issue-703.pdf

28
ቅፅ 13 ቁጥር 703 ቅዳሜ ሰኔ 29 ቀን 2005 ዓ.ም ብር 8.00 ህብረተሰብ ገፅ 9 ህብረተሰብ ገፅ 7 ነፃ አስተያየት ገፅ 5 ጥበብ ገፅ 18 አበባየሁ ገበያው አለማየሁ አንበሴ አበባየሁ ገበያው ገፅ 3 ምንጩ ያልታወቀ ትኩሳት አለብዎ? ዩኒቨርሳል ከፍተኛ ክሊኒክ ታይፎይድ፣ ፌቨር መሆኑን ተጠራጥረዋል? ወይስ ወባ? በ3 ደቂቃ በሽታው እንዳለብዎ ወይም እንደሌለብዎ ማረጋገጥ ይችላሉ፡፡ ልዩ መመርመሪያ አዘጋጅተናል!! በኢንተሮቼክ ቴስት እና በማላስካን ስትሪፕ ወዲያውኑ ውጤቱን ያገኛሉ!! አድራሻ ቸርችል ጎዳና ቴዎድሮስ አደባባይ ከፍ ብሎ ኤሌክትሪክ ወርልድ ሕንፃ አጠገብ ስልክ 011-1-55033 6 ገፅ 10 መልዕክት ወደ ገፅ 24 ዞሯል ነፃነት ወደ ገፅ 2 ዞሯል ሽልማት ወደ ገፅ 2 ዞሯል እስር ወደ ገፅ 2 ዞሯል ሚኒስትር ወደ ገፅ 2 ዞሯል ጠ/ሚኒስትር ኃ/ማርያም ደሳለኝ “ይቅርታን የደፈሩ መሪ”! የዓመፅ ፍሬ! “ከዚህ አይነት ህይወትስ እስከ ወዲያኛው…” ምክኒያታዊነት እና እንባ “የማህበረ ስላሴ ዘደቂቀ ኤልያስ” አባላት፤ ከቅዱሳን አባቶች የተላክነውን የቅዱስ ኤልያስን መልዕክት ለአዲሱ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ ክርስቲያን ፓትሪያሪክ አቡነ ማቲያስ እንዳናደርስ ተከለከልን አሉ፡፡ አርቲስት ጀማነሽ ሰለሞን የተካተተችበት መልዕክት አድራሽ ቡድን፤ ባለፈው ማክሰኞ ረፋዱ እነ አርቲስት ጀማነሽ “የቅዱስ ኤልያስ”ን መልዕክት ለፓትሪያሪኩ እንዳናደርስ ተከለከልን አሉ የመንግስት ቤቶች ኤጀንሲ ዋና ዳሬክተር አቶ ተፈሪ ፍቅሬና ሁለት ምክትል ዳይሬክተሮች በኪራይ ሰብሳቢነት ተገምግመው ከስራ የመንግስት ቤቶች ኤጀንሲ ዋና ዳሬክተርና 2 ምክትሎቻቸው ከሃላፊነታቸው ተነሱ ሃላፊነታቸው እንደተነሱ ተገለፀ፡፡ ተጠሪነቱ ለስራና ከተማ ልማት ሚኒስቴር የሆነው የቤቶች ኤጀንሲ ከትላንት በስቲያ ሶስቱን ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ከሥራ ሃላፊነታቸው ያነሳው በተለያየ ደረጃ ግምገማ ከተካሄደ በኋላ እንደሆነ ምንጮቻችን ገልፀዋል፡፡ የፀረ ሙስና ኮሚሽንም ከአንድ ዓመት በላይ በሥራ ሃላፊዎቹ ላይ ምርመራ ሲያደርግ እንደቆየ የጠቀሱ ምንጮች፤ ሃላፊዎቹ በኪራይ ሰብሳቢነትና ሃላፊነትን በአግባቡ ባለመወጣት ተገምግመው ነው ከሥራ ሃላፊነታቸው የተነሱት ብለዋል። ማተሚያ ቤት እስከገባንበት ሰዓት ድረስ በተነሱት ሃላፊዎች ምትክ ማን እንደሚሾም አልታወቀም፡፡ በ“ቢግ ብራዘር አፍሪካ” የሪያሊቲ ሾው ውድድር ላይ የተሳተፈችው የ26 ዓመቷ ኢትዮጵያዊት ቤተልሄም አበራ፤ በቅርቡ በተለያዩ ድረገፆች በተሰራጨው ቪዲዮ ላይ ወሲብ ስትፈጽም መታየቷ በወንጀል የሚያስከስሳት መሆኑን የገለፁ የህግ ባለሙያዎች፤ ፍ/ቤት የጥፋተኝነት ብይን ከወሰነባት የ5 ዓመት እስር እንደሚጠብቃት ተናገሩ፡፡ በወጣቷ ላይ ክስ ለመመስረት ዝግጅታቸውን እንዳጠናቀቁ ለአዲስ አድማስ የገለፁት የህግ ባለሙያዎቹ አቶ ጳውሎስ ተሰማ እና አቶ ተስፋሁን ፀጋዬ፤ ቤቲ የፈፀመችው ተግባር የህብረተሰቡን ባህል የሚቃረን በመሆኑና ይህም በሚዲያ በመተላለፉ በኢትዮጵያ ህግ ያስከስሳታል ብለዋል፡፡ እንኳን ድርጊቱን በአደባባይ የፈፀመ ቀርቶ ለመፈፀም ሙከራ ያደረገም በወንጀል እንደሚጠየቅ የገለፁት ጠበቆቹ፤ ቤቲ በአደባባይ የኢትዮጵያውያንን ባንዲራ ይዛ መልካም ገጽታችንን ማሳየት ሲገባት ባህላችን በፌስቡክ ላይ እርቃን ፎቶግራፍ መለጠፍ በህግ ያስቀጣል ቤቲ ጥፋተኛ ከተባለች የ5 ዓመት እስር ይጠብቃታል “አዲስ ጉዳይ” መጽሔት የዓለም አቀፍ ጋዜጠኞች ማዕከል ሽልማት አሸናፊ ሆነ ላለፉት ሶስት ዓመታት የሣይንስ እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር በመሆን የሰሩት አቶ ደሴ ዳልኬ፤ የደቡብ ክልል ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳደር ሆነው የቀድሞው የሣይንስ እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር የደቡብ ክልል ፕሬዚዳንት ሆነው ይሾማሉ እንደሚሾሙ ምንጮች ገለፁ፡፡ ላለፉት ስምንት ዓመታት የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር በመሆን ያገለገሉት አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ከትላንት በስቲያ የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ሀይማኖታችንና ህጋችን የማይፈቅደውን ነገር በአደባባይ ፈጽማለች ብለዋል፡፡ ክሱን መመስረት ያስፈለገው ሌሎች በተመሳሳይ ተግባር ውስጥ የተዘፈቁ ላይ መልዕክታቸውን ጋዜጠኞች ባሉበት ለፓትርያርኩ ለማቅረብ ፓትሪያሪኩ ጽ/ ቤት በር ላይ ተገኝተው የነበረ ቢሆንም የጥበቃ አባላት “ለማነጋገር ፍቃድ የላችሁም” ብለው መልሰዋቸዋል፡፡ ከማህበሩ አባላት መካከል አርቲስት ጀማነሽ ሰለሞን እና መ/ር ወልደመስቀል ፍቅረማርያም ለአዲስ አድማስ እንደገለፁት፤ ለሁለት ጊዜያት ያህል 4 ኪሎ በሚገኘው መንበረ ፓትሪያሪክ ጽ/ቤት በመሄድ ከአባቶች የተላኩትን መልዕክት ለማድረስ ቢሞክሩም ከጽ/ ቤቱ የጥበቃ ሃላፊዎች ማለፍ አልቻሉም። “በመጀመሪያው ቀን ከማህበረ ስላሴ መልዕክት ይዘን መምጣታችንን ለጥበቃዎች በመንገር ወደ ውስጥ እንድንገባ ከተፈቀደልን በኋላ ሌሎች በግቢ ውስጥ የነበሩ ጥበቃዎች በድጋሚ አስቁመውን ከስላሴ ካቴድራል ማኅበር የመጣችሁ መስሎን ነው እንጂ እናንተ መግባት አትችሉም በማለት ፓትሪያሪኩን እንዳናገኝ ተደርገናል” የሚሉት መ/ር ወልደመስቀል፤ በተለይ አንዲት ሴት የጥበቃ አባል ከአግባብ ውጭ ጀማነሽን እየገፈታተረች እንድትወጣ ማድረጓን ገልፀዋል፡፡ በሚዲያ ሳይቀር ቅዱስ ፓትሪያሪኩ ማንም ሰው ያለከልካይ በአካል መጥቶ ሊያነጋግረኝ ይችላል ያሉትን መነሻ “አዲስ ጉዳይ” መጽሔት በታፈኑ ዕውነቶች አምድ ላይ ለንባብ ባበቃው “ቀናት የሚታደጓቸው እድሜ ልኮች” የሚል ተንታኝ ሃተታ (ፊቸር ስቶሪ) የዓለም አቀፉን የጋዜጠኞች ማዕከል (ICFJ) የሁለተኛ ደረጃ ቀዳሚ ሽልማት አሸነፈ፡፡ ማዕከሉ ከአፍሪካ የጤና ጋዜጠኞች ማህበር እና ከአረብ ሚዲያ ፎረም ጋር በመተባበር ባዘጋጀው በክትባት ጉዳይ ላይ የሚያተኩር የዘገባ ውድድር ላይ 200 የእስያ፣ የአፍሪካና ስድስት የባህረሰላጤው አገራት ሚዲያዎች እንደተሳተፉ ታውቋል፡፡ የአቶ ግርማ ሰይፉ “ነፃነት ዋጋው ስንት ነው” ረቡዕ ይመረቃል ተቃዋሚዎች በሂደቱ ላይ እንጂ በግድቡ ላይ ተቃውሞ የለንም አሉ ናፍቆት ዮሴፍ በፓርላማ ብቸኛው የተቃዋሚ ተወካይ በሆኑት አቶ ግርማ ሠይፉ የተፃፈው “ነፃነት ዋጋው ስንት ነው” የተሰኘ መፅሀፍ የፊታችን ረቡዕ ይመረቃል፡፡ በአገሪቱ ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታ ላይ ያጠነጥናል የተባለው መጽሐፍ፤ በዋናነት ሰዎች እንዴት ነፃነታቸውን አሳልፈው እየሰጡ እንደሆነ በሚያሳዩ እውነተኛ ታሪኮች ላይ እንደሚያተኩር አቶ ግርማ ተናግረዋል፡፡ በ240 ገፆች የተቀነበበው መጽሐፉ፤ የ97 እና የ2002 ዓ.ም ምርጫዎችን በስፋት ይዳስሳል ብለዋል - ፀሐፊው፡፡ “አብዛኛው ሰው ግርማ በ97 ምርጫ ዓለምን ዝም ያሰኘና ውግዘት ያልነካው መፈንቅለ መንግስት አለማየሁ አንበሴ እና መልካሙ ተክሌ አቶ ደሴ ዳልኬ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ

Upload: muhudin-mohammed-seman

Post on 03-Jan-2016

409 views

Category:

Documents


1 download

DESCRIPTION

hn

TRANSCRIPT

Page 1: Issue-703.pdf

ቅፅ 13 ቁጥር 703 ቅዳሜ ሰኔ 29 ቀን 2005 ዓ.ም ብር 8.00

ህብረተሰብ ገፅ 9

ህብረተሰብ ገፅ 7

ነፃ አስተያየት ገፅ 5

ጥበብ ገፅ 18

አበባየሁ ገበያው

አለማየሁ አንበሴ

አበባየሁ ገበያው

ገፅ 3

ምንጩ ያልታወቀ ትኩሳት አለብዎ?

ዩኒቨርሳል ከፍተኛ ክሊኒክ

ታይፎይድ፣ ፌቨር መሆኑን ተጠራጥረዋል? ወይስ ወባ? በ3 ደቂቃ በሽታው እንዳለብዎ ወይም እንደሌለብዎ ማረጋገጥ ይችላሉ፡፡ ልዩ መመርመሪያ አዘጋጅተናል!! በኢንተሮቼክ ቴስት

እና በማላስካን ስትሪፕ ወዲያውኑ ውጤቱን ያገኛሉ!! አድራሻ ቸርችል ጎዳና ቴዎድሮስ አደባባይ ከፍ ብሎ ኤሌክትሪክ ወርልድ ሕንፃ አጠገብ

ስልክ 011-1-550336

ገፅ 10

መልዕክት ወደ ገፅ 24 ዞሯል ነፃነት ወደ ገፅ 2 ዞሯል

ሽልማት ወደ ገፅ 2 ዞሯል

እስር ወደ ገፅ 2 ዞሯልሚኒስትር ወደ ገፅ 2 ዞሯል

ጠ/ሚኒስትር ኃ/ማርያም ደሳለኝ

“ይቅርታን የደፈሩ መሪ”!

የዓመፅ ፍሬ!

“ከዚህ አይነት ህይወትስ እስከ

ወዲያኛው…”

ምክኒያታዊነት እና እንባ

“የማህበረ ስላሴ ዘደቂቀ ኤልያስ” አባላት፤ ከቅዱሳን አባቶች የተላክነውን የቅዱስ ኤልያስን መልዕክት ለአዲሱ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክርስቲያን ፓትሪያሪክ አቡነ ማቲያስ እንዳናደርስ ተከለከልን አሉ፡፡ አርቲስት ጀማነሽ ሰለሞን የተካተተችበት መልዕክት አድራሽ ቡድን፤ ባለፈው ማክሰኞ ረፋዱ

እነ አርቲስት ጀማነሽ “የቅዱስ ኤልያስ”ን መልዕክት ለፓትሪያሪኩ እንዳናደርስ ተከለከልን አሉ

የመንግስት ቤቶች ኤጀንሲ ዋና ዳሬክተር አቶ ተፈሪ ፍቅሬና ሁለት ምክትል ዳይሬክተሮች በኪራይ ሰብሳቢነት ተገምግመው ከስራ

የመንግስት ቤቶች ኤጀንሲ ዋና ዳሬክተርና 2 ምክትሎቻቸው ከሃላፊነታቸው ተነሱ

ሃላፊነታቸው እንደተነሱ ተገለፀ፡፡ተጠሪነቱ ለስራና ከተማ ልማት

ሚኒስቴር የሆነው የቤቶች ኤጀንሲ ከትላንት በስቲያ ሶስቱን ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ከሥራ ሃላፊነታቸው ያነሳው

በተለያየ ደረጃ ግምገማ ከተካሄደ በኋላ እንደሆነ ምንጮቻችን ገልፀዋል፡፡ የፀረ ሙስና ኮሚሽንም ከአንድ ዓመት በላይ በሥራ ሃላፊዎቹ ላይ ምርመራ ሲያደርግ እንደቆየ የጠቀሱ ምንጮች፤ ሃላፊዎቹ

በኪራይ ሰብሳቢነትና ሃላፊነትን በአግባቡ ባለመወጣት ተገምግመው ነው ከሥራ ሃላፊነታቸው የተነሱት ብለዋል። ማተሚያ ቤት እስከገባንበት ሰዓት ድረስ በተነሱት ሃላፊዎች ምትክ ማን እንደሚሾም አልታወቀም፡፡

በ“ቢግ ብራዘር አፍሪካ” የሪያሊቲ ሾው ውድድር ላይ የተሳተፈችው የ26 ዓመቷ ኢትዮጵያዊት ቤተልሄም አበራ፤ በቅርቡ በተለያዩ ድረገፆች በተሰራጨው ቪዲዮ ላይ ወሲብ ስትፈጽም መታየቷ በወንጀል የሚያስከስሳት መሆኑን የገለፁ የህግ ባለሙያዎች፤ ፍ/ቤት የጥፋተኝነት ብይን ከወሰነባት የ5 ዓመት እስር እንደሚጠብቃት ተናገሩ፡፡

በወጣቷ ላይ ክስ ለመመስረት ዝግጅታቸውን እንዳጠናቀቁ ለአዲስ አድማስ የገለፁት የህግ ባለሙያዎቹ አቶ ጳውሎስ ተሰማ እና አቶ ተስፋሁን ፀጋዬ፤ ቤቲ የፈፀመችው ተግባር የህብረተሰቡን ባህል የሚቃረን በመሆኑና ይህም በሚዲያ በመተላለፉ በኢትዮጵያ ህግ ያስከስሳታል ብለዋል፡፡

እንኳን ድርጊቱን በአደባባይ የፈፀመ ቀርቶ ለመፈፀም ሙከራ ያደረገም በወንጀል እንደሚጠየቅ የገለፁት ጠበቆቹ፤ ቤቲ በአደባባይ የኢትዮጵያውያንን ባንዲራ ይዛ መልካም ገጽታችንን ማሳየት ሲገባት ባህላችን

በፌስቡክ ላይ እርቃን ፎቶግራፍ መለጠፍ በህግ ያስቀጣል

ቤቲ ጥፋተኛ ከተባለች የ5 ዓመት እስር ይጠብቃታል

“አዲስ ጉዳይ” መጽሔት የዓለም አቀፍ ጋዜጠኞች ማዕከል ሽልማት አሸናፊ ሆነ

ላለፉት ሶስት ዓመታት የሣይንስ እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር በመሆን የሰሩት አቶ ደሴ ዳልኬ፤ የደቡብ ክልል ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳደር ሆነው

የቀድሞው የሣይንስ እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር የደቡብ ክልል

ፕሬዚዳንት ሆነው ይሾማሉ

እንደሚሾሙ ምንጮች ገለፁ፡፡ ላለፉት ስምንት ዓመታት የደቡብ

ክልል ርዕሰ መስተዳድር በመሆን ያገለገሉት አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ከትላንት በስቲያ የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር

ሀይማኖታችንና ህጋችን የማይፈቅደውን ነገር በአደባባይ ፈጽማለች ብለዋል፡፡

ክሱን መመስረት ያስፈለገው ሌሎች በተመሳሳይ ተግባር ውስጥ የተዘፈቁ

ላይ መልዕክታቸውን ጋዜጠኞች ባሉበት ለፓትርያርኩ ለማቅረብ ፓትሪያሪኩ ጽ/ቤት በር ላይ ተገኝተው የነበረ ቢሆንም የጥበቃ አባላት “ለማነጋገር ፍቃድ የላችሁም” ብለው መልሰዋቸዋል፡፡

ከማህበሩ አባላት መካከል አርቲስት ጀማነሽ ሰለሞን እና መ/ር ወልደመስቀል ፍቅረማርያም ለአዲስ አድማስ እንደገለፁት፤ ለሁለት ጊዜያት ያህል 4 ኪሎ በሚገኘው መንበረ ፓትሪያሪክ

ጽ/ቤት በመሄድ ከአባቶች የተላኩትን መልዕክት ለማድረስ ቢሞክሩም ከጽ/ቤቱ የጥበቃ ሃላፊዎች ማለፍ አልቻሉም።

“በመጀመሪያው ቀን ከማህበረ ስላሴ መልዕክት ይዘን መምጣታችንን ለጥበቃዎች በመንገር ወደ ውስጥ እንድንገባ ከተፈቀደልን በኋላ ሌሎች በግቢ ውስጥ የነበሩ ጥበቃዎች በድጋሚ አስቁመውን ከስላሴ ካቴድራል ማኅበር የመጣችሁ መስሎን ነው እንጂ እናንተ

መግባት አትችሉም በማለት ፓትሪያሪኩን እንዳናገኝ ተደርገናል” የሚሉት መ/ር ወልደመስቀል፤ በተለይ አንዲት ሴት የጥበቃ አባል ከአግባብ ውጭ ጀማነሽን እየገፈታተረች እንድትወጣ ማድረጓን ገልፀዋል፡፡

በሚዲያ ሳይቀር ቅዱስ ፓትሪያሪኩ ማንም ሰው ያለከልካይ በአካል መጥቶ ሊያነጋግረኝ ይችላል ያሉትን መነሻ

“አዲስ ጉዳይ” መጽሔት በታፈኑ ዕውነቶች አምድ ላይ ለንባብ ባበቃው “ቀናት የሚታደጓቸው እድሜ ልኮች” የሚል ተንታኝ ሃተታ (ፊቸር ስቶሪ) የዓለም አቀፉን የጋዜጠኞች ማዕከል (ICFJ) የሁለተኛ ደረጃ ቀዳሚ ሽልማት አሸነፈ፡፡ ማዕከሉ ከአፍሪካ የጤና ጋዜጠኞች ማህበር እና ከአረብ ሚዲያ ፎረም

ጋር በመተባበር ባዘጋጀው በክትባት ጉዳይ ላይ የሚያተኩር የዘገባ ውድድር ላይ 200 የእስያ፣ የአፍሪካና ስድስት የባህረሰላጤው አገራት ሚዲያዎች እንደተሳተፉ ታውቋል፡፡

የአቶ ግርማ ሰይፉ “ነፃነት ዋጋው

ስንት ነው” ረቡዕ ይመረቃል

ተቃዋሚዎች በሂደቱ ላይ እንጂ በግድቡ ላይ ተቃውሞ የለንም አሉ

ናፍቆት ዮሴፍ

በፓርላማ ብቸኛው የተቃዋሚ ተወካይ በሆኑት አቶ ግርማ ሠይፉ የተፃፈው “ነፃነት ዋጋው ስንት ነው” የተሰኘ መፅሀፍ የፊታችን ረቡዕ ይመረቃል፡፡

በአገሪቱ ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታ ላይ ያጠነጥናል የተባለው መጽሐፍ፤ በዋናነት ሰዎች እንዴት ነፃነታቸውን አሳልፈው እየሰጡ እንደሆነ በሚያሳዩ እውነተኛ ታሪኮች ላይ እንደሚያተኩር አቶ ግርማ ተናግረዋል፡፡ በ240 ገፆች የተቀነበበው መጽሐፉ፤ የ97 እና የ2002 ዓ.ም ምርጫዎችን በስፋት ይዳስሳል ብለዋል - ፀሐፊው፡፡

“አብዛኛው ሰው ግርማ በ97 ምርጫ

ዓለምን ዝም ያሰኘና ውግዘት

ያልነካው መፈንቅለ መንግስት

አለማየሁ አንበሴ እና መልካሙ ተክሌ

አቶ ደሴ ዳልኬአቶ ሽፈራው ሽጉጤ

Page 2: Issue-703.pdf

Website: www.addisadmassnews.com

አዲስ አድማስ ሰኔ 29 ቀን 2005 ዓ.ም ገፅ 2 ዜናሚኒስትር ከገፅ 1 የዞረ

እስር ከገፅ 1 የዞረ

ሽልማት ከገፅ 1 የዞረ

ነፃነት ከገፅ 1 የዞረ

www.addisadmassnews.com ይጐብኙን

አለማየሁ አንበሴ

ፓርቲ ከገፅ 21 የዞረየተዘበራረቀ ስሜትን ስለሚያመጣ መንግስት አጠቃላይ ሂደቱን ለህዝቡ በግልጽ ማስረዳትና ህዝቡም እምነት እንዲጥልበት ማድረግ እንዳለበት አሳስበዋል፡፡ “የተፋሰስ አገሮቹ የአካባቢያዊ ተጽእኖ ሁኔታ እስካልተሰራ ድረስ ትክክል ይሁን አይሁን አይታወቅም” ያሉት ኢንጂነር ይልቃል፤ እንዲህ አይነት ብዥታ ባለበት ሁኔታ አቋም መውሰድ እንደሚያስቸግርም ጨምረው አብራርተዋል፡፡

መድረክ ግድቡ አይሰራ የሚል አቋም የለውም ያሉት የፓርቲው ከፍተኛ አመራር ፕ/ር በየነ ጴጥሮስ፤ በአካሄዱ ላይ ያሉትን ችግሮች ግን እንደማይቀበል ተናግረዋል፡፡ “በ2003 ዓ.ም የግድቡ ስራ መሠራት ሲበሰር ጀምሮ አካሄዱ ግልጽ ይሁን የሚል ጥያቄ አቅርበናል” ያሉት ፕ/ር በየነ፤ ከዚያ ውጭ አባይን ጨምሮ ሌሎቹም የአገሪቱ ወንዞች መጐልበት እንዳለባቸው በመድረክ የፖለቲካ ፕሮግራም ላይ መቀመጡን ተናግረዋል፡፡ “ይሁን እንጂ በዚህ ጉዳይ ላይ አቋም ለመያዝ ስርዓቱ አልፈቀደልንም፤ የራሱን አካሄድ አስቀምጦ በዚያ እንድንጓዝ ነው የሚያደርገን ያሉት” ፕ/ር በየነ፤ እኛ በመሠረተ ሃሳቡና በግድቡ ግንባታ ላይ ተቃውሞ ባይኖረንም በአካሄዱና ውሳኔ ላይ በተደረሰበት መንገድ ላይ ቅሬታ እንዳለን ገና ሲበሰርም ገልፀናል ብለዋል፡፡ “ይህ ግድብ ሊሠራ ሲታሰብ መድረክም ሆነ ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ማወቅ ነበረባቸው” ያሉት ፕ/ሩ፤ መድረክ እንደፓርቲ መንግስትና ህዝብ

የሚያውቀው ከመሆኑም በላይ በምርጫ ያሸነፈ ፓርቲ ሆኖ ስለ ጉዳዩ ምክክር ሳይደረግ ስራውን መጀመሩ አግባብ ነው ወይ? የሚለውን በተደጋጋሚ ፓርቲው ማንሳቱን ተናግረዋል፡፡

“የ80 ቢሊዮን ብር ትልቅ ፕሮጀክት በደሀው ህዝብ ጫንቃ ላይ መጣሉም አንዱ የማንቀበለው ነገር ነው” የሚሉት የመድረክ አመራር፤ እነዚህን ሂሶች በወቅቱ አቅርበው እንደነበርና አሁንም 21 በመቶ ተገንብቷል የሚባለው ግድብ፤ በድሀው አቅም ፍፃሜ ላይ ይደርሳል ወይ የሚለው የመድረክ ሃሳብ እንዳለ መሆኑን አብራርተዋል፡፡ ይህን ሁሉ አልፎ ግድቡ ከተጠናቀቀ ግን ማንም ጤነኛ አዕምሮ ያለው ሰው የሚከፋውና ጠብ ያለሽ በዳቦ የሚልበት ምክንያት እንደሌለም አክለው ገልፀዋል፡፡ “እኛ በምን አቅም ነው የሚጠናቀቀው የሚል ጥርጣሬ አለን? ለምን ጥርጣሬ አስቀመጣችሁ የሚል የለም” ያሉት ፕ/ር በየነ፤ ላለፉት ሁለት ዓመታት የህዝቡ ደሞዝ ተጠራቅሞ 10 ቢሊዮን መድረሱን እንኳን እንደሚጠራጠሩ ገልፀው፤ አሁን ከቦንድ ሽያጭና ከደሞዝ የተገኘው ብር ከፕሮጀክቱ ፍላጐት ጋር ሲታይ አባይን በጭልፋ ነው በማለት መድረክ የግድቡ ፍፃሜ ላይ ያለውን ጥርጣሬ አብራርተዋል፡፡ “ግልጽ ለመናገር መድረክ በግድቡ አሠራር ላይ ሂስ አለው፤ ግን ይቁም አይሰራ የሚል አቋም የለውም” ብለዋል፡፡

መድረክ ይሰራ የሚል አቋም ካለው በሙያ፣

በሃሳብና በገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ አስቧል ወይ በሚል ለተነሳው ጥያቄ፤ መድረክ የህብረተሰቡ አካል እንደመሆኑ የመድረክ አባላት መሃንዲሶች፣ የአካባቢ ጥበቃ ባለሙያዎችና ሌሎች አባላትም እንደሚሳተፉ የገለፁት ፕ/ር በየነ፤ መድረክ ፓርቲ እንጂ መንግስት ባለመሆኑ በአባላቱ በኩል የተለያዩ ተሳትፎዎችን እያደረገ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡ “መድረክ አባላቱ በተለያየ መልኩ እንደሚሳተፉ ነው የሚያውቀው፤ እኛስ የመድረኩ አመራሮች ቦንድ ገዝተን የለም እንዴ?” ያሉት አመራሩ፤ የአባላት ተሳትፎ መድረክ በህዳሴው ግድብ ላይ ይሳተፋል በሚል እንደሚመነዘር ገልፀዋል፡፡ መድረክ ግን እንደፓርቲ ልማት ላይ ኢንቨስት የሚያደርግበት አግባብም አቅምም እንደሌለው ተናግረዋል - ፕሮፌሰሩ፡፡ ህዝቡ ቦንድ በደሞዙ መግዛቱን በተመለከተ መድረክ “ህዝቡ ቦንድ እየገዛ ያለው በግዳጅና በጭንቀት ነው እንጂ በፍላጐት አይደለም” ማለቱን በማስታወስ አሁን ቦንድ መግዛታቸውን ያምኑበት እንደሆነ ጠይቀናቸው ሲመልሱ“ይህ በሁሉም የአገሪቱ ዜጐች ላይ የመጣ በመሆኑ እኛንም ለይቶ እንደማይተው ሃቁ ያሳያል” ያሉት የመድረክ ከፍተኛ አመራር፤ “ኢህአዴግ በፕሮፖጋንዳው ደሞዝ ያለው ሁሉ ይክፈል ሲል እኛም ለአገራዊ ቁምነገር አምጡ ስንባል ዝም ብሎ ማለፉ ተገቢ አልመሰለንም” ብለዋል፡፡ አናምንበትም በሚል ፍ/ቤት ተከራክረው ብራቸውን ያስመለሱ አንዳንድ አባላት መኖራቸውንም ገልፀዋል

- ፕሮፌሰሩ፡፡ አንዳንድ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የብሔራዊ ኮሚቴ

አባል ሆነው እየተሳተፉ መሆናቸውን በማንሳት ለምን ፓርቲያቸው በኮሚቴ አባልነቱ አልተጋበዘም ወይም ለምን አባልነቱን አልጠየቀም? ቢጋበዝስ አባልነቱን ይቀበል ነበር ወይ በሚል ለጠየቅናቸው “መድረክ ግብዣ አልቀረበለትም፤ አባል የሆኑትም ብቃት አለን ብሔራዊ ኮሚቴ እንሁን ብለው አይደለም” ያሉት ፕ/ሩ፤ ገዢው ፓርቲ መርጦ ነው ያስገባቸው ብለዋል፡፡ መንግስት አቋቁሜያለሁ ብሎ ማወጁን፣ ነገር ግን አባል መሆን የምትፈልጉ ተሳተፉ አለማለቱን የጠቆሙት ፕሮፌሰር በየነ፤ አንዳንድ አባል ሆኑ የተባሉ ተቃዋሚ ፓርቲዎችም የኢህአዴግ ልዩ ባለሟሎች እንደሆኑና ገንዘብም ተሠፍሮ የሚሰጣቸው በመሆኑ የብሔራዊ ኮሚቴው አባልነታቸው የሚያስገርም አለመሆኑን ገልፀዋል፡፡ ግብዣ ቢቀርብ ትቀበሉት ነበር ወይ ለተባለው “አሁን ብቻዬን የምመልሰው ሳይሆን እንደመድረክ የሁሉም ሃሳብ ተካቶ የሚመለስ በመሆኑ በግሌ እንቀበላለን አንቀበልም ለማለት እቸገራለሁ” ብለዋል፡፡

“ኢህአዴግ እኛን አግልሎናል፤ መድረክ ከዚያ ሁሉ ችግር ጋር ባለፈው አገር አቀፍ ምርጫ 38 በመቶ የህዝብ ድምጽ ያገኘ ፓርቲ እንደመሆኑ በሀገሪቱ በሚደረጉ ጉዳዮች ላይ ሊያሳትፈን ሲገባ በተለያዩ መንገዶች አድልኦና መገለሉን እያሳየ ነው፤ የብሔራዊ ኮሚቴ አሰባሰቡም ከዚህ አካሄድ የተለየ አይደለም” ብለዋል፤ ፕ/ር በየነ፡፡

በተከታታይ ከፍተኛ እድገት እያስመዘገበ ነው በተባለው የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ውስጥ ከፍተኛውን ድርሻ የሚወስደው ከግል ባለሃብቱ ኢንቨስትመንት ይልቅ የመንግስት ኢንቨስትመንት መሆኑን አንድ ጥናት ሰሞኑን ጠቆመ፡፡

ቀደም ሲል የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ መምህር እና በንግድ ሚኒስቴር የአለም ንግድ ድርጅት (WTO) ዋና አማካሪ የሆኑት አቶ ማሞ ምህረቱ ሰሞኑን በሂልተን ሆቴል “The investment Climate in Ethiopia; some reflections” በሚል ርዕስ ለምጣኔ ሃብት ባለሙያዎችና ለባለድርሻ አካላት ባቀረቡት ጥናት፤ እየተመዘገበ ባለው እድገት ውስጥ የግል ኢንቨስትመንቱ ሚና እየተዳከመ፣ በአንፃሩ የመንግስት ኢንቨስትመንት ከጊዜ ወደ ጊዜ ከፍተኛ ድርሻ እየያዘ መምጣቱን አስረድተዋል፡፡ እንደጥናት አቅራቢው፣ በ2011/12 ዓ.ም የአለም ባንክ ባወጣው ሪፖርት፣ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በ8.5 በመቶ ማደጉን ያመለከተ ሲሆን በዚህ እድገት የመንግስት ኢንቨስትመንት 63 በመቶ ድርሻ ይዟል ተብሏል፡፡ የዓለም ባንክን ሪፖርት በመጥቀስ፣ ይህ አሃዝ ከሌሎች ሃገራት ጋር ሲነፃፀርም አገሪቱን ከአለም አገራት በመንግስት ኢንቨስትመንት ድርሻ በ3ኛ ደረጃ ያስቀምጣታል ብለዋል - ጥናት አቅራቢው፡፡

ለማሳየነት በተጠቀሰው የእድገት ዘመን

የግል ኢንቨስትመንት እየቀጨጨ፣ የመንግስት እየጎላ መጥቷል ተባለ • ለኢኮኖሚው ግንባታ አሉታዊ አስተዋፅኦ እንዳለው ተገልጿል

በቱርኬሚስታን የመንግስት ኢንቨስትመንት ለአመታዊ ምርት እድገት (GDP) ያለው ድርሻ 38.6 በመቶ የነበረ ሲሆን አገሪቱን ከአለም ሃገራት በ1ኛ ደረጃ ያስቀምጣታል፣ ቀጥሎ ያለችው ኢኳቶሪያል ጊኒ ስትሆን መንግስት የ24.3 በመቶ ድርሻ አለው፤ በ3ኛ ደረጃ በምትከተለው ኢትዮጵያ ደግሞ የመንግስት ኢንቨስትመንት ለዓመታዊ ምርት እድገት ያለው ምጣኔ የ18.6 በመቶ መሆኑ ተመልክቷል፡፡

የግል ኢንቨስትመንት ኢትዮጵያ ውስጥ በጣም ትንሽ መሆኑን የገለፁት ጥናት አቅራቢው፣እሱም ቢሆን ከአመት አመት እየቀነሰ በአንፃሩ የመንግስት ኢንቨስትመንት ሚና እየጎላ መጥቷል ብለዋል፡፡ ለመንግስት ኢንቨስትመንት መጨመር ማሳያ በማለት አጥኚው ሁለቱ አካላት ከባንክ የሚበደሩትን የብድር አቅም መጠን በማነፃፀር አቅርበዋል፡፡ በጥናት ውጤቱ ለማሳያነት በተጠቀሰው የ2011/12 አመት ከባንኮች በአጠቃላይ 224 ቢሊዮን ብር በብድር የተወሰደ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 57 በመቶውን የመንግስት የኢንቨስትመንት ድርጅቶች ሲወስዱ፣ 15 በመቶውን ብቻ የግል የኢንቨስትመንት ድርጅቶች ወስደዋል፡፡ መንግስት ከወሰደው ብድር 90 በመቶውን ያዋለው ለኢንቨስትመንት መሆኑም በጥናቱ ተመልክቷል፡፡

የግል ኢንቨስትመንቱ አሽቆልቁሎ የመንግስት እንዴት ሊጨምር ቻለ ለሚለው ጥናት አቅራቢው

ምክንያት ያሏቸውን ነጥቦች የዘረዘሩ ሲሆን ከነዚህ መካከል የታክስ አስተዳደር ችግሮች፣ የመንግስት ኢንቨስትመንት መጠናከሩ፣የደንበኞች እጦት፣የሰው ሃይል አቅርቦት እጥረት፣ የሃይል እጥረት፣ የገንዘብ አቅርቦት፣ በመሰረተ ልማት ግንባታ ዘርፍ የግል ባለሃብቶች አለመጉላት እንዲሁም በየጊዜው ተለዋዋጭ ፖሊሲዎች መኖራቸው የሚሉት ይገኙበታል፡፡

የግል ኢንቨስትመንቱ መቀጨጭ ለኢኮኖሚ ግንባታው አሉታዊ አስተዋፅኦ እንዳለው የገለፁት አቶ ማሞ፤ መንግስት በቀጣይ የግል ባለሃብቱ ኢንቨስትመንት ድርሻ ጎልቶ እንዲወጣ ከፈለገ የተለያዩ ዘመናዊ አሰራሮችን መዘርጋት እንዳለበት አሳስበዋል፡፡ በዚህ ረገድ አዋጭ አሰራር በሚል ካቀረቡት መካከል፣ የኤሌክትሮኒክስ የአንድ መስኮት አገልግሎትን መጠቀም ይገኝበታል፡፡ ይህ አገልግሎት በአንድ የኮምፒውተር መስኮት ባለሃብቱ በተለያዩ የመንግስት መስሪያቤቶች ያሉትን ጉዳዮች ቢሮው ቁጭ ብሎ እንዲጨርስና ከተራዘመ የቢሮክራሲ ውጣ ውረድ እንዲድን ያደርገዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም የታክስ ኮንፈረሶችን ማካሄድ፣ከግል ኢንቨስተሮች ጋር መወያየትና ችግሮችን አጥርቶ ማወቅ እንዲሁም የኤሌክትሪክና የመሳሰሉ የሃይል አቅርቦት ችግሮችን ለመፍታት የኢንዱስትሪ ዞን ግንባታዎችን አጠናክሮ መገንባት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

በመሆን መሾማቸው የሚታወስ ሲሆን፤ እሳቸውን በመተካት አቶ ደሴ ዳልኬ የክልሉ ፕሬዚዳንት ሆነው ይሾማሉ ተብሏል፡፡ ባለፈው ሐሙስ በፓርላማ በተካሄደው የካቢኔ ሹመት ወ/ሮ ዳሚቱ ሐሚሳ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ሆነው መሾማቸው ይታወቃል፡፡ በመጪው ሳምንት የደቡብ ክልል ምክር ቤት ጉባኤ የክልሉን ርዕሰ መስተዳደር ሹመት ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ባለፈው ሳምንት ከአስር በላይ የሚኒስትሮች ሹመት በፓርላማ መጽደቁ ይታወቃል፡፡

አካላትን ለማስተማር ታስቦ እንደሆነ ባለሙያዎቹ ተናግረዋል፡፡ እንደ ህግ ባለሙያነታቸው የማንም ውክልና ሳያስፈልጋቸው ክሱን በቅርቡ እንደሚመሰርቱና በወቅቱም በጉዳዩ ዙሪያ ጋዜጣዊ መግለጫ እንደሚሰጡ ባለሙያዎቹ አስታውቀዋል፡፡

እርቃን ምስሎችን በኢንተርኔት መለጠፍ በሕግ ያስከስሳል ብለዋል - ባለሙያዎቹ፡፡

ቤቲ የፈፀመችው ድርጊት በተለያዩ ድረ ገፆች መለቀቁን ተከትሎ ኢትዮጵያውያን በጉዳዩ ላይ ጐራ ለይተው በመደገፍና በመንቀፍ አስተያየታቸውን ሲሰጡበት የነበረ መሆኑን ያስታወሱት የህግ ባለሙያዎቹ፤ እኛ ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት ለመውሰድ ስናስብ ምን አገባችሁ ያሉንም አሉ፤ እነዚህ ግለሰቦች ግን በህጉ መሠረት ይህን የማለት መብት የላቸውም ብለዋል። ለመልካም ፀባይ ተቃራኒ የሆኑ ድርጊቶችን መፈፀም ከ1 ዓመት እስከ 5 አመት በሚደርስ እስራት ሊያስቀጣ ይችላል ያሉት ባለሙያዎቹ፤ የቤቲ ጉዳይም እስከ 5 አመት እስር ሊያስቀጣ ይችላል ብለዋል፡፡

ዋናው አላማችን ቤቲን እንደማሳያ ወስደን እንዲህ አይነት ድርጊቶችም እንደሚያስቀጡ ለማሳየት ነው የሚሉት ጠበቆቹ፤ ዛሬ በፌስቡክና በተለያዩ የማህበራዊ ድረገፆች ላይ ሴቶች እርቃናቸውን ሆነው የተነሱትን ፎቶ እየለጠፉ መሆኑ ከዚህ የህግ ግንዛቤ ክፍተት መሆኑን አስረድተዋል፡፡

“ከቢግ ብራዘር አፍሪካ” ውድድር የተባረረችው ቤቲ፤ በተለያዩ ሚዲያዎች በሰጠችው ቃለምልልስ፤ ድርጊቱን አለመፈፀሟንና የታየው ነገር ለውድድሩ አስፈላጊ በመሆኑ በትወና የተደረገ እንደሆነ ገልፃለች፡፡

መጽሔቱ በኢትዮጵያ የክትባት ተደራሽነት አናሳ መሆኑን አስመልክቶ የሰራው ተንታኝ ሃተታ፤ ከመላው አፍሪካ፣ ከእስያና ከባህረሰላጤው ሀገራት ሚዲያዎች ጋር ተወዳድሮ ነው ያሸነፈው፡፡

ከ14 ሀገራት በተውጣጡ በሙያው አንቱ በተባሉ ጋዜጠኞች በተዋቀረው ኮሚቴ በተሰጠው ዳኝነት ከ200 ዘገባዎች ውስጥ የአዲስ ጉዳይ “ቀናት የሚታደጓቸው እድሜ ልኮች” ከሁለተኛ ደረጃ ተሸላሚዎች የአንደኝነት ደረጃን ለማግኘት ችሏል፡፡

“ኢትዮጵያን ወክለን መወዳደራችንና ማሸነፋችን ዝግጅት ክፍሉን በጣም አስደስቶታል፡፡ በተለይም በአሁኑ ወቅት አዲስ ጉዳይን በአዲስ መልክ ለአንባቢያን ለማቅረብና በይዘቱ ላይ መጠነኛ ማሻሻያ አድርገን በባለሙያዎች የሚሰራ መጽሔት ለማድረግ ከልዩ ልዩ ዘርፎች ባለሙያዎችን እና አማካሪዎችን ቀጥረን እየተንቀሳቀስን ባለንበት ወቅት ይህ ውጤት መገኘቱ ሞራላችንን ገንብቶታል፡፡ ለበለጠ ስራም አነሳስቶናል” ብሏል የመጽሔቱ ዋና አዘጋጅ አቶ ዮሐንስ ካሳሁን፡፡

የውድድሩ ዋና አላማ በክትባት ማጣት ሳቢያ በየዓመቱ ህይወታቸውን የሚያጡ ህጻናትን ቁጥር ለመቀነስና ለከፍተኛ የአካል ጉዳት የሚዳረጉ ዜጐችን ጤና መታገድ የሚያስችል እውቀት መፍጠር ሲሆን የመጽሔቱ ዘገባ ኢትዮጵያ ያለችበትን ወቅታዊ ሁኔታ በማሳየት ህብረተሰቡ ግንዛቤ እንዲኖረውና መንግስትም ክፍተቶቹን እንዲደፍን መረጃ የሚያስጨብጥ ነው ተብሏል፡፡

ቢሮውን ዋሽንግተን ዲሲ ያደረገው የአለምአቀፉ ጋዜጠኞች ማህበር ፕሬዚዳንት ጆይስ ባርናታን አሸናፊዎቹ ይፋ በተደረጉበት ስነስርዓት ላይ እንደተናገሩት፤ “አሸናፊዎች ያቀረቧቸው ስራዎች እንደ ፖሊዮ ያሉ ከፍተኛ ጉዳት አድራሽ የሆኑ ነገር ግን በቀላሉ መከላከል የሚቻሉ በሽታዎችን መቋቋምና ማሸነፍ የሚቻልባቸውን መንገዶች ያመላከቱ ትምህርት ሰጪ ዘገባዎች ናቸው፡፡ ለህዝባቸው እና ለጤና ባለሙያዎቻቸው እንቅፋትን አስወግደው ስኬትን የሚያገኙባቸውን መንገዶችም የጠቆሙ ናቸው” ብለዋል፡፡

በውድድሩ አንደኛ የወጡት የናይጀሪያ “ቲቪሲ ኒውስ” ቴሌቪዥን ጣቢያ፣ የፓኪስታኑ “ኒውስ ዋን” ቴሌቪዥን ጣቢያ፣ የኮትዲቩዋሩ “አቬኑ 225 ኒውስ ሳይት” ድረገጽ እና የተባበሩት አረብ ኢምሬቶች “ፊላንትሮፒ ኤጅ ማጋዚን” ሲሆኑ ጽሑፎቹ አንደኛ የወጡት ሚዲያዎቻቸው ሰፊ ተደራሽነት ያላቸው የቴሌቪዥን ኔትወርኮች በመሆናቸውና በኢንተርኔት ቴክኖሎጂ በታገዘ ስርጭታቸው አህጉራዊ ሽፋን በመፍጠራቸው መሆኑን የውድድሩ አዘጋጆቹ ተናግረዋል፡፡ ዋና አዘጋጁ አቶ ዮሐንስ እንዳለው፤ አዲስ ጉዳይ መጽሔት ከነዚህ ታዋቂ አህጉራዊ ሚዲያዎች ጋር ተወዳድሮ በ2ተኛ ደረጃ ተሸላሚነት ከተመረጡት የዩጋንዳው “ኤንቲቪ”፣ የፓኪስታኑ “ሳውዝ ኤሺያን ሜጋዚን”፣ እና የሳውዲአረቢያው “ሳውዲ ኒውስፔፐር ቱዴይ” ጋር የላቀ ውጤት በማስመዝገብ አንደኛ ደረጃ አግኝቷል፡፡ ይህ ውጤትም ኢትዮጵያውያን ሚዲያዎች በቴክኖሎጂ ቢታገዙና መልቲሚዲያ ቢሆኑ አህጉራዊ ተደራሽነትና ከየትኛውም አገር ጋር የሚፎካከር ሥራ መሥራት እንደሚችሉ ያመላከተ ነው፡፡

የተከሰተ ነው ሲል ሌሎች በ2002 ምርጫ የመጣሁ ይመስላቸዋል” ያሉት አቶ ግርማ፤ በመጽሐፋቸው ይሄንን ብዥታ ለማጥራት ስለራሳቸው፣ ከ97 ምርጫ በፊት ስለነበራቸው የፖለቲካ ተሳትፎና ተያያዥ

ጉዳዮች መጠነኛ መረጃ እንዳቀረቡም ጨምረው ገልፀዋል፡፡

የፊታችን ረቡዕ በ10 ሰዓት ተኩል ላይ በውሀና ኢነርጂ ሚኒስቴር የመሰብሰቢያ አዳራሽ ተጋባዥ

እንግዶች፣ ፖለቲከኞችና ጋዜጠኞች በተገኙበት የሚመረቀው “ነፃነት ዋጋው ስንት ነው” መጽሐፍ፤ ከምረቃው ዕለት ጀምሮ በ50 ብር ለሽያጭ ይቀርባል ተብሏል፡፡

Page 3: Issue-703.pdf

Website: www.addisadmassnews.com

አዲስ አድማስ ሰኔ 29 ቀን 2005 ዓ.ም ገፅ 3 የሰሞኑ አጀንዳ

ዮሃንስ ሰ.

ማስታወቂያ

የአፍሪካ “ዲሞክራሲ” እዚህ ደረጃ ላይ ደርሷል። አመፅና አብዮት ይለኮሳል። የቀድሞውን ባለስልጣን ወደ እስር ቤት ወርውሮ በሆታ ምርጫ ይካሄዳል። ከዚያ ውዝግብና ቀውስ ተባብሶ፣ እንደገና ወደ አመፅና አብዮት ይመለሳል። የአፍሪካ ፖለቲካ፣ ከዚህ አዙሪት መላቀቅ ያቃተው አንዳች የጎደለና የተሳሳተ ነገር ቢኖር ነው። በዜጎች የተቃውሞ ድምፅና አመፅ አማካኝነት ስልጣን የያዘ ፓርቲና ፖለቲከኛ፣ በተራው በሌላ ዙር ተቃውሞና አመፅ ከስልጣን ይወርዳል። የፕሬዚዳንት መሀመድ ሙርሲ የስልጣን ዘመንም፣ የዚህ አዙሪት ውጤት ስለሆነ፣ በዚያው ልክ የአዙሪቱ ሰለባ ሆኗል - አጭር የቤተመንግስት ቆይታቸው በድንገት ተቋጭቶ፣ ወደ እስር ቤት!

ሰሞኑን የተካሄደው የግብፅ አብዮት፣ በተደጋጋሚ ያየነው የለመድነው አፍሪካዊ አዙሪት ቢሆንም፣ እንደ አዲስ እንገረምበታለን። በጣም አስገራሚው ጉዳይ ግን ሌላ ነው - ለምሳሌ የአሜሪካና የአውሮፓ አገራት ሲንተባተቡ፣ ብዙዎቹ የአረብ መንግስታት ደግሞ ፈንድቀዋል። “ያለፈው አልፏል” የሚል ስሜት ያዘለ የተባበሩት መንግስታት ምላሽና የአፍሪካ ህብረት ዝምታም ያስገርማል። ህገመንግስት ሲፈርስና በምርጫ ስልጣን የያዘ ፕሬዚዳንት ሲታሰር… መንተባተብና መፈንደቅ ምን ይባላል? አይቶ ማለፍና ዝምታስ? “የግለሰብ ነፃነት” ጉዳይ ዋነኛው የፖለቲካ መመዘኛ መሆኑን ከልብ ለማመንና በግልፅ ለመናገር አለመፈለጋቸው ነው ችግሩ።

የግለሰብ ነፃነትን ለመጣስና ሃይማኖታዊ የፋሺስት ስርዓት ለመፍጠር የተነሳው muslim brotherhood የተሰኘውን የአክራሪዎች ቡድን በመወከል ስልጣን የያዙት መሀመድ ሙርሲ፤ ህገመንግስት ማፅደቃቸውና በምርጫ ማሸነፋቸው አይካድም። ነገር ግን ህገመንግስቱና ምርጫው ትርጉም የላቸውም። ቀድሞ ነገር፣ ህገመንግስት ማፅደቅና ምርጫ ማካሄድ ያስፈለገውኮ፣ የግለሰቦችን ነፃነት ለማስከበር ነዋ። የህጋዊነት ትክክለኛ መሰረት፣ የግለሰቦችን ነፃነት ማስከበር እንደሆነ አሜሪካዊያኑና አውሮፓውያኑ በግልፅ ለመናገር አለመድፈራቸውና መንተባተባቸው ነው አስገራሚው ነገር።

ከግብፅ ዳግማዊ አብዮት የምንማረው ነገር አለ። በግለሰብ ነፃነት ላይ ያልተመሰረተ ህገመንግስት፣ ዲሞክራሲና ምርጫ ዋጋ እንደሌለው በግልፅ ያሳያል። በምርጫ ስልጣን ይዞ የዜጎችን ነፃነት የሚጥስ ሃይማኖታዊ አምባገነንነትም ሆነ ወታደራዊ አምባገነን መንግስት መሰረታዊ ልዩነት የላቸውም።

ዓለምን ዝም ያሰኘና ውግዘት ያልነካው መፈንቅለ መንግስትየሁለት ቀን እና የ48 ሰዓታት አማራጭአስገራሚው ነገር የአሜሪካዊያኑና የአውሮፓውያኑ

መንተባተብ ነው ብልም፤ በሶስት ቀናት የተቃውሞ ሰልፍ መንግስት ሲፈርስና ፕሬዚዳንት ሲታሰር ማየት፣ … በየአገሩ በተደጋጋሚ የሚያጋጥም ተራ ነገር ነው ማለቴ አይደለም። በሁለት አመት ውስጥ፣ አለምን ጉድ የሚያሰኙ ሁለት አመፆችንና አብዮቶችን የምታስተናግድ አገር አስገራሚነቷ አያጠራጥርም። እንደዘበት በ48 ሰዓታት ወታደራዊ ማስጠንቀቂያ፣ ያ ሁሉ የመሀመድ ሙርሲ ስልጣን ድንገት ማክተሙ ሳያንስ እስረኛ ሆነዋል። ለካ፣ የጄነራሎቹ ማስጠንቀቂያ የቀልድ አልነበረም፤ የመፈንቅለ መንግስት ዝግጅት መጠናቀቁን የሚጠቁም እንጂ። የ48 ሰዓት የጊዜ ገደብ ሲጠናቀቅ፣ ብረት ለበስ መኪኖችና ታንኮች በካይሮ ጎዳናዎች የተሰማሩትም ለማስፈራራት ብቻ አልነበረም፤ የመፈንቅለ መንግስት ሂደት መጀመሩን የሚያሳይ እንጂ።

ለነገሩ፤ እሁድ ምሽት በቴሌቪዥን የተሰራጨው የጄነራሎቹ ማስጠንቀቂያ፣ በደንብ ላደመጠው አሻሚ ትርጉም የሚያስተላልፍ አይደለም። ማስጠንቀቂያው፣ ቃል በቃል ዛቻን ያዘለ ባይሆንም፣ መሀመድ ሙርሲን ከስልጣን ለማስወገድ ያነጣጠረ እንደሆነ፣ የግብፅን ፖለቲካ በቅርበት ለሚከታተሉ ታዛቢዎች ግልፅ ነበር። ለምን ቢባል፤ የጄነራሎቹ ማስጠንቀቂያ ከተቃዋሚ ፓርቲዎች ማሳሰቢያ ጋር ይመሳሰላል። በጊዜ አቆጣጠርና በአገላለፅ ብቻ ነው የሚለያዩት። ተቃዋሚ ፓርቲዎች የሁለት ቀን የጊዜ ገደብ ሲሰጡ፣ ጄነራሎቹ ደግሞ የ48 ሰዓት የጊዜ ገደብ! ይሄው ነው ልዩነቱ።

እሁድ እለት የተቃውሞ ሰልፍ ዘመቻቸውን የጀመሩት ተቃዋሚ ፓርቲዎች፤ ፕሬዚዳንቱ እስከ ማክሰኞ እለት ከስልጣን እንዲወርዱ የሁለት ቀናት የጊዜ ገደብ አስቀምጠዋል። የተቃውሞ ሰልፈኛው፣ እሁድ እለት የካይሮ ጎዳናዎችንና የታህሪር አደባባይን ሲያጥለቀልቅ ከሄሊኮፕተር ላይ ሆነው የተመለከቱ የጦር ጄኔራሎች በፊናቸው፣ በዚያው እለት ያንን ዝነኛ ማስጠንቀቂያ በአዋጅ ለማስነገር ወሰኑ። ፕሬዚዳንቱ ማስጠንቀቂያውን የሰሙት ከሌላው ህዝብ ጋር በቴሌቪዥን ነው።

ለተቃውሞ የወጣው በሚሊዮን የሚቆጠር ሰልፈኛ፣ የግብፅን ህዝብ እውነተኛ ፍላጎት ያንፀባርቃል ያሉት

የአገሪቱ መከላከያ ሚኒስትር ጄነራል አብደልፋታህ አልሲሲ፤ የአገሪቱ ጦር ሃይል ከህዝቡ ጎን እንደሚቆምና የህዝቡ ፍላጎት ምላሽ ማግኘት እንዳለበት ተናገሩ። ምን ማለታቸው እንደሆነ ግልፅ ነው። ሰልፈኛው በተደጋጋሚ የሚያስተጋባው ጩኸት አንድ ጥያቄ ላይ ብቻ ያተኮረ እንደሆነ ይታወቃላ - ሙርሲ ይውረዱ የሚል ጥያቄ ብቻ። ከሰልፈኛውና ከህዝቡ ጥያቄ ጎን ቆመናል ብሎ መናገር፤ ፕሬዚዳንቱ ከስልጣን እንዲወርዱ እንፈልጋለን ብሎ ከመናገር አይለይም። በዚያ እለትም ነው፤ አምስት የጦር ሃይል ሄሊኮፕተሮች የአገሬውን ባንዴራ እያውለበለቡ በታህሪር አደባባይ ዙሪያ በማንዣበብ ለተቃውሞ ሰልፈኛው ድጋፋቸውን የገለፁት።

ፕሬዚዳንቱ በ48 ሰዓታት ውስጥ ከተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር ተስማምተው ለህዝቡ ምላሽ ካልሰጡና አዲስ አቅጣጫ ካልቀየሱ፣ የራሴን እርምጃ እወስዳለሁ ብሎ ማስጠንቀቅስ ትርጉሙ ግልፅ አይደለም? ፕሬዚዳንቱ፣ ከተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር መስማማት ከፈለጉ፣ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ባስቀመጡት ቀነ ገደብ መሠረት እስከ ማክሰኞ ድረስ ከስልጣን መልቀቅ ይኖርባቸዋል። በጄነራሎቹ አባባል ደግሞ፣ በ48 ሰዓት ማለት ነው።

መሀመድ ሙርሲ፣ የጄነራሎቹን ማስጠንቀቂያ ሲሰሙ፣ የስልጣን ቆይታቸው እንዳበቃለትና በሰዓታት ወይም በቀናት ብቻ የሚቆጠር ጊዜ ብቻ እንደቀራቸው የገባቸው ይመስላል። ማብቂያው እንደተቃረበ ካልገባቸውና ተጨማሪ ምልክት ካስፈለጋቸው፣ ዞር ዞር ብለው ማየት አያቅታቸውም። ማስጠንቀቂያው በተሰጠ ምሽት፣ ወደ ገዢው ፓርቲ ዋና ፅህፈት ቤት የዘመቱ ተቃዋሚ ሰልፈኞች ቢሮዎቹን ገለባብጠው ህንፃው ላይ እሳት ለቀውበታል - የፀጥታ ሃይሎችም ተሳትፈውበታል። አገሬውን በሃይማኖታዊ መንግስት ስር አፍኖ ለመግዛት የሚገለገሉበትና በእጅጉ የሚጓጉለት የፕሬዚዳንትነት ስልጣናቸው ከእጃቸው ማፈትለክ መጀመሩን ካልተገነዘቡት ሞኝነት ይሆናል።

መዘዙ ግን ከዚህም ያልፋል። አገሬውን አፍኖ ለመግዛት የሚፈልግ ገዢ፣ ከስልጣን ሲወርድ የአፈና ሰለባ መሆኑ አይቀርም። ለነገሩ፣ ገና ከስልጣን ሳይወርዱ ነው፣ ፕሬዚዳንቱና የፓርቲያቸው መሪዎች ከአገር እንዳይወጡ

የጉዞ እገዳ እንደተጣለባቸው የተነገረው። ብዙም ሳይቆይ፣ የፕሬዚዳንቱ መጨረሻ እስር ቤት ሆነ። ፕሬዚዳንቱ ለምንድነው የታሰሩት ተብሎ ለቀረበ ጥያቄ፣ በተደጋጋሚ ፍርድ ቤትን ተዳፍረዋል የሚል ምላሽ ተሰጥቷል። ይሄ ተራ ፕሮፓጋንዳ ነው። እውነታውኮ፣ ብዙም ሚስጥር አይደለም። አምባገነን ለመሆንና ዜጎችን አፍኖ ለመግዛት የሚፈልግ ፓርቲና ፖለቲከኛ፣ ከስልጣን ሲወርድ በተራው የአምባገነንነት ሰለባ መሆኑ አይቀርለትም - የአዙሪቱ አካል ነውና። እናም፣ ከፕሬዚዳንቱ በተጨማሪ ወደ 40 የሚጠጉ የአክራሪው ገዢ ፓርቲ መሪዎችና ባለስልጣናት ታስረዋል። ሌሎች 300 የሚሆኑ መሪዎችና አባላት ላይም የእስር ትዕዛዝ ተቆርጦባቸው እየታደኑ ነው።

በሙርሲ ደጋፊዎችና በተቃዋሚዎች መሃል በተፈጠሩት ግጭቶች ሳቢያ የበርካቶች ህይወት ባይጠፋ ኖሮ፣ ሰሞነኛው የግብፅ አብዮት ማራኪ የ“ሪያሊቲ ሾው” ትዕይንት ይወጣው ነበር። ጉዳዩ በሃይማኖታዊ የፋሺዝም መንግስት ስር የመሰቃየት ወይም በወታደራዊ ትዕዛዝ ስር የመገዛት ዘግናኝ አጣብቂኝ ባይሆን ኖሮ፤ የአገሬው ፖለቲካ አዝናኝ ድራማ ተብሎ ለመጠቀስ ምንም አይጎድለውም።

“አዝናኝ ነው” ባንለውም እንኳ፣ ድራማነቱን ግን መካድ አይቻልም - ለዚያውም እየተጧጧፈ የሚጦዝ ልብ አንጠልጣይ ድራማ። የሆስኒ ሙባረክ ደጋፊ የነበረው የጦር ሃይል፣ የህዝብ ተቃውሞ ሲበረታ ሙባረክን በማውረድ ተወዳጅነትን ለማትረፍ የበቃው የዛሬ ሁለት አመት ነው። ግን ተወዳጅነቱ ከአንድ አመት በላይ አልዘለቀም። ስልጣን ላለማስረከብ ሲያንገራግር የህዝብ ተቃውሞ ስለተነሳበት፣ በምርጫ ላሸነፉት መሀመድ ሙርሲ ስልጣኑን አስረከበ። የድራማው ውጥረት ለጊዜው ቢረግብም፣ እንደገና አቅጣጫውን ቀይሮ ለመጦዝ ጊዜ አልፈጀበትም። ጦሩ የዛሬ አመት ለሙርሲ ያስረከበውን ስልጣን ሰሞኑን መልሶ ሲወስድ፣ እንደገና በእልልታና በሆታ አቀባበል ተደረገለት። አንድና ሁለት የለውም… በታህሪር አደባባይ በርችት ትዕይንት የተጠናቀቀው የተቃውሞ ሰልፍና የጄነራሎቹ መፈንቅለ መንግስት (በጥቅሉ የግብፅ አብዮት)… አጃኢብ የሚያሰኝ ድራማ ነው። ይበልጥ የሚያስገርም ድራማ የታየው ግን ከግብፅ ውጭ ነው - በአለማቀፍ መድረክ።

ውግዘት ወደ ገፅ 4 ዞሯል

Page 4: Issue-703.pdf

Website: www.addisadmassnews.com

አዲስ አድማስ ሰኔ 29 ቀን 2005 ዓ.ም ገፅ 4 `°e ›”kî

ታኅሣሥ 29 ቀን 1992 ዓ.ም ተመሰረተዘወትር ቅዳሜ የሚታተም ሳምንታዊ ጋዜጣ

አሣታሚ አድማስ አድቨርታይዚንግ ኃ.የተ.የግ.ማ.

አታሚ ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት

አራዳ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 17 / የቤት ቁ.984

አድራሻ:- ካዛንችስ ሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚ/ር ገባ ብሎ ከጤና ጣቢያው ጀርባ ቂርቆስ ክ/ከ ቀበሌ 31 የቤት ቁ.376

ስልክ 0115-155-222/ 0115-153-660 ሞባይል 0921-622-040/0911-201-357 ፋክስ 0115-547373 ፖ.ሳ.ቁ 12324

E-mail :- [email protected]/[email protected]/ website www.addisadmassnews.com

ሥራ አስኪያጅ:- ገነት ጎሳዬ (ልደታ ክ/ከ ቀበሌ 04/06 የቤ.ቁ.581) ስልክ 0911-936787

ዋና አዘጋጅ:- ነቢይ መኮንን (ቂ/ክ/ከ ቀበሌ 08/09 የቤት.ቁ.213)ም/ዋና አዘጋጅ:- ኢዮብ ካሣ

ከፍተኛ አዘጋጅ:- ሰለሞን ገ/እግዚአብሔር አዘጋጅ:- ጽዮን ግርማ፣ ኤልሳቤት ዕቁባይ

ከፍተኛ ሪፖርተሮች:- መንግስቱ አበበ፣ ግሩም ሠይፉ፣ አበባየሁ ገበያው፣ መልካሙ ተክሌ፣ መታሰቢያ ካሳዬ፣ ሰላም ገረመው፣ ናፍቆት ዩሴፍ፣ አለማየሁ አንበሴሌይ አውት ዲዛይነር:- ኮክ አሰፋ፣ ንግሥት ብርሃነ አርቲስት:- ሠርፀድንግል ጣሰው፣ ሽያጭና ስርጭት:- ሰለሞን ካሣ፣ ፎቶግራፈር:- አንተነሀ አክሊሉ ዌብፔጅ:- አሰቴር ጎሳዬ፣ ኮምፒውተር ጽሑፍ:- የወብዳር ካሣ

ውግዘት ከገፅ 3 የዞረ

ከነአያ አንበሶ በታች ያሉት የዱር አራዊት ሁሉ ተሰብስበው ትልቅ ግብዣ ተደረገና ዳንሱ፣ ጭፈራው፣ ዳንኪራው ቀለጠ! ደራ!ከደናሾቹ መካከል ጥንቸል ተነስታ፤ “ዝም ብለን ከምንደንስ እንወዳደርና ምርጥ ዳንሰኛው ይለይ!” አለችና ሃሳብ አቀረበች፡፡ በሃሳቡዋ ሁሉም ተስማሙና ጭፈራው ቀጠለ፡፡ ሁሉም በተራ በተራ ወደ መድረክ እየወጣ ችሎታውን አሳየ፡፡ በመጨረሻ ዳኞች ተሰይመው ውጤት ተነገረ፡፡ በውጤቱ መሰረት አንደኛ - ዝንጀሮ፣ ሁለተኛ ቀበሮ፣ ሶስተኛ - ጦጣ ሆኑ፡፡ ዝንጀሮ መመረጡን በማስመልከት መድረክ ላይ ወጥቶ ተጨማሪ ዳንስ በማሳየት ታዳሚዎቹን አራዊት አዝናና፡፡ ንግግርም አደረገ፡፡ አራዊቱ በጣም በመደሰት ንጉሣችን ይሁን ብለው ወሰኑ፡፡ በዝንጀሮ ንጉሥ መሆን ቀበሮና ጦጣ ቅናት እርር ድብን አደረጋቸው፡፡ ስለዚህ መዶለት ጀመሩ፡፡ ጦጣ፤ “አያ ቀበሮ መቼም ከዳኝነት ስተት ነው እንጂ ዝንጀሮ ከእኛ በልጦ አይመስለኝም፡፡ አንተስ ምን ይመስልሃል?” ቀበሮም፤ “እኔም እንዳንቺው ነው የማስበው፡፡ የዘመድ ሥራ ነው የተሰራው፡፡ ግን አንዴ ሆኗል ምን ይደረጋል?”ጦጣ፤ “አንዴ ሆኗል ብለንማ መተው የለብንም”ቀበሮ፤ “ምን እናደርጋለን ታዲያ?”ጦጣ፤ “እኔ ወጥመድ ላዘጋጅ፡፡ አንተ እንደምንም ብለህ ወጥመዱጋ አምጣልኝ” አለችው፡፡ “ወጥመድ ላይ ሥጋ አድርጌ እጠብቃችኋለሁ፡፡ አንተ ዝንጀሮን ትጋብዘዋለህ”ቀበሮ በሃሳቡ ተስማምቶ ዝንጀሮን ሊያመጣው ሄደ፡፡ ዝንጀሮ በአዲስ የሹመት ስሜት እንደሰከረ፤ እየተጐማለለ ይመጣል፡፡ “ይህን የመሰለ ሙዳ ሥጋ አስቀምጬልሃለሁ” አለው ወደ ሥጋው እያሳየው፡፡ ዝንጀሮም፤ “አንተስ? ለምን አልበላኸውም?” ይሄን የመሰለ ሙዳ እንዴት ዝም አልከው?” አለው፡፡ ቀበሮ፤ “ውድ ዝንጀሮ ሆይ! ለንግሥናህ ክብር ይሆን ዘንድ ብዬ ያዘጋጀሁት ነውና ስጦታዬን ተቀበለኝ?” አለው እጅ በመንሳት፡፡ ዝንጀሮ “ስጦታህን ተቀብያለሁ፤” ብሎ ወደወጥመዱ ዘው አለ፡፡ እዚያው ታስሮ ተቀረቀረ!!ተናደደ!! በምሬትና በቁጭት በደም ፍላት ተናገረ፤ “ለዚህ አደጋ ልትዳርገኝ ነው ለካ ያመጣኸኝ? አንት ሰይጣን! ለንዲህ ያለ ወጥመድ ነበር ለካ ስታባብለኝ የነበረው? አረመኔ!” አለው፡፡ ቀበሮም፤ እየሳቀ፤ “ጌታዬ ዝንጀሮ ሆይ! የአራዊት ንጉሥ ነኝ እያልክ፤ ግን እቺን ቀላል አደጋ እንኳን ማለፍ አልቻልክም!” ይሄ የመጀመሪያ ትምህርት ይሁንህ ብሎ ጥሎት ሄደ፡፡

***“ሹመት ያዳብር” የሚለውን ምርቃት የሀገራችን ህዝብ ጠንቅቆ ያቃል፡፡ በልቡ ግን “አደራዬን ተቀበል” የሚል ጠንካራ ማስጠንቀቂያና ጠንካራ መልዕክት ልኮ ማስገንዘቡ ነው፡፡ ካልሆነ አደራ በላ ትሆናለህ! አደራ! ሲባል፤ የመብራት የውሃዬን ነገር አደራ ማለቱ ነው፡፡ አደራ! ሲባል፤ የትምህርትን ነገር ጠንቅቀህ ምራ ማለት ነው፡፡ ውስጡን በደምብ መርምር ማለት ነው፡፡ አደራ ሲባል፤ የኢንዱስትሪውን ሂደት፤ የትራንስፖርቱን (የባቡሩን፣ የመኪናውን፣ የአየሩንና የእግሩን ጉዞ) ነገር በቅጡ በቅጡ ያዙት ማለት ነው፡፡ የአካባቢ ጥበቃውንና የሳይንስና ቴክኖሎጂው ጉዳይ ዕውነተኛ አሠራር፣ ብስለትና ከዓለም ጋር የሚሄድ እንዲሆን ማድረግ ዋና ነገር ነው ማለት ነው፡፡ አደራ! ሲባል በተለይ የገቢዎችን ነገር፣ እከሌ ከእከሌ ሳትሉ ኢወገናዊ በሆነ ዐይን በማየት፤ የታረመ፣ የተቀጣ፣ ከስህተቱ የተማረ አካሄድ እንድትሄዱ ማለት ነው፡፡ አደራ ሲባል በአጭሩና በጥብቁ ቋንቋ “አደራ - በላ አትሁኑ” ማለት ነው፡፡ በተለምዶ እኛ አገር “ባለፈው ሥርዓት” የሚል ፈሊጥ አለ፡፡ “ያለፈው ሹም ጥፋተኛ ነበር፣ ደካማ ነበር እኔ ግን አንደኛ ነኝ…” ዓይነት አንድምታ ያለው ነው ያለፈው ሹም የበደላችሁን እኔ እክሳለሁ! እንደማለትም አለበት፡፡ ይህን እንጠንቀቅ፡፡ የተሻሪም የተሿሚም ሂደት ተያያዥ ሥርዓት ነውና ሰንሰለቱ ተመጋጋቢ ነው፡፡ እንጂ የወረደው ጠፊ፣ የተሾመው ነዋሪ ነው ማለት አይደለም፡፡ በቅንነት፣ በሰብዓዊነት፣ በለሀገር አሳቢነት ካላየነው፤ ሁሉም ነገር ከመወነጃጀል አይወጣም፡፡ በተሰበሰበ ቀልብ፣ በሙያ ክህሎትና በዲሞክራሲያዊ አረማመድ ነው ፍሬያማ ለመሆን የሚቻለው፡፡ ያንን ካልተከተልን “ንጉሥ ነኝ እያልክ ይቺን ቀላል አደጋ እንኳን ለማለፍ አቃተህ” እንባባላለን፡፡ ጐባጣውን የምናቃናው፣ ጐዶሎውን የምንሞላውና የምናስተካክለው፤ መዋቅር የምናጠናክረው፣ እዚህጋ ተሳስተናል እንተራረም የምንባባለው፤ ለሀገር ይበጃል፣ ብለን ነው፡፡ የሾምነውና ያስቀምጥነው ሰው ተስተካክሎ የተበጀውን ሥርዓት ለግል ጥቅሙ ካዋለ፤ አደራውን ከበላ፣ አድሎኛ ከሆነ፣ በመጨረሻም ያለውን ሁኔታ ከመጠበቅ አልፎ በማሻሻል፤ ለውጥ ካላመጣ፣ የወላይትኛው ተረት እንደሚለው፤ “ፈርጅ ያለው ነጠላ አሰርቼ፤ መልክ የሌለው ሰው ይለብሳል” ሆነ ማለት ነውና ከወዲሁ እንጠንቀቅ፡፡ “ሲሾም ያልበላ ሲሻር ይቆጨዋል”ን እንዋጋ! “ሸክላ ሲሰበር ገል ይሆናል፡፡ መኳንንትም ሲሻሩ ህዝብ ናቸው” የሚለውንም አንዘንጋ!

ፈርጅ ያለው ነጠላ አሰርቼ መልክ የሌለው ሰው ይለብሳል

አሜሪካና አውሮፓ አላወገዙም፤ የ“መፈንቅለ መንግስት” ትርጉም ተቀየረ እንዴ?

በተቃውሞው ማዕበል ያልተደሰቱና መፈንቅለ መንግስቱን የተቹ መንግስታት 3 ብቻ ናቸው - ደግሞም ባይደሰቱ አይገርምም። የኢራኑ ሃይማኖታዊ መንግስት አንዱ ነው። ሃይማኖታዊ መንግስት በቱኒዚያ ላይ ለመጫን የሚታገለው የቱኒዚያ ገዢ ፓርቲም እንዲሁ የመሀመድ ሙርሲ አይነት እጣ እንዲደርሰው ስለማይፈልግ የግብፅ ጄነራሎችን ተቃውሟል። ወደ ሃይማኖት የሚያዘነብለው የቱርክ ገዢ ፓርቲም በተመሳሳይ ምክንያት መፈንቅለ መንግስቱን ተችቷል።

አብዛኞቹ የአረብ መንግስታት ግን ተደስተዋል። የሳውዲ አረቢያ፣ የሶሪያ፣ የተባበሩት የአረብ ኢሜሬት፣ የኢራቅ … በአጠቃላይ ብዙዎቹ የአረብ መንግስታት የግብፅ ጄነራሎችን ውሳኔ በማድነቅ የደስታ መግለጫቸውን አስተላልፈዋል። ምክንያታቸው ግልፅ ነው - እንደ መሀመድ ሙርሲ የመሳሰሉ የለየላቸው የሃይማኖት አክራሪዎች ስልጣን ላይ ከወጡ፣ የአረብ መንግስታት መናወጣቸው አይቀርም። በሙርሲ ውድቀት ቢደሰቱ ምን ይገርማል?

አቋማቸውን በግልፅ መናገር ያልቻሉት፣ የአሜሪካና የአውሮፓ መንግስታት ናቸው። የአፍሪካ ህብረትና የተባበሩት መንግስታት ድርጅትም እንዲሁ። ለምን? ከህገመንግስት ውጭ ስልጣን መያዝ፣ በዲሞክራሲያዊ አሰራር የተዋቀረውን መንግስት ማፍረስ፣ በምርጫ ያሸነፈውን ፕሬዚዳንት ማውረድ ተገቢ ነው እንዴ?

ተደጋግሞ እንደምንሰማው ቢሆን ኖሮ፣ በፖለቲካ ስርዓት ውስጥ እንደ ትልቅ ቁም ነገር የሚቆጠረው፣ “በህገመንግስትና በምርጫ የሚመራ” የዲሞክራሲ ስርዓት ብቻ ነው። የመሀመድ ሙርሲ መንግስት ደግሞ እነዚህን ነገሮች ያሟላል። ህገመንግስት አለው፤ በምርጫ አሸንፏል። እንግዲህ፤ ይህን “መመዘኛ” የሚያሟላ ዲሞክራሲያዊ መንግስት ነው በህዝብ ተቃውሞና በጄነራሎች ውሳኔ የፈረሰው። ታዲያ የአውሮፓና የአሜሪካ መንግስታት ለምን አላወገዙትም? የአፍሪካ ህብረትና የተባበሩት መንግስታት ለምን ተቃውሟቸውን አልገለፁም?

“ከህገመንግስት ውጭ ስልጣን መያዝ ክልክል ነው” የሚል ግልፅ መመሪያ በመያዝ የመፈንቅለ መንግስት ድርጊቶችን እያወገዘ ከአባልነት ሲያግድ የቆየው የአፍሪካ ህብረት፣ እስካሁን ዝምታን መርጧል። በእርግጥ፣ የአሜሪካና የአውሮፓ መንግስታት ቅሬታቸውን ገልፀዋል። “የጄነራሎቹ ውሳኔ ያሳስበናል” ብለዋል። በቃ። “ያሳስበናል” ከማለት ውጭ፣ መፈንቅለ መንግስቱን አላወገዙትም። ከነጭራሹም፣ “መፈንቅለ መንግስት” ብለው አልጠሩትም። “ወታደራዊ ጣልቃ ገብነት ያሳስበናል” በሚል አለዝበውታል።

“የዓለም መንግስታት መፈንቅለ መንግስቱን አለማውገዛቸውና “መፈንቅለ መንግስት” ብለው ከመጥራት መታቀባቸው በእጅጉ አሳዛኝ ነው” ያሉት የመሀመድ ሙርሲ ፓርቲ ቃል አቀባይ፤ በ21ኛው ክፍለ ዘመን እንዲህ አይነቱ መፈንቅለ መንግስት መካሄዱና በዝምታ መታለፉ አስገራሚ ነው ብለዋል። ዞር ብለው የራሳቸውን ፓርቲ ሲያዩም ተመሳሳይ ሃሳብ መናገር ነበረባቸው። መገረም ነበረባቸው። በ21ኛው ክፍለዘመን ሃይማኖታዊ የፋሺስት አገዛዝ ለመመስረት የሚፈልግ ፓርቲያቸው ስልጣን መያዙና ዓለም ሁሉ መሀመድ ሙርሲን በዝምታ ተቀብሎ ሲያስተናግድ መቆየቱ ይገርማል። ሂትለርምኮ በምርጫ ነው ስልጣን የያዘው።

ይሄ ሁሉ መምታታት የተፈጠረው፣ በአንድ ጉድለት ምክንያት ነው - በአንድ መሰረታዊ ጉድለት ምክንያት። ዋነኛ የፖለቲካ ስርዓት መመዘኛ የነበረው፣ “የግለሰቦች ነፃነት” ወደ ጎን ገሸሽ መደረጉ ነው ዋናው ጉድለት። ምርጫና ህገመንግስት በቁንፅል ዋነኛ የፖለቲካ መመዘኛ እንዲሆኑ በመደረጉ፤ በዝምታ የሚስተናገድ ሃይማኖታዊ የፋሺስት ስርዓትና በዝምታ የሚታለፍ መፈንቅለ መንግስት ለማየት በቅተናል። ሃሙስ እለት 237ኛ አመቱ የተከበረው የአሜሪካ የነፃነት መግለጫ ላይ በግልፅ የሰፈረው የፖለቲካ መሰረታዊ

መመዘኛ፣ ቀስ በቀስ ገሸሽ ባይደረግ ኖሮ እንዲህ አይነት አሳፋሪ አለማቀፍ ድራማ ባልተፈጠረ ነበር።

እያንዳንዱ ሰው ከተፈጥሮው የማይነጠሉ መብቶችን የተጎናፀፈ መሆኑን በመግለፅ የሚጀምረው የአሜሪካ የነፃነት መግለጫ፣ ከእነዚህ መብቶች መካከልም፣ እያንዳንዱ ሰው የራሱን ህይወት የመጠበቅ፣ የራሱን ህይወት የመምራትና በራሱ ጥረት ደስታን የመሻት መብቶችን ይጠቅሳል። የእያንዳንዱን ሰው መብቶች ለመጠበቅም ነው፣ መንግስት በሰዎች መልካም ፈቃድ የሚቋቋመው በማለትም ዋነኛ የፖለቲካ መመዘኛውን ቁልጭ ባለ ቋንቋ አስፍሯል - መግለጫው። ያለ ሰዎች መልካም ፈቃድ (ያለ ምርጫ) ስልጣን መያዝ ህገወጥ ነው። ለምሳሌ በመፈንቅለ መንግስት አማካኝነት ስልጣንን የሙጢኝ ይዞ መቀጠል አይቻልም። ዋናው ቁም ነገር ግን ይሄ አይደለም። ዋናው የፖለቲካ መመዘኛ፤ “መንግስት የግለሰቦችን ነፃነት ለማስከበር የሚቋቋም መሆን አለበት” የሚለው ነው። አለበለዚያ ህጋዊነት አይኖረውም።

“ማንኛውም አይነት መንግስት”፣ የግለሰብ መብቶችን የሚፃረር ከሆነ፣ ሰዎች ይህንን መንግስት የመለወጥ ወይንም የማስወገድ እንዲሁም አዲስ መንግስት የማቋቋም መብት አላቸው ይላል መግለጫው። … to secure these rights, Governments are instituted among Men, deriving their just powers from the consent of the governed. That whenever any Form of Government becomes destructive of these ends, it is the Right of the People to alter or to abolish it, and to institute new Government…

የአሜሪካ መስራቾች፣ “ማንኛውም አይነት መንግስት” በሚል አገላለፅ በመግለጫው ላይ ያሰፈሩት አለምክንያት አይደለም። የአፍጋኒስታኑ ታሊባንና የሶማሊያው አልሸባብ በተፈጥሯቸው ልክየለሽ አምባገነኖች አይደሉ? በምርጫም ሆነ ያለ ምርጫ ስልጣን ቢይዙ ለውጥ የለውም። ሂትለር ስልጣን የያዘው በዲሞክራሲያዊ ምርጫ ስለሆነ፣ ፋሺስትነቱንና አምባገነንነቱን አያስቀርለትም። ከውጭ የመጣ ቅኝ ገዢም ሆነ የአገር ውስጥ ገዢ፣ የትውልድ ሃረግ ቆጥሮ አልያም የሃይማኖት እምነቶችን ታቅፎ ዘውድ የደፋ መንግስት፤ በመፈንቅለ መንግስትም ሆነ በምርጫ ስልጣን የያዘ ፓርቲ፣ የትኛውም አይነት ቢሆን፣ የግለሰብ መብቶችን የሚፃረር ከሆነ፤ ሰዎች ይህንን መንግስት የመጣልና የማስወገድ መብት አላቸው። የግለሰብ ነፃነት ላይ ያልተመሰረተ መንግስትና ህገመንግስት ዋጋ የላቸውም።

በዚህ የፖለቲካ መመዘኛ ስናየው፣ የመሀመድ ሙርሲ መንግስትን ማስወገድ ተገቢ ነው - ሃይማኖታዊ እምነታቸውን በሁሉም ሰዎች ላይ ለመጫን (በጅምላ የግለሰቦችን ነፃነት ለመጣስ) ዘመቻ የጀመረ መንግስት ነውና። የሃይማኖት አክራሪዎች አላማ፣ ሁሌም የግለሰቦችን ነፃነት ለማጥፋት ያነጣጠረ ነው። በተግባርም፣ ስልጣን ሲጨብጡ ምን እንደሚያደርጉ በተደጋጋሚ አይተናል … መዝፈንና መደነስ አይቻልም፤ ቴሌቪዥን መመልከትና ኳስ መጫወት አይቻልም…። መበደርና ማበደር፣ ፂም ማሳደግና አለማሳደግ፣ ፊትንና ፀጉርን መሸፈን ወይም አለመሸፈን፣ መፆምና መስገድ፣ ማተብ ማሰርና አለማሰር፣ መጠመቅና አለመጠመቅ የእያንዳንዱ ሰው የግል ነፃነት ሆኖ ሳለ፤ ይህን ነፃነት ለመጣስና ለማጥፋት ቆርጦ የተነሳን ፓርቲና ፕሬዚዳንት ከስልጣን አሽቀንጥሮ መጣል ጥሩ ነው። ለምን? ዋነኛው የፖለቲካ መመዘኛ፣ የግለሰብ ነፃነት ነውና። ይህ፣ ለአሜሪካ ታላቅነት መነሻ የሆነ ትክክለኛ የፖለቲካ መመዘኛ ወደ ጎን ገሸሸ ባይደረግ ኖሮ፣ እነ አሜሪካና አውሮፓ ሰሞኑን እንዳየናቸው በግብፅ መፈንቅለ መንግስት ሳቢያ ባልተንተባተቡ ነበር። የሙርሲ ከስልጣን መወገድ መልካም ነው። በዚያው መጠን፤ በትክክለኛው የፖለቲካ መመዘኛ መሰረት፣ ስልጣን ላይ ለመቆየት ከአገሬው ሰዎች መልካም ፈቃድ ማግኘት ስለሚያስፈልግ፣ ጄነራሎቹ ስልጣንን የሙጢኝ ይዘው መቀጠል የለባቸውም።

Page 5: Issue-703.pdf

Website: www.addisadmassnews.com

አዲስ አድማስ ሰኔ 29 ቀን 2005 ዓ.ም ገፅ 5 ’í ›e}Á¾ƒ

ፓርቲ ወደ ገፅ 21 ዞሯል

የዘወትር አገልጋይዎ የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት

ማስታወቂያ ማስታወቂያ

ዓመታዊ የፖስታ ሣጥን ኪራይ ውል ማደሻ ጊዜ ከሐምሌ 1-30 ቀን 2005

ዓ.ም በመሆኑ በተጠቀሰው ጊዜ ውልዎትን እንዲያድሱ እያስታወቀ፤

በተገለፁት ቀናት ውስጥ የሣጥን ኪራይ ውልዎትን ካላደሱ ግን ለሌላ ተጠቃሚ ለማስተላለፍ እንደሚገደድ

ያስታውቃል፡፡

ለፖስታ ሣጥን ተከራይ ደንበኞች በሙሉ

የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ሊቀመንበር ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ፤ አባይን የመገደብ ጥያቄ በኢህአዴግ ዘመን ብቻ ሳይሆን ከጥንትም የነበረ ስለሆነ መገደቡን

እንደማይቃወሙ ገልፀው፣ የአገዳደቡ ሂደት ግን ችግር አለው ብለዋል፡፡ የግድቡን መገንባት ካልተቃወማችሁ ድጋፍ ለማድረግስ ፓርቲው ምን አስቧል በሚል ለሊቀመንበሩ ላነሳነውም ጥያቄ “እኛ እንደፓርቲ የምንናገረው አባይን የመገደብ መብት ተፈጥሯዊ እና አገራዊ መብት ነው፤ በዚህ ላይ ክርክር አናነሳም፣ ተቃውመንም አናውቅም” ካሉ በኋላ፣ ነገር ግን ኢህአዴግ “የአባይ ጉዳይ የኔ ብቻ ነው” በሚል ለፓለቲካ ፍጆታ ማዋሉን፣ ያለ ብሔራዊ መግባባትና ግልጽነት በጐደለው መንገድ ብቻውን በባለቤትነት መያዙን ግን እንደሚቃወሙ ተናግረዋል፡፡ ኢህአዴግ የግድቡን ስራ በብቸኝነት ለመያዙ እንደ ማሳያ የጠቀሱት የወንዙን አቅጣጫ ያስቀረበት ቀን ከግንቦት 20 በዓል ጋር መገናኘቱን ሲሆን “ይህ የፖለቲካ ትርፍ ለማጋበስ የታለመ እቅድ ነው” ብለዋል ዶ/ር ነጋሶ፡፡

የሆኖ ሆኖ አሁን ግድቡ እየተሰራ መሆኑንና ፓርቲያቸው የግድቡን ግንባታ ለማገዝና ለመደገፍ

እቅድ እንዳለው ተጠይቀውም “እኛ አሁንም የግድቡን ስራ አንቃወምም፣ ነገር ግን የግድቡ ስራ ቀጣይነት እንዲኖረውና ሁሉንም የፖለቲካ ፓርቲዎች እና ህዝቡን በቀጥታ ተሳታፊ በማድረግ ብሔራዊ መግባባት ላይ መደረስ አለበት፡፡ ከዚያ በኋላ አስፈላጊ በሆነው ነገር ፓርቲያችን ድጋፍ ከመስጠት ወደ ኋላ አይልም” በማለት መልሰዋል፡፡ “አሁን ግን በውድም በግድም ገንዘብ አምጡ ከማለት በስተቀር ህዝቡ በግድቡ ላይ ቀጥተኛ ተሳታፊ ነው ብዬ አላምንም” ብለዋል ዶ/ር ነጋሶ፡፡

“የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ሲበሰር እንቅስቃሴ የጀመርነው በድጋፍ ነው” ያሉት የኢዴፓ ፕሬዚዳንት አቶ ሙሼ ሰሙ፤ ነገር ግን እንደዜጋም እንደፓርቲም የራሳቸው የሆኑ ስጋቶችና ጥርጣሬዎች እንደነበራቸው ተናግረዋል፡፡ አቶ ሙሼ ጥርጣሬና ሥጋቶች ካሏቸው ነጥቦች ውስጥም የ80 ቢሊዮን ብር ፕሮጀክት ለማስተናገድ ምን ያህል ተጨባጭ የኢኮኖሚ አቅም አለን፣ የውሃ ሃይል አቅርቦቱ፣ ቴክኖሎጂውና ማይክሮ ኢኮኖሚው ይደግፈዋል ወይ የሚሉት እንደነበሩ ተናግረዋል፡፡ የግድቡን ጉዳይ የብሔራዊ ኮሚቴ አባል ሆነው በቅርበት እየከታተሉት እንደሆነ የሚናገሩት አቶ ሙሼ ፤ አሁን ግድቡ አመርቂ በሆነ ሁኔታ እየተገነባ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ ትልልቅ ከተሞች እንጂ አብዛኛዎቹ

የገጠር ከተሞችና የገጠር መንደሮች የመብራት ተጠቃሚ እንዳልሆኑ የገለፁት አቶ ሙሼ፤ እዚህች አገር ላይ ሰፋ ያለ የኢንቨስትመንት ስራ ለመስራት የሀይል አቅርቦት ትልቁ ግብአት በመሆኑ የህዳሴው ግድብ ግንባታ መከናወኛ ጊዜው እንደሆነ ነው የተናገሩት፡፡

“ለምሳሌ የብረታ ብረት ማቅለጫ ኢንዱስትሪ ልገንባ ቢባል ያለው የሃይል አቅርቦት የትም አያደርስም፤ እነዚህ የተደራረቡ ችግሮች ስላሉ የሃይል አቅርቦቱን ከፍ ማድረግ እንደሚገባ በማኒፌስቶአችን ላይ ገልፀናል” ያሉት የኢዴፓ ፕሬዚዳንት፤ “እኛ እንደውም በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ውስጥ የሀይል አቅርቦቱ እስከ 10ሺህ ሜጋ ዋት ከፍ ማለት አለበት ብለን ነበር” ይላሉ፡፡ አሁንም ግን የሚሠራው ግድብ ከሌሎቹ ጋር ተደምሮ የሃይል አቅርቦቱን ወደ 10ሺህ ሜጋ ዋት ማድረስ ይችላል ብለዋል - አቶ ሙሼ፡፡

ግድቡ በተያዘለት ጊዜ ይጠናቀቅ እንደሆነ ተጠይቀውም ሲመልሱ፤ጥያቄው በጣም አስቸጋሪና ቴክኒካል እንደሆነ ገልፀው፤ በሁለት ዓመቱ ግድቡ 21 በመቶ መሠራቱንና በቀሪዎቹ ሶስት ዓመታት ይጠናቀቃል ወይ የሚለውን መመለስ አዳጋች እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

“ባለሙያዎቹ እንደገለፁት ዋና ዋና የግድቡ ስራዎች መሬቱን መጥረግና ማመቻቸት እንዲሁም

የወንዙን አቅጣጫ ማስቀየስ ነው” ያሉት አቶ ሙሼ፤ እነዚህ ስራዎች መገባደዳቸውን ጠቁመው ግንባታው ከታቀደለት ጊዜ ሁለትና ሶስት ዓመታት ቢጨምር ብዙም እንደማይገርም ገልፀዋል፡፡ “አስዋን ግድብ በአምስት ይጠናቀቃል ተብሎ ከአስር ዓመት በላይ ወስዷል” ያሉት የኢዴፓ ሊቀመንበር፤ ታላቁ የህዳሴ ግድብ በቁሳቁስ አቅርቦትና በመሰል ጉዳዮች ሁለት እና ሶስት ዓመት ቢራዘም ሊያስደንቅ አይችልም ሲሉ ተናግረዋል፡፡ መንግስት የግድብ ሥራው በስኬት እንዲጠናቀቅ የላይኛውና የታችኛው ተፋሰስ አገራትን በዲፕሎማሲ ወደ አንድ አቅጣጫ እንዳመጣ ሁሉ፣ በግድቡ ተጠቃሚ ከሚሆኑት እንደ ግብጽና ሱዳን ያሉ ሀገራት ተጨማሪ ገንዘብ ለማሰባሰብ ከፍተኛ የዲፕሎማሲ ስራ እንደሚያስፈልግም አቶ ሙሼ ገልፀዋል፡፡ “ህዝቡ ከአንድ ጊዜ በላይ ለማዋጣት አቅሙ ያለው አይመስለኝም” ያሉት ሊቀመንበሩ፤ የህዝቡ የኑሮ ሁኔታ አስቸጋሪ በሆነበት በአሁኑ ወቅት የ80 ቢሊዮን ብር ፕሮጀክት በህዝብ መዋጮ እንደማይጠናቀቅና መንግስት ሶስት ጉዳዮች ላይ ማተኮር እንዳለበት ይመክራሉ፡፡ በረጅም ጊዜ የሚከፈልና ወለዳቸው አነስተኛ የሆነ ብድር የሚያገኝበትን መንገድ ማመቻቸት፣ ግሽበቱን ለመቀነስ የሚረዱ መንገዶችን ማመቻቸትም ሌላው

ተቃዋሚዎች በሂደቱ ላይ እንጂ በግድቡ ላይ ተቃውሞ የለንም አሉ

*አባይን የመገደብ መብት ተፈጥሯዊ እና አገራዊ መብት ነው - አንድነት

*መንግስት በርካታ የገንዘብ ማስገኛ መላዎችን መዘየድ አለበት - ኢዴፓ

*የግንባታውን ሂደት ለሁሉም አካል ግልጽ ለማድረግ ጊዜው አልረፈደም- ሠማያዊ ፓርቲ

*አባይን ጨምሮ የአገሪቱ ወንዞች መጐልበት እንዳለባቸው በፕሮግራማችን ላይ ተቀምጧል- መድረክ

ናፍቆት ዮሴፍ

Page 6: Issue-703.pdf

Website: www.addisadmassnews.com

አዲስ አድማስ ሰኔ 29 ቀን 2005 ዓ.ም ገፅ 6 ህብረተሰብ

ምድር ወደ ገፅ 24 ዞሯልማስታወቂያ

በኦሪዮን ወ/ዳዊት

የትግራይ ጉዞ ማስታወሻ

ባለፈው ሳምንት ጉዞውንም ጽሑፉንም በይደር አቆይተነው ነበር፡፡ እነሆ ከዚያው ቀጥለናል፤ የቆምንበትን ቦታ ለማስታወስ ያህል አስደናቂ ለውጥ ወዳየሁበት ግራ ካ/ሀ ልመልሳችሁ፡፡ ግራ ካሱ መለመላውን የቆመ ሰው ይመስል ነበር፡፡ አሁን የተፈጥሮ ክብሩን ተጐናጽፏል፡፡ ሰው እና እንስሳት እንዳይደርሱበትም ሰባ የጥበቃ ሰራተኞች ተቀጥረውለታል፡፡

አቶ ከበደ አማረ የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ኤጀንሲ ኃላፊ እንደነገሩን፤ ቁጥራቸው የተጋነነ ባይሆንም በግራ ካሱ ደን ውስጥ ሰስ፣ ድኩላ፣ አነር፣ ጥንቸልና የመሳሰሉት በመራባት ላይ ናቸው፡፡ ሆኖም እንስሳቱን የውሃ እጥረት ያጋጥማቸዋል፡፡ በግራ ካሱ ሰሜናዊ ምዕራብ አቅጣጫ የሚገኘው “ጉምብርዳ” የተባለው ቦታም በደን ተሸፍኖ የተመልካችን ቀልብ መግዛት ችሏል፡፡ ጉምብርዳና ግራ ካሱ ከፍተኛ ጥበቃ የሚደረግላቸው የመንግስት ጥብቅ ደኖች ናቸው፡፡

በግራ ካሱ ተራራ ላይ የተገነባውን መንገድ ሲያስተውሉት ተጣጥፎ የተኛ ዘንዶ ይመስላል፡፡ ዚግዛግ እየመቱ ከአንድ ቦታ ላይ መመላለስ የግራ ካሱን ተራራ ለመውጣት የሚያስፈልግ የውዴታ ግዴታ ነው፡፡ ድሮ መንገዱ ጠባብ፣ ተራራውም ራቁት ስለነበረ ጉዞው አስፈሪም ዘግናኝም ነበር፡፡ አሁን ግን ተራራው በደን በመሸፈኑ፣ መንገዱም በመስፋቱ ያ ልብን እንደቄጠማ ያርድ የነበረ ጉዞ ተቀይሯል፡፡ እንዲያውም በተቃራኒው መንፈስን በሐሴት ይሞላል፡፡

ግራ ካሱን በዚህ ዓይነት ሁኔታ ካለፍን በኋላ “ጨለማ ዱር” ከሚባለው ቦታ ደረስን፡፡ ግን ዱር የለም፤ ድሮ ጥቅጥቅ ያለ ደን እንደነበር ሰምተናል፡፡ አሁን የእርሻ ቦታ ነው፡፡

ብዙም ሳንርቅ የግራ ካሱን ተራራዎች ባየንበት ዓይናችን ለጥ ያለውን የኃያሎ ሜዳ ሐናይ “ተፈጥሮ

ተናጋሪዋ ምድርምን ዓይነት ድንቅ ናት” ማለታችን አልቀረም፡፡ ጥንታዊቷን የኃያሎ ማርያም ቤተክርስቲያን በቅርብ ርቀት እያየን ወደፊት ስንገሰግስ፣ የጥንታዊቷ ኮረም ከንቲባ አቶ ኃይሌ ምስጉን፤ ከከተማው ህዝብና ባለሥልጣናት ጋር ሆነው ልክ አላማጣ ላይ በተደረገልን መንገድ በደማቅ ስነሥርዓት ተቀበሉን፡፡ ኮረም ድረስ የሸኙን የአላማጣ ከተማ ከንቲባ አቶ ገብረ ትንሣኤ ፍስሃና ሌሎች የሥራ ባልደረቦቻቸውም ለኮረም ከተማ ባለሥልጣናትና ህዝብ አስረክበውን ወደ አላማጣ ተመለሱ፡፡

የኮረም ከተማ ህዝብና ባለሥልጣናት ከከተማዋ ወጥተው በሆታና በባህላዊ ጭፈራዎች ሲቀበሉን የጥበብ ተጓዦች አድናቆታቸውን የሚገልጹበት መንገድ የጠፋባቸው መስለው ነበር፡፡

ሆኖም አንዳንዶች ከህዝቡ ጋር እየጨፈሩ፣ ሌሎች በካሜራና በማስታወሻ ደብተራቸው ላይ ያዩትን ለመክተብ ሲጣደፉ ተመልክቻለሁ፡፡ የደቡባዊ ዞን ባህልና ቱሪዝም ኤጀንሲ አስተባባሪ አቶ ኢያሱ ታረቀኝ እንዳስረዱን፤ ሮማን እንደ ገብስ ያመሳት ጀግናቸው ዘርዓይ ደረስ ኮረም ላይ በመምህርነት አገልግሏል፡፡ ኮረም የብዙ ዘግናኝ ድራማዎች መከወኛ መድረክም ነበረች፡፡ በ1977 ዓ.ም ተከስቶ በነበረው ድርቅ ከ100ሺህ በላይ ህዝብ በዳቦ ዕጦት እንደቅጠል ረግፎባታል፡፡ ክቡሩ የሰው ልጅ ከእንስሳት ባነሰ መንገድ ተጐሳቁሎባታል፤ የራበው ጅብ በሰው ልጆች አጥንት ተዘናንቶባታል፤ በአጠቃላይ መከራዎች ሁሉ ተጠራርተው የቅጣት ዳፋቸውን አውርደውባታል፡፡

ረሃቡንና ያስከተለውን ዘግናኝ እልቂት በፊልም የተመለከተው ዝነኛው አቀንቃኝ ቦብ ጊልዶፍ “ዊ አር ዘ ወርልድ” በሚል መሪ ቃል ታዋቂ አለምዓቀፍ

የኪነት ሰዎችን ማስተባበር የጀመረውም ያኔ ነው፡፡ ባደረገው ሰብአዊ እንቅስቃሴም “ባንድ ኤይድ” የተባለ ዘመናዊ ሆስፒታል ለከተማዋ ህዝብ መገንባት አስችሏል፡፡

ኮረም ከረሃቡ ሌላ በህወሓትና በወቅቱ መንግሥት መካከል ከፍተኛ ጦርነት የተካሄደባት፤ በጦርነቱም ከግራ ቀኙ ወገኖች በርካታ ህዝብ የወደቀባት ቦታ መሆኗን አስጐብኚያችን ነግረውናል፡

ወደ መጥፎ ትዝታዎቿ ተሳብሁና አሁን ያለችበትን ሁኔታ ረሳሁ፡፡ ኮረም አሁን ሰላም ናት፡፡ እንደ ሌሎቹ የሃገራችን ከተሞች በእድገት ግስጋሴ ላይ ትገኛለች፡፡ ያ ሁሉ ህዝብ የዕለት ዳቦ አርሮበት፣ በዓይኑ ላይ እህል እየተንከራተተበት፣ እንደ ቅጠል የረገፈባት ቦታ ዛሬ ተፈጥሮ ፊቱን አዙሮላት ፍጹም ለምለም ናት፡፡ ለነገሩ ያኔም ቢሆን ያለቀው ዕርዳታ ፍለጋ ከየወረዳውና ከየአካባቢው የመጣው ምስኪን ህዝብ ጭምር እንጂ የኮረም ከተማ ህዝብ ብቻ አልነበረም፡፡ ያም ሆነ ይህ የጥበብ ተጓዡ የኮረምን ዘግናኝ ታሪኮች ከባለስልጣናቱ ካደመጠ በኋላ በከንቲባው በአቶ ኃይሌ ምስጉን አማካይነት የምሳ ግብዣ ተደረገለት፡፡ ዝነኛው የኮረም ኮረፌም የምሳው አንድ አካል ነበር፡፡

ጉዞው ቀጥሏል፤ የኮረምን ህዝብና ባለሥልጣናት አቀባበል እያደነቅን፣ ጉዟችንን ቀጥለን ሳለ በክልሉ ብቸኛ የሆነው የአሸንጌ ሃይቅ ድንገት ከፊትለፊታችን ድቅን አለ፡፡ አካባቢው የኦፍላ ወረዳ ነው፡፡

በዚያ አካባቢ በ16ኛው ክፍለ ዘመን በግራኝ አህመድ በሚመራው እና በክርስቲያኑ የኢትዮጵያ ንጉሥ ልብነ ድንገል መሃል መራራ ጦርነት ተካሂዷል፡፡

አፄ ልብነ ድንግልን ሊረዳ ከፖርቱጋል መጥቶ

የነበረው የባስኮ ደጋማ ወንድም ዝነኛው ክርስቶፎር ደጋማ የተገደለው እዚያ አካባቢ ነው፡፡

በ1928 ዓ.ም የጣሊያን ፋሽስቶች ሀገራችንን ሲወርሩ አሸንጌ አካባቢ በርካታ ህዝብ አልቋል፡፡ ቸኮዝሎባኪያዊው ወዶ ዘማች አዶልፍ ፓርለስክ

ለመሆኑ ለምን ተሸነፍን? አምባራዶም ላይ የጣሊያንን መንጋ

አፈር ያስጋጠ ጀግና ሠራዊት እንዴት ማይጨው ሲደርስ ተሸነፈ? ንጉሠ

ነገሥቱ በውጊያው ወቅት ምን ሚና ነበራቸው? ከውጊያው በፊትስ የኢትዮጵያ ህዝብ ከእርሳቸው

ጋር የሚሰለፍበትን ሁኔታ አመቻችተው ነበር? በአጠቃላይ

የአድዋ ድል ለምን ማይጨው ላይ አልተደገመም? እጅግ በርካታ ጥያቄዎችን ማንሳት ይቻላል፡፡ ግን

ያኔም ሆነ አሁን መልስ ያላገኙና የማገያኙ ጉዳዮች በርካታ ናቸውና የጥያቄ ሰልፈኛ መደርደሩ ብዙም

ርባና ያለው አይመስልም፡፡

Page 7: Issue-703.pdf

Website: www.addisadmassnews.com

አዲስ አድማስ ሰኔ 29 ቀን 2005 ዓ.ም ገፅ 7 ህብረተሰብ

ኤፍሬም እንዳለ

እንዴት ከረማችሁሳ! ይኸው ለ‘በጀት መዝጊያ’ ደረስን አይደል!

ስሙኝማ…ይሄ የፈረንካው በጀት እንደሚዘጋ ሌሎች ዓመቱን ሁሉ አብረውን ያሉ ነገሮች አብረው ቢዘጉ እንዴት አሪፍ ይሆን ነበር! የመናናቅ፣ የመጣጣል፣ ከ“እኔ በላይ” የማለት፣ የጉልበተኝነት…ምናምን ነገሮች ጥርቅም ተደርገው የሚዘጉበት ዓመት ናፍቆናል፡፡

ስሙኝማ…ጨዋታን ጨዋታ ያነሳው የለ… ይሄ የጉልበተኝነት ነገር በብቃት ማረጋገጫ የሚሰጥ ነገር ሆነ እንዴ! ግራ ገባና! እኔ የምለው… ይሄ ደንብ ማስከበር ምናምን የሚሉትን ነገር ካነሳን አይቀር...በዛ ሰሞን በከተማው አንድ ክፍል ያየሁትን ስሙኝማ… እድሜያቸው ገፋ ያሉ ሁለት ‘ደንብ ማስከበሮች’ የሆነ ካልሲና ውስጥ ሱሪ አንጥፎ ይሸጥ የነበረን ልጅ ከነበረበት ያባርሩታል፡፡ እናማ… አንደኛው ምን ይል መሰላችሁ… “በዱላ ወገቡን መስበር ነበር…” ይሄኔ በዕድሜ በለጥ ያለ የሚመስለው ሰውዬ ምን ቢል ጥሩ ነው…“የምን ዱላ፣ በጫማ ጥፊ ማለት ነበር፡፡”እናላችሁ…የውቤ በረሀ ትዝታ ካልለቀቀውና “ቀን ባይጥለኝ ኖሮ…” የሚል አንጋፋ አይግጠማችሁ፡፡

ስሙኝማ…ስኖውደን የተባለው ሰውዬ ‘ታላቋን አገር’ ናጣት አይደል! (በነገራችን ላይ ስኖውደን የአማሪካንን ጉድ ከዘከዘከ በኋላ የጆርጅ ኦርዌል ‘1984’ መፅሐፍ ሽያጭ በአማዞን በ6000% አድጓል ተብሏል፡፡)

እናላችሁ…በዚህ ‘የሰለጠነ ዘመን’ ወዳጅ የሚባል ነገር እንደሌለ አያችሁልኝ አይደል! እናማ… ‘ወዳጃችን፣’ ‘የምናምን አጋራችን’ ብሎ ነገር የለም። አሀ… “በ‘አማሪካን’ ሳንባ ሊተነፍሱ ምንም

“ከዚህ አይነት ህይወትስ እስከ ወዲያኛው…”

አይቀራቸው…” የሚባሉት አገሮች… “አሜሪካንን ያመነ ጉም የዘገነ…” ብለው አረፉት አይደል!

ስሙኝማ…ጨዋታን ጨዋታ ያነሳው የለ…የአገሮቹ ይሁን እዚህ እኛ ዘንድ ጠቅላላ እርስ በእርሳችን ስንሰላለል አይደል እንዴ የምንውለውና የምናመሸው!

ለምሳሌ…እሱ የሆነ እድገት ለማግኘት እናንተን በስጦታ ወረቀት ሳይጠቀልል በደረቁ ‘መታያ’ ሊያደርጋችሁ የሚፈልግ አይነት ሰው ገጥሟችሁ አያውቅም! እናማ…ደህና ከማንም ጋር የማያናክሰውን፣ ከማንም ጋር “የቡድንና የቡድን አባቶች…” የማያስብለውን የጆሴ ሞሪንሆን ወሬ እያወራችሁ በመሀል…“ስማ…” ይላችኋል፡፡ “እነዚህ ሰዎች አሁንስ አላበዙትም እንዴ!…” ምናምን ይላል። (“እነዚህ ሰዎች…” ስንባባል ትርጉሙ ‘የማያሻማ’ ወደ መሆኑ እንደተቃረበ ይታወቅልንማ!)

ታዲያላችሁ…እናንተ ደግሞ “ሂድና ምስር ወጥ፣ ካቲካላና ‘እንትን ሰፈርን’ የለመደ የቻይና ባቡር ሀዲድ ሠራተኛ ብላ…” ትሉና ጭጭ፡፡ ይቀጥልና ምን ይላል መሰላችሁ… “እንደው የያዘ ይዞኝ ነው እንጂ እነሱን የማላይበት ቦታ፣ ለምን ቱራ ቦራ አይሆንም እሄድ ነበር…” እናንተ ደግሞ…ጭጭ! እናላችሁ…እንዲህ አይነት…አለ አይደል… ኳሷን ሆነ ብሎ ወደ እናንተ ክንድ ወርውሮ “ዳኛ… ማኖ ሲነካ ዝም ትላለህ እንዴ! ቀይ ስጠው እንጂ!” የምንል አይነት ሞልተንላችኋል፡፡

ስሙኝማ…እንደው እዚች ከተማችን እንኳን ያለ የእንትናና የእንትናዬ የመሰላለል ታሪክ አይደለም

የስኖውደን የሲ.አይ.ኤ. ኮምፒዩተሮች አይችሉትም። “የፍላጎት እንጂ የአቅርቦት ችግር የለም…” በተባለበትና የሶዶምና ገሞራን ታሪክ ቀሺም የፊልም ጽሁፍ በሚያስመስል ዘመን…የእሷና እሱ መሰላለል በሽ ነው፡፡

ልክ ነዋ…“ትናንት አሥር ሰዓት ላይ አብረሽው ፒያሳ ስትሄጂ የነበርሽው ሰውዬ ማነው?” “ቅድም ሃያ ሁለት አብረሀት ሻይ ስትጠጣ የነበረችው ማናት?” አይነት ጥያቄዎች እኮ ያው የስለላ ውጤቶች ናቸው። “የት፣ የት እንደምትውል የማላውቅ መሰለህ…” “ተሰብስባችሁ ምን እንደምታወሩ የማልሰማ መሰለሽ!” ምናምን በሙሉ ከስለላ የሚገኙ መረጃዎች ናቸው፡፡

ስሙኝማ…“ትናንትና ቺቺንያ ቢራውን ላይ በላይ ትጨልጥ ነበር አሉ…” የሚል ነገርም የስለላ ውጤት ነው፡፡ አሀ…የምትጠጡትን ቢራ ቁጥር የሚያሰላ…አለ አይደል… ለስለላ ካልሆነ ለምንድነው?

ደግሞላችሁ…የሆነች የምታውቋት እንትናዬ አለች፡፡ እና የሆነ እንትና ልቡ ይፈቅዳታል፡፡ እናላችሁ… ግንኙነታችሁ ምን እንደሆነ እርግጠኛ ስላልሆነ… ‘ይሰልላል’፡፡

“ከእንትና ጋር ትቀራረባላችሁ?” ይላል፡፡ እናንተም… “አዎ፣ በጣም…” ትላላችሁ፡ እሱዬውም “ስሰማ እኮ በጣም ቅርብ ናችሁ አሉ…” ይላል፡፡ ‘በጣም’ ላይ ጫን ይላል፡፡ እናንተም “አዎ፣ በጣም…” ትላላችሁ፡፡ ከዛ ወዴት ይመጣል መሰላችሁ… “እንዴት ነው… ማለቴ እንትን ነገር…” ምናምን ብሎ ባላለቀ ቀለበት መንገድ ላይ አቅጣጫ ይጠፋዋል። ይሄኔ… “አቦ፣ ስለላውን ተውና ሄደህ ለራሷ ማመልከቻህን አስገባ…” ማለት ነው፡፡ እናላችሁ…በየቀኑ ስንሰላለል ነው የምንውለው፡፡

ደግሞላችሁ ...ሳይታወቃችሁ ለስለላ የምትመለመሉበት ጊዜ አለ፡፡ “ስማ… መሥሪያ ቤታችሁ ለአካውንታት ሠራተኛ ማስታወቂያ ሊያወጣ ነው ሲሉ ሰምቻለሁ…” ይላል፡፡ ከዛ አከታትሎ… ምን ይላል መሰላችሁ…“እስቲ ለቦታው ያጩት ሌላ ሰው ካለ ሰልልኝ!” እናላችሁ መልማዮች ሲ.አይ.ኤና ኬ.ጂ.ቢ. ብቻ አይደሉም፡፡

“አንቺ… ያቺ ጓደኛሽን ሥራ አስኪያጁ ሙድ ያዘባት አሉ፡፡ እስቲ በእናትሽ ሳይታወቅብሽ ሰልያት…” የሚል አይነት ምልመላ አለ፡፡

በነገራችን ላይ… “ሙድ መያዝ” የሚሉት በንግግር ውስጥ የካርታውን ‘ጆከር’ ቦታ ይዞላችኋል፡፡ “ሙድ ይዛብሀለች…” ማለት ወይ “ተመችተሀታል” ወይም “ለዓይኗም አስጠልተሀታል” ማለት ሊሆን ይችላል፡፡

ስሙኝማ…እንግዲህ ጨዋታም አይደል…ከዚህ በፊት ያወራትን እንድገማትማ…ሰውየው የሆነ አልቤርጎ ተከራይቶ ለሽ ብሏል፡፡ እናማ… ድንገትም ጎኑ ካለውና የሆኑ ‘እሷና እሱ’ ከተከራዩበት ክፍል ድምጾች መስማት ይጀምራል፡፡ “እነሆ በረከት ተጀመረ ማለት ነው…” ይልና ጆሮውን አቁሞ ያዳምጣል፡፡ ሰውየው “አንቺ ከላይ ሁኚ…” ይልና አተነፋፈሶች ላይ የኦክሲጅን እጥረት ይከሰታል። ቀጥሎ ደግሞ ሴትዮዋ “አንተ ከላይ ሁን…” ትልና አሁንም አተነፋፈስ ላይ የኦክሲጅን እጥረቱ ይባባሳል፡፡ ታዲያላችሁ…ትንሽ ቆይቶ ሰውየው ምን ሲል ሰማ መሰላችሁ… “ሁለታችንም ከላይ እንሁን…” “ጉድ ነሽ የአንኮበር ቅጠል…” ማለት ይሄኔ ነው! እናላችሁ… ክፍሉ ከወደጣሪያው ክፍተት ስለነበረው “ይህንን የዘመናችንን ፈጠራማ ማየት አለብኝ…” ብሎ ወንበር ላይ ይቆምና ተንጠራርቶ ያያል፡፡ እናላችሁ… ምን ቢያይ ጥሩ ነው…ለካ ሁለቱ ሰዎች ሻንጣ አልዘጋ ብሏቸው ለመቆለፍ መከራቸውን እያዩ ነበር፡፡

እናማ…“ሁለታችንም ከላይ እንሁን…” ስንል ብትሰሙን ለ‘ሌላ ጉዳይ’ ብቻ ሳይሆን… ሻንጣ አልዘጋ ብሎን ሊሆን እንደሚችል ይታወቅልንማ! ቂ…ቂ…ቂ…

የስለላ ነገር ካነሳን አይቀር…ስታሊን ሠራተኞቹ እንዴት እንደሚኖሩ ለማየትና ስለ እሱ ምን

እንደሚሉ ለማወቅ ራሱን ለውጦ ከክሬምሊን ሹልክ ብሎ ይወጣል፡፡ ትንሽ ዘወር፣ ዘወር ብሎ ይቆይና ሲኒማ ቤት ይገባል፡፡ እናላችሁ…ፊልሙ ሲያልቅ ስክሪኑ ላይ የስታሊን ፎቶ በትልቁ ይታያል፡፡ ይሄኔ ሁሉም ሰው ተነስቶ ይቆምና መዝሙር መዘመር ይጀምራል፡፡ ያልተነሳው ራሱ ስታሊን ብቻ ነበር፡፡ እናማ…ጎኑ የነበረው ሰውዬ ጎንበስ ብሎ ምን አንሾካሾከለት መሰላችሁ…“ስማ ጓድ፣ እንዳንተ እኛም ይሄንን ሰይጣን ሰውዬ አንወደውም፡፡ ግን ሰላዮቹ እንዳይበሉህ፤ ተነስተህ ብትዘምር ይሻለሀል፡፡” አሪፍ አይደል!

ስሙኝማ…እንግዲህ ጨዋታን ጨዋታ ያነሳው የለ…ስለ‘ኮሚ’ ዘመን ካነሳን አይቀር…ይቺን ስሙኝማ… ኢቫኖቭ የተባለ ሩስያዊ ሰው የኮሚኒስት ፓርቲው አባል ለመሆን አመልክቶ የፓርቲው ኮሚቴ ቃለ መጠይቅ እያደረገለት ነው።

“ጓድ ኢቫኖቭ፣ ታጫሳለህ?”“አዎ፣ ባይበዛም አጨሳለሁ፡፡”“ጓድ ሌኒን እንደማያጨስና ኮሚኒስቶች

እንዳያጨሱ እንደሚመክር አታውቅም?”“ጓድ ሌኒን እንዲሀ ካለማ ማጨስ አቆማለሁ።”“ትጠጣለህ?”“አዎ፣ አልፎ፣ አልፎ፡፡”“ጓድ ሌኒን መጠጥን እንደሚያወግዝ

አታውቅም?”“እንግዲያው ሁለተኛ አልጠጣም፡፡”“ጓደ ኢቫኖቭ፣ ሴቶች ታበዛለህ?”“ይሄን ያህል ባይሆንም…”“ጓደ ሌኒን እንዲህ አይነት ከሞራል ውጪ የሆኑ

ጉዳዮችን እንደሚያወግዝ አታውቅም?”“ጓድ ሌኒን እንዲህ ካለ ከእንግዲህ ሴት አጠገብ

አልደርስም፡፡”“ጓድ ኢቫኖቭ፣ ህይወትህን ለፓርቲው ለመሰዋት

ፈቃደኛ ነህ?”“በደንብ አድርጌ፣ ከዚህ አይነት ህይወትስ

እስከወዲያኛው ፍግም ብል ይሻለኛል፡፡”የምር ግን…“ምን በላ…” “ምን ጠጣ…” “የት

ገባ…” “የት ወጣ…” “ከማን ዋለ…” “ከማን አመሸ…” አይነት ጆፌ መጣል አሪፍ አይደለም፡፡ ከሀያ አራት ሰዓት ሀያ ሦስት ሰዓት ከሀምሳ አምስት ደቂቃውን…የራሳችንን ህይወት የምናይበትን ዘመን ያምጣልንማ! በደጉም፣ በክፉም “ያገባኛል ባይ…” የበዛበት ህይወት “ከዚህ አይነት ህይወትስ እስከወዲያኛው…” ማለት ያመጣል፡፡

እናላችሁ…እኛ ዘንድ እርስ፣ በእርስ መሰላለል በሽ ነው…ላይ ‘ዋናዎቹ’ ቦሶች፣ የቅርብ አለቆች፣ እንትናና እንትናዬዎች፣ ጎረቤቶች፣ የልብ ጓደኞች፣ የሥራ ጓደኞች…ልጄ፣ ዘመኑ አንዳችን አንዳችንን የመሰላለል ዘመን ነው፡፡

ደህና ሰንብቱልኝማ!

በነገራችን ላይ… “ሙድ

መያዝ” የሚሉት በንግግር ውስጥ

የካርታውን ‘ጆከር’ ቦታ ይዞላችኋል፡፡ “ሙድ ይዛብሀለች…” ማለት ወይ “ተመችተሀታል”

ወይም “ለዓይኗም አስጠልተሀታል” ማለት

ሊሆን ይችላል፡፡

ማስታወቂያ

www.virtualethio.comበድረ ገፃችን ላይ ለሚመዘገቡ 5% ቅናሽ ያግኙ፡፡

Page 8: Issue-703.pdf

Website: www.addisadmassnews.com

አዲስ አድማስ ሰኔ 29 ቀን 2005 ዓ.ም ገፅ 8 ማስታወቂያ

Page 9: Issue-703.pdf

Website: www.addisadmassnews.com

አዲስ አድማስ ሰኔ 29 ቀን 2005 ዓ.ም ገፅ 9 ህብረተሰብ

እንባ ወደ ገፅ 12 ዞሯልማስታወቂያማስታወቂያ

ወደ ለቅሶ ቤትም ሆነ ሠርግ ቤት አዘውትሮ መሄድ አልወድም፡፡ ሠርግ ቤት የግብዣ ካርድ ሲደርስህ ብቻ መሄድ ትችላለህ፡፡ ለለቅሶ ቤት የግብዣ ካርድ አያስፈልግም፡፡ የዳሱም ሆነ የድንኳኑ አዘጋጆች የገንዘብ ወጪ (ጣጣ) አለባቸው፡፡ ታዳሚውን ለማስደሰትም ሆነ ለማሳዘን ዝግጅት ያስፈልጋል፡፡

እኔ ሁለቱንም አላዘወትርም፡፡ ግዴታ ሲሆኑብኝ ብቻ ጐራ እላለሁ፡፡ ስለ ደስታ ቤቱ ለጊዜው ልተውና ለቅሶው ላይ ላተኩር፡፡ ምናልባት፤ ለቅሶ ቤት መሄድ የምፈራው የለቅሶን ትርጉም ስለማላውቅ ይሆናል፡፡ አልቅሼ አላውቅም አይደለም ያልኩት፡፡ ለቅሶ ራሱ ለሰው ልጆች ምናቸው እንደሆነ ነው ያላወኩት፡፡

The Logic of the Moist eye የምትል ምዕራፍ ከአርተር ኮስለር መፅሐፍ ላይ አገኘሁ፡፡ መረጥኳት፡፡ ጨመቅኳት፡፡ ጠብ የሚል ካለ እንደ እንባ ጨው ጨው ባይልም እስቲ ቅመሱት፡፡

ለቅሶ ለሰው ልጆች የመጀመሪያ ቋንቋ ነው፡፡ በተወለድንበት ቅፅበት አለምን የምናናግርበት፡፡ ለቅሶ የመጨረሻም ቋንቋ ነው፡፡ ከእንግዲህ ላለመናገር/ላለመኖር አለምን ጥሎ የሚጓዝ ሰውን እንሸኝበታለን፡፡ የመጀመሪያና የመጨረሻ ብቻ ሳይሆን የእድሜ ልክም ቋንቋ ነው፡፡ ያልተወለደ እና በህይወት ያልኖረ… ማልቀስ አይችልም፡፡

ለምንድነው የምናለቅሰው? ብለን

ምክኒያታዊነት እና እንባሌሊሳ ግርማ

ስንጠይቅ አንድ ሳይሆን ብዙ መልሶች እናገኛለን፡፡ ለቅሶ ሀዘንን ብቻ ገላጭ አይደለም፡፡ ለቅሶ ማለት የእንባ ከረጢት የሚያመነጨው ፈሳሽ ማለት ብቻም አይደለም፡፡ ለቅሶ ያለው በሞት አለም ውስጥ ሳይሆን ህይወት ባለበት አለም ላይ ነው፡፡ የለቅሶ መኖር የሰው ልጅን የስሜት ሙቀት ከታችኛው እርከን እስከ ከፍተኛው ጥቅል ፍቅር አንድነት መድረስ እና መመለስ መቻልን አመልካች ነው፡፡ለቅሶ ለፈረንጆቹ ሁለት ስያሜ አለው Crying & Weeping.

ህፃን ልጅ ጡት ፈልጐ ሲያለቅስ ለቅሶው ማስጠንቀቂያ ወይንም ፍላጐቱን ማሟያ ነው፡፡ ፍላጐቱ እንዲሰጠው በመሻት ሲወራጭ ድርጊቱ መፍጨርጨርን… እልህን… ትግልን ያሳያሉ፡፡ ህይወት ላይ ለመቆየት ከሚያስፈልጉ ትግሎች ጋር የሚያነሳሳ ምክንያት ሲደነቀርበት ሰው አፀፋውን በአፀፋ መመለሱን የሚገልጽባቸው (Self asserting) አንዱ ነው፡፡ ራስን ከተፈጥሮአዊ ህልውና ጋር ለማመሳሰል ለማፎካከር የሚጠቅም ስሜት ነው፡፡

ይህ ስሜት እንዲመነጭ የሚያነሳሳ ምክንያት ሲደነቀርበት ሰው አፀፋውን በአፀፋ መመለሱን የሚገልጽባቸው መቆጣት፣ መፍራት፣ መታገል፣ ረሐብ፣ በሰውነት አካል ላይ የሚሰሙት ህመሞች… የተወሰኑት ናቸው፡፡

እነዚህ ምክኒያቶች የሚፈጥሩት ስሜት Self asserting እርምጃዎች በሰውየው አማካኝነት እንዲተገበሩ ያስገድዳሉ፡፡ ሁሉም ስሜቶች፤ በጡንቻ

ስብራት ታመራለች፡፡ ወደ መቀበል፡፡እዚህ ላይ እንባ የተሰበረ ቅስምን

በሚያሻማ መልኩ የሚጠቁም ማረጋገጫ አይደለም፡፡ ሀዘኑን በተሸከመው ሰው ሰውነት ላይ የሚገለፁ የእንቅስቃሴ ምልክቶች ግን የሚያሻሙ አይደሉም፡፡

በሳቅ ምክንያት የሚፈስ እንባ እና በሀዘን ምክንያት የሚፈሰው በመጠንም ሆነ በሌላ መለኪያ አንድ ቢሆኑም… በሳቅ ወቅት ሰውነት ከመጠን ያለፈ ይፍታታል፡፡ ጭንቅላት ወደ ማጅራት ከንበል ይላል፡፡ ሰውነት አይጨበጥም፡፡

በሀዘን ወቅት (ሀዘንን መቀበል ከመጣ በኋላ) ጭንቅላት በጉልበቶች ላይ ወይንም ወደ ደረት በትከሻ መሀል ይጣላል፡፡ ራስን በራስ… እጅን በወገቡ አዙሮ መታቀፍ፣ በሰው ትከሻ

ሀዘንተኛው ራስን ለድጋፍ ማሳረፍ፣ ሰው ላይ ተጠምጥሞ መንሰቅሰቅ… ሀዘንን ለማምለጥ የተደረገው የአካላዊ መወራጨት እንደተቻለ በሰውነት መፍጨርጨር… ሳይቻል ሲቀር በፋንታው “መቀበል” መተካቱን የሚያሳዩ አካላዊ የእንቅስቃሴ መግለጫ ናቸው፡፡ ድጋፍ፣ ሀዘኔታ እና ፍቅር እንሻለን ማለታቸውም ነው፡፡

በደስታ ምክንያት ከሳቅ የፈለቀ እንባን ሳቂው ይቋቋመዋል፡፡ ድጋፍም አይሻም፡፡

ሌላ ምሳሌ፡- ህፃኑ ልጅ አሁን አድጓል፡፡ ወደ እናቱ እቅፍ እየሮጠ… ድንገት ደንጋይ ቢያደናቅፈው እና ቢወድቅ፤ ልክ ድንገተኛ ሞትን እንደተረዳችው የቅድሟ ሴትየው መጀመሪያ ይደነግጣል፡፡ ድንጋጤው ፊቱ ላይ የሚስተዋለው… በመውደቅ ላይ ባለበት ቅጽበት ነው፡፡ መሬቱ አጉል ቦታ እንዳይመታው በደመነብስ በሚወራጭበት ሰከንድ፡፡ ለመትረፍ የሚያደርገው መፍጨርጨር እስኪያከትም የድንጋጤ ገጽታ በፊቱ ላይ መታየቱን ይቀጥላል፡፡ እሱን ለማትረፍ የቀለጠፉት ጡንቻዎቹ መሬት ከተንከባለለ በኋላ… እና ተጨማሪ አደጋ አለመኖሩን ሲገነዘቡ መልሰው ይላላሉ፡፡ የጡንቻ መላላት፤ የአድሪናሊን ሆርሞን መመንጨት ማቆሙን ገላጭ ነው፡፡ የመጀመሪያው የፍርሐት ክፍለ ጊዜ አልፏል፡፡ ፊቱ ላይ ያለው ገፅታ ከፍርሐት ወደ ሐዘኔታን መሻት ይለወጣል፡፡ ይኼኔ፤ ያለቅሳል፡፡

አማካኝነት ወደ ተግባር የሚቀየሩ ናቸው፡፡ ጡንቻ የሚያበረታው፣ እንዲፈጥን… እንዲቀለጥፍ የሚረዳው ሆርሞን (አድሬናሊን) አጋራቸው ነው፡፡ ያለዚህ ሆርሞን ሰው የተፈጥሮን ጫና መቋቋም አይችልም፡፡

ለምሳሌ፤ ሴትየዋ ባሏ መሞቱ ሲነገራት፤ በመጀመሪያ ደንዝዛ ትደርቃለች፡፡ የሰማችውን ማመን ያቅታታል፡፡ …የተከሰተውን ነገር መገንዘብ ስትጀምር ጨርቋን ጥላ ልትሮጥ ሁሉ ትችላለች… ከተከሰተው መከራ በስነ ልቦናዋ ላይ የደረሰውን ስቃይ በአካሏ አማካኝነት ተወራጭታ ለማምለጥ ትሞክራለች፡፡ ህመሙ እና ስቃዩ በእሷ መፍጨርጨር ጥሏት እንደማይሄድ ስትገነዘብ ወደ ቅስም

ለ2006 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የትምህርቱን ሥራ በሚገባ ለማንቀሳቀስ ይቻል ዘንድ፣ ከዚህ በታች ለተገለፁት የሥራ መደቦች ቃለምልልስ (Interviews) እናደርጋለን፡፡ በመሆኑም አመልካቾች የመሸኛ ደብዳቤያቸውን፣ የትምህርትና የልምድ ማስረጃቸውንም ለዋናው መስሪያ ቤታችን ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ጠንካራና ትጉህ ባለሙያዎች ብቻ እንዲቀርቡ ይፈለጋል፡፡ ሴቶች አመልካቾች በከፍተኛ ደረጃ ይበረታታሉ፡፡• የመጀመሪያና ከፍተኛ 2ኛ ደረጃ መምህራን በሁሉም ትምህርቶች

አሐዳዊ ክፍል - እንግሊዝ፣ ሒሳብ፣ የሕብረተሰብ ትምህርት /ጆግራፊ ወይም ታሪክ/ አማርኛ፣ ኢኮኖሚክስ፣ ቢዝነስ፣ ቴክኒካልድሮዊንግና ሣይንሶች/ፊዚክስ፣ ኬሚስትሪ፣ ባይሎጂ/ፈረንሳይኛ፣ አረብኛ፣ የአካል ማጐልመሻ እና ሥዕል ለማስተማርያ ያመለከቱ ሁሉ፣ BA, BSC, BED ዲግሪ ወይም በትምህርት መስክ ከዚህ በላይ በየሰለጠኑበት እንዲኖራቸው ያስፈልጋል፡፡ የላቀ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ችሎታና ቀደም ያለ ልምድ ከማስረጃ ጋር እንዲሁም ልጆችን ለማገልገል ከፍተኛ ፍላጐትና ግፊት እንዲኖረው/እንዲኖራት ይገባል፡፡• የአፀደ ሕፃናት መምህራን

ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ወይም ከኮተቤ የመምህራን ኮሌጅ በትምህርት መስክ ዲፕሎማ ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል፡፡ በተጨማሪም ብቁ የእንግሊዝኛ ቋንቋ የፅሁፍና የንግግር ችሎታ ያላቸው፣ በአፀደ ሕፃናት ውስጥ የማስተማር ልምድ እና እንዲሁም የአፀደ ሕፃናት ትምህርት ሥልጠና ያገኙ እንዲሆኑ ያስፈልጋል፡፡• ረዳት መምህራን/የተማሪዎች ሱፐርቫይዘሮች

በአፀደ ሕፃናትና በ1ኛ ደረጃ የሚያስተምሩ ረዳት መምህራን /የተማሪዎች ሱፐርቫይዘሮች/ በትምህርት መስክ በዲፕሎማ ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ ወይም ከታወቀ ዩኒቨርስቲ ከዲፕሎማ ጋር ተመጣጣኝ የሆነ ወይም አቻ የሆነ ክሬዲት አወር (Credit Houer) ያሰባሰቡ ሲሆኑ፣ ብቁ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ፅሁፍና የንግግር ችሎታ እንዲሁም ኃላፊነትን የመሸከም አቅም ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል፡፡ በመምህራን ማሰልጠኛ ወይም በአፀደ ሕፃናት መምህራን ማሰልጠኛ ተቋም ያለፉና የእንግሊዝኛ ቋንቋ ፅሁፍና የንግግር ብቃታቸውን ያስመሰከሩ ለሆኑ ብቻ አስተያየት ሊሰጣቸው ይችላል፡፡ የአፀደ ሕፃናት ኮርሶችን የወሰዱና ጥንካሬያቸውን ያረጋገጡ (Child Care Aide) በሕፃናት ሞግዚትነት ሊመደቡ ይችላሉ፡፡ ከትምህርት መስክ ውጪና በዲግሪ ደረጃ ያሉ አመልካቾች በረዳት መምህርነት ይመደባሉ፡፡• ፀሐፊዎችና ታይፒስቶች

በዲፕሎማ ከታወቀ ተቋም ወይም ድርጅት ጠንካራ የእንግሊዝኛ ንግግርና ፅሁፍ ችሎታ ያላቸው፣ በእንግሊዝኛና በአማርኛ ታይፒንግ ከፍተኛ ችሎታ ያዳበሩና ቢያንስ የአንድ ዓመት ልምድ ያላቸው ይፈለጋሉ፡፡• የቤተ መፃህፍት ባለሙያዎች

በቤተ መፅሐፍት ሳይንስ በዲፕሎማና ከዚያም በላይ፣ ቢያንስ የአንድ ዓመት ልምድ ያለው/ያላት፣ እጅግ በጣም የዳበረ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ችሎታ፣ ጠንካራ የሥራ ባህል እና የDewey Decimal System ያደረጃጀት እውቀት ያለው/ያላት ይፈልጋል፣• የትምህርት ቤት ነርሶች

በክሊኒካል ነርሲንግ ዲፕሎማ ያላት፣ ከፍተኛ የእንግሊዝኛ ችሎታና የአንድ ዓመት ከልጆች ጋር የመስራት ልምድ ያካበተች/ያካበተ ትፈለጋለች/ይፈለጋል፡፡

ተመጣጣኝ ደመወዝ የሚገኝበት አካባቢ፣ ጠንካራ የሥራ ውጤት የሚበረታታበትና የሚሸለምበት፡፡በ0116-62-83-12 ወይም 0116-61-01-50 ለበለጠ መረጃ ያግኙን፡፡

Gibson School Systems

የሥራ ቅጥር እድሎች

Page 10: Issue-703.pdf

Website: www.addisadmassnews.com

አዲስ አድማስ ሰኔ 29 ቀን 2005 ዓ.ም ገፅ 10 ፖለቲካ በፈገግታ

ኤልያስ

ይቅርታ ወደ ገፅ 12 ዞሯል

ከእለት ወደ እለት እየተባባሰ የመጣውን የመብራት መቆራረጥ በየጊዜው ስፅፍ “እህ” ብሎ የሚያደምጠኝ አግኝቼ አንዳች ነገር ይሻሻላል

ወይም ይለወጣል በሚል ተስፋ እንዳልሆነ ለውድ አንባብያንም ሆነ ለኮርፖሬሽኑ ሃላፊዎች በትህትና ላስታውቃቸው እወዳለሁ፡፡ (እንዲሳሳቱብኝ አልፈልግማ!) ይሄኔ የመ/ቤቱ ሃላፊዎች “ታዲያ ምን ለመፈየድ ነው በየጊዜው የምትሞነጭረው ?” ብለው ሊናደዱብኝ ይችላለሉ (የእነሱ ብሶ!) እኔ ግን መልሴ በጣም አጭር ነው - በየጊዜው የመብራት ኃይልን ጥፋቶች እየነቀስኩ የምፅፈው ለሌላ ሳይሆን “እያስመዘገብኩ ነው” ለማለት ያህል ነው፡፡ “ወይ አዲስ አበባ” በተሰኘ ውብ ልብወለዱ እውቅናን ያተረፈው ተወዳጁ ደራሲ አውጎቾ ተረፈ፤ “እያስመዘገብኩ ነው” በሚል ርዕስ በፃፈው ድንቅ አጭር ልብወለዱ ውስጥ የቀረፀው ገፀባህርይ፣ በደርግ ዘመን የቀበሌ አብዮት ጠባቂዎችና ካድሬዎች የሚያደርሱበትን በደል በህጋዊ መንገድ ተጋፍጦ መከላከል ከአቅሙ በላይ ሲሆንበት፣ ጠጅቤት ውስጥ ላገኘው ጠጪ ሁሉ የሰሩትን በደል እየዘከዘከ “ይሄንንም እያስመዘገብኩ ነው!” ከማለት ውጪ ሌላ ምንም ማድረግ አለመቻሉን እናስተውላለን፡፡ እኔም አሁን ምንም የማድረግ አቅም የሌለውን መብራት ቦግ ድርግም የሚልበት ነዋሪ ወክዬ “እያስመዘገብኩ ነው” እያልኩ ነው፡፡ (እንጂማ ተስፋ ከቆረጥንማ ብዙ ክረምቶች ጠቡ!)

እናላችሁ --- ባለፈው ረቡዕ ከሰዓት በኋላ ላይ እንደተለመደው መብራት ተቋርጦ ነበር - ለአንድ ሰዓት ያህል፡፡ (ይሄንንም እያስመዘገብኩ ነው!) የአሁኑን ሳምንት የመብራት መቋረጥ ልዩ የሚያደርገው ምን መሰላችሁ? ከአንድ ሰዓት በኋላ ተመልሶ ሲመጣ በከፊል ነበር - በአንድ ቢሮ ውስጥ ከነበሩ ሶስት አምፑሎች አንዱ ብቻ ነበር የሚበራው። ኮምፒውተሮችም ሙሉ በሙሉ አይሰሩም - በኃይል አቅም ማነስ፡፡ (ይሄንንም እያስመዘገብኩ ነው!) የሚገርማችሁ ግን እሱም ከአንድ ሰዓት በኋላ ድርግም ብሎ ጠፋ - “ይለይላችሁ” በሚል፡፡ ከዚያ በኋላ ከአራት ሰዓት በኋላ ነው ተመልሶ የመጣው። “ይሄንንም እያስመዘገብኩ ነው” (ለታሪክ!!) እስቲ አስታውሱኝ ----የትኛው ገጣሚ ነው “አገርህ ናት በቃ” የሚል ከሃሳብ ድካም የሚገላግል ቅኔ የተቀኘው? አሁን ያማረኝ መብራት ሳይሆን እሱን ግጥም በሻማ ወይም በፋኖስ እየኮመኮሙ መቆዘም ብቻ ነው፡፡

እስቲ አሁን ደግሞ ትንሽ ፈገግ የሚያሰኝ ወግ እናውጋ፡፡ መብራት ባይኖርም እኮ ማውጋት ይቻላል፡፡ የፈገግታን ጧፍ አቀጣጥለን። ይኸውላችሁ በመዲናችን አንድ ጥግ ላይ የነዋሪዎችን ልብስ እየጠቀመ ኑሮውን የሚገፋ አንድ ብርቱ ኢትዮጵያዊ አለ፡፡ በተረት ዓለም ሳይሆን በገሃዱ ዓለም፡፡ እዚህችው አዲስ አበባችን - ሸገር እምብርት ላይ፡፡ ልብሳቸውን ለሚጠቅምላቸው ደንበኞቹ ታዲያ ቀልድ ይመርቃል አሉ - መራራ ኑሮን ማጣፈጫ ፡፡ ይሄ ልብስ ሰፊ ከመዲናዋ በርካታ ልብስ ሰፊዎች የሚለይበት ነገር አለ ከተባለ በኑሮ ፈተናና ውጣ ውረድ አለመማረሩ ነው፡፡ ይልቁንም እንደዘበት ቀልዶበት ያልፋል፡፡ ቀልዱ ታዲያ ከራሱም አልፎ በየራሳቸው የግል ህይወትና ችግር ምርር ያሉ ደንበኞቹን በሳቅ ይሸኝበታል፡፡

የዚህን ልብስ ሰፊ ታሪክ የማወጋችሁ ደንበኛው የሆነች ወዳጄ ከነገረችኝ ነው፡፡ ልብስ ሰፊው ሥራውን የሚከውንበት ዳስ ቢጤ እንኳን የለውም - ፈረንጆቹ እንደሚሉት “ኦፕን ኤር” ላይ ጭንቅላቱን ከጠራራዋ ፀሃይ በሚጠቅማቸው ልብሶች እየተከላከለ ሲጠግን፣ ሲጠቅም ይውላል።

• ሃይ ባይ ያጣውን የመብራት መቆራረጥ “እያስመዘገብኩ ነው” (ለታሪክ!!) • በአባይ ላይ የተደረገው የኢህአዴግና የተቃዋሚዎች ውይይት “የጨበራ ተዝካር” ተብሏል!

• የአገር ፍቅር መለኪያ ቴርሞሜትር የሚያስፈልግበት ዘመን ላይ ደርሰናል! (አባቶቻችን እንዳይሰሙ)

ጠ/ሚኒስትር ኃ/ማርያም ደሳለኝ “ይቅርታን የደፈሩ መሪ”!

የደንበኞቹን ልብስ - የደንበኞቹን ኑሮ፡፡ በግንቦት ወር አጋማሽ ላይ የአፍሪካ ህብረት ምስረታ የ50ኛ ዓመት የወርቅ ኢዮቤልዩ በዓል ሊከበር ጉድ ጉድ ሲባል፣ ከዚህ ቀደም አይቷቸው የማያውቅ ቁጣ ቁጣ የሚላቸው ካድሬዎች ካለበት ተነስቶ ወደ ውስጥ--- በጣም ውስጥ--- እንዲገባ በማስፈራርያ የታጀበ ትዕዛዝ አስተላልፈው ሄዱ - ምክንያቱን እንኳን ለማስረዳት ሳይጨንቃቸው፡፡ (“ሚስትህ አረገዘች ወይ ቢሉት ማንን ወንድ ብላ” አለ አሉ) መቼም ሰው አይደል --- “ምን አጥፍቼ ነው አስፈራርተውኝ የሄዱት? አብሉኝ አጠጡኝ አላልኩ?” እያለ ትንሽ መብከንከኑ አልቀረም፡፡ በኋላ ግን “ለመንግስት ስንትና ስንት ሺ ብር ግብር እንከፍላለን” እያሉ ይመፃደቁበት የነበሩ የግሮሰሪዎችና ጠጅቤቶች የበረንዳ ዳሶች ሳይቀሩ መፍረሳቸውን ሲመለከት ግን ተረጋጋ፡፡ ውስጥ በጣም ውስጥ ገብቶ አንድ ጥግ ላይ የደንብኞቹን ልብስ መጥቀሙን ቀጠለ። የአፍሪካ ህብረት ምስረታ በዓል ተከብሮ ከተጠናቀቀ በኋላ (በነገራችሁ ላይ የአፍሪካ የነፃነት አባቶች እየተባሉ የሚሞካሹት መሪዎች ጭምብል ያጠለቁ አምባገነኖች መሆናቸውን አያችሁልኝ አይደል?) ወዳጄ የምታስጠግነው ልብስ ኖሯት ወደዚህ ልብስ ሰፊ ደንበኛዋ ትሄዳለች፡፡ በሰው ሰው ተጠቁማም ውስጥ ድረስ ዘልቃ ታገኘውና ጥያቄ ታቀርብለታለች-

“አንተ ጉደኛ ፤ ደግሞ እዚህ ውስጥ ምን ከተተህ እባክህ?” ትለዋለች - መልሱን በጉጉት እየጠበቀች፡፡

ቀልደኛው ልብስ ጠቃሚም ፈገግታውን በማስቀደም፤ “እድሜ ለፀሃዩ መንግስታችን----ፀሃይ እንዳይነካህ ብሎ ወደ ውስጥ አስገባኝ--- ትንሽ ቆይቶ ደግሞ ምን አግኝተህ ነው ያማረብህ ብሎ ወደ ፀሃዩ መልሶ ያወጣኝ ይሆናል” ብሎ እንዳሳቃት አውግታኝ አስቃኛለች፡፡ ኑሮአቸውን ነጋ ጠባ እያማረሩ ከሚነጫነጩና የጨጓራቸውን እድሜ ከሚያሳጥሩ የእኔ ቢጤዎች የእዚህ ልብስ ሰፊ የኑሮ ስትራቴጂ አይመረጥም ትላላችሁ? (አረ በስንት ጣዕሙ!)

አንድ በቅርቡ የሰማሁትና ኮፒራይቱ የህዝብ የሆነ ቀልድ ደግሞ ልንገራችሁ (ጠያቂውም ተጠያቂውም ህዝብ ነው እያልኳችሁ እንደሆነ ይታወቅልኝ) ኢህአዴግ በቀድሞው ጠ/ሚኒስትር ምትክ የሾማቸው አዲሱ ጠ/ሚኒስትር፣ በአፍሪካ ህብረት 50ኛ ዓመት የወርቅ ኢዮቤልዩ በዓል ላይ የአፍሪካ መሪዎች ውስኪና ሻምፓኛቸውን ሲራጩ እሳቸው ግን በራሳቸው የግል ምክንያት ለስላሳ ያዛሉ፡፡ ያዘዙት መጥቶላቸው ሲጠጡ የተመለከተ አንድ ከፍተኛ የኢህአዴግ አመራር ደንግጦ ወደ ጠ/ሚኒስትሩ ጠጋ ይልና “ክቡር ጠ/ሚኒስትር፤ የቀድሞው ጠ/ሚኒስትራችን እኮ ወይን ነበር የሚጠጡት” ይላቸዋል፡፡ ጠ/ሚኒስትሩ ድንግጥ ብለው “በል ይሄን ውሰድና ወይኑን አስመጣልኝ” ይላሉ - ለስላሳውን በመመለስ፡፡ ወይኑ እንደመጣላቸውም እየመረራቸውም ቢሆን መጎንጨት ይጀምራሉ፡፡ ቀደም ሲል ለስላሳ ይዘው እንደነበረ ያስተዋለ አንድ የአፍሪካ አገር መሪ “ክቡር ጠ/ሚኒስትር ምን ያዙ?” ሲል ይጠይቃቸዋል - ከለስላሳ ወደ ወይን የመሻገራቸውን ሰበብ ለማወቅ በውስጡ ጉጉት ተፈጥሮበት፡፡ ጠ/ሚኒስትሩም በብርሃን ፍጥነት “መለስ የጀመረውን---” ሲሉ ይመልሱለታል፡፡ (የቀልዱ ኮፒራይት የህዝብ መሆኑ እንዳይረሳ በድጋሚ አሳስባለሁ!)

ከጀመርኩ አይቀር ሌላ የህዝብ ቀልድ ልጨምራ - አሁንም በኢህአዴግ ዙሪያ ነው ቀልዱ (የህዝብ ፓርቲ ስለሆነ በህዝብ ቀልድ አይቀየምም ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ!) በዘንድሮው የ“ቢግ ብራዘር አፍሪካ” ውድድር ላይ ተሳትፋ “ጉድ ሰራችን” የተባለችው ወጣት ኢትዮጵያዊት “የወሲብ ቅሌት” በፌስቡክ ዋና የአገር አጀንዳ (እናት አገሯን አስደፍራለች እስከመባል መደረሱን ያስታውሷል) የሆነ ሰሞን፣ በመንግስት ደረጃም ለውይይት ቀርቦ ነበር ይላሉ - የቀልዱ ምንጮች፡፡ (ኮፒራይቱ የህዝቡ ነው ማለቴ

ይሰመርበት) እናም የአገሪቱ ከፍተኛው የመንግስት ባለሥልጣን የሆኑት ጠ/ሚኒስትሩ አንጋፋ የኢህአዴግ መሥራችና ሚኒስትር የሆኑ የሥራ ባልደረባቸውን እንዲህ ሲሉ ይጠይቃሉ -

“እኔ የምለው የዚች ልጅ ጉዳይ --- የአገርን ገፅታ አያበላሽም እንዴ?”

ሚኒስትሩም “ህግመንግስቱን የሚንድ ተግባር እስካልፈፀመች ድረስ የሚያሳስብ ነገር የለውም” በማለት እንዳረጋጓቸው የቀልዱ ምንጮች ያወሳሉ፡፡

ይሄ እንግዲህ ቀልዱ ነው፡፡ ወደ እውነቱ ስንመጣ ግን በ“ቢግ ብራዘር አፍሪካ” ላይ የተሳተፈችውና የወሲብ ቅሌት ፈፅማለች የተባለችው ወጣትና ድርጊቱን በቲቪ የቀጥታ ስርጭት አስተላልፏል የተባለው ጣቢያን ፍርድቤት እንገትራቸዋለን የሚል በወኔ የታጀበ መረጃ ሰምቻለሁ፡፡ እንደሚመስለኝ ምክንያቱ ደግሞ የአገርን ገፅታ ማበላሸታቸው ነው። ለእኔ ግን ከዚህ ይልቅ የአገርን ገፅታ የሚያበላሸው ከኋላቀር የፖለቲካ ባህላችን ጋር ተያይዞ በሚከሰተው የሥልጣን ሽኩቻ ሳቢያ የሚደርሰው የነፃነት አፈናና የሰብዓዊ መብት ጥሰት ይመስለኛል (ተረት ለማድረግ የዛትንበት ድህነታችንም ሳይረሳ!) እናም ጉልበታችንን፣ አቅማችንና ገንዘባችንን በተጨባጭ ለሚጠቅመን ጉዳይ ብናውለው ይሻላል ባይ ነኝ (ለምሳሌ የነፃነትና የሰብዓዊ መብትን ፋይዳ በሚያስገነዝብ ትምህርትና ስልጠና ላይ!)

እኔ የምላችሁ ---- ሰሞኑን ኢህአዴግና

ተቃዋሚዎች በአባይ ወንዝ ዙሪያ ያደረጉትን ውይይት (የፖለቲካ ተንታኞች ግን የጨበራ ተዝካር ብለውታል) ተከታትላችሁልኛል ? እኔ ግን ከሁሉም በፊት አንድ ጥያቄ መሰንዘር እፈልጋለሁ፡፡ “አገር ወዳዱን” እና “ከሃዲውን” ፓርቲ መለየት የሚቻልበት መንገድ የተቀመጠበት መፅሃፍ አለ እንዴ? መቼም ኢህአዴግም ሆነ ተቃዋሚዎች በሚያውቁት የጋራ ህገመንግስታችን ላይ ይሄ ነገር እንዳልሰፈረ “መከራከር” እንችላለን፡፡ (የኢህአዴግ ተወካዩ “በአባይ ጉዳይ ላይ ኮንሰንሰስ ስለመኖሩ መከራከር እንችላለን” እንዳሉት!) መቼም ይሄንን ማለት በምንም መመዘኛ “ከሃዲ” እንደማያስብል እርግጠኛ ነኝ፡፡ በዚህ አጋጣሚ ከማንኛውም በሥልጣን ላይ ያለም ሆነ ከሥልጣን ውጭ የሆነ ፖለቲከኛ ያነሰ የአገር ፍቅር እንደሌለኝ ልገልፅ እወዳለሁ፡፡ በነገራችን ላይ የአገር ፍቅር መለኪያ ቴርሞሜትር የሚያስፈልግበት ዘመን ላይ መድረሳችንን ልገልፅ እወዳለሁ! (የጥንት አባቶቻችን ይሄን ቢሰሙ ከልባቸው ማዘናቸው አይቀርም! )

ከምሬ እኮ ነው --- በኢህአዴግና በተቃዋሚዎች መካከል በአባይ ጉዳይ ላይ ብሄራዊ መግባባት (ኮንሰንሰስ) ያመጣል ተብሎ የተገመተው የኢቴቪ ውይይት፤ በሚያሳዝን የእርስ በእርስ “ፍረጃ” ተጠናቀቀም አይደል፡፡ ደግነቱ ግብፆቹ በራሳቸው ጉዳይ ተጠምደዋል እንጂ እንዴት ይታዘቡን እንደነበር አልነግራችሁም! እንደውም

ማስታወቂያ

Page 11: Issue-703.pdf

Website: www.addisadmassnews.com

አዲስ አድማስ ሰኔ 29 ቀን 2005 ዓ.ም ገፅ 11 ማስታወቂያ

Page 12: Issue-703.pdf

Website: www.addisadmassnews.com

አዲስ አድማስ ሰኔ 29 ቀን 2005 ዓ.ም ገፅ 12 እንባ ከገፅ 9 የዞረ

ይቅርታ ከገፅ 10 የዞረ

ግን የሚያለቅሰው፤ ሀዘኔታን የሚሰጠው ሰው ካለ ነው፡፡ እናቱ ወይንም ሌላ “አይዞህ ባይ” በአቅራቢያ ከሌለ ሀዘኔታ መሻቱ ስለማያዋጣው… ሌላ የሚያዋጣ አማራጭ ይፈልጋል፡፡ ግራ መጋባት ፊቱ ላይ ከድንጋጤው በኋላ የሚከተል ይሆናል፡፡ ግራ ከመጋባት ሲያገግም፤ ከት ከት ብሎ ይስቃል፡፡

የእናቱ ማባበል… ወይንም የአይዞህ ባይ ሆይ ሆይታ ካየለ ግን በተቃራኒው ሀዘኔታን መሻቱ ወይንም ፍቅር ይገባኛል ባይነቱ ይባባሳል፡፡ ለቅሶው በቀላሉ ላይቆም ይችላል፡፡ ብቻውን ያለ “እኔ ልውደቅ” ባይ እንቅፋቱ ሲጥለው፤ ለፍርሐቱ እና በወቅቱ ለተሰማው ስሜት ምክንያታዊ አማራጭ በደመነፍሱም ቢሆን ይፈጥራል፡፡

ወደፊት ሲያድግ፣ ሀዘኔታ ፈላጊ አዝማሚያውን በአጭሩ የቀጨ፣ ቆፍጣና ሰው ሊሆን ይችላል፡፡ ለፍርሃቱ በሙሉ “ለቅሶ እና ማባበያ” የማይፈልግ መሆኑ ጥሩ ቢሆንም፤ በአግባቡ ሰአት እና ሁኔታ አለማልቀስ ግን በስሜት ተሸካሚው ላይ ከፍተኛ

ጉዳትን ያመጣል፡፡የተወጠሩ፣ የደነገጡ፣ በስቃይ የደከሙ ስሜቶች

እና የጡንቻ አውታርን… በለቅሶ እንዲያርፉ ካልተደረጉ ባለስሜቱ ጉዳት ይጠበቅዋል፡፡

ምናልባት የሞተባቸው ሰውን ተከትለው የሚሞቱ ሀዘንተኞች…የሞታቸው ምክንያት ቅስማቸው መሰበሩ ሳይሆን፤ የተሰበረውን ቅስም በማሳረፉ በለቅሶ አማካኝነት… ሃዘናቸውን ከራሳቸው አቅም ውጭ ለሆነው ሙሉኤ ኩሉው ህግ (Cosmic justice) በእንባ መልክ አሳልፈው መስጠት ባለመቻላቸው መሆኑ ይታመናል፡፡ ህይወት ላይ ራሳችንን ለማጠንከር፣ ጫና ለመፍጠር ለማስከበር… የምናለቅሰው ለቅሶ crying ሲሆን … ይህ ከራስ አቅም ውጭ ለሆነ የበላይ፣ ልዕለ አንድነት ሀዘናችንን አሳልፈን ስንሰጥ የሚወጣን እንባ ግን “Weeping” (በአማርኛ ትርጉሙን አላቀውም) ተብሎ ይጠራል፡፡

ባለቅኔው ቴኒስን፣ የጀግናው አስከሬን ከጦር ሜዳ (?) ሲመጣ በሀዘንዋ መብዛት ሳቢያ ማልቀስ ስላልቻለችው (በግጥሙ ለሟቹ ያላት ቅርበት ግልጽ

ባይደረግም) ሚስት እንደሚከተለው ይቀኛል? Home they brought the warrior dead she

nor swooned nor uttered cry/ All her maidens, watching said/ “She must weep or she will die.” ለቅሶ ቤት ውስጥ ከገጠሙኝ ለቀስተኞች (በበለጠ

የተጐዳው ማን እንደሆነ ማወቅ እፈልጋለሁ፡፡ የበለጠ የተጐዳው ያልተቀበለው ነው፤ የሟቹን

ሞት ያልተቀበለው፡፡ ወደ መፍጨርጨር ወደ ደረት መምታት፤ ወደ “ጉርጓድ ተከትዬ ልግባ” የሚያደላው እሱ ወደ “መቀበል” ደረጃ ያልደረሰ ነው ብዬ ከእንግዲህ የምመዝን ይመስለኛል፡፡

እንባ ከሳቅም ጋር ዝምድና እንዳለው ሁሉ ከምክንያት አልባው ደመነፍስም ጋር ይዛመዳል፡፡ በሪፍሌክስ አክሽን (reflex action) ጠለቅ ያላለ የስሜት ፍቺ ከማይፈልጉ የነርቭ መዋቅሮችም ጋር የእንባ ስሜት ይጣመራል፡፡

ለምሳሌ አፍንጫ ሲመታ አይን ያለቅሳል ማለት…

ባል ሲሞት ሚስት ታለቅሳለች እንደማለት ያህል ጠለቅ ያለ ውስጣዊ የስሜት ጉዳት ደረጃን ወይንም የአእምሮ የፍቺ ተሳትፎን አይጠይቅም፡፡ ባል ሲሞት ሚስት የምታለቅሰው…ከፍ ያሉ መረዳቶችን በስሜት አማካኝነት…ከድንጋጤ እስከ መቀበል በተለያየ ደረጃ አስተናግዳ ሲሆን፤ “አፍንጫ ተመትቶ አይን የሚያለቅሰው” ግን ስሜትም ሆነ ምክንያታዊነት የሌለው ደመ ነብስ በመሆኑ ነው፡፡

ሁሉም የተፈጥሮ ፍጡር እጣፈንታ ከውልደት እስከ ሞት የሚያስተሳስረው እንቆቅልሽ በሞት ቋጠሮ ሲጠናቀቅ ለሚመለከት ሁሉ የስሜቱን ውጥረት በእረፍት ለማደስ፣ ለመቀበል…ተቀብሎም ለመቀጠል፤ ለቅሶ ብቸኛ አማራጩ ነው፡፡

እንደኔ እይታ ሞትን በጭፈራ፣ በፉከራ እና በዘፈን የሚሸኙ ማህበረሰቦች መቀበል ደረጃ ላይ የደረሱ አይመስለኝም፡፡ ገና ፍርሐት ላይ ናቸው፡፡ እንደኔ እይታ ሞት የሚሞተው በሀዘን ነው፤ ሀዘን ደግሞ የሚሞተው በመቀበል ብቻ ነው፡፡ በለቅሶ፡፡

ኢትዮጵያውያን በግድቡ ጉዳይ አንድ አቋም የላቸውም የሚል አቋም የሚይዙት የኢቴቪን ውይይት ካዩ በኋላ ነበር የሚሆነው፡፡ እንዴ --- የኢህአዴጉ ተወካይ እኮ እስካሁን ኢህአዴግ ሲል የቆየውን ነው ያፈራረሱት። ሌላው ቀርቶ ጠ/ሚኒስትሩ በቅርቡ ለጋዜጠኞች ጥያቄ በሰጡት ምላሽ “አባይን በተመለከተ በህዝቡ ዘንድ ብሄራዊ መግባባት አለ--- ተቃዋሚዎችን ጨምሮ” ማለታቸው የሚታወቅ ነው፡፡ ለነገሩ እኮ ራሳቸው በውይይቱ የተሳተፉት የኢህአዴግ ተወካይም መጀመርያ ላይ “ከታላቁ ህዳሴ ግድብ በፊት አገራዊ መግባባት ያስፈልጋል” በማለት የተሟገቱትን ተቃዋሚዎች ለመርታት “በአባይ ጉዳይ ኮንሰንሰስ የለም የሚል ካለ መከራከር እንችላለን” ሲሉ ሰምተናቸዋል፡፡ ትንሽ ቆይተው ግን (ወደ ውይይቱ መጠናቀቂያ ላይ ይመስለኛል) ራሳቸው “ኮንሰንሰስ” እንደሌለ አሳይተውን ቁጭ አሉ - መድረክና አንድነት የተባሉት ተቃዋሚ ፓርቲዎች በአባይ ጉዳይ ላይ በክህደት የሚያስጠረጥር መግለጫ ሲያወጡ መቆየታቸውን በመዘርዘር፡፡ (በነገራችሁ

ላይ ጋዜጠኛው በውይይቱ ላይ የነበረውን ሚና ለተመልካችና ለታሪክ ትቼዋለሁ!) እኔ የምለው ግን ---- የኢህአዴግ የፓርቲ ባህል ተቀይሯል እንዴ? (ግራ ገባን እኮ!) እንግዲህ ጠ/ሚኒስትሩን ጨምሮ ከሁነኛ የፓርቲው ሰዎች በአደባባይ ስለኢትዮጵያ ተቃዋሚዎች የሰማነው በውይይቱ ላይ የተሳተፉት ተወካይ ከተናገሩት ፍፁም የተለየ ነገር ነው (ኢህአዴግ ሳይነግረን አቋሙን ለውጦ ይሆን እንዴ?) ወይስ ተወካዩ በውይይቱ ላይ ሳያውቁት በስሜት ተወስደው የራሳቸውን አቋም ይሆን ያስተጋቡት? (አንዳንዴ ፖለቲካ እኮ አቅል ያስታል!) እርግጠኛ ነኝ ተወካዩ በስሜት ተወስደው ከሆነ ያንን ሁሉ የተናገሩት ገና ሳይጠይቁን እኛ ራሳችን ይቅርታ እናደርግላቸዋለን (“ከሰው ስህተት ከብረት ዝገት አይጠፋም ” የሚለውን ጥንታዊ ብሂል በመጥቀስ ) እንዲያም ሆኖ ግን እሳቸውም ይቅርታ መጠየቃቸው አይቀርም - እኛን ሳይሆን አውራ ፓርቲያችንን ኢህአዴግን! (እኛ ማለት ኢህአዴግ ፤ ኢህአዴግ ማለት ደግሞ እኛ መሆናችንን ልብ ይሏል!) በዚህ አጋጣሚ በዚያው ተመሳሳይ ውይይት ላይ

ኢህአዴግ (መንግስት) የግብፆችን ድንፋታ ተከትሎ “ህዝቡን ለአገርህ ዘብ ቁም!” በሚል ለጦርነት ቀስቅሷል ሲሉ የተናገሩት የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ፣ ነገሩን ከየት እንዳመጡት አናውቅምና እሳቸውም ተረጋግተው ካሰቡ በኋላ ኢህአዴግንና ህዝቡን ይቅርታ መጠየቅ እንደሚገባቸው የሚያጠራጥር ነገር ያለ አይመስለኝም (የጦርነት አዋጁን የሰሙት በህልማቸው ከሆነ ግን ሳንከራከር እንቀበላቸዋለን!) በነገራችን ላይ --- ለእውነት ዋጋ መስጠትን እንዲህ ቀስ በቀስ ብንለማመድ ሸጋ ይመስለኛል (ከእውነት ጋር ለመታረቅ እኮ ከአንድ ትውልድ በላይ ፈጅቶብናል!)

በቅርቡ ጠ/ሚኒስትሩ ከአክስዮን ማህበራት የዲቪደንድ ጉዳይ ጋር ተያይዞ ለተሰራው ጥፋት ነጋዴዎችን ይቅርታ ትጠይቃላችሁ ወይ በሚል ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄ የሰጡትን ምላሽ ሰምታችኋል ብዬ አምናለሁ (ካልሰማችሁት ግን አምልጧችኋል!) መጀመርያ ጉዳዩ መጣራት አለበት ያሉት ጠ/ሚኒስትሩ፤ “ተጣርቶ ጥፋተኛ ከሆንን ግን ይቅርታ የማንጠይቅበት ምክንያት የለም” ነው

ያሉት፡፡ በዚህም “ይቅርታን የደፈሩ መሪ” የሚል ክብርና ሞገስ ተቀዳጅተዋል ሲባል ሰምቼአለሁ። የቀድሞው ጠ/ሚኒስትር “አባይን የደፈሩ መሪ” እንደተባሉት ማለት ነው፡፡ (የጦቢያን ሥር የሰደደ የይሉኝታ ባህል አሽቀንጥረው በመጣልና ያመኑበትን በመናገር አዲስ የድፍረት አብዮት የለኮሱት አንጋፋው የኢህአዴግ ታጋይ አቦይ ስብሃት ግን በዚህ አይስማሙም፡፡ እንዴት ቢሉ ---- “አባይን የደፈረው የኢትዮጵያ ህዝብ እንጂ ኢህአዴግም ሆነ ጠ/ሚኒስትሩ አይደሉም” ባይ ናቸው) እናላችሁ ወዳጆቼ ---- በዚህች ይቅርታ መጠየቅ አቀበት የመውጣት ያህል ፈተና በሆነባት ጦቢያችን፤ የተከበሩ አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ “ተጣርቶ ስህተት ከሆነ ይቅርታ እንጠይቃለን” ብለው በአደባባይ መተንፈሳቸው የሽንፈት ምልክት ሳይሆን የበሳልና ስልጡን ፖለቲከኛ ምልክት መሆኑን ልብ ማለት የአባት ነው፡፡ ይሄ አጋጣሚ የብዙዎቹ ፖለቲከኞች ዓይነጥላ መግፈፊያ ይሆንልን ዘንድም ከልባችን እንፀልይ! (የአሜሪካ ፖለቲከኞች ለትንሽ የምላስ ማዳለጥ ሳይቀር ይቅርታ እንደሚጠይቁ ልብ ይሏል!)

ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያዎች ማኅበር የ2005 ዓ.ም በጀት ዓመት ሂሳቡን ለማስመርመር ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ የኦዲት ድርጅቶች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን፣

መሟላት ያለባቸው መስፈርቶች፡-• በሙያ ብቃትና በሕጋዊነት ታውቀው በመንግሥት

የተመዘገቡ፣• የዘመኑን ግብር ከፍለው በ2005 በጀት ፍቃዳቸውን

ያሳደሱና የኦዲቲንግ የሥራ ልምድ ያላቸው፣ የታክስ መለያ ቁጥር ያላቸው መሆን አለባቸው፡፡

ተወዳዳሪዎች ለአገልግሎት የሚያስከፍሉትን ዋጋና ሥራውን ሠርተው የሚያስረክቡበትን ጊዜ በመጥቀስ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ቀናት ውስጥ ከዚህ በታች በተጠቀሰው አድራሻ ማስረጃዎቻቸውን አያይዘው በሥራ ሰዓት በማኅበሩ ጽ/ቤት እንዲያመለክቱ እናሳውቃለን፡፡

የኦዲት ሥራ ማስታወቂያ

ስልክ ቁጥር፡- 0115-53-01-22/ 0913-22-17-82፣ E-mail:- [email protected]

ከፖስታ ቤት አጠገብ ኪዳኔ በየነ ሕንፃ 1ኛ ፎቅ

Page 13: Issue-703.pdf

Website: www.addisadmassnews.com

አዲስ አድማስ ሰኔ 29 ቀን 2005 ዓ.ም ገፅ 13

750 አልጋዎች ይኖሩታል ተብሏል

ª“¨< Ö?“

መታሰቢያ ካሣዬ

የአፍሪካ ህብረትን ጨምሮ የበርካታ ታላላቅ አለም አቀፋዊ ድርጅቶች መናኸሪያ ነች፡፡ ከተማችን አዲስ አበባ በከፍተኛ ፍጥነት እያደገች መሄዷ ቢነገርላትም በፅዳትና

በንፅህናዋ ረገድ ያለችበት ሁኔታ እጅግ አሳሳቢ ነው፡፡ ዋና ዋና የከተማይቱ ጎዳናዎችና ትላልቅ አደባባዮች ሳይቀሩ የቆሻሻ ማጠራቀሚያና ዋጋ የማይከፈልባቸው መፀዳጃ ቦታዎች በመሆን እያገለገሉ ይገኛሉ፡፡ እዚህም እዚያም እየተንጠባጠቡ የሚታዩትን እዳሪዎችን ላለመርገጥ እየዘለሉ መራመድ በብዙ የከተማዋ አካባቢዎች የተለመደ ተግባራት ናቸው፡፡ ከሶስት ሚሊዮን በላይ ህዝብ እንደሚኖርባት በሚነገርላት በዚህችው ከተማ ውስጥ የሚገኙ የህዝብ መፀዳጃ ቤቶች አንድና ሁለት ተብለው የሚቆጠሩ ናቸው፡፡

እነዚህም ቢሆኑ በማህበር ተደራጁ ለተባሉ ቡድኖች ተሰጥተው ለተጠቃሚው አገልግሎት የሚሰጡት ገንዘብ እየተከፈለባቸው ሆኗል፡፡ ለመፀዳጃ ቤት አገልግሎቱ ገንዘብ የመክፈል አቅም የሌላቸው የጎዳና ተዳዳሪዎች፤የኔ ቢጤዎችና ከተማዋን በአግባቡ የማያውቁ እንግዳ መንገደኞች የተፈጥሮ ጥሪን የመመለስ ግዴታ አለባቸውና እዳሪያቸውን በመንገዱና በየአደባባዩ ለመውጣት ይገደዳሉ፡፡ ይህ ሁኔታ በከተማዋ እጅግ የተለመደና እንደ ባህል ሆኖ የኖረው ጉዳይ ነው፡፡

“ሐበሻ መንገድ ላይ ሲበላ እንጂ ሲፀዳዳ አያፍርም” እየተባለ ሲተረትበትም ኖሯል፡፡ በአፄ ሚኒሊክ ዘመነ መንግስት፣ ንጉሱ ህዝቡ ሜዳ ላይ ከመፀዳዳት እንዲቆጠብ የሚያሳስብ አዋጅ አስነግረው የመፀዳጃ ቤትን ጠቀሜታ ለህዝባቸው ለማስተማር ጥረት አድርገው ነበር፡፡ ይህ ሁኔታ በአፄ ኃይለስላሴም ሆነ በደርግ ዘመነ መንግስታት ሲከናወን የቆየ ተግባር ነው፡፡ የህዝብ የመፀዳጃ ቤቶች በከተማው ዋና ዋና ስፍራዎች ላይ እንዲገነቡ ተደርገው ለአገልግሎት ክፍት በማድረግ ህብረተሰቡ ከመፀዳጃ ቤት ውጪ መጠቀምን እንዲፀየፍ ለማድረግ ሙከራዎች ተደርገዋል፡፡

የከተማዋ ነዋሪ ህዝብ ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ በመምጣቱና የህዝቡም የአኗኗር ሁኔታ የተጨናነቀና የተፋፈገ እየሆነ ከመምጣቱ ጎን ለጎን፣ የመፀዳጃ ቤት እጥረቱ እየተስፋፋ በመሄዱ ጎዳናዎችና አደባባዮች ሁሉ አገልግሎቱን ለመስጠት ተገደዱ፡፡ ዛሬ አዲስ አበባ ጎዳናዎቿ፣አደባባዮቿ የገበያና የመዝናኛ ስፍራዎቿና የእምነት ተቋሞቿ ሳይቀሩ ለአይን የሚያስፀይፍ እና መጥፎ ሽታ ያላቸው እዳሪዎች መጠራቀሚያ ሆነዋል፡፡ በከተማዋ በየትኛውም አካባቢ የሚገኙ ጥጋጥጎች፣የሆቴልና የቡና ቤት ደጃፎችና መካነ መቃብሮች የመፀዳጃ ስፍራዎች ሆነዋል፡፡ ይህንን ሁኔታ የሚቃረን ተግባር ከሚከናወንባቸው የደቡብ ክልል ወረዳዎች በአንደኛው ተገኝቼ፣ ህብረተሰቡን ሜዳ ላይ ከመፀዳዳት ነፃ የወጣበትን ቀን ሲያከብር አብሬ ታድሜ ነበር፡፡ ስፍራው በደቡብ ክልል ሸበዲኖ ወረዳ ውስጥ ነው፡፡ በወረዳው ውስጥ ከሚገኙ ቀበሌዎች መካከል ፋራ የተባለው ቀበሌ ሜዳ ላይ ከመፀዳዳት ነፃ የወጣው የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ ወረዳ ሆኗል፡፡

በ1999 ዓ.ም በዚህ ቀበሌ የተጀመረውን ሜዳ ላይ መፀዳዳትን የሚያስቀር ዘመቻ ብዙዎቹ የአካባቢው ቀበሌዎችና ወረዳዎች ተከትለውታል፡፡ ዘመቻውን በድል ያጠናቀቁ በርካታ በወረዳው ውስጥ የሚገኙ ቀበሌዎች፣ ራሳቸውን ሜዳ ላይ ከመፀዳዳት ነፃ አውጥተው የነፃነታቸው ምልክት የሆነውን ነጭ ባንዲራ በግዛታቸው እንዲውለበለብ አድርገዋል፡፡ የሸበዲኖ ወረዳ ጤና ቢሮ ኃላፊ የሆኑት አቶ ቡረሳ ብላሾ እንደገለፁልን፤ በአካባቢው ሜዳ ላይ መፀዳዳት እንደ ትልቅ ነውር የሚታይና በህብረተሰብ ዘንድ ያለውን ተቀባይነት የሚያሳጣ ተግባር ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪም አካባቢው ሜዳ ላይ ከመፀዳዳት ነፃ መሆኑ እንደየደረጃው በሚሰጠው ቢጫ፣ አረንጓዴና ነጭ ባንዲራዎች

ታላቋ የአፍሪካ መዲና ከትንሿ ሸበዲኖ ምን ትማር?

ስለሚገልፅ ህብረተሰቡ ራሱ ደረጃው ከጎረቤት ቀበሌዎች ያነሰ እንዳይሆንና ውርደት እንዳያገኘው በማሰብ ከፍተኛ ጥረት ያደርጋል፡፡ በዚህ ዘመቻ ውስጥ ለማይሳተፍ ቀበሌ የሚሰጠውን ቀይ ባንዲራ ላለማግኘት ሁሉም በዘመቻው ውስጥ ይሳተፋል፡፡

በወረዳው ባለፈው ሰኔ 18 ቀን 2005 ዓ.ም በተካሄደው “ከመፀዳጃ ቤት ውጪ ከመፀዳዳት ነፃ የመውጣት ቀን” (open deification free day) (ODF) በዓል አከባበር ስነስርዓት ላይ የወረዳው የጤና ቢሮ ኃላፊዎችና በዘመቻው ላይ ተሳታፊ የነበሩ ወገኖች የነፃነት አረንጓዴ ባንዲራቸውን ተቀብለዋል፡፡ በቀጣይነት ሊሻሻሉ የሚገባቸውን ነገሮች በማስተካከልም ነጩን ባንዲራ (ሙሉ በሙሉ ነፃ የመውጣት ምልክት) የሆነውን ባንዲራ ለመቀበል እንደሚሰሩም በዚሁ ጊዜ ተናግረዋል። ለዚህ ዘመቻ መሳካት “ፕላን ኢንተርናሽናል” የተባለው መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት እያበረከተ ያለው አስተዋፅኦ በቀላሉ የሚገመት አለመሆኑንም በዚህ ወቅት ተነግሯል፡፡

በአዲስ አበባ በ348 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በደቡብ ክልል ውስጥ በምትገኘው በዚህች ወረዳ ውስጥ ተገኝቼ ይህንን እንደ አዲስ አበባ ላሉ ታላላቅ ከተሞች እንኳን አርዓያ ሊሆን የሚችል ተግባር ለመመልከት እና የበዓሉ ታዳሚ ለመሆን የቻልኩት “Because I am a girl” (ሴት በመሆኔ እንደማለት) በሚል ዘመቻ ሴቶችን በትምህርት፣ በጤና፣ በኢኮኖሚና በማህበራዊ ጉዳዮች የማብቃት ተግባር ላይ ተሰማርቶ በሚገኘውና “ፕላን ኢንተርናሽናል” በተባለ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት አማካኝነት ነው፡፡ ድርጅቱ በተለያዩ የአገሪቱ ክልሎች በተለይም በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል ውስጥ በሚገኙ የተለያዩ ወረዳዎችና ቀበሌዎች ውስጥ አመቺ የትራንስፖርት አቅርቦት በሌለባቸው ቦታዎች እየሄደ የሚያከናውናቸውን የልማት ተግባራትና እነዚህ ሥራዎች ለህብረተሰቡ እየሰጡ ያለውን ጠቀሜታ መመልከቱ የጉዞዬ ዋንኛ አላማ ነበር፡፡

ድርጅቱ በሸበዲኖ ወረዳ ለኩ ከተማ ውስጥ ያስገነባው የወጣቶች መዝናኛ ማዕከል ደረጃውን የጠበቀ ሆኖ ወጣቶች በትምህርት፣ በስፖርትና በጤና ራሳቸውን እያነፁ ለማሳደግ የሚረዳቸው እንዲሆን ታስቦ መገንባቱን የማዕከሉ አስተዳዳሪ አቶ ተስፋዬ ዳባሶ ገልፀውልናል፡፡

ማዕከሉ ወጣቶች የኮምፒዩተር፣ የምግብና የፀጉር ሥራ ስልጠና እንዲያገኙ በማድረግ ራሳቸውን ለማስቻልም ከፍተኛ ጠቀሜታ እየሰጣቸው እንደሆነ የአካባቢው ነዋሪ ወጣቶች ይናገራሉ፡፡ ቀደም ባሉት አመታት አካባቢው በድርቅ የሚጠቃ በመሆኑ እንዲህ ዓይነት ተፈጥሮአዊ ችግሮች በሚከሰቱበት ወቅት፣ ህብረተሰቡ በምግብ እጥረት እንዳይጐዳ ለማድረግ እንዲያስችልም የእህል መጋዘን በመሥራት ለወረዳው አስተዳደር አስረክቧል፡፡ መጋዘኑ በአሁኑ ወቅት የማዳበሪያና የምርጥ ዘር ማከማቻ በመሆን ወረዳውን እያገለገለ ይገኛል፡፡

የምንጭ ውሃን በሶላር ኢነርጂ በሚሰራ የውሃ መሳቢያ በመሳብ፣ ንፁህ የመጠጥ ውሃ ለህብረተሰቡ ማዳረስ ከድርጅቱ ሥራዎች መካከል የሚጠቀስ ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የሶላር ኢነርጂውን ወደ

ኤሌክትሪክ ኃይል በመቀየር ለትምህርት ቤቶች፣ ለጤና ኬላዎችና ጤና ጣቢያዎች አገልግሎት እንዲሰጥ የማድረጉ ተግባር በድርጅቱ ከተከናወኑ ሥራዎች ውስጥ የሚገኙ ሲሆን፤ ለትራንስፖርት እጅግ አስቸጋሪ በሆኑ አካባቢዎች ላይ በድርጅቱ የገነቡት ሁለት ትምህርት ቤቶች በጋዜጠኞች ቡድኑ ከተጐበኙት ሥፍራዎች መካከል የሚጠቀሱ ናቸው። የሀርቤሻሾ እና የጐናዎ ጐዳ ት/ቤቶች በፕላን ኢንተርናሽናል ተገንብተው የተለያዩ የመሳሪያና የቁሳቁስ ድጋፍ የተደረገላቸው የሸበዲኖ ወረዳ ውስጥ የሚገኙ ት/ቤቶች ናቸው፡፡ ድርጅቱ በክልሉ ወረዳዎች ላይ እየተንቀሳቀሰ የሚያከናውናቸውን የተለያዩ የልማት ተግባራት በመደገፍና እንደመንገድ ያሉ አጋዥ የልማት ተግባራትን በማከናወን ረገድ የክልሉ መንግስት እያደረገ ያለው እንቅስቃሴ እምብዛም አጥጋቢ አለመሆኑን ታዝበናል፡፡ ስለጉዳዪ የጠየቅናቸው የሽበዲኖ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታረቀኝ ጋቤራ፤ ድርጅቱ በአካባቢው እያከናወነ የሚገኘውን የልማት ስራ ለማገዝና ለመደገፍ ጥረት እያደረጉ መሆናቸውን ጠቁመው ለስራው እንቅፋት ከሚሆኑ ጉዳዩች መካከል ዋነኛው የሆነውን የመንገድ ስራ ግንባታ በቅርቡ እንደሚጀምሩ ገልፀውልናል፡፡

ምንም መሰረተ ልማቶች ባልተሟሉበት ሁኔታ በወረዳው ገጠራማ አካባቢዎች በድርጅቱ የተገነቡት ተቋማት የአካባቢውን ነዋሪ ህዝቡ ኑሮ ለማሻሻልና በተለይም ሴት ህፃናትን ለማስተማር እንዲሁም ያለዕድሜ ከመዳር ለመታደግ እያበረከቱት ያለው አስተዋፅኦ በቀላሉ የሚገመት አይደለም። ድርጅቱ በወረዳው ከ230 ሚሊዮን ብር በላይ ኢንቨስት አድርጎ ከሚያከናውንባቸው የልማት ስራዎች መካከል

በአንድ ቢሊዮን ብር ወጪ በደሴ ከተማ ውስጥ ይገነባል ለተባለው የወሎ ተርሸሪ ኬርና ቲቺንግ ሆስፒታል ግንባታ የሚውል ገቢ የማሰባሰብ ሥራ

በይፋ ተጀመረ፡፡ ለሆስፒታሉ ማሰሪያ የሚሆን ገቢ የማሰባሰቡ ሥራ ባለፈው ረቡዕ በሸራተን አዲስ በይፋ በተከፈተበት ወቅት እንደተገለፀው፤ ሆስፒታሉ በብሔራዊ ደረጃ ከፍተኛ የህክምና ተቋም እንዲሆን ከማድረጉ በተጨማሪ የስልጠናና የምርምር ማዕከል ይሆናል፡፡

ከ750 በላይ አልጋዎች ይኖሩታል ለተባለው ለዚህ ሆስፒታል ግንባታ፤ የወሎ ተወላጆች የሆኑ ባለሀብቶችና በውጭ አገር የሚኖሩ የአካባቢው ተወላጆች ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደርጋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም በዚሁ ወቅት ተገልጿል፡፡

የኢፌዲሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የትምህርት ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንንን ጨምሮ የክልሉ ተወላጆች የሆኑ ታላላቅ የመንግስት ባለስልጣናት በተገኙበት በሸራተን አዲስ በተካሄደው ፕሮግራም ላይ እንደተገለፀው፤ በመጪው ዓመት የሆስፒታሉ ግንባታ የገቢ ማሰባሰቢያ ዓመት እንዲሆን እቅድ ተይዟል፡፡ የደሴ ከተማ አስተዳደር ጢጣ በተባለው ሥፍራ ለሆስፒታሉ ግንባታ የሚውል 40 ሄክታር መሬት የሰጠ ሲሆን የሆስፒታሉ የመሰረት ድንጋይም ህዳር 16 ቀን 2004 ዓ.ም የኢፌዲሪ ምክትል ጠቅላይ ሚ/ር እና የትምህርት ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን፣ የአማራ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ አያሌው ጐበዜና የፕሮጀክቱ የበላይ ጠባቂ ሼክ አሊ መሐመድ ሁሴን አልአሙዲ በተገኙበት መቀመጡ የሚታወስ ነው፡፡

ወሎ ውስጥ በ1ቢ ብር ወጪ

ሆስፒታል ሊገነባ ነው

በጤናው ዘርፍ የተከናወኑትን ተግባራት በስፋት የማየት አጋጣሚውን አግኝተን ነበር። በወረዳው የተለያዩ አካባቢዎች ከተገነቡት ስምንት ጤና ጣቢያዎች አብዛኛዎቹ የመድኃኒትና የመሳሪያዎች አቅርቦትም ተደርጎላቸዋል፡፡ የኤሌትሪክ ሃይል በማይደርስባቸው የወረዳው ገጠራማ አካባቢዎች ላይ ለተገነቡት ለነዚህ የጤና ጣቢያዎች የክትባት አገልግሎት እንዲዳረስ ለማድረግ እንዲቻል ተቋማቱ በፀሃይ ኃይል የሚሰራ የኤሌትሪክ ኃይል ተጠቃሚ እንዲሆኑ መደረጉንም የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታረቀኝ ጋቤራ ነግረውናል፡፡ በድርጅቱ የተከናወኑት የልማት ተግባራት፣ የትራንስፖርት አገልግሎት እንደልብ በማይገኝባቸውና እራቅ ባሉ ገጠራማ አካባቢዎች መሆኑ ድርጅቱን የሚያስመሰግነው ተግባር እንደሆነም አስተዳዳሪው ገልፀዋል፡፡

- ግራፊክ ዲዛይን- ቢል ቦርድ- ባነር- እስቲከር- ላይት ቦክስ

ደረጃቸውን ለጠበቁና ጥራት ላላቸው አጠቃላይ የህትመት ሥራዎች

ኢምር ማስታወቂያ

ለማስታወቂያ ድርጅቶች ልዩ ቅናሽ አለንአድራሻባምቢስ ዮርዳኖስ ሆቴል ፊት ለፊት እናት ታወር 2ኛ ፎቅ

ስልክ፡- 0911-00-43-57/0911-13-01-58/0118-30-56-56

- ቲሸርትና ኮፊያ- መፅሔት- ብሮሸር የመሳሰሉትን

የህትመት ሥራዎች በጥራትና በፍጥነት እናደርሳለን፡፡

Page 14: Issue-703.pdf

Website: www.addisadmassnews.com

አዲስ አድማስ ሰኔ 29 ቀን 2005 ዓ.ም ገፅ 14 ማስታወቂያ

Page 15: Issue-703.pdf

Website: www.addisadmassnews.com

አዲስ አድማስ ሰኔ 29 ቀን 2005 ዓ.ም ገፅ 15 ማስታወቂያ

Page 16: Issue-703.pdf

Website: www.addisadmassnews.com

አዲስ አድማስ ሰኔ 29 ቀን 2005 ዓ.ም ገፅ 16

ኤልሳቤት እቁባይ

የእርስዎ ድምፅ!

1. ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ እንዳትጠቀም ለማደናቀፍ የግብፅ መንግስት እስከ ጦርነት ድረስ የሚሄድ ይመስልዎታል?

A. አይሄድም አልልም B. በዛሬ ዘመን? ቢያንስ በአደባባይ

ጦርነት አያውጅም C. እኔጃ2. የግብጽ መንግስት ኢትዮጵያ

ውስጥ የእርስ በእርስ ግጭት በመፍጠር ዓላማውን ያሳካል ብለው ያስባሉ?

A. በፍፁም አይሳካለትም B. የኛ ጥንካሬና ድክመት አንድነትና

ልዩነት ነው ወሳኙ C. የሚሆነውን ማን ያውቃል?

3. ከግብጽ በኩል ሊመጣ የሚችል ችግር ያሳስብዎታል?

A. እንዴት አያሳስበኝ! ጦርነትንኮ እናውቀዋለን

B. አያድርገው እንጂ ከመጣ እጅ የሚሰጥ አይኖርም

C. የምንፈራ መስሏቸው እንጂ አይሞክሯትም

4. ግብጽ እና ኢትዮጵያ ወዳጅነት ፈጥረው በሰላም የሚተባበሩበት ጊዜ የሚመጣ ይመስልዎታል?

A. እንዴት ተደርጐ B. መምጣቱ አይቀርም ጠላትነት

አይጠቅመንም C. የፖለቲካ ነገር ምኑ ይታወቃል

የግብፅና የህዳሴ ግድብ ጉዳይ!

ማስታወቂያ

ንግድና ኢኮኖሚ

ክፍት የሥራ ቦታ ማስታወቂያ

1. የሥራ መደቡ መጠሪያ የሰው ሀይል አስተዳደር ዋና ክፍል ኃላፊ የትምህርት ደረጃ በሰው ሀይል አስተዳደር የመጀመሪያ ዲግሪ የሥራ ልምድ በሙያው አራት (4) አመት የሰራ/የሰራች ብዛት 1 (አንድ)2 የሥራ መደቡ መጠሪያ ሹፌር ተፈላጊ ችሎታ አስረኛ ክፍል ያጠናቀቀና 3ኛ መንጃ ፍቃድ ያለው የሥራ ልምድ 2 አመት በሙያው የሰራ ብዛት 3 (ሦስት)3. የሥራ መደቡ መጠሪያ ቴክኒሺያን የትምህርት ደረጃ ከቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ዲፕሎማ የተመረቀ 10+3/10+2 የሥራ ልምድ 10+3 0 አመት / 10+2 ሁለት አመት ብዛት 3 (ሦስት) ደመወዝ በስምምነት የሥራ ቦታ አዲስ አበባ

ድርጅታችን ከዚህ በታች በተመለከቱት ክፍት የሥራ መደቦች ላይ ባለሞያዎችን

አወዳድሮ ለመቅጠር ይፈልጋል፡፡

አመልካቾች የትምህርትና የሥራ ልምድ ማስረጃችሁን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 (ሰባት) ተከታታይ የሥራ ቀናት በድርጅቱ አስተዳደር ፅ/ቤት ወይም በሚከተለው አድራሻ መላክ የምትችሉ መሆኑን እናስታውቃለን፡፡

ስልክ ቁጥር 011-645-98-17/011-645-98-18/011-646-34-82

የመ.ሳ.ቁ 8191አዲስ አበባ

ሴትስ ጄነራል ትሬዲንግ ኃ.የተ.የግ.ማ

እስቲ ገምቱ!

መልሱን በገፅ 23 ይመልከቱ

1- ሁለት የኦሎምፒክ ማራቶኖችን ያሸነፈ የመጀመርያው አትሌት ማነው?

2- እ.ኤ.አ በ1985 ዓ.ም “No More Vitenasm” የተሰኘውን መፅሐፍ የፃፉ የቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ማን ናቸው?

3- ሼክስፒር ከፃፋቸው ትያትሮች ውስጥ ሻይሎክ የተሰኘ ገፀባህርይ የሚገኝበት ትያትር የትኛው ነው?

4- በዓለም በከፍተኛ ቡና አምራችነቷ የምትታወቅ አገር ማን ናት?

5- ከለውዝ አምራች ገበሬ ቤተሰቦች የተወለዱት የአሜሪካ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ማናቸው?

የማህበራዊ ጥናት መድረክ ሰሞኑን “የወጣቶች ስደት” በሚል ርዕስ ባዘጋጀው ፕሮግራም ወደ ደቡብ አፍሪካ እና መካከለኛው ምስራቅ የሚደረጉ የስራ ጉዞዎች ላይ ጥናታዊ ፅሁፎች ከመደረጋቸውም በላይ ውይይቶችም ተካሂደዋል፡፡ ወደ ደቡብ አፍሪካ የሚደረገውን ጉዞ አስመልክቶ ጥናት ያቀረቡት ዶክተር ዘርይሁን በጥናታቸው መግቢያ ላይ፤ ፍልሰት በአገሪቱ ረጅም ታሪክ ያለው እንደሆነ ጠቅሰው፤ የቅርብ ጊዜውን የፍልሰት ታሪክ በሶስት አበይት ክፍሎች በመለየት አስቀምጠዋል፡፡

የመጀመሪያው ዘመን ቅድመ 1966 አብዮት ሲሆን፤ በጣም ውሱን ፍልሰት የታየበት እንደነበርና ይሄ ዘመን ህብረተሰቡ ተምሮ ወደ አገር የመመለስ ሁኔታው የጎላበት ወቅት መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ ሁለተኛው ከ1966 እስከ 1983 ዓ.ም ያለውን ጊዜ የሚያካልል ሲሆን በአብዛኛው ወደ ምእራቡ አለም የፖለቲካ ስደት የበዛበት፤ ወደ መካከለኛው ምስራቅ የሚደረገውም የስራ ፍልሰት የጀመረበት ወቅት ነበር፡፡ በዚህ ዘመን ፍልሰትን በአሉታዊነት የሚመለከት ፖሊሲ እንደነበረም በጥናቱ ተጠቁሟል፡፡

ሶስተኛው ድህረ 1983 ሲሆን የመንቀሳቀስ ይሄ ወቅት መብት የተከበረበት፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ስደት እንዲሁም ከፍተኛ የስራ ፍልሰት የታየበት እንደሆነ አጥኚው አመልክተዋል፡፡ ወደ ደቡብ አፍሪካ የሚደረገው ፍልሰት ከ1990ዎቹ ወዲህ እንደተስፋፋ የጠቆመው ጥናቱ፣ ለዚህም ምክንያቱ በአገር ውስጥ አና በደቡብ አፍሪካ የታዩ ለውጦች እንደሆኑ ተገልጿል፡፡ በአገር ውስጥ ከታየው የመንቀሳቀስና ሰነዶችን በቀላሉ የማግኘት የመብት ለውጥ ባሻገር በደቡብ አፍሪካም የአፓርታይድ

• ለትዳር ሽምግልና ሲላክ “አረብ አገር ትልካታለህ ወይ” ተብሎ መጠየቅ ተጀምሯል• መምህራን፣ ፖሊሶችና የጤና ኤክስቴንሽን ሠራተኞች ጭምር እየተሰደዱ ነው

ስደት የከፋ ማህበራዊ መዘዝ እያስከተለ ነው!ውጪ ያሉ የስራ አማራጮች ውሱን መሆንና የጓደኛና የቤተሰብ ተጽእኖ ይገኙበታል፡፡ ወደ መካከለኛው ምስራቅ ከሚፈልሱት የህብረተሰብ አባላት መካከል በስራ ላይ ያሉ መምህራን፣ ፖሊሶችና የጤና ኤክስቴንሽን ሰራተኞች ጭምር እንደሚገኙበት ጥናቱ ይጠቁማል፡፡

በጉዞ ወቅት የሚገጥሙ ችግሮችን አስመልክቶ በጥናቱ ላይ እንደቀረበው፣ የደቡብ አፍሪካ ጉዞ በአብዛኛው የሚደረገው በህገወጥ መንገድ በመሆኑ ዋናው ችግር ያለው ደቡብ አፍሪካ እስኪገባ ባለው የጉዞ ሂደት ውስጥ ሲሆን በህጋዊ መንገድ የሚደረገው የመካከለኛው ምስራቅ ጉዞ ችግር የሚጀምረው ደግሞ መዳረሻ አገር ላይ ነው፡፡ ወደ ደቡብ አፍሪካ የሚደረገው ጉዞ ከአገር ውስጥ እስከ ደቡብ አፍሪካ የተዘረጋ ጠንካራ ኔትወርክ ባላቸው ደላሎች የሚካሄድ ሲሆን በመንገድ ላይ ለሚደርስ እንግልት፣ ስቃይና ሞት ማንም ተጠያቂ አካል እንደሌለ ተጠቁሟል፡፡

የመካከለኛው ምስራቅ ጉዞ ከአገር ከተወጣ በኋላ በህጋዊ መንገድ በሄዱት እና በህጋዊ መንገድ ባልሄዱት መካከል ልዩነት እንደሌለ ያመለከተው ጥናቱ ፤ ለዚህ ደግሞ ዋናው ምክንያት ወደ ሳኡዲ የሚደረገው ጉዞ በቀጣሪ ኤጀንሲዎች ስምምነት ብቻ የሚከናወን በመሆኑ ተቀጣሪዎች ወደ ተቀባይ አገሮች የሚሄዱትና የሚኖሩት በአሰሪው መልካም ፈቃድ እንደሆነ ይጠቁማል፡፡ ኤጀንሲዎች ህገወጡንና ህጋዊውን ቀላቅለው ይሰራሉ የሚል ጥርጣሬ ማረበቡም ተጠቅሷል፡፡

ፍልሰቱ በአገር ላይ ከፍተኛ አሉታዊ ተፅዕኖዎች እያስከተለ መሆኑ በጥናቱ የተገለፀ ሲሆን ወደ ደቡብ አፍሪካ በሚደረገው ጉዞ በተለይ በደቡብ ክልል ባሉ አካባቢዎች በመንግስት ስራ ላይ ያሉ ሳይቀሩ በመፍለሳቸውና አብዛኞችም ለጉዞው ያኮበኮቡ በመሆናችው የተማረ የሰው ሀይል ላይ የሚያስከትለው መመናመን በአፅንኦት ሊታሰብበት እንደሚገባ ተጠቁሟል፡፡

ፍልሰቱ በተስፋፋባቸው አካባቢዎች ከስደት ይልቅ በአገሩ ሰርቶ መኖር የሚመርጥ ግለሰብ ቢገኝ እንኳን ከህብረተሰቡ ያለበት ጫና ቀላል አለመሆኑን የጠቀሱት አጥኚዎቹ፤ ጎረምሳ ልጅ ያለ ስራ ተቀምጦ ከታየ “ከአንተ የደቡብ አፍሪካ ሬሳ ይሻላል፤ ቢያንስ ሞባይል ይዞ ይመጣል” መባሉን በማሳያነት ጠቅሰዋል፡፡ ለዚህ ምክንያቱ ሰው ሞቶ አስከሬኑ ሲላክ ንብረቶቹ አብረው ስለሚላኩ ቢያንስ ሞባይል ከንብረቱ መሀል ስለማይጠፋ እንደሆነ በጥናቱ ተጠቅሷል፡፡

በአማራ ክልል ሴቶች በብዛት ወደ አረብ አገሮች በሄዱባቸው አካባቢዎች ማህበራዊ ለውጦች እየታዩ እንደሆነ የተጠቆመ ሲሆን እናቶች በብዛት በመፍለሳቸው የተነሳ ትንንሽ ሴት ልጆች ላይ ከፍተኛ የስራ ጫና እየተፈጠረ ነው፡፡ በዚህም ምክንያት ልጆቹ በትምህርታቸው እየደከሙ እንደመጡ ታውቋል፡፡

ባሎች ደግሞ ከዚህ በፊት የማይሰሯቸውን የቤት ውስጥ ስራዎች መስራት እንደጀመሩ ጥናቱ ይጠቁማል - ለምሳሌ ወሎ ውስጥ እንደ ሮቢት ባሉ ሴቶች በብዛት ወደ አረብ አገሮች በሄዱባቸው አካባቢዎች፣ ወንዶች የቤት ውስጡን ስራ ሚስቶቻቸውን በመተካት እየሰሩ ይገኛሉ ተብሏል - እንጀራ በመጋገርና ወጥ በመስራት፡፡

በጥናቱ ላይ ከተጠቀሱት ሌሎች ለውጦች መካከልም ህብረተሰቡ ለሴቶች የሚሰጠው ቦታ እየጨመረ መምጣቱ አንዱ ሲሆን የሴቶች ከቤተሰብ ቁጥጥር ውጪ መንቀሳቀስ፣ ሴቶች በተለይ አንደኛ ደረጃን ጨርሰው ትምህርታቸውን ማቋረጥ፣ ዕድሜያቸው 18 ያልሞላ ልጆች ፓስፖርት በማውጣት ፍልሰቱን መቀላቀላቸው እና በሚላከው ገንዘብ የተነሳ በቤተሰብና በትዳር ጓደኛ መሀል ግጭት መፈጠር እንዲሁም በአንዳንድ ቦታዎች ለትዳር ሽምግልና ሲላክ “አረብ አገር ትልካታለህ ወይ” የሚል ጥያቄ መቅረብ መጀመሩ ይጠቀሳሉ፡፡

የጥናት ጽሁፎቹ ከቀረቡ በኋላ በተደረገው ውይይት፤ የሁለት ጎራ ሀሳቦች ከተሳታፊዎች የተሰነዘረ ሲሆን አንደኛው አገር ወስጥ ሰርቶ

መለወጥ ይቻላል የሚል ሲሆን ሁለተኛው በአገር ውስጥ መለወጥ ከባድ ነው የሚሉ ናቸው፡፡ መንግስት ለወጣቶች ምቹ እድል መፍጠር አለበት የሚለው ጎልቶ የወጣ ሀሳብ ሲሆን በውይይቱ ላይ ልምዷን ያካፈለች ወጣት ስትናገር፤ “እኔ ውጤት አምጥቼ ዩኒቨርሲቲ ስገባ የጎረቤት ልጆች ውጤት ስላላመጡ ወደ አረብ አገር ሄዱ፤ እኔ ተማሪ ሆኜ እነሱ የራሳቸውንና የቤተሰባቸውን ሕይወት ለውጠዋል፤ እኔ ከተመረቅሁ በኋላ ስራ አላገኘሁም፤ የሚወጣው ማስታወቂያ በሙሉ ከአምስት አመት በላይ የስራ ልምድ ይጠይቃል፤ ሌላ ትምህርት እንዳልማር ወጪ መጋራት በሚለው አሰራር ክፍያ አላጠናቀቅሁም፤ ደቡብ አፍሪካ እህት አለችኝ፤ በየቀኑ እኔም የምወጣበትን መንገድ እንድታመቻችልኝ ነው የምጠይቃት” ብላለች፡፡ እንግዲህ በግልፅ እንደቀረበው ምክንያቱ ምንም ይሁን ምንም ትውልዱ ልቡ ለስደት አሰፍስፏል፡፡ አሳዛኙ ደግሞ ሃይ ባይ ተቆጭ እንኳን አለመኖሩ ነው፡፡ ጎበዝ! ትውልድ ተሰዶ ከማለቁ በፊት ብንወያይበትና መላ ብንዘይድ አይሻልም፡፡

ስርአት መውደቅ ያመጣው ምቹ ሁኔታ እንዲሁም በኬኒያ እና በኢትዮጵያ የተደረሰው የቪዛ ስምምነት ተጠቅሰዋል፡፡

ወደ መካከለኛው ምስራቅ የሚደረገውን ፍልሰት ታሪካዊ ዳራ አስመልክቶ ጥናት ያቀረቡት ዶክተር አስናቀ በበኩላቸው፤ ጉዞው ከ1970ዎቹ አንስቶ ቢጀመርም ኢትዮጵያዊያን በብዛት ወደ ሥፍራው መጓዝ የጀመሩት ግን ከ1983 ዓ.ም ወዲህ መሆኑን ጠቅሰው፣ የሴት ተጓዦች ቁጥር በከፍተኛ መጠን በማሻቀብ ላይ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡

በሁለቱም ጥናቶች ላይ የፍልሰቱ ዋነኛ ምክንያት ኢኮኖሚያዊ መሆኑ የተጠቆመ ሲሆን በመዳረሻ አገሮች ያለው ሰርቶ የማግኘት እድልም ሳቢ ምክንያት እንደሆነ ተጠቅሷል፡፡ ወደ መካከለኛው ምስራቅ ለመሄድ የሚገፋፉ ምክንያቶች ተብለው ከተጠቀሱት መካከል፣ በአገር ውስጥ የስራ እድል አለመስፋፋት፣ በተለይ ለገጠር ሴቶች ከግብርና ስራ

የደቡብ አፍሪካ ጉዞ በአብዛኛው የሚደረገው በህገወጥ መንገድ በመሆኑ ዋናው ችግር ያለው ደቡብ አፍሪካ እስኪገባ ባለው የጉዞ ሂደት ውስጥ ሲሆን በህጋዊ መንገድ የሚደረገው የመካከለኛው ምስራቅ ጉዞ

ችግር የሚጀምረው ደግሞ መዳረሻ አገር ላይ ነው፡፡ ወደ ደቡብ አፍሪካ የሚደረገው ጉዞ ከአገር ውስጥ እስከ ደቡብ አፍሪካ የተዘረጋ

ጠንካራ ኔትወርክ ባላቸው ደላሎች የሚካሄድ ሲሆን በመንገድ ላይ ለሚደርስ እንግልት፣

ስቃይና ሞት ማንም ተጠያቂ አካል እንደሌለ ተጠቁሟል፡፡

Page 17: Issue-703.pdf

Website: www.addisadmassnews.com

አዲስ አድማስ ሰኔ 29 ቀን 2005 ዓ.ም ገፅ 17

አማረ ታየ

ጥበብ

ማስታወቂያሲኒማ ወደ ገፅ 21 ዞሯል

ስኩል ኦፍ አይጐዳ

ስኩል ኦፍ አይጐዳ•ለትምህርት ጥራትና ለመልካም ባህሪ ግንባታ ተግቶ የሚሰራ ት/ቤት

•በልዩ ዝግጅት የዓመቱን የዕውቀት ክህሎት ሰኔ 30 ቀን 2005 ዓ.ም በሳሪስ ካምፓስ ያከብራል

•ይምጡና የት/ቤታችንን ለውጥ ይጐብኙ

•ልዩ የክረምት ማጠናከሪያ ትምህርት ሐምሌ 8 ቀን 2005 ዓ.ም እንጀምራለን፡፡

•በየትኛውም አቅጣጫ የሰርቪስ አገልግሎት እንሰጣለን፡፡ስልክ፡- ሳሪስ - 0114-40-43-78/79 ቡልቡላ - 0913-06-90-34 አዲስ ሰፈር - 0114-40-42-17

ፊልሙ የሚጀምረው በሁለት አብሮ አደግ ጓደኛሞች (ሮማንና ሮቤል) መካከል በሚጠነሰስ ስውር የፍቅር ታሪክ ሲሆን ሮቤል ፍቅሩን

በይፋ መግለጽ አቅቶት ሲቸገር ይስተዋላል፡፡ ሮማን አባቷ በመኪና አደጋ ሁለት ዓይኖቻቸውን ያጡ በመሆናቸው፣ ትምህርቷን አቋርጣ በአንድ ድርጅት ውስጥ በጽዳት ሰራተኛነት በመቀጠር ቤቱን ታስተዳድራለች፡፡ ሮቤልም በዚሁ ድርጅት ውስጥ፣ የኤሌክትሪክ ሠራተኛ ሆኖ አብሯት ይሰራል፡፡ ታዲያ ከቀን ወደቀን በልቡ ውስጥ እየተፀነሰ የመጣውን ፍቅር ለመግለጽ የተለያዩ ዘዴዎችን ቢጠቀምም፣ ሮማን ግን ፍቅሩን አትረዳለትም፡፡ ይብሱኑም እንደወንድሟ እንደምታየው ትነግረዋለች፡፡ የኋላ ኋላ ግን ጨክኖ በደብዳቤ እንደሚወዳት ፅፎ ይሰጣታል፣ እቤቷ ገብታ እንድታነበው በማስጠንቀቅ፡፡

እንደአጋጣሚ ሆኖ ግን ደብዳቤውን ይዛ ወደቤት ስትገባ፣ አባትዋ በሕመም ራሳቸውን ስተው ወድቀው ታገኛቸዋለች፡፡

በዚህ አጋጣሚ ሮቤል ከእሷው አጠገብ ሆኖ ስለአባትየው ሕመም አብሮ ይጨነቃል - ከሮማን ጋር፡፡ የአባትየው ህመም ግን ቀላል አልነበረም፡፡ ሁለቱም ኩላሊቶቻቸው ከአገልግሎት ውጭ መሆናቸውንና በየሳምንቱ 5ሺህ ብር እየተከፈለ የኩላሊት እጥበት (ዲያሊስስ) ሕክምና እንደሚያስፈልጋቸው ከሃኪሞች ይገለጽላቸዋል። (በነገራችን ላይ ስለኩላሊት ሕመምና ሕክምናው ስለሚያስወጣው ወጪ ደራሲው ሲጽፍ ጥናት አድርጐና በእውቀት ላይ ተመስርቶ እንደሆነ ፊልሙ

“የማትበላ ወፍ” ይመሰክራል) ይሄ ሕመም የሮቤል የፍቅር ዓላማና ግብ እንዳይሳካ የሚያደርግ የመጀመሪያው መሰናክል በመሆን ይጋረጣል፡፡

ሮቤል የሮማንን አባትን ለማሳከም የማይፈነቅለው ድንጋይ የለም፡፡ የማታ ትምህርቱን ትቶ፣ የቤት ዕቃዎቹን ሁላ በመሸጥና ከጓደኞቹም ጭምር በማሰባሰብ፣ የተጠየቀውን ገንዘብ ለማሟላት መከራውን ሲበላ ይታያል፡፡ በሌላ በኩል የድርጅታቸው ሥራ አስኪያጅ የሆነው ዮናስ፣ ለሮማን አባት የአንድ ወር ክፍያ በመሸፈን፣ የአባትየውን ሕይወት የታደገ በመምሰል፤ በዚህ ውለታም ከሮማን ጋር የፍቅር ግንኙነት ለመጀመር ዳር ዳር ይላል፡፡ ሮማን ለአባቷ የህክምና ወጪ ስትል ከዮናስ ጋር መቀራረብ ግድ ይሆንባታል፡፡ ይሄኔ ደግሞ ሮቤል በቅናት ይጨሳል፡፡ የሮማን አባት የኩላሊት ህመም እየተባባሰ ይሄድና በሌላ ኩላሊት መተካት እንዳለባትና ለዚህም ከሁለት መቶ ሺህ ብር በላይ እንደሚያስፈልግ ይነገራታል፡፡ እዚህ ጋ ነው አጣብቂኝ ውስጥ የምትገባው፡፡ የሮቤል ፍቅር የት ይደርስ ይሆን? የሮማን አባት ከ200ሺ ብር በላይ ከየት ተገኝቶ ይታከማሉ? ወይስ ይሞታሉ? የሥራ አስኪያጁስ መጨረሻ? እንዲህ ስሜትን ወጥሮና ልብን አንጠልጥሎ እስከታሪኩ መቋጫ ይዞን የሚፈስ ድንቅ ፊልም ነው፡፡

የፊልሙ ታሪክ ቀላልና ግልጽ ነው፡፡ በሁሉም የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኝ ሰው በቀላሉ ሊረዳው የሚችል፡፡ የደራሲው ቋንቋ፣ የገፀባሕሪያቱ አሳሳል፣ የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴና ምልልሳቸው ግሩም ነው። ከሁሉም ያስደነቀኝ ደግሞ ደራሲው የምናውቀውን የተለመደ የፍቅር ታሪክ በሌላ አቅጣጫ አዙሮ የተናገረበት ወይም ዳሬክተሩ የተረከበት መንገድ እስከፊልሙ ፍጻሜ ድረስ በጉጉትና በስሜት ይዞ

መዝለቁ ነው፡፡ ለእኔ ታሪኩ አስተማሪና አዝናኝም ጭምር ነው፡፡ ባህሌን፣ እሴቴን፣ ቋንቋዬን እና አኗኗሬን ቁልጭ አድርጐ ያሳየኝ፣ ኢትዮጵያዊ ፊልም ነው ማለት እችላለሁ፡፡

ታሪኩን ወደፊት ለማስኬድና ፍሰቱን ለማሰናሰን፣ ሴራ ወሳኝ የፊልም አላባ እንደሆነ ይታወቃል። በ”የማትበላ ወፍ” ውስጥ ያለው ሴራ፣ ፊልሙን ከአንድ ሰዓት በላይ ቁጭ ብለን በተመስጦ እንድናየው ያስገድደናል፡፡ ሴራውንም ለማሰናሰን ደራሲው የተጠቀማቸው ተምሳሌቶች፣ ለፊልሙ ልዩ ውበትን አላብሰውታል፡፡ ለምሳሌ አባትየው ለሮቤል ብለው ያዘጋጁለትን የአንገት ልብስ፣ ሮማን አንስታ ለዮናስ የምትሰጥበት ሁኔታ የታሪኩ አቅጣጫ ሲለውጥ እናያለን፡፡ ሮቤል እንደትልቅ ስጦታ የሚቆጥረውን ሐብል ሲሸጥ ሲለውጠው፣ ታሪኩን ወዲህና ወዲያ ይወዛወዛል፡፡ ሌላው ደግሞ በምናብ የተፈጠረችው “ኢነርጂ” የምትባል የሮቤል የሕልም ዓለም ፍቅረኛ፣ በሮማን ውስጥ የምትፈጥረው ስነልቦናዊ ግጭትም አለ፡፡ በአጠቃላይ ከጅምሩ አንስቶ ዕድገቱና ድምዳሜው ሁሉ በጥንቃቄ ታስቦ የተሰራ መሆኑን ያየ ሁሉ ይመሰክራል፡፡

ታሪኩና ባለታሪኮቹ፣ ታሪኩን የፈፀሙበት ቦታና ጊዜ፣ አግባብነት ያላቸውና የኢተዓማኒነት ጥያቄ ፈፅሞ የማያስነሱ ናቸው፡፡ እግረመንገዱንም የማኅበረሰባችንን እውነተኛና ያልተበረዘ (ማስመሰል የሌለበት) አኗኗር ያሳያል፡፡ ባለታሪኩቹ የሚኖሩባቸው ቤቶች፣ አካባቢዎች እንዲሁም ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ይዞታቸውን ተከትሎ የሚውሉባቸው ቦታዎች፣ በጥንቃቄ ከታሪኩ ጋር ተዛምደው፣ መመረጣቸውን ማስተዋል ይቻላል፡፡

በተለይ ፊልሙን ልዩ የሚያደርገው ደግሞ ገፀባሕሪያት ከሚያጋጥማቸው ችግርና የስሜት

መዋዠቅ ጋር ተያይዞ፣ ከበስተኋላ የምናያቸው የቦታና የጊዜያት ለውጦች ናቸው፡፡ ለምሳሌ ሮማን ወደ ዮናስ ጋ ስትሄድ፤ ሮቤል በሐዘን ተመትቶ በፈራረሱ ቤቶች መሃል አቋርጦ ሲሄድ፤ በቦታውና በሁኔታው ላይ ያለውን ስሜት ይበልጥ የሚያጎላው ነው፡፡

የድምፁን ጥራት ሳነሳ ፊልሙን በዓለም ሲኒማ ደጋግሜ ከተመለከትኩት ተነስቼ የምሰጠው አስተያየት እንደሆነ ይታወቅልኝ፡፡ አንድም ቦታ ጆሮን ሊረብሹ፣ ስሜትን ሊያውኩ የሚችሉ ድምፆች፣ አላስተዋልኩም፡፡ የድምጽ ባለሙያውን ብቃትና ጥረት ሳላደንቅ አላልፍም፡፡ በተጨማሪም ድምፁ ከፍና ዝቅ ሳይል ተመጥኖ መጠናቀሩ ብዙ እንደተለፋበት ያሳያል፡፡

ምስል ቀረጻውም አሁን በአገራችን ካለው ቴክኖሎጂ አንጻር የሚደነቅ ነው፡፡ በአእምሮ ውስጥ የተፈጠረን ታሪክ፣ የፎቶ ማንሻ በምታክል ካሜራ (7ዲ) ምስሉ በተሟላ ሁናቴ መደራጀቱ አስደምሞኛል፡፡ ምስል ቀረጻው፣ ከታሪኩ ጋር ተደጋጋፊ ሆኖ እንዲቀርብ የተደረገበት ሁኔታም ምርጥ ነው፡፡ ለምሳሌ ሮማንና ዮናስ ቆመው፣ ሮቤል ከርቀት ሆኖ የተመለከተበት፣ ማለትም ሦስቱም በአንድ ፍሬም ውስጥ ተቆራኝተው የቀረቡበት መንገድ፣ ታሪኩን ሳይንዛዛ በአጭሩ ገልፆታል። ሌላው ሮቤል በተንጋደደ ፍሬም ውስጥ ሆኖ ደብዳቤውን ሲያነሳው የታየበት ምስል፣ በቀጣይ ጉዞው የሚያጋጥመውን የተንጋደደ ሕይወት ጠቋሚ ነው፡፡ በአጠቃላይ የፍሬም አመራረጥ፣ የብርሃን አጠቃቀምና አመጣጠን፣ እንዲሁም ተዋንያን ከካሜራው ጋር ያላቸውን እርቀትና ቅርበት በመለካት፣ ከሌንስ አጠቃቀሙ ጋር ያላቸውን ቁርኝት

መታየት ያለበት ኢትዮጵያዊ ሲኒማ!

Page 18: Issue-703.pdf

Website: www.addisadmassnews.com

አዲስ አድማስ ሰኔ 29 ቀን 2005 ዓ.ም ገፅ 18 ጥበብኪነጥበባዊ ዜና ግሩም ሠይፉ

እንኳን ደስ ያለሽሰኔ 29 ቀን 2005 ዓ.ም ከአዲስ አበባ

ዩኒቨርስቲ በሶሻል ወርክ ማስተርስ ዲግሪ ለተመረቅሽው እህታችን ሐረገወይን

ታምሩ እንኳን ደስ አለሽ!

ህይወት ሙሉጌታናአስቻለው ታምሩ

የመጀመያው አብዮተኛ ሰይጣን ነበር ይባላል፡፡ በዝንተ አለማዊው የእግዚአብሔር አገዛዝ ላይ በተቃውሞ የተነሳ የመላእክት አለቃ፡፡ ይህን አባባል ተቀብለን ለተቃውሞው፣ ለአመፃው ተግባር በመንስኤነት የምናገኘው ሰበብ ቢኖር መሰልቸት ነው፡፡ መሰልቸት ከእጦትም ከቅንጦትም ይመነጫል፡፡ ሊቀ - መልዓኩ በዚያ ፅንፍ አልባ ህዋና በነዚያ ሁሉ እልፍ አእላፍ መላእክት ላይ ሰልጥኖ ሲኖር …ሲኖር አንዳች የሚጐድል፣ አንዳች የሚዛነፍ ነገር የለምና ሰለቸው፡፡ በኛ እምነትም አብዮት ከመለኮት የተገኘ የውርስ ዳፋ ነው፡፡ እንዴት? ቢሉ እልቅናውን የተነጠቀውና ወደ ጥልቁ የተወረወረው ሰይጣን፣ እሱ በተጠመደበት የመሰልቸት ወጥመድ በተራው ሰውን ስላጠመደው፡፡ እንደ ሰይጣን ሁሉ ሰውም (አዳም) በገነት በሙሉ ስልጣን ተሰይሞ ጫፍ እስከ ጫፍ እየተዘዋወረ ያሻውን ይፈጽም ዘንድ ሁሉ በፊቱ ነበር፡፡ ይሄ ፍቃድ በራሱ ለመሰልቸትና ለመተላለፍ በቂ ሆኖ እያለ ሌላ ለሰይጣን ወጥመድ የተመቸ ገደብ ከፈጣሪ ለፍጡሩ ተላለፈ፡፡ “ከህይወት ዛፍ የበላህ እንደሆነ ሞትን ትሞታለህ” የሚል፡፡ ሰይጣን አዳምና ሄዋን በገነት እየተዘዋወሩ እስኪዘሉ፣ እስኪቦርቁ፣ እስኪሰይሙ ታገሳቸው፡፡ የግዜው ርዝመት በራሱ ወደሱ ዓላማ እንዲያመጣቸው ገብቶታል ወደ መሰልቸት፡፡ ግዜው ሲደርስ በጥናቱ መሰረት ተራማጅ ነች ብሎ ወዳመነባት ሄዋን በመሄድ…”አማን ነው ሄዋን”፤ አላት ከወደ ኋላዋ ድንገት ደርሶ “ቆሌህ ይገፈፍ አቦ! ኮቴህም አይሰማም እንዴ!?” አለች እየተበሳጨች አሳቀችው….”እንዴ ኮቴ እኮ የሰው ልጅ ግዴታ ነው፡፡ የኔ መምጣት በምንም ነገር ውስጥ ታምቆ ለመገለጽ አይገደድም” አለ በአካሄዱ እንደመደነስ እየቃጣው፡፡ ለተናገረው ብዙም ትኩረት ሳትሰጥ “እሺ ምን ፈልገህ ነው?” ስትል ጠየቀች፡፡ በተራው ተበሳጭቶ “ወይኔ ሄዋን መፈለግ መመኘት ለናንተ ለስንኩሎቹ የተተወ መባዘን ነው፡፡ እኔ ከዚያ በላይ ያለ ፍቃድ ያለ እግድ የምኖር ነኝ” አላት፡፡ አግድም እያየችው “ማነው ይሄንን ላንተ ብቻ የሰጠው? እኛስ ብንሆን ምን ጐደለብን? እንዳሻን አይደል እንዴ የምንኖረው?” በማስቀናት መልክ ትከሻዋን ነቀነቀች፡፡ “ስቄ ልሞት አለች…እ ትላለች ማለቴ ወደፊት” አለ እየሳቀ፡፡ “እንዳሻን አልሺኝ --- ለዚህ ነዋ ለአዳም ከህይወት ዛፍ ፍሬ የበላህ እንደሆነ ትሞታለህ ብሎ እግዚአብሔር ያስጠነቀቀው!?” ሲል አፋጠጣት፡፡ ሳታስበው ተይዛለችና የምትመልሰው አልነበራትም፡፡ አዳም ከአንበሳ ሲላፋ ትታው የመጣችው የነገሮች ድግግሞሽ አሰልችቷት ነበር፡፡ አሁን ደግሞ ሰይጣን ከዚህ ሁሉ የበረከት ጋጋታ አንድ ዛፍ መከልከሉን እየነገራት ነው፡፡ “ታዲያ ምን ችግር አለው? በገነት ያለው በረከት በሙሉ በእጃችን ነው-- የአንድ ዛፍ ፍሬ ቢቀርብን ምን እንሆናለን?” ስትል ጠየቀች፡፡ ከመከራከር፣ ከመከላከል ድምፀት ጀርባ ያለውን መሸርሸር፣ ከኋላ ያለውን መዳከም ሰይጣን ነጥሎ አድምጦታል፡፡

“ተይ እንጂ ሄዋን፣ ቢያንስ እኮ ከነዚህ ሁሉ ቁጥር አልባ ዛፎች ተመርጦ የከለከለበት ምክንያት አንድ ልዩ ነገር ቢኖረው ነው፡፡ ተራ ዛፍ አይደለም፡፡ ታዲያ እዚህ ፍሬ ሆድ ውስጥ ያለው ምስጢር እንዴት አያጓጓም ብለሽ ታስቢያለሽ?” ተፈታተናት፡፡ ከሰይጣን ጋር በውይይት በገፋች ቁጥር እየሰላች ከርሱ ጋርም ባልታሰበና ግልጽ ባልሆነ አቅጣጫ እየተስማማች ሄደች፡፡ “በርግጥ ሊያጓጓ ይችላል፤ ግን በውስጡ ያለውን ለማወቅ ከፍሬው መብላት የግድ ነው፡፡ ፍሬውን መብላት ደግሞ ከአምላክ ትዕዛዝ ውጭ መሆን ነው” በስውር አመነታች፡፡ “እሱ እኮ ነው ቁም ነገሩ” አለ ሰይጣን፤ተክለፍልፋ ወደ ወጥመዱ ስትገባለት “የፍሬው ሃይል ገደብ አልባ ያደርግሻል እግዚብሔር በስስት ከአንቺ የጋረደውን አለም ይገልጥልሻል፣ ከአዳዲስ ስሜቶች ጋር ያስተዋውቅሻል፡፡ ፍሬውን ከበላሽ በኋላ አዲስ ምዕራፍ ይከፈታል፣ አሁን የምታውቂውን ያህል የሚሰፋ አለም ላይ ትሰለጥኛለሽ፣ ሌላው ቀርቶ አሁን ባለሽ መረዳት ልትገነዘቢ የማትችይውን በአዳም ላይ ያለሽን የበላይነት ትቀዳጃለሽ” እራሱም በትረካው ተመስጦ ነበር፡፡ “ግን አንተ ይሄን በምን አወቅህ?” በነገሩ በመመሰጧ ስላወቀበት መንገድ እንጂ ስላወቀው ነገር እውነትነት ጥርጣሬው ከውስጧ ጠፍቶ ነበር፡፡ ሳቀ፡፡ ረጅም ሳቅ ሳቀ፡፡ በትንፋሹ ሃይል አዕዋፍ ከዛፍ ሸሽተው እስኪበሩ፣ የየዛፉ ቅጠሎች እስኪረግፉ፣ በግዮን ወንዝ ማዕበል ተነስቶ መስኩን እስኪያጥለቀልቀው፣ ሄዋን ራሷ ቋጥኝ ስር ተደብቃ እስክትንዘፈዘፍ…ሳቀ፡፡ ወዲያው ግን ነቃ ብሎ በኩራት “እንዴ እኔማ ከፈጣሪ መኖር ትንሽ ዘግይቼ ነበርኩ፡፡ ከፈጣሪ እውቀት ትንሽ ብቻ ሲጐድልብኝም ሁሉን አውቃለሁ፡፡ እናም ያንቺና የአዳም ውስንነት ያሳዝነኛል፡፡ ከጽንፍ አልባ አለም ተገድባችሁ ገነት በምትባል ትንሽ መስክ መጣላችሁ ግፍ መሆኑ ይሰማኛል፡፡ ለዚህም ነው ገመድሽን ፍቺ እንዳሻሽ፤ ወዳሻሽ ብረሪ የምልሽ” ይህን ሲናገር መንገድ ጀምሮ ነበር፡፡ አይኗ እሱን ከመከተል ዞር ከማለቱ ከዛፎቹ እንደ አንዱ ሆኖ ይከታተላት ጀመር፡፡ ሃሳብ ሳይሆን መንፈስ የተጋባባት ይመስል እመር ብላ ከተቀመጠችበት ተነስታ አዳምን ትታው ወደመጣችበት አቅጣጫ በትካዜ መሬት መሬቱን እያየች ሄደች፡፡ አዳም እንደተለመደው የተለመደው ተፈጥሮ ብርቅ ሆኖበት በአንክሮ ሲመለከት አገኘችው፡፡ “አዳምዬ?” አለችው እጆቿን ትከሻው ላይ ጣል እያደረገች፡፡ እንዲህ ስትጠራው ልቡ ለምን ድክም እንደሚልበት እየተገረመ “ወዬ ሄዋን” አለ፡፡ የሚሆነው ሁሉ እንደሚሆን እርግጠኛ የሆነው ሰይጣን፡፡ በቅርብ ርቀት ሆኖ በተስፋ ሲቃ የተሞላ ፈገግታው ሁለቱ ፍጡራን ላይ አብርቶ ነበር፡፡ ከሁሉም ጀርባ ሁሉንም በትዝብት የሚመለከተው ፈጣሪ የመከፋቱ ስሜት ዙሪያ ገባውን አደናግዞታል፡፡ አዳምና ሄዋን ብቻ በማይዘልቀው ሰይጣናዊ ብርሃን ስር ሆነው፣ ወደ አዲስ የጨለማ ምዕራፍ እየተሸጋገሩ ነው፡፡

የዓመፅ ፍሬ!ሚካኤል ዲኖ ወግ

በታዋቂ የካርቱን ኮሚክ መፅሃፍት ላይ በሚገኙ ጀብደኛ ገፀባህርዮች ላይ ተመስርተው በድጋሚ የተሰሩ እና በተከታታይ ክፍሎች ለእይታ የበቁ የሱፕር ሂሮ ፊልሞች የ21ኛው ክፍለዘመን የሆሊውድ ፋሽን መሆናቸውን ዴይሊ ቴሌግራፍ አስታወቀ፡፡ በተወዳጅነት እና በገበያው ስኬታማ እየሆኑ የመጡት የሱፐር ሂሮ ፊልሞች ባለፈው ዓመት በመላው ዓለም 3.8 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ያስገኙ ሲሆን ዘገባው ዘንድሮ ገቢያቸው እስከ 4.5 ቢሊዮን ዶላር ሊደርስ እንደሚችል ተገልጿል፡፡ በሆሊውድ ፊልሞች የገበያ ታሪክ ከፍተኛ ገቢ ከተገኘባቸው 10 ፊልሞች ስድስት ያህሉ የሱፕር ሂሮ ፊልሞች መሆናቸው ያላቸውን አዋጭነት ያሳያል ተብሏል፡፡ በሱፕርሂሮ ፊልሞች ታዋቂዎቹ ኩባንያዎች ማርቭል እና ዲሲ ከፍተኛ ፉክክር ውስጥ መግባታቸውን የገለፀው ዘጋርድያን፤ ማርቭል ፒክቸርስ ባለፉት 15

በቅርቡ “ላይፍ ሃፕንስ” የተባለ አዲስ አልበም በእስራኤል ለገበያ ያበቃችው ቤተእስራኤላዊቷ ድምፃዊት ኤስተር ራዳ፤ በእስራኤል የሙዚቃ ኢንዱስትሪ መድመቅ ጀምራለች ተባለ፡፡ የኤስተር ራዳ አዲስ አልበም አርቲስቷ ኢትዮጵያዊ የዘር ግንዷን ሙሉ ለሙሉ የገለፀችበት ነው ያለው “ኒውስፖይንት አፍሪካ” ፤ “ላይፍ ሃፕንስ” በተባለው ዘፈኗ ዋሽንትና ማሲንቆን እንደተጠቀመች ጠቅሷል፡፡ የ28 አመቷ ድምፃዊት፤ የዘፈን ግጥም ደራሲ እና ተዋናይቷ በአዲሱ አልበሟ ውስጥ “ላይፍ ሃፕንስ” የተሰኘውን የአልበሙን መጠርያ ጨምሮ “ሞንስተርስ”፤ “ኤኒቲንግ ፎር ዩ” እና “ኩድ ኢትቢ” የተባሉ ዘፈኖችን አካትታለች፡፡ በኢትዮ ጃዝ እና በሶል የሙዚቃ ስልቶች የተሰሩት የድምፃዊቷ ዘፈኖች በእስራኤላውያኖቹ እውቅ የሙዚቃ ባለሙያዎች ኩቲ እና ሳቦ የተቀናበሩ እንደሆኑ ለማወቅ ተችሏል፡፡ የኤስተር ቤተሰቦች እ.ኤ.አ በ1983 ዓ.ም በተከሰተው ረሃብ ሳቢያ ኢትዮጵያን ለቅቀው ወደ እስራኤል የተሰደዱ ሲሆኑ ኤስተር የተወለደችው ቤተሰቦቿ እስራኤል ገብተው ኪራያት ኡባ በተባለ ስፍራ መኖር ከጀመሩ ከአንድ አመት በኋላ ነው፡፡ ኤስተር እና ቤተሰቧ 10ኛ ዓመቷን እስክትይዝ ድረስ በሄብሮን ዳርቻ የኖሩ ሲሆን እድሜዋ ለእስራኤል የውትድርና አገልግሎት ሲደርስ ወደ ውትድርናው ገብታ እግረመንገዷን እዚያው በነበረ

ቤተ-እስራኤላዊቷ ድምፃዊት በእስራኤል ደምቃለች

የሚሊታሪ ባንድ ድምፃዊ በመሆን ሰርታለች፡፡ ቤተእስራዔላዊ ብትሆንም በፀጉረ-ልውጥነቷ ብዙ አሳዛኝ ገጠመኞችን በወጣትነቷ ያሳለፈችው ኤስተር፤የሚሰማትን የመገለል ስሜት በሙዚቃዋ ስትከላከልና ስትዋጋ እንደኖረች አልደበቀችም፡፡ የውትድርና አገልግሎቷን ከጨረሰች በኋላ ኑሯዋን በቴል አቪቭ በማድረግም ወደ ትወና ሙያ እንደገባች ትናገራለች፡፡ በተዋናይነቷ የቴሌቭዥን ፊልሞች የሰራችው ኤስተር፤ ከአራት በላይ የሙሉ ጊዜ ፊልሞች ላይ መተወኗንና “ስቲል ዎኪንግ” እና “ዘ ሩቫቤል” የተባሉት ሁለት ፊልሞች በእስራኤል ፊልም አፍቃሪያን ዘንድ ተወዳጅነት ያተረፉ መሆናቸውን ገልፃለች፡፡

የአቫታር ፊልም ዲያሬክተር ጀምስ ካሜሮን እና የሚያከፋፍለው ኩባንያ “20 ሴንቸሪ ፎክስ” በኮፒራይት ጥሰት ለአራተኛ ጊዜ መከሰሳቸውን የዲጂታል ስፓይ ዘገባ አስታወቀ፡፡ በፊልሙ ላይ የሚታዩት የሌላ ዓለም ፍጡራን የሆኑ ገፀባህርያት “ከእኔ በተወሰዱ የጥበብ ሥራዎች የተሰሩ ናቸው” ያለው ዊልያም ሮጀር ዲን የተባለ እንግሊዛዊ ሰዓሊ፤ ሰሞኑን ክስ በመመስረት የ50 ሚሊዮን ዶላር ካሳ እንዲከፈለው ጠይቋል፡፡ ከሁለት ወራት በፊት አንድ ሌላ አርቲስት ፊልሙ የፈጠራ ሃሳቤን ሰርቋል በሚል ክስ መመስረቱ የተዘገበ ሲሆን ከዓመት በፊትም “ባትስ ኤንድ በተርፍላይስ” ከተባለው መፅሃፌ የአቫታር ፊልም ጭብጥ ተወስዶብኛል ሲል አንድ ደራሲ ከስሶ እንደነበርም ተወስቷል፡፡ሆኖም የፊልም ዳሬክተሩ ጀምስ ካሜሮን፤ ሰሞኑን ፊልሙን ሙሉ በሙሉ ከራሱ ምናባዊ ሃሳብ አመንጭቶ እንደሰራው የሚገልፅ ባለ 45 ገፅ ሰነድ ይፋ አድርጓል፡፡ በ2009 እ.ኤ.አ ላይ በ237 ሚሊዮን ዶላር በጀት ተሰርቶ በመላው ዓለም ከ2.8 ቢሊዮን ዶላር በላይ ያስገባው አቫታር፤ በገቢው ከፍተኛነት የምንግዜም ፊልሞች የገቢ ደረጃን በአንደኛነት

ጀምስ ካሜሮን በኮፒራይት ጥሰት ለ4ኛ ጊዜ ተከሰሰ

እንደሚመራ ይታወቃል፡፡ ዲያሬክተሩ ሰሞኑን በሰጠው መግለጫ፤ ከእንግዲህ ስራው የአቫታር ተከታታይ ክፍል ፊልሞችን መስራት እና ከፊልሙ ጋር ተያያዥ ንግዶችን ማከናወን እንደሆነ ገልጿል፡፡ ባለፉት 10 ዓመታት ከአቫታር ፊልም ባሻገር 5 ጥናታዊ ፊልሞችን የሰራው ጀምስ ካሜሮን፤ ቀጣዮቹ ክፍል 2 እና 3 የአቫታር ፊልሞች በአንድ ወጥ ስክሪፕት እንደሚሰሩ የገለፀ ሲሆን አቫታር 2 በ2015 ፤ አቫታር 3 በ2016 እንዲሁም አቫታር 4 በ2017 ለእይታ ለማብቃት እንደሚያስብ ገልጿል፡፡

በርካታ የሱፐር ሂሮ ፊልሞች ይጠበቃሉ

ዓመታት 28 የሱፕር ሂሮ ፊልሞች ሰርቶ 11 ቢሊዮን ዶላር ዲሲ ፒክቸርስ ባለፉት 35 ዓመታት 23 ሰርቶ 4 ቢሊዮን ዶላር ገቢ እንደሰበሰቡ አመልክቷል፡፡በቅርቡ ለእይታ ከሚበቁ የሱፐር ሂሮ ፊልሞች መካከል ሰሞኑን የሚመረቀው “ኪክ አስ 2”፤ ከወር በኋላ ለመጀመርያ ጊዜ ለእይታ የሚበቁት “ሪፕድ”፣ “ዘ ዎልቨሪን”፤ በሚቀጥሉት ሦስት ወራት ደግሞ “300፡ ራይዝ ኦፍ አን ኢምፓዬር”፣ “ሬድ 2”፣ “ሮቦካፕ ሪቡት” ፣ “2 ገንስ” ፣ “ሲን ሲቲ፡ ኤዴም ቱ ኪል ፎር” እና “ቶር ፡ ዘዳርክ ዎርልድ” ተጠቃሾች ናቸው፡፡ በ2014 ላይ “ኖህ” ፣ “ካፒቴን አሜሪካ፡ ዘ ዊንተር ሶልጀር”፣ “ዘ አሜዚንግ ስፓይደር ማን 2” ፡ “ኒንጃ ተርትልስ”፣ “ትራንስፎርመርስ 4” እና “ኤክስ ሜን” እንዲሁም በ2015 ደግሞ “ዘ አቬንጀርስ 2” እና “አንትማን” የተባሉ የሱፐር ሂሮ ፊልሞች ለእይታ እንደሚበቁ ይጠበቃል፡፡እንኳን ደስ አለሽ!

Page 19: Issue-703.pdf

Website: www.addisadmassnews.com

አዲስ አድማስ ሰኔ 29 ቀን 2005 ዓ.ም ገፅ 19

በ ታ ዋ ቂ ው አሜሪካዊ ደራሲ ዋላስ ዲ. ዋትልስ የተጻፈው The Science of Getting Rich በ ጋ ዜ ጠ ኛ ና ተርጓሚ ኢዮብ ካሣ የብልጽግና ሳይንሳዊ መንገድ በሚል ርዕስ ተተርጉሞ የታተመ ሲሆን በመጪው ሳምንት ገበያ ላይ ይውላል፡፡ ዘመን ተሻጋሪ የብልጽግና መርህ መሆኑ የተመሰከረለት መጽሃፉ፣ በመላው አለም በሚሊዮን ኮፒዎች የተሸጠውን The secret ጨምሮ፣ ለሌሎች ታዋቂ የብልጽግና መፃህፍት መነሻ እንደሆነ ይነገራል፡፡

ዋላስ ዲ. ዋትልስ በዘመናችን የስኬትና የብልጽግና ሊቃውንት ዘንድ በቀዳሚነት የሚጠቀስ ደራሲ ሲሆን በስኬትና በብልጽግና ንድፈሃሳቦችና ተግባራዊ ትምህርቶች ተጽእኖ ፈጣሪ መሆኑ ይነገርለታል፡፡

ጋዜጠኛና ተርጓሚ ኢዮብ ካሣ፣ የአዲስ አድማስ ጋዜጣ ምክትል ዋና አዘጋጅ ሲሆን ከዚህ ቀደም ተአምራዊ ሃይል እና ታላላቅ ህልሞች የተሰኙ በስኬትና በብልጽግና ላይ ያተኮሩ ሁለት የጋራ ትርጉም መፃህፍትን ለንባብ ከማብቃቱ በተጨማሪ፣ በአዲስ አድማስ ጋዜጣ ላይ በሚያወጣቸው የስኬትና የብልጽግና ጽሁፎቹ ይታወቃል፡፡ ፖለቲካ በፈገግታ እና የመፅሐፍ ቅዱስ ታሪኮች ለልጆች የተሰኙ መፃህፍትንም ለንባብ አብቅቷል፡፡ ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ በገበያ ላይ የሚውለው የብልጽግና ሳይንሳዊ መንገድ ፣ 179 ገጾች ያሉት ሲሆን ዋጋው 40 ብር ነው፡፡ በቅርቡም የዓለማችን ባለፀጎች ያልተነገረ የገንዘብ ምስጢር የተሰኘ መፅሃፉ ለህትመት እንደሚበቃ ለማወቅ ተችሏል፡፡

ጥበብኪነጥበባዊ ዜና

መልካሙ ተክሌ

ሌሊሣ ግርማ

ፍርሐት ወደ ገፅ 26 ዞሯል

… እያነበበ ነበር የቆየው እስከ ምሽቱ አራት ሰአት ድረስ፡፡ መፅሐፍ በህይወት ዘመኑ ከሶስት የበለጠ አንብቦ አያውቅም፡፡ ሶስተኛውን ሊጨርስ ትንሽ ነው የቀረው፡፡ ሦስት ሰአታት ማንበብ ቢቀጥል ይጨርሰዋል፡፡

ዝናቡ ድንገት ሲቆም ፀጥታ በቤቱ ውስጥ እና ዙሪያ ሰፈነ፡፡ ከጫጫታ ለመራቅ ብሎ ነው ከሳምንት በፊት እዚህ አገር ቂጥ፣ ጫካ መሐል ገና ጭቃው ያልደረቀ ቤት በ600 ብር የተከራየው፡፡ ከጫካው በታች ወንዝ አለ፡፡

ፀጥታው ለምን ድንገት እንደረበሸው ሊገባው አልቻለም፡፡ መፅሐፉን አጥፎ በሰላ ጆሮው ማድመጥ ያዘ፡፡ የቤቱ ጣሪያ ላይ የባህር ዛፍ ቅጠል ይራገፍና ይንገዋለላል፡፡ ደስ የማይል ስሜት ተሰማው፡፡ መፅሐፉን ዘርግቶ ማንበብ ቀጠለ፡፡

ከአረቄ ለመራቅ ሲል ነበር ከድሮ ሰፈሩ ወጥቶ ጫካ የገባው፡፡ ያሸፈተው የአረቄ ሱስ … ከፋኖ ጫካው እየጠራ፣ ሲያስወጣው ቁርጥ ውሳኔ ወሰነ። የዛሬዋን እለት ከቤት ንቅንቅ ሳይል እንደሚውል ለራሱ ማለ፡፡ አረቄው ሲጠራው አልሰማም ብሎ መፅሐፉን አይኑ ላይ ከልሎ፣ ሲያነብ - ሲያነብ። በማያስቀው ታሪክ ሲስቅ … ባልገባው ጥልቀት ሲዘፈቅ … “መክሸፍ እንደ ኢትዮጵያ ታሪክ” ይላል የመፅሐፉ አርዕስት፡፡ ዋናው ነገር መፅሐፉን አንብቦ መጨረሱ ብቻ ነው፡፡ ከዋናው ነገር በላይ ደግሞ በመፅሐፉ የአረቄውን በል-በልታ አሻፈረኝ ብሎ መተኛት፡፡ ተሳክቶለታል፡፡ ከምሽቱ አራት ሰአት ሞልቷል፡፡ “አረቄ ሱስ የለውም ማለት ነው” ሲል ቆየ፤ ከምሽቱ አንድ ሰአት ጀምሮ፡፡ መፅሐፉ ላይ ያሉ የተወሰኑ አረፍተ ነገሮችን ያዋሰው ሰው ነገ ቢያወራው በወሬው እንዲሳተፍ ይዟል፡፡ ሸምድዷል፡፡ ለወሬ ያህል፡፡ ከወሬ ጃንጥላ ውጭ መሆን ያስፈራዋል፡፡

መፅሐፉ ስለምን እንደሆነ ማወቅ አይጠበቅበትም፡፡ ስለ መክሸፍ ነው፤ እሱ ዛሬ በመፅሐፉ አማካኝነት የአረቄ ሱሱን ማክሸፍ ችሏል። ስለ “መክሸፍ” በማንበብ “ማክሸፍ” ይቻላል፡፡

ፀጥታው ረበሸው፡፡ ንባቡን መቀጠል አልቻለም።

“ፍሬ ነገሩ ኢጣልያኖች በአርባ አመት ጊዜ ውስጥ በጣም ተለውጠው፣ ተሻሽለው፣ በልፅገውና ጠንክረው …” ብሎ ሊቀጥል ሲዳዳ… ጆሮው ከውጭ የሆነ ነገር ያሰማውና ወደ ውጭ ይጠራዋል፡፡ የልቡን ምት እያደመጠ ከበስተውጭ ያለውን በአልጋው ውስጥ ሆኖ እየተንጎራደደ መመርመር ጀመረ፡፡

ፀጥታውን አልወደደውም፡፡ ወደ መፅሐፉ ተመልሶ “ወኔና ጀግንነት ብቻውን እንደማያዋጣ …” ብሎ ሊቀጥል ሲል በመፅሐፉ አናት ላይ በጨረፍታ በሚታየው የእይታው ክልል … አንድ ነገር ውልብ አለበት፡፡ መፅሐፉን አስቀመጠ፡፡ በተጠንቀቅ፡፡ የፍርሐት ዛር ወረደ፡፡

አድብቶ ሲያደምጥ ምንም የለም፡፡ አልጋውን በእጁ ለመነቅነቅ ሞከረ፡፡ ምናልባት … ሹክሹክታው በአልጋው መወዛወዝ የመጣ ሊሆን ይችላል፤ ብሎ ስለተመኘ፡፡ ድምፅም መፍጠር ስለፈለገ ነው፡፡ ፀጥተው ረብሾታል፡፡

በክፍሉ ውስጥ ያሉትን እቃዎች በጥንቃቄ ቃኘ። ምን አልባት፤ ውልብ ያለው አይጥ ከሆነ … እንደገና ሲንቀሳቀስ እጅ ከፍንጅ ለማየት እንዲችል፡፡ አይጥ ከሆነ፤ ብዙ ተደብቆ መቆየት አይችልም፡፡ ሲቆረቁር ከቆይታ በኋላ ይሰማዋል፡፡ ወይ ጥግ ጥጉን እንደ አይነ ስውር … ግርግዳውን እየታከከ ሲሄድ ያየዋል፡፡

ብዙ ጠበቀ አፍጥጦ፡፡ ሁሉንም መስማት እና ማየት እንዲችል አይኑን ሁሉም ቦታ እንደ ብይ በተነው፡፡ ጆሮውን ደግሞ በኩኩሉ ጨዋታ እንደተደበቁ ህፃናት በየስርቻው አስደፈጣቸው፡፡ ምንም የለም፡፡

“ሙዚቃ ለምን አልከፍትም?” አለ ጮክ ብሎ። ከአልጋው ወርዶ ወደ ሬዲዮኑ ግን ማምራት አስፈራው፡፡ በእሱ እና በሬዲዮኑ መሀል ያለውን ፀጥታ እንዴት ይሻገረዋል?

አረቄ ባለመጠጣቴ ምክንያት የተፈጠረ ፍርሐት ነው፤ ብሎ ገና ከማሰቡ … ከውጭ ሳቅ የሰማ መሰለው፡፡ ልክ ከበሩ ደፍ ስር፡፡ የሆነ ሰው የሱን ሀሳብ ሲያደምጥ ቆይቶ ድንገት በመጨረሻው ሀሳብ

ፍርሐት አጭር ልብወለድ

ሳቁ ያመለጠው ነው የሚመስለው፡፡ ጭንቅላቱን ወዘወዘ፤ ራሱን ከፍዘት ለማንቃት።

ተነስቶ ወደ በሩ ሄደ፡፡ በሩን ከፈተ፡፡ ንፋስ እና ቅዝቃዜ አንድ ላይ አሸማቀቁት፡፡ ሸሚዙን እየቆለፈ በግማሽ ሰውነቱ ወደ ውጭ ብቅ አለ፡፡ ዙሪያውን ተመለከተ፡፡

የኢትዮጵያ ጀግኖች ትዝ አሉት፡፡ የታንክ አፈ ሙዝን … በጎራዴ ለመቁረጥ የሚሞክሩት … በሙከራቸው ላይ ሲሞቱ የተመለከቱት ደግሞ ከኋላ እየፎከሩ የሟቾቹን ሙከራ በሞታቸው ለመድገም የሚንደረደሩት …፡፡

ማን ይሄንን ታሪክ በሬዲዮ ሲተርክ እንደሰማ ለማስታወስ እየጣረ ወደ ደጅ ራቅ ብሎ ወጥቶ ለመንጐራደድ ራሱን አደፋፈረ፡፡ ታች ማዶ ያለው ወንዝ አይታይም፡፡ ለነገሩ ወንዝ ተባለ እንጂ በቁሻሻ ፌስታል የተሞላ የድቡልቡል ድንጋዮች ክምችት ነው፡፡ ወንዝ መፍሰሻውን ፈርቷል፡፡ ደርቋል፡፡ ከሽፏል፡፡

መጥፎ መንፈሶች ከወንዝ አካባቢ ይመጣሉ፤ ብሎ ስለሚያምን ነው ታቹ ያስፈራው፡፡ ጤናማ ምሽት ነው፡፡ ሰማዩም፤ መሬቱም፣ ዛፉም … የአፈሩ ሽታም መሬቱም … ሀገሩም ከእግሩ ስር አሉ፡፡ ወደ ቤቱ ተመለሰ፡፡ እየተመለሰ ከኋላው የሆነ ጥላ ከበደው፡፡ በፍጥነት ዞሮ አየ፡፡ በጨለማ ውስጥ ጥላ የለም፡፡ ግን ይሄንን ማወቁ የልቡን ቅዝቃዜ አልቀየረለትም፡፡ ደግሞ ጥላው በእግሩ የቆመ መስሎ ተሰማው፤ በአይኑ ባያየውም፡፡

በሩን ዘግቶ ውስጥ ገባ፣ በፍጥነት (የሆነ ነገር ሸሚዙን ይዞ ሳይጐትተው በፊት) ወደ አልጋው እየሄደ ድንገት ደርቆ ቀረ፡፡ ሽምቅቅ፡፡

አልጋው ስር ሁለት ጫማዎች አሉ፡፡ ጫማዎቹ የእሱ አይደሉም፡፡ እና ታዲያ ምን የሚያስፈራ ነገር አለው? የልቡ ምት የጆሮውን ታምቡር ሊሰነጥቀው ነው፡፡ ጫማ ሳይሆን እግር ያየ ነው የመሰለው፡፡

ትላንት ማታ፤ እሱ ከተማ ሄዶ አረቄ ሲጠጣ፣ አማኑኤል ደውሎ የቤቱን ቁልፍ እንዲሰጠው ሲጠይቀው ትዝ አለው፡፡ በስካሩ መሃል… ቁልፍ በሩ ስር መልሶ እንዳስቀመጠ ነግሮታልም፡፡

አማን፤ ሴት ጓደኛውን በወንድ ጓደኛው አልጋ አቀባበል ሊያደርግላት ፈልጐ ነው ቁልፍ የጠየቀው።

እሱ በአረቄ ሰክሮ ሲመለስ አማንና ሴቲቱ የአቀባበል ስነስርዓቱን አጠናቀው፣ አልጋውን እንደነበረ ወጥረው …ወጥተዋል፡፡ አረቄ የማስረሳት ሀይል አለው፡፡ የአማን ጫማ ሊሆን ይችላል፤ ብሎ ገመተ፡፡ ግን አማኑኤል ምን ተጫምቶ ሄደ? ተጫምቶ የመጣውን በእሱ አልጋ ስር ትቶ? ምናልባት ሚስቱ አዲስ ጫማ ገዝታለት ይሆናል፤ ብሎ ተጽናና። በልቡ ምት የተደፈነው ጆሮውም ተከፈተለት፡፡ ቀልቡም ረጋ አለ፡፡ አልጋው ላይ ወጥቶ ተጋደመ፡፡

“የኔን ጫማ መቼም አድርጐ ሊሄድ አይችልም፤ እኔ አንድ ጫማ ብቻ ነው ያለኝ…” ማሰቡን ቀጥሏል።

አልጋው ስር አጐንብሶ ማየት አልፈለግም። ጫማ ብቻ ሳይሆን በጫማው ውስጥ እግር ቢኖረውስ? ምን ነክቶኛል፤ አለ ለራሱ፡፡ ጭንቅላቱን ወዘወዘ፡፡ የሆነ ነገር የግርግዳውን ዙሪያ እየጫረ

በቀስታ ሲያልፍ ሰማ፡፡ እየጫረ የሚሄደው ነገር ልክ የሱ በር ጋ ሲደርስ ቆመ፡፡…እየጫረ የመጣው ነገር ዝም አለ፡፡ እሱ አፉን ከፍቶ እየጠበቀው ነው፡፡ በሩን ቢያንኳኳበትስ?...እጀታውን ቢሞክርስ?...አረቄ ማን ተው አለኝ?...እያለ ያስባል፤ ተጨማሪ ድምጽ በጆሮው አስልቶ ጠበቀ፡፡

ውሻ ሊሆን ይችላል… የምሽት ድምፆች በፀጥታው ውስጥ ይጐላሉ…አይደል እ? እ?...ራሱን ጠየቀ፤ ራሱን ለማጽናናት፡፡ በጭንቅላቱ ውስጥ የተፈጠሩ ረብሻዎች እንደሆኑ እርግጠኛ ሆነ፡፡ በራሴ ጭንቅላት ውስጥ የተፈጠሩ ድምፆች መሆናቸውን ማወቁ ራሱ ጤነኝነቴን ይመሰክራል፤ ብሎ ምራቁን ዋጠ፡፡

“የፍርሐቴ ምንጭ ራሴ ነኝ፡፡ ነቅቼበታለሁ። ከተነቃ ከሽፏል፡፡ ከሽፏል!...” አለ ጮክ ብሎ፡፡ እያወራም ልቡ ግን ፍርሐት - ፍርሐት ይለዋል፡፡ ፍርሐቱ ከሱ ውጭ ላለ ሀገር፣ ወይ ነገር ሳይሆን፤ ለራሱ ነው፡፡ ፍርሐቱ ለአሁኗ ሰአት ናት፡፡ “የአሁናን ሰአት ካለፋት ፍርሐቱ እንደሚሸነፍ እርግጠኛ ነው፡፡ ዛሬን ማለፍ ከቻለ ደግሞ ነገ ያን ያህል አያስቸግረውም፤” እያለ የሚያስብ የሆነ ተራኪ ድምጽ በውስጡ አለ፡፡ ልክ እንደ ሬዲዮ ነው ድምፁ የሚተርከው፡፡ ሬዲዮው አልበራም፡፡

“ፍርሐት ከሽፏል” አለ፡፡ ብርድልብሱን ለበሰ፡፡ “መክሸፍ እንደ ኢትዮጵያ ታሪክ” የሚለውን መጽሐፍ በእጁ ዳብሶ አልጋው ላይ አጣው፡፡ አልጋው ስር ወድቋል፤ ማለት ነው፡፡ ነገ ጠዋት ያነሳዋል፡፡ ዛሬ ማታውኑ ግዴታ አንብቦ መጨረስ አይጠበቅበትም። የሆነ ሳቅ አሁንም የሰማ መሰለው። ከደጅ፡፡ ግን ብዙም አላስደነገጠውም፡፡

የሚያደርጋቸውን ነገሮች በደንብ መታዘብ አለበት፡፡ መጽሐፉን አልጋ ስር ፈለገው፡፡ የአማን ጫማ ብቻ ነው ያለው፡፡ አልጋውን አራገፈ፡፡ ወደ በሩ ተመለከተ፡፡ በሩ ጐን ባለው በርጩማ ላይ ተቀምጧል፡፡ “መክሸፍ እንደ ኢትዮጵያ ታሪክ”… የሱም የጭንቀት፣ የፍለጋ ታሪክ መጽሐፉን በማግኘት ከሸፈ፡፡ ቅድም በሩን ከፍቶ ሲወጣ በርጩማው ላይ ጣል ማድረጉ ትዝ አለው፡፡

ራዲዮኑ መጫወት ጀምሯል፡፡ በቀስታ። አሁን አልደነገጠም፡፡ ትዝ ይለዋል ሲያበራው። ቤቱን ከውጭ የሚጭረውም ውሻ ነው…ከውጭ የሚስቀው ድምጽም የዛፎቹ ነው፡፡…

“ለምን አረቄ ጠጪ ሆንኩ? የኑሮ፣ የብቸኝነት፣ የደስታ ማጣት፣ ባይተዋርነቴ ጣጣ እንዳያሳስበኝ፤ እንዳያሳብደኝ፡፡ ለምን አረቄ አቆምኩ? አረቄው በዝቶ፤ ስራ አላሰራ፣ ምግብ አላስበላ፣ ከሰው ጋር አላስማማ ስላለኝ፡፡ ለምን አረቄ መጀመር እንደገና ፈለግሁ…ፍርሐት፣ ፀጥታ፣ የራሴ አእምሮ አንድ ላይ አብረው እንዳያሳብዱኝ፡፡” እያለ ለራሱ ያሰላስላል። “ማበድ ከሆነ በሁሉም ጐኑ የተጠመደብኝ…እኔ ደግሞ አላብዳትም” ብሎ እጁን ጨብጦ ፎከረ፡፡

በዚህ መሀል ሽንቱ ወጥሮታል፤ “እንደ ትንሽ ልጅ ቤት ውስጥ በማስታጠቢያ አልሸናም? ቆሜ ነው የምሸናት፡፡ እደጅ፡፡ ከራሴ ቤት ራቅ ብዬ…ጅብ የለ፣

ነዋሪነቱ በሰሜን አሜሪካ በሆነው ገጣሚ ሳምሶን ይርሳው ጌትነት የተጻፈው ምልክት የተሰኘ የግጥም መድበል የገጣሚው ቤተሰቦችና የጥበብ አፍቃሪዎች በተገኙበት ትናንት በብሄራዊ ቤተ መዛግብት አዳራሽ ተመረቀ፡፡ከዚህ በፊት በአሜሪካ የተመረቀው የግጥም መድበሉ 100 ገጾች ያሉት ሲሆን፣ በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ የሚያጠነጥኑ ግጥሞች ተካተውበታል፡፡ ለገጣሚው የመጀመሪያ ስራው እንደሆነ የተነገረለት መድበሉ በ23 ብር እየተሸጠ ይገኛል፡፡

“የብልጽግና ሳይንሳዊ መንገድ” በገበያ ላይ ይውላል

“ምልክት” የግጥም መድበል ትናንት ተመረቀ

በየዓመቱ አዳዲስ የሥነ ጽሑፍ ሥራዎቹን የ ሚ ያ ስ ነ ብ በ ን ታዋቂው ወጣት ደራሲ ይስማዕከ ወርቁ፣ ዘንድሮም “ክቡር ድንጋይ” የተሰኘ ረጅም ልቦለድ ለንባብ አቀረበ፡፡ ባለ 200 ገፁ መጽሐፍ ለገበያ የቀረበው በ45 ብር ነው፡፡ ደራሲው ከዚህ ቀደም በ100ሺ ቅጂዎች የተቸበቸበለትን ዴርቶጋዳን ጨምሮ ራማቶሐራና ተከርቸም ሌሎች የረዥም ልቦለድ ሥራዎች ለንባብ ያቀረበ ሲሆን፤ በግጥም መድበሎቹም ዝናን ማትረፉ ይታወቃል፡፡

የይስማዕከ ወርቁ፣ “ክቡር ድንጋይ” ልቦለድ ለገበያ ቀረበ

በሻሸመኔ ከተማ እና አካባቢዋ ኪነጥበባት አፍቃሪዎች የተቋቋመው “ከአድማስ ፊት” የኪነጥበብ ማህበር 43ኛ ወርሃዊ ዝግጅቱን እና የተመሰረበትን አምስተኛ አመት እንደሚያከብር አስታወቀ፡፡ ነገ ከሰዓት በኋላ በከተማዋ ሁለገብ አዳራሽ በማህበሩ አባላት እና የአካባቢው ማህበረሰብ በተጨማሪ አርቲስት ሜሮን ጌትነት እና አርቲስት ዘላለም ኩራባቸው በክብር እንግድነት ይገኛሉ፡፡ በዝግጅቱ የማህበሩን የአምስት ዓመት ጉዞ የሚያሳይ ዘጋቢ ፊልም የሚቀርብ ሲሆን ሽልማት የሚያሰጥ የግጥም ውድድርም ይኖራል፡፡

“ከአድማስ ፊት” 43ኛ ዝግጅቱን ያቀርባል

Page 20: Issue-703.pdf

Website: www.addisadmassnews.com

አዲስ አድማስ ሰኔ 29 ቀን 2005 ዓ.ም ገፅ 20

ደረጀ በላይነህ

ፍልስምና ወደ ገፅ 26 ዞሯል

ሕይወት የጤዛ ጠብታን ያህል አንሣ የምትታሰበን ጊዜ አለ፡፡ በተለይ ፍልስፍናና ሃይማኖት ውስጥ! ከዚያ ጤዛ ውስጥ

ግን ፀሐፍት ዝንታለም የሚኖር ቀለም ያወጣሉ። ያንን ያወጡትን ቀለም በየመልኩ እንደየዘመኑ ያቀጣጥሉታል፡፡ ትውልድ ደግሞ ያንን ምድጃ አቅፎ ይቃጠላል፤ ወይም ይሞቃል…ለዚህ ነው ጠለቅ ያሉ ፍልስፍናዊ ሃሳቦችና ፍልስፍና የተሻሹ፣ ወይም የተቀላቀሉ ግጥሞችም በየጅማቶቻችን ሥር እየነደዱ የሚያነድዱን! ሕያው የሆነ አሳቢን ማለቴ እንጂ ፍሙ ቢጫንባቸው ሕይወታቸውን ሙሉ በድብርት የሚተኙ ሰዎች እንደሚበዙ ዘንግቼው አይደለም! ጥበብ የማንን በር እንደምታንኳኳ ይታወቃል፡፡ ከጭራሮ አጥር ጋር አትቀልድም…ከብረት በር ጋር ትቧቀሳለች እንጂ!

ዛሬ የምዳስሰው መጽሐፍ የፍልስፍናውና የሃይማኖቱን ሰፈር ስለሚነካ ነው ልቤ እየዘለለች ጥበብ አጥር ላይ ፊጥ ማለት ያማራት፡፡ ስለጥበብ አናወራም፡፡ ጥበባዊ መዐዛ ስላለው የቴዎድሮስ ተክለአረጋይ መጽሐፍ ግን እኔ ጥቂት እላለሁ። አንባቢዎቼ ደግሞ ያነብቡና እኔንና መጽሐፉን እያመሳከሩ ያነብባሉ፡፡

ቴዎድሮስ “ፍልስፍና 1 እና 2” እያለ የሀገራችንን ሰዎች ፍልስፍናና እምነት በመፈልፈል ወደ 3ኛ አድርሶናል፡፡ ጋዜጠኛና ፀሐፌ ተውኔቱ ቴዎድሮስ በተለያዩ መጽሔቶችና ጋዜጦች ላይ በሚሠራበት ጊዜ አንጀት የሚያርሱ ቃለ ምልልሶችን በድፍረት ስለሚሰራ ብዙዎቻችን በአድናቆት አንገታችንን ነቅንቀንለታል፡፡ ታዲያ እነዚህ መጽሐፍትም በቃለ ምልልስ መልክ የቀረቡ ስለሆነ ሸጋ አድርጐ ይሠራዋል የሚል እምነት ይዘን ያነበብን ይመስለኛል። በእነዚህ መጽሐፍት ውስጥ ትልቁ ነገር አጠያየቁ ቢሆንም

“የፍልስምና ፫” መረቦችተገቢ ሰዎችን አስሶ ማግኘትም ቀላል ጉዳይ አይደለም፡፡ ይህንን መሠረት አድርጐም ባሁኑ “ፍልስፍና ፫” - የፍልስፍና መምህርና የቀለም ተመራማሪ፣ የአዕምሮ ሀኪሞች፣ የሥነ ከዋክብት አዋቂ (ወዳጅ) እና ሌሎችን አካትቶ አቅርቧል፡፡

የኔ ትኩረት ግን ወደሰው ልጆች ጥያቄ ቀረብ የሚሉትንና ነፍስን የሚንጡትን ፍልስፍና ጉዳዮች ማየት ነው፡፡ በዚህ ትኩረት ደግሞ አቶ ዜና ላይኩኝ (የእምነት የለሽነት ተከታይ) አቶ ተፈሪ ንጉሤ (የገዳ ሥርዓት ተንታኝ)፣ ቀዳሚዬ ይሆናሉ፡፡ የጌታሁን ሄራሞ (ኬሚካል ኢንጂነር) የቀለም ትንታኔ ጥሞና የሚጠይቅ፣ አዲስና ያልተለመደ ሳይንስ ስለሆነ እርሱን ለብቻ ማጤን የሚያስፈልግ ይመስለኛል፡፡ ሌሎቹም ብዙ መልክ አላቸው፡፡

የኔ ቀዳሚ ተመስጦ ግን የገዳ ሥርዓት ተንታኝ ላይ ነው፡፡ ስለገዳ ሥርዓት አቶ ተፈሪ ያነሱት ነገር “ኢትዮጵያዊ በመሆኔ እኮራለሁ” ለሚለው አባባል ትልቅ አቅም የሚጨምር ይመስለኛል። የኦሮሞ ሕዝብ የገዳ ሥርዓት ከግሪክ ሥልጣኔ ዘመን የቀደመ መሆኑን አቶ ተፈሪ መናገራቸው፤ ቴዎድሮስም ይህንን ነገር ጉዳዬ ማለቱ በራሱ ትልቅ ደስታ ይፈጥራል፡፡ ኢትዮጵያውያን የአክሱም ሀውልት፣ የላሊበላና የፋሲል ግንብ ባለቤቶች ብቻ ሳይሆን የዴሞክራሲም ማህፀኖች መሆናችን… አቦ ደስ ይላል! ይህንን ነገር ከጓዳ አውጥቶ በአደባባይ መናገርም በራሱ ታሪክ ነው፡፡ በጣም የሚገርመው ደግሞ አንድ ሰው አባ ገዳ ሆኖ ለመመረጥ የኦሮሞ ብሔር ተወላጅ ብቻ መሆን የለበትም፤ በባህሉ መሠረት ሌላው ብሔርም በጉዲፈቻና በሌላም መንገድ የብሔሩ አባል ሆኖ ሊመረጥ ይችላል፡፡ (ለመሆን የሚጠበቅበት ጊዜ ግን አለ)

አቶ ተፈሪ አንድ ልጅ ወደ አባገዳነት የሚደርስበትን እርከን ሲናገሩ “አንድ ሕፃን እስከ 8 ዓመቱ ድረስ “ኢቲመኮ” ነው የሚባለው፡፡ እነዚህ

ሕፃናት ገና እንደተወለዱ በዚያ ዓመት ያለው አባ ገዳ አባላት ነው የሚሆኑት፡፡ ልጆቹ በዚህ ዕድሜያቸው የሚማሩት ዋናው ነገር ማህበራዊ ግንኙነት ነው። ህዝቡን ማወቅ፣ ባህሉንና ቋንቋውንም ማወቅ አለባቸው፡፡ እንዲታወቁ ሊማሩ ግድ ይላል፡፡ ከ9-16 ዓመት እድሜ ያሉት ደግሞ “ደበሌ” ይባላሉ። እነሱ ደግሞ ልምምድ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል። ልምምዱ ውሃ ዋና፤ ፈረስ ግልቢያ፣ ከብቶች መጠበቅ፣ መላላክ የመሳሰሉት ናቸው፡፡ ደበሌ ፎሌ፣ ዶሪ የሚባሉትን የዕድሜ እርከኖች ሲያልፉ 40 ዓመት ይሞላቸዋል፡፡ ከዚያ ከ41-48 ያለው የነርሱ አባገዳ ይሆናል፡፡ ለምሳሌ በሕብረተሰቡ ውስጥ የፍትህ መጓደል ሲከሰት በቀጥታ የሚመለከተው በፎሌ የዕድሜ ክልል ያለውን ነው፡፡ በኦሮሞ ብሔር የውሃ ዋና፣ ተኩስና የመሳሰሉት ሥልጠና የሚወሰድበት ዕድሜ ይህ ነው፡፡ 40 ዓመት ሲሞላው ሕዝብን ለማስተዳደር ይወዳደራል፡፡ ሌላው አስገራሚ ነገር አንድ ሰው ምንም ያህል በሕዝቡ ቢወደድና አስተዳደሩ የተመቸ ቢሆን ከስምንት ዓመት በላይ ሥልጣን ላይ እንዳይቆይ ሥርዓቱ ይከለክላል፡፡ ምርጥ ዴሞክራሲ!

የአቶ ተፈሪ ቃለ ምልልስ ስለ ገዳ ሥርዓት ሲያወራ የሴቶችን መብት፣ የሕፃናት ፓርላማ ጉዳይ ሁሉ ያነሳል፡፡ ለገዳ ሥርዓት ይህ አዲስና ብርቅ አይደለም በማለት፡፡ ያ ብቻ አይደለም ስለግሪክ ፍልስፍና ቀዳሚ ያለመሆን ሲናገር እንዲህ ይላል፡-

“ሶቅራጥስ ግብጽ መጥቶ ነው የተማረው። ሶቅራጥስ አንድም ነገር አልጻፈም፡፡ ፕሌቶ ነው የጻፈው፡፡ ፕሌቶ ደግሞ አርስቶትልን ያስተምራል። ታሪክ የሚያረጋግጥልን፣ ብዙ ተሸላሚ መጽሐፍት ለምሳሌ ማርቲን ባርናል የፃፈው The Black Atena” መጽሐፍ የሚያሳየን የግሪክ ፍልስፍና የሚባለው የአፍሪካ ፍልስፍና እንደሆነ ነው፡፡ ጆርጅ ጀምስ “The Stolen legacy” የሚለውን መጽሐፍ

ጽፎ በአምስተኛው ቀን ተገድሏል፡፡ ያስገደለው የግሪክ ፍልስፍና የግሪክ ሳይሆን የአፍሪካ ፍልስፍና መሆኑን በግልጽ ስላሳየ ነው፡፡

አቶ ተፈሪ ብዙ ጉዳዮችን አንስተዋል፡፡ ከገዳ ጋር በተያያዘ ስለዋቄ ፈና ተንትነዋል፡፡ እኔን ያረካኝና ያስደሰተኝ ጠቅለል ያለው የገዳ ሥርዓት ዴሞክራሲያዊ ውልደትና ውበት በሀገራችን መሆኑ ነው፡፡ ምናልባት በሌሎቹ ነገሮች ወደኋላ እንደተመለስነው በዚህም ወደኋላ ተመልሰናል የሚያሰኝ ይመስለኛል፡፡ ይሁንና በእኒህ ተንታኝ ላይ ያየሁዋቸው ችግሮች አሉ፡፡ አንደኛው “እምነቴ ፕሮቴስታንት ነው” ማለታቸው paradox (አያዎ) ነው፡፡ ምክንያቱም ለምሳሌ ስለሚነትኑት የዋቄፈና እምነት ሲያወሩ ሰይጣን የሚባል ነገር የለም፤ ከሁሉ በላይ የሆነ አምላክ ብቻ ነው እያሉ አጠቃላይ የክርስትናንና ሌሎቹንም እምነቶች በዋቄ ፈና ወገን ሆነው ይናገራሉ፡፡ መልሰው ደግሞ ጓደኞቼ ስለ ክርስቶስ አወሩልኝና ፕሮቴስታንት ሆኜ ነበር ይላሉ፡፡ የሚያምኑት ግን በዋቄፈና ነው፡፡ ስለዚህ የሚጫወቱበትን ሜዳና መለያ ቀይረዋል፡፡ አሁን ያሉበትን እምነት እንጂ ቀድሞ የነበሩበትን መናገራቸው ስህተት ነው፡፡ ለሁሉም እምነትና ፖለቲካ አሁን ያለንበት ነው ተጠቃሽ፡፡ ይሁንና ስለገዳ ሥርዓት በመረጃ በሰጡት ዕውቀት፣ ባጐናፀፉን የማንነት ክብር ተደስቻለሁ፡፡

ስድስተኛ እንግዳ ሆኖ የቀረበው ዜና ለይኩን፤ እግዚአብሔርም ሆነ ሰይጣን የሉም የሚል እምነት አለው፡፡ ቴዎድሮስ ኢ - አማኝነት ከየት መጣ? ሲል ለጠየቀው ጥያቄ ዜና የመለሰው እንዲህ ነው፡-

ሃይማኖት ያላቸው ሰዎች ሃይማኖት የሌላቸው ሰዎች ላይ የሚያሳድሩት ጫና ነው ኢ- አማኝነትን የፈጠረው፡፡ ከግሪክ ታሪክ ጀምሮ ብታይ አለማመን ያስገድል ነበር፡፡ ሶቅራጥስን ያስገደለችው አንዲት

ጥበብ

For Further Information, please call: 0118-96-18-79Piassa Tewodros Square, Eshetu Mamo Commercial Building 2nd floor

Main Office - back of Kality Prison, Tel. 011-4396574

ኤን ኤች ቤይ ፈርኒቸር በኢትዮጵያ የስድስት ዓመት ታሪክ አለው!

በዝቅተኛ ዋጋ ከፍተኛ የጥራት ደረጃ ያላቸው ምርቶችን ያመርታል!

ኤን ኤች ቤይ ፈርኒቸር ወደተሻለ ህይወት ይመራዎታል!

NH Bay Furniture has six years history in Ethiopia. With a lower price but higher quality,

NH Bay Furniture will lead you into a better life!

Page 21: Issue-703.pdf

Website: www.addisadmassnews.com

አዲስ አድማስ ሰኔ 29 ቀን 2005 ዓ.ም ገፅ 21

ሲኒማ ከገፅ 17 የዞረ

ፓርቲ ከገፅ 5 የዞረ

ሳይ፣ የፊልም ቀራጩንና አዘጋጁን አድንቄያቸዋለሁ፡፡ ከዚህ አንፃር የሀገራችን ባለሙያዎች፣ ዕድሉ ገጥሟቸው “ሆሊውድ” የሚጠቀምበትን መሣሪያዎች ቢያገኙ፣ የተሻለ የፊልም ሥራ ይዘው መቅረብ እንደሚችሉና እንደሚያስደምሙን እተማመናለሁ፡፡

ሙዚቃ ቅንብሩ የልብ አድርስ ነው፡፡ በርካታ ሀገርኛ ፊልሞቻችን ብዙውን ጊዜ የሚታጀቡት በውጪ ሙዚቃዎች ነው (አንድ ቀን የኮፒራይት ጥያቄ አይቀርላቸውም) “የማትበላ ወፍ” ግን ሀገርኛ ዜማ ያላቸውን የሙዚቃ ሥራዎች፣ ከታሪኩ ጋር በማቆራኘት አስደምጦናል፤ አሳይቶናል፡፡ ለምሳሌ “የማትበላ ወፍ ሙዚቃ”፣ የ “እናቴ ናፈቅሽኝ ሙዚቃ” ወዘተ … ከታሪኩ ጋር ተዛምዶ መግባቱ፣ ፊልሙን ይበልጥ አፍክቶታል፡፡ በፊልሙ ውስጥ የሚገኙ ጥልቅ ስሜቶች በዋሽንት ደምቀዋል፡፡ ይህም በራስ ጥበብ መጠቀምና መኩራት እንደሚቻል

ማለፊያ ምስክር ነው፡፡ በፊልሙ ውስጥ የተጫወቱት ተዋንያን ያሳዩትን

ድንቅ ብቃት ሳላደንቅ አላልፍም፡፡ ሮቤልንና ሮማንን የተጫወቱት ሄኖክ ወንድሙ እና ሜላት ነብዩ ተጠቃሽ ናቸው - ሚናቸውን በአሳማኝ ሁኔታ ተጫውተውታል፡፡ ሮማንም ከአባቷ ጋር፣ ከሮቤል ጋር፣ ከአለቃዋ ጋር ባላት ግንኙነቶች፣ እንዲሁም ከታሪኩ ለውጥ ጋር የምታሳያቸው ትወናዎች (የስሜት ለውጦች) ፈታኞች ቢመስሉም እርሷ ግን በብቃት ተወጥታዋለች፡፡ ፊልሙን በማይበት ወቅት አብረውኝ ይመለከቱ የነበሩ ሰዎች ሮማን “የደሀ ልጅ አትመስልም፣ ቆንጆ ናት” የሚል አስተያየት ሲሰነዝሩ ሰምቼአለሁ፡፡ (ለመሆኑ የደሃ ልጅ ቆንጆ አይደለም ያለው ማነው?)

የሮማንን አባት ሆነው የተጫወቱት ጋሼ አፈወርቅም ድንቅ የአተዋወን ብቃት አሳይተዋል።

አባትየው፣ በታሪኩ ውስጥ በሃዘን የተመቱ፣ ውስጣዊ ቅራኔ የበዛባቸውና የልጃቸው (ሮማን) ከቁም ነገር መድረስ የሚያስጨንቃቸው ሆነው እናገኛቸዋለን፡፡ አስመስለው ሳይሆን ገፀባሕሪውን ተላብሰው ተውነዋል፡፡

ዳዊትን ሁላችንም የምናውቀው በአንጋፋ ሙዚቀኛነቱ (ድምጻዊነቱ) ነው፡፡ ሆኖም በፊልሙ ውስጥ ዮናስ የተባለውን መልከ መልካም፣ ሀብታምና ደግ ሰው ሆኖ ሲተውን እናያለን፡፡ ለትወና የተፈጠረ እንጂ ገና ጀማሪ አይመስልም። እናም “ብራቮ” ዳዊት!! ብየዋለሁ፡፡

አስቂኝ (ኮሜዲ) ፊልሞች በብዛት እየተመረቱ፣ ለተመልካች በሚቀርቡበት በአሁኑ ሰዓት ድራማዊ ዘውግ ያለውን ፊልም ለመሥራት ማሰብ በራሱ ትልቅ ድፍረት ይጠይቃል፡፡ ፕሮዱዩሰሩ ናሆም ገ/መድህንና ታዛ ፊልም ፕሮዳክሽን፣ ሁሉም ትኩረት ሊሰጥበት

የሚገባ ማኅበራዊ ፋይዳ ያለው ፊልም ለመስራት መዋዕለ ነዋያቸውን አፍሰዋልና ይደነቃሉ፡፡

ደራሲውና ዳይሬክተሩም ከአድናቆቱ ሊያገኙ ይገባል፡፡ ድርሰቱ ወደ ምስል ተቀይሮ የተተረከበት መንገድ፣ የዳይሬክተሩን ጥልቅ ምናብ ያሳያል። የገፀባሕሪያትን ስሜቶች የሚያሳዩ ትዕይንቶች፣ የታሪክ መሸጋገሪያዎች፣የታሪክ አቀጣጠልና አቆራረጡ፣ የታሪኩ ፍጥነትና ዝግመት፣ የፍሬም አጠቃቀም፣ ሙዚቃው ከታሪኩ ጋር ያለው ቁርኝት፣ የእንቅስቃሴ ቦታ “ብሎኪንግ”፣ የካሜራ እንቅስቃሴ “ሴትአፕ” ወዘተ … ድንቅ ናቸው፡፡

በመጨረሻ የማትበላ ወፍ የተሰኘው ድንቅ ኢትዮጵያዊ ፊልም መታየት የሚገባው ነውና እዩት እላችኋለሁ፡፡ በእኔ ይሁንባችሁ ትወዱታላችሁ፡፡ ያለዚያም ትታዘቡኛላችሁ፡፡

መንገድ ነው ያሉት አቶ ሙሼ፤ ነጋዴውና የመንግስት ሠራተኛውን በየጊዜው ገንዘብ አምጣ ብሎ ማሰላቸት ህዝቡን ሊያማርርና አስተሳሰቡን ወደሌላ ሊቀይር ስለሚችል መንግስት አሁንም በርካታ የገንዘብ ማስገኛ መላዎችን መዘየድ አለበት ብለው እንደሚያምኑ በአጽንኦት ገልፀዋል፡፡ ስጋታቸው ከነዚህ የሃብት አቅርቦቶች ጋር የተያያዙ መሆናቸውን የገለፁት ፕሬዚዳንቱ፤ የግድቡን የማጠናቀቂያ ጊዜም ሊያራዝመው ይችላል የምንለው ይሄ ነው ይላሉ፡፡

መንግስት ይህን በርካታ ገንዘብ ማሰባሰብ ከማይችልባቸው ምክንያቶች ዋነኛው በርካታ ፕሮጀክቶችን በአንድ ጊዜ መዘርጋቱ ነው የሚሉት የኢዴፓ ሊቀመንበር፤ የስኳር፣ የባቡር እና የመንገድ ፕሮጀክቶቹ ከፍተኛ በጀት የሚያስፈልጋቸው በመሆናቸው የግድ ሌሎች የሀብት ማሰባሰቢያ ዘዴዎችን መቀየስ ይኖርበታል ባይ ናቸው፡፡

ኢዴፓ የግድቡን መገንባት በሃሳብ ከመደገፍ ባለፈ እንደ ፓርቲ የገንዘብና የሙያ ድጋፍ ላይ ይሳተፍ እንደሆነ ተጠይቀው “እዚህ ውስጥ ሶስት ነገሮች ይካተታሉ፤ አንደኛ እንደዜጋ የምንወጣው አለ”ያሉት አቶ ሙሼ፤ በሁለተኛ ደረጃ ፓርቲው እንደ ፓርቲ አገራዊ ግዴታውን የሚወጣበት አካሄድ መኖሩንና የብሔራዊ ኮሚቴ አባል

እንደመሆናቸው የሚወጣቸው ሚናዎች እንዳሉ አብራርተዋል፡፡ በብሔራዊ ኮሚቴው ውስጥ ገንቢ ሃሳቦችን በማፍለቅ፣ መረጃዎችን በመለዋወጥና ማህበረሰቡ ግንዛቤ እንዲኖረው በማድረግ ረገድ የፓርቲ ሚናቸውን እየተወጡ መሆኑን የገለፁት ፕሬዚዳንቱ፤ከአለምአቀፍ ማህበረሰብና ከዲፕሎማሲ ቡድኖች ጋር በመገናኘት እና በመወያየት በየትኛውም አቅጣጫ ስለግድቡ በጐ ገጽታና ምልከታ እንዲኖር ኢዴፓ እየሰራ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡ በሶስተኛ ደረጃ እንደ ግለሰብና እንደዜጋ ከየመስሪያ ቤታችን ከደሞዛችን እየተቆረጠ ቦንድ ገዝተናል፤ በግልም ቦንድ የገዛን አለን፤ ከዚህ የበለጠ ሚና ሊኖረን አይችልም” ብለዋል፡፡

ኢዴፓ ቦንድ ገዝቶ እንደሆነ ተጠይቀውም ፤ ፓርቲው ለፖለቲካ ስራው የሚያውለው እንጂ ለግድቡ ቦንድ ለመግዛት የሚያስችል የተለየ ገንዘብ እንደሌለው ገልፀው፤ የኢዴፓ አባላት ግን እንደማንኛውም ዜጋ በየመስሪያ ቤታቸው ከደሞዛ\ቸው ቦንድ መግዛታቸውንና በግልም ቦንድ የገዙ መኖራቸውን ተናግረዋል፡፡

ታላቁን የህዳሴ ግድብ ግንባታ አስመልክቶ በግብጽ በኩል ተንኳሽና የኢትዮጵያን ክብር ዝቅ የሚያደርጉ መግለጫዎች ሲለቀቁ አቋማቸውን

በግልጽ ማስቀመጣቸውን የተናገሩት የሰማያዊ ፓርቲ ፕሬዚዳንት ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት፤ ኢትዮጵያ በወንዟ ስትለማ ማየት ላይ ችግር እንደሌላቸው ጠቁመው “ተቃውሟችን የግድቡ የግንባታ ሂደት ግልጽነት የጐደለው መሆኑ ላይ ነው” ብለዋል፡፡ ግልጽነት የጐደለው ሲባል ምንን ያካትታል በሚል ለተጠየቁትም፤ ግድቡ የ80 ቢሊዮን ብር ፕሮጀክት እንደመሆኑ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አለመጽደቁን፣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ያልተወያየበትና በአምስት አመቱ የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ውስጥ አለመካተቱ ሂደቱን ግልጽነት የጐደለው ለማለት ምክንያት እንደሆናቸው ተናግረዋል፡፡ “ለምሳሌ ጨረታውን ማን እንደወሰደ አይታወቅም፤ እንዲህ ዓይነት ትልቅ አገራዊ ጉዳይ ሁሉም ሳይመክርበት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስላዘዙ ብቻ የሚደረግ ከሆነ በቀጣይነቱም በጥራቱም ላይ እምነት ለመጣል ይከብዳል” ሲሉ አብራርተዋል፡፡ ፓርላማ ሳያፀድቀው፣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ሳይወያይበት እና ሰፊ ውይይት ሳይደረግበት እንዲህ በችኮላ የሚሰራና የፖለቲካ ሞቲቭ ያለበት ሥራ ውሎ አድሮ ችግር ማስከተሉ እንደማይቀር ጠቁመው፤ በተፋሰሱ አገሮች በኩል ገና ያላለቁ ሥራዎችን፣ ብድርና እርዳታ ለማግኘት በርካታ

ዲፕሎማሲያዊ ሥራዎች እንዲሰሩ፣ ጉዳዩ በግልጽና ክፍት በሆነ መልኩ ለውይይት መቅረብና በአስተማማኝ ሁኔታ ላይ መመስረት እንዳለበት በጽኑ እንደሚያምኑ ገልፀዋል፡፡ “በተረፈ ግን በገዛ አገራችን ላይ በሚመነጭ ወንዝ ለመልማትና መብታችንን ለመጠቀም በሚደረግ እንቅስቃሴ ላይ እንዴት ተቃውሞ እናነሳለን?” ሲሉም ጠይቀዋል - ኢንጂነር ይልቃል፡፡

አሁንስ ጉዳዩ ወደ ፓርላማና ተወካዮች ምክር ቤት እንዲቀርብ ትጠብቃላችሁ ወይ በሚል ለተጠየቁት “አንጠብቅም ግን አሁንም መንግስት የግንባታውን ሂደት ለሁሉም አካል ግልጽ ለማድረግ ጊዜው አልረፈደም” በማለት መልሰዋል፡፡ “እኛ አሁንም ግልጽነቱ ላይ ነው ጥያቄያችን፤ባለፈው መግለጫቸው ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዲዛይንና ግንባታው የሚሰራው ደረጃ በደረጃ ነው” ሲሉ ሰምቻለሁ ያሉት የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር፤ በየደረጃውና በሂደት የዲዛይን ክለሳ ካለ፣ የግድቡ አቅምና ሃይል የማመንጨት ጉልበቱም እንደየሁኔታው ከፍም ዝቅም ሊል እንደሚችል አብራርተው፣ እንደገና የአካባቢያዊ ተጽእኖ ጥናቱ የሱዳንና የግብጽን መረጃ አላከታተም መባሉ ሁሉ

ፓርቲ ወደ ገፅ 2 ዞሯል

Page 22: Issue-703.pdf

Website: www.addisadmassnews.com

አዲስ አድማስ ሰኔ 29 ቀን 2005 ዓ.ም ገፅ 22 ማስታወቂያ

Page 23: Issue-703.pdf

Website: www.addisadmassnews.com

አዲስ አድማስ ሰኔ 29 ቀን 2005 ዓ.ም ገፅ 23 ማስታወቂያ

Page 24: Issue-703.pdf

Website: www.addisadmassnews.com

አዲስ አድማስ ሰኔ 29 ቀን 2005 ዓ.ም ገፅ 24

ምድር ከገፅ 6 የዞረ

መልዕክት ከገፅ 1 የዞረ

እማያ ትልቅነትሽ መልካም ሰብዕናሽሰው አክባሪነትሽ ፍፁም ትህትናሽታቦታት ዘካሪ አምላክሽን ፈሪለተራበ አጉራሽ ደካማን ነሽ ጧሪለትንሽ ትልቁ አርአያ ሆነሻልየተመሰገነ ስምሽን ትተሻልየተባረከ ዘርም አፍርተሻልእሙዬ ፍፁም ነሽ ገነትን ወርሰሻል

ሁሌም የምናስብሽ የምንወድሽ ልጆችሽ

የወ/ሮ አለሚቱ ልዑልሰገድ ይመርየአራተኛ ዓመተ ዕረፍት መታሰቢያ

የውድ እናታችን የወ/ሮ አለሚቱ ልዑልሰገድ ይመር የአራተኛ ዓመት ዕረፍት መታሰቢያ ማክሰኞ ሐምሌ 2 ቀን 2005 ዓ.ም በጐፋ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን በፀሎትና በፍትሐት እንዲሁም ነድያንን በመዘከር ታስቦ ይውላል፡፡

እንደሚለው፤ የኢትዮጵያ የጦር ሚኒስትር የነበሩት ራስ ሙሉጌታ ይገዙ ከእነ ልጃቸው የተገደሉት አሸንጌን ሲያቋርጡ ነው፡፡ ኪውባዊው ኮሎኔል ዴል ባዬ ግን “ሚኒስትሩ የሞቱት መቀሌ አካባቢ በተካሄደ ጦርነት ነው” ብሎ ጽፏል፡፡

በአካባቢው ንጉሥ ኃይለሥላሴ ከጣሊያን አውሮፕላኖች ድብደባ ተደብቀውበት የነበረ “የንጉሥ ዋሻ” የሚባል ቦታ መኖሩንም አስጐብኚያችን አስረድተውናል፡፡ “ወርጭጋ” ከሚባል በአካባቢው ከሚገኝ ሌላ ዋሻም ተደብቀው ከጣሊያን መቅሰፍት ድነዋል፡፡ እንዲህ እያሰብን፣ እንዲህ እየቃኘን ታሪካዊቷ ማይጨው ከተማ ስንደርስ ከንቲባውና የከተማው ህዝብ ልክ እንደ አላማጣና ኮረም ተሰልፈው በሆታና በዕልልታ ተቀበሉን፡፡ በነገራችን ላይ በየደረስንበት ከተማ ሁሉ ባህላዊ ዳቦ የግድ የተባለ እስኪመስል ድረስ በገፍ ይቀርብልን ነበር፡፡ ማይጨውም ቄጠማ ጐዝጉዛ፣ ደግሳና ተዘጋጅታ በክብር ተቀበለችን፡፡

የማይጨው ስም ሲነሳ የ1928ቱ አሳፋሪ ውድቀት መነሳቱ የግድ ነው፡፡ በረጅሙ ታሪካችን ድል የሆንባቸው ጊዜያት በጣም ጥቂት ናቸው፡፡ ከእነዚህ ጐላ ብለው የሚጠቀሱት የማህዲስቶች ድል (መተማ ላይ) እና የጣሊያኖች ድል (ማይጨው ላይ) ናቸው፡፡

ለመሆኑ ለምን ተሸነፍን? አምባራዶም ላይ የጣሊያንን መንጋ አፈር ያስጋጠ ጀግና ሠራዊት እንዴት ማይጨው ሲደርስ ተሸነፈ? ንጉሠ ነገሥቱ በውጊያው ወቅት ምን ሚና ነበራቸው? ከውጊያው በፊትስ የኢትዮጵያ ህዝብ ከእርሳቸው ጋር የሚሰለፍበትን ሁኔታ አመቻችተው ነበር? በአጠቃላይ የአድዋ ድል ለምን ማይጨው ላይ አልተደገመም? እጅግ በርካታ ጥያቄዎችን ማንሳት ይቻላል፡፡ ግን ያኔም ሆነ አሁን መልስ ያላገኙና የማገያኙ ጉዳዮች በርካታ ናቸውና የጥያቄ ሰልፈኛ መደርደሩ ብዙም ርባና ያለው አይመስልም፡፡

የጥበብ ተጓዦች ታሪካዊቷ ማይጨው ከተማ ላይ ስለሚገኙ ነው ይህን ያህል የጥያቄ ጋጋታ ያስነሳው፡፡ ማይጨው ላይ መገኘት ብቻ ሳይሆን በከተማው ደቡባዊ ጫፍ ላይ በተሰራ አነስተኛ ሙዚዬም ውስጥ የተቆለለ የምስኪን ኢትዮጵያውያን ጭንቅላትና አጽም ነው ብዙ እንድንናገር ሰበብ የሆነን፡፡ የእኒያ ጀግኖች አጽም፣ የእኒያ ወኔ ሙሉ አርበኞች የራስ ቅል በመደርደሪያ ሆኖ ዘግናኝ ትዝታውን ይመሰክራል፡፡

ያ ሁሉ አጥንት የተለቀመውና ቢያንስ ለዚያ ደረጃ የበቃው የአምስት ዓመቱ ወረራ ካበቃ በኋላ፣ አገር ሰላም ከሆነች በኋላ መሆኑን ተረድተናል፡፡ ከተለያዩ የሃገራችን አካባቢዎች ስንቁንና መሳሪያውን ተሸክሞ ለስድስትና ሰባት ወራት በእግሩ ኳትኖ አገርን ከነጭ አራዊት ሊታደጋት በሙሉ ወኔ ገስግሶ በአካባቢው የደረሰው ያ ሁሉ ኩሩ አርበኛ፣ ለሀገሩና ወገኑ ሲል በሀገሩ አፈር ላይ እንደ ገብስ ታጭዶና ተወቅቶ ማይጨው ላይ ቀርቷል፡፡

አካሉ ከዚያች ለትንግርት የተፈጠረች ከምትመስል አካባቢ ወድቆ ቢቀርም ታሪኩ ግን ዓለም እና ትውልድ እስከቀጠሉ ድረስ በክብር ሲዘከር ይኖራልና እኛም ከአንገታችን ሳይሆን ከልባችን ሸብረክ ብለን በክብር አሰብነው፡፡

ጉዞው ቀጥሏል፤ ሁለመናዋ የታሪክና የዕውቀት ምድር የሆነችው ትግራይም ምስጢሯን ማውጋትዋን ቀጥላለች፡፡ ወደ አላጄ እየተጠጋን ነው፡፡ አምባ አላጄም ሌላ ታሪክ አላት፡፡ ደጃዝማች ገበየሁ በ1888 ዓ.ም የጣሊያንን መንጋ አይቀጡ ቅጣት ቀጥቶ የወደቀው እዚሁ ቦታ ነው፡፡ የአድዋ ድል ዋዜማ የተበሰረውና ጣሊያኖች ለመጀመሪያ ጊዜ

ድባቅ የተመቱትም እዚሁ አምባአላጄ ነው፡፡ በትግራይ ክልል ተራራ ሞልቷል፤ ግን ዝም ብሎ

የቆመ አይደለም፤ የሚመሰክረው፣ የሚናገረው እጅግ ብዙ ምስጢር አለው፡፡ አላጄም እንደዚያ ነው፡፡

የአላጄ ከተማ ነዋሪዎችና ባለስልጣናትም ደግሰው በሆታ፣ በጭፈራ ነው የጥበብ ተጓዦችን የተቀበሉን፡፡ አላጄን ከሌሎች ልዩ የሚያደርገው ሁኔታም ተከስቷል፡፡ አላማጣ፣ ኮረምም ሆነ ማይጨው ስንደርስ ጠንከር ያለ ፀሐይ ነበር፡፡ ህዝቡም ያን ጠንካራ ሙቀት ተቋቁሞ ነው የተቀበለን፡፡ አላጄ ግን ከባድ ዝናብ ነበር፡፡ በዚያ ከባድ ዝናብም ቢሆን ህዝቡ ፍቅሩን አልነፈገንም፡፡ በሆታና በእልልታ ተቀብሎ ደግሶ አስተናግዶናል፡፡

መቀሌ ገብተን ማደር ስላለብን መፍጠን ያስፈልጋል፡፡ ግን ትግራይ ገብቶ መፍጠን ተገቢ አይሆንም፤ የሚታየው ማራኪ መልክዓምድር፣ የሚደመጠው ታሪክ፣ የህዝቡ መስተንግዶ በቀላሉ መንቀሳቀስ አያስችሉም፡፡ አምባ አላጀንና ጦርነቱ የተካሄደባቸውን አካባቢዎች በተደሞ ስንጐበኝ ቆይተን፣ ወደፊት ስንገሰግስ የሜርሲ ውሃ ፋብሪካ “የጥበብ ጉዞና ውሃ አይነጣጠሉም” ብሎ እጅግ በርካታ እሽግ ውሃ አውቶቡሳችን መያዝ እስኪያቅተው ድረስ ለገሰን፡፡ እውነትም ጉዞ ከንፁህ ውሃ ጋር ይሰምራልና የጥበብ ተጓዦች ሜርሲ ውሃን እየተጐነጩ፣ የፋብሪካውን የሥራ ሃላፊዎችና ሠራተኞች በማመስገን ጉዞአቸውን ቀጠሉ፡፡ በነገራችን ላይ በየደረስንበት ቦታ የሚደረገው አቀባበልና ግብዣ በቀጣዩ ከተማ ህዝብ ላይ መጉላላትን ከማስከተሉም በላይ በጊዜ ወደታሰበው ቦታ የመድረስ ችግርም በተደጋጋሚ ተስተውሏል፡፡ አሁን ደግሞ የመቀሌ ከተማ ከንቲባ፣ የክልሉ የካቢኔ አባላትና ህዝቡ ኲሃ ላይ ተሰልፈው እየጠበቁን ናቸውና መፍጠን ያስፈልጋል፡፡ ግን ጊዜው እንዴት ባከነና መሰላችሁ እየመሸ ነው፡፡

ስለዚህ ከአላማጣ ተቀብለውን አብረውን የሚጓዙት የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ኤጀንሲ ሃላፊ አቶ ከበደ አማረና የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍስሃየ አለማየሁ የሚጠብቀን ህዝብ መጉላላት የለበትምና በስልክ እንዲነግሩ ማድረግ ግድ ሆነ፡፡

ሆኖም ከምሽቱ 1፡30 አካባቢ ኲሃ ስንደርስ ህዝቡም ባለሥልጣናቱም ቆመው ሲጠብቁን አገኘናቸው፡፡ በእውነቱ ያን ያህል ጊዜ ማስጠበቅ ከባድ ነበር፡፡ እርግጥ ነው የትግራይ ህዝብ እንግዶቹን በፍቅርና በክብር እንደሚቀበል ባለፍንባቸው ከተሞች ሁሉ ያየነው ስለሆነ የመቀሌው ልዩ ላይሆን ይችላል፡፡

ለማንኛውም መቀሌ በሰላም ገባን፡፡ መቀሌ ታምራለች፤ በተለይ ማታ ላይ እንዳ ኢየሱስ ላይ ሆኖ ቁልቁል ሲመለከቷት ከዋክብት ህዋቸውን ትተው የረገፉባት መስክ ትመስላለች፡፡ ልዩ ልዩ ቀለማት ያሏቸው የመንገድና የቤት መብራቶች ልዩ ውበት፣ ልዩ ድምቀት ለግሰዋታል፡፡ መቀሌ መንገዶችዋ ጽዱ ናቸው፡፡ አዲስ አበባ ላይ አናት የሚበጠብጠው አስቀያሚ ሽታ መቀሌ የለም፡፡

ከዚህ ሌላ የጫት ገረባ በየፍሳሽ ማስወገጃ ቱቦው አይታይም፡፡ በጥርብ ድንጋይ የተሰሩት መንገዶች ያምራሉ፡፡ የሁለተኛው ቀን ውሏችን የተጠናቀቀው በርዕሰ መስተዳድሩ የራት ግብዣ ነው፡፡ ሚላኖ ሆቴልም ከፍተኛ ቅናሽ በማድረግ እንግዶቹን አስተናግዷል፡፡ ለነገሩ የትግራይን ምድር በሰላም የረገጠ ሁሉ እንግድነቱ ለህዝቡም ለመንግሥትም ነውና አይደንቅም፡፡ ጉዞውም ጽሑፉም አልተጠናቀቀም፡፡

ማስታወቂያ

መልስ1- አበበ ቢቂላ2- ሪቻርድ ኒክሰን3- የቬኒሱ ነጋዴ4- ብራዚል5- ጂሚ ካርተር

Tilahun Chala Import and Export would like to invite qualified applicants to apply for the following post.Position – sales person Qualification – Diploma in Accounting or Marketing or relative field Experience – 2 years of experience or more in related position and computer knowledge is mandatory.Salary – Negotiable Sex – Female Interested applicants who fulfill the above requirements can submit their applications with cvs, original documents and non returnable copies of relevant documents with in 5(five) days from the date of this announcement through the email [email protected] or to the following addresses:

Tilahun Chala import and Export Merkato Cinema Ras Area

Kennedy Shopping Center 1st floor 103 Tel. +251 118 95 97 32

Vacancy Announcement

አድርገን በመጀመሪያ ቀን ያለቀጠሮ የሄድን ቢሆንም ለሁለተኛ ጊዜ ቀጠሮ ለማስያዝ ብንፈልግም የሚያስተናግደን አካል በማጣታችን ለመመለስ ተገደናል የሚሉት መ/ር ወልደመስቀል፤ ጥበቃዎቹ የሄድንበትን ጉዳይ ጠይቀውን ከተረዱ በኋላ ፈጽሞ መግባት አትችሉም፤ ቀጠሮ ማስያዝ ከፈለጋችሁ አንድ እማሆይ አሉ፤ እሣቸውን አነጋግሩ ተባልን፤ የተባሉት ግለሰብ ግን ፍቃድ ወጥተዋል የሚል ምላሽ አገኘን ብለዋል፡፡ “አሁንም ለሶስተኛ ጊዜ ስንሄድ ጥበቃዎቹ ፈጽሞ መግባት አትችሉም፡፡ አካባቢውን ለቃችሁ ሂዱ አሉን” ብለዋል - የማህበሩ አባላት፡፡ ባለፈው ማክሰኞ 10 የሚደርሱ ሴቶችና ወንዶች የማህበሩ መገለጫ የሆነውን ነጭ ባለቀስተ ደመና ጥለት ልብስ ለብሰው ፓትሪያርኩ ጽ/ቤት በሩ ላይ ቆመው ነበር፡፡

የነብዩ ኤልያስ መልዕክት ምንድነው ብለን የጠየቅናት አርቲስት ጀማነሽ ሠለሞን “መልዕክቱ ለፓትሪያሪኩ ስለሆነ እሳቸው ከሰሙ በኋላ ለህዝብ እንድታደርሱ ይነገራችኋል” ብላለች፡፡

የመንበረ ፓትሪያሪክ ልዩ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ታምሩ አበራ ከአዲስ አድማስ ስለ ጉዳዩ ማብራሪያ ተጠይቀው “እስካሁን ጥያቄ ያቀረበልን የለም፤ ቤተክርስቲያኒቷ የራሷ የቅሬታ አቀራረብ ሥርዓት አላት፡፡ ለቅሬታም ሆነ ለቡራኬ የሚመጡትን በቀጠሮ እናስተናግዳለን፡፡ እስከ ሀምሌ 21 ቅዱስ ፓትሪያሪኩን በስልክ ለማነጋገር የተያዙ ቀጠሮዎች አሉ” ብለዋል፡፡ ከነብዩ ኤልያስ መልዕክት አለን

ያሉት ግለሰቦች “ኦርቶዶክስ” የሚለው ስያሜ “ለተንኮል” የገባ ስለሆነ የቤተክርስቲያኒቱ ስያሜ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን መባሉ ቀርቶ “የኢትዮጵያ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን” መባል አለበት በሚል አላማ እንደሚንቀሳቀሱ ይታወቃል፡፡

ማረሚያባለፈው ሳምንት በስፖርት አምድ የደደቢት ተጨዋቾች እና የብሄራዊ ቡድን ሚናቸው በሚል ባቀረበነው የፎቶ ዘገባ ላይ ቢያድግልኝ ኤልያስ የናይጄርያውን ሞሰስ ሲያጨናንቅ በሚል ያቀረብነው መረጃ ስህተት በመሆኑ የሚመለከታቸውን ሁሉ በታላቅ ትህትና ይቅርታ እንጠይቃለን፡፡ ቢያድግልኝ ኤልያስ የቅዱስ ጊዮርጊስ እና የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ወሳኝ ተጨዋች እንደሆነ ይታወቅልን፡፡

Page 25: Issue-703.pdf

Website: www.addisadmassnews.com

አዲስ አድማስ ሰኔ 29 ቀን 2005 ዓ.ም ገፅ 25 ማስታወቂያ

Page 26: Issue-703.pdf

Website: www.addisadmassnews.com

አዲስ አድማስ ሰኔ 29 ቀን 2005 ዓ.ም ገፅ 26 ፀሐይ ተፈረደኝ (ከኢሶግ)

ይህንን አምድ አዘጋጅቶ የሚያቀርብላችሁ ESOG-Ethiopian Society of Obstetricians and Gynecologists (የኢትዮዽያ የፅንስና የማህፀን ሀኪሞች ማኅበር) ነው፡፡ (በፖ.ሣ.ቁ 8731 ስልክ 011-5-506068/69 ልታገኙን ትችላላችሁ)

ላንቺና ላንተ

ፍርሐት ከገፅ 19 የዞረውሻ የለ…ቢኖርም…እኔ ክቡር የሆንኩ የሰው ልጅ ነኝ…በቤቴ ሸንቼ አልቀርም” በሩን በኃይል ከፍቶ ወደ ውጭ ወጣ፡፡ ለብቻው እየፎከረ፡፡

“አያቶቼ ከጣሊያን ጋር ነው ብዙ ሆነው…መድፍን በጐራዴ የወጉት፡፡ እኔ ከማይታዩ ሀይሎች ጋር ነው የምዋጋው፡፡ ብቻዬን፡፡ እነሱ የሀገርን ድንበር ነው አላስደፍርም ያሉት፡፡ እኔ የጤነኝነት ድንበሬን ለእብደት አላስደፍርም?”… እያለ ሸንቶ ጨረሰ፡፡

…ከቤቱ ውስጥ በበራው መብራት ውጋጋን ጅብ አየ፡፡ ጅቡ ስሪያ ላይ ነው፡፡ ስሪያ ላይ ያለው ጅብ በፊት እግሩ የወጣባት እና የሚደቀድቃት ሴት ጅብ መሆን አለባት፡፡ ነበረባት፡፡ ለእሱ ግን የታየችው ሌላ እንስሳ ናት፡፡ ከጅብ ጋር በጭራሽ የማትመጣጠን እንስሳ፡፡ ነፍሳት ናት፡፡

“ደግሞ ብላችሁ ብላችሁ ቁንጫና ጅብ ስሪያ

ሲፈጽሙ አሳየነው ልትሉ ነው፡፡ አላምንም፡፡ አላብድም፡፡ አልፈራም፡፡…እንዴት ይሆናል ብዬ እንድቀውስ ነው?...አልቀውስም፡፡ አልከሽፍም። …ሬዲዮውን ሳላበራው ለምን በራ…አላውቅም የሰራውን ሰው ጠይቁት፡፡ ጥፋቱ ግን ከእኔ አይደለም እመ ብርሐንን! ሳልጠጣ ለምንድነው የምጮኸው? አላውቅም! እንዳላብድ ነው፡፡ ስፈራ አይደለም የማብደው? … አልፈራም … መክሸፍ እንደ ኢትዮጵያ ታሪክ በኔ አይሰራም፡፡ እኔ ታሪክ አይደለሁም፡፡ እኔ እኔ ነኝ፡፡ ታሪክ አልሆንም፡፡ በሩን ክፍት ትቶ ወደ ቤቱ ገባ፡፡ አንድ ያለችው ጫማ በር ላይ እንደወለቀች ናት፡፡ ጫማ አድርጎ ለሽንት እንደወጣ እርግጠኛ ነው። አሁን ሲመለስ ጫማው በእግሩ ላይ እያለም ወልቆ ቁጭ ብሏል፡፡ … እንባው መጣበት። እያበደ እንደሆነ ግልፅ ሆነለት፡፡ ጥርሱን ነከሰ። የጨበጠውን እጁን ፈታ፡፡

ፍልስምና ከገፅ 20 የዞረትንሽ ጥያቄ ነች፤ አይደል? ግን ትክክለኛ ጥያቄ አልነበረችም፡፡ በዱሮው ዘመን የመጀመሪያው ጥያቄ “እግዚአብሔር ሁሉን ቻይ ከሆነ፤ ሁሉን አድራጊ ከሆነ ለምን ይህን ያህል ክፉ ነገር በዓለም ላይ ይኖራል?” የሚል ነው፡፡ ይህ የእኔ ብቻ ሳይሆን የማንም አማኝ ጥያቄ መሆን አለበት፡፡ ለእኔማ እግዚአብሔር የለም፡፡ ስለሌለ በዓለም ላይ ክፉ ነገሮች ብዙ አሉ፡፡ በመኖራቸው አዝናለሁ፡፡ ግን የሕይወት መንገድ ነው፡፡” እያለ ነው ዜና የሚቀጥለው፡፡ እዚህ ቃለ ምልልስ ላይ ቴዎድሮስ (ጠያቂው) እና ዜና (ተጠያቂው) በሃሳብ ቡጢ ሁሉ ይገጥማሉ፡፡ ዜና መጽሐፍ ቅዱስን ይጠቅሳል፤ ሌሎች መጻሕፍትንም ጭምር፡፡ ለምሳሌ ቴዎድሮስ “የእግዚአብሔርን መኖር ፋይዳ እና ጥበቡ ሌላ ቢቀር በሥነ ምግባር ትምህርት ቤትነቱ እንኳ አስፈላጊ አይሆንም?” ሲል ይጠይቃል፡፡ ዜና አይሆንም፡፡ ግብረገብን የፈጠረው ሃይማኖት አይደለም፡፡ ከሰብዕና ላይ ነጥቆ የወሰደው ነው፡፡ ቡድሂስቶች ጋ ሂድ፡፡ ከኛ የበለጡ ደጐች ናቸው፡፡ ክርስትና ወይም እስልምና አይደለም ደግ ያደረጋቸው፡፡ ክርስትናን ወይም መጽሐፍ ቅዱስን አያውቁም፡፡ ማንኛውም ሃይማኖተኛ ጥቅምን አስቦ ነው እግዚአብሔርን ያመነው፤ ዘላለማዊ ሕይወትን ለማግኘት፡፡ እኔ ደግ ስሆን ግን ምንም አስቤ አይደለም፡፡ ደግ መሆን ስላለብኝ፤ ሌላ ሰው ደግ ቢሆንልኝ ፋለምፈልግ ነው፡፡

ሁሉንም ሃሳቡን መዘርዘር ባልችልም ዜና ለይኩን መጽሐፉ ውስጥ የተሻለ ምክንያት ይዘው ከተሟገቱት ወይም ከተነተኑት ይመደባል፡፡ ምናልባት የጥያቄው አቅጣጫ ብቻ ይህንን ያደርጋል ማለት አይቻልም፡፡ መልስ

የመስጠት አቅሙም የበረታ ነው፡፡ ይሁንና ቀደም ባሉት አንቀፆች ላይ ስለቡድሀ

ሃይማኖት ሲጠቀስ፣ እነርሱም አምላክ አለ ብለው ስለሚያምኑ ከእርሱ እምነት ጋር ይጋጫል፡፡ በእርሱ መልስ ከሄድን ክርስትናና እስልምናን ብቻ የሚሞግት ነው፡፡ ይህንን ቴዎድሮስን እንዴት ዝም ብሎ እንዳለፈ አልገባኝም፡፡ አንዳንድ ቦታ ጥሩና ተገቢ ጥያቄዎችን ሲጠይቅ መገኘቱ ነው ቴዎድሮስን የልብ አድራሽ የሚያደርገው፡፡

እዚሁ ዜና ጋ ሌላም ግራ አጋቢ ነገር አለ፡፡ “ደግ እንዲያደርግልኝ ደግ አደርጋለሁ” ይላል፤ ይህ ማለት’ኮ እርሱ ጥቅም ፈልገው ነው እንዳላቸው ሰዎች ጥቅም መፈለጉን ነው የሚያሳየው፡፡ ከዚያም ስለ ቡድሂስቶች ሲናገር “ከኛ የበለጡ ደጐች ናቸው፡፡” በማለት ይገልፃል፡፡ እሱ ማነው?...አማኝ ነው እንዴ? የተጋጨ ሃሳብ ነው፡፡ እንዴት ልብ እንዳላለው አልገባኝም፡፡

እዚህ ጥራዝ ውስጥ በጣም የደነቁኝና የተመቹኝ ያሉትን ያህል ቀለል ያሉብኝና ከዛፍ እንደረገፈ ቅጠል ዝም ብለው የተንኮሻኮሹብኝም አሉ። ለምሳሌ የሥነ ክዋክብቱ ጉዳይ ምንም ስሜት አልሰጠኝም፡፡ ገለባ ሆኖብኛል፡፡ ይህንን ስል ግን ተጋባዡ ዕውቀቱን አላካፈለም እያልኩ አይደለም፡፡ በቂ የሆነ አቅም ያለውና ለቦታው ተመጣጣኝ ሰው ነው፡፡ “ፍልስምና” በሚለው የጥበብ ሰማይ ላይ የዚህ ዓይነት ፈዛዛና ተራ ሃሳቦች ሚዛን ደፊ ናቸው ብዬ አላስብም፡፡ ምናልባት ባለፉት ዓመታት የወጡ የህትመት ውጤቶች ጉዳዩን እያነሱ አሰልችተውን ይሆን? ከፍልስምናም ዘር ጡንቻ ያለው የየዕለቱ ሞጋች

“....በአለማችን ሴት ልጆች የወር አበባ የሚጀምሩበት እድሜ ወደ 11 እና ከዚያም በታች ዝቅ በማለት ላይ ይገኛል፡፡ ቀደም ባሉት ጊዜያት ከ13-15 አመት እድሜ ባለው ጊዜ ይመዘገብ የነበረው የወር አበባ መምጫ ጊዜ በዚህ መልኩ የመቀነሱ ምስጢር የአኑዋኑዋርን ደረጃ ባማከለ መልኩ መሆኑን ጥናቶች ያስረዳሉ....”ከላይ ያነበባችሁት ዶ/ር ታደሰ ኪቲላ የማህጸንና ጽንስ ሕክምና ባለሙያ የተናገሩት ነው፡፡ በዚህ እትም ለንባብ የምንለው በወር አበባ ምክንያት የሚፈጠር ሕመምንና ህመም አልባነትን የሚመለከት ይሆናል፡፡ የወር አበባ ሴቶች በእድሜያቸው ከ11-13 አመት ጀምሮ እስከ 45-50 አመት ድረስ በየወሩ ከማህጸናቸው የሚፈሳቸው ደም ነው፡፡ ዶ/ር ታደሰ ኪቲላ እንደገለጹት ሴቶች ከወር አበባ ጋር በተያያዘ የተለያዩ ሕመሞችን ለሐኪማቸው ይገልጻሉ፡፡ አንዳንዶች• ደሙ በትክክለኛው ስሌት መሰረት በየወሩ አይፈስም ፣• ወይንም ወቅቱን ሳይጠብቅ ይፈሳል፣• መጠኑ ትንሽ ነው ወይንም ይበዛል፣• ወቅቱን ሳይጠብቅ ተቋርጦአል...ወዘተከላይ ከተጠቀሱት ምክንያቶች በተጨማሪም አንዳንድ ሴቶች የወር አበባ በሚመጣ ጊዜ ጭርሱንም ተንቀሳቅሶ ስራራን ለመስራራት የሚቸገሩበት ሁኔታም ያጋጥማል፡፡ የወር አበባ ሲመጣ የሰውነት ለውጥ ይታያል፡፡ እረፍት ማጣት ፣መቅበዝበዝ ፣በቀላሉ መናደድ፣ አልፎ አልፎ የሚሰማ የእራራስ ምታት ፣የአግር ማበጥ፣ ክብደት መጨመር፣ ጡት የማጋት የመሳ ሰሉት ይከሰታሉ፡፡ የተጠቀሱት ምክንያቶች የሚከሰቱት በተፈጥሮአዊ ሁኔታ በሆርሞን መለወወጥ ምክንያት ሲሆን ነገር ግን እንደችግር የሚቆጠሩ አይደሉም፡፡ ሕመም ነው አይደለም የሚለውን ለመለየት ግን የተጠቀሱት ምክንያቶች ድግግሞሽ ሁኔታውን ይወስነዋል፡፡ የወር አበባ ሲመጣ ሊታዩ የሚገባቸው ተፈጥሮአዊ የሰውነት ለውጦች በአካበቢ ለውጥ ሁኔታ፣ ከስነልቡና ጋር በተያያዘ ፣የስራራ ጫና፣የቤተሰብ ሁኔታ የመሳሰሉት መጠኑን ሊያሰፉት ወይንም ሊያባብሱት ስለማችሉ ሕመሙ ሐኪም ዘንድ መቅረብ ሊያስፈልገው ይችላል፡፡ ከላይ ከተጠቀሰው በተጨማሪ በወር አበባ ምክንያት የሚፈጠር ሕመም ወይንም ስቃይ ተብሎ የሚገለጸው በሁለት ዋና ዋና ክፍሎች ይከፈላል፡፡ 1. Primary Dysmenorrhea የሚባለው ሲሆን

“....የወር አበባ መዛባት ....”ይኼውም አንዲት ሴት ልጅ የወር አበባ ካየች ጊዜ ጀምሮ ለሁለት እና ሶስት አመታት ያህል ስቃይ ያለው ሕመም መሰማት ነው፡፡ የዚ ህም ምክንያት የማህጸን የውስጥ ግድግዳ አካባቢ ያለው ሆርሞን የወር አበባ በሚፈ ስበት ጊዜ ጥንካሬ ስለሚሰማው ሕመምን ያስከት ላል፡፡ ይህ ሁኔታ ረጅም አመታት ሳይቆይ ሕመሙ ሊቀረፍ የሚአወለወ ሆነወ ሁኔታው ሳይቋረጥ ለብዙ አመታት ከቀጠለ ግን በመድሀኒት እንዲታገስ ይደረጋል፡፡ 2. በማህጸን ወይንም እንቁላል ማምረቻው አካባቢ ባለ እጢ ምክንያት ሕመም ካለ Secondary Dysmenorrhea ይባላል፡፡ ይህም ምክንያታዊ በሆነ መንገድ የሚሰማ ሕመም ነው፡፡ ስለዚህም ሴትየዋ የወር አበባ ሲመጣባት የሚሰማትን ሕመም ለማከም ሕመሙን ያመጣውን ነገር ማስወገድ ተገቢ ይሆናል፡፡ • እጢ ከሆነ እጢውን ማውጣት፣ • የወር አበባው የሚፈስበት መንገድ መዘጋት ወይንም መጥበብ ከሆነ መፍትሔ እንዲያገኝ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ የወር አበባ ሲመጣ ሕመም የሚሰማቸው ሴቶች ባል ሲያገቡ ወይንም ልጅ ሲወልዱ ሕመሙ ይወገድላቸዋል የሚለው አባባል ተለምዶአዊ እንጂ ሳይንሳዊ አይደለም፡፡ ዶ/ታደሰ እንደሚገልጹት ሕመሙ ምክንያት ያለው ወይንም Secondary Dysmenorrhea ከሆነ (...የማህጸን በር ወይንም የማህጸን አንገት ተዘግቶ ከሆነ...) ምክንያቱን ለማስወገድ አስፈላጊውን ሕክምና ማድረግ ተገቢ ይሆናል፡፡እንደ ዶ/ር ታደሰ ኪቲላ የማህጸንና ጽንስ ሕክምና እስፔሻሊስት ማብራራሪያ የወር አበባ ጊዜውን ጠብቆ የሚመጣው በእድሜያቸው ከ20-40 አመት ድረስ ባሉ ሴቶች ነው፡፡ ነገር ግን በመጀመሪያው ወቅት የሆርሞን መስተካከልንና የሰውነት መልመድን ስለሚፈልግ በሶስት ወር ወይንም ከዚያ በታች እና በላይ በተዛባ ሁኔታ ሊታይ ይችላል፡፡ እንደዚሁም (T@•þ´)የወር አበባ ሊቋረጥ በሚዘጋጅበት ጊዜም እንደዚሁ ወቅቱን ሳይጠብቅ በተዛባ ሁኔታ ይፈሳል፡፡ በሁለቱ ጫፍ ያለው የወር አበባ አፈሳሰስ ባህርይ የሆርሞኖችን መዛባት የሚያመለከት ነው፡፡ ነገር ግን በመሀከል ላይ ባለው እድሜ የወር አበባ በየወሩ ወቅቱን ጠብቆ የማይፈስ ከሆነ ከአካላዊ ችግር ከአካባቢ ጋር ...መኖሪያን የመለወጥ ...ወዘተ ሲያጋጥም አንጎልና እንቁላልን የሚያመርተው ክፍል በሚያደርጉት ግንኙነት ወይንም መረበሽ ምክንያት የሚከሰት ችግር ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ሕመሙ ሆርሞንን ከሚያመነጨው ክፍል እና ከማህጸን ግድግዳ ጋር

በተገናኘ ከሆነ የህመም ምክንያቱ ተፈልጎ መገኘትና መታከም ይገባዋል፡፡ የተለያዩ መረጃዎች እንደT>ÁSK¡~ƒ የወር አበባ ወቅቱን አለመጠበቅ ወይንም በተዛባ ሁኔታ የሚፈስ ከሆነ ሴትየዋ፡- ሰውነትዋ ከልክ በላይ የሆነ ውፍረት አጋጥሞታል፣ የተዛባ የምግብ ስርአትን እየተከተለች ነው፣ የአእምሮ ጭንቀት ይዞአታል፣ ከልክ በላይ የአካል እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ነች፣ በተለያዩ ምክንያቶች ሕመም ገጥሞአታል፣ ረዥም ጉዞ አድርጋለች ...ወዘተ የመሳሰሉት የወር አበባ አፈሳሰሱን ሊያዛቡ ከሚችሉ ምክንያቶች መካከል ናቸው፡፡ ከዚህ በተጨማሪም የወር አበባን አፈሳሰስን ሊቀንሱ ወይንም ሊጨምሩ ከሚችሉ ምክንያቶች • እንደ እርግዝና መከላከያ የመሳሰሉ መድሀኒቶች፣ • የሆርሞን ችግር ፣• ሱስ አስያዥ እጾችን መጠቀም፣• የአከርካሪ ወይንም የጀርባ አጥንት የደም ጋን ችግር፣• ጡት ማጥባት ...ወዘተ የወር አበባ አፈሳስን በትክክለኛው መንገድ እንዳይሆን ከሚያደርጉ መካከል ናቸው፡፡ ጡት ማጥባት እንደችግር የሚወሰድ ሳይሆን እንዲያውም በትክክል ልጆቻቸውን የሚያጠቡ እናቶች እርግዝናን እንደT>ŸLŸML†¨< መረጃዎች ÃÖlTK<፡፡›”Ç=ƒ ሴት ጡት በማጥባት ምናልባት ከ60-65 በመቶ ወሊድን መከላከል ትችላለች፡፡ ማጥባት ሲባልም ሙሉ ጊዜዋን በማጥባት ላይ ያለች ሴት እና አልፎ አልፎ የምታጠባ ሴት እርግዝናውን የመከላከል አቅማቸው የተለያየ መሆኑ እሙን ነው፡፡ እቤት ውስጥ የሚውሉ እናቶች ብዙ ጊዜ ስለሚ ያጠቡ ያልተፈለገ እርግዝናን የመከላከል አቅማቸውም ከፍተኛ ነው፡፡ ነገር ግን በተለያዩ ምክንያቶች አልፎ አልፎ የሚያጠቡ እናቶች ማጥባቱ ወሊድን የመከላከሉ አቅም በዚያኑ መጠን ዝቅ ይላል፡፡ ዶ/ር ታደሰ እንደሚገልጹት የወር አበባ መምጫ እድሜ በእጅጉ እየቀነሰ በመሄዱ ዛሬ ዛሬ ለሴት ልጆች ትምህርቱ መሰጠት ያለበት እድሜያቸው አስር አመት ከመድረሱ አስቀድሞ መሆን አለበት ፡፡ በአለማችን የተለያዩ ክፍሎች ውስጥ እንደሚታየው ባደጉት አገሮች በተመቻቸ ሁኔታ የሚያድጉ ልጆች በእድሜያቸው ገና አስር አመት ሳይደርሱ የወር አበባ የሚያዩበት አጋ ጣሚ ሲኖር ኑሮው እጅግ ዝቅተኛ በሆነበት

አካባቢ ግን እስከ አስራራ አምስት አመትም ዘግይቶ ሊታይ ሚችልበት አጋጣሚ አለ፡፡ ለማንኛውም ግን ማንኛውም ወላጅ ፣ትምህርት ቤቶች ወይንም የሚመለከተው አካል ለሴት ሕጻናቱ እድሜያቸው ወደ አስር አመት ሲደርስ ትምህርት መስጠት አለበት፡፡ ትምህርቱም ማተኮር ያለበት ተፈጥሮአዊውን ሁኔታ በመግለጽ ሴት ልጅ ይህንን ተፈጥሮአዊ ክስተት በጸጋ ተቀብላ ማስተናገድ እንደሚገባት እና በምን መልክ የሚለውን እንዲሁም ሌሎች ተያያዥ ነገሮችን ያካተተ መሆን ይገባዋል፡፡ የወር አበባ በእራራሱ ምንም አይነት የጤና እክልን የማያስከትል ሲሆን እንዲያውም በሰላም ጊዜውን ጠብቆ ከፈሰሰና ካበቃ የጤንነት ምልክት መሆኑን ሳይንሱ ያስረዳል፡፡ በሌላ በኩል ግን የወር አበባ በሚፈስበት ጊዜ ለጥንቃቄ ተብለው የሚለበሱ ልብሶች የጤንነት ሁኔታን የማያዛቡ መሆን እንደT>Ñv†¨< ሳይንሱ ያስረዳል፡፡ ንጽህናቸው የተጠበቁ የውስጥ ሱሪዎች አንዲሁም ከሱሪዎቹ ስር የሚደረጉ ሞዴስ ወይንም እንደ ሞዴስ የሚያገለግሉ ልብሶች ንጽህናቸው የተጠበቀ መሆን ይገባዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ዶ/ር ታደሰ ኪቲላ እንዳስረዱት የወር አበባ በሚፈስበት ጊዜ ሊታገድ አይገባውም፡፡ አንዳንድ ጊዜ ሴቶች ከሚውሉበት የስራራ ሁኔታና ከለበሱት ልብስ እንዲሁም ከሚያደርጉት እንቅስቃሴ አይነት በመነሳት ደም ሳይፈስ እንዲውል ለማድረግ አላስፈላጊ እርምጃ ይወስዳሉ፡፡ ትክክለኛ አጠቃቀም የሚሆነው ግን የሚ ፈሰው ደም ሳይታወክ እንዲፈስ ማድረግና በተወሰነ ጊዜ የሚÖkS<uƒ” መቀበያ በማስወገድ ወይንም በመለወጥ ንጽህና ሳይዛባ ማስተናገድ ነው፡፡

ዶ/ር ታደሰ ኪቲላ

“መክሸፍ” የሚለው መፅሐፍ ከበርጩማው ላይ ቅድም አንስቶት ነበር፤ አሁንም በርጩማው ላይ ተቀምጧል፡፡ አልጋው ላይም ቢፈልገው ምናልባት ያገኘው ይሆናል፡፡ እንባው ወረደ፡፡ “እንቢየው! አላብድም፡፡ እኖራለሁ፡፡ መብቴ ነው ጤነኛ መሆን” አለ በሹክሹክታ፡፡ “ኧረ ባክህ?! አብደሀል፤ ጤነኛ የመሆን መብት የለህም” አለው አንድ ሌላ ድምፅ፡፡ አሁን ግን ድምፁ … በክፍሉ ውስጥ በአካል ያለ ሰው ይመስል ለሱ ጆሮ የቀረበ ነው፡፡ ድምፁ ቀጠለ፡- “መኖር ብትቀጥልም ታብዳለሀ፣ በአረቄ ውስጥ መደበቅ ብትቀጥልም ታብዳለህ፡፡ መፍራት ብትቀጥልም ታብዳለህ፡፡ … አሁን እየጮህክ እንዳለኸው … መድፈር ብታበዛም … እሱም የእብደት አይነት ነው፡፡ ስለዚህ ከሽፈኻል፡፡

“አላበድኩም፤ አላብድም … ስለ መክሸፍ የሚያወራ

መፅሐፍም ሁለተኛ አይለምደኝም … አላነብም፡፡ ሁለት እግር ነው ያለኝ፤ አንድ ህይወቴ ላይ እራመድበታለሁ” “ተመልከት አልጋህ ስር ጫማዎቹ ስንት እንደሆነ ትመለከታለህ? … አለው ድምፁ፡፡ ቅድም የአማኑኤል ነው አልክ፡፡ አሁንስ? … ስድስት ጥንድ ሆነውልሀል። የጭንቅላትህ ሀሳብስ ስንት ጥንድ እንደሆነብህ ትመለከታለህ፡፡ ከሽፈሀል፡፡ “አላብድም” የሚል የእብደት ንግግር በእርግጥ ለመናገር አንተ የመጀመሪያው ነህ፡፡

ይጨበጨብልሀል፤ ግን እውነታውን ይሄ አይለውጠውም፡፡ አብደሀል” ከራሱ ጋራ እየጮኸ ማውራቱን ገፋበት እስከ ንጋት፡፡

አልፈራም! እያለ ሲጮህ … ሌሎች ፈርተው ሸሹት፡፡ እሱ ፍርሀቱን ያሸነፈበት መንገድ ለእነሱ እብደት ተብሎ ተተረጎመ፡፡

ሲሆን ደስ ይላል፡፡ በዘመን ቅደም ተከተል የተሰጡ ሁለት ሃሳቦችም በዚሁ መጽሐፈ የተጋጩ ይመስለኛል፡፡ የዶክተር መስፍንና የኢንጂነር ጌታሁን ሄራሞ ሃሳቦች፡፡ ዶ/ር መስፍን፤ ሕፃን ልጅ ሲወለድ አእምሮው እንደነጭ ወረቀት ነው ሲሉ፣ ኢንጂነር ጌታሁን ሄራሞ ደግሞ የቅርብ ጊዜ መረጃዎችን ጠቅሶ የሰው ልጅ ሲወለድ ከእናቱ ማህፀን የተወሰነ ዕውቀት ይዞ ነው እያለ ይሞግታል፡፡ የአዳማ ዩኒቨርስቲ የፍልስፍና መምህሩ ፈቃዱ ቀነኒሳም በብዙ ዘርፎች ፍልስፍናን ይተነትናል፡፡ ያሁኑ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ መምህር ግን ከቀድሞው መምህር

እሸቱ አለማየሁ ጋር ሲተያዩ የዕውቀት ልዩነት የተፈጠረ ይመስላል። መጋቢ ሃዲስ እሸቱ አለማየሁኮ ልበ ብርሃን፣ ጣፋጭና ልዩ ዓይንና አተያይ ያላቸው ብሩና ናቸው። ከሃይማኖቱ ጐራ ተለቅ ያለ ሃሳብ፣ አንፀባርቀዋል፡፡

በጥቅሉ “ፍልስምና ፫ ለእኔ እጅግ በተሻለ ሁኔታ በሳል ሰዎችን የያዘችና አዳዲስ ነገሮችን ያሳየች ናት። አንዳንዴ እየሾለኮ ያመለጡ ሃሳቦችን የቴዎድሮስ መረብ ማስገር ቢሳነውም! ዕውቀትና በሣል ሃሳብ የሚገኘው ታዋቂ ከመሆን ሳይሆን ከአዋቂነት ስለሆነ ጥሩ ጥሩ ሃሳቦች ተነስተዋል ቢባል ማጋነን አይሆንም!

ቅዳሜ ሰኔ 29 ቀን 2005 ዓ.ም ከአዲስ አበባ

ዩኒቨርስቲ በሕግ (LLB) ለተመረቅሽው ትግስት አበራ

እንኳን ደስ ያለሽ

እንኳን ደስ ያለሽ

Page 27: Issue-703.pdf

Website: www.addisadmassnews.com

አዲስ አድማስ ሰኔ 29 ቀን 2005 ዓ.ም ገፅ 27 ስፖርት አድማስ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከ31 ዓመት በኋላ ለአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎ መብቃቱ ብዙ ነገር እየቀየረ ነው፡፡ ብሄራዊ ቡድኑ በዓለም ዋንጫ ማጣርያ ምድቡን በመምራት ከቆየ ወዲህም ለውጦች ይታያሉ፡፡ በእነዚህ የኢትዮጵያ እግር

ኳስ የእድገት ምዕራፎች ሳቢያ በተለያዩ አገሮች በሚገኙ ክለቦች የኢትዮጵያውያን ተጫዋቾች ተፈላጊነት በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መጥቷል፡፡ ኢትዮጵያውያኑ እየተፈለጉ ያሉት በደቡብ አፍሪካ፤ በሱዳን፤ በሊቢያ እና በእስራኤል ክለቦች ነው፡፡ ፊፋ ከሰሞኑ ይፋ ባደረገው ወርሃዊ የእግር ኳስ ደረጃ ላይ ኢትዮጵያ ባለፈው ወር ከነበረችበት የ106ኛ ደረጃ 11 እርከኖችን ወደላይ በመምጠቅ 95ኛ ላይ ደርሳለች፡፡ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በዓለም ዋንጫ የምድብ ማጣርያ ተሳክቶለት ምድቡን ማሸነፍ በመቻል 10 ብሄራዊ ቡድኖች ለሚተናነቁበት የደርሶ መልስ ጥሎ ማለፍ ከሚገቡት ከበቃ እና አፍሪካን የሚወክሉ 5 ቡድኖች አንዱ በመሆን በታሪክ ለመጀመርያ ጊዜ ለዓለም ዋንጫ ካለፈ ይሄው የእግር ኳስ ደረጃ በከፍተኛ ደረጃ መሻሻል በማሳየት ከ70 በታች ለመመዝገብ ይበቃል፡፡ በዚህ ደረጃም ፕሮፌሽናል ተጨዋች ለመቅጠር የአገርን እግር ኳስ ደረጃ ከሰባ በታች እንዲሆን በሚፈልጉ እና ፕሮፌሽናል ሊግ ባላቸው የአውሮፓ አገራት ኢትዮጵያውያኑ የፕሮፌሽናልነት እድል እንዲያገኙ መንስኤ መሆኑ አይቀርም፡፡ በትራንስፈርማርኬት ድረገፅ አጠቃላይ የዋጋ ተመኑ 650ሺ ፓውንድ እንደሚያወጣ የተተመነው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የተጨዋች ስብስብ ከዓመት በኋላ በሚሊዬን ፓውንድ መገመቱም ይጠበቃል፡፡ በተያያዘም በኢትዮጵያ ለመጫወት ከአፍሪካ 6 አገራት የተውጣጡ ከ26 በላይ ተጨዋቾች በ7 ክለቦች በመቀጠር ለቀጣይ የውድድር ዘመን ህጋዊ እውቅና ማግኘታቸው ታውቋል፡፡ የእግር ኳስ ፌደሬሽን ለዝግጅት ክፍላችን በላከው ዝርዝር መሰረት በኢትዮጵያ ፕሪሚዬር ሊግ በቀጣዩ የውድድር ዘመን ለመጫወት እውቅና ያገኙት 26 የሌላ አገር ተጨዋቾች 8 ከካሜሮን፤ 7 ከናይጄርያ፤ 6 ከጋና፤ 3 ከኡጋንዳ እንዲሁም ከኬንያ እና ከደቡብ አፍሪካ የመጡ ናቸው፡፡ ከ26ቱ የሌላ አገር ተጨዋቾች ጊዮርጊስ 7፤ ኤልፓ እና ሀረር ቢራ እያንዳንዳቸው 5፤ ደደቢት 4፤ ኢትዮጵያ ቡና እና ድሬዳዋ ከነማ እያንዳንዳቸው 2 እንዲሁም ኒያላ ለ1 ተጨዋች ቅጥር በፌደሬሽኑ የእውቅና ማረጋገጫ ተሰጥቷቸዋል፡፡ በዚህ ፅሁፍ በኢትዮጵያ እግር ኳስ በተጨዋቾች የዝውውር ገበያ ያሉ ሁኔታዎችን ለመዳሰስ ተሞክሯል፡፡

የዝውውር ገበያው ድሮና ዘንድሮበኢትዮጵያ እግር ኳስ የተጨዋቾች ዝውውር ገበያ እየተሟሟቀ የመጣው በተለይ ካለፉት አራት ዓመታት ወዲህ ነው፡፡ የፕሮፌሽናል እግር ኳስ የንግድ እንቅስቃሴ ዋና መሰረት የዝውውር ገበያ ነው፡፡ የፕሪሚዬር ሊግ ፉክክር በሶስት እና አራት ክለቦች መካከል እየተጠናከረ ከመጣ በኋላ ገበያው ተሟሟሙቋል ማለት ይቻላል፡፡ የቀድሞው ታዋቂ ተጨዋች መንግስቱ ወርቁ ድሮ ኳስ ተጨዋቾች ስፖርቱን ለፍቅር እንጅ ለገንዘብ አይጫወቱም ይሉ ነበር፡፡ ክቡር ይድነቃቸው ተሰማ በተጨዋችነት ዘመናቸው መጀመርያ ለጊዮርጊስ ሲጫወቱ ከልምምድ በኋላ ስሙኒ ይከፈላቸው እንደነበር ያስታውሷል፡፡ የኢትዮጵያ እግር ኳስ የዝውውር ገበያ ብዙም የረባ ነገር የሚገኝበት አልነበረም፡፡ ካለፈው 4 ዓመት ወዲህ ግን ነገሮች ተቀይረዋል፡

የተጨዋቾች ዝውውር ገበያ በኢትዮጵያ

፡ በ50ሺ ብር የፊርማ ክፍያ ተጀምሮ፤ ወደ 100ሺ ብር ከዚያም ወደ 200ሺ ብር፤ 300ሺብር እየሆነ ቆይቶ ዛሬ የአንድ ተጨዋች የዝውውር ሂሳብ በአማካይ ወደ 500 ሺ ብር ደርሷል፡፡ በኢትዮጵያ እግር ኳስ የንግድ እንቅስቃሴ እንዳያድግ ተፅእኖ የፈጠረው በከፍተኛ የአገር ውስጥ ውድድሮች ተሳታፊ የሆኑ ክለቦች ከሞላ ጎደል በመንግስት የበጀት ድጎማ በመንቀሳቀሳቸው ሳይሆን አይቀርም፡፡ ለዚህም ባለፈው ዓመት የፌዴራል ስፖርት ኮሚሽን የተሰራውን ጥናት ሲጠቅስ በፕሪሚዬር ሊግ ተወዳዳሪ ከሆኑ ክለቦች 84 በመቶ የሚሆኑት በባለቤትነት የሚተዳደሩትና የገንዘብ ድጎማ ያላቸው ከመንግስት ተቋማት መሆኑን፤ በግል ባለቤትነት የተያዙት 8 በመቶ፤ ህዝባዊ አስተዳደር ያላቸው 13 በመቶ እንዲሁም በግል እና በህዝብ የሚደገፉ ክለቦች 4 በመቶ እንደሚሆኑ በዝርዝር ማስቀመጡን መጥቀስ ይቻላል፡፡ በመንግስት ተቋማት የሚደጎሙ ክለቦች በዓመት እስከ 50 ሚሊዮን ብር በጀት እንደሚያንቀሳቅሱ ሲታወቅ እንደ ጊዮርጊስ እና ደደደቢት አይነት ክለቦች በየዓመቱ ከ16 እስከ 25 ሚሊዮን ብር እንደሚያንቀሳቅሱ ይገመታል፡፡ ይሄ የበጀት አቅም በኢትዮጵያ እግር ኳስ ከፍተኛ ደረጃ ያላቸውን የሌሎች አገራት ተጨዋቾች በተፈለገው አቅም ለማሰባሰብ፤ የአገር ውስጥ ተጨዋቾችን የዝውውር ሂሳብ እና ደሞዝ በከፍተኛ ፍጥነት ለማሳደግ እና የሊግ የውድድር ደረጃን በፕሮፌሽናል ደረጃ ለማጠናከር በቂ አይደለም፡፡ ስፖርቱን በከፍተኛ የንግድ እንቅስቃሴ ለማካሄድ የክለቦች ባለቤትነት ከመንግስት ተቋማት ይልቅ በባለሃብቶች እና በደጋፊ ማህበራት ማስተዳደር ሁነኛ አመራጭ እንደሆነም በአፍሪካ እና በሌሎች የዓለም ክፍሎች በሚደረጉ ፕሮፌሽናል ሊጎች ተመክሮ በማስረጃነት መጥቀስ ይቻላል፡፡ሁለቱ የዝውውር መስኮቶች እና ሂሳቦችበኢትዮጵያ እግር ኳስ የተጨዋቾች የዝውውር ገበያ በአንድ የውድድር ዘመን በሁለት ወቅቶች ይካሄዳል፡፡ የመጀመርያው በውድድር ዘመን አጋማሽ ላይ ወይንም በፈረንጆች አዲስ አመት መግቢያ አካባቢ ለ1 ወር ክፍት ሆኖ የሚቆየው የዝውውር መስኮት ነው፡፡ ሁለተኛው ደግሞ አንድ የውድድር ዘመን ካበቃ በኋላ በሰኔ ለ1 ወር የሚዘልቀው የዝውውር መስኮት ነው፡፡ በእነዚህ ሁለት የዝውውር ወቅቶች ላይ ማንኛውም ክለብ በዝውውር ስምምነቱ የሚያስፈርመው ተጨዋች በፌደሬሽኑ የእውቅና ማረጋገጫ የተሰጠው ብቻ ይሆናል፡፡ የኢትዮጵያ ክለቦች በዝውርር ለሚያስፈርሟቸው ተጨዋቾች በአመዛኙ የሁለት ዓመት የኮንትራት ውል በማስፈረም ይታወቃሉ፡፡በተጨዋቾች የዝውውር ገበያው ለአንድ ተጨዋች የሚከፈለው የፊርማ ገንዘብ ወይም የዝውውር ሂሳብ በአማካይ እስከ 500ሺ ብር ነው፡፡ እስከ 17,675 ፓውንድ ማለት ነው፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ ለአንዳንድ ተጨዋቾች እስከ 1 ሚሊዮን ብር የዝውውር ሂሳብ እንደሚከፍል ቢነገርም በኢትዮጵያ እግር ኳስ ከፍተኛው የፊርማ ክፍያ ሆኖ በሪከርድነት የሚጠቀሰው ደደቢት ከ2 ዓመት በፊት አዲስ ህንፃ ኮንትራቱን እንዲያራዝም የከፈለው 700ሺ ብር ነው፡፡ በተገባደደው የኢትዮጵያ ፕሪሚዬር ሊግ የውድድር ዘመን በዝውውር ገበያው ለአንዳንድ ተጨዋቾች ተከፍለዋል የተባሉትን የፊርማ ክፍያዎች በመዘርዘርም በኢትዮጵያ እግር ኳስ ለተጨዋቾች ያለውን የዋጋ ተመን ማገናዘብም ይቻላል፡፡ አይናለም ሃይሉ ከመከላከያ ወደ ደደቢት በ600ሺ ብር፤ ሲሳይ ባንጫ ከሲዳማ ቡና ወደ ደደቢት በ550ሺ ብር እንዲሁም በረከት ይስሃቅ ከሃዋሳ

ከነማ ወደ መብራት ሃይል በ450ሺ ብር የፊርማ ክፍያ ዝውውራቸውን ፈፅመዋል፡፡

ፈርቀዳጁ ሳላዲንትራንስፈርማርኬት የተባለ የዩናይትድ ኪንግደም የእግር ኳስ የዝውውር ገበያ አጥኚ እና ተንታኝ ድረገፅ ድረገፅ 28 ተጨዋቾች ለሚገኙበት የአሁኑ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በዝውውር ገበያ የዋጋ ተመኑ 650ሺ ፓውንድ እንደሆነ ያመለክታል፡፡ በዚህ ተመን በብሄራዊ ቡድኑ የዝውውር ገበያ ላይ ዋጋ አላቸው ተብለው የተጠቀሱት ሶስት ተጨዋቾች ብቻ ናቸው፡፡ የመጀመርያው የ21 ዓመቱ የፊት አጥቂ እና በ29ኛው የአፍሪካ ዋንጫ የብሄራዊ ቡድኑ አባል የሆነው ፉአድ ኢብራሂም ሲሆን አሁን የሚጫወትበት ክለብ ባይኖረውም የዋጋ ተመኑ 75ሺ ፓውንድ ተብሏል፡፡ ሁለተኛው ተጨዋች ደግሞ ቶቦ ኮስተኒ ለተባለ ክለብ በመጫወት ላይ የሚገኘው፤ በ29ኛው የአፍሪካ ዋንጫ የብሄራዊ ቡድኑ አባል የነበረውና የግራ ክንፍ ተጨዋች የሆነው ዩሱፍ ሳላህ ሲሆን የዋጋ ተመኑ 275ሺ ፓውንድ ነው፡፡ ሶስተኛው ደግሞ የኢትዮጵያዊ ብሄራዊ ቡድን ውድ ተጨዋች ተብሎ በትራንስፈርማርኬት የተጠቀሰው እና በኢትዮጵያ እግር ኳስ ተጨዋቾች የፕሮፌሽናል ጉዞ በርካታ ፈርቀዳጅ ሁኔታዎችን በማለፍ የሚነሳው አጥቂው ሳላዲን ሰኢድ ነው፡፡ ከ2 ዓመት በፊት ይጫወትበት ከነበረው የቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ ወደግብፁ ዋዲ ደጋላ ሲዛወር 158.4 ሺ ፓውንድ የዝውውር ሂሳብ የተከፈለበት ሳላዲን ሰኢድ በወቅቱ የወጣበት ሂሳብ ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ሪከርድ የነበረ ነው፡፡ ሳላዲን ሰኢድ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ታሪክ ሪከርድ የሆነውን የዝውውር ሂሳብ ማስገኘቱ ብቻ ሳይሆን ወደ ግብፅ ክለብ በመሄድም ፈርቀዳጁ ነበር፡፡ ከ2 የውድድር ዘመናት በኋላም በተጨዋቾች የዝውውር ገበያ ለኢትዮጵያዊ በተከፈለ ሂሳብ እና በተዛወረበት አገር ሁለት አዳዲስ ፈርቀዳጅ ታሪኮችን ሳላዲን ሰኢድ ሊሰራ በቅቷል፡፡ በትራንስፈርማርኬት ድረገፅ የኢትዮጵያ ውዱ ተጨዋች የተባለው የ24 ዓመቱ ግብ አዳኝ ሳላዲን ሰኢድ የዋጋ ተመኑ ከሁለት ዓመት በኋላ በእጥፍ እድገት አሳይቶ 300ሺ ፓውንድ የደረሰ ነው፡፡ ሳላዲን አሁን በሚጫወትበት የስዊድኑ ክለብ ላርሴ ኤስኬ ክለብ በወር እስከ 10ሺ ዶላር ደሞዝ የሚታሰብለት ሲሆን በኢትዮጵያ እግር ኳስ ታሪክ አውሮፓ በመጫወት ፈርቀዳጅ ሆኗል፡፡ከየመን በኋላ ወደተለያዩ 5 አገራት

የሰፋው ተፈላጊነት ከአምስት እና ስድስት ዓመታት በፊት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ተጨዋቾች ከአገር ውጭ የመጫወት እድል ያላቸው በየመን ሊግ ብቻ ነበር ፡፡ ከ7 ዓመታት በፊት ጀምሮ የብቃት ደረጃቸው ጫፍ የደረሰላቸውና የተጨዋችነት ዘመናቸው በማብቂያ ዋዜማ ላይ የሚገኙ ከ12 በላይ ኢትዮጰያዊ ተጨዋቾች በተለያዩ የየመን ሊግ ተወዳዳሪ ክለቦች በመጫወት አሳልፈዋል፡፡ ባለፉት ሁለት ዓመታት ደግሞ ሳላዲን ሰኢድ በከፈተው በር ኢትዮጵያውያኑ ተጨዋቾች ከየመን ባሻገር ወደ ሌላ አገራትም በሚገኙ ጠንካራ ሊጎች በሚወዳደሩ ክለቦች እየተፈለጉ ናቸው፡፡ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ዓለም አቀፍ አምባሳደር ሊባል የሚችለውና በሁለቱ ታዋቂ የደቡብ አፍሪካ ክለቦች ሱፕርስፖርት ዩናይትድ እና ኦርላንዶ ፓይሬትስ ለመጫወት የበቃው ፍቅሩ ተፈራ በነበረው ፈርቀዳጅነት መጠቀስ ያለበት ነው፡፡ ከፍቅሩ በኋላ የመጣው ሳላዲን ሰኢድ በግብፅ እና በአውሮፓ አገር በሚካሄድ የሊግ ውድድር በሚሳተፉ ክለቦች በመጫወት መስመሩን ገፋበት፡፡ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ለአፍሪካ ዋንጫ መብቃቱ ደግሞ

ኢትዮጵያውያን ተጫዋቾች በተለያዩ አገራት ባሉ ክለቦች ለመፈለጋቸው አበይት ምክንያት ሆኗል፡፡ ኢትዮጵያውያኑ እየተፈለጉባቸው ከሚገኙ አገራት ደቡብ አፍሪካ፤ ሱዳን፤ እስራኤልና ሊቢያ ይጠቀሳሉ፡፡ከሰሞኑ የሚሰሙ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ከ5 በላይ ኢትዮጵያውያን ተጨዋቾች ወደ የተለያዩ አገራት በመጓዝ የሚጫወቱበት እድልን ለመጠቀም በስምምነት፤ በድርድር እና በጥናት ላይ ይገኛሉ፡፡ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተሰላፊ ከሆኑ ተጨዋቾች ለዘንድሮው የፕሪሚዬር ሊግ ሻምፒዮን ክለብ ይጫወት የነበረው አዲስ ሕንፃ ለሱዳኑ ክለብ አልሃሊ ሸንዲ በ80 ሺ ዶላር የዝውውር ሂሳብ ተከፍሎት እና 2500 ዶላር ሳምንታዊ ደሞዝ እየታሰበለት ለመጫወወት መስማማቱ ቀዳሚው ነው፡፡ የደደቢት እግር ኳስ ክለብ እና የብሄራዊ ቡድኑ ግብ አዳኝ ጌታነህ ከበደ እንዲሁም የጊዮርጊስ ክለብ አማካይ ተጨዋች እና የብሄራዊ ቡድኑ የመሃል ክፍል ሞተር ሽመልስ በቀለ ወደ ደቡብ አፍሪካ እና ወደ ሊቢያ ክለቦች ለመዘዋወር አስፈላጊውን የህክምና ፈተና እና የኮንትራት ድርድር ማካሄዳቸው ሌላው አስደናቂ የዝውውር ሂደት ነው፡፡ ሽመልስ በቀለ ወደ ሊቢያ በመጓዝ ለአገሪቱ ትልቅ ክለብ አል ኢትሐድ ለሦስት ዓመት የሚጫወትበት ኮንትራት እንደፈረመ እየተገለፀ ሲሆን 200ሺ ዶላር የዝውውር ሂሳብ እንደሚከፈለው እና 8ሺ ዶላር የወር ደሞዝ ሊታሰብለት ነው ተብሏል፡፡ በሌላ በኩል በዘንድሮው የኢትዮጵያ ፕሪሚዬር ሊግ በ22 ጎሎቹ ኮከብ ግብ አግቢነቱን የያዘውና በዓለም ዋንጫ የምድብ ማጣርያ በ5 ግቦቹ ከፍተኛ ግብ አግቢ የሆነው የደደቢቱ ጌታነህ ከበደ ወደ ደቡብ አፍሪካ በማቅናት በዚያ አገር ሊግ ዘንድሮ 4ኛ ደረጃ ላይ ላለው ቢድቪስት ዊትስ ዩኒቨርስቲ ክለብ ለመጫወት ተስማምቶ በ3 ዓመት የኮንትራት ውል 550ሺ ዶላር የዝውውር ሂሳብ ተከፍሎታል፡፡ ጌታነህ ከበደ በሌላው የደቡብ አፍሪካ ክለብ ኦርላንዶ ፓይሬትስ ተፈልጎ እንደነበርም ተገልፆ ነበር፡፡ ሌሎች ሁለት የብሄራዊ ቡድን ወሳኝ ተጨዋቾች የሆኑት የደደቢቱ ምንያህል ተሾመ እና የመብራት ኃይሉ አስራት መገርሳ ከእስራኤል ክለቦች በቀረበላቸው የዝውውር ፍላጎት በድርድር ሂደት ላይ ናቸው፡፡

አዲስ ሕንፃ ወደ ሱዳን ጌታነህ ከበደ ወደ ደ/አፍሪካ ምንያህል ተሾመ ወደ እስራኤል? አስራት መገርሳ ወደ እስራኤል?

ሽመልስ በቀለ ወደ ሊቢያ?

ሳላሃዲን ሰኢድ

ግሩም ሠይፉ

Page 28: Issue-703.pdf

Website: www.addisadmassnews.com

አዲስ አድማስ ሰኔ 29 ቀን 2005 ዓ.ም ገፅ 28 ማ

ስታ

ወቂ