st john the devine cathedral _amharic

11
1 ቅዱስ ዮሐንስ ካቴድራል በግደይ /ኪዳን antiglobalconspiracy.blogspot.com / [email protected] የኒው ዮርክ ከተማ መውደም እላዩ ላይ የተቀረፀበት፣ ባእድ ምልክቶች የወረሩት፣ በውስጡ እንግዳ አምልኮዎች የሚካሄዱበት፣ በይፋ አዲስ የአለም ሃይማኖት ማምጣት የሚሻ የመረዳት ቤት አምልኮ (Temple of Understanding) የተባለ ክርስትያናዊ ያልሆነ ተቋም መቀመጫ የሆነይህ ካቴድራል በእርግጥም አንዳንዶች ሊሉ እንደሚችሉት ለየት ያለ ነው፡፡ አው ልዩ የሚያደርገው አዲሱ- አረመኔያዊ-ሴጣናዊ-ስነምህዳሩ-ከሰው-ሂወት-ይበልጣል የሚል አምልኮ መሆኑ ነው፡፡ ሰው በግሉ የፈለገውን ክፋት ቢያምን በግሉ ይጠየቅበታል ቤተ ክርስቲያን እየሄድን ነው የሚሉትን እንዲህ ማሳሳት ግን እጅግ በጣም ክፉ ድርጊት ነው፡፡ የአረመኔያዊ (ፓጋን) ምሁራን ዋና ሃሳቦቻቸውን የክርስቲያናዊ ቃላት ጨርቅ ያለብሳሉ፣ የምልክቶቻቸውን መፍቻ ግን ከሚስጥር ለተቋደሱና በቃል ኪዳን ለታሰሩ ብቻ ይገልፁላቸዋል፡፡(Manly P. Hall, The Secret Teachings of All Ages) የካቴድራሉ ቅድመ ታሪክ ይህ ያላለቀ ህንፃ በዓለም ትልቁ ካቴድራል ነው ይባላል፡፡ የዓለም ቁንጮ ከበርቴዎች ሲደጉሙና የኒው ዮርክ ሜሶኖች ዋና አለቃ (ግራንድ ማስተር) ሲደግፉ እንዲህ ለመስራት መመኘቱ ቅዠት አይሆንም፡፡ በፍሪሜሶኖች የህንፃው ምርቃት ከፍተኛ ቦታ የተሰጠው የነበረ ሲሆን ሜሶኒክ ዎርልድበተሰኘ ህትመታቸው የህዳር 1925 ቅፅ ላይ የፊት ሽፋን ላይ ስእሉ ወጥቶ ነበር፡፡ በውስጡ የሚከተለውን ፅሁፍ አውጥቶ ነበር፡- በታላቁ የካቴድራሎች ግንባታ ዘመን ዋና ገንቢዎች የነበሩት ሜሶኖች አሁን ደግሞ

Upload: giday-geberkidan

Post on 22-Oct-2014

236 views

Category:

Documents


0 download

DESCRIPTION

የኒው ዮርክ ከተማ መውደም እላዩ ላይ የተቀረፀበት፣ ባእድ ምልክቶች የወረሩት፣ በውስጡ እንግዳ አምልኮዎች የሚካሄዱበት፣ በይፋ አዲስ የአለም ሃይማኖት ማምጣት የሚሻ የመረዳት ቤት አምልኮ (Temple of Understanding) የተባለ ክርስትያናዊ ያልሆነ ተቋም መቀመጫ የሆነ… ይህ ካቴድራል በእርግጥም አንዳንዶች ሊሉ እንደሚችሉት ለየት ያለ ነው፡፡ አው ልዩ የሚያደርገው አዲሱ-አረመኔያዊ-ሴጣናዊ-ስነምህዳሩ-ከሰው-ሂወት-ይበልጣል የሚል አምልኮ መሆኑ ነው፡፡ ሰው በግሉ የፈለገውን ክፋት ቢያምን በግሉ ይጠየቅበታል ቤተ ክርስቲያን እየሄድን ነው የሚሉትን እንዲህ ማሳሳት ግን እጅግ በጣም ክፉ ድርጊት ነው፡፡

TRANSCRIPT

Page 1: St John the Devine Cathedral _Amharic

1

ቅዱስ ዮሐንስ ካቴድራል በግደይ ገ/ኪዳን antiglobalconspiracy.blogspot.com / [email protected]

የኒው ዮርክ ከተማ መውደም እላዩ ላይ የተቀረፀበት፣ ባእድ ምልክቶች የወረሩት፣ በውስጡ እንግዳ አምልኮዎች የሚካሄዱበት፣ በይፋ አዲስ የአለም ሃይማኖት ማምጣት የሚሻ የመረዳት ቤት አምልኮ (Temple of Understanding) የተባለ ክርስትያናዊ ያልሆነ ተቋም መቀመጫ የሆነ… ይህ ካቴድራል በእርግጥም አንዳንዶች ሊሉ እንደሚችሉት ለየት ያለ ነው፡፡ አው ልዩ የሚያደርገው አዲሱ-አረመኔያዊ-ሴጣናዊ-ስነምህዳሩ-ከሰው-ሂወት-ይበልጣል የሚል አምልኮ መሆኑ ነው፡፡ ሰው በግሉ የፈለገውን ክፋት ቢያምን በግሉ ይጠየቅበታል ቤተ ክርስቲያን እየሄድን ነው የሚሉትን እንዲህ ማሳሳት ግን እጅግ በጣም ክፉ ድርጊት ነው፡፡ “የአረመኔያዊ (ፓጋን) ምሁራን ዋና ሃሳቦቻቸውን የክርስቲያናዊ ቃላት ጨርቅ ያለብሳሉ፣ የምልክቶቻቸውን መፍቻ ግን ከሚስጥር ለተቋደሱና በቃል ኪዳን ለታሰሩ ብቻ ይገልፁላቸዋል፡፡” (Manly P. Hall, The Secret Teachings of All Ages) የካቴድራሉ ቅድመ ታሪክ ይህ ያላለቀ ህንፃ በዓለም ትልቁ ካቴድራል ነው ይባላል፡፡ የዓለም ቁንጮ ከበርቴዎች ሲደጉሙና የኒው ዮርክ ሜሶኖች ዋና አለቃ (ግራንድ ማስተር) ሲደግፉ እንዲህ ለመስራት መመኘቱ ቅዠት አይሆንም፡፡ በፍሪሜሶኖች የህንፃው ምርቃት ከፍተኛ ቦታ የተሰጠው የነበረ ሲሆን “ሜሶኒክ ዎርልድ” በተሰኘ ህትመታቸው የህዳር 1925 ቅፅ ላይ የፊት ሽፋን ላይ ስእሉ ወጥቶ ነበር፡፡ በውስጡ የሚከተለውን ፅሁፍ አውጥቶ ነበር፡- “በታላቁ የካቴድራሎች ግንባታ ዘመን ዋና ገንቢዎች የነበሩት ሜሶኖች አሁን ደግሞ

Page 2: St John the Devine Cathedral _Amharic

2

በአሜሪካ ታላቁን ካቴድራል ለመገንባት በሚደረገው እንቅስቃሴ ሰፊ ቦታ መያዛቸው ተገቢ ነው፡፡ … በካቴድራል ግንባታው ዘመን ስለ ፍሪሜሶኖች ታሪክ

ብዙ መናገር አያስፈልግም፣ ሃውልቶቹ እንደ ብልሃቱ፣ እምነቱ እና ምልክቶቹ ምርጥ ታሪኮቹ ናቸው፡፡” ፅሁፉ በግልፅ ካቴድራሎቹ የወንድማማችነቱ ምርጥ ትውፊቶች መሆናቸውን ይገልፃል፣ ምልክቶቹም በግልፅ እንዲታዩ ተደርጓል፡፡ ብዙሃኑ ግን ይህን ከጥበቡ በስተጀርባ ያለውን መልእክት ለመረዳት ብዙ ይቀራቸዋል፡፡

እናም መመልከትና ሳይረዱ ማድነቅ ብቻ ይሆናል ተግባራቸው፡፡

በግራ፡ ካቴድራሉ ላይ የመገኝ የፒራሚድ ስራ ከጫፉ ዶላር ላይ

እንዳለው ዓይን አለው፡፡

ፍሪሜሶኖች እራሳቸውን እንደ ጥንታዊ ሚስጥር ጠባቂዎች አድርገው ያቀርባሉ፡፡ እኚህ ታድያ በአሰቃቂ ቃለመሃላ ለሚያስሯቸው አባሎቻቸው የሚሰጡት የባእድ አምልኮና የጥንታዊ እምነት ትምህርቶቻቸው ናቸው፡፡ እኚህ ትምህርቶች ከጥንታዊ ግብፅ፣ ከባቢሎን፣ ከይሁዴዎቹ ካባላ፣ እና ከግኖስቲሳውያን አስተምህሮዎች የተገኙ ናቸው፡፡ የሚስጥር ማህበራት በቤተክርስቲያን እንዳይወገዙ እምነቶቻቸውን ይሸፋፍናሉ፡፡ በአውሮፓ ፍሪሜሶኖችና መሰሎቻቸው፡- ሮዚክሩሳውያን እና የቤተመቅደሱ ባለሟሎች (ናይትስ ቴምፕላርስ) በሙሉ በሴጣን አምልኮ ተግባር ይከሰሳሉ፡፡ ከታች መዓርግ ያሉት ፍሪሜሶኖች ቀና ክርስቲያን ሲሆኑ ከላይ መአርግ መድረስ የሚፈልጉት ግን የጥንታዊ ሚስጥራዊ እምነቶችን መመርያዎችንና ፍልስፍናዎችን እንዲያጠኑ ይደረጋሉ፡፡ ፍሪሜሶኖች ህዝቡ የነሱን እምነት እንዲቀበል አይጠብቁም፣ ይህ ከሚስጥራቸው ለሚካፈሉት ብቻ የሚሰጥ ነው፡፡ ሆኖም ግን በሂወት ከፍተኛ ቦታ ላይ የወጡ ሜሶኖች ህዝቡ የነሱን አረመኔ (ፓጋን) እምነት ቀለል ባለ መልኩ እንዲቀበል ይሰራሉ፡፡ ከስር እናየዋለን፡፡

Page 3: St John the Devine Cathedral _Amharic

3

በካቴድረሉ ያሉ ምልክቶች ካቴድራሉ ከደጅ ለሚያየው ሰው እጅግ የሚደንቅና የሚያንበረክክ ነው፡፡ ምንድን ነው የሚያንበረክከው? በዙርያው ያለው የጥበብ ስራን አንመለከታለን፡፡ ዘመነ ፍፃሜ የህንፃው ምእራባዊው ግንብ በኩል እንግዳ ስሜት የሚፈጥሩ ቅርፃች ተሰርተዋል፡፡ ከሁሉም የሚገርመው የኒው ዮርክ ከተማ ውድመትን የሚያሳየው ነው፡፡

ኒው ዮርክ ከተማ ሲፈራርስ፡፡ ይህ ንድፍ የዓለም ንግድ ማእከል መንትያ ማማዎች ከመፍረሳቸው 4 ዓመት በፊት በ1997 ነው የተቀረፀው፡፡ ሌሎችም የታወቁ ሰማይ ጠቀስ ህንፃዎች ይታያሉ፡፡ ከስር የሚታየው አምድ ላይ

የተቀረፀው ትእይን ለኒው ዮርክ ከተማ ነዋሪዎች አስፈሪው ሊሆን ይችላል፡፡ ብርቅዬ ድልድያቸው የብሮክሊን ድልድይ ሲገመስና መኪኖች ሲገለበጡ፣ በቀኙ በኩል የነፃነት ሃውልቷ ውሃ ውስጥ ስትሰጥም፣ የኒው ዮርክ የድርሻ ገበያም በዙርያው ሰዎች እቃ ሲሸጡ ይታያል፡፡ ከስራቸውም እባብ፣ ጊንጥ፣ እቁራሪት፣ አፅመ ሰብ ይታያል፡፡ (በሽታና ቸነፈር?) የዚህ አስገራሚ ቅርፅ ዓላማ ምንድን ነው? የፍፃሜ ዘመንን የፃፈልን ቅዱስ ዮሐንስ ነው ካቴድራሉም በስሙ ነው፡፡ ይህ የተቀረፀው ቅርፅ ኒው ዮርክን ታላቂቱ ባቢሎን ያደርጋታል ማለት ነው፡፡ ከተማይቱ በእግዛብሔር ቁጣ እንደምትጠፋ መፅሐፍ ቅዱስ ይናገራል፡-

“በብርቱም ድምፅ፡- ታላቂቱ ባቢሎን ወደቀች፣ ወደቀች፣ የአጋንንትም ማደርያ ሆነች፣ የርኩሳንም መናፍስት ሁሉ መጠጊያ የርኩሳንና የተጠሉም ወፎች ሁሉ መጠግያ ሆነች፤ አህዛብ ሁሉ ከዝሙትዋ ቁጣ ወይን ጠጅ የተነሳ ወድቀዋልና፣ የምድርም ነገስታት ከእርስዋ ጋር ሴሰኑ የምድርም ነጋዴዎች ከቅምጥልነትዋ ኃይል የተነሳ ባለጠጋዎች ሆኑ ብሎ ጮኸ፡፡” (ራዕይ 18፣ 2-3)

Page 4: St John the Devine Cathedral _Amharic

4

ቀራጩ አልተሳሳተም በኒውዮርክ ከተማና መፅሃፉ በሚላት ታላቂቱ ባቢሎን መካከል ብዙ መመሳሰል አለ፡፡

1. የምድርን ነገስታት የምትገዛቸው ብዙ ውሃዎች፣ ህዝቦች፣ ሃገሮችና ቋንቋዎች ላይ የተቀመጠችው ወርቃማ ዋንጫ የያዘችው “ታላቂቱ ጋለሞታ”፡፡ የነፃነቷን ሃውልት ይመስላል፡፡

Page 5: St John the Devine Cathedral _Amharic

5

2. “ነጋዴዎች ከቅምጥልነትዋ ኃይል የተነሳ ባለጠጋዎች” የሆኑባት፣ “የመርከባቸውንም ጭነት ከእንግዲህ ወዲህ የሚገዛ የለምና የምድር ነጋዴዎች ያለቅሱላታል…” የኒው ዮርክ የድርሻ ገበያ፡፡

እስከ ዛሬ ድረስ ከመቶ ሰባ በላይ የዓለም ካፒታል በኒው ዮርክ ድርሻ ገበያ ነው የሚዘዋወረው፡፡ ለዚህም ነው ህንፃው በአምዱ ላይ የተቀረፀው፡፡ ይህ የራእዩ አንዱ ገፅታ ነው በመፅሐፍ ቅዱስም በተደጋጋሚ ይህን ይላል፡-

“እነዚህን የነገዱ በእርስዋም ባለ ጠጋዎች የሆኑት እያለቀሱና እያዘኑ፡- በቀጭን ተልባ እግርና በቀይ ሐምራዊም ልብስ ለተጎናፀፈች በወርቅና በከበረ ድንጋይም በዕንቁም ለተሸለመች ለታላቂቱ ከተማ ወዮላት፣ ወዮላት ይህን የሚያህል ባለጠግነት በአንድ ሰዓት ጠፍቶአልና እያሉ ሥቃይዋን ከመፍራት የተነሳ በሩቁ ይቆማሉ፡፡” (ራዕይ 18፣ 15-17) “…፤ ነጋዴዎችሽ የምድር መኳንንት ነበሩና፣ በአስማትሽም አህዛብ ሁሉ ስተዋልና፡፡” (ራዕይ 18፣ 23)

የኒው ዮርክ ከተማ ዋና ገፅታ የሆነው የቅዱስ ዮሐንስ ካቴድራል የከተማዋ መውደምን በሚገርም ዝርዝር ያሳያል፡፡ ያልተለመደ ነው፡፡ የአረመኔያዊ ሃውልቶች

በካቴድራሉ ዙርያ ከክርስትና ጋር የማይገናኙ ቅድመ ክርስትና እምነቶች የተገኙ የሚመስሉ ሃውልቶች ይገኛሉ፡፡ ከጎን የሚታየው ሃውልት በመልካምና ክፉ መሃከል ያለውን ትግል የሚያሳይ ሲሆን በአረመኔ እምነቶች የሚገኙ ቅርፆችን ይዟል፡- የፀሃይ አምልኮ፣ የአፈ-ታሪካዊ እንስሳት፣ የፀሃይና ጨረቃ ጥንዳዊነት..፡፡ ይህ “የሰላም ፏፏቴ” የተሰኘው ሃውልት ከእውናዊው ዓለም ውጪ የሆኑ አገላለፆችን ይጠቀማል፡፡ ፈገግታ ከምታሳይ ፀሃይ ብዙ አይነት እንስሳት ይወጣሉ፡፡ ይህ የፀሃይ አምልኮን ያመላክታል (ፀሃይ ሂወት ሰጪ ነች ከሚለው እይታ፡፡) ሃውልቱ ወደ ምስራቅ ገፁ ያደረገ ነው፡፡ ይህ ጥንታዊ የአረመኔዎች ልማድ ነው፡፡ የሆነ

የተጠላለፈ የሰው ዘረ መል (ዲ.ኤን.ኤ.) የሚመስል ቅርፅም አለ፡፡ (ይህ በካቴድራሉ መግቢያም የሚገኝ ነው፡፡)

Page 6: St John the Devine Cathedral _Amharic

6

አስቀያሚ የሰውነት ቅርፅ ያለው ቀንዳም ፍጥረት ተጋድሞ ይታያል፡፡

እንግዳ በአላት የመናፍስቱ ሰልፍ

በየአመቱ የሃሎዊን በአላቸው ግዜ በቅዱስ ዮሐንስ ካቴድራል “ታላቁ የመናፍስት ሰልፍ” የተሰኘ እንግዳ በአል ይከበራል፡፡ ይህ በአል በካቴድራሉ ውስጥ ሰዎች እንደ አጋንንት፣ ሙት መናፍስት፣ ጭራቆችና ሌሎች አስቀያሚ ነገሮች ጭምብል ለብሰው የአስፈሪ ኦርጋን (ፒያኖ) ሙዚቃ እየጠደመጠ ተሰልፈው የሚያልፉበት በአል ነው፡፡ ይህ የባእድ አምልኮ ተከታዮች በራቸውን ዘግተው ከሚያካሂዱት አምልኮ ጋር የሚመሳሰል ነው፡፡ ይህ የክርስትና እምነት ቦታ ነው ከሚባል ጋር የማይሄድ ከነዚህ አጋንንትን ለመምሰል ከሚደረጉ ጭምብሎች በተጨማሪም በቀጥታ ክርስትና ላይ ለማላገጥ የሚደረጉ ጭምብሎችም ይታያሉ፡፡ ለምሳሌ ከላይ ያለው ምን ይመስላል? ሌሎች ስእሎችን ከስር ይመልከቱ፡፡

Page 7: St John the Devine Cathedral _Amharic

7

ከላይ በግራ፡ የሃይማኖታቸው ቄስ አለባበስ ከነመስቀሉ ያደረገ አውሬ የሚመስል፡፡

ከጎን፡ ከስሩ በሰልፍ ሲያልፉ መስበኪያው ላይ የጳጳስ ልብስ አድርጎ የቆመ፡፡

በሴጣን አምልኮ በአላት ግዜ የሚደረገው ስነ ስርአት በክርስትና እምነት ስነ ስርአቶች ላይ ማሾፍና መገዳደር ነው፡፡ እዚህ የሚታየውም እንዲሁ ሲደረግ ነው፡፡ ሰልፍ የአረመኔዎች (ፓጋን) ልማዶች ናቸው ለምሳሌ ከጎን እንደሚታየው በጀርመን የሚደረግ የፓጋን ሰልፍ ግዜ ተመሳሳይ ትእይንቶች ነበሩ፡፡ እንሰሳትን መባረክ ሌላው አስገራሚው ትእይንት በየአመቱ በመስከረም የሚያደርጉት የእንስሳት መባረክ በአል ነው፡፡ በካቴድራሉ ውስጥና ውጪ የእንሰሳት መአት ይሰብባሉ፡፡ ከመቼ ጀምሮ ነው እንስሳት ማምለክ የጀመሩት፡፡ ይህ በካቴድራሉ ውስጥ ከሚደረጉት የፓጋን በአሎች አንደኛው ነው፡፡ ስነስርአቱን የሚያካሂዱት የለበሱትን ልብ ስንል (ነጭ ቀሚስ) ከፓጋን በአል አከባባር አለባበስጋ የሚመሳሰል ሁኖ እናገኘዋለን፡፡

Page 8: St John the Devine Cathedral _Amharic

8

ነጭ ሽርጦቹን በፓጋን አምልኮ ላይም ማየት ይቻላል ከስር ከሚታዩት ጋር ማነፃፀር ይቻላል፡፡

በተጨማሪም ቪድዮዎችን ብንመከት የማያጠራጥር መመሳሰሎችን እናገኛለን፡፡ ብስክሌቶችም ቡራኬ አላቸው ከስር ይታያል፡፡ ስለዚህ ማውራት አያስፈልግም

ምስሉን ይመልከቱ፡፡ ስነምህዳሩ እምነታችን ነው እያሉ ይሆናል፡፡ የፓዉል የዊንተር ሶሊስታይስ በአል የዊንተር ሶሊስታይስ ቀን ማለት በፈረንጆቹ ታህሳስ/ዲሴምበር 22 ቀን ፀሃይ በደቡባዊ ንፍቀ ክበብ ጫፍ የምትደርስበት እለት ሲሆን ከፀሃይ አምልኳቸው ጋር የተያያዘ ነው፡፡

Page 9: St John the Devine Cathedral _Amharic

9

ከጎን የሚታየው ስእል የአዲስ ዘመን እምነት ተከታዩ ዝነኛው የሙዚቃ አቀናባሪው የፓጋን እምነት አከባበር ዋናው የሆነውን የዊንተር ሲሊስታይስ ካቴድራሉ ውስጥ ሲያካሂድ የሚያሳይ ነው፡፡

የመረዳት ቤት አምልኮ (Temple of Understanding) ይህ ካቴድራል በተጨማሪም የመረዳት ቤት አምልኮ የተሰኘ ተቋም ዋና መቀመጫ ነው፡፡ ይህ ተቋም ሰዎችን ከቀደመችው እምነት በማስወጣት የተለያዩ ሃይማኖቶች ቅልቅል የሆነ በአዲስ ዘመን እንቅስቃሴ ፍልስፍና፣ አዲስ ፓጋንነትና የተለያዩ ሃይማኖቶች ልማዶችን በመቀላቀል የሚመራ መንፈሳዊነትን ማስፋፋት አላማው ያደረገ ተቋም ነው፡፡ ይህን ተቋም እንዲመሰረት ጁልየት ሆሊስተርን የረዱ “ወዳጆች” ስም የሚገርም ነው፡- ጆን ዲ. ሮክፌለር 2ኛ፣ 14ኛው ዳላይ ላማ፣ ፖፕ ጆን 23ኛ፣ ኤሊኖር ሮዘቬልት፣የተመድ ነበር-ዋና ፀሃፊ ዩ ታንት፣ ኢንተርናሽናል ፕላንድ ፓረንትሁድ እና የአይሁድ ስነመለኮታዊ ሴሚናሪ ናቸው፡፡ ጂን ሁስቶን የአዲስ ዘመን እንቅስቃሴ ቁንጮ ሰውና የዚህ ተቋም ደጋፊ “የትሮይ ፈረስ” በሚለው መፅሃፏ እንደሚከተለው ትላለች፡- “[የተቋሙ] ዓላማ ሁሉም ሃይማኖቶች፣ እምነቶችና በአላት ተቀባይነት ማግኘትን በማቀላጠፍ አንድ የአለም ሃይማኖትን ማፋጠን ነው፡፡ የመረዳት ቤተአምልኮ የተመስጦ ክፍሉ “የአብርሆት አዳራሽ” (“Hall of Illumination”) ሊባል ተብሎ ነበር፣ በዚህ ክፍልም አብርሆቱ ያላቸው (ኢሉሚናቲ) የጥበብ ሊቃውንት፣ የመረዳት ቤተ አምልኮ መሪዎቻችን ህዝቡን በአዲስ ሰዋዊ አምልኮ ያሰለጥናሉ…” ተቋሙ ሙሉ የተባበሩት መንግስታት ድጋፍ አለው፣ በተ.መ.ድ. መንፈሳዊ ክፍልም ቁልፍ ሚና ይጫወታል፡፡ የመረዳት ቤተ አምልኮ ዳይሬክተሮች ወይም አማካሪዎች የሚባሉ አስራሁለት ግለሰቦችም በተ.መ.ድ. የግሎባል ፎረም ካውንስል አባሎች ይደረጋሉ፡፡ እኚህ ፎረሞች በምድር አምልኮ ላይ የተመሰረተውን አዲስ-አረመኔያዊ እምነት በግልፅ የሚያራምዱ ተናጋሪዎችን ተቀብሎ በተደጋጋሚ አስተናግዷል፡፡ ከነዚህ አንዱ ጄምስ ላቭሎክ “ጋያ” (ማለትም መሬትን እንደ አምላክ መጥሪያ ጥንታዊ ስሟ) የሂወት ሰጪና እራሷን የመፈወስ ሃይል ያላት ናት ሲል ተናግሮ ነበር፡፡ ሰዎችንም ሲገልፅ ለጋያ እራሷን ለመፈወስ እጅግ አስቸጋሪ እንደሆኑ

Page 10: St John the Devine Cathedral _Amharic

10

ካንሰር አድርጎ ነበር፡፡ በሌላ አገላለፅ ሰዎች ጋያ ላይ ጥገኛ የሆኑ ተዋህስያን አድርጎ ቆጥሯቸዋል፡፡ (ጄምስ ላቭሎክ ግማሽ እውነት እየተናገሩ ከሚያስቱ ሳይንቲስቶች ዝነኛው ነው፡፡) አልጎር በካቴድራሉ ብዙ ግዜ በእንግድነት ተገኝቷል፡፡ እዚህም ያለህፍረት “እግዚአብሔር ከምድር የተነጣጠለ አይደለም፡፡” “God is not separate from the Earth.” ብሏል፡፡ በክርስትና፣ ይሁዴ እና እስልምና ፈጣሪ ከምድር የተሳሰረ አይደለም (በመንግስተ ሰማያት እንጂ፡፡) አልጎር የአሜሪካ ነበር ም/ፕሬዚደንት ነው፡፡ እያለ ያለው እግዚአብሔር = ምድር = ምድር እግዚአብሔር ነው ነው፡፡ የአረመኔ ቡድኖች ጎርን በጣም ይወዱታል፡፡ በ1996 የክሊንተን/ጎር ምርጫ ስኬት ዋዜማ የሚከተለውን እንኳን ደስ ያለህ መግለጫ ፅፈውለት ነበር፡

“እኛ አዲስ-አረመኔዎች (ኒዮ-ፓጋን) ነን፣ ማለትም ከጥንታዊ የተፈጥሯዊ ሃይማኖቶች እየመረጥን ዳግም በመገንባትና ከሌሎች ስልጣኔዎች ሚስጥራዊና መንፈሳዊ ትውፊቶች ጋር በማዋሃድ ማለት ነው - እና የኛም እምነቶችና እሴቶች የኔ ብለህ ከምትገልፃቸው የሚለዩ አይደሉም፡፡ Earth in Balance የሚለው መፅሃፍህ በክብር ለያዝናቸው ነገሮች ሁላ መግለጫ (ማኒፌስቶ) ተደርጎ ነው የሚወሰደው፡፡… አንተን የሚደግፉና ድምጻቸውን የሚሰጡህና ምድርን ለማዳን እና ታላቁን ቤተሰብ ዳግም ለማዋሃድ ያሉህን ፖሊሲዎች ለመደገፍ ካንተጋ የሚሰለፉ እስከ ግማሽ ሚሊዮን ፓጋኖች እንዳሉ እወቀው፡፡”

ሌላ የመረዳት ቤተ አምልኮ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባል ቶማስ ቤሪ ነው፡፡ እሱ እንደሚያምነው ከሆነ አሁን አለም በሃማኖት ስር የመሰባሰብ የእምነት ዘመን አብቅቶለት ለአዲስ እምነት መሬትን እንደ ሂወት ያለው አካል እና ሰዎች ደሞ ህሊናዋ እንደሆኑ የሚቀበል እምነት የሚሰርፅበት ግዜው እንደደረሰ ያምናል፡፡ (ይህም ሰው ከዝነኛ ቅጥረኛ አሳሳቾች አንዱ ነው፡፡) ይህ ሁሉ ምን ማለት ነው? ከፊት ገፆች የጆርጅያ መሪ ድንጋዮች የሚለውን ካነበባችሁት በዓለም ላይ አዲስ መንፈሳዊነት ማምጣት የሚሹ ሃይሎች እንዳሉ ተረድታቹሃ፡፡ ይህን አዲስ እምነታቸውን ሰው እንዲወደው ለማድረግ ቁልፍ ቃላቶችን ይጠቀማሉ፡ “ሰላም”፣ “ከተፈጥሮ ጋር ሚዛን መጠበቅ”፣ “ወሰን ከሌለው ጋር መጣጣም”፡፡ እንዴት እንድ ሰው ሰላምን መቃወም ይችላል? አይችልም፡፡ እኚህ ቃላቶች ግን የሚመጡበትን መንገድ አይገልፁም፡ “ሰላም” የሚመጣው አንድ የዓለም መንግስት ሲኖር ነው፡፡ “ከተፈጥሮ ጋር ሚዛን” የሚጠበቀው የዓለም ህዝብ ቁጥር እጅጉኑ ሲቀንስ ነው፡፡ “ወሰን ከሌለው ጋር መጣጣም” የሚገኘው ዓለም ያሏትን ሃይማኖቶች እርግፍ አርጋ ትታ አዲሱ-አረመኔያዊ ሰዋዊ እምነትን ስትቀበል ነው ብለው እንደሚያምኑ ወዲያው አይገልፁም፡፡ ይህንንም እዚሁ እየሰሩበት ይገኛሉ፡፡ በተለያዩ ፎረሞችና የተመድ ጉባኤዎች የመረዳት ቤተ አምልኮ የተለያዩ እምነቶች መሪዎችን በማሰባሰብ ሁለገብ የሆነ መልእክት እንዲያስተላልፉ ይጋብዛቸዋል፡፡ መልእክቱ በኋላ ላይ ለብዙሃኑ በየአምልኮ ቦታቸው ይደርሳቸዋል፡፡ በዝግታና ያልተቋረጠ ጉዞ ሁሉም እምነቶች ወደ አንድ አይነት እሴቶች እየተራመዱ ይገኛሉ፣ በስተመጨረሻም በአንድ ሰዋዊ ሃይማኖትነት ይዋሃዳሉ፡፡

Page 11: St John the Devine Cathedral _Amharic

11

የዚህ ዋናው ምሳሌ በካቴድራሉ ውስጥ ከመስራቾቹ አንዷ በሆነችው ማደላይን ለኢግል የሚሰጡት ትምህርቶች ናቸው፡፡ ትምህርቶቿ ሻማኒዝም (ከመናፍስት አለም ጋር እንገናኛለን የሚል እንሰሳዊ የመተተኞች እምነት)፣ ሳይሞቱ ነፍስን ከአካል የማውጣት ጥበብ፣ ወደ ከዋክብት መሄድ፣ በታሮት ካርድ መጠንቆል፣ የምድር አምልኮ፣ የሳይኪክ ስራዎች፣ ዮጋ፣ ታንትሪክ ቶጋ (የጥቁር አስማት ወሲባዊ ገፅታው)፣ ኮኮብ ቆጠራ ናቸው፡፡ እኚህ ድርጊቶች በክርስትና እምነት የተወገዙ ናቸው፣ በካቴድራሉ ውስጥ ግን ይሰበካሉ፡፡

ከጎን፡ የተለያዩ እምነት መሪዎች ስብሰባ በመረዳት ቤተ አምልኮ፡፡ በዓለም ዙርያ መቀበል ያለበት እሴት ስነ-ምህዳራዊነት ነው፡፡ ስለ ተፈጥሮ መራቆትና መጥፋት የፍራቻ ስሜት በመፍጠር ተቀባይነት የማይኖራቸው ህጎችን ማስፀደቅ ይችላሉ፡፡ በዚሁም ብዙሃኑን ከእምነታቸው ወደ ምድር አምልኮ ማዞር

ይችላሉ፡፡ እኚህ የአዲስ ዘመን መንፈሳዊነት እምነት ተከታዮች ለዚህ ሁነኛ መሳርያ ይሆኗቸዋል፡፡ ተፈጥሮ ሃይማኖት ሲሆን ሰውን እንደ ጥገኛ ህዋስያን መቁጠር ይጀመራል፣ ይህም የብዙሃኑን ቁጥር ለመቀነስ ማስተባበያ ይሆናል፡፡ መደምደምያ ከዚህ የምንገነዘበው አንድ ነገር ቢኖር ካቴድራሉ ክርስትያናዊ አይደለም፡፡ እንዲያውም ህንፃው ሃማኖትን ለማጥፋት እየሰሩ ያሉ ሰዋች መቀመጫም ነው፡፡ መጀመርያ ላይ እንዳልነው እራስህን ማሳሳት አንድ ነገር ነው ሌሎች ሰዎችን ግን ያልሆንከውን መስለህ ወደ ስህተት መምራት እጅግ ሲበዛ ሴጣናዊ ነው፡፡ ሴጣን በማሳሳት ጥበቡ ይታወቃል፡፡ ወደ ካቴድራሉ የሚሄዱ ሰዎች ባልጠበቁት መንገድ እየተታለሉ ነው፡፡ የዓለም ሃይማኖቶች ለሰላም እናስተባብር በሚል ስም አማኞችና የሃይማኖት መሪዎቻቸው እየተታለሉ ናቸው፡፡ ጳውሎስም የቆረንቶስ ሰዎችን እንዲህ ሲል አስጠንቅቋቸዋል፡-

“እንደ እነዚህ ያሉ ሰዎች የክርስቶስን ሐዋርያት እንዲመስሉ ራሳቸውን እየለወጡ፣ ውሸተኞች ሐዋርትና ተንኮለኞች ሠራተኞች ናቸውና፡፡ ይህም ድንቅ አይደለም ሰይጣን ራሱ የብርሃንን መልአክ እንዲመስል ራሱን ይለውጣልና፡፡ እንግዲህ አገልጋዮቹ ደግሞ የጽድቅን አገልጋዮች እንዲመስሉ ራሳቸውን ቢለውጡ ታላቅ ነገር አይደለም፤ ፍጻሜአቸውም እንደ ሥራቸው ይሆናል፡፡” (2ኛ ወደ ቆረንቶስ 11፣ 13-15)