በመጋቢ ሊዮን ኢማኒኤል - free · pdf fileምልጃ 2016 3 መግቢያ...

61
ምልጃ 2016 0 www.tlcfan.org በመጋቢ ሊዮን ኢማኒኤል

Upload: vonguyet

Post on 15-Feb-2018

533 views

Category:

Documents


58 download

TRANSCRIPT

ምልጃ 2016

0 www.tlcfan.org

በመጋቢ ሊዮን ኢማኒኤል

ምልጃ 2016

1 www.tlcfan.org

ምልጃ የመጀመሪያ እትም

Copyright ©2016 የሁለተኛ እትም REVISED 2016

መብቱ የተጠበቀ ነው፦

All rights Reserved to: Bible Teacher Pastor Leon Emmanuel

FOUNDER OF

THE LION S CALL FOR ALL NATION INTERNATIONAL MINISTRY

Permission is granted to copy and quote freely

from this publication for non-commercial purposes.

ምልጃ 2016

2 www.tlcfan.org

ማውጫ

ርዕስ ገጽ

1. መግቢያ .............................................................................................. 3

2. የምልጃ ጸሎት ................................................................................... 5

3. ሦስቱ የምልጃ ደረጃዎች ...................................................................... 6

4. መመሳሰል ........................................................................................... 7

5. የነብዮ ሕዝቅኤል የምልጃ ሕይወት ....................................................... 8

6. የነብዮ ሆሴዕ የምልጃ ሕይወት ............................................................ 11

7. የነብዮ ኢሳያስ የምልጃ ሕይወት ......................................................... 14

8. ነብዮ አብርሃምና ይሳቅ ....................................................................... 17

9. በደልን መሸከም ................................................................................. 21

10. የሌላውን ሸክም የመሸከም ሕይወት .................................................. 26

11. ትንሳኤ ............................................................................................ 56

Copyright © 2016

All rights Reserved to Leon

ምልጃ 2016

3 www.tlcfan.org

መግቢያ

ምልጃ ታላቅ የአንድ አማኝ የክህነቱ አገልግሎት አየሚፈጸምበት አገልግሎት

ነው። ሁሉ ለመጸለይ ተጠርተዋል ነገርግ ሁሉ የሚማልዱ ወይም የምልጃ ሕይወት ውስጥ

የገቡ አይደሉም። የናዝሬቱ ኢየሱስ ለዚህ እውነተኛው ምሳሊያችን ነው። ምልጃ ከመጸለይ

ያለፈ ነው። ምልጃ የአንድ ሰው ሽክምና ሃጢያት ተሸክሞ በእግዚአብሔር በሃጢያተኛው

መከከል መቆም ነው።

ከአባቶቻችን መካከል ለሕባቸው ለቤተሰቦቻቸው የማለዱ ሰዎች ነበሩ። ዳንኤል

በዋንኛነት ተጠቃሽ ነው። ዛሬም ይህ መንፈሳዊ እውነት ካልገባን ለመማለድ የተጠራንም

ብንሆን ትክክለኛ ምልጃን ወደ እግዚአብሔር ማስገባት ያስቸግረናል። በነብዮ ኢሳያስ

እደተነገረው ትንቢት እኔ በዛን ሰዓት ደንቆሮና እውር ነበርኩ እንዳለ ማለት ነው። ኢሳ.29፥

10

“10. እግዚአብሔር የእንቅልፍ መንፈስ አፍስሶባችኋል ዓይኖቻችሁን ነቢያትንም

ጨፍኖባችኋል ራሶቻችሁን ባለ ራእዮችን ሸፍኖባችኋል፣”

He has shut your eyes, the prophets; and

ነገር ግን እግዚአብሔር ዕውሮችንና ደንቆሮችን በማያውቋት መንገድ

እመራቸዋለሁ ጨለማውንም ብርሃን አደርጋለሁ ያለው የእግዚአብሔር ቃል ልንስብና

ራሳችንን እውነቱን ለማወቅ ልናተጋ ይገባል። ይህንንም ማመን እግዚአብሔር አዲስ

ልምድን እንዲያለማምደን በር ይሀፍታል። ኢሳ.42፥16

“16. ዕውሮችንም በማያውቋት መንገድ አመጣቸዋለሁ፥ በማያውቋትም ጎዳና

እመራቸዋለሁ፤ በፊታቸውም ጨለማውን ብርሃን አደርጋለሁ፥ ጠማማውንም አቀናለሁ።

ይህን አደርግላቸዋለሁ፥ አልተዋቸውምም። 17፤ በተቀረጹትም ምስሎች የሚታመኑ፥

ቀልጠው የተሠሩትንም ምስሎች። አምላኮቻችን ናችሁ የሚሉ ወደ ኋላቸው ይመለሳሉ

ፈጽመውም ያፍራሉ። 18፤ እናንተ ደንቆሮች፥ ስሙ፤ እናንተም ዕውሮች፥ ታዩ ዘንድ

ተመልከቱ። 19፤ ከባሪያዬ በቀር ዕውር ማን ነው? እንደምልከው መልእክተኛዬስ በቀር

ደንቆሮ የሆነ ማን ነው? እንደ ፍጹሙ ወይስ እንደ እግዚአብሔር

ባሪያ ዕውር የሆነ ማን ነው?”

ምልጃ 2016

4 www.tlcfan.org

በዚህ መጽሐፍ ከመንፈሳዊ አባቶቼ የተማርኩትን የምልጃ መርሆች

እንመለከታለን። የምንማልድና የምልጃ ሕይወት ውስጥ ያለን ወደ በለጠ የምልጃ ሕይወት

እንደምንገባና የምልጃን ሚስጥር እንደረዳ አምናለሁ።

የምልጃ ሰው ብዙ መከራ የበዛበት ሰው ነው። ይህ ሚስጥሩ ምን እንደሆነም

በዚህ መጽሐፍ ውስጥ እንመለከታለን። ስንማልድ ምንም እንኳን በሕይወታችን የሚሆነው

ነገር የማናውቀውና ግራ የሚያጋባ ቢሆን እንኳን እግዚአብሔር መጠየቅና ልስን ከእርሱ

ብቻ መጠበቅ የአንድ በሳል የሚማልድ ሰው ሕይወት መልክ ነው። እግዚአብሔር ለሁሉ

መልስ አለው።

በእይወቴ ምልጃን የተለማመድኩት ምልጃ መሆኑን አውቄ አይደለም። በጸሎት

ትጋት ውስጥ እውቀቱ ሳይኖረኝ ወደ ምልጃ ሕይወት ውስጥ በፍቃዱ አስገብቶኝ ነበር።

የእግዚአብሔር ቃልን እውቀ ሳውቅ ደግሞ ጥንቃቄን የምልጃ ጸሎት መርሆችን ተማርኩ።

ለጸሎትም ሆነ ለምልጃ ጸሎት ለእግዚአብሔር ግን ሁል ጊዜ የምንገኝ ጊዜ የሰጠን ልንሆን

ይገባናል። ዳንኤል በቀን ሶስት ጊዜ መስኮቱን ወደ ኢየሩሳሌም በመክፈት ወደ

እግዚአብሔር ይጸልይና ለእስራኤል ይማልድ ነበር። ይህ ትጋትና ለእግዚአብሔር ራስን

ማስገኘት የምልጃ ሕይወት መጀመሪያ መሆኑን መሰረት ጥሎልን አልፏል። ስለ ምልጃ

አንብበን ስልጨርስ ትልቅ የምልጃ ሰዎች እንደምንሆንና በምልጃ ውስጥ በመረዳት

የምናልፍበትን መንገድ መመልከት እንደሚሆንልን አምናለሁ።

ምልጃ 2016

5 www.tlcfan.org

የምልጃ ጸሎት

ምልጃ ምን ማለት ነው? ምልጃ የሚለው ቃል ከላቲን ቃል የመጣ ሲሆን

በሁለት መካከል ጣልቃ በመግባት መቆም ማለት ነው። ምልጃ ከማንኛውም አይነት

ጸሎቶች የተነየ ጸሎት ነው። ይህም ምልጃ የክህነትን ቢሮ የሚጠይቅ ሰለ ሆነ ነው። ስለዚህ

የማያምኑ ሰዎች መማለድ አይችሉም ማለት ነው።

ሁሉ አማኝ ደግሞ በአዲስ ኪዳን ከጌታ ከመወለዱ የተነሳ ካህን ሰለ ሆነ

የምልጃን ሕይወት መለማመድ ሁሉ አማኝ ይችላል ማለት ነው። ከልምዴ ደግሞ እንደ

ተረዳሁት በምልጃ ወቅት አንድ ሰው ሰለ ሚፈጽመው ነገር የግድ ማወቅ እንደ ሌለበት

ተረድቻለሁ። ብዙ ሰዎች በጸሎት ሕይወት እየተጉ ምንም ሳያውቁ ባላወቁት ነገርና ችግር

ውስጥ ራሳቸውን ያገኛሉ። ይህ ሲሆን ሳያውቁት በምልጃ ሕይወት መንገድ ላይ እንዳሉ

እንዲረዱና እንዲያስተውሉ እወዳለሁ። ይህ መጽሐፍ የሚማልድ ሰው ማንና ምን አይነት

ሰው እንደ ሆነ እንድንረዳም ያደርገናል።

ልክ መጽሐፍ ቅዱስ አንድ እስራኤላዊ ካህን በሙላት አገልግሎቱን

ለመጀመር እስከ 30 ዓመቱ ድረስ እንደ ሚሰለጥን ሁሉ ለሚማልድ ሰውም እንዲሁ የሁል

ጊዜ ስልጣኝ ነው። ይህን ስንል ስጋዊ እድሜን ማለታችን ሳይሆን የስልጠናን ጊዜ የብስለት

ጊዜ ማለታችን ነው። 30 ዓመት በእስራኤል ሕብረተሰብ የብስለት “maturity” እድሜ ነው።

ካህን ወደ እዚህ አይነቱ ብሰለት ላይ ካልመጣ እንደ ካህን በመቅደስ በምልጃ ወይም በሰውና

በእግዚአብሔር መካከል ቆሞ አያገለግልም።

ማንኛውም አማኝ የክህነት ስልጣኑን በሙላት መጠቀምና በሥራ ላይ ማዋል

እስኪ ጀምር ድረስ በመንፈሳዊ ነገር ማደግ የግድ ያፈልገዋል። ይህም ክህነቱን በምልጃ

ላይ ሲያውል ውጤታማ የሆነ አገልግሎትን በመቅደሱ ለመፈጸም ያስችለዋልና ነው።

የአሮን ልጆች አገልግሎታቸውን በ20 ዓመታቸው ይጀምሩ ነበር። ይህም

በሙሉ ክህነት በ30 ዓመታቸው እስከ ሚቀቡና አገልግሎቱን እስከሚረከቡ ድረስ ለ10

ዓመታት ያህል ከቀደሙት ካህናት ስር በመሆን ሥልጠናን ይወስዱና ከእነርሱ በታች

በመገዛት እንዲማሩ ይደረጋል። በአንዳድ የመቅደሱ ክፍሎች በተለያዮ ሥፍራዎች ላይ

ሌሎችን ካህናት በማገዝ እያገለገሉ ለ10ዓመት ይሰለጥናሉ። በ30ኛው አመታቸው

በእግዚአብሔር ፊት ካህን ሆነው ይቀባሉ ደግሞም አገልግሎታቸውንም ይረከባሉ።

ምልጃ 2016

6 www.tlcfan.org

ሦስቱ የምልጃ ደረጃዎች

ሶስት የተለያዮ የምልጃ ደረጃዎችን በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እናገኛን።

ከእነርሱም ሁለተኛው ደግሞ የራሱ የሆነ ስድስት ደረጃዎችን ያካትታል። እነርሱም፦

1. መመሳሰል

2. የሌሎችን ሃጢያት መሸከም፦ (ስድስት ደረጃዎችን ያካትታል)

1) ሥም አልባነት

2) መታዘዝ

3) ክስን መሸከም

4) የፍርድን መጠን ማስተካከል

5) እምነት ነገር ግን ትንሽ መረዳት

6) ሞት

3. ትንሣኤና መከር

የእግዚአብሔር መንፈስ እንደ ረዳንኝ መጠን እነዚህን ሃሳቦች በሚቀጥሉት

የጥናት ምዕራፎች ውስጥ በዝርዝር እንመለከታቸዋለን፡ ይህም የምልጃ ደረጃ ማወቅ ለአንድ

ማላጅ አማኝ ወሳኝ ነው ብዮ አምናለሁ። እያወቅን የምናደርገው ነገር ሁል ጊዜ እርካታ

አለው። ስለዚህ በምልጃ ትምህርታችን ውስጥ ያለውን ሃላፊነትና ክብር መመልከት

እንደሚሆንልን አምናለሁ።

ምልጃ 2016

7 www.tlcfan.org

መመሳሰል

“በነገር ሁሉ ወንድሞቹን ሊመስል ተገባው።”

ዕብ.2፥17 ኢየሱስ ሊቀ ካህናችን እንደ መሆኑ መጠን ለእኛ ቀዳሚና ዋነኛ የምልጃና

የክህነት ሕይወት ምሳሌያችን ነው። ዕብ.7፥25 ለእኛ ማላጅ ለመሆን በነገር ሁሉ እኛን

ሊመስል እኛ እንደ ተፈተን በሁሉ ነገር ሊፈተን ተገባው። ዕብ.2፥14-17 ላይ እንዲህ

ይላል።

“14-15 እንግዲህ ልጆቹ በሥጋና በደም ስለሚካፈሉ፥ እርሱ ደግሞ በሞት ላይ ሥልጣን

ያለውን በሞት እንዲሽር፥ ይኸውም ዲያብሎስ ነው፥ በሕይወታቸውም ሁሉ ስለ ሞት

ፍርሃት በባርነት ይታሰሩ የነበሩትን ሁሉ ነጻ እንዲያወጣ፥ በሥጋና በደም እንዲሁ ተካፈለ።

16 የአብርሃምን ዘር ይዞአል እንጂ የያዘው የመላእክትን አይደለም። 17 ስለዚህ የሕዝብን

ኃጢአት ለማስተስረይ፥ ለእግዚአብሔር በሆነው ነገር ሁሉ የሚምርና የታመነ ሊቀ ካህናት

እንዲሆን፥ በነገር ሁሉ ወንድሞቹን ሊመስል ተገባው። 18 እርሱ ራሱ ተፈትኖ መከራን ስለ

ተቀበለ የሚፈተኑትን ሊረዳቸው ይችላልና።”

“24 እርሱ ግን ለዘላለም የሚኖር ስለሆነ የማይለወጥ ክህነት አለው፤ 25 ስለ እነርሱም

ሊያማልድ ዘወትር በሕይወት ይኖራልና ስለዚህ ደግሞ በእርሱ ወደ እግዚአብሔር

የሚመጡትን ፈጽሞ ሊያድናቸው ይችላል።”

ኢየሱስ ከእኛ ጋር በነገር ሁሉ ሊመሳሰለን ተገባው ይህም ብቁ የሆነ ማላጅ

እንዲ ሆን ነው። ይህ መርህ ግን በኢየሱስ ብቻ ላይ ያቆመ አይደለም። እኛም በዚህ ዘመን

ከሌሎች ጋር እራሳችን በማመሳሰል “identified” በማድረግ ብቁ ማላጆች እንድንሆን

የሚያበቃን መለኮታዊ መርህ ነው።

በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ ሌላ ለእኛ ምሳሌ እንዲሆኑ የተቀመጡ ቃሎች

እናገኛለን። በእነዚህም ጥቅሶች ላይ የተለያዮ በተለያዮ ዘመን የነበሩ ቅዱሳን ራሳቸውን

ከሌላው ሰው ጋር ወይም ከሕዝቡ ጋር በማመሳሰል ሲማልዱ እንመለከታቸዋለን። ይህ

ደግሞ በዘመናቸው ውጤታማ የሆኑ ማላጂዎች አድርጓቸው እንዳለፈ እንመለከታለን።

እነዚህ ቅዱሳኖች ከሰዎች ችግርና ሁኔታ ጋር ራሳቸው በማመሳሰላቸው ለትውልዱ ተጠቃሽ

የሚታወቁና በዘመናቸው ታላቅ ማላጂዎች ሆነው እንዲያልፉ አድርጓቸዋል።

ምልጃ 2016

8 www.tlcfan.org

የነብዮ ሕዝቅኤል የምልጃ ሕይወት

ሕዝቅኤል መጽሐፍ ምዕራፍ አራትን ብንመለከት ነብዮ ስለ እስራኤል በሃጢያት

እስራት ሥር መውደቅ ሲማልድ እናገኘዋለን። ነብዮ ራሱን ከሕዝበ እስራኤል ጋር አንድ

አድርጎ ማመሳሰሉን በሁለት መልኩ እንመለከታለን።

በመጀመሪያ ከሰው በሚወጣ ፋንድያ ላይ የገብስ እንጎቻውን መጋገሩና

መብላቱ ነው። ሕዝ.4፥12 ይህም ነብዮ ራሱን ከሕዝቡና የሰው ወግና በዓል ካበሏቸው

ካህናቶች ጋር አንድ ይሆን ወይም ይመሳሰል ዘንድ ነው። ይህም ካህናቶቹ ሕዝቡን

ያበሏቸው ቃል ከእግዚአብሔር ሳይሆን ከሰው የወጣ የማይጠቅም እንደ ፋንድያ ነበር።

“12.እንደ ገብስ እንጐቻም አድርገህ ትበላዋለህ፥ ከሰውም በሚወጣ

ፋንድያ በፊታቸው ትጋግረዋለሁ። 13. እግዚአብሔርም። እንዲሁ

የእስራኤል ልጆች እነርሱን በምበትንባቸው በአሕዛብ መካከል

ርኩስ እንጀራቸውን ይበላሉ አለ።”

የዕብራይስጡ ቃል ፋንድያን “gelel” “ጌል” ኳስ ማለት ነው። ይህም ከፍየል

የሚወጣን ፋንድያን (በጠጥን) ያመለክታል። ይህ ቃል ዕብራይስጡ መጽሐፍ ቅዱስ

ለጣዖትም ሥም ይጠቀመዋል። በአጠቃላይ ከሰው ከሚወጣ ዕዳሪና ጣዖት ተመሳሳይ ስም

እንዳላቸው ካወቅን የበቃናል። ምክንያቱም ወደ ፊት ቃሉን እያጠናን ስንሄድ ጣኦት

የሚለውን ቃል ለመረዳት ይጠቅመናልና ነው።

እንግዲህ ቃሉ ይህን ማለቱ በዚያን ዘመን የነበሩ ካህናት እውነተኛውን

በእግዚአብሔር እሳት የበሰለውን ገብስ ለራሳቸው በልተው ሕዝቡን ግን ከእነርሱ የወጣውን

እዳሪ ይመግቡት ነበር ማለት ነው። ካህናቱ የሚያስተምሩት ሰዋዊ የሆነ የሰው ወግና

በሰዋዊ አስተሳሰብ የተተረጎመ ቃልን በውጡ ያለው ነገር ተሟጦ ያለቀለት የማይጠቅም

ትምህርት ነበር።

ከሰው እዳሪ የሚወጣው ምግቡ በሆድ ውስጥ ከተብላላ የሚጠቅመው የምግቡ

ክፍል ቀድሞ በበላው ሰው ሰውነት ለጥቅም ከተሰራጨ በኃላ የማይጠቅመው ክፍል

ከሰውየው በእዳሪ መልክ ፋንድያ ሆኖ ይወጣል። ካህናቱም በልባቸው ያብላሉትን ቃል

መልካም መልካሙን ለራሳቸ በመውሰድ እዳሪውንና የማይጠቅመውን ፋንድያውን ለሕዝቡ

ይመግቡ ነበር። ይህ በኢየሱስ ዘመን እንደ ነበሩ ጻፎችና ፈሪሳዊያንም አገልግሎት ማለት

ነው።

ምልጃ 2016

9 www.tlcfan.org

ምልጃ ጸሎት መሳሰልን የሚጠይቅ ነው። ሕዝቅኤልም ይህ የመሳሰል ሕይወት

ሚስጥር ገብቶታል ስለዚህም የእግዚአብሔር የምልጃ ትዕዛዝ መቀበልና መማለድ

አላዳገተውም። በነብዮ ሁለተኛው መመሳሰል ደግሞ የምናየው ነብዮ በግራ ጎኑ 390 ቀን

ስለ እስራኤል ቤት ሃጢያት በጎኑ በመተኛት የተከናወነው መመሳሰል ነው። ሕዝ.4፥4,5,6

“4.አንተም በግራ ጐድንህ ተኛ የእስራኤልንም ቤት ኃጢአት አኑርባት፤

በምትተኛበትም ቀን ቍጥር ኃጢአታቸውን ትሸከማለህ። 5. እኔም

የኃጢአታቸውን ዓመታት ለአንተ የቀን ቍጥር እንዲሆንልህ ሦስት

መቶ ዘጠና ቀን ሰጥቼሃለሁ፤ የእስራኤልንም ቤት ኃጢአት ትሸከማለህ።

6. እነዚህንም በፈጸምህ ጊዜ በቀኝ ጐድንህ ትተኛለህ፥

የይሁዳንም ቤት ኃጢአት ትሸከማለህ፤ አንድን

ዓመት አንድ ቀን አድርጌ አርባ ቀን ሰጥቼሃለሁ።”

ይህን በማድረጉ ነብዮ ራሱን ከእግዚአብሔር በመጣው ሳይሆን በሰው ተብላቶ

በወጣው ወግ ከሚመገቡት ሕዝበ ከእስራኤልና ከይሁዳ ቤት ጋር እራሱን አንድ አደረገ፣

አመሳሰለ። ይሁንና በሃገሪቱ መካከል የሚቀሩ የእግዚአብሔር ቅሬታዎች ሁሌም

አይጠፉም። እነዚህም ቅሬታዎች ወይም ድል ነሺዎች ሁል ጊዜ ትክክለኛ የሆነ

የእግዚአብሔር ቃል መረዳት ያላቸውና በየዘመኑ እግዚአብሔር በሕዝብ መካከል ሸሽጎ

የሚያኖራቸው እርሱ ሲፈልግ ብቻ የሚገልጣቸው ገንዘቦቹ ናቸው። ነገር ግን ጳውሎስ

እንዳለው ከቅሬታዎቹ በስተቀር ሌሎቹ በሙሉ ስለሚሆነው ነገር ዕውሮች ናቸው።

ከቅሬታዎቹ ውጭ ሌላው የሚሆነው ነገር መመለከት አይችሉም። ፋንድያ በልተው

ለፋንድያ የሚቆሙ ለፋንድያ የሚከራከሩ ይህን የመሰለ የተላያየ ነገር የሚያደርጉ ድል

መንሳት የተሳናቸ ከሰዋዊ ሃሳብ በታች የወደቁ ሁሉ እውሮች ናቸው። ሮሜ.11፥5-7

ይህ 390ቀን ምልጃ ሕዝበ እስራኤል በረጅሙ የባርነት ግዞት ውስጥ

የሚለቀቀውን እንዳይጠፉ የሚረዳቸውንና የሚጋርዳቸውን ጸጋ መጠንም ያሳያል። ከአሦር

ከተባረሩበት ቀን አንስቶ ከ745 B.C. እስከ 1986 A.D. ዓመት ድረስ 7 x 390 ዓመት

ሲሆን፥ ይህም 1986 ዓመታት ሲሆን ከአዳም መፈጠር ጀምሮ ስንቆጥር 120ኛው ኢዮቤልዮ

ዓመት ነው።

ይህ ዓመት በምድር ላይ የተለያዮ አስደሳች ያል ሆኑ ክስተቶችን ይዞ ልክ

እንደ ጥንቱ ዘመን በሕዝብ መካከል ደግሞ ተገልጧል። ከሞላ ጎደል ከካህናቱ የሰሩት

የሃጢያት ሥራ ጋርና ከሕዝቡ የሃጢያት ሥራ ጋር የተያያዘ ነው።

ምልጃ 2016

10 www.tlcfan.org

ይህ ሁሉ ችግር የእግዚአብሔር ልጆች በምድር ላይ በሚገለጡበት ወቅት

የሚጠቀለል ነው። “የእግዚአብሔር ዘመን አቆጣጠር” በሚለው መጽሐፌ ላይ በዝርዝር

ክስተቶችና ፍጻሜያቸው የሚሆንበትን ዘመኖች ተቀምጦ ያገኛሉ።

ይህ የ40 ቀን ምልጃ የይሁዳ ቤት በሮም ከመጥፋቱ በፊት የተሰጠ የጸጋ

ዘመን ምሳሌ ነበር። ይህም ከመጥምቁ ዮሐንስ መገደል አንስቶ ሮም መቅደሱን

እስካፈረሰችበት ቀን ድረስ የቆየ ዘመን ነው። ይህ የምልጃ ዘመን እንዲህ ባለ መልኩና

ዘመን በትክክል በትንቢታዊ መልኩ ደግሞ ተፈሟል። ዘመኑ የቆየው ከ30 A.D. እስከ 70

A.D ነበር። ቀኑ ደግሞ የጀመረውም ሆነ የጨረሰው በፋሲካ በዓል ቀን ላይ ነበር። ነገር

ግን ይህ ጥላዊ ምልጃ በዚህ አላበቃም። ነገር ግን ሌላ ዘመንንም በሌላ መልኩ ያመለክታል።

ይህም ገና የሚመጣን ዘመንን ነው።

ለምሳሌ በዚያው ዘመን ሌላ አርባ የጸጋ ዘመንን እንመልከታለን። ከኢየሱስ

ስቅለት ከ33 A.D ቀን አንስቶ እስከ “Masada” በፋሲካ ቀን በሮም ጦር ሥር እስከ

ወደቀችበት ቀን እስከ 73 A.D የቆየውን ዘመን ነው።

ከዛም ሌላው ዘመን ደግሞ አርባው ኢዮቤልዮ የጸጋው ዘመን ነው። (40 x

49 ዓመት ነው) ከኢየሱስ ከስቅለቱ አንስቶ እስከ 1993 A.D. ዓመት ድረስ የቆየ ነው።

ይህ ዓመት በዚህ ባደገው ዘመን ያሉትን ማላጆች ወደ ልዮ ወደ ሆነ እስከ 2000 ዓመት

ድረስ የቀጠለ ምልጃና መንፈሳዊ ውጊያ ውስጥ ያስገባ ልዮ ዘመን ነው።

እነዚህ በታሪክ በጣም ወሳኝ የሆኑ ዓመታቶች ነበሩ። ምክንያቱም

የእግዚአብሔር ልጆችን መገለጥ የሚያመጣን መንገድ የሚጠርጉ ማላጆች በሃይል

የተነሱበት ዘመን ነበር። ይህም ሰፊ ሃሳብ በዚች ትንሽ መጽሐፍ ሊብራራ የሚችል

ትንቢትና ሚስጥር አይደለም። ነገር ግን የእግዚአብሔር ማላጆች እንደ ትንቢቱ በየሰፍራው

መነሳታቸውን የምስራች አበስራለሁ።

ነገር ግን የሕዝቅኤል ምልጃ ምን ያህል ትንቢታዊ ግቦች እንዳለውና ይህ

ዘመን ከትውልድ ትውልድ እየዞረ እኛ ዘመን ድረስ የመጣ ታላቅ ምልጃ መሆኑን ካወቅን

ለትምህርታችን ይበቃናል። ከዚህም በመነሳት ምልጃ ከዘመን ዘመንም የሚሻገር ጸሎት

ነው። ይህም የተጸለየው ጸሎት መልስና ፍጻሜ እስከሚያገኝ ነው። ሕዝቅኤል በሕይወቱ

ያሳየን አንዱ ሚስጥር ይሄ ነው።

ምልጃ 2016

11 www.tlcfan.org

የነብዮ ሆሴዕ የምልጃ ሕይወት

ሌላው ራስን ከሌላው ጋር አንድ አድርጎ ለምልጃ ማመሳሰል የሚለውን ሃሳብ

የሚያሳየን የእግዚአብሔር ባሪያ ነብዮ ሆሴዕ ነው። ነብዮ በእግዚአብሔር ጋለሞታይቱን

እንዲያገባ ተደርጓል። ይህም እንዲመሳሰል ነው፦ ሆሴ.1፥2,3

“2. እግዚአብሔር መጀመሪያ በሆሴዕ በተናገረ ጊዜ፥ እግዚአብሔር

ሆሴዕን። ምድሪቱ ከእግዚአብሔር ርቃ ታላቅ ግልሙትና ታደርጋለችና ሂድ፤

ጋለሞታን ሴትና የግልሙትናን ልጆች ለአንተ ውሰድ አለው። 3.

እርሱም ሄዶ የዴቤላይምን ልጅ ጎሜርን አገባ፤ እርስዋም

ፀነሰች ወንድ ልጅንም ወለደችለት።”

እግዚአብሔር ለምን ጋለሞታይቱን እንዲያገባ እንዳዘዘ በቃሉ ላይ በግልጽ

ተቀምጧል።እግዚአብሔር እስራኤልን አግብቷት ነበር። ነገር ግን እስራኤል በእግዚአብሔር

ላይ ሌላ አምላክን ወድዳ ልታመልክ ራስዋን ከሌላ አማልክቶች በታች በማስገዛትዋ

በእግዚአብሔር ላይ ገልሙታለች። ሆሴዕ በዚህ ምልጃ ላይ እራሱን ከእግዚአብሔር ጋር

አመሳስሏል። በምልጃ የተገለጠው ከእግዚአብሔር ጋር አንድ ሆኖና ተመሳስሎ ነው።

በዚያን ዘመን የነበሩ ካህናት ምን ሊሉ እንደ ሚችሉ መገመት አንችልም።

ነገር ግን እግዚአብሔር በዚያን ዘመን እንዲ ማልዱለት እራሱን ከእነርሱ ጋር አላመሳሰለም።

ነገር ግን እግዚአብሔር ራሱን ከሆሴዕ ጋር በማመሳሰል ሆሴዕን ለምልጃ ተጠቀመው።

ዛሬም በእኛ ዘመን እንዲሁ ሊሆን ይችላል። እግዚአብሔር ለምልጃ ይመርጠን ይሆንን?

ሆሴዕ በዘመኑ ሊማልድ በእግዚአብሔር የተመረጠ ነብይ ነው።

የሆሴዕ ምልጃ ፍጻሜው አስደሳች ነበር። ሚስቱ ከከዳችው በኃላ ሆሴዕ

እንደገና መልሶ ተቤዣት። ይህ አስደሳች የሆነ የእግዚአብሔር ለቤተክርስቲያንም ሆነ

ለኢየሩሳሌም የሰራው ስራ ነው። ሆሴ.3፥2

“1. እግዚአብሔርም። የእስራኤል ልጆች ወደ ሌሎች አማልክት ቢመለሱና

የዘቢብ ጥፍጥፍን ቢወድዱ እንኳ፥ እግዚአብሔር እንደሚወድዳቸው አንተም

ውሽማዋን የምትወድደውን አመንዝራይትን ሴት ውደድ አለኝ። 2፤ እኔም

በአሥራ አምስት ብርና በአንድ ቆሮስ መስፈሪያ ተኩል ገብስ ገዛኋት። 3፤

ከእኔ ጋር ብዙ ወራት ተቀመጪ፥ አታመንዝሪም፥ ለሌላ ሰውም አትሁኚ፤

እኔም እንዲሁ እሆንልሻለሁ አልኋት።”

ምልጃ 2016

12 www.tlcfan.org

ይህም እግዚአብሔር ግልሙትናዋ በእስራት ቀንበር የጣላትን እስራኤል መልሶ

እንደ ሚቤዣት እግዚአብሔር አሳየ። ይህ በሰሜን በኩል ላሉት እስራኤላዊያን በዘመኑ

ታላቅ የሆነ የመጽናናት ቃልና ትንቢት ነበር። ምክንያቱም በዚያን ወቅት 10 የእስራኤል

ትውልድ ከሰሜን ወደ አሦር ባርነት ግዞት ተወስደው ነበርና ወደ ቤታቸውም ሊመለሱ

አልቻሉም ነበርና ነው።

ሆሴ.2፥6 እነርሱ በእግዚአብሔር የግልሙትናዋ ልጆች ተብለው ይታወቃሉ።

እነዚህ የይሁዳ ዘር ያልሆኑ እስራኤላዊያኖች በሌላ ስፍራ ደግሞ “የተበተኑት የእስራኤል

ወገኖች” በመባል ሲጠሩ እንመለከታለን። ያቆ.1፥1

ሰው ምናልባት ረስቷቸው ይሆናል እግዚአብሔር ግን ፈጽሞ

አልረሳቸውም። የእስራኤል ሕዝብ በስደት የቆዮበት ዘመናት በትንቢቱ መሰረት 2,520

ዓመት ናቸው። (7 x 360) ይህም ከ745 B.C. ጀምሮ እስከ 1776 A.D. ድረስ የቆየ ዘመን

ነው። የእስራኤል ሁሉ የተበተኑ ወገኖች በሰሜን አሜሪካ እንደ ሚሰባሰቡ ትንቢቱ ይናገር

ነበር።

ሁለተኛ 2,520 - ዓመት ዙር መጀመሪያው በ721 B.C., ሰማርያ በአሦር

ግዞት ከተያዘዝበት ቀን የሚጀምር ነው። ከዚያ ቀን መጀመሪያ ተነስተን ዘመኑን ስንቆጥር

2,520 ዓመት በኃላ ትንቢቱ የተፈጸመበትን ቀንና ዘመን እናገኛለን። ይህም በ1800 A.D.

በአሜሪካ ዋና ከተማ በዋሽንግተን ዲሲ ትንቢቱ ፍጻሜን አግኝቷል።

ሌላው መንፈሳዊ መረዳት ደግሞ እስራኤል ማለት ያቆብ ከመላዕኩ ጋር

ከተታገለ በኃላ የተሰጠው የተቀየረለት ሥም ነው። ዘፍ.32፥28 ያቆብ እስራኤል የሚል

ሥም ይዞ አልተወለደም። ነገር ግን ሰለ እግዚአብሔር ማወቅ የሚገባውን በሕይወቱ ተምሮ

ካበቃ በኃላ ከእግዚአብሔር ጋር ካለው ሕብረት የተነሳ የተቀበለው ሥም ነው። ይህ ኢየሱስን

መልክ በላያቸው ላይ የሚያንጸባርቁ እንደ ያቆብ በሕይወት ልምምድ ከእግዚአብሔር ጋር

ሕብረት የሚያደርጉ የድል ነሺዎች ሌላ ሥም ነው።

በዚህ መረዳት መሰረት ሁሉን ስንመለከት የሕዝቅኤል የሰዓት መደብ ዙር

በዚህ ላይ ልንመለከተው የሚገባ አስፈላጊ ነገር ነው። ይህም ዘመን 7 x 390 ዓመት ነው።

ይህም ትንቢት እስከ 1986 A.D. ያመጣናል። ይህ እግዚአብሔር ገብሱን ከስንዴ መለየት

የጀመረበት ዓመት ነው።

ምልጃ 2016

13 www.tlcfan.org

ይህም ቤተክርሲያንን በሁለት መልኩ ያስቀምጧታል ወይም ከፍሏታል።

ይህም ስንዴ ከገብስ ጋር እንደማይዘራ ቤተክርሲያንና ድል ነሺዎች የራሳቸው እርሻ

ይኖራቸዋል ማለት ነው። ይህም በእግዚአብሔር ሕግ መሰረት ነው። ሰንዴ በመጽሐፍ

ቅዱስ ውስጥ የቤተክርሲያን ምሳሌ ሲሆን ገብስ ደግሞ ከየቤተክርሲያኑ ድል ለሚነሱ

አማኞችን የዘመኑ ቅሬታዎች ምሳሌ ነው። ሕጉ እንዲ ከማዘዙ የተነሳ ገብስ ከስንዴ ሊለይ

ግድ ነው። ዘዳ.22፥9

“የዘራኸው ዘርና ከወይኑ የወጣው አንድ ሆነው

እንዳይጠፉብህ በወይንህ ቦታ ላይ ሁለት ዓይነት ዘር አትዝራ።”

ከ1986.ዓ.ም በፊት እግዚአብሔር ድል ነሺ ክርስቲያኖችን በሙሉ

የሚመለከታቸው ከበዓለ አምሣ በታች በነበረችውና ባለችው ቤተክርሲያን ሕብረት ውስጥ

ነበር። ነገር ግን ከዚህ ዘመን በኃላ እግዚአብሔር ድል ነሺዎችንና ቤተክርሲያንን በተለያየ

እርሻ ሊዘራቸው ወዷል። ይህም የበዓለ አምሣ ወቅት ከሕዝቡ ጋር የተቀላቀለውን እርሾ

ድል ነሺዎቹን ፈጽሞ እንዳያረክሳቸው ከእነርሱ እንዲወገድ ተቃጥሎ ይጠፋ ዘንድ ነው።

ዘሌ.23፥11

ምልጃ 2016

14 www.tlcfan.org

የነብዮ ኢሳያስ የምልጃ ሕይወት

ነብዮ ኢሳያስ ለመማለድ የሚያስደንቁ ነገሮችን አድርጓል። በትንቢተ ኢሳያስ

ላይ ያለውን ምሳሌነቱን እንመልከት፦ ኢሳ.20፥2-5 ኢሳያስ በዚህ ጥቅስ መሰረት ራሱን

ከግብፅና ከኢትዮጲያ (ከኩሽ) ጋር አንድ በማድረግ ያመሳስላል።

“2. በዚያ ዓመት እግዚአብሔር የአሞጽን ልጅ ኢሳይያስን። ሂድ፥ ማቅህን ከወገብህ

አውጣ ጫማህንም ከእግርህ አውልቅ ብሎ ተናገረው። እንዲህም አደረገ፥ ራቁቱንም

ባዶ እግሩንም ሄደ። 3. እግዚአብሔርም አለ። ባሪያዬ ኢሳይያስ በግብጽና በኢትዮጵያ

ላይ ሦስት ዓመት ለምልክትና ለተአምራት ሊሆን ራቁቱንና ባዶ እግሩን እንደ ሄደ፥

4. እንዲሁ የአሦር ንጉሥ የግብጽንና የኢትዮጵያን ምርኮ፥ ጐበዛዝቱንና

ሽማግሌዎቹን፥ ራቁታቸውንና ባዶ እግራቸውን አድርጎ ገላቸውንም ገልጦ፥ ለግብጽ

ጕስቍልና ይነዳቸዋል። 5. እነርሱም ከተስፋቸው ከኢትዮጵያ ከትምክሕታቸውም

ከግብጽ የተነሣ ይፈራሉ ያፍሩማል 6. በዚያም ቀን በዚች ባሕር ዳርቻ የሚቀመጡ።

እነሆ፥ ከአሦር ንጉሥ እንድን ዘንድ ለእርዳታ ወደ እነርሱ የሸሸንበት ተስፋችን

ይህ ነበረ፤ እኛስ እንዴት እናመልጣለን? ይላሉ።”

ቁጥር ስድስት እስራኤል ከአሦር ንጉስ ይድን ዘንድ ከኢትዮጲያና ከግብፅ

እርዳታን ይጠብቅ እንደ ነበር ተስፋም አድርጓቸው እንደ ነበር እንመለከታለን። ኢትዮጵያ

የእነርሱ ተስፋ ፣ ግብፅ ደግሞ የእነርሱ ክብር እንደ ነበረች እናያለን። ይህን ከማድረግ

ይልቅ ወደ እግዚአብሔር በንስሃ ሊመለሱ ይገባችው ነበር። እርዳታ ከእግዚአብሔር እንጂ

ከሌላ መጠየቅ አልነበረባቸውም። ምክንያቱም ሁሉ ችግር ያገኛቸው የእግዚአብሔር ሕግ

ስለ ተላለፉ ሃጢያት ስለ ሰሩ ነበር። ከእግዚአብሔር እንጂ ከሰው መፍትሄ መፈለግ

የለባቸውም ነበር።

የኢየሩሳሌም ሕዝብ በንጉስ ሕዝቅያስ ዘመን ወደ እግዚአብሔር ጸልዬ

እግዚአብሔር አሦርን አጥፍቶላቸው ነበር። ኢሳያስ ይህን ትንቢቱን በዚያን ዘመን መናገሩ

በዚያ ዘመን የነበሩትን ከጥፋት አድኗቸዋል። ይህም ትንቢት ትውልዱ ሳያጠፉ ተከልሎና

ተዘሎ መኖርን አምጥቶላቸዋል። ነገር ግን ከ100 ዓመት በኃላ ግብፅ እስራኤልን ከግብርና

እዳና ቀረጥ በታች ጣላት። የግብፅም ንጉስ ኢዮአክስን ወደ ግብፅ ለግዞት ወስዶ ወንድሙን

ኤልያቄምን በይሁዳና በኢየሩሳሌም ላይ ለይስሙላ አነገሰው። 2.ዜና.36፥1-5 ይህ አይነቱ

ቅንጅት ግብፅን በሃላፊነት ሥፍራ ላይ ያወጣታል። ምክንያቱም ማንኛውም መንግስት

ኢየሩሳሌምንና ይሁዳን ሊወጋ ቢወጣ ከግብፅ ጋር እንደ ተጣላ ይቆጠራልና ነው።

ምልጃ 2016

15 www.tlcfan.org

ወንድሙን በዙፋን ላይ ማውጣቱ ለሕዝቡ እይታና ለአሰራሩ እንዲ ጠቅመው

ለይስሙላ እንጂ ወንድሞ በወንድሙ ፋንታ እንዲገዛ ፈልጎ አልነበረም። ምክንያቱም ከዚያ

በመቀጠልም የግብፅ ወገንተኛ የሆኑት ኢትዮጲያዊያንና ባቢሎናውያን ኢየሩሳሌምን ከዛን

በኃላ ይገዟት ጀመር። 2.ዜና.36፥6

ኢሳያስ የተናገረው ትንቢት በዚህ መልኩ ተፈጸመ። ኢሳያስ እንደ ተናገረው

እስራኤላዊያን ወደ አሦር ተወሰዱ። ነገር ግን የይሁዳ ፍርድ ዘገየ ይህም ንጉስ ሕዝቅያስ

ንስሃ ስለ ገባ ነው። ስለዚህም ይሁዳ በአሦር ከመወሰድ አመለጠች። ከዚያም በኃላ የይሁዳ

ንጉስ እግዚአብሔር እንዴት ከአሦር እንዳዳነው በመጨረሻ ዘነጋ።

ኢየሩሳሌም እንዳደረገችው ይሁዳም በግብፅ ታመነች ከዚህም የተነሳ ይሁዳ

ደግሞ በባቢሎን ከምድርዋ ለግዞት ተጠርጋ ተወሰደች። የኢሳያስ ምልጃ እንግዲህ የቆየው

ሦስት ዓመት ያህል እንደ ሆነ ከዚህ መመልከት እንችላለን። ይህም እግዚአብሔር በግብፅና

በኢትዮጲያ ላይ የሚያደርገውን ፍርድ ለማድረግ ጽዋው እስኪሞላና ዘመኑን ለመወሰንም

ጭምር ነው።

ስለ ፍርድ ስንናገር የእግዚአብሔር ፍርድ ለማረምና ለማስተካከል እንጂ

ለማጥፋት እንዳልሆነ በአዕምሯችን ሊቀመጥ ይገባል። የእግዚአብሔር ሕግ ፍርድ ሁል ጊዜ

ሰውን ሕጉ በሚጠይቀው መልኩ ቀጥቶ ትክክለኛውን ሥፍራ የሚያሲዝ ነው። ይህም

የተቀጣውን ሰው ከፍርድ በኃላ ከጸጋ በታች እንዲሆን ለማድረግ ነው።

ስለዚህም እግዚአብሔር አስቀድሞ ሌላ እንዳያስብ ለኢሳያስ እግዚአብሔር

እንዴት አድርጎ ግብፅን እንደ ሚፈውሳት ነገሮታል። ኢሳ.19፥22 ግብፃዊያን የእግዚአብሔር

ሕዝብ እንደሚሆኑ በቃሉ እግዚአብሔር ጆሮ ላለን ለምንሰማ ሰዎች ሁሉ ይናገራል።

“22. እግዚአብሔርም ግብጽን ይመታታል፤ ይመታታል ይፈውሳታልም፤

ወደ እግዚአብሔርም ይመለሳሉ እርሱም ይለመናቸዋል ይፈውሳቸውማል።

23.በዚያ ቀን ከግብጽ ወደ አሦር መንገድ ይሆናል፥ አሦራዊውም ወደ ግብጽ፥

ግብጻዊውም ወደ አሦር ይገባል፤ ግብጻውያንም ከአሦራውያን ጋር ይሰግዳሉ። 24፤25.

የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር። ሕዝቤ ግብጽ፥ የእጄም ሥራ አሦር፥

ርስቴም እስራኤል የተባረከ ይሁን ብሎ ይባርካቸዋልና በዚያ ቀን እስራኤል

ለግብጽና ለአሦር ሦስተኛ ይሆናል፥ በምድርም መካከል በረከት ይሆናል።”

ምልጃ 2016

16 www.tlcfan.org

እንግዲህ እግዚአብሔር የኢሳያስን ምልጃ እግዚአብሔር ጊዜውን በሦስት

ዓመት ብቻ የወሰነው እግዚአብሔር በግብፅና በኢትዮጲያ ላይ የፍርድ ዘመን መጠን ሊወስን

ሰለ ፈቀደ ነው። የምልጃው መጨረሻው አላማው ይህ ነበር። ነብዮ ልብሱን ሲለብስና

ጫማውን ሲያደርግ ይህ የሚያሳየው የፍርዱ ዘመን እንዳበቃ እንደ ተፈጸመ ነው። የኢሳያስ

ምልጃ ክፉ ሳይሆን መልካም ክፍል ያለው ነው።

ግብጽ፣ ኢትዮጲያናና አሦር እነርሱን መጠን በሌለው ባርኮት እግዚአብሔር

ይባርካቸዋል። የእነርሱ ሕዝቦቻቸውም ሁሉ ወደ እግዚአብሔር በንስሃ ይመለሳሉ።

ለእርሱም ይሰግዳሉ እጃቸውንም ለእግዚአብሔር ይሰጣሉ። የእነርሱ ትውልዶችም

በእግዚአብሔር መንግስት ውስጥ ይጠቃለላሉ። ይህም በመጨረሻው በመሲሁ ዘመን

የሚሆንና የሚፈጸም ትንቢት ነው። ይህን ብዙ ጊዜ የዳስ በዓል ዘመን በማለት የምንጠራው

በዓላ አምሣን ቀጥሎ የሚሆን የእግዚአብሔር ታላቁ የዳስ በዓል ቀን ነው።

ምልጃ 2016

17 www.tlcfan.org

ነብዮ አብርሃምና ይሳቅ

አብርሃም የእምነት አባት በመባል ይታወቃል። ይህም እምነት የሚለው

ሃሳብና ቃል ከእርሱ ዘመን በመነሳት እያደገ ስለ መጣ ነው። ነብዮ አብርሃም ራሱን

ከእግዚአብሔር ጋር እንዲያመሳስል ተጠርቷል። ይህም ብቸኛ ልጁ የሆነውን የተስፋው

ዘር የሚመጣበትን ልጁን መስዋዕት ለማድረግ ነው። ይህ አይነቱ ድምፅ ወደ እርሱ ሲመጣ

ምን አይነት ሃሳብ ሊያስብ ምን አይነት ሃሳብ ወደ ልቡ ሊመጣ እንደሚችል መገመት

ቀላል አይደለም።

እኛ ሁል ጊዜ ጥንት ስለ ነበሩ ቅዱሳን አባቶች ያለን መረዳት ትክክለኛ

መልኩን አንድ አንዴ ይስታል። እነርሱ የእግዚአብሔር ድምፅ ሲሰሙ በአንድ ጊዜ ሁሉ

ነገር ይታዘዙ እንደ ነበረ አድርገን እንገምታለን። እነርሱ እንደኛው ሰው ናቸው። ስለዚህ

ከእኛ በተለየ መልኩ አይታዘዙትም። ያቆ.5፥17

አንድ ሰው አንድ እርሱ ካልጠበቀው ውጪ የሆነ ድምፅ ቢመጣለት የሚለውን

ሁሉ እነርሱም ይላሉ። ከኛ ለየት የሚያደርጋቸው ግን ነገሩን በትጋት በመመርመር ወደ

ፍጻሜው በእምነት ይመጣሉ። የእግዚአብሔር ፈተና በጣም እውነት ነው። ኢየሱስ እንኳን

ወደ መታዘዝ የመጣው ከተቀበለው መከራ የተነሳም ጭምር ነው። ዕብ.5፥8

በመጀመሪያ እግዚአብሔር ለአብርሃም ሰው ሊሰማው በሚችለው ድምፅ አይነት

ጮክ ብሎ ተናግሮታል ማለት አንችልም። ምክንያቱም እግዚአብሔር በቁጣ በጠንካራ

ትዕዛዝ ማንንም አያዝምና ነው። ነብዮ ኤልያስ እግዚአብሔር በነጎድጓድ፣ በምድር

መንቀጥቀት ወይም በመብረቅና እሳት እንደ ማይናገር ጠንቅቆ ተምሯል። ሳሙኤልም

ይህን ለእኛ ጽፎልናል። እግዚአብሔር በዝምታ ጸጥ ባለ ነገር ውስጥ ልክ ከሰው አፍ

በዝግታ እንደሚወጣ ንፋስ ሃሳቡን ወደ ሰው መንፈስ ያነፍሳል። 1.ዜና.19፥11-

“a sound of gentle blowing” (NASB)

“a still small voice” (KJV).

እግዚአብሔር ጮሆ ቢናገር በሰማይ ያሉ እንኳን ሳይቀሩ ልጆቻቸውን

መስዋዕት ያደርጉ ነበር። ነገር ግን እግዚአብሔር ለአብርሃም በውስጥኛው ክፍል በመንፈሱ

ተናገረው። ይህ ታላቅ ፈተና ነው። ይህ አብርሃም በቀላሉ ይቀበለው ዘንድ ቀላል የሆነ

ነገር አይደለም። አብርሃም እግዚአብሔር እንደ ተናገረው በመጀመሪያ እርግጠኛ ሊሆን

ይገባዋል። ክፉው ዲያቢሎስ ወይም ሥጋዊ አዕምሮው ይህን ሃሳብ እንዳላፈለቀለት

መመርመር እንደ ማንኛውም ሰው ይጠበቅበታል።

ምልጃ 2016

18 www.tlcfan.org

አብርሃም እግዚአብሔር ሰውን በመስዋዕትነት እንደ ማይቀበል ያውቃል። ይህ

ብቻ አብርሃምን ልጁን መስዋዕት ከማድረግ ለማቆምና ሊያጠራጥረው የታዘዘውን ከማድረግ

ሊገታው ይችላል። አብርሃም እንዴት የእግዚአብሔር ድምፅ መሆኑ እንደ ለየ ለእኛ

ሚስጥሩ አልተነገረንም። እንዴትም ከእግዚአብሔር ቃል ማረጋገጫ እንዳገኘ አናገኝም።

ነገር ግን አብርሃም እንደታዘዘ ተቀምጦልናል። ይህም እግዚአብሔር ልጁን ከሞት እንኳን

እንደሚያስነሳው በመታመን ብቻ እንጂ የታሰረውን በግ ስላየ መሰዋዕት አላደረገም።

አብርሃም እግዚአብሔርን ከሚያውቀው ባሕሪው በመነሳት የመጣውን ቃል በመፈጸም

ሊያከብረው ሊታዘዘው ፈቀደ።

ለአብርሃም እግዚአብሔርን እንደ ሴጣን ከእርሱ እንዲርቅ ገስፆ ለልጁ ለይሳቅ

ሴጣን እንድትሞት ፈልጓሃልና ተግተህ ጸልይ ማለት ሊያስጠነቅቀው ይችል ነበር።

የመጀመሪያው ፈተና አብርሃም በእግዚአብሔር ፍርድ ውሳኔ ላይ ይደገፍ ወይም አይደገፍ

እንደ ሆነ ማየቱ ነው። ምሳሌ.3፥5

ብዙዎቻችን እንደ እዚህ አይነት ፈተና በአንድም ሆነ በሌላ መልኩ

ከእግዚአብሔር ዘንድ ተቀብለናል። ይህን አይነቱ የፈተና ሥፍራ የማይመችና የሚቆረቁር

ነው። ነገር ግን በመጨረሻ ላይ እግዚአብሔር የሚሰራው ነገር አለው የሚል እምነት ላይ

ያመጣናል። ይህ ደግሞ ሰዎች ሰለ እግዚአብሔር ከሚረዱት ባሕሪ ውጪ ተለይተን

እንድንኖር ያስገድደናል። ቃላተኛና ጥቅሰኛ መሆናችንን ያስጥለናል። ከዛም የሰዋዊ

መረዳትን ግድግዳ ሁሉ አፍርሰን በእምነት እንገሰግሳለን።

ይህም ፈተና ጥልቅ የሆነን ማንም ሊነካውና ሊያፈርሰው የማይችለውን እውነት

በውስጣችን ተክሎ ያልፋል። አብርሃም ከእግዚአብሔር ጋር ራሱን በዚህ አስቸጋሪ በሆነ

ነገር ውስጥ እዲመሳሰልና እግዚአብሔር አድንያ ልጁን ኢየሱስ ለሰው ልጆች ሁሉ አሳልፎ

ለመስዋዕትነት መስጠት ምን ማለት እንደ ሆነ በጥልቅ በሕይወቱ የምልጃ መመሳሰል

ሕይወት የእግዚአብሔር ፍቅር ጥልቀት ተረዳ።

አብርሃም የእግዚአብሔር ልብ ለማወቅ የተጠራ ሰው ነው። ከአባቶቻችን እንደ

እርሱ ያለ ሰለ ኢየሱስ መሰዋዕት ሆኖ ለሰው ልጆች መሰዋት ሚስጥር የሚያውቅ አለ

ለማለት ያስቸግራል። አብርሃም የእግዚአብሔር ሕመም፣ ጣር፣ ፍቅርና የትንሳኤውን

ክብርና የልጁን የኢየሱስን ቀን ተመልክቷል። አብርሃም ቀኔን አየ ብሎ ክርስቶስ

መስክሮለታል።

ምልጃ 2016

19 www.tlcfan.org

እኛም የአብርሃም ልጆች የሆንን በመንፈስ ቅዱስ በመመራት የአብርሃም

አይነት ሕይወት ልምምድ ውስጥ እንገባለን። ከዛም የእግዚአብሔርን ልብ እርሱ በሰጠን

በመንፈሱ እንመለከታለን። ይህም በመጀመሪያው የምልጃ መርህ ውስጥ የሚገኝ በረከት

ነው። እርሱም ራስን ከሌላው ጋር አንድ አድርጎ ማጣመር፣ ማመሳሰል እራስን ልክ ሌላው

ሰው ቦታ ማቆም መተካትና ነገሩ እንደራሳችን እንዲሰማን ማድረግ ነው። ይህም

በእንግሊዘኛው “identification” የምንለው ነው። የምልጃ ዋንኛውና መሰረቱ ራስን ከሌላው

ጋር ማመሳሰል ነው። ራስን ማመሳሰል የምልጃ ሕይወት በር ከፋች መርህ ነው።

ምልጃ በሁለት መካከል መቆም ማለት እንደ ሆነ ከላይ ተነጋግረናል። ስለዚህ

ይህ የሚማልድ ሰው ሁለት አይነት መልክ ይይዛል። 1.ጢሞ.2፥5 የመጀመሪያው ራስን

ከሃጢያተኛው ሰው ጋር ማመሳሰል ወይም የእርሱ ሥፍራ ይዞ መቆም ነው። ሁለተኛው

ደግሞ ከእግዚአብሔር ጋር መሰማማትና፣ መመሳሰል የእርሱን ቦታ ይዞ ነገሩን መመልከት

ነው። ይህ ትክክለኛ የምልጃ ጸሎትን ያመጣል።

ሕዝቅኤልና ኢሳያስ ከሃጢያተኛ ሰው ጋር ራሳቸውን አመሳስለዋል ይህም

በፋንድያ ላይ የበሰለን በመብላትና ራቁትን ለሦስት ዓመት በመጓዝ ነው። ነብዮ ሆሴና

ነብዮ አብርሃም ደግሞ ራሳቸውን ከእግዚአብሔር ጋር አመሳስለው እናገኛለን። ይህም ሆሴዕ

ጋለሞታይቱን በማግባትና አብርሃም ደግሞ እንደ እግዚአብሔር ልጁን መስዋዕት አድርጎ

በማቅረብ ነው።

በምልጃ ውስጥ ያለው የመመሳሰል መርህ ሕይወት ማላጆቹን ሰራተኞች አድርጎ

ለሕዝቡ በመኖርና በማድረግ የሆነ አሰተማሪዎች አድርጎ ያቆማቸዋል። እግዚአብሔር

የምንማልድ ሰዎችን መንገዳችንን ቀድመን እንድንረዳ ሁሌ አያደርገንም። ይልቁንም

ከመረዳታችን በፊት እንድንኖረው ይጠራናል። ከዛም በኑሮ መካከል ሁሉን መንገዳችንን

እንማራለን የሚሰራውንም ሥራ ወይም የሰራውን ስራ እንረዳለን።

ይህ በጣም አስጨናቂ የማይመች ነገር ሊመስል ይችላል። ይህን በዚህ መልኩ

ለምን እንደ ሆነም ለመረዳት ያዳግታል። በሚቀጥለው ክፍል ላይ እንደ ምናጠናው

የሚማልድ ሰው በእምነት እንጂ በመረዳትና በእውቀት የሚሄድ ሰው አይደለም። ኢየሱስ

ለእኛ እንደ ማለደ እንደሚማልድ እናምናለን። ነገር ግን እርሱ እራሱ በመስቀል ላይ እኛን

መሰሎ በተተካን ጊዜ አምልኩ ለምን እንደዚያ እዳደረገው በመከራው ሰዓት ለምን እንደ

ተወው አልተረዳም። ስለዚህም “አምላኬ አምላኬ ለምን ተውከኝ” ብሎ ጮኸ ጠየቀ።

ምልጃ 2016

20 www.tlcfan.org

እግዚአብሔር እንደ እዚሁ አንዳንድ ነገር በሕይወታችን ሲያልፍ ውጤቱን

ሳናይ ለምን አሁን በሕይወታችን የሚያልፈውን እንደሚያደርግ አናውቅም። ነገር ግን

እግዚአብሔር በሚማልድ ሰው ሕይወት እንዲህ ያደርጋል። እግዚአብሔር ሁሉን የማሳወቅ

ግዴታ የለበትም። ሚስጥሩ ለአምላካችን ነው ሥራውን እንድንሰራ ሥራው የተገለጠልን

ደግሞ ለእኛ ለምንማልድ ሰዎች ሁሉ ነው።

እግዚአብሔር የእኛ ጠባብ አዕምሮ ከምታስበው ዓላማ በላይ ታላቅ አላማ እንደ

ሚኖረው ማመን ይጠበቅብናል። በእርግጥ ደግሞ ሁሉ የማየው የማልፍበት ነገር ምንም

እንኳን መልካም ባይሆን ለመልካም እንዲደረግ ይህን አውቃለሁ። ሮሜ.8፥28 የሚማልድ

ሁል ጊዜ በእምነት ሁሉን የሚያደርግና የሚኖር ሰው ነው።

ምልጃ 2016

21 www.tlcfan.org

በደልን መሸከም

ኢሳያስ 53 ላይ በጣም ታዋቂ የሆነውን ስለ ኢየሱስ ሞት የሚናገረውን

ትንቢትን እናገኛለን። በቁጥር 11 ላይ እንዲህ ይላል፦

“11 ከነፍሱ ድካም ብርሃን ያያል ደስም ይለዋል፤ ጻድቅ ባሪያዬም

በእውቀቱ ብዙ ሰዎችን ያጸድቃል፥ኃጢአታቸውን ይሸከማል።”

ይህን የኢየሱስ አንዱ የምልጃ ሥራው እንደ ሆነ ሁላችን እናውቃለን። ነገር

ግን ይህ መርህ ለማንኛውም ማላጅ ላይ የሚሰራ መሆኑን ግን የምንገነዘብ ሰዎች ጥቂቶች

ነን። አንዳዶች የሌሎችን በደል መሸከም እግዚአብሔርን መቃወም የእርሱን ስፍራ እንደ

መውሰድ አድርገው ይቆጥሩታል። ኢየሱስ ብቻ ነው የሰዎችን ሃጢያት መሸከም የሚችል

ይላሉ። እውነት ነው ኢየሱስ ብቻ ነው የዓለምን ሁሉ ሃጢያት መሸከም የሚችል። ነገር

ግን እኛም የእርሱ ልጆች የሁሉን ሰው ልጆች ሳይሆን የጥቂቶችን ሰዎች ሃጢያት መሸከም

እንችላለን። ምን ማለቴ ምን እንደ ሆነ በደንብ አብራራለሁ።

እግዚአብሔር በሌዋውያን ክህነት በሙሴ ዘመን ሃጢያት የሰሩ ሰዎች

መስዋዕታቸውን ይዘው ወደ ማደሪያው ድንኳን ይመጡ ነበር። ዘሌ.6፥25-29 ላይ እንዲህ

ይላል፦

“25. አሮንንና ልጆቹን እንዲህ ብለህ ተናገራቸው። የኃጢአት መሥዋዕት ሕግ ይህ

ነው፤ የሚቃጠል መሥዋዕት በሚታረድበት ስፍራ የኃጢአቱ መሥዋዕት

በእግዚአብሔር ፊት ይታረዳል፤ እርሱ ቅዱስ ቅዱሳን ነው። 26. ለኃጢአት

የሚሠዋው ካህን ይበላዋል፤ በመገናኛው ድንኳን ዙሪያ ባለው አደባባይ በተቀደሰ

ስፍራ ይበላል። 27.ሥጋውን የሚነካ ሁሉ ቅዱስ ይሆናል፤ ማናቸው ልብስ ደም

ቢረጭበት የተረጨበትን በተቀደሰ ስፍራ ታጥበዋለህ። 28.የሚቀቀልበትም ሸክላ

ይሰበራል፤ በናስም ዕቃ ቢቀቀል ይፈገፈጋል፥ በውኃም ይለቀለቃል። 29. ከካህናት

ወገን የሆነ ወንድ ሁሉ ከእርሱ ይበላል፤ እርሱ ቅዱስ ቅዱሳን ነው።”

ካህናቶቹ የሃጢያቱን መስዋዕቱን ይበሉ ነበር። ይህም ቅድስተ ቅዱሳን መግባት

ያህል ነው። ይህም ካቀረበው ሰው ጋር አንድ ይሆኑና ራሳቸውን ከሰውየው ጋር “identify”

ያደርጉ ያመሳስሉ ዘንድም ነው። እንስሳው የሚወክለው ሃጢያተኛውን ሰው እንደ ሆነ

ካህናቶቹም የሚመሳሰሉት ከእርሱ ጋር ነው። ይህም ሃጢያቱን በመሸከም ወይም በብሉይ

አጠራር በመብላት ነው። በመጀመሪያ ከሰውየው እጅ ፈጽሞ ይወስደዋል። ሁለተኛ በልኩ

በእርሱ ፋንታ በመሆን ቅጣቱን ለእርሱ ይከፍልለታል።

ምልጃ 2016

22 www.tlcfan.org

የሃጢያት መስዋዕት ሰለ እኛ ሃጢያት የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን የሚወክል

ነበር። 2.ቆሮ.5፥2 የዕብራይስጡ ቃል ሃጢያትን (khataw) ሲለው የሃጢያት መስዋዕትን

ደግሞ (khatawth) ይለዋል። ሁለቱም አንድ አይነት ቃል ናቸው። ኢየሱስ ሃጢያት

አልሆነም። ነገር ግን የሃጢያት መስዋዕት ሆኗል። የቆሮንጦስ ትርጉም በዕብራይስጡ

መሰረት የሃጢያት መስዋዕት ሆነ ተብሎ ሊስተካከል ይገባዋል።

የሃጢያት መስዋዕት የሃጢያተኛውን ሃጢያት ይሸከማል። ይህም የሰውየውን

ቅጣት እንዲካፈል ነው። የሚሰዋው እንስሳ ራሱን የሚያመሳስለው ከሃጢያተኛው ሰው

ሃጢያት ጋር ነው። ይህም ሃጢያቱ በእንስሳው ላይ ልክ እንስሳው የሰውየውን ቦታ ሲወስድ

ሃጢያቱ ወደ መስዋዕቱ በግ ይተላለፍበታል። በመጀመሪያ እንስሳው በራሱ ንጹህ ነው።

ከዛም እንስሳው ሃጢያቱን እራሱ እንዳደረገ ሆኖ ለሃጢያተኛው ይከፍልለታል ወይም

በፋንታው ይሞርለታል።

ይህ ኢየሱስ ከሰራው ከመስቀሉ ሥራ ጋር አንድ ነው። ኢየሱስ ሃጢያታችንን፣

በደላችንን ተሸከመ። ሰለ እኛ የሃጢያት መስዋዕት ሆነ እንጂ በመጀመሪያ በሰማይም ሆነ

በምድር የተመሰከረለት ንጹ በግ ነበር። ራሱ ሃጢያቱን እንደ ሰራው ያህል የሁላችንን

ሃጢያት ተሸከመ። እኛም ልክ እንደ ካህናቱ የእርሱን የመስዋዕቱ ሥጋ የኢየሱስን ሥጋ

እንድን በላ በኢየሱስ በራሱ እንጋብዛለን። ይህ ሚስጥር ታላቅና በእግዚአብሔር ሕግ

መሰረት ልንመለከተው ይገባል። ዮሐ.6፥53-56 ይህም እኛም እንደ ካህናት የሌሎችን ሸክም

መሸከም እንድንችል የምልጃ ሕይወትን ብቃት ያገኘነው በዚሁ ምክንያት ነው። ስጋውን

ያልበላ ወይም ደሙን ያልጠጣ የምልጃ ሕይወት መለማለድ አይችልም።

“53 ስለዚህ ኢየሱስ እንዲህ አላቸው። እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ የሰውን

ልጅ ሥጋ ካልበላችሁ ደሙንም ካልጠጣችሁ በራሳችሁ ሕይወት የላችሁም።

54 ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ የዘላለም ሕይወት አለው፥ እኔም

በመጨረሻው ቀን አስነሣዋለሁ። 55 ሥጋዬ እውነተኛ መብል ደሜም እውነተኛ

መጠጥ ነውና። 56 ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ በእኔ ይኖራል እኔም

በእርሱ እኖራለሁ። 57 ሕያው አብ እንደ ላከኝ እኔም ከአብ የተነሣ ሕያው

እንደምሆን፥ እንዲሁ የሚበላኝ ደግሞ ከእኔ የተነሣ ሕያው ይሆናል።”

እየሱስ እየተናገረ ያለው መሰማት (መብላት) ና (መጠጣት) ማመንን/ማየት

ነው። ኢየሱስ ፍጥረታዊ ሥጋውን ወይም ደሙ ጠጡና ብሉኝ ማለቱ አልነበረም። ሥጋውን

መብላት ከሰማይ የመጣውን መና ከመብላት ጋር ተመሳስሏል። ዮሐ.6፥5-8

ምልጃ 2016

23 www.tlcfan.org

ይህም ድምጹን ሰምቶ መታዘዝን የሚያሳይ ነው። ደሙን መጠጣት ደግሞ

ሕይወትና ብርሃንን ማመንና እርሱን በማንነቱ መመልከትን የሚያመለክት ነው። በመጽሐፍ

ቅዱስ ውስጥ የሚማልዱ ሰዎች የሌሎችን ሃጢያት ሲሸከሙ እንመለከታለን። በመጀመሪያ

መሸከም ማለት የሚማልደው ሰው የሚማልድለትን ሰው ሃጢያት ዋጋ ይከፍላል ወይም

ፍርዱን በእርሱ ፋንታ ይቀበላል ማለት ነው። ይህ የሰዎችን እዳ ከፍሎ ሰዎች ነጻ እንደ

ማውጣት ወይም ሰለ ሌሎች ሲሉ የራስን ነገር መተውን የሚጠይቅ ሥራ ነው። በመጽሐፍ

ቅዱስ ላይ የምልጃን ትክክለኛ ልብ ከተረዳን ምልጃ ሰለ ሌላው ሰው ሥራ ራስን ተክቶ

ተጠያቂ ማድረግ መሆኑን በቀላሉ እንመለከታለን።

ሃጢያተኛ ሁል ጊዜ ለሰራው ሃጢያት ተጠያቂ ነው። ለምሳሌ ይህ ሰው ቅጣቱ

በጅራፍ መገረፍ ቢሆን ለዚህ ሰው የሚማልድ ሰው መጥቶ በእርሱ ፋንታ ለጅራፉ

ጀርባውን ይሰጣል ማለት ነው። ሌባ ሲሰርቅ በሰረቀው ላይ ሁለት እጥፍ ጨምሮ እንዲከፍል

እንደ እግዚአብሔር ሕግ ይደረጋል። ነገር ግን አንድ ሰው መጥቶ ለዚህ ሰው እዳውን

ቢከፍልለት ይህ ሰው ለእርሱ ማላጅና የተቤዥው ቤዛው ሆነ ማለት ነው። ይህም

የሃጢያተኛውን እዳ በመሸከም ያገኘው ስፍራ ነው።

ይህም የሆነ በትልቁ ካየነው ከኢየሱስ የመሰቀሉ ስራ የተነሳ ነው። በመስቀል

ላይ ኢየሱስ ሁሉን ይቅር ብሏል ምህረትን ለሰው ልጆች ስጥቷል። ነገር ግን ይህን ምሕረት

ሁሉ ገና አልተረዳውም። ማላጆች አሁን ራሳቸውን ከጌታቸው ጋር በማመሳሰል ወይም

ይህንን እውነተኛውን የእግዚአብሔር በግ ስጋና ደም በመብላትና መጠጣት ለሌሎች

ይማልዳሉ። ይህም በጌታ የተሰጣቸውን የማስታረቅን ክህነት ስራ በምልጃ ሕይወት

ይፈጽማሉ።

ቀደም ብለን ሕዝቅኤልን በምሳሌነት ተመልክተነዋል። ሕዝቅኤል የእስራኤልን

ቤትና የይሁዳን ሃጢያት ይሸከም ዘንድ ለ390 ቀን በግራ ጎኑ እንደ ገና ደግሞ ለ40ቀን

በቀኝ ጎኑ እንደ ተኛ አይተናል። ለምን ይህን ሁሉ ነገር ማድረግ ተገባው? ሕዝ.4፥4-6

አሁንም አወቅንም አላወቅንም በእኛ መካከል የምልጃ ሰዎች አሉ። የሌሎችን

ሃጢያት የሚሸከሙ ሌሎችን የሚበዡ የምልጃ ሰዎች ብዙ ናቸው። ይህ ምልጃቸው ግን

የኢየሱስ ሥራ ጎዶሎ የሚያደርግ ሳይሆን ወደ ሙላት የሚያመጣ ነው። እነዚህ ሰዎች ልክ

እንደተማሩት ሲያደርጉ በተለያየ ሥፍራና ሃገር እናያቸዋለን።

ምልጃ 2016

24 www.tlcfan.org

ለአንዳዶች ሲታዮ የሚማልዱ ሰዎች ለመመልከት ደም ግባት ያላቸው ሰዎች

አይደሉም። ከሚሸከሙት የተነሳ የተጎዱ የተጎሳቆሉም ናቸው። አንዳዴ ደግሞ በተገላቢጦሽ

እናገኛቸዋለን። ልክ እንደ ነብዮ ዳንኤል ሕይወት ማለት ነው። ይህ ግን ለሁል ጊዜ የሚሆን

አይደለም። በምልጃ ውስጥ ያለውን ክብር አንድ ቀን መልበሳቸው አይቀርም። ዮሐንስ

በአንደኛ መልዕክቱ 2፥6 ላይ እንዲህ ይለናል፦

“6 በእርሱ እኖራለሁ የሚል እርሱ እንደ

ተመላለሰ ራሱ ደግሞ ሊመላለስ ይገባዋል።”

“The one who says he abides in Him ought himself

so to walk in the same manner as He walked”

ደግሞም ነብዮ አብድዮ በቁጥር 21 ላይ እንደ ተነበየው አዳኞች “saviors”

(KJV) ወይም ነጻ አውጪዎች “deliverers” (NASB) ከጽዮን ተራራ (ዕብ.12፥22) ይነሳሉ።

የሚልን ትንቢት ይተነብያል። የኤሳው ተራራ ላይ ለመፍረድ የሚነሱ አዳኝና ነጻ

አውጪዎች አሉ። ይህ የኢየሱስ አዳኝነትና ነፃ አውጪነት መጋፋት ሳይሆን በእርሱ መልክ

የሚገለጡትን የእግዚአብሔር ልጆችን የድል ነሺ አማኝ ክርስቲያኖችን ባሕሪባ ስራ

የሚያመለክት ነው።

እኛ የእርሱ አካል ነን የእርሱም እቅድ እርሱ በእኛ ውስጥ መኖሩን እኛን

ማደሪያው ማድረጉ ነው። ይህም በእኛ የምልጃን የማዳንን የነጻ ማውጣትን ሥራ እንዲሰራ

ነው። ማንኛውም ይህን ሚስጥር የማያውቅ ሰው ገና የኢየሱስን ሥጋ አልበላም ደሙንም

ገና አልጠጣም። በምልጃ ባለ ሕብረት ጋር ከእርሱ ጋር ምንም አይነት ሕብረት የለውም።

የምልጃ ሕይወት ከመጀመሪያው ትንሳኤ ጋር የተያያዘ ነው። ይህን ስንል የማይማልዱ

ሰዎች የመጀመሪያውን ትንሳኤ አይቀበሉም እያልኩ አይደለም።

እርሱ የራሱን አላማ በሕይወታችን ይፈጽማል። እኛ ካህናት፣ የምንማልድ፣

አምንቤዥ፣ የምናድንና ነጻ የምናወጣ ልንሆን ይገባናል። ይህም የእግዚአብሔር ልጆች

ከመሆናችንና እርሱን በልተን ከመጠጣታችን የተነሳ ነው። ኢየሱስ ደግሞ ለሁሉ ዋነኛ

ምስሌያችን ነው። እርሱ በጠቅላለው ለሰው ልጆች ያደረገውን ሥራ እኛም በተጠራንበት

ትውልድ መካከል ለተጠራንለት ትውልድ እንደ ሕዝቅኤል፣ ኢሳያስ፣ ጳውሎስ ፍርድን

አቅልለን የመማለድን ሥራ አድርገን ልናልፍ ይገባናል። ነገር ግን እኛ የምናደርገው ይህ

የእርሱን የመሰለ አገልግሎት እርሱ በእኛ ከመሆኑ ከተሰጠንም ክህነት የተነሳ እንጂ በራሳችን

ምንም ልናደርግ አንደማንችል ልናውቅ ይገባል።

ምልጃ 2016

25 www.tlcfan.org

ደግሞም እኛ የምናገለግለው ይህ አገልግሎት ኢየሱስ ከሰራው ጋር ቢመዛዘን

በጣም ጥቂት ነው። እንግዲህ እግዚአብሔር የጠራን ለዚህ ለጥቂቱ ነገር ግን ታላቅ ዋጋን

ለሚያስከፍለው አገልግሎት ነው።

በብሉይ ኪዳን በነበረች ቤተክርሲያን ዘመን የነበሩ ካህናት የሰዎች በደል

መሸከም ሆነ የእነርሱ እዳ መክፈል ሃጢያተኛውን ነጻ ማውጣት የተለመደ ነገር ነው። ይህ

አሁን ደግሞ በአዲስ ኪዳን የቀረ ሳይሆን ከበፊቱ በተሻለ መንገድ ካህን እንደ መሆናችን

መጠን የተሰጠን የአማኞች አገልግሎታችን ነው። በብሉይ ኪዳን የሚቻል ከሆነ በአዲስ

ኪዳንም እዴት አብልጦ አይቻልም?

እኛ መንፈሱ ማደሪያው ያደረገን በመንፈስ የተሞላን ካህናትም እንዴት

ከአሮጌው ኪዳን አብልጠን ልናደርግ እንችላለን? እንግዲህ ከእግዚአብሔር ከቃሉ በመነሳት

ራሳችንን ማሳመን ይጠበቅብናል። ካህናት ነን ካልን ከካህንነት የሚጠበቅብንን ማንነትና

ስራ ከእግዚአብሔር ቃልና ሕግ ተምረን ስንናደርግና ስንኖር ልንገኝ ይገባል።

እርግጥ ነው በአሁን ዘመን ለብሉይ ኪዳን ያለን ሃሳብ ከታሪክ መጽሐፍ ያለፈ

ስላልሆነ የክህነታችን ምንነትና ሥልጣን ምን እንደ ሆነ በግልጽ መረዳት እንዳንችል

ለብዙዎቻችን ዳገት ሆኖብናል። እግዚአብሔር ግን ሕጉን መቼም ቢሆን ሊሽር

አይፈቅድም። ብሉይ ኪዳን አሁንም በተሻለ በአዲስ ኪዳን መንገድ ይሰራል ይፈጸማል

እንጂ ሕጉን አይሽርም። ሕጉ ሊፈታልንና ሊተረጎምልን ይገባል። ይህ ሲሆን በጌታ ካህናት

መሆናችንን ብቻ ሳይሆን በክህነት አግልግሎት ውስጥ በእግዚአብሔር የተሰጠንን ስፍራ፣

ብቃት፣ ስራና ሕይወት ምን እንደሆነ እንረዳለን እናውቃለን። ይህ ሲሆን ደግሞ በትክክል

እግዚአብሔር እንደሚወደው ስንኖር ራሳችንን እናገኛለን።

የብሉይ ኪዳኑ የካህናት ሕግ የአዲስ ኪዳኑም የካህናት ሕግ ያውን አንዱ ሕግ

ነው። ኪዳኑ እንጂ ሕጉ አልተለወጠም። ሕጉ በሥራ የሚተረጎመው እንደ ብሉይ ኪዳን

ሳይሆን በበለጠ በከበረና ስርዓት ባለው በመንፈሳዊ መልኩ ነው። ብሉይ ኪዳን የምልጃ

መሰረታዊ እውነቶችን የምናገኝበት ከእግዚአብሔር የተሰጠን ቅዱስ እስትንፋሳችን ነው።

ይህ መጽሐፌ ብሉይ ኪዳንን ለማጥናት ያነቃቃችኃል ብዮ አምናለሁ።

ሰው የሌላውን መተላለፍ፣ በደል ወይም ሃጢያት ሲሸከም የሚሸከምባቸው ስድስት

ወሳይ የሆኑ ደረጃ አሉ። እነዚህ ደረጃዎች በኢየሱስና በሌሎች ጻድቃን በመጽሐፍ ቅዱስ

ውስጥ ተጠቅሰው በሚገኙ ማላጆች ሕይወት ውስጥ ግልጽ ተደርጎ ተቀምጦ እናገኘዋለን።

ምልጃ 2016

26 www.tlcfan.org

የሌላውን ሸክም የመሸከም ሕይወት

የእግዚአብሔርን ቃል እርስ በእርሳችን እንድንሸካከም፣ እርስ በርሳችን

እንድንዋደድ፣ እርስ በእርሳችን እንድናዘዝ፣ እርስ በእርሳችን ይቅር እንድንባባል፣ ይቅር

የምንላቸው ይቅር እንደሚባልላቸው፣ የምንይዝባቸው እንደሚያዝባቸው፣ የሚቀበሉን

እርሱን እንደሚቀበሉት . . . ወዘተ ይህንና ይህን የሚመሳስሉ ቃሎችን በእግዚአብሔር

ቃል ውስጥ እናገኛለን። እነዚህን አምነን የምኖርና ስናደርጋቸው የምንገኝ ጥቂቶች ነን።

አደራረጉን ካላወቅን እንዴት ማድረግ እንችላለን? እንዴት? ለምን? ማን? የሚሉትን

ጥያቄዎች በልባችን በማጠንጠን እነዚህን ቃሎች ልናጠናቸው ይገባል።

ማላጂዎች የሌላውን ሰው ሸክም እንደ ካህና እንደ አማላጅ ሲሸከሙ

የሚሸከሙት ሰዎች የሚያልፉባቸው ሕይወቶችና መንግዶች አሉ እነዚህን ከዚህ መቀጠል

በዝርዝር እንመልከታለን።

1ኛው ደረጃ ሥም አልባነት ሕይወት፦

በራሱ ምንም ነገር የሌለበት ንፁ ሰው ሰለ ሌላው እዳን ለመክፈል ሲል ቢሰቃይ

ወይም ቢጎዳ የእርሱ ሥም፣ ባሕሪ፣ አቋም በሰዎች ዘንድ ከፍ ያለን ስፍራና ሥምን ይህ

ሰው ያገኛል። ይሁንና የእግዚአብሔር ማላጂዎች ከሰው ምንም አይነት የሥራቸውን ዋጋ፣

ክብርና ሥም ለመቀበል አልተጠሩም። ለዚህም ነው ብዙዎቹ የእግዚአብሔር ባሪያዎች

በድሮ ዘመን በድንጋይ ተወግረው የሞቱት። ማቴ.23፥29-31 በዚህ በምልጃ ዘመናችን

ከሰዎች የሥራችንን ውጤት ከጠበቅን በእውነት ከእግዚአብሔር ደሞዝ ዋጋ ጎድለናል

ማለት ነው። ማቴ.6፥16

ኢየሱስ ስለ ጾም የተናገረውን መርህ ለሁሉ መልካም ለሆነ መንፈሳዊ ሥራ ሁሉ

የሚሰራ መርህ ነው። ደሞዛችንን ለመምረጥ ፍቃድ ተሰጥቶናል። የሰውን ደሞዝ ወይም

የእግዚአብሔርን ደሞዝ መቀበል መምረጥ እንችላለን። የእግዚአብሔር ደሞዝ በስውር

በሆነው በእግዚአብሔር ባንክ ውስጥ የሚቀመጥ በኃላም ለሰራተኛው የሚሰጥ የሚመነዘር

ነው። የሰው ደግሞ የሚታይና ጊዜያዊ የሆነ ነው። ማቴ.6፥17,18

“17-18 አንተ ግን ስትጦም፥ በስውር ላለው አባትህ እንጂ እንደ ጦመኛ ለሰዎች እንዳትታይ

ራስህን ተቀባ ፊትህንም ታጠብ፤ በስውር የሚያይ አባትህም በግልጥ ይከፍልሃል። 19 ብልና

ዝገት በሚያጠፉት ሌቦችም ቆፍረው በሚሠርቁት ዘንድ ለእናንተ በምድር ላይ መዝገብ

አትሰብስቡ፤ 20 ነገር ግን ብልም ዝገትም በማያጠፉት ሌቦችም

ምልጃ 2016

27 www.tlcfan.org

ቆፍረው በማይሠርቁት ዘንድ ለእናንተ በሰማይ መዝገብ ሰብስቡ፤ 21 መዝገብህ ባለበት

ልብህ ደግሞ በዚያ ይሆናልና።”

“your Father who is in secret; and your Father who

sees in secret will repay you.”

አንድ ሰው በትውልድ መካከል ለምልጃ ሲጠራ በሰዎች መካከል ሁል ጊዜ

እርሱ የተሳሰተ ሃጢያተኛና በደለኛ ሆኖ ይቆጠራል ይታያል። ነገር ግን በማየት ሳይሆን

እግዚአብሔርን በመስማት የሚፈርዱ ሰዎች ግን ማላጆችን በምልጃ ዘመናቸው ወቅት

የሚወዷቸው፣ የሚያግዟቸውና የሚረዷችው እነርሱ ናቸው። ኢሳያስ. 53፥3 እንደ ሚናገር

“3.የተናቀ ከሰውም የተጠላ፥ የሕማም ሰው ደዌንም የሚያውቅ ነው። ሰውም ፊቱን

እንደሚሰውርበት የተናቀ ነው። እኛም አላከበርነውም።” ይላል

Isaiah 53:3 “He was despised and forsaken of men.”

Phil. 2:7 says, “emptied Himself”

ጳውሎስ ደግሞ በፊሊ.2፥7 ላይ ራሱን ባዶ አደረገ ብሎ ስለ ኢየሱስ ባሕሪ

ይነግረናል። ክብሩን ጥሎ የባሪያን መልክ እንደ ወሰደ ያስረዳናል። በዕብራውያን ላይ

ደግሞ ሁሉን በመስቀል እንደ ቻለ ያሰቀምጥልናል።

Heb. 12:2 “endured the cross, despising the shame.”

ይህን ሁሉ ሲያደርግ ሁሉን እንዳጣ እንደ ተቀማ ሰው ራሱን አልቆጠረም።

ማንም የኢየሱስ ክርስቶስን የምልጃ ሕይወት እከተላለሁ የምልጃ ጸሎት ጸላይ ነኝ ቢል

ከሰዎች ዘንድ ይህን ሊቀበልና አገልግሎቱ ይህን እንደሚመስል አስቀድሞ ሊያውቅ

ይገባዋል። ምልጃ ከምንገምተው በላይ ጥልቅ የሆነ የእግዚአብሔርን መርህ የያዘ መልኮታዊ

ስርዓት ያለው ጸሎት ነው።

ማንም የክርስቶስን የእግር ፍለጋ እንደ አማላጅነት ሊማልድ እከተላለሁ ቢል

ከማንም ሰው የሚያገኘውን ማንኛውንም ነገር ሊያቆም ሥሙን ክብሩን ሊያጣ የግድ ነው።

ይህ መከራ ከውጭ ካሉት ብቻ የምንጠብቀው ሳይሆን በውስጥም ከሚገኙት ክርስቲያን

ወንድሞችና እህቶችም ጭምር ነው። ምክንያቱም በቤተክርሲያን ያሉ ክርስቲያኖች በማየት

አለ መፈረድ ምን እንደ ሆነ የተማሩ ገና ጥቂቶች ናቸውና ነው። ይህ በሕይወት ዘመናችን

ሁሉ ልንማረው ልናስተውለው የሚገባን ትምህርት ነው።

ምልጃ 2016

28 www.tlcfan.org

በጥቅሉ ለመናገር አንድ ሰው ሰለሚማልደው ሰው ለማወቅ የግድ ሰማያዊ

መገለጥ ያስፈልገዋል ማለት ነው። የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል በማወቅ ማላጁን ሰው እረዳዋለሁ

አውቃለሁ ማለት ከንቱ ነው። ቃል በትክክል ባለመተርጎሙና እውነትን ሳያውቁ ቃል

እናውቃለን የሚሉ ኢየሱስ ላይ ፈርደውበታል፣ ሰቅለውታል። እኛንስ? ቃል ከጀርባው

ሴጣን ቆሞ ሃሳቡን ሊያገለግልበት ሲሞክር በኢየሱስ የምድረ በዳ ፈተና አልታየምን? ከቃሉ

ጀርባ የቆመውን መንፈስ መለየት ይጠበቅብናል። ነገር ግን ይህ ያለ እግዚአብሔር መንፈስ

የሚቻል ነገር አይደለም።

ዋናው ቁም ነገሩ ደም ግባት አለው የለውም የተናቀ የተከበረ ለማለት

አይደለም። ነገር ግን ማላጁ የተሸከመውን ሃላፊለትና ሥራ ለማስተዋል የሚያበቃው

በመንፈስ መረዳት ስንችል ነው። ሃጢያተኞች ጻድቃንን ሊያመሰግኑ ሊያከብሩ ይችላሉ።

ነገር ግን ጻድቃን ለመክበር ወይም ራሳቸውን ከፍ ከፍ ለማድረግ ሳይሆን ስለ ሃጢያተኞች

ሊናቁ ተጠርተዋል። ሃጢያተኛ ጻድቃንን አይቶ ሁለት ነገር ይላል ወይም ያስባል።

(1) ምናለ እንደ እርሱ ብሆን ኖሮ ወይም (2) እንደ እርሱ መልካም ልሆን

አልችልም የሚል ሃሳብ ነው። ምክንያቱም በዚህ መጥፎ ዓለም የምኖር ደካማ ሃጢያተኛ

ሰው ነኝ ይላል። የሚማልዱ ማላጆች የእኛ ድካምና ውድቀት ሊሸከሙት የሚታያቸው

ሰዎችን እንጂ ይህቺ ዓለም የምትፈልገው ንፁህ መስለው የሚታዮ በውጫዊ ልብስ

ውስጣቸውን የሸፈሩ የዘመኑ ፈሪሳዊ የሚመጻደቁ ጻድቃኖችን አይደሉም።

ሰዎች ለምን ይመስላችኃል ቤቱ ካሉት ይልቅ ከውጭ ከሃጢያተኝነት ሕይወት

እንደ ጳውሎድ የተቀየረውን ወይም የተመለሰውን ሰው ሲመሰክር መስማት የሚፈልጉት?

ተራ ሰውን መዳን የማይገባው ሰው እንዴት እግዚአብሔርን እንዳገኘ ማወቅ ሰለ ሚፈልጉ

ነው። ምክንያቱም ይህን ሰው እግዚአብሔር ይህን ያደረገውን ሰው ከማረው እኔንም

ይምረኛል የሚል ተስፋ በውስጣቸው ስለሚያድርባቸው ነው። ይህ ፍላጎታቸው ምንም

የከፋ ባይሆንም እነርሱ ያሉበትን እውቀት ዝቅተኛ ስፍራም ያሳያል። ይህም የእግዚአብሔር

ፍቅርና ምሕረት ጥልቀት ካለማወቅ የሚመጣ ነው።

አንድ ሰው የሚማልድ አማኝ ለመሆን ሄዶ ሃጢያት መስራት ይገባዋል እያልኩ

አይደለም። ወደ ፍጽምና ያልመጣ ማንኛውም አማኝ ሃጢያትን ሊያደርግ ይችላል። ነገር

ግን እግዚአብሔር ለምልጃ ሕይወት የዓለምን ደካም የሆነውን ሰውን ይመርጣል። ሕይወቱን

እግዚአብሔር ይለውጠውና የሌሎችን ለመለወጥ ይጠቀምበታል።

ምልጃ 2016

29 www.tlcfan.org

ይህ ደካማውን ሰው ይጠቀመዋል ስንል ግን ሃጢያተኛ መሆን አለበት ማለት

አይደለም። ማንኛውም ሰው ይህን የምልጃ መርህና ውጤቶች ለመቀበቅ የክርስቶስን ምልጃ

ለማገልገል የወደደ ሁሉ መማለድ ለሌሎች መማለድ ይችላል።

ኢየሱስ በራሱ ምንም ችግር የለበትም ነገር ግን ከሃጢያት በስተቀር በሁሉ

የተፈተነ ነው። ይህም ፈተናው መልካም የሆነና እግዚአብሔርን የሚታዘዝ ማላጅ አድርጎ

ቀረጸው። እርሱ ንጹህ ሆኖ ሳለ ግን ሥሙ ምን እውቅና በዘመኑ አላገኘም ነበር።

ከቤተመንግስት ይልቅ በግርግም ተወለደ፣ የካህን ልጅ ሆኖ ከማደግ ይልቅ የአናጢ ልጅ

ሆኖ አደገ። በመጨረሻም ሞት የተገባው ሰው ውሸተኛ የስህተት ስው ሆኖ ተቆጠረ ይህም

እስከ ሞት አበቃው። ለምልጃ የተጠራ ሁሉ ይህን የኢየሱስን የምልጃ ሕይወትንና ኑሮን

አገልግሎቱን ሊቀበልና እንዴትም እንደ ነበር ሊያውቅ ይገባል።

እንግዲ የምልጃን ሕይወት የሚወድ ሁሉ የሰውን ደሞዝ ይራቅ። የከበሬታን

ሥፍራ የሙጥኝ ከማለት ለደሃ አደጉና ለሃጢያተኛው ትክክለኛ ማላጅ በመሆን

የሚመጣበትን መከራ በደስታ ይቀበል እንጂ ከማን የማሞገሻ ስም አይቀበል። ይልቁኑ

በሕዝቡ መካከል ስም አልባ “የሹ” ይባል። በዮሐንስ.2፥24-25 ላይ ኢየሱስ ስለ ሰው

እንዲነግረው ሌላ ሰው አላስፈለገውም ነበር ይላል። ምክንያቱም በሰው ውስጥ ያለውን ራሱ

ያውቅ ነበርና ነው።

John 2:24, “He Himself knew what was in man.”

ኢየሱስ በመካከላቸው በአባቱ ተመርቶ ሰላደረገው ተዓምር ምልክት ከሰው

ደሞዝን ሆነ ሙገሳን አይፈልግ ነበር። ይልቁኑ ተዓምሩን የተቀበለውን ሰው ለማንም

እንዳይነግሩ ያዛቸው ነበር። ምክንያቱም የሚያስፈልጋቸው ከተዓምርና ከፈውስ ያለፈ ነገር

እንደ ሆነ ያውቅ ሰለ ነበር ነው። ከሁሉ አሰቀድሞ እግዚአብሔርን እንዲያውቁ ይፈልጋል።

እኛም እንዲህ ያለውን አገልግሎት በመረዳት ወደዚህ አይነቱ የጌታ ልብና አግልግሎት

ለማምጣት መትጋት ይጠበቅብናል። በዚህ ዘመን ተዓምርንና ምልክትን ስንፈልግ ራሳችንን

በውሽት ጠላልፈን እንኳን ልንማልድ ለእኛ የሚማልድልን እያስፈለገን ያለንበት ዘመን

ይህ አሁን ያለንበት ዘመን ነው።

በዓለምም ሆነ በእግዚአብሔር ቤት ያሉ ሰዎች የሚሰጡንን ምስጋናና አድናቆት

ሆነ ጥላቻና ክፋት በእኛ ላይ ምንም ነገር ወደ ማያመጣበት የእድገት ደረጃ ካልመጣን ገና

ሕጻናቶች ነን። ይህን የምናደርግ ከሆንን በሰው ፊት ለሰዎች የልባችንን ጣዖት እንጂ

የምናገለግለው እግዚአብሔርን እንዳልሆነ እንድናውቅ ወዳለሁ።

ምልጃ 2016

30 www.tlcfan.org

ራሳችንን ምንም ሃጢያት እንዳልሰራን ሰርቶም እንደማያውቅ ብንኮፍስና

ሌላውን በቃል በጥቅስ እያነሳን ብንኮንን ብንሰብር የቱ ላይ ነው ማላጆች የሆንነው? እንደ

ኢዮብ ዛሬ የምልጃ ነገር ሲገባን የማናውቀውን ነገር እንደ ተናገርን አውቀን በጊዜው

አፋችን ላይ እጃችንን ልንጭን ይገባል። እግዚአብሔር ለምልጃ ጠርቶኛል የሚል ሁሉ

የእግዚአብሔር ሕግ በሕይወቱ ሊማር ይገባዋል። ይህም ፍቅር፣ ምሕረትና ከእኔ በቀር ሌላ

አምላክ ላንተ አይሁን የሚለው ነው።

“Thou shalt have no other gods before Me.”

ገንዘብ፣ ክብር፣ ሙገሳ፣ የተሻለ ኑሮ፣ ውሸት፣ ዝሙትና ሰካራምነት….ወዘተ

እንደ አምላክ የሆኑልን ስንቶቻችን እንደ ሆንን እግዚአብሔር ያውቃል። ዛሬ በልባን ያለው

ጣኦት ምንድን ነው?

ምልጃ 2016

31 www.tlcfan.org

2ኛው ደረጃ፦ በእምነት መታዘዝ

ጳውሎስ በሮሜ.10፥17 እምነት ከመስማት እንደ ሆነ መስማትም በእግዚአብሔር

ቃል ውስጥ እንደ ሆነ ይናገራል። እኛ ቃሉን በተለያየ መንገድ እንሰማለን። አንድ አንዴ

ተነስተን ቃሉን ስናነብ በልባችን ውስጥ ለብዙ ጊዜ ጥያቄ የሆነብን ነገር መልስ ሲያገኝ

እናያለን። አንድ አንዴ ደግሞ ሰባኪው ምንም እንኳን እንደ ሆነ የተናገረውን ሳያውቅ

ሲናገር የተናገረው ቃል የአንድን ሰው ቤት ሊያፈርስ ሲደርስ ሰውን ከሰውና ከእግዚአብሔር

ጋር ሲያጣላ ይገኛል። በጸሎትና ራሳችን በተለያየ መልኩ በእግዚአብሔር ፊት

በምናደርግበት ወቅት እግዚአብሔር በብዙ መልኩ ይናገረናል። 2.ነገ.19፥12 በውስጣችን

የምንሰማው ይህ ድምፅ ልክ እንደ ሃሳብ ወደ ልብ የመፍሰስ ባሕሪ ያለው ነው።

አንዳንድ ሰዎች እግዚአብሔርን ድምፅ ልክ ከሰው እንደ ምንሰማው አይነት

ድምፅ እንደ ሰሙ ይናገራሉ። በአዲስ ኪዳን የእግዚአብሔር ድምፅ በዚህ መልኩ የሰሙት

ሰዎች አሉ። ነገር ግን አብረዋቸው የነበሩ ሰዎች ከነጎድጓድ በቀር ምንም ነገር አልሰሙም

ነበር። በውጭ የሚሰማ ድምጽ በኢየሱስ ሕይወትም ቢሆን ብዙ አንመልከትም። ነገር ግን

እግዚአብሔር በውጭም በውስጥም ይናገራል። ብዙውን ጊዜ በጸጥታ ውስጥ ስንሆን

በመንፈሳችን የእግዚአብሔር ድምፅ ይመጣል። መንፈሳዊ የውስጥ ጆሯችን ከተከፈተ

ድምፁ እንሰማለን። እግዚአብሔር ይናገር እንጂ የማይሰማ አይኖርም።

ይህ እንደዚህ እንዳለ ዋናው ቁም ነገሩ እርሱ ይናገረናል እኛ ደግሞ ድምፁን

ሰምተን እንታዘዛለን ወይ ነው። ሕዝበ እስራኤል ከድምፁ ራቁ ይህም እንሞታለን ብለው

ሰለ ፈሩ ነው። ዘጸ.20፥19 ሰለ ድምፁ ስናወራ ሁል ጊዜ ሥጋዊ አዕምሯችን ችግር ውስጥ

ይወድቃል። ይህም ሥጋዊ አዕምሮ ሞትን ከምንም ነገር በላይ ይፈራልና ነው።

የእግዚአብሔርን ድምፅ ስንሰማ ሥጋዊ አዕምሯችን መሞት ይጀምራል። ይህን አይነት

ሞት የምንፈራ ከሆንን ለእግዚአብሔር ማላጆች ለመሆን ያዳግተናል።

ሕዝቅኤል ከላይ እንዳየነው ለዚህ ምሳሌያችን ነው። እግዚአብሔር በፋንድያ

የተጋግረ ዳቦ እንዲበላ አድርጎታል። ሕዝቅኤልም እግዚአብሔር ያዘዘውን በመፈጸም

ለእግዚአብሔር ታዟል። በዚያን ዘመን የነበሩ ካህናት ሕዝቅኤል ሃጢያትን እያደረገ እንደ

ሆነ ራሳቸውን አሳምነዋል። እርሱንም እደ ሃጢያተኛ ቆጥረው አግልለውታል። ይህም

የእግዚአብሔር ድምፅ ስለሰማና ስለታዘዘ ነው። የእግዚአብሔር ድምፅ ሰምተው የሚታዘዙ

በሃይማኖተኞችና እኛ ብቻ አዋቂነን በሚሉ ሰዎች መገፋትና መነቀፋቸው አይቀርም።

ምልጃ 2016

32 www.tlcfan.org

ሕዝቅኤል እግዚአብሔርን ከመስማቱ የተነሳ ያ የእግዚአብሔር ነብይ እየተባለ

የሚጠራበት የክብር ሥም አበቃለት በክብር ፋንታ ውርደትን ተቀበለ። ከዚህ በኃላ በእምነት

እንጂ በሰው ድጋፍም ሆነ በራሱ መረዳት ሊደገፍ የማይችልበት ቦታ ላይ በእግዚአብሔር

መንፈስ ተስቦ መጣ። በእርግጥ እግዚአብሔር ለካህናቱ እንዲህ አድርጉ ብሎ

አይናገራቸውም። ምክንያቱም አያዳቸውም እግዚአብሔር ሊሰሙት ሆነ ክብራቸውን

ሊጥሉለት አይፈልጉምና ነው። ዛሬም እንዲሁ ነው እግዚአብሔር ወይ ክብርህን ወይስ

ክብሬን? በማለት በዚህ ዘመን ያሉትንም አገልጋዮች ያስመርጣል።

እነርሱ እግዚአብሔርን በእምነት ከመታዘዝ ይልቅ ሕዝቡንና እነርሱን ደስ

የሚያሰኛቸውን ማድረግ ይወዳሉ። በፈለጉ ቀን መንፈሳዊ ድግስን ያዘጋጃሉ ለጆሯቸው

የሚመቹትን ሰዎችና ባልጀሮች ለሕዝቡ በፋንድያ የተጋገረ ቂጣ ለማቅረብ ይጋብዛሉ።

እነርሱ ክብራቸውንና ስማቸውን ሰለ ወደዱ በልባቸው ጣዖታቸውን ስለ ያዙ ሊማልዱ

ራሳቸውን ለእግዚአብሔር አላዘጋጁም።

እነርሱ ሕዝቡን ማገልገል የሚችሉት የሚመስላቸው በእነርሱና በሕዝቡ

መካከል ርቀት ካለ ነው። በሕዝቡ መካከል የአገልግሎት ልብሳቸውን ለብሰው በኩራት

በመጎራደድ ደሃውን ከግሩፓቸው አርቀው ፊት በመንሳት ሞገስ የሚያገኙ ይመስላቸዋል።

በእጃቸው መልካም ነገር ከማድረግ ይልቅ የቅዱሳንን ደም የሚያፈሱ ከሥራቸው ይልቅ

ምላሳቸው የረዘመ በልባቸው ጣኦትን የያዙ ካህናት ናቸው። በመጣው የእግዚአብሔር

ቃልና ትንቢት ላይ አቃቂር በማውጣት ደግሞ ቀዳሚውን ስፍራ ይይዛሉ። እንደዚህ አይነት

ካህናት ከመሆን እግዚአብሔር ይጠብቀን። የቆምንም እንዳንወድቅ እንጠንቀቅ።

ምልጃ ግን በድምጽ መርዘም፣ በድምፅ ማወፈር ወይም ማቅጠን የሚገኝ

ሕይወት አይደለም። ካህናቱ ከሕዝቡ ራሳቸውን ማራቃቸው የአላማቸው ምንም አይነት

ድካማቸው ለሕዝቡ እንዳይታወቅ ለማድረግና ደግሞም ጥሩ ሥምና የሃይማኖታዊ መልክ

ለራሳቸው ለመስጠት ነው። ሕዝቡን ሲያስተምሩ ሆነ ሲያናግሩ ድምጻቸውን ያወፍርሉ።

እርምጃቸውን ይቀይራሉ። በጥቅሉ ከእነርሱ በቀር እግዚአብሔርንና ቃሉን ማንም

እንደማያውቅ አድርገው ራሳቸውን ይኮፍሳሉ፣ ይቆጥራሉ። ካልታመሙ ወይም ካልሞቱ

በቀር ሥፍራቸውን ማንም እንዳይነካባቸው አጥብቀው በሕይወታቸው ሙሉ ዙሪያቸውን

በወዳጆቻቸው ከበው ይጠብቃሉ። በራሳቸውን ጥበብ ስፍራቸውን ይዘዋልና እንደ ሕዝቅኤል

አይነቱ ብቅ አለ ማለት ያኔ ለካህናት ድንጋይ የመሰብሰቢያ ጊዜ እንጂ እንዴትን ንስሃ

ሊገቡ ይችላሉ።

ምልጃ 2016

33 www.tlcfan.org

ይህ ሁሉ ባሕሪያቸው የሚያሳየው እግዚአብሔርን ሳይሆን ራሳቸውንና

ሰዎችን የሚያገለግሉ መሆናቸውን ነው። አገልግሎታቸው በእግዚአብሔር ሳይሆን

በራሳቸው የተጠበቀ ለእግዚአብሔር ድምጽና ለሕዝቡ ለመማለድ ብቁ ያልሆኑ መሆናቸውን

በዘመናቸው የሰሩት ሥራ ሁሉ ማንነታቸውን የሚያንጸባርቅ ነው።

ሕዝቅኤል ግን እግዚአብሔር ያዘዘውን በእምነት ታዘዘ ስለ ሥሙ ሆነ ሰዎች

ምን ይሉኝ ይሆን ብሎ አልተጨነቀም። ስለዚህ ሕዝቅኤል ለ390 ቀን ሰዎችም ሆኑ ካህናት

ለሚሰነዝሩበት ቃል ፈጽሞ ፍንክች አላለም። አምላኩን በእምነት እየታዘዘ ራሱን

ለማላገጫነት ሰጠ። ቃሉን የሰሙ ሁሉ ከካህናት ወገን ሆነው በሕዝቅኤል ላይ ቃላቸውን

ድንጋያቸውን አነሱ። ሕዝቅኤል እንደ ሃጢያተኛ ከተቆጠረ በኃላ እንዴት በመቅደስ

ሊያገለግል ይችላል? ራሱንስ ዝቅ ካደረገ በኃላ እንዴት ብሎ ከፍ ሊል ይችላል? ብለን

ልናስብ እንችላለን። እውነት ከእግዚአብሔር ስምቶ ከሆነ ለሰው የማይቻል ነገር ሁሉ

ለእግዚአብሔር ይቻላል። የእግዚአብሔር ጥበብ ከሰው እውቀትም ሆነ መረዳት ፈጽሞ

የራቀ ነው።

እግዚአብሔር የዓለምን ሞኝ የተናቀ ነገር ለሥራው በመጠቀም በዚያ ሰው

ክብሩን ሁሉ እርሱ ብቻ ይወስዳል። 1.ቆሮ.1፥27 ጳውሎስ የዚህ ዓለም ጥበብ ብሎ

የሚጠራው የሰዎችን አዕምሮ ያጨልማል። ጥቂት ሰዎች ብቻ የምልጃ ሕይወት ውስጥ

የገቡ ሰዎች ምን እይነት እንደ ሆኑ ይረዳሉ።

የሚማልዱ ሰዎች የእምነት ኑሮ ስለ ሚኖሩ ብዙ ሰዎች ያሉበትን ሁኔታ ምን

እንደ ሆነ አይረዱትም። አንድ አንዴ ማላጁ ራሱ የሚያልፍበት ሕይወት አያውቀውም።

ሰለዚህም ካህናቱም ሆነ ሕዝቡ በራሳቸው የመሰላቸውን ሥምና ማንነት ይሰጧቸዋል።

የሕዝቅኤል የምልጃ አላማ እግዚአብሔርን ለሚስሙ ሁሉ ግልጽ ነው። እርሱ

ራሱን ያመሳሰለው ከእስራኤል ፋንድያን የሰውን ሃሳብ ከንጹሕ ከሆነው ከእግዚአብሔር ቃል

ጋር ቀላቅለው ስለ በሉ ሰዎች ነው። ይህ የሰው ወግና ዶክትሪን ሕዝብን መመገብ ኢየሱስ

በምድር በነበረበት ወቅት የነበሩ መሪዎች፣ ካህናትና የፈሪሳውያንም ችግር ነበር። ማር.7፥

9-13

“8 የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ትታችሁ ጽዋን ማድጋንም እንደ ማጠብ የሰውን ወግ

ትጠብቃላችሁ፥ ይህንም የመሰለ ብዙ ሌላ ነገር ታደርጋላችሁ። 9 እንዲህም አላቸው።

ወጋችሁን ትጠብቁ ዘንድ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ እጅግ ንቃችኋል።

ምልጃ 2016

34 www.tlcfan.org

10 ሙሴ። አባትህንና እናትህን አክብር፤ ደግሞ። አባቱን ወይም እናቱን የሰደበ ፈጽሞ

ይሙት ብሎአልና። 11 እናንተ ግን ትላላችሁ። ሰው አባቱን ወይም እናቱን። ከእኔ

የምትጠቀምበት ነገር ሁሉ ቍርባን ማለት መባ ነው ቢል፥ 12 ለአባቱና ለእናቱ ምንም

እንኳ ሊያደርግ ወደ ፊት አትፈቅዱለትም፤ 13 ባስተላለፋችሁትም ወግ የእግዚአብሔርን

ቃል ትሽራላችሁ፤ እንደዚሁም ይህን የሚመስል ብዙ ነገር ታደርጋላችሁ። 14 ደግሞም

ሕዝቡን ጠርቶ። ሁላችሁ እኔን ስሙ አስተውሉም።”

ፈሪሳውያን እንዳደረጉ ሁሉ የምናደርግ በዚህ ዘመን ያለን ሰዎች ከእነርሱ

የተለየን አይደለንምን? ፈሪሳውያን፣ ሰዱቃዊያንና ጻፎች ልክ በዚህ ዘመን እንዳሉ ብዙ

ሰዎች ቃሉን በራሳቸው ሃሳብ ይተረጉሙትና እንደሚመቻቸው አድርገው ይሰብኩ ነበር።

በራሳቸው ሃሳብ ቃሉን ከበሉና ካብላሉ በኃላ ለሕዝቡ የተረፋቸውን ለእነርሱ በሕዝቡ

መካከል በስልጣን መቆም የሚያስችላቸውን ይመግቡት ነበር። ዛሬም የእግዚአብሔር ቃል

በመንፈስ መገለጥ ወደ እኛ ካልመጣ በቀር እኛም ብንሆን ቃሉን የምናገለግለው በአዕምሮ

በሰዋዊ ሃሳብ ይሆናል። በሕቅኤልም ዘመን ካህናቶቹ ለእነርሱ የሚመቻቸውን ቃል ከበሉ

በኃላ ፋንድያውን ለሕዝቡ ይሰጡት ነበር። እኛም ከእግዚአብሔር ድምጽና ከዘመኑ ትንቢት

ከራቅን ከእነርሱ የማይለይ ውድቀት ውስጥ ራሳችንን እናገኛለን።

ቃሉን ከእግዚአብሔር መሰማት የእምነት ምንጭ ነው። ነገር ግን የሰውን ሃሳብ

ወይም በሰው ሃሳብና አዕምሮ የተተረጎመን ቃል መስማት እምነትን ስለማያመጣ የሰውል

ቃልና የአሮጊቶችን ተረት መስማት ልናቆም ይገባል። ይህም ቃሉን በምናነብ ጊዜ ቃሉ

በቃሉ ብቻ እንዲፈታና እንዲተረጎምልን ለመንፈስ ቅዱስ በመፍቀድ ነው። በውስጡ

ያለውን መንፈስ ለማግኘት ከቃሉ ጀርባ ያለውንም መንፈስ መመዘንና መለየት

ይኖርብናል። ይህ ደግሞ የአንድ ሰው የግል ውሳኔ ነው እንጂ ሰውን በመስማት የሚመጣ

አይደለም። እምነት የሚያመጣን የእውነት ቃል መንፈስ ለመስማት መምረጥ ሁል ጊዜ

የግል ውሳኔያችን ነው።

እውነተኛ የምልጃ ሰው ለመሆን እምነት ያስፈልገናል። እምነት ደግሞ በጸሎት

የሚመጣ ነገር ሳይሆን የእግዚአብሔር ቃል በመስማት የሚመጣ ነው። ቃሉን ስንሰማ

እምነት ይፈጠራል። ደጋግመን ስንሰማ ደግሞ እምነታችን በተለያየ መልኩ ያድጋል፣

ይጠነክራል። በሕይወታችን እርምጃ ላይ ስናውለው ደግም በእግዚአብሔር ያለ

መታመናችን ይጨምራል። የእምነታችን ውጤቶችን በእኛና በሌሎች ላይ ማየት

እንጀምራለን። ይህ እግዚአብሔር ከማስደሰቱም በላይ ለአገልግሎቱ ብቁ የሚያደርግን

አቋም በላያችን ላይ ያመጣል።

ምልጃ 2016

35 www.tlcfan.org

3ኛው ደረጃ፦ የሰዎችን ሃጢያት በማላጁ ላይ ማሸከም

በሮሜ ምዕራፍ ሁለት ላይ ጳውሎስ ሕዝቅኤል.36፥20 ና 23 ላይ የተናገረውን

የሃይማኖት መሪዎችን ችግር ደግሞ ሲጠቅሰው እንመለከታለን። ይህም የእግዚአብሔርን

ሥም ከኑሮውቸውና ከሚሰሩት ስራ የተነሳ የሚያሰድቡት ጻድቃን የሚወቅስበት ነው።

ሮሜ.2፥24,

24 For the name of God is blasphemed among the Gentiles [ethnos, “nations”] because of

you, just as it is written.”

ይሁንና ፈሪሳውያን በዚያን ዘመን የነበሩ ካህናት ኢየሱስ የሚማልድ መሆኑን

ስላልተረዱ፣ ትምህርቱና ስብከቱ ስህተት እንደ ሆነ ስለ ገመቱ፣ እስከ መስቀል ሞት ድረስ

አድርሰውታል። ምንም እንኳን እነርሱ ለክፋት ቢያደርጉትም እግዚአብሔር በቀደመ

እውቀቱ፣ እቅዱስና ፍቃዱ ሁሉን ለበጎ ለውጦ እቅዱን ፈጽሞበታ። ማር.14፥64

ይህ ኢየሱስ የሌሎችን በደል የሚሸከምበት የሚማልድበት መንገድን እንደከፈተ

ያሳያል። በብሉይ ኪዳን የሃጢያት መስዋዕት የሚሆነው በግ በካህኑ ፊት ይመጣና ካህኑ

እጁን ጭኖ የሕዝቡን ሃጢያት ሁሉ በላዮ ላይ ይጭንበታል ወይም ያሸክመዋል። ይህም

የሰውየውን ሃጢያት በበጉ ላይ እንዲሆን በበጉ ራስ ላይ እጅ በመጫን ለበጉ ያሸክመዋል።

ልክ እንደዚሁ ኢየሱስ በሕዝቡና በካህናቱ ምንም እንኳን ንጹ ቢሆን ሃጢያተኛ

እንደ ሆነ ተቆጠረ ይህም የሰው ልጆች ሁሉ ሃጢያት በእርሱ ላይ ይጫንበት ዘንድ ተገባ።

ይህም በእርሱ በደልን መሸከም የሌሎች ጽድቅ ይፈጸም ዘንድ ነው። እነርሱ አላወቁም

እንጂ በኢየሱስ ላይ የፈረዱበት ፍርድ ኢየሱስ በዓለም ላይ ያለውን ሁሉ ሃጢያት እንደ

ሰራ ያሕል ቆጥረው ነው። ነብዮ ኢሳያስ በ53፥4 ላይ እንዲህ ይላል፣

“4.በእውነት ደዌያችንን ተቀበለ ሕመማችንንም ተሸክሞአል፤

እኛ ግን እንደ ተመታ በእግዚአብሔርም እንደ

ተቀሠፈ እንደ ተቸገረም ቈጠርነው።”

ካህናት ኢየሱስን በእግዚአብሔር እንደ ተቀሠፈ ቆጠሩት። ያገኘው ፍርድ ሁሉ

የሚገባው የእጁ እንዳገኘ፣ የእግዚአብሔር ቁጣ በላዮ ላይ እንደ ነደደበት ያህል ቆጠሩ።

በኢየሱስ ላይ የፈረዱበት ፍርድ ከመለኮታዊው ሕግ የወጣና እግዚአብሔር ትክክል ነው

ብሎ አምኖ ይተሰማማበት እንደሆነ በዚያን ዘመን የነበሩ መሪዎች ቆጠሩ። የእግዚአብሔር

ትንቢት ሳገባቸው ተፈጸመቸው።

ምልጃ 2016

36 www.tlcfan.org

ነገር ግን በዚያን ዘመን የነበሩ ክርስቲያኖች ሆኑ ደቀመዛሙርቱ፣ ካህናቱ ፣

ፃፎችና ፈሪሳዊይን ከዚህ ያለፈ እርሱን ለማጥፋት ያነሳሳቸው ነገር እንዳለ ያምናሉ። ዮሐንስ

በመንፈስ ቅዱስ ተመርቶ በጻፈው ወንጌል ላይ አንዲ ሲል የካህናቱ ፍላጎታቸው ተጽፎ

እናገኘዋለን። ዮሐ.11፥48

“47 እንግዲህ የካህናት አለቆችና ፈሪሳውያን ሸንጎ ሰብስበው። ምን

እናድርግ? ይህ ሰው ብዙ ምልክቶች ያደርጋልና። 48 እንዲሁ

ብንተወው ሁሉ በእርሱ ያምናሉ፤ የሮሜም ሰዎች መጥተው አገራችንን

ወገናችንንም ይወስዳሉ አሉ።”

ኢየሱስ ራሱ ደግም ሰለ ጻፎችና ፈሪሳዊያን የልብ መሻት ምን እንደ ሆነ

ያውቃል። ሰለ ወይን አትክልት ቦት ስላሉ ሰራተኞች በተናገረው ምሳሌ ላይ ግልጽ አድርጎ

አስቀምጦታል። ይህም ኢየሱን የገደሉበት የእነርሱ ፍልጎት ነው። ማቴ.21፥38

“38 ገበሬዎቹ ግን ልጁን ባዩ ጊዜ እርስ በርሳቸው። ወራሹ

ይህ ነው፤ኑ፥ እንግደለውና ርስቱን እናግኝ ተባባሉ። 39

ይዘውም ከወይኑ አትክልት አወጡና ገደሉት።”

ካህናት ኢየሱስ ማን እንደ ሆነ ጠንቅቀው ያውቃሉ። ኢየሱስ መሲሁ እንደ ሆነ

ከሚሰራው ስራ በደንብ ጠንቅቀው ያውቃሉ። ከእነርሱ አንዱ የሆነው ኒቆዲሞስ ወደ እየሱስ

መጥቶ ይህን አረጋግጦለታል። ዮሐ.3 ሌላው ደግም ኢየሱስ እንደ መሲህ ከተቀበሉት

እነርሱ ደግሞ ሥራቸውን ያጣሉ። ስለዚህም ይገድሉት ዘንድ ተማከሩ ርስቱንም እናግኝ

ለእኛ እንውሰድ ተባባሉ። ነገር ግን ኢየሱስ በቁ.43 ላይ እንዲህ ብሎ ተነበየባቸው።

“43 ስለዚህ እላችኋለሁ፥ የእግዚአብሔር መንግሥት ከእናንተ

ትወሰዳለች ፍሬዋንም ለሚያደርግ ሕዝብ ትሰጣለች።”

መንግስቱ ፍሬን ለሚያደርግ ሰው እንደምትሰጥና እነርሱ በትክክለኛ መንገድ

ስላልወሰዱት ከእነርሱም እንደሚወሰድባቸው ተናገረ። እግዚአብሔር ማላጆችን

የሚያስተምረው የተሰወሩ ሃጢያቶችን ወደ አደባባይ በማውጣት እንዴት እንደ ሚፈርድ

በሕይወቱ በማሳየት ነው። ከኢየሱስ በቀር ሁሉ ማላጅ ሃጢያትን አድርጓል ሊያደርግም

ይችላል። እግዚአብሔር ማላጆችን ያሰለጥናል ስልጠናው ግን ከሥራ በፊት ብቻ ሳይሆነ

በሥራው ላይና በሥራው ውስጥ እያለንም የምንወስደው ስልጠና ነው። ይህ ደግሞ ለሰዎች

በድካማቸው የመሸከምን ካልፍነው ሕይወት እንማራለን።

ምልጃ 2016

37 www.tlcfan.org

እግዚአብሔር ማላጁ በሰው ሁሉ ፊት የወደቀ ያህል እስከ ሚናቅ ድረስ

የሚሄድበትን መንገድ እንዲያውቅና ለምልጃ ሕይወት የምሕረትን ልብን ለመፍጠር

በሕይወቱ መከራ በማሳለፍ ያስተምረዋል። በክርስቶስ ለማደግ ከፈለግን አንዱ ልናውቀው

የሚገባው በሥጋችን (flesh) ምንም መልካም ነገር እንደ ሌለው ማወቅና መግደል ነው።

(ሮሜ11፥11) የእግዚአብሔርን የበላይነት ማወቅም ወሳኝ ነው። ያለ እርሱ ምንም ልናደርግ

እንደማንችል ተረድተን ሌሎችን እንጠቅም ዘንድ በአምላካችን ስር ራሳችንን ልናዋርድ

ይገባል። በሥጋ የምንመካበት ምንም ነገር ቢኖር እንደ ጳውሎስ ልንጥል እንደሚገባን

እንወቅ። ይህም ለሌሎች ሰዎችና ለሚደክሙ ሁሉ ስለሃጢያታቸው ከእግዚአብሔር

ምሕረትን በምልጃ እንድንለምን ይረዳናል።

እግዚአብሔር መሰናክል በሚበዛበት መንገድ አንድን ሰው ሲመራ ማላጁ ሰው

ውስጥ የተደበቀውን ሃጢያት ለማጥራት ብቻ ሳይሆን የሌሎችን በደል በእርሱ ላይ አድርጎ

አንድ ላይ ከእርሱ ሃጢያት ጋር ለመፍረድም ጭምር ነው። ይህን የመሰለ ስልጠና ሲወስዱ

የሌላውን ሽክም መሸከም ብቻ ሳይሆን በስዎች ላይ መጠቆማቸውን ያቆማሉ። ምልጃን

የማያውቁ ሰዎች ግን የሰዎችን ድካም በመጠቆምና ሰርስሮ ወደ አደባባይ በማውጣት

አንደኛው ስራቸው ነው። እግዚአብሔር እንዲህ በሚያደርገው አይደሰትም

በሚያስተራርቀውና በሚሸከመው ሰው እንጂ። እግዚአብሔር ጻድቃንን ሳይሆን የሚጠራው

ሃጢያተኖችን ነው። መዳኒትም የሚያስፈልጋቸው በሽተኞች ናቸው እንጂ ጤነኞች

አይደለንም። ስለዚህ የእግዚአብሔርን ፍቅርና ምህረት ለሌሎች መግለጥ የማላጆች ብቃት

ነው። ማር.2፥17

“17 ኢየሱስም ሰምቶ። ሕመምተኞች እንጂ ብርቱዎች ባለ መድኃኒት

አያስፈልጋቸውም ኃጢአተኞችን እንጂ ጻድቃንን ልጠራ አልመጣሁም

አላቸው። 18 የዮሐንስ ደቀ መዛሙርትና ፈሪሳውያን ይጦሙ ነበር። መጥተውም።

የዮሐንስና የፈሪሳውያን ደቀ መዛሙርት የሚጦሙት የአንተ ደቀ መዛሙርት

ግን የማይጦሙት ስለ ምንድር ነው? አሉት።”

ከዚህ እንደምናየው ኢየሱስ በራሳቸው ሥራ ራሳቸውን ጻድቅ አድርገው

የሚቆጥሩትን ደግሞም ሌሎቹን ሃጢያተኛ አድርገው የሚያዮትን ማለቱ እንደ ሆነ

እንገነዘባልን። ራሳቸውን ጻድቅ አድርገው የሚቆጥሩ ሰዎች ከእግዚአብሔር በረከትን

መቀበል እንደሚገባቸው አድርገው ያምናሉ። ኢየሱስ ሃጢያትን ሰው እንዲሰራ

አይወድድም ሃጢያትንም ይጠላል። ነገር ግን ሃጢያተኛ እንደ ሆኑ የሚያምኑናና በራሳቸው

ጽድቅ የማይደግፉትን መርዳትና አብሯቸው መሆንን መደገፍንና ማገዝን ከሃጢያት ባርነት

ነጻ ማውጣት ይወዳል። እግዚአብሔር ሃጢያትን ጠልቶ ሃጢያተኛውን ግን ይወደዋል።

ምልጃ 2016

38 www.tlcfan.org

ጤነኛ እንደ ሆኑ በራሳቸውን የሚያምኑና የሚመኩ ምንም ዶክተር ለእነርሱ

አያስፈልጋቸውም ማለት ነው። ማንኛውም በራሱ ሃጢያተኛ እንደ ሆነ የማያምን ምንም

አዳኝ አያስፈልገኝም እያለ ነው። ኢየሱስ እዚህ ላይ እያወራ ያለው ስለ ዶክትሪን ሥራ

አይደለም። ከዶክትሪን እይታ ከሆነ ፈሪሳዊያን ራሳቸው ጽድቃቸው የመርግም ጨርቅ

እንደ ሆነ በቃሉ መሰረት ያምናሉ። ነገር ግን እውነቱን በሕይወታቸው አያደርጉትም

ወይም አይኖሩትም። ብዙዎቻችን ራሳችን ሃጢያተኛ እንደ ሆንን የምናውቀው በቃል

ወይም በዶክትሪን ነው። በእርግጥ ሃጢያተኛ እንደ ሆንን ራሳችንን አጥርተን በእውነተኛ

ማንነታችንና ራሳችንን አይተን በራሳችን ባሕሪ ላይ መፍረድ የምንችል በጣም ጥቂት

አማኞች ነን። ሁሉ የቃል መረዳት ከልምምድና ከጽድቅ ሥራ ውጭ ከሆነ በጣም በፍጥነት

ሊታረም የሚገባው የጥፋት መንገድ መሆኑ ማወቅ ተገቢ ነው።

ሃጢያተኝነትንና ስለ ሃጢያት መቀጣትን ያልተማሩ በእግዚአብሔር እጅ ያሉ

ይለተቆራረሱ ሕዝቡን ሊያጠግቡ የማይችሁ እርሾ የተሞሉ ዳቦዎች ዛሬም ብዙ ናችው።

እግዚአብሔር በየትኛውም ሥፍራ ያሉ አገልጋይ ባሪዎቹ እኔን ጨምሮ በብዙ ፈተና

በመውደቅና በመነሳት ያሉ ብዙ መጥራት ገና የሚጠብቅባቸው ደካሞች መሆናቸውን

እግዚአብሔር ያውቃል። እነርሱም ደካማና ያለርሱ የማይጠቅሙ መሆናቸውን በደንብ

ይረዳሉ። ዋናው ቁም ነገሩ ግን አልችልም ብሎ በሃጢያት ኑሮ ውስጥ መስጠም

አይድለም። ነገር ግን በእግዚአብሔር ችሎታና በመንፈስ ቅዱስ እገዛ ከሃጢያት መላቀቅል

እንደ ቀድሞ የሃጢያት ኑሯችን መኖርን ማቆም ነው።

ሕዝቡን ለመመገብ ማን እንደ ሆንን ራሳችንን በግልጽ ልናውቅ

በእግዚአብሔርም በሰው ፊትም አንድ አይነት መልክ ሊኖረን ይገባል። በእግዚአብሔር

ዘንድ ግልጽ መሆን ይቻላል። ነገር ግን በሰው ፊት ድካምን መግልጥ ግን አገልግሎትን

የሚያሳጣ መሰሎ ስለ ሚታየን ራሳችንን ከስማይ የወረድን ነጭ መላዕክ የሆንን ያህል

ራሳችንን አድርገን በሰዎች ፊት ልዮ ስዕልን የምንስል ብዙዎች ነን። ይህ እውነትና ትክክል

አይደለም። ሌሎች መሰናከያና የእግዚአብሔርን ስም እናሰድባለን።

ሰው የራሱ ማንነት ማወቅ ሲሳነው በጣም ከባድ አደጋ ላይ ነው። ሰው የራሱን

ማንነት በሕይወትና በመለኮታዊ መገለጥ ሊረዳ ፈጽሞ ይገባዋል። ሁላችን ሰለ ማንነታችን

በእውቀት ደረጃ የተወሰነ መረዳት አለን። ነገር ግን ይህ ብቻ በቂ አይደለም። እውነተኛ

መነቃቃት ሆነ የእግዚአብሔር ነገር የሚገኘው ራሱን የተገባው አድርጎ በማይቆጥር ሰው

ላይ ነው።

ምልጃ 2016

39 www.tlcfan.org

ይህን ስል ራሱን ዝም ብሎ የሚኮንን ሰው ማለቴ ሳይሆን ማንነቱን በመንፈስ

በመረዳት ትክክለኛ ሥፍራውን የያዘ ሰው ማለት ነው። አካል እንጂ ራስ እንዳልሆነ የገባው

ትሁንት ሰው ምህረትንና ፍቅርን በመከራ ውስጥ በማለፍ ወይም በመንፈስ ቅዱስት የተማረ

ሰው ማለት ነው።

እንዲህ አይነት ሰዎች የራሳቸውን ሃጢያት በሌላው ላይ የሚያላክኩ ሳይሆኑ

የሰዎችን ሃጢያት በመሸከም የእግዚአብሔር ፍርድ በሕጉ የሚቀበሉና ለሌላው የሚማልዱ

ናቸው። ሃጢያተኛ መሆናቸውን በደንብ የተረዱና ነጻ የወጡ በመውጣት ላይም ያሉ ሰዎች

የእግዚአብሔር ጸጋውንና ምሕረቱን የሚረዱ ለሌላው ነፍስ የሚራሩ ማላጆች እነርሱ

ናቸው። ስለሌላው ቀናን ነገር የሚያስቡ እነርሱ ናቸው። ሉቃ.7፥47

“47 ስለዚህ እልሃለሁ፥ እጅግ ወዳለችና ብዙ ያለው ኃጢአትዋ ተሰርዮላታል፤ ጥቂት ግን

የሚሰረይለት ጥቂት ይወዳል።”

“He who is forgiven little, loves little” (Luke 7:47)

ቤተክርሲያን በሁለት በተለያዮ የአማኞች አቋም ትከፈላለች። አንደኞቹ አማኞች

የራሳቸውን ሃጢያት ሳይቀር በሌላው ላይ የሚጭኑ የሚያመካኙ ሲሆኑ። ሁለተኞቹ

አማኞች ደግሞ የስዎችን ሃጢያት የሚሸከሙ ሰለ ሌሎች የሚማልዱ ናቸው።

ጳውሎስ ስለ ሃጢያትን መሸከም “imputation” ሲናገር “ያለውን እንደ ሌለ”

አድርጎ መቁጠር እንጂ ሌሎች ላይ መጫን ብሎ አላስተማረም። መሸከም የሌሎችን ሸክም

መሸከም እንጂ በላያቸው ላይ ሸክምን ጨማምሮ መጫን አይደለም።

ሁለተኞቹ የሚማልዱ አማኞች ያለውን ችግር እንደ ሌለ በመቁጠር ሃጢያቱን

ሰላደረጉት ሰዎች ይማልዳሉ። ከእግዚአብሔር ዘንድ ስለ ሃጢያተኛው ምሕረትን

ይጠይቃሉ። እግዚአብሔር ደግሞ የሌለውን ጽድቅ እንዳለ አድርጎ ይቆጥርላቸዋ

እግዚአብሔር ምልጃቸውን ይሰማል። ለሚማልዱለትም ሰው ሞት የሚገባው ሃጢያት

ካልሰራ እግዚአብሔር ያንን ሰው ይመልሰዋል። መልሶ ያቆመዋል። ሮሜ.4፥17

“is calling the things that be not as being”

(Young’s Literal Translation).

ምልጃ 2016

40 www.tlcfan.org

እግዚአብሔር መጨረሻችንን ከመጀመሪያ ማየት ስለሚችል ጻድቅና ፍጹም

እንደ ሆንን አድርጎ በልጁ የመስቀል ስራ በኩል ይቆጥረናል። በተቃራኒው የመጀመሪያዎቹ

አማኞች የሌለውን እንዳለ አድርገው ይቆጥራሉ። ለምሳሌ በኢየሱስ ላይ ምስክር አቁመው

ብዙ ሃጢያትን ጫኑበት እንደ እዚህ አይነቶቹ ክርስቲያን አማኞች በቤተክርሲያን አሁንም

አሉ። ባልሰሙትና ባላዮት የሚፈርዱ፣ የሚያሙ የስድብንና የቀልድን አሽሙር የሚያወጡ

ከእነዚህ ወገን ናቸው። የእግዚአብሔር ሕግ እንኳን ከሁለቱም ወግን ሳንሰማ እንዳንፈርድ

ሁለቱም ወገን ከሌለ ደግሞ ባላየነውና ባልሰማነው እንዳንመሰክርና እንዳንፈርድ ያዛል።

በሃሰት የሚመሰክሩ ደግሞ የተናገሩት ሃሰት ከሆነ ያወሩት በላያቸው ላይ እንደሚመጣባቸው

ይናገራል። የእግዚአብሔር ለእግዚአብሔር መተው መንፈሳዊ ብስለት ነው።

ይህን ስል ደግሞ ሰዎች ሃጢያት ሲሰሩ እያየን አንገስጽ ማለቴ አይደለም።

በመስቀል ላይ የተሰቀለው ሰው እንኳን ባልጀራውን ስለ አንደበቱ ክፉ ቃል ገስጾታል።

የሚማልድ ሰው ሃጢያት ሳያደርግ ምንም በደል ሳይገኝበት እንደ ኢዮብ ሌሎች ሃጢያተኛ

አድርገው ይቆጥሩት ዘንድ ግድ ነው። ነገር ግን በዚያን ወቅት የሌሎቹን ሃጢያት

እየተሸከመ እንዳለ ማላጁ ሊያውቅ ይገባዋል። በዚህ መልኩ እግዚአብሔር ማላጁን ወደ

ድል ነሺነት ሕይወት ይሳድገዋል። የውሸትን ክስ ህመም የሚረዱ በምልጃ ሕይወት ያለፉ

ብቻ ናቸው። የሌሎችን ሃጢያት በመሸከም ለሌሎች ምሳሌም ይሆናሉ። ኢዮብ ለባልጆሮቹ

ማላጅና የእነርሱን ሸክም ተሸክሞ ወደ እግዚአብሔር ምሕረት ዙፋን ቀረበላቸው።

እግዚአብሔር የኢዮብን የምልጃ ጸሎት ሰማ።

በኢየሱስ ዘመን የነበሩ ካህናት እስራኤልን ብቻ ሳይሆን የሰው ልጆችን ሁሉ

የሚወክሉ ነበሩ። ዓለም ሁሉ በኢየሱስ ላይ ሃጢያትዋን አሸከመች። ኢየሱስም ስላላደረገው

ነገር እንዲፈረድበት አደረግች። ይህ መለኮታዊ እቅድ ነበር። ኢየሱስ ከዚህ ውጪ ሊሆን

ምንም አይችልም ነበር። ጻድቅ የሆነው ሃጢያተኛ ሆኖ ተቆጠረ። ይህም ሃጢያተኛ የሆኑት

ጻድቅ ሆነው ይቆጠሩለት ዘንድ ሸክማቸውን ሁሉ ይሸከም ዘንድ ነው።

የቤተክርሲያን ማላጆች የእርሷን ሃጢያት ሊሸከሙ የተጠሩ ናቸው። ይህም

የቁጣዋ ጽዋ እንዳይሞላ ፍርዱ እንዲዘገይ ለማድረግ የእግዚአብሔር ምሕረት ለመቀበል

ነው። ይህ የእግዚአብሔርን ፍርድ ማዘግየት ብቻ ሳይሆን ቅዱሳኑ ወደ ክርስቶስ

እንዲያድጉና የእርሱን ኑሮ መኖር እንዲለማመዱ በቂ በመንፈስ የማደጊያን ጊዜን ያገኙ

ዘንድ ነው። በሌላ አባባል የምልጃ ጸሎት በትጋት ማድረግና የሌሎችን ሽክም ማክበድ

ሳይሆን ማቅለል እንድታስወግድ ሳይሆን ድል ነሺዎችን ከመካከልዋ እንድታሳድግ

ይረዳታል። ይህ የሚደንቅ በምልጃ ሕይወት ውስጥ ያለ የእግዚአብሔር እቅድ ነው።

ምልጃ 2016

41 www.tlcfan.org

የትክክለኛ ካህን ባሕሪ የሌሎችን በደል መሸከም ስለ ሌሎች መማለድ በእነርሱ

ፋንታ እራሱ የሚናቅ፣ ዝቅ የሚልና የሚጣል ሰው ነው። በዓለም በሃይማኖተኛ ሰዎች

ማፈሪያና የተናቀ ሥፍራ የሌለው ቢሆንም በእግዚአብሔር ዘንድ ግን የሌሎችን ሸክም

የሚሸከም የከበረ የእግዚአብሔር ልጅና ባሪያ ነው። የሚማልዱ ሰዎችን ስለ ሚከተላቸው

ፍርድ በእነርሱም ሆነ በክፉ ምክንያት እንደመጣባቸው አድርጎ መቁጠርን ከሕዝቡ ለይቶ

ማግለል ተገቢ አይደለም። የምልጃ ሕይወት ያልገባው በራሱ ሊፈረድበት ዘመን ሲመጣ

በሌሎች ላይ ያለክ ክፉ ንግግር፣ ቃልና ክስ ያወጣል። በእራሱ አንደበት እንደ ኢዮብ

ወዳጆች በፍርድ ላይ ራሱን ይጥላል።

ሁሉን ነገር ቢቀበሉ የተቀበሉት ከእራሱ ከእግዚአብሔር እጅ ነው። ያለ እርሱ

ፍቃድ በሕይወታቸው አንድ ነገር እንኳን አይሆንም ከቶም ሊሆንም አይችልም። የሰዎችን

በደል በመሸከም በተለያየ ፍርድ ውስጥ የሚያልፉ ሰዎች በጎ የማይመስለው ነገር በመጨረሻ

እግዚአብሔር ለበጎ እንደሚለውጠው አምነን የሚማልዱ ሰዎችን ልናከብራቸው ይገባል።

ሮሜ.8፥28

ምልጃ 2016

42 www.tlcfan.org

4ኛው ደረጃ፦ የሰዎቹ የራሳቸውን ፍርድ መጠን መወሰን

በሕዝቅኤል ዘመን የነበሩ ሰዎች የረከሰ በፋንድያ የበሰለ ምግብ በመብላታቸው

ምንም አይነት ክፉ ነገር በእግዚአብሔር እንዳላደረጉ ራሳቸውን ይቆጥሩ እንደ ነበር ግልጽ

ነው። በእግዚአብሔር ፊት ትክክል የሆኑና የእግዚአብሔር ሃሳብ የሚያገለግሉ ያህል

ይሰማቸው ነበር። በጊዜው በጣም ቅንዓት የሞላባቸው ሃይማኖተኛ ሰዎች እግዚአብሔር

የሚያገለግሉ የሚመስላቸው ሰዎች ነበሩ። ይህ ግን አልነበረ። ኢየሱስ በዘመኑ እንደ እነርሱ

አይነቶችን ሃይማኖተኞች ገጥመውት ነበር። ኢየሱስም እንዲ አላቸው፦ ማቴ.23፥24

“24.እናንተ ዕውሮች መሪዎች፥ ትንኝን የምታጠሩ ግመልንም

የምትውጡ። 25 እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን፥ በውስጡ ቅሚያና ስስት

ሞልቶ ሳለ የጽዋውንና የወጭቱን ውጭ ስለምታጠሩ፥ ወዮላችሁ።”

ኢየሱስ ጻፎችና ፈሪሳዊን ሲመለከታቸው ያያቸው ሃይማኖታዊ ኑሯቸው ሲታይ

በሰው ዘንድ ንጹህ የሆነ ነገር ግን በውስጥ ሕይወታቸው ሲታዮ ልክ እንደ ሕዝቅኤል ዘመን

ካህናት የረከሰን ነገር የሚመግቡና የሚመገቡም ናቸው። ግመል የሚያመለክተው

የሚመገቡትን ሰዋዊ ትምህርት ነው። ግመል ደግሞ በእግዚአብሔር ሕግ መሰረት የማይበላ

እንስሳ ነው። እነርሱ ግን እግዚአብሔር የማይፈቅደውን እነርሱም እንዲመገቡት

የማይወደውን ነገር መመገብ ብቻ ሳይሆን ይውጣሉ። ከወጋቸው አንዱ ደግሞ

ከመብላታቸው በፊት እጃቸውን መታጠብ ነው። ይህም ምናልባት ጠረጴዛውን የሞተ ዝንብ

ነክቶት ይሆናል ስለሚሉ ራሳቸውን ንጹ ነን ለማለት ወይም ለማንጻት ነው።

በሌሎች ላይ እንዴት እንደ እግዚአብሔር ቃል እንደምንፈርድ ማወቅ አለብን።

ምክንያቱም በምንፈርድበት ፍርድ እኛው ላይ ደግሞ የሚፈረድብ በዚያው በፈረድንበት

መው። በእግዚአብሔር ሕግ መሰረት ፍርድ ይፈረድብናል። ኢየሱስ እንዲህ ብሎ

ያስተምረናል፦ ማቴ.7፥1,2

“1-2 እንዳይፈረድባችሁ አትፍረዱ፤ በምትፈርዱበት ፍርድ ይፈረድባችኋልና፥

በምትሰፍሩበትም መስፈሪያ ይሰፈርባችኋል። 3 በወንድምህም ዓይን ያለውን

ጉድፍ ስለምን ታያለህ፥ በዓይንህ ግን ያለውን ምሰሶ ስለ ምን አትመለከትም?

4 ወይም ወንድምህን። ከዓይንህ ጉድፍ ላውጣ ፍቀድልኝ እንዴትስ ትለዋለህ?

እነሆም፥ በዓይንህ ምሰሶ አለ። 5 አንተ ግብዝ፥ አስቀድመህ ከዓይንህ

ምሰሶውን አውጣ፥ ከዚያም በኋላከወንድምህ ዓይን ጉድፉን

ታወጣ ዘንድ አጥርተህ ታያለህ።”

ምልጃ 2016

43 www.tlcfan.org

በሌላ መልኩ ለሰዎች ምሕረትን ብናበዛ ለእነርሱ ባበዛንበት መጠን ለእኛም ስለ

ሃጢያታችን በሚፈረድብን ጊዜ ምሕረት ይበዛልናል። ይህም በእግዚአብሔር ሕግ በዘዳ.25፥

13-15 ላይ የሚገኝ የሚዛን ሕግ ነው። አናስተውልም እንጂ ብዙ ጊዜ ፍርዳችንን

የምንወስነው ራሳችን ላይ ራሳችን ነን። ሌላው ላይ የምንሰፍርበት መሰፈሪያ የእኛም

መስፈሪያ ያው እርሱ መሆኑን እንዘነጋለን። አፋችን በፍርድ ሊቸኩል ሲል ዞር ብለን

ራሳችንን ማየት ከቻልን በጣም አስተዋዮች ነን።

“13.በከረጢትህ ውስጥ ታላቅና ታናሽ የሆነ ሁለት ዓይነት ሚዛን አይኑርልህ።

14፤ በቤትህ ውስጥ ታላቅና ታናሽ የሆነ ሁለት ዓይነት መስፈሪያ አይኑርልህ።

15፤16፤ ይህን የሚያደርግ ሁሉ ክፋትንም የሚያደርግ ሁሉ በአምላክህ

በእግዚአብሔር ዘንድ የተጠላ ነውና አምላክህ እግዚአብሔር በሚሰጥህ ምድር ላይ

ዕድሜህ ይረዝም ዘንድ እውነተኛና ፍጹም ሚዛን ይሁንልህ፤ እውነተኛና ፍጹም

መስፈሪያም ይሁንልህ።”

እግዚአብሔር የተለያየ የፍርድ ሚዛን አይጠቀምም። ለተመሳሳይ ነገር ሁሉ

ፍርዱና የቅጣት መጠኑ አንድ ነው። በሰው ላይ በፍጥነት የሚፈርዱ ስዎች የሰለሞንን

ምክር ሊቀበሉ ይገባቸዋል። እየሱስ ሰለ ፍርድ ሲያስተምር የሰለሞንን ምክር እያሰላሰለ

ይመስለኛል። ማቴ.7, ምሳሌ.20፥22,23 ላይ ሰለሞን እንዲህ ይላል።

“22 ክፉ እመልሳለሁ አትበል፤ እግዚአብሔርን ተማመን፥ እርሱም ያድንሃል።

23 ሁለት ዓይነት ሚዛን በእግዚአብሔር ዘንድ አስጸያፊ ነው፥ ሐሰተኛ

ሚዛንም መልካም አይደለም። 24 የሰው አካሄዱ ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው፤

እንግዲያስ ሰው መንገዱን እንዴት ያስተውላል?”

ከልምዴም እንደ ተማርኩት እግዚአብሔር የሚፈርድብን በተመሳሳይ ሃጢያት

በሌሎች ላይ በፈረድንበት መፍረድ ነው። አንዳንድ ጊዜ በሰዎች ላይ ሰለ አንድ ሃጢያት

ከፈረድኩ በኃላ እግዚአብሔር በውስጤ ያለውን ተመሳሳይ ሃጢያት ይገልጥልኛል። ያን

ጊዜ እግዚአብሔር በዚያው በፈረድኩበት ፍርድ እንደ ሚቀጣኝና እንደ ሚያርመኝ አውቄ

ራሴን በእጁ ሥር አዋርዳለሁ። ይህን ከተማርኩ በኃላ ፍርድን ለእግዚአብሔር መተውንና

ከፈረድኩም በጽድቅ ለመፍረድ ራሴን በእግዚአብሔር ሕግ አበረታለሁ።

ምልጃ 2016

44 www.tlcfan.org

ይህ ሁሉ መርህ ሰው በእግዚአብሔር የራሱን ፍርድ እንዲፈርድ እንደሚደረግ

በዳዊት ሕይወት በደንብ መመልከት እንችላለን። ይህን ስንል ፍርድ ሁሉ ለሰው ልጆች

ተሰጥቷል እያልኩ አይደለም። ነገር ግን እግዚአብሔር አንዳዴ የፍዳችንን መጠን በራሳችን

አፍ ይቀበለዋል። ዳዊት ከቤርሳቤ ጋር አመነዘረ ባልዋን ዖሪዮንን አስገደለ። ነብዮ ናታን

ሊገስጸው ከእግዚአብሔር ዘንድ ተላከ። 2.ሳሙ.12 ናታንም የእርሱን ሃጢያት የሚያሳይ

አንዲት ትንሽ ምሳሌያዊ ታሪክ ነገረው።

“1፤ እግዚአብሔርም ናታንን ወደ ዳዊት ላከ፥ ወደ እርሱም መጥቶ አለው።

በአንድ ከተማ አንዱ ባለጠጋ አንዱም ድሀ የሆኑ ሁለት ሰዎች ነበሩ። 2፤

ባለጠጋውም እጅግ ብዙ በግና ላም ነበረው። 3፤ ለድሀው ግን ከገዛት አንዲት

ታናሽ በግ በቀር አንዳች አልነበረውም፤ አሳደጋትም፥ ከልጆቹም ጋር በእርሱ ዘንድ

አደገች፤ እንጀራውንም ትበላ፥ ከዋንጫውም ትጠጣ፥ በብብቱም ትተኛ ነበር፥ እንደ

ልጁም ነበረች። 4፤ ወደ ባለጠጋውም እንግዳ በመጣ ጊዜ ከበጉና ከላሙ ወስዶ

ለዚያ ወደ እርሱ ለመጣው እንግዳ ያዘጋጅለት ዘንድ ሳሳ፤ የዚያንም የድሀውን ሰው

በግ ወስዶ ለዚያ ለመጣው ሰው አዘጋጀ። 5፤ ዳዊትም በዚያ ሰው ላይ እጅግ

ተቈጥቶ ናታንን። ሕያው እግዚአብሔርን! ይህን ያደረገ ሰው የሞት ልጅ ነው።

6፤ ይህን አድርጎአልና፥ አላዘነምና ስለ አንዲቱ በግ አራት ይመልስ አለው። ......

አሁንስ በፊቱ ክፉ ትሠራ ዘንድ የእግዚአብሔርን ነገር ለምን አቃለልህ?

ኬጢያዊውን ኦርዮን በሰይፍ መትተሃል፥ ሚስቱንም ለአንተ ሚስት ትሆን ዘንድ

ወስደሃል፤ እርሱንም በአሞን ልጆች ሰይፍ ገድለሃል። 10፤ ስለዚህም

አቃልለኸኛልና፥ የኬጢያዊውንም የኦርዮን ሚስት ለአንተ ሚስት ትሆን ዘንድ

ወስደሃልና ለዘላለም ከቤትህ ሰይፍ አይርቅም። 11፤ እግዚአብሔር እንዲህ

ይላል። እነሆ፥ ከቤትህ ክፉ ነገር አስነሣብሃለሁ፤ ሚስቶችህንም በዓይንህ ፊት

እወስዳለሁ፥ ለዘመድህም እሰጣቸዋለሁ፥ በዚህችም

ፀሐይ ዓይን ፊት ከሚስቶችህ ጋር ይተኛል።”

እኩል በሆነው በእግዚአብሔር ሚዛን ሕግ መሰረት ዳዊት እንዲሞትና አራት

እጥፍ በግ እንዲከፍል በራሱ ላይ ፈረደ። ዳዊት ንስሃ በመግባቱ ቅጣቱ እንዳለ ሆኖ ሞቱ

እንዳይመጣበት በጸጋው ተሸፈነ። ነገር ግን ምንም እንኳን ዳዊት ባይሞትም የግድ እኩል

ሚዛን ሕግ ፍጻሜ እንዲያገኝ በእርሱ ምትክ የበኩር ልጅ መሞት ግድ ነበረበትና ከቤርሳቤህ

የወለደው የበኩር ልጁ በእርሱ ፋንታ ሞተለት። ልጁ ምንም የሌለበት ንጹ ልጅ ነበር።

ስለ ዳዊት ሃጢያት ግን ምትክ ሆኖ ሞተ። 2.ሳሙ.12፥14

ምልጃ 2016

45 www.tlcfan.org

እኛም የሰው ልጆች ከሰራነው ሃጢያት የተነሳ እንደ ዳዊት መሞት ሲገባን

ምሕረትን አገኘን። በመንፈሳዊ ጥላነቱ የዳዊት የበኩር ልጅን የሚወክለው የናዝሬቱ ኢየሱስ

ክርስቶስ ነው። እርሱ በእኛ በሰው ልጆች ሁሉ ፋንታ በመሞቱ የሃጢያት እዳችንን ለሁላችን

ከፈለ ከሞት አዳነን። ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ ዳዊት ልጅ ምንም ሃጢያትን ያልሰራ ንጹ

ልጅ ነው። ወደ ዳዊት ታሪክ ስንመልሰ ግን ዳዊት ራሱ ላይ በዘጸ.22፦1 መሰረት በወሰደው

በግ ወይም ቤሳቤህ ፋንታ አራት እጥፍ እንዲከፍል በራሱ ላይ ፈረደ፣

“1.ሰው በሬ ወይም በግ ቢሰርቅ፥ ቢያርደው ወይም ቢሸጠው፥ በበሬው

ፋንታ አምስት በሬዎች፥በበጉም ፋንታ አራት በጎች ይክፈል፣”

የዳዊት እንደ እግዚአብሔር ሕግ ፍርድ እርሱ እራሱ በራሱ ላይ እንደ ፈረደው

በላዮ ላይ አንድ በአንድ አራቱም ተፈጽሞ ተጠናቀቀ። ከቤርሳቤ የተወለደውን ልጅ ብቻ

ሳይሆን ሊሎች ሦስት ልጆችንም ጨምሮ አጥቷል። አምኖን (2.ሳሙ.13፥33) አቤሴሎም

(2.ሳሙ.18፥15) አዶንያስ (1.ነገ.2፥24) ናቸው።

በመጽሐፍ ቅዱስ ብዙን ጊዜ ሰዎች የራሳቸውን ፍርድ እንዲፈርዱ ሲደረጉ

እናያለን። በሕዝቅኤል፣ በሆሴዕና በኢሳያስ እንደ ሆነ በእኛም እንዲሁ ነው። የእግዚአብሔር

ይህ አሰራሩ ላይገባን ይችላል። ለምንም እንዲህ እንደሚያደርግ ሊደንቀን ይችላል። ነገር

ግን እግዚአብሔር ይህንን ማድረጉን አሁንም አይተውም።

ይህ በእግዚአብሔር ሕግ እንደ ተጻፈው መሰረት እግዚአብሔር ሃጢያት ላይ

የሚፈርድበት አንዱ መንገዱ ነው። የእኩል ሚዛን ሕግ ከገባን ቶሎ ንስሃ በመግባት የጸጋን

ዘመን በላያችን ላይ በማርዘም ከብዙ ነገር ልናመልጥ እንችላለን። እኔ ማን ነኝ? ከዚህ

ሰውስ የተሻለ ምን ሰርቻለሁ ብለን አስቀድመን ልናስብና ቀድመን በራሳችን ልፈርድ

ይገባል።

ሃጢያት የሌለበት ይውገር የሚለውን የጥበብ ቃል አንዘንጋው። ነገር ግን

እናስተውል ቀድመን እናስብ ዝም ብለን ቶሎ ከመፍረድ እንቆጠብ። እግዚአብሔር ስለ

ሃጢያታችን ልጆቹንና አማኞችን ሁሉ መቅጣቱ ግን ፈጽሞ አያቆምም። ይህ ሁሉ ለገዛ

ጥቅማችን ነው። እግዚአብሔር ከእርሱ መለኮታዊ ባሕሪ እንድካፈል ዘንድ

ያስተጠነቅቀናል፣ይቀጣናል፣ የገርፈናል. ዕብ.12 እንግዲህ የእግዚአብሔርን ሕግ ጠንቅቀን

በማወቅ በላያችን ላይ የቅጣትን ጉልበት ማቅለልና ጸጋው በላያችን እንዲ በዛ ወደ ምሕረት

ዙፋን በምልጃ መቅረብን መማር ይጠበቅብናል። ሮሜ.6፥1

ምልጃ 2016

46 www.tlcfan.org

የምልጃ ጸሎት የምንማረው ነው። ደቀመዛሙርት ኢየሱስን እንዴት መጸለይ

እንደሚገባቸው እንዲያስተምራቸው ጠይቀውታል። እርሱም አስተምሯቸዋል። የምልጃ

ጸሎት ከእግዚአብሔር የሆነን ትምህርትም ይጠይቃል።

ጳውሎስ እንደ ተናገረው የሁሉ ክርስቲያን ሥራ በእሳት እንደሚፈተን በግልጽ

አስቀምጧል። 1.ቆሮ.3፥11-15 የእሳቱ አላማ ይህ አማኝ ክርስቲያን ወይም ክርስቲያን

እንዳልሆነ ለመለየት አይደለም። ነገር ግን የሥራውን መጠንና የሽልማቱን መጠንና

የደሞዙን መጠን ለመወሰን ነው። ይህ ከደህንነት ያለፈ ነገር ነው።

ኢየሱስ ስለ እኛ በመስቀል ላይ የሰራልን ሥራ የመጀመሪያው ደረጃ ሥራ

ሲሆን ይህ ጳውሎስ የሚናገረው የአማኙ ሥራ ደግሞ ሁለተኛው ሰው ከዳነ በኃላ

የሚያደርገው እንጂ ለመዳን የሚያደርገው እንዳልሆነ አስቀድመን ሁላችን ልናውቅ

ይገባናል። ኢየሱስ የመጀመሪያውን የደህንነት ሥራ ቢሰራውም እግዚአብሔር በቅዱሳኑ

ሆነ በማያምኑት ላይ በግል በሚሰሩት የሃጢያት ሥራ መፍረዱን አሁንም አላቆመም። ነገር

ግን ይህ ፍርድና ቅጣት የመጀመሪያውን የኢየሱስን ሥራ የሚያጠፋ አይደለም።

የሚማልደው ሰው በሚማልድላቸው ሰዎች ፊት የወደቀ እስኪ መስል

እንዲታይና ሰዎች እንዲፈርዱበት እግዚአብሔር ያደርጋል። ይህም ሰዎቹ የራሳቸውን

ፍርድ በላያቸው ላይ እንዲ ፈርዱ ለማድረግ የፍዳቸውን መጠን በገዛ እራሳቸው ለማሳየትም

ጭምር ነው። በማላጁ የእነርሱን ሃጢያት መሸከም ምሳሌ የሆነው ሰው ላይ የሚያወጡት

ፍርድ ሁሉ የእነርሱ የፈራጆቹ ፍርድ ይሆናል ማለት ነው። እንደፈረዱ ይፈረድባቸዋል።

ይህንን በሕይወት ዘመኔ በብዙ መልኩ በራሴም ሆነ በሰዎች አይቼዋለሁ። የሚሰራና እውነት

የሆነ የእግዚአብሔር መርህ እንደ ሆነ እመሰክራለሁ።

ማላጁ ላይ እንደፈርዱበት መጠን በእነርሱ ላይ ይፈረዳል። የዳዊት ልጅ

የአባቱን ሃጢያት ፍርድ እንደተሸከ አንድ አንዴ ማላጁ የሃጢያተኛውን ፍርድና ቅጣት

ይሸከማል። የእርሱ መቀጣት የእነርሱን ወደ ንስሃ የመግባት በር ይከፍታል። ዳዊት በንስሃ

እንደ ተመለሰ ለእነርሱም ማላጁ ፍርዱ ከመውሰዱ የተነሳ በላያቸው ላይ የእግዚአብሔር

ጸጋ ትገናለች ወደ ንስሃ ለመምጣት ልባቸው በእግዚአብሔር ፊት ራስዋን ታዋርዳለች።

ይሁንና ሃጢያቱን የሰሩት ሰዎች ከሁሉ ቅጣት አያመልጡም። ከማላጁ የተነሳ ብዙና

ጠንካራ ፍርድ ይቀልላቸዋል። በፈረዱበት ፍርድ ራሳቸው ይቀጡበታል። ሁሉን

የማይቀጡት ማላጁ የተወሰነውን ሰለ እነርሱ ሰለ ሚቀጣላቸውም ነው።

ምልጃ 2016

47 www.tlcfan.org

ዳዊት በልጁ ሞት ሕይወቱን አተረፈ እንጂ አልተጎዳም። ልጁ ባይሞት ኖሮ

ዳዊት ይሞት ዘንድ ይገባው ነበርና ነው። የሆሴዕ ጋለሞታይቱ ማግባት ደግሞም መቤዥት

ከእርሱ ታላቅ መከራና ዋጋ መክፈል ነው። የእስራኤልን ሕዝብ በምልጃ ስለ ተሸከመ

ለሕዝቡ ቅጣት ከመቀጽበት እንዳይመጣና ከእግዚአብሔር ድጋሚ ሕብረት የሚያደርጉበት

የንስሃ ሕይወት ውስጥ እንዲገቡ ሕዝቡን እረዳቸው። በእርሱ መከራና ጭንቀት ሕዝቡ

ተጠቀመ። ሚስቱን እንደ ተሸጠች ትቷት ቢሆን ኖሮ እስራኤል ከባርነት ግዞት ፈጽማ ነጻ

አትወጣም ነበር። ዛሬም በመካከላችን ያሉ ማላጆች የራሳችንን ፍርድ እንድንበይንና ከክፉ

ቅጣት እንድናመልጥ በእኛና በእግዚአብሔር መካከል ጣልቃ የሚገቡ እውነተኛ የበሰሉ

የእግዚአብሔር ካህናቶች ናቸው። ሆሴ.3፥2

ሕዝቅኤልም በፋንድያ ላይ የበሰለ ዳቦ ስለ ሕዝቡ በመመገቡ የእግዚአብሔር

ጸጋ ዘመን አረዘመላቸው። ሕዝቡም ምንም እኳን ቢንቁት ቢያላግጡበትም በእርሱ መከራና

ጭንቀት እነርሱ ተጠቀሙ። ይህ ደግሞ ሁሉ ቅጣት ለዳዊት ልጁ እንዳልወሰደለት ከእዚያም

በኃላ እንደ ሕጉ በእራሱ ላይ አራት እጥፍ እንደ ፈረደ ሦስት ልጅ ጨምሮ አጣ። ሁሉም

እንደተናገረው ከሞት በቀር እንዲሁ እንደ ፈረደው ሆነበት።

በሕዝቅኤል ዘመንም የነበረው ሕዝብ ቅጣቱ በዚህ ዘመን ብቻ ያበቃ

በሕዝቅኤል ቅጣት ብቻ የተጠናቀቀ አልነበረም። ከ390 ቀን በኃላ በመነሳቱ ከእነዚህ ቀኖች

በኃላ ፍርዱ ሁሉ እንደሚነሳላቸ ትንቢትን የሚተነብይ ኑሮ በፊታቸው ኖሮ ጨረሰ።

ከዚያም የቀረው ሃጢያት ሁሉ ተቀጥቶ ካለቀ በኃላ እግዚአብሔር ከ7 x 390 ዓመት በኃላ

ድል ነሺዎችን አስነስቶ ሕዝቡ በፋንድያ የተጋገረ እንጀራ የማይበላበት ዘመን ላይ

ያመጣቸዋል፣ ይገልጣቸዋል። ይህን ስል የመጪውን ዘመን መልክ በቃሉ ትንቢት

እናገራለሁ። ይህም የሚመጣው ዘመን የሰዎችን ሰርዓትና ወግ ትምህርት የማያስተምሩ

የእግዚአብሔር ቃል ብቻ በመንፈስ ቅድስ መሪነት የሚያገለግሉ የእግዚአብሔር ልጆች

የሚነሱበት ዘመን ነው።

እነዚህ በትንቢት የተነገረላቸው ካህናትና ድል ነሺ የእግዚአብሔር ልጆች ሲነሱ

ቃላቸናንና የሚናገሩበትን መንፈስ ሊቋቋም የሚችል ማንኛውም አይነት ሰው አይኖርም።

እነዚህ አሁን በመጨረሻው ዘመን የሚያስነሳቸው ልጆች የሕዝቅኤል ትንቢት መፈጸሙ

ማረጋገጫ ናቸው። ሕዝቅኤል ከ390 ቀን በኃላ እንደ ተነሳ እነርሱ ከተኙበት በዚህ

በመጨረሻ በእግዚአብሔር በዓል በዳስ በዓል ላይ ፈጽመው ይነሳሉ። ሕዝቡን ከሰማይ

የወረደን እንጀራ ይመግባሉ።

ምልጃ 2016

48 www.tlcfan.org

ይህን ሁሉ በጊዜው ውብ አድርጎ የሚፈጽም ምንም አጋዥ የማይፈልገው

አምላካችንና አባታችን እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን። እርሱ በሥራው ድንቅ በጥበቡና

በማሰተዋሉ ወደር የለውም። እግዚአብሔር ከማንም ጋር ሊወዳደር በሰውም ሃሳብ ሊገመት

የማይችል የምሕረት አባት ነው።

ምልጃ 2016

49 www.tlcfan.org

5ኛው ደረጃ፦ መጀመሪያ እምነት ከዛም መረዳት

ታላቁ የምልጃ ክፍል ማላጁ ምንም ሳያደርግ የሚደርስበትን ችግርና መከራ

መረዳት ነው። ብዙ የሚማልዱ ሰዎች በሕይወታቸው ምን እየሆነ እንዳለ ለማወቅ በጣም

ይቸግራቸዋል። በእግዚአብሔር ፊት በጽድቅ እየተመላለሱ ይህ ሁሉ በእነርሱ ላይ ለምን

እንደሚመጣ የማያውቁ ብዙ አማኖች ናቸው። ታላላቅ እንደሚማልዱ የማያውቁ ነገር ግን

ማላጆች የሆኑ ሕይወት ገጽታ በአብዛኛው እንዲህ ነው።

በእነርሱ ሕይወት የሚያልፈውና የሚሆነው ነገር ሁሉ ምንም ሰሜት የማይሰጥ

ነገር ነው። በውስጣቸው በጽድቅ ከመሄዳቸው የተነሳ እነርሱ ምንም ሳያደርጉ በእነርሱ ላይ

ሰለ ሚደርሰው ነገር አይገባቸውም ግራም ያጋባቸዋል። እንደ ኢዮብ ምንም ነገር

እግዚአብሔር እንዳልበደሉ ሰለ ሚረዱና ስለሚያምኑ በውስጣቸው በእግዚአብሔር ላይ

በግልጽ ያልወጣና በአንደበታቸው ምሬት ቃል ይሰማባቸዋል። እንደ እነዚህ አይነት

ሰዎች የሚማልዱ ስዎች ናቸው። ነገር ግን ምልጃ ምን እንደ ሆነ ካለማወቃቸው የተነሳ

ያሉበትን ሥፍራ ስለማያውቁ ይህ አይነት ምሬትና ጥርጣሬ በሕይወታቸው ያድጋል። ይህ

ደግሞ ያልበሰለ የምልጃ ሰው የሆነ አማኝ ባሕሪ ነው።

አንድ ሰው በሚማልድበት ወቅት ይህ የሚገባው ነው የምንለው ነገር በሕይወቱ

አይመጣበትም። ማለት በማላጁ ሕይወት የሚያልፈው ሕይወት ሁሉ በጻድቅ ሕይወት

ከሚያልፈው ሕይወት ተገላቢጦሽ ስለሚመስል ነው። እግዚአብሔር ጻድቅ ከሆነ በፊቱ

በጽድቅ የሚሄዱትን የሚያከብር ከሆነ ይህ ለምን? በእኔ ሕይወት ለምን ይህ ሆነ? የሚለው

ጥያቄ ከብዙ የምልጃ ጸሎት ከሚጸልዮ አማኞች የሚመነጭ ጥያቄ ነው።

ይልበሰለ ማላጅ የሆነ የምሬት ቃል የሚያመነጨው ሆሌ በጥያቄ ነው። ይህ

አይነቱ ጥያቄ የሚመጣው ስለ ምልጃ ያላቸው የመረዳት ወይም የእውቀት እጥረት ነው።

እግዚአብሔር ሰውን የምልጃ ሕይወት ውስጥ ሲያስገባ አማኙን በሕይወቱ ብዙ ነገር

በማሳለፍ የሚያሰለጥነው ምልጃ በእምነት እንጂ በመረዳትና በእውቀት የሚሆን ስላልሆነም

ነው። ይህም የማላጁም እምነትና ሕይወት መፈተኛ መጥሪያም ሥፍራ ነው። የኢዮብን

ሕይወት ብንመለከት ብዙ ትምህርትን መውሰድ እንችላለን። እግዚአብሔር ሰለ እንደዚህ

አይነቱ ጥያቄ አንድ መጽሐፍ ሙሉ በቃሉ ጽፎልናል። ይህም መጽሐፈ ኢዮብ ነው።

በሕይወቱ ተምሮ ለሌሎች ማላጅ የሆነውን የምልጃ ሰው ታሪክ ከመጀመሪያው እስከ

መጨረሻው እናገኛለን።

ምልጃ 2016

50 www.tlcfan.org

እግዚአብሔር በሕይወታችን እንዲያሰቃየን ከመጣ ማንኛው ነገር የበላይ

ተቆጣጣሪ እግዚአብሔር ራሱ ነው። እርሱ ሳይፈቅድለት አንዳች ነገር በእኛ ላይ ሊሆን

ሰልጣን የለውም። በእኛ ውስጥ ያለው ደግሞ ከውጭ ካለው ሁሉ በላይ ነው። እግዚአብሔር

ሂድ ወይም ቅረብ ካላለው በቀር ወደ እኛ መቅረብ ማንም አይችልም።

የኢዮብ ሚስት እግዚአብሔርን ሰድቦ እንዲሞት መከረችው ይህን ከደካማ

ነፍሳችን የሚመጣ አንዳንድ ማላጆች ለራሳችን የምንነግረው የውስጥ የነፍሳችን ጩኸት

የሚያሳይ ነው። በጌታ መሆኔ ምን ይጠቅኛል? ያኔ በዓለም እያለሁ ይሻለኝ ነበር?

ከመልካም ነገር ይልቅ በሕይወቴ የበዛው ክፉ ነገር ነው እንላለን። ይህ ሁሉ የምልጃ

ሕይወት ሚስጥር እውቀትና መረዳት ከመጉደል የሚመጣ ጥያቄ ደግሞም የጥርጣሬና

በእግዚአብሔር ያለመታመን ምልክት ነው። ኢዮብ ግን ለሚስቱ እንዲህ በሎ መለሰ፦

ኢዮ.2፥10

“9. ሚስቱም። እስከ አሁን ፍጹምነትህን ይዘሃልን? እግዚአብሔርን ስደብና ሙት

አለችው። (የሚቀጥለው ከግሪክ የተጨመረ ነው) ዳግመኛ እግዚአብሔርን ጥቂት

ወራት ደጅ እጠናዋለሁ፤ ዳግመኛም መከራውን እታገሠዋለሁ፥ የቀድሞ ኑሮዬንም

ተስፋ አደርገዋለሁ ትላለህን? አለችው። እንደዚህሳ እንዳትል ከዚህ ዓለም እነሆ ስም

አጠራርህ ጠፋ፤ ሴቶች ልጆቼና ወንዶች ልጆቼም ሞቱ እኔስ ዘጠኝ ወር ሳረግዝ

ሳምጥ ስወልድ ሳይረቡኝ ሳይጠቅሙኝ በከንቱ ደከምሁ አለች። አንተም በመግል

ተውጠህ በትል ተከብበህ ትኖራለህ፤ ሌሊቱን ሁሉ ስትዛብር ታድራለህ። እኔ ግን

እየዞርሁ እቀላውጣለሁ። ከአንዱ አገር ወደ አንዱ አገር ከአንዱ ቤት ወደ አንዱ ቤት

እሄዳለሁ፤ ከድካሜ በእኔ ላይ ካለ ከችግሬም አርፍ ዘንድ ከጧት ጀምሮ ፀሐይ እስኪገባ

ድረስ እጠብቃለሁ፤ አሁን ግን እግዚአብሔርን የማይገባ ቃል ተናግረኸው ሙት

አለች።/ 10፤ እርሱ ግን አንቺ ከሰነፎች ሴቶች እንደ አንዲቱ ተናገርሽ፤

ከእግዚአብሔር እጅ መልካሙን ተቀበልን፥ ክፉ ነገርንስ አንቀበልምን?

አላት። በዚህ ሁሉ ኢዮብ በከንፈሩ አልበደለም።”

ኢየሱስ ታላቁ ምሳሊያችን በዚህ አይነቱ የምሬትና የሕይወት ጥያቄ ውስጥ ለልፏል።

ኢየሱስ በአገልግሎትይ ዘመን ሁሉ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር እንዳለ እርሱን ያየ

እግዚአብሔር እንዳየ እንዲያውቅ አስተማረ። ነገር ግን የሁሉን ሃጢያት በመስቀል ተሸክሞ

አለሙን ከአብ ጋር ሲያስታርቅ እንዲህ አለ፦ ማቴ.27፥46

“በዘጠኝ ሰዓትም ኢየሱስ። ኤሎሄ ኤሎሄ ላማ ሰበቅታኒ?

ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ። ይህም። አምላኬ አምላኬ፥

ስለ ምን ተውኸኝ? ማለት ነው።”

ምልጃ 2016

51 www.tlcfan.org

ኢየሱስ በእግዚአብሔር ታምኖ የሚሆነውን ሁሉ የቀረበለትን ጽዋ ጠጣ።

አምላኬ አምላኬ ለምን ተውከኝ በማለት ሰለ ሚሆነው ሰለሚከናወነው ነገር ሁሉ ሙሉ

ጭልቀቱን ለእኛ አሳየ አመለከተ ይህም ሰዋዊ ማንነቱ ነው። ይህም ለእኛ ለምሳሌና

ለትምህርት ይሆንልን ዘንድ የተጻፈ ነው።

የሚማልድ ሰው በጭፍኑ እግዚአብሔርን ሊያምን ይገባዋል። ኢየሱስ

የእግዚአብሔርን ፍቃድ በመንፈሱ ይረዳዋል። ነገር ግን ነፍሱ ይህን መረዳትና በስቃይ

ጊዜ አቃታት። ኢየሱስ ስለ ሌሎች ተሰቃየ በምልጃ ሕይወት ውስጥ ስለ ገባ እምነቱም

ተፈተነ። በሁሉ ሁሉን እስከ መጨረሻው ታገሰ በመስቀል ላይ የሮማ ወታደሮች ሕመሙን

የሚቀንስ ማስታገሻ ጋበዙት ግብዣቸውን ግን እንቢ አለ። ስለ ሁሉ እርሱ ተሰቃየ ሞት።

“34.በሐሞት የተደባለቀ የወይን ጠጅ ሊጠጣ

አቀረቡለት፤ ቀምሶም ሊጠጣው አልወደደም።”

ማቴ.27፥34

ለኢየሱስ የመስቀሉን ጣርና ሕመም የሚያጠፋ በወይን ጠጅ የተቀላቀለ ሃሞት

አቀረቡለት። እርሱ ግን ይጠጣው ዘንድ አለወደደም። ለምን? ሃሞት የሰው ልብ ምሬት

ምሳሌ ነው። ኢየሱስ ከሃጢያት በቀር በሁሉ ተፈተነ። ምሬት ግን በአፉ አልተገኘም

በሆዱም አልገባም። ዕብ.4፥15 ምንም እንኳ ነፍሱ በዚያ ስዓት በስቃይ ብትጮህም

እግዚአብሔር የተዋት ቢመስላትም ኢየሱስ ምሬት ወደ ውስጡ ገብቶ የሚያልፍበትን ነገር

ለጊዜው ሕመሙን እንዲያስረሳው አልፈለገም። ምሬት ወደ ውስጡ እንዳይገና በሆዱም

እንዳይዋሃድ ፈጽሞ እንቢ ምሬትን አልቀበልም አለ። በሚሰራው የእግዚአብሔር የመስቀል

ስራው ወቅት ኢየሱስ እንደሰው የተተወ መስሎ ቢሰማውን የአምላኩን ፍቃድ እሺ ብሎ

በስቃይም ውስጥ ታዘዘ።

እኛም ምንም እንኳን እንደ ኢየሱስ ያለ ነገር ባይገጥመንም በምልጃ ሕይወት

ስንኖር የኛ ያልሆነ መከራና ስድብን እንጠግባለን። በዚያን ወቅት ጠላት የሚጋብዘንን

ለጊዜው መከራን የሚያስረሳውን ምሬትና የጊዚያዊ እረፍትን አንንቢ ልንል ይገባል።

እግዚአብሔር የማያከብር በውስጣችን በአዕምሯችን የሚፈሰውን ማንኛውንም ነገር ሁሉ

ልናወጣ ይገባናል። በአንጻሩ ደግሞ በእግዚአብሔር በመታመን በእርሱ እጅ ላይ ራሳችንን

እንደ ኢየሱስ አሳልፈን ልንሰጥና በእርሱ በአባታችን ልንተማመን ይገባናል። ያን ጊዜ

እውነተኛ ድል ነሺዎች እንሆናለን።

ምልጃ 2016

52 www.tlcfan.org

በእንዲህ ባለ መከራ ስናልፍ በውስጣችን የሚመጣውን እንደ ኢየሱስ

የምንቀምሰውን መራራ ነገር ሁሉ አንጠጣም በምንልበት ወቅት እግዚአብሔር በውስጣችን

ምሬት የሚባል ነገር ለዘላለም እንዳያገኝ አድርጎ ከእኛ ያስወግደዋል። ልባችንን ለእርሱም

ሆነ ለሰው ልጆች የሚመች ንጹህ አድርጎ ያጠራዋል።

የሚማልዱ ሰዎች በልምድ እግዚአብሔር በመንፈሳቸው መስማትን ይማራሉ።

የነፍሳቸውን ወይም አዕምሯቸው ካለ መረዳት የምታመጣውን ጥያቄ ሁሉ ድል የሚነሱበትን

የሃይል ብቃት ደረጃ ላይ ያመጣቸዋል። የሚማልድ ሰው መንፈሱ ከእግዚአብሔር መንፈስ

ጋር የተጣመረና የተቆራኘ መንፈስ ነው። መንፈስ ቅዱስ እራሱ ዋንኛ አማላጅ ነው።

ለሚማልድ ሰው ከመረዳትና ከእውቀት በፊት እምነት ሊኖረው ይገባል።

እምነት የነገር ሁሉ ቁልፍ ስለ ሆነ ማላጁ እግዚአብሔርን የሚያስደስትበት ታላቅ መንፈሳዊ

መርህ ነው። ማላጁ ለእምነቱ ማደግ የእግዚአብሔርን ቃል መስማት ሊወድድ ግድ ነው።

እምነት ያለ እግዚአብሔር ቃል መስማት ፈጽሞ አይመጣም።

ምልጃ 2016

53 www.tlcfan.org

6ኛው ደረጃ፦ የሚማልደው ለሰጋው መሞት አለበት

በእግዚአብሔር ቃል እንደ ምንመለከተው ሰለ እኛ የሚማለደውና የማለደው

ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰው ልጆች ሁሉ ሃጢያት ምትክ ሆኖ እንደ ሞተ እናውቃለን። እንደ

ክርስቲያን ደግሞ ኢየሱስን በሞትም ሆነ በትንሳኤ እንድንመስለው ተጠርተናል። ሮሜ.6፥

4,5 ጳውሎስ ይህን ሰለ ጥምቀት በተናገረ ጊዜ ግልጽ አድርጎ አስቀምጦታል።

“ 4 እንግዲህ ክርስቶስ በአብ ክብር ከሙታን እንደ ተነሣ እንዲሁ

እኛም በአዲስ ሕይወት እንድንመላለስ፥ ከሞቱ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ በጥምቀት

ከእርሱ ጋር ተቀበርን። 5 ሞቱንም በሚመስል ሞት ከእርሱ ጋር ከተባበርን

ትንሣኤውን በሚመስል ትንሣኤ ደግሞ ከእርሱ ጋር እንተባበራለን፤

6 ከእንግዲህስ ወዲያ ለኃጢአት እንዳንገዛ የኃጢአት ሥጋ ይሻር ዘንድ

አሮጌው ሰዋችን ከእርሱ ጋር እንደ ተሰቀለ እናውቃለን፤

የሞተስ ከኃጢአቱ ጸድቋልና።”

የሚደንቀው የእግዚአብሔር አሰራር ግን እኛ የሰው ልጆች ለሰራነው ሁሉ

ሃጢያት እኛን ተክቶ የሞተው ኢየሱስ መሆኑ ነው። ሰዎች ሰለ ሰዎች በታሪክም በዓለም

ያሉ ሰዎች ቢሆኑ በቤቱ ያሉ ቅዱሳን ለሰው ብለው ሞተዋል ያም ራሱን የቻለ የምልጃ

ሌላው ምሳሌ ክፍል ነው። ይሁንና ለሰው ሃጢያትና በደል ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ

በመሰቀል ላይ የሞተውና ከሙታን ሞትን ድል አድርጎ የተነሳው ደግሞ በክብር ወደ አባቱ

ያረገው ዳግም መንግስቱን ይዞ በስልጣን ወደ ምድር የሚመለሰው ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ

ነው።

እግዚአብሔር የሚማልዱለትን ሰዎች ሲጠራ ግን እንደ ኢየሱስ አይነት የከፋ

ነገር እንዳይደርስባቸው ሁሌ ይጠብቃልቸዋል። ይጠነቀቅላቸዋል። ይህን ሕይወት እንዲያፉ

ከተሰጣቸው ከጥቂት ሰዎችና ሐዋሪያት በቀር በአሁን ዘመን የምንቀበለ ማንኛውም አይነት

መከራ ጊዚያዊና ከእነርሱ የቀለለ ነው። ማላጁ ሊሄድበት ከሚችለው በላይ እግዚአብሔር

ሊያስኬደው ወይም ሊፈትነው አይወድድም። ብዙ በሞት ዙሪያ ያለው ምልጃ የማላጁን

በፍቃደኝነት ነፍሱን በእግዚአብሔር እጅ ላይ አሳልፎ መስጠትን ይጠይቃል እንጂ ሁሉ

ማላጅ በሥጋ እንዲ ሞት የእግዚአብሔር ፍቃድ አይደለም። ይህ ለተሰጣቸው ሰማዕታት

እንዲሆኑ ለተመረጡ ብቻ ነው።

ምልጃ 2016

54 www.tlcfan.org

እግዚአብሔር አንድን ሰው ለሞት ምልጃ ከጠራው የሚጠራው የዚህ ሰው

የምድር ሩጫ ያበቃ ከሆነ ብቻ ነው። ነገር ግን እኔ በዚህ መጽሐፍ የማላጁ ሰው ሞት ብዮ

ልናገርበት የምወደው ሞት ማልጁ ለሥጋዊ ባሕሪ (flesh) የሚሞትበትን ሞት ነው።

ጥምቀት የመጠመቃች አንዱ ምክንያት ኢየሱስን በሞቱና በትንሳኤል

እንመሰልው ዘንድ ከእርሱ ጋር ለመሳሰልና ለመተባበር አንድ ለመሆን ነው። ከእርሱ ጋርም

በጥምቀት ተባበርን። ደግሞም ሁል ጊዜ የሚማልድ ሰው የእግዚአብሔርን ድምጽ

በሚሰማበት ወቅት የሚሰማው ነገር ከሥጋዊ አዕምሮ ወይም ከነፍሱ ሃሳብ ጋር የሚቃረን

ሰለ ሆነ በእርሱ ሥጋዊ አዕምሮ ላይ ሞትን የሚያመጣ ሃይልን የሚሰጥ ድምጽ ነው።

ለድምፁ እሺ ካለ ነፍሱን ለእግዚአብሔር መንፈስና ለመንፈሱ ያስገዛል። ነፍሱ

ይህን ነገር ላለመቀበልና የራሳስዋን ግዛት ቃል ከፍ ለማድረግ ከመንፈስ ጋር ትታገላለች።

ነገር ግን የሚማልደው ሰው በመንፈሱ የሰማውን የእግዚአብሔር ድምፅ አጽንቶ ቢይዝ

በውጡ ያለ ማንኛውም የነፍስ ሃሳብ መሞት ይጀምራል። ሰዋዊ አዕምሯችን ከመታዘዝ

በፊት ምን እንደሚሰራ ምን እንደሚሆን ቀድሞ ሰራው ከመስራቱ በፊት ማወቅና መረዳት

ሁል ጊዜ ይወዳል። የእምነት ሕይወት ደግሞ የዚህ ተቃራኒ ነው።

መንፈሳችን ግን ምንም ባይረዳ እንኳን እግዚአብሔር በማመን ራሱን ከቃሉና

ከድምፁ በታች በማስገዛት ይታዘዛል። ሁል ጊዜ ማላጁ የሥጋዊ ሃሳብና የነፍሱን ሃሳብ

ሲክድ ለመንፈሱ ብቻ አሜን እሺ ብሎ ሲታዘዝ ማንኛውንም የሥጋዊ ሃሳብ ከእግሩ በታች

መርገጥ ይጀምራል። ይህም በእግዚአብሔር ችሎታ የሚደረግ ነገር ነው። ባቢሎናዊ ሃሳብ

ሁሉ በኢየሩሳሌማዊ በእግዚአብሔር ሃሳብ ፈጽሞ ይገዛል።

የሰው መንፈሱ የእግዚአብሔር ማደሪያ ነውና መንፈሳችን እግዚአብሔርን

ሊጠራጠር ፈጽሞ አይወድም። የሚጠራጠሩ ነፍሳችንና ሥጋዊ አዕምሯችን ናቸው።

እግዚአብሔርን በመታመን አማኝ ማላጅ ሰው ሥጋውን ሁሌ “flesh” ከክርስቶስ ጋር

ይሰቅላል። በእግዚአብሔር ላይ ማጉረምረምን ሆነ ለምን የሚባል ጥያቄ ከአንደበቱ ፈጽሞ

ይጠፋ ዘንድ ራሱን ለእግዚአብሔር ያስገዛል። ይህ የሆነለት ሰው በሥጋ ቢኖር እንኳን

የሞተ ክርስቲያን በመባል ይታወቃል። ማላጁ ለሰዋዊ ለነፍስ ሃሳብና ለሥጋዊ ሃሳብ መሞት

ያለበት ከሞት በመነሳት በላዮ ላይ የትንሳኤል ሃይል እንዲገለጥ ለማድረግም ጭምር ነው።

ይህ ትንሳኤ ግን መንፈሳዊ ትንሳኤ ነው። በየእለቱ የሚነሳው ትንሳኤ ነው።

ምልጃ 2016

55 www.tlcfan.org

እነዚህ ከላይ ያየናቸው ስድስት የማላጁ ሕይወት ኑሮ ደረጃዎች ብዙዎች

ምልጃን ቀላል እንደሚያደርጉት እንዳልሆነ እድንረዳ ያደርጉናል ብዮም አምናለሁ።

የምልጃ ሕይወት በጣም ከእኛ የሚጠይቀው ነገር አለው። ነገር ግን እግዚአብሔር ለምልጃ

የጠራቸው ሳያውቁም በምልጃ ሕይወት ያሉ ቢሆኑ ከአሁን በኃላም ምልጃን ለመለማለድ

ለሚፈልጉ ሁሉ ከእግዚአብሔር ዘንድ ሽልማት የሥራቸው ዋጋ ከታላቅ ክብር ጋር

ተዘጋጅቷል። ሁሉ የሰራበትን ደሞዝ በጊዜው ይቀበላል። ደሞዛችን ግን ከእግዚአብሔር

ብቻ እንዲሆንልን ከሰው አንዳችን አንቀበል ያለን ይብቃን። በኪስ ከሚገባና ከሚጠፋው

ጊዚያዊው ደሞዝ ይልቅ የማይጠፋውን በሰማይ ባንክ በእግዚአብሔር ዘንድ እናጠራቅም።

ከዚህ በመቀጠል በመጨረሻ በጥቂቱ እንድንመለከት የምፈልገው እግዚአብሔር

ያዘጋጀውን ሽልማት ምን እንደሆነ ነው። ይህም የእግዚአብሔር ለድል ነሺዎች የሚሰጠው

ታላቁ ሽልማት የሆነው ትንሳኤ ነው።

ምልጃ 2016

56 www.tlcfan.org

ትንሳኤ

“5.ሞቱንም በሚመስል ሞት ከእርሱ ጋር ከተባበርን ትንሣኤውን በሚመስል

ትንሣኤ ደግሞ ከእርሱ ጋር እንተባበራለን።”

ሮሜ.6፥5

የሚማልዱ ሰዎች ዋጋ ከፍለው ለሥጋቸውና ለነፍሳቸው አዕምሮ ሲሞቱ

ከእግዚአብሔር ዘንድ የሚያከብር ትንሳኤ ይዘጋጅላቸዋል። የወረዱበትን ያህል ወደ ላይ

ደግሞ ይወጡ ዘንድ ይህ የእግዚአብሔር ፍጹም ፍቃድ ነው። ይህ የትንሳኤ ጊዜ ምልጃው

የወሰደውን ጊዜና ወቅትም የሚመልከት ነው።

ለሕዝቅኤል ምልጃውና ሞቱ የቆየበት 390 ቀን ለእስራኤልና 40 ቀን ለይሁዳ

ቤት ነው። በጠቃላይ 430 ቀን ነው። ለኢሳያስ ምልጃው የወሰደበት ጊዜ ሦስት ዓመት

ነው። ለሆሴዕ የወሰደው የጋብቻ ጊዜውን በሙሉ ነው።

ለምሳሌ ኢየሱን ደግሞ ብንመለከት እራሱን ለዮሐንስ ሊጠመቅ ካቀረበበት ቀን

አንስቶ እስከ ትንሳኤ እስከሚሆንበት ቀን ድረስ ሦስት ዓመት ተኩል የቆየ ነበር።

ከትንሳኤው በፊትም ለሦስት ቀን ያህን በመቃብርም ቆይቷል።

ምንም እንኳን መሞት የምልጃ ሕይወት ክፍል ቢሆንም እግዚአብሔር ግን

ትንሳኤን ለማላጁ እንደ ስጦታ አዘጋጅቷል። ይህ ትንሳኤ በሥጋም ሆነ በነፍስ በመንፈስ

የሚገለጥ ነው። ለምሳሌ ለሕዝቅኤል፣ ለኢሳያስና ለሆሴዕ በነፍስና በመንፈስ የሆነ ትንሳኤ

ነበር። ነገር ግን ሁሉ ያንቀላፉ ማላጆች የሥጋን ትንሳኤ ደግሞ ይቀበሉ ዘንድ ገና ይጠብቁ

ዘንድ አላቸው። ኢየሱስ ግን በሁሉ ትንሳኤን ተቀብሎ ለእኛ እውነትኛ የትንሳኤ ምሳሌና

መልክ ሆነ። ትንሳኤ የእግዚአብሔር ድል ለሚነሱና በትክክለኛ ሕይወት ውስጥ ለሚመላለሱ

ማላጆች የሚሰጠው ደሞዝም ጭምር ነው። ዕብ.2፥9,10

“9 ነገር ግን በእግዚአብሔር ጸጋ ስለ ሰው ሁሉ ሞትን ይቀምስ ዘንድ፥

ከመላእክት ይልቅ በጥቂት አንሶ የነበረውን ኢየሱስን ከሞት መከራ የተነሣ

የክብርና የምስጋናን ዘውድ ተጭኖ እናየዋለን። 10 ብዙ ልጆችን ወደ ክብር

ሲያመጣ የመዳናቸውን ራስ በመከራ ይፈጽም ዘንድ፥ ከእርሱ የተነሣ ሁሉ

በእርሱም ሁሉ ለሆነ፥ ለእርሱ ተገብቶታልና። 11-12 የሚቀድሰውና

የሚቀደሱት ሁሉ ከአንድ ናቸውና።”

ምልጃ 2016

57 www.tlcfan.org

ብዙዎች የሚበልጠውን ትንሳኤ ለማግኘት በመጋዝ ተሰንጥቀዋክል በጥቅሉ

ሰማዕታት ሆነዋል። ይህም ለሌሎች ሲማልዱና እግዚአብሔር ሲያገለግሉ ነው። ኢየሱስ

ደግሞ በእርሱ መከራ ብዙ ልጆችን ወደ ክብር አምጥቷል። ኤፌ.4፥8

“8 ስለዚህ። ወደ ላይ በወጣ ጊዜ ምርኮን ማረከ ለሰዎችም ስጦታን ሰጠ

ይላል። 9 ወደ ምድር ታችኛ ክፍል ደግሞ ወረደ ማለት ካልሆነ፥

ይህ ወጣ ማለትስ ምን ማለት ነው? 10 ይህ የወረደው ሁሉን ይሞላ

ዘንድ ከሰማያት ሁሉ በላይ የወጣው ደግሞ ያው ነው፣”

“He led captive a host of captives and He gave gifts to men.” Eph. 4:8

ኢየሱስ ምርኮኛ የነበሩትን በሞቱ ነጻ አውጥቷል። በዚያን ዘመን ወጉ እንዲህ

ነበር። አንድ ሰው አንድን ሰው ቢያድነው የዳነው ሰው ላደነው ሰው ራሱን ያስገዛ ወይም

የእርሱ ሕይወት ባለቤት ያዳነው ሰው እንደ ሆነ ይቆጠር ነበር።

አንድ ጀነራል መጥቶ አንድን ከተማ ቢወርና ቢያሸንፋት በሕይወት

የተረፉትንም በነጻ እንዲኖሩ ቢፈቅድላቸው ነገር ግን ሌላ ጀነራል መጥቶ ጀነራሉን ገጥሞ

ቢያሸንፈው ሁሉ ለሁለተኛው ጀነራል ላሸነፈው ጀነራል ይሆናሉ። ጀነራሉም በእስር ለነበሩ

ነጻ ሲወጡ ከመጀመሪያው ጀነራል በጦር የበዘዘውን በስጦታ ለሕዝቡ ያከፋፍላል።

ይህም እያንዳዱ በግዞት ያለ ወደየቤቱ እንዲመለስና ሕይወቱን በተቀበለው

ስጦታ እንዲመራ እንዲያስተዳድር ነው። ኢየሱስ ሞት የሚባለውን ጀነራል በማሸነፍ ለእኛ

ደግሞ ስጦታን ሰጠን። ከአዳም ሃጢያት ጀምሮ በባርነት ሞት ይዞን የነበረንን ኢየሱስ

በሞቱ ከሞት ግዛት ሥር አስለቀቀን። ኢየሱስ ሁላችንን ነጻ አወጣን።

ከዛም ኢየሱስ የመንፈስን ሰጦታና መንፈስ ቅዱስን ከአባቱ ተቀብሎ ለእኛ

ሰጠን። ይህም ወደ ምድራች እግዚአብሔር ተስፋ ወደ ገባልን ምድር እንድንመለስ

መያዢያ ማሕተም ወይም ቀብዲ ነው። ኢየሱስ ለዓለም ሕዝብ እንዳደረገ ሁሉ ሕዝቅኤል

ደግሞ ለእስራኤላዊያን አደረገ። ጊዜውም ሲፈጸም የትንሳኤ ጥላ በሆነው ቃል መሰረት

ከተኛበት ተነስቶ በሕዝቡ መሃል ቆመ። በፋንድያ የተጋገረን ዳቦ መብላትን አቆመ። ይህን

በማድረጉ ደግሞ እስራኤል ሁሉ በእግሩ እንዲቆም እንዲነሳ ትንሳኤ እንዲሆንለት እስራቱና

ቀንበሩ ሁሉ እንዲፈታ ትንቢታዊ ጥላን ጥሎ አለፈ።

ምልጃ 2016

58 www.tlcfan.org

ይህ ደግሞ ሕዝበ እስራኤል በሰማያዊው መና እንዲመገቡ ተስፋን ጥሎላቸው

አለፈ። እስራኤል የሕዝቅኤል ትንቢት ሲፈጸም የስው ትምህርትና ዶክትሪን ሰዋዊ ሃሳብ

የአባቶች ወግ የምትበላበት ቀን ያከትምላታል። ይህ በመጪውም ዘመን የሚፈጸምም

ትንቢት ነው።

ይህ የምልጃ ዋጋና ደሞዝ ነው። ሕዝቅኤልም ብዙ በባርነት የነበሩትን

በምልጃው ነጻ አወጣ። የእግዚአብሔርንም ስጦታ ተቀብሎ ለሕዝቡ አከፋፈለ። ይህም

ሕዝቡ ሁሉ ከግዞት ወጥቶ የእግዚአብሔር መገኘት ወዳለበት ወደ ኢየሩሳሌም ይሰብሰብ

ዘንድ ነው። ይህችም የሰላም ከተማ ነች።

ሕዝቅኤል በዚያን ወቅት አማኝ እንደ ነበር ግልጥ ያለ እውነት ነው። ስለዚህም

ሁሉ በሕዝቅኤል ሕይወት ያለፈው ነገር ሁሉ ቀዳሚ ተወዳሽና ተመስጋኝ ሊሆን የሚገባው

በሕዝቅኤል ሕይወት ውስጥ የተገለጠው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እርሱ ከፍ ባለ

ወቅት ሁሉ ከእርሱ ጋር እንድ የሆኑ አካላቸውን ለእርሱ የሰጡ ሁሉ ደግሞ አብረውት ከፍ

ከፍ ማለታቸው ፈጽሞ የማይቀር ነገር ነው።

እግዚአብሔር ሰውን ሁሉ አይባርክም ስጦታም አይሰጥም እያልኩ አይደለም።

እግዚአብሔር ምንም እንኳን ያለ እርሱ አንዳች ነገር ሊያደርጉ ባይችሉም እንኳን

እግዚአብሔር ባሪያዎቹን ማክበርና ከፍ ማድረግ ያውቅበታል። ይህ ባሪያዊቹን

የሚያከብርበትና የሚሾምበት ሹመት ከሌሎቹ ፈጽሞ የሚለይ ነው።

ብዙ አማኞች ለምን መንፈሳዊ ውጊያና መከራ እንደሚከታተላቸው ያስባሉ

በሚሆነውም ነገር ይደነቃሉ። ራሳቸውንም ሆነ የቀረቧቸውን የእግዚአብሔር ባሪያዎች

ይጠይቃሉ። እግዚአብሔር ከመከራቸው ሁሉ ሊያድናቸው ለምን ጩኸታቸውን

እንደማይሰማ ይጠይቃሉ። መልሱ ግን እነዚህ ሰዎች ለምልጃ የተጠሩ በምልጃ ውስጥ ያሉ

ነገር ግን የምልጃ ሰዎች መሆናቸውን የማያውቁ ሰዎች መሆናቸውን መገንዘብ ነው። ይህም

የሚመጣባቸው ሁሉ ሰለ ራሳቸው ሃጢያትና በደል ላይሆን ይችላል። ስለሌላው በመማለድ

የሚማልዱለት ሰው ሕይወትና መከራ በምልጃ ወቅት ስለሚካፈሉ ነው።

ሰለዚህ ቤተክርሲያን ሰለ ሚጸልዮላቸው ዘመዶች ይህ መከራ እነርሱን

አግኝቷቸዋል። ይህ በእነርሱ ላይ የተጫነው ቅጣት ማብቂያ ዘመን አለው። ይህ ሲሆን

ለእነርሱም ሆነ ለሚማልዱላቸው ሰዎች ፍጹም ነጻነት ይሆናል።

ምልጃ 2016

59 www.tlcfan.org

አሰተውሉ በብሉይ ኪዳን የነበረው የእኛ ምሳሌ የሆኑት ካህናት ስለ እራሳቸው

ብቻ ሳይሆን ሰለ ሕዝቡም ሃጢያት ራሳቸው መስዋዕቱን ያቀርቡ ነበር። ዋናው ግን እንደ

ሳሙኤል መማለድ የሚገባን ለማን እንደ ሆነ ማወቅ መከራችንን ያቀለዋል። ሳሙኤል

ለሳኦል መማለድ እንደማይገባው እግዚአብሔር አስታወቀው። ስለዚህም ለእርሱ በመማለድ

ጊዜውን ከማጥፋትና ከንቱ መከራን ከመቀበል እግዚአብሔር በመስማት ተረፈ። ስለዚህም

ምልጃ በእግዚአብሔር ድምጽ ምሪት ሊሆን ፈጽሞ ይገባዋል።

የብሉይ ኪዳን ካህናትና የመቅደሱ አግልጋዬች ከሃጢያተኛው ሸክም

መካፈላቸንም ለማሳየት ከተሰዋውን መስዋዕት ሥጋውን ይበሉ ነበር። ይህ የሚያሳየው ከላይ

እንዳየነው የሌሎችንም በደል መሸከም ነው። ሁል ጊዜ ግን አንሸከምም። የተሸክምነው

የእኛም ሆነ የሰዎች ሸክም ከላያችን ላይ የሚንከባለልበት ቀንና ዘመን አለው። ስለዚህም

ልንማልድ የተጠራን የተጠራንለት ጥሪ ምንም እንኳን ከባድ ቢሆን ፍጻሜው ከመከራው

ሁሉ ይልቅ ከፍ ያለና በክብር ስለሚሆን አንታክት፣ አናጉረምርም፣ እግዚአብሔርን ተስፋ

እናድርገው። እግዚአብሔር ያሸከመንን እንሸከም ሸክሙ ቀሊልነውና ልባችንን

ከሚደርስብን መከራ የተነሳ አናስመርር፣ አንደበታችንንም እንጠብቅ በእግዚአብሔር ቃል

ሉጓም እናበጅለት።

ማላጆች የክህነት ሥራቸውን የሚፈጽሙ በቀዳሚነት የሚቀመጡ አማኞች

ናቸው። ይህም የራሳቸውን በደል ሳይሆን የሰውን በደል ይዘው በእግዚአብሔርና በሰው

መካከል የሚቆሙ የእግዚአብሔርን ቁጣን ፍርድ የሚያበዱ የሚያቀንሱ መካከለኞች

ናቸው።

የምልጃ ሰው ሆነን እንደ ተጠራን ከተማርነው ትምህርት የተነሳ ከተገነዘብን

ራሳችንን ማየት ከሆነልን እግዚአብሔርን እንታመን። ምንም እንኳን እግዚአብሔር

የሚሰራው ምን እንደ ሆነ ባናውቅ እንኳን እርሱን እንጠብቅ። በእግዚአብሔር እንደገፍ

እርሱን ብቻ ተስፋ እናድርግ። እግዚአብሔር ነገሩን ሁሉ አሁን በዙሪያችን ያለውን

መልካምና በጎ ያልሆነውን ነገር ሁሉ ለበጎ መቀየሩ አይቀርም። ምክንያቱም እግዚአብሔር

ጠርቶናልና ነው። ሮሜ.8፥28

ስለዚህ ራሳችንን ከልብ መራርነት እንጠብቅ ለዚህ ፈጽሞ አልተጠራንምና ነው።

እግዚአብሔር ስለ ተለያየ ነገር ለምን እያልን ከምንነዘንዝና ጉርምርምታችን በእርሱ ላይ

ከማሰማት በፊት የእግዚአብሔር ፍቅርና ምሕረት እንመልከት ዘንድ አይናችንን እንዲከፍት

ወደ እግዚአብሔር እንጸልይ።

ምልጃ 2016

60 www.tlcfan.org

የማናውቀውንና የማይገባንን ነገር እንደ ኢዮብ ተናግረን የኃላ ኃላ እግዚአብሔር

ነገሩን ሲገለብጥ አፋችንን ከመያዝ ያድነናል። በነገር ሁሉ ሰለ ምናልፍበት ስለ ሌለን፣ ስለ

ተባልነው፣ ሰለ ሚጠሉን፣ ስለ ሚነቅፉን፣ የተለያየ ነገር ሰለ ሚያደርጉን ሁሉ

እንጸልይላቸው ስለ ሁሉ ነገር እግዚአብሔር እንድናመስግነው ይገባል።

ኢየሱስ ዓለምንና በዓለም ያለውን እንዳሸነፈ እንወቅ። እርሱ ደግሞ በእኛ ውስጥ

ነው። ከእርሱም የተነሳ ከአሸናፊዎችና የቀደሙን ከመሰለን ሁሉ በላይ ቀድመን እንገኛለን፣

እንነሳለን፣ ከአሸናፊዎች በላይ ሆነን እንገለጣለን። ለሥጋችን መሞት (death of the flesh)

ራሳችንን በእግዚአብሔር እጅ ሥር ብናስገዛና ብናዋርድ እግዚአብሔር ደግሞ ከስጋዊ ሞት

በትንሳኤው ሃይል ሊያስነሳን የታመነ ብርቱ አምላክ ነው። በጊዜውም ብንዘራ በጊዜው

ደግሞ የዘራነውን ሁሉ እናጭዳለን። በውርደት ተዘርተን በክብር ደግሞ በትንሳኤ እንነሳለን።

ማራናታ!!!

........................................... ተፈጸመ ……………………………

ሌሎች መጽሐፎችን ማገኘት ከለጉ ይህ ድረ ገጽ ይጠቀሙ

www.tlcfan.org