በአባይ ግድብ ውስጥ 3 ንደ -...

24
ሰንደቅ 9ኛ ዓመት ቁጥር 431 ታህሳስ 02 2006 ዋጋ 6 ብር ኢኮኖሚ...8 ፖለቲካ...6 መዝናኛ...10 የኔ ሃሳብ...20 ኮሎኔል መንግስቱ ኃ/ማርያም ስለማንዴላ ይናገራሉ ለማንዴላ የ100ሺ ዶላር ድጋፍ ሰጥተናል ታመው አስታመናል በጋዜጣው ሪፖርተር ቀድሞ የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ኮሎኔል መንግስቱ ኃይለማርያም የማንዴላን ሞት በማስመልከት ሰሞኑን ከኤስቢኤስ ሚዲያ ጋር ባደረጉት ቃለመጠይቅ ማንዴላ እንደተፈቱ ወደ ኢትዮጵያ በመጡበት ወቅት የ100ሺ ዶላር ገንዘብ ልገሳ እንዳደረጉላቸው አስታወቁ። ኮሎኔል መንግስቱ በዚሁ ቃለምልልሳቸው ማንዴላ እንደተፈቱ መጀመሪያ ዙምባቡዌ ቀጥሎም ወደ ኢትዮጵያ መምጣታቸውን አስታውሰው ኢትዮጵያ የመጡት በአፍሪካ መሪዎች ስብሰባ ላይ ለመካፈል እንደነበር ጠቅሰዋል። ለስብሰባ አዲስአበባ በመጡበት ወቅት ገና የመፈታታቸው ጊዜ ስለነበር ጠና ያለ ሕመም አጋጥሞአቸው በአዲስአበባ አንድ ሳምንት የፈጀ ሕክምና መከታተላቸውና ማስታመማቸውን ገልጸው በዚህ አጋጣሚ ስለግለታሪካቸው፣ ስለእስራቸው ሁኔታ በስፋት የመወያየት ዕድል እንዳጋጠማቸው ተናግረዋል። በወቅቱ ገና ከእስር የተፈቱበት ወቅት ስለነበር ምን እንድርግልዎ ብለው እንደጠየቁዋቸውና እሳቸውም ምንም እንደማይፈልጉ ምላሽ እንደሰጡዋቸው የተናገሩት ኮሎኔሉ በራሳቸው ውሳኔ ማንዴላ በስውር ወደኢትዮጵያ መጥተው ወታደራዊ ስልጠና መከታተላቸውን፣ በወቅቱ የአሜሪካ እና የእስራኤል መንግስታት ለደቡብ አፍሪካ አፓርታይድ መንግስት ይወግኑ ስለነበር ሁኔታውን እግር በእግር ሲከታተሉት እንደቆዩ አስታውሰዋል ወደ ገፅ 3 ዞሯል ወደ ገፅ 6 ዞሯል ወደ ገፅ 3 ዞሯል በአሸናፊ ደምሴ የፌዴራሉ ሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን በሙስና ወንጀል በመጠርጠር በሶስት የተለያዩ መዝገቦች ስር ከባለስልጣናትና ባለሀብቶች ጋር ክስ የመሰረተባቸው አቶ መላኩ ፈንታ፤ ሚኒስትር በመሆኔ ጉዳዬ መታየት ያለበት በጠቅላይ ፍርድ ቤት ነው በማለት ባቀረቡት መከራከሪያ መሰረት ችሎቱ ጉዳዩ የሕገ መንግስት ትርጉም ያስፈልገዋል ሲል ለፌዴሬሽን ም/ ቤት የሕገመንግስት አጣሪ ጉባኤ መርቶታል። ጉባኤውም ይህንኑ ጉዳይ መርምሮ የሚሰጠው ውሳኔ በነገው ዕለት ይፋ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል። የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 15ኛ ወንጀል ችሎት ባለፈው ህዳር 11 ቀን 2006 ዓ.ም ባስቻለው ችሎቱ ላይ የቀድሞው የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር የነበሩት አቶ መላኩ ፈንታ ያነሱትን ክርክር ተከትሎ ብይን ለመስጠትና ጉዳያቸው መታየት ያለበት በከፍተኛው ፍርድ ቤት ነው? ወይስ በጠቅላይ ፍርድ ቤት? የሚለውን ለመወሰን ለታህሳስ 3 ቀን 2006 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱ ይታወሳል። ፍርድ ቤቱ የአቶ መላኩ ፈንታን ጉዳይ የሕገ-መንግስት ትርጓሜ ያስፈልገዋል ብሎ በዝርዝር ትንታኔ እንዲታይ ከማድረጉ በፊት የግራ ቀኙን የተከራካሪ ወገኖች ሀሳብ አድምጦና መዝገቦችንም አገላብጦ ባገኘው መረጃ መሰረት፤ በፌዴራል ፍርድ ቤቶች ማቋቋሚያ አዋጅ እና በተሻሻለው የፀረ-ሙስና ልዩ የስነ- ሥርዓትና የማስረጃ ሕግ መሰረት፣ ሚኒስትሮችን ጨምሮ የፌዴራል መንግስቱ ባለስልጣናት በስራ ኃላፊነታቸው ምክንያት ተጠያቂ በሚሆኑባቸው ወንጀሎች (ሙስናን ጨምሮ) በማናቸውም የወንጀል ጉዳዮች የፌዴራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የመጀመሪያ ደረጃ የስረ-ነገር ክርክር ማስኬጃ እንዲሆን ስልጣን የተሰጠው መሆኑ በግልፅ ተደንግጓል ብሏል። ሆኖም የነዚህ ሁለት አዋጆች ንዑሳን አንቀፆች ሕገ-መንግስታዊ ናቸው ወይም አይደሉም? የሚለው የተጣራ ትርጉም ያስፈልገዋል በሚል ጉዳዩን እልባት ለመስጠት ለፌዴሬሽን ምክር ቤት፣ የሕገ-መንግስት ጉዳዮች አጣሪ ኮሚቴ አጣርቶ ምላሽ እንዲሰጠው ትዕዛዝ ሰጥቷል። ይህም በመሆኑ ነገ ታህሳስ 3 ቀን 2006 ዓ.ም የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 15ኛ ወንጀል ችሎት በአቶ መላኩ ፈንታ ጉዳይ ላይ ሕገ-መንግስታዊ ትርጉሙ ላይ መቋጫ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል። እንደሚታወቀውም የፌዴራሉ የሥነ- ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን አቶ መላኩ ፈንታን ጨምሮ ከ31 በላይ ባስልጣናትንና ባለሀብቶችን በሶስት መዝገቦች ስር በሙስና ወንጀል ክስ መስርቶባቸዋል። በአቶ መላኩ ፈንታ ጉዳይ የተያዘው የሕገ-መንግስት ጥያቄ ነገ እልባት ያገኛል ሰዓታትን በአባይ ግድብ ውስጥ 2 ኢትዮቴሌኮም የሞሰ㠁됀呪 ቀፎ ምዝገባ ሊሰ눁簀묀愁阀 • የተሰረቁ የሞባይል ስልኮች አገልግሎት እንዳይሰጡ የሚያደርግ ቴክኖሎጂም ስራ ላይ ይውላል በፀጋው መላኩ ኢትዮቴሌኮም አሁን ባለው የቴሌኮም ማጭበርበር (Telecom fraud) ጋር በተያያዘ እየተፈጠረ ላለው ችግር መፍትሄ ለመስጠት በሞባይል ቀፎዎች ላይ ምዝገባ ለማካሄድ እየተዘጋጀ ነው። ምዝገባው የሚካሄደው የስልክ ቀፎዎቹ ሀገር ውስጥ በሚገቡበት ወቅት እና ከሥራ ላይ ያሉትም በመመዝገብ ሲሆን እያንዳንዱ የሞባይል ስልክ ሲመረት በራሱ መለያ ቁጥር ያለው በመሆኑ ምዝገባውም የሚከናወነው በዚሁ መሰረት መሆኑ ታውቋል። በዚሁ ዙሪያ ለሰንደቅ ማብራሪያ የሰጡት የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የሚኒስትሩ የቴክኒክ አማካሪ ዶ/ር መስፍን በላቸው በቀጣይ በሀገሪቱ ኔትወርክ ሲስተም ውስጥ እንዲሰሩ የሚደረጉት በኢትዮቴሌኮም የተመዘገቡ የሞባይል የስልክ ቀፎዎች ብቻ ናቸው። እንደ ዶ/ር መስፍን ገለፃ የሞባይል ቀፎ ምዝገባን ማካሄዱ ያልተፈቀዱ ሞባይል ቀፎዎች በኢትዮጵያ ኔትወርክ ውስጥ እንዳይሰሩ በማድረግ የቴሌኮም ማጭበርበርን መከላከል የሚያስችል ነው። ከዚህም በተጨማሪ በአንድ ደንበኛ ስም በኢትዮቴሌኮም የተመዘገበ ሞባይል መጥፋቱ በባለቤቱ ከተረጋገጠና ኩባንያው ቀፎው

Upload: vonga

Post on 29-Aug-2019

250 views

Category:

Documents


0 download

TRANSCRIPT

Page 1: በአባይ ግድብ ውስጥ 3 ንደ - ethioforum.orgethioforum.org/wp-content/uploads/2013/12/Sendekdec102013.pdfሰንደቅ 9ኛ ዓመት ቁጥር 431 ታህሳስ 02 2006

ሰንደቅ 9ኛ ዓመት ቁጥር 431 ታህሳስ 02 2006 ዋጋ 6 ብር

3

ኢኮኖሚ

...8

ፖለቲ

ካ...6

መዝናኛ

...10

የኔ ሃ

ሳብ...20

ሰንደቅኮሎኔል መንግስቱ ኃ/ማርያም ስለማንዴላ ይናገራሉ • ለማንዴላ የ100ሺ ዶላር ድጋፍ ሰጥተናል • ታመው አስታመናል

በጋዜጣው ሪፖርተር

የቀድሞ የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ኮሎኔል መንግስቱ ኃይለማርያም የማንዴላን ሞት በማስመልከት ሰሞኑን ከኤስቢኤስ ሚዲያ ጋር ባደረጉት ቃለመጠይቅ

ማንዴላ እንደተፈቱ ወደ ኢትዮጵያ በመጡበት ወቅት የ100ሺ ዶላር ገንዘብ ልገሳ እንዳደረጉላቸው አስታወቁ።

ኮሎኔል መንግስቱ በዚሁ ቃለምልልሳቸው ማንዴላ እንደተፈቱ መጀመሪያ ዙምባቡዌ ቀጥሎም ወደ ኢትዮጵያ መምጣታቸውን አስታውሰው ኢትዮጵያ የመጡት በአፍሪካ መሪዎች ስብሰባ ላይ ለመካፈል እንደነበር ጠቅሰዋል። ለስብሰባ አዲስአበባ በመጡበት ወቅት ገና የመፈታታቸው ጊዜ ስለነበር ጠና ያለ ሕመም አጋጥሞአቸው በአዲስአበባ አንድ ሳምንት የፈጀ ሕክምና መከታተላቸውና ማስታመማቸውን ገልጸው በዚህ አጋጣሚ ስለግለታሪካቸው፣ ስለእስራቸው ሁኔታ በስፋት የመወያየት ዕድል እንዳጋጠማቸው ተናግረዋል። በወቅቱ ገና ከእስር የተፈቱበት ወቅት ስለነበር ምን እንድርግልዎ ብለው እንደጠየቁዋቸውና እሳቸውም ምንም እንደማይፈልጉ ምላሽ እንደሰጡዋቸው የተናገሩት ኮሎኔሉ በራሳቸው ውሳኔ

ማንዴላ በስውር

ወደኢትዮጵያ መጥተው

ወታደራዊ ስልጠና

መከታተላቸውን፣ በወቅቱ

የአሜሪካ እና የእስራኤል

መንግስታት ለደቡብ

አፍሪካ አፓርታይድ

መንግስት ይወግኑ ስለነበር

ሁኔታውን እግር በእግር

ሲከታተሉት እንደቆዩ

አስታውሰዋል

ወደ ገፅ 3 ዞሯል

ወደ ገፅ 6 ዞሯል

ወደ ገፅ 3 ዞሯል

በአሸናፊ ደምሴ

የፌዴራሉ ሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን በሙስና ወንጀል በመጠርጠር በሶስት የተለያዩ መዝገቦች ስር ከባለስልጣናትና ባለሀብቶች ጋር ክስ የመሰረተባቸው አቶ መላኩ ፈንታ፤ ሚኒስትር በመሆኔ ጉዳዬ መታየት ያለበት በጠቅላይ ፍርድ ቤት ነው በማለት ባቀረቡት መከራከሪያ መሰረት ችሎቱ ጉዳዩ የሕገ መንግስት ትርጉም ያስፈልገዋል ሲል ለፌዴሬሽን ም/ቤት የሕገመንግስት አጣሪ ጉባኤ መርቶታል። ጉባኤውም ይህንኑ ጉዳይ መርምሮ የሚሰጠው ውሳኔ በነገው ዕለት ይፋ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።

የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 15ኛ ወንጀል ችሎት ባለፈው ህዳር 11 ቀን 2006 ዓ.ም ባስቻለው ችሎቱ ላይ የቀድሞው የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር የነበሩት አቶ መላኩ ፈንታ ያነሱትን ክርክር ተከትሎ ብይን ለመስጠትና ጉዳያቸው መታየት ያለበት በከፍተኛው ፍርድ ቤት ነው? ወይስ በጠቅላይ ፍርድ ቤት? የሚለውን

ለመወሰን ለታህሳስ 3 ቀን 2006 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱ ይታወሳል።

ፍርድ ቤቱ የአቶ መላኩ ፈንታን ጉዳይ የሕገ-መንግስት ትርጓሜ ያስፈልገዋል ብሎ በዝርዝር ትንታኔ እንዲታይ ከማድረጉ በፊት የግራ ቀኙን የተከራካሪ ወገኖች ሀሳብ አድምጦና መዝገቦችንም አገላብጦ ባገኘው መረጃ መሰረት፤ በፌዴራል ፍርድ ቤቶች ማቋቋሚያ አዋጅ እና በተሻሻለው የፀረ-ሙስና ልዩ የስነ-ሥርዓትና የማስረጃ ሕግ መሰረት፣ ሚኒስትሮችን ጨምሮ የፌዴራል

መንግስቱ ባለስልጣናት በስራ ኃላፊነታቸው ምክንያት ተጠያቂ በሚሆኑባቸው ወንጀሎች (ሙስናን ጨምሮ) በማናቸውም የወንጀል ጉዳዮች የፌዴራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የመጀመሪያ ደረጃ የስረ-ነገር ክርክር ማስኬጃ እንዲሆን ስልጣን የተሰጠው መሆኑ በግልፅ ተደንግጓል ብሏል። ሆኖም የነዚህ ሁለት አዋጆች ንዑሳን አንቀፆች ሕገ-መንግስታዊ ናቸው ወይም አይደሉም? የሚለው የተጣራ ትርጉም ያስፈልገዋል በሚል ጉዳዩን እልባት ለመስጠት ለፌዴሬሽን ምክር ቤት፣ የሕገ-መንግስት ጉዳዮች አጣሪ ኮሚቴ አጣርቶ ምላሽ እንዲሰጠው ትዕዛዝ ሰጥቷል።

ይህም በመሆኑ ነገ ታህሳስ 3 ቀን 2006 ዓ.ም የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 15ኛ ወንጀል ችሎት በአቶ መላኩ ፈንታ ጉዳይ ላይ ሕገ-መንግስታዊ ትርጉሙ ላይ መቋጫ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል። እንደሚታወቀውም የፌዴራሉ የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን አቶ መላኩ ፈንታን ጨምሮ ከ31 በላይ ባስልጣናትንና ባለሀብቶችን በሶስት መዝገቦች ስር በሙስና ወንጀል ክስ መስርቶባቸዋል።

በአቶ መላኩ ፈንታ ጉዳይ የተያዘው የሕገ-መንግስት ጥያቄ ነገ እልባት ያገኛል

ሰዓታትንበአባይ ግድብ ውስጥ2

ኢትዮቴሌኮም የሞባይል ቀፎ ምዝገባ ሊያካሄድ ነው

• የተሰረቁ የሞባይል ስልኮች አገልግሎት እንዳይሰጡየሚያደርግ ቴክኖሎጂም ስራ ላይ ይውላል

በፀጋው መላኩ

ኢትዮቴሌኮም አሁን ባለው የቴሌኮም ማጭበርበር (Telecom fraud) ጋር በተያያዘ እየተፈጠረ ላለው ችግር መፍትሄ ለመስጠት በሞባይል ቀፎዎች ላይ ምዝገባ ለማካሄድ እየተዘጋጀ ነው። ምዝገባው የሚካሄደው የስልክ ቀፎዎቹ ሀገር ውስጥ በሚገቡበት ወቅት እና ከሥራ ላይ ያሉትም በመመዝገብ ሲሆን እያንዳንዱ የሞባይል ስልክ ሲመረት በራሱ መለያ ቁጥር ያለው በመሆኑ ምዝገባውም የሚከናወነው በዚሁ መሰረት መሆኑ ታውቋል። በዚሁ ዙሪያ ለሰንደቅ ማብራሪያ የሰጡት የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የሚኒስትሩ የቴክኒክ አማካሪ ዶ/ር መስፍን በላቸው በቀጣይ በሀገሪቱ ኔትወርክ ሲስተም ውስጥ እንዲሰሩ የሚደረጉት በኢትዮቴሌኮም የተመዘገቡ የሞባይል የስልክ ቀፎዎች ብቻ ናቸው። እንደ ዶ/ር መስፍን ገለፃ የሞባይል ቀፎ ምዝገባን ማካሄዱ ያልተፈቀዱ ሞባይል ቀፎዎች በኢትዮጵያ ኔትወርክ ውስጥ እንዳይሰሩ በማድረግ የቴሌኮም ማጭበርበርን መከላከል የሚያስችል ነው። ከዚህም በተጨማሪ በአንድ ደንበኛ ስም በኢትዮቴሌኮም የተመዘገበ ሞባይል መጥፋቱ በባለቤቱ ከተረጋገጠና ኩባንያው ቀፎው

Page 2: በአባይ ግድብ ውስጥ 3 ንደ - ethioforum.orgethioforum.org/wp-content/uploads/2013/12/Sendekdec102013.pdfሰንደቅ 9ኛ ዓመት ቁጥር 431 ታህሳስ 02 2006

ሰንደቅ 9ኛ ዓመት ቁጥር 431 ረቡዕ ታህሳስ 02 2006

አታሚ፤ ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት አድራሻ፤ አራዳ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 07 የቤት ቁጥር 984

የአሳታሚው አድራሻ:- ቦሌ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 05/03 የቤት ቁጥር 027 ከአትላስ ሆቴል በስተጀርባ 011-6-62 81 90/ 011-6-18 40 34/ 0911 73 59 18 / 0911 95 58 16 ፖ.ሣ.ቁ. 80964

“ሰንደቅ” ጋዜጣ በሰንደቅ የሕትመትና የማስታወቂያ አገልግሎት ኃ/የተ/የግ/ማኅበር በንግድ ሚኒስቴር በንግድ ሥራ ፈቃድ ቁጥር 14/673/7498/2004፣ በብሮድካስት ባለሥልጣን የምዝገባ ቁጥር 38/2001 የተመዘገበ ሳምንታዊ ጋዜጣ ነው

የገበያ ጥናት፤የማስታወቂያ እና ስርጭት

ባይለየኝ ወርቁ 0921 56 95 030912 95 67 95

ዋና አዘጋጅ ፍሬው አበበቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 የቤት ቁጥር 12/201

0911 61 79 [email protected]

ም/ዋና አዘጋጅፋኑኤል ክንፉ 0911 [email protected]

ከፍተኛ አዘጋጅ ዘሪሁን ሙሉጌታ [email protected]

አዘጋጅ ፀጋው መላኩ

ከፍተኛ ሪፖርተሮች አሸናፊ ደምሴ መስከረም አያሌው

ግራፊክ ኤዲተርነብዩ መሥፍን 0911 18 09 [email protected]

ኮምፒዩተር ጽሁፍ አለምነሽ ታከለሰብለወንጌል ንጉሴ ምናለሸዋ ተ/አረጋይ

ርዕሰ አንቀጽ

ቁጥሮች16489621487965214569856154685548565541857985648985654+689554465418956898+548655544 16489621487965214569856154685548565541857985648985654+689554465418956898+548655544 16489621487965214569856154685548565541857985648985654+689554465418956898+548655544251845586854178854818565

2

መ ል ዕ ክ ቶ ች

ህትመት ክትትልና ስርጭት በዛብህ ተክሉ 0911 41 68 00

114ሺ 320ከሳዑዲአረቢያ እስካለፈው እሁድ ድረስ

የተመለሱ ኢትዮጵያዊያን ቁጥር

ከ10-15ሺበቀጣይ ቀናት ይገባሉ ተብሎ

የሚጠበቁ ኢትዮጵያዊያን ቁጥር

ከ50-80ሺየውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የነበረው

የተመላሾች ቁጥር ግምት

ምንጭ - የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር¾

ህዳር 26/2006 ዓ.ም በኤፍ ኤም አዲስ 97.1 ከጠዋቱ ሶስት እስከ አምስት ሰዐት በገበያኑ ቢዝነስ ፕሮሞሽን የሚዘጋጀውን የ“አገልግል” ፕሮግራም የቀጥታ የስልክ ጥያቄ እና መልስ ውድድር እየሰማሁ ነበር። ከቀረቡት ጥያቄዎች መካከል ለአንዱ የተሰጠውን መልስ፣ “ስህተት” ብሎ ከማለፍም በላይ ያናድዳል።

ጥያቄው፣ “የ‘ወንጀለኛው ዳኛ’ መጽሐፍ ደራሲ ማን ይባላሉ?” የሚል ሲሆን አንድ አድማጭ ገባና፣ “ሀዲስ ዓለማየሁ” አለ። ጥያቄውን ያቀረበው ሰሎሞን ሹምዬ ቆጣ ብሎ፣ “ትክክል አይደለም!” አለ።

ይህን መጽሐፍ ስላነበብሁት እና በስነ ጽሑፍ ትምህርት

ላይም ስለተማርሁበት እንዲሁም ዛሬ ቢጠፋብኝም ለረጅም ጊዜ ቤቴ ስለነበር ያለ ጥርጥር የሀዲስ ዓለማየሁ ስለመሆኑ እተማመንበታለሁ። ቢሆንም፤ ሰሎሞንን የሚያክልና፣ “የንባብ ልምድ አለው” የሚባል ሰው ይሳሳተዋል ብዬ አልገምትም። እናም፤ ተናድጄ በሬዲዮ በሰጠን የጽሑፍ መልዕክት መላኪያ ቁጥር ተግሳፅ ያዘለ ማረሚያ ላክሁለት። ብዙም ሳይቆይ ሌላ አድማጭ ደውሎ ለዚሁ ጥያቄ መልሱን፣ “ሀዲስ ዓለማየሁ” አለ። ሰሎሞን ግን አሁንም ግትርነቱ ላይ ሆኖ፣ “ተሳስተሃል” አለ።

እሱ ይህን ሲል የእኔም ንዴት ጨምሮ ስልክ ወደ 97.1 ስቱዲዮ መታሁ፤ ግን አልተሳካም። የፕሮግራሙ መጨረሻ ላይ ማጠቃለያ መልስ ሲሰጥ ግን ንዴቴን እንኳን ሬዲዮውን የሰማ፤ የዚህን

ጽሑፍ ያነበበውም ይጋራዋል።“የ‘ወንጀለኛው ዳኛ’ መጽሐፍ ደራሲ ማን ይባላሉ? ብለን

ለጠየቅነው ጥያቄ አንድም ሰው መልስ አለማግኘቱ በጣም ነው የገረመኝ። ይህን የሚያክል መጽሐፍ ደራሲ ሀዲስ ዓለማየሁ ሳይሆኑ በዐሉ ግርማ ነው” አለና አረፈዋ!

ጎበዝ፣ ይህንን ምን ይሏል? በበኩሌ፣ “ሳይገድሉ ጎፈሬ፤ ሳያጣሩ ወሬ” ወይም፣ “ከመጠምጠም፤ መማር ይቅደም” ብዬዋለሁና መቶ በመቶ እርግጠኛ ያልሆንበትን ነገር አየር ላይ ይዘን ባንወጣ!

እስክንድር ከአ/አ¾

የ“ወንጀለኛው ዳኛ” መጽሐፍ ደራሲ፤

ሐዲስ ዓለማየሁ ወይስ በዓሉ ግርማ?

የነጻነትና ታጋይና ተምሳሌቱ ኔልሰን ማንዴላ ከዚህ ዓለም በሞት መለየት ባሳለፍነው ሳምንት ሲሰማ መርዶው ድፍን ዓለምን አሳዝኗል። አገራት የኔልሰን ማንዴላ ደግነት፣ አርቆ አሳቢነት፣ ይቅርባይነት በማስታወስ ሐዘናቸውን በመግለጽ ላይ ይገኛሉ። ማንዴላ ከ50 ዓመት በፊት ወደኢትዮጵያ መጥተው ወታደራዊ ስልጠና ማግኘታቸው፣ በወቅቱ አገራችንም ለጸረ አፓርታይድ ትግሉ ያበረከተችው አዎንታዊ አስተዋጽኦ የጎላ መሆን በራሱ ኢትዮጵያዊን ለማንዴላ የተለየ ትኩረትና የተቆርቋሪነት ስሜት እንድናጎለብት አድርጎናል። እሳቸውም ከ27 የእስርና የመከራ ዓመታት ቆይታ በኋላ በነጻነት ወቅት በጻፉት “Long Walk To Freedom” መጽሐፋቸው ኢትዮጵያ በእሳቸው ውስጥ ልዩ ስፍራ ያላት አገር መሆኗን መስክረዋል። አያይዘውም “በፈረንሳይ፣ በእንግሊዝ እና በአሜሪካ ያደረኳቸው ጉብኝቶች ቢደመሩ እንኳን፤ በኢትዮጵያ ከነበረኝ ቆይታ አይበልጡም” ሲሉ ያላቸውን ልዩ ስሜት ተናግረዋል።

የማንዴላ ሕልፈተ ሕይወት ከተሰማ በኋላ የተለያዩ መንግስታት ሐዘናቸውን የገለጹ ሲሆን የኢትዮጵያም ፓርላማ ካለፈው ሰኞ ዕለት ጀምሮ ዛሬ የሚያበቃ፤ የአገሪቱ ባንዲራ ዝቅ ለሦስት ቀናት ብሎ እንዲውለበለብል

ወስኖ ተግባራዊ በመሆን ላይ ይገኛል። የአፍሪካ ህብረትም ሊቀመንበሩ አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ በተገኙበት ከትላንት በስቲያ የመታሰቢያ ስነስርዓት በአዲስአበባ አከናውኗል።

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ፤ ኔልሰን ማንዴላ የያኔዋን አፍሪካ ገጽታ የሚያሳዩን መስታወት ነበሩ ካሉ በኋላ አፍሪካ ከመከፋፈል ይልቅ ለጋራ ጥቅም በጋራ መስራትን ከማንዴላ ተምራለች ብለዋል።

በእርግጥም ከማንዴላ የምንማረው የትየለሌ ቁምነገሮች አሉ። በአፓርታይድ አገዛዝ ኢ-ሰብዓዊ ድርጊቶችን ሲፈጽሙና ሲያስፈጽሙ የኖሩ ዘረኞችን ጭምር በይቅርታና በፍቅር መቅጣት የቻሉ እንዲሁም ቂም በቀልና ጥላቻ በሕዝቦች መካከል ምንም የሚፈይደው ነገር እንደሌለ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በተግባር ማሳየት፣ ማስተማር የቻሉ ተወዳጅ የሰላም መሪ ነበሩ። እንደተወደዱ፣ እንደተከበሩ ወደማይቀረው ዓለም የተጓዙት ማንዴላን ስናስብ ጥለውልን በሄዱት መልካም አስተምህሮዎቻቸው እየተጽናናንም ጭምር ነው። ነፍሳቸውን በገነት ያኖርልን ዘንድ ምኞታችን ነው።¾

ማንዴላን ስናስብ

Page 3: በአባይ ግድብ ውስጥ 3 ንደ - ethioforum.orgethioforum.org/wp-content/uploads/2013/12/Sendekdec102013.pdfሰንደቅ 9ኛ ዓመት ቁጥር 431 ታህሳስ 02 2006

ሰንደቅ 9ኛ ዓመት ቁጥር 431 ረቡዕ ታህሳስ 02 2006 3ዜና

በዓለም፣ በኤድናሞል፣ በሴባስቶፖል (ኤግዚቢሽን)፣ በሴባስቶፖል (ላፍቶ ሞል)፣ በሀበሻ፣ በሀድሜስ፣ በእምቢልታ፣ በሰበታ ጂም፣ በዮፍታሔ፣ በሆሊሲቲ፣ በካፍደም፣ በቤተል ሲና፣ በዋፋ፣ በሻሎም፣ በፍፁም፣ በአጐና፣ በእዮሐ እና

በአጠቃላይ በሁሉም የግል ሲኒማ ቤቶች በመታየት ላይ ነው፡፡

የደብረማርቆስ ከተማ በስኳር እጥረት እየታመሰች ነው

• 1 ኪሎ ስኳር እስከ 40 ብር እየተሸጠ ነው

በዘሪሁን ሙሉጌታ

በአማራ ክልል የምስራቅ ጎጃም ዞን ዋና ከተማ በሆነችው ደብረ-ማርቆስ ከተማ በከፍተኛ የስኳር ምርት እጥረት እየታመሰች ነው። የከተማዋ ነዋሪዎች በስፍራው ለነበረው የሰንደቅ ጋዜጣ ሪፖርተር እንደገለፁት፤ በከተማዋ ውስጥ የአንድ ኪሎ ስኳር ዋጋ ከ30 እስከ 40 ብር እየተሸጠ መሆኑን ተናግረዋል።

በከተማዋ የስኳር እጥረቱ ቢባባስም በአጎራባች ወረዳዎች ግን በቂ ስኳር መኖሩ ሁኔታውን እንቆቅልሽ እንዳደረገባቸው ነዋሪዎቹ ተናግረዋል። የስኳር እጥረቱ በመከሰቱ ነዋሪዎች፣ ባለሆቴሎችና ሌሎች የሕዝብ አገልግሎት ተቋማት ላይ ችግር ማስከተሉን ከነዋሪዎች ገለፃ መረዳት ተችሏል። እንደነዋሪዎቹ ገለፃ፤ ለከተማዋ ከጅንአድ የተመደበው ወርሃዊ የስኳር ኮታ ተጠልፎ ለሕገ-ወጥ ነጋዴዎች ተላልፎ በመሰጠቱ ሰው ሰራሽ የስኳር እጥረት መፈጠሩን ተናግረዋል።

በጉዳዩ ላይ መረጃ እንዲሰጥ የተጠየቀው የምስራቅ ጎጃም ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ ችግሩ መከሰቱን አምኖ እርምጃ መውሰድ መጀመሩን አስታውቋል።

የቢሮው ኃላፊ አቶ አማረ አለሙ ችግሩን በተመለከተ በከተማዋ የስኳር እጥረት ሳይሆን የስርጭት ችግር አለ ብለዋል። ለደብረማርቆስ ከተማ ለድርጅቶችም ሆነ ለተጠቃሚው በነፍስ-ወከፍ በአንድ ወር ዘጠኝ ኪሎ ግራም እንዲደርሳቸው መመደቡን አስታውሰው፤ ነገር ግን በስኳር ስርጭቱ ከጅንአድ፣ ወደ ጅምላ አከፋፋይ እንዲሁም ወደ ቸርቻሪ በተጨማሪም ከቸርቻሪ በልማት ቡድን አማካኝነት ወደኅብረተሰቡ እንዲወርድ ቢደረግም የጅምላ አከፋፋዮቹ ከጅንአድ ያወጡትን ስኳር በቀጥታ በጥቁር ገበያ በመሸጣቸው እንዲሁም ቸርቻሪዎች በተረከቡት የስኳር መጠን ልክ ለኅብረተሰቡ ባለማሰራጨታቸው ችግር መፈጠሩን ደርሰንበታል ብለዋል።

በከተማዋ በጠቅላላ 160 ቸርቻሪዎች እንዳሉ የጠቀሱት ኃላፊው 23 ባለሙያዎች ተመድበው ችግሩን የመለየት ስራ መሠራቱንና ለማርቆስ ከተማ ተብሎ የወጣው ስኳር ወደ ሌላ ቦታ ተወስዶ በመሸጡ እንደሆነ ገልፀዋል። ለከተማዋ ከጅንአድ በወር 1 ሺህ 658 ኩንታል መሆኑን የጠቀሱት ኃላፊው የስኳር መጠኑ ለተጠቃሚው፣ ለሆቴሎች እና ለዩኒቨርሲቲው መሆኑን ጠቅሰው፤ በነፍስወከፍ ለአንድ ሰው እስከ ዘጠኝ ኪሎ ግራም ይደርሰዋል ብለዋል። ቢሮው የቁጥጥርና የክትትል ችግርም ስለነበረበት የከተማ አስተዳደሩ ንግድና ትራንስፖርት ጽ/ቤት ሂስና ግለ ሂስ ተደርጎ አሰራሩን እንደገና በማዋቀር ላይ በመሆኑ እጥረቱ ይፈታል ብለዋል። ችግር አለባቸው የተባሉ አንዳንድ ቸርቻሪዎች ሱቃቸው መታሸጉን በመስሪያ ቤት ደረጃ ችግር ያለባቸውን ሰዎች በቀጣይ የዲሲፕሊን እርምጃ ይወሰዳል ሲሉ ኃላፊው ጨምረው ገልፀዋል።¾

አዲስ የጋዜጠኞች ማኅበር ሊመሰረት ነው

• በነገው ዕለት የማኅበሩን ምስረታ በተመለከተ ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣል

በዘሪሁን ሙሉጌታ

በሀገሪቱ የሚገኙ የሁሉንም ጋዜጠኞች መብትና ጥቅም በተሻለ መንገድ ለማስጠበቅ፣ ከሌሎች በሙያው ከሚሰሩ አካላት ጋር ግንኙነት ለማጠናከርና በዘርፉም መልካም ስራ ላበረከቱ ጋዜጠኞች እውቅና መስጠትን ያለመ አዲስ የጋዜጠኞች ማኅበር ሊመሠረት ነው።

መጠሪያውን “የኢትዮጵያ የጋዜጠኞች መድረክ” (ኢጋመ) በማለት የሚመሠረተው ይኸው አዲስ ማኅበር ወደ ስድስት ዓላማዎች እንዳሉት መስራቾቹ ካሰራጩት መግለጫ ለመረዳት ተችሏል። የማኅበሩ ስድስት ዓላማዎች በኢፌድሪ ሕገ-መንግስት አንቀጽ 29 መሠረት የተፈቀደውን ኀሳብን በነፃ የመግለፅ ነፃነት መብት ተግባራዊ ለማድረግ፣ የጋዜጠኞችን መብትና ጥቅም ማስጠበቅ፣ በተከታታይ ትምህርትና ስልጠና የጋዜጠኞችን ሙያ ማሳደግ፣ በኢትዮጵያ ጋዜጠኞች መካከል ያለውን ግንኙነት ማጠናከር፣ አስፈላጊ ሆኖ በተገኘ ጊዜም ለጋዜጠኞች የገንዘብና ሕጋዊ ድጋፍ ለመስጠት እና በዘርፉ አስተዋፅኦ ላደረጉ ጋዜጠኞች እውቅና መስጠት የሚሉ አላማዎችን አንግቧል።

ማኅበሩ የሚመሠረተው በሕገ-መንግስቱ አንቀጽ 30 በተፈቀደው የመደራጀት መብት መሆኑን መስራቾቹ ካዘጋጁት መተዳደሪያ ደንብ ላይ የተገለፀ ሲሆን፤ የመድረኩ መተዳደሪያ ደንብ ከበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማኅበራት አዋጅ ቁጥር 621/2001 ጋር ተጣጥሞ መዘጋጀቱም ታውቋል።

የማኅበሩ መስራቾች በአሁኑ ወቅት በተለያዩ ሚዲያዎች ላይ በመስራት ላይ የሚገኙ ሲሆን፤ ካለፈው ጥቅምት 30 ቀን 2006 ዓ.ም ጀምሮ በማኅበር ምስረታው ላይ ተከታታይ ውይይት በማድረግ፣ ስምንት አባላት የተካተቱበት የመስራች ኮሚቴ አባላትን በማዋቀር ሲንቀሳቀሱ ቆይተዋል።

ለማኅበሩ መመስረት የተዋቀረውም ኮሚቴ የማኅበሩ ሰነዶች በአማርኛና በእንግሊዘኛ በማዘጋጀት፣ የማኅበሩን መተዳደሪያ በማርቀቅ፣ ለሀገር ውስጥና ለውጪ አካላት የማኅበሩን ፕሮፋይል በማዘጋጀት፣ የአባላት መመዝገቢያ ቅጽ እና የማኅበሩ ገንዘብ ማሰባሰቢያ ቅጾችና ሌሎች ተግባራትን ሲያከናውኑ መቆየታቸውም ታውቋል።

በነገውም ዕለት ማኅበሩ በምስረታ ላይ መሆኑ በይፋ ከተገለፀ በኋላ ከጥቂት ቀናት በኋላ የማኅበሩን ጠቅላላ ጉባኤ በማካሄድ የአመራሮች ምርጫ እንደሚከናወንም መስራቾቹ ለሰንደቅ ጋዜጣ ገልፀዋል።

ለማኅበሩ መመስረት በወሳኝ መልኩ በሀገሪቱ የጋዜጠኞች መብትን ከማስጠበቅ፣ ሙያን ማዕከል ያደረገና በኃላፊነት መንፈስ የታነፀ ፕሬስ ከመገንባት ባሻገር በቅርቡ በኢትዮ-ምህዳር ጋዜጠኛ ኤፍሬም በየነ ላይ የደረሰው ከፍተኛ አደጋ በስራ ላይ ባሉ ጋዜጠኞች ላይ ከፍተኛ መደናገጥን በመፍጠሩ መሆኑም ከማኅበሩ መስራቾቹ መረዳት ተችሏል። በቀጣይም ማኅበሩን እውን በማድረግ በጋዜጠኞች ላይ ከየትኛውም አቅጣጫ የሚመጣን አደጋ ለመከላከል ታልሞ ማኅበሩ ለመመስረት መታሰቡን ከመስራቾቹ መረዳት ተችሏል።¾

በአክስቱ ላይ በስለት የታገዘ ዝርፊያ ሊፈፅም የነበረው ወጣት ተቀጣ

በአሸናፊ ደምሴ

የቅርብ ዝምድና ካላቸው አክስቱ ወርቅ እና ገንዘብ ለመዝረፍ ሲል በስለት የታገዘ ውንብድና ፈፅሟል ሲል የፌዴራሉ ዐቃቤ ሕግ ክስ የመሠረተበት ወጣት፤ በፈፀመው ከባድ የውንብድና ሙከራ ወንጀል ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ በትናንትናው ዕለት በ5 ዓመት ጽኑ እስራት ተቀጣ።

የፌዴራሉ ዐቃቤ ሕግ በክስ መዝገቡ እንዳስረዳው መብራቱ ገናናው የተባለው ይህ ወጣት ካልተያዘ ግብር-አበሩ ጋር በመሆን ኮልፌ ቀራኒዮ ወረዳ 8፣ ቢራ ሰፈር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ከሚገኘው የአክስቱ ቤት በመግባትና ተበዳይን በስለት በማስፈራራት ያለሽን ወርቅና ብር ስጪኝ ማለቱን ያተተው የዐቃቤ ሕግ መዝገብ፤ የግል ተበዳይም የድረሱልኝ ጥሪ በማሰማታቸው ጐረቤት ደርሶ ያስጣላቸው መሆኑንና የተከሳሽ ግብረ-አበር ግን ወዲያው መሰወሩን በዝርዝር ያትታል። በመሆኑም ተከሳሽ በፈፀመው ከባድ የውንብድና ሙከራ ወንጀል ሊከሰስ ይገባል ያለው ዐቃቤ ሕግ የሰውና የሰነድ ማስረጃዎችን ለፍርድ ቤቱ ያቀረበ ሲሆን፤ የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 3ኛ ወንጀል ችሎትም ተከሳሹ የተመሠረተበትን ክስ በአግባቡ አልተከላከለም ሲል ጥፋተኛ ብሎት ነበር።

ለቅጣት በተያዘው ቀጠሮ መሠረትም ተከሳሹ ያቀረበውን የቅጣት ማቅለያና ዐቃቤ ሕግ ያሰፈረውን የቅጣት ማክበጃ ከግምት ውስጥ በማስገባት፤ ፍርድ ቤቱ በጥፋተኛው ላይ ትናንት ህዳር 1 ቀን 2006 ዓ.ም የቅጣት ውሳኔውን አስተላልፏል። በዚህም መሠረት ወጣቱ እጁ ከተያዘበት ዕለት አንስቶ በሚታሰብ የ5 ዓመት ፅኑ እስራት ቅጣት ተላልፎበታል።¾

የ100ሺ ዶላር ገንዘብ በቼክ እንደለገሱዋቸው አስረድተዋል።

ማንዴላ በወቅቱ ሶሻሊዝምን ማራመድ ይፈልጉ እንደነበርና የሶቪየት ህብረት መፈራረስ ጉዳይ ላይ በቂ መረጃ ስላልነበራቸው ስለሁኔታው እንዲያስረዱዋቸው እንደጠየቁዋቸው ኮሎኔል መንግስቱ ተናግረዋል። እሳቸውም ስለሁኔታው ካስረዱዋቸው በኋላ ደቡብ አፍሪካ ሶሻሊዝም ለመከተል ከመወስንዋ በፊት የዓለም ሁኔታን በደንብ እንዲመረምሩ ምክር እንደለገሱዋቸው ተናግረዋል።

ማንዴላ ከሰልጣናቸው ከወረዱ በኋላ በደቡብ አፍሪካ

በስደት ላይ ያሉ ኢትዮጵያዊያን ችግር እንደገጠሙዋቸው በሰሙ ጊዜ በወቅቱ በስልጣን ላይ ለነበሩት ታምቦ ምቤኪ ኢትዮጵያዊያን ማንም እንዳይነካ በሚል ማሳሰቢያ በመስጠታቸው ችግሩ መፈታቱን ኮሎኔሉ አስታውሰዋል።

በዙምባቡዌ ስደት ላይ እያሉ በአንድ ስብሰባ ላይ ከኔልሰን ማንዴላ ጋር የመተያየት ዕድል ገጥሞአቸው እንደነበር ያስታወሱት ኮሎኔል መንግስቱ ነገርግን በሰው መብዛት ምክንያት ለመነጋገር እንዳልቻሉ ጠቅሰዋል።

ማንዴላና የተወሰኑ ተከታዮቻቸው በአፄ ኃይለስላሴ ዘመነ መንግስት ለመጀመሪያ

ጊዜ ወደኢትዮጵያ ሲመጡ ወጣት እንደነበሩ የሚናገሩት ኮሎኔል መንግስቱ የሰሙትን መረጃ ዋቢ አድርገው ሲናገሩም ማንዴላ በስውር ወደኢትዮጵያ መጥተው ወታደራዊ ስልጠና መከታተላቸውን፣ በወቅቱ የአሜሪካ እና የእስራኤል መንግስታት ለደቡብ አፍሪካ አፓርታይድ መንግስት ይወግኑ ስለነበር ሁኔታውን እግር በእግር ሲከታተሉት እንደቆዩ አስታውሰዋል። በኋላም ማንዴላ ከአዲስአበባ ወደሞሮኮ ሄደውና ጎብኝተው ወደደቡብ አፍሪካ ሲመለሱ ተይዘው እንደታሰሩ ተርከዋል።¾

ኮሎኔል መንግስቱ...

እንዳይሰራ እንዲያደርግ ጥያቄ ከቀረበለት ቴሌኮም ኩባንያው ስልኩ እንዳይሰራ የሚያደርግ ቴክኖሎጂንም ይጠቀማል ተብሏል።

የተመዘገቡ ሞባይል ስልኮች ቢጠፉም እንኳን ሌላ ሰው እንዳይጠቀምባቸው ስለሚደረግ ሞባይሎች ካልተፈታቱና ለሌላ አገልግሎት ካልዋሉ በስተቀር አገልግሎት የማይሰጡ መሆናቸውን ዶ/ር መስፍን ገልፀዋል። ኢትዮቴሌኮም በተለይ ከሲም ካርድ ሽያጭ ጋር በተያያዘ ኩባንያው

ሲሞቹን ለአከፋፋዮች ካስረከበ በኋላ አከፋፋዮቹ በበኩላቸው ለተለያዩ ቸርቻሪዎች የሚያከፋፍሉ ሲሆን ይሁንና በየሱቁ ሲም ካርዶችን የሚሸጡ ግለሰቦች የሲም ገዢዎችን አድራሻ በትክክል አጣርተው የተዘጋጀውን ፎርም በመሙላት የሲም ሽያጭ የሚያከናውኑ ባለመሆናቸው ክፍተቶችና ፈጥሮ ቆይቷል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ አንዳንድ ግለሰቦችን በርካታ ሲሞችን በመግዛት ከውጪ በሚደወሉ ስልኮች ላይ በሀገር ውስጥ መነሻ ኮድ (+251) በመጠቀም

የቴሌኮም ማጭበርበር ስራን እየሰሩ ሲሆን በቀጣይ ስራ ላይ የሚውለው የሞባይል ቀፎ ምዝገባና የተመዘገበ የሞባይል ቀፎዎች ብቻ በሀገሪቱ ኔትወርክ ውስጥ እንዲሰሩ ማድረጉ ለችግሩ መፍትሄ ለመስጠት ያስችላል ተብሏል። የሚካሄደው የሞባይል ቀፎ ምዝገባ በተለያዩ የሀገሪቱ ድንበሮች በኮንትሮባንድ ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ ቀፎዎችንም በቀላሉ ለመቆጣጠር ያስችላል ተብሏል።

ኢትዮቴሌኮም...

Page 4: በአባይ ግድብ ውስጥ 3 ንደ - ethioforum.orgethioforum.org/wp-content/uploads/2013/12/Sendekdec102013.pdfሰንደቅ 9ኛ ዓመት ቁጥር 431 ታህሳስ 02 2006

ሰንደቅ 9ኛ ዓመት ቁጥር 431 ረቡዕ ታህሳስ 02 20064

የማንዴላ ውልደትና እድገት ሮሊሂላላ ማንዴላ ሚቭዞ በምትባል አንዲት ትንሽ መንደር ውስጥ ምባሺ ወንዝ ዳርቻ ትራንስኪ ውስጥ እ.ኤ.አ ሐምሌ 18ቀን 1918 በደቡብ አፍሪካ ተወለደ ። ሮሊሂላላ በዞሳ ቋንቋ ቃል በቃል ሲተረጎም የባህር ዛፍን ቅርንጫፍ ለመገንጠል መታገል ማለት ሲሆን በተለምዶ አዋኪ ፣ ረባሽ በሚል ይተረጎማል።የኔልሰን ማንዴላ አባት የጎሳ መሪ እና የጎሳ መሪዎች መማክርት ሆነው ለበርካታ ዓመታት ያገለገሉ ሲሆን፤ ሁለቱንም ሥልጣናቸውን በጊዜው ከነበሩ የቀኝ ገዢዎች ጋር በፈጠሩት እስጣ አገባ አጥተውታል። በዚህ ጊዜ ማንዴላ ብቸኛ ልጅ ነበር። የአባቱ ከስልጣን መነሳት እናቱ ቤተሰቡን ከሚቬዞ በስተደቡብ የምትገኝ ኩኑ የምትባል ትንሽ መንደር ይዛ ለመዘዋወር ምክንያት ሆናት። በማንዴላ አባት ጉዋደኛ ሀሳብ አመንጪነት ማንዴላ ሜቶዲስት ቤተክርስቲያን ተጠመቀ። ከቤተሰቡ የመጀመሪያው ትምህርት ቤት የገባ ልጅም ሆነ። በወቅቱ በተለምዶ እንደሚደረገው እንዲሁም በደቡብ አፍሪካ ላይ የእንግሊዝ የትምህርት ሥርዓት ተጽዕኖ በማሳደሩ ምክንያት የማንዴላ የመጀመሪያ መጠሪያ ሥሙ ኔልሰን እንዲሆን የማንዴላ መምህር ገለጹለት።ማንዴላ በ9 ዓመቱ የአባቱ በሳንባ በሽታ መሞት የህይወቱን አቅጣጫ በአስገራሚ ሁኔታ ቀይሮታል። ማንዴላ ጆንጊታባ ዳሊን ዲዬቦ በተባሉ የጎሳ መሪና አባቱ በህይወት እያሉ የጎሳ መሪ እንዲሆኑ ሀሳብ ባቀሩቡላቸው ሰው እንደ ውለታ መሥራት አይነት በጉዲፈቻ ልጅነት ወሰዱት። ማንዴላ በትንሿ ኩኑ መንደር ያገኝ የነበረውን እንክብካቤና ነጻነት ዳግም እንደማያገኝና የሚወዳትን መንደር ተመልሶ ሊያያት እንደማይችል እያሰበ በስጋት ትቷት ተጓዘ። ማንዴላ የቴምቡላንድ ጊዜያዊ ከተማ ወደ ተባለችው የንሳን ቤተሰብ አለቃ መኖሪያ ምኪኪዚዌኒ በሞተር ሳይስክል ተጓዝ። ማንዴላ ምንም እንኳን የሚወዳትን ኩኑ መንደር ያልረሳ ቢሀንም አዲሷንና ግራ የምታጋባውን ምኪኪዚዌኒ ከተማ በቀላሉ ተለማመዳት።ማንዴላ የጎሳ መሪው የበኩር ልጅ የሆነው ጀስትስ እና ኖማፉ ከተባለች ሴት ልጁ ያላቸውን አይነት ክብርና ኃላፊነት እኩል ተሰጠው። ማንዴላ ከቤተ መንግስቱ አጠገብ በሚገኘው ባለ አንድ ክፍል ትምህርት ቤት ውስጥ ገብቶ እንግሊዝኛ፣ ዞሳ፣ ታሪክና የህብረተሰብ ሳይንስ ትምህርት ተማረ። በዚህን ግዜ ነበር ማንዴላ ስለ አፍሪካ ታሪክ የማወቅ ፍላጎት ያደረበት። እ.እ.አ በ1939, ማንዴላ የጥቁሮች ብቸኛ የከፍተኛ ትምህርት ማዕከል በሆነው ፎርት ሐሬ ዩኒቨርስቲ ኮሌጅ ገባ። በወቅቱ ፎርት ሐሬ ዩኒቨርስቲ እንደ ኦክስፎርድና ሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ ጋር በእኩል የሚታይና ከሰሃራ በታች ያሉ ሀገራት ምሁራንን ያፈራ ነበር። በዩኒቨርስቲው የመጀመሪያው ዓመት ቆይታው አስፈላጊውን ኮርሶች የወሰደ ቢሆንም ህብረተሰቡን ለማገልገል እንዲረዳው በወቅቱ ለጥቁሮች የሚሰራውን ምርጥ ሞያ ተብሎ የሚወሰደውን የህግ ተርጋሚኒትና ጸሐፊ ሞያ በማጥናት የሮማን ደች ህግ ትምህሩት ላይ ትኩረትን አደረገ።በዩኒቨርስቲ ቆይታው ሁለተኛ ዓመት ሲሞላው የተማሪዎች ተወካይ መማክረት ሆኖ ተመረጠ። በተወሰነ ጊዜ ተማሪዎች የሚቀርብላቸውን ምግብና የተማሪዎች መማክርት ያለው ሥልጣንን አስመልክቶ እርካታ የላቸውም ነበር። በምርጫው ወቅት አብዛኛው ተማሪ ጥያቂአቸው ካልተመለሰ ምርጫውን ጥሎ ለመውጣት በእጅ ብልጫ ወሰኑ። በዚህን ጊዜ ማንዴላ ከአብዛኛው ተማሪ ጎን በመሆን ከተማሪዎች መማክርት ተወካይነት ራሱን አገለለ። የዩኒቨርስቲው ኃላፊ ዶ/ር ኬር ማንዴላን ከትምህርት ቤቱ በማባርር የተማሪዎችን መማክርት ተወካይነቱን የሚቀጥል ከሆነ ትምህርቱን ሊያስቀጥለው እንደሚችል መደራደሪያ አቀረቡለት። ወደ ቤቱ ሲመልሰ የጉዲፈቻ አባቱ

የኔ ሃሳብበዚህ ዓምድ ስር የሚወጡ ጽሁፎች የፀሐፊውን እንጂ የኤዲቶሪያሉን አቋም አያንፀባርቁም

በቁጣ አስተናግደውት የሚለውን ሳያዳምጡ አቋሙን ቀይሮ ወደ ትምህርት ቤቱ እንዲመለስ አዘዙት።

የማንዴላ እስር ጉዳይማንዴላ ወደ መኖሪያ ቤቱ ከተመለሰ ከጥቂት ጊዜያት በኃላ የጉዲፈቻ አባቱ ሬጀንት ጆንጊታባ ሚስት እንዲያገባ አስፈላጊውን ዝግጅት ማጠናቀቃቸውን ገለጹለት። የማንዴላ የጉዲፈቻ አባት ማንዴላ የተስተካከል ህይወት እንዲመራ የራሳቸውን ዝግጅት ትክክል ነው የሚሉትን ተግባር በማድረግ በሀገሩ ባህል መሰረት አደረጉ። ይሀንን አስደንጋጭ ዜና የሰማው ማንዴላ አሁን ያለው አማራጭ ትዕዛዙን አክብሮ መቀበል ብቻ መሆኑንና ወጥመድ ውስጥ እንደገባ ሲሰማው መኖሪያ ቤቱን ለቆ ጠፋ። ጉዞውን ወደ ጆሃንስበርግ አድርጎም ዘበኝነትን እና ጸሐፊነትን ጨምሮ ኑሮውን የተለያየ ሥራ በመስራት ይገፋ ጀመረ። በዊትዋትረሰታንድ ዩኒቨርስቲም ህግ ትምህርት ለማጥናት ተመዘገበ።ወዲያውኑ የዘአፍሪካ ናሽናል ኮንግረስ (ኤአንሲ) ውስጥ እ.ኤ.አ በ1942 በመቀላቀል የፀረ አፓርታድ ትግል እንቅስቃሴ በንቃት ይሳተፍ ጀመር። በኤ ኤን ሲ ውስጥ የአፍሪካ ናሽናል ኮንግረስ የወጣቶች ህብረት የሚል ቁጥራቸው አናሳ የሆኑ የወጣት አፍሪካውያን ስብስብ ነበር። የዚህ ህብረት ዓላማ ኤኤን ሲን የሰፊው ህዝብ ሥር ነቀል እንቅስቃሴ ማድረግ፣ በሚሊየን የሚቆጠሩ በአገዛዙ ምንም ድምጽ የሌላቸውን በገጠር የሚገኙ ጭሰኛ ገበሬዎችንና የሠራተኛው ክፍልን የማጠናከርና የማብቃት ሥራ መስራት ነበር። በተለይ ህብረቱ የኤኤንሲ ያረጀ የህዝቡን ድጋፍ የማግኛ ዘዴው ውጤታማ አይደለም የሚል ነው። እ.ኤ.አ በ1942 ኤኤንሲ የወጣቶቹ ረግጦ የመውጣት፣ የዓመጽ፣ የዓለመታዘዝና ያለመተባበር የትግል ዘዴን የእኩል ዜግነት ፣የመሬት ክፍፍል ፣የንግድ ማህበር መብቶች፣ ነጻና አስገዳጅ የሆነ የህፃናት የመማር መብት የፖሊሲን ግብ ይፋዊ በሆነ መልኩ የራሱ የትግል ዓላማ አድርጎ ተቀበለው።ለ20 ዓመታት እ.ኤ.አ የ1952ቱን የትግል ዘመቻና እ.ኤ.አ የ1955 የህዝብ መማክርትን እንቅስቃሴን ጨምሮ ማንዴላ በሠላማዊና ኃይል ያልተቀላቀለበት ትግል በደቡብ አፍሪካ መንግስት ላይ የሚደረገውን እንቅስቃሴ መርቷል። ማንዴላና ታምቦ የህግ

አገልግሎት ድርጅት የሚባል ፎርት ሄር ዩኒቨርስቲ ሲማር በጉብዝናው ከሚያውቀው ኦሊቨር ታምቦ ጋር በመሆን በጋራ ከፍተዋል። የህግ ድርጅቱ በነጻ የህግ አገልግሎት ድጋፍ ላልተወከሉ ጥቁሮች ያደርግ ነበር።እ.ኤ.አ በ1956 ማንዴላ እና 150 ሰዎች በፖለቲካዊ ምክክር በሚል ምክንያት ክስ ተመስርቶባቸው ታሰሩ። በዚህን ጊዜ ኤኤንሲ አፍሪካውያኖች (Africanist) አዲሱ የጥቁር ታጋዮች(black activist) ውልዶች ነን በሚሉና የኤኤንሲ የሠላማዊና የዝምታ መንገድ ውጤት ዓልባ ሆኗል በሚሉ ሰዎች እንቅስቃሴ ነውጥ ውስጥ ገብቶ ነበር። አፍሪካውያኖች ወዲያውኑ ከኤኤንሲ በመነጠል ፓን አፍሪካዊያን ኮንግረስ የሚል አቃቁመው ኤኤኒሲ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ያሳደሩ ሲሆን ኤኤን ሲ አብዛኛው ታጣቂ ደጋፊዎቹን አጥቶበታል።በ1961 ሃይል ያልተቀላቀለበት ትግል ያስኬዳል በማለት ሲሟገት የነበረው ማንዴላ በስተመጨረሻ የትጥቅ ትግል ብቸኛው አማራጭ ነው ወደ የሚለው ድምዳሜ ደርሶ ነበር። በማስከተልም ዩምኮንቶ ዊ ሲዚዊ ወይም ኤም ኬ የተሰኘ አፓርታይድን ለመጣል የሚረዳ ሸማቂ ኃይል ከአቋቋሙት መካከል አንዱ ሆነ። በ1961 ማንዴላ የሶስት ቀን ብሄራዊ የሥራ ማቆም አድማ አቀናብሮ በቀጣዩ ኣመት ዓመጽ በማስነሳት በሚል በ1963 ዓ.ም የ5 ዓመት የእስር ውሳኔ ተወሰነበት።በድጋሚ ፍርድ ቤት ቀርቦ ማሴርና ፖለቲካዊ ጥቃቶች በሚል ክስ እሱና አሥር የኤኤኒሲ መሪዎች የዕድሜ ልክ እሥራት ተፈረደባቸው።ኒልሰም ማንዴላ ከ27 ዓመት የእሥር ቆይታው 18 ቱን ዓመትን በሮቢን ደሴት ነው ያሳለፈው። በእስር ቆይታው የሳምባ ነቀርሳ በሽታ ይዞት የነበረ ሲሆን እንደማንኛውም ጥቁር የፖለቲካ እስረኛ በደካማ ህክምና አገልግሎት በእስር ቤቱ ሠራተኞች ነበር የተሰጠው። ምንም እንኳን በህመም ላይ ቢሆንም ማንዴላ የህግ ትምህርቱን ከሎንደን ዩኒቨርስቲ በተልዕኮ አግኝታል።እ.ኤ.አ በ1981 የደቡብ አፍሪካ የደህንነት ወኪል በሆነው ጎርደን ዊንተር አማካኝነት በደቡብ አፍሪካ

ማንዴላ! ጠላቶቹን ጭምር በትዕግስትና በፍቅር ያሸነፈ መሪ

በዝራው አሻግሬ[email protected]

ካለፈው ሳምንት መጨረሻ ጀምሮ ዓለም ዓቀፍ ሚዲያው ላይ ወደር የሌለው ሽፋን በማግኘት በደቂቃና በሰከንድ ውስጥ ዜና ፣ዘገባ፣መጣጥፍ እና ዶክመንተሪ ፊልም ዘገባ ሲካሄድባቸው የነበሩት አሁንም እየተዘገበላቸው ያለው የደቡብ አፍሪካው የነፃነት ታጋይ የኔልሰን ማንዴላ በ95 ዓመታቸው ባለፈው ሳምንት ሐሙስ ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት መለያታቸው ነው። ማንዴላ ለአፍሪካ እንዲሁም ለዓለም መንግስታት መሪዎች አርአያ ሊሆኑ የሚችሉ መሆናቸውን የዓለም ህዝብ እንዲሁም የተለያዩ መሪዎች ያለምንም ቀስቃሽ ስሜታቸው

እየናጣቸው ማንዴላ የተለየ መሪ መሆናቸው አረጋግጠዋል። ማንዴላ ማናቸው? አስተዳደጋቸውስ እንዴት ነበር? ህይወታቸው ምን ይመስላል? በተወሰነ እንመልከት።

በገፅ 21 ዞሯል

Page 5: በአባይ ግድብ ውስጥ 3 ንደ - ethioforum.orgethioforum.org/wp-content/uploads/2013/12/Sendekdec102013.pdfሰንደቅ 9ኛ ዓመት ቁጥር 431 ታህሳስ 02 2006

ሰንደቅ 9ኛ ዓመት ቁጥር 431 ረቡዕ ታህሳስ 02 2006 5ወቅታዊ

በፍሬው አበበ

በሚድሮክ ኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ግሩፕ አዘጋጅነት የሚካሄደው የእህትማማችና የተጋባዥ ተቋማት የወዳጅነት የስፖርት ውድድር እሁድ ህዳር 29 ቀን 2006 ዓ.ም በታላቅ ድምቀት ተጀምሯል።

ለሶስተኛ ጊዜ የሚካሄደው የሚድሮክ ኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ኩባንያዎችና ተጋባዥ ተቋማት የወዳጅነት የስፖርት ውድድር በመቻሬ ሜዳ ኮርፖሬት ሴንተር ግቢ ሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ (መቻሬ) ከፖልሪዬስ ባደረጉት የእግር ኳስ ግጥሚያ በይፋ ተከፍቷል፡፡

ለአምስት ወራት በሚቆየው በዚህ የወዳጅነት የስፖርት ውድድር የቴክኖሎጂ ግሩፑን ኩባንያዎች ጨምሮ ፖልሪዬስ፣ ዳሽን ባንክ፣ ኢትዮ ቴሌኮም፣ ናሽናል ሞተርስ፣ ሞሐ ለስላሳ መጠጥ ኢንዱስትሪ፣ አዲስ ካተሪንግ፣ ሸራተን አዲስ፣ ኒያላ ኢንሹራንስ፣ ሆራይዘን አዲስ ጎማ፣ ኢኳቶሪያል ቢዝነስ ግሩፕና ሜፓ ኩባንያዎች ተካፋይ ይሆናሉ።

ስፖርታዊ ውድድሮቹ በእግር ኳስ፣ በመረብ ኳስ፣ በገመድ ጉተታ፣ በሜዳ ቴኒስ፣ በሩጫ፣ በዱላ ቅብብሎሽ፣ በጠረጴዛ ቴኒስ፣ በቼዝና በዳማ የሚካሄዱ ይሆናሉ፡፡

ይህንኑ ስፖርታዊ ውድድር አስመልክቶ ዶ/ር አረጋ ይርዳው የሚድሮክ ኢትዮጵያ ቺፍ ኤግዚኪዩቲቭ ኦፊሰር ከጋዜጠኞች ጋር ያደረጉት አጭር ቃለምልልስ እንደሚከተለው ቀርቧል።

ስፖርታዊ ውድድሩ ከሌሎች ጊዜያት ለየት ስለሚልበት ጉዳይ፣

ዘንድሮ ትንሽ ለየት የሚያደርገው አንደኛ የተወሰኑ እህት ኩባንያዎች ተጨምረዋል፤ ስለዚህ ቁጥራችን በዛ ብሏል። በአገሪቷ በስፖርቱ ላይ ዘንድሮ የተደረገው እንቅስቃሴ እዚህም ላይ በጎ ተፅዕኖ አለው። ስለዚህ ብዙዎቹ መሳተፍ ፈልገዋል። ይሄ የሚያሳየው ስፖርታችን በአጠቃላይ ወደጥሩ አቅጣጫ፣ ወደማደጉ እየሄደ መሆኑን ነው።

ስፖርቱን ስንጀምረው የነበረው ዓላማ ሼህ ሙሐመድ ሁሴን ዓሊ አልአሙዲ እዚህ አገር ያላቸው ኩባንያዎች እያንዳንዳቸው የኩባንያዎቻቸው የራሳቸው የስፖርት ቡድኖች ኖሯቸው ከዚያ በኋላ በአንድ ላይ ሆነው የሚጫወቱበት ሁኔታ እንዲፈጠር ነው። የቴክኖሎጂ ግሩፕ ቡድኖች ወደ ዘጠኝ ገደማ ይመስለኛል፣ የመቻሬ ቡድንም አለን። ከሶስትና አራት ዓመት በፊት ጀምሮ እንዲሳተፉ አደረግን። ከጎረቤታችን የቴሌኮሙኒኬሽን ቡድን አለ፣ ጎረቤታችን ስለሆነ ፈቅደናል። ሌሎችም የእህት ኩባንያዎች እየመጡ ነው። ወደፊት የምንፈልገው የሼህ ሙሐሙድ ምናልባት በኢትዮጵያ ከ20ሺ በላይ ሠራተኞች ይኖሩዋቸዋል። ቴክኖሎጂ ግሩፕ ብቻ ወደ ሰባት ሺ ያህል ሠራተኞች አሉት። በሙሉ ኩባንያዎቹ የሚመጡበትን ጊዜ እየናፈኩኝ ነው። ሼህ ሙሐመድ በዚህ መድረክ ተገኝተው በሠራተኞች መካከል ያለውን መተሳሰብና ፍቅር እንዲያዩ እፈልጋለሁ።

እኛ የምናካሂደው ስፖርት ለማሸነፍም ለመሸነፍም ነው። ስፖርት ለሥራ ቅልጥፍናና በሰዎች መካከል ለሚደረጉ ግንኙነቶች ማጠናከሪያ እንዲሆን ነው። ጥረታችን ፕሮፌሽናል ስፖርተኞችን ለማፍራት አይደለም። ሠራተኞቻችን ከሥራ ውጪ ያላቸውን ጊዜ በአግባቡ እንዲጠቀሙበት ዕድል ለመፍጠር ነው። በአገራችን ሌሎች የመዝናኛ ሁኔታዎች ባለመስፋፋታቸው ሠራተኞቻችን በትርፍ ጊዜያቸው የሚዝናኑበት ቦታ ሊቸግራቸው ይችላል። ስለዚህ ፍላጎቱ ያለው ሠራተኛ አመቺ ሁኔታ ቢፈጠርለት በጥሩ ቦታ ላይ ትርፍ ጊዜውን ያሳልፋል በሚል ተግባራዊ ያደረግነው ነው። ይህ ሲሆን ሠራተኞች ከአልባሌ ቦታ ራሱን ይጠብቃል ማለት ነው፣ ጤነኛ ይሆናል ማለት ነው። ጤነኛ የሆነ ሠራተኛ ደግሞ ምርታማ ነው። ሌላው በኅብረት እንዲገናኙ ማድረግ ነው። አንድ ጊዜ ሜዳ ላይ ሠራተኞች ሲገናኙና ሲነጋገሩ (ሥራ መሪውንም ጨምሮ) ፍቅራቸው ይጠነክራል።

የውድድሩ ዓላማ በፕሮፌሽናል ተጫዋቾችን ማፍራት ይሆን?ድሮ ድሮ የስፖርተኞች መፍለቂያ ቦታ

ት/ቤቶች ነበሩ። አገራችን በስፖርት እንድታድግ ከተፈለገ መፍለቂያ ቦታም መዘጋጀት አለበት። ከነዚህ ውስጥ ኩባንያዎች መፍለቂያ ቦታ ሊሆኑ ይችላል ብዬ አምናለሁ። በዚህ በኩል አስተዋፅኦ አለው። እኛ ሠራተኞቻችን ፕሮፌሽናል ተጫዋች ሆነው ደመወዝ ለመክፈል አናስብም። እዚህ የምታዩዋቸው ስፖርተኞች ገሚሱ አካውንታት ነው፣ ገሚሱ ካሸር ነው፣ ገሚሱ ማኔጀር ነው። ሁሉም የራሱ መደበኛ ሥራ አለው። ግን በትርፍ ጊዜያቸው በስፖርት እንዲያሳልፉ፣ ቤተሰባቸው ወደሜዳ ይዘው እንዲመጡ እንፈልጋለን። ይሄ አይነት ነገር እንዲዳብር እናደርጋለን። በአሁኑ ጊዜ የሜዳ ቴኒስ

መጫወቻ ሜዳ አዘጋጅተናል። እድሜያቸው ገፋ ያሉ ሰዎች ከሥራ ሲወጡ እዚህ ቦታ ተጫውተው ቢሄዱ ከጤናም አኳያ ጠቀሜታ አለው።

ለሠራተኛው ሕፃናት መዋያ አዘጋጅተናል። ሠራተኞች ሕፃናቱን ቤታቸው የሚጠብቅላቸው ካጡ ይዘዋቸው መጥተው ሥራቸውን እየሰሩ፣ በመካከል ልጆቻቸውን በቅርብ እንዲከታተሉ እያደረግን ነው። በቴክኖሎጂ ግሩፕ ውስጥ የመዋዕለ ሕፃናት ት/ቤት ከፍተናል። ይህን ያደረግነው ሕጻናቱ ወላጆችና ሠራተኞች መ/ቤቱ እየደጎማቸው የተወሰነ ክፍያ በመክፈል ልጆቻቸውን እንዲስተምሩና ከፍ እያሉም ሲሄዱ ወደዩኒቲ ዩኒቨርስቲ ተሸጋግረው ከፍተኛ ትምህርታቸውን እንዲማሩ ለማድረግ ነው። ሠራተኞችን የምትደግፈው በደመወዝ ብቻ አይደለም። ሠራተኛ የምትደግፍባቸው የተለያዩ ነገሮች አሉ። ለሥራው ፍቅር እንዲኖራቸው፣ ሲነጋ ወደቢሮዬ ልሂድ እንዲል ማድረግ ያለብን ይመስለኛል። ከማኔጅመንት መሳሪያዎች ስፖርትን የመሰለ የለም።

ስለመቻሬ የቀድሞ ተሳትፎ፣ቴክኖሎጂ ግሩፕ መቻሬ የሚባል ቡድን

ነበረው።ፕሪሚየርሊግ ውስጥ መሳተፍ ጀምረን ነበር። የወጣንበት ምክንያት ተጫዋቾቻችን ሰነፍ ሆነው አይደለም። ፌዴሬሽኑ የራሱ የሆነ መመሪያ አለው። እኛ ደግሞ በኩባንያ ደረጃ የራሳችን መመሪያ አለን። የእኛ መመሪያ በአጭሩ ስፖርተኞች ኩባንያዎቻቸውን ይዘው ወደሜዳ ሲገቡ ኩባንያዎቹን ያስተዋውቃሉ። መጥፎ ሥራ ከሰሩ በመጥፎ ስራ ነው የሚታወቀው። ጥሩ ከሆነ በጥሩነቱ ነው የምንታወቀው። በመጥፎ እንዳንታወቅ አስጠንቅቀን ከተጫዋች ጋር

መጨቃጨቅ፣ ቀይ ካርድ ማየት ይህን የመሳሰሉ ነገሮች ከገጠሙ ውድድሩ እንደሚቋረጥ መመሪያ አውጥተን ነበር። ይህን ቀይ መስመር ስለታለፈ ቡድኑ እንዲወጣ አድርገናል። ይህምን ማለት ነው፣ በአጭሩ እኛ የምንሄድበት ሜዳ ለእኛ አልተስማማንም ወይንም እኛ ገና አልደረስንም። የተጫዋቾቹ ጨዋነት ብቻ አይደለም የሚፈለገው። የተመልካች ጨዋነት ይፈለጋል። እኛ አገር ስታዲያም ውስጥ ብዙ ካርዶች ይታያሉ። ብዙ አልባሌ ነገሮች ይሰማሉ። እነዚህ መስተካከል መቻል አለባቸው። በሰዎች መካከል ስሜታዊ የሆነ የድጋፍ አሰጣጥ አይኑር ማለቴ አይደለም። ይህ በሰለጠነው ዓለም ላይም እናያለን። ነገር ግን መጥፎ ቃላትን መወርወር፣ ህፃናት ይህን መጥፎ ነገር እንዲቀስሙ ማድረግ ተገቢ አይደለም። ስታዲየም መማሪያ ነው ፤ጥሩም መጥፎም ነገር ያስተምራል። በእኔ እይታ አሁን ባለንበት ሁኔታ ጨዋ ሁኔታ አለ ብዬ አላምንም። ጥሩ በሆነበት ወቅት እንሳተፋለን።

ስፖርታዊ ውድድሩ መካሄድ ስላስገኘው ለውጥ፣

የቴክኖሎጂ ግሩፕ ከተመሰረተ 14ኛ ዓመቱ ነው፣ በነዚህ ዓመታት አንድም ግዜ የሠራተኛና የማኔጅመንት አለመግባባት(ሌበር ኬዝ) ተከስቶ አያውቅም። ይህ ጥሩ ነገር የተገኘው ሠራተኛው እርስ በርሱ እንዲገናኝ በማድረጋችን ጭምር ነው። የቤተሰብ በዓል አለን። የደንበኞች በዓል አለ። ስፖርቱ አለ፣ የአገርህን እወቅ ፕሮግራም አለ፤ ይህን በምናደርግበት ጊዜ በሰዎች መካከል መቀራረብ፣መግባባት፣ ፍቅር ይሰፍናል። ሰው ማህበራዊ እንሰሳ ነው። እንደዚህ ዓይነት ሁኔታ ከፈጠርክለት ይቀራረባል። ይህን በማድረጋችን ሠራተኞቻችን ኩባንያዎቹ የእኛ ናቸው የሚል ስሜት በውስጣቸው እንዲዳብር አድርገናል። ከዚያ ቀጥሎ ቤተሰቦቻቸው እንቅስቃሴያችንን በቅርብ እንዲያዩና እንዲገነዘቡ ዕድል ፈጥረናል። ይህ ሁኔታ ሠራተኞቻችን ብቻ ሳይሆን ቤተሰቦቻቸው ጠቅላላ የእኛነት ስሜት እንዲያዳብሩ ረድቷል።

ይህ ስፖርታዊ ውድድር ለጤና ከምናደርገው ጥረት አንዱ ነው። የራሳችን ክሊኒክ አለን።ግን የሠራተኛውን ጤና እንዲያስተካክል እንዲህ አይነት ስፖርታዊ መድረኮች በተጨማሪ መፍጠር ነበረብን። ስፖርት ትልቅ መሣሪያ ነው። በተለይ እንደእኛ ዓይነት ለማደግ በጣም የጓጓ አገር የስፖርት ዓይነት መሳሪያ ያስፈልገዋል።

የቡድን ውጤትን በተመለከተ፣ሜዳ ላይ 11 እግር ኳስ ተጨዋቾችን

ስትመለከት አንድ ኩባንያ ላይ ያሉ ሰዎችን ትመለከታለህ። ዋና ሥራአስኪያጅ ሊሆን ይችላል። አካውንታንቱ፣ ሂዩማን ሪሶርስ ወዘተ አሉ። እነዚህ ሰዎች ተቀናጅተው የሚሰሩት ሥራ ነው ኩባንያውን ትርፋማ የሚያደርገው። የ11ዱ ሰዎች ውጤት ነው ቡድኑን እንዲያሸንፍ የሚያደርገው። እኔ አንድ ወይንም ሁለት ተጨዋቾች ላይ የሚደረግ ትኩረትን አልደግፍም። እኔ የምደግፈው 11ዱንም ተጨዋቾች ነው። ኳስ እንደምንም ሲደርሰው ጎል የሚያስገባውን ብቻ የምናደንቅ ከሆነ ፤በማኔጅመንትም አካባቢ ቀረብ፣ ቀረብ የሚለውን ወይም አመራር ላይ ያለውን ሰውዬ ብቻ የምናደንቅ ከሆነ ትክክል አይደለንም። ለምሳሌ እኔ ሠራተኞቼ ባይኖሩ ምንም አይደለሁም፡፡ ሥራመሪን፣ ሥራ መሪ የሚያደርገው ሠራተኞች ናቸው። ስለዚህ 11ዱ የቡድን አባላት እኩል ልናይ ይገባል፣ እኩል ሊከበሩም ይገባል። በዓለም አቀፍ ደረጃ ጭምር እከሌ ይህን ያህል ጎል አስገባ የሚለው ነገር ድሮም መጥፎ ነው፣ አሁንም ትክክል አይደለም፣ ወደፊትም መታረም አለበት። ጎል ያገባውን ብቻ ሳይሆን ጎል እንዲገባ አስተዋፅኦ ያደረጉትንም የቡድኑ አባላት ማክበር ያስፈልጋል። ጥቂት ሰዎች ላይ ብቻ የምናተኩር ከሆነ፣ በቢሮም ሥራ ዋና ሥራአስኪያጁ ላይ ብቻ የምናተኩር ከሆነ ቢሮ የሚያጸዱ፣ ሻይ የሚያቀርቡና የመሳሰሉ ሠራተኞቻችንን ጭምር የማናስታውስ ከሆነ ማኔጅመንቱ ውስጥ ችግር አለ ብዬ አምናለሁ።

ግብ አስቆጣሪውን ብቻ ሳይሆን ግብ እንዲቆጠር ያደረጉ የቡድኑ አባላትንም ልናከብር ይገባል

ዶ/ር አረጋ ይርዳውየሚድሮክ ኢትዮጵያ ቺፍ ኤግዚኪዩቲቭ ኦፊሰር

ሜዳ ላይ 11 እግር ኳስ ተጨዋቾችን ስትመለከት አንድ ኩባንያ

ላይ ያሉ ሰዎችን ትመለከታለህ። ዋና ሥራአስኪያጅ ሊሆን ይችላል።

አካውንታንቱ፣ ሂዩማን ሪሶርስ ወዘተ አሉ። እነዚህ ሰዎች ተቀናጅተው

የሚሰሩት ሥራ ነው ኩባንያውን ትርፋማ የሚያደርገው። የ11ዱ ሰዎች

ውጤት ነው ቡድኑን እንዲያሸንፍ የሚያደርገው

ዶ/ር አረጋ ይርዳው እና የቴክኖሎጂ ግሩፑ ከፍተኛ የሥራ መሪዎች

የስፖርቱ ተሳታፊ ኩባንያዎች

Page 6: በአባይ ግድብ ውስጥ 3 ንደ - ethioforum.orgethioforum.org/wp-content/uploads/2013/12/Sendekdec102013.pdfሰንደቅ 9ኛ ዓመት ቁጥር 431 ታህሳስ 02 2006

ሰንደቅ 9ኛ ዓመት ቁጥር 431 ረቡዕ ታህሳስ 02 20066 ፖለቲካ

በዘሪሁን ሙሉጌታ

ባለፈው እሁድ ከተለያዩ የመገናኛ ብዙኃን የተውጣጡ ጋዜጠኞች የታላቁ የህዳሴ ግድብን የመጎብኘት አጋጣሚን አግኝተው ነበር። አብዛኛዎቹ ጋዜጠኞች ከዚህ ቀደም ስለግድቡ በርካታ ሀተታዎችን ለሕዝብ ቢያቀርቡም በተግባር ግድቡን የመጎብኘት ዕድል ያላገኙ በመሆኑ የግድቡን የስራ እንቅስቃሴ ለመጎብኘት ከፍተኛ ፍላጎት እንደነበራቸው ከሁኔታቸው መረዳት ይቻላል።

ወደ ግድቡ የተደረገው የጋዜጠኞቹ ጉዞ በከፍተኛ ደረጃ በውጣ ውረድ የተሞላ ቢሆንም፤ ታሪካዊ የሆነውን የታላቁ የህዳሴ ግድብ በማየት ለማካካስ ሞክረዋል። ወደ ግድቡ የሚወስደው ጥርጊያ መንገድ መሆኑና የአካባቢው ሙቀት ከፍተኛ መሆን ጉዞአችንን ቢያከብደውም በግድቡ ላይ የሚካሄደው የግንባታ እንቅስቃሴ አድካሚውን ጉዞ የሚያስረሳ ነበር።

በታላቁ ህዳሴ ግድብ እንደደረስን በታላቅ አክብሮትና ፈገግታ የተቀበሉን የታላቁ የህዳሴ ግድብ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ስመኘው በቀለ ነበሩ። በጉብኝታችን ወቅት የግድቡ የቀኝ አካል በሚያርፍበት ግድቡ የሚያርፍበትን የወለል ቦታ ለመድረስ የሚደረገውን ቁፋሮ በቅድሚያ ተመልክተናል። በአብዛኛው የቁፋሮው ስራ በመጠናቀቅ ላይ መሆኑንም ኢንጂነር ስመኘው ገልፀውልናል። በተመሳሳይ በዚሁ የግድቡ የቀኝ አካል ለሚተከሉት አስር የኃይል ማመንጫ ዩኒቶችን ጥልቅ የሆነ የቁፋሮ ስራ እየተከናወነ ሲሆን፤ ጎን ለጎንም የአርማታ ሙሌት ስራም እየተከናወነ ነው። በግድቡ የቀኝ ክፍል ስራዎች በሰፊው እየተከናወኑ ነው። የከርሰ ምድር ፍተሻውም ተጠናቆ የመሠረት ወለሉ በአርማታ እየተሞላ እንደሆነም ለማየት ችለናል። የአርማታ መሙላቱ በኃይል ማመንጫ ዝቅተኛው ቦታ ተጀምሮ የሚሞላ ሆኖ ከባህር ጠለል በላይ 468 ሜትር መሆኑም ተነግሮናል።

በአሁኑ ወቅት በግድቡ የቀኝ ክፍል ከፍተኛ ስራ እየሰሩ ያሉት ሁለት ተቋራጮች ናቸው። የጣሊያኑ የኮንስትራክሽን ኩባንያ ሳሊኒ የሲቪል ስራውን እያከናወነ ሲሆን፤ የኤሌክትሮ ሜካኒካልና የኃይድሮ ሜካኒካል ስራውን እንዲሁም ተዛማጅ ስራዎችን እያከናወነ ያለው የመከላከያ

ሰዓታትንበአባይ ግድብ ውስጥ2

የብረታ ብረት ኢንጂነሪግ ኮርፖሬሽን ናቸው። በወቅቱ በጉብኝታችን ላይ እንደተመለከትነው ግድቡ ከፍተኛ ውሃ በሚሸከምበት ወቅት ለማስተንፈሻ የሚረዱ ግዙፍ የብረት ግንባታዎች እየተከናወኑ ነው። ግንባታዎቹንም ለማከናወን መጠኑ ግዙፍ የሆነ ክሬን ተተክሎ አንድ ግዙፍ ሕንፃ የሚመስል ግንባታም በግድቡ መካከለኛ ስፍራ ላይ እየተገነባ ነው።

ይሄንኑ ግንባታ ለማከናወን ቁጥራቸው በርካታ የሆኑ ሰራተኞችና ማሽነሪዎች በእንቅስቃሴ ላይ ነበሩ። በኢንጂነር ስመኘው ገለፃ በአሁኑ ወቅት በፈረቃ የሚሰሩ ወደ ስድስት ሺህ ሰራተኞች በቦታው ላይ ይገኛሉ። የግድቡን የቀኝ ክፍል ስራ ለማጠናቀቅም በአብዛኛው አውሮፓ ሰራሽ የሆኑ ከ1 ሺህ 600 በላይ የመቆፈሪያ፣ የማጓጓዣና የመሰርሰሪያ ማሽነሪዎች በእንቅስቃሴ ላይ ናቸው።

በአካባቢው ከፍተኛ ፀሐይና ሙቀት ቢኖርም፤ ስራው ከተፈጥሮ ጋር በሚደረግ ትንቅንቅ ጭምር እየተተገበረ ነው። ግድቡ ከወረቀት ንድፍ አልፎ በየሰዓቱና በየሰከንዱ ሳይቋረጥ ለሃያ አራት ሰዓታት እየተሰራ ነው።

በግድቡ ቀኝ ክፍል የነበረንን ቆይታ ካጠናቀቅን በኋላ በመቀጠል ያመራነው ወደ ግራ ክፍሉ ነበር። በሁለቱ ግራና ቀኝ መሐል የአባይ ወንዝ በፀጥታ እያለፈ ነው። በላዩም ላይ ትልቅ ድልድይ ተሰርቶ በቀላሉ በግድቡ ግራና ቀኝ መመላለስ ይቻላል። በግድቡ ግራ ክፍል ስድስት የኃይል ማመንጫ ጣቢያዎች ይገኛሉ። በግድቡ ግራና ቀኝ በጠቅላላ 16 የኃይል ማመንጫ ጣቢያዎች ሲኖሩ እያንዳንዳቸው 375 ሜጋ ዋት በማመንጨት በጥቅሉ 6‚000 ሜጋ ዋት እንዲያመነጭ ተደርጎ እየተገነባ ነው።

በአሁኑ ወቅት በወሳኝ መልኩ እየተሰራ ያለው ሥራ የወንዙ ተፈጥሮአዊ አቅጣጫ ባለፈው ግንቦት ወር 2005 ዓ.ም በጊዜያዊነት እንዲቀየር ከተደረገ በኋላ በቋሚነት ግዙፍ የሆነ አራት የብረት አሸንዳ (Box Culvert) ግንባታ ነው። የብረት አሸንዳዎቹ አላማ ግድቡ ከተገነባ በኋላ የውሃው መጠን ሲበዛ እንደማስተንፈሻ የሚያገለግሉ ሆነው እንዲከፈቱና እንዲዘጉ ተደርገው እየተገነቡ ነው። እነዚህን የውሃ ማስተላለፊያዎች ለመገንባት ግዙፍ ክሬን ተተክሎ ብረቶቹን የማዋቀር ተግባር እየተከናወነ ነው። ከዚህ ጎን ለጎን የአርማታ ሙሌቱን ለማከናወን በምህንድስናው አጠራር Convoy Belt ወይም

በአጠቃላይ ግድቡ በዛ በረሃ ውስጥ አንድ ከተማ የፈጠረ

ይመስላል። በግድቡ ዙሪያ የተሰሩ የኮንክሪት ማዘጋጃ

ፋብሪካዎችን ጨምሮ በርካታ ቤቶች ተሰርተዋል

በግድቡ መሐል እየተሰራ ያለ ማስተንፈሻ

Page 7: በአባይ ግድብ ውስጥ 3 ንደ - ethioforum.orgethioforum.org/wp-content/uploads/2013/12/Sendekdec102013.pdfሰንደቅ 9ኛ ዓመት ቁጥር 431 ታህሳስ 02 2006

ሰንደቅ 9ኛ ዓመት ቁጥር 431 ረቡዕ ታህሳስ 02 2006 7

ምልከታ

ፖለቲካ

ሰዓታትንበአባይ ግድብ ውስጥ

የተቦካውን አርማታ ከተቦካበት ስፍራ የሚያጓጉዙ ረጃጅም የማጓጓዣ መስመሮች ተዘርግተዋል። የዚህ መሳሪያ ተግባር የተቦካውን ኮንክሪት በቀላሉ ወደ ግድቡ ቦታ በፍጥነትና ባለማቋረጥ ለማጓጓዝ እንዲያስችል ነው።

ይሄንን መሳሪያ ለጊዜው አገልግሎት ባይሰጥም፤ የግድቡ ግንባታ በተወሰነ ደረጃ ቁመቱ ከፍ ሲል በጥቅም ላይ እንደሚውል ከኢንጂነሩ ገለፃ መረዳት ተችሏል። ለጊዜው የተቦካውን ኮንክሪት ለማጓጓዝ ደግሞ ግዙፍ ገልባጭ ተሽከርካሪዎች በማጓጓዝ ላይ ይገኛሉ።

በግድቡ ግራም ሆነ ቀኝ ክፍል ግድቡ የሚያርፍበትን አስተማማኝ ቦታ ለማግኘት ቀደም ሲል በተካሄደ የከርሰ ምድር ፍተሻ መሠረት አስተማማኝ ቦታ ለማግኘት የደማሚት ፍንዳታዎች እንደሚከናወኑ ተገልጾልናል። በዕለቱ እኛም ጉብኝቱን ባካሄድንበት ወቅት ሁለት የደማሚት ፍንዳታዎች ሲካሄዱ አስተውለናል። የደማሚት ፍንዳታው ከመድፍ ያልተናነሰ ግዙፍ ፍንዳታ ሲሆን፤ እንደ በረዶ የተጋገረውን የአለት ንጣፍ በማፈንዳት ወደ ስብርባሪ ቋጥኝ ሲቀየርም አስተውለናል። በፍንዳታው ወቅት አብዛኛዎቹ ተሽከርካሪዎችና ማሽነሪዎች እንዲሁም ሰራተኞች ከአካባቢው እንዲርቁ ይደረጋል። ከፍንዳታውም በፊት የአደጋ ድምፅ የሚሰማ ሲሆን፤ ለጥቂት ጊዜም ቢሆን አካባቢው የልማት ሳይሆን የጦርነት ቀጠና ይመስላል።

ከግድቡ ዋነኛ አካላት አንዱ የሆነው የውሃ ማስተንፈሻ (Box Culvert) እየተሰራ ያለው በመከላከያ የብረታ ብረት ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ነው። ስራው ሳሊኒ ከሚያካሂደው የሲቪል ስራ ጋር ተናቦ እየተከናወነ እንደሆነም ከኢንጂነር ስመኘው ገለፃ መረዳት ይቻላል። ግድቡ በአሁኑ ወቅት በአመዛኙ በቁፋሮ ላይ ቢገኝም፤ በአንዳንድ ክፍሎቹ ቁፋሮው ተጠናቆ የአርማታ ሙሌት ስራ መጀመሩን ለመታዘብ ችለናል። ከአርማታ ሙሌቱ ጎን ለጎን በምህንድስናው አጠራር ‘Hydrolick Steel Structure’ ወይም የብረታ ብረት ተከላ ስራውም እየተከናወነ እንደሆነም ለማየት ችለናል።

“ሁሉም ነገር በተቀመጠለት የአሰራር ዘዴ እንዲሁም በከፍተኛ ወኔ እና ሞራል ባለው ሁኔታ እየተሰራ ነው” የሚሉት ኢንጂነሩ፤ የግድብ ስራው በአግባቡ እየተከናወነ መሆኑን ነው የገለፁት።

በጉብኝታችን ወቅት ያገኘናቸው የመከላከያ ብረታ ብረት ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን የኢሬክሽን እና ኢንስታሌሽን ኃላፊ የሆኑት ሻምበል ዳንኤል መኮንን በበኩላቸው፤ የሥራው ሂደት ውጤታማ እንደሆነና የውሃ ማስቀየሻው የብረት ተከላ በወጣለት እቅድ መሠረት እየተከናወነ መሆኑን አስረድተዋል። የብረት መዋቅሩም በኮርፖሬሽኑ እየተካሄደ መሆኑን ጠቅሰው፤ ከሳሊኒ ጋር በቅንጅት እየሰሩ መሆኑንም ተናግረዋል።

ከመስክ ጉብኝት በኋላ ኢንጂነር ስመኘው ግድቡን አስመልክተው ሰፋ ያለ ገለፃ አድርገውልን ነበር። ግድቡ በቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ አማካኝነት መጋቢት 24 ቀን 2003 ዓ.ም ጀምሮ የመሠረት ድንጋይ ከተቀመጠ በኋላ ቀንና ሌሊት እየተሰራ መሆኑን አብራርተዋል። ግድቡም ሀገራዊ መግባባትን በመፍጠር ረገድ የሁሉም ሕዝብ አሻራ አርፎበት እየተገነባ ያለ የባንዲራ ፕሮጀክት መሆኑን አስረግጠው ተናግረዋል። ግድቡም በዚህ ዘመን የተገኘ የሀገሪቱና የሕዝቦቹ ትልቅ ስጦታ መሆኑንም ጠቅሰዋል። እየተገነባ ያለው ግድብ በአለም በረጅሙ ወንዝ ላይ መሆኑ ብቻ ሳይሆን በአሁኑ ወቅት በአፍሪካ አንደኛ በዓለም ደግሞ በስምንተኛ ደረጃ እንደሚገኝም

ኢንጂነሩ ሳይጠቅሱ አላለፉም። ግድቡን ወደ ድንበር ያመጣው

የምህንድስናው ሳይንስ በማስገደዱ ነው ያሉት ኢንጂነሩ፤ ኃይል ለማመንጨት የሚያስችለው አባይ ኢትዮጵያን ለቆ ከመውጣቱ ከ20 እስከ 40 ኪሎ ሜትር ባለውና አሁን ግድቡ ባረፈበት ‘ጉባ’ ተብሎ በሚጠራው በረሃማና ሞቃታማ ስፍራ ነው።

ከኢንጂነር ስመኘው ገለፃ መረዳት እንደሚቻለው ከታላቁ የህዳሴ የኃይል ማመንጫ ግድብ በተጨማሪ ማንዲያ፣ ካራዶቢ፣ ሚቢልና ባሽሎ የሚባሉ አካባቢዎች ላይ ተጨማሪ የኃይል ማመንጫ ግንባታ ማከናወን እንደሚቻልም ፍንጭ ሰጥተዋል። ተፋሰሱ በሀገራችን ደረጃ 172 ሺህ ስኩዌር ኪሎ ሜትር እንደመሸፈኑ መጠን በተፋሰሱ ላይ ከሚሰራው የአካባቢ ጥበቃ ስራ ጎን ለጎን ተጨማሪ ግድቦችን ለመገንባት የሚያስችሉ

የምህንድስና ውጤቶች መኖራቸውን ጠቁመዋል። ግድቡ የዓለም አቀፍ ደረጃን የጠበቀ

የአዋጪነት ጥናት ተካሂዶ መጀመሩን፣ በተጨማሪ ስራውም ዓለም አቀፍ ደረጃውን ጠብቆ እየተሰራ መሆኑን አስረድተዋል። ይሄንኑም ለማረጋገጥ አስተማማኝ የላብራቶሪ ፍተሻ እየተደረገ መሆኑን ኢንጂነሩ ገልፀዋል።

ቀደም ሲል የግብፅ የግድብ ኤክስፐርቶች የህዳሴው ግድብ የሚያርፍበት ቦታ አለታማ በመሆኑ ግድቡ ሊናድ ይችላል የሚለውን አስተያየት ተቀባይነት እንደሌለው ገልፀዋል። ግድቡ ዓለም አቀፍ ደረጃውን በጠበቀ ቤተ-ሙከራ አማካኝነት እየፈተሸና እየተነተነ የሚሰራ ስራ እንደሆነም አረጋግጠዋል። በዚህ ሂደትም በርካታ ባለሙያዎች ከፍተኛ እውቀት እየቀሰሙ በመሆኑ ከሀገራችን አልፈው በሌሎች አገሮችም ተወዳዳሪ የምንሆንበት ደረጃ ላይ እየደረስን ነው ብለዋል።

ግድቡ ሙሉ ውሃ በሚያጠራቅምበት ጊዜ ወደኋላ 246 ኪሎ ሜትር እንደሚተኛና ውሃውም ለዓሣ እርባታና ለቱሪስት መስህብ ከመሆን አልፎ ሰፋ ያለ የውሃ ምህንድስና ምርምሮች የሚከናወኑበት ቦታ ሆኖ እንደሚያገለግልም ተገልጿል። ውሃው በሚተኛበት ሰፊ መሬት ላይ የሚኖሩ ነዋሪዎች ተነስተው ወደ ሌላ ቦታ እንዲሰፍሩ በክልሉ መንግስት በኩል እንቅስቃሴ እየተደረገ ነው። ውሃ ወደኋላ በሚተኛበት ቦታ ያሉ ተራራዎችም በሚጠራቀመው ሐይቅ ላይ ደሴት በመሆን ይበልጥ ለቱሪስት መስህብና ለመዝናኛነት እንደሚያገለግሉም ተገልጿል። ከፍተኛ መጠን ያለው የዓሣ እርባታ ይከናወንበታል። አካባቢው በዓለም ላይ ሊታዩ ከሚጓጓባቸው አካባቢዎች አንዱ የመሆን እድሉም ከፍተኛ እንደሆነም ተገልጿል።

“የአባይ ግድብ እንደ አድዋው ድል እስከወዲያኛው ለትውልድ የሚዘከር ነው” የሚሉት ኢንጂነር ስመኘው የግድቡ ፕሮጀክት ተራ ፕሮጀክት ሳይሆን የኢትዮጵያውያንን ቋሚ ሐውልት እንደሆነም ገልፀዋል። መጪውም ትውልድ የዚህን ትውልድ ፅናትና አይበገሬነት እያደነቀና እያከበረ እንዲኖር የሚያደርግ ነውም ብለዋል። ፕሮጀክቱ የሰላም ፕሮጀክት እንደሆነ የገለፁት ኢንጂነሩ፤ ለታችኛው ተፋሰስ አገሮች ጉዳት እንደሌለው በድጋሚ አረጋግጠዋል። የግድቡ እድሜ እንዲረዝም በተፋሰሱ ላይ የአካባቢ ጥበቃ ስራዎች የተጀመረው ጥረት በከፍተኛ መጠን ተጠናክሮ እንዲቀጥልም ተናግረዋል።

በአጠቃላይ ግድቡ በዛ በረሃ ውስጥ አንድ ከተማ የፈጠረ ይመስላል። በግድቡ ዙሪያ የተሰሩ የኮንክሪት ማዘጋጃ ፋብሪካዎችን ጨምሮ በርካታ ቤቶች ተሰርተዋል። ከሀገር ውስጥ ሰራተኞች በተጨማሪ አውሮፓውያን ሠራተኞችም መኖሪያቸውን በእዛው በረሃ ውስጥ አድርገዋል። ግድቡ እስከአሁን ስራውን እያንቀሳቀሰ ያለው በጄኔሬተር ኃይል ቢሆንም፤ በቅርቡ ወደ ግድቡ የሚያመራ ትልቅ የኤሌክትሪክ ምሰሶ እየተገነባ ነው። ለግድቡ የሚያገለግሉ ግዙፍ ማሽኖችና በርካታ ቁሳቁሶች ከጅቡቲ ወደብ አንስቶ ያለምንም መስተጓጎል የአባይን በረሃ አቋርጠው ወደ ስፍራው እየተጓጓዙ ነው። ቀያይ ዩኒፎርምና ሄልሜት ያደረጉ ኢትዮጵያውያን በግድቡ ውስጥ እየተርመሰመሱ ነው። ግዙፎቹ ተሽከርካሪዎችና የቁፋሮ ማሽኖቹ ያለማቋረጥ በረሃውን እያረሱ ነው። ግድቡን ሄዶ ለተመለከተ ሁሉ የግድቡን መጠናቀቅ በናፍቆት መጠበቁ አይቀርም። እስካሁን ባሉት ጊዜያትም ግድቡ ከአጠቃላይ ሥራው 30 በመቶ ያህሉ መጠናቀቁ ተገልጿል።¾

የአባይ ግድብ እንደ

አድዋው ድል እስከወዲያኛው

ለትውልድ የሚዘከር

ነው” የሚሉት ኢንጂነር

ስመኘው የግድቡ ፕሮጀክት

ተራ ፕሮጀክት ሳይሆን

የኢትዮጵያውያንን ቋሚ

ሐውልት እንደሆነም

ገልፀዋል

የድማሚት ፍንዳታ ሲካሄድ

ኢንጂነር ስመኘው በቀለ

Page 8: በአባይ ግድብ ውስጥ 3 ንደ - ethioforum.orgethioforum.org/wp-content/uploads/2013/12/Sendekdec102013.pdfሰንደቅ 9ኛ ዓመት ቁጥር 431 ታህሳስ 02 2006

ሰንደቅ 9ኛ ዓመት ቁጥር 431 ረቡዕ ታህሳስ 02 20068

ሰንደቅ፡- አሁን የሚካሄደው የቴሌኮም ኔትወርክ ማስፋፊያ ቀደም ሲል በሥራ ላይ የነበረውን አሮጌ የኔትወርክ መሳሪያዎች በማንሳት ወይም በመንቀል የሚካሄድ ነው። እንደሚታወቀው የኔትወርክ ትውልዶች ቴክኖሎጂ (Network generations) በየአስር ዓመቱ ነው የሚቀየሩት። ከዚህ አንፃር አሁን በአዲስ መልክ የሚሰራው ማስፋፊያ ምን ያህል መጪውን ቴክኖሎጂ ታሳቢ ያደረገ ነው?

ዶ/ር መስፍን፡- እስከአሁን ስንሰራበት የነበረው የቴሌኮም ቴክኖሎጂ መጪውን ቴክኖሎጂ ታሳቢ ያደረገ ነው ማለት አያስችልም። የነበረው ሁኔታ አንድ ቴክኖሎጂ ሲተከል ከመጪው ቴክኖሎጂ ጋር ከመናበብ ይልቅ ብቻውን በራሱ የቆመ ነበር። አንድ ቴክኖሎጂ ሲዘረጋ ሊናበብ የሚችለው ከአንድ ወይም ከተወሰነ ቴክኖሎጂ ጋር ብቻ ነበር። ይህም በመሆኑ ነው በአሁኑ ሰዓት ኔትወርኩን እንደ አዲስ እየዘረጋን ያለነው።

በአዲሱ የኔትወርክ ዝርጋታ ላይ ግን የቀደመው አሰራር እንዳይከሰት ጥንቃቄ አድርገናል። የአሁኑ የኔትወርክ ቴክኖሎጂ “upward compative” ይባላል። ይህም ማለት ወደላይ እየወጣ ከሚሄደው የኔትወርክ ቴክኖሎጂ ጋር እየተናበበ የሚሄድ ማለት ነው። በተለይ LTE የተባለው ቴክኖሎጂ ከዚህ አንጻር ሊጠቀስ የሚችል ነው። ይህ ቴክኖሎጂ ኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ የሚገነባ ሳይሆን በዓለም አቀፍ ደረጃ ሁሉም ቴሌኮም ኦፕሬተሮች ወደዚሁ LTE ቴክኖሎጂ እየመጡ ነው። ይህም በመሆኑ አሁን የምንገነባውን ቴክኖሎጂ አፈራርሰን በቀጣይ ሌላ የቴሌኮም ቴክኖሎጂ ሲመጣ እንደ አዲስ የምንገነባበት ሁኔታ አይኖርም። በቀጣይ ከሚመጣው ቴክኖሎጂ ጋር ለማጣጣም ተጨማሪ የቴሌኮም ማስፋፊያ ሳናደርግ ካርዶችን ብቻ በመጨመር በተገነባው መሰረተ ልማት ላይ ተጨማሪ ቴክኖሎጂ እሴትን እየጨመርን የምንሄድበት ሁኔታ ነው የሚኖረው።

ሰንደቅ፡- አሁን ከሚካሄደው የቴሌኮም ማስፋፊያ ጋር በተያያዘ በደንበኛ አገልግሎት አሰጣጣችሁ ላይ የሚፈጠሩ የጥራት መጓደሎች ይኖራሉ ተብሎ ይጠበቃል?

ዶ/ር መስፍን፡- ወደማስፋፊያው ሥራ ከመግባታችን በፊት በደንበኞች አገልግሎት አሰጣጥ ላይ የጥራት መጓደሎች እንዳይፈጠሩ ቅድመ ሁኔታዎችን አድርገናል። ሁልጊዜም ቢሆን አንድ ነገር ሲሰራ ተግዳሮቶች ይኖራሉ። ሆኖም ወደስራ ከመገባቱ በፊት በስራው ሂደት ሊመጡ የሚችሉትን ተግዳሮቶች ለመቋቋም እንደመንግስት ሙሉ በሙሉ ተዘጋጅተናል ብለን እንገምታለን።

በመሆኑም መንገራገጮቹ አይኖሩም ተብሎ ይገመታል። ነገር ግን ምናልባት አንዳንድ ችግሮች ቢኖሩ እንኳን “የግንባታው ሂደት ነው” በሚል ህዝቡ ይረዳናል ብለን እንገምታለን። በማንኛውም ሁኔታ የኔትወርክ ችግር ተፈጥሮ ደንበኞች አገልግሎቱን ማግኘት ሳይችሉ ሲቀር ተጎጂ የሚሆነው ደንበኛው ብቻ ሳይሆን መንግስትም ራሱ ነው። በዚህ በኩል መንግስት ከፍተኛ ገንዘብ የሚያጣ መሆኑ መታወቅ አለበት። ጉዳቱ የጋራ ነው።

ሰንደቅ፡- የሞባይል ሲም ካርዶችን ሽያጭ በተመለከተ ኢትዮቴሌኮም ለአከፋፋዮች ከሰጠ በኋላ አከፋፋዮች በበኩላቸው በየሱቁ የሚያከፋፍሉበት ሁኔታ አለ። ሆኖም በየሱቁ ሲሸጥ ሲም የሚገዛው ሰው ትክክለኛ መታወቂያና አድራሻ ተጣርቶ የማይሞላበት ሁኔታ በመኖሩ ማንነታቸው ለማይታወቁ ሰዎች ሳይቀር ሲም ካርድ በብዛት እየተሸጠ ኢትዮቴሌኮም ለቴሌኮም ማጭበርበር አደጋ ጭምር እየተጋለጠ ነው። አንዳንድ ባለሱቆች እንደውም በየጊዜው አድራሻ ይቀያይራሉ። በተለይ ከሀገር ደህንነት አኳያ አሁን ያለው አሰራር እንዴት ይታያል?

ዶ/ር መስፍን፡- እውነት ነው፤ ክፍተቶች እንዳሉ የምንገምተው ነው። የቴሌኮም ማጭበርበሮች (Telecom fraud) አለ። ለምሳሌ ሰዎች ከውጭ ሲደውሉ ስልኮች ስክሪን ላይ የሚወጣው ቁጥር የተደወለበት ሀገር መነሻ ኮድ ሳይሆን የሀገር ውስጥ መነሻ ኮድ (+251) ነው። ይህ በቀጥታ ከማጭበርበር ጋር የተያያዘ ሥራ ነው። ይህ ችግር ሊከሰት የቻለው ሲም ካርዶች በትክክል ባለመሸጣቸው ነው። እኛ ይህ ችግር ሲፈጠር “ሲሙን የገዛው ማነው?” ብለን ለማጣራት የምንሞክርበት ሁኔታ አለ። ነገር ግን አስቸጋሪ ነው። ከዚህም በተጨማሪ ሌሎች በትክክል የማናውቃቸው ጉዳዮች ሊኖሩ ይችላሉ።

ሆኖም አሁን ያለው ችግር መፍትሄ ማግኘት አለበት። ለዚህ ጉዳይ መፍትሄ ለመስጠት በሚኒስቴር መስሪያቤቱና በኢትዮቴሌኮም ደረጃ የሲም አሰጣጡን ስርዓት ዲጂታላይዝ ለማድረግ ቀደም ሲል በፎቶና በወረቀት የሚያዘውን መረጃ ዲጂታል የሆነ ሲስተምን በመዘርጋት ቁጥጥሩን ለማጠናከር እየሰራን ነው።

ከዚህም በተጨማሪ አሁን እየተከሰተ ላለው ችግር መፍትሄ ለመስጠት ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ የሞባይል ቀፎዎች በሙሉ እንዲመዘገቡ ይደረጋል። ይህ በኢትዮጵያ ኔትወርክ ውስጥ ማንኛውም ያልተፈቀደለት ሞባይል እንዳይሰራ የሚያደርግ አሰራር ነው። ይህንን ለማድረግ ግን መጀመሪያ የሞባይል ቀፎ ምዝገባ (Mobile device registration) መካሄድ ይኖርበታል። ይህንን ማድረግ ስንችል በዚህ በኩል የሚታየውን የደህንነት ስጋትንም እየቀረፍን እንሄዳለን። እውነት ነው ብዙ ቀዳዳዎች አሉ፤ ሆኖም መፍትሄ ይገኛሉ።

ሰንደቅ፡- የሞባይል ቀፎ ምዝገባው

በምን መልኩ ነው የሚከናወነው?ዶ/ር መስፍን፡- የሞባይል ስልክ

ቀፎ ምዝገባ ሲባል እያንዳንዱ ሞባይል

ስልክ በራሱ የሆነ መለያ ቁጥር አለው፣ በጉምሩክ በኩል በሚያልፍበት ወቅት ይህ የሞባይል ቀፎ በኢትዮጵያ ኔትወርክ ውስጥ እንዲሰራ በኢትዮቴሌኮም ተመዝግቦ የመጠቀሚያ ፍቃድ እንዲያገኝ ይደረጋል። ሞባይል ቀፎው ከተመዘገበ በኋላ ባለቤቱ በግልጽ ይታወቃል። ሌባ ቢሰርቀው እንኳን ሌባው እንዳይጠቀምበት ማድረግ የሚያስችል ቴክኖሎጂ ነው። በኢትዮቴሌኮም የተመዘገበን ሞባይል ቀፎ ሌባ ከሰረቀው በኋላ ምን አልባት መጠቀም የሚችለው ሞባይል ቀፎን ፈታቶ ለሌላ መለዋወጫ በመጠቀም ብቻ ነው። ይህ አሰራር ደረጃቸውን ሳይጠብቁ በድንበር በኩል የሚገቡትን የሞይል ቀፎዎችንም ከስራ ውጪ በማድረግ ለመከላከል ያስችላል። ማንም ደንበኛ በኢትዮቴሌኮም የተመዘገበ ስልኩን መሰረቁን ካመለከተ ወዲያው ሞባይሉ ከሲስተሙ ውጪ እንዲሆን ይደረጋል።

ሰንደቅ፡- ይህ አሰራር ተግባራዊ ይሆናል ተብሎ የሚጠበቀው ከመቼ ጀምሮ ነው?

ዶ/ር መስፍን፡- ይህ አሰራር በትክክል በዚህ ወቅት ሥራ ላይ ይውላል ብዬ ቁርጥ ያለ ጊዜን ማስቀመጥ አልችልም። ሆኖም ከአዲሱ የማስፋፊያ ስራ ጋር አብሮ ሥራ ላይ እንዲውል ይደረጋል ብዬ እገምታለሁ። ኢትዮቴሌኮም ግን በዚህ አገልግሎት የሚውሉ ቴክኖሎጂዎች ወደሀገር ውስጥ በማስገባት ላይ ነው።

ሰንደቅ፡- ሰሞኑን ኔትወርክ በከፍተኛ ተረጃ የጥራት መጓደል ይታይበታል። ይህ ችግር ከማስፋፊያው ጋር የተያያዘ ነው?

ዶ/ር መስፍን፡- ከተለመደው ውጪ ከሰሞኑ የተለየ የኔትወርክ ችግር አለ የሚል እምነት የለኝም። ቢኖርም እንኳ ያው የተለመደው እንጂ ከማስፋፊያ ስራው ጋር አይገናኝም። የጥራቱ ጉዳይ ከማስፋፊያው ስራ ጋር በተያያዘ በሂደት የሚፈታ ነው። አንዳንዱ የኔትወርክ የጥራት ችግር ከኢትዮቴሌኮም ቁጥጥር ውጭ ነው። ለምሳሌ የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ በዚህ አቅጣጫ ሊጠቀስ የሚችል ነው።

ሰንደቅ፡- የኔትወርክ አቅሙና የተጠቃሚው ቁጥር እየተቀራረበ መሄዱ አንዱ ለኔትወርክ መጨናነቅ እና ጥራት መጓደል ምክንያት መሆኑ ይነገራል። ከዚህ አንፃር ለምን አዲስ ሲም እንዲሸጥ ይደረጋል?

ዶ/ር መስፍን፡- በአሁኑ ሰዓት ወደ አስራ ስምንት ሚሊዮን የሚጠጋ በስራ ላይ ያለ ሲም አለ። ሲም የገዛ ሁሉ በመስመሩ የሚጠቀምበት ሁኔታ የለም። አሁን ባለው አሰራር መሰረት ሲም መሸጥ ከማቆም ይልቅ ለተወሰነ ጊዜ ከስራ ውጪ የሆኑትን ሲሞች በመለየትና በመዝጋት መልሰው ስራ ላይ የሚውሉበት አሰራር (SIME RECYCLING) እየተጠቀምን ነው። ይህ አሁን ያለውን መጨናነቅ ቢያንስ ማስፋፊያው እስኪጠናቀቅ በተወሰነ ደረጃ እንዲቀንስ ያደርጋል።

“ከተለመደው ውጪ ሰሞኑን የተለየ የኔትወርክ ችግር አለ የሚል እምነት የለኝም”

መስፍን በላቸው (ዶ/ር)

በመገናኛ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የሚኒስትሩ የቴክኒክ አማካሪ

ኢትዮ ቴሌኮም በሀገር አቀፍ ደረጃ የኔትወርክ ማስፋፋት ስራውን ለማከናወን ከሁለቱ የቻይና ኩባንያዎች፣ ዜድ ቲ ኢ እና ሁዋዌ ጋር ስምምነት ላይ ከደረሰ ከጥቂት ወራት በኋላ ወደ ፕሮጀክቱ ትግበራ የገባ መሆኑን አስታውቋል። ፕሮጀክቱን ሙሉ በሙሉ ለማጠናቀቅ ሁለት አመታትን የሚፈጅ ሲሆን በአዲስ አበባ ደረጃ ግን ከ6 እስከ 8 ወራት ብቻ የሚፈጅ መሆኑ ታውቋል። የኔትወርክ

ማስፋፊያው ሥራ ሲጠናቀቅ የአዲስ አበባንም ሆነ የመላ ሀገሪቱን የኔትወርክ የጥራት ደረጃና አቅም በከፍተኛ ደረጃ ያሳድገዋል ተብሎ ይጠበቃል። የአፍሪካ የመረጃና የመገናኛ ቴክኖሎጂ ሳምንት ከህዳር 23 እስከ 27 ቀን 2006 ባሉት ቀናት ኢትዮጵያን ጨምሮ በመላው አፍሪካ ተከብሯል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ በመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የሚኒስትሩ የቴክኒክ አማካሪ ከሆኑት ዶ/ር መስፍን በላቸው ጋር አጭር ቆይታ አድርገናል። ከዶ/ር መስፍን ጋር በነበረን ቆይታ በዋነኝነት ያነሳንላቸው ጥያቄዎች ከወቅታዊው የኢትዮ ቴሌኮም እንቅስቃሴ ጋር የተያያዘ ነው።

በፀጋው መላኩ

ከተለመደው ውጪ ከሰሞኑ የተለየ የኔትወርክ ችግር አለ

የሚል እምነት የለኝም። ቢኖርም እንኳ ያው የተለመደው

እንጂ ከማስፋፊያ ስራው ጋር አይገናኝም። የጥራቱ ጉዳይ

ከማስፋፊያው ስራ ጋር በተያያዘ በሂደት የሚፈታ ነው

መስፍን በላቸው (ዶ/ር)

Page 9: በአባይ ግድብ ውስጥ 3 ንደ - ethioforum.orgethioforum.org/wp-content/uploads/2013/12/Sendekdec102013.pdfሰንደቅ 9ኛ ዓመት ቁጥር 431 ታህሳስ 02 2006

ሰንደቅ 9ኛ ዓመት ቁጥር 431 ረቡዕ ታህሳስ 02 2006 9

የሶኒ ምርቶችን የሚያስመጣው ግሎሪየስ ኃላፊነቱ የተወሰ የግል ማህበር በአይነታቸው ለየት ያሉ የቴክኖሎጂ እሴቶችን የያዙ የቴሌቭዥን

ምርቶችን አስመጥቶ ለሀገር ውስጥ ገበያ አቀረበ። ሶኒ ወደ ሀገር ውስጥ በማስገባት ከሰሞኑ ካስመረቃቸው የቴሌቭዥን ምርቶች መካከል አንዱ 4k ብራቪያ ኤል ኢ ዲ ሶኒ የተባለው ሲሆን የተለመደውን የኤችዲ የምስል ጥራትን በአራት እጥፍ አሳድጎ የሚያሳይ ነው።

ከዚህም በተጨማሪ ለገበያ የቀረበው ሌላኛው የሶኒ ቴሌቭዥን የምስል ጥራት በተመሳሳይ መልኩ የሙሉ ኤች ዲ ምስሎችን (Full HD contents) የጥራት ደረጃን በአራት እጥፍ ከፍ አድርጎ የሚያሳይ ሲሆን (Near Feelld Communication) (NFC) በተባለ ቴክኖሎጂ አማካኝነት ከሞባይል ስልክ ጋር በመናበብ በስልክ ላይ የሚገኝን የቪዲዮ ምስል በርቀት አንብቦ ፊልሙን

ከ150 በላይ የሆኑ የቻይና ታላላቅ ኩባንያ ባለሀብቶች የተሳተፉበት የቻይና ባለሀብቶች ኤክስፖ በአዲስ አበባ የሚሊኒየም አዳራሽ ተካሄደ። ኤክስፖው የተካሄደው ከህዳር 26 እስከ 28 ባሉት ቀናት ነው። ፉጃን፣ ሀናን፣ ሻንዶግ እና ሻንጋይ ከተባሉ የቻይና ግዛቶች የተውጣጡ ባለሀብቶች ኤክስፖው ላይ የተሳተፉ ሲሆን በርካቶቹም በኢትዮጵያ በተለያዩ ኢንቬስትመንት ዘርፎች የመሰማራት ፍላጎት ያላቸው መሆኑን አስታውቀዋል። በኤክስፖው ላይ ከቀረቡት በርካታ ምርቶች መካከል የአውቶሞቢል ምርቶች፣ የግንባታ የቴክኖሎጂ መሳሪያዎችና የመሳሰሉት ይገኙበታል። በኩባንያ ደረጃ ሁዋዊ፣ ዜድ

ቲ ኢ፣ ቻይና ፓወር፣ ሺዳስቲል፣ ሊፋን ግሩፕ በመባል የሚታወቁ ታላላቅ የቻይና ኩባንያዎች ምርቶቻቸውን በኤክስፖው ላይ አቅርበዋል።

በኤክስፖው ላይ ባለሀብቶቹ ከበርካታ ኢትዮጵያዊያን አስመጪዎችና ላኪዎች ጋር የሀሳብና የአድራሻ ልውውጥ በማድረግ አንዳንዶቹ በቀጣይ አብረው ሊሰሩ የሚችሉበትን ሁኔታ አመቻችተዋል። ቻይናውያኑ በኢትዮጵያ ያለውን የኢንቨስትመንት አማራጭ ፈትሸው መዋዕለ ነዋያቸውን እንዲያፈሱ ሰፊ ማብራሪያ የሰጡት በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የኢትዮጵያ ኢንቬስትመንት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ፍፁም

አረጋ ናቸው። እሳቸውም በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለውን ሰፊ የመሰረተ ልማት እንቅስቃሴንም በምሳሌነት አንስተዋል። ቻይናውያኑ ኤክስፖውን ከሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ይልቅ በኢትዮጵያ ለማድረግ የመረጡባቸውን የተለያዩ ምክንያቶችን በመዘርዘር በቀጣይ በኢትዮጵያ መዋዕለ ነዋያቸውን ለማፍሰስ የራሳቸውን ጥናት የሚያደርጉ መሆናቸውን አስታውቀዋል። ኢትዮጵያን ለኤክስፖው ማዘጋጃ ቦታነት እንድትበቃ አድርገዋታል ከተባሉት ምክንያቶች መካከልም ሀገሪቱ በተከታታይ ባለሁለት አሀዝ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገቧ እንዲሁም የአፍሪካ ህብረት መቀመጫ መሆኗ በዋነኝነት ተጠቅሰዋል

የቻይና ባለሀብቶች ኤክስፖ ተካሄደ

በሙሉ ስክሪኑ እንዲታይ ማድረግ የሚያስችል ነው። ቴሌቭዥኑ ከዚህም በተጨማሪ በተለይ ለኳስ ተመልካቾች ኳስ በቴሌቭዥን ቢመለከቱበት ወቅት ስቴዲየም ያሉ ያህል ስሜቱ እንዲሰማቸው ለማድረግ በስቴዲየም ያለው የተመልካች ድምፅ ዙሪያቸው እንዲከብ በማድረግ እዚያው ያሉ ያህል የስቴዲየም ድባብን መፍጠር የሚያስችል ነው። ይህንን ስሜት ለመፍጠርም የኳስ ኮሜንታተሩን ድምጽም ለማጥፋት የሚያስችልም ቴክኖሎጂ ተገጥሞለታል።

ቴሌቭዥኑ በስልክ ላይ ያለን መረጃ በNEC ቴክኖሎጂ እንዲታይ ማድረግ ከመቻሉም በተጨማሪ ከኢንተርኔት ጋር በመገናኘት ፌስቡክና ሌሎች የኢንተርኔት ውጤቶችን መጠቀም የሚያስችል የኢንተርኔት ቴሌቭዥን ነው። ቴሌቭዥኑ በተለያዩ የኢንች ስፋት ደረጃዎች በተለያዩ ዋጋዎች ለደንበኞች የቀረበ ነው። የኩባንያውን ምርቶች የሚጠግኑ ቴክኒሺያኖችም በተለያዩ መልኩ እንዲሰለጥኑ የተደረገ መሆኑ የተመለከተ ሲሆን ስልጠናው ወደተለያዩ ሀገራት ቴክኒሽያኖች እንዲላኩ ተደርጎ እንዲሁም በኦንላይን የሚሰጥ መሆኑ ታውቋል። ለማንኛውም የሶኒ ምርት በጥገና ማእከላቱ አገልግሎቱን የሚያገኝ ሲሆን ይሁንና ከዋናው የሶኒ ምርት ጋር ተመሳስለው ከደረጃ በታች የተሰሩ ምርቶች (Substandard products) ተፈትሸው ኦርጅናል ምርት አለመሆናቸው ሲረጋገጥ ሳይጠገኑ ወደመጡበት እንዲመለሱ የሚደረጉ መሆኑ ታውቋል። የአለም ዋንጫ ከመቃረቡ ጋር በተያያዘ ህብረተሰቡ በምርቶቹ እንዲጠቀም ቴሌቭዥኖቹ ለገበያ የቀረቡ መሆኑ ታውቋል።

ግሎሪየስ አዳዲስ የቴሌቭዥን ምርቶችን ወደገበያ አስገባ

ቴሌቭዥኑ በስልክ ላይ ያለን መረጃ

በNEC ቴክኖሎጂ እንዲታይ ማድረግ

ከመቻሉም በተጨማሪ ከኢንተርኔት ጋር

በመገናኘት ፌስቡክና ሌሎች የኢንተርኔት

ውጤቶችን መጠቀም የሚያስችል

የኢንተርኔት ቴሌቭዥን ነው

Page 10: በአባይ ግድብ ውስጥ 3 ንደ - ethioforum.orgethioforum.org/wp-content/uploads/2013/12/Sendekdec102013.pdfሰንደቅ 9ኛ ዓመት ቁጥር 431 ታህሳስ 02 2006

ሰንደቅ 9ኛ ዓመት ቁጥር 431 ረቡዕ ታህሳስ 02 200610

ወደ ገፅ 21 ዞሯል

ሰንደቅ፡- ብዙዎች በስራዎችህና በመፅሔቶች ላይ በምትሰጣቸው የፊልም ሂሶች ያውቁሃል። ለመጀመር ያህል እስቲ በቅርቡ “የአቡጄዲ ግርግር” የተሰኘ መፅሐፍ ለንባብ አብቅተሃል፤ ስለመፅሐፉ ትንሽ ነገር በለኝ?

ፍቃዱ፡- መፅሐፌ በአብዛኛው የኢትዮጵያ ፊልሞች ላይ የሚያጠነጥን ነው። በርካታ ምርምሮችና ጥናቶችን አካትቼ ስለፊልም ታሪካዊና ቴክኒካዊ ጉዳዮች ለመጠቃቀስ ሙከራ ያደረኩበት ስራዬ ነው ማለት እችላለሁ።

ሰንደቅ፡- በፊልም ጉዳይ ላይ የሚያጠነጥኑ በጣት የሚቆጠሩ መፅሐፍት አይተናል፤ ያንተን የተለየ የሚያደርገው ነገር ምንድነው?

ፍቃዱ፡- መፅሐፉ ለየት የሚያደርገው አንደኛው ነገር በፊልም ባለሙያ መፃፉ ነው። እኔ የሀገራችን ፊልሞችን ክፍተቶች አውቃለሁ ብዬ አስባለሁ። ስለዚህ ችግሮቹን በሚያውቅ ሰው መፃፉ አንድ ነገር ነው። ለምሳሌ ፊልም መስራት የምንችል ባለሙያዎች ሆነን ራሱ በሙያው ውስጥ ያሉትን ሙያዊ ቃላት አናውቅም። እነርሱን ለማስተዋወቅ ሞክሬያለሁ። ሌላው በመፅሐፉ ውስጥ የተካተተውና ብዙዎች ካነበቡት በኋላ የተጠቀሙበት የሚመስለኝ ውል እንዴት እንደሚፃፍ ማሳየቴ ነው። በተጨማሪም በስራ ሂደት፣ በቀረፃ ወቅት የሚነሱ ያልኳቸውን ተደጋጋሚ ችግሮች ለማሳየት ችያለሁ። ሌላው በፊልም አፃፃፍና በቴአትር አፃፃፍ መካከል ያሉትን ጉልህ ልዩነቶች ለማሳየት ሞክሬያለሁ ማለት እችላለሁ። ከታሪኩ አንፃር ስንመለከት ደግሞ በርካታ ዶክመንቶችን ለማስፈር ችያለሁ። ይሄ ሌላው መፅሐፉን ልዩ የሚያደርገው ነገር ነው። ባህልና ቱሪዝምን ጨምሮ የስራው ባለቤቶች እንኳን የማያውቋቸውን “ፖስተሮች” አሰባስቤ አቅርቤያለሁ። የኢትዮጵያ ፊልም ከየት ተነስቶ የት ደረሰ የሚለውን ጠቁሜያለሁ። ለቀጣይ ስራዎች ጥሩ መነሻ የሚሆን መፅሐፍ ነው።

ሰንደቅ፡- ለመፅሐፍህ መረጃ በምታሰባስብበት ወቅት ፈታኙ ነገር ምን ነበር?

ፍቃዱ፡- በመፅሐፌ ውስጥ ያካተትኳቸው ፊልሞች 493 ሲሆኑ እስከ ሐምሌ 2005 ዓ.ም ድረስ የተሰሩ ፊልሞች ናቸው ብዬ ገልጫለሁ። መረጃ የማሰባሰቡ ስራ በጣም ከባድ ነበር። ቅድም እንደነገርኩህ የአንዳንዶቹ ፊልሞች “ፖስተር” ባለቤቱም የሌላው ሆኖ አግኝቻለሁ። ከኢንተርኔት፣ ከተለያዩ ሰዎች በመለመንም፣ ከጋዜጣና ከመፅሔት ስብስቦችም ነው መረጃዎቹን ለማግኘት የሞከርኩት። ሲኒማ ቤቶችንም ደጅ ጠንቻለሁ። እናም ብዙዎችን ያስደነቀ ስብስብ አምጥቻለሁ። ለምሳሌ “ሒሩት አባቷ ማነው?” ፊልም በስም ብቻ ነው የሚታውቀው እኔ ግን “ፖስተሩን” አፈላልጌ አሳይቻለሁ። ይህ ፊልም በ1957 ዓ.ም የተሰራ የኢትዮጵያ የመጀመሪያው ፊልም ነው። የቆዩ ፊልሞችን የአንዳንዶቹን ከነታሪካቸው ለማስቀመጥ ሞክሬያለሁ፤ ስለዚህ “ቻሌንጁ” ከፍተኛ ነበር ማለት ይቻላል።

ሰንደቅ፡- መፅሐፉ ለፊልም ባለሙያዎች በተለየ ምን ጥቅም ይኖረዋል?

ፍቃዱ፡- መፅሐፉ በርካታ ጠቃሚ ጉዳዮችን ይዟል። ለምሳሌ ለፊልም ስራ የሚበጁ 21 ነጥቦችን አንስቻለሁ። ችግሮቹን በግልፅ አስቀምጫለሁ መፍትሔዎቹን መፈለግ እንችላለን። ስለዚህ መጽሐፉ በፊልም ስራ ላይ ለተሰማሩ ባለሙያዎች ጥሩ ግብዓት መስጠት የሚችል ይመስለኛል።

“በኢትዮጵያ ሲኒማ ውስጥ

የነጋዴው ድርሻ በዝቷል”ፍቃዱ ልመንህ

(የፊልም፣ የሥነ-ፅሁፍና የጋዜጠኝነት ባለሙያ)

በአሸናፊ ደምሴ

“የአቡጄዲ ግርግር” በቅርቡ አሳትሞ ለንባብ ያበቃው በፊልም ጉዳዮች ላይ መረጃ የሚሰጥ መፅሐፉ ነው። ይህን መፅሐፍ ከማዘጋጀቱ በፊት “ጥቁር ነጥብ”፣ “ሰርፕራይዝ” እና “ጓንታናሞ” የተሰኙ ፊልሞችን በድርሰት፣ በዳይሬክተርነት እና በፕሮዲዩሰርነት ሰርቷቸዋል። የዛሬው የመዝናኛ አምድ እንግዳችን ወጣቱ የፊልም ባለሙያ፣ ሃያሲና ጋዜጠኛ ጭምር ነው፤

ፍቃዱ ልመንህ። በስራዎቹና በህይወት ገጠመኞቹ ዙሪያ አፍታ ቆይታ አድርገናል መልካም ንባብ።

አንተ እንደባለሙያም ስትታዘበው ምን ትላለህ?ፍቃዱ፡- የአገራችን ሲኒማ አብዛኛውን

ድርሻ በግለሰቦች ላይ የወደቀ ነው። ከ “ሒሩት አባቷ ማነው” ጀምሮ በግለሰቦች ትብብር የተሰራ ነው። ከዚያ በኋላ በአንድ ወቅት የፊልም ኮፖሬሽን ተቋቋመ፤ እሱም ትንሽ ሰራና ሰማኒያዎቹ መጀመሪያ የአካባቢ ላይ መንግስት በአዋጅ አፈረሰው። ከዚያ በኋላ የኢትዮጵያ የፊልም ስራ ተመልሶ ግለሰቦች እጅ ላይ ወድቋል። መንግስትም ራሱ ጥበቡን ገፍቶታል ማለት ትችላለሁ። በተደጋጋሚ መንግስት እጁን እንዲያስገባ ቢጠየቅም የመንግስት ድርሻ ከመቆጣጠር ያለፈ ደጋፊ መሆን አልቻለም። መቆጣጠርና መርዳትን አብሮ ቢያደርገው ጥሩ ነው ብዬ አስባለሁ። ገና ወደፊትም ሙሉ ስቱዲዮ ከሌለህ፤ እንዲሁም ካሜራዎችና ባለሙያዎቹ ከሌለህ ከዚህ በኋላ ፊልምን በግለሰብ ደረጃ መስራት አትችልም የሚባለው ነገር በራሱ ሲሰማ የፊልሙን እድገት የሚያቀጭጭ ነው። ገንዘብ ቢኖርህም እንኳን ባለሙያዎችን ቀጥረህ ማሰራት አትችልም የሚል አዲስ አዋጅ እየመጣ ነው። ይህ ደግሞ ኢንዱስትሪውን ይጎዳዋል ባይ ነኝ። “አርቱ” የሚፈልገውን ነፃነት እያጣ መጥቷል። በደርግ ጊዜ ቀረጥ 40 በመቶ ነበር፤ አሁን 20 ሆኗል። አዋጁን በማርቀቅ ላይ የሚገኙት የመንግስት አካላት በኋላ ሊፀፀቱበት የማይገባቸውን ስራ ቢሰሩ ደስ ይለኛል። አዋጁ ከፀደቀ ሁኔታው ግን መፅሐፍ የሚፅፍ ሰው ማተሚያ ቤት ይኑረው እንደማለት ይቆጠራል።

ሰንደቅ፡- በመፅሐፍህ ውስጥ በርካታ ነገሮች ተነስተዋል። ነገር ግን አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች፤ “ያነሳቸው ጉዳዮች መልካም ሆነው ሳለ ጥልቅ ትንታኔ ይጎላቸዋል” ይላሉ። ይህ ጉዳይ በመፅሐፉ ምረቃ ወቅትም ተነስቷል። አንተ ምን ትላለህ? በቀጣይስ እንዴት ልትጠቀምበት አስበሃል?

ፍቃዱ፡- እንደምታስታውሰው “የአቡዴዲ ግርግር” መጽሐፍ ሲመረቅ የፊልም ባለሙያው ብርሃኑ ሽብሩን እኔ ነኝ በመፅሐፌ ላይ ዳሰስ እንዲያቀርብ የጋበዝኩት። መፅሐፌን ስሰጠውም ጠበቅ ያለ ነገር እንዲሰራበት ጭምር ፈልጌ ነው። ከመድረኩ እንደሰማኽው ጥሩ-ጥሩ ነገሮችን አንስቷል። ነገር ግን አንድ ነገር ቅር ያለኝ ምንድነው ምንም “ፖዘቲቭ” ነገር አላነሳም። ምንም በጎ ነገር ሳያነሳ ከመድረኩ መውረዱ ትክክል አይመስለኝም። በመፅሀፉ የቀረቡት አንዳንድ ነገሮች እስካሁንም ያልታዩ ነገሮች እንደሆኑ ያውቃል። በጥልቀት አልተዳሰሱም። አንድ ነገር ሆኖ ሳለ ጉዳዮቹ መነሳታቸውን በራሱ ግን እውቅና መስጠት ተገቢ ይመስለኛል። በነገራችን ላይ እኔ መነሻ መሆን ነው አላማዬ። የእኔን ፅሁፍ ተንተርሰው ሌሎች ብዙ ሊሰሩ፣ ሊወያዩ፣ ሊከራሩ ሁሉ ይችላሉ። መፅሐፌ ውስጥ እንደገለፅኩት ይህ ጉዳይ ይመለከተናል የሚሉ አካላት በትኩረት ካልሰሩ በቀጣይም እኔ መፃፌ እንደማይቀር ጠቁሜያለሁ። ያለውን የሰጠ ንፉግ አይባልም አይደል?

ሰንደቅ፡- የኢትዮጵያ ፊልም አሁን ያለበትን ደረጃ እንዴት ትገመግመዋለህ?

ፍቃዱ፡- ምንድነው መሰለህ፤ እኛ በተስፋ ውስጥ ነው ያለነው። ኧረ ፊልም መስራት ምን ያደርጋል እንድትል የሚያደርጉ ፊልሞች የመኖራቸውን ያህል አልፎ-አልፎም ቢሆን ጥሩ-ጥሩ ፊልሞች ይመጣሉ። ባለሙያው፣ ተመልካቹና ነጋዴው የሚጓተትበት መስክ ሆኗል። ይህ የሆነበት ምክንያት ደግሞ በኢትዮጵያ ሲኒማ ውስጥ

ሰንደቅ፡- የተማርከው ጋዜጠኝነት ሆኖ ሳለ እንዴት ወደፊልሙ ስራ ገባህ?

ፍቃዱ፡- የሰራሁት ሶስት ፊልም ነው። “ጥቁር ነጥብ”፣ “ሰርፕራይዝ”፣ እና “ጓንታናሞ” ይባላሉ። ከዚያ በፊት በስነ-ፅሁፍ አካባቢ መቆየቴ ተፅዕኖ ያሳደረብኝ ይመስለኛል። በባህርዳር ዩኒቨርሲቲም ዲፕሎማዬን በቋንቋና ሥነፅሁፍ ካገኘሁ በኋላ ወደአዲስ አበባ መጥቼ በዩኒቨርስቲው የጋዜጠኝነትና ኮሚኒኬሽን ዘርፍ ዲግሪዬን ሰርቻለሁ። ጥበብ ደግሞ ቤተሰቧ ሰፊ ነው፤ ጋዜጠኝነትም ለጥበብ ቅርብ የሆነ ሙያ ነው። በጋዜጠኝነቴ “ዳና” የምትባል መፅሄት ነበረችኝ። ስለዚህ ጥበቡና ሙያው የተያያዙ ነገሮች ናቸው ማለት ይቻላል።

ሰንደቅ፡- ከ“ሒሩት አባቷ ማነው?” የሚጀምረው የኢትዮጵያ የሲኒማ ታሪክ በጉዞው ከፍና ዝቅን አልፏል።

Page 11: በአባይ ግድብ ውስጥ 3 ንደ - ethioforum.orgethioforum.org/wp-content/uploads/2013/12/Sendekdec102013.pdfሰንደቅ 9ኛ ዓመት ቁጥር 431 ታህሳስ 02 2006

ሰንደቅ 9ኛ ዓመት ቁጥር 431 ረቡዕ ታህሳስ 02 2006

አንዳንድ

11

በመስከረም አያሌው

የጭን ሥር ብሌኖችነጋሪት ይጎሰም፣ መለከት ይነፋየኛ አዳም ይፈለግ፣ ወዴት እንደጠፋይታሰስ ከተማው፣ ይበርበር ሽጥ መስኩ“አዳም ሆይ ወዴት ነህ?” ይባል ከመድረኩ/ያኔም ይኸው ነበር/በኩር ሆኖ ያልታደለው፣ ያ አዳም የጥንቱመልካሙን ፍሬ የበላለት፣ ወስዶ ከሴቲቱመራቆቱን አይቷል፣ የሱም የሷም ገላሲከፈቱ አይኖቹ፣ ከግብዣው በኋላ። /ከዚያች ቀን ጀምሮ … /የበለስ ቅጠል አገልድመው፣ ሲሸፈን ጊዜ እርቃናቸው “መግለብ” የሚል ቃል ፈጠሩልን፣ መተኛኛት ሲያምራቸው። ሲወርድ ሲዋረድ መጥቶ፣ “መግለብ” የሚሉት ቃልይኸው የኛም ዘመን አዳም፣ ተግባሩን ተክኖታል። በዝሙት ጋኔን ተለክፎ፣በየአደባባዩ - በየጥጋጥጉመግለብ የሚያምረውን አዳም፣ውጡና ፈልጉ

የጭን ሥር ብሌኖች - በእስጢፋኖስ በፈቃዱ (አቢ)¾

እንቅልፍ በአውሮፕላን ውስጥ ያስረሳልቶም ዋጐነር ከሊውሲኒያ ወደ ካሊፎርኒያ የሚያመራው አውሮፕላን ውስጥ ከገባ በኋላ ትንሽ ሽልብ

ያደርገዋል። እንቅልፉ የምር ይሆንና ድብን ያለ እንቅልፍ ተኛ። አውሮፕላኑ ቡሽ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ደርሶ ሲቆም ሁሉም እየወረደ ወደየቤቱ አመራ። ቶም ግን እዚያው አውሮፕላኑ ውስጥ ለሽ ብሏል። የአውሮፕላኑ ሰራተኞች የዕለት ተግባራቸውን አጠናቀው መብራት አጠፋፍተው ከጨረሱ በኋላ ቆላልፈው ወደየአቅጣጫቸው ሄደዋል።

“ከእንቅልፌ ስነቃ ብቻዬን ነው ያለሁት። መብራቶቹም ጠፍተዋል። ምን እየተካሄደ እንዳለ ግራ ነበር የገባኝ” ያለው ቶም፤ ትንሽ ካሰበበት በኋላም ወደ ሴት ጓደኛው ስልክ መደወልን ነበር እንደአማራጭ የወሰደው። “ሞባይሌን አንስቼ ለጓደኛዬ ደወልኩላት። የቀወስኩ ነበር የመሰላት። ዴቢ በአውሮፕላን ውስጥ ተቆልፎብኛል። እውነቴን ነው የምልሽ። ወደ ሆነ ቦታ ሄደሽ ከዚህ ቦታ የሚያወጣኝ ሰው ፈልጊ ስል ነገርኳት” ብሏል ቶም።

በሴት ጓደኛው ጥረትም ከዩናይትድ አየር መንገድ ወደ አውሮፕላን ማረፊያው የተላከው ሰው አውሮፕላኑን ሲከፍት ቶም ተገኘ። ከነቃበት ጊዜ ጀምሮ ለግማሽ ሰዓት ያህል በአውሮፕላኑ ውስጥ የቆየው ቶምም ከወጣ በኋላ “ለመሆኑ የጤንነት ችግር ቢኖርብኝስ፣ ወይ ደግሞ የልብ ድካም ኖሮብኝ ብሞት ምን ይፈጠር ነበር? እንዴት አውሮፕላኑን ዝም ብለው ቆልፈው ይሄዳሉ?” ሲል በንዴት መናገሩን የገለፀው ዩናይትድ ኤክስፕሬስ፣ አየር መንገዱ ቶምን ይቅርታ የጠየቀው ሲሆን፤ እንዴት ሊረሳ እንደቻለም በማጣራት ላይ መሆኑን ዘግቧል።¾

ሰነፍ ተማሪአንድ ሰነፍ ልጅ ገና ተማሪ ቤት የገባ ዕለት ፊደል መቁጠር ጀመረ። ከ‘ሀ’ እስከ ‘ፐ’ ድረስ አንድ

ጊዜ ብቻ የፊደሉን ተራ ወጣና ከሁለተኛው ላይ መምህሩ መልሶ ሲመራው ‘ሀ’ በል ሲባል ተማሪው እምቢ አለ። ቢያባብለው ቢለምነው፤ ቢለው ቢያደርገው አሻፈረኝ ብሎ እያለቀሰ ከተማሪ ቤት ወጥቶ ሄደ።

በመንገድ ላይ እያለቀሰ ሲሄድ አንድ ሰው አግኝቶት ምነው ምን አገኘህ እንደዚህ ታለቅሳለህ ቢለው፤ “መምህሬ ‘ሀ’ በል ብለውኝ እንቢ ብዬ ተጣልተን ነው የማለቅሰው” ሲል መለሰለት። ሰውዬው ‘ሀ’ ለማለት ታዲያ ምን የሚያስቸግር ነገር አገኘህበት? ሲል ጠየቀው። ልጁም እነዚህ መምህሮች መቼ ጣጣቸው በ‘ሀ’ ብቻ ያበቃል። ‘ሀ’ ስል ‘ሁ’ በል ይሉኛል። ‘ሁ’ ስል ‘ሂ’ በል ይሉኛል። ‘ሂ’ ስል ‘ሃ’ በል ይሉኛል። እንደዚህ እያሉ እስከ ‘ፐ’ ድረስ የፃፉትን ፊደሎች ሁሉ አንድ በአንድ ሲያስቆጥሩኝ ያለበትን ድካም አንድ ጊዜ ቀምሼው አንገፈገፈኝ። ከእንግዲህ ወዲያ ይግደሉኝ እንጂ ምንም ቢሆን ሁለተኛ ‘ሀ’ ብዬ አልጀምርም አለ።

ታሪክና ምሳሌ - በከበደ ሚካኤል¾

Page 12: በአባይ ግድብ ውስጥ 3 ንደ - ethioforum.orgethioforum.org/wp-content/uploads/2013/12/Sendekdec102013.pdfሰንደቅ 9ኛ ዓመት ቁጥር 431 ታህሳስ 02 2006

ሰንደቅ 9ኛ ዓመት ቁጥር 431 ረቡዕ ታህሳስ 02 200612ሕይወት

በመስከረም አያሌው

ባለፈው ሳምንት የዓለም አቀፍ ደረጃ የተከበረውን የአካል ጉዳተኞች ቀን አስመልክቶ በአዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ አካል ጉዳተኛ ጋዜጠኞች በስራው ዓለም ላይ ያላቸውን ፈተናን በተመለከተ የውይይት መድረክ አካሂዶ ነበር። በውይይት መድረኩ ላይ ከተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን የተውጣጡ አካል ጉዳተኛ ጋዜጠኞች ተገኝተው የስራ ተሞክሯቸውን ለታዳሚው አካፍለዋል። ጥሪ የተደረገላቸው ከተለያዩ የአካል ጉዳተኛ ማህበራት የተውጣጡ ተሳታፊዎች ተገኝተዋል። የጋዜጠኛ ተስፋዬ ገብረማርያም እና የጋዜጠኛ ማርታ ደጀኔን ተሞክሮ እነሆ፡-

አብዛኛው በወጣትነት እድሜ ላይ ያለ ሰው በኢትዮጵያ ሬዲዮ የቅዳሜ መዝናኛ ትረካዎች ላይ ድምፁን ያውቀዋል። በሚያስገመግም ድምፁ የሚያቀርባቸው ትረካዎች እና መነባንቦች በብዙዎች ልብ ውስጥ ቢቀሩም፤ ተስፋዬ ማነው? የሚለውን ግን ማንም አያውቅም። ጋዜጠኛ ተስፋዬ ገብረማርያም ቀደም ሲል በኢትዮጵያ ሬዲዮ አሁን

ደግሞ የአየር ሰዓት በመግዛት በተለያዩ የሬዲዮ ጣቢያዎች ላይ በአካል ጉዳተኝነት ላይ የሚያጠነጥኑ ፕሮግራሞችን ያዘጋጃል።

ጋዜጠኛ ተስፋዬ እስከ ስድስት ዓመት ዕድሜው ድረስ ጤነኛ ልጅ የነበረ ሲሆን ከዚያ በኋላ ግን በሁለቱም እግሮቹ ላይ ጉዳት ደርሶበት የክራንች ተጠቃሚ ለመሆን ችሏል። “እስከ 6 ዓመቴ ድረስ ወላጆቼ ደብቀው ነበር ያሳደጉኝ። ቡዳ ይበላዋል እየተባለ ጓዳ ውስጥ ይደብቁኝ ነበር። በዚያ ላይ ደግሞ ለቀቅ ሲያደርጉኝ መቀመጥ አልወድም። ምግብ እንኳን ለመብላት በመከራ ነው። ሁሌ መጫወት እና መሮጥ ነበር የኔ ፍላጎት። በጣም ቀዥቃዣ ነበርኩ” ሲል ከአካል ጉዳተኝነቱ በፊት የነበረውን ህይወት ያስታውሳል ተስፋዬ። ያም ሆኖ ግን ተስፋዬ ከዚህ እድሜው በኋላ አካል ጉዳተኛ በመሆኑ ቤተሰቡም ለእርሱ መንሰፍሰፉን ትቶ ሞቱን ይመኝለት ጀመር።

“እለቱ የማርያም ቀን ስለነበር ፀበል ሊቀምሱ በመጡ ሰዎች መካከል እሯሯጥ ነበር። ከዚያም አስመለሰኝና ደካከመኝ። ሀኪም ቤት ተወስጄ መርፌ ስወጋ እግሮቼ ወደኋላ ዞሩ፡ ከዚያ በኋላ አካል ጉዳተኛ ሆንኩኝ ማለት ነው። ቤተሰቤም የእኔን ሞት ነው የተመኘው። ምነው ባልተወለድክ ኖሮ፤ ምነው ሆዴ ውስጥ ውሃ ሆነህ በቀረህ ተባልኩኝ። ቤተሰቤ በእኔ ሙሉ ለሙሉ ተስፋ በመቁረጡ ሌላ ልጅ ላለመውለድ ወሰኑ” ይላል ተስፋዬ።

ተስፋዬ በዚህ መልኩ ከቤተሰቡ ያልጠበቀው ነገር ቢፈጠርበትም ህይወትን መግፋቱን ቀጠለ። በክራንች እየታገዘም ትምህርቱን ቆይታውም በትምህርት ቤት ሚኒሚዲያ ከፍተኛ ተሳታፊ ነበር። ለመጀመሪያ ጊዜም የ9ኛ ክፍል ተማሪ ሳለ በሚኒሚዲያ ባቀረበው ስራው በርካቶች ስለተደመሙበት እርሱም ጋዜጠኛ የመሆን ተስፋውን አለመለመ።

ተስፋዬ ለጋዜጠኝነት

ከነበረው ሙያ የተነሳ ከደብረዘይት አዲስ አበባ ድረስ በአውቶቡስ እየተመላለሰ ሲሰራ ነበር።ይሄንን የሚያደርገው ከቤተሰቦቹ ተደብቆ ሲሆን አውቶቡስ መሳፈሪያ ገንዘብ የሚያገኘውም ከመምህራኑ እንደነበር ይናገራል። በመቀጠልም ከዩኒቲ ዩኒቨርስቲ በጋዜጠኝነት በመመረቅ ወደ ስራው አለም አመራ። በስራው አለምም ቢሆን ለተስፋዬ ቀላል የማይባሉ ፈተናዎች ገጥመውታል።

ሌላዋ በዚህ ዝግጅት ላይ ተገኝታ አካል ጉዳተኝነት በሞያዋ ላይ ያለውን ተፅዕኖ ያስረዳችው ብዙዎቻችን በሬዲዮ ስሟን የምንሰማው ጋዜጠኛ ማርታ ደጀኔ ናት። ማርታ አካል ጉዳተኛ በመሆኗ ምክንያት ውሎዋና አዳሯ በቤት ውስጥ ነበር። በዚህ ጊዜ ታዲያ ለዛሬው ህይወቷ መሰረት ጣለች። “እንደ ጤነኛ ልጆች አኩኩሉ እና አባሮሹን ተሯሩጬ መጫወት ባለመቻሌ ጊዜዬን የማጠፋው ጋዜጦች እና መፅሔቶችን በማንበብ ነበር። ሁልጊዜም የተለያዩ የሬዲዮ ጣቢያዎችን እከታተል ነበር። አንብቤ እና ሰምቼም የተሰማኝን ነገር በስልክ እና በደብደቤ አስተያየት እሰጥነበር” ትላለች ማርታ።

የልጅነት ጊዜዋን በአድማጭ እና አንባቢነት ያሳፈችው ማርታ ከፍ ስትል በተለያዩ ጽሑፎች መሳተፍ ችላለች። በአካል ጉዳተኝነት ላይ የሚያተኩሩ የመገናኛ ብዙሃን ባለመኖራቸው የራሷን ድርሻ ለመወጣትም ብዙ ጥረት አድርጋለች። የ12ኛ ክፍል ተማሪ ሳለች የራሷን እና በአካል ጉዳተኝነት ላይ ያተኮረ ጋዜጣም እስከማሳተም ደርሳ ነበር። በአሁኑ ወቅት በዛሚ ኤፍ ኤም ሬዲዮ ላይ በመስራት ላይ ትገኛለች። በተጨማሪም ማእዶት የተባለ እና በአካል ጉዳተኞች ላይ ያተኮረ ፕሮግራም በኢቲቪ 3 ላይ ታቀርባለች።

ተስፋዬ ስራ ለመቀጠር በሄደበት ሀሉ “ስራው መሯሯጥን የሚጠይቅ ነው። እንደ አንተ በክራንች ለሚሄድ ሰው አይሆንም” እየተባለ ይመለስ ጀመር። እርሱ ግን

ከአካል ጉዳተኝነቱ በስተጀርባ ያለውን ችሎታ ለማሳየት የተቻለውን ሁሉ አደረገ። በተለይ በድምፁ በኩል ያለው ተሰጥኦ አግዞት ስራውን ኤፍ ኤም 97.1 ላይ ጀመረ። በመቀጠልም በተለያዩ ጣቢያዎች ላይ ከአካል ጉዳተኝነት ጋር የተያያዙ ስራዎችን የሰራ ሲሆን በአሁኑ ወቅትም በዛሚ ኤፍ ኤም ላይ “ድርሻችን” የተሰኘ ፕሮግራምን ያዘጋጃል። ከዚህ ጎን ለጎንም በኢቢ ኤስ ላይ ፕሮግራም ለመጀመር በዝግጅት ላይ ይገኛል።

ተስፋዬ የአካል ጉዳተኝነት ችግሩ ከቤተሰብ ይጀምራል ባይ ነው። እርሱ አካል ጉዳተኛ ከመሆኑ በፊት እና ከሆነ በኋላ ከቤተሰቡ ይሰጠው የነበረው ግምት ደግሞ ለዚህ ማሳያው ነው። “አካል ጉዳተኛ ከሆንኩ በኋላ ስእል ስስል ይቀድዱብኛል። ሬዲዮ ጭምር ሳዳምጥ ይዘጉብኛል። ምንም ነገር ማድረግ እንደማልችልና ምንም እንደማያስፈልገኝ ነበር የሚያስቡት” የሚለው ተስፋዬ፤ በስራው አለምም ቢሆን መንቀሳቀስ የማይፈልገውን የስልክ ኦፕሬተር ትሆናለህ እያሉ ይወስኑለት እንደነበር ያስታውሳል።

“እኔ አንድ ቀን ትልቅ እንደምሆን ይሰማኝ ነበር። አንድ ሙስሊም አባት ተስፋዬ ከእንግዲህ አይድንም፤ ነገር ግን ትልቅ ስራ ሰርቶ ያኮራችኋል” ብለው ለወላጆቼ ተናግረው ነበር። እኔም ይሄንን አውቅ ነበር። አሁን ወደዚያ ትልቅነት እየገባሁ ነው። እኔ በስራ ከመጣችሁ አካል ጉዳተኛ አይደለሁም” ይላል ተስፋዬ። አሁን እየሰራ ባለው ስራ እና በደረሰበት ስኬትም የወላጆቹን አመለካከት ጭምር መቀየር ችሏል። “በአሁኑ ወቅት እኔ ለስራዬ እስከ አስራ ሁለተኛ ፎቅ ልወጣ እችላለሁ። ያስፈለገው ቦታ ሁሉ ደርሼ ስራዬን እየሰራሁ ነው። ምነው ባልተወለደ ሲሉ የነበሩ ወላጆቼም ከስንት ጊዜ በኋላ ልጆች ለመውለድ በቅተዋል” ይላል።

ማርታ ከተስፋዬ በተቃራኒው አካል ጉዳተኛ በመሆኗ በልጅነት ህይወቷ ብዙም ፈተና እንዳልነበረባት ነው ያጫወተችን። ነገር ግን ወደ ስራው አለም ስትመጣ በርካታ

በፈተና መካከል ያለፈ ትጋት

እኔ አንድ ቀን ትልቅ እንደምሆን ይሰማኝ ነበር።

አንድ ሙስሊም አባት ተስፋዬ ከእንግዲህ አይድንም፤

ነገር ግን ትልቅ ስራ ሰርቶ ያኮራችኋል” ብለው

ለወላጆቼ ተናግረው ነበር። እኔም ይሄንን አውቅ

ነበር። አሁን ወደዚያ ትልቅነት እየገባሁ ነው

ጋዜጠኛ ማርታ ደጀኔ ጋዜጠኛ ተስፋዬ ገ/ማሪያም

Page 13: በአባይ ግድብ ውስጥ 3 ንደ - ethioforum.orgethioforum.org/wp-content/uploads/2013/12/Sendekdec102013.pdfሰንደቅ 9ኛ ዓመት ቁጥር 431 ታህሳስ 02 2006

ሰንደቅ 9ኛ ዓመት ቁጥር 431 ረቡዕ ታህሳስ 02 2006 13ምልከታ

ከሄኖክ ስዩም

ከሃገራችን የረጅም ዘመን ስልጣኔ ጋር አብረው ከሚጠቀሱ ከተሞች ደብረታቦር አንዷ ናት። ከስድስት መቶ አመታት በላይ እደሜ ያስቆጠረችው ደብረታቦር እንደ አንዳንድ ሰነዶች በአፄ ሰይፈ አርዕድ ዘመነ መንግስት ከ1327 እስከ 1361 ዓ.ም ባለው ግዜ እንደተቆረቆረች ይገለፃል። ከከተማዋ ራስጌ በሚያምር ሞገሱ ተኮፍሶ የሚታየው የደብረ ታቦር እየሱስ ተራራ ለከተማዋ ስያሜ መጠሪያም ለመሆን ችሏል።

የራስ ጉግሳ ወሌ የግዛት ዘመን ለደብረ ታቦር ከተማ መፃኢ እድል አንድ የምስራችን የሰነቀ ነበር የያኔዋ ጁራ ከተማ በወቅቱ ከነበሩ የሃገራችን ደማቅ ከተሞችም አንዷ ነበረች። ከባላባት ስርዓት እጅ ወጥቶ በከተማ ወግ የተዘረጋ የመሬት ስሪት እንዲኖርባት በማድረጉ ረገድ ግን ራስ ጉግሳ ወሌ ቀዳሚውና ተጠቃሽ ናቸው ይህም በ1894 ዓ.ም የተከናወነ በነር።

የደብረታቦር ከተማና በራስጌዋ ያለው ተራራ በእየሩሳሌም ከሚገኘው የደብረ ታቦር ተራራ ጋር የሚያመሳስላቸው ብዙ ነገር ስላለ ደብረ ታቦር የሚለው ሰያሜ የከተማዋ መገለጫ እንደሆነም የሚገልፁ አሉ። በሃገር ውስጥ ስሟ እንዲገንና በውጪ ፀሐፍት ብዕር እንድትከተብ ካስቻሏት የታሪክ ምዕራፎች ውስጥ በጉልህ የሚጠቀሰው የአፄ ቴዎድሮስ ዘመነ መንግስት ነው። ጀግናው መሪ ኢትዮጵያን ሲሰንቁ የመረጧት ከተማ ደብረ ታቦርን ነበር። አፄ ቴዎድሮስ ደብረ ታቦርን ከመውደድ እና በከተማዋ ከመቀመጥ ባለፈ በወቅቱ የሃገሪቱ ሁኔታ ውጥረት ሲሰማቸው እረፍት ለማግኘት ጭምር የሚመርጧት ከተማ እንደነበረች ጥናቶች አስፍረዋል።

መቼም በሀገራችን ከሚገኙ ከተሞች ሁሉ በ”ደ” ፊደል የሚጀምሩት ብዙ የሚያመሳስላቸው

ነገር አለ። አይቶአቸው ለማያውቅ ምስስላቸው ከታሪካቸው ብቻ የተቀዳ ይመስለዋል። ባህር ዳርን የምትበልጣት ደብረ ማርቆስ፣ ከአዲስ አበባ የምትቀድመው ደብረ ብርሐን፣ ከጎንደር የላቀ እድሜ ያላት ደብረ ታቦር፣ የጥንት ከመሆን ባሻገር ለኑሮ የማይመቹ ያልሰለጠኑ ወደ ኋላ የቀሩ ከተሞች ነበሩ። ይህንን ታሪካቸውን የቀየረው የተማሪዎች እንቅስቃሴ ነው። የፈጣን እድገታቸው ምክንያት ደግሞ አዳዲሶቹ ዩንቨርስቲዎች። እናም ሁሉም አሁን ሌት ተቀን እየሰሩ ነው።

ብዙ ዓመታትን ለሽ ብላ ተኝታ የነበረችው ደብረታቦር ከጉና ራስጌ ከተጋደመችበት የዘመናት እንቅልፍ እየነቃች ነው። የግንባታ ድምጽ ጩኽት እንዳትተኛ ቀስቅሷታል። የተማሪ ጫጫታ አይኗን እንድትገልጥ አድርጓታል። የት ሄጄ ነበር በሚመስል ፍጠነት እራሷን እያደሰች ነው።

ይህች ከተማ ጋፋትን ጎኗ ሸጉጣ ኢንዱስትሪ ለምኔ ስትል የኖረች ነበረች። ስሟን መሸከም አቅታቷ ዘመናትን ኖራለች። የእነ እቴጌ ጣይቱ ብጡል ሀገር ደብረ ታቦር፤

ጋፋት በከተማዋ ከሚገኙ መስህቦች አንዱ ነው። የአጼ ቴዎድሮስ መድፍ የተሰራበት ስፍራ፤ ዛሬም አፈርና ብረት ተቀላቅሎ መሬት ረግፎ ይታያል። ይህ ቅሪት ደብረ ታቦርን ለዘመናት ሲታዘባት የኖረ ነበር፤ አሁን እፎይ ማለት የጀመረ ይመስላል። ከተማዋ ለ100 ዓመት ተኛች አንጂ የእነ አጼ ዩሐንስ 4ኛን ሁሉ ቀልብ ስባ ነበር። ሕሩይ ጊዮርጊስ በአጼ ዩሐንስ ዘመን መንግስት በራሳቸው የተገነባ ቤተ ክርስቲያን ነው። በወቅቱ የኢትዮጵያ ባንዲራን እራሳቸው አጼ ዩሐንስ 4ኛ ለህሩይ ጊዮርጊስ አበርክተው ዛሬም ድረስ አለ። ከህሩይ ጊዮርጊስ አናት ያሰሩት ቤተ መንግስት ፍራሽ

እንደቆመ የደብረ ታቦርን ገናና ታሪክ ይመሰክራል።

ታዲያ ይህች ከተማ ሰሞኑን የነቃችው ለዘመናት ምን ነክቷት ይሆን ትሉ ይሆናል። መልስ የለውም….ማንም የማይመልሰው አዚም ነበር…እነሆ ደብረታቦር ባና ልብ የሚያፈርሰው መንገዷ በአስፋልት ተቀይሮ ውስጥ ለውስጥ ኮብል ስቶን ሆና….ይሔም አለ እያለች ነው። እንዳየኋት…..የእሷን እኔ ተደሰትኩላት…ይህቺ ቴዎድሮስ አብልጦ የሚወዳት ከተማ የዛሬን አያድርገውና ከበጌምድር ሰው በላቀ ድፍን የሀገሬን ሰው ያስጎመጀች ነበረች።

ከሁለት ዓመት በፊት ከጋሪ ውጭ ሌላ ቴክኖሎጂ ያለ የማይመስላት ደብረ ታቦር ባጃጅ ሲሮጥባት ይውላል። ሀገሬው ከእስቴ እስከ ስማዳ ከጋይንት እስከ ፋርጣ ከደራ እስከ ሊቦ ከምከም ከንፋስ መውጫ እስከ ወረታ ዘልቆ ያደምቃታል። የደቡባዊው ጎንደር ክፍል ዋና ከተማ ናትና……

ደግሞ ደብረ ታቦርን ሳያት መልሼ እራሴን እጠይቃለሁ….ያ ሜዳማ ፎገራ ወረታ የሚባል ድንቅ መዲና ገንብቶ ስታይ ምን ብላ ይሆን….የእሷ የእንቅልፍ ዘመን ስንት ከተሞችን እየወለደ ነው። እነ ንፋስ መውጫ በጉም ተሸፍነው ዘመኑ….እነ ወረታ ትርፍ አምራቹ የፎገራ ገበሬ አበባ አደረጋቸው….ደብረታቦር ስትነቃ እውነታው ይሄ ነበር፤

ከአራት ዓመት በፊት ሶስት ሆቴል ይዛ ትገባበት ያጣችው መዲና ዛሬ የመንገዷ ዳርቻዎች ጎኑን የሚያሳርፍ በሚጠባበቁ ፔንሲዮኖች ተገጥግጠዋል። እንዲያም ሆኖ ሙዚየም የላትም፤ እንዲያም ሆኖ ሎጂ ገንቢዎች አላዩዋትም። ገና ከእንቅልፏ እየነቃች በመሆኑ ስራ በዝቶባታል። ስታዘባት እንኳን ቀና ብላ አላየችኝም….. አይዞሽ እሺ ደብረ ታቦር…..

ከዘመናት እንቅልፏ እየነቃች ያለችው

ደብረታቦር

ከአራት ዓመት በፊት ሶስት

ሆቴል ይዛ ትገባበት ያጣችው

መዲና ዛሬ የመንገዷ ዳርቻዎች

ጎኑን የሚያሳርፍ በሚጠባበቁ

ፔንሲዮኖች ተገጥግጠዋል።

እንዲያም ሆኖ ሙዚየም

የላትም፤ እንዲያም ሆኖ ሎጂ

ገንቢዎች አላዩዋትም

ፈተናዎች አጋጥመዋታል። “እኔ እንኳን እንደምንም እወጣዋለሁ። ፕሮግራሜን ስሰራ በርካታ ደረጃዎችን በክራንቼ እየወጣሁ ነው። ብዙ አስቸጋሪ ቦታዎች ያጋጥሙኛል። ለሌሎች ሰዎች እንደ ውበት የሚያገለግሉት ወለሎች ለእኔ እና ለጓደኞቼ የክራንች ጎማ ግን አመቺ አይደሉም። ይሄ የሁላችንም አካል ጉዳተኞች ችግር ነው” ትላለች።

ማርታ ከራሷ ችግር ይልቅ እርሷ በምታገኛቸው ሰዎች ላይ የሚደርሰው ችግር ያሳስባታል። “ብዙ ጊዜ በፕሮግራሜ ላይ እንዲሳተፉ የማመጣቸው ሰዎች አሉ። እነርሱ ወደኔ ቢሮ ለመግባት በጣም ሲቸገሩ አያለሁ። ዊልቸር እና ክራንቻቸው አሊያም ሌላው መሳሪያ ለዚያ መንገድ የማይመቹ ይሆናል። ይሄ ትልቅ ችግር ነው። ያለው መሰረተ ልማት አካል ጉዳተኞችን ታሳቢ ያደረገ አይመስለኝም። መብራት ከጠፋ አሊያም ሊፍት ከሌለ ረጃጅም ፎቆችን በክራንቻችን ለመውጣት እንገደዳለን” ትላለች ማርታ።

ያም ሆኖ ግን ማርታ ከሌሎች ሰራተኞች ባላነሰ ሁኔታ ስራዋን በአግባቡ ታከናውናለች። ነፍስ ጡር ሆና ሳይቀር ፎቆችን እየወጣችና እየወረደች ስራዋን ትሰራ እንደነበር ትናገራለች። “አርግዤ እስከ ሰባተኛ ወሬ ድረስ ስራዬን እሰራ ነበር። ቢሮዬ ፎቅ ላይ ቢሆንም በቀን ሶስቴ አራቴ ወጥቼ እገባ ነበር። እኔ ከዚያም በኋላ ለመስራት አስቤ የነበረ ቢሆንም ጤነኛ ልጅ መውለድ ስላለብኝ ብቻ ከሰባት ወሬ ጀምሮ እረፍት እንዳደርግ ስለተነገረኝ እረፍት ወጣሁ” ትላለች።

ተስፋዬም ሆነ ማርታ አካል ጉዳተኝነታቸው ሳይበግራቸው ልክ እንደ ሌላው ሰው ሰርተው መለወጥን እና ለታላቅ ደረጃ መብቃትንም አሳይተዋል። በሚሰሩት ስራም የጥቂቶችንም ህይወት ቢሆን መለወጥ ችለዋል። ተስፋዬም በአሁኑ ወቅት በአካል ጉዳተኝነት ላይ የመጣው ለውጥ አበረታች ነው ባይ ነው።

“እኔ በበኩሌ ከቤተሰቤ ጀምሬ አካል ጉዳተኞች ሰርተው ትልቅ ደረጃ መድረስ እንደሚችሉ አሳይቼያለሁ። እድሜዬን ሙሉ ሰዎችን ለማሳመን ብዙ ስራዎችን ሰርቻለሁ። በእኔ ጥረት ብቻ ባይሆንም ለውጥ መጥቷል። ሌላ ሌላው እንዳለ ሆኖ በአሁኑ ጊዜ በዊልቸር እና በክራንች የሚሄዱ በርካታ አካል ጉዳተኞችን መንገድ ላይ መመልከት ችለናል። በፊት በፊት እኮ አካል ጉዳተኛ አደባባይ አይወጣም ነበር። ጓዳ ውስጥ ነበር የሚደበቀው። አሁን ግን መንገድ ላይ፣ ከተማ ውስጥ መንቀሳቀስ ጀምሯል። ይሄ ለኔ ትልቅ ለውጥ ነው” ይላል ተስፋዬ።

ማርታ በበኩሏ የአመለካከት ለውጥ ለማምጣት አሁን እየተሰራ ያለው ነገር በር ከፋች ቢሆንም ገና ብዙ ልንሰራቸው የሚፈለጉ ስራዎች እንዳሉ ትገልፃለች። “ዋናው የአመለካከት ለውጥ ማምጣት ነው። እኔ በምሰራቸው የስራዎች ያሰብኩትን ያህል ምላሽ አላገኘሁም። በዚህም ነው ብዙ መስራት እና የህዝቡን አመለካከት መቀየር ያስፈልጋል የምለው” ትላለች።

በዝግጅት ላይ በተገኙ ከተለያዩ አካል ጉዳተኞች ለተሰነዘረላቸው ጥያቄዎችም ጋዜጠኞቹ መልስ ሰጥተዋል። ከሁሉም በላይ ጋዜጠኞቹ አፅንኦት ሰጥተው የተናገሩት በአካል ጉዳተኞች እና አካል ጉዳተኝነት ላይ ለውጥ ለማምጣት የሁሉም ድርሻ መሆኑን ነው።

Page 14: በአባይ ግድብ ውስጥ 3 ንደ - ethioforum.orgethioforum.org/wp-content/uploads/2013/12/Sendekdec102013.pdfሰንደቅ 9ኛ ዓመት ቁጥር 431 ታህሳስ 02 2006

ሰንደቅ 9ኛ ዓመት ቁጥር 431 ረቡዕ ታህሳስ 02 200614ዜና

በመስከረም አያሌው

በሚ ቀ ጥ ሉ ት ሁለት ዓመታት ውስጥ ትውልደ ኢ ት ዮ ጵ ያ ዊ

ወታደር እስረኞችን ቁጥር በ15 በመቶ የመቀነስ እቅድ እንዳለው የእስራኤል ጦር ገለፀ።

እስራኤል ኒውስ የእስራኤል ፐርሶኔል ዳይሬክቶሬትን ጠቅሶ እንደዘገበው፣ በእስራኤል ጦር ውስጥ ከሚገኙ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ወታደሮች

መካከል 30 በመቶዎቹ በአገልግሎት ዘመናቸው ቢያንስ አንድ ጊዜ የሚታሰሩ በመሆኑ ይሄንን ቁጥር ለመቀነስ ታቅዷል። የፐርሶኔል

ዳይሬክተሩ ሄላ ሀልፐሪን እንደገለፁትም በእስራኤል ጦር ውስጥ በአሁኑ ወቅት 20 በመቶ የሚሆኑት ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ወታደሮች በአስተዳደር ስራ ላይ ተሳትፈው ይገኛሉ። በመሆኑም የእነዚህን ወታደሮች እስረኞች በመቀነስ በምትኩ 10 በመቶ የሚሆኑትን በቀጣዮቹ ሁለት ዓመታት ውስጥ የአየር ኃይል፣ ደህንነት፣ በቴክኖሎጂ፣ ሎጂስቲክስ እና በመሳሰሉ ቦታዎች ላይ ለመመደብ ታቅዷል።

ት ው ል ደ ኢትዮጵያዊያን የእስራኤል ወታደሮች የጦሩን ሶስት በመቶ የሚሸፍኑ ሲሆን፤ ከጦር እስረኞቹ ደግሞ 13 በመቶውን ይይዛሉ እንደ እስራኤል ኒውስ ዘገባ። ይሄንን ቁጥር ለማመጣጠንም የእስራኤል ጦር ባለፉት ዓመታት በርካታ ስራዎችን ሲሰራ እንደነበር የገለፀው ዘገባው ይህ የጦር እስረኞችን ቁጥር የመቀነስ እቅድም የዚህ እቅድ አካል መሆኑን ጠቁሟል። በተለይ ወንድ ትውልደ ኢትዮጵያዊ ወታደሮች 38 በመቶዎቹ በአገልግሎት ዘመናቸው ቢያንስ አንድ

ጊዜ የሚታሰሩ ሲሆን በአጠቃላይም አንድ አራተኛዎቹ ከአንድ ጊዜ በላይ የሚታሰሩ መሆናቸውን ዳይሬክቶሬቱ ገልፀዋል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እነዚህን ትውልደ ኢትዮጵያዊ የእስራኤል ወታደሮች በውትድርናው መስክ ውስጥ ያላቸውን አገልግሎት እንዲያሻሽሉ ለማገዝ በወጣው እቅድ መሰረት ብዙዎቹ የጦር እስረኞችን መልሶ የማቋቋም ስራ በመስራት ላይ ይገኛል።

ከ ዚ ህ በተጨማሪም የእስራኤል ጦር የተሰጣቸውን ኃላፊነት ሳይወጡ እና የአገልግሎት ዘመናቸው ሳያጠናቅቁ የሚሰናበቱ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ወታደሮችን ቁጥር ለመቀነስ እቅድ ይዟል። በተለያዩ ምክንያቶች የውትድርና አገልግሎት ጊዜያቸውን ሳያጠናቅቁ የሚሰናበቱ ትውልደ ኢትዮጵያዊን ወታደሮች ቁጥር ከጊዜ ወደጊዜ እየጨመረ የመጣ ሲሆን፣ በ2012 ብቻ አንድ አራተኛዎቹ የአገልግሎት ጊዜያቸውን ሳያጠናቅቁ ተሰናብተዋል።

በአሸናፊ ደምሴ

ከ300 በላይ አ ረ ጋ ው ያ ን ን ና የ አ እ ም ሮ ህ ሙ ማ ን ን

በመንከባከብ ላይ የሚገኘው መቄዶኒያ የአረጋውያንና የአእምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል ተጨማሪ ወገኖችን ለመርዳት በመንቀሳቀስ ላይ እንደሚገኝ ተገለፀ። ትናንት በማዕከሉ ቅጥር ግቢ የተገነቡትን አዳዲስ ቤቶችንና

በኪራይ የተገኙትን ህንፃዎች ለሚዲያ ባለሙያዎች ባስጎበኘበት ወቅት የማዕከሉ ሰራተኞች እንዳስታወቁት፤ በአሁኑ ወቅት ዕርዳታ እየተደረገላቸው የሚገኙት ወገኖች ቁጥር ከ300 በላይ የደረሱ ሲሆን ይህንን ቁጥርም በእጥፍ ለማሳደግ እየሰራን ነው ብለዋል።

ከ ተ ለ ያ ዩ በጎፈቃደኛ ወገኖች ድጋፍ እያገኙና እየተበረታቱ እንደሚገኙ ያስታወቁት

የማዕከሉ ሰራተኞች በቀጣይም የማዕከሉን አቅም በማሳደግ እስከ 600 የሚደርሱ ደጋፊና ተንከባካቢ ያጡ ወገኖችን ለመርዳት ማሰባቸውን ጠቁመዋል። ለዚህም እንዲረዳ ሲባል በመጪው ታህሳስ 13 ቀን 2006 ዓ.ም በግሎባል ሆቴል የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ሊካሄድ መታቀዱን አስታውቀዋል።

በገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራሙ ላይ እስካሁን

የተሰሩ የማዕከሉን ስራዎች በማስተዋወቅና የተረጂ ወገኖቹን የእጅ ስራዎች እና ስዕሎች በጨረታ በመሸጥ፣ ዶክመንተሪዎችን በማሳየትና የግጥም ፕሮግራም በማዘጋጀት እንደሚከበር ለማወቅ ተችሏል። ታህሳስ 13 በግሎባል ሆቴል በሚካሄደው በዚህ ፕሮግራም ላይም በርካታ እንግዶች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በመቄዶኒያ መርጃ ማዕከል ድጋፍ የሚደረግላቸው

ወገኖች ቁጥር 300 ደረሰ• የመርዳት አቅሙን በእጥፍ ለማሳደግ ታህሳስ 13 የገቢ ማሰባሰቢያ ያካሂዳል

ኢትዮጵያዊያን ወታደር እስረኞችን በ15 በመቶ እቀንሳለሁ አለ

www.sendeknewspaper.comwww.sendeknewspaper.comwww.sendeknewspaper.comwww.sendeknewspaper.com www.sendeknewspaper.comwww.sendeknewspaper.com www.sendeknewspaper.comwww.sendeknewspaper.com

www.sendeknewspaper.comwww.sendeknewspaper.comwww.sendeknewspaper.comwww.sendeknewspaper.com www.sendeknewspaper.comwww.sendeknewspaper.com www.sendeknewspaper.comwww.sendeknewspaper.com

www.sendeknewspaper.comwww.sendeknewspaper.comwww.sendeknewspaper.comwww.sendeknewspaper.com www.sendeknewspaper.comwww.sendeknewspaper.com www.sendeknewspaper.comwww.sendeknewspaper.com

www.sendeknewspaper.comwww.sendeknewspaper.comwww.sendeknewspaper.comwww.sendeknewspaper.com www.sendeknewspaper.comwww.sendeknewspaper.com www.sendeknewspaper.comwww.sendeknewspaper.comww

w.se

ndek

news

pape

r.com

የእስራኤል ጦር

በተለያዩ ምክንያቶች የውትድርና አገልግሎት ጊዜያቸውን

ሳያጠናቅቁ የሚሰናበቱ ትውልደ ኢትዮጵያዊን ወታደሮች ቁጥር

ከጊዜ ወደጊዜ እየጨመረ የመጣ ሲሆን፣ በ2012 ብቻ አንድ

አራተኛዎቹ የአገልግሎት ጊዜያቸውን ሳያጠናቅቁ ተሰናብተዋል

Page 15: በአባይ ግድብ ውስጥ 3 ንደ - ethioforum.orgethioforum.org/wp-content/uploads/2013/12/Sendekdec102013.pdfሰንደቅ 9ኛ ዓመት ቁጥር 431 ታህሳስ 02 2006

ሰንደቅ 9ኛ ዓመት ቁጥር 431 ረቡዕ ታህሳስ 02 2006

ኪነጥበብ-ዜና በአሸናፊ ደምሴ

15

በአሸናፊ ደምሴ ......... [email protected]

“የድሮ አፈር ከዘንድሮ ብሎኬት...”

ይሄ ቀን ቶሎ ባለፈ ያስባላቸው መሆናቸውን ስትረዱ አለ አይደል፤ “ወይ ከድሮ ጋር ፍቅር!” ብላችሁ ትገረሙባቸዋላችሁ።

እናላችሁ ነገር አለሙን ሁሉ እየረገሙ ድሮን በምስጋና ስም የሚደጋግሙ ሰዎች ከገጠሟችሁ ጀርባቸውን ለማጥናት ሞክሩ ባይገርማችሁ የሚያንገሸግሽ ታሪክ ያላቸው ሆነው ልታገኟቸው ትችላላችሁ። ሚስትም ድሮ ቀረ፣ ባልም ድሮ ቀረ፣ ኑሮም ድሮ ቀረ፣ ስራም ድሮ ቀረ፣ ልጅም ድሮ ቀረ፣ ንግድም ድሮ ቀረ፣ ይባስ ብሎ ቴክኖሎጂም ድሮ ቀረ የሚል ሰው ሲገጥማችሁ ምንትላላችሁ?

መቼም አንዳንዱ ሰው ከትናንት ባሳደረው መልካም ስምና ትናንት ባሳለፈው መልካም ዘመን ለመነገድ ሲል የማይፈነቅለው ድንጋይ የለም። ይህቺን ለማለት ያነሳሳኝ ሰሞኑን ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ያስነገራት አሽሟጣጭ ማስታወቂያ ኮርኩራኝ ነው። ጎበዝ!. . . ማስታወቂያዋን አልሰማችሁ ከሆነ ቃል -በቃልም ባይሆን የሚከተለውን ትመስላለች።

ሰውዬው በባቡር ግንባታው ምክንያት ቤቱ ከፈረሰባቸው ሰዎች አንዱ ነው። እናም ከወዳጁ ጋር እየተነጋገረ ነው። “አሁን የሚመጣው ሰው ገምቶ ካሳ የሚያስከፍለው ድርጅት ባልደረባ ነው። እርሱ

በገመተው ልክ ነው የካሳ ክፍያው የሚፈፀመውና እርሱን ልንከባከበው ይገባናል” ይላል ጓደኛ። ቤቱ የፈረሰበትም፣ “እንዴት ነው ግን የግምቱ አካሄድ?” ብሎ ይጠይቃል። “ቀላል ነው፤ ሰውዬው ያንተ ቤት የአፈር ቤት ቢሆንም የብሎኬት ነው፤ ቪላ ቤት ነው ካለ ስለሚሰማ ዳጎስ ያለ ካሳ ታገኛለህ፤ አንተም ለሱ የሚገባውን ትሰጣለህ ማለት ነው።” “እከክልኝ ልከክልህ መሆኑ ነው!” (ሳይል አይቀርም ሰውዬው በሆዱ)

እናም ካሳ ገማቹ ሰውዬ ሲመጣ ሰዎች ተሽቆጥቁጠው ይቀበሉታል። “ያው እንደምናየው ቤትህ የአፈር ነው። እኛ ግን የብሎኬት ነበር ብለን ሪፖርት እናደርጋለን” ይለዋል። በዚህ ጊዜ ባለቤቱ ምን ቢል ጥሩ ነው? . . . “እሺ ጌታዬ! መቼም የድሮ አፈር ከዘንድሮ ብሎኬት አያንስም፤ ያው ነው፤ የድሮ አፈር እኮ ብሎኬት ማለት ነው” ብሎላችሁ እርፍ።

አያችሁልኝ አይደል ከአፈር አቅም እንኳን ከዘንድሮ ብሎኬት ጋር እንዲቀራረብ ሲደረግ? ድሮ እኮ ችግር ያልነበረ፤ ሁሉ ነገር አልጋ-በአልጋ የሆነበት ዘመን ሲመስል ድንቅ ነው የሚለን። እኔ የምለው እኛም አርጅተን ዘመን ካለፈ በኋላ ለልጆቻችንን ዘመን እየረገምን የነበርንበትን ዘመን

ለታላቁ መሪ ኔልሰን ማንዴላ “ነፍስ ይማር!” ስንል እጅ ከነሳን በኋላ ወደዛሬው ወጋችን ብናልፍ ምን ይለናል?. . .

መቼም ዘንድሮ ብዙ ነገር ድሮ ቀርቷል። እውነት ነው አባቶቻችን

ድሮ በሚሉት ዘመን ውስጥም ቢሆን፤ እነርሱም ድሮ የነበረን ነገር ትተው ድሮ ቀርቶባቸው እንደነበር ባናውቅ እንኳን መጠርጠር አይገደንም። እኔን ግርም የሚለኝ ግን ድሮና ዘንድሮ በንፅፅር ሚዛን ላይ የሚጣዱት የድሮን በጎ ነገር ለማግዘፍ፤ የዘንድሮን ክፉ ነገር ደግሞ ለማጉላት መሆኑ ላይ ብቻ ነው። በተለይ የድሮዎቹ ሰዎቻችን “እንቁልልጬ” ይሉን ይመስል ያላየነውንና የማናውቀውን ድሮን ሲያነሳሱ አንዲትም እንኳን ክፉ ነገር ጠብ ያላለበት ፀሀዳ ነጠላ ያስመስሉታል።

ይህውና ሰሞኑን አንድ ወዳጄን አገኘሁት። ይህ ወዳጄ ቤቱ የትዳር ቤተ-ሙከራ ይመስል ፍቅር በሚመስል ነገር ታቅፎና ገብቶ፤ ሰንብቶ ተጣልቶ የማይወጣ ሴት የለም። ለምን አታገባም ለሚሉት እናቱና ወዳጆቹ ሁሉ የሚሰጠው መልስ፣ “ዘንድሮ እኮ ሴት እንጂ ሚስት የለም፣ እኔ ደግሞ እንደናቴ የምትሆንልኝ ሴት ካላገኘሁ በስተቀር ኮሜዲያን ደረጄ ሃይሌ እንዳለው “በተገረዝኩበት አልጋ ላይ እገነዛታለሁ” እንጂ አላገባም የሚል” ሆኗል። (አያችሁልኝ ይሄን ሰው፤ ይህቺም ዕድሜ ሆና በእናቱ ላይ ተንጠልጥሎ እናቱን የምትተካለት ሚስት ሲጠብቅ ሁለት ፀጉር ማየቱ ምን ይባላል?). . . መቼም ድሮን የማይናፍቅ ሰው ማግኘት ብርቅና ድንቅ ሆኗል።

ታዲያ ይሄ የኛ ወዳጅ “ሚስት ድሮ ቀረ!” ብሎ ምስክርነት መስጠት ከጀመረ ማን ቀረ ሊባል ነው?. . . በተለይ በተለይ ዕድሜያቸው 50ን የተሻገረላቸው (ያሻገራቸው ልንል እንችላለን) ሰዎችማ ድሮን አሞግሰው ዘንድሮን አኮስሰው ጥንብ እርኩሱን ሲያወጡት ስታዩ እነዚህ ሰዎች ድሮ ምን ነበሩ? እንድትሉ ያገፋፋችኋል። እናላችሁ መለስ ብላችሁ ስታዩዋቸው ድሮ የቸገራቸውን፣ ድሮ የባላባት ልጅ ነበሩ እንዴ? . . ፣ ድሮ ተስፋ የሌላቸው፣ ድሮ ምናለ

ደግሞ እያሞጋገስን እንቀጥል ይሆን? ሁሉን ነገር ድሮ ቀረ እያሉ በድሮ አፈር ችርቻሮ ውስጥ መግባቱ በጣም ነው የሚያስተዛዝበን። (ይሄኔ ነው በድሮ በሬ ያረሰ የለም ብሎ በተረት ጠቅ ማድረግ አይደል?)

አንድ ነገር ግን ግልጥ ነው ዛሬ ከትናንት የሚሻልባቸው በርካታ አጋጣሚዎች የመኖራቸውን ያህል ድሮም ከዘንድሮ የሚሻልባቸው የራሱ መልካም ጎኖች እንደነበሩት ሳንክድ አብሮ መጓዝ እንጂ አንዱን ጥሎ ሌላውን አንጠልጥሎ መንጎድ ግንጥል ጌጥ ከማሰኘት በቀር ፋይዳ የለውም።

አገራችን ኢትዮጵያውያንን በሙሉ አሳፍራ የምንቀዝፋት ብቸኛ መርከባችን ናት። በውስጧ ያለነው ህዝቦቿም የጋራ ባህል፣ ቋንቋና ትውፊት ያለንን ያህል በተናጠልም እንዳለን አውቆና ተባብሮ መኖር እንጂ በተናጠል ቆርጦ መቀጠሉ ምን ፋይዳ አለው? ድሮ-ድሮ እያሉ ዘንድሮን ማጣጣሉም የራስን ዋጋ ማውረድ ነው።

እዚህች ጋር ከመሰነባበታችን በፊት አንዲት ወግ እንካችሁ፤ በአንድ ሀገር ውስጥ እድሜው የገፋና የታወቀ ከበርቴ ነበር። ይህ ከበርቴ ታዲያ በርካታ መርከቦች ነበሩት። በመርከቦቹም ወደ ተለያዩ አገራት በመጓጓዝ የንግድ ስራውን ይሰራ ነበር።

ከእለታት በአንዱ ቀን በጣም የታወቁ ከበርቴዎች ብዙ እቃዎችን ጌጣጌጦችንና የከበሩ ድንጋዮችን ጭምር በመርከቧ አስጭነውት ጉዞ ሊጀምር ሆነ። በዚህ ጊዜ የመርከቡ ባለቤት ወደ መርከቡ ካፒቴን ጠጋ ብሎ፤ “ስማ በዚህ መርከብ ውስጥ እጅግ ውድ የሆኑ የጥንት ቅርሶች ሁሉ ተጭነዋል። ያስጫኑት ከበርቴዎችም እንግዶቻችን ሆነው ተሳፍረዋል፤ መርከቧን ተጠንቅቀህ ዘውር” ይለዋል። ይሄን ጊዜ ካፒቴኑ ምን ቢመልስ ጥሩ ነው? “ጌታዬ በመርከቧ ውስጥ እኔስ አለሁ አይደል? ማንስ ቢሆን ከራሱ የበለጠ ለማን ያስባል ብለው ነው” አለ ይባላል። ጎበዝ! ስለድሮዎቹ መልካም ነገሮች ብቻ ስንተርክ የዘንድሮዎቹንም የምናይበት ልቦና ይስጠን። አንድዬ የድሮን አፈር እየጠራን ከመቸርቸር ይሰውረን፤ ቸር እንሰንብት።

“እኔ ሀብታም” የተሰኘ የአጫጭር ልቦለዶች ስብስብ ለንባብ በቃ

በደራሲ አንተነህ እሸቱ የተፃፈው “እኔ ሀብታም” የተሰኘ አስራ ስድስት አጫጭር ልቦለዶችን ያካተተ መፅሐፍ ባሳለፍነው ሳምንት ለንባብ በቃ።

“እኔ ሀብታም” መፅሐፍ 168 ገጾች ያሉት ሲሆን፤ ዋጋው 35 ብር መሆኑም ታውቋል። ደራሲው አንተነህ እሸቱ ከዚህ ቀደም በፃፈው “ከግድግዳው ጀርባ” በተሰኘ የአጫጭር ልቦለድ ስብስቦች የሚታወቅ ፀሐፊ ነው።

በባህላዊ ውዝዋዜዋ እና ዘፈኖቿ የምትታወቀው ስንታየሁ ዘነብ (ሚሚ)

በካናዳ ጥገኝነት ጠየቀች ከ10 ዓመታት በላይ በባህል ምሽቶችና ጭፈራ ቤቶች በባህላዊ

ውዝዋዜ እና ዘፈኖቿ ዕውቅናን ያተረፈችው ስንታየሁ ዘነበ (ሚሚ) በካናዳ፤ ቶሮንቶ ለትርኢት በሄደችበት የጥገኝነት ጥያቄ ማቅረቧ ተሰማ።

የአርቲስቷ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ለዝግጅት ክፍላችን እንደጠቆሙት የባህል ሙዚቃ ተጫዋቿ እና ተወዛዋዥዋ ስንታየሁ ዘነበ በተለያዩ የአውሮፓና የአረብ አገራት ተዘዋውራ ዝግጅቶቿን ያቀረበች ሲሆን፤ በካናዳ ከባህል ቡድኑ ጋር ለትርኢት የሄደች ቢሆንም፤ መመለስ ባለመፈለጓ ጥገኝነት መጠየቋ ታውቋል።

የባለትዳርና የአንዲት ሴት ልጅ እናት የሆነችው ስንታየሁ ዘነበ (ሚሚ) በምን ምክንያት ጥገኝነት መጠየቅ እንዳስፈለጋት ለመናገር ያልፈለገች ሲሆን፤ በአሁኑ ወቅት በካናዳ ቶሮንቶ ላቀረበችው የጥገኝነት ጥያቄ መልስ እየጠበቀች ነው ሲሉ ምንጮች ተናግረዋል።

“የአርበኛው ልጅ” ፊልም ተመረቀ

በደራሲና ዳይሬክተር አንተነህ ኃይሌ ተሰርቶ ትሩዝ ፊልም ፕሮዳክሽን ያቀረበው “የአርበኛው ልጅ” የተሰኘ የፍቅር ኮሜዲ ፊልም ባሳለፍነው እሁድ ህዳር 29 ቀን 2006 ዓ.ም በአዲስ አበባ ባሉ የግል ሲኒማ ቤቶች ተመርቆ በመታየት ላይ ይገኛል።

“የአርበኛው ልጅ” ፊልም ላይ ካሳሁን ፍሰሃ (ማንዴላ)፣ የትምወርቅ ኑቨርዣ፣ ሰለሞን ተካ፣ ጌታቸው ታደሰ፣ ታደሰ ሽፈራውና ሌሎችም አንጋፋና ወጣት ተዋንያን ተሳትፈውበታል።

ትሩዝ ፊልም ፕሮዳክሽን “የአርበኛው ልጅ” ፊልምን ጨምሮ የባል ጋብቻ፣ አዲስ እንግዳ፣ ፍቅር በራዲዮ፣ ኢቫንጋዲ እና አየሁሽ የተሰኘ ስራዎችን ለተመልካች ማድረሱ ይታወሳል።

እናላችሁ ነገር አለሙን ሁሉ እየረገሙ ድሮን በምስጋና ስም የሚደጋግሙ ሰዎች

ከገጠሟችሁ ጀርባቸውን ለማጥናት ሞክሩ ባይገርማችሁ የሚያንገሸግሽ ታሪክ

ያላቸው ሆነው ልታገኟቸው ትችላላችሁ። ሚስትም ድሮ ቀረ፣ ባልም ድሮ ቀረ፣

ኑሮም ድሮ ቀረ፣ ስራም ድሮ ቀረ፣ ልጅም ድሮ ቀረ፣ ንግድም ድሮ ቀረ፣ ይባስ

ብሎ ቴክኖሎጂም ድሮ ቀረ የሚል ሰው ሲገጥማችሁ ምንትላላችሁ?

Page 16: በአባይ ግድብ ውስጥ 3 ንደ - ethioforum.orgethioforum.org/wp-content/uploads/2013/12/Sendekdec102013.pdfሰንደቅ 9ኛ ዓመት ቁጥር 431 ታህሳስ 02 2006

ሰንደቅ 9ኛ ዓመት ቁጥር 431 ረቡዕ ታህሳስ 02 200616 5

ኪነ-ጥበብ እና ባህል

በጥበቡ በለጠ

ተስፋዬ ለማ በኢትዮጵያ ሙዚቃ ላይ ለአርባ ዓመታት ጥናትና ምርምር ሲያደርግ ቆይቷል። ይህ ልፋቱ ታዲያ በቅርቡ በመፅሀፍ ታትሞ “የኢትዮጵያ ሙዚቃ ታሪክ ከ1898 እስከ 1983 ዓ.ም” በሚል ርዕስ ተዘጋጅቶ በአሜሪካን ሀገር ተሰራጭቷል። መፅሐፉ 340 ገፆች ያሉት ሲሆን በርካታ ርዕሰ ጉዳዮችን አካቷል። በመፅሐፉ ውስጥ ከተዘረዘሩት ጉዳዮች ውስጥ የተወሰኑትን ለዛሬ በአጭሩ ቀነጫጭቤ አቀርብላችኋለሁ።

የኢትዮጵያ ሙዚቃ በዩኒቨርስቲ ደረጃ እስኪቋቋም ድረስ በባሕል ሙዚቃ ጥሩ እውቀት ያላቸውን ሙዚቀኞች በማሰባሰብ በ1960 ዓ.ም በቀዳማዊ ኃይለስላሴ ዩኒቨርስቲ ቤተ-ኪነ-ጥበባት ወቴአትር ሥር ተቋቋመ። ኦርኬስትራ ኢትዮጵያ ሲወጠን ዋና ዓላማው ወደፊት በጥናት ላይ ለሚመሰረተው የኢትዮጵያ ሙዚቃ ማደራጃ እንዲሆን ነበር። የዚህ የሙዚቃ ቡድን መሥራችም በትውልድ ግብፃዊ በዜግነት አሜሪካዊ የሆኑት ከፍተኛ የሙዚቃ ባለሙያ ፕሮፌሰር ሐሊም ኤልድሃብ ነበሩ።

ለአንድ ሀገር ዩኒቨርስቲ ከሚያስፈልጉና ከፍተኛ ግምት ከሚሰጣቸው መሠረታዊ የጥናት መስኮች አንዱ ባህል ነው። በመሆኑም ኪነ-ጥበባት ወቴአትርን ለማቋቋም ከአሜሪካ ሀገር የመጡት ሶስት የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች ፕሮፌሰር ፊሊፕ ካፕላን፣ ማርሻል ጆን ኮክስና ፕሮፌሰር ሐሊም ኤልድሃብ በካርኔኒ ድርጅት ረዳትነት ይህንኑ ማዕከል በከፍተኛ ደረጃ ለማቋቋም ተዘጋጅተው ነበር። ሆኖም በዘመኑ የነበሩት የዩኒቨርስቲው ባለሥልጣናት ዐቢይ ትኩረታቸው ለሳይንስና ቴክኖሎጂ እንጂ ለዘፈንና ለቴአትር አለመሆኑን በማስታወቃቸው በትልቁ ታስቦ የነበረው የዩኒቨርስቲው የባህል ተቋም ሊጨናገፍ ችሏል። በዚሁ ጉዳይ የመጡት ባለሙያዎችም ተስፋ ቆርጠው ወደ ሀገራቸው ተመለሱ።

የኦርኬስትራ ኢትዮጵያ የባህል ቡድን ሲመሰረት የተሰባሰቡት ሙዚቀኞች ቁጥር አርባ ያህል ነበር። ሆኖም ዩኒቨርስቲው በዚህ እንዲቀጥል ባለመፈለጉና በጀት ባለመመደቡ አስራ አምስት የሚሆኑትን ብቻ በማስቀረት ሌሎቹን አሰናበተ። በዚሁ ወቅት ነው በአስራ ስምንት አመቱ ተስፋዬ ለማ ወደ ዩኒቨርስቲው ቤተ-ኪነ ጥበባት ወቴአትር በመሄድ ከኦርኬስትራ ኢትዮጵያ ጋር የተቀላቀለው።

ኦርኬስትራ ኢትዮጵያን በየጊዜው ከነበሩት የቀዳማዊ ኃይለሥላሴና የሀገር ፍቅር ቴአትር ቤቶች ለየት የሚያደርገው ቡድኑ ያቀፋቸው የሙዚቃ መሣሪያዎች በሌሎቹ የሙዚቃ ቡድኖች የሌሉ መሆናቸው ነው። በተለይ ተተኪ ሳይኖራቸው ያለፉት የመጨረሻዎቹ የእምቢልታ ተጫዋቾች የኦርኬስትራ ኢትዮጵያ አባላት እንደነበሩ ይታወቃል።

ኦርኬስትራ ኢትዮጵያ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ1969 ወደ አሜሪካ ተጉዞም ለሁለት ወራት ያህል የተለያዩ ክፍለ ግዛቶች በመዘዋወር ትርኢቱን አሳይተዋል። በዚህም ወቅት ታዋቂው የኒውዮርክ ታይምስ ጋዜጣ ዝግጅቱን አድንቆ ፅፏል። ከዚህም በካናዳና በአውሮፓ ከፍተኛ ተመልካች በነበረው “The Ed Sullivan Show” የተባለ የቴሌቭዥን ፕሮግራም ለመቅረብ ችሎ ነበር። በአጠቃላይ ቡድኑ በዘመኑ ከነበሩት ተመሳሳይ የሙዚቃ ቡድኖች አንጋፋውን ሚና ሊጫወት ችሏል።

የኦርኬስትራ ኢትዮጵያ አባላት ከዩኒቨርስቲው ከወጡ በኋላ ሺ ሰማንያ በሚባለው አካባቢ ቤት ተከራይተው ሲለማመዱ ነበር። ሆኖም ቋሚ የገቢ ምንጭ ስላልነበራቸው መቸገራቸው አልቀረም። ስለዚህ አንድ ቀን የወቅቱን የዩኒቨርስቲውን ፕሬዚዳንት ዶ/ር አክሊሉ ሀብቴን ጋብዘዋቸው የተከራዩትን የመለማመጃ ቦታ አሳይዋቸው። እሳቸውም ሁኔታውን ተመልክተው “ዩኒቨርሲቲው በገንዘብ ሊረዳቸው ባይችልም እንኳ የኪነ-ጥበብ ወቴአትርን አዳራሽን ለልምምድና ለቢሮ አገልግሎት ልትጠቀሙበት ትችላላችሁ” በማለት ስለፈቀዱ ኦርኬስትራ ኢትዮጵያ ወደዚያው ሊዛወር ቻለ።

ሆኖም ጊዜው የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የተቃውሞ ሰልፍና ረብሻ የሚያደርጉበት ነበር። በዚህም የተነሳ ፖሊሶች ወደግቢው እየገቡ ተማሪዎቹን በመመደብና አልፎ አልፎም በማሰር ያንገላቷቸው ነበር። በዚያ ላይ የተማሪዎች ጥያቄ የጠነከረበት፣ የመንግስት ልዩ ትኩረት የሰጠበትና ፖሊሶችም ጥብቅ ክትትል የሚያደርጉበት በመሆኑ የዩኒቨርስቲው አካባቢ የሚያስፈራ ነበር።

በዚያን ጊዜ ኦርኤስትራ ኢትዮጵያ ለተማሪዎችና ለዩኒቨርስቲው ማህበረሰብ በየሁለት

ወሩ የሙዚቃ ትርኢት ያቀርብ ነበር። በወቅቱም ግዛቴ ተሾመ የሚባልና ከጎንደር የመጣ ወጣት በኦርኬስትራው ተቀጥሮ ይሰራ ነበር። እድሜው 15 ዓመት ሲሆን፣ ጥሩ ተሰጥኦም ነበረው። አንድ ቀን እንደተለመደው ፖሊሶች ወደ ዩኒቨርስቲው ገብተው ተማሪዎቹን ሲያሳድዱ ይህ ወጣት ከተማሪዎቹ አንዱ መስሏቸው በዱላ ደበደቡት። ይህ በሆነ በሁለተኛው ቀን ኦርኬስትራ ኢትዮጵያ ትርኢቱን ለተማሪዎችና ለዩኒቨርስቲ ማህበረሰብ ያቀርብ ነበር፡ ታዲያ ያኔ ግዛቴ በዘፈኑ መሃል እንዲህ የሚል ግጥም ጨመረበት።

“ትተኩሱ እንደሆን፣ ወንድ ይከተላችሁ

ባልረባ ግርግር፣ ሰው ታስፈጃላችሁ።”

ይህን የሰሙትና የልጁን የአዘፋፈን ስልት የወደዱት ተማሪዎች አድናቆታቸውን ባልተቋረጠ ጭብጨባ ከመግለፃቸው በላይ “ይደገም፣ ይደገም” እያሉ በመጮሃቸው ዘፈኑ ሶስት ጊዜ ተደገመ። የደርግ መንግስት ሲመጣ በግል የሚንቀሳቀሱ የባህል ተቋማት ስለ ተወረሱ ኦርኬስትራ ኢትዮጵያ ወደማዘጋጃ ቤቱ የባህልና ቴአትር አዳራሽ ተዛወረ።

የኦርኬስትራ ኢትዮጵያ ባለሙያዎች በሚል በሰፊው የሚታወቁትም የሚከተሉት ናቸው። ተስፋዬ ለማ፣ ዮሐንስ አፈወርቅ፣ ዘሪሁን ቀለ፣ ፀሐይ እንዳለ፣ አረሩ ሸገን፣ ንጉሡ ረታ፣ ከበደ ወ/ማርያም፣

አልማዝ ጌታቸው፣ በቀለች ፀጋዬ፣ ፋንታነሽ ደበላ፣ ምስራቅ ከበደ ናቸው።

ኦርኬስትራ ኢትዮጵያ ዛሬ የለም። ለዚህ ኦርኬስትራ ዝነኛነት ብዙ የዋተተው ተስፋዬ ለማ ጥር 24 ቀን 2005 ዓ.ም በአሜሪካ ሀገር ዋሽንግተን ዲሲ ሕይወቱ አልፋለች። ይሄው የኢትዮጵያ ሙዚቃ ተመራማሪ የሆነው ተስፋዬ ለማ ያዘጋጀው መፅሀፉ በአሜሪካን ሀገር ታትሞ ተሰራጭቷል። ርዕሱ “የኢትዮጵያ የሙዚቃ ታሪክ ከ1889 እስከ 1983 ዓ.ም” የሚል ነው። በውስጡ አያሌ ነገሮችን ይዟል። ስለዚህ መፅሃፍ ይዘትም ወደፊት አጫውታችኋለሁ።

ኦርኬስትራ ኢትዮጵያ

በታሪክ ውስጥ

የግል ሙዚቀኞች ማቆጥቆጥ የጀመሩት በ1962 ዓ.ም ገደማ እንደነበር የኢትዮጵያ የሙዚቃ ታሪክ የፃፈው ተስፋዬ ለማ ይገልጻል። በወቅቱ የኦርኬስትራ

ኢትዮጵያ ቡድን በዋቢ ሸበሌ ሆቴል በየሳምንቱ ሐሙስ ምሽት በተለይ ለቱሪስቶች የባህል ሙዚቃ ፕሮግራም ያቀርብ ነበር።

በሆቴሉ መቅረብ የሚገባው ዘመናዊ የሙዚቃ ዝግጅት ምን መምሰል እንዳለበት የሆቴሉ ባለንብረቶች የልዑል መኮንን ቤተሰቦችና የሆቴሉ ሥራ አስኪያጆች ወስነው ነበር። በዚህ መሰረት በአዲስ አበባ ከሚገኙ ሙዚቀኞች ዋቢ ሸበሌ ሊያቀርብ ላሰበው የዳንስ ምሽት ፕሮግራም የሚመጥኑ ሙዚቀኞች እንደሌሉ በመግለፅ አቶ ሙላቱ አስታጥቄ ወደ ኬኒያ ሔዶ ሙዚቀኞችን እንዲያመጣ ታዘዘ ይላል ተስፋዬ ለማ በአዲሱ መፅሃፉ። እናም ‘አሸንቴ የተባለውን የሙዚቃ ቡድን ሊያስመጣ ቻለ’ በማለትም ይተርካል።

ሆኖም በዚያን ዘመን በተደራጀ መልክ የሚገኙ ሙዚቀኞች ባይኖሩም ከአዲስ አበባ እና ከአስመራ የመጡ ወጣት ሙዚቀኞች ክበብ አቋቋሙ። የክበቡም አባላት አሸንቴዎችን መተካት የሚችሉና ለሆቴሉም ደረጃ ብቁ መሆናቸውን በማሳየት ወደ ዋቢ ሸበሌ ሆቴል ለመግባት ቸለዋል። በዚያን ዘመን ለመጀመሪያ ጊዜ የተደራጀ የሙዚቃ ቡድን ቢኖር ሶል ኢኮስ ግንባር ቀደሙ ነው። በመቀጠል ይህን የተመለከቱ ሌሎች ሙዚቀኞች በመሰባሰብና በተለያየ ስም በመደራጀት ሰርተዋል።

የግል ሙዚቀኞች መመስረትና መፍረስ ራሱን የቻለ ሂደት አለው። ስራው የንግድ ፀባይ ያለው በመሆኑ ከግል መረዳጃነት ይልቅ በሥራው በልጦ መገኘትን የሚጠይቅ ነው። የተሻሉ ሙዚቀኞች የተሻለ ዝናና ክፍያ ወደሚያገኙበት ክፍል በመሄድ ስለሚለያዩ አንዳንዶቹ የመፍረስ እድል ሲገጥማቸው ሌሎች ደግሞ በአዲስ መልክ ይፈጠሩ ነበር። ከፊሎቹ ደግሞ ተጠናክረው ሊዘልቁ ችለዋል።

በዚያን ወቅት ጎልተው ከወጡት መካከል አይቤክስ በራስ ሆቴል፣ ዳህላክ በግዬን፣ ዋሊያስ ደግሞ በዋቢ ሸበሌና ኃላም በሂልተን

የተጫወቱ ሲሆን ቀስ በቀስ የውጪ ሙዚቀኞችን በመተካት ሥራውን ሊቆጣጠሩት በቅተዋል። ስለ ምሽት ክበባት ወይም የግል የሙዚቃ አደረጃጀት ይህን መንደርደሪያ ካስቀደምን አሁን ደግሞ ስለነዚሁ የሙዚቃ ክፍሎች የተገለፀውን እንመልከት።

ከአድዋ ድል በኋላ የጅቡቲን የባቡር መስመር መከፈትና የንግድ መስፋፋትን ተከትሎ በርካታ አዝማሪዎች ወደ አዲስ አበባ መሰባሰብ ስለመጀመራቸው የታወቀ ነው። አርመኖች፣ ግሪኮችና አረቦች መጠጥ ቤቶችንና ሱቆችን፤ ሌላው ወገን ደግሞ ጠጅ ቤቶችና ጠላ ቤቶችን ከፈተ። በ1890 ዓ.ም ገደማም በአዲስ አአባ የእንግዶች መቀበያ ሆቴል ስላልነበር የመጀመሪያው ሆቴል በእቴጌ ጣይቱ ስም ተከፈተ። ይህ ታሪካዊ ሆቴል በቀድሞው አጠራር አራዳ /ዛሬ ፒያሳ/ የሚገኝና በዘመነ ደርግ “አውራሪስ ሆቴል” የሚል ስያሜ ተሰጥቶት የነበረው ነው። ቀደም ሲል የስዊስ ሙዚቀኞች በዚህ ሆቴል ውስጥ ይጫወቱ ነበር። ከዚህ በኋላ ደግሞ የክቡር ዘበኛ አንደኛ ኦርኬስትራ አባላት ዓለም አቀፍ ይዘት ያላቸውን የውጭ ሙዚቀኞች ያቀርቡበት ነበር።

ከታሀሳሱ የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ በኋላ ግን የተወሰኑት የኦርኬስትራው አባላት፡-1.ባሕሩ ተድላ (ከበሮ)

2.ተፈራ መኮንን (ፒያኖ)

3.ጥላሁን ይመር (ደብል ቤዝ)

ከቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ቴአትር ሙዚቀኞች፡-

1.ወዳጄነህ ፍልፍሉ (ቴነር ሳክስፎን ክላርአት)

2.አሰፋ ባይሳ (ትራምፔት)

ጋር ሆነው ሥራቸውን ቀጠሉ። ድምጻዊያን ግርማ በየነ እና ባህታ ገ/ሕይወትን በመጨመርም የራስ ባንድን አቋቁመው መሰራት ጀመሩ።

በሌላ በኩል በመርካቶው የአቶ ካሳ ገብሩ “ሾፌሮች ቡና ቤት” የምሽት ክበብ ተጀመረ፡ አቶ ካሳ ክበባቸውን በማስፋፋትም ኃብተጊዮርጊስ ድልድይ በሚገኘው አዲስ አበባ ሆቴል ውስጥ

የደመቀ የምሽት ክበብ ከፈቱ። በዚህ ሆቴል የክብር ዘበኛዎቹ እሳቱ ተሰማ፣ ተዘራ ኃይለሚካኤል፣ አየለ ማሞ እና ተፈራ ካሳ ይጫወቱ ነበር። ጣሊያኖችና ግሪኮችም ሳንሱሲ፣ ለማስኮትና ኦሎምፒያ የሚባሉ የምሽት ክበቦችን ከፍተው ነበር። ሌላው የመዝናኛ ቦታ ምን ጊዜም የማይረሳው ደጃች ውቤ ሰፈር ነበር። ይህ ቦታ የተለያዩ የመጠጥ ቤቶች የሴት አዝናኞችን ይዘውና በቀይ መብራት አሸብርቀው ከአሜሪካ የገቡ የሸክላ ሙዚቃዎችን የሚጫወቱበትና ሰውም የውጭ ሀገር ዳንስ የሚደንስበት ነበር።

በዚያን ወቅት የቃኘው ሻለቃ ጦር ሰፈር በአስመራ የተቋቋመበት በመሆኑ በጣቢያው የሚዘፈኑ ሙዚቃዎችን ሸክላ የአስመራ ልጆች ወደ አዲስ አበባ ያስገቡ ነበር። በፒያሳና በአራዳ ሻይ ቤቶችን በመክፈትም የአሜሪካ ሙዚቃ እንዲስፋፋ አድርገዋል። በዘመኑ በአዲስ አበባ የሚገኙ ሲኒማ ቤቶች የእነ ኤሊሺስ ፕሪስሊን፣ ናት ኪንግ ከልን፣ ፍራክ ሲናተራና የመሳሰሉትን ፊልሞች የሚያቀርቡበት ስለነበር የአሜሪካ ባህል በተለይ በወጣቱ ዘንድ ትኩረት ያገኘበት ጊዜ ነበር።

አዲስ አበባ የአፍሪቃ አንድነት ድርጅት መናኸሪያ በመሆኗም በከተማዋ በርከት ያሉ የአለም አቀፍ ድርጅቶች፣ ምግብ ቤቶች፣ መጠጥ ቤቶች በተለይም በነፋስ ስልክ አካባቢ የአሜሪካን ከተሞችና ዝነኛ ስሞች የያዙ የምሽት ክበቦች ተከፈቱ። ከእነሱም መካከል ዛንዚባር፣ ካሊፎርኒያን፣ ሆሊውድና ሰንሻይን የሚባሉት ይገኙበት ነበር።

ከነዚህም በተከታታይ ዲ አፍሪካ ባንድ (በሆቴል ዲ አፍሪክ)፣ ሸበሌ (በዋቢ ሸበሌ)፣ ቬኑስ (በቬኑስ ክለብ)፣ ዙላ (በዙላ ክለብ)፣ ዳህላክ፣ አይቤክስ፣ ኢትዮ ስታር፣ ሮሃና ዋሊያስ ሊቋቋሙ ችለዋል። እነዚህ በዘላቂነት ረዘም ላለ ጊዜ ይቆዩ እንጂ በነፋስ ስልክና በአራዳ ለአጫጭር ጊዜ የተቋቋሙ ሌሎች ባንዶችም ነበሩ። አንዳንዶቹ የመፍረስ እድል ሲገጥማቸው ሌሎች ደግሞ በአዲስ መልክ ይቋቋሙ ነበር። በየጊዜው ስለነበረው የምሽት ክበብ ሙዚቀኞች አደረጃጀት በመጠኑም ቢሆን የሚያሳዩ መረጃዎች ወደፊት እንገልጻቸዋለን።

የግል የምሽት ክበባት አመሰራረት

በኢትዮጵያ

በተከታታይ ዲ አፍሪካ

ባንድ (በሆቴል ዲ

አፍሪክ)፣ ሸበሌ (በዋቢ

ሸበሌ)፣ ቬኑስ (በቬኑስ

ክለብ)፣ ዙላ (በዙላ

ክለብ)፣ ዳህላክ፣

አይቤክስ፣ ኢትዮ

ስታር፣ ሮሃና ዋሊያስ

ሊቋቋሙ ችለዋል

Page 17: በአባይ ግድብ ውስጥ 3 ንደ - ethioforum.orgethioforum.org/wp-content/uploads/2013/12/Sendekdec102013.pdfሰንደቅ 9ኛ ዓመት ቁጥር 431 ታህሳስ 02 2006

ሰንደቅ 9ኛ ዓመት ቁጥር 431 ረቡዕ ታህሳስ 02 2006 17ኢንቫይሮመንት

በአይቸው ደስአለኝ

ነባርና ሀገር በቀል የእህል ዘሮች ዓለምን እየናጣት ያለውን የሙቀት መጨመርና የአየር ንብረት ለውጥን ከመቋቋም አንጻር አዋጭ መሆናቸው በሳይንቲስቶች ተረጋግጧል። ጠቀሜታቸው ከዚህ አልፎ በሽታን በመቋቋምና ምርታማነትን በማሳደግ ይታወቃል። ለአጠቃላይ ስነምህዳራዊ

መስተጋብርም የበቃ ሚና ይጫወታሉ። በአሁኑ ወቅት የዘሮች ጠቀሜታ ከተመራማሪዎች ዘንድ አልፎ በገበሬዎች ዘንድ ስለታወቀ ገበሬዎች ራሳቸው በማባዛትና በመዝራት ለዘርነትም እያከማቹ ይገኛሉ። ከዚያ ባለፈም በማህበር ተደራጅተው ከመንግስትና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋር በመተባበር የዘር ባንክ እስከ ማቋቋም መድረሳቸው የሀገራችን የተፈጥሮ ሀብት በመጤ ዘሮች ሳይዋጥ የአፈር፣ የውሃ ሀብት ብክለት ተጠብቆ ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዲተላለፍ ያደርጋል። የተያያዝነውን በምግብ ራስን የሚቻል ጥረት ዕገዛ ያደርጋል።

ከሰሞኑም ከአዲስ አበባ 30 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው የወልመራ ወረዳ ፎከታ ተራራ አካባቢ የሚገኙ የተለጮ አርሶ አደሮች ከወረዳው አስተዳደርና ከመልካ ኢትዮጵያ መንግስታዊ ካልሆነ ድርጅት ጋር በመተባበር አንድ የነባር ዘሮች ማደራጃ ባንክ በርካታ እንግዶችና የአካባቢው ባለስልጣኖች በተገኙበት ተመርቆ ተከፍቷል። የመልካ ኢትዮጵያ ማህበር ሙያተኛ የሆኑት አቶ ሽመልስ ተገኝ እንደሚገልፁት የነባር ሰብል ዝርያዎች ከአየር ንብረት ለውጥ አማካኝነት የሚከሰቱ ችግሮችን ለመቋቋም ያስችላሉ። የባንክ መቋቋምም በገበሬዎች አነስተኛ ማሳ ላይ ዘሮቹን ማስለመድና ማስፋፋት ያስችላል።

እንደሚታወቀው የነባር ሰብል ዝርያዎች ከላይ ከተጠቀሱት ጠቀሜታዎች በተጨማሪ የተለያዩ የምግብና የመጠጥ አይነቶችን ለመስራት ያገለግላሉ። በዕለቱ ፐሮግራም ላይም በአካባቢው ገበሬዎች በተዘጋጀው ኤግዚቢሽን ላይ የሰብሎቹ ውጤት የሆኑትን ዳቦ፣ ጨጨብሳ፣ ቂጣ፣ ዳቦቆሎ፣ ገንፎ፣ ቅንጬ፣ አነባበሮ እንዲሁም ጠጅ፣ ጠላና አረቄ ለዕይታ ቀርበዋል። ከዚህ አንፃር እነኚህ ምግብና መጠጦች ለመጭው ትውልድ እንዲተላለፍ ከተፈለገ ነባር ዘሮቹ ተጠብቀው እንዲቆዩ ማድረግ ያስፈልጋል። ከዚሁ ጋር መታወቅ የሚገባው የምግብና መጠጦቹ አዘገጃጀት ራሱን የቻለ ዕውቀት እንደመሆኑ ሀብት ነው። ይህ ሀብት ከዘመናት ጀምሮ ከትውልድ ወደ ትውልድ መተላለፍ የቻለውም በተግባር በተሞክሮ እያደበረ ነው። በርግጥ ዝግጅቱ እና አሰራሩ ከባህላዊ ዘዴ ያልተቀየረ ቢሆንም ወደፊት ሳይንስና ቴክኖሎጂ እየደበረ ሲሄድ ምርቱ በስፋት ወደገበያ በመቅረብ የገበሬዎችን ህይወት እንደሚቀይርና ገበያቸውንም እንደሚያሳድግ መገመት አያስቸግርም። ምግቡና መጠጡም የባህላዊም ቢሆን ያው የባዮቴክኖሎጂ ውጤት እንደሆነ መገንዘብ ያሻል። በስፋት ጥናትና ምርምር ቢደረግ የእርሻውን ኢኮኖሚ ወደ ዘመናዊነት ለመቀየር ከፍተኛ እገዛ ይኖረዋል። ከነባር ሰብሎች የተዘጋጁ ምግቦች ሌላው ጠቀሜታ በንጥረ ነገር ከመበልፀጋቸው በተጨማሪ በጤና ላይ አንዳችም አይነት ጉዳት አለማስከተላቸው ነው። እንደሚታወቀው በአሁኑ ወቅት ምርታማነትን ለማሳደግ በሚል አዝርዕቶች የዘረመል ለውጥ በላቦራቶሪ በማዘጋጀት የአለም ገበያን እያጥለቀለቁ ይገኛሉ። ትርፍን ብቻ አልመው በሚንቀሳቀሱ ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች የሚመረቱ ዱቄት፣ ዘይት፣ ብስኩትና ዳቦ ወዘተ በተመጋቢው ጤንነት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እየፈጠረ እንደሚገኝ በሀገራችን በተጨባጭ ሁኔታ እየተገነዘብን ነው። የተዳቀሉ ዝርያዎች ከዚህ በተጨማሪ በብዝሃነት ላይ ውድመት በማስከተላቸው ዓለምን እያስጨነቀ ይገኛል። ከዚህ አኳያ በአነስተኛ የገበሬዎች ማሳ ነባር የሰብል ዘሮችን መትከልና ማራባት ስነምህዳር ሳይዛነፍ እንዲቆይ የማድረግ ጠቀሜታቸውን ቸል ማለት አይገባም። ከዚህ አኳያ የሀገራችን ነባር ዘሮች መፃኢ እድልን ከአደጋ ለማዳን በገበሬዎች፣ በተመራማሪዎች፣ በመንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፣ ፖሊስ አውጭ አካላትና ከግብርና ጋር ተያያዥነት ያላቸው ባለድርሻ አካላት ግንኙነታቸውን አጠናክረው ጥረቱን መቀጠል ይኖርባቸዋል።

በዕለቱ በኤግዚቪሽን ቀርበው ስለነበሩ የነባር ሰብሎችና ምግቦችን በተመለከተ ገለፃ ሲያደርግ ያነጋገርኩት የወልመራ ወረዳ አንደኛ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር የሆኑት አቶ ሌሊሳ መልካሳ እንደገለፁልኝ ትምህርት ቤታቸው በመልካ ኢትዮጵያ ስር በሚካሄደው የሰኚ ፕሮግራም አባል በመሆኑ ነባር ዘሮችን በመንከባከብና ለገበሬዎች በማሰራጨት እንዲሁም በአካባቢያቸው የአፈርና የውሃ ጥበቃ ስራ በመስራት ላይ ይገኛል። በቦታው

ላይም እየተንከባከቧቸው የሚገኙ 19 የገብስ ዝርያዎችን 12 ለመድሃኒትነት የሚያገለግሉ የቅጠላ ቅጠል ዝርያዎችን ለመመልከት ችያለሁ። ከእነኚህ በተጨማሪም የነባር ሰብል ዝርያ ውጤት የሆኑ ምግቦች ገንፎ፣ ቂጣ፣ ዳቦ፣ ጨጨብሳ፣ ቆሎ፣ ጭኮና አነባበሮ ለዕይታ ቀርበዋል። ደማከሴ የተባለው ቅጠል በተለይ ለምች መድሃኒት ስለሚያገለግል በህብረተሰቡ በስፋት ጥቅም ላይ እንደሚውል ርዕሰ መምህሩ አስረድቷል።

ሌላው በኤግዚቪሽን ላይ በምርምር ያገኛቸውን ነባር ዘሮች ለጎብኝዎች ሲያስተዋውቁ አግኝቼ ያናገርኳቸው የተለጮ ቀበሌ ገበሬ ማህበር ነዋሪ የሆኑት አቶ እንግዳወርቅ አስፋው ናቸው። እንደ እርሳቸው ገለፃ በአካባቢያቸው ነባር የሆኑት የነጭና የጥቁር ጤፍ ከ15 በላይ የሆኑ የስንዴና የገብስ ዝርያዎችን የሱፍና የተልባ ሰብሎችን ከየቦታው በማሰባሰብ ከወረዳው የእርሻ ተመራማሪዎች ጋር በመቀናጀት በምርታማነታቸው፣ በሽታን በመቋቋም ችሎታቸው የታወቁትን ዘሮች አሰባስበው በማራባት ለገበሬዎች በማከፋፈል ላይ ይገኛሉ። እንደ እርሳቸው ገለፃ ዘሮቹ ለገበሬዎቹ በነፃ ይታደላሉ። ገበሬዎችም ጥቅማቸውን በመረዳት ራሳቸው በማራባት ለዘር ያከማቿቸዋል። የነባር ዘሮች ምርምር ለሶስት ዓመታት ያክል ይከናወናል። ከዚያም ለአካባቢው አፈርና ውሃ፣ አየር ንብረትና ስሕነምህዳር ምቹ መሆናቸው ሲረጋገጥ ይሰራጫሉ። በተለጮ ቀበሌ ገበሬ ማህበር የተቋቋመው የነባር ዘሮች ባንክ የሚሰጠውን ጠቀሜታ በተመለከተ የጠየቅኳቸው አቶ እንግዳወርቅ አስፋው ሲገልፁ፤ ባንኩ ነባር ዘሮች በጥንቃቄ ተቀምጠው ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዲተላለፍ በማድረግ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንደሚሰጥ ጠቅሰው በማሳ የተዘራው እህል በተፈጥሮ አደጋ ውድመት ቢደርስበት በባንኩ የተከማቸውን ዘር በማውጣት ችግሩን መቋቋም እንደሚቻል አስረድተዋል። ከዚሁ ጋር ገበሬዎች የአካባቢውን ስነምህዳር ሊጎዳ የሚችል መጤ ዘር እንዳይጠቀሙና በአነስተኛ ማሳ ምርታማነትን መጨመር እንዲችሉ ያግዛቸዋል ብለዋል።

ከላይ ለመጥቀስ እንደተሞከረው ብዝሃነትን መጠበቅ አካባቢን ከውድመት ማዳን የሚያስችል ነው። በአሁኑ ወቅት ግን በዓለም ላይ የግብርና ምርትን ለማሻሻል እንዴት ይደረግ በሚለው ጥያቄ ዙሪያ ሁለት አይነት ፍልስፍናዎች የሚራሙዱ ሲሆን፤ አንደኛው ከሌላኛው በጣም የተራራቀ ነው። የመጀመሪያውን ፍልስፍና የሚያራምዱ በአሁኑ ወቅት እየጨመረ የሚሄደውን የህዝብ ብዛት ለመቀለብ እንዲቻል የምግብ እህል ምርት መጨመር አለበት። ይህን ለማድረግም ቴክኖሎጂን፣ ፀረ ተባይ መድሃኒትንና ማዳበሪያን በስፋት በመጠቀም በትራክተር በሚታረስ ሰፋፊ እርሻ ላይ ተመሳሳይ ዝርያ ያላቸውን እህሎች ዘርቶ ማምረት አዋጭነት አለው በማለት ይከራከራሉ። የዚህን አስተሳሰብ ነቃፊዎች በበኩላቸው አካሄዱ ሰፋፊ መሬትን በጥቂት የእርሻ ኩባንያዎች እጅ እንዲገባ የሚያደርግ በመሆኑ በርካታ ገበሬዎችን ከመሬት ያፈናቅላል። ከዚህ በተጨማሪ ብዝሃነትን ከግምት ስለማያስገባ ለአካባቢ ውድመት የበኩሉን አስተዋፅኦ ያደርጋል ይላሉ። ከዚሁ ጋር በእርሻው ላይ የሚረጨው ፀረ ተባይ መድሃኒት በአፈር ላይ የሚገኙና ለአፈር ምርታማነት ከፍተኛ ሚና የሚጫወቱ ኦርጋኒክ አካላትን ከጥቅም ውጭ ስለሚያደርግ ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል ይላሉ። በተጨማሪም ከፍተኛ ውሃን ስለሚጠቀም የውሃ እጥረት ስለሚያስከትል አዋጭ አለመሆኑንም ይጠቅሳሉ። ሁለተኛውን አስተሳሰብ የሚያራምዱ ወገኖች የእርሻ ምርታማነት መኖር እንዳለበት ያምናሉ። ይህን ለማድረግ ግን በመጀመሪያው አካሄድ ሳይሆን ብዝሃነትን እንደተጠበቀ በማስቀጠል በአነስተኛ ገበሬዎች ማሳ ላይ ምርታማነታቸው የተረጋገጠላቸውን ነባር ዘሮች በመጠቀም ዓላማውን ማሳካት ይችላል ብለው ያምናሉ። አሁን በተጨባጭ በሀገራችን ያለውን ሁኔታ ስንመለከት አብዛኛው የእርሻ ምርት የሚመረተው በገበሬዎች ማሳ ላይ ነው። ከዚህ አኳያ በስነምህዳር ላይ ይህነው የተባለ ጉዳት እያደረሰ አይደለም። ይሁን እንጂ ሀገራችን በከፍተኛ ደረጃ በምግብ እጥረት ከሚሰቃዩ ሀገሮች ተርታ ውስጥ የምታገኝ ነች። ይህን የምግብ እጥረት መቋቋም የተቻለውም ከለጋሽ ሀገሮች በሚገኝ ምፅዋት ነው።

የ2011 በኢትዮጵያ የዓለም ባንክ ተጠሪ ቢሮ ባወጣው መግለጫ በዚያን ዓመት ሀገራችን የ804 ሚሊዮን ዶላር የምግብ እርዳታ በለጋሽ ሀገሮች እንደተቀበለች በመግለጫው አመልክቷል። ይህ ሁኔታ ለረሀብ ሊጋለጥ የሚችለውን ህብረተሰብ ከረሀብ ማዳን ቢቻልም በሀገሪቱ ላይ ሊያደርስ የሚችለው የምስል ክስረት መገመት አያዳግትም። ስለዚህ ይህ የምግብ እጥረት እንዲቃለል ዘመናዊ እርሻን ከብዝሃነት ጋር አጣጥሞ እንዴት ይተገበር የሚለውን ጥያቄ ፖሊሲ

አውጭዎች በተደጋጋሚ ሊያጤኑት ግድ ይላል። በሌላ በኩል መንግስት ያለበትን የውጭ ምንዛሪ እጥረት ለማቃለል በሚል ለውጭ ኩባንያዎች ሰፋፊ መሬቶችን በመስጠት የተለያዩ ሰብሎችን አምርተው ለሀገራቸው ገበያ እንዲያቀርቡ እያደረገ ይገኛል። ይህ በተለምዶ የመሬት ቅርምት ተብሎ የሚታወቀው አካሄድ ትራክተርንና ፀረተባይ መድሃኒትን የሚጠቀም እንዲሁም አንድ አይነት ዘሮች መዝራቱ በስነምህዳርና በብዝሃነት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እያስከተለ መሆኑ በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሙያተኞች ዘንድ ትችት እየቀረበበት ይገኛል። የገበሬዎችን መሬት ይዞታን ከማጠናቀቁም ባሻገር ከፍተኛ የውሃ መጠን ስለሚጠቀም በተፈጥሮ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ አስከትሏል። ከዚህ አኳያ ለሀገራችን የትኛው አካሄድ ያዋጣል የሚለውን በተገቢው ማጤን ለዛሬውም ሆነ ለመጭው ትውልድ ማሰብ እንደሆነ ግንዛቤ መውሰድ ተገቢ ነው። አማትሳይ የተባለ ህንዳዊ የኖቤል ሽልማት ተሸላሚ ኢኮኖሚስት እንደሚገልፀው በአሁኑ ወቅት በዓለም ላይ ለሰው ልጅ የሚበቃ የእህል ምርት አለ የምግብ ስርጭቱ ፍትሃዊ ባለመሆኑ በርካታ የአለም ህዝብ ለምግብ እጥረት እንደተጋለጠ ይገልፃል።

በሌላም በኩል ተለበቃ የአለም የአግሮ ቢዝነስ ኩባንያዎች በሰፋፊ እርሻዎቻቸው የሚያመርታቸውን የእህል ምርቶች ለባዮፊውል መስሪያነት መጠቀማቸው ለምግብ ዋጋ መናርና ለብዝሃነት ውድመት የበኩሉን አስተዋጽኦ እያደረገ እንደሚገኝ ሙያተኛው ይገልፃሉ። ከዚህ አኳያ ነባር ዘሮችን በመጠቀምና ብዝሃነትን በመጠበቅ በአነስተኛ ማሳ ላይ ምርታማነትን ማሳደግ እንደሚሻልና ይህም በተለያዩ ምሁራን እየተደገፉ መምጣቱን መረዳት ይቻላል።

ከዚህ አኳያ ገበሬው ብዝሃነትን በመጠበቅ ምርታማነትን እንዲጨምር ከመንግስት ጋር መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችም እያደረጉ የሚገኙትን ጥረት አጠናክረው መቀጠል ይኖርባቸዋል። ገበሬው ኑሮው ከእጅ ወደ አፍ ነው። በዘመናት ያካበተው የአስተራረስ ልምድና የአዝርእት አይነት እውቀት ቢኖረውም የቴክኒክ እገዛ ሊደረግለት ግድ ይላል። መልካ ኢትዮጵያ ማህበር ከዚህ አንፃር በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች ከገበሬዎች ጋር እጅና ጓንት በመሆን ብዝሃነትና አካባቢ እንዲጠበቅ የበኩሉን አስተዋፅኦ በማድረግ ላይ ይገኛል። የማህበሩ ሙያተኛ የሆኑት አቶ ሽመልስ ተገኝ እንደሚገልፁት ማህበሩ ገበሬዎች የአካባቢን ጥበቃ ጉዳይ በባለቤትነት ስሜት ይዞት ቢንቀሳቀስ በአጭር ጊዜ ለውጥ ሊያመጣ እንደሚችል ማህበራቸው እምነት አለው። ከማህበራቸው ተሞክሮ በመነሳት መግለፅ እንደሚቻለው በዚያው በወልመራ ወረዳ ብቻ ከአንድ የዝናብ ወቅት የተተከሉ ሀገር በቀል ዛፎች አካባቢን በደን ሸፍነው ከአፈር መከላት አካባቢውን ታድገዋል። በዚህ አማካኝነትም ወደ መሬት ስር መግባት የሚገባው ውሃ በተክሎቹ አማካኝነት ወደውስጥ በመግባቱ የአፈርን ርጥበት ለመጠበቅ አስችሏል። መልካ ማህበር የብዝሃ ህይወት በአካባቢ ገበሬዎች ማኔጅመንት ትኩረት እንዲያገኝ የማድረግ ስራውን የጀመረው እ.ኤ.አ በ2012 ሲሆን፤ ይህ እውን እንዲሆንም ገበሬዎችና የወረዳ አስተዳደር የግብርና ጽህፈት ቤት ያላሰለሰ እገዛ አድርገዋል። ከተለጮ ገበሬ ማህበር ጋር የሚሰራው ዓላማ ገበሬዎች አካባቢን በመጠበቅ ረገድ የሚጫወቱትን ሚና ማገዝ ነው ብዝሃነት ሲጠበቅም በአየር ንብረት ለውጥና በሙቀት መጨመር ሳቢያ የሚከሰተውን አሉታዊ ተፅዕኖ መላመድና መቋቋመ እንድችል ነው። መርሃ ግብሩ በኖርዌይ የልማት ድርጅት የሚደገፍ ሲሆን እስከ 2015 ድረስ ይቀጥላል። በእለቱ የተካሄደው ስብሰባ መረዳት እንደተቻለው ከዚህ ቀደም የአካባቢው ገበሬዎች ነባር ዝርያዎችን በተለያዩ ምክንያቶች የተነሳ ሊያጧቸው የቻሉ ሲሆን ዋንኛዎቹ ምክንያቶችም የተፈጥሮ አደጋዎች ማለትም ድርቅ ዝናብና ጎርፍ ሲሆኑ የሰው ልጅ በሚያካሂደው ተግባርም ለውድመት ተጋልጠው ቆይተዋል። በዚህ አካሄድም የሚጠቀሰው የተሻሻሉ ምርጥ ዘሮችን መጠቀም ይጠቀሳል። እኒህ ዘሮች መዘራት ሲጀምር ገበሬዎች ነባሮቹን በመዘንጋት መዝራት አቆሙ። አለመዘራት ደግሞ ሰብሉ ተመልሶ እንዳይመረትና ጥቅም ላይ እንዳይውል አድርጓል። ይሁን እንጂ ከዓመታት በኋላ ከሙያተኞች በተደረገላቸው ገለፃ መሰረት የነባሮቹን ዘሮች ጠቀሜታ ተረድተው እንደገና መዝራት ችለዋል። አዲስና የተሻሻሉ የተባሉት ዘሮች ለአጭር ጊዜ ውጤታማ ቢሆንም ቀጣይነታቸው ግን አልተረጋገጠም። ዘሮቹም ከፍተኛ ኬሚካልን የሚጠቀሙ በመሆናቸው በአፈር ላይ የሚያደርሱት ተፅዕኖ እንዳለ ሆኖ የኬሚካሉ ዋጋም ለገበሬዎች የሚቀመስ ባለመሆኑ ነበር። ከዚህ አኳያ ሊጠፉ ተቃርቦ የነበረው ነባር ዘር ጠቀሜታው ታውቆ እንደገና በገበሬው መዘውተሩ ለብዝሃነት አይነተኛ ጠቀሜታ አለው። በተለጮ ገበሬ ቀበሌ ማህበር የተቋቋመው የነባር ሰብል ዘሮች ባንክም ይህን ለማሳካት ትልቅ እገዛ ይኖረዋል።

የሀገር በቀልና ነባር ዘሮች በባንክ

ከላይ ለመጥቀስ

እንደተሞከረው

ብዝሃነትን መጠበቅ

አካባቢን ከውድመት

ማዳን የሚያስችል

ነው። በአሁኑ ወቅት

ግን በዓለም ላይ

የግብርና ምርትን

ለማሻሻል እንዴት

ይደረግ በሚለው ጥያቄ

ዙሪያ ሁለት አይነት

ፍልስፍናዎች የሚራሙዱ

ሲሆን፤ አንደኛው

ከሌላኛው በጣም

የተራራቀ ነው

Page 18: በአባይ ግድብ ውስጥ 3 ንደ - ethioforum.orgethioforum.org/wp-content/uploads/2013/12/Sendekdec102013.pdfሰንደቅ 9ኛ ዓመት ቁጥር 431 ታህሳስ 02 2006

ሰንደቅ 9ኛ ዓመት ቁጥር 431 ረቡዕ ታህሳስ 02 200618

ፍልስፍና/ስነልቦና

ሕግበኪዳኔ መካሻ

[email protected]

የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታዎች ሙስና እና ሕገወጥ የሰዎች ዝውውር

ባሳለፍናቸው ሳምንታት በርካታ በሕገወጥ መንገድ ወደ ሳዑዲ ዓረቢያ የገቡ ወይም በሀገሪቱ የመኖሪያ ፈቃዳቸው ያለታደሰና ተገቢው የሕጋዊ ስደተኝነት ማረጋገጫ የላቸውም ያለቻቸውን ስደተኞች ሀገሪቱ ማስወጣት መጀመሯ በሀገራችንም ሆነ በውጨ የመገናኛ ብዙሀን ትኩረትን ስቦ ከርሟል። በተለይም በሕገወጥ መንገድ ወደ ሳዑዲ አረቢያ ገብተዋል ወይም የመኖሪያ ፍቃድ የላቸውም በሚል በሳዑዲ የሚገኙ ወገኖቻችን ላይ ድብደባ፣ ግድያ፣ እንግልትና ማዋከብ መፈፀሙ ብዙዎቻችንን ያስቆጨ ነው። የሀገራችን መንግስትም የተባረሩት ዜጐቹን ወደ ሀገር ቤት እየመለሰ ይገኛል። ቁጥራቸው ከመቶ ሺ የዘለሉት ዜጐቻችንን ወደ ሀገራቸው የመመለስ ስራ ተሰርቷል።

ይህ አጋጣሚ የሚያሳየን ከሀገራችን በሕገወጥ መንገድ የሚሰደዱ ስደተኞች ቁጥር ምን ያህል እንደናረና የሕገወጥ የሰዎች ዝውውር ወንጀል አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን ነው። በሌላ በኩል ደግሞ በሕገወጥ መንገድ የሚሰደዱ ወገኖቻችን ከመነሻቸው ጀምሮ በመተላለፊያ ሀገራትም ሆነ በመድረሻ ሀገራት ሊገጥማቸው የሚችሉትን የተለያዩ የመብት ረገጣዎችና የሚፈፀሙባቸውን የተለያዩ ወንጀሎች እና ዘርፈ ብዙ ጥቃቶች ይጠቁማል። በሳዑዲ ዓረቢያ በወገኖቻችን ላይ የደረሰው ጥቃትም አንዱ ማሳያ ነው። ለመሆኑ ይህ ሁሉ ሲሆን ሕገወጥ ስደትን የሚከላከል ለሕገወጥ ስደተኞችም ጥበቃ የሚያደርግ ሕግ በሀገራችንም ሆነ ሕገወጥ ስደተኞች በሚጓጓዙባቸው ሀገራት የለም? ካለስ ለምን ተግባራዊ አልሆነም የሚለውን እናንሳ፤

የፓሌርሞው ኰንቬንሽንና

አጋዥ ፕሮቶኰሎችህዳር 6 ቀን 1993 ዓ.ም በጣሊያን ፓሌርሞ

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አባል ሀገራት የተደራጁ ድንበር ዘለል ወንጀሎችን ለመቆጣጠር ዓለም አቀፍ ኰንቬንሽን ፀድቋል። ይህንን ኰንቬንሽን ተግባራዊነት ለማረጋገጥ ደግሞ ህዳር 15 ቀን 1996 ዓ.ም ሕገወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመከላከል፣ ለመግታትና ሕገወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎችን በተለይም ሴቶችና ህፃናትን አዘዋዋሪዎችን ለመቅጣት ያለመ ፕሮቶኰል ተግባራዊ እንዲሆን ተወሰነ። እስከ ሀምሌ 2004 ዓ.ም ድረስም 152 የተመድ አባል ሀገራት በዚህ ስምምነት ተገዢ ለመሆን ፈቅደው አጽድቀውታል። ሀገራችን የዚህ የቃል ኪዳን ሰነድ አካል የሆነውን በተለይም ሴቶችና ህፃናትን በሕገወጥ መንገድ ማዘዋወርን ለመከላከል የወጣውን ፕሮቶኰል የሀገሪቱ ሕግ አካል አድርጋ በአዋጅ ቁጥር 737104 እና 736/04 ተቀብላ ከሚያዝያ 2 ቀን 2004 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ እንዲሆኑ አውጃለች። ሳዑዲ ዓረቢያ ከ1997 ጀመሮ ሌሎች የመን፣ ሊቢያ፣ አማን፣ ዩናይትድ ዓረብ ኢሚሬትስ፣ እስራኤል እና ሶሪያም ኰንቬንሽኑን ተቀብለው አፅድቀውታል።

ይህ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽኖችና ፕሮቶኰልን አላማ ያደረጉ ድንበር ዘለል የተደራጁ ወንጀሎችን ሕገወጥ የሰዎች ዝውውርን በተለይም ሴቶችና ሕፃናትን በሕገወጥ መንገድ ማዘዋወርን ለመከላከል፣ ለመግታትና ሕገወጥ አዘዋዋሪዎችን በመቅጣት ላይ ብቻ አይደለም። በተጨማሪም ሕገወጥ ስደተኞችም በደረሱበት ሀገር ተገቢው ጥበቃ እና እንክብካቤ እንዲደረግላቸው ሰብአዊ መብታቸው እንዱጠበቅና ክብራቸውንና ደህንነታቸውን በጠበቀ መልኩ በስደት በገቡበት ሀገር መቆየት የማይችሉ ከሆነ ወደ ሀገራቸው በአግባቡ እንዲመለሱ ፈራሚ ሀገራት ላይ ግዴታ የሚጥሉ ናቸው። በዝርዝር ወደ ዓለም አቀፍ ስምምነቶቹ ውስጥ ባንገባም በሀገራችንም ሆኑ በሌሎች ሀገሮች እነኚህ ዓለም አቀፍ ስምምነቶችና የየሀገራቱ ሕጐች እያሉ ለምን ሕገወጥ የሰዎች ዝውውር ይህን ያህል ተስፋፍቶ አስጊ ደረጃ ላይ ሊደርስ እንደቻለ እንመልከት።

የሙስና ሚና ሊገባደድ ቀናት በቀሩት በያዝነው

የፈረንጆቹ ዓመት የተባበሩት መንግስታት የአደንዛዥ ዕፅ እና የወንጀል መቆጣጠሪያ ጽ/ቤት አንድ ወቅታዊ የጥናት ሰነድ ይፋ አድርጓል። ሰነዱ በዓለም አቀፍ

ደረጃ በሙስና ወንጀልና በሕገወጥ ስደት መካከል ያለውን ትስስር የሚዳስስ ነው። የጥናት ውጤቱ እንዳሰመረበት በሙስና እና በሕገወጥ ስደት መካከል ዘርፈ ብዙና ውስብስብ ቁርኝቶች አሉ። ጥቂቶቹ ትስስሮች በቀላሉ የሚደረስባቸው አይደሉም። አብዛኞቹን ግን በተደጋጋሚና በተለያዩ ሁኔታዎች ላይ በቀላሉ መታዘብ ይቻላል። ሁለቱ ወንጀሎች ግንኙነታቸው በብዙ መልኩ ነው። የወንጀሎቹ ስፋትና መጠን እንደየሀገራቱ የእድገት ደረጃ፣ የተለያዩ ተቋማቶቻቸው የተቀናጀ አሰራርና እንደየ ሀገራቱ ተቋማት ሙስናን የመከላከልና የመዋጋት አቅም የተለያየ በመሆኑ በሕገወጥ ስደት ውስጥ ሙስና የሚጫወተው ሚና ከሀገር ሀገር የተለያየ ነው።

ሙስና በሕገወጥ መንገድ ስደተኞችን ከሀገር በማስወጣትና በማስገባቱ ሂደት በየትኛውም ደረጃ ከመነሻው፣ በመተላለፊያ ሀገራት ወይም በመዳረሻ ሀገራት ላይ ሊከሰት ይችላል። በየሀገራቱ ያለውን ድንበሮችን የመጠበቅ፣ ስደትን የመቆጣጠር፣ ስደተኞችን የመጠበቅ እና ሕጐችን የማስፈፀም እርምጃዎችን በማዳከም ሕገወጥ ስደትን የመከላከሉ እንቅስቃሴ ላይ ሁነኛ አሉታዊ ተፅዕኖ ያሳርፋል። ስደተኞችን በሕገወጥ መንገድ ከሀገር በማስወጣትና በማስገባት ሰዎችን በሕገወጥ መንገድ በማዘዋወር የሚገኘው ዳጐስ ያለ ገቢ ደግሞ ሕገወጥ አዘዋዋሪዎች በሰፊው መደለያና ጉቦ ማቅረብ እንዲችሉ አድርጓቸዋል። ጉቦና ሌሎች የሙስና አይነቶች ሕገወጥ የስደት ተግባር የሚካሄድበትን እድል ፈጥሯል። የሚመለከታቸው አካላት ሕጋዊነትን ያላሟሉ ስደተኞችን እንዳይከላከሉ እና አይተው እንዳላዩ እንዲያልፉ አድርጓቸዋል። ተገቢውን ሕጋዊ ሰነድ ያላሟሉ ስደተኞች በሰበብ አስባቡ በሕግ አስከባሪዎች እንዲበዘበዙ በማረጋገጥ የሕገወጥ ስደት ተግባር ላይ ሕግ ጣልቃ እንዳይገባና አጥፊዎች እንዳይቀጡ አድርጓል። በዚህ ብቻ ሳይወሰን ሕገወጥ ስደትን ለመዋጋት የሚደረገው ዓለም አቀፍ ትብብር ላይ እንቅፋት ፈጥሯል። ሊኖር የሚገባውን በመተማመን እና በጋራ ጥቅም ላይ የተመሰረተ ድንበር ተሻጋሪ ግንኙነቱን በማቀጨጭ የድንበር ጥበቃ፣ የስደተኞች ቁጥር፣ የወንጀል ምርመራና የመረጃ መቀባበል ስራዎች ውጤታማ እንዳይሆኑ ማድረጉን የተመድ የጥናት ውጤት አስቀምጦታል። በመቀጠል ደግሞ ሕገወጥ ስደትን በሚያስፋፋው የሙስና ወንጀል ውስጥ በጥናቱ ላይ የተጠቀሱ ዋና ዋና ተዋናዮች እነማን እንደሆኑ እንመልከት።

የመንግስት ተቋማት ተዋናዮችየመንግስት ሰራተኞች ከተሳተፉበት

በሕገወጥ የሰዎች ዝውውር የሙስና ተግባር ውስጥ በከፍተኛም ሆነ በዝቅተኛ ደረጃ ያላቸው ሰራተኞች በሙስና ሊዘፈቁ ይችላሉ። ከሚኒስትሮች አንስቶ ዲፕሎማቶች፣ የቆንስላ ሰራተኞች እስከ የድንበር ጠባቂዎች ፖሊሶች በአይሮፕላን ጣቢያዎች የመንገደኞች ተቆጣጣሪ ሰራተኞች ድረስ በሙስና ሊነካኩ ይችላሉ የሚለው የተመድ ጥናት ለምሳሌ በከፍተኛ ደረጃ ቪዛ የሚሰጡ ባለስልጣናትና የስደተኞች ጉዳይ ኃላፊዎች ጉቦ በልተው ወይም በጥቅም ተደልለው የማይገባ አገልግሎት ሊሰጡ ወይም ሕገወጦችን ‘አይኔን ግንባር ያድርገው’ ብለው አይተው እንዳላዩ ሊያሳልፉ ይችላሉ። በዝቅተኛ ደረጃ ደግሞ የስደተኞች ጉዳይ፣ የደህንነት፣ የአየር ማረፊያ ጣቢያዎችና የአየር መንገድ ሰራተኞች ገንዘብ ተቀብለው ሰነዶችን ሳያጣሩ የማረጋገጫ ማህተም እንደማድረግና የፍተሻ በሮችን ክፍት የማድረግ ስራዋችን ሊሰሩ ይችላሉ። ቁጥጥር ካልተደረገባቸው በዝቅተኛ ደረጃ የሚፈፀሙ የሙስና ተግባራት አጠቃላይ በስርዓቱ ውስጥ ተሰራጭተው ተቋሙን የማንቀዝ ጉልበታቸው ኃይለኛ ነው። እንደ ሙስና ሕገወጥ ስደትን የመከላከል ተቋሙ ውስጥ ዘልቆ ከገባ ሕገወጥ ስደትን የመቆጣጠሩን ስራ ፈታኝ፤ ማጥፋቱን ደግሞ እጅግ በጣም ከባድ ያደርገዋል።

ጥናቱ እንደደረሰበት አብዛኞቹ በየሀገራቱ የሚገኙ በሙስና የተዘፈቁ የመንግስት ሰራተኞች በሕገወጥ ስደት ውስጥ ያላቸው ተሳትፎ ሲገኝ ጉቦ የመብላት እድልን ብቻ ሳይሆን ከሕገወጥ አዘዋዋሪዎች ጋር በመመሳጠር እራሳቸውም የወንጀሉ አንድ አካል እስከመሆን ሊደርሱ ይችላሉ። ሶማሊያ ውስጥ የሚሰጡ አብዛኞቹ የተጭበረበሩ ቪዛዎች ላይ የሚኒስትሮች የከፍተኛ ባለስልጣናት እና የተመድ ዲፕሎማቶች እጅ እንዳለበት በ2010 የወጣው የተመድ ሪፖርት እንዳጋለጠ ጥናቱ ለአብነት

ጠቅሷል። በሌላ መልኩ ደግሞ ከፍተኛ የመንግስት ኃላፊዎች በተለያየ የሕገወጥነት እና የማጭበርበር ተግባራት ውስጥ ሊሰማሩና ለሕገወጦችም ከሕግ እንዲያመልጡ ጥበቃ ሊሰጡ ይችላሉ። አንዳዴ ደግሞ በቀጥታ በሕገወጥ ስደቱ ተግባር ሳይሳተፉ በሌላ መንገድ ትርፍን የሚጋሩና ሰነድ አልባ ስደተኞችን እና ስደተኞችን በመበዝበዝ ኪሳቸውን የሚያደልቡ ባለስልጣናት እንደማያጋጥሙ ጥናቱ አልሸሸገም።

የሕግ አስከባሪ እና የድንበር ቁጥጥር ተቋማት ላይ የሚታየው ሙስና ደግሞ ለቁጥጥር አዳጋችነቱ ልዩ ባህሪ ያሰጠዋል። ለአብነት ያህልም የሚደረግባቸው ዝቀተኛ የስራ ቁጥጥር፣ የስራቸው ባህሪ በአብዛኛው ሚስጥራዊነታቸው ተቋማቱን በይበልጥ ለሙስና ተጋላጭ አድርጓቸዋል። የእነኚህ ተቋማት ሰራተኞች ከጠቋሚዎችና ከሌሎች የወንጀል የፍትህ ስርዓቱ ግብአቶች ጋር ያላቸው ተደጋጋሚ ግንኙነትም በሙስና ውስጥ ለመዘፈቅ ያጋልጣቸዋል። አንዳንድ ሙስናዎችም በባህሪያቸው ለሕግ አስከባሪዎችና ለድንበር ጥበቃ ሰራተኞች ብቻ የሚሰጡ ናቸው።

በመሆኑም አጠቃላይ የሙስና መስፋፋትና ሙስናን ለመቆጣጠር ያለው ፖለቲካዊ ቁርጠኝነት አናሳ መሆን ተነጣጥለው የማይታዩ ስለሆኑ ከሕገወጥ ስደት ትርፍ የሚያካብቱ ሙሰኛ ባለስልጣናት ወይም ሰነድ አልባ ስደተኞችን በማዋከብ የግል ጥቅም የሚያካብቱ የመንግስት ኃላፊዎች እያሉ ሕገወጥ ስደትን ለመከላከል የሚወሰዱ እርምጃዎች ውጤታማ እንደማይሆኑ መተንበይ እንደማይከብድ የተመድ የጥናት ሰነድ አስቀምጦታል።

የግሉ ዘርፍ ተሳትፎበመንግሥት ባለሥልጣናት ላይ ከማትኮር

በተጨማሪ የሕግ ወጥ ስደተኞች አጓጓዦች ከግሉ ዘርፍም ተባባሪዎችን ያገኛሉ። አብዛኛውን ጊዜ ቀላል በሆነ የግሉ ዘርፍ እና ድርጅት ሠራተኞችን የእቃ አጓጓዦች፣ የመንገደኞች አጓጓዦች፣ የሥራና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች፣ አሰሪዎች፣ የጥበቃ አገልግሎት ሰጪዎች የትምህርት ተቋማት ወይም የወደቦችና የኤርፖርት ሠራተኞችን በማግባባት ወይም ሙስና በመስጠት ተባባሪ ያደርጓቸዋል፡ ወደኚህ ተቋማት ውስጥ ሰርጎ መግባቱንም ይችሉበታል። የነኚህ የግል ተቋማት የሚፈልጉት ሚስጥራዊ መረጃ ይኖራቸዋል ወይም የሀሰት የሰነድ ማስረጃዎችን (የነዋሪነት ማስረጃ፣ የሰራተኝነት ማስረጃ የነዋሪነት የምስክር ወረቀት፣ የታሳሪነት (የተመራማሪነት) ማስረጃ ወዘተ ለማስገኘት ቪዛ፣ የስደተኛነት ወይም የዋነኛነት ማመልከቻዎችን ተቀባይ የሚያደርጉ የሀሰት ሰነዶችን ለማዘጋጀት ይረዳቸዋል። በአይሮፕላን ጣቢያ ወይም በሌሎች የቁጥር ጣቢያዎች ላይ በግል የጥበቃ አሰሪዎች አማካኝነት የተሰማሩ ሠራተኞችም ሕገወጥ ስደተኞች ላይ ቁጥጥር እንዳይኖር በማድረግ ይረዳሉ።

በሌላ በኩል ደግሞ የተደራጁ ወንጀለኞች በሕገወጥ ስደት ውስጥ ሙስናን በመጠቀም የሚሳተፉበት አጋጣሚ መኖሩን የተመድ ጥናት ጠቁሟል። የተደራጁ የወንጀል ቡድኖች በስደተኞች

ቁጥጥር ላይ ያለውን ክፍተት በድንበር ጥበቃና በደህንነት ስርዓቱ ውስጥ ያለውን ድክመት ለመጠቀም ሁሌም ተዘጋጅተው ስለሚጠብቁ ሙስና ያዳክመውን አሰራር ለራሳቸው ኣላማ ይጠቀሙበታል። እንደማንኛውም የንግድ ስራ ወንጀለኞች የሚሳተፉት ወጪያቸውን በመቀነስ ትርፋቸውን ለማብዛት ሲሆን የመያዝ እድላቸውን ለመቀነስና ከተጋለጡም እስርና ቅጣትን ለማምለጥ በሕገወጥ ስደት አጓጓዦችን ይጠቀማሉ።

ከሕገወጥ ስደት ውስጥ የሙስናን ሚና በትክክል ለመገመት አስቸጋሪ እንደሆነበት ልሸሸገው የተመድ የጥናት ቡድን ለዚህ ምክንያቱ ሀገራት በፍትህ ስርዓታቸው በድንበር ጥበቃ እና በስደት ቁጥጥር ተቋማቶቻቸው የሚከሰተውን የሙስና መጠን እና አይነት ይፋ ለማውጣት ፈቃደኛ አለመሆናቸው መሆኑን ገልጿል። ሆኖም ሙስና ህገወጥ ስደትን በማስፋፋት በአንዳንድ ሀገራት አስጊ ደረጃ ላይ መድረሱን የሚያሳዩ በርካታ ማስረጃዎችን ለማግኘት ተችሏል። ለምሳሌ በበርካታ የአፍሪካ አካባቢዎች የድንበር ቁጥጥር የሚካሄደው በዋና ዋና ድንበር መሻገሪያዎች ላይ በመሆኑ በሀገራት መካከል ያሉት ረጅም ድንበሮችና የድንበር ጥበቃው ደካማ በመሆኑ ስደተኞችን ማስገባት ማስወጣት ያስችላል። የስደተኞች ጉዳይ ኃላፊዎችም አብዛኛውን ጊዜ ለሙስና የተጋለጡ ናቸው። ከአፍሪካ ለመውጣት ከሊቢያ እስከ ሊባኖስ በሚል ርዕስ በ2007 የተደረገውን የጥናት ውጤት የተመድ ጥናት በአብነት ጠቅሶታል። በአፍሪካ አህጉር ሙስና ሕገወጥ ስደትን ትልቅ የንግድ ዘርፍ እንዲሆን ለማድረግ ብቻ ላይሆን የሕግ አስፈፃሚውን እና የድንበር ቁጥጥር ተቋማትን እንቅስቃሴ በማዳከም ተቀባይነታቸውና በህዝብ ዘንድ ያላቸውን አመኔታ እንዲያጡ አድርጓቸዋል። በአንዳንድ አካባቢዎች በከፍተኛ ሙስና ምክንያት የሀገሪቱ ተቋማት ላይ የሚጣለው አመኔታ በማነሱ የስደተኞች ጉዳይ የድንበር አስተዳደርና ቁጥጥር የሕግ ማስከበርና የጥገኛ ስደተኞ ጥበቃ ላይ ያው ዓለም አቀፍ ትብብርን እስከጥፋት ደረጃ ደርሷል።

የሕገወጥ ስደት የተለያዩ ዘዴዎችበተለያዩ ዘዴዎች ሕገወጥ ስደተኞች

ከሀገር ለማስወጣትም ሆነ ለማስገባት ሙስና ሚናውን የሚጫወተው በሕገወጥ መንገድ በየብስ፣ በባህር፣ በአየር ከሀገር በማስወጣት በሕገወጥ መንገድ በገቡበት ሀገር እንዲቆዩ በማድረግና ለዚሁም የሀሰት ወይም በሀሰት መረጃዎች የተገኙ የስደተኞች የሰነድ ማስረጃዎችን መስጠት ነው። የሕገወጥ ስደተኞች አዘዋዋሪዎች ሁነኛ ዘዴያቸው ሕጋዊ የሆኑትን የስደት አካሄዶች የጥገኝነት አጠያየቅን፣ የቤተሰባዊ ጥምረትን የስራ እና የትምህርት ፍቃዶን የቱሪስት ቪዛ እና የመሳሰሉትን ለሕገወጥ ተግባራቸው መጠቀም ነው። ይህንም ለማድረግ በመንግስትም ሆነ በግል ተቋማት አሰራርን በሙስና በመጠቀም የሀሰት የዝምድና ወይም የጉዲፈቻ ማስረጃዎችን የማስመሰል የጋብቻ ሰነዶችን ያገኛሉ።

ጥናቱ በጠቀሳት አንዲት የአፍሪካ ሀገር ውስጥ ስደተኞችን ከመቆጣጠር ስራ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት የሌላቸው ኃላፊዎች በሀገሪቱ ዜጎችና በውጭ ሀገር ዜጎች መካከል ለሕገወጥ ስደትና ቋሚ የመኖሪያ ፍቃድ ለማግኘት ሲባል የተደረጉ በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ የሀሰት ጋብቻዎችን በማሳያነት አንስቷል። የፖለቲካ ጥገኝነት ለማግኘትና የአለም አቀፍ የስደተኞች ጥበቃ ተጠቃሚ ለመሆን ሲባል በርካታ የሀሰት ክስ እና ሌሎች ጥገኝነት የሚያስገኙ ሰነዶች ተዘጋጅተው እንደሚቀርቡም የተመድ የጥናት ቡድን ገልጿል።

በሕገወጥ ስደት ውስጥ በሌሎች ሀገራ የመንግስት ሰራተኞች እና በሕገወጥ ስደተኛ አዘዋዋሪዎቹ መካከል በሚደረግ መመሳጠር በወታደሮችና በፖሊሶች ለዘረፉ መዳረጋቸውን የገለፁ ሲሆን በቦሳሶ፣ በፑንት ላንድ እና በየመን አጥኚዎቹ ያነጋገሯቸው ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በጉዞአቸው ላይ በወታደሮች መዘረፋቸውን መስክረዋል። በአንዳንድ ሀገራት መዘረፍ፣ ጥቂት ገንዘብ ለማግኘት መደብደብ ወይም በፖሊስና በሌሎች የመንግስት ሰራተኞች ሰነድ አባል ለሆኑ ስደተኞች ላይ አዘውትሮ የሚያጋጥም መሆኑን ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ለአጥኚዎቹ ገልጸዋል።

ጥናቱ በምሳለኔ የጠቀሳቸው በመካከለኛው ምስራቅ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ሰነድ አልባ ስደተኞች የመኖሪያ ፍቃዳቸው የእድሳት ጊዜው በማለፉ በአካባቢው የሕግ አስከባሪዎች መጉላላት ወከባ የሚደርስባቸው ሲሆን ተገደው ወደ ሀገር ቤት ለመመለስ ሲሉም ለህግ አስከባሪዎች በየወሩ የተወሰነ ገንዘብ እንደኪራይ ክፍያ ለመክፈል እንደሚገደዱ ገልፀዋል።

ከላይ በጥቂቱ በገለፅኩት መልኩ የተባበሩት መንግስታት ሙስና በአለም አቀፍ ደረጃ ለሕገወጥ ስደት መስፋፋት እየተጫወተ ያለው ሚና አሳሳቢ መሆኑን በጥናት አረጋግጧል። በኛውስ ሀገር ከሌሎች ከሚጠቀሱ ችግሮች በተጨማሪ በሕገወጥ ስደት ውስጥ የሙስና ሚና እስከምን ድረስ ነው የሚለው መጠናትና ተገቢው እርምጃ መወሰድ አለበት።¾

ሕገወጥ ስደትና የሙስና ሚና- የተባበሩት መንግስታት በዓለም አቀፍ ደረጃ ሙስና ሕገወጥ ስደትን አሳሳቢ ደረጃ እንዳደረሰው አዲስ ጥናት ይፋ አድርጓል

- ሙስና ሚናውን የሚጫወተው በምን መልኩ ነው?

o የመንግስት ተቋማት

o የግል ዘርፍ

o የተደራጁ ወንጀለኞች በሕገወጥ ስደት መስፋፋት ከፍተኛ ተሳትፎ እንዳላቸው ዓለም አቀፍ ጥናት አረጋግጧል

-የእኛስ ሀገር ሁኔታ እንዴት ነው?

በተለያዩ ዘዴዎች ሕገወጥ ስደተኞች ከሀገር

ለማስወጣትም ሆነ ለማስገባት ሙስና

ሚናውን የሚጫወተው በሕገወጥ መንገድ

በየብስ፣ በባህር፣ በአየር ከሀገር በማስወጣት

በሕገወጥ መንገድ በገቡበት ሀገር እንዲቆዩ

በማድረግና ለዚሁም የሀሰት ወይም በሀሰት

መረጃዎች የተገኙ የስደተኞች የሰነድ

ማስረጃዎችን መስጠት ነው።

Page 19: በአባይ ግድብ ውስጥ 3 ንደ - ethioforum.orgethioforum.org/wp-content/uploads/2013/12/Sendekdec102013.pdfሰንደቅ 9ኛ ዓመት ቁጥር 431 ታህሳስ 02 2006

ሰንደቅ 9ኛ ዓመት ቁጥር 431 ረቡዕ ታህሳስ 02 2006 19ስነልቦና/ ፍልስፍና

የቁማር ሥነልቦናዊ ቀውስ

ደረጃ የመድረስ ዕድላቸው የሰፋ ነው” በማለት ያስጠነቅቃል።

የሃርቫርድ የሕክምና ትምህርት ቤት የሱሰኝነት ጥናት መምሪያ ዲሬክተር የሆኑት ዶክተር ሃዋርድ ጄ ሻፈር “ወጣቶች የሚጫወቷቸው ሕገወጥ ቁማሮች ሕጋዊ ከሆኑ ቁማሮች ባልተናነሰ መጠን እየተስፋፉ እንደመጡ የሚጠቁሙ መረጃዎች እየተበራከቱ ነው” ብለዋል። የቁማር ሱሰኞች በኢንተርኔት ቴክኖሎጂ ከአግባብ ውጭ ሊጠቀሙ ስለመቻላቸው ሲናገሩ “ክራክ ኮኬይን ማጨስ የኮኬይንን ጣዕም ጨርሶ ሊለውጥ እንደቻለ ሁሉ ኤሌክትሮኒክስም በቁማር አጨዋወት ላይ ትልቅ ለውጥ ሳያመጣ አይቀርም ይህ በመሆኑም በርካታ ወጣቶች አእምሮአቸው በስነልቦና ተፅእኖ ስር ወድቋል” ብለዋል።

የቁማር ኢንዱስትሪ ማንንም የማይጎዳ ጨዋታ እንደሆነ ብዙ ጊዜ ይነገራል። ይሁን እንጂ ቁማር በጉርምስና ዕድሜ ላይ የሚገኙ ወጣቶችን ከማንኛውም ሕገወጥ ዕፅ በማይተናነስ ሁኔታ ሱሰኛ ሊያደርጋቸው የሚችል ከመሆኑም በላይ ወደ ወንጀለኝነት ሊመራ ይችላል። በእንግሊዝ አገር የተደረገ አንድ ጥናት ቁማር ከሚጫወቱ በጉርምስና ዕድሜ ላይ የሚገኙ ወጣቶች መካከል ‘46 በመቶ የሚሆኑት ሱሳቸውን ለማርካት ሲሉ ከቤተሰቦቻቸው እንደሚሠርቁ አረጋግጧል።

እውነታው ይህ ሆኖ ሳለ አንድ ተደማጭነት ያለው የቁማር ማኅበር “ቁማር ከሚጫወቱ አሜሪካውያን መካከል አብዛኞቹ ምንም ዓይነት ችግር ውስጥ አይወድቁም” በማለት ቁማር ሊስፋፋ የሚገባ መሆኑን ለማሳመን ሞክሯል። ቁማር በገንዘብም ሆነ በጤና ረገድ ምንም ዓይነት ጉዳት እንደማያደርስብህ ቢሰማህ እንኳ በህይወትህ ላይ ምን ዓይነት ጉዳት ሊያደርስ ይችላል? ከቁማር የምትርቅበት በቂ ምክንያት ይኖራልን?

የአሜሪካ የሥነ አእምሮ ሕክምና ማኅበር ባወጣው መረጃ መሠረት አንድ ሰው በሚከተሉት

መመዘኛዎች በመጠቀም በቁማርተኝነት ሱስ መለከፍና አለመለከፉን ማወቅ ይችላል። ከመመዘኛዎቹ መካከል በርካታዎቹ የሚታዩብህ ከሆነ ልማደኛ ቁማርተኛ እንደሆንክ፣ አንዳቸው እንኳን የሚታዩብህ ከሆነ ደግሞ ልማደኛ ቁማርተኛ የመሆን ዕድልህ ከፍተኛ እንደሆነ እንደሚያመለክት ብዙ ሊቃውንት ይስማማሉ።

መጠመድ ቁማር የተጫወትክበትን ጊዜ፣ ልትጫወት ያሰብክበትን ቦታ ወይም የምትጫወትበት ገንዘብ የምታገኝበትን መንገድ ብዙ ጊዜ ታስባለህ።

በቃኝ አለማለት ከአሁን አሁን አገኛለሁ በሚል ስሜት የምታስይዘውን ገንዘብ ለመጨመር ትገፋፋለህ።

ለመላቀቅ መሞከር ቁማር መጫወት ለመቀነስ ወይም ለማቆም በምትሞክርበት ጊዜ የመበሳጨት ወይም የመቅበጥበጥ ስሜት ይሰማሃል።

ማምለጫ ቁማር የምትጫወተው ከችግር ለመሸሽ ወይም ተስፋ የመቁረጥ፣ የበደለኝነት፣ የሥጋት ወይም የጭንቀት ስሜት እንዳይሰማህ ብለህ ነው።

ማሳደድ በቁማር ገንዘብ ከተበላህ በኋላ የተበላኸውን ገንዘብ ለማስመለስ ሌላ ጊዜ ትመለሳለህ።

መዋሸት የቁማር አመልህ ምን ያህል የከፋ መሆኑ እንዳይታወቅብህ ስትል ለቤተሰቦችህ፣ ለሐኪሞችህ ወይም ለሌሎች ትዋሻለህ።

ለመቆጣጠር አለመቻል ቁማር መጫወትህን ለማቆም፣ ለመቆጣጠር ወይም ለመቀነስ በተደጋጋሚ ሞክረህ አልሆነልህም።

ሕገወጥ ድርጊቶች ቁማር መጫወቻ ገንዘብ ለማግኘት እንደ ማጭበርበር፣ ሥርቆት ወይም ዘረፋ የመሰለ ድርጊት ፈጽመሃል።

የሚያስከትለው መዘዝ ቁማር ትልቅ ግምት ከምትሰጣቸው ሰዎች፣ ከትምህርት ወይም ከሥራ ሊያቆራርጥህ ይችላል።

ዕዳ መግባት በቁማር ምክንያት ከባድ ኪሣራ ደርሶብህ ዕዳህን ሌሎች እንዲከፍሉልህ

ለመጠየቅ ተገድደሃል።ምንጭ:- National Opinion Research

Center at the University of Chicago, Gemini Research, and The Lewin Group.

የሎተሪ ማስታወቂያዎች የሚያስተላልፉት መልእክት

ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ በሚገኘው ዱክ ዩኒቨርሲቲ የሚሠሩ ተመራማሪዎች ለብሔራዊው የቁማር ጠንቅ ጥናት ኮሚሽን ባቀረቡት ሪፖርት “ቁማር ማስተዋወቅ . . . ትክክለኛ እሴቶችን እንደ ማስተማር ተደርጎ ሊታይ ይችል ይሆናል። ቁማር ብዙም ጉዳት የማያስከትል፣ እንዲያውም እንደ ጥሩ ድርጊት ሊታይ የሚገባ ነገር እንደሆነ ያስተምራል” ሲሉ ገልጸዋል። ሎተሪ ማስተዋወቅ በአንድ ማኅበረሰብ ላይ ምን ዓይነት ውጤት ሊያስከትል ይችላል? ሪፖርቱ እንዲህ ይላል:- “የሎተሪ ማስታወቂያዎች የሚያስተላልፉት መልእክት መጥፎ ጠንቅ የሚያስከትል ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም። የተሳካ ውጤት ማግኘት ትክክለኛ ቁጥር በመምረጥ ላይ የተመካ ነው ብለው ያስተምራሉ። ይህ ዓይነቱ የሎተሪ ድርጅቶች አጉል ‘ትምህርት’ በረዥም ጊዜ ውስጥ የኢኮኖሚ እድገት እንዲጓተት በማድረግ የመንግሥት ገቢ እንዲቀንስ ያደርጋል። በተለይ የሎተሪ ማስታወቂያ፣ ሰዎች የሥራ፣ የቆጣቢነትና ራስን በትምህርትና በሥልጠና የማሻሻል አስፈላጊነት እንዳይታያቸው የሚያደርግ ከሆነ ውሎ አድሮ ምርታማነት እንዲዳከም ማድረጉ አይቀርም። ያም ሆነ ይህ፣ ተአምር ይመጣል ብሎ መጠበቅ ለልጆቻችን ልናስተምረው የሚገባ አመለካከት አይደለም።”

ቁማር አጫዋች ድርጅቶች አዲስ የቁማር ማጫወቻ ድርጅት ለማቋቋም ከሚጠይቀው ገንዘብ በጣም ባነሰ ወጪ ከኢንተርኔት ጋር የተገናኘ ኮምፒውተር ያለበትን ቤት ሁሉ የካዚኖ መጫወቻ ሊያደርግ የሚችል የዌብ ገጽ ሊያዘጋጁ ይችላሉ። በ1990ዎቹ አጋማሽ ላይ ቁማር የሚያጫውቱ የኢንተርኔት ገጾች ከ25 አይበልጡም ነበር። በአሁኑ ወቅት 1,200 በላይ የደረሱ ሲሆን በኢንተርኔት አማካኝነት ከሚካሄድ ቁማር የሚገኘው ገቢ በየዓመቱ በእጥፍ እያደገ መጥቷል። በ1997 ቁማር አጫዋች የዌብ ገጾች 300 ሚልዮን ዶላር አስገብተዋል። በ1998 ያስገኙት ገቢ 650 ሚልዮን ዶላር ደርሷል። በ2000 ደግሞ 2.2 ቢልዮን ዶላር ያስገቡ ሲሆን “ይህ አኃዝ በየአመቱ እያደገ ነው” ይላል የሮይተርስ ዜና ዘገባ።

ልማደኛ ቁማርተኛ መሆን የሚላስ የሚቀመስ እስከ ማጣት ያደርሳል።

በገፅ 21 ዞሯል

አለሙ ታዬ

“ወደ 290,000 የሚጠጉ አውስትራሊያውያን ልማደኛ ቁማርተኞች ሲሆኑ እነዚህ ሰዎች የሚያደርሱት የገንዘብ ኪሣራ በዓመት ከ3 ቢልዮን ዶላር ይበልጣል። ይህም በልማደኞቹ ቁማርተኞች ላይ ብቻ ሳይሆን በዚህ ምክንያት በሚደርሰው የገንዘብ ኪሣራ፣ ፍቺ፣ የራስን ሕይወት የማጥፋት ድርጊትና ከሥራ የመቅረት ልማድ ሳቢያ ጉዳት በሚደርስባቸው 1.5 ሚልዮን የሚያክሉ ሰዎች ላይም ከባድ ችግር ያስከትላል።”— ጄ ሐዋርድ፣ የአውስትራሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር፣ 1999

ከጊዜ በኋላ ደግሞ በየቀኑ ቁማር መጫወት ጀመርኩ። ሙሉ ደመወዜን በቁማር ተበልቼ ቤተሰቤን የማበላው ወይም የቤቴን ዕዳ የምከፍልበት ገንዘብ የማጣበት ጊዜ ነበር። አሸንፌ ብዙ ገንዘብ በማገኝበት ጊዜ እንኳን ቁማር መጫወቴን አላቆምም። እስረኛ አድርጎ የያዘኝ ማሸነፍ የሚያስገኘው ደስታ ነበር” ይላሉ ቁማርተኞቹ።

በአሁኑ ወቅት መላው ኅብረተሰብ በቁማር በሽታ የተለከፈ ይመስላል። ዩ ኤስ ኤ ቱዴይ የተባለው መጽሔት ከ1976 እስከ 1997 ባሉት ዓመታት በዩናይትድ ስቴትስ ሕጋዊ በሆኑ ቁማሮች ውርርድ የተደረገበት ገንዘብ መጠን 3,200 በመቶ አድጓል ብሏል።

ዘ ግሎብ ኤንድ ሜይል  የተባለው የካናዳ ጋዜጣ “ሥነ ምግባራዊም ሆነ ማኅበራዊ ተቀባይነት አጥቶ የኖረው የቁማር ጨዋታ ዛሬ ተቀባይነት ያገኘ የጊዜ ማሳለፊያ ሆኗል” ይላል። ይኸው ጋዜጣ ይህንን የመሰለ የአመለካከት ለውጥ ሊኖር የቻለበትን ምክንያት ሲያመለክት “ሰዎች አመለካከታቸው ሊለወጥ የቻለው መንግሥት በካናዳ ታሪክ ውስጥ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ከፍተኛ ወጪ በማውጣት ለረጅም ጊዜ ባካሄደው የሎተሪ ሽያጭ የማስታወቂያ ዘመቻ ምክንያት ነው” ይላል። ቁማርን ለማስተዋወቅ የተደረገው ጥረት በአንዳንድ ማኅበረሰቦች ላይ እንዴት ያለ ውጤት አስከትሏል?

የልማደኛ ቁማርተኝነት ወረርሽኝየሃርቫርድ የሕክምና ትምህርት ቤት

የሱሰኝነት ጥናት መምሪያ በሰጠው ግምታዊ መረጃ መሠረት በ1996 “በአሜሪካ 7.5 ሚልዮን የሚያክሉ ለአካለ መጠን የደረሱ ልማደኛና ሱሰኛ ቁማርተኞች” ነበሩ። ከነዚህ በተጨማሪ “7.9 ሚልዮን የሚደርሱ አሜሪካውያን ጎረምሶች ልማደኛና ሱሰኛ ቁማርተኞች ናቸው።” እነዚህ አኃዞች የአገሪቱ ብሔራዊ የቁማር ጠንቅ ጥናት ኮሚሽን (ኤን ጂ አይ ኤስ ሲ) ለዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት ባቀረበው ሪፖርት ላይ የተካተቱ ናቸው። ሪፖርቱ የቁማርተኝነት ልማድ ያለባቸው አሜሪካውያን ቁጥር በዘገባው ላይ ከሠፈረው በእጅጉ ሊበልጥ እንደሚችል አክሎ ገልጿል።

በቁማር ልማደኝነት ምክንያት የሚደርሰው ሥራ ማጣት፣ የጤና እክል፣ ለሥራ አጦች የሚከፈል ድጎማና ለሕክምና የሚወጣው ወጪ በአሜሪካ ኅብረተሰብ ላይ በየዓመቱ በቢልዮን ዶላር የሚገመት ኪሣራ ያስከትላል። ይሁን እንጂ ይህ አኃዝ በልማደኛ ቁማርተኝነት ምክንያት በሚፈጸመው ስርቆት፣ ዝርፊያ፣ ራስን መግደል፣ የኃይል ድርጊትና በልጆች ሥቃይ በሚጎዱ ቤተሰቦች፣ ወዳጆችና የሥራ ባልደረቦች ላይ የሚደርሰውን በደልና ሥቃይ አያካትትም። አንድ በአውስትራሊያ የተደረገ ጥናት በአንድ ልማደኛ ቁማርተኛ ምክንያት እስከ አሥር የሚደርሱ ሰዎች ቀጥተኛ ጉዳት ሊደርስባቸው እንደሚችል አረጋግጧል። የዩናይትድ ስቴትስ ብሔራዊ የምርምር ጉባኤ ያወጣው አንድ ሪፖርት “50 በመቶ የሚያክሉ ባለ ትዳሮችና 10 በመቶ የሚያክሉ ልጆች የቁማር ሱሰኛ በሆነው የትዳር ጓደኛቸው ወይም ወላጃቸው አካላዊ ጥቃት ተፈጽሞባቸዋል” ይላል።

ተላላፊ ሱስልማደኛ ቁማርተኝነት እንደ አንዳንድ

በሽታዎች ከወላጅ ወደ ልጅ የሚተላለፍ ይመስላል። ኤን ጂ አይ ኤስ ሲ ያወጣው ሪፖርት “የቁማር ሱሰኛ የሆኑ ወላጆች ያሏቸው ልጆች እንደ ማጨስ፣ መጠጣትና አደገኛ መድኃኒቶችና ዕፆች መውሰድ ላሉ መጥፎ ድርጊቶች በእጅጉ የተጋለጡ ሲሆን ልማደኛ ቁማርተኛ ወይም የቁማር ሱሰኛ የመሆን ዕድላቸውም ከፍተኛ ነው” ይላል። በተጨማሪም ይኸው ሪፖርት “ለአካለ መጠን ከደረሱ ቁማርተኞች ይልቅ በአፍላ ጉርምስና ዕድሜ ላይ የሚገኙ ቁማርተኞች ወደ ልማደኛ ቁማርተኛነት ወይም ወደ ቁማር ሱሰኝነት

በዚህ ምክንያት የቁማር ደጋፊዎች ሕጋዊ ቁማር ጥሩ

መዝናኛ ከመሆኑም በላይ ሥራ ይፈጥራል፣ የታክስ

ገቢ ያስገኛል፣ በኢኮኖሚ የተጎሳቆሉ አካባቢዎችን

ያጠናክራል ብለው ይከራከራሉ

Page 20: በአባይ ግድብ ውስጥ 3 ንደ - ethioforum.orgethioforum.org/wp-content/uploads/2013/12/Sendekdec102013.pdfሰንደቅ 9ኛ ዓመት ቁጥር 431 ታህሳስ 02 2006

ሰንደቅ 9ኛ ዓመት ቁጥር 431 ረቡዕ ታህሳስ 02 200620 የኔ ሃሳብበዚህ ዓምድ ስር የሚወጡ ጽሁፎች የፀሐፊውን እንጂ የኤዲቶሪያሉን አቋም አያንፀባርቁም

ከስሜ በልቤ[email protected]

ሁሉም ሰው የራሱ ህይወት ወደ ተሻለ ደረጃ ለማድረስ የተለያዩ ጥረቶች ያደርጋል። አንዱ ትምህርት ተምሮ ዶክተር መሆን እፈልጋለሁ ይላል። ሌላኛው ወደ ንግድ ገብቶ ሃብታም እንዲሆን ይመኛል። ሌላኛውም ሌላ። እኔም ቤተሰቤ ተምረህ ጥሩ ደረጃ ደርሰህ በመጀመሪያ ላንተ፣ ከዚያም ለኛ ብሎም ለአገርህ እንድትሆን ነው ፍላጎታችን እያሉ ስላሳደጉኝ እና የሁሉ ጊዜ ምኞታቸውም ይህን ስለሆነ ሁሌ ሲመርቁኝ እግዚአብሔር ጤና ይስጥህ ትምህርትህንም ይግለጥልህ እያሉ ነው። እኔም የቤተሰቦቼን ምኞት እና ሕልም ለማሳካት ሌትና ቀን በማጥናት ወደ ዩኒቨርስቲ በመግባት፣ ጥሩ ውጤት በማምጣት እና በመመረቅ ብሎም የመንግስት ቅጥረኛ በመሆን የልባቸውን አደረስኩላቸው። የልባቸው እንኳን አላደረስኩላቸውም። ምክንያቱም ተምሬ ለራሴ መሆን ጀመርኩ እንጂ ለነሱ አልሆንኩ!

ከስድስት ዓመት በፊት የትግራይ ክልላዊ መንግስት ተተኪ አመራሮች ማፍራት አለብን ብሎ ባስቀመጠው አቅጣጫ እኔም ወጉ ደርሶኝ በአንድ ወረዳ በምክትል ፅሕፈት ቤት ደረጃ ተሾምኩ። ደምወዙም ከሲቪል ሰርቪስ ስኬል በትንሽ ይበልጥ ነበር። በዚህ ሹመት እጅግ ተደስቼ በታታሪነት እየሰራሁ ሳለ አንድ ቀን የወረዳው አስተዳዳሪ በአስቸኳይ እንደሚፈልገኝ በስልክ ሲነግረኝ፣ ለምን እንደፈለገኝ በውስጤ እያሰላሰልኩ ወደ ቢሮው አመራሁ። ለነገሩ ብዙም አልተጨነቅኩም። ምክንያቱም የወረዳው አስተዳዳሪ በካቢኔው ካሉ ታታሪ ሰዎች በቁጥር አንድ ከማስቀምጣቸው ውስጥ አንዱ እኔ መሆኔ በተደጋጋሚ ይናገር ስለነበር፣ በራስ መተማመን ነው ወደ ቢሮው የገባሁት።

ወደ ቢሮው ገብቼ ለምን እንደፈለገኝ ስጠይቀው ከፌዴራል ደብዳቤ ተልኮልናል እና በስራ አፈፃፀሙ የተመሰገነ በወጣትነት ዕድሜ የሚገኝ አንድ ሰው በአስቸኳይ እንድትልኩልን ተብለናል እና እኛም አንተ እንድትሄድ መርጠንሃል ሲለኝ፣ ከድሮ ጀምሬ ወደ አዲስ አበባ ሂጄ ስራ እንድቀጠር የነበረኝን ህልም በአቋራጭ ማግኘቴ ደስ ብሎኛል። እኔም ምንም ችግር እንደሌለውና ከነበርን ወጣቶች እኔን መምረጣቸው አመስግኜ ወጣሁ።

በዛን ጊዜ በመላ አገሪቱ በሚገኙ ሁሉም ወረዳዎች እና ከተሞች ተተኪ ወጣት እየተመለመለ አዲስ አበባ በመምጣት ከሁለት ወር በላይ በመንግስት ፖሊሲና ስትራተጂ፣ ብሎም በህዝብ ግንኙነት እና ኮምዩኒኬሽን ሰፊ እና ጥልቀት ያለው ስልጠና ወስዶ ወደ ስራ ተሰማራ። መቼም በዛ ጊዜ የወሰድኩት ስልጠና ያለማጋነን ነው ምላችሁ ሁሌ በተደጋጋሚ ብወስደው ደስ ይለኛል። ምከንያቱም አንድም ብቃት ባላቸው እና ቱባ ቱባ በሚባሉ ባለስልጣኖች ስልጠናውን መውሰዳችን፣ በሌላም ከወረዳ መጥተን እነዚህን ባለስልጣኖች በአካል ማየታቸን ኩራት ኩራት እያለን በአንዴ የሚኒስትርነት ማዕረግ ያገኘን ያክል ነው የሚሰማን የነበረው። በስልጠናው ጊዜ አንድ ያስተዋልኩት ጉዳይ ቢኖር ከትግራይ ክልል የመጡ ሰልጣኞች አብዛኛዎቹ በ 22-30 ዕድሜ ያላቸው ሲሆን፣ ከሌሎች ክልሎች የመጡ ሰልጣኞች ግን አብዛኛዎቹ በዕድሜ ገፋ ያሉ መሆናቸው ነው።

ይህንን ስልጠና በሚገባ አጠናቅቀን ወደ ተለያዩ የፌዴራል መስሪያቤቶች በህዝብ ግንኙነት እና ሚዲያእንዲሁም በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተሰማራን። እኛ በምንሰማራበት ወቅት የማስታወቂያ ሚኒስቴር ፈርሶ የኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅሕፈት ቤት ማቋቋሚያ አዋጅ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ፀድቆ የተዋቀረበት ጊዜ ነው የነበረው። ከትግራይ ክልል የመጣን ሹመኞች በምክትል ፅ/ቤት ደረጃ 1418 ብር ወርሃዊ ደሞዝ ነበረን። ከሌሎች ክልሎች የመጡ ሹመኞች ግን በምክትል ፅ/ቤት ደረጃ ወርሃዊ ደሞዝ 2500 ብር ነበር። አብዛኛዎቹ የመጡ በዕድሜ ገፋ ያሉ ስለነበር ሁሉም ማለት ይቻላል በፅ/ቤት ሃላፊነት ደረጃ የሚገኙ በመሆናቸው ደምወዛቸው ዳጎስ ያለ ነው። መንግስትም የያዛችሁት ደሞዝ ይዛችሁ ነው የምትቀጥሉት ብሎ አቅጣጫ ስላስቀመጠልን፣ አንድ ዓይነት ስራ እየሰራን እኛ ከትግራይ ክልል የመጣን ተተኪዎች ከሌሎች ክልሎች ከመጡ ተተኪዎችበደረጃ እኩል ብንሆንም እጅግ ያነሰ ወርሃዊ ደሞዝ እየተከፈለን ፍዳችን ማየት ጀመርን።

በወረዳ ሁኜ ወላጆቼን በየወሩ እየቆነጠርኩ የምልካት የነበርኩ ብርም አቆምኩ። በስልጠናው ላይ የሚኒስትር ማዕርግ እንደተሰጠኝ ያክል ሲሰማኝ የነበረ ሁሉ እያሰብኩ ሃፍረት እየወረረኝ መጣ። ለምንድነው በአንድ የመንግስት ፖሊሲ የሚተዳደሩ ክልሎች በተመሳሳይ ሹመት የተለያዩ ደምወዝ የሚከፈሉት እያልን ጥያቄ ማንሳት ጀመርን። የትግራይ ክልል ወርሃዊ ደምወዝ እጅግ ዝቅተኛ የሚሆንበት ምክንያትስ ለምንድነው ብለን ጥያቄውንማቀጣጠል ተያያዝነው። ከሌላ ክልል የመጡ አንዳንድሰልጣኞችየትግራይ ተወላጆች በመሆናችን ብቻ የተለያዩ ጥቅሞች እንደምናገኝ አድርገውሲያወሩናሲቀባጥሩ ስሰማ እና በተለያዩ ጋዜጦች ይህንኑ ሲስተጋባ ደሜ ነው የሚፈላኝ የነበረው።

የሆነ ሆኖ ለምን የኛ የትግራይ ክልል የወረዳ ሹመኞች ከሌላ ክልል የወረዳ ሹመኞች እኩል አይከፈለንም የሚል ጥያቄ ለመንግስት ማንሳት አለብን ካልሆነ ግን ኑሮአችን ከሌሎች ክልል ባልደረቦቻችን እኩል ሊሆን ይገባል እንጂ መሰቃየት የለብንም። ይህንን ጥያቄ በአስቸኳይ ካልመለሱልን ወደመጣንበት እንመለሳለን የሚል አቋም ለመያዝ በአንድ ተሰባስበን ሃሳብ መለዋወጥ ጀመርን። እንደኔ ዓይነት አዲስ አበባ ውስጥ ለመስራት ፍላጎት የነበራቸው ሰዎች፣ የደመወዝ ጥያቄ ማንሳት አለብን የሚለው ያስማማናል፣ ወደ ወረዳ መመለስ የሚል ግን አያዋጣም የሚል ሃሳብ አመጣን። ይህንን ሁሉ ስናደርግ ግን የተሰጠንን የመንግስት ተልዕኮ ሳናዛንፍ ቆርጠን በመስራት ሊሆን ይገባል በሚል ተስማምተን በደላችንን በፅሑፍ ለሚመለከተው አካል አሳወቅን። ጥያቂያችን የሚመልስ አካል ጠፍቶ እንዲሁ በነበረችን ደምወዝ ለአንድ ዓመት እየተሰቃየን ዘለቅን። ከአንድ ዓመትበºላ ግን መንግስት ከሌሎች ክልሎች የደምወዝ ስኬል እኩል አደረገልን። እሱ ብቻ አይደለም፣ አዲስ አበባ ከመጣንበት ጊዜ ጀምሮ ያልተከፈለን ክፍያ (Back Payment) እንዲሰጠን ተወሰነልን። እኛም ደስ አለን። ለቤተሰቦቻችንም መደወል ጀመርን። የደበዘዘው የቤተሰብ ምርቃትም መጉረፍ ጀመረ።

እዚህ ላይ ሳልጠቅሰው የማላልፈው ጉዳይ ከወረዳ ለመጣን ተተኪዎች መንግስት ቤት መስጠቱ ነው። ካለን ዝቅተኛ ደምወዝና የኑሮ ሁኔታ አንፃር ሁላችን ሰልጣኞች በመንግስት ቤት እንድንገባ አድርጓል። እውነት ነው ምለው መንግስት ከሌሎች ዜጎች ሲነፃፀር ከሚገባ በላይ እንክብካቤ ነው ያደረገልን። ስለ እንክብካቤው አመሰግነዋለሁ ግን አልልም። መንግስት ለሁሉም ዜጎች እኩል እንክብካቤ ማድረግ ስላለበት! የሆነ ሆኖመንግስት ለኛ ለተተኪዎች ቤት ሲያከፋፍል ትዳር ያለውና ትዳር የሌለው ወይም ልጅ ያለውና ልጅ የሌለው እኩል እያከፋፈለ አልነበረም። ትዳር ላለው እንደምንም ለብቻው ቤት የሚያገኝበት ወይም ቅድሚያ የሚሰጥበት፣ ትዳር የሌለው ደግሞ በአንድ ጠባብ ክፍል ሁለት ሰዎች እና ከዚያ በላይ ሆኖ እንዲኖር የተወሰነበት ነበር። እኛ ከትግራይ የመጣን ተተኪዎች ሁላችን በሚባል መልኩ ትዳር የሌለን ነን። ምክንያቱ አብዛኛዎቻችን በ22 እና 30 የዕድሜ አካባቢ ስለሆንን። በቤቱ ጉዳይም ጭቅጭቅ ሆነ። ከሁሉም ክልሎች የመጣን ተተኪዎች እኩል ዕድል ማግኘት ሲገባን አሁንም ጫናው በኛ ላይ በመሆኑ።

እኛ ከትግራይ የመጣን ተተኪዎችም በምናደርገው ግንኙነት ራሳችን በራሳችን አንስማማም ነበር። በደሞዛችን ስንጎዳ ቆየን፣ አሁንም በቤት አሰጣጥ ዙሪያ ለምን እንጎዳለን? እንዲህ መሆን የለበትም ብሎ አንዱየመብት ጥያቄ ሲያነሳ፣ ሌላኛው ደግሞ ይሄ ኮ እኛ ዕድለኞች ሆነን ነን ያገኘነው። ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን ኮ ይህንን አልታደሉትም። እኛ ይህንን እንድናገኝ በማሰብነው በየበረሃው የቀሩ ይላል። እንዳንዴ በጣም ይገርመኝ ነበር። አሁን ይሄ እንዴት ነው ያያያዘው እላለሁ። ለአንዱ የተሰጠው መብት አንዱ መጠየቅ የለበትም ብለው ነው እንዴ ይህንን ታላቅና ክቡር መስዋዕትነት የከፈሉት ብዬ ከራሴ ጋ እከራከር ነበር። ብቻ በቤት አሰጣጥ ዙሪያም እንዲህ ተበድለን እየኖርን ነው። አሁን ትዳር ስለሌላችሁ ነገ ትዳር የማድረግ እና ልጅ የመውለድ ብሎም የማሳደግ መብት የላችሁም ብለው አፍ አውጥተው አልተናገሩንም እንጂ አንደዛ ነው የሚመስለው። አሁንም አብዛኛዎቻችን በጠባቧ የእርግብ ቤት የምትመስል ቤት እየኖርን ነው። አንዱ ኑሮውን ከብዶት ቤቱ ትቶ ወደ

“ተተኪ” ኮምዩኒኬተሮች እና

የብሔር ጭቆና!

መጣበት ክልል ሲመለስ፣ ጠባብ ቤት ላለው ወንድ ላጤ ቤት መስጠት አይታሰብም፣ ለባለትዳሩ እንጂ። በቃ ከትግራይ የመጡ ተተኪዎች እንዲህ እያሳለፉት ነው።እዚህ ላይ አንባቢው እንዲረዳልኝ የምፈልገው፣ ተበድለናል እያልኩ ያለሁት ከሌሎች ዜጎች በማነፃፀር አይደለም። ከሌሎች ዜጎች ሲነፃፀር ከበቂ በላይ እንክብካቤ ማግኘታችን አልክደውም። ይሁን እንጂ “ከተተኪዎች” አንፃር ሳየው ነው ተበድለናል እያልኩ ያለሁት። ምክንያቱም ከሁሉም ክልሎች የተውጣጣን ተተኪዎች እኩል ዕድል ማግኘት ስለነበረብን!

ኸረ ይሄ ብቻ አይደለም። የመንግስት ኮምዩኒኬሽን ፅሕፈት ቤት አዲስ መዋቅር ከሰራ በºላ ወደ ተለያዩ የፌዴራል መስሪያ ቤቶች መድቦናል ብያችሁ ነበር። መዋቅሩ ከሲቪል ሰርቪስ ስኬል ሲነፃፀር የተሻለ የደመወዝ ስኬል ነው የተጠናው። ይሁን እንጂ በሃላፊነት የሚቀመጠው የዕድሜ ባለፀጋ እንጂ ብቃት እና ችሎታን መሰረት በማድረግ አይደለም የሚል አቅጣጫ ተቀመጠ። ይሄው አሁንም ከሌሎች ክልሎች የመጡ የዕድሜ ባለፀጋዎች ሃላፊነቱን በሙሉ ጥርግርግ አድርገው ወሰዱት። የትግራዩ “ተተኪ” ደግሞ ከዕድሜው የሚመጣጠን የተራ ሰራተኝነት ካባ አጥልቆ ፀጥ ለጥ ብሎ እንዲሰራ ተፈረደበት።አብዛኛው ከዚህ ክልል የመጣ በታታሪነቱ እና አመራሩ የተሻለ ስለነበር፣ የአመራር ክህሎቱን ለማሳደግ በተለያዩ የአመራር ቦታዎች መመደብ ሲገባው፣ የነበረበት የወረዳ ደረጃ እንኳን ተነፍጎት ፣ የመወሰን አቅሙ ተዳክሞ ሌሎች ያከናወኑትን በዜና መልክ

እየዘገበ፤ አንዴ ካላንደር አሳተምኩ ሌላም አጀንዳ አከፋፈልኩ እያለ ጊዜውን እንዲያሳልፍ ተፈርዶበታል። ይገርማችሃል በተመደብንበት መስሪያቤቶች ሁላችንም ማለት ይቻላል ከሃላፊዎቻችን ጋር አይጥ እና ድመት ነን። እኛ ይሄ ትክክል አይደለም ስንል እነሱ ደግሞ አርፋችሁ የባለሙያ ስራችሁ በታዘዛችሁ መሰረት ተግብሩ ሲሉ ስራዎቹ በኛ አስተሳሰብ ሳይሆን ሌሎች ባዘዙን መሰረት እየሰራን ነው።ደመወዛችን ከሌሎች ሲነፃፀር ዝቅተኛ፣ የመወሰን አቅማችን ዝቅተኛ፣ የምንኖርበት ቤት እንዲሁ በቃ … አንዳንዶቻችን በመስሪያቤታችን የመልካም አስተዳደር እጦት አለ ብለን እስከ እዛኛው ጫፍ በመድረሳችን ልንባረር ሁሉ ጫፍ ደርሰናል። የአክሱሟ ፅዮን ትጠብቀን እንጂ!

በኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ያለው አሰራር ሲታይ ባላወራው እመርጥ ነበር። ግን በጣም የማከብራቸው የኮምዩኒኬሽን ከፍተኛ አመራር ሁሌ ማውራት አለብህ ብለው ስላስተማሩኝ ማውራቱን መረጥኩ። የኮመዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ሙሉ በሙሉ ሊባል በሚችል መልኩ የሰው ሃይሉ የመጣው ቅድም ካልኩት ከወረዳዎች ነው። በሃላፊነት ደረጃም ያሉት እነሱ ናቸው። አሁን በተጨባጭ በኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅሕፈት ቤት ውስጥ ከኛ ከትግራይ ክልል የመጣ ተተኪ አንድም የለም። ይሄ በመሆኑ አንዳንድ የሃላፊነት ቦታ ክፍተት ሲኖር ለዚህ ለትግራዩ ተተኪ የሚያስታውሰው የለም። በተለይ ለፌዴራል እና ለክልል ህዝብ ግንኙነቶች የሚቆጣጠር አንድ ክፍል አለ፣ በዘመድ አዝማድ እየተሳሳቡ እና አየተጠቃቀሙ ጥቅም አለበት የሚሉትን ቦታ ካለ ከአንድ መስሪያ ቤት ወደ ሌላ መሰሪያቤት እንዲዘዋወሩ በማድረግ ላይ ይገኛሉ። እኛ ተተኪዎቹ ደግሞ ከቅርብ ሃላፊዎቻቸን ከዛ አልፎም ከዋናዎቹ ይሄ አሰራር ትክክል አይደለም እያልን እነሱም ዋጋቸንን እያቀመሱን ኑሮአችን እየገፋን ነው።

በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተመደቡት ከትግራይ ክልል የመጡ ተተኪዎች ጉዳይ እንዲሁ ከሌሎች የፌዴራል መስሪያ ቤቶች ከተመደቡት ተተኪዎች የሚለይ አይደለም። በተለያዩ ኢምባሲዎች ለመመደብ ሲፈለግ፣ የስራ ዘመንን እንደ ቁልፍ መስፈርት ነው የተቀመጠው። ከሌሎች ክልሎች የመጡ ተተኪዎች በዚህም ተጠቃሚ ናቸው። ከሌሎች ክልሎች የመጡት ተተኪዎች ለምን ተጠቀሙ የሚል አስተሳሰብ የለኝም ግን ሁሉም በእኩል መጠቀም አለበት የሚል እምነት አለኝ። አሁን በዚህ ሚኒስቴር መስሪያቤት ዕድሜ ጠገቡ በሙሉ ማለት ይቻላል ወደ ተለያዩ ኢምባሲዎች እና ቆንስላዎች ተመድበዋል። የትግራዩ ተተኪ ግን በአፍላ ዕድሜ ያለ ስለሆነ ከአንድ ዳይሬክተር ጀነራል ወደ ሌላ ዳይረክተር ጀነራል እየተዘዋወረ የዕድሜ ባለፀጋነትን እየተመኘ እየኖረ ነው።

አንዳንዱ የትግራይ ብሔር ሰዎች እየተጠቀሙ ነው ሲለን በዛ በቅርበት በማውቀው አሁን ባለሁት መስክ እንኳን ሳይ አንድ ዓይነት ደረጃ ባለው ሹመት አንዱ ክልል 2500 ብር ሲወስድ የኛ ክልል 1418 ብር ነው የሚወስደው። ይሄ ለምን እንደዛ ሆነ? ይሄ የብሔር ጭቆና አይደለምን? መንግስት ወጣት ተተኪዎች ቤተሰብ ያልመሰረቱ ላኩ ሲል የትግራይ ክልል በተሰጠው አቅጣጫ መሰረት ተግባራዊ ሲያደርግ፣ ሌሎች ክልሎች ግን ተግባራዊ አላደረጉም። በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት የላከ ነው ሊበረታታ የሚገባው ወይስ ከዛ ውጪ የላከ? የሆነው ግን በተቃራኒው ነው። የትግራይ ተወላጅ ቢበደልም ይሸከመዋል የሚል እጅግ አደገኛ አስተሳሰብ በከፍተኛ አመራሮቻችን ውስጥ በመኖሩ፣ የኛ ጭቆና እንደ አንድ ተራ ነገር እያዩ መዝለቅ የተያያዙት ይመስለኛል።

አባቴ ሁሌ የሚመርቀኝ የነበረ ምርቃት…ልጄ ተምረህ መጀመሪያ ላንተ ከዛ ለቤተሰብህ ብሎም ለአገርህ ሁን ነው። ከነዚህ አንዷ አሳክቻለሁ መማሬ። ተምሬ ግን አንድም የተሻለ ገቢ አግኝቼ ለቤተሰቤ አልረዳሁ፣ ሌላም ለአገሬ አንድ ነገር ማድረግ ይቅርና ሌሎች የሰሩትን አስተጋባ እየተባልኩ መኖር ዕድሌ ሆኗል። ይሄ ነው ከአብዛኛዎቹ የትግራይ ወረዳዎች እና ከተሞች በታታሪነታችን እና በቁርጠኝነታችን ተመርጠን ወደ መዲናችን የተላክን ሰዎች የተተኪነት ስራ!

ቸር ይግጠመን!

በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

የተመደቡት ከትግራይ

ክልል የመጡ ተተኪዎች

ጉዳይ እንዲሁ ከሌሎች

የፌዴራል መስሪያ ቤቶች

ከተመደቡት ተተኪዎች

የሚለይ አይደለም። በተለያዩ

ኢምባሲዎች ለመመደብ

ሲፈለግ፣ የስራ ዘመንን

እንደ ቁልፍ መስፈርት ነው

የተቀመጠው። ከሌሎች

ክልሎች የመጡ ተተኪዎች

በዚህም ተጠቃሚ ናቸው

Page 21: በአባይ ግድብ ውስጥ 3 ንደ - ethioforum.orgethioforum.org/wp-content/uploads/2013/12/Sendekdec102013.pdfሰንደቅ 9ኛ ዓመት ቁጥር 431 ታህሳስ 02 2006

ሰንደቅ 9ኛ ዓመት ቁጥር 431 ረቡዕ ታህሳስ 02 2006 21

መንግስት ማንዴላን ከእስር ቤት እንዲያመልጥ ሁኔታዎችን በማመቻቸትና ከእስር ቤት ሊያመልጥ ሲል ነው በማለት በጥይት ሊመቱት ሴራ ተጎንጉኖለት በእንግሊዝ የደህንነት ኣማካኝነት ከሽፋል። (ኢትዮጵያ ውስጥም በኮልፌ ፈጥኖ ደራሽ የፖሊስ ማሰልጠኛ ተቋም የግድያ ሙከራ የተደረገበት መሆኑ በቅርብ ጊዜ እተገለጸ ያለ ዜና ነው።) ማንዴላ የጥቁሮች የነፃነት ምልከት ተደርጎ በዓለም ላይ መናኘቱ ቀጥሎ እርሱን የማስፈታት እንቅስቃሴዎች ተበራክተው ነበር። እ.ኤ.አ በ1982 ማዴላና ሌሎች የኤኤን ሲ መሪዎች ከደቡብ አፍሪካ መንግስት ጋር ለመነጋገር እንዲያመች ወደ ፖልስሙር እስርቤት ተዘዋወሩ። እ.ኤ.አ በ1985 ፒ .ደብሊው ቦሳ የትጥቅ ትግልን በማቆምንና ማንዴላ ለመፍታት የፈለገ ቢሆንም ታሳሪዎቹ ሀሳቡን አጣጥለውታል። በአቅራቢያውና በዓለም ዓቀፍ ደረጃ በደቡብ አፍሪካ መንግስት ላይ ከፍተኛ ግፊት ይደረግ የነበረ በመሆኑ መንግስት ከማንዴላ ጋር ለመደራደር ብዙ ንግግር አድርጎ ግን ምንም አይነት ስምምነት ላይ አልተደረሰም። ይህ ድርድር ፒ ደብሊው ቦሳ ሥልጣናቸውን ለቅቀው ፍሬድሪክ ዊሊያም ዲ ክለርክ ፕሬዚዳንት በመሆን የማንዴላ ከእስር መፈታት እ.ኤ.አ የካቲት 11,1990 ድረስ ድርድሩ አልተሳካም ነበር። ዲክሌርክ ማንዴላን ከማስፈታት በስተጨማሪ የኤኤን ሲ ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ እገዳ እንዲነሳ እንዲሁም የፖለቲካ ቡድኖች እንቅስቃሴ ላይ የተጣለው እገዳዎች እንዲነሳም አድርገዋል።

ከእስር መፈታትና የፕሬዝዳንትነት ጊዜ

ኒልሰን ማንዴላ ከእስር ከተፈቱ በኃላ ወዲውኑ ለውጭ ሃይሎች የደቡብ አፍሪካ መንግስት ህገመንግስታዊ ሪፎረም እንዲያደርግ ግፊታቸውን እንዲቀጥሉ ጥያቄያቸውን ያቀርቡ ጀመር። ከዚህው ጎን ለጎን በሰላማዊ እንቅስቃሴ ረገድና የኤኤኔሲ የትጥቅ ትግል የአብዛኛው ጥቁሮች በድምጽ የመወሰን መብት እስኪረጋገጥ ድረስ መቀጠል እንዳለበት አወጁ። እ.ኤ.አ በ1991 ማንዴላ የህይወት ዘመን ባልደረባው የሆኑት ኦሊቨር ታምቦ የአፍሪካን ብሔራዊ ኮንገረስ ሊቀመንበር ሆኖ ሲመረጡ ኔልሰን ማንዴላ ደግሞ ፕሬዚዳንት በመሆን ተመረጡ። ማንዴላ ከኤፍ ደብሊው ክለርክ ጋር ሁሉን አቀፍ ምርጫ እንዲካሄድ ድርድር ማድረግ ጀመሩ። በዚህ ወቅት ነጭ ደቡብ አፍሪካኖች ሥልጣን መጋራት የሚፈልጉ ሲሆን ጥቁሮቹ ደግሞ አሜሪካኖች ሙሉ በሙሉ ስልጣን መረከብ የሚፈልጉ በመሆኑ በዚህምክንያት በተለያየ ጊዜ ብጥብጥ እየተነሳ የኤኤኒሲ መሪዎችም መታሰራቸው አልቀረም።ማንዴላ በዚህን ወቅት ማንዴላ ሚዛናዊ የሆነ ፖለቲካዊ አቅም እንዲኖርና ህዝባዊ እንቅስቀሴውና የትጥቅ ትግሉ መካከል ድርድሩ ላይ ግፊት ነበር።እ.ኤ.አ በ1993 ማንዴላና ፕሬዚዳንት ዲ ክለርክ አፓርታየድን ለማስወገድ ባደረጉት ጥረት በጋራ የሠላም ኖቬል ሽልማት አግኝተዋል። ደቡብ አፍሪካ የራሷን የመጀመሪያ ዲሞክራሲያዊ ምርጫ አካሂዳ ግንቦት 10,1994 ኔልሰን ማንዴላ በ77 ዓመታቸው የአገሪቱ የመጀመሪያ ጥቁር ፕሬዚዳንት ሆነው የተመረጡ ሲሆን ዲ ክለርክም ምክትላቸው ሆነው ተመረጡ። በዚሁ ዓመት ማንዴላ በአብዛኛው እስር ላይ በነበሩት ወቅት ጽፈውት የነበረውን የነፃነት ጉዞ( Long Walk to Freedom) የተሰኘውን የግል ታሪካቸው የሚያሳይ መጽሐፍ አሳተሙ።

የማንዴላ ተግባራቶች- እ.ኤ.አ ከ1994 እስከ ጁን 1999 እ.ኤ.አ ማንዴላ ከጥቂት ነጮች የአገዛዝ ሥርዓት ወደ ብዙኃኑ ጥቁሮች እንዲለወጥ ከፍተኛ ጥረት አድርጋል፣- ስፖርታዊ ዝግጅቶችን ጥቁርና ነጭን የማግባቢያና የማስታረቂያ መድረክ አድርገዋል፣- ማንዴላ በእርሳቸው የአገዛዝ ዘመን አገሪቱ ሊገጥማት የነበረውን የኢኮነሚ ውድቀት ለመከላላከል ሠርተዋል፣ በእሳቸው የመልሶ ግንባታ የልማት ዕቅድ የጥቁር አሜሪካ መንግስት ለዜጎቹ የሥራ ዕድል፣ የመኖሪያ ቤት አቅርቦትና የጤና እንክብካቤ ለማመመቻቸት ችለዋልል፣- እ.ኤ.አ በ1996 ማንዴላ በአብላጫ ድምጽ የሚመራ አዲስ ጠንካራ የማዕከላዊ መንግስት፣ የአነሳ ቡድኖች መብት የሚያከብር እና የሀሳብ ነጻነትን የሚያረጋግጥ አዲስ ህገመንግስት ተግባራዉዊ እንዲሆን አድርገዋል፣- በጡረታቸው ጊዜም በእርሳቸው ስም በተቋቋመው ፋውንዴሽን በደቡብ አፍሪካ በየገጠሩ ት/ቤትና ክሊኒክ እንዲገነባ አድርገዋል። - በብሩንዲ የእርስ በእርስ ጦርነት በሸምጋይነት ሰርተዋል፣- በህይወት ዘመናቸውና በትግል ሂደታቸው ዙሪያ የሚያትቱ መጽሐፍቶች አበርክተዋል ። ለአብነት ያህልም ለነጻነት መንገዱ ጨርቅ አይደለም (No Easy Walk to Freedom)፣ ኒልሰን ማንዴላ(Nelson Mandela) መታገል ህይወቴ ነው( The Struggle is my Life) እና የኔልሰን ማንዴላ ተወዳጅ የአፍሪካ አፈታሪኮች ( Nelson Mandela’s Favorite African Folktales) የተወሰኑት ናቸው፤- ማንዴላ እ.ኤ.አ ጁላይ 18, 2007 ዴዝሜንቱቱን ጨምሮ ታዋቂ የአገር ሽማግሌዎች ያሉበት › ሽማግሌዎቹ › የሚባል ቡድን ሰብስበው በኢሲያ ፣ሩቅ ምስራቅና አፍሪካ ላይ ሰላምን፣ የሴቶች እኩልነትና የሰብአዊ ሥራ ላይ ቀላል የማይባል ተግባር አከናውነዋል፤- ማክጋቶ የተባለው ወንድ ልጃቸው የሞተበትን የኤች አይቪ ኤድስ በሽታን በመከላለከል ዘመቻ ረገድ ላይም ተሳትፈዋል፤

የማንዴላ የጋብቻ ሁኔታማንዴላ እ.ኤ. አ በ19 44-1957 ኤቪሊን ንቶኮ ማዚ ከተባለች የመጀመሪያ ሚስቱ አራት ልጆች የወለደ ሲሆን በ1958 እ.ኤአ የተፋቱ ሲሆን፤ በዚሁ ዓመት ዊኒ ማዲኬዚላን በማግባት ሁለት ሴት ልጆች ወልደው፤ ለሁለተኛ ጊዜ ከእርሷ ጋር ፍቺ ፈጽመው እ.ኤ.አ በ1998 ከቀድሞ የሞዛምቢኩ መሪ ባለቤት ከነበሩት ግራሳ ማቼል ጋር ለሦስተኛ ጊዜ ጋብቻ ፈጽመዋል።

የማንዴላ አሟሟትኒልሰን ማንዴላ እ.ኤ.አ በ2001 የፐሮስቴት ካንሰር በሽታ ተጠቅተው የታከሙ ሲሆን፤ ለመጨረሻ ጊዜ ለህዝብ የታዩት በ2010 በደቡብ አፍሪካ በተደረገው የዓለም የእግር ኳስ የዋንጫ ውድድር ላይ ሲሆን ከዚያ ወዲያ ጊዚያቸውን የሚያሳልፉት የልጅነት መኖሪያቸው በነበረው የኩኑ መንደር ህብረተሰብ ጋር ነበር። ማንዴላ በ2011 ላይ በሰንባ ኢንፌክሽን ታምመው ሲሰቃዩ ቆይተው የተለያየ ህክምና ሲሰጣቸው ቆይተው ከዚህ ዓለም በ95 ዓመታቸው ዴሴምበር 5,2013 በሞት ተለይተዋል።እ.ኤአ በ2009 የኒልሰን ማንዴላ የልደት ቀን የሆነው ጁላይ 18, የማንዴላ ቀን በማለት በአለም ደረጃ እንዲከበር በማድረግ ሠላምን ለማበራታትና የደቡብ አፍሪካዊው መሪን ሌጋሲ ለማከበር ታውጇል።

የማንዴላ አስተምህሮማንዴላ ለመላው የጥቁር ህዝብና ለዓለም ትግስትን፣ ለዓላማ ታማኝነትን፣ ውጣውረድን፣ ለህዝብ ጥቅም ህይወትን አሳልፎ መስጠትን፣ የዓላማ ጽናትን ፣ መልካምነትን እንዲሁም ሥልጣን ሲይዙ ተቃናቃኞቻቸውን ድምጥማጥ የሚያጠፉ መሪዎች በበዙባት የአፍሪካ ምድር እርቅ ያወረደ የተበደለበትን ጊዜ ወደ ኃላ ያላየ፣ በህዝቡ ላይ ይቅርታ መንፈስ እንዲሰፍን የደቡብ አፍሪካ የእውነትና የእርቅ ኮሚሽን የተሰኘ ፍርድ ቤት መሰል አግባቢ ተቋም ከእነ ዲዘሞንቱቱ ጋር በማቋቋም ተቀናቃኞቹና የማድቀቂያ የሥልጣን መንበር በቁጥጥሩ ስር ሆኖ ሳለ ብሔራዊ መግባባትና የይቅርታ በመላ አገሪቱ እንዲሰፍን ያደረገ ብልህ መሪ ነው። የኔልሰን ማንዴላ መታሰቢያ ማዕከል ድረገጽ እንዲህ የሚል ጹህፍ አስፍሯል፡- “ ሚስተር ማንዴላ የ67 ዓመት ዕድሜ ዘመኑን ለሰው ልጅ መብት መከበር በመታገል አሳልፏል ! አሁን እኛ የምንጠይቀው እውን ቢያንስ ለ67 ደቂቃ ም ያህላችን ነን ለሰብአዊ ተግባር ወይም የአካባቢያችን ህብረተሰብ ለማገልገል የምናውልው?! ” ብሎ ይጠይቃል:: እውነት ነው ማናችን ለህዝብ ጥቅም ብለን ምንም በግላችን ባላጠፋነው ጥፋት የቀለም ልዩነት፣ የዘር ቆጠራ ይቅር፣ በእኩል ዓይን እንታይ ስላልን 27 ዓመት ተፈርዶብን በትግስት የያዝነውን አቋም ይዘን በጽናት እንቆያለን?! ከአሳሪዎቻችን ጋር አንደራደርም በጋሮ በኩል? ወይም የህዝብ መሪነን እያልን በአፍ ቀላጤነት ላይ ላዩን እያመስን የእስር ጉዳይ ፊት ለፊችን ሲደቀን የምንመራውን ትተን የጨበጥነውን በትነን በአሳሪዎቻችን ጉያ ሥር አንወሸቅም?! ልጄን ሚስቴን የወጣትነት የማደጊያ የሠርቶ መብያ ጊዜዬን ብለን ከዓላማችን በተቃራኒ የማንቀመጥ ወይ ደግሞ እጃችንን አጣምረን በደልን አልሰማውም፣ አላየሁም ብለን የምንመለከተስ የለንም?! በጊዚያዊ ጥቅምስ ዓላማችንን አንቀይርም? ሥልጣን በእጃችን ገብቶስ በመብራት እየፈለግን ጠላቶቻችን ናቸው የምንለውን አናሳድድም?! ማንዴላ ግን ይህንን አላደረገም!! በትግስትና በፍቅር ያሸነፈ ጠላቶቹንም ጭምር ማሸነፍ የቻለ፣ድፍን ዓለም ያነባለት የክፍለዘመኑ መሪ ለመሆን በቅቷል።

ማንዴላ...

የነጋዴው ድርሻ ስለበዛ ነው ብዬ አስባለሁ። ብዙዎቹ ፕሮዲዩሰሮች ነጋዴዎች ናቸው። ባለሙያዎችና ነጋዴዎች አልተጣጣሙም። ነጋዴው ብሩ የሚመለስበትን ሲያሰላ፤ ባለሙያው ደግሞ ጥበቡን ስለመስራት ሲያስብ ልዩነታቸው “አርቱን” ይጎዳዋል። እኔ ተመልካቹን የምወቅስበት አንድ ምክንያት ቢኖር በድሮ ዝና የሚደረግ ማበረታታት አለ፡፤ ባለፈው የሚያስቅ ነገር ሰርተህ ዛሬ የሚያስለቅስ ነገር ይዘህ ስትመጣ የድሮውን እያሰበ ተመልካቹ ይስቃል። ይህ ደግሞ ተመሳሳይ ዘውግ ያላቸው የኮሜዲ ስራዎች እንዲበረታቱ እንድ ምክንያት የሆነ ይመስለኛል።

ሰንደቅ፡- አንተ ሶስት ፊልሞች ሰርተሃል ተግዳሮቶቹ ምን ነበሩ?

ፍቃዱ፡- በጣም ጭንቀት የበዛበት ስራ ነው። እኔ ለምሳሌ ፊልሞቼን ስሰራ ፕሮዲዩሰርም፣ ዳይሬክተርም ደራሲም ሆኜ ስለምሰራ በጣም ይከብደኛል። መሀል ላይ እንዳልተወው ጥበብ ይጎትተኛል። አንዳንዴ ደግሞ የተዋንያኑ ስነ ምግባር ለምን አልተወውም ያሰኝሃል። መልስህ ደግሞ ያወጣኸው ገንዘብ ይቆጭሃል። ሰርቼ መጨረስ አለብኝ ብለህ እልህ ትገባለህ።

አንድ ነገር ተረድቻለሁ። ፕሮዲዩሰርም፣ ዳይሬክተርም ሆነ የምትሰራ ከሆነ ፊልሙን ትጎዳዋለህ ይህን አውቄያለሁ። ብዙ ነገሮች ፊልሙ እንደምንም ብሎ ይለቅ ከሚል አንጻር ብቻ እንድትመለከተው ያስገድድሃል። የፊልም መንገዶች ሁሉ ጠባቦች ናቸው። ጥበቡ እንቅፋት ይበዛበታል።

ሰንደቅ፡- ሶስት ፊልሞችን ሰርተሃል በራስህ ፊልም ላይ ሂስ ጽፈህ ታውቃለህ?

ፍቃዱ፡- አዎ! “ጓንታናም” በተሰኘው የመጨረሻ ስራዬ ላይ ነው። መስጠትም የነበረብኝ፤ ምክንያቱም ለነፃነቴም ጥሩ እንዲሆን ለራሴም ስራ የማልመስ እንደሆነ እንዲታወቅ ስል በደንብ አድርጌ ነው ድክመትና ጥንካሬውን ለይቼ ያሳየሁት።

ሰንደቅ፡- በምትፅፍባቸው መፅሔቶች ላይ ፊልሞችን ስትተች የነበረው “ቻሌንጅ” እንዴት ይገለፃል? ለማለት የፈለኩት በፃፍከው ፅሁፍ ጓደኛነትህን አጥተሃል? በወዳጆችና በአንባቢዎች መካከል መሆን የሚፈጥረውን ፈተና ምንድነው?

ፍቃዱ፡- በጣም ከባድ ነው፤ አንደኛ ይሄነገር ገና አልተለመደም። ብዙ ጊዜ በጎ ነገርህ እንዲነሳልህ ነው እንጂ ደካማ ነገርህ እንዲነሳ አትፈልግም። የሂስ ዓላማ ነገሮችን ማፅዳት ነው። ችግሮችን መጠቆምና ማስወገድ ነው፤ የሂስ ዓላማው። ይሄን ግን ብዙዎች አልተገነዘቡትም። አይተህ እንዳላየ እንድታልፋቸው የሚፈልጉ ብዙዎች ናቸው።

ሰንደቅ፡- ፊልሞችን እንዴት ነው ሂስ ለመፃፍ

የምትመርጣቸው? ከሰው ላለመጋጨት የዘለልካቸው ፊልሞችስ ነበሩ?

ፍቃዱ፡- እኔ በመጀመሪያ ደረጃ ፊልሙ ለሂስ ይመጥናል፣ አይመጥንም ብዬ አያለሁ። በጣም ድክመቶች ከበዛበት አልሰራበትም። ምክንያቱም አንደኛ ትምህርት አይሆንም፣ ሁለተኛ መድረክ ሊሰጠው አይገባም ብዬ አስባለሁ። ሶስተኛ ደግሞ ከፃፍኩበት በጣም ልጎዳው ስለምችል ብተወው እመርጣለሁ። እናም መማማሪያ እንዲሆን ጥሩ ሰርተው ግን ችግር የማይጠፋቸውን ፊልሞች እመርጣቸዋለሁ። ፊልም አካባቢ ስለምሰራ የብዙዎቹ ወዳጅ ነኝ። ነገር ግን በሰሩት ስራ ላይ ስፅፍ ስላምታ የነሱኝም አሉ። ገብቷቸው የመጡም አሉ።

ሰንደቅ፡- በራስህ ፊልም ላይ ጠንከር ያለ ሂስ ከሰጠህ በኋላ ጓደኞህ ምን አሉህ?

ፍቃዱ፡- ብዙዎቹ አክብሮታቸውን ገልፀውልኛል። አሁን አላማዬ ምን እንደሆነ ተረድተውኛል። ማንንም ሰው ለማስደሰትም ሆነ ለማሳዘን ብዬ የሰራሁት እንዳልሆነ ተረድተውኛል። ደግሞ ምን አምናለሁ መሰለህ? . . . ሂስ ማለት የላሉ ብሎኖችን እንደማጥበቅ ነው። ስለዚህ አንተ በሰራህው ፊልም ላይ እኔ ሂስ ስሰጥ ትምህርትነቱ ላንተም፣ ለኔም የሚቀጥለውን ስራ ይዞ ለሚመጣውም ባለሙያ እንዲሁም ለአንባቢውም ጭምር ነው ብዬ ነው የማስበው።

ሰንደቅ፡- እስቲ አንድ -ሁለት- ብለህ ላንተ ጥሩ ናቸው የምትላቸውን ሀገረኛ ፊልሞች በግልፅ ንገረኝ?

ፍቃዱ፡- ሚስጥር ልታስወጣኝ ነው። በርግጥ ሁሉንም የአገራችንን ፊልሞች አላየሁም ካየኋቸው ውስጥ ግን በ “አቡጄዲ ግርግር” መፅሐፍ ሽፋን ላይ የተጠቀምኩባቸውን (ጤዛ፣ ስርየት፣ ይፈለጋል፣ ከመጠን በላይ፣ ሔርሜላ እና ሶስት ማዕዘን) ፊልሞች ለኔ በጣም ጥሩ ስራዎች ናቸው ብዬ አምናለሁ።

ሰንደቅ፡- መዝናኛ አምድ ላይ ሆነህ ሳልጠይቅህ የማላልፈው ጥያቄ፤ ምን ያዝናናሃል?

ፍቃዱ፡- በምን እንደምዝናና አላውቀውም፡፤ ፊልም የማየው እንደስራ ነው። ለመዝናናት ብዬ ሲኒማ ገብቼ ስራ ይሆንብኛል። መዝናናቴን የምፈጥረው በቤቴ ነው። ከቤተሰቦቼ ጋር ነው።

ሰንደቅ፡- ወደፊት ምን የመስራት ሀሳብ አለህ?ፍቃዱ፡- በፅሁፍ ደረጃ ያዘጋጀዋቸው

የፊልም ፅሁፎች አሉ። መፅሀፍትም፣ ቴአትሮችም አሉኝ። አሁን ግን በጣም ፈሪ ሆኛለሁ። እኔ ሰዎችን ሂስ ሳደርግ ቆይቼ ምን አይነት ስራ ይዤ ልመጣ ነው ብዬ እጨነቃለሁ። አንዳንዶቹን ደጋግሜ እፅፋቸዋለሁ። ጊዜያቸው ሲደርስና በስለዋል ብዬ ሳምን አወጣቸዋለሁ የሚል ተስፋ አለኝ።

“በኢትዮጵያ ሲኒማ...

በቁማር ሱስ የተለከፉ ወላጆች ያሏቸው ልጆች ራሳቸው ልማደኛ ቁማርተኞች የመሆን እድላቸው የሰፋ ነው፡፡

ቁማር ብዙዎችን የማረከ ልማድየስኮትላንድ ተወላጅ የሆነው ጆን ሁልጊዜ

የሚያልመው ሎተሪ ስለማግኘት ነው። “በየሳምንቱ ሎተሪ እገዛለሁ” ይላል። “የቲኬቱ ዋጋ በጣም ትንሽ ሲሆን ስመኝ የኖርኩትን ነገር ሁሉ የማገኝበት ተስፋ የተመካው በዚህ ቲኬት ላይ ነው።” ይላል፡፡

በጃፓን የሚኖረው ካዙሺጌ ፈረስ ግልቢያ ይወዳል። “በፈረስ ግልቢያ መወዳደሪያ ቦታ ከጓደኞቼ ጋር መወራረድ በጣም ያስደስተኛል። ብዙ ገንዘብ የማገኝበትም ጊዜ አለ” በማለት ያስታውሳል።

የአውስትራሊያ ነዋሪ የሆነችው ሊንዳ ደግሞ “የቢንጎን ያህል የምወደው ጨዋታ የለም” ትላለች። “ይህ ልማድ በሳምንት እስከ 250 ብር የሚደርስ ወጪ የሚያስወጣኝ ቢሆንም በጨዋታው አሸናፊ መሆን በጣም ያስደስተኝ ነበር።”

ጆን፣ ካዙሺጌና ሊንዳ ቁማር ብዙም ጉዳት የማያስከትል መዝናኛ ነው የሚል አመለካከት ነበራቸው። በዓለም ዙሪያ የሚገኙ በመቶ ሚልዮን የሚቆጠሩ ሰዎችም ተመሳሳይ የሆነ አመለካከት አላቸው። በ1999 የተደረገ አንድ የሕዝብ አስተያየት ጥናት እንደሚያሳየው ከአሜሪካውያን መካከል ሁለት ሦስተኛ የሚሆኑት ቁማርን ይደግፋሉ። በ1998 አሜሪካውያን ቁማርተኞች 50 ቢልዮን ዶላር የሚደርስ ገንዘብ ሕጋዊ ለሆኑ የቁማር ጨዋታዎች ያጠፉ ሲሆን ይህ ገንዘብ ለፊልም ቲኬቶች፣ ለሙዚቃ ቅጂዎች፣ ስፖርታዊ ጨዋታዎችን ለማየት፣ ፓርኮችን ለመጎብኘትና ለቪዲዮ ጨዋታዎች በጠቅላላ ካወጡት ገንዘብ ይበልጣል።

አንድ በቅርቡ የተደረገ ጥናት እንዳረጋገጠው ከአውስትራሊያ ነዋሪዎች መካከል ከ80 በመቶ በላይ የሚሆኑት ጥናቱ በተደረገበት ዓመት ውስጥ ቢያንስ አንድ ጊዜ ቁማር የተጫወቱ ሲሆን 40 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ በየሣምንቱ ቁማር ተጫውተዋል። በዚህች አገር የሚኖሩ ለአካለ መጠን የደረሱ ሰዎች በአማካይ በየዓመቱ ከ3,000 ብር በላይ የሚሆን ገንዘብ ለቁማር ያወጣሉ። ይህ አኃዝ አውሮፓውያን

ወይም አሜሪካውያን ከሚያወጡት ገንዘብ በእጥፍ የሚበልጥ ሲሆን አውስትራሊያውያን በቁማር ወዳድነት ከዓለም የአንደኛነትን ቦታ እንዲይዙ አድርጓቸዋል።

ብዙ ጃፓናውያን ፓቺንኮ የተባለው ጨዋታ ሱስ የሆነባቸው ሲሆን በየዓመቱ በዚህ ጨዋታ በሚያደርጉት ውርርድ በብዙ ቢልዮን ዶላር የሚገመት ገንዘብ ያጠፋሉ። በብራዚል ቢያንስ ቢያንስ በየዓመቱ 4 ቢልዮን ዶላር ለቁማር ይውላል። ከዚህ ውስጥ አብዛኛው የሚውለው የሎተሪ ቲኬት ለመግዣ ነው። ይሁን እንጂ የሎተሪ ቲኬት ፍቅር የተጠናወታቸው ብራዚላውያን ብቻ አይደሉም። ፐብሊክ ጌሚንግ ኢንተርናሽናል የተባለው መጽሔት “በ102 አገሮች 306 ሎተሪዎች” እንደሚኖሩ ገምቷል። በእርግጥም ቁማር በዓለም አቀፍ ደረጃ ብዙዎችን የማረከ ልማድ ሆኗል። ይህ ልማድ ትልቅ ጥቅም አለው ብለው የሚያስቡም አሉ።

ፐብሊክ ጌሚንግ ሪሰርች ኢንስቲትዩት የተባለው ተቋም ተወካይ የሆኑት ሻሮን ሻርፕ በዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት ከ1964 እስከ 1999 ባሉት ዓመታት “ከሎተሪ ሽያጭ 125 ቢልዮን ዶላር የሚያክል ገቢ ያገኘ ሲሆን ከፍተኛውን ገቢ ያገኘው ከ1993 ወዲህ ባሉት ዓመታት ነው” ብለዋል። ከዚህ ገንዘብ ውስጥ አብዛኛው ለሕዝብ ትምህርት ማስፋፊያ ፕሮግራሞች፣ ለብሔራዊ ፓርኮች ማስፋፊያና ለስፖርት ማዘውተሪያ ቦታዎች መሥሪያ ውሏል። ከዚህም በላይ የቁማር ኢንዱስትሪ ብዙ የሥራ ዕድል አስገኝቷል። በአውስትራሊያ ብቻ 100,000 ሰዎች ከ7,000 በሚበልጡ የቁማር ኢንዱስትሪ ድርጅቶች ውስጥ ተቀጥረው ይሠራሉ።

በዚህ ምክንያት የቁማር ደጋፊዎች ሕጋዊ ቁማር ጥሩ መዝናኛ ከመሆኑም በላይ ሥራ ይፈጥራል፣ የታክስ ገቢ ያስገኛል፣ በኢኮኖሚ የተጎሳቆሉ አካባቢዎችን ያጠናክራል ብለው ይከራከራሉ።

እኛ ኢትዮጵያውያን በሎቶሪ፣ በጆተኒ፣ በከረምቦላ፣ በቢንጎ፣ ወዘተ… የምንሳተፍባቸው ቁማሮች የስንቶቻችንን ህይወትና ኑሮ ተፈታትነው ይሆን? የኛን ፈለግ የተከተሉ ልጆቻችንስ ዕጣ ፋንታ ምን ሆኖ ይሆን?

የቁማር...

Page 22: በአባይ ግድብ ውስጥ 3 ንደ - ethioforum.orgethioforum.org/wp-content/uploads/2013/12/Sendekdec102013.pdfሰንደቅ 9ኛ ዓመት ቁጥር 431 ታህሳስ 02 2006

ሰንደቅ 9ኛ ዓመት ቁጥር 431 ረቡዕ ታህሳስ 02 200622ስፖርት

በቆንጂት ተሾመ

ባለፈው ሀሙስ የተሰማው የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት የኔልሰን ማንዴላ ህልፈተ ህይወት እንደማንኛውም የሀገር መሪ በፖለቲካው መድረክ ብቻ መነጋገሪያ ዜና አይደለም። እንደ አንድ ታላቅ ስፖርተኛ ወይም የስፖርት መሪ ሞት የስፖርቱንም አለም ትኩረት በስፋት አግኝቷል። ማንዴላ የአለም ስፖርተኞች ፍቅርና አክብሮት ከሁሉም አቅጣጫ ጎርፎላቸዋል።

የቀድሞ የአለም ቦክስ ሻምፒዮኑ መሀመድ አሊና የብራዚል የምንግዜም ኮከብ የእግር ኳስ ተጫዋች ፔሌ “ጀግናዬ” ሲሉ አሞካሽተዋቸዋል። እሁድ ዕለት ዲድየር ድሮግባ ለጋላታሳራይ ግብ አስቆጥሮ “ማዲባ እናመሰግናለን” ሲል በውስጥ ቲሸርቱ ላይ የተጻፈ ጽሁፍ ለቴሌቭዝን ካሜራዎች አሳይቷል። አሜሪካዊው የቅርጫት ኳስ ተጫዋቹ ኮቤ ብራያንትና የጎልፍ ተጫዋቹ ታይገር ውድስ “የአለማችን ታላቅ ሰውን በሞት አጣን” ሲሉ ሀዘናቸውን ገልጸዋል። የሪያል ማድሪዱ ኮከብ ክርስቲያኖ ሮናልዶ በማንዴላ ሞት መደንገጡን ገልጾ ለደቡብ አፍሪካውያንና ለመላው ቤተሰባቸው መጽናናትን ተመኝቷል። የቀድሞው የማንቸስተር ዩናይትድ ኮከብ ዴቪድ ቤካም “የዓለማችን ታላቅ ሰው ማንዴላ መሞት ቢያሳዝነውም ስራቸው ግን ምንግዜም ህያው ያደርጋቸዋል” ሲል፣ የአጭር ርቀት ንጉሱ ጃይካዊው ዩሴን ቦልት ደግሞ ማንዴላን በሞት ማጣት ትልቅ ጉዳት ቢሆንም “የማይቻለውን ሁሉ ችለው ያሳዩን የጽናት ተምሳሌት” መሆናቸውን ገልጿል።

በተመሳሳይ ሁኔታ እጅግ ብዙ የአለማችን ስፖርተኞች ለማንዴላ ያላቸውን ክብርና ፍቅር በስፋት ተናግረዋል። የዚህ ምክንያት እሳቸው ከአለማችን መሪዎች የተለየ የስፖርት ፍቅር ስለነበራቸው አይደለም። በፖለቲካ ትግል ህይወታቸው በሰሩት ስራና ባተረፉት የታላቅነት ስኬት ነው። ይህም ሲባል ለስፖርቱ ያላቸው ፍቅር ምንም ነው ማለት አይደለም። እንደውም ስፖርትን ከልባቸው የሚወዱና ያለውንም ሀይል ተረድተው ለመልካም አላማ ሊጠቀሙበትም የቻሉ መሪ ነበሩ።

ማንዴላ የስፖርት ፍቅራቸው የይስሙላ ወይም የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት የተጠቀሙበት አይደለም። ፖለቲከኛ ከመሆናቸው በፊት ስፖርት ይወዳሉ፣ ይወዳደሩም ነበር። የስፖርት ፍቅራቸው ከቦክስ ይጀምራል።

ቦክሰኛው ማንዴላማንዴላ የሰላም ሰው፣ ማንዴላ የፍቅር

ሰው፣ ማንዴላ የመቻቻልና አንድነት ሰባኪ፣ ማንዴላ የተጣሉን አስታራቂና ጸብን የሚያወግዙ፣ በውይይት እንጂ በዱላና ጠመንጃ ሀይል የማያምኑ መሆናቸው ሲታወቅ ከምንም በላይ የቦክስ ስፖርትን ማፍቀራቸው ብዙዎችን ለማመን ያስቸግራቸዋል። እውነት ነው ማንዴላ ከምንም በላይ በወጣትነታቸው ጥሩ ቡጢኛ ነበሩ። በጥቁሮች መንደር ሶዌቶ የቦክስ ተወዳዳሪ ነበሩ።

በእርግጥ ማንዴላ ጸብ ፈላጊና ተደባዳቢ ሆነው ወይም ራሰቸውን ከጉልበተኛ በጉልበት ለመከላከል አይደለም ቦክሰኛ የሆኑት። በአፍላ ወጣትነታቸው ፍጹም የተረጋጉና ጸብንም የሚያወግዙ ነበሩ። የብዙ ነጭ ደቡብ አፍሪካውያን ሙያ በነበረው የህግ ሙያ እየሰሩ ይደርስባቸው ከነበረው የቆዳ ቀለም መድልዎ ጭንቀትን የሚያስረሳቸውና የሚያቀልላቸው ነበር። እርሳቸው ግን ከዚህም በላይ ለስፖርቱ ያላቸው ፍቅር እንዲህ ሲሉ ገልጸው ነበር።

“ቦክስ ለሁሉም እኩል መብትና እድል የሚሰጥ ነው። የተጋጣሚን ጥንካሬና ድክመት በምትፈልግበት ጊዜ ስለ ቆዳ ቀለሙ ወይም ስለ ኑሮ ደረጃው አታስብም። ሪንግ ውስጥ የውጤት ደረጃ፣ እድሜ፣ የቆዳ ቀለምና የሀብት መጠን ቦታ የላቸውም”

በቦክስ ስፖርቱ የላቀ ደረጃ ደርሰው በተወዳዳሪነት ስኬታማ ሳይሆኑ የአፓርታይድ ትግል ውስጥ ጠልቀው ቢገቡም የስፖርቱን መሰረታዊ

መርሆችና እውነቶች በፖለቲካው መድረክም ተግባራዊ በማድረግ ውጤታማ ሆነውበታል። እ.ኤ.አ. በ1990 ከእስር ከተፈቱ በኋላ ከነጭ የደቡብ አፍሪካ መሪዎች ጋር አራት ፈታኝ አመታቶችን በብሔራዊ እርቅና መግባባት ድርድር ላይ ተግባራዊ አድርገውታል። “ቦክስ መቼና እንዴት እንደምታጠቃና እንደምትከላከል፣ እንዲሁም በረጅም ጊዜ ሊወስድ በሚችል ውድድር ላይ በምን ያህል ፍጥነት መጓዝ እንዳለብህ ያስተምራል” ሲሉም ይናገራሉ።

ከ1990 ጀምሮም ማንዴላ ከጊዜ ወደ ጊዜ የስፖርት ስትራቴጂን እንደ ፖለቲካዊ መሳሪያ ተጠቅመውበታል። ይኸውም፣ መጀመሪያ ነጭ ደቡብ አፍሪካውያን በብቸኝነት የተቆጣጠሩትን ስልጣን ማካፈል እንዳለባቸው እንዲሰማቸው አደረጉ፤ ከዚያም ከብቀላና ቅጣት ይልቅ የተለያዩ ዘሮች የሚኖሩባት ደቡብ አፍሪካን ለመገንባት ስፖርቱን ተጠቅመውበታል።

ከቦክስ ስፖርት ሌላ አትሌቲክስን በተለይም የአጭር ርቀት ሩጫን ይወዱ እንደነበርም ይነገርላቸዋል። የቦክስ ልምምድ ከመስራታቸው በፊት ሰውነታቸውን በሩጫ ማሟሟቅ ልማድ ነበራቸው። ከአቻዎቻው ጋርም ብርቱ ፉክክር ያደርጉ ነበር።

የነጭ ደቡብ አፍሪካውያን የበላይነትና የአፓርታይድ አራማጆች ስፖርት እንደነበረ የሚታወቀው ራግቢ ማንዴላ ከሩጫ ቀጥሎ የሚወዱት ስፖርት ነው። ነገር ግን በስፖርቱ

በስፖርት የተገነባው የኔልሰን ማንዴላ ታላቅ ስብዕና

የራግቢ አለም ዋንጫ የደቡብ አፍሪካውያንን አንድነት ለማጠናከር

የተጠቀሙበት ማንዴላ እግር ኳስን ደግሞ ደቡብ አፍሪካና አፍሪካ ታላቅ

ውለታን ሰርተዋል። የአለም ዋንጫ ለመጀመሪያ ጊዜ በአፍሪካ ምድር

እንዲዘጋጅ ደቡብ አፍሪካን ወክለው ተሟግተዋል

Page 23: በአባይ ግድብ ውስጥ 3 ንደ - ethioforum.orgethioforum.org/wp-content/uploads/2013/12/Sendekdec102013.pdfሰንደቅ 9ኛ ዓመት ቁጥር 431 ታህሳስ 02 2006

ሰንደቅ 9ኛ ዓመት ቁጥር 431 ረቡዕ ታህሳስ 02 2006

ለኪንታሮትለወሲብ ድክመት /ለመንስኤ እስኬት/ለአሜባበቆዳ ላይ ለሚከሰቱ ቁስሎችለአልማዝ ባለጭራለነቀርሣለጃርዲያለታይፎይድለጨጓራ ሕመምለራስ ምታትለወባለጥርስ ሕመምለሆድ ትል

ለአዕምሮ ጭንቀትለጆሮ ሕመም /ለሚመግል/ለደም ብዛትለጡት ሕመምለኩላሊትለማኅፀን ኢንፌክሽንለጉበትለእጀሰብለአፍና ለአፍንጫ ጠረንለወር አበባ ብዛትለተቅማጥለሪህ

አብይ ደስታበተለያዩ ሕመምና ደዌ ለምትሰቃዩ ሁሉ ሐኪም ፍቅረሰብ መኮንን የባሕላዊ ሕክምናን መነሻ በማድረግ በዕፅዋት ቅመማ ሕክምና አገልግሎት ብቃትና ችሎታቸውን ይዘው ይበልጥ ብዙሀኑን ህዝብ በእግዚአብሔር እርዳታ ለማገልገል በተለያዩ በሽታ ደዌ ለሚሰቃዩ ሁሉ የአልጋ ቁራኛ የሆኑትን ፈውስ ለመስጠት ጠበብት ሙያቸውን ይዘው ይገኛሉ። ይህንን ሙያቸውን ይበልጥ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ የባሕላዊ መድኃኒት ቅመማ ሕክምና ጥናት ማኅበር ብቃታቸውን በማሳወቅ የአባልነት መታወቂያና የሙያ ማስረጃ ተሰጥቷቸዋል። ማየት ማመን ነው ሐኪም ፍቅረሰብ መኮንን ፈውስ ከሚያስገኙባቸው በሽታዎች መካከል እንደሚከተለው ቀርበዋል።

እንዲሁም ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥራችን ወይም በአካል በሕክምና ቦታችን መጥተው ማነጋገር ይችላሉ። አድራሻችን ቁጥር 1፡- አዲስ አበባ የካ ክፍለ ከተማ 22 ከትራፊክ ጽ/ቤት ጀርባ

ለበለጠ መረጃ ሞባይል 0911-43 71 87 የመሥሪያ ቤት ስልክ 011-6-51 84 35ስለምንገኝ ደውለው ይጠይቁን

ፖ.ሳ.ቁ 1790 ኮድ 1250 አዲስ አበባ ኢትዮጵያWeb:- www.fikreseb.com E-mail: [email protected]

23ስፖርት

ለምስራቅና መካከለኛው ሀገሮች (ሴካፋ) ዋንጫ ወደ አዘጋጇ ሀገር ኬንያ ያመራው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን እንደተጠበቀው ከውድድሩ በጊዜ ተሰናብቷል። ቡድኑ የምድብ ማጣሪያውን በቀላሉ አልፎ ሩብ ፍጻሜ ቢገባም በሱዳን ተሸንፎ ወደ ሀገሩ ተመልሷል።

በአሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው የተመራው የሴካፋው ዋልያ በምድብ ማጣሪያ ከኬንያ ያለ ግብ አቻ ተለያይቶ፣ ዛንዚባርን 3ለ0፣ ደቡብ ሱዳንን 2ለ0 አሸንፎ ሩብ ፍጻሜ መግባቱ ይታወሳል። በሩብ ፍጻሜ ከሱዳን በአደረገው ጨዋታ በግብ ሙከራም ሆነ በጨዋታ እንቅስቃሴ ተበልጦ 2ለ0 ተሸንፏል።

አስቀድሞም ብዙ እንዳይጠበቅበት ከአሰልጣኞቹና ፌዴሬሽኑ

አመራሮች የተነገረለት የሴካፋው ዋልያ በወድድሩ ወቅት ያሳየው እንቅስቃሴ አንጻር ከተጋጣሚዎቹ ብቃት አንጻር ለዋንጫም ተጠብቆ ነበር። ይሁንና ቡድኑ ከውድድሩ የሚጠብቀው ምንም ውጤት እንደሌለ ተደርጎ ስለተዘጋጀ ቡድኑ ከእለት ወደ እለት ውህደት አሳይቶ የተሻለ ነገር ማስመዝገብ አልቻለም።

በሩብ ፍጻሜ ጨዋታም በሱዳን በጨዋታ የበላይነት ጭምር ተበልጦ በመሸነፍ ከውድድሩ የተሰናበተው የሴካፋው ዋልያ በትክክል የቡድኑን ክፍተቶች የታየበት ነበር። ይህንንም ክፍተት ማጥናትና የእርምት እርምጃዎችን ሊወስድ ይገባል። በቡድኑ ውስጥ በግል ችሎታቸው የላቀ ብቃት ያሳዩ ተጫዋቾችን በመለየትም ለተሻለ ደረጃ ማብቃት ይጠበቃል።¾

ለመሳተፍና ለመወዳደር የቆዳ ቀለማቸው እንቅፋት ሆኖባቸው ነበር። የዛሬን አያድርገውና የራግቢ ስፖርት በደቡብ አፍሪካ የነጮች ብቻ ነበር። ማንዴላ ግን ጥቁሮችን የማያሳትፈው ስፖርትን ከልባቸው ይወዱና ይከታተሉ ነበር። ነጮች ብቻ የነበሩበት የሀገሪቱ ብሄራዊ ቡድን ግጥሚያ ሲኖረው እንዲያሸንፍ ይመኛሉ፣ ድጋፋቸውንም ይሰጣሉ።

እግር ኳስ ከእስር ቤት እስከ ዓለም ዋንጫኔልሰን ማንዴላ በእግር ኳሱ ስፖርት

የአለማችን ዝነኛ ተጫዋቾች፣ ክለቦችና ከፍተኛ መሪዎች ዘንድ ፍቅርና ተወዳጅነትን ያተረፉ ናቸው። በተለይም ጥቁር ተጫዋቾች “ጀግናዬ” ይሏቸዋል፣ ተምሳሌት ሲሉ ያደንቋቸዋል። ከፔሌ እስከ ሳሙኤል ኤቶና ዲድየር ድሮግባ፣ ከዲያጎ ማራዶና እስከ ዴቪድ ቤካምና ክርስትያኖ ሮናልዶ በየዘመናቱ ኮከብ የሆኑ እግር ኳስ ተጫዋቾች ዘንድ ታላቅነታቸው በብዙ መንገድ ተገልጿል።

ማንዴላ የብዙዎችን የታላላቅ እግር ኳሰኞችን ልብ ያሸነፉት የስፖርቱ አፍቃሪና ደጋፊ በመሆናቸው አይደለም። ይልቁንም ማንዴላ እንደ ብዙ ጥቁር ደቡብ አፍሪካውያን የደሀ መዝናኛ የሚባለው እግር ኳስ የሚመስጣቸው ስፖርት አልነበረም።

እንደ ክዋሜ ንክሩማህና ኬኔዝ ካውንዳን የመሳሰሉ የቀድሞ የአፍሪካ መሪዎች ለእግር ኳስ ቅልጥ ያለ ደጋፊና አፍቃሪም ላይሆኑ ይችላሉ። ግን ከማናቸውም የአለማችን መሪዎች በላቀ ሁኔታ እግር ኳስን ሀያልነት በተግባር ያስመሰከሩ፣ በደቡብ አፍሪካና በአለም ላይ በጎ ተጽዕኖ መፍጠር የቻሉ ናቸው።

ማንዴላና እግር ኳስ የተቀራረቡት በአፓርታይድ ዘመን በሮቢን አይስላንድ እስር ቤት ሳሉ ነበር። እስር ቤቱ ከሚወዱት ቦክስ ስፖርትና ሩጫም አርቋቸው ነበር። እስር ቤት ሀያ አመታት ከቆዩ በኋላ ግን ከእግር ኳስ ጋር ተቀራረቡ። ከእሳቸው ጋር ያሉ ሌሎች እስረኞች ሲጫወቱ እኔም ልግባ ብለው ተቀላቀሉ።

“እስር ቤት ሳለን በጣም የሚያስደስተን ነገር ቢኖር እግር ኳስ መጫወት ነበር” ሲሉም በአስጨናቂው የሮቢን ደሴት እስር ቤት ዘመናቸው እግር ኳስ የደስታቸው ምንጭ እንደነበር ተናግረው ነበር። የማንዴላ እግር ኳስን መጫወት መጀመር ግን የእስር ቤቱ ሀላፊዎችን አላስደሰተም። ሌሎች ታሳሪዎች ላይ ተጽዕኖ በመፍጠር አብዮቱን ያቀጣጥላል በሚል ስጋት የኳስ ጨዋታ እንዲቀር ከለከሉ። እስረኞቹ ቢያንስ በሳምንት አንዴ ብቻ ለመጫወት ፈቃድ ጠየቁ፣ በተደጋጋሚ ተከለከሉ። አልፎ አልፎ ግን ትዕዛዙን ጥሰው ይጫወቱ ነበር። ያን ቀን ታዲያ ምግብ ተከልክለው በረሀብ ይቀጣሉ።

ማንዴላና መሰል እስረኞች ግን የምግብ ቅጣቱ ሳይበግራቸው እግር ኳስን መጫወታቸውን አልተውም። ተደጋጋሚ ቅጣት፣ ተደጋጋሚ የእግር ኳስ ጨዋታ ቀጠለ። በመጨረሻም እግር ኳስ አሸነፈ። የእስር ቤቱ ሀላፊዎችም ምንም ማድረግ ባለመቻላቸው እነ ማንዴላ በእስር ቤቱ እግር ኳስ እንዲጫወቱ ፈቃዳቸውን ለመስጠት ተገደዱ።

የጸረ-አፓርታይድ ትግሉ መቋጫ አግኝቶ ኔልሰን ማንዴላ ከ27 አመታት እስር በኋላ ከእስር ሲለቀቁ እግር ኳስንም ሮቢን ደሴት ጥለው አልወጡም። በቀጣይ የፖለቲካ ጉዟቸውና ትግላቸው ዋነኛ መሳሪያ አደርገው ተጠቀሙበት።

ኔልሰን ማንዴላ ከአፓርታይድ መደምሰስ በኋላ ደቡብ አፍሪካ ለመጀመሪያ ጊዜ በአፍሪካ ዋንጫ መድረክ እንድትሳተፍና አዘጋጅ እንድትሆን የላቀ ሚና ተጫውተዋል። እ.ኤ.አ. በ1996 ደቡብ አፍሪካ የአፍሪካ ዋንጫ ስታዘጋጅ ጥቁሮች ይበዙበት የነበረው ብሔራዊ ቡድን ውስጥ ነጮችም እንዲካተቱ፣ ህዝቡም በአንድነት ድጋፉን እንዲሰጥ አድርገዋል።

“ስፖርት አለምን የመለወጥ ሀይል አለው” ብለው የሚያምኑት ማንዴላ ደቡብ አፍሪካ በ1995 በአዘጋጀችው የራግቢ የአለም ዋንጫ ፍጻሜ ላይ ተገኝተው በነጭ ተጫዋቾች የተሞላውን የሀገራቸውን ብሔራዊ ቡድን አበረታተዋል፤ ውድድሩን ሲያሸንፍም ዋንጫውን በፍጹም የደስታ ስሜት ዋንጫውን አንስተው ሸልመዋል። በነጮች በተሞላው ስታዲየም ከቡድኑ አባላት ጋር ደስታቸውን ገልጸዋል። የራግቢ አለም ዋንጫው ማንዴላ በነጭ ደቡብ አፍሪካውያን ላይ ምንም ቂምና ጥላቻ እንደሌላቸው ያረጋገጡበትና ብዙሀኑ ጥቁር ደቡብ አፍሪካዊ የእሳቸውን መንገድ እንዲከተል አርአያ በመሆን የህዝባቸውንን የተራራቀ ልብ ያቀራረቡበት ታላቁ የስፖርት መድረክ እንደነበር ይታመናል።

የራግቢ አለም ዋንጫ የደቡብ አፍሪካውያንን አንድነት ለማጠናከር የተጠቀሙበት ማንዴላ እግር ኳስን ደግሞ ደቡብ አፍሪካና አፍሪካ ታላቅ ውለታን ሰርተዋል። የአለም ዋንጫ ለመጀመሪያ ጊዜ በአፍሪካ ምድር እንዲዘጋጅ ደቡብ አፍሪካን ወክለው ተሟግተዋል። መጀመሪያ የ2006 የአለም ዋንጫ ለማዘጋጀት ያቀረቡት ጥያቄ ሳይሳካ ቢቀርም ቀጣዩን የ2010 የአለም ዋንጫን ለማሸነፍ የሚችሉትን ሁለ እንደሚያደርጉ ቃል ገቡ። በአለም ላይ ያላቸውን ተሰሚነትና ተጽዕኖ ፈጣሪነት ተጠቅመውም ደቡብ አፍሪካ የ2010 አለም ዋንጫን እንድታዘጋጅ አስቻሉ። በወቅቱ ማንዴላ 85ኛ እድሜያቸው ላይ ሆነው “አሁንማ

ገና የ15 አመት ልጅ የሆንኩ ያህል ተሰማኝ” ሲሉ ነበር መደሰታቸውን የገለጹት።

በአንድ ወቅት በሮቢን ደሴት እስር ቤት ውስጥ እግር ኳስን እንዳይጫወቱ ተከልክለው የነበረው እግር ኳስን አለም ዋንጫ መድረክ ሀገራቸው እንድታዘጋጅ ባስቻሉት የ2010 አለም ዋንጫ ውድድር ፍጻሜ በተካሄደበት ሶከር ሲቲ ስታዲየም ተገኝተው ህልማቸው እውን መሆኑን አይተዋል። በኬፕታውን ግዛት ለ27 አመታት በታሰሩበት ሮቢን ደሴት አቅራቢያም ከአፓርታይድ ስርአት ውድቀት በኋላ ግዙፍ ስታዲየም ተገንብቶ የአለም ዋንጫ ጨዋታዎችን ማስተናገድ ችሏል።

“ስፖርት ልዩነቶችን የሚያቀራርብ ድልድይ የሚገነባ፣ የልዩነታችንን ግድግዳ

የሴካፋው ዋልያ እንደተጠበቀው ተሰናብቷል

የሚያፈራርስና የጋራችን የሆነ ሰብአዊነትን የሚገልጽ ነው ብለው የሚያምኑ ልዩ ሰው ናቸው” ሲሉ ማንዴላን የሚገልጿቸው የአለምአቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዝዳንት ቶማስ ባች የጥቁር ህዝቦች ታጋዩ ሰው በስፖርት ላይ የነበራቸውን ጽኑ እምነት ገልጸዋል።

የፊፋው ፕሬዝዳንት ሴፕ ብላተርም “ማንዴላ ህዝቦችን ለማቀራረብና አንድ ለማድረግ ስፖርትን መሳሪያ ያደረገ የአለማችን ታላቅ ሰው” ሲሉ ታላቅነታቸውን በይፋ መስክረዋል። በቀጣይ በፊፋ የሚካሄዱ ኢንተርናሽናል ጨዋታዎች ላይም ታላቁ ሰው የሚታወሱበት እንዲሆኑ ሲያደርጉ ሰውየው የሚገባቸው ክብር ከዚህም በላይ እንደሆነ በመናገር ነው።¾

Page 24: በአባይ ግድብ ውስጥ 3 ንደ - ethioforum.orgethioforum.org/wp-content/uploads/2013/12/Sendekdec102013.pdfሰንደቅ 9ኛ ዓመት ቁጥር 431 ታህሳስ 02 2006

ሰንደቅ 9ኛ ዓመት ቁጥር 431 ረቡዕ ታህሳስ 02 200624ማስታወቂያ