australian citizenship test book - ahmaric...4 የአውትራሊያ ዜግነት: የጋራ...

40
ከአሁን ጊዜ ጀምሮ በእግዚአብሔር ስም፣ ለአውስትራሊያና ህዝቦቿ ታማኝ ለመሆን ቃል እገባለሁ፣ ባለው የዲሞክራቲክ እምነት ተሳታፊ እሆናለሁ፣ ያሉትን መብቶችና ነጻነቶች እንደማከስብር እና ባሉት ህጎች እንደምገዛና እንደምከተል ነው። የአውስትራሊያ ዜግነት የጋራ ማስተሳሰርሪያችን

Upload: others

Post on 15-Mar-2020

5 views

Category:

Documents


0 download

TRANSCRIPT

Page 1: Australian citizenship test book - Ahmaric...4 የአውትራሊያ ዜግነት: የጋራ መተሳሰሪያችን የአውስትራሊያ ዜጋ ስለመሆን በአውስትራሊያ

www.citizenship.gov.au

ከአሁን ጊዜ ጀምሮ በእግዚአብሔር ስም፣

ለአውስትራሊያና ህዝቦቿ ታማኝ ለመሆን ቃል እገባለሁ፣

ባለው የዲሞክራቲክ እምነት ተሳታፊ እሆናለሁ፣

ያሉትን መብቶችና ነጻነቶች እንደማከስብር እና

ባሉት ህጎች እንደምገዛና እንደምከተል ነው።

የአውስትራሊያ ዜግነትየጋራ ማስተሳሰርሪያችን

የአውስት

ራሊያ ዜ

ግነት

: የጋራ ማ

ስተሳሰር

ሪያችን

Page 2: Australian citizenship test book - Ahmaric...4 የአውትራሊያ ዜግነት: የጋራ መተሳሰሪያችን የአውስትራሊያ ዜጋ ስለመሆን በአውስትራሊያ

የአውስትራሊያ ዜግነትየጋራ ማስተሳሰርሪያችን

Page 3: Australian citizenship test book - Ahmaric...4 የአውትራሊያ ዜግነት: የጋራ መተሳሰሪያችን የአውስትራሊያ ዜጋ ስለመሆን በአውስትራሊያ

© የአውስትራሊያ መንግሥት (Commonwealth of Australia) 2009

ለዚህ ጽሁፍ የቅጂ መብት የተጠበቀ ነው። ይህንን ጽሁፍ ይዘቱን ሳይቀይር ለመክፈት፣ ማየት፣ ማተምና ማባዛት ሲችሉ እንዲሁም ይህን ማሳሰቢያ በመከተል ለግለሰብ፣ ለንግድ ባልሆነ ወይም በድርጅትዎ ውስጥ መጠቀም ይቻላሉ። በቅጅ መብት አንቀጽ ህግ Act 1968 (Copyright Act 1968) ዓ.ም መሰረት ከተፈቀደው ባሻገር ለመጠቀም ሌሎች መብቶች ሁሉ የተጠበቁ ናቸው።

የበለጠ ስልጣን ለማግኘት ወደሚከተለው ይመራል:በኮመንዌልዝ የቅጂ መብት አስተዳድር (Commonwealth Copyright Administration) Copyright Law Branch Attorney-General’s Department Robert Garran Offices National Circuit Barton ACT 2600

ፋክስ: 02 6250 5989 ኢሜል: [email protected]

በኢሚግሬሽንና የዜግነት የአገር አቀፍ ግንኙነት ቅርንጫፍ የታተመ አድርራሻ፡

6 Chan Street Belconnen ACT 2617

ISBN 978-1-92446-96-2

የክህደት ቃል:በዚህ ጽሁፍ ውስጥ የሞቱ ሰዎች ስእሎችን ስለሚይዝ ለአቦርጅናልና ቶረስ ስትራት አይላንደርስ አንባቢዎች ያስጠነቅቃል።

በአውስትራሊያ የዜግነት ፈተና ለመቀመጥ የሚያስፈልግዎ መረጃ በሞላ በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ይገኛል። የዜግነት ፈተና ለማለፍ ተብሎ ይህንን መጽሐፍ መግዛትና በሌላ ግለሰብ ወይም ድርጅቶች የተዘጋጀን የዜግነት ጽሁፎች መውሰድ አይኖርብዎም። ለዜግነት ፈተና ለማለፍ ይረዳል ተብሎ ለሚቀርብ ማንኛውም ጽሁፍ የኢሚግሬሽን መምሪያ አይደግፈውም።

Page 4: Australian citizenship test book - Ahmaric...4 የአውትራሊያ ዜግነት: የጋራ መተሳሰሪያችን የአውስትራሊያ ዜጋ ስለመሆን በአውስትራሊያ

ይዘት

መልእክት ለርስዎ 3

መፈተሽ ያለበት ክፍል

ክፍል 1 – አውስትራሊያና ህዝቦቿ 8

ክፍል 2 – በአውስትራሊያ የዲሞክራቲክ እምነት፣ መብትና ነጻነት 16

ክፍል 3 – በአውስትራሊያ ውስጥ መንግሥትና ህግ 22

መፈተሽ የሚገባው የቃላት ፍቺ ክፍል 30

በፈተና ጥያቄዎች ላይ ልምምድ ማድረግ 34

መፈተሽ የማይገባው ክፍል

ክፍል 4 – አውስትራሊያ በዛሬ ቀን 38

ክፍል 5 – የአውስትራሊያችን ታሪክ 54

መፈተሽ የማይገባው የቃላት ፍቺ ክፍል 72

ለበለጠ መረጃ 74

ምስጋና 76

Page 5: Australian citizenship test book - Ahmaric...4 የአውትራሊያ ዜግነት: የጋራ መተሳሰሪያችን የአውስትራሊያ ዜጋ ስለመሆን በአውስትራሊያ

የአውስትራሊያ ዜግነት ብዛት ያለው ሽልማቶችን ለማግኘት ይጠቅማል።

የአውስትራሊያ ዜግነት ስያገኙ ልዩ በሆነ የአገር አቀፍ ማህበረሰብ ውስጥ ይሳተፋሉ።

Page 6: Australian citizenship test book - Ahmaric...4 የአውትራሊያ ዜግነት: የጋራ መተሳሰሪያችን የአውስትራሊያ ዜጋ ስለመሆን በአውስትራሊያ

3መልእክት ለርስዎ

መልእክት ለርስዎ የአውስትራሊያ ዜጋ ለመሆን በመምረጥዎ እንኳን ደስ አለዎት። በአዲስ አገር ለመኖርና ሙሉ በሙሉ እንደ ዜጋዊ ተሳትፎ ለማድረግ ጉብዝናን፣ ጥረትንና መስዋእነትን ይጠይቃል። ዲሞክራሲያዊና ሰላማዊ በሆነ ሕብረተሰባችን ውስጥ የርስዎን አስተዋጽኦ ዋጋ እንሰጠዋለን።

በርስዎ የስደት ታሪክ ውስጥ የአውስትራሊያ ዜግነት ማግኘቱ ጠቃሚ እርምጃ ይሆናል። የአውስትራሊያ ዜጋ መሆን ማለት ለአውስትራሊያና አገሪቷ ለቆመችበት ዓላማ ሁሉ ለመክፈል የማያቋርጥ መስዋእትነት ያደርጋሉ። እንዲሁም በአውስትራሊያ ማህበረሰብ ውስጥ መደበኛ አባልነትን የሚጀምሩበት ጊዜ ይሆናል። ‘እኔ አውስትራሊያዊ ነኝ ማለት የሚችሉበት ደረጃ ይሆናል።

የአውስትራሊያ ዜግነት ብዛት ያለው ሽልማቶችን ለማግኘት ይጠቅማል። የአውስትራሊያ ዜግነት ስያገኙ ልዩ በሆነ የአገር አቀፍ ማህበረሰብ ውስጥ ይሳተፋሉ። አገራችን በጣምራ ይተውጣጣ አስተዋጽኦ ማለት በአገር ተወላጆቻችንና ከዚያም በኋላ ከሞላው ዓለም በመጡ ሰዎች የታነጸች ትሆናለች። ይህንን ልዩ ስለመሆን በዓል እናከብራለን እንዲሁም በጣምራ ለመኖርና ተስማሚ አገር እንድትሆን ነው።

የአውስትራሊያ ማህበረሰብ ጥንካሬ ማለት አውስትራሊያ ታላቅ አገር እንድትሆን ያሉትን ችግሮች በጋራ አብሮ መፍታት ይሆናል። የተረጋጋ የመንግሥት አሰራር ዘዴ ስላለን ስለዚህ ማንኛውም አውስትራሊያዊ የመንግሥት ባለሥልጣንና ህጎችን ያከብራል። የተረጋ መንግሥታችን፣ ባህላችን እና ህጎቻችን በታሪካችን ሂደት ይስተካከላሉ። በአውስትራሊያ ማህበረሰብ ውስጥ ተሳትፎ ሲያደርጉ ለዚህ ታሪክ ወራሽ በመሆን ያለዎትን አስተዋጽኦ ለማድረግ ይችላሉ።

አውስትራሊያ የጥንት መሬት ናት። ይህም ሰፊና ልዩ ነው። አውስትራሊያ የበርሀ ዛፍና የእንጨት መሬት፣ ወርቃማ የባህር ዳርቻና ደረቅ ምድረ በዳ ያለባት አገር ናት። የአገሬው ተወላጆቻችን ባህሎች የጥንት ሲሆኑ በዓለም ውስጥ ቀጣይነትር ያላቸው ባህሎች ናቸው። እንዲሁም ለጋ አገር ስንሆን የስደተኞች ህዝብ አገር ናት። በአውስትራሊያ ውስጥ የአውሮፓ ሰፋሪዎች የጀመረው በ1788 ዓ.ም ሲሆን እስከ አሁን ድረስ አዲስ ስደተኞችን/ማይግራንትስ እየተቀበልን ነው። ከ200 በላይ አገሮች ለመጡ ሰዎች አውስትራሊያ የመኖሪያ ስፍራቸው ሆናለች። በዚም ውጤት ሕብረተሰባችን በዓለም ውስጥ የተለያየ ባህሎች ካሉት አንዷ አድርጓታል። በአውስትራሊያ የጎሳዎችና የባህላዊ ቡድኖች ውህደት በአገር አቀፍ ውጤት አሳይቷል። ዜግነት ሁላችንም በአንድነት ያስተሳስራል።

አውስትራሊያ ዲሞክራሲ የሰፈነበት ነው። የአገራችንን ዲሞክራቲክ ለማነጽ ተሳትፎ ለማድረግ ዜግነት ሲያገኙ እድሉን ይሰጥዎታል። ይህም እንደ መደበኛ የአውስትራሊያ ማህበረሰብ አባል መሆን ያለብዎን ሃላፊነት ለማሟላት ዝግጁ ነዎት ማለት ነው። የእያንዳንዱን ሰው ክብርና ነጻነት፣ የወንዶችንና ሴቶችን እኩልነት እንዲሁም ህገ ደንብን ማክበር የአውስትራሊያኖች እምነት ነው። የአውስትራሊያ ዜግነት ሲያገኙ በየቀኑ ስለሚኖርዎ ሕይወት ከነዚህ ልምዶች ነጻ ይሆናሉ።

በአውስትራሊያ ዜግነት ቃል መግባትበአውስትራሊያ ዜግ የሆነ ሁሉ ስለ መብታችንና ግዴታችን ማወቁ አስፈላጊ ሲሆን ይህም በትውልድም ሆነ እንደምርጫችን በአውስትራሊያ ዜጋ መሆን ምን ማለት እንደሆነ መረዳት። ይህ አገራችንን ለማነጽ ወሳኝ ክፍል ይሆናል።

በአውስትራሊያ ዜግነት ክብረ በዓል ላይ ለማክበር ሲሄዱ የአውስትራሊያ ዜግነት ስለመሆን ቃል ይገባሉ። ይህንን በማድረግ ለአውስትራሊያ ህዝባዊ መስዋእትነትን እንደሚከፍሉና የዜግነት ስለመሆን ያለውን ሃላፊነትና ነጻነት እንዳመኑ ነው። ቃል ከገቡ በኋላ ትርጉሙን መማሩ አውስትራሊያዊ በመሆንና ስለ ዜግነት ያለውን ሃላፊነትና ነጻነት በበለጠ እንዲያውቁት ይረዳዎታል።

ይህ የሚገቡት ቃል ኪዳን ይሆናል:

ከአሁን ጊዜ ጀምሮ በእግዚአብሔር ስም*

ለአውስትራሊያና ህዝቦቿ ታማኝ ለመሆን ቃል እገባለሁ፣

ባለው የዲሞክራቲክ እምነት ተሳታፊ እሆናለሁ፣

ያሉትን መብቶችና ነጻነቶች እንደማከስብር እና

ባሉት ህጎች እንደምገዛና እንደምከተል ነው።

* አንድ ሰው “በእግዚአብሔር ስም” የሚለውን ቃል ለመጠቀም ወይም አለመጠቀም ይችላል።

ስለ ቃል መግባት ትርጉምን ለማወቅና እንዴት በአውስትራሊያ ሕብረተሰብ ውስጥ ሚና መጫወት እንደሚችሉ ይህንን መጽሐፍ ሲያነቡ ይረዱታል።

Page 7: Australian citizenship test book - Ahmaric...4 የአውትራሊያ ዜግነት: የጋራ መተሳሰሪያችን የአውስትራሊያ ዜጋ ስለመሆን በአውስትራሊያ

4 የአውትራሊያ ዜግነት: የጋራ መተሳሰሪያችን

የአውስትራሊያ ዜጋ ስለመሆን በአውስትራሊያ የስደተኛ ታሪክ ከ200 ዓመታት በላይ ይሆነዋል። በዚህ ላይ አሁንም ገና ለጋ አገር እንደሆንና እርስዎም የታሪካችን ተካፋይ እንደሆኑ ነው። እንደ አውስትራሊያ ዜጋ መሆንዎ መጠን የሚወስዱት ውሳኔ ለወደፊት እድላችን ይረዳል።

የአውስትራሊያዊ ዜግነት ፈተና ስለ አውስትራሊያና ዜግነት ስለሚኖር ሃላፊነትና ነጻነት በቂ ግንዛቤ ካለዎት ለማጣራት ሲባል ለአውስትራሊያዊ ዜግነት ፈተና እቅድ ወጥቷል።

እንዲሁም የእንግሊዝኛ መሰረታዊ ችሎታ ካለዎት ለማጣራት ሲባል የዜግነት ፈተና ወጥቷል። እንግሊዝኛ የሃገራችን ብሄራዊ ቋንቋ ነው። በእንግሊዝኛ ቁንቋ ግንኙነት መፍጠሩ በአውስትራሊያ ማሕበረሰብ ታላቅ ሚና እንዲጫወቱ ይረዳዎታል። ይህም ኣውስትራሊያ በምታቀርበው የትምህርት፣ የሥራና ሌሎችን እርዳታ ለማግኘት እድሉን ይከፍትልዎታል፡

ለዜግነት ፈተና በኮምፑውተር ሲቀርብ ይህም በእንግሊዝኛ ሆኖ በምርጫ ይሆናል። ከብዙ ጥያቄዎች ውስጥ ለፈተና 20 ጥያቄዎች አልፎ አልፎ ይመረጣል። ፈተናውን ለማለፍ ከመቶ 75 እጁን መመለስ ወይም ከ20 ጥያቄዎች ውስጥ 15’ቱን በትክክልል መመለስ አለብዎት።

በአውስትራሊያ ውስጥ የዜግነት ፈተናዎች በኢሚግሬሽንና ዜጎች መምሪያ ጽ/ቤት ይካሄዳል። በተጨማሪም በአውስትርሊያ ክልላዊ አስተዳደር ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች እና በአንዳንድ የውጭ አገር የመልእክተኛ ሚሽን በኩል ለፈተናዎች ፕሮግራም ይወጣል።

ይህንን ፈተና በማለፍና ለስአውስትራሊያዊ ዜግነት ቃል በመግባት ስለሚያካሂዱት መስዋእትነት በተግባር ማሳየት እንደሚችሉ ነው።

የአውስትራሊያ ዜግነት ፈተና ለመውሰድ ስለመዘጋጀት ለፈተናው ለመዘጋጀት ይህንን መሰረታዊ መገልገያ መጽሐፍ ማንበብ ይኖርብዎታል።

ስለ መገልገያ መጽሐፍበዚህ መገልገያ መጽሐፍ ውስጥ መፈተሽ የሚገባውና የማይፈተሽ ክፍል ይኖረዋል።

መመዘን ያለበት ክፍልእርስዎ ይህንን ፈተና ለማለፍ ማወቅ የሚገባዎ መረጃዎች ሁሉ በዚህ መጽሐፍ የመጀመሪያዎቹ ክፍሎች ውስጥ ይገኛል:

• ክፍል 1 - አውስትራሊያና ህዝቦቿ

• ክፍል 2 - የአውስትራሊያ ዲሞክራቲክ እምነት፣ መብትና ነጻነት

• ክፍል 3 - በአውትርሊያ ውስጥ መንግሥትና ህግ

መፈተሽ ባለበት ክፍል ውስጥ ያለውን መረጃ በሚገባ ማወቅና መረዳት ያስፈልግዎታል ስለዚህ በዜግነት ፈተና ውስጥ ለሚቀርቡት ጥያቄዎች መልስ ለመስጠት ይችላሉ።

መመዘን ስለማያስፈልግ ክፍልበፈተና መመዘን በማይኖርበት ክፍል ውስጥ ጠቃሚ የሆኑ መረጃዎች ሲኖሩት ታዲያ በአውስትራሊያ ያለውን ታሪክና ባህል ለማወቅ ይረዳዎታል። በዚህ ክፍል ያለውን ስላለው መረጃ አይፈተኑም።

• ክፍል 4 - አውስትራሊያ በዛሬ ቀን

• ክፍል 5 - የአውስትራሊያውያን ታሪካችን

ለመለማመጃ ጥያቄዎችለርስዎ የዜግነት ፈተና ለመዘጋጀት ይረዳዎ ዘንድ በፈተና መመዘን ያለበት ክፍል ውስጥ 200 የመለማመጃ ጥያቄዎች አሉ።

የቃላት ትርጉምበሚመዘንና በማይመዘኑ ክፍሎች መጨረሻ ላይ የቃል ትርጉም (የዋና ቃላቶች ትርጉም ዝርዝር) ይኖራል።

የዚህ መገልገያ መጽሐፍ ትርጉምይህ የመገልገያ መጽሐፍ በ37 የማህበረሰብ ቋንቋዎች እንደተተረጎመና ታዲያ ለወደፊት ዜጋ ለሚሆኑ ሰዎች የማንበብ ብቃት ካላቸው ከእንግሊዝኛ ባሻገር በሌላ ቋንቋ እንዲያነቡት ነው። የአውስትራሊያ ዜግነት ድረገጽን www.citizenship.gov.au በመክፈት ብቻ እነዚህ የትርጉም ጽሁፎች ይቀርባሉ።

Page 8: Australian citizenship test book - Ahmaric...4 የአውትራሊያ ዜግነት: የጋራ መተሳሰሪያችን የአውስትራሊያ ዜጋ ስለመሆን በአውስትራሊያ

5መልእክት ለርስዎ

ድቭድ/DVDየወደፊት ዜጎች ለፈተና እንዲዘጋጁ ይረዳ ዘንድ በእንግሊዝኛ በሚታይ ድምጽ ድቭድ ቀርቧል። በድቭድ ውስጥ ከመመዘን ያለበት ክፍል ቁልፍ በሆኑ ነጥቦች የቀረበን ንግግር ሲቀርብ እንዲሁም 20 የፈተና መለማመጃ ጥያቄዎች ይኖሩታል። አነስተኛ የእንግሊዝኛ ችሎታ ላላቸው ደንበኞች ለማጥናት እንዲረዳቸው በሚል ይህ ድቭድ ወጥቷል። ይህ ድቭድ በትእዛዝ ሲቀርብ ወይም ከአውስትራሊያ ዜግነት ድረገጽ ስwww.citizenship.gov.au ላይ ይቀርባል።

በአውስትራሊያ የዜግነት ፈተና ጊዜ እርዳታአብዛኛው የአውስትራሊያ ዜጋ የሚሆኑ ሰዎች የማንበብና የመጻፍ ችሎታ እንደሚኖራቸውና ያለ እርዳታ ፈተናውን እንደሚያጠናቅቁ ይገመታል። ይሁን እንጂ አነስተኛ የእንግሊዝኛ ማንበብና መጻፍ ችሎታ ላላቸው ሰዎች ሃላፊው ጥያቄዎችን በማንበብና መልስ ሊሆኑ የሚችሉትን በማቅረብ ሊረዳ ይችላል። እንዲሁም አነስተኛ የኮምፑተር ችሎታ ላላቸው ወይም የአካለ ጉዳተኛ ለሆኑ ስዎች እርዳታ ይቀርብላቸዋል። የዜግነት ፈተና በሚወስዱበት ጊዜ እርዳታ ካስፈለግዎ እባክዎን የዜግነት ሃላፊን ያማክሩ።

የጋራ መተሳሰሪያችን: በአውስትራሊያ የዜግነት ኮርስ ትምህርትበኮምፑተር በኩል ፈተና ከመውሰድ ፋንታ የአውስትራሊያ የዜግነት ኮርስ ትምህርት ለማካሄድ ሊፈቀድልዎ ይችላል።

በዚህ መጽሐፍ ያሉትን በፈተና መመዘን ያለበት ክፍልንና መረጃዎችን በሞላ የዜግነት ኮርሱ ያካተተ ይሆናል። ይሁን እንጂ መሰረታዊ የእንግሊዝኛ ችሎታ ስለመኖርዎት እና በአውስትራሊያ የዜግነት ቃል መግባት ምን ያህል እንደተረዳዎት ማሳየት ይኖርብዎታል።

ስለ ኮርሱ የበለጠ መረጃ በአውስትራሊያ የዜግነት ድረገጽ www.citizenship.gov.au ላይ ቀርቧል።

በበለጠ መረጃ ለማግኘትለዜግነት መረጃ ማቅረቢያ መስመር በስልክ 131 880 (ከሰኞ እስከ ዓርብ ሰዓት 8.30 am እስከ 4.30 pm) መደወል ይችላሉ።

የአስተርጓሚ አገልግሎትን ከፈለጉ እባክዎ በስልክ 131 450 ይደውሉ።

እንዲሁም በአውስትራሊያ የዜግነት በድረገጽ www.citizenship.gov.au ላይ መጎብኘት ይችላሉ።

በአውስትራሊያ የዜግነት ክብረ በዓል የአውስትራሊያ ዜግነት ክብረ በዓል አጭር ሊሆን ይችላል፤ ይህም ጥቂት ሰዎችን ሲያካትት ወይም በጣም ብዙ ማለት በመቶ ወይም በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ያቀፈ ይሆናል። በአዲስ ዜጎች መካከል ያለው ጥልቅ ስሜትና ኩራት በጣም ደስ የሚያሰኝ ክብረ በዓል እንዲሆን የሃላፊዎቹ ሥራ ውጤት ይሆናል።

የዜግነት ክብረ በዓል ሲጀምር በአካባቢዎ የባህል ባለቤት በሆኑት የአገሬው ተወላጅ ተወካይ በሆኑት አማካኝነት የእንኳን ደህና መጡ አቀባበል ይደረጋል። ከሌሎች የአካባቢዎ ማህበረሰብ ወይም መንግሥታዊ ተወካይ መሪዎች የእንኳን ደህና መጡ ድምጽና ማበረታቻ ቃላት ይሰማሉ።

በአውስትራሊያ የዜግነት ስለሚሰጥ ቃል ኪዳን ማንበብ ወይም ከሌሎች ከተመረጡ አዲስ የአውስትራሊያ ዜጎች ጋር ሆኖ በድጋሜ ማንበብ። ይህ በጣም አስፈላጊ የሆነው የክብረ በዓሉ ክፍል ይሆናል። ለአውስትራሊያ መስዋእት ለመክፈል ቃል እስኪገቡ ድረስ የአውስትራሊያ ዜግነት አያገኙም። በመሃላ ጊዜ ለመያዝ መጽሐፍ ቅዱስ ይዘው መምጣት ሲችሉ፣ ነገር ግን ግዴታ አይደለም።

ስለ ዜግነት ትርጉምና ምንነት ከማህበረሰብዎ መሪዎች ወይም ከመንግሥት ተወካዮች አጭር ንግግር ይደረጋል። የአውስትራሊያ ዜግነት ምስክር ወረቀትዎን በማግኘት ከዚያም ከማህበረሰቡ ትንሽ ስጦታ ሊያገኙ ይችላሉ። ማንኛውም ሰው ‘Advance Australia Fair’ የሚለውን በመዘመር ከዚያም ከሌሎች የአውስትራሊያ ጓደኞችዎ ጋር ተገናኝተው ለማክበር እድል ይኖርዎታል።

የአውስትራሊያ ዜጋ በመሆንዎ ጥሩ እየተመኘንልዎ ለወደፊት በአውስትራሊያ ሕይወትዎ በሰላም ቀጣይ ይሆን ዘንድ ምኞታችን ነው።

አዲስ የአውስትራሊያ ዜጎች በዜግነት ክብረ በዓል ላይ

Page 9: Australian citizenship test book - Ahmaric...4 የአውትራሊያ ዜግነት: የጋራ መተሳሰሪያችን የአውስትራሊያ ዜጋ ስለመሆን በአውስትራሊያ
Page 10: Australian citizenship test book - Ahmaric...4 የአውትራሊያ ዜግነት: የጋራ መተሳሰሪያችን የአውስትራሊያ ዜጋ ስለመሆን በአውስትራሊያ

በፈተና መመዘኛ ክፍል ስለመጀመር

Page 11: Australian citizenship test book - Ahmaric...4 የአውትራሊያ ዜግነት: የጋራ መተሳሰሪያችን የአውስትራሊያ ዜጋ ስለመሆን በአውስትራሊያ

ክፍል 1አውስትራሊያና ህዝቦቿ

ከአሁን ጊዜ ጀምሮ በእግዚአብሔር ስም*

ለአውስትራሊያና ህዝቦቿ ታማኝ ለመሆን ቃል እገባለሁ፣

ባለው የዲሞክራቲክ እምነት ተሳታፊ እሆናለሁ፣

ያሉትን መብቶችና ነጻነቶች እንደማከስብር እና

ባሉት ህጎች እንደምገዛና እንደምከተል ነው።

* አንድ ሰው “በእግዚአብሔር ስም” የሚለውን ቃል ለመጠቀም ወይም አለመጠቀም ይችላል።

Page 12: Australian citizenship test book - Ahmaric...4 የአውትራሊያ ዜግነት: የጋራ መተሳሰሪያችን የአውስትራሊያ ዜጋ ስለመሆን በአውስትራሊያ

ክፍል 1 – አውስትራሊያና ህዝቦቿ 9

አውስትራሊያና ህዝቧበዜግነት ክብረ በዓል ላይ ለአውስትራሊያና ህዝቧ ታማኝ ለመሆን ቃል ገብተዋል። ስለዚህ ስለአውስትራሊያ ማህበረሰብና ህዝብ፣ የአገር ቅርሳችንን ያካተተ ማወቁ ጠቃሚ ነው። በተጨማሪም ስለ አውስትራሊያ እድገት ማለት ካልተጠበቀው የብሪቲሽ ቅኝ አገዛዝ ጀምሮ ወደተረጋጋና ውጤታማ የሆነ የዛሬዋ መድብለ ባህላዊ አገር ስለመሆን ማወቁ አስፈላጊ ነው።

በታሪካችን ላይ አስተዋጽኦ ስላደረጉት ድርጊቶች በዚህ ክፍል ውስጥ ያነባሉ። ስለ እኛ መስተዳድር ግዛትና ተሪቶሪስ መረጃ ሲሆን እንዲሁም የአውስትራሊያውነትን የሚያሳይ ባህልና ምልክት መግለጫስ ስላለን ያኮራናል።

ህዝባችንየአገር ተወላጅ አውስትራሊያኖችበአውስትራሊያ የመጀመሪያ ሰፋሪዎች አቦርጅናልና ቶረስ ስትሪት አይላንደርስ ነበሩ። እነሱም የአውስትራሊያ የአገሬው ተወላጆች ናቸው። የአውስትራሊያ ተወላጅ ባህሎች የጥንትና በዓለም ውስጥ ቀጣይነት አለው።

በታሪክ የአቦርጅናል ሰዎች አመጣጥ ከዋናው የአውስትራሊያና ታዝማኒያ ይሆናል። እነሱም በዚች አገር ላይ ከ40 000 እስከ 60 000 ዓመታት ኖረዋል።

ቶረስ ስትሬት አይላንደርስ ከስሜን ኩንስላንድ ካለች ደሴት ናቸው። የራሳቸው መለያ የሆነ ባህል አላቸው።

የአገር ተወላጅ ሰዎች ይጋራ እምነትና ባህል ሲኖራቸው ይህም እስከ አሁን ድረስ መመሪያቸው ይሆናል። ስለነሱ ታሪክ፣ ስነ-ጥበብና ዳንስ በሚገልጽ መሬት ላይ ከፍተኛ ግንኙነት አላቸው።

የአውሮፓ ሰፋሪ በመጀመሪያ ጊዚያትየአውሮፓ ሰፋሪ በመጀመሪያ 11 ወንጀለኛ መርከቦች ሲደርሱ እንደጀመረና ይህም “የመጀመሪያ ጉዞ” በመባል ሲጠራ ከታላቋ ብሪቴን ጥር/ January 26 ቀን 1788 ዓ.ም እንደደረሰ ነው።

በዚህን ጊዜ የብሪቴን ህግ ጥብቅ እንደነበርና በወንጀል ለተያዙት ቁራቸው ብዙ ስለሆነ እስር ቤት ሊበቃ እንዳልቻለ ነው። ይህንን ችግር ለማቃለል ሲባል እንነህን ወንጀለኞች ወደ ሌላ የዓለም ክፍል፤ አዲስ የቅኝ ግዛት ወደሆነችው ወደ ኒው ሳውዝ ዌልስ ለማጓጓዝ የብሪትሽ መንግሥት ወሰነ።

የመጀመሪያው የኒው ሳውዝ ዌልስ ገዥ Captain Arthur Phillip ይባሉ ነበር። የአውሮፓ ሰፋሪዎች እንደመጡ ለመጀመሪያ ዓመታት ችግሮችን እንደተቋቋመ ነው። የቅኝ አገዛዙ በመቀጠል የበለጠ ወንጀለኞችና ነጻ የሆኑ ሰፋሪዎች በመድረስ አገሪቷ እያደገችና እየበለጸገች ሄደች። በሌላው የአገሪቷ ክፍሎች በበለጠ ቅኝ አገዛዙ ትመሰረተ።

የመጀመሪያዎቹ ነጻ ሰፋሪዎች ከታላቋ ብሪቴንና አይላንድ ነበሩ። የብሪቲሽና የአይሪሽ ቅርስ በአውስትራሊያ ታሪክ፣ ባህልና የፖለቲካ ተቋማት ላይ ከፍተኛ ተጽእኖ አሳድሮበታል።

በ1851 ዓ.ም ውስጥ በኒው ሳውዝ ዌልስና በቪክቶሪያ ቅኝ ግዛት ውስጥ ወርቅ እንደተገኘ ነበር። ሰዎች ከሞላው ዓልም ዙሪያ እድላቸውን ለመሞከር ወደነዚህ ቅኝ ግዛቶች መጡ። በዚህን ጊዜ ከአውሮፓ ከተሰደዱት ከቻይና የመጡት የሰው ብዛት በቁጥር የመጀመሪያው ነበር። በ10 ዓመታት ውስጥ የህዝቡ ቁጥር ከእጥፍ በላይ ጨመረ።

የአውስትራሊያ አገርየተለያዩ ቅኝ ግዛቶች በአንድ መንግሥት ስለመሆን ሃሳብ ለተከታታይ አሰር አመታት ተወያይተዋል።

በ1901 ዓ.ም ውስጥ የቅኝ ግዛቶች በመጣመር የፌደሬሽን አስተዳደር ግዛቶች በመፍጠር ይህም የኮመንዌልዝ አውስትራሊያ መንግሥት ተባለ። በዚህን ጊዜ የአውስትራሊያ ህዝብ ብዛት ሲቆጠር ወደ አራት ሚሊዮን ገደማ ነበር። ይህ ቁትር የአገር ተወላጁን ህዝብ አያካትትም።

በመጀመሪያ አጋማሽ 20ኛው መቶ ዓመት፣ የመጤው ደረጃ ከፍና ዝቅ ይል ነበር። የብሪቲስህ መጤዎችን እዚህ ለማስፈር ለማበረታታት ተብሎ የወጣ ፕሮግራም እንደነበርና ብዙዎች እንደመጡ ነው።

ከሁለተኛው ዓለም ጦርነት በኋላ የብሪቲሽ ስደተኞች ያልሆኑና ከአውሮፓ በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ትውልድ አገራቸውን እንዲለቁ ሲደረግ በቅጽበት እንደመጡ ነው። ብዛት ያላቸው ወደ አውስትራሊያ የመጡት አዲስ ኑሮን ለመመስረት ነበር።

በቅርብ ዓመታት ውስጥ ያለን የማይግሬሽንና የስደተኛ ፕሮግራም ከሞላው ዓለም ስሰዎን ወደ አውስትራሊያ እያመጣ ነው። ሰዎች ወደዚህ የሚመጡት ከቤተሰቡ ጋር ለመቀላቀል፣ በለጋ አገር አዲስ ኑሮን ለመመስረት ወይም ከድህነት፣ ጦርነት ወይም ከስቃይና በደል ለመሸሸት ሲባል ነው።

ዛሬ የአውስትራሊያ ህዝብ ቁጥር ወደ 22 ሚሊዮን ይሆናል። ከህዝቡ አንድ አራተኛው እጅ በላይ የተወለደው በውጭ አገር ነው። እነዚህ ህዝቦች ለአገራችን በሚያደርጉት አስተዋጽኦ ታላቋ አውስትራሊያ አሰኝቷታል። የተለያዩና ብዛት ያለው የአውስትራሊያን በዓላት በምናከብርበት ጊዜ እንዲሁም በአንድነት የተጣመረ አገር ለመገንባት በሚል ዓላማ ነው።

የአውስትራሊያ ብሄራዊ ቋንቋ እንግሊዝኛ ነው። ይህም የብሄራው መለያችን አካል ነው። በአውስትራሊያ ውስጥ ማንናውም ሰው የእንግሊዝኛ ቋንቋ እንዲማር በማበረታታት ስለዚህ በአውስትራሊያ ሕብረተሰብ ውስጥ ለመሳተፍ እንግሊዝኛን መጠቀም ይሆናል። በአውስትራሊያ ሲኖሩና ሲማሩ በእንግሊዝኛ ግንኙነት መፍጠሩ ጠቃሚ ይሆናል። እንዲሁም ሌሎች ቋንቋዎችም ዋጋ አላቸው። በአውስትራሊያ ብዛትና የተለያየ ሕብረተሰብ ውስጥ ከ200 በላይ ቋንቋዎች ይነገራሉ።

Page 13: Australian citizenship test book - Ahmaric...4 የአውትራሊያ ዜግነት: የጋራ መተሳሰሪያችን የአውስትራሊያ ዜጋ ስለመሆን በአውስትራሊያ

የአውትራሊያ ዜግነት: የጋራ መተሳሰሪያችን 10

የአውስትራሊያ መስተዳድር ግዛትና ተሪቶሪስየኮመንዌልዝ አውስትራሊያ መንግሥት ከመስተዳድር ግዛትና ተሪቶሪስ በፈደሬሽን የተመሰረት ነው። ስድስት የመስተዳድር ግዛቶችና ሁለት የዋናው መሬት ተሪቶሪስ ይህም የርሱ የሆነ ርእሰ ከተማ አለው።

መስተዳድር ግዛት ርእሰ ከተማ

New South Wales (NSW) Sydney

Victoria (Vic.) Melbourne

Queensland (QLD) Brisbane

Western Australia (WA) Perth

South Australia (SA) Adelaide

Tasmania (Tas.) Hobart

ትሪቶርይ/Territory ርእሰ ከተማ/Capital city

Australian Capital Territory (ACT) Canberra

Northern Territory (NT) Darwin

እንዲሁም Canberra የአውስትራሊያ ርእሰ ከተማ ናት

Darwin

Brisbane

Hobart

Melbourne

Australian Capital Territory

Perth

Adelaide

Queensland

New South Wales

Northern Territory

Western Australia

South Australia

Tasmania

Victoria

CanberraSydney

Page 14: Australian citizenship test book - Ahmaric...4 የአውትራሊያ ዜግነት: የጋራ መተሳሰሪያችን የአውስትራሊያ ዜጋ ስለመሆን በአውስትራሊያ

ክፍል 1 – አውስትራሊያና ህዝቦቿ 11

አውስትራሊያን ካፒታል ተሪቶርይ (Australian Capital Territory)

ኒውሳውዝ ዌልስ (New South Wales)

ክዊንስላንድ (Queensland)

South Australia

ታዝማኒያ (Tasmania)

ቪክቶሪያ (Victoria)

Western Australia

ኖርዝ ተሪቶርይ (Northern Territory)

የመስተዳድር ግዛትኒውሳውዝ ዌልስ/New South Wales የመጀመሪያዋ በብሪቲሽ የተመሰረተች ቅኝ ግዛት ነበረች። የኒውስዝ ሳውስ ዌልስ ርእሰ ከተማ ሲድኒ ስትሆን በሃገሪቷ ታላቁ ከተማ ናት። የስድነይ ሃርቦር ድልድይ/Sydney’s Harbour Bridge እና የኦፐራ ሃውስ/Opera House የሃገሪቷ ምስል ምልክት ናቸው።

ቪክቶሪያ/Victoria ከዋና የመስተዳድር ግዛቶች ውስጥ ትንሿ ናት። በቪክቶሪያ ውስጥ ብዝዎቹ አስደንቂ ህንጻዎች የሰሩትን በ1850 ዎቹ ከተገኘው የወርቅ ሀብት ነበር። የቪክቶሪያ ርእሰ ከተማ ሜልበርን ነው።

ክዊንስላንድ/Queensland ሁለተኛው ታላቁ የመስተዳድር ግዛት ነው። በስሜን በኩል የቶረስ ስትሬት አይላንደርስ፣ የትሮፒካል ተፈትሮ ጫካ፣ ውሃ አዘል የጠርፍ አካባቢና ብዙጊዜ ደረቅ የሆነ ምድረ በዳ ይገኝበታል። በዓለም የታወቀው ዝነኛው ታላቁ የባህር ጠረፍ እስከ ምሥራቅ ጠረፍ ድረስ ተዘርግቷል። የኩውንስላንድ ርእሰ ከተማ ብሪስባን ነው።.

Western Australia ትልቁ የመስተዳድር ግዛት ነው። ምሥራቃዊ የግዛት ክፍል አብዛኛው በርሀ ምድረ በዳ ሲሆን የደቡባዊ ምዕራብ ክፍል ደግሞ ለም የእርሻና የወይን ተክል የሚበቅልበት አካባቢ ነው። የመስተዳድር ግዛቱ ለብዙ ትላልቅ የማእድን ማውጫ ፕሮጀክቶች የሚገኝበት ስፍራ ነው። በመስተዳድር ግዛት ካለው የህዝብ ብዛት ውስጥ ሶስት አራተኛው እጅ በርእሰ ከተማ ፐርዝ ውስጥ ይኖራል።

South Australia አባጣ ጎርባጣ የሆነ የባህር ጠረፍ ሲኖረው እንዲሁም ብዙ የታወቀ የወይን ክልሎች አሉት። አደላይድ ርእሰ ከተማ ሲሆን ብዛት ያለው የቅኝ አገዛዝ ንድፈ ጥበብ ምሳሌዎች ይገኛል።

ታዝማኒያ/Tasmania አነስተኛው የመስተዳድር ግዛት ሲሆን ይህም ከዋና መሬት የተለየው Bass Strait በተባለ ጠባብ የባህር ወሽመጥ ይሆናል። ደሴቱ በአብዛኛው በጫካ የተከበበ መሬት አለው። የታዝማኒያ ርእሰ ከተማ ሆባርት ይባላል።

ተሪቶርይስአውስትራሊያን ካፒታል ተሪቶርይ/Australian Capital Territory የሚገኘው በስይድነይ እና ሜልበርን መካከል ነው። የአገሪቱ ርእሰ ከተማ ካንበራ ይገኝበታል። ካንበራ ጠቃሚ የሆኑት ብሄራዊ ተቋማት ማለት እንደ የፓርሊያመንት ሀውስና በአውስትራሊያ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሚቀመጡበት ይሆናል።

ኖርዝ ተሪቶርይ/Northern Territory በሰሜን በኩል ሀሩና ሞቃት እንዲሁም በደቡብ ቀይ የምድረ በዳ አፈር አለው። አነስተኛ የሆነው ህዝብ ብዛት በአብዛኛው የሚኖረው በርእሰ ከተማው ዳርዊንና አሊስ ስፕሪንግስ እንደሆነና ከዳርዊን እስከ አሊስ ስፕሪንግስ ባለው ዋና አውራ መንገድ ተከትሎ ሲሆን ይህም በማእከላዊ አውስትራሊያ አጠገብ ዋናው ከተማ ነው።

Page 15: Australian citizenship test book - Ahmaric...4 የአውትራሊያ ዜግነት: የጋራ መተሳሰሪያችን የአውስትራሊያ ዜጋ ስለመሆን በአውስትራሊያ

የአውትራሊያ ዜግነት: የጋራ መተሳሰሪያችን 12

ብዙዎቹ የዜግነት ክብረ በዓላት በየዓመቱ የአውስትራሊያ ቀን ይካሄዳል በAnzac ቀን የወታደር ሰልፍ

ባህልና ምልክቶችለአውስትራሊያ ጠቃሚ ቀናትየአውስትራሊያ ቀንየአውስትራሊያ ቀንን በየአመቱ 26 ጥር/January እናከብራለን። በአውስትራሊያ ውስጥ ባሉ እያንዳንዱ ግዛትና ተሪቶርይ ይህ ህዝባዊ በዓል ነው።

ብሞላው አውስትራሊያ ክልል ያሉ ትላልቅና ትናንሽ ማህበረሰባት ስለ አውስትራሊያ ታላቅነትና አውስትራሊያዊ መሆን ልእመግለጽ የአውስትራሊያን ቀን ይያክራሉ።

የክብር ታሪካችንና ታላቅ አገር እንድትሆን ላደረጉ ሰዎች በሞላ የሚታወስበት የአውስትራሊያ ቀን ይባላል። በዚህ ቀን በአካል ተገናኝቶ ለወደፊት በደስታ አብሮ ለመኖር ቃል የሚገባበት ጊዜ ነው። ስለዚህ በዚህ ቀን በአገር ውስጥ ብዙ የዜግነት ክብረ በዓል የሚካሄደው በዚህ ምክንያት ይሆናል።

ወንጀለኞችን በማስፈር ለብሪቲሽ መንግሥት መፍትሄ ለማስገኘት ሲባል ጥር/January 26 ቀን 1788 ዓ.ም የመጀመሪያው ጦር መርከብ ከታላቋ ብሪቴን ተነስቶ የደረሰበት ቀን ስለሆነ ይከበራል። የመጀመሪያው የጦር መርከብ መሪ ኮማንደር Captain Arthur Phillip ነበሩ።

በካንበራ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስለ የዓመቱ ተሸላሚዎች በአውስትራሊያ ቀን ዋዜማ ላይ ያሳውቃሉ።

የአንዛክ ቀን/Anzac Dayበየዓመቱ ሚያዚያ/April 25 ቀን Anzac ቀን ተመዝግቧል። በአንደኛው የዓለም ጦርነት ጊዜ ሚያዚያ/April 25 ቀን 1915 ዓ.ም የአውስትራሊያና ነው ዚላንድ ጦር ሠራዊት ከቱርከይ ወደ ጋሊፖሊ Gallipoli ሲያርፉ Anzac ቀን ተባለ።

Anzac የተከበረ ቀን ሲሆን በጦርነት ውስጥ በማገልገል፣ በሰላም አስከባሪ አሰራር ላይ በመሳተፍ የስቃይ፣ የሞት መስዋእትነት ለከፈሉ አውስትራሊያውያን በሞላ በጽሞና የምናስታውስበት ቀን ይሆናል። እንዲሁም በጀግንነትና በቆራጥነት አገልግሎት ለሰጡ ወንዶችና ሴቶች በሞላ እናከብራለን።

ስለ አውስትራሊያ ቀን፣ Anzac Day ቀን እና ሌሎች ጠቃሚ የሆኑ ብሄራዊ ቀናትና ክብረ በዓላት የበለጠ መረጃ በክፍል/Part 4, Australia today ውስጥ ሊገኝ ይችላል።

Page 16: Australian citizenship test book - Ahmaric...4 የአውትራሊያ ዜግነት: የጋራ መተሳሰሪያችን የአውስትራሊያ ዜጋ ስለመሆን በአውስትራሊያ

ክፍል 1 – አውስትራሊያና ህዝቦቿ 13

የአውስትራሊያ አቦርጂናል ባንዴራ ጥቁር፣ ቀይና ብጫ ነው

የአውስትራሊያ አቦርጂናል ባንዴራ ጥቁር፣ ቀይና ብጫ ነው

የአውስትራሊያ ባንዴራዎችአውስትራሊያ ሶስት ህጋዊ የሆኑ ባንዲራዎች ሲኖራት እነዚህም የአውስትራሊያ ብሄራዊ ባንዴራ የአውስትራሊያ አቦርጂናል ባንዴራና የቶረስ ስትሬት አይላንደርስ ባንዴራ ናቸው።

በተጨማሪም እያንዳንዱ መስተዳድር ግዛትና ተሪቶርይ የራሱ የሆነ ባንዴራ ይኖረዋል። እነዚህም በገጽ 11 ላይ ሊገኙ ይችላሉ።

የአውስትራሊያ ብሄራዊ ባንዴራ ሰማያዊ፣ ነጭና ቀይ ነው

የአውስትራሊያ ብሄራዊ ባንዴራየአውስትራሊያ ብሄራዊ ባንዴራ ሰማያዊ፣ ነጭና ቀይ ነው። ሶስት ጠቃሚ ክፍሎች አሉት:

• የታላቋ ብሪቴን ባንዴራ Union Jack ተብሎ ሲጠራ በባንዴራው በስተግራ ላይኛው ጫፍ ላይ ይገኛል። ባንዴራው የሚወክለው ለብሪቲሽ ሰፈራ ታሪካችን ይሆናል።

• የኮመንዌልዝ ኮከብ በ Union Jack ስር ይገኛል። ይህ ኮከብ ሰባት ነጥቦች ሲኖሩት አንዱ ነጥብ ለእያንዳንዱ ስድስት መስተዳድር ግዛቶችና አንደኛው ደግሞ ለተሪቶሪስ ይሆናል።

• በስተቀኝ በኩል የደቡባዊ መስቀል ሲሆን ይህም በደቡባዊ ሰማይ ላይ የምናየው የኮዋክብት ስብስብ ይሆናል።

የአውስትራሊያ አቦርጂናል ባንዴራየአውስትራሊያ አቦርጂናል ባንዴራ ጥቁር፣ ቀይና ብጫ ነው። ሶስት ጠቃሚ ክፍሎች ሲኖሩት ቀለምን ለመተርጎም በጣም የተለመዱት:

• ግማሹ የላይኛው ክፍል ጥቁር ሲሆን ይህም በአውስትራሊያ የአቦርጅናልን ህዝብ ይወክላል።

• የታችኛው ግማሽ ክፍል ቀይ ሲሆን ይህም መሬትን ሲወክል መንፈሳዊ ከመሬት ጋር ያልለን ግንኙነት ያሳያል።

• የብጫ ክብ ድግሞ ፀሐይን ይወክላል።

የቶረስ ስትሬት አይላንደርስ ባንዴራየቶረስ ስትሬት አይላንደርስ ባንዴራ አረንጓዴ፣ ሰማያዊ፣ ጥቁርና ነጭ ነው።

• የአረንጓዴ ነጠብጣብ መሬትን ይወክላል።

• በመሃከል ላይ ያለው የሰማያዊ ማስጌጥ ባህርን ይወክላል።

• ጥቁር መስመር የቶረስ ስትሬት አይላንደርስን ህዝብ ይወክላል።

• በመሃከል ያለው ነጭ የዳንስ ጭንቅላት ልብስ ለሁሉም ቶረስ ስትሬት አይላንደርስ ምልክት ይሆናል።

• በነጭ ኮከብ ያለው ነጠብጣብ በቶረስ ስትሬት የአይላንድ ቡድኖችን ይወክላል።

• ነች ቀለም የሰላም ምልክት ይሆናል።

Page 17: Australian citizenship test book - Ahmaric...4 የአውትራሊያ ዜግነት: የጋራ መተሳሰሪያችን የአውስትራሊያ ዜጋ ስለመሆን በአውስትራሊያ

የአውትራሊያ ዜግነት: የጋራ መተሳሰሪያችን 14

በኮመንዌልዝ ጋሻ ላይ ያለ አርማይህ በአውስትራሊያ ኮመንዌልዝ መንግሥት ህጋዊ የሆነ ምልክት ነው። የብሄራዊ አንድነታችንን ያሳያል። ይህ በአውስትራሊያ ኮመንዌልዝ መንግሥት ባለሥልጣንና ንብረት የሆኑትን ለይቶ ይገልጻል።

• በመሃከል ያለው ጋሻ የስድስቱን መስተዳድር ግዛትና የፈደራዊ ጣምራ መንግሥትን ይገልጻል።

• ካንጋሮ እና ኢምዩ ወፍ በጋሻው ግራና ቀኝ ላይ ይደገፋሉ። ካንጋሩዎች በአውስትራሊያ ውስጥ የተፈጠሩ እንስሳት ሲሆኑ ኢምዩ የአውስትራሊያ ተወላጅ ወፍ ይሆናል።

• ከጋሻው በላይ ወርቃማ የአውስትራሊያ ኮዋክብት ተቀምጧል።

• የስሩ መነሻ ወርቃማ የተጠላለፈ እንጨት፣ የአውስትራሊያ ብሄራዊ አበባ ነው።

የአውስትራሊያ ብሄራዊ አበባየአውስትራሊያ ብሄራዊ አበባ ወርቃማ የተጨላለፈ እንጨት ነው። ይህ ትንሽ ዛፍ በአብዛኛው በደቡብ ምሥራቃዊ ክፍል ይበቅላል። ደማቅ የሆነ አረንጓዴ ቅጠሎች እና በጸደይ ወራት ብዙ ወርቃማ የሆኑ ቅጠሎች ይኖሩታል። በአውስትራሊያ እያንዳንዱ ግዛትና ተሪቶርይ የራሱ የሆነ በአበባ ማስጌጥ አርማ ይኖረዋል።

የአውስትራሊያ ብሄራዊ ቀለማትየአውስትራሊያ ብሄራዊ ቀለም አረንጓዴና ወርቃማ ሲሆኑ ወርቃማ የተጠላለፈ እንጨት ቀለማት ነው። የብሄራዊ ስፖርት ቡድኖቻችን መለያ ልብስ አብዛኛው አረንጓዴና ወርቃማ ቀለም ይሆናል።

የአውስትራሊያ ብሄራዊ መከበሪያ ድንጋይኦፓል/መረግድ የአውስትራሊያ ብሄራዊ መከበሪያ ድንጋይ ነው። በአቦርጅናል አፈታሪክ አባባል የሰማይ መቀነት መሬትን በመንካት የኦፓል/መረግን ቀለማት ተፈጠረ።

በኮመንዌልዝ ጋሻ ላይ ያለ አርማ

የአውስትራሊያ ብሄራዊ ቀለም አረንጓዴና ወርቃማ

ወርቃማ የተጠላለፈ ተክል

ኦፓል/Opal

Page 18: Australian citizenship test book - Ahmaric...4 የአውትራሊያ ዜግነት: የጋራ መተሳሰሪያችን የአውስትራሊያ ዜጋ ስለመሆን በአውስትራሊያ

ክፍል 1 – አውስትራሊያና ህዝቦቿ 15

የአውስትራሊያ ብሄራዊ መዝሙር

‘አግባብ ያለው እድገት በአውስትራሊያ/Advance Australia Fair’ የአውስትራሊያ ብሄራዊ መዝሙር ነው። ለብሄራዊ ጥቅም አስፈላጊነት በሚኖርበት ጊዜ ይዘመራል። እንዲሁም የአውስትራሊያ ዜግነት ክብረ በዓል፣ በታላቅ የስፖርት ድርጊትና በትምህርት ቤት ላይ ይዘመራል።

ይህ ሃገሪቷን ወደ አንድነት በማጣመር አውስትራሊያዊ መሆን ስለሚያስደስትና ስለሚያኮራ የህዝቡ መግለጫ ይሆናል።

Advance Australia Fair

Australians all let us rejoice,

For we are young and free;

We’ve golden soil and wealth for toil;

Our home is girt by sea;

Our land abounds in nature’s gifts

Of beauty rich and rare;

In history’s page, let every stage

Advance Australia Fair.

In joyful strains then let us sing,

Advance Australia Fair.

Beneath our radiant Southern Cross

We’ll toil with hearts and hands;

To make this Commonwealth of ours

Renowned of all the lands;

For those who’ve come across the seas

We’ve boundless plains to share;

With courage let us all combine

To Advance Australia Fair.

In joyful strains then let us sing,

Advance Australia Fair.

*በአውስትራሊያ ብሄራዊ መዝሙር ላይ ፈተና ሲያካሂዱ በመዝሙር ቃላት ላይ እንደማፈተኑ ነው።’

Page 19: Australian citizenship test book - Ahmaric...4 የአውትራሊያ ዜግነት: የጋራ መተሳሰሪያችን የአውስትራሊያ ዜጋ ስለመሆን በአውስትራሊያ

ከአሁን ጊዜ ጀምሮ በእግዚአብሔር ስም*

ለአውስትራሊያና ህዝቦቿ ታማኝ ለመሆን ቃል እገባለሁ፣

ባለው የዲሞክራቲክ እምነት ተሳታፊ እሆናለሁ፣

ያሉትን መብቶችና ነጻነቶች እንደማከስብር እና

ባሉት ህጎች እንደምገዛና እንደምከተል ነው።

* አንድ ሰው “በእግዚአብሔር ስም” የሚለውን ቃል ለመጠቀም ወይም አለመጠቀም ይችላል።

ክፍል 2በአውስትራሊያ የዲሞክራቲክ እምነት፣

መብትና ነጻነት

Page 20: Australian citizenship test book - Ahmaric...4 የአውትራሊያ ዜግነት: የጋራ መተሳሰሪያችን የአውስትራሊያ ዜጋ ስለመሆን በአውስትራሊያ

ክፍል 2 – በአውስትራሊያ የዲሞክራቲክ እምነት፣ መብትና ነጻነት 17

የአውትርሊያ ዲሞክራቲክ እምነት፣ መብትና ነጻነት በህጉ መሰረት ህሉም አውስትራሊያዊ እኩል እንደሆነና ከህግ በላይ ማንም ሰው ወይም ቡድን አይኖርም። ይህም ‘የህግ ተገዥነት’ ተብሎ ይጠራል። በአውስትራሊያ ማህበረሰብ ውስጥ ስልጣን የያዙ ሰዎች ለአውስትራሊያ ህጎች ብመከተል መገዛት አለባቸው። በዚህ ውስጥ የሚካተቱት መንግሥት፣ ማህበረሰብና የሃይማኖት መሪዎች፣ እንዲሁም የንግድ ሰዎችና ፖሊስ ይሆናል።

በሰላማዊ ስለመኖርየተረጋጋ መንግሥታዊ አሰራር ባለበት አገር በመኖራችን ያኮራናል። በውይይት፣ በሰላማዊ መተማመና ዲሞክራቲክ በሆነ አሰራር ለውጥ እንደሚመጣ እምነታችን ነው። በጠበ ጫሪነት ጸባይ የአንድን ሰው አስተሳሰብ ወይም ህግ ለመቀየር የሚደረገውን አሰራር አንቀበልም።

ከየትም ይምጣ ሁሉንም ግለሰብ ማክበርከሞላው የዓለም ዙሪያ አገሮች፣ ሰዎች በአውስትራሊያ ለመስፈር ይመጣሉ። ብዙ ሰዎች የተለያየ ባህላዊ ቅርስ ከተለያየ እምነትና ልምዶች ጋር አላቸው። ዲሞክራቲክ በሆነው ሕብረተሰባችን ውስጥ የአውስትራሊያን ህግ ካልጣስን በስተቀር፣ እነዚህን እምነቶችና ልምዶች አብሮ ለመከተል ሁላችንም ነጻ ነን።

ሁላችንም ይህን ነጻነት ዋጋ በመስጠት የሰዎችን ጎሳ፣ የትውልድ አገር፥ ጾታ፣ የግብረስጋ ግንኙነት ፍላጎት፣ የጋብቻ ሁኔታ፣ እድሜ፣ የአካለ ጉዳተኛ፣ ባለው ቅርስ፣ ባህል፣ ፖለቲካ፣ ጤንነት ወይም ሃይማኖትን ሳይለዩ አውስትራሊያኖች በሞላ በኩራትና በክብር እንዲቀራረቡ ይጠበቃል።

ለሁሉም ሰው ክብር ሲባል ለዚህ የጋርዮሽ አከባበር ዋጋ እንሰጣለን።

ለተቸገሩ ርህራሄ ማድረግበአውትራሊያ ውስጥ በመንፈስ ‘መጣመድ’ አለ። ይህ ማለት እያንዳንዳችን በችግር ጊዜ ስንፈልግ እርዳታ በመቀበልና በመስጠት ይሆናል። ብዙ ጊዜ መጣመድ ጓደኛ መሆን ሲሆን ነገር ግን ምንም ከማይተዋወቁ ጋር ሊሆንም ይችላል። መተዋወቅ በእድሜ ከገፉ ጎረቤት ጋር አብሮ መብላት፣ ጓደኛን ወደ ሕክምና ቀጠሮ ወይም ብቸኛ የሆነን ሰው ሂዶ መጠየቅ ሊሆን ይችላል።

በዚህ በመንፈሳዊ መጣመድ የተነሳ ብዙ ግለሰቦችና ቡድኖች በፈቃደኛ የማህበረሰብ ሥራ አማካኝነት ያለክፍያ ሌሎች ሰዎችን ይረዳሉ። እርስዎም ያለክፍያ የፈቃደኛ ሥራ ማካሄድ ይችላሉ። በፈቃደኝነት ይሚሰራው በጣም አርኪ ሊሆን ይችላል። እንዲሁም እውቀትን ለማካፈል፣ አዲስ ችሎታን ለመማርና በአውስትራሊያ ማህበረሰብ እንዲሳተፉ ያለዎትን ስሜት ለመጨመር ታላቅ እድል ይከፍትልዎታል። እንዲሁም መንግሥታችን፣ ችግር ላለባቸው አውስትራሊያኖችን በማህበራዊ ዋስትና እና ሌሎች አገልግሎቶች አማካኝነት ይረዳቸዋል።

የአውስትራሊያን ዲሞክራቲክ እምነቶችን ከሌሎች ሰዎች ጋር አብሮ ለመካፈልና የአውስትራሊያ ህዝብን መብትና ነጻነት ለማክበር በዜግነት ክብረ በዓል ላይ ቃለ እንደገቡ ነው።

አውስትራሊያ ዲሞክራቲክ አገር ናት። ዲሞክራሲ የመንግሥት አሰራር ዘዴ ሲሆን አገሪቷን የሚያስተዳድሩ ተወካዮች በዜጎች በኩል ነሳ የሆነ ምርጫ በማካሄድና እነሱን በመወከል ህጎችን እንደሚያወጡ ነው።

ሰላም፣ መከባበር፣ ነጻነትና እኩልነት ስለመኖር የአውስትራሊያ እምነት ይሆናል። ከርስዎ የተለየና ምርጫዎች ላላቸው ሰዎች፣ ምንም እንኳን በነዚህ ምርጫዎች ላይ ባይስማሙበትም ማክበሩ አውስትራሊያዊነት ስለመሆን ጠቃሚው ክፍል ይሆናል። ይህም ሰዎችን በአግባቡ ማስተናገድ ሲሆን የሰዎች ከየትም ይምጡ፣ ባላቸው ባህል ወይም ወንድ ወይም ሴት ሳይለዩ ለሁሉም አውስትራሊያዊ የእኩልነ መብትና ነጻነት እድል ማስጠበቅ ይሆናል።

አገራችንና ባህላችን በነዚህ ዲሞክራቲክ እምነቶች ስለስተካከለ፣ ስለዚህ ብዙ ሰዎች አውስትራሊያዊ ለመሆን ይፈልጋሉ። ስለሆነም እነዚህን ዲሞክራቲክ እምነቶች ተረድተው ሁሉም አውስትራሊያዊ የሆነ ህዝብ ስለ መብቶችና ነጻነቶች ማክበር እንዳለበት በጣም አስፈላጊ ነው።

ስለዲሞክራቲክ እምነታችንፓርሊያመንታዊ የሆነ ዲሞክራሲየአውስትራሊያ መንግሥታዊ አሠራር በፓርሊያመንት የህዝብ ዲሞክራሲ ድጋፍ ይሆናል። ይህ ማለት እንዴት አገሪቷ መስተዳድረ እንዳለባት ሁሉም አውስትራሊያዊ የሆነ ተሳትፎ ይኖረዋል። የአውስትራሊያ መንግሥት ስልጣን የሚመጣው ከአውስትራሊያ ህዝብ ሲሆን ምክንያቱም ለአውስትራሊያ ዜጋዎች በፓርላማ ውስጥ እንዲወክላቸው ብዙጊዜ ለምርጫ ድምጽ ስለሚሰጡ ነው። አገሪቱን ማስተዳደሪያ የሚሆን ህጎችን ለማውጣትና ለመቀየር ስልጣን የሚኖረው ፓርላማ ብቻ ነው።

በፓርሊያመንታሪ ዲሞክራሲ ውስጥ ያሉ የፓርላማ ተወካዮች፣ ስለ አዘጋጁት ውሳኔ በተመለከተ ለህዝቡን በምርጫው በኩል መልስ መስጠት አለባቸው።

ህገ ደንብበአውስትራሊያ ውስጥ ለሚኖሩ ሰዎች የአውስትራሊያ ህጎች አስፈላጊ ናቸው። ሰላማዊና ስርዓት ያለው ሕብረተሰብ ለመፍጠር የህጎችን በላይነት ዋጋ በአውስትራሊያኖች መታወቅ አለበት። አውስትራሊያዊ በሞላ በአውስትራሊያ ሕጎች በኩል መብታቸው ይጠበቃል።

ማንኛውም ሰው ለአውስትራሊያ ህግ ተገዥ መሆን አለበት። ህጉን ካልተከተሉና ካላከበሩ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ሆነው ወደ ፍርድ ቤት ሊሄዱ ይችላሉ።

Page 21: Australian citizenship test book - Ahmaric...4 የአውትራሊያ ዜግነት: የጋራ መተሳሰሪያችን የአውስትራሊያ ዜጋ ስለመሆን በአውስትራሊያ

የአውትራሊያ ዜግነት: የጋራ መተሳሰሪያችን 18

አውስትራሊያኖች መንግሥት በወሰነውና ባወጣው ህጎች ላይ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ ነጻ ናቸው

ስለእኛ ነጻነቶችየመናገር ነጻነትና የራስን መግለጽ ነጻነትሰዎች ያሰቡትን ለመናገርና ለመጻፍ እንዲሁም ሃሳባቸውን ከሌሎች ጋር አብሮ ለመወያየት በመናገር ነጻነት በኩል ይፈቅድላቸዋል። የራስን መግለጽ ነጻነት ደግሞ ሰዎች ያላቸውን ሃሳብ በስነ-ጥበብ፣ ፊልም፣ ሙዚቃና በስነ-ጽሁፍ አድርገው ለመግለጽ ይፈቅድላቸዋል።

በአውስትራሊያ ውስጥ ስለምናስበው ማንኛውም አርእስት በግል ወይም በአደባባይ ለመናገርና ለመጻፍ ነጻ ነን። ይሁን እንጂ ሌሎችን በማይጎዳ መልኩ ነው።

የውሽት ክርክር ማቅረብ አንችልም፣ ለሌሎች ህጉን እንዲጥሱ አናበረታታም ወይም ዝና ለማግኘት ሌላ ሰው መጉዳት አንችልም። የአንድን ሰው ጥሩ ስም በውሽት እንዳይጠፋ የሚከላከሉ ህጎች አሉ።

ሌሎች ሰዎች እንዲጠሉ ለማድረግ መሞከር ወይም በሌሎች ባህል፣ ጎሳ ወይም አመጣጥ መነሻ አድርጎ ጠብ መጫር ህገ-ወጥነት ነው።

ለማሕበራዊ ወይም ለፖለቲካ ውይይት በህዝብ ወይም የግል ቦታዎች ላይ ለመገናኘት ነጻ ነን። ሰላማዊ በሆነ የተቃውሞ ሰልፍ መንግሥት የወሰናቸውን በመቃወም ህጎች ይቀየሩ ዘንድ ዘመቻ በማድረግ መንግሥትን መቃወም እንችላለን።

በተጨማሪም የሌሎች ሰዎችን የመናገር ነጻነት እና የራስን መግለጽ ነጻነት ማክበር አለብን።

ጋዜጣዎች፣ ተለቪዥንና ራዲዮ ተመሳሳይ የሆነ ነጻነት አላቸው።

በማሕበር የመሰብሰብ ነጻነትአውስትራሊያኖች በማንኛውም ህጋዊ የሆነ ድርጅት ማለት እንደ የፖለቲካ ፓርቲ፣ የንግድ ማሕበር፣ ሃይማኖት፣ ባህላዊ ወይም ማሕበራዊ ቡድን ለመሳተፍ ነሳ ናቸው። እንዲሁም ሰዎች ላለመሳተፍ መወሰን ይችላሉ።

መንግሥት ወይም ድርጅት በወሰደው እርምጃ ተቃውሞ ለመግለጽ አውስትራሊያኖች ክሌሎች ጋር መሰባሰብ ይችላሉ። ይሁን እንጂ የተቃውሞ ሰልፉ በሞላ ህጉ በሚፈቅደው መሆን አለበት። ይህ ማለት ሰላማዊ መሆን እንዳለባቸውና ለማንም ሰው ወይም ንብረት ጉዳት ማድረስ የለባቸውም።

የሃይማኖት ነጻነትና አለማዊ መንግሥትአውስትራሊያ የጁዳኦ-ክርስትና/Judaeo-Christian እምነት ቅርስ ሲኖራት እንዲሁም ብዙ አውስትራሊያኖች እራሳቸውን እንደ ክርስቲያን አድርገው ይናገራሉ። አውስትራሊያ በክርስቲያን ክብረ ቀናት ማለት እንደ ስቅለት፣ እሁድ ፋሲካና የገና ቀን ህዝባዊ በዓላት አሏት።

ስለዚህ በአውስትራሊያ ውስጥ መንግሥት አለማዊ ነው። ይህ ማለት በህግ የታወቀ ብሄራዊ ሃይማኖት የለም።

ስሰች የአውስትራሊያን ህግ ካልጣሱ በስተቀር በአውስትራሊያ ውስጥ የፈለጉትን ሃይማኖት ለመከተል የመምረጥ ነጻነት አላቸው። ከክርስቲያን በተጨማሪም ቡድሂዝም፣ እስላም፣ ሂንዱዝም እና ብዛት ያላቸው ሃይማኖቶች በአውስትራሊያ ውስጥ ነጻ በሆነ መልኩ እንደሚካሄዱ ነው።

እንዲሁም አውስትራሊያኖች ሃይማኖትን ላለመከተል ነጻ መብት አላቸው። የሰዎችን ሃይማኖትና እምነት ሳይለይ መንግሥት ሁሉንም ዜጎች በእኩልነት ያስተናግዳል።

በአውስትራሊያዊ ወኔ ቀስቃሽ የሆነ የመድብለ ባህላዊ ሕብረተሰብ እንዲፈጠር ይህ የሃይማኖት ውህደት አስተዋጽኦ ያደርጋል።

ብዙዎች ሃይማኖቶች ደንቦች ሲኖራቸው፣ ነገር ግን እነዚህ በአውስትራሊያ ውስጥ ህጎች አይደሉም። ለምሳሌ፡ የባልና ሚስት ፍት አሰራር፣ እንዲሁም የህጻናትን አሳዳጊ መብትና የንብረት መካፈል ያካተተ በአውስትራሊያ ፓርላሜንት የተላለፈው ህጎችን መከተል አለበት። ሁሉም አውስትራሊያዊ በነዚህ ህጎች የመከላከል መብት አለው። አንዳንድ የሃይማኖት ወይም የባህል ልምዶች ማለት በተመሳሳይ ጊዜ ከአንድ ሴት/ወንድ በላይ ማግባት ከአውስትራሊያ ህግ አንጻር ነው።

Page 22: Australian citizenship test book - Ahmaric...4 የአውትራሊያ ዜግነት: የጋራ መተሳሰሪያችን የአውስትራሊያ ዜጋ ስለመሆን በአውስትራሊያ

ክፍል 2 – በአውስትራሊያ የዲሞክራቲክ እምነት፣ መብትና ነጻነት 19

ወንዶችና ሴቶች በጦር ሃይል፣ ባህር ሃይልና በአየር ሃይል ውስጥ መሳተፍ ይችላሉ

በአውስትራሊያ ሰዎች የፈለጉትን ሃይማኖት ለመከተል ነጻ ናቸው

አውስትራሊያውያን በሞላ ወደ ዩኒቨርሲቲ የመግባት እድል አላቸው

የእኛ እኩልነትበአውስትራሊያ ውስጥ እኩልነትሰዎች በሚኖራቸው ጾታ፣ ጎሳ፣ አካል ጉድለት ወይም እድሜ ከሌሎች ሰዎች በተለየ ሁኔታ እንዳይስተናገዱ ለማረጋገጥ በአውስትራሊያ ውስጥ ብዙ ህጎች እንዳሉ ነው።

የወንዶችና ሴቶች እኩልነትበአውስትራሊያ ውስጥ ወንዶችና ሴቶች እኩል መብቶች ይኖራቸዋል። አንድን ሰው በጾታ ለይቶ መበደል ህገ-ወጥነት ያሰኛል።

ሁለቱም ወንዶችና ሴቶች ስለ ግላዊ ጉዳዮች እንደ ትዳር የራሳቸውን ምርጫ ለማካሄድ መብታቸው ሲሆን እንዲሁም ከዛቻ ውርጅብኝ ወይም ከጠበ ጫሪነትና በህግ መከላከያ ይደረግላቸዋል።

ወንዶቹም ሆኑ ሴቶችም የትምህርትና የሥራ እኩል አቅርቦት ይኖራቸዋል። ሁለቱም ወንዶችና ሴቶች ድምጽ በመስጠት ለፓርላማ መቆም ይችላሉ። ሁለቱም ወንዶችና ሴቶች በአውስትራሊያ የመከላከያ ጦር ሃይልና ፖሊስ መግባት ይችላሉ። በፍርድ ቤቶች ህግ ፊት ወንዶችና ሴቶች በእኩልነት ይስተናገዳሉ።

የእኩልነት መብትበሕብረተሰባችን ውስጥ በደረጃ ልዩነት መታወቅን አውስትራሊያውያን አያምኑበትም። ነገር ግን አግባብ ባለው ሕብረተሰብ በማመን እያንዳንዱ ‘በአግባቡ መጓዝን” እናምናለን። ይህ ማለት አንድ ሰው በሕይወቱ ያገኘው ጥሩ ውጤት በራሱ ከባድ ሥራና ተሰጥኦነት እንጂ ባለው ሀብት ወይም ካለፈው የታሪክ አመጣጡ አይደለም። ለምሳሌ፡ አንድ ሰው ሥራ ወይም እድገት ማግኘት ያለበት ካለው ሙያ፣ ችሎታና ልምድ እንጂ ካለፈው ታሪክ አመጣጡ አይሆንም።

አዲስ መጤዎች ባላቸው ከባድ ጥረትና ተሰትኦ በንግዶች፣ በሙያተኛ፣ በስነ-ጥበባት፣ ህዝባዊ አገልግሎትና በስፖርት ውስጥ ስለመሳተፋቸው የሚገልጽ በአውስትራሊያ ብዙ ታሪኮች አሉ።

Page 23: Australian citizenship test book - Ahmaric...4 የአውትራሊያ ዜግነት: የጋራ መተሳሰሪያችን የአውስትራሊያ ዜጋ ስለመሆን በአውስትራሊያ

የአውትራሊያ ዜግነት: የጋራ መተሳሰሪያችን20

በፈደራል፣ መስተዳድር ግዛት ወይም ተሪቶሪና በአካባቢ መንግሥት ምርጫ ላይ ድምጽ በመስጠት ድርሻችንን እናበረክታለን

የአውስትራሊያ ዜግነትን በማግኘት ሃላፊነትና ልዩ ጥቅምበአውስትራሊያ ቋሚ ነዋሪ እንደመሆንዎ መጠን ነጻ በሰፈነበትና ዲሞክራቲ በሆነ ሕብረተሰብ ውስጥ በመኖር እንደተደሰቱ ነው። የአውስትራሊያ ዜግነትን ሲያገኙ አዲስ ሃላፊነት ይኖርዎታል። እንዲሁም የተለያዩ አድዲስ ጥቅሞችን ይያገሉ።

ሃላፊነቶች – ለአውስትራሊያ ምን እንደሚሰጡ አውስትራሊያዊ ዜጋ እንደ መሆንዎ መጠን ማድረግ ያለብዎት:

• ህግን መከተል

• በፈደራልና በመስተዳድር ግዛት ወይም ተሪቶሪ እንዲሁም በሪፈረንዱም ህዝብ ውሳኔ ምርጫዎች ላይ ድምጽ መስጠት

• አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ ለአውስትራሊያ መከላከል

• በዳኝነት ለመሰየም ከተጠሩ ማገልገል ይሆናል።

ልዩ ጥቅሞች– ለአውስትራሊያ ምን እንደሚሰጡአውስትራሊያዊ ዜጋ እንደ መሆንዎ መጠን ማድረግ ያለብዎት:

• በፈደራልና በመስተዳድር ግዛት ወይም ተሪቶሪ እንዲሁም በሪፈረንዱም ህዝብ ውሳኔ ምርጫዎች ላይ ድምጽ መስጠት

• በአውስትራሊያ ህዝባዊ አገልግሎት ወይም በአውስትራሊያ መከላከያ ጦር ሃይል ውስጥ ለመሥራት ማመልከት

• ለፓርሊያመንት ምርጫ መጠየቅ

• ለአውስትራሊያ ፓስፖርት ማመልከትና ያለምንም ገደብ ወደ አውስትራሊያ እንደገና መግባት

• በውጭ አገር ሆኖ ከአውስትራሊያ ባለሥልጣን እርዳታ ማግኘት

• በዘር ትውልድ ከአውስትራሊያዊ ዜጋ በውጭ አገር የተወለዱ ህጻናትን ማስመዝገብ።

ሃላፊነቶችህግን መከተልበመንግሥት የወከልናቸው ህግን በማውጣት ስነ-ስርአት እንዲኖር፣ ነጻና ደህንነቱ የተጠበቀ ሕብረተሰብ እንዲመስረትና መብታችን እንዲተበቅ ያደርጋሉ። አውስትራሊያዊ የሆነ ሁሉ በአውስትራሊያ ፓርላሜንት፣ በመስተዳድር ግዛትና ተሪቶሪይ ፓርላሜንት እንዲሁም በአካባቢ መንግሥት የወጡትን ህጎች መከተል አለበት።

በአውስትራሊያ ውስጥ ስላሉ አንዳንድ ጠቃሚ ህጎች የበለጠ መረጃ በክፍል 3, በአውስትራሊያ መንግሥትና ህጉ በሚለው ውስጥ ይገኛል።

በፈደራልና መስተዳድር ግዛት ወይም በተሪቶሪይማ ሪፈረንዱም ምርጫ ላይ ድምጽ መስጠትለአውስትራሊያ ዜጎች በሞላ በምርጫ ላይ ድምጽ መስጠት ለመብትም ሆነ ሃላፊነት ጠቃሚ ሚና ይጫወታል። በፓርላማ ውስጥ ይወክሉናል ብለን ላመነው ሰው ድምጽ በመስጠት እንመርጣለን። ይህን በማድረግ እንዴት አገሪቷ እንደምትተዳደርና ለወደፊት የአውስትራሊያ እድል ሁላችንም ያለንን አቅርበናል ማለት ነው።

እንደ ዜጋ መሆንዎ መተን ብዙጊዜ በፈዴራልና መስተዳድር ግዛት ወይም በተሪቶሪ ምርጫ ላይ ድምጽ ይሰጣሉ። አንዳንድ ጊዜ የአውስትራሊያን መተዳደሪያ ህግ ለመቀየር በሚደረግ የሪፈረንዱም ህዝባዊ ምርጫ ላይ ድምጽ ይሰጣሉ። ስለ አውስትራሊያ መተዳደሪያ ህግ የበለጠ መረጃ በክፍል 3, በአውስትራሊያ መንግሥትና ህጉ በሚለው ውስጥ ይገኛል።

የአውስትራሊያ ዜጎች እድሚያቸው 18 ዓመት ወይም ከዚያ በላይ የሆነው በመራጭ ዝርዝር ላይ ስማቸውንና አድራሻቸውን መመዝገብ አለባቸው። ስምዎ በመራጭ ዝርዝር ውስጥ ከሆነ በኋላ እድሜያቸው 18 ዓመት ወይም ከዚያ በላይ የሆኑ የአውስትራሊያ ዜጋዎች በፈደራልና መስተዳድር ግዛት ወይም ተሪቶሪ የሚደረግ ምርጫ ላይ ድምጽ መስጠት ግዴታቸው ነው።

በአንዳንድ መስተዳድር ግዛቶች ለአካባቢ መንግሥት ምርጫ ድምጽ መስጠት ግዴታ አይደለም።

አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ አውስትራሊያን መከላከልበአውስትራሊያ መከላከያ ጦር ምገልገል በፈቃደኝነት ሲሆን፣ ነገር ግን አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ ማንኛውም የአውስትራሊያ ዜጋ በጋራ በአንድነት ሆኖ አገሪቷንና ሕይወቱን ለመከላከያ መስዋእት መክፈል አለበት።

Page 24: Australian citizenship test book - Ahmaric...4 የአውትራሊያ ዜግነት: የጋራ መተሳሰሪያችን የአውስትራሊያ ዜጋ ስለመሆን በአውስትራሊያ

ክፍል 2 – በአውስትራሊያ የዲሞክራቲክ እምነት፣ መብትና ነጻነት 21

በዳኝነት ለመሰየም ከተጠሩ ማገልገልእድሜው 18 ዓመት ወይም ከዚያ በላይ የሆነው የአውስትራሊያ ዜጎች በዳኝነት የማገልገል ሃላፊነት አለባቸው። ዳኞች ሲባል ተራ የሆነ አውስትራሊያዊ ወንድና ሴት በቡድን ሆኖ በፍርድ ቤት ችሎት ስለቀረበ ጉዳይ ማስረጃ በማዳመጥና ሰውየው ወንጀለኛ ወይም ወንጀለኛ ስላለመሆኑ ይወስናል።

በምርጫው የተመዘገበ ማንኛውም አውስትራሊያዊ በችሎት ዳኝነት ይገለግል ዘንድ ሊጠራ ይችላል።

የፍርድ ቤቱ አሰራር ዘዴ ግልጽና አግባብነት እንዲኖረው ለማረጋገጥ የዳኞች አገልግሎት ቡድን ይረዳል።

ልዩ ጥቅሞችበአውስትራሊያ ህዝባዊ አገልግሎትና በአውስትራሊያ መከላከያ ሃይል ውስጥ ለመሥራት ማመልከትየአውስትራሊያ ዜጋ ከሆኑ በአውስትራሊያ ህዝባዊ አገልግሎት በመሳተፍ ለአውስትራሊያ መንግሥት ለመሥራት ማመልከት ይችላሉ፣ ለምሳሌ፡ በሴንተርሊንክ (Centrelink)፣ ሜዲኬር (Medicare) ወይም በአውስትራሊያ የቀረጥ ጽህፈት ቤት (Australian Taxation Office) ውስጥ ማመልከት ይቻላል።

የአውስትራሊያዊ ዜጎች በአውስትራሊያ መከላከያ ሃይል (በውትድርና፣ ባህር ሃይል፣ አየር ወለድ) ውስጥ ሥራ ለማመልከት መብት አላቸው።

ለፓርሊያመንት ምርጫ ስለመፈለግእድሜዎ 18 ዓመትና ከዚያ በላይ የሆነ አውስትራሊያዊ ዜጎች በፈደራል፣ መስተዳድር ግዛት በተሪቶሪ ደረጃ በሚደረግ ምርጫ ላይ መሳተፍ ይችላሉ። በአውስትራሊያ ፓርላመንት ውስጥ ለማገልገል ይህ ክብርና ከባድ ሃላፊነትን ይጠይቃል።

የአውስትራሊያ ፓስፖርት በማመልከት ወደ አውስትራሊያ እንደገና ያለችግር መግባትየአውስትራሊያ ዜግነትን ሲያገኙ በአውስትራሊያ ውስጥ ነጻ በሆነ መልኩ ለመኖር መብት ይኖርዎታል።

የአውስትራሊያ ፓስፖርትን ለማመልከት መብት አለዎ። እንደ የአውስትራሊያዊ ዜጋ መሆንዎ መጠን ወደ ውጭ አገር የመጓዝና ወደ አውስትራሊያ የመመለስ ነጻነት አለዎ። ወደ አውስትራሊያ ለመመለስ ቪዛ አያስፈልግዎም።

በውጭ አገር እያሉ ከአውስትራሊያ ባለሥልጣን እርዳታ ስለማግኘትአውስትራሊያ በብዙ አገሮች ውስጥ ኢምባሲ፣ ከፍተኛ ኮሚሽን ወይም ወኪል አሏት። በውጭ አገር በሚሆኑበት ጊዜ አስፈላጊ ከሆነ ከባለስልጣኑ እርዳታ ለማግኘት መጠየቅ ይችላሉ።

ይህም የድንገተኛ ችግርን ማለት እንደ የህዝብ አለመረጋጋትንና የተፈጥሮ ጥፋት አደጋን ያካትታል። እንዲሁም በድንገተና አደጋ ጊዜ ባለሥልጣኖች ፓስፖርቶችን በመስጠት እንዲሁም በድንገተኛ ገጠመኝ፣ ከባድ ህመም ሲከሰት ወይም ለሞት በሚያበቃ ጊዜ ምን እንደሚደረግ ምክርና ድጋፍ ያቀርባሉ።

በሌላ አገር ሲሆኑ የዚያን አገር ህጎች መከተል አለብዎ።

በዘር ከአውስትራሊያ ዜጋ በውጭ አገር ለተወለዱ ህጻናት ስለማስመዝገብየአውስትራሊያ ዜጋዎች በውጭ አገር ህጻናት የተወለዱ ህጻናት ሊኖራቸው ይችላል። ስለዚህ ልጆቻቸውን እንደ የአውስትራሊያ ዜጋ አድርጎ ማስመዝገብ ይቻላል። ከዚያም ህጻናት እንደ አውስትራሊያ ውስጥ የተወለዱት ዜጎች እነዚህም ህጻናት እኩል መብትና ግዴታ ይኖራቸዋል።

በአውስትራሊያ ሕብረተሰብ ውስጥ ስለመሳተፍሁሉም ዜጋ በሕብረተሰብ ውስጥ ተሳታፊ ይሆን ዘንድ አውስትራሊያ ታበረታታለች።በሕብረተሰብ ውስጥ የሚሳተፉ ዜጎች ለአውስትራሊያ በብዙ መንገድ አስተዋጽኦ ያደርጋሉ። በጎረቤታሞችና በአካባቢ ማህበረሰባት ውስጥ መሳተፍ ይችላሉ። ለማሕበራዊና ማህበረሰብ አገልግሎት በፈቃደኝነት መሥራት ይችላሉ። በስነ-ጥበብ ወይም ባህላዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ መሳተፍ ይችላሉ። እንዲሁም በፖለቲካ ሕይወት እንቅስቃሴ ላይ መሳተፍ ይችላሉ።

ግብር ቀረጥ በመክፈል ለአውስትራሊያ ማህበረሰብ በቀጥታ አስተዋጽኦ ማድረጉ ሌላው ጠቃሚ መንገድ ይሆናል። ከሥራ፣ ንግድ ወይም በኢንቨስትሜንት ከሚያገኙት ገቢዎት የሚቆረጠው ገንዘብ ታክስ ግብር ይባላል።

አውስትራሊያን የሚዝናኑበት አብዛኛው የገንዘብ ድጎማ የሚገኘው በቀረጥ ክፍያ በኩል ይሆናል። የቀረጥ ገንዘብ በአገልግሎቶች ላይ ስጠፋ ይህም ለጤንነት፣ ለትምህርት፣ ለመከላከያ፣ ለመንገድና ለባቡር ሃዲድ ሥራ፣ ለማሕበራዊ ዋስትና ያካትታል። እየሰሩ ግብር በመክፈል ታዲያ ለነዚህ የአውስትራሊያ ማህበረሰብ ጠቃሚ አገልግሎቶች ለማካሄድ መንግሥትን መርዳት ይችላሉ። ዛሬ አውስትራሊያ ሰላማዊና ሀብታም አገር እንድትሆን እነዚህ አገልግሎቶች እረድተዋል። በተጨማሪም በመስተዳድር ግዛትና ተሪቶሪ መንግሥት እንዲሁም ቀረጥ ሲሰበስቡ እንዲሁም ለሚቀርብ አገልግሎት ክፍያ ስሲክሄ በአካባቢ ምክር ቤቶች በኩል ቀረት ይሰበሰባል።

ግብር መክፈል በህግ ያስገድዳል። በአውስትራሊያ የቀረጥ ጽህፈት ቤት (ATO) በኩል ከንግድ ተቋም ሆነ ከግለሰቦች ላይ ቀረጥ ይሰበሰባል። ዜጋዎች በሞላ ስለ በትክክለኛ መጠን እንዲከፍሉ ያላቸውን መብትና ግዴታ ለማረጋገጥ ጽ/ቤቱ (ATO) ይሰራር።

Page 25: Australian citizenship test book - Ahmaric...4 የአውትራሊያ ዜግነት: የጋራ መተሳሰሪያችን የአውስትራሊያ ዜጋ ስለመሆን በአውስትራሊያ

22 የአውትራሊያ ዜግነት: የጋራ መተሳሰሪያችን

ከአሁን ጊዜ ጀምሮ በእግዚአብሔር ስም*

ለአውስትራሊያና ህዝቦቿ ታማኝ ለመሆን ቃል እገባለሁ፣

ባለው የዲሞክራቲክ እምነት ተሳታፊ እሆናለሁ፣

ያሉትን መብቶችና ነጻነቶች እንደማከስብር እና

ባሉት ህጎች እንደምገዛና እንደምከተል ነው።

* አንድ ሰው “በእግዚአብሔር ስም” የሚለውን ቃል ለመጠቀም ወይም አለመጠቀም ይችላል።

ክፍል 3በአውስትራሊያ ውስጥ መንግሥትና ህግ

Page 26: Australian citizenship test book - Ahmaric...4 የአውትራሊያ ዜግነት: የጋራ መተሳሰሪያችን የአውስትራሊያ ዜጋ ስለመሆን በአውስትራሊያ

ክፍል 3 – በአውስትራሊያ ውስጥ መንግሥትና ህግ 23

በአውስትራሊያ መንግሥትና ህጉበዜግነት ክብረ በዓል ላይ የአውስትራሊያ ህጎችን ለመያዝና ለመከተል ቃል እንደገቡ ነው። የአውስትራሊያን መንግሥታዊ አሰራር ማለት እንዴት አድርጎ ዲሞክራሲያዊ በሆነው ፓርሊያመንታችን ህጎች እንደወጡና እንዴት ህጎቹ እንደሚተዳደሩ ምወቁ ለርስዎ አስፈላጊ ነው። እንዲሁም እንደ ዜጋ መሆንዎ መጠን ባለው የአገር አመራር ላይ ያለዎትን ሃሳብ እንዴት ማቅረብ እንደሚችሉ ማወቁ ተቃሚ ነው።

እንዴት ሀሳቤን መስጠት እችላለሁ?በምርጫ ድምጽ በመስጠትበአውስትራሊያ ውስጥ እድሚያቸው 18 ዓመት ወይም በላይ የሆኑ ዜጎች በፈደራል ለምርጫ ድምጽ መስጫ መመዝገብ አለባቸው። ድምጽ በመስጠት እርስዎን በፓርላመንት ውስጥ ማን እንደሚወክልዎ ሃሳብ ለመስጠት እድል እንዳገኙ ነው። በትክክል ካልተመዘገቡ በምርጫው ጊዜ ድምጽ መስጠት አይችሉም።

እርስዎ በመራጭ ምዝገባ ከገቡ በአውስትራሊያ ፈደራልና መስተዳድር ግዛት ወይም ተሪቶሪይ ምርጫዎች ላይ ድምጽ መስጠት ግዴታ ይሆናል። በምርጫው ላይ ድምጽ ላለመስጠት በቂ ምክንያት ከሌለዎት በገንዘብ ቅጣት ይከፍላሉ። ለድምጽ መስጠት ግዴታ የተደረገበት ምክንያት የምንመርጣቸው ሰዎች አብዛኛው ህዝብ የሚፈልጋቸው ስለመሆኑ ለማረጋገጥ ይሆናል።

የአውስትራሊያ ምርጫ ኮሚሽን (AEC) ይኮመንዌልዝ መንግሥት ተወካይ ነው። የፈደራል ምርጫዎችንና የሪፈረንዱም ህዝባዊ ምርጫ በማካሄድ እንዲሁም በኮመንዌልዝ ለምርጫ ዝርዝር ምዝገባን ያስተዳድራል። ለመራጮች ሃቀኛን ተገቢ የሆነ ምርጫዎች ለማቅረብ ክኮሚን (AEC) ይረዳል። ኮሚሽኑ (AEC) በመንግሥት ተጽእኖ የሌለበትበራሱ የሚመራ አካል ነው። በኮሚሽኑ (AEC) ውሳኔ ላይ የፖለቲካ ቡድኖች ወይም የመንግሥት አካል ሰዎች ተጽእኖ ማሳደር አይችሉም። የድምጽ የሚቀርበው ሚስጢራዊ በሆነ ካርድ ሲሆን ስለዚህ ለማንም እጩ ተመራጭ ድምጽ ለመስጠት ነጻና ደህንነቱ የተጠበቀ ይሆናል። ለምን ድምጽ እንደሰጡ ማንም ሰው ሊያይ አይችልም። ለማን ድምጽ እንደሰጡ ለሌሎች ሰዎች መናገር ይችላሉ ነገር ግን እንዲናገሩ ማንም ሰው ሊያስገድድዎት አይችልም።

ጉዳዮችን ከርስዎ ተወካዮች ጋር አንስቶ መናገርበአውስትራሊያ ውስጥ በርስዎ በተመረጠ ተወካይ ጋር አሳሳቢ ጉዳይ ሲኖርዎ አንስቶ ለመነጋገር መብት አለዎ። በፓርሊያመንት አዲስ ህጎች ሲያወጣ ወይም ያለውን ህግ ሲቀይር እርስዎ ያቀረቡት ሃሳብ ግምት ውስጥ ሊገባ ይችላል። ለምሳሌ፡ ስለ ኢሚግሬሽን አሰራር እንዴት ማሻሻል እንደሚቻል አስተያየት ካለዎት፣ ከአካባቢዎ የፓርላመንት አባል ጋር ለመወያየት ቀጠሮ ምቀናጀት ነው። እንዲሁም ሃሳብዎን በጽሁፍ አድርገው ደብዳቤ መላክ ይችላሉ።

በዚህ ዘዴ የመንግሥትን ፖሊሲዎችና ህጎች በማውጣት ማንኛውም ተራ አውስትራሊያዊ ያለውን ሃሳብ ማካፈል ይችላል።

የእኛን መንግሥት አሰራር ዘዴ እንዴት ለማውጣት ቻልን?ፍደራሽንከ1901 ዓ.ም በፊት፣ አውስትራሊያ ከስድስት የተለያዩና በራስ ከሚተዳደሩ የብሪቲሽ ቅኝ ግዛቶች የተሰራች ነበር።

በእያንዳንዱ ቅኝ የግዛት ክልል ለራሱ የሆነ ህገ-ደንብ መተዳደሪያ እና ከራሱ ህጎች ጋር የተዛመደ የመከላከያ፣ ኢሚግሬሽን፣ የፖስታ አገልግሎት፣ ንግድና ትራንስፖርት ነበራቸው።

ሰዎች በተለያየ ምክንያቶች እነዚህን ቅኝ ግዛቶች አጣምሮ አንድ የአውስትራሊያ አገር ለመመስረት ፍላጎት ነበራቸው። በቅኝ ግዛቶች መካከል ንግድና ለመጓጓዝ በጣም ውድና ፈጣን አልነበረም። በደንበሮች ዙሪያ ህጉን ለማስከበር አስቸጋሪ ነበር። እንዲሁም በተለያዩ የቅኝ ግዛቶች የመከላከያ አሰራር ዘዴያቸው የተዳከመ ነበር። በጣም ጠቃሚ የሆነው የአውስትራሊያ ብሄራዊ መለያ ምስረታ እየጀመረ መጣ። የስፖርት ቡድኖች አውስትራሊያን በዓለም አቀፍ መወከል ጀመሩ፣ እንዲሁም በአይነቱ አንድ የሆነው የአውስትራሊያ ባህል በታወቁ ዘፈንች/መዝሙር፣ ግጥሞች፣ ታሪኮችና ስነ-ጥበብ አድርጎ ማደግ ጀመረ።

አገሪቷን ወደ አንድነት ለማምጣት አስቸጋሪ ተግባር ቢሆንም ከጊዜ በኋላ ግን የአንድ አውስትራሊያን አገር ምስረታ ሀሳብ እውን ሆነ። አውስትራሊያኖች አገራቸው በትግል ሂደት ወይም በደም መፍሰስ በኩል የተመሰረተች ሳይሆን ነገር ግን በድርድርና በህዝብ ምርጫ ረፈረንዱም በመሆኑ አውስትራሊያኖች ይኮራሉ።

ጥር/January 1 ቀን 1901 ዓ.ም የቅኝ ግዛቶች በመጣመር የፈደሬሽን መስተዳድር ግዛቶችን ሲመሰርቱ ይህም የአውስትራሊያ ኮመንዌልዝ ይባላል።

Page 27: Australian citizenship test book - Ahmaric...4 የአውትራሊያ ዜግነት: የጋራ መተሳሰሪያችን የአውስትራሊያ ዜጋ ስለመሆን በአውስትራሊያ

የአውትራሊያ ዜግነት: የጋራ መተሳሰሪያችን 24

የአውስትራሊያ ህገ መንግሥትበአውስትራሊያ ኮመንዌልዝ ህገ መንግሥት አንቀጽ ህግ 1900 ዓ.ም መሰረት ይህ ህጋዊ የሆነ ሰነድ ሲሆን ይህም ለአውስትራሊያ መንግሥት የሚሆን መሰረታዊ ደንቦችን አውጥቷል። የአውስትራሊያ ህገ መንግሥት እንደ ብሪቲሽ የፓርሊመንት አንቀጽ ህግ 1900 ዓ.ም አካል በመሆን መጀመሪያ ተላልፎ እንደነበር ነው። ጥር/January 1 ቀን 1901 ዓ.ም ህገ መንግሥቱ ተግባራዊ በሚሆንበት ጊዜ የአውስትራሊያ ቅኝ ግዛቶች ወደ አንድ ትገኛ ያልሆነ አገር በመሆን የአውስትራሊያ ኮመንዌልዝ ተባለ።

የአውስትራሊያ ህገ መንግሥት በኮመንዌልዝ አውስትራሊያ ፓርሊያመንት በኩል ሲመሰረት፣ የስርወ መንግሥት ተወካዮችንና የህግ መወሰኛ ምክር ቤት እካላትን አቋቋመ። እንዲሁም ህገ መንግሥቱ የአውስትራሊያን ህጎች በመተርጎም ተግባር ላይ ስልጣን ያለው የአውስትራሊያ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተቋቋመ።

የአውስትራሊያ ህገ መንግሥት ሊቀየር የሚችለው ለየት ባለ የህዝብ ምርጫ ድምጽ ረፈረንዱም በተባለው አማካኝነት ብቻ ይሆናል።

የአውትራሊያ ህገ መንግሥት እንደሚቀየር በረፈረንዱም ውስጥ የብዙሃኑ እጥፍ ፍላጎት መሆን አለበት። ይህ ማለት በአብዛኛው የመስተዳድር ግዛቶች እና በአገሪቷ ዙሪያ ያለው አብዛኛው ድምጽ ሰጪ ለለውጥ መምረጥ አለባቸው።

እንዴት የመንግሥት ስልጣን መቆጣጣር እንደሚቻል?የአውስትራልያ ህገ መንግሥት ስልጣንን በሶስት የመንግሥት ክንዶች ይከፋፍላል። ይህም አንድ ሰው ወይም ቡድን አውስትራሊያን ለማስተዳደር ሁሉንም ስልጣን ከመቆጣጠር ያግደዋል።.

የህግ በላይነት ፓርሊያመንት ህግን ለማውጣት ስልጣን አለው። ፓርሊያመንት በአውስትራሊያ ህዝብ በተመረጡ ወኪሎች የተመሰረተ ነው።

የውሳኔ ሰጭ ስልጣንይህ ህግን ተግባራዊ የሚያደርግ ስልጣን ነው። በውሳኔ ሰጪ አካል ውስጥ የአውስትራሊያ መንግሥት ሚኒስቴሮችና ጠቅላይ ገዥውን ያካተተ ይሆናል። እያንዳንዱ ሚኒስቴር ለአንድ ወይም ከዚያ በላይ የመንግሥት መምሪያ ጽ/ቤቶች ሃላፊ ይሆናል።

የህጋዊ ፍትህ ስልጣን ዳኞች ህጉን በመተርጎም ለመጠቀም ስልጣን አላቸው። ፍርድ ቤቶችና ዳኞች ከፓርሊያመንትና መንግሥት ተጽእኖ ነጻ ናቸው።

እነዚህ ስልጣናት በአውስትራሊያ ህገ መንግሥት ውስጥ ተጽፈዋል።

የአውስትራሊያ መስተዳድር ግዛት የበላይ አስተዳደር ማን ነው?የአውስትራሊያ መስተዳደር ግዛት የበላይ አስተዳደር የአውስትራሊያ ንግስት፣ ግርማዊት ንግስት ኢልዛበት/ Queen Elizabeth II ይባላሉ።

በአውስትራሊያ ውስጥ ንግስቲቷ በየቀኑ መንግሥት ውስጥ ለሚደረጉት ተግባራት ሃልፊነት የላቸውም። ንግስቲቷ የአውስትራሊያን ጠቅላይ ሚኒስቴር በማማከር ጠቅላይ ገዥ በአውስትራሊያ እንዲወክላቸው ይመርጣሉ። ጠቅላይ ገዥው ከማንም የፖለቲካ ቡድኖች ነጻ በሆነ መልኩ ይሰራል።

በእያንዳንዱ ግዛት ላይ ንግስቲቷን የሚወክል ገዥ ሲኖር ተግባሩም ከጠቅላይ ገዥው ጋር ተመሳሳይ ይሆናል።

ንጉሳዊ አገዛዝአውስትራሊያ የንጉሳዊ አገዛዝ አሰራር አላት። በአንድ አገር መስተዳድር ግዛት ላይ ንጉስ ወይም ንግስት በህገ መንግሥቱ መሰረት በበላይነት ሲመራ የንጉሳዊ አገዛዝ ይባላል።

የአውስትራሊያ ዲሞክራሲያዊ ፓርላመንታሪይ አሰራር ከብሪቲሽ አሰራር የመጣና ከብዙ ዓመታት በኋላ ያደገ ዘዴ ነው። በአውስትራሊያ አሰራር ዘዴ፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የአውስትራሊያ መንግሥት መሪ ናቸው።

የአውስትራሊያ ህገ መንግሥት

Page 28: Australian citizenship test book - Ahmaric...4 የአውትራሊያ ዜግነት: የጋራ መተሳሰሪያችን የአውስትራሊያ ዜጋ ስለመሆን በአውስትራሊያ

ክፍል 3 – በአውስትራሊያ ውስጥ መንግሥትና ህግ 25

ስለጠቅላይ ገዥ የሥራ ድርሻጠቅላይ ገዥው:

• በአውስትራሊያ ፓርላመንት ባቀረበው የህግ ርቂቅ ላይ መፈረም (ይህ ሮያል አሰንት ይባላል)

• በደንቦች ላይ መፈረም

• በክብረ በዓላት ስነ-ስራአት ማካሄድ

• በአውስትራሊያ መንግሥትና ሚኒትሮቹ፣ በፈደራል ዳኞችና ሌሎች ባለሥልጣኖች ለሚቀናጅ ቀጠሮ ማጽደቅ ይሆናል።

እንዲሁም ጠቅላይ ገዥው “የራሱ የሆነ ስልጣን/ reserve powers’ የሚባል ልዩ የሆነ ስልጣን ሲኖረው ይህም ለየት ባለ ሁኔታ ላይ መጠቀም ይቻላል።

አንዳንድ የአውስትራሊያ መሪዎች እነማን ናቸው?የመንግስት መሪ/ ርእሰ አስተዳደር የአውስትራሊያ ንግስት

ጠቅላይ ገዥ/ ርእሰ መንግሥትበአውስትራሊያ ውስጥ የመንግሥት መሪ ተወካይ

ዋና አስተዳዳሪየእናንዳንዱ የአውስትራሊያ መንግሥት መሪ ተወካይ

ጠቅላይ ሚኒስተር የአውስትራሊያ መንግሥት መሪ

ርእሰ መስተዳድር ግዛት ፕረኔርይመስተዳድር ግዛት መንግሥት መሪ

የሚኒስተር የበላይ ሹም የተሪቶሪ መንግሥት መሪ

የመንግሥት ሚኒስተርበመንግሥት መሪ የሚመረጥና የፓሪያመንት አባል ሲሆን ስለመንግሥት ጉዳይ ሀላፊነት ይኖረዋል

የፓሪያመንት አባል (MP)በአውስትራሊያ ፓሪያመንት ወይም ግዛት ወይም በተሪቶሪ ፓሪያመንት ተወካይ ሲሆን በአውስትራሊያ ህዝብ የተመረጠ ነው

የህግ መወሰኛ ምክር ቤት አባልበአውስትራሊያ ፓሪያመንት ውስጥ ለመስተዳድር ግዛት ወይም ተሪቶሪ እንዲወክል የተመረጠ ነው

ከንቲባ ወይም የገጠር ፕረሲደንትየአካባቢ ምክር ቤት መሪ

ኮንስለር አማካሪ

ለአካባቢ ምክር ቤት የተመረጠ አባል

እንዴት አውስትራሊያ ትተዳደራለች?የአውስትራሊአ መንግሥትእንዲሁም የአውስትራሊያ መንግሥት ፈደራል መንግሥት ወይም የኮመንዌልዝ መንግሥት ተብሎ ይጠራል።

የአውስትራሊያ ፓሪያመንት ሁለት መቀመጫዎች አሉት:

• የተወካዮች መቀመጫ

• የህግ መወሰኛ ምክር ቤት ናቸው።

በሁለቱም መቀመጫዎች አባላት የሚመረጡት በፈደራል ምርጫዎች ጊዜ በቀጥታ በአውስትራሊያ ህዝብ ነው። በፈደራል ምርጫ ጊዜ ደምጽ ሲሰጡ ብዙ ጊዜ ለሁለቱም መቀመጫዎች የሚሆኑ ተወካዮችን ይመርጣሉ።

አሮጌው የፓሪያመንት መቀመጫ በካንበራ ውስጥ በ1927 ዓ.ም ተከፈተ

አዲስ የፓሪያመንት መቀመጫ በካንበራ ውስጥ በ1988 ዓ.ም ተከፈተ

Page 29: Australian citizenship test book - Ahmaric...4 የአውትራሊያ ዜግነት: የጋራ መተሳሰሪያችን የአውስትራሊያ ዜጋ ስለመሆን በአውስትራሊያ

የአውትራሊያ ዜግነት: የጋራ መተሳሰሪያችን 26

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት

የህግ መወሰኛ ምክር ቤት

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤትየተወካዮች ምክር ቤት አንዳንድ ጊዜ የንኡሳን ምክር ቤት ወይም የህዝብ ምክር ቤት ተብሎ ይጠራል።

አውስትራሊያ በፈደራል መራጮች ትከፋፈላለች። በተወካዮች ምክር ቤት ላይ ይወክላቸው ዘንድ በአውስትራሊያ የሚካሄድ ምርጫ ላይ ለአንድ ሰው ምርጫ ድምጽ ያቀርባል። ይህ ተወካይ የፓሪያመንት አባል (MP) ይባላል።

በእያንዳንዱ መስተዳድር ግዛትና ተሪቶሪ የሚሰየም የፓሪያመንት አባል (MP) በህዝቡ ብዛት ይወሰናል። ለፓሪያመንት መቀመጫ በአውስትራሊያ ህዝብ በኩል በጠቅላላ 150 አባላት የመረጣሉ።

በታቀዱት አዳዲስ ህጎች ወይም የህጎች ለውጥ ላይ ውይይትና የድምጽ ምርጫ እንዲካሄድ ማድረግ የተወካዮች ወንበር መቀመጫ ጠቃሚ ሥራ ይሆናል። እንዲሁም በተወላይ ወንበር መቀመጫ አባላት ስለ ሃገራዊ ጠቀሜታ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ይወያያሉ።

የህግ መወሰኛ ምክር ቤትይህ አንዳንድ ጊዜ የበላይ ወንበር መቀመጫ፣ የግምገማ ማካሄጃ መቀመጫ ወይም የመስተዳድር ወንበር መቀመጫ ተብሎ ይጠራል።

የመስተዳድር ግዛቶች ባላቸው የህዝብ ብዛት ሳይሆን በህግ መወሰኛ ምክር ቤት ውስጥ በእኩልነት ይወከላሉ። በእያንዳንዱ ግዛት 12 ተወካዮች ይመረጣሉ። ደሴት ያልሆኑት ሁለቱም ተሪቶሪዎች እያንዳንዳቸው ሁለት ተወካዮች ይመርጣሉ። በጠቅላላ 76 ተወካዮች ሶመረጡ እነሱም የህግ መወሰኛ ምክር ቤት አባላት ይባላሉ።

የህግ መወሰኛ ምክር ቤት አባላት በታቀዱ አዳዲስ ህጎች ወይም የህጎች ለውጥ ላይ ውይይትና የድምጽ ምርጫ እንዲካሄድ ይደርጋል። እንዲሁም የህግ መወሰኛ ምክር ቤት አባላት ለሃገሪቷ ጠቃሚ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ይወያያሉ።

የመስተዳድር ግዛትና የተሪቶሪ መንግሥትበአውስትራሊያ ውስጥ ስድስት መስተዳድር ግዛቶችና ሁለት በደሴት ላይ ያልሆኑ ተሪተሪዎች አሉ። እይንዳንዱ ግዛት የራሱ ህገ መንግሥትና የራሱ ፓሪያመንት ይኖረዋል። የመስተዳድር ግዛትና ተሪቶሪ መንግሥታት የራሳቸው ርእሰ ከተማዎች አሉት።

የመስተዳድር ግዛት መሪ ጠቅላይ ሚኒስቴር/ፕረሜር ሲሆን የተሪቶሪ መንግሥት ደግሞ የሚኒስቴር በላይ ሹም ይባላል።

የመስተዳድር ግዛት መንግሥታት እንደ የአውስትራሊያ መንግሥት በተመሳሳይ መልኩ ይሰራሉ። በእያንዳንዱ መስተዳድር ያለ ገዥ ለአውስትራሊያ ንግሥት ይወክላል። በሰሜናዊ ተሪቶሪ ክልል ውስጥ አስተዳዳሪ በጠቅላይ ገዥው በኩል ይመረጣል። የአስተዳዳሪው የሥራ ድርሻና ሃላፊነት እንደ ሌላው የዛት ገዥ ተመሳሳይ ይሆናል።

በአውስትራሊያ መንግሥት ሰዎች ለአካባቢያቸው ተወካይ የሚሆን ለመምረጥ ድምጽ ይሰጣሉ። ታዲያ እነዚህ ተወካዮች በግዛት ወይም በተሪቶሪ ፓርሊያመንት ውስጥ አባል ይሆናሉ።

የአካባቢ መንግሥትየመስተዳድር ግዛትና ተሪቶሪ በአካባቢ መንግሥት የተከፋፈሉ ናቸው። እነዚህም በተማዎች፣ ገጠሮች፣ በከተማ ማእከላት ወይም በማዘጋጃ ቤቶች ስም ሊጠራ ይችላል። በእያንዳንዱ አካባቢ የራሱ ማዘጋጃ ቤት ይኖረዋል። ማዘጋጃ ቤት ለአካባቢው ማህበረሰብ አገልግሎቶችን ማቅረብና ለክተማ ፕላን እቅድ አወጣጥ ሃላፊነት አለበት። በእያንዳንዱ መንግሥት ያሉ ዜጎች ለአካባቢ አማካሪ ጠበቃዎች ምርጫ ላይ ድምጽ ይሰጣሉ።

Page 30: Australian citizenship test book - Ahmaric...4 የአውትራሊያ ዜግነት: የጋራ መተሳሰሪያችን የአውስትራሊያ ዜጋ ስለመሆን በአውስትራሊያ

ክፍል 3 – በአውስትራሊያ ውስጥ መንግሥትና ህግ 27

ለብሄራዊ ኢኮኖሚ ማስተዳደር የአውስትራሊያ መንግሥት ሃላፊነት ይሆናል

ሆስፒታሎችን ማስተዳደር ሃላፊነት የመስተዳድር ግዛትና ተሪቶሪ መንግሥት ነው

ለመጫወቻ ሜዳዎች ሃላፊነቱ የአካባቢ መንግሥታት ይሆናል

ሶስት የመንግሥት ደረጃዎች ምን ያደርጋሉ?የአውስትራሊያ መንግሥት ሃላፊነት:

• ለግብር ማስገባት

• ለብሄራዊ ኢኮኖሚ ማስተዳደር

• ለኢሚግሬሽንና ዜግነት

• ለሥራና ቀጣሪ

• ለፖስታ አገልግሎትና ለመገናኛ ሥራ ቅንጅት

• ለማህበራዊ ዋስትና/social security (ለጡረታ አበልና ለቤተሰብ እርዳታ)

• ለመከላከያ ሃይል

• ለንግድ

• ለአውሮፕላን ማረፊያዎችና ለአየር ላይ ደህንነት

• ለውጭ አገር ጉዳዮች (ከሌች አገሮች ጋር ግንኙነት) ማድረግ ይሆናል።

ለውጭ አገር ጉዳዮች (ከሌች አገሮች ጋር ግንኙነት) ማድረግ ይሆናል:

• ለሆስፒታሎችና ለጤና ጥበቃ አገልግሎቶች

• ለትምህርት ቤቶች

• ለባቡር ሀዲዶች

• ለመንገዶና ለትራፊክ ቁጥጥር

• ለደን ልማት

• ለፖሊስ

• ለህዝብ ማጓጓዣ ይሆናል።

የአካባቢ መንግሥታት ሃላፊነት:

• ለመንገድ ምልክቶች፣ የትራፊክ ቁጥጥር

• ለአካባቢ መንገዶች፣ ለእግር መተላለፊያዎች፣ ድልዲሎች

• ለቆሻሻ ማስወረጃ ቦይ

• ለመናፈሻ ፓርክ፣ ለመጫወቻ ቦታዎች፣ ለመዋኛ ገንዳዎች፣ ለስፖርት ሜዳዎች

• ለእረፍት ጊዜ የሰፈራ ካምፕና የካራቫን ፓርክ

• ለምግብና ስጋ ቁጥጥር

• ለጫጫታና እንስሳ ቁጥጥር

• ለቆሻሻ መሰብሰብ

• ለአካባቢ ቤተ መጽሐፍት፣ አዳራሾችና ለማህበረሰብ ማእከላት

• ለአንዳንድ የህጻን እንክብካቤና በእድሜ ለገፉ እንክብካቤ ጋር በተያያዙ ጉዳዮች

• ለህንጻ ሥራ ፍቃዶች

• ለማሕበራዊ እቅድ አወጣጥ

• ለአካባቢ ሁኔታ ጉዳዮች ይሆናል።

በተለያዩ የመንግሥት ደረጃዎች መካከል አንዳንድ ሃላፊነቶችን ይካፈላሉ። በአውስትራሊያ መንግሥት ምክር ቤት (COAG) የተቋቋመው በተለያዩ የመንግሥት ደረጃዎች መካከል ሕብረት እንዲፈጠር ለማበረታታት ነው።

Page 31: Australian citizenship test book - Ahmaric...4 የአውትራሊያ ዜግነት: የጋራ መተሳሰሪያችን የአውስትራሊያ ዜጋ ስለመሆን በአውስትራሊያ

የአውትራሊያ ዜግነት: የጋራ መተሳሰሪያችን 28

በአውስትራሊያ የአስተዳደር ዘዴ ላይ ፖለቲካ ቡድኖች ምን የሥራ ድርሻ አላቸው?የፖለቲካ ቡድን የሰዎች መሰባሰብ ሲሆን ስለ አገሪቷ አስተዳደር እንዴት መሆን እንዳለበት ተመሳሳይ የሆኑ ሀሳቦችን ይለዋወጣሉ። ፓርቲው/ቡድኑ ያቀረበው ሀሳብ ወደ ህግ እስኪቀየር ድረስ በጋራ አብረው ይሠራሉ። በአውስትራሊያ ውስጥ ዋና የፖለቲካ ቡድኖች የአውስትራሊያ ሌበር ፓርቲ፣ የአውስትራሊያ ሊበራል ፓርቲ፣ ናሽናልስ እና የአውስትራሊያ ግሪንስ ናቸው።

አብዛኞቹ የፓሪሊያመንት አባላት እና የህግ መወሰኛ ምክር ቤት አባላት የመጡት ከማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ ነው። እነሱም ከተጽእኖ ነጻ የሆኑ በሚል ይጠራሉ።

በአውስትራሊያ ውስጥ በራስዎ ምርጫ በፖለቲካ ቡድን ውስጥ ለመሳተፍ ይችላሉ።

የአውስትራሊያ መንግሥት እንዴት ተመሰረተ?ከምርጫ በኋላ፣ የፖለቲካ ቡድን ወይም የቡድኖች ቅንጅት ከአብዛኛው የተወካዮች ወንበር መቀመጫ አባላት ጋር በመሆን የአውስትራሊያ መንግሥት ይመሰረታል። የዚህ ቡድን መሪ፣ የአውስትራሊያ መንግሥት፣ ጠቅላይ ሚኒስቴር ይሆናል።

በተወካይ ወንበር መቀመጫ ውስጥ በቁጥር ብዛት ሁለተኛ የሆነ የቡድን ወይም የቡድኖች ቅንጅት አባላት ሲኖር ይህም ተቃዋሚ ተብሎ ይጠራል። የነሲ መሪ የተቃውሞ መሪ ይባላል።

ጠቅላይ ሚኒስቴሩ ከፓሪያመንት አባባላት (MPs) ወይም ከህግ አርቃቂ ምክር ቤት አባላት ውስጥ ሚኒስቴሮች እንዲሆኑ ይመርጣሉ። በመንግሥት ላሉ ጠቃሚ ክፍሎች ማለት እንደ ሥራ፣ በአገሬው ተወላጅ ጉዳይ ወይም በንብረት ቁጥጥር ላይ የሚኒስቴሮች ሃላፊነት ይሆናል። አንጋፋና ጥሩ ታሪክ ያላቸው ሚኒስቴሮች የካቢነት ምክር ቤት ሲፈጥሩ ይህም ለአውስትራሊያ መንግሥት ዋናው የውሳኔ ሰጪ አካል ይሆናል።

እንዴት ህጎች ይወጣሉ?

አዲስ ህግ ወይም የህግ ለውጥ በአውስትራሊያ ፓርሊያመንት አባል በኩል ይታቀዳል። ይህ ሀሳብ የህግ ማሻሻያ መጠይቅ ይባላል።

የተወካዮች መቀመጫና የህግ መወሰኛ ምክር ቤት ለቀረበው የህግ ማሻሻያ ጥያቄ ከተስማሙበት ተወያይተው በድምጽ ለማሳለፍ ግምት ውስጥ ያስገቡታል።

በእያንዳንዱ የፓርሊያመንት መቀመጫ ያሉት አብዛኛው አባላት ለቀረበው የህግ ማሻሻያ ጥያቄ ካመኑበት ወደ ጠቅላይ ገዥው ይሄዳል።

ጠቅላይ ገዥው በህግ ማሻሻያው ጥያቄ ላይ ሲፈርሙበት ህግ ይሆናል። ይህም የንጉሳዊ ክህሎት/ንብረት ተብሎ ይጠራል።

የመስተዳድር ግዛትና ተሪቲሪ ፓርሊያመንት ብበመሳሳይ መንገድ የራሳቸውን ህግ ያወጣሉ።

ህጎች እንዴት ይመራሉ?ፍርድ ቤቶችበአውስትራሊያ ውስጥ ፍርድ ቤቶች ህጉን የመተርጎምና ተግባራዊ ለማድረግ ሃለፊነት አላቸው። እነዚህም ከመንግሥት ተጽእኖ ነጻ ናቸው። አንድ ሰው ህጉን ለመጣስና አለመጣስ ፍርድ ቤቶች በማጣራት ቅጣት ይወስናሉ። በችሎት ላይ የሚቀርቡትን ማስረጃዎች መነሻ አድርገው ፍርድ ቤቶች ውሳኔ ይሰጣሉ። በፍርድ ቤት ውስጥ ማንኛውም ሰው በህግ ጠበቃ ሊወከል መብት አለው። ፍርድ ቤቶች ውሳኔ መስጠት የሚችሉት ከፊታቸው በቀረበው መረጃ በመነሳት ብቻ ይሆናል።

ዳኞችና የአጥቢያ ዳኞችዳኞች ወይም አጥቢያ ዳኞች በፍርድ ቤት ውስጥ ከፍተኛ ስልጣን ናቸው። ዳኞችና አጥቢያ ዳኞች በማንም ተጽእኖ የሌለባቸውና ምን መወሰን እንዳለባቸው ማንም ሊነግራቸው አይችልም።

ዳኞችና የአጥቢያ ዳኞች የሚመረጡት በመንግሥት ሲሆን ባቀረቡት ውሳኔ ላይ ካልተስማማ መንግሥት ከሥራ ማስወጣት አይችልም።

በአውስትራሊያ ፓርሊያመንት ውስጥ ተወካይ ይሆን ዘንድ ሰዎች በአውስትራሊያ ዜግጎች ይመረጣሉ።

ለአገሪቷ ጥቅም ሲባል ህጎችን በማውጣትና በመቀየር የአውስትራሊያ ፓርሊያመንት ጉዳይ ነው።

የአውስትራሊያ ከፍተኛ ፍርድ ቤት

Page 32: Australian citizenship test book - Ahmaric...4 የአውትራሊያ ዜግነት: የጋራ መተሳሰሪያችን የአውስትራሊያ ዜጋ ስለመሆን በአውስትራሊያ

ክፍል 3 – በአውስትራሊያ ውስጥ መንግሥትና ህግ 29

እንደ ሌሎች አገሮች እንዲሁም በአውስትራሊያ ውስጥ በሌላ ሰው ላይ ጠበ ጫሪነት ህገ-ወትነት ሲሆን በጣም ከባድ ወንጀል ነው። በቤት ውስጥና በትዳር መካከል የሚከሰት ሁከት ሲያካትት ይህም የቤት ውስጥ ብጥብጥ ወይም የቤተሰብ ብጥብጥ ተብሎ ይጠራል። ይባላል። በቤት ውስጥ ብጥብጥ የሚካተት ድብደባ፣ በግብረስጋ ወይም በስነ-አእምሮ የሚነካ ስድብ ወይም ጉዳት፣ ሀይልን ተጠቅሞ የግብረስጋ ግንኙነት ማድረግ፣ በግዳች ከሰው ገለልተኛ ማድረግ ወይም የኢኮኖሚ ጫና መፍጠር ይሆና።

የጦር መሳሪያ መያዝ ማለት እንደ ቢላዋ ወይም ጠበንጃ መያዝ በአውስትራሊያ ህጉ አይፈቅድም። አንድ ሰው ጠበንጃ እንዲኖረው ከፈለገ፣ ለምሳሌ፡ በእርሻ ቦታ ላይ ለመጠቀም መጀመሪያ የጦር መሳሪያ ፈቃድ ከፖሊስ ማውጣት አለበት።

የትራፊክ ህጎችን መጣስመንገዶችና የትራፊክ ደንቦች በመስተዳድር ግዛትና ተሪቶሪ መንግሥታት ቁጥጥር ስር ናቸው። ሰዎች የትራፊክ ህጎችን በሚጥሱበት ጊዜ ብዙ የገንዘብ ቅጣት ሊያገኙ ይችላሉ ወይም እስር ቤትም መግባት ይችላሉ። በአውስትራሊያ ውስጥ መኪና ለመንዳት በመጀመሪያ የአካባቢ መንጃ ፈቃድና የተመዘገበ መኪና ማግኘት አለብዎ።

በመኪና ውስጥ ሆኖ የሚጓዝ ሁሉ ቀበቶ ማሰር አለበት። ለህጻናት በተፈቀደ የህጻን ማሰሪያ ውስጥ ሆኖ መጓዝ አለበት። ከፍጥነት ገደብ በላይ ስለመንዳት፣ አልኮሆል ወይም አደገኛ እጽ ከወሰዱ በኃላ ስለመንዳት የትራፊክ ህጎች በጣም ጥብቅ ናቸው። እንዲሁም መኪና በሚነዱበት ጊዜ በእጅ የሚያዝ ሞባይል ስልክ መነጋገር ህገ-ወጥነት ይሆናል።

ማጠቃለያዲሞክራቲክ የሆኑት ተቋማችን፤ ሰላማዊና የተረጋጋ ሕብረተሰብ እንዲፈጠር አድርጓል። አብሮ ለመጠቀም የበለጸገና ልዩ የሆነ ባህል አለን። የአውስትራሊያ ዜጋ በመሆንዎ በብሄራዊ ታሪካችን ተካፋይ እንደሆኑና ለወደፊት እድላችን አስተዋጽኦ እንደሚያደርጉ ነው። አውስትራሊያ በደህና ትቀበልዎታለች። ዜግነት የጋራ ማስተሳሰሪያ ነው።

ለዜግነት ፈተና ለመዘጋጀት በገጽ 34 እና 35 ባሉት የመለማመጃ ጥያቄዎች ላይ ለመሥራት ይሞክሩ።

ከነዋሪዎች የተመረጡ ዳኞች/Juriesበአንዳንድ ጉዳዮች ላይ ሰውየው ህጉን ስለመጣሱ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ ላይ ለመድረስ ከነዋሪ የተመረጡ ዳኞችን ይጠቀማል።

እነዚህ ዳኞች ከአጠቃላይ ተራ ነዋሪ ህዝብ ውስጥ አልፎ አልፎ የተመረጠ ቡድን ነው። ዳኛው ስለ ህጉ ማብራሪያ ለተመረጡት ዳኞች ያቀርባል። በወንጀል ፍርድ ችሎት ላይ ሰውየው በተመረጡት ዳኞች ጥፍተኛ ሆኖ ከተገኘ ታዲያ ዳኛው የቅጣት ውሳኔ ይሰጣል።

በአውስትራሊያ ህግ መሰረት ሰዎች ፍርድ ቤት ቀርበው ጥፋተኛ ሆነው እስካልተገኙ ድረስ ወንጀለኛ አይባሉም።

ፖሊስፖሊስ በማህበረሰቡ ያለውን ሰላም በማስከበር ስነ-ስርዓት ያስይዛል። ለሕይወትና ንብረት ድህንነትን ማስጠበቅ ሥራቸው ይሆናል። ፖሊስ ከመንግስት ተጽእኖ ነጻ ይሆናል። አንድ ሰው ህጉን ጥሷል ብሎ ፖሊስ ካመነበት አስረው ወደ ፍርድ ቤት ህግ ያቀርባሉ። ፖሊስ በፍርድ ቤት ውስጥ ማስረጃ ሊያቀርብ ሲችል፣ ነገር ግን ሰውየው ጥፋተኛ ወይም ከወንጀል ነጻ ስለመሆኑ ፍርድ ቤት ይወስናል።

የመስተዳድር ግዛቶችና የሰሜናዊ ተሪቶሪ ክልል የራሳቸው የፖሊስ ሀይል አላቸው። ወንጀል ነክ ለሆነ ጉዳይ የሚታየው በመስተዳድር ግዛትና ተሪቶሪ ህጎች መሰረት ይሆናል።

እንዲሁም አውስትራሊያ በአገር አቀፍ የፖሊስ ሀይል ሲኖራት የአውስትራሊያ ፈደራል ፖሊስ ተብሎ ይጠራል። በፈደራል ህጎች አንጻራዊ በሆኑ ወንጀሎች ላይ የአውስትራሊያ ፈደራል ፖሊስ ምርመራ ያካሂዳል፤ ለምሳሌ፡ ድብቅ የአደገኛ እጽ ንግድ፣ በንሄራዊ ደህንነት ላይ ወንጀል እና በአካባቢ ማበላሸት ወንጀል ይሆናል። በተጨማሪም በአውስትራሊያ የተሪቶሪ ርእሰ ከተማ ውስጥ የፈደራል ፖሊስ ይሰራል።

በአውስትራሊያ ውስጥ ፖሊስና ማህበረሰቡ ጥሩ ግንኙነት አላቸው። ለወንጀል ሲፈጸምና እርዳታ ሲፈልጉ ለአካባቢዎ ፖሊስ ሪፖርት ማድረግ ይችላሉ።

በአውስትራሊያ ውስጥ ያለውን ህግ ማወቁ ለርስዎ አስፈላጊ ሲሆን ህግን ባለምወቅ ለሚከሰት የህ መጣስ ምክንያት አይሆንም።

ልፖሊስ መኮነን ጉቦ መስጠት ከባድ ወንጀል ነው። እንዲሁም ፖሊስ ግቦን ከተቀበለ ወንጀለኛ ነው።

በአውስትራሊያ ውስጥ ወንጀለኞችአንዳንድ በጣም ከባድ ከሆኑት ወንጀሎች ውስጥ የሚካተቱ፤ ነብስ ግድያ፣ የስድብ ውርጅብኝ፣ የወሲባዊ ጥቃት በደል፣ በሰዎች ወይም በንብረት ላይ ሁከት መፍጠር፣ ጦር መሳሪያ ይዞ ዝርፊያ ወይም ስርቆት፣ እድሚያቸው ከሚፈቀደው ህግ በታችና ፈቃደኛ ካልሆኑ ህጻናት ወይም ወታቶች ጋር የግብረስጋ ግንኙነት መፍጠር፣ አደገኛ የመኪና አነዳድ፣ ህገ-ወጥ የሆኑ አደገኛ እጾችን ማቅረብና መጠቀም እንዲሁም ማጭበርበር ይሆናል።

Page 33: Australian citizenship test book - Ahmaric...4 የአውትራሊያ ዜግነት: የጋራ መተሳሰሪያችን የአውስትራሊያ ዜጋ ስለመሆን በአውስትራሊያ

የአውትራሊያ ዜግነት: የጋራ መተሳሰሪያችን 30

መመዘን ያለበት የቃላት ትርጉም ክፍልየአውስትራሊያ ህዝባዊ አገልግሎትየመንግሥት መምሪያ ቢሮዎችና በነሱ የተቀጠሩ ሰዎች ፓዎል/ Paul በአውስትራሊያ ህዝባዊ አገልግሎት ስራ በማግኘት እንደ ሴንተርሊን/Centrelink ሀላፊ ይሰራል።

ህዝባዊ አመጽ ሽብርበብዙ ሰዎች አመጽ የሚደረግ ሰላማዊ ሰልፍ ሲሆን ይህም ብዙ ጊዜ መንግሥት በወሰነው ወይም ባወጣው ፖሊሲ ላይ ተቃውሞ ለማሰማት ይሆናልመንግሥት በህዝባዊ ያልታወቀ ህጎችን ሲያስተላልፍ ህዝባዊ አመጽ እንደነበር ነው።

ቅንጅትብዙጊዜ መንግሥትን ወይም ተቃዋሚን ለመመስረት ሁለት ወይም ከዚያ በላይ የፖለቲካ ቡድን ፓርቲዎች ይጣመራሉ።ከምርጫ በኋላ በተወካይ ወንበር መቀመጫ ውስጥ ብላጭ ድምጽ ያለው ፓርቲ ስለማይኖር ታዲያ እነዚህ ሁለት ፓርቲዎች ተመሳሳይ ከሆነ ሀሳብ ጋር በመጣመር ለቅንጅት ይፈጥራሉ።

ኮሚሽንይህ ከሥልጣን ጋር ሃላፊነት ያለው የሰዎች ቡድንተጽእኖ የሌለበት ኮሚሽን ለምርጫ ሁኔታዎችን ያቀናጃል።

የንጉሳዊ አገዛዝ ህገ መንግሥትበኮመንዌልዝ አውስትራሊያ ያለን ህገ መንግሥት የዩናይትድ ኪንግዶም/የእንግሊዝን ንጉሳዊ/ንግሥታዊ አገዛዝ እንደ የአገሪቷ መስተዳድር ርእሰ መሪ ተደርጎ እንደወጣ ነው።በኮመንዌልዝ አውስትራሊያ ያለን ህገ መንግሥት የዩናይትድ ኪንግዶም/የእንግሊዝን ንጉሳዊ/ንግሥታዊ አገዛዝ እንደ የአገሪቷ መስተዳድር ርእሰ መሪ ተደርጎ እንደወጣ ነው።

ፍርድ ቤትስለ ህጋዊ የሆኑ ጉዳዮች በዳኛ ወይም አጥቢያ ዳኛ የሚሰየምበት ቦታ ነውሰዎች ህጉን ሲጥሱ ወደ ፍርድ ቤት ሊቀርቡ ይችላሉ።

ወንጀል ነክ ፍርድ መቅረብበቀረበው የወንጀል ክስ ፍርድ ቤቱ በማዳመጥ፣ አንድ ሰው ወንጀለኛ ወይም ከወንጀል ነጻ ስለመሆኑ የሚወሰንበት ችሎት ነው።ከወንጀል ችሎት በኋላ የባንክ ዘራፊው ወንጀለኛ ወደ እስር ቤት ተላከ።

ደሞክራሲሰዎች ተወካዮቻቸውን በመምረጥ የሚቋቋም መንግሥትግራስ/Grace በፓሪያመንት ውስጥ የራሷን ተወካይ በምትመርጥበት ዲሞክራሲያዊ የሆነ አገር በመኖሯ ደስተኛ ናት።

በድብቅ የአደገኛ እጽ ንግድአደገኛ እጽን ለሽያጭ ብሎ መያዝ ወይም መግዛት ህገ-ወጥነት ይሆናልጀስ/Jess በድብቅ የአደገኛ እጽ በመነገዷ እስር ቤት ገብታለች።

ኢኮኖሚያዊ ብልሽትይህ እንደ የቤት ውስጥ ብጥብጥ ሲሆን በባልና ሚስት መካከል አንደኛው ገንዘብ እንዳያገኝና እንዳይዝ ማድረግ ይሆናልሊን/Lin ባለቤቷ ገንዘብ ስለማይሰጣት የኢኮኖሚ ችግር አጋጥሟታል።

ምርጫዜጎች በፓሪያመንት ውስጥ ለሚወክላቸው ሰው የሚመርጡበት ጊዜ ይሆናልእድሜው 18 ዓመት ወይም በላይ የሆነ የአውስትራሊያ ዜጋ በምርጫው ላይ ድምጽ መስጠት አለበት።

Page 34: Australian citizenship test book - Ahmaric...4 የአውትራሊያ ዜግነት: የጋራ መተሳሰሪያችን የአውስትራሊያ ዜጋ ስለመሆን በአውስትራሊያ

መፈተሽ የሚገባው የቃላት ፍቺ ክፍል 31

የመራጮች ስም ዝርዝርበምርጫ ወይም በህዝባዊ ምርጫ ሪፈረንዱም ላይ ድምጽ ለመስጠት የሚችሉ ሰዎች ስም ዝርዝርጃን/Jan በድምጽ መስጫ ማእከል ላይ ስትደርስ በመራጭ ዝርዝሩ ውስጥ ስሟ ካለ ሀላፊው ያየዋል።

የህግ ተገዥነትሰዎች ህጉን ስለመከተላቸው ማረጋገጥፖሊስ ህግን በማስከበር ሰላምን ያስይዛል።

የውሳኔ ሰጭ አካል ስልጣን ህጎችን ለማስተዳደር የሚሰጥ ስልጣንና ሀይል ሲሆን ይህም በአውስትራሊያ ህገ መንግሥት ውስጥ ከሶስቱ ስልጣናት አንዱ ይሆናልየአውስትራሊያ መንግሥት ሚኒስቴሮችና ጠቅላይ ገዥዎች በአውስትራሊያ ፓሪያመንት የወጣውን ህጎች የመወሰን ስልጣን ይኖራቸዋል።

ማእከላዊ አስተዳደር ፈደሬሽንየቅኝ ግዛቶች በማሕበር ወደ አንድ ብሄራዊ አገር ማምጣት ሲሆን ለአንዳንድ ቅኝ ግዛት ስልጣናት ሳይለወጥበ1901 ዓ.ም የቅኝ ግዛቶች ወደ ማእከላዊ አስተዳደር ፈደሬሽን የተዋሀዱበት ሲሆን ይህም የኮመንዌልዝ አውስትራሊያ ይባላል።

የመጀመሪያ ጦር መርከብ ጉዞበካፕቴን Captain Arthur Phillip የተመሩ 11 መርከቦች ከብሪቴን በመነሳት በኒው ሳውዝ ዌልስ ውስጥ የወንጀለኞች ሰፈራ ለማማቁቋም ነበርበአውስትራሊያ ቀን፣ ጥር/January 26 ቀን 1788 ዓ.ም የመጀመሪያው ጉዞ ወደ ስድነይ የባህር ወሽመጥ የደረሰበትን ቀን እናስታውሳለን።

በአበባ ያጌጠ አርማየብሄራዊ አበባበአበባ ያጌጠው የአውስትራሊያ አርማ በወርቃማ እንጥልጥል ይመሰላልs።

ለመገለል መገደድይህ የቤት ውስጥ ብጥብጥ ዓይነት ሲሆን በባልና ሚስት ግንኙነት መካከል አንደኛው የሚያየውን ሰውና የሚናገረውን፣ ምን እንዳነበቡና የት እንደሄዱ በሌላው ጥንድ ቁጥጥር ምድረግ ነውስንዲ/Sandi ጓደኞቿንና ቤተሰቧን እንድታይ ባለቤቷ ስላልፈቀደላት ገለልተኛ እንድትሆን ተገዳለች።

ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ለወደፊትከአሁን ጊዜና ለወደፊቱ በዜግነት ክብረ በዓል ላይ ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ለአውስትራሊያ ታማን ለመሆን ቃል ገብተዋል።

ምልክትበጣም የታወቀ የምስል ቅርጽኦፐራ ሃውስ/ Opera House በስድነይ የታወቀው ምስል ቅርጽ ነው።

የአገሬው ተወላጅ ህዝብበመሬቷ ላይ ለመጀመሪያ የሰፈሩ – በአውስትራሊያ የአቦሪጂናል እና ቶረስ ስትሬት አይላንደር ህዝቦች ሲሆኑበአውስትራሊያ የህዝብ ቁጥር ውስጥ እስከ ከመቶ 2.5 የሚሆነው የአገሬው ተወላጅ ህዝብ ይሆናል።

የጁዳ ክርስቲያን/Judaeo-Christianሁለቱም ማለት የጀዊሽና የክርስትና ሃይማኖቶችየጁዳ ክርስቲያን/ Judaeo-Christian ከመጽሐፍ ቅዱስ ባለ ትምህርት ላይ ያምናል።

Page 35: Australian citizenship test book - Ahmaric...4 የአውትራሊያ ዜግነት: የጋራ መተሳሰሪያችን የአውስትራሊያ ዜጋ ስለመሆን በአውስትራሊያ

የአውትራሊያ ዜግነት: የጋራ መተሳሰሪያችን32

ህጋዊ የሆነ ስልጣንህጎችን ለመተርጎምና ተግባራዊ ለማድረግ ስልጣን ማግኘት በአውስትራሊያ ህገ መንግሥት ስር ካሉት ሶስት ስልጣኖች አንደኛው ይሆናልበአውስትራሊያ ፍርድ ቤቶች ውስጥ ህጎች በዳኞች በኩል እንዲተረጎምና ተግባራዊ እንዲሆን ስልጣን አላቸው።

ለህግ አውጭነት ስልጣንህግን የማውጣትና መለወጥ ስልጣን በአውስትራሊያ ህገ መንግሥት ስር ካሉት ሶስት ስልጣኖች ውስጥ አንደኛው ይሆናልበህገ መንግሥቱ መሰረት ፓሪያመንት ህጎችን ለማውጣት ስልጣን ይኖረዋል።

ነጻነቶች (ነጻነት)የግላዊነት መብትና ነጻነትዲሞክራሲያዊ በሆነው ሕብረተሰባችን ውስጥ ሰዎች የመናገር፣ የእራሳቸውን ሃሳብ የመግለጽ፣ በሃይማኖትና በማሕበር የመሰባሰብ ነጻነት አላቸው። ለነዚህ መብት ነጻነቶች ዋጋ ክብር እንሰጣለን።

አጥቢያ ዳኛበዝቅተኛ ደረጃ ላለ ፍርድ ቤት ዳኛ (መሪ)የአጥቢያ ዳኛው ዘራፊውን ጥፋተኛ ሆኖ ስላገኘው ወደ እስር ቤት ላከው።

ጓደኛሞችበተለይ በችግር ጊዜ መረዳዳት ማለት እርዳታ መቀበልና ለሌሎች መስጠትመኪናዮ በሚበላሽበት ጊዜ ታዲያ መኪናዋን በመግፋት ሌላው ሹፌር በጓደኝነት መንፈስ ይረዳኛል።

ብሄራዊ መዝሙርየብሄራዊ መዝሙርየአውስትራሊያ ብሄራዊ መዝሙር ‘Advance Australia Fair’ ይባላል።

በፓርላማ ህዝባዊ ዲሞክራሲ አስተዳደር በመደበኛ ምርጫ ጊዜ በዜጎች ለፓርላማ ተወካይነት የመምረጥ መንግሥታዊ አሰራር ዘዴበፓሪያመንት ህዝባዊ አስተዳደር ሰዎች የራሳቸውን ተወካይ ይመርጣሉ።

በቋሚ ነዋሪነትበአውስትራሊያ ውስጥ ለመኖርና ለመሥራት ያለ ገደብ የፍቃድ ቪዛ ያለው ሰው ይሆናልየአብዱል/ Abdul’s ጃፓናዊ የሆነ ጎረቤት በአውስትራሊያ የቋሚ ነዋሪነት ስላለው በባንክ ውስጥ ይሠራል።

የፖለቲካ ፓርቲስለ አገሪቷ አስተዳደርና እንዴት መሆን እንዳለበት ተመሳሳይ ሀሳብ ያላቸው ሰዎች ስብስብ ቡድን ነውየፖለቲካ ፓርቲ አባላት ብዙጊዜ ይሰበሰባሉ፤ ለምሳሌ፡ ስለ የህዝብ ማጓጓዣ ማሻሻል ጉዳይ ለመነጋገር ይሆናል።

ህዝባዊ አገልግሎትለአገሪቷ ብልጽግና ያለን ጊዜ፣ ሀይል ወይም ችሎታ መጠቀምበአውስትራሊያ ውስጥ ስደተኞች እንዲላመዱ ጆሰ/Jose ጠቃሚ የሆነ ህዝባዊ አገልግሎት አቅርቧል።

ህዝባዊ ውሳኔ/referendumበአውስትራሊያ ህገ መንግሥት ላይ ስለታቀደው ለውጥ በሁሉም መራጮች የሚሰጥ ድምጽበ 1967 ዓ.ም ውስጥ በተደረገው የህዝብ ውሳኔ ላይ በድምጽ መስጫ ቆጠራ ላይ የአውስትራሊያ ተወላጅ ህዝብ ድምጽ ተቆጥሯል።

Page 36: Australian citizenship test book - Ahmaric...4 የአውትራሊያ ዜግነት: የጋራ መተሳሰሪያችን የአውስትራሊያ ዜጋ ስለመሆን በአውስትራሊያ

33

ተወካይለሌሎች ወክሎ የሚሰራ ወይም የሚናገር ሰውያለኝን ሀሳብ የአካባቢየ ምክር ቤት ተወካይ ስለወደደው በምክር ቤት ስብሰባ ላይ አቅርቦታል።

ግምግማለታቀደው አዲስ ህግ ግምት ውስጥ በማስገባት ለማጽደቅ ወይም ውድቅ ለማድረግ መወሰንየህግ መወሰኛ ምክር ቤት እንደ ገምጋሚ አካል መጠን ከበታች አካል በቀረበው የህግ ማሻሻል ጥያቄ ላይ ይነጋገራል።

ምስጢራዊ የድምጽ መስጫ ካርድሰዎች ለብቻቸው ሆነው የምርጫ ድምጽ የሚሰጡበት ዘዴ ሲሆን ታዲያ ምርጫ በሚያስገቡበት ጊዜ ሌላ ሰው ጣልቃ ወይም ሊያስገድድ አይችልምሰዎች ለብቻቸው ሆነው የምርጫ ድምጽ የሚሰጡበት ዘዴ ሲሆን ታዲያ ምርጫ በሚያስገቡበት ጊዜ ሌላ ሰው ጣልቃ ወይም ሊያስገድድ አይችልም።

አለማዊ መንግሥትከሃይማኖት የተለየ በአለማዊ ህብረተሰብ ውስጥ በህግ የታወቀ ሃይማኖት የለም።

ማቋቋምለማነጽ፣ ለመመስረት፣ ለመጀመር በአስተዳደር ገዥ ፊሊፕ/ Governor Phillip በኩል በኒው ሳውዝ ዌልስ ውስጥ የመጀመሪያውን ቅኝ ግዛት ሰፈራ ተቋቋመ።

ገጠርየአካባቢ መንግሥት ክልልበምኖርበት ገጠር ያሉት መንገዶች ደህንነቱ በጣም የተጠበቀ ነው።

ማሕበራዊ ዋስትና/ social securityየመንግሥት ጡረተኞች ወይም ለማይሰራ ሰው አበል፣ አካለ ጉዳተኛ፣ በእድሜ የገፉና ሌሎች ለሚያስፈልጋቸውትራንግ/Trang ከሥራ ስትወጣ ለማሕበራዊ ዋስትና ማመልከት አለባት።

እድልዎን መሞከርእድልን ማየትበየዓመቱ በመልበርን የፈረስ ውድድር በ$10 ዶላር በመግባት እድሌን እሞክራለሁ።

በፈቃደኝነት ሥራለአንድ ሰው ወይም ድርጅት ያለክፍያ ያለውን ጊዜ መስዋእት ማድረግራዛ/Raza ሰዎችን በቤታቸው ውስጥ የእንግሊዝኛ ትምህርት በፈቃደኝነት ያስተምራል።

መፈተሽ የሚገባው የቃላት ፍቺ ክፍል

Page 37: Australian citizenship test book - Ahmaric...4 የአውትራሊያ ዜግነት: የጋራ መተሳሰሪያችን የአውስትራሊያ ዜጋ ስለመሆን በአውስትራሊያ

1. በአንዛክ ቀን/Anzac Day ምን እናስታውሳለን?

ሀ. የአውስትራሊያና ኒውዚላንድ የጦር ሰራዊት በጋሊፓኦሊ/Gallipoli መሬት ላይ መድረሱን

ለ. ከብሪቲሽ ነጻ የሆኑ የመጀመሪያ ሰፋሪዎች የደረሱበት

ሐ. በስይድነይ የባህር ወሽመጥ የመጀመሪያው ጦር መርከብ ያረፈበት

2. የአውስትራሊያ አቦርጂናል ባንዴራ ቀለሞች ምንድ ናቸው?

ሀ. ጥቁር፣ ቀይና ብጫ

ለ. አረንጓዴ፣ ነጭና ጥቁር

ሐ. ስማያዊ ነጭና አረንጓዴ

3. በየትኛው ህጋዊ የሆነ ምልክት ነው፣ አውስትራሊያ የኮመንዌልዝ ንብረት ስለመሆኗ የሚያሳየው?

ሀ. የብሄራዊ መዝሙር

ለ. የአውስትራሊያ ብሄራዊ አበባ

ሐ. የኮመንዌልዝ ጋሻ ባለ አርማ

አውስትራሊያና ህዝቦቿ

የአውስትራሊያ ዲሞክራሲያዊ እምነቶች፣ መብቶችና ነጻነት

4. ስለ አውስትራሊያ መንግሥት አሰራር ከነዚህ ጽሁፎች ውስጥ የትኛው ነው ትክክል?

ሀ. የአውስትራሊያን ፓርሊያመንት ለማቋቋም ሰዎች በአውስትራሊያ ንግሥት በኩል ይመረጣሉ

ለ. መንግሥት በህዝብ የተመረጠ ነው

ሐ. የፓሪያመንት አባሎቻችን በጠቅላይ ሚኒስቴሩ በኩል ይመርወጣሉ

5. ስለ መናገር መብት ምሳሌ ከነዚህ ውስጥ የትኛው ነው?

ሀ. ጋዜጦች ስለ ማንኛውም አርእስት መጻፍ ይችላሉ

ለ. በፍርድ ቤት ህግ ሴቶችና ወንዶች እኩል ይስተናገዳሉ

ሐ. አውስትራሊያኖች ሃይማኖት ላለመከተል ነጻ ናቸው

6. ከነዚህ ጽሁፎች ውስጥ ስለ አውስትራሊያ መንግሥት የትኛው ነው ትክክል?

ሀ. ለአንዳንድ ሃይማኖቶች መንግሥት አይፈቅድም

ለ. በአውስትራሊያ ውስጥ ያለ መንግሥት አለማዊ ነው

ሐ. የሃይማኖት ህጎች በፓርላማ ይተላለፋል

7. በአውስትራሊያ ውስጥ የእኩልነት ምሳሌ ከነዚህ ጽሁፎች ውስጥ የትኛው ነው ትክክል?

ሀ. ሁሉም ተመሳሳይ ሃይማኖት ይከታተላል

ለ. ወንዶችና ሴቶች እኩል መብት አላቸው

ሐ. እያንዳንዱ ከአንድ ዓይነት ፖለቲካ ፓርቲ መሆን

8. እድሜው 18 ዓመትና ከዚያ በላይ ለሆነ የአውስትራሊያ ዜጎች ሃላፊነት ከነዚህ ውስጥ የትኛው ነው?

ሀ. በአካባቢ ምክር ቤት ስብሰባዎች ላይ ለመገኘት

ለ. በምርጫዎች ላይ ድስምጽ ለመስጠት

ሐ. ወቅታዊ የሆነ ፓስፖርት ለመያዝ

9. እድሜው 18 ዓመትና ከዚያ በላይ ለሆነ የአውስትራሊያ ዜጎች ሃላፊነት ከነዚህ ውስጥ የትኛው ነው?

ሀ. በአካባቢ ማህበረሰብ ለማገልገል

ለ. በማንኛውም ጊዜ ፓስፖርት ለመያዝ

ሐ. በህዝባዊ ዳኝነት ከተመረጡ ለማገልገል

ለፈተና መለማመጃ ጥያቄዎች

10. ከነዚህ ጽሁፎች ውስጥ ስለፓስፖርት ትክክለኛ የትኛው ነው?

ሀ. የአውስትራሊያ ዜጎች ፓስፖርት ለማግኘት ማመልከት ይችላሉ

ለ. ቋሚ ነዋሪዎች የአውስትራሊያን ፓስፖርት መያዝ ይችላሉ

ሐ. የአውስትራሊያ ዜጎች ወደ አውስትራሊያ ለመመለስ ፓስፓርትና ቪዛ ያስፈልጋል

Page 38: Australian citizenship test book - Ahmaric...4 የአውትራሊያ ዜግነት: የጋራ መተሳሰሪያችን የአውስትራሊያ ዜጋ ስለመሆን በአውስትራሊያ

በፈተና ጥያቄዎች ላይ ልምምድ ማድረግ 35

16. ከነዚህ ውስጥ የትኛው ነው የጠቅላይ ገዥ ሥራ ድርሻ?

ሀ. የመስተዳድር ግዛት ጠቅላይ ሚኒስቴር መምረጥ

ለ. በአውስትራሊያ ፓሪያመንት ያለፈን ህግ ማሻሻያ ጥያቄ ላይ መፈረም

ሐ. የመስተዳድር ግዛት መሪን መምረጥ

17. ከነዚህ ጽሁፎች ውስጥ ስለ መስተዳድር መንግሥታት ትክክለኛ የትኛው ነው?

ሀ. ሁሉም ግዛቶች ተመሳሳይ ህገ መንግሥት አላቸው

ለ. እያንዳንዱ ግዛት የራሱ የሆነ ህገ መንግሥት አለው

ሐ. የመስተዳድር ግዛቶች ህገ መንግሥት የላቸውም

18. በተወካዮች ስውረ መንግሥት ውስጥ በሚደረግ ምርጫ በቁጥር የአባላት ብዛት ሁለተኛ የሆነው ፓርቲ ወይም የቅንጅት ፓርቲዎች ስም ማን ይባላል?

ሀ. መንግሥት

ለ. ተቃዋሚ

ሐ. ህግ መወሰኛ ምክር ቤት

19. በፓርላማ ውስጥ ህግ ለማውጣት የቀረበ ጥያቄ ስም ማን ይባላል?

ሀ. የንጉሳዊ ንብረት

ለ. የህግ ማሻሻያ ጥያቄ

ሐ. ክርክር

20. በአውስትራሊያ ሰላም እንዲኖርና ስነ-ስርዓት የሚያስይዝ ማን ነው?

ሀ. ህዝባዊ አገልግሎቶች

ለ. ፖሊስ

ሐ. ዳኞች

11. ከነዚህ ጽሁፎች ውስጥ ስለ አውስትራሊያ የምርጫ ድምጽ አሰጣጥ ትክክለኛ የትኛው ነው?

ሀ. ሰዎች በምርጫ ድምጽ አሰጣጥ ላይ የፈለጉትን ተወዳዳሪ የመምረጥ ነጻነት አላቸው

ለ. የድምጽ ምርጫ እጅን በማውጣት ነው

ሐ. ሰዎች በድምጽ መስጫ ወረቀቱ ላይ ስማቸውን መጻፍ አለባቸው

12. ጥር/ January 1 ቀን 1901 ዓ.ም በአውስትራሊያ ውስጥ ምን ተደረገ?

ሀ. የአውስትራሊያ ህገ መንግሥት በህዝባዊ ምርጫ ረፈረንዱም በኩል ተቀየረ

ለ. የአውስትራሊያ ህገ መንግሥት ተግባራዊ ሆነ

ሐ. የአውስትራሊያና ኒውዚላንድ ጦር ሰራዊት ተመሰረተ

13. የአውስትራሊያ መንግሥትን ለማስተዳደር የወጣው ህጋዊ ስነድ ስም ምን ይባላል?

ሀ. የአውስትራሊያ ፈደሬሽን

ለ. የአውስትራሊያ ኮመንዌልዝ

ሐ. የአውስትራሊያ ህገ መንግሥት

14. ህዝባዊ ምርጫ/referendum ምንድ ነው?

ሀ. መንግሥትን ለመለወጥ ድምጽ መስጠት

ለ. የአውስትራሊያን ህገ መንግሥት ለመቀየር ድምጽ መስጠት

ሐ. ጠቅላይ ሚኒስተሩን ለመቀየር ድምጽ መስጠት

15. ህጎችን ለመተርጎምና ተግባራዊ ማድረግ የሚችለው የትኛው የመንግሥት አካል ነው?

ሀ. የህግ አውጪ

ለ. ውሳኔ ሰጭ አካል

ሐ. የፍትህ ሰጭ አካል

በአውስትራሊያ ውስጥ መንግሥትና ህጉ

በፈተና ጥያቄዎች ላይ ልምምድ ማድረግ 35

1ሀ, 2ሀ, 3ሐ, 4ለ, 5ሀ, 6ለ, 7ለ, 8ለ, 9ሐ, 10ሀ, 11ሀ, 12ለ, 13c, 14b, 15c, 16ለ, 17ለ, 18ለ, 19ለ, 20ለ

መልሶች:

Page 39: Australian citizenship test book - Ahmaric...4 የአውትራሊያ ዜግነት: የጋራ መተሳሰሪያችን የአውስትራሊያ ዜጋ ስለመሆን በአውስትራሊያ
Page 40: Australian citizenship test book - Ahmaric...4 የአውትራሊያ ዜግነት: የጋራ መተሳሰሪያችን የአውስትራሊያ ዜጋ ስለመሆን በአውስትራሊያ

መፈተን ያለበት ክፍል አለቀ