ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ...ምሳሌ 24:10 በመከራ ቀን ተስፋ...

80
ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ ...በእየለቱ የሚነበብ መንፈሳዊ መጸሐፍ Chris Oyakhilome

Upload: others

Post on 17-Mar-2021

42 views

Category:

Documents


1 download

TRANSCRIPT

Page 1: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ...ምሳሌ 24:10 በመከራ ቀን ተስፋ እንዳንቆርጥ ወይም እንዳንሸነፍ ይመክረናል፤ ይልቁኑ እኛ

ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ

...በእየለቱ የሚነበብ መንፈሳዊ መጸሐፍ

Chris Oyakhilome

Page 2: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ...ምሳሌ 24:10 በመከራ ቀን ተስፋ እንዳንቆርጥ ወይም እንዳንሸነፍ ይመክረናል፤ ይልቁኑ እኛ

www.rhapsodyofrealities.orgemail: [email protected]

All rights reserved under International Copyright Law. Contents and/or cover may not be reproduced in whole or in part in any form without the express written permission of LoveWorld Publishing.

USA:Believers’ LoveWorld4237 Raleigh StreetCharlotte, NC 28213Tel: +1 980-219-5150

CANADA:Christ Embassy Int’l Office, 50 Weybright Court, Unit 43BToronto, ON MIS 5A8Tel.:+1 647-341-9091

UNITED KINGDOM: Believers’ LoveWorldUnit C2, Thames View Business Centre, Barlow Way Rainham-Essex, RM13 8BT. Tel.: +44 (0)1708 556 604Fax.: +44(0)2081 816 290

NIGERIA:Christ Embassy Plot 97, Durumi District, Abuja, Nigeria.

LoveWorld Conference CenterKudirat Abiola Way, OregunP.O. Box 13563 Ikeja, LagosTel.: +234-812-340-6547 +234-812-340-6791

USA:Christ Embassy Houston,8623 Hemlock Hill DriveHouston, Texas. 77083 Tel.: +1-281-759-5111; +1-281-759-6218

SOUTH AFRICA:303 Pretoria AvenueCnr. Harley and Braam Fischer, Randburg, Gauteng South Africa.Tel.:+27 11 326 0971Fax.:+27 113260972

KuKÖ S[Í“ }ÚT] KT²´:

ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ ...በእየለቱ የሚነበብ መንፈሳዊ መጸሐፍISSN 1596-6984ነሐሴ 2010 editionCopyright © 2018 by LoveWorld Publishing

u}K¾ G<’@� “M}Ökc ue}k` G<KU Øpf‹ ŸSÅu—¨< ¾SêNõ pÆe ¾}¨cÆ “†¨<::

Page 3: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ...ምሳሌ 24:10 በመከራ ቀን ተስፋ እንዳንቆርጥ ወይም እንዳንሸነፍ ይመክረናል፤ ይልቁኑ እኛ

የ 2010 ዓ.ም. ተወዳጁ “ የራኘሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ “ እትም፣ የመንፈሳዊ ህይወትህ እርምጃና እድገት ለማሳደግ በተለየና ባማረ ሁኔታ ለተሻለ ነገር በሚያነሳሳ

መልኩ የተዘጋጀ ነው፡፡ በመረጃና በመገለጥ ከተሞሉ ፁሁፎች በተጨማሪ የዚህ ወር ዕትም በየዕለቱ የእግዚአብሔርን መለኮታዊ መገኘት ለማወቅ በምታደርገው ጉዞ እምነትህን በእግዚአብሔር ቃል ላይ እንድታሳድግ በተመቻቸ ሁኔታ ተዘጋጅቶ ቀርቦልኃል፡፡ በየቀኑ ባጠናኽው፣ ባሰላሰልከውና በአፍህ በተናገርከው ወይም ደግሞ ባወጅከው መጠን እየታደስክ ትሄዳለህ፡፡

የእግዚአብሔርን ቃል በየቀኑ በወሰድን ጊዜ የእግዚአብሔርን የክብር መገኘትና ድል ዓመቱን በሙሉ እንዲደሰቱበት ጥሪ እናደርጋለን፡፡ በጣም እንወዳችኋለን፡፡ እግዚአብሔር ይባርካችሁ!

- ይህንን መነቃቅያ እንዴት በበለጠ መጠቀም ይቻላል -

መግቢያ

-ፓስተር ክሪስ ኦያኪሎሜ

ይህን ጽሁፍ አንብብና በጥንቃቄ አሰላስል፡፡ ፀሎቶቹንና የአፍ ምስክርነት ቃሉን

በየቀኑ ለራስህ ድምጽህን ጎላ አድርገህ መናገርህ የእግዚአብሔር ቃል በሕይወትህ

እንዲያልፍ ያደርጋል፡፡

የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ወይም በአዲሱ የሁለት ዓመት የመጽሐፍ

ቅዱስ ጥናት በሚገባ አንብቡ

የዕለታዊው የመጽሐፍ ቅዱስ ንባቡን በጠዋትና በማታ ከፍለህ ማንበብ ትችላለህ

መነቃቅያውን በጸሎት ተጠቀሙበትና በእያንዳንዱ ወራት ያላችሁን ግብ ጻፉና

ከአንዱ ግብ ወደ ሌላው ግብ ያላችሁን ስኬት በሚገባ ለኩ

Page 4: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ...ምሳሌ 24:10 በመከራ ቀን ተስፋ እንዳንቆርጥ ወይም እንዳንሸነፍ ይመክረናል፤ ይልቁኑ እኛ

eU

݃^h

eM¡

¾ÓM S[Í

Page 5: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ...ምሳሌ 24:10 በመከራ ቀን ተስፋ እንዳንቆርጥ ወይም እንዳንሸነፍ ይመክረናል፤ ይልቁኑ እኛ

ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ

www.rhapsodyofrealities.org

...በእየለቱ የሚነበብ መንፈሳዊ መጸሐፍ

Page 6: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ...ምሳሌ 24:10 በመከራ ቀን ተስፋ እንዳንቆርጥ ወይም እንዳንሸነፍ ይመክረናል፤ ይልቁኑ እኛ

amharic

ጌታ ኢየሱስ ካለ ስልጣን ሁሉ ከፍተኛው የሆነው ቦታ ይዟል፤ ከአብ ቀኝ፥ ከአለቅነትና ከሥልጣንም ከኃይልም ከጌትነትም ሁሉ በላይ እና ከሚጠራው ስም ሁሉ በላይ ተቀምጦአል:: እናንተስ በእርሱ ውስጥ መሆናችሁን ታውቃላችሁ? ከአለቅነትና ከሥልጣንም ከኃይልም ከጌትነትም ሁሉ በላይና ከሚጠራው ስም ሁሉ በላይ ሆናችሁ ከእርሱ ጋር በክብር ተቀምጣችኋል:: “ነገር ግን እግዚአብሔር በምሕረቱ ባለ ጠጋ ስለ ሆነ፥ . . . ከእርሱ ጋር አስነሣን በክርስቶስ ኢየሱስም በሰማያዊ ስፍራ ከእርሱ ጋር አስቀመጠን”(ኤፌሶን 2: 4-6)።

በክርስቶስ ኢየሱስ የበላይነትን እንድንለማመድ፤ በእርሱም እንደ ጌቶችና አሸናፊዎች እንድንኖር ተጠርተናል:: በእርሱ እና በእርሱ ውስጥ በሰይጣን፥ በጨለማ፥ በአለም እና በፍጥረት ሁሉ ላይ ነግሰናል:: ራእይ 5:10 ክርስቶስ ኢየሱስ መንግሥትና ካህናት እንደተደረግን እና በምድርም ላይ እንደምንነግስ ይነግረናል::

እግዚአብሔር ለኢየሱስ በፍጥረት ሁሉ ላይ ሥልጣን ሰጥቶታል:: በተራራ ላይ ሳሉ ከሰማይ እንዲህ ብሎ ተናግሯል፡- “በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት” የሚል ድምፅ ከሰማይ መጣ (ማቴዎስ 17:5):: ሕይወት ያለውም ሆነ ሕይወት የሌለው ሁሉ ለኢየሱስ እንዲገዛ አዟል፤ እናም እናንተ በእርሱ ውስጥ ስለሆናችሁ ለእናንተም እንዲገዙ አዟል ማለት ነው:: የእርሱ ምትክ ሆናችሁ እንድትሰሩ ውክልና ሰጥቷችኋል:: እናንተ ተራ አይደላችሁም:: ቃላቶቻችሁ በመለኮት ኃይል ከተደገፉበት ከከፍታ ግዛት ሆናችሁ ትንቀሳቀሳላችሁ::

የእርሱ ስልጣን አለን

በአንዱም በደል ሞት በአንዱ በኩል ከነገሠ፥ ይልቁን የጸጋን ብዛትና የጽድቅን ስጦታ ብዛት የሚቀበሉ በአንዱ በኢየሱስ

ክርስቶስ በኩል በሕይወት ይነግሣሉ (ሮሜ 5:17)።

ረቡዕ 1

Page 7: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ...ምሳሌ 24:10 በመከራ ቀን ተስፋ እንዳንቆርጥ ወይም እንዳንሸነፍ ይመክረናል፤ ይልቁኑ እኛ

Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org

ለተጨማሪ ጥናት:

የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

ሮሜ 6:1-14 & መዝሙረ ዳዊት 56-59

ኤፌሶን 5:1-8 & ትንቢተ ኢሳያስ 52

የሉቃስ ወንጌል 10:19 AMPC; 1ኛ ዮሐንስ 4:17

ኢየሱስ የተናገረው ቃል ሁሉ ተፈጽሟል፤ እርሱ ሁሉም ሥልጣን በሰማይም ሆነ በምድር ላይ ስላለው ተስፋ የሌላቸውን ሁኔታዎች ለወጠ፤ ለቤተክርስቲያን ማለትም ለእናንተ እና ለእኔ ተመሳሳይ ሥልጣንን ሰጠን:: በማቴዎስ 28:18-19 እንዲህ አለ፡- “…ሥልጣን ሁሉ በሰማይና በምድር ተሰጠኝ። እንግዲህ ሂዱና…”፤ ስለዚህ እያንዳንዱን በር በሚከፍተው በእርሱ ስም እንሄዳለን፡፡

ማንኛውንም የህይወታችሁን ሁኔታዎች በመለወጥ ከእግዚያብሔር ፍጹም ፍቃድ ጋር ማጣጣም የምትችሉበት ስልጣን እንዳላችሁ ተገንዘቡ:: ስለዚህ የስልጣንን ቃል ተናገሩና በሰዎች ህይወት ላይ ያለውን የሰይጣንን ተጽእኖ ስበሩ፤ እንዲሁም ይህ የከበረ የወንጌል ብርሃን በእነርሱ ላይ እንዲያበራ አድርጉ::

እኔ በሰይጣን፥ በጨለማ እና በአለም ላይ በመግዛት እመላለሳለሁ:: በክብር፥ በመግዛት እና በኃይል ከክርስቶስ ጋር ተቀምጫለሁ:: ብርሃኔ ከመቼውም በላይ በደማቅ ይበራል፤ እናም በክርስቶስ የህይወቴን አላማ በክብር እፈጽማለሁ፤ በኢየሱስ ስም:: አሜን::

ጸሎት

Page 8: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ...ምሳሌ 24:10 በመከራ ቀን ተስፋ እንዳንቆርጥ ወይም እንዳንሸነፍ ይመክረናል፤ ይልቁኑ እኛ

amharic

የእግዚአብሔር መንፈስ በሕይወታችን ከሚያደርገው ውብ ነገሮች መካከል አንዱ፣ ለመንፈሳችሁ መንፈሳዊ ነገርን ከማካፈል ባሻገር የዕለት ተዕለት ነገሮችን መረዳት እንድትችሉ ያደርጋችኋል:: 1ኛ ቆሮቶስ 12:8 እንዲህ ይላል፡- “ለአንዱ ጥበብን መናገር በመንፈስ ይሰጠዋልና፥ ለአንዱም በዚያው መንፈስ እውቀትን መናገር ይሰጠዋል::”

ከላይ ባለው ጥቅስ ላይ እውቀት የሚለው የግሪኩ ቃል “ግኖሲስ” የሚለው ሲሆን፣ ትርጉሙም በሳይንስ ወይም በአዕምሯዊ እንቅስቃሴ ላይ የተመሠረተ እውቀት ማለት ነው:: እግዚአብሔር በአዕምሯዊ እውቀት ልቀት እንዲኖራችሁ ሊያደርግ ይችላል:: ልእለ ተፈጥሯዊ የሆነ፣ በሳይንሳዊ ወይም በአዕምሮአዊ እውቀት ላይ የተመሰረተ፣ ሀሳብ ወይም ሳይንሳዊ እውቀት ሊሰጣችሁ ይችላል:: እንደ እግዚአብሔር ልጆች ይህንን በይበልጥ እንድናውቅ ያስፈልጋል::

የእግዚአብሔር መንፈስ የእውቀት መንፈስ መሆኑን የበለጠ ማወቅ አለብን፤ እርሱ ሁሉን ነገር ያውቃል:: ኢየሱስ ክርስቶስ የሁሉም ጥበብ እና እውቀት መገለጫ ነው (ቆላስይስ 2:3)፤ እፅዋትን፥ እንስሳትን እና በአለም ላይ ያለውን ነገር በሙሉ የሰራው እርሱ ነው (ቆላስያስ 1:16):: ስለዚህ ስለሰራቸው ነገሮች ሁሉ ሊያስተምራችሁ ይችላል::

ዓለም መፍትሄዎችን በመፈለግ ላይ ነው፤ እናም እግዚአብሔር ልጆቹ ለዓለም ችግሮች መፍትሄዎች እንዲሆኑ ይፈልጋል:: ከስራችሁ ጋር የተየያዙ እውነታዎችን በተመለከተ ያልተለመደ እይታን ሊሰጣችሁ ይችላል:: በቤታችሁ እየጸለያችሁ አለም በመጠባበቅ ላይ ላለው መፍትሄ የሚሆን እውቀት ልትቀበሉ ትችላላችሁ፤ በእግዚአብሔር መንፈስ

እርሱ እውቀትን ሊሰጣችሁ ይችላል

አብ በስሜ የሚልከው ግን መንፈስ ቅዱስ የሆነው አጽናኝ እርሱ ሁሉን ያስተምራችኋል እኔም የነገርኋችሁን ሁሉ

ያሳስባችኋል (ዮሐንስ 14:26)።

ሐሙስ 2

Page 9: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ...ምሳሌ 24:10 በመከራ ቀን ተስፋ እንዳንቆርጥ ወይም እንዳንሸነፍ ይመክረናል፤ ይልቁኑ እኛ

Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org

ለተጨማሪ ጥናት:

የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

ሮሜ 6:15-7:1-6 & መዝሙረ ዳዊት 60-63

ኤፌሶን 5:9-16 & ትንቢተ ኢሳያስ 53

መጽሀፈ ምሳሌ 2:5; መጽሀፈ ምሳሌ 8:10-12; ቆላስያስ 1:9-10

በተካፈላችሁት እውቀት፣ ተፈጥሮአዊ የሆኑ ነገሮችን የማስረዳት ችሎታ እንዳላችሁ ታውቃላችሁ:: ዓለማችሁን የሚቀይር ሀሳቦችን ከእርሱ ልትቀበሉ ትችላላችሁ:: ማድረግ የሚያስፈልጋችሁ ነገር ቢኖር፣ ከእርሱ ጋር ለመስራት እራሳችሁን መስጠት ብቻ ነው::

ውድ አባት ሆይ፥ በህይወቴ ውስጥ ምሥጢራትን እና የተሰወረውን እንዳውቅ ለሚያደርገኝ፥ በሚያስደንቁ የፈጠራ ግኝቶች፣ መንፈሴን ለሚሞላው እና ለመንፈሴ ለሚያካፍለው ውድ የመንፈስ ቅዱስ አገልግሎት እውቅና ሰጣለሁ:: እኔ ከእርሱ የተማርኩ ነኝ፤ ስለዚህ ሁሉንም ነገር አውቃለሁ:: ሃሌሉያ!

የእምነት አዋጅ

Page 10: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ...ምሳሌ 24:10 በመከራ ቀን ተስፋ እንዳንቆርጥ ወይም እንዳንሸነፍ ይመክረናል፤ ይልቁኑ እኛ

amharic

2ኛ ጢሞቴዎስ 2:3 እንዲህ ይላል፡- “እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ በጎ ወታደር ሆነህ፥ አብረኸኝ መከራ ተቀበል::” በተለያዩ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች ውስጥ የተለያዩ ቃላት ትዕግስት ተብለው ተተርጉመዋል:: ነገር ግን ትዕግስት ለሚለው ቃል በጣም የተሻለው ተመሳሳይ ቃል፣ “ጽናት” የሚለው ነው፤ በመከራ ውስጥ ታጋሽ የመሆን ብቃት ማለትም ተስፋ በማድረግ መከራን በጽናት መቋቋምን ያስረዳል:: ይህም ማለት ሁልጊዜም እንደምታሸንፉ በማወቅ፣ ማንኛውንም ተቃውሞ ሳትናወጡ ለመጋፈጥ ትችላላችሁ ማለት ነው::

ምሳሌ 24:10 በመከራ ቀን ተስፋ እንዳንቆርጥ ወይም እንዳንሸነፍ ይመክረናል፤ ይልቁኑ እኛ ባገኘነው ድል መጽናት ይኖርብናል:: ምናልባት እምነታችሁን በማሳደግ የመጀመሪያ ደረጃ ላይ ልትሆኑ ትችላላችሁ፤ እናም ነገሮች በጣም አስቸጋሪ እና ፈታኝ ሊመስሉ ይችላሉ፤ ነገር ግን በቃሉ ላይ እምነት ይኑራችሁ:: ታገሱ እና በህይወታችሁ እና በሁኔታዎቻችሁ ላይ ቃሉ እንዲሰራ ጊዜ ስጡት:: ጽኑ:: ያ ሁኔታ ለምስክርነታችሁ ነው!

በሚያምኑት ነገር ላይ እንዴት መጽናት እንዳለባቸው የማያውቁ አንዳንድ ሰዎች አሉ:: ለምሳሌ ስለ እምነታቸው ሲተቹ፣ ተስፋ ወደ መቁረጥ ያዘነብላሉ፤ ያ ስህተት ነው! እንደዚህ ዓይነት ትችቶችን ተቋቋሙ፤ ምክንያቱም እነሱ ለእናንተ እድገት የተቀረጹ ናቸው:: አንድ የሥራ ባልደረባችሁ ከክርስትና ጋር የተቃረነ አስተያየት ስለሰጠ ብቻ፣ እምነታችሁን አትተዉ:: ይልቁኑ ከክርስቶስ ጋር ባላችሁ ማንነት እና ህብረት ኩራት ይሰማችሁ:: ነፍሳትን ማዳን ቀጥሉ::

አሁን የሚቀልዱባችሁ ሰዎች በህይወታችሁ ያለውን የእግዚአብሔርን ክብር እና ኃይል የሚመለከቱበት ጊዜ ሩቅ አይደለም:: ስለዚህ አሁን

“በመከራ ጊዜ ትዕግስተኛ”

በተስፋ ደስ ይበላችሁ፤ በመከራ ታገሡ፤ በጸሎት ጽኑ (ሮሜ 12:12)።

አርብ 3

Page 11: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ...ምሳሌ 24:10 በመከራ ቀን ተስፋ እንዳንቆርጥ ወይም እንዳንሸነፍ ይመክረናል፤ ይልቁኑ እኛ

Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org

ለተጨማሪ ጥናት:

የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

ሮሜ 7:7-25 & መዝሙረ ዳዊት 64-67

ኤፌሶን 5:17-24 & ትንቢተ ኢሳያስ 54

መጽሀፈ ምሳሌ 24:10; ገላትያ 5:22 NIV; ዕብራውያን 10:35-36

በሚያጋጥማችሁ ፈተና ወይም ተግዳሮት ታገሡ:: ጌታ ኢየሱስ በሉቃስ 21:19 ላይ እንዲህ አለ፡- “በመታገሣችሁም ነፍሳችሁን ታገኛላችሁ።” መቼም ልትሽነፉ ወይም ልትተቁ እንደማትችሉ በማወቅ፣ ተስፋ በማድረግ ተግዳሮቶችን ታገሡ:: በሙሉ እምነት ከፊታችሁ የተሻለ እና ብሩህ ቀን እንዳለ ተስፋ አድርጉ! ያንን የድል እና የስኬት ምስል በአዕምሯችሁ ፍጠሩ እና በዚያ ላይ ጸንታችሁ ቁሙ::

ውድ አባት ሆይ፥ በክርስቶስ ስላለኝ አስደናቂ ልቀት፥ ስልጣን እና ኃይል አመሰግንሃለሁ:: በልዩ ልዩ ፈተናዎች ሳልፍ እንደ ሙሉ ደስታ እቆጥረዋለሁ፤ ምክንያቱም እኔ ማን እንደሆንኩ አውቃለሁ፥ እኔ በማንኛውም ግፊቶች እና አሉታዊ ሁኔታዎች የማልናውጥ ፥ አስቀድሞ ለመግዛት፥ ለማሸነፍ፥ እና ለልቀት የተሰራሁ በህይወት አሸናፊ ነኝ፤ በኢየሱስ ስም:: አሜን::

ጸሎት

Page 12: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ...ምሳሌ 24:10 በመከራ ቀን ተስፋ እንዳንቆርጥ ወይም እንዳንሸነፍ ይመክረናል፤ ይልቁኑ እኛ

amharic

የጳውሎስን ቃላት አመራረጥ በጥንቃቄ እንድታስተውሉ እፈልጋለሁ፤ እንዲህ ብሏል፡- “…ከመታወቅም የሚያልፈውን የክርስቶስን ፍቅር ለማወቅ ትበረቱ ዘንድ::” እንዴት ከመታወቅ የሚያልፍን ነገር ልታውቁ ትችላላችሁ? እዚህ ላይ ሁለት አይነት እውቀቶችን ማለትም የመገለጥ እውቀትን እና የሳይንሳዊ እውቀትን ልዩነት አስቀመጠ:: ከላይ የተጠቀሰው “ማወቅ” የሚለው ቃል የተተረጎመው “ጊኖስኮ” ከሚለው ቃል ሲሆን ትርጉሙም በመገለጥ የሚገኝ እውቀት ማለት ነው::

ሐዋሪያው ጳውሎስ “ከመታወቅ “ ተብሎ ለተተረጎመው ቃል “ግኖሲስ” የሚል የተለየ የግሪክ ቃል ተጠቀመ፥ ይህም ማለት በሳይንስ ወይም በአዕምሯዊ መረዳት ላይ የተመሰረተ እውቀት ነው:: ይህ በአካላዊ ስሜት የሚገኝ እውቀት ነው:: የክርስቶስን ፍቅር መረዳት ከሳይንሳዊ ወይም ከአዕምሯዊ እውቀት ያለፈ ነው፤ የክርስቶስን ፍቅር ለመረዳት የመንፈስ ቅዱስ መገለጥን ይጠይቃል::

በሳይንስ ውስጥ ፍፁም የሆነ መረዳት የለም፤ የሳይንስ ሁሉም ሕጎች የተመሠረቱት በንድፈ ሀሳቦች እና በግምቶች ነው:: ነገር ግን በመገለጥ እውቀት ውስጥ ግምቶች የሉም:: ሳይንስ ኢየሱስ ክርስቶስ በጎልጎታ መስቀል ላይ ያሳየውን ፍቅር ሊያስረዳችሁ አይችልም::

የትኛውንም የዚህ አለም መጽሐፍ ብታጠኑ፣ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ሞት፥ መቀበር እና ትንሳኤ አስፈላጊነት መቼም ልታውቁ አትችሉም:: ምናልባት ስለ ክስተቱ ልታውቁ ትችላላሁ፥ ምናልባትም በመስቀል ላይ የተከናወነውን ማብራራት ትችሉ ይሆናል፤ ነገር ግን ለእናንተ ሊሰጣችሁ

ከስሜታችሁ ባለፈ እርሱን ማወቅ

…ከመታወቅም የሚያልፈውን የክርስቶስን ፍቅር ለማወቅ ትበረቱ ዘንድ፥ እስከ እግዚአብሔርም ፍጹም ሙላት

ደርሳችሁ ትሞሉ ዘንድ (ኤፌሶን 3:18-19)።

ቅዳሜ 4

Page 13: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ...ምሳሌ 24:10 በመከራ ቀን ተስፋ እንዳንቆርጥ ወይም እንዳንሸነፍ ይመክረናል፤ ይልቁኑ እኛ

Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org

ለተጨማሪ ጥናት:

የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

ሮሜ 8:1-17 & መዝሙረ ዳዊት 68-69

ኤፌሶን 5:25-33 & ትንቢተ ኢሳያስ 55

1ኛ ቆሮንጦስ 2:14; ፈልጵሱዮስ 3:8-10

የሚችለው በእግዚአብሔር ቃል መገለጥ ብቻ ስለሆነ፣ ልትረዱት አትችሉም::

የመክፈቻ ጥቅሳችን እንዲህ ተብሎ ሊጻፍ ይችላል “…ከጊኖስስ የሚያልፈውን የክርስቶስን ፍቅር ለጊኖስኮ ትበረቱ ዘንድ…”፤ ይህም ማለት የክርስቶስን ፍቅር ከስሜታችሁ እና በሰው ከተሰጡ ትርጉሞዎች ባለፈ ማለትም በመገለጥ ማወቅ ማለት ነው:: ለብዙ ዓመታት ክርስቲያን ወይም ሰባኪ የሆናችሁ ቢሆንም እንኳን፣ አሁንም የእግዚአብሔር ፍቅር ምን እንደሆነ ላትረዱ ትችላላችሁ::

የእኛ ጥሪ የእግዚኣብሔርን ፍቅር ማወቅ እና መግለፅ ነው:: በህይወታችችሁ ካሉት የመንፈስ ቅዱስ አገልግሎቶች መካከል አንዱ፣ ይህንን የመገለጥ እውቀት ለእናንተ መስጠት ነው፤ ቃሉን ያስተምራችኋል፤ እንዲሁም ለመንግሥቱ ሚስጢራት እና የተሰወሩ ነገሮች መገለጥን ይሰጣችኋል:: ስለዚህ በእርሱ ላይ መደገፍ እና ቃሉን ስታጠኑ እርሱ ሊያስተምራችሁ እና ቃሉን ሊገልጥላችሁ ከእናንተ ጋር እንዳለ ማረጋገጥ በጣም አስፈላጊ ነው::

ውድ አባት ሆይ፥ እውነተኛ እውቀት በቃልህ ውስጥ ብቻ እንደሚገኝ እንድመለከት ዓይኖቼን ስለከፈትክ አመሰግንሃለሁ:: ዳግም በመወለዴ፣ መለኮታዊ በሆነ መነቃቃት በአንተ ሙላት ውስጥ እንድመላለስ ወደሚያደርገኝ ወደዚህ ልዩ እውቀት ገብቻለሁ፤ በኢየሱስ ስም:: አሜን::

ጸሎት

Page 14: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ...ምሳሌ 24:10 በመከራ ቀን ተስፋ እንዳንቆርጥ ወይም እንዳንሸነፍ ይመክረናል፤ ይልቁኑ እኛ

amharic

ምንም እንኳን በዓለም ዙርያ ችግር፥ ስቃይ እና የክፋት መስፋፋት ቢኖርም፣ እናንተ ግን የሚያስፈራችሁ ምንም ነገር የለም፤ ምክንያቱም የምትኖሩት በክርስቶስ ውስጥ ነው:: መዝሙር 91:1 እንዲህ ይላል፡- “በልዑል መጠጊያ የሚኖር ሁሉን በሚችል አምላክ ጥላ ውስጥ ያድራል።” ጌታ ሕዝቡን ይጠብቃል፥ ይንከባከባል:: በክርስቶስ እኛ መቼም ቢሆን ፈጽሞ ተጎጂ አይደለንም፤ ፈጽሞ ልንሆንም አንችልም፤ እኛ አሽናፊ እንጂ ተጎጂ አይደለንም፤ ጌታ ኢየሱስ በዚህ የሚናወጥ ዓለም ውስጥ ሰላም እና ደኅንነትን አረጋግጦልናል::

የጌታን እጅግ የሚያጽናና ንግግር በዮሐንስ 16:33 ላይ አንብቡ፤ እንዲህ ብሏል፤- “በእኔ ሳላችሁ ሰላም እንዲሆንላችሁ ይህን ተናግሬአችኋለሁ። በዓለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ፤ ነገር ግን አይዞአችሁ፤ እኔ ዓለምን አሸንፌዋለሁ።” እርሱ ለእናንተ አለምን አሽንፎ ድሉን ስጥቷችኋል:: በሰይጣን፥ በሁኔታዎች እና በዓለም ላይ የበላይነት አላችሁ:: ዓለም ውስጥ ችግር እና ፈተና ቢኖርም እኛ ግን በእርሱ ሰላም፥ ማረጋገጫ፥ ደኅንነት እና ጥበቃ አለን (ዮሐንስ 16:33)::

መንፈሳዊ ስፍራችሁ ክርስቶስ ነው፥ የመኖሪያ ስፍራችሁ ያ ነው:: ስለዚህ እናንተ ሁሉን ቻይ ከሆነው ከእግዚአብሔር ጥበቃ ጥላ ስር ናችሁ:: ሐዋሪያው ጳውሎስ በመንፈስ ይህን ነግሮናል፡- “ስለዚህ ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው . . .” (2ኛ ቆሮንቶስ 5:17):: ክርስቶስ የመኖርያ ስፍራችሁ መሆኑን የሚያሳየንን “በክርስቶስ” የተሰመረበትን የሚለውን ቃል አስተውሉ፥:: ክርስቶስ ማለትም ሰው የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ ስብዕና ያለው ነው፤ በተጨማሪም ክርስቶስ በእግዚአብሔር ውስጥ ስፍራ ነው::

ደፋር እና ጠንካራ ሁኑ፥ መፍራትን እምቢ በሉ:: የምትኖሩት በክርስቶስ

በእርሱ ውስጥ ትኖራላችሁ

አቤቱ፥ አንተ ለትውልድ ሁሉ መጠጊያ ሆንህልን (መዝሙር 90:1)።

እሁድ 5

Page 15: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ...ምሳሌ 24:10 በመከራ ቀን ተስፋ እንዳንቆርጥ ወይም እንዳንሸነፍ ይመክረናል፤ ይልቁኑ እኛ

Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org

ለተጨማሪ ጥናት:

የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

ሮሜ 8:18-39 & መዝሙረ ዳዊት 70-73

ኤፌሶን 6:1-9 & ትንቢተ ኢሳያስ 56

ትንቢተ ኢሳያስ 43:2; የዮሐንስ ወንጌል 16:33; ቆላስያስ 3:2-3

ውስጥ ነው፤ ስለዚህ ከጉዳት፥ ከክፋት እና ከጥፋት የተጠበቃችሁ ናችሁ:: በእርሱ ውስጥ ትኖራላችሁ፥ ትንቀሳቀሳላችሁ፤ ማንነታችሁም በእርሱ ውስጥ ነው:: እርሱ በመዝሙር 91: 7 ላይ እንዲህ ይላችኃል፡- “በአጠገብህ ሺህ በቀኝህም አሥር ሺህ ይወድቃሉ ወደ አንተ ግን አይቀርብም።”፡፡

ክርስቶስ በእኔ ውስጥ የህይወቴ ክብር ነው፥ እኔ በህይወት እገዛላሁና እመራለሁ:: መለኮታዊውን የክብር እና የድል ሁኔታ ተሸክሜ በውስጡ እኖራለሁ:: እኔ ስመጣ ጨለማ ይሽሻል፤ ምክንያቱም እኔ በጨለማው ዓለም ውስጥ ብርሃን ነኝ:: እግዚአብሔር ይባረክ!

የእምነት አዋጅ

Page 16: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ...ምሳሌ 24:10 በመከራ ቀን ተስፋ እንዳንቆርጥ ወይም እንዳንሸነፍ ይመክረናል፤ ይልቁኑ እኛ

amharic

ክርስትና የምትናገሩትን የምታገኙበት የእምነት ህይወት ነው:: እናምናለን ስለዚህም እንናገራለን:: በሁኔታዎች ሳይሆን በቃሉ ላይ ባለን እምነት እንናገራለን::

በዮናስ 2:1-4 ላይ ዮናስ የተናገረውን የሚያበነሳሳ አነጋገር ያስታውሰናል:: ዮናስ በችግር ውስጥ ነበር፤ ነገር ግን የእምነት አዋጁን አንብቡ፡- “…በዓሣው ሆድ ውስጥ ሆኖ ወደ አምላኩ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፥ እንዲህም አለ፦ በመከራዬ ሳለሁ ወደ አምላኬ ወደ እግዚአብሔር ጮኽሁ፥ እርሱም ሰማኝ በሲኦልም ሆድ ውስጥ ሆኜ ጮኽሁ፥ ቃሌንም አዳመጥህ። ወደ ጥልቁ ወደ ባሕሩ ውስጥ ጣልኸኝ፥ ፈሳሾችም በዙሪያዬ ነበሩ ማዕበልህና ሞገድህ ሁሉ በላዬ አለፉ።”

ዮናስ እንደዚያ ባለ አስጨናቂ ሁኔታ ውስጥ ቢሆንም፣ የጸሎቱን ይዘት አስቡት፥ እግዚአብሔር ወደ ነነዌ እንዲሄድ እና ቃሉን እንዲናገር ያዘዘውን ከጣሰ በኋላ፣ አንድ ትልቅ ዓሣ ውጦት ነበር:: በዓሣው ሆድ ውስጥ ሆኖ ተስፋ መቁረጥን አሻፈረኝ አለ፤ ይልቁኑም ድሉን ተነበየ:: “ወደ ቅዱስ መቅደስህ ደግሞ እመለከታለሁ!” አለ::

ይህ ትንቢታዊ ጸሎት ነው፤ በመንፈስ ቅዱስ በመነሳሳት የእግዚአብሔርን ፍቃድ እውን ለማድረግ እንዲህ ዓይነት ጸሎት መጸለይ ለእግዚአብሔር ህዝቦች አስፈላጊ ነው:: በመቀጠል ዮናስ በዓሳ ሆድ ውስጥ ሳለ የተናገረውን ትንቢታዊ ቃል አስተውሉ፤- “…ከንቱነትንና ሐሰትን የሚጠብቁ ምሕረታቸውን ትተዋል። እኔ ግን በምስጋና ቃል እሠዋልሃለሁ የተሳልሁትንም እከፍላለሁ። ደኅንነት ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው” (ዮናስ 2: 8-9)።

ይህንን እያነበባችሁ “መልካም፤ ዮናስ ይህን የተናገረው ከዓሣ

ድላችሁ እና ነጻ መውጣታችሁን አውጁ

ነገር ግን። አመንሁ ስለዚህም ተናገርሁ ተብሎ እንደ ተጻፈ ያው አንዱ የእምነት መንፈስ ስላለን፥ እኛ ደግሞ እናምናለን

ስለዚህም እንናገራለን (2ኛ ቆሮንቶስ 4:13)።

ሰኞ 6

Page 17: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ...ምሳሌ 24:10 በመከራ ቀን ተስፋ እንዳንቆርጥ ወይም እንዳንሸነፍ ይመክረናል፤ ይልቁኑ እኛ

Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org

ለተጨማሪ ጥናት:

የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

ሮሜ 9:1-29 & መዝሙረ ዳዊት 74-77

ኤፌሶን 6:10-20 & ትንቢተ ኢሳያስ 57

መዝሙረ ዳዊት 27:1-3; መዝሙረ ዳዊት 91:2; ሮሜ 4:17; Mark 11:23

ሆድ ውስጥ ከወጣ በኃላ ነው” ብላችሁ ልታስቡ ትችላላችሁ፥ እንደዚያ አይደለም:: እርሱ እነኛን ቃላቶች የተናገረው ገና በዓሳው ሆድ ውስጥ እያለ ነበር:: ሁኔታዎችን ከተመለከተ፣ የእግዚአብሔርን ምህረት እንዲረሳ እንደሚያደርገው ያውቅ ነበር:: እግዚአብሔር አዳኝ እና ታዳጊ መሆኑን ተገንዝቧል፤ ስለሆነም፣ ትኩረቱን በችግሩ ላይ ማድረግን አሻፈረኝ አለ::

ስለሆነም፣ በችግር ውስጥ እያለ ዮናስ ነጻ ስላወጣው እግዚአብሔርን ማመስገን ጀመረ:: እርሱ የእግዚአብሔርን ቃል የተረዳ የእግዚአብሔር ነብይ ነበር:: እግዚአብሔር የሌለውን እንዳለ አድርጎ እንደሚጠራ ያውቅ ነበር (ሮሜ 4:17)::

አሁን ባላችሁበት መልካም ያልሆነ ሁኔታ አትናወጡ፥ የማጣት ወይም የተጓደለ የጤና ሁኔታ አሉታዊ ምልክቶች ላይ አታተኩሩ፥ የድላችሁን ትንቢት ተናገሩ:: ቃሉን አውጁ:: ተስፋ-ቢስ በሚመስል ሁኔታ ውስጥ ጌታን አምልኩ:: እንዳሸነፋችሁ አውጁ፥ ነጻ ስለ መውጣታችሁ እና ስለ ድላችሁ አመስግኑት::

ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል በልቤ እና በአፌ ውስጥ ነው፥ በእርሱ ድል አደርጋለሁ:: በአፌ ውስጥ ያለው የእግዚአብሔር ቃል ማለት እግዚአብሔር እየተናገረ ነው ማለት ነው! በማያቋርጥ ድል ውስጥ እየተመላለስኩ፣ በቃሉ ስለምኖር፣ ለእኔ ምንም የማይቻል የለም፤ በኢየሱስ ስም:: አሜን::

ጸሎት

Page 18: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ...ምሳሌ 24:10 በመከራ ቀን ተስፋ እንዳንቆርጥ ወይም እንዳንሸነፍ ይመክረናል፤ ይልቁኑ እኛ

amharic

አንዳንድ ክርስቲያኖች የራሳቸውን ኃላፊነት የእግዚአብሄር ሃላፊነት ለማድረግ ይሞክራሉ፡፡ በብዛት አንድ ደስ የማይል ነገር ሲፈጠር “የእግዚአብሄር ፈቃድ ነው፣ ባይሆን ኖሮ እንዴት እንዲህ እንዲሆን ይፈቅዳል?” ብለው ይደመድማሉ፡፡ እንደነዚህ አይነት ሰዎች በዚህ ምድር ላይ ነገሮችን የመቀየር እንዲሁም ህይወታችንን እንደፈለግነው ውብ የማድረግ ስልጣን ለእኛ መሰጠቱን ማወቅ ይገባቸዋል፡፡ በእግዚአብሄር ቃል መሰረት በመኖር ህይወታችሁን አድደናቂ ማድረግ ትችላላችሁ፡፡

በማቴዎስ 17፡20፣ ጌታ ኢየሱስ በአጽንዖት እንዲህ ብሏል፡- “…እውነት እላችኋለሁ የሰናፍጭ ቅንጣት የሚያክል እምት ቢኖራችሁ ይህንን ተራራ ከዚህ ወደዚ እለፍ ብትሉት ያልፋል የሚሳናችሁም ነገር የለም”፡፡ በእግዚአብሄር ቃል ላይ ያላችሁን እምነት በሥራ ላይ በማዋል፣ የራሳችሁን የድል ህይወት መፍጠር እንደምትችሉ ግልጽ አድርጓል፡፡ እርሱ አስቀድሞ የምትፈልጉትን ለውጥ ለማምጣት የሚችል የእምነት መጠን ሰጥቷችኋል፡

በማርቆስ 9፡23፣ እርሱ እንዲህ ብሏል፡- “…ለሚያምን ሁሉም ይቻላል”፡፡ ጥያቄው ታምናላችሁ ወይ? ነው፡፡ ካመናችሁ ከፊታችሁ ማለቂያ የሌላቸው የሚቻሉ ነገሮች ያሉበት ህይወት አለ፡፡ ቃሉን በህይወታችሁ እንዲሰራ አድርጉና፣ ሁልግዜም ድል አድራጊ ትሆናላችሁ፡ ቃሉ በህይወታችሁ እስኪፈጸም አትጠብቁ፤ ይልቁኑ ቃሉን የምትሰሩት እናንተ ናችሁ፡፡

ፊልጵስዮስ 2፡12 “…በፍርሃትና በመንቀጥቀጥ የራሳችሁን መዳን ፈጽሙ” ይላል፡፡ ቃሉን በህይወታችሁ ፈጽሙና ውጤት እንዲያመጣ አድርጉት፡፡ እምነታችሁን በመጠቀም መሆን የምትፈልጉትን መሆን ትችላላችሁ፤ መለወጥ የምትፈልጉትን ነገር ትለውጣላችሁ፤ ማድረግ

ቃሉን “አድርጉ”

እያንዳንዱ የገዛ ራሱን ሸክም ሊሸከም ነውና (ገላቲያ 6፡5)።

ማክሰኞ 7

Page 19: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ...ምሳሌ 24:10 በመከራ ቀን ተስፋ እንዳንቆርጥ ወይም እንዳንሸነፍ ይመክረናል፤ ይልቁኑ እኛ

Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org

ለተጨማሪ ጥናት:

የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

ሮሜ 9:30-10:1-21 & መዝሙረ ዳዊት 78

ኤፌሶን 6:21-24 & ትንቢተ ኢሳያስ 58

የማርቆስ ወንጌል 11:23; Á°qw 1:22-25

የምትፈልጉትንም ታደርጉታላችሁ! በእግዚአብሄር መንግስትም ውስጥ፣ እምነት ገንዘባችን እና “የማድረግ ሃይል “ ነው፡፡

እግዚአብሄር አስቀድሞ በህይወታችሁ ያሉትን ነገሮች በመቀየር ከእርሱ ፍጹም ፍቃድ ጋር እንዲጣጣሙ በማድረግ የድል ህይወት ለመፍጠር እንድትችሉ የበላይነትንና ስልጣኑን ሰጥቷችኋል፡፡ በቃሉ መኖር ቀጥሉና፤ የእግዚአብሄር ክብርም በምታደርጉት ነገር ሁሉ ይገለጣል፡፡

ክርስቶስ ህይወቴ እና የሚያስፈልገኝ ሁሉ ነው፡፡ ስለዚህ ህይወቴ ማለቂያ የሌለው ክብር፣ ደስታ፣ ድል፣ ስኬት እና ማድረግ በምችላቸው ነገሮች የተሞላ ነው! ሃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን ማድረግ እችላለሁ፡፡ ለእኔ የማይቻል ነገር የለም፤ እኔ በክርስቶስ የማምን ነኝ፣ በመሆኑም እኔ ሁሉም ነገር አለኝ!ሃሌሉያ!

የእምነት አዋጅ

Page 20: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ...ምሳሌ 24:10 በመከራ ቀን ተስፋ እንዳንቆርጥ ወይም እንዳንሸነፍ ይመክረናል፤ ይልቁኑ እኛ

ከጭንቀት ነጻ የሆነ ሥፍራ?ሃዘንተኛ እና እረፍት አልባ የሆኑ ብዙ ሰዎች ባሉበት በዚህ ዓለም፣ ከጭንቀት ነጻ የሆነ ሥፍራ ሊኖር ይችላል? በሚገባ! በማቴዎስ 11፡28 ላይ ጌታ ኢየሱስ እንዲህ ብሏል፡- “እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ።” በክርስቶስ ውስጥ ከሆናችሁ፤ ሰዎችን ከሚደብቱ ትግሎች፤ ጭንቀቶችና መከራዎች ነጻ በሆነ፤ የእረፍት፣ የደስታ እና የክብር ሥፍራ ውስጥ ትኖራላችሁ፡፡ አንዳንድ ሰዎች መጨነቅ ይወዳሉ፡፡ መጨነቅ ማለት ኃላፊነትን የመውሰድ ምልክት አድርገው ስለሚያስቡ፤ ስለ ስራቸው፣ ገንዘባቸው፣ ጤናቸው፣ የትዳር አጋሮቻቸው እና ሌሎችም ብዙ ነገሮች ይጨነቃሉ፡፡ ያ የክርስቲያን ህይወት አይደለም፡፡ በህይወታችሁ ስለ ማንኛውም ነገር ወይም ሁኔታ በፍጹም መጨነቅ የለባችሁም፡፡ ጭንቀት ስለእናንተ በስራ ላይ ያለውን የእግዚአብሄርን ኃይል ያቋርጠዋል፡፡ እግዚአብሄር ለእናንተ ያለው መሻት፤ ከመጨነቅ ይልቅ፤ ምንም ዓይነት ሁኔታዎች ቢጋረጡባችሁ፤ በቀን ሃያ አራት ሰዓት ሙሉ በሐሴት እንድትሞሉ ነው፡፡ እግዚአብሄር ከእናንተ የሚጠብቀው፤ በተግዳሮቶች ውስጥም ሆናችሁ እንድትደሰቱ ነው! ፊሊጵስዮስ 4፡4 እንዲህ ይላል፡- “ሁልጊዜ በጌታ ደስ ይበላችሁ፤ ደግሜ እላለሁ፥ ደስ ይበላችሁ።” ሁሉ ነገር መልካም ሲሆን ብቻ ሳይሆን፤ በመከራዎች መካከል እንኳን ደስተኛ መሆን ይገባችኋል፡፡ ምንም ነገር ሊያስጨንቃችሁ አይገባም፡፡ በምንም ነገር መቼም ቢሆን ተስፋ የቆረጠና ግራ የገባው ገጽታ አይታይባችሁ፡፡ በመጥፎ ስሜት ተውጣችሁ ቀኑን አትዋሉ፡፡ ይልቁኑ፤ የጌታ ደስታ ብርታታችሁ እንደሆነ በማወቅ፤ በመንፈስ ቅዱስ ሳቁ፤ ተደሰቱም፡፡ ቃሉ የሚለውን አድርጉ፤ እርሱ ስለ እናንተ ያስባልና የሚያስጨንቃችሁን ሁሉ በእርሱ ላይ ጣሉት (1ኛ ጴጥሮስ 5፡7)።

Page 21: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ...ምሳሌ 24:10 በመከራ ቀን ተስፋ እንዳንቆርጥ ወይም እንዳንሸነፍ ይመክረናል፤ ይልቁኑ እኛ

Te ¨h

Te ¨

h

Page 22: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ...ምሳሌ 24:10 በመከራ ቀን ተስፋ እንዳንቆርጥ ወይም እንዳንሸነፍ ይመክረናል፤ ይልቁኑ እኛ

amharic

እንደ ክርስቲያን “ነገሮች የተጨናነቁ ናቸው፤ መጠንቀቅ አለብኝ፣ ብዙ ከሰጠሁና ካጠፋሁ ምንም ነገር አይቀርልኝም” አትበሉ፡፡ እንደዚህ አይነት አስተሳሰብ እራሳችሁን ወደ ጉዳትና የገንዘብ ቀውስ ወዳለበት ስፍራ ትወስዱታላች፡፡ ማጣትን አትናገሩ፤ ምክንያቱም እናንተ የአብርሃም ዘር ናችሁ፤ ሁሉም ነገር በክርስቶስ የእናንተ ነው፡- “እናንተም የክርስቶስ ከሆናችሁ እንኪያስ የአብርሃም ዘር እንደተስፋውም ቃል ወራሾች ናችሁ” (ገላቲያ 3፡29)፡፡

እግዚአብሄር፣ መንፈሳዊ አይኖቻችሁ ተከፍተው አለም ሁሉ የእናንተ እንደሆነ በምታዩበት ከፍተኛ የመንፈሳዊ ንቃተ ህሊና ውስጥ እንድትኖሩ ይፈልጋል፡፡ እራሳችሁን ሆን ብላችሁ በእግዚአብሄር ቃል ስትገነቡ፣ ለህይወትና እግዚአብሄርን ለመምሰል የሚያስፈልገውን ነገር ሁሉ አስቀድሞ እንደሰጣችሁ ታስተውላላችሁ፡፡ በቃሉ ብርሃን እየተመላለሳች፣ የእራሳችሁ የሆኑትን ነገሮች ያዙ፡፡

ቃሉ በሚናገረው፣ በክርስቶስ ኢየሱስ የእናንተ በሆነው የመንግስቱ መብቶች፣ ጥቅሞች እና ርስቶች፤ ንቃተ ህሊና ተመላለሱ፡፡ “እግዚአብሄር እረኛዬ ነው፤ ስለዚህ ማጣትን እንቢ እላለሁ፤ የእድል በሮች ለእኔ ተከፍተዋል፤ እኔ ተባርኬያለሁ፤ በክርስቶስ ኢየሱስ የእግዚአብሄር የክብር ባለጠግነት የሚያስፈልጉኝ ነገሮች ሁሉ ተትረፍርፈው ቀርበውልኛል “ ብላችሁ አውጁ፡፡

የእግዚአብሄር ፍቃድና የጠራችሁ የተትረፈረፈ ህይወት እርግጠኝነት፣ በመክፈቻ ጥቅሳችን በግልጽ ተገልጧል፡፡ ሁልጊዜም፣ በሁሉም ሁኔታዎች፣ ፍላጎታችሁ ምንም ይሁን ምን፣ በበቂ ሁኔታ ምንም እርዳታ ሳያስፈልጋችሁ

የአቅርቦትና የመትረፍረፍ ንቃተ ህሊና ይኑራችሁ

በተነ ለምስኪኖች ሰጠ ጽድቁ ለዘላለም ይኖራል ተብሎ እንደተጻፈ እግዚአብሄር ሁል ጊዜ በነገር ሁል ብቃትን

ሁሉ አግኝታችሁ ለበጎ ስራ ሁሉ ትበዙ ዘንድ ጸጋን ሁሉ ሊያበዛላችሁ ይችላል (2ቆሮ 9፡8)፡፡

ረቡዕ 8

Page 23: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ...ምሳሌ 24:10 በመከራ ቀን ተስፋ እንዳንቆርጥ ወይም እንዳንሸነፍ ይመክረናል፤ ይልቁኑ እኛ

Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org

ለተጨማሪ ጥናት:

የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

ሮሜ 11:1-24 & መዝሙረ ዳዊት 79-81

ፈልጵሱዮስ 1:1-8 & ትንቢተ ኢሳያስ 59

2ኛ ቆሮንጦስ 8:9; ፈልጵሱዮስ 4:19; መዝሙረ ዳዊት 23:1

እና ለሁሉም መልካም ሥራና በጎነት የሚበቃ የተትረፈረፈ ነገር ኖሯችሁ፣ ራሳችሁን የቻላችሁ እንድትሆኑ፤ ሁሉም ጸጋ፣ ሁሉም ሞገስ፣ እና ምድራዊ በረከት በብዛት ወደእናንተ እንዲመጡ ይፈልጋል፡፡

በክርስቶስ ያላችሁ ህይወት ማለቂያ የሌለው አቅርቦትና መትረፍረፍ እንደሆነ እወቁ፣ እመኑ እና አውጁ፡፡ እግዚአብሄር ለልጆቹ ስላለው የገንዘብ እቅድ፣ ማለትም ስለ አስራትና መባ፣ ዘር መዝራትና ማጨድ፣ መስጠትና መቀበል፤ ቃሉ ምን እንደሚል ተማሩ፡፡ ተለማመዷቸውና የእግዚአብሄር በረከት በህይወታችሁ ሲበዛ እዩ፡፡

ውድ ጌታ፣ አንተ እረኛዬ ነህ፤ ስለዚህ ላጣ አልችልም! በብልጽግናዬ ብርሃን እየተመላለስኩ ነው፤ ተነግሮ ወደማያውቅ ሃብት ገብቻለሁ! እጦት የህይወቴ አካል አይደለም፤ ምክንያቱም በክርስቶስ ሁሉም የእኔ ነው!

የእምነት አዋጅ

Page 24: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ...ምሳሌ 24:10 በመከራ ቀን ተስፋ እንዳንቆርጥ ወይም እንዳንሸነፍ ይመክረናል፤ ይልቁኑ እኛ

amharic

የእግዚአብሄር ቃል ለእኛ የተገለጠው ፍቃዱ ነው፤ ስለዚህ እንደ ፈቃዱ መጸለይ እንደ ቃሉ መጸለይ ማለት ነው፡፡ በእግዚአብሄር ቃል ሥልጣን መጸለይ፣ ብዙዎች የማይረዱትና የማይለማመዱት በጣም አስፈላጊ የጸሎት ይዘት ነው፡፡ ስንጸልይ፣ በቃሉ በኩል ከእግዚአብሄር በሚሰጠን መገለጥና ዕይታ ላይ የተመረኮዘ መሆኑ በጣም አስፈላጊ ነው። በእግዚአብሄር ቃል ላይ በመመርኮዝ፣ በጸሎት እምነታችንን መተግበር አለብን፤ ጉዳዩ በእግዚአብሄር ቃል ውስጥ የተካተተ ከሆነ፣ መልስን ለመቀበል በእምነት እንደፍራለን፡፡

በመክፈቻ ጥቅሳችን እንዳነበብነው እንደ ፈቃዱ ማለትም እንደ ቃሉ ስንጸልይ፣ ይሰማናል፡፡ አስራ አምስተኛው ቁጥር እንዲህ ይላል፡- “የምንለምነውን ሁሉ እንዲሰማን ብናውቅ ከእርሱ የለመንነውን ልመና እንደተቀበልን እናውቃለን፡፡” ይህ ማለት እንደፈቃዱ (እንደ ቃሉ) ስትጸልዩ፣ እርሱ ይሰማል፤ እናም ጸሎታችሁን ይመልሳል፡፡

አንዳንድ ሰዎች ሲጸልዩ፣ እየተናገሩት ያሉት ከእግዚአብሄር ቃል ጋር አብሮ መሄዱ ወይም አለመሄዱ ግድ ሳይላቸው፣ እንዲሁ ያወራሉ፡፡ ጸሎታችሁ ውጤታማ እንዲሆን፣ ከቃሉ ጋር የተጣጣመ መሆን አለበት። እንዲሁ በዘፈቀደ አትጸልዩ፤ ቃሉን ጸልዩ፡፡ በክርስቶስ ኢየሱስ ለእኛ የሰጠንን በሙሉ፣ እኛን ያደረገንን ሁሉ፣ እና እኛ ማድረግ የምንችለውን ሁሉ ለማሳየት፤ እግዚአብሄር አስቀድሞ ቃሉን ሰጥቷል ፡፡

ስለዚህ ስትጸልዩ ቃሎቻችሁ በክርስቶስ ከእርሱ መለኮታዊ አቅርቦት ጋር እስካልተጣጣመ ወይም እስኪጣጣም ድረስ፣ የምትጸልዩት በከንቱ ነው፡፡ ወደ እርሱ ስትጸልዩ፣ እምነት እንዲኖራችሁ፣ እንዴት መጠየቅ

ቃሉን መጸለይ

በእርሱ ዘንድ ያለን ድፍረት ይህ ነው፣ እንደ ፈቃዱ አንዳች ብንለምን ይሰማናል (1ኛ ዮሃ 5፡14)።

ሐሙስ 9

Page 25: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ...ምሳሌ 24:10 በመከራ ቀን ተስፋ እንዳንቆርጥ ወይም እንዳንሸነፍ ይመክረናል፤ ይልቁኑ እኛ

Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org

ለተጨማሪ ጥናት:

የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

ሮሜ 11:25-36 & መዝሙረ ዳዊት 82-84

ፈልጵሱዮስ 1:9-14 & ትንቢተ ኢሳያስ 60

መዝሙረ ዳዊት 27:1-6; የማቴዎስ ወንጌል 24:35; ትንቢተ ኤርምያስ 1:12

እንዳለብን፣ ወደ እርሱ ስትጸልዩ እምነት እንዲኖራችሁ፣ እንዴት መጠየቅ እንዳለብን፣ እንዴት መጸለይ እንዳለብን እና ጥያቄዎቻችን ምን ይዘት ሊኖራቸው እንደሚችል ገልጾልናል፡፡ የእግዚአብሄርን ቃል ስትማሩ ደግሞ እምነታችሁ ያድጋል፡፡ የበለጠ የእግዚአብሄርን ቃል ስታውቁ፣ የበለጠ እምነት ይኖራችኋል፤ እንዲሁም ጸሎታችሁ የበለጠ ትክክለኛ እና ፍሬያማ ይሆናል፡፡

ውድ አባት ሆይ፣ በቃልህ ከፍ ብያለሁ! በመለኮታዊ መንገድህ እና ለህይወቴ ባለህ ፍጹም ፍቃድ በእውነትህ ተቀይሬአለሁ፤ እመራለሁም፡፡ በቃልህ ስለምኖር፤ ዛሬ በጥንካሬ፣ በጤንነት እና በድል እመላለሳለሁ፤ በኢየሱስ ስም፡፡ አሜን፡፡

ጸሎት

Page 26: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ...ምሳሌ 24:10 በመከራ ቀን ተስፋ እንዳንቆርጥ ወይም እንዳንሸነፍ ይመክረናል፤ ይልቁኑ እኛ

amharic

በ2ኛ ዜና መዋዕል 20፡15 ላይ፣ ይሁዳ በጠላት ሃገር በተያዘችበት ጊዜ ንጉስ ኢዮሳፍጥ ያደረገውን የሚያነሳሳ ነገር እናነባለን፡፡ እሱና የይሁዳ ጦር ሙሉ በሙሉ በብዘት ተበልጠው ነበር፤ በእራሱም ቃል የይሁዳን ለጥቃት መጋለጥ ቢናገርም፣ በመጀመርያ ከእግዚአብሄር እርዳታን ሳይጠይቅ አልቀረም፡፡ እንዲህም ብሎ ጸለየ፡- “አምላካችን ሆይ አንተ አትፈርድባቸውም? ይህን የመጣብንን ታላቅ ወገን እንቃወም ዘንድ አንችልም፤ የምናደርገውንም አናውቅም፤ ነገር ግን አይኖቻችን ወደ አንተ ናቸው” (2ኛ ዜና መዋልእ 20፡12)፡፡

ከዚያም ቁጥር 14-17 አንድ የተዋበ ነገር ይነግረናል፤ እንዲህ ይላል፡- “የእግዚአብሄር መንፈስ ከአሳፍ ወገን በነበረው በሌዋዊው በማትያን ልጅ…መጣ…. እንዲህም አለ…..ሰልፉ የእግዚአብሄር ነው እንጂ የእነንተ አይደለምና ከዚህ ታላቅ ወገን የተነሳ አትፍሩ አትደንግጡም ነገ በነርሱ ላይ ውረዱ እነሆ በጺጽ አቀበት ይወጣሉ በሸለቆውም መጨረሻ በይሩኤል ምድበዳ ፊት ለፊት ታገጉአቸዋላችሁ፣ እናንተም በዚህ ሰልፍ የምትዋጉ አይደላችሁም ይሁዳና እየሩሳሌም ሆይ ተሰለፉ ዝም ብላችሁ ቁሙ የሚሆነውንም የእግዚአብሄርን መድሃኒት እዩ እግዚአብሄርም ከእናንተ ጋር ነውና አትፈሩ፣ አትደንግጡም ነገም ወጡባቸው”፡፡

ለኢዮሳፍጥ ከእግዚአብሄር ዘንድ የተሰጡ የሚያጽናኑና የሚያስተማምኑ ቃላቶች እነዚያ ነበሩ፡፡ ነገር ግን የጠላትን ወራሪ ጦር ለመጋፈጥ ዝግጁ ሆኖ፣ ኢዮሳፍጥ ያደረገውን ቀጣይ ነገር አስተውሉ፤ “ምህረቱ ለዘላለም ነውና እግዚአብሄርን አመስግኑ …” (2ኛ ዜና መዋዕል 20፡21)፣ እያሉ የቅድስናውን ውበት በማመስገን የሚዘምሩ፣ ለእግዚአብሄር ዘማሪዎችን አቆመ፡፡ ይህ የድል ዝማሬ ነበር፡፡

ወደ ጠላት ሠፈር እየዘመሩ ሲገሰግሱ፣ በ2ኛ ዜና መዋዕል 20፡22 ላይ መጽሃፍ ቅዱስ ሲናገር “ይሁዳን ሊወጉ ከመጡት በአሞንና በሞአብ ልጆች በኔይርም ተራራ ሰዎች ላይ እግዚአብሄር ድብቅ ጦርን አመጣባቸው፤ እነርሱም ሞቱ” ይላል፡፡ የይሁዳ ጦር ከዘማሪዎቹ በስተኋላ ሲደርስ፣ የጠላት

የድል ዝማሬ

…እግዚአብሄር እንዲህ ይላችኋል ሰልፉ የእግዚአብሄር ነው እንጂ የእናንተ አይደለምና…. (2ኛ ዜና መዋልእ 20፡15)።

አርብ 10

Page 27: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ...ምሳሌ 24:10 በመከራ ቀን ተስፋ እንዳንቆርጥ ወይም እንዳንሸነፍ ይመክረናል፤ ይልቁኑ እኛ

Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org

ለተጨማሪ ጥናት:

የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

ሮሜ 12:1-16 & መዝሙረ ዳዊት 85-88

ፈልጵሱዮስ 1:15-22 & ትንቢተ ኢሳያስ 61

መዝሙረ ዳዊት 149:1-6; 2ኛ ቆሮንጦስ 2:14-15 MSG

ተዋጊዎቹ እርስ በርስ ተጠፋፍተው አለቁ፡፡ ኢዮሳፍጥ ከጦሩ ጋር ካለውጊያ ምርኮውን ወሰደ! ይህ ያልተለመደ አካሄድ ሲሆን እኛም እንድንማርበት ነው፡፡

በከባድ ሁኔታዎች ውስጥ፣ ስንዘምርና ስናመልክ ለጠላታችን ሽንፈትን እንናገራለን፡፡ ተግዳሮታችሁን ምንም ያህል የከፋ ነው ብላችሁ ብታስቡም፤ ከድል ቃሉ በመነሳት፣ ጌታን አምልኩት፤ ዘምሩለትም፡፡ ጠላትና ችግሮች ጉልበት ቢኖራቸውም፣ ተስፋ አትቁረጡ! የድል ዝማሬ ዘምሩ፡፡

አባት ሆይ፣ በዚህ ምድር ላይ አሸናፊ ስላደረግከኝ፣ በድል ስላራመድከኝና አንደበቴንም በድል መዝሙር ስለሞላህ አመሰግንሃለሁ! በሃይል የተሞላሁ ነኝ፤ የህይወትን ተግዳሮቶች ለማሸነፍ ብቃት አለኝ፤ ለስምህ ክብርና ምስጋና ይሁን፤ በኢየሱስ ስም፡፡ አሜን፡፡

ጸሎት

Page 28: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ...ምሳሌ 24:10 በመከራ ቀን ተስፋ እንዳንቆርጥ ወይም እንዳንሸነፍ ይመክረናል፤ ይልቁኑ እኛ

amharic

ዳግም ስለተወለዳችሁ፣ የመንፈስ ቅዱስ ቤተመቅደስ ናችሁ፤ የእግዚአብሄርን ሃይል ትሸከማላችሁ፤ ታስተላልፋላቸሁም፡፡ ከጳውሎስ አካል በተወሰደው ልብስ ላይ የእርሱ ሃይል እንደተላለፈው ሁሉ (ሐዋ 19፡11-12)፣ ከእናንተ የሚመጣ ማንኛውም ነገር ወይም እናንተ የነካችሁት ነገር ሁሉ፣ የእግዚአብሄርን ሃይል ይካፈላል፡፡ በእንደዚያ ዓይነት መካፈል ውስጥ ደግሞ ትልቅ ብቃት ይመጣል፡፡

ከእናንተ ጋር ተነካክቶ፣ የመንፈስ ቅዱስ መገኘት በላዩ ላይ የማይቀር ምንም ነገር የለም፤ ምክንያቱም የእግዚአብሄርን መለኮታዊ መገኘት ትሸከማላችሁ፤ እናንተ እግዚአብሄርን የምትሸከሙ እቃዎች ናችሁ፡- “…እኛ የእግዚአብሄር ቤተመቅደስ ነንና እግዚአብሄርም ተናገረ እንዲህ ሲል በእነርሱ እኖራለሁ በመካከላቸውም እመላለሳለሁ …”(2ኛ ቆሮ 6፡16)፡፡ እናንተ የእግዚአብሄር ዋና መስርያ ቤት ማለትም የሚሰራበት ዋና ቦታ ናችሁ፤ የእርሱን ፍቅር በእናንተ በኩል ያሳያል፤ ይገልጣልም፡፡ የእርሱን ጸጋና መለኮታዊ መልካምነት አከፋፋዮች ናችሁ፤ መክፈቻ ጥቅሱን እንደገና አንብቡ፡፡

ለምሳሌ ቃሉን ካንድ ሰው ጋር እየተካፈላችሁ ከነበረ፣ በቃላችሁ ቅባቱን ወደዛ ሰው ልታስተላልፉ ትችላላችሁ፡፡ ፍቅሩ፣ ፍህራሄውና መገኘቱ ከእናንተ ወደነሱ ይፈሳል፤ የፍቅሩንና የጸድቁን ንቃተ ህሊናም ያመጣላቸዋል፡፡

በጌታ ኢየሱስ እና ከሐዋርያቶቹ አገልግሎት የምናየው ይህንን ነው፡፡ ያደረጉትን የሚያስደንቅ ድንቅና ተአምራት ለእኛ የተጻፉት፣ እንድናነባቸው እና እንድናውቃቸው ብቻ ሳይሆን፤ እኛም በጊዜያችን በዛው መንፈስ ያንን

የእርሱ ሃይል በእናንተ በኩል

እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእርሱን በጎነት እንድትናገሩ የተመረጠ ትውልድ፣ የንጉስ

ካህናት፣ ቅዱስ ህዝብ፣ ለርስቱ የተለየ ወገን ናችሁ (1ኛ ጴጥ 2፡9)።

ቅዳሜ 11

Page 29: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ...ምሳሌ 24:10 በመከራ ቀን ተስፋ እንዳንቆርጥ ወይም እንዳንሸነፍ ይመክረናል፤ ይልቁኑ እኛ

Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org

ለተጨማሪ ጥናት:

የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

ሮሜ 12:17-13:1-14 & መዝሙረ ዳዊት 89

ፈልጵሱዮስ 1:23-30 & ትንቢተ ኢሳያስ 62

1ኛ ዮሐንስ 4:4; የሐዋርያት ስራ 1:8; ቆላስያስ 1:27-29

እንዴት ማድረግ እንደምንችል እንድናውቅ እና እንድንነሳሳ ነው፡፡የእግዚአብሄርን መለኮታዊ መገኘት ተሸካሚ እንደሆናችሁ እወቁ፤

የእርሱ ክብር የሚወጣበት መሳርያ ናችሁ፡፡ በቋሚነት በመንፈስ ቅዱስ እንድንሞላ የሚፈልግበትም አንዱ ምክንያት ይህ ነው (ኤፌ 5፡18)፤ በመንፈስ ስትሞሉ የእርሱ ኃይል ተትረፍርፎ በእናንተ በኩል ይፈሳል፡፡

ውድ አባት ሆይ፣ አሁን በእኔ በኩል ለሌሎች ጸጋንና ጽድቅን እያካፈለ በእኔ ውስጥ ስለሚሰራው ሃይል አመሰግንሃለሁ፡፡ በመንፈስ ቅዱስ ሃይል፣ ጥበብ እና ልቀት እየሰራሁ፣ ሙሉ በሙሉ በመለኮታዊው ጸጋህ በረከቶች እና በክርስቶስ ብቃት እመላለሳለሁ፤ በኢየሱስ ስም፡፡ አሜን ፡፡

ጸሎት

Page 30: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ...ምሳሌ 24:10 በመከራ ቀን ተስፋ እንዳንቆርጥ ወይም እንዳንሸነፍ ይመክረናል፤ ይልቁኑ እኛ

amharic

ክርስትና ማለት ክርስቶስ በእናንተ ውስጥ ሲገለጥ፤ በእናንተ ውስጥ የክርስቶስ ህይወት ሲገለጥ ማለት ሲሆን፣ ይህ ማለት ግን ክርስቶስን “ለመምሰል መሞከር” ማለት አይደለም፡፡ ይሄንን መረዳት እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡ በክርስትና እኛ ክርስቶስን ለመምሰል አንሞክርም፤ እኛ የክርስቶስን ህይወት እንኖረዋለን፡፡ ክርስቶስ በእናንተ ውስጥ ይኖራል፤ እርሱ ህይወታችሁ ነው (ቆላስይስ 3፡3)፤ ስለሆነም እናንተ ማድረግ ያለባችሁ ነገር ቢኖር የክርስቶስን ህይወት መኖር ነው፡፡

ቆላስይስ 1፡26-27 እንዲህ ይላል፡- “ይህም ቃል ከዘላለምና ከትውልዶች ጀምሮ ተሰውሮ የነበረ ምሥጢር ነው፥ አሁን ግን ለቅዱሳኑ ተገልጦአል። ለእነርሱም እግዚአብሔር በአሕዛብ ዘንድ ያለው የዚህ ምሥጢር ክብር ባለ ጠግነት ምን እንደ ሆነ ሊያስታውቅ ወደደ፥ ምሥጢሩም የክብር ተስፋ ያለው ክርስቶስ በእናንተ ዘንድ መሆኑ ነው።” የክርስቶስ በእናንተ ውስጥ መገለጥ የእግዚአብሄር ፍላጎት ነው፤ ክርስትና ይህ ነው! እናንተ በክርስቶስ ውስጥ ናችሁ፤ እርሱም በእናንተ ውስጥ ነው፡፡ እናንተ የእርሱ ጽድቅ፣ ክብር እና ጸጋ መገለጫዎች ናችሁ፡፡

የእግዚአብሔርን ዓላማ ቃሉ ሲናገር፤ የእርሱ ጥበብ አሁን በቤተ ክርስቲያን በኩል በሰማያዊ ስፍራ ውስጥ ላሉት አለቆችና ሥልጣናት ትታወቅ ዘንድ፤ ነው (ኤፌሶን 3፡10) ቢል አያስደንቅም፡፡ እውነተኛ መንፈሳዊ እድገት በእናንተ ውስጥ እና በኩል ክርስቶስ በተገለጠበት መጠን ይወሰናል፡፡ የክርስቶስ በእኛ ውስጥ መገለጥ ማለት በዋነኛነት የእርሱን ባህርይ፣ ህይወት እና ክብር መረዳትና በእኛ በኩል መግለጥ ማለት ነው፡፡

ለምሳሌ እንደ ክርስቲያን በፍቅር ስንመላለስ እናንተ ለማፍቀር

የክርስቶስን ህይወት መግለጥ

የኢየሱስ ሕይወት ደግሞ በሚሞት ሥጋችን ይገለጥ ዘንድ እኛ ሕያዋን የሆንን ከኢየሱስ የተነሣ ዘወትር ለሞት አልፈን

እንሰጣለንና (2ኛ ቆሮንቶስ 4፡11)።

እሁድ 12

Page 31: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ...ምሳሌ 24:10 በመከራ ቀን ተስፋ እንዳንቆርጥ ወይም እንዳንሸነፍ ይመክረናል፤ ይልቁኑ እኛ

Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org

ለተጨማሪ ጥናት:

የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

ሮሜ 14-15:1-4 & መዝሙረ ዳዊት 90-93

ፈልጵሱዮስ 2:1-11 & ትንቢተ ኢሳያስ 63

ኤፌሶን 3:10 AMPC; 1ኛ ጴጥሮስ 2:9 AMPC

ጥረት ማድረጋችሁ ብቻ ሳይሆን፣ በእናንተ ውስጥ ያለው የክርስቶስ ህይወት መገለጫ ስለሆነ ነው፡፡ እናንተ ለሌሎች የምታሳዩት እና እነርሱ የሚለማመዱት ፍቅርና ቸርነት በመንፈሳችሁ ውስጥ ያለው የክርስቶስ ህይወትና ተፈጥሮ መገለጫ ነው፡፡ እግዚአብሄር የሚፈልገው፣ በእናንተ ውስጥ ክርስቶስ እንዲገለጥ፤ በእናንተ አማካኝነት እየሰራ እየነካና ህይወትን እየቀየረ ክርስቶስ በእናንተ ውስጥ ህያው እንዲሆን ነው፡፡ እርሱ ዛሬ በምድር ላይ ሊያደርገው የሚፈልገው ሁሉ በእናንተ በኩል ነው፡፡ እናንተ የእርሱ የተዘረጋ ክንድ ናችሁ፡፡

ኢየሱስ በዮሐንስ 15፡5 “እኔ የወይን ግንድ ነኝ እናንተም ቅርንጫፎች ናችሁ…” ብሏል፡፡ ፍሬ የሚያፈራው የወይን ክፍል ቅርንጫፍ ነው፡፡ ስለዚህ የክርስቶስን ውበትና ክብር ትገልጣላችሁ፡፡ የእርሱን ህይወት በመግለጥ ጽድቁን ታሳያላችሁ፡፡ ሃሌሉያ!

ውድ አባት ሆይ በእኔ ውስጥ ስላለው ክርስቶስ ህይወት አመሰግንሃለሁ፡፡ እኔ ክርስቶስ ህይወትን በመኖር ለዓለም የእርሱን ባህርይ፣ ክብርና ህይወት ለመግለጥ ተወልጃለሁ፡፡ እኔ የእርሱ ህያው መስርያ ቤት እና ስራውን ማከናወኛ ቦታ ነኝ፤ በእኔ አማካኝነት ሁልጊዜም በሚጨምር መጠን የእርሱ ክብር ውበት ጥበብ ፍጽምና እና ጽድቅ ለዓለም ይገለጣል፤ በኢሱስ ስም፡፡ አሜን፡፡

ጸሎት

Page 32: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ...ምሳሌ 24:10 በመከራ ቀን ተስፋ እንዳንቆርጥ ወይም እንዳንሸነፍ ይመክረናል፤ ይልቁኑ እኛ

amharic

ሐዋርያው ጳውሎስ በመንፈስ ተመርቶ በመክፈቻ ጥቅሳችን ላይ እኛ ለኃጥያት እንደሞትንና ለእግዚአብሄር ሕያዋን እንደሆንን በድፍረት አረጋግጧል፡፡ ይህም የሆነበት ምክንያት በጽድቅ አስተሳሰብ ኢየሱስ ሲሞት እናንተም በእርሱ ውስጥ ሞታችኋል፤ ነገር ግን ሌላም ተጨማሪ ነገር አለ፤ እግዚአብሄር ኢየሱስን ከሙታን ሲያስነሳው እናንተም አዲስ ሰው ሆናችሁ ከእርሱ ጋር ተነስታችኋል፡፡ ይህ ህጋዊ የሆነው ክፍል ነው፤ ነገር ግን ዳግም ስትወለዱ ይህ ህያው ልምምድ ሆኗል፤ እናንተ ለእግዚአብሄር ነቅታችኋል፤ እናንተ በመንፈሳችሁ ህያው ሆናችኋል፡፡

አሁን ዳግም ተወልዳችኋልና፤ እናንተ ለእግዚአብሄር መንግስት እውነታዎች ማለትም ለእርሱ ህይወት ግዛት ነቅታችኋል፡፡ ኤፌሶን 2፡1-5 እንዲህ ይላል፡- “በበደላችሁና በኃጢአታችሁ ሙታን ነበራችሁ፤… ሕይወት ሰጠን (ህያው አደረገን)፣…፡፡ “ ይህ የተስፋ ቃል አይደለም፤ አስቀድሞ ተደርጓል! እናንተ ለእግዚአብሄር ህያው ስለሆናችሁ እና እርሱም ለእናንተ እውነት ስለሆነ፣ የእርሱን ድምጽ ሰምታችሁ ማወቅ ትችላላችሁ፤ ሃሳቦቹንና ፈቃዱን ማወቅና ለህይወታችሁ ባለው መለኮታዊ ፍጻሜ መመላለስ ትችላላችሁ፡፡

ዳግም ያልተወለደ ማለትም ክርስቲያን ያልሆነ ሰው ለእግዚአብሄር ህያው አይደለም፤ እርሱ ለሰማያዊው ግዛት እውነታዎች የነቃ አይደለም፡፡ እርሱ ከእግዚአብሄር ህይወት ተለይቶ ተስፋ ቢስ በሆነ ጨለማ ውስጥ ይኖራል፤ መንፈሳዊ እውነታዎች ለእርሱ ሞኝነት ናቸው፡- “ለፍጥረታዊ ሰው የእግዚአብሔር መንፈስ ነገር ሞኝነት ነውና አይቀበለውም፤ በመንፈስም የሚመረመር ስለ ሆነ ሊያውቀው አይችልም” (1ኛ ቆሮንቶስ 2፡14)፡፡ ለምሳሌ እኛ የእግዚአብሄርን ድምጽ ስለስማት ስንናገር፣ ያ እንዴት እንደሚቻል ግራ ይገባዋል! ከድንግል ስለመወለድ እና ሌሎች መንፈሳዊ እውነታዎች ለእርሱ

ለእርሱ የህይወት ግዛት ህያው መሆን

እንዲሁም እናንተ ደግሞ ለኃጢአት እንደ ሞታችሁ፥ ግን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን ሆናችሁ ለእግዚአብሔር ሕያዋን እንደ ሆናችሁ ራሳችሁን ቁጠሩ (ሮሜ 6፡11)።

ሰኞ 13

Page 33: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ...ምሳሌ 24:10 በመከራ ቀን ተስፋ እንዳንቆርጥ ወይም እንዳንሸነፍ ይመክረናል፤ ይልቁኑ እኛ

Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org

ለተጨማሪ ጥናት:

የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

ሮሜ 15:5-13 & መዝሙረ ዳዊት 94-98

ፈልጵሱዮስ 2:12-18 & ትንቢተ ኢሳያስ 64

1ኛ ቆሮንጦስ 2:7-10; የማቴዎስ ወንጌል 13:10-11

ሚሥጥራት ናቸው፡፡ለእናንተ ግን እንደዚህ አይደለም! እናንተ የእግዚአብሄር መንግስት

እውነታዎችን ትረዳላችሁ፤ እናንተ በእርሱ የህይወት ግዛት ውስጥ ስለምትኖሩ፣ የእግዚአብሄርን ነገሮች ታውቃላችሁ፡፡ በሉቃስ 8፡10 ላይ ኢየሱስ እንዲህ ቢል አያስገርምም፡- “…ለእናንተ የእግዚአብሔርን መንግሥት ምሥጢር ማወቅ ተሰጥቶአችኋል፤…፡፡” በመንፈሳችሁ ውስጥ እግዚአብሄር ብርሃን ስለሚያበራ፣ እናንተ ልትረዱት የማትችሉት ምንም መንፈሳዊ እውነታ የለም፤ ቃሉ በውስጣችሁ ይሰራል፡፡ ለእርሱ ጽድቅ፣ ጥበብ እና ጸጋ የነቃችሁ ናችሁ! እናንተ ከእርሱ ጋር አንድ ስለሆናችሁ (1ኛ ቆሮንቶስ 6፡17)፣ ከውስጣችሁ ምክርና ምሪት አላችሁ፡፡ እግዚአብሄር ይባረክ!

እኔ ለእግዚአብሄር፣ ለጥበቡ፣ ለጽድቁ፣ ለፍቅሩ እና ለጸጋው ህያው ነኝ፤ አሁን እንኳን ለመንግስቱ ሚሥጥራትና የተሰወሩ ነገሮች በጥልቅና በተሟላ ሁኔታ ዕይታ እንዲኖረኝ እና እንዳውቅ የሚያደርገኝ፣ የእርሱ ቅባት በእኔ ውስጥ እየሰራ ነው፡፡ የማስተዋል ዓይኖቼ ለወንጌሉ እውነታዎችና እውነቶች በርተዋል፤ በኢየሱስ ስም፡፡ አሜን፡፡

ጸሎት

Page 34: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ...ምሳሌ 24:10 በመከራ ቀን ተስፋ እንዳንቆርጥ ወይም እንዳንሸነፍ ይመክረናል፤ ይልቁኑ እኛ

amharic

እኛ በክርስቶስ ወደ ተጨባጭ፣ እውነተኛ እና የሚሰራ መንግስት ውስጥ ተወልደናል፡፡ አሁን የምንኖርበት ሥፍራ ያ ነው፡፡ እኛ ምንኖረውና የእለት እለት ተግባሮቻችንን የምናከናውነው ከዚያ መንፈሳዊ መንግስት ነው፡፡ ነገር ግን፣ በዚያ የህይወት ግዛት ውስጥ ለእናንተ በሆኑት በረከቶች ለመጠቀም፤ በቂ የሆነ የቃሉ እውቀት፣ የእግዚአብሄር መንግስት መርሆዎችን መረዳትና በዚያም መሰረት መንቀሳቀስ ይጠበቅባችኋል፡፡

ብዙ ክርስቲያኖች በመንፈሳዊ መንግስት ውስጥ እንደሆኑ ገና ሙሉ በሙሉ አልተገነዘቡም፤ እነርሱ የሚያውቁት በአካላዊው ግዛት ውስጥ ያሉትን ነገሮች ብቻ ነው፡፡ እንደነዚህ ያሉ ሰዎች፣ ለምሳሌ ከእኛ ጋር እና በዙርያችን ስላሉት እልፍ አእላፍ መላእክት እምብዛም አያውቁም፡፡ መንፈስ ቅዱስ በአገልግሎቱ በውስጣቸው ሲያናግራቸውና በሁሉም የህይወት ጉዳዮች ምሪትን ሲሰጣቸው፣ ገና አልተጠቀሙበትም፤ በመሆኑም ተራ ህይወትን ይኖራሉ፡፡

የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል፣ ከስሜት ግዛት ያለፈ የመንፈሳዊ ህይወት ወንጌል ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ሲናገር፡- “ስለ ሥጋ ማሰብ ሞት ነውና፥ ስለ መንፈስ ማሰብ ግን ሕይወትና ሰላም ነው” (ሮሜ 8፡6) ይላል፡፡ በኢየሱስ ክርስቶስ የሚያምን ማንኛውም ሰው ከሞት ወደ ህይወት ተሸጋግሯል፤ ይህም ማለት ወዲያውኑ ከጨለማው ግዛት ወደ ህይወት ግዛት ማለትም ወደ ፍቅሩ ልጅ መንግሥት ፈልሳችኋል (ቆላስይስ 1፡13)፤ ይህም መንፈሳዊ መንግስት ነው፡፡ አሁን በመንፈሳዊ መንግስት ውስጥ ትኖራላችሁ፡፡

በዓለም ውስጥ ብትሆኑም ከዓለም ግን አይደላችሁም፡፡ ስለሆነም በዚህ አካላዊ ዓለም መርሆዎች ለመኖር አትችሉም፡፡ እውነተኛ ስኬት መንፈሳዊ ነው፤ መሰረት ያደረገውም መንፈሰዊ መርሆዎችን ነው፡፡ ስለ

መንፈሳዊ መንግስት

ስለ ሥጋ ማሰብ ሞት ነውና፥ ስለ መንፈስ ማሰብ ግን ሕይወትና ሰላም ነው (ሮሜ 8፡6)።

ማክሰኞ 14

Page 35: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ...ምሳሌ 24:10 በመከራ ቀን ተስፋ እንዳንቆርጥ ወይም እንዳንሸነፍ ይመክረናል፤ ይልቁኑ እኛ

Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org

ለተጨማሪ ጥናት:

የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

ሮሜ 15:14-33 & መዝሙረ ዳዊት 99-101

ፈልጵሱዮስ 2:19-30 & ትንቢተ ኢሳያስ 65

ቆላስያስ 1:12-13; ቆላስያስ 3:1-2

መንፈሳዊው ግዛት እወቁና ከዚያ ግዛት ሆናችሁ ነገሮችን ተቆጣጠሩ፡፡ በመንፈሳዊው ግዛት ላይ አተኩራችሁ ከተንቀሳቀሳችሁ፣ በዚህ አካላዊ ዓለም ውስጥ የህይወታችሁን ስኬት እና ድሎች ሊገታ የሚችል ምንም ነገር አይኖርም፡፡

እኔ ለእግዚአብሄር ማለትም የማያልቁና ዘላለማዊ የሆኑ ድሎች ላሉበት ዓለም ህያው ነኝ፡፡ ልዩ በሆኑ የእግዚአብሄር ቃል ደንቦች እየተመራሁ ስኖር፣ እኔ ስኬትን ብቻ እለማመዳለሁ፡፡ በዚያ የህይወት ግዛት የእኔ በሆኑት ነገሮች ሁሉ እየተጠቀምኩ፤ እኔ የምኖርበትን መንፈሳዊ መንግስት ሙሉ በሙሉ አውቄ እመላለሳለሁ፤ እኖራለሁም፤ በኢየሱስ ስም፡፡ አሜን፡፡

የእምነት አዋጅ

Page 36: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ...ምሳሌ 24:10 በመከራ ቀን ተስፋ እንዳንቆርጥ ወይም እንዳንሸነፍ ይመክረናል፤ ይልቁኑ እኛ

Te ¨h

Te ¨

h

amharic

Page 37: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ...ምሳሌ 24:10 በመከራ ቀን ተስፋ እንዳንቆርጥ ወይም እንዳንሸነፍ ይመክረናል፤ ይልቁኑ እኛ

Te ¨h

Te ¨

h

Page 38: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ...ምሳሌ 24:10 በመከራ ቀን ተስፋ እንዳንቆርጥ ወይም እንዳንሸነፍ ይመክረናል፤ ይልቁኑ እኛ

amharic

በመክፈቻ ጥቅሳችን የተጠቀሰው እውነት የሚለው ቃል፣ እውነታ ማለት ነው፤ ይህም ማለት ከመንፈስ ቅዱስ አገልግሎቶች አንዱ ለእናንተ በእርግጥ እውነታ ምን እንደሆነ ለማሳየት፣ እናንተን ወደ ጥልቅ መንፈሳዊ እውነታዎች መምራት ነው፡፡ እርሱ የእውነታ መንፈስ ስለሆነ፣ ውጤታማ በሆነ መልኩ ይህንን የማድረግ ችሎታ አለው፤ የእግዚአብሄር ቃል እውነታ (እውነት) ነው፡- “…ቃልህ እውነት ነው” (ዮሐንስ 17፤17)።

እውነታ ምን እንደሆነ ካለመረዳት፣ ብዙዎች በህይወት ጥላን ይከተላሉ፡፡ ህይወት ከስሜቶች ባሻገር እንደሆነ ባለመረዳት፣ እውነታ ሊያዩት፣ ሊዳስሱትና በስሜት ሊያውቁት የሚችሏቸውን ማንኛውንም ነገሮች ነው ብለው ያስባሉ፤ ህይወት መንፈሳዊ ነው፡፡ አንዳንድ ሰዎች በዙርያችው የሚከሰቱትን ነገሮች ማለትም የህይወት ሁኔታዎችን በሚመለከት እውነታውን እንጋፈጥ እያሉ ሲናገሩ ሰምታችሁ ይሆናል፡፡ ያለው አንድ እውነታ ብቻ ነው፤ ያም የእግዚአብሄር ቃል ነው፡፡ እግዚአብሄር ቃል እውነታ ነው፡፡

አትኩሮታችሁን በቃሉ ላይ ብቻ አድርጉ፤ በቀሉ ተመልከቱ፡፡ በቃሉና በቃሉ ውስጥ ኑሩ፡፡ ቃሉ መቼም ቢሆን አይሳሳትም፡፡ ቃሉን ማመንና በዚያም መሰረት መተግበር፣ በህይወታችሁ ቃሉን ውጤታማ የማድረጊያ መንገድ ነው፤ በህይወት መንገዳችሁን የበለጸገ የሚያደርገው ይህ ነው፡፡ ቃሉን ማመን ብቻ በቂ አይደለም፤ በቃሉ መሰረት መተግበር ይገባችኋል፡፡ ቃሉን መተግበራችሁ እንዳመናችሁት ማስረጃ ነው፡፡

የቃሉ በረከቶች፣ ከቃሉ በስተቀር ምንም ሌላ አማራጭ ለሌለው ሰው ነው፤ የእርዳታ ምንጩ ቃሉ ብቻ ለሆነ ሰው ነው፡- “ነገር ግን ነጻ የሚያወጣውን ፍጹሙን ሕግ ተመልክቶ የሚጸናበት፥ ሥራንም የሚሠራ እንጂ ሰምቶ የሚረሳ ያልሆነው፥ በሥራው የተባረከ ይሆናል” (ያዕቆብ 1፡

የእግዚአብሄር ቃል፣ ብቸኛው እውነታ

ግን እርሱ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል፤… (ዮሐንስ 16፡13)

ረቡዕ 15

Page 39: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ...ምሳሌ 24:10 በመከራ ቀን ተስፋ እንዳንቆርጥ ወይም እንዳንሸነፍ ይመክረናል፤ ይልቁኑ እኛ

Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org

ለተጨማሪ ጥናት:

የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

ሮሜ 16 & መዝሙረ ዳዊት 102-103

ፈልጵሱዮስ 3:1-12 & ትንቢተ ኢሳያስ 66

የማቴዎስ ወንጌል 24:35; ትንቢተ ኢሳያስ 55:11; ዕብራውያን 4:12

25)፡፡ የእግዚአብሄር ቃል ታማኝነት ጥያቄ ውስጥ የሚገባ ነገር አይደለም፡፡ “ቃሉ ይህንን እና ያንን ይላል፤ ነገር ግን…” በፍጹም አትበሉ፤ ቃሉን በተግባር አውሉ፡፡ ቃሉ፣ በእናንተ የእምነት ተግባር አንዴ ከተቀጣጠለ፣ ውጤትን ለማምጣት የሚችል የመፍጠር ኃይል አለው!

ቃሉን በመኖር ከክብር ወደ ክብር እደጉ፡፡ የእግዚአብሄርን ቃል የግላችሁ አድርጉት፣ ለራሳችሁ ያዙት፤ እናም የያዘውን እውነታ ለእናንተና በእናንተ ውስጥ ያፈራላችኋል፡፡ ያ የምትመኙት የገንዘብ፣ የጤና እና የቤተሰብ ለውጥ በእግዚአብሄር ላይ ሳይሆን በእናንተ ላይ የተመረኮዘ ነው፡፡ ምሳሌ 119፡89 እንዲህ ይላል፡- “አቤቱ፥ ቃልህ በሰማይ ለዘላለም ይኖራል።” የእርሱ ቃል በሰማይ ጸንቷል፤ ነገር ግን እናንተ በማረጋገጥ በህይወታችሁ ልታጸኑት ይገባል፤ የእግዚአብሄርን ቃል እንደ ፍጹም እውነት አድርጋችሁ በመውሰድ፣ ከእግዚአብሄር ጋር በመስማማት ያንኑ በተመሳሳይ መናገር ይኖርባችኋል፡፤ ሃሌሉያ!

የተባረክህ አባት ሆይ፣ ቃልህ በየእለቱ የምኖርበት እውነት እና ህይወቴ ነው፡፡ በክርስቶስ ያለኝን ርስት እንዳውቅና እንድይዝ፣ መንፈሴ በመንፈስ ቅዱስ በርቷል፤ በኢየሱስ ስም፡፡ አሜን፡፡

የእምነት አዋጅ

Page 40: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ...ምሳሌ 24:10 በመከራ ቀን ተስፋ እንዳንቆርጥ ወይም እንዳንሸነፍ ይመክረናል፤ ይልቁኑ እኛ

amharic

እግዚአብሄር መንፈስ እንደሆነው ሁሉ፣ ሰውም መንፈስ ነው፤ ምክንያቱም ሰው የተፈጠረው በእግዚአብሄር አምሳል እና መልክ ነው፡፡ ስለሆነም፣ ማንነታችሁ አካላችሁ አይደለም፤ አካላችሁ ቤታችሁ ማለትም የመንፈሳችሁ መኖርያ ቤት ነው፡፡ የእናንተ አካለዊ ዓይኖች በራሳቸው ማየት አይችሉም፤ ዓይኖቻችሁ መንፈሳችሁ በዙርያችሁ ያለውን ዓለም የሚያይበት መስኮቶች ናቸው፡፡

ሮሜ 12፡1 እንዲህ ይላል፡- “እንግዲህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ ሰውነታችሁን እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝና ሕያው ቅዱስም መሥዋዕት አድርጋችሁ ታቀርቡ ዘንድ በእግዚአብሔር ርኅራኄ እለምናችኋለሁ፥ እርሱም ለአእምሮ የሚመች አገልግሎታችሁ ነው።” እውነተኛው ማንነታችሁ የእናንተ አካል ቢሆን ኖሮ፣ ለእግዚአብሄር እንዴት አድርጋችሁ ልታቀርቡት ትችላላችሁ? አካላችሁን ከሆነ የምታቀርቡት፣ ታዲያ ያንን የሚያቀርበው ማን ነው? ይህ ከአካላችሁ ያለፈ ማንነት እንዳላችሁ እንድትገነዘቡ ያደርጋችኋል፤ እናንተ መንፈሳዊ ማንነት ያላችሁ ናችሁ፡፡

እውነተኛው ማንነታችሁ፣ ጴጥሮስ “የተሰወረ የልብ ሰው” ብሎ የሚጠራው ነው (1ኛ ጴጥሮስ 3፡4)፡፡ ሐዋርያው ጳውሎስ “የውስጡ ሰውነታችን” ብሎ የሚጠራውም ያንኑ ነው (2ኛ ቆሮንቶስ 4፡16)፡፡ የውስጥ ሰውነታችን፣ የሰው መንፈስ ነው፤ በአካላዊው ዓይኖቻችን ሊታይ የማይችለው ነው፡፡ የውጪው ሰውነታችን አካላችን ከአምስቱ የስሜት ህዋሳቶቻችን ጋር ነው፡፡ እውነተኛው ማንነታችሁ ውጪያዊው ሰውነታችሁ ሳይሆን የውስጥ ሰውነታችሁ ነው፡፡ ስትናገሩ፣ በአፋችሁ አማካኝነት የተናገረው የውስጥ ሰውነታችሁ ነው፡፡

ብዙዎች መንፈሳቸውን ለማሳደግና ለማሰልጠን የሚያስፈልገውን ትኩረት ሳይሰጡ፣ በሰውነታቸው ውስጥ እየሆነ ስላለው ነገር ብቻ

እውነተኛው ማንነታችሁ

እግዚአብሔር መንፈስ ነው፥ የሚሰግዱለትም በመንፈስና በእውነት ሊሰግዱለት ያስፈልጋቸዋል። (ዮሐንስ 4፡24)

ሐሙስ 16

Page 41: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ...ምሳሌ 24:10 በመከራ ቀን ተስፋ እንዳንቆርጥ ወይም እንዳንሸነፍ ይመክረናል፤ ይልቁኑ እኛ

Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org

ለተጨማሪ ጥናት:

የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

1ኛ ቆሮንጦስ 1 & መዝሙረ ዳዊት 104-106

ፈልጵሱዮስ 3:13-21 & ትንቢተ ኤርምያስ 1

ፈልጵሱዮስ 3:3; 2ኛ ቆሮንጦስ 4:16; መጽሀፈ ምሳሌ 20:27 NKJV

ይጨነቃሉ፡፡ እግዚአብሄር የሚሰራበትና ከእናንተ ጋር የሚገናኝበት የውስጥ ሰውነታችሁ ማለትም መንፈሳችሁ እንጂ ውጪያዊው አካላችሁ አይደለም፡፡ ጌታ እናንተን ለመምራትና አቅጣጫ ለማስያዝ ከመንፈሳችሁ ጋር ግንኙነት ያደርጋል፤ ከእናንተ ጋር ግንኙነት የሚያደርገው በመንፈሳችሁ አማካኝነት ነው፡፡ በዚህ አስተሳሰብ እና ንቃተ ህሊና በመመላለስ፤ ከአካላዊ ሁኔታዎች ባሻገር ኑሩ፡፡

የእግዚአብሄር ህይወት የሚኖረው በመንፈሳችሁ ውስጥ ነው፡፡ መንፈስ ቅዱስን ስትቀበሉ፣ እርሱ ከመንፈሳችሁ ጋር በመቀላቀል በማይነጣጠል ቁርኝት አንድ ሆኗል (1ኛ ቆሮንቶስ 6፡17)፡፡ አሁን እግዚአብሄር ለምን በእርግጥም ግድ የሚለው መንፈሳችሁ እንደሆነ በተሻለ መረዳት ትችላላችሁ፡፡

በመንፈሳችሁ እንዴት መንቀሰቀስ እንዳለባችሁ መማር በጣም አስፈላጊ ነው፤ ይህንን የማድረጊያ መንገድ ደግሞ የእግዚአብሄር ቃል ላይ በማተኮር፣ ስሜቶቻችሁ በሚነግሯችሁ ነገሮች መናወጥን አሻፈረኝ ብላችሁ፤ ከውስጥ ወደ ውጪ መኖር ነው፡፡

ውድ አባት ሆይ፣ በመንፈሴ ውስጥ ስላለው ብርሃንን አመሰግንሃለሁ፤ በውስጤ ስላለው የአንተ ህይወትና ክብር ሙሉ በሙሉ በማወቅ፣ እኔ ከውሰጥ ወደ ውጪ እኖራለሁ፡፡ በአካላዊ ሰሜቶቼ መመራትን አሻፈረኝ እላለሁ፤ ነገር ግን ከክብር ወደ ክብር በሚለውጠኝ ዘላለማዊ ቃልህ ላይ ትኩረቴን አደርጋለሁ፤ በኢየሱስ ስም፡፡ አሜን፡፡

ጸሎት

Page 42: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ...ምሳሌ 24:10 በመከራ ቀን ተስፋ እንዳንቆርጥ ወይም እንዳንሸነፍ ይመክረናል፤ ይልቁኑ እኛ

amharic

በብሉይ ኪዳን፣ ዳንኤል መልካም መንፈስ ያለው ሰው በመሆኑ የተከበረ ነበር፡፡ በመልካም ጥበብ ተባርኳል፡፡ ሌላኛው ምሳሌ ደግሞ፤ ኢየሱስ እስኪሚመጣ ድረስ፣ ከዚያ በፊት ከነበሩ ሰዎች ሁሉ በላይ ጥበበኛ በመሆኑ የሚወደስ የነበረ፣ ንጉስ ሰለሞን ነው፡፡ ነገር ግን፣ ምንም ያህል የሰለሞንና የዳንኤልን ልቀትና ጥበብ የምናደንቅ ብንሆን፣ በአዲስ ኪዳን ዘመን ሁለቱም ሰዎች ያልነበራቸው አንድ ነገር እናገኛለን፤ ይኸውም የእኛ ጥበብ የሆነውን ክርስቶስን ነው፡፡

ቆላስይስ 2፡3 ላይ የጥበብና የእውቀት መዝገብ ሁሉ በክርስቶስ ተሰውሯል ይላል፡፡ በሌላ አነጋገር፣ እርሱ የጥበብና የእውቀት ሁሉ አርአያ ነው፡፡ 1ኛ ቆሮ 1፡30-31 ላይ ይኸው ክርስቶስ ስለእናንተ ጥበብ ሆኗል ይላል፡- “…ከእግዚአብሔር ዘንድ ጥበብና ጽድቅ ቅድስናም ቤዛነትም በተደረገልን በክርስቶስ ኢየሱስ የሆናችሁ ከእርሱ ነው።”፡፡ ስለሆነም፣ በክርስቶስ ውስጥ የጥበብ እና የእውቀት ሁሉ መዝገብ አላችሁ፡፡

ይሄ ሰለሞን ከነበረው ጥበብ የላቀ እና የሚበልጥ ነው፡፡ ለሰለሞን ጥበብን የሰጠው እና እራሱም ጥበብ የሆነው፣ በእናንተ ውስጥ ይኖራል፡፡ ኢየሱስን የህይወታችሁ ጌታ ባደረጋችሁት እና እርሱ ልባችሁን መኖሪያው ባደረገ ጊዜ፣ ጥበብም በእናንተ ውስጥ መኖሪያውን አድርጓል፡፡

ስለዚህ ኢየሱስ አዳኛችሁ እና ጌታችሁ ብቻ ሳይሆን፣ እርሱ ጥበባችሁም ጭምር ነው፤ ይህም ማለት ደግሞ እናንተ ጤነኛ፣ አስተዋይ፣ ጥበበኛ፣ ብልሀተኛ እና አመዛዛኝ ናችሁ ማለት ነው፡፡ ይህንን አረጋግጡ! “ክርስቶስ ጥበቤ ነው፤ ስለሆነም ሁልጊዜም በጥበብ እናገራለሁ፤ በጥበብ እመላለሳለሁም፡፡ ሀሳቤን እርሱ ይመራዋል፡፡ የተቀደሱ ሀሳቦችን እንድቀበል

ክርስቶስ የእናንተ ጥበብ

የአማልክት መንፈስ እንዳለብህ፥ እውቀትና ማስተዋልም መልካምም ጥበብ እንደ ተገኘብህ ስለ አንተ ሰምቻለሁ

(ዳንኤል 5፡14)፡፡

አርብ 17

Page 43: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ...ምሳሌ 24:10 በመከራ ቀን ተስፋ እንዳንቆርጥ ወይም እንዳንሸነፍ ይመክረናል፤ ይልቁኑ እኛ

Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org

ለተጨማሪ ጥናት:

የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

1ኛ ቆሮንጦስ 2 & መዝሙረ ዳዊት 107-108

ፈልጵሱዮስ 4:1-7 & ትንቢተ ኤርምያስ 2

መጽሀፈ ምሳሌ 4:7-8; ኤፌሶን 1:17; 1ኛ ቆሮንጦስ 1:30 NIV

አእምሮዬን ቀብቶታል፤ በእኔ ውስጥ ሁልጊዜም ጥበብ ይደመጣል፤ ይታያልም::” እያላችሁ ተናገሩ!፡፡

በክርስቶስ ኢየሱስ ለእናንተ በተሰጣችሁ የእግዚአብሄር ጥበብ በመጠቀም ሁልጊዜ በአሸናፊነት ኑሩ፡፡ በጥበብ አማካይነት ቤታችሁን፤ ቤተሰባችሁን፤ ንግዳችሁን፤ ገንዘባችሁንና የእናንተ የሆነውን ነገር ሁሉ እንዴት ማስተዳደር እንዳለባችሁ ታውቃላችሁ፡፡ የእግዚአብሄርን ቃል ያለማቋረጥ በመማር፣ መለኮታዊ ጥበብ በሚያስገኘው መብትና ጥቅም ተጠቃሚዎች ሁኑ፡፡

ውድ የሰማይ አባት ሆይ በክርስቶስ ለእኔ ስለተሰጠኝ ጥበብ አመሰግንሀለሁ፡፡ ሀሳቤ ንግግሬና ድርጊቴ ሁሉ የላቀ ውጤት ለማስገኘት የተቀባ ነው፡፡ በእኔ ውስጥ በሚሰራው በጥበብህ አማካይነት፣ ወደ ክብር እና ከፍታ ስፍራዬ ተወንጭፌያለሁ፤ በኢየሱስ ስም፡፡ አሜን፡፡

ጸሎት

Page 44: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ...ምሳሌ 24:10 በመከራ ቀን ተስፋ እንዳንቆርጥ ወይም እንዳንሸነፍ ይመክረናል፤ ይልቁኑ እኛ

amharic

አንዳንድ ሰዎች፣ ለዓለም ሁሉ ወንጌልን ለማሰራጨት ለሆነው የእግዚአብሄር ራእይ ራሳቸውን ሳይሰጡ፣ በራስ ወዳድነት የራሳቸውን ፍላጎት ብቻ እያሳደዱ ይኖራሉ፡፡ እግዚአብሄር የእርሱ ህልም ከእናንተ ህልም ጋር እንዲያያዝ ይፈልጋል፤ ይህንን ስታደርጉ የልባችሁ መሻት፣ ሁልጊዜም ሰዎች ሁሉ እንዲድኑ እና እውነትን እንዲያውቁ እርሱ ያለውን ራእይ የሚያንጸባርቅ ይሆናል፡፡

ነፍሳትን ማዳን፣ በህይወታችሁ የሚያንቀሳቅሳችሁ እና የሚገፋፋችሁ ኃይል መሆን አለበት፡፡ ፖለቲከኛ፤ መምህር፤ የባንክ ባለሙያ ወይንም ተማሪ ወዘተ፣ ከመሆናችሁ አስቀድሞ፣ ክርስቲያን ናችሁ፤ ሰለዚህ የወንጌል ጥሪያችሁን ፈጽሙ፡፡ መሻታችሁ ወንጌል ይሁን! የህይወታችሁ አንቀሳቃሽ የእግዚአብሄር መንግስት መስፋፋት ይሁን፤ ምክንያቱም እውነተኛ ደስታ፤ እርካታ እና መቼም የምትፈልጓቸው በረከቶች ሁሉ የሚገኙት እዛ ውስጥ ነው፡፡

ማቴዎስ 24፡14 ላይ ለአሕዛብም ሁሉ ምስክር እንዲሆን ይህ የመንግሥት ወንጌል በዓለም ሁሉ ይሰበካል፥ በዚያን ጊዜም መጨረሻው ይመጣል ይላል፡፡ ይሄ ለፓስተሮችና ለወንጌላውያን ብቻ ሳይሆን በስሙ ለሚምኑ ሁሉ ጌታ ኢየሱስ የሰጠው ትእዛዝ ነው፡፡ እናንተ የአዲስ ኪዳን አገልጋዮች ናችሁ (2 ቆሮ 3፡6)፤ የመዳንን የምስራች ዜና ተሸካሚዎችና አከፋፋዮች ናችሁ፡፡ በጨለማ ውስጥ ላሉት የወንጌልን ብርሀን እንድታበሩ ኃላፊነት ተሰጥቷችኋል፡፡

የሐዋርያት ሥራ 13፡47 እንዲህ ይላል፡- እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ለማዳን ትሆን ዘንድ ለአሕዛብ ብርሃን አድርጌሃለሁ ብሎ አዞናልና፡፡ እናንተ ለጨለማው አለም ብርሀን ስለሆናችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል አብሩ፡

የወንጌል ጥሪያችሁን ፈጽሙ

ነገር ግን የሆነው ሁሉ፥ በክርስቶስ ከራሱ ጋር ካስታረቀን የማስታረቅም አገልግሎት ከሰጠን፥ ከእግዚአብሔር ነው፤

(2ኛ ቆሮ 5፡18)።

ቅዳሜ 18

Page 45: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ...ምሳሌ 24:10 በመከራ ቀን ተስፋ እንዳንቆርጥ ወይም እንዳንሸነፍ ይመክረናል፤ ይልቁኑ እኛ

Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org

ለተጨማሪ ጥናት:

የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

1ኛ ቆሮንጦስ 3 & መዝሙረ ዳዊት 109-112

ፈልጵሱዮስ 4:8-13 & ትንቢተ ኤርምያስ 3

የማቴዎስ ወንጌል 5:14-16; ትንቢተ ዕምባቆም 2:14; የማቴዎስ ወንጌል 28:19-20

፡ እነርሱም ብርሃን ይሆኑ ዘንድ፣ ለሌሎች በማያቋርጥ ድምቀት የወንጌልን ብርሃን አብሩ፡፡

ወንጌልን ለመስበክ እድሉ ባጋጠማችሁ ጊዜ ሁሉ ያለፍርሀት ስበኩት፡፡ የህይወትን ቃል ይዛችሁ በመገሥገሥ፣ የጠፉ ሰዎችን ዓይን በመክፈት፣ ከጨለማ ወደ ብርሃን ከሰይጣንም ሀይል ወደ እግዚአብሄር መንግስት እየመለሳችሁ፣ ለዚህ ጊዜ የእግዚአብሄር ሰው መሆናችሁን አውቃችሁ፣ ደፋር ሁኑ፡፡ እንዴት የሚያስደንቅ ጥሪ ነው! እንዴትስ የሚያስደንቅ አገልግሎት ነው!

ውድ አባት ሆይ፣ አሁን እንኳን ልጆችህ በአለም ዙሪያ ወንጌልን እየሰበኩ ባለበት ሁኔታ እየሰራ ስላለው የማዳን ጸጋ አመሰግንሀለሁ፡፡ ብዙዎች ዛሬ ወንጌልን ሰምተው ሲቀበሉ ከጨለማ ወደብርሀን ከሰይጣንም ሀይል ወደ እግዚአብሄር ተመልሰዋል፤ በኢየሱስ ስም፡፡ አሜን፡፡

ጸሎት

Page 46: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ...ምሳሌ 24:10 በመከራ ቀን ተስፋ እንዳንቆርጥ ወይም እንዳንሸነፍ ይመክረናል፤ ይልቁኑ እኛ

amharic

ለምሳሌ፣ አይ ፎን የተሰኘው ምርት፣ አፕል የተባለ ኩባንያ የእጅ ስራ ውጤት እንደሆነ ሁሉ፣ እናንተም የእግዚአብሄር የእጅ ስራዎች እንደሆናችሁ ታውቁ ኖሯል? እስኪ ለአንድ አፍታ ይህንን ልብ ብላችሁ አስቡት፤ እናንተ የእግዚአብሄር የእጅ ስራዎች ናችሁ፤ የሰራችሁ እርሱ ነው፡፡ የእርሱን ምልክት በላያችሁ ላይ አድርጓል፤ እግዚአብሄር ደግሞ ፍጹም ያልሆነ ምንም ነገር አይሰራም፤ በመሆኑም እናንተ ፍጹም እና ሙሉ በሙሉ ልቀት ያላችሁ ናችሁ፡፡

እግዚአብሄር ለበሽታ፤ ለድህነት ወይንም ከንቱ እንድትሆኑ አድርጎ አልፈጠራችሁም፤ ይልቁንም እናንተን የፈጠራችሁ ለመልካም ስራ እና መልካም ህይወት እንድትኖሩ ነው፡፡ የመክፈቻውን ጥቅስ እንደገና አንብቡ፡- እኛ የእግዚአብሄር ፍጥረቱ (የራሱ የእጅ ሥራ) ነንና፤ (ለእኛ አስቀድሞ ያቀደውን መንገድ እየተከተልን) እንመላለስበት ዘንድ (አስቀድሞ እርሱ ያስተካከለው እና ለእኛ ያዘጋጀውን መልካም ህይወት እንኖርበት ዘንድ)፤ እግዚአብሔር አስቀድሞ ያዘጋጀውን መልካሙን ሥራ ለማድረግ በክርስቶስ ኢየሱስ ተፈጠርን (እንደ አዲስ ተወለድን)፡፡

ወደ አለም የመጣችሁት በአጋጣሚ አይደለም፤ እግዚአብሄር ለህይወታችሁ አላማ አለው፤ ይህም አላማ የእናንተን ህይወት፣ እርሱን የሚያስደስቱ የማያቋርጡ የእምነትና የጽድቅ ስራዎች ምንጭ ማድረግ ነው፡

ለመልካም ስራ ተፈጥረናል

እኛ የእግዚአብሄር ፍጥረቱ (የራሱ የእጅ ሥራ) ነንና፤ (ለእኛ አስቀድሞ ያቀደውን መንገድ እየተከተልን) እንመላለስበት ዘንድ (አስቀድሞ እርሱ ያስተካከለው እና ለእኛ ያዘጋጀውን

መልካም ህይወት እንኖርበት ዘንድ)፤ እግዚአብሔር አስቀድሞ ያዘጋጀውን መልካሙን ሥራ ለማድረግ

በክርስቶስ ኢየሱስ ተፈጠርን (እንደ አዲስ ተወለድን) (ኤፌሶን 2፡10 የአምፕሊፋይድ ትርጉም)፡፡

እሁድ 19

Page 47: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ...ምሳሌ 24:10 በመከራ ቀን ተስፋ እንዳንቆርጥ ወይም እንዳንሸነፍ ይመክረናል፤ ይልቁኑ እኛ

Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org

ለተጨማሪ ጥናት:

የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

1ኛ ቆሮንጦስ 4 & መዝሙረ ዳዊት 113-116

ፈልጵሱዮስ 4:14-23 & ትንቢተ ኤርምያስ 4

የሐዋርያት ስራ 10:38; የዮሐንስ ወንጌል 14:12; ቲቶ 2:13-14

፡ የህይወታችሁ ትርጉም ይሄ ነው፡፡ እናንተ ለልቀትና ለስኬት የተቀረጻችሁ ልዩ ህዝብ ናችሁ፡፡

ስለሆነም፤ በሰፈራችሁ፤ በቤታችሁ፤ በመስሪያ ቤታችሁና በትምህርት ቤታችሁ፤ ወይንም እራሳችሁን በምታገኙበት በማንኛውም ስፍራ፣ የእግዚአብሄርን ክብር ግለጡ! ወንጌልን በድፍረት ስበኩ፡፡ የታመሙትን ፈውሱ፤ አጋንንትን አውጡ፤ ለምጻሞችን አንጹ፤ ሙታንንም አስነሱ! እናንተ ዛሬ የክብሩ ተሸካሚዎች እና አንጸባራቂዎች፤ የጽድቁ ምልክቶች እና የጥበቡና የጸጋው አከፋፋዮች ናችሁ፡፡ ሀሌሉያ!!!

የእግዚአብሄርን ክብር እየገለጥኩ አስቀድሞ በተዘጋጀልኝ መንገድ እመላለሳለሁ፤ እኔ ስኬታማ ነኝ፡፡ ህይወቴ ለእግዚአብሄር ክብር ነው፤ በነገር ሁሉ እርሱን እያስደሰትኩ፣ በምሰራው ሁሉ የእርሱን ጽድቅ አፈራለሁ፤ እገልጣለሁም፤ በኢየሱስ ስም፡፡ አሜን፡፡

ጸሎት

Page 48: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ...ምሳሌ 24:10 በመከራ ቀን ተስፋ እንዳንቆርጥ ወይም እንዳንሸነፍ ይመክረናል፤ ይልቁኑ እኛ

amharic

ማንኛውም ወንድ ወይንም ሴት፤ ልጃገረድ ወይንም ጎረምሳ እስካሁን የተወለደም ይሁን ወደፊት የሚወለድ በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት አስቀድሞ “ድኗል”፡፡ ጌታ ሲሞት የሞተው የሰውን ልጅ ሁሉ ለማዳን ነው፡፡

ይሁን እንጂ መዳን በሰው ህይወት ውስጥ ህያው ልምምድ ሊሆን የሚችለው፣ ሆን ብሎ ወይም ብላ በህይወቱ ወይም በህይወቷ ላይ የኢየሱስ ክርስቶስን ጌትነት ለመሰከረ ወይም ለመሰከረች ሰው ብቻ ነው፡፡ መዳንን የምትቀበሉት ወይም የዳናችሁት በክርስቶስ በማመን ብቻ ሳይሆን፣ ቀጣዩን እርምጃ ስትወስዱ ማለትም የእርሱን ጌትነት ስትመሰክሩ ነው፡፡

የመክፈቻ ጥቅሱን ደግማችሁ አንብቡትና “እግዚአብሄርን እየጮህክ አድነኝ ብትለው ትድናለህ“ እንደማይል ታስተውላላችሁ፡፡ መጽሀፍ ቅዱስን መሠረት ያደረገ የደህንነት መንገድ በእንባ ወይንም በመልካም ስራ አይደለም፤ ደህንነት የእግዚአብሄር ስጦታ ነው፤ ጸጋው በእምነት አድኖአችኋልና፤ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም (ኤፌ 2፡8)፡፡

መጽሀፍ ቅዱስ አንድ ቆርኔሊዮስ ስለሚባል የሮማ ሰው ይነግረናል፡፡ እርሱ እግዚአብሄርን የሚያመልክና የሚፈራ ምጽዋትንም ማድረግ የሚወድ ቢሆንም ነገር ግን አልዳነም ነበር፡፡ (ሐዋርያት ሥራ 10፡2)

አንድ ቀን የእግዚአብሄር መልአክ ወደእርሱ መጣና እንዲህ አለው፡- ወደ ኢዮጴ ሰዎች ልከህ ጴጥሮስ የተባለውን ስምዖንን አስመጣ፤እርሱም አንተና የቤትህ ሰዎች ሁሉ የምትድኑበትን ነገር ይነግርሃል (የሐዋርያትሥራ 11፡13፣14)፡፡ ደህንነት ትክክለኛውን ቃል በመናገር የሚገኝ የእግዚአብሄር ስጦታ ነው፡፡ አንዴ እግዚአብሄር ኢየሱስን ከሙታን እንዳስነሳው በልባችሁ

የመዳን መሰረታዊ ሀሳብ

ኢየሱስ ጌታ እንደ ሆነ በአፍህ ብትመሰክር እግዚአብሔርም ከሙታን እንዳስነሣው በልብህ ብታምን ትድናለህና፤ ሰው

በልቡ አምኖ ይጸድቃልና በአፉም መስክሮ ይድናልና (ሮሜ 10፡9-10)፡፡

ሰኞ 20

Page 49: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ...ምሳሌ 24:10 በመከራ ቀን ተስፋ እንዳንቆርጥ ወይም እንዳንሸነፍ ይመክረናል፤ ይልቁኑ እኛ

Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org

ለተጨማሪ ጥናት:

የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

1ኛ ቆሮንጦስ 5 & መዝሙረ ዳዊት 117-118

ቆላስያስ 1:1-8 & ትንቢተ ኤርምያስ 5

ሮሜ 10:6-10; ዕብራውያን 13:5-6

ካመናችሁና በህይወታችሁ ላይ ጌታ መሆኑን በአፋችሁ ከመሰከራችሁ ወዲያውኑ የእግዚአብሄር ልጅ ሆናችኋል፡፡ የዘላለም ህይወት ወደ መንፈሳችሁ ገብቷል፡፡ ይሄ የሚያስደንቅ ተአምር ነው!

ደህንነትን መቀበል በፍጹም አስቸጋሪ ጉዳይ እንዳልሆነ አለም ሁሉ ሊገነዘብ ይገባል፡፡ በከንቱ ለሀጢያታችሁ ስርየትን ለማግኘትም ሆነ በመልካም ስራችሁ እግዚአብሄርን ለማስደመም መሞከር ምንም ጥቅም የሌለው ነገር ነው፡፡ በዙርያችሁ ካት ሁሉ በበለጠ በጣም መልካም ወይንም ትሁት ሰው መሆናችሁ ምንም ልዩነት አያመጣም፤ የእራሳችሁ መልካም ስራ እንደሚያድናችሁ ልትተማመኑ አትችሉም፡፡ ደህንነትን ለማግኘት የሚያስችል አንድ የተወሰነ ተግባር አለ፤ ይኸውም እግዚአብሄር ከሙታን እንዳስነሳው በልባችሁ በማመን፣ የጌታ ኢየሱስን ጌትነት መመስከር ነው፡፡

ውድ አባት ሆይ፣ ቃልህ በህይወቴ ውስጥ ስላለው ውጤታማነት አመሰግንሀለሁ፡፡ እኔ ከአብ ጋር አንድ ነኝ፤ ስለሆነም ከመለኮት ጋር አንድ ነኝ፡፡ ጤንነት፣ ሀብት፣ ብልጽግና፣ ህይወት፣ እና ስኬት የየእለት ልምምዶቼ ናቸው፡፡ በአስደናቂው በክርስቶስ ወንጌል የበረከት ሙላት ውስጥ እኖራለሁ፡፡ በእኔ ውስጥ ያለው በአለም ካለው ይበልጣልና፤ እኔ አሸናፊ ነኝ፤ በኢየሱስ ስም፡፡ አሜን፡፡

ጸሎት

Page 50: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ...ምሳሌ 24:10 በመከራ ቀን ተስፋ እንዳንቆርጥ ወይም እንዳንሸነፍ ይመክረናል፤ ይልቁኑ እኛ

amharic

ልጆች የሚለው ቃል በግሪክ ትርጉሙ “ቴክኖን“ የሚለው ቃል ሲሆን፣ ትርጓሜውም የተወለደ ልጅ ማለት ነው፡፡ ስለሆነም ዮሀንስ ከላይ በተጠቀሰው ጥቅስ ላይ እኛ የእግዚአብሄር ልጅ እንደሆንን እያሳየን ነው፤ እኛ ከእርሱ የተወለድን ነን፡፡

ዳግም ስትወለዱ የሆነው አንድ ሀይማኖታዊ ክስተት ሳይሆን፣ ተጨባጭ የሆነ መንፈሳዊ ውልደት ነው፤ ከቃሉ ተወልዳችሁ፣ አዲስ ፍጥረት በመሆን ህያው ሆናችኋል፤ እናም የእግዚአብሄር ቃል ማለት ደግሞ እግዚአብሄር እራሱ ማለት ነው፡- ”ዳግመኛ የተወለዳችሁት ከሚጠፋ ዘር አይደለም፥ በሕያውና ለዘላለም በሚኖር በእግዚአብሔር ቃል ከማይጠፋ ዘር ነው እንጂ።” (1ኛ ጴጥሮስ 1፡23)፡፡

የአለም ሰዎች፣ የእኛን መለኮታዊ ምንጭ እና የማንነታችንን እውነታ ሊረዱት የሚችሉት ነገር አይደለም፡፡ የመክፈቻ ጥቅሳችን ቀጥሎ ካለው ቁጥር ሁለት ጋር በድጋሚ አንብቡት፡- ”… ስለዚህ ምክንያት ዓለም እርሱን ስላላወቀው እኛን አያውቀንም። ወዳጆች ሆይ፥ አሁን የእግዚአብሔር ልጆች ነን፥ ምንም እንደምንሆን ገና አልተገለጠም። ዳሩ ግን ቢገለጥ እርሱ እንዳለ እናየዋለንና እርሱን እንድንመስል እናውቃለን።” 1ኛ ዮሐንስ 3፡1-2)፡፡

እኛ እግዚአብሄርን ከሚመስሉት ጋር ህብረት ያለን ነን፤ ይህ የአሁኑ ሰአት እውነታ ነው፡፡ መጽሀፍ ቅዱስ ሲናገር እርሱ (ኢየሱስ) እንዳለ እኛ ደግሞ እንዲሁ በዚህ አለም ነንና ይላል (1ኛ ዮሀ 4፡17)፡፡ እኛ የእርሱ ህይወት አለን፤ ስሙ አለን፤ እኛ በእርሱ ውስጥ እርሱም በእኛ ውስጥ ነው፡፡ ገና ወደ ሰማይ ስንሄድ ሳይሆን፣ አሁን የእግዚአብሄር ልጆች ነን፡፡ ቃል በቃል ከእግዚአብሄር እንደተወለዳችሁ እና ህያው እንደሆናችሁ ልጆች፣ የልጅነት መብታችሁን ተጠቀሙበት! እግዚአብሄር አባታችሁ ነው፤ አለም ሁሉ ደግሞ የእርሱ ነው፤ እናንተንም ከክርስቶስ ጋር አብሮ ወራሽ አድርጓችኋል፡፡ ሊኖራችሁ የማይችል ምንም ነገር የለም፡፡ ለዘለአለም

ከእግዚአብሄር የተወለደ

የእግዚአብሔር ልጆች ተብለን ልንጠራ አብ እንዴት ያለውን ፍቅር እንደ ሰጠን እዩ፥… (1ኛ ዮሐንስ 3፡1)፡፡

ማክሰኞ 21

Page 51: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ...ምሳሌ 24:10 በመከራ ቀን ተስፋ እንዳንቆርጥ ወይም እንዳንሸነፍ ይመክረናል፤ ይልቁኑ እኛ

Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org

ለተጨማሪ ጥናት:

የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

1ኛ ቆሮንጦስ 6 & መዝሙረ ዳዊት 119:1-112

ቆላስያስ 1:9-18 & ትንቢተ ኤርምያስ 6

የዮሐንስ ወንጌል 1:10-13; ሮሜ 8:16-17; ገላትያ 4:6-7

ለስሙ ክብር ይሁን! እዚህ ጋ አንድ ጥልቅ የሆነ ነገር አለ፤ መጽሀፍ ቅዱስ ከእግዚአብሄር

የተወለደ ሁሉ አለምን ያሸንፋል ይላል (1ኛ ዮሀ 5፡4)፡፡ ሁሉ የሚለው ቃል ማንኛውም ሰው ሁሉ በውስጡ ይጨምራል፡፡ 1ኛ ዮሀ 4፡4 ደግሞ ”ልጆች ሆይ፥ እናንተ ከእግዚአብሔር ናችሁ አሸንፋችኋቸውማል፥ በዓለም ካለው ይልቅ በእናንተ ያለው ታላቅ ነውና።” ይላል፡፡ እናንተ ከእግዚአብሔር ናችሁ ማለት የመጣችሁት ከእግዚአብሄር ነው ማለት ነው፤ ምንጫችሁ እግዚአብሄር ነው ማለት ነው፤ የተወለዳችሁትም ከእርሱ ነው፤ ስለሆነም ከአሸናፊዎች ትበልጣላችሁ፤ በዚህ ህይወት አሸናፊዎች ናችሁ፡፡ ሀሌሉያ!

ውድ አባት ሆይ፣ በክርስቶስ በወንጌል ስለወለድከኝ አመሰግንሀለሁ፡፡ እግዚአብሄርን ከሚመስሉት ጋር ህብረት ያለኝ በመሆን፣ ያንተ ተብዬ መጠራቴ፣ እንዴት አይነት ክብርና ጥቅም ነው! እንዴት ያለ መለኮታዊ እውነታ ነው፤ አለማትን ከፈጠረው አምላክ ጋር አንድ ነኝ፤ የልኡልም ወራሽ ነኝ! ለእኔ ይበዛል የሚባል ነገር የለም፤ ከመልካም ነገር ምንም አልከለከልም፤ በኢየሱስ ስም፡፡ አሜን፡፡

ጸሎት

Page 52: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ...ምሳሌ 24:10 በመከራ ቀን ተስፋ እንዳንቆርጥ ወይም እንዳንሸነፍ ይመክረናል፤ ይልቁኑ እኛ

Te ¨h

Te ¨

h

amharic

Page 53: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ...ምሳሌ 24:10 በመከራ ቀን ተስፋ እንዳንቆርጥ ወይም እንዳንሸነፍ ይመክረናል፤ ይልቁኑ እኛ

Te ¨h

Te ¨

h

Page 54: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ...ምሳሌ 24:10 በመከራ ቀን ተስፋ እንዳንቆርጥ ወይም እንዳንሸነፍ ይመክረናል፤ ይልቁኑ እኛ

amharic

የየትኛውም ዘር አላማ መኸር ነው፡፡ አንድ ዘር ምርት የማይሰጥ ወይም ሊሰጥ የሚችል ካልሆነ ጥቅም የለውም፡፡ ይህንን ከተረዳችሁ፣ የመስጠትንና የመቀበልን መርህ መረዳት ለእናንተ ቀላል ይሆናል፡፡ በእግዚሃብሄር መንግስት ውስጥ መዝራትና ማጨድ መንፈሳዊ ህግ ነው፡፡ በገንዘብም ሆነ በቁሳቁስ ዘርን ስትዘሩ፣ ትኩረታችሁ በምትዘሩት ዘር ላይ ሳይሆን በምታጭዱት መኸር ላይ መሆን አለበት፡፡ ገላቲያ 6፡7 እንዲህ ይላል፡- “አትዛቱ እግዚሃብሄር አይዘበትበትም፡፡ ሰው የሚዘራውን ሁሉ ያንኑ ደግሞ ያጭዳልና::”

የብርቱካንን ዘር ስትዘሩ፣ መጠበቅ ያለባችሁ የብርቱካንን ፍሬ ነው፤ ነገር ግን መጀመሪያ ዛፉ ማደግ አለበት፤ ከዚያም በኋላ ብርቱካንን ማፍራት አለበት፡፡ የበቆሎን ዘር ስትዘሩ፤ የበቆሎ መኸርን ትጠብቃላችሁ፡፡ ዘሩ የተዘራው በትክክለኛው አካባቢ ከሆነ፤ መሬት ምርት እንድትሰጥ መጸለይ አይጠበቅባችሁም፡፡ የመዝራትና የማጨድ ህግ በስራ ላይ ከዋለ፤ ጸሎት አስፈላጊ አይደለም፡፡ ለጌታ ስትሰጡ፤ የእናንተ መኸር የተረጋገጠ ነው፡፡

ብዙዎች ሲሰጡ ትኩረታቸውን በመኸር ላይ ማድረግ ሲኖርባቸው ባለማድረጋቸው ስተዋል፡፡ ገንዘብን እንደ ዘር ዘርተው፤ ምንም እንኳን ማጨዳቸው ለዚያውም ከዘሩት ዘር የበለጠ ማጨዳቸው የተረጋገጠ ቢሆንም ስለዘራቸው እየጸለዩ ነው፡፡ አንድ ዘር ብቻ የተትረፈረፈ መኸርን ለማምጣት ይችላል፡፡

ጌታ ኢየሱስ የእግዚሃብሄር መንግስትን አሰራር ከዚህ ጋር አመሳስሎታል፡- “በምድር ዘርን እንደሚዘራ ሰው የእግዚሃብሄር መንግስት እንደዚህ ናት ሌሊትና ቀን ይተኛልም ይነሳልም፡፡ እርሱም እንዴት እንደሚሆን ሳያውቅ ዘሩ ይበቅላል ያድግማል፡፡ ምድሪቱም አውቃ በመጀመሪያ ቡቃያ ኋላም ዛላ ኋላም በዛላው ፍጹም ሰብል ታፈራለች፡፡ ፍሬ ግን ሲበስል መከር ደርሷልና ወዲያው ማጭድ ይልካል” (ማርቆስ 4፡26-29)፡፡

የመዝራት ወይም የመስጠት ስራ ምሥጢር ስላልሆነ ለእናንተም

በምታጭዱት ነገር ላይ ትኩረት አድርጉ

በምድር ዘመን ሁሉ መዝራት ማጨድ፤ ብርድና ሙቀት፤ በጋና ክረምት፤ ቀንና ሌሊት አያቋርጥም (ዘፍጥረት 8፡22)፡፡

ረቡዕ 22

Page 55: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ...ምሳሌ 24:10 በመከራ ቀን ተስፋ እንዳንቆርጥ ወይም እንዳንሸነፍ ይመክረናል፤ ይልቁኑ እኛ

Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org

ለተጨማሪ ጥናት:

የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

1ኛ ቆሮንጦስ 7 & መዝሙረ ዳዊት 119:113-176

ቆላስያስ 1:19-29 & ትንቢተ ኤርምያስ 7

መጽሀፈ መክብብ 11:1-4; የሉቃስ ወንጌል 6:38

ምሥጢር ሊሆንባችሁ አይገባም፡፡ ዘራችሁን ስትዘሩ በአእምሮአችሁ መኸራችሁን በመሳል፣ በመተማመን እና በታላቅ መጠባበቅ ዝሩ፡፡ መኸሩ እንዴት ይመጣል? እያላችሁ አታስቡ፡፡ በሰጣችሁ ቁጥር ሊሻር የማይችል ህግን አንቀሳቅሳችኋል፤ እናም በዚህ ህግ መሰረት የሰጣችሁት ሁሉ በምትሰፍሩበት መስፈሪያ ተመልሶ ይሰፈርላችኋልና፤ የተጨቆነና የተነቀነቀ የተትረፈረፈም መልካም መስፈፈሪያ በእቅፋችሁ ይሰጣችኋል” (ሉቃስ 6፡38)፡፡

ውድ አባት ሆይ! ዛሬ ወደ መንፈሴ ስለመጣው የቃልህ እውቀት አመሰግንሃለሁ፡፡ አሁን ስዘራ የመዝራትና የማጨድ ህግ በተግባር ላይ እንደሚውል አውቃለሁ፤ በመሆኑም፣ ቃልህ እርግጠኛ የሆነውን ያህል፣ የእኔም ማጨድ እንደዚያው እርግጥ ነው፡፡ የዘራሁትን ዘር ስላበዛህልኝ እና የጽድቅ ፍሬዎቼን ስለጨመርህልኝ አመሰግንሃለሁ፤ በኢየሱስ ስም፡፡ አሜን፡፡

ጸሎት

Page 56: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ...ምሳሌ 24:10 በመከራ ቀን ተስፋ እንዳንቆርጥ ወይም እንዳንሸነፍ ይመክረናል፤ ይልቁኑ እኛ

amharic

የእግዚሃብሄር ቃል በህይወታችሁ ላይ ያለውን ፈቃድ ከማሳየት ባሻገር፤ በክርስቶስ ያላችሁን ውርስ ይገልጽላችኋል፡፡ 2ኛ ቆሮንቶስ 8፡9 ይህንን ያውጃል፡- “የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ቸር ስጦታ አውቃችኋልና፤ ሀብታም ሲሆን እናንተ በእርሱ ድህነት ባለጠጎች ትሆኑ ዘንድ ስለእናንተ ድሃ ሆነ፡፡” ኢየሱስ እኛ ሀብታም እንድንሆን ዘንድ፣ እርሱ ድሃ ሆነ፡፡ እርሱ በሰጣችሁ የባለጸግነትን ህይወት ለመጠቀም የሚያስፈልገን ነገር ቢኖር፣ በቃሉ መኖር ብቻ ነው! እግዚአብሄር የፈጠረን፤ በህይወት እንድንታገል ወይንም እንድንጨነቅ ሳይሆን፤ የፈጠራችሁ ለክብሩ ነው፡፡

በህይወታችሁ እንደ መጨረሻ ስልጣን ለእግዚሃብሄር ቃል መገዛት፤ በክርስቶስ ባላችሁ ውርስ ለመኖር እና በህይወት በሙላት ደስተኛ ለመሆን ቁልፍ ነው፡፡ እግዚሃብሄር ለእናንተ ያላደረገላችሁ ምንም ነገር የለም፡፡ ኤፌሶን 1፡3 እንዲህ ይላል፡- “በክርስቶስ በሰማያዊው ስፍራ በመንፈሳዊ በረከት ሁሉ የባረከን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባትና አምላክ ይባረክ፡፡” መቼም ልታስቡት ከምትችሉት በላይ በረከቶችን ሁሉ አስቀድሞ ሰጥቷችኋል፡፡ ይህ ደግሞ ከመግቢያ ጥቅሳችን ጋር አብሮ ይሄዳል፤ ለህይወታችሁና እርሱን ለመምሰል የሚሆነውን ነገር ሁሉ ሰጥቷችኋል፡፡

ስለዚህ የእናንተ ህይወት በየእለቱ፣ በማንኛውም ስፍራ፤ ጌታን ሁልጊዜ ከፍ የማድረግ፣ ክብር የመስጠት፣ እና ምስጋና የመስጠት መሆን አለበት፡፡ መጽሀፍ ቅዱስ ሲናገር የተጠራችሁት ለድህነት፣ ለበሽታ፣ ለህመም፣ ለጉዳት ሳይሆን ለክብርና ለበጎነት ነው (2ኛ ጴጥሮስ 1፡3) ይላል፡፡ ህይወታችሁ ለእግዚሃብሄር ክብር ነው፡፡

መጽሐፍ ቅዱስ፤ የብሉይ ኪዳን ነብያት ስለክርስቶስ ስቃይና ስለሚከተለው ክብር አስቀድመው መመስከራቸውን አሳይቶናል (1ኛ ጴጥሮስ

ህይወታችሁ ለእርሱ ክብር ነው

የመለኮቱ ኃይል በገዛ ክብሩና በበጎነቱ የጠራንን በማወቅ፤ ለህይወትና እግዚሃብሄርን ለመምሰል የሚሆነውን ነገር ሁሉ ስለሰጠን በእግዚሃብሄርና በጌታችን በኢየሱስ እውቀት ጸጋና

ሰላም ይብዛላችሁ (2ኛ ጴጥሮስ 1፡3)፡፡

ሐሙስ 23

Page 57: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ...ምሳሌ 24:10 በመከራ ቀን ተስፋ እንዳንቆርጥ ወይም እንዳንሸነፍ ይመክረናል፤ ይልቁኑ እኛ

Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org

ለተጨማሪ ጥናት:

የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

1ኛ ቆሮንጦስ 8 & መዝሙረ ዳዊት 120-127

ቆላስያስ 2:1-7 & ትንቢተ ኤርምያስ 8

መጽሀፈ ምሳሌ 4:18; 1ኛ ዮሐንስ 5:4; 2ኛ ቆሮንጦስ 3:18

1፡11)፡፡ ከክርስቶስ ስቃይ በኋላ ወዲያው፤ የክብር ህይወት ቀጥሏል፡፡ እናንተ በክብር ትኖሩ ዘንድ፣ እርሱ ተሰቃየ፡፡ አሁን በዛ ክብር ውስጥ ናችሁ፡፡ ማንም ሰው አሁን በስቃይ ውስጥ ካለ፤ ይህ ስቃይ አስፈላጊ አይደለም፡፡

ለምሳሌ በሰውነታችሁ ላይ ችግር ያላችሁ ከሆነ፣ ምናልባትም በሰውነታችሁ ላይ ያለ አንድ ዕጢ ቢሆን፤ እንዲሞት እዘዙት፡፡ ስለ ህመሙ አታጉረምርሙ፡፡ በመቃወም ቃሉን ተጠቅማችሁ ተቃወሙት፡፡ ፈውሳችሁና ጤንነታችሁን አውጁ፡፡ ብልጽግናችሁን አውጁ፡፡ ህይወትን ተናገሩ፡፡ የህይወታችሁ ጉዞ አንድ አቅጣጫ ማለትም ወደ ላይና ወደ ፊት ብቻ እንደሆነ አውጁ፡- ፡፡ ሁሌም አሸናፊ እንደሆናችሁና፤ ህይወታችሁ ለእግዚሃብሄር ክብር እንደሆነ አውጁ፡፡

ህይወቴ ለእግዚሃብሄር ክብር ነው! ሁሌም አሸናፊ ነኝ፤ የህይወት ጉዞዬ በአንድ አቅጣጫ ማለትም ወደ ላይ እና ወደ ፊት ብቻ ነው፡፡ ዛሬ እምነቴ ህያውና ጠንካራ ነው፡፡ በመንፈስ ቅዱስ የበላይነት ስለምንቀሳቀስ፣ ዓለም ለእኔ የተገዛ ነው፡፡ እግዚሃብሄር ይባረክ!

የእምነት አዋጅ

Page 58: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ...ምሳሌ 24:10 በመከራ ቀን ተስፋ እንዳንቆርጥ ወይም እንዳንሸነፍ ይመክረናል፤ ይልቁኑ እኛ

amharic

ለብዙ ዓመታት፤ ሰዎች በእግዚሃብሄር ፊት ጻድቅ ለመሆን፤ ጽድቅን አፈላልገዋል፡፡ ነገር ግን የእግዚሃብሄር ጽድቅ የሚገለጠው በክርስቶስ ወንጌል ብቻ ነው፡፡ የክርስቶስ ወንጌል የእግዚሃብሄርን ጽድቅ መግለጥ ነው፤ ወንጌሉ፣ የእግዚሃብሄር ጽድቅ ወንጌል ነው፡፡ ስለዚህ ማንም ሰው የክርስቶስን ወንጌል ካልተቀበለ፤ የጻድቅ ህይወትን ለመኖርም ሆነ የእግዚሃብሄርን ጽድቅ ለማወቅ አይችልም፡፡

ጽድቅ ማለት ምንም ኩነኔ፣ ፍርሃት፤ የጥፋተኝነት እና የበታችነት ስሜት ሳይኖረን በእግዚሃብሄር ፊት ሊያቆመን የሚያስችለን የእግዚሃብሄር ተፈጥሮ ነው፡፡ ከእግዚአብሄር ጋር ህብረት ለማድረግ እና በትክክለኛነት ለመቆም የሚያስችል ብቃት ነው፡፡ ከኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል በስተቀር፣ ወደዚህ አስደናቂ የጽድቅ ህይወት እና ከጌታ ጋር አንድነት ሊያመጣን የሚችል መንገድ የለም፡፡

ስለወንጌሉ ዝም ልንል የማንችልበት ምክንያትም ይህ ነው፡፡ ወንጌሉ ለሰው ልጅ ለቅሶ መልስ ነው፡፡ ልክ ሌላ አማራጭ መንገድ እንዳለ አናስመስል፤ ወንጌሉ ሌላ አማራጭ የለውም፡፡ ከኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ውጪ፣ ሰዎች የእግዚሃብሄርን ጽድቅ ለመማር፣ ለመቀበል፣ ወይም ለመረዳት የሚችሉበት ምንም ሌላ መንገድ የለም፡፡ ስለዚህ በመንደራችሁ፣ በአካባቢያችሁ፣ በከተማችሁ እና በአገራችሁ ዝም አትበሉ፤ በድፍረት ወንጌልን ስበኩ፡፡ የጽድቅን መልካም ዜና አሰራጩ፡፡

ለሰዎች መዳን ቁልፉን ይዛችኋልና፤ ወንጌልን እየሰበካችሁ

የጽድቅ ወንጌል

በወንጌል አላፍርምና፤ አስቀድሞ ለአይሁዳዊ ደግሞም ለግሪክ ሰው፤ ለሚያምኑ ሁሉ፤ የእግዚሃብሄር ኃይል

ለማዳን ነውና፡፡ ጻድቅ በእምነት ይኖራል ተብሎ እንደ ተጻፈ የእግዚሃብሄር ጽድቅ ከእምነት ወደ እምነት በእርሱ

ይገለጣልና (ሮሜ 1፡ 16-17)፡፡

አርብ 24

Page 59: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ...ምሳሌ 24:10 በመከራ ቀን ተስፋ እንዳንቆርጥ ወይም እንዳንሸነፍ ይመክረናል፤ ይልቁኑ እኛ

Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org

ለተጨማሪ ጥናት:

የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

1ኛ ቆሮንጦስ 9 & መዝሙረ ዳዊት 128-134

ቆላስያስ 2:8-15 & ትንቢተ ኤርምያስ 9

ትንቢተ ኤርምያስ 20:9; ሮሜ 3:21-22; ሮሜ 5:17

የእግዚሃብሄርን ጽድቅ ለእነርሱ ግለጹላቸው፡፡ የእነርሱ የእግዚሃብሄርን ጽድቅ ፍለጋ፣ መልስ ሁኑ፡፡

የእግዚሃብሄር ተፈጥሮና ህይወት አለኝ፡፡ ክብሩን እየገለጽኩና በሁሉም ቦታ ጽድቁን እያጸናሁ፣ እኔ በምድር ላይ የክርስቶስ ተወካይ ነኝ፡፡ የዛሬ የድህነት መልእክት ወደ ሰዎች ልብ ሲገባ፤ ዘላለማዊ ህይወት ለመንፈሳቸው ስለሚካፈል፤ የእግዚሃብሄርን ጽድቅ ለመቀበል እና ለማንጸባረቅ፣ በውስጣቸው እምነት ይቀጣጠላል፤ በኢየሱስ ስም፡፡ አሜን፡፡

ጸሎት

Page 60: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ...ምሳሌ 24:10 በመከራ ቀን ተስፋ እንዳንቆርጥ ወይም እንዳንሸነፍ ይመክረናል፤ ይልቁኑ እኛ

amharic

አምላካችን የከበረና ደግ ነው፤ ርህሩህና ምህረቱ የበዛ ነው፡፡ ቃሉ፣ በመዝሙረ ዳዊት 78፡38 ላይ፣ እርሱ ርህራሄ እንዳለው ብቻ ሳይሆን፣ በርህራሄ የተሞላ እንደሆነ ይናገራል፡፡ ርህራሄው የማይነጥፍ ነው፡፡ ርህራሄ በሃዘኔታ ሳይሆን በፍቅር፣ የሌላን ሰው ህመም ለማስጣል የሚያስችል ሀይል ወይም መነቃቃት ነው፡፡ እግዚሃብሄር ከፍቅር የተነሣ፣ ልጁን ለአለም ሁሉ ሃጢያት እንዲሞት በመስጠት፣ ርህራሄውን አሳይቷል (ዮሐንስ 3፡16)፡፡

እንዴት ያለ ደስታ ነው! እግዚሃብሄር በፍጹም በእናንተ ላይ እንደማይናደድባችሁ ማወቅ እንዴት ያጽናናል! ይልቁንም ለእናንተ ያለው ፍቅርና ምህረት በየዕለቱ አዲስ ነው፡፡ የምንዘምረውን አንድ ውብ የሆነ መዝሙር ያስታውሳል፡- “ታማኝ የሆነው የጌታ ፍቅር መቼም አያልቅም፤ ምህረቱ ማብቂያ የለውም፤ ማለዳ ማለዳ አዲስ ነው፤ ታማኝነትህ ብዙ ነው ጌታ ሆይ፤ ታማኝነትህ ብዙ ነው”፡፡ ለእኛ ያለው ምህረት ዘላለማዊ ነው፡፡ ሁሌም ያያችኋል፤ ይመራችኋል፤ ይጠብቃችኋል፡፡ ለእናንተ ያለው ፍቅር ማለቂያ የለውም (ኤፌሶን 2፡4)፡፡

ለአለም የፍርድ አምላክ ሊሆን ይችላል፤ ለእናንተ ግን ፍቅር ብቻ ነው፡፡ በኤርሚያስ 31፡3 እንዲህ አለ፡- “በዘላለም ፍቅር ወድጄሻለሁ፤ ስለዚህ በቸርነት ሳብሁሽ”፡፡ ወደ ክብር ዙፋኑ በእምነት በመቅረብ ምህረትን አግኙ፤ በሚያስፈልጋችሁ ግዜም ሞገስን አግኙ ብሎ ቢነግረን አያስገርምም (ዕብራዊያን 4:16)፡፡ በእግዚሃብሄር ጸጋና ምህረት ተጠቀሙበት፡፡

በሰራችሁት ስህተት የተነሣ ራሳችሁን አትኮንኑ፤ ምክንያቱም እርሱ በፍጹም እናንተን አይኮንናችሁም፡- “በክርስቶስ ለሆኑት ምንም አይነት ኩነኔ የለባቸውም” (ሮሜ 8፡1) ሁሌም የሚመለከተው የእናንተን ምርጥ ነገር ነው፤ በራሳችሁና በዙሪያችሁ ባሉ ሌሎች ሰዎች ውስጥም ምርጡን ነገር እንድትመለከቱ፣ ይጠብቅባችኋል፡፡ ጳውሎስ ለጢሞቴዎስ ሲጽፍ እንዲህ ብሏል፡- “እንግዲህ ልጄ ሆይ፤ አንተ በክርስቶስ ኢየሱስ ባለው ጸጋ በርታ”

የእርሱ አስደናቂ ርህራሄ

ያልጠፋነው ከእግዚሃብሄር ምህረት የተነሳ ነው፤ ርህራሄው አያልቅምና፤ ማለዳ ማለዳ አዲስ ነው፤ ታማኝነትህ ብዙ ነው

(ኤርሚያስ 3፡22-23)፡፡

ቅዳሜ 25

Page 61: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ...ምሳሌ 24:10 በመከራ ቀን ተስፋ እንዳንቆርጥ ወይም እንዳንሸነፍ ይመክረናል፤ ይልቁኑ እኛ

Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org

ለተጨማሪ ጥናት:

የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

1ኛ ቆሮንጦስ 10:1-13 & መዝሙረ ዳዊት 135-138

ቆላስያስ 2:16-23 & ትንቢተ ኤርምያስ 10-11

መዝሙረ ዳዊት 103:1-4; ኤፌሶን 2:4-5; የሉቃስ ወንጌል 10:30-37

(2ኛ ጢሞቴዎስ 2፡1)፡፡ በሌላ አነጋገር፣ “በኢየሱስ ክርስቶስ ያለውን ጸጋ ተጠቃሚ ሁኑ::” ማለት ነው፡፡

አሁን እንኳን፣ የእርሱን ሞገስና ምህረት በመጠቀም ካንሰርን፤ የስኳር በሽታን፤ ወይንም ማንኛውም በሰውነታችሁ ውስጥ ያለ ህመምና በሽታን ለመገሰጽ ልትጠቀሙበት ትችላላችሁ፡፡ ታላቅ የሆነውን ፍቅሩን እና ርህራሄውን በማወቅና በመጠቀም፣ ከማንኛውም ችግርቸቀውስ ውጡ፡፡ እርሱ ይወዳችኋል፤ እጅግ የላቀ ህይወት ትኖሩ ዘንድ፣ ለእናንተ አስፈላጊ የሆነውን ነገር በሙሉ አድርጓል፡፡ ከዚህ ያነሰ ምንም ነገር አትቀበሉ፡፡

የተባረክ አባት ሆይ! መልካምነትህና ምህረትህ ዘላለማዊ ናቸው፡፡ ጸጋህና ርህራሄህ በህይወቴ ውስጥ በዝቷል፤ ስለሆነም ስምህን እባርካለሁ፤ ድንቅ የሆነውን ፍቅርህንም እመሰክራለሁ፡፡ በእኔ ውስጥ እና በእኔ በኩል ስለተገለጠው በረከትህ፣ ውበትህ፤ ፍጹምነትህ እና ልቀትህ አመሰግንሃለው፤ በኢየሱስ ስም፡፡ አሜን፡፡

ጸሎት

Page 62: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ...ምሳሌ 24:10 በመከራ ቀን ተስፋ እንዳንቆርጥ ወይም እንዳንሸነፍ ይመክረናል፤ ይልቁኑ እኛ

amharic

ከላይ በተቀመጠው ጥቅስ የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ማለትም ኢየሱስ ክርስቶስን እና እርሱ ያመጣውን መዳን የሚመለከተው የእግዚሃብሄር ቃል፤ የእግዚሃብሄር ሀይል ነው፡፡ የሚያምኑትን ከሀጢያት ነጻ አውጥቶ ወደ ጽድቅ የሚያመጣበት ሃይል፤ በጸጋው ወንጌል ተጠቃሏል፡፡ የእግዚሃብሄርን ጽድቅ ለመማር፤ ለመቀበል ወይንም ለመረዳት ከወንጌል ውጪ ሌላ መንገድ የለም፡፡

በመቀጠልም፣ በ2ኛ ጢሞቴዎስ 1፡10 ሐዋሪያው ጳውሎስ ሌላ የሚያነቃቃ ሀሳብ አካፍሎናል፡- በወንጌሉ አማካኝነት ህይወትና ዘላለማዊነት ወደ ብርሃን ወጥተዋል፡፡ እየተናገረ ያለው ስለ ምን አይነት ህይወት ነው? ስለ መለኮታዊ ህይወት ነው፤ የእግዚሃብሄር ዓይነት ህይወት፤ ሰዎችን የእግዚሃብሄር ልጆች የሚያደርገው ህይወት፤ ይህም ህይወት በኢየሱስ ክርስቶስ ውስጥ ነው፡፡ “ይህ ህይወት በልጁ ውስጥ ነው፤ ልጁ ያለው ህይወት አለው፤ የእግዚሃብሄር ልጅ የሌለው ህይወት የለውም” (1ኛ ዮሐንስ 5፡11-12)፡፡

ዳግም በመወለዳችን፤ የሆንነው ጻድቅ ብቻ ሳይሆን፤ የእግዚሃብሄር ጽድቅ መገለጫዎችም ጭምር ነው፡፡ 2ኛ ቆሮንቶስ 5፡21 እንዲህ ይላል፡- “እኛ በእርሱ ሆነን የእግዚሃብሄር ጽድቅ እንሆን ዘንድ ኃጢአት ያላወቀውን እርሱን ስለእኛ ኃጢአት አደረገው፡፡” ጽድቅ የእናንተ መንፈስ ባህሪይ ሆኗል፡፡ ትክክለኛ የመሆንን ብቃት፤ ትክክለኛ የሆነውን የመስራት፤ ጽድቅን የመስራት ብቃት በመንፈሳችሁ ውስጥ አለ፡፡ ከውስጥ እግዚሃብሄር የሰጣችሁን ትክክል የመሆን ተፈጥሮ ማለትም የጽድቅ ህይወት ከውስጥ ወደ ውጪ ልትኖሩት ትችላላችሁ፡፡

ህይወትና ጽድቅ በወንጌሉ አማካኝነት

በወንጌል አላፍርምና፤ አስቀድሞ ለአይሁዳዊ ደግሞም ለግሪክ ሰው፤ ለሚያምኑ ሁሉ የእግዚሃብሄር ሀይል ለማዳን

ነውና (ሮሜ 1፡ 16-17)።

እሁድ 26

Page 63: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ...ምሳሌ 24:10 በመከራ ቀን ተስፋ እንዳንቆርጥ ወይም እንዳንሸነፍ ይመክረናል፤ ይልቁኑ እኛ

Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org

ለተጨማሪ ጥናት:

የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

1ኛ ቆሮንጦስ 10:14-11:1 & መዝሙረ ዳዊት 139-141

ቆላስያስ 3:1-11 & ትንቢተ ኤርምያስ 12

የዮሐንስ ወንጌል 3:15-17; ሮሜ 3:24-26; ሮሜ 5:17-21;

በተጨማሪም ልእለ-ተፈጥሮአዊ የሆነ ህይወት አላችሁ፤ ልትኖሩትም ትችላላችሁ፤ ይህ ማለት ከሰይጣን፣ ከጨለማ፣ ከሽታን፣ ከህመም፣ ከውድቀት፣ ከሞት፣ በላይ ሆነን ድል እንድንነሳ የሚያደርገን፤ ከዚህ አለም ባሻገር የሆነ ህይወት ነው! ይህ ድንቅ የሆነ ህይወት ከጽድቅ ሥጦታ ጋር ተደምሮ በወንጌሉ አማካኝነት በክርስቶስ ተሰጥቶናል፡፡

ድንቅና ቅዱስ የሆንክ አባት፣ ከአንተ ጋር አንድ ስላደረገኝ በመንፈሴ ውስጥ ስላለው የክርስቶስ ህይወት አመሰግንሃለሁ፤ በእኔ ውስጥ ያለው ያንተ ጽድቅ፤ በየቀኑ በአሸናፊነት እያራመደኝ፤ ትክክለኛውን ነገር እንድሰራ እና በትክክል እንድኖር እያደረገኝ፣ ወደ ህይወቴ ፍጹምነትንና ልቀትን አምጥቷል! በእኔ ውስጥ ባለው የመለኮታዊ ህይወት ኃይል ሙሉ በሙሉ እየተጠቀምኩ፣ በክርስቶስ ውስጥ ባለኝ ማንነት እውነታ እራመዳለሁ፤ በኢየሱስ ስም፡፡ አሜን፡፡

ጸሎት

Page 64: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ...ምሳሌ 24:10 በመከራ ቀን ተስፋ እንዳንቆርጥ ወይም እንዳንሸነፍ ይመክረናል፤ ይልቁኑ እኛ

amharic

እምነት የክርስቲያን ጉዞ መርህ ነው፡- “…በእምነት እንጂ በማየት አንመላለስምና…” (2ኛ ቆሮንቶስ 5፡6-7)፡፡ ያለ እምነት እግዚአብሄርን ደስ ማሰኘት እንደማይቻል መጽሐፍ ቅዱስ በአጽንዖት ይገልጻል (ዕብራውያን 11፡6)፡፡ እንደ መክፈቻ ጥቅሳችን ሁላችንም አንድ አይነት የእምነት መጠን ስለተቀበልን እምነት የሌለው ክርስቲያን የለም፤ የሚያስፈልጋችሁ የእምነታችሁን መጠን ማሳደግ ነው፡፡

ቃሉ እንዴት ጠንካራ እና ውጤታማ እምነትን ማሳደግ እንደሚቻል ይገልጣል፡፡ በመጀመሪያ በቃሉ ውስጥ በቀጣይነት መቆየት አለባችሁ፤ ቃሉም በመንፈሳችሁ ውስጥ እምነትን ይቀሰቅሳል፡- “…እምነት ከመስማት ነው መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነው” (ሮሜ 10፡17)። የእግዚአብሄርን ቃል በሰማችሁ መጠን የጨመረ እምነት ይኖራችኋል፡፡ ወደ መንፈሳችሁ ያነሰ ቃል በተቀበላችሁ መጠን፣ የህይወት ተግዳሮቶች በገጠሟቸሁ ጊዜ ለማሳየት የምትችሉት ያነሰ እምነት ይሆናል፡፡

ደግሞም ሳታሰልሱ በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ስትካፈሉና ከሌሎች አማኞች ጋር ክብረት ስታደርጉ፣ እምነታችሁ ይገነባል (ዕብራውያን 10፡25)፡፡ በቤተ ክርስቲያን ቃሉን ትማራላችሁ፣ ወዲያውም እምነታችሁን የሚያበረታውን የመንፈስ ቅዱስ ጥልቅ የሆነ ህብረት ትደሰቱበታላችሁ፡፡ ያም ሆኖ እምነታችሁን መግለጽ ግድ ይላል፡፡ ያዕቆብ 1፡22 እንዲህ ይላል፡- “ቃሉን የምታደርጉ ሁኑ እንጂ ራሳችሁን እያሳታችሁ የምትሰሙ ብቻ አትሁኑ።” በቃሉ ላይ ያለማሰለስ በማሰላሰልና ቃሉንም በህይወታችሁ ውስጥ በስራ ላይ በማዋል አሸናፊ የሆነ እምነትን ትገነባላችሁ፡፡

እንደ ቃሉ ማድረግ ማለት እምነት ሲገለጽ ነውና፣ ዓለሙንም የሚያሸንፈው እምነታችን ነው፡፡ ያልተገለጸ እምነት ሊያሸንፍ አይችልም፡

እምነት፤ የክርስቲያን ጉዞ መርህ

እግዚአብሔር ለእያንዳንዱ የእምነትን መጠን እንዳካፈለው፥… (ሮሜ 12፡3)፡፡

ሰኞ 27

Page 65: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ...ምሳሌ 24:10 በመከራ ቀን ተስፋ እንዳንቆርጥ ወይም እንዳንሸነፍ ይመክረናል፤ ይልቁኑ እኛ

Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org

ለተጨማሪ ጥናት:

የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

1ኛ ቆሮንጦስ 11:2-34 & መዝሙረ ዳዊት 142-145

ቆላስያስ 3:12-25 & ትንቢተ ኤርምያስ 13

2ኛ ጢሞቴዎስ 2:15; የሐዋርያት ስራ 20:32; ዕብራውያን 11:6; Á°qw 2:17

፡ እምነት ሁልጊዜ ከተጣጣመ ተግባር ጋር መሆን አለበት፡- “እንደዚሁም ሥራ የሌለው እምነት ቢኖር በራሱ የሞተ ነው።” (ያዕቆብ 2፡17 እና 26)፡፡ ስለሆነም፣ ሁልጊዜ እምነታችሁን በቃላትና በተግባራት ግለጹ፡፡

ቃሉን ተግብሩት እንጂ ስለሁኔታዎቻችሁ ወደ እግዚአብሄር አትጩኹ፣ ወይም አታጉረምርሙ፡፡ እምነታችሁን ተጠቀሙበት፡፡ የሠናፍጭ ቅንጣት ያህል እምነት ቢኖራችሁ፣ ተራራውን እንዲሄድ ልትነግሩት ትችላላችሁ፤ ተራራውም ይታዘዛችኋል ሲል ኢየሱስ ተናግሯል፡፡ ያላችሁ እምነት በቂ ነው፤ በዚያ አንድ ነገር አድርጉበት፡፡ ተጠቀሙበት፤ ልትመኙ ለምትችሉት ሁሉ መግዣችሁ ነውና፡፡ ሃሌሉያ!

ቃሉ በእኔ ውስጥ ተግደሮቶችን ለማሸነፍና በክርስቶስ ውስጥ ያለውን ድል አድራጊ ህይወቴን ለመጠበቅ እምነትን ያነቃቃል፡፡ ለእኔ ያለውን የእርሱን ፍጹም ፈቃድ ለሟሟላት በእግዚአብሄር ቃል ውስጥ ስኖር፣ ስመራና በመለኮታዊ ጥበብ ስነቃቃ፤ የጽድቅ፣ የስኬት፣ የመለኮታዊ ጤንነት፣ የድል ነሺነትና የብልጽግና ኃይሎች በህይወቴ ውስጥ ስራ ይጀምራሉ፤ በኢየሱስ ስም፡፡ አሜን፡፡

ጸሎት

Page 66: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ...ምሳሌ 24:10 በመከራ ቀን ተስፋ እንዳንቆርጥ ወይም እንዳንሸነፍ ይመክረናል፤ ይልቁኑ እኛ

amharic

እንደ ክርስቲያኖች እኛ ተራ ህዝቦች አይደለንም፤ በህይወታችሁ ተጠቂዎች ልንሆን ከቶ አይገባም፡፡ ራሳችሁን ነአንዳው ምንም ይሁን ለማሸነፍ የሚያስፈልጋችሁ አላችሁ፡፡ አንዳች ነገር በእናንተ ውስጥ አለ፤ ያም ለውጥን ለማምጣት የሚችል የመንፈስ ቅዱስ ህይወትና ኃይል ነው፡፡

በመክፈቻ ጥቅሳችን ላይ ያለው “ኃይል” የሚለው ቃል በእርግጥም (በግሪኩ) “ዱናሚስ” ማለት ሲሆን፣ ይህም ለለውጥ መንስዔ የሚሆን ወይም ለውጥን ማምጣት የሚችል ብርቱ ኃይል ማለት ነው፡፡ ይህም ከራሳችሁ በላይ የሆነ ኃይልና አቅምን፤ ተአምራት የማድረግ ብርታትን ያመላክታል! ይህም የማድረግ ኃይል ሲሆን አልፎ አልፎም “ችሎታ” ተብሎ ይተረጎማል፡፡ የልቀት ኃይል ማለትም ነው፡፡ ያም በምታደርጉት ሁሉ፣ ብቁና ውጤታማ ለመሆን የሚያስችል ከተለመደው በላይ የሆነ አቅም ነው፡፡ ይህ ነው እንግዲህ በክርስቶስ ውስጥ ያለን ህይወት፤ በመንፈስ ቅዱስ በኩል የሆነ ልዕለ ተፈጥሯዊ ምርታማነት እና ለዘወትር የሚጨምር የክብር ህይወት!

እርሱ በ2ኛ ቆሮንቶስ 3፡5 ላይ “ብቃታችን ከእግዚአብሔር ነው እንጂ፥ በገዛ እጃችን እንደሚሆን አንዳችን እንኳ ልናስብ ራሳችን የበቃን አይደለንም፤” ቢል አይገርምም፡፡ ማናቸውንም ነገር ለማድረግ የእናንተ ብቃት፣ በማናቸውም ነገር ስኬታማ ለመሆን የእናንተ ምክንያት፤ ለልቀት እና ለአዲስ ሃሳብ አመንጪነት የእናንተ ኃይል፣ በእናተ ውስጥ ያለው መንፈስ ቅዱስ ነው፡፡ 2ኛ ቆሮንቶስ 4፡7 እንዲህ ይላል፡- “…የኃይሉ ታላቅነት ከእግዚአብሔር እንጂ ከእኛ እንዳይሆን ይህ መዝገብ በሸክላ ዕቃ ውስጥ አለን፤”፡፡

ስለዚህ በህይወታችሁ እየታገላችሁ ካላችሁ፣ ብዙ ጥረት እያደረጋችሁ እና ከጥረታችሁ ጋር የማይመጣጠን ስኬት እያስመዘገባችሁ ከሆነ፣ ምናልባትም ምክንያቱ በእናንተ ውስጥ ስላለው ስለ መንፈስ ቅዱስ ኃይል ግንዛቤው ስለሌላችሁ እና እየተጠቀማችሁበት ስላልሆነ ነው፡፡ ጳውሎስ “በእኔ ውስጥ ባለው በክርስቶስ ኃይል ሁሉን ማድረግ እችላለሁ” ብሏል፤

የመንፈስ ቅዱስ ኃይል

ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ በወረደ ጊዜ ኃይልን ትቀበላላችሁ፥ (የሐዋርያት ሥራ 1፡8)፡፡

ማክሰኞ 28

Page 67: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ...ምሳሌ 24:10 በመከራ ቀን ተስፋ እንዳንቆርጥ ወይም እንዳንሸነፍ ይመክረናል፤ ይልቁኑ እኛ

Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org

ለተጨማሪ ጥናት:

የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

1ኛ ቆሮንጦስ 12 & መዝሙረ ዳዊት 146-150

ቆላስያስ 4:1-9 & ትንቢተ ኤርምያስ 14

ሮሜ 15:18-19; የሐዋርያት ስራ 6:8; የሉቃስ ወንጌል 4:14

ነብዩ ሚክያስ “…በእግዚአብሔር መንፈስ ኃይልንና ፍርድን ብርታትንም ተሞልቻለሁ።” ሲል አስረግጧል (ሚክያስ 3፡8)፡፡

መረዳቱ ይኑራችሁ እና በውስጣችሁ ያለውን የመንፈስ ቅዱስ ኃይል ተጠቀሙበት፡፡ በዚያ ኃይልም እናንተ የማይታሰበውን፣ የማይታለመውን እና የማይቻለውን ማድረግ ትችላላችሁ (ኤፌሶን 3፡20)፡፡ ክርስትና እንዲህ ነው፤ የመግዛት ህይወት ነው፡፡ የምትሹት ኃይል ሁሉ በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት በእናንተ ውስጥ ነውና እርዳታንና ኃይልን ፍለጋ ከሥፍራ ሥፍራ መባዘን አያስፈልጋችሁም፡፡ ሥራ ላይ አውሉት፡፡

እኔን የሚመለከተውን ሁሉ፣ ጌታ ይፈጽማል፤ ሁልጊዜ እርሱን ደስ የሚያሰኘውን እንድሻ እና እንዳደርግ እያደረገ የእርሱ ኃይል በእኔ ውስጥ በሥራ ላይ ነው፡፡ በክርስቶስ ውስጥ ያለኝን ፍጻሜ እያሟላሁና ጌታም በእኔ ውስጥ ዛሬም፣ ሁሌም እየከበረ ነው፤ በኢየሱስ ስም፡፡ አሜን፡፡

ጸሎት

Page 68: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ...ምሳሌ 24:10 በመከራ ቀን ተስፋ እንዳንቆርጥ ወይም እንዳንሸነፍ ይመክረናል፤ ይልቁኑ እኛ

Te ¨h

Te ¨

h

amharic

Page 69: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ...ምሳሌ 24:10 በመከራ ቀን ተስፋ እንዳንቆርጥ ወይም እንዳንሸነፍ ይመክረናል፤ ይልቁኑ እኛ

Te ¨h

Te ¨

h

Page 70: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ...ምሳሌ 24:10 በመከራ ቀን ተስፋ እንዳንቆርጥ ወይም እንዳንሸነፍ ይመክረናል፤ ይልቁኑ እኛ

amharic

ለክርስቲያን የሆነ መንፈሳዊ ቋንቋ አለ፡፡ እንደ እግዚአብሄር ልጅ ልዕለ ተፈጥሯዊ የሆነው ህይወታችሁ የተመሰረተው በአንደበታችሁ ስለሆነ፣ ቃሉን በከንፈሮቻችሁ ላይ ማስቀመጥ የሚገባችሁ ለዚያም ነው፡፡ አንደበታችሁ ህይወታችሁን ይመራዋል፡፡ ኢየሱስ በማቴዎስ 12፡36-37 ላይ እንዲህ ይላል፡- “እኔ እላችኋለሁ፥ ሰዎች ስለሚናገሩት ስለ ከንቱ ነገር ሁሉ በፍርድ ቀን መልስ ይሰጡበታል፤ ከቃልህ የተነሣ ትጸድቃለህና ከቃልህም የተነሣ ትኰነናለህ”።

ቃል በቃል አንድ ሰው ወደ መንግሥተ ሰማይ ወይም ወደ ገሃነም የሚሄደው ከገዛ ቃሉ የተነሣ ነው ማለት ነው፡፡ በሮሜ 10፡8-10 ላይ ያለውን ስለ ደህንነት ሐዋርያው ጳውሎስ ያስቀመጠውን አነጋገር አንብቡ፡- “…ኢየሱስ ጌታ እንደ ሆነ በአፍህ ብትመሰክር እግዚአብሔርም ከሙታን እንዳስነሣው በልብህ ብታምን ትድናለህና፤ ሰው በልቡ አምኖ ይጸድቃልና በአፉም መስክሮ ይድናልና”።

ሐዋርያው ያዕቆብ አንደበትን አንድ የመርከብ መሪ መርከብን ወደፈለገው አቅጣጫ እንዲሄድ ከሚመራበት ከአንድ ትልቅ መርከብ ጋር አመሳስሎታል (ያዕቆብ 3፡4-5)፡፡ እንዲሁም በተመሣሣይ፣ ህይወታችሁ ቃሎቻችሁ የሚነበብበት ፊደል ነው፡፡ ቃሎቻችሁ ጤናማ ከሆኑ፣ ህይወታችሁ ፍጹም የላቀ እና ክብር የሞበት ይሆናል፡፡ ምሳሌ 15፡4 “ፈዋሽ ምላስ የሕይወት ዛፍ ነው…” ይላል፡፡ ኢየሱስ የምታገኙት የምትናገሩትን ነው ሲል አስተምሯል (ማርቆስ 11፡24)፡፡

የምትናገሩትን አስተውሉ፤ ህይወታችሁን የሚቆጣጠሩት ንግግሮቻችሁ ናቸውና፡፡ በራሳችሁ ቃሎች ራሳችሁን በጤና፣ በደህንነት፣ በብልጽግና እና በድል ነሺነት መጠበቅ ትችላላችሁ፡፡ በእምነት በተሞሉ እወጃዎቻችሁ ህይወታችሁን እግዚአብሄር ለእናንተ ወዳለው የፍጻሜ አቅጣጫ ምሩት፡፡

ቃሎቻችሁ እና ህይወታችሁ

በአፍህ ቃል ተጠመድህ በአፍህ ቃል ተያዝህ (ምሳሌ 6፡2)።

ረቡዕ 29

Page 71: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ...ምሳሌ 24:10 በመከራ ቀን ተስፋ እንዳንቆርጥ ወይም እንዳንሸነፍ ይመክረናል፤ ይልቁኑ እኛ

Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org

ለተጨማሪ ጥናት:

የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

1ኛ ቆሮንጦስ 13 & መጽሀፈ ምሳሌ 1-2

ቆላስያስ 4:10-18 & ትንቢተ ኤርምያስ 15

የማርቆስ ወንጌል 11:23; መዝሙረ ዳዊት 34:12-13; መጽሀፈ ምሳሌ 18:21

ሁልጊዜም ስኬትና መጨመርን ብቻ ተናገሩ፡፡1ኛ ጴጥሮስ 3፡10 “ሕይወትን ሊወድ መልካሞችንም ቀኖች ሊያይ

የሚፈልግ ሰው፥ መላሱን ከክፉ ከንፈሮቹንም ተንኰልን ከመናገር ይከልክል፤” ይላል፡፡ ምሳሌ 18፡21 “ሞትና ሕይወት በምላስ እጅ ናቸው የሚወድዱአትም ፍሬዋን ይበላሉ።” ይላል፡፡ የከበረ ህይወታችሁን በቃሎቻችሁ ፍጠሩና አጽኑ፡፡ በራሳችሁ ቃሎች፤ መሆን የምትፈልጉትን ማናቸውንም ነገር መሆን፣ ማግኘት የምትችሉትን ማናቸውንም ነገር ማግኘት፣ እና መፈጸም የምትፈልጉትን ማናቸውንም ነገር መፈጸም ትችላላችሁ፡፡

ህይወቴ የላቀና የከበረ ነው፤ በመንፈስ ቅዱስ መግዛት ውስጥ ሆኜ እመላለሳለሁ፡፡ የእኔ የህይወት ጉዞ ወደ ላይ እና ወደ ፊት ብቻ ነው፡፡ እኔ በስኬት፣ በድል ነሺነት እና በዘላለማዊ ብልጽግና ጎዳና ላይ ነኝ፡፡ እግዚአብሄር ለእኔ ባለው ፍጻሜ ውስጥ እየተመላለስኩ እና እያሟላሁ ነኝ፡፡

ጸሎት

Page 72: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ...ምሳሌ 24:10 በመከራ ቀን ተስፋ እንዳንቆርጥ ወይም እንዳንሸነፍ ይመክረናል፤ ይልቁኑ እኛ

amharic

በመክፈቻ ጥቅሳችን ላይ ጥቅም ላይ የዋለው “ቤዛነት” የሚለው ቃል “ሉትሮሲስ” ከሚለው ከግሪኩ የተወሰደ ሲሆን ትርጓሜውም መቤዠት (ወይም ገንዘብ ከፍሎ ማስለቀቅ)፣ ነጻ ማውጣት፣ ማዳን ወይም ከመከራ ማውጣት ማለት ነው፡፡ የእርሱ ደም ለዓለሙ ሁሉ የከፈለው የኃጥያት ዋጋ ሆኖ ጌታ ኢየሱስ ሰውን ከኃጥያት በመስቀሉ ላይ ተቤዠው፡፡ ከዚያም እርሱ ተቀበረ፤ በሦሥተኛውም ቀን እግዚአብሄር እርሱን ከሙታን በአዲስ ህይወት፣ በትንሣዔ ህይወት አስነሳው፡፡ በእርሱ የሚያምን እያንዳንዱ የተቀበለውም ይህንኑ የትንሣዔ ህይወት ነው፡፡

እንዲሁም ዳግም ተወልዳችሁ የትንሣኤው ህይወት ያላችሁ፣ የክርስቶስ የቤዛነት ሥራ ፍሬዎች ናችሁ “የተቤዣችሁ” አይደላችሁም፡፡ አዲሱ ፍጥረት እንደ “ተቤዠ” ተደርጎ የሚገለጽበትን የመጽሃፍ ቅዱስ ሥፍራ ሲያጠኑ አንዳንድ ሰዎች ግራ ይጋባሉ፡፡ ለምሳሌ በራዕይ 5፡9-10 ላይ መጽሐፍ ቅዱስ መጽሐፉን ትወስድ ዘንድ ማኅተሞቹንም ትፈታ ዘንድ ይገባሃል፥ ታርደሃልና፥ በደምህም ለእግዚአብሔር ከነገድ ሁሉ ከቋንቋም ሁሉ ከወገንም ሁሉ ከሕዝብም ሁሉ ሰዎችን ዋጅተህ ለአምላካችን መንግሥትና ካህናት ይሆኑ ዘንድ አደረግሃቸው፥ በምድርም ላይ ይነግሣሉ እያሉ አዲስን ቅኔ ይዘምራሉ። ይላል፡፡

በዚህ ሥፍራ ላይ “ዋጅተህ” የሚለው ቃል በስህተት የተተረጎመ ነው፤ ይኸውም ከግሪኩ “አጎራዞ” ከሚለው የተወሰደ፣ ትርጓሜውም ግዢ መፈጸም፣ አንድን ነገር በስጦታ መልክ ለአንድ ሰው ለመስጠት መግዛት ማለት ነው፡፡ እንደ “ሉትሮሲስ” መልሶ መግዛት ማለት ሳይሆን፣ እንደ አዲስ መግዛት ማለት ነው፡፡ ክርስቶስ በደሙ ገዛንና ለእግዚአብሄር እንደ ስጦታ አበረከተን፡፡

በርካታ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች ይህን ጥቅስ በእርግጥ ትክክለኛውን ትርጓሜ ሰጥተውታል፡፡ አዲሱ መደበኛ ትርጉም፡- በደምህም ለእግዚአብሄር ከነገድ ሁሉ፣ ከቋንቋም ሁሉ ከወገንም ሁሉ ከሕዝብም ሁሉ

በደም ተገዝተናል

የዘላለምን ቤዛነት አግኝቶ አንድ ጊዜ ፈጽሞ ወደ ቅድስት በገዛ ደሙ ገባ እንጂ በፍየሎችና በጥጆች ደም አይደለም

(ዕብራውያን 9፡12)።

ሐሙስ 30

Page 73: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ...ምሳሌ 24:10 በመከራ ቀን ተስፋ እንዳንቆርጥ ወይም እንዳንሸነፍ ይመክረናል፤ ይልቁኑ እኛ

Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org

ለተጨማሪ ጥናት:

የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

1ኛ ቆሮንጦስ 14 & መጽሀፈ ምሳሌ 3-4

1ኛ ተሰሎንቄ 1:1-10 & ትንቢተ ኤርምያስ 16

ዕብራውያን 4:14-16; 1ኛ ቆሮንጦስ 6:20

ሰዎችን ገዛህ ይላል፡፡ ህያው ቃል መጽሐፍ ቅዱስ ደግሞ፤- “…ታርደሃልና፣ ደምህም ከሕዝብ ሁሉ ሰዎችን ለእግዚአብሄር እንደ ስጦታ ገዝቷልና፡፡” ይላል፡፡ እናንተ በኢየሱስ ለእግዚአብሄር ስጦታዎች ናችሁ፤ እርሱ በዋጋ ማለትም በደሙ ገዝቷችኋል!

አሁን እናንተ የእግዚአብሄር ናችሁ፡፡ እናንተ ኢየሱስ በመስቀሉ ላይ ሲሞት ከዲያብሎስ “ነጻ የወጣችሁ”፣ “ነጻ በመውጣት” ላይ ያላችሁ ሰዎች አይደላችሁም፤ ከሰይጣን፣ ከዓለም፣ ከሚወድቀው ስርዓቱ እና ይዘቱ በላይ ሆናችሁ የተወለዳችሁ አዲስ ፍጥረቶች ናችሁ፡፡ እግዚአብሄርን ከሚመስሉ ጋር ህብረት አድራጊዎች ናችሁ፡- ስለ ክፉ ምኞት በዓለም ካለው ጥፋት አምልጣችሁ ከመለኮት ባሕርይ ተካፋዮች በተስፋ ቃል እንድትሆኑ፥ በእነዚያ ክብርና በጎነት የተከበረና እጅግ ታላቅ የሆነ ተስፋን ሰጠን። (2ኛ ጰየጥሮስ 1፡4) ይላል፡፡

ቸር አባት ሆይ፣ ከዓመጻ ሁሉ ስለነጻሁበት ክቡር ስለሆነው ስለ ኢየሱስ ደም አመሰግንሃለሁ፡፡ እኔ በክርስቶስ ላለኝ የጽድቅ ህይወት በምሰጋና የተሞላሁ፣ እንደ እግዚአብሄርን ከሚመስሉ ጋር ህብረት ያለኝ፣ አዲስ ፍጥረት ነኝ፡፡ በህይወቴ ውስጥ እየሰራ ባለው የአንተ ኃይልና ክብር ሃሴት አደርጋለሁ፤ በኢየሱስ ስም፡፡ አሜን፡፡

ጸሎት

Page 74: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ...ምሳሌ 24:10 በመከራ ቀን ተስፋ እንዳንቆርጥ ወይም እንዳንሸነፍ ይመክረናል፤ ይልቁኑ እኛ

amharic

የእርሱ መንግስት በልባችን ውስጥ

ዮሐንስም አልፎ ከተሰጠ በኋላ ኢየሱስ የእግዚአብሔርን መንግሥት ወንጌል እየሰበከና። … ወደ ገሊላ መጣ

(ማርቆስ 1፡14)።

አርብ 31

ኢየሱስ የእግዚአብሄርን መንግስት ወንጌል እየሰበከ መጣ፡፡ ዘመኑ ተፈጸመ፤ የእግዚአብሄር መንግስት ቀርባለች አለ (ማርቆስ 1፡14-15)፡፡ የእግዚአብሄር መንግስት ምንድነው?

በመጀመሪያ የእግዚአብሄር መንግስት አንድ ስፍራ አይደለም፤ የእርሱን ክብር እና የእርሱን ክብር እና የእርሱን በጎነት፣ እርሱ ራሱን የሚገልጥበት፤ እርሱ የሚገዛበት፣ የሚመራበት፣ እርሱ አለቃ የሚሆንበት፣ እርሱ ጌታ የሚሆንበት የእግዚአብሄር መንገሥ ነው፡፡

ኢየሱስ የእግዚአብሄር መንግስት በዚያ ወይም በዚህ ናት ቢሏችሁ አትመኗቸው፤ ምክንያቱም መንግስቱ በመጠባበቅ አትመጣምና፤ በመካከላችሁ ናት ያለውም ለዚያ ነው (ሉቃስ 17፡20-21)፡፡ እግዚአብሄር እቅድ መንግስቱን በሰዎች ልብ ውስጥ መመስረት ነው፤ ሆኖም ያ መንፈሳዊ መንግስት ነው፡፡

በዮሀንስ ወንጌል ምዕራፍ 18 በቁጥር 36-37 ላይ ኢየሱስ በጲላጦስ ፊት የቀረበበትን አስታውሱ፤ ጲላጦስ ለጠየቀው አንዳንድ ጥያቄዎች እርሱ ሲመልስ “…መንግስቴ ከዚህ ዓለም አይደለችም…“ አለ (ዮሐንስ 18፡36)፡፡ የእግዚአብሄር መንግስት አካላዊ ተቋም አይደለቸም፤ ያም ሆኖ ግን ኢየሱስ፡- “ቀርባለች” አለ፤ በእርግጥም ቀርባለች፤ በልባችሁ ውስጥ ናት፡፡ ኢየሱስ የሰበከው የመንግስቱ ወንጌል፡- “ሁላችሁ ስሙ፣ የእግዚአብሄር መንግስት አሁን በእናንተ ልብ ውስጥ ልትመሰረት ትችላለች፤ ደርሳለች! ይህንን የሚያምን ማንም ሰው አሁኑ የእግዚአብሄር ዋና መስሪያ ቤት እና የተግባር ማዕከል መሆን ይችላል፡፡” የሚል ነው፡፡ ይህ ግን በአብርሃም፣ በሙሴ፣ በኤልያስ፣ በኤልሣዕ፣ በዳዊት፣ በሰለሞን እና ጥንታዊ አበው ዘመን

Page 75: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ...ምሳሌ 24:10 በመከራ ቀን ተስፋ እንዳንቆርጥ ወይም እንዳንሸነፍ ይመክረናል፤ ይልቁኑ እኛ

Leave comments on today’s devotional at www.rhapsodyofrealities.org

ለተጨማሪ ጥናት:

የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የሁለት ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

ውድ አባት ሆይ፣ የክብርን ህይወት ወደ ውስጤ እንዲህ ይዞ ስላመጣልኝ፣ በልቤ ውስጥ ስለተመሰረተው የእግዚአብሄር መንግስት አመሰግንሃለሁ፡፡ ህይወቴ ለአንተ ክብር እንደሆነ አውጃለሁ፤ ደግሞም የአንተን በጎነት፣ ልቀት፣ ፍጹምነት፣ እና ውበት እገልጣለሁ፤ በኢየሱስ ስም፡፡ አሜን!

ጸሎት

1ኛ ቆሮንጦስ 15:1-34 & መጽሀፈ ምሳሌ 5-7

1ኛ ተሰሎንቄ 2:1-9 & ትንቢተ ኤርምያስ 17

የሉቃስ ወንጌል 17:20-21; ቆላስያስ 1:27; 2ኛ ቆሮንጦስ 4:6-7

የሚቻል አልነበረም፤ በእኛ ጊዜ ግን ተችሏል፡፡ኢየሱስ በመጣ ጊዜ መንግስቱን በውስጡ ይዞ መጣ፡፡ እኛ ደግሞ

አሁን እርሱን ተቀብለናልና፣ መንግስቱ በልባችን ውስጥ አለን፤ የእግዚአብሄር ሰላሙ፣ ውበቱ፣ ክብሩ፣ ጸጋው እና ህይወቱ በልባችን ውስጥ ተመስርቷል! አሁን እግዚአብሄር በእናንተ ውስጥ እየኖረ ነው፡፡ እንደምን ያለውን ህይወት ይዞ አመጣልን፤ እናም እኛን አስገባን! እንዴት ያለ ወንጌል ነው!

Page 76: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ...ምሳሌ 24:10 በመከራ ቀን ተስፋ እንዳንቆርጥ ወይም እንዳንሸነፍ ይመክረናል፤ ይልቁኑ እኛ

united kingdom: +44 (0)1708 556 604

nigeria:+234 812 340 6547+234 812 340 6791

canada:+1-647-341-9091

usa:+1 (0) 980-219-5150+1-281-759-5111+1-281-759-6218

south africa: +27 11 326 0971

በዚህ መጸሐፍ እንደተባረካችሁ እናምናለን፡፡ ክርስቶስ ኢየሱስን በሕይወታችሁ ጌታ እንድታደርጉ እንጋብዛችኋለን፡፡

ጌታ እግዚአብሔር ሆይ ኢሱስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ፤ በሙሉ ልቤ አምነለሁ ፡፡ ለእኔ ሲል እንደሞተ እና እግዚአብሔርም ከሞት እንዳስነሳው አምናለሁ፡፡ ዛሬ ሕው እንደሆነ አምናለሁ፡፡ ከዛሬ ጀምሮ ኢየሲስ ክርስቶስ የሕይወቴ ጌታ እንደሆነ በአፌ አውጃለሁ፡፡ በእርሱ በኩል እና በስሙ ዘላለማዊ ሕይወት አለኝ፡፡ዳግም ተወልጃለሁ፡፡ ጌታሆይ ነብሴን ስላዳንካት አመሰግንሀለሁ! አሁን የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ፡፡ ሀሌሉያ!

እንኳን ደስ ያልዎት፤ አሁን የእግዚአብሔር ልጅ ኖት፡፡ እንደክርስቲያን በመንፈሳዊ ሕይወትዎ እንዲያድጉ ከኋላ በተጻፈውን ስልክ ቁጥር ይደውሉ፡፡

የደህንነት ጸሎት

amharic

Page 77: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ...ምሳሌ 24:10 በመከራ ቀን ተስፋ እንዳንቆርጥ ወይም እንዳንሸነፍ ይመክረናል፤ ይልቁኑ እኛ

Pastor Chris Oyakhilome, the President of Believers’ LoveWorld Inc., a dynamic, multifaceted, global

ministry, is the author of Rhapsody of Realities, the world’s #1 daily devotional, and more than 30 other books. He’s a dedicated minister of God’s Word whose message has brought the reality of the divine life to the hearts of many.

Millions have been affected by his television broadcast, “Atmosphere For Miracles,” which brings God’s divine presence right into people’s homes. The scope of his television ministry extends throughout the world with LoveWorld satellite television networks, delivering qualitative Christian programming to a global audience.

A t the wor ld - renowned Hea l ing Schoo l , he manifests the heal ing works of Jesus Christ and has helped many receive healing through the operation of the gifts of the Spirit.

Pastor Chris has a passion to reach the peoples of the world with God’s presence—a divine commission he’s fulfilled for more than 30 years through various outreaches, crusades, as well as several other platforms that have helped millions experience a victorious and purposeful life in God’s Word.

ABOUT THE AUTHOR

Page 78: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ...ምሳሌ 24:10 በመከራ ቀን ተስፋ እንዳንቆርጥ ወይም እንዳንሸነፍ ይመክረናል፤ ይልቁኑ እኛ

Te ¨h

Te ¨

h

amharic

Page 79: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ...ምሳሌ 24:10 በመከራ ቀን ተስፋ እንዳንቆርጥ ወይም እንዳንሸነፍ ይመክረናል፤ ይልቁኑ እኛ

Te ¨h

Te ¨

h

Page 80: ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ...ምሳሌ 24:10 በመከራ ቀን ተስፋ እንዳንቆርጥ ወይም እንዳንሸነፍ ይመክረናል፤ ይልቁኑ እኛ

Te ¨h

Te ¨

h

amharic