mcps grade k curriculum in amharic

16
የወላጆች መመርያ ለሙአለህፃናትስርአተ ትምህርት 2.0 ለወደፊቱ መማር Amharic MCPS

Upload: nazret

Post on 11-Mar-2016

267 views

Category:

Documents


18 download

DESCRIPTION

Montgomery County, Maryland Public Schools Grade K Curriculum in Amharic

TRANSCRIPT

Page 1: MCPS Grade K Curriculum in Amharic

የወላጆች መመርያ ለሙአለህፃናትስርአተ ትምህርት 2.0

ለወደፊቱ መማር

Amharic

MCPS

Page 2: MCPS Grade K Curriculum in Amharic

የትምህርት ቦርድMr. Christopher S. Barclay (ሚ/ር ክሪስቶፈር ኤስ ባርክሌይ)ፕሬዚደንት

Mr. Philip Kauffman (ሚ/ር ፊሊፕ ካውፍማን)ም/ፕረዚደንት

Ms. Shirley Brandman (ወ/ት ሺርልይ ብራንድማን)

Dr. Judith R. Docca (ዶ/ር ጁዲት አር ዶካ)

Mr. Michael A. Durso (ሚ/ር ማይክል ኤ ዱርሶ)

Mrs. Patricia B. O’Neill (ወ/ሮ ፓትሪሻ ቢ ኦኔይል)

Mrs. Rebecca Smondrowski (ወ/ሮ ሬቤካ ስሞንድሮውስኪ)

Mr. Justin C. Kim (ሚ/ር ጀስቲን ሲ ኪም) ተማሪ አባል

የትምህርት ቤት አስተዳደርDr. Joshua P. Starr (ዶ/ር ጆሹዋ ፒ ስታር)የትም/ቤቶች የበላይ ተቆጣጣሪ

Mr. Larry A. Bowers (ሚ/ር ላሪ ኤ ባወርስ)Chief Operating Officer (ዋና ስራ አስኪያጅ)

Dr. Beth Schiavino-Narvaez (ዶ/ር ቤት ስኪያቪኖ-ናርቫኤዝ)የትም/ቤት ድጋፍና መሻሻል ም/የበላይ ተቆጣጣሪ

Dr. Kimberly A. Statham (ዶ/ር ኪምበርሊ ኤ ስታታም)የማስተማር፣ የመማር፣ እና ፕሮግራሞች ም/የበላይ ተቆጣጣሪ

ራእይለአያንዳንዱና ለማንኛውም ተማሪ እጅግ የላቀውን ሕዝባዊ ትምህርት በማቅረብ ትምህርት እንዲሰርፅ እናደርጋለን።

ተልእኮእያንዳንዱ ተማሪ በኮሌጅም ሆነ በስራ ስኬታማ እንዲሆን አካዴሚያዊ፣ የችግር አፈታት ፈጠራ፣ እና የማህበራዊ ስሜት ችሎታዎች ይኖሩታል።

የአላማ ፍሬ ነገርሁሉም ተማሪዎች በወደፊት ኑሮአቸው እንዲለሙ/እንዲበለፅጉ ማዘጋጀት

አይነተኛ እሴቶችመማር ግንኙነቶች ማክበር ብቃት ፍትህ

Page 3: MCPS Grade K Curriculum in Amharic

MCPS CURRICULUM (ስርአተ ትምህርት) 2.0 3

ስርአተ ትምህርት 2.0 ሙሉ ልጅን ለማሳተፍ ትምህርትን ከንባብና

ከሂሳብ ባሻገር ያሰፋዋል። በአሌሜንታሪ ደረጃ አስር የርዕስ መስኮች -ኪነጥበብ፣ የጤና ትምህርት፣ የመረጃ

መሰረተ ትምህርት፣ ሂሳብ፣ ሙዚቃ፣ የአካል ማጠንከርያ ትምህርት፣ ንባብ፣ ሳይንስ፣ ማህበራዊ ጥናቶች፣

እና ፅሁፍ- ተማሪዎች ለእድሜ ልክ ትምህርት በሚያስፈልጓቸው በሂሳዊና በፈጠራ አስተሳሰብ እንዲሁም

በአካዴሚያዊ ስኬት ችሎታዎች አካባቢ እንደገና እንዲያተኩሩ ተደርጓል። ስርአተ ትምህርት 2.0 አራት ዋና ዋና

ገፅታዎች እሉት፤

እዲስ በአለምአቀፍ ደረጃ የተመሩ መመዘኛዎች በሂሳብ፣ በምንባብ፣ እና በፅሁፍ፡- ሂሳብ፣

ምንባብ፣ እና ፅሁፍ የተመሰረቱት Common Core State Standards (CCSS) ተብለው

በታወቁ አዲስ የተጠናከሩ መመዘኛዎች ነው። እነዚህ መመዘኛዎች በሜሪላንድ በጁን 2010

ተቀባይነት ያገኙ ሲሆን ተማሪዎች በየክፍሉ ደረጃ መማር ያለባቸውን ይዘት የሚገልፁና የዩ-ኤስ

ተማሪዎችም ከአለም ዙርያ ተማሪዎች ጋር በአወንታዊ እንዲወዳደሩ የተተለሙ ናቸው።

ልጅን በሞላ ለማስተማር ተሃድሶ ያገኘ ትኩረት፡- ስርአተ ትምህርቱ ከሂሳብ፣ ንባብ፣

እና ፅሁፍ ጋር በማዋሃድ እንደ ኪነጥበብ፣ የመረጃ መሰረተ ትምህርት፣ የአካል ማጠንከርያ

ትምህርት፣ ሳይንስ፣ እና ማህበራዊ ጥናቶችን የመሰሉ ርእሶች ላይ ተጨማሪ የትምህርት ትኩረት

ያቀርባል። ተማሪዎች በኤሌሜንታሪ ትም/ቤት በሁሉም የትምህርት አይነቶች ትምህርት ይሰጣሉ።

የተዋሃደ አስተሳሰብ፣ አገላላፅ፣ እና ፈጠራ፡- የአስተሳሰብና የአካዴሚያዊ ስኬት ችሎታ

መዋሃድ - ወይም በትብብር ፕሮብሌሞችን ለመፍታት፣ በርካታ እይታዎችን ለመተርጎም፣

ውስብስብ መረጃዎችን ለመተንተን፣ በተለያዩ ሃሳቦች ግንኙነቶችን ለመገንዘብ የሚያስችሉትን

እነዚያን ሙያዎች ለተማሪው የፈጠራ አቅም ማበርከት - የስርአተ ትምህርት 2.0 ልዩና ብቸኛ

ገፅታ ነው። እነዚህ ሙያዎች/ችሎታዎች በ21ኛው ክፍለ-ዘመን በእውቀት በተመሰረተ አለምአቀፍ

ኤኮኖሚ ለመበልፀግ አስፈላጊ መሳርያዎች መሆናቸው በትምህርታዊ ምርምር ተለይተዋል።

የተማሪ ግስጋሴ በተሻሻለ "በመመዘኛዎች-የተመሰረተ" ሪፖርት ካርድ ማስተላለፍ፡- የኤሌሜንታሪ ትም/ቤት ረፖርት ካርድ በስርአተ

ትምህርት 2.0 በየማርክ መስጫ ወቅት ከሚሰጡት ፅንሰሃሳቦችና ርእሶች ጋር የሚጣጣም ነው። የየሩብ አመቱ ሪፖርት ካርድ ተማሪዎች በክፍል

ደረጃ ከሚጠበቀው እንፃር በምን ሁኔታ የአካዴሚ መመዘኛዎችን እንዳለፏቸው ለተማሪዎችና ለወላጆች ምላሽ መረጃ ይሰጣል።

ስርአተ ትምርት 2.0 ተማሪዎችን በተሻለ ሁኔታ በመጥመድ በትም/ቤትና ከዚያም ባሻገር የሚያስፈልጓቸውን ሙያዎች እንዲያዳብሩ

ያግዛቸዋል።

እኛ ተማሪዎቻችንን ለወደፊታቸው

ማዘጋጀት ያስፈልገናል፤

እኛ ላሳለፍነው አይደለም።

Ian Jukes (አያን ጁክስ)Educator and

Futurist (አስተማሪና ትንቢታዊ)

Page 4: MCPS Grade K Curriculum in Amharic

4 ስርአተ ትምህርት 2.0 ሙአለህፃናት

ማሰብ/አስተሳሰብና የአካዴሚያዊ ስኬት ችሎታዎች

በአካዴሚ፣ በማህበራዊ ተዋስኦ፣ እና በስሜት የሚበለፅጉ ተማሪዎች ከተራ እውነታዎች በላይ ያውቃሉ። ለመማርና

ከሞላ ጎደል በማንኛውም አካባቢ ስኬታማ ለመሆን የሚያስችሏቸው የተወሰኑ ችሎታዎች አሏቸው። እነዚህም ሂሳዊ

አስተሳሰብ፣ የፈጠራ አስተሳሰብ፣ እና የአካዴሚያዊ ስኬት ችሎታዎችን ያካትታሉ። በስተቀኝ የሚገኘው ሰንጠረዥ

ተማሪዎች በኤሌሜንታሪ ትም/ቤት በሚገሰግሱበት ወቅት በስርአተ ትምህርት 2.0 በሞላ ተዋህደው የሚገኙትን

የአስተሳሰብና የአክዴሚያዊ ስኬት ችሎታዎችን ይገልፃል።

Page 5: MCPS Grade K Curriculum in Amharic

MCPS CURRICULUM (ስርአተ ትምህርት) 2.0 5

የፈጠራ አስተሳሰብ ችሎታዎች

የፈጠራ አስተሳሰብ እውነታዎችን፣

ፅንሰሃሳቦችን፣ እና መርሆዎችን እብሮ

ማስቀመጥና በነገሮች አስተያየትና

አተገባበር አዲስ መንገድ ማሳየትን

ያካትታል።

ማብራርያ

• በአፃፃፍዎ፣ አነጋገርዎ፣ እና በኪነጥበብ ስራዎ የመግለጫ ዝርዝሮች ማካተት

• አንድን ነገር ልክ እንደሆነ አድርጎ መግለፅ ጊዜ ይወስዳል

• አስተሳሰብዎን ይግለፁ

• ግትር ያለመሆን

• የሌሎችን ሃሳቦችና ግንዛቤዎች ማመዛዘን

• የተሰጠዎትን መልስ መጠየቅ/ማረጋገጥ

• "ለምን" የሚሉ ጥያቄዎችን ማቅረብ

• በማስረጃና በአዳዲስ ሃሳቦች መሰረት አስተሳሰብዎን መለወጥ

የቋንቋ ቅልጥፍና

• በርካታ አዳዲስ ሃሳቦችን ማፍለቅ

• ሃሳቦችዎን ወይም አመለካከቶችዎን በፅሁፍ፡ በስእል፡ በንግግር ወይም በድርጊት መግለፅ

• አንዱን ነገር በተለያዩ መንገዶች ማሳየት

• አንድን ጥያቄ በተለያዩ መንገዶች መመለስን ማወቅ

የወጥ ፈጠራ ችሎታ

• አዳዲስ ሃሳቦችና ምርቶች መፍጠር

• መልሶችዎን ባዳዲስና በፈጠራ መንገዶች መግለፅ

• የሌሎችን ሃሳቦችና ምርቶች ወደ አዲስ ነገር መለወጥ

• አንድን ነገር ባዲስ መንገድ ለመፍታት ፕሮብሌሞችን እንደ እድል ማየት/መቁጠር

አካዴሚያዊ ስኬት ችሎታዎች

አካዴሚያዊ ስኬት ተማሪዎች

በአካዴሚያዊ አካባቢ በሙሉ ሃይላቸው

ለመገስገስ ተገቢ አቋምና ስነ ምግበር

መጨበጣቸውን ያካትታል።

ትብብር

• የሌሎችን ሃሳቦች ማክበር

• ሌሎች ሰዎችን ምን እንደሚያስቡ መጠየቅ

• ግብን ለመምታት ወይም ስራን ለመፈፀም ከሌሎች ጋር አብሮ መስራት

• ቡድንን እንዴት መምራትና የቡድን አባል መሆንን ማወቅ

ጥረት/ተነሳሽነት/ብርታት

• አስቸጋሪ ስራዎችን ለማከናወን ራስን መፈታተን

• ሁኔታዎች ሲከብዱ ግብን ለመምታት ስለ ተጨማሪ መንገዶች ማሰብ

• ምን ጊዜም እጅን አለመስጠት። መማር ሲያስቸግር እርዳታ መጠየቅ

የአስተሳሰብ ድፍረት/አደጋዎችን መጋፈጥ

• እንዲገባዎ ለመታገዝ ጥያቄዎችን ማቅረብ - በየዕለቱ

• በቡድን ውስጥ ሆነው የሚያስቡትን ማጋራት

• ሃሳብዎን ማጋራትና ለጥያቄዎች መልስ መስጠት፣ እርግጠኛ ባይሆኑም እንኳ

• ወደሚቀጥለው ደረጃ ለመውጣት ራስን መፈታተን

ስለራስ አስተሳሰብ (Metacognition) -

ስለማሰብ ማሰብ

• ተጨማሪ ከመማርዎ በፊት ስለርእሱ ቀድሞውኑ ምን እንደሚያውቁ ማሰብ

• በምን አይነት ሁኔታ ይበልጥ መማር እንደሚችሉ ማስተዋልና በሚታገሉበት/በሚቸገሩበት ወቅት እርዳታ መጠየቅ

• አስተሳሰብዎን መግለፅ

የሂሳዊ አስተሳሰብ ችሎታዎች

ሂሳዊ አስተሳሰብ በማስረጃና በጠራ

አስተሳሰብ በመመስረት፣ ምን ማድረግ

ወይም ምን ማመን እንዳልብህ

በምታስብበት ወቅት፣ ከስሜት ነፃና ባለ

ክፍት አእምሮ መሆንን ያካትታል።

ትንተና

• ምን እንደሚመሳሰልና ምን እንደሚለያይ ማስተዋል

• ምንና ምን ክፍሎች/አካሎች ሙሉውን እንደሚገነቡ መግለፅ

• ቅጦችን መፈለግ

• ነገሮች እንዴት በአንድ ላይ እንደሚገጣጠሙ ማየት/መገንዘብ

• ነገሮችን በያይነቸው/በየጠባያቸው መለያየት

ግምገማ

• እውነታዎችንና አባባሎችን መጠየቅ/መጠርጠር፡ የራስንም ጭምር

• ማስረጃ መጠየቅ

• የምትመለከተውን ወይም የምታነበውን መረጃ እስተማማኝነቱን ማረጋገጥ

• ሁለት የመረጃ ምንጮች ሲጋጩ ምን ማድረግ እንዳለብህ/ሽ ማወቅ

• በመስፈርት መሰረት አማራጮችን ቅደምተከተል መስጠት

ገንቢ ትንተና

• ነገሮችን ከበተኑ በኋላ እንደገና መገጣጠም

• እንዴት አዲስ ሃሳቦች ከሌሎች ሃሳቦች እንደሚመጡ ማየት/መገንዘብ

• ከነበሩህ/ሽ ክፍሎች አዲስ ነገር መስራት

• ሃሳብዎን ማደራጀት

Page 6: MCPS Grade K Curriculum in Amharic
Page 7: MCPS Grade K Curriculum in Amharic

MCPS CURRICULUM (ስርአተ ትምህርት) 2.0 7

በስርአተ ትምህርት 2.0፣ ሙአለህፃናት፣ ለያንዳንዱ ማርክ መስጫ ወቅት የተወሰነ ሂሳዊና የፈጠራ

አስተሳሰብ እና የአካዴሚያዊ ስኬት ችሎታዎች ተለይተዋል። እነዚህ ሙያዎች በአስሮቹ የይዘት መስኮች

ፅንሀሳቦችና ርእሶች አማካይነት ትምሀርት የሚሰጥባቸው ናቸው እናም ርእሶቹ ባጠቃላይ ለመወሀሀድ

ትኩረት ያቀርባሉ።

ኪነጥበብ የሰዉነት ማጠንከርያ ትምህርት

አጠቃላይ ሙዚቃ ንባብ/የቋንቋ ስነጥበባት

የጤና ትምህርት ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ ፣ እና ምህንድስና

የመረጃ መሰረተ ትምህርት የህብረተሰብ ሳይንስ

የሂሳብ ትምህርት ፅሁፍ

የሚከተሉት ገፆች በያንዳንዱ የማርክ መስጫ ወቅት ለሙአለህፃናት ተማሪዎች የትምሀርት ትኩረት

የተጣለባቸው ሂሳዊ አስተሳሰብ፣ የፈጠራ አስተሳሰብ፣ እና የአካዴሚያዊ ስኬት ችሎታዎች ከስርአተ

ትምህርቱ ፅንሰሀሳቦችና ርእሶች ዋና ዋናዎቹ ላይ ቅንጭብ ማብራርያ ይሰጥባቸዋል።

ስርአተ ትምህርት 2.0 የተገነባው ወደ ኮሌጅና ለ21ኛው ክፍለ ዘመን ለስራ

ዝግጁነት በሚያመሩት የተማሪን ሂሳዊና የፈጠራ አስተሳሰብ፣ እንዲሁም

መሰረታዊ የአካዴሚያዊ ስኬት ችሎታዎች በማዳበር ዙርያ ነው።

“ ለፈጠራ ማስተማር አላማው በራስ መተማመን፡ የህሊና ነጻነትና ለራስ የማሰብን አቅም ማበረታታት ነው።”

Sir Ken Robinson (ሰር ኬን ሮቢንሰን)፣ Out of Our Minds: Learning to be

Creative (ከአእምሮአችን ውጭ ፡ ፈጣሪ ለመሆን መማር)

Page 8: MCPS Grade K Curriculum in Amharic

8 ስርአተ ትምህርት 2.0 ሙአለህፃናት

ማርክ መስጫ ወቅት 1 MARKING PERIOD 1

ትንተና (የሂሳዊ አስተሳሰብ ችሎታዎች)—እንድን ሙሉን ነገር ወደ

ክፍሎች ወዲያውኑ ግልፅ እንዳይሆኑ አድርጎ መሰባበር እና የሙሉውን መዋቅር

ለመገንዘብ እንዲቻል ክፍሎቹን ማመዛዘን።

• መለያ ባህርያትን መለየትና መግለፅ።

• ተመሳሳይነቶችንና ልዩነቶችን በመለየት ማመዛዘን።

• መመደብ እና መከፋፈል ወደ ፈርጆች።

• መለየት እና መግለፅ ቅጦችን እና በቅጦች መካከል ያሉ ግንኙነቶችን።

ትብብር (የአካዴሚያዊ ስኬት ችሎታ) - የቡድን ግብ ለመምታት

በውጤታማነትና በመከባበር መስራት።

• ማሳየት ንቁ ሰሚና ተግባቢ መሆን ከቡድን አባላት ባለ ግንኙነት።

• መጠየቅ እና በርካታና የተለያዩ አስተያየቶችን ማክበር መግባባትን ለማስፋትና

ጥልቀት ለመስጠት።

• ማሳየት የቡድን ስራ ከሌሎች ጋር በምርታማነት በመስራት።

ማህበራዊ ጥናቶች• Civics (የዜግነት ጥናቶች): የመማርያ ክፍል እለታዊ ስራዎችና ፕሮግራሞች፤ የደንቦች

አስፈላጊነት፤ መብቶችና ሀላፊነቶች በትም/ቤትና በቤት፤ የታወቁ የዩናይትድ ስቴትስ

ምልክቶችና ልምዶች፤ የሰዎች አስተዋፅኦዎች ለዩናይትድ ስቴትስ።

ሳይንስ ቴክኖሎጂ፣ እና ኤንጂኔሪንግ• መሬት ህዋ ሳይንሶች፣- ያየር ጠባይ – ትዝብቶች፣ ባህርያት፣ ቅጦች፣ የወራት

ለውጦች።

• የህይወት ሳይንሶች፡- የአትክልትና የእንስሳ ህይወት ኡደቶች፤ የውጭ ገፅታዎች፤

ስብጥርነት፤ ለመትረፍ/ለመኖር ለውጦች።

በቀይ የተመለከቱ ፅንሰሃሳቦች በሪፖርት ካርድ ማርክ የተስጠባቸው ለማርክ መስጫ ወቅት 1 ነው።

የአካል ማጠንከርያ ትምህርት• ጤና-አበልፃጊ አካላዊ ብቃትና እንቅስቃሴ፡- የካላዊ ልምምድ ውጤቶች (ልብ)።

• የመንቀሳቀስ ችሎታዎችና ፅንሰ ሀሳቦች፡- የመንቀሳቀስ ችሎታዎች (መራመድ፣ መሮጥ፣

ጡብ ጡብ ማለት፣ መዝለል፣ መጋለብ)።

ስርአተ ትምህርቱ ከሂሳብ፣ ንባብ፣ እና ፅሁፍ ጋር በማቃመም እንደ ስነጥበባት፣ የመረጃ መሰረታዊ ትምህርት፣ የአካል ማጠንከርያ ትምህርት፣ ሳይንስ፣ እና ማህበራዊ ጥናቶች በመሳሰሉት ርእሶች ተጨማሪ የትምህርት ትኩረት ያቀርባል።

ንባብ/የቋንቋ ስነጥበባት• መሰረታዊ ችሎታዎች የህትመት ገፅታዎች መገንዘብን ማሳየት፣ ከፍተኛና ዝቅተኛ

ፊደሎች፣ የተነገሩ ቃላት፣ የቃላት ክፍሎች (syllables)፣ የፊደልና የድምፅ

ዝምድናዎች፤ የክፍል ደረጃ ስነ-ድምፆችን (phonics) ማወቅና ተግባራዊ ማድረግ።

• የፅሁፍ ንባብና ግንዛቤ፡- ግጥም፣ ልቦለድ፣ የአበው ተረቶች፣ እና የመረጃ ፅሁፍ፤

ከአላማና ከግንዛቤ ጋር ማንበብ፤ ከአስነሽና ከድጋፍ ጋር—ተወናውያንን፣ አካባቢ/

አቀማመጥን፣ ዋና ክውነቶችን እና የመፅሀፍን ገፅታዎች መለየት፤ በፅሁፍ ውስጥ

ስላልታወቁ ቃላት ጥያቄዎችን ማቅረብና መመለስ፤ በቡድን የንባብ እንቅስቃሴዎች

መሳተፍ፣ በስእሎችና በፅሁፍ ያለ ዝምድና መግለፅ።

Page 9: MCPS Grade K Curriculum in Amharic

MCPS CURRICULUM (ስርአተ ትምህርት) 2.0 9

ትንተናና ትብብር

ፅሁፍ• የሃሳቦችና የአመለካከት አገላለፅ (Expression)፡- የትረካ ፅሁፎችን ለመድረስ ስእል፣

የቃል መልእክት፣ እና ፅሁፍ መጠቀም።

• ሂደቶች፡- ከአመራር ጋር—ፅሁፍን ለማጠናከርና ዝርዝሮች ለመጨመር ለጥያቄዎች

መመለስና አስተያየት መስጠት፤ ለጥያቄዎች ለመመለስ ተሞክሮዎችን ማስታወስ

ወይም መረጃ መስብሰብ፤ ለፅሁፍ ዝርዝር ለመስጠት ስእሎችን ወይም እይታዎችን

መጨመር።

ቋንቋ• የፅሁፍ ቋንቋ እድቦች፡- ከፍተኛና ዝቅተኛ ፈደሎች፤ ስሞችና ግሶች፤ የብዙ ስሞች፤

መስተዋድዶች፤ በጋርዮሽ ቋንቋ እቅስቃሴዎች አረፍተነገሮችን ማራዘም፤ የአረፍተነገር

መጀምርያ ቃል ካፒታላይዝ ማድረግ፤ ስርአተምልክት መጨረስ፤ ኮንሶናንትና ቫወል

ድምፆችን መፃፍ፤ ቀላል ቃላትን በስነድምፅ (phonetically) ስፔል ማድረግ።

ሂሳብ• ጂዮሜትሪ፡- አቅጣጫዊና የቦታ አቀማመጥ ቃላት።

• አለካክና አሀዞች፡- የአሀዞች አሰባሰብ—አሞሌ ሰንጠረዥ (bar graphs)፣ ስእላዊ

ሰንጠረዥ (pictographs)፤ ባህርያት—መመደብ፣ የመመደብ ህጎች ማብራራት።

• መቁጠርና የቁጥሮች ይዘት/ጠባይ፡- መቁጠርና ቁጥሮች።

ስነጥበብ• ስነጥበብ መፍጠር/የስነጥበብ ምላሽ፡- መስመር—አቅጣጫ፣ መንቀሳቀስ፤ ቅርፅ—

መለየት፣ ጠባዮች፤ ቀለም—መለየት፣ ተቀዳሚ፣ ተከታይ፣ ማደባለቅ።

አጠቃላይ ሙዚቃ• ሙዚቃ መጫወት/ማቅረብ፡- የረጋ ምትን መመርመር።

• ለሙዚቃ ምላሽ፡- ለተለያየ ሜትሮች በመንቀሳቀስ ምላሽ መስጠት፤ የተለያዩ የቃልና

የመሳርያ ቃና ቀለሞችን ማሳየት/ማቅረብ።

• የሙዚቃ ንባብ፡- ከፍተኛና ዝቅተኛ፣ ረጅምና አጭር አዶዎችን (icons) ማንበብ።

የጤና ትምህርት • ስሜቶች።

• የግል እንክብካቤ።

• መንገድና የእግረኛ ደህንነት።

• መገናኛ

• ህመምና በሽታ መከላከል።

• ላስቸኳይ ሁኔታ ምላሽ።

የመረጃ መሰረተ ትምህርት• ሂደቶችና ደንቦችን መበደር።

• የመፅሀፍ ምርጫና ጥንቃቄ።

• የቤተ መፃህፍት ሚድያ ማእከል ድርጅት።

• የታሪክ ንጥረነገሮች።

• ስልቶችን መጠየቅ/መመርመር።

Page 10: MCPS Grade K Curriculum in Amharic

10 ስርአተ ትምህርት 2.0 ሙአለህፃናት

ማርክ መስጫ ወቅት 2 MARKING PERIOD 2

የቋንቋ ቅልጥፍና (የፈጠራ አስተሳሰብ ችሎታ)—

ለአንድ ፕሮብሌም ወይም አንድ ሀሳብ በርካታ መልሶች ማፍለቅ።• በርካታ ሀሳቦችማፍለቅ።

• በተለያዩ መንገዶች ሀሳቦችን ወይም መፍትሄዎችን መወከልና መግለፅ።

አእምሯዊ ድፍረት (የአካዴምያዊ ስኬት

ችሎታ)—አጠራጣሪነት መቀበል ወይም ግብን ለመምታት ደምብን/እዱብን

መፈታተን።

• መለወጥ እና ማስተካከያዎች ማድረግ መፍትሄዎችን ሲፈልጉ መፈታተንን

ለመቀበል።

• ሃሳቦችን በመጋራት፣ ጥያቄዎችን በማቅረብ፣ ወይም አዳዲስ ተግባራት በመሞከር

አጠራጣሪ ሁኔታዎችን የመቀበል ፈቃደኛነት ማሳየት።

ማህበራዊ ጥናቶች• ጂዮግራፊ፡- የመሬትን ገፅ ለመግለፅ ጥቅም ላይ የዋሉ መሳርያዎች (ስእሎች፣

ካርታዎች፣ እና ሉሎች)፤ የመሬትን ገፅ ለመግለፅ ጥቅም ላይ የዋሉ ሰው ሰራሽና

የተፈጥሮ አካላዊ ዝርዝሮች፤ ሰዎች ይለወጡ እና አካባቢውን መስለው ይኖራሉ።

ሳይንስ ቴክኖሎጂ፣ እና ኤንጂኔሪንግ• የህይወት ሳይንሶች፡- የአትክልትና እንስሳት መሰረታዊ ፍላጎቶች፤ የአትክልቶችና

እንስሳት የህይወት ኡደቶች፤ በተወላጆችና በወላጆች መካከል ያለ ንፅፅር።

በሰማያዊ የተመለከቱ ፅንሰሃሳቦች በሪፖርት ካርድ ማርክ የተደረገባቸው በማርክ ማድረጊያ ወቅት 2 ነው።

ንባብ/የቋንቋ ስነጥበባት• መሰረታዊ ሙያዎች፡- የህትመት ገፅታዎች፣ ከፍተኛና ዝቅተኛ ፊደሎች፣ የተነገሩ

ቃላት፣ የቃላት አካሎች (syllables)፣ የከፍተኛና የዝቅተኛ ፊደሎች፣ የፊደልና የድምፅ

ዝምድናዎች ግንዛቤ ማሳየት፤ የክፍል ደረጃ ስነድምጾች (phonics) ማወቅና ተግባራዊ

ማድረግ።

• የፅሁፍ ንባብና ግንዛቤ፡- ግጥም፣ ልቦለድ፣ የአበው ተረቶች፣ እና የመረጃ ፅሁፍ፤

Junior Great Books፤ ከአላማና ግንዛቤ ጋር ማንበብ፤ ከአነሳሽና ድጋፍ ጋር—ስለ

ቁልፍ ዝርዝሮችና ያልታወቁ ቃላት መጠየቅና ለጥያቄዎች መመለስ፤ በስእሎችና

ከታሪኩ ወይም ከፅሁፉ ጋር ያለውን ግንኙነት መግለፅ፤ በቡድን የንባብ እንቅስቃሴዎች

መሳተፍ።

ፅሁፍ• የሀሳቦችና የአመልካከቶች መግለጫ (Expression)፡- የትረካ ፅሁፎችን ለመድረስ

በስእል፣ የቃል መልእክት፣ እና ፅሁፍ መጠቀም።

• ሂደቶች፡- ከመመርያ ጋር—ዝርዝሮችን ለመጨመርና ፅሁፍን ለማጠናከር ለጥያቄዎችና

ለአስተያየቶች መልስ መስጠት፤ ለጥያቄዎች ለመመለስ ተሞክሮዎችን ማስታወስ ወይም

መረጃ መሰበሰብ፣ ለፅሁፍ ዝርዝር ለመስጠት ስእሎች ወይም አይታዎች መጨመር።

ቋንቋ• የፁሁፍ ቋንቋ እድቦች፡- ከፍተኛና ዝቅተኛ ፊደሎች፤ ስሞችና ግሶች፤ ቃላትን መጠየቅ፣

በተጋሩ ቋንቋዎች አረፍተነገሮችን ማራዘም፤ ስርአተ ምልክትን መጨረስ፤ የክንሶናንትና

የቫወል ድምፆችን መፃፍ፤ ቀላል ቃላትን በስነድምፅ (phonetically) ስፔል ማድረግ።

Page 11: MCPS Grade K Curriculum in Amharic

MCPS CURRICULUM (ስርአተ ትምህርት) 2.0 11

ያነጋገር ቀልጣፋነት እና አእምሯዊ ድፍረት

የአካል ማጠንከርያ ትምህርት• የመንቀሳቀስ ችሎታዎችና ፅንሰሀሳቦች፡- ከነገሮች ጋር ግንኙነቶች (በውስጥ/ውጭ፣

በዙርያ፣ በውሽጥ፣ ከታች/ከላይ፣ የበራ/የጠፋ፣ አቋራጭ፣ ቅርብ/ሩቅ፣ እና

ፊትለፊት/በስተጀርባ)፤ በራስ የተወረወሩ ነገሮችን በራስ አካባቢ መያዝ፤ ከስተበታች

መወርወር።

• ሙያዎች/ፅንሰሀሳቦች ከ MP1 ጤና-አበልፃጊ አካላዊ ብቃትና እንቅስቃሴ በሴመስተር

1 ሪፖርት ካርድ ተመዝግበዋል።

ሂሳብ• ግብረቶችና አልጄብራዊ አስተሳሰብ፡- በተለያዩ መንገዶች የቁጥሮች ለ10 መወከል/

መያያዝ።

• መቁጠርና ካርዲናሊቲ፡- የቁጥር ፅንሰሀሳብ—እስከ 20 ቁሶች መቁጠር፣ ቁጥሮች መፃፍ

(0-20)፣ እስከ 100 መቁጠር በ1ዶችና በ 10ሮች፤ ነገሮች ማወዳደር—ይበልጥ፣ ያነሰ

(በሚዛን ወይም በቁጥር)፣ ወይም እኩል።

ስነጥበብ• ስነጥበብ መፍጠር/ለስነ ጥበብ ምላሽ መስጠት የሚዳሰስ አንፃር የሚታይ ሽካራነት/

ለስላሳነት፤ የሁለትዮሽና የሶስትዮሽ ማእዘን ስነጥበብ፤ ቅጦችን መፍጠርና መለየት፤

በድርሰት ውስጥ የነገሮች ዝምድና።

አጠቃላይ ሙዚቃ• ሙዚቃ ማቅረብ/ማሰማት፡- የረጋ ምትን መመርመር።

• ለሙዚቃ ምላሽ መስጠት፡- ለተለያዩ ሜትሮች በእንቅስቃሴ ምላሽ መስጠት፤ የተለያዩ

የቃልና የመሳርያ ቃና ቀለሞች ማሳየት።

• የሙዚቃ ንባብ፡- ከፍተኛና ዝቅተኛ፣ ረጅምና አጭር አዶዎች (icons) ማንበብ።

የጤና ትምህርት • የምግብ መደቦች (የምግብ ይዞታ ጥቅም)።

• ስሜቶች።

• ምግብና የሀይል ምንጮች።

• የግል እንክብካቤ።

• መንገድና የእግረኛ ደህንነት።

የመረጃ መሰረተ ትምህርት• በቤተመፃህፍት መገልገያዎች መካከል ጠባዮችና ግንኙነቶች

• የአጠያየቅ (ምርመራ) ስልቶች በመረጃ ፍላጎት የተመሰረተ (ማን፣ ምን፣ የት፣ መቼ፣

ለምን፣እንዴት)።

• ለጥይቄዎች መልሶች ለማግኘትና ለመመዝገብ ስልቶች።

Page 12: MCPS Grade K Curriculum in Amharic

12 ስርአተ ትምህርት 2.0 ሙአለህፃናት

የማርክ መስጫ ወቅት 3 MARKING PERIOD 3

ገንቢ ትንተና (የሂሳዊ አስተሳሰብ ችሎታ)—ሙሉ ፅንሰሀሳብ

ግንዛቤ ለመገንባት ወይም አዲስ ወይም ሙሉ ለመቀረፅ አካሎችን አንድላይ

ማሰባሰብ።

• አዲስ ወይም ሙሉ ለመቀረፅ አካሎችን ማደራጀት።

ጥረት/ተነሳሺነት/ብርታት (የአካዴሚያዊ

ስኬት ችሎታ) - ግብን ለመምታት ወይም ፕሮብሌም ለመፍታት ተግቶ

መስራትና ውጤታማ ስልቶችን ተግባራዊ ማድረግ፤ በእንቅፋቶችና በተወዳዳሪ

ተፅእኖዎች ሳይበገሩ ወደፊት መግፋት።

• ግብ ለመምታት ወይም አንድ ፕሮብሌም ለመፍታት ስልቶች ማሳየት።

• ግብ ለመምታት ወይም አንድ ፕሮብሌም ለመፍታት የስልቶችን ውጤታማነት

በራስ መገምገምና የጥረቶችን አቅጣጫ እንደገና መቀየር።

ማህበራዊ ጥናቶች• ኤኮኖሚክስ፡ ምርጫ የሚደረግባቸው ሁኔታዎች፤ ሰራተኞችና የሚያከናውኗቸው

ተግባሮች፤ ሰዎች የሚሰሯቸውና የሚያሳድጓቸው ሸቀጦች፤ ሸቅጥ ማፍርያና

አገልግሎቶች ማቅረቢያ መገልገያዎች፤ የእጅና ሌሎች ባለሞተር መተግበርያና

መጫወቻ መሳርያዎች፤ ሸቀጦችና አገልግሎቶች ማግኛ መንገዶች።

ሳይንስ ቴክኖሎጂ፣ እና ኤንጂኔሪንግ• የህይወት ሳይንሶች፡- ለመትረፍና ለመኖር አገልግሎት ላይ የሚውሉ የአትክልቶችና

የእንስሶች የውጭ ገፅታዎች፤ የአካባቢ አትክልትና እንስሳትን መለየት፤ የእንስሳትን

እንደየአይነታቸው መመደብ፤ በተለያዩ አትክልቶች መካከል ማወዳደር፤ በተለያዩ

እንስሳት መካከል ማወዳደር፣ ሰዎችን ጨምሮ።

በአረንጓዴ የተመለከቱ ፅንሰሃሳቦች በሪፖርት ካርድ ማርክ የተሰጥባቸው ማርክ መስጫ ወቅት 3 ነው።

የአካል ማጠንከርያ ትምህርት• ጤና-አበልፃጊ አካላዊ ብቃትና እንቅስቃሴ፡- የጤና ብቃት የሚያራምዱ እንቅስቃሴዎች

(ጤናማና ጤናማ ያልሆኑ ምርጫዎች)።

• የመንቀሳቀስ ችሎታዎችና ፅንሰ ሀሳቦች፡- መሰረታዊ የመዝለልና የማረፍ ቅጦች (በሁለት

እግር ዘሎ ማረፍ)፤ የቁመ ሚዛን፤ የክብደት ሽግግር (እጆችና እግሮች)።

ንባብ/የቋንቋ ስነጥበባት• መሰረታዊ ሙያዎች፡- የህትመት ገፅታዎች መገንዘብ፣ ከፍተኛና ዝቅተኛ ፊደሎች፣

የተነገሩ ቃላት፣ የቃላት አካላት፣ የፊደል ድምፅ ዝምድናዎች፤ የክፍል ደረጃ ድምፆችን

አውቆ ተግባራዊ ማድረግ።

• ፅሁፍ ማንበብና መገንዘብ፡- ግጥም፣ ልቦለድ፣ ተረት ተረቶች፣ እና የመረጃ ፅሁፍ፤

Junior Great Books፤ ከአላማና ከግንዛቤ ጋር ማንበብ፤ ከአንሳሽና ከድጋፍ ጋር—

በፅሁፍ ስለ ቁልፍ ዝርዝሮችና ያልታወቁ ቃላት መጠየቅና ለጥያቄዎች መልስ መስጠት፤

በአንድ ታሪክ ውስጥ ተወናውያንን፣ ሁኔታዎችን፣ እና አይነተኛ ክውነቶችን መለየት፤

የፅሁፍ አይነቶችን ማወቅ፤ የተወናውያንን ተሞክሮዎች ማወዳደር/ማነፃፀር፤ ዋና ርእስን

መለየትና ቁልፍ ዝርዝሮችን መልሶ መንገር፤ በቡድን የንባብ እንቅስቃሴዎች መሳተፍ።

ስርአተ ትምህርት 2.0 የተተለመው በራስ

መተማመንን የሚገነቡ፣ ስኬት የሚያፈልቁ፣

እና ልጆችን በ21ኛው ክፍለዘመን ለመበልፀግ

የሚያዘጋጁ አካዴሚያዊ፣ ፈጠራዊ፣ እና

የሂሳዊ አስተሳሰብ ችሎታዎችን ለተማሪዎች

በማስተማር በኩል የተሻለ ውጤት እንዲያሳይ

ተደርጎ ነው።

Page 13: MCPS Grade K Curriculum in Amharic

MCPS CURRICULUM (ስርአተ ትምህርት) 2.0 13

ገንቢ ትንተና እና ጥረት/ተነሳሽነት/ብርታት

ፅሁፍ• የሀሳቦች እና የግንዛቤዎች ገለፃ (Expression፡-) ስእል፣ ምሪት (dictating)፣

እና ፅሁፍ በመጠቀም— መረጃ ሰጭ/ገላጭ ፅሁፎችን መድረስ፤ የትረካ ፅሁፎችን

መድረስ።

• ሂደቶች፡- ከአመራር ጋር—ዝርዝሮች ለመጨመርና ፅሁፍን ለማጠናከር ለጥያቄዎች

መመለስና አስተያየት መስጠት፤ ጥያቄዎች ለመመለስ ተሞክሮዎችን ማስታወስ ወይም

መረጃ መሰብሰብ፤ ለፅሁፍ ዝርዝር ለመስጠት ስእሎች ወይም እይታዎች መጨመር፤

የተለመዱ ሰዎችን፣ ቦታዎችን፣ ነገሮችን፣ እና ክውነውቶችን ማብራራት።

ቋንቋ• የፅሁፍ ቋንቋ ደንቦች፡- ከፍተኛና ዝቅተኛ ፊደሎች፤ ስሞችና ግሶች፤ በጋራ ቋንቋ

እንቅስቃሴዎች አረፍተነገሮችን ማስፋፋት፤ የአረፍተነገርን መጀመርያ ቃል ካፒታላይዝ

ማድረግ፤ ስነምልክት መጨረስ፤ ኮንሶናንትና ቫወል ድምፆችን መፃፍ፤ ቀላል ቃላትን

በቃል ስፔል ማድረግ።

ሂሳብ• ጂዮሜትሪ፡- ባለ2 እና ባለ 3 ማእዘን ቅርፆች፡- ባህርያት፣ ማወዳደር፤ የቅርፆች

አሰሳ—መድረስና ማፍረስ፤ የአቅጣጫና ያቀማመጥ ቃላት—በአካባቢ ቅርፆችን

መግለፅ።

• አለካክና አሀዞች፣ ቁመትና ክብደት - ቀጥታ ውድድር፣ መጠናቸው ያልተጠበቀ

መለኪያዎች።

ስነጥበብ• ስነጥበብን መፍጠር/ለስነጥበብ ምላሽ መስጠት ከትዝብትና ከህልም መውሰድ፣ ሸክላ

ስራዎች፣ ጨርቃጨርቅና ቅጦች።

አጠቃላይ ሙዚቃ• የሙዚቃ ንባብ፡- ረጅምና አጭር፣ የደመቀና ለስላሳ ድምፆች ለሚወክሉ አዶዎች

(icons) ምላሽ ድምፅ ማምረት።

• የሙዚቃ አቀራረብ፡- የግጥሚያ ዘፈኖችና የጣት ጨዋታዎች ማሳየት።

• ለሙዚቃ መመለስ፡- በሙዚቃ የተደገሙ ክፍሎችን መለየት።

የጤና ትምህርት • በሽታ መከላከል (ንፅህና)።

• የጠባይ ምልክቶችና ግላዊነት።

የመረጃ መሰረተ ትምህርት• መጠይቅና ቁልፍ ቃል (መጠይቅ/ምርመራ) በመረጃ ፍላጎት የተመሰረቱ ስልቶች።

• ለጥያቄዎች መልሶች መፈለጊያና መመዝገቢያ ስልቶች።

• ምንጮችን እንዴትና ለምን መጥቀስ።

• ስነፅሁፋዊ ፅሁፍ (ፕሮብሌምና መፍትሄ፣ አስተያየት፣ ዋና ሃሳብ፣ ቅጦችና

ዝምድናዎች)።

Page 14: MCPS Grade K Curriculum in Amharic

14 ስርአተ ትምህርት 2.0 ሙአለህፃናት

4ኛ የማርክ መስጫ ወቅት MARKING PERIOD 4

ፈጠራ (የፈጠራዊ አስተሳሰብ ችሎታ)—ለግለሰቡ፣ ለቡድኑ፣ ወይም

ለሁኔታው አዲስ ወይ ብቸኛ የሆኑ ሀሳቦችና መፍትሄዎች ማፍለቅ።

• በርካታና የተለያዩ ቅርፀቶችን በመጠቀም አዲስ ሀሳብ፣ ሂደት፣ ወይም ምርት

መፍጠር።

• ለአንድ ችግር ወይም ሁኔታ አዲስ፣ ልዩ፣ ወይም አማራጭ መፍትሄ ማቀድና

ማዘጋጀት።

• አንድን ሃሳብ፣ ሂደት፣ ወይም ውጤት ወደ አዲስ ቅርጽ መቀየር።

ስለራስ እውቀት (የአካዴሚያዊ ስኬት ችሎታ)—ስለግል

ሃሳብ ማወቅና መንቃት እንዲሁም የራስን ሀሳብ ለመቆጣጠርና ለመገምገም

ችሎታ መኖር።

• ማገናዘብ የራስን አስተሳሰቦች ከበስትኋላ ያለን እውቀት ለመለየት።

• የአስተሳሰብ ሂደቶችን መግለጽ።

ማህበራዊ ጥናቶች• ባህል፡ ፍላጎቶችን ለማርካት ሰዎች የሚያደርጓቸው ምርጫዎች (መሳርያዎች፣

መጫወቻዎች፣ መጓጓዣ፣ መገናኛ፣ ምግብ፣ መጠለያ)፤ ልዩ ልምዶች፣ ወጎች፣

ሙያዎች፣ እና የህብረተሰብ አባላት ጥቅሞች፤ የቤተሰብ ቅርስ።

• ባለፈው፣ በዛሬ፣ እና በወደፊት ገዜዎች መካከል ልዩነቶች፤ እለታዊ ኑሮና የዛሬና

የቀድሞ ግዜ አላማዎች።

ሳይንስ ቴክኖሎጂ፣ እና ኤንጂኔሪንግ• የህይውት ሳይንሶች፡-የውጭ ገፅታዎችና ለውጦች ተመሳሳይነቶችና ልዩነቶች፤

የእፅዋእትና የእንስሳት በአካባቢው ለመኖር የሚያካሂዷቸው ለውጦች፤ በእፀዋትና

በእንስሳት እንዲሁም በአካባቢው ያሉ ግንኙነቶች።

በብጫ የተመለከቱ ፅንሰ ሃሳቦች በሪፖርት ካርዱ ነጥብ የተደርገላቸው ለነጥብ መስጫ ወቅት 4 ነው።

የአካል ማጠንከርያ ትምህርት• የእንቅስቃሰሴ ችሎታዎችና ፅንሰሀሳቦችቀላል ነገሮችን በእጅ መምታት፤ በእግር መምታት

(የቆመ ኳስ)።

• የግልና የማህበራዊ ሃላፊነት፡- መተባበር፣ ሃላፊነት፣ እና በአካላዊ እንቅስቃሴ መካከል

መከባበር።

ንባብ/የቋንቋ ኪነ ጥበባት• መሰረታዊ ችሎታዎች፡-የህትመት፣ ከፍተኛና ዝቅተኛ ፊደሎች፣ የተነገሩ ቃላት፣

ከፊል-ቃላት፣ ፈደልና ድምፅ ግንኙነቶች፤ በክፍል ደረጃ ድምፆችን አውቆ ተግባራዊ

ማድረግ።

• ፅሁፍ ማንበብና መገንዘብ፡-ግጥም፣ ልብወለድ፣ ተረት ተረት፣ እና የመረጃ ፅሁፍ፤

Junior Great Books፤ ከአላማና ከግንዛቤ ጋር ማንበብ፤ እያነሳሱና እየደገፉ—ስለ

ቁልፍ ዝርዝሮችና የማይታወቁ ቃላት መጠያቅና ለጥያቄዎች መልስ መስጠት፤ የፅሁፍ

አይነቶችን ማወቅ፤ የተወናውያንን ተሞክሮዎች ማወቅ/ማወዳደር፤ ዋና አርእስትንና

ደራሲ ነጥቦችን ለመደገፍ የሚሰጣቸውን ምክንያቶች ማወቅ፤ በቡድን የንባብ

እንቅስቃሴዎች መሳተፍ።

የሰርአተ ትምህርት 2.0 ሪፖርት ካርድ

ለተማሪዎችና ለወላጆች በአመቱ ውስጥ

በክፍላቸው ከሚጠበቅባቸው አንፃር ተማሪዎች

እንዴት ግዴታቸውን እየተወጡ ወይመ

አካዴሚያዊ መመዘኛዎችን እንዴት እየላቁ

እንደሆነ መግለጫ ይሰጣል።

Page 15: MCPS Grade K Curriculum in Amharic

MCPS CURRICULUM (ስርአተ ትምህርት) 2.0 15

ፈጠራዊነትና ስለእውቀት ማወቅ

ጽሑፍ• የሀሳቦች እና ፅንሰሀሳቦች አገላለፅ፡- ስእል መሳል፣ በቃል ማስፃፍ፣ እና መረጃዊ/ገላጭ

ቁራሾችን ለመደረስ መፃፍ፤ ትረካዎችን መፃፍ፣ አስተያየቶችን መፃፍ።

• አፈፃጸሞች፡- ከአመራር ጋር—ዝርዝሮች ለመጨመርና እና ፅሁፍ ለማጠናከር

ለጥያቄዎችና ለአስተያየቶች መልስ መስጠት፤ ፅሁፍ ለማምረት በዲጂታል መሳርያዎች

መጠቀም፤ በጋራ ምርምርና የፅሁፍ ፕሮጀክቶች መሳተፍ፤ ለጥያቄዎች መልስ

ለመስጠት ተሞክሮዎችን ማስታወስ ወይም መረጃ መሰብሰብ፤ ለፅሁፍ ዝርዝር

ለመስጠት ስእሎችን ወይም እይታዎችን መጨመር፤ የተለመዱ ሰዎችን፣ ቦታዎችን፣

ነገሮችን፣ እና ክውነቶችን መግለፅ።

ቋንቋ• የፅሁፍ ቋንቋ ደንቦች፡- ከፍተኛና አነስትኛ ፊደላት፤ ስሞችና ግሶች፤ በአረፍተነገር

የመጀመርያውን ቃል ካፒታል ማድረግ፤ የመጨረሻ ስርአተምልክት፤ ክንሶናንትና

ቫወል ድምፆችን መፃፍ፤ ቀላል ቃላትን በድምፅ-ስጭ ፊደላት መጥራት።

ሂሳብ• የአስሮሽ ቁጥርና ግብረቶች፡- ቁጥሮችን መገንባትና ማፍረስ (11–19): አስር አንዶችና

ተጨማሪ ጥቂት አንዶች።

• ግብረቶችና አልጄብራዊ አስተሳሰብ፡- በከፊል-ሙሉ ፅንሰ ሀሳብ (እስከ 10)፤ ብዛት

(እስከ 10 ማገናኘትና መለያየት)።

• መቁጠርና ካርዲናሊቲ፡- ከ1 ቁጥር ሌላ ወደፊት መቁጠር።

ስነጥበብ• ስነጥበብ መፍጠር/ለስነጥበብ ምላሽ መስጠት፡-Monoprints (ከሌላ የማይመሳሰሉ

ልዩ ህትመቶች)፤ አሻንጉሊቶችና ተረት ትረካ፤ ህንፃዎችና አርኪተክቸር፤ የመፅሃፍ

ስነጥበባት።

አጠቃላይ ሙዚቃ• ሙዚቃ አቀራረብ፡- ረጅም ምትን ማገናዘብ።

• የሙዚቃ ንባብ፡- ረጅምና አጭር፣ የጩኸትና ልዝብ ድምፆችን ከሚወክሉ አዶዎች

(icons) በመነሳት ድምፆች ማምረት።

• ለሙዚቃ ምላሽ፡- ለተለያዩ የሙዚቃ ሜትሮች በእንቅስቃሴ ምላሽ መስጠት።

• ድምፆችን በማቀናጀት ብጣሽ ሙዚቃ መፍጠር።

• በተወስኑ ኖታዎች መካከል መዝፈን።

የጤና ትምህርት • ስሜቶችና ፍላጎቶች

• አወንታዊ የጠባይ ምልክቶች።

• ግላዊ ልዩ መሆን።

• የቤተሰብ ህዋስ መዋቅር (አባሎች፣ የትውልድ ቅደም ተከተል)።

የመረጃ መሰረተ ትምህርት• መጠየቅና የቁልፍ ቃል (ምርምር) ስልቶች።

• የፍለጋ፣ ድርጅት፣ እና ለጥያቄዎች መልስ መመዝገቢያ ስልቶች።

• እንዴት እና ለምን ምንጮች ለመጥቀስ።

• የማምረቻ ስልቶች።

• የስነፅሁፍ ፁሁፍ (ለራስ ግንኙነቶች መፃፍ፣ ፕሮብሌምና መፍትሄ፣ ጭብጦች)።

Page 16: MCPS Grade K Curriculum in Amharic

ወላጆች እንዴት

እንደሚያግዙ

ልጅዎ በትም/ቤትም ሆነ በህይወቱ/ቷ ስኬታማ እንዲሆን/እንድትሆን

ይፈልጋሉ። እሱን/እሷን ግቡን/ግቧን እንዲመታ/እንድትመታ በርካታ

ማበረታቻ መንገዶች አሉ። ልጅዎ ከትም/ቤት በላቀ ሁኔታ ለመጠቀም

እንዲችል/እንድትችል በበኩልዎ ሊያግዙ የሚችሉባቸው በጥቂቱ የሚከተሉት

ናቸው፡-

• ግድ እንዳለዎት ያሳዩ ልጅዎ ትም/ቤት በሚሰራው/በምትሰራው።

• ከፍተኛ አላማዎች ለልጅዎ ያስቀምጡ። ትም/ቤት ከሁሉም በላይ

ቀደምትነት የሚሰጠው መሆን እንዳለበት ቁልጭ አድርገው ያስተውቁ።

• ቢያንስ 15 ደቂቃ መድበው በየእለቱ ከልጅዎ ጋር መነጋገርና ከሱ

ወይም ከሷ ጋር ማንበብ።

• ፀጥታ ያለው ቦታ ያቅርቡ ለልጅዎ ማጥኛ።

• ልጅዎን ያግዙት/ዟት በቤት ስራው/ዋ።

• ልጅዎ የሚያየውን/የምታየውን የቴሌቪዥን ሰአት ይወስኑ በቴሌቪዥን

ስለታየውም ያውያዩት/ያወያይዋት።

• ጊዜውን ይቆጣጠሩ ልጅዎ ቪድዮ ጨዋታም ሆነ ኢንተርኔት በመጎብኘት

የሚያሳልፈውን/የምታሳልፈውን።

• ለአገልግሎት በፈቃደኝነት ይቅረቡ በትምህርት ቤት እንቅስቃሴዎች ለማገዝ

ሌሎች ወላጆችም እንዲሳተፉ ግፊት ያድርጉ።

• በየወቅቱ የልጅዎን አስተማሪዎች ያነጋግሩ ስለልጅዎ ግስጋሴና በብኩልዎ

እሱን/እሷን ለማገዝ ማድረግ ስለሚችሉት።

• ልጅዎን ያደፋፍሩ ፈታኝ ስራ እንዲያከናውን/እንድታከናውን።

የተወረሰው ከA Parent’s Guide to Achievement Matters Most (ስኬት ከሁሉም በላይ

- የወላጅ መመርያ) Maryland State Department of Education (የሜሪላንድ ስቴት

የትምህርት መምርያ)።

MCPS Parent Academy ወላጆች የልጆቻቸውን የትም/ቤት ስኬት ለመደገፍ

ስለሚያስፈልጓቸው መረጃዎችና መገልገያዎች ነፃ ትምሀርት ያቀርባል። ለተጨማሪ መረጃ፣

www.mcpsparentacademy.org ይጎብኙ

ስለ ስርአተ ትምህርት 2.0 ተጨማሪ መረጃ በwww.montgomeryschoolsmd.org/

curriculum/2.0/ ይገኛል።

Montgomery County Public Schools (የምንትጎመሪ ካወንቲ የህጽብ ትም/ቤቶች)

850 Hungerford Drive Rockville, Maryland 20850 301.309.6277 www.montgomeryschoolsmd.org

አሳታሚ፡ Department of Materials Management for the Office of Curriculum and Instructional Programs

ትርጉም ፡ Language Assistance Services Unit • Division of ESOL/Bilingual ProgramsOffice of Curriculum and Instructional Programs

0406.14ct • Editorial, Graphics & Publishing Services • 9/13 • 200