልችውን እሰጥ አገባ አልመለስበትም።

በአስፓልት ዳር

በእግር መሄድ የማንችልባት ከተማችን ባለፉት ሃያ አመታት ያስመዘገበችው እድገት እያልን በኤፍ ኤምና በቴሌቪዥን ብንለፍፍ ነገሩ ሁሉ ያው ያልነው ውሃ ቅዳ ውሀ መልስ ነው።

ጠዋት ከቤቱ ሲወጣ የተወለወለች ጫማ ያደረገ አንድ ሰው ወደ ማታ እቤቱ ሲገባ የጭቃ ረጋጭ ጎሳ ተጫምቶ ይመለሳል። ይሄ ወዶ ያደረገው አይደለም። አስፓልቱ ላይ የሚተኛ ጎርፍ በመኪኖች የተረጨ የእግረኛ መንገዶችን የሚያጥለቀልቀውን ጎርፍ እየተቋደሰ ነው።

ዝናብ ጠብ ካለባት መቶ ሜትር እና በጎርፍ ላይ ሳይረማመዱ የሚሄዱበት የአዲስ አበባ ጎዳና የትኛው ይሆን? መኪኖች ምንም ያክል ተጠንቅቀው ቢነዱ ጎርፍ እንደ ርችት የማይበትኑበት አደባባይና አስፓልት በየትኛው መንገድ ነው ያለው? ይህችኑ ከተማችን ከተረከብንባት ገፅታ የረባም ያክል ለውጥ ሳናደርግባት ከተማችን በስኬት በእድገት በስልጣኔ መንገድ ላይ ናት ብንል ታአማኒነቱ እንዲሁ ያክል ብቻ ነው።

አዲስ አበባ ጎርፍ የሚያንቀላፋበት አስፓልት ብቻ አይደለም ያላት። ቅልጥ ያለ የቦካ ጭቃ በብዙ ሰፈሮች አለ። ሌላው ቀርቶ በዋና ዋና አስፓልቶች ላይ የሚከመሩ አሸዋና ቀይ አፈር ጨቅይቶ እናያለን።

ጽዱና አረንጓዴ ተብሎ እንደዘመቻ በአንድ ሰሞን በከተማ አስተዳደሩ ብዙ የሚዲያ ሽፋን አግኝቶ የነበረው ጉዳይም ለውጥ አናሳ ነው። ከየት የት ድረስ ያለው ጎዳና ነው ጽዱ እና አረንጓዴ የሆነው? የትኛው ክፍት ቦታስ አረንጓዴ ለበሰ? ለህዝብ ማረፊያ ማንበቢያ አየር ማግኛ ማንሰላሰያ እና የጥሞና ቦታ

የሆነው የትኛው ቦታ ነው? እስኪ እውነት ይሄ ጽዱና አረንጓዴ የሚባለው ነገር የቱ በእቅድ ተይዞ የቱ እንደተከናወነ በግልፅ ሪፖርት ይጠቀስ? በአይናችን ልናየው የምንችለው ከዚህ እስከዚህ ተብሎ ይነገረን።

አዲስ አበባችን እንዲህ ክረምት ሲገባ ሰፋሪዎቿን የሚያማርሯቸው ጎርፍና ጭቃ ብቻ አይደሉም። ወይም የሀገሪቱ ማደግ ያስገባውን የጎርፍ ማስወገጃ ለምለም የመናፈሻ ስፍራ ብቻ አይደለም የምጠይቀው። አንዳንዴ ከባድ ዝናብ ሲዘንብ ሁሉን ዝናብ እየተደበደቡ እቤት ድረስ መጓዝ አለ። /የትራንስፖርት ነገር ብዙ የተጮኸበት በመሆኑ ከታክሲ አውቶብስ ከአውቶብስ እግር የመረጡ ብዙ የበጎ ተጓዦች አሉ/

የተጀመረው የታክሲ የዞን ምደባ በግሌ ያን ያክል ለውጥ አምጥቶ አልታየኝም ከሜክሲኮ ቄራ ጎፋ ሳሪስ ላፍቶ መብራት ሀይል ወዘተ ከዞን ስምሪት በፊት የነበረ ትርምስ ዛሬም እንዳለ ምሳሌ መጥቀስ እችላለሁ።

የ ክ ረ ም ት የትራንስፖርት እጥረት የበለጠ አስከፊ ነው ከዝናብ ከሰው ከጭቃ ከጎርፍ ጋር ትግል መግጠም ነው። እናቶች አስልጧቸው ሽማግሌዎች ብርድ አናዝዟቸው ወዘተ ታክሲ ተራ ላይ ማየት የሁለት አሀዝ እድገታችን ለአዲስ አበባ የሰጠው ገፅ በረከት ይሆን?

ይሄ እድገት የምንለው ነገር በግለሰቦች ለውጥ አላመጣልንም ከተባለ የአፍሪካ መዲና በሆነችው ከተማ ላይ ለውጥ አላመጣም ከተባለ እድገቱ የቁጥር ወይስ ገሃዳም እድገት?

ይህንን ጥያቄ ስጠይቅ አንዳንድ ወገኖች እድገቱ በመሠረተ

በታዲዎስ ጌታሁን

ኢትዮጵያዊ የመሆን ፈተና

አዲስ አበባዊ ክረምትበደሳለኝ ስዩም

በ ገፅ 23

በ ገፅ 23

ከቀጫጫ ኑሮ የደለበ ሞት ይሻላል። የወፍራም ወይም የተደላደለ ኑሮ ፍቺው ሰንጋ ማጋደምና የገነት አምሳል ለመሆን

በሚቃጣቸው ውብ ቤቶች ውስጥ መኖር ብቻ አይደለም። ከዛ በላይ የሆነ ረቂቅና ምስጢራዊ ትርጉም አለው - የተደላደለ ኑሮ።

የክረምት የትራንስፖርት እጥረት የበለጠ አስከፊ ነው ከዝናብ ከሰው ከጭቃ ከጎርፍ ጋር ትግል

መግጠም ነው። እናቶች አስልጧቸው ሽማግሌዎች ብርድ አናዝዟቸው ወዘተ ታክሲ ተራ ላይ ማየት የሁለት አሀዝ እድገታችን ለአዲስ አበባ የሰጠው ገፅ በረከት ይሆን?

Page 9: Awramba Times Issue 179

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 179 ቅዳሜ ሐምሌ 30/ 2003

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

9

ኢትዮጵያዊ የመሆን ፈተና

እንዲያው ይቺ ለወሬ የማትመች ቅጥ የለሽ ከተማችን አዲስ አበባ ለአንዱ ሙቀትን ለሌላው ውጋትን በሚያከናንብ የምን

ግዴታ እቅፏ የያዘቻቸውን ልጆቿን ብዛት አስረግጦ የሚነግረን ሁነኛ ሰው ባገኘን። አንደበቶች በተከፈቱ ቁጥር የሚጠራው አሃዝ ለየቅል ሆኖ ቢቸግረን ነው ይሄን ማለታችን። በየአጋጣሚው ሁለት ሚሊዮን ተኩል፣ ሶስት ሚሊዮን፣ ሶስት ሚሊዮን ተኩል፣ አራት ሚሊዮን ህዝብ አላት ይባላል። የ1999 አመተ ምህረቱ ህዝብ ቆጠራ ይፋዊ ግኝት እንኳን የሚዋልለውን ቁጥር ሸክፎ በአንድ አላረጋንም። እንደዘበት ሚሊዮን ሰዎች ይጨመሩበታል ወይ ይቀነሱባታል። ብቻ መካድ የማይቻለው ሃቅ ኗሪዋ ከቀን ወደ ቀን እየበረከተ፣ የሰፈረችበት ስፍራም እንደጉድ እየተለጠጠ የመሄዱ ነገር ነው።

ግዝፈቷን የሚቋቋም አቅም ማደራጀቷ ግን ያጠያይቃል። ከኗሪዎቿ ፍላጎቶች ጋር የሚመጣጠኑ በብዛትም በጥራትም አቅረቦቶች አዘጋጅታለች ማለትም

ይከብዳል። የሀገሪቱ አውራ ከተማ እንደመሆኗና የአህጉሪቱ መናገሻ ነኝ እያለች እንደመኮፈሷ ገና ያልደረሰችባቸው ብዙ ከፍታዎች አሉ። ያልተሞሉ ክፍተቶች፣ ያልተደፈኑ ቀዳዶች፣ ያልተሸፈኑ ጉዶች። መገለጫዋ እጥረት እንጅ መትረፍረፍ አይደለም። መረጃ ኃይልነቱ በሚታወጅበት በዚህ ዘመን መረጃ ሊያጥር፣ አይነቱም ሊያንስ እንደማይገባ እናውቃን። አዲስ አበቤ ግን ጥቂት ሳምንታዊ ጋዜጦችና ወርሃዊ መፅሄቶች፣ ከግማሽ ደርዘን የማይበልጡ የኤፍ ኤም ሬዲዮ ጣቢያዎችና አንድ ቴለቪዥን ታቅፎ በጠብ ጠብ በሚወርድ መረጃ ጥሙን ሊቆርጥ እንዲሞክር ተፈርዶበታል። ኅሳቡን የሚያንሽራሽርበት ጎዳና ጠቦት ተቸግሯል።

በሌሎች ሀገራት ያሉ ብጤ ከተሞችን ለማነፃፀሪያነት መጥራት አያስፈልገንም። እዚህ ለመድረስ የተጓዝንበትን ጠመዝማዛና በጥሻ የታጨቀ መንገድ አንዘነጋውም። ሆኖም አንዳንዴ ያለፈውን ትቶ አሁን ሊኖር የሚገባውን ሁኔታ በማሰላሰል በልኩ ራስን መመዘን ይጠቅማል። መዲናችንን ከዚህ ተነስተን ስንፈትሽ ልቅ ገላዋ ላይ ጣል ካደረገችው የመረጃና የመዝናኛ እራፊ የሚሻል ወፈር ረዘም ያለ ጋቢ እንደሚያስፈልጋት እንረዳለን። ጋዜጦቹ አይበቋትም። ቴሌቭዥኑ ያንስባታል። ሬዲዮ ጣቢያዎቹ አያኩራሩም። ድረ ገፅን አታውቀውም ማለት በአጉል ድፍረት አያስወነጅልም። እርግጥ ነው። በመገናኛ ብዙሃን ረገድ ወደኋላ ቀርታለች። አራት ነጥብ።

የሚዲያ ሰራ የህዝብ አይን፣ ጆሮ እና ድምፅ የመሆን፤ ማህበረሰብን የመምራትና የመግራት፤ የማቅናትና የማንቃት፣ የማወቅና የማሳወቅ የማክበርና የማስከበር ስራ ነውና ወትሮውንም

ቢሆን የከበደ ኃላፊነት ያሸክማል። የአማራጮች ጥቂትነት ደግሞ ክብደቱን ይጨምረዋል። ብዕር ሲመዘዝ፣ ማይክራፎን ሲያዝ፣ ካሜራ ሲደገን ከእጅ የገባውን እንቁ ዕድል በቅጡ ተጠቅሞ ረብ ያለው ነገር ለመስራት ካልተጣረ በረሃ መኃል የተገኘችን ውድ ውሃ በከንቱ እንደማባከን ይቆጠራል።

የአዲስ አበባ ኤፍ ኤሞች የውሃን ውድነት አስተውሎ የሚገባትን ጥንቃቄ ባለማድረግ መነቀፍን ለምደዋል። ከዝግጅት ሰዓታቸው ዘለግ ያለውን ጊዜ ለፍሬ ከርስኪ የስፖርትና ርካሽ የመዝናኛ ወጐች ማዋላቸው ነው የትችቶቹ መነሻ ከድህነትና አይነቱ በዝቶ እንደእድር ከተፈተለ ማህበራዊ ቀውስ ጋር ጉሮሮ ለጉሮሮ ተናንቃ በምትፍጨረጨር ከተማ ስንት ገንቢ ዝግጅቶች ከአየር ጠፍተው ቢናጡም ቢጨመቁም አንዳች ትርጉም ፍጭ የማይላቸው፣ በጋ ከክረምት ቢጠበቁም አንዲት ዘለላ ፍሬ ሊያሸቱ የማይቻላቸው እንቶ ፈንቶ ወሬዎች መትረፍረፋቸው ስለ እውነትም ያበሳጫል። ፀሐፊ ተውኔት ኃይሉ ፀጋዬ እንደሚለው ደግሞ በር ስለተከተላቸው ብቻ ዘው ብለው ወደ ስቱዲዮ የዘለቁ ብዙ ጋዜጠኛ ተብዬዎች አማርኛን በስርዓቱ አዋቅረው የማይጐረብጥ አረፍተ-ነገር መመስረት ዳገት የሚሆንባቸው፤ አድማጮቻቸውን የማያከብሩ ደንታ ቢሶች ናቸው። ኃይሉ ከኤፍ ኤም ሬዲዮዎች በአንደኛው ተገኝቶ ከገጣሚና የሬዲዮ ጋዜጠኛ ቴድሮስ ፀጋዬ ጋር ባካሄደው ቃለ-ምልልስ አስተያየቱን ሲሰጥ ከዚህም አልፎ ጣቢያዎቹን የእናቱን ሐረግ በመዋስ ‹‹የብልግና ማስተማሪያ›› ሆነዋል ሲል ወርፏል። ገጣሚው ቲዎድሮስ በበኩሉ ያንኑ ዕለት በቴሌቭዥን ቀርቦ ‹‹የሚዲያ ሰዎች የማህበረሰቡን ስነ-ምግባር የመጠበቅና የማስጠበቅ

ግዴታቸውን እየዘነጉት ነው›› የሚል አመለካከቱን ከነለዛው ተናግሯል።

ይህ ለስነ-ምግባር ግድ የማጣት አባዜ ተዝናኑባቸው ተብለው በሚለቀቁልን ዘፈኖች ላይ ጎልቶ ይታያል። እንግሊዘኛ ከሆነ ስድብም፣ አዋራጅ ሃሳቦችና ቃላትም ጉዳት እንደማያመጡ የተረጋገጠ እስኪመስል ድረስ ጋጠ ወጥ ዘፈኖች ይከታተሉልናል። በአንዳንድ ጊዜያትማ ሬዲዮውን የጎረጎረ አድማጭ ልሳኑን ሙሉ በሙሉ እንግሊዝኛ ያደረገ አንድ እና አማርኛና እንግሊዝኛን እኩል በኩል አደብለው/አዳቅለው የሚገለገሉ ሶስት አልያም አራት ጉራማይሌ ጣቢያዎች እንዳሉ ሊያስብ ይችላል።

ሬዲዮ በአዲስ አበባ አካሄድ አይረባም ወደሚል የስንፍና መደምደሚያ እንደተንደረደርን አይደለም። በጭራሽ ይልቁን ኩንታል ሙሉ ገለባ የተከመረባት ቁና ስንዴው ሊያጠራ እንደሚተጋ ገበሬ ፍራፍሬውን ለቃቅመን በቅርጫት ብናጠራቅመው ሌላ መልክ እናገኛለን። ከቁጥር ብርካቴ ይልቅ በጭብጥ ጥንካሬና በአቀራረብ ጨዋነት የደመቀ ብሩህ መልክ። አንገቱን ቀና፣ ድምፁን ጎላ ማድረግን የደፈረ፤ ልበ ሙሉነትና ርግጠኝነት የተዋሃዱት መልካም መንፈስ ይስተዋል ጀምሯል። የዚህ መንፈስ ዋነኛ ወገኛ ይሄው ተብጠልጣይ ሬደዮ ነው።

የመንፈሱ አነቃናቂዎች በአብዛኛው ወጣቶች ናቸው። በሚገባ የተማሩ፣ ታላላቆቻቸውን የሚያከብሩ ለሀገራቸው ባህልና ታሪክ የሚቆረቆሩ፣ የእውቀትን ዋስትናነት አበክረው የሚገልፁ ናቸው። የዝግጅቶቻቸው አቅጣጫ በኪነ-ጥበብ ወደ መበልፀግ፣ በመፅሃፍት ወደመታነፅ፣ በስራ ወደመታተር ያዘነብላል።

ህብረተሰቡን በሰፊው

አዲስ አበባዊ ክረምትታሳቢ አድርገው የተደራጁና በነቢብም በገቢርም አክብሮታቸውን ሊያሳዩ የሚጥሩ ጣቢያዎች አሉ። ሆኖም ትልቁን ስራ እየከወኑ ያሉት የሌላ ሙያ ባለቤት ሆነው ከጣቢያዎቹ ጋር በመተባበር ደረጃውን የጠበቀ ዝግጅት የሚያቀርቡት ትጉኃን ናቸው።

የዘንድሮው ክረምት ያስተናገዳቸው ሁለት ክስተቶች እንደ አብነት ይነሱ። የመጀመሪያው የደራሲ አዳም ረታ ወደሀገር ቤት ተመልሶ ከአድናቂዎቹ ጋር መወያየት ሲሆን ሌላኛው የሙዚቀኛ ሙላቱ አስታጥቄ በነዚህ ቀኖች መሸለም ነው። ሁለቱ የስነ ፅሁፍና የሙዚቃ ማማዎች በጉብዝናቸው ወራት ተለኩሶ እስከአሁንም ያልበረደ ልፋታቸው የኋላ ኋላ የሸመተላቸውን ክብርና አድናቆት ከማሳየትም በላይ አዲሱ ድልድይ ቀጣይ መንፈስ ወደኋላ ተመልሶ ወደፊት ሊፈናጠር ሲያኮበኩብ የሚከተለው ዱካ መያዙ የፈጠረበትን ደስታና ጉጉት ያመላክታል።

ለሥነ ስርዓቶቹ የተሰጠው የሬዲዮ ሽፋን ከላይ የጠቃቀስነውን ትዝብት ያጠናክርልናል። በተለይ የሀገር ፍቅሩን የአዳምና አድናቄዎቹ ውይይት በማስፈፀምም ትልቅ ስራ ሰርተዋል - ልባሞቹ ዝግጅቶች።

መንፈሱ ያልዳሰሳቸው ዘርፎችን እየነካካ፣ ጥላውን እየዘረጋ ሀገር እያካለለ ለሰናይ ግብ ያነሳሳናል? በምናባችን ይዘናት ልንደርስበት ብዙ የሚቀረን ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ ያበረታናል? ወይስ ተጎንትሎም ተልፈስፍሶም ይጨናጎላል? መላሹ ጊዜ ነው። እስከዛው ግን ለሬዲዮ አዘጋጆች እውነት እንጅ ቅዥት አትቀልቡን። እውቀት እንጅ ፌዝ አትመግቡን። መፅሃፍ እንጅ ናፕኪን አትሸልሙን እንላለን።

በኃይለየሱስ ካሳ

የኤፍ ኤም ባለባና ፍሬ

ሬዲዮ በአዲስ አበባ አካሄድ አይረባም ወደሚል

የስንፍና መደምደሚያ እንደተንደረደርን አይደለም። በጭራሽ

ይልቁን ኩንታል ሙሉ ገለባ የተከመረባት ቁና ስንዴው

ሊያጠራ እንደሚተጋ ገበሬ ፍራፍሬውን ለቃቅመን በቅርጫት

ብናጠራቅመው ሌላ መልክ እናገኛለን።

ዘልቆ የሚሰማ ሕመም ቢሆንም፣ በደቡብ ሱዳን መገንጠል ሰሜን ሱዳን ከደረሰባት ጉዳት ጋር ሲነፃፀር ሱዳን ነች ተጎጂዋ፡፡ ይኸውም ለም አፈር፣ ወርቅ፣ ነዳጅ እና የከብት ሃብት በብዛት ያለው ደቡብ ነው ስለዚህ ያለደቡብ ሱዳን ‹‹ሱዳን›› የማይታሰብ ነው፡፡ ሰሜኖቹ አሁን የቀራቸው በረኻው ነው፡፡ አሸዋው ነው፡፡ ይኼ ብቻ አይደለም፤በምስራቅና ምዕራብ ሌላ ውጥረት አለ፡፡ እኛ ሱዳኖችን ከአንድ ወንዝ የምንጠጣ ነን፣ ኩታ ገጠም ድንበርተኞች ነን፣ ተመሳሳይ ቋንቋና ባሕል ያለን ሕዝቦች ነን፣ በፋሺስት ጣሊያን ወረራ ጊዜ ኢትዮጵያዊያን ሱዳን ነው የተጠለሉት ብለን ለምነናቸዋል፡፡ ደግ ደጉን በማሰብ ፋንታ በአገራችን የውስጥ ጉዳይ ጣለቃ መግባታቸው አግባብ እንዳልሆነና ካላረፉ በእነሱ ቁስል እንጨት መስደድ እንደምንችል ነገር ግን ለጥፋት መልሱ ጥፋት አይደለም ስለዚህ ከድርጊታችሁ ታቀቡ ብለን ከአንድም ሁለት ሦስት ጊዜ አገራቸው ድረስ ሄደን ለምነናቸዋል፡፡ ግን ሊሰሙን አልፈቀዱም፡፡ ስለዚህ የእጃቸውን አግኝተዋል፡፡ከእንግዲህም ወዲያ የሱዳን ድንበር የዐረቦች የጥቃት መንደርደሪያ እንደመሆኑ መጠን ዛሬ ነፃነቱን ያገኘው አፍሪካዊ ሀገር ተጠናክሮ የቆመ እንደሆነ በዚያ በኩል ለኢትዮጵያ ያለው ስጋት በጣም የቀነሰ አሊያም የተወገደ ሊሆን እንደሚችል ዕምነት አለኝ፡፡

ስለ ሶማሊያ ዛሬ ሶማሊያ ለእኛ ስጋት አይደለችም፡፡ በምንም ዓይነት ተዐምር አንሰራርታ ኢትዮጵያን የምታሳስብ አገር አይደለችም፡፡ ወደ አለመኖር እያመራች ያለች ነች፡፡ ስለዚህ በሱዳንና በሱማሊያ በኩል የደተረገው ነገር በእኛ ቂመኛነት ሳይሆን በእነሱ ዕብሪተኛነትና በእኛ ላይ ለሰነዘሩት ጥቃት የተወሰደ የመከላከል ዕርምጃ ነው፡፡ በዚህ ረገድ ኢትዮጵያዊያኖች ሁሉ ሊኮሩ ይገባል፡፡ ከአገር ሉዓላዊነት አኳያ የሚያስደስት ድል ነው፡፡ …የምለው ይኼንን ነው፡፡

ለኢትዮጵያዊያን ያስተላልፉት መልዕክት

በአሁኑ ሰዓት ኢትዮጵያ በምን ዓይነት ሁኔታ ላይ እንዳለች ለማንም ኢትዮጵያዊ ግልፅ ነው፡፡ እርግጥ ነው ግንዛቤያችንና አመለካከታችን እንደየንቃተ ሕሊናችንና እንደመረጃ ግኝታችን የተለየ ሊሆን ይችላል፡፡ ስለዚህ ኢትዮጵያ አሁን ካለው አገዛዝ ነፃ መውጣት አለባት፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ ማንም መተኛት የለበትም፡፡ ይኽ ካልሆነ ለዘለዓለም ትውልድ አስወቃሽ እና በጣም አሳፋሪ የታሪክ ቡሉኮ ለብሰን ነው የምንኖረው፡፡ … አመሰግናለሁ፡፡

ስለ ኢትዮጵያ ጋዜጠኞችና ስለ አዲሱ መጽሐፋቸው

ወደ ዋናው ጉዳይ ከመግባቴ በፊት እኔ ባጠቃላይ እስከዛሬ ድረስ ብዙ እንዳንተ ያሉ ኢትዮጵያውያን ጋዜጠኞች በተለያየ ጊዜ በተለያየ ርዕስ ላይ ሊያናግሩኝ ፈልገዋል፡፡ እንዲህ ዓይነቱን ጥያቄ ለማስተናገድ ፍላጎት የለኝም፡፡ በአጠቃላይ የኢትዮጵያ ሕዝብ አብዮት ታሪክ በሚመለከት ያዘጋጀሁት መፅሐፍ ለብዙዎቹ ጥያቄዎች መልስ ይሰጣል ብዬ አስባለሁ፡፡ (መጽሐፉ) እስከ ቅፅ ሦስት ድረስም ይቀጥላል፡፡ ኢትዮጵያውያን ወንድሞቼና እህቶቼ ከእኔ መረዳት የሚፈልጉትን ከመፅሀፉ ሊያገኙ ይችላሉ፡፡ ከዚህ በተረፈ ግን ጋዜጠኞችን የማስተናገድ ፍላጎት የለኝም፡፡ ምናልባት ከዚህ አንጻር ብዙዎቹን ጥያቄዎችህን ላልመልስህል እችላለሁ፡፡ ስለ ደቡብ ሱዳን ነፃነትና የኮሎኔል መንግስቱ ሚናደቡብ ሱዳንን የረዳንበት እና ለዛሬው ነፃነታቸው ያበቃንበት ብዙ ምክንያት አለ፡፡ ከሁሉ በላይ እኔና ጓደኛቼ ከእነሱ ጎን የቆምነው በእውነቱ ከደቡብ ሱዳን ሕዝብ ታሪክ፣ ብሶትና አረቦች (ሰሜኖች) ከሚያደርሱባቸው ባርነትና ረገጣ አኳያ እጅግ የሚያሳዝን ሕይወት እየገፉ ስለነበር በንፁህ አፍሪካዊ እና ሰብዓዊ ስሜት ነው፡፡ አገሪቷ ችግር ላይ እያለች ያንን ያክል ድጋፍ ያደረግንላቸው እና 8ዐ ሺህ ጠንካራ ሚሊሺያ ልናስታጥቅላቸው የቻልነው አገሩ ሰፊ ከመሆኑም ሌላ መላው የዐረብ መንግስታት በእነኛ ጭቁን ድሆች ላይ ይረባረቡ ስለነበር ጥቃታቸውን መመከት ስላስፈለገ ነው፡፡ ጦር አስታጥቀናቸዋል፣ አሰልጥነናቸዋል እንዲሁም ጠቅላላ የጦር ስትራቴጂ አካፍለናቸዋል፡፡ በአገራችን በሙሉ ተዋጊዎቹ ብቻ ሳይሆኑ ስደተኞቹም ጭምር ከ1ዐ እና 15 ዓመት በላይ ኢትዮጵያ ውስጥ ነው የተጠለሉት፡፡ ለውጊያው አስፈላጊ የነበረውን በሙሉ ሳናቋርጥ አቅረበናል፡፡ በእኛ ድጋፍና በእነሱ ፅናት፣ ብዙ ደምና ላብ ከፈሰሰ በኋላ ዛሬ ነፃነታቸውን ሊቀዳጁ ችለዋል፡፡ ይኼ ምን ማለት ነው? ከሁሉ በፊት እንደዛ ሲበደልና ሲጨቆን የነበረ አፍሪካዊ ሕዝብ ከምንም በላይ ያስደስታል፡፡

የሰሜን ሱዳን መንግስት ለኤርትራ መገልጠል ስላበረከተው ድርሻ

የሰሜን ሱዳን መንግስት በአገራችን ሰሜናዊ ክፍል የነበረውን ችግር ከመነሻው ጀምሮ አረቦችን እያስተባበረ ሲያደማንና ሲያስወጋን የነበረ እና ኢትዮጵያ ዛሬ ለደረሰችበት ደረጃ ያበቃና ኤርትራን ያስገነጠለ መንግስት ነው፡፡ በዚህም የተነሳ 64 ሺህ ካሬ ኪ.ሜ የቆዳ ስፋት ካለው ግዛታችን እና ከወገናችን ተነጥለናል፡፡ እንዲሁም ወደባችንን አጥተናል፡፡ በአጠቃላይ የኤርትራ መገንጠልና ከወገናችን መነጠላችን የሚያሳዝንና አጥንት ድረስ

ኮሎኔል መንግስቱ ይናገራሉ የቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ኮሎኔል መንግስቱ ኃይለማርያም፣ ከትናንት በስቲያ አውስትራሊያ ለሚገኘው ‹‹ኤስ ቢ ኤስ›› ሬዲዮ ቀጥሎ ያለውን ቃለምልልስ ሰጥተዋል፡፡

የሬዲዮ ጣቢያው አዘጋጅ ካሳሁን ሰቦቃ ለቃለምልልሱ መነሻ ያደረገው የደቡብ ሱዳንን ወቅታዊ ሁኔታ ቢሆንም፣ ፕሬዚዳንቱ ስለ ኤርትራ መገንጠልና ወደብ አልባ ስለመሆናችን፣ ስለ ሶማሊያና አሁን ስላለው የኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታም ሀሳብ ሰንዝረዋል፡፡

Page 10: Awramba Times Issue 179

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 179 ቅዳሜ ሐምሌ 30/ 200310

p Ç T@ S ´ “ —

በናፍቆት ዮሴፍ

ከዚህ ቀደም የሮበርት ቶማስን ቴአትር ‹‹ስምንቱ ሴቶች›› በሚል ተርጉማ ለመድረክ ያበቃችው አርቲስት አዜብ ወርቁ፣ አሁንም በፈረንሳያዊው ሮበርት ቶማስ የተፃፈውን ይህን ቴአትር ‹‹የሚስት ያለህ›› በሚል ተርጉማ፣ አዘጋጅታና ፕሮዲዩስ አድርጋ እነሆ በረከት ብላለች።

በተለያዩ ቴአትሮች ላይ በርካታ አስተዋጽኦ የነበራት አዜብ ወርቁ የፈረንሳይ ቴአትሮችን በመተርጎምና በማዘጋጀት ለኪነ-ጥበቡ ያላትን ፍቅርና አስተዋኦ እያሳየች ትገኛለች። የሁለት ሰዓት ርዝማኔ ያለው ‹‹የሚስት ያለህ›› በብሔራዊ ቴአትር ቤት በእይታ ላይ ይገኛል። ይህ ቴአትር ከልብ አንጠልጣይ ኮሚዲ ዘውግ የሚመደብ ሲሆን በአንዲት ሙሽራ ደብዛ መጥፋት ላይ ያጠነጥናል።

ሽመልስ አበራ ዋናውን ገፀ-ባህሪይ፣ ዳንኤልን ሆኖ በተለመደው የጥበብ ዛሩ አዳራሹን ከዳር እስከዳር በስሜት ጨምድዶ ይዞታል። የጠፋችው ሙሽራ፣ ወ/ሮ ኤልሳቤጥ የዳንኤል ሚስት ናት የታሪኩም ውጥረት ከዚህ ይጀምራል። ዳንኤልና ሚስቱ ወ/ሮ ኤልሳቤጥ ከቬነስ ተነስተው ለጫጉላ ሽርሽር ወደሌላ ከተማ በመጓዝ ጓደኛው ቤት አርፈዋል። እነዚህ ሙሽሮች ለሽርሽር በመጡበት በዚህ ከተማ ለአገሩ እንግዳ፣ ለሰውም ባዳ ናቸው። ይባስ ብሎም አዲሷ ሙሽራ ባልታወቀ ምክንያት ተሰውራለች። በሚሊየነሩ አጎቷ እጅ ተቀማጥላ ያደገችው ይህቺ ሙሽራ ከመጥፋቷ ትንሽ ቀደም ብሎ አጎቷ በጠና ታሞ መሞቱም ተሰምቷል። ታዲያ የአጎቷን እጅግ በርካታ ሀብት ወራሿ ይህቺ ሙሽራ የባሏን ፍቅርና የጫጉላ ሽርሽር ሳትጠግብ በማታውቀው አገር ማን ሰወራት? ዋናው የታሪኩ አንኳር ይህ ነው።

ዳንኤል በሚስቱ ድንገት መሰወር ሌት ከቀን ይባዝናል፤ ማንንም በማያውቅበት በዚያ አዲስ ከተማ ጓደኝነቱን ከአልኮል ጋር አቆራኝቶ ይበሳጫል። በዚህ ድርጊቱ አዳራሹ ውስጥ ያለ ተመልካች በተለያየ አቅጣጫ ሀሳቡን ልኮ ሚስቱን የሚያፋልገው ይመስላል። ይህ መረጃ የደረሰው የከተማዋ ፖሊስ

መጠን የለሽ የአልኮል መጠጥ ተጨምሮበት አሳዛኝ አድርጎታል።

በዚህ መሀል በአካባቢው ቄስ አብሳሪነት ሚስቱ ኤልሳቤጥ መምጣቷ ይነገረዋል። ሆኖም ባለቤቱ ኤልሳቤጥ ነኝ ብላ የመጣችዋን ሴት አያውቃትም። ‹‹የኔ ሚስት ይህቺ አይደለችም›› እያለ የሚጮኸው ዳንኤል ሰሚ አላገኘም። ይልቁኑም የቄሱና የኮማንደሩ ተግሳፅ ሊያፈናፍነው አልቻለም። ይኼኔ እርስዎ ተመልካች የሰሚ ያለህ እያለ ለሚጮኸው፣ ሚስቱ በሰው አገር ለብቸኝነት ዳርጋው ለጠፋችው ዳንኤል ያዝናሉ።

ከታሪኩ ዙር መክረር የተነሳ ዳንኤል ወደ ማበድ እንደሚሄድ ሁሉም ገምቷል። ኮማንደሩም ቢሆን በዚህ ቴአትር የእድር ዳኛ እንጂ ኮማንደር ባይመስሉም ይህን አቀራረብ የመረጡበት መንገድ አለና ተሳክቶላቸዋል።

ብቻ ምርመራው ቀጥሏል። ከመታወቂያ ጀምሮ እስከ ጋብቻ ምስክር ወረቀት ድረስ አሰርታ ሚስቱ ኤልሳቤጥ ነኝ የምትለው ሴት ዳንኤልን ባይሆንም ቄሱንና ኮማንደሩን ለማሳመን ጫፍ ላይ ደርሳለች። ሚስቱ ሳትሆን ሚስቱ ነኝ የምትለው ሴት አላማዋ ምን ይሆን?

ደግሞስ ዳንኤል ሚስቱ እንዳልሆነች ሲናገር የሴቷን ያህል ቄሱና ኮማንደሩ ለምን አይሰሙትም? የታሪኩ ሂደት በጥያቄ የተሞላና ልብ አንጠልጣይ ነው። የሆነ ሆኖ የዳንኤልን ብቸኝነት፣ ሰሚ ማጣትና የበዛ ጭንቀት ሲመለከቱ በአንድ ወቅት በእውኑ ዓለም ውሸት የእውነትን ቦታ ተክታ አድማጭ ያጡበት፣ ሰሚ ጆሮ የተነፈግዎት ጊዜ ካለ ዳንኤልን እያዩ ስሜትዎ ይነካል። ቢደርስብኝስ ብለው ይጨነቃሉ።

በጥያቄዎች የተሞላው

‹‹የሚስት ያለህ››

በኮማንደሩ አማካኝነት ምርመራውን ቀጥሏል። በዚህ ቴአትር ላይ የኮማንደሩን ገፀ-ባህሪይ ወክሎ የሚጫወተው ሚካኤል ታምሬ በተያዩ ፊልሞች ላይ የምናውቀው ሲሆን አጠቃላይ የኮማንደር ዓይነት ባህሪይ አይታይበትም። ይልቁንም የእድር ዳኛ ዓይነት ባህሪይና አለባበስ አለው - በእኔ እይታ። ምርመራው ቢቀጥልም ምንም ጠብ ያለ ነገር የለም።

ዳንኤል ከሚስቱ ናፍቆትና ጭንቀት በላይ

ዳንኤል በሚስቱ ድንገት መሰወር ሌት ከቀን ይባዝናል፤ ማንንም በማያውቅበት በዚያ አዲስ ከተማ ጓደኝነቱን ከአልኮል ጋር አቆራኝቶ ይበሳጫል። በዚህ ድርጊቱ አዳራሹ ውስጥ ያለ

ተመልካች በተለያየ አቅጣጫ ሀሳቡን ልኮ ሚስቱን የሚያፋልገው ይመስላል።

ግን ደግሞ እውነት ብትሰለስልም አትበጠስም፣ አንድ ቀን መውጣቷ አይቀርም ብለው ተስፋ በማድረግ በውጥረት መመልከትዎን ይቀጥላሉ።

አርቲስት ሽመልስ አበራ በሳምንት አምስት ቴአትሮችን በመስራት አድናቆትን ያተረፈበት ጊዜ ሩቅ አይደለም። በአሁን ሰዓትም ቢሆን በሳምንት ውስጥ ሁለት ቴአትሮችን ይጫዎታል። ሽመልስን እንድናደንቀው የሚያስገድደን ግን ብዙ ቴአትሮችን መጫዎቱ ሳይሆን ቴአትሮቹን በልዩነትና በድንቅ ችሎታ መጫዎቱ እንጂ። ምክንያቱም በሚጫወታቸው ቴአትሮች ላይ የሚወክላቸው ገፅ-ባህሪያት እጅግ ልዩነት ያላቸው ናቸው።

‹‹የሚስት ያለህ›› ቴአትር ላይ አዕምሮዎ ሌላ ነገር እንዳይጠረጥርና በኋላም ባለመጠርጠርዎ እንዲፀፀቱ የሚያደርግዎት የዚህ አርቲስት ድንቅ ችሎታ ነው ማለት ይቻላል።

አርቲስት አዜብ ‹‹የሚስት ያለህ›› ቴአትሯ ላይ በትወናውም ሰፊ ሚና አላት በዚህ ቴአትር ላይ የወከለቻት ገፀ-ባህሪይ ሚስትህ ኤልሳቤጥ ነኝ ብላ ወደ ዳንኤል ቤት የመጣችዋን እንግዳ ሴት ሲሆን ወትሮም በምታውቀው መድረክ ላይ ከነብቃቷ ናኝታበታለች።

በዚህ አጋጣሚ የቄሱን ገፀ-ባህሪይ የተላበሰው አርቲስት ፈለቀ አበበ ያሳየውን ድንቅ የአተዋወን ብቃት ሳላደንቅ አላልፍም።

በአጠቃላይ የታሪኩ ፍሰት፣ የአርቲስቶቹ ስብጥር ቴአትሩን አዝናኝና አጓጊ አድርጎታል። ወደ ቴአትሩ መጨረሻ ሲሄዱ ታሪኩ አቅጣጫውን ይቀይርና ሌላ ነገር ይከሰታል። ይኼ ዱብእዳ ነው ይላሉ። ታዲያ ያልገመቱትና ያልጠበቁት ክስተት ሲፈጠር እርስዎ በየዋህነትዎ፣ ባለመጠርጠርዎ እጅግ ይፀፀታሉ። ተፀፅተውም የታሪኩን ፍጭት፣ የፖሊሶችን የምርመራ ብቃት ያደንቃሉ። ይህን አድናቆትዎን ሳይጨርሱ ምን ዓይነት ልብ አድርቅ ኮማንደር ናቸው? ብለው የተማረሩበትን ያህል፣ የእድር ዳኛ ይመስላሉ ብለው፣ ልብ አውልቅ ብለው የተቀየሟቸው ኮማንደር ምን እንደሆኑ ሲገባዎት አዕምሮዎን ወደ ሌላ መደነቅ ያሸጋግራሉ።

ከላይ ቴአትሩ በጥያቄ መሞላቱን ገልጸናል መልሱን ከቴአትሩ ያግኙታል።

በሰለሞን ገብሬ ተፅፎ የተዘጋጀውና ሶላር ፊልም ፕሮዳክን ተሰርቶ በሰለሞን ነጋሽ ፕሮዲውሰርነት የቀረበው ‹‹አልሞትም›› ፊልም ነገ በ15 ክልል ከተሞች እና በአዲስ አበባ ሁሉም ሲኒማ ቤቶች ዋናውን የምረቃ ስነ-ስርዓት በአምባሣደር ሲኒማ 7፡30 ጀምሮ በማድረግ ይመረቃል።

‹‹የተሳሳተ ጥሪ›› ፊልም ይመረቃልገበያኑ ኢንተርቴይንመንት ‹‹የተሳሳተ ጥሪ›› (wrong number)

የተሰኘውን የሰለሞን ሹምዬ አዲስ ፊልም ሳምንት ቅዳሜ ነሐሴ 7 ቀን 2003 ዓ.ም ከቀኑ በ8፣ በ10 እና 12 ሰዓት በሁሉም የአዲስ አበባ ሲኒማ ቤቶች ለእይታ አንደሚያቀርብ ገለፀ። እንዲሁም ሰኞ ነሐሴ 9 ቀን 2003 ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ተጋባዥ እንዶች በሚገኙበት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ያስመርቃል።

ሰኞ በብሔራዊ ቴአትር በሚደረገው ምርቃት ታዋቂ ግለሰቦች እንደ አመጣጣቸው በቀይ ምንጣፍ አልፈው ወደተዘጋጀላቸው ቦታ ያመራሉ። ፊልሙ ከመጀመሩ አስቀድሞ በሚኖረው የሰላሳ ደቂቃ ልዩ ፕሮግራም አስከ ነሐሴ 7 ድረስ የፊልሙ የፕሮሞሽን አካል በሆነው የ833 የስልክ መስመር አጭር የፅሁፍ መልዕክት በመላክ የዕጣው ውጤት እሁድ ነሐሴ 8 ቀን ለሁሉም ባለ ዕድሎች ተገልጾ ለአሸናፊዎቹ 115 ሰዎች የተዘጋጀላቸውን አንድ ባለ 32 ኢንች ሳምንግ ኤል ሲዲ ቴሌቪዥን፣ ሁለት ሳምሰንግ ሞባይሎች፣ አስራ ሁለት የአምባሳደር ሙሉ ልብሶች እና አንድ መቶ የፊልሙ ምርቀት ላይ መገኛ ትኬቶች ሽልማት ይረከባሉ።

‹‹ማሕሙድ ጋ ጠቢቂኝ›› የተሰኘ የወግ መፅሐፍ ታተመበአሮን አሳታሚነት የቀረበው በቀድሞው የአዲስ ነገር ጋዜጠኛ

መሐመድ ሰልማን የተፃፈው ‹‹ማሕሙድ ጋ ጠቢቂኝ›› የተሰኘ ልዩ ልዩ ወጎችና የጉዞ ማስታወሻዎችን የያዘ መጽሐፍ ለህትመት በቃ። ጋዜጠኛ መሐመድ ሰልማን በማህበራዊ አምድ ስር በአዲስ ነገር ጋዜጣና ድረ-ገጽ ላይ ተነባቢ የነበሩ ከ15 በላይ ጽሁፎችን አሰባስቦ ለንባብ እንዳቀረበ ተገልጿል። ‹‹ማሕሙድ ጋ ጠብቂኝ›› የተሰኘው ተራኪ ወግ የአዲስ አበባዋን ፒያሳ ህይወትና ገጽታ የሚያስቃኝ ጽሁፍ ሲሆን ከዚህ ቀደምም በሸገር ሬዲዮና በቪኦኤ በከፊል ቀርቧል። የቀድሞው የአዲስ ነገር ማኔጂንግ ኤዲተር አቶ መሰፍን ነጋሽ እና በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሶሲዮሎጂ መምህር አቶ ደረሰ ጌታቸው ለመፅሓፉ መግቢያ እንደጻፉ ተገልጿል።

በመላው አለም በሳተላይት የሚሰራጨው የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ሰርቪስ (EBS TV) ላለፉት አራት ወራት ሲተላለፍ የቆየው ሀበሻ ዊክሊ የተባለው ፕሮግራም ለቀጣይ ሲዝን የተሻሉ ፕሮግራሞችን አሻሽሎ ሊቀርብ ነው። ይህ የአንድ ሰዓት ፕሮግራም በሀበሻ ቱሪዝምና መዝናኛ ላይ አተኩሮ የሚሰራ ሲሆን አላማውም የሀበሻ ኪነ-ጥበብና ቱሪዝምን ለአለም

ማሳወቅ እንደሆነ የፕሮግራም ዳይሬክተርና ፕሮዲዩሰር የሆነው ወጣት አዶኒክ ገልጿል።

በኢቢኤስ ቴቪ ከሚያስተላልፋቸው ፕሮግራሞቹ የፊልም ቦክስ ኦፊስ፣ አምስት ከአምስት፣ ታለንት ሰርች፣ ኪነ ጥበባዊ ዝግጅቶችና ኮማዱ ሾው በተጨማሪ የቴአትር ቦክስ ኦፊስ፣ የፊልም ዳሰሳና ስፖርት ሀበሻ የተሰኙ አዳዲስ ፕሮግራሞችን እሁድ እና ረቡዕ

ምሽት ሁለት ሰዓት ላይ ለማቅረብ መዘጋጀቱን የፕሮግራሙ አዘጋጆች በዮድ አቢሲኒያ የባህል አዳራሽ በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።

ዲሽ ለሌላቸው ተመልካቾች ከኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቭዥን አየር ሰዓት በመግዛት፣ ዌብ ሳይት በመክፈትና ሀበሻ ዊክሊ ዲስክ የተሰኘ መፅሄት አዘጋጅቶ መጨረሱም በመግለጫው ታውቋል።

ሀበሻ ዊክሊ ፕሮግራሞቹን አሻሽሎ እንደሚቀርብ አሳወቀ

ፕሮዲውሰሩ ከዚህ በፊት ‹‹ላገባ ነው›› የተሰኘውን አስቂኝ የፈቅር ፊልም ያቀረበ ሲሆን ‹‹አልሞትም›› በድርጊት የተሞላ ልብ አንጠልጣይ ፊልም መሆኑን፤ ፊልሙን ሠርቶ ለማጠናቀቅ የአንድ አመት ጊዜ እንደወሰደ እና 350 ሺህ

ብር እንደወጣበት ገልጿል። ሰለሞን ገብሬ፣ ታጠቅ

መለሰ፣ አዲያም ሰለሞን፣ ኤደን ሽመልሰ ህፃን ቅዱስ እና ሌሎች ከ50 በላይ ተዋንያን ተሣትፈውበታል።

‹‹አልሞትም›› ፊልም ነገ ይመረቃል

Page 11: Awramba Times Issue 179

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 179 ቅዳሜ ሐምሌ 30/ 2003

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

‹‹ወደ ቤተ-ክርስቲያን የምንሄደው እግዚአብሔርን ለማገልገል ሳይሆን በእርሱ ለመገልገል ነው››

ሸዋፈራው ደሳለኝ [ተዋንያን]

11

p Ç T@ S ´ “ — አ ፍታ1የሚቀንሰው እግዚአብሔር ነው። ሙያው ደግሞ ፈጠራን ይፈልጋል።

አድናቂዎችህ ‹‹ሸዋፈራው አዝናኝ ነው›› ብለው ወይስ ‹‹ብቁ የጥበብ ባለሙያ

ነው›› በማለት የሚረዱህ ይመስልሀል? [በርግጥ ጥናት የሚፈልግ ሀሳብ ነው]

ያዝናናል የሚሉም፣ ጥሩ ተዋናይ ነው የሚሉም አሉ። በርካታ የሰራኋቸው ኮሜዲ ስራዎች በመሆናቸው ‹‹ሸዋ ከእንደዚህ አይነት ፍሬም ውስጥ መውጣት አይችልም›› የሚል አስተያየት ተመልካቾች እና ሚዲያው አካባቢ ስለነበር ‹‹ሰውዬው›› የሚለው አዲሱ ፊልሜ በአዲስ አቅጣጫ መጥቷል [አውራምባ ታይምስ ላይም ይህን አስመልክቶ ሙያዊ ትችት ቀርቦበት እንደነበር ይታወሳል።]

‹‹ሰውየው››ን ባለፈው ሰኞ ሲመረቅ አይቼዋለሁ። በርግጥ አንተ ከኮሜዲ ገፀ ባህሪ ተቃራኒ ሆነህ መጥተሀል። ፊልሙ… ግን አዲስ ሀሳብ አለው?

‹‹ሰውየው›› በራሴ ድርጅት የቀረበ የመጀመሪያ ፊልሜ ነው። ሰውም የተጫወትኩትን ሴረኛ ገፀ ባህሪ አስገርሞት ፀጥ ረጭ ብሎ ተከታትሎታል። [እኔ ግን በተወሰነ መልኩ የሚሰንቁንም ታዝቤያለሁ።] 1፡35 የሚፈጀው ይህ ፊልም ነጥብ በነጥብ የታሪክ መዛባት እና መንዛዛት ሳይኖር የሚያልቅ ነው። ያለ ምክንያት የገባ ገፀ ባህሪ እንደሌለ እርግጠኛ ነኝ። [በፎርም ማስታወቂያ ይመስላል፡፡]

በኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ዘንድ ነገ የፍልሰታ ጾም ይጀመራል፡፡ የሚጾምበትን ምክንያት ታውቀዋለህ?እመቤታችን በስጋ ካረፈች በኋላ አስከሬኗ በቀጥታ ያረገው ወደሰማይ ስለነበር ሐዋርያቶች አስከሬኗን ለማግኘት ሱባዔ የገቡበት ወቅት ስ ለ ሆ ነ

እኔ የምልህ… ሰዉ ገና ሲያይህ ሳቁ የሚመጣው ለምንድን ነው?

[ሳቅ እያለ] ይሄን ማወቅ አስቸጋሪ ነው። እንደምገምተው ከሆነ ግን በሲኒማም ሆነ በመድረክ የሰራኋቸው ስራዎች ወደ ኮሜዲ ስለሚያደሉ ይመስለኛል።

የተሳተፍክባቸው ስራዎች ስንት ደረሱ? መቶ ስንት? [ሳቅ]

[እየሳቀ] በአጠቃላይ አገሪቱስ ላይ መቶ ‹‹ተሰራ›› እንዴ? ትክክለኛ ቁጥሩ ‹‹ይሄ ነው›› ማለት አልችልም። ፊልም ከ20 በላይ፣ ቲያትርም ወደዚያው ገደማ ይመስለኛል።

የጥበብ ቤተሰብዎች ግን ሲያገኙህ በይበልጥ የቱ ስራህን ያነሱብሃል?

አስተያየቶች በወቅታዊ ነገር ላይ ያተኩራሉ። በይበልጥ ግን የሰለሞን አለሙ ድርሰት በሆነው ‹‹ከልፀዳል›› በሚለው የቴሌቪዥን ድራማ ያስታውሱኛል። ከልካይ የሚባል ተንኮኛ ስራ አስኪያጅን ወክዬ የተጫወትኩበት ነው።

እውቅና ወቅቱን ጠብቆ የመጣ ነው ወይስ በድንገት የደረሰብህ?

እውቅና እና ዝና ተፈልጎ ሊመጣ አይችልም። ዝና ለሰው ልጅ የተገባ ነው ብዬም አላስብም። ለመናገር ‹‹ዝነኛ ነኝ›› ብዬ አላስብም። ዝነኛ የፈጠረኝ አምላክ ብቻ ነው። እግዚአብሔር ማንንም ሰው ያለ አላማ አይፈጥርም። ባለሁበት ሙያ ለህብረተሰቡ ጠቃሚ ስራ ሰጥቼ እና አገልግዬ ማለፍ አለብኝ። የጥበብ ሰዎች ለሚዲያ ቅርብ ስለሆንን ሰው በቅርብ ስለሚያገኘን ነው እንጂ ሁሉም ሰው በየሙያ መስኩ ዝነኛ ነው። ከእግዚአብሔር በታች ህይወት የሚያተርፈው የህክምና ባለሙያ፣ የምንምነሸነሽበትን መንገድ የሚሰሩ ማሀንዲሶች እያሉ እኛ ‹‹ዝነኛ ነን›› ማለት ይከብደኛል። ራሴን የማየው እንደ አንድ አስፈላጊ የሙያ ሰው ብቻ ነው።

ስኬትህን የምትለካው እንዴት ነው? በአገኘኸው ገንዘብ ልክ? ሰዎች

ባጨበጨቡልህ (በሰጡህ አድናቆት ልክ) ወይስ…?

ከዚህ ወጣ ባለ መልኩ… ስኬትን በሙያዬ አገሬን እና ወገኔን ባገለገልኩት ልክ እረዳዋለሁ። ቅድም እንዳልኩህ የተፈጠርኩበት አላማ ‹‹ግቡን እየመታ ነው›› ብዬ አስባለሁ። ካልሆነ ግን ተወልዶ፣ ኖሮ፣ ሞተ ነው የሚሆነው።

መለኪያህ ይሄ ከሆነ ያለህበት ደረጃን ስትመትረው…?

ይሄን እኔ ሳይሆን የምትመለከቱት እናንተ ብትናገሩ መልካም ነው። መስታወቴ ሚዲያው እና ሦስተኛ ወገን ነው።

አንተ ባትወለድ ኖሮ ኪነ ጥበብ እና ተመልካቾች የሚቀርባቸው ነገር ያለ

ይመስልሀል?በትክክል! የሚቀርባቸው ነገር ነበር። እኔ ባልመጣ ኖሮ በሙያው እያደረግኩ የነበረው አስተዋጽኦ አይኖርም ነበር። በዚህ ሙያ ውስጥ የነበሩ ትልልቅ አርቲስቶችን ተመልከት፤ እነሱ ባይኖሩ ብዙ ነገር ይቀርብን ነበር።

‹‹የሀብታም እንኳን ሰርጉ ለቅሶው ያምራል›› እንደሚባው አንተን ስመለከት ያልከው ሀሳብ ሳቅ ፈጥሮ ሳይሆን አንተ ስለሆንክ ብቻ የሚስቁ ያጋጥመኛል።

ይህ የተለየ ምክንያት የለውም። አሁን ካንተጋ እያደረግኩ ያለሁትን ቆይታ ከሌላ ጋዜጠኛ ጋር ባደርግ ሁለታችሁም የምትሰነዝሩት ሁኔታ የተለየ ነው። እኔን እንደ ቧንቧ እየኝ፤ ውሃውን የሚከፍተው፣ የሚጨምረውና

በ ገፅ 18

እንጾመዋለን፡፡ በዚህ አጋጣሚ ቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ በጣም አሳዛኝ ነገር ተፈጥሯል፡፡ ‹‹የሆኑ›› የሚበተኑ ሲዲዎች እና ለዚያ ምላሽ የሚሰጡ አካላት አሉ፡፡ ከእዚህ ጋር ተያይዞ የሚነሳ ማኀበር አለ፡፡ እነዚህ ነገሮች ተገቢ ናቸውን? ቢያንስ አሁን የጾም ጊዜ በመሆኑ ልንቻቻል እና ይቅርታ ልንባባል ይገባል ብዬ አስባለሁ፡፡

ይህንን ጉዳይ ‹‹በሃይማኖት ውስጥ ሊኖር የማይገባው የአንደኛነት እሽቅድድም›› የሚሉት አሉ፡፡

ከእግዚአብሔር ውጪ ማንም አንደኛ የለም፡፡ ‹‹እከሌ የሚባለው ሰባኪ አንደኛ ነው›› ብትለኝ አልቀበልህም፡፡ አንተም አውደ ምህረት ላይ ብትቆም መንፈስ ቅዱስ ሊያቀብልህ ይችላል፡፡ እግዚአብሔር በፈለገ ጊዜ ማንንም ሊያናገር ይችላል፡፡ ‹‹አንደኛ ነን›› የሚሉትን ጠራርጎ አውጥቶ እነሱ የሚቀመጡበትን ህንፃ አፍ አውጥቶ ሊያናግር ይችላል፡፡ ቀይ ባህርን ለሁለት የከፈለ የእኔ አምላክ ይሄ አይሳነውም፡፡ ወደ ቤተ-ክርስቲያን የምንሄደው እግዚአብሔርን ለማገልገል ሳይሆን በእርሱ ለመገልገል ነው፡፡ ሰባኪም፣ ዘማሪም፣ ቄስም፣ ጳጳስም የሚሄደው ለመገልገል ነው፡፡ ልትገለገል በሄድክበት ቤት ውስጥ ‹‹ባለቤት ነኝ›› ብሎ ፀብ ማንሳት ትልቅ ስህተት ነው፡፡ ይህቺ ቤተ-ክርስቲያን የራሷ ቀኖናና ዶግማ (ሥርዓትና እምነት) ያላት፣ ታላላቅ ሊቃውንቶች የነበሩባት እና ያለባት ነች፡፡ እዚህ ሁለት እና ሦስት ዓመት መፅሐፍ ቅዱስ ተምረናል ከሚሉት ሰዎች የበለጠ አንድ ሰው ሁለተኛ ደግሪውን በማሰራበት አድሜ (ሰባትና ስምንት ዓመት) የቤተ ክርስቲያን ትምህርት የሚማሩ ታላላቅ ሰዎች በየገዳማቱ እና አድባራቱ ያሉባት ቤተ-ክርስቲያን ነች፡፡ [ያወራነው አራት

ኪሎ ከሚገኘው ቢሮው ሲሆን ‹‹እዚህ›› ሲል የጠቆመኝ

ወደ ቅድስት ስላሴ መ ን ፈ ሳ ዊ

ኮሌጅ ነው፡፡] የእነ

አቡነ ተክለኃይማኖት፣ አቡነ ቴዎፍሎስ፣ ጥራልኝማ ... እ የአቡነ ጴጥሮስ ቤተ-ክርስቲያን ነች፡፡ ዛሬ ዛሬ ወጣቱ አካባቢ ቡድን ሰርቶ የሚታየው ነገር አይሰራም (ተገቢ አይደለም፡፡) በእግዚአብሔር ቤት የሀሳብ ንግድ አለ፡፡ [መዝሙር እና ስብከት ሽያጩን ለማለት ነው፡፡] ቤተ-ክርስቲያኗን የማፍረስ አላማ ያላቸው ሰዎች ሊጠነቀቁ ይገባቸዋል፡፡ መንፈሳዊ ጉዳይ ጥንቃቄ ያስፈልገዋል፡፡ የቤተ-ክርስቲያን አባቶች ‹‹ሃይ›› ሊሉም ይገባል፡፡

አባቶቹስ ‹‹ሃይ›› ሊባሉ አይገባቸውም?አዎ! በሁሉም ፅንፍ ያሉት ‹‹ሃይ›› ሊባሉ ይገባቸዋል፡፡ ሰዎች ‹‹ቤተ-ክርስቲያን ተበጠበጠች›› ብለው ይሰጋሉ፤ በእየሱስ ክርስቶስ የተዋጀች ስለነበረች ግን ምንም አትሆንም፡፡ እግዚአብሔር በክብሩ የሚደራደር አምላክ ስላልሆነ ክብሩን ልንጠብቅ ይገባል፡፡ ካልሆነ ግን ቁጣው ኃይለኛ ነው፡፡ [በነገራችን ላይ ሸዋፈራው እድገቱ ቤተ ክርስቲያን ነው፡፡ በከፈትኩለት ቀዳዳ ጨዋታችንን መንፈሳዊ ያደረገውም ለዚህ ነው፡፡]

ወደ ሌላ ጥያቄ;ለ… ባሰብከው ልክ እየተጓዝክ ነው?

ሊገርምህ ይችላል፡፡ አንድም ርምጃ ባቀድኩት መጠን ሄጄ አላውቅም፡፡ ተወልጄ ያደግኩት አዲስ አበባ ነው፡፡ የወጣሁት ‹‹ድሃ›› ከሚባል ቤተሰብ ነው፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ እግሬ ላይ ቆዳ ጫማ ያደረግኩት የዘጠነኛ ክፍል ተማሪ እያለሁ ነው፡፡ እግዚአብሔር አቅዶ ፈጥሮኛል፡፡ ማየት የሚገባኝን የችግር ጊዜ አሳይቶኛል፡፡ አሁን ደግሞ በእኔ ላይ መስራት የሚፈልገውን እያደረገ ነው፡፡

እቅድህ ካልተሳካ ምን ትላለህ?እግዚአብሔር አልፈቀደም፡፡

እግዚአብሔር አይፈቅድም ብለህ ታስባለህ?

[በፍጥነት] of course! አንተ ልክ ነው ብለህ የምታስበው ነገር ቢሳካልህ መጥፎ (መጥፊያ ጉድጓድህ) ሊሆን ስለሚችል አምላክ ይጠብቅሀል፡፡ እኔ አሁን 200 ሺህ ብር ቢጠፋብኝ [200 ሺህ ብር ቢጠፋብኝ ብሎ ለምሳሌ ያዋለ ስንት እንዳለው መገመት ነው፡፡] እንደ ሰው ልበሳጭ፣ ለፖሊስ ላመለክት እችላለሁ፡፡ ነገር ግን ያ ብር እንደሚመለስ እርግጠኛ ነኝ፡፡ ሁሌም የማስበው እንዲህ ነው፡፡

አሁን አንድ ሰው ደውሎ አዲሱ ፊልምህ (ሰውየው) ሲዲ ተሰርቆ እየተባዛ ነው

ቢልህ?[በጣም ከልቡ የማይመስል ሳቅ እየሳቀ] በእርግጠኝነት የምነግርህ እግዚአብሔር እኔን የሚጎዳ ነገር አያደርግም፡፡ በተዓምር!

የተደወለልህ ግን ሆነ (ተሰረቀ) ተብሎ ነው፡፡

በተዓምር አይሆንም ስልህ፡፡ አይሆንም!

የውጪ አገር ፕሬዝዳንት ሆነው ኢትዮጵያ ውስጥ ሆቴል ያላቸው

ሰው አሉ፡፡ ስማቸውን ልታስታውሰኝ ትችላለህ?

የጅቡቲው ፕሬዝዳንት ይመስሉኛል፡፡ ሆቴሉም ያለው ድሬዳዋ ውስጥ ነው፡፡ አማርኛ ጥርት አድርገው ይናገራሉ፡፡ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተምረዋል፡፡ [ለማብራሪያው አመሰግናለሁ፡፡ ስማቸውን ግን አለፍካት፡፡ መች ኦማር ጊሌ አልክ?] ጓደኛሞቹ፣ ባልቻ አባ ነፍሶና የብሩክታይት ስጦታ ከቲያትር፣ የወንዶች ጉዳይ 1 እና 2፣ ቀይ ስህተትና ዘኪዎስ ከፊልም፤ ከሰራቸው ውስጥ ጥቂቶቹ ናቸው፡፡

ብዙዎች የጥበብ ስራዎቹን እያዩ ይቅርና በመንገድም ሲያዩት ሳቃቸውን መቆጣጠር ያቅታቸዋል። የጥበብ ጉዞ ከጀመረ 11 ዓመት አልፎታል። ‹‹በአቀድኩት መጠን አንድ ስንዝር ሄጄ አላውቅም›› የሚለው ትሁቱ ተዋንያን ሸዋፈራው ደሳለኝጋ አንዳፍታ ቆይታ አድርገናል።

Page 12: Awramba Times Issue 179

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 179 ቅዳሜ ሐምሌ 30/ 2003

የቢስ አትክልትና ፍራፍሬ አክሲዮኖች

በፍጥነት በመሸጥ ላይ ናቸው።

እርሶም ፈጥነው የዚህ ግዙፍና ትርፋማ

አክሲዮን ባለቤት ይሁኑ!!!

12

የፌዴራል የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን በአዋጅ ከተቋቋመ አስር አመት አልፎታል፡፡ በዚህ ጊዜ ውስጥ በእናንተ ላይ ከሚነሱ ትችቶች መካከል አንዱ ‹‹ትንንሽ አሳዎችን እንጂ ትላልቆቹን ሻርኮች ደፍራችሁ አትነኩም›› የሚል ነው። ምን ምላሽ አልዎት?

በመሠረቱ እንዲህ ማለት የሚገባው ኮሚሽኑ ተፈትኖ ፈተናው ከወደቀ ነው። ኮሚሽኑን ‹‹ወደ ምርመራና ክስ ለመግባት የሚያበቃው መረጃ ቀርቦለት፣ እንደዚህ እንደዚህ አይነት በቂ ነገር ሰጥተነው ፈርቶ ውጤት ላይ ሳያደርሰው ቀረ›› ብንባል ይመቻል። እናንተም እንደሚዲያ፣ ‹‹እንዲህ አይነት ጠንካራ ጥቆማና ጠንካራ ጉዳይ አቅርበን እንዲህ አልሆነም፣ ውጤት አላገኘም። ኮሚሽኑ እየታማ ነበር፣ አሁን እውነቱን አገኘነው›› ብትሉ ጥሩ ነው። … ነገር ግን፣ አንዱ የራሳችን ድክመትም

አለ። እስካሁን እኛ የምንሰራው በጠቋሚዎቻችን ጥቆማ ላይ ተመስርተን መሆኑ ነው። ጠቋሚዎቻችን ደግሞ እንደዚያ አይነቱን ነገር አላመጡም። እኛ የራሳችንን ኃይል አጠናክረን በትልልቅ ባለስልጣናት፣ የሥራ ኃላፊዎችና ሕብረተሰቡ ጥርጣሬ በሚያሳድረው አካባቢ የራሳችንን ኢንተለጀንስና ሰርቬይላንስ (መረጃና ክትትል) አጠራቅመን መግፋት ያለብን መሆኑን እናውቃለን። ይኼ ድክመታችን ነው። ወደ ፊት ይኼንን ስናጠናክር የበለጠ ውጤታማ ሥራ እንሰራለን። … ሌላው ግን፣ ‹‹ትልልቆችን›› ሲባል በደንብ ቢገለፅ ጥሩ ነው? እስከምን ድረስ?

ለምሳሌ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጨምሮ እስከ ሌሎች ከፍተኛ ባለስልጣናትን።… ሀሳባችን ትልልቅ ሰዎች ላይ ጉብ ብለን ጀግና መባል አይደለም፤ በእውነትና በመረጃ ላይ የተመሰረተ

ነገርን መያዝ እንጂ። ማግኘት ያለብን ፍርድ ቤት ይዘን ቀርበን የማናፍርበት ጉዳይ ነው። በዚህ ረገድ አንዳንዴ አንዳንድ ስራዎች ስትሰራ እነዛ ሰዎች ትልቅነታቸው መሆን ይቀርና ትንሽ ይሆናሉ። ወይም እነዛ ትልልቅ የተባሉ ሰዎች ሲከሰሱና ሲታሰሩ የፖለቲካ ትርጉም ይሰጠዋል እንጂ … ለምሳሌ በሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ብዙም ባልታየ ሁኔታ በእኛ አገር ጠቅላይ ሚኒስትር፣ የመከላከያ ሚኒስትርና ሌሎች በሚኒስትርነት ደረጃ ያሉ ግለሰቦች ተከስሰው ተፈርዶባቸዋል። እነዛ ትልልቅ አልተባሉም። ስለዚህ ‹‹ትልልቅ አሳዎች ላይ ድፍረት ያንሳችኋል፣ የምትበረቱት ትንንሾቹ ላይ ነው›› የሚባለው ነገር በአንድ በኩል ተገቢ ወቀሳ አለመሆኑን ታየዋለህ። ትልልቆቹ ሲታሰሩ

‹‹ጠ/ሚኒስትሩን ለመክሰስ ምንም የሚከለክል ነገር የለም፤ ደግሞም ክስ ቀርቦባቸው ያውቃል››

አቶ ዓሊ ሱሌይማን/የፌዴራል የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር/

በ ገፅ 16

በተለምዶ ለገሐር ተብሎ በሚታወቀው አካባቢ ከመድን ድርጅት ቀጥሎ በሚገኘው ረጅም ህንጻ ላይ የሚገኘው የፌደራል ስነምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሽን ቀደም ሲል የፍትህ ሚኒስቴር ም/ሚኒስትር በነበሩት አቶ ዓሊ ሱሌይማን ይመራል፡፡ ወደ ኮሚሽነር ዓሊ ቢሮ

ሲገቡ የጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ፎቶግራፍ በትልቁ ተሰቅሎ ይታይዎታል፡፡ ይህ አይነቱ ድባብ የኮሚሽኑን ገለልተኝነት ጥያቄ ውስጥ ለመክተት ጠቋሚ ምልክት ተደርጎ ሊወሰድ ቢችልም አቶ ዓሊ ግን ተቋሙ ‹‹ፍጹም ገለልተኛ›› እንደሆነና መረጃ ከቀረበ፤

አቶ መለስን ጨምሮ ማንንም ከመክሰስ ወደ ኋላ እንደማይል አጥብቀው ይከራከራሉ፡፡ ትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል ሙስናን አስመልክቶ በየአመቱ በሚያወጣው የሀገራት የሙስና ደረጃ (Corruption Perception Index) አገራችን ሙስና በከፍተኛ ደረጃ ከሚገኝባቸው አገሮች ተርታ ቢመድባትም አሊ ሱሌይማን ግን ‹‹የአክራሪ ኒዮ ሊብራሎች ጥላሸት ነው›› በማለት ተቋማቸው በሁለትና

ሦስት ዓመታት ውስጥ ደረጃውን በአስራዎቹ ቤት እንዳሻሻለ ይገልጻሉ፡፡ ‹‹80 ሚሊዮን ሕዝብ ባለበት ሀገር በዓመት 200 ሰው ማስቀጣታችን የምንፈልገው ደረጃ ላይ መድረሳችንን አያሳይም፤ በእውነትና በመረጃ ላይ የተመሰረተ ነገርን መያዝ እንጂ፤ትልልቅ

ሰዎችን ከሰን ጀግና መባል አንፈልግም›› የሚሉትን ዓሊ ሱሌይማን ባልደረባችን ኤሊያስ ገብሩ እንደሚከተለው አነጋግሯቸዋል፡፡

Page 13: Awramba Times Issue 179

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 179 ቅዳሜ ሐምሌ 30/ 2003

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

እ ን ግ ዳ

13ማ ስ ታ ወ ቂ ያ

Page 14: Awramba Times Issue 179

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 179 ቅዳሜ ሐምሌ 30/ 2003

እ ን ግ ዳ

14

ዓ ለም አቀፍ

በናፍቆት ዮሴፍ

እለቱ ሰኞ ሐምሌ18 ቀን 2003 ዓ.ም ወደ ዝግጅት ክፈላችን አንድ የስልክ ጥሪ መጣ። ስልኩ የተደወለው ከቦሌ ከፍለ ከተማ ወረዳ አራት ነው። ‹‹ህጋዊ የግንባታ ፈቃድ አውጥተን እየገነባን ያለውን ህንፃ ፈራሽ በመሆኑ ግንባታውን አቁማችሁ ቦታውን አስለኩ ተብለናልና ያለ አግባብ መብታችን እየተጣሰ ነው›› የሚል ቅሬታ ነበር ከደዋዮቹ የሰማነው። በዚህን ጊዜ ብዙም ሳንቆይ ወደ ቦታው አቀናን። እኛ በቦታው ስንደርስ ፖሊሶችና የሚለኩ ባለሞያዎች በቦታው ደርሰው ከባለይዞታዎች በደረሰባቸው ተቃውሞ ተመልሰው መሄዳቸውን ሰማን። ባለይዞታዎችንም አነጋግርን። አቶ ኩመል ረዲ የ60 ዓመት አዛውንት ናቸው። ይህ ቦታ ከ1959 ዓ.ም ጀምሮ በግል ይዞታነት ሲጠቀሙበት እንደቆዩ ገልጸውልናል። ቦታውም ቦሌ ክ/ከተማ ቀበሌ 14 የቤት ቁጥር 279 የሚገኝ ሲሆን በተለምዶ ሃያ ሁለት ማዞሪያ በሚባለው አካባቢ ከትራፊክ ጽ/ቤት ፊት ለፊት ጎላጎል ትሬዲንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ ከሚያስገነባው ትልቅ ህንፃ ጀርባ ይገኛል። አቶ ኩመል ረዲ ይህን ቦታ

ለጠቅላላ (ቅይጥ) አገልግሎት የሚውል ባለ 5 ፎቅ ህንፃ ለመገንባት በ25/07/2000 ዓ.ም የግንባታ ፈቃድ ማውጣታቸውን በማስረጃ አስደግፈው ይናገራሉ። በዝግጅት ክፍላችን እጅ የሚገኘው የግንባታ የምስክር ወረቀትም ይህን ያረጋግጣል። 1.3 ሚሊዮን ብር ካፒታል የተመደበለት ይሄው ግንባታ ‹‹በቀረበው የግንባታ ሰነድ መሠረት መካሄድ ይችላል›› የሚል ማረጋገጫም ሰፍሮበታል። የግንባታው ፈቃድ ምስክር አካል የሆኑ አባሪ ሰነዶችም ተዘርዝረው ሰፍረውበታል። እንደ አቶ ኩመል ገለፃ የግንባታ ፈቃዱን በበቂ ሁኔታ መውሰዳቸው ብቻ ሳይሆን የግንባታ ማስጀመሪያ ማረጋገጫ አግኝተው ግንባታ መጀመራቸውንና አሁን G+2 ላይ መድረሳቸውን ያስረዳሉ። የግንባታ ማስጀመሪያ ማረጋገጫው

የተሰጣቸው በቦሌ ክ/ከተማ አስተዳዳር ሥራና ከተማ ልማት ቢሮ የግንባታ ሬጉላቶሪ እና አቅም ግንባታ ወሳኝ የስራ ሂደት መሆኑን አያይዘው ያቀረቡት የግንባታ ማስጀመሪያ ማረጋገጫ ያሳያል በማረጋገጫውም ላይ ‹‹በአዲስ አበባ ከተማ ኢንቨስት ለማድረግ መርጠው ግንባታ ለመጀመር በመወሰንዎ እናመሰግናለን። በግንባታ ሂደቱ የግንባታ ክትትል በማድረግ አስፈላጊውን ድጋፍ ለመስጠት ዝግጁ መሆናችንን እየገለፅን ሥራዎ የተሳካ እንዲሆን እንመኛለን›› የሚል ማበረታቻ ሰፍሮበታል። በዚህ ማረጋገጫ ላይ የአቶ ኩመል ስም፣ የግንባታው አይነት፣ የሚገነባበት በጀት፣ ቦታው የሚገኝበት ክ/ከተማ፣ ቀበሌና የቤት ቁጥር፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የምዝገባ ቁጥር እና የፈቃዱ ቁጥር ሰፍሮበት በሱፐርቫይዘሩ በአቶ ፈድሉ ቡሽራና የግንባታ ክትትልና ቁጥጥር ኦፊሰር በሆኑት አቶ አሸናፊ አላምቦ ዳላ ተፈርሞበት፣ ማረጋገጫውን የሰጠው የስራ ሂደት ማህተም አርፎበታል። አቶ ኩመል አንደማስረጃ ካቀረቧቸው ሰነዶች መካከል በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር ባለስልጣን የተሰጠ የይዞታ ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት(ካርታ) ይገኝበታል። በዚህ መልኩ የቀጠለው ይህ ግንባታ በአስቸኳይ እንዲቆምና ቦታው እንዲለካ በተከታታይ ማስጠንቀቂያ እንደደረሳቸው አቶ ኩመል ለአውራምባ ታይምስ ይገልፃሉ።

ግንባታው ለምን እንዲቆም ተፈለገ?

ይሄ ሁሉ ማስረጃ ካለዎት ለምን ግንባታው እንዲቆም ተፈለገ? የሚል ጥያቄ አቅርበንላቸው ነበር። አቶ ኩመልም እንዲህ በማለት መልሰዋል። ‹‹እኔ ከ1959 ዓ.ም ጀምሬ ባለይዞታ ነኝ ውዝፍ ግብርም እዳም የለብኝም በ2000 ዓ.ም ከማዘጋጃ ቤት የግንባታ ፈቃድ አውጥቼ ግንባታ ከጀመርኩ አንድ አመቴ ነው›› ካሉ በኋላ አሁን ግን ግልጽ ባልሆነ ምክንያት ‹‹ለጎላጉል ትሬዲንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ ባለቤት ለአቶ ጎይቶም ግርማይ ሰጥተናል›› የሚል ምላሽ እንደሰጧቸው እንባና ሳግ በተቀላቀለበት ስሜት ያስረዳሉ።

‹‹እስካሁን ከቀበሌው እና ከፖሊስ ጣቢያ ከ10 ጊዜ በላይ ቦታውን እንዳስለካ የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ደርሶኛል። ሆኖም ህጋዊ ባለይዞታ መሆኔና የግንባታ ፈቃድ ያለኝ በመሆኔ አላስለካም ብዬ እየተሟገትኩ ነው። ለግንባታውም እስካሁን አምስት ሚሊዮን ብር አውጥቻለሁ›› በማለት ያስረዳሉ። በመጀመሪያ አካባቢ እንዲህ አይነት ማስጠንቀቂያ ሲደርሳቸው የግንባታ ፈቃዱን ወደሰጣቸው ማዘጋጃ ቤት ሄደው ለቅሬታ ሰሚ አካል አቤት እንዳሉና መጥተው ቦታውን አይተው ግንባታውን እንዲቀጥሉ መፍቀዳቸውን ይናገራሉ -አቶ ኩመል። ይሁን እንጂ አሁንም ማስጠንቀቂያው በተከታታይ ገፍቶ መምጣቱን ይናገራሉ። አቶ መሀመድ ኩመል የአቶ ኩመል

ልጅ ነው። በ2000 ዓ.ም ከማዕከል /ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር/ የግንባታ ፍቃድ ወስደውና ከቦሌ ክ/ከተማ ማስጀመሪያ ተቀብለው በ2002 ዓ.ም ግንባታ መጀመራቸውን ያረጋግጣል። ‹‹ቀበሌያችን ከዚህ በፊት ሁለትና ሶስት ጊዜ ሰብስቦን የመልሶ ማልማት ሥራ ላይ ስለሆንን ቅድሚያ ለባለይዞታ ስለሆነ በማህበርም ሆነ በግል መስፈርቱን አሟልታችሁ ማልማት ከቻላችሁ መብት አላችሁ። የማትችሉ ከሆነ ደግሞ በምትክ እና ካሳ ክፍያ ተነስታችሁ ለሌላ ይሰጣል ብለው ነበር›› ይላል ወጣት መሀመድ። ሆኖም እነርሱ (አቶ ኩመል) ይህ ስብሰባ ከመደረጉ በፊት ግንባታ መጀመራቸውን በስብሰባው ላይ እንደተናገረ ያብራራል። ‹‹ቀበሌው ግንባታ ለመጀመራችሁ ህጋዊነት ያለው ማስረጃ አቅርቡ ባለን መሠረት አሟልተን መረጃ አቀረብን›› በማለት ግንባታ መጀመራቸውን ክ/ከተማውም ይሁን ቀበሌው ጠንቅቆ እንደሚያውቅ ነው ለአውራምባ ታይምስ የሚያስረዳው። ይሁን እንጂ ሰኔ 15/2003 ቦታው ለጎላጉል ትሬዲንግ ስለተሰጠ ግንባታ አቁማችሁ እንድታስለኩ የሚል የቃል ማስጠንቀቂያ እንደደረሳቸው ነው የሚናገረው። ‹‹ቀጥሎም ደብዳቤ ይዘው መጥተው አናስለካም ብለን መለስናቸው›› የሚለው መሀመድ በሌላ ቀን ቀበሌ መጥታችሁ እናወያያችሁ የሚል ደብዳቤ እንዳፃፉላቸውና በቀበሌው አስተዳደር ፅ/ቤት ለውይይት መቀመጣቸውን ገልጾ የቀበሌው ስራ አስኪያጅም ‹‹በእርግጥ ስህተት እንዳለ እናውቃን። ግን እኛ ከታች ያለን ትዕዛዝ አስፈፃሚ ስለሆንን የታዘዝነውን እናስፈፅማለን›› ማለታቸውን በአፅንኦት ይናገራል። ‹‹አንድ ሰው ህሊና እያለው ስህተት መሆኑን እያወቀ አስፈፃሚ ነኝ አስፈፃማለሁ ሲል መስማት ከህግ ተጠያቂነትም ከህሊና ወቀሳም አያድንም›› የሚለው መሀመድ ‹‹እኛ ዜጋ ነን ዜጋ አይደላችሁም ካሉ ሁለተኛ ዜግነት ይስጡን ያለበለዚያ መብታችንን ለማስከበር እስከሚኬድበት ድረስ እንሄዳለን›› ይላል። የቀበሌው ሥራ አስኪያጅ ለውይይት ቢሮው በሰበሰበን ጊዜ ጎላጉል ትሬዲንግ ኃላ/የተ/የግ/ኩባንያ በሊዝ መግዛቱንና ለእርሱ መሰጠቱን የሚያረጋግጥ 11 ገፅ ያህል እንዳነበበላቸው የሚገልፀው መሀመድ ቦታውን ለመለካት በሚመጡ ጊዜ ለማስለካት እንዲፈርም እንደተጠየቀና አልፈርምም ብሎ መውጣቱንና ከዚያም በተከታታይ ደብዳቤ መምጣቱንና ‹‹ህጋዊ ነን አናስለካም›› በማለታቸው አባቱና ወንድሞቹ ለአንድ ቀን ታስረው በዋስ መለቀቃቸውን ይገልፃል።‹‹አዲስ አበባ መስተዳድር

ውስጥ ለሚገኘው ሊዝ ማህበረሰብ ቅሬታቸውን አቅርበው የሊዝ ማህበረሰቡ ዋና ኃላፊው አቶ ፈለቀና የቦሌ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ መጥተው ቦታውን ካዩ በኋላ አቶ ፈለቀ ‹‹የግንባታ ፈቃድ እያላቸው ለምን አቁሙ አላችኋቸው›› በማለት ለአቶ አሳልፈው ጥያቄ እያቀረቡ ተያይዘው መውጣታቸውን ነው መሀመድ የሚገልጸው። የችግሩ ሰለባ ሆነናል የሚሉት አቶ ኩመል ብቻ አይደሉም። አቶ ዘላለም የተባሉ ግለሰብም ጭምር እንጂ። አቶ ዘላለም በዚሁ ግቢ ተወልደው ያደጉ የአቶ ኩመል ጎረቤት ናቸው። ችግሩ ተፈጠረ በተባለበት በዚያ ቦታ እና በቀበሌው ከአንድ ሺህ ህዝብ በላይ እንደለ ይናገራሉ - አቶ ዘላለም። ‹‹ከሶስት ወር በፊት የቀበሌው ሰዎች

የክ/ከተማው ሥራ አስኪያጅና ስራ አስፈፃሚዎች ተሰብስበን በራሳችን ማልማት እንችል እንደሆነ ሰው ማፈናቀል አንፈልግም ማልማት ትችላላችሁ ማልማት ያልቻለ ምትክና ካሳ ተሰጥቶት ይሄዳል አሉን›› ይላሉ። /እኔና አቶ ዘላለም የምናወራበት ቦታ አቶ ኩመል ግንባታ የጀመሩበት የግንባታ አናት ላይ ሆነን ነው/ ‹‹ይሄ የምታይው ቦታ የአቶ ኩመል የራሳቸው ነው። ከእርሳቸው ቤት ቀጥሎ ሁለት የቤት ቁጥር አለ›› በማለት ቤቶቹን በጣታቸው አመለከቱኝ። እነ አቶ ኩመል ቀደም ሲል ፈቃድ አውጥተው እየገነቡ በመሆናቸው፣ አቶ ዘላለምም በማህበር ለማልማት መስማማታቸውንና ይህን የሚያረጋግጥ ፎርም አንደሞሉ በቦሌ ክ/ከተማ ሥራ አስኪያጆችና በሌሎች ስድስት አባላት የተሰጣቸው ፎርም እጃቸው ላይ ይገኛል። አቶ ዘላለም እናለማለን ብለው የተስማሙት የቀበሌው ነዋሪዎች ኮማቴ ሰብሳቢም ናቸው። ፎርሙ ስምምነቱን ህዝቡ

ቢጥስ ተወካዮቹ እነ አቶ ዘላለም ሊጠየቁ የመንግስት ኃላፊዎቹ ጋር ጉድለት ቢኖር ሊጠየቁ የሚያስማማ ነው። መመሪያው ማንኛውም የቀበሌው ነዋሪ የግልም ይዞታ ይሁን የቀበሌ ቤት ያለው የከተማዋን ውበት በጠበቀ መልኩ ማንኛውንም ግንባታ መገንባት የሚችል መሆኑን አቶ ዘላለም ያብራራሉ። አንችልም የሚሉም በ15 ቀን ውስጥ በፎርሙ ላይ ሞልተው እንዲያሳውቁ የሚያዝ ነው። ‹‹እኛን ህዝቡ ኮሚቴ አድርጎ ከመረጠን በኋላ የክ/ከተማው ስራ አስኪያጅ አቶ አሳልፈው ኮሚቴውን እንደገና ሰብስበው አቅም ካለን ማልማት እንደምንችል አረጋገጡልን›› ይላሉ አቶ ዘላለም። አክለውም በስድስት ወር ውስጥ ቦታውን አፅድታችሁ ግንባታ ካልጀመራችሁ ቦታው ይወሰዳል መባላቸውንና በፍጥነት ሂደቱን ጨርሰው ግንባታ የሚጀምሩበትን ቀን እየተጠባበቁ እንደነበረ ነው የሚናገሩት። G+8 መስራት ትችላላችሁ። በካሬ ሜትር 13617 ብር ትከፍላላችሁ መባላቸውንና መስማማታቸውን ጨምረው ይናገራሉ። ‹‹መንግስትን ወክሎ የመጣ ኃላፊ ህዝብን ይዋሻል የሚል እምነት የለኝም›› የሚሉት አቶ ዘላለም ቦታውን ልናለማ እንደምንችል በአደባባይ ለህዝቡ ካወጁ እና ለስኬታማነቱ ተባባሪ ነን ብለው ፊርማቸውን ካኖሩ በኋላ ቦታችንን ለአንድ ባለሃብት ሰጥተነዋል መባሉ አሳፋሪ ነው›› በማለት ማዘናቸውን ይገልፃሉ። ቀበሌ ሄደው ሲጠይቁ ከላይ የመጣ ትዕዛዝ እንደሆነ ምላሽ ማግኘታቸውን የመሐመድን ቃል በሚያጠናክር መልኩ ነው የተናገሩት። ‹‹እየተሰራ ያለው ሥራ መንግስትና ህዝብን የሚያጋጭ በመሆኑ እስከላይ ድረስ ያሉ ባለስልጣናት እንደያውቁት እንፈልጋለን። እኛም ዜጋ ነን ባለሃብቱም ዜጋ ነው እኛም መስፈርቱን አሟልተን እንገነባለን አርሱም እየገነባ ነው ስለዚህ ፍትህ እንሻለን›› ሲሉ ያማርራሉ። እንደ አቶ ዘላለም ገለፃ ሊዝ ቦርድና ሊዝ ማህበረሰብ አመልክተው ጉዳያቸው እየታየ መሆኑን ገልፀው ‹‹የጎላጉል ትሬዲንግ ባለቤት በየጊዜው እያፃፉ የሚያሰለጥፉብን ማስጠንቀቂያ ጉዳያችን እልባት እንዳያገኝ እንቅፋት ሆኖብናል ይላሉ። አቶ ዘላለም ሲያክሉም ‹‹ጎላጉል

ትሬዲንግ ግንባታ ያካሄደበትን ቦታ ሲገዛ በምን መልኩ እንደሆነ ባልታወቀ ሁኔታ የእኛንም ቤት ከካርታ ጋር አካቶ ከወሰደ በኋላ አባቴን ጠርቶ 150 ሺህ ብር እሰጥሀለሁ፡፡ ቦታውን ልቀቅና ውጣ አለው›› ይላሉ። መንግስት ተነሱ ሳይል መነሳት እንደሌለባቸው ለአባታቸው ምክር ሰጥተው ለሥራ ከሄዱበት ሌላ አገር (ከኢትዮጵያ ውጭ) መጥተው ጠበቃ ገዝተውና ተከራክረው ቦታውን ያስመለሱበትን ሰነድ በእጃቸው ይዘዋል። ‹‹የእኛ ቤት ተካቶ ቢገነባ ኖሮ ህንፃው አሁን የያዘውን ቅርፅ አይዝም ነበር›› ያሉት አቶ ዘላለም የአባታቸው ቦታ ሲመለስ ህንፃው ከጀርባው ተጣሞ (ቅርፁ ተበላሽቶ) መሠራቱን አሳዩኝ። ‹‹እኔ መንግስት ዜጋን ከዜጋ ያበላልጣል

የሚል እምነት ስለሌለኝ ችግሩ ያለው ታች ካሉት በኩል ከሆነ በደላችንን ህዝብም መንግስትም ይስማው›› በማለት ሃሳባቸውን ቋጭተዋል።

የኃላፊዎቹ ምላሽበቦታው ላይ ተገኝቼ ተበደልን

የሚሉትን ሰዎች አነጋግሬና ቦታውን ተመልክቼ ስወጣ የቦሌ ክ/ከተማ ሥራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ አሳልፈውን፣ በክ/ከተማው የመሬት ልማት ባንክና መልሶ ማደስ ፕሮጀክት ዋና የስራ ሂደት መሪ የሆኑትን አቶ ጊዮንንና ከወረዳ 4 የመጡ አቶ ዮሴፍ የተባሉትን ሰው አግኝቼ ላናግራቸው ሞክሬያለሁ ሆኖም ‹‹ቢሮአችን መጥተሽ ካልሆነ እዚህ ልታናግሪን አትችይም›› የሚል ምላሽ ስለሰጡኝ በእለቱ ሳይሳካልኝ ቢቀርም ቢሮአቸው ድረስና በስልክ ሙከራ ባደርግም አልተሳካልኝም። ሆኖም ግንባታውን እንዲያቆሙ ደብዳቤ በተደጋጋሚ የፃፉትን አቶ ሽመልስ ደጀኔን አነጋግሬያቸዋለሁ። አቶ ሽመልስ ደጀኔ በቦሌ ክፍለ ከተማ የወረዳ አራት ዋና ሥራ አስኪያጅ ናቸው። በመልሶ ማልማቱ ሂደት ሰዎች ማልማት ከቻሉ ቅድሚያ እንደሚሰጣቸው የወጣ መመሪያ አለ። በዚህ መሠረት የግንባታ ፈቃድ አውጥተው እየገነቡ ያሉት እነ አቶ ኩመል እንዴት ግንባታ እንዲያቆሙ ተደረገ? በማለት ከአውራምባ ታይምስ ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ በመልሶ ማልማቱ ሥራ ሁለት ዋና ዋና ነገሮች እንዳሉ በመግለፅ ነበር ምላሻቸውን የጀመሩት። አነዚህ ሁለት ነገሮች አንደኛ የኪስ ቦታ ልማት መመሪያ እና ሁለተኛው የመልሶ ማልማት መመሪያ ናቸው። የኪስ ቦታ ልማት መመሪያ ለባለ ይዞታዎች ቅድሚያ ይሰጣል የመልሶ ማልማት መመሪያው ደግሞ ለባለይዞታዎች ቅድሚያ አይሰጥም አንደ አቶ ሽመልስ ገለፃ። በኪስ ቦታ ልማት ላይ ህብረተሰቡን በማወያየት ወደ ትግበራ እንደገቡ የሚናገሩት አቶ ሽመልስ አሁንም በኪስ ቦታ ልማት ፕሮጀክት ውስጥ ያሉት ቅድሚያ እንደሚሰጣቸው ያረጋግጣሉ። የእነ አቶ ኩመልን ጉዳይ በተመለከተ ሲመልሱ ምንም እንኳ አሁን የተጠቀሰው ቦታ በኪስ ቦታ ልማት ውስጥ የሚገኝ ቢሆንም የከተማ አስተደደሩ ሊዝ ቦርድ የከተማዋን ገፅታ ሊቀይሩ ለሚችሉ ልማቶች የሚያቀርቡት ፕሮጀክት ታይቶ በአካባቢ ሊዝ ዋጋ መሬትን በሊዝ የሚያስተላልፍበት በአዋጅ የተሰጠው ሥልጣን እንዳለ ያብራራሉ። ሲያክሉም ደረጃውን ለጠበቀ ትምህርት፣ አለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የጤና ሴክተር፣ አለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ እና የውጭ ቴክኖሎጂን ይዘው ለሚገነቡ ባለ አምስት ኮከብ ሆቴሎች እና ለመሳሰሉት የሊዝ ቦርዱ ለከተማዋ የሚያመጡትን ገፅታ ግምት ውስጥ በማስገባት ቦታዎችን አዘጋጅቶ የመስጠት በአዋጅ የተሰጠው ስልጣን እንዳለው ያብራራሉ። ‹‹የእነ አቶ ኩመል ቦታ የግንባታ

ፈቃድ አውጥተው ግንባታውን ጀምረዋል ህጋዊ አይደሉም ማለት

ነው?›› ለሚለው የአውራምባ ታይምስ ጥያቄ እነ አቶ ኩመል በ25/07/2000 ዓ.ም የግንባታ ፍቃድ ቢያወጡም ግንባታውን ማጠናቀቅ የነበረባቸው በ25/07/2003 ዓ.ም እንደነበረ የሚገልፁት የወረዳው ሥራ አስኪያጅ የግንባታ ፈቃዱ ያለፈበት ግንባታ እያካሄዱ መሆናቸውን ይናገራሉ። ‹‹ሌላው ቀርቶ የግንባታ ፈቃዳቸውን እንኳን አላደሱም›› ይላሉ አቶ ሽመልስ። አርሳቸው ይህን ይበሉ እንጂ እነ አቶ ኩመል በበኩላቸው የግንባታ ጊዜው ማለፉን አምነው ፈቃዱን ለማደስ ቢጠይቁም ከ50 ሜትር ገባ ብለው ላሉ ግንባታዎች አዲስ መመሪያ እስኪመጣ ፈቃድ ማደስ እንደማይቻል ምላሽ ማግኘታቸውን ያስታውሳሉ። ግንባታውን ‹‹አስቁሙ ያላችሁ አካል ማን ነበር ስል አቶ ሽመልስን ጠይቄያቸው ሲመልሱ ጎላጉል ትሬዲንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ለግንባታ ማስፋፊያ ባቀረቡት ፕሮጀክት ምክንያት የሊዝ ቦርዱ ተስማምቶበት ቦታው እንዲሰጣቸው መወሰኑንና ከወሰኑት የቦርዱ አባላት መካከል ደግሞ ከንቲባ ኩማ ደመቅሳም እንደሚገኙበት ገልፀዋል ይህንንም ከስማቸውና ከፊርማቸው ለመረዳት ችለናል። የህንፃ ከፍታው ዝቅተኛው አምስት

(G+5) ከፍተኛው ስምንት (G+8) እንደሆነ ጠቁመው የአካባቢው የህንፃ ከፍታ ማስተር ፕላን በየጊዜው የሚታደስ በመሆኑ በአሁኑ ሰዓት ዝቅተኛ 13 (G+13) ከፍተኛው 21 ፎቅ (G+21) በመሆኑ እነ አቶ ኩመል የሚገነቡት አራት ፎቅ (G+4) አሁን ካለው ፕላን ጋር ፈፅሞ የማይገናኝና የከተማዋን ውበት የማይጠብቅ እንደሆነ ሲናገሩ እነ አቶ ኩመል በበኩላቸው ‹‹እኛ ዝቅተኛው G+5 ከፍተኛው G+8 እንደሆነ ስለምናውቅ እየገነባን ያለነው G+5 ነው›› ካሉ በኋላ ውሃ ልማት አካባቢ እንደ እነርሱ አይነት ቦታ ላይ አምስት ፎቅ ተፈቅዶላቸው እየገነቡ እንደሚገኙ ይገልፃሉ። አቶ ሽመልስ ደግሞ የከተማው አስተዳደር ለከተማዋ ውበት ደረጃ ሲባል እስካመነበት ድረስ በኪስ ቦታ ልማት ላይ ያሉም ቢሆን በሊዝ የመስጠት ሥልጣን እንዳለው ይናገራሉ። ስለሆነም እነ አቶ ኩመልን ጨምሮ ሌሎች ቤቶችን የሚያካትት 667 ካ.ሜ ቦታ ለፓርኪንግ አገልግሎት የሚውል ሆኖ በመገኘቱ ለጎላጎል ትሬዲንግ እንዲሰጠው መወሰኑን ያብራራሉ። እዛ ቦታ ላይ ሌሎች ግለሰቦችም ሆነ እነ አቶ ኩመል 13 ወይም 21 ፎቅ እስካልገነቡ ድረስ ቦታው በሊዝ ቦርድ ተወስኖ ተሰጥቷል ባይ ናቸው። የሁለቱንም ወገኖች ሃሳብ በዚህ መልክ ተመልክተን ስንጨርስ የክፍለ ከተማውን የመሬት ልማት ባንክና መልስ ማደስ ፕሮጀክት ኃላፊ የሆኑትን የአቶ ጊዮንን ሃሳብ ለማካተት ቢሮ ነይ ባሉኝ መሠረት በተደጋጋሚ ብመላለስም፣ ስልክ ብደውልም ሆነ መልዕክት ባስቀምጥ ላገኛቸው ባለመቻሌ በዚህ ዘገባ ውስጥ ሃሳባቸውን ማካተት አልተቻለም።

ተበዳዮች:-

‹‹መንግስት ዜጋን ከዜጋ ያበላልጣልን››ተ ጠ የ ቅ

በኪስ ቦታ ልማት ላይ ህብረተሰቡን በማወያየት ወደ ትግበራ እንደገቡ

የሚናገሩት አቶ ሽመልስ አሁንም በኪስ ቦታ ልማት ፕሮጀክት ውስጥ ያሉት ቅድሚያ እንደሚሰጣቸው ያረጋግጣሉ። የእነ አቶ

ኩመልን ጉዳይ በተመለከተ ሲመልሱ ምንም እንኳ አሁን የተጠቀሰው ቦታ በኪስ ቦታ ልማት ውስጥ የሚገኝ ቢሆንም የከተማ አስተደደሩ ሊዝ ቦርድ የከተማዋን ገፅታ ሊቀይሩ ለሚችሉ ልማቶች የሚያቀርቡት

ፕሮጀክት ታይቶ በአካባቢ ሊዝ ዋጋ መሬትን በሊዝ የሚያስተላልፍበት በአዋጅ የተሰጠው

ሥልጣን እንዳለ ያብራራሉ።

እንዲፈርስ የተደረገው ህንፃ

የጎላጉል ትሬዲንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ ይዞታ

Page 15: Awramba Times Issue 179

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 179 ቅዳሜ ሐምሌ 30/ 2003

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

15ማ ስ ታ ወ ቂ ያ

እንዲፈርስ የተደረገው ህንፃ

Page 16: Awramba Times Issue 179

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 179 ቅዳሜ ሐምሌ 30/ 200316

ደግሞ ‹‹በፖለቲካ ምክንያት ነው›› ይባላል።

ላነሳ የነበረውን ጥያቄ ቀደሙኝ መሰለኝ . . . የቀድሞ መከላከያ ሚኒስቴር ሚኒስትር የነበሩት አቶ ስዬ አብርሃ፣ በሕወሓት ውስጥ በተፈጠረ የፖለቲካ ልዩነት “ተነጥለው ሊመቱ ታስቦ፣ የጸረ ሙስና ኮሚሽን ተመሰረተ የመጀመሪያ ሰለባም እርሳቸውና አብሮአቸው የታሰሩ ሰዎች ሆኑ” ተብሎ ይገለፅ ነበር።

አዎ። ይሄ እንግዲህ ብዙ ጊዜ ሕብረተሰባችን በዚህ በኩል ይቅርታ አለው። አንድ ባለስልጣን ከስልጣን ሲወርድ የሕዝቡ ልብ ይራራል። [እየሳቁ] አስታውሳለሁ፣ የደርግ ባለስልጣናት ላይ ክስ በተመሰረተበት ወቅት ሰዎች፣ ‹‹ባለፈው ጉዳይ ላይ ምንድን ነው ስንመላለስ የምንገኘው?›› ይሉ ነበር። ይቅርታ መኖሩ ጥሩ ነው። ነገር ግን መመዘን ያለበት እንደሕግ ባለሙያ ‹‹ያስከስሳል/አያስከስስም?›› የሚለው ነው። በስሜት ላይ ብቻ መሆን አያስፈልግም። ጉዳዩ በፍርድ ቤት ክስ ተመስርቶና በማስረጃ ተደግፎ በግልፅ አደባባይ ክርክር የተደረገበት ሲሆን እንዲህ አይነት ነገር የሚነሳው ሰው እንደፈለገ ስለሚተረጉመው ነው። … ለማንኛውም ትልልቅ ባለስልጣናትን አልከሰሳችሁም አንባልም። ሌላ ትርጉም ቢሰጠውም ተከስሰዋል። ወደፊትም ደግሞ የኢንተለጀንስና የሰርቬይላንስ አቅማችንን አጠናክረን እንሰራለን። ሕብረተሰቡ ደግሞ እኛን ለመታዘብ ትልልቅ ጉዳዮችን በትልልቅ ሰዎች ላይ አምጥቶልን ‹‹ወድቃችኋል›› ቢለን ሌላ ጊዜ ወቀሳውን እንቀበላለን።

ግን እኮ . . . የአቶ ስዬ ጉዳይን በተመለከተ . . . [ጥያቄዬን ሳልጨርስ]

[ፈጠን ብለው] እሱን ብትተወው ጥሩ ነው። የሞተና ብዙ የተባለለት ጉዳይ ስለሆነ አይጠቅምም። ወደሌላም ትርጉም ሊወስድ ስለሚችል።

ስለዚህ ተቋማችሁ በትልልቅ ባለስልጣናት ላይም መረጃ ካገኘ በገለልተኝነት ከሶ ለማስፈረድ ወደኋላ አይልም እያሉኝ ነው?

በእኛ በኩል አዎን። ለምንድን ነው የምንፈራው!? በሀገሪቱ ውስጥ ያለ አንድ ከፍተኛ የመንግስት አካል/ባለስልጣን፣ እስካሁን ድረስ ባካሄድናቸው ምርመራዎችም ሆነ በምናከናውናቸው ክሶች ላይ አንድም ቀን ጣልቃ ተገብቶ ‹‹ለምን እንዲህ አደረጋችሁ?›› ብሎን አናውቅም። እኛ ምንም ምክንያትና መረጃ ካገኘን ማንንም ከመመርመርና ከመክሰስ የሚያግደን፣ የሚያሰጋን፣ የሚያስፈራን አጋጣሚና ጫና የለብንም - አሁን የምናገረው ቃል የሚታመን ከሆነ። ይኼ አለመኖሩን ለማረጋገጥ እንደገለፅኩልህ ሰው ጠንካራ ጥቆማ ይስጠንና ‹‹በዚህ መንገድ አልመረመራችሁም›› ይበለን። ጉዳዩ የሚያስከስስ መሆን/አለመሆኑን ካወቅን ምን ያስፈራናል? የመንግስት ግልፅ አቋም አለ። ሙስናና ብልሹ አሠራርን ለመዋጋት ምንም አይነት ርህራሄ መንግስት እስከሌለው ድረስ በእኛ በኩል ማንን እንፈራለን ብለህ ነው?

ባለፈው ሳምንት (ሐምሌ 23/2003 ዓ.ም) የተቋማችሁን 10ኛ ዓመት የምስረታ ክብረ-በዓል አክብራችኋል። በዕለቱ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ በእነዚህ ዓመታት ውስጥ በሥራ ስኬታማ እንደነበራችሁ ገልፀዋል። በእርግጥ ስኬታማ ነበራችሁ?

“Well” . . . በእኛ ዕይታ እንደ ጀማሪ ተቋም ስኬታማ ነበርን። ረዥም ዓመት ያስቆጠሩ ተቋማት አሉ። ለእኛም ከእነዚህ 10 ዓመት ውስጥ ሁለቱ አሠራርና አካሄድን የምንቀምርበት፣ ልምዶችን የምናገኝበት የመደራጃ ጊዜያት ነበሩ። በዚያ ጊዜ ውስጥ የወሰድናቸው ስለሙስና የማስተማር፣ የመከላከልና የሕግ ማስከበር ስራዎች ቁጥራቸው ብዙም አይደሉም። የሕዝብ ትብብር ለማግኘትም ጊዜ ይፈጃል። በተለይ በመጀመሪያዎቹ ዓመታት ኮሚሽኑ ተቀባይነትና የሕዝብ ድጋፍ እንዳያገኝ የተሰሩ አሉታዊ ቅስቀሳዎች ነበሩ። ያንን ሁሉ በመቋቋም ታልፏል። ከዛም በኋላ ወደተሻለ እንቅስቃሴ ተገብቷል።በትልቅ ዕቅድነት ይዘን የገባነው ሙስና ለሀገር ልማት፣ ለዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ እንቅፋት መሆኑንና ጠንክረን ልንዋጋው የሚገባ መሆኑን ለሕብረተሰቡ ማስተማር ነበር። ሕብረተሰቡም ሙስና ለሀገር ዕድገት፣ ልማት እና ብልፅግና የማይበጅ መሆኑን አውቆ የመከላከል ሥራ መስራት የሚገባው መሆኑ ሌላኛው የዕቅዳችን አካል ነበር። የሀገራችን ነባሩ መልካም ሥነ-ምግባር እንዲመለስ፣ ሙስናና ብልሹ አሰራር እንዲወገዱ ሰፊ ትምህርት ተሰጥቷል። ሁሉንም የሚዲያ አውታሮች ተጠቅመናል።እያንዳንዱን ፖለቲከኛ የሚፈትነውን ሙስና ምን ያህል ተዋግተዋል? የሚለው ጥያቄ አንዱ የእኛ የስኬት ምልክት ነው። ሁለተኛው፣ ሙስናን በተመለከተ ጥቆማና ምስክርነት ለመስጠት ቀደም ሲል በጣም ይሰጋና ይፈራ የነበረ የሕብረተሰብ ክፍል ዛሬ በራስ መተማመን ላይ ተመርኩዞ ሙሰኞችን በማጋለጥና በእነሱ ላይ በመመስከር የተሻለ ትብብር አድርጓል። በሦስተኛ ደረጃ ቀደም ሲል የነበሩ የሙያና የበጎ አድራጎት፣ የወጣቶችና የብዙሃን ማሕበራት፣ እንዲሁም ሌሎች አካላት ከመንግሥት ውጪ ባሉ አደረጃጀቶች አሁን በፀረ-ሙስና እንቅስቃሴ ላይ የድርሻቸውን ለመወጣት ተደራጅተው ተንቀሳቅሰዋል። በምድራዊ ሕግ የተጠላው ሙስና፣ በመንፈሳዊ ሕግም የተጠላና የተወገዘ መሆኑን የሃይማኖት ተቋማት ለተከታዮቻቸው ማስተማራቸውም ሌላኛው የስኬት መገለጫ መሆኑን አምናለሁ።

በየመንግስት መስሪያቤቶች ሙስናን ለመዋጋት የሚያስችል ጠንካራ እንቅስቃሴ እየተካሄደ ይገኛል ማለት እንችላለን?

በየመንግሥት መሥሪያ ቤቱ ሙስናን ለመዋጋት እንቅስቃሴ ተጀምሯል። በየተቋማቱ ያለው የቢዝነስና የግዥ አያያዝ ለብልሹ አሰራርና ለስራቆት አመቺ ነው ወይ? የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ ጥናት እየተጠና ችግር ያለባቸው እንዲስተካከሉና አፈፃፀሙን በመከታተል የማስተካከያ ሀሳቦችን በአግባቡ መዋላቸውን እየተከታተልን ነው። በሕግ ማስከበርና በማስፈፀም በኩል ጥሩ ሥራ ሰርተናል ብለን እናምናለን። በተለያዩ ጥናቶችና በመሬት ወረራ ላይ ብዙ ነገሮች ተሰርተዋል። በዚህም ሕገ-ወጥነት ተገትቷል። ከጉምሩክ፣ ከገቢዎችና ከኮንትሮባንድ ሕገ-ወጥ ድርጊቶች ጋር ተያይዞ የተፈረደባቸው ግለሰቦች በርካቶች ናቸው። በቅርቡም የመንግሥት ባለሥልጣናትን፣ ሹመኞችን፣ ሰራተኞችና ሌሎች የሚመለከታቸውን አካላት ኃብት ከ50 በመቶ በላይ ማሳወቅና ምዝገባ ተደርጓል። ምዝገባው እንዳለቀ ለሕዝብ ይፋ ይሆናል። ከዛ እውነተኝነቱን የማረጋገጫ ሥራ እንሰራለን፣ ንብረትም እናጣራለን።

ከሙስና ክሶችና ከፍርድ ሂደት ጋር በተያያዘ የሚያዙ የተለያዩ ንብረቶች ተይዘው ለረዥም ጊዜ ካለአንዳች ግልጋሎት ይቆያሉ። ይህ ችግር መኖሩን ያምናሉ?

ልክ ነው፤ ችግር አለ። እኛ በወቅቱ ንብረቶች ዕግድ እንዲያገኙ እናደርጋለን። በሙስና የሚኖረው ሁለት ዓይነት ኃብት ነው፡- በቀጥታ የሙስና ውጤት የሆነና በሙስና በተገኘ ገንዘብ የሚፈጠር ነው። ለምሳሌ መሬት ስናሳግድ የሙስና ውጤት ነው እንላለን። ነገር ግን ሙሰኛው ኃብት አፍርቶና ገንዘብ ዘርፎ የገዛቸው ቤቶች፣ ተሽከርካሪዎችና ሌሎች የተለያዩ ንብረቶችና ጌጣጌጦች ይኖራሉ። መጨረሻ ላይ ፍርድ ከተሰጠ በኋላ የሕዝብ ኃብት መመለሱን ማረጋገጥ ስላለብን ሙሰኞችን ከማሳሰር ባለፈ የተያዙ ንብረቶች በፍርድ ቤት ውሳኔ እንዲመለሱ እናደርጋለን። ‹‹ይወረሱ›› ተብለው ውሳኔ የተሰጠባቸው ሀብቶች፣ ንብረቶች እና እቃዎች ተሽጠው ለመንግሥት ገቢ ይሆናሉ። ለምሳሌ መሬት እንዳለ ተመላሽ ይሆናል። ከዚህ አንፃር ምዝበራው የተካሄደባቸው የመንግሥት ተቋማትም በጉዳዩ ላይ ፍላጎት አላቸው። ኃብቱ የሚመለስላቸው ለእነሱ ነው። ነገር ግን፣ በተለያዩ ጉዳዮች በወቅቱ ውሳኔና ንብረቶቹም ቶሎ ውርስ ካለማግኘታቸው ጋር ተያይዞ ኮሚሽኑ በዚህ ጉዳይ የልምድ ማነስ ችግሮች አሉበት። አሁንም እንደምታየው ግቢያችን ውስጥ በርካታ ተሽከርካሪዎች ይገኛሉ። ለሰዎቹ እንዳንመልስ ችግሩ ከጥቅም ውጪ ያደርጓቸዋል። ስለዚህ መጨረሻ ላይ የምንተካውን እናጣለን ብለን እንሰጋለን። በተለይ በመጀመሪያው የኮሚሽኑ ሥራ ተሞክሯችን የክስ መዛግብት ጋር ተያይዞ በርካታ ሀብቶች ተከምረው ነበር። እነዚህን ሀብቶች የማስተዳደሩ ሥራ ውጤታማ ሆኖ አላገኘነውም። ተከሳሾችም ነፃ ወጥተው ንብረታቸው ሲመለስላቸው በተገቢው ሁኔታ ሳያገኙት ቀርተዋል። ለመንግስት ይሰጥ ሲባል ደግሞ ተገቢ ሆኖ አልተገኘም። ስለዚህ ያ ችግር አለ። ይኼንን አይነት ሥራ የሚሰራ የግልም

ሆነ መንግስታዊ ተቋም አለመኖሩ ችግር ነው። ተሽከርካሪዎችን እያሰራ ገቢያቸውን በልዩ አካውንት እያስቀመጠ በራሱ ኃላፊነት እንደ ባለቤት ሆኖ የሚሰራ ተቋም ቢኖር ይኼን ሁሉ ችግር ይወገድ ነበር።

በአንዳንድ ክልሎች በመንግስታዊት ኃላፊነት ላይ የተመደቡ ባለሥልጣናት ከሙስና ጋር በተያያዘ ከኃላፊነታቸው ተነስተው አካባቢያቸውን በመቀየር በሌላ ቦታ እንደሚሾሙ፣ ምርጫ እንደሚወዳደሩና የመንግስት አማካሪ እንደሚሆኑ ይነገራል። ሰዎቹ ሹመት ሲያገኙም ሆነ ምርጫ ሲወዳደሩ ከሙስናና ከሥነ-ምግባር ችግሮቻቸው ጋር ነው። ይሄ ማሕበረሰቡንና በአጠቃላይ ሀገርን ክፉኛ አይጎዳም? ኮሚሽኑስ ችግሩን እንዴት ያየዋል? መፍትሄውስ?

ከሁሉም በላይ አንድ ሿሚ አካል ከመሾሙ በፊት የሚሾመውን ግለሰብ/የታጨውን ሰው ምንነት ለይቶ ማወቅ አለበት። … ‹‹ግለሰቡን ወደሕዝብ ላቀርበው ነው፤ ብሾመው ያለፈ የታሪክ ሪከርዱ ምን ይመስላል? ሕዝቡ ይቀበለኛል/አይቀበለኝም? መንግስትስ ይቀበለዋል/አይቀበለውም?›› ብሎ አርቆ ማሰብ ይገባዋል። ስለዚህ በተለይ ከሙስና ጋር ንክኪ ያላቸውን ሰዎች ቦታ አዘዋውሮ በመሾም ችግሩን ልትፈታው አትችልም። … በምርጫ ረገድ እንደምረዳው በየደረጃው የሚያጣሩ አካላት አሉ። ከእነዚህ አንዱ የማጣራት ኃላፊነት የተጣለባቸው ሰዎች በሥነ-ምግባር ጉድለትና በሙስና መካከል ያለውን ልዩነት ነው። በአጣሪዎችም ዘንድ በተመሳሳይ መልኩ የሥነ-ምግባር ግድፈትና የተጣለባቸውን ኃላፊነት በብቃት ያለመወጣት ችግር አለ።በመንግስት ፖሊሲና አቅጣጫ ኮሚሽኑም በሚቀበለው መንገድ ከሙስና፣ ከብልሹ አሠራርና ከሥነ-ምግባር ግድፈት ንኪኪ ወይም ችግር ውጪ የሆነ ሰው ለሕዝብ ምርጫና ለመንግስታዊ ኃላፊነት እንዲቀርብ እንፈልጋለን። እኛ ሰው ስንቀጥር ስለተቀጣሪው ያለፈ ታሪክ አጥንተን ነው። ስናጠናም በሰዎች ምስክርነት ላይ እንንተራሳለን። በእነሱ እውነተኝነትና ታማኝነት ላይ እንመሰረታለን። የምንጠይቃቸው ሰዎች ታማኝ ናቸው ብለን እናምናለን፣ እንገምታለን። ይኼ ትክክለኛ አስተሳሰብ ነው። ኢትዮጵያ የጋራ ሀገራችን ናት። የምንጠቀመውም የምንጎዳውም በጋራ እንደመሆኑ፣ ለምንሰጠው ምስክርነት ኃላፊነት የሚሰማን ከሆነ ሌባን ‹‹ሌባ ነው›› ብለን መናገር አለብን። ስለዚህ ምስክርነት የሚሰጠውም ሆነ የሚያጣራው ሰው ሁሉ በኃላፊነት ስሜት ተንቀሳቅሰው የሚሄዱ ከሆነ በሙስናና በብልሹ ሥነ-ምግባር የተበከለን ሰው ለኃላፊነት ቦታ ማጨት ተገቢ ነው ብለን አናምንም። መወገድ ያለበት ነገር ነው። ያልከው ተደርጎ ከሆነ ስህተት ነው። የሁሉም ሰው የማጣራት ሂደት ገደብ አለው። የዚህ ችግር ይኖራል። እኛ እንደ ኮሚሽን የሥነ-ምግባርና ብልሹ አሠራር በሙስና መጥፎ ስም ያለው ሰው በመንግስት ኃላፊነት ቦታ መመደብ አለበት ብዬ አልልም። ይኼ ሰውዬ ከነችግሩ ቢመደብ ያን ክፉ ሥራውን ከማስፋፋትና ተቋማዊ ከማድረግ ያለፈ ሥራ አይሰራም። እንዲያውም ንፁሃን ሰዎችን ከማጥፋት ያለፈ ውጤታማ፣ መንግስትና ሕዝብን የሚያቀራርብ ሥራ ይሰራል ብዬ አላምንም።

በተቋሙ ነፃነትና ገለልተኝነት ላይም ጥያቄ ይነሳል። ‹‹ኮሚሽኑ ተጠሪነቱ ለፓርላማው መሆን ሲገባው ለጠቅላይ ሚኒስትሩ መሆኑ በነፃነቱ ላይ ችግር ያመጣል፤ በአስፈፃሚው አካል ተፅዕኖ ስር ስለሚወድቅም ገለልተኝነቱ አደጋ ውስጥ ነው›› የሚሉ ወገኖች አሉ፡፡

ይሄ የሌሎች ሀገራትን የፀረ-ሙስና ተቋማት አደረጃጀት ካለማወቅ የሚነሳ ይመስለኛል። ምክንያቱም ሁለቱም አማራጮች ይሰራባቸዋል። በጣም ውጤታማ ናቸው የሚባሉት ተቋማትን ብናይ በአስፈፃሚው አካል ስር ያሉት ናቸው። ይሄም ምክንያታዊ ሲሆን አንድን መንግስት ‹‹ሙስናን ተዋግተሃል/አልተዋጋህም?›› የሚለው በስልጣን ላይ ያለን መንግስት ነው። ስለዚህ ያ መንግስት ሙስናን ለመዋጋት መሳሪያ ያስፈልገዋል። መሳሪያውን ከእጁ ነጥቀህ ሙስናን ተዋጋ ብትለው የሌላውን ሰው ስራ ነው የምትሰራው።

ስለዚህ አሁን ስልጣን ላይ ያለው መንግስት ከሌሎች ሀገራት ለየት የሚያደርገው ይኼንን ኮሚሽን ያቋቋመው ያለአንዳች ዓለም አቀፋዊና ሀገራዊ ግፊት ነው። ኮሚሽኑ ሲቋቋም በርካታ ሀገራት ተጠንተዋል። በወቅቱ የነበሩን ሰነዶች ስናያቸው ከፊሎቹ በጣም በከፍተኛ ሁኔታ በሙስና ተዘፍቀው የነበሩና በኋላም ከችግራቸው የወጡ ሀገራት ናቸው።

በዚህ ረገድ ምሳሌ ማቅረብ ይቻላል? ማለቴ ተጠሪነታቸው ለአስፈጻሚው አካል እንዲሆን ተደርጎ የተደራጀ የጸረ ሙስና ተቋም ያላቸው አገሮች አሉ?

ምሳሌ ለመጥቀስ ያህል ሆንግ ኮንግ፣ ማሌዥያና ኮሪያ ይጠቀሳሉ። በሌላ በኩል ደግሞ በአደረጃጀታቸው ለየት ያሉ የምዕራብ አውሮፓ ሀገራትም ታይተዋል። ስለዚህ ለእኛ ይበልጥ ኮሚሽኑን ውጤታማ ያደርገዋል ተብሎ የታሰበው የሆንግ ኮንጉ ሲሆን ሀገሪቷ በዓለም ላይ በሙስና ምዝበራ የተጎሳቆለች ነበረች። ከ20 ዓመታት በፊት የእነሱ ጥናት የተጀመረው በፖሊስ አካባቢ በነበረው የሙስና እንቀስቃሴ ላይ ‹‹ምን እናድርግ?›› ተብሎ በጥናት ውጤታማ ሥራ ስለተሰራ የሆንግ ኮንግ ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ተቋቁሟል። ተጠሪነቱ ለመንግስት አስፈፃሚ አካል ነው። ይኼም ዋጋ ሳያሳጣው በዓለም መድረክ ላይ እየተጠራ ልምድህን አካፍል የሚባል ትልቅ ተቋም ሆነ። በማሌዥያና ሲንጋፓርም የተቋሞቹ ተጠሪነት ለጠ/ሚ/ሩ ነው። ስለዚህ እነዚህን ከችግር ያወጣው አደረጃጀት የትኛው ነው ተብሎ ነው የተወሰደው።

እያንዳንዱ አገር የየራሱ የሆነ ተጨባጭ ሁኔታ አለው፡፡ በእኛ አገር ነባራዊ ሁኔታ የሆንግኮንግ ልምድ ኢትዮጵያ ላይ በትክክል ለመስራቱ ምን ማረጋገጫ አለ?

የእኛ አደረጃጀት ያልታየ ሳይሆን ታይቶ ውጤታማ የሆነ ነው። ይኼንን መጠቀም ይበልጥ ውጤታማ ሥራ እንድንሰራ ያስችለናል ብለን እናምናለን። ለምሳሌ አሁን ባለን አካሄድ የሙስና መከላከልን፣ የመንግስት ተቋማትና መ/ቤቶችን … የተመለከቱ ጉዳዮች ላይ ግፊት የምናደርገው ዓመት ጠብቀን ለፓርላማ በምናቀርበው ሪፖርት ሳይሆን በአስፈፃሚው ጉልበት ነው። ስለዚህ ለእኛ ይበልጥ ተግባራዊ የሆነ ድጋፍ ወይም ጉልበት የሚሰጠን በሀገራችን ተጨባጭ ሁኔታ ተጠሪነቱ ለአስፈፃሚው ወይም ለጠ/ሚኒስትሩ መሆኑ ሲሆን ይኼም ተገቢነት አለው። ገለልተኝነታችንን አልነፈጉንም። በአዋጁ ላይ በግልፅ እንደተቀመጠውና ለገለልተኝነት አስፈላጊ መሠረቶች ምንድናቸው ብለን ስናስብ አንዱ በቂ በጀት ነው። ግልፁን ለመናገር፣ አሁን ባለው ሁኔታ ኮሚሽኑና እኛ የምንወቀሰው የዓመት በጀታችንን አስተርፈን በመመለስና የተመደበልንን በጀት በሙሉ ባለመጠቀማችን ነው እንጂ የበጀት እጥረት ገጥሞን አያውቅም። በሁለተኛ ደረጃ ሕጉ ተቋሙ ራሱን ችሎ ተቋቁሟል ይላል። በግልፅ እንደተገለፀው ማንም አካል በኮሚሽኑ የምርመራና የክስ ሂደት ላይ ጣልቃ መግባት እንደማይችል የሕግ ከለላ ተቀምጧል። ሌላው ደግሞ የኮሚሽኑን ኮሚሽነር ወይም ኃላፊውን በስልጣን የማቆየት ነገር ነው። ኮሚሽነሩ በጠ/ሚ/ሩ ቢሾምም ከስልጣኑ የመነሳት ስርዓት እንደሌለው አካል እንደተፈለገ የሚሆን አይደለም። በቂ የሆነ ማብራሪያ ለፓርላማ ይቀርባል። ለነፃ ዳኞች የተሰጠው ዓይነት ሕጋዊ አደረጃጀት ለኮሚሽነሩም ተሰጥቷል። እነዚህን ነገሮች ስታያቸው የአንድ ተቋም የነፃነቱ መጠበቂያዎች ናቸው። ለእኛ ሁሉም ተሟልተው ተገኝተዋል። በጠ/ሚ/ሩ ወይም በመንግስት ግፊት ‹‹እንዲህ አይነት ምርመራ እንዲቀር›› ተብሎ የተገለፀ ነገር የለም። ይኼንን የሚያውቁ አካላት አሉ። በግፊት ‹‹ምርመራ ወይም ክስ እንድታነሱ ተደርጋችኋል›› ተብለን ብንወቀስ ደግሞ የበለጠ ተጨባጭ ይሆናል። በነፃነት በኩል የምናቀርበው ቅሬታ የለንም። ድክመት በእኛ በኩል ኖሮ፣ ‹‹ይገምገም ወይም ይነሳ›› የሚባል ነገር ከሌለ በስተቀር የሌላ አካል የተቋረጠ ወይም ሥራ እንዳንሰራ የተደረግንበት ነገር የለም።

‹‹ጠ/ሚኒስትሩን ለመክሰስ . . .

በ ገፅ 20

Page 17: Awramba Times Issue 179

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 179 ቅዳሜ ሐምሌ 30/ 2003

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

17 ል ዩ ቅኝት

መንዙማ… ሌላኛው የኢትዮጵያ መገለጫ ቅዱስ ረመዳን መግባቱን ተከትሎ በስፋት ከሚስተዋሉ ነገሮች ውስጥ መንዙማ አንዱ ነው።

ሱራፍኤል ግርማ ያዘጋጀው ተከታዩ ጽሁፍ ይህ ፍጹም ኢትዮጵያዊ የሆነው ጥበብ አደጋ እንደተጋረጠበት ያሳያል።

አሰላም አሌይክ ያ ሸምሰል ሁዳ አሰላም አሌይክ ያ ሸምሰል ሁዳ

ሙስጠፋ ተያረን ነዳ።ለመንኩህ ሶመድ በአህመድ ሙሀመድ …

በኢስላማዊ የዘመን መቁጠሪያ ውስጥ ዘጠነኛ ወር የሆነው ረመዳን፣ ለ23 ዓመታት ከአላህ ወደ ነብዩ መሐመድ ቅዱስ ቁርዓን መውረድ የጀመረበት በመሆኑ በእስልምና ተከታዮች ዘንድ ቅዱስ ነው። ቅዱስና የትዕግስት ወር

በሆነው ረመዳን በስፋት ከሚስተዋሉ ኹነቶች ውስጥ ደግሞ አንዱ መንዙማ ነው።

‹‹መንዙማ›› ቃሉ የአረብኛ ሲሆን፣ በጥሬ ትርጉሙ ‹‹ቃላትን በጥሩ ሁኔታ ማስቀመጥ›› የሚል ፍቺ ይሰጣል። ጥሬ ትርጉሙ በደንብ ሲብራራ ደግሞ ቆንጆ መልዕክትን ለማስተላለፍ የሚያገለግል ግጥም ይሆናል። በኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ ደግሞ መንዙማ ከግጥምም በላይ ነው፤ ዜማ ተጨምሮበት አላህ የሚመሰገንበት፣ ነብዩ መሐመድ የሚሞገሱበትና የእስልምና ትምህርት የሚሰጥበት ጥበብ ነው።

መንዙማ እና ኢትዮጵያየመንዙማና የኢትዮጵያ ቁርኝት

የሚጀምረው ከእስልምና የመጀመሪያዎቹ ዓመታት አንስቶ መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ። ነብዩ መሐመድ በሕይወት በነበሩበት ወቅት በሳዑዲ አረቢያ መካ የነበሩ ሐበሾች (ኢትዮጵያዊያን) የአላህን መልዕክተኛ በመንዙማ ያወድሱ እንደነበር የሚያስታውሱት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ጥናትና ምርምር ተቋም መምህር አቶ ከማል አብዱልወሀብ ‹‹የሚገርመው ደግሞ ሐበሾቹ በራሳቸው ቋንቋ ነበር ውዳሴውን ያቀርቡ የነበረው›› በማለት የመንዙማን ፍጹም ኢትዮጵያዊነት መስክረዋል።

ሐይማኖታዊ ክዋኔን በመንዙማ በማጀብ የሚታወቁት ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች እንጂ በሌሎች ክፍላተ ዓለም ያሉ የእስልምና ተከታዮች አለመሆናቸውን የሚገልጹት አቶ ከማል፣ ከአትዮጵያ ውጪ ያሉ ሙስሊሞች ሐይማኖታዊ ክዋኔዎቻቸውን የሚያጅቡት ‹‹ነሺዳ›› በተባለ ዝማሬ መሆኑን ይናገራሉ።

የመንዙማንም ኢትዮጵያዊነት ‹‹ነሺዳ ቋንቋው አረብኛ ነው። መንዙማ ግን በኦሮምኛ፣ አደርኛ አማርኛ፣ ስልጢኛ ወዘተ ነው የሚባለው›› ሲሉ ከ‹‹ነሺዳ›› ጋር በማነፃፀር ሀሳባቸውን ያጠናክራሉ።

መንዙማ በኢትዮጵያ ውስጥ የተለያየ ስያሜ ያለው ሲሆን፤ በሐረር ‹‹ዚክሪ››፣ በባሌና አርሲ ‹‹ባሮ/ሰርመዴ›› በሚሉ መጠሪያዎች ይታወቃል። ነገር ግን ከመንዙማ ስያሜዎች ጋር በተያያዘ ሙስሊም ባልሆኑ ሰዎች ዘንድ አንድ የተለመደ ስህተት መኖሩን የዕምነቱ ተከታዮች አይሸሽጉም። የተለመደው ስህተትም በአረብኛ ሰላምታን የሚወክለው ‹‹ዝየራ›› የመንዙማ ሌላኛው ስያሜ ተደርጎ መወሰዱ ነው።

መንፈሳዊ ዝማሬው በትክክል በየትኛው የኢትዮጵያ ክፍል እንደመነጨ ባይታወቅም ወሎ ጥበቡ ያበባት፣ የጎመራባትና ፍሬዎችን ያፈራባት በመሆኗ ስለመንዙማ ሲታሰብ ይህች ስፍራ ወደ አዕምሮ ቀድማ ትከሰታለች።

በ18ኛው ክ/ዘመን ከእስልምና ክፍሎች ውስጥ አንዱ የሆነውን ሱፊ የሚከተሉ ሙስሊሞች ከሐረር ተነስተው ወሎ ይገባሉ። እናም አላህን ለመለማመንና ለማመስገን፣ ነብዩ መሐመድን ለማወደስ እንዲሁም ያለፉ ታላላቅ የሐይማኖት አባቶችን ለማስታወስ አንዳች መግነ-ጢሳዊ ኃይል ያለውን መንዙማ በመጠቀም የሚታወቁት ሱፊዎች ይህን ድንቅ ባሕላቸውን ወሎ ላይ አስፋፉት።

ከቅዱስ ረመዳን ጋርልዩ ቁርኝት አለውን?ምንም እንኳን ከሌላው ጊዜ በተለየ መልኩ

መንዙማ በወርሃ ረመዳን በርክቶ ቢደመጥም፣ ሐይማኖታዊ ሙዚቃው ከጾሙ ጋር ልዩ ቁርኝት እንደሌለው በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ጥናትና ምርምር ተቋም መምህር የሆኑት አቶ ከማል ገልፀውልናል። በአቶ ከማል ገለፃ መሠረት ረመዳን ሲገባ የመንዙማ ድምጾች በየአካባቢው የሚበረክቱትና የመንዙማ ካሴት ሽያጭም የሚደራው በዚህ ወር

ሙስሊሙ ሕብረተሰብ በይበልጥ ለሐይማኖታዊ ጉዳዮች ትኩረቱን ስለሚሰጥ ሁኔታውን ለመጠቀም ነው።

ከዚህ በተጨማሪ አውራምባ ታይምስ ያነጋገራቸው አንዳንድ የእስልምና ተከታዮች መንዙማን አስመልክቶ የተለየ ሐሳብ ሰንዝረዋል። ‹‹ረመዳን የፅሞና ጊዜ ነው፤ ስለዚህ የሚያስፈልገው ፀጥታና ፀሎት ብቻ ነው›› ያሉት አስተያየት ሰጪዎች፣ የመንዙማ ዘና የማድረግ ባሕርይ ከረመዳን ጋር አብሮ አለመሄዱን በምክንያትነት አቅርበዋል።

ከቅዱሱ ወር ይልቅም የነብዩ መሐመድ ልደት በሚከበርበት የሞውሊድ በዓል እና የአንድ አካባቢ ሰዎች በተወሰነ የጊዜ ልዩነቶች ተሰባስበው በሚተገብሩት ሐይማኖታዊ ክንውን (ወዳጃ) ላይ መንዙማ በስፋት እንደሚዘወተር አውራምባ ታይምስ ያሰባሰበችው መረጃ ያሳያል።

መንዙማ ለማነው የተፈቀደው?መንዙማ ራሱን የቻለ ጥበብ እንደመሆኑ

መጠን የተለያዩ ተሰጥዖዎችን ይፈልጋል። የመጀመሪያውና ወሳኙ መንፈሳዊ መሆንና ግጥም ማፍለቅ ሲሆን፣ ሌላኛው ደግሞ በግሩም ሁኔታ የተሰናዳውን ግጥም ጆሮ ገብ በሆነ ድምፅ አሳምሮ ማዜም ነው።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ በአሁኑ ሰዓት የሚደመጡትና የእስልምና ዕምነት ተከታይ ያልሆኑትን ሳይቀር የማስደመም አቅም ያላቸው መንዙማዎች ግጥማቸው የተፃፈው ከክ/ዘመናት በፊት መሆኑ ግርምትን ያጭራል።

በኢትዮጵያ የጥናትና ምርምር ተቋም ያገኘናቸው ምሁርም ይህንኑ ሐቅ በመመስከር ‹‹ኢትዮጵያዊያኑ የመንዙማ ገጣሚዎች በጣም ታዋቂዎች ናቸው። ግጥሙንም የሚፅፉት የሆነ ነገር ሲበራላቸው ነው›› የሚል ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በጣም ታዋቂ ከነበሩ የመንዙማ ገጣሚዎች ውስጥ በራያ አካባቢ በ19ኛው ክ/ዘመን የኖሩት ዘመን አይሽሬ ግጥሞችን በአረብኛ ያበረከቱት ሼህ ጀማል አል ዲን አል አኒና ተማሪዎቻቸው ሼህ ሲራጅ ውዲን

እንዲሁም ሼህ አህመድ አመዲን፣ በ20ኛው ክ/ዘመን ደግሞ ሼህ ጫሊና

ሼህ አደም ደርቃ የወሎ ኗሪ የነበሩ በአማርኛ ቋንቋ መንዙማ የገጠሙ ሊቆች ናቸው።

ወንዶችና ሴቶች አንድ ላይ ተደባልቀው ማዜም አለመቻላቸው እንደተጠበቀ ሆኖ፣ መንዙማ ‹‹የወንድ›› ‹‹የሴት›› ተብሎ የተከፈለ አይደለም። የተወሰኑ መስመሮችን ከፍ ብሎ እንደሰፈረው መንዙማ በአብዛኛው የሚባለው ‹‹ወዳጃ›› ላይ እንደመሆኑ መጠን ሴቶች የራሳቸው በሆነው ‹‹ዱበርቲ ወዳጃ›› ላይ ከወንዶች ባልተናነሰ ሁኔታ መንዙማን ያንቆረቁሩታል። (በነገራችን ላይ ‹‹ዱበርቲ›› ማለት በኦሮምኛ ሴት ማለት መሆኑን ልብ ይሏል) ኧረ እንዲያውም ወሎ ውስጥ ከቤታቸውና ከአካባቢያቸው አልፈው በአገር አቀፍ ደረጃ ታዋቂ የሆኑ ሴት መንዙማ ባዮች እንደነበሩ ታሪክ ያስረዳል።

የመንዙማ ድሮና ዘንድሮምንም እንኳን በአሁኑ ሰዓትም ቢሆን

በአብዛኛው የሚደመጠው መንዙማ እንደ ጥንቱ በድቤ፣ ከበልና እብሪቅ ባሉ ባሕላዊ መሳሪያዎች

የታጀበ ቢሆንም፣ በዘመናዊ የሙዚቃ መሳሪያዎች የታጀቡ መንዙማዎችም መደመጥ ጀምረዋል። ይህም ድርጊት ጥበቡን እንዳያዳክመውና ባሕላዊ ለዛውን እንዳያሳጣው አስግቷል።

በኢትዮጵያ ጥናትና ምርምር ተቋም መምህር የሆኑት አቶ ከማል አብዱል ወሀብ ሁኔታውን ‹‹ይህ ክስተት በጊዜ ሂደት የህዝበ-ሙስሊሙን ታሪካዊና ሀይማኖታዊ ዕሴቶች ይሸረሽራል›› ሲሉ ነው የሚገልፁት። መንዙማን የሚያሳትሙትና የሚሸጡት ከእስልምና ሀይማኖት ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ነገሮች በማሳተም፣ በመሸጥና በማሰራጨት የሚታወቁት ድርጅቶች ሳይሆኑ ሌሎች ዓለማዊ ድርጅቶች መሆናቸው ችግሩን በማባባስ ረገድ ሚና እንዳለው ግን አልሸሸጉም።

በሌላ በኩል ደግሞ ከመገናኛ ብዙኃን ሥርጭት መስፋፋት ጋር ተያይዞ ከተለያዩ አረብ ሀገራት የሚተላለፉ የአረብኛ፣ የሱዳንኛና የእንግሊዝኛ ነሺዳዎች (መዝሙሮች) እና ዘፈኖች መበራከት የመንዙማ አፍቃሪዎችን አሳስቧል። የተጠቀሱት ‹‹የዘንድሮ›› ችግሮች እንዳሉ ሆነው የመንዙማን ሕልውና አደጋ ላይ የሚጥል ችግር ከድሮ ሲንከባለል መምጣቱን ሁኔታውን በንቃት የሚከታተሉ ወገኖች ይናገራሉ።

ይኸውም መንዙማን ጨምሮ ሌሎች ኢስላማዊ የኢትዮጵያ ቅርሶች ተገቢውን ትኩረት አለማግኘታቸው ነው። ሐሳባቸውን ለአውራምባ ታይምስ ካካፈሉ ምሁራንና ሌሎች ተቆርቋሪዎች መረዳት እንደተቻለው፣ በዐረብኛና በተለያዩ ሀገራዊ ቋንቋዎች የተፃፉ በርካታ የመንዙማ ኪታቦች (መፅሐፎች) በቂ ጥበቃ ተደርጎላቸውና ምሉዕ ሆነው ለአሁኑ ትውልድ አልተላለፉም።

ለቀጣዩ ትውልድም ሊያሸጋግራቸው የሚያስችል ዕውቅናና ጥበቃ ከሚመለከታቸው አካላት ሳይሰጣቸው በመቆየቱም በአረብኛ የተፃፉ የኢትዮጵያ ቅርሶች እንደ ውጭ አገር ንብረት ተቆጥረው ከሀገር ሲወጡ ቆይተዋል። ለዚህም በምሳሌነት የሚጠቀሱት ወደ ግብፅ የተወሰደው የሼህ ጫሌ ‹‹ሙህመል››፣ በቅዱስ ፒተርስበርግ (ራሺያ) እንዲሁም ጀርመን የሚገኙት የሼህ ጀማል አል ዲን አል አኒን የግጥም ሥራዎች ናቸው።

የሆነው ሆኖ መንዙማ የኢትዮጵያ መገለጫ ከሆኑ ባሕላዊና መንፈሳዊ ዕሴቶች ውስጥ አንዱ መሆኑ አያጠራጥርም። በአንፃሩ ደግሞ ‹‹ይኼ አንጡራ ሐብታችን ለአደጋ ተጋልጧልና እንጠብቀው›› የሚሉ ጥሪዎች ጎላ ብለው እየተሰሙ ነው። (መንዙማ ያስፈልጋል አያስፈልግም በሚሉ ወገኖች መካከል ያለው ሙግት እንዳለ ሆኖ) እኛ ግን ቅኝታችንን መግቢያ ባደረግነው የመሀመድ አወል የመንዙማ ስንኞች ልንቋጭ ግድ አለን።

… ፈይዱህ ይዘምበል ለእኔ ይድበልበል ሆኖ ሺህ ማዕበል ውዱህ ሲነዳ የውዱህ ካባ ለእኔ ይገባየሐድራ አበባ ለእኔ ይፈንዳ።

ረመዳን ከሪም

በአሁኑ ሰዓት የሚደመጡትና የእስልምና

ዕምነት ተከታይ ያልሆኑትን ሳይቀር

የማስደመም አቅም ያላቸው መንዙማዎች

ግጥማቸው የተፃፈው ከክ/ዘመናት በፊት

መሆኑ ግርምትን ያጭራል።

Page 18: Awramba Times Issue 179

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 179 ቅዳሜ ሐምሌ 30/ 200318

ሴት

ከፍ ብለን የምንጠይቀውን

ያህል ዝቅ ብለን እንስጥ

ህፃናትን (ሴት/ወንድ) ከቤተሰቦቻቸው ጉያ ነጥቀን በማምጣት እንኳንስ ሊማሩ ብዕር ባለፈበት እንዳያልፉ በማድረግ ከአቅም በላይ ስራ በማሰራት ህይወታቸው የስቃይ እንዲሆንና የጎዳናን ህይወት እንዲመርጡ የምናደርግ ቀላል አይደለንም። ያ ብቻም አይደለም፡- የቤት ሰራተኛ ፈልገን ደላላ ስናነጋግር ‹‹ትማራለች? ኡ… ባትማር ጥሩ ነበር።›› የምንልም አለን። ነገር ግን በዚሁ በሴቶች ቀን ‹‹‹ትምህርት እድል ለሴቷ›› የሚል መፈክር ያለው ፅሀፍ እጃችን ከፍ አድርጎ ይዟል።

ነገሮችን በቅጡ እንኳ የማትለየዋን አንድ ፍሬ ልጅ በማጫወት •እና በ‹‹ዝምድና›› ሰበብ የደፈራት ዘመድሽ/ድህ ሊሆን ይችላል። እሷ ህመሙን መቋቋም አልቻለችምና ተናገረች። ያን እያወቅህ/ሽ ‹‹ይሄ ጉድ ነው። እንዴት ብዬ ዘመዴን አሳልፌ እሰጣለሁ… የዘመድ ጥል የስጋ ትል›› ማለትህ/ሽ ሳያንስ ይህቺን አንድ ፍሬ ልጅ ስለዚህ ጉዳይ ለአንድ ሰው ትንፍሽ እንዳትል አላደረግህ/ሽ ይሆን? ታዲያ አንተ/ቺ በሴቶች ቀን ስለ ‹ሴት ልጅ መደፈር› አቤት ብትል/ይ የደንቆሮ ጩኸት አይሆን ይሆን?

የትምህርት ውጤቷ ለምትከውነው የሥራ ድርሻ ብቁ ሆኖ ሳለ •ባቀረብክላት ‘የጾታ ጥያቄ’ ምክንያት ‹‹አልቀበልም›› ብትልህ እሷንም የትምህርት ማስረጃዋንም ከቢሮህ አሽቀንጥረህ የጣልክበት አጋጣሚ ብዙ ነው። ታዲያ፣ ምናልባትም ያንተ ልጅ በትምህርቷ ጥሩ ነጥብ ያላት ሆና ሳለ ከ‹‹መምህሯ›› የቀረበላትን የጾታ ትንኮሳ ጥያቄ ባለመቀበሏ ውጤቷ ሊበላሽ ነው። አንተን ይሄ ያበሳጭህ ይሆን? የሰው ልጅ የዘራውን ያጭዳል።

እርግጥ ከላይ የጠቀስኳቸው ጉዳዮች ብቻ አይደሉም። እኛ ሳንሰጥ ሌላውን የምንጠይቃቸው ብዙ ጉድለቶች አሉብን። እነዚህ እርስ በርስ የሚጣረሱ ተግባራት እያሉ ‹‹ፍትህ›› እንዴት ይኖራል። አንዱ የሚክበውን አንዱ እያበላሸ ልንጠነቀቅ ይገባ ነበር። ዛሬ የሴቶች በደል በ10 ፐርሰንት ቢቀንስ ነገ እኛው ራሳችን እንዲጨምር እድል እንከፍትለታለን። ይሄ አይሆንም፣ የሴት ልጅ ግርዛት፣ ያለ እድሜ ጋብቻ፣ ጾታዊ ጥቃት ይቅር እያልን ለሃብት፣ ዝና እና እኛ ለተተበተብንበት እዳ ማወራረጃ ሴት ልጃችንን ያለፍላጎቷ አሳልፈን የሸጥንበት ወቅት የለም እንዴ? ሊያውም አይን ባወጣ ሁኔታ።

ህብረተሰቡ ብቻ አይደለም ይሄን የሚንደው። አንዳንዴም እኛ እራሳችን /ሴቶች/ መብታችንን ራሳችን ረግጠነው ሳለ ‹‹እንዲህ ካልሆነ› ብለን ተሟግተን እናውቅ ይሆን? ‹‹ይሄማ በእኔ አይከወንም። በጣም ከባድ ነው። ሊሰራ የሚችለው በወንድ ነው›› ብለን ራሳችንን ዝቅ አድርገን ‹‹ለምን ከወንድ እኩል አልሆንም?›› ብለን ብንጮህ አስቂኝ ጩኸት ነው።

ስለዚህ የሴቶች የበላይነት፣ እኩልነት ውሳኔ ሰጪነት … ይኑር እያልን ብንጮህ ነገ ያንን ነገር በማፍለስ ስለምናወራርደው የደንቆሮ ጩኸት ይሆናል ብዬ ነው የማስበው። ከፍ ብለን ፍትህን ስንጠይቅ ዝቅ ብለን ፍትህን መስጠትንም በዚያው እንልመድ። አለዚያ ይህ በየሚዲያ የምንሰማው ‹‹የሴቶች ጉዳት በዚህን ያህል ቁጥር ቀንሶ ታይቷል›› አይነት አባባል፣ ከአባባልና ከቁጥር የዘለለ አይሆንም።

ፍትህን እየጠየቅን፣ ስለ ፍትህ እየሰበክን እኛ የማናደረገው ከሆነ ምን ዋጋ አለው? ትርፉ ቀኑን ቆጥሮ በዓመቱ መጮህ ብቻ ነው። ትርፉ በግራ እጅ ሰጥቶ በቀኝ እጅ መንጠቅ ነው። ትርፉ ፍትህ ፈላጊውን አካል ማጓጓት ነው። ከምንም በላይ ትርፉ ጉንጭ ማልፋት ነው።

በመቅደስ ፍስሐ [email protected]

ድርጊቶች እንዳይረሱ በቀን እንደሚታወሱ /ሊታወሱ/ ግድ ይላል። አንድ ሰው ጥሩ ድርጊት የሰራበትም ያልሰራበትም ዘመን ተቆጥሮለት ይታወሳል። በሰለጠነው ዓለም ያሉ ሰዎች ሲሞቱ ኃውልታቸው ላይ የሚያጽፉት ቀን ቁምነገርን ሰራሁ ያሉበት ቀን ብቻ እንደሆን እናውቃለን። ጥሩ የሚባል ነገር ብንሰራም ባንሰራም ልደታችንን ማክበር ግድ ነው - ለመታወስ።

ወደ ዋናው ጉዳይ እንመለስ። ሁሌም ተግባራዊ እንዲሆን የምንፈልገው ነገር ግን ያን ነገር ራሳችን እያበላሸነው ያለ ነገር የለም ይሆን?

የማቀርበው ኃሳብ ወቅቱን የጠበቀ ላይሆን ይችላል። ነገር ግን እኔ፣ አንዳንዴ “የዓለም የሴቶች ቀን” ብለን የምናከብርበት ቀን በየዓመቱ ሳይሆን በየወሩ በሆነ እላለሁ።

‹‹የሴት ልጅ ግርዛት ከአምናው በ __ ፐርሰንት ያህል ቀነሰ፣ ተገዶ መደፈር በ __ ፐርሰንት ያህል ቀነሰ›› ይባላል። ሁሌም የቀነሰበት ፐርሰንት ይነገረናል። መቼ ይሆን እልም ብሎ የሚጠፋው? ምናልባትም በየወሩ ቢከበር? አዎ! ለዛ ነው ‹ምን አለ በየወሩ ቢከበር› ማለቴ። ነገር ግን መቀነሱንና አለመቀነሱን፣ እነሱ ሲሉን እንጂ እኛ አናውቅም።

አንዳንዴም ጉዳቱ እንዳይቀንስና እንዳይጠፋ ‹‹ይሄ ነገር ይቁም›› ብለው እጅ የሚያነሱት ሰዎችም ዋና ተጠያቂዎች አይሆኑ ይሆን?

እንዲህ ነው፡- ‹‹ሴት ልጅ መገረዝ አለባት…›› ብላ የምታምን እናት ቀላል •

አይደለችም። ለምን? አትታዘዝም፣ እቃ ትጨርሳለች እንዲሁም ባህሪዋ የተገራ አይሆንም ነው መልሱ የሚሆነው። ነገር ግን ይቺ እናት ምናልባትም በሴቶች ቀን ላይ በሚደረግ ሰልፍ ድምጿን ከፍ አድርጋ ‹‹የሴት ልጅ ግርዛት ይቁም›› ትል ይሆናል። የሚጣረስ ነው።

ልጅዎ ምናልባትም ‹‹ምን መሆን ትፈልጊየለሽ?›› ሲሏት •ፍላጎቷ ኳስ መጫወት ይሆናል። ያ በእርስዎ ቤት አይደፈርም። ‹‹እንደ ወንድ ልትራገጥ ያምራታል እንዴ!?›› ይሉ ይሆናል። ነገር ግን የሚሆነው ሌላ ነው፤ አርስዎ በዚያ ስለሴቶች መከራ መቆም በሚሰበክበት ቀን ‹‹የሴት ልጅ እኩልነት…›› የሚል አርማ ይዘው ከሰልፉ መሐል አሉ።

አንዳንዴ የማንሆነው ቃል ገብተን ምንም የማያውቁ ጨቅላ •

በኢትዮጵያ የግሉ ክፍለ-ኢኮኖሚ ከ60 ዓመታት በፊት ጀምሮ ፖሊሲ ተቀርጾለት እንቅስቃሴ ውስጥ የነበረ ቢሆንም፣ አሁንም ድረስ በዳዴ ላይ ይገኛል፡፡ በዘውዳዊው ሥርዓት ጊዜ ለሀገር ውስጥ ባለኃብቶች፣ እንዲሁም ለውጭ ሀገር ኢንቨስተሮች (በተለይም ለደቾች፣ ጣሊያኖችና ግሪኮች) በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ከፍተኛ እንቅስቃሴ እንዲያደርጉ ረድቷቸው እንደነበር ይታወቃል፡፡ የኢንዱስትሪው ዘርፍ በወቅቱ በአፍሪካም ደረጃ ሲታይ በአንፃሩ የተሻለ እንደነበር ማስረጃዎች ያሳያሉ፡፡ደርግ ይህን መልካም ጅምር ቀለበሰው፡፡ በተለይም ይከተለው በነበረው ርዕዮተ-ዓለም ምክንያት በማቆጥቆጥ ላይ የነበሩትን ፋብሪካዎች በመውረሱና ለግል ባለኃብቱ የኢንቨስትመንት ጣራ በመደንቀሩ፣ የኢንዲስትሪ ልማት በመንግስት እጅ ብቻ የተንጠለጠለ እንዲሆን አደረገው፡፡ በመሆኑም ደርግ የግሉ ክፍለ-ኢኮኖሚ ሊጫወት የሚገባውን ሚና ነፍጎ፣ በርዕዬተ-ዓለም ተተብትቦ የለውጥ በሩን ጠርቅሞ ዘጋው፡፡ ይሁንና በደርግ የመጨረሻ የጣር ዓመታት የቅይጥ ኢኮኖሚ መስመር ለመከተል እና የኢንቨስትመንት ገደብን ለማንሳት ተንቀሳቅሷል፡፡በተራው የገዢነት መንበሩን የተቆናጠጠው ኢሕአዴግ በድል አጥብያ፣ በ1982 ዓ.ም፣ በዓለም ዓቀፍ ደረጃ የተዳከመውን የሶሻሊስታዊ አስተሳሰብ ሸሽጎ በፓርቲው ፕሮግራም ለማምታታት ይረዳው ዘንድ ለግሉ ክፍለ-ኢኮኖሚና ለመድበለ ፓርቲ አስተሳሰበ እውቅና ሰጥቻለሁ ብሎ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ለረጅም ዓመታት ሲመራበት የነበረው የማርክሲስት-ሌኒኒስት (ማሌ) አስተሳሳሰብ በሥልጣነ-መንበሩ ላይ ከተፈናጠጠም በኋላ የአገዛዙ ርዕዮተ-ዓለም እንደሆነ በተግባር ቀጥሏል፡፡ኢህአዴግ እሰከ አሁንም አዳብሎ የሚከተለው አብዮታዊ ዴሞክራሲ የሚሉት ሶሻሊስታዊ አመለካከት አርሶ አደሩንና የሠራተኛውን ክፍል እንደ ስልጣን መደላድል አድርጎ የሚቀበልና፣ የግሉን ክፍለ-ኢኮኖሚ እንደ ወላዋይና ሊታገሉት የሚገባ ባላንጣ መደብ አድርጎ የሚወስድ ነው፡፡ በዚህ የግሉን ክፍለ-ኢኮኖሚ በጠላትነት የሚፈርጅ አስተሳሰብ እየተነዳ ለመሬት ፖሊሲ ለውጥ፣ ለፋይናንሻል ገበያው መከፈት፣ በቴሌ-ኮሙኒኬሽን ሴክተር መሳተፍ ወዘተ ፍፁም እንዳይቻል እንቅፋት ሆኗል፡፡ እነዚህ የአገዛዙ ደንቃራ ፖሊሲዎች ከግብርና ወደ ኢንዱስትሪ ሊደረግ የሚገባውን ሽግግር የማይቻል አድርጎታል፡፡ከ1997 ዓ.ም. ወዲህ ደግሞ አገዛዙ እየተከተለ ያለው መንግስታዊ ካፒታሊዚምን (State Capitalism) ነው፡፡ የዚህ አስተሳሰብ ግብ ጥቂት የከተማ አድርባይ ነጋዴውን ክፍል ይዞ የግንባሩን የረጅም ጊዜ የገዥነት ቅዠት ማረጋገጥ ነው፡፡ መንግስታዊ ካፒታሊዚም በባህሪው እጅግ የተለጠጠና ትልቅ መንግስትንና እዚህ ግባ የሚባል ሚና የሌለውን የግል-ክፍለ ኢኮኖሚ የሚፈጥር ነው፡፡ ለዚህም ነው በኢሕአዴግ የአምስት ዓመት የዕድገትና መሠረታዊ ለውጥ ዕቅድ (Growth and Transformation Plan) 99.6% ይሳካል ተብሎ የሚለፈፈው፡፡አንድነት እንደ ኢትዮጵያ ባለ ሰፊ የመዋቅራዊ ችግር ባለበት ሀገር፣ መንግሥት በኢኮኖሚው ሚና አይኑረው የሚል ክርክር አያነሳም፡፡ ይሁን እንጂ ለዴሞክራሲ መጎልበት እርሾ ሆኖ ሊያግዝ የሚገባውን የግል ክፍለ-ኢኮኖሚ ትርጉም አልባ ማድረግ የሀገራችንን ዴሞክራሲያዊ ሽግግርንና የልማት ጭላንጭል ገደል መክተት ነው፡፡ ከአንድ አገዛዝ የእድሜ ዘመን የዘለለ ኃብት ማፍራት ከማይችሉ ጥቂት ነጋዴዎች ይልቅ፣ ለጥሮ ግሮ አዳሪ ነጋዴዎች ቦታ መስጠት የሚያስፈልገው ለዚህ ነው፡፡በተሳሳተ የፖለቲካ መስመር እየተመራ ያለው አገዛዙ ኢትዮጵያን በገዛባቸው የሃያ ዓመታት የእውር ድብር ጉዞው የግሉን ዘርፍ በዓለም ገበያ ይቅርና ከውጭ ወደ ሀገር ቤት ከሚገቡ የቻይና ሸቀጦች ጋር የመወዳደር አቅም መፍጠር አልቻለም፡፡ የማኑፋክቸሪንግ መሠረቱንም አሳፋሪ በሆነ ደረጃ ካጠቃላይ ኢኮኖሚው ከ5 በመቶ ያልዘለለ እንዲሆን አድርጎታል፡፡ የአገዛዙ ዘይቤ በጥረትና በፈጠራ ከሚገኝ ዕድገት ይልቅ፤ በእኖር ባይነትና በአድርባይነት ላይ የተመሠረተ በመሆኑ ነው፡፡አገዛዙ ለዚህ የተለጠጠና ውጤት አልባና የጭቆና መሣሪያ ለሆነው የ“ልማታዊ መንግሥት” አቅጣጫው የግሉን ክፍለ-ኢኮኖሚ እንደ መስዋዕት አቅርቦታል፡፡ አጠቃላይ የመንግሥት ወጪ በ1997 ዓ.ም ከነበረበት 20 ቢሊየን ብር በ2003 ዓ.ም ወደ 75 ቢሊየን ብር ከፍ አድርጐታል፡፡ አንድነት መጀመሪያውንም የተስተካከለ የኢኮኖሚ ፖሊሲና የኢኮኖሚ መሠረት ቢኖር የበጀቱን ከፍ ማለት እንደ በጎ እርምጃ በወሰደው ነበር፡፡ ነገር ግን እየተወሰደ ያለው እርምጃ በግብር ይውጣና የኢኮኖሚው አቅም ሊሸከመው ከሚችለው በላይ በመሆኑ ነው፡፡ ይህ ቅጥ ያጣ የመንግስት በጀት የዋጋ ውድነቱን ከማባባሱ በተጨማሪም በግብር ከፋዩ ላይ ከፍተኛ ጫናን ፈጥሯል፡፡ በ1997 የመንግስት ገቢ 14 ቢሊየን ብር የነበረ ሲሆን፣ በ2002 ደግሞ 51 ቢሊየን ብር ተሰብስቧል፡፡ የሚሰበሰበው ታክስ መልሶ የንግዱን

ተወዳዳሪነትና ምርታማነትን ከማሻሻል ይልቅ፣ ለከፍተኛ ምዝበራ የተጋለጠ እንዲሆን ማድረጉ በገሃድ የሚታወቅ ነው፡፡ ትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል በሚያወጣው ዘገባ መሠረት ኢትዮጵያ ከፍተኛ ሙስና ከሚታይባቸው ሀገሮች አንዷ እንደሆነች ተዘግቧል፡፡አብዛኛው የአገዛዙ ሹመኞች በሙስና መጨማለቃቸውን ታክስ ከፋዩ ጠንቅቆ ያውቃል፡፡ በአቋራጭ የቪላ፣ የፎቅ ቤት፣ የዘመናዊ መኪናና የመሬት ባለቤት ያልሆነ የስርዓቱ ሹመኛ አለ ማለት አያስደፍርም፡፡ በቅርቡ የወጣው የተባበሩት መንግሥታት የልማት ድርጅት (UNDP) ሪፖርት እንደሚያስረዳው ከኢትዮጵያ 140 ቢሊየን ብር በላይ መመዝበሩን በግልፅ አሳይቷል፡፡ ታዲያ ይህ ሲታይ “ጥገኛና ክራይ ሰብሳቢ” የሚለው አባባል ከኢህአዴግ ይልቅ ለማን ይቀርባል?ነጋዴው በቅርቡ በተጣለበት ከፍተኛ ግብር የተነሳ እሮሮ ከፍ አድርጎ እያሰማ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ፈፅሞ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ ከ40 እና 50 እጥፍ በላይ ግብር ተጨምሮበታል፡፡ አገዛዙ ግን ግብር የጨመርኩት የነጋዴው የእለት ሽያጭ በመጨመሩ ነው የሚል ፌዝ ቢጤ ሃሣብ ሰንዝሯል፡፡ ይህንም የዘፈቀደ አሠራሩን “በጥናት የተደረሰበት” እንደሆነ እየገለፀ ነው፡፡ በጥናት ላይ ተመሠረተ የሚባለው የግብር ልኬት በተግባር ሲገለፅ ግን አጠቃላይ ያለው የቁሳ-ቁስ መጠን አምስት ሺህ ብር የማይሞላን ንግድ ቤት፤ ስምት ሺህ ብርና ከዚያ በላይ እንዲከፍል የሚያስገድድ እንደሆነ የአደባባይ ምስጢር ነው፡፡ኢህአዴግ ነጋዴው ዓመቱን ሙሉ በዋጋ ቁጥጥር፣ ለአባይ መዋጮና በእንደገና ምዝገባ ስም ሲያካልበው አርፍዶ፤ በዓመቱ መገባደጃ ደግሞ ከፍተኛ የሆነ የግብር ተመን ጭኖበታል፡፡ ልክ እንደ ደርግ ነጋዴው አወናባጅና አጭበርባሪ የሚል ስም ወጥቶለት ከሕብረተሰቡ ጋር ለማቃቃር ገዢው ፓርቲ በሚቆጣጠራቸው ሚዲያዎች ሁሉ ተዘምቶበት እንደነበር የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው፡፡ አገዛዙ “በጥናት ደረስኩበት” ተብሎ በተገለፀው የዋጋ ተመን መሠረት የነጋዴውን የትርፍ መጠን እቀንሳለሁ ብሎ ገዥው ፓርቲ ተንቀሳቅሷል፡፡ ገብያውንም ለብዙ ምስቅልቅል ዳርጎት ነበር፡፡ ታዲያ የነጋዴው ትርፉ መቀነስ ከተቻለ፣ ነጋዴው አስጨናቂ ለሆነ የገቢ ግብር መዳረግ የለበትምየንግዱ ማሕበረሰብ ይህን ኢ-ፍትሐዊ የሆነ በግብር ስም የሚደረግ ብዝበዛ አቤት ብሎ የሚከላከልበት የፍትሕ አደባባይ ጠፍቷል፡፡ የግብር ቢሮ ሹማምንት በግብር የጎበጠውን ነጋዴ አጥጋቢ ምላሽ ከመስጠት ግማሹን ከፍለህ ተከራከር ማለትን የፍትሕ አልፋና ኦሜጋ አድርገውታል፡፡ በየሚዲያው የሚሠጡት መግለጫዎችም ከዚህ የከፉ ናቸው፡፡ ነጋዴው በግብሩ ከተማረረ፣ የተወሰነበትን ከፍሎ ንግዱን ዘግቶ መሄድ መብቱ እንደሆነ በማንአለብኝነት እየተናገሩ ነው፡፡ የንግዱ ማሕበረሰብ መድረሻ የለውም ብለው ካልሆነ በስተቀር፣ የነጋዴው ሕይወት ሲፋለስ እነርሱም የቆሙበት መሬት እንደሚከዳቸው ረስተውት አይመስለንም፡፡ ኢሕአዴግ ነጋዴው ከየትም ተፍገምግሞ የሚከፍለውን እያንዳንዱን ብር በግልፅነት፣ በፍታዊነት፣ በተጠያቂነትና ውጤታማ በሆነ መንገድ የመጠቀም ልማድ የለውም፡፡ የሚሰበስበውም ብር ለከፍተኛ ሙስናና ለተዝረከረከ የመንግሥት ወጪ ሲውል ተደጋግሞ ታይቷል፡፡ ለምሳሌ በቅርቡ “የልማት ሠራዊት ግንባታ” በሚል ፈሊጥ የግብር ከፋዩን ብር የካድሬ ማሰልጠኛ ሲያደርጉት ተስተውሏል፡፡ ኢ-ህገመንግሥታዊ በሆነ ሁኔታ የመንግሥትና የፓርቲ ሥራ እንዳይለይ ተደርጎ እንደተዋሃደ ይታወቃል፡፡ በተመሳሳይ መንገድም የኢሕአዴግና የመንግሥት በጀት ተለይቶ የመያዙም ሁኔታ ይኖራል ተብሎ አይጠበቅም፡በየወረዳው የስርዓቱ ካድሬዎች የሚረጩት ገንዘብ በተጠያቂነት ስሜት አይወጣም፡፡ በእከክልኝ ልከክህ ዓይነት የመንግስት አስተዳደር ዘይቤ የሚመራ ሀገር የተሰበሰበውን የግብር ብር ከሠፊው ነጋዴ ነጥቆ፣ ለአድርባይ ባለፀጎች የፕሮጀክት ማሟያ የሚሆን ነው፡፡አንድነት ዜጎች በአገራቸው ሠርተው ከሚያገኙት ግብር መክፈል አለባቸው፤ የዜግነትም ግዴታ ነው ብሎ ያምናል፡፡ ይሁን እንጂ መንግሥትም ግዴታ አለበት፡፡ ግብር ክፈሉ ብሎ መጠየቅ ብቻ ሳይሆን፣ የዜጎች የኢኮኖሚና ፖለቲካ መብት ማክበር ያስፈልጋል፡፡ አገዛዙ ነፃ ምርጫን አይፈቅድም፣ በነፃነት የመናገርና የመደራጀት መብትን አያከብርም፡፡ በሕዝብ ሃብት የሚተዳደሩ መገናኛ ብዙሃን ለአንድ ወገን ጭፍን ድጋፍ እንዲሰጡ ሆነው የተዋቀሩ ናቸው፡፡ ታክስ ክፈሉ ብሎ ደረቱን ሞልቶ የሚጠይቅ መንግሥት ለማንኛውም ዕድል መስፈርቶቹን የፓርቲ አባልነትና ታማኝነት ሊያደርግ አይገባም፡፡ መመዘኛው ችሎታና ብቃት ሊሆን ይገባል፡፡ የትምርት ዕድል (በተለይ ድህረ-ምረቃ) በገዢው በፓርቲ የሚወሰን ሳይሆን፣ በነፃ ውድድር መግባት ሲቻል ነው፡፡ ይህ ባልተሟላበት ግብርን በፈቃደኝነት መክፈል የሚታሰብ አይሆንም፡፡ የሕዝብ ፍላጎት ለማሟላት ፈቃደኝነት የሌለው መንግሥት ከሕዝብ ፈቃደኝነት ሊጠብቅ አይችልም፡፡

በብዙ የአፍሪካ ሀገሮች ውስጥ ከሚታየው ሁኔታ አንፃር በኢትዮጵያ የመንግሥት የታክስ ገቢ ድርሻ ከአጠቃላይ ኢኮኖሚ መጠን ዝቅተኛ ነው፡፡ እንዲሁም በኢትዮጵያ የታክስ ከፋይ መሠረቱ እጅግ በጣም ትንሽ ነው፡፡ በተጨማሪም የታክስ ገቢው በዋነኝነት ከኢንዱስትሪውና ከአገልግሎት ዘርፍ የሚገኝ ነው፡፡ ኢንዱስትሪው በስብጥርና በስፋት አነስተኛ ነው፡፡ በመሆኑም ያለውንም ትንሽ የንግድ እንቅስቃሴ ላለማዳፈን መጠንቀቅ ይገባል፡፡አንድነት ፓርቲ አሁን ካለው ጊዜ ይልቅ መጪው ጊዜ ለግል ክፍለ-ኢኮኖሚ እጅግ አስቸጋሪ እንደሚሆን ይገነዘባል፡፡ በ2004 ዓ.ም መንግስት ከ76 ቢሊየን ብር በላይ ግብር ለመሰብሰብ አቅዷል፡፡ በኢህአዴግ የአምስት ዓመት የዕድገትና መሠረታዊ ለውጥ ዕቅድ (Growth and Transformation Plan) መሠረት በ2007 ዓ.ም መንግሥት ከ127 ቢሊየን ብር በላይ ከታክስ ገቢ ለመሰብሰብ አቅዷል፡፡ ይህ በግልፅ የሚያሳየው መንግሥት በግሉ ክፍለ-ኢኮኖሚ ላይ ተንፈራጦ ከፍተኛ የአፈና መዋቅር ለመገንባት ላይ ታች እያለ እንደሆነ ነው፡፡ በተለይ እንደ ኢህአዴግ በሕዝብ ያልተመረጠና ግልፅነት የሌለው መንግሥት መኖሩ ችግሩን አወሳስቦታል።በመሆኑም የንግዱ ከፍለ-ኢኮኖሚ ለራሱ ህልውና ብሎ ተባብሮ መቆም አለበት፡፡ ነጋዴው በነፃነት በሀገሩ መስራት ተስኖት፣ በገዛ አገሩ እንደባላንጣ “መመንጠር ያለበት ጫካ” ተደርጎ እየተወሰደ ነው፡፡ ወደ ግሉ ክፍለ-ኢኮኖሚ መቀላቀል ለእስርና እንግልት የሚጥል ተግባር ተደርጎ እየታየ ነው፡፡ ስርዓቱ የሥራ ፈጠራ ክህሎት እንዲዳብር ከማበረታታት ይልቅ፣ የንግዱ ማሕበረሰብ በሰቀቀን የሚኖርበትና ለኢኮኖሚ ዕድገት ጭራሹንም አስተዋፅኦ ማድረግ ወደማይችልበት ደረጃ ጨርሶ እየገፋው ነው፡፡መንግሥት ከሚከተለው የፖለቲካ ርዕዮተ-ዓለም አንፃር የሚጠበቅ ቢሆንም፤ በመንግሥትና በንግዱ ማህበረሰብ መሃል ያለው መተማመን ከመሻሻል ይልቅ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተበላሸ ነው፡፡ ገዢው ፓርቲ በግሉ ክፍለ-ኢኮኖሚ ላይ የሚከተለውን የተሳሳተ ፖሊሲ መቀየር ይገባዋል፡፡ ስለሆነም፤

ኢህአዴግ ራሱ ነጋዴ ነው፤ 1. ራሱ ሕግ አውጪም፤ ራሱ ሕግ አስፈፃሚም ነው፡፡ ይህም የግሉን ክፍለ-ኢኮኖሚ እንደ ባላንጣ እንዲያይ አስገድዶታል፡፡ ገዥው ፓርቲ ከእንዲህ ዓይነት አካሄድ ተቆጥቦ የግሉን ክፍለ-ኢኮኖሚ በወሬ ብቻ ሳይሆን በተግባር የኢኮኖሚ ሞተርነት ተቀብሎ መስራት ይጠበቅበታል፡፡

በዘመቻ ዕቅድ ለማሳካት መሯሯጥ 2. ብቻ ሳይሆን፣ በጥሞና የታክስ ከፋዩን ሮሮ የሚሰማ ጆሮ ሊኖረው ይገባል፡፡

በንግዱ ክፍለ-ኢኮኖሚ ላይ 3. የተጫነውን አስጨናቂ የሆነ ግብር መከለስ ይገባዋል ብሎ አንድነት ያምናል፡፡ ያለችውንም ጠባብ የግብር መሠረት ከመናድ ይልቅ የተዝረከረከውን የመንግስት አስተዳደር ወጪ መቀነስ፣ ሙስናን መዋጋት ትኩረት ሊሰጠው ይገባል፡፡

በኢትዮጵያ ከ40 በመቶ በላይ 4. የሆነው የንግድ እንቅስቃሴ ከሕጋዊ ማዕቀፍ ውጪ (Informal Economy) እንደሆነ ይታወቃል፡፡ እነዚህ ዜጎች ደረጃ በደረጃ ወደታክስ ሥርዓቱ የሚገቡበት ሁኔታ ላይ ማተኮር ያስፈልጋል፡፡

ገዥው ፓርቲ ከሀገር ጥቅም ይልቅ 5. ለስልጣን ማስቀጠያ ይጠቅመኛል በሚል ለአፈና በሚያወጣው ወጪ ሊጠየቅ ይገባዋል፡፡ ዜጎች ለልማት እንዲውል የሚከፍሉት ታክስ ድረ-ገፆችን ለማገድ፣ የቪኦኤና የጀርመንን ድምፅን ለማፈን፣ ኢሳት በኢትዮጵያ እንዳይተላለፍ በማገድ የግብር ከፋዩን ብር የአምባገነንነት ማጠናከሪያ ሊሆን አይገባም፡፡ ይህን መሰሉ አሠራር ዴሞክራሲያዊና ሰብዓዊ መብቶችን ከመርገጡም በላይ የታክስ ከፋዩን የላብ ውጤት ለአፍራሽና አንዳች ሀገራዊ ፋይዳ ለሌለው የአፈና ተግባር ማዋል ነው ብሎ አንድነት ያምናል፡፡

የታክስ አስደዳደሩን ውጣ ውረድ 6. በማቃለል፣ የተቀላጠፈ አሰራር መዘርጋት እጅግ አንገብጋቢ ጉዳይ ነው፡፡

በንግድ ሥራዓቱ ውስጥ ግልፅነት 7. ያስፈልጋል፡፡ የፓርቲ የንግድ ድርጅቶች በየዓመቱ ኦዲት እየተደረጉ ውጤቱ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ይፋ መሆን አለበት፡፡

አንድነት ፓርቲ ሕዝቡን የሥልጣን ባለቤት ለማድረግና ተጠያቂነት ያለው መንግሥት ለመመስረት በሚደረገው ትግል የግሉ ክፍለ-ኢኮኖሚ የጎላ ሚና ይጫወታል ብሎ ያምናል፡፡ በመሆኑም የንግዱ ማሕበረሰብ ጥቅሞቹና መብቶቹ ተከብረውለት ለሀገር እድገትና ብልፅግና ሊያበረክተው የሚችለው አስተዋፅኦ ሳይገደብ እንዲንቀሳቀስ አንድነት አበክሮ ይታገላል፡፡

ሐምሌ 29 2ዐዐ3 ዓ.ምአዲስ አበባ

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት)UNITY FOR DEMOCRACY AND JUSTICE PARTY (UDJ)

በንግዱ ሕብረተሰብ ላይ የተጣለው የግብር ጫና ፍትሐዊነት የጎደለው የሞኝ በትር ነው!ከአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ

ልጅዎ ምናልባትም ‹‹ምን መሆን ትፈልጊየለሽ?›› ሲሏት ፍላጎቷ ኳስ መጫወት ይሆናል። ያ በእርስዎ ቤት አይደፈርም። ‹‹እንደ ወንድ

ልትራገጥ ያምራታል እንዴ!?›› ይሉ ይሆናል። ነገር ግን የሚሆነው ሌላ ነው፤ አርስዎ በዚያ ስለሴቶች መከራ መቆም በሚሰበክበት ቀን ‹‹የሴት

ልጅ እኩልነት…›› የሚል አርማ ይዘው ከሰልፉ መሐል አሉ።

Page 19: Awramba Times Issue 179

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 179 ቅዳሜ ሐምሌ 30/ 2003

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

ዜ ና ዎ ች 19

በሱራፍኤል ግርማ

በድርቅና በረሃብ ለተጎዱ ሶማሊያውያን የምግብ ዕርዳታ በደንብ ለማድረስ መፍትሔው በሶማሊያ የሚገኘውን የአፍሪካ ሕብረት ሰላም አስከባሪ ጦር ማገዝ እንደሆነ ከፍተኛ የአሜሪካ ባለሥልጣናት ገለፁ።

ብሩስ ዋርተን፣ ዶ/ር ሩበን ብራይቲ እና ጆን ብራውስ የተባሉ ባለሥልጣናት ከተለያዩ ሀገራት ከተውጣጡ ጋዜጠኞች ጋር ባደረጉት የስልክ ኮንፍረንስ አብዛኛውን የሶማሊያ ክፍል ተቆጣጥሮ የሚገኘው አል-ሻባብ የዕርዳታ ሥራዎችን እያስተጓጎለ መሆኑን የተናገሩ ሲሆን፣ ችግሩን ለመቅረፍ ያለው አማራጭ ለሰላም አስከባሪ ጦሩ ድጋፍ ማድረግ እንደሆነ ገልፀዋል።

አል-ሻባብ፣ የድርቅና ረሃብ ሰለባ የሆኑ ሶማሊያውያን ዕርዳታ ሊያገኙ ወደሚችሉባቸው ኢትዮጵያና ኬንያ እንዳይሸሹ በማገድ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እየፈፀመ መሆኑን ለገለፁት የአሜሪካ ባለሥልጣናት፣

በስፍራው የነበረው የፕሮግራሙ ባልደረባ ዘግቧል። ሆኖም በዘገባው ያልተደሰቱት

የሳያት ደምሴ ቤተሰቦች ዘገባው የድምፃዊቷን ሃሳብ ያላካተተና ሚዛናዊ አለመሆኑን በመግለፅ ‹‹የፕሮግራሙ አዘጋጆችና ሬዲዮ ጣቢያው በይፋ ይቅርታ ሊጠይቁ ይገባል›› የሚል ጥያቄ አቅርበው ነበር። ነገር ግን የፕሮግራሙ አዘጋጆች ዘገባው ሃቅን መሠረት ያደረገ መሆኑን በመግለፅ፣ ‹‹ይቅርታ የሚያስጠይቀን ነገር የለም›› ሲሉ ጥያቄውን ውድቅ አድርገውታል። በአንፃሩ ደግሞ የፕሮግራሙ አዘጋጆች ይቅርታ ባይጠይቁም፣ ሬዲዮ ጣቢያው በተናጠል ተደጋጋሚ

አዳማ ለኮንፈረንስ ቱሪዝም ንግድ ምቹ መሆኗ ተጠቆመ

የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት መቀመጫ የሆነችው አዳማ ከተማ፣ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የኮንፈረንስ ቱሪዝም ንግድ እየሰጠች እንደምትገኝና ለዘርፉም ምቹ መሆኗን ከሁለት ሳምንት በፊት የተመረቀው የከረዩ ሂል ሪዞርት ሆቴል ባለቤት ተወካይ የሆኑት አቶ ሲሳይ ወልደሚካኤል ለአውራምባ ታይምስ ገለፁ።በባለኃብቱ አቶ ወልደሚካኤል ተሰማ አማካኝነት የተገነባው የባለ

አራት ኮከብ ደረጃ ሪዞርት፣ ከ55 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ የግንባታ ኢንቨስትመንት ተሰርቶ የተጠናቀቀ ሲሆን፣ በከተማው መግቢያ ላይ ከሚገኘው አባ ገዳ ገልማ አዳራሽ ፊት ለፊት 30 ሺህ ካሬ ሜትር ቦታን ይዞ የተሰራ ነው።ከተማዋ ለኮንፍረንስ ቱሪዝም ንግድ አመቺ እየሆነች መምጣቷም

በቀጣይ ሌሎች ሪዞርት ሆቴሎች እንዲገነቡ በር ከመክፈት ባለፈ፣ ዓለም አቀፍ ኮንፍረንሶች የሚካሄዱባት ስፍራ እንደምትሆን አቶ ሲሳይ አስረድተዋል።ሪዞርቱ 60 የመኝታ ከፍሎች፣ መዋኛ ገንዳ፣ የሕፃናትና የጎልፍ

መጫወቻ ሜዳዎች፣ አምስት የመሰብሰቢያ አዳራሾች፣ ሶስት ፋውንቴኖች ያሉት ሲሆን፣ ደንበኞች የተራራ መውጣት (Hiking) ስፖርት እና ጅቦችን መጎብኘት የሚችሉበት ሁኔታ መመቻቸቱን የሪዞርቱ ማርኬቲንግ ኃላፊ አቶ ደረጀ መኮንን ገልፀዋል።በዚህ ሁለት ሳምንት ውስጥ የተ.መ.ድ የልማት ድርጅት፣ ሌሎች

የእርዳታ ድርጅቶች፣ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች በሪዞርቱ ሰፋ ያለ ስብሰባ ማካሄዳቸውን የጠቀሱት አቶ ሲሳይ፣ ‹‹በቀጣይ ሌሎች ባለኃብቶች በዘርፉ ቢሰማሩ ለራሳቸው፣ ለከተማዋና ለአገር ጥሩ የገቢ ምንጭ ማስገኘት ይችላሉ›› ብለዋል።

‹‹ልጆቻቸውን በአግባቡ የሚያጠቡ እናቶች 49% ብቻ ናቸው››

ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር

ናፍቆት ዮሴፍ

ልጆቻቸውን ያለምንም ተጨማሪ ምግብ እስከ ስድስት ወር የሚያጠቡ የኢትዮጵያ እናቶች 49 ፐርሰንት ብቻ መሆናቸውን የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ይህን ያስታወቀው ባለፈው ሰኞ የዓለም የጡት ማጥባት ሳምንት መክፈቻን አስመልክቶ ባዘጋጀው ፕሮግራም ላይ ነው፡፡ምንም እንኳን 96 ፐርሰንት የኢትዮጵያ ሕጻናት የእናት ጡት ወተት

ተመግበው የሚያድጉ መሆናቸውን ያስታወቀው ሚ/ር መስሪያ ቤቱ፣ ትክክለኛውን የጡት ማጥባት ሥርዓት ተከትለው የሚያጠቡ እናቶች ቁጥር አናሳ መሆኑንና ይህን ቁጥር ለማሳደግ በርካታ ስራዎች እየተሰሩ እንደሆነ ተነግሯል፡፡ዘንድሮ በኢትዮጵያ ለሶስተኛ ጊዜ በሐምሌ 26፣ “በሁሉም ስፍራ

ስለጡት ማጥባት እንወያይ›› በሚል መርህ ቃል የተጀመረው የዓለም የጡት ማጥባት ሳምንት፣ እስከ ነገ ነሐሴ 1/2003 ድረስ ይከበራል።በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የስርዓተ-ምግብ አስተባባሪ የሆኑት አቶ መስፍን

ጐሴ እንደተናገሩት፣ ከግንዛቤ ማነስ እናቶች ስድስት ወር ሳይሞላቸው ለህፃናት ተጨማሪ ምግብ በመስጠት ለችግር አንደሚያጋልጧቸውና ህፃናት በተወለዱ በአንድ ሠዓት ውስጥ እንገር የተባለውን የጡት ወተት ጨምሮ እስከ ስድስት ወር ድረስ ከጡት ውጭ ውሃን ጨምሮ ምንም አይነት ተጨማሪ ምግብ ሊሰጣቸው እንደማይገባ ገልፀዋል።

የ“ገመና” ጉዳይ ለ2004 ተቀጠረበኤልያስ ገብሩ

በቅጅና ተዛማጅ መብቶች ጥበቃ አዋጅ “የፈጠራ መብቶች ባለቤትነት እንዲከበር” በሚል “ገመና” ከተሰኘ የቴሌቭዥን ተከታታይ ድራማ ጋር በተያያዘ በቀረበው ክስ፣ በፌዴራል ከ/ፍ/ቤት፣ በስምንተኛ ፍትሐ-ብሔር ችሎት የከሳሽ ምስክሮችን ለማድመጥ ለትላንት በስቲያ ተይዞ በነበረው ቀጠሮ ዋናው ዳኛ ሳይገኙ ቀሩ።የገመና ቁጥር 1 ደራሲ አቶ አድነው ወንድይራድ (አዶኒስ) ጠበቃ

የሆኑት አቶ ጳውሎስ ተሰማ፣ ዋናው ዳኛ በተዘዋዋሪ ችሎት ምክንያት አሶሳ ሄደዋል መባላቸውን ለአውራምባ ታይምስ ገልፀዋል።በዕለቱም በተከሳሾች ላይ የከሳሽ ምስክር ሆነው አቶ አድነው ወንድይራድ፣

አርቲስት ፍቃዱ ተክለማሪያም፣ አርቲስት አስቴር አለማየሁ (የብሌን እናት)፣ አርቲስት አላዛር ሳሙኤል እና ጋዜጠኛ ወሰንሰገድ ገ/ኪዳን ተገኝተው ነበር።በዕለቱ በነበረው ችሎት በቢሮ ረዳት ዳኛ ቢሰየሙም የምስክሮችን

ቃል ማድመጥ ባለመቻሉ፣ ለጥቅምት 22 ቀን 2004 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ መሰጠቱን የጠቀሱት የከሳሽ ጠበቃ፣ ጉዳዩን የያዙት ዋና ዳኛ አለመኖራቸው ቢገለፀልንም፣ “ከበስተጀርባ ምን እንዳለ አናውቅም” ሲሉ ለአውራምባ ታይምስ አስረድተዋል።ከጉዳዩ ጋር ተያይዞም ሰኔ 22 ቀን 2003 ዓ.ም ላይ በነበረው ችሎት

የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቭዥን ድርጅት ጠበቃ መገኘት ባለመቻላቸው፣ ተቋሙ በሌለበት ጉዳዩ እንዲታይ ሲል ፍርድ ቤቱ መወሰኑ ይታወሳል። ሆኖም ከትላንት በስቲያ በነበረው ችሎት የድርጅቱ ነገረ-ፈጅ፣ የድርጅቱ ጠበቃ ቤተሰባቸውን ጥየቃ ከአዲስ አበባ ውጪ ሄደው ሲመለሱ መንገድ ላይ የመኪና ብልሽት አጋጥሟቸው ለፍ/ቤቱ ቀነ-ቀጠሮ መድረስ አለመቻላቸውን ጠቅሰው፣ ጠበቃው ወደ ክርክሩ እንዲመለስ ለፍ/ቤቱ አቤቱታ አቅርበዋል።የከሳሽ ጠበቃ የሆኑት አቶ ጳውሎስ አቤቱታውን ፍ/ቤቱ ውድቅ

እንዲያደርግላቸው በቀጣይ ሳምንት ለፍ/ቤቱ በጽሑፍ ጥያቄ እንደሚያቀርቡ ገልፀዋል። በከሳሽ ደራሲ አድነው ክስ የቀረበባቸው ሰዎች የሜጋ ኪነ-ጥበባት

ማዕከል ሥራ አስኪያጅ የነበሩት አቶ ዕቁባይ በርሄ፣ የዳዕማት መልቲ ሚዲያ ፕሮዳክሽን ሥራ አስኪያጅ አቶ ሀብታሙ በርሄ እና የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቭዥን ድርጅት መሆናቸው ይታወሳል።

ይቅርታ ጠይቋል። ይቅርታ ከመጠየቅም ባሻገር፣ የሳያትን ዘፈኖች በየቀኑ ከይቅርታው በኋላ ሲያስደምጥ ቆይቷል።የፕሮግራሙን በድጋሚ መጀመር

አስመልክቶ አስተያየቱን ለአውራምባ ታይምስ የሰጠው አዘጋጁ ተወልደ በየነ (ተቦርነ)፣ ከጣቢያው ጋር በመነጋገር ችግሩ መፈታቱን ከገለፀ በኋላ፣ ‹‹የባከነ ይቅርታ የለም›› ብሏል። ዘገባው በተጨባጭ ማስረጃ ላይ ተመስርቶ የተሰራ ስለመሆኑ አፅንኦት የሰጠው ተቦርነ፣ ሳያት በፕሮግራሙ ጉዳት ደርሶብኛል ብላ ካሰበች ወደ ሕግ መሄድ እንደምትችል ገልጿል። በሌላ በኩል ‹‹ሳያት ይቅርታ

መጠየቅ አለባት›› በሚል ዕምነት ድምፃዊቷን ለተከታታይ አምስት ቀናት በየዕለቱ ለሁለት ጊዜ ይቅርታ ሲጠይቅ የቆየው ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 የሥራ ኃላፊዎች በጉዳዩ ላይ አሰተያት ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆኑም።በመጀመሪያ በስልክ ያገኘነው

አርቲስት አበበ ባልቻ ‹‹ጉዳዩ እኔን ሳይሆን ተፈሪን ነው የሚመለከተው›› ያለ ሲሆን፣ ‹‹ይመለከተዋል›› የተባለው አርቲስት ተፈሪ ዓለሙ ደግሞ ‹‹ስብሰባ ላይ ነኝ›› በሚል ምክንያት ሃሳቡን ሳይገልፅልን ቀርቷል።

ሸገር ኤፍ.ኤም...‹‹የባከነ ይቅርታ የለም››ተቦርነ

በኤልያስ ገብሩ

የፌዴራል የሥነ-ምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን በከባድ የእምነት ማጉደል የሙስና ወንጀል ክስ የመሰረተባት ግለሰብ በሰባት ዓመት ፅኑ እስራትና በ15 ሺህ ብር እንድትቀጣ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 1ኛ ወንጀል ችሎት ባለፈው ማክሰኞ በዋለው ችሎት ውሳኔ አስተላለፈ።

ተከሳሽ ትዕግስት ደርቤ በኢትዮጵያ ጉምሩክ ባለሥልጣን ዋና መሥሪያ ቤት ውስጥ የዕለት ገቢ ሰብሳቢ ሆና ከነሐሴ 10/1997 ዓ.ም እስከ ሚያዚያ 25 ቀን 1998 ዓ.ም ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ ስትሰራ ያልሆነ ብልፅግና ለማግኘት ማሰቧን የክስ ዝርዝሩ ያስረዳል።

በዚህም መሠረት ለገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር እንዲደርስ ባንክ ገቢ በማድረግ ገቢ ስለመሆኑ ከባንክ የሚሰጠውን ዲፓዚት ክሊፕ ትክክለኛ ቅጂ ለባለሥልጣን ዋና መስሪያ ቤት ማቅረብ ሲገባት፣ በመንግስት የተሰጣትን አደራ ወደ ጎን በመተው በፈፀመችው ሙስና ወንጀል መከሰሷን ክሱ ያብራራል።

በመሆኑም፣ ተከሳሿ በገቢ ደረሰኝ በአደራ ከሰበሰበችው ገንዘብ ውስጥ እ.አ.አ ከየካቲት 13 ቀን 2006 እስከ ሚያዚያ 17 ቀን 2006 ድረስ ለባንክ ገቢ ያደረገችው የገንዘብ መጠን ድምር ብር 6205.90 ሆኖ ሳለ ይኸው ገንዘብ ገቢ ስለመሆኑ ከባንክ በተሰጣት አራት ዲፖዚት ስሊፕ ቅጂ ላይ ቁጥር ጨምራ ትገኝታለች። ‹‹በድምሩ ብር 66,205.90 ለባንክ

ገቢ አደረግኩ›› በሚል አጭበርብራ ለባለሥልጣኑ ዋና መ/ቤት በማቅረብ ለባንክ ገቢ ያላደረገችውን ቀሪ ብር 60,000 የመንግስት ገንዘብ ለግል ጥቅሟ በማዋሏ፣ እንዲሁም ከ05/8/98 ዓ.ም እስከ 25/08/98 ዓ.ም ድረስ በሥራዋ አጋጣሚ ድምሩ ብር 17,500.76 የመንግስት ገንዘብ ባንክ ገቢ ሳታደርግ በመውሰድ የተሰወረች በመሆኑ በከባድ የእምነት ማጉደል የሙስና ወንጀል መከሰሷን መዝገቡ ያስረዳል።

ተከሳሿም የቀረበባትን የሰነድና የሰው ማስረጃ መከላከል ባለመቻሏ ፍርድ ቤቱ በሌለችበት ከላይ የተጠቀሰውን ቅጣት አስተላልፎባታል።

77 ሺህ ብር ያጭበረበረች ግለሰብ ተፈረደባት

‹‹የአል-ሻባብን ድርጊት ለማስቆም አሜሪካ ወታደራዊ እርምጃ ልትወስድ ትችላለች?›› የሚል ጥያቄ ቀርቦ ነበር።

ባለሥልጣናቱም አሜሪካ ወታደራዊ እርምጃ በቀጥታ እንደማትወስድ በማስገንዘብ፣ ‹‹በአሁኑ ሰዓት በሀገሪቱ ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን የአፍሪካ ሕብረት ጦር የቻለውን እያደረገ ነው። በእኛ በኩል እንደ አማራጭ የተያዘው ለጦሩ ድጋፍ ማበርከት ነው›› የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

ከዚህ በተጨማሪ አል-ሻባብ ወደ ኢትዮጵያና ኬንያ በሚሰደዱ ሶማሊያውያንን ላይ ግርፋትና ድብደባ መፈጸሙ እጅግ አሳዛኝ እንደሆነ የገለፁ ሲሆን፣ በረድዔት ተቋማት በኩል ለሶማሊያ ህዝብ በሚላከው ዕርዳታ አል-ሻባብ እንዳይጠቀም ከፍተኛ ጥንቃቄ እየተወሰደ መሆኑን ተናግረዋል።

በሌላ በኩል የአሜሪካ የሰላም ጓዶች በኢትዮጵያ ለማገልገል ቃለ-መሐላ ፈፅመዋል። ትናንት

ረፋዱ ላይ አዲስ አበባ በሚገኘው የዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ ኤምባሲ በተካሄደ ሥነ-ሥርዓት ቃለ-መሐላ የገቡት 69 የሰላም ጓዶች፣ በተለያዩ ማሕበራዊ አገልግሎቶች ላይ ተሳታፊ ይሆናሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ከበጎ ፈቃደኛ የሰላም ጓዶቹ ውስጥ 35ቱ በመምህራን ማሰልጠኛ ተቋማት በእንግሊዘኛ መምህርነት የሚያገለግሉ ሲሆን፣ የተቀሩት 34 ጓዶች ደግሞ ኤች.አይ.ቪ/ኤ.አይ.ዲ.ኤስን በመከላከል ላይ ይሰማራሉ።

በጎ ፈቃደኛ የሰላም ጓዶቹ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር በሆኑት ዶናልድ ቡዝ አማካኝነት በኢትዮጵያ ለማገልገል ቃለ-መሐላ በፈፀሙበት ሥነ-ሥርዓት ላይ፣ የኢፌዴሪ ምክትል ጠ/ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ኃ/ማርያም ደሳለኝ እና የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድኃኖም መገኘታቸውን የኤምባሲው ምንጮቻችን አረጋግጠዋል።

በሶማሊያ ዕርዳታ ለማድረስ የአፍሪካ ሕብረት ሰላም አስከባሪ ጦርን ማገዝ መፍትሔ መሆኑ ተነገረ

Page 20: Awramba Times Issue 179

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 179 ቅዳሜ ሐምሌ 30/ 2003ጤ ና20

በእንግሊዘኛ <<Courage>>፣ በአማርኛ ‹‹ወኔ›› ብለን የምንጠራው ቃል የመጣው ከላቲን ቋንቋ ሲሆን ‹‹cor›› ወይም ‹‹ልብ›› የሚል ፍቺ አለው። እውነተኛ ወኔ ከስሜት ይበልጥ በጥሩ የአዕምሮ የማገናዘብ ብቃት ላይ የተመሰረተ መሆኑ ይገለፃል። ይኼም ልዩ የሆነ የሰው ልጅ አዕምሮ ክፍል (ኒዮኮርቴክስ)ን መጠቀም የሚጠይቅ ሲሆን ስሜታዊው የአዕምሮ ክፍል (ሊምቢክ ብሬይን) ግለሰቡን እንዳይቆጣጠረው ጥቅሙ የላቀ ነው። ስሜታዊው የአዕምሮ ክፍልን መጠቀም የሰው ልጅ ከአጥቢ እንስሳት ጋር የሚጋራው ሁነት መሆኑን መረጃዎች ያስረዳሉ። ሊምቢክ ብሬይን አደጋ መኖሩን ይጠቁማሉ። ነገር ግን፣ ኒዮኮርቴክስ አደጋው እውነት አለመሆኑን በምክንያትነት ያቀርባል። ስለዚህ ሰው በቀላሉ ፍርሃት ቢሰማውም እርምጃ ከመውሰድ የሚያግደው ነገር የለም። አንድ ሰው በፍርሃት ላይ እርምጃ መውሰድን ይበልጥ በተማረ ቁጥር ይበልጥ ሰብዓዊ ይሆናል።

ከአጥቢ እንስሳት ጋር መመሳሰል

ሰው ፍርሃትን ይበልጥ ከተከተለ እንደ አነስተኛ አጥቢ እንስሳቶች መኖሩ ግድ መሆኑን በዘርፉ ጥናት ያደረጉ ልሂቃን ምስክርነት ይሰጣሉ። በዚህም፣ ‹‹ሰው ወይስ አይጠመጎጥ መሆን ነው?›› የሚለው ጥያቄ የነርቭ በሽታዎችን በሚያጠኑ ኒውሮሎጂስቶች በተደጋጋሚ ይነሳል። በወኔ የተሞሉ ሰዎች አሁንም ይፈራሉ። ነገር ግን፣ ፍርሃት አስሮ እንዲያስቀምጣቸው አይፈቅዱለትም። ወኔ የሚያንሳቸው ሰዎች ከማያንሳቸው በበለጠ ወደ ፍርሃት የሚሳቡ ሲሆን፣ የረዥም ጊዜ ተፅዕኖን ፈጥሮባቸው ፍርሃቱ ይጠናከርባቸዋል። ሰዎች ፍርሃትን ከመጋፈጥ ይርቁና ‹‹ፍርሃቱን አመለጥነው›› በማለት በእፎይታ ስሜት ውስጥ ይቀመጣሉ። ይኼም ምላሽ በሥነ-ልቦናዊ ሽልማቱ የአጥቢዋን አይጠመጎጥ አይነት የፍርሃት ማምለጫ ፀባይ አላብሶ ሰውን በቀጣይ ሕይወቱ ፍርሃትን እንዳይገፈጥ ያግደዋል። እንዲሁም፣ ችግሩ ስር እየሰደደ ሄዶ በፍርሃት ላይ የመቆም አቅምና ችሎታ የሚያሳጣ ሲሆን ፍርሃትን እንደስጦታና እውነት የመቀበሉ ጉዳይ የማይቀር ሃቅ ነው። ከዚያም ለተከመሩ ፍርሃቶች ራስን መውቀስ፣ በእስር በተቀፈደደ ደስታ አልባ ትዳር ውስጥ መኖር፣ ኃላፊነት የማያስወስድ ሥራን መስራት፣ በምቾት ዞን ውስጥ የሚያስቀምጥ ገቢን ማግኘት… የግለሰቡ መገለጫዎች ይሆናሉ። ግለሰቡ 㜎የሚረዳው ቤተሰብ ቢኖረውም ኃላፊነት አይወስድም። የሥራ መስኩን ለመቀየር ያስብና የእርጅና ስሜት ይሰማዋል። ‹‹ከወላጅ የተወረሰ የውፍረት ዘረ-መል አለኝ›› ብሎ ስለሚያስብ ደግሞ ቅጥ ያጣ ውፍረቱን መቀነስ ይሳነዋል። አምስት፣ አስር፣ ሀያ…ዓመታት አልፈውም የግለሰቡ ሕይወት ያን ያህል ለውጥ አይኖረውም።

ሥነ-ልቦናን ለማጠናከርከ20ኛው ክፍለ ዘመን መጨረሻ ጀምሮ ወኔ በሥነ-ልቦና የትምህርት ዘርፍ ውስጥ እያደገ የመጣ ፅንሠ ሀሳብ ነው። እ.አ.አ በ2004 ክርስቶፈር ፒተርሰን እና ማርቲን ሴሊግማንስ በፃፉት መፅሐፍ ውስጥ ሰብዓዊ ፍጡራንን ወደ ላቀ ሰብዓዊነት በተመሳሳይ መንገድና በአዎንታዊ ደረጃ ከፍ እንደሚያደርጉ አፅንዎት ከተሰጣቸው ባህሪያታዊ መገለጫዎች መካከል ‹‹ወኔያም›› መሆን ቁልፍ የሆነ የላቀ የሞራል ልዕልና ነበር። ሁለቱ ፀሃፍትም፣ ቨርቹ ኢን አክሽን (VIA) የተባለ ኢንስቲትዩት በማቋቋምና የቪ.አይ.ኤ የዳሰሳ ጥናት በማድረግ ብዙኃን የሰው ልጆችን በተመሳሳይ ምድብ ውስጥ ሊያመጣ የሚችል ተስፋ መኖሩን አስታወቁ። ቨርቹ ኢን አክሽን የሰዎችን ጥንካሬ ሰፋ ባሉ ስድስት ምድብ ውስጥ ከፈላቸው። እነዚህም፣ ጥበብና ዕውቀት፣ ወኔ፣ ሰብዓዊነት፣

ፍትሕ፣ ቴምፐራንስ (ከሞራል አንፃር ፀባይን መቆጣጠር)፣ እና ትራንሴንደንስ (ከተለመደውና ገደብ ካለው የሰው ልጅ እሳቦት በላይ መሄድ) ናቸው። ወኔም ጀግንነት፣ ፐርስቨራንስ (ችግሮች ቢኖሩም የሆነ ዓላማን ለማሳካት ያለማቋረጥ የሚደረግ ጥረት)፣ ታማኝነትና ዜስት (ጥልቅ ደስታ) በሚባሉ በአራት ዋና ዋና ንዑስ ክፍሎች ተከፍሏል።

ወኔ፣ ፍርሃት አልባነት? ጦረኝነት?

ፍርሃት፣ ‹‹አቅም ያለው አደጋን መቀበልና አደጋውን ተከላክሎ እርምጃ ለመውሰድ መነቃቃት ነው›› የሚል ትርጓሜ ይሰጠዋል። ሰዎች አደጋውን ለመጋፈጥ ወይም ለማምለጥ ዝግጁ ይሆናሉ። ወኔም በአንፃሩ ከፍርሃት ነፃ መሆን ማለት አይደለም። ይልቅ አንድ ሰው/አካል የያዘውን ዓላማ ዳር ለማድረስ እቅዱ ላይ ጠንክሮ የመቆየት ብቃትን የያዘ ሲሆን ፍርሃትን የመጋፈጥ እርምጃን ይወስዳል። ፍርሃት ራስህን ለመከላከል ሲረዳ ወኔ ደግሞ በዓላማ ላይ ግፊት በማሳደር ከፍርሃት በላይ የሚገኝ ተፈጥሯዊ ባህሪ ነው። ፍርሃት ለመኖር፣ ወኔ ደግሞ ለስኬት አስፈላጊ ነገሮች መሆናቸው ይጠቀሳሉ። ሆኖም፣ ‹‹ፍርሃትን አትፍራው። ፍርሃት እንዲያቆምህ አትፍቅድለት። በወኔ የተሞላ እርምጃ የምትወስድ ሁን። ወኔና ፍርሃት እጅ ለእጅ ተያይዘው የሚሄዱ ነገሮች ናቸው።›› በማለት የዘርፉ ተመራማሪዎች ምክራቸውን ይለግሳሉ። በጫናና በውጥረት የተሞሉ ሁኔታዎች ሲያጋጥሙን እንርበተበታለን? እንጨነቃለን? ወይስ እንፈራለን? …በፍርሃት ተሞልቶ ስጋት ውስጥ የመግባት የአኗኗር ዘይቤን በመቀየር ወኔ ወደ ተሞላ ስብዕናን መሸጋገር ግን ይቻላል። እንዴት?በእያንዳንዱ ስጋትና ጭንቀት ውስጥ ፈንቅሎ መውጣትን የሚጠባበቅ ፍርሃት አልባ ጦረኝነት አለ። በዚህ ፅሁፍ አገላለፅ፣ ‹‹ጦረኛ›› መሆን ማለት በጦር ሜዳ ውጊያ ማካሄድ አይደለም።

ይልቅ ጠንካራ ሆኖ መቆምን፣ በራስ ማንነት ማመንን እና ወኔ መያዝን ይጠይቃል። በዚህም፣ ‹‹ትልቅ አደጋና ችግር ይከሰታል›› ብሎ እያሰበ የሚገኘውን ውስጣዊ ኃይላችንን በመቀየር ሁኔታዎችን በተረጋጋና ድፍረት በተቀላቀለበት ሁኔታ ተቆጣጥሮ ኃይልን በተገቢው ሁኔታ መጠቀም ነው። በስጋት የተሸበቡና የሚጨነቁ ሰዎች አዕምሯቸውን ፍርሃት አዘል በሆኑ አስተሳሰቦች ይሞሉታል፡- ጥቅም አልባና አቅም የማጣት ስሜት እስከሚሰማቸው ድረስ። ጦረኞች ደግሞ ጠንካራ እምነታቸውን በእውነተኝነት ጨብጠው የሚያጋጥማቸውን መሰናክልና ፍርሃት ለማሸነፍ ሁልጊዜ ዝግጁ ናቸው።

ላእላይ ወኔን መጨበጥ

አጥብቆ መጨነቅን አቁሞ ወደ ላቀ የወኔ ደረጃ ለመሸጋገር የተለያዩ ዘዴዎች አሉ። ጥቂቶቹን እንጥቀስ፡-1. አስከፊ ነገር ከማሰብ ማቆም፡- ሀሳቦች ኃይላቸው ከፍተኛ ነው። አሉታዊ ወይም በፍርሃት የተሞሉ አስተሳሰቦች ሰዎችን ቀፍድደው በመያዝ እንዳይንቀሳቀሱና ስሜት አቅም አልባ እንዲሆኑ ሊያደርጓቸው ይችላሉ። ስለዚህ በተቻለ አቅም በአሁን ወቅት እየተደረገ ስላለው ሁኔታ መልካምና አዎንታዊ አስተሳሰብን መያዝ ያስፈልጋል። በአውሬነት አስተሳሰብ የተሞላውን አዕምሮ በእርጋታ ቀይሮ ከፍ በማድረግና አስደሳች ምናባዊ እይታን በመፍጠር የራስ ውስጣዊ ኃይልን በአዎንታዊ ስሜት መሙላቱ ጥቅሙ የላቀ ነው። 2. ወደ አሁንነት ቅፅበታዊ ጊዜ መንቀሳቀስ፡- የሰዎች አስተሳሰብ እና የሕይወት አንቀሳቃሽ ውስጣዊ ኃይል ተመልሰው ሊያገኙት ወደማይችሉት ያለፈ ወይም ገና ወዳልጨበጡት የወደፊት ጊዜ ላይ ትኩረት አድርገው አስከፊ ነገርን በማሰብ ከተጠመዱ በአሁን ወቅት በእጃቸው የምትገኘዋን ቅፅበታዊ ውድ ጊዜ ሊጠቀሙባት

ስለማይችሉ ምንም አይነት የአሁንነት ኃይል አይኖራቸውም። ከላይ የገለፅናቸው ጦረኞች ሙሉ ትኩረታቸው በአሁንነት ላይ ነው። ይህቺን ድጋሚ የማትገኝ ውድ ጊዜ በደስታ ያጣጥሟታል። ስለዚህ በአሁን ወቅት ሁሉም ነገር በመልካም ሁኔታ ውስጥ እየተጓዘ መሆን/ አለመሆኑን ለማወቅ

ሁሉም ራሱን መጠየቅ አለበት። የአሁኗ ቅፅፈት መልካም ሆና ከተገኘች በዚያ ውስጥ ራስን ዘና ማድረግ ነው። 3. ማዕከላዊነትን በራስ ውስጥ ማድረግ፡- ጦረኞች ነገሮቻቸው የተበታተኑ አይደሉም። ተፈጥሯዊ የሆኑ ሁሉም ኃይሎቻቸውን ይዘዋል። ትኩረታቸውን ያደረጉት

በኤልያስ ገብሩ[email protected]

ከገለልተኝነት ጥያቄ ሳልወጣ፣ በተለይ በአፍሪካ በአምባገነን መንግስታት ውስጥ ለረዥም ዓመታት በስልጣን የቆዩ መሪዎች በሙስና የመዘበሩት የሕዝብ ኃብት በፋይል መልክ ተመዝዞ የሚወጣው ከስልጣናቸው ከወረዱ በኋላ ነው። የእኛንም ሀገር ያየን እንደሆነ ጠ/ሚ/ር መለስ ለረዥም ዓመት በስልጣን ላይ ይገኛሉ። እንበልና፣ እሳቸውም በስልጣን ዘመናቸው ላይ እያሉ ‹‹የሙስና ወንጀል ፈፅመዋል›› ተብለው ቢጠረጠሩ በአሁን ወቅት ተጠሪነቱ ለእሳቸው የሆነውና እርስዎ በዋና ኃላፊነት እየመሩት የሚገኘው ተቋም በአቶ መለስ ላይ መረጃ በማሰባሰብ ክስ የመመስረት ድፍረትና ብቃት አለው?

እንግዲህ … ንድፈ-ሀሳባዊ እንዳይሆንብኝ ፈርቼ ነው። ምክንያቱም ሁለት ንድፈ-ሀሳባዊ መላምቶች (theoretical assumption) አሉ። በመጀመሪያ ጠ/ሚ/ሩ ሙስና ፈፅመዋል ወይ? ይከሰሳሉ ወይ? እሳቸው ጣልቃ ይገባሉ ወይ? እናንተስ ትቸገራላችሁ ወይ? የሚሉ ግምቶች ናቸው። ስለዚህ ባልተጨበጡ ጉዳዮች ላይ ክርክር ብናደርግ አይጠቅመንም።

ጥያቄዬ የተቋማችሁ ተጠሪነት በቀጥታ ለእሳቸው ከመሆኑ አንፃር ነው?ተጠሪነታችን ለእሳቸው መሆኑ በርካታ ነገሮችና ሥርዓቶች አሉት። … ሌላው ቢቀር ጠ/ሚ/ሩ

እንደሚከሰሱ መታወቅ አለበት! ባለፈው በፖለቲካ የተወሰነ ችግር በነበረበት ወቅት ጠ/ሚ/ሩ ክስ ቀርቦባቸው ነበር። እሳቸውን ለመክሰስ ምንም የሚከለክል ነገር የለም። ስለዚህ ጠ/ሚ/ሩ ሰው ናቸው። እንደሰው እኩል ይታያሉ። ራሳቸው የሚያስፈፅሙትን ሕግ ይጥሳሉ የሚል ዕምነት የለኝም።

ግን ... በአፍሪካ እንደ ባህል ሆኖ የአብዛኞቹ መሪዎች የሙስናም ሆነ የወንጀል ዶሴ የሚከፈተው በትረ-ስልጣናቸውን ከለቀቁ በኋላ ነው። በምሳሌነት የቀድሞ የግብፅ ፕሬዝዳንት ሆስኒ ሙባረክን ማንሳት ይቻላል። ምክንያቱ ምንድን ነው ይላሉ? የዴሞክራሲ ዕጦት ወይስ በአፍሪካ አምባገነንነት ስለሰፈነ?

በዚህ ጉዳይ ላይ አሁን ጥናት ባላደረኩበትና ባልተዘጋጀሁበት ሁኔታ መልስ ብሰጥ አይጠቅምም። የእያንዳንዱን ሀገር ተጨባጭ ሁኔታ ማየት ይጠበቃል። የየሀገራትን የፖለቲካ ሥልጣን አያያዝና መሪዎቻቸው ከኢኮኖሚው እንቅስቃሴ ጋር ያላቸውን ግንኙነት ማየትንም ይጠይቃል። የእኛ ሀገር የፋይናንስ አያያዝ … ወዘተ ስናየው ከሌላው ለየት የሚልባቸው ሁኔታዎች ስላሉ ያንን ተጨባጭ ሁኔታ አጥንቶ አስተያየት መስጠት ጠቃሚ ይመስላል።

እ.አ.አ በ2010 ትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል ሙስናን አስመልክቶ ባወጣው የሀገራት የሙስና ደረጃ (Corruption Perception Index) ላይ ኢትዮጵያን ከ178 ሀገራት መካከል በ116ኛ ደረጃ ላይ አስቀምጧታል። በዚህም መሠረት ሙስና በከፍተኛ ደረጃ የሚገኝባቸው ሀገራት ምድብ ተርታ ተመድባ ከ10 ነጥብ 2.7 ውጤትን ይዛለች። እነዚህ የሙስና ችግር መኖራቸውን ጠቋሚዎች እንጂ ትክክል የሙስናውን ሁኔታ ያሳያሉ?

አብዛኛዎቹ እይታዎች ጥናት ተከናውኖባቸው የሚደረጉ አይደሉም። ለምሳሌ እ.አ.አ በ2006 ዋሽንግተን የሚገኝ ግሎባል ኢንተግሪቲ የሚባል ተቋም ጥናት አጠናሁ ብሎ ኢትዮጵያን ዝቅተኛ ሙስና ይፈፀምባቸዋል ከተባሉ ጥሩ ሀገራት ተርታ አስቀምጧት ነበር። ይኼንን የሚገመግመው ከሌሎች ሀገራት አንፃር ሙስናን፣ ሌሎች አስተዳደርን የተመለከቱ ጉዳዮችን፣ ሚዲያን፣ የሲቪል ማሕበራት እንቅስቃሴዎችን፣ ምርጫንና ሌሎች ነገሮችን አይቶ ነው፡፡ እነሱ መመዘኛ ብለው ያስቀመጧቸው በርካታ ነገሮች አሉ። በቀጣዩ ዓመት ደግሞ በመጨረሻዎቹ ተርታ አስቀመጠን። ነገር ግን፣ የተጀመረ የዴሞክራሲ ስርዓት ያላት ኢትዮጵያ በምንም ተዓምር ከአንድ ዓመት በኋላ ደረጃዋ ታች አይወርድም። ስለዚህ ጥናቶች ችግር እንዳለባቸው ታያለህ።

ምን አይነት ችግር?

በዚህ አጋጣሚ አውቀን የለየነው ነገር ቢኖር እነዚህ አካላት ደረጃዎችን ዝም ብለው በስማቸው ሲያወጡ ትልቅና ግዙፍ ይመስላሉ እንጂ ቅፅ የሚያስሞሉት የአንድ ሰው እይታን ተመርኩዘው ነው። ያስሞሉትንም ሰው አውቀነዋል፡፡ ለምሳሌ አንተ ለዚህ መንግስት መልካም አስተሳሰብ ከሌለህና በቀናነት የማታየው ከሆነ ያለውን ጥላሸት ሁሉ ትቀባዋለህ። ተቋማቱም ያንን ተቀብለው ሪፖርት ያደርጋሉ። ያ ሁሉ ተደማምሮ ለትራንስፓይረንሲ ኢንተርናሽናል ቀርቦ አማካኙ ነጥብና ደረጃ ይወጣል። የሚሰራው በዚህ መልኩ ነው። በዚህ ብዙ ሀገራት አይስማሙም። ነገር ግን፣ እኛ በእነሱ መለኪያም ቢሆን ተሽለን መገኘት አለብን የሚል እምነት አለን። እንደምታውቀው ከ138ኛ ወደ 116ኛ ደረጃ ነው የመጣነው። ሌሎች ሀገራት ወደ ላይ እየወጡ ሲገኙ እኛ ግን ወደታች እየወረድንና እየተሻልን ነው። ደረጃህን በአንድ ማሻሻል እንኳን ከባድ ሲሆን እኛ በሁለትና ሦስት ዓመታት ውስጥ ደረጃችንን በአስራዎቹ ቤት አሻሽለናል።ተቋማት ምርጫ፣ የአሰራር ግልፅነትና ሌሎች መለኪያዎች አሏቸው። እነዚህ ብቸኛ የሙስና መለኪያ አይደሉም። ተቋማቱም ቢሆኑ የራሳቸውን ተልዕኮ ያራምዳሉ። ለምሳሌ፣ ፍሪደም ሀውስ የምዕራባዊያን አክራሪ ዓላማ ለማራመድ የሚሞክር ነው። በሁለተኛ ደረጃ ደረጃዎች ትክክለኛ ጥናት ተደርጎባቸው የተገኙ አይደሉም።ሆኖም ግን ጥናት የሚያደርጉ

አሉ። ለምሳሌ፣ የዓለም ባንክ በየሀገሩ በየዓመቱ ጥናት ያደርጋል። በዚህም ጥሩ ከምንባል ሀገራት ውስጥ አንዱ ነን። አበዳሪ ሀገራትም ያበደሩት ገንዘብ በትክክል ሥራ ላይ መዋሉን አጣርተው ከሁሉም የአፍሪካ ሀገራት ኢትዮጵያ የተሻለች ሆና አግኝተዋታል። ስለዚህ እይታው ካለማወቅ ሊመጣና የተጋነነም ሊሆን ይችላል። በተጨማሪም የችግሩን አካባቢ አይነግርህም። ያለፈው የተረጋጋ ማሕበረሰብ ከኢኮኖሚ ዕድገት ጋር ሊደናገጥ ስለሚችል ሁልጊዜ እይታዎች እውነት አይደሉም። በጥናት በኩል በእኛና በውጭዎች ተከናውኖ በመሬት አስተዳዳራችንና በቴሌኮም ላይ የነበረው የግዥ አሰራር ሁኔታ የራሳቸው የሙስና ችግሮች እንደነበረባቸው ታውቋል። በዚህ ላይ በትኩረት እየተሰራበት ነው።

በሀገራችን ከጊዜ ወደጊዜ የሙስና ችግሮች ውስብስብ እየሆኑና የተከሳሾችም ቁጥር እየጨመረ መጥቷል። ሙስና በቀጣይ የኢትዮጵያ ዋነኛ ስጋት አይሆንም ይላሉ?

ስጋቱ በጣም ትክክል ነው። ሁልጊዜ ሀገራት በዕድገት ጎዳና ላይ ሲገቡ ብዙ ውሎችን ያደርጋሉ። ለመሰረተ-ልማት ብዙ ገንዘብ ይወጣል። ከዚያም ሌባው የድርሻውን ለማንሳት ጥረት ማድረጉ አይቀርም። መንገድ፣ ድልድይ፣ ሕንፃ፣ ግድብ፣ የባቡር ሃዲድ … የማታሰራ ከሆነ ኮንትራት የለም። ኮንትራት ስለሌለ ከችግር ትጠበቃለህ። ነገር ግን፣ ገንዘብ ማውጣት ስትጀምር በዛ ላይ ችግሮች ሊኖሩ ይችላሉ። የሚጠቅመው ችግሩን አውቀህ ራስን ማዘጋጀት ነው። አንዳንድ

‹‹ጠ/ሚኒስትሩን ለመክሰስ . . .

ተፈጥሯችሁ ነውና ‹‹ወኔ›› ይኑራችሁ!ወደ ውስጣዊ ማንነታቸው ነው። እርምጃ መውሰድ አስፈላጊ በሚኮንበት ጊዜ ዝግጁ ናቸው። በውስጣዊ ማንነት ውስጥ ማዕከላዊነትን መፍጠር ትኩረትን ሁሉ ከውጫዊ ነገሮች ማራቅን ግድ ይላል። በዚህም በሰውነት ውስጥ ጠቃሚና ወሳኝ የሆነው የኃይል ፍሰት ንፁህ ስሜት እስኪፈጥርና የተረጋጋ እስኪሆን ድረስ አጠቃላይ ትኩረትን በአተነፋፈስ ሥርዓት ላይ ማድረግ ያስፈልጋል። 4. አካል ከመሬት ጋር ኑባሬ እንዲፈጥር ማስቻል፡- ጦረኞች በራሪዎች አይደሉም። የእግሮቻቸው መዳፍ ከሚረግጡት ወለል ጋር በጥብቅ ተቆራኝተው ከመሬት ጋር የግንኙነት ኑባሬን ይፈጥራሉ። ከመሬት ጋር ሕብረት ፈጥሮ የመቆየት ምክንያት ፍርሃትና ጭንቀቶች ከሰውነት ውስጥ ወጥተው ወደ መሬት ውስጥ ሰርገው እንዲገቡ ማድረግ እንደሚያስችል መረጃዎች ያስረዳሉ። የሰውነት አካል በእግር መዳፎች አማካኝት ከመሬት ጋር ግንኙነት ሲፈጥር ስሜቱን መረዳትና በሰውነት ውስጥ ያሉ ሁሉም ውጥረቶች ከአካል ወጥተው መሬት ውስጥ እንደሚገቡ በማሰብ ድርጊቱን ማከናወን እንደሚቻል የባለሙያዎች ጥናት ያመላክታል። 5. የማንነት ውስጣዊ ጥበብን ማመን፡- እያንዳንዱ ሰው በውስጡ የተቀመጠውን የላቀ እውነቱንና ጥበቡን መገንዘብ ይችላል። አንድ ሰው ለራሱ የሚሰጠውን ከፍ ያለ ቦታ በፍርሃት አስተሳሰብ ውስጥ ሆኑ አእምሮውን ማድመጡ በአሁን ወቅት ለተከሰተው ሁኔታ ተገቢውን መፍትሄ ለመስጠት አይረዳውም። ጦረኞች አዕምሯቸውን ለማረጋጋት ጊዜ ይወስዳሉ። ከዚያም ትክክለኛውን ምሪት ለማግኘት ውስጣቸውን ያዳምጣሉ። በራስ ውስጣዊ ማንነት ውስጥ ማዕከላዊነትን ፈጥረው ከተረጋጉም በኋላ በቀጣይ ምን ማድረግ እንደሚገባቸው ጠሊቁን ውስጣዊ ማንነት መጠየቅ ብቻ ነው።

አንድ ሰው ለራሱ የሚሰጠውን ከፍ ያለ ቦታ በፍርሃት አስተሳሰብ

ውስጥ ሆኑ አእምሮውን ማድመጡ በአሁን ወቅት ለተከሰተው ሁኔታ

ተገቢውን መፍትሄ ለመስጠት አይረዳውም።

Page 21: Awramba Times Issue 179

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 179 ቅዳሜ ሐምሌ 30/ 2003

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

21ሳይንስና ቴክኖሎጂ

በአብዱ መሐመድ

ኑክለር ወደር የማይገኝለት የልማትና የጥፋት መሣሪያ ነው። ስለኑክለር ሲነሳ በእያንዳንዱ አእምሮ ውስጥ የሚመላለሰው ወደ አውዳሚ ቦንብ ተቀይሮ ስለሚደርሰው ጥፋትና በሺህ ዓመታት የማይመክን ገዳይ የጨረር ዝቃጭ ነው።

ይህንን ጥቁር ጠባሳ ካሳረፉ ክስተቶች መካከል አንዱ አሜሪካ በ1945 በጃፓን ሄሮሺማ እና ናጋሳኪ ከተሞች ላይ ያደረሰችውና ከ50 ሺህ ህዝብ በላይ የፈጀው የአቶሚክ ቦንብ ጥቃት በቀዳሚነት ይጠቀሳል።

የበለፀጉ ሀገራት በጠላትነት የሚመለከቷቸውና ልዩ ርዕዩተ-ዓለም የሚያራምዱ ሀገራትን ድንበር ጥሰው ጦር የሚሰብቁትና በማዕቀብ የሚያሽመደምዱት፣ የኑክለር ቦንብ የመገንባት ዕቅድ ነድፈው በምስጢር እየተንቀሳቀሱ መሆናቸውን በሚገልፅ ፕሮፓጋንዳ ነው።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ ከሩሲያ ቼርኖቤል የኑክለር ማብለያ አፈትልኮ የወጣ ጨረር ያደረሰው ጥፋትና በቅርቡ በጃፓን ፉኩሺማ በሱናሚ ምክንያት የደረሰው አደጋና ያስከተለው ስጋት እስከ አሁን ድረስ እያነጋገረ ነው።

በተቃራኒው ደግሞ ንፋስ ነፈሰ አልነፈሰ፣ ፀሐይ ወጣች አልወጣች፣ ወንዞች ኖሩ አልኖሩ ምንም የማይመለከተው አንዲት ቅንጣት በካይ ጋዝ ወደ ከባቢ አየር ሳይለቅ ከሁሉም የዓለማችን የኃይል ምንጮች እጅግ ብዙ እጥፍ የላቀ ኃይል የመስጠት ብቃት የተላበሰ ነው - ኑክለር።

ለኑክለር የኃይል ማመንጫም ሆነ ለኑክለር ቦንብ ዋናው ጥሬ ቁስ ወይም ግብዐት ከፈተኛ የኑክለር ጨረር የተሸከሙ እንደ ዩራኒየም እና ፕሉቲኒየም ያሉ ማዕድናት ናቸው።

በእነዚህ ማዕድናት ውስጥ የሚገኙ እምቅ ጨረሮች

ወደቦንብ ወይም የኤሌክትሪክ ብርሀን የሚቀየሩት ማዕድኖቹ የተሰሩበትን የመጨረሻ ቅንጣት (በአተም ኑክለስ ውስጥ የሚገኙ ፓርቲክሎች) ግጭት ወይም ውህደት እንዲፈጥሩ በማድረግ ነው።

በከፍተኛ ወጪ እስከ 10 ቢሊየን ዶላር በሚፈጅ ገንዘብ የሚገነቡ የኑክለር ማብለያዎች እና የኑክለር ጠበብቶች ዋና ተግባር በሶስት ዋና የሥራ ዘርፎች ላይ ያተኮረ ነው። የመጀመሪያው ‹‹ራዲዩ አክቲቭ ዲኬይ›› የተባለው ያልተረጋጋ ኑክለስ ያላቸውን ኢለመንቶች እንዲረጋጉ በማድረግ በሂደት የሚወጣውን ኃይል ለቦንብ ወይም ለኃይል ፍጆታ ማዋል ነው። ሁለተኛው ‹‹ፊዥን›› የተባለው የአተም ኑክለስን ለሁለት ወይም ከሁለት በላይ በመክፈል የሚፈጠር ኃይል ነው።

የመጨረሻው ‹‹ፊዥን ሪአክሽን›› የተባለ ሁለት ቀላል ክብደት ያላቸው እንደኃይድሮጅን ያሉ ኢለመንቶችን በማዋሀድ (ኃይድሮጅን ቦንብ) የሚፈጠረውን ኃይል ለተፈለገው በጎ ወይም አጥፊ ዓላማ የመለወጡን ተግባር ያከናውናሉ።

አሁን በዓለማችን ከመጠን በላይ እየናረ በመጣው የነዳጅ ዘይት ዋጋና ፍላጎት የኑክለር ኃይል ማመንጫዎችን መገንባት በመንግስታት ለድርድር የማይቀርብ አብይ አጀንዳ ሆኗል።

ዓለም አቀፉ የኑክለር ቁጥጥር መሥሪያ ቤት መረጃ እንደሚጠቁመው ዓለማችን 15 በመቶ የኃይል ፍጆታዋን የምታወራርደው በ30 ሀገራት በተገነቡ 488 የኑክለር ኃይል ማመንጫዎች ነው።

የኑክለር ኃይል ማመንጫ በመገንባት ቀዳሚ የሆነችው አሜሪካ ከ104 ማመንጫዎች 75 በመቶ የኤሌክትሪክ ፍጆታዋን ታመነጫለች። በሶስተኛ ደረጃ ላይ የምትገኘውና 54 የኑክለር ኃይል ማመንጫዎችን የገነባችውን

ጃፓንን፣ የ37 ማመንጫዎች ባለቤት የሆነችውን ሩሲያን በመከተል ከ15-22 የኑክለር ኃይል ማመንጫዎችን የገነቡ ሀገራት (በደረጃ በቅድም ተከተል) ሕንድ፣ ካናዳ፣ እንግሊዝ፣ ጀርመን፣ ደቡብ ኮሪያ፣ ቻይና እና ዩክሬይን ናቸው።

ስዊዲን፣ ቤልጂየም፣ ስሎቫኪያ፣ ሀንጋሪ፣ ስሎቫኒያ፣ ቼክ ሪፑብሊክ፣ ፊንላንድ፣ አርመኒያ፣ ቡልጋሪያ፣ ስዊዘርላንድ፣ ሮማኒያ፣ አርጀንቲና፣ ብራዚል፣ ሜክሲኮ፣ ኔዘርላንድስ፣ ፓኪስታንና ደቡብ አፍሪካ ከ2-15 የኑክለር ኃይል ማመንጫዎችን መገንባታቸውን የመሥሪያ ቤቱ መረጃ ይጠቁማል።

በእነዚህ ሀገራት የተገነቡ የኑክለር ኃይል ማመንጫዎች የዓለማችንን 15 በመቶ የኃይል ፍጆታ ከመሸፈናቸውም በላይ ፍላጎቱን ለማሟላት ነዳጅ ቢቃጠል በየዓመቱ ወደ ክባቢ አየር ይዘልቅ

የነበረውን 2 ቢሊየን ቶን የተቃጠለ አየር እንዲቀር ከፍተኛ ዕገዛ አድርገዋል።

የኑክለር ኃይል ማመንጫዎች ከብክለት የፀድ ከመሆናቸው በተጨማሪ ኃይል የማመንጨት ብቃታቸው የላቀ ነው።

የዚህ ብቃታቸው አይነተኛ ማሳያ የዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ ፕሬዝዳንት የነበሩት ኤይዘን አወር የካርል ማርክስና የከባቢ አየር ብክለትን ለመከላከል ከታዳሽ ኃይል ምንጮችና ከኑክለር ኃይል ማመንጫዎች የተሻለ አማራጭ የለም የሚል አቋም የሚያራምዱትን የፕሬዝዳንት ኦባማን ፍላጎትና ራዕይ የፈታው ‹‹ሀይፐሪዩን›› የተባለ ተንቀሳቃሽ የኑክለር ኃይል ማመንጫ ዓለምን እያስደመመ ነው።

ፕሬዝዳንት ኤይዘን አወር በ1950 በነደፉት ሰላማዊ የአቶሚክ ግንባታ ፖሊሲ

ተንቀሳቃሽ የሆኑ የኑክለር ኃይል ማመንጫዎችና ባትሪ የመገንባት ራዕይ ላይ ያተኮረ ነበር። ካርል ማርክስ ይህ ዛሬ የጥፋት መሳሪያ የሆነው የኑክለር ቦንብ ወደፊት ወደር የማይገኝለት የቴክኖሎጂ ግብዐት እንደሚሆን ያለውን እምነት ገልጾ ነበር።

ሀይፐሪዩን (Hyperion Power Generation) በአሜሪካ ሎስ አልሞስ ብሔራዊ የምርምር ተቋም ባለፈው የካቲት ለውጤት የበቃ ተንቀሳቃሽ የኑክለር ኃይል ማመንጫ ወይም ባትሪ ነው።

መጠኑና ብቃቱ አሁን ሥራ ላይ ከዋሉ 15 ሜትር ርዝመት ካላቸው የኑክለር ኃይል ማመንጫዎች ጋር ሲነፃፀር አርባ እጥፍ ያነሰ የተሟላ የኢንተርኔት አገልግሎት ከሚሰጥ ኮምፒዩተርና በአይፎን ሞባይል መካከል ካለ ልዩነት ጋር የሚስተካከል ነው።

የምርምር ተቋሙን ኃላፊ ጆን ግሪልዚንን ጠቅሶ

‹‹ኃይፐሪዮን›› ተንቀሳቃሽ የኑክለር ኃይል ማመንጫበታይም መጽሔት በቀረበው ዘገባ ከፍሪጅ የማይበልጥ 1.5 ሜትር በ2.5 ሜትር መጠን ያለው ሀይፐሪዩን ባትሪ ለ20 ሺህ መኖሪያዎች በቂ የኤሌክትሪክ ኃይል፣ ለማዕድን መቆፈሪያ ማሽኖችና ለወታደራዊ ካምፖች አስፈላጊውን ኃይል የሚመግብ 25 ሜጋ ዋት የሚያመነጭ ብቃት የተላበሰ ነው። ትላልቆቹን የኑክለር ኃይል ማመንጫዎች በመገንባት የሚገኘውን የኤሌክትሪክ ኃይል ለማግኘት የሚወጣውን ወጪ በ60 በመቶ በመቀነሰ እያንዳንዱ በ100 ሚሊየን ዶላር ለሽያጭ እንደሚቀርብ ገልፀዋል።

በሌላ አነጋር 1000 ሜጋ ዋት የሚያመነጭ ግዙፍ የኑክለር ማብላያ 10 ቢሊየን ዶላር ወጪ ይጠይቃል። ይህን ያህል መጠን ያለው ኃይል ለሚያመነጩ 40 የኃይል ሀይፐሪዩን ባትሪ የሚወጣው ወጪ 4 ቢሊየን ዶላር ነው።

እንደግዙፎቹ የኑክለር ኃይል ማመንጫዎች ለሚሳየልና ለአሸባሪ ጥቃት የማይጋለጥ ጥልቅ ጉድጓድ ውስጥ በሚሰራ ኮንክሪት ውስጥ የሚቀበርና ከማብለያው የሚወጣው ዝቃጭ ከግዙፉ በ40 በመቶ የቀነሰ ከመሆኑ በተጨማሪ፣ በካምፓኒው ግንባታው ተጠናቅቆ ኃይል ማመንጨት ከመጀመሩ በፊት ትልቁ ጥንቃቄ የሚጠይቀው ነገር በመኪና ሲጓጓዝ በአሸባሪዎች እንዳይጠለፍ የመጠበቁ ሥራ ይሆናል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ ባትሪውን የሚገዙ ሀገራት ለማመንጫው የጥሬ ቁስ፣ ግብዐት የሚሆነውን ዩራኒየም ወይም ፕላቲኒየም ወደ ቦንብ እንዳይቀይሩት ማዕድኑ ተብላልቶ የሚቀርበውና ወደማብለያው የሚገባው በአቅራቢው ካምፓኒ መሆኑን የአሜሪካ የኑክለር ቁጥጥር መሥሪያ ቤት ያቀረበው መረጃ ይገልፃል።

ሀገራት ባትሪውን ሲገዙ ከአምራቹ ካምፓኒ ጋር በሚገቡት ውል ባትሪው ከተገጠመ በኋላ ማንም ሰው ሊከፍተውና ጥሬ ግብዐቱን ማውጣት በማይችል በርቀት መቆጣጠሪያ በሚመራ የኮምፒዩተር ፕሮግራም የሚቆለፍና የሚንቀሳቀስ ነው። ይህ ደግሞ የኑክለር ኃይል ማመንጫ እንገነባለን እያሉ የኑክለር ቦንብ ለመገንባት የሚያደርጉትን ሩጫና ውዝግብ ያስቀራል።

ከሁሉም የላቀው የኃይል ፍላጎት መጨመርና የነዳጅ ዋጋ ንረት ባስከተለው ጦስ ሁሉም ሀገራት ወደኑክለር ኃይል ማመንጫና ወደኃይድሮ ፓወር ግድብ ግንባታ ፊታቸውን በማዞር የተፈጠረውን ውጥረት የሚያስቀር መሆኑ ነው።

አሁን በዓለማችን ሶስተኛውን ጦርነት ያስነሳል ተብሎ ከፍተኛ ሥጋት የፈጠረው በወንዞች ላይ የሚገነቡ የኃይል ማመንጫ ግድቦችና የውሃ ኃብት ነው። ሌላው ሩሲያ 20፣ ቻይና 30፣ ሳኡዲ አረቢያ 8፣ ኳታር 8፣ ብራዚል 4፣ ግብፅ 4 የኑክለር ኃይል ማመንጫ ለመገንባት ያቀረቡትን ጥያቄ ጨምሮ ከ300 በላይ የግንባታ ጥያቄዎች መቅረባቸውን የዓለም አቀፍ ኑክለር ቁጥጥር መሥሪያ ቤት ያቀረበው ሪፖርት ያመለክታል።

ለእነዚህ ጥያቄ ምላሽ የሚሰጠው ሃይፐሪዩን የኃይል ማመንጫና ባትሪ በየካቲት 28/2011 ለውጤት መብቃቱና ግንባታው መጧጧፉን ተከትሎ ኬንያን ካምቦዲያን እና ሳኡዲ አረቢያን ጨምሮ ሌሎች ሀገራት ያቀረቡት የግዢ ጥያቄ 130 የደረሰው በሶስት ወራት ውስጥ ነው። አሁን የሚጠበቀው የአሜሪካ ኮንግሬስ ሕግ አርቅቆ ለገበያ እንዲቀርብ የሚያስተላልፈው ውሳኔ ብቻ ነው።

ሰዎች በትምህርትና በሚዲያ የምናቀርበውን ‹‹የሌለውን አጋንናችሁታል›› ይሉናል። እኛ ደግሞ፣ ‹‹የለም፤ ወደፊት ሀገራችን እያደገች ስትሄድ የሙስና ስጋቱ ስለሚጨምር የሕዝቡ አስተሳሰብ ከኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከት ወጥቶ በልማት ሰርቶ በማደግ ላይ መሆን ስለሚገባው ማስተማር አለብን። ችግር ውስጥ ከተገባ በኋላ መመለስ አስቸጋሪ ነው›› በሚለው መንገድ እንሄዳለን። ስለዚህ ይኼ ስለሚያጋጥም ቅድመ ዝግጅት ማድረግ አለብን። በሁለተኛ ደረጃ የሙስና ዕድገት በየዓመቱ እየጨመረ ነው ብሎ ማሰብ ይቻል ይሆናል። ነገር ግን የእኛ የማስፈፀም አቅምም እየጨመረ መጥቷል። በፊት የሚደበቁ ነገሮች አሁን ወደ አደባባይ እየወጡ ነው። ከምንከስሰው የበለጠ ወንጀል ይፈፀማል። ለእኛ ሳይደርሱ የሚቀሩ በርካታ ነገሮች አሉ። 80 ሚሊዮን ሕዝብ ባለበት ሀገር በዓመት ከ200-300 ሰው አስቀጥተህ ምን በዛ ይባላል? የምንፈልገው ደረጃ ላይ አልደረስንም። ከዚህ የበለጠ ጠንክረን መስራት ይጠበቅብናል።

ሙስና ለዋጋ ንረቱ፣ የዋጋ ንረቱ ደግሞ ለሙስና አስተዋጽኦ እያደረገ እንደሚገኝ ይገለፃል። ይስማማሉ? 40 በመቶ የደረሰው የዋጋ ንረትስ በዚህ ከቀጠለ አደጋው ከባድ መሆኑ አይቀርም?

በትክክል። ሁለቱ ይተጋገዛሉ። ወላጅ ለልጁ ት/ቤት መክፈል ሲያቅተው፣ ሰው ወደ ቤቱ ዳቦ ይዞ መግባት ከከበደው ወደ ወንጀል አያመራም አልልም። ይኼንን ለመቋቋም ጠንካራ የመንፈስ ጥንካሬ ይጠይቃል። አንዳንድ ሰዎች ደግሞ ወደ እቋራጩ መንገድ ሊገቡ ይችላሉ።

ነገር ግን፣ የፈለገው አይነት ድህነት ገጥሟቸው ከድህነት ጋር እየተፋተጉ ጨዋና ኩሩ ሆነው የሚኖሩ ሰዎችም አሉ። ስርቆት እያንዳንዱ በማንነቱ ላይ ባለው ዕምነት የሚወሰን እንጂ ዋጋ ስለናረ ብቻ ሕዝቡ ቶሎ ወደ ስርቆት ይገባል ማለት አይደለም። የዋጋ ንረትና ድህነት ድሮም አለ። አሁን ኃብትና ሥራ የሚያገኙ፣ በቅርብ ጊዜ ውስጥ ተነስተው የሚያድጉ ሰዎች እየመጡ ነው። ድሮም ሆነ አሁን የማይሰርቁ ጠንካራ ሥነ-ምግባር ያላቸው ሰዎች አሉ። ደካማዎችና በቀላሉ የሚሸነፉ ደግሞ ወደ ስርቆቱ ይገባሉ።

በቅርቡ ለፓርላማ ቀርቦ የነበረውን የዋና ኦዲተር ሪፖርት ተመልክተው ነበር?

አዎ።እንዴት አገኙት?የዋና ኦዲተር ሪፖርት የኦዲት ቋንቋ አለ። ለምሳሌ የፋይናንስ አስተዳደሩን ሕግ በትክክል ያለመከተል፣ የሰነዶች በብዛት መቀመጥ … የሚሏቸው ነገሮች አሉ። በእነሱ በኩል ችግሮች ብለው የሚያስቀምጧቸው ለሙስናና ለምዝበራ በር የመክፈት አቅም አላቸው የሚሏቸውን ነገሮች እንጂ በትክክል ሙስና ተፈፅሟል ብለው ሪፖርት አላደረጉም። ሪፖርታቸው ‹‹ይኼ ገንዘብ ተበልቷል፣ በእከሌ ተመዝብሯል፣ እንዲህ አጉድላችኋል›› የሚል አይደለም። እነሱ ሙያዊ ሥነ-ስርዓታቸው በሚጠይቀው መንገድ ተቋማትን ኦዲት አድርገው ያቀርባሉ። በዚህም ብዙ ግዙፍ ቁጥር ሊነሳ ይችላል። በትክክለኛው መንገድ ያልተወራረዱ የሂሳብ አይነቶች ይቀርባሉ።

... ለማንኛውም ከዋና ኦዲተሩ መ/ቤት ጋር በቀጣይ ተጋግዘን ለመስራትና የጋራ ፎረም ለመመስረት ሃሳብ አለን። ኦዲቱ ‹‹ምዝበራ ተከናውኗል፣ ገንዘብ ጠፍቷል›› ብሎ ካለን ለእርምጃ ወደ እኛ እንዲልክልን እንመርጣለን። ወደ ፊት በፓርላማ በኩል በጋራ ተገናኝተንና በምንደጋገፍበት ነገርና በመ/ቤቱ ግኝት ላይ እርምጃ በምንወስድበት ሁኔታ ላይ እየሰራን ነው። አሁንም ቢሆን በምንፈልገው ደረጃ ባይሆንም ከእነሱ ጋር ትብብር አለን። እኛም ችግር ሲኖርብን፣ ነፃና ገለልተኛ ኦዲት በሚያስፈልገን ጊዜ ኦዲት እንዲያደርጉልን እንጠይቃቸዋለን። እነሱም ግኝታቸውን ያሳውቁናል።

እርስዎም እንደገለፁት፣ ሪፖርቱ በርካታ መንግስታዊ ተቋማት አሰራራቸው ለሙስና በር ይበልጥ ክፍት መሆኑን አሳይቷል። ከሪፖርቱ መውጣት በፊት የዚህ መረጃ ነበራችሁ? ከሪፖርቱስ በኋላ በተቋማቱ ላይ እርምጃ ለመውሰድ ምን አደረጋችሁ?

ከሪፖርቱ በፊት መረጃው አልነበረንም። ሪፖርቱም አይደርሰንም። ሪፖርቱን እንዲሰጡን እንፈልግ ነበር። እነሱ ግን የእኛን የተጠሪነት ጉዳይ ያነሳሉ። ‹‹ተጠሪነታችን ለፓርላማ ስለሆነ ሪፖርቱን የምንሰጠው ለፓርላማ ነው›› ብለውናል። እኛ ግን ‹‹ለእርምትና እርምጃ ይገባል የምትሉት ነገር ካለ ላኩልን። የእናንተ ጥናት መደርደሪያ ላይ እንዲቀመጥና ለሚዲያ ፍጆታ ብቻ እንዲሆን መሆን የለበትም፣ ለእርምት መጥቀም አለበት›› እንላለን። ሆኖም አሁን መረጃዎችን የበለጠ ስርዓት ባለው መንገድ ለመቀባበልና መስመር ለመፍጠር ተዘጋጅተናል።

ተጠሪነታችሁ ለፓርላማ አለመሆኑ ይኼንን ችግር አምጥቶባችኋል። በቀጣይ እንዴት ትፈቱታላችሁ?

አይደለም። እነሱ፣ ‹‹ሪፖርቱን ለእናንተ የመስጠት ኃላፊነት የለብንም። የምናቀርበው ለፓርላማ ብቻ ነው›› ብለዋል። ጉዳዩን አስመልክቶ በፓርላማው የሕግ አስተዳዳር ቋሚ ኮሚቴ በኩል ተነጋግረናል። በጋራ እርምጃ ስለሚወስድባቸው ጥናቶችና ሪፖርቱን በፓርላማ ውስጥ የምናገኝበትን ነገር እያስተካከልን ነው።

በቅርቡ አንድ ዓለም አቀፍ ተቋም ከኢትዮጵያ የተመዘበረ 8.4 ቢሊዮን ዶላር ገንዘብ በውጪ ባንክ መገኘቱን ይፋ አድርጓል። ስለዚህ ምን ምላሽ አለዎት?አንድ ግሎባል … የሚባል አካል አለ። ከታክስ ኢቬዥን፣ ከዋጋ በታች (Under Pricing) … የሚባሉ ቴክኒካል ነገሮች አሉ። ለምሳሌ አንድ ነጋዴ የ10 ሚሊዮን ብር ግብይት ፈጽሞ ያስገባው ግን ስምንት ሚሊዮን ቢሆንና ሁለት ሚሊዮኑን በዛው [ባንክ] እንዲቀር አድርጎ ይሆናል የሚሉ እንደዚህ … እንደዚህ አይነት ጥናቶች ነው ያሉት። ይኼንን ጥናት በተመለከተ ከተቋሙ ጋር ተነጋግረናል። የብሩ መጠን የብዙ ዓመት ድምር ውጤት ነው። የእኛ በዚህ ጉዳይ ላይ በአጋጣሚ የኤክስፖርትና የውጭ ግብይት ምንዛሪ ልውውጥ (Foreign Transaction) አጭር በመሆኑ እንጂ የሌሎች ሀገራት ከ30-40 ትሪሊዮን ድረስ አለ። በዚህ ስታወዳድረው … ያም ቢሆን ሌሎች ታሳቢ ምክንያትና ጉዳዩች አሉ።

ብሩ በኢትዮጵያ አቅም በቀላሉ

የሚታይ ነው እንዴ!?ግድ የለህም . . . ይ . . . ሄ . . .ን . . . ን ከጥያቄው ብታወጣው? ሌላ አላማ ስላለው ነው። ከሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር (Money Laundry) ጋር አብሮ ተያይዞ የሚመጣ ነገር አለ። ስለዚህ ለእናንተ ለሚዲያው የማይጠቅም ነገር ስላለ ነው። [ተጨማሪ ነገር መግለፅ አልፈለጉም]

በንድፈ-ሀሳባዊ የሙስና ሂደት መሰረት ሶስት ዓይነት ሙሰኞች መኖራቸው ይጠቀሳል። አንደኛ ፖለቲካው የሚደግፋቸውና ከለላ የሚሰጣቸው ጥቂቶች፣ ሁለተኛ ፖለቲካው እንደማይደግፋቸው እያወቁ ይደግፈናል የሚሉ፣ ከተያዙ ግን መንግስት የማይራራላቸው ብዙዎች፣ እና በሶስተኛ ደረጃ ያሉት ደግሞ በገዥው መንግስት ስርዓት ውስጥ ሆነው በሙስና የተዘፈቁ ሲሆኑ በሙስና ወንጀል መነካካታቸው ስለሚታወቅ ለፓርቲያቸው እስከመጨረሻ ታማኝ ናቸው። ታማኝነታቸውን የሚያጎድሉ ከሆነ የሙስና ፋይላቸው ስለሚመዘዝ ራሳቸውን ለስርዓቱ አስረው ይኖራሉ። በዚህ ላይ ምን የሚሉት ነገር አለ?

ይኼን እኔም አላውቀውም። … እኛ የምናስራቸውና የምንመረምራቸው ሰዎች ከፊሎቹ ፖለቲከኞችና የድርጅት አባላት ናቸው። ‹‹እነዚህ የድርጅት አባላት ናቸውና ለምን ይከሰሳሉ?›› ያለን አካል የለም። በታማኝነት ልንገርህ፤ መንግስት በፖለቲከኞች ላይ ጠንከር ይላል። ፖለቲከኞች በሙስና ተዘፍቀው ከተገኙ ጫናውም ይበዛል። እንዲመረመሩና እርምጃ እንዲወሰድባቸው መንግስት ይፈልጋል። … “I think it is betrayal” (ክህደት ነው ብዬ ነው የማስበው።)

Page 22: Awramba Times Issue 179

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 179 ቅዳሜ ሐምሌ 30/ 2003ስ ፖ ር ት22

በውበቱ አባተ

[የኢትዮጵያ ቡና አሰልጣኝ]

ባለፈው ሳምንት በወጣው አውራምባ ታይምስ ጋዜጣ ስፖርት አምድ ላይ እድሉ ደረጀ ከኢትዮጵያ ቡና ለመልቀቁ እኔን በምክንያትነት የፈረጀበትን ፅሁፍ ተመልክቼዋለሁ። እንደ አሰልጣኝ እሱ በተናገራቸው ጉዳዮች ውስጥ በጥልቀት ገብቶ አስተያየት መስጠት የሙያው ስነ ምግባር ባይፈቅድም ባለፈው ሳምንት የዚሁ አምድ አዘጋጅ የወጣውን ፅሁፍ ሚዛናዊ ለማድረግ ደውሎልኝ በእኔ አለመመቸት ሀሳቤን ለመሰንዘር ለዛሬ ቀጠሮ ስለያዝኩ፣ በርካታ የኢትዮጵያ ቡና አፍቃሪዎች እድሉን የተናገረውን አንብበው የተዛባ አመለካከት በክለቡም ሆነ በእኔ ላይ እንዳይኖራቸው በማሰብ እውነቱን እንዲያውቁ ከማድረግ አኳያ እሱ ባነሳቸው አንዳንድ ነጥቦች ላይ መልስ እሰጥበታለሁ። ዴቪድ ቤካም ከማን.ዩናይትድ ወጥቷል።

ካንቶና ድንገት እግር ኳስን ተሰናብቷል። ቴሪ ኦንሪ ከአርሰናል ጋር ተለያይቷል። ከስንብታቸው ጀርባ በርካታ ምክንያት ቢኖራቸውም የክለባቸውን ገመና እና የግለሰብን ስብዕና የሚነካ አስተያየት ለአደባባይ ሲያውሉ አልታየም። የእድሉ ደረጀ ግን ከዚህ ተቃራኒ ነው። እኔ ስለራሴ ከማውራት ይልቅ ተግባሬ

ቢገልፅልኝ የምመርጥ ሰው ነኝ። እድሉ ከክለቡ እንዲለያይ ያደረግኩት በቂመኝነት አይደለም። እሱ በክለቡ እንዲቆይ ከሚፈልጉ ሰዎች መሀከል የመጀመሪያው በመሆኔ በቡድኑ ከሚቀጥሉት ተጨዋቾች ዝርዝር ውስጥ ስሙን አስተላልፌ ነበር። ኮንትራታቸው ተጠናቆ የተለያየን፣ በብቃት ማነስ የቀነስናቸው፣ የጠየቁንን ሂሳብ መክፈል ስላልቻልን የሸኘናቸው፣ ከሌላ ክለብ ያመጣናቸው፣ ኮንትራታቸው የተጠናቀቀ የክለቡን ተጨዋቾች ለማቆየት የሰራናቸው ስራዎች አሉ። እድሉንም አንድ ዓመት አብሮን እንዲቆይ ጥያቄ አቅርበንለታል። ይህም እንደምንፈልገው ማሳያ ነው። በአንድ ዓመት የገደብንበት የራሳችን የሆነ ምክንያቶች ነበሩን። ቂም ካለ፤ በደል አለ ማለት ነው።

‹‹አልፈረምኩም››‹‹ለምን አልፈረምክም?››‹‹ስላልተስማማሁ››‹‹ካልተስማማህ በቃ ማለት ነው?››‹‹ለምን ይበቃል ስድስት ዓመት የለፋሁበት

ቡድን እኮ ነው!››‹‹እና ታዲያ ሄደህ ቢሮ አነጋግረሀቸው ለምን

አትፈርምም?››‹‹ያደለው እኮ ሀዋሳ ድረስ ሄዶ ፈርም

ይባላል›› ‹‹አሀ እንደዛ ነበር ማድረግ የነበረብን?››‹‹አዎ እኔኮ ታሪክ የሰራሁ ተጨዋች ነኝ››‹‹የምን ታሪክ?›› [ይህን ያልኩት እኔ

የማላውቀው ታሪክ ካለው ብዬ ነው። እኔ አሰልጣኝ፣ እሱ ተጨዋች ሆኖ ያገኘውን የሊግ አሸናፊነት ታሪክ ከሆነ ይሄ የእኔና የእሱ ብቻ ታሪክ አይደለም። ሙዝ እና ዳቦ እየበሉ ክፍለ አገር ድረስ እየሄዱ ዝናብ እና ፀሃይ እየተደበደቡ ያበረታቱን ደጋፊዎች ጭምር ታሪክ ነው። ይህን ማውራት ያለባቸው ደግሞ ሌሎች ናቸው ብዬ ስለማምን ነው።] ‹‹አይገርምህም ትልቅ ታሪክማ ሰርቻለሁ››

አለኝና ይሄን ተከትሎ አሁን በሚዲያ ልገልፀው የማልፈልገውን ኃይለ ቃል ተናገረኝ። [ብሎኛል ያለውን ለአምዱ አዘጋጅ ተናግረል፡፡] ብዙ ተናግሮኝ ያሳለፍኳቸው ነገሮች ቢኖሩም አሁን ግን ከእኔ ጋር አብሮ መቀጠል ፍላጎት እንደሌለውም ተረዳሁ። የተናገረኝ በፍፁም አብረን ልንቀጥል የሚያስችል ባለመሆኑ ኮንትራቱ እንዳይታደስ አድርጌያለሁ። ስነ ልቦናዊ ጥቃት እያደረስኩበት እንደነበር

የገለፀው በጣም አሳዝኖኛል። እኔ የምታወቀው ለተጨዋቾች ነፃነት በመስጠት እና በራሳቸው ተማምነው አቅማቸውን እንዲያወጡ በማድረግ ነው። አዳዲስ ተጨዋቾች መምጣታቸውን ተከትሎ የቡድናችን ስኳድ በመስፋቱ በሚቀጥለው ዓመት ለመሰለፍ ፉክክር እንዳለበት ነግሬዋለሁ። ‹‹በሚቀጥለው ዓመት መለያ አድርጎ መግባት የለም›› ስለው ከፍተኛ የመሰለፍ ፉክክር እንደሚኖር ለመጠቆም ነው፡፡›› ተጨዋቾች (ተጨዋቾቼ) ጥሩ ሲጫወቱ

ቡድኔ እንደሚያሸንፍ እና እኔም ጎበዝ አሰልጣኝ እንደምባል እያወቅኩ እንዴት የተጨዋቼን ስነ

የማስታውሰው እድሉ የበደለኝ ነገር ስለሌለ ቂም የምይዝበት ምክንያት የለም። በርግጥ ባለመስማማት ሳቢያ በውድድር ላይ እያለንም ሆነ ውድድር ከተጠናቀቀ በኋላ ያወራንባቸው ነገሮች ነበሩ። ተገናኝተን አውርተን የተለያየነው አንድ ዓመት እንዲፈርም ተስማምተን ነበር።

የስራ ድርሻን አለማወቅበክለቡ ውስጥ ሁላችንም የተለያየ ድርሻ

ቢኖረንም አንዳችን ለአንዳችን አጋዦች ነን። በአለቃነት ስሜት በቁጣ ተጨዋቾችን የሚያስበረግግ ፀባይ የለኝም። ተጨዋች ኃላፊነት ስላለበት በመነጋገር አምናለሁ። አንዳንድ ተጨዋቾች ግን የተሰጣቸውን ኃላፊነት አለአግባብ ሲጠቀሙበት ይስተዋላል። እድሉ ጋዜጣው ላይ እንደገለፀው የቡድን ተጨዋቾቹን ስም ጠቅሶ ከፊንጫ ስኳር ጋር ባደረግንበት ጨዋታ ላይ መጫወት እንዳልነበረባቸው ተናግሯል። አምበል ስለሆነ ሀሳቡን እንዲገልፅ ብፈቅድለትም ሀሳቡን በግድ የማፅፈፀም/ ሀሳቡ መፈፀም ነበረበት የማለት መብት እንደሌለው እና እንዲህ ማለቱ በተጨዋቾች ስነ ልቦና ላይ የሚያመጣውን የስነ ልቦና ችግር የተረዳው አልመሰለኝም። በፊንጫ ስኳር ጋር ለነበረብን ጨዋታ

አጠቃላይ የቡድኑን ተጨዋቾች ይዤ ሄጄ ነበር። ለዚህም ምክንያቱ በስምንት ቀን ውስጥ (ከግንቦት 06-14) ሦስት ጨዋታ ስለነበረን ሲሆን ታሞ ስለነበር በጨዋታው ላይ እሱን አልተጠቀምኩበትም። [‹‹ተጨዋቾች ለሌላ ቡድን ፈርመዋል፣ ለፈረሙበት ቡድን ያለቃሉ›› ይባል ስለ ነበር ሁሉንም ይዣቸው መሄዴ ዋናው ምክንያቴ መሆኑን ልብ በሉ።] አለማጫወት የእኔ ኃላፊነት ቢሆንም ሲጠይቀኝ ቀጣይ ጨዋታ ከቅ/ጊዮርጊስ ጋር በመሆኑ ጉልበቱን እንዲሰበስብ እና ወደ ሙሉ ጤንነቱ እንዲመለስ በሚል እንዳላጫወትኩት ነገርኩት፤ ሊቀበለኝ ግን አልቻለም። ስለ ዳዊት እስጢፋኖስ አለመሰለፍም ሲጠይቀኝ 4 ቢጫ ስላለው አምስተኛ ተመልክቶ በቅ/ጊዮርጊስ ጨዋታ ላይ እንዳያርፍ ብዬ እንደሆነ ገለፅኩለት። አዕምሮ ውስጥ በጥርጣሬ ያለውን ነገር

ገልጾ መልስ ማግኘት ለአንድ ዓላማ ከተሰለፈ ሰው የሚጠበቅ ቢሆንም ‹‹ዳዊት መጫወት ነበረበት›› ካለኝ ግን አሰልጣኙ እሱ ነው ማለት

ነው። ይህም የስራ ድርሻን ካለማወቅ የመጣ ስህተት ነው። እሱ 2360 ደቂቃ እንዳይጫወት (እንዳይደክም) ሌሎች ሊያግዙት ይገባል። ይሄን ግን አልተቀበለም። አለመቀበሉ ደግሞ የእኔን ስራ መቃወም ነው። ተጨዋች እኔ ያቀድኩትን ስትራቴጂ የመተግበር ኃላፊነት አለበት። ከቅ/ጊዮርጊስ ጋር አቻ በመለያየት ወደ

አራተኛነት ከተንሸራተትንበት ጨዋታ በኋላ ተሰብስበን ስንነጋገር ያቀረበው ሀሳብ እና ያቀረበበት መንገድ ክለቡን አደጋ ላይ የሚጥል ነበር። ለማይሰለፉ ልጆች ተቆርቋሪ መስሎም በሚያነሳሳ መልኩ ተናገረ። ከፊንጫ ስኳር ጨዋታ በኋላ ተሰልፈው የማያውቁ ተጨዋቾች ‹‹ለምን ተሰለፉ?›› ማለት አሁን ደግሞ ‹‹ለምን አይሰለፉም?›› ብሎ ተቆርቋሪ መምሰል ሁለት ተቃራኒ ሀሳብ መሆኑን ተመልከቱ። በወቅቱ በወሳኝ ሰዓት ምስቅልቅል እንዳይመጣ አስተያየታቸውን ‹‹ገንቢ›› ብዬ አለፍኩት። ሲሳይ፣ አቡበከር፣ ተክሉ ተናግረዋል። ቂም በቀል ቢሆን ኖሮ ግን እነዚህ ተጨዋቾችም ኮንትራታቸው ስላለቀ እንዳይቀጥሉ አደርግ ነበር።

ለመጨረሻ ውሳኔ ያበቃኝ የእድሉ ሌላ ስህተት

የሚቻለንን መስዋዕትነት እሱም ሆነ ሌሎች የቡድኑ አባላት ከፍለን የፕሪምየር ሊጉን ዋንጫ ካነሳን በኋላ ቀጣዩ ስራ ስለሚጥለው ዓመት እቅድ ነድፎ መንቀሳቀስ ነው። በዚህ እቅዳችን ውስጥ እድሉን ስላካተትነው ለአንድ ዓመት ለማስፈረም ባቀረብንለት ጥያቄ ላይ ቅሬታውን ሲገልፅ አዲስ የመጣ ተጨዋችን ስም በመጥቀስ ‹‹የከሌ እድሜው ከእኔ እኩል ሆኖ ለእሱ ሁለት ዓመት ኮንትራት አቅርባችሁ ለእኔ እንዴት አንድ ዓመት ብቻ?›› በማለት ነበር። ከተሰጠው ኃላፊነት አሁንም እየወጣ ስለሆነ ከስህተቱ እንዲታረም ነግሬዋለሁ። ‹‹ለምን ሰው ገደልክ?›› የተባለ ሰው ‹‹እኔ ብቻ አይደለሁም ገዳይ›› ማለቱ መልስ ሊሆን አይችልም። በሌላ ቀን ደውሎልኝ ተገናኝተን አወራን።

‹‹ዳዊት እስጢፋኖስ የእኔ አጨዋወት ስላልተመቸው አብርሃም ይስሃቅ [ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ወደ ኢትዮጵያ ቡና የተዛወረ]

ይመጣ ብሎሀል› አለኝ። ናኒ ማን.ዩናይትድ የገባው በክርስቲያኖ ሮናልዶ ጎትጓችነት ነው። ሮናልዶ ራሱ የመጣው በጆን ኦሼ እና በጋሪ ኔቭል ጉትጎታ ነው። ሮናልዶ አሁንም ሩኒ መጥቶ በማድሪድ አብረው እንዲጫወቱ ጥያቄ አቅርቧል። ዣቪ፣ ፒኩዌና ኢንየስታ ፋብሪጋዝ ካልመጣ እያሉ ነው። ዳዊት እንዲህ ማለት ባይችልም ቢል እንኳን ሀሳቡን ስለሆነ ያቀረበው ኃጢያት አይደለም። ተጨዋች ስለፈለገ ብቻ አሰልጣኝ ካላመነበት የሚዛወር ተጨዋች አይኖርም። እድሉን ባልፈልገው ለተጨማሪ አመት

እንደማላስፈርመው እና ከዳዊት ጋር ተጣጥሞ ባይጫወት ኖሮ 2360 ያህል ደቂቃ ሊጫወት እንደማይችል እንዴት እንዳልገባው ገርሞኛል። አመት ሙሉ አብረው ተጫውተው ‹‹አንግባባም›› ብሎ ማሰቡም ሌላው አስገራሚ ነገር ነው። አብርሃምን ከበፊት ጀምሮ እፈልገው እንደነበር ነግሬው ተማምነን ነበር የተለያየነው። የትልቅ ቡድን አሰልጣኝ በመሆኔ እድሉ

ያነሳቸውን ጥቃቅን ነገሮች አልፌያቸዋለሁ። ጥቃቅን ችግሮችን ችዬ በማለፌም እኔ፣ ቡድኑና ደጋፊው ተጠቃሚ እንድንሆን አድረጓል። ግጭት ውስጥ ገብቼ ቢሆን ኖሮ ያ ሁሉ ደስታ ባልታየ ነበር። እሱ የጠቀሳቸው ትምህርት፣ በብሔራዊ

ቡድን እና በክለብ የዳበረ ልምድ ሳይኖራቸው ጎዳና ላይ ያደጉ፣ ጠጪ እና ምንም ያልተማሩ ነገር ግን ዓለምን ቁጭ ብድግ ያደረጉ ተጨዋቾችን አውቃለሁ። እድሉ ያሉት እነዚህ ጥሩ ነገሮች እኔ ላይ የሚፈጥረው ነገር የለም። ጀማሪ አሰልጣኝ መሆኔን ስለማውቅ ተጨዋች አይደለም አሰልጣኝ እንኳን ሆኖ ከእሱ የበለጠ ሲቪ ቢኖረው ‹‹ቦታዬን ይቀማኛል›› የሚል ስጋት የለብኝም። የምመዘነው ሜዳ ላይ ቡድኔ በሚያሳየው ብቃት ነው። ይህ ካልሆነ ግን ፕሮፌሰርም ብሆን ቦታው ላይ አልቀመጥም። ለራሴ የተለየ ክብር የምሰጥ ሰው አይደለሁም። ስልኬን ዘግቼ ለእረፍት ከባለቤቴ ጋር ባህር ዳር ነበርኩ። ድንገት በከፈትኩበት አጋጣሚ አንድ ደጋፊ ደውሎ የእድሉን አለመፈረም ነገረኝ። እኔ ደግሞ ለመፈረም መልካም ሂደት ላይ እንደነበረ ስለማውቅ ደውዬ አለመፈረሙን ጠየቅኩት። ‹‹አልፈረምክም?››

እድሉ ደረጀ ለሰነዘረው ሀሳብ የውበቱ አባተ ምላሽ

እዚህ አገር እግር ኳስ ውስጥ ሆኜ ራሴን እንደተለየሁ አሰልጣኝ ከቆጠርኩ አብጃለሁ ማለት ነው

2ኛው የስፖርት ም/ቤት መደበኛ ስብሰባ ተደረገ

የግንዛቤ ተመጣጣኝ አለመሆን ♦በችግርነት ተነስቷል

በዓመቱ አጋማሽ የምስረታ እና አንደኛ መደበኛ ጉባኤውን ያደረገው የስፖርት ምክር ቤት ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤውን ከትላንት ጀምሮ በግዮን ሆቴል እያካሄደ ነው። ጉባኤው ዛሬ ይጠናቀቃል።

እንደ ፌዴራል ስፖርት የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ናስር ለገሰ ገለፃ የፌዴራል ስፖርት ምክር ቤቱ የስድስት ወራት የንቅናቄና ተሳትፎ እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት በስፖርት ኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር አንበሴ እንየው ቀርቦ ተገምግሟል። ሪፖርት ያሳየው ህብረተሰቡ በስፖርት ጉዳይ ላይ ግንዛቤ እንዲያገኘ አሳታፊ የሆኑ የአሰራር ዝርጋታዎች እንደተደረጉ፣ እቅዶችን ከፋፍሎም ለባለ ድርሻ አካላት የማዳረስ ሥራ መሰራቱ ተገልጿል። በሂደትም የክትትል ስራዎች እንደሚኖሩ ተጠቁሟል።

የስፖርት ምክር ቤቱ ከስፖርት ኮሚሽኑ ጋር ጎን ለጎን እንዲሰራ በአዋጅ የተቋቋመ ሲሆን የምክር ቤቱ ሰብሳቢ የፌደራል ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነሩ አቶ አብዲሳ ያደታ ናቸው።

መመሪያዎችን ማፅደቅ፣ ለሚወጡ እቅዶች ገንቢ ሀሳቦችን መስጠት፣ አቅጣጫዎችን ማስቀመጥ፣ ሪፖርቶችን የመሰብሰብ፣ ክፍተቶችን መለየት፣ ስፖርቱን በበላይነት ከኮሚሽኑ ጋር ጎን ለጎን መምራት የምክር ቤቱ በአዋጅ የተደነገገ ኃላፊነቶቹ ናቸው።

በጉባኤው ላይ ከአፋር በስተቀር ሁሉም የክልል ኮሚሽነሮች፣ የስፖርት ማኅበራት፣ የፅህፈት ቤት ዳይሬክተሮች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል። የመከላከያ እና የፖሊስ ሰራዊት የስፖርት ውድድር አሰራር ማኑዋል ቀርቦ ግብዓት ተሰብስቦ እና አስተያየት ተሰብስቦ እንዲፀድቅ መደረጉን አቶ ናስር ለገሰ ለአውራምባ ታይምስ ገልፀዋል።

ከግንዛቤ እጥረት ሳቢያ የሁሉም ስፖርት ማኅበራት ወደ እኩል ያለመራመድ ችግር እንደታየ ተነግሯል። ‹‹መንግስት ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ለዘርፉ ትልቅ ትኩረት ሰጥቷል። የሚጠበቅባቸው ግን ያልሄዱ በመኖራቸው በጥያቄነት ተነስቷል። ስፖርት እንደ ልማት አካል በመወሰዱ ህብረተሰቡን አሳትፎ ያለመሄድ ችግሮች ነበሩ። እኩል ስፖርትን ተረድቶ ያለመራመድ ችግር አለ›› ብለዋል አቶ ናስር።

ስፖርትን ለማሳደግ ከተለምዷዊ አሰራር መላቀቅ አስፈላጊ መሆኑን ተጠቁሟል።

አቶ አብዲሳ ያደታ የስድስር ወር የምክር ቤቱን ሪፖርት ያቀረቡበት ይህ ጉባኤ ዛሬም የሚቀጥል ሲሆን የ2004 ዓ.ም. የስራ ዘመን የእቅድ እና አቅጣጫ የማስቀመጥ ውይይት ይካሄዳል ተብሎ ይጠበቃል።

የኢትዮጵያ ቡና አምበል የነበረው እድሉ ደረጀ በትላንትናው ዕለት ጠዋት ከኢትዮጵያ ቡና የመልቀቂያ ደብዳቤውን ወሰደ። የመለያ እና የእግር መከላከያ (መጋጫ) ተብሎ 1200 እንዲከፍል ተደርጓል።

ትላንት ጠዋት ወደ ክለቡ ፅ/ቤት ያመራው እድሉ 750 ብር ለመለያ እንዲሁም 450 ብር ለመጋጫ ተብሎ ከፍሎ መልቀቂያ እንደተሰጠው ለአውራምባ ታይምስ ገልጿል።

‹‹መለያውን ዋንጫ ስንበላ ለደጋፊዎች ወርውሬው ነው። ሌሎች የወረወሩ ግን አልከፈሉም። ሌሎች ለመጋጫ የከፈሉት 120 መሆኑን ሰምቻለሁ። እኔን ግን 450 ብር አስከፍለውኛል። ስድስት ዓመት የተጫወትኩበት ቡድን ይህን ሲጠይቀኝ ትልቅ ሀዘን ተሰምቶኛል›› የሚለው እድሉ ‹‹በክብር መሸኘት ሲገባቸው ብር አስከፍለው መሸኘታቸው ያስከፋል። “ለስማችሁም ጥሩ አይደለም” ብዬ ነው የወጣሁት›› ብሏል። ጉዳዩን አስመልክቶ የክለቡ ስራ አስኪያጅ አቶ ፀጋዬ ደስታን በስልክ አነጋግረናቸው ዛሬ መስሪያ ቤት ስላልነበሩ በጉዳዩ ላይ እጃቸው ላይ መረጃ እንደሌለ ቢናገሩም የመልቀቂያ ደብዳቤ ላይ ያረፈው የእሳቸው ፊርማ መሆኑን እድሉ ገልጿል።

ከኢትዮጵያ ቡና ጋር ኮንትራቱ ተጠናቆ የተለያየው እድሉ ደረጀ የአንድ ዓመት ኮንትራት ከ100 ሺህ ብር የዝውውር ገንዘብ ጋር ቀርቦለት እየተነጋገረ የነበረ ሲሆን ከአሰልጣኙ ጋር በተፈጠረ ቅሬታ አሰልጣኙ ለክለቡ የ‹‹ልቀቁት›› ደብዳቤ በማስገባቱ እድሉ ስድስት አመት የለበሰውን መለያ ለማውለቅ ተገዷል። ተጨዋቹ ሳምንት አሰልጣኙን የተቸበት ፅሁፍ በዚሁ ጋዜጣ መስተናገዱ ይታወቃል።

እድሉ ደረጀ መልቀቂያውን ትላንት ወሰደክለቡ 1200 ብር አስከፍሎታል

Page 23: Awramba Times Issue 179

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 179 ቅዳሜ ሐምሌ 30/ 2003

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

23

}SdeK¨< Ÿ}c\ ð×” ¾h¨` ¨<H TVmÁ U`„‹ ÃÖ”kl ƒ¡¡K—¨<” ¾w^²=M

¾h¨` ¨<H TVmÁ ÃÖkS<

Brazmart International General Trading Plc. Address!- •Urail Alem Brehan Plaza 1st Floor #106 1. ›<^›?M u?} ¡`e+Á” ›”vu= ¯KU w`H” ýL³ 1— öp u=a lØ` 1062. Ku< ›Åvvà òƒ Kòƒ dS<›?M I”íuT”—¨<U ¾vD”vD“ ¾h¨` u?ƒ �n ዎ ‹ SgÝ“ �”Ç=G<U u¾I”í SX]Á SÅwa‹ ÁÑ–<�M::

c=Ѳ< ƒ¡¡K— ¾w^²=M U`ƒ SJ’<” Á[ÒÓÖ<! Tel. 251-11 552 -6011 /12 Fax 251-11-5526012

ሰፋ ብሎ ውሃየሚያወርድ

ምቾት እናጥራት ያለው

ከበቂ መለዋወጫ ጋር

ለጥንቃቄዎ የተመሳሰሉትን

ይለዩ

ልማት ግንባታ ላይ ነው ብለው ሊመልሱ ይችላሉ። እንዲህም ከሆነ የሁል ጊዜ ጥያቄዬን /በዚህ ጋዜጣ እንኳ ደጋግሜ መናገሬን ልብ በሉ/ አዲስ አበባ በዚህኛው

መንግስታችን ስንት ሆስፒታል ተሰራላት ስንት ስቴዲየም ስንት ቴአትርና ሲኒማ ወዘተ?

እነ እከሌ በዓለም አቀፉ ደረጃ ያመኑበትና ያረጋገጡት

ዕድገት አሳይተናል ቢባልም ሀገር ውስጥ ገብተው የሚወጡ ነጮች ያዩትን ከመፃፍ ወደኋላ አላሉምና እንደመነሻ ያሰፈርኩት ለዚህ ነበር።

ሰላም ያገናኘን።

አዲስ አበባዊ . . .

አንድ ሰው የመንግስት ዓይን ውስጥ በገባ ቁጥር የሚናገረው፣ የሚፅፈው (አንዳንዴም የሚያስበው ሳይሆን ይቀራል?) በብዙ አንቀጾች ይተረጎምበታል። የዛኔ አፉን ይዘጋል። አፍ ሲዘጋ የመናገር ነፃነት አብሮ ይዘጋል። ብዕር ሲዘቀዘቅ የመፃፍ መብትም

አብሮ ይዘቀዘቃል። … ከዚህ አንፃር ኢትዮጵያዊ መሆን ወይም ለማኅበረሰብ መኖር ‹በሽታ› ቢሆንም፣ የማታ ማታ የሚገኘው ድል ግን ‹መድኃኒት› ይሆናል።

ለማኅበረሰብ መኖር እንደየአገሩ የእድገት ደረጃ ይለያያል። እንደ አሜሪካዊ ወደ ወገኑ እየተጠጋ

በሔደ ቁጥር (በአብዛኛው) መዳረሻው የሚሆነው BMW መኪና፣ ውድ ቤቶች … ናቸው። አንድ ኢትዮጵያዊ ለማኅበረሰቡ ሲኖር እናማ በማኅበረሰቡን በተጠጋ ቁጥር መዳረሻው (በአብዛኛው) የአውቶብስ ሰልፍ ግፊያ፣ የስራ አጥ ግፊያ… ነው።

ኢትዮጵያዊ የመሆን . . .

የገረሰሰው ሥር-ነቀል ሕዝባዊ አብዮት እና በ1997 የተካሄው አፍቃሬ-ዴሞክራሲ ሰልፎች ናቸው፡፡በሁለቱም ሁነቶች ኢትዮጵያውያን እንደ አንድ ሕዝብ ታግለዋል፤ እንደ አንድ ሕዝብ ተቃውሞአቸውን

አሰምተዋል፡፡ ልዩነቶችና ተመሳሳይነች እንዳሉ ሆነው፣ ኢትዮጵያውያን ግብፅ እና ቱኒዚያ ለሰላማዊ ለውጥ ተሞክሮ የሚሰጡ ናቸው የሚል ስሜት አሁን ድረስ አላቸው፡፡ አሁን በቅርቡ የኢትዮጵያውያን መነቃቃት እና የአረብ ስፕሪንግ የተሰኘ ፎረም ዳያስፖራ ኢትዮጵያውያን አካሂደው ነበር፡፡ በፎረሙም ታዋቂ ግብፃውያን በህዝብ መር እና ሥር-ነቀል አብዮቶች ተሞክሮዎቻቸውን አካፍለዋል፡፡ በሶስቱም ሀገራት፣ እንደሁም በአምባገነናዊና ፍፁማዊ አገዛዝ ስር በሚተዳደሩ በርካታ የስሃራ-በታች የአፍሪካ ሀገራት የፃነት፣ ፍትህ፣ የሕግ የበላይነት እና ሕዝብን ማዕከል ያደረገ አስተዳደር መሻት አለ። ከዚህ በተጨማሪ፣ በኢትዮጵያ፣ እና በሌላ በኩል ደግሞ በግብፅና ቱኒዚያ መካከል ያሉት ልዩነቶች መሰረታዊ ናቸው። ቱኒዚያ ቁጥሩ እየጨመረ ያለ የተማረ ወጣት፣ በከተማ ኑዋሪ ሕዝብ አላት።

አፈና ጭቆና፣ በተውሰኑ ሰዎች የኃብት መከማቸት፣ የወጣቱ ሥራ-አጥነት፣ የምግብ ዋጋ ንረትና ርትዓዊ ያልሆነ ገቢ በሶስቱም ሀገራት ስር የሰደዱ ናቸው፡፡ ለምሳሌ፣ በሚያዚያ 2010 የታተመውና ግብፅን የተመለከተው የአይ.ኤም.ኤፍ ‹‹ካንትሪ ሪፖርት››፣ ከ2004 አንስቶ የተወሰዱ ተከታታይና ዘርፈ-ብዙ ማሻሻያዎች የፊሲካል፣ ሞኒታሪና የውጭ ተጋላጭነትን መቀነሳቸውንና የኢንቨስትመንት ሁኔታውን ማሻሻሉን ገልፆ ነበር፡፡ የአይ.ኤም.ኤፍ ተወካይ ስለ ኢትዮጵያ የተናገሩት ልክ ከግብፅ ጋር አንድ አይነት ሊባል የሚችል ነበር። ኢትዮጵያ በዓለም እጅግ ርሃብተኞች የሚገኙባት ሀገር ናት፡፡ ከ60 እስከ 70 በመቶ ገደማ የኢትዮጵያ ወጣት ሥራ-አጥ ነው፡፡ አምስት ሚሊዮን እናትና አባት የሞተባቸው ህፃናት በሀገራቱ ውስጥ ይገኛሉ፡፡ እውነታው ይህ ቢሆንም፣ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በዜጎች አኗኗር ላይ ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ ውጤትና መሻሻል አስከትሏል ሲል ያደንቃል፡፡

ድርሰቱ ለሁሉም ሀገራት ተመሳሳይ ይመስላል፡፡ የኢትዮጵያ ምሁራን እንደሚሉት አይ.ኤም.ኤፍ እጅግ አስከፊ የዋጋ ግሽበት፣ የውጣቱ ሥራ-አጥነት፣ እና በሕገ-ወጥ መንገድ በዓለም እጅግ ኋላቀርና ድሃ ከሆነች ሀገር ወደ ባለጠጎቹ በቢሊየኖች ዶላር ከሀገር መውጣቱን ስህተት ሆኖ አላገኘውም፡፡ ግብፅን በተመለከተ ተቋሙ ባወጣው ሪፖርት የግብፅ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ከተጠበቀው በላይ የተሻለ መሆኑን ቢናገርም፣ ግሽበቱ አናት ላይ እንዳለ ይገኛል፡፡ በርካታ ኢትዮጵያውያን ኤሊቶች እንደ አይ.ኤም.ኤፍ እና የዓለም ባንክ ያሉ ተቋማት በማህበሪዊ ቀውስ ውስጥ ለሚገኙ ሀገራት ያማሩ ምስሎችን በማቅረብ በድሃውና ወጣቱ ላይ ጩቦ ይሰራሉ የሚል ስሜት አላቸው፡፡ የአይ.ኤም.ኤፍን ትኩረት ያመለጡ፣ አልያም ተቋሙ ሪፖርት ላለማድረግ የመረጣቸው እጅግ አስቸኳይ መፍትሄ የሚያስፈልጋቸው በርካታ ችግሮች ነበሩ።

በሶስቱም ሀገራት እንዳለው ከፍተኛ የህዝብ ቁጥር ሁሉ፣ ከፍተኛ የሆነ ሥራ አጥነት ሶስቱንም ያመሳስላቸዋል። 40 ሚሊየን ገደማ ኢትዮጵያውያን የተወለዱት ከ1991 በኋላ ነው ማለት ይቻላል፡፡ በእስከዛሬው ህይወታቸው የአንድ ገዥ ፓርቲና መሪ ተሞክሮ ነው ያላቸው፡፡ የኢትዮጵያ ጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊ የሚገዙት በብርቱ ክንድ ሲሆን፣ ከ1991 አንስቶም ሥልጣን ላይ እንዳሉ ይገኛሉ፡፡ ለሚሊየኖች ቱኒዚያውያን እና ግብፃውያን ይህ እውነት ተመሳሳይ ነው፡፡

እንደ ብሉምበርግ ግምት፣ ቱኒዚያ በየዓመቱ ሥራ ለሚፈልጉ፣ በየዓመቱ አንድ ሚሊየን የሥራ ዕድል መፍጠር ይጠበቅባታል። ኢትዮጵያ ለሚሊየኖች ሥራ በመፍጠሩ ረገድ ጥረት ማድረጓን የተወች ይመስላል። በሺህዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች ሀገር ቤት ምንም ተስፋ ባለመመልከታቸው ወደሁለቱ የዓለም ጥጋ ጥጎች ይሰደዳሉ። በኢትዮጵያ ቱኒዚያ እና ግብፅ ውስጥ ያለው ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታዎች ሙሉ በሙሉ ተመሳሳይ ናቸው ማለት ይቻላል። አስከፊነቱ እየተባባሰ የሄደ ኢኮኖሚ፣ ከፕሬዝዳንት ቤን አሊ አፈናና ሙስና ጋር ተደማምሮ ቱኒዚያን ለሕዝባዊ ተቃውሞ ዳርጓታል። የ26 ዓመት የፍራፍሬና አትክልት ሻጭ - ሞሃመድ ቦዛዚ - በታህሳስ 17/2010 ራሱን በእሳት ባያያዘበት ወቅት ነበር የቱኒዚያው አብዮት የተጀመረው። ወደጃዝሚን አብዮት ባመራው የሞሃመድ ሞት ኢትዮጵያውያን በመገረም ሰሜታቸው ተነክቷል። ብዙ ኢትዮጵያውያን እንደሚሉት በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የአንድ ፓርቲ መንግስት አፈና እና ጭቆና ከቱኒዚያው እጅግ የባሰ ነው።

የሀገሪቱ የሁለት አሃዝ ዕድገት ልክ እንደ ቱኒዚያ እና ግብፅ በኢትዮጵያ ያለውን መዋቅራዊና የፖሊሲ መጣረሶችና መዛነፎች የሚሸሽጉ ናቸው። እነዚህ መዋቅራዊ መዛነፎችና የሚያስከትሉት ርትዕ-አልባነት በየዕለቱ በሚሊየኖች ላይ ሚደርስ ነው። በተለይ በሀገራቱ ወጣቶች። ነዳጅ ዘይት አምራች ካልሆነች ኢትዮጵያ ጋር ተመሳሳይነት ባለው መልኩ፣ የቱኒዚያ ዕድገት ከፍተኛ ሥራ-አጥነትን፣ የዋጋ ንረትና በኃብታሙና በድሃው መካከል ያለውን የገቢና የአኗኗር ልዩነት አባብሶታል።

ከግብፅና ቱኒዚያ በባሰ ድሃና ዝቅተኛ የዕድገት ደረጃ ላይ የምትገኝ ናት - ኢትዮጵያ፡፡ ብሉምበርግ፣ በ2010 መጨረሻ ላይ፣ የቱኒዚያ ዓመታዊ የነፍስ ወከፍ ገቢ 9ሺህ 500 የአሜሪካ ዶላር፣ የኢትዮጵያ ደግሞ 370 ዶላር እንደሆነ ግምቱን ሰጥቶ ነበር፡፡ 67 በመቶ የቱኒዚያ ህዝብ ከተማ የሰፈረ ነው፡፡ 80 በመቶ የኢትዮጵያ ህዝብ ደግሞ በገጠር ኑዋሪ ነው፡፡ ማንበብና መፃፍ በሚችሉ ዜጎች ብዛት ቱኒዚያ ከፍተኛውን ሰፈራ ትይዛለች፤ ኢትዮጵያ ደግሞ ከዓለም ዝቅተኛዎቹ መካከል አንዷ ናት፡፡ ማንበብና መፃፍ የሚችለው ህዘብ ቁጥር ከፍተኛ መሆን፣ እየጨመረ የሚሄድ የመካከለኛ ገቢ ህብረተሰብ፣ በራዲዮ፣ ቴሌቪዥን፣ ኢንተርኔት፣ ሞባይል ስልኮች፣ ‹‹ዩ ቲዩብ››፣ ቲዊተር፣ እና ጋዜጦች የተጠናከረ ማህበራዊ የመረብ ትስስር በቱኒዚያ ውስጥ ያለውን ግንኙነት አጠናክረዋል፡፡ አፈናና ፍርሃት መረጃን በፍጥነትና ውጤታማ በሆነ መልኩ ከማደራጀትና ከማሰራጨት የቱኒዚያን ህዝብ ወደ ኋላ እንዲል አላደረገውም።

በተፃራረው ኢትዮጵያ በአፍሪካ በግንኙነት መረቦች ዝቀተኛ ትስስር ያለባትና በከተማዎች በርካታ ህዝብ የማይኖርበት ሀገር ናት፡፡ በዓለም ዝቅተኛው ማንበብና መፃፍ የሚችል ህዝብ ያለበት ነች፡፡ ከ15-29 የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ከአጠቃላዩ የሀገሪቱ የህዝብ ቁጥር 50.3 በመቶ ይሆናል ተብሎ ይገመታል፡፡ ይህ መጠን ከቱኒዚያ ጋር አንድ ነው ማለት ይቻላል፡፡ በዚህ የዕድሜ ክልል የሚገኝ የማህበረሰብ ክፍል ነው ያልተገደበ የፖለቲካ መብቶችና ሲቪል ነፃነቶች እና በትምህርት፣ ጤና፣ መጠለያ፣ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ እና ቅጥር የሚጠይቀው፡፡

ልክ እንደቱኒዚያ፣ የኢትዮጵያ መንግስት ለደካማ አስተዳደርና በሀገር ቤት ለታጣው የስራ ዕድል እንደ ቋሚ መፍትሄ በዚህ የዕድሜ ክልል ያሉ ወደውጭ ሃገራት በሚያደርጉት ያልተቋረጠ ስደት ይተማመናል፡፡ ኢትዮጵያውያን፣ እንደግብፃውያንና ቱኒዚያውያን የመረጃ ቴክኖሎጂን ለማጠናከር እና በሚሊየኖች የሚቆጠሩ ሰዎችን ሊቀጥሩ የሚችሉ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞችን ለመፍጠር የኢትዮጵያ መንግስት ያልተገደበ ነፃነት መፍቀድ አለበት ይላሉ።

ከቱኒዚያ በተለየ በኢትዮጵያ ውስጥ መገለል አንዱ የአኗኗር መንገድ ነው፡፡ መጠነኛ ግንኙነት መረቦች ቁርኝት አለ፡፡ ለዜናና መረጃ ያለው ተደራሽነት ከዓለም እጅግ ዝቅተኘዎቹ መካከል አንዱ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ድሃ ዝቅተኛ ወይም ምንም ትምህርት ያልተከታተለ ነው፡፡ በት/ቤቶች ያለው የሴቶች ቁጥርና የሥልጣን ውክልና ከአፍሪካ ከዝቅተኞቹ ይመደባል፡፡ ከቱኒዚያውያንና ግብፃውያን በተቃራኒ፣ ድሃው ኢትዮጵያዊ ተነጣጥሎ ነው የሚኖረው፡፡ እንዲሁም በብሄር ተከፋፍሏል፡፡ እርስ በእርስ መረጃ መለዋወጥ አይችሉም፡፡ ይህም ሁኔታ ሥርዓቱና የብሄር ኤሊቶች ለማወናበድ፣ ለመከፋፈል፣ ለማላኮስና ድሃውንና የተነጠለውን ለመቆጣጠር ያመቸዋል።

ሥርዓቱ ድሃውንና የተማረውን የሚደልልና እንዲቀለቀሉትም የሚያስገድድ ነው። ከቱኒዚያ ወይም ግብፅ በበለጠ ኢትዮጵያ በዕርዳታ ላይ የተደገፈች ናት፡፡ ከአፍጋኒስታንና ኢራቅ በመቀጠል በዓለም ደረጃ ግዙፏ የውጭ ዕርዳታ ተቀባይ ሀገር ስትሆን በአፍሪካ ደግሞ ቀዳማዊ ናት፡፡ ሥርዓቱ እርዳታን እንደ መቅጫና መቆጣጠሪያ መሳሪያ ይገለገልበታል፡፡ ፍርሃት በማህበረሰቡ መካከል ነግሷል፡፡ ለአፈና፣ ጭቆናና ድህነት ቆራጥ ምላሽ ከመስጠት ይልቅ ይበልጥ ፍርሃት የሚፈለፈል ነው የሚመስለው፡፡ ይህንንም የፍርሃት ባህል መቀበል የተረጋገጠ ትንበያ ሆኗል፡፡

/አክሎግ ቢራራ (ፒኤች.ዲ)፣ በዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ ውስጥ በሚገኘው ትሪኒቲ ዩኒቨርስቲ ተባባሪ ፕሮፌሰር ናቸው፤ በዓለም ባንክ ውስጥም ከፍተኛ አማካሪ በመሆን አገልግለዋል። /

ኢትዮጵያውያንን . . .

የእኛ ቢታኒያ

እደጊልን፤ ተመንደጊልን፤ መሠረትሽ ይጠንክር፤ ፍሬሽ ይባረክ!!

ወላጆችሽ መሲ እና ፍሬ

ልቦና አዳክማለሁ? እድሉ የተረዳኝ መንገድ በጣም የተሳሳተ ነው።

እድገት የሚመጣው መከባበር ሲኖር ነው

እኔ የትኛውን ደረጃ አግኝቼ? ምን ሰራሁ ብዬ? ከፍ ማለት እንደጀመርኩ አላውቀውም። ለዓለም ዋንጫ የምድብ ማጣሪያ ውስጥ ለመግባት ኢትዮጵያ የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታ ለማድረግ የተመደበችው ከሶማሊያ ጋር መሆኑ ደረጃችን ዝቅተኛ መሆኑን ያሳያል። እዚህ አገር እግር ኳስ ውስጥ ሆኜ ራሴን እንደተለየሁ አሰልጣኝ ከቆጠርኩ አብጃለሁ ማለት ነው። ሀሳብ መሰንዘር እና ተናግሮ

ቡድንን መረበሽ የተለያየ ነገር ነው። የሚሰነዘረው ሀሳብ ሌሎችን የሚያሳንስ፣ ክለብን አደጋ ላይ የሚጥል መሆን የለበትም፤ ወደ መፍትሄ የሚወስድ መሆን አለበት እንጂ። በእድሉ ተግባር የተነሳ ተጨዋቾች በነፃነት ከመናገር እንዲቆጠቡ አላደርግም። የአለቃን (አሰሪን) ትዕዛዝ መዘንጋት ግን ተገቢ አይደለም። እድገት የሚመጣው መከባበር ሲኖር ነው። በርካታ ትልልቅ ተጨዋቾች በክለባቸው ውስጥ አልፈው ሌሎች መተካታቸው በሂደት ውስጥ የሚፈጠር ነው፤ አሳልጣኞችም እንዲሁ። ከኢትዮጵያ ቡና ጋር መቼ እና በምን አይነት ሁኔታ ልለያይ እንደምችል ባላውቅም የቅጥር ውል ሲሰጠኝ አንድ ቀን ደግሞ የስንብት ውል እንደሚሰጠኝ ዘንግቼ አላውቅም። ቡና ከሁላችንም በላይ ስለሆነ ቅድሚያ

መስጠት የሚያስፈልገው ለክለቡ ነው። ማንም ተጨዋች እና አሳልጣኝ ከዚህ በላይ አይሆንም። ሚዲያ ማስተማሪያ በመሆኑ የቡድንን ገመና (ሊገለፁ የማይገባቸው ነገሮች) ለፍጆታ ማዋል ስህተት መሆኑን ሁላችንም ልንረዳ ይገባል፤ ከስፖርታዊ ስነ ምግባርም ውጪ ነው። እኔ እና እድሉ በግል ፀብ የለንም።

በስራ ግን ስላልተግባባን መስራት አንችልም። ይህ ማለት እድሉ ሌላ ክለብ ወይም ቡና አይጫወትም ማለት ሳይሆን እኔ እስካለሁ ግን አብረን ልንሰራ አንችልም፤ ስለማንግባባ። አብረን ቀጠልን ማለት ክለቡ ከእኛ የሚጠበቀውን ምርት ያሳጣዋል። ይህ ደግሞ ጎጂ ስለሆነ እንደተለያየን ሊታወቅ ይገባል።

ማስታወሻ፡- የኢትዮጵያ ቡናው አሰልጣኝ ውበቱ አባተ

ይህን ሀሳብ ለአውራምባ ታይምስ የሰጠው በድምፅ ሲሆን

ወደ ፅሁፍ የቀየረው አቤል ዓለማየሁ ነው፡፡

Page 24: Awramba Times Issue 179

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 179 ቅዳሜ ሐምሌ 30/ 200324 ማ ስ ታ ወ ቂ ያብርሃ

ንና ሰ

ላም ማ

ተሚያ ድ

ርጅት