ማርከሻ ለ የሞት መርፌ -...

60
ደጃዝማች አብቹ ማርከሻ -የሞት መርፌ 0 ማርከሻ - የሞት መርፌ ከደጃዝማች አብቹ 2005

Upload: buidiep

Post on 15-Feb-2018

339 views

Category:

Documents


52 download

TRANSCRIPT

Page 1: ማርከሻ ለ የሞት መርፌ - api.ning.comapi.ning.com/files/poTC6m2b82rkMz38uXDa*sLOeRr2Zc*dkAn32... · ውስጥ እያለ ‘’ የቡርቃ ዝምታ’’ በሚል

ደጃዝማች አብቹ ማርከሻ ለ-የሞት መርፌ

0

ማርከሻ

ለ-

የሞት መርፌ

ከደጃዝማች አብቹ

2005

Page 2: ማርከሻ ለ የሞት መርፌ - api.ning.comapi.ning.com/files/poTC6m2b82rkMz38uXDa*sLOeRr2Zc*dkAn32... · ውስጥ እያለ ‘’ የቡርቃ ዝምታ’’ በሚል

ደጃዝማች አብቹ ማርከሻ ለ-የሞት መርፌ

1

ምስጋና

ከሁሉም አስቀድሜ ተንኮልና መሰሪነትን ለጊዜው ቢታገስም ከናካቴው ተሰውሮ

እንዳይቀር በማድረግ ለሚሰራው ፈጣሪ ቀዳሚው ምስጋናዬ ይግባው!! በመቀጠልም

በኢትዮጵያ ላይ ስውር መጋዝ ሁኖ የሚገዘግዛትን ደመኛ በትልቅ ትጋት ተከታትለህና

አስተማማኝ መረጃዎች ከጉያው ፈልቅቀህ ወስደኸ የሻአብያን የሚስጥር ስራ

ለአደባባይ ያበቃኸውን ትንታጉን አለማየሁ መሰለን ደግሞ ለብሄራዊ ጀግና የሚሆን

የምስጋና ሽልማቴን ላቀርብልህ እወዳለሁ። ማንም ሊረዳ እንደሚችለው የህይወት

ወጋ ሊያስከፍልህ እንደሚችል ሁሉ የምትረዳ ቢሆንም በህይወትህ ተወራርደህ

ለሃገርህ ውለታ ውለህላታልና ለኔ ብሄራዊ ጀግና ነህ።

ዳኛ ወልደሚካኤልም ትልቁን ጉድ ጽፈው ሎሚ መጽሄት ላይ እንድናነብ ስላደረጉንና

ከተስፋዬ ለጣቂውን ሃላፊነት ስለወሰዱ፣ ሎሚ መጽሄትም ይህን አገራዊ ፋይዳ ያለው

ጽሁፍ ለንባብ በማብቃት ለዋለችው ውለታ ላቅ ያለ ምስጋናዬን ላቀርብ እገደዳለሁ።

የእናንተ ሁሉ በጎ ጥረት ተስፋዬ ገ/አብን ጥርጣሬ ፈንጣቂ ከሆኑ ምክኒያቶች አልፌ

በማሰረጃ በተደገፈ ሰላይነት እና የኢትዮጵያ ጠላትነት እንዳውቀው በማድረግ ለአገሬ

እና ለህዝቤ እንድቆጭ እርሱም ለሚረጨው መርዝ ምክኒያታዊ ማርከሻ እንድሻ

አገዘችሁኝ።

Page 3: ማርከሻ ለ የሞት መርፌ - api.ning.comapi.ning.com/files/poTC6m2b82rkMz38uXDa*sLOeRr2Zc*dkAn32... · ውስጥ እያለ ‘’ የቡርቃ ዝምታ’’ በሚል

ደጃዝማች አብቹ ማርከሻ ለ-የሞት መርፌ

2

ማውጫ

መግቢያ 3

ቅድመ ነገር 6

የሰላዩ ማስታወሻ 9

እንጥፍጣፊ ነገር/ያለቀበት 11

ጀጎልም አንዲያድም 11

ቀልድ ወደ ደም 15

ተረኞቹ ተጋጭዎች 17

አብቹ ነጋ ነጋ 20

የበጋው መብረቅ ጃጋማ ኬሎ 23

ዘር ማጥራት 26

ሆድ ማስባሻ 28

ህልመ ሻአብያ- የምስራቅ አፍሪቃ ቅርጫ 34

ተስፋዬና ቡርቃ 37

ልጆች ጠብ ወራሾች- የኦሮማይዋ ፊያሜታ ግላይ 39

ማብቂያ የሌለው ተሸማቃቂ 40

ፈረንጅ ቅኝ በገዛን 43

መደምደሚያና አዲሱ ግብረ ተስፋዬ 47

አቻ ግብረ ተስፈዬ/ ዳንኤል ግዛው 47

የድግሱ ሳህን 47

የዳንኤል ግዛው የሞት ቅመሞች 48

ያፋለሱት ታሪክ 49

ሙት የውሰጥ ህሊና/ ፍርደገምድል 51

ተስፋዬና መዝሙር 53

ደቂቅ ክቡር ተስፈዬ¡¡ 54

ማጠቃለያ 56

ዋቤ መጽሃፍት 58

Bibliography 59

Page 4: ማርከሻ ለ የሞት መርፌ - api.ning.comapi.ning.com/files/poTC6m2b82rkMz38uXDa*sLOeRr2Zc*dkAn32... · ውስጥ እያለ ‘’ የቡርቃ ዝምታ’’ በሚል

ደጃዝማች አብቹ ማርከሻ ለ-የሞት መርፌ

3

መግቢያ

እንዲህ ያለ ጽሁፍ እጽፋለሁ ብዬ አስቤ አላውቅም። ለዚህ አስቀድሞ ያነሳሱኝ

በተስፋዬ ገ/አብ ብልጣብልጥ አቀራረብ የተታለሉ ወገኖቼ በየድህረ ገጾቻቸው አሁን

ቅርብ ጊዜ በኢንተርኔት የለቀቀውን ‘’የስደተኛ ማሰታወሻ’’ የሚል መጽሃፉን

እንድናነብለት በአዳናቂ ቃላት እያንኳሹ ሲጋብዙን ማየቴ ባበሸቀኝ ብሽቀት የተነሳ

ለእነሱ የማንቂያ ደወል ለማሰማት በማሰቤ ነበር። ከዚያም መጽሃፉን ኪኢንተርኔት

ወደ ኮመፒዩተሬ ገልብጬ ማንበብ እንደጀመርኩ የጠረጠርኩትን መርዘኛነቱን

አረጋገጥኩ። ሲለጥቅም በአለማየሁ መሰለ የተገኘው የሻአብያው ሰላይ ተስፋዬ ገ/አብ

የእለት ማስታወሻ የበለጠውን አንደረደረኝ።

ቢያንስ ግማሽ ምእተአመት ለሚጠጋ ጊዜ በኢትዮጵያ ላይ ሲያሴር የኖረው ሻአብያ

አሁንም በአገሪቱ ላይ እኩይ ጥፋቱን ለመፈጸም እየተጋ ነው። ለሰላሳ አመት በዘለቀ

ጦርነት የመቶሽዎች ህይወት እንዲቀጠፍ፣ የብዙዎች ኑሮና ትዳር እንዲፈርስ፣ ልጆች

ያለወላጅ እንዲቀሩና አገራችን ኢትዮጵያ በኢኮኖሚያዊ አቅሟ ደቃ እንድትቆይ

ያደረገ ጦርነት ከዚሁ አገር ገንጣይ ሃይል ጋር አካሂደናል። በዚሁ ጦርነት መጨረሻም

የሺዎች አመታት ታሪካችን አብሯት የተሳሰረውን ኤርትራን እና ህዝቧን ገንጥሎ

ወስዷል። ወደብ አልባ አገርም አድርጎናል። ይህም ሁሉ ሳያንሰው ኢትዮጵያውያን

ዛሬም በሰላም እንዳንኖር ህዝብ ከህዝብ ጋር የሚተላለቅበትን የክፋት ድግስ

ይደግስልናል’።

ሻአብያ በተላላኪዎቹ በኩል በሚያካሂደው ደባ በብሄር ተቧድነን እንድንተላላቅ

ሁሌም የሚቀሰቅስ ሲሆን ለዚሁ ስራ ከሚጠቀምባቸው አንዱ የቀድሞው የኢሐዴግ

ባለስልጣንና የሻአብያ ሰላይ ተስፋዬ ገብረአብ ነው። ተስፋዬ ገ/አብ እዚሁ ኢትዮጵያ

ውስጥ እያለ ‘’ የቡርቃ ዝምታ’’ በሚል ርእስ ኦሮሞን እና አማራን የሚያፋጅ መጽሃፍ

የጻፈ ሲሆን ከአገር ከወጣም በጛላ ያንንው መሰሪ ስራውን ቀጥሏል። በተለያየ ጊዜ በጻ

ፋቸው ‘’የጋዜጠኛው ማሰታወሻ’’፣ ‘’የደራሲው ማሰታወሻ’’ እና ‘’ አሁን በመጨረሻም

‘’የስደተኛው ማስታወሻ’’ በሚሉ መጽሃፍቶቹ እጅግ በረቀቀ ዘዴ ኢትዮጵያውን

በሰላም እንዳንኖር እና እንደሃገር አንድ ሆነን እንዳንዘልቅ መርዝ ሲረጭ ኖሯል።

በቅርቡ ከተሰደዱ ህዝቦቹ በሚያገኛት ገቢ አገር የሚያሰተዳድረው ሻአብያ ለሰላዩ

ተስፋዬ ገ/አብ ቤት ተከራይቶ ማኖር ባለመቻሉና ተሰፋዬም ዝንጉ ተቀጣሪም

በመሆኑ ሻብያ ደህና ሙክቱን በአንበሳ ሲያስበላ ተስፋዬም ለአመታት ያደለበውን

ፈሪዳ ከነራሱ ሰውቷል። የሄውም ተስፋዬ ገ/አብ የእለት ክንውኑን እና እቅዱን

የሚመዘግብበት የደለበ ማሰታወሻ አለማየሁ መሰለ የሚባል ተስፋዬን አስጠግቶ

ያኖረው የነበረ ትንታግ ኢትዮጵያዊ እጅ በመግባቱና አለማየሁም ይህንንው መረጃ

Page 5: ማርከሻ ለ የሞት መርፌ - api.ning.comapi.ning.com/files/poTC6m2b82rkMz38uXDa*sLOeRr2Zc*dkAn32... · ውስጥ እያለ ‘’ የቡርቃ ዝምታ’’ በሚል

ደጃዝማች አብቹ ማርከሻ ለ-የሞት መርፌ

4

ይፋ በማድረጉ ነው። ይህ እጅግ ጠቃሚ መረጃ የያዘ ማሰታወሻ ደብተር እና

አለማየሁ እለት በለት ተከታትሎ የተስፋዬን የስልክ ንግግሮች ማድመጥ መቻሉ

ተስፋዬ ማን እንደሆነ ማወቅ ብቻ ሳይሆን ተስፋዬ የሚጽፋቸውን መጽሃፍት መፍቻ

ቁልፍ ሁኖ በማገልገል ሻአብያ በኢትዮጵያና በምስራቅ አፍሪቃ ላይ የሚከተለውን

ፖሊሲ ጭምር ማወቅ የሚያስችል ሁኗል ለማለት እደፍራለሁ።

በዚህ ‘’ማርከሻ ለ-የሞት መርፌ’’ በሚል ባዘጋጀሁት ጽሁፍ ውስጥ አሁን በመጨረሻ

ጊዜ ለህትመት ተዘጋጅቶ በውስጡ በያዘው ህዝብ አፋጅ ነገር ምክኒያት አታሚዎች

ለማተም ፈቃደኞች እንዳልሆኑ ሲነግሩት የጥፋት እቅዱ ግቡን ሳይመታ እንዳይቀር

በኢንተርኔት በለቀቀው ‘’ የስደተኛው ማስታወሻ’’ በሚል ርእስ በጻፈው መጽኃፍ ላይ

የሚያተኩር ሲሆን አልፎ አልፎ ቀደም ያሉትን በማጣቀሻነነት ነካክቷቸዋል።ተስፋዬ

በሁሉም መጽሃፎቹ አዘናጊ በሆነ ሁኔታ በውብ ስነጽሁፍ እያዋዛ ግለሰብን ከግለሰብ፣

ወገንን ከወገን እና ህዝብን ከህዝብ በሚለያይ አጣይና አበጣባጭ ትንኮሳዎች የተሞሉ

መጽሃፍት የደረሰ ቢሆንም ሁሉንም በዚህ ጽሁፍ ማዳረስ አልቻልኩም። ስለዚህም

በዋነኛነት አሁን በመጨረሻ ባቀረበው መጽሃፍላይ በማተኮር የተንኮል አካሄዱን

ለማጋለጥ ሞክሬያለሁ። በዚህ በመጨረሻ መጽሃፉ ሰላይ ተስፋዬ አማራን ከትግሬ፣

አሮሞን ከትግሬና ካማራ፣ ሐረሪን ከአማራ፣ከትግሬ፣ ከኦሮሞና ከሱማሌ፣ ጉራጌን

ከአማራ እና ወዘተ የሚያበጣብጥና አገር የሚከፋፍል ስራ የሰራ ሲሆን ይህንንው

አላማውንም ቅድም በጠቀስኩት ማሰታወሻው ላይ መዝግቦት ተገኝቷል።

ከዚህም በተጨማሪ አቻ ተስፋዬ ገ/አብ የሆነ በ 1998 እ.ኤ.አ በ ዳንኤል ግዛው The

Prince of Africa በመባል ተጽፎ በተከበሩ አቶ በረከት ስምኦን አነሳሽነትና

በመዝሙር ፈንቴ ተርጓሚነት ‘’የአፍሪካው ልዑል’’ በመባል ወደአማርኛ የተተረጎመ

ከዛም በላይ አዲስ አበባ በሚገኘው በፋና ሬዲዮ በመተረክ ላይ ያለ ሌላ አገር

አበጣባጭ መጽኃፍ በዚሁ ’ማርከሻ ለ-የሞት መርፌ’’ በሚል ባቀረብኩት ጽሁፍ

ወደመጨረሻ ላይ በጭሩ ለመዳሰስ ተሞክሯል። በዳንኤል ግዛው ተጽፎ በመዝሙር

ፈንቴ የተተረጎመው ይህ መጽሃፍ ያተኮረው አስካሁን በአንጻራዊ ሰላም

ከኢትዮጵየውያን ወገኖቹጋር እየኖረ ያለው ‘’ደቡብ ሕዝቦች’’ ተብሎ የሚጠራው

ህዝብ ላይ ሲሆን ልክ እነ ተስፋዬ እንደሚያደርጉት ይህኛው መጽሃፍ ደግሞ አማራን፣

ኩሎን፣ ወላይታን፣ ኦሮሞን እና መንጃን ሊያፋጅ የታለመ ስራ ነው።

እንግዲህ በአገሪቱ እነዚህን መሰል ኢንተርሃሞያዊ ቅስቀሳ እየተካሄደ፣ ህዝብ በሀዝብ

ላይ እንዲተላለቅ እየተቀሰቀሰ እና አገሪቱን ወደ ትንንሽ ጎሳዊ አገራት ቅርጫ

ለመለወጥ ሲሰራ አገራችንንና ህዝባችንን የምንወድ ኢትዮጵያውያን ዝም ማለት

አንችልምና የበኩሌን ላደርግ ተነሳሁ።

Page 6: ማርከሻ ለ የሞት መርፌ - api.ning.comapi.ning.com/files/poTC6m2b82rkMz38uXDa*sLOeRr2Zc*dkAn32... · ውስጥ እያለ ‘’ የቡርቃ ዝምታ’’ በሚል

ደጃዝማች አብቹ ማርከሻ ለ-የሞት መርፌ

5

ውድ አንባቢያን በዚህ ጽሁፍ በአገራችን ጎሳዊ ቅስቀሳዎች ያስከተሉትን ቀውስ

አስቀድሜ ተስፋዬ ገ/አብና ዳንኤል ግዛው ያነሷቸውን አገር እና ህዝብ አፋጅ ጉዳዮች

ተራ በተራ በመምዘዝ ያቀረቧቸው ጭብጦች ከአውነት የራቁ፣ ታሪክን እና

ትክክለኛውን አመክኒዮ ያፋለሱ መሆናቸውን በዝርዝር ላሰረዳ ሞክሬያሉ። የዚህም

ጽሁፌ አላማ የተንኮለኞችን ተንኮልና ውሸት ማጋለጥ ሲሆን ህዝባችን በተለይም

‘’በአዛኝ ቂቤ አንጓችነታቸው’’ ሊያታልሉት ያለሙት ህዝብ እንዲሁም ወጣቱ

ትውልድ አውነቱን በመረዳት በአጥፊ ተንኮላቸው እንዳይመረዝ መከላከል ነው።

ይህንንም ውስብስብ ስራ ኢትዮጵያውን የሆንን ሁሉ በየደረስንበት ስፍራ፣ ባገኘነው

አጋጣሚና አቅማችን በፈቀደ መጠን ተረባርበንበት አገር እና ህዝባችንን ከጀግኖቹ

አርበኞች ወላጆቻችን እንደተረከብነው ለመጪው ትውልድም ለማስረከብ ጠንክረን

እንድንሰራ ማስታወስ እወዳለሁ። በተያያዥም በሩዋንዳ የተነሳውን ፍጅት አይነት

በኢትዮጵያም እንዲደገም የሚተጉትን የሩዋንዳ መሰል ጋዜጠኞችም ሆኑ

ተባባሪዎቻቸውን የአለምአቀፉ ማህበረሰብ ችግሩ ከመፈጠሩ በፊት እንዲያወግዝና

ወደ ህግም ፊት እንዲያመጣ ኢትዮጵየውያን ሁሉ እንድትሰሩ ማሳሰብም እፈልጋለሁ።

መልካም ንባብ እመኛለሁ

ከጽሁፉ አቅራቢ

Page 7: ማርከሻ ለ የሞት መርፌ - api.ning.comapi.ning.com/files/poTC6m2b82rkMz38uXDa*sLOeRr2Zc*dkAn32... · ውስጥ እያለ ‘’ የቡርቃ ዝምታ’’ በሚል

ደጃዝማች አብቹ ማርከሻ ለ-የሞት መርፌ

6

ቅድመ ነገር

በወርሃ ሰኔ 1983 ዓ.ም በኦሮሚያ ካሉት ዞኖች ( የቀድሞ ክፍለሃገር) በአንዱ ዋና

ከተማ በሚገኘው አብዮት አደባባይ ለአካባቢው ነዋሪ በቀረበው የስብሰባ ጥሪ

መሰረት ቁጥረ ብዙ ባይሆንም ህዝብ ተሰብሰቧል። በወቀቱ በተደረገው አይነተኛ

የመንግስት ለውጥ ክፍለሃገሩን እንዲያሰተዳድሩ የተመደቡት አስተዳዳሪ ወደ መድረኩ

ብቅ ብለው ንግግር ማደረግ ጀምረዋል። ንግግራቸው ፈጽሞ የተለየ እና ካዛ በፊት

በአደባባይ ለህዝብ ሲባል ሰምቼው የማላውቀው ነበር። ተወልጄ ያደግኩባት

‘’ወደፊት ተምሬ ይህንን እና ያንን ችግሯን እቀርፍላታለሁ ‘’ብዬ የማስብላት

የተውልድ አካባቢዬ እንዲህ አንደዛሬው ያለ ጉድ ሰምቼባት አላውቅም ነበር።

የአስተዳዳሪው ንግግር በኦሮሞ ህዝብ ላይ ተባሉ የሚባሉ ተረቶችን እና ስድቦችን

ሁሉ ‘’ እንዲህ ስትባል፣ እንዲህ ስትባል…ኖረሃል’’ የሚል ነበርና በህዝብ አደባባይ ላይ

ህዝብን የሚለያይ እና የሚያፋጅ ነገር ያውም ‘አዲስ ቀን አመጣንልህ’ ለተባለ ህዝብ

ተስፋ አስቆራጭ ሆነ። አኔም ከአዲሶቹ መሪዎቼ የሰማሁት ጉድ ልቤን ክፉኛ ጎዳው።

‘’ አይ አገሬ ዛሬም አያለፍልሽም? ደግሞ ከድጡ ወደማጡ ሄድሽ?’’ ብዬ እንባዬን

በተቀመጥኩበት አፍስሼ እርሜን አውጥቻለሁ። አንድ በመካከለኛ እድሜ ላይ ያለ

ኢማማ የጠመጠመ ጎልማሳ ለተሰብሳቢዎች የንግግር እድል ሲሰጥ ወደመድረኩ

በመሄድ ‘’ እኔና የአማራ ልጆች ልዩነት ኖሮን አያውቅም አብረን ከብት ጠብቀን

አብረን ተምረን ነው ያደግነው። አባቶቻችን እና አባቶቻቸውም ኢማማ ጠምጥመው

አብረው ሲያርሱ፣ ሲበሉና ሲጠጡ እንጂ ዘሬ እንደምትሉት ሲሰዳደቡ አላውቅም’

አላቸው። ሌልኛው የከተማው ቄስ/ ዲያቆን እንደሆነ የማውቀው ሰው ‘’

እግዚአብሔር እረድቷችሁ እንደ ዳዊት ሃያሉን ጎሊያድን አሸንፋችኁ መጥታችጛል

እናንተም ደግማችሁ ህዝብን ከዛሬው ልትበድሉ ብትጀምሩ ያው አንደሚገጥማችሁ

እወቁ’’ ነበር ያላቸው።

ንግግሩ ያስከፋው እና ቀድሞውንም ቢሆን ደህና ነገር አልጠበቀ የነበረው ህዝብ

የስብሰባውን ቦታ ጥሎ ለመሄድ መንቀሳቀስ ጀመረ። ይሁንና ስፍራውን ይጠብቁ

በነበሩ የታጠቁ ሃይሎች በግድ እና በሃይል መሳሪያ እየተደገነበት ሲመለስ ‘’ እንዴ

ዲሞክራሲ ማለት ይሄ ነው እንዴ? ዲሞክራሲያዊ መብቶቻችሁን ልናረጋግጥ መጣን

አላችሁን፣ ካሁኑ በጠመንጃ ታሰገድዱናላችሁ ምንድነው ጉዱ? ብሎ በግድ ስብሰባ

ወደሚካፈልበት እና ህዝብን ከህዝብ የሚያፋጅ ስድብ እየተነገረ ቅስቀሳ

ወደሚደረግበት አደባባይ ተመለሰ።

Page 8: ማርከሻ ለ የሞት መርፌ - api.ning.comapi.ning.com/files/poTC6m2b82rkMz38uXDa*sLOeRr2Zc*dkAn32... · ውስጥ እያለ ‘’ የቡርቃ ዝምታ’’ በሚል

ደጃዝማች አብቹ ማርከሻ ለ-የሞት መርፌ

7

ይህ ሁሉ ህዝብን በህዝብላይ የማስነሳት ቅስቀሳ ውጤቱ የታለመ ነበር። ይህንንም

ተከትሎ በጎባ ሮቤ አውሮፕላን ማረፊያ ላይ አውሮፕላን ለመሳፈር በመጠባባቅ ላይ

የነበሩ 14 ሰዎች ታረዱ ሲባል ሰምቻለሁ። ይህ የእልቂት ጎርፍ በልዩ ልዩ ስፍራ

ቀጥሎ በሃረር በደኖ ትልቁን የግፍ ጽዋ ለህዝብ በማድረስ አሮጊት እና ሽማግሌዎችን

ሳይቀር በጭካኔ አንዲጨፈጨፉ አድረጓል።

ግን ይሄ ለምን ሆነ? በእረግጥ ኢትዮጵያ የሚያስፈልጋት ይሄ ነበር? በአስራ ሰባቱ

አመታት የደርግ አገዛዝ ወቅት አነሰም አደገም ሰው ሁሉ እኩል አንዲሆን በደንብ

ተቀጥቅጦ ተሰርቶ ሳለ እንደገና ልዩነት መፍጠር እና የሌለውን እንዳለ ማድረግ ለምን

አስፈለገ?

አዎ የኦሮሞ ህዝብ ቁጥረ ብዙ እና ሰፊ ነው። የአማራውም አንደዛው። እነዚህ ሁለት

ህዝቦች የሃገሪቱን ህዝብ ቁጥር ከግማሽ በላይ የያዙ ሲሆን በአገሪቱ የፖለቲካ እና

ወታደራዊ አሰላላፍ ላይ ከፍተኛ ተጽእኖ ሊያደርሱ እንደሚችሉ ሳይታለም የተፈታ

ነው። እነዚህ የኢትዮጵያ ህዝቦች አብረው የኖሩና እርስ በርሳቸው የተጋቡ የተዋለዱ

ከመሆናቸውም በላይ በመካካላቸው የጠነከረ ህብረትም የመሰረቱ ናቸው።

በኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነትም ላይ ያላቸው የጠነከረ አቁዋም አገሪቱን ከማናኛውም

አደጋ ለመከላካል ፍጹማዊ ቆራጥነት ተለይቶት አያውቅም። ይህ ማንነታቸው ግን

በዛንወቅት በበጎ የታይ አልሆነም። ይልቁኑ አስጊ ነው። ስለዚህም በመካከላቸው

የነበረ፣ የቆየ እና የተረሳ ቂም እና ቁርሾ ቀስቅሶ፣ አጋኖና አባብሶ ማጣላት እና

ማገዳደል፣ በዚህም እንዳይስማሙ አድረጎ ማለያየት አጅግ አጅግ አስፈላጊ ብቻ

ሳይሆን ፍጹም ተገቢ ነው። እናም ይህንን ሊያስፈጽሙ የሚችሉ በመራራ የኖረና

የተረሳ ታሪክ የታጨቁ፣ ጠመንጃ የታጠቁ እና በህዝብ ላይ መራራ ግፍ በመፈጸም

የማይረሳ ጠባሳ የሚተዉ ካድሬዎችን ከገዳይ መርዝ ጋን አጠገብ አስጠግቶ መጋት

እና የብቃታቸውም ማረጋገጫ አርሱ እንደሆነ አበክሮ ማስገንዘብ በጣም አስፈላጊ

ነበር። አዎን ከሞላ ጎደል ይህ እቅድ በታለመለት ሁኔታ ተገባዷል።

እቅዱ እነዚህን ሁለት ትልልቅ ህዝቦች ብቻ በመነጣጠል የሚያበቃ አይደለም

ኢትዮጵያውያንን ሁሉ እንጂ። ሶማሌውን፣ ሓረሪውን፣ ከፋውን፣ አፋሩን፣ሲዳማውን፣

ጉራጌውን፣ አኙዋኩን፣ ኒዌሩን፣ ኩሎውን፣ ጊሚራውን፣ ሸካውን፣ሸኮን፣ መጀንግሩን፣

የሙን፣ ጉራጌውን፣ ወላይታውን፣ ከንባታውን፣ሃድያውን፣ ገሙሙዙን፣ትግሬውን

ወዘተ ሁሉ በብሔር ተኮር ፖለቲካ አጡዞ እና አንዱ በሌላው ላይ በተለይ በአማረው፣

ጥላቻ እነዲያድርበት እና እኔ እኔ እያለ እንዲተራመስ ሆን ተብሎ ተሰርቷል። ከዚህም

የሚጠበቅ ውጤት ሲቻል የተበታተነች ሳይቻል አጅግ የተዳከመች እና አንድነት

ያጣች ኢትዮጵያን ማየት ነው።

Page 9: ማርከሻ ለ የሞት መርፌ - api.ning.comapi.ning.com/files/poTC6m2b82rkMz38uXDa*sLOeRr2Zc*dkAn32... · ውስጥ እያለ ‘’ የቡርቃ ዝምታ’’ በሚል

ደጃዝማች አብቹ ማርከሻ ለ-የሞት መርፌ

8

ይህ ደግሞ ተመልሳ ኤርትራን የማትወጋ ይልቁንም የምትጠቅም ከማድረጉም በላይ

ለዘመናት እንዳታንሰራራ ሁና መውደቁዋን ለሚመኙላት የአርብ ሃገራት እፎይታን

መስጠትም አንዱ የቅጥረኞቹ ግብ ነው።

የዚህ የሞት ያውም የሀገር ሞት ጥንስሱ እና ጋኑ ደግሞ ተቀማጭነቱ ኤርትራ ሲሆን

የመርዙ አደባላቂ ሻብያ ነው። በስሩ ያሉት ጭፍሮች አንዳንዶቹ አውቀውና ሆን

ብለው ሌሎቹ በሚነገራቸው የተንኮል ቅስቀሳ ተታለው ይህን ሀገር በታኝ ቅስቀሳ

ለታለመለት ህዝብ ያዳርሳሉ።

መቼም ለዚህ እማኝ ንቀስ አልባልም። ምክኒያት ብትሉ በየእለቱ እየኖርነው ያለና

እንደ አየር የምንስበው ውስጣችንን የሚከነክነን እና እየገዘገዘ ሊጥለን የሚታገል

አውነት ስለሆነ። በሰሞኑ ግን እምንጠረጥረው ግን ሁነኛ ማረጋገጫ አላገኘንለት

የነበረውን ይህን ጉዳይ አስተማማኝ መደምደሚያ የተገኘንለት ይመስላል። ለሻቢያ

ሲሰልል እና ገዳይ መርዙን ሲያሰራጭ የኖረው የቀድሞው የኢሀዴግ ባለስልጣን

ተስፋዬ ገብረ አብ ውሎዎቹን እና እቅዶቹን ይመዘግብበት የነበረ ማሰታወሻ መገኘቱ

ሻቢያ እና ተባባሪቹ በኢትዮጵያ ላይ የሚፈጽሙትን ደባ አጋላጭ ሁኗል።

እስኪ ዳኛ ወልደሚኪያኤል መሸሻ ፣አለማየሁ መሰለ የሚባል ኢትዩጵያዊ ከተስፋዬ

ወስዶበት ከሰጣቸው ድልብ ማሰታወሻ ደብተር ላይ ቆንጥረው ለንባብ ካበቁት የ

ተስፋዬ ገ/አብ የእጅ ጽሁፍ ላይ አዲስ አበባ የሚታተመው ሎሚ መጽሄት በቅጽ ሶስት

ቁጥር 77 ጥቅምት 2006 ’’ተስፋዬ ገብረአብ ከሻብያ ጋር የተለዋወጣቸው ምስጢራዊ

ማስታወሻዎች’’ በሚል ርእስ ያቀረበውን እንመልከት።

Page 10: ማርከሻ ለ የሞት መርፌ - api.ning.comapi.ning.com/files/poTC6m2b82rkMz38uXDa*sLOeRr2Zc*dkAn32... · ውስጥ እያለ ‘’ የቡርቃ ዝምታ’’ በሚል

ደጃዝማች አብቹ ማርከሻ ለ-የሞት መርፌ

9

የሰላዩ ማስታወሻ

‘’ ለመጀመሪያጊዜ ከሻብያ ጋር በመገኛኘት ኤርትራ ለተባለች ሀገሬ ቀጥተኛ

አገልግሎት ለመስጠት የወሰንኩት የ29 አመት ጎረምሳ ሳለሁ ነበር። አሁን 41

አመቴ ነው።ኤርትራዊነት ይሰማኝ የነበረው ግን ገና ህጻን ልጅ ሳለሁ ነበር።የሻብያ

ታጋይ ብሆን ምኞቴ ነበር። በታሪክ አጋጣሚ አልሆነም።ዘግይቼም ቢሆን ሃገሬን

ለማገልገል በመቻሌ ግን እኮራበታለሁ። በአንድ ነገር እርግጠኛ ነኝ እኔ ከኤርትራ

ፕሬዚዳንት እኩል ኤርትራን አፈቅራታለሁ። …በኤርትራ እና በኤርትራዊነት ጉዳይ

ለይ ጽኑና እልከኛ ነኝ።….. በፖለቲካ አመለካከቴ አኔ ጸረ-ወያኔ አቁዋም የያዝኩት

ወያኔ ጸረ ኤርትራውያን ወይም ጸረ-ሻብያ አቁም በመያዙ ብቻነው።…በትግሉ

ወቅት ለዚህ ያበቃው የትግል አጋሩ ላይ ክህደት ፈጽሟል።… ለዚህ ክህደቱ

ዋጋውን ማግኘት እንዳለበት አምናለሁ። ለዚሁ እታገላላሁ።.. እስከእለተ ሞቴ

እበቀለዋለሁ። ‘‘

ይለናል። የጅብፍቅር እስኪቸግር እንዲሉ መሆኑ ነው¡¡

ስለሚጥፋቸው መጽኃፎቹም አላማና ጥቅማቸውም ሲያትት

‘’ባለፉት 10 አመታት ለሻብያ መረጃ እና ጥቆማ በመስጠት ሰርቻለሁ። ከሰጠሁት

ጥቆማ በላይ እነዚህን ጥቆማዎች ለመስጠት በተደረገ እንቅስቃሴም ሁለት

መጻህፍት ( የጋዜጠኛው እና የደራሲው ማስታወሻ) ለመጻፍ ችያለሁ። እነዚህ

ሁለት መጻኅፍት ያስገኙት ፖለቲካዊ ፋይዳ በጣም ከፍተኛ መሆኑን ለመገንዘብ

በአንድ ባለሙያ ማስጠናት ብቻ በቂ ነው።’’ ይላል።

አሁን በቅርቡ ሊያሳትመው አዘጋጅቶት በዚህ ሚስጥራዊ ሰነድ መገኘት እና መበተን

ምክኒያት ሳይታተም ቀርቶ ነገር ግን የጥፋት ድግሱ ሳይበተን እንዳይቀር ባለው

ቁርጠኛ ሃሳብ በድኅረ ገጾች ላይ ስለለቀቀው መጽኃፉ ሲያወራም ( ከመ’ጻፉ በፊት

ማለት ነው)

‘‘የስደተኛው ማሰታወሻን’ ሆላንድ ሆኜ መስራት አልቻልኩም።በጣም ሞከርኩ ግን

አልሆነም። መስራት ካለብኝ ኤርትራ መመለስ አለብኝ።ኤርትራ ከተመለስኩ

ያገኘሁት የሆላንድ ዜግነት ሊቋረጥ ይችላል።… ጥቅምና ጉዳቱን ስመዝነው ግን

ሆላንድ ላይ ያገኘሁት ዜግነት ተሰርዞ ወደ ኤርትራ ብመለስ የስደተኛው ማሰታወሻ

የተባለውን መጽኃፍ ጽፌ መጨረስ የተሻለ ነው። ምክኒያቱም ‘የስደተኛው

ማሰታወሻ’ ፖለቲካዊ ፋይዳው የላቀነው።’’ ይላል። (ሎሚ መጽሄት ቅጽ ሶስት

ቁጥር 77 ጥቅምት 2006 ’’ተስፋዬ ገብረአብ ከሻብያ ጋር የተለዋወጣቸው

ምስጢራዊ ማስታወሻዎች’’ )

Page 11: ማርከሻ ለ የሞት መርፌ - api.ning.comapi.ning.com/files/poTC6m2b82rkMz38uXDa*sLOeRr2Zc*dkAn32... · ውስጥ እያለ ‘’ የቡርቃ ዝምታ’’ በሚል

ደጃዝማች አብቹ ማርከሻ ለ-የሞት መርፌ

10

እንደተናገረውም የፖለቲካ ፋይዳው እንደቀድሞ ስራዎቹ ሁሉ ከፍተኛ የሆነና

ኢትዮጵያውንን የሚያበጣብጥ፣ የሚለያይ እና አገራዊ መስተጋብርና አንድነት

እንዳይኖረን የሚያደርግ ክፋት ደጉሶልናል።

እርሱ እንዲህ የአገር ጠላት ሁኖ ሳለ ግን

‘’ኢትዮጵያነቴን ይዤው ወደ መቃብር እሄዳለሁ” ቀደም ብዬም

ተናግሬያለሁ። ማንም ሊከለክለኝ አይችልም። ማንም ሊሰጠኝ አይችልም። አገር

ውስጥ እንዳልገባ ልከለከል እችል ይሆናል። የልብ ስሜቴን መንጠቅ የሚችል

አንድም ሰው የለም። ይህንን ስሜቴን ነው ባጭሩ ማነገር የምፈልገው።ማንም

አይቻለውም። ኢትዮጵያዊያን ወንድሞቼ ሚሊዮኖች አሉ።በተለያዩ ምክንያቶች

አገር ቤት መግባት አይችሉም። ከጥቂት ጊዜያት በሁዋላ ግን እንደጎርፍ ነው ወደ

አገራችን የምንገባው።’’ ይለናል

(http://addisuwond.wordpress.com/2013/10/21/ኢትዮጵያነቴን-ይዤው-ወደ-

መቃብር-እሄዳ/)

ለአለማየሁ እና ለዳኛ ወልድሚካኤል ምስጋና ይድረሳቸውና አገራችንን እና

ህዝባችንን ከአበጣባጩ ግብዣ ማትረፍ ብቻ ሳይሆን አሁን ለፈንጣጣ በሽታ

ከፈንጣጣ አምጪ ህዋስ ክትባት እንደተሰራ እኛም የህንንው የምናደርግበት ጊዜ ነው።

ተስፋዬ ገብረአብ በዚህ ‘’የስደተኛው ማስታወሻ’’ በሚል አሁን ቅርብ ጊዜ (2006

ዓ.ም) በኢንተርኔት የለቀቀው መጽሀፍ ላይ ያነሳቸው ቁጥረ ብዙ ርእሶች አሉት።

ተስፋዬ ከወጥ ጽኁፍ ይልቅ ይህኛውን አጻጻፍ የሚመርጥበት አንድ ምክኒያት ነው

ብዬ የምገምተው የተለያየ ርእስ በመምዘዝ ብዙ የተንኮል ሴራዎችን መበተን

እንዲያመቸው ነው። በዚህ መጽኃፉ 39 የተለያዩ ርእሶች ያነሳ ሲሆን እያንዳንዱን

ለዚሁ የጥፋት አላማው በክፋት በተካነ የስነጽኁፍ፣ ያተራረክ እና አቀራረብ ችሎታው

ደርሶልናል። በአደራደሩም በየማህሉ የሚያዋዙ ምእራፎች ጣልቃ እያስገባ ይዞን

ወደሞት ባህሩ ሊያነጉደን ይንደረደራል። በአላጎሪክ አገላላጹ በጉን፣

አእዋፎችን፣ውሻውን አና ሌሎችንም እያነሳ የሚጎነጉነውን ተንኮል ከዚህ ቀደም

‘የጋዜጠኛው ማሰታወሻ’ በሚል ርእስ በጻፈው መጽሀፍ ‘የቁንድዶ ፈረሶች’ በሚል

ርእስ የመሰጠረውን ክፋት አሁን በዚህኛው መጽሀፉ እንደፈታልን እራሱ ወደፊት

አስኪገልጽልን ለጊዜው ወደጎን ትቼ በቀጥተኛ አገላለጽ የተናገራቸውን ብቻ አብረን

እንይ።

Page 12: ማርከሻ ለ የሞት መርፌ - api.ning.comapi.ning.com/files/poTC6m2b82rkMz38uXDa*sLOeRr2Zc*dkAn32... · ውስጥ እያለ ‘’ የቡርቃ ዝምታ’’ በሚል

ደጃዝማች አብቹ ማርከሻ ለ-የሞት መርፌ

11

እንጥፍጣፊ ነገር/ያለቀበት

ተስፋዬ ገና አሃዱ ብሎ በጀመረበት ‘ጉዞ ወደገነት’’ በሚለው ርእስ ስለ ሆላንድ

ስደተኝነቱ እየነገረን በዛ አበሾችን ማግኘቱን እና መገረሙን አስታኮ እና አበሻ የሌለበት

የአለም ክፍል የለም የሚለውን አሰተሳሰቡን አንተርሶ ገጽ 13 ላይ ‘አንድ የቆየ ቀልድ

ታወሰኝ። አሜሪካውያን ለአፄ ሃይለስላሴ፣ጨረቃ ላይ ደርሰን መጣን’ቢሉት፣ ’ታዲያ ትግሬ

አላገኛችሁም?’ ሲልጠየቀ።’’ ይለናል። እንግዲህ ልብ በሉ ንጉሱ ትግሬን ይንቁ ነበር

ወይም ተንከዋታች ነው ብለው ነው የሚያምኑት አይነት መልእክት በማስተላላፍ ያኔ

ህውሃት እና ሻብያ ይጠቀሙበት የነበረውን ስልት አሁንም በመድገም የትግራይን

ህዝብ ልብ በቁርሾ ሊመርዘው ይጽፋል። እንደአውነቱ ከሆነ የኢትዮጵያ ህዝብ

ስደተኛ መሆን የጀመረው ከንጉሱ በጛላ እንጂ በንጉሱስ ዘመን በክብር ለትምህርት እና

ለልዩልዩ ጉዳዮቹ ካገር ይወጣ ነበር። ስደተኛ ቢኖርም እንዲህ እንዳሁኑ አልነበረም።

ጀጎልም አንዲያድም

ተስፋዬ ተራ በተራ የሃገሪቱን ህዝቦች ማዳረሱን እየቀጠለ አስከዛሬ ያልተነካውን

በአብዛኞቻችን ልብ ውስጥ በተዋበ ቁንጅናቸው፣ በገርነት እና በፎልፏላነታቸው

የሚታወቁትን ሀረሪ ዎች ይነከካብናል። ሊያበጣብጠን። እንደእውነቱ ከሆነ እኔ እንደ

አብዛኛው ኢትዮጵያዊ ከልጅነቴ ጀምሮ ስለነሱ የምሰማው ይህንን ተወዳጅነታቸውን

ነው። አርሱ ግን ‘’የጀጉል ልባዊ ወግ’’ በሚል ርእስ ‘’ያስደተኛው ማስታወሻ’’ ላይ ከ

ገጽ 42 አስከ 48 ላይ ካሰፈረው ሌላ ‘’የቁንድዶ ፈረሶች’’ በሚል ርአስ ‘የጋዜጠኛው

ማሰታወሻ’ በሚለው መጽኃፉ ላይ የጻፈውም በፈረሶች ተመስሎ የተመሰጠረ ታሪክም

ሃረሪዎች ተገንጥለው ጎጆ እነዲወጡ ይቀሰቅሳል። ጠየቅኳቸው የሚላቸውን እናት

የጠየቃቸው ሁሉ በማወዳደር እና መሪ ጥያቄዎች ( leading questions) ሲሆን

አላማውም ወደክፋት ግቡ ማድረስ ነው።ያን ጊዜ አማራውን በየደረሱበት ማጥላላት

እና ማስጠላት የታቀደበት ዘመን ነበር እና ቃለመጠይቁን የጨለንቆውን ጦርነት

አንተርሶ አጼ ሚኒሊክን እና አማራውን ለማጥላላት ተጠቀመበት። አሁንም ያው

ቁስል እንዲያመረቅዝ ብቻ ሳይሆን የበለጠ የአገር አንድነት ላይ አደጋ እንዲደርስ

ደግሞ ይገፋፋል። የሰማውን ሰምቶም ከሆነ ያን ጊዜ ለምን በጋዜጠኝነቱ

አላቀረበውም? አዎን የጊዜ ቦምብ ለማፈንዳት ለአሁን ጊዜ ቀጠረለት።

Page 13: ማርከሻ ለ የሞት መርፌ - api.ning.comapi.ning.com/files/poTC6m2b82rkMz38uXDa*sLOeRr2Zc*dkAn32... · ውስጥ እያለ ‘’ የቡርቃ ዝምታ’’ በሚል

ደጃዝማች አብቹ ማርከሻ ለ-የሞት መርፌ

12

ይህንንም ሳያውቅ ወይም አምልጦት ሲያሰረዳን

በወቅቱ አረጋውያኑ ከነገሩኝ መካከል ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታ የሚያገለግለውን

ብቻ መርጬ “እፎይታ መፅሄት”ላይ ማተሜን አስታውሳለሁ። ከአመቱላ ሻሽ

አቦኝ ጋር ያደረግሁትን ቆይታ ግን፣“ጊዜህን ጠብቅ”አልኩና ወደ ማስታወሻ

ጎተራዬ ወረወርኩት። እነሆ! ለመነበብ ጊዜው ደረሰ... ‘’ብሎ በመጻፍ ሀሪፍ

ጊዜ ጠብቆ አፈንጂ እንደሆነ ሳይሸሽገን አጫወትን¡

ከቅኝ ገዥዎች ህዝብን የመነጣጠያ ዘዴ በቀዳው መንገድ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት

ላይ አደጋ የሚጥልበትን አካሄድ ተክኗል። ስለዚህም ዛሬ ያን ጊዜ በህውሃት ውስጥ

ህልሙን እውን ማድረግ ይፈልገው የነበረው ሻብያ በከፊልም ቢሆን እንዳልተሳካለት

ሲያውቅ ሌልኛውን የመጠባበቂያ ከምሱር በማላላት በራሱ በኢሃዴግ መንግስትና

በአገዛዙ ላይ ከዛም በላይ በዋናው በኢትዮጵያ አንድነት ላይ አንደሚከተለው አደጋ

ለኮሰ።

በዚህ ጸሁፉ ተስፋዬ ለሀረሪ ህዝብ ቁጥር መቀነስ ተጠያቂው እንደተለመደው

ሚኒሊክ እና አማራው ነው ይልና ጨርሶ ሊጠፋ እና ከምድሩም ላይ ሊነቀል

እንደነበር ምስክር ይቆጥርልናል። በስተመጨረሻም መፍትኄ የሚለውን በዘዴ

ያመላክታል። አስኪ አንስማው

ጠያቂ ተስፋዬ“ከግብፆች፣ ከጣልያኖችና ከሃበሾች ማንኞቹ ይሻሉ ነበር?” መልስ፡-

አመቱላ ሻሽ አቦኝ ሳያመነቱ መለሱ፣ “ሁሉም አይሻሉም። ምንም ቢሆን የኛዎቹ

አሚሮች ይሻሉ ነበር። አሚር አብዱላሂ ላይ ተቋረጠብን።

የመጨረሻ ጥያቄ ልጠይቆት? ከደርግ መውደቅ በሁዋላ የሃረሪ ህዝብ ራሱን በራሱ

እያስተዳደረ ነው። የቀድሞ ግዛታችሁም ቢሆን ተመልሶአል። በአዲሱ ስርአት ደስተኛ

ናችሁ?” የሚል ጥያቄ እንዳቀረበ እና በመልሱም አኛ የ 80 -85 አመት

እድሜ እንዳላቸው የነገረን እና በ 1990 ዓ.ም ቃለመጠይቅ ያደረገላቸው

አመቱላ ሻሽ አቦኝ እነዲህ ብለው መለሱልኝ ይለናል ‘ራሳችንን ማስተዳደር

የምንፈልገው ነው። በርግጥ ጎረቤቶቻችን በበጎ አያዩንም። ‘ትግሬ ሲባረር

በመሃረም ጠቅልሎ ይዞአችሁ ይሄዳል’ እያሉ ይዝቱብናል። ራሳችንን

ማስተዳደር እንፈልጋለን። ሰላምም እንፈልጋለን። ሁለቱንም ብናገኝ በጎ ነበር።

ከሁለቱ አንዱ ከጎደለ መልሶ ያው ነው።

አሉ ብሎን 100 አመት ያለፈ ታሪክ ጠቅሶ ከአማራው ጋር ከ 15 አመት በፊት ባደረ

ቂም ያጣላው አንሶ አሁን ደግሞ አንድም ሀረሬውን ከጎረቤቱ ኦሮሞ እና ሶማሌ ጋር

ያጋጨዋል። ትግሬውም ለካስ አይወዱኝም ብሎ በነዚሁ ህዝቦችላይ እንዲያቄም

ያነሳሳዋል። አለበላዚያም የሚኒሊክን ጦር ለመግጠም ሀረሪው፣ ሶማሌው እና

Page 14: ማርከሻ ለ የሞት መርፌ - api.ning.comapi.ning.com/files/poTC6m2b82rkMz38uXDa*sLOeRr2Zc*dkAn32... · ውስጥ እያለ ‘’ የቡርቃ ዝምታ’’ በሚል

ደጃዝማች አብቹ ማርከሻ ለ-የሞት መርፌ

13

ኦሮሞው ጨለንቆ ላይ ግንባር ፈጥረው ተዋግተው ጉዳት ደረሰባቸው ብሎ የውሸት

አዛኝነቱን እንደገለጸው ሁሉ አሁን ደግሞ ‘ትግሬ ሲባረር በመሃረብ ጠቅልሎን

ላይሄድ አርፈን ከጎረቤቶቻችን ተስማምተን ከትግሬውም እንለይ’ እንዲሉ

ይቀሰቅሳል።

ለመሆኑ የሃረሬ ህዝብ ማነው? ከኢትዮጵያስ ጋር ያለው ትስስር ምንድን ነው?

ሚኒሊክስ ወደዛ ለምን ዘመቱ? የሚሉ ጥያቄ ዎች እና መልሶሳቻቸው ከላይ ተስፋዬ

በከንቱ የዘነቋቆለና ሊያደፈርሰው የሞከረውን ነገር ያጠሉታል። ፐሮፌሰር ባህሩ

ዘውዴ እና ፓውል ሄንዝ ስለ ኢትዬጵያ በጻፉት ታሪክ ሁለቱም አለቃ ታዬን

በመጥቀስ በሀረር ግምብ ውስጥ የሚኖሩት ህዝቦች ያንድ ብርቱ / ሃያል የሆ

የሃማሴን ሰው ልጆች ሲሆኑ በንጉስ ዳዊት ዘመን (1374 -1405) ወደስፍራው

መጥተው እንደሰፈሩ ይነግሩናል። የእነዚህ ህዝቦች ለረጅም ጊዜ ቋንቋቸው ትግርኛ

እነደነበረና የኢትዮጵያ መንግስት እስከተዳከመበት ጊዜ ድረስ ግብር ለመንግስቱ

ይከፍሉ እንደነበር ይተርካሉ። ሐረሪዎች አሁንም ቢሆን ቋንቋቸው ከትግርኛ ጋር

እንደሚቀራረብ እንደውም በቋንቋ ብቻ ሳይሆን በባህልም ዝዋይ አካባቢ

ከሚኖሩት የጉራጌ ማህበረሰብ ጋር እንደሚመሳሰሉ ፓወል ሄንዝ ጽፈዋል።

ሓረሪዎች የኢትዮጵያ ማእከላዊ መንግስት በተዳከመበት ጊዜ በቱርኮች ሲገዙ የቆዩ

ሲሆን ቋንቋቸውም በጊዜ ብዛት ተለውጧል። በአካባቢው ባሉ የኦሮሞ እና

የሱማሌ ጎሳዎች ከሚደርስባቸው ጥቃት ለመከላከልም ሲሉ አምስት በር ያለው

ግንብ በመገንባት በውስጡ ተከልለው ይኖራሉ። ከ 1867 -1877 ባለው ጊዜ

ውስጥ በግብጾችም ሲተዳደሩ ቆይተዋል። እንግዲህ ግብጾች ከለቀቁ ከኁለት አመት

በጛላ ነው ንጉስ ሚኒሊክ የቀድሞውን የኢትዮጵያን ግዛት ለማስከበር የሄዱት። (

Henze,Paul, Layers of Time: A History of Ethiopia,(2000) p114; Baheru

Zewde, A History of Modern Ethiopia(2002) 1855-1991, )

ግብጾች እንደወጡ በአካባቢው ይንቀሳቀሱ ከነበሩት የአውሮፓ ሃይሎች አንዱ መልሶ

ሃረርን በመውረር የኢትዮጵያን ግዛት ለመውሰድ ከመሞከሩ በፊት ሚኒሊክ ቦታውን

መቆጣጠር ነበረባቸው። ከዛ በተጨማሪም የአካባቢውን ጸጥታ ለማስከበር በስፍራው

ከሚያንዣብቡት ሃይሎችጋርም ስምምነት ተደርሶ ነበር። (Baheru Zewde, A

History of Modern Ethiopia(2002) 1855-1991, )

ከሁሉም በላይ አጼ ሚኒሊክ በአጼ ልብነድነግል ዘመን (በ16ኛው ክፍለዘመን) ከዚሁ

አካባቢ በመነሳት በቱርክ አጋዥነት እና አነሳሽነት ግራኝ አህመድ ኢትዮጵያን ወሮ

Page 15: ማርከሻ ለ የሞት መርፌ - api.ning.comapi.ning.com/files/poTC6m2b82rkMz38uXDa*sLOeRr2Zc*dkAn32... · ውስጥ እያለ ‘’ የቡርቃ ዝምታ’’ በሚል

ደጃዝማች አብቹ ማርከሻ ለ-የሞት መርፌ

14

የደረሰውን ጥፋት ያውቃሉ። ግራኝ አህመድ ይህን ጦርነት ከማካሄዱ በፊት

በሽንብራ ኩሬ ከልብነ ድንግል ሰራዊት ጋር ተዋግቶ ካሸነፈ በጛላ እራሱን በደንብ

ለማደራጀት እና ስልጣኑንም ለማደላደል ወደጛላ ተመልሶ ነበር። በዚህ እቅዱም

መጀመሪያ ደዋሮን ቀጥሎም ኦሮሞዎች የሰፈሩትን እና አዝማች ደግልሃን በሚባል

የልብነ ድንግል ሹም ይተዳደር የነበረውን ባሌን ሙልጭ አድረጎ ዘረፈ። በዚህ

የተዘረፈ ሀብት መድፍና ጠመንጃ ገዝቶ እና የማረከውንም ሰው ጭምር አስከትቶ

ዳግም ንጉሱ ላይ ጦርነት ከፈተ። በዚህ ጊዜ የግራኝ አህመድ አላማ ኢትዮጵን አስልሞ

መግዛት ነበርና ህዝቡን በግድ እያሰለመ ንጉሱንም ከሸዋ ወደወሎ፣ ከዚያም ወደትግሬ

እያሳደደ ገሰገሰ። በዚህ ለአስራአምስት አመት በዘለቀ ጦርነት ስንት ህዝብ እንደታረደ፣

የለመለመ ተክል እና ዛፍ አንኳን ሳይቀር እንደተጨፈጨፈ፣ ገዳማት እና

አብያተክርስቲያናት እየተቃጠሉ የታነጹበት እና ያከማቹት ወርቅ እና አልማዝ

እንደተዘረፈ በ19ኛው ክፍለዘመን የተነሱት ንጉሱ ሚኒሊክ ታሪክ ነውና ያስታውሳሉ።

ይህ ጥፋት ዳግም እንዲደርስ ሃይሉ የበረታ እና አገሩን የሚወድድ ንጉስ ደግሞ

የሚፈቅደው ጉዳይ አይደለም። እንግዲህ እነዚህ ሁሉ ተዳምረው ሚኒሊክ

ወደስፍራው ሲንቀሳቀሱ ጨለንቆላይ ጦርነት ተካሄደ። ጦርነት ሁሌም አውዳሚ ነው

እና ህይወት እና ንብረት ጠፋ። (Baheru Zewde, A History of Modern

Ethiopia 1855-1991, (2002) p63; ይልማ ደሬሳ, የኢትዮጵያ ታሪክ

ባሰራስድስተኛው ክፍለዘመን( 1959) ገጽ36--)

የሆነስ ሆነና አሁን ተስፋዬ የሚቆሰቁሰው ድፍን ኢትዮጵያን የሚያዳርስ እሳት ብርድ

እንዲያስጥለን እና ምግብ አንዲያበስልልን ይሆን? የኛ ቂቤ አንጓች¡ ሃረሪዎች፣

ኦሮሞዎች እና ሌሎችም እሱ በሚሰብከው የሻአብያ የተበጣጠቀች እና አቅም ያጣች

ኢትዮጵያን የመፍጠር ህልም የኢትዮጵያ ግዛት ሲፈራርስ ኬክ እየተቆረሰ የሚኪያሄድ

የሚመስለን ይመስለዋል ማለት ነው? ግንእኮ እሱ አውቆ የዘነጋው ነገር ግራኝ

አህመድም ሀረርን መገንጠል አልነበረም ሃሰቡ ኢትዮጵያን መግዛት እንጂ። እንደዛማ

ባይሆን ‘’ወሰኔ እዚህ ድረስነው ከዚህ ብታልፉ ውርድ ከራሴ’’ ብሎ ድንበር በመከለል

ያበቃ ነበር።

ስለዚህ ሐረር እና ሐረሪዎች በትውልድ ከኢተዮጵያውያን ደም የተቀዱ

ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ በግዛትም ከጥንት ጀምሮ የኢትዮጵያ ምድር በሆነ ስፍራ

የሚኖሩ ናቸው። የኢትዮጵያ ማእከላዊ መንግስት ሲዳከም ቱርኮች እና ግብጾች

ለተወሰነ ጊዜ አስተዳድረዋቸዋል። ኢትዮጵያ መንግስቷ ሲደራጅ እና ሲጠነክር ደግሞ

የግዛት ወሰኑን በማሰከበር የራሱን ህዝቦች እና አገሩን በመሰብሰብ ማሰተዳደሩን

ቀጥሏል። ይሄውነው። ተስፋዬ ቃለመጠይቅ አደርግኩላቸው የሚላቸው ሴት ወይ

Page 16: ማርከሻ ለ የሞት መርፌ - api.ning.comapi.ning.com/files/poTC6m2b82rkMz38uXDa*sLOeRr2Zc*dkAn32... · ውስጥ እያለ ‘’ የቡርቃ ዝምታ’’ በሚል

ደጃዝማች አብቹ ማርከሻ ለ-የሞት መርፌ

15

የወሬ ወሬ የሰሙት ታሪክ ከእድሜያቸው ጋር ተደማምሮ ተዛብቶባቸዋል ወይም አሱ

እንደለመደው ሆን ብሎ አዛብቶታል። እንዲህ በአሉባልታ እና መሰረተቢስ በሆነ ወሬ

ደግሞ የሚቆረስ ድንበርም ሆነ የሚለያይ ህዝብ የለም።

ቀልድ ወደ ደም

ተፋዬ በዚህ ክፍል ሌላ ያነሳው ህዝብ ጉራጌ ነው። ጉራጌ በሀረር እንዳይነግድ

የሚኒሊክ ወታደሮች እያሰሩ አስወጥተውታል ብሏል። ትንሽ አለፍ ብሎ ደግሞ ‘’

ጉራጌን እንደፈሪ በመሳል የቀልድ ሙያ መለማመጃ ሲያደርጉት ይታያሉ’’(ገጽ 262)ይለናል።

በተደጋጋሚም በቀድሞው ፕሬዚዳንት መንግስቱ ሃይለማሪያም ስለረሸኑት ጀግናው

ታሪኩ አይኔ እያነሳ ጀነራሉ ጉራጌ ስለሆነ ይህ ግፍ እንደተሰራበት ሊያሳምን

ይጣጣራል (ገጽ 216--)። አንዲህ አድረጎ እጅግ ሰላማዊውን ፣ ጠንካራ ሰራተኛውንና

ቀልዱን በፍቅር ተቀብሎና አብሮ ስቆ በስራውላይ ብቻ አተኩሮ የሚኖረውን ውብ

ህዝብ ለተንኮል አላማው ደጋግሞ ቀዳዳ እየፈለገና ብጥቅጣቂ ነገሮች እየደረተ

ይወተውተዋል።

ተስፋዬ ይህን ይበል እነጂ የጉራጌ ህዝብ የሌለበት የኢትዮጵያክፍል ያለ

አይመስለኝም። ደመቅመቅ ያለ ሱቅ እና ሸቀጣ ሸቀጥ ካለ ያሱቅ የጉራጌ ነው። ንግድ

ተፈጥሮዋዊ ተሰጥኦው እስኪመስል ድረስ ያምርለታል። ደግሞ በጣም በቀላሉ

ተግባቢ ስለሆነ የትኛውም ሃገር ሄዶ ሰዎች ይለምዱታል እሱም ይለምዳቸዋል። ለዚህ

ምስክር አልጠራም እራሱ የጉራጌ ህዝብ እና መላው ኢትዮጵያዊ ይህን የውቃልና።

ስለ ግድያ ካወራን የደርግ መንግሰት ጀነራል ታሪኩን ብቻ ሳይሆን በደርዘን የሚቆጠሩ

ጀነራሎችን ረሽኗል። እዛው የኤርትራ ምድር ላይ የሶማሌን ወረራ የመከቱልንን

ጅግናው ጀነራል ደምሴ ቡልቱን እና ሌሎችንም አስገድሎ እሬሳቸውን ሳይቀር

በመኪና መሬት ለመሬት እንዳስጎተተው ሰምተናል። ተስፋዬ ግን ተረኛውን ለአመጽ

ተቀስቃሽ ጉራጌን የሚቀሰቅስበት ብጥቅጣቂ የነገር ዲሪቶ ሁሉ ሰባሰቦ በአገር እና

በብዙ ሰዎችላይ ይፈጸም የነበረን በደል በአንድ ህዝብ ላይ ብቻ እንደደረሰ አድረጎ

ያቀርበዋል።

ኢትዮጵያ በሁሉም ልጆቿ መስዋእትነት ታፍራ እና ተከብራ የኖረች ሀገር ናት።

የጉራጌ ልጆች ፈሪ ናቸው ለጦርነት አላሰልፋቸውም ብላም አታውቅም። ለዚህም ነው

ጀግናው ታሪኩ አይኔን፣ ጀነራል ተስፋየን፣ እና ሌሎችንም ጀነራል አድርጋ ትልልቅ

እና ወሳኝ የጦር ብረጌዶቿን እንዲመሩ ያደረገችው። እነርሱም በጀግንነት እና በብቃት

ተወጥተዋል። ደግሞስ በነዛ ዘመናት ኢትዮጵያዊ ከመሆን ሌላ የሃገሪቱ ሰራዊት አባል

Page 17: ማርከሻ ለ የሞት መርፌ - api.ning.comapi.ning.com/files/poTC6m2b82rkMz38uXDa*sLOeRr2Zc*dkAn32... · ውስጥ እያለ ‘’ የቡርቃ ዝምታ’’ በሚል

ደጃዝማች አብቹ ማርከሻ ለ-የሞት መርፌ

16

ለመሆን የብሄር ኮታ መች ተደልድሎ የውቅና? ተስፋዬ ይህን እውነት ጥሶ አገር

አድማ በጉራጌ ላይ የተሳለቀች አስመስሎ ይጽፋል። የመንደር ወሬ እና የዋዘኞች

ቧልት የሃገር አቁዋም ወይም የአንድ ህዝብ መለኪያ ተደርጎ ሊወሰድ አይችልም።

በዚህ አጋጣሚ ግን አንድ ነገር ማለት እፈልጋለሁ። በኛ ሃገር አማረልን ብለው እንዲህ

በእሳት ላይ ቤንዚን በሚረከፈከፍበትና መቻቻል ባቃተን ዘመን ኮሜዲያን እና

የየመንደሩ ተዘማናኞች ሃላፊነት በጎደለው ሁኔታ በዘር እና በቋንቋ ላይ የሚቀልዱት

ቀልድ ፖለቲካዊና ማህበራዊ መዘዙ ብዙ ነው እና መጠንቀቅ ያሻል።

ተስፋዬ ስለ አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ እና ተክለሃይማኖት ባነሳበት ክፍል ከእርሱ

በፊት ርእሰ ጉዳዩን ያነሱ ሰዎችን ያስታውሰንና ልቡን ሰቅዞ ወደያዘው ህዘቦችን

ወደማጋጨቱ አብይ ነገሩ በፍጥነት ይታጠፋል። እንዲህ በማለት’’…….ዳኛቸው ወርቁ የሸዋ

አማራ ልጅ በመሆኑ ተረፈ እንጂ ጸሃፊው ላፒሶ ዴሌቦ ቢሆን ኑሮ ጉዳዩ የፖለቲካ መልክ መያዙ

አይቀርም ነበር (ገጽ 316)።’ ተስፋዬ ከጠቀሰው ስም (ላፒሶ ዴሌቦ) እንደምንረዳው

አንግዲህ አሁን ደግሞ ተራው የከንባታ ወይም የሃዲያ መሆኑ ነው። ጽጌ ስጦታው

እና በአውቀቱ ስዩም በዚሁ ጉዳይ ላይ እንደጻፉ ነግሮን አነዚህ ሁለቱም አማራና

ኦርቶዶክስ በመሆናቸው በቀላሉ ታልፈዋል ይለናል። መልሶ ግን ጽጌ ለህይወቱ ፈርቶ

ተሸሽጎ ነበር በእውቀቱ ደግሞ ተደብድቦ ጉዳት ደርሶበት ነበር ብሎናል (ገጸ 317)።

ታዲያ ከዚህ በላይ ምን እንዲሆኑ ነበር የሚፈልገው? ሌላ ማንስ ቢሆን የጻፈው ከዚኅ

የበለጠ ምን ጉዳት ይደርስበት ነበር?

በአለም ላይ በእምነት ጉዳይ የመስቀል ጦርነትን ጨምሮ ብዙ ግጭቶች ተነስተዋል።

በጥንቷ ሮማ ብዙ ክርስቲያኖች በሮማ ቄሳሮች ላራዊት እእየተሰጡ፣ በሳት

እየተቃጠሉ፣ በሰይፍ እየተሰየፉ፣ በዘይት እየተቀቀሉ ተፈጅተዋል። ምድር ጠፍጣፋ

ሳትሆን ክብ ናት፣ ምድር በጸሃይ ዙሪያ ትዞራለች እና የመሳሰሉትን ሳይንሳዊ

አስተሳሰብ ለአለም በመጀመሪያ ያቀረቡ አባቶች ከእምነት ተጻራሪ (ኑፋቄ) አስተምህሮ

ተቆጥሮባቸው ህይወታቸውን አጥተዋል። ከእምነት አፈንጋጭ ነው በተባለ

አስተሳሰባቸው ምክኒያት በአለም በየትኛውም እምነት ተከታዮች መሃል በሚነሳ

አለመግባባት ብዙዎች ህይወታቸውን አጥተዋል። ይህ ግን ምናልባት የእምነቱ

አስተምህሮ የፈጠረው ሁኖ ሳይሆን በሰዎች የግንዛቤ ደረጃ እና ተፈጥሮዋዊ ማንነት

የመጣ ሊሆን ይችላል። እንዲህ ያለውን አለማቀፋዊ ችግር አካባቢያዊ አስመስሎ

በማቅረብና ኢትዮጵያዊያንን ለመበጥበጥ መሞከር ደግሞ ከንቱ ጥረት ነው።

ተረኞቹ ተጋጭዎች

Page 18: ማርከሻ ለ የሞት መርፌ - api.ning.comapi.ning.com/files/poTC6m2b82rkMz38uXDa*sLOeRr2Zc*dkAn32... · ውስጥ እያለ ‘’ የቡርቃ ዝምታ’’ በሚል

ደጃዝማች አብቹ ማርከሻ ለ-የሞት መርፌ

17

ተስፋዬ በሆላንድ ስደቱ የስደተኞች መቀበያ ካምፕ ውስጥ ስለተዋወቀው ብሩክ

የሚባል ኦሮሞ ልጅ እና ስለደረሰበት አስከፊ ነገር ያወጋናል (ከገጽ 51-53) ። አሁን

ደግሞ ተራው የኦሮሞ እና ትግሬ ነው። ብሩክ አገርቤት እያለ በኦነግነት ተጠርጥሮ

ስቃይ ደርሶበታል። ሰለመጠርጠሩ እያወጋ የኦነግ አባል ሳይሆን ነህ የተባለበትን ነገር

ለተስፋዬ ሲያስረዳ

‘’ ችግሩ ምን መሰለህ? ገራፊዎቹም መርማሪዎቹም ትግሬዎች ነበሩ። ኦሮሞ

የሚውጣቸው ስለሚመስላቸው ይፈሩታል። ‘መስማት የተሳናቸው’ ይላቸዋል

ሰው ሁሉ።…አስገብተው ተጫወቱብኝ። ተመልከቱ ጀርባዬን…” ‘’ አለን ይለንና

‘ለሶስተኛ ጊዜ ከናቴራውን አውልቆ ጠባሳውን አሳየን። እንደ ገጠር የእግር

መንገድ የቀጠኑና የተሰባጠሩ መስመሮች ጀርባው እስኩዌር ደብተር እስኪመስል

ድረስ ወረውታል።’’

ብሎ ልጁ የደረሰበትን መከራ የአይን እማኝነቱን ይሰጠናል። እነዚህ ነገሮች

አልደረሱም ብሎ መከራከር አይቻልም ይሆናል እነዚህ ነገሮች ግን ለተለየ የፖለቲካ

አላማ እንዲውሉ ሲደረጉ መጠንቀቅ ያሻል። አስገራሚው ግን ትላንት እሱ

ከኢህአዴግ ጋር ሁኖ አማራውን ለማስጠላት እንደሰራው ዛሬ ደግሞ ትግሬን

ለማሰጠላት መስራቱ ነው። ተስፋዬ አውነት እና ፍትህ ፈልጎ ቢሆን ይህን ያደረገው

አበጀ በተባለለት። እርሱ ግን አስቀድሞ እንደተጠቀሰው የሻብያን ስውር ተንኮል

አሳክቶ ኢትዮጵያ ስትበጣበጥ እና ስትፈራርስ ለማየት እንደቀድሞው ሁሉ ቤንዚን

እሳቱላይ ያርከፈክፋል። ያራግባል። ደግሞስ ሆን ብሎ እንጂ አንድ ጎሳን ለይቶ

በገራፊነት ምን አስጠራው? ያንጊዜ ‘’የቡርቃ ዝምታን’’ ጽፎ አማራን እና ኦሮሞን

ሊያፋጅ ሲሰራ ‘’ አሹ!’ ያሉለትን አሁን ደግሞ በተመሳሳይ መስፈሪያው እየዘገነላቸው

ነው። ሁሉም ጥረቱ ግን ኢትዮጵያን ለማፍረስ ነው እና ‘ኢትዮጵያዊነኝ!’ አና

‘ኢትዮጵያን እወዳለሁ!’ የሚል ሁሉ ልብ ሊገዛ ያስፈልጋል። በሌላው ህዝብ ኪሳራ

እና ውድቀት ላይ የሚመሰረት መንግስትም ሆነ ስልጣን እርም ብለን ልንተው

ይገባናል።

ተስፋዬ ከዚህ ቀደም በጻፈው ‘የጋዜጠኛው ማስታወሻ’ የሚል መጽሃፉ እንዴት አጅግ

በጣም ከቅን አሳቢነት ወደ ዘረኛነት እንደተለወጠ እና ማን እንደለወጠው ይነግረናል።

ተስፋዬ እጁን ሰጥቶ/ ኮብልሎ ከሕውሃት እንደተቀላቀለ ኢያሱ የሚባል የሕውሓት

ሰው

‘‘ የብሄር ጭቆና መኖሩን አታምንም? ሲል ጠየቀኝ፣

ተስፋዬ፡ ‘‘አስቤው አላውቅም’’

Page 19: ማርከሻ ለ የሞት መርፌ - api.ning.comapi.ning.com/files/poTC6m2b82rkMz38uXDa*sLOeRr2Zc*dkAn32... · ውስጥ እያለ ‘’ የቡርቃ ዝምታ’’ በሚል

ደጃዝማች አብቹ ማርከሻ ለ-የሞት መርፌ

18

ኢያሱ፡ ‘በአማራ ገዢ መደብ ተጽእኖ ስር ስላደግህ ለጊዜው ልታየው

አትችልም።አማራ ባትሆንም በአመለካከትህ የአማራው ገዢ መደብ ሰለባ ሆነሃል’

አለኝ’’ ይለንና

‘’የአማራው ገዢ መደብ የሚለው ቃል በተደጋጋሚ ይነሳ የነበረ ሲሆን መጀመሪያ ላይ

በፍጹም ልረዳው ተቸግሬ ነበር። በዘራቸው አማራ የሆኑትን የልጅነት ጓደኞቼን

በማሰብ፣በስነጽኁፍ እንድዳብር ከልብ የሚያግዙኝን በዘራቸው አማራ የሆኑ

ደራሲዎች በማሰታዎስ፣ አሳቡን በአእምሮዬ ቦታ ሰጥቼ ላሰተናግደው በጣም

ተቸገርኩ። እኔና አብሮ አደግ ጓደኞቼ የዘር ጉዳይ ልዩነቱን በፍጹም አናውቅም ነበር።

እናቶቻችን እሳትና እንጀራ እየተበዳደሩ አሳድገውናል። ስለ አማራ ገዢ መደብ

ማንሳት ያንን የዳበረ የልጅነት ፍቅር፣ ማንነቴ የተገነባበትን መሰረት የሚያፈርሰው

እየመሰለኝ እጨነቅ ነበር።’’ ብሎን ያሳርጋል ። ከዛም ይሄው ኢያሱ የሚባል ሰው

ስለ ሕውሓት አላማ ሲያስረዳው ‘’……’ደርግን በመጣል ከተቃዋሚ ሃይላት ጋር

ሁሉ እንስማማለን! የሚያለያየን ደርግ ከወደቀ በጛላ አገሪቱ የምትመራበት ፖሊሲ

ነው’ ‘’ እንዳለው ጨምሮ ያበስረናል። ( ተስፋዬ ገ/አብ፣ የጋዜጠኛው

ማሰታወሻ፣ ገጽ 62፣64)

ተስፈዬ ይህን ሁሉ ሲል አውነቱን ይሆናል። ደግሞም ነው። አሁን ጥያቄው ይህን

የሚነግረን እንደተራ ያለፈ ዘመን ትረካ ነው ወይስ ሌላ አላማ አለው? የሚለው ነው።

ተስፋዬ አሁን በዘረኝነት እንደሚያምን ተረጋግጧል! በማመኑም ነው ኦሮሞን እና

አማራን ለማፋጀት ከዚህኛው መጽሃፉ በፊት ‘’የቡርቃ ዝምታ’ የሚለውን መጽኃፍ

በ1992 ዓ.ም የጻፈው። በቅርብ በተገኘበትም መረጃ ‘’ኤርትራዊነት ይሰማኝ የነበረው

ግን ገና ህጻን ልጅ ሳለሁ ነበር’…በፖለቲካ አመለካከቴ አኔ ጸረ-ወያኔ አቁዋም የያዝኩት ወያኔ

ጸረ ኤርትራውያን ወይም ጸረ-ሻብያ አቁም በመያዙ ብቻነው’’ ብሏል። ይህን ማንነቱን እና

አቋሙን ከተረዳን ታዲያ ከላይ ከመጽኃፉ የጠቀስኩትን ያለው ለምንድን ነው

የሚለውን ጥያቄ መመለስ ይቀለናል። አሩቅ ሳንሄድም ተስፋዬ እራሱ

‘’ባለፉት 10 አመታት ለሻብያ መረጃ እና ጥቆማ በመስጠት ሰርቻለሁ። ከሰጠሁት

ጥቆማ በላይ እነዚህን ጥቆማዎች ለመስጠት በተደረገ እንቅስቃሴም ሁለት መጻህፍት

( የጋዜጠኛው እና የደራሲው ማስታወሻ) ለመጻፍ ችያለሁ። እነዚህ ሁለት መጻኅፍት

ያስገኙት ፖለቲካዊ ፋይዳ በጣም ከፍተኛ መሆኑን ለመገንዘብ በአንድ ባለሙያ

ማስጠናት ብቻ በቂ ነው።’’

ብሎ ጀብዱውን ሲያበስር ከላይ የጠቀስኩትን የጻፈበትን ምክኒያት ነገረን። ይህ ጀብዱ

ደግሞ እበቀለዋለሁ ያለውን ሕውሓትንና የትግራይን ህዝብን በቀሪው ኢትዮጵያዊ

ማሰጠላት ነው። ቀሪዎቹ ኢትዮጵያውያን ‘’እንዲህ ቅኑን ሰው ሊያበላሹ እንደሰበኩት

በኢትዮጵያ ህዝብ መሃል የመጣውን መለያየት እና ያለመተማመን ያመጡት ሕውሓት

Page 20: ማርከሻ ለ የሞት መርፌ - api.ning.comapi.ning.com/files/poTC6m2b82rkMz38uXDa*sLOeRr2Zc*dkAn32... · ውስጥ እያለ ‘’ የቡርቃ ዝምታ’’ በሚል

ደጃዝማች አብቹ ማርከሻ ለ-የሞት መርፌ

19

አና ይህም ድርጅት የፈለቀበት ህዝቦች ናቸው። እንዲህም አድርገው ኢትዮጵያን

በዘረኝነት በጠበጧት’’ ብሎ ህዝብ እንዲነሳባቸው በረቀቀ መንገድ ይቀሰቅሳል።

ተስፋዬ አሁን በጻፈው መጽኃፉ ላይ ደብረዘይት ያውቃት የነበረች አንዲት ልጅ

ደቡብ አፍሪካ አግኝቷት ስለ እናቷ ስትነግረው ‘እናቴ እንደድሮው ሹሩባ አትሰራም፣

በወርቆቿ አታጌጥም…’ ብላ እንደነገረቸው እና እናቷ ተሳቀው እና ተሸማቀው

እንደሚኖሩ ነግሮናል። እንግዲህ ይህን ነው በጥናት ሊረጋጋጥ ይችላል የሚለንና

የትግራይ ህዝብ በሌላው ኢትዮጵያዊ እንዲጠላ ማድረጉን የሚያውጀው።

ኢትዮጵዊያዊያን ያንን የሚያጓጓ ተስፋዬ ባደገበትን ዘመን የነበረ የህዝባችንን ትስስር

ጠብቀን ለመኖር አሁን ነው መንቃት። ያንን ውብ ማንነታችንን ሊያናጋ እና

ኢትዮጵያን ሊያፈራርስ ዛሬም ጉድጓድ የሚቆፍረው ሻአብያ የሚሸርበውን ሴራ

ሳናውቅ ተባባሪዎች ልንሆን አይገባም። የትግራይ ህዝብ የኢትዮጵያ ጌጥ ነው! ባህሏ፣

ትሁፊቷ፣ ቁዋንቋዋ፣ ሃይማኖቷ፣ ጀግንነቷ…. በዚህ ውብ ህዝብ የተጌጠ እና አገሩ

ኢትዮጵያ እና ወገኖቹ ኢትዮጵያውያንም የሚኮሩበት ነው። ‘’በጥባጭ ካለ ጥሩ ውሃ

አይጠጣም’’ እንዲሉ ነገሮች መልካቸውን እንዳይለውጡ ግን ህዝባዊ ትስስሩን እና

መከባባሩን ተጠንቅቀን መጠበቅ ይኖርብናል። ‘’የዘመድ ጥል፣ የስጋ ትል’’ እነዲሉ እኛ

መሃል የተፈጠረ ነገር ቢኖር እንኳን የእኛው የቤተሰቡ አባላት ጉዳይ ነው። ለሁሉም

ይህ ሰውዬ የሚጽፈው ‘ደግ’ የሚመስል ነገር ሁሉ በጥንቃቄ መፈተሽ የሚያሻው ሆኖ

አግኝቼዋለሁ። ይህንንም ለአብነት እንዲሆን ብቻ ነው ቀንጭቤ ያቀረብኩት።

ተስፋዬ ‘በአባት አገር’ ፍቅር ተይዞ ህሊናውን ሳይስት አይቀርም¡¡ ያን ጊዜ የኢሃደግ

ባለስልጣን ሆኖ ያራመደውን ፖሊሲ ዛሬም ከፊት ይልቅ አባብሶት ሳለ የቀበሮ

ባህታዊ ለመሆን የሞከረው ሙከራ ምን ያህል ቂል እና ህሊናውን የሸጠ እንደሆነ

አብሳሪነው። ኤርትራ የእናት አባትህ አገሩ ናትና አትውደዳት የሚለው የለም። እኛም

አኮ እንወዳታለን። እሷን የመውደዱ ማረጋገጫ ግን ኢትዮጵያውያንን ማስተራረድ

እና ኢትዮጵያን ማፍረስ መሆኑ አሳዛኝም አስገራሚም ነው። እኛ ኢትዮጵያውያን

ኤርትራን እና የኤርትራን ህዝብ የሚነካብን ዛሬም ቢሆን ያስቆጣናል። ተስፋዬና

መሰሎቹ ቢለያዩንም አሁንም ቢሆን የኢትዮጵያ የተፈጥሮ ወሰኗ ቀይ ባህር ሲሆን

የህዝቦቿም ምንጫችንም፣ ደማችንም አንድ ነው።

አብቹ ነጋ ነጋ

Page 21: ማርከሻ ለ የሞት መርፌ - api.ning.comapi.ning.com/files/poTC6m2b82rkMz38uXDa*sLOeRr2Zc*dkAn32... · ውስጥ እያለ ‘’ የቡርቃ ዝምታ’’ በሚል

ደጃዝማች አብቹ ማርከሻ ለ-የሞት መርፌ

20

ተስፋዬ ከላይ የጠቀስኩትን ብሩክ የተባለ ወጣት የዘፈን ችሎታ አሰታኮ ‘አብቹ

ነጋናጋ’ የሚለውን የቆየ የኦሮምኛ ዘፈን አንተርሶ ወደሌላ ነገሩ ይወስደናል ።

‘’ያለፈው ዘመን ታሪክ ፀሃፊዎች የሙስሊሙንና የኦሮሞውን ታሪክ

በመዝለልና በማጠልሸት ከፍተኛ ጉዳት ማድረሳቸው ይታመናል። ለኢትዮጵያ

ውለታ ከመስራት አንፃር የወረጃርሶው አቢቹ (ልጁ) ከበላይ ዘለቀ የላቀ ሚና

ነበረው። ኤርትራውያንን ጨምሮ ከመላው ኢትዮጵያ የተውጣጡ ወጣት

አርበኞችን በመምራት ፋሽስት ጣሊያንን ያርበደበደ ጀግና ነበር። በታሪክ ውስጥ

ግን የማግለል ወንጀል ተፈፅሞበታል። አቢቹ ዝነኛ ስለነበር፣ አፄ ሃይለስላሴ

ስልጣናቸውን እንደተጋፋ ባላንጣ ሊመለከቱት ተገደው ነበር። በመሆኑም አፄ

ሃይለስላሴ ለአቢቹ ታሪክ መጥፋት ቀዳሚ ተጠያቂ ለመሆን ችለዋል።’’ ይለናል።

(የስደተኛው ማስታወሻ ገጽ 58-59)

ታሪኩን ሊያጣቅስ የሞከረው በ አዶልፍ ፓርለሳክ ተጽፎ በተጫነ ጆብሬ

ከተተረጎመው እና ስለ ኢትዮጵያና ጣሊያን የ 1928 ዓ.ም ጦርነት የሚዘክር ‘‘የሃበሻ

ጀብዱ’’ ከተሰኘ እጅግ ግሩም መጽሀፍ ነው። የመጽኃፉ ጸሀፊ ኮሎኔል አዶለፍ

ፓርለሳክ በኢትዮጵያ በራስ ካሳ ይመራ ለነበረው ጦር የጦር አማካሪ የነበሩ ሲሆን

ከአጼ ኃይለስላሴም ጋር በቅርበት የነበሩ ማይጨው ላይ በነበረው የመጨረሻ ጦርነት

የተዋጉ ሰው ናቸው። ይህን የጦርነት ታሪክ ነው የጻፉት። በዚህ አጋጣሚ ለመጽኃፉ

ተርጓሚ ልባዊ ምስጋናዬን ማቅረብ አፈልጋለሁ። እኝህ ሰው -ኮሎኔል አዶለፍ

ፓርለሳክ በትረካቸው ውስጥ ስለ አንድ ልብን ለዘላላሙ ስለሱ በአክብሮት

እነዲታሰብ የሚያስገድድ በጣም ወጣት የኦሮሞ ልጅ በሰፊው ተርከውልናል። ወጣቱ

ልጅ የወረጃርሶ ጦር ፊታውራሪ ልጅ ሲሆን አባታቸው በዘመቻው ሰሞን ታመው

በመሞታቸው ከሁለት ታላቅ ወንድሞቹ ጋር ጦሩን መርቶ የዘመተ ነው። በጦርነቱ

አብቹ ( ልጁ)ብለው አዛዡ ደጃዝማች አበራ ካሳ እና እነ ኮለኔል የሚጠሩት ይህ

ወጣት የጣሊያኑን ጦር ቁም ስቅሉን አሳይቶታል። ይሁንና ድርጊቱ ሌላ የዲፕሎማሲ

ጥረት እያደረጉ በከንቱ ከሚደክሙት ንጉሰ ነገስት ጋር ለጊዜው አጋጨው።

ነገሩ እንዲህ ነው አምባሳደር ዘውዴ ረታ “ የተፈሪ መኮንን ረጅሙ የስልጣን ጉዞ’

በሚለው መጽኃፋቸው አና ሌሎችም እንደ ጻፉት አጼ ሐይለስላሴ ኢጣሊያ

ልተወራቸው ድንበር ስትዘልቅ ለአለም መንግስታቱ ማህበር/ liege of Nations /

በማህበሩ ደንብ መሰረት ድጋፍ እንዲሰጣቸው አቅርበዋል። የአለም መንግስታቱም

ማህበር አውቆ አድፍጦ ሳለ ጣሊያን ወረራዋን አጧጡፋለች። ምንም እንኳን ንጉሱም

ከነሰራዊታቸው ወደ ውጊያው መንደር ቢዘምቱም ይህ ባዶ ተስፋቸው የሳቸው

ሰራዊት በመከላከል ላይ ብቻ እንዲያተኩር እና ጣሊያኖች ‘ወግተውን ነው

Page 22: ማርከሻ ለ የሞት መርፌ - api.ning.comapi.ning.com/files/poTC6m2b82rkMz38uXDa*sLOeRr2Zc*dkAn32... · ውስጥ እያለ ‘’ የቡርቃ ዝምታ’’ በሚል

ደጃዝማች አብቹ ማርከሻ ለ-የሞት መርፌ

21

የወጋናቸው፣ የጦርነቱ ጀማሪዎች እነሱ ናቸው’ እንዳይሉና የ አለም መንግሰታቱ

ማህበር በእኛ ላይ ምክኒያት እንዳያገኝ ብለው ሰራዊታቸው የመከላከል እንጂ

የማጥቃት ውጊያ እንዳያካሂድ አዘዋል። ይህንንም ትእዛዝና ምክኒያቱንም ኮሎኔል

አዶለፍ ፓርለሳክ በዚሁ መጽሃፍ ላይ ጽፈውልናል። ይህ በእንዲህ እያለ አለፍ ገደም

በሚደረጉ ግጭቶች አንድ ወንድሙን (የወረጃርሶውን ሰራዊተ የጦር መሪ) በሞት

ያጣውና ለጊዜውም ቢሆን ሌልኛው ወንድሙ የት እንደደረሰ ያልታወቀው አብቹ

ይህን ደም ሊበቀል እና የጠፋውንም ወንድሙን ሞቶም ከሆነ አግኝቶ ሊቀብር

፣ተማረኮም ከሆነ በሃይል ሊያስለቅቅ ሁለት መቶ ጦር ይሰጠኝ ብሎ ደጃዝማች

አበራን አስፈቅዶ የዘመተ ጀግና ነው። ምንም እንኩዋን የጠፋው ወንድሙ ቆስሎና

አገግሞ ወደ ወገን ጦር ቢመለስና ጦሩን መምራት ቢቀጥልም አብቹግን ጣሊያንን

እያደባ ከፍተኛ ሰብአዊ እና ቁሳዊ ጥፋት እያደረሰ ከመቀጠሉም በላይ በአካባቢው

ሽፈታ ሁነው እና ለጣሊያን ወግነው የሚያሰቸግሩትንም ነዋሪች የዚህ ጽዋ ቀማሽ

አደረጋቸው። በዚህ ጊዜ ነው ታዲያ ይሳካልኛል ብለው እያስታመሙ የያዙት

የዲፕሎማሲ ጥረታቸው መበላሸቱ የተሰማቸው ንጉሰ ነገስት ‘’ ልጁን አስቁሙት!’

ብለው ቀጭን ትዛዝ ለነ ራስ ካሳ የላኩት። (ተጫነ ጆብሬ, የሃበሻ ጀብዱ (1989) ገጽ

183-190፣ 233)

ተስፋዬ ገ/ አብ ታዲያ ከዚያ አኩሪ ታሪክ ውስጥ ብዙ ለሱ ያማየመቸው የታሪክ

አውነታ እንዳለ ስለሚየውቅ የነገሩን መደምደሚያ ሆን ብሎ ትቶ የነገሩን መጀመሪያ

ብቻ ነጥሎ በማውጣት ለተለመደው አማራን በጥቅሉ ንጉሱን እና መንግስቱን በነጠላ

ከጀግናው እና ለሃገሩ ድንበር መከበር ግንባሩን ከማያጠፈው ሁሌም የፊት ለፊት

ተሰላፊ ከሆነው የኦሮሞ ዝብ ጋር ሊያጣላው ነገር የመዘዘው። በነገራችን ላይ በዚህ

መጽሀፍ ( የሃበሻ ጀብዱ) ላይ ጣሊያኖች የኢትዮጵያ ጦር ትግራይ በነበረበት ጊዜ

የትግራይን ህዝብ“ አማራና ኦሮሞ ሊጨቁኗችሁ ነው’’ ብለው እንደቀሰቀሱ ተጽፏል።

ምናልባትም ይህ በብዙ አፍሪካ ሀገራት ቀኝ ገዚዎች የዘሩት እና ዛሬም ሻብያና

ውላጆቹ እነ ተስፋዬ የሚጠቀሙበት ክፉ ዘር የተዘራው ያኔ ነው። ጣሊያኖች

ወደመሃል አገር ከገቡ በጛላና ወደምእራብ ኢትዮጵያ ሲዘልቁ ደግሞ ኦሮሞ አማራን

እንዲያጠፋ ቀስቅሰው እነደነበር በፍቅረማርቆስ ደስታ በተጻፈው የጀነራል ጃጋማ ኬሎ

ታሪክ ላይ እና ጥቁር አንበሳ በሚል የተጻፈ የጥቁር አንበሳ አርበኞችን ታሪክ በሚዘክር

መጻህፍ ላይ ማንበብ ይቻላል። ይህንንው ፈለግ የሚከተለው ተስፋዬም ፋሽኑ

ቢያልፍበትም ለኛ ለ ኢትዮጵያውኑ ገና ትኩስ እና ሁነኛ የማበጣበጫ ቀመር ሁኖለት

እየተገበረው ነው።

Page 23: ማርከሻ ለ የሞት መርፌ - api.ning.comapi.ning.com/files/poTC6m2b82rkMz38uXDa*sLOeRr2Zc*dkAn32... · ውስጥ እያለ ‘’ የቡርቃ ዝምታ’’ በሚል

ደጃዝማች አብቹ ማርከሻ ለ-የሞት መርፌ

22

የሆኖ ሆኖ አብቹ እና ንጉሱ ተጣልተው ሳይሆን የቀሩት እንደሚኮራበት እና

አንደሚሳሳለት ልጅ አትንኩብኝ ተብሎለት ነው። የተወደዱ ኮሎኔል አዶለፍ ፓርለሳክ

ከራስ ካሳ ጦር ንጉሱ ወደሚመሩት የጦር ግንባር ሲደርሱ የሆነውን እንደሚነግሩን

ጃንሆይ ‘’ ልጁን አይታችሁት ታውቃላችሁ? ሲሉ ጠየቁን” ይሉንና ስለልጁ እና

ቀድሞ ከንጉሱ ጋር ስለነበረው ታሪክ የሚያውቁት ኮሎኔሎች በጥርጣሬ መልስ

መስጠት ሳይፈልጉ ሲቀሩ ንጉሱ መልሰው ‘’ግድየለም እንደናንተም ባይሆን ይህች

አንድፍርዬ ደጃዝማች ከኛም በላይ ትልቅ ጀብዱ እየሰራች አንደሆነ እንሰማለን’’ አሉ

ይሉናል። ከዚህም በላይ ጦርነቱ በሽንፈት ተጠናቆ እና ንጉሱ በተቻለ መጠን

ህይወታቸው ተርፎ እንዲመለሱ የጦር አለቆች ሁሉ በሚመክሩበት ሳአት የልጁ ጦር

በራያና አዘቦዎች ተከቦ ውጊያ ላይ ስለነበር ንጉሱ ‘’ አሻፈረኝ ልጁን ብቻውን ጥለን

አንሄድም’’ ብለው ነበር ይሉናል። ((ተጫነ ጆብሬ, የሃበሻ ጀብዱ(1989)፣ ገጽ 288፣

316)

ልጁ ከጦር አዣዡ ከራስ ካሳ ልጅ ከደጃዝማች አበራ ጋር ከታላቅ እና ታነሽ

ወንድምነትም የጠነከረ ፍቅር የሞላባቸው እና አንዳቸው ለሌላቸው በጣም የሚሳሱ

እንደሆኑ መጽኃፉን ያነበበ ሁሉ በእንባ ጭምር የሚረዳው ነው። ወጣቱ ደጃዝማች

አበራ እና አብቹ እንደገና ሊገናኙ እና ውጊያቸውን ሊቀጥሉ የሰላሌ ሜዳ ላይ

ተስማምተው መለያየታቸውን የነገሩን ኮሎኔል አዶለፍ ደጃዝማች አበራ ጦሬን በኔ

ምክኒያት አላሰጨርስም ብሎ በጣሊያኖች ተይዞ እንደተገደለም ነግረውናል። (ተጫነ

ጆብሬ, የሃበሻ ጀብዱ(1989)፣ ገጽ 317፣ 318፣243)

እንግዲህ የደጃዝማች አበራም ይሁን የ አብቹ እንዲሁም እልፍ አእላፋት በየፈፋው

ለዚህች አገር የወደቁና የጆብራ እራት ሆነው የቀሩ ጀግኖች ታሪካቸው ሳይጻፍ

በጅምላ ግን እየተዘከሩ ይኖራሉ። እውነት ነው የዚህ የአብቹ ታሪክ ግን ካለበት ታስሶ

ሊወጣ ይገባ የነበረ ሲሆን ይመስለኛል የ ደጃዝማች አበራም መሞት ተጨምሮበት

አልተጻፈም። ተስፋዬ ግን ይህንን ለክፉ አላማው ተጠቀመበት። ጨምሮም የጎጃሙን

በላይ ዘለቀን በመጥቀስ ዙሪያገብ ቁርሾ ቀስቃሽ ‘’አዛኝ ቂቤ አንጓች’’ ሆነ። በላይ

ዘለቀን ባነሳበት ቅጽበት እንኳን ቢሆን በለመደው ‘’እገሌ ከገሌ ይበልጣል’’ የቅኝ

ገዚዎች ተንኮል እነዚህን ውድ አርበኞች አና በነርሱ ዙሪያ ያሉ ህዝቦችን ፉክክር

ውስጥ ማሰገባት ይፈልጋል እነዲህ ብሎ ‘’ለኢትዮጵያ ውለታ ከመስራት አንፃር

የወረጃርሶው አቢቹ(ልጁ) ከበላይ ዘለቀ የላቀ ሚና ነበረው። ‘’ ። እንደአውነቱ ከሆነ ግን

ማንም ለሃገሩ የመጨረሻ ኅቅታውን ሊሰጥ እስከጨከነና ያንንም አስካደረገ ድረስ

አገር ለዚህ ውለታ አመሳሶ አታወጣም። ሕይወት የመጨረሻ ዋጋ ነዋ!

Page 24: ማርከሻ ለ የሞት መርፌ - api.ning.comapi.ning.com/files/poTC6m2b82rkMz38uXDa*sLOeRr2Zc*dkAn32... · ውስጥ እያለ ‘’ የቡርቃ ዝምታ’’ በሚል

ደጃዝማች አብቹ ማርከሻ ለ-የሞት መርፌ

23

ታሪክንና የአብቹንም ሆነ ሌሎች የያንጊዜውን የጀግኖቻችን የጦር ሜዳ ውሎ

በተመለከተ ግን ኮለኔሉ ከሳት ተርፈው ባገኙት ደህና አጋጣሚ ባይጽፉት በዛ የጭንቅ

ወቅት ብዙ ልጆቿን ላጣች ሀገር እና የመጻፍ ልምዱም ላልነበረው ህዝብ ስለምንም

ነግረ ለማወቅ ባልተቻለ ነበር። ተስፋየ ግን ልክ ያንጊዜ የነበረ እና ንጉሱ ያደረጉትን

ሁሉ እንደተከታተለ ሰው በስሜት ይህን ሁሉ ለማለት መድፈር ባልተገባውም ነበር።

ግን አንደው እንደዚያ በመልካምድራዊ ተፈጥሮዋ እና በደጋግ ህዝቦቿ አሞላቃ እና

አስቦርቃ ላሰደገች አገር እና ለደጋግ ልጆቿ ምላሿ ይህ መሆኑ ለተስፋዬ ጥሩ ሆኖ

ይሆን?

የበጋው መብረቅ ጃጋማ ኬሎ

ተስፋዬ ‘’የአብቹ ታሪክ ሳይጻፍ ቀረ’ ብሎ ‘መሪር ሃዘኑን’ እየገለጠ በወቅቱ በነበራቸው

እድሜ እና በፈጸሙት እጅግ የሚደንቅ ጀብዱ የአብቹ እኩያ የሆኑትና የኢትዮጵያ

የዘላለም ባለውለታ ሁነው ሲወደሱ የሚኖሩትን አንድ የኦሮሞ ልጅ ግን ዛሬ በህይወት

ተጘኝተው ታሪካቸው ተጽፎ ታሪክ መስካሪ በመሆኑ ሲያጣጥላቸው እና

ሲወነጅላቸው ይታያል። የእሱ አላማ ባገኘው ቀዳዳ የነገር ሰበዝ መዞ ኦሮሞን

ማነሳሳት እንደሆነ የሚያሳብቅበትም አንዲህ ያለው ነገሩ ነው። እኝህ ሰው ጣሊያንን

መውጫ መግቢያ ያሳጡ በወቅቱ ከ16 አመት የማይበልጣቸው ወጣት የነበሩ እና

ከአዲስ አበባ 40 ኪ.ሜ ላይ በምትገኘው አዲስ አለም ሰፍሮ የነበረውን የጣሊያንን

ጦር ጨፍጭፈው የጦር መጋዘኑን ዘርፈው በትልቅ ፍርሃት እንዲርበደበድ ያደረጉ፣

በጅማና አከባቢዋ ሰፍሮ የነበረውን የጣሊያንን ጦር አውድመው በመቶዎች

የሚቆጠሩ ጣሊያኖች የማረኩና ሌሎች ቁጥረብዙ ጀብዱዎች የፈጸሙ ምርጥ

የኢትዮጵያ ጀግና ልጅ ናቸው። ጀነራል ጃጋማ ኬሎ ይባላሉ!!!!

ጀነራል ጃጋማ ኬሎ አባዶዮ የሚባሉ ሰው የአጎት ልጅ ሲሆኑ አባዶዮ በጣም

አስተዋይና የአጼ ኃይለስላሴ መንግስት ፓርላማ አባል ሆኖም የመንግስትም ተቃዋሚ

የሆኑ የኦሮሞ ባላባት ናቸው። ከዚህ ቀደም እንደጠቀስኩት ጣሊያን የኦሮሞን ህዝብ

ቀስቅሶ አማራን ሊያስደመስስ እና እርስ በርስ አጠፋፍቶን ለራሱ ሊያርፍ ሲሰራ ይህን

ተንኮሉን አባዶዮ’በጥበብ አክሽፈውበታል። ‘’ኦሮሞና አማራ እንደሰርገኛ ጤፍ

የተደባለቀ ነውና ከራሳችን ልንለየው ስለማንችል አንዳትነኩት’’ ብለው በጣሊያን ‘’

ከኣማራ ነጻ የምትወጡበት ጊዜ አሁን ነው’’የሚል ቅስቀሳ ተቀስቅሰው አማራን

ለመደምሰስ ምክር ለጠየቋቸው የኦሮሞ ልጆች የጥበብ ምክር ሰጥተው ጣሊያንን ጉድ

አርገውታል። ከዛም በላይ የውስጥ አርበኛ በመሆን የጣሊያንን ሚስጥር እያወጡ

Page 25: ማርከሻ ለ የሞት መርፌ - api.ning.comapi.ning.com/files/poTC6m2b82rkMz38uXDa*sLOeRr2Zc*dkAn32... · ውስጥ እያለ ‘’ የቡርቃ ዝምታ’’ በሚል

ደጃዝማች አብቹ ማርከሻ ለ-የሞት መርፌ

24

ለጀግናው ወጣት ጃጋማ ኬሎ በመስጠት ድርብርብ ድል አስመዝግበዋል። (

ፍቅረማርቆስ ደስታ፣ ጃጋማ ኬሎ፡የበጋው መብረቅ (2001)፣ ገጽ 15-18)

እንግዲህ ይህ በፍቅረማርቆስ ደስታ የተጻፈው የህይወት ታሪካቸው ተስፋዬን እና

መሰሎቹን አልተመቻቸውም። በዚህም ምክኒያት በ’’የስደተኛው ማስታወሻ’’ ላይ

‘’የሻንቡ ንጉስ’’ በሚለው ክፍል ጀነራሉን በነዋቆ ጉቱ የተመራውን የኦሮሞ አማጺ ጦር

ደምስሷል ብሎ ይወነጅላቸዋል። “ኦሮሞን በኦሮሞ መምታት የቆየ ስልት ነበር። በሃይለስላሴ

ዘመን የዋቆ ጉቱን እና የጃራ አባገዳን ንቅናቄ የቀጠቀጠው ጃጋማ ኬሎ ነበር (የስደተኛው

ማስታወሻ ገጽ 185)።” በማለት።

ተስፋዬ በደንብ ቢያመዛዝን ኑሮ (ለነገሩ አይፈልግም) አባዶዮንም ሆነ የዛሬውን

ጀነራል የያኔውን የ16 አመት ወጣት አገራቸውን እና ህዝባቸውን ከጥፋት ለመታደግ

እንደዛ ያረባረባቸውና ከጣሊያን ጋር ያስተናነቃቸው የንጉስ ትእዛዝ አልነበረም።

በውስጣቸው የነበረው ጽኑ ኢትዬጵያዊነት እንጂ። ንጉሱ እራሳቸውም አልነበሩማ።

ቢኖሩ እንኳን አባ ዶዮ መቼ ከንጉሱ ጋር ተስማምተው ያውቁና!? ይህ እንዲህ ከሆነ

ደግሞ ጀነራል ጃጋማ ኬሎን ከነዋቆ ጉቱ ጋር ተዋግተው ኢትዮጵያን ከጥፋት

እንዲያድኑ ያደረጋቸው የኢትዮጵያን አንድነት መውደዳቸው እንጂ ተስፋዬ እንዳለው

የንጉሱ ኦሮሞን በኦሮሞ የመደምሰስ ጥበብ አይደለም።

ይህን ለማረጋገጥ ጀነራል ጃጋማ ኬሎ ኢህአዴግ ስልጣን ሲይዝ ‘ቶኩችማ’ የሚባል

የኦሮሞ ድርጅት ሊቀመንበር ሆነው ወንበር ከተሰጣቸው ጀነራል ዋቆ ጉቱጋር

ሲጨዋወቱ ጀነራል ዋቆ ‘’ ጀነራል ለምንድን ነው የኦሮሞ ድርጅትን የማይደግፉ….”

ብለው ለጠየቋቸው ጥያቄ ጀነራል ጃጋማ ኬሎ መልስ ሲሰጡ፡

‘’ እኔ ኢትዮጵያዊ አሮሞ ነኝ፣ የኢትዮጵያ አሮሞ ደግሞ ከአምስት መቶ አመት በላይ

ኢትዮጵያ ውስጥ የኖረ ነው። ስለዚህ እዚህች አገር ከኦሮሞ የበለጠ ኢትዮጵዊ የለም ብዬ

አምናለሁ። በመሆኑም አሮሞ የኢትዮጵያ ግንድ ነው። ግንድ እንዴት ይገነጠላል?! ግንድ

አይገነጠልም። ግንድ ከተገነጠለ ዛፉ ወደቀ ማለት ነው፣ የሚገነጠል ቅርንጫፍ ነው። አሮሞ

የኢትዮጵያ አለኝታ ነው፣ ብዛት አለው፣ ጭንቅላት አለው፣ ጀግንነት አለው፣ ህብረት

አለው…ተምረን፣ ታግለን፣ የተለያዩ ቁዋንቋወች አውቀን ኢትዮጵን መምራት አለብን እንጂ

ተጠያቂው ልገንጠል ብሎ ጠያቂ ሲሆን ልተባበረው አልችልም… ’’ ያሉትን ማየት በቂ

ነው።

ይህን ተከትሎም ጀነራል ዋቆም ከዚህ ጊዜ በጛላ የቅርንጫፍነቱን ሃሳብ ትተው

በግንዱላይ አተኩረዋል። (ፍቅረማርቆስ ደስታ፣ ጃጋማኬሎ (2001) ገጽ 210)

Page 26: ማርከሻ ለ የሞት መርፌ - api.ning.comapi.ning.com/files/poTC6m2b82rkMz38uXDa*sLOeRr2Zc*dkAn32... · ውስጥ እያለ ‘’ የቡርቃ ዝምታ’’ በሚል

ደጃዝማች አብቹ ማርከሻ ለ-የሞት መርፌ

25

ከዚህ በተጨማሪ አንድ አገር የተወሰነ አካባቢ የጦርነት ችግር ሲገጥማት የአካባቢውን

መልካምድር፣ የህዝቡን ቋንቋ እና ባህል የሚያውቅ የጦር መሪ መላክ በአለም ሁሉ

ያለ ወታደራዊ ስኬትን አጎና ጻፊ ታክቲክ ስለሆነ ንጉሱ ይህን አድርገውት እንኳን

ቢሆን የሚያሳማ አይደለም። ጀነራሉ ጀነራል የሆኑት አገራቸውን ከማንኛውም ጥቃት

ሊከላከሉም ስለሆነ በወታደራዊ ብቃታቸው ላይ ከላይ የጠቀስኩት መስፈርት የበለጠ

ተመራጭ አድርጓቸዋል። አበቃ።

አሮሞ እንዲበጣበጥ በነሻአብያ ተስፋ ተጥሎባቸው የነበሩት ጀነራል ዋቆም ከጀነራል

ጃጋማ ጋር ሀሳብ ከተለዋወጡ በጛላ የቀደመውን ሃሰባቸውን ሰርዘው በግንዱ ላይ

የሚያተኩሩ መሆናቸው ሻአብያን እና ተላላኪውን ተስፋዬን አስቆጥቷል። ለዚህም

ነው ጀግናውን ጀነራል ጃጋማ ኬሎን በኦሮሞ ህዝብ ሊያስነቅፍ የተነሳው። አውነቱ

ግን ይሄ ነው ‘አሮሞ ግንድ ነው’ ቅርንጫፍ ብቻ ነው ልገንጠል የሚለው። ጦሰኛውን

ሻአብያን ጥሎባት ነው እንጂ ኤርትራም ግንዱ የበቀለባት ስር ነች!! አሮሞ ደግሞ

በቀለም እና ወረቀት ባይጻፍም የተጻፈ ታሪክ አለው። አሱ እራሱ እና አገሩ፣

ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውንም ታሪክ ናቸዋ። የባለታሪኮች አገር እራሷ ታሪክ ነች!

ዘር ማጥራት

Page 27: ማርከሻ ለ የሞት መርፌ - api.ning.comapi.ning.com/files/poTC6m2b82rkMz38uXDa*sLOeRr2Zc*dkAn32... · ውስጥ እያለ ‘’ የቡርቃ ዝምታ’’ በሚል

ደጃዝማች አብቹ ማርከሻ ለ-የሞት መርፌ

26

በዚሁ የሻንቡ ንጉስ በሚለው ክፍሉ ተስፋዬ በወለጋ ጫብሬ የሰፈሩ እውነተኛ

ኦሮሞ ያልሆኑ ጎንደሬዎች አሉ ብሎ እንደተለመደው ሊያጠፋፋቸው ይሰብካል

(ገጽ 186)።

‘’ጫብር ሆሮ አውራጃ የሚገኝ የቦታ ስም ሲሆን፣ ነዋሪዎቹ ጫብሬ ይባላሉ። በምኒልክ ጊዜ

ወታደር ሆነው ከጎንደር መጥተው የሰፈሩ ናቸው ይባላል። ኢህአዴግ ስልጣን እንደያዘ

የኦህዴድ አባል የሚሆን ሰው ማግኘት በመቸገሩ እንደ ጫብር ከመሳሰሉ አካባቢዎች ኦሮሞ

ያልሆኑ ኦሮምኛ ተናጋሪዎችን በብዛት መልምሎ የጎደለውን የኦህዴድ አመራር ሞልቶበታል።’’

ይላል

አውነተኛው ታሪክ ሲታይ ግን ኦሮሞዎች ከ 17ኛው ክፍለዘመን ጀምሮ ከጎንደሩ

ቤተመንግስት ጋር ቅርብ እነደነበሩ፣ በጋብቻ እንደተሳሰሩ በስተመጨረሻም ከወሎ

እነራስ አሊ እና ከሳቸውም በፊት የነበሩ የኦሮሞ መሳፍነትቶች ኢትዮጵያን

እንደገዙ እና ራስ አሊ ውብ ልጃቸውን ለቴውድሮስ እንደዳሩ የታሪክ መጽሀፍት

ጽፈውት ስላለ ማንበብ ይቻላል። የሸዋው ነገስታት አጼሚኒሊክም ይሁኑ አጼ

ኃይለ ስላሴ ከኦሮሞ እና ከጉራጌ ጋር ድብልቅ ደም እንዳላቸው የትውልድ

ታሪካቸው ይመሰክራል። ከላይ የጠቀስናቸው ጀነራል ጃጋማ ኬሎም በራሰቸው

በንጉሰ ነገስት ኃይለ ስላሴ ‘’እኛ ነን የምንድርህ’’ ተብለው ለአምቻነት ታጭተው

ነበር፣ ጀነራሉ አልፈለጉም እነጂ። (እሸቱ ኢራና ዲባባ፣ የኦሮሞ ታሪክ( 2001)፣

ገጽ 85-91፣ ብርሃኑ አስረስ፣ የታህሳስ ግርግር እና መዘዙ (2005)፣ገጽ 21፣

ፍቅረማርቆስ ደስታ፣ ጃጋማኬሎ (2001) ገጽ 114)

ይህ እንዲህ ሆኖ ሳለ በዚህኛው ክፍሉም ሆነ ጫልቱ እንደ ሄለን በሚለው ክፍሉ

ተስፋዬ የዘር ማጥራት ቅስቀሳውን ( አማራዎች በኦሮሞ መሃል እንዳይኖሩ) የጭቃ

ውስጥ እሾክ በሆነ ዘዴ ይቀሰቅሳል። የሸዋው አሮሞ ከሸዋ አማራ ጋር ሲደባለቅ

ኖሯል። ጎንደሬው ቢያንስ ከ 17 ኘው ክፍለዘመን ጀምሮ ከቤተመንግስቱ ነገስታት

አንስቶ እስከ ወታደሩ እና ሕዝቡ ድረስ ከወለጋ እና የየጁ አሮሞ ጋር ተጋብቶ

ተደባልቋል። አሮሞ በ 16ኛው ክፍለዘመን በጎንደር ሰፍሮ እንደነበርና የመንግስት

አሰተዳፈሩ አካል እንደነበረም የታሪክ መዛግበት ይናገራሉ። እራሱ ተስፋዬ

እንደነገረንም የሸዋውም ሰው በዘመነ ዛጉዬ ከትግራይ በተሰደዱ ካህናት እና

ቤተሰቦቻቸው ምክኒያት ከትገሬም ተደባልቋል (ገጽ306)። ከዚያም ወዲህ

ትግሬውና አማራው በጉርብትናም በጋብቻም ተቀላቅለዋል። ታዲያ የትኛው ዘር

ከማንኛው ነው የሚጠራው? አብዛኛው ኢትዮጵያዊ በቅርቡ ያለውን ይጠቅስ

Page 28: ማርከሻ ለ የሞት መርፌ - api.ning.comapi.ning.com/files/poTC6m2b82rkMz38uXDa*sLOeRr2Zc*dkAn32... · ውስጥ እያለ ‘’ የቡርቃ ዝምታ’’ በሚል

ደጃዝማች አብቹ ማርከሻ ለ-የሞት መርፌ

27

ይሆናል እንጂ በእርግጠኝነት ደሜውስጥ የሌላ ጎሳ ደም የለም ብሎ መከራከር

መቻሉ ተገቢነት አጠራጣሪ ነው። ይታያችሁ ከግማሽ ክፍለዘመን በላይ እርስ

በርሱ ሲጋባና ሲዋለድ የኖረ ህዝብ ደሙን ከሌላው ዘር ደም እንዲያጠራ

ሲመከር።(እሸቱ ኢራና ዲባባ፣ የኦሮሞ ታሪክ( 2001)፣ ገጽ 85-91)

እዚህጋ የተስፋዬና የላኪው ሻአብያ አላማ ኢትዮጵያን መበታተን ስለሆነ አሮሞን

አሁን የሚቀሰቅሰው ድሮ በቀሰቀሰበት መልኩ ሳይሆን በጀርባ ዞሮ ኢሐዴግን እና

ኦሕዴድ’ን በሚያጠቃበት መንገድም ነው። ወያኔን እበቀለዋለሁ ብሎ የለ።

በዚህም ምክኒያት ኦሆዴድ’ን ‘’እውነተኛ ኦሮሞዎች ያልሆኑ ኦሮሞዎችን( የአማራ

ድቅሎች) ወያኔ ትግራይ ላይ ሰብስቦ ያደራጃቸው ናቸው’’ ይለንና በኦሮሞውስጥ

አንጃ በመፍጠር አሮሞውም እርስ በእርሱ እንዲተላለቅ የሞት መርዙን

ይቀምምለታል።ሲቀጥል የሜጫና የቱለማ አሮሞ ማለቱ ደግሞ አይቀሬ ነው።

በአንጻሩ ደግሞ ሌሎች ጀግኖች የሚላቸውን ቡድኖች ስማቸውን በማነሳሳት እና

የእነሱ ወገን ነው ትክክል ብሎ አጽዳቂ በመሆን የብጥብጥ እና የጦርነት ወኔ

ቀስቀሽነቱን ዙፋን ይቆናጠጣል። አሪፍ ‘’ኢንተር ሃሞይ’’ ማለት ይሄ ነው። እንደ

ሂትለር ንጹህ የአርያን ዝርያ ፈጣሪ ሁኖ ሌሎችን በማስወገድ ኦሮሞን ወደማያባራ

መተላለቅ ፣ ኢትዮጵያንም ወደመበታተን ይመራታል። ለዚህ ጉዳይ የኢትዮጵያ

መንግስት ተስዬፋን እና ላኪውን ሻአብያን ወደህግ ፊት ሊያመጣቸው በተገባ።

ዳግም ሩዋንዳን ሊፈጥሩ እየሰሩ ነውና። ውድ ወንድሞቼና እህቶቼ የኦሮሞ ልጆች

ይህን ‘’በካብ ስር ያለ እባብ’’ እኛም በሌላ ካብ ስር ሆነን ልናየው እንደሚገባ አሁን

በደንብ እወቁ። ልብ ያለው ልብ ይበል።

ሆድ ማስባሻ

Page 29: ማርከሻ ለ የሞት መርፌ - api.ning.comapi.ning.com/files/poTC6m2b82rkMz38uXDa*sLOeRr2Zc*dkAn32... · ውስጥ እያለ ‘’ የቡርቃ ዝምታ’’ በሚል

ደጃዝማች አብቹ ማርከሻ ለ-የሞት መርፌ

28

ተስፋዬ ጫልቱ እንደ ሄለን በሚለው ክፍል (የስደተኛው ማስታወሻገጽ 66) ደግሞ

የኦሮሞ ቋንቋ፣ ስም፣ ባህል፣እምነት እና ማንነት እንዴት ተቀባይነት እንዳጣ ገሃዳዊ

እውነት በሚመስል መልኩ ይተነትናል ። ጫልቱ የምትባል አንድ ትንሽ ኦሮሞ ልጅ

ካደገችበት አካባቢ አዲስ አበባ መጥታ በንቅሳቷ፣ በስሟ፣ በቁንቋዋ፣ በእምነቷ

የደረሰባትን ነገር በመዘርዘር እና አሉታዊ ሰበቦችን በውሸት ጭምር እያገጣጠመ

የኦሮሞን ህዝብ ሆድ በሚያስብስ መልኩ እና ከአማራው ጋር ሊያጋጨው ሰበብ

ሊሆን በሚችል ሁኔታ ያቀርባል።

በኢትዮጵያ በብዙ ገጠራማ አካባቢዎች ንቅሳት የተለመደ ነው። ከየትኛውም ዘር

ይሁን ንቅሳት ያላቸውን አህቶቻችንን ‘’ባለንቅሳቷ’’ ብሎ በልዩ ምልክቷ መጥራት ልክ

‘’ባለጎፈሬው’’፣ ‘’ሹሩቤዋ ‘’ አንደማለት የተለመደ ነው። ተስፋዬ እንደጠቀሰው ደግሞ

ከተሜነት የሚሰማቸው አንዳንድ ወጣቶች ‘’ንቅሴ’’ ይሉ ይሆናል። ይህ ከሆነ ደግሞ

ኦሮሞዋ ጫልቱ ብቻ ሳትሆን አብዛኞቹ ንቅሳት ያላቸው ሰዎች ወደከተሞች ሲመጡ

የሚባሉት ነገርና የሚሰማቸው ስሜት ተመሳሳይ ስለሆነ ኦሮሞን ብቻ ነጥሎ የዚህ

ሰለባ እንደሆነ ማውራት ብልግና ነው። በዚህ ሁሉ‘’ ከሰደበኝ መልሶ የነገረኝ የበለጠ

ሰደበኝ ‘’ የሚለውን ያገራችንን ብሂል ልብ ማለት ደግ ነበር። ለመሆኑ ‘’ ከኤርትራ

ደቡባዊውን የኢትዮጵያ ክፍል ሁሉ ‘’ ወዲ ሃድጊ!፣ ጻዳ አፍንጫ!’’ ብለው

የሚሳደቡት ሻኣብያዎች ስለ አንዱ ወገን ስድብ ብቻ ይህን ያህል እነዴት ከነከናቸው?

ነገሩ ‘‘ሊበሏት ያሰቧትን አሞራ ጅግራናት ይላሉ’’ መሆኑ ነው። መቼም አማራ

የሻአብያ እና መሰሎቹ የጦስ ዶሮ ከሆነ ሰንብቶ የለ? እርሱ ደግሞ የዚህን ሁሉ በደል

የአንበሳውን ድረሻ ወሰዶ ሁሌም ይሰደባል። ለነገሩ የተስፋዬ እና የሻአብያ ፍልስፍና

‘’የጨዋታውን መሪ መምታት’’ ነው።

ስለስምም ካነሳን ስንቱ በተለያየ የሀገሪቱ ክፍል የሚኖር ኢትዬጵያዊ ወደከተማ ብቅ

ሲል ስሙን ቀይሯል። ደበረኝ ብሎ። በገጠሩ አካባቢ የሚወጡ ለቀበሌው ምርጥ

የነበሩ ስሞች ( እነ ጫልቱ፣ ዘቢደር፣ ትንቧለል፣ ጥንፍ የለሽ…..) ወደመሃል ከተማ

ሲዘልቁ በ’ሱዚ’፣ ሳባ፣ ሶሲ፣ ምናምን ተቀይረው የለ እንዴ? ምን የሚያስደንቅ ሆኖ

ነው ኦሮሞው ብቻ ይህ እጣ እንደ ፍረጃ የወደቀበት ተደርጎ እንዲቆጣ፣ እንዲቀየም

የሚጎነተለው? ከየትም ቦታ ይምጡ የማንም ወገን ይሁኑ ስም ቀያሪዎቹ እኮ

ስማቸውን የቀየሩት በአዲሱ የመኖሪያ ቦታቸው ባለው ህዝብ ምልከታ ነው። በቃ

ጫልቱም ልክ እንደዚሁ ስሟ ሄለን ተባለ። እርሷ ኦሮሞ ስለሆነች ሳይሆን ‘’ስልጡን

ሆንኩ’’ ያለው ማህበረሰብ በሁሉም ‘’ገጠሬ’’ ባላቸው ስሞች ላይ ባሰረፈው ጫና

ነው።

Page 30: ማርከሻ ለ የሞት መርፌ - api.ning.comapi.ning.com/files/poTC6m2b82rkMz38uXDa*sLOeRr2Zc*dkAn32... · ውስጥ እያለ ‘’ የቡርቃ ዝምታ’’ በሚል

ደጃዝማች አብቹ ማርከሻ ለ-የሞት መርፌ

29

በጣም ዘግናኙ እና ይሉንታ ያጣ ትረካ ሆኖ ያገኘሁት ‘‘ጌጃ’’ የሚለውን ቃል የግድ

ከአንድ የኦረሞ ህዝብ ከሚኖርበት ስፍራ መጠሪያ የተወሰደ በማድረግ የቦታውን ስም

እንደ ስድብ ተደርጎ ከኦሮሞ ህዝብ ጋር የተቀላቀለበት ዘበዘብ ትረካ ነው። ጌጃ ሰፈር

የሚባል ስም አዲስ አበባም ካላት የአካባቢ መጠሪያዎች አንዱ ከመሆኑ ሌላ ይህ

‘’አራዳዎች’’ የገጠር ልጆችን የሚሳደቡበት ስድብ ( ጌጃ!) ተስፋዬ በጠቀሰው የደርግ

ዘመን እና ጊዜ በዚህ መልኩ ጥቅም ላይ አልዋለም ። አዚህጋ ተስፋዬ ዋሽቶ አሊያም

ተሳስቶ በዛን ጊዜ ይህ ቃል (ጌጃ) ያንድን አካባቢ ስም በመውሰድ መሰደቢያ

እንደተደረገ አድረጎ አቅርቦታል። ይህ ከሆነ ደግሞ ገገማ፣ ፋራ፣ ጤባ፣ገጠሬ ወዘተ

ስድቦች ሁሉ ነገ የአንዱ አካባቢ መጠሪያ ናቸው ተብሎ ለአንዱ ብሄር

መሰደቢያናቸው እንዳንባል ያሰጋል። ሌሎች ‘መሬው’፣ ‘ቆምጬ፣ ‘ጺላ’ እና

የመሳሰሉ ለአማራ እና ለትግሬ የተሰጡ አጫጭር መጥሪያ ቃሎችን ደግሞ ወደፊት

የዚሁ አባዜ ሰለባ መሆናቸው አይቀሬ ነው።የሚሰማ ካተገኘ።

በዚሁ ክፍል ኦሮሞዎች ‘’አቴቴ ( አያና ሃዳ)’’ ብለው ስለሚያመልኳት ልጅ

እንደምትሰጥ የምትታመን የእናትነት እንስት አምላክ ይነግረንና አሮሞዋ ጫልቱ አዲስ

አበባ ሰትመጣ ይህ እምነቷ አንዴት አንደተጥላላባት ይተርክልናል። በተዘዋዋሪም

አሮሞዎች አምልኳቸው እንዴት እንደተናቀ እና ተቀባይነት እንዳጣ ይጠቁማል ማለት

ነው። አዚህጋ አንድም በደንብ በማያውቀው ነገር ገብቶ አሊያም ሆንብሎ

ሊያስተላላፍ በፈለገው መልእክት ምክኒያት የአማልክቱ ጋብቻ መፈጸም ነበረበት

ወይም ‘አቴቴ’ የኦሮሞ ስለሆነች መነካት አልነበረባትም ይለናል።

በቀደመውም ዘመንም ይሁን አሁንም አለማችን የተለያዩ አማልክቶችን የሚያመልኩ

(Polytheistic) እና በአንድ አምላክ ብቻ የሚያመልኩ (Monotheistic ) ህዝቦች

አሏት። ኢየሱስ ክርስቶስ ወደምድር በመጣበት እና ሐወሪያቱ ወንጌልን በሰበኩበት

ዘመን የነበረውን አምልኮ ብንመለከት ግሪኮች እና ሮማውያን የተለያዩ አማልክቶችን

ያመልኩ እንደነበር እንረዳለን። እነዚህም አማልክቶች የሰማይ፣ የምድር እና የውሃ

አማልክቶች ተብለው የሚከፋፋሉ ሲሆኑ በጾታም ሴት ( godess ) ወይም ወንድ (

god) ሊሆኑ ይችላሉ። ለምሳሌ ዚየስ ፣ አስክሊፖስ (Asklepios) አፖሎ ( Apollo)

የተባሉ በወንድ የተሰየሙ አማልክቶች ሲሆኑ የሰማይዋ ንግስት ( Quen of the

haven) ፣ አፍሮዳይተስ (Aphrodite)፣ ሄራ አጋኤ ( Hera Argaea) ፣አርጤምስስ

(Artemsess) የሚባሉ እና ሌሎችም በሴት ጾታ የተገለጹ አማልክት በኤሺያ እና

በአውሮጳ ይመለኩ እንደነበር መጽሃፍ ቅዱሳዊ አና ሌሎች የታሪክ ማስረጃዎች

ይገልጻሉ። (Ben Witherington III, Conflict & Community in Corinth,

pp12,14)

Page 31: ማርከሻ ለ የሞት መርፌ - api.ning.comapi.ning.com/files/poTC6m2b82rkMz38uXDa*sLOeRr2Zc*dkAn32... · ውስጥ እያለ ‘’ የቡርቃ ዝምታ’’ በሚል

ደጃዝማች አብቹ ማርከሻ ለ-የሞት መርፌ

30

እንደነዚህ ምንጮች ገለጻ ከላየ ከጠቀስኳቸው ውስጥ አፍሮዳይተስ (Aphrodite)የምትባለውን አማልክት ብንወስድ ግሪኮች ያመልኳት የነበረች የውበት፣ የፍቅር እና የመዋለድ አምላክ ስትሆን ሄራ አጋኤ ( Hera Argaea) ደግሞ የጋብቻ በተለይም የሴቶች ወሲባዊ ህይወት አምላክ ነች። (Ben Witherington III, Conflict & Community in Corinth, pp12,15-16)

መጽሃፍ ቅዱሳዊ መረጃዎች እና የሌሎች መሰል ማስረጃዎች እንደሚጠቁሙት

የክርስቶስ ወንጌል እነዚህ አማልክት በሚመለኩበት አገር እና ህዝብ መሃከል ሲሰበክ

ታዲያ ወንጌሉን ተቀብለው ወደክርስትና እምነት የሚቀላቀሉት ሁሉ ከቀደመው

አምልኳቸው ፈጽሞ ተለይተው እግዚአብሔር አምላክን ብቻ ለማምለክ ልባቸውን

እና ፊታቸውን ማዞር ግድ ነበር። ምክኒያቱም የወንጌሉ ቃል

‘’.. በእርሱ በሚያምን አይፈረድበትም በማያምን ግን በአንዱ በእግዚአብሄር ልጅ ስም

ስላላመነ አሁን ተፈርዶበታል።’ የዮሃንስ ወንጌል 3፡-18

“መዳን በሌላ በማንም የለም እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች

ሌላ የለምና( ከኢየሱስ ክርስቶስ ስም በስተቀር)’’ ሐዋሪያት ስራ 4፡12 በሚሉና ሌሎች

ይህን በመሰሉ ከአምላክ ጋር የመታረቂያ ብቸኛ መንገድ ጠቋሚ ትምህርቶች እና

ትእዛዞች የተዋቀረ ሲሆን ከዚሁ የፈጣሪን ጽድቅ የማግኛ መንገድ ጋር ሌሎችን

አዳብለው መሄድ እንዳይችሉም ‘’ ከማያምኑ ጋር በማይመች አካሄድ አትጠመዱ ጽድቅ

ከአመጻ ጋር ምን ተካፋይነት አለውና?...ለእግዚአብሄር ቤተመቅደስም ከጣኦት ጋር ምን

መጋጠም አለው?..ስለዚህም ፡ ከመካከላቸው ውጡና የተለያችሁ ሁኑ እርኩሱንም አትንኩ..’’

(2ኛ ቆሮንቶስ 6፡-14-18) ይላል። በዚህም ግልጽ እና የማያወላዳ ትምህርት መሰረት

በዛ ዘመን እና አሁንም ያሉ ይህ ወንጌል የተሰበከላቸውና የተቀበሉት ህዝቦች

አማልክቶቻቸውን ትተው ብቸኛውን አምላክ ያለደባል ያመልኩታል ማለት ነው።

ወደ ኢትዮጵያ ስንመጣም በቅድመክርስትና የተለያዩ አማልክቶች ይመለኩ እንደነበር

ጠቋሚ ማስረጃዎች አሉ። ከነዚህም ውስጥ የፋርስ አማልክት እንደሆነ የሚነገርለት

በዘንዶ ማምለክ እና ለርሱም ግብር ማቅረብ በአክሱም ዘመነ መንግስት እንደነበረ

በድንጋይ ላይ የተቀረጹ ቅረጾች እና ሃውልቶች በአስረጅነት ቀርበዋል። ከዛም ሌላ

ዚየስ፣ፖሲዲየን እና ኦሬስ የተባሉ የግሪክ አማልክቶችም ይመለኩ እነደነበር በአክሱም

በተገኙ ጥንታዊ ሀውልቶች ተረጋግጧል። ሌሎች የጸሃይ፣ የጨረቃ እና የሰማይ

አማልክትም በአክሱም አካባቢና በዙሪያው ይመለኩ ነበር። ታዲያ በ330 ዓ.ም

ወንጌል በንጉሱ ኢዛና ዘመን በነ ፍሬምናጦስ(አባ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን)

ከቤተመንግስት ጀምሮ ሲሰበክ እና ቆይቶም ዘጠኙ ቅዱሳን በ 5 መቶኛው ክፍለዘመን

ሲመጡ እነዚህ አማልክት ከላይ በጠቀስኩት ሁኔታ ስፍራቸውን መልቀቅ

Page 32: ማርከሻ ለ የሞት መርፌ - api.ning.comapi.ning.com/files/poTC6m2b82rkMz38uXDa*sLOeRr2Zc*dkAn32... · ውስጥ እያለ ‘’ የቡርቃ ዝምታ’’ በሚል

ደጃዝማች አብቹ ማርከሻ ለ-የሞት መርፌ

31

ነበረባቸው። ( ፍቃዱ ጉርሜሳ ኩሳ፣ የወንጌል እምነት እንቅስቃሴ

በኢትዮጵያ(1999ዓ.ም)፣ ገጽ30-32፣ 36-37)

እንግዲህ ይሄንንው ፈለግ ተከትሎ ነው የኢትዮጵያዋ አቴቴ ልክ አፍሮዳይተስ

(Aphrodite) ወይም ሄራ አጋኤ ( Hera Argaea) ወይም የትንሹ እስያ አርጤምስስ

ቦታቸውን እንደለቀቁት ለወንጌል ቦታዋን የለቀቀቸው እንጂ የኦሮሞ ስለሆነች ተንቃ

ወይም ተቃላ አይደለም ማለት ነው። በእነዚህ ጥንታዊ አምልኮ ውስጥ ያሉ የዘንዶ

አምልኮቶች እና ሌሎችም በኢትዮጵያ ቀድሞም የነበሩ አሁንም ያሉ የውቃቢ፣ የዛር

እና የመሳሰሉት እምነቶች ማንም ይከተላችው ማንም የክርስቲያኖች ወንጌል

ያለማዳላት በአለም እንደተደረገው ሁሉ ተቃውሟቸው ስፍራ እንዳስለቀቃቸው ከዚህ

መረዳት ቻላል።

ክርስትናን የተቀበሉትን እና የወንጌል አስተምህሮ የደረሳቸውን አማኞች ቀይጣችሁ

አምልኩ፣ ወይም የኦሮሞ እምነት አይደለምና ክርስትናን ተዉ ማለት ደግሞ

በማይገባባት ተገብቶ የእምነት አስተምህሮ ቀያጅነት አሊያም የእምነት ነጻነታቸውን

መጋፋት ነው። ይህ እንዲህ ከሆነ ታዲያ ተስፋዬ ያለእውቀት እዚህ ነገርውስጥ ገብቶ

እምነትን ከእምነት እና በእግረመንገዱም ዘርን ከዘር ሊያጋጭ የሄደበት አካሄድ ከንቱ

ከመሆኑም በላይ በቅጡ በማያውቀውም ነገር ጭምር ‘’የእርጎ ዝንብ’’ መሆንንም

አይፈሬ ነው ማለት ነው።

ክርስትናን አማራ ያመጣው ነው ተብሎ የሚታሰብም ከሆነ ትልቅ ስህተት ነው።

በዚህ አካሄድ ኤርትራ ላይ ሚሲዮናዊያን በባርነት ተሽጦ ያገኙት እና ነጻ በማውጣት

ለኦሮሞው ማህበረሰብ የዎንጌል መልእክተኛ ያደረጉትን በጛላም መጽሃፍ ቅዱስን ወደ

ኦሮምኛ የተረጎመውን የኦሮሞውን ልጅ አናሲሞስ ነሲቡንና አስቴር ገኖን አማራ

ናቸው እንባል ይሆን? በወለጋ የህዳር ወረርሽኝ ተነስቶ ህዝብ እንዳይቀስፍ ተፈርቶ

ችግሩን ለመቅረፍ በጭንቅ ላይ የነበሩትን አገረ ገዢ እና ህዝቡን ለመርዳት ሱዳን

ውስጥ ለነበሩትን የሱዳን ኢንትሪየር ሚሺን ሚሺነር ፣ዶክተር ቶማስ ላምቤ

በደጃዝመቹ ጥያቄ ቀርቦላቸው ወደ ኢትዮጵያ በመግባት በቄለም ወለጋ የህክምና

እርዳታ ሰጥተዋል። በዚያው አጋጣሚም ክርስቲያናዊውን መጽኃፍ ቅዱስን በወለጋ

እና አካባቢው ሰብከዋል። ሌሎች ቁጥረብዙ የውጭ ሀገር ሚሲዮናውያንም ለኦሮሞ

ሀዝብ መጽኃፍ ቅዱስን ሰብከዋል። ( ፍቃዱ ጉርሜሳ ኩሳ፣ የወንጌል እምነት

እንቅስቃሴ በኢትዮጵያ(1999ዓ.ም)፣ ገጽ240፣262-263፣ 207-234)

እነዚህ ሚሲዮናዊያን ጨርሶም ከአማራውጋ ንክኪ የሌላቸው ከመሆኑም በላይ

የመጽኃፍ ቅዱስ አስተምህሮዋቸውም አማራ ወደ ኦሮሞ ይዞት ገብቷል እየተባለ

Page 33: ማርከሻ ለ የሞት መርፌ - api.ning.comapi.ning.com/files/poTC6m2b82rkMz38uXDa*sLOeRr2Zc*dkAn32... · ውስጥ እያለ ‘’ የቡርቃ ዝምታ’’ በሚል

ደጃዝማች አብቹ ማርከሻ ለ-የሞት መርፌ

32

አለማቀፋዊ መሆኑ ቀርቶ ፖለቲካዊ ይዘት ከተሰጠው የኢትዮጵያ የኦረቶዶክስ

ቤተክርስቲያን አሰተምህሮ በመጠኑ የተለየና የፕሮቴስታንት ነው። ሌሎች አማልክትን

በተመለከተ ያሰተማሩት ትምህርት ግን ተመሳሳይ ነው። ምክኒያቱም ሁሉም

የሚሰብኩት ‘’ እኔ አምላክህ ቀናተኛ ነኝ እና ከእኔ በቀር ሌላ አምላክ አታምልክ’’ (

ዘጻት 20፡3-6 ) የሚለውን የመጽሃፍ ቅዱስ ቃል ነው። እንዲህ ከሆነ ታዲያ አማራው

በኦሮሞ ሃይማኖት እና እምነት ላይ አፍራሽ ተጽእኖ እንዴት አሳድሯል ይባላል?

አንድን አለማቀፋዊ እውነት ከባቢያዊ ተጽእኖ አድርጎ ማቅረብ ከይሉኝታ ቢስነት እና

ህዝብን የሚያገናዝብ አእምሮ እንደሌለው ቆጥሮ ከመናቅ በቀር ምን ሊሆን ይችላል?

ከዚህ ክፍል የማይስተባበለው ነገር ኦሮሞ ብቻ ሳይሆን ሌላውም አማርኛ ሁለተኛ

ቋንቋው የሆነ ተናጋሪ በአማርኛ አነጋገሩ ቅላጼ ይፎተት ነበር። ይህ ሊታረም

የሚገባው የነበረ ሲሆን በደርግ ጊዜ በሚገባ አሁን ደግሞ ከሚገባውም በላይ ታርሞ

ኢትዮጵያውያን እርስ በርሳችን የምንግባባበት ሌላ ቋንቋ ለመፍጠር ወደምንገደድበት

አሊያም የውጭ አገር ቋንቋ ምናልባትም እንግሊዘኛ ወደምንጠቀምበት ደረጃ እየገፋን

ነው። ለነገሩ አለመግባባታችን በጣም ተፈላጊ እና ጠቃሚ ስለሆነ ለዚሁ በብርታት

የሚሰሩ ‘አርበኞች’ አሉ።

ተስፋዬ በ ሆላንድ አገር ያገኘሁት ገረሱ የሚባል ሰው ነገረኝ እንዳለን ጫልቱ ስሟ

በመቀየሩ፣ በእምነቷ ላይ በተሰጣት አስተያየት እና በንቅሳቷ ምክኒያት የማንነት

መዘባረቅ ደርሶባታል። ይሁንና በነዚህና ሌሎች መሰል ሁኔታዎች የማንነት መቀዣበር

/ Identity Crises የደረሰባት ኦሮሞዋ ጫልቱ ብቻ አይደለችም። ድፍን

አካባቢያቸውን የቀየሩ ካደጉበት እና ከለመዱት ቀዬና ያም ማህበረሰብ ከሚከተላቸው

ወጎች እና ልማዶች የተለዩ ሁሉ እንጂ። ይህን ደግሞ ተስፋዬ ‘’ስርአታዊ ሽብር

(systemic Violence) ብሎ መጥራት እንዴት እንደቻለና ልክ እንደሚሆን አልገባኝም

(የስደተኛው ማስታወሻገጽ 99)። በስንቱ የአማራ ስሞች ሲዘፈንባቸው እና

ሲቀለድባቸው ይዋል የለእንዴ። አንድ የሰሜን ሰው ‘’ኧረ በወሰንጋላ ወይም በጠቋር’’

ብሎ እነዚህ አማልክቶች ባእድ አምልኮ እንደሆኑ በሚታመንብት ስፍራ ቢናገር

የሚደርስበት ውግዘት ምናልባት ከጫልቱ የባሰ እንጂ ያነሰ አይደለም።በዚህረገድ

ተዘማጅ በሆኑ ምክኒያቶች ቁጥረ ብዙ ልብወለድ መጻህፍት እና ሌሎችም የሀገሪቱን

የተለያዩ አካባቢ ነዋሪዎች እየጠቀሱ ስለደረሰባቸው የማንነት ቀውስ ጽፈዋል።

ተስፋዬን ልዩ የሚያደርገው ግን ይህ ችግር የአንድ ህዝብ /የኦሮሞ ብቻ ጉዳት

አስመስሎ እና ከአማርኛና ከአማራጋ አጣይ ብሶት ቀስቃሽ ሆኖ መቅረቡ ነው።

Page 34: ማርከሻ ለ የሞት መርፌ - api.ning.comapi.ning.com/files/poTC6m2b82rkMz38uXDa*sLOeRr2Zc*dkAn32... · ውስጥ እያለ ‘’ የቡርቃ ዝምታ’’ በሚል

ደጃዝማች አብቹ ማርከሻ ለ-የሞት መርፌ

33

ተስፋዬ- ጫልቱ አንድ የደርግ መንግስት ባለስልጣን አግብታ እንደነበርና በጛላ

ኢሕአዴግ ስልጣን ሲይዝ ባሏ በመታሰሩ ኑሮዋ እንደተናጋና በቡናቤት ሰራተኝነት

ተቀጥራ እራሷን እንድታሰተዳድር ሰወች ሲመክሯት አሻፈረኝ ማለቷን ነግሮን የዚህ

ሁሉ ድምር ውጤት ከላይ ለጠቀስኩት የማንነት መቀዣበር እንደዳረጋት ያወሳል።

ትዳራቸውን የተነጠቁ፣ ልጆቻቸውን ለችጋር እና ለርዛት ላለማጋለጥ ስጋቸውን ሽጠው

እንዲተዳደሩ የተገደዱ እልፍ አእላፋት ኢትዮጵያውያን አሉ። ከነዚህ ውስጥ የተፋዬ

አሳዳሪ ሻአብያ በለኮሰው የጦርነት እሳት ለዚህ እስከፊ ኑሮ የተዳረጉት እጅግ ብዙዎቹ

ናቸው። የ 17 አመቱ ጦርነት ቀርቶ የፍቺ ወረቀት ከሰጠነው በጛላ እንኳን በቀሰቀሰው

ጦርነት ከ 70 ሺ ሰው በላይ እንዳለቀ ይነገራል። ታዲያ ኦሮሞዋ ጫልቱ የዚህ የአገር

ሙሉ ችግር ሰለባ ተጋሪ ሁና ሳለ ይህ የደረሰባት አሮሞ ስለሆነች አድርጎ መውራት

ከህሊና ቢስነት ሌላ ምን ሊሆን ይችላል? የሴቶቻችን ትዳር አልባነት እና የልጆች

አባት እጦት በነርሱ በሻአብያዎችና ቅጥረኞቻቸው ምክኒያት ሆኖ ሳለ እነሱ ግን

መተውን እራሳችንን መተን እንዳለቀስን እንድንቆጥር የመክሩናል። ከዚህ በላይ ንቀት

ግን ምንአለ? ይሄም ሳያንሰን አሁንም ጨምረን እርስበርስ እንድንተላላቅ እና

ጉዳታችን እንዲጨምር ይመክሩናል። አሰዛኙ ግን የራሳችንንም ወንድሞች እና እህቶች

በገዛ ህዝባቸው ላይ ይህን አበሳ እንዲቀጥል ማነሳሳት መቻላቸው ነው። እንኪያስ

ተስፋዬ የጠቀሳችሁ ገረሱ እና ዳዊ ( የምር በአካል ያላችሁ/ የፈጠራ ካልሆናችሁ/)

ለዚህ ጥፋት የተመለመላችሁ ብቁአን ከመሆን አምላክ እንዲጠብቀችሁ ምርቃቴ

ነው። ከሰመረልኝ።

ተስፋዬ ደቡብ አፍሪካ ምን ይሰራ ነበር? በዛ አንዳንድ ኦሮሞ ነን የሚሉ ሰዎች ‘’ ከየት

ነው የመጣችሁት?’ ተብለው በኢሚግረሺን ባለስልጣናት ሲጠየቁ ‘’ ኦሮሚና’’

ከሚባል አገር እነደሆነ ነግረው በአለም ላይ እንደዚህ በመባል የታወቀ አገር ስለሌለ

በዚህ አገር ስም ልንመዘግባችሁ አንችልም እየተባሉ ውዝግብ እንደሚነሳ አዲስ

አድማስ ጋዜጣላይ በ2005 ዓ.ም ማንበቤ ትዝ ይለኛል። እንግዲህ ይህን ግሩፕ

ተስፋዬ አለማደራጀቱን ወይም ቢያንስ ‘የቡርቃ ዝምታን’ በመጻፉ በሆላንድ ‘’ኦቦ’’

የሚል ማእረግ እንደተሰጠው ከነገረን ሌላ ለነዚህ መሰል ድምር ውለታዎቹስ ጭምር

አለመሆኑን ማን የውቃል? ይህ ከሆነ ደግሞ ተስፋዬ በአፍሪቃ (ኬኒያና ደቡብ

አፍሪካ)፣ በአውረጳ እና አሜሪካ እየተዘዋወረ የስለላ ስራ የሚሰራ እና የምስራቅ

አፍሪቃን አተራማሽ ፖለቲካ የሚዘራ ማሽን ሆነ ማለት ነው።

ህልመ ሻአብያ- የምስራቅ አፍሪቃ ቅርጫ

Page 35: ማርከሻ ለ የሞት መርፌ - api.ning.comapi.ning.com/files/poTC6m2b82rkMz38uXDa*sLOeRr2Zc*dkAn32... · ውስጥ እያለ ‘’ የቡርቃ ዝምታ’’ በሚል

ደጃዝማች አብቹ ማርከሻ ለ-የሞት መርፌ

34

ተስፋዬ ‘’ባልና ሚስት’’ (የስደተኛው ማስታወሻ ገጽ 114-)በሚል ርእስ በጻፈው ክፍል

ውስጥ አንድ የዋህ ኢትዮጵያዊ በቤቱ ጋብዞት ስለ ኢዮጵያ የወደፊት በጎ እጣ

ያወያየዋል። ይህ ኢትዮጵያዊ አረንጓዴ፣ ቢጫ፣ ቀይ የተቀባ ኤርትራን የጨመረ ካርታ

እቤቱ ስቅሏል (የስደተኛው ማስታወሻ ገጽ 117)። እተስፋዬ ልብውስጥ ያለው ካርታ

ግን ከዚህም ይሁን አሁን ካለው የኢትዮጵያ እና የጎረቤት አገሮች ካርታ ፈጽሞ የተለየ

ነው። በዚህ ክፍል ውስጥ ሻብያ እና ጉዳይ አስፈጻሚው ተስፋዬ ስለምስራቅ አፍሪካ

የጠነሰሱት የፖለቲካ የጥፋት ድግስ ቁልጭ ብሎ የታየ ይመስለኛል። ተስፋዬ ጋባዡ

ሰው “በኤርትራ ጉዳይ ላይ አቋምህ ምንድነው?”በሚል ላነሰው ጥያቄ

“…ደቡብ ሱዳንም ሉአላዊ አገር ሆናለች። ሊቀጥል ይችላል። በአፍሪቃ ቀንድ ደረጃ

ማሰብ ካልተጀመረ መሰነጣጠቁ ማቆሚያ ሊኖረው አይችልም። የአካባቢው 150

ሚሊዮን ህዝብ HOA የሚል ፅሁፍ ያለበት ፓስፖርትና ገንዘብ እንዲጠቀም በማድረግ

የመፍትሄውን በር መክፈት ይቻል ይሆናል። ጎሳ እና ቋንቋ፣ ወደብና ድንበር የግጭት

ምክንያት ሆነው መፍትሄ ሊገኝ አይችልም። የአካባቢው ህዝብ በኢኮኖሚው መተሳሰር

አለበት። ብሄሮች ወይም አገራቱ በአንድ ዘዴ መያያዝ አለባቸው። አንዱ ሌላውን

ለማፈን እየሞከረ ሰላምና እድገት ሊታሰብ አይችልም። መገነጣጠሉ ኦጋዴን፣ ዳርፉር፣

ኦሮሚያ፣ ታላቋ አፋር፣ ፑንት ላንድ፣ ጁባ ላንድ እያለ ከቀጠለ መጨረሻው የት ይሆናል?

ጅቡቲን የሚያካክሉ አገራት እስኪፈጠሩ ድረስ ሊቀጥል ይችላል። መፍትሄ ግን

አይሆንም። በመሰረታዊ ጥያቄዎችና የአካባቢው ችግር ላይ መግባባት ይገባል። የብሄር

ጥያቄን ማፈን አይቻልም። ፈንድቶአል። ለዚህ የአካባቢያችን ችግር የተሟላ መፍትሄ

ማግኘት የሚቻለው በአፍሪቃ ቀንድ ማእቀፍ ውስጥ ነው ብዬ አምናለሁ።”

(የስደተኛው ማስታወሻ ገጽ 117)

ብሏል። ይህ ትንታኔ ቅን ቢመስልም የጎረቤት አገሮችን ሁሉ አቅም አዳክሞ

እራሱን ለማግነን ሁሉንም ለሚተነኩሰው ሻብያ ግን ውስጡን በመርዝ የለወሰው

መሰሪ ሃሳብ ነው። ሱዳኖች የሻቢያ ነገር‘’ቁጭ ብለው የሰቀሉት ቆሞ ማውረድ

ይከብዳል’’ እንዲሉ ሆኖባቸዋል። ሻአቢያ ሶማሌን እና በዛበኩል ኢትዮጵያን

የሚወጉ ሃይሎችን ያስታጥቃል። ይሄው እነተስፋዬ ኦሮሞውን፣ ሃረሬውን፣ ወዘተ

አምጾ እንደ ኤርትራ የተገነጠለ ሃገር እንዲሆን ይሰብካሉ። በዚህም ጥረታቸው

ስኬት‘’ የብሄር ጥያቄን ማፈን አይቻልም። ፈንድቶአል።’’ ብሎናል። ከዛም ወደዛ

ወደተውጠነጠነው የተበታተነች ኢትዮጵያና ሱዳን በመጨረሻም የሃይል

ሚዛናቸው በፍጹም ለኤርትራ አስጊ ያልሆኑ ብጥቅጣቂ አገሮች ሉአላዊነታቸውን

ጠብቀው ወደሚሰባሰቡበት የአፍሪቃ ቀንድ አገሮች ህብረት/ ጥላ እንዲያመሩ

መንገድ በ’ታላቁ’ ቀያሽ ሻቢያ ተተልሞላቸዋል ማለት ነው። ‘ለዚህ የአካባቢያችን

Page 36: ማርከሻ ለ የሞት መርፌ - api.ning.comapi.ning.com/files/poTC6m2b82rkMz38uXDa*sLOeRr2Zc*dkAn32... · ውስጥ እያለ ‘’ የቡርቃ ዝምታ’’ በሚል

ደጃዝማች አብቹ ማርከሻ ለ-የሞት መርፌ

35

ችግር የተሟላ መፍትሄ ማግኘት የሚቻለው በአፍሪቃ ቀንድ ማእቀፍ ውስጥ ነው ብዬ

አምናለሁ።” እንዳለን ማለት ነው።

ከዛም የንግድ ትስስር በመፍጠር ህዝቧን እንደሚገባ መመገብ የሚቸግራት

ኤርትራ ሰብል ሊያመርቱ ምቹ መሬት ካላቸው ጎረቤቶቿ በወላጅ አባትነት ክብር

( የተስፋየን አባት ሀግረ ህልም ልብ ይሏል) የፈለገቸውን እና የጠየቀችውን

ትወስዳለች ማለት ነው። እዚህጋ ተስፋዬ ከአዛውንቱ ሆላንዳዊ ጋር በገጽ 409

ላይ ሲጨዋወቱ የተናገረውን “ቀንድ አፍሪቃዊ” ማንነት መገንባት ቢቻል እንደሚሻል

አነሳሁ። በርግጥ ይህን ለመሞከር የሚፈልጉ መኖራቸውና ብዙም ሊገፉበት ግን እንዳልቻሉ

አብራራሁ’’ ያለው ሊጤን ሚገባ ነው። ያን ጊዜ ‘ኦቦ’ ተስፋዬ ገ/አብም ‘’HOA

የሚል ፅሁፍ ያለበት ፓስፖርት’’ ( Horn of Africa መሆኑ ነው) ይዞ የ’ኦሮሚና’ዋ

ደብረዘይት ይመጣና በታላቅ ባለውለታነት በሚሰጠው ቦታ በቢሾፍቱ ሃይቅ ዳር

ጎጆ ይቀልሳል፣ እንስሳት ያረባል፣ ቀዩን ዛፍ/ ኤርትራውያንን በድፍን የረር እና ከረዩ

ይተክላል (ተስፋዬ ገ/አብ፣ የጋዜጠኛው ማስታወሻ፣ ገጽ 410) ። ለዚህም ይመስላል

አስቀድሜ እንደጠቀስኩት ‘ከጥቂት ጊዜያት በሁዋላ ግን እንደጎርፍ ነው ወደ አገራችን

የምንገባው’‘ ያለው። አዎ ከላይ እንዳብራራሁት ኢትዮጵያ የኦሮሞ ልጆችና ሌሎች

ህዝቦቿ ሁሉ አርስ በእርሳቸው እንዲተራረዱ አድርጎና ከኢትዮጵያንም ገነጣጥሎ

በዚህ ጦስ ህዝብ አልቆ ባዶ መሬት በሆነ ምድር እሱ ይሰፍራል። ዘግናኝ ነው።

አሁን ሱዳን ከተገነጠለቸው ደቡብ ሱዳን ሌላ ሶስት ግዛቶቿ ጦርነት ከፍተዋል፣

ደቡብ ኩርዱፋን፣ ናይል እና ዳረፉር። ሻአቢያ በሱዳን አና በሱማሌስ እንደ ተስፋዬ

ገብረአብ ያሉ ሰዎች እንዳሉት ማን ያውቃል? ኢትዮጵያስ ምን ይጠብቃት ይሆን?

(‘’ቀዩን ዛፍ/ ኤርትራውያንን በአገሩ ሁሉ ይተክላል የሚለውን ’’ አንበሳው ይብራ

የተባለ ሰው በሎሚ መጽሄት በቅጽ ሶስት ቁጥር 77 ጥቅምት 2006 “ ተኝተሽ ተገኘሽ

መተማማን ጠፋ’’ ስለተስፋዬ ገ/አብና ተያያዥ ጉዳዮች’’ በሚል ካቀረበው መጻጽፍ

የወሰድኩት ነው)

ሻኣብያ በዚህ የመበታተን ስራው የረጅም ዘመን ልምድ አለው። ስር ለስር

በመቦርቦርም እንደዛው። አንዳንዶች የታህሳስ ግርግር የሚባለው የነጀነራል መንግስቱ

ነዋይ ግርግር እና የደርግ የንጉሱን ባለስልጣናት ርሸና ከጣሊያን ጋር ኢትዮጵያ

ባደረገችው ጦርነት ላገራቸው ውለታ የዋሉትን አንደ ራስ አበበ አረጋይና ራስ መስፍን

ስለሺ የመሳሰሉ አርበኞችን፣ ኤርትራን ከኢትዬጵያ ለማዋሃድ እጅግ ብርቱ ድካም

የደከሙትን ጸሃፌ ትእዛዝ አክሊሉ ሐብተዎልድን እና ሌሎችን ለማሰወገድ በኤርትራ

ገንጣይ ሃይሎች እና በጣሊያን ባለሟሎች የተጠነሰሰ ሴራ ነው ብለው ያምናሉ።

(ፋንታሁን እንግዳ, በቀዳማዊ ሐይለስላሴ አሰተዳደር ጎልተው የወጡ የፖለቲካ

Page 37: ማርከሻ ለ የሞት መርፌ - api.ning.comapi.ning.com/files/poTC6m2b82rkMz38uXDa*sLOeRr2Zc*dkAn32... · ውስጥ እያለ ‘’ የቡርቃ ዝምታ’’ በሚል

ደጃዝማች አብቹ ማርከሻ ለ-የሞት መርፌ

36

ችግሮች እና ትግሎች በቅርብ ባለሟላቸው የህይወት ታሪክ መነሻነት ሲገመገም

(1997))

ሻአብያ በንጉሱ መውደቅ ዋዜማ እና ማግስት ኢሕአፓ ን ያደራጀ እና የመገንጠል

ጥያቄውን ጉዳይ አስፈጻሚ ያደረገ ሲሆን በጛላም በጎሳ ላይ የተመሰረተ የትጥቅ ትግል

የሚያካሂደው ሕውሓት (ወያኔ) ዘላቂ አዋጭ ሁኖ ተገኝቶለታል። ( ካሕሳይ አብርሃ,

የአሲምባ ፍቅር (2005) ገጽ 101፣162፣ ብርሃኑ አባዲ, ጽንአት ( 2002)) በደርግ

ዘመንም በምእራብ ኢትዮጵያ የትጥቅ ትግል ያደርጉ ከነበሩ ሃይሎች ጋር የሻአብያ

ተዋጊዎች አብረው ይገኙ እነደነበር የመንግስት ሚዲያዎች ይናገሩ ነበር። ሻአብያ

ይሄው ልማዱ ስለማይተወው ዛሬም በሱማሌ በኩል ኢትዮጵያን ለመውጋት ተዋጊ

ሃይል እና የውጊያ ቁሳቁስ እንደሚያቀርብ በየሚዲያው ከሰማነው ሌላ ምንጭ

ጠቅሰው “Peace or war? Viwes on the Ethio- Eritrean conflict (2010)”

በሚል ርእስ መጽሃፍ የጻፉት ዶ/ር ዮሃንስ ኪሮስ ነግረውናል። ይሄንን ሁሉ

ጨማምረን ስናይ ተስፋዬ የሚያደረገው ብርቱ ጥረት የሻአብያ ኢትዮጵያን እና

ምስራቅ አፍሪካን የመበታታን ሁለገብ ትጋት አንድ ክፍል ነው ማለት ነው።

Page 38: ማርከሻ ለ የሞት መርፌ - api.ning.comapi.ning.com/files/poTC6m2b82rkMz38uXDa*sLOeRr2Zc*dkAn32... · ውስጥ እያለ ‘’ የቡርቃ ዝምታ’’ በሚል

ደጃዝማች አብቹ ማርከሻ ለ-የሞት መርፌ

37

ተስፋዬና ቡርቃ

ሻአብያ የቁርሾ መዘብዘብ እና የበታችነት እና የመናቅ ስሜት የሚጭሩ አጋጭ

ስብከቶችን መፍጠር የቆየ እስተራቴጂው ነው። በዚህም ምክኒያት ተስፋዬ ዛሬም

በወንዞች እየመሰለ ህዝቦችን መጎነታተሉን አልተወም። በተለይ አሮሞን ለጠብ

መቀስቀሱን ተያይዞታል። አዎን በአንዴ ለሻአብያ ብዙ ትረፍ ሊያስገኝ የሚችለው እና

ኢትዮጵያን ቀጥሎም ምስራቅ አፈሪካን የሚበትነው ይህ ህልሙ እውን ቢሆን ነው

እና ተስፋ ሳይቆርጥ መወተወወቱን ተያይዞታል።

በዚህም ምክኒያት፡

‘’ልቤን የሚነካው ቡርቃ ወንዝ ነው። ቡርቃ ያሳዝነኛል። በአፍሪቃ ቀንድ ውስጥ ግዙፍ ወንዝ ሆኖ ሳለ

ድምፁና ነፃነቱ ታፍኖአል። እንደ ጋሞው ኩርፓዬ ከተራራ ወደ ገደል እየተፈጠፈጠ የወንዞችን ወግ

ማእረግ ለማየት አልበቃም። እንደ አባይ፣ እንደ አዳባይ አልተዘመረለትም። ተከዜ እንኳ ቀንቶት

በአቅሙ አገሩን ማገልገል ሲጀምር ቡርቃ ጨለማ ውስጥ እንደተቀበረ ዝም ብሎአል’’ ( ገጽ 330)

እያለ አሁን ስላለው የፖለቲካ ስልጣን ክፍፍል እና በወንወዞች ስለወከላቸው ህዝቦች

በአሽሙር ይናገራል። በወንዞቹ አስመስሎም በአማራ፣ በትግሬና በወላይታ ህዝቦች

መካካል የስልጣን መቀናናት እንዲኖርና ለኦሮሞው ‘አንተ ከማን አንሰህ ነው አገር

የማትመራው?’ የሚል መሰሪ መርዝ ይረጫል። ኢትዮጵያ እና ህዝቦቿ ማንም

ይምራቸው ማንም ሻአብያን የሚያገባው ነገር ምንድን ነው? የአዞ እንባ እያነባ

በስልጣን ስንፋጅ ቆሞ ሊስቅ?¡¡ አሮሞ በብዛቱም ሆነ በችሎታው እዚህ ቀረህ

አይባልም። አገር በአንድ ጊዜ አንድ መሪ ብቻ ስለሚያስፈልጋት ሁኔታዎች

የተመቻቹለት ያመሪ ይመራታልና ኢትዮጵያም አንዲሁ ከማድረጓ በቀር አመሳሶ

አውጥታ እንዳልሆነ ማንም የፖለቲካ ሀ-ሁ የቆጠረ የሚስተው አይደለም። ደግሞም

መሪዎቻችን ‘’ተራው አሁን የእገሌ ጎሳነው’’ እያሉ የመንደር አህያ እንደሚጋልቡ

ህጻናት የሚፈናጠጡት መንበረ ስልጣን የለንም። አይኖረንምም። ይህ አስተሳሰብ

በዘረኝነት ከተጨማለቀ አእምሮ የሚወጣ ዝቃጭ ነው። ኢትዮጵያ በፖለቲካ

ስብእናቸው የምትመርጣቸው ልጆቿ ያስተዳድሯታል። አበቃ!!

የተስፋዬ ህልም የኦሮሞ ህዝብ መገንጠል ነው። በዚህም ምክንያት ግዙፍ የሆነው

የኦሮሞ ህዝብ ጥያቄ እንዳልተፈታ እና የጥገና ለውጥ ብቻ እንደተደረገ፣ ኦሮሞን

በማስገደድ ኢትዮጵያዊ እንደተደረገና ኦሮሞ ካልተገነጠለም የምስራቅ አፍሪቃ ችግር

እንደማይፈታ የቀሰቅሳል። (ገጽ409) ተስፋዬ ከአንድ የእናቱ ዘመድ የሆነ የሻአብያ

Page 39: ማርከሻ ለ የሞት መርፌ - api.ning.comapi.ning.com/files/poTC6m2b82rkMz38uXDa*sLOeRr2Zc*dkAn32... · ውስጥ እያለ ‘’ የቡርቃ ዝምታ’’ በሚል

ደጃዝማች አብቹ ማርከሻ ለ-የሞት መርፌ

38

ታጋይ ጋር ስለሃገራቸው ሲያወጉ ዘመዱ ‘’እየሰራን ነው ለሚቀጥለው ትውልድ ጣጣዋ

ያለቀላት ኤርትራ ማስረከብ አላማችን ነው’’ (ገጽ 251) ብሎታል። አዎን ምስራቅ

አፍሪቃን በታትኖ ማንም ስጋቷ ያልሆነ፣በእርሷ አባት ሃገርነት ጥላ የሚኖሩ፣

ቁርጥራጭ የባህር በር የሌላቸው ብዙ ሀገራት የከበባት፣ ኤርትራን ለመጭው

ትውልድ ማሰረከብ ነው አላማው። ሻአብያ በስንፍናው አንድን ሰፊ ህዝብ አዘቅዝቆ

ያየህበትን እና እንደቦይ ውሃ ወደፈለግኩበት ልነዳው እችላላሁ ለልጅ ልጅም

የማታሰጋ የፈራረሰች ኢትዮጵያ አቆያለሁ ብሎ ያሰበበትን ይህን ትልቅ ንቀት እና

እብሪት ማቆሚያው አሁን ነው። ለዚህ ሁሉ መሰሪነት በእርግጥ ፈጣሪ ለእያንዳንዱ

እንደስራው መክፈል እንደሚችል መዘንጋት የለበትም። እኛም ብንሆን ፍቅርን

እንወዳለን እንጂ ለሻአብያ ተንኮል ብድር መመለስ አያቅተንም። ደግሞስ ኤርትራስ

የኛው አይደለች? በምን አንጀታችን ተንኮል እንሰራባታለን?

ተስፋዬም ስለራስህ ‘’ክቡር ሰው እሳቸው - የተስፋው ጀማሪ በሚያለቅሱት ሰዎች - ዋይታና እሪ! መደሰት ጀመሩ - አቁመው አዝማሪ ‘’ (የስደተኛው ማስታወሻ ገጽ 289)

ብለህ የገጠምክልንንም አንስተውም አማርኛውስ የኛው አይደል? እንግዲህ

አንተ ‘’ዋይ አስባዩ’’¡¡.. ዋይ ባዩን ካልተውከው፣

በተራህ ‘ዋይ !’’ ስትል…ከራርመህ ማየት ነው….!!!!

እልሃለሁ።

Page 40: ማርከሻ ለ የሞት መርፌ - api.ning.comapi.ning.com/files/poTC6m2b82rkMz38uXDa*sLOeRr2Zc*dkAn32... · ውስጥ እያለ ‘’ የቡርቃ ዝምታ’’ በሚል

ደጃዝማች አብቹ ማርከሻ ለ-የሞት መርፌ

39

ልጆች ጠብ ወራሾች- የኦሮማይዋ ፊያሜታ ግላይ ሻብያ ህጻናቱን እንኳ ጥላቻ በተረት እና ግጥም ጭምር እየነገረ እንደሚያሳድጋቸው

ተስፋዬ በድረጊቱ ይመሰክርልናል።

(ገጽ 241 ) ተስፋዬ በመንገድ ሲያልፍ እየተሰዳደቡ የሚላቀሱ ልጆች ያያል-

‘’ዮሃና መላጣ... ሰላጣ... ናይ ቀደም (የድሮ) ጋዜጣ...” ተባብለው። የድሮ ጋዜጣ ተብሎ የተሰደበው ስሙ

ዮሃና ሚባል ልጅ ( ነጠብጣቦቹ ሌላም ይኖራቸው ይሆናል) ያለቅሳል። አብሻቂዋ

ልጅ ስሟ ‘ፊዮሪ’ ነው። ምን ያህል አስቀያሚ ነገር ቢባል እንዳለቀሰ አስቡ። ከዚያ

ይህን የሚያለቅስ ልጅ አባ’ባዩ ተስፋዬ ለአንድ የሚገባትን ክፍያ ትውልድ ሁሉ

እነዲከፍላት ለተመኘላት ሴት በልጅቱ ስም አሳቦ ግጥም ገጠመላት እና ለልጁ

በብሽሽቁ ጫወታ አብሻቂዎቹን አብሽቆ ብድሩን እንዲመልስ ላከው። አንዲህ ብሎ

‘’ፊዮሪ ወይዘሮ...

ናይ ቀደም (የድሮ) ከበሮ... ።’’ ነጠብጣቦቹ ተጨማሪም ስድብ እንዳለው እንገምት።

ተስፋዬ ፊያሜታ ጊላይ( በኦሮማይ የባእሉ ግረማዋ) እውነተኛ ስሟ ‘’ፊዮሪ’’ ነው

ይለናል (የስደተኛው ማሰታወሻ ገጽ 274)። በባአሉ ግርማው ‘’ኦሮማይ’’ መጽኃፍ

‘’ፊያሜታ ጊላይ’’ የደራሲው የጸጋዬ( የደርግ የቀይኮከብ ጥሪ ዘመቻ የፐሮፖጋንዳ

ሃላፊ) ወዳጅ እና ለሻአብያ ሰላዮች መጋለጥ ምክኒያት የነበረች ሴት ተደርጋ ስሟ

ተቀይሮ ( ከፊዮሪ ወደ ፊያሜታ) የተሳለች ገጸባህሪ ናት። በአሉ ግርማ በሻአብያ

ሰላዮች ያን ጊዜ አንደተገደለች አድርጎ ቢተርካትም አልሞተችም በህይወት አለች።

ተስፋዬ ኤርተርራ ሄዶ አይቷታል(የስደተኛው ማስታወሻ ገጽ 274) ። እናም

ለቀድሞው ‘’ጥፋቷ’’ ለትውልድ የሚተላላፍ በህጻናት አፍ የሚለፈፍ የስድብ ግጥም

ይሸልማታል። አቤት አበሳዋ! ልጆቿም እሷም ሲሰደቡ መኖራቸው ነው። እዚህ

ኢትዮጵያ የኛው ልጅ ቴዲ አፍሮ ደግሞ ‘’ፊዮሪና’ እያለ የፍቅር ዜማ ያንቆረቁርላታል።

(በአሉ ግርማ፣ አሮማይ፣ ገጽ 360-368)

ይህን የበቀል ሰንሰለት ለህጻናቱ ካስጨበጠ በሁዋለ ተስፋዬ የሱን መሰረታዊ መርሆ

እነዲህ ብሎ ይነግረናል

“ማጥቃትን በማጥቃት መከላከል” የተባለው የፕሮፓጋንዳ ስራ እንዲህ

እንደሚሰራ እያስታወስኩ መንገዴን ቀጠልኩ። ማልቀስ ለዮሃና መፍትሄ

አልነበረም። መፍትሄው የጨዋታውን መሪ መምታት ነበር። በትክክል ፊዮሪ

ሳታስበው ወደ መከላከል ገባች። ሌላው ተከታይ ነበር’’ ብሎናል።

Page 41: ማርከሻ ለ የሞት መርፌ - api.ning.comapi.ning.com/files/poTC6m2b82rkMz38uXDa*sLOeRr2Zc*dkAn32... · ውስጥ እያለ ‘’ የቡርቃ ዝምታ’’ በሚል

ደጃዝማች አብቹ ማርከሻ ለ-የሞት መርፌ

40

ይህ እንግዲህ ልብ በሉ ኢትዮጵያ ላይ የሚከተለው ፍልስፍና ነው። ምናልባትም

የጠላ መጠጫ እና ምናምን የሚያደርጋቸውን ታላቁን ንጉስ ሚኒሊክን እና

ከእሳቸውም ጋር አማራውን መጀመሪያ ማሸማቀቅ በዚህም እሱ የኢትዮጵያ አንድነት

መሪ ሃይል ነው የሚለውን ወገን መምታት ሊሆን ይችላል። (በኤርትራ በተዘጋጀ

የጥያቄና መልስ ውድድር ላይ ‘’ጠላ ለማዘጛጀት ከሚያሰፈልጉት ሶስቱን ጥቀስ’’ በሚል

ለቀረበ ጥያቄ…. መላሹ ሲመልስ ‘’--ሴት-- ሚኒሊክ -- እንግዶች ‘’፣ ብሎ እንደመለሰ

ተስፋዬ ነግሮናል። ኤርትራ ‘’ሚኒሊክ የሚባል የጠላ መቅጃ’’ አንኮላ እንዳለ

የተረከልን ተስፋዬ ቃሉን የሚጠቀምበት ግን በምጸት ነው ( የስደተኛው ማሰታወሻ

ገጽ፡ 254)

ማብቂያ የሌለው ተሸማቃቂ

የሻአብያው ተላላኪ ተስፋዬ አማራውን ደጋጋሞ አዋራጅ በሆነ ስላቅ ተሳልቆበታል።

ለማኝ፣ በባዶ ጉራ ተኮፋሽ፣ ፈሪ፣ ጽዳት የሌለው እና ጽዳትም የማይወድ አድርጎ

ጎንደሬውን በብእሩ ሲስለው በአንጻሩ የኤርትራ ለማኝ ለማኝ ሳይሆን ለስለላ ስራ

ለማኝ መስሎ የሚለምን፣ አገሩ ንጹህ እና ለምለም፣ የጀግና አገር ነው እያለ

ይደሰኩራል- ስለ ‘’አባት ሀገሩ’’ (ገጸ 188-192፣ 238-272)። አጥባቂ ኦርቶዶክስ

አማኙን የመራቤቴውን አማራ ጫልቱ እንደ ሄለን በሚለው ክፍሉ በዶክተር ጌታቸው

ወክሎ የኦሮሞ ባህል እና ሃይማኖት ጨፍላቂ አድርጎታል። የሚኒሊክ ሰራዊት ወደ

ሃረር ሲዘምት ንጉሱና ባለሟሎቻቸው ጭምር ልብስ የማያውቁ በመሆናቸው

በሀሬዎቹ ልብስ መደነቃቸውን እና በጛላም ሸማ ለቤተመንግስቱም እንዲላክ ሀረሮችን

መጠየቃቸውን በማተት ንጉሱና ሰራዊታቸው ላይ ተሳልቋል (ገጽ 44-45)። እውነት

ነው ንጉሱም ሆኑ ሰራዊቱ እንደዛሬው የተሰናዳ የደንብ ልብስ አልነበራቸው ይሆናል።

የህ በሸዋ አብሮ ከኖረው የኦሮሞ እና የአማራ ህዝብ ቀጥሎም ወደግዛታቸው

የተጨመረው የአርሲ ህዝብ እና ሌሎችም የሰራዊቱ አባላት የሆኑለት ጦር ከቆዳ

የተሰራ የጦር ልብስ ለብሶ ይሆናል። የሄ ግን በምንም አግባብ ያለመሰልጠን መለኪያ

ሊሆን አይችልም። ሆኖም ከሆነ አቶ ይልማ ደሬሳ ፍራንቼስኮ አልባሬዝ የተባለ ጸሃፊ

ታሪክ በሚባለው መጽሃፉ የጻፈውን ጠቅሰው እንዳሰፈሩት ገና በ16ኛው ክፍለዘመን

ለንጉስ ልብነ ድነግል ከጎጃም አልባሳት፣ ፈረሶች እና ወርቅ ግብር ሆኖ ሲቀርብ

የባህረነጋሹ የትግሬ ገዢ ደግሞ የራሱን ግዛት ግብር ሊያቀርብ ሲዘጋጅ አልባሬዝ

መመልከቱን ይነግሩናል። እንኪያስ ታዲያ በ 19ኛው ክፍለዘመን የመጡት ንጉስ

ሚኒሊክ ሸማ አይተው የማያውቁ እንዴት ሆኑ? ነገሩ ወዲህ ነው። ተስፋዬ

ያልሰለጠኑ ልብስ እንኳን አይተው የማያውቁ ህዘቦች ገዙዋችሁ! በሚል ህዝብ

ለማነሳሳት የተጠቀመበት ተንኮል ነው። ሐረሬዎች ግን ግራኝ አህመድ በጦርነቱ ወቅት

Page 42: ማርከሻ ለ የሞት መርፌ - api.ning.comapi.ning.com/files/poTC6m2b82rkMz38uXDa*sLOeRr2Zc*dkAn32... · ውስጥ እያለ ‘’ የቡርቃ ዝምታ’’ በሚል

ደጃዝማች አብቹ ማርከሻ ለ-የሞት መርፌ

41

(ባ16ኛው ክፍለዘመን) አሁን ተስፋዬ አልሰለጠኑም ከሚላቸው አካባቢዎች ምን ምን

እንዳገኘ ሳየውቁ አይቀሩምና የተስፋዬን ስድብ ማስተባበላቸው አይቀርም። ያም ሆነ

ይህ አልባሳት የስልጣኔ መለኪያ ተደርገው መወሰዳቸው አወዛጋቢ ነው። (ይልማ

ደሬሳ፣ የኢትዮጵያ ታሪክ በአስራስድስተኛው ክፍለዘመን፣ ገጽ37)

ስለስልጣኔ ከተነሳ ኢትዮጵያን ሁለት ጊዜ የወረሩትን ጣሊያኖች ኢትዬጵያውያን

ጀግኖቻችን የጣሊያንን የጦር ምርኮኞ እንዴት ባለ ስርአት፣ ለሰብአዊነት ክብር የሰለጠ

የጀግና ሰው ጠባይ አሳይተው እንደያዧቸው እራሳቸው መስክረዋል። በአደዋው

ጦርነት ጊዜ አስቀድሞ መቀሌ ላይ መሽጎ የነበረው ጦር በውሃ እጦት ምሽጉን

እንዲለቅ ሲገደድ እጅ የሰጠው ጦር በሞቱበት እቃ የሚያጓጉዙ እንስሳት ምትክ እንኳ

ንጉስ ሚኒሊክ ፈረስ እና በቅሎ ሰጥተው በሰላም ከሃገር እንዲወጣ ሸኝተውታል። ይህ

ተስፋዬ የሰለጠነነና አሰልጣኝ የሚያደርገው የጣሊያን ጦር ግን ቃሉን አጥፎ ከቀሪው

የጣሊያን ጦር ጋር ተደባልቆ አድዋ ላይ መልሶ ተዋግቶ አይቀሬውን ሽንፈፈት

ተጎነጽፏል። አስገራሚው ነገር ይህን ጦር ይመራ የነበረው አዛዥ በዚህ ጦርነት ላይ

ሲሞት ኢትዬጵያዊያኑ ለጀግና የሚገባውን ወታደራዊ የቀብር ስረአት ፈጽመውለታል።

ስልጣኔ ማለት ይሄ ነው። ንጉስ ሚኒሊክ ይህንንው ድረጊት በአገር ውስጥ ጦርነቶች

አድርገዋል። ከጎጃሙ ንጉስ ተክለይማኖት ጋር ተዋግተው ንጉስ ተክለሃይማት ቆስለው

ተማርከው ሲመጡ ንጉስ ሚኒሊክ ‘’ከዙፋናቸው ተነስተው አቅፈው ስመው

‘’ወንድሜን እንኳን ክርስቶስ በህይወተወ አገኛኘን’ ቁስሉን እኔነኝ የምጠርግለት’’

ብለው ቁስላቸውን ጠርገው አስታመው አድነዋል።የ ወላይታው ንጉስ ጦና

በተመሳሳይ ሁኔታ ሲማረኩ ልክ እንደዚሁ ‘’ወንድሜን ወንድሜን’’ ብለው ተመሳሳዩን

በማድረግ አስታመው በማዳን አገራቸውን አንዲያሰተዳድሩ መልሰው በቦታቸው

አድርገዋል።( ጳውሎስ ኞኞ፣ አጤ ሚኒሊክ(1984ዓ.ም፣ ገጽ 37፣71፣188፣190-91)

ሽክ ያለ ልብስ በለበሰ ጦርሰራዊት፣ በዘመናዊ የጦር ተሽከርካሪወች፣ መሳሪያዎች እና

የጦር ጀቶች እየታገዘች ጣሊያን ለሁለተኛ ጊዜ ስትወረንም የሃበሻ ጀብዱ በሚለው

መጽኃፍ ላይ ደጃዝማች አበራ የጦር ምርኮኞችን እንዴት ባለ እንክብካቤ ይዧቸው

እንደነበር ተጠቅሷል። ይሁንና ጣሊያኖች አለማቀፉን ድንጋጌ ጥሰው በመርዝጋዝ

ሲፈጁን፣ የጦር ምርኮኞቻቸውን እንደዛ አቀማጥሎ የያዘውን ደጃዝማች አበራን

ሳይቀር ሲረሽኑ፣ መንፈሳዊ ስልጣናቸውን ተጠቅመው ኢትዮጵያውያን ለጣሊያን

እንዲገዙ ለማድረግ የግዝት ቃል አልናገርም ያሉትን ሰላማዊ እና ሃይማኖተኛ የሆኑትን

አቡነ ጴጥሮስን ወንፊት አስኪሆኑ በመትረየስ ሲደበድቡ፣ በሶስት ቀን ውሰጥ ድፍን

የአዲስ አበባን እና የደብረ ሊባኖስን ህዝብ በአከፋ እና ዶማ ገድለው

ሲፈጁ፣በየደረሱበት የተማረኩትን አርበኞች እና ሌሎች ከነርሱ ጋር የተባባሩ ሰዎችን

Page 43: ማርከሻ ለ የሞት መርፌ - api.ning.comapi.ning.com/files/poTC6m2b82rkMz38uXDa*sLOeRr2Zc*dkAn32... · ውስጥ እያለ ‘’ የቡርቃ ዝምታ’’ በሚል

ደጃዝማች አብቹ ማርከሻ ለ-የሞት መርፌ

42

በያደባባዩ ሲሰቅሉ የነበሩት ጣሊያኖች ደግሞ የሰለጠኑና አሰልጣኞች ተደርገው

መወሰዳቸው አስገራሚም አሳፋሪም ነው። ዳሩ ይሄ ለባለጌዎች እና ህሊና ቢሶች ምን

እፍረት ያመጣል? ምናልባት ኢሳያስ አፈወርቄ ባንድ ወቅት ‘’ ፓሰታ በሹካ ስበላ

ስልጣኔ ይሰማኛል’’ አሉ ሲባል እንደሰማሁት የያንጊዜዎቹ ጣሊያኖች ይህን አድርገው

ይሆናል። ጨምረውም ህዝብን እንዴት መከፋፋል እና ማጨራረስ እንደሚቻልም

ስልጠና ሰጥተዋል።( ተጫነ ጆብሬ፣ የሃበሻ ጀብዱ(1989)፣ ገጽ 243፣ ፍቅረማርቆስ

ደስታ፣ ጃጋማ ኬሎ ( 2001)፣ ገጽ 61-66፣ መስፍን ወልደማሪያም (2005)፣ መክሸፍ

እንደኢትዮጵያ ታሪክ፣ ገጽ 215-224፣ Ian Campbell, The plot to kill Graziani,

pp 220,227-232,241-246…..)

ስለ አንድ ህዝብ እኩልነት ስንከራከር የሌላውን ህዝብ ሰብእናና ክብር ነክተን

አይደለም። ተስፋዬ ግን ቀደም በጠቀስኩት ‘የጨዋታውን መሪ መምታት’ በሚለው

የተወላገደ ፍልስፍናው አማራው ላይ ዘመተበት። የህም ለኢትዮጵያውያን አስቦልን

ሳይሆን የጠብ ምክኒያት ሲፈልግልን ነው።

Page 44: ማርከሻ ለ የሞት መርፌ - api.ning.comapi.ning.com/files/poTC6m2b82rkMz38uXDa*sLOeRr2Zc*dkAn32... · ውስጥ እያለ ‘’ የቡርቃ ዝምታ’’ በሚል

ደጃዝማች አብቹ ማርከሻ ለ-የሞት መርፌ

43

ፈረንጅ ቅኝ በገዛን

ተስፋዬ በአባይ መስሎ ምናልባት ግን አባይን የሚያዋሰኑትን ህዝቦች አስወክሎ (

በጆፌ) ስለ ኦሮሞ ነጸነት አሁንም ይከራከራል። በንግግሩም ‘ኋላቀሮቹ አቢሲኒያውያን

ከሚገዙን ነጮች ቢገዙን ይሻል ነበር’ የሚለውን የኦሮሞ ልሂቆች ክርክር አውቀዋለሁ። ነጮች

ገዝተውን ቢሆን ኖሮ ግን ኦሮሞነት ጭራሹን ይጠፋ ነበር። ኦሮሞነትን ያቆየው

የአቢሲኒያውያን ሁዋላ ቀርነት ነው...” አለኝ ‘ጆፌው’ ይለንና ተስፋዬ “ከድክመት ለተገኘ

በጎነት ምስጋና ይጠበቃል? ብዬ መልሼ ጠየቅኩት ይለናል። ( ገጽ- 323)

አንደእውነቱ ከሆነ የኦሮሞን ማንንት ያቆየው እራሱ ኦሮሞ እና ተጋብቶና ተዋልዶ

የተሳሰረው ሌላው ኢትዮጵያዊ ሁሉ ነው። ምክኒያቱም ኢትዮጵዊነት የአንድ ህዝብ

ብቻ ማንነት ሳይሆን የሁሉም ድምር ውጤት ነውና። ደግሞስ የተቀላቀለ ህዝብ

የብቻዬ የሚለው እጅግ ጥቂት ካል ሆነ ምን አለ? ‘’ጣሊያን በገዛን ኑሮ’ ‘’የሚሉ

‘የኦሮሞ ልሂቃን’’ ካሉ ነጻነታቸውን በመንገድ እና በህንጻ ቀይረው ስብእናቸውን

ሊያጡ የሚፈልጉ በመሆናቸው ነው። እነዚህ ሰዎች ራሳቸውን እና ተስፋዬን

የመሰሉትን እስከትለው ወይም እየተመሩ ደጉን፣ የዋሁን እና ጨዋውን የኦሮሞ ህዝብ

የሚቀሰቅሱት ለእርሱ አስበው ሳይሆን በእርሱ ስም በእራሱ ላይና ለጥቀውም

በመላዋ ኢትዮጵያ የስልጣን ኮርቻላይ ተፈናጠው ሊገዙት ስለሚቁዋምጡ ነው።

ለመሆኑ አፈሪካ ውጥ የተፈጠሩ ወገን ቀስቃሽ ፖለቲከኞች እና አመጸኞች በቀስቀሱት

ህዝብ ደም ያገኙትን ስልጣን ለቀሰቀሱት ኅዝብ ልእልና ተጠቅመውበት መች

ያውቁና? እሩቅ ሳንሄድ ተስፋዬ ኢትዮጵያን አበጣባጭ የሆነለት ኢሳያስ አፈወርቄ

ያደረገውን እና የሚያደርገውን፣ የኤርትራ ህዝብ በምን ሁኔታ ላይ እንዳለ እና አሁንም

ሌሎች የኤርትራ ህዝብ ነጻ አውጭዎች ጠመንጃ ይዘው እንደሚፋለሙ እኛም አሱም

ቀስቃሻችን እናውቃለን። በቅርቡ ያገኘጛት አንዲት ከኤርትራ የተሰደደች ሴት

‘’የኤርትራ መንግስት እስርቤት ከፍቶ ዜጎቹን ያሰራል መባል ሳይሆን ያለበት አገሪቱን

እስርቤት አድረጓታል ነው’’ ብላኛለች። ይህ ብዙዎቹ የሚጋሩት ሃሳብም ነው።

በነገራችን ላይ የዛሬው ኢህአዴግ ጥንስሱ በጎሳ ላይ የተመሰረተ ቡድን/ ሕውሓት

እንደነበር ትዝ ይልሃል? ያን ጊዜ የትግራይ ‘’ነጻ አውጭ’’ ብቻ እንደነበረስ? አሁን ግን

ዋነው የኢትዮጵያ መሪ ሃይል ነው። እናም የኸውላችሁ ተፋዬ ደፋ ቀና የሚልላቸው

‘’ልሂቃን’ ህልማቸው ይሄው ነው።

ስልቱ የተመረጠበትም ምክኒያት በየበታችንት ስሜት ቅስቀሳ የሚናጥ ህዝብ ጨካኝ

እና መራራ ስለሚሆን ከዛ ሁኔታ ለመላቀቅ እና ታላቅ ለመሆን ጨካኝ እርምጃ

ለመራመድ አመቺ ነው ተብሎ መታማኑ ሲሆን ወደሁለተኛው ልእቀት ማለትም

Page 45: ማርከሻ ለ የሞት መርፌ - api.ning.comapi.ning.com/files/poTC6m2b82rkMz38uXDa*sLOeRr2Zc*dkAn32... · ውስጥ እያለ ‘’ የቡርቃ ዝምታ’’ በሚል

ደጃዝማች አብቹ ማርከሻ ለ-የሞት መርፌ

44

ሌላውን ህዝብ ሁሉ በስሩ ለማድረግ ሲነገረው ደግሞ ፍጹም ታላቅነት ስለሚሰማው

ያለማመንታት ይንቀሳቀሳል። ከዛም የስልጣን ጥመኞቹን ጥም ያረካና እርሱም

እንደሌሎቹ ሁሉ አብሮ የገዘውዎቹን ቀንበር ይሸከማታል። በመጨረሻ ይህ ህዝብ

የሚተርፈው ነገር ቢኖር በስሙ በሌሎች ህዝቦችላይ የተፈጸመው በደል

የሚያስከትለው ትዝብት እና ሲከፋም ጥላቻ ነው። ይህን የምለው እኛ ሁላችን

ከምናውቀው የህይወት ተሞክሮ እና አንዳንድ በጠመንጃ ስለሚገኝ ስመ ዲሞክራሲን

አጋልጠው ከተጻፉ መጽሃፍት ተነስቼ ነው።

እንደው አውነት እንነጋገር ከተባለ ግን በ 17ቱ አመት የደርግ እና ላፉት 22 አመታት

የኢሕአዴግ አገዛዝ ወቅት የበታች ተደርጎ የሚታሰብ ህዝብ አለ? ያውም ድሮ

ተጨቁኖ ነበር የሚባል ህዝብ? አማራ፣ጉራጌ፣አሮሞ ወዘተ መሆኑን ከመስማቱ እና

ከማወቁ የዘለለ በዛ ጎሳ አባልነቱ የተለየ ክብር እና ጥቅም የፈለገ ወይም ያገኘ አለ?

ደርግ ወደስልጣን ሲመጣ የተወለደ ልጅ አሁን አድሜው 39 አመት ነው። ይህ አዲስ

ትውልድ በማያውቀው ነገር ተወቃሽ እና ተከሳሽ ማድረግ ፋይዳው ምን እንደሆን

አየገባኝም። ደግሞስ አማራ ብቻ ነበር እንዴ ባላባት፣ ጉልተኛ ወዘተ? የሚመስለኝ

መጠላላት እና መጠላላፍ ይወድ የነበረው የቀደመው ‘’የምሁራን ጎራ’’ እርሾው ገና

ተሟጦ አላላቀም እና በዞረ ድምር አዲሱንም መርዞ እና መራራ ዋጋ አስከፋዩን ጽዋ

አቀብሎት ሊያልፍ በጣር እየተወራጨ ነው። በመጭው ዘመን ሀገር እና ሀገርን

የመምራቱ እጣ በእሱ እጅ የሚያርፈው ቀጣይ ትውልድ እዚህጋ ቆም ብሎ ተወጋጁን

ከቀጣዩ የሚለይበት ሰአት ነውና ብርቱ ስራውን በአግባቡ እንዲወጣ ማሳሰብ

እወዳለሁ። ዋነው ቁምነገር ኢትዮጵያን ማን ገዛት ሳይሆን እንዴት አድረጎ

አስተዳደራት ነው? እንደኔ ጎጥላይ በተመሰረተ ክልላዊ ምርጫ ሳይሆን

ኢትዬጵያውያን ሁሉ በጋራና በነጻነት ድምጽ ሰጥተውት/ዋት በአብላጫ ድምጽ

የሚመረጥ/ የምትመረጥ፣ በጎሳ ማንነቱ/ቷ ሳይሆን በፖለቲካዊ ስብእናው/ዋ

የሚወዱት/ዷት፣ ቅን የህዝብ አገልጋይ የሚሆን/ የምትሆን ፐሬዚዳንት ወይም

ጠቅላይ ሚኒሰቴር በኖረን እላለሁ። እንዲህ ቢሆን አሁን ያለውን ትግሬ፣ አሮሞ፣

አማራ፣ ወላይታ፣ ወዘተ ገዛን የሚለውን አስተሳሰብ በእጅጉ ሊያጠበው እና

ሊያቀራርበን እንደሚችል በማመኔ ነው።

ተስፋዬ የሚላቸው ‘’ጣሊያን በገዛን ኖሮ’’ የሚሉ ‘’ልሂቃኖች’’ የምር ካሉ እና የፈጠራ

ካልሆኑ ሳይታወቃቸው የመጨረሻ ሰነፎች መሆናቸውን አውጀዋል። ይህ በአካፋ እና

ዶማ ተጨፍጭፈው፣ ታጥቦ እንደተሰጣ ልብስ በየአደባባዩ በገመድ ተንጠልጥለው፣

ከነሙሉ ቤተሰባቸው ጭምር ቤት እየተዘጋባቸው በእሳት ጋይተው፣ በመርዝ ጋዝ

ተበጣጥሰው ነጻነነትን ያቆዩንን አባቶቻችንን እና እናቶቻችንን እንደመርገም እና

ማቃለል ይቆጠራል። የምናማርረውም በዚህ በታላቅ ተጋድሎ በቆየለን ነጻ አገር

Page 46: ማርከሻ ለ የሞት መርፌ - api.ning.comapi.ning.com/files/poTC6m2b82rkMz38uXDa*sLOeRr2Zc*dkAn32... · ውስጥ እያለ ‘’ የቡርቃ ዝምታ’’ በሚል

ደጃዝማች አብቹ ማርከሻ ለ-የሞት መርፌ

45

ተምረን እና አስተምረን አገረራችንን ማሰማመርና ቀጣይ ድርሻችንን መወጣት ያቃተን

ደካሞች ስለሆንን ነው። መንገዱን፣ ትምህርት ቤቱን፣ ሆሰፒታሉን፣ አውሮጳ እና

አሜሪካ አሁን ሌሎች በደከሙበት በስደተኝነት ስም ወገኖቻችን የሚቀማጠሉበትን

መኖሪያ ቤት እና ‘’ስልጣኔ’’ የሚሉትን ሁሉ ማድረግ ያልቻልን ስንኩላኖች ሆነን

በሌሎች ትከሻ እነዚህ ሁሌ እንዲሟሉልን ናፋቂ ስለሆንን አባቶቻችን ጣሊያንን

በማባረራችው እናማርራለን። ይህን ስንፍናችንን በአለም ወደሚደነቁት አባቶቻችን

ማላከካችን ደግሞ ከነጻነት ይልቅ ባርነት የምንመርጥ የአለም መሳቂየዎች ያደርገናል።

እንዲህ ከሆነስ ይህን ውርደት ማየት የማይፈልጉት እነዛ ጀግኖቻችን ከሞቱም በጛላ

እየተነሱ ይህን ሁሉ አሰማምረው በሰሩልን! እነዲህ ከሞት ተቀስቅሰው የሚሰሩልን

ስራ እነሱ እና እኛ በጣሊያን እንዳንገዛ በማድረጋቸው ላመለጠን ነገር በአርበኞቹ

የምንከፈለው ካሰ በሆነን ነበር¡¡ በእውነት ይህስ ያሳፍራል!!

ሌላው የተስፋዬ ስብከት የኦሮሞን ህዝብ እና ኢትዮጵን መበጥበጡ ላለፉት አርባ

አመት ልሂቃኑ በፈለጉት መንገድ ውጤት ባያመጣም የደቡብ አፍሪካው ANC ለ 82

አመታት እንደታገለው አሮሞ መታገል አለበት ይለናል( ገጽ 330-331)። በእውነት

አርሱ የጠቀሳቸው ልሂቃን ይህን ብለው ከሆነ ለዚህ የተራዘመ ብጥበጣ ከማሰብ እና

ለስልጣን እየቋመጡ ህዝብን አምሶ የባሰ ወደጛላ ከማስቀረት ግማሽ ሚሊኒየም

ለሚጠጋ ጊዜ ስልጣን እና መንግስት እየተጋራ፣ እርስ በርሱ እየተጋባ፣ ሀገር ድንበሩን

እየተከላካለ፣ ክፉ ደጉን እየተካፈለ እና እየተቻቻለ የኖረውን ህዝብ የእውነት ስልጣኔ

እና ክብር ተመኝተውለት ቢሆን ለዚህ ጊዜያቸውን እና አውቀታቸውን ቢያውሉት

ጥሩ በሆነ ነበር። ኢትዮጵያውያን ሁሉ የዚህ ትሩፋታችሁ ተካፋዮች ሁነው ለዚህ

የማይረሳ ግልጋሎታችሁ የሁሌም ተታወሸ ልጆች በሆናችኁላቸው። ዳሩ እነ ‘’ገረሱ’’

ተስፋዬ እንደነገረን ሻብያ የመርዝጋን ስር ኤርትራ ኄዳችኁ ከከረማችኁ ይኅን ማየት

ሳይቸግራችኁ አይቀርም። ቢሆንም ጊዜው አልረፈደም እና አሁንም እንናፍቃችጛለን።

ተስፋዬ እነደሚተርከው ሆላንድ ያገኘው ዳዊ የሚባል ሰው የተዛነፈ የኢትዮጵያዊነት

ትንታኔ ያለው ከመሆኑም በላይ ‘’ኢትዮጵያዊነት ሲነካ አንደኛው ቀድሞ ይቆጣል’’

ባይ ነው። (የስደተኛው ማሰታወሻ፣ ገጽ 332) ንግግሩ ትግሬውን እና አማራውን

ጠቅሶ ኦሮሞው ኢትዮጵያዊነት ሲነካ እንደማይቆጣ በምናቡ ያሰበውን ወይም

የተመኘውን በኦሮሞ ህዝብ ላይ ያሳብባል። ይህ ትልቅ ያመለካከት ችግር ከመሆኑ

ባላፈ ታሪክ የሚለውን የጣሰ እና በጥናትም የልተደገፈ፣ አመክኒዮ የሌለው ባዶ ሃሳብ

ነው። ስንቱ ኦሮሞ ነው ኢትዮጵያ ስትነካ የማይቆጣው? የሩቁን እንተወውና ሻአብያ

የኢትዬጵያውያንን አንድነት ያናጋ በመሰለው ጊዜና በተሳሰተ ስሌት ባድመንን እና

አካባቢውን ሲወር ትግሬ ብቻ ይዋገኛል ብሎ ገምቶ የነበር ይመስለኛል። እዛ ድንበር

ላይ ግን ማን ጉድ እንደሰራው እርሱ የውቃል። ይህ ስጋቱም ነው የሌት እንቅለፍ

Page 47: ማርከሻ ለ የሞት መርፌ - api.ning.comapi.ning.com/files/poTC6m2b82rkMz38uXDa*sLOeRr2Zc*dkAn32... · ውስጥ እያለ ‘’ የቡርቃ ዝምታ’’ በሚል

ደጃዝማች አብቹ ማርከሻ ለ-የሞት መርፌ

46

አሳጥቶት ኢትዮጵያን ለመበታተን የሚሰራው። በተሳሳተ የጊዜ ስሌትና ሁሉም ነገር

እንዳሰበው ተሳክቶ ኢትዬጵውን ተኳርፈዋል ብሎ ሲያስብ የፈጸመው ስህተት

እራሱን በራሱ ‘’ የጅብ ችኩል ቀንድ ይነክሳል’’ እንዲል አሰገድዶታል። እናም አሁን

ጊዜ ወስዶ እና በስፋት ለምስራቅ አፍሪካ የሚሆን መላ እየሸረበነው። ይልቁኑ ዳዊ

ምናልባት ያነሳው ጥያቄ ‘’ኦሮሞ ኢትዮጵያዊነት ሲነካ አንደማይቆጣ ወይም

እንደማይሰማው ለምን ይቆጠራል?’’ ሆኖም ሊሆን ይችላል። እንዲህ ከሆነ ደግሞ

አሮሞን በዚህ ሊያማው የሚደፍር ኢትዮጵያዊ ሊኖር አይችልም የለምም። አሮሞ

ለኢትዮጵያ ብቻ ሳሆን የጥቁር ህዝቦች አንገት ቀና ብሎ እንዲሄድ ካደረጉ ባለዝና

ኢትዮጵየውን አንዱ ነውና። እንዲህ ያለ ስሜት የሚሰማው ካለ ከንቱ ሃሜት ሰምቶ

ያመነ እና ይህን ክርክር የሚያነሳ ብቻ ነው።

ተስፋዬ፣ ገረሱ ‘’በንጉሰ ነገስቱም ሆነ በደርግ ዘመን በስልጣን ላይ የነበሩት የኦሮሞ

ተወላጆች የኦሮሞን ህዝብ ወክለው አይደለም ስልጣን ላይ የነበሩት’’ አለ ይለናል ።

ግን ግን የትኞቹ ባለስልጣናት ናቸው ታዲያ ጎሳዎቻቸውን እየወከሉ ስልጣን ላይ

የነበሩት። ለነገሩ አድሎ ሊኖር እንደሚችል ባይካድም የስልጣን ሹም ሽሩ

በኢትዮጵያዊነት እንጅ በጎሳ ቅርጫ አልነበረም። እራሰቸው ንጉስ ሚኒሊክም

‘‘ቁምነገሩ ከማን ተወለድክ ሳይሆን ምን በጎ ነገር ሰራህ’’ ፍልስፍናቸው እንደነበር

ይነገራል። ለዚህም ይመስላል ትልቁን ስልጣን የያዙት አሮሞዎቹ ራስ ጎበና ዳጮ እና

ፊታውራሪ ኃበተጊዮረጊስ ዲነግዴ (አባ መላ) የሃገሪቱ የጦር አዛዦች የሆኑት። ይሁንና

እነዚህን የአገር አባቶች እና አውራዎች ከንጉስ ኃይለ ስላሴ መውደቅ ዋዜማ አና

ማግስት ጀምሮ ሻአብያ ያደራጃቸው አስገንጣዮች ‘ባንዳ’ ብለው ስም

ለጥፈውላቸዋል። ገረሱ ተናገረ አንደተባለው በ ሽደጸኛወው ማሰታወሻ ገጽ 336 ላይ

ያለው አቁዋሙ ለኦሮሞ ህዝብ በጎነገር መደረጉ ሳይሆን ዋነው ጥሙ ስልጣን ነው!!

ሥልጣን!! የሚያጓጓው የኦሮሞን ህዝብ ከኢትዮፕያ ገንጥሎ የመግዛት ስልጣን። ይህ

ግን የሻአብያ ጉጉት እና ስብከት የፈጠረው ጉምዠት ነው።

Page 48: ማርከሻ ለ የሞት መርፌ - api.ning.comapi.ning.com/files/poTC6m2b82rkMz38uXDa*sLOeRr2Zc*dkAn32... · ውስጥ እያለ ‘’ የቡርቃ ዝምታ’’ በሚል

ደጃዝማች አብቹ ማርከሻ ለ-የሞት መርፌ

47

መደምደሚያና አዲሱ ግብረ ተስፋዬ

ወደመደምደሚየው ስንሄድም ተስፋዬ በተሰጠው የሰላይነት ሃላፊነቱ በእግረ መንገዱ

በተያያዥ ጉዳዮች ላይ ጽፏል። አላማውም ተልእኮውን አጋዥ ነገር በተደራቢነት

መስራት ነው። እርሱም ኢትዮጵያን እና ምስራቅ አፍሪካን መበታተን። በዚህ ግቡ ዋና

ማእከል ያደረገው ኦሮሞን ሲሆን ሃረሬው፣ ጉራጌውን፣ ወላይታውን፣ እና ከምባተውን

ደግሞ ያቅሙን ያህል በአመጽ ቅስቀሳው ‘ተደራሽ’ አድርጓል። ተስፋዬ ለዚኁ አላማ

በኬኒያ፣ በደቡብ አፍሪካ፣ ቀጥሎ ደግሞ ወደፈረንሳይ በተደረገው የኢራን አብዮት

ድጋፍ ጉዞ ላይ መግባቢያ ቁዋንቋው ኦሮሚኛ ለመሆን እስከመብቃት የደረሰ ሰፊ

የኦሮሞ ልጆች የሚኖሩበት የሆላንድ እና ወሰንተኛ አገሮች / እንደነ ጀርመን/ ሰላይ እና

የሻአብያ አምባሳደር ሆኖ ተቀማጭነቱን በሆላንድ/ ኢሮፕ አድርጓል።

አቻ ግብረ ተስፈዬ/ ዳንኤል ግዛው

የድግሱ ሳህን

እንግዲህ አገር ገንጥሎ ወስዶም የፍቺ ወረቀት ሰጥተንም ልንፋታ ያልቻልነው ሻአብያ

ከደገሰልን ሁሉ ኢትዮጵያውያን እጃችንን በፍቅር አስተሳስረን አገራችንን

የምንጠብቅበት ዘዴ እና ህብረት ለመመስረት አእምሮዋችንን ለመክፈት ጥሩ ማንቂያ

አግኝተናልና መረባረብ ይጠበቅብናል። በዚሁ አጋጠሚ ኢትዮጵያን እየመሩ ያሉ

ባለስልጣኖቻችንም አውቀውም ይሁን ሳየውቁ የኢትዮጵያ አንድነት ላይ አደጋ

ሊፈጥሩ ከሚችሉ መሰል ድርጊቶች ሊቆጠቡ ይገባል። በዚህ ረድፍ በዳንኤል ግዛው

The Prince of Africa ተብሎ ተጽፎ ተርጓሚው መዝሙር ፈንቴ ‘’ያስጀመረኝም እሱ

የስጨረሰኝም እሱ’’ በማለት ባንቆላጰሳቸው በተከበሩ አቶ በረከት ስምኦን አነሳሽነት

እና ‘’የእለት ተለት ፍጹም ክትትልና ድጋፍ’’ ‘’የአፍሪካው ልኡል’’ ተብሎ ተተርጉሞ

በቀድሞው ምክትል ጠቅላይ ሚኒሰትር እና የወጭ ጉዳይ ሚኒሰትር በአሁኑ ጠቅላይ

ሚኒሰትራችን “የፍቅር እስከመቃብር አቻ ነው’’ የሚል መወድስና ቡራኬ የተሰጠው

መጽሃፍ ተልእኮው ሊመዘን ይገባው ነበር። ይህም አልበቃ ብሎ በሬዲዮ ፋና

እየተተረከ የሻአብያን ስውር ተንኮል በገዛ ሬዲዮናችን ግማሽ መንገድ ሄደን እያገዝነው

መሆናችንን

አመላከች ሆኗል። ‘’የቡርቃ ዝምታና’ ‘’የስደተኛው ማሰታወሻስ’’ መቼ ይሆን በሬዲዮ

የሚተረኩልን?¡¡

Page 49: ማርከሻ ለ የሞት መርፌ - api.ning.comapi.ning.com/files/poTC6m2b82rkMz38uXDa*sLOeRr2Zc*dkAn32... · ውስጥ እያለ ‘’ የቡርቃ ዝምታ’’ በሚል

ደጃዝማች አብቹ ማርከሻ ለ-የሞት መርፌ

48

የዳንኤል ግዛው የሞት ቅመሞች

የዳንኤል ግዛው መጽኃፍ አማራን፣ ኩሎን፣ ጉራጌን፣ ማናን ፣ ኦሮሞንና ሌሎቹን

ያልነበረም ይሁን የነበረ የተረሳ በደል ቀስቅሶ አበጣባጭ አይነት ነው። ሚኒሊክን ‘ቀኝ

ገዢ ይላቸዋል’ (መዝሙር ፈንቴ፣ የአፍሪቃው ልዑል፣ ገጽ 247) አማራን ሰይጣን

(120) መንጃን ‘ አውሬ፣ ባሪያ’ (273) ማናን ‘ቡዳ’ (343) እያለ የተለመደውን

መዘዘኛ ቃላት ይጠቀማል። በዚህ መጽኃፍ ፈረንጅ አሰልጣኝ ሲሆን የጣሊያን ወረራ

ኢትዪጵያን ከተኛችበት የጛላ ቀርነት እንቅለፍ ቀስቃሽ ሁኖ ቀርቧል( ገጽ 366)። ይህ

ደግሞ የውሸት ውሸት ነው።

ጸኃፊው በሚያሳፍርና ለቀኝ ገዚዎቹ የሻቀለ በሚመስል ሁኔታ ስለጅማ ሲያወራ

‘’የአዳም ዘር በሙሉ መሰልጠኗን ሲያየው ማመን ይቸገራል፣በፈረንጁ ስራ እየተደነቀ

ብቻውን የወራል’’( 434) ሲለን አገረገዢውን ግን ‘አውሬ’ ብሎ ይሰድባቸዋል(

432)። እስከ ገጽ 436 ካነበባችሁት ሻቃላነቱ ለእውነተኛ ኢትዮጵያውያን

ያቅለሸልሻል። መረሳት የሌለበት ግን በወረራው ጊዜ የብዙ ኢትዮጵያውያን አንገት

ጅማ ላይ እየተቆረጠ ለጣሊያኖች ይቀርብ እንደነበርነው። እንዲህ ያለው አባዜ የጥቁር

ህዝቦችን ልእልና ጭምር ከፍ አድርጎ ያሳየውን እና እኛንም ለአፍሪካ የአፍሪካ ነጻነት

መሪ ያደረገንን አርበኝነት አዋራጅ ነው። አቦ እኔ ግን ተጸየፍኳቸው። የሆኖ ሆኖ

ጣሊያን ከመግባቱ በፊት ኢትዮጵያ በመሰረተ ልማት፣ በጤና እና በትምህርት ጥሩ

ግስጋሴ ላይ ነበረች። ዘመናዊ የውትድርና ተቋማትም እያደራጀችም ነበር።በተቃራኒው

ጣሊያን አገሪቱ ያስተማረቻቸውን ልጆች ፈጅቶ፣ ህዝባዊና ማህበራዊ ትስስሮችን

አደፍርሶ እና አንዳንድ የተገነቡ ልማቶቿን አፍርሶ ችግር ውስጥ ጨምሯታል። ( ጥቁር

አነበሳ)

ስለ ተዋራጅነት ከተነሳ ደግሞ በኢትዮጵያም ሆነ በመላው አለም በተለያ ምክኒያቶች

አንዱ ማህበረሰብ ሌላኛው ላይ የሆነ ምክኒያት ፈጥሮ የንቀት ወይም ሌላ የበታች

አድራጊ ስም ይለጥፍበታል። በኩሎው ግዛትም የሆነው ይሄው ነው። ይህ ድርጊት

ደግሞ በኢትዮጵያ የተለያዩ ግዛቶችም ከባህል እና እምነት ጋር ተወራርሶ በሁሉም

የአገሪቱ አካባቢ ሊባል በሚችል መልኩ የተዳረሰ ነው። ለምሳሌ በአማራውና

በትግሬው አካባቢ ቡዶች ናቸው ተብሎ የሚታሙ ሲኖሩ እንዲሁ ሌላም ሌላም ስም

እየተለጠፈላቸው በየአካባቢው የሚሳቀቁ አያሌዎች ናቸው። ይህ በኩሎ ያለው ሁኔታ

በአም ላይ ያለ እና በኢትዮጵያም የተፈጸመ ስለሆነ ጸሃፊው እንዲህ ያለው ጎጂ

አስተሳሰብ እና ድረጊት ከሀገሪቱ ባጠቃላይ እንዲወገድ ሊያሰተምሩን ቢጽፉ

በተደነቀላቸው ነበር። እሳቸው ግን ግብረ ተስፋዬ አበር ናቸውና የጻፉትን የጻፉት

በአፍራሽ ጎኑ ነው።

Page 50: ማርከሻ ለ የሞት መርፌ - api.ning.comapi.ning.com/files/poTC6m2b82rkMz38uXDa*sLOeRr2Zc*dkAn32... · ውስጥ እያለ ‘’ የቡርቃ ዝምታ’’ በሚል

ደጃዝማች አብቹ ማርከሻ ለ-የሞት መርፌ

49

ያፋለሱት ታሪክ

ተረጓሚው በትርጉም ስህተት አሊያም ደራሲው ይሉኝታ ቢስ ታሪክ

ዘጋቢነታቸውንም አስመስክረዋል። በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል ውስጥ ሲካሄድ

የነበረውን የስልጣን ሽኩቻ እና እሱንም ተከትሎ የነበሩትን ጦርነቶች በሙሉ

አማራዎች በመጥፎ ማንነታቸው ምክኒያት አርስበርስ ሲጫረሱ የኖሩበት ነው ይሉናል

(ገጽ 371-372)። እውነቱ ግን ከዚህ የራቀ እንደነበር ፍንትው ብሎ የጠራና ታሪክ

ዘጋቢዎች በሙሉ የጻፉት ነው። (‘ተረጓሚው በትርጉም ስህተት’ ያልኩት የመጽኃፉን

የእንግሊዘኛ ቅጅ አግኝቼ ማየት ስላልቻልኩ ጥፋቱን አንድ ስው/ ደራሲው ላይ ብቻ

ሳላውቅ ላለመደፍደፍ ነው)

ከዘመነ መሳፍንቱ መግቢያ ጀምሮ እስከፍጻሜው ድረስ የነበረው የስልጣን ግብግብ

ኦረሞዎች፣ ትግሬ ዎች እና አማራዎች ሲፈራረቁበት የነበረ የአሸናፊነት ትንንቅ ታሪክ

ነው። የታሪክ ጸሃፊዎች ከ 18ኛው ምእተአመት መግቢያ ጀምሮ አሮሞዎች በጎነደሩ

ቤተመንግስት አካባቢ መደላደል እንደጀመሩ ይነግሩንና እንደውም ንጉስ ኢዮአስ

እናታቸው አሮሞ ሲሆኑ ንጉሱም አፍመፍቻው ቋንቋ አሮምኛ እንደነበር

ይመሰክራሉ። ‘’It was in the 1720’s that the Oromo got a foothold at the court.

Their influence gradually increased. The Emperior Iyoas (1755-1769) whose

mother was a Yeju Oromo and who himself spoke only Oromo comes to

power’’ (Gustave Aren, Evangelical Pioneers in Ethiopia (1978), p39)።

እኝህ ንጉስ የአጼ በካፋ ልጅ የንጉስ ኢያሱ ልጅ ናቸው። ንጉሱ የእናታቸውን

ወንድሞች እና ዘመዶች( አሮሞዎቹን) አገረ ገዥ አድርገው ሾመው እንደነበርም ታሪክ

ይናገራል። እንግዲህ የዘመነ መሳፍነቱ አንድ መቶ አመት ጊዜ የስልጣን መራኮቻ

ነበር። በዚህ ጊዜ ውስጥ የጎንደሩን ስልጣን የትግሬው ራስ ስሁል ሚካኤል፣ ደጃች ሳባ

ጋዲስ፣ደጃች ውቤ፣ የአማራው እነ ደጃች ማሩ፣ የሸዋው ንጉስ ኃይለመለኮት እና

ሳህለስላሴ. ከአሮሞው እነራስ አሊ እና ቅድም እንደጠቀስኩት የንጉስ ኢዮአስ ዘመዶች

ሲፈራረቁበት እና የንጉስ ዘር አለው ያሉትን ሲያነግሱበት እንደኖሩ መጥቀስ ይቻላል።

ከዚህ ትንንቅ ፈቀቅ ብለው የኖሩት ሸዋወቹ እንደነበሩ አቶ ተክለጻዲቅ

ነግረውናል።(ተክለጻድቅ መኩሪያ፣አጼ ቴዎድሮስ አና የኢትዮጵያ አንድነት(1961)፣ ገጽ

49-590)

ይሁንና ህሊናቸውን ሸጠው ይህን የዳጎሰ መጽሃፍ የጻፉት ሰው ስብእናቸውን ዝቅ

በሚያደርግ አጎብዳጅነት ለምን እና ለማን እንደጻፉት እራሰቸውን በሚያጋልጥ መልኩ

ይህን ቅጥፈት በታሪክ ላይ ፈጽመዋል።

Page 51: ማርከሻ ለ የሞት መርፌ - api.ning.comapi.ning.com/files/poTC6m2b82rkMz38uXDa*sLOeRr2Zc*dkAn32... · ውስጥ እያለ ‘’ የቡርቃ ዝምታ’’ በሚል

ደጃዝማች አብቹ ማርከሻ ለ-የሞት መርፌ

50

ዳንኤል ግዛው ጽፎት መዝሙር ፈንቴ የተረጎመው ይህ መጽኀፍ ውቅያኖስ አቋርጠው

ከተለያዩ አገራት ተውጣጥተው ደቡባዊቷን አፍሪካን ከያዙት ነጮች ጋር ንጉስ

ሚኒሊክን እና ሰራዊታቸውን ቁርጥ የአንድናት ልጆች ያደርጋቸዋል

(375፣377፣386፣) ። ቀሽም ፍልስፍና ነው። በጥቁሮች አገርና በጥቁሮች መካከል

የተደረገን ያውም የቆየና በአባቶቻቸው ዘመን የነበረን የግዛት ወሰን ለማስከበር

የተደረገን እንቅስቃሴ ከድንበር ዘለል ወራሪዎችጋር እንዴት ይመሳሰላል? ብቻ ሁለ

ነገሩ በሚያምር ትረካ፣ እንደ ፏፏቴ በሚንደረደሩ ውብ ቃላት እና በአድማቂ

የስነጽኁፍ ውበት በማር የተለወሰ መርዝ ነው።ልክ እንደ የተስፋዬ ገ/አብ የቡረርቃ

ዝምታ። ልብን ሰቅዞ በሚይዝ አንብቡኝ ባይ ጎታች ውስጥ እያዘናጋ በነገር የሚወጋ

635 ገጽ ሙሉ ክፉ ነገር። ተስፋዬ እንደሚጠቀምበት አሌጎሪ በእንሽላሊት፣በአውሬ፣

በውሻ፣ በትል፣ በምናምን ብዙ የተመሰጠሩ ነገሮች የሚናገር ደራሲ እና መጽሃፍ።

የሚያወድስ መስሎ የሚጀምረው ነገር ሁሉ በክፋት የሚደመደም አጉል ሳሚ። የህሊና

አውነተኛነት እና ታማኝነት በሚመስሉ አይነርግብ ውስጥ ተከልሎ እና ቅቤ አንጓች

ተሁኖ ተሳዳቢነትን፣ አዋራጅ እና አንኳሳሽነትን የተካነ ልብ አደፍራሽ እና ቂም

አስረጋዥ ያፈጀ ዘመን (60 አመት) ትረካ ነው። እንዲህ ሆኖ ሳለ ነው ታዲያ ከእውቁ

የአዲስ አለማየሁ ‘ፍቅር እስከመቃብር’ መጽኃፍ ጋር ተወዳዳሪ የተደረገው።

ለመሆኑ ፍቅር አስከመቃብር የትቦታ ነው ዘርን ከዘር አወዳዳሪ እና እንዲህ አፍራሽ

የሆነው? እውነተ ነው ‘ፍቅር እስከመቃብር’ የህዝብን ጭቆና አንስቷል ይሁንና ዘርን

ከዘር እያማረጠ ሳይሆን መደባዊ ልዩነትን በግልጽ በማውጣት አንቂ ደወል ነበር።

ይሄኛው ‘‘የአፍሪቃ ልዑል’’ ደግሞ ማህበረሰብ/ጎሳ ቀስቃሽ እና ጸኃፊው ባደገበት

ዘመን ‘‘የኢትዮጵያ ጥያቄ የብሄር ጥያቄ ነው’’ ከሚሉት ወገን በሆነ ቅኝት ከሮ የተቀኘ

ነው። ይህ ውትወታ ደግሞ ቀድሞውንም በሻአብያ የተደረተ ተንኮል ሲሆን ኤርትራን

በማሰገንጠል ስራውን አከናውኗል። ግን አሁንም የቀረውን የቤት ስራ ሻአብያ

‘ራሰችንን’ ጭምር እያሰራን ነው። አሁን ከህዝብ ሁሉ ጋር በሰላም እየኖረ ያለው

‘’ደቡብ ሕዝቦች’’ ተብሎ የተከለለውና የብዙ ደጋግ ጎሳዎች መኖሪያ የሆነው አካባቢ

አለመተራመሱ እና ዛሬም እንዲጠላ ከሚፈለገው አማራጋ በፍቅር መሆኑ አሳሳቢ የሆነ

ይመስላል። እናም ሁነኛ መላ ተፈላልጎ ተገኘና የአካባቢው ህዝብ በእርስ በርሱ መሃል

እና በጣም ሊጠላ በሚገባው ዘር ላይ ጥላቻን እና መለያየትን የሚያመጣ ደራሲ እና

ድርሰት ተገኘለት። መቸም 21 ጊዜ መድፍ ሳይተኮስ አልቀረም። ድርሰቱ መንጃና

ኩሎን፣ ወላይታን እና ኩሎን፣ ኩሎ በራሱ ዘር መሃል ማና/ ቡዳ ብሎ የለያቸውንና

ኩሎውን፣ኩሎን፣ መንጃንና ጉራጌን ባሪያ አድርጎ ሸጦናል ከሚሉት ከኦሮሞጋር ከ

ከዛም ከሁሉም በላይ መጠላት ያለበትን አማራን ሁሉምአንዲጠሉትና እንዲጠላሉ

የተደጎሰ መርዝ ነው።

Page 52: ማርከሻ ለ የሞት መርፌ - api.ning.comapi.ning.com/files/poTC6m2b82rkMz38uXDa*sLOeRr2Zc*dkAn32... · ውስጥ እያለ ‘’ የቡርቃ ዝምታ’’ በሚል

ደጃዝማች አብቹ ማርከሻ ለ-የሞት መርፌ

51

ባጠቃላይ ደራሲው እራሳቸው በአሜሪካን አገር የጆርጂያ ግዛት ምክርቤት አባል

የነበረ እና ለዘረኛ ቅስቀሳ ‘ዘ አጉሰተ ኩርየር’ የሚል ‘የሁከት መንፈስ የሚያነሳሳ’

ጋዜጣ የሚያዘገጅ ሰው እንደነበር እንደነገሩን አኔ ደግሞ እሳቸውም አሱን ቁርጥ

እንደሆኑ ልነግራቸው እፈልጋለሁ (ገጽ 622-623)። የዚህን ሰው መዘዘኛነት

ለማጠፋፋት አንድ ብልጣብልጥ ሰው የተናገረውን አስተያየት መዘውም እሳቸውም

ሊጠቀሙበት ድሪቶ አበጅተዋል። ደራሲው ከ620 ገጽ በላይ ህዝብ አፋጅ ነገር

ሲጽፉ ቆይተው አይረቤ ማሰተዛዘኛቸውን የመጨረሻ ገጾቻቸው ላየ በመለጠፍ

የጥፋት መከለያ ሊያደርጉት የፈልጋሉ። ትዝብት ነው። ይህ የያን ዘመኑ አብዮተኞች

ሀቀኛ ለመምሰል ይሯሯጡበት የነበረ የግብዝነት አገር የፍራሽ ዛር አሁንም እያጓራ

ቀጣዩን ትውልድ ለመልከፍ የሚያደረገው ትንቅንቅ አካል ነው። ‘’ጓድ!’’ ጊዜው

ያለፈበት ስልትነውና አራስዎትን ከጊዜውጋር ያረምዱ!! እናንተ በማከም ስም መርዝ

መውጋቱን ስታቆሙ እውነተኛውን ችግር ከነትክክለኛ መፍትሄው የሚያውቅ ጊዜና

አዲሱ ተውልድ መድህን ያመጣለታል።

ሙት የውሰጥ ህሊና/ ፍርደገምድል

አንድ ሰው ወይም ወገን በሌላው ላይ ለመፍረድ ባለው የተሻለ አውቀት ወይም

ችሎታ ተጠቅሞ ከሚኮንነው ግለሳብ ወይም ማህበረሳብ የተሻለ ነገር ፈጽሞ መገኘት

ይኖርበታል። የዚህ መጽሃፍ ደራሲ ግን ይህን ማደረጋቸውን እጠራጠራለሁ። እንዳው

እሰኪ ዳንኤል ግዛውን ለጠይቅዎት፡ በዛ በድቅድቅ ጨለማ ዘመን ኢትዮጵያ የብርሃን

ወጋገን እንድታገኝ ይደክሙ በነበሩት ንጉስ እና እርስዎ ፋዘር በሚሉት ፈረንጅ

ተምረው ለኢትዮጵያ ምን ሰሩ? አንድ ሁለቴ ዛዲ(የተውልድ መንደርዎ) ብቅ ብለው

ከአባተዎ ጋር አታካራ ከመግጠም እና ጎምለል ጎምለል ብለው በህዝቡ እንደልዩ ነገር

ከመታየትዎ በቀር ያንን ድንቁርና አበሳውን የሚያስጠብሰውን ህዝብ እመሃሉ

ተጘኝተው በምን እረዱት? ፋዘር እያሉ የሚጠሩት ነጩ ሰው ምን እስተማረዎት?

እንዳሞራ በሮ ለእንግሊዞቹ የሱን ገድል ማውራት (ያውም እስካሁን ያልተሳካ) ብቻ

ነው ወየስ እሱ እንዳደረገው በህዝብዎት መሃል ቁጭ ብለው በጊዜ ብዛት አሰለጠኑት?

ልብዎ ሰራዋን እስክታቆም? ማለቴ ያ ነጩ ሰው ህይወቱ እስክታለፍ ለኢትዮጵያ

እንደዋለው ውለታ እርስዎም ፈለጉን ተከተሉ ወይስ በቃ ‘’ድህነት እና ድንቁርና

ወደሌለበት’’ ወደ አሜሪካ ከበለሉ ? አጼ ኃይለ ስላሴ አምጥተወውት አርስዎን

እንዳሰተማረዎት ነጩሰው ካላደረጉ ያሉትን ለማለት ሁሉ የሞራል ብቃት

የለዎትም። እንደውም አደራ በል ስለሆኑ ኢትዮጵያውያን ሁሉ ለወቀሳ

ይፈልጉዎታል። ለምን ቢሉ አርስዎን ሲያሰለጥን ይደርሱልኛል ብሎ ጠብቆ ነበራ።

Page 53: ማርከሻ ለ የሞት መርፌ - api.ning.comapi.ning.com/files/poTC6m2b82rkMz38uXDa*sLOeRr2Zc*dkAn32... · ውስጥ እያለ ‘’ የቡርቃ ዝምታ’’ በሚል

ደጃዝማች አብቹ ማርከሻ ለ-የሞት መርፌ

52

ባይሰልጥኑ ኖሮ ዛሬ በዛዲ ካሉት እንዳንዱ ባሰቡ ነበር። እናም የዛሬውን ተዘማናኝ

ፍርድ ባልሰጡም።

ትዝ ይልዎታል ያኔ ጅማን አይተው ሲደነቁ ማለቴ በነጩ ሰው ስራ? ልብዎት ያኔ

ጀምሮ ሻቅሎነበራ። ደግሞ ‘ቅኝ ብንገዛ ይሻለን ነበር’ ስብከት እኮነው በመጽሃፍዎ

የሰበኩን። አዎን አሁን እሱ በብዛት ያለበት፣ የማህበረሰባቸውን ሳንካ ለህዝበቸው

ሙሉ አቅማቸውን አንጠፍጥፈው ስጥተው የሰውን ስብእና እንዲከበር እመሃሉ ቁጭ

ብለው በዘዴ በማረቅ ስልጡን የሚባል ህዝብ የፈጠሩበት ቦታ ሲደርሱ በቃ ድሎቱ

ማርክዎት ቀሩ ይሆን? ለነገሩ እርስዎ እንደነገሩን ገና ወጣት ሳሉ ህልምዎት አሜሪካ

ነበር። አይወግ እቴ ለሀገር አሳቢ፣ አንዲህ አርጎም የለ ላገር ተጨናቂ ። እንዲህ ከሆነ

እማያማስሉትን ወጥ አይጣዱ ብዬ በቀጥታ ልነግዎት እፈልጋለሁ። እውነቱን

ልንገርዎት ከእርስዎ አቶ መኩሪያ ቁጥር የሌለው ጊዜ ይሻላሉ። እርስዎ ለመንጃው

ጀግና ‘ጋዳፉ’ በሰጡት ብጥቅጣቂ ነገር ያን ያህል እግርዎ ላይ ተወድቆ በእንባ ጭምር

ከተመሰገኑ ስንት ዛዲዎች የማየውቁትን ነገር አገር አቆራርጠው ከአዲስ አበባ

በማምጣትና በማሳየት ውለታ የዋሉት አቶ መኩሪያማ እንዴታ!!?? እንደርስዎም ያሉ

ሌሎች ካሉም ይሄው መልእክቴ ይድረሳቸው። እኔም አራስዎን እንዳሉት

ግብዞች!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!1 አልኩ።

የዚህ ጽሁፍ አቅራቢ መንጃዎችን የውቃቸዋል። በቤታቸው ተስተናግዷል።

አብሯቸው አድሯል ውሏል በልቷል ጠጥቷል። ለአንዴ ብቻ አይደለም ለቀናት እና

ለአመታት። ከህዝብ እንዴት እንደተገለሉ እና ምን ያህል ልብ የሚሰብር እንደሆነ

የውቃል። ለዚህ ጉዳታቸው ግን አሁንም እንደተለመደው አጼሚኒሊክንና አማራውን

ተወቃሽ ተደርጎ የቀረበበትን አግባብ ግን ጊዜ አግኝቶ እውነትን እስኪገልጥ

ይጠብቃል።

ለመሆኑ በ 1985 እና በ1994 ዓ.ም የነበረውን የቴፒን እና አካባቢውን ህዝብ ፍጅትና

እልቂት ማን አቀናብሮት ይሆን? ከዛ ጊዜ በፊት መዠንግሩ፣ ከፋው፣ ሸካው፣

ጊሚራው፣ ሸኮው፣ ዲዙው፣አማራው፣ ትግሬው፣ ጉራጌው፣ ወዘተ በሰላም ይኖሩባት

የነበረው፣ አብረው ጠጃቸውን ጠጥተው፣ ሲሰክሩም በፍቅር ተደጋጋፈው

ወደየቤታቸው ይዘልቁባት የነበረቸው ከተማ ለምን ተበጠበጠች? ከራርሞ ይሄም

በአንዱ ብሄር ካልተሳበበ ለአሁን ያለው እውነት ግን ኢትዮጵያን በጎሳ ከፋፍሎ

በማፋጀት ለመበተን በሚደረገው ክፉ ጥረት ነው።

Page 54: ማርከሻ ለ የሞት መርፌ - api.ning.comapi.ning.com/files/poTC6m2b82rkMz38uXDa*sLOeRr2Zc*dkAn32... · ውስጥ እያለ ‘’ የቡርቃ ዝምታ’’ በሚል

ደጃዝማች አብቹ ማርከሻ ለ-የሞት መርፌ

53

ተስፋዬና መዝሙር

ይህንን ‘የአፍሪቃው ልኡል፣ የሚል መጽኃፍ ተስፋዬ ገ/አብ ከሚያደርገው ክፉ ጥረት

ለጣቂ አድርጌ አይቼዋለሁ። አስገራሚው ነገር ተስፋዬ ጽፎት ተገኘ በተባለው

ማሰታወሻውም ላይ የሚጽፈው መጽኃፍ 600 ገጾች ያሉትና በ 2011 እ.ኤ.አ

የሚታተም መሆኑን ጠቅሶ ነበር። አሁን ሊያሳትመው ብሎ ባለመሳካቱ በኢንተርኔት

የለቀቀውን መጽኃፍ (የስደተኛው ማስታወሻ) ግን 417 ገጾች ብቻ ሲኖሩት ሊታተም

የነበረበትም ጊዜ 2013 ነው። ‘’የአፍሪካው ልኡል’’ ተብሎ በመዝሙር ፈንቴ

የተተረጎመው መጽሃፍ ደግሞ በ 1998 እ.ኤ.አ በዳንኤል ግዘው ተጽፎ በተከበሩ አቶ

በረከት ስምኦን አነሳሽነት በመዝሙር ፈንቴ ባለ 635 ገጽ ሲሆን የታተመው በ 2011

ነው። ስለዚህ ተስፋዬ በነቢይነት ‘’የአፍሪቃው ልኡል’’ን በ2011 ስድስት መቶ ገጾች

ኖረውት ሲታተም ታይቶት ነበር ማለት ነው? ግን ለምን አይታየውም ይታየዋል

እንጂ።

መቸም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከስራ ብዛት የተነሳ በተጣበበ ጊዜ ሳያስተውሉ አንብበውት

መሆን አለባት ለዚህ መጽኃፍ ያን የመሰለ መወድስ ቡራኬ የሰጡት። ቀድሞውንስ

እሳቸው በመጽኃፉ የጀርባ ሽፋን ላይ የሚወጣውን የመጻህፈት መግለጫ ዋና ጽሁፍ

እንዲጽፉ ለምን ተመረጡ? የሆነስ ሆነና በዚህ ፍቅር እና መተሳሰብ በናፈቀን ዘመን

ይህን መሰል መጽኃፍ ማሰተርጎም ለምን አስፈለገ ይሆን?

Page 55: ማርከሻ ለ የሞት መርፌ - api.ning.comapi.ning.com/files/poTC6m2b82rkMz38uXDa*sLOeRr2Zc*dkAn32... · ውስጥ እያለ ‘’ የቡርቃ ዝምታ’’ በሚል

ደጃዝማች አብቹ ማርከሻ ለ-የሞት መርፌ

54

ደቂቅ ክቡር ተስፈዬ¡¡

በስተመጨረሻ ግን ተፋዬ አሳዝኖኛል። ያዘንኩለትም ‘ሁሉን አዋቂ ጠሃፊ’ ( እራሱ

እንዳለው) መሆኑ እና በአምላክ ላይ በመሳለቁም ነው። እርሱ ተስፋዬ እንዳለው

‘አምላክ’ ነው ምክኒያቱም ህሊና አለው። ህሊናው ያመዛዝናል እናም አልሞተም

በዚህም ምክኒያት ተስፋዬ አምላክ እንደሆነ ያምናል። ተስፋዬ ከአማልክቶች የትኛው

እንደሆነ ባላውቅም አግዚአብሔር እንዳልሆነ ግን አሳምሬ አውቃለሁ። ለነገሩ

የጥንታዊያኑን የኖሰቲክስ (Gnostics )ፋለስፎችን ትምህረት ቀነጫጭቦ እና በአእምሮ

መጠበብ ወደ አምላክነት ከፍ ያደርጋል ብሎ በከንቱ በመኮፈሱ ነው። ግና

የሚያመዛዝን ህሊናው በህዝቦች መካካል ጦርነት እንዲቀሰቀስ፣ አንዲበጣበጡ እና

እንዲጣሉ ሌት ተቀን ስልት ይነድፋል። ታላቁ ህሊናውም ሻአብያ የሰጠውን እና

እርሱም በእልከኝነት አና ልበሙሉነት የሚተገብረውን ምስራቅ አፍሪካን በታትኖ

ከኢሳያስ አፈወርቄ እኩል የሚወዳትን ሀገሩን የምስራቅ አፍሪካ ቁንጮ እና አባት

ሃገር ማድረግ በሚያስችል ሁኔታ ያንቀሳቅሰዋል። የጥበቡ ልክም ‘ኦቦ’ ተብሎና

በታላቅ ክብር ተከብሮ በደብረዘይት በመኖር በርሱ ምክኒያት የኤርትራ ልጆች

እንደልባቸው በኢትዮጵያ ሲቀማጠሉ ያስተነብየዋል። ሚስኪን!!! ግንኮ ለኤርትራዊያን

ኢትዮጵያ ዛሬም ቤታቸው፣ ሲከፋቸው ማኩረፊያ፣ የእናት አባት፣ የታለቅወንድምና

አህት፣ የዘመድ አዝማድ ጎጇቸው ነች። በነጻነት ሰርተው ያለሰቀቀን የሚኖሩባት

አገር። እንዲህ ከሆነ ደግሞ ተስፋዬና ላኪዎቹ የህን ሁሉ የሚሰሩት ኤርትራውያንን

ማለቂያ በሌለው የግፍ ጉረኖ ውስጥ ለማቆየት የሚያስችል አምባገነን ስልጣናቸውን

ለዘላለም ለማኖር ነው እንጂ ለኤርትራ ህዝብ አስበው አይደለም።

‘’ክቡር ሰው እሳቸው ፍፁም ቀና ነበር - አጀማመራቸው በደስታ ሚስቁ - ተሳክቶ ኑሮአቸው ሰዎችን በማየት - በደስታ ማንባት - ነበር ምኞታቸው ግልባጩ ሆነ - ነገሩ ተሳክሮ ስደት በረከተ - ሰቆቃ እና ሮሮ ክቡር ሰው እሳቸው - የተስፋው ጀማሪ በሚያለቅሱት ሰዎች - ዋይታና እሪ! መደሰት ጀመሩ - አቁመው አዝማሪ ‘’

ተ/ገ (የስደተኛውማስታወሻ ገጽ 289)

ክቡርሰው እሳቸው መንግሰትን በመክዳት አጀማመራቸው ሁለተኛው መንግሰት ቢያቀማጥላቸው ለካ ‘ሳቸው ኑሮ.. ከሌላ ልባቸው.. ከሌላ ውላቸው ግልባጩ ሆነ ተሳክሮ ቀልባቸው። ክቡርሰው እሳቸው አጽማትን ቀስቅሰው ከጥንት እንቅልፋቸው ማበጣበጥ ሆነ የቀን ሌት ህልማቸው ሲጫረሱ ሊያዩ ተፋሶ ደማቸው።

ከዚህ ጽሁፍ አቅራቢ

Page 56: ማርከሻ ለ የሞት መርፌ - api.ning.comapi.ning.com/files/poTC6m2b82rkMz38uXDa*sLOeRr2Zc*dkAn32... · ውስጥ እያለ ‘’ የቡርቃ ዝምታ’’ በሚል

ደጃዝማች አብቹ ማርከሻ ለ-የሞት መርፌ

55

ተስፋዬ አይናቸውን ጨፍነው ዝሆን ምን እንደሚመስል ስለጎበኙ ሶስት ሰዎች

የሰማሁትን ቀልድ መሰለኝ እናም አዘንኩለት። ስለሰወቹ ሁኔታ እኔ ለጥንቃቄ

ቀይሬዋለሁ። ሰዎቹ አይናቸውን ጨፍነው ዝሆን ምን እንደሚመስል ሲጎበኙ

አስጎብኝው ላንደኛው የዝሆኑን ጆሮ ያስዳስሰውና ዝሆን ማለት ይሄነው ይለዋል።

ለሁለተኛው ደግሞ ኩንቢውን ያስዳብስና ዝሆን ማለት ይሄነው፣ ለሶስተኛውን ደግሞ

የዝሆኑን ታፋ ያስይዝና ዝሆን ማለት ይሄነው ይለዋል። በጛላ እነዚህ ስለ ዝሆን ሙሉ

እውቀት ያካበቱ ጎብኝዎች ሲጠየቁ እንዲህ ብለው ለየጠያቂዎቻቸው መልሰዋል።

ዝሆን ማለት እንደ ብረት ምጣድ ጠፍጣፋ እና ለስላሳ የሚተጣጠፍ ነገርነው አለ ጆሮ

የያዘው። ሲቀጥል ዝሆን ማለት ወፈር ያለ እና ቆልመም ያለ እንደ ዱላ አይነት ነው

አለ ኩምቢውን የዳሰሰው። ሶስተኛውና የዝሆን ታፋ ታቅፎ ዝሆንን ያየው ደግሞ

ዝሆን ማለት ወፈር እንዳለ ግንድ ሆኖ ለስለስ ያለ ነው አለ። እንግዲህ ተስፋዬም

ስለእግዚአብሄር የሚየውቀው እንዲሁ ሆኖ በአንዲት ገራገር ሴት፣ በአንድ ፓሰተር(

በእረግጥ ተስፋዬ የተሰጠው መልስ ፓሰተሩ አለኝ እንዳለው መሆኑን ማረጋገጥ

ባይቻልም (የፓስተሩንም ስም አውቆ ስላልነገረን) እና እራሱን እንደ አምላክ እንዲያይ

ባደረጉት ምንባቦቹ በፈጣሪ ላይ እይታው ተበላሽቷል።

እናም የምሬን አዘንኩለት።

ተስፋዬ አንባቢ ነው፣ ጸሃፊ ነው፣ስለብዙ ነገር የማወቅ ጉጉት አለው። ይሁንና ይህ

ጉጉቱ ኢትዮጵያን አፈራራሽ ቦምብ መቀመሚያ ንጥረ ነገር ለማግኘት ከሆነስ? የሚል

ስጋት አለኝ። አንዳንዴ ደግሞ እየተምታታበት ነው ጥሩ ነገር ሲናገር የምሰማው?

ወይስ ላደገኛው መልእክቱ መሳጭ ማሳለጫ እና ማዘናጊያ እያደረገው? ወይስ ግራ

ይጋባል? ብዬ እረሴን የጠየቅኩባቸው ብዙ ጊዜያት ኖረውኛል- መጽኀፉን ሳነብ።

አባት አገሩን ከኢሳያስ አፈወርቄ እኩል በእልህ ጭምር የሚወደው ተስፋዬ ግን ገር

ልባችንን እያሞኘ ዶሮማታ ብሎ መርዝ የሚወጋ ለአላማው የማያወላውል ሰላይ ነው

እንጂ ግራ የሚጋባም ሆነ ለኢትዮጵውያን ደግ የሚያስብ አይደለም። ሰዎችን ወደ

በጎነት የማያደርስ እውቀት ሁሉ የሞተ ነውና ተስፋዬ ሙትነው። እራሱ ተስፋዬ

እንዳለው ለዚህ ሰዎችን ለሚበጠብጥ አላማ አስከ ቆመ ድረስ ህሊናው ሞቷልና

እርሱም የቱንም ያህል ቢያነብ እና ቢያውቅ ሙት ሁኗል። የሰውልጅ መብራት

የሆነውን ህሊናን የፈጠረ ፈጣሪ ያንቃው!! በጣም ያስገረመኝ ነገር ቢኖር አነበብኩ

የሚላቸውን በጣም የቆዩ ኢትዮጵያ ውስጥ የተጸፉ መጽሃፍ ሁሉ ማን ይሆን

እየሰበሰበ የሚሰጠው? ሻአብያ ለዚህ ስራ የመደባቸው ይኖሩት ይሆን? ማለቴ እዚሁ

ኢትዮጵያ ውስጥ።

Page 57: ማርከሻ ለ የሞት መርፌ - api.ning.comapi.ning.com/files/poTC6m2b82rkMz38uXDa*sLOeRr2Zc*dkAn32... · ውስጥ እያለ ‘’ የቡርቃ ዝምታ’’ በሚል

ደጃዝማች አብቹ ማርከሻ ለ-የሞት መርፌ

56

ማጠቃለያ

የኢትዮጵያ ህዝብሆይ እንዲህ መከራ ከሚታይበት የአንድነትህ መፍረስና በአፍሪቃ

እና በአለም ላይ ያለህ ታሪከዊ ጉልህ ስፈራ መናድ እራስህን መከላከል የአንተና የአንተ

ሃላፊነት እና መብትም ብቻ ነው። ወጣቱ እና ተተኪው ትውልድ የሀገሩን ታሪክ

ጠንቅቆ ከማወቅ ይልቅ በእንቶ ፈንቶ ነገሮች እተወሰደ ባለበተ ጊዜ እነተስፋዬ ገ/ አብ

እና መሰሎቻቸው የሻብያን በጥንቃቄ የተቀመመ አገር በታኝ ህዝብ አጫራሽ ተንኮል

ሊግቱት ሲሯሯጡ ሃላፊነት የሚሰማችሁ ኢትየጵያውያን ሁሉ ትውልዱን እና

አገራችሁን ለማትረፍ የሚቻላችሁን ሁሉ ማድረግ የሚጠበቅባቸሁ ጊዜም እንደሆነ

እወቁ። ታላላቆቻችን እርስ በርስ በመጠላላፍ እና በመጠላላት ያሰለፈችሁት አገር ጎጂ

ነገር አሁን ይብቃቸሁ። አሁን ከእንቅለፋቸሁ ነቅታቸሁ ላገራቸሁ እና ለህዝባቸሁ በጎ

ነገር ለማውረስ፣ በጥሩም ለመካስ ለተውልድ ትልምን ተልሙ።

እንገዲህ የፈንጣጣው ገዳይ ህዋስ እስከተገኘ ድረስ መድሃኒቱም ተገኝ ማለት አይደል?

አሁን ለወረርሽኙ ፈጣን ክትባት የማዳረስ ዘመቻ ይጠበቅብናል። አሁን

ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውን የተባበረ ክንዳቸሁን አንሱ።

በእንቅስቃሲያችንም የሻአብያን አገር የማፍረስ ድግስ የሚቋቋም ስብእና በእውቀት

መገንባት የእያንዳንዳችን ግዴታ ሆኖ ተከታዩንም ትውልድ ይህን ሃላፊነቱን

እንዲያውቅና እንዲወጣም ማድረግ ይጠበቅብናል። ‘’የጠላቴ ጠላት ወዳጄ ነው’’

በሚል መፈክር እራሳችንን ያሞኘን ካለንም አቅጣጫችንን እንደገና መተለም

ይገባናል። ለረጅም አመታት ታቅዶ እና ተሰልቶ፣ የወደፊት ውጥን ውጤቱ ተናፍቆ

በረቀቀ ስልት ሲሰራ የኖረውን ይህን ደባ ለቅመን የምናስወግድበት ሰፊ ትእግስት እና

ብልሃትም ያስፈልገናል። ከምንም በላይ ለኛ ለኢትዮጵያውያን ከኛ ይልቅ

የሚያውቅልን፣ የሚጠነቀቅልንና የሚከውንልን እንደሌለ አበክረን ልናስብ እና ይንንም

አስከትለን ለኛ የሚበጀንን ሁሉ ተመካክረን እና ተቻችለን ማድረግን ደግሞ መልመድ

ይኖርብናል።

የኢንተር ሃሞዮቹ የሻአብያ እና የተላላኪው ተስፋዬ ውጥን እንደተጋለጠው ሁሉ

ሙሉ ለሙሉ ይከሽፋል!!!!!!!!!!!

ግን ግን ገራሚው ነገር እነርሱ አገሬን ለማፍረስ በነጻነት ሲጽፉ አኔ ግን አገሬን

ለማዳን ይህንን ነጻነት ማጣቴ ወይም መፍራቴ ነው። ምንላርግ?! ትንሽ አንኳን

ብከርም ብዬ ነው። መቼም እነዚህን ነገሮች የነካካ ከርሞ አይከርም።

Page 58: ማርከሻ ለ የሞት መርፌ - api.ning.comapi.ning.com/files/poTC6m2b82rkMz38uXDa*sLOeRr2Zc*dkAn32... · ውስጥ እያለ ‘’ የቡርቃ ዝምታ’’ በሚል

ደጃዝማች አብቹ ማርከሻ ለ-የሞት መርፌ

57

ውድ አንባቢያን! ፈጣሪ በቸር ያገናኘን! አገራችንንም ይባርክ!

‘’ትልቅ ነበርን ትልቅም እንሆናለን…!!!!!!’’ ሁሌ በሬዲዮ ስሰማው ደስ የሚለኝ ንግግር

Page 59: ማርከሻ ለ የሞት መርፌ - api.ning.comapi.ning.com/files/poTC6m2b82rkMz38uXDa*sLOeRr2Zc*dkAn32... · ውስጥ እያለ ‘’ የቡርቃ ዝምታ’’ በሚል

ደጃዝማች አብቹ ማርከሻ ለ-የሞት መርፌ

58

ዋቤ መጽሃፍት

ኃይላይ ሐድጉ፡ ተርጓሚ ብርሃኑ አባዲ፣ ፅንአት፣ 2002 ዓ.ም

መስፍን ወልደማሪያም፣ መክሸፍ እንደኢትየጵያ ታሪክ፣ 2005

ብርሃኑ አስረስ፣ የታህሳሱ ግርግር እና መዘዙ፡ማን ይናገር የነበረ፣ Ethiopia: Addis Ababa University Printing Press, 2005 ዓ.ም

በአሉ ግርማ፣ ኦሮማይ፣ አዲስ አበባ፡ ቦሌ ማተሚያቤት፣ 1984

ተስፋዬ ገብረአብ፣ የጋዜጠኛው ማስታወሻ፣ ኬፕ ታውን ደቡብ አፍሪካ፣ 2001 ዓ.ም/2009እ.ኤ. አ

ተስፋዬ ገብረአብ፣ የስደተኛው ማሰታወሻ፣ ኔዘርላንድ፣ 2006 ዓ.ም/ 2013 እ.ኤ. አ ተክለጻድቅ መኩሪያ፣ አጼ ቴዎድሮስ አና የኢትዮጵያ አንድነት፣ አዲስ አበባ፡

አርቲስቲክ ማተሚያ ቤት፣ 1981 ዓ.ም

Parlesak, Adolf, ተርጓሚ ተጫነ ጆብሬ፡ የሃበሻ ጀብዱ፣ Ethiopia: Addis Ababa University Printing Press, 2012እ.ኤ. አ

ታዲዮስ ጌታሁን፣ ሎሚ መጽሄት፡ተስፋዬ ገብረአብ ከሻብያ ጋር የተለዋወጣቸው ምስጢራዊ ማስታወሻዎች፣ቅጽ ሶስት ቁጥር 77 አዲስ አበባ፡ ሔሪቴጅ ማተሚያና ንግድ ኃ/የተ/የ.ግ.ማ፣ ጥቅምት 2006

እሸቱ ኢራና ዲባባ፣ የኦሮሞ ታሪክ፡ ከጥንት እስከ 1890ዎቹ መጨረሻ፣ አዲስ አበባ፡ 2001ዓ.ም/ 2009እ.ኤ. አ

ካሕሳይ አብርሃ፣ የአሲምባ ፍቅር፣ አዲስ አበባ፣2005

ዳንኤል ግዛው፡ ተርጓሚ መዝሙር ፈንቴ፣ የአፍሪካው ልዑል፣ 2004ዓ.ም

ፋንታሁን እንግዳ፣ በቀዳማዊ ኀይለስላሴ አስተዳደር ጎልተው የወጡ የፖለቲካ ችግሮች እና ትግሎች በቅርብ ባለሟላቸው የህይወት ታሪክ መነሻነት ሲገመገም፣ አዲስ አበባ፡ብርሃንና ሰላም ማተሚያቤት፣ 1997 ዓ.ም

ፍቃዱ ጉርሜሳ ኩሳ፣ የወንጌል እምነት እንቅስቃሴ በኢትዮጵያ፣ አዲስ አበባ፡መካነየሱስ የምስራች ድምጽ ስነጽሁፍ ክፍል፣ 1999 እ.ኤ. አ

ፍቅረማርቆስ ደስታ፣ ጃጋማ ኬሎ፡ የበጋው መብረቅ (የህይወተወ ታሪክ)፣ አዲስ አበባ፡ ማስተር ማተሚያ ቤት፣ 2001ዓ፣ም

ይልማ ደሬሳ፣ የኢትዮጵያ ታሪክ ፡በአስራ ስድስተኛው ክፍለዘመን፣ አዲስ አበባ፡1959 ዓ.ም

ጳውሎስ ኞኞ፣ አጤ ሚኒሊክ፣ አዲስ አበባ፣ 1999 ዓ.ም

Page 60: ማርከሻ ለ የሞት መርፌ - api.ning.comapi.ning.com/files/poTC6m2b82rkMz38uXDa*sLOeRr2Zc*dkAn32... · ውስጥ እያለ ‘’ የቡርቃ ዝምታ’’ በሚል

ደጃዝማች አብቹ ማርከሻ ለ-የሞት መርፌ

59

Bibliography

Baahru Zewde (PhD), A history of Modern Ethiopia: 1855-1991, Ethiopia: Addis Ababa University Printing Press, 2002

Campbell, Ian, The Plot to Kill Graziani: The Attempted Assassination of Mussolini’s Viceroy, Ethiopia: Addis Ababa University Printing Press, 2010

Henze, B. Paul, Layers of Time: A History of Ethiopia, Addis Ababa, Shama Books, 2004

Yohannes Kiros (PhD), Peace or war? Views on Ethio- Eritrean Conflict, Mekelle, Ethiopia: DESTA Publishing Press, 2010

WitheringtonIII, Ben, Conflict and Community in Corinth: A Socio- Rhetorical Commentary on 1 and 2 Corinthians, Grand Rapids, Michigan: William B. Erdmann’s publishing Company, 1998