“ለራሱ ኩራት ለአካባቢው አገሮች ደግሞ የብቃት ......ገጽ 2...

14
በውስጥ ገጾች ገጽ 2 ገጽ 9 ማስታወቂያ በምዕራብ አርሲ ዞን ሙሉ ለሙሉ ከወደሙ 121 መኖሪያ ቤቶች 87ቱ ተገንብተው አገልግሎት መስጠት ጀመሩ የአግሮ ፕሮሰሲንግ ዘርፍን ማስፋፋት ለላቀ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት በኢትዮጵያና በጀርመን ... ወደ ገጽ 4 ዞሯል ፕሮፌሰር መስፍን ... ወደ ገጽ 4 ዞሯል 80ኛ ዓመት ቁጥር 021 መስከረም 21 ቀን 2013 ዓ.ም ዋጋ 5:75 ሐሙስ ብዕራችን ለኢትዮጵያ ህዳሴ ይተጋል! በጋዜጣው ሪፖርተር አዲስ አበባ፦ ፕሮፌሰር መስፍን በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል በህክምና ሲረዱ ቆይተው ከትናንት በስቲያ ማምሻውን ከሌሊቱ ስድስት ሰዓት ገደማ በ90 ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ - ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በፕሮፌሰሩ ሞት የተሰማቸውን ጥልቅ ኀዘን ገለጹ “ለራሱ ኩራት ለአካባቢው አገሮ ደግሞ የብቃት ምንጭ የሆነ የፖሊስ ሠራዊት የመገንባት ጥረት ተጠናክሮ ይቀጥላል” - ዶ/ር አብይ አህመድ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ጠቅላይ ሚኒስትር ገጽ 3 መላኩ ኤሮሴ አዲስ አበባ፡- በኢትዮጵያ እና በጀርመን መንግሥታት መካከል የ4 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር የበጀት ድጋፍ ስምምነት ተፈረመ። የጀርመን መንግሥት በዚህ ወቅት ያሳየው ጽኑ ድጋፍ የጠንካራ አጋርነት ማረጋገጫ መሆኑም ተገለፀ። በኢ.ፌ.ዴ.ሪ.የገንዘብ ሚንስቴር አዳራሽ ትናንት በተካሄደው የፊርማ ሥነ ሥርዓት ላይ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. በኢትዮጵያና በጀርመን መንግሥታት መካከል የ4 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር የድጋፍ ስምምነት ተፈረመ

Upload: others

Post on 19-Dec-2020

14 views

Category:

Documents


0 download

TRANSCRIPT

Page 1: “ለራሱ ኩራት ለአካባቢው አገሮች ደግሞ የብቃት ......ገጽ 2 አዲስ ዘመን ሐሙስ መስከረም 21 ቀን 2013 ዓ.ም ዜና አዲስ አበባ፦

በውስጥ

ገጾች

ገጽ 2 ገጽ 9

ማስታ

ወቂ

በምዕራብ አርሲ ዞን ሙሉ ለሙሉ ከወደሙ 121 መኖሪያ ቤቶች 87ቱ ተገንብተው አገልግሎት መስጠት ጀመሩ

የአግሮ ፕሮሰሲንግ ዘርፍን ማስፋፋት ለላቀ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት

በኢትዮጵያና በጀርመን ... ወደ ገጽ 4 ዞሯል

ፕሮፌሰር መስፍን ... ወደ ገጽ 4 ዞሯል

80ኛ ዓመት ቁጥር 021 መስከረም 21 ቀን 2013 ዓ.ም ዋጋ 5:75 ሐሙስ ብዕራችን ለኢትዮጵያ ህዳሴ ይተጋል!

በጋዜጣው ሪፖርተር

አዲስ አበባ፦ ፕሮፌሰር መስፍን በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል በህክምና ሲረዱ ቆይተው ከትናንት በስቲያ ማምሻውን ከሌሊቱ ስድስት ሰዓት ገደማ በ90

ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ- ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በፕሮፌሰሩ

ሞት የተሰማቸውን ጥልቅ ኀዘን ገለጹ

“ለራሱ ኩራት ለአካባቢው አገሮች ደግሞ የብቃት ምንጭ የሆነ የፖሊስ ሠራዊት የመገንባት ጥረት ተጠናክሮ ይቀጥላል”

- ዶ/ር አብይ አህመድየኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ጠቅላይ ሚኒስትር ገጽ 3

መላኩ ኤሮሴ

አዲስ አበባ፡- በኢትዮጵያ እና በጀርመን መንግሥታት መካከል የ4 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር የበጀት ድጋፍ ስምምነት ተፈረመ። የጀርመን መንግሥት በዚህ ወቅት ያሳየው ጽኑ ድጋፍ የጠንካራ አጋርነት ማረጋገጫ መሆኑም ተገለፀ።

በኢ.ፌ.ዴ.ሪ.የገንዘብ ሚንስቴር አዳራሽ ትናንት በተካሄደው የፊርማ ሥነ ሥርዓት ላይ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ.

በኢትዮጵያና በጀርመን መንግሥታት መካከል የ4

ነጥብ 3 ቢሊየን ብር የድጋፍ ስምምነት ተፈረመ

Page 2: “ለራሱ ኩራት ለአካባቢው አገሮች ደግሞ የብቃት ......ገጽ 2 አዲስ ዘመን ሐሙስ መስከረም 21 ቀን 2013 ዓ.ም ዜና አዲስ አበባ፦

አዲስ ዘመን ሐሙስ መስከረም 21 ቀን 2013 ዓ.ምገጽ 2

ዜና

አዲስ አበባ፦ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ላይ ሊያጋጥም የሚችል የትኛውም የጠላት እንቅስቃሴ ማስቀረት የሚያስችል የተሟላ ዝግጁነት እንዳለው የኢትዮጵያ አየር ኃይል አስታወቀ።

የኢትዮጵያ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሜጀር ጄነራል ይልማ መርዳሳ፣ የኢትዮጵያ አየር ኃይል አሁን ያለበትን ወቅታዊ ብቃትና ዝግጁነት በማስመልከት ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንዳስታወቁት፣ የኢትዮጵያ አየር ኃየል ከየትኛውም ጊዜ በላቀ መልኩ ብቃት ባላቸው አባላትና በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ተደራጅቷል።

ቀደም ሲል የአጭር ጊዜ በረራ ብቻ ያደርጉ የነበሩት ተዋጊ አውሮፕላኖች አሁን ከአራት ሰዓት በላይ መብረር የሚችሉና ዲጂታል መሆናቸውን ጠቁመው፣

የኢትዮጵያን የአየር ክልል በመጠበቅ ሂደት በአንድ ማዕከል በመሆን መቆጣጠር፣ ትእዛዝ መስጠትና ግዳጆች በፍጥነትና ውጤታማ በሆነ መልኩ እንዲፈፀም ማድረግ የሚያስችል አሠራር መዘርጋቱን ገልፀዋል።

ሌሎች ትላልቅ ፕሮጀክቶችን ጨምሮ በተለይ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን ከየትኛውም ጥቃት መጠበቅ የአየር ኃይላችን ዋነኛ ተልዕኮ መሆኑን በአግባቡ እንገነዘባለን ያሉት ዋና አዛዥ፣ በግድቡ ዙሪያ የማይቋረጥ ክትትልና ጥበቃ እንደሚደረግ አመልክተዋል። በዚህ ዙሪያ ማንኛውንም ትንኮሳም ይሁን የጠላት እንቅስቃሴ የመመከትና የማስቀረት አስተማማኝ ብቃት እንዳለውም ጠቁመዋል።

ቀድሞም ስመ ገናናነቱ የሚወሳው የኢትዮጵያ አየር

ኃይል ተልዕኮውን በማሳካት፣ በጀግንነትና ውጤታማነቱ የሚታወቅ እንደሆነ ያመለከቱት ሜጀር ጄነራል ይልማ ፣ የኢትዮጵያ አየር ኃይል አሁን ለደረሰበት ያለፈው ዋነኛ መሠረቱ መሆኑን ገልፀዋል። አሁን ላይ የዘመኑን ቴክኖሎጂ የታጠቀ፣ በአጭር ጊዜም በብቃት ተልዕኮ የመፈፀም ብቃት ያለው እንደሆነም አስታውቀዋል።

አየር ኃይል አሁን ላይ በአቪየሽንና በአየር መከላከያ ዘመኑ የተደረሰበትን ቴክኖሎጂ በመጠቀም ላይ መሆኑን፣ የባለሙያዎች ስልጠና በዘመናዊ የምስለ በረራ ስልጠና የታገዘ እና ስልጠናውም ይሁን ተዋጊ አውሮፕላኖች ከአናሎግ ወደ ዲጂታል መቀየራቸውን ገልፀዋል።

የኢትዮጵያ አየር ኃይል የአገሪቱን የአየር ክልል

በመቆጣጠርና ተልዕኮዎች እንዲፈፀሙ ለማድረግ በአንድ ማዕከል በመሆን ትእዛዝ መስጠትና መከታተል የሚያስችል አሠራር ተግባራዊ መደረጉንም አመልክተዋል።

የኢትዮጵያ አየር ኃይል በቀድሞው አጠራር ከታ ሜዳ አሁን ደግሞ ሐረር ሜዳ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በ1936 ዓ.ም እንደተመሰረተ መረጃዎች ይጠቁማሉ።

የመጀመሪያው የኢትዮጵያ አየር ኃይል አዛዥ ስዊዲናዊው ካውንት ቮሮንስ ሲሆኑ ከእርሳቸው በኋላ በ1953 ዓ.ም ኢትዮጵያዊው ጄኔራል አሰፋ አያና መሪነቱን ተረክበው በኢትዮጵያዊያን ቅብብሎሽ እየተመራ 77 ዓመታትን አስቆጥሯል።

የኢትዮጵያ አየር ኃይል በታላቁ ህዳሴ ግድብ ላይ ሊያጋጥም የሚችል ማንኛውንም ጥቃት የተሟላ ዝግጁነት እንዳለው ተገለፀ

ኢያሱ መሰለ

አዲስ አበባ፡- የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳን ድንገተኛ ግድያ ምክንያት በማድረግ በምዕራብ አርሲ ዞን በጥፋት ሃይሎች ሙሉ ለሙሉ ከወደሙት 121 መኖሪያ ቤቶች ውስጥ 87ቱ ተገንብተው አገልግሎት መስጠት መጀመራቸውን የምዕራብ አርሲ ዞን አስታወቀ፡፡

የምዕራብ አርሲ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አበራ ቡኖ ለአዲስ ዘመን እንደገለፁት። የተወዳጁን አርቲስት ህልፈት የጥፋት አጀንዳ አድርገው የተንቀሳቀሱ ሃይሎች በዞኑ ሰላማዊ ዜጎች ላይ ግድያ ፈጽመዋል፤ ንብረት አውድመዋል፡፡ በጥፋት ሃይሎቹ በአጠቃላይ 228 መኖሪያ ቤቶች ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡ ከነዚህ ውስጥ ሙሉ ለሙሉ ከወደሙ 121 መኖሪያ ቤቶች ውስጥ 87ቱ በአካባቢው ህብረተሰብ፣ በካቢኔ አባላትና በወረዳዎች ድጎማ ግንባታቸው ተጠናቆ ነዋሪዎቹ እንዲገቡባቸው ተደርጓል፡፡

በአዲስ መልክ በብሎኬት የተገነቡት መኖሪያ ቤቶች በሻሸመኔ፣ በነገሌ አርሲ፣ በሻላ፣ በኮኮሳ ፣ በአዳባና በሌሎች ወረዳዎችም የሚገኙ መሆናቸውንም ጠቁመው፣ ለቤቶቹ ግንባታ ከህዝቡ የተደረገ የገንዘብ ድጋፍ ከአሰር ሚሊዮን ብር በላይ እንደሆነ አስታውቀዋል።

ለግንበታው ከወረዳዎች ባጀትና ከመንግሥት ሠራተኞች አንድ ነጥብ ስድስት ሚሊዮን ብር

መሰብሰቡን ያመለከቱት ዋና አስተዳዳሪው፣ ህዝቡ ካደረገው የገንዘብና የቁሳቁስ ድጋፍ በተጨማሪ በጉልበቱም ጭምር እንደተሳተፈ አመልክተዋል።

በየአካባቢው ያሉ ባለሀብቶች ከገንዘብ ድጋፍ በተጨማሪ አሻዋና ድንጋይ በማቅረብ ከፍ ያለ አስተዋጽኦ ማበርከታቸውን ጠቁመው፣ በአንዳንድ አካባቢዎች ቀይመስቀልና የተለያዩ በጎ አድራጎት ድርጅቶችም የአልባሳትና የቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጋቸውን ገልፀዋል።

ሙሉ ለሙሉ ከወደሙ ቤቶች ውስጥ ተጀምረው ያልተጠናቀቁ 30 አካባቢ ቤቶች መኖራቸውን የጠቀሱት ዋና አስተዳዳሪው፣ እነዚህንም እስከሚቀጥለው ወር ድረስ ለማጠናቀቅ እየተሠራ ነው ብለዋል፡፡

ጉዳት ከደረሰባቸው መኖሪያ ቤቶች ውስጥ ተጠግነው አገልግሎት መስጠት የሚችሉ 107 መኖሪያ ቤቶች መለጣቸውን አመልክተው፣ ከነዚህ ውስጥም ለ103ቱ ጥገና ተደርጎላቸው ነዋሪዎቹ እንዲገቡባቸው ተደርጓል ብለዋል፡፡ የተቀሩት አራት ቤቶችም በአጭርጊዜ ውስጥ ጥገና እንደሚደረግላቸው ዋና አስተዳዳሪው ገልፀዋል፡፡

በአጠቃላይ ቤቶቹን ወደ ነበሩበት ለመመለስ ህብረተሰቡ ከፍተኛ ርብርብ በማድረግ አጋርነቱን መግለፁን ያስታወቁት ዋና አስተዳዳሪው፣ ይህ የአንድነት፣ የወንድማማችነትና የትብብር መንፈስ የጥፋት ሃይሉን አንገት ያስደፋና ተስፋ ያስቆረጠ ድንቅ

ተግባር እንደሆነም አመልክተዋል።በዞኑ በተመሳሳይ መልኩ ውድመት የደረሰባቸው

የንግድ ቤቶችን መለስተኛና ከፍተኛ በማለት በሁለት ከፍሎ ለመመልከት መሞከሩን ጠቁመው፣ መለስተኛ የንግድ ተቋማትን በተመለከተ የአካባቢው ነዋሪዎችና ባለሀብት ‹‹ መንግሥት ሰላምን ብቻ ይጠብቅልን እንጂ እኛ እራሳችን እንገነባቸዋለን›› በሚል ቃል ገብተው አንዳንዶችም ተገንብተው ወደ ሥራ ገብተዋል ብለዋል።ለአብነትም በነጌሌ አርሲ፣ ሻላና ዶዶላ የሚገኙ ሥጋ ቤቶችናን መጠጥቤቶችን ጠቅሰዋል፡፡

ከፍተኛ ወጪ የሚጠይቁ አንዳንድ የንግድ ተቋማትና ፎቆችንም መልሶ ለመገንባት ከሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት ጋር ውይይት እየተደረገ መሆኑን የገለፁት አቶ አበራ፣ መንግሥትም ባለሀብቱን በምን መልክ መርዳት እንዳለበት እየመከረ መሆኑን አስታውቀዋል። በቅርብ ጊዜ ተገንብተው ወደ ሥራ የሚገቡበት ሁኔታ እየተጠና ነውም ብለዋል።

የጥቃቱ ሰለባ የነበሩና ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉ አንዲት የአዳባ ከተማ ነዋሪ በበኩላቸው፣ በአካባቢው ህዝብ፣ በበጎአድራጎት ድርጅቶችና በመስተዳድሩ ስለተደረገላቸው ድጋፍና ርብርብ አመስግነዋል። የተሠራላቸው ቤት በብሎኬት መሆኑና አፋጣኝ ምላሽ ማግኘታቸው ቢያስደስታቸውም በርና መስኮት ያልተገጠመለትና ኩሽናም የሌለው መሆኑ ኑሯቸውን አስቸጋሪ እንደሚያደርገው ስጋታቸውን

ገልፀዋል፡፡ ከሁሉ በላይ መንግሥት ደህንነታቸው ተጠብቆ እንዲኖሩ የሚያስችል ዋስትና ሊሰጣቸው እንደሚገባም አመልክተዋል።

የተገነቡት ቤቶች ኩሽና የሌላቸውና አንዳንዶቹም በርና መስኮት ያልተገጠመላቸው ናቸው በሚል በተፈናቃዮቹ የሚነሱ ቅሬታዎች እውነትነት እንዳላቸው የተናገሩት ዋና አስተዳሪው በቀጣይም ጉድለቶችን ለማስተካከል ይሠራል ብለዋል፡፡

የሕግ የበላይነትን ከማስከበርና የአካባቢውን ሰላም ከማስጠበቅ አንፃር የመንግሥት የፀጥታ ሃይሎች ከህብረተሰቡ ጋር በመሆን ተግተው እየሠሩ መሆናቸውን ገልፀው፣ ከሁሉም በላይ ህብረተሰቡ እንዲህ አይነት ፀያፍ ተግባር እንዳይፈፀም ድርጊቱን ከማውገዝ አልፎ አጥፊዎችን እያጋለጠ መሆኑንም አመልክዋል፡፡

አስተዳደሩ የአካባቢውን ሰላምና ደህንነት ለመጠበቅ ከፀጥታ ሃይሉ ጋር እጅና ጓንት ሆኖ እየሠራ በመሆኑ መሰል ችግር ዳግም ይከሰታል ተብሎ እንደማይታሰብ ያመለከቱት ዋና አስተዳዳሪው፣ በምዕራብ አርሲ ዞን ከዚህ በኋላ እንኳን የሰውን ህይወት ማጥፋትና ንብረት ማውደም ቀርቶ መንገድ የመዝጋት ሙከራ አይደረግም ብለዋል። ነዋሪዎችም እየተሠራ ካለው አስተማማኝ ሥራ አንፃር የሰላምና ደህንነት ዋስትና እንዳላቸው ሊጠራጠሩ እንደማይገባ አስታውቀዋል፡፡

በምዕራብ አርሲ ዞን ሙሉ ለሙሉ ከወደሙ 121 መኖሪያ ቤቶች 87ቱ ተገንብተው አገልግሎት መስጠት ጀመሩ

Page 3: “ለራሱ ኩራት ለአካባቢው አገሮች ደግሞ የብቃት ......ገጽ 2 አዲስ ዘመን ሐሙስ መስከረም 21 ቀን 2013 ዓ.ም ዜና አዲስ አበባ፦

አዲስ ዘመን ሐሙስ መስከረም 21 ቀን 2013 ዓ.ም ገጽ 3

ዜና

ኃይማኖት ከበደ

አዲስ አበባ:- ለራሱ ኩራት ለአካባቢው አገሮች ደግሞ የብቃት ምንጭ የሆነ የፖሊስ ሠራዊት የመገንባት ጥረት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ አረጋገጡ። የፖሊስ ኃይሉ የሕግ የበላይነትን ለማስከበርና የሚሰጠውን መመሪያ ተቀብሎ በብቃት ለመፈፀም በሚያስችል መልኩ በቂ ዝግጅት ማድረጉም ተጠቆመ ።

የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ትናንት “ከራስ በላይ ለህዝብና ለሀገር በሚል መሪ ቃል በመስቀል አደባባይ በተከበረው የፌዴራል ፖሊስ ዓመታዊ ክብረ በዓል ላይ ተገኝተው የሥራ መመሪያ የሰጡት ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድ፣ ኢትዮጵያችን ለማንም ጠላት ሸብረክ ሳትል የጀመረችውን የብልጽግና ጉዞ አጠናክራ እንድትቀጥል ለራሱ ኩራት ለአካባቢው አገሮች ደግሞ የብቃት ምንጭ የሆነ የፖሊስ ሠራዊት የመገንባት ጥረት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል።

‘ዕለቱ በተለይም ራሱን ለአገሩና ለህዝቡ አሳልፎ የሚሰጥና ከሚመጣውና ከሚሄደው ጋር የሚሄድ ሳይሆን ሁሌም ከኢትዮጵያ መገለጫ ባንዲራ ጋር የሚዘምት እንደሆነ ለማሳየት እየተደረገ ያለው ጥረት መሳካቱን የሚያመለክት ትርኢት የታየበት ነው’’ ብለዋል።

የቀረበው ትርኢት ሠራዊቱ አገር ወዳድ፣ ህዝብ አክባሪ፣ ቅንና ለአገሩ ታማኝ መሆኑን የሚያመለክት መሆኑን የገለፁት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ሠራዊቱ ባሳየው ትርኢት በእጅጉ መኩራታቸውን አስታውቀዋል።

የፌዴራል ፖሊስ ሠራዊት ዘመኑን የዋጀ ዘመናዊ ሠራዊት እንዲሆን ባለፉት ሁለት ዓመታት የተጀመሩት ለውጦች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ጠቁመው፣ በዜጎች ውስጥ ሆነው የሚያጠፉትን የመለየት ተግባር ውስብስብ በመሆኑ ፖሊስ ራሱን ማብቃት እንዳለበት አሳስበዋል። ፖሊስ መጥፎ ዜጎችን ከሰላማዊ ዜጎች የመጠበቁ ሥራ ልክ እንደተለየ ጠላት ተኩሶ የሚገድል ወይም ምሽግ ቆፍሮ የሚከላከለው እንዳልሆነም አስታውቀዋል።

በህዝብ ውስጥ ሆነው እያጠፉ ያሉትን የመለየት ሥራ እጅግ ውስብስብ መሆኑን አመልክተው፣

ይህንን ውስብስብ ሁኔታ ለመወጣት የፖሊስ ሠራዊት ራሱን ማብቃት እንዳለበት አስገንዝበዋል።

“ለራሱ ኩራት ለአካባቢው አገሮች ደግሞ የብቃት ምንጭ የሆነ የፖሊስ ሠራዊት የመገንባት ጥረት ተጠናክሮ ይቀጥላል”

- ዶ/ር አብይ አህመድየኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ጠቅላይ ሚኒስትር

ለዚህም በሕግ፣ በሥነ-ልቦና፣ በቴክኖሎጂ በሌሎች የዕውቀት ዘርፎች ራስን ማብቃት እንደሚገባ ጠቁመዋል።

ፖሊስ እንደ ሕግ አስከባሪ ሕግን ጠንቅቆ የሚያውቅ፤ እንደ ወንጀል መርማሪ የወንጀል ምርመራ ክህሎት ያለውና የሥነ ባህሪ ጥናት ያጠና፤ እንደ ሠራዊት ወታደራዊ ብቃት ያለው፤ እንደ አድማ በታኝ የተሟላ ተክለወስነት ያለው ዘመናዊ ሠራዊት እንዲሆን እየተሠራ መሆኑን አመልክተዋል።

ፖሊስ እንደ ደህንነት ተቋም መረጃን መሰብሰብና መተንተን የሚችል፤ ዘመኑን ለመዋጀት የቴክኖሎጂ ብቃትና ግንዛቤ ያለው ዘመናዊ ሠራዊት እንዲሆን የፌዴራል መንግሥት ሁለንተናዊ ድጋፍ እንደሚያደርግም አስታውቀዋል።

“የእኛ ሠራዊት እኛ ስናንቀላፋ የማይተኛ፤ ስንዝናና የማይዝናና፤ የበዓላት ጊዜውን እኛን በመጠበቅ የሚያከብር ሠራዊት ነው” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ፤ ከ365 ቀናት ውስጥ 364 ቀኑ ሰላም ቢሆን ለማመስገን ብዙ ሰዎች አይነሳሱም፤ አንድ ቀን ቢጠፋ ግን ብዙ ወቃሽ ብዙ ረጋሚ ይኖራልም” ብለዋል።

የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር እንዳሻው ጣሰው በበኩላቸው፤ ላለፉት ሁለት ዓመታት የፖሊስን ተቋም ለማዘመን የተለያዩ ሥራዎች ሲከናወኑ መቆየታቸውን አመልክተዋል። ፖሊስ እንደሁልጊዜው የሕግ የበላይነትን ለማስከበርና የሚሰጠውን መመሪያ ተቀብሎ በብቃት ለመፈፀም በሚያስችል መልኩ በቂ ዝግጅት ማድረጉን አስታውቀዋል።

በአሁኑ ወቅት በህዝቦች መካከል ያለውን ሰላምና አንድነት ለመናድ የሃሰትና የሽብር ወሬዎችን በመንዛትና ጊዜንና ወቅትን በመለየት ለረብሽና ለብጥብጥ የሚጋብዙ ቡድኖችና አካላት እንዳሉም አመልክተው፣ ህብረተሰቡ መሰረተ ቢስ በሆኑ አሉባልታዎች ተነሳስቶ በእኩይ ተግባር እዳይሳተፍና ለግጭት እንዳይዳረግም ኮሚሽነሩ ጥሪ አቅርበዋል።

በአሁኑ ወቅትም ሆነ በማንኛውም ጊዜ የአገር ሰላምና የዜጎችን ደህንነት ሥጋት ውስጥ የሚከቱ ድርጊቶችንና አካላትን ለመመከት ኮሚሽኑ ነቅቶ እየሠራ እንደሚገኝ አስታውቀዋል።

ጥናትን መሰረት ያደረጉ የሪፎርም ሥራዎች በኮሚሽኑ የተሠሩ መሆናቸውን ገልፀው፤ በእዚህም ዘመናዊ፣ በእውቀትና በብቃት የጎለበቱ የፖሊስ አባላትን ማፍራት እንደተቻለ አስታውቀዋል።

ኮሚሽኑ በመረጃ ልውውጥና በግብአት እጅግ ዘመናዊ አሠራርን እየተከተለ መሆኑን በመጠቆም ፣ በአሁኑ ወቅት አገሪቷንና ህዝቧን የሚመጥን የፖሊስ ኃይል መኖሩን አመልክተዋል።

በተለያዩ ጊዜያት በሚከሰቱ ግጭቶች ሳቢያ የፖሊስ አባላት አካላቸውንና ህይወታቸውን በማጣት ጭምር ህብረተሰቡን እየታደጉ መሆናቸውን አስታውሰው፣ በቀጣይም ህዝብና አገርን የመጠበቅ ኃላፊነታቸውን በሚገባ እንደሚወጡ አረጋግጠዋል። ህዝቡ ከፀጥታ አካላት ጎን በመሆን ለሰላሙ የድርሻውን እንዲወጣም ጥሪ አቅርበዋል።

የሠላም ሚኒስትሯ ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል በበኩላቸው በኢትዮጵያ እየተገነባ ላለው የዴሞክራሲ ሥርዓት የሠላም ኃይሉ መሪ ሚና እየተጫወተ መሆኑን አስታውቀዋል። ዕለቱ ፖሊስ ለአገር ሠላምና ደህንነት ያለውን ሚና ማሳያ እንደሆነ ገልፀዋል።

የሠላም ኃይሉ ዓላማውን በሚገባ የለየ ነው ያሉት ሚኒስትሯ፣ ከቀደምት ታሪክ መልካም ነገሮችን እየያዘ ማረም ያለበትን እያስተካከለ የሚጓዝበትን መንገድ እያደረጀ መሆኑን ጠቁመዋል። በአገሪቷ እየተገነባ ላለው የዳበረ ዴሞክራሲ መሪ ሚናን እየተጫወተ ይቀጥላል ብለዋል። ሕዝቡም ይህን በመገንዘብ ከፀጥታ አካላት ጋር ለሠላሙና ለአገሩ ደህንነት በጥምረት መሥራት አንደሚጠበቅበት አሳስበዋል።

ጌትነት ተስፋማርያም

አዲስ አበባ:- ፍትህን እና የሕግ የበላይነትን የማስከበር ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የኦሮሚያ ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ እና የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቁ። ችግር ለመፍጠር የሚያስቡ አካላት ካሉ ፖሊስ አስፈላጊውን እርምጃ ለመውሰድ እንደሚገደድም ተናገሩ፡፡

የኦሮሚያ ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ እና የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ትናንት በጋራ በሰጡት መገለጫ እንዳስታወቁት፤ በክልሉ የፍትህ እና የፀጥታ አካላት የሕብረተሰቡን ሠላም እና ደህንነት ለማስጠበቅ በቅንጅት የሚያከናውኑትን ሥራ አጠናክረዋል። ፍትህ ለማስፈን እና የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ የሚደረገው ጥረት በቀጣይ ይጠናከራል።

የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር እና የወንጀል ምርመራ ዘርፍ ኃላፊ ግርማ ገላን እንደገለፁት፤ የክልሉን ፀጥታ ለማረጋገጥ እና ለሰላም

የሚደረገው ጥረት ላይ የፀጥታ ኃይሉ ከምንጊዜውም በላይ አሰላለፉን አጠናክሯል። ሰሞኑንም ከመስከረም 25 በኋላ መንግሥት የለም በሚል የሚናፈሰውን ወሬን ተከትሎ ችግር ለመፍጠር የሚያስቡ አካላት ካሉ ፖሊስ አስፈላጊውን እርምጃ ለመውሰድ ይገደዳል።

መንግሥት የለም ብለው የሚያስቡ ካሉ ተሳስተዋል ያሉት ምክትል ኮሚሽነር ግርማ፤ ወጣቶች የዕቃ ዕቃ ጫዋታ የመሰለውን ፖለቲካ ተከትለው አደጋ ውስጥ እንዳይገቡ ህብረተሰቡ ጥንቃቄ ሊያደርግ እንደሚገባ ተናግረዋል። በተለይ በገጠሩ አካባቢ የሚገኙ እና ስለሁኔታው ምንም ግንዛቤ የሌላቸው ወጣቶች መንግሥት ከሳምንት በኋላ የለም የሚለውን ውዥንብር ተከትለው እጃቸውን እንዳያስገቡ መረጃ ማቀበል እንደሚገባ አስረድተዋል። ከዚህ ውጭ ሆኖ መንገድ ላይ በመውጣት ችግር ለመፍጠር የሚያስብ ካለ ግን አስፈላጊውን እርምጃ ለመውሰድ ዝግጅት መደረጉን ገልፀዋል።

ክልሉ ለሕግ የበላይነት ያለውን ቁርጠኝነት

የሚያሳዩ ሥራዎች እያከናወነ መሆኑን ያነሱት ምክትል ኮሚሽነር ግርማ፤ ከአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ጋር ተያይዞ በተከሰተ ረብሻ እንደተሳተፉ በማስረጃ የተረጋገጠባቸው 4 ሺህ 173 ሰዎች ጉዳያቸው ወደክስ መቅረቡን አስታውሰዋል። በ15 ዞኖች እና ከተሞች የተፈጠረውን ችግር በማረጋጋት እጃቸው ያለበትን የመንግሥት ሃላፊዎች እና በየደረጃው የሚገኙ የመንግሥት ሠራተኞችን እና ወጣቶችን ለሕግ የማቅረብ ሥራው በተደራጀ ሁኔታ መቀጠሉን አስታውቀዋል። በቀጣይም ወንጀል ሠርቶ መደበቅ እና ከሕግ በላይ መሆን እንደማይቻል የሚያሳዩ ክንውኖች በፀጥታ አካላት እንደሚከናወኑ ተናግረዋል።

የኦሮሚያ ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ አቶ ሁሴን ኡስማን በበኩላቸው እንደገለፁት፤ የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት ህብረተሰቡን ባማከለ ሁኔታ ከፀጥታ አካላትን እና ዓቃቤ ሕግ ጋር ተቀናጅተው እየሠሩ ይገኛል። ከዚህ ጋር በተያያዘ ከአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ በኋላ በወንጀል

ተሳትፈዋል የተባሉ ግለሰቦችን ጉዳይ ውሳኔ እንዲያገኝ እየተሠራ ነው። በመሆኑም በሕግ ጥላ ሥር የሚገኙ ጉዳዮችም ያለምንም ርህራሄ በሕግ አግባብ እንዲዳኙ ይደረጋል።

እንደ አቶ ሁሴን ገለፃ፤ ከአርቲስት ሃጫሉ ግድያ በኋላ በተነሳው ረብሻ እና የንብረት ውድመት መሳተፋቸው በማስረጃ ተደገፎ ክስ ከተመሰረተባቸው ሰዎች መካከል የ247ቱ ክስ ውሳኔ አግኝቷል። አሁንም በአሰላ፣ ጅማ፤ ባሌ እና በተለያዩ አካባቢዎች በተሰየሙ ፍርድ ቤቶች ሥር የተከሳሾች ክርክር በመሰማት ላይ ይገኛል። የክስ ሂደቱም በየአካባቢው በማድረግ ምስክሮች ሳይንገላቱ ፍርድ ቤት እማኝነታቸውን እንዲያቀርቡ እና ተከሳሾችም አፋጣኝ ምላሽ እንዲያገኙ ጥረት ተደርጓል። በቀጣይም በክልሉ የሕግ የበላይነትን ለማስከበር እና ፍትህን ለማስፈን አድልዎን ባስወገደ መልኩ የፍርድ ሂደቶች ሥርዓታቸውን ጠብቀው የሚከናወኑ ይሆናል።

በኦሮሚያ ክልል የተጀመረው ፍትህን የማስከበር ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገለፀ

Page 4: “ለራሱ ኩራት ለአካባቢው አገሮች ደግሞ የብቃት ......ገጽ 2 አዲስ ዘመን ሐሙስ መስከረም 21 ቀን 2013 ዓ.ም ዜና አዲስ አበባ፦

ገጽ 4

ዜና

አዲስ ዘመን ሐሙስ መስከረም 21 ቀን 2013 ዓ.ም

ከ1ኛው ገጽ የዞረ

ዓመታቸው ህይወታቸው አለፈ። ፕሮፌሰሩ በኮሮናቫይረስ ተይዘው በቅዱስ

ጳውሎስ ሆስፒታል ላለፉት 10 ቀናት የህክምና ክትትል ሲደረግላቸው እንደቆየና ባለፉት ጥቂት ቀናት ህመማቸው እንደበረታ ከቤተሰቦቻቸው የተገኘ መረጃ ያመለክታል።

ፕሮፌሰር መስፍን ከአባታቸው አቶ ወልደማርያም እንዳለ እና ከእናታቸው ወይዘሮ ይመኙሻል ዘውዴ በሚያዚያ ወር 1922 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሽሮ ሜዳ አካባቢ ተወለዱ።

የመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በተፈሪ መኮንን ትምህርት ቤት የተከታተሉ ሲሆን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የሃይማኖት ትምህርት ተከታትለው ዲቁና አግኝተዋል።

ፕሮፌሰር መስፍን የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን እ.አ.አ በ1951 ከፑንጃብና ቻንዲጋር ዩኒቨርሲቲ አግኝተዋል።

በኢትዮጵያ የገጠር ክፍል የሚኖሩ ዜጎች የረሃብ ተጋላጭነት በተመለከተ ባቀረቡት የመመረቂያ ጽሁፍ የማስተርስ ዲግሪያቸውን አሜሪካ ከሚገኘው ክላርክ ዩኒቨርሲቲ ማግኘት ችለዋል።

ትምህርታቸውን አጠናቀው ሲመለሱም በቀድሞው ቀዳማዊ ኃይለስላሴ ዩኒቨርሲቲ በአሁኑ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከ1951 እስከ 1965 ዓ.ም ጂኦግራፊ የትምህርት ክፍል ሃላፊነትን ጨምሮ በመምህነት ሰርተዋል።

በ1970ዎቹ መጀመሪያ ወደ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ዳግም በመመለስ በጡረታ እስከተገለሉበት ጊዜ በዩኒቨርሲቲው በመምህርነት አገልግለዋል።

ረጅም የአካዳሚክ ሕይወት ያላቸው ፕሮፌሰር መስፍን በኢኮኖሚ፣ በታሪክ፣ ፖለቲካ፣ ጂኦግራፊ፣ ሰብዓዊ መብት፣ ድርቅ፣ ረሃብና ሌሎች ጉዳዮች ላይ

በርከት ያሉ ጥናታዊ ጽሁፎችንና የተለያዩ መጽሐፎችን አበርክተዋል።

በተለያዩ ዓለም አቀፍ መድረኮች ላይ የተለያዩ ጥናታዊ ጽሁፎች ያቀረቡ ሲሆን ፕሮፌሰር መስፍን ባገኟቸው መድረኮች ያላቸውን እውቀት፣ ልምድና ምልከታ በስፋት አካፍለዋል።

ከአካዳሚ እውቀታቸው በተጨማሪ በ1967 ዓ.ም ከ30 በላይ ግጥሞችን በያዘችው “እንጉርጉሮ” መድብል ማህበራዊ ችግሮች በመንቀስ የሞራል እሴቶችን ለመዳሰስ ሞክረዋል።

“አዳፍኔ: ፍርሃትና መክሸፍ”፣ “አገቱኒ ተምረን መጣን”፣ “ስልጣን ባህልና አገዛዝ ፖለቲካና ምርጫ” እና “አደጋ ያንዣበበት የአፍሪካ ቀንድ” ካሳተሟቸው መጽሐፎች መካከል ይጠቀሳሉ።

“The horn of Africa: conflict and pover-ty”፣ “Somalia: The problem child of Africa” እና “Suffering under GOD’S environment” የሚሉ መጽሐፎችንም በእንግሊዝኛ ቋንቋ አሳትመዋል።

በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥም ተሳትፎ የነበራቸው ፕሮፌሰር መስፍን በ1993 ዓ.ም ከተማሪዎች በተሰበሰበ ፊርማ የአካዳሚ ነጻነትን አስመልክቶ ከፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ጋር በኢትዮጵያ ብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር መሰብሰቢያ አዳራሽ ውይይት ያደረጉ ሲሆን ፕሮፌሰር መስፍን በውይይቱ አማካኝነት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አመጽ እንዲነሳ አድርገዋል በሚል ክስ ሳይመሰረትባቸው ለሁለት ወር ገደማ ታስረው ነበር።

በ1998 ዓ.ም ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም በአገር መክዳት፣ የሕገ መንግስቱን ሥርዓት አደጋ ላይ በመጣልና ሌሎች ወንጀሎችን ፈጽመዋል ተብለው

ከሌሎች የአንድነት ለፍትህና ዴሞክራሲ ፓርቲ አባላቶቻቸው መታሰራቸውን የሚታወስ ነው።

በ2000 ዓ.ም ፕሮፌሰር መስፍንን ጨምሮ ሌሎች የተፎካካሪ ፓርቲዎች አባላት እስራት ከተፈረደባቸው በኋላ በይቅርታ እንዲፈቱ ተደርጓል።

ፕሮፌሰር መስፍን የሃሳብ ነጻነት እንዲሰፍን፣ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት እንዲገነባና የፖለቲካ ምህዳር እንዲሰፋ ትግል አድርገዋል።

ፕሮፌሰር መስፍን ሁለት ሴቶችና አንድ ወንድ ልጅ አፍርተዋል።

የፕሮፌሰሩን ህልፈተ ህይወት ተከትሎ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድም በፕሮፌሰር መስፍን እረፍት የተሰማቸውን ኀዘን ገልፀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኀዘን መግለጫቸው የሃሳብ ልዕልና ምልክት፤ የሰላማዊ ትግል አርአያ፣ ላመኑበት ነገር እስከ መጨረሻቸው ሞጋች፣ ላመኑበት እውነት ብቻ የሚቆሙት ፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም በማረፋቸው ጥልቅ ኀዘን እንደተሰማቸው ገልጸዋል።

“ለቤተሰቦቻቸው፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸው እና ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ መጽናናትን እመኛለሁ” ብለዋል ።

በተመሳሳይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ በፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም ህልፈት ህይወት የተሰማቸውን ኀዘን ገለጸዋል።

ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ ፕሮፌሰር መስፍን ትልቅ የእ ውቀት አባት፣ ቁርጠኛ ሰላማዊ ታጋይ፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች እና ላመኑበት ጉዳይ ማንኛውንም መስዋዕትነት ለመክፈል ወደኋላ የማይሉ የጽናት ተምሳሌትና የአዲሱ ትውልድ አርአያ ናቸው ብለዋል።

ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ፣ ለቤተሰቦቻቸው፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸው እና ለአድናቂዎቻቸው ርዕሰ መስተዳድሩ መጽናናትን ተመኝተዋል።

በተመሳሳይ ዜና ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ህልፈተ ህይወት የተሰማቸውን ሐዘን ገለፀዋል።

ፕሬዚዳንቷ በሀገራችን የፖለቲካ ምህዳር አንጋፋ ቦታ የነበራቸው፣ ሐሳባቸውን ካለ ምንም ይሉኝታና ፍርሃት በመግለጽ የምናውቃቸው ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ከዚህ ዓለም በሞት ስለተለዩን በጣም አዝኛለሁ ብለዋል። ለቤተሰቦቻቸው እና ለወዳጆቻቸው መጽናናትን ተመኝተዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በተመሳሳይ መልኩ በፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ህልፈተ ህይወት የተሰማቸውን ሐዘን ገልፀዋል። ለቤተሰቦቻቸው፣ ለወዳጆቻቸው እና ለጓደኞቻቸው መፅናናትን እመኛለሁ ብለዋል።

የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ በፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ሞት የተሰማቸውን ሐዘን ገልፀዋል። የኢትዮጵያ አንጋፋ ምሁር፣ ፖለቲከኛና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች የሆኑት ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ዜና ዕረፍት ስሰማ ጥልቅ ሐዘን ተሰምቶኛል ብለዋል። ለቤተሰባችውና ወዳጅ ዘመዶቻቸው እንዲሁም ለኢትዮጵያ ህዝብ መፅናናትን ተመኝተዋል።

ፕሮፌሰር መስፍን የሚናገሩትና የሚሠሩት ተመሳሳይ ስለሆነ በርግጥም አስተማሪ ነበሩ፣ የአቅም ሰው ስለነበሩ አደንቃቸዋለሁ ብለዋል።

ፕሮፌሰር መስፍን...

የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ እንዳስታወቁት፣ የበጀት ድጋፍ ስምምነቱ ለብሔራዊ የኮቪድ-19 ዘርፈ ብዙ የዝግጅት እና የምላሽ ዕቅድ አፈፃፀም ድጋፍ የሚውል ነው ።

የኮሮና ወረርሽኝ እያስከተለ ባለው በርካታ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጽዕኖዎች ምክንያት የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ዕድገት የከፋ አደጋ ውስጥ እንዳይወድቅ ድጋፉ በጣም ወሳኝ ነው ያሉት አቶ አህመድ፤ የኢትዮጵያ መንግሥት ይህንን የበጀት የገንዘብ ድጋፍ በመጠቀም ቁልፍ የኢኮኖሚ ተግባራት ቀጣይነትን ለማረጋገጥ እና የጤና ዘርፉን በማጠናከር የወረርሽኙን ምላሽ አሰጣጥ በስኬታማነት ለማስቀጠል ይረዳል ብለዋል።

ድጋፉ ለአደጋ ተጋላጭ የሆኑ ዜጎችን፣ በተለይም የምግብ እና አስፈላጊ አገልግሎቶችን ለሚፈልጉ ዜጎች የሚያስፈልገውን ወጪ ለመሸፈን እንደሚረዳ አመልክተው፣ የወረርሽኙን መስፋፋትን እና ተጽዕኖ ለመቋቋም እንደሚያግዝ አመልክተዋል።

“በሕይወት ትውስታ ውስጥ ካየነው ከማንኛውም ነገር እጅግ በጣም ውስብስብ፣ የበለጠ እርግጠኛ መሆን የማይቻልበት እና እጅግ በጣም ከባድ የሆነው የኮቪድ- 19 የጋራ ቀውስ ሲገጥመን የጀርመን መንግሥት ያሳየው አጋርነትና ጽኑ ድጋፍ የጠንካራ አጋርነታችን ማረጋገጫ ነው”ብለዋል።

አገራቱ ከሰባት አስርት ዓመታት በላይ የዘለቀው በመከባበር እና በመተማመን ላይ የተመሰረተ ግንኙነት እንዳላቸው የጠቆሙት አቶ አህመድ፤ የጀርመን መንግሥት ለሀገሪቱ ሁለንተናዊ ድጋፍ በማድረግ ትልቅ አሻራ ማሳረፉን ጠቁመዋል።

በተለይም ኢትዮጵያ ሪፎርምን ተግባራዊ ለማድረግ ጥረት እያደረገች ባለችበት ወቅት ሳይታሰብ የተከሰተው የኮቪድ 19 ወረርሽኝ የሪፎርሙን አጀንዳ እንዳያከሽፍና እና በድህነት ቅነሳ፣ በማህበራዊ አገልግሎት አሰጣጥ እና በሥራ ዕድል ፈጠራ የተመዘገቡትን የሀገሪቱን ዋና ዋና ስኬቶች እንዳይሸረሽር ሥጋት መኖሩን አመልክተዋል።

የወረርሽኙ ተጽዕኖ ሪፎርሙ ላይ እንዳያጠላ እና ባለፉት ጊዜያት የተመዘገቡ ስኬቶችን እንዳይሸረሽሩ የኢትዮጵያ መንግሥት የተለያዩ ሥራዎች እየሠራ ነው። ነገር ግን ብዙ የሚጠበቅ ነገር አለ ብለዋል። እንደ ኢትዮጵያ ያለ ሀገር ኮቪድ 19 እያስከተለ ያለውን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጽኖዎች ብቻውን ምላሽ መስጠት ይከብደዋል። በተለይም የገንዘብ እጥረት ከባድ ተግዳሮት መሆኑ የማይቀር እንደሆነ አስታውቀዋል።

በወረርሽኙ ምክንያት የሚመጣውን ቀውስ ለማቃለል በቂ ሀብት ማሰባሰብ በጣም አስፈላጊ ነው ያሉት አቶ አህመድ፣ ከጀርመን መንግሥት የተደረገው አስቸኳይ የገንዘብ ድጋፍ አገራዊ የኮቪድ 19 የባለ ብዙ ዘርፍ ዝግጁነት እና ምላሽ ዕቅድን እውን ለማድረግ የመንግሥትን ጥረት ያግዛል ብለዋል።

በኢትዮጵያ የጀርመን አምባሳደር ስቴፈን አወር በበኩላቸው፤ ኢትዮጵያ ለጀርመን በጣም ጠቃሚ ስትራቴጂክ አጋር መሆኗን ገልፀው፣ ከዚህ በመነሳት ለኢትዮጵያ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ድጋፍ እንደምታደርግ አመልክተዋል። የጀርመን መንግሥት ለሀገሪቱ የሚሰጠውን ድጋፍ አጠናክሮ ለመቀጠል ዝግጁ መሆኑንም አስታውቀዋል።

በኢትዮጵያና በጀርመን...ከ1ኛው ገጽ የዞረ

Page 5: “ለራሱ ኩራት ለአካባቢው አገሮች ደግሞ የብቃት ......ገጽ 2 አዲስ ዘመን ሐሙስ መስከረም 21 ቀን 2013 ዓ.ም ዜና አዲስ አበባ፦

Website - www.press.et Email - [email protected] Facebook - Ethiopian Press Agency

ርዕሰ አንቀፅ

ግንቦት 30 ቀን 1933 ዓ.ም ተቋቋመ

አዲስ ዘመን

የዝግጅት ክፍል ፋክስ - 251-011-1-56-98-62

ምክትል ዋና አዘጋጅ

ስልክ ቁጥር - 011-1-26-42-00

አዘጋጆችሀብታሙ ስጦታውፍሬህይወት አወቀለምለም መንግስቱ

የገበያ ልማትና ፕሮሞሽን ዘርፍኢሜይል - [email protected] ስልክ - 011-156-98-73ፋክስ - 011-156-98-62

የማስታወቂያ መቀበያ ክፍልስልክ ቁጥር - 011-156-98-65

የማስታወቂያ ሽያጭ ማስተባበሪያስልክ - 011-1-26-43-39

ማከፋፈያስልክ ቁጥር - 011-157-02-70

አዲስ ዘመን ሐሙስ መስከረም 21 ቀን 2013 ዓ.ም ገጽ 5

እያሱ መሰለታምራት ተስፋዬመላኩ ኤሮሴ

ይህ አምድ በተለያዩ ፖለቲካዊ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ዜጎች ነፃ ሀሳባቸውን የሚሰጡበት ነው። በዓምዱ ላይ የሚወጡ ጽሁፎች የዝግጅት ክፍሉን አቋም አያመለክቱም። ነፃ

ሀሳብ

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዋና ስራ አስኪያጅ

ስልክ ቁጥር - 011-126-42-22ዋና አዘጋጅ

አንተነህ ኃ/ብርሃን ወ/መድህንአድራሻ

ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከወረዳ 06የቤት ቁጥር 319ኢሜይል - [email protected]ስልክ ቁጥር - 011-1-26-42-40

ይቤ አብርሃ ከውቤ በረሃ

ኦሮሞ በምሥራቅ አፍሪካ ካሉት ብሔሮች መካከል ሠፊውን የኢትዮጵያ ማኅበረሰብ ያካተተ ህዝብ ነው። ከኩሽ ነገዶች ውስጥ የሚካተተው ኦሮሞ ከአፍሮ እስያ ተናጋሪዎች ይመደባል። የኦሮሞ ብሔር በትውፊት ሲወርድ ሲዋረድ በመጣው በባህላዊው የገዳ አመራር ሥርዓት ሲተዳደርና ሲገለገል ቆይቷል።

ተመራጩ አባገዳ በገዳ በሥርዓቱና በባህሉ መሠረት የስምንት ዓመታት አባገዳነቱ ሲያበቃ ለቀጣዩ ተመራጭ መሪ ወይም አባገዳ ሥልጣኑን ያስረክባል።ይህም በሠለጠነው ዓለም ዴሞክራሲ ከመታሰቡ በፊት ኦሮሞ በገዳ ሥርዓት አመራሩን መርጦ ሲተዳደር እንደነበር የሚያሳይ ነው። ይህ አኩሪው የገዳ ሥርዓት ከኢትዮጵያ የማይዳሰሱ ቅርሶች አንዱ ሆኖ በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኒስኮ) ተመዝግቧል።

በአዲስ አበባ መስከረም 23 ቀን 2013 ዓ.ም. የሚከበረው የእሬቻ በዓል (ሆራፊንፊኔ)፣ አባ ገዳዎች በሚወስኑት ተሳታፊዎች ቁጥር ብቻ እንደሚከበር ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ ያስታውቁ ሲሆን የመዲናዋ አስተዳደር የመሬት ልማትና ከተማ ማደስ ኤጀንሲም 27ሺ776.7 ሜትር ካሬ ለሆራ ፊንፊኔ ክብረ በዓል ማከናወኛ የሚሆን የይዞታ ማረጋገጫ ለኦሮሚያ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ አስረክቧል።

የእሬቻ በዓል አባ ገዳዎች በሚያዘጋጁት የመለያ መግቢያ ካርድ ብቻ የሚስተናገድ ሲሆን ፤ በአዲስ አበባ የሚከበረው ሆራ ፊንፊኔ በዓል መስከረም 23 ቀን 2013 ዓ.ም በፊንፊኔ ፣ በማግስቱ እሁድ መስከረም 24 ቀን ደግሞ በቢሾፍቱም እሬቻ ይከበራል ። በየዓመቱ ክረምት ከወጣ በኋላ የሚከበረው እሬቻ የገዳ ሥርዓት አካልና የምስጋናና የሰላም ቀን ነው።ከክረምቱ ጨለማ ወደ ፀደይ ብርሃናማ ላሸጋገረ ፈጣሪ ምስጋና የሚቀርብበት ምዕራባውያን Thanks giving day (የምስጋና ቀን) እንደሚሉት ዓይነት በዓል ነው ሲል የዊኪፒዲያ ኢንሳይክሎፒዲያ ድረገፅ ይገልፃል።እሬቻ በባህላዊ ስነሥርዓት ሲከበር ለአዲሱ ዓመት ያደረሳቸውን አምላክ ለማመስገን ብቻ ሳይሆን በአዲሱ ዓመት የተዘራው እህል አፍርቶ ጎተራው በእህል ተሞልቶ የሰላም ዘመን እንዲያደርግላቸው የሚለምኑበት ቀን መሆኑን ከድረገፁ ያገኘነው መረጃ ያስረዳል።

በኦሮሞ ባህል መሠረት እሬቻ ሲከበር ፀብና ጥላቻ ተወግዶ እርቅና ፍቅር የሚመሠረትበት ስለሆነ እሬቻ ጥላቻና ሽኩቻ የሚሸነፍበት በዓል ነው ማለት ይቻላል።ባህሉም የአብሮነት እንጂ የመለያየት አለመሆኑን ከተለያዩ ብሔር ብሔረሰቦች የተውጣጡ ሽማግሌዎችና ወጣቶች ተገኝተው በዓሉንም ሲታደሙ ስታዩ ልትደመሙ ትችላላችሁ። ከኦሮሚያም ከአራቱም አቅጣጫ የሚመጡ ኦሮሞዎች እንደ አካባቢያቸው የተለያየ የክትና የባህል ልብሳቸውን ለብሰው አሸብርቀውና ደምቀው ታያላችሁ።ኮረዶች፣ ጉብሎች፣ ጎልማሶችና አዛውንት እንዲሁም አባወራዎችና እማወራዎች በዓሉን ጠብቀው ይታደሙበታል። ይህም የበዐሉን ድምቀት የሚያጎላ ነው ማለት ይቻላል።

እሬቻ ከላይ እንደጠቀስነው ከክረምቱ ዝናባማና ጨለማ ጊዜ ወደ ፀደይ ብርሃናማ ላሸጋገረ ዋቃ (አምላክ) ምስጋና የሚቀርብበት ሲሆን ምድር በልምላሜና በአደይ አበባ የምታሸበርቅበት ጊዜ መሆኑ እና በዓመት የሚከበር ስለሆነ ይደምቃል።ገበሬዎችና ቤተሰቦቻቸው አሰልቺውንና አታካቹን የክረምት ወቅት በእርሻ አሳልፈው ፋታና እፎይታ የሚያገኙበት ወቅት መሆኑም ለበዐሉ ድምቀት የራሱ አስተዋፅዖ አለው።

የክረምቱ ወራት በኦሮሞዎች ዘንድ እንደ አስቸጋሪ ወቅት የሚታይ፤ በክረምቱ ኃይለኛ ዝናቦች ወንዞች የሚሞሉበት፤ ህዝብን የሚያፈናቅሉ የጎርፍ መጥለቅለቅ የሚታይበት በዚህም ሰዎች፣ ከብቶች፣ ሰብሎችና መኖሪያ ቤቶች ለአደጋ የሚጋለጡበት ወቅት ነው። በተለይ ያለፍነው የክረምት ወቅት ከሌሎች ክረምቶች በላቀ መልኩ ዝናብ የበዛበት ሰዎች ያፈናቀለበት መሆኑ የክረምትን አስቸጋሪነት ማሳያ ይሆናል ። በተጨማሪም ከከተማ ውጪ በሆኑ ቦታዎች የቤተሰብና የዘመድ መጠያየቅ ወንዞች ስለሚሞሉ አስቸጋሪ ይሆናል ።ያለፈውን ዓመት አስቸጋሪ ወቅት ያሳለፍከን ቀጣዩንም ዓመት በሰላም ያደረስከን በማለት ህዝቡ ተሰብስቦ በባህላዊ መልኩ ያከብረዋል።

የመስቀል ደመራ፣ የጥምቀት ከተራ፣ የሲዳማው ፍቼ ጨምበላላ አከባበሮች በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት የሳይንስና የባህል ድርጅት በማይዳሰሱ ዓለም አቀፍ ቅርሶች መመዝገባቸው ይታወሳል። የአሸንዳ ጭፈራ፣ ከአረፋ በኋላ በትግራይ አል ነጃሺ የሚከበረው አሹራ እና የኢሬቻ አከባበርን ለማስመዝገብ የሚደረግ

ጥረት መጠናከር አለበት።እሬቻ የበዓሉን ትውፊት በጠበቀ መልኩ ፀጥታና

ውበት ባለው መልኩ እንዲከበር የፀጥታ አስከባሪዎች ግዴታቸውን ለመወጣት ጥረት ማድረግ ኅብረተሰቡም ከኮቪድ 19 እራሱን ለመጠበቅ የአፍና የአፍንጫ ጭምብል ማድረግ ይገባዋል።

እሬቻ ባህላዊ መድረክ ነው፤ በዓሉ ሲከበር ለምለም ሣር ይዘው ምስጋና እያቀረቡ ኮረዶችና ጉብሎች የተለያዩ ባህላዊ አለባበሶችን ለብሰው በየአካባቢያቸው ያለውን ጭፈራ የሚያሳዩበትና የሚደሰቱበት ቀን ነው። በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያኖች የተለያዩ በዓሎች ሲከበሩ ሰው ቤቱ ለምለም ሣር ይጎዘጎዛል ። ድርጊቱ የሃይማኖቱ ግዴታ ሳይሆን ሰው በባህል የሚከውነው ነው። ይህም ለምለም ሣር በጎ ምሳሌ መሆኑንና የህዝቡ ባህል እርስ በርስ መወራረሱን ያሳያል።

እሬቻ በዩኔስኮ እንዲመዘገብ ከተፈለገ አላስፈላጊ የፖለቲካ መልዕክቶች ጥላውን እንዳያሳርፉበት ለማንፃት ጥረት መደረግ አለበት። እሬቻ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ለማወደስና ለመውቀስ የሚወጣበት መድረክ አይደለም።ለፓርቲዎች ያለንን ድጋፍ የምናሳይበት ወይም ያለንን ተቃውሞ ለመግለፅ የምንሰበሰብበት አለመሆኑ ሊታወቅ ይገባል። የፖለቲካ ፓርቲዎች አጋጣሚውን ህዝብ በተሰበሰበበት ሊገልጡ ስለሚፈልጉ ወጣቱ ለአላስፈላጊ የፖለቲካ አታካራ እንዳይገባ የኦሮሞ አባገዳዎች ኅብረትና የሚመለከታቸው አካላት ኃላፊነት አለባቸው። እሬቻ ለዘመናት ሲከበር የነበረ በዓል ነው፤ ጥላቻና ሽኩቻ በእሬቻ አከባበር የለም። የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች አርማንም እያውለበለቡ በዓሉ ላይ መገኘትም በዓሉን ያደበዝዘዋል።

እሬቻ እንደ ባህል በአግባቡ ከተከበረ በተመድ የሳይንስና የባህል ድርጅት በማይዳሰሱ ቅርሶች ለማስመዝገብ ለሚደረገው ጥረት ሠፊ አስተዋፅዖ ይኖረዋል።በዓሉ በባህሉ መሠረት እንዲከበር የባህል ሚኒስቴርና የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮን ጨምሮ የሚመለከታቸው አካላት ይረባረቡ። በዓሉን የልዩነት ሰበዝ በመምዘዝ ለማደብዘዝ የሚደረግ ጥረት ይወገዝ።የፖለቲካ ጥላዎች ሳያጠሉበት እንደ ባህል እንዲከበር እና በዩኔስኮ በማይዳሰሱ የኢትዮጵያ ቅርሶች ውስጥ እንዲመዘገብ ግዴታችንን እንወጣ። ‘ቢራን በሪኤ በረ ሀራ በገ ጌሰኒ! ‘

ጥላቻና ሽኩቻ የሚሸነፍበት እሬቻ

መንግስት ከለውጡ ማግስት ጀምሮ የጸጥታና የፍትህ ተቋማት ሀገራዊ ተልእኳቸውን በስኬት መወጣት እንዲችሉ የተለያዩ የሪፎርም ፕሮግራሞችን ተግባራዊ በማድረግ ላይ ይገኛል ። እነዚህ ፕሮግራሞች ተቋማቱ የተሰጣቸውን ሀገራዊና ህዝባዊ ተልእኮዎች አስተማማኝ በሆነ የማስፈጸም ብቃት ላይ ሆነው እንዲያከናውኑ የማስቻል አላማ ያነገቡ ናቸው ።

ከለውጡ በኋላ ወደ ሪፎርም ከገቡ ከእነዚህ ተቋማት መካከል የሀገሪቱ የፖሊስ ሰራዊት አንዱና ዋነኛው ነው። የፖሊስ ሰራዊቱ ህግና ስርአትን በማስከበር የህግ የበላይነት የሰፈነበት ስርአት ከመፍጠር አንጻር ያለውን ተቋማዊ ተልእኮ በብቃት መወጣት እንዲችል ተግባራዊ እየሆነ ያለው የሪፎርም ፕርግራም የሰራዊቱን ሁለንተናዊ አቅም እና የግዳጅ ዝግጁነት ብቃት አስተማማኝ ለማድረግ የሚያስችል ነው።

ቀደም ባሉት ዘመናት የፖሊስ ኃይሉ ከነበረበት የተደበላለቀ ተልእኮ ወጥቶ በህግና በህገመንግስቱ የተሰጠውን ሕግንና ህግን ብቻ የማስከበር እና የማስፈን ተልእኮውን በጠራ መሰረት እና አስተሳሰብ ላይ በመገንባት የተሻለ ሙያዊ ቁመና እንዲይዝ የሚያስችለው ነው። ከዚህም በላይ ፖሊስ ፖሊስ ሆኖ ሁለንተናዊ ዝግጁነት እንዲኖረው የሚያግዝ ጭምር ነው።

በተለይም ሀገሪቱ የጀመረችውን የለውጥና የብልጽግና ጎዳና በስኬት ለማጠናቀቅ ሰላም ካለው የማይተካ ሚና አንጻር የሪፎርም ፕሮግራሙ የሚኖረው ስትራቴጂክ አስተዋጽኦ ከፍ ያለ ነው ። በሀገራችን ተግባራዊ እየሆነ ያለው ለውጥ ከቀደሙት ለውጦች በአብዮት መንፈስ የተቃኘ አለመሆኑ ደግሞ የፖሊስን ፖሊሳዊ ሁለንተናዊ ዝግጅት ከመቼውም ጊዜ በላይ የሚጠይቅ ሆኗል።

ራሱን ለአገሩና ለህዝቡ አሳልፎ የሚሰጥ ፣ መጥቶ በሚሸኝ የፖለቲካ አስተሳሰብ የማይጠለፍ፣ ሁሌም ፖሊስ ሆኖ ሕጋዊነትንና ህጋዊ ስርአትን በመፍጠር ሂደት ውስጥ ንቁ ተሳታፊ እና ለዚህም እራሱን ያዘጋጀ ፣ ለተልእኮው ስኬት የሞራል ልእልና የተላበሰ እንዲሆን ያስችላል።

ከሁሉም በላይ ህግና ህጋዊነት ለአንድ ሀገር ሁለንተናዊ እድገት የሚኖረውን ከፍ ያለ ስፍራ በአግባቡ በመረዳት

፣ ይህንን ከፍ ያለ ማህበራዊ እሴት የመጠበቅ ትልቅ ኃላፊነት ያለበት መሆኑን የተገነዘበ ፣ የህግ ማስከበር ተልእኮውም ከዚህ እውነታ የመነጨና ጥልቅ ኃላፊነት መሆኑን የተረዳ እንዲሆን ይረዳዋል።

ህዝብ የሀገር ትልቁ እና መተኪያ የሌለው ሀብት መሆኑን በመረዳት ህዝብ አክባሪ ፣ ቅንና ለአገሩ ታማኝ መሆን እንዲችል ፣ ተልእኮውን ባከበረ መጠን በህዝብ ልብ ውስጥ የተሻለ ቦታ እንደሚኖረው ፣ ይህ ደግሞ ለተልእኮው ስኬት አልፋና ኦሜጋ መሆኑን መረዳት ያስችለዋል።

የፖሊስ ስራ ተልእኮ አነጣጥሮ ቃታ ከመሳብ ያለፈ የብዙ እውቀት ባለቤትነትን የሚጠይቅ ፣ ብዙ ማንበብ ፣ ብዙ ማሰብ ፣ በብዙ የኃላፊነት መንፈስ መያዝ ፣ ለኃላፊነት ስኬት ቁርጠኛ መሆንን የሚጠይቅ ነው። የኃላፊነቱ ስኬት በየእለቱ ከሚከሰቱ አዳዲስ ክስተቶች ጋር ፈጥኖ እራስን ማስተካከልና ከፍ ብሎ እና በቅቶ መገኘትን የሚጠይቅ ነው።

በተለይ በለውጥ ወቅት በአዲሱ እና በአሮጌው አስተሳሰብ መካከል የሚፈጠሩ ተቃርኖዎች በመነጋገርና በውይይት የማይፈቱበት ደረጃ ሲደርሱ የሚፈጠረው የተቃርኖ ግጭት ሕዝብ እና ሀገርን ዋጋ እንዳያስከፍሉ የፖሊስ ፖሊስ የሆነ በሙሉ ቁመና መገኘት ወሳኝ ነው።

በለውጥ ወቅት በሚከሰቱ ተቃርኖዎች የሚፈጠሩትን ውስብስብ ሁኔታዎች አሸንፎ ለመውጣት የፖሊስ ፖሊሳዊ ብቃት ወሳኘ ነው። ብቃቱ የተሰጠውን ተልእኮ መሰረት ያደረገና ለዛም የተገዛ ሊሆን ይገባል። ወቅታዊ ሁኔታዎችን በአግባቡ ከመተንተን ጀምሮ በህግ፣ በስነ-ልቦና፣ በቴክኖሎጂ በሌሎች የዕውቀት ዘርፎች ራስን ማብቃት ይኖርበታል ።

ለዚህም ነው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ፖሊስ በሙያው እንደ ህግ አስከባሪ ህግን ጠንቅቆ የሚያውቅ፣ እንደ ወንጀል መርማሪ የወንጀል ምርመራ ክህሎት ያለውና የሥነ ባህሪ ጥናት ያጠና፤ እንደ ሰራዊት ወታደራዊ ብቃት ያለው፤ እንደ አድማ በታኝ የተሟላ ተክለሰውነት ያለው ዘመናዊ ሰራዊት ሊሆን ይገባል። ፖሊስ እንደ ደህንነት ተቋም መረጃን መሰብሰብና መተንተን የሚችል፣ ዘመኑን ለመዋጀት የቴክኖሎጂ ብቃትና ግንዛቤ ያለው ሊሆን ይገባል ማለታቸውም ለዚህ ነው።

በለውጥ ወቅት የሚፈጠሩ የአስተሳሰብ ተቃርኖዎች ዋጋ እንዳያስከፍሉን ፖሊስ ፖሊስ ሆኖ በሙሉ ቁመና መገኘቱ ወሳኝ ነው !

Page 6: “ለራሱ ኩራት ለአካባቢው አገሮች ደግሞ የብቃት ......ገጽ 2 አዲስ ዘመን ሐሙስ መስከረም 21 ቀን 2013 ዓ.ም ዜና አዲስ አበባ፦

አዲስ ዘመን መስከረም 21 ቀን 2013 ዓ.ምገጽ 6

ንግድ/ ኑሮ

በጤና እክል ምክንያት ትምህርቷን ከዘጠነኛ ክፍል እንዳቋረጠች ትናገራለች። የስድስት አመት ልጅ አላት። ወጣትነትና የልጅ እናት መሆን ሥራ ሳይኖር ከባድ እንደሆነ መገመት አያዳግትም። ወጣትዋ ይሄን ከባድ ጊዜ ለማለፍ ልጇን በትውልድ ቦታዋ ጎጃም ውስጥ ለወላጅ እናቷ ትታ አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ሰርታ እርስዋን፣ልጅዋን እናትዋን ማስተዳደር ከጀመረች ስምንት አመታት ተቆጥሯል። ባለታሪኳ ጤና ሽፈራው ትባላለች።

ወጣት ጤና አዲስ አበባ ከተማን እንዳሰበችው በቀላሉ ኑሮን ለመምራት የማይቻልባት እንደሆነች ለመረዳት ጊዜ አልወሰደባትም። ኑሮን ለማሸነፍ በብዙ ትግል ውስጥ ማለፍ ግድ መሆኑን በእንግድነት ለጊዜው ባረፈችበት ዘመድ ቤት ውስጥ ሆና ለማየት ችላለች። ስለኑሮዋ እንዳጫወተችኝ ወደ አዲስ አበባ ከተማ ስትመጣ ስለምትኖርበት ቤት፣ የዕለት ጉርሷን እንዴት እንደምታሟላ፣ በአጠቃላይ እንዴት እንደምትኖር አላሰበችም።

ብቻ አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ኑሮዋን ለመቀየር ነው አመጣጧ። ካረፈችበት ዘመድ ቤት ወጥታ ኑሮን ‹ሀ› ብላ የጀመረችው በሰው ቤት ውስጥ ተቀጥራ በመሥራት ነበር። የሰው ቤት ቆይታዋ ግን ብዙም አላስደሰታትም። ለተወሰነ ጊዜ ካሳለፈች በኋላ ሥራ ስትፈልግ በአንድ የግል ትምህርት ቤት ውስጥ የጽዳት ሥራ አገኘች። ወርሃዊ ደመወዝዋም አንድ ሺ አምስት መቶ ብር ነው።

የማር ልማት ሥራ ተጠቃሚው ጋር እስኪደርስ ድረስ ብዙ የግብአት አቅርቦት እንደሚያስፈልግ የዘርፉ ባለሙያዎች ይገልጻሉ። ከግብአቶቹ ወይንም ከማናቢያ ቁሳቁሶች ንብ አናቢው

በእንክብካቤ ወቅትና በማር ቆረጣ ጊዜ በንብ መንጋ እንዳይነደፍ ከራስ ፀጉሩ እስከ እግሩ ድረስ የሚጠቀመው መከላከያ ወይንም አልባስ ሲሆን፤ማሩን ከሰፈፉ ለይቶ አጣርቶና አሽጎ ተጠቃሚው ጋር ለማድረስም የማር ማጣሪያ መሳሪያና ማሸጊያ አስፈላጊ ከሆኑት ግብአቶች መካከል ይጠቀሳሉ።

የማር ልማትን ለማሳደግ ደግሞ የተሻሻለ የማር ቀፎ ወሳኝ ነው። በመሆኑም የማር ልማቱ ሰንሰለቱን ይዞ ሸማቹ ጋር እንዲደርስ ግብአቶቹን የሚያቀርብ አምራችና ነጋዴ መኖር አለበት። በአጠቃላይ የእነዚህ ግብአቶች አስፈላጊነት ከማር ልማት ዕድገት ጋር ይያያዛል። በኢትዮጵያ የማር ልማትን ለማዘመን አበረታች የሆኑ እንቅስቃሴዎች ቢኖሩም ሙሉ ለሙሉ ከባህላዊ አመራረት የተላቀቀ ባለመሆኑ ለግብአቶቹ አቅርቦት ያለው ፍላጎት ዝቅተኛ መሆን ወይንም በስፋት ጥቅም ላይ አለመዋል እንደ አንድ ምክንያት ይጠቀሳል።

የማነቢያ ቁሳቁሱ ያን ያህል ጥቅም ላይ እየዋለ ባይሆንም እንደ ሀገር ግን ጅምሩ መኖሩንና በተለይም ዘመናዊ የማር ልማት ሥራ እንቅስቃሴ ባለባቸው አካባቢዎች ጥቅም ላይ እየዋለ ነው። በዋጋ ውድና ተደራሽነቱም የሚፈለገውን ያህል ባይሆንም ተግዳሮቱን የሚያቃልል ተስፋ ሰጭ ሥራ እየተሰራ ነው። በመሆኑም የንብ ማናቢያ ቁሳቁሶችን በሀገር ውስጥ በማሟላት ለግብአቱ የሚወጣውን የውጭ ምንዛሪ ለማስቀረትና ዘጌችም ግብአቱን አምርተው በመሸጥ ተጠቃሚ እንዲሆኑ በአማራ ክልል እየተከናወነ ስላለው የግብአት ንግድ እንቅስቃሴ የቃኘንበትን እንደሚከተለው አቅርበናል።

በአማራ ክልል የእንስሳት ሀብት ልማት ማስፋፊያ ኤጀንሲ የንብና ሀር ልማት ባለሙያ አቶ መሐመድ ጌታሁን እንደገለጹልን ፤ የንብ ማናቢያ ቁሳቁሶች በተለይ አልባሳቱ ከውጭ ሀገር በተለይም ከቻይና ሀገር ነበር በስፋት ተገዝቶ ሀገር ውስጥ የሚቀርበው። የአይን ዕርግብ የሚባለው መከላከያ አንዱ እስከ አራት መቶ ብር፣ቱታው ደግሞ አምስት መቶ ብር ነበር ገበያ ላይ የሚቀርበው። ዋጋውም ከማር አልሚው አቅም በላይ ከመሆኑ በተጨማሪ ከውጭ የሚገቡት አልባሳት በመጠንም በቀለምም ተመራጭ ባለመሆናቸው እንከኖች ነበሩባቸው።

ለምለም መንግሥቱ

ለምለም መንግሥቱ

ወጣት ጤና እራስዋን ችላ ለመኖር መጠንከር እንዳለባት ለራስዋ በመንገር የኑሮ ውጣ ውረዱን ተያያዘችው። እንደአቅሟ በሰባት መቶ ብር መኖሪያቤት

ችግሮቹን ለመቅረፍ፣የውጭ ምንዛሪንም ለማዳንና የአካባቢው ወጣቶች አዘጋጅተው በማቅረብ በገቢው ተጠቃሚ ለማድረግ እንዲሁም በተመጣጣኝ ዋጋ ግብአቱን ተደራሽ ለማድረግ ኤጀንሲው ከክልሉ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኤጀንሲ፣ቴክኒክና ሙያ ቢሮ እንዲሁም በክልሉ በማር ልማት ሥራ ላይ ለተሰማሩ ወጣቶች ድጋፍ እያደረገ ከሚገኘው በዓለምአቀፍ ሥነነፍሳት ሳይንስና ሥነምህዳር ምርምር ማዕከል (አይ ሲ አይ ፒ ኢ)ሥር ካለው ሞይሽ ፕሮጀክት ጋር በጋራ በመተባበር በማህበር ለተደራጁ ወጣት ኢንተርፕራይዞችን በመሠረታዊ ሥልጠና አብቅቶ ሥራ ላይ ከተሰማሩ ወዲህ በአቅርቦት፣በዋጋ በጥራት የተሻለ ግብአት ተመርቶ በመቅረብ ላይ ይገኛል።

እንደ አቶ መሐመድ ማብራሪያ ፣በአሁኑ ጊዜ ባህርዳር፣ቡሬ፣ኮምቦልቻ፣ደብረማርቆስ፣ወልዲያና በተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች ተመርቶ ለገበያ በመቅረብ ላይ ሲሆን፤ሙሉ አንዱ መከላከያ ልብስ እስከ አንድሺ ብር በሆነ ዋጋ ይሸጣል። ከውጭ የሚገባው ግን ዋጋው ከዚህ ይልቃል። በመሆኑም ሸማቹ ወይንም ተጠቃሚው በዋጋም በጥራትም በአቅርቦቱም በሀገር ውስጥ የሚመረተውን እየመረጠው በመምጣቱ ከውጭ የሚገባው ምርት በሀገር ውስጥ መተካት ጀምሯል። ይሄ አበረታች የሆነ አቅርቦት ከተጠናከረ የውጭ ምንዛሪ ወጭን ማዳን ይቻላል። ተጠቃሚውም ፍላጎቱ ይሟላለታል።

ሌላው ለማር ምርታማነት መጨመር ትልቅ አስተዋፅኦ ያለው ዘመናዊ የንብ ቀፎ አምርቶ ለማቅረብ ክህሎት ባለመኖሩ በክልሉ የንብ ቀፎዎቹ ለረጅም ጊዜ በባህርዳር እና ኮምቦልቻ ከተሞች በሚገኙ የገጠር የግብርና ሜካናይዜሽን ድርጅቶች ተመርቶ ሲቀርብ እንደነበር አስታውሰዋል።አሁን ግን ወጣት ኢንተርፕራይዞች ክህሎቱን እያገኙ ሥራው ከድርጅቶቹ ወጥቶ በስፋት በመቅረብ ላይ ነው ብለዋል።

ኤጀንሲው ሙያዊ ክህሎት እንዲያገኙ፣ደረጃውን

ተከራየች። የትራንስፖርት ወጭን ለመቀነስ በሥራ አቅራቢያዋ ነበር የተከራየችው። ወጭን ለመቀነስ መላ ያለችው ያን ያህል ኑሮዋን አላቃለላትም። የቤት ኪራይ ከፍላ፣ የዕለት ኑሮዋን ደጉማ፣ ለእናቷና ለልጇ የሚያስፈልጋቸውን ለማሟላት ወርሃዊ ደመወዝዋ በቂ ባለመሆኑ ተጨማሪ ገቢ ለማግኘት አማራጭ መፈለግ ነበረባት።

አማራጩ ደግሞ በአቅሟ የሚሸጥ ነገር በመያዝ ተጨማሪ ገቢ ማግኘት ነው። በዚሁ መሰረትም ከአስር ሰአት በኋላ ከሥራ ስትወጣ የበቆሎ እሸት ጥብስና እሸቱን እንደሸማቹ ፍላጎት እስከ ምሽት ድረስ እንደምትሸጥ ነው የነገረችኝ። ሶስቱ የበቆሎ እሸት በ20ብር፣አንዱን የበቆሎ ጥብስ ደግሞ በአስር ብር ነው የምትሸጠው። ከነጋዴ የምትረከበው በማዳበሪያ በመሆኑ አንዳንዴ ታተርፍበታለች፣አንዳንዴ ደግሞ ዋናዋን ብቻ እንደምታገኝ ነው የገለጸችልኝ። እርስዋ እንዳለችው የምትረከበው በኪሎ ባለመሆኑ አንዳንዴ ይጎላል። ለበቆሎ መጥበሻ ከሰልም ስለሚያስፈልግ ኪሲራና ትርፉ ለከሰል የሚወጣውንም ወጭ ያካትታል። ሌሎች ነጋዴዎች እንደሚያደርጉት በሂሳቡ ውስጥ የጉልበት ቢካተት ንግዱ አዋጭ ላይሆን ይችል ነበር።

በአሁኑ ጊዜ ከክረምቱ መውጣት ጋር ተያይዞ የበቆሎ እሸት አቅርቦት እየቀነሰ በመምጣቱ ወጣት ጤናም ንግዷን ለመቀየር ተገዳለች። ሞክራ የማታውቀውን የተነከረ ትኩስ የባቄላ ቆሎ በጎዳና ላይ በመሸጥ ላይ ትገኛለች። ከሰሏን፣ብረትምጣዷን ከነመቁያው ከቀኑ ዘጠኝ ሰአት ጀምሮ እስከ አመሻሽ

የጠበቀ ምርት እንዲመረት ክትትልና ድጋፍ በማድረግ ወጣቶችን እያገዘ መሆኑንም አመልክተዋል። አቶ መሐመድ እንዳሉት፤ አንዱ የተሻሻለ የንብ ቀፎ ዋጋም እስከ ሁለትሺ ሶስት መቶ ብር ዋጋ ያወጣል። አንድ ሰው በብዛት አምርቶ መሸጥ ከቻለ ከሽያጩ እስከ ሰባት መቶ ሺ ያገኛል። ምርቱንም ያለገደብ የፈለገበት ቦታ ወስዶ መሸጥ የሚቻልበት ዕድል መፈጠሩ ተጠቃሚው በአካባቢው በቀላሉ እንዲያገኝ አስችሎታል።

የተጣራ ማር ታሽጎ ለገበያ የሚቀርበው እንዲሁ ከውጭ ሀገር በሚገባ የማሸጊያ ቁሳቁስ በመሆኑ ይሄንንም ለማስቀረት አንድ ግለሰብ በባህርዳር ከተማ ውስጥ ማሸጊያውን አምርተው ለማር አልሚው ለማቅረብ የፋብሪካ ግንባታ ዝግጅታቸውን በማጠናቀቅ ላይ በመሆናቸው በዚህ አመት ምርቱ እንደሚደርስ ይጠበቃል።

ዘመናዊ የንብ ቀፎ አምርተው በማቅረብ ተጠቃሚ ከሆኑት መካከል በክልሉ ምዕራብ ጎጃም ቡሬ ውስጥ ነዋሪ የሆኑት አቶ ዘሪሁን ጥሩነህ አንዱ ናቸው። እርሳቸው እንዳሉት ያመረቱት ዘመናዊ ቀፎ በግለሰብም በድርጅትም ተወዳድሮ ለገበያ የሚቀርብ ሲሆን፤ እርሳቸውም አዋጭ በሆነው ዋጋ በመሸጥ ይጠቀማሉ። በዚህ መሠረትም አንዱን ዘመናዊ ቀፎ በሁለት ሺ ሶስት መቶ ብር የሚያቀርቡ ሲሆን፤በ2012ዓ.ም ማጠናቀቂያ ላይ ወደ አንድ ሺ ዘመናዊ ቀፎ በማቅረብ ተጠቃሚ ሆነዋል። አቶ

ዘሪሁን ጣውላ ስለሚያመርቱና የቀፎ መሥሪያ ማሽንም ስላላቸው ቀፎውን በቀላሉ ነው የሚያመርቱት። ከጣውላ የሚወጣው ተረፈ ምርትም መልሶ ጥቅም ላይ የሚውል በመሆኑ ትርፋማነቱ የበለጠ እንደሆነ ይናገራሉ። ከራሳቸው አልፈው ለሌሎችም የሥራ ዕድል ፈጥረዋል። አቶ ዘሪሁን የቴክኒክና ሙያ መምህር ሆነው ማገልገላቸው አሁን ላሉበት ሥራ እንደጠቀማቸው ያስረዳሉ። ወደፊት ንብ በማነብ ላይም በመሰማራት በዘርፉ ውስጥ ውጤታማ ለመሆን አቅደዋል።

በ1993 ዓ.ም 12ኛ ክፍል ትምህርቱን አናጠናቅቆ ወደ ቀጣይ ክፍል ለመሸጋገር የሚያበቃ ውጤት ባለማምጣቱ ኑሮውን ለመለወጥ ሥራ መሥራት እንደነበረበት የሚናገረው ወጣት ሙሉጌታ አለኸኝ የልብስ ስፌት ሥራ መጀመሩን ይገልጻል። ወጣቱ እንዳለው የስፌት ሥራው ደግሞ ለንብ አናቢዎች የሚሆን አልባሳት አዘጋጅቶ ለማቅረብ ቀላል ሆኖለታል። የልብስ ሥራ ሙያው ቢኖረውም በክልሉ በተዘጋጀው የአቅም ግንባታ ስልጠና በመካፈል ተጨማሪ አቅም አግኝቷል። ወጣት ሙሉጌታ ገበያው አዋጭ እንደሆነም ይናገራል። እራሱን በማስተዋወቅ ገበያውን በስፋት ለመቆጣጠር በመሥራት ላይ ይገኛል። የማር ልማቱን ለማዘመን እየተደረገ ያለው እንቅስቃሴ ግለሰቦቹንም ሀገርንም ተጠቃሚ በማድረግ ተስፋ የሚያሳድር መሆኑን መገመት አያዳግትም።

የጎዳና ላይ የባቄላ ቆሎ ንግድ

የንብ ማናቢያ ቁሳቁስ ምርትና ንግድ

ድረስ ለወጭ ወራጁ የምትሸጠው ወጣት ጤና የባቄላ ቆሎ ንግዱን ከጀመረች ገና አጭር ቀን በመሆኑ አንድ ቀን አስር ብር በሌላኛው ቀን ደግሞ 15 ብር በማግኘቷ ተበረታታለች። አጠገቧ ሆኜ የንግድ ሥራዋን እንዳየሁት። በአንድ የቡና ስኒ የተፈሰረውን ቆሎ በአምስት ብር ነው የምትሸጠው። ብዙዎቻችን የምናውቀው በቤት ውስጥ ተቆልቶ በዕቃ ታዳጊዎች እያዞሩ ሲያቀርቡ ነው። ነገር ግን ትኩስ ቆሎ ማቅረቡ ለሸማች ተመራጭ የሆነ ይመስላል። አልፎ የሄደ መንገደኛ መለስ ብሎ ቆሎውን በማየት ገዝቶ አፉ አድርጎ እየቆረጠመ ይጓዛል።

በአምስት ብር የሚሸጠው ቆሎ ግን መንገደኛውን ብዙ መንገድ የሚያስጉዘው አይደለም። የማነሱን ነገር ለወጣት ጤና አንስቼባት አንድ ኪሎ ጥሬ ባቄላ በ50 ብር ገዝታ ከከሰል ወጭው ጋር አዋጭ እንዳልሆነ ትናገራለች። ከቆሎው ትርፍ ለማግኘትም ሽያጩ ላይ ጥበበኛ መሆን ያስፈልጋል ትላለች። አንዳንዴ በሥራው ላይ ካሉት ጋር እራስዋን ስታወዳድር በስፍር ወቅትና ስትመርቅ መጠኑን እንደምታበዛውና ለትርፏ ማነስም ምክንያት እንደሆነ አጫውታኛለች።

እርስዋ እንደምትለው ንግዱ ብዙ አዋጭ ባይሆንም ተወዳዳሪዎቹ ግን ብዙ ናቸው። ወጭ ወራጅ የሚበዛብትን ቦታ ለሽያጭ ቀድሞ ለመያዝ መሽቀዳደሙ መኖሩን ታዝቤያለሁ። ለሽያጭ በመጠን የሚይዙት ባቄላም ከሁለት ኪሎ የበለጠ አይደለም። ግን በየቀኑ የባቄላ ቆሎ በጎዳና ላይ ከችብስ፣ከሳምቡሳና ከቦቦሊኖ ጋር ተወዳዳሪ ሆኖ እየቀረበ ይገኛል።

ከውጭ የሚገቡት አልባሳት በመጠንም በቀለምም ተመራጭ

ባለመሆናቸው እንከኖች ነበሩባቸው

Page 7: “ለራሱ ኩራት ለአካባቢው አገሮች ደግሞ የብቃት ......ገጽ 2 አዲስ ዘመን ሐሙስ መስከረም 21 ቀን 2013 ዓ.ም ዜና አዲስ አበባ፦

ገጽ 7አዲስ ዘመን ሐሙስ መስከረም 21 ቀን 2013 ዓ.ም

ፋይናንስ/ቢዝነስ

የባንኮች ደንበኞች ተንቀሳቃሽ ንብረቶችን አስይዘው እንዲበደሩ የሚፈቅድ አዋጅና መመሪያ ባለመኖሩ ምክንያት ላለፉት በርካታ ዓመታት በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ የንግድ ባንኮች ቋሚ ንብረት እንደ መያዣ ማቅረብ ለማይችሉ ሰዎች ብድር አያቀርቡም ነበር። ቋሚ ንብረት እንደመያዣ ለሚያቀርቡ ሰዎች ብቻ ብድር ሲያቀርቡ ኖረዋል። በዚህም ምክንያት ተንቀሳቃሽ ሀብት እያላቸው ተበድረው ስራ መስራት የሚፈልጉ የፋይናንስ ተጠቃሚ እንዳይሆኑ እንቅፋት ሆኖ ቆይቷል።

በተለይም ለሀገሪቱ ኢኮኖሚ ከፍተኛውን ድርሻ የሚያበረክተው እና ለበርካታ ሰዎች የኑሮ መሰረት በሆነው በአነስተኛ የግብርና ስራ ላይ የተሰማረው አርሶ አደርና አርብቶ አደር የፋይናንስ ተጠቃሚ መሆን አልቻለም። በዚህ አብዛኛውን ህዝብ ባገለለው የባንኮች የብድር አሰጣጥ ሳቢያ ባንኮችም ሆኑ ብድር ፈላጊ ደንበኞች ሲቸገሩ ኖረዋል። ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው እና ለመበደር የሚያስይዙት ቋሚ ንብረት የሌላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች የፋይናንስ ተጠቃሚ እንዳይሆኑ ተግዳሮት ሆኖ ቆይቷል።

ይህም ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው የህብረተሰብ ክፍል ኑሮ እንዳይሻሻል ብሎም የሀገሪቱ ኢኮኖሚ እድገት በሚፈለገው ልክ እንዳይሆን የራሱን አስተዋጽኦ አበርክቷል። ይህንን ሁኔታ ለመቀየርና ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው የህብረተሰብ ክፍሎችን በተለይም አርሶ አደሩን፣ አርብቶ አደሩን እና በከተሞች አነስተኛ የንግድ ስራዎች ላይ የተሰማሩ ዜጎችን የፋይናንስ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማስቻል በቅርቡ አዲስ መመሪያ ወጥቷል።

መመሪያው ተንቀሳቃሽ ንብረትን ማለትም ማሳ ላይ ያለ ሰብል፣ ከብት፣ ማሽኖች፣ ደን፣ የፈጠራ ሃሳብ ማለትም የንግድ ሃሳብ አልያም የትምህርት ማስረጃ ወዘተ ማስያዣ አድርጎ መያዝንም ሆነ መበደርን ፈቅዷል። ይህ መፈቀዱ ቁጠባን እና ኢንቨስትመንትን ለማበረታታት ከፍተኛ ሚና ይጫወታል ተብሎ ተስፋ ተጥሎበታል። ብሄራዊ ባንክ በአዲሱ በመመሪያው ዙሪያ ከፋይናንስ ዘርፍና ከሌሎች ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት ማድረጉም የሚታወስ ነው።

ለዋስትና ማስያዣ የሚሆኑት ንብረቶች ተመን አወጣጥ እና የተንቀሳቃሽ ንብረት ምዝገባና እና በመመሪያው አተገባበር ላይ የሚያጠነጥን ጽሑፍ ያቀረቡት በብሔራዊ ባንክ የፋይናንስ አካታችነት ሴክሬታሪያት ዳይሬክተር አቶ ተመስገን ዘለቀ እንደተናገሩት፤ መመሪያው ለአርሶ አደሩ እና አርብቶ አደሩ አለፍ ሲልም ለሀገሪቱ ኢኮኖሚ መለወጥ የላቀ ሚና ይኖረዋል።

የፋይናንስ አቅርቦት ለአንድ ሀገር ኢኮኖሚ እድገት ቁልፍ ነው ያሉት አቶ ተመስገን፤ ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ ባንኮች እጅግ ጥቂት የህብረተሰብ ክፍልን ብቻ ፋይናንስ ሲያደርጉ አብዛኛውን የሀገሪቱ ህዝብ ያገለሉ ሆነው መቆየታቸውን አብራርተዋል። በተለይም ለሀገሪቱ ጠቅላላ ምርት ከፍተኛውን ድርሻ ለሚያበረክተው የግብርና ዘርፍ የሚሰጠው ብድር እጅግ አነስተኛ ነው። በአሁኑ ወቅት ከሚቀርበው ብድር ውስጥ ለግብርና ዘርፍ እየቀረበ ያለው 8 በመቶ ብቻ መሆኑን ጠቁመዋል።

ዘርፉ ለሀገሪቱ ካለው አስተዋጽኦ አንጻር ግብርናን መለወጥ ሀገርን መለወጥ ነው ያሉት ዳይሬክተሩ፣ ለዘርፉ ሲቀርብ የነበረው ብድር ግን ግብርናውንም ሆነ ሀገርን ለመለወጥ የሚያስችል አልነበረም ብለዋል። ግብርናን የሚያክል ወሳኝ ዘርፍ በመዘንጋት ሀገሪቱን ከድህነት ማውጣት የማይታሰብ በመሆኑ የፋይናንስ አካታችነትን መተግበር የግድ በመሆኑ መመሪያው መውጣቱን ተናግረዋል።

እንደ አቶ ተመስገን ማብራሪያ መመሪያው ፍትሃዊና ዘላቂ የብድር አሰጣጥን ለማስፈን የሚረዳ ነው። በተለይም የግብርናው ዘርፍ ፍትሃዊ እና ዘላቂ የብድር አቅርቦት ተጠቃሚ መሆን ለግብርና ዘርፍ ትራንስፎርሜሽን ብሎም ምርትና ምርታማነት እንዲረጋገጥ ይረዳል። ለግብርና ዘርፍ ብድር መቅረብ

ተንቀሳቃሽ ንብረት አስይዞ መበደር ዘርፈ ብዙ ፋይዳዎችና ውስን ስጋቶች

ምርትና ምርታማነትን ከማሳደግ ባሻገር ከፍተኛ የስራ እድልም የመፍጠር አቅም አለው። በመሆኑም መመሪያው ትልቅ ትርጉም ያለውን ነው።

መመሪያውን ተግባራዊ በማድረግ ፍትሃዊ፣ እኩል እና ዘላቂ የብድር ስርዓት ለመዘርጋት ብዙ ስራዎች ተሰርተዋል ያሉት አቶ ተመስገን፤ ከተሰሩት ስራዎች መካከል ጉዳዩን የሚመለከት አዋጅ ወጥቶ መጽደቁ እና አዋጁን ተከትሎ መመሪያ መውጣቱን አንስተዋል። ይህንን የብድር አሰጣጥ ስርዓትን ለማስፈጸም ከዓለም ባንክ ጋር በመተባበር ከፍተኛ ገንዘብ ወጪ በማድረግ የኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ቴክሎጂ ተዘርግቷል። በሀገሪቱ ውስጥ የሚገኙ ሁሉም የንግድ ባንኮች፣ 23 ማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት እንዲሁም 3 የሊዝ ኩባኒያዎች በአይሲቲ ስርዓት ውስጥ መግባታቸውን ተናግረዋል።

የአርሶ አደሩ እና የአርብቶ አደሩን ንብረት በትክክል መመዝገብና መተመን እና የመለያ ቁጥሮች የመስጠት ስራ ይሰራል ያሉት አቶ ተመስገን፤ ምዝገባ፣ ትመና እና ቁጥር አሰጣጥ ሂደት የተለያዩ ባለድርሻ አካላትን የጋራ ርብርብ የሚፈልግ ነው። ሁሉም የየራሱን ሚና መጫወት አለበት። የግብርና ሚኒስቴር አዲሱን የብድር አሰጣጥ በማስተዋወቅ፣ የአዕምሯዊ ንብረት ጽህፈት ቤት ለያንዳንዱ መለያ መታውቂያ እንደሚሰጥ አብርርተዋል።

የብሔራዊ ባንክ ገዥው ዶክተር ይናገር ደሴ በበኩላቸው፤ ከዚህ በፊት በአብዛኛው በህንጻ፣ በቤት እና መኪና የመሳሰሉት ንብረቶችን በማስያዝ ከባንኮች መበደር የሚቻል ቢሆንም፤ ከዚህ ውጪ ያሉ ሌሎች ተንቀሳቃሽ ንብረቶችን አስይዞ መበደር አይቻልም ነበር። ከፋይናንስ ዘርፉ የብድር አገልግሎት የሚያገኘው የህብረተሰብ ክፍል ከ6 ሚሊየን አይበልጥም ነበር። አሁን ማሳ ላይ ያለ ሰብል፣ ከብት እንዲሁም የአዕምሯዊ ንብረቶችን ዋስትና አስይዞ ብድር መበደር መፈቀዱ የዋስትና መሰረቱን እንደሚያሰፋ አብራርተዋል።

መላኩ ኤሮሴ

አርብቶ አደር፣ አርሶ አደር እንዲሁም በከተሞች በአነስተኛ የንግድ ስራዎች ላይ የመሰማራት እድል ያላቸው ሰዎች የብድር ተጠቃሚ እንዲሆኑ ያስችላቸዋል ብለዋል።

አዲስ በወጣው መመሪያ መሰረት በኢትዮጵያ የሚገኙ የንግድ ባንኮች ከሚያቀርቡት ብድር 5 በመቶውን በተንቀሳቃሽ ንብረት ለሚሰጥ የብድር አይነት እንዲያውሉት የሚያዝ መሆኑን ያነሱት ዶክተር ይናገር ተንቀሳቃሽ ንብረትን እያስያዘ አርሶ አደሩ ሀብቱን ወደ ምርት እንዲቀይር መፈቀዱ እንደ ሀገር ትልቅ ትርጉም ያለው ነው ብለዋል። ኢንቨስትመንት፣ የስራ እድል እንዲሁም ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ትልቅ አቅም ይፈጥራል። የፋይናንስ አካታችነት የድህነት መጠን ለመቀነስም ከፍተኛ ሚና ይኖረዋል ብለዋል።

የፋይናንስ ሚኒስትር ዲኤታው ዶክተር እዮብ ተካልኝ እንደተናገሩት፤ እስካሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ ባንኮች የገጠሩ በማህበረሰብ እና በከተሞች ለሚኖረው ዝቅተኛ ገቢ ያለው የማህበረሰብ ክፍል ፋይናንስ በማቅረብ ረገድ ክፍተቶች የሚለውን የዶክተር ይናገር ሀሳብ አጽንኦት ሰጥተዋል። በዚህም ምክንያት የሀገሪቱ ኢኮኖሚ በመሰረታዊነት መለወጥ አልቻሉም።

አሁን ግን ይህ አይነት አካሄድ ሊቀጥል አይገባም ያሉት ዶክተር እዮብ ባንክን ጨምሮ ሁሉም የፋይናንስ ተቋማት ሀብት ማፍራት የሚችልበትና የሀገሪቱ ልማት ዘላቂ የሚያደርገውን የገጠሩን ማህበረሰብ ፋይናንስ ሊያደርጉ ይገባል።

የገጠሩ ማህበረሰብ እና የከተማው አነስተኛ ገቢ ያለው ማህበረሰብ ህይወት እየተለወጠ በሄደ ቁጥር የሀገሪቱ ኢኮኖሚ መሰረቱ እየሰፋ ይሄዳል ያሉት ዶክተር እዮብ፣ የኢኮኖሚ መሰረት መስፋት ደግሞ ለፋይናንስ ዘርፍም ጠቃሚ ነው።

እንደ ዶክተር እዮብ ተካልኝ ማብራሪያ፤ ባንኮች ከዚህ ቀደም በነበራቸው አሰራር ምክንያት “ኢትዮጵያ

ውስጥ የተገነባው የባንክ ኢንዱስትሪ ጸረ ድሃ ነው፣ ጸረ አርሶ አደርና አርብቶ አደር ነው የሚል ክስ” እየተነሳበት ነው። ይህንን እሳቤ በመሰረታዊነት መቀየር ያስፈልጋል። ለዚህም እድሉ አለ። የፋይናንስ ዘርፉ ይህንን ለመቀየር መስራት አለባቸው።

ባንኮች አፈጻጸማቸውን ሲገመግሙ አንዱ መስፈርታቸው ምን ያህል አርሶ አደሩንና አርብቶ አደሩን ተጠቃሚ አደረግኩ የሚለውን ማካተት አለባቸው። አንዳንድ መስዋዕትነትንም ለመክፈል መዘጋጀት አለባቸው።

መመሪያው አስፈላጊ ሆኖ ከመመሪያው በተጨማሪ የአተያይ አብዮት ማምጣት ተገቢ ነው ያሉት ዶክተር እዮብ፤ የአስተሳሰብ አብዮት ካልመጣ መመሪያ ብቻ ችግሩን መቅረፍ አይችልም ብለዋል። የፋይናንስ ተቋማት የተበዳሪዎችን ቁጥር እንዴት እንጨምራለን በሚለው ላይ ትኩረት በማድረግ ሊሰሩ እንደሚገባ ነው ያብራሩት።

የኢኮኖሚክስ ባለሙያው አቶ ዋሲሁን በላይ መመሪያው ዘርፈ ብዙ ፋይዳዎች እንዳሉት ጠቁመው ከፋይዳዎቹ ጎን ለጎን ስጋቶችንም ያነሳሉ። የተንቀሳቃሽ ንብረት በፍጥነት የመለዋወጥ እድል ስለሚኖረው በጥንቃቄ ካልተመራ ለባንኩም ለተበዳሪዎችም ከፍተኛ ኪሳራ ሊያሳርፍ ስለሚችል በጥንቃቄ መርምሮ መወሰን ያስፈልጋል ይላሉ።

ለአብነት ያህል አንድ ባንክ በአንድ ግለሰብ የተተከሉ 10 ሺህ ዛፎችን በዋስትና ይዞ 100 ሺ ብር ቢያበድር ተበዳሪው ጊዜውን ጠብቆ መክፈል ካልቻለ ባንኩ ያለው አማራጭ ዛፉን አስቆርጦ መሸጥ ነው ሲሉ ይገልፃሉ። ነገር ግን ዛፉ በገበያ ያለው ፍላጎት ቢቀንስ እዳው ለባንኩ የመሆን እድል እንደሚኖር ያብራራሉ።

በተመሳሳይ አንድ ባንክ በአንድ ግለሰብ ስር ያሉ 50 የቀንድ ከብቶችን ይዞ ቢያበድር እና ተበዳሪው ሳይከፍል በዋስትና የተያዙት ከብቶች በበሽታ ድንገት ቢሞቱ እዳው ለባንኩ ይሆናል የሚል ስጋት የሚያነሱት አቶ ዋሲሁን፤ ነገር ግን ባንኮች በብዛት እየተከፈቱ ሲሄዱ አሰራር እየዘመነ ስለሚመጣ ኪሳራ እየወሰዱም በገበያው መፎካከር መጀመራቸው እንደማይቀር አብራርተዋል።

እንደ አቶ ዋሲሁን ማብራሪያ ታሳቢ ሊደረጉ የሚገቡ ከሌሎች ስጋቶችም አሉ። ከኮሌጅ ተመርቀው ኦርጅናል የትምህርት ማስረጃ ይዘው የስራ መጀመሪያ አነስተኛ ብድር ለሚፈልጉ ባንኮች ብድር የማቅረብ ስራ ቢሰሩ እና ቀጣሪ ድርጅቶች ደግሞ ኦርጅናል ማስረጃ ያላመጣን ስራ አንቀጥርም ሊሉ ስለሚችሉ ከአሁኑ ሊታሰብበት ይገባል። በመሆኑም መሰል ችግሮች እንዳይፈጠሩ ብሔራዊ ባንክ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን አሁኑ በትኩረት ሊሰራበት ይገባል።

የኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ተመራማሪው አቶ ዳዊት ተሻለ በበኩላቸው፤ መመሪያው ከዚህ ቀደም እንደሚወጡ መመሪያዎች ሁሉ እጅግ መልካም የሚባል ነው። ብዙ ፋይዳዎችም ይኖሩታል። የተበዳሪ ቁጥርን በከፍተኛ ሁኔታ የመጨመር እድልን ይፈጥራል፣ ተበዳሪዎች ኢንቨስትመንት ላይ የሚሳተፉ ከሆነ ደግሞ ጠቅላላ ሀገራዊ ኢኮኖሚው እንዲነቃቃ ያደርጋል ይላሉ። በዚህ ባንኮችም ተበዳሪዎችም ተጠቃሚ የመሆን እድል ይኖራቸዋል።

ነገር ግን ከዚህ ቀደምም ሀገሪቱ የመመሪያ፣ የፖሊሲ እና የአዋጅ ችግር የለባትም የሚሉት አቶ ዳዊት፤ ዋናው ችግሩ የአፈጻጸም ችግር ነው ይላሉ። በመሆኑም መመሪያው ስራ ላይ እንዲገባ ማስቻል ላይ ልዩ ትኩረት መሰጠት አለበት። በመሆኑም መመሪያውን መተግበር ላይ ልዩ ትኩረትና ክትትል ሊደረግ ይገባል ብለዋል።

እንደ አቶ ዳዊት ማብራሪያ፤ እንደነ ከብት እና ሰብል ያሉ ንብረቶችን አስይዞ መበደር በኢትዮጵያ ውስጥ አዲስ ልምምድ ስለሆነ ለባንኮች፣ ለማይክሮ ፋይናንስ ተቋማትና ለሌሎች ባለድርሻ አካላት እጅግ ከባድ የቤት ስራ መሆኑ አይቀሬ ነው።በተለይም ማኔጅመንቱ በጣም ከባድ ነው የሚሆነው። ከማበደር ይልቅ በብዙ ሚሊየኖች የሚቆጠሩ ተበዳሪዎችን መቆጣጠር ከባድ ነው።

Page 8: “ለራሱ ኩራት ለአካባቢው አገሮች ደግሞ የብቃት ......ገጽ 2 አዲስ ዘመን ሐሙስ መስከረም 21 ቀን 2013 ዓ.ም ዜና አዲስ አበባ፦

አዲስ ዘመን ሐሙስ መስከረም 21 ቀን 2013 ዓ.ም ገጽ 8

የገበያና ግብይት ቅኝት

ዳግማዊት ግርማ

ሰዎች ብቻችንን ላንሆን የተፈጠርን፤ ብዙ ጉዳዮቻችንን ከሌሎች ጋር መጋራት ተፈጥሯችን የሆነ። ብዙ የደስታም የሀዘንም ቀናት ያሉን በመሆናችን ህመም ሀዘናችንን መደሰት መከፋታንን ሰርግና ለቅሷችንን የሚጋራን እንፈልጋለን።

ትተው በማይተዉን ከኛ በማይነጠሉ የህይወት ገጠመኞቻችን ላይ ደግሞ በአንድም በሌላም መንገድ ከሰው ሳንለይ አብረን በብዛት ሆነን እናሳልፋለን። ተሰባስበን የምናከብራቸው ነገሮች ላይ ደግሞ ቢጤያችንን ፈልገን ተመሳስለን መታየት እንሻለን።

በደስታና በሀዘኑ በማይነጣጠለው ማህበረሰባችን ውስጥም ብዙ ሰው በጋራ ሆኖ የታመመን፣ የወለደን፣ የታሰረን መጠየቅ፣ የሞተን መቅበር፣ ባለሰርግን አጅቦ መዳር፣ ለምርቃትና ለሌሎችም ማህበራዊ ኃላፊነቶች አብሮ መሆንን እንመርጣለን፤ የተከፋን አፅናንቶ ደስተኛን ደስታውን ተጋርቶ ማሳለፍም ሌላው የሰውነታችን መገለጫ ነው።

አሁን አሁን በእነዚህ ሁሉ የጋራ ጊዜያት ደምቆ ለመታየት ተመሳሳይ የሆኑ አልባሳትን መልበስ እየተለመደ ከመምጣቱ የተነሳ ቤተሰብ አንድ ላይ፣ ጓደኛሞች፣ የሰፈር አብሮ አደጎች፣ የስራ ባልደረቦች ተመሳሳይ የሆኑ የሀገር ባህል ልብሶችን፣ የተለያዩ አይነት ቲሸርቶችን እየለበሱ መታየትም ማህበራዊ ግንኙነታችንን ለማድመቅ ከምንጠቀምባቸው ነገሮች ግንባር ቀደሙ እየሆነ ነው።

ኢትዮጵያውያን የመስቀል በአልን ካከበርን የቀናት እድሜ ያህል ብቻ አልፈዋል፤ በቀጣይ ደግሞ የኦሮሞ ህዝብ ባህላዊና ትውፊታዊ መገለጫ የሆነው የኢሬቻ በአል ይከበራል። እንደዚህ አይነት በሆኑ የበአልና መሰባሰቢያ ወቅቶች ላይ ደግሞ በተመሳሳይ ህትመት ያሸበረቁ ቲሸርቶችን መልበስ የኑሯችን አንድ አካል ሆኗል።

እኛም በገበያና ግብይት አምዳችን ክብረ በዓላትንና የተለያዩ ሁነቶችን ምክንያት በማድረግ

ቲሸርትና የአውደ ዓመት ሽያጩ

አለም በቴክኖሎጂና በውጤቶቹ ቅጥ አምባሯ ጠፍቷል። ይኸው አዲስ አለም ያለ የሌለ አቅሙን ተጠቅሞ ጡንቻውን እያስጎበኛት

ነው። ሳር ቅጠሉ አርቴፊሻልነትን ተከናንቧል። በፍጥነት በምትበር ጥድፊያ ባረበባት አለም ላይ የጉዞው መልህቅ ቴክኖሎጂ ነው።

የማህበራዊ ሚዲያም የቴክኖሎጂው አንድ አካል ነው። በዚህ የመዘመን ጥጋት ላይ ያረፈ ፍጥረትም ቤቱ ቁጭ ብሎ ከመላው አለም ጋር ይገናኛል።በየአንዳንዱ የቀን ቅንጣት ላይ ብዙ ሰው የዚህኛው የዲጂታሉ አለም አካል እየሆነ ነው።እልፍ ሰውም ኑሮው መግባት መውጣቱ ሁሉ ነገሩ አጠገቡ ካለው የእጅ ስልኩ ጋር የተገናኘ እየሆነ መጥቷል።

የኑሯቸን አንድ አካል የሆነው ማህበራዊ ሚዲያ ፈጣን መረጃ መስጠቱ፣ ቁምነገሮችን ማስጨበጡ፣ አንዳንዴም ውሃ አጣጭ እስከማስገኘት የደረሰን ውለታ መዋሉ፣ ሰዎች ስራቸውን ማስተዋወቅ መቻላቸው አልፎም ነግደው ለማትረፍ መታደላቸው አዎንታዊ ገጽታው ሲሆን የደግም ክፉ የመልካምም መጥፎ አለውና የራሱ ውስንነቶችን ታቅፎ ነው የተፈጠረው።በተለይም በአካል ካለመገናኘትና ካለው ርቀት የተነሳ የሚፈጠሩ ብዙ ጉዶች አሉ።አሁን ላይ

የማህበራዊ ሚዲያ ጣጣዎች

የሚታተሙ ቲሸርቶችን እየሸጡ ህይወታቸውን

የሚገፉ ሰዎች ገቢያቸው ምን እንደሚመስልና

የበአል የቲሸርት ገበያን ለመታዘብ ሞክረናል።

ወይዘሪት ስመኝሽ እሸቱ ህይወቷን የምትገፋው

በቲሸርት ሽያጭ ነው። የአሃዝ ህትመትና ዲዛይን መስራችና ባለቤትም ናት። ብዙ ሰዎች ለአዲስ አመት የተሰራውን ቲሸርት በመግዛታቸው የበአሉና ሰሞንኛ ገበያ ጥሩና ትርፋማ እንደነበር ትናገራለች።

በቀጣይ ለሚመጣው የኢሬቻ በአል ቲሸርቶችን በመስራት እየሸጠች መሆኗን በመግለጽ ቲሸርቶቹን ከትልቅ ልብስ ማምረቻዎች በመረከብ ህትመት (ፕሪንት) ማድረጉን ግን ቤት ውስጥ እንደምትሰራ ትናገራለች።

ስራዎቿን በማህበራዊ ሚዲያ አማካኝነት በቀጥታ (ኦንላይን) በማስተዋወቅ አዲስ አበባ እንዲሁም በክልሎች ላይ ለተጠቃሚው በቻልነው መጠን አድርሰናል የምትለው ወይዘሪት ስመኝሽ ከዚህ በፊት ለህትመትና ለትራንስፖርት የሚወጣው ወጪ ብዙ የነበረ ቢሆንም አሁን ማተሚያ ማሽን በመግዛቷ ወጪዋ ቀንሶ ለገበያ በምታቀርባቸው ቲሸርቶች ላይም እስከ 50 በመቶ የዋጋ ቅናሽ መድረጓን ተናግራለች።

ኮሮና ቫይረስ ወደ ሀገራችን የገባ ሰሞን የተለያዩ የቲሸርት መሸጫ ስፍራዎች መዘጋት ተጠቃሚዎችም እንቅስቃሴያቸው መወሰኑ የህትመት ስራቸውን በጣም ጎድቶት እንደነበረ በመግለጽ በወቅቱ ተጠቃሚው በመረጠው ምስል ያሸበረቁ የፊት መሸፈኛ ጭንብሎችን በመሥራት እና ለገበያ በማቅረብ ችግሩን መቋቋም መቻሏን ታብራራለች።

ከአንድ ፍሬ ጀምሮ እስከ ብዙ ሺህ ቲሸርቶችን በአንድ ጊዜ እንደሚታዘዙ የተናገረችው ወይዘሪት ስመኝሽ የቲሸርቶቹ፣ የኩባያዎቹ፣ የባነሮቹና የቢዝነስ ካርዶቹ የመሸጫ ዋጋ እንደሚያስፈልገው ብዛት መጠን፣ እንደወጣባቸው ወጪ፣ እንደፈጁት ቀለምና የስራ አስቸጋሪነት እንዲሁም በወሰዱት ጊዜ ልክ የተለያየ መሆኑን አብራርታለች።

በስራ ቦታ ላይም ወቅቱ የሚጠይቀውንና የጤና ሚኒስቴር መመሪያዎች የሚያዙትን ከግምት በማስገባት ራሷንና ሌሎችን ከኮሮና ቫይረስ ለመጠበቅም ከፍተኛ ጥንቃቄ እንደምታደርግ ነው ያብራራችው።

የሚሰሙ ተራ የሚመስሉ ነገር ግን የተታለሉ ሰዎችን በብዙ የሚጎዱ ማታለሎችም የዚሁ የማህበራዊ ሚዲያ ትሩፋቶች ናቸው፡፡

ማህበራዊ ሚዲያው ከታለመለት ርቀትን ቀንሶ አብሮነትን የማጠናከር ዓላማ ውጭ በመዋል ብዥታ የሚፈጥሩና ተአማኒ ያልሆኑ ጉዳዮች ሲቀርቡበት ይታያል።ዘረኝነት፣ የሀሰት መረጃዎች፣ የጥላቻ ንግግርና ህዝብን ከህዝብ የማጋጨትና ሰላምን የማደፍረስ ስራዎች በዚሁ በማህበራዊ ሚዲያ እየተሰሩ መጥፎ ውጤትም ሲያመጣ ከርሟል።

በማህበራዊ ሚዲያው የሚረጨው የተበከለ መርዝ እነዚህ ብቻ አይደሉም።ማጭበርበርና ስርቆት የዛሬው የትዝብት መነሻዬ ነው።

በማህበራዊ ሚዲያ አማካኝነት በብዛት ተጭበርባሪ የሚሆኑት በአረብ ሀገር የሚኖሩ እህቶቻችን ናቸው።በሰው ሀገር ብቸኝነት ስለሚያጠቃቸውና ሰው ስለሚፈልጉ በብዛት ከስራ የተረፋቸውን ጊዜ በዚሁ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ያሳልፏሉ። በዚህም በገዛ ስልካቸው ውድ ጊዜና ገንዘባቸውን አውጥተው ለአጭበርባሪዎች ሲዳረጉ ይስተዋላሉ። የመፅሐፍ ማሳተሚያ በሚል የሚያጭበረብሩ

እነዚህ አይነት ሰዎች በማህበራዊ ሚዲያ የተለያዩ ፅሑፎችን ሲፅፉ ይታያሉ። እንደብዙዎቹ

ገጣሚዎች አንገታቸው ላይ ስካርፍ በመጠምጠምና ፀጉራቸውንና ፂማቸውን አጎፍረው ይታያሉ። ብዙ ተከታይ ስላላቸውም በሰዎች ዘንድ ይታመናሉ።ምናልባት በሚረዷቸው ሰዎች አማካኝነት መፅሐፋቸውን ማሳተማቸው በራሱ ችግር ላይኖረው ይችላል።የእንደነዚህ አይነት ሰዎች መጥፎ ባህሪ ግን ምናልባት ብሩን የሚያገኙት በብድር ይሆንና የተበደሯቸውን ሰዎች ይክዱ ይሆናል።አልያም ደግሞ ያላቸውን የሰው እምነትና ተቀባይነት በመጠቀም ከብዙ ሰዎች መፅሐፍ ላሳትም ነው በማለት ሲያጭበረብሩ ይስተዋላሉ።በፍቅር ሰበብ የሚያጭበረብሩ

እነዚህ አይነቶቹ ደግሞ አፈቅሬሻለሁ በማለት ብር የሚያጭበረብሩ ናቸው።እንዲህ የሚያደርጉ ሰዎች በብዛት ወንዶች ሲሆኑ የነዚህ አይነቶቹ ሰዎች ግን የሚነቀፈው ባህሪያቸው በአንዴ ብዙ ሴቶችን በወጥመዳቸው ስር ማስገባታቸው ነው።

ብዙዎቹም ሴቶቹን የሚቀርቡት ለብራቸው ሲሉ በቢሆንም በታቃራኒው ወገን ወይም በሴቶቹ ዘንድ ግን ይህ እኩይ ተግባራቸው በቶሎ ተገልጾ ስለማይታያቸው ያላቸውን ነገር ካለመሰሰት ይሰጣሉ።አፍቃሪያቸው የበግ ለምድ የለበሰ ተኩላ መሆኑን ያወቁ ጊዜው ጅብ ከሄደ ውሻ እንደሚሉት አይነት እስከሚሆን የጠፋውን ጊዜያቸውን

ገንዘባቸውን ብሎም ተስፋቸውም መመለስ ሳይችሉ ይቀራሉ፣ በዚህ ምክንያት ደግሞ ለብዙ ስነ ልቦናዊ ጉዳትም ይዳረጋሉ፣

እንደዚህ ያጭበረበሩት ሰዎች ምናልባት ባለትዳርና የልጆች አባት ሊሆኑ ይችላሉ።በእንደዚህ አይነት አጋጣሚዎች ላይ የሚጭበረበሩት ሚስቶቻቸውም ጭምር ተጎጂ መሆናቸው ደግሞ የማይቀር ነው።ራሳቸውን ወይም የቤተሰባቸው አባል ታመውብን ነው በማለት የሚያጭበረብሩ

እነዚህን አይነቶቹ ደግሞ በሰው ሰብአዊ ርህራሄ ላይ የሚቀልዱ ናቸው።ብዙ ሰው ለህመምና ስቃይ ስለሚራራ ብዙ ብሮችን የማግኘት እድል ይኖራቸዋል።በብዛት እናቴ የቅርቤ ሰው ወይም ራሴ ታመምኩ እያሉ በውሸት ብር ያሰባስባሉ።በብዛት የተለመዱ በሽታዎችም ኩላሊት፣ ልብና ካንሰር ናቸው።ብዙዎቹ በእነዚህ ህመም አሳበው የሰው ብር የሚያጫርሱ ግን ምንም አይነት ህመም የሌለባቸው ናቸው፡፡

ከላይ እንዳልነው ማህበራዊ ሚዲያ በጎውንም ደጉንም በጋራ አቅፎ የያዘ ነው።ጥቅሙ እንዳለ ሁሉ የራሱም ጉዳት አለው።አንባቢም ከበጎ ጎኖቹ እየተቋደሰ መጥፎ ነገሮችን በመጠንቀቅ ቢጠቀም አትራፊ ይሆናል ለማለት እንወዳለን።

ዳግማዊት ግርማ

Page 9: “ለራሱ ኩራት ለአካባቢው አገሮች ደግሞ የብቃት ......ገጽ 2 አዲስ ዘመን ሐሙስ መስከረም 21 ቀን 2013 ዓ.ም ዜና አዲስ አበባ፦

አዲስ ዘመን ሐሙስ መስከረም 21 ቀን 2013 ዓ.ም ገጽ 9

በግብርና የሚመራውን የአገሪቷን ኢኮኖሚ ለማሳደግ የአግሮ ፕሮሰሲንግ ኢንደስትሪያል ፓርኮች በቀዳሚነት የሚጠቀሱ ናቸው። የአግሮ ፕሮሰሲንግ ኢንዱስትሪያል ፓርኮች በአካባቢው የሚመረተውን ሰፊ የግብርና ምርት በግብዓትነት የሚጠቀሙ በመሆናቸው የግብርናውን እና የኢንዱስትሪውን ትስስር ይበልጥ ማጠናከር እንደሚችሉ ይታመናል።

ይህንን ተሳቢ በማድረግ መንግስት በአገሪቷ በተመረጡ አራት ክልሎች ላይ የአግሮ ፕሮሰሲንግ የኢንዱስትሪያል ፓርኮችን አቋቁሞ ወደ ሥራ መግባቱ ይታወሳል። መንግስት ካቋቋማቸው የአግሮ ፕሮሰሲንግ ኢንደስትሪያል ፓርኮች በተጨማሪም ዘርፉን የተቀላቀሉት ባለሃብት አቶ ሙላቱ መንገሻ ይባላሉ። አቶ ሙላቱ፤ የአገሪቷ ኢኮኖሚ በግብርና መር የሚመራ በመሆኑ ሰፊ የሰው ኃይል በመያዝ ከፍተኛ ገቢ የሚገኘው ከግብርናው በመሆኑ ወደ ዘርፉን መቀላቀል እንደቻሉ ተናግረዋል።

ግብርናውን መሰረት ባደረገው የማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ መሳተፍ ውጤታማ ያደርጋል የሚል እምነት ያላቸው አቶ ሙላቱ፤ የአግሮ ፕሮሰሲንግ ዘርፉን የተቀላቀሉት ከአንድ ቻይናዊ ጓደኛቸው ባለሀብት ጋር በጋራ መሆኑን አስረድተው፤ ሪች ላንድ የተባለውን ድርጅት እንዳቋቋሙ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ወደ ማኑፋክቸሪንግ ሽግግር ያደርጋል ሲባል ከግብርና የሚገኘውን ምርት ወደ አግሮ ፕሮሰሲንግ ኢንደስትሪ ማሸጋገር ማለት እንደሆነ አቶ ሙላቱ ይናገራሉ። ድርጅታቸው ይህን በመገንዘብ በወቅቱ በአገሪቷ እየተመረቱ ያሉ የምርት መጠንና ወደፊትም ምርቱን ለማሳደግ ምቹ ሁኔታዎች ያሏቸውን በቆሎና የአኩሪ አተር ምርቶችን በጥናት መለየት ችሏል።

እነዚህ ምርቶችም ድንበርተኛ በሆኑት ምዕራብ ጎጃም እና ምስራቅ ወለጋ አካባቢዎች ላይ መመረት ይችላሉ። የአካባቢው አየር እና የአፈር ሁኔታ ለምርቶቹ እጅጉን ተስማሚ በመሆኑ በቀላሉ ምርቶቹን ማግኘት እንደሚቻል በጥናት መረጋገጡን አቶ ሙላቱ ተናግረዋል። ከዚህ በተጨማሪም ከሀገር ውስጥ በሚገኝ ጥሬ ዕቃ የሚመረት ምርት አዋጭነቱ ከፍተኛ እንደሆነ አመልክተዋል። ነገር ግን በሀገሪቱ የሚገኙ በርካታ ኢንቨስትመንቶች ከውጭ በሚገቡ ጥሬ ዕቃዎች ጥገኛ በመሆናቸው ለአገሪቷ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ዘላቂ መፍትሔ የሌላቸው እንደሆኑ አቶ ሙላቱ ያስረዳሉ፤

ለአገሪቷ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ከፍተኛ ሚና የሚጫወተው የግብርና ዘርፍ እንደመሆኑ ሪች ላንድ የተሰኘው ድርጅታቸው በሀገር ውስጥ የሚገኘውን አኩሪ አተር እና በቆሎ ላይ እሴት በመጨመር በፕሮቲን የበለፀገ የአኩሪ አተር ምርት ወደ ውጭ ሀገር ይልካል። ፋብሪካው ሁለቱን ምርቶች በማቀነባበር የሚገኘውን 80 በመቶ ያህል ምርት ወደ ውጭ ሀገር በመላክ የውጭ ምንዛሪ ለሀገሪቷ ማስገኘት እንደሚችል አስረድተዋል።

ከበቆሎ የሚገኘው ስታርች ወደ ውጭ ይላካል ያሉት አቶ ሙላቱ፤ በተመሳሳይ ከአኩሪ አተር የሚገኘው ዱቄት ከ46 በመቶ በላይ የፕሮቲን ይዘት ያለው መሆኑን ተናግረዋል። ይህ በፕሮቲን የበለፀገ የአኩሪ አተር ዱቄትም ለውጭ ሀገር ገበያ የሚቀርብ ይሆናል ያሉት አቶ ሙላቱ፤ ከአኩሪ አተር ሀገር ውስጥ የሚቀረው ዘይት ደግሞ በሀገሪቷ እጅግ ተፈላጊና መሰረታዊ ሸቀጥ በመሆኑ ለሀገር ውስጥ ገበያ ይቀርባል ብለዋል። በመሆኑም በከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ወደ አገሪቷ እየገባ ያለውን ዘይት ሙሉ ለሙሉ ማስቀረት ባይችልም መቀነስ እንደሚቻል አቶ ሙላቱ ተናግረዋል።

እነዚህን ተግባራት ለማከናወንም በቂ የሆነ የምርት መጠን ማግኘት በሚቻልበት አቅራቢያ በምዕራብ ጎጃም ዞን ቡሬ ከተማ ላይ ፋብሪካውን አቋቁመዋል። ፋብሪካው የተገነባው መንግስት ባቋቋመው የአግሮ ፕሮሰሲንግ የኢንዱስትሪያል ፓርክ ውስጥ በአስር ሄክታር መሬት ላይ መሆኑን የጠቆሙት አቶ ሙላቱ፤ በአሁን ወቅትም ምዕራፍ አንድ የሆነው የአኩሪ አተር ፋብሪካ ሥራ መጀመሩን እና ምርቱን ወደ ውጭ ሀገር ለመላክ በዝግጅት ላይ እንደሆነ አመልክተዋል። አገሪቷ የአኩሪ አተር ፕሮቲን ዱቄት ደረጃ የሌላት መሆኑን አቶ ሙላቱ አስታውሰው፤ በአሁን ወቅት የዓለም ደረጃን በመውሰድ በሚመለከተው የመንግስት አካል የሚፀድቅ ከመሆኑም በላይ ምርቱ በአጭር ጊዜ

ውስጥ ወደ ውጭ እንደሚላክ ተናግረዋል። በአገሪቷ በአመት እስከ ሁለት ሚሊዮን ኩንታል የአኩሪ

አተር ምርት እንደሚመረት የጠቆሙት አቶ ሙላቱ፤ የሪች ላንድ ድርጅት ደግሞ በአመት አንድ ነጥብ አምስት ሚሊዮን ኩንታል የአኩሪ አተር ምርት እንደሚፈልግ ተናግረዋል። ፋብሪካቸው 75 በመቶ የሚሆነውን የአገሪቷን የአኩሪ አተር ምርት በግብአትነት የሚጠቀመው መሆኑን አስረድተዋል።

አኩሪ አተሩን እሴት በመጨመር ዱቄቱ ወደ ውጭ ሀገር ሲላክ ሀገር ውስጥ የሚቀረው ተረፈ ምርት ዘይት ይሆናል። በመሆኑም ከአንድ ነጥብ አምስት ሚሊዮን ኩንታል አኩሪ አተር በአማካኝ 22 ሚሊዮን 750 ሺ ሌትር የአኩሪ አተር ዘይት ማግኘት እንደሚቻል አቶ ሙላቱ አስረድተዋል። በተመሳሳይ ይህን ያህል መጠን ያለው ዘይት ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባት ከ40 እስከ 45 ሚሊዮን ዶላር ይጠይቃል ብለዋል። ድርጅታቸው ይህን ወጪ ማዳን መቻሉንም ተናግረዋል። በሀገር ውስጥ የሚገኝ ምርትን በመጠቀም እሴት መጨመርና ወደ ውጭ መላክ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ እንዳለው አመልክተዋል። በጥሬ ከሚላከው አኩሪ አተር ይልቅ እሴት ተጨምሮ የሚላከው ገቢ በእጥፍ የሚበልጥ መሆኑንም አብራርተዋል።

ፋብሪካው የአኩሪ አተር ምርቱን የሚያገኘው በሁለት መንገድ መሆኑን የተናገሩት አቶ ሙላቱ፤ አንደኛው አገሪቷ የውጭ ምንዛሪ ከምታገኝበት የእርሻ ምርቶች አንዱ በመሆኑ ከኢትዮጵያ ከምርት ገበያ ይገኛል። ነገር ግን እንዲህ ላለ ትልቅ ፋብሪካ ገበያ እየጠበቁ ብቻ መንቀሳቀስ ስለማይቻል ሁለተኛ በኮንትራት እርሻ ማሳረስን እንደመረጡ ተናግረዋል። ይህንንም ተግባራዊ ለማደረግ አራት አካላትን ያሳተፈ እቅድ ለንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር መቅረቡን ያስታወሱት አቶ ሙላቱ፤ እነዚህ አካላትም የገንዘብ ተቋማት፣ የመንግስት አካላት፣ ገበሬው እና የሪች ላንድ ፋብሪካ መሆናቸውን ተናግረዋል።

ይህ የአራትዮሽ ግንኙነቱ በተለይም ገበሬውን ከፍተኛ ተጠቃሚ ያደርገዋል ያሉት አቶ ሙላቱ፤ ድርጅቱ ገበሬውን ለማገዝ ዝግጁ መሆኑን እና ለሚያመርተው ምርትም ተገቢውን ክፍያ እንደሚፈፅም አስረድተዋል። ከዚህ በተጨማሪም ገበሬው ወደ ዘመናዊ የግብርና ሥራ መግባት ቢችል በምርት መጠንና ጥራት ላይ የጎላ ሚና የሚጫወት በመሆኑ ድርጅቱ ገበሬውን ወደ ዘመናዊ ግብርና እንዲመጣም ያግዛል ብለዋል።

ድርጅቱ በቡሬ ከተማ ከሚገኘውና አኩሪ አተር ከሚያመረተው ምዕራፍ አንድ ኢንቨስትመንት በተጨማሪ በባህር ዳር ከተማ አቅራቢያ ምዕራፍ ሁለት ኢንቨስትመንት መጀመሩን አስረድተዋል። ይህ ምዕራፍ ሁለት ኢንቨስትመንትም ከ50 ሄክታር በላይ በሚሆን መሬት ላይ ግንባታው መጀመሩን አመልክተዋል። ይህ ኢንቨስትመንትም አንድ ሚሊዮን ኩንታል በቆሎ የሚፈልግ

መሆኑን ጠቁመዋል። ፋብሪካው እሴት በመጨመር ከበቆሎ የሚገኘውን ስታርች ግሉኮስና ተዛማጅ የሆኑ ምርቶችን ወደ ውጭ እንደሚልክ አቶ ሙላቱ ተናግረዋል። ከዚህ በተጨማሪም መጠኑ አነስተኛ ቢሆንም ለሀገር ውስጥ ፍጆታ የሚውል የበቆሎ ዘይት በአመት እስከ ስድስት ሚሊዮን ሊትር የሚገኝ መሆኑንም አስረድተዋል።

ከሁለቱም ምርቶች በተረፈ ምርትነት የሚገኘው ከፍተኛ መጠን ያለው የምግብ ዘይት ለሀገር ውስጥ ፍጆታ የሚውል መሆኑን የገለፁት አቶ ሙላቱ፤ በሚቀጥሉት አራት አመታት ሁለተኛው ፋብሪካም ወደ ሥራ ገብቶ ሁለቱም ሙሉ ለሙሉ ወደ ምርት ይገባሉ። በዚህም 48 ሚሊዮን 5 መቶ ሺ ሊትር ዘይት ለሀገር ውስጥ ገበያ ይቀርባል። በጥቅሉ ሁለቱም ፋብሪካዎች በአመት ከስምንት መቶ ሚሊዮን ዶላር በላይ ቀጥተኛ ገቢ ለሀገሪቷ የሚያስገኙ ይሆናለም ብለዋል።

በአሁን ወቅት ሥራ የጀመረው ፋብሪካ በዋናነት የአኩሪ አተር ዱቄት ያመርታል፤ ከአኩሪ አተር በሚገኘው ተረፈ ምርት ደግሞ ንፁህ የተጣራ የምግብ ዘይት እያመረተ እንደሚገኝ አቶ ሙላቱ ተናግረዋል። እንደሳቸው ማብራሪያ ፋብሪካው በአሁን ወቅት በቀን 75 ሺ ሊትር ዘይት እያመረተ ይገኛል። ከጥቅምት መጨረሻ ጀምሮ ዘይቱ ወደ ገበያ የሚወጣና ለህብረተሰቡ ተደራሽ እንደሚሆንም አቶ ሙላቱ ተናግረዋል። የሚመረተው ዘይትም ደረጃውን የጠበቀና በዘመናዊ መሳሪያ የተቀነባበረ መሆኑን አስረድተዋል።

ፋብሪካው በዋናነት የሚጠቀመውን የአኩሪ አተር ምርት በበቂ መጠንና ጥራት ለማግኘት መንግስት ድጋፍ አድርጓል ያሉት አቶ ሙላቱ፤ መንግስት በየአካባቢው ባሉ የንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮዎች ዕውቅና እንዲያገኝ እገዛ አድርጓል ብለዋል ። በአሁኑ ወቅት አርሶ አደሩ አስፈላጊውን መረጃ ያገኘ በመሆኑ የአኩሪ አተር ምርቱን እየሰበሰቡ እንደሆነ አመልክተዋል። በዚህም እስካሁን ባለው ጊዜ ውስጥ ከ160 ሺ ኩንታል በላይ የአኩሪ አተር ምርት በመጋዘናቸው እንዳለ ተናግረዋል። ወቅቱ የግብርና ምርቶች ወደ ገበያ የሚወጡበት በመሆኑ በቀጣይ ሁለት ሳምንታት የሚደረጉ ግዥዎችን መሰረት በማድረግም ከሁለት መቶ ሺ ኩንታል በላይ የአኩሪ አተር ምርት እንደሚገዙ ጠቁመዋል።

ኢንቨስትመንቱን ለማገዝ መንግስት እያደረገ ያለው ድጋፍ ሊበረታታና ሊያስመሰግነው የሚገባ ነው ያሉት አቶ ሙላቱ፤ እስካሁን ባለው እንቅስቃሴም ከ70 በመቶ በላይ እገዛ ማድረጉን ተናግረዋል። በዚህም ፋብሪካው ሲገነባ የግንባታ እቃዎች ከቀረጥ ነፃ እንዲገቡ በማድረግ እና ሌሎች ማበረታቻዎችንም አድርጓል ብለዋል። ይህ በተጨባጭ የሚያታይ ትልቅ እገዛ ነው ያሉት አቶ ሙላቱ፤ ከዚህም አልፎ በተለይም ኢንደስትሪያል ፓርክ ውስጥ ላሉና ወደ ውጭ ሀገር ምርት ለሚልኩ ድርጅቶች እስክ ዘጠኝ ዓመት የሚቆይ የግብር እፎይታ ሰጥቷል። ይህ ደግሞ ኢንቨስትመንቱ ለሀገር ያለውን ጠቀሜታ የሚያጠናክርና

ሊበረታታ የሚገባው ነው ብለዋል። ይህ ትልቅ ማበረታቻ እንደመሆኑ ዕድሉን ያገኙት ባለሀብቶች በሙሉ በአግባቡ ሊጠቀሙበት እንደሚገባ አቶ ሙላቱ አሳስበዋል።

ድርጅቱ ለአካባቢው ህብረተሰብና ከዛም አልፎ ለሀገር የሚያበረክተው ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታው ዘርፈ ብዙ ነው ያሉት አቶ ሙላቱ፤ በተለይም የሚፈጥረው የስራ ዕድል ዘርፈ ብዙ ነው። በፋብሪካው ውስጥ ተቀጥረው የሚሰሩት ሰራተኞች ጥቂት ናቸው። ነገር ግን ከዚህ ባለፈ ፋብሪካው የግብርና ምርት የሚጠቀም በመሆኑ ምርቱን የሚያመርቱ በርካታ ገበሬዎችን ተጠቃሚ ያደርጋል። ገበሬው የሚያመርተውን ምርትም ለማን እና በምን ያህል ዋጋ እንደሚሸጥ ያውቀዋል። ስለዚህ ገበያ መር ኢኮኖሚን ተግባራዊ ማድረግ ይቻላል። ሌላው ምርቶቹን ከፋብሪካው ተረክቦ ለህብረተሰቡ የሚያሰራጩ በርካታ የህብረተሰብ ክፍሎች ይፈጠራሉ። ከዚህ በተጨማሪም ምርቶቹ ወደ ውጭ የሚላኩ በመሆናቸው ከፋብሪካው ወደ ወደብ የሚያዘዋውሩ የትራንስፖርት ካምፓኒዎች የስራ ዕድሉ ተጠቃሚዎች በመሆናቸው የስራ ዕድሉ ዘርፈ ብዙ ነው ብለዋል።

አቶ ሙላቱ አያይዘውም፤ እንዲህ አይነት ትላልቅ ኢንቨስትመንቶች ቢበራከቱ የሀብት ክፍፍሉን ሚዛናዊ ለማድረግ እንደሚያግዙም ተናግረዋል። ከዚህም በተጨማሪ አገሪቷ ያለባትን የውጭ ምንዛሪ እጥረት መቅረፍ እንደሚቻል የገለፁት አቶ ሙላቱ፤ በተለይም የሀገር ውስጥ የግብርና ምርቶችን ተጠቅመው እሴት በመጨመር ወደ ውጭ ሀገር ምርት የሚልኩ አምራቾች ከፍተኛ ገቢ ማግኘት ይችላሉ። ታድያ እንዲህ አይነት ኢንቨስትመንቶች በትክክልም የአገሪቷን ኢኮኖሚ ማሳደግ የሚችሉ ናቸውም ብለዋል። በተመሳሳይ ከውጭ ሀገር የሚገቡ ጥሬ ዕቃዎችን መሰረት ያደረጉ ምርቶች ከፍተኛ ገቢ ማምጣት አይችሉም። ስለዚህ ከአቅም በላይ ካልሆነ በስተቀር በውጭ ሀገር ጥሬ ዕቃ ላይ ጥገኛ አለመሆኑ የሚመረጥ ነው ሲሉም አመልክተዋል።

መንግስት ለአግሮ ፕሮሰሲንግ ዘርፍ ትልቅ ትኩረት በመስጠት በአገሪቷ አራት ክልሎች የአግሮ ፕሮሰሲንግ ፓርኮችን የገነባ መሆኑን ያስታወሱት አቶ ሙላቱ፤ ከዚህም በላይ በዘርፉ የተሰማሩ ባለሃብቶችን በማበረታታት ውጤታማ እንዲሆኑ እያደረገ ያለው እገዛ ሊያስመሰግነው እንደሚገባ ተናግረዋል። ይህ ደግሞ በአገሪቷ የኢኮኖሚ እድገት ላይ የጎላ አስተዋፅኦ ያበረክታልም ብለዋል።

ሪች ላንድ ድርጅት በኢትዮጵያዊው አቶ ሙላቱ መንገሻ እና በአንድ ቻይናዊ ግለሰብ የተቋቋመ ሲሆን፤ የድርጅቱ ከፍተኛ ተካፋይ የሆኑት አቶ ሙላቱ 51 በመቶ እንዲሁም ቻይናዊው ባለሀብት ደግሞ 49 በመቶ ድርሻ አላቸው። በአሁን ወቅትም ድርጅቱን በበላይነት እየመሩ የሚገኙት አቶ ሙላቱ መንገሻ መሆናቸው ይታወቃል።

ፍሬህይወት አወቀ

የአግሮ ፕሮሰሲንግ ዘርፍን ማስፋፋት ለላቀ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት

Page 10: “ለራሱ ኩራት ለአካባቢው አገሮች ደግሞ የብቃት ......ገጽ 2 አዲስ ዘመን ሐሙስ መስከረም 21 ቀን 2013 ዓ.ም ዜና አዲስ አበባ፦

አዲስ ዘመን ሐሙስ መስከረም 21 ቀን 2013 ዓ.ም ገጽ 10

የምጣኔ ሀብት እንግዳ

አዲስ ዘመን፡- ከለውጡ በፊት የነበረው የአገሪቱን ኢኮኖሚ እንዴት ይገልጹታል?

አምባሳደር ጥሩነህ፡- በመጀመሪያ ደረጃ ለውጡ የመጣበት አንዱ ምክንያት ኢኮኖሚው ትንሽ ችግር ላይ ስለነበር ነው። ከለውጡ በፊት ቀደም ብሎ በጣም በከፍተኛ ምኞት ላይ የተመሰረተ የኢኮኖሚ እቅድ ነበር። ብዙ ፕሮጀክቶች የተጀመሩበት ወቅትም ነበር። ብዙዎቹን ደግሞ በራሳችን አቅም እናከናውናለን ብለን የጀመርንበትም ጊዜ ነበር። ሁኔታው ግን በፈለግነው ፍጥነት ሊሄድ አልቻለም። ችግሮች ነበሩ። የእቅዱና የምኞቱ ጉዳይ ሳይሆን የአስተዳደር ችግር ነበር ከለውጡ በፊት የነበረው።

አዲስ ዘመን፡- የነበረውን የአስተዳደር ችግር ለአብነት ያህል መጠቀስ ከተቻለ?

አምባሳደር ጥሩነህ፡- ለምሳሌ የተጀመሩ የስኳር ፋብሪካዎች፣ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ጭምር ወደመቆም ደረጃ ነበር የደረሱት። አሁን አሁን ነው ስራው በተቀና ሁኔታ በመካሄድ ላይ ያለው። እነዚህ ሁኔታዎች ኢኮኖሚው ላይ ትንሽ ችግር ፈጥረው ነበር። በእርግጥ ይህ ሁኔታ ለለውጡ ዋና ምክንያት ባይሆንም የራሱ ድርሻ ግን ነበረው።

በእርግጥ ከዛ በፊት የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በጣም በፍጥነት እያደገ እና አገሪቱም በዓለም አቀፍ ደረጃ በጣም በከፍተኛ ሁኔታ በማደጓ የብዙዎቹን ቀልብ ያገኘች ስለመሆኗ የሚዘነጋ አይደለም። በወቅቱም በዓለም አቀፍ ደረጃ ተሰሚነቷም በጣም የላቀ እንደነበር የሚታወስ ነው። እንዲያውም የኢትዮጵያ መንገድ ብዙዎቹ ለመከተል የጓጉበት ሁኔታም ተፈጥሮ ነበር። ይህ እንግዲህ ከለውጡ ሶስት እና አራት ዓመት ቀደም ብሎ በነበረበት ጊዜ ማለት ነው።

እኤአ በ2016 እስከ 2018 አካባቢ ጥሩ አልነበረም። ምናልባትም ከአቶ መለስ መሞት በኋላ ኢኮኖሚው ብዙም ሳይቆይ መንገራገጭ የጀመረበት ሁኔታ ነበር። ይህ በእንዲህ እንዳለ ነው ለውጡ የመጣው። እንዳልኩሽ ቀደም ብሎ የነበረው የኢኮኖሚው ሁኔታ ጥሩ የሚባል ነበር። ከለውጡ አምስት ዓመት በፊት የነበረችው ኢትዮጵያ እጅግ የምታጓጓና የምታኮራ አገር ነበረች። ለውጡ ሊመጣ ሁለትና ሶስት ዓመት ቀደም ብሎ የነበረው ኢኮኖሚ መጥፎ ሁኔታ ውስጥ ያለ ነበር። ትንሽም ድርቅ ብጤ ነበር። ያለችንን የውጭ ምንዛሪም ከውጭ ስንዴ በመሸመት ስለጨረስናት ለግድቡና ለመሳሰሉት ነገሮች የውጭ ምንዛሪ እጥረት የተፈጠረበት ጊዜ ነበር።

አዲስ ዘመን፡- ከለውጡ በፊት እጅግ የምታጓጓና የምታኮራ አገር መሆኗን የሚያሳዩ ነገሮችን ሊጠቅሷቸው ይችላሉ?

አምባሳደር ጥሩነህ፡- እንዴ! በጣም እንጂ! በዓለም ላይ በጣም በከፍተኛ ፍጥነት እያደገች ያለች አገር ነበረች። ለምሳሌ ኢንቨስትመንት ድሮ ይመጣ የነበረው 100 ሚሊዮን ዶላር ቢበዛ ደግሞ 200 መቶ ሚሊዮን ዶላር የነበረው ወደ ሁለትና ሶስት ቢሊዮን የደረሰበት ጊዜ ነበር። ያ ማለት ገንዘባቸውን ወደ ኢትዮጵያ የሚያመጡ ሰዎች በኢትዮጵያ ምቹ ሁኔታ አለ፤ አገሪቱ እያደገች ነው፤ ለወደፊትም ተስፋ አላት። ስለዚህ በኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋያችንን ማዋል ጠቃሚ ነው ብለው አምነው ነው። የኢንቨስተሮቹ ወደ አንድ

«እውነቱን ለመናገር ከለውጡ በኋላ ብዙ ጊዜ ያጠፋነው ከኢኮኖሚው ይልቅ በፖለቲካ ላይ ነው»

- አምባሳደር ጥሩነህ ዜናየምጣኔ ሀብት ባለሙያና የቀድሞው የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር

አገር መምጣት ማለት እና ገንዘባቸውን ማፍሰስ ማለት ለዛ አገር ለኢኮኖሚ እድገቱ ምቹ ነው፤ የወደፊት ተስፋውም በጣም ከፍተኛ ነው የሚሆነው። ይህ አንድ ማሳያ ነው።

ሌላው ደግሞ ኢትዮጵያ በተቸገረችበት ጊዜ ብድር ጠይቃ ቦንድ ሸጣለች ። ለመጀመሪያ ጊዜ ቦንዱ በአንድ ቀን ነበር ተሸጦ ያለቀው። እንግዲህ ይህ ማለት የአንድ አገር መንግስትን ቦንድ የውጭ አገር ሰዎች ሲገዙ ትርጉሙ የዚያ አገር የኢኮኖሚው ሁኔታ በጣም ጥሩ ደረጃ ላይ ነው ያለው ማለት ነው፤ ሊከፍል ይችላል የሚል እምነት መኖሩን ነው የሚያሳየው። ከዚህም የተነሳ ኢትዮጵያ ያቀረበችው ቦንድ ያለቀው ወዲያው ነው። ይህ ሁሉ የሚያሳየው አገሪቱ በጣም በጥሩ ሁኔታ ላይ መሆኗን ነው። ነገር ግን አልቆየም። በተለይ ፕሮጀክቶቹ አልደረሱም። ለምሳሌ ለስኳር ፋብሪካው የተበደርነው ገንዘብ ብዙ ነው፤ ስኳር መመረት ቢጀምር ኖሮ ከውጭ የምናስመጣውን ስኳር ከማስቀረትም በዘለለ ተጨማሪ እኛ ራሳችን ወደውጭ ወደመላኩ በመሸጋገር የውጭ ምንዛሬም ማምጣት እንችል ነበር። ለስኳር ግዥ ወደውጪ የሚወጣውን በብዙ መቶ ሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ እናስቀር ነበር። ይሁንና ይህን ማድረግ አልተቻለም። በመሆኑም የማኔጅመንት ችግር ያልኩት ይህን ነው።

እቅዱ ትክክል ነው፤ ምኞቱም ቢሆን አገርን ከችግር ለማላቀቅ እና መንጥቆ ለማውጣት የሚያበቃ እቅድ ነው። ነገር ግን ያንን ማኔጅ ማድረግ አልተቻለም። ከዚህም የተነሳ የታሰበው ሳይሳካ እየቀረ መጣ።

አዲስ ዘመን፡- ከለውጡ በኋላ ኢኮኖሚውን ለማነቃቃት እየተወሰዱ ያሉ እርምጃዎችን እንዴት አገኟቸው?

አምባሳደር ጥሩነህ፡- ኢኮኖሚውን ለማነቃቃት የተወሰዱ እርምጃዎች ትልቅ ናቸው ብዬ ልጠቅስ የምችለው አሁን እየተጀመረ ያለውን ነው። በእርግጥ እውነቱን ለመናገር ብዙ ጊዜ ያጠፋነው ከኢኮኖሚው ይልቅ በፖለቲካ ላይ ነው። ከለውጡ በኋላ ባለው ወቅት በፖለቲካ ላይ ነው ብዙ ጊዜ የባከነው ማለት ይቻላል።

ዋናው ነገር የኢኮኖሚ ነገር መረሳት የለበትም። ብዙ ጊዜ ትኩረት ተሰጥቶት አስተያየት የሚሰነዘረውም በፖለቲካ ጉዳይ እንጂ ኢኮኖሚ ላይ ያተኮረ ነገር አይደለም። ነገ በዚህች አገር መኖር አለመኖራችን የሚወሰነው አሁን ላይ እያወራን ባለነው የፖለቲካ ጉዳይ ሳይሆን የኢኮኖሚ ጉዳይ ላይ ጠንክረን ስንሰራ ነው።

ወጣቶች አሁን እየተሯሯጡ ያሉበት ምክንያት ተስፋ ስለቆረጡ ነው። የወደፊት እድላቸው ብሩህ ሆኖ ስላልታየ ነው። ለወደፊቱ ስራ ይዤ፣ ትዳር መስርቼና ልጆቼን አሳድጌ የሚል ተስፋ ስላልታያቸው እና ትምህርት ተምረው ቤት ቁጭ ካሉ የሚሆነው ምንድን ነው? ይህ ደግሞ ለወጣቱም ሆነ ለቤተሰቡ ከፍተኛ ተስፋ የሚያስቆርጥ ነገር ነው። ስለዚህም ነው ወጣቱ የተነሳው። ነገር ግን ፖለቲከኞቹ ወጣቱን ያንቀሳቀስኩት እኔ ነኝ፣ አንተ አይደለህም በሚል ሲሻሙ በመስማት ላይ ነኝ። ትልቁ ነገር የእነሱ ሽሚያ አይደለም። ወጣቱ ያነሳቸው ዋናው መሰረት የራሱን የወደፊት እጣ ፈንታ አስተውሎ ነው ። ጉዳዩ ተስፋ

የሚሰጥ አልነበረምና። በእርግጥ እየነደደ ባለ ነገር ላይ ጋዝ ማርከፍከፍ እንዳለ አውቃለሁ።

የወጣቱን መነሳሳትና የሕዝቡ እርስ በእርስ ግጭት ላይ ትኩረት እየተደረገ ፖለቲካ በማየሉ ምክንያት የኢኮኖሚው ጉዳይ እየተረሳ ሄደ። የተረሳው ደግሞ ፈረንጆቹ (Elephant in the room) እንደሚሉት ትልቁ ነገር ነው የተረሳው። ይህ ደግሞ ትንሽ ዋጋ

ሊያስከፍል ይችላል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ እያደረጉ ያለው ነገር ጥሩ ነው።

ምክንያቱም አሁን ፖለቲካውን ብቻ ሳይሆን አገሪቱን ወደፊት ሊያስኬዳት የሚችለው ኢኮኖሚው ነው በሚል በመንቀሳቀስ ላይ ናቸው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቀደም ሲል በአዲስ አበባ አሁን ደግሞ እንደ አገርም በአንዳንድ ክልሎች እንዲሰራ የጀመሩት ነገር ጥሩ

ፎቶ

- ሐ

ዱሽ

አብ

ርሃ

በቀጣይ አስር ዓመት የኢኮኖሚውን እድገት በማፋጠን ኢትዮጵያን በተምሳሌትነት ልትጠቀስ

የምትችል አገር ለማድረግ እንደሚሰራ መንግስት መግለጹ ይታወቃል፡፡ በተለይም በሁሉም ዘርፍ ጠንካራ

ስራ በመተግበርና የኢትዮጵያውያንን ገቢ በማሳደግ አገሪቱ መካከለኛ የኢኮኖሚ ገቢ ያላት እንድትሆን

የሚያስችል የብልጽግና ፍኖተ ካርታ መዘጋጀቱም የሚታወስ ነው፡፡ በዚህ በ10 ዓመት መሪ የልማት

ዕቅድ አማካይነትም በአማካይ በአመት የ10 በመቶ እድገት ለማስመዝገብ ታቅዷል፡፡ ለስኬታማነቱም

ልዩ ትኩረት የተሰጣቸው መስኮች እንዳሉ ተነግሯል፡፡ አገሪቱ በኢኮኖሚው ዘርፍ ከዚህ ቀደም ስለነበራት

ሁኔታና በቀጣይ ስለሚኖራት ተስፋ እና ስጋት ከምጣኔ ሀብት ባለሙያው ከቀድሞ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን

ኮሚሽነር አምባሳደር ጥሩነህ ዜና ጋር ያደረግነውን ቃለ ምልልስ እንደሚከተለው አቅርበናል፡፡

አስቴር ኤልያስ

Page 11: “ለራሱ ኩራት ለአካባቢው አገሮች ደግሞ የብቃት ......ገጽ 2 አዲስ ዘመን ሐሙስ መስከረም 21 ቀን 2013 ዓ.ም ዜና አዲስ አበባ፦

ገጽ 11አዲስ ዘመን ሐሙስ መስከረም 21 ቀን 2013 ዓ.ም

የምጣኔ ሀብት እንግዳ

የሚባል ነው። በየአቅጣጫውም የልማት መስኮት እየከፈቱ ናቸው። ይህ ደግሞ ሰው ተስፋ እንዲያደርግና ኢኮኖሚው እንዲነሳሳም የሚያግዝ ነው። የተከፈቱት መስኮቶች ብቻቸውን ብርሃን ይፈነጥቃሉ ማለት ሳይሆን የተስፋ ጭላንጭል ይሰጣሉ። እነሱ ተሳክተው ሲታዩ የሚያነሳሱ ይሆናሉ። ከዚህ ቀደም ወደኋላ ያስቀረን በጊዜ ፕሮጀክቶችን ያለመፈጸም ችግር ነው። አሁን እየተደረገ ያለው ነገር ሲታይ ግን የህዝቡ ተስፋ ሊያንሰራራ ይችላል።

በእርግጥ አንዳንድ የተባለው ነገር ያስደነገጠን ነበር። ለምሳሌ የኢትዮጵያን አየር መንገድ እንሸጥ በተባለ ጊዜ መብረቅ የወረደብን ያህል አስበርግጎን ነበር። ይህ ማለት ምን ማለት መሰለሽ የኢትዮጵያን አየር መንገድ እንሽጥ ሲባል ማስደንገጡ መታወቂያ ሰንደቃችን በመሆኑ ነው። አሁን ግን ረጋ ያለ ይመስላል። ሳይሰበር አትጠግን የሚል አባባል አለ። ይህ ማለት ደግሞ በጣም በጥሩ ሁኔታ እየተጓዘ ያለውን ተቋም ለምን የሚያስብል ነው።

እንዲህም ስል ሁሉም አይሸጡ ማለቴ አይደለም፤ አንዳንድ መሸጥ ያለባቸው የንግድ ድርጅቶች አሉ፤ ለምሳሌ ስኳሩን ጨምሮ አንዳንድ ፕሮጀክቶች ቢሸጡ ችግር የለም። ነገር ግን አየር መንገዱ በአፍሪካም ሆነ ዓለም አቀፍ ደረጃ ምርጥ አፈጻጸም እያሳየ ያለ ሆኖ ሳለ ወደሽያጭ መገባቱ አስቸጋሪ ነው።

የኢትዮጵያ አየር መንገድን በጣም በልፋት ያቋቋሙት በ1940ዎቹ ገደማ የድሮው ጠቅላይ ሚኒስትር አክሊሉ ሀብተወልድ ናቸው። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ አገሪቱ ክፍተት ባሳየችበት ሁሉ እየገባ ቀዳዳውን እየደፈነ ዛሬ ላይ የደረሰ ትልቅና አዋጭ የሆነ ተቋም ነው።

ከለውጡ በኋላም ጥንቃቄ የተደረገበት እና ድሮ የነበረው ነገር በጣም ጥበብ በተሞላበት ሁኔታ የቀጠለው ነገር ካፒታል ሊብራላይዜሽን ነው። የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ እጅግ

በከፍተኛ ደረጃ ተከራክረው አላደርገውም ብለው በ1980ዎቹ ውስጥ የካፒታል ሊብራላይዝ ያደረጉ አገሮች ኢኮኖሚያቸው ሲደቅና ሲወድቅ ኢትዮጵያ ብዙ ነገር ሳይደርስባት የወጣችና በተባበሩት መንግስታት ድርጅት መድረክ ኢትዮጵያ እንደ ምሳሌ የተነሳች መሆኑም የሚታወስ ነው፤ በወቅቱ ይህም አካሄዷ ትልቅ ጥበብና ውሳኔ የታየበት ነው ብለው ነበር የጠቀሱት።

ካፒታል ሊብራላይዜሽን የሚባለው ነገር ችግር በሚፈጠርበት ጊዜ ጉዳቱን ማወቅ ይቻላል፤ በእርግጥ ጥቅም አለው። በጥሩ ጊዜ ካፒታልን ወደአገር ውስጥ ይስባል። ነገር ግን አሁን እየተፈጠረ ያለው ነገር በሚከሰትበት ጊዜ በተለይ እየተፈጠረ ያለው የኢኮኖሚ ቀውስ በኮቪድ ምክንያትም ጭምር ነው። አንድ ነገር ቢፈጠር ካፒታል ፍላይት ይኖራል። ካፒታል ከታዳጊ አገር ወደመጣበት ተመልሶ ይሄዳል። ይህ ካፒታል ሊብራላይዜሽን እኛ አገር ስላልተደረገ አያሰጋንም። አንድ ኢኮኖሚው እያደገ ነው። ከቻይና በስተቀር ዓለም ላይ ያለው ኢኮኖሚ በሙሉ ሲቀዘቀዝ የእኛ እያደገ ነው። በእርግጥ ባልነው መጠን እያደገ አይደለም። ይሁንና ቀንሶም ቢሆን እድገት እያሳየ ነው። ይህ ደግሞ ትልቅ ነገር ነው። የኢትዮጵያ አየር መንገድና የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ዓለምን በሚያስደነቅ ሁኔታ እየፈጠነ ነው ።

ያቺ ድሃ አገር እንዴት ነው እንዲህ ፈጣን እድገት እያመዘገበች የመጣችው ያሉት ዛሬም ከኮቪድ በኋላ እንዲሁ ሊያደንቁ ይችላሉ። እንዲያውም ከለውጡ አራትና አምስት ዓመት በፊት ወደነበርንበት ቦታ ልንመለስ እንችላለን ብዬ አስባለሁ።

በሌላ በኩል አንዳንድ ነገሮች በሚሸጡበትና በሚለውጡበት ጊዜ ጥንቃቄ ያስፈልጋል። ምክንያቱም በሽያጭ ወቅት በጣም ከፍተኛ ሙስና ይመጣል። በሚሸጥበት ጊዜ አሻሽጦ አንድ ነገር ለማግኘት ሲል ተፍ ተፍ የሚለው ብዙ ነው። ያልጋገረውን ለመቁረስ

የተሰበሰበ አካል በርካታ ነው። ስለዚህ ይህ ነገር ተከስቶ ደሃውም እንዳይጎዳ እና ሳይመቸው ያጠራቀመውን ሀብት ጥቂቶች መጥተው በኮሚሽን ስም ይዘው ቢሄዱ ለመንግስትም የሚከሰተው ነገር መጥፎ ነው። ስለዚህም መንግስት ጥንቃቄ ማድረግ ይጠበቅበታል።

እኔ በውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ስራ በጀመርኩበት በ1970ዎቹ አካባቢ የኢትዮጵያ ጠቅላላ ምርት 10 ቢሊዮን አካባቢ ነበር። በአሁኑ ወቅት ግን ወደ 100 ቢሊዮን ነን። በእርግጥ የሰውም ፍላጎት በእጥፍ ጨምሯል። በቀጣይ ግን ትልቅ ተስፋ አለን። ከነበርንበት ጋር ሲተያይ ወደፊት መጥተናል ባይ ነኝ።

ሩሲያውያን ለውጥ እናደርጋለን ብለው ተጣድ ፈው ሄደው የሆነው ነገር ግን ስኬት የራቀው ነው። አንዴ ጊዜ በ1993 ገደማ ኒዎርክ ነበርኩና ለእኛ ለኢትዮጵያውያን ጨምሮ ለሌሎች ድሃ አገሮች፣ ሀብታም አገሮቹ ይህን ያህል እንሰጣለን እያሉ የሚያውጁበት መድረክ ነበር። ለሶቪዬት ህብረትም ከእኛ ከድሃ አገሮች እኩል ተጠየቀ። በወቅቱ በጣም ደነገጥኩ። ምክንያቱም ኃያል የነበረ አገር በአጭር ጊዜ ውስጥ ወድቆ ከድሃ አገሮች እኩል ተቆጥሮ ለዱቄትና ስንዴ ከእኛ ጋር ተሰለፈ። ይህ የሆነው ለምንድን ነው ቢባል ለውጥን በአግባቡ ካለመምራት የተነሳ ነው።

እንደሚታወቀው ለውጥ ካለንበት ችግር መንጥቆ ማውጣት የሚችል ኃይል ነው። ይህ የሚሆነው ግን በአግባቡ መመራት ከቻለ ነው። ይህ ካልሆነ ልክ የሩሲያውያን ጽዋ ሊደርስ ይችላል። እኔ የአይን ምስክር ነኝ፤ ኢትዮጵያና መሰል አገሮችም ሆኑ እኔ ለልመና ነው በዛ መድረክ የተገኘነው፤ ሕዝባችን ተርቧል እያልን ነበር ስንወተውት የነበረው። የሩሲያ ግን በዛ መድረክ ተገኝቶ መለመን ትንሽ ከበድ ያለ ነው። በእርግጥ ከዚህ በኋላ እኛ ወደዚህ አይነት ልመና እንሄዳለን ብዬ አላስብም፤ ግን የተገኘውን ለውጥ በአግባቡ መምራት የግድ ይላል።

በሌላ በኩል ቻይናውያን በ1978 አካባቢ የዓለም ጠቅላላ ኢኮኖሚ ድርሻቸው ሁለት በመቶ ብቻ ነበር። ለውጡን በአግባቡ በመምራታቸው ዛሬ እንዲያውም አሜሪካንን እስከማለፍ ደርሰዋል እየተባለ ነው።

አዲስ ዘመን፡- ባለሀብቱን ዋነኛ አገራዊ አቅም ለማድረግ የሚደረገው ጥረት ባለሀብቶቻችን ከመጡበት ጠማማ መንገድ አንጻር ዋጋ ሊያስከፍል ይችላል የሚሉ አሉ፤ ይህን እንዴት ያዩታል?

አምባሳደር ጥሩነህ፡- ቀደም ሲል የጠቀስኩት ካፒታል ሊብራላይዜሽንን መንግስት አልተወም። ካፒታልን ሊብራላይዝድ ለማድረግ በዲሲፒሊን የተሞሉ ባንኮች መኖር አለባቸው። የአካውንታንት ማህበር መኖር አለበት። ሌሎቹ ስቶክ ማርኬትን ሊቆጣጠሩ የሚችሉ አካላት ማደግ አለባቸው። ብዙዎቹ እንደሚያታውሱት ብዙ የአሜሪካ ኩባንያዎች ከስረው ነበር። እንዳልነበሩም ሆነዋል። ብዙዎቹ ገንዘብ ያስቀመጡት በስቶክ ማርኬት ነው። ለጡረታዬ ይሆናል ብለው ገንዘባቸውን ከወጣትነታቸው ጀምረው ያስቀመጡ ግለሰቦች ገንዘባቸው ዜሮ ነው የሆነው። አንዳንዶቹን ሀብታሞቹ አጭበርብረው የሌለውን አለ ብለው ሚሊዮኑን ቢሊዮን ብለው እንዲሁም የውሸት አካውንት አቅርበው እየሸጡ እና እየለወጡ በመጨረሻ ላይ ሲታይ ግን ባዶ ነው የሆነው። በእነሱ አገር መቶ ያህል ዓመት ልምድ ያላቸው ብዙም ዲሲፒሊን ያለው አገር እንዲህ ከሆነ የኛ አገር ምንም የማያውቅ፤ ድህነት በጣም የሚያጠቃውና ዲሲፒሊን የሌለው ፣ በተለይ ደግሞ ነጥቆ ለመሸሽና ለመሮጥ በጣም የተዘጋጀ ህብረተሰብ ባለበት ይህንን ከፍቶ ህዝቡን ላልተገባ ነገር ማጋለጥ አደጋ ነው። ስለዚህ መቆየት አለብን። ቦንድ መሸጥ አለብን።

በሌላ በኩል ደግሞ ሰዎች ተሰብስበው ማህበር አቋቁመው ይህንን አይነት ፋብሪካ እናቋቁማለን፤ ያንን እንሰራለን ከግለሰቦች ገንዘብ በመውሰድ ከዛ ለራሳቸው 10 እና 20 በመቶ ኮሚሽን እንወስዳለን ብለው አስፈረሟቸው ኮሚሽኑን ከወሰዱ በኋላ ግን ምንም ሳይሰራ የት ይዘው እንደገቡም አይታወቅም። ይህንን መንግስት በደንብ ቢቆጣጠር እና ለዛ ጉዳይ ህግ ቢያወጣ መልካም ነው፤ በጣም ከፍተኛ ገንዘብ ከተማ ውስጥ አለ። ያ ገንዘብ ወደኢንቨስትመንት ይሄዳል። እሱ ግን አልተደረገም። ከመስራት ይልቅ ወደ ስቶክ ማርኬት እንሩጥ የሚሉት ለመመንጨቅ ነው የሚል ስጋት ያስነሳል።

አዲስ ዘመን፡- በከፍተኛ ብድር አደጋ

ውስጥ ያለውን የአገሪቱን ኢኮኖሚ ለማነቃቃት የሚወሰደው ተጨማሪ ብድር በራሱ ለኢኮኖሚው ተግዳሮት ሊሆንበት እንደሚችል እየተነገረ ነው፤ ይህን እንዴት ያዩታል?

አምባሳደር ጥሩነህ፡- መንግስት ሲበደር አገሪቱ ሊጎዳ ነው ብለው የሚጮሁ አሉ፤ በእርግጥ የእኛ መንግስት እውነቱን እንነጋገር ከተባለ በአጼ ኃይለስላሴም ዘመን ገንዘብ ሚኒስቴር ውስጥ ሰርቻለሁ፤ በደርግ ዘመንም በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ውስጥ ሆኜ በኢኮኖሚው ዘርፍ ቅርብ ሆኜ ሰርቻለሁ። የኢኮኖሚም ተደራዳሪ ነበርኩ። ዋናው ለማለት የፈለኩት ነገር መንግስታችን በጣም ጠንቃቃ መሆኑን ነው። የመንግስት ሲቪል ሰርቪስ አሁን አሁን በጣም ሙሰኛ ሆነ እንጂ በጣም ዲሲፒሊን እና እውቀት ያለው ብሎም አገሩን የሚወድ የነበረ ነው። እንደሱ አይነት ዲሲፒሊን ስለነበር በሁለቱም መንግስት ብድር ወስደን ሳንከፍል የቀረንበት ጊዜ የለም።

በርካታ አገራት በተለይ አፍሪካና ላቲን አሜሪካ አገራት መክፈል አልችልም በማለታቸው ብድር አይሰጣቸውም፤ አገራቱ ከብድር ሰጪዎቹ ጋር ያላቸው ህብረት ይቆማል። እንደእነ አርጀንቲና፣ ሜክሲኮ የመሳሰሉ ትልልቅ አገራት መክፈል አልችልም ሲሉ የተደመጡበት ጊዜ ነበር፤ ኢትዮጵያ ግን እስካሁን ባለው መንግስት ጭምር ሁልጊዜ የተበደረችውን በመክፈል ነው የምትታወቀው።

ወደ ዋናው ጥያቄሽ ስመጣ ብድር ካልተበደርሽ በታዳጊ አገር ውስጥ ለማደግ አይታሰብም። የምንበደርበትም ዋናው ነገር ኢንቨስት ለማድረግ ያለን ፍላጎት ከቁጠባችን ጋር ስለማይመጣጠን ነው። ድሃ ስለሆንን የምንቆጥበው ትንሽ ነው። ቁጠባ ከሌለ ደግሞ ኢንቨስትመንት ከየትም ሊመጣ አይችልም ። ስለዚህ የሚመጣው በብድር ነው።

ሌላው ትልቁ ማሰብ ያለብን እኛ ከውጭ ማምጣት ያለብን ብዙ ነገር አለ፤ ነገር ግን ወደውጭ የምንልከው ያንን ከምናስገባው ጋር የሚመጣጠን አይደለም። ስለዚህ ብድር በታዳጊ አገር የግድ አስፈላጊ ነው። ታድያ መቼ ነው መጥፎ የሚሆነው የምትይኝ ከሆነ ፤ የተበደርነውን ገንዘብ ለፍጆታ ፤ ዝቅተኛ ምርት ላለው ነገር ስናውለውም ነው። ለምሳሌ በጣም ጥሩ ጥሩ ቤቶች ላይ ካዋልነው ። ምክንያቱም እነሱን ወደውጭ በመላክ የውጭ ምንዛሬ ለማግኘትና ብድር ለመክፈል አይቻልም ። ስለዚህ መበደር በእርግጥ ይኖርብናል፤ ነገር ግን በአግባቡ መጠቀም የግድ ይላል። የተበደርነውን ነገር ማጥፋት የለብንም። ይህን ካደረግን ገቢያችን ያድጋል፤ ገቢ አደገ ማለት ደግሞ ቁጠባም ያድጋል። እንዲሁም የሰራተኛው ገቢም ያድጋል። የኢኮኖሚ እንቅስቃሴም ይፈጠራል። በሚፈጠረው ገቢ ደግሞ እዳ መክፈል ይቻላል።

አዲስ ዘመን፡- የዓለም አቀፍ ተሞክሮ የሚያሳየው ይህንን ነው ? እስኪ ይሄ እንዴት ይገለጻል?

አምባሳደር ጥሩነህ፡- የዓለም አቀፍ ተሞክሮ የሚያሳየው መቶ በመቶ ይህንን ነው። ለምሳሌ ላቲን አሜሪካን መውሰድ እንችላል። ከመንግስት ውጭ ሀብታሞቹ በቀጥታ ከባንኮች ይበደሩ ነበሩ፤ በተበደሩበት ገንዘብ ቆንጆ መኪና በመግዛት ተንሸራሸሩበት፤ ያንን በማድረጋቸውም ገንዘቡን ያለኢንቨስትመንት አባከኑት። ገንዘቡ ኢንቨስትመንት ላይ ስላልዋለ የተበደሩትን መክፈል አልቻሉም። የዓለም አቀፉ ተሞክሮ የሚያሳየው ይህንን ነው፤ መበደር አለብን፤ ግን ስራ ላይ ማዋል ይጠበቅብናል።

በብድር ጊዜ ውስጥን ውጪንም ነው በአግባቡ መቃኘት የሚገባው። ለምሳሌ ብድሩን የወሰድነው ቡና እርሻን ለማስፋፋት ከሆነ እና አሁን በተከሰተው ኮቪድ ምክንያት ተቀባይ አገራት መውሰድ አልችልም ቢሉ ውድቀት ይከተላል ማለት ነው። በእርግጥ ኢትዮጵያ አሁን የብድሩ ሬሾ ጂዲፒ ሲታይ በ50 እና በ60 በመቶ መካከል ነው። እኔ ኒዮርክ እያለሁ ኢትዮጵያ እስከ 90 በመቶ ይደርስ ነበር፡፡ በእርግጥ በወቅቱ 760 ሚሊዮን ዶላር እዳ ነበረብን፤ ተደራድረን 670 ሚሊዮን ዶላር አሰረዝን። ይህን ለማለት ትንሽ ቢከብደኝም ኢትዮጵያ አሁን የውጭ ጉዳይን ማጠንከር ይኖርባታል።

እንደ ኮቪድ አይነት ነገር በሚከሰትበት ጊዜ እዳ ሰርዙ እንዲህና እንዲያ አድርጉ በማለት መደራደር ያለባት ኢትዮጵያ ብቻ አይደለችም። እዳ መሰረዝ አለበት። ሀብታሞችም መርዳት አለባቸው። የሚሰረዘው እንዴትና የት ነው ሲባል

Page 12: “ለራሱ ኩራት ለአካባቢው አገሮች ደግሞ የብቃት ......ገጽ 2 አዲስ ዘመን ሐሙስ መስከረም 21 ቀን 2013 ዓ.ም ዜና አዲስ አበባ፦

በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሁላችንም አንድ ላይ በመጮህ ነው። በወቅቱ እንደ ቡድን 20 እና 7 አባል አገራት በተሰበሰቡበት ነው 670 ሚሊዮን ዶላሩን ያሰረዝነው። ይህ የሆነው በ2000 አካባቢ ነው። እዳ እንዳልኩሽ በድርድር ይሰረዛል፤ እዳ ሳይኖርብን ሲቀር ደግሞ ሌላ ለመበደር ምቹ ሁኔታን ይፈጥርልናል። ለመጣው እድገታችን መሰረት የፈጠረውም አንዱ ይሄ ነው። ስለዚህ ያኔም ቢሆን እኛ መክፈል አንችልም አላልንም። ተደራድረን አሰረዝን እንጂ።

አዲስ ዘመን፡- መክፈል አንችልም በማለትና እዳችንን ሰርዙልን በሚል መካከል ያለውን ልዩነት ያብራሩልን እስኪ?

አምባሳደር ጥሩነህ፡- አዎ በሁለቱ መካከል ትልቅ ልዩነት አለ። መክፈል አልችልም ማለት ዝቅ ማለት ነው፤ ተደራድሮ ማሰረዝ ደግሞ በዓለም አቀፍ ደረጃ የአንድ አገር የዲፕሎማሲ ችሎታና የማሳመን ጥበብ ነው። ኢትዮጵያ እንደ አገር እንደሌሎቹ አገራት ብድር ብዙ አትደፍርም። ዜጎቿም ቢሆኑ በተናጠል ሲታዩ ብድር ላይ ደፋር አይደሉም። ብዙ ተበድረን ያጠፋን አገር አይደለንም። ከለውጡ ሁለትና ሶስት ዓመት ያለችው ጊዜ ናት እንጂ ከዛ በፊትም የነበረው ሁኔታ ኢትዮጵያ በብድር ተሽመድምዳ አታውቅም።

አዲስ ዘመን፡- ቀደም ብለው ጠቅስ ወዳደረጉት ጉዳይ ልመልስዎትና መንግስት የልማት ድርጅቶችን ወደግል ይዞታ ለማዞር እየሄደበት ያለው መንገድ የፈጠነ ነው የሚሉ አስተያየቶች እየተደመጡ ነው፤ በዚህ ላይ ምን ይላሉ?

አምባሳደር ጥሩነህ፡- በእርግጥ ዝርዝሩን አላውቅም፤ መቼ ነው መሸጥ ያለበት ሲባል የዓለም ኢኮኖሚ እንዲህ በተንኮታኮተበት በዚህ ጊዜ እንሽጥ ቢባል ዋጋው ዝቅ ነው የሚለው። ምክንያቱም ተፈላጊነቱ ይቀንሳል። ስለሆነም አሁን ወቅቱ ምቹ አይደለም። ይቅርታ ይደረግልኝና በጉዳዩ ዙሪያ ያሉት በርካታው ክፍል ወጣትና ሰፋ ያለ ምኞት ያላቸው ከመሆናቸውም በተጨማሪ ለነገሮቹ አዲስ የሆኑ ናቸው። ጉዳዩ ውስብስብ በመሆኑ ልምድን የሚጠይቅ ነው። ስለዚህ ስንሸጥ ብዙዎች ጠልፈው ለመጣል የሚያርጉት ጥረት ይኖራልና ያንን ለመቋቋም የሚያስችል ነገር ሊኖረን ይገባል ባይ ነኝ። ሌላው ደግሞ ዲሲፒሊኑስ አለን ወይ፤ ለኮሚሽንና ለመሳሰለው ነገር እንዳንጎመጅ ቁርጠኝነቱ አለን ወይ፤ እንዲያም ሆኖ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ውጭ መሸጥ ያለባቸው ሊሸጡ ይችላሉ።

ይህ አዲስ አይደለም። ከዚህ በፊትም ያላችሁን ሽጡ፤ ፕራይቬታይዝ አድርጉ፤ መንግስት አይቆጣጠር። ይህን ካላደረጋችሁ ብድር አንሰጥም የተባለበት ጊዜ ነበር። እኛ ግን ያንን እምቢ ብለን ነው ዛሬ ላይ የደረስነው። አዲስ ላለመሆኑ ቀደም ያሉ ሰነዶችን ብቻ ማገላበጥ በቂ ነው ።

ነገር ግን መንግስት ከኢኮኖሚው በሚወጣበት ጊዜ ማነው ኢኮኖሚውን የሚቆጣጠረው ቢባል የኢትዮጵያ የግል ዘርፉ አይደለም፤ የውጪዎቹ ናቸው። ምክንያቱም የኢትዮጵያ የግሉ ዘርፍ አቅም የለውም። ለምሳሌ ኢትዮ ቴሌን ገዝቶ ለመቆጣጠር አይችልም። ሽጡ ያሉት በእጅ አዙር ራሳቸው የሚቆጣጠሩት ይሆናል። ከፍተኛ ጫና የነበረብን ወዳጆቻችን ናቸው በተባሉት አገራት ቀንና ሌሊት ቴሌኮሙኒኬሽኑንና የፋይናንስ ዘርፉን ፕራይቬታይዝ አድርጉ በማለት ነው።

እኔ በዚህ መንግስት አንድ ያየሁት መልካም ነገር የፋይናንስ ዘርፉን አለመልቀቁ ነው። ይህ መልካም ነው። የኢትዮጵያ አየር መንገድም እንደገና ይታይ ባይ ነኝ። ቴሌኮሙኒኬሽኑም ቢሆን እየታየ ይሂድ። ሌሎቹ እንደ ስኳር ዘርፉ ለኢትዮጵያውያኑ ሊሸጡ የሚችሉ ናቸው። ስለሆነም በእነሱ እንጀምር።

አዲስ ዘመን፡- በቅርቡ ብሄራዊ ባንክ ያወጧቸው አዳዲስ መመሪያዎች እና ክልከላዎችን እንዴት አገኟቸው? ኢኮኖሚውን ለማነቃቃት ያላቸው አስተዋጽኦ በምን ይገለጻል?

አምባሳደር ጥሩነህ፡- ባንኮቹ ከውጭ ይበደሩ የሚለውን አይቻለሁ። መበደር ችግር አይደለም፤ ብድር መበደር አለብን፤ ነገር ግን ተበድረን ሀመር የሚባለው አይነት መኪና አንግዛ ነው። አምጥተን ሀመር ከገዛን በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ወንጀል ሰራን ማለት ነው። በብድር የመጣው ገንዘብ ምን ላይ ዋለ የሚለው ነው ዋናው ቁም ነገር። መንግስት እዚህ ላይ

ሊወሰዱ ይገባል የሚሏቸው የፖሊሲ እርምጃዎች ካሉ?አምባሳደር ጥሩነህ፡- መንግስት በአንደኛ ደረጃ

ከየሰው ገንዘብ በመሰብሰብ እንዲህ አይነት ኩባንያ ወይም አክሲዮን አቋቁመናል እያሉ የሚያጭበረብሩትን ይቆጣጠር። እኔ እና ጓደኞቼም ጭምር በዚህ ጉዳይ ተጭበርብረናል። በዚህ ረገድ የሚቆጣጠር ማንም የለም፤ የሚጭበረበረው ግን በጣም ብዙ ገንዘብ ነው። መንግስት መቆጣጠር ያለበት የራሱን ብቻ አይደለም። የህዝብ ሀብት ነው የሚባለው እኮ የመንግስት ገንዘብ አይደለም፤ የእኔና የአንቺ ገንዘብ የሚሰራው ነገር በሙሉ ነው የሕዝብ ሀብት የሚባለው። ከሕዝብ

የተሰበሰበ ገንዘብ በብልጣብልጦች እየተበላ ስለሆነ መቆጣጠር የግድ ይላል።

ሌላው መንግስት ማድረግ ያለበት ሁለት ነገር ነው። ኢትዮጵያ አገር ሆና ለመቀጠል ኢኮኖሚዋ ማደግ አለበት። በነገራችን ላይ ግብጽ በቀጣዮቹ 30 ዓመታት በዓለምአቀፍ ደረጃ ትልቅ ኢኮኖሚ ካላቸው 10 አገራት መካከል ትገባለች ተብሎ ይጠበቃል። አሜሪካ ደግሞ በቀጣይ አስር ዓመት ውስጥ ሶስተኛ ትሆናለች ተብሎ ይጠበቃል። በዚያን ወቅት ህንድ ከአሜሪካን እንደምትበልጥ ነው የሚነገረው። የዓለምአቀፉ ሁኔታ በዚህ አይነት በጣም በከፍተኛ ደረጃ በመለዋወጥ ላይ ይገኛል። እኛ ደግሞ በዚያ ጊዜ ራሳችንን መቻል ይኖርብናል። ሌላው የነፍስ አባት አለው፤ ድሮ ቅኝ ወደገዛው ጉያ ሊገባ ይችላል። እኛስ? ዞር በል ያለችው ጣይቱ የለችም፤ ስለዚህ ጠንክረን ነው መስራት የሚገባን። ጠንካራ የኢኮኖሚ አቅምና ጠንካራ መከላከያ ከሌለን አገር ሆነን ለመቀጠል አንችልም። ጠንካራ ኢኮኖሚ እንዲኖረን ደግሞ ሆድ ከመሙላት የዘለለ ስራ መስራት አለብን። ከውጭ የሚመጣን ብድር ለትልቅ ኢንቨስትመንት ብቻ ማዋል አለብን።

በቅርቡ ከሱፐርማርኬት ጥሩ ዓሳ ነው ብዬ ከገዛሁ በኋላ ሳየው ከአረብ አገር የሚመጣ ዓሳ ሆኖ አገኘሁት፤ ደግሜ አልገዛሁም። ከውጭ አገር በውጭ ምንዛሪ የገባ ዓሳ ነው። መስራትና ማምረት ስንችል ማለት ነው። እንዲህ ሆነን ግን መቀጠል አንችልም። ስለዚህ የውጭ ምንዛሬ ለፍጆታ እቃ መዋል የለበትም። በመሆኑም መንግስት የውጭ ምንዛሬን በጣም በመቆጣጠር ለኢንቨስትመንት እንዲውል ማድረግ አለበት። ጠንካራ ኢኮኖሚ እና መከላከያ ለመገንባት የውጭ ምንዛሬ ብሎም ጠንካራ አስተዳደር ያስፈልጋል። መንግስት ደግሞ ከኢኮኖሚው መውጣት የለበትም፤ መቀጠል አለበት። በውስጡ ያሉ የግል ዘርፎችን ማሳደግ አለበት። የውጭ ኢንቨስተሮች መጥፎ ነገር ሲመጣ በተለይ ካፒታል ሊብራላይዝድ ሲሆን ጥለውን ይሄዳሉ።

ሌላው በከተማችን ውስጥ ያሉ ቤቶች ሲታዩ በሙሉ የተሰሩት ከውጭ አገር በውጭ ምንዛሪ በመጣ መስታወት ነው ማለት ያስደፍራል። ለምን በእምነበረድ አልሆኑም? እምነበረድ እዚሁ በአገራችን ስላለ ብቻ ሳይሆን ከመስታወትም በመሻሉ ነው። መንግስት እንዲህ አይነቱን አጥንቶ ወደአገር ውስጥ መግባታቸውን መከልከል አለበት። ዶክተር፣ ፕሮፌሰር፣ ኢንጂነር የሚል መጠሪያ ብቻ ይዞ መንቀሳቀስ ሳይሆን ያሉት ምሁራን እንዲህ አይነቱን ችግር በማጥናት ጉዳትና ጥቅሙን ለማሳየት መንቀሳቀስ ይኖርባቸዋል። የምሁራን ጋጋታ ችግር ፈቺ ካልሆነ ምን ሊረባ ነው ታድያ። በቅርቡ አሜሪካ ለኢትዮጵያ ትሰጥ የነበረውን ድጋፍ ልታቋርጥ ነው የሚባል ነገር ሰማሁ፤ በእንዲህ አይነት ሁኔታ እግር እየሳምን ልንሄድ አንችልም። ስለዚህ እንዲህ ላለመሆን ትንሽ ቀበቷችንን ጠበቅ ፊታችንን ደግሞ ኮስተር ማድረግ አለብን።

አዲስ ዘመን፡- የአገሪቱ ኢኮኖሚ ቀጣይ ስጋቶችና ተስፋዎች ምንድን ናቸው?

አምባሳደር ጥሩነህ፡- ስጋቱ ካፒታልን ቶሎ ብሎ ሊብራላይዝ ማድረግ ነው። ተስፋዎቹ አሉ፤ ለምሳሌ መሬትና የሰው ኃይል አለን። አመራርነት ከሰጠነው ደግሞ አገሩን የሚወድ ህዝብ አለን። በተለይ የምንበላውንና የምንለብሰውን እዚሁ ከውጭ ላናመጣ እንችላለን። በዛ ዘርፍ ራሳችንን ከቻልን እናድጋለን። ያለን መቶ አስር ሚሊዮን አካባቢ ሕዝብ ነው፤ ይህ ሕዝብ የፍጆታ ተጠቃሚ ነው።

እነ እስያ ያደጉት ርካሽ የሰው ጉልበት በመኖሩ ነው፤ በቀጣይ አስር ዓመት ውስጥ ግን እሱ ሊኖራቸው አይችልም፤ የሚኖረው ታድያ የት ነው ቢባል አፍሪካ ነው፤ ከአፍሪካ ደግሞ ብዙ ህዝብ ያለው ጅቡቲ አይነት አገር ሳይሆን 100 ሚሊዮን ወዳለውና ዲሲፒሊን ወዳለው አገር ኢትዮጵያ ነውና ወደዚህ ነው።

ሌላው ለኢትዮጵያ አደጋ ቁጥር አንድ ሰላም መታጣት ነው። አንድ ኢንቬስተር ከውጭ ወደ ኢትዮጵያ ለመምጣት ገና ከማሰቡ በፊት የሕዝብ ቁጥር፣ ዴሞክራሲና ሌላ ነገር ሳይሆን የሚያስቀድመው አገሪቱ ውስጥ ሰላም አለ ወይ የሚለውን ነው። ስለዚህ መንግስት ቶሎ ብሎ ኢኮኖሚውን ሊብራላይዝድ ማድረግና ሰላምን ማስጠበቅ የግድ ይለዋል።

አዲስ ዘመን፡- ለሰጡን ሰፊ ማብራሪያ ከልብ አመሰግናለሁ።

አምባሳደር ጥሩነህ፡- እኔም አመሰግናለሁ።

አዲስ ዘመን ሐሙስ መስከረም 21 ቀን 2013 ዓ.ም ገጽ 12

የምጣኔ ሀብት እንግዳ

ቁጥጥር ማድረግ ይጠበቅበታል። የግሉን ዘርፍ ማሳደግ ማለት ልጅ እንደማሳደግ ነውና ቁጥጥርም በማድረግ መሆን አለበት። መንጭቆ ለመሮጥ በብዙ ተዘጋጅቶ የሚመጣም ስለሚኖር እኔ በግሌም አውቃለሁና ነው ይህን የምናገረው። ብዙ አስመሳይ እንዳለም ማስተዋሉ መልካም ነው። ገንዘቡን ወስዶ ለየትኛው ኢንቨስትመንት ነው ያለው የሚለውን መንግስት መፈተሽ አለበት።

አዲስ ዘመን፡- አሁን መንግስት እየወሰዳቸው ካለው የኢኮኖሚ ማሻሻያ እርምጃዎች በተጨማሪ

መንግስት በአንደኛ ደረጃ ከየሰው ገንዘብ በመሰብሰብ

እንዲህ አይነት ኩባንያ ወይም አክሲዮን አቋቁመናል

እያሉ የሚያጭበረብሩትን ይቆጣጠር።

Page 13: “ለራሱ ኩራት ለአካባቢው አገሮች ደግሞ የብቃት ......ገጽ 2 አዲስ ዘመን ሐሙስ መስከረም 21 ቀን 2013 ዓ.ም ዜና አዲስ አበባ፦

አዲስ ዘመን ሐሙስ መስከረም 21 ቀን 2013 ዓ.ም ገጽ 13

ታምራት ተስፋዬ

ያልተጨበጨበለት የአፍሪካውያን ስኬትኮቪድ 19ኝ በቴክኖሎጂ የመጠቁ፣ በኢኮኖሚ የበለፀጉና

በህክምና አገልግሎት አቅርቦትም ሆነ ጥራት ከፊተኞቹ ተርታ ስማቸው የሚጠራላቸው ጣልያን፣ ፈረንሳይ እንግሊዝ እና ስፔንን አብረክርኳል። አቅምና ጉልበት አሳጥቶ ገንዘብ እና እውቀታቸውን ከንቱ አድርጎል። የልእለ ሀያሏም አገር አሜሪካ ዝና አርክሶ፣ በሟች ቁጥር ‹‹አንደኛ››አስብሏታል።

ወረርሽኙ በተሻለ የጤና ዘርፍ አደረጃጀትና የቴክኖሎጂ ብቃት ለሚታወቁት ብሎም በኢኮኖሚ ልዕልና አንቱ ለሚባሉት ለሃያላን አገራት አልተበገረምና ደሃ ለምትባለው እና በቂ የህክምና አገልግሎትና ጥራት ለሌላት አህጉራችን አፍሪካ ያልተጨነቀ እና ያልተቆጨ አልነበረም።

ድህነት ከእለት የእጅ ወደ አፍ ኑራቸው ጋር ተዳምሮ የአህጉሪቱ ዜጎች ከመንግስት የመጣ ትዕዛዝን የማይቀበሉና ከመቀበላቸው በፊት ጥያቄ የሚያቀርቡ መሆናቸውም ወረርሽኙን የመከላከልን የመቆጣጠር ስራን ፈታኝ ፣ ቅጣቱንም መሪር እንደሚያደርገው በርካቶች ጥርጥር አልነበራቸውም።

ወረርሽኙ በሌሎች አህጉራት ካስመለከተው ኪሳራ በላይ አፍሪካ የጥፋት በትሩን እንደሚያሳርፍ ጥርጥር ያልነበራቸው በርካቶችም ዜጎቻንም ኢኮኖሚዋንም በቀላሉ የምትነጠው ተስፋ የሌላት አህጉር ሲሉ ገልፀዋት ነበር። የዓለም ጤና ድርጅትም ቢሆን በወርሃ መጋቢት ይፋ ባደረገው ጥናት ተገቢው ጥንቃቄ ካልተደረገ በ12 ወራት ውስጥ እስከ 190ሺ ዜጎች በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸው ሊነጠቁ እንደሚችሉ መላምት አስቀምጦ ነበር።

ወረርሽኙ ዜጎችን ጤና ከማሳጣት ባሻገር የአህጉሪቱን ኢኮኖሚ ክፉኛ እንደሚያንኮታኩተው እና ይሕን ቀውስ ተከትሎም በየአገራቱ የተለየዩ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያው ፖለቲካ ቀውሶች እንደሚፈጠሩ በርካቶች ከስጋት ባለፈ እርግጠኞች ነበሩ።

ይሕ ሁሉ ስጋት እና ቅድመ ግምት ግን እስካሁን ባለው ሂደት እውን መሆን አልቻለም። በአለም አቀፍ ደረጃ በርካታ አገራት በኮሮና ቫይረስ ቀውስ እየታመሱ ይይዙት ይጨብጡት በጠፋባቸው በዚህ ወቅት አፍሪካ ግን በአንፃራዊነት መልካም ቁመና ላይ ተገኝታለች።

የተለያዩ መገናኛ ብዙሃንና ምሁራንም ፣ወረርሽኙ አፍሪካ ምድር ላይ አቅም ማጣቱን እና የተፈራውን ያህል ጉዳት ማድረስ አለመቻሉን ዋቢ በማድረግ በጉዳዩ ላይ ሰፊ ትንታኔ በመስራትን አስተያየቶችን በማስጠት ላይ ይገኛሉ።

የዓለም ጤና ድርጅትም በአፍሪካ በኮቪድ-19 የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በአማካይ እየቀነሰ መምጣቱን አሳውቋል።የኮሮና ቫይረስ ይበልጥ ታይቶባቸዋል የሚባሉት፣ አልጄሪያ፣ ካሜሮን፣ ኮትዲቫር፣ ኢትዮጵያ፣ ጋና፣ ኬንያ ማዳጋስካር፣ ናይጄሪያ እና ሴኔጋልም አዲስ የመያዝ ምጣኔ እየቀነሰ መምጣቱን፣ የሞት ቁጥርም ቢሆን ዝቅተኛ ሆኖ መስተዋሉን የተለያዩ መረጃዎች አመላክተዋል።

በርካታ የአፍሪካ ምሁራን እና የጤናው ዘርፍ ባለሙያዎች እንዲሁም ምዕራባውያን አቻዎቻቸውም የኮሮና ቫይረስ አፍሪካ ላይ በተፈራው ልክ አቅሙን ማሳየት እንዳልቻለ በማስረዳት ላይ ናቸው። ከእነዚህ ምሁራን መካከል የዩጋንዳ አሩዋ ሪፈራል ሆስፒታል ባልደረባ ዶክተር ሳም አጋትሬ ኦኩንዚ ይገኙበታል።

ከወራት በፊት በዩጋንዳ ምድር እስከ መስከረም ወር 600ሺ የኮቪድ ተጠቂዎች እና 30 ሺ ሞት ይከሰታል የሚል ግምት መሰጠቱን የሚያስታወሱት ዶክተሩ፣ ይህ ግምት ግን በአሁን ወቅት ሙሉ በሙሉ በሚባል መልኩ ስህተት ሆኖ መገኘቱን አስረድተዋል። እንደ ጆን ሆፕኪንስ ዪኒቨርሲቲ መረጃ ከሆነም በአሁን ወቅት ዩጋንዳ 8ሺ በላይ ዜጎች የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሲሆን የሟቾች ቁጥር ደግሞ 75 ብቻ ነው።

በወረርሽኙ ጅማሬ በርካታ የአህጉሪቱ አገራት የጤና መሰረተ ልማት ደካም የሚባል ነበር። ይሁን እና አህጉሪቱ እስካሁን በኮቪድ ቫይረስ ተጠቂ የሆኑ ዜጎች ቁጥር 1ነጥብ4 ሚሊየን ፤ የሟቾች ቁጥር ደግሞ 35 ሺ በላይ ነው። ቫይረሱ አለባቸው ከሚባሉት ዜጎች መካከል 670 ሺ የሚሆኑት ደቡብ አፍሪካ ውስጥ ናቸው። በወረርሽኙ ጅምሬ የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ማድረግ የሚያስችል አቅም ያላቸው ሁለት አገራት ብቻ ነበሩ። አሁን ግን ሁሉም አገራት የኮሮና ቫይረስ ምርመራን በራስ አቅም ማድረግ ችለዋል።

ከዚህ በአንጻሩ 330 ሚሊየን ህዝብ እንዳላት በሚገመተው ዩናይትድ እስቴትስ 7 ሚሊየን ዜጎች የኮሮና ተጠቂ ሆነዋል። 204 ሺ በላይ ዜጎች ሕይወታቸው ሲነጠቁ 4 ነጥብ 5 ሚሊየን የሚሆኑት ደግሞ ከቫይረሱ ማገገም

ችለዋል።በተለይ በዩናይትድ እስቴትስ እና በአፍሪካ መካከል

ያለው የአሃዝ ልዩነት ከማስገረም አልፎ በርካቶች ምክንያቱ ምን ይሆን እንዲሉ እና ምላሽ ለማድረግ እንዲማትሩ እያደረጋቸው ይገኛል። ዘ ግሪዩ [TheGrio] የተሰኘው የአሜሪካ የዜና እና የመዝናኛ ዌብሳይት ላይ ሰፊ ሀተታውን ያሰፈረው ማቲው አለንም፣ ምእራባውያኑ የጥናት ባለሙያዎች በሌሎች አህጉራት በተለየ አፍሪካን ወረርሽኙ ለምን አልደቆሳትም በሚል ግርምት በጉዳዩ ላይ ምርምር በማድረግ መጠመዳቸውን አስነብቧል።

የኤደንበርግ ዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰር ፍራንሲስካ ሙታፒ ፣ ወረርሽኙ አፍሪካ ላይ ለምን አቅም አነሰው በሚል ከተመራመሩት አንዱ ናቸው። ዚምባቤውን ላይ ትኩረት በማድረግ የመከላከል አቅም ልዩነት እና ደረጃ ለማጥናት ደፋ ቀና ያሉት ፕሮፌሰሩ፣ ደረስንበት ባሉት መረጃ መሰረት‹‹በርካታ የአፍሪካ ህዝብ ከከተማ ይልቅ ገጠር ውስጥ መኖሩ እና አብዛኛው ጊዜውን ከቤት አሊያም ከቅጥር ግቢ ውስጥ የማይወጣ መሆኑ ቫይረሱ እንደ ልብ እንዳይስፋፋ አድርጎታል››ብለዋል።

በአፍሪካ በኮቪድ-19 የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በአማካይ እየቀነሰ ለመምጣቱም ባለሙያዎቹ በምክንያትነት ከጠቀሷቸው መካከል የአህጉሪቷ ነዋሪዎች ወጣት መሆናቸው ነው። ቫይረሱ በአለም አቀፍ ደረጃ የከፋ ጉዳት ያስከተለው እና መራር ቅጣቱን ያሳረፈው ደግሞ እድሚያቸው የገፋ አዛውንቶች ላይ ነው።

ይህ ዋቢ የሚያደርጉት ፕሮፌሰር ፍራንሲስካ ሙታፒም፣ በአብዛኞቹ የአፍሪካ አገራት እድሜያቸው ከ 65 አመት በላይ የሆኑ ዜጎች ቁጥር ከሶስት በመቶ የማይበልጥ መሆኑ አፍሪካ በቫይረሱ ምክንያት በርካቶችን ከመቅበር እንደገላገላት አብራርተዋል።

ኮቪድ 19ኝን ለመከላከል ተግባራዊ የተደረጉ የእንቅስቃሴ ገደቦች ምንም እንኳን የአህጉሪቱን ኢኮኖሚ ቢያንገጫግጩም የዜጎችን ሕይወት በመታደግ ረገድ ግን ተጨባጭ ለውጥና አስተዋፆኦ ማበርከታቸውንና ገደቦች ባይተገበሩ የተጠቂዎችም ሆነ የሟቾች ቁጥር ከዚህም ይልቅ እንደነበር ተመላክታል።

በርካታ የመገናኛ ብዙኃን እና የጤና ዘርፍ ምሁራንም ዩናይትድ እስቴትስ እና አፍሪካን ሚዛን ላይ አስቀምጠው አፍሪካ ከፍ ብላ መታየቱ እያስደነቃቸው ይገኛል። በዚህ ረገድ ሰፊ ሀተታን ዋሽንግተን ፖስት ላይ ያሰፈረችው ኬረን አቲሃ፣ ደካማ የጤና መሰረተ ልማት፣ ስር የሰደደ ሙስና እና ድህነት እንዲሁም የመንግስታት ውጤታማ የውሳኔ አሰጣጥ ድክመት አፍሪካ በቫይረሱ ይበልጥ እንድትቆስል ሊያደርጋት ይችላል ሲባል መቆየቱን ታስታውሳለች።

አለምም አፍሪካን ከማይቀረው አስከፊ ቀውስ ለመታደግ ካልተቻለም በቶሎ እንድታገግም ለማድረግ ለመንግስታት ብድር እና የብድር እፎይታን ጨምሮ የተለያዩ ድጋፎችን ለመስጠት ሲውተረተሩ መቆየቱን የምታስታውሰው ፀሃፊዋ፣ ‹‹ይሁንና እያደር አፍሪካ ምድር ላይ የተስተዋለው

እንደተፈራው አልሆነም››ትላለች። ምስጋና ለመንግስታት ውጤታማ ውሳኔ ፣ በጠንካራ የጤና ባለሙያዎች ጥረት እና በህዝቡ ተባባሪነት አፍሪካ አስቀድሞ ከተገመተባት አስከፊው የኮቪድ ቅጣት እያመለጠች መሆኗን አትታለች።

ለዚህ ደግሞ በተለይ በርካታዎች የምእራብ አፍሪካ አገራት የኢቮላ ወረርሽን ቀውስን ለመሻገር ሲተገብሩት የቆዩትን ዘዴዎችን ከክስተቱ ያካበቱን ልምድ እና አቅም በኮቪድ 19ኝን ወረርሽን ለመከላከል እና ለመቆጥጠር እንዳይቸገሩ እና አፈፃፀማቸውም ስኬታማ እንዲሆን አብይ ምክንያት መሆኑን አስታውቃለች ።

በአሁን ወቅት ዩናይትድ እስቴትስ በሟቾች ቁጥር አለምን እየመራች አፍሪካ በአንፃሩ ወረርሽኙን በመከላከል እና በመቆጣጠር ረገድ ስኬታማ ስራ በመስራት ላይ ስለመሆኗ ያተተችው ፀሃፊዋ፣ ‹‹ይህ የአፍሪካ ስኬት ሊጨበጨብለት የሚገባው ቢሆንም ምዕራባውያን ግን ይህን ለማድረግ ሲተናነቃቸው ለማድነቅም አይናቸው ታውሯል›› ብላለች።

የአሾሽየትድ ፕሬስ ፀሃፊዋ ካራ አናም/ Cara Anna/እንደ ዩናይትድ እስቴትስ ያሉ ሃያላን አገራት የኮሮና ቫይረስን ቀውስ ለማቋቋም ተቸግረው ሲብረከረኩ በሚስተዋልበት በዚህ ወቅት አፍሪካ በአንፃሩ በአመዛኙ ቀጥ ብላ መቆሟ የሚያስደንቃት ነው ብላለች።

የአፍሪካ የበሽታዎች መከላከያ መቆጣጠሪያ ማእከል ዳይሬክተር ጆን ንኬንጋሶንግ (ዶ/ር) የአፍሪካ አገራት በአንፃሩ ለወረርሽኙ የሰጡት ምላሽ ዩናይትድ እስቴትስን ጨምሮ ሃብታም ነን ከሚባሉ አገራት ሳይቀር የተሻለ ውጤታማ መሆኑን ይመሰክራሉ።

‹‹አፍሪካ ሌላው አለም ማድረግ እና ማሳካት ያልቻለውን በርካታ ተግባራትን ፈፅማለች››ያሉት የአሜሪካ መንግስት ዓለም አቀፍ የልማት ኤጀንሲ (ዩኤስኤአይዲ) የቀድሞ ባልደረባ ጌየል ስሚዝ,፣አለምን ትመራለች የምትባለው ዋሽንግተን አቅም አንሷት በየአቅጣጫው ስትማስን አፍሪካ ግን ሊነገር እና ሊታወቅ የሚገባ ስኬታማ ታሪክ መፃፋን አድንቃለች።

አናዶሉ ኤጀንሲ፣ አለም አቀፉ የጤና ድርጅት ለአፍሪካ ያለውን አድናቆት መግለፁን አስነብቧል።በአለም አቀፉ የጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጠና ዳይሬክተር ዶክተር ማቲሺዲሶ ሞይቲ፣አፍሪካ አገራት በርካቶች የፈሩትን የኮቪድ ቫይረስ ቀውስ በመቆጣጠር ረገድ ስኬታማ ስራ መስራታቸውን መስክረዋል።

የወረርሽኙ ስርጭት ሲጀመር በርካታ አገራት መንግስታት እንቅስቃሴን እና አንድ ላይ መሰብሰብን ጨምሮ የተለያዩ ክልከላዎችን ይፋ ማድረጋቸው ወረርሽኙ እንደፈለገ እንዳይሆን የተጠቂዎች ቁጥሩ እንዲቀነስ ማድረጉን ብሎም የጤና ማዕከላትን የስራ ጫና በማቃለል ረገድ ጉልህ ሚና ማበርከቱን አስረድተዋል። ለውጤቱ መገኘት መንግስታትን ብቻ ሳይሆን ማህበረሰቡ እና አጋር አካላት አመስግነዋል።

በአሁን ወቅት በርካታ የመገናኛ ብዙኃን እና ምሁራን የአፍሪካውያን ስኬት ሊደነቅ የሚገባው መሆኑን

በማስገንዘብ ላይ ቢሆኑም አንዳንዶች በአንፃሩ ስኬቱን ከማሞካሸት ይልቅ ድክመቶች ማጉላት ላይ ያማተረ አቋም አንፀባርቀዋል።

‹‹የምርመራ አቅም ተደራሽነት ደካማ መሆንም አፍሪካ ቫይረሱን በመቆጣጠር ሂደት ስኬታማ ነኝ እንዳትል ያደርጋታልም››ብለዋል።ለዚህ መልስ የሚሰጡት በአንፃሩ‹‹የምርመራ ተደራሽነት ውስንነት እንዳለ ሆኖ የሞት ምጣኔ ከፍተኛ ሆኖ አለመታየቱ ቫይረሱን አቅም የማሳጣት ስራው ውጤታማነት ምስክር ነው›› ብለዋል።

በእርግጥ ሁሉም የአፍሪካ አገራት ተመሳሳይ ስኬት አስመዝግበዋል ማለት አይደለም። አብዛኞቹ አገራት ወረርሽኙን በመከላከል ሂደት የሚያስጨበጭብ ውጤትን ማቀዳጀት ቢችሉም አንዳንዶቹ በአንፃሩ ወደ ኃላ ቀርተው ታይተዋል። በአፍሪካ ምድር የኢኮኖሚ ከፍታ ማሳያ የሆነችው ደቡብ አፍሪካም ኮሮናን በመከላከል ሂደት ደካማ ከተባሉ አገራት አንዷ ናት።

ደቡብ አፍሪካ በአሁን ወቅት በኮሮና ቫይረስ ስርጭት በአፍሪካ ቀዳሚ ነች። 650 ሺህ በላይ ሰዎች በቫይረሱ ተጠቅተዋል። 15 ሺህ ዜጎችም ሕይወታቸውን አጥተዋል። አገሪቱ ከአሜሪካ፣ ብራዚል፣ ሩሲያና ህንድ ቀጥሎ በቫይረሱ በተያዙ ሰዎች ቁጥር ከአለም አምስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች።

የተለያዩ መገኛኛ ብዙሃን፣ የምጣኔ ሃብት እና የፖለቲካ ምሁራንም የኮሮና ቫይረስ በደቡብ አፍሪካ ምድር ከጤና ማሳጣት ቅጣት ባሻገር ያስከተከተለው የኢኮኖሚ ቀውስ እጅግ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ስለመድረሱ በመወትወት ላይ ናቸው።

በአለም አቀፉ የጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጠና ዳይሬክተር ዶክተር ማቲሺዲሶ ሞይቲ፣ ይህ በአገራት መካከል ያለው ልዩነት የአህጉሪቱን ስኬት ሙሉ እንደማያደርገው አፀዕኖት ሰጥተውታል። አገራትም የመከላከል እና የመቆጣጠር ፍልሚያቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ እንዲሁም መረጃዎች በየጊዜው ይፋ እንዲያደርጉ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

አፍሪካው ኮቪድ 19ኝን ከመከላከል እና ከመቆጣጠር ባሻገር ለወረርሽኙ ፍቱን መፍትሄ ለመስጠት የሚያስችሉ ክትባቶችንም ታሳቢ ማድረግ እንዳለባት የሚያስገንዝቡም ቁጥራቸው ቀላል አይደለም። አፍሪካውያን ክትባቱን ማግኘት ቢቸገሩ እንኳን በክትባቱ ስርጭት ሂደት የጋራ አቋም መያዝ እና የቀሪው አለም ጥገኛ የሚያደርጋቸው ሳይሆን በፍትሃዊነት ተደራሽ ሊሆን የሚችሉበትን አግባብ መፍጠር ግድ ይላቸዋል›› ተብሏል።

በጉዳዩ ላይ ሰፊ ዘገባዎችን በመስራት ላይ የሚገኙ መገናኛ ብዙሃንም ሆነ የተለያዩ አስተያየቶችን በማጋራት ላይ የሚገኙ ምሁራን ከችግሩ አሳሳቢነትን ከሚያስከትለው ሁለንተናዊ ጥፋት አንፃር በተገኘው ስኬት ከመኩራራት ይልቅ በተለይ ፍቱን መድሃኒት እስኪገኝ ህብረተሰቡ የራሱን ጥንቃቄ አድርጎ ሕይወቱን ማቆየት እንዳለበት አፅዕኖት ሰጥተውታል።

Page 14: “ለራሱ ኩራት ለአካባቢው አገሮች ደግሞ የብቃት ......ገጽ 2 አዲስ ዘመን ሐሙስ መስከረም 21 ቀን 2013 ዓ.ም ዜና አዲስ አበባ፦

በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ታተመ

መስከረም 21 ቀን 2013 ዓ.ምገጽ 36

አዲስ ዘመንስፖርትሐሙ

ይህ ቦታለማስታወቂያ

ክፍት ነው

በበዛብህ ገብረየስ በየነ

(ክፍል 2)የመንግስት አገልግሎት ዘርፍ ፍኖተ-ካርታ

ከላይ የተመለከቱትን ንድፈ ሀሳባዊ መነሻዎች እንደ አስፈላጊነቱ በሚጠቅሙበት ቦታ አጣምሮ ወይም ተነጣጥሎ በመጠቀምና ሀሳቦቹን የተሻሉ ከሚባሉት ከአለም አቀፋዊ ተሞክሮዎችና ልምዶች፣ እንዲሁም ከቀደምት ሀገራዊ እውቀቶችና ወረቶች ጋር አዋዶ ለመጠቀም የተቀረጸ ነው።መዳረሻ ግቡም የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራትን ማረጋገጥ፣ የመንግስት አስተዳደር ሥርዓቱን ሀያ አንደኛውን ክፍለ ዘመን የሚመጥን ማድረግ፣ በሁሉም የእድገት መለኪያ መስፈርቶች ሀገራዊ እሴትን (ቁሳዊና ቁሳዊ ያልሆነ) ማሳደግ እና በስራ አመራር ስልቱ የመንግስት ስራ ከፖለቲካ ፓርቲ አሰራር ጋር የማይደበላለቅበት፣ ነገር ግን ሁለቱም ተሰናስነው የዜጎች እርካታ ማረጋገጥ የሚቻልበት እንዲሆን ማስቻል ነው።ፍኖተ ካርታው አራት ዋና ዋና የትኩረት መስኮችን አካቶአል፡።

የመጀመሪያው የትኩረት መስክ ነጻ፣ ገለልተኛና ብቃት ያለው አገልጋይ፣ ሰውና ተቋም የመገንባት ሂደትና ቁቦቹ የተብራራበት ነው።ሁለተኛው የትኩረት መስክ ደግሞ ከቀድሞው ሰዎችን በክፍል ውስጥ ኮልኩሎ በማሰልጠን/በማስተማር ላይ ትኩረት አድርጎ የሚሰራበትን የሰው ሀብት የማልማት ስልት ከክህሎት ክፍተት ልየታ ተነስቶና በብቃት ማረጋገጫ ማእቀፍ ታግዞ አቅም ወደሚገነባበት ወይም ሰራተኞች የሚመደቡበትን

ከኢፌዴሪ የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ጋር በመተባበር

ዘወትር ሐሙስ በየሳምንቱ የሚቀርብ

ስራ በሚገባ “መፈጸምና ውጤት ማምጣት መቻላቸው” ወደሚረጋገጥበት አሰራር መለወጥ ላይ ትኩረት አድርጎ ለመስራት ያለመ ነው።

ሦስተኛው የለውጥ አጀንዳ “የእሴት ግንባታና ስነምግባር”ን የሚመለከት ሲሆን፣ ቀደም ሲል በመድረኮች፣ በብዙኃን መገናኛዎች በሚተላለፉ ትምህርቶችና ማስታወቂያዎች፣ በትምህርት ቤቶች በሚሰጥ ትምህርት እና በሃይማኖት ተቋማት አማካይነት የሚካሄዱ ስብከቶች/ አስተምህሮዎች የሰራተኞችን ስነምግባር ለማረቅ፣ ከዚያም አልፎ ሲገኝ በሕጎች ግዴታዎችን በመጣል ለማስገደድ የተሞከረባቸውን አሰራሮች ለማጠናከር በሰዎች ላይ እሴቶችን ወደ መገንባት በመለወጥ የሚሰራ ነው።የእሴት ግንባታ ሂደቱ መነሻ ለሰራተኞች ተለይቶ የሚሰጥ ስራና ከሚጠበቀው ውጤት ጋር ስነምግባራዊ ፋይዳ ያላቸውን እሴቶች ተላብሰው እንዲገኙ ቅድመ ሁኔታዎችን በምልመላ፣ መረጣና ስምሪት ወቅት በመስፈርትነት ማካተት ነው።አዲስ ሰራተኞች ወደ መንግስት ስራ ከመግባታቸው በፊት ስራው የሚፈልገውን እሴት እንዲላበሱ ለማድረግ ቅድመ-ስምሪት ፍተሻ አካሂዶ ክፍተቶችን መሙላት፣ ከዚህ ሥርዓት በፊት በስራ ላይ ለቆዩትም ቢሆን በአዳዲሶቹ የስራ ሂደቶች ውስጥ የሚገነቡትን እሴቶች ቀርጾ እንዲላበሷቸው አድርጎ ማሰማራት የአዲሱ ስርዓት መለያ ይሆናል።የፍኖተ-ካርታው የመጨረሻው ትኩረት ደግሞ ከላይ የተዘረዘሩት ድምር ውጤት ለዜጎች በሚቀርበው ውጤት ላይ የሚያርፍበትን አመክንዮ ታሳቢ አድርጎ የተቀረጸ ሲሆን፣ በለውጥ መርሀ-ግብሮቹ

ይዘት የመንግስትን የአገልግሎት አሰጣጥ ማሻሻያ ግብ በበይነመረብ ወደሚቀርብበት ደረጃ ማድረስን ታሳቢ አጉልቶ፣ በመጀመሪያዎቹ የትግበራ አመታት ምቹ መደላደል የሚፈጠርበት ይሆናል፡፡

በመንግሥት አገልግሎት ዘርፍ ፍኖተ-ካርታ የተመለከቱ የለውጥ አጀንዳዎች እንደማንኛውም በመንግስት አገልግሎት ዘርፍ የሚካሄዱ ለውጦች በርካታ መሰናክሎችና ፈተናዎችም ሊያጋጥሟቸው ይችላል።ከእነዚህም መካከል የለውጡ መሪዎችና ፈጻሚዎችም ለመንግስት ስራ ፖለቲካዊ ገጽታ የሚሰጡት ትኩረት አናሳ መሆን ይገኝበታል። በሌላ በኩል በሌሎች አገራት ተሞክሮ ውጤት ያስገኘን ሀሳብ ሀገራዊ ነባራዊ ሁኔታዎች ሳያገናዝቡና ይዘታቸውም ሳይፈትሽ እንደመጡ ወደ ትግበራ ማስገባትም ሊጤን የሚገባው ተገማች ሳንካ ነው።ከለውጥ ሀሳቦች በተጨማሪም በሌሎች ሀገራት የተሰራባቸው ወይም እየተሰራባቸው ያሉ አደረጃጀቶችን ከራስ ተጨባጭ ሁኔታ ጋር ሳያዛመዱ እንዳሉ ከመቅዳትም መታቀብ ሊታሰብበት የሚገባ ጉዳይ ነው።በለውጥ ሰበብ ሰራተኞችን በጅምላ ከስራ ማሰናበትና የስራ ዋስትና ማሳጣትም በዘርፉ የሚካሄዱ ለውጦችን ሕዝባዊ መሰረት ከሚያሳጡና እንዲጠላ ከሚያደርጉ መሰናክሎች ውስጥ ይመደባሉ።የለውጥ አጀንዳዎችን ከሰፊው የፖሊሲና ተቋማዊ ማእቀፍ ጋር አለማስተሳሰርና በተገቢ የሰው ሀብትና የገንዘብ በጀት ደግፎ ከማስቀጠል ይልቅ የወጪ ቅነሳ አሰራርን አጋኖ የመውሰድ አደጋዎችንም በተገቢ መመከት መቻል ለለውጡ ስኬት ወሳኝ እርምጃ ነው።ከሁሉም በላይ

በዚህ ፍኖተ-ካርታ የታቀደው የመንግስት አገልግሎት ዘርፍ ለውጥ ለሀገራችን አዲስ እንደመሆኑ መጠን በውጥን እንዳይቀርና ከትግበራ በኋላም ፈጥኖ ወደኋላ እንዳይመለስ ራሱን በቻለ ህግ መመራት እንዳለበት ማጤን ጠቃሚ ነው።ለዚህም የለውጥ አስተዳደር ዘዴዎች እንደየለውጦቹ ዓይነት የተለያዩ መሆናቸውን ከግምት ያስገባ የለውጥ አስተዳደር ዘይቤን ተከትሎ መምራት ተገቢነት ይሆናል።

በአብዛኛው የመስኩ ተመራማሪዎች ስምምነት የተደረሰበት ለስኬት የሚያበቃ የለውጥ አስተዳደር ሞዴል የለውጡን ትግበራ ሂደት ማቀድ፣ የለውጡን መሪ ተዋናዮች፣ ባለድርሻ አካላት እና አስተዳዳሪዎች ለይቶ ማዋቀርና ሚናቸውን ማሳወቅ፣ ቁርጠኛ የለውጥ መሪ/አመራር መመደብ፣ ያልተቋረጠና አካታች የሆነ የአሕዝቦትና ተግባቦት ሥርዓት ዘርግቶ መተግበር እና ለውጡን በፌዴራል፣ በክልሎችና በከተማ አስተዳደሮች ሥር ባሉት የመንግሥት አስፈጸሚ አካላት ቅንጅታዊ አተገባበር መምራትን ያካትታል።

በአጠቃላይ የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን የዘርፉን ለውጥ እውን ለማድረግ በደንብ ቁጥር 1097/2011 አንቀጽ 32 (1) በተሰጠው ተግባርና ኃላፊነት መሰረትና ያለውን የሙያ ነጻነት ተጠቅሞ አበርክቶውን ለማጎልበት በሙሉ አቅሙ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል።በዚህ የለውጥ ጉዞ ማህበረሰቡ፣ የሙያ ማህበራት፣ የመንግሥት ሰራተኞችን፣ የመንግሥትና የግል አማካሪና አቅም ገንቢ አካላት በሙሉ ትብብር እንዲያደርጉለት አገራዊ ጥሪውን ያቀርባል።

የመንግሥት አገልግሎት ዘርፍ ለውጥ ዳና እና ፋይዳዎች

ቦጋለ አበበ

ለወራት አሰልጣኝ አልባ የነበረው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን(ዋልያዎቹ) ከበርካታ ቀናት ንትርክ በኋላ አዲስ አሰልጣኝ አግኝተዋል። ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ ቀናት ብሔራዊ ቡድኑን በዋና አሰልጣኝነት ለመምራት የተሰየሙት አሰልጣኝ ውበቱ አባተ በትናንትናው እለት ለአርባ ተጫዋቾች ጥሪ በማድረግ ስራቸውን በይፋ ጀምረዋል። አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ምክትል አሰልጣኞቻቸውን ይፋ ሲያደርጉም አንዋር ያሲንና አስራት አባተን ምርጫቸው አድርገዋል። ደሳለኝ ገብረጊዮርጊስም የግብ ጠባቂ አሰልጣኝ ሆኖ አብሯቸው እንደሚሰራ ታውቋል።

ዋልያዎቹ በቅርቡ ለሚኖርባቸው የአፍሪካ ዋንጫና የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዎች አሰልጣኝ ውበቱ ጥሪ ካደረጉላቸው ተጫዋቾች መካከል በአሰልጣኝ አብርሃም መብራቱና ከዚያ በፊት በነበሩ አሰልጣኞች ስር ሆነው ቡድኑን ሲያገለግሉ የቆዩ በርካታ ተጫዋቾች የተካተቱ ሲሆን አዳዲስ ተጨዋቾችን እንዳካተቱም ጥሪ ከተደረገላቸው ተጫዋቾች ስም ዝርዝር ማረጋገጥ ተችሏል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ቀጣይ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታውን ለማድረግ የአንድ ወር ጊዜ ብቻ ቀርቶታል። ለ2021 የካሜሩን አፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ ዋልያዎቹ በአሰልጣኝ አብርሃም መብራቱ መሪነት ሁለት ጨዋታዎችን አድርገው በአንዱ(በማዳጋስካር 1ለ0) ሽንፈት የገጠማቸው ሲሆን በሁለተኛው ጨዋታ የምድቡን ጠንካራ ተፎካካሪ ኮትዲቯርን በባህርዳር ስታድየም አስተናግደው 2ለ1 መርታታቸው ይታወሳል።

ዋልያዎቹ በሚገኙበት የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ

አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ለዋልያዎቹ ጥሪ አደረጉ

አሁን ላይ ማዳጋስካር በ2 ጨዋታ፣ በ6 ነጥብና በ5 ንፁህ ግብ ምድቡን ትመራለች። ኢትዮጵያ በ2 ጨዋታ፣ በ3 ነጥብና በ0 ግብ ሁለተኛ ስትሆን ኮትዲቯር ከዋልያዎቹ ጋር በተመሳሳይ ነጥብና የግብ ልዩነት ትቀመጣለች። ኒጀር በ2 ጨዋታ በ0 ነጥብና በ5 የግብ ዕዳ መጨረሻ ላይ ትገኛለች። ይህ ዋልያዎቹን ከስምንት ዓመታት በኋላ በአፍሪካ ዋንጫ ለመመልከት ካለፉት ጥቂት ዓመታት የተሻለ እድል እንደሆነ የሚናገሩ የስፖርት ቤተሰቦች አዲሱ አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ይህን እድል ለመጠቀም በአጭር ጊዜ የሚያዋቅሩት ቡድን ጥንካሬ ወሳኝ እንደሚሆን ይጠበቃል። ቀጣይ የማጣሪያ ጨዋታዎች ከበርካታ ወራት በኋላ በቀጣዩ ወር የሚጀምሩ ሲሆን ዋልያዎቹ በቀጣይ ከኒጀር ብሔራዊ ቡድን ጋር የደርሶ መልስ ጨዋታ ያደርጋሉ። ዋልያዎቹ በሜዳቸው የገነደሱት

የምድቡ ኃያል ቡድን ኮትዲቯር ጋር የሚያደርጉት የመልስ ጨዋታ የማጣሪያው የመጨረሻ ጨዋታ ሲሆን ዝሆኖቹን ከመግጠማቸው አስቀድመው ከኒጀር ጋር ከሚያደርጉት የደርሶ መልስ ጨዋታ በተጨማሪ ማዳጋስካርን በሜዳቸው ይገጥማሉ።

በሜዳዋ ሁለት ሽንፈቶችን ከቀመሰችውና የምድቡ ደካማ ቡድን ከያዘችው ኒጀር ጋር በሚኖሩት የደርሶ መልስ ጨዋታዎች ዋልያዎቹ ቢያንስ አራት ነጥብ ማግኘት ከባድ እንደማይሆንባቸው ይጠበቃል። ዋልያዎቹ ኒጀርን በሜዳዋ ገጥመው አንድ ነጥብ ይዘው ከተመለሱ በሜዳቸው ሦስት ነጥብ መሰብሰብ ይሳናቸዋል ተብሎ አይጠበቅም። ቀጣይ ተጋጣሚ ማዳጋስካር እንደመሆኗ ከዚህ ጨዋታም ቀላል ባይሆንም ሦስት ነጥብ የማግኘት እድል ሊኖራቸው ይችላል። ማዳጋስካርን በመጀመሪያው የማጣሪያ ጨዋታ በሜዳዋ

1ለ0 ማሸነፏ የሚታወስ ቢሆንም ከሜዳዋ ውጪ ያን ያህል ከባድ ተጋጣሚ እንደማትሆን ይታመናል። ይህን ስሌት ዋልያዎቹ ማሳካት ከቻሉ የመጨረሻውን ማጣሪያ ከሜዳቸው ውጪ በኮትዲቯር ቢሸነፉ እንኳን ወደ ካሜሩን የሚወስዳቸውን ትኬት ለመቁረጥ እድላቸው ጠባብ እንደማይሆን ይታመናል። በዚህ ስሌት መሰረት ነገሮች ሊጓዙ የማይችሉበት አጋጣሚ እንዳለ ሁሉ እንደ ኮትዲቯሩ ጨዋታ ያልተጠበቁ ድሎች ሊመዘገቡ እንደሚችሉም ከግምት ማስገባት ይቻላል። ይህም ለዋልያዎቹ ቀጣይ የአፍሪካ ዋንጫ ጉዞ ትልቅ የስነ ልቦና ስንቅ ሆኖ ያገለግላቸዋል። ይህን ተስፋ እንዳይከስም ግን የወዳጅነት ጨዋታዎችን ጉዳይ ባለችው አጭር ጊዜም ቢሆን ከወዲሁ አጥብቆ መያዝ ለነገ የሚባል የቤት ስራ ይሆናል።

አሰልጣኝ ውበቱ አሁን ላይ ከሰበታ ከተማ ጋር ቀሪ የአንድ ዓመት ውል ያላቸው ቢሆንም የቀረበላቸውን አገራዊ ጥሪ ተቀብለው ወደ ስራ ገብተዋል። አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ከአገር ውጪ በሱዳን አልሃሊ ሼንዲን፣ በአገር ውስጥ ደደቢትን ፣ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን፣ ኢትዮጵያ ቡናንና ፋሲል ከነማን፣ ሃዋሳ ከነማን እንዲሁም ሰበታ ከነማን አሰልጥነዋል። በተለይም በ2003 ኢትዮጵያ ቡናን ለመጀመሪያ ግዜ የፕርሚየር ሊግ ዋንጫ እንዲያነሳ ያደረጉ ሲሆን ሃዋሳ ከነማን እንዲሁም ፋሲል ከነማን አሰልጥነው ብርቱ ተፎካካሪ እንዲሆኑ እንዲሁም ለተመልካች ሳቢ የሆነ እግር ኳስ እንዲጫወቱ አድርገዋል። በተለይም ፋሲል ከነማ የጥሎ ማለፍ ዋንጫን አሸንፎ በታሪኩ ለመጀመሪያ ግዜ በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ካፕ እንዲሳተፍ ኃላፊነታቸውን መወጣታቸው አይዘነጋም።

ዋልያዎቹ በቀጣዩ ወር ከኒጀር ጋር ለሚያደርጉት የደርሶ መልስ ጨዋታ በቅርቡ ዝግጅት እንደሚጀምሩ ይጠበቃል፣