የ‹‹ሼህ ሙሐመድ ይፈቱ›› ዘመቻ ትውስታዎች · የሚጠቅሙ...

24
MIDROC Newsletter Special Issue # 58 April 2019 Addis Ababa, Ethiopia Special Issue # 58 April 2019 A BI-MONTHLY PUBLICATION OF THE OFFICE OF THE CHIEF EXECUTIVE OFFICER This Newsletter provides customers, employees, suppliers, shareholders and the community at large with current information on major performance and other activities of the companies under the leadership of the CEO Special Issue # 58 የ‹‹ሼህ ሙሐመድ ይፈቱ›› ዘመቻ ትውስታዎች

Upload: others

Post on 30-Oct-2019

22 views

Category:

Documents


0 download

TRANSCRIPT

Page 1: የ‹‹ሼህ ሙሐመድ ይፈቱ›› ዘመቻ ትውስታዎች · የሚጠቅሙ እንደ ህዳሴ ግድብ ላሉ ሜጋ ፕሮጀክቶች ግንባታ፣ ለስፔስ

MIDROC NewsletterSpecial Issue # 58 April 2019

1Addis Ababa, Ethiopia

Special Issue # 58 April 2019

A BI-MONTHLY PUBLICATION OF THE Office Of the chief executive OfficerThis Newsletter provides customers, employees, suppliers, shareholders and the community at large with current information

on major performance and other activities of the companies under the leadership of the CEO

SpecialIssue # 58

የ‹‹ሼህ ሙሐመድ ይፈቱ›› ዘመቻ ትውስታዎች

Page 2: የ‹‹ሼህ ሙሐመድ ይፈቱ›› ዘመቻ ትውስታዎች · የሚጠቅሙ እንደ ህዳሴ ግድብ ላሉ ሜጋ ፕሮጀክቶች ግንባታ፣ ለስፔስ

MIDROC NewsletterSpecial Issue # 58 April 2019

2Addis Ababa, Ethiopia

ማውጫ

ገጽ

• መግቢያ

ሼህ ሙሐመድ ሁሴን አሊ አል አሙዲ ማን ናቸው? .............................. 1

• አስደንጋጩ ዜና....................................................................................... 1

• የ‹‹ሼህ ሙሐመድ ይፈቱ›› ዘመቻ መጀመር ............................................... 2

• በቺፍ ኤግዚኪዩቲቭ ኦፊሰር በኩል የተደረጉ ጥረቶች ................................ 10

• የሼህ ሙሐመድ መለቀቅ ....................................................................... 13

• በመቻሬ ኮርፓሬት ሴንተር የነበረ የደስታ ድባብ ....................................... 17

• ከጥረት (TIRET) መጽሔት የተገኘ ......................................................... 20

• ማጠቃለያ ............................................................................................ 21

Page 3: የ‹‹ሼህ ሙሐመድ ይፈቱ›› ዘመቻ ትውስታዎች · የሚጠቅሙ እንደ ህዳሴ ግድብ ላሉ ሜጋ ፕሮጀክቶች ግንባታ፣ ለስፔስ

MIDROC NewsletterSpecial Issue # 58 April 2019

1Addis Ababa, Ethiopia

የ“ሼህ ሙሐመድ ይፈቱ” ዘመቻ ትውስታ

መግቢያ

ሼህ ሙሐመድ ሁሴን አሊ አል አሙዲ

ማን ናቸው?

ሼህ ሙሐመድ ሁሴን አሊ አል-አሙዲ የሚድሮክ

ቴክኖሎጂ ግሩፕ አባል የሆኑትን ሃያ ስድስት

ኩባንያዎችን ጨምሮ ከ75 ያላነሱ ልዩ ልዩ

ኩባንያዎችን የያዘው የሚድሮክ ኢትዮጵያ

ኢንቨስትመንት ባለቤትና ሊቀመንበር ናቸው፡፡

ሼህ ሙሐመድ በአገራችን በተለያዩ የኢኮኖሚ ዘርፎች

በተሰማሩ እነዚህ ኩባንያዎች ከመቶ ሺህ ለማያንሱ

ኢትዮጵያውያን የሥራ ዕድሎች የፈጠሩ ናቸው፡፡

ከዚህም ሌላ ኩባንያዎቹ ግብር፣ ታክስ፣ ሮያሊቲና

የመሳሰሉትን ለመንግሥት የሚከፍሉ በመሆኑ

ከዚህም አቅጣጫ ሼህ ሙሐመድ በኢትዮጵያ ፈር

ቀዳጅ ኢንቨስተርነትና የኩባንያዎች ባለቤት በመሆን

ለኢኮኖሚ ዕድገቷ የበኩላቸውን የጎላ አስተዋጽዖ

እያደረጉ ያሉ ናቸው፡፡

ሼህ ሙሐመድ ለአገራችን የኢኮኖሚ ዕድገት

በኢንቨስተርነታቸው አስተዋጽዖ እያደረጉ ብቻም

ሳይሆን በኩባንያዎቻቸው አማካኝነት የማህበራዊ

ኃላፊነትን በመወጣት በመልካም ፈቃድና ልግስና

የሚያበረክቱት ድጋፍ በኢትዮጵያ ህዝብ ዘንድ

መልካም ስምና ዝና ያሰጣቸው ነው ማለት ይቻላል።

በዚህም ረገድ ሼህ ሙሐመድ ለአገርና ህብረተሰቡ

የሚጠቅሙ እንደ ህዳሴ ግድብ ላሉ ሜጋ ፕሮጀክቶች

ግንባታ፣ ለስፔስ ኦብዞርቫቶሪና የምርምር ማዕከል

መቋቋም፣ ለትምህርት ቤቶች መቋቋምና መስፋፋት፣

በጤና ረገድም እንደ የልብ ህክምና ማዕከልን

ማቋቋም፣ እንዲሁም በጤና ምክንያት ህክምና

ለሚያስፈልጋቸው ለተቸገሩ ታዋቂ ወገኖቻችን

በተለይ የውጭ አገር ህክምና እንዲያገኙ መታደግ፣

በድርቅ ለተጎዱና ከአካባቢያቸው ለተፈናቀሉ ወገኖች

ድጋፍና መቋቋሚያ እንዲያገኙ ማድረግ፣ የአገሪቱን

ስፖርት እንዲያድግ ድጋፍ በማድረግ በኩል

በአጠቃላይ በተጠቀሱ ጉዳዮችና በሌሎችም በብዙ

ሚሊዮን የሚቆጠሩ ብሮች በማውጣት ድጋፎችን

ያደረጉ ባለሀብት ናቸው፡፡

ሼህ ሙሐመድ ሁሴን አሊ አል አሙዲ በኢትዮጵያ

እና ከኢትዮጵያ ውጭም የኩባንያዎች ባለቤት

መሆናቸው ከዓለም ቢሊየነሮች አንዱ ለመሆን

ያበቃቸው ሲሆን በቢሊየነርነታቸውም ስማቸው ሲነሳ

የኢትዮጵያም ስም አብሮ እንዲነሳ በማስቻል ለአገሪቱ

ስምና ዝና ምክንያት የሆኑ ሰው ናቸው፡፡

አስደንጋጩ ዜና

የሼህ ሙሐመድ ሁሴን አሊ አል አሙዲ ሀብት

የሆኑ ኩባንያዎች በሥራ ፈጠራ፣ በግብርና እና

በሮያሊቲ ላቅ ያለ ገንዘብ በየዓመቱ ለመንግሥት

በመክፈል ለአገራችን ኢኮኖሚ የጀርባ አጥንት በመሆን

ለአገሪቱ ልማትና ዕድገት አዎንታዊ ሚናቸውን

እየተወጡ ባለበት ሁኔታ በህዳር ወር 2010 ዓ.ም.

ከዓለም አቀፍና ከአገር ውስጥ የዜና አውታሮች

የሳዑዲ አረቢያ መንግሥት ቁጥራቸው በዛ ያለ

የሳዑዲ አረቢያ ልዑላን ቤተሰቦች፣ ባለሥልጣናትና

ባለሀብቶችን ሊቀመንበራችንን ጭምር በታላቁ

የሪትዝ ካርልተን ሆቴል እንዲቆዩ ተደርጐ ምርመራ

እየተደረገባቸው ስለመሆኑ ዜናው ተሰማ፡፡ ይህም

ዜና በተለይ ለሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ኩባንያዎች

Page 4: የ‹‹ሼህ ሙሐመድ ይፈቱ›› ዘመቻ ትውስታዎች · የሚጠቅሙ እንደ ህዳሴ ግድብ ላሉ ሜጋ ፕሮጀክቶች ግንባታ፣ ለስፔስ

MIDROC NewsletterSpecial Issue # 58 April 2019

2Addis Ababa, Ethiopia

ዶ/ር አረጋ ይርዳው ንግግር ሲያደርጉ ለሠራተኞች

የማኔጅመንት አባላትና ሠራተኞች አስደንጋጭና

አሳዛኝ ነበር፡፡

ከዚህም አንጻር የቴክኖሎጂ ግሩፑ ቺፍ ኤግዚኪዩቲቭ

ኦፊሰርና ፕሬዚዳንት የሆኑት ዶ/ር አረጋ ይርዳው

‹‹አለቃዬ፣ ወንድሜ፣ አብሮ አደጌ›› የሚሏቸውን ሼህ

ሙሐመድን አስመልክቶ የተሰማው ነገር ከሌሎች

ይልቅ የእርሳቸውን ስሜት ይበልጥ እንደሚነካ

የሚታመን ቢሆንም እርሳቸው ግን በአርቆ አስተዋይነት

ወዲያው የቴክኖሎጂ ግሩፑን የማኔጅመንት አባላትና

አጠቃላይ ሠራተኛውን በመሰብሰብ ስለ ሼህ

ሙሐመድ በተሰማው ዜና ሳይደናገጡ ሥራቸውን

እንደተለመደው እንዲያከናውኑ፣ ኩባንያዎቹም

የየራሳቸው ሕጋዊ አመሠራረትና ሂደት ያሏቸው

መሆኑንም በመጥቀስ በተፈጠረው ችግር ሳቢያ

ሥራቸው እንደማይደናቀፍ በማስረዳት፣ ሠራተኛው

ተረጋግቶ ሥራውን በተገቢው በማከናወን፣

ከሊቀመንበራችን የተሰጠውን የሥራ ኃላፊነት

እና አደራ መወጣት እንደሚኖርበት በማስገንዘብ

አረጋግተዋቸዋል፡፡ ሠራተኛውም ከተደረገለት ገለጻ

ግንዛቤ አግኝቶ ተግባሩን ባለማስተጓጐል ሲያከናውን

ቆይቷል፡፡

የ“ሼህ ሙሐመድ ይፈቱ” ዘመቻ መጀመር

የቴክኖሎጂ ግሩፑ ኩባንያዎች ሥራ አመራር አባላትና

ሠራተኞች ሼህ ሙሐመድ ከገጠማቸው የእስር ችግር

እንዲላቀቁ የዘወትር ፍላጐትና ምኞታቸው የነበረ

ሲሆን፣ ቺፍ ኤግዚኪዩቲቭ ኦፊሰራችን የቴክኖሎጂ

ግሩፑ ኩባንያዎች አመራሮችና ሠራተኞች ሰኔ 14 ቀን

2010 ዓ.ም. በቴክኖሎጂ ግሩፑ ዋና መ/ቤት መቻሬ

ሜዳ እንዲገኙ በማድረግ የኢትዮጵያ መንግሥት

ሼህ ሙሐመድን ለማስፈታት የሚያደርገውን

ጥረት የሚያደንቁ መሆኑንና ዲፕሎማሲያዊ ጥረቱ

መቀጠል እንደሚገባው በመጥቀስ ‹‹የቴክኖሎጂ

ግሩፑ አመራሮችና ሠራተኞችም በበኩላችን ሼህ

ሙሐመድ ከእስር እንዲለቀቁ ተጽዕኖ ለመፍጠር

‹ሼህ ሙሐመድ ይፈቱ› የሚል ዘመቻ በይፋ ዛሬ

ጀምረናል›› ሲሉ አስታወቁ፡፡

በማያያዝም ዶ/ር አረጋ ሼህ ሙሐመድ ታሰሩ

ከተባለበት ዕለት ጀምሮ ከቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር

አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ጋር በጋራ በመሆን

ሼህ ሙሐመድን ለማስፈታት ዲፕሎማሲያዊ

ግንኙነት የተደረገ መሆኑን ነገር ግን በአገራችንም

ሆነ በሳዑዲ አረቢያ መንግሥት ተከስተው በነበሩ

ለውጦች ምክንያት ጉዳዩ መፍትሔ ሳያገኝ መቆየቱን

በማስታወስ ‹‹ክቡር ዶ/ር አብይ አህመድ አዲሱ

ጠቅላይ ሚኒስትር በመሆን ሥራ በጀመሩ በአጭር

ጊዜ ውስጥ ከሳዑዲ አረቢያ መንግሥት ጋር በመነጋገር

ሊቀመንበራችን እንደሚፈቱ የሰጡን ተስፋ አበረታች

ነበር በማለት ሠራተኞችም፡ እኛም የኩባንያዎቻችን

Page 5: የ‹‹ሼህ ሙሐመድ ይፈቱ›› ዘመቻ ትውስታዎች · የሚጠቅሙ እንደ ህዳሴ ግድብ ላሉ ሜጋ ፕሮጀክቶች ግንባታ፣ ለስፔስ

MIDROC NewsletterSpecial Issue # 58 April 2019

3Addis Ababa, Ethiopia

ዶ/ር አረጋ ከሠራተኞች ጋር

አለኝታ የሆኑትን የክብር ዶ/ር ሼህ ሙሐመድ ሁሴን

አሊ አል አሙዲን ለመቀበል በጉጉት እንድንጠባበቅ

አሳስበዋል፡፡ ዶ/ር አረጋ ንግግራቸውንም በመቀጠል

ታዳሚውን ‹‹ዲፕሎማሲ ግንኙነት ከፈጠርንበት

ቀን ጀምሮ ወቅታዊ ቲሸርት በአስቸኳይ በማሠራት

‹‹ሊቀመንበራችንን አንረሳም፣ ኩባንያዎቹን በአደራ

እንደተረከብን በአደራ ማስረከብ አለብን፡ በአስቸኳይ

ይፈቱልን›› በማለት ዝግጅት የተጀመረ ቢሆንም

በወቅቱ አገሪቱ ከነበረችበት ሁኔታዎች አኳያ የሰላማዊ

ሰልፍ ፈቃድ ሳናገኝ ለመቆየት መገደዳችንን፣ በርካታ

የሆኑ አጋር ድርጅቶችና ያገባናል ባይ ግለሰቦች

የሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ኩባንያዎች ሠራተኞችም

በአካል በመቅረብ ግጥሞችና ደብዳቤዎችን በመላክ

ለሊቀመንበራችን ያላቸውን በጐ አመለካከት

መግለጻቸውን›› አስረድተዋል፡፡

‹‹የኢትዮጵያ መንግሥት የገባው ቃል እንዲከበርና

ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቱም እንዲፋጠን የ‹ሼህ

ሙሐመድ ይፈቱ› ጥያቄ ዘመቻችንን እንገፋበታለን››

ያሉት ሲ.ኢ.ኦ. ሼህ ሙሐመድ ከእስር እስኪፈቱ

ድረስ እርሳቸውን ለማሰብ ስለ እርሳቸው መረጃ

ለመለዋወጥ፣ እንቅስቃሴውንም ሕዝቡ እንዲያውቀው

ለማድረግ፣ የሼህ ሙሐመድን ምስልና “Free

Mohammed” የሚል መልእክት ያለበትን ቲሸርት

አመራሩና ሠራተኛው በየኩባንያዎቻቸው በየሳምንቱ

ሁለት ቀናት በመልበስና ጧት ሥራ ከመጀመሩ

በፊት በግቢ ውስጥና ከግቢ ውጭም በአንድ ላይ

እንቅስቃሴ የሚደረግበት ፕሮግራም እንዲኖር

መወሰኑን አስታውቀዋል፡፡ በማጠቃለልም ለጠቅላላ

ሠራተኛው ሥራችንን እየሠራን ሼህ ሙሐመድን

እንድናስባቸው ያሳሰቡት ሲ.ኢ.ኦ. ‹‹ይህንንም

የምናደርገው ለእርሳቸው፣ ለህሊናችንና ለአገራችን

ነው፡፡ ዛሬም በተቀናጀና ህግን ባከበረ መልኩ

እንዲፈቱልን የምናደርገውን ጥረት አጠናክረን

እንቀጥላለን›› ብለው ነበር፡፡

Page 6: የ‹‹ሼህ ሙሐመድ ይፈቱ›› ዘመቻ ትውስታዎች · የሚጠቅሙ እንደ ህዳሴ ግድብ ላሉ ሜጋ ፕሮጀክቶች ግንባታ፣ ለስፔስ

MIDROC NewsletterSpecial Issue # 58 April 2019

4Addis Ababa, Ethiopia

ከ‹‹ሼህ ሙሐመድ ይፈቱ›› ዘመቻ ጋር በተያያዘ

በወጣው ፕሮግራም መሠረት አመራሩና ሠራተኛው

በየሳምንቱ ሁለት ቀናት እየተገናኘ ሼህ ሙሐመድን

የሚመለከቱ መረጃ ካለ ከሲኢኦአችን ሲደመጥ

ቆይቷል፡፡ ሼህ ሙሐመድ የአገራችን ፈር ቀዳጅ

ታላቁ ኢንቨስተር፣ የሀገር አለኝታ፣ ለተቸገረ አዛኝና

ለጋስ መሆናቸውን የሚያወሱ መጣጥፎችና ግጥሞች

እየቀረቡ በሠራተኞች ዘንድ የሊቀመንበራችን ስም

እየተነሳ ተግባራቸውም ሲወደስ ነበር፡፡ ሠራተኞች

ከየኩባንያዎቻቸው ግቢ በመውጣትም በቅጥር

ግቢው ዙሪያ በመታየት በአቅራቢያ የሚተላለፈው

ሕዝብ ሠራተኛው ሼህ ሙሐመድን ሁልጊዜ እያሰበ

መሆኑንና ካሉበት ሁኔታም እንዲላቀቁ ምኞትና

ፍላጐቱ መሆኑን እንዲገነዘቡ እና ሕዝቡም ለዘመቻው

የበኩሉን ድጋፍ የማድረግ ስሜት እንዲፈጠርበት

እንቅስቅሴ ያደርጉ ነበር፡፡ ኩባንያዎቹ ባሉበት ቅጥር

ግቢም፣ አጥሮችና መግቢያ በሮች ላይም “Free

Mohammed”፣ ‹‹የኩባንያዎቻችን አለኝታ ነዎት››፣

‹‹አልረሳንዎትም በልባችን ነዎት›› ወዘተ የሚሉ

መልእክቶችን የያዙ ባነሮች እንዲሰቀሉና መልእክቶች

እንዲያስተላልፉ መደረጉም ሌላው የዘመቻው

እንቅስቃሴ አካል ነበር፡፡ የ‹‹ሼህ ሙሐመድ ይፈቱ››

ዘመቻ በይፋ መጀመርም በአገር ውስጥ አንዳንድ

ሚድያዎች ለሕዝብ ተገልጿል፡፡

የ‹‹ሼህ ሙሐመድ ይፈቱ›› ዘመቻ ከያዛቸው ፕሮግራሞች መካከል መጣጥፎችን አዘጋጅቶ ሠራተኞች

እንዲሰሙት ማድረግ የነበረ ሲሆን በዚህ መሠረት በሠራተኞች ተዘጋጅቶ ለሠራተኞች ቀርበው ከነበሩ

ግጥሞች መካከል የሚከተሉትን ለአንባቢያን አቅርበናል፡፡

ሁሉ ለበጎ

ሁሉ ለበጎ ለበጎ ይሁን ብለን

እንፀልይ ሁላችን ወደ አምላካችን

ሲኖር የሰው ልጅ በዚች ምድር ላይ

ፈተና ምልካም ነው ቆም ብሎ የነገን እንዲያይ

እስኪ ወገን እንፀልይ ከልብ ከአንጀታችን

ይፈታ ዛሬ ሙሐመድ ደጉ አባታችን

አንተ ስትኖር ከመሀላችን

በተስፋ ይሞላ ጉጉ ልባችን

Page 7: የ‹‹ሼህ ሙሐመድ ይፈቱ›› ዘመቻ ትውስታዎች · የሚጠቅሙ እንደ ህዳሴ ግድብ ላሉ ሜጋ ፕሮጀክቶች ግንባታ፣ ለስፔስ

MIDROC NewsletterSpecial Issue # 58 April 2019

5Addis Ababa, Ethiopia

ስንት አረጋዊያን በአንተ ታክመው ዳኑ

ስንት ህፃናት ባንተ ታክመው ዳኑ

ሲያወሩ ሰማሁ በአይናቸው እምባ እየደገኑ

አንተ ቅን ነህ ከቅንም ቅን

ሁሌም ለዜጋህ የምትባክን

እስቲ ትንሽ ልናገር በጆሮዬ የሰማሁትን

ትንሽም ላውራ በአይን ብሌኔ ያስተዋልኩትን

ወገን ከዚህ በላይ ምን አለ ውለታ

ልጅን አስተምሮ ከማድረግ በላይ ለሀገር መከታ

አንቺስ ምነው ዝም አልሽ ተናገሪ መስክሪ ወልድያ የደጋጐቹ ሀገር

በሜዳሽ ኮርተሻል እንኳን ለኢትዮጵያ ለአፍሪካ ምድር

ዝምታው ይሰበር

ሰአታት አልፈው ሲተኩ ቀናት

ቀናቶችም አልፈው ሲተኩ ሳምንታት

ሳምንታት አልፈው ሲተኩ ወራት

ይዘነጋል ነገር ከጊዜ ብዛት

እንይ ወደ ላይ እንይ ወደ ታች

እንይ ወደ ግራ እንይ ወደ ቀኝ

ዝም አንበል ወገን ቀያሽ መሐንዲስ እንሁን

ሁሉም መፍትሄ አለው እኛ ካልቦዘን

አንድም ለፈጣሪ ለላይኛው ጌታ

መልሱን ለሚሰጠን በቅፅበት በአፍታ

አጥብቀን እንፀልይ በቅርብ እንዲፈታ

ጊዜውም የጸሎት የሱባኤ ወቅት

አብልጠን በመፆም ምንጸልይበት

ጸሎት ድልድይ ነው ለሁሉም እምነት

የሰው ልጅ ከአምላኩ ሚገናኝበት

ቸር አምላክ ይሰጣል ለጸሎትህ ምላሽ

አጥብቀን እንጸልይ ከፊቱ ሳንሸሽ

እናም ስንሄድ ሁላችን በየእምነታችን

ሁሌም እናስበው በቅን ልባችን

እስኪ ደግመን እንስጥ ምላሽ ለውለታ

ምንድነው ተጠቅሞ እንደጋን ዝምታ

ቅንነት ደግነት ሆኖ መሠላል

ያወጣሀል አምላክ ወደላይ አሀዱ እንበል

ነገም ህልመኛ ነህ ብዙ ትሠራለህ

እንደትናንት ዛሬም ታሪክ ትደግማለህ

አንተን የሚፈልግ እንደ ዋርካ ጥላ

ሚሊዮን ሕዝብ አለ ናና እስኪ በለው መላ

አምናለሁ አምናለሁ በፈጣሪ ሥራ

ነገ ተነገ ወዲያ አንተም ተደምረህ እንደማይህ ከወገንህ ጋራ

(ከዋንዛ ሠራተኛ)

ሁሌም እናስበው በቅን ህሊናችን

ሌላውም ለመንግሥት ሀገር ለሚገዛ

ነገሩን እንዳይተው በዋዛ ፈዛዛ

በጀመረው ጅምር ፈንጥቋል ደስታችን

ጅምሩን ይቀጥል ያስፈታው ይጩህ መንግሥታችን

ደጋግሞ ደጋግሞ ማስታወስ መልካም ነው

ሁሉም የሚያምረው በጊዜው ሲሆን ነው

ቢሆንም ቢሆንም ሁሉም የሚሆነው በጊዜው በወቅቱ

እንሁን ጠንካራ ሳንሰለች መሰረተ ብርቱ

ኧረ ለምን ወገን

የስራ አጋሮቼ

አይገባውም ይኸ ለሱ

መላውን እንቀይስ

መላውን ቀይስ

ዛሬውን ይፈታ

ይህ የሀገር ማገር የሀገር ባለውለታ

ዝምታው ይሰበር እናቅርብ ቅሬታ

(ከአዲስ ጋዝ ሠራተኛ)

Page 8: የ‹‹ሼህ ሙሐመድ ይፈቱ›› ዘመቻ ትውስታዎች · የሚጠቅሙ እንደ ህዳሴ ግድብ ላሉ ሜጋ ፕሮጀክቶች ግንባታ፣ ለስፔስ

MIDROC NewsletterSpecial Issue # 58 April 2019

6Addis Ababa, Ethiopia

የ‹‹ሼህ ሙሐመድ ይፈቱ›› ዘመቻ እንቅስቀሴ አስመልክተው ዶ/ር አረጋ ይርዳው የሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ቺፍ ኤግዚኪዩቲቭ ኦፊሰር ለሠራተኞች ንግግር ሲያደርጉ

የ‹‹ሼህ ሙሐመድ ይፈቱ›› ዘመቻ በተለያዩ እንቅስቀሴዎች ሲገለጽ

Page 9: የ‹‹ሼህ ሙሐመድ ይፈቱ›› ዘመቻ ትውስታዎች · የሚጠቅሙ እንደ ህዳሴ ግድብ ላሉ ሜጋ ፕሮጀክቶች ግንባታ፣ ለስፔስ

MIDROC NewsletterSpecial Issue # 58 April 2019

7Addis Ababa, Ethiopia

Page 10: የ‹‹ሼህ ሙሐመድ ይፈቱ›› ዘመቻ ትውስታዎች · የሚጠቅሙ እንደ ህዳሴ ግድብ ላሉ ሜጋ ፕሮጀክቶች ግንባታ፣ ለስፔስ

MIDROC NewsletterSpecial Issue # 58 April 2019

8Addis Ababa, Ethiopia

በሌላም በኩል በቴክኖሎጂ ግሩፑ በተጀመረው በ‹‹ሼህ ሙሐመድ ይፈቱ›› ዘመቻ መሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም

ሰው ዕድሉን መጠቀም እንዲችል www.freemohammed.org የሚል ድረ ገጽ (Website) ቴክኖሎጂ ግሩፑ

በመክፈት ይህም ስለመደረጉ በተለያዩ መንገዶች ማለትም በቴክኖሎጂ ግሩፑ ዌብሳይት፣ በጋዜጦች፣ ብሮሸሮችንም

በማሠራጨት ህዝቡ እንዲያውቀው ተደርጓል፡፡

በዚሁ መሠረት ድረ ገጹ በተከፈተ በአጭር ጊዜ ውስጥ የቴክኖሎጂ ግሩፑን ‹‹ሼህ ሙሐመድ ይፈቱ›› ዘመቻን

በመደገፍ ስለ ሼህ ሙሐመድ ያላቸውን በጎ አመለካከት ያንፀባረቁ ተሳታፈዎች ቁጥር በዛ ያለ ሲሆን ከድረ ገጹ

ከተወሰዱ አስተያየቶችም የሚከተሉት ይገኙበታል፡፡

• ዝምታ ብንመርጥም ባንችል ማንገራገር፤

እረስተን አይደለም ዕውነት ለመናገር፤

ስላልቻልን እንጂ ነው መክሰስ መደራደር፡

ሙስሊሙ በዱዓ ክርስቲያን በፀሎት፤

ሁሉም ከጎንህ ነው አትስጋ የኛ አባት፤፡

(ንጋቱ አበበ)

• ከማንም በመቅደም በዚህ በኛ ዘመን

“ኢትዮጵያዊነትን” ሲያዜም ሲያስደምመን

ለነበረው ጀግና ምን ዝም ያሰኘናል!!??

“ፍትህ ለሙሐመድ!!” መጮህ ግድ ይለናል፡፡

“ሀገሬ…..ሀገሬ ሀገሬ እናቴ

ካንቺ በላይ ማንም ሕይወት ሆነ ሀብቴ”

የሚል የቁርጥ ቀን ልጅ ማን ነበር እንደሱ!!??

የድሆቹን አባት ሙሐመድን አትርሱ!!

(ታፈሰ ሣህሌ)

• ፍትህ ለሙሐመድ ብለን ተነስተናል

እኛ ስንጀምረው አላህ ይፈጽማል

ኢትዮጵያ ሀገሬ ሞኝ ነሽ ተላላ

የታደገሽ ታስሮ የገደለሽ በላ

ለቸገረው ደራሽ ሩህሩህ ለጋሽ

ማን አለ ለወገን እንደሱ ደራሽ

ሌላ እንኳን ባናደርግ እንሁን አስታዋሽ፡፡

(ሐፊዛ መሐመድ)

• Let the government of Saudi Arabia absolve

our beloved chairman Sheikh Mohammed

Hussein Ali Al-Amoudi, the benevolent son

of Ethiopia. (DANIEL)

• አንድ ነው ለእናቱ

እስኪ ሰው ጥሩልኝ ሁለት ከወለደች ከሱ ጎን

የሚቆም

ሀገር ያፈራችው ከሁሉም የሚቀድም

ማነው ከቶ ያለ ሀገር ተቆርቋሪ

ሮጦ የሚደርስ ሰምቶ የእናት ጥሪ

ተከፋ ታረዘ ታመመ ለሁሉም ደራሽ ነሁ

የስንቶችን ህይወት በተስፋ የሞላሁ

እስላም ነው ክርስቲያን ምንድን ነው ብሔርህ

ብለሁ የማጠይቁ ልዩነት የሌለሁ

ኢትዮጵያዊነትን በውስጥህ ሰንቀሁ

ከብዙ ልጅ መሐል አንድ ነሁ ለእናትሁ

ከእልፍ አላፋት መሐል አንድ ነሁ ለእናትሁ

ከሚሊዮኖች መሐል አንድ ነሁ ለእናትሁ

ጎርፍ ገባባቸው ተጫናቸው ቆሸ

መስጠት የማትፈሩ ያገር ልጅ ደራሸ

ታረዙ ተራቡ ሆኑ ወላጅ አልባ

ትሰጣለሁ አንቱ ሁሉም እንዲበላ

ሀገራችን ትደግ ፋብሪካ ትከሉ

አልባሌ ቦታ ወጣቶች አይዋሉ

ብለሁ በማሰብ ነው ፊትኩን የመለስከው

ማነው እናቱን ወዳጅ እንዳንቱ ያለ ሰው

ማነው ሀገር ወዳጅ እንዳቱ ያለ ሰው

ስንቱ ሥራ ሰርቶ የልፋቱን ዋጋ

እንዲያገኝ ላረኩት ከአዋቂ እስከ ሎጋ

ይክፈልሁ ፈጣሪ ለዋልኩት ውለታ

እኛም ለምነናል ጤናሁንም ይስጥሁ ጉልበትሁ ይበርታ

Page 11: የ‹‹ሼህ ሙሐመድ ይፈቱ›› ዘመቻ ትውስታዎች · የሚጠቅሙ እንደ ህዳሴ ግድብ ላሉ ሜጋ ፕሮጀክቶች ግንባታ፣ ለስፔስ

MIDROC NewsletterSpecial Issue # 58 April 2019

9Addis Ababa, Ethiopia

ከቶ እንዳትበገሩ ከቶ እንዳትሸነፍ በወሬ አሉባልታ

ኢትዮጵያም አትርሳሁ ነሁ ባለውለታ

ሌት ተቀን የምትሰሩ እንቅልፍ የማተኛ

ቆራጥ የትግል ሰው የልማት አርበኛ

እድሜሁን ከጤና እንደማቱሳላአግኝተሁ ማየት ነው የምንሻው እኛአግኝተሁ ማየት ነው የምንሻው እኛ

(ሰርካለም እሸቱ)

• “free mohammed ” በደጉ ብቻ ሳይሆን በክፉ ጊዜ ውስጥም ከጐንህ ነን

(ሔለን በላይ)

• ጸሎታችን ይድረስ

ስለ ደግነትሁ ወሬው ሳይዳረስ

መልካምነትሁን መስክሬ ሳልጨርስ

አሁን በምን ጊዜ መጥፎው ፈጥኖ ይድረስ

ታሰሩ መባሉን እንዴት ልቀበልስ

መስጠት የለመደው ዕጅሁ አይታሰር

ፍቅር የሚሰጠን ቅስምሁ አይሰበር

የዋህነትሁን ለዓለም እናብስር

ላገር ፍቅር ብለሁ ብታዩ መከራ

ምንም ብተክዙ ቢደርስ ፈተና

አንድ ቀን አይቀርም መልካምነትሁም በዓለም ላይ ሲወራ

ጸሎታችን ይድረስ አምላካችን ፊት

እንባችንም ይረጭ ይደረስ ሰማይ ቤት

የሚከፋው ሆድ ነው መቸ ሆነና ፊት

ሐዘናችን ሁሉ ሆነብን ከአንጀት

ከቶ ለስንቶቹ ሆነሁን ሰበብ

እጅሁን ጠባቂ ብዙ ሚሊየን ህዝብ

ፈጣሪ እንዲፈታሁ አሁን በመሰብሰብ

ላምላክ ጥሪ አቀረብን ዛሬ እንዲትፈቱ

ጸሎታችን ምድር አይቀርብን ከንቱ

ፈጣሪ ታደገን ሼሐችን ይፈቱ

ፈጣሪ ታደገን ሼሐችን ይፈቱ

አ ሜ ን

(አሸብር ደመቀ)

• ከትላንት የሚበልጥ ከዛሬ ደግሞ የሚሻል ነገ ተስፋ

እያደርግን ሁሌም ከጐንህ ነን፡፡ “ፍትህ ለሙሐመድ

ፍትህ ለሙሐመድ ፍትህ ለሙሐመድ”

(ማስረሻ መላኩ)

• አገርን በተግባር የደገፈና ዜጎችን በችግራቸው

ወቅት የደረሠላቸው ስለሆነ ነፃ መውጣት ይገባዋል፡

እላለሁ፡፡

(ሰሎሞን ፀጋዬ)

• Sheik Mohammed Ali Al Amoudi is selfless

person who committed himself to millions

of poor people. He is in the hearts of all

Ethiopian people. King of Saudi we beg

you in the name of God to free Sheik

Mohammed Ali Al Amoudi.

(JOTE DEGEFU)

• Sheik Mohammed Hussein Al-Amoudi is a

major investor who invested inseveral sector

of the Ethiopia economy, his detention

has an impact on the well being of many

Ethiopians, so that we request, the Saudi

government to release our icon soon.

(WENDYERAD SIMEGNE )

• Everything has an end and let God

brings the end of your case soon. Free

Mohammad!!

(DANIEL DEMISSIE )

• በማይመች ሁኔታ ውስጥ በድፍረት ሀገራቸው

ላይ መዋእለ-ነዋያቸውን በማፍሰስ ለበርካታ ዜጎች

የስራ እድል ፈጥረዋል፡፡ በማህበረሰብ ልማት

ስራዎች ላይ ግንባር ቀደም ተሳታፊ ናቸው።

በስፖርት፤በጤና፤በትምህርት ዘርፍ የእሳቸው

እጅ ያልዳበሰው ፕሮጀክት የለም፡፡ ሌሎች ንብረት

ሲያሸሹ ፤ያለምንም ቅደመ-ሁኔታ ሀገራቸዉ ላይ

ኢንቨስት አድርገዋል፡፡ ያልተዘመረላቸዉ ብሄራዊ

ጀግናችን ናቸው፡፡ ያጎረሰንን መንከስ፤ የበላንበት

ወጪት መስበር ፤ወርቅ ላበደረ ጠጠር መመለስ

መታረም ያለበት መጥፎ ልማዳችን ነው፡፡ ሌላው

ዓለም ቢሆን ኖሮ ጉዳዩ በጦዘ ነበር፡፡ የአንድ

Page 12: የ‹‹ሼህ ሙሐመድ ይፈቱ›› ዘመቻ ትውስታዎች · የሚጠቅሙ እንደ ህዳሴ ግድብ ላሉ ሜጋ ፕሮጀክቶች ግንባታ፣ ለስፔስ

MIDROC NewsletterSpecial Issue # 58 April 2019

10Addis Ababa, Ethiopia

ሀገርን ባለሀብት ማሰር ቀጥታ የኢኮኖሚ ጦርነት

እንደማወጅ ተወስዶ የተለያዬ እርምጃ ይወሰዱ ነበር

የእኛ ነገር ……..ለማንኛውም አሁንም አልረፈደም

መንግሥት በዲፕሎሚሲው ጠንክሮ ይግፋ፤ ሕዝቡ

በተለያየ መንገድ እንዲፈቱ ለዓለም-አቀፍ ተቋማት

ድምጹን ያሰማ ፡፡

(EYOB )

• Shiek Mohammeed Hussien Al-Amoudi is

the major investor and helps Ethiopian

economy in different aspects. So free

Mohammed.

(HABTAMU GETAHUN )

• እንደ ሼክ መሐመድ ብዙ ኢትዮጵያዊያንን

በልተው እንዲያድሩ የጣረ ግለሰብ ብዙ ህመምተኛ

ኢትዮጵያዊንን ያሳከመ ሰው ኣላውቅም ለኔ ቢንያም

በለጠና ሼክ መሐመድ የዋሉልንን ውለታ መርሳት

ሰብኣዊነትን መርሳት መስሎ ይታየኛል

(ይርጋ ኪዳኑ ለገሰ)

• እውነት ለመናገር እንዳንድ ኢትዮጵያዊ ስመለከተው

ይህ ባለ ሃብት የሳኡዲ መንግስት ያደረገው ነገር

በጣም አሳዛኝ ነገር ነው። ስንት ልማት የሚያለሙ

ባለ ሃብት አሰሮ ማስቀመጥ ተገቢ አይደለም

ኢሰባዓዊነት ነው ሊወገዝ ይገባል ችግር ካለ እንኳ

በዋስትና መደራደር ሲቻል ሞራልም፤ ስነ-ልቦናም

መጉዳት ተገቢ አይደለም ፡፡ ዜግነታቸውን ወዲያ

ወርውረው በደሚወዷት ሃገራቸው ይምጡልን፡፡

(አብዱራህማን ከማል)

• Please be strong, have patience, address

your pray to Allah & make “dua”, Insha

Allah you will be free within short period of

time.

(ABDELLA SULTAN )

• Mohamed Al-Amudi, May God of heaven

and earth intervene on your issues. May the

covenant keeper God set you free for you

have done for my country. In Jesus name,

you are the reminder of the poor, lover of

our beloved country Ethiopia. Thank you

for every concerned bodies for this petition.

(TSEDEY MESFIN)

• The great billionaire hardworking Ethiopian

is very generous to help his poor people by

investing in his loved poor country Ethiopia.

He is not using his wealth to finance the

world terrorists. Let him the Honorable

Sheikh Alamoudi be released!!!

(DOCTOR G.EGZIABHER ALEMAYEHU GEZEHEY K.)

• I am always appreciating Mohammed Al-

Amoudi for his generosity and heartfelt

love for his mother land, Ethiopia. He did

and invest mega million dollar for country

projects. He will do more when he become

free in short time. Mohammed Al-Amoudi

have done to his best for Ethiopia since he

arrived to the country.

(SISAY KIFLE)

• እንደምሰማው እና እንደማየው የድሀ አባት ነዎት

ስለዚህ ለኢትዮጵያ ድሀ ህዝብ የሚያስፈልጉ አባት

ነዎት የእግዚአብሄር ፈቃድ ሆኖ በቶሎ እንዲፈቱ

እጸልያለሁ፡፡

(ማህሌት)

• Shiek Mohammeed Hussien Al-Amoudi is

the major investor and helps Ethiopian

economy in different aspects. So free

Mohammed

(KALKIDAN GETACHEW )

• ማንም ሰው በእስር እንዲገላታ አንፈቅድም የተከበሩ

ሸህ ሙሀመድ አላሙዲ የሀገር ባለሀብት ብቻ

አዛኝ ወዘተ የሚለው አይገልፃቸውም የሀገር ሀብት

ናቸው እንወዳቸዋለን እነሳሳላቸዋለን ፍቱልን

(ነቢዩ አብርሃም)

Page 13: የ‹‹ሼህ ሙሐመድ ይፈቱ›› ዘመቻ ትውስታዎች · የሚጠቅሙ እንደ ህዳሴ ግድብ ላሉ ሜጋ ፕሮጀክቶች ግንባታ፣ ለስፔስ

MIDROC NewsletterSpecial Issue # 58 April 2019

11Addis Ababa, Ethiopia

በቺፍ ኤግዚኪዩቲቭ ኦፊሰር በኩል የተደረጉ ጥረቶች

‹‹ሼህ ሙሐመድ ይፈቱ›› ዘመቻ መጀመሩ ይፋ እንደተደረገ ዶ/ር አረጋ ይርዳው በቴክኖሎጂ ግሩፑ አመራሮችና ሠራተኞች ስም ለኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር አብይ አህመድ ሰኔ 14 ቀን 2010 ዓ.ም. በቁ. CEO-GOV-2018-1183 በጻፉት ደብዳቤ

‹‹እኛ የሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ኩባንያዎች አመራርና ሠራተኞች የሀገር ባለውለታና የቁርጥ ቀን ልጅ ናቸው የምንላቸው ሼህ ሙሐመድ ሁሴን አሊ አል-አሙዲ ከጥቅምት ወር 2010 ዓ.ም. ጀምሮ እስካሁን በሳዑዲ አረቢያ እስር ላይ መሆናቸው በእጅጉ አሳስቦናል፡፡ ይህም ስሜታችን የሌሎች ኢትዮጵያውያን ስሜት ስለመሆኑ የሚያውቁት ጉዳይ ነው፡፡ ለዚህም ምስክሩ ክቡርነትዎ በተገኙበት በኢዩቤልዩ ቤተመንግሥት በሚሊኒየም አዳራሽ እና ጐንደር ከተማ በነበሩ ህዝባዊ ስብሰባዎች ህዝቡ ለሼህ ሙሐመድ ያለው በጎ አመለካከት ማንጸባረቁ ነው፡፡

ሼህ ሙሐመድ ከእስር ተፈትተው ወደ አገራቸው ኢትዮጵያ እንዲመለሱ የኢትዮጵያ መንግሥት በተለይ ጠቅላይ ሚኒስትራችን ያደረጉትን ዲፕሎማሲያዊ ጥረት እጅግ አድንቀናል፡፡ ለዚህም ከፍ ያለ ምስጋናችንን እናቀርባለን ጥረትዎ ውጤት እንደሚያስገኝም እምነታችን የፀና ነው፡፡ የሚድሮክ

ኢትዮጵያ ባለሀብትና ሊቀመንበር የሆኑት ሼህ ሙሐመድ ደህንነትና ጤንነታቸው ሳይጓደል በነፃነት ያሏቸውን ኩባንያዎች እንደወትሮው መምራት ቢችሉ እኛም ብቻ ሳይሆን ሀገራችንና ህብረተሰቡንም ይበልጥ ተጠቀሚ እንደሚያደረግ ሁሉም የሚያምንበት ነው፡፡

ስለዚህም ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ሊቀመንበራችንን አስመልክተው ‹‹ትንሽ ጊዜ ቢቆዩ እንጂ እንደሚፈቱ ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ›› ያሉት ቃል በእያንዳንዳችን ልብ ውስጥ ትልቅ ተስፋ ያሳደረ መሆኑን እየገለጽንልዎ በዚህ ረገድ በሊቀመንበራችን ሁኔታ ላይ የተፋጠነ አስደሳች ለውጥ ለማየት እንዲያበቁን በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡ ፈጣሪ አሁን የያዙትን የሰላም ችቦ ከዳር እስከ ዳር አስፋፍቶ ውድ አለቃችንም ካሉበት ፈተና እንዲታደጋቸው እንጸልያለን››

ብለዋል፡፡ በቀጣይም ዶ/ር አረጋ ክቡር ጠ/ሚ ዶ/ር አብይንም በግንባር ሁለት ጊዜ አግኝተው ጥያቄያቸውን አጠናክረው ገልጸዋል፡፡ ደብዳቤውም በመንግሥት በኩል ሼህ ሙሐመድ እንዲለቀቁ የተደረገው ጥረት ውጤት እንዲያስገኝ ይበልጥ ጥረት እንዲደረግ የሚያሳስብ ጥያቄ ነበር፡፡

በሌላም በኩል ሼህ ሙሐመድ በቁጥጥር ስር የነበሩት በሳዑዲ መንግሥት ግዛት ውስጥ እንደመሆናቸው

በመቻሬ ሜዳና በሥራ ቦታዎች አካባቢ ‹‹ሊቀመንበራችንን ይፈቱ!!›› በሚል ድምፅ ጉዞዎች ተደርገዋል

Page 14: የ‹‹ሼህ ሙሐመድ ይፈቱ›› ዘመቻ ትውስታዎች · የሚጠቅሙ እንደ ህዳሴ ግድብ ላሉ ሜጋ ፕሮጀክቶች ግንባታ፣ ለስፔስ

MIDROC NewsletterSpecial Issue # 58 April 2019

12Addis Ababa, Ethiopia

እንዲፈቱ ከሚደረግ ጥረት አኳያ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚናም እንዳለው በማመን፣ ዶ/ር አረጋ በወቅቱ ለሚኒስቴሩ መ/ቤት ሚኒስትር ለሆኑት ክቡር ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ ሰኔ 15 ቀን 2010 ዓ.ም. በቁ. CEO-GOV-2018-1184 በጻፉት ደብዳቤ ሚኒስቴር መ/ቤቱ እና አባላቱ ሊቀመንበራችንን አስመልክቶ በቅርቡ ለተገኘው ተስፋ አጫሪ ሁኔታ አስተዋጽዖው ከፍተኛ እንደሆነና ለዚህም ከቴክኖሎጂ ግሩፑ አመራርና ሠራተኛው ምስጋና መቅረቡን በመጥቀስ፣ ሼህ ሙሐመድ እንዲፈቱ የተጀመረው ጥረት ተጠናክሮ እንዲቀጥልና የኢትዮጵያ መንግሥት የገለጸው ተስፋና የሳዑዲ መንግሥት ሼህ ሙሐመድን ከእስር ለመፍታት የገባው ቃል ፍጻሜ እንዲያገኝ የክቡር ሚኒስትሩ እርዳታ አስፈላጊ መሆኑን በመግለጽ በሳዑዲ የኢትዮጵያ አምባሳደር በኩል ያላሰለሰ ጥረት እንዲደረግ የኢትዮጵያ ፐብሊክ ዲፕሎማሲም በጉዳዩ የሚገባበት ሁኔታ እንዲመቻች መመሪያዎች እንዲሰጡ ጠይቀው ነበር፡፡

በተጨማሪም ቀደም ሲል ከክቡር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ፣ ከክቡር አቶ ደመቀ መኰንንና ከክቡር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ጋርም በመነጋገር ከፍተኛ ድጋፍ ለማግኘት የተደረገው ጥረትና መረባረብ የማይረሳ ምስጉን ተግባር ነው፡፡

በሌላም በኩል የተጀመረው ‹‹ሼህ ሙሐመድ ይፈቱ›› ዘመቻ በቴክኖሎጂ ግሩፑ ኩባንያዎች አመራርና ሠራተኞች በየሥራ ቦታቸው በሚያደርጉት እንቅስቃሴ ብቻ ሳይወሰን የሚመለከታቸው አካላት ትብብርና አስተዋጽዖም አስፈላጊ መሆኑን በማመን ቺፍ ኤግዚኪዩቲቭ ኦፊሰራችን አገር አቀፍ ለሆኑት የአሠሪ እና ሠራተኛ ማህበራት ማለትም ለኢትዮጵያ አሠሪዎች ፌዴሬሽን እና ለኢትዮጵያ ሠራተኛ ማህበራት ኮንፌዴሬሽን ሰኔ 15 ቀን 2010 ዓ.ም. በቁ. CEO-GOV-2018-1185 እና በቁ. CEO-GOV-2018-1187 ደብዳቤዎች ጽፈው ነበር። በደብዳቤዎቹም ሼህ ሙሐመድ በሳዑዲ አረቢያ በእስር ላይ ከሚገኙበት እንዲፈቱ በመንግሥት በኩል የተደረገው ዲፕሎማሲያዊ ጥረት በተወሰነ ደረጃ ውጤት እንዳስገኘ፣ በቴክኖሎጂ ግሩፑ አመራሮችና ሠራተኞች ዘንድ ሼህ ሙሐመድ በተከበረው የኢድ አል ፈጥር ጾም መፍቻ በዓል ይፈታሉ ብለው ከፍተኛ ጉጉትና ተስፋ አድርገው እንደነበርና ይህም

ሳይሆን በመቅረቱ አመራሮቹና ሠራተኞቹ ከፍተኛ ጭንቀት ያደረባቸው መሆኑን፣ በመንግሥት እና ለሚመለከታቸው አካላትም ሁኔታውን በማሳወቅ ጉዳዩ ትኩረት እንዲያገኝ እንቅስቃሴ መጀመሩን፣ ከዚህም አኳያ ከቴክኖሎጂ ግሩፑ ውጭ ያሉ አካላትም ድጋፍ ቢታከል ቴክኖሎጂ ግሩፑ ለሚያደርገው ጥረት መሳካት እጅግ የሚረዳ መሆኑ ታምኖበት ፌዴሬሽኑ እና ኮንፌዴሬሽኑ አጋር በመሆን ለጥረቱ ውጤታማነት ከቴክኖሎጂ ግሩፕ ጐን እንዲቆሙ፣ የተቻላቸውን የግንዛቤ ማስጨበጥና የአቤቱታ ሥራ እንዲያደርጉ ትብብር ጠይቀው ነበር፡፡

ቺፍ ኤግዚኪዩቲቭ ኦፊሰሩ በቀጣይም ሼህ ሙሐመድ ከእስር እንዲፈቱ ጫና ለመፍጠር አጋጣሚዎችን በመጠቀም ተጽዕኖ የሚፈጥሩ መልእክቶችንም ያስተላልፉ ነበር፡፡ በዚህም ረገድ ተጠቃሽ የሚሆነው የዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ ሐምሌ 21 ቀን 2010 ዓ.ም. ለ35ኛ ጊዜ ያሠለጠናቸውን ተማሪዎች ሲያስመርቅ በዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንትነታቸው ንግግር ሲያደርጉ ያስተላለፉት መልእክት ነው፡፡ ዶ/ር አረጋ በዕለቱ ንግግራቸው ስለ ሼህ ሙሐመድ ሁኔታ በማንሳት ‹‹ያ፣ለስፖርተኛው፣ ለአርቲስቱ፣ ለደራሲው፣ ለጋዜጠኛው፣ ለተማሪው፣ ለተቸገረው፣ ወዘተ እጁን የሚዘረጋው ሊቀመንበራችን ሙሐመድ ሲያደርግላቸው የማወደስ መዝሙርና ከበሮ ይመቱ የነበሩት ሁሉ አሁን ሲቸገር የት ገቡ? አፋልጉኝ! አዎ አፋልጉኝ!›› በማለት ያስተላለፉት ጥሪ ተጽእኖ ፈጣሪና የብዙዎቹን ልብን የነካ መልእክት ነበር፡፡

ቴክኖሎጂ ግሩፑ የ‹‹ሼህ ሙሐመድ ይፈቱ›› ዘመቻውን እንቅስቃሴ ያደርግ በነበረበት ወቅት ስለሼህ ሙሐመድ በጐ አመለካከት ያላቸው አካላት እንደ ወጣቶች ማህበር፣ ሚድያ፣ ድርጅቶችና ሌሎችም በጋራ በመሆን ሼህ ሙሐመድ ካሉበት ሁኔታ እንዲለቀቁ የሚቻለውን እናድርግ ሲሉ ለቴክኖሎጂ ግሩፑ ጥያቄ ያቀረቡ ነበሩ፡፡ አንዳንዶችም አጋጣሚዎችን በመጠቀም ሼህ ሙሐመድ እንዲፈቱ ያላቸውን መልካም ፍላጐት አንፀባርቀዋል፡፡

ከዚህም አንጻር የሚጠቀሰው የወልድያ ህዝብ ሰኔ 24 ቀን 2010 ዓ.ም. የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ጠቅላይ ሚኒስትርን የዶ/ር አብይ አህመድን የለውጥ ሥራዎች አስመልክቶ በወልድያ ከተማ ለምሥጋና ድጋፍ በወጣበት ጊዜ ”free mohammed” የሚሉ ባነሮችን በመያዝ

Page 15: የ‹‹ሼህ ሙሐመድ ይፈቱ›› ዘመቻ ትውስታዎች · የሚጠቅሙ እንደ ህዳሴ ግድብ ላሉ ሜጋ ፕሮጀክቶች ግንባታ፣ ለስፔስ

MIDROC NewsletterSpecial Issue # 58 April 2019

13Addis Ababa, Ethiopia

ለሊቀመንበራችን ያለውን ፍቅርና ስሜት መግለጹ ነው። በወቅቱ የሕዝባዊ ሰልፉ አስተባባሪዎች በመድረክ ላይ ባደረጉት ንግግር መንግሥት ሼህ ሙሐመድ እንደሚፈቱ በገለጸው መሠረት በአጭር ጊዜ ውስጥ በሳዑዲ ካሉበት እስር እንዲፈቱ እንዲደረግ የሕዝቡ ተወካዮች በኢዩቤልዩ ቤተመንግሥት በመገኘት ለክቡር ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አብይ ጥያቄ ማቅረባቸውን በማስታወስ ለሕዝቡ ገልጸው እንደነበር ታውቋል፡፡

በሌላም በኩል በወልድያ ሙሐመድ ሁሴን አሊ

አል አሙዲ ስታዲየም በነበረ የእግር ኳሱ ጨዋታ ውድድር መክፈቻ ሥነ ሥርዓት ላይ የወልድያ ወጣቶች ሼህ ሙሐመድ እንዲፈቱ የሚጠይቁ ባነሮች በመያዝ በስታዲየሙ ውስጥ በመንቀሳቀስና ትዕይንቶች ለሕዝብ አቅርበው እንደነበርም ታውቋል።

ይህም ሁኔታ ሼህ ሙሐመድ ከእስር እንዲፈቱ ከቴክኖሎጂ ግሩፑ ህብረተሰብ ውጪ ሌሎች ተቆርቋሪዎችም የነበሩአቸው መሆኑን ያመለክታል፡፡

የሼህ ሙሐመድ መለቀቅ

የ‹‹ሼህ ሙሐመድ ይፈቱ›› ዘመቻን የቴክኖሎጂ ግሩፑ አመራሮችና ሠራተኞች በተለያዩ መንገዶች ሲያራምዱ

ባሉበት ሁኔታ ጥር 19 ቀን 2011 ዓ.ም. ከአገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ሼህ ሙሐመድን የሚመለከት መልካም

ዜና ተሰማ፡፡

የሊቀመንበራችንን መለቀቅ ያበሰረው ዜና ሲሰማ ተዘጋጅቶ በየቦታው የተተከለው ባነር

በተጠቀሰው ቀን የተለያዩ የመገናኛ ብዙሀን እንደ ዋልታ፣ ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን (ETV) እና የአሜሪካ ድምፅን (VOA) ጨምሮ ሼህ ሙሐመድ በሳዑዲ ካሉበት እስር መለቀቃቸውን ዶ/ር አረጋ ይርዳው አረጋግጠውልናል ሲሉ ጉዳዩን በአበይት ዜናነት አቀረቡት፡፡ አያይዘውም ለሼህ ሙሐመድ ሁሴን አሊ አል አሙዲ ከእስር መፈታት የጎላ ድጋፍ ላደረጉት ለክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድና ለሌሎችም ድጋፍ ላደረጉ ሁሉ ዶ/ር አረጋ ይርዳውና ሌሎችም የሚድሮክ ኢንቨስትመንት አመራሮች አቶ አብነትና አቶ ተካን ጨምሮ የምሥጋና መልእክት አስተላልፈዋል ሲሉ የመገናኛ ብዙኋኑ አስታወቁ።

በዚህ መልኩ ዜናውን ሌሎችም የሚድያ አካላት በመቀባበል ቀኑን ሙሉ ሲያስተላልፉ ቆይተው እንደነበር ይታወሳል፡፡

የሼህ ሙሐመድን ከእስር መለቀቅ አስመልክቶ በአገር ውስጥ ዜናውን ካሰራጩት ቀዳሚው ዋልታ ቴሌቪዥን ነበር፡፡ ዋልታ ቴሌቪዥን በጥር 19 ቀን 2011 ዓ.ም. የቀን ዜናው ‹‹ሼህ ሙሐመድ ሁሴን አሊ አል አሙዲ ከእስር ተለቀቁ›› ባለሀብቱ ከእስር መለቀቃቸውን የሚድሮክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር አረጋ ይርዳው ለዋልታ ቴሌቪዥን ገልጸዋል ሲል ዜናውን አስደምጧል፡፡

Page 16: የ‹‹ሼህ ሙሐመድ ይፈቱ›› ዘመቻ ትውስታዎች · የሚጠቅሙ እንደ ህዳሴ ግድብ ላሉ ሜጋ ፕሮጀክቶች ግንባታ፣ ለስፔስ

MIDROC NewsletterSpecial Issue # 58 April 2019

14Addis Ababa, Ethiopia

ቴሌቪዥኑ በማያያዝም የሳዑዲ መንግሥት ዋና ዋና የልዑላን ቤተሰቦች ጨምሮ በርካታ የሀገሪቱን ቱጃሮች ማሰሩንና የሼህ ሙሐመድን መታሰር ተከትሎ እርሳቸውን ከእስር ለማስፈታት የኢትዮጵያ መንግሥት በርካታ ዲፕሎማሲያዊ ጥረት ማድረጉን፣ ለአብነትም ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ በሳዑዲ አረቢያ ይፋዊ ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት የሳዑዲ መንግሥት ሼህ ሙሐመድን እንዲለቅ መጠየቃቸውንና ከፍተኛ የዲፕሎማሲያዊ ጥረት እያደረጉ ስለመሆናቸውም ከጉብኝታቸው መልስ መግለጻቸውን ጠቅሶ፣ ከዚሁ ጋር በተያያዘ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ‹‹ሼህ አል አሙዲንን በሚመለከት እንደ ሀገር ያለንን ጽኑ አቋም አመላክተናል ለእኛ ሀብታምም ደሀም ዜጋ ነው፡፡ ሼህ ሙሐመድ አሊ አል አሙዲን የማንፈልጋቸው ሰዎች ያለን እንደሆነ ሲመጡ እንነግራቸዋለን እንጂ በባይተዋር ሰዎች ሲታሰሩ የሚጨክን ልብ ኢትዮጵያውያን የለባቸውም፡፡ ይሄ ጠንካራ አቋማችንን ያወቁት ክራውን ፕሪንሱ አሳዛኝ ቢሆንም ማታ 10 ሰዓት ላይ ተግባብተን ጠዋት ሊሰጡን ከወሰኑ በኋላ ቤተሰቦቻቸው ባደረጉባቸው ከፍተኛ ጫና አሁን ከእኛ ጋር ሊመጡ አልቻሉም፡፡… የሼህ አል አሙዲን መታሰር በዓለም ላይ ያሉ ዲያስፖራዎች ሁሉ አጀንዳ መሆን አለበት ምክንያቱም ኢትዮጵያ አንተ አንቺ ከሆንሽ አንድ ኢትዮጵያ ታስራለችና ኢትዮጵያ ስትታሰር ዝም ማለት የሚያስችለው ሌላ ኢትዮጵያዊ መኖር የለበትም፡፡ የጀመርነውን ዲፕሎማቲክ ጫና በማስቀጠል ጊዜውን መናገር ብቸገርም በቅርብ ጊዜ ውስጥ ወደ አገራቸው እንደሚመለሱ እርግጠኛ ሆኜ እናገራለሁ›› ሲሉ ያሰሙትን ንግግር በአስታዋሽነቱ አስደምጧል፡፡

የኢትዮጵያ ቴሌቪዥንም ከላይ በተጠቀሰው ዕለት በምሽት ዜናው ‹‹ከሳዐዲ አረቢያ በእስር ላይ የነበሩት ትውልደ ኢትዮጵያዊ ባለሀብት ሼህ ሙሐመድ አሊ አል አሙዲን ከእስር መፈታታቸውን የሚድሮክ ኢትዮጵያ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር አረጋ ይርዳው ለኢትዮጵያ ቴሌቪዥን አረጋግጠዋል›› ሲል ገለጸ፡፡ በማያያዝም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ወደ ሳዑዲ አረቢያ በተጓዙበት ወቅት ከተወያዩባቸው ጉዳዮች አንዱ የሼህ ሙሐመድ አሊ አል አሙዲን ጉዳይ መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት መግለጹንና ሼህ ሙሐመድም በሰላም እንዲመለሱ ጽ/ቤቱ መልካም ምኞቱን ማሳወቁን

ቴሌቪዥን አስታውቋል፡፡ በዜናው ሥርጭት ወቅትም ዜና አምባቢው፣ ስለ ሼህ ሙሐመድ መፈታት ጉዳይ ዶ/ር አረጋ ማብራሪያ እንዲሰጡበት በቀጥታ የስልክ መስመር ላይ መገኘታቸውን ጠቅሶ፣ ስለጊዜያቸውም በማመስገን ስለ ሁኔታው ይንገሩን ሲል ላቀረበላቸው ጥያቄ ዶ/ር አረጋ ይርዳው፣

‹‹ሼህ ሙሐመድ አሊ አል አሙዲ በአሁኑ ጊዜ ተፈትተው ወደቤታቸው እየገቡ ነው›› ሲሉ መልሰዋል፡፡ ዜና አምባቢው በመቀጠል ምናልባት ዛሬ ማምሻውን ይገባሉ እያሉን ነው ያሉት? ሲል በድጋሚ ካቀረበላቸው ጥያቄ አኳያም ዶ/ር አረጋ ‹‹በአሁኑ ጊዜ ወደቤታቸው እየሄዱ ነው አዎ ከሌላ ቦታ ስለነበሩ ከሪያድ ወደ ጂዳ መሄድ ስለነበረባቸው ከጂዳ ደግሞ ወደቤታቸው እየገቡ ነው አዎ›› በማለት ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

በሌላም በኩል የአሜሪካን ድምፅም (VOA) ጥር 19 ቀን 2011 ዓ.ም. ምሽት ላይ የሼህ ሙሐመድን ከእስር መፈታት አስመልክቶ ሰፊ ዘገባ አቅርቦ የነበር ሲሆን፣ በጉዳዩም ላይ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት የፕሬስ ኃላፊ ከሆኑት አቶ ንጉሱ ጥላሁን ጋር ቃለ ምልልስ አድርጓል፡፡

የፕሬስ ኃላፊው ከሼህ ሙሐመድ መፈታት ጋር በተያያዘ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ስላደረጉት ጥረት መግለጫ ከመስጠታቸው በፊት የሼህ ሙሐመድን ከእስር መፈታት አስመልክተው ‹‹ከሁሉ አስቀድሜ ለወዳጆቻቸው፣ ለዘመዶቻቸው፣ ለቤተሰቦቻቸውና ለሚድሮክ ሠራተኞች በአጠቃላይ ለኢትዮጵያውያንም እንኳን ደስ ያላችሁ ማለት እፈልጋለሁ›› ብለዋል፡፡ ከዚያም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ለሕዝብ ንግግር ባደረጉበት ጊዜ ሼህ ሙሐመድ እንዲፈቱ ጥረት እንደሚያደርጉ ገልጸው እንደነበር፣ ሳዑዲ በሄዱ ጊዜም ጥያቄውን እንዳቀረቡ፣ ሕዝቡም እንደሚያውቀው በመጥቀስ ‹‹ጠቅላይ ሚኒስትር ጥረቱን ቀጥለውበት እነሆ በዛሬው ዕለት መለቀቃቸውን ሰምተናል እውነት ነው›› በማለት ስለ ሼህ ሙሐመድ ከእስር መፈታት አስረድተዋል፡፡

የአሜሪካን ድምፅ ዘጋቢም ከሼህ ሙሐመድ መፈታት ጋር አያይዞ ‹‹ዛሬ የተለያዩ የመገናኛ ብዙኋን የጠቀሱት የሚድሮክ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር አረጋ ይርዳው ጠቅላይ ሚኒስትሩን አመስግነዋል፣ ስለዚሁ

Page 17: የ‹‹ሼህ ሙሐመድ ይፈቱ›› ዘመቻ ትውስታዎች · የሚጠቅሙ እንደ ህዳሴ ግድብ ላሉ ሜጋ ፕሮጀክቶች ግንባታ፣ ለስፔስ

MIDROC NewsletterSpecial Issue # 58 April 2019

15Addis Ababa, Ethiopia

ይህ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥረት ውጤት ነው ማለት እንችላለን?›› በማለት ላቀረበላቸው ጥያቄ የፕሬስ ኃላፊው አዎን በማለት ጠቅላይ ሚኒስትር ሼህ ሙሐመድ እንዲፈቱ ጥረት ሲያደርጉ መቆየታቸውንና አሁንም ለተደረሰበት ውጤት ከፍተኛ አስተወጽዖ ያደረጉ መሆኑን በመግለጽ ምላሽ ሰጥተውበታል፡፡

TG Ethiopian Television የተባለ በአሜሪካን የሚገኝ ድርጅትም ሼህ ሙሐመድ መታሰራቸው በአብዛኛው ሕዝብ ዘንድ ከፍተኛ ሐዘን ፈጥሮ እንደነበርና ጥር 19 ቀን 2011 ዓ.ም. ሲለቀቁም በአብዛኛው ሕዝብ ዘንድ ከፍተኛ ደስታ መፍጠሩን በመጥቀስ በሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ዋና መ/ቤት የነበረው የደስታ አከባበር ሥነ-ሥርዓት አስደሳች እንደነበር በሰፊው ዘግቧል፡፡

በደስታ አከባበሩ ሥነ ሥርዓት ወቅትም የቴሌቪዥኑ ዘጋቢ የሼህ ሙሐመድ መፈታትን አስመልክቶ ምን ተሰማዎት? ምን ይሉናል? በማለት ለዶ/ር አረጋ ይርዳው ቃለ መጠይቅ አቅርቦላቸው ነበር፡፡ ዶ/ር አረጋም በሰጡት ምላሽ ‹‹አብሬ ከነበርኳቸው ሰዎች ጋር የሼህ ሙሐመድን ከእስር መለቀቅ ሰበር ዜናውን እሁድ ከሰዓት በኋላ ስንሰማ መነጋገር አቅቶን ነበር፡፡ በኋላም ደስታው ፈንቅሎ ለቅሶ በለቅሶ ሆነን ነበር፣ ዛሬ ሰኞ በጧት ይኸው ከቴክኖሎጂ ግሩፑ ሠራተኞች ጋር ተሰባስበን ለሼህ ሙሐመድ የተዘጋጀ ሙዚቃ እየሰማን የደስታ በዓሉን እያከበርን ነው፡፡ በተፈጠረው ደስታም ብዙ ሲታገል የነበረው የቴክኖሎጂ ግሩፑ ሠራተኛ ሳምንቱን በቤቱ ሆኖ ይበልጥ እንዲደሰት እረፍት እንዲያደርግ ፈቅደናል›› ብለዋል፡፡

አያይዘውም ሼህ ሙሐመድ ትልቅ የሀገር ባለውለታ ሰው መሆናቸውንና ማንም ኢንቨስተር ወደ አገራችን ባልመጣበት ወቅት ቀዳሚው ኢንቨስተር መሆናቸውንና አገሪቱ ብዙ ብር በፈለገችበት ወቅት የደረሱላት አጋር መሆናቸውን በመጥቀስ፣ ክብር ሊሰጣቸው እንደሚገባ ጠቅሰው ማንም ሰው ማስረጃና ሀቅ ሳይኖር ስለርሳቸው አፍራሽ ነገር መናገር ተገቢ አለመሆኑንና የሰውን ልጅ ዝቅ በማድረግ ጉዳት እንጂ የሚገኝ ትርፍ እንደሌለ በቃለ ምልልሱ ለዘጋቢው ጋዜጠኛ አስረድተዋል፡፡

ዋልታ ቴሌቪዥን በድጋሜ ከሼህ ሙሐመድ እስር መፈታት ጋር በተያያዘ ጥር 20 ቀን 2011 ዓ.ም. ባሰራጨው ዜናው የሚድሮክ ግሩፕ ሠራተኞችና

አመራሮች የሼህ ሙሐመድ ሁሴን አሊ አል አሙዲንን ከ14 ወራት የሳዑዲ አረቢያ እስር መለቀቅን አስመልክተው ደስታቸውን ተሰባስበው እንዳከበሩ በመጥቀስ ዜናውንና የደስታ አከባበሩን ሥነ ሥርዓት ከሚያሳይ ቪዲዮ ቅንብር ጋር አስተላልፏል፡፡

ቴሌቪዥኑ ዝርዝር ጉዳዮችንም በማንሳት የሼህ ሙሐመድ መፈታት ባስከተለው ደስታ ምክንያት ለሠራተኞቹ የደመወዝ ጭማሪ እና የእዳ ስረዛ መደረጉን፣ ከድርጅቱ ቤቶችን ተከራይተው ለሚኖሩ ሠራተኞች የአንድ ወሩን ነፃ የተደረገላቸው ስለመሆኑ፣ የድርጅቱ የተወሰኑ ሠራተኞች በቡራዩ ከተማ አካባቢ ላይ በሚገነቡት የመንደር የቤት ሥራ ቀሪ ክፍያ የሰረዘ መሆኑንና ደስታው ከቴክኖሎጂ ግሩፕ ውጭ ላሉም መሆኑን በመገንዘብ በዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ እና በዩኒቲ አካዳሚ ለሚማሩ ተማሪዎችም የአንድ ሴሚስተር ትምህርት በነፃ እንዲሆን መወሰኑን፣ ለዓይን ባንክ 250 ሺህ ብር እንዲሁም የኤልፎራ እርሻ ባሉባቸው አካባቢዎች ላሉ የተመረጡ ት/ቤቶች የአንድ ሚሊዮን ብር ድጐማ መለገሱንም መናገራቸውን ገልጿል፡፡ ጥር 19 ቀን በየዓመቱ በቴክኖሎጂ ግሩፑ ኩባንያዎች ዘንድ በዓል በመሆን ሠራተኛው በየቤቱ በመሆን እያስታወሰው እንዲውል እንደሚሆን በቴክኖሎጂ ግሩፑ መሪ ተገልጿል፡፡

ዶ/ር አረጋ ይርዳው ከዚሁ ቴሌቪዥን ጋር በነበራቸው ቆይታ ይህ ጥቂት ነገር የተደረገው ደስታውን አስመልክቶ መሆኑን ተናግረው ሚድሮክ በባለሀብቱ መታሰር ድርጅቱ ጫና ውስጥ የነበረ ቢሆንም ሀገራዊ የልማት አስተዋጽዖው ተጠናክሮ ይቀጥላል ማለታቸውን እንደገለጹና አያይዘውም ሚድሮክ ላይ የነበረው ተግዳሮት በጣም በጣም ትልቅ እንደነበር ገልጸዋል፡፡ ቀጥለውም ‹‹ሼህ አሊ አል አሙዲ ለኢትዮጵያ ያላቸው አስተሳሰብና አስተያየት የተለየ ነው፡፡ ሁሉም ሰው ያውቀዋል፡፡ ባለፉት ሃያ ዓመታት በቀዳሚ ኢንቨስተርነት ሲያገለግሉ ቆይተዋል፡፡ አሁንም ደግሞ በእስር ላይ ሆነው እንኳን ድርጅቶቻቸው አልተነቃነቁም፣ ሁላችንም ስንሠራ ነው የነበርነው፣ የተፈናቀለ፣ የተሰረዘ ኩባንያ የለንም፣ አሁንም ደግሞ እሳቸው በመውጣታቸው ከእስከ ዛሬ ከምናደርገው በበለጠ መልክ ይስፋፋል ብዬ አምናለሁ›› በማለት መግለጻቸውን ቴሌቪዥኑ ዘግቧል፡፡

ዶ/ር አረጋ ይርዳው ሼህ ሙሐመድ በተፈቱ ማግስት

Page 18: የ‹‹ሼህ ሙሐመድ ይፈቱ›› ዘመቻ ትውስታዎች · የሚጠቅሙ እንደ ህዳሴ ግድብ ላሉ ሜጋ ፕሮጀክቶች ግንባታ፣ ለስፔስ

MIDROC NewsletterSpecial Issue # 58 April 2019

16Addis Ababa, Ethiopia

ጥር 20 ቀን 2011 ዓ.ም. ጧት በመቻሬ ኮርፖሬት ሴንተር መቻሬ ሜዳ በተዘጋጀው ሥነ ሥርዓት ላይ ተገኝተው ለተሰበሰበው የቴክኖሎጂ ግሩፑ አመራሮችና ሠራተኞች ሊቀመንበራችን ከእስር መለቀቃቸውን ተናግረዋል፡፡ በዚህ ጊዜም በሥነ

ሥርዓቱ ላይ የነበረው ታዳሚም በደስታ ተውጦ ስሜቱን በሙዚቃ፣ በጭፈራ፣ በእልልታ፣ ግጥም በማቅረብና በመሳሰሉት ገልጿል፡፡ በዚህ ሥነ ሥርዓት ላይም ዶ/ር አረጋ ከሼህ ሙሐመድ መፈታት ጋር በተያያዘ ለታዳሚው ንግግር አድርገዋል፡፡

ሠራተኞች በጭፈራ ደስታቸውን ሲገልጹ

ዶ/ር አረጋ ይርዳው በንግግራቸው መግቢያም ሠራተኛውን ሼህ ሙሐመድ በመፈታታቸው እንኳን ደስ ያላችሁ ካሉ በኋላ፣ በሼህ ሙሐመድ እስር ቆይታ ወቅት አመራሮችና ሠራተኞች በየጊዜው እየተገናኙ እርሳቸውን በማሰብ ሲያደርጉ የነበረውን እንቅስቃሴና በጐ ምኞች በማድነቅ አመስግነዋል፡፡ የተፈጠረውን ደስታም ምክንያት በማድረግ በደመወዝ፣ በቦነስ፣ በዕዳዎች ስረዛ፣ የትምህርት ወጪን በመሸፈን ረገድ ሠራተኛው ተጠቃሚ እንዲሆን መወሰኑን ገልጸዋል፡፡ የተደረገው ችሮታም የዕለቱን የደስታ ፕሮግራም ይበልጥ ደማቅ እንዲሆን ሊያደርገው እንደበቃ መገንዘብ ተችሏል፡፡

ዶ/ር ንግግር ሲያደርጉ

Page 19: የ‹‹ሼህ ሙሐመድ ይፈቱ›› ዘመቻ ትውስታዎች · የሚጠቅሙ እንደ ህዳሴ ግድብ ላሉ ሜጋ ፕሮጀክቶች ግንባታ፣ ለስፔስ

MIDROC NewsletterSpecial Issue # 58 April 2019

17Addis Ababa, Ethiopia

በመቻሬ ኮርፓሬት ሴንተር የነበረ የደስታ ድባብ

ሼህ ሙሐመድ ጥር 19 እሁድ ከእስራት መለቀቃቸው

በተሰማ ማግስት ሰኞ ጥር 20 ቀን 2011 ዓ.ም.

የሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ዋና መ/ቤት በሚገኝበት

በመቻሬ ኮርፖሬት ሴንተር ግቢ ከጧቱ ሥራ መግቢያ

ሰዓት ጀምሮ የነበረው የሰው እንቅስቃሴ ከወትሮው

ለየት ያለ ነበር፡፡ ሠራተኞች ከሥራ ባልደረቦቻቸውና

ከአለቆቻቸው፣ የሥራ አመራሮቹም እንዲህ ሲገናኙ

ፈገግታ በተሞላት ሁኔታ እርስ በእርስ በመጨባበጥ

በመተቃቀፍና በመሳሳም ደስታቸውን ሲለዋወጡ

ይታዩ ነበር፡፡ ሁኔታውን በትኩረት ለተከታተለው

ትልቅ ትዕይንት ሲታይ ነበር ማለት ይቻላል፡፡

ዶ/ር አረጋ ዘወትር ጧት ጧት ወደ ቢሮአቸው

ከመግባታቸው በፊት በግቢው ውስጥ ለአንድ

ሰዓት ያህል በመቆምና በመንቀሳቀስ የአካባቢውንና

የሠራተኛውን ሁኔታ መቃኘት፣ የሚፈልጋቸውንም

ማነጋገር፣ ገጠመ ለተባሉ ችግሮች መፍትሔዎችን

እና የሥራ መመሪያዎችን መስጠት የዕለት ተዕለት

ተግባራቸው ስለነበር በዚሁ የደስታ ቀን የማኔጅመንት

አባላትም ሆኑ ሌሎች ሠራተኞች ከዶ/ር አረጋ ጋር

በመጨባበጥና በመተቃቀፍ ስለ ሼህ ሙሐመድ

መፈታት የተሰማቸውን ደስታ ሲለዋወጡ ታይተዋል።

እዚህ ላይ ስለመቻሬ አመራሮችና ሠራተኞች

የሚከተለውን መግለጽ ተገቢ ይሆናል፡፡ ሠራተኛው

ሼህ ሙሐመድ በሳዑዲ አረቢያ ታሰሩ ከተባለበት

ጊዜ ጀምሮ አንዳንድ የቀድሞ ሁኔታዎች

ተለውጠው እንደነበር የቴክኖሎጂ ግሩፑ ህብረተሰብ

የሚያስታውሰው ነው፡፡ በሊቀመንበራችን መታሰር

የተነሳ እንደሌላው ጊዜ ክራቫት አስሮ ፕሮቶኮል

በጠበቀ ሁኔታ ለብሶ መታየት፣ እንደወትሮው

በአንዳንድ ኦፊሺያል በሆኑ ጥሪዎች ላይ መገኘትንና

የመሳሰሉትን መሪያችን እርግፍ በማድረግ ትተውት

እንደነበር የቴክኖሎጂ ግሩፑ አመራሮችና ሌሎችም

ሠራተኞች የሚመሰክሩት የሚያስታውሱት ነው፡፡

ታዲያ እነዚህን ሁኔታዎች የምትሽር ቀን ጥር 19

ቀን 2011 ዓ.ም. በመምጣቷ የተለየች ቀን ነበረች

ማለት ይቻላል፡፡ በመሆኑም ሼህ ሙሐመድ ከእስር

በመለቀቃቸው ምክንያት የመሪያችን ደስታ ሌሎች

ከተሰማቸው ደስታ ሁሉ የላቀ ነበር ብሎ ደፍሮ

ለመናገር ይቻላል፡፡

ለዚህም ይመስላል የሼህ ሙሐመድን መፈታት

ምክንያት በማድረግ በቴክኖሎጂ ግሩፑ መቻሬ

ሜዳ በነበረው የደስታ አከባበር ሥነ ሥርዓት

ላይ የመድረኩ አስተናጋጅ ‹‹ዛሬ ከቁጥጥር ሥር

የተለቀቁት ሊቀመንበራችን ሼህ ሙሐመድ ብቻ

አይደሉም፤ የመሪያችንና የሁላችንም ጭምር እንጂ››

በማለቱ ሠራተኛው ከመቀመጫው ተነስቶ በጣም

ሞቅ ባለና ሳያቋርጥ በቆየ ጭብጨባና እልልታ

ደስታውን የገለጸው፡፡

ሼህ ሙሐመድ ለአስራ አራት ወራት ያህል

በእስር በቆዩበት ወቅት ከነበሩበት ሁኔታ እንዲፈቱ

በቴክኖሎጂ ግሩፑ የነበረው የይፈቱልን ዘመቻ በዚህ

መልኩ የሚታወስ ነበር፡፡ የሊቀመንበራችን ከእስር ነፃ

መሆን የቴክኖሎጂ ግሩፑን ህብረተሰብ ብቻ ሳይሆን

ጠቅላላውን የሚድሮክ ኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት

ሠራተኞችንና አጠቃላይ ህብረተሰቡን ሁሉ ያስደሰተና

ያስፈነጠዘ ነው፡፡ በቀጣይም ሼህ ሙሐመድ በቅርብ

ጊዜ ውስጥ ወደ አገራቸው ኢትዮጵያ መጥተው

እንደሚቀላቀሉት የቴክኖሎጂ ግሩፑ ህብረተሰብ

እምነቱ የፀና ነው፡፡

ሊቀመንበራችን ሼህ ሙሐመድ ከእስር መፈታታቸውን

በማስመልከት ከቴክኖሎጂ ግሩፑ ኩባንያዎች

ሠራተኞች ከቀረቡ የደስታ መግለጫና ምስጋና

ግጥሞች መካከል የተወሰኑትን እንሆ፡-

Page 20: የ‹‹ሼህ ሙሐመድ ይፈቱ›› ዘመቻ ትውስታዎች · የሚጠቅሙ እንደ ህዳሴ ግድብ ላሉ ሜጋ ፕሮጀክቶች ግንባታ፣ ለስፔስ

MIDROC NewsletterSpecial Issue # 58 April 2019

18Addis Ababa, Ethiopia

‹‹ክብር ለሱ ይሁን ለፈጠረን ጌታ››!!

አስተርዮ ማሪያም በአሉ ሊከበር ሲቀር አንድ ማታ፤

በዕለተ ሰንበት በታላቁ መላክ!

ጥር 19 ቀን 2011 የገብርኤል ለታ፤

ዶ/ር ሼህ ሙሐመድ ከእስር ተፈታ፡፡

ክብር ለሱ ይሁን ይህን ላደረገው ለፈጠረን ጌታ

በ2010 በታላቁ ፆም ውስጥ ያውም በረመዳን፤

ኢትዮጵያና ህዝቧን ወስኖ ለማዳን፤

ግብፅና ሳዑዲ፣ ኬኒያና ሱዳን፤

ዜጎቻችን ታስረው ያለምን ምክንያት፤

ጨለማ ውጧቸው ታፍነው ለወራት፤

አለናችሁ የሚል አጥተው ወዳጅ ዘመድ፤

ኢትዮጵያዊ ነብይ ተነስቶ በመሄድ፤

ድንገት አስፈታቸው ዶ/ር አብይ አህመድ፡፡

እንዲህ ነው መባረክ እንዲህ ነው መወደድ፤

ኢትዮጵያ ሀገሬ!!!

እንዲህ አይነቱን ልጅ መንታ፣ መንታ ትውለድ፡፡

ከነሱም መካከል አለ ሼህ ሙሐመድ፤

እሱን ለማስፈታት በመውጣት በመውረድ፤

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለከፈሉት ዋጋ፤

ምስጋናችን ይድረስ ብለናል በአንድ ድምፅ

የኢትዮጵያ ዜጎች ከቆላ እስከ ደጋ፡፡

ክብር ሼህ ሙሐመድ!!!

ሰርቶ ከማሰራት ከመስጠት በስተቀር፣

ለስብሰባ ሄዶ ሳዑዲ እንደሚቀር፣

እሱስ መች ገምቶ ይህ እንደሚፈጠር፡፡

ጊዜና ሁኔታ ያመጡትን ነገር፣

ምን ሊባል ይችላል!

ለበጎ ነው ብሎ ከማለፍ በስተቀር፡፡

ብዙ የሚሰራ ሀገር የሚያኮራ፣

እንዳልተቀናብን በሱ ስንጠራ፣

ውዷ ሀገራችን በኢኮኖሚ ከስራ፣

ዛሬ መጎዳቷን ማን ስለሱ ያውራ፡፡

ተቸገርን ሲሉት፣

ገንዘብ እንዳልሰጠ ከኪሱ እያፈሰ፣

ሰው ታመመ ሲሉት ቀድሞ እየደረሰ፣

በስሙ ታክሞ እንዳልተፈወሰ፣

ያሁሉ ተመፅዋች ዛሬ የት ደረሰ?!

እንኳንስ ለወራት ሰው ወገን እርቆት፣

ለቀናት ይከብዳል የቤተሰብ ናፍቆት፣

ዶ/ርም ተከፍተው በደስታቸው ጊዜያት፣

የሚያምርባቸውን ሱፍና ከረቫት፣

አለበሱም ነበር እስከአሁኗ ሰዓት፡፡

ሠራተኛው ሁሉ ነጩን ቲሸርት ለብሶ፣

አይታይም እንጂ እንባው ከውጪ ፈሶ፣

የማይጸልይ የለም ለፈጣሪ አልቅሶ፡፡

ያጨለማ ዘመን ላይመጣ መልሶ፣

እኛ ነጩን ቲሸርት እሱ ሱፉን ለብሶ፣

ዛሬ ከእኛ እርቋል ሐዘንና ለቅሶ፡፡

ተቃቅፎ ሲሳሳም ወዳጅና ዘመድ፣

ለእኛ ይሰማናል ደግሞ እንደመወለድ፡፡

ሁሉም እንዲደሰት እዲሞቅ ቤታችን፣

ይህን ምክንያት አርገው ዶ/ር አባታችን፣

የአንድ ሣምንት ዕረፍት ሰጥተው ለሁላችን፣

ደሞዛችን ላይ በፐርሰንት ጨምረው፣

የሕክምና ዕዳ ላለባቸው ሽረው፣

250 ሺህ ለአይን ባንክ ደጉመው፣

ዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ለሚማሩ፣

የአንድ ሴሚስተር ክፍያን ሲቸሩ፣

ሚድሮክ በሰራው ቤት ገዝተው ለሚኖሩ፣

ቀሪ ዕዳው ሲሰረዝ በደስታ ጨፈሩ፡፡

ዘመን መለወጫ አዲስ ዓመት ሲደርስ፣

ስለፈቀዱልን የሁለት ወር ቦነስ፣

ደስታችን አልጠፋም እስከዛሬ ድረስ፡፡

ይህን ሁሉ ነገር ስላሰቡ ለእኛ፣

ከልብ አመስግኗል መላው ሠራተኛ፡፡

ሳያውቁ የጎዱን ዛሬ ቢሳቀቁም፣

ይቅር እንባባል እኛ ቂም አናውቅም፡፡

ክብር ሼህ ሙሐመድ!!!

በአሸናፊነት በድል ስለመጡ፣

የኢትዮጵያን ቡና አቦል እየጠጡ፣

እረፍት ያስፈጋል እዚህ ይቀመጡ፡፡

በስተመጨረሻም የምመኝለዎት፣

ዕድሜና ጤናውን ፈጣሪ ሰጥቶዎት፣

ይኑሩልን እንጂ ብቻ ደስ ብልዎት፣

ውለታስ ለመክፈል እኛ አለንለዎት፣

(ከኤምቢአይ ሠራተኛ)

Page 21: የ‹‹ሼህ ሙሐመድ ይፈቱ›› ዘመቻ ትውስታዎች · የሚጠቅሙ እንደ ህዳሴ ግድብ ላሉ ሜጋ ፕሮጀክቶች ግንባታ፣ ለስፔስ

MIDROC NewsletterSpecial Issue # 58 April 2019

19Addis Ababa, Ethiopia

ምስጋና ለእግዚአብሔር

ሼክ ሙሐመድ ሑሴን ደጉ ሽቁጥቁጡ

በሰላም በጤና እንኳን ደህና መጡ

ሼክ ሙሐመድ ሁሴን የእሳቸው መፈታት በዜና ሲሰማ

ሀገር ተደሰተች እልልታ ተሰማ

ሼክ ሙሐመድ ሑሴን በድንገት ተይዘው በመታሰራቸው

ከልብ አዝና ነበር እናት ሀገራቸው

አለች እናት ሀገር ልጄ ምንም አይሁን አይንካብኝ ክፉ

በተንኮል ያሰቡህ ከምድረ ገጽ ይጥፉ

ዘጠኝ ወር በሆዴ ተሸክሜ 3 አመት አጥብቼ ያሳደኩህ

ምነው ጠፋህ በዐይኔ ልጄ ምን በደልኩህ

አለሁ በለኝ ልጄ ከአለህበት ድምጽህን አሰማኝ

በአንተ መጥፋት ተጨነኩኝ ተጠበብኩኝ መላው ጠፋኝ

ሰው ተርቦ ውሃ ጠምቶት

መሄጃ አጥቶ ግራ ገብቶት

ከእግዚአብሔር ጋር አንተ ነበርክ መድኃኒቱ

የረሃቡ የውሃ ጥም የርዛቱ

ብላ ተናገረች ኢትዮጵያ እናታቸው

ጸሎቷን ስማና አንተ ጠብቃቸው

ኢትዮጵያ ያፈራችው ስመ ጥሩ ጀግና

እንደ ሼክ ሙሐመድ አሁን ማን አለና

ሼክ ሙሐመድ ሁሴን እግዚአብሔር ይስጣቸው

ሕዝባቸውን እና ሀገር ወዳድ ናቸው

እስከ አለምዳርቻ ይነገር ሥራቸው

ሀገርን በማልማት ወገንን በመርዳት አንድ

ቁጥር ናቸው

ይናገር ኦሮሞ ይናገር ሱማሌ

በረሀብ ለተጎዱ ለተፈናቀሉ አያውቁም መጨከን ይሰጣሉ ሁሌ

ከአምላክ የተቸሩ ጥሩ አባት ናቸው

እግዜር አትረፍርፎ አብዝቶ ይስጣቸው

በብሔር ብሔረሰብ ሁሉም በእኩልነት ሰርቶ የሚበላበት

ሚድሮክ ኢትዮጵያ ነው ቢባል ምን አለበት

ዘር ሃይማኖት ሳይለይ ቀለም ያልመረጠ

ሁሉን በእኩል ያየ ያላበላለጠ

እውነቴን ነው እኮ እኔ የምነግራችሁ

በሚድሮክ ኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰብ በአይነት አለላችሁ

የዶ/ር አረጋ የስራው ደራሴ የእውቀት መምህር

ወልድያ እስቴድየም ዘመናዊ ህንፃ ይቅረብ ለምስክር

ትናገር ኤምቢአይ ይመስክር ስራቸው

አቅዶ በመስራት ወደርም የላቸው

መማር እንደ አረጋ አመራር መስጠት

ችሎታን አውጥቶ ሰርቶ ማሳየት

ያቺ ኤምቢአይ አምራለች ደምቃለች

በብልሁ መሪ በዶ/ር አረጋ ታክማ ድናለች

አሁን ኤምቢአይ እንዴት አምሯል ደምቆ

በእጽዋት በአበባ ግቢው አሸብርቆ

አሁንም ዘመናይ ነገም ዘመናይ

የምንጭ ጸበል ናት ያቺ ኤምቢአይ

አንቺን ተስፋ አድርጎ ስንት አለ የሚኖር

አንዱ እኔነኝ እኮ እውነቱን ልናገር

(ከዘመናዊ ኢንዱስትሪ ሠራተኛ)

Page 22: የ‹‹ሼህ ሙሐመድ ይፈቱ›› ዘመቻ ትውስታዎች · የሚጠቅሙ እንደ ህዳሴ ግድብ ላሉ ሜጋ ፕሮጀክቶች ግንባታ፣ ለስፔስ

MIDROC NewsletterSpecial Issue # 58 April 2019

20Addis Ababa, Ethiopia

ከጥረት (TIRET) መጽሔት የተገኘ

የሚድሮክ ኢትዮጵያ ግሩፕ ኮርፓሬት መጽሔት የሆነው ጥረት/TIRET በማርች 2019 እትሙ ሼህ ሙሐመድን አስመልክቶ የዘገበውን እንደሚከተለው አቅርበናል፡፡

መጽሔቱ በፊት ለፊት ሽፋን ገጹ የሊቀመንበራችንን የሼህ ሙሐመድ ሁሴን አሊ አል አሙዲን ምስል፣ በምስሉም ግርጌ ‹‹ሙሐመድ አል-አሙዲ በደህና ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለሱ እንመኛለን›› የሚል የመልካም ምኞት መልእክትና መልእክቱም የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት መልእክት መሆኑን በሚገልጽ አኳኋን ካሰፈረ በኋላ በማስከተልም የሚከተለውን ዘግቧል፡፡

ሼህ ሙሐመድ ሁሴን አሊ አል-አሙዲ ከኢትዮጵያዊት እናታቸው እና ከሳዑዲ አባታቸው በጁላይ 21 ቀን 1946 በሰሜን ማዕከላዊ ኢትዮጵያ በደሴ ከተማ ተወልደው ታዋቂ የዓለም የንግድ ሰው ለመሆን የቻሉ ናቸው፡፡

ሼህ ሙሐመድ ሰፊ ሀብት በመፍጠርና የንግዱን ሥራ በመሥራት ረገድ በብቃታቸውና ለጋስነታቸው የሚታወቁ ናቸው፡፡ ለሀብታምነታቸውም መነሻው በሳዑዲ አረቢያ የኮንስትራክሽንና የሪል እስቴት ቢዝነስ ነው፡፡

በአሁኑ ጊዜም በተለያዩ አገሮች ያሉ ብዙ ሰዎች የሼህ ሙሐመድ ከሆኑት የንግድ ሥራዎች ተጠቃሚዎች ሲሆን ዋነኞቹ ንግዶችም ነዳጅ ድፍድፍ ዘይት ማጣራትና ሥርጭት፣ በኮንስትራክሽን ሥራ፣ የአምራችነትና የአገልግሎት ኢንዱስትሪዎች ናቸው፡፡

በምድራችን ላይ የላቀ ሀብታም ከሆኑት ጥቂት ጥቁር ሰዎች አንዱ የሆኑት ሼህ ሙሐመድ ለኢንቨስትመንት ጠንካራ የገንዘብ አቅም እንዳላቸው በንግድ አጋርነታቸው፣ እንዲሁም የተለያዩ የባህል መሠረት ያላቸው ስለመሆኑ በኢትዮጵያ መንግሥትና ህዝብ ትኩረትን ያገኙ ሰው ናቸው፡፡ በሪያድ ሪትዝ ካርልተን ሆቴል ክስተት ምክንያት ከኖቬምበር 4, 2017 ጀምሮ ተለይተው ከቆዩ በኋላ በጃንዋሪ 27, 2019 (ጥር 19 ቀን 2011 ዓ.ም.) ከቤተሰባቸው ጋር መቀላቀላቸው በአጠቃላይ በህዝቡ በተለይ ደግሞ በሠራተኞቻቸውና ጓደኞቻቸው ዘንድ ትልቅ ደስታን የፈጠረ ነው፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት ዲፕሎማቲክ ጥረት በተለይም የጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ቆራጥ ጥረት ለሼህ ሙሐመድ መፈታት ከፍተኛ ሚና ተጫውቷል፡፡

ስለሼህ ሙሐመድ መልካም ዜና ያበሰረው የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ነበር፡፡ ጽ/ቤቱ በኦፊሽያል ፌስ ቡኩ ‹‹እንደሚታወሰው በ2018 መግቢያ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ወደ ሳዑዲ አረቢያ ተጉዘው ከሳዑዲ አልጋ ወራሽ ሙሐመድ ቢን ሰልማን ጋር በብዙ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡ የሙሐመድ አል-አሙዲ መፈታትም የውይይቱ አንዱ ጉዳይ ነበር፡፡ በኋላም ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በግንቦት ወር 2018 በሚሊኒየም አዳራሽ ንግግር ባደረጉት ወቅት የሼህ ሙሐመድን የመመለስ ጉዳይ ይበልጥ አረጋግጠዋል፡፡››

‹‹ሙሐመድ አል አሙዲ በደህና ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለሱ እንመኛለን›› በማለት የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት መልካም ምኞቱን ይገልጻል፡፡

ለሼህ ሙሐመድ ታማኝ ከሆኑ የሥራ መሪዎች ባደረጉት የስልክ ግንኙነትም ሼህ ሙሐመድ በመልካም የጤንነት ሁኔታ ላይ ይገኛሉ፡፡ በጂዳ ከቤተሰባቸው ተቀላቅለዋል፤ ከከፍተኛ የሥራ አመራር እና የቢዝነስ ተባባሪዎችም ጋር ተገናኝተዋል፡፡

ሼህ ሙሐመድ በሚድሮክ ኢትዮጵያ ሥር በመካሄድ ላይ ያሉ የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴዎች በዘላቂነት መልካም በሆነ ሁኔታ እንዲቀጥሉና ይበልጥ እንዲጠናከሩ ያደርጋሉ፡፡

ሼህ ሙሐመድ በፎርቢስና ብሉምበርግ ቢሊየነሮች ዝርዝር ውስጥ በስም የተጠቀሱ በሲዊድን የትልቁ የዘይት ኩባንያ ባለቤት፣ በተወለዱበት ኢትዮጵያ ደግሞ ግዙፍ ኢንቨስትመንት የሆኑ በሁሉም ዘርፎች፣ በግብርና አግሮ ኢንዱስትሪ፣ በኮንስትራክሽን፣ በማዕድን፣ በማኒፋክቸሪንግ፣ በሆቴል፣ በትምህርት፣ በጤና፣ በትራንስፖርት እና በሎጂስቲክ ሥራ የተሰማሩ ኩባንያዎች ባለቤት ናቸው፡፡

ሼህ ሙሐመድ ገንዘባቸውንና ሌሎችንም ንብረቶች በመመደብ በሳዑዲ አረቢያ፣ በዩኤስ፣ በአውሮፖ እና አፍሪካ ለጤና ማዕከል እና ለስፖርት ድጋፍ በማድረግ የሚያስመሰግን ሥራ የፈጸሙ ናቸው፡፡

ታዋቂው የአሜሪካን የቢዝነስ መጽሔት ፎርቢስ በ2013 ከሼህ ሙሐመድ ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ ‹‹እሱ ደግሞ የአገሪቱ ዋና ፍሬያማ በጎ አድራጊ ነው›› ብሎ ነበር፡፡

Page 23: የ‹‹ሼህ ሙሐመድ ይፈቱ›› ዘመቻ ትውስታዎች · የሚጠቅሙ እንደ ህዳሴ ግድብ ላሉ ሜጋ ፕሮጀክቶች ግንባታ፣ ለስፔስ

MIDROC NewsletterSpecial Issue # 58 April 2019

21Addis Ababa, Ethiopia

ማጠቃለያ

የክብር ዶ/ር ሼህ ሙሐመድ ሁሴን አሊ አል አሙዲ የሚድሮክ ኢትዮጵያ ባለሀብትና ሊቀመንበር

በኢንቨስትመንት ረገድ ለአገራችን ፈር ቀዳጅ ኢንቨስተር ብቻም ሳይሆኑ በዓለም የቢሊኒየሮች ስም ሲነሳ

ኢትዮጵያም አብራ የምትነሳ አገር እንድትሆን በማድረግ ለአገሪቱ ስምና ዝና ምክንያት የሆኑ የአገራችን

ቁጥር አንድ ባለሀብት መሆናቸው ይታወቃል፡፡

ሼህ ሙሐመድ በአገራችን በተለያዩ የኢንቨስትመንት ሥራዎች በመሠማራት በሚድሮክ ቴክኖሎጂ ሥር

ከተካተቱት ሃያ ስድስት የሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ኩባንያዎች በተጨማሪ በባለሀብቱና ቤተሰቦቻቸው

አማካኝነት ያቋቋማቸው በጠቅላላው 75 ያህል ኩባንያዎች (በውስጣቸው ደርባ ሲምንት ግሩፕ፣ ሆራይዘን

ግሩፕ የመሳሰሉትን ጨምሮ) ለበርካታ ኢትዮጵያውያን የሥራ ዕድል በመፍጠር ከመቶ ሺህ ለማያንሱ

ኢትዮጵያውያን ዜጐች የሥራ ዕድልና መተዳደሪያ የፈጠሩ ናቸው፡፡

ሼህ ሙሐመድ በአገራችን በፈጠሯቸው የተለያዩ የኢኮኖሚ ዘርፍ የሥራ መስኮች ለሀገሪቱ በግብርና በታክስ

በሮያሊቲና በመሳሰሉት አስተዋጽዖ በማድረግና እንዲሁም አገሪቱ የውጭ ምንዛሬ ገቢ እንድታገኝና ልማቷን

እንድታፋጥን በማድረግ ተጠቃሚ እንድትሆን የበኩላቸውን ድርሻ እየተወጡ የሚገኙ ባለሀብት መሆናቸው

ይታወቃል፡፡

እኚህ የአገር አለኝታ፣ አገር ወዳድ፣ አዛኝ፣ ለጋስና ሆደ ሰፊ የሆኑት ሼህ ሙሐመድ ከህዳር 2010 አንስቶ

አሥራ አራት ወራት ያህል በሳዑዲ አረቢያ በእስር ላይ እንዲቆዩ በመደረጉ የተነሳ ብዙ ኢትዮጵያውያን

በተለይም አጠቃላይ የሚድሮክ ኢንቨስትመንት አመራሮችና ሠራተኞት አዝነውና ተጨንቀው ነበር፡፡

በሂደትም በኢትዮጵያ መንግሥት በኩል በተለይም በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ እና

በተለያዩ ከፍተኛ የመንግሥት ባለስልጣናት ጭምር በተደረገው የጎላ ዲፕሎማሲያዊ ጫናና በዶ/ር አረጋ

ይርዳው ሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ቺፍ ኤግዚኪዩቲቭ ኦፊሰርና ፕሬዚዳንት አመራር ‹‹ሼህ ሙሐመድ

ይፈቱ›› የሚለው የሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ አመራሮችና ሠራተኞች ዘመቻ እንቅስቃሴና የሌሎችም

የቴክኖሎጂ ግሩፑን ህብረተሰብ ጨምሮ ሌሎች ለሼህ ሙሐመድ በጎ ምኞትና ፍቅር ባላቸው ሰዎች ትብብር

እንዲሁም ሁሉም እንደ እምነቱ ባደረገው ልመናና ጸሎት በፈጣሪ ተሰምተው ጊዜው ደርሶ ሊቀመንበራችን

ትላንት ከነበሩበት የእስር ሁኔታ ተላቀዋል፡፡ የሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፑን የሼህ ሙሐመድ ይፈቱ ዘመቻ

እንቅስቃሴና ጥረት በዚህ መልኩ እናስታውሰዋለን። ሊቀመንበራችን የክብር ዶ/ር ሼህ ሙሐመድ ሁሴን

አሊ አል አሙዲ ከነበሩበት በአሁኑ ጊዜ ነፃ በመሆናቸው የቴክኖሎጂ ግሩፑ አመራሮችና ሠራተኞች በእጅጉ

ደስተኛ ናቸው ፈጣሪ ለሊቀመንበራችን ጤንነትና ረጅም እድሜ እንዲሰጣቸው ይመኛሉ፡፡

Page 24: የ‹‹ሼህ ሙሐመድ ይፈቱ›› ዘመቻ ትውስታዎች · የሚጠቅሙ እንደ ህዳሴ ግድብ ላሉ ሜጋ ፕሮጀክቶች ግንባታ፣ ለስፔስ

MIDROC NewsletterSpecial Issue # 58 April 2019

22Addis Ababa, Ethiopia

u’í ¾T>�ÅM (Distributed at no Cost)