semayawi1/newly formed political party the blue (semayawi) founder, professor mesfin wolde mariam

28
ቅጽ 1 ቁጥር 1 ጥቅምት 2005 ዓ.ም 1

Upload: ethio-afric-news-en-views-media

Post on 25-Jan-2015

380 views

Category:

News & Politics


10 download

DESCRIPTION

Newly formed political party the blue (Semayawi) founder, Professor Mesfin Wolde Mariam explain future politic ideology TO Ethiopia.

TRANSCRIPT

Page 1: Semayawi1/Newly formed political party the blue (Semayawi)  founder, Professor Mesfin Wolde Mariam

ቅጽ 1 ቁጥር 1 ጥቅምት 2005 ዓ.ም

1

Page 2: Semayawi1/Newly formed political party the blue (Semayawi)  founder, Professor Mesfin Wolde Mariam

ቅጽ 1 ቁጥር 1 ጥቅምት 2005 ዓ.ም

2

ጋዜጣችንን ማሳተም እንድንችል ዛሬም እንጠይቃን!

ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት የዛሬ አንድ መቶ ዓመት ገደማ ለሀገራችን ዕድገት ብሩህ ራዕይ በነበራቸውና ሕዝብ መረጃንና ዕውቀት እንዲያገኝ መልካም ምኞት በነበራቸው አባቶቻችንና እናቶቻችን የተመሠረተ ድርጅት መሆኑ ይታወቃል፡፡ የተቋቋመበትን አብይ ዓላማ ዕውን ለማድረግም ብርሃንና ሰላም በሀገራችን የእውቀት አድማስ እንዲሠፋና ዜጐችም መረጃ እንዲያገኙ ባበረከተው የረጅም ጊዜ አገልግሎት ባለውለታነቱና ፈር ቀዳጅነቱ በታሪክ ተመዝግቦ የሚቀመጥለት አኩሪ ሃቅ ነው፡፡ ብርሃንና ሰላምን ለማቋቋም ምንም እንኳን የግለሰቦች ባለብሩህ ራዕይነት ባይካድም ድርጅቱ የተቋቋመውም ሆነ ሲተዳደር የኖረው ከእያንዳንዱ ዜጋ በግብር እና በታክስ መልክ በሚሰበሰብ ገንዘብ በመሆኑ ንብረትነቱም የኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ ሃብት መሆኑ ግልፅ ነው፡፡ ስለሆነም ዜጐችን በተናጠልም ሆነ የሀገሪቱን ተቋማት እንደተቋም በእኩልነትና በግልፅነት ማገልገል እንዳለበት ለድርጅቱም ሆነ ለሕዝብ የተገለፀ ሃቅ ነው፡፡

እነዚህን ከላይ የተዘረዘሩ መሠረታዊ እውነታዎች በመመርኮዝ ፓርቲያችን በነሐሴ 22/2004 ዓ.ም በተፃፈ ደብዳቤ በብርሃንና ሰላም የሕትመት አገልግሎት ለማግኘት ጠይቆ ነበር፡፡ ለጥያቄአችን መልስ የሚሠጥ በማጣታችን የፓርቲያችን አመራር አባላት በአካል በመገኘት የድርጅቱን የተለያዩ የሥራ ክፍል ኃላፊዎች ቢያነጋግሩም መፍትሔ የሚሰጥ ሰው አልተገኘም፡፡ የፓርቲያችን አመራሮች በአካል ያነጋገሯቸው የተለያዩ ክፍሎች የሥራ ኃላፊዎች ጥያቄውን አስመልክቶ በቃል የሰጧቸው መልሶች የተለያዩ፤ ነገር ግን ጋዜጣችንን ለማተም የማይችሉ መሆኑንና ጋዜጣችንን ላለማተም የሚያቀርቡልን ምክንያቶች ደግሞ እጅግ የተለያዩና የተድበሰበሱ ሆነው ተገኝተዋል፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ ድርጅቱን የጠየቀው በጽሑፍ ስለሆነ ጋዜጣችንን የማታትሙበትን ምክንያት የሚመለከተው አካል በጽሑፍ መልስ እንዲሰጠን በማለት ብንጠይቅም እንኳን ለጥያቄያችን መልስ ልናገኝ ቀርቶ በሕጋዊ አካልነትና በሰውነት እንኳ የሚቆጥረን አካል አጥተናል፡፡ ይህ ጥያቄያችን መፍትሄ እንዲያገኝም ተቋሙን በበላይነት ለሚመራው ቦርድ እንደገና በጽሁፍ አቤት ብለናል፡፡ መልስ ግን አሁንም የለም

እንዲህ ዓይነት ኃላፊነት የጐደለውና ተጠያቂነት የጠፋበት ተቋም ይዘን፤ በመንግሥት በኩል በየመሥሪያ ቤቱ ተለጥፈው የምናያቸውን የሥነ-ምግባር መርሆችን በሥራ ላይ ማዋል ቀርቶ ማሰብ እንኳን የማይቻል እንደሆነ ነጋሪ አያሻውም፡፡ እኛ የጠየቅነው የሕትመት አገልግሎት ጥያቄ ለቦርድ አባላት ቀርቦ ጊዜአቸውን የሚያጠፉበት ጉዳይ ሳይሆን ተራ የቀን ተቀን አገልግሎት ጥያቄ ነበር፡፡ ነገር ግን ይህ ክስተት ተጠያቂነት በጐደለበት ቦታ ሁሉ የሀገር ሀብትና ጊዜ እየባከነ የዜጐችም መጉላላት እየበረከተ እንደሚሄድ ማሳያ ጉልህ ማስረጃ ነው፡፡

በመሆኑም ፓርቲያችን በገበያ ዋጋ የሚጠበቅበትን ከፍሎ፣ በሕግ ማሟላት የሚገባውን አሟልቶ ዛሬ ብዙ ዓይነት ሕትመቶችን ማከናወን ከሚችል ግዙፍ ድርጅት የአንድ ሣምንታዊ ጋዜጣ የሕትመት አገልግሎት ለማግኘት ለቀረበው ጥያቄ መልስ እንኳን የሚሰጠው አካል ማጣት (ምንም እንኳን የአንድን ድርጅት ድክመት ብቻ መነሻ አድርጐ መወሰን በቂ ባይሆንም) ሀገራችን በእውነት ያለችበት የአስተዳደር ችግር እና የተቋማት ምክነት የት እንደደረሰ አመላካች ነው፡፡ ይህ ድርጊት የሕሊናና የታሪክ ተጠያቂነት የሚያመጣ ሲሆን መልካም አስተዳደር በሰፈነበት ሀገር ደግሞ የሕግም ተጠያቂነት ያመጣ ነበር፡፡

ፓርላማ ተገኝተው የ ሶስተኛ አመት የፕሬዘደንቱን መክፈቻ ንግግር ማብራሪያ ያቀረቡት አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትርም በአንድነት ፓርቲ ተወካይ በኩል ለተጠየቁት ጥያቄ ሲመልሱ ኢህአዴግ ተጠያቂነትን እንደማይፈራና ለዚህም ስጋት እንዳይገባቸው የሚያስተማምን ነበር፡፡ ይህ ከሆነ ዘንዳን የአዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር አስተዳደር፤ የመንግስት ተቋማት የሆኑ የንግድ ድርጅቶች በአግባቡ ሥራቸውን እያከናወኑ እንደሆነ መከታተልና መቆጣጠር የሚኖርበት የበላይ አካል እንደመሆኑ፤ የብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅትንም በዚሁ መልክ በመቃኘትና በመጠየቅ ተጠያቂነትን በዚህ አግባብ ሊያሰፍን ይገባል፡፡ ዜጐችን በእኩል ዐይን አይቶ በፍትሐዊነት እያገለገለ ካልሆነም አስፈላጊው የእርምት እርምጃ በአስቸኳይ ሊወሰድበት ይገባል፡፡ በመንግስት ድርጅትነት ስም ብልሹ አስተዳደርን፣ ኪራይ ሰብሳቢነትን እና በጥቅማ ጥቅም በአድሎ የመሥራት ሁኔታም ካለ ድርጅቱን ከላይ እስከታች መፈተሽ ያስፈልጋል፡፡ በመንግስታዊ ሌባም የመንግስት ፖሉሲ፣ አሠራርና መልካም ስም እየጐደፈ እንዳይሆን ማጣራት ያሻል፡፡ አለበለዚያ እንደው በደፈናው ይህ የንግድ እንጂ የአስተዳደር ጉዳይ አይደለም! ብሎ ጆሮ ዳባ ልበስ ማለት የጠቅላይ ሚኒስትሩን “አዲስ” አካሄድ ወይም አመራር ያስጠረጥራል፡፡ እንደቀድሟቸው ሁሉ እኚህም ጠቅላይ ሚኒስትር መሬት ካለው ሀቅ ጋር የማይሄዱ ነገሮችን በርቱዕ አንደበት በመናገር ብቻ ችግር እንደሌለ ማስመሰል ችግሩን በምንም ዓይነት አይቀርፈውም፡፡ እንደውም ያባብሰዋል!

በመሆኑም ዛሬ የዚህች ሀገር ዜጐች በምናወጣው አንጡራ ሀብት የሚተዳደረውና የሕዝብ ሀብት የሆነው የብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት የሥራ አመራር ቦርድ እንዲሁም አዲሱን የጠቅላይ ሚኒስትሩ አስተዳደር እንዲህ ዓይነት ድርጊቶች ለምን እንደሚፈፀሙ አጣርቶ መልስ እንዲሰጠንና ወደፊትም እንዳይደገሙ የማስተካከያ እርምጃዎች እንዲወስድ እየጠቆምን

አፅንዖት ሰማያዊበሰማያዊ ፓርቲ በየ15 ቀኑ

ዕየታተመ የሚወጣ መፅሄት ነው፡፡

ዋና አዘጋጅአናኒያ ሶሪ

አድራሻ፡ አዲስ ከተማ ክ/ከወረዳ 8 የቤት ቁጥር 377

ኢ-ሜይል፡- [email protected]

ኮምፒውተር ጽሁፍበሰማያዊ ፓርቲ

ሌይአውት ዲዛየንበሰማያዊ ፓርቲ

አከፋፋይ ፡-ነብዩ ሞገስ

ህትመት ክትትልየሽዋስ አሰፋ

አሳታሚው፡- ሰማያዊ ፓርቲ

አድራሻ፡-

አራዳ ክ/ከወረዳ፡- 7

የቤት ቁጥር- 227

ስልክ፡- 0116514240

ፖ.ሳ.ቁ፡- 180298

ድረ-ገጽ፡ www.semayawiparty.org

ኢ-ሜይል[email protected]

አታሚ፡-ስፕሪንግ ማተሚያ ቤተስልክ፡- 0911844887 0911410926

Page 3: Semayawi1/Newly formed political party the blue (Semayawi)  founder, Professor Mesfin Wolde Mariam

ሰማያዊ፡- በቅድሚያ ለቃለ-መጠይቁ ስለተባበሩን በጣም ነው የምናመሰግነው፡፡ በቀጥታ ወደ ጥያቄው ስገባ፡- በጠ/ሚኒስትር አቶ መለስ ሞት ምን እንደተሰማዎ ቢገልፁልንና ከዚያ ብንጀምር…..

ኘሮፌሰር መስፍን፡- የአቶ መለስ ሞት ድንገተኛ ነው፤ ድንገተኛ በመሆኑም ያስደነግጣል፡፡ ለማናችንም ቢሆን ሞት የማይቀር መሆኑንም ብናውቅ፤ እንኳን እንደዚህ በድንገት ሲሆንና ታመውም ቆይተው በሚሞቱበት ጊዜ ማዘን አይቀርም፡፡ ምንም አይነት ሰው ይሁን! እኔ በመለስ ሞት ያደረብኝ ስሜት፤ ከዚህ በፊት በጠ/ሚኒስትርነቱ ወይም በኘሬዚዳንትነቱ አሊያም በፈላጭ ቆራጭነቱ ያደረገው ነገር አይደለም፡፡ ድንገት በመሆኑ፣ ዕድሜ ለንስሃ ሳያገኝ መቅረቱ ያሳዝናል፡፡ …… እና …. መቼም…..እእእ….. የሱ ሞት ለብዙዎቻችን እንደዚሁ እንደማንም እንደሰው የሰው ባህርይ ሆኖ የመጣ መሆኑን ብንገነዘበውም፤ ለጓደኞቹ ደግሞ እንደዚህ አልነበረም ይመስለኛል፡፡ እነሱ ይበልጥ የደነገጡ፣ የተደናበሩ፣ ሞትን ለመደበቅ የሞከሩ፣ የማይደበቀውን ለመደበቅ የሞከሩ በመሆናቸው ትንሽ የመለስን ሞት እእ….. አንድ ያጠላበት አጉል ነገር ነበረና እሱ ያሳዝናል፡፡ እሱም በራሱ በኩል ሆነ፤ ለርሱም የሚቆም ሰው-የሚመለከተው፣ ለቤተሰቡ ያ ሁኔታ እና ለመደበቅ የተደረገው ሽር-ጉድ (እስካሁንም ድረስ ብዙ ነገር ተደብቋል) ያ ደግሞ ይበልጥ ያሳዝናል- ከሞቱም ይበልጥ ያሳዝናል-አሟሟቱ! ይኸው ነው፡፡

ሰማያዊ፡- በዚህ ዙሪያ ግን በዚያን ሰሞን በተካሄደ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ኃላፊ የሆኑት አቶ በረከት ሰምኦን ተጠይቀው፡- “ይሄ በፓርቲያችን የተለመደ ባህል ነው፤አዲስ አይደለም፡፡ የአንድ ሰው መታመም ወይም መሞት ብዙ ስለማያስደንቀን በአደባባይ መግለፁንም

ያን ያክል አሳሳቢ አድርገን አናየውም” ብለው ነበረ፡፡ በዚህ ረገድ ሌሎች ደግሞ፡- “የኢትዮጵያ ህዝብ የማወቅ መብት ነበረው፤ ሊደበቁ የሚገቡ ነገሮች ብሔራዊ የደህንነት ምስጢሮች ወይም የመከላከያ ምስጢሮች ተብለው ሊያዙ የሚችሉ የመኖራቸውን ያህል ስለአንድ የአገሩ ጠቅላይ-ሚኒስትር ግን ለዚያውም የህዝብ ኃላፊነት ቦታ እና ስልጣን እንደመያዛቸው፤ህዝቡ በይፋ ማወቅ ይገባው ነበረ” ብለው የሚከራከሩም አሉ፡፡ ለዚህ ደግሞ የጋናውን ኘሬዚዳንት ሞትና ወዲያው ለህዝቡ በይፋ መገለፁን ብሎም በተገቢው ወቅት ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር መካሄዱን እንደአብነት ጠቅሰው ያስረዳሉ፡፡ እርስዎ በዚህ ላይ ምን አስተያየት አልዎት?

ኘሮፌሰር መስፍን፡- እንግዲህ በረከት እኛ ሲል እነማን ናቸው እነሱ? እኛ የሚለው! እንደዚህ ልዩ ባህል ያለው! የተለየ የሆነው! ከኢትዮጵያ ህዝብ ባህል፣ ከኢትዮጵያ ህዝብ ልማድ ውጭ የቆመ ማን ነው እሱ? ማነው በረከትና ቡድኑ? ኢህአዴግን እንደሆነ ኢህአዴግ አንድ የፖለቲካ ቡድን ነው፤ግንባር ነው፤ ብዙዎች አሉበት ውስጡ-ሰዎች! አሁን እንደዚህ ‘መርዶ ባህላችን አይደለም’ ሲሉ ከዚህ በፊትም ሰምቻለሁ በሌላ አጋጣሚ፡፡ ነገር ግን ኢትዮጵያ ውስጥ ነው ያሉት እኮ! የኢትዮጵያን ህዝብ ነው የሚያስተዳድሩት፤ ለኢትዮጵያ ህዝብም ኃላፊነት አለባቸው፡፡ ካልሆነ ይሄ የተለመደው የነሱ ግዴታቸውን ቸል የማለት እና ‘እኛ ነን ሁሉንም ነገር የምንወስነው- ልማድንም ባህልንም የምንወስነው እኛ ነን፤ ከእኛ በላይ ማንም የለም! ህዝቡም ቢሆን የራሱ ባህል የለውም! የማወቅም መብት የለውም፤ ማለት ይችላል በረከት ከዚህ በፊት በሌላም ነገር እንዳለው፡፡ ነገር ግን ይሄ ቅድም እንዳልኩት፡- በመለስ ሞት ምክንያት ተደናብረው እንጂ በረከት ስቶት አይደለም፡፡ በመሆኑም፡- በድንብርብር

ውስጥ ሆነው አንዴ ‘ታሟል!፣ አንዴ ‘ደህና ነው!፣ አንዴ አሁን ነው!፣ “እንዲህ ነው….እንዲህ ነው….” እያሉ ቆይተው ስለነበረ፤ በእውነቱ የነሱን መደናበር እና በትክክለኛው አእምሮ ውስጥ እንዳልነበሩ የሚያሳይ ነው፡፡

ሰማያዊ፡- በአቶ መለስ ሞት ላይ መደናበሩን ምን አመጣው ይላሉ?

ኘሮፌሰር መስፍን፡- ስለራሳቸው ነውኮ እነሱ የሚደናበሩት እንጂ መለስማ ሞቷል፡፡

ሰማያዊ፡- ለማለት የፈለግሁት፡- ‘የፖለቲካ ድርጅት ወይም ቡድን ነን፣ የምንመራበት መስመር አለን የሚሉ እስከሆኑ ድረስ በቀጣይነት ተተኪው ነገር….

ኘሮፌሰር መስፍን፡- አልተዘጋጁም! ድንገተኛ ነበር ይሄ ነገር፡፡ በእርግጥ እንዲህ ቢሆን እንዲህ እናደርጋለን ብለው፣ ህጉ ግልፅ ሆኖ ፣ የሚፈለግ ሰው ወዲያው የሚተካ ቢሆን፤ አንዳንድ አገር…. ቅድም እንደተናገርከው ጋና እንደዚህ ሆኗል፡፡ እ… አሜሪካ ኬኔዲ በሞተ ጊዜ ምክትል ኘሬዚዳንቱ ወደዋሽንግተን ሲመለስ አውሮኘላን ላይ ቃለ-መሐላ ፈፀመና ኘሬዚዳንት ሆነ፡፡ እንደዚህ በቀጥታ ህጉ የሚከበርበት አገር ምንም ችግር የለም፡፡ እዚህ ህጉ እኮ እነሱ በፈለጉት መንገድ እንዲሄድ ነው የሚፈልጉት፡፡ እና አሁንም በህጉ ምክትል ጠ/ሚኒስትሩ ይግባ ከተባለ፣ አሁን ያለው ምክትል ጠ/ሚኒስትር ይግባ ከተባለ እነሱ ያንን የጠ/ሚንስትርነቱን ቦታ እንዲይዝ ይፈልጉታል ወይ? ወይስ ደግሞ ሌላ ያንን ቦታ የሚፈልግ አለ? ሌላውም ቦታውን በሚፈልጉትና ይህ ሰው እዛ ቦታ ላይ እንዲሆን በማይፈልጉት መሃከል ፉክክር ይነሳል፡፡ ያ ፉክክር ነው እንግዲህ መደናበር ውስጥ የከተታቸው፡፡ ምን እናድርግ? ምን እንሁን? እንዴት እናድርገው? እንዴት እንስማማ? በሚሉና በረድ ብለው በሰከነ አይምሮ እስኪወስኑ ድረስ መጀመሪያው ላይ በጣም ተደናበሩ፡፡ ያ መደናበር ነው ያን ሁሉ ነገር ያመጣው የሚመስለኝ እኔ፡፡

ሰማያዊ፡-ምናልባት ይሄ “ሥልጣን ባህልና እና አገዛዝ” በሚል መጽሐፍዎ ላይ ያነሱት “ሥልጣንን እስሁንም ድረስ መግራት አልቻልንም-እንደኢትዮጵያውያን!” ብለው ነበር፡፡ እና ከዚያ ጋር የሚያያዝ ነፀብራቅ ይኖረው ይሆን?

ኘሮፌሰር መስፍን፡- ሁልጊዜም አለ እሱ እኮ! እሱ ባህላችን ነው-አገዛዝን ሳንገራ አለን እስካሁን ድረስ፤ ታሪካችን ነው፡፡ እና….. ውስጣችን ነው እሱ!

ሰማያዊ፡- ኢህአዴግ ግን አሁን በአብዮታዊ

ይህ ቃለ መጠይቅ ሰኞ በ21/1/2ዐዐ5 ዓ.ም. በኘሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም መኖሪያ አፓርትመንት ውስጥ በሚገኘው የግል-ቢሮአቸው የተካሄደ ሲሆን በአቶ መለስ ሞት ዙሪያ፣ ትተዋቸው ባለፏቸው መታሰቢያዎች(legacy)፣ እንዲሁም በመፃዒ የኢህአዴግ እና የኢትዮጵያ ዕጣ ፈንታዎች ላይ ያነጋገራቸው የሰማያዊ ፓርቲ ልሳን የሆነው

የ“ሰማያዊ” ሚድያ ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ አናንያ ሶሪ ነው፡፡ መልካም ንባብ!

ቅጽ 1 ቁጥር 1 ጥቅምት 2005 ዓ.ም

3

Page 4: Semayawi1/Newly formed political party the blue (Semayawi)  founder, Professor Mesfin Wolde Mariam

ዴሞክራሲያዊ መስመር ሥልጣንን በማሸጋገር በገዥነት መቀጠል እችላለሁ ብሎ በይፋ የሚናገር ድርጅት ነው፡፡ አሁን ደግሞ ያሉት ነገሮች (ከመጋረጃ ጀርባ ያሉት እንደተጠበቁ ሆነው) እስካሁን ሰላማዊ የሥልጣን ሽግግር የተደረገ ያስመስላል፡፡ እና ምናልባት ይሄ ኢህአዴግን ልክ ያሰኘው ይሆን?

ኘሮፌሰር መስፍን፡- አልገባኝም!

ሰማያዊ፡- ማለት ብዙዎች ከአቶ መለስ በኋላ የሚመጣው ስርዓት ያልተደላደለ፣ ሰላማዊ የማይሆን፣ ብዙ የሥልጣን ሽኩቻ የሚኖርበት ሲሉ ተንብየውና ተንትነው ነበር፡፡ በአንፃሩ ግን የሆነው፡- ም/ጠ/ሚ የነበሩት አቶ ኃ/ማርያም ደሳለኝ ናቸው በቦታው የተተኩት፡፡ እና ይሄ ሰላማዊ የሥልጣን ሽግግር በዚች አገር አለ ሊያስብል ይችላል?

ኘሮፌሰር መስፍን፡- ገና ነን እኮ! አሁን ለሁሉም የተመቸ በመሆኑ የኃ/ማርያምን ጠቅላይ ሚኒስትርነት አፀደቁ፡፡ ነገር ግን የኃ/ማርያም አሠራር በሥልጣኑ መጠቀም ሲጀምር ከማን ጋር ይሰለፋል? ከነማን ጋር አይሰለፍም? ማንን ያስቀይማል? ማንን ይደግፋል? በየትኛው መስመር ይሄዳል? ገና ነው….. ገና አልተጀመረም፤ ይሄ ሁሉ ሆኗል! ደህና ተረጋግቷል! ሰላም ነው! ምን የሚባል ነገር የለም ለኔ፡፡ ገና ነው! ጊዜ ይፈልጋል ይሄ፡፡

ሰማያዊ፡- አቶ መለስ በጠ/ሚኒስትርነት ዘመናቸው ብቁ አመራር ነበራቸው! የሚሉ ወገኖች አሉ፡፡ በዓለም-አቀፍ መድረክም በአገር-አቀፍም አስማሚ ሰው ናቸው! ሁሉንም ከሞላ ጐደል አቻችለው ይሄዱ ነበረ ብለው የሚያምኑ አሉ፤ የለም እሳቸው ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብት የሚጥሱ በስልጣናቸው ብቻ ሲያስቡ

የኖሩና ለአገር ደግሞ ብዙም ግድ የሌላቸው ናቸው! የሚሉም አሉ፡፡ በዚህ መሃል አሁን በተያዘው የኘሮፖጋንዳ ስራ ላይ አቶ መለስን እንደቅዱስ የሚስሉ ክስተቶች አሉ፡፡ የሁሉ ነገር ባለራዕይ፣ ሃሳብ አመንጪና የልማት ሁሉ አርበኛ እስከማለት የደረሱ አሉ፡፡ በተቃራኒው ደግሞ፡- የሰብዓዊ መብትን የደፈጠጡ፣ ብዙዎችን ያሰሩ፣ የኘሬስ ነፃነትን የተጋፉ፣ እንዳሻቸው ህግን በአንድ ዕለት ያወጡ ናቸው ብለው የሚኮንኗቸው አሉ፡፡ የርስዎ አስተያየት በዚህ ላይ ምንድነው?

ኘሮፌሰር መስፍን፡- ይሄ እኮ ምን….. ለኔ ጥያቄው ባዶ ነው፡፡ ባዶ የሚሆንበት ምክንያት ምንድነው.... መለስን እየካቡ የሚናገሩት ሰዎች እነማን ናቸው? ሊክቡት የሚገባቸው ሰዎች ናቸው፡፡ ከሱ ጋራ የተሰለፉ ሰዎች ናቸው፡፡ ከዛ ሌላ ከዛ ውጪ ሊወጡ አይችሉም፡፡ ስለዚህ እነሱ ያንን የተናገሩት ለነሱ እውነት ነው፡፡ በአንፃሩ ደግሞ፡- የለም መለስ ስልጣንን ጨብጦ ለራሱ ብቻ ይዞ ሲጠቀምበት የነበረ ጉልበተኛ ነው፤ አምባገነን ነው የሚሉ ሰዎች የፖለቲካ ቡድኑ የስልጣን ተካፋይ እንሁን ብለው የሞከሩ ያቃታቸው ሰዎች ናቸው፡፡ የነሱም ልክ ነው፡፡ በነሱ በኩል ሆነህ ስታየው፡፡ ስለዚህ ይሄንን ልታወዳድረው አትችልም፡፡ ይሄም ከሱ በኩል ሆነህ ስታየው ልክ ነው፤ ያኛውም ከሱ በኩል ሆነህ ስታየው ልክ ነው፡፡ እንደው በኢትዮጵያዊ ዓይን ብቻ ከፖለቲካዊ የስልጣን ትግሉ ወጣ ብለህ ልመልከተው ያልከው እንደሆነ ግን፤ መለስ የአርቆ ማስተዋል ችሎታ አለው ብዬ እኔ አልገምትም፡፡ ይሄንን አርቆ ማየት አለመቻሉን እኮ አሟሟቱ ራሱ ይገልፀዋል፡፡ በደንብ አድርጐ ይገልፀዋል-ለእኔ፡፡ አሟሟቱ፣ የፓርቲው መርበድበድ፣ መረበሽ ይሄ ሁሉ ቀደም ብሎ ያልታየ ያልታሰበበት ነገር መሆኑን የሚያመለክት

ነው፡፡ በመሆኑም መለስ…. እ…. ኖረ ለማለት እንኳን እኔ በእውነት አልችልም፡፡ በፍርሃት ኖሮ….. ከቤቱ ወጥቶ አውሮኘላን ማረፊያ እስኪደርስ ድረስ ስንት ወታደር በየመንገዱ ላይ ቆሞ በዚያ ዓይነት ፍርሃትና ጭንቀት ውስጥ የኖረ ሰው ነው፡፡ እ…. ምናልባት ለራሱ ትንሽ ነፃነት ቢሰጥና ያንን ነፃነትም ለሌሎች እንደዚሁ ቢያስተጋባ ምንአልባት ልንገራችሁ ከማለት ብቻ ወጥቶ የማዳመጥም (የማይፈልገውንም ነገር ቢሆን የማዳመጥ) ችሎታ ቢያዳብር ኖሮ በብዙ ነገር ችሎታውን ይስልለት ነበር፡፡ እ…. ለኢትዮጵያም ህዝብ….እንደው ከልብ እ…..እንደው ከሱ ኋላ መቆም የሚችልበትን ሁኔታ መፍጠር አያቅተውም ነበር ይመስለኛል፡፡ ግን ሁሉንም እንደጠላት አድርጐ በመገመት ሊያደርግ የሚችለውን ሊያስማማው የሚችለውን ኢትዮጵያንም ሊለውጣት የሚችለውን የኢትዮጵያን ህዝብም ሊለውጥ የሚችለውን ነገር ሁሉ አደረገ- ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር ለማለት አልችልም እኔ፡፡ እ…..እሱ የሚፈልገውን ነገር፣ እሱ በሚፈልገው መንገድ፣ እሱ ባለው ጊዜ አድርጓል፡፡ ያ ስንት ሰው አስከፍቷል? ስንት ሰውስ ጐድቷል? ስንት ሰው አስደስቷል? ይሄ እንግዲህ ታሪክ-ፀሐፊዎች ወደፊት የሚናገሩት ነገር ነው፡፡

ሰማያዊ፡-ስለዚህ ምናልባት ዴሞክራሲያዊና አሳታፊ አለመሆናቸው ኢትዮጵያዊነታቸው ላይ የጥያቄ ምልክት ያሳርፍ ይሆን?

ኘሮፌሰርመስፍን፡- እኔ ኢትዮጵያዊነቱ ላይ የጥያቄ ምልክት አላስቀምጥም፡፡ ኢትዮጵያዊነቱ ሌላ ነገር ነው፡፡ በተፈጥሮው ያገኘው ነገር ነው-ማንም ሊወስደው አይችልም፤ እሱ ራሱ እኔ አይደለሁም ካላለ በቀር እንደኢሳይያስ አፈወርቂ! ይሄ ሲወለድ ያገኘው ነው፡፡ ማንም ኢትዮጵያዊ አይደለህም ሊለው አይችልም፡፡ ማንም ሌላውን ሰው አንተ ከእኔ ያነስክ ኢትዮጵያዊ ነህ በኢትዮጵያዊነት ብሎ ማለት የሚችል የለም፡፡ እንደዚህ ዓይነት ሚዛን በእጁ የጨበጠ አንድም ሰው የለም፡፡ ሁላችንም እኩል ነን፡፡ ሁላችንም እንደታየን፣ እንደተሰማን፣ እንዳስተዳደጋችን፣ እንደትምህርታችን” ኢትዮጵያን ሀገራችን ኢትዮጵያውያንን ወገናችን ብለን እንሰየማለን፡፡ ነገር ግን አንተ ያነስክ ኢትዮጵያዊ ነህ፤ አንተ የተሻልክ ኢትዮጵያዊ ነህ ማለት የሚቻልበት መንገድ ምንም የለም፡፡ ስለዚህም፡- መለስ ከማናችንም የማያንስ ከማናችንም የማይበልጥ ነው- በኢትዮጵያዊነቱ፡፡ ያንን እሱ ራሱ እንደፈተለው ነው የሚሸመነው፡፡

ሰማያዊ፡- ከዚህ ጋር ተያይዞ አንዳንዶች የሚያነሱት፡- ከ97 ወዲህ ምርጫውን ተከትሎ ነው ኢህአዴግ የኢትዮጵያን ህዝብ የልብ ትርታ እየገመተ ከተቃዋሚ ጐራውም ቢሆን አጀንዳዎችን ኮርጆ የባንዲራ ቀን እስከማክበር፣ ብሔር-ብሔረሰቦችን በኢትዮጵያዊነት ጥላ ስር እስከማቀፍና ብሔራዊ አጀንዳ የሚባሉ ነጥቦችን ማንሳት ያጐላው ብለው የሚያዩ አሉ፡፡ እና በዚህ ረገድ አቶ መለስም በታሪክ ትተው ለማለፍ የፈለጉት ነገር ኢትዮጵያዊነትን የሚወክል ሲሆን ይህን ሃሳባቸውን ሳያሳኩት በአጭር ባይቀጩ ኖሮ ብዙ ህልም ነበራቸው የሚሉ

ቅጽ 1 ቁጥር 1 ጥቅምት 2005 ዓ.ም

4

አሁን መለስ የለም! መለስ ከሞተ በኋላእንዲህ ነው እንዲህ ነው ብዬ እሱን ለመውቀስ አልፈልግም፡፡ እኔ ከወደቀ እና ከሞተ ጋር መታገል አልወድም፡፡ ከመንግሥቱ ኃ/ማርያምም ጋር ከኃይለ ሥላሴም ጋራ! አንድ ጊዜ ከሄዱ በኋላ ከነሱ ጋር መታገል አያሻም፡፡ መታገል ኃይል ካለው፤ ሊያናግርህ ሊያነጋግርህ ከሚችል ኃይል ጋር ነው፡፡ ከሌለ ኃይል ጋራ ስለሱ ስላለፈው ነገር ማውራቱ

ምንም ጥቅም የለውም፡፡

Page 5: Semayawi1/Newly formed political party the blue (Semayawi)  founder, Professor Mesfin Wolde Mariam

አሉ፡፡ ከክልላዊ ማዕቀፍ ይልቅ ኢትዮጵያዊ ብሔራዊ ስሜትን የሚያጐሉ እርምጃዎችን እየወሰዱ እንደነበርም በቁጭት ያነሳሉ፡፡ በህይወት ኖረው ቢቀጥሉ ኖሮ የብሔር ፖለቲካውንና በዚሁ ላይ የቆመውን አወቃቀር እያሻሻሉት በሂደት እየቀየሩት ይሄዱ ነበር ብለው የሚያስቡ አሉ፡፡ እዚህ ላይስ የርስዎ አስተያየት?

ኘሮፌሰር መስፍን፡- ምን እላለሁ በዚህ ላይ? ምን አውቃለሁ? እነዛ የሚያውቁ ሰዎች የሚያውቁትን ነገር ሲነግሩን ምናልባት እንነጋገር ይሆናል፡፡ እኔ ምንም አላውቅም፤ ስለዚህ የሰማሁት ነገር የለም፡፡ እኔ መለስ በሚያደርጋቸው ነገሮች በሚናገራቸው ነገሮች ባለፉት 21 ዓመታት ውስጥ ብዙ ብያለሁ፣ ፅፌያለሁ፣ ተናግሬያለው፡፡ እና አሁን መለስ የለም! መለስ ከሞተ በኋላ እንዲህ ነው እንዲህ ነው ብዬ እሱን ለመውቀስ አልፈልግም፡፡ እኔ ከወደቀ እና ከሞተ ጋር መታገል አልወድም፡፡ ከመንግሥቱ ኃ/ማርያምም ጋር ከኃይለ ሥላሴም ጋራ! አንድ ጊዜ ከሄዱ በኋላ ከነሱ ጋር መታገል አያሻም፡፡ መታገል ኃይል ካለው፤ ሊያናግርህ ሊያነጋግርህ ከሚችል ኃይል ጋር ነው፡፡ ከሌለ ኃይል ጋራ ስለሱ ስላለፈው ነገር ማውራቱ ምንም ጥቅም የለውም፡፡ ተናግሬዋለሁ ደግሞ! ያልተናገርኩት ነገር የለም፡፡ መለስ ባደረጋቸው ነገሮች ሁሉ፤ በተናገራቸው ነገሮች ሁሉ እሱ ባለበት ጊዜ ተናግሬዋለሁ፡፡ እና አሁን ትርፍ ነው፡፡ እንደ ስብሐት ነጋ አልሆንም! ማለት…. ማንትሴ ሞተ ማንትሴ

ሞተ መለስም ሞተ! የሚባለው ነገር…. እኔ እንደዛ ዓይነት ድረስ አላወርደውም፡፡ እ…. ግን….የለም አሁን፡፡ በሌለበት ይሄን አደረገ- ይሄን አደረገ- ይሄን አደረገ ብለን መነጋገሩ ለኔ ለህሊናዬ ምንም ዋጋ የለውም፡፡

ሰማያዊ፡-ከአቶ መለስ ሞት በኋላስ የኢህአዴግና የኢትዮጵያ ዕጣ - ፈንታ ምን ሊሆን ይችላል?

ኘሮፌሰር መስፍን፡- ይሄ….. በምን?…. እኔ….አላውቀውም በውነቱ፤ ጠንቋይ አይደለሁም! ነገሩ….. ሰዎች ሁላችንም በጐ መንፈስ ካደረብን ብዙ ነገር ካለፉት 21 ዓመታት ልንማራቸው የምንችላቸው ነገሮች አሉ፡፡ የመለስ ሞት ራሱ ያስተምረናል-ሁላችንንም! የኢህአዴግም ሌሎቹንም ያሉትን ባለሥልጣኖች ይሄ ሊያስተምራቸው ይገባል፡፡ የአቡነ ጳውሎስ አለመኖር ሊያስተምር ይገባል- ሌሎቹን ጳጳሳት፤ ሌሉቹን መንፈሳዊ መሪዎች! እና እንዲህ ነው፡፡ ዕድሜያችን በጉልበትም እንኳን በሃይለኞችም እንኳን ባይቀጭ፤ ኃይለኞችም ብንሆን ጉልበተኞችም ብንሆን፤ ከላይ ደሞ የሚመጣ ያንኑ ህይወት የሚቀጨው ሞት አለ-ሁልጊዜ፡፡ በተፈጥሯችን ሰው በመሆናችን ያለ ነገር ነው፡፡ ስለዚህ በጐ መንፈስ በላያችን እንዲያድር ብናደርግ፣ መርዝ ለመንዛት ባንጥር! ምሳሌ፡- የአቶ ኃ/ማርያም ደሳለኝን ጠቅላይ ሚኒስትርነት ተመልክቶ ስብሐት ነጋ ይሄ ሆነ ብለን ያደረግነው እና የጠቅላይ ሚኒስትርነቱን ወንበር ከኦርቶዶክስ እና ከአማራ እንዲወጣ

ለማድረግ ያደረግነው ነው አለ፡፡ ይሄ አባባል መርዝ ነው፡፡ መርዝነቱ እንዴት ነው…. ኃ/ማርያም ደሳለኝ ማነው ብለው ለማያውቁ ሰዎች ኃ/ማርያም ደሳለኝ አማራ አይደለም፤ ኃ/ማርያም ደሳለኝ የኦርቶዶክስ ክርስቲያን አይደለም ብሎ ለማወጅ ነው ስብሐት ነጋ የፈለገው፡፡ እነዚህን ሁለት አስፈላጊ ያልሆኑ ነገሮች ለማወጅ ደግሞ አማራን እዛ ውስጥ አስገብቶ ይጨፈልቀዋል፡፡ ያንን ጥላቻውን ያመጣል፡፡ ይሄ መርዝ ነው- ሁለቱም! ኃ/ማርያም ኦርቶዶክስ ሆነ አልሆነ፤ አማራ ሆነ አልሆነ እኔ እንደሚመስለኝ ለኔ ጉዳዬ አይደለም፡፡ በፍፁም! ከሚዛን ውስጥ የሚገባ አይደለም ሁለቱም፡፡ ሚዛን ውስጥ የሚገባው እንዴት ነው? ለምሳሌ፡- ሃይማኖቱ ሚዛን ውስጥ ሊገባ ይችላል፡፡ በኃ/ማርያም ደሳለኝ በራሱ አንደበት ያነበብኩት እኔ እውነት ከሆነ፣ እውነት ብሎት እንደሆነ እውነት ተናግሮት እንደሆነ ‘ለእናቴ እፀልያለሁ አልዳነችም’ የሚል ነገር አንብቤያለሁ ይመስለኛል፡፡ እንግዲህ ይሄ በጣም በጣም አስደንጋጭ ነው! እንኳን ለአንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ለአንድ መደበኛ ፖለቲከኛም እንደዚህ ዓይነት አስተሳሰብ እንደዚህ ዓይነት አስተያየት አደገኛ ነው፡፡ እናቱን፣ ኃ/ማርያም ብለው ስም ያወጡለትን ሰው ‘አልዳኑም…. እኔ ድኛለሁ!’ …. በዛ ሂሳብ 99.9 የኢትዮጵያ ህዝብ አልዳነም- ከኃ/ማርያም ደሳለኝ ጋራ፡፡ ያ አደገኛ ነው፡፡ ይሄ ዳነ አልዳነም አደገኛ ነው፡፡ ነገር ግን የእግዚአብሔር ስም በማይጠራበት ቦታ ላይ እግዚአብሔርን የሚያምን ሰው፣ ፈሪሃ-እግዚአብሔር ያለው ሰው እዛ መቀመጡ

ቅጽ 1 ቁጥር 1 ጥቅምት 2005 ዓ.ም

5

ወደ ገጽ 18 ዞሯል

Page 6: Semayawi1/Newly formed political party the blue (Semayawi)  founder, Professor Mesfin Wolde Mariam

አይዞህ አትደንግጥ! ልብህ አይሸበር! እንዲህም አትሸማቀቅ! ግራ-ቀኝህን በጥርጣሬና በፍራቻ መቃኘትም አያሻህ! እረ አትገለማመጥ! እንዲህ መርበድበድ ምንድነው? በቅድሚያ ጽሁፉን አንብበህ ጨርስና ከዚያ በኋላ የራስህን/የራስሽን አቋም ትወስዳለህ፡፡ ጽሁፉን በሙሉ ሳታነብ ግን ቸኩለህ አትደምድም፡፡ ከስህተት ላይ ትወድቃለህና! የጅብ ችኩል ቀንድ ይነክሳልና! የብዙዎቻችን ችግርስ ምን ሆነና?! ይኸው በወሬ እና በስሚ-ስሚ እየተፈታን ብሎም እየተነዳን አይደለ እንዴ በዘመናችን ሁሉ የተቀለደብን?! ጦር ከፈታው ወሬ የፈታው! እንዲል ተረቱ፡፡ ስለዚህ “አንድን መጽሐፍ በሽፋኑ ብቻ አትፍረደው!” /Never Judge a book by its cover/ እንደሚባለው የፈረንጆቹ አባባል በርዕሱ ብቻ ተመርተህ የጽሑፉን ጭብጥ እንዳገኘኸው ሆኖ አይሰማህ፡፡ ርዕሱ ቁንጽል ሀይለ-ቃል ብቻ ነው፡፡ ቁም-ነገሩን በዝርዝሩ ውስጥ ነው የምታገኘው፡፡ “ሰይጣኑ ያለው በዝርዝሮቹ ውስጥ ነው” /The Devil is in the details/ ይላሉ ፈረንጆች ስለአንድ ጉዳይ አብጠርጥሮ ለማወቅ፤ ነገሩን በዝርዝር እና በጥሞና መመርመር እንደሚያስፈልግ ሲያስገነዝቡ፡፡ አለበለዚያ የአገራችን ቀደምት ሊቃውንት አዋቂ-መሳይ አላዋቂን እንደሚሰይሙት “ጥራዝ-ነጠቅ” መሆን ይከተላል፡፡ በጥራዝ-ነጠቅነት ደግሞ መፍትሄ አይገኝም፡፡ እንኳንና መፍትሄ ጉዳዩን በቅጡ መረዳትም አይኖርም፡፡ በመሆኑም ርዕስ አንጠልጥሎ ጭብጥ ጥሎ፤ የሚደረግ ውይይትና ንግግር አሊያም ገረፍ-ገረፍ ንባብ የባሰ መደናበር እና ግራ መጋባትን በማስከተል የጉዳዩን ውል ያሳጣናል፡፡

በዚህም ማናችንም አንጠቀምም፡፡

ለማንኛውም ወደ ርዕሰ-ጉዳዩ በቀጥታ ልሂድና ለማለት የፈለግኩትን ልበል፡፡ አትነሳም ወይ?! ከእንቅልፍ ነው? ከሞት ነው? ከሞት ከበረታ ድንዛዜ ነው? ፎቶ ነው? ራጂ ነው? ክርስትና ነው? …. በክፉ ነው የምትነሳው? በደግ ነው የምትነሳው? በትንሳዔ-ሙታን ነው የምትነሳው? በምንድነው የምትነሳው? ለምንድነው የምትነሳው? ወዴት ነው የምትነሳው? መቼ ነው የምትነሳው? እንዴትስ ነው የምትነሳው?

መቼም ኢትዮጵያውያን በባህላችን ብልፅግና የተነሳ አንድ ትልቅ ሰው ወይም አረጋዊ ከውጭ መጥቶ ወደቤት ውስጥ ሲገባ ከተቀመጥንበት ብድግ ብለን ተነስተን “ኖር! ኖር!” እንላለን፡፡ ምላሹም “በእግዜር!” አሊያም “እረ በልጆቻችን!” ይሆናል፡፡ ታዲያ አንተ ወንድሜስ ለእንዲህ ዓይነቱ የትልቅ ሰው አክብሮት የሚገባውን መነሳት ነው የምትነሳው? ማለቴ-ክብር ለሚገባው ክብርን ለመስጠት፡፡ አሊያስ ከወደቅህበት ረግረግ እና ረመጥ ውስጥ ነው የምትነሳው?

ወይ ኪስህ ወይ ቀኑ ጐደሎብህ፣ ወይ ርቦህ አሊያም ታመህ፣ ወይ ደክሞህ ፣ ወይ መሄጃ አጥተህ፣ ወይ ጭንቀትህን ማራገፊያ ወይ ጊዜህን ማሳለፊያ አጥተህ፣ ወይ ድህነትን አሊያም ጭቅጭቅን ሸሽተህ፣ ወይ ሰክረህ ወይ አብደህ ከየአውራ-ጐዳናዎቹ ጥጋጥግ እስከ ጫት ቤቶች ምንጣፍ እንዲሁም ከየካቲካላ ቤቶች ደጃፍ እስከምናምንቴ ‘አልጋ-ቤት’ ተብዬዎች ፍራሽ የተረፈረፍከው ወጣት አወዳደቅህ ምንኛ አሳዛኝ እና ታላቅ ኖሯል?!

ኦ ወንድሜ …. ከዚህ የበለጠ ውድቀትስ ምን አለ; በቁም ከመሞት የበለጠ ሞትስ በወዴት አለ; አደራ-አልሞትኩም ብለህ ራስህን እንዳታታልል፡፡ ሰው ከፈጣሪው ከእግዚአብሔር ዓላማ የተለየ ዕለት ሞቷልና! የእግዚአብሔር ዓላማ ላንተ ደግሞ መልካምና ያማረ እንጂ የተዋረደና የረከሰ አይደለም፡፡ የእግዚአብሔር ዓላማ አንተ፣ እኔ፣ እሷ፣ ሁላችን በጥሩ ጤንነት፣ በረከት፣ ነፃነት እና ክብረት እየተዋደድን ብሎም እየተሳሰብን በፍቅር እንድንኖር እንጂ በአምባገነኖች እና በሱሶች ተረግጠን ከእግራቸው መረገጫ በታች አይወድቁ አወዳደቅ ወድቀን በግፍ እንድንገዛ አይደለም፡፡ ከቶም የእግዜአብሔር ዓላማ ይኸ ሆኖ አያውቅም! በአምሳሉ ለፈጠረን ውድ ልጆቹ እግዚአብሔር ይኼን አይመኝልንም፡፡ ይህ የጨለማው የዚህ ምድር ገዢ የክፉው ሀሳብ ነው፡፡

ከድቅድቅ ጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃን ሊያወጣህ ደግሞ እነሆ የብርሃናት አምላክ የሆነው እርሱ በደጅህ ቆሞ ይጠራሃል፡፡ እውነት ያናግርሃል፤ ህይወት ኑርብኝ! እያለ ይጋብዝሃል፤ መንገድ ና! ተጓዝብኝ! ይልሃል፡፡ አዎ-አምላክህ ይጠራሃል! ፈጠን ብለህ አቤት! በለው፡፡ የልብህን በር ወለል አርገህ ክፈትለት፡፡ “ተነስተህ ሂድ! እምነትህ አድኖሃል” እንዲልህ” ሽባነትህን እንዲፈውሰው ከወደቅህበት እንዲያነሣህ ፈጥነህ ታዘዝ፡፡

አንቺስ እህቴ፡- ከወደቀው ጋር አብረሽ የምትወድቂ ውዳቂ የሆንሽው ከቶ ስለምንድነው? የወደቀውን እንደማንሳት አንቺ የቆምሽውን ሲጥልሽ መንፈስሽ የማይቆጣው ህሊናሽ የማይቆጠቁጠው በምን የተነሳ ነው? ስጋሽ እህል በራበው ቁጥር ከህሊናሽ እምነትሽን ቆርሰሽ እያበላሽው እስከመቼ ከራስሽ ጋር ተጣልተሽ ትዘልቂያለሽ? አምላክሽስ ምን ይላል? ከመብልስ ነብስ እጅጉን አይበልጥምን? ከልብስስ ሰውነት አይሻልምን? ታዲያ አስቀድመሽ ጽድቁንና መንግሥቱን አለመሻትሽ ስለምንድነው? ሌላው ሁሉ እንደሚጨመርልሽ ዘንግተሽው ነው? ለልብስና ለመብል ስትይስ እስከመቼ ነፍስሽንና ሰውነትሽን አራቁተሽ የአምላክሽን ትዕዛዝ ተላልፈሽ ትኖሪያለሽ? እኒያ ደጋግ እናቶችሽ ያወረሱሽ የመንፈስ ቅርስ ይሄ ነውን; እምነትን መብላትስ የመልካም ሴት ምግባር ነውን? ለዚች አጭር ምድራዊ ህይወትስ ዘላለማዊቷን ነፍስ መቨጥ ይገባልን? ለሚያልፍ ችግር ብለሽ ንፁህ ማንነትሽን ማጉደፍስ ተገቢ ነው? የሰውነት ክብርን ወደ ሸቀጥነት ተራ አውርዶ ለገበያ ማቅረብና ነውርን መነገድስ ለህሊና እረፍት ይሰጣል?

በሰው ውርደትና ስቃይ ሰይጣናዊ እርካታ ለማግኘት ሲባል የአምላክ ፍጡርን በገንዘብ የሚሸጥ የሚለወጥ ቁስ ደረጃ አሽቀንጥሮ ቁልቁለቱ ላይ መጣልስ ከሰብዓዊነት እና ከወንድማዊነት ይጠበቃል? የፈጠረን አምላክ በፈቀደልን መንገድ ላይ ትዕዛዙን አክብረን በጥንቃቄ ብንጓዝ ኖሮስ ከቶ ይቸግረን ነበር? ፈጣሪያችን የሰጠንንስ የሚከለክለን ማነው?

“ለምኑ ይሰጣችሁማል! ፈልጉ ታገኙማላችሁ! መዝጊያን አንኳኩ ይከፈትላችሁማል፡፡ የሚለምነው ሁሉ ይቀበላልና! የሚፈልገውም ያገኛል! መዝጊያንም ለሚያንኳኳ ይከፈትለታል፡፡ ወይስ ከእናንተ ልጁ እንጀራ ቢለምነው ድንጋይን የሚሰጠው ከእናንተ ማን ሰው ነው? ዓሣስ ቢለምነው እባብን ይሰጠዋልን? እንኪያስ እናንተ ክፉዎች ስትሆኑ ለልጆቻችሁ መልካም ስጦታ መስጠትን

አትነሳም ወይ?!

አናንያ ሶሪ

ቅጽ 1 ቁጥር 1 ጥቅምት 2005 ዓ.ም

6

Page 7: Semayawi1/Newly formed political party the blue (Semayawi)  founder, Professor Mesfin Wolde Mariam

ካወቃችሁ በሰማያት ያለው አባታችሁ ለሚለምኑት እንዴት አብልጦ መልካም ነገርን ይሰጣቸው? እንግዲህ ሰዎች ሊያደርጉላችሁ የምትወዱትን ሁሉ እናንተ ደግሞ እንዲሁ አድርጉላቸው! ሕግም ነቢያትም ይህ ነውና፡፡”

ታዲያ ዛሬ እኛ፡- ሰዎች እንዲያደርጉልን የምንወደውን ነው ለሰዎች እያደረግን ያለነው? ለሰዎች ቀና ቀናውን እናስባለን? እንደግፋቸዋለን? ወይስ እንጠልፋቸዋለን? እንረማመድባቸዋለን ወይስ እናራምዳቸዋለን? በሰው ስቃይ እናዝናለን ወይስ ሀሴት እናደርጋለን? እዚህ ሁሉ የሞራል አዘቅት ውስጥ ሆነንስ የምንለምነውን መቀበል፣ የምንፈልገውን ማግኘት፣ የምናንኳኳውን ማስከፈት ከቶ ይቻለናልን? ልባችን ሳይለወጥ፣ ከአምላካችን ጋር በንስሃ ሳንታረቅ በያዝነው የመሸነጋገል እና የማታለል ብሎም እውነታውን የመካድ ጠማማ መንገድ ከቀጠልን ጉዟችን ሁሉ መጨረሻው ተያይዞ የመጥፋት ገደል ነው፡፡ እርስ በርስ ካልተዋደድን፣ ካልተዛዘንን፣ ካልተረዳዳን በምን ተዓምር ኑሯችን ሰላምና ፍቅር ይኖረዋል? በምን ተዓምርስ በሃጢያት ድካም ከወደቅንበት ትቢያ ላይ እንነሳለን?

‘እኔ ምን ጐደለብኝና? ምንስ አገባኝ? ከራስ በላይ ንፋስ!’ እያልክ እንደሰነፍ ከንቱ ሰው አትዘናጋ፡፡ አንተ ብቻህን የምትኖር ደሴት አይደለህም፡፡ ወንድም፣እህት፣ ጓደኛ፣ ጐረቤት፣ ሚስት፣ ልጅ፣ ወገን፣ ዘመድ-አዝማድ፣ የሙያ አጋር፣ የሥራ ባልደረባ ያለህ፣ የፍጥረት አቻህ የሆኑ የሰው ልጆች በሞላ የምትኖርበት ምድርን አብረው የሚጋሩህ ማህበራዊ-ፍጡር ነህ፡፡ ብቻህን ልትደሰት አትችልም፤ ስታዝንም ስትደሰትም ሰው ትሻለህ! “ሰው ብቻውን ይሆን ዘንድ መልካም አይደለምና” ብሏል መፅሐፉም፡፡ በመሆኑም ከቤተሰብ እስከ ማህበረሰብ ድረስ በተለያዩ ውስብስብ የማህበራዊ ድርና-ማጐች (social fabric) የተሳሰርን ስንሆን፣ በአንድም ሆነ በሌላ መልኩ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የአንዱ ማጣት ማዘንና መከፋት ሌሎቻችንን የሚነካን ፍጥረቶች ነን፡፡ አካባቢያችን ተተራምሶ ቤታችን የሰላም ሰገነት ሊሆን አይችልም፡፡ ስለሆነም፡- ከቤት እስከ ጐረቤት፣ ከሰፈር እስከሃገር፣ ከሃገር እስከ አህጉር፣ ከአህጉር እስከዓለም፣ ድረስ የማያገባን ጉዳይ የለም፡፡ ይመለከተናል!

የወንድምህ ጐዳና ላይ መውደቅ የአንተ ቤተሰባዊነት እና ኢትዮጵያዊነት መዋረድ ነው! የእህትህ በየባዕድ አገራቱ ጐዳና ላይ ለገበያ መቅረብ የቤተሰብህ እና የአገርህ አንገት መደፋት ነው! የአገርህ መራብ እና መረገጥ እንዲሁም እጅግ ኋላ-መቅረት እግርህ በረገጠበት የዓለሙ ዳርቻዎች ሁሉ መታወቂያህ እና ማፈሪያህ ነው!

ታዲያ አንተ ወንድሜ ራስህን እንደሰጐን አሸዋ ውስጥ ቀብረህ የእውነታውን ዓለም እያየህ እንዳላየህ ሆነህ የምትኖረው እስከመቼ ነው? እውነታው እንደሆነ

አፍጥጦ አፍንጫህ ድረስ መምጣቱን አይተው! በዛች በተሸጐጥክባት ጠባብ ቢሮ ውስጥ ተወስነህ የሚከናወኑ ደባዎችን እየተመለከትህ አንደበትህን ለጉመህ፣ ህሊናህን ጠፍረህ፣ ለእንጀራህ ስትል ብቻ ዝም ማለትህ በስተመጨረሻ ላንተስ ይበጅ ይመስልሃል? የሙያ ስነ ምግባርህ የሚያዝህስ ከመቃብር የሚያስፈራ ዝምታን ነውን? እረ እልፍ በል! ያንተ ፍፃሜ ይኼ ብቻ አይደለም፡፡ ተቀጥሮ ደሞዝ ከመብላት ባለፈ በሙያህ ለማህበረሰብህ የምታበረክተው ውድ ስጦታም አለ፡፡ ወንድሜ፡- በስጋ ለመኖር ስትል በነፍስህ አትሙት! ነፍስህ ደግሞ እውነትን ማወጅ ትወዳለች! ነፃነትን ትጠማለች! ፍትህን ትናፍቃለች! ፈጠራን ታፈልቃለች! አዲስ ነገርን ትሻለች! ታዲያ አንተ ወንድሜ፡- ስለምን ነፍስህን ትጨቁናታለህ? እስከ መቼስ ነፍስህ እሆድ-ዕቃህ ውስጥ እንደወደቀች ትቀራለች? አትነሳም ወይ?!... ነፍስህ! አትነሳም ወይ?!… አንተ!

ኑሮ እጅ-እጅ ያለህ እና ያንገፈገፈህ አንተ ሥራ-አጥ ወጣትስ እስከመቼ የምስኪኗን እናትህን የመሃረብ ቋጠሮ የምታስፈለቅቅ ብኩን የወጣት-ተጧሪ ትሆናለህ? ይሄ ቀንስ መቼ ነው የሚያልፈው? 4ኪሎና ጊዮርጊስ እየተመላለስክ በየሥራ-ማስታወቂያው ግድግዳ ላይ እንጀራህን ስትፈልግ የምትንከራተተው እውነት ላንተ ሥራ ጠፍቶ ነው? የተማርክበት የትምህርት ፖሊሲ የመጨረሻ ግቡ አንተን ሥራ-ፈላጊ ተንከራታች ማድረግ ነውን? ወትሮውንስ ይህ ከሆነ ዓላማው ጊዜህን ለምን በትምህርት ቤት አሳለፍክ? አፍላውን የወጣትነት ዕድሜህን በነፃነት ለሥራ እንድትጠቀምበት ያልቻልከውስ ከምን የተነሳ ነው?

የዴሞክራሲ፣ የነጻነት፣ የእኩልነት፣ የብልጽግና፣ እንደልብ የመናገር፣ ሀሳብን የመግለፅ፣ ሠርቶ ጥሮ-ግሮ የማደግ ተስፋን በየዕለቱ እየመገቡህ እና እነዚህን ሁሉ እንደሚሰጡህ እየማሉና እየተገዘቱ ቃል የገቡልህ መሪዎችህ አንዳቸውን እንኳ በቅጡ ሳይለግሱህ ወሽመጥህን ቆርጠው እነርሱ በተደላደለ መንበራቸው ላይ

ከተቀመጡ ይኸው 21 ዓመት ሆናቸው፡፡ አንተስ? አንተና አንቺ የ21 ዓመት ወጣት የሆናችሁት ብላቴኖችስ? በዚህ ዕድሜያችሁ ምን አላችሁ? ምን ጥሪት ቋጥራችኋል? ሥራ-አለሽ? ገቢ አለህ? ኑሮህ/ሽ ዋስትና ያለው ዘላቂ ነው? ወይንስ እንደቁማር የዕድል ኑሮ ነው? ‘ ባገኝ በልቼ ባጣ ተደስቼ’ የሚሉት ዓይነት ይሆን ህይወትህ? የአየር-ባየር ኑሮ የሚያዋጣው ታዲያ እስከመቼ ነው? አንተ እና አንቺ ተመልካች፤ ሌሎች ኗሪ የሆናችሁት እረ ስለምንድነው? አይበቃህም የግፍ አገዛዝ? አይበቃሽም የግፍ አገዛዝ? አልተንገሸገሻችሁም?የጉልቤ-አስተዳደር አላስመረራችሁም? አላሳደዳችሁም? አላሰደዳችሁም? በኢኮኖሚ-የዘር-ማጥፋት እና በኢኮኖሚ-አፓርታይድ እንደቅጠል አላረገፋችሁም? ወላጆች፡- የልጆቻችሁን የፍላጐት ዓይኖች በመሸሽ አልተሳቀቃችሁም? ልጆችስ፡- የወላጆቻችሁን ከቀድሞው የክብር ደረጃ መዋረድ እና መጎሳቆል ላለማየት ቤቱ አላስጠላችሁም? የጐረቤቱ ማባሪያ-የሌለው ጭቅጭቅና አለመተማመን ነብሳችሁን አላሰቀቃትም?

ንገሩኝ እስቲ እናንት የ21 ዓመት ወጣቶች? እስቲ ሳትፈሩ የልባችሁን አውጉኝ! የልጅነት ህልማችሁን በእውን እየኖራችሁት ነው? የልጅነት ህልማችሁንስ ማን ሰረቀው? ራዕያችሁን ማን ሰለበው? ትልቅ እንዳትመኙ በትናንሽ ‘ሥራዎች’ የጠመዳችሁ ማነው? እናንተስ ቻይና ሄዶ መማር፣ ዘመናዊ መኪና መንዳት፣ በምቹ ቤት ውስጥ መኖር፣ በውጭ ንግድ መሠማራት፣ አስመጭና ላኪ መሆን፣ በጥሩ አለም-አቀፍና አገር-አቀፍ መሥሪያ-ቤቶች ውስጥ በወፍራም ደሞዝ መቀጠር፣ ኑሮን ማደላደል፣ መልካም ምግብ መመገብ፣ ያማረ መልበስ፣ ከከተማ ወጣ ብሎ መዝናናት፣የንግድ ድርጅት ማቋቋም፣ በነፃነት መመራመር፣ ትዳር መያዝ፣ ልጆች ማፍራት፣ ጥሪት መቋጠር አይወድላችሁም? እናንተ የእንጀራ ልጆች ናችሁ? ለዚህ ሁሉ ክብርና ማዕረግስ ያልተገባችሁ የሰው-መናኛ የምርጦች-ትራፊ ናችሁ? እናንተ ለለቅሶ፣ለድጋፍ ሰልፍ፣ ለጦር-ግንባር አሊያም ለኮብልስቶን

ቅጽ 1 ቁጥር 1 ጥቅምት 2005 ዓ.ም

7

ኢህአዴግ ሆይ፡- ለራስህ ስትል ጣፍጥ አሊያ ድንጋይ ነው ብለን ወደደጅ አውጥተን

እንጥልሃለን!

ወደ ገጽ 24 ዞሯል

Page 8: Semayawi1/Newly formed political party the blue (Semayawi)  founder, Professor Mesfin Wolde Mariam

የሰው ልጅ በጊዜያቶች መቀያየር ያመጣውን የዲፕሎማሲ ዘመን ከማግኘቱ በፊት ያለፈበት የእንስሳዊ ባህሪ ነበረው ይህም የሰው ልጅ የመጀመሪያው ማህበራዊ አኗኗር ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ እስከ አሁን ያለውን ጊዜ ያጠቃልላል የሰው ልጅ ማህበራዊ ህይወት ጀምሮበታል የሚባለው ጊዜ አደን እያደኑ መብላት ከጀመሩበት ጊዜ አንስቶ ነው አብዛኛዎቹ ሣይንቲስቶች ሰዎች ይሏቸዋል አንዳንድ ሣይንቲስቶች ግን ሰው ነበሩ ለማለት ያዳግታል ይላሉ

ይህ የሰው ልጅ ፍራፍሬ ለቅሞ ከመብላት ወደ አደን የተሸጋገረበት ጊዜ ነበር አደን ለብቻ አስቸጋሪ የሚፈለገውን ውጤት ለብቻ ሆኖ ከማግኘት አንፃር አዳጋች ከመሆኑም በላይ ሊያጠቃ የመጣን አውሬ ለሁለት ለሶስት ሆኖ መከላለከል ተመራጭ ስለነበር መተጋገዝ የተጀመረው በዚህ ጊዜ ነው እንደሚታወቀው ቀደም ባለው ሂወታቸው ፍራፍሬ ለቅሞ መብላት የቡድን ህብረትን የማይጠይቅ እንዲሁም ከአውሬ ራስን ለመከላከል በአራት እግር ይጠቀሙ ስለነበር ማለትም ሁለት እጃቸውንና ሁለት እግራቸውን ሮጠው ዛፍ ላይ በመውጣት ያመልጡ ነበር ከዚህ ሁሉ ጊዜያት መቀያየር በኃላ እንግዲህ እነዚህ አዳኝ ሰዎች የተፈጠሩት ከአደን መልስም የታደነውን የአውሬ ስጋ ቀስ በቀስ እያበሠሉ መመገብ ጀመሩ ይህ ክስተት የሰው ልጅ እሣት ከፈጠረበት ጊዜ ጋር የሚያያዝ ነው፡፡ ይህ ቀን ቀን ምግብ ለማብሰልና ፀሀይ ስትጠልቅ ደግሞ የብርድ ቆፈን እጅና እግርን ሲቆላልፍ እራስን ከብርድና ከአውሬ ለመከላለከል የሚከቡት እሳት የመገናኘታቸውን አንድ ላይ የመተሣሠራቸውን ባህል አሠፋው ይህ ልማድ እያደገ ሄዶ ቤተሠብ እስከመመስረት ማህበረሰብ ሠፈር እያለ ሀገር የሚለው ደረጃ ላይ ደረሰ የሰው ልጅ በዚያን ጊዜ እሣት ባይኖር ኖሮ እንደ አንዳንድ ሳይንቲስቶች አገላለፅ አሁን የሰው ዘር ላይገኝ የሚችልበት እድል ሊኖር ይችል ነበር

ኢትዮጵያዊ እሣት!!

ታዲያ ሀገራችን በአሁን ወቅት ልክ ይህ እሣት የዛን ጊዜ ሰዎች እንደታደጋቸው እኛም እዚህ እንድንገኝ ምክንያት እንደሆነን ሀገራችንንም የሚታደርጋት አንድ ሀይል በአሁን ሰአት ያስፈልጋታል ኢትዮጵያዊ እሳት ልክ እንደቀድሞው ሰዎች በዙሪያው ከበን የምንወያይበት ከአደጋ የምናመልጥበት መሸሸጊያ ማኩረፊያ ማለት ነው ይህ ኢትዮጵያዊ እሣት ግለሠብ ሊሆን ይችላል ድርጅት ሊሆን ይችላል ነገር ግን በእውነት እና በእውቀት ላይ የተመሠረተ አላማ ያለው በጎ አሣቢ የተጣላውን አስታራቂ የተሰደደውን ሠብሣቢ ለእውነት የሚሞት ጀግና ሀገራችን ትፈልጋለች ይህን ኢትየጰጵያ እሣት ለማቀጣጠል የሚችለው ማንም ሊሆን ይችላል ነገር ግን ህዝባዊ ተቋማትና ድርጅቶች እንዲሁም ትልቅ የሚባሉት በዙሪያቸው ብዙ ህዝብን ያስከተሉ ግለሰቦች ከፍተኛውን ድርሻ ሊወስዱ ይችላሉ ይህም ከፍተኛ ሀላፊነት ጋር አብሮ የሚመጣ ነው በዙሪያቸው እሣቱን ሊሞቅ የሚመጣውን የሰው ቁጥር ማብዛት ወይም የራሳቸውን ሀሳባዊ ፖለቲካ ማስፈን ሳይሆን የቆሙለትን አላማ ማሳካትና በጎ ነገር ለሀገር ማበርከት መሆን አለበት አለበለዚያ ይህ እሣት ለነፍሳችን መዳን ለሀገራችን መታደጊያ ከመሆኑ ይልቅ አጥፊነቱ ሊያመዝን ይችላል መጠንቀቅና ትልቅ ሀላፊነትን መውሰድ ያስፈልጋልይህ ኢትዮጵያ እሳት እስከዛሬ በሀገራችን ሊቀጣጠል ያልቻለበትን ምክንያት በሶስት ከፍን ማወቅ ጠቃሚ ሊሆን ይችላል ለዚህም ያለፉትን ሶስት አይነት የኢትዮጵያ አመራሮችን መመልከት እንችላለን ፡፡1ኛው በነበረው የአመራር ክፍተት እንዲሁም በአጋጣሚዎች ሾልከው ስልጣን ላይ የወጡ መሪዎች ሲሆኑ ያመራር ብቃታቸውም የአስተሣሠብ ደረጃቸውም ሀገር ለመምራት አይመጥንም ነበር ለዚህም ድክመቶቻችውን በአምባገነንነት በከባድ እርምጃዎች ነበር የሚሸፍኑት ስለዚህም ቀርቦ ስህተቶቻቸውን ለማረምም ለመወያየትም እጅግ አስፈሪና የማይታሰብ ነበር ለዚህም እንደ ምሳሌ ጓድ ሻለቃ መንግስቱ ሀይለማርያምን መጥቀስ ይቻላል ነገር ግን በነበራቸው የሀገር ፍቅር እና ወኔ ሀገራቸውን ሣይሸጡ ሣያስደፍሩ አቆይተዋታል፡፡

2ተኛው የመሪዎቹ አቅም ከፍተኛ ሆኖ ሣለ የሚመሩትን ህዝብ በተሻለ የአስተሳሰብ ደረጃ ላይ ማድረስ ያልቻሉ ወይም የህዝቡ አስተሣሠብ ኃላ ቀር የነበረ በመሆኑ የመሪዎችንና የተመሪዎችን አስተሣሠብ አጣጥሞ ለመሄድ አስቸጋሪ ሁኔታዎች የተፈጠሩበት የአመራር አይነት ነው

ለዚህም ምሣሌ አፄ ቴውድሮስን እና አጼ ሚኒሊክን መጥቀስ ይቻላል አፄ ቴውድሮስ በጊዜው ከነበረው ከዘመነ መሳፍንት እኔ ልግዛው እርስ በርስ እልቂት እንዲያወጡና የተሻለች ኢትዮጵያን እንዲፈጥሩ ያስቻላቸው የነበራቸው ሀገራዊ ራዕይና የመምራት ብቃት ነው ይህም ሁሌም ቢሆን በኢትዮጵያ የዐንድነት ታሪክ ውስጥ ትልቅ ስፍራን ያሰጣቸዋል፡፡አፄ ሚኒሊክን ኢትዮጵያውያን ካላቸው ፍቅር አንፃር እምዬ ምኒሊክ ይሏቸዋል፡፡ በአድዋ በሰሩት ታሪካዊ ገድል ጎልተው ቢታወሱም አሁን በየኪሳችን ከተነው ለምንዞረው ስልክ ከቦታ ቦታ ለምንቀሳቀስበት መኪና ከውጭ የሚመጡ እንግዶቻችንን በተንደላቀቀ ሁኔታ የሚስተናገዱበትን ሆቴል የባቡር ትራንስፖርት በየቤታችን ለሚመጣልን የኤሌክትሪክ ብርሀን መነሻው አፄ ሚኒሊክ ናቸው፡፡ ለዚህም ስራቸው በመጀመሪያም ብዙ ተወቅሰዋል፡፡ የሰይጣን ስራ ነው በሚልም በአማካሪዎቻቸው ተመክረዋል ፡፡ ነገር ግን ይህን ምክር ተቀብለው በጨለማ አላስቀሩንም ይልቁን በነበራቸው የተሻለ የአስተሣሠብና የአመራር ብቃት ተጠቅመው ሀገራቸውን ወደ ተሻለ ቦታ አድርሰው አልፈዋል፡፡

3ተኛው የአመራር አይነት የመምራት አቅም የማገናዘብ ችሎት ያላነሣቸው ነገር ግን የመምራት ችሎታቸውንና አቅማቸውን ለመጠቀም ያሉበት ሁኔታ ወይም ስርአት የማይፈቅድላቸው ወይም በጎ ፍቃዳቸው ሲሆን ጥሩ የሚሠሩ ወይም እንደ ሚሠሩ የሚያስመስሉ ናቸው ለዚህም ምሳሌ የቀድሞውን ጠቅላይ ሚኒስቴር መለስ ዜናዊን መጥቀስ ይቻላል ምዕራባውያን ጠ/ሚኒስቴር መለስ ዜናዊ ከፍተኛ ያመራር አቅም እንዳላቸው ነገር ግን የተተበተቡበት አብዮታዊ ዲሞክራሲ ያላቸውን ችሎታ አውጥተው እንዲጠቀሙበት አላስቻላቸውም ይላሉ ለኔ ግን ምክኒያቱ ይህ አይመስለኝም አንድን ሀገር በፈለጉት አውጥቶ በፈለጉት ማስገባት ህገ መንግስቱን እንደፈለጉት መተርጎም የትኛውንም ሰው በስልጣናቸው የፈለጉትን ማድረግ የሚችሉ ሰው በአብዮታዊ ዲሞክራሲ መተብተብ ብቻ የአመራር ችሎታቸውን ሊያወጡ አልቻሉም የሚለውን ሀሳብ አልቀበለውም፡፡ ይልቁንም በጎ ነገር ለመስራት ፍቃዳቸው ሣይሆን ቀርቶ እንጂ አብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ እድሜህን በስልጣን ላይ ጨርሰህ ሙት የሚል አይመስለኝም ፡፡

እነዚህ ሶስቱ የአመራር አይነቶች ኢትዮጵያዊ እሳት ማቀጣጠል ባይችሉም ይህ የእሣት ጭላንጭል በሀገራችን መጀመሩን ሣናይ አልቀረንም በድሮ ባህልና ወጋቸው አባቶች ዛፍ ስር ሰብስበው እንደሚመክሩት እንደሚያስትሩት ሁሉ ከተመሰረተ አመት

እሣት!!

ዳዊት ሙሉጌታ

ቅጽ 1 ቁጥር 1 ጥቅምት 2005 ዓ.ም

8ወደ ገጽ 15 ዞሯል

Page 9: Semayawi1/Newly formed political party the blue (Semayawi)  founder, Professor Mesfin Wolde Mariam

በመዲናችን አዲስ አበባ ከሜክሲኮ-ልደታ ወደ ጦር ኃይሎች አደባባይ በሚወስደው በዋና መንገድ በእግርዎም ሆነ በተሽከርካሪ ሲጓዙ ወደ መኮንኖች ክበብ የሚያስገባውን የቀኝ እጥፋት ትንሽ አለፍ እንዳሉ፣ የአገር መከላከያ ሚኒስቴር ዋና በር ጋር ከመድረስዎ በፊት ወታደራዊ የማዕረግ ልብሳቸውን እንደለበሱ የሚታዩ የአንድ ሰው ፎቶግራፍ በትልቁ ተተክሎ ያገኛሉ፡፡ እኚህ ሰው ሜጀር ጄኔራል ሀየሎም አርአያ ናቸው፡፡ ጄኔራሉ በሕወሓት የትጥቅ ትግል ወቅት ከደርግ ጋር በነበራቸው ፍልሚያና መራራ ጦርነት ጠንካራ የጀግንነት ገድል እና የጦርነት አመራር ብቃት መፈፀማቸው ዛሬም ድረስ ይነገርላቸዋል፡፡ ነገም ቢሆን ታሪክ ያወሳቸዋል፡፡ከደርግ ውድቀት ማግስት ጀምሮ እስከ 1989 ዓ.ም. ድረስ ጄኔራል ሀየሎም በኢፌዴሪ የአገር መከላከያ ሚኒስቴር ውስጥ የጦር ኃይል ክፍሉን በበላይነት ከሚመሩት ጄኔራሎች መካከል ግንባር ቀደሙ ነበሩ፡፡ ሆኖም በ1989 ዓ.ም ኦሎምፒያ አካባቢ በሚገኝ አንድ ሆቴል ውስጥ በአንድ ቅጥረኛ ኤርትራዊ ነፍስ ገዳይ በአሳዛኝ ሁኔታ በጥይት ተመትተው ተገድለዋል፡፡ አሟሟታቸውን አስመልክቶ በወቅቱ ብዙ የተባለበት ጉዳይ ነው… የሆነ ሆኖ ከላይ በመግቢያዬ ከገለፅኩት የሜጀር ጄኔራል ሀየሎም ፎቶግራፍ ጐን ‹‹…ጀግና ሁን!›› የሚል ፅሁፍ ሰፍሯል፡፡ትክክል ነው፤ ጀግንነት ያስደስታል፣ ያኮራል፣ ያስመሰግናል… ሌላም ሌላም፡፡ የሀየሎም ንግግር እውነተኛ ነበር፡፡ የሰው ልጅ በምድር ላይ ሲኖር ጀግና መሆን አለበት፡፡ ጀግንነት ተፈጥሯዊ እሴት ነው - በተለይም ለእኛ ለኢትዮጵያውያን፡፡ በዚህም አፄ ዮሐንስንና አፄ ቴዎድሮስን በቀደምትነት እናነሳቸዋለን፡፡ በፋሽስት ጣሊያን ወረራ ወቅት አኩሪ የጀግንነት ገድልን በበላይነት በመምራት

አፄ ምኒሊክንና ባለቤታቸው እቴጌ ጣይቱን ልናስባቸው ግድ ይላል፡፡ የዛሬ 113 ዓመት በአድዋ ጦርነት ላይ ድልን የተቀዳጁ ጀግኖች አርበኞችን፣ ቅድመ አያቶቻችንን እና በዚያን ጊዜ የነበሩትን ህዝቦቻችንን ልናከብራቸውና ልናመሰግናቸው ይገባል - ለዛሬዋ ኢትዮጵያና ህዝቦቿ የአኩሪ ታሪክ መሠረት ስለሆኑም፡፡ ምን ይኼ ብቻ! ዓለም ለጥቁር አፍሪካውያን የነፃነት ተምሳሌት አድርጋን የለም እንዴ?!

‹‹ጀግናው የኢህአዴግ ሰራዊት…››

ሕወሓት/ኢህአዴግ ደርግን ለመጣል አድርጐት በነበረው የ17 ዓመት እልህ አስጨራሽ መራራ ትግል ወቅት ደም ፈስሷል፤ አጥንት ተከስክሷል፡፡ ውድ ሕይወት ተገብሯል፡፡ መራብ መጠማት፣ በበረሃ መንከራተት፣ መታመምና ወድቆ መነሳት… የያኔው ሃቅ ነበር፡፡ አፍላ ወጣትነትን፣ ከቤተሰብ ጋር የመኖር ሕልምን፣ አጓጊው የወጣትነት ፍቅርን፣ ናፍቆትን… መስዋዕትነት አድርገዋል - ታጋይ ወንድና ሴቶች፡፡ …ሁሉም አለፈና ግንቦት 20/1983 ዓ.ም. የመንግስታቶቻችን መቀመጫ የሆነችውን አዲስ አበባን ኢህአዴግ ተቆጣጠራት፡፡ በኢትዮጵያ ሬዲዮ ‹‹የዘመናት ብሶት የወለደው ጀግናው የኢህአዴግ ሰራዊት ደርግ ሲጠቀምበት የነበረውን የሬዲዮ ጣቢያ ተቆጣጥሮታል…›› የሚል የአንድ ታጋይ ንግግር ተደጋግሞ በኢትዮጵያ ምድር ተደመጠ፡፡ምንም እንኳን ህወሓት በየካቲት ወር 1967 ዓ.ም. አላማ አድርጐ ወደ ደደቢት በረሃ ለትጥቅ ትግሉ የገባበትና በመካከል ሲይዛቸውና ሲለቃቸው የነበሩት አላማዎች የተደበላለቁ ቢሆኑም በአፍሪካ አስፈሪ ጦር የነበረውን ደርግን ታግሎ ማሸነፉ ግን ጀግንነት ነው፡፡ከዚያም ስልጣን የተቆጣጠረው ኢህአዴግ በሀገሪቷ ላይ በተለያዩ ነገሮች ለውጥ እንዲመጣ በንግግር፣ በፅሁፍና በተግባር የተገበራቸው ጉዳዮች ነበሩ፡፡ ለአብነት ጥቂቱን ልጥቀስ፡- ሕገ-መንግስትን አርቅቆ ማፅደቅ፣ ሪፈረንደም፣ የሽግግር መንግስት ማቋቋም፣ ብሔራዊ ምርጫ፣ ነፃ ፕሬስን መፍጠር፣ ዴሞክራሲን መገንባት፣ ልማት፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች እንዲኖሩ ማድረግ፣ የብሔር ብሔረሰቦችን መብትና ቋንቋ አረጋግጦ እውቅና መስጠት፣ ከተለያዩ የውጭ አገራት ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ዲፕሎማሲያዊና የሁለትዮሽ ግንኙነት መጀመር ይገኙበታል፡፡ለኢህአዴግ በጥቂቱም ቢሆን የተሳኩለት ነገሮች መኖራቸው አይካድም፡፡ በአንፃሩም ፖለቲካዊ ትርፍና ኪሳራቸው ታይቶ ለአንድ ሉዓላዊት አገርና ህዝቦቿ መሠረታዊ የሆኑ ነገሮች በርተው የጠፉበት ሁኔታም አለ፡፡ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ በሰበብ አስባቡ የጠበቡ ምህዳሮች፣ የተወሰዱ ከባድ እርምጃዎች፣ አይንን በጨው በማጠብ ሽምጥጥ ተደርገው

የተካዱና የተለወጡ አጀንዳዎች ሌላም ሌላም….ባሳለፍነው 21 ዓመታት ውስጥ መኖራቸውን መዘንጋት አይቻልም፡፡በመናገር፣ ሀሳብን በነፃነት በመግለፅ፣ በመደራጀት፣ በመሰብሰብ፣ በምርጫ፣ ድጋፍንም ሆነ ተቃውሞን በአደባባይ በመግለፅ… ወዘተ ዙሪያ ጠርናፊ፣ አሸማቃቂና ነፃነትን የሚጥሱ ሕጐች፣ አዋጆችና ደንቦች በተለያየ አኳኋን ህዝቡ ዘንድ መድረሳቸው ትናንት በገሃድ የታየ እውነት ነው፡፡ ዛሬም አለ፡፡ ነገም ከዚህ በበለጠ ሊቀጥል ይችል ይሆናል፡፡

ዛሬ…ብዙ ነገሮችን በሀሳብ አውጥቼ አውርጄ፤ የሚነበቡ ነገሮችን አገላብጬ፣ የኅብረተሰቡን የዕለት ተዕለት ኑሮን በመመልከት፣ በማድመጥና በመጠየቅ ‹‹አሁን ያለውን ኢህአዴግ በምን ጀግና እንበለው?›› ስል እጠይቃለሁ፡፡ሕገ-መንግስትን አክበሮ በማስከበሩ?፣ የፖለቲካ ምህዳሩን በማስፋቱ?፣ ዴሞክራሲን በየደረጃው ከፍ አድርጐ በማስፈኑ?፣ ሰብዓዊ መብቶችን በአግባቡ በማክበርና በመጠበቁ?፣ ድህነትን ተረት በማድረጉ?፣ በቀን ሶስት ጊዜ ህዝብን በማብላቱ?፣ የተረጋጋ ኢኮኖሚን በመፍጠሩ?፣ ፍትሃዊ የሀብት ክፍፍል እንዲኖር ጤናማ ፖሊሲን በመከተሉ?. . . በየትኛው ይሆን ኢህአዴግ ጀግና መንግስት የሚባለው?! ኧረ ሌላም አለኝ፡፡ኢትዮጵያዊ ባህልና ዕሴቶቻችንን ጠብቆ በማቆየቱ?፣ ከአጓጉል ነገር የፀዳ ትውልድን ፈጥሮ ውጤታማ በማድረጉ?፣ ሥራ አጥነትን በመቅረፉ?፣ ነፃነት የሚሰማው ትውልድን በመፍጠሩ?፣ ‹‹እንከን የለሽ›› ምርጫ በማድረጉ?፣ ሰላማዊ ትግልን በመደገፉ?፣ በምርጫ ቢሸነፍ ስልጣኑን በሰላም ለመልቀቅ ዝግጁ በመሆኑ?፣ ከመንግስት ሥራ አስፈፃሚ አካል ነፃና ገለልተኛ የፍትህ ስርዓትን በማቋቋሙ?… ወዘተ በእነዚህ ሁሉ ለኔ የኢህአዴግ ጀግንነት አይታየኝም፡፡ ይኼ ጨለምተኝነት ወይም ራሱ ኢህአዴግ ብዙ ጊዜ እንደሚናገረው ስርዓቱን የማጠልሸት እኩይ ዕሳቦት አይደለም፡፡ በስርዓቱ ትላንት ያየነው፣ ዛሬ እያየነው ያለውና ነገም ልናየው የምንችለው ነገር በመሆኑ ነው፡፡

‹‹የዴሞክራሲ ኦክስጅን›› አሌክስ ቶኪዊቪል የተባለው የፈረንሳይ የፖለቲካ ፀሃፊ አሜሪካንን ከሁለት መቶ አመት በፊት ሲጐበኝ እንደታዘበው ‹‹ያለዴሞክራሲ እውነተኛ ጋዜጦች ሊኖሩ አይችልም፣ ዴሞክራሲም ያለ ጋዜጠኞች ሊኖር አይችልም›› ሲል ተናግሯል፡፡ በተያያዘም፣ የዩናይትድ ስቴትስ ሶስተኛው ፕሬዚዳንት የነበሩት ቶማስ ጄፈርሰን በ1787 እ.ኤ.አ እንደፃፉት ‹‹የመንግስታችን መሠረት የህዝብ አስተያየት እንደመሆኑ መጠን የመጀመሪያው አላማችን ያንን መብት መጠበቅ ነው፤ መንግስት ያለ ጋዜጣ ወይም

የዛሬውን ኢህአዴግ በምን ጀግና እንበለው?!

በኤልያስ ገብሩ

ቅጽ 1 ቁጥር 1 ጥቅምት 2005 ዓ.ም

9

ወደ ገጽ 16 ዞሯል

Page 10: Semayawi1/Newly formed political party the blue (Semayawi)  founder, Professor Mesfin Wolde Mariam

ሰማያዊ፡- የሰማያዊ ፓርቲ ምሰሶ የሚባሉ ዋና ዋና የሚያራምዳቸው ፖለቲካዊ አቋሞች ምንድናቸው?

ኢ/ር ይልቃል፡- ፖለቲካ በየጊዜው እንደሁኔታው የሚለወጥ፣ የሚሻሻልና የሚያድግ ቢሆንም! ሰማያዊ ፓርቲ ከአጠቃላይ የኢትዮጵያ ታሪክና ካሉብን ችግሮች በመነሳት ዋና ዋና የምንላቸው ነገሮች የሚከተሉት ናቸው፡-

አንደኛ፡- ኢትዮጵያ ውስጥ ለረጅም ጊዜ አብረው የኖሩ የተለያየ ልማድ፣ ባህል፣ ቋንቋ እና እምነት ያላቸው የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የጋራ የወል ስነ-ልቦና አዳብረው በአንድነት የሚኖሩበት አገር ነው ብለን

በአብዛኛው በወጣቶች የተቋቋመው ሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር የሆኑት ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት በተለያዩ ሃገራዊና ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከሰማያዊ ፓርቲ ድረ-ገጽ ጋር ያደረጉት ቃለ-ምልልስ እጅግ አንኳርና አንገብጋቢ ነጥቦችን ይዞ ቀርቧል፡፡ የመጀመሪያውን ክፍል እነሆ ብለናል፡-

እናምናለን፡፡ ይህም ስለሆነ፡- የኢትዮጵያ ፖለቲካ በመሠረቱ ማተኮርና መነሳት ያለበት ከዜግነት እና ከግለሰብ መብት ላይ መሆን አለበት ብለን እናምናለን፡፡ እነዚህም የዜግነት እና ሰብዓዊ መብቶች እስከተከበሩ ድረስ የማይከበር የመብት ዓይነት የለም! ብሎ ነው ፓርቲያችን የሚያምነው፡፡ ከዚያ ውጭ ያሉ መብቶች እንዳሉ እንገነዘባለን፡፡ ባለሙያዎች በሙያቸው ተደራጅተው የሚጠይቁት የጋራ መብት ይኖራቸዋል! ሠራተኞች በጋራ ተሰባስበው የሚጠይቁት መብት ይኖራቸዋል፡፡ ወጣቶችም በዕድሜያቸው፣ ሴቶችም በጾታቸው እንዲሁም የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ባህላቸውን፣ ዕምነታቸውን ለማበልፀግ የራሳቸው መብቶች አሏቸው፡፡ ነገር ግን እነዚህ

ሁሉ መብቶች ከዜግነት እና ከሰውነት መብት በላይ አይደሉም፡፡ በመሆኑም፡- የዜግነት እና የሰውነት መሠረታዊ መብቶች በተከበሩ ጊዜ ሌሎቹ የጠቀስኳቸው መብቶች ሁሉ አብረው ይከበራሉ ብለን እናምናለን፡፡

ሁለተኛውና ዋናው ነገር፡- በኢትዮጵያ ውስጥ ድህነትና ግብርና ላይ የተመሠረተ ኋላ ቀር አኗኗር በመኖሩ! በዚህም ዓይነት የኑሮ ዘይቤ ብዙው የህብረተሰብ ክፍል በገጠሮች ውስጥ የሚገኝና ህልውናውን በመሬት ላይ መሠረት ያደረገ ስለሆነ ይህ የህብረተሰብ ክፍል እንዲያድግ እና ኑሮው እንዲሻሻል ማድረግ የሚቻለው ሙሉ ነፃነቱን በማቀዳጀትና በመሬቱ ላይ ብቸኛ ወሳኝ ተዋናይ ለማድረግ መሬቱን የግል-ንብረቱ እንዲሆን በማስቻል ነው ብሎ ያምናል ፓርቲያችን፡፡ ይሄ በተለያዩ ጥናቶችም የተረጋገጠ ትክክለኛው አቋም ነው፡፡ ነፃነት የሌለው ህዝብ በምንም ዓይነት መንገድ ልማትን እንደማያመጣ! በአገራችን ያሉት ገበሬዎችም ነፃነት እስካላገኙ ድረስ ከኢትዮጵያ ውስጥ ችጋር እንደማይጠፋ የኛም አገር አንጋፋ-ምሁራን ያጠኑት ነው፡፡ ዓለማቀፍ ዕውቅ ምሁራንም ለምሳሌ አማርትያ ሴን (የኖቤል ተሸላሚ ኢኮኖሚስት) በጥናቱ በሚገባ እንዳብራራው ነፃነት ለልማት መሠረቱ መሆኑን ነው፡፡ ኘሮፌሰር መስፍንወ/ማርያምም Suffering under God’s Environment በሚለውና Rural vulnerability to famine in Ethiopia በሚለው መጽሐፋቸው በአመርቂ ሁኔታ እንዳስረዱት ገበሬው ነፃ እስካልወጣ ድረስ ችጋር ኢትዮጵያ ውስጥ እንደሚቀጥል ነው፡፡ ስለዚህ ገበሬው ነፃ ይሁን ከተባለ የሚያርሰው መሬት የራሱ መሆን አለበት፡፡ በፊት የፊውዳል ጭሰኛ እንደነበረው ዛሬ ደግሞ የመንግሥት ጭሰኛ መሆን የለበትም፡፡ በመሆኑም የፓርቲያችን አቋም በዚህ ጉዳይ ላይ በገጠርም የሚታረሰው ሆነ በከተማ የሚኖርበት መሬት የዜጐች የግል ይዞታ መሆን አለበት ነው፡፡ በዚህም አግባብ ገበሬዎችም ሆኑ የከተማ ነዋሪዎች በሙሉ ነፃነት እና ያለምንም ዋስትና-የማጣት ስሜት የመሬትን የገበያ ዋጋ በተገቢው መንገድ ለመጠቀም ይችላሉ፡፡ በተጨማሪ ገበሬውም ከካድሬና ከመንግሥት ጭሰኝነት ነፃ ከሆነ እምቅ አቅሙን አውጥቶ በመጠቀም መሬቱን የመጠበቅ፣ የመንከባከብ፣ የማልማት፣ በባንክ የማስያዝ እንዲሁም የማውረስ፣ የመሸጥ እና የመለወጥ መብት ይኖሩታል ማለት ነው፡፡ ይሄ ለቴክኖሎጂ ሽግግርም ራሱን የቻለ አስተዋፅኦ አለው ብለን እናምናለን፡፡ ስለዚህ እነዚህ የጠቀስኳቸው አቋሞች መሠረታዊ እሴቶቻችን ናቸው፡፡ በፌዴራል አወቃቀር ላይ ያለን አቋም ደግሞ ኢትዮጵያ በታሪኳ ለዚህ ዓይነት የመንግሥት ቅርፅ እንግዳ ባለመሆኗ እና በተለያየ ጊዜ የዚህ አካባቢ ንጉስ የዚያ አካባቢ ንጉስ ከዚያም ንጉሠ-ነገሥት እየተባለ በሰፊው በባህላዊ

ቅጽ 1 ቁጥር 1 ጥቅምት 2005 ዓ.ም

10

Page 11: Semayawi1/Newly formed political party the blue (Semayawi)  founder, Professor Mesfin Wolde Mariam

የአገዛዝ ዘመንም የተለማመድነው በመሆኑ! ይህንኑ ማዳበርና ዘመናዊ ይዘት እንዲኖረው ማድረግ ያሻል፡፡ ይሄም ሆኖ ግን የአስተዳደር ምቹነትን፣ መልክዓ-ምድርን የህዝቦች አሰፋፈርን፣ ባህልን፣ ቋንቋን ግምት ውስጥ አስገብቶ የሚደረግ እንጂ እንደው አሁን እንደሚባለው በጐሣ ከረጢት ውስጥ ያሉ ጎሳዎች ተስማምተው አገሪቷን ገና እንደአዲስ እየፈጠሯት እንደሆነ የሚያስመስለው አቀራረብ ትልቅ ስህተት ነው፡፡ ቀደም ብዬ እንደገለፅኩልህ ኢትዮጵያ የረዥም ጊዜ የሀገረ-መንግሥትነት ታሪክ ያለውና የረጋ ህዝብ ብሎም የጋራ ስነ-ልቦና ያለው ህብረተሰብ የሚኖርባት አገር ነች፡፡ በመሆኑም፡- እነዚህ ግምት ውስጥ ገብተው የሚዋቀር ፌዴራላዊ ቅርፅ ነው ለሀገራችን የሚበጃት ብለን እናምናለን- እንደሰማያዊ፡፡ ታሪክን በመፈልሰፍ አንድ ጐሣና አንድ ጐሣ እንደተዋጉ የሚያስመስለው አቀራረብም በፍፁም የተሳሳተና አውዳሚ ነው፡፡ መንግሥት ከመንግሥት፣ የአካባቢው አገዛዝ ከአካባቢው አገዛዝ ተጣልተው ያውቃሉ እንጂ አንድ ብሔረሰብ ከሌላው ብሔረሰብ ጋር በታሪክ ለዚያውም በታቀደ ሁኔታ ጎሣን መሠረት አድርጎ የተደረገ የፖለቲካ ትግል የለም በአገራችን ውስጥ፡፡ ይሄ ከቅርብ ጊዜ በኋላ በጥራዝ ነጠቅነት ሣር-ቅጠሉ ኮሚዩኒስት በነበረበት ከ66ቱ አብዬት ጋር ተያይዞ እንደወረደ ስለተቀበልነው የመጣ ነገር እንጂ የአገራችንን እውነተኛ ገፅታ የሚያሳይ አይደለም ብለን እናምናለን፡፡ እነዚህ ናቸው እንግዲህ መሠረት የጣልንባቸው እና አጥብቀን የያዝናቸው ዋና ዋና አቋሞቻችን፡፡

ሰማያዊ፡- አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ዋነኛ ፖለቲካዊ ችግር ምንድነው ብላችሁ ነው የምትገነዘቡት? የብሔር ጭቆና ነው? የመደብ ልዩነት ነው? ወይስ አምባገነን የመንግሥት ሥርዓት?

ኢ/ር፡ይልቃል፡- እንግዲህ ኢትዩጵያ እስካሁን ድረስ ከአገዛዝ ወደ ዴሞክራሲ አልሄደችም፡፡ ያለው አገዛዝ ከባህላዊ አገዛዝ የጀመረ እና በ1967 ለውጥም መጣ ተብሎ ከንጉሳዊ አገዛዝ ወደጠብመንጃ አገዛዝ ተዘዋውረናል፡፡ እስካሁን ያለው መንግሥት ድረስ ምርጫ በሚመስል ሁኔታ ልባስ ተሰጥቶት ቅቡልነት ያለው ለማድረግ ቢሞከርም የምር ፖለቲካውን ካየነው ኢትዮጵያ ከጠብመንጃ አገዛዝ እስካሁንም ድረስ አልተላቀቀችም፡፡ ስለዚህ የጉልበት አገዛዝ ነው መሠረቱ፡፡ አንዳንዶቹ ፍልስፍናዊ ቅርፅ በመስጠትና በውጭ አገር ከነበሩ የፖለቲካ እምነቶች ጋራ ለማዛመድ የየራሳቸውን ተቀፅላ ይጨምሩበት ይሆናል እንጂ እስካሁንም ድረስ ኢትዮጵያውያን በጠብመንጃ አገዛዝ ስር ነን፡፡ በመሆኑም ሰማያዊ የሚያምነው የሰዎች የዜግነት እና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ከተከበረ እንዲሁም ስልጣን የህዝብ ከሆነ ከዚያ በኋላ የሚመጡት ነገሮች በሁለተኛ ደረጃ የሚታዩ ናቸው፡፡

በሁለተኛ ደረጃ የሚታዩት፡- የዜጐች ባህላቸውን የማበልፀግ ጉዳይ፣ እምነታቸውን በነፃ የማራመድ መብት፣ በሙያቸው ተሰባስበው የሙያቸውን መብት የመጠየቅ ሁኔታ እና የመሳሰሉት ሁሉ ነገሮች ሥልጣን የህዝብ ከሆነ በኋላ የሚመጡ ቁም ነገሮች ናቸው፡፡ በመሆኑም ዋናው ችግር ሥልጣን የአገሬው ህዝብ የኢትዮጵያ ህዝብ ባለቤትነት ውስጥ ለመሆን አለመቻሉና በጠብመንጃ አገዛዝ ስር መውደቁ ነው፡፡ ሌሎች ፍልስፍናዊ ዓይነት ይዘት የተሰጣቸው ነገሮች ሁሉ ከዚህ በመለስ ያሉ ነገሮች ናቸው፡፡

ሰማያዊ፡- በቅርቡ የተካሄደውን የኢህአዴግ የስልጣን ሽግሽግ በተመለከተ ፓርቲያችሁ ያለው አስተያየት ምን ይመስላል?

ኢ/ር፡ይልቃል፡- እ….. በመጀመሪያ ደረጃ የተካሄደው የስልጣን ሽግሽግ አይደለም፡፡ እ…ባዶ ነበር ቦታው… በመሆኑም ያ ባዶ ቦታ መተካት ነበረበት፡፡ ስለዚህ ጠ/ሚኒስትሩ በሌሉም ጊዜ ቢሆን የሚተኩት ምክትል ጠ/ሚኒስትሩ ነበሩ፡፡ ስለዚህ ጠ/ሚኒስትሩ ለዘላለሙም ሲሄዱ ከኋላ ዘሎ ከማምጣት ምክትሉን መተካት ይሻላል በሚል በዚሁ መሠረት ተካሄደ፡፡ ስለዚህም የተከናወነው የስልጣን ሽግግርም አይደለም! ሌላ ዴሞክራሲያዊ የተለየ ነገርም አልተደረገም፡፡ በታሪካችን እንዲሁ ያለውን ነገር ምናልባትም በተሻለ ሁኔታ የዛሬ 1ዐዐ ዓመት ገደማ ኢትዮጵያ ውስጥ ተደርጓል፡፡ ንግሥት ዘውዲቱ በሞቱ ጊዜ አልጋ ወራሽ ተፈሪ መኮንን ንጉሠ-ነገሥት ሆነው ተሰይመዋል፡፡ የንግሥት ዘውዲቱም የቀብር ስነ-ስርዓት በተሟላ የመንግሥት ደንብ protocol በክብር ተፈፅሟል፡፡ የአፄ ኃ/ሥላሴም ንግስና ሥርዓት ጠብቆ ቤተክርስቲያን በጊዜው ባላት ሥልጣን መሠረት በአግባቡ ተፈፅሟል፡፡ እና ይሄ ዓይነቱ የስልጣን መተካት ከሆነ በፊትም ተደርጓል፡፡ ስለዚህም ኢህአዴግ ታሪክ ሠራ ተብሎ ኢህአዴግን የተለየ ሊያደርገው የሚችል ነገር አልተፈጠረም፡፡ የስልጣን ሽግግር ሊባል የሚችለው አንደኛ፡- ከአንድ ፓርቲ ወደ ሌላ ፓርቲ ቢሄድ ወይም ደግሞ አቶ መለስ እያሉ ተወዳድረው በሌላ አካል ተበልጠው ቢሸነፉ ነው፡፡ አሊያም ደግሞ በቃኝ ብለው ለቀው ሌሎች ተወዳድረው ቢያሸንፉ ያኔ የስልጣን ሽግግር ተካሄደ ሊያስብል ይችላል፡፡ ከሞቱ በኋላ ግን በሌላ ሰው መተካት ግዴታ ነው፡፡ ቦታው ባዶውን መቅረት የለበትምና! በመሆኑም ፓርቲው የመረጠውን ሰው ተካ፡፡ ስለዚህ ይህ የስልጣን ሽግግርም ሆነ ሽግሽግ ሊባል አይችልም፡፡

ሰማያዊ፡- የኢህአዴግ አብዬታዊ-ዴሞክራሲያዊ መስመር የራሱ የሆነ ሥልጣን የማሸጋገሪያ ቀመር እና አካሄድ አለው! ብለው የሚያነሱ የፓርቲው ሰዎች አሉ፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ እውነተኛ የስልጣን ሽግግር ከፓርቲው መጠበቅ የዋህነት ነው! የሚሉም አልታጡም፡፡ በዚህ መሃል ደግሞ የፓርቲውን የመተካካት ጉዞ የሚታዘቡ ሰዎች ምናልባት ስልጣን በትጥቅ ከታገሉት ወደ ሲቪል-ኢህአዴጎች እየሄደ ከመጣ ተስፋ ይኖር ይሆናል! የሚሉ አሉ፡፡ እናንተ ደግሞ እንደተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ ሊያሳትፋችሁ የሚችል የስልጣን መጋራት መንገድ ከኢህአዴግ ትጠብቃላችሁ?

ኢ/ር፡ይልቃል፡- እውነቱን ለመናገር እኔ መጀመሪያም ከኢህአዴግ ዓይነት ድርጅት የምር የምጠብቀው ነገር የለም፡፡ ፓርቲው በራሱ እጅግ የጠቅላይነት (Totalitarian) አስተሳሰብ ያለው አምባገነን ነው፡፡ አንድ ጠንካራ ፓርቲ በመመስረት እና የልማታዊ

መንግሥት ምስል ለራሱ በመፍጠር ከዚህ በኋላ ለ3ዐ እና 4ዐ ዓመት ለመግዛት የሚያልም ፅኑዕ የሥልጣን ሱሰኝነት የተፀናወተው ድርጅት ነው፡፡ የአገዛዝን ነገር ፍልስፍና ለማላበስ የሚጥር! ለሥልጣኑ መቀጠል ሲል እጅግ በአያሌው ጂምናስቲክ ሲሰራ የኖረ ፓርቲ ነው፡፡ እንደ ደቡብ ኮሪያ እና ታይዋን ያሉ የማይዛመዱን አገሮችን በአርአያነት እየጠቀሰ እነዚህ አገራት በአንድ ወቅት ሲያራምዱት የነበረውን ፖለቲካዊ ፍልስፍና በኢትዮጵያ ላይ በመጫን ለረዥም ዓመታት ሊገዛን የሚፈልግ አስመሳይ-አምባገነን ሥርዓት ነው፡፡ እነዚህ አገራት ግን በቀዝቃዛው የዓለም ጦርነት ወቅት በነበረው የጐራ ልዩነት ከአሜሪካ ያገኙትን የዕርዳታ ቁሳቁስ የቴክኖሎጂ ድጋፍ፣ እና የገንዘብ እገዛ ካላቸው ልምድ ጋር በማቀናጀት በራሳቸው ሁኔታ ያደጉ ናቸው፡፡ ነባራዊ ሁኔታቸውም ከኢትዮጵያ ጋር በፍፁም አይገናኝም፡፡ እንደውም እኮ ኢህአዴግ እስከ 97 ሲል የነበረው ‘ጠንካራ ተቃዋሚ አጣን! ብናገኝ እስከግማሽ መንገድ ድረስ ሄደን እንቀበላለን!’ ምናምን የሚሉ ባዶ ቃላትን ነበር፡፡ እንዳለመታደል ሆኖ ግን 97 ላይ የዴሞክራሲው መንገድ እንደማያዋጣና ሥልጣንን በአጭር ጊዜ እንደሚያስለቅቅ ሲያውቁ አምባገነንነትን ፍልስፍና ለማላበስ የተፈጠረ አብዬታዊ-ዴሞክራሲ እንጂ የምር ስልጣንን ማጋራት የሚችል አሳታፊ ስርዓት አይደለም፡፡ በመሆኑም የኢህአዴግ መንግሥት አንድ ወጥ የሆነ አገዛዝ፣ ሌላውን ሁሉ የሚያንቋሽሽ የሚያቃልል፣ በመደብ ቅራኔ ውስጥ ነገሮችን ከፋፍሎ ወዳጅ እና ጠላት ብሎ የሚያይ እስካሁን ድረስ የሚታገልላቸውና የሚታገላቸው አመለካከቶች ያሉት እንጂ ፖለቲካዊ መስመሩን አስተካክሎ የሌላውንም ድምፅ ግምት ውስጥ አስገብቶ የሚሄድ ሥርዓት ነው ብዬ አላስብም፡፡ ስለዚህ በህዝብ የምር ትግል መለወጥ ይቻል እንደሆን እንጂ ኢህአዴግ በውስጡ በራሱ እያደገ በሚሄድ ዴሞክራሲ ይቀየራል የሚል እምነት የለኝም፡፡

ሰማያዊ፡- እንግዲህ የህዝብ የምር ትግል ሲባል ብዙ ጊዜ የሚነሳው ከ97 ወዲህ የህዝቡ ለፖለቲካ ፍላጎት የማሳየት ሁኔታ እጅግ እንደተዳከመ ነው፡፡ በዚህ ረገድም ከዚህ ወቅት በኋላ! ሰው በሰላማዊ የፖለቲካ ትግል ተስፋ አድርጐ ከእናንተም ጋር አብሮ ቆሞም ቢሆን ወደነፃነት እና ዴሞክራሲ የሚጓዝ ይመስላችኋል? እናንተስ አዋጪ መንገድ አለን ትላላችሁ?

ኢ/ር፡ይልቃል፡- የ97ቱ ጉዳይ ብዙ ጊዜ ይነገራል፡፡ ራሳችንን በተስፋ ለመመገብም ጭምር እየፈለግን እንጂ እኔ የ97ቱን ጉዳይ ብዙ ሰው በትክክል የተረዳው አይመስለኝም፡፡ እንዴት መጣ? የሚባለውን ነገር በትክክል ካየነው በ1993 ዓ.ም. ህወሓት ከኤርትራ ጦርነት በኋላ ከተከፋፈለ ጀምሮ! በብዛት አንድ ሰው ጐልቶ እየወጣ የነበረበት! የአፍሪካ መሪ እየተባለ የኔፓድ መሪ…. የዚህ መሪ…. በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን ጨምሮ አቶ

ቅጽ 1 ቁጥር 1 ጥቅምት 2005 ዓ.ም

11ወደ ገጽ 19 ዞሯል

Page 12: Semayawi1/Newly formed political party the blue (Semayawi)  founder, Professor Mesfin Wolde Mariam

ከኘሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረ ማርያምትርጉም ከነፃነት ለሀገሬ

በድጋሚ እውነት፣ሃይልን ለተነፈጉ

ላለፉት በርካታ ስለ ሥልጣን ተጠቃሚዎች ዕውነትን ስናገር ነበር፡፡ የጦማሬ ገጼ መግቢያ መስመሩ ለሰብዓዊ መብት ተሟገት፡፡ ስለሥልጣን ተጠቃሚዎች እውነትን መስክር; ነው የሚለው፡፡ ይህ ደሞ ልዩ ትርጉም ያለው፣ ጠንካራ ሞራልና ስልጣናቸውን መከታ በማድረግ አላግባብ የሚጠቀሙበትን፣ ከመጠን በላይ ለሚተማመኑበት ኢሰብዓዊ ድርጊት ማስገንዘቢያ የሆነ ስንኝ ነው፡፡ ለባለሥልጣናት ነን ባዮች እውነትን መናገር፣ ተናጋሪው በዚህ ባለስልጣናት ላይ ስልጣናቸው የተዘረጋው በሃሰት ላይ መሆኑን ምስክርነቱን ያረጋግጣል፡፡ አልፎ አልፎም ሃቅን መናገር የስልጣን ሰለባ ለሆኑትም አስፈላጊ ነው፡፡ ስልጣን አልባዎች በምንም መልኩ ስልጣንን ሊያዛቡ የሚችሉበት ሁኔታ የለም፡፡ ስህተታቸው ግን የስልጣናቸውን እውነተኛ መብት አለማወቃቸው ነው፡፡ ሥልጣንን መከታ በማድረግ ግፍ የሚፈጽሙት ጉልበተኛ ሆነው ቢታዩም የስልጣን ተነፋጊዎች ደግሞ የሥልጣን ባለቤትነት መብት አላቸው፡፡ የሥልጣን እውነታነትና መብት ነው የሥልጣን ተነፋጊዎች በትግላቸው ሂደት ሊጠቀሙበትና ለድል የሚያበቃቸውን መንገድ ሊከተሉ የሚገባቸው፡፡ ዶ/ር ማርቲን ሉተር ኪንግ ይህን አስመልክተው፣ ለጊዜው ትክክለኛነት ቢሸነፍም፣ ከሰይጣናዊና እኩይ ድል የበለጠ ነው; ብለዋል፡፡

በሰኔ 2ዐ1ዐ፣ እውነትን ስልጣን ለተነፈጉ መናገር; የሚል ጦማር ጽፌ ነበር፡፡ በዚያም ጦማሬ ላይ በግንቦት 2ዐ1ዐ፣ ቀን በቀን በገዢው ፓርቲ የተሰረቀውንና ድሌ 99.6 በማለት ፓርላማውን የተቆጣጠረበትን የምርጫ ውጤት በተመለከተ፣ የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ፓርቲዎች እንቅስቃሴ የፖለቲካ መሽመድመድ የታየበትና አንዳችም ተግባር ያልተከወነበት ሂደት እንደነበር አሳስቤ ነበር፡፡ ተቃዋሚ

ፓርቲዎች በጥንቃቄ ትኩረት ሰጥተው ራሳቸውን ማስተካከያ መንገድ እንዲፈልጉም አሳስቤ ነበር፡፡ ዓላማዬ ዲስኩር ለማድረግ ወይም ተቃዋሚዎችን ለመኮርኮም ሳይሆን ሃሳባችንን በማጽዳት ቆሻሻውን በመጣልና ወደ ዴሞክራሲ የሚያደርሰንን ረጂሙን መንገድ ቀና ለማድረግ ለመርዳት መሆኑን በወቅቱ አስረድቻለሁ፡፡ እውነት ይጎዳል; ቢባልም እኔ አልስማማበትም፡፡ እውነት ለማገገም ይረዳል፡ ሃይል ይሰጣል፡ ታጋዮችንም ነጻ ያወጣል፡፡;

የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ኃይሎች በገዢው ፓርቲ እይታ

የ2ዐ1ዐን ምርጫ ተከትሎ እንደተቃዋሚ ፓርቲዎች፣ የነጻው ኘሬስ ጋዜጠኞች፣ እና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች በገዢው ፓርቲ የሚደርስባቸውን ሰቆቃ በተመለከተ የገዢው አመራሮች አገኘን ለሚሉት ድልና የምርጫ ውጤት ስለተቃዋሚ ፓርቲዎች /ስለህዝቡ/ ያላቸው ግንዛቤና አመለካከት ያስገርመኛል፡፡ ያን ጊዜም አሁን እንደማስበው፡ በገዢው ባለስልጣናት እይታ ተቃዋሚዎችን መመልከት፣ ተቃዋሚዎችን በተለይም የተቃዋሚ ፓርቲዎችን ያለውን ሁኔታ በማገናዘብ ሊከተሉት የሚገባውን መንገድ ያመላክታል ብዬ አምናለሁ፡፡

……መለስ ተቃዋሚዎች እራሳቸውን ለክተው እንደማያውቁ ያውቃል፡፡ በሚገባ አጥንቷቸዋል፣ አስጠንቷቸዋልና ስራቸውን እንዴት እንደሚያከናውኑ /እንደማያከናውኑ/ ጠንቅቆ ያውቃል፡፡ በጥንቃቄ የተበጠሩት ሕዝባዊ ዲስኩሮቹ ላይ ዘወትር የማይለወጥና መጥፎ አመለካከቱን ያሳያል፡፡ ተቃዋሚዎችን በችሎታቸውን በእውቀትም የበታቾቹ አድርጎ አስቀምጧቸዋልና በፈለገው ስዓትና ወቅት በአስተሳሰብ እንደሚበልጣቸው፣ በአመለካከት እንደሚያልፋቸው፣ በተንኮል እንደማይደርሱበት፣ በእኩይ አስተሳሰብ እንደማይስተካከሉትና ባሻው ጊዜ ድል እንደሚያደርጋቸው ያምናል፡፡ በመለስ አስተባሰብ፣ እንቅስቃሴያቸው ድውይ፣ የማያድጉና ያልበሰሉ፣ አድሮ ጥጃ፣ በመሆናቸው ሥልጣኑን የሚያሰጉት እንዳልሆኑ አረጋግጧል፡፡ በንግግሮቹ ሁሉ ተቃዋሚዎች ላይ ያለውን ንቀትና ጥላቻ ብቻ ነው የሚያንፀባርቀው፡፡ እድገታቸውን እንዳልጨረሱ ሕጻናት እለት ተእለት ክትትል የሚያስፈልጋቸውና ስርዓት እንዲኖራቸውም የዲሲኘሊን ሽንቆጣ እንደሚያስፈልጋቸው ነው የሚደሰኩረው፡፡ ልክ ሕጻናትን እንደማታለል አይነት፣ ለአንዳንዶች፣ ስኳር ያልሳቸዋል፣ በሥራ፣ በመኪና ችሮታ፣ በቤት ስጦታ፣ እና አፋቸውን ሊያፍን የሚያስችለውን ሁሉ ያደርግላቸዋል፡፡ በዚህ ሊደልላቸው የማይችላቸውን ደሞ በመከታተልና ሲገቡ ሲወጡ በመተንኮስ፣ በስለላ አባላት በማስጨነቅ በመጨረሻውም አስሮ ይፈርድባቸዋል፡፡አብዛኛውን ጊዜ ተቃዋሚዎችን ያታልላቸዋል፣ ይቀልድባቸዋል፡፡ ሽማግሌዎችን ለእርቅ በመላክ፣ ጊዜ እየገዛ የቆመበትን መሰረት ያሳጣና፣ ድርድር በሚል ዘዴ እያታለለ የራሱን

ድል ይገነባል፡፡ የተለመደ አስማታዊ የሆነውን የተንኮል ጠበል ይረጭና ያንኑ ውጤት አልባ የሆነውን ጨዋታውን ጀምሮ በመጨረሻው እንቅልፍ አስወስዷቸው በድል ደወል ሲነቁ ማርፈዱን ይገነዘባሉ፡፡ በዚህም ተቃዋሚዎች የጨበጡትን ሁሉ ለቀው ተሸናፊ ሆነው ይሰለፋሉ፡፡

በኢትዮጵያ ተቃዋሚው ሃይል ማነው?

ይህ ጥያቄ ምናልባትም አወዛጋቢና እንዲያውም ቁርጥ ያለ መልስም ሊገኝለት የማይችል ይሆናል፡፡ አሁን በሃገሪቱ ውስጥ የተጠናከረና ጉልበት ኖሮት የተዋቀረም ፓርቲ አለ ማለት ያስቸግራል፡፡ በዚህም የተነሳ ተቀናጅተውና ሃይላቸውንና አቋማቸውን አስተባብረው ገዢውን ፓርቲ ሊሞግቱና ገዢውን ፓርቲ ሊቋቋሙት ብቃት ያላቸው ፓርቲዎች ውህደት አይታይም፡፡ በምሁራንም የተጠናከረና የተዘጋጀ ተቃዋሚ የለም፡፡ ከሲቪል በማህበረሰቡም፣ ከማህበራት፣የተዋቀረ ፓርቲም የለም፡፡ የህብረተሰቡን ሃይል ያካተተም እንቅስቃሴም ሆነ ተቃዋሚ ሃይል የለም፡፡ በኢትዮጵያ ያለው የፖለቲካ ተቃዋሚዎች ችግር ከ196ዐዎቹ ጀምሮ የኖረው የአፍሪካ ያረጀው ችግር ነው፡፡ በአፍሪካ አንድ ሰው አንድ ፓርቲ በማለት በጋና በከዋሚ ንክሩማ ዘመን የተፈጠረ ሂደት ነው፡፡ ንክሩማ ተቃዋሚዎቹን፣ አጠፋ፣ አጋዘ፣ ለፍርድ አቅርቦ ያለአግባብ አስፈረደባቸው፡፡ በዚህም ሂደት ውስጥ ዳኞች፣ የማህበራት መሪዎች፣ ተካተዋል፡፡ ባለፈው ግማሽ ምዕተ ዓመት ውስጥ፣ በኢትዮጵያ በጉልበት ስልጣን የወጡትን ገዢዎች የተቃወመ ሁሉ፣ በፖለቲካው መድረክ መወቀስና መወገዝ ብቻ ሳይሆን፣ ያለአግባብ በፍርድ ስም መሰቃየትና ከዚያም አልፎ ለሞት መዳረግ የታየበት ዘመን ነው፡፡ የኢትዩጵያን የተቃዋሚ ሃይላት ምንነትና ሁኔታ እንዲህ ነው ለማለት እቸገራለሁ፡፡ ከሜይ 2ዐ1ዐ ምርጫ በኋላ ባቀረብኩት ጦማሬ ላይ አንስቼው እንደነበረው! ያ ተስፋ የቆረጥንበት ተቃዋሚ ሃይል፣ የተከፋፈለ፣ ያ በነጋ በመሸ ቁጥር በረባ ባልረባው ጉረሮ ለጉረሮ የሚተናነቀውና ዋናውን ሊታገሉት የሚገባውን ሃይል የዘነጉት ናቸው አሁንም ተቃዋሚ ናቸው የምንላቸው? ወይስ እነዚያ በደካማው የሚንቀሳቀሱትን እንደአመቺነቱ ብቅ ጥልቅ የሚሉትን የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች፣ የሲቪክ ማህበረሰቡ አሰባሳቢዎች፣ጋዜጠኞች፣ እና ሌሎቹን የሚዲያ ባለሙያዎችና ምሁራኑን ናቸው? ወይስ ለመሳርያ ትግል ታጥቀውና ቆርጠው የተነሱትንና ገዢውን ፓርቲና አፋኝና ጨቋኝ ሥርዓቱን ለማጥፋት የተነሱትን ናቸው ተቃዋሚ የምንላቸው?;

ሁሉም ናቸው ወይስ ሁሉም አይደሉም?

በኢትዮጵያ ትክክለኛው የተቃዋሚዎች ተግባር ምንድን ነው?

የፖሊስ ጭቆናዊ አስተዳደር በተንሰራፋበት ሃገር ውስጥ በተቃዋሚነት መቆም እጅጉን አስቸጋሪና አደገኛም ነው፡፡ የሜይ 2ዐዐ5ቱን ምርጫ ተከትሎ ሁሉም የተቃዋሚ ፓርቲ

የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ፖለቲካ የዴሞክራሲ ጮራ ስትወጣ

ቅጽ 1 ቁጥር 1 ጥቅምት 2005 ዓ.ም

12

Page 13: Semayawi1/Newly formed political party the blue (Semayawi)  founder, Professor Mesfin Wolde Mariam

አመራሮች፣ በርካታ የሲቪክ ማህበረሰቡ አመራሮች፣ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች፣ የነጻው ኘሬስ አባላት፣ ከያሉበት በመታደን ለሁለት ዓመታት ያህል ወህኒ ተጥለው ነበር፡፡ ላለፈው 6 ዓመታት ተቃዋሚ ፓርቲዎች ማንኛውንም እንቅስቃሴ ተነፍገውና ታግደው፣ በጠበበው የፖለቲካ መድረክ ውስጥ እንዲሹለከለኩ ብቻ ነበር የተፈቀደላቸው፡፡ ከዚያ ባለፈ ግን ተቃዋሚ የሆኑትን የነጻው ጋዜጣ ባለቤቶችና አባሎቻቸው፣ ሌሎችም የተቃዋሚ ደጋፊዎችና አባላት እየተገፉና ከመስመር እንዲወጡ ጫና እየተደረገባቸው፣ በገዢው ጭቆናዊ አመራር እየተሰቃዩ፣ እየታሰሩ፣ ከሕብረተሰቡ ጋር እንዳይገናኙ እየተደረገ እነዚህ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች ተዳክመው፣ ሕዝባዊ ግንኙነታቸው እንዲቋረጥ አድርገውባቸው፣ ከገዢው ፓርቲ ጨቋኝ ስርአት የተለየ እንዳለና ተቃዋሚዎችም ለዚህ የቆሙ መሆናቸውን የሚያሳውቁበት መንገድ ባለመኖሩ ተዳክመዋል፡፡ በሌላም ወገን አንዳንዶቹ ተቃዋሚዎች ተጠያቂነትን በመዘንጋት፣ ግልጽነትን በመሸሽ ከአባሎቻቸው ጋር ተቃቅረዋል፡፡ ሌሎች ደግሞ ተቃዋሚ ነን እያሉ በውስጣቸው ግን ዴሞክራሲያዊነትን መቀበልና መተግበርን ስለሚፈሩት አቅቷቸዋል፡፡ ከዚያም አልፎ እራሳቸውን እንደሚቃወሙት ገዢ ፓርቲ ፈላጭ ቆራጭ በማድረግ የራሳቸውን የበላይነት ለማስጠበቅ ሲሉ በፓርቲው አባላት መሃል፣ ግጭትንና አለመግባባትን መቃቃርን ፈጥረዋል፡፡

በኢትዮጵያ ያሉትን ተቃዋሚዎች በምንም መልክ ይፈረጁ በምንም፣ በገዢው ፓርቲ አሸናፊ ነኝ አባባል የተጠቀሰው የ99.6 የምርጫ ውጤት ከ2ዐዐ5ቱ የተቃዋሚ ድርጅቶች አሸናፊነት ከተመዘገበው ሃገር አቀፍ ከፍተኛ ድል ጋር ሲተያይ እጅጉን የተለየና የእውነትና የሃሰት ድል የታየበት የተቃዋሚዎች ብርታትም የተመሰከረበት ለመሆኑ አጠያያቂ አይደለም፡፡ ካለፈው የ6 ዓመት ሁኔታ የተቃዋሚው ፓርቲ አባላት ሊማሩና ሊያውቁ የሚገባቸው ጉዳይ ቢኖር ዝም ብሎ መቃወም መቃወም፣ ደሞም መቃወም; ለመቃወም ብቻ ሊሆን አይገባም፡፡ የተቃዋሚዎች ሁኔታ ገዢውን ፓርቲና ፖለቲካዊ ዝግመቱንና ያለፈበትን መቃወም ብቻ ሳይሆን፣ ከዚያም ባሻገር ማሰብ ይገባቸዋል፡፡ ዋናው ዓላማቸው ለሃገራችን ዴሞክራሲያዊ አስተዳደርን እስከመዘርጋት ሊጓዝ የግድ ነው፡፡ ዘወትራዊ ተግባራቸው ሳይሰለቹና ሳይደከሙ ሊያካሂዱት የሚገባ ትግላቸው ግልጽነትንና ተጠያቂነትን አበክረው መጠየቅና ለዚያ መታገል ሊሆን ይገባል፡፡ የገዢውን ፓርቲ እለታዊ እንቅስቃሴ በማጤን አግባብነት የሌለውን በመጠየቅ ለመስተካከሉ መቆም፣ መታገል፣ ሂስ ማድረግና በመተቸት፣ ያንንም ይፋ ማድረግ ሲኖርባቸው ከገዢው ፓርቲ የተሻለ አመለካከትና መመሪያም በማውጣት ለሕዝቡ እያቀረቡ ብቃታቸውን ማረጋገጥ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ተቃዋሚዎች የገዢውን ፓርቲ ድክመት ብቻ እያነሱ ያንን መኮንን ብቻ ሳይሆን የነሱን የተሻለ ሃሳብም ማሰማት ይገባቸዋል፡፡

ገዢውን ፓርቲና አመራሮቹን በስድብ ክምር ማጥላላትን፣ ጥርስን በመንከስ ማንኳሰስ የተቃዋሚውን ፓርቲ አስተሳሰብ ከፍተኛነት ከማቅለሉ ባሻገር ምንም ፋይዳ የለውም፡፡ ተቃዋሚዎች ለተጠያቂነትና ለመልካም አስተዳደር ያላቸውን ሃሳብና ራዕይ ያዛንፍባቸዋል እንጂ የሚያስገኝላቸው

ጠቀሜታም ሆነ ትርፍ የለውም፡፡ አብዛኛዎቹ የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት በስልጣን ላይ ስላለው ገዢ ሃይል የሚጠቀሙበት ቋንቋ ቁጣ፣ ፍርሃት፣ የበታችነት ስሜትን የሚያሳይ ነው፡፡ ጥቂቶች ብቻ ናቸው እውነትን ይዘው በቆራጥነትና በሎጂክ የሚናገሩትና የሚሟገቱት፡፡ የገዢውን ፖሊሲዎች፣ ኘሮግራሞችና ኘሮጄክቶች፣ በሰከነ ጥናትና ግምገማ፣ በምርምር አቅርበው የሚናገሩና በምትኩም የተሻለ ጥናት የሚያቀርቡ ጥቂቶች ናቸው፡፡ ለምሳሌ ገዢው ፓርቲ የሃገሪቱን ለም መሬቶች በሽርፍራፊ ዋጋ ለውጭ ዜጎች መሸጡን ይፋ ያወጡትና ሕዝቡ እንዲያውቅ ያደረጉት ሃገራዊ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ሳይሆኑ መንግሥታዊ ያልሆኑ የውጭ አገር ድርጅቶችና ተመራማሪዎች ናቸው፡፡ በተለያዩ የሃይድሮ ኤሌክትሪክ ግድቦች ሳቢያ የሚከሰተውን የአካባቢን ችግር በተመለከተም ጉዳዩን ይፋ ያደረጉት የውጭ አገር ተመራማሪዎች ናቸው፡፡ የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ ፖሊሲውን ግምገማ፣ ምንነትና ድክመቱንም በተመለከተ ይፋ እያወጡ ጥናታቸውን ያቀረቡት የውጪ አበዳሪ አካላት ሲሆን ጥቅምን ከመጠበቅ አኳያ ጥናታቸው አጠያያቂ ነውና እውነታው ይፋ የሚሆነው በታወቁ የሚዲያ አጥኚዎች ነው፡፡ ገዢውን ፓርቲ በተጨባጭና በሃቅ ላይ በተመሠረተ የፖሊስና የኘሮግራም አቀራረጹን መተቸት ባለመቻላቸው ተቃዋሚዎቹ በሕዝቡ ዘንድ ተቀባይነትን ወደማጣቱ ደርሰዋል፡፡ የሚያስፈልገው የቃላት ውግዘት አይደለም፡፡ የሚያስፈልገው ክሪቲካል የሆነ ሚዛን የሚያነሳ ግምገማና የገዢውን ፓርቲ የኘሮግራሙን፣ የፖሊሲውን መክሸፍ በተጨባጭ ማሳየትና ለዚያም ማስረጃዎችንና ጥናቶችን በተገቢው ማቅረብ ነው፡፡ በዚህም ነው ሕብረተሰቡ ከገዢው ፈላጭ ቆራጭ የተሻለና የተለየ ራዕይ ከተቃዋሚዎች ሊጠብቅና ሊያልም የሚችለው፡፡

የተቃዋሚ ፓርቲዎች ለምርጫ ውድድር ከመዘጋጀት ባሻገር ብዙ ሊጫወቷቸው የሚችሏቸው ሚናዎች አሏቸው፡፡ የአባሎቻቸውን የደጋፊዎቻቸውንና የጠቅላላውን ሕብረተሰብ ንቃተ-ሕሊና ማዳበርና ለትግሉም ማዘጋጀት ይጠበቅባቸዋል፡፡ ፖሊሲያቸውን በሚገባ በማዳረስና በማስረዳት ሕብረተሰቡን ማስተማር አለባቸው፡፡ ክርክርና ውይይት በማዘጋጀት፣ በአስፈላጊ ርእሶች ላይ በመነጋገርና ሕዝቡንም ተሳታፊ ማድረግ ሁኔታዎችን እያነሱ ችግሮችን በማንሳትና መፍትሔዎችን በመጠቆም የሃገሪቱን የወደፊት ራዕይ መጠቆም አለባቸው፡፡ ሁኔታዎችን በማስተካከል የዴሞክራሲ ባሕል የሚዳብርበትን መንገድ ቀያሽ ሊሆኑ ይገባል፡፡ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ስኬታማ መሆን የሚችሎት ለወጣቱና ለሴቶች አስፈላጊውን የአመራር ስልጠና ለመስጠት ማቀድና መተግበር ይኖርባቸዋል፡፡ የብዙዎቹ ተቃዋሚ ድርጅቶች አመራሮች ሃምሳውን ዓመት የዘለሉ ሲሆኑ በአመራሩ ላይ ያሉትም የሴቶች ቁጥር አናሳ ነው፡፡ ዕድሜ ቁጥር እንጂ ሌላ አይደለም; በወጣቱና በዕድሜ ጠገብ ፖለቲካ መሃል ግልጽ የሆነ ልዩነት አለ፡፡ ወጣቱ ትውልድ ታላቅ የመነሳሳት ፍላጎት፣ ቅልጥፍና፣ ቆራጥነት፣ በዓላማው ላይ መራመድን ይቀይሳል፡፡ ያንንም ተግባራዊ ለማድረግ ፈጣንና ቆራጥ ነው ያደርገዋል፡፡ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ከሚዲያውና ከሲቪል በማህበረሰቡ ጋር በመሆን ተቀናጅተው ወደ ሕዝቡ መድረስ አለባቸው፡፡

አልፎ አልፎም ተቃዋሚዎች በስልጣን ላይ ካለውም ኃይል ጋር በትክክለኛው ጉዳይ ላይ

በመስማማት የሕብረተሰቡን ፍላጎት ማሟላት ይችላሉ፡፡ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በ2ዐዐ7 ላይ ሃሳባቸውን ሲገልጹ፡- ሃሳባቸው ኢትዮጵያን ከተዘፈቀችበት የችግር አረንቋ ማውጣት ብቻ ሳይሆን; በመልካም አስተዳደርና በዴሞክራሲ ግንባታም ላይ; ያተኮረ እንደነበር ተናግረዋል፡፡ አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትርም የመለስን ራዕይ ተግባራዊ ለማድረግ መነሳታቸውንና ያም ዓላማቸው እንደሆነ በግላጭ ደጋግመው ቃል ገብተዋል፡፡ ሃይለማርያም የመለስን ራዕይ ለመተግበር ለመልካም አስተዳደርና ለዴሞክራሲ ግንባታ በሚያደርጉት እንቅስቃሴ አብሮ መሰለፍ ጉዳት የለውም፡፡ መልካም አስተዳደርን ለመገንባት፣ የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱም ሰፊ የዴሞክራሲ ግንባታም እንዲሰፍን በማድረጉ በኩል ተቃዋሚዎች ሃይለማርያምን ተጠያቂ በማድረግ መንቀሳቀስ አለባቸው፡፡

ምን ዓይነት ተቃዋሚ ነው የሚያስፈልገው?

የገዢው መንግሥት መኖርና የበላይነት የተረጋገጠለት በኢትዮጵያ ያሉት ተቃዋሚ ኃይላት ስምምነት ማጣትና ዘወትር እርስ በርስ መናቆር የተነሳ ነው፡፡ ተቃዋሚዎች ተከፋፍለውና የጎሪጥ በመተያየት በየፊናቸው ባይረግጡ ኖሮ በገዢው ፓርቲ እንደዚህ ተጠናክሮ ሕጉን እንዳሻው በማውጣትና በመለወጥ ሊዘባነን ባልቻለ ነበር፣፣ ስለዚህ ታዲያ ምን ዓይነት ተቃዋሚ ነው የሚያስፈልገው?

ታማኝ ተቃዋሚ?

በአንዳንድ የፓርላማ ስርአት ውስጥ ታማኝ ተቃዋሚ; የሚባለው በህግ አውጪው አካል አስተዳደራዊ ተግባር ውስጥ ያልተካተቱትን ለማለት ነው፡፡ በተግባራዊው የዴሞክራሲያዊ ፓርላማ ስርአት ውስጥ ግን የገዢውን ፓርቲ ኘሮግራምና ፖሊሲ ያለአንዳች ፍርሃትና ይሉኝታ፣ መሳቀቅ በነጻነት እየተከታተለ በትክክሉ በማስተግበር በኩል ከፍተኛውን ሚና የሚጫወት ማለት ነው፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ ግን ገዢው ፓርቲ የፓርላማውን ወንበር 99.6ቱን ተቆጣጥሮያለሁ በሚልበት ሁኔታ ውስጥ ታማኝ ተቃዋሚ ጨርሶ ሊኖር አይችልም፡፡ የአንድ ብቸኛ ሰው ታማኝ ተቃዋሚ ሊኖር አይችልም፡፡

ጸጥተኝና ወይም የታፈነ ተቃዋሚ?

በገዢው ክፍል ውስጥ ብዙ ዝም ያለ ወይም የታፈነ ተቃዋሚ አለ፡፡ የሚያስከትለውን ሁኔታ በመፍራት ብዙሃኑ የህብረተሰብ አባላት ለገዢው አካል ያላቸውን ተቃውሞ ከማንሳት ተቆጥበው አሉ፡፡ ገዢውን ፓርቲም ሆነ ወይም በውስጡ ያሉትን አመራሮች ላይ ተቃውሞ ቢያሰሙ ወይም አቃቂራቸውን ቢያመላክቱ ሥራቸውን ሊያጡ፣ ከትምህርት ገበታቸው ሊባረሩ፣ የኢኮኖሚ ጫና ሊደርስባቸው አሊያም ለባሰ መከራና ሰቆቃ ሊዳረጉ ይችላሉ፡፡ ሰዎች ገዢውን ፓርቲ እንቃወማለን በማለታቸው ብቻ ለእስር ይዳረጋሉ፡፡ በጣም በሚያስደንቅ ሁኔታ በቅርቡ አራት ሰዎች እንኳንም መለስ ሞተ፣ ግልግል፣ በመሞቱ አላዝንም፣ መንግሥት ሞቷል፣ መንግሥት የለም፣; ብለው በአደባባይ በመናገራቸው ለእስር ተዳርገዋል፡፡ በጣም ብዙዎች በግላቸው ተቃውሟቸውን የሚያሳዩ አሉ በአደባባይ ወጥቶ በይፋ ለመናገር ግን

ቅጽ 1 ቁጥር 1 ጥቅምት 2005 ዓ.ም

13

Page 14: Semayawi1/Newly formed political party the blue (Semayawi)  founder, Professor Mesfin Wolde Mariam

ክስንና እስራትን በመፍራት ታፍነዋል፡፡

ያልተደራጀ ተቃዋሚ?

ማንዘራሽ፣ ያልተደራጀና ግልፍተኛ ተቃዋሚ በገዢው ፓርቲ ላይ አንዳችም ተጽእኖ ሊያሳድር አይችልም፡፡ የዚህን የመሰሉ ተቃዋሚ ምንም እቅድ ስለሌለውና ብቃቱም ስለማይኖረው ፖሊሲ የመንደፍም ችሎታ ስለማያገኝ ሕዝቡን አስተባብሮ ለማነሳሳት ጨርሶ ተቀባይነት የለውም፡፡

የተከፋፈለ ተቃዋሚ?

የተከፋፈለ ተቃዋሚ ግልጋሎቱ ለገዢው ፓርቲ የመኖር ሕልውና መሆን ነው፡፡ የገዢው ፓርቲ ሃይልም ሆነ ተቃዋሚውን አሳንሶ ማየትና እንዳሻው መሆን ዋናው መሳሪያና ምክንያት የተከፋፈለ ተቃዋሚ ነው፡፡

የተባበረ፣አቋሙ የተስተካከለ፣ዴሞክራሲያዊ ተቃውሞ?

ለኢትዮጵያ የሚያስፈልጋት ይሄ ነው፡፡ እንዲህ አይነቱ ተቃዋሚ ታዲያ በመቻቻል በስምምነት በመግባባት ላይ መሰረቱን ያዋቀረ የተባበረና የብዙሃኑን ፍላጎትና ራዕይ መሰረት ያደረገ ተቃዋሚ ሃይል ነው፡፡ ሕብረቱ በሕዝቡ ፍላጎትና እምነት ላይ መሰረቱን ያደረገ ሲሆን ሂደቱ ለምርጫ ውድድር መዘጋጀት ብቻ ሳይሆን ሰፊ ምህዳር ያለው ፖሊሲ በመቅረጽ የሰፋ ውክልና ሊኖረው የሚችልና ለምርጫውም ቢሆን ሰፊ ድጋፍ የሚቸረው ሕዝባዊ ተቀባይነትና አመኔታ የተጣለበት አለኝታ ይሆናል፡፡ በሕብረት ውስጥ ሰፊ የሆነ ሃሳብና እቅድ የሚቀርብ በመሆኑ ይህንንም ወደ ተግባር ለመለወጥ የከረረ ውይይትና እሰጥ አገባ ተካሂዶበት ወደ ዴሞክራሲያዊ ውሳኔ ስለሚደርስ የአብዛኛውን ሕዝብ ፍላጎት የሚያካትት ዓላማቸውን የሚያስፈጽም በመሆኑ ሊፈጠር የሚችለውን አለመግባባት ሁሉ በውይይት ፈትቶ ለውሳኔ ይደርሳል፡፡ የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ፓርቲ እራሱን በሕብረት በሚያጣምር ፖሊሲ ላይ በማጠናከር መቆም ሲችልና በአንድነት አንድ ሆነው ሲንቀሳቀሱ ገዢውን ፓርቲና ፖሊሲዎቹን ለመሞገት ብቃት ይኖረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ተግባሩ ምን ሊሆን ይገባል?

የ201ዐን ምርጫ አስከትዬ የምክር ሃሳቤን ለኢትዮጵያ ተቃዋሚዎች አቅርቤ ነበር፡፡ በወቅቱ ምክሬ አንድም ተቀባይ ያገኘ አይመስለኝም፡፡ እኔ ደግሞ ያመንኩበትን በይሉኝታ ለመቀልበስ ዝግጁ አይደለሁም! እና አሁንም ደግሜ ያንኑ ምክሬን በማጠናከር የፖለቲካ ጨዋታው መለወጡን እየጠቆምኩ የገዢው ፓርቲ ግን ተደጋጋሚ የማስመሰያ ቃላት ከመሰንዘር ባለፈ ምንም ለውጥ ያላሳዩ ናቸውና እንደነበሩት ለመቀጠል ነው ሃሳባቸው፡፡ ባልታሰበ መንገድ ሁኔታዎች መለወጥ ጀምረዋል፡፡ ይህ ጅማሮም በፈጠነ ሂደት ላይ መጓዙን አጠናክሮ ከፈላጭ ቆራጭ አገዛዝ ወደ ዴሞክራሲ ለውጥ ጉዞውን መቀጠሉ ማቆሚያ የሌለው ነው፡፡ በምድር ላይ ምንም አይነት ሃይል ይህን የለውጥ ጅማሬ ሊያቆመው ጨርሶ አይችልም፡፡ በስልጣን ላይ ያሉት ፈላጭ ቆራጭ ገዢዎች ባሻቸው መንገድ ሊያከሽፉትና ለራሳቸው እንዲመች ለማድረግ ቢጥሩ ከፈላጭ ቆራጭ ወደ ዴሞክራሲያዊ

ስርአት ለውጡን ማቆም ምኞት እንጂ ተግባራዊ ሊሆንላቸው አይችልም፡፡ አሁን የቀረውና መልስ የሚፈልገው አንድ ጥያቄ ብቻ ነው፡፡ እገሌ እገሌ ተገሌ ሳይባል በሁሉም በገዢው በፓርቲ የተጨቆኑና የግፍ ሰለባ የሆኑ ተቃዋሚ ሃይላት ማሕበራት፣ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች፣ የዴሞክራሲ ናፋቂዎች፣ ሁሉም በአንድነት ከግፍ አገዛዝ ወደ ዴሞክራሲያዊ ስርአት በኢትዮጵያ ለሚደረገው ሂደት ምን ማድረግ ይጠበቅባቸዋል?

ከሕዝቡ ጋር ይቅር ለእግዚአብሔር ተባብሎ እርቅ መመስረት፣

በ2ዐዐ5 በተካሄደው ምርጫ የተሳተፉት የተቃዋሚ ፓርቲዎች አመራሮች ሁሉም ወደሕዝቡ ተመልሰው፣ ባለፈው ተስፋውን፣ ሕልሙን፣ መነሳሳቱን ያጨለሙበትን ሕዝብ ይቅርታ በመጠየቅ እርቅ ሊያደርጉ ተገቢ ነው፡፡ ለሕዝቡም ያለምንም ይሉኝታ #ባለፈው አሳዝነናችኋል፣ በዚያም በምር አዝነናል፣ ከናንተም ያጣነውን አመኔታና ድጋፍ ለማግኘት እንድንችል ጠንክረንና ካለፈው ተምረን እንክሳችኋለን; ለማለት ብቃቱና ወኔው ሊኖረን የግድ ነው፡፡ ሕዝቡ ከተቃዋሚ መሪዎች ቅጥ ያለው ይቅርታ ይገባዋል፡፡ ይህንንም ቢያደርጉ የኢትዮጵያ ሕዝብ ጨዋ፣ ይቅር ባይ፣ መሃሪ፣አዛኝ ነውና ይቅር ይላቸዋል፡፡

ካለፈው ስህተት መማር፣

ካለፈው ስህተታቸው መማር የማይችሉና ፍቃደኝነቱም የሌላቸው ያንኑ ያለፈውን ስህተታቸውን መድገማቸው አይቀሬ ነው፡፡ ባለፈው በተቃዋሚዎች በርካታ ስህተቶችና ውድቀቶች ተከናውነዋል፡፡ እነዚህ ስህተቶች ተነቅሰው ሊወጡ ይገባል፡፡ ከነዚህም ስህተቶች በመነሳት ላይደገሙ ትምህርት ሊወሰድባቸውና ዳግም እንዳይመጡም ሊገቱ ተገቢ ነው፡፡

የተቃዋሚውን ተቃዋሚዎች ማወቅ፣ የተቃዋሚዎች ተቃዋሚዎች ቸል ሊባሉ አይገባም፡፡ሃይላቸው ተከፋፍሎ በመግዛትና በብሔር በማለያየት ድብ ድብ ጨዋታ ነው፡፡ ተቃዋሚዎች ተሰባስበውና ተባብረው በአንድ ቢሆኑባቸውና አንድ የጋራ አጀንዳ ቢኖራቸው ገዢዎቹ የተቃዋሚ ተቃዋሚዎች አቅመቢስ ልፍስፍስ ናቸው፡፡

ተጎጂነትን ማቆም፣

ከተቃዋሚዎች ጥቂቶቹ የተጎጂነት አስተሳሰብ; ይዘዋል፡፡ ማንም ሰው የተጎጂነት ስሜት ሲያድርበት ከተግባርና ከሃላፊነት ይርቃል፡፡ ስለታሰሩት ጋዜጠኞች በቅርቡ ለተደረገለት ቃለመጠይቅ በሰጠው ይፋ መግለጫ ላይ ሃይለማርያም መልስ ሰጥቶ ነበር፡፡ ለአሜሪካን ድምጽ በሰጠው ምላሽ ላይ በሃገሪቱ ያሉት የፖለቲካ እስረኞች ሽብርተኞች; እና ከተወገዙ ድርጅቶች ጋር ሁለት ባርሜጣ አድርገው የሚሰሩ ናቸው፡፡ አንደኛው ሕጋዊ; ሌላው ደግሞ ሕገ ወጥ፡፡ የፖለቲካውን መድረክ ለመክፈትና ለማረጋጋት ስላለው ሃሳብ ምንም አላለም፡፡ ያም ሆነ ይህ ሃይለማርያምም ሆነ ገዢው ፓርቲ ያሻቸውን ይበሉም፣ አይበሉም ተቃዋሚዎች ሳይደክሙና ሳያስተጓጉሉ አበክረው ሁሉም የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ መጠየቃቸውን መቀጠል አለባቸው፡፡ ተጠያቂነት ማለትም ይሄው ነው፡፡ ተቃዋሚው ሁልጊዜ ለትክክለኛው ጉዳይ መቆም አለበት፡፡ የፖለቲካ

ሰዎችን ከወህኒ መልቀቅ ትክክል ነው፣ በወህኒ ማጎር ግን ስህተት ነው፡፡

በመንስኤዎችና በጉዳዮች ላይ የጋራ አጀንዳ ማዘጋጀት፣ በሁሉም ተቃዋሚዎች ተቀባይነት ያለው የዴሞክራሲ፣ የሰብአዊ መብት፣ የሕግ የበላይነት፣ የሕዝቦች አንድነት፣ የኢትዮጵያ ሕዝቦች ጥምረት ነው ማዕከሉ፡፡ እነዚህን ጉዳዮች ለማገዝና ለማራመድ የሚሆን አጀንዳ በጋራ መቅረጽ ምን ችግር አለው?

ከስምምነቱ ሳይርቁ ላለመስማማት፣ ይሄን ከኔ በሃሳብ ጋር መቶ በመቶ ካልተስማማህ ጠላቴ ነህ; የሚለውን ጎጂ እምነት የተቃዋሚ አመራሮችና ደጋፊዎቻቸው፣ ጨርሰው ማጥፋት አለባቸው፡፡ ከህሊናቸው ጋር ያሉ ሰዎች በሃሳብ ባይስማሙ ምንም በማለት አይደለም ጉዳትም የለውም፡፡ እነዚህ ደግሞ የዴሞክራሲ ባህሪ ናቸው፡፡ ተቃዋሚው በውስጡ የሃሳብ ልዩነትን ሳይቀበል የገዢውን ፓርቲ መቻቻልን አለመቀበል ሊያወግዝ ተገቢ ነው?

ግለሰብተኝነት ተመላኪነትን መከላከል፣

በኢትዮጵያ ተቃዋሚዎች ሂደት ውስጥ በጣም አስቸጋሪው ጉዳይ የሆነው የግለሰቦች ተመላኪነት ነው፡፡ በተለያየ ጊዜ በተደጋጋሚ ተቃዋሚው ጀግኖችን በመፍጠር እነሱን ከምንም በላይ አድርጎ በመመልከትና ለማመን በሚያስቸግር ሁኔታ እያሞካሸና እያሞገሳቸው ከማምለክ ባልተናነሰ መጠን ከበሬታ ሰጥቷቸዋል፡፡ ይህንን ባደረግን ቁጥር ደግሞ የወደፊት ፈላጭ ቆራጭ ገዢዎች እያሳደግን መሆኑን መዘንጋት የለብንም፡፡

ዘወትር በቀናነት መንቀሳቀስ፣ ተቃዋሚዎችም ሆኑ አብረዋቸው የተሰለፉት ሁሉ በቀና መንገድ መጓዝን መልመድ አለባቸው፡፡ ግለሰባዊም ሆነ ድርጅታዊ ግንኙነታቸው በቀናነት የተመሠረተ ሊሆን ይገባል፡፡ የምንለውን መሆንና የምንሆነውን ማለት ይገባናል፡፡ የአንድ ሰው ግለኛ የበላይነት ከሚያስፈልግ ደሴት ውስጥ ያስቀምጠናል፡፡

በጥቅሉ እያሰብን፣ ተግባራችን ወቅታዊ፣ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ የሚደረግ ትግል ምርጫን ማሸነፍ አሊያም የስልጣን እርካብን ረግጦ ለሕዝባዊ ቢሮ መብቃት ብቻ አይደለም፡፡ ትግሉ ለታላላቅ ጉዳዮች ነው፡፡ ዘላቂነት ያለው ዴሞክራሲያዊ መሰረት ለመዘርጋት፣ በኢትዮጵያ ሰብአዊነትን ማክበርና መጠበቅ እንዲሁም ተጠያቂነትንና የሕግን የበላይነት በአግባቡ አክብሮ ማስከበር፡፡ ይህንን እውነታ አምነን ከተቀበልንም ትግሉ አሁን ላለነው ለኛ ብቻ ሳይሆን፣ ለሚመጣው ትውልድም ጭምር ነው፡፡ የምናደርገው ሁሉ ከኛ አልፎ ለተተኪዎቹ ልጅ ልጀቻችን የሚተላለፍ ኢትዮጵያችን ውድና የምትናፈቅ፣ ኖረንባት የማንጠግባት እንድትሆን በማድረግ ነው፡፡

ወጣቱ ትውልድ ለመሪነት እንዲበቃ ዕድሉን መስጠት! በተቃዋሚ ፓርቲ ውስጥ ያለን የእድሜ ባለጸጎች ብዙዎቻችን ለመቀበል የሚያስቸግረን ጉዳይ አለ፡፡ ያም ችግራችን ቦታውን መልቀቅና ለወጣቱ ማስረከብን መማርና መቀበል አለብን፡፡ ለወጣቱ አመራሩን እንዲይዝ ዕድሉን እንስጠው፡፡ ወደድንም ጠላንም መጪው ዘመን የእነሱ ነው፡፡ ከኛ ስህተቶች እንዲማሩ ብናግዛቸውና ወደበለጠ አስተሳሰብና ዘዴ

ቅጽ 1 ቁጥር 1 ጥቅምት 2005 ዓ.ም

14

Page 15: Semayawi1/Newly formed political party the blue (Semayawi)  founder, Professor Mesfin Wolde Mariam

እንዲዘልቁ ብናደርግ በእጅጉ ተጠቃሚዎች እንሆናለን፡፡ በዓለም አቀፍ ተቀባይነትን ያገኘው ወጣቶችን የሚመለክት አንድ እውነታ ቢኖር! ከምንም በላይ ነጻነትን መውደዳቸው ነው፡፡ የመጀመርያዋ የሴት ፖለቲካ መሪ የሆነችው ብርቱካን ሚዴቅሳ ትለው እንደነበረው! የዕድሜ ባለጸጋ የሆኑት መሪዎቻችን እኛ ተማሪዎቻቸውና ተረካቢዎቻቸው ለምንገነባት የወደፊቷ ሃገር ኢትዮጵያ; እነሱ ውሃውን ያቀብሉን እኛ ከዚያ ባሻገር ያለውን ሁሉ እያደረግን ሃገርን እንገንባ፡፡

ሃሳባችን እንደ ድል አድራጊ እንጅ እንደ ተሸናፊ አይሁን! ድል፣ድል አድራጊዎች እንደሚያስቡት! ሽንፈትም ተሸናፊዎች እንደሚያስቡት አይደለም፡፡ በድል ውስጥ ሽንፈት እንዳለ ሁሉ በሽንፈት ውስጥም ድል ይገኛል፡፡ በ99.6 ምርጫውን ድል ያደረጉት በገጽታቸው ላይ የአሸናፊነት ምስል ይታይባቸዋል፡፡ የተገኘው ድል ግን በተንኮልና በቅሚያ፣ በእፍርታምነት የተገኘ መሆኑን አስረግጠን እናውቃለን፡፡ ዋናው ቁም ነገር ግን ተቃዋሚዎች እንደ አሸናፊ ስብስብ ወይም ተሸናፊ መመልከቱ ላይ ነው፡፡ አሸናፊዎች እንደአሸናፊ ያስባሉ ተሸናፊዎችም በተቃራኒው፡፡

የተቃዋሚው ጎራ እራሱን እንደገና መፍጠር አለበት!

ገዢው ፓርቲ ምንም የለውጥ ፍንጣቂም ባያሳይ ደጋግሞ ግን በየሕዝባዊ ንግግሩ፣ እራሴን እንደገና እያደስኩ ነው ይላል፡፡ ያም ሆኖ ግን ምንም የሚለወጥ የለም; ማለታቸውን ከቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ጊዜ ካለው ሁኔታ አሁን ምንም ለውጥ አይኖርም ነው የሚሉት፡፡ ተቃዋሚዎችም ቢሆኑ እራሳቸውን እንደገና መፍጠር አለባቸው፡፡ ለውጣቸውም እራሳቸውን ለዴሞክራሲያዊ እውነታ በማስገዛት፣ ሕዝቡንም በጠራ አመለካከት ላይ በማሰለፍ ሕብረትና አንድነት፣ መግባባትና መተሳሰብ ጠቀሜታው ታላቅ እንደሆነ ተገንዝቦ በማስገንዘብ፣ ድርጅታዊ ሃላፊነቱም በሕዝቡ ፈቃደኛነት ላይ የተገነባ መሆኑን በማረጋገጥና ሁል ጊዜም ዓላማቸው ለትክክለኛው ሁኔታ በመቆም በሃይል የሚደረገውንና አድርጊውንም ለመዋጋት መቆማቸውን በማረጋገጥ ላይ ሊሆን ይገባል፡፡

ተቃዋሚው ጨርሶ ተስፋ መቁረጥ አይገባውም፣ሰር ዊንስተን ቸርችል ፈጽሞ እጃችሁን አትስጡ፡፡ ፈጽሞ ፈጽሞ ፈጽሞ በምንም መልኩ ቢሆን፡፡ በትልቅም ይሁን ትንሽ ፈፅሞ እጃችሁን አትስጡ!! ለክብርና ለመልካም ስሜት በታማኝነት ካልሆነ በስተቀር ፈጽሞ ፈጽሞ!! ሃይል አለኝ ለሚለው አትንበርከኩ፡፡ከአፍ እስከ ገደፉ ለታጠቀው ጠላትና አብረውት ሽር ጉድ ለሚሉት ሾካኮች ፈጽሞ እጅ አትስጡ!!የኢትዮጵያ ተቃዋሚዎች ይህን ስልት ነው መከተል ያለባቸው እንጂ ለገዢው ፓርቲ አካኪ ዘራፍና የግፍ አፈና ሊሸነፉ አይገባም፡፡

ፈጽሞ ፈጽሞ ፈጽሞ!! ድል አድራጊዎች መንገዳቸው ይሄ ብቻ

ነው፡፡

ቅጽ 1 ቁጥር 1 ጥቅምት 2005 ዓ.ም

እሣት!!...ሊሞላው ትንሸ የቀረው ሰማያዊ ፓርቲ ውስጥ ህዝብን የሚያሰባስብ ፖለቲካው በእውቀት ላይ የተመሰረተ እንዲሆን የሚያስችል ውይይቶችን ዝግጅቶችን ዘወትር እሁድ ከጠዋቱ 3፡30 ጀምሮ ያዘጋጃል ይህም ወጣቶች አባቶች ያላቸውን ልምድ እንደቀስሙ የሰሩትንም ስህተት እንዳይደግሙ እንዲሁም የፖለቲካና የሞራል ትጥቅ እንደታጠቁ ያግዛቸዋል ከዚህም ቀደም በፓርቲው ፅህፈት ቤት ፕሮፌሰር መስፊን ወልደማርያም ዶ/ር ያዕቆብ ኃ/ማርያም ፕሮፌሰር በፍቃዱ ደግፌ ፕሮፌሰር ዝናቡ አበራ ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት ዶ/ር ዳኛቸው አሠፋ አቶ አበባው አያሌው አቶ ታዲዮስ ታንቱ እንዲሁም አቶ ወረታው ዋሴ ሰፊ የመወያያ እርእሳቸውን አቅርበዋል ይህም ይበል የሚያስብል በሌሎች ፓርቲዎችም ቤት ሊገባ የሚገባው ባህል ነው ፡፡የነፃነት የፍትህ የሰላምና የአንድነት እሳትም ይቀጣጠል ዘንድ የሁላችንም አስተዋፅኦ አስፈላጊ መሆኑን አውቀን የበኩላችንን እንወጣ፡፡ ኢትዮጲያ ለዘላልም ትኑር!!!

ኢማ ጎልድማን...

15

ሁሉ ያወራሁት በምኖርበት እምነቴ ማንኛችሁም በሰውነታችሁ ለሰብአዊነት ታዛዥ፣ ለእውነት ታማኝ፣ በሃቅ ለመቆም ቆራጥ እና ምንም ሳትጠራጠሩ እናንተን ላሳመናችሁ እውነት ብቻ ለመፍረድ የወሰናችሁ ትሆናላችሁ ብዬ ስለማምን ብቻ ነው፡፡ አናርኪስት መሆናችንን እባካችሁ እርሱት፡፡ አመፅን ቀስቅሰዋል እየተባልን የተወነጀልንበትም እርሱት፡፡ እኔ ከዛሬ ሦስት አመት በፊት በብዙ ሺህ ማይልስ ርቀት ላይ በነበርኩበት ጊዜ “ማዘር ርዝ” በተሰኘው መፅሄታችን ወጥቷል ተብሎ የተከሰስንበትንም ጉዳይ እርሱት፡፡ እነዚህን ሁሉ እርሱና የቀረቡብንን ማስረጃዎች ብቻ ለውሳኔያችሁ መነሻ አድርጉ፡፡ የቀረቡብንን ማስረጃዎች በሴራ ውስጥ መሳተፋችንን ያመላክታሉ? ሴራስ መኖሩን አረጋግጠውላችኋል? ህገ ወጥ ድርጊትስ ፈፅመናል? ህገ ወጥ የተባሉ ድርጊቶችስ መፈፀማቸው በማስረጃ ተረጋግጠዋል? በእኛ በተከሳሾች በኩል የምንለው በጣም አጭር ነው፤ አሱም “አልተረጋገጡም!!!”፡፡ እናም የእናንተ ውሳኔ የሚሆነው “ተካሳሾች ንፁሃን ናቸው!!” የሚል ነው፡፡ ነገር ግን ምንም ውሳኔ ይወሰን ትግሉ ይቀጥላል፡፡ እኛም በድቅድቅ ጨለማ ላይ ብርሃንን በመፈንጠቅ ለማይቆመው የየሰው ልጅ ትግል መሰረት እንሆናለን፡፡ የሰው ልጅ ዘርን ወደ ፍትሃዊ የኢኮኖሚ፣ የፖለቲካና መንፈሳዊ ነፃነት ለሚወስደው የነፃነት መንገድ የመነሻ አስኳልም እንሆናለን፡፡

----------------------------------------ኢማ ጎልድማንና አሌክሳንደር በርክማን በዚህ ክስ ጥፋተኛ ተብለው እያንዳንዳቸው የሁለት ዓመት እስርና የ10,000.00 ዶላር ቅጣት

ታዛቢ በምርጫ የሕዝብን የሥልጣን ባለቤትነት ማረጋገጥ ይቻላል የሚል ሙሉ እምነት ያለው፣ ለዴሞክራሲያዊ ምርጫ የታዛቢዎች ሚና ወሳኝ መሆኑን ያመነ፣ ለዚህም የሚጠይቀውን መስዋዕትነት ለመክፈል የወሰነ መሆን አለበት፡፡ ስለሆነም በቂ ግዜ ተወስዶ የምልመላና የሥልጠና ሥራ መስራት ያስፈልጋል፡፡

ለአንድ ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ወሳኝ የሆነው የምርጫ ቦርድ ጉዳይም ከላይ ከተገለጹት ጉዳዮች ባልተናነሰ ፓርቲው ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ነው፡፡ ስለ ምርጫ ቦርድ ጉድለትም ሆነ ድክመት የሚነሳው በምርጫ ማግስት መሆን የለበትም፡፡ ብለን ነበር ለማለት ያህልም ምክንያት ሲያገኙ ብቻ በመግለጫ መጮኹም አይጠቅምም፡፡ ቦርዱ በምርጫ ማግስት እንደሚባለው ነጻም ገለልተኛም ካልሆነ ጥያቄው መነሳት ያለበት አስቀድሞ በረዥም ጊዜ በጥናት ነው፡፡ ጥያቄያችሁ ትክክል ቢሆንም በጥያቄያችሁ መሰረት ማስተካከያ ለማድረግ ያቀረባችሁበት ጊዜ አጭር ስለሆነ የሚቻል አይደለም የሚል መከራከሪያ! የሚያሳጣ ምላሽም ሊኖር እንደሚችል ማሰብ ያስፈልጋል፡፡ ስለሆነም የቦርዱ ተቋማዊ አደረጃጀት፣ በቦርድ አባልነትም ሆነ በጽ/ቤት ኃላፊነት የተቀመጡ ሰዎች ማንነት፣ በራስ የመተማመን አቅማቸው” በነጻነት የመስራት ነጻነታቸው፣ የሕዝብን ድምጽ ወደ ሥልጣን የመቀየር ከባድ ኃላፊነት ለመሸከም መቻላቸው በሚገባ ተጠንቶ እንዲሁም ምርጫ ለማስፈፀም የወጡ አዋጆችና መመሪያዎች ተመርምረው ጥንካሬና ድክመትን ሙሉነትንና ጉድለትን የሚያሳይና ፓርቲው መሆን አለበት የሚለውን አማራጭ የያዘ ሰነድ ማዘጋጀትና በተገቢው ወቅት የምርጫ የጊዜ ሰሌዳ ከመውጣቱ አስቀድሞ ለሚመለከታቸው ሁሉ መድረስ አለበት፡፡ የተጠየቀው ምላሽ እንዲያገኝም ያልተቋረጠ ክትትል ያስፈልጋል፡፡ ምላሽ ካልተገኘም የቀረቡት ጉዳዮች የምርጫውን ዴሞክራሲያዊነት የማዛባት አቅማቸው ተገምግሞ እርምጃ መውሰድ ያስፈልጋል፡፡

የውድድር ነጻነት የሚጨናገፈው፣ ድምጽ አሰጣጥ የሚዛነፈው፣ ውጤት የሚጭበረበረው በድምጽ መስጫ አልያም በምርጫ ጣቢያዎች ነው፡፡ ስለሆነም ጠንካራ ተወዳዳሪ ፓርቲ ይህን ጉዳይ በረዥም ጊዜ ውስጥ አጥንቶ ችግሮችን ማሳየት መፍትሄውን ማቅረብ ለተፈጻሚነቱም ተግቶ መስራት ያስፈልገዋል፡፡

በምርጫ ብቁ ተወዳዳሪ ለመሆን የሚያስብ ፓርቲ የራሱን አቅም፣ የሕዝቡን ሥነ-ልቦና፣ የተወዳዳሪዎችን አቅምና ዝግጅት” መንግሥት ለነጻና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ያለውን ቁርጠኝነት እንዲሁም የአስፈጻሚውን ተቋም (ቦርድ) ሁኔታ ያገናዘበ የምርጫ ቅጽ አስቀድሞ ማዘጋጀት አለበት፡፡ ምርጫ ተጭበረበረ ብሎ ከመጮህ በፊት የተወዳዳሪዎቹን የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴም በተቻለ አቅም ለማወቅ መጣር አለበት፡፡ ለመጭበርበር የሚያስችሉ ቀዳዳዎችን ሁሉ አስቀድሞ እየደረሱ ለመዝጋት እቅድን ከዕለት-ዕለት አጠቃላይ የምርጫ እንቅስቃሴ ጋር እያገናዘቡ መስራት ያስፈልጋል፡፡ አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ የስልትም የእቅድም ለውጥ ይደረጋል፡፡

እነዚህ ተግባራት በወረቀት ላይ እንደሚጻፈው ቀላል እንዳልሆኑ ይታወቃል፡፡ በመሆኑም ነው ምርጫ በረዥም ጊዜ ሥራ እንጂ በሩጫ የሚገቡበት አይደለም ያልነው፡፡ እናም ለምርጫ 2ዐዐ7 ዝግጅት የመጀመሪያ ጊዜው በጣም ረፍዷል፡፡ በሩጫ ተከናውኖ የመጨረሻው መጨረሻ እንዳይሆንም ያሰጋልና ዛሬውኑ የታቀደና የተጠናከረ ሥራ መጀመር ይኖርበታል፡፡

ከገጽ 23 የዞረ

ከምርጫ...

Page 16: Semayawi1/Newly formed political party the blue (Semayawi)  founder, Professor Mesfin Wolde Mariam

ቅጽ 1 ቁጥር 1 ጥቅምት 2005 ዓ.ም

ዛሬ ጠዋት ሊነጋጋ ሲል ነበር ከቤት የወጣሁት፡፡ ከ3 ወር በፊት የተቀጠርኩበትን የፓስፖርት ማሳደስ ሒደት ላከናውን፡፡ ከጥቁር አንበሣ ሆስፒታል ጀምሮ ያለው ግርግር ይገርማል! እነዛን በፎቅ የተንቆጠቆጡ አረብ ሃገራትን ይቅርና አዲስ አበባን እንኳን በቅጡ የማያውቁ ሴት እህቶቼ በሰልፍ ተደርድረዋል” ለማየት ያሳዝናሉ እንኳን ስራ ለማሰራት! የቀጠሮ ወረቀቴን አሣይቼ ወደ ግቢው ዘለቅኩ፡፡

…….ውጪ ከነበረው ሠው የሚበልጥ ሕዝብ ውስጥ አለ፡፡ ኸረ ጉድ ነው!

እነዚህ ፈሪዎች የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅዱን ጥለው ወዴት እየሄዱ ነው? ብዬ አዘንኩባቸው” ስለ ህዳሴያችን አላነበቡም እንዴ? ስለ ኤኮኖሚያችን ባለ ሁለት አሐዝ እድገትስ አልሰሙም? ለዓለም ምሣሌ በሆንበት በዚህ የለውጥ ጊዜ ሰው እንዴት ከሃገር ይወጣል? ቀሽሞች ልላቸው አልኩና ከጎኔ የተሰለፉት ሁሉም ማለት ይቻላል አማርኛ አይሠሙም፡፡ እኔ ደግሞ ከክልል ቋንቋ የማውቀው አንድም የለም!

አብዛኞቹ እህቶች አዲስ አበባ ከገቡ ወራት አልፏቸዋል፡፡ ፓስፖርት የሚቀበሉበት ቀን እስኪደርስና ወደዛ ቤተሰባችንን እንለውጥበታለን ብለው ወደሚያስቡበት ሃገር እስከሚገቡ ኑሮን በአስማት ይኖሩታል፡፡ ደላሎቹ የሚሰሯቸውን በሌላ ጊዜ እናወራዋለን፡፡ በአጠቃላይ ህይወታቸው ያሣዝናል! #ሴት መሆኔን ጠላሁት! ለዚህ ሁሉ ተጠያቂው ደግሞ መንግስት ነው; አለቺኝ እድሳቱን የምታከናውንልኝ እህት ፊቷ ላይ ሐዘን እየተነበበ” ሣምንት መጥቼ የታደሰውን ፓስፖርት መውሰድ እንደምችል ነግራኝ ተለያየን፡፡

እውነት ሃገሬ ወዴት እየሔደች ነው?ኢትዮጵያዬ እድገትሽን አሳይኝ!

ዮናስ የተባለ አንድ ወጣት በፌስ ቡክ ማህበራዊ ድረ-ገጹ ካሰፈረው ጦማር የተወሰደ

ጋዜጣ ያለመንግስት ይኑረን የሚለው ውሳኔ ለመወሰን ለእኔ ቢተውልኝ የመጀመሪያውን ለመምረጥ ለመቅፅበትም አላንገራግርም›› ብለው ነበር፡፡ በአንፃሩ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትራችን አቶ መለስ ዜናዊ በአንድ ወቅት በፓርላማ እንደተናገሩት ከሆነ የመንግስት ልሳን የሆነው ‹‹አዲስ ዘመን››ንም ሆነ የግሉ ‹‹አዲስ ነገር›› ጋዜጣን አያነብቡም፡፡ ምርጫቸው ‹‹ዘ-ኢኮኖሚስት›› ነበር፡፡ ዳሩ የሀገር ውስጥ ምን ይሰራላቸዋል? የጋዜጠኝነት ሀሁ አልገባንም፡፡ ጋጠ-ወጦች ነን፡፡ ዝም ብለን እንጣጣለን፡፡[በወቅቱም ከላይ የተጠቀሱትን ስድብ አዘል ቃላቶች ሲሰነዝሩ በጋጠ-ወጥነት ያላደግን አዝነንና ተናድደን ነበር]ሕወሓትን ከ1971 ዓ.ም. እስከ 1981 ዓ.ም ድረስ በሊቀመንበርነት የመሩትና በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ የሰላምና የልማት ኢንስቲትዩትን በዋና ዳይሬክተርነት በመምራት ላይ የሚገኙት አቶ አቦይ ስብሐትም ባለፈው ዓመት ለሰንደቅ ጋዜጣ በሰጡት ቃለ ምልልስ ስለሚዲያው እንዲህ ብለው ነበር፡-‹‹…በነገራችን ላይ እጅግ የሚገርመውና ለኋላቀርነታችን መሠረት የሆነው ይኼ ነፃ ፕሬስ የምንለው ነው፡፡ አብዛኛው ነፃ ፕሬስ ኢትዮጵያዊ አይደለም፡፡ አገርን ማዕከል አድርጐ አይደለም የሚነሳው፤ ጥላቻን ነው የሚሰብከው፡፡ የኢትዮጵያን የጥላቻ ፖለቲካ ለማጥናት የተትረፈረፈ መረጃ የሚገኘው ከኢትዮጵያ ነፃ ፕሬስ ነው፡፡ በአንድ ጋዜጣ አራትና አምስት ዕትም ለማስተርስ ዲግሪ የሚሆን የመመረቂያ ፅሁፍ መፃፍ ይቻላል፡፡ የመንግስት ሚዲያም ቢሆን ያላደገ “Undeveloped” ነው፡፡ የጋዜጠኝነት ሙያ የራሱ የሙያ ሥነ-ምግባር ያለው ይመስለኛል፡፡ ህዝብን ማገልገል ደግሞ ቀዳሚው ይመስለኛል፡፡ በዚሁ ሲለኩ የመንግስትም ሆነ ነፃ ፕሬስ ፍርድ ቤት ቢሄዱ ቅር አይለኝም፡፡ ትክክለኛና ወቅቱን የጠበቀ መረጃ ህዝቡ ማግኘት አልቻለም››አቦይ፣ ‹‹አብዛኛው ነፃ ፕሬስ ኢትዮጵያዊ አይደለም…›› ሲሉ ፕሬሱ ኤርትራዊ፣ አሜሪካዊ፣ ቻይናዊ፣ ኮሎምቢያዊ፣ ጀርመናዊ… ይሆን?! አገርን ማዕከል ካላደረገስ ለባዕድ ሀገር ነው የሚሰራው ማለት ነው? ‹‹ጥላቻ መስበክ›› ማለትስ ምንድን ነው? የጥላቻ ቋት የት እንዳለና ምንጩ ከየት እንደሆነ እስኪ እያንዳንዳችን ልቦናችንን እንፈትሽ፡፡ … አብዛኛውን ጊዜ ‹‹የዴሞክራሲ ኦክስጅን›› ተብሎ የሚጠራው ነፃ ፕሬስ ዛሬ በአገራችን በምን ደረጃና በምን አይነት ሁኔታ እንደሚገኝ ህሊናውን ለእውነት የሰጠ ቅን ሰው ሀቁን በቀላሉ ያገኘዋል፡፡

‹‹ፈሪዎች ከመሞታቸው በፊት ደጋግመው ይሞታሉ››ፍርሃት ‹‹አቅም ያለው አደጋን መቀበልና አደጋውን ተከላክሎ እርምጃ ለመውሰድ መነቃቃት ነው›› የሚል ትርጓሜ ይሰጠዋል፡፡ በዚህ ሰዎች አደጋውን ለመጋፈጥ ወይም

ለማምለጥ ዝግጁ ይሆናሉ፡፡ ጀግንነት ከፍርሃት ነፃ መሆን ማለት አይደለም፡፡ ይልቅ አንድ ሰው/አካል የያዘውን ዓላማ ዳር ለማድረስ ዕቅዱ ላይ ጠንክሮ የመቆየት ብቃትን የያዘ ሲሆን ፍርሃትን የመጋፈጥ እርምጃን ይወስዳል፡፡ ድፍረት ወይም ወኔ በዓላማ ላይ ጫና በማሳደር ከፍርሃት በላይ የሚገኝ ተፈጥሯዊ ባህሪ ነው፡፡ ለዚህም ነው በዘርፉ ጥናት ያደረጉ ምሁራን፣ ‹‹ፍርሃትን አትፍራው፡፡ ፍርሃት እንዲያስቆምህ አትፍቀድለት፡፡ በድፍረትና በወኔ የተሞላ እርምጃ የምትወስድ ሁን›› በማለት ምክራቸውን የሚለግሱት፡፡ ሆኖም አንዳንዶች በተሳሳተ እምነት /Illusion/ በውስጣቸው ፍርሃትን ፈጥረው እንደሚሰቃዩ ጥናቶች ያመላክታሉ፡፡ በዚህም ሳቢያ ፈሪዎች ከመሞታቸው በፊት ደጋግመው እንደሚሞቱ ፈረንጆቹ አንድ አባባል አላቸው፡፡ “Cowards die many times before their death”በአገራችንም በፍርሃት ላይ ጥናት ተደርጐ ትክክለኛውን አሃዝ መናገር ባይቻልም ኢህአዴግን በምክንያትም ሆነ መሠረት በሌለው ሁኔታ የሚፈሩ (ደረጃው የሚለያይ) ዜጐች አሉ፡፡ ምንም ሆነ ምን መንግስት እንደመንግስት መከበር እንጂ መፈራት የለበትም፡፡ በአገሪቱ ውስጥ ያለውን ሕገ-መንግስት፣ ሕጐች፣ አዋጆች፣ ደንብና ሥነ-ስርዓቶች ከፍርሃት ነፃ ሆኖ ማክበር፤ ብሎም ማስከበር ይቻላል፡፡ እነዚህን ማክበርም ተገቢ ነገር ነው፡፡ በፍርሃት ቆፈን ውስጥ ሆኖ ግን መገዛትና ሕግን ማክበር ጤናማነት አይደለም፡፡ በአጉል ፍርሃት ያልታሰበ ስህተትና ወንጀል ሊፈጠር ይችላል፡፡ ስርዓቱን ከማክበር ባለፈ መፍራት ተገቢ አይደለም፡፡ ፍርሃት መንግስትንም ሆነ ዜጐችን ይጠቅማል የሚል እምነት የለኝም፡፡ እኛ ሰዎች በፍርሃት ሰበብ በውስጣችን ያለውን ዕምቅ ሀይል ሳንጠቀምበት እንዲሁ አባክነን እናስቀረዋለን፡፡ እሱ ነው በህይወታችን ትልቁን ለውጥ ሊያመጣልን የሚችለው፡፡ በግለሰብ፣ በቤተሰብ፣ በአገርና በዓለም አቀፍ ደረጃ የላቀ መልካም ለውጥንና እድገትን የሚያጐናፅፈን ውስጣዊ ማንነታችን ነው፡፡…ሆኖም ግን፣ ፈራንም አልፈራንም፣ ብንወድድም ባንወድም፣ ቢዋጥልንም ባይዋጥልንም፣ ብናምንም ባናምንም፣ ደስ ቢለንም ብናዝንም፣ ህሊናችንን ሸጥንም አልሸጥንም፣ ለሆዳችን አደርንም አላደርን፣ ለገዢዎች አጐበደድንም አላጐበደድንም፣ ከህሊና ሞራል ይልቅ ጥቅምን አስቀደምንም አላስቀደምንም… ገዢው ኢህአዴግን በስልጣን ላይ የማናገኝበት ጊዜ ይመጣል፡፡ ይኼ በምርጫም ሊሆን ይችላል፣ አሊያም አቶ በረከት ስምኦን ባለፈው ዓመት የ‹‹ሁለት ምርጫዎች ወግ›› በሚል ርዕስ ለንባብ ባበቁት በመፅሐፍ ምርቃታቸው ዕለት በሸራተን ሆቴል እንደተናገሩት 40 ዓመት ሞልቷቸው ወይም በማናውቀው በሌላ…፡፡ ነፍሳቸውን ይማረውና አቶ መለስ አንድ ቀን የዚህች አገር የመንግስት አስተዳደር ቁንጮ

የዛሬውን ኢህአዴግ...

16

Page 17: Semayawi1/Newly formed political party the blue (Semayawi)  founder, Professor Mesfin Wolde Mariam

ቅጽ 1 ቁጥር 1 ጥቅምት 2005 ዓ.ም

ሆነው የሚታዩበት ጊዜ ከትሞ እንደሚገኝ ብዙ ጊዜ አስብ ነበር፡፡ ወገኖቼ ይኼ ብዙ አያስገርምም፡፡ የዓለማችንን አንዳንድ ታሪኮች ወደኋላ መለስ ብለን ብንመለከት በቂ መልስ እናገኛለን፡፡ስማቸው በመጥፎ የሚነሱትና አስፈሪ የነበሩት ፋሽስቱ ሞሶሎኒንና የናዚ ጀርመኑ አዶልፍ ሂትለር የስልጣን ፍፃሜ የተጠናቀቀው በአሳዛኝ ሁኔታ ነበር፡፡ ለሃያላን መንግስታት ብሎም ለዓለም ስጋትና አስፈሪ መስለው ታይተው የነበሩትና በጉድጓድ ውስጥ ተደብቀው የተገኙት የቀድሞ የኢራቁ ፕሬዚዳንት ሳዳም ሁሴን መጨረሻቸውም ታይቷል፡፡ በአምባገነንነትና በጭካኔያዊ ድርጊቱ ተምሳሌት የሆነውና በአፍሪካ ውስጥ አስፈሪ ጦር የነበረው የደርግ መንግስት የርዕሰ ብሔሩ መንግስቱ ኃ/ማርያምና የጓዶቹ ፍፃሜ የእኛው አገር የቅርብ ጊዜ ትዝታዎች ናቸው፡፡በዓረቡ ዓለም አብዮት የቱኒዚያውን ቤን አሊ፣ የግብፅን ሆስኒ ሙባረክ የሊቢያው ሙአመር ጋዳፊ፣ የየመኑ አሊ አብደላ ሳለህን ፍፃሜ ታሪክ ተራ በተራ በገሃድ እያሳየን ይገኛል፡፡ ነገም ተረኛውን እናይ ይሆናል፡፡በዓለም ታሪክ ውስጥ አስፈሪ የነበሩ የተለያዩ የፖለቲካ ስርዓቶችና ቁንጮ መሪዎቻቸው ከመንበረ ስልጠናቸው ተከብረው፣ ተዋርደው፣ ተገድለው፣ ተፈጥሯዊ ሞትን ሞተው መውረዳቸውና በሌላ የመተካታቸው ሂደት ተፈጥሯዊና ታሪካዊ ሃቅ ነው፡፡ ለዚህም ጥሩ ምሳሌ የሚሆኑት በቅርብ ጊዜያት የሞቱት የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪ ሚል ሱንግ፣ የጋናው ፕሬዚዳንት ዶ/ር አታ ሚልስ እና የእኛው ጠ/ሚ/ር መለስ ዜናዊ ይጠቀሳሉ፡፡የጥቁር አሜሪካውያን የነፃነት ታጋይ ማርቲን ሉተር ኪንግ፣ የሕንዱ የሰላማዊ ፖለቲካ ታጋይ መሀተመ ጋንዲ፣ የላቲን አሜሪካ የነፃነት ታጋይ ቼ ጉቬራ፣ ጃማይካዊው ማርከስ ጋርቬይ፣ ደቡብ አፍሪካን ከአፓርታይድ ቅኝ ግዛት ያላቀቋት ኔልሰን ማንዴላ በፖለቲካው ጐራ ዓለም በታላቅ ተምሳሌትነት ሲያወሳቸው ይኖራል፡

፡ ስለዚህ እናንተ ኢትዮጵያውያኖች ዛሬ በፍርሃት ላይ ዳንኪራ እንምታ፡፡ ዛሬ ፍርሃታችን አያሸንፈን! በእኛነታችን አምነን ደፍረን እንቁም!

….የትናንት ጀግንነታችሁን ዛሬም አሳዩን?

ኢህአዴጐች እስኪ ዛሬም ያ የትናንቱን ጀግንነታችሁን አሳዩን፡፡ ጀግና ጀግናን ማፍራት አለበት፡፡ ጀግና ሆናችሁ ጀግና ህዝብን ፍጠሩ፡፡ ደፋር ሆናችሁ ደፋሮችን አሳዩን፡፡ ጠንካራ ሆናችሁ ጠንካራ ተቃዋሚ እንዲኖር አድርጉ፡፡ ኮሽ ባለ ቁጥር ሳትደናገጡ በችግሮችና በፈተና የማይናወጥ ትውልድን ቅረፁ፡፡ ልበ-ሙሉ ሆናችሁ ትውልድን ልበ-ሙሉ ማድረግ ይጠበቅባችሁ ነበር፡፡ ይኼንን ግን አላደረጋችሁም፡፡ ይልቅስ ቀላል የማይባል ህዝብን ተጠራጣሪ፣ በራሱ የማይተማመን፣ ፈሪ፣ በሆነ ባልሆነው የሚሰጋና የሚጨነቅ፣ እውነትን ከመጋፈጥ ይልቅ በውሸት ዓለም ውስጥ ራሱን እንዲደብቅ በርካታ በር ከፍታችሁለታል - ምንም እንኳን ምርጫው የግለሰቡ ቢሆንም፡፡ የስደት በሩም ክፍት ነው፡፡ በአገሩ ከመኖር ይልቅ በተለያዩ የውጭ አገራት ለመሰደድ የቆረጠን የዜጐች ጋጋታ ዘወትር በሥራ ቀናት የኢሚግሬሽን፣ የማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች እና የቆንፅላ ጽ/ቤቶችን በርና ደጃፍ መመልከት በቂ ነው፡፡ትናንት ጀግና ተብሎ የደርግ ሰራዊትን የገረሰሰው አካል ዛሬ በጀግንነት ለምን ላናየው ቻልን? ጀግንነት ያለውና የሚኖረው በጦር ሜዳ እና በትጥቅ ትግል ብቻ ነውን? በትግል ደማቸውን ያፈሰሱትና ህይወታቸውን የገበሩት፣ ለፍትህ፣ ለዴሞክራሲ፣ ለዕድገት፣ ለመልካም አስተዳደር አይደለምን?!

‹‹አሟሟቴን አሳምርልኝ!››ብዙ ጊዜ ቅድመ አያቶቻችን፣ እናትና አባቶቻችን ዕድሜያቸው እየገፋ ሲመጣ ፈጣሪያቸውን በፀሎት እንዲህ ሲሉ ይጠይቃሉ - ‹‹አሟሟቴን አሳምርልኝ››

በማለት፡፡ አዎን፣ ‹‹ፍፃሜን ማሳመር›› ተገቢና ብልህነት ነው፡፡ ‹‹ብልጥ ከሰው ሞኝ ደግሞ በራሱ ከደረሰ በኋላ ይማራል›› ይባላል፡፡ ኢህአዴጐች ለረዥም ዓመታት በስልጣን ማማ ላይ ተቀምጣችሁ ትገኛላችሁ፡፡ በዘመናችሁ ሰራን የምትሏቸው መልካም ነገሮች ይኖራሉ፡፡ ያጠፋችኋቸው በርካታ ነገሮች መኖራቸውም ግልፅ ነው፡፡ ይኼንን በድፍረት አምናችሁ ባትናገሩም ልቦናችሁ ግን ያውቀዋል፡፡ዛሬ ግን ያለፈ ታሪካችሁን የምትመረምሩበትና የመጣችሁበትን መንገድ ቆም ብላችሁ በጥሞና የምታሰላስሉበት ጊዜ ነው፡፡ አሁን ሰራን የምትሏቸው መልካምና መጥፎ ነገሮችን በድፍረት ለይታችሁ ለህዝብም ባይሆን ለህሊናችሁ የምታምኑበት ወቅት መሆን አለበት፡፡ መስመር የሳተውንና የጐበጠውን፣ የጠፋውንና እየጠፋ ያለውን ንቁ ሆናችሁ ልትመለከቱት ይገባልም እላለሁ፡፡ በፖለቲካና ተያያዥ ጉዳች ተከስሰው የተፈረደባቸውን ግለሰቦች ይቅርታ እያስጠየቁ ይቅርታ መስጠት ብቻ ሳይሆን እናንተም እስከዛሬ ላጠፋችኋቸው ነገሮች ለምታስተዳድሩት ሕዝብ ‹‹በዚህ በዚህ ጉዳይ ላይ አጥፍተናል፤ በቅንነት እንታረማለን›› በማለት ይቅርታ መጠየቅን መልመድ አለባችሁ፡፡ ተቋጥሮ የነበረ ቂም በቀላችሁን ማራገፍ ይኖርባችኋል፡፡ ከህዝብ ጋር ተፈራርቶ ወይም ሆድና ጀርባ ሆኖ ሳይሆን ከልብ ተከባብሮ የምትኖሩበትን መስመር ዘርጉ፡፡ ከእናንተ ሀሳብ በተቃራኒ የሚቆሙና በምክንያታዊነት የሚተቿችሁን የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ፖለቲከኞች፣ የፖለቲካ አቀንቃኞች፣ ግለሰቦች፣ ነፃ ሚዲያዎች፣ ጋዜጠኞች…እንደጠላት ከማየት በመቆጠብ መቻቻልና ማፍቀርን ልትለምዱት ይገባል፡፡ ስህተትን አምኖ ንስሐ መግባትና ምንም ሳይፈልጉ ማፍቀር መቻል የጀግና መንገድና ባህሪያት ናቸው፡፡ አለበለዚያ የዛሬዎቹ ኢህአዴጐች፡- በምን ጀግና እንበላችሁ?!

…ሆኖም ግን፣ ፈራንም አልፈራንም፣ ብንወድም ባንወድም፣ ቢዋጥልንም ባይዋጥልንም፣ ብናምንም ባናምንም፣ ደስ ቢለንም ብናዝንም፣ ህሊናችንን

ሸጥንም አልሸጥንም፣ ለሆዳችን አደርንም አላደርን፣ ለገዢዎች አጐበደድንም አላጐበደድንም፣

ከህሊና ሞራል ይልቅ ጥቅምን አስቀደምንም አላስቀደምንም… ገዢው ኢህአዴግን በስልጣን ላይ

የማናገኝበት ጊዜ ይመጣል፡፡

17

Page 18: Semayawi1/Newly formed political party the blue (Semayawi)  founder, Professor Mesfin Wolde Mariam

ምንም የሚያሰጋ ነገር የለበትም፡፡ የሚያሰጋው ‘እኔ ድኛለው እናንተ አልዳናችሁም! ዳኑ! መዳን አለባችሁ!’ ብሎ ሊያስገድደን የመጣ ጊዜ ያን ጊዜ ችግር ይፈጠራል፡፡ ፖለቲከኛ መቻቻልን ሁሉንም የሚችል…. ድነሃል አልዳንክም የሚባል አይደለም፣ ሁላችንም አብረን እንሂድ! አንተም በሃይማኖትህ ድነሃል፣ ይሄም በሃይማኖቱ ድኗል፣ እናቴም በሃይማኖቷ ድናለች የሚል እንጂ አልዳነችም እፀልይላታለሁ እንድትድን የሚል ለኔ ፀያፍ ነው ይሄ፡፡ እንደዚህ አይነት አዝማሚያዎች በጊዜው እየታረሙ ካልሄዱ አደገኞች ናቸው፡፡ ከዚህም ከዚያም የሚሰነዘሩ አጉል ሃሳቦች፡፡ ግን በጐ-መንፈስ እንዲያድርብን እግዚአብሔርን እየለመን በሁላችንም ላይ በጐ መንፈስ ካደረብን መነጋገር መወያየት ጀምረን ከችግራችን የምንወጣበት ጊዜ ይመጣ ይሆናል፡፡

ሰማያዊ፡-የህዝቡን የሀዘን ስሜት በተመለከተስ? የለቅሶ ሥነ-ሥርዓቱ ለአንድ ሳምንት ያህል የተከናወነ ነበር፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ በታሪኩ መሪውን ለመቅበር ዕድል እንዳለማግኘቱም በአቶ መለስ ሞት ምክንያት የታየው የለቅሶና የቀብር ክንውንስ ስለህዝቡ ስነ-ልቦና፣ ባህል ወይም ልማድ፣ እና ጠባይ ምን ይናገራል?

ኘሮፌሰር መስፍን፡- እኔ… ምንም…እ…. እንደው በነገራችን ላይ ይሄ እኮ መለስን የሚመለከት ነገር አይደለም፡፡ መለስ የለም፡፡ ይሄንን አድርጉልኝ አላለም፡፡ ምናልባትም አይፈልግም ይሆናል ይሄንን፡፡ ይሄንን ያደረጉት እነማን ናቸው? እኔ እውነቱን እና ውሸቱን ለይቶ ለማወቅ አልችልም- በአሁኑ ጊዜ፡፡ ግን ትንሽ ነው ያየሁት፤ ብዙም አላየሁም፡፡ ካየሁት ያ እውነት የስሜት መግለጫ ከሆነ ያ ሁሉ ሰው ስሜቱን የገለፀው በእውነት ከሆነ መለስ ዜናዊ የብዙ ሰዎቹን ኑሮ በጥሩ መልኩ ነክቷል፣ አሻሽሏል ማለት…እ…. እንግዲህ ያልታወቀ ስታትስቲክስ ከየት እንደምናመጣው አላውቅም…እ…. አለ ማለት ነው፡፡ ግን በሌላ በኩል ደግሞ ሲነገር፡- ገንዘብ ተከፍሎ ምን ተብሎ…. ይሄ ማንን ይጠቅማል? መለስ ዜናዊን አይጠቅመውም፡፡ ቤተሰቡን አይጠቅምም፤ የእሱን ታሪክ አይጠቅምም፡፡ ከሱ ታሪክ ጋራ ይሄ ሌለው በተፃራሪ የሚባለው ነገር አብሮ ይመጣል፡፡ ስታበዛው….. ስላበዛኸው ያንን በተፃራሪ መንገድ የሚመለከተው አስታኮ የሚያቀርበው ሃሳብ ሁሉ አፍራሽ ይሆናል፡፡ እና በእውነቱ ለሱ የሚጠቅመው አይደለም-ለታሪኩም ጭምር፡፡ ለነገሩ ይሄ ማንንም የሚጐዳ አይደለም፡፡ ሰዎቹ ከፈለጉ ተከፍሏቸውም ይሆን ሳይከፈሉ አለቀሱ፣ እዬዬ አሉ፣ ስሜታቸውን ገለፁ- መልካም! ምንም የሚያመጡት ነገር የለም፡፡ ምንም የሚለውጡት ነገር የለም፡፡

ሰማያዊ፡- ነገር ግን ኢህአዴጎች ይሄንን ነገር ህዝቡ የአቶ መለስን ፈለግ እንድንከተል እና የያዙትን መንገድ እንድንገፋበት ድጋፉን

እየሰጠን ነው ብለው እንደማስመስከሪያ እየወሰዱት ነው...ኘሮፌሰር መስፍን፡- ይሄንን የጊዜውን ሁኔታ አትመልከተው፡፡ አሁን እኮ ገና በትኩሱ ነው፡፡ እያደር እኮ ይሄ ነገር እውነቱ እየወጣ፣ እውነቱ እየወጣ፣ እውነቱ እየወጣ ሲሄድ፤ ብዙ ነገር ይገለጣል፡፡ አሁንም እየተገለጠ ነው አንዳንድ ነገር፡፡ ክፍያው ምን ያህል እንደሆነ እንደዚህ አንዳንድ ሰዎች እየተናገሩ ነው በራዲዮ፡፡ እና መዋሸት ማስዋሸት አይቻልም፡፡ አይጠቅምም፡፡ ለማንም አይጠቅምም፡፡ እና እውነቱ ይመጣል፡፡

ሰማያዊ፡- ለኢህዴግስ የሚያስተላልፉት ምን መልዕክት አለ? አሁን ባለበት ወቅት ላይ ይሄን አካሄድ ትቶ ይሄን አካሄድ ቢከተል ለአገር ይበጃል፤ ሁላችንንም ሊጠቅም ይችላል የሚሉት ሃሳብ ካለ ይሄንን እንደመደምደሚያም አርገን ይቀራል የሚሉትንም ሃሳብ ጨምረው በዚሁ ቃለ-ምልልሱን ብንቋጭ…..

ኘሮፌሰር መስፍን፡- እኔ በነርሱ በኩል….እ…. ስልጣኑን ወደ ህዝብ ለህዝብ በእውነተኛ መንገድ በትክክለኛ መንገድ የሚያስተላልፉበት ጊዜ የተቃረበ ይመስለኛል፡፡ ይህንን አውቀው እነሱ መንገዱን ቢጠርጉትና በተቻለ መጠን የኢትዮጵያን ህዝብ አንገቱን ቀና አድርጐ በኩራት በክብር፣ መብቶቹ ሁሉ ተከብረውለት፣ በህጋዊ ስርዓት ውስጥ ያለምንም ፍርሃት በሙሉ ነፃነት ኖሮ ወደብልፅግና ወደእኩልነት እና ወደነፃነት እንዲሸጋገር ቢያደርጉ የራሳቸውን ታሪክ የሚያሳምሩ ይመስለኛል፡፡ የኢትዮጵያንም ስም ማደስ የሚችሉ ይመስለኛል፡፡ ሳይዘገይ ብዙ ችግር ውስጥ ሳንገባ በተቻለ መጠን በበጐ መንፈስ ህዝቡን ቢመለከቱትና ቢደግፉት፤ እንዲደግፋቸው ቢያደርጉ ምናልባት ብርሃን የምናይበት ቀን ይመጣ ይሆናል፡፡ አሁን ግን ያለው የአፈና ስርዓት ይሄንን ቶሎ ብለው ማስወገድ አለባቸው፡፡ አሁን የአፈና ስርዓት አለ፡፡ የታሠሩት ሁሉ በሆነ ባልሆነው ነገር፣ ለምን ተናገራችሁ? ለምን ፃፋችሁ? ተብሎ... ዛሬ….መፃፍ ይቻላል መናገር ይቻላል- ኢትዮጵያ ውስጥ ባይሆን ውጭ ማሳተም ውጭ መናገር ይቻላል፡፡ እንደዛ ሁሉንም ሰው የተናገረውን ሁሉ የፃፈውን ሁሉ አሸባሪ እያሉ ወህኒ ከተውት አይዘልቁትም፡፡ አያዛልቅም፡፡ እና ይሄንን ይሄንን ማደስ አለባቸው፤ ማሻሻል አለባቸው፡፡ ከፈት ማድረግ አለባቸው፡፡ ከፍርሃታቸው ትንሽ ድፍረት ማግኘት አለባቸው፡፡ ወኔ ማግኘት አለባቸው፡፡ ይሄን ሁሉ የሚያመጣው ፍርሃት ነው፡፡ ፍርሃት ጥሩ ስሜት አይደለም፤ ስለዚህ እግዚሐር ከእዚህ ያውጣቸው ነው፡፡

ሰማያዊ፡- ምናልባት የቀረ የሚሉት ነገር ካለ….

ኘሮፌሰር መስፍን፡- ይኸው እኮ አልኩ! እግዚአብሔር ያውጣቸው ብዬ?! /ፈገግታ/

///

ቅጽ 1 ቁጥር 1 ጥቅምት 2005 ዓ.ም

18

ኘሮፌሰር መስፍን...

ማንም ሌላውን ሰው አንተ ከእኔ ያነስክ ኢትዮጵያዊ ነህ በኢትዮጵያዊነት ብሎ ማለት የሚችል የለም ፡፡ እንደዚህ ዓይነት ሚዛን በእጁ የጨበጠ አንድም ሰው የለም፡፡

ስለዚህም፡- መለስ ከማናችንም የማያንስ

ከማናችንም የማይበልጥ ነው- በኢትዮጵያዊነቱ፡፡

Page 19: Semayawi1/Newly formed political party the blue (Semayawi)  founder, Professor Mesfin Wolde Mariam

መለስ የክብር ዲግሪ እያገኙ! ቀልብ የሚስብ ንግግር እያደረጉ እጅግ የተሞካሹበት ወቅት ነበረ፡፡ በዚህ ጊዜም ነበር አቶ መለስ ከነጆርጅ ቡሽ እና ከነቶኒ ብሌየር ጋር ትከሻ-ለትከሻ እየተሻሹ ዴሞክራሲን የህልውና ጥያቄ ነው ብለው በነርሱ ፊት ቅቡልነት እና የበለጠ ተወዳጅነት ለማትረፍ የሻቱት፡፡ ከጓዶቻቸው በተለየም እርሳቸው ዴሞክራሲያዊ መሆናቸውን ለማሳየት እና ብቻቸውን እየፈጠሩ ያሉትን ሥርዓት ለማደላደል ያንን በር በተለየ ሁኔታ ከፈቱት፡፡ ስለዚህ እንደልብ እንድንናገር” እንደልብ እንድንደራጅ ሆነ! ትላልቅ ሰዎች አይተን በማናውቀው ሁኔታ ወደፖለቲካው መጡ፡፡ በመሆኑም ያንን መደገፍ ከፖለቲካ ትግል ጋር በእኩል የሚነፃፀር አልነበረም፡፡ በቃ ነፃነቱ ተሰጠን! ከዛ ተከለከልን፡፡ መሪዎችም እስር ቤት ገቡ! ወጣቶች እኔን ጨምሮ በሺህዎች በየካምፑ ታጐርን፡፡ ከዛ በኋላ ሲፈቱ ተቃዋሚዎችም ተበታተኑ፣ ፖለቲካውም አበቃ ተባለ፡፡ ስለዚህ ያኔ ፖለቲካውም በትግል፣ በልምድ፣ በዕድገት፣ በጥንካሬ የመጣ አልነበረም፡፡ የተፈቀደ ነው፡፡ እንደገፀ-በረከት የተሰጠ ነው፡፡ ሲፈቀድልን የልባችንን ተናገርን! ስንከለከል እቤታችን ተቀመጥን፡፡ ስለዚህ ይሄንን የምር የፖለቲካ ትግል ብለን እንወስደው ያዳግታል፡፡ የምር የፖለቲካ ትግል የምንለው፡- በአገራችን አፋኝ ስርዓት አለ፣ ለረጅም ጊዜ ሊገዛን የተዘጋጀ መንግሥት አለ፣ ይሄ ደግሞ ለኢትዮጵያውያን አይገባንም፣ ትልቅ ህዝብ ነን፣ ትልቅ ታሪክ አለን፣ የነፃነት ምልክት የሆንን ህዝቦች ነን! ብለን ተነስተን ክብራችንን እና ነፃነታችንን ለመቀዳጀት የምናካሂደው ነው፡፡ በዘመናቸው የነበሩ አባቶቻችን በዘመናቸው የሚጠበቀውን የትውልድ ድርሻ ተወጥተዋል፡፡ እኛም በዘመናችን አፋኝ ስርዓቶችን በዴሞክራሲያዊ ሥርዓት በመተካት የበኩላችንን ልናደርግ ይገባናል፡፡ በመሆኑም፡- ከነዚህ ነገሮች የሚነሳ ቁርጠኛ የሆነና በሃሳባውያን የተነሳ ርዕዬተ-ዓለማዊ ትግል ነው የምር ትግል ብለን የምንወስደው፡፡ በመበለጥ ስሜት፣ በቅራኔ ስሜት እና በሌላ ዓይነት ስሜት ሳይሆን በሃሳብ ዴሞክራሲን የምር ለማምጣት የሚደረግ! ራስን ለማህበረሰብ በመስጠት የሚደረግ የፖለቲካ ትግልና መነቃቃት አጠቃላይ ማህበራዊ መነቃቃት ያስፈልጋል፡፡ ይሄ ደግሞ በስራ የመጣ እንደሆነ ህዝቡ የለውጡ ባለቤት እና ተቆጣጣሪ ይሆናል! በልበ-ሙሉነትም እውነተኛ የስልጣን ሉዓላዊነቱን በሥራው ያረጋግጣል፡፡ አምባገነን ህዝብን አሸንፎ ሊቀጥል አይችልም፡፡ በመሆኑም ይህን አውቆ የሚያስከፍለውን ዋጋ ከፍሎ በትግል ዴሞክራሲና ነፃነትን ማምጣት ይቻላል፡፡ያንን ነው የምር ትግል የምንለው እኛ፡፡ ስለዚህ ተስፋ መቁረጥ ሰርተህ አልሳካልህ ሲል የሚመጣ ስሜት ነው፡፡ እርግጥ ነው ኢህአዴግ በፈቀደልን ነገር ተነስተን ጀምረን ብዙዎቻችን ዋጋ ከፍለናል፡፡ ታስረናል፣ ተገርፈናል፣ ብዙ ሰው ሃብቱን አጥቷል፣ ተፈናቅሏል ያንን እየካድኩ አይደለም፡፡ ነገር ግን በፖለቲካ ትግልና በፖለቲካ ልምድ በድል የመጣ ነገር እስካሁን አልጀመርነውም! መሥራት አለብን!

ሰማያዊ፡- ስለዚህ የያዛችሁት ትግል ረጅም ነው እያሉኝ ነው?

ኢ/ር፣ይልቃል፡- አድካሚ ነው በርግጥ! ብዙም ዋጋ ያስከፍላል፡፡ እ….ደግሞ ለመታገል መሠረታዊ የሚሆኑ በቂ ምክንያቶች ስላሉ የምር ከተሠራ ጊዜውንም ማሳጠር ይቻላል፡፡ የያዝከው እና ያነገብከው ዓላማ ነው ትግሉን ትልቅም

ትንሽም የሚያረገው፡፡ ኢህአዴግ ምንም ዓይነት መሬት የያዘ የፖለቲካ መሠረትና ድጋፍ የሌለው! ያለችውን ትንሽ ሃብት ሰጪና ከልካይ ሆኖ ብቻ ነው ፖለቲካውን የሚያራምደው፡፡ ምንም ዓይነት የሃሳብ እና የእምነት መሠረት ያለው ነገር የለውም፡፡ ስለዚህ ይሄን ለመለወጥ የምር በሃሳብ ኢህአዴግን የሚያሸንፍ እና የመሪነት ሚናን የሚጫወት ስብስብ እስከተገኘ ድረስ እኔ ትግሉ ረዥም አይመስለኝም፡፡ ግን ቁርጠኛነትን ይጠይቃል! ዋጋም ያስከፍላል!

ሰማያዊ፡- እንደሰማያዊ ተሰባስባችሁ ያላችሁት የፖለቲካ ተዋንያን ለመሪነት የሚያበቃው ልምድ፣ ዕድሜ፣ ራዕይ እና ቁርጠኝነት አለን ብላችሁ ታስባላችሁ? እና ከዚሁ ጋር ተያይዞ ደግሞ ታስሬ ነበር ብለውኛልና ስለሱም ትንሽ ቢያብራሩልን?

ኢ/ር፡ይልቃል፡- አይ….እሱ እንኳን እንደቁም ነገር የሚቆጠር ጀብድ አይደለም፡፡ በዛን ዘመን እኔም ገና ከዩኒቨርሲቲ እንደተመረቅኩ በሥራ ላይ 2 ወይም 3 ዓመት ያህል ነው ያስቆጠርኩት…. እና ክፍለ ሃገር ነበር የምሠራው፡፡ እ… እና ለዛ መነቃቃት ውስጥ እንደማንኛውም የኢትዮጵያ ወጣት ትላልቅና የተማሩ ሰዎች ወደፖለቲካው ሲገቡ እኛንም አነሳስተውን ስለነበረ በፖለቲካው ውስጥ መነቃቃትን ፈጥረን በንቃት በአካባቢያችን ተንቀሳቅሰን ነበር፡፡ ወዲያውም ኢህአዴግ ሁሉንም ነገር መጨምደድና ማጥፋት ሲጀምር በየጦር ካምፑ አሠረን፡፡ እና እኔም እዛው እሠራበት የነበረው አካባቢ ላይ በብር ሸለቆ ካምኘ ከብዙ ኢትዮጵያውያን ጋራ ቆይቻለሁ፡፡ በመሆኑም ከጥያቄዎችህ ጋር ሳያይዘው፡- ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ለፖለቲካው ቅርብ ስለነበርን ድካሙንም ጥንካሬውንም በቀጥታ ለማየት ዕድል አግኝተናል፡፡ እ… በመውደቅ በመነሳት ውስጥ አልፈናል፡፡ መሪዎችንም በታሪክና በስማ በለው ሳይሆን በቅርበት ለማየት ችለናል፡፡ ስለዚህ መማር የሚችል ልቦና ካለ ከዛ በቂውን ነገር ተምረናል የሚል ሃሳብ አለኝ፡፡ ከዛ በተረፈ መሪነት አሁን እንደሚባለው ‘ ከሞቱም በኋላ ራዕይ አለንና እንደመንፈስ አባት በዛ መንገድ ይመራል!’ የሚለው ሳይሆን! ፓርቲያችን የሌሎችን ችሎታ መጠቀም ነው መሪነት ብሎ በዋናነት የሚገነዘበው፡፡ ሰዎችን ለጋራ ዓላማችን ብለው የመጨረሻውን እምቅ ሃይላቸውን አንጠፍጥፈው እንዲጠቀሙ ማስቻል ነው መሪነት፡፡ በመሆኑም ሰማያዊ፡- ኢትዩጵያውያን ችሎታና አቅማቸውን በያላቸው ሙያ አውጥተው እንዲጠቀሙ የማሰባሰብ፣ የማስተባበር፣ ሃሳብ የማሳየትና! ይህንን የተለያየ እምቅ ሃይል ወደ አንድ በጐ እሴት መለወጥ እንጂ የሁሉ ነገር አዋቂ መሆን አያስፈልገውም-መሪ ለመሆን፡፡ መሪ ኃላፊነት ያለው፣ መልካም ስነ-ምግባር ያለው፣ ከራሱ አብልጦ ለሀገሩ ዋጋ መክፈልን እንደክብርና እንደጥሩ ዓላማ የሚቆጥር እስከሆነ ድረስ የሁሉ ነገር አዋቂ መሆን አይጠበቅበትም፡፡ አይችልምም! መሪ ምናልባትም በባህሪው እና በስነ-ምግባሩ የሚከበርና ጓደኞቹም እሱ የሚለውን የሚያዳምጡት፣ ያላቸውን ችሎታ ሁሉ ለበጐ ነገር አነሳስቶ ሊጠቀም የሚችል ሰው

መሆን ብቻ ነው ወሳኙ እና አንኳሩ ጉዳይ ያም እንዳለ ሆኖ ግን በአንፃራዊ አቅጣጫ ብቃት የሚለውን ስናወዳድር! የተማሩና ትላልቅ ሰዎች ይህንን ፓርቲ ለመደገፍ ባልተለመደ ሁኔታ በየቢሮአችን እየመጡ ያላቸውን ልምድና ሃሳብ ለማካፈል ከዚህ ወጣት ጋር ለመስራት ዝግጁነታቸውን ገልፀዋል፡፡ ስለሆነም በአንድ ወይም በሌላ መንገድ ሰማያዊ የመሪነት ሚናውን እየተወጣ ነው ማለት ነው፡፡

በተረፈ ብዙዎቹ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች በግል ሙያ ከ1ዐ ዓመት ባላነሰ ጊዜ የተሰማሩ እና የዩኒቨርሲቲ ምሩቆች ናቸው፡፡ በመሆኑም ሰማያዊ ፓርቲ አሁን ባለበት ሁኔታ እንኳ ሀገር ቢመራ ከኢህአዴግ የተሻለ እንደሚሆን እኔ ምንም ጥርጥር የለኝም፡፡ ነገር ግን መረሳት የሌለበት ጉዳይ ቢኖር የመሪነት አካሄድ አንድ ቡድን ይሄን ያውቃል አያውቅም ሳይሆን! ሌላውን ለማሰባሰብና የኢትዮጵያውያንን ችሎታ በሙሉ ባሉበት ቦታና ሁኔታ ጭምር ለሃገር እንዲጠቅም ማድረግ ስለሆነ እኔ በችሎታና በልምድ ችግር ይፈጥራል ብዬ አላስብም፡፡

ሰማያዊ፡- በዚህ ረገድ ሃገር-አቀፍ ፓርቲ እንደመሆናችሁ መጠን ከጫፍ እስከ ጫፍ ያለውን የኢትዮጵያ ህዝብን የሚወክል አጀንዳ በማንሳት ምልዓተ-ህዝቡን ማነቃነቅ ግድ ይላችኋልና! ከዚህ አኳያ እናንተ እንደሰማያዊ ፓርቲ ከፍተኛ ድጋፍና ተቀባይነት እናገኛለን ብላችሁ የምታስቡበት የተለየ አካባቢ ይኖር ይሆን? ወይንስ እንደአገር-አቀፍ ፓርቲነታችሁ ሁሉንም መማረክ የሚችል ሃሳብ አለን ነው የምትሉት?

ኢ/ር፡ ይልቃል፡- በኛ እምነት በኢትዮጵያ የፖለቲካ መልክዓ-ምድር ላይ ከኢህአዴግ ጋር ተያይዞ የመጣው ይሄ በጎሣ፣ በመንደር፣ በሰፈር የመደራጀቱ የአየር-ባየር የፖለቲካ ንግድ ሰው-ሰራሽ እና በተለይም በፖለቲካ ልሂቃኑ አካባቢ ጐልቶ የሚታይ የእበላ-ባይ እኩይ ቁማር ነው፡፡ ቅድምም እንደገለፅኩልህ በ196ዐዎቹ አካባቢ ይነፍስ በነበረው ዘመን-አመጣሽ ባዕድ ሃሰብ ሳር ቅጠሉ ሁሉ የኮምዩኒስት አስተሳሰብ ተሸካሚ በነበረበት ጊዜ የአገራችን የዚያ ዘመን ወጣቶች በጥራዝ-ነጠቅነት በላያችን ላይ የጫኑብን የታሪክ መሠረትም ሆነ ተጨባጭ ነባራዊነት የሌለው ወንጋራ አስተሳሰብ ነው፡፡ ስለዚህ የኢትዮጵያዊነት ስነ-ልቦና ከዕድሜ-ጠገብነቱ እና ረዥም የታሪክ ትስስሮሹ አንፃር ከጎሣ ፖለቲካ ልቆ በኢትዮጵያውያን ነፍስ ውስጥ በደማቁ የታተመ አሁንም ህያው ቀዳሚ-ማንነታችን በመሆኑ ኢህአዴግ-ወለድ የጎሣ ፖለቲካን የምር እንደሚያሸንፍ ቅንጣት ታክል አንጠራጠርም፡፡ አንዳንድ ሰዎች ግን ይህንን በኢትዮጵያዊ ብሔረተኝነት ላይ ያለንን የማያወላውል ልበ-ሙሉነት ባለማወቅ ወይም በግንዛቤ እጥረት ከአክራሪ-ብሔረተኝነት /ultra nationalism/ እና ጀብደኝነት ጋር አምታተው እንዳይመለከቱብን ማሳሰብ እንሻለን፡፡ ኢትዮጵያዊነት በአራቱም የኢትዮጵያ ማዕዘናት ያለ! ህዝብ የሚደግፈውና የሚያምንበት! አብሮ የኖረበት! ብሎም አብሮ

ቅጽ 1 ቁጥር 1 ጥቅምት 2005 ዓ.ም

ኢ/ር፡ይልቃል...

19

Page 20: Semayawi1/Newly formed political party the blue (Semayawi)  founder, Professor Mesfin Wolde Mariam

የሞተለት ጭምር የጋራ ማንነት ነው፡፡ እኛ በኢህአዴግ የብሔር-ብሔረሰቦች ዘመን ያለን ሰዎች እኮ! ሌሎች ቀደምት ኢትዮጵያውያን ሰዎች በመሠረቷት ኢትዮጵያ ውስጥ የምንኖር ነን- በአጉል አካሄድ ሄደን እስካላፈረስናት ድረስ! በመሆኑም ይሄ በኢትዮጵያዊነት ላይ የተገነባ ፅኑዕ እምነት ኢትዮጵያን ከነሙሉ ነፃነቷ እና ክብሯ ጠብቆ ያኖረ፣ ስሟን በዓለም ያስጠራ፣ ህዝቦቿን በአንድነት የያዘ፣ በማህበራዊ ህይወት ያስተሳሰረ የኢትዮጵያውያን ሁሉ መተሳሰሪያ ገመድ ነው፡፡ ይሄን ደግሞ በአላዋቂነት በጣጥሰን ጥለን አንበሳ የማናስር የተበጣጠስን ድር እንዳንሆን መጠንቀቅ አለብን፡፡ ኢትዮጵያውያን እኮ በታሪካቸው ለኢትዮጵያዊነት ሞተዋል! ከአራቱም አቅጣጫዎች ተሰባስበው ሄደው ለኢትዮጵያዊነት ሞተዋል፡፡ ባንዲራችንን ግመሎቻችን እንኳን ያውቁታል የሚሉት የዳር-አገር ኢትዮጵያውያን ሳይቀሩ የተሰውለት ነው-ኢትዮጵያዊነት! በመሆኑም፡- ሁሉም ኢትዮጵያዊ ከትናንሽ ሃሳብና ላንድ የግል የፖለቲካ ጥቅም ሲባል ወደየጎሣ ኮሮጆው ካልገባ በስተቀር! እኔ ኢትዮጵያዊነት ዛሬም አሸናፊ እንደሚሆን ከልብ አምናለሁ፡፡ ኢትዮጵያዊነት አሁንም ከኢትዮጵያውያን ልብ ላይ ያልተፋቀ እንደውም ውስጥ-ውስጡን ስር-እየሰደደና እየተብላላ የሚሄድ እጅግ ግዙፍ የማንነት መሠረታችን ነው፡፡ ከዚህም በላይ ኢህአዴግ ብቸኛ እውቅና የሚሰጠው መጤ ፖለቲካዊ የጎሣ ማንነት አሁን አሁን እውነተኛ መልኩ እየታየበትና አመኔታ እያጣ የመጣ የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች መነገጃ ሆኖ እየተጋለጠ ነው፡፡ የቅርቡን የኦህዴድ ሁኔታ ብቻ መመልከቱ ለዚህ በቂ ነው፡፡ የጎሣ-ኢንተርኘረነሮች (ነጋዴዎች) ለግል ቁሳዊ ፍላጎታቸው የሚጠቀሙበት የሀሰት መሳሪያ ነው-የጎሣ ፖለቲካ፡፡ በመሆኑም ይህ ለኢትዬጵያውያን ባዕድ የሆነ አስተሳሰብ በስነ-ልቦናችንም ውስጥ ጭምር ያልተዋሃደ ስለሆነ ምንም እንኳ ለጊዜው እንደግርዶሽ ሆኖ ባይናችን ላይ ቢያጠላብንም በቀላሉ የሚገፈፍና የሚናድ ዓይነ-ጥላ ነው፡፡

ሰማያዊ፡- እዚህ ላይ ግን አንዳንድ የኢህአዴግም ባለሥልጣናት እንደሚያነሱት- የብሔርን ወይንም ደግሞ እንደናንተ አገላለፅ የጎሣን ፖለቲካ ሊያመጣ የቻለ በኢትዮጵያ ውስጥ የነበረው ነባራዊ የመገለል ሁናቴ እንደሆነ ነው፡፡ በብሔር-ምክንያት የመጎዳት እና ከሥልጣን የመራቅ ሁኔታ ያመጣው ነው ባዬች ናቸው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ የብሔር-ጭቆና በኢትዮጵያ ውስጥ መሠረት የሌለው ነው! የሚሉም አሉ፡፡ እናንተ እንደሰማያዊ ፓርቲ በኢትዮጵያ የኋላ ታሪክ ውስጥ የግዛት ማስፋፋት በሚደረግበት ጊዜ የተካሄዱ ነገሮችን እንዴት ነው የምትመለከቷቸው?

ኢ/ር፡ይልቃል፡- አንደኛ፡- መሪ ስትሆን እ….. በመርህ ደረጃ…… የምር መሪ ከሆንክና …..ለታክቲክና ለፖለቲካ ብለህ ብቻ የማትናገር ከሆነ……እ……. የኋላውን አስከፊ ታሪክ ብቻ ሳይሆን ማየት ያለብህ የፊቱን ብሩህ መዳረሻ ጭምር ነው፡፡ ህዝብን የሚከፋፍለውንና በአንድ የታሪክ ወቅት ያጋጠመን ችግር ሳይሆን! በጋራ አንድ የሚያረገውንና ወደፊት አብሮ የሚያኖረውን ነው፡፡ በቂም-

በቀል ተነሳስቶ ሂሳብ ለማወራረድ ፖለቲከኛ ፖለቲካ ውስጥ አይገባም፡፡ ለዛውም በዚህ በ21ኛው ክ/ዘመን ውስጥ፡፡ ይህ አንድ ራሱን የቻለ የመርህ ጉዳይ ሆኖ ወደ ኢትዮጵያ ታሪክ ስንሄድ ደግሞ፡- ለኢትዮጵያ ብቻ አዲስ የሆነ በኢትዮጵያ ውስጥ የተፈጠረ የተለየ ታሪክ የለም፡፡ አሜሪካ እንደዚህ ዓይነት አገር ሆኖ የተፈጠረው እንዴት ነበር? እና ማንም አገር በፊሽካ… በቃ! ከዚህ ጀምሮ ልክ እንደ ኦሪት፡- ‘ብርሃን ይሁን አለ-ብርሃንም ሆነ!’” ‘እንዲህም ይሁን አለ- እንደዚያም ሆነ!’ እንደሚለው ሳይሆን! በሰዎች የኑሮ ዑደትና ሂደት ውስጥ ነው አገር እየተመሠረተ የሚሄደው፡፡ በመሆኑም በኢትዮጵያም በአገር-ግንባታ ሂደት ውስጥ በተለይም በደቡቡ የኢትዮጵያ ክፍል ውስጥ የባህል፣ የእምነትና፣ የቋንቋ ተፅዕኖ ነበረ፡፡ ነገር ግን እነዚህ ጥያቄዎች አሁን ጥያቄ ናቸው ወይ? አይደሉም! አሁን የኢትዮጵያ ህዝብ የሚፈልገው ሌላ ነገር ነው፡፡ እንደዛ ዓይነቱን ነገር ላድርግ ብሎ የሚመጣ መንግሥት የለም! እንደዛ ዓይነቱም ነገር አሁን በዜጎች ውስጥ የለም! በማለያየት ይሄንን የታሪክ እክል አስታውሶ፣ ቆስቁሶና፣ እንዳይሽር ነካክቶ ለራስ የፖለቲካ ጥቅም ማዋል ነው አሁን የተያዘው ፈሊጥ! እንደውም በዘር ተቧድኖ በእኔ እበልጥ! እኔ-እበልጥ! ስሜት አገርን ሊጐዳና አደጋ ላይ ሊጥል የሚችል ነገር ያለው አሁን ነው፡፡ የብሔረሰቦችን ችግር ፈታሁ የሚለው ኢህአዴግም ይህንን ለራሱ እኩይ የፖለቲካ ፍላጎትና የስልጣን ጥማት አውሎታል፡፡ የብሔረሰብ አስተዳደር እኮ የለም አሁን በኢትዮጵያ ውስጥ! ብሔረሰቦች በውክልና ራሳቸውን የሚያስተዳድሩ ከሆነ አቶ መለስ ለ21 ዓመታት ጠቅላይ ሚኒስትር መሆን አልነበረባቸውም፡፡ እንደእነሱ የጎሣ ፖለቲካ ቀመር ከሆነ፡- የኦሮምኛ ተናጋሪው ብዙ ቁጥር አለው፣ አማርኛ ተናጋሪው ብዙ ቁጥር አለው- ስለዚህ በውክልና ከሆነ ከነዚህ ቋንቋ ተናጋሪዎች የመጡ ሰዎች ናቸው ጠቅላይ ሚኒስትር መሆን ያለባቸው፡፡ በጎሣ ስም ተደራጅቶ በተቀነባበረ እና ዘመናዊ በሆነ ሁኔታ ላይ ጭቆና እየተካሄደ ያለው እንደውም አሁን ነው፡፡ ሌሎች ቀደምቶችስ ህይወትን ለመግፋትና በአገር-ግንባታ ሂደት ውስጥ በደመ-ነፍስ በመውተርተር የተፈጠረ ስህተት ነው፡፡ ይሄ ደግሞ አገር ሲገነባ የሚጠበቅ ሂደት ነው፡፡ የትም አገር የሆነው እንዲሁ ነው! በተጨማሪ አገር እንዲሁ ዝም ብሎ ቀጥ ያለ ታሪክ አይኖረውም፡፡ የግለሰብም ይሁን፣ የድርጅትም ይሁን፣ የአገርም ታሪክ የራሱ ደካማና ጠንካራ ጎኖች ያሉት እንጂ እንደመላእክት ታሪክ እንከን-የለሽ አይደለም፡

፡ ስለዚህ የኢትዮጵያ ታሪክም በዚሁ መልክ መታየት አለበት ብለን እናምናለን፡፡ ምናልባትም እኮ በአገር-ግንባታ ረገድ በኢትዮጵያ ታሪክ የተፈጠረው ስህተት ከሌላው አገር ጋር ሲነፃፀር ቀለል ያለና እዚህ ግባ የማይባል ይሆናል፡፡ በአሁኑም ጊዜ በተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች መካከል ያለ መሠረታዊ ችግር የለም፡፡ በአገዛዙና በዜጎች መካከል ግን ሁልጊዜም ችግር ይኖራል- ከአገዛዝ እስከአልወጣን ድረስ ጠመንጃ የያዘው ሃይል ሁሉንም ነገር በጉልበቱ ከማድረግ ወደኋላ ስለማይል ችግር ውስጥ መቆየታችን አይቀርም፡፡ ይሄንን መለወጥ የምንችለው ሥልጣን የህዝብ ሲሆን ብቻ ነው፡፡ ሥልጣን በዴሞክራሲያዊ መንገድ ወደህዝብ ሲተላለፍ የዜጎች ሁለንተናዊ መብቶች ሁሉ የሰውነት እና የዜግነት መብቶችን ጨምሮ አብሮ መከበር ይጀምራሉ፡፡ እንጂ፡- የባህልም፣ የእምነትም፣ የቋንቋም ተፅዕኖ በአገር-ግንባታ ሂደት ውስጥ ነበረ፡፡

ሰማያዊ፡- ከዚህ ጋር ተያይዞ በብሔር ስም የተደራጁና መንግሥትን በአመፅ ጭምር ገርስሰው ‘ነፃ መውጣት’ የሚሹ የፖለቲካ ሃይሎች አሎ፡፡ እና እነሱንስ እናንተ እንደፓርቲ እንዴት ነው የምትመለከቷቸው? እነዚህን ዓይነት ጥያቄዎች ሲከሰቱስ ምላሽ የምትሰጡበት አግባብ እንዴት ያለ ነው? ፓርቲያችሁ እንደሚለው ህዝባዊ-መንግሥት/ዴሞክራሲ/ በዚች አገር ቢመሰረት የእነዚህ ኃይሎች ዕጣ ፈንታና ጥያቄ ምን ይሆናል?

ኢ/ር፡ ይልቃል፡- አንደኛ እነዚህ በብሔር-ስም የተደራጁ ነፃ አውጪ ድርጅቶች እያደጉ ነው ያሉት ወይስ እየከሰሙ? የሚለውን ብናይ /መሠረታዊ የሆኑ ምክንያቶች እያሉ እንኳ! በመንግሥት አሠራር ውስጥ ቅር የሚያሰኙና ወደ ዳር የሚገፉ ነገሮች እንዳሉ እኛም እናምናለን/ ለጥያቄው ከፊል-ምላሽ ይሆናል፡፡ ይህ ጊዜ እያለፈበትና እየሳሳ የሄደ ከንቱ አማራጭ ነው፡፡ ነገር ግን ከነዚህ ኃይሎች ጋር በችግሩ ላይ እንደመስማማታችን መጠን በመፍትሄው አቅጣጫ ዙሪያ እንለያያለን፡፡ ፍፁም ተቃራኒ ነን ማለቱ ሳይሻል አይቀርም፡፡ ከጠመንጃ ትግል ይልቅ የፖለቲካ ትግልን መርጠን በሃሳብ የበላይነት ለማሸነፍ የምንጥር ህጋዊ ድርጅት ነን እኛ፡፡ በኢትዮጵያዊነት ጥላ ስር በዜግነት መብት ላይ ተንተርሰን መብቶችን ሁሉ ያለመሸራረፍ እስካከበርን ድረስ! እነዚያ ድርጅቶች ህዝባዊ የፖለቲካ ሥልጣን

ቅጽ 1 ቁጥር 1 ጥቅምት 2005 ዓ.ም

20

በተፈጥሮ ህግም ቢሆን ስርዓት ያረጃል፣ ቅቡልነቱ እየሳሳ እና እያለቀ ካፒታሉን

እየበላ በሄደ ቁጥር ስርዓት እርስ-በራሱም ተጠላልፎ ይወድቃል፡፡ የኛ ሚና ህዝብን

አደራጅቶ የሚመጣው ለውጥ የተጠና የታቀደና አስቀድሞ የተመራ እንዲሆን ማድረግ ነው፡፡ ለዚህም እንዲረዳ የህዝብን የፖለቲካ-ንቃት

ማሳደግ ነው ሚናችን፡፡ ስለዚህ ለውጡ በግድም ሆነ በውድ አይቀሬ ነው፡፡

Page 21: Semayawi1/Newly formed political party the blue (Semayawi)  founder, Professor Mesfin Wolde Mariam

በተመሰረተ ማግሥት እነርሱ እንደፖለቲካ አጀንዳ የሚያነሱት ጥያቄ ይኖራል ብዬ አላምንም፡፡ እዛጋ ያበቃል ሁሉም ነገር! አሁን እኮ እነዚህ ኃይሎች እያሉ ያሉት፡- ‘የፖለቲካ ትግል ማድረግ አይቻልም! መንግሥቱ አፋኝ ነው! ሥልጣን የህዝብ አልሆነም!’ ነው፡፡ በመሆኑም ከጎሣ አቅጣጫም ሆነ ከሀገር- አቀፍ አቅጣጫ የሚመጡት የኃይል-አማራጭ የሚከተሉ የፖለቲካ ቡድኖች የሚያነሱት ዋነኛ ጥያቄ ከመሠረቱ ካየነው ከህዝባዊ መንግሥት አለመኖር የሚመነጩ ናቸው፡፡ ስለዚህ ይሄ በሰላማዊ የፖለቲካ ትግል ከተቀየረ እነዚህ ድርጅቶችም በጠመንጃ የሚዋጉት ኃይል አይኖርም-የጠመንጃ መንግሥት በሌለበት ሁኔታ፡፡ ጥያቄው በመሠረቱ እዚያ ላይ አብቅቷልና! አሁንም አንተ ስትጠይቀኝ ከጥያቄህ ውስጥ ያለው ግምታዊ መነሻ /presumption/፡- አንድ የፖለቲካ ቡድን ስልጣን እንደወሰደ አርገህ በማሰብ ነው! እንጂ ስልጣን የህዝብ መሆኑን እና ሥልጣኑን የያዘው ቡድንም በተወሰነ የጊዜ ገደብ ከህዝብ የተሰጠው አደራ እንደሆነ አርገን ብናየው በዚህ ሁኔታ እነዚያ ኃይሎች የሚታገሉት ቡድን አይኖርም እዛጋ፡፡ በጎሣ መደራጀት እንፈልጋለን ብለው ካሉ ጥያቄያቸውን ለህዝብ በግልፅ የፖለቲካ መድረክ ያቀርባሉ! የሚጠቅምና የሚያምንበት ሆኖ ሲገኝ ይደግፋቸዋል ካልሆነም ይጥላቸዋል፡፡

ሰማያዊ፡- ስለሰላማዊ ትግል ይሄን ያህል ተስፋ የሰጣችሁ ነገር ምንድነው? ብዙዎች እንደሚያነሱት እጅግ አፋኝ ህጎች (የፀረ ሽብርና የመያዶች የመሳሰሉት) ባሉበትና እንዲሁም አሁን እንኳን በቅርቡ እንደምናየው በጣት የሚቆጠሩ አማራጭ የኘሬስ ውጤቶች እየታገዱ ባሉበት ሁኔታ! ይሄን ያህል ተስፋ ያሰነቃችሁ ነገር ምንድነው?

ኢር፣ይልቃል፡- እንግዲህ ተስፋ እንድንሰንቅ ያረጉን እነዚሁ ችግሮች ናቸው በራሳቸው፡፡ በእኛ እምነት እነዚህ ነገሮች የሚያሳዩን፡- ኢህአዴግ ምንም ዓይነት የፖለቲካ መሠረት አጥቶ ጉልበቱ ብቻ እንደቀረ ነው፡፡ አንድ ጋዜጣ በታተመ ጊዜ መንግሥቴ ይፈርሳል ብሎ ከሰጋ! በህዝብ ሠራሁት እና አደረግሁት የሚለው ነገር ሁሉ የሀሰት መሆኑንና እርሱም አየር ላይ ተንጠልጥሎ የቀረ መንግሥት እንደሆነ አመላካች ነው፡፡ ስለዚህ ህዝቡ ይህንን ፖለቲካው ያለበትን ዙር ተረድቶ የኢህአዴግ ጭቆና ማብዛት ቅጥ እያጣ ከመጣ ፍርሃትና ከአቅመ-ቢስነት መመንጨቱን መገንዘብ አለበት፡፡ ይህ ሁሉ ከፍራቻና ከአቅመ-ቢስነት የመጣ እንጂ ከጥንካሬ አይደለም፡፡ ስለዚህ በፖለቲካ ትግል በቀላሉ የሚለወጥ ነባራዊ ሁኔታ ላይ ደርሰናል፡፡ ሆኖም ግን ሰው ብዙ የማይረዳው ነገር ሰላማዊ ትግል የጠመንጃ ትግል የሚያስከፍለውን ያህል ዋጋ እንደሚያስከፍል ነው! ሞትን፣ ስቃይን፣ መሰደድን፣ ሁሉንም ነገር ያደርጋል፡፡ ይሄ እንደውም ከመሪዎቹ የሚጀምር ክስተት ነው-ባብዛኛው፡፡ ይሄን ዋጋ ለመክፈል እስከተዘጋጀን ግን ለመለወጥ እጅግ ቀላል ነገር ነው፡፡ በሃሳብ ስትሸነፍ ነው ከባድ የሚሆነው፡፡ አንድን የፖለቲካ ትግል ከባድ የሚያደረገው በህዝቡ ውስጥ ስር-ያልሰደደን ሃሳብ አሳምነህ አስተምረህ በዛ ውስጥ አሰባስበህ ያንን እምነት በተግባር ለመለወጥ የሚደረገው ጉዞ ነው፡፡ አሁን በኛ በኩል በሃሳብ ችግር የለብንም፣ነባራዊ ሁኔታን በመረዳትም ችግር የለብንም፡፡ አሁን የሚያስፈልገው ነገር ቢኖር ተስፋ የሚሰጥ ሀይል ሆኖና ዋጋ ከፍሎ ብሎም ያንን ውጤት እንደሚያመጣ አሳይቶ የፖለቲካ ትግል ማድረግ ነው፡፡ስለዚህ የችግሮቹ መባባስም የሚያመላክተው ነገር ቢኖር ችግሮቹን ለመለወጥ መነሳሳት እንዳለብን ነው፡፡ ይህ ኃላፊነት እንደዜጋ ከሁላችንም

የሚጠበቅ ነውና፡፡ ሌላው ደግሞ፡- ይሄ ሁኔታ የሚያሳየው ኢህአዴግ በህዝቡ ውስጥ እንደሌለና ሥርዓቱን ለመታገልም በጣም ቀላል እንደሆነ ነው፡፡ ስለዚህ እነዚህ ሁለት ነገሮች በተስፋ እንድንሰራና ነገሮችን እንድንለውጥ የሚያበረታቱ ናቸው፡፡

ሰማያዊ፡- ከዚህ አንፃር ከዚሁ ጋር ተያይዞ የህዝበ-ሙስሊሙ የእምነት ነፃነት ጥያቄና ጥያቄውን እያቀረበበት ያለውን መንገድ ከሰላማዊ ትግል አንፃር ፓርቲያችሁ እንዴት ይገመግመዋል?

ኢ/ር፡ይልቃል፡- ስለዚህ ጉዳይ በጣም የሚገርመው እና የሚደንቀው ነገር፡- ዜጎች መንግሥት በሀሰት ክስና በሀሰት ወንጀል ተጠያቂ አድርጐ ያስረኛል ብለው እጅግ ሰላማዊና ህጋዊ ለመሆን ሲጥሩ” በአንጻሩ መንግሥት ደግሞ ኃላፊነት የጎደለው ሥራ ሲሰራ መታየቱ ነው፡፡ መንግሥት አገርን ለመረበሽ፣ አንዱን ሃይማኖት ከሌላው ጋር ለማናከስ፣ በሃይማኖቶቹም ውስጥ ሰርጐ-በመግባት ለመከፋፈል ሲጥርና ሰላማዊያንን በሽብርተኝነት ሲከስ ማየቱ” በሌላ በኩል ዜጎች ደግሞ ከልክ በላይ ሲጠነቀቁ ለማስተዋል ተችሏል፡፡ ይሄ በእውነት በጣም የሚያሳዝንና የሚያሳፍር ነገር ነው፡፡ ዜጎች ይህን ያህል ለእውነትና ለህጋዊነት ሲጠነቀቁ፣ መንግሥት ደግሞ ሌላ እኩይ መንገድ ሲከተል ማየቱ አሳዛኝ ነገር ነው፡፡ መንግሥት ለ17ቱ የህዝበ-ሙስሊም ኮሚቴዎች ዕውቅና ሰጥቶ ሲደራደር ከቆየ በኋላ፣ በዚህ ነጥብ ተስማማን፣ በዚህ ነጥብ አልተስማማንም ሲል ከርሞ መጨረሻ ላይ ጥያቄያቸው የህዝብ ድጋፍ ሲያገኝ ሽብርተኛ ናቸው ብሎ አሰራቸው፡፡ እነዚያን ሰዎች ሲያስራቸው ደግሞ እባክህን ፍታልን ብለው ነጭ መሃረብ እያውለበለቡ ድምፃቸውን ሳያሰሙ እጅግ በሚገርም ሁኔታ ሃሳባቸውን ገለፁ፡፡ እና ይሄ የኢትዮጵያ ህዝብ የምር በእውነት የሚመራው ካገኘና የጋራ የሚያደርጉትን አስተሳሰቦች ወደፊት ይዞለት ከወጣ ለሰላማዊ ትግል ዝግጁ መሆኑን ያየሁበት ሁኔታ ነው፡፡ ለምሳሌ፡- ሰሞኑን አንድ አሜሪካዊ በሰራው ፊልም ሳቢያ በአረብ አገራት በሙሉ ብዙ የንብረት ውድመት፣የህይወት መጥፋት፣ ያለመረጋጋት ደርሷል፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ግን ይሄ ሁሉ ከሃይማኖት ጋር የተያያዘ ችግር እንኳ እያለ ጉዳዩ በዚያ መልኩ አልተገለፀም፡፡ እንግዲህ ኢትዮጵያዊነት ከሃይማኖትም፣ ከጎሠኝነትም በላይ ነው ብለን ስንናገር ይሄ የተግባር ማሳያ ምሳሌው ሊሆነን ይችላል፡፡ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ነብዩ መሃመድን ሳይወዷቸው ቀርተው አይደለም-እንዲህ ያለውን ነገር ያላደረጉት፡፡ ከሳዑዲ-አረቢያ በፊት እስልምናን የተቀበለች አገር ናት ኢትዮጵያ፡፡ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞችም ሃይማኖታቸውን ያከብራሉ! ነገር ግን አንድ አሜሪካዊ ሰውዬ ነብዩ መሃመድን የሚያቃልል ነገር ሰራ ተብሎ ፀረ-አሜሪካ ወይም ፀረ-መንግሥት የሆነ እንቅስቃሴ ማድረግ እንደማይገባ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች በአስተዋይነታቸው ተረድተዋል፡፡ በሙስሊምነታቸው ከሆነ አረቦች ያደረጉትን ነገር ማድረግ ነበረባቸው፡፡ የሆነው ግን ያ አልነበረም፡፡ ስለዚህ፡- ኢትዮጵያዊነት የማመዛዘን የጨዋነት ምልክት ነው ስንል የምር ይሄ ነው የሚነግረን፡፡ ከዚህ በላይ

ምን ነጋሪ ያስፈልገናል?!

ሰማያዊ፡- ፓርቲያችሁ ከአዲሱ የአቶ ኃ/ማርያም አስተዳደር የሚጠብቀው እና ተስፋ የሚያደርገው ነገር አለ?

ኢ/ር፡ይልቃል፡- እንግዲህ እሱ ገና አቅጣጫው ያልተለየ ጉዳይ ነው፡፡ ምናልባትም የበለጠ ጭቆናው የበዛበት ነገር በሁለት መልኩ ካየኸው፡- ሊነጋ ሲል ይጨልማል ዓይነት ነገርም ሊሆን ይችላል” አሊያ ደግሞ በበፊቱ መንገድ የመቀጠልና ራስን በራስ የማጥፋት /suicidal/ ጉዞ ሊሆን ይችላል፡፡ ለማንኛውም አሁን ያለው የኘሬስ አፈናና እቀባ ዘላቂ የሆነ ስልት ላይሆን ይችላል፡፡ ኢህአዴጎች አያያዙን ሊያውቁበት ይገባል፡፡ አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ ብዙ ሰው ሥራ-አጥ ነው፣ የኑሮ ውድነቱ በተለይ የምግብ ዋጋ ንረት ሰማይ ደርሷል፣ ሙስናው በየቦታው ተንሰራፍቷል፣ በመንግሥት አስተዳደር ላይ የሚታየው አለመተማመን እና የህዝቡ አመኔታን ማጣት ከፍተኛ ሆኗል፡ይሄ ሁሉ ነገር ተደማምሮ ሌላ ጣጣ ሊያመጣ ይችላል ቢባል እርግማን መጥራት አይሆንም፡፡ በመሆኑም ሁላችንም ወደማንመኘው ማህበራዊ ቀውስ እንዳንገባ ያሰጋናል፡፡ ስለዚህ ለእነዚህ ሁሉ ችግሮች ሁነኛ መፍትሄ ለመስጠት የፖለቲካ አሳታፊነቱ እና መድረኩ ከፈት ካልተደረገ፣ የሁሉም ኢትዮጵያውያን በችግሩ ላይ መረባረብ ከሌለ፣ በአገሩ ኃላፊነት በተሰማበት ሁኔታ የተፈጠረውን ችግር ለመቅረፍ ሁሉም ሰው የየራሱን ድርሻ ካልወሰደ፣ ኢህአዴግ ሁሌም እንደሚለው ችግሩንም የማውቀው እኔ ነኝ መፍትሄውም እኔ ነኝ ካለ መጀመሪያ እንደ ድርጅት የሚጐዳው ኢህአዴግ ራሱ ነው፡፡ ከዚያ በኋላ ነው እንግዲህ እንደአገር የምንጎዳው-ኢህአዴግ የአገር መሪ በመሆኑ የተነሳ የድርጅቱ ጉዳት ለአገሪቱም ጉዳት ስለሚፈጥር! እንግዲህ በተስፈኝነት የምናምነው ነገር ቢኖር ኢህአዴግ ለራሱም ሲል ይስተካከላል የሚለውን ነው፡፡ ያ እማይሆን ከሆነ ግን ለሁላችንም የማይበጅና እንደአገርም የተደከመውን ነገር ሁሉ ወደኋላ የመመለስ ነገር ሊመጣ ይችላል፡

ሰማያዊ፡- ነገር ግን የአቶ ኃ/ማርያም አካሄድ ከቀድሞው ጠ/ሚኒስትር ብዙም ያልተለየ እንደሆነ በቅርቡ ከቪ.ኦ.ኤ. ጋር ያደረጉት ቃለ-ምልልስ ጥቁምታ ሰጥቷል፡፡ በታሰሩ ጋዜጠኞችና በመሳሰሉት ጉዳዬች ላይም ተመሳሳይ አቋም አራምደዋል፡ ታዲያ እንደው ዕድል ለመስጠት ያህል ብቻ ነው ኢህአዴግ ይስተካከላል እያሉ ያሉት ወይስ አቶ ኃ/ማርያም አንዳች አዲስ ሙከራ ይሞክሩ እንደሆን ብለው ነው?

ኢ/ር፡ይልቃል፡- እኔ የነገሮች ተፈጥሯዊ ውጤታቸውን /Natural consequence/ ነው እየተናገርኩ ያለሁት፡፡ ኢህአዴግ ይህን ማድረግ ግዴታው ነው” በአቶ መለስ ጊዜ እየተከማቹ እየተከማቹ የሄዱ ችግሮች እና በውል ያልተፈቱ በማለባበስ ብቻ እየተድበሰበሱ የመጡ ነገሮች አሉ፡፡ ስለዚህ በዚሁ መንገድ እቀጥላለሁ ካለ ኢህአዴግ

ቅጽ 1 ቁጥር 1 ጥቅምት 2005 ዓ.ም

21

Page 22: Semayawi1/Newly formed political party the blue (Semayawi)  founder, Professor Mesfin Wolde Mariam

ወደገደሉ እየተጓዘ እንደሆነ ማስተዋል አለብን፡፡ ይሄ ትንቢት ተናጋሪ መሆንን አይጠይቅም፡፡ ሥራ-አጥነት፣ ችጋር እና ድርቅ እኮ ንጉሱንም አውርደዋል፡፡ በዚህ የኑሮ ውድነት፣ የዋጋ ግሽበት እና የህይወት ዋስትና ማጣት ውስጥ እንዴት በስልጣን ተደላድሎ መቀጠል ይችላል? በተፈጥሮ ህግም ቢሆን ስርዓት ያረጃል፣ ቅቡልነቱ እየሳሳ እና እያለቀ ካፒታሉን እየበላ በሄደ ቁጥር ስርዓት እርስ-በራሱም ተጠላልፎ ይወድቃል፡፡ የኛ ሚና ህዝብን አደራጅቶ የሚመጣው ለውጥ የተጠና የታቀደና አስቀድሞ የተመራ እንዲሆን ማድረግ ነው፡፡ ለዚህም እንዲረዳ የህዝብን የፖለቲካ-ንቃት ማሳደግ ነው ሚናችን፡፡ ስለዚህ ለውጡ በግድም ሆነ በውድ አይቀሬ ነው፡፡

ሰማያዊ፡- በዚህ ረገድ ከሌሎች የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር አገራዊ በሆኑ አጀንዳዎች ላይ ተቀራርቦና ጥምረት ፈጥሮ የመስራት እንቅስቃሴያችሁ ምን ያህል ነው?

ኢ/ር፡ይልቃል፡- ሰማያዊ ፓርቲ በዚህ ረገድ፡- እ---- እንደኢህአዴግ ቃል አታርግብኝ እንጂ፡- ምንም በሌለበት መልካም ጅምሮች እያለ ተስፋ የሚሰጠን ነገር አለ እና----/ፈገግታ/ እና እነዚህ ነገሮች በጥንካሬና በራዕይ ጥራት ከተያዙ መልካም የሆኑ ጅምሮች አሉ፡፡ በፊትም እንደገለፅኩልህ እንደ አዲስና ጀማሪ ፓርቲ ሳይሆን ትላልቅ ሰዎች የፓርቲ አባል ሳይሆኑ ወጣቶችን ለመደገፍና የራሳቸውን ዜግነታዊ ኃላፊነት ለመወጣት ዝግጁ የሆኑበት ምናልባት በፖለቲካ ታሪካችንም የመጀመሪያው በሆነ መልኩ ፓርቲያችንን ለመደገፍ የበኩላቸውን አድርገዋል፡፡ የፖለቲካ ፓርቲዎችን በተመለከተ ደግሞ፡- በአሰራርና በፖለቲካ እምነት ተለያይተን ብንወጣም አንዳንዶቻችን አንድነት ውስጥ የነበርን ከመሆናችን አንፃር ከፓርቲው ጋር አዎንታዊ ግንኙነት አለን፡፡ ፓርቲያችንን ስናቋቁምም ተጋባዥ እንግዶች ነበሩ፡፡ በቅርብ ጊዜም የነእስክንድር እና አንዷለም አንደኛ ዓመት መታሰር ምክንያት አድርጐ የሻማ ማብራት ዝግጀት ሲያደርግ እኛም ተጋብዘን ተገኝተናል፡፡ እኔም ተናጋሪ ነበርኩ በዚያ ዝግጅት ላይ፡፡ ስለዚህ በፖለቲካ ተለያይተን እንኳ መልካም ግንኙነቶቻችን ቀጥለዋል፡፡ ከመኢአድም ጋር እንዲሁ ኘሮግራሞቻቸው ላይ እየተካፈልን ነው፡፡ ባለፈው የአድዋ ድልን ሲያከብሩም ጠርተውን ነበር፡፡ ከመድረክ አመራሮችም ጋር ቢሆን ጥሩ ግንኙነት አለን፡፡ ስለዚህ ይሄን የማዳበር ነገር ነው ያለብን፡፡ አሁን እንደበፊቱ የመፈራረጅ ነገር ጠፍቶ እንደአቻ ተከባብረን እየሰራን ነው በተግባር፡፡ እነዚህ ግንኙነቶች በየደረጃው እያደጉ እንዲሄዱ ማድረግ ደግሞ ከሁላችንም የሚጠበቅ ኃላፊነት ይሆናል፡፡ በዚህ ረገድ የፖለቲካ ባህላችንም እጅግ ዳርና ዳር የቆመ ከመሆኑም አኳያ፣ በፖለቲካ መሸናነፍ እንደመልካም ባህል መታየት ገና ባለመጀመሩ፣ ፓርቲዎች ብዙ ጊዜ የሚመሰረቱት በግለቦች ስብዕና ላይ በመሆኑ እጅግ አያሌ ስራ ይጠበቅብናል፡፡

ሰማያዊ፡- እንግዲህ ከተነሳ አይቀር በግለሰብ ተክለ-ስብዕና ላይ ካለመመስረት አንፃር የናንተ ፓርቲ እንዴት ነው? ይህንን መጥፎ ባህል ቀርፏል ይላሉ?

ኢ/ር፡ይልቃል፡- እሱ በሽታ ቀስ እያለ ካልመጣ እኛጋ ብትሄድ አሁን ሰማያዊን የሚያውቀውን ያክል ሰው ይልቃልን እንደፓርቲው ሊቀመንበር የሚያውቀው አይመስለኝም፡፡ ይሄ ለኔ አንዱ

ማሳያ ነው፡፡ ምክንያቱም፡- ከሊቀ-መንበሩ በፊት ስለፓርቲው ብዙ ሰው አወቀ ማለት እንግዲህ ፓርቲው በመሪው ላይ አልተንጠለጠለም ማለት ነው ለኔ የሚገባኝ፡፡ ከዛ አለፍ ስትል ደግሞ ብዙዎቻችን ለረዥም ጊዜ ጓደኛማቾች ሆነን በቅርብ ለመተቻቸት በድፍረት ለመነጋገር እና በጋራ አቋም ለመውሰድ በተመሳሳይ ዕድሜና የግንዛቤ ደረጃ ላይም በመሆናችን አንዱ የሌላው ተገዢ እንዳይሆን መልካም አጋጣሚ ይፈጥርልናል፡፡ ብዙ ጊዜ በኢትዮጵያ ውስጥ ተፅዕኖ ያላቸው እንደዕድሜ፣ በትምህርት መራራቅ፣ በባህልና በአስተሳሰብ መራራቅ የለም ብዙዎቻችን ጋር፡፡ስለዚህ አንዱ ከላይ አንዱ ከታች ላለመሆን መልካም አጋጣሚዎችም አሉ፡፡ ችግሩንም ደግሞ አስቀድሞ መገንዘቡ አለ፡፡ ያንንም ነገር ለመከላከል በፓርቲያችን መዋቅር ውስጥ ባሉ አግባቦች ተጠቅመን የየራሳችንን ጥረት እናደርጋለን፡፡ አንድ ሰው ሁሉን ነገር የሚሰራና የሚመራ እንዳይሆንም በተለይ በደንባችን ውስጥ በሰፊው ያየነው ጉዳይ ነው፡፡ እና ያ ዓይነቱ አደጋ በኛ ውስጥ እንደማይከሰት ተስፋ አለን እንግዲህ፡፡

ሰማያዊ፡- በአቶ መለስ አስተዳደር ወቅት በእንጥልጥል የቀሩ ጉዳዮች አሉ ሲሉ የሚደመጡ አካላት አሉ፡፡ ለምሳሌ፡- የአሰብን ወደብ የማግኘት ጉዳይ፣ ያልተቋጨው የባድመ መሬት መካለል ጉዳይ፣ የዋጋ-ግሽበት ንረትን መቆጣጠር ያለመቻል፣ ሙስናን መግታት ማቃትና እንደውም ‘መንግሥታዊ-ሌባ’ አለ ብሎ እስከማመን ጫፍ ላይ የደረሰ የአስተዳደር ንቅዘት፣ወዘተረፈ… በነዚህ ጉዳዮች ላይ ፓርቲያችሁ ምን መፍትሄ ይዞ መጥቷል?

ኢ/ር፡ይልቃል፡- እነዚህ ሁሉ ነገሮች በራሳቸው ችግር ሳይሆኑ የችግር ማሳያዎች ናቸው፡፡ እነዚህ የችግሮቹ መለኪያ-ጠቋሚዎች /Verifiable Indicators/ የሚባሉት ናቸው በኘሮጀክት ቋንቋ፡፡ በመሆኑም መሠረታዊ ችግሩ ስልጣን የህዝብ አለመሆኑ ነው፡፡ ኢህአዴግ ደግሞ ከግራ ርዕዬተ-ዓለም የተቀዳና ማዕከላዊ-ዴሞክራሲያዊነት በሚል ሁሉንም ነገር በራሱ የያዘ መንግሥት ነው፡፡ ስለዚህ ስልጣን ለማስጠበቅ ሲባል ነው እንደዚህ ዓይነት ነገሮች የሚፈጠሩት፡፡ አሰብን ለኤርትራ ባይሰጥና ኤርትራ ያኔ እፎይታ ባይሰጠው የአቶ መለስ መንግሥት መደላደል አይችልም ነበር፡፡ እንደዚሁም ደግሞ፡- በህዝብ ተቀባይነት የሌለው መንግሥት ስለሆነ የኢትዮ-ኤርትራን ጉዳይ እንዲሁ ተለባብሶ እንዲቀር ዘላቂ የሆነ መፍትሄ ለመስጠት የተቸገረው የፈረንጆች ተፅዕኖም ተጨምሮበት ቡድኑንም እስከመክፈል ድረስ የሄደው ለህዝብ ተጠያቂ የሆነ መንግሥት ያለመኖር ናቸው፡፡ ስለዚህ ፖለቲካውም ደግሞ ህዝብን በማገልገልና በሃሳብ ላይ የተመሠረተ ሳይሆን በጥቅም ላይ የተንጠለጠለ በመሆኑ ነው፡፡

ሰማያዊ፡- ለምዕራባውያን ኃይሎች በተለይ ለኢህአዴግ አጋር ሆነው ለቆዩት የሚያስተላልፉት መልዕክት ይኖራል?

ኢ/ር፣ይልቃል፡- ፈረንጆቹ ለጥናት

እንዲመቻቸው ሲሉ ከፋፍለው ያጠኑትን የኢትዮጵያ ታሪክ ወደፖለቲካዊ አተያይም አምጥተው የኢትዮጵያን ገፅታም በተከፋፈለ ሁኔታ ለማየት ባይሞክሩ ጥሩ ነው እላለሁ፡፡ እኔ እሱን ሊረዱት ይገባል ብዬ አስባለሁ፡፡ ለምሳሌ፡- የኢትዮጵያ መረጋጋት የመጣው በገዢው ፓርቲ ላይ ባለው የጦር-ኃይል ወይም የአመራር ብቃት ወይም ተፅዕኖ ፈጣሪነት ነው ብለው ያምናሉ ሁልጊዜ፡፡ እሱ ግን በጭራሽ አይደለም፡፡ ኢትዮጵያውያን አጠቃላይ የወል ስነ-ልቦናቸው የሰላም፣ የጨዋነት፣ አብሮ የመኖር፣ የእርቅና የሽምግልና ነው፡፡ የመረጋጋታችንም ምንጭ ይሄው ነው፡፡ ሌላ አይደለም! በመሆኑም እነዚህ የምዕራብ ኃይሎች ከህዝቡ ጋር ቢቆሙና ለዴሞክራሲ ቢታገሉ ኪኢትዮጵያ ጋር በአቻነት የተመሠረተ አጋርነት ሊኖራቸው ይችላል፡፡ ቀጠናው በኢህአዴግ ሞግዚትነት ካልተዳደረ በቀር ይተራመሳል ብለው ባያስቡ መልካም ነው፡፡ ኢትዮጵያውያን እንደህዝብ በአቻነት፣ በእኩልነት ለቀጠናችንም ሆነ ለዓለም-ዓቀፍ ሰላም አስተዋፅኦ የማድረግ ታሪክ ያለን እንደመሆናችን ይህንኑ ምኞታቸውን ከአምባገነን አገዛዞች ጋር ሳይሆን ከህዝብ ጋር ቢያደርጉት ጥሩ ነው ባይ ነኝ፡፡ ቀጠናውን የሚያረጋጋው ጠመንጃ ወይንም በአንድ የፖለቲካ ቡድን እንዳልሆነ አውቀው ከህዝብ ጋር ቢቆሙ መልካም ነው እላለሁ፡፡

ሰማያዊ፡- በብዙ ዘርፈ-ብዙ የሞራል ቀውስ ውስጥ እንዲገባ ለሆነው ወጣት ፓርቲያችሁ ምን መልዕክት ይኖረው ይሆን? እናንተም ባብዛኛው ወጣቶች ከመሆናችሁ አንጻር-----

ኢ/ር፣ይልቃል፡- እንግዲህ ----እ------ ይሄ ከባድ ጥያቄ ነው፡፡ በራሱ በምርጫው ያደረገውም አይደል ወጣቱ፡፡ ይሄ ከከተሜነት ህይወት ጋር የተያያዘ ውጥንቅጥ ያለበት፣ ድህነት ያለበት፣ የዓለም-ዓቀፍ የባህል ተፅዕኖዎች ያለበት ጉዳይ ነው፡፡ በመሆኑም እነዚህ-እነዚህ ነገሮች ሁሉ ተደምረው ካቅሙ በላይ ሆኖ በነዚህ ነገሮች ቢሸነፍ የሚገርም አይሆንም፡፡ ነገር ግን ሽንፈቱ ዘላቂ እንዳይሆን ማድረግ ይኖርበታል፡፡ ወደአሸናፊነት ለመውጣት ሁልጊዜ ተሸንፌያለሁ በቃ! ብሎ አለመቅረት አንዱ ወሳኝ የመፍትሄ ጉዞ ነው፡፡ ከዛ ባለፈ ደግሞ የህይወት መርህ መመዘኛውን ወይም የሞራል እሴት መሠረቱን /Value-Judgment/ መቀየር ነው፡፡ ሰው አካል አለው፣ አእምሮ አለው፣መንፈስ አለው፡፡ ለአካሉ ነው የሚመገበው፡፡ ይህ የእንስሳነት ባህሪያችን ነው፡፡ እኛን ከእንስሳት የለየን ሰውነታችን በሞራል-መመዘኛ ስለሌሎች ማሰብ መቻላችን ነው፡፡ ይህም ነው የሰውነት ልዩ ባህሪያችን፡፡ ስለዚህ፡- ስለሌሎች ማሰብ፣ ኢ-ፍትሃዊነትን አለመቀበል፣ አለመስረቅ የሞራል መርሆዎቻችንና የሰውነት መገለጫዎቻችን ናቸው፡፡ ሰው ስንባል አምላክ ሲፈጥረን ይሄ አብሮ የተሰጠን ነገር ነው፡፡ በመሆኑም አምላክ የሰጠኝን ሰውነቴን አላዋርደውም ይበል-ወጣቱ! ስጋዬ ብቻውን አልተፈጠረም-አካልም፣ አእምሮም፣ መንፈስም አንድ ላይ ያለኝ ነኝ ሊል ይገባዋል፡፡ ስለዚህ የአእምሮዬን የመንፈሴንና የሰውነቴን ባህሪ ትቼ በእንስሳነቴ ብቻ አልኖርም ብሎ ቆራጥ አቋም መውሰድ ይኖርበታል፡፡ ያ በሆነ ጊዜ ከወድቀታችንም ለመቃናት ራሳችንንም ተጠያቂ ለማድረግ ዕድል ይሰጠናል የሚል እምነት አለኝ፡፡

ቅጽ 1 ቁጥር 1 ጥቅምት 2005 ዓ.ም

22

Page 23: Semayawi1/Newly formed political party the blue (Semayawi)  founder, Professor Mesfin Wolde Mariam

ቅጽ 1 ቁጥር 1 ጥቅምት 2005 ዓ.ም

23

ያለፈው የዓለም ታሪክ እንደሚመሰክረውም ሆነ የዛሬው ትውልድ እንደሚያሳየው የመንግሥትነት ሥልጣን የሚያዘው በጡንቻ ወይም በምርጫ ነው፡፡ሁለቱም የየራሳቸው የተለያየ መንገድ አላቸው፡፡ እኛ ኢትዮጵያውያን በረዥም ዘመን ታሪካችን የጡንቻውን አይተነዋል፡፡ከሀገራት ሁሉ የቀደመ ሀገረ-መንግሥት ኖሮን በሥልጣኔ የሁሉ ጭራ የመሆናችን፣ ምቹና ተስማሚ የአየር ንብረት፣ ለም ተፈጥሮና የማይነጥፍ የውሃ ሀብት ይዘን ስንዴ ተመጽዋች የመሆናችን፣ ተደጋግፎና ተቻችሎ የመኖር ልማድ፣ ልዩነትን የመፍቻና ጠብን የማስታረቂያ ባህል የነበረን ሕግ አክባሪዎች ዴሞክራሲ የሚናፍቀንና የሕግ የበላይነት ፊቱን ያዞረብን የመሆናችን ዋናው ምክንያት ሥልጣን በጡንቻ የመያዝ ባህላችን መሆኑ በቀዳሚነት ይጠቀሳል፡፡ችግሩ በሁሉም ዘንድ ቢታወቅም በመፍትሄው ላይ የጋራ ስምምነት መፍጠር አቅቶት ዛሬም ድረስ ሥልጣንን በጠመንጃም በምርጫም ለመያዝ የሚደረግ ትግል እናያለን፣እንሰማለን፡፡ ሥልጣን በጠመንጃ አልበጀንምና ይህን ባሕል ለውጠን በህዝብ ውሳኔ በምርጫ የሚያዝ እንዲሆን እንታገል ያሉ ወገኖች ይህ በኢትዮጵያ አይቻልም የሚል ተቃውሞ አስተናግደዋል፡፡ ቢሆንም በአቋማቸው ጸንተው ለሥልጣን መገዳደሉ ይብቃ! ጠመንጃን በጠመንጃ መተካቱ ያቁም፣ “ንጉስ ለመቀየር” ሳይሆን ሀገራዊ ለውጥ ለማምጣት እንስራ! ብለው የጀመሩት ትግል በ92 ምርጫ ምልክት አሳየ፡፡ በምርጫ 97 ደግሞ በሌሎች ሀገሮች እንደሚታየው ሁሉ በኢትዮጵያም በምርጫ ለውጥ ማምጣት እንደሚቻል ያረጋገጠ ውጤት ተመዘገበ፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ በድምጹ የሚፈልገውን ሥርዓት ለማምጣት ዕውቀቱም ብቃቱም ጨዋነቱም እንዳለው ያስመሰከረና ዓለምን ያስገረመ ሂደት ታየ፡፡ነገር ግን ፍጻሜው ያለማማሩ ይልቁንም የሕይወትና የንብረት መስዋዕትነት ማስከፈሉ በኢትዮጵያ “ሥልጣን በጡንቻ እንጂ በምርጫ አይቻልም” ሲሉ የነበሩ ወገኖች ‘ብለን ነበር!’ እንዲሉ አስቻላቸው፡፡ አቋማቸውን አጠናክረው ለመከራከርም በማስረጃነት የሚጠቅሱት ሆነ፡፡ ከምርጫ ውጪ ሌላ ምርጫም አማራጭም የለም ብለው ሰብከው ያሳመኑ! መርተው ያታገሉ፣ ቀስቅሰው ሕዝብን ያሰለፉ፣ በተግባር ሞክረን አይተነው በኢትዮጵያ በምርጫ ለውጥ ለማምጣት እንደማይቻል አረጋግጠናል! በማለት እምነታቸውን ለውጠው የትግል መስመራቸውን ቀይረው ሌላ አቅጣጫ ለመያዝ በቁ፡፡ ይህም በኢትዮጵያ በምርጫ ለውጥ ማምጣት አይቻልም የሚለውን ወገን አስተሳሰብ የሚያጠናክር ሆነ፡፡ ይህ ሁሉ ቢሆንም ሥልጣን በምርጫ በሚለው እምነታቸው የጸኑት የ97ን ምርጫ እያስታወሱና ውጤቱን እያለሙ በ2ዐዐ2 ምርጫ ተሳተፉ፡፡ የተገኘው ውጤት ግን ስለምርጫ ያለውን አመለካከት ይበልጥ የሚያጨልምና ተስፋ የሚያስቆርጥ! በአንጻሩም ‘ምርጫ በኢትዮጵያ አያዋጣም’ የሚሉ ወገኖችን መከራከሪያ ይበልጥ የሚያጠናክር ሆነ፡፡ ምርጫ በሩጫ ተካሂዶ ውጤት፣ በጡጫ ተከናውኖም አመኔታ እንደማያስገኝ ምርጫ 2ዐዐ2 በበቂ አሳይቶናል፡፡የዚህ ጽሁፍ ዓላማ በምርጫ (በሰላማዊ ትግል) ለውጥ ማምጣት ይቻላል አይቻልም? በሚለው

በየጊዜው የተነሳ እና ብዙ በተባለበት ጉዳይ ላይ እንደ አዲስ የመነጋገሪያ አጀንዳ መክፈት አይደለም፡፡ አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ ከሚነገረው ሳይሆን በተግባር ከሆነው፣ ከዳር ሆነን ከታዘብነው ሳይሆን ተሳታፊ ሆነን ካለፍንበት መረጃም ማስረጃም እየጠቀሱ መነጋገር ይቻላል፡፡ በልጦ ለመታየት ሳይሆን ለመደማመጥ መነጋገር ከቻልን፤ እውነት ያለው እኔ ጋር ብቻ ነው በሚል ስሜት የሌላውን ላለመቀበል ህሊናችንን ሳንቆልፍ ለጋራ ጠቀሜታ የጋራ እውነት ፍለጋ ላይ የምናተኩር ከሆነ፣ በጽሁፍም ሆነ በቃል መነጋገሩ መልካም ነው፡፡ የአባቶቻችንን ሳንይዝ ወይ ከዓለም ሥልጣኔ ጋር ሳንቀላቀል የቆምንበትን ዘመንና ቦታ እንኳን በውል ሳናውቅ መሀል መንገድ ላይ አቁሞ ያስቀረን ዋናው ችግራችን የውይይት ባህል የሌለን መሆናችን ነው፡፡ መናገር እንጂ መነጋገር የለም፡፡ እኔን አዳምጡ እንጂ ሌላውን ማዳመጥ የለም፣ ተቀበሉኝ እንጂ ከሌላውም የሚጠቅም ሀሳብ አይጠፋም ብሎ ለመቀበል መዘጋጀት የለም፡፡ ይህን ሀገራዊ በሽታችንን ኘ/ር መስፍን ወ/ማርያም የገዢነት በሽታ ይሉታል፡፡ “ሥልጣን ባህልና አገዛዝ ፖለቲካና ምርጫ” በሚለው መጽሀፋቸው “....የሚያጣላንና የሚያናቁረን ማን ይጠፍር፣ ማን ያስገድድ፣ ማን ይደብድብ የሚለው ጉዳይ ነው! የአገዛዝ ሰንኮፍ ከውስጣችን ስላልወጣ እያንዳንዳችን ፖለቲካ ምን ማለት እንደሆነ ሳይገባን በፖለቲካ መሳተፍ የምንፈልግ ሁሉ ቢቻል ንጉስ አለዚያ ራስ ወይንም ደጃዝማች ወይንም ከንቲባ መባል እንፈልጋለን፡፡ ለነዚህ ሹመቶች ወንበሮቹ አንዳንድ ብቻ ናቸው! እኛ ብዙዎች ነን ችግሩ ይህ ነው፡፡” በማለት ገልጸውታል፡፡ (ገጽ 12) ፖለቲከኞቻችን ከዚህ በሽታ ካልተላቀቁ ምርጫ 2ዐዐ7 የመጨረሻው መጨረሻ እንዳይሆን ያሰጋል፡፡ የዚህ ጽሁፍ አብይ ምክንያትም ይሄው ስጋት ነው፡፡

“የዴሞክራሲያዊ ሥርዓት አንዱ መሰረታዊ ባሕርይ መስተዳድራዊ ሥልጣን ከዜጎች ፈቃድ የሚመነጭ መሆኑ ነው፡፡ የሕዝብን ፈቃድና ፍላጎት ለመለየት ደግሞ አይነተኛው ዘዴ ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ነው፡፡ ስለዚህ ምርጫ በዴሞክራሲ ሥርዓት ውስጥ ወሳኝ ሚና አለው፡፡” (“በዴሞክራሲ ሥርዓት የፖለቲካ ፓርቲዎች ተግባራትና ሚና” ከሚል መጽሀፍ የተወሰደ) ምርጫ የሕዝብን ፈቃድና ፍላጎት በትክክል በማሳየት ወሳኝ ሚናውን ሊወጣ የሚችለው ከጡጫም ከሩጫም በጸዳ ሁኔታ በእምነት በበቂ ዝግጅትና በቁርጠኝነት ሲከናወን ነው፡፡ በምርጫ ሂደት ወሳኙ መሳሪያ ድምጽ ነው፡፡ ድምጽ የሚገለጸው ደግሞ በምርጫ ካርድ ነው፡፡ ለዚህም ነው “የምርጫ ካርድ ከግዑዛን መሳሪያዎች ሁሉ የላቀ ኃይል አላት” የሚባለው፡፡ ይህ ኃይሏ ተፈላጊውን ዒላማ መትቶ ውጤት እንድታስገኝ አጠቃቀሟን ማወቅና በበቂ ዝግጅት ተግባራዊ ማድረግን ይጠይቃል፡፡ የምርጫ ካርድን ነጥቆ ድምጽን ተኩሶ ዒላማን ለመምታትና ዓላማን ለማሳካት፣ የዓላማ ጽናት የትግል ቁርጠኝነትና የመሪነት ብቃት ያለው፣ የሥልጣኑ ባለቤት ሕዝብ መሆኑን የሚያምን ብሎም ለሕግ የበላይነት የሚገዛ መሪ ፓርቲ ያስፈልጋል፡፡ በየምርጫው ዓይነት (ለሀገራዊና ለአካባቢያዊ) ለውድድር የሚቀርብ ብቁ ተወዳዳሪ ያስፈልጋል፡፡ መራጩ ሕዝብም የሚመርጠው ብቁ አመራጭ እንዳለው አምኖ በድምጹ ለውጥ ማምጣት እንደሚችል ጠንካራ እምነት እንዲያድርበት ያስፈልጋል፡፡

የተሰማራበትን ኃላፊነት ክብደት የተረዳና የሱ መጠንከር ለሚፈለገው ውጤት መገኘት ወሳኝ መሆኑን የተገነዘበና በቁርጠኝነት የሚሰለፍ ታዛቢ ያስፈልጋል፡፡ በገለልተኝነት አወዳድሮ፣ በታማኝነት ድምጽ ቆጥሮ፣ በነጻነት ወስኖ የምርጫ ካርድ ውጤትን (ድምጽን) ወደ ሥልጣን የመቀየር አቅም ብቃትና ነጻነት ያለው ምርጫ አስፈጻሚ (ቦርድ) ያስፈልጋል፡፡ከዚህ በላይ የተጠቀሱትና ሌሎችም ለዴሞክራሲያዊ ምርጫ ዕውን መሆን የሚያበቁ ተግባራት ባልተሟሉበት ምርጫ ቢካሄድ ድምጽ ሳይቆጠር አስቀድሞ ውጤቱን መተንበይ ይቻላል፡፡ ጉዳቱም ከአሁን ይልቅ የወደፊቱ ስለሚብስ የከፋ ይሆናል፡፡ በሰላማዊ ትግል በምርጫ የሕዝብን የሥልጣን ባለቤትነት ማረጋገጥ አይቻልም የሚሉ ወገኖች አቋምም የበላይነትም ተቀባይነትም እንዲያገኝ የሚረዳ ይሆናል፡፡ በምርጫ የተወዳደሩትም ሥልጣን ላይ ያለውን ኃይል ዕድሜ ለማራዘም የተሰለፉ በሚል የሚቀርብባቸው ክስና ወቀሳ ተባብሶ ሊቀጥል ይችላል፡፡ ከሁሉም በላይ ደግሞ የሥልጣኑ ባለቤት የሆነውና በድምጹ ሊወስን የሚገባው መራጭ ሕዝብ በምርጫ እምነት ያጣል! በሠላማዊ ትግሉ ተስፋ ይቆርጣል! በታጋዮችም (በፖለቲከኞቹ) ዕምነት ያጣል-በመንግሥትም ጭምር፡፡ እናም ዝምታን ምርጫው ያደርጋል፣ ያለቀሰ መሳቅን፣ የጠላ የወደደ መምሰልን፣ የተራገመ ማሞገስን ሥራው ያደርገዋል፡፡ ጊዜ የሰጠው ቅል ድንጋይ ይሰብራል! እያለ ጎመን በጤናን እየተረተ በሚታይ ተቃውሞ ሳይሆን በዝምታው ይሸኛል፡፡አሁን እዚህ ደረጃ ስላለመደረሱ እርግጠኛ ሆኖ መናገር አይቻልም፡፡ አልተደረሰ ከሆነ እሰየው ነው፡፡ ተደርሶ ከሆነ ደግሞ ሕዝብ ተስፋ ሲቆርጥ፣ በወደፊት ላይ ዕምነት ሲያጣና ዝምታን ምርጫ በማድረግ “እሱ ያመጣውን እሱ እስኪመልሰው” በማለት ነገሩን ሁሉ ለፈጣሪው መተው ሲጀምር ትክክለኛ ኘሮግራም በመንደፍ የሕዝብን ስሜት የማቃናትና ተስፋ የማሳደር የፖለቲካ ርምጃ መውሰድ የፖለቲካ መሪዎች ተግባር ይሆናል፡፡ ይህ ጉዳይ ደግሞ የሚመለከተው ሥልጣን ላይ ያለውን ፓርቲ ሳይሆን ለሥልጣን የሚፎካከሩትን ነው፡፡ ምክንያት ቢባል በሥልጣን ላይ ያለው ኢህአዴግ አሁን ለምንገኝበት ሁኔታ ዋንኛ ባለድርሻ ሲሆን የሚለወጥም የሚሻሻልም ነገር የለም አይኖርምም ብሎ አቋሙን ያሳወቀ፣ ለመጪውም በኢትዮጵያ መኖር ያለበት አንድ አውራና ሌሎች ታማኝ ፓርቲዎች ናቸው ብሎ አውጆ ይህንኑ ዕውን ለማድረግ እየጣረ ያለ፣ የምርጫ 2ዐዐ2 ድሉ እንዳይቀለበስም ከምርጫው ማግስት ጀምሮ ደቂቃ ሳያባክንና አንድም አማራጭ ሳያስቀር እየሰራ ነውና ነው፡፡ በአንጻሩ ተቃዋሚዎቹ (ተፎካካሪ ቢባሉ ሳይሻል አይቀርም) በምርጫ 2ዐዐ2 ማግስት እንደቆሙ ናቸው ይባል ካልሆነ በስተቀር ተስፋ የሚፈነጥቅ ነገር አይታይባቸውም፡፡ በዚህ ሁኔታቸው ከርመው የምርጫ ቦርድ የግዜ ሰሌዳ ሲያወጣ በሩጫ ወደ ምርጫ መግባታቸው ደግሞ የማይቀር ነውና ያለበቂ ስራ ወደ ምርጫ ገብተው ካለፈው የባሰ ተስፋ አስቆራጭ ሥራ እንዳይሰሩ ያሰጋል፡፡ ስለሆነም ምርጫ በሩጫ የማይሳካና የአራት አመት ዝግጅት የሚያስፈልገው ቢሆንም እነርሱ ግን ግዜ ጥሎአቸው እየሄደ እንደሆነ ማስታወስና

ምርጫ በጡጫም በሩጫም አይሆንምታምራት ታረቀኝ

ወደ ገጽ 26 ዞሯል

Page 24: Semayawi1/Newly formed political party the blue (Semayawi)  founder, Professor Mesfin Wolde Mariam

ቅጽ 1 ቁጥር 1 ጥቅምት 2005 ዓ.ም

ብቻ የምትፈለጉ የምርጦች ጌቶች የጉልበት ሠራተኞች አሊያም የመስዕዋት በጐች ናችሁን? ከ’ዕድገቱ’ በየ’ደረጃው’ የተዋረድ የምትጠቀሙ 2ኛና 3ኛ ዜጐች ናችሁ? ኢህአዴግስ ይወዳችኋል? ወይስ ይጠቀምባችኋል? ተናገሩ እስቲ እናንተ የትናንት ‘አደገኛ-ቦዘኔዎች’ የዛሬ ‘አደገኛ-ሊጐች’ እና ‘ፎረሞች’! ተናገሩ------

የኢህአዴግ ቀለም-አልባው ሽብር

በየጐዳናው ጥጋጥግ እና በየአውቶቡስ ፌርማታው ውስጥ የላስቲክ ዳስ ዘርግታችሁ የወዳደቃችሁ የኢትዮጵያ ልጆች ሆይ፡- ስለእናንተስ ግድ የሚለው ማን ይሆን? ሰብሳቢያችሁስ ከወዴት አለ? በዕቃ-መያዣ ማዳበሪያዎች ውስጥ እንደአልባሌ ግዑዝ ነገር ተወሽቃችሁ በየሱቆች ደጃፍ ከውሻ ጋር ተቃቅፋችሁ የምታድሩ ኢትዮጵያውያን የሰው ልጆችስ መጨረሻችሁ ምን ይሆን? በውድቅተ-ሌሊት እሳት አንድደውና ዙሪያውን ከበው ሲተክዙ የሚያድሩ ወንድም እና እህቶቻችንስ ሰቀቀናቸው መቼ ያበቃል? ቤንዚን እየሳቡና የሲጃራ ኩስታሪ እየለቃቀሙ ሲያጨሱ የሚውሉ የጐዳና ላይ ታዳጊ ሴት ልጆች እና ብላቴኖችስ ወገን አላቸው? ማን ከዚህ መዓት ያወጣቸዋል?

በአፍላ-ዕድሜያቸው መንታ-መንታ ጨቅላ ህፃናትን ታቅፈው ከቦታ ቦታ የሚንከራተቱ ኮረዳ-እናቶች፣ ወንድ ልጁን በጫንቃው ላይ አኑሮ እንባውን እያዘነበ የሚለምን ጐልማሳ አባት፣ ህፃናት ልጆቻቸውን አውላላ መንገድ ላይ ነስንሰው አስተኝተው ከነመላ ቤተሰባቸው የሚለምኑ አረጋዊ አባወራዎች እና እማወራዎች፣ በቆሻሻ ገንዳ ውስጥ የተጣለ ምግብ ለቃቅመው በልተው እዚያው ስር ተኝተው የሚውሉ ምስኪን እኩዬቻችን ዜጎች፣ በተበላሹ የቴሌ የስልክ ማስደወያ የብረት-ቤቶች ውስጥ የሚያድሩ የዕድሜ ታናናሾቻችን ጐዳና ተዳዳሪዎች፣ ዕድሜ ልካቸውን ክምር እንጨት እና ቅጠል ተሸካሚ ሆነው የኖሩ ጐስቋላ እናቶች እና እህቶች፡- “እረ የወገን ያለህ!?” እያሉ እየተጣሩ ነው፡፡ ከድህነት ወለል በታች ወድቀው አይዞአችሁ! የሚላቸው ጠፍቶ፣ እጁን ዘርግቶ የሚያነሳቸው የአገር-ልጅ አጥተው በዝምታ ቀስ-በቀስ እየሞቱ ነው፡፡ ወገኖቻችን ወድቀዋል! ግና ማን ያነሳቸዋል?

------- ተነሳ ተራመድ ክንድህን አበርታ ለሀገር ብልፅግና ለወገን መከታ ------

አንተ እና እኔ እንዳናነሳቸው ደግሞ፡- እኛ ራሳችን በሺሻ፣ ሀሺሽ፣ ጫት፣ ሴሰኝነት፣ ልቅ-ወሲብ፣ ዳንኪራ፣ አልኮል፣ ትምባሆ፣ ወፈፌነት/ከንቱነት ነፍዘን በዚያ ላይ ጧት ማታ የኢ.ቲ.ቪን. የሀሰት ኘሮፖጋንዳ

እየተጋትን አይምሮአችን ተሳክሮብን፣ እውነታው ተምታቶብን ግራ እንደተጋባን አለን፡፡ ሌሎቻችን ደግሞ 22 ሰዎች ለሁለት ቡድን ተከፍለው ሲጠልዟት በሚኖሩ ኳስ ተጫዋቾች ህይወት ተማርከን ራሳችንን እና ኑሯችንን ረስተን ኮብልለናል፡፡ በአውሮፓ አገራት ስታዲየሞች ውስጥ ወድቀናል፡፡ አካባቢያችንን እንረሳ ዘንድ ኢ.ቲ.ቪ. እና ዲ.ኤስ.ቲቪ ግንባር ፈጥረው ግንባራችን ውስጥ ያለውን ማመዛዘኛ መስተሐልይ ለመስለብ ሌት-ተቀን ይደክማሉ፡፡ ማሰቢያ-አይምሮአችንም በቴሌቪዥን ሣጥን ውስጥ ተከርችሞ ተቆልፎበታል፡፡ በዚህ ዘመን ያለን ወጣቶች መብታችን ተከብሮልናልÌ አዎ- መብታችንም፡- ‘የወጣቶች የራስን ዕድል በራስ መወሰን እስከመሴሰን፣መስከር፣መዘሞት፣መጦዝ፣መጀዘብ፣መነሁለል’ ነው፡፡

በመቃም፣በማጤስ፣በመጠጣት፣በመዘሞት፣ አለም-አቀፍ ውድድሮች ውስጥ ተገብቶ ዋንጫና ገንዘብ ይገኝ ይመስል በየሰፈራችን እንደአሸን የፈሉ ሃጢያት መለማመጃ ቦታዎች ተኮልኩለውልናል፡፡ ከነዚህ ሁሉ የተረፍነው ደግሞ በፑል እና ጆተኒ ማጫወቻ ጠረጴዛዎች ላይ እየቆመርን በደረታችን ወድቀን የምንውል ነን፡፡ ሌሎቻችን በየሰፈሩ ስርቻዎች ውስጥ በሚገኙ ፊልም-ቤቶች ታጭቀን ልቅ የወሲብ ፊልምና የወንጀል ታሪክ ያላቸውን ሲኒማዎች ስንጋት አመሻሽተን እኩለ-ሌሊት ላይ ለወንጀል የምንሠማራ የትውልድ ማጅራት-መቺዎች ነን፡፡

ምስኪኖችን የምናጠቃ የጉድ-ትውልድ! በአካል ብቻ ሳይሆን በመንፈስም ጭምር የወደቅን! ነብሳችን በበካይ እና መራዥ ክፉ የሥጋ ምኞቶች የተተበተበ ብላሽና መርዛማ ትውልድ ነን፡፡ በሃጢአት ድካም ፣ በኑሮ ፈተና፣ በሰው እንቅፋት የወደቅን መንፈሰ-ሰባራዎች ነን፡፡ የመለኮት ህክምና የሚያሻን የነፍስ ድውያን ነን፡፡ አለባበሳችን የሰውነታችንን ጉድፍ የደበቀልን፣ አበላላችን የነፍሳችንን ገመና የጋረደልን እንደሳጥናኤል የተዋብን እንደልቡም የከፋን ሰው-መሳይ እፉኝቶችና ሻርኮች ነን፡፡ በማለዳ ቤተ-መለኰት ሄደን የምንፀልይ በእኩለ-ቀን ለጣኦት የምንሰግድ በየጥንቆላ ቤቱ ወለል ላይ ወዳድቀን የምንንደባለል አስመሳዬች እና ግብዞች ነን፡፡ ፈጣሪን ለማታለል በከንቱ ስሙን የምንጠራ ትዕቢተኞች ነን-ደግነቱ አምላክ አይዘበትበትም! ስጋውን እንጂ ነብሱን የማይጠብቅ፤ በዳያስፖራ ሴፍቲ-ኔት ታቅፎ ዶላር እና ዩሮ በመለቃቀም ራሱን የሚያኳኩል ሰው የአገሪቷን ዋና ዋና መታያ እና የሰው መገበያያ ቦታዎች ያጨናነቀባት የኃጢአት ንግድ የሚጦፍባት ሆናለች-ኢትዮጵያ!

እንዲህ ያለኸው ወንድሜ፡- ስለምን ዕለቱን የኮረዶችን ስልክ ቁጥር ከመቀበል አሊያም ከባዕድ-አገር የመጡ እንስቶችን ማጥመጃ ዘዴዎች ከማሰላሰል የዘለለ ዓላማና ግብ

አትሰጠውም? ቀንህ የምትቅመውን የጫት አይነት በመጎምዥት የምታስብበት ብቻስ ለምን ይሆናል? እረ እልፍ በል! ከዚህ የተሻለ የህይወት ተልዕኮና ፍፃሜ ይኑርህ፡፡ ሰው እኮ ነህ! ፍፁም አቻ በሌለው እንከን-አልባ አምላክ አምሳል የተሰራህ!

ዝና በሚባለው ፍራሽ ላይ የተኛችሁ ከያኒያንስ የጥበብ ሰው ዋጋው ይሄ ነው? እንደቀኟችሁ የምትቀኙ የገዢ-መደብ መሣሪያ ሆናችሁ እስከመቼ? ግዴለም-ከሞራል እንቅልፋችሁ ንቁ! ……… ወገኔ ተነስ-ተነስ- ተነስ ባዲስ ወኔ፣ ወገኔ ተነሽ ተነሽ ተነሽ ባዲስ ወኔ ………

‘አዲሱም’ የኢህአዴግ አስተዳደር ድርጅቱ ከወደቀበት የአፍቅሮተ-ሥልጣን ቁልቁለት ሊነሳ ይገባዋል! ከግል-ጥቅመኝነት እና ከፍርሃት ስርቻ ውስጥ ሊነሳ ግድ ይለዋል፡፡ በየቀኑ ከሚለፍፈው ሃሳዊ-ህዳሴ ወደእውነተኛው ህዳሴ ሊሸጋገርና ሁላችንንም ሊጠቅም በሚችል ፍኖት ጉዞ ሊጀምር ብሎም የመንፈስ-ወኔን ሊያሳይ ጊዜው ደርሶበታል፡፡ ህዳሴ /Renaissance/ የሰዎችን እምቅ-ሃይል በነፃነት እንዲለቀቅ የሚያደርግ የአብርሆት/Enlightenment/ መንገድ እንጂ በሰዎች ውስጥ ያለው ብርሃን እንዲዳፈንና እንዳይገለጥ የሚያደርግ መክሊት-ቀባሪ የአምባገነንነት የጨለማ ድንብርብር አይደለም፡፡ ኢህአዴግ ሆይ፡- አንተስ አትነሳም ወይ? ራስህን ከማታለል እንቅልፍ! ህዝቡ ከኔ ጋራ ነው ብለህ ስለምን ትኩራራለህ? ህዝብማ እንኳን ከአንተ ጋር ከእውነተኛው አምላክ ከኢየሱስም ጋር አልነበር! ከሙሴም ጋር እንደዚያው! ታዲያ ስለምን በሀሰት ኘሮፖጋንዳህ አቅል እየነሳህ በፍርፋሪ የሰበሰብካቸውን መንፈሰ-ደካማዎች ተማምነህ ረጅም ጉዞ ታስባለህ? ወይንስ 5ቱን እንጀራ እና 2ቱን ዳቦ በተዓምር ቀይረህ ተዓምራዊ ሊባል የሚችል ዕድገት አስመዝግበህ ሁላችንንም ታጠግበናለህ? ለማንኛውም በአሸዋ ላይ የተገነባ ቤት ዝናም ጐርፍና ነፋስ በመጣ ጊዜ እንደሚፈርስ ከቶም አትዘንጋው! ኢህአዴግ ሆይ፡- ለራስህ ስትል ጣፍጥ አሊያ ድንጋይ ነው ብለን ወደደጅ አውጥተን እንጥልሃለን!

ከህዝቡ ጫንቃ ላይ እንደመዥገር ተጣብቃችሁ የህዝቡን ደም ስትመጡ እና አጥንቱን ስትግጡ የምትኖሩ ጥገኛ-ተውሳክ ካድሬዎች ሆይ፡- ከኢኮኖሚያችን፣ ከፖለቲካችን፣ እና ከማህበራዊ-ህይወታችን ላይ ተነሱ! አሊያ ግን የህዝብ እንባና ሮሮ ጐርፍ ሆኖ ይጠራርጋችኋል-በጊዜ ንቁ!

ይቀጥላል………ብዬ............ አስባለሁ.........

አትነሳም ...

24

Page 25: Semayawi1/Newly formed political party the blue (Semayawi)  founder, Professor Mesfin Wolde Mariam

ቅጽ 1 ቁጥር 1 ጥቅምት 2005 ዓ.ም

ባለፉት ተከታታይ ሁለት ወራት በሀገራችን ውስጥ የተከሰቱና እየተመለከትናቸው ያሉ ጉዳዬች የፈጠሩት ነገር ስለገረመኝ ብዕሬን ለማንሣት ከጀልኩ፡፡

ሰኔ መጨረሻ አካባቢ የቀድሞው ጠ/ሚኒስቴር መሞታቸው በተለያዩ መንገዶች መሰማት ከጀመረ ወዲህ! የተለያዩ አስተያየቶችን በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሲወራ ሰምተናል፡፡ መታመማቸውን የነገሩን የሴኔጋሉን ኘሬዚዳንት ጨምሮ” መሞታቸውን አስቀድመው ተናገሩ የተባሉት አውሮፓዊ መሆናቸው ይበልጥ የሚያስገርመን ጉዳይ ሆኖ አልፏል፡፡

ተባራሪ ወሬዎችን በተለያየ አቅጣጫ ስንሰማ ብንቆይም የሁሉም ወሬዎች ማሣረጊያ የጠ/ሚኒስትሩ በይፋ መሞት የመጨረሻው ዕውነታ ሆኖ አልፏል፡፡

አሁንም በጋዜጦች ላይና በሰዎች አንደበት የሚናፈሱ አስገራሚ ጉዳዮችን እየሰማን እንገኛለን፡፡ ሁሉም ወሬዎች፣ ሹክሹክታዎች የሚያሣዩን ሰኔና ሀምሌ ላይ የነበረው አይነት ክፉ ክፉውን ነው፡፡ ይኼን ወሬ ማመን ይከብዳል! እንዳንል ያለፈውን አመት እንድናስታውስ ያደርገናል፡፡ ፍንጭ ሣይኖር ይኼ ሁሉ አይወራም! የሚል መነሻ ግን መያዝ እንችላለን፡፡

ከጉዳዮቹ አንድምታዎችም መሀል፡- ጠ/ሚኒስትሩ ራሣቸውንና አስተዳደራቸውን ከህወሓት አመራር ጫና ነጥለው ለማስተዳደር የሚያደርጉት እንቅስቃሴ ከፍተኛ ተጽዕኖ እንደገጠመው በተለያዩ ማሣያዎች መመልከት እንችላለን፡፡

ከዚህ ውስጥም፡-1. ሀይለማርያም ደሣለኝ የጠ/ሚኒስትርነቱን መንበር ከጨበጡ ከወር በላይ የሆናቸው ቢሆንም! የሀገሪቱ መራኼ-መንግሥት በሚኖርበት ቤትና የሥራ ቦታ /ጽህፈት ቤት/ መጠቀም አለመጀመራቸውና ቤቱንም አልለቅም ያሉት የቀድሞ ጠ/ሚኒስትር ባለቤት ወ/ሮ አዜብ መስፍን በህወሓት ውስጥ የሥራ-አስፈፃሚ አባል መሆናቸው!

2. አቶ መለስ ዜናዊ ከሞቱ በኋላ በይፋ ሀገሪቱን የሚመራ ጠ/ሚኒስትር ሣይመደብና የተመደበውም ሥራውን ሣይጀምር 34 የጦር ጄኔራሎችን መሾም! ይህም #የመከላከያ ሠራዊቱ ብሔራዊ ተዋጽኦው ሚዛናዊነትን ያካተተ እንዲሁም በጠቅላይ ሚኒስትሩ አቅራቢነት ከፍተኛ ውትድርና ማዕረጐችን ይሰጣል; የሚለው በግልፅ የተጣሰ መሆኑ!

3. አቶ ኃይለማርያም ደሣለኝ ቀድሞ

በኃላፊነት ይሠሩበት የነበረውን የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ኃላፊነትና” የኦህዴድ አመራር በግምገማ ከኃላፊነት አነሣቸው የተባሉትን ሌሎች ባለሥልጣናት ጨምሮ በራሣቸው የአመራር ፍልስፍና አብረዋቸው ሊሠሩ የሚችሉ ሚኒስትሮችን አለመሾማቸው!

4. በኢህአዴግ የአገዛዝ ዘመን ውስጥ ከ21 ዓመት በኋላ የኢህአዴግ ሊቀመንበርና የሀገሪቱ ጠ/ሚኒስትር ሆነው የተመረጡት ጠ/ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ በፓርላማ ተገኝተው ቃለ-መሃላ መፈፀማቸው በወቅቱ በሀገሪቱ ውስጥና ለፓርላማው ትልቁ ትዕይንት ቢሆንም ከፍተኛ የህወሓት መሪዎች በወቅቱ አለመታየታቸው ‘የሰውዬው በመሪነት መምጣት አልተዋጠላቸውም’ የሚለውን የሚያሳይ መሆኑ!

5. በመተካካቱ የኢህአዴግ የአምስት አመት ዕቅድ መሠረት በተለያዩ አባል ድርጅቶች ውስጥ ያሉትን የቀድሞና በተለይም በትጥቅ ትግሉ ወቅት የተሣተፉትን ከፍተኛ አመራር አባላትን በአዲስና በወጣት አመራር የመተካቱ ሂደት የሚታይ ቢሆንም በተቃራኒ በህወሓት ተግባራዊ አለመደረጉና መልሶ የቀድሞ አመራሮቹን በሊቀ-መንበርነትና ም/ሊቀ-መንበርነት መምረጡ!

እነዚህ ወደፊት በጠ/ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ በህወሓት በኩል ተግዳሮቶች እየገጠማቸው መሆኑንና ወደፊት በሙሉ ልብ በሥልጣን ወንበራቸው ተቀምጠው ሀገሪቱን ለማስተዳደር በሚያደርጉት ጥረት ከፊታቸው ጋሬጣ እንደሚጠብቃቸው አመላካች ሁኔታ ነው፡፡የአዲሱ ጠ/ሚኒስትር ወደ አዲሱ መኖሪያ ቤታቸው አለመግባትና ከሚኖሩበት ቤት ወደሥራ ሲሄዱ የሚታየው የጥበቃ አጃቢዎች ብዛት (ኘሮቶኮል) ምናልባት በቀድሞው መሪ አቶ መለስ ዜናዊ ጊዜ ከነበረው አንፃር ብዙ የሚያሰኝ ቢሆንም ያየሁትን ጥቂት ልበል፡-አቶ መለስ ዜናዊ ምናልባት ከሀገር ሲወጡ ወይንም ወደተለያየ ቦታ ለመሄድ ከቤተመንግሥት ሲወጡ ካላጋነንኩ የሚያልፉበት መንገድ ከመጀመሪያው ጫፍ እስከመጨረሻው ዝግ ይሆናል! ፌዴራል ፖሊሶች በመንገዶች ግራና ቀኝ እና በህንፃዎች ጣራ ላይ በመሆን ጥብቅ ጥበቃ ያደርጋሉ! ወደሚያልፉበት መንገድ የሚያስገቡ መጋቢ መንገዶች ላይ የሚሰሩ የግንባታ እንቅስቃሴዎች ይቆማሉ! ፓርላማ ለስብሰባ ከመጡ አካባቢው ጥብቅ በሆነ ልዩ የመከላከያ ሠራዊት ይጠበቃል፡፡ በተቃራኒው አሁን ጠ/ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ ከቤታቸው ወደ ሥራ ሲሄዱ ከፊት ለፊት አንድ ሞተረኛ የትራፊክ ፖሊስ መንገድ ያስከፍታል! ከኋላው የቤተ-መንግሥቱ የሴኪውሪቲ መኪና ይከተላል! በመቀጠል

አንድ የትራፊክ ፖሊስ ሞተረኛ ከኋላ ይከተላል፡፡ ጠ/ሚኒስትሩም በመንገዱ ሲጓዙ መንገድ አይዘጋ! ግራና ቀኝ ነፍስና ስጋ የሚያዋክቡ የፌዴራል ፖሊሶች የሎም! በመኪና የሚዘጋ መጋቢ መንገድ የለም፡፡ ጠ/ሚኒስትሩ በመንገድ ሲያልፉ የትራፊክ ሞተረኛ የመንገድ ልቀቁልኝ ድምፅ ብቻ በቂ ነው፡፡የጠ/ሚኒስትር ኃይለማርያም የኘሮቶኮል ጉዳይ ያስታወሠኝ አቶ መለስ ዜናዊ በ1986 በወሎና በጎንደር አካባቢ በወቅቱ የክልሉ ኘሬዚዳንት ከሆኑት ከአቶ አዲሱ ለገሠ ጋር ጉብኝት ሲያደርጉ ከህዝቡ ጋር የነበራቸው ግንኙነት በጣም የሚያስገርም ነው፡፡ በዕድሜአቸው ጠና ካሉት ጋር እንደልጅ፣ ከእኩዮቻቸው ጋር ደግሞ የጓደኝነት ያህል የቀረበ ነበር፡፡ ት/ቤቶችንና የእርሻ ማሣዎችን ሲጋራ እያጨሱ በእግራቸው ላይ ታች ብለው አካባቢውን ሲጎበኙ! ከሀገር ሽማግሌዎች ጋር በርጩማ ላይ ተቀምጠው አንገታቸውን ደፍተው ሲያዳምጡና ህዝቡ በነፃነት የልቡን ሲነግራቸው እሣቸውም በፍፁም ጨዋነትና መግባባት ስሜት ሲወያዩ ለመከታተል ችለናል፡፡እንግሊዛዊው ደራሲ ጆርጅ ኦርዌል የአገዛዝ ትዕይንቶችንና አብዬታውያንን ከድል በኋላ በሚያደርጉት የታዘበውን የከተበበት #የእንስሳት ዕድር; ወይም ‘Animal farm’ መጽሐፉ ከጠቀሣቸው ገፀ-ባህሪያት መሀከል ናፖሊዬን ስለተባለው ዓሣማ ትንሽ ካነበብኩት ላካፍል፡፡ በመፅሐፉ ላይ ታሪካቸው የተገለፀው በሰው ልጆች አገዛዝ እጅግ የተማረሩ እንስሳት” አብዮት አስነስተው ከሰው ልጅ አገዛዝ ነፃ በመውጣት ሁሉንም እንስሳት በእኩልነት ህግ አስተካክለው መኖር መጀመራቸውን ይጠቅሣል፡፡ አብዮቱን የመሩት ዓሣማዎችም ከጊዜ ቆይታ በኋላ በመሪነት መንበሩ ላይ ስልጣኑን እንዳደላደሉ ከእንስሳቱ ህግ ውጭ መሪያቸው ናፖሊዬን የተባለው ዓሣማ በፊት ይኖርበት ከነበረው ከተራ የእንስሳት ጋጣ በመውጣት ደረጃውን የጠበቀ ያማረ ቤት ውስጥ መኖር ሲጀምር” ከእንስሳቱ ለመጡ ቅሬታዎች የቀረበው ምክንያት፡- #የዕርሻው አንጐል የሆኑት ዓሣማዎች የሚሠሩበት ቦታ ፀጥታ ያለው እንዲሆን ፍፁም አስፈላጊ መሆኑን! በተጨማሪም ለመሪው ክብር ተገቢ እንደሆነ; መገለፁ ከመጽሐፉ ላይ የምናገኘው ቁም ነገር ምናልባት የወደፊቱን የጠ/ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝን ጉዞ ከወዲሁ መናገር ባይቻልም! አቶመለስ ዜናዊ በገበሬዎች መሀከል በነፃነት እየተዘዋወሩ ይወያዩ ነበር፡፡ በመጨረሻ እሣቸው በመንገድ እንኳን ሲያልፉ የሚደረገው የደህንነት ጥበቃ፣ ሰውዬውን የሚጠብቋቸው በአይን እንዳይታዩ; ጭምር ነው እንዴ? መባል ደረጃ ደርሶ እንደነበረ ያስታውሰናል፡፡ለጠ/ሚኒስትር ኃ/ማርያም ደሣለኝ የሚደረገው ኘሮቶኮል ከለመድነው አንፃር የተለየ ቢሆንም በፊት ለደህንነታቸው ጥበቃ ተብሎ ለአቶ መለስ ዜናዊ ይደረግ የነበረው ዋንኛው የኢትዮጵያዊነት መገለጫ የሆነውን የአስተዋይነት፣ የሚዛናዊነትና የጨዋነት ባህርይ ከግንዛቤ ያልከተተ ተግባር ነበር፡፡ ጠ/ሚኒስትሩ ኘሮቶኮላቸውን በጀመሩት መልኩ ከቀጠሉ አስተዳድረዋለሁ ከሚሉት ህዝብ ጋር ለሚኖራቸው ቅርርብና ብሔራዊ መግባባት የበኩሉን አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ግምቴን ሳልገልጽ አላልፍም፡፡

ጠ/ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ እና የህወሓት ተጽዕኖ!በጌታነህ ባልቻ

25

Page 26: Semayawi1/Newly formed political party the blue (Semayawi)  founder, Professor Mesfin Wolde Mariam

ቅጽ 1 ቁጥር 1 ጥቅምት 2005 ዓ.ም

26

ከመኝታቸው መቀስቀስ ያስፈልጋል፡፡ የሚሰሩትን አያውቁም ብለን ዝም እንዳንላቸው ጉዳዩ የሀገር ጉዳይ ነው፡፡ በየግልም ስራቸው ባይጠቅምም ዳፋቸው ለብዙው መትረፉ አይቀርም፡፡ በሌላ መልኩ ከውጤት በኋላ ለምን ብሎ ከመጠየቅና ከመውቀስ ሰሚ ኖረም አልኖረም ከወዲሁ እንዲህ ቢሆን ይሄ ቢደረግ ወዘተ… በማለት አስተያየት መስጠቱና ምክር መለገሱ ቢያንስ የህሊና ነጻነት ይሰጣል፡፡

ምርጫ የሚጭበረበረው የድምጽ መስጫ ወረቀት ኮሮጆ ውስጥ ሲጨመር ወይንም ኮሮጆ ተዘርግፎ ድምጽ ሲቆጠር ብቻ አለመሆኑ ግንዛቤ ያገኘ አይመስልም፡፡ ለምርጫ ውጤታማነት የአራት አመታት ተከታታይ ስራ ወሳኝ ነው፡፡ ኘ/ር መድሀኔ ታደሰ በምርጫ 97 ዋዜማ ከአንድ መጽሄት ጋር ባደረጉት ቃለ-ምልልስ “በምርጫ ተወዳድሮ ለሥልጣን ለመብቃት የሚያስብ ግለሰብም ይሁን ፓርቲ በየዕለቱ የሚያካሂደው እንቅስቃሴ ለፍላጎቱ መሳካት አሉታዊ ወይንም አወንታዊ አስተዋጽኦ አለው፡፡ ስለሆነም እያንዳንዱ ተግባሩ ለውጤት የሚያበቃው መሆን አለበት፡፡ ለምርጫ የሚደረግ ተግባር የም/ቦርድ የግዜ ሰሌዳ ካወጣ በኋላ የሚከናወን መሆኑ በቂ አይደለም፡፡” በማለት መክረው ነበር፡፡

ምርጫ 97 የመጀመሪያው መጀመሪያ

ዓለምን ያስደመመውና ለካንስ የኢትዮጵያን ሕዝብ አናውቀውም ነበር ያስባለው የምርጫ 97 ትዕይንትና ውጤት በሀገራችን የምርጫ ታሪክ የመጀመሪያው መጀመሪያ ነበር ማለት ይቻላል፡፡ እስከ ድምጽ መስጫው ዕለት የዘለቀው ዴሞክራሲያዊ ሂደት ከውጤት መገለጽ በኋላ መስመሩን ባይስት ለሀገራችን ትልቅ የለውጥ እመርታ ነበር፡፡ ያለመሆኑ ያስቆጫል፡፡ የጠፋው የሰው ሕይወትና የወደመው ንብረት ያሳዝናል፡፡ ሁሉም የድርሻ የድርሻውን ወስዶ ከዛ ለመማር ፈቃደኛ ያለመሆኑ ደግሞ ይበልጥ ያሳዝናል” ተስፋ ያሳጣል፡፡ በዚህ ስሜትና ተስፋ-ቢስነት ውስጥ ተሁኖ ከተካሄደው ምርጫ 2ዐዐ2 የተገኘው ውጤት “አሸናፊውን” ሳይቀር ያስደሰተ አይደለም፡፡ ‘ያልጠበቅነውን ውጤት በማግኘታችን ዕቅዳችንን ለመከለስ ተገደናል’ ማለታቸውን እናስታውሳለን፡፡ከራስ በላይ ለሀገር አስቦ ለዛሬ ሥልጣን ብቻ ሳይሆን ትውልድ ተሻጋሪ የሆነ ራዕይ ሰንቆ ለምርጫ 97 ውጤት መበላሸት የእኔ ወይንም የእኛ ድርሻ ምን ነበር? ብሎ በስክነት ተነጋግሮና በግልጽ ተወያይቶ (ይሄ ኢህአዴግን አይመለከትም) ድክመትን አርሞ ጥንካሬን ለማጎልበት የሚያበቃ ስራ ሳይሰራ! በምርጫ 2ዐዐ2 ደርሶ የሆነው ሆነ፡፡

ተፎካካሪ ፓርቲዎችን ባለ አንድ ወንበር ያደረገው ምርጫ 2ዐዐ2 ካለፈ ሦስተኛ ዓመቱን ያዘ፡፡ የፓርላማውን ወንበር የጠቀለለው ውጤቱን አስጠብቆ ለመኖር ከምርጫው ማግስት ጀምሮ ድክመት ጥንካሬውን ገምግሞ ድምጽ ሊያሳጡት የሚችሉ ቀዳዳዎችን ሁሉ የሚደፍን ሥራ እየሰራ ነው፡፡ ተሸናፊዎቹ ግን በምርጫው ማግስት ካሰሙት “የተሸነፍነው ምርጫው ተጭበርብሮ ነው” ከሚል ክስና ወቀሳ በስተቀር የእኛ ድክመትና ጉድለት ምን ነበር? ብለው መነጋገራቸውን አልሰማንም፡፡ የእያንዳንዷ ቀን እንቅስቃሴያቸው በምርጫው ውጤት ላይ አወንታዊ ወይንም አሉታዊ አስተዋጽኦ እንዳለው በመገንዘብ ለመራጩ ሕዝብ በገሀድ የሚታይ እንቅስቃሴ ሲያደርጉ አይስተዋሉም፡

፡ ከፊት ለፊታቸው ስላለው የአካባቢም ሆነ ሀገራዊ ምርጫ እያሰቡም አይመስሉም፡፡ እንደለመዱት በሩጫ መወዳደራቸው ግን አይቀሬ ነው፡፡ ይህን ስናስብ የምርጫ 2ዐዐ7 ውጤት ከወዲሁ ያሰጋናል፡፡

ምርጫ 2ዐዐ7 የመጨረሻው መጨረሻ እንዳይሆን ምርጫ መካሄዱ ሳይሆን የምርጫው እንዴትነት ነው ወሳኙ፡፡ አማራጮች የቀረቡበት በቂና ብቁ ተወዳዳሪዎች የተገኙበት ግልጽና ነጻ የሆነ ፉክክር የተካሄደበት! ሕዝብ በፍላጎት በነቂስ የተሳተፈበት ውጤቱም የተወዳዳሪዎችንና የመራጩን አመኔታ እንዲሁም የዓለም-ዓቀፉን ማሕበረሰብ ይሁንታ ያገኘ ሲሆን ነው፣ ምርጫ ምርጫ የሚሆነው፡፡ ያለመታደላችን ተገፎልን ተሸናፊው አሸናፊውን እንኳን ደስ ያለህ! የሚልበት አሸናፊውም ድጋፍህን እሻለሁ አብሬ ለመስራት ዝግጁ ነኝ የሚልበት ደረጃ ላይ ብንደርስ ምርጫ የምንሳቀቅበት ሳይሆን በጉጉት የምንጠብቀው ይሆን ነበር፡፡ እዚህ ደረጃ ለመድረስ ግን እንደገና መፈጠር ሳያስፈልገን አይቀርም፡፡

ለዚህ ባንበቃም ምርጫ 2ዐዐ7 የመጨረሻ ተስፋ አሟጣጭ እንዳይሆን ለውድድር የሚቀርቡ ፓርቲዎችን ተኝታችኋልና ንቁ! እንበላቸው፡፡ በሀገራችን ሕግ መሰረት በምርጫ የሚወዳደሩት ፓርቲዎችና የግል ተወዳዳሪዎች ናቸው፡፡ ከምርጫ በሚገኘው ድምጽ መንግሥት የሚመሰረተው በአሸናፊው ፓርቲ ወይንም ፓርቲዎች በመሆኑ የግል ተወዳዳሪዎች የቱንም ያህል ቁጥር ያለው ወንበር ቢይዙ ለመንግሥት ምሥረታ አስተዋጽ™ አይኖራቸውም፡፡ በየምርጫዎቹ እንደታየውም ብዙም የግል ተወዳዳሪ አይቀርብም! መራጩም አማራጭ ካላጣ በስተቀር የግል ተወዳዳሪዎችን አይመርጥም፡፡

ስለሆነም የሕዝብን ፈቃድና ፍላጎት በትክክል ለመለየት የሚያስችል ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ስናስብ የምንነጋገረው ስለ ፓርቲ ነው፡፡ ከግዑዛን መሳሪያ ሁሉ የላቀ ኃይል ያለውን የምርጫ ካርድ ለመራጩ ሕዝብ አስታጥቆ ለምን፣ መቼ፣ እንዴት፣እንደሚጠቀምበት አስተምሮና የእያንዳንዱ መራጭ ድምጽ ለውጥ የማምጣት ኃይል እንዳለው አሳምኖ የምርጫ ካርድን ውጤታማ የሚያደርግ! የሚለውን ሆኖ የሚገኝ” የሚናገረውንና የሚጽፈውን ተግባራዊ የሚያደርግ የተግባር ፓርቲ ያስፈልጋል፡፡በምርጫ ቦርድ ተመዝግቦ ፓርቲ የሚለውን መጠሪያ መያዝ ብቻውን ፓርቲ አያደርግም፡፡ የፓርቲ ኘሮግራም የተጻፈው ለመመዝገብ የግድ ስለሚያስፈልግ አባላትንም ለማሰባሰብ የሚጠቅም ስለሆነ ብቻ ሳይሆን ታምኖበት የተጻፈ ለተግባራዊነቱም በጽናት የሚታገሉለት መሆኑን ፓርቲው በዕለት-ተዕለት እንቅስቀሴው በተግባር ማሳየት አለበት፡፡ መተዳደሪያ ደንቡም የታይታ የወረቀት ላይ ጌጥ ሳይሆን ከአባል እስከ ሊቀ-መንበር (ኘሬዝዳንት) በኩል የሚገዙበት መሆኑ በፓርቲው የዕለት-ተዕለት እንቅስቃሴ ተግባራዊ ሆኖ መታየት አለበት፡፡ በደንቡ ላይ የሰፈሩት የፓርቲ መዋቅሮች ጠቅላላ ጉባዔ ምክር ቤትና ሥራ አስፈጻሚ በስምና በቁጥር ሳይሆን በአካል መኖር፣ የየድርሻ ተግባራቸውንም በሚገባ የሚያከናውኑ መሆን አለባቸው፡፡ ግልጽነትና ተጠያቂነት ተቋማዊ አሰራርና ዴሞክራሲያዊነት በፓርቲ ደረጃ ካልጀመሩትና ካልተለማመዱት መንግሥት ሲሆኑ የሚታሰብ አይሆንም፡፡ ከዚህም ሌላ ሥልጣን የያዘው ፓርቲ ሲያደርገው የሚያወግዙትን በእነርሱ የማይፈጽሙት!

እርሱ እንዲፈጽመው የሚጠይቁትን እነርሱ አቅምና ሁኔታው በሚፈቅድላቸው መጠን በፓርቲያቸው ውስጥ ተግባራዊ አድርገው የሚያሳዩ መሆን አለባቸው፡፡ ይህኛውን ትንሽ ዘርዘር አድርገን እንየው፡-ሥልጣን ላይ ያለውን ፓርቲ በዴሞክራሲ ነፋጊነት ሲከሱ እነርሱ በፓርቲያቸው ውስጥ ዴሞክራሲያዊ አሰራርን አስፍነው፣ የሕግ የበላይነት አልተከበረም ሲሉ እነርሱ ቢያንስ ለፓርቲያቸው ህገ-ደንብ ተገዢ ሆነው፣ ሀሳብን የመግለጽ ነጻነት ተነፍጓል ሲሉ በፓርቲያቸው ውስጥ ሀሳብን የመግለጽ ነጻነትን ተግባራዊ ያደረጉ፣ ነጻና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ የለም ብለው ሲከሱ እነርሱ በፓርቲያቸው ውስጥ ነጻና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ተደርጎ ለሥልጣን የበቁ መሆን አለባቸው፡፡ ሌላው ሲያደርገው የሚቃወሙትን እነርሱ ከፈጸሙት ሌላው እንዲፈጽመው የሚጠይቁትን እነርሱ በአቅማቸው በቤታቸው ተግባራዊ ማድረግ ካልቻሉ አመኔታን አያገኙም፡፡ የሚሉትን ሆኖ መገኘት ነው-መታመንን የሚያቀዳጀው፡፡ መታመን ከሌለ ደግሞ መመረጥ አይኖርም፡፡እነዚህና ሌሎች መሰል ተግባራትን በኘሮፖጋንዳ ሳይሆን በተግባር ተፈጻሚ ያደረገና የመሪነት ብቃቱን ያሳየ ፓርቲ ነው በምርጫ ካርድ ውጤት ለማምጣት የሚችለው፡፡ በዕለት-ተዕለት እንቅስቃሴው በኘሮግራሙ ያሰፈረውን አቅምና ሁኔታ በፈቀደለት መጠን ተግባራዊ ያደረገ የመራጩን ሕዝብ ቀልብ መሳብ የቻለ ፓርቲ! መራጩ ሕዝብ በምርጫ ለውጥ ማምጣት ይቻላል የሚል ተስፋው ጎልብቶ የተሻለ አስተዳደር አገኛለሁ የሚል አመኔታም አሳድሮ በነቂስ ወጥቶ እንዲመዘገብና ከግዑዛን መሳሪያ ሁሉ የላቀ ኃይል ያላትን ድምጹን ለመጠቀም የምታስችለውን ካርድ ለመያዝ እንዲበቃ ፓርቲው ቢመረጥ ተግባራዊ የሚያደርገውን ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ አመራጮቹን ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡ የሚያቀርበው አማራጭም በምርጫ ፉክክሩ ወቅት በልጦ ለመታየት ተብሎ የሚቀርብ ቀልብ አማላይ ሳይሆን ከሀገሪቱ ተጨባጭ ሁኔታ አንጻር በትክክል ተግባራዊ ሊሆን የሚችል ስለመሆኑ መራጩ ሕዝብ አምኖ የሚቀበለው ሊሆን ይገባል፡፡

የፓርቲነት ብቃቱን በማሳየትና ቢመረጥ ሀገር የሚያስተዳድርበትን አማራጭ በማቅረብ መራጩ “በድምጼ ለውጥ አመጣለሁ” በሚል እምነት የምርጫ ካርዱን እንዲይዝ ማድረግ ከተቻለ የሚቀጥለው ወሳኝ ስራ ስፋትና ጥልቀት ያለው የምርጫ ዘመቻ ነው፡፡ ይህ ደግሞ በአዳራሽና በመገናኛ ብዙሀን የተወሰነ ቅስቀሳ ብቻ አይደለም፡፡ የተለያዩ መንገዶች እየተፈለጉና እየተፈጠሩ ፓርቲውን ለመምረጥ የወሰኑ ሰዎች በተለያየ ምክንያት ውሳኔያቸውን እንዳይለውጡ፣ ገና ያልወሰኑም እሱን ለመምረጥ እንዲወስኑ ተከታታይነት ያለው ሥራ መሥራት ይኖርበታል፡፡ ይህም ብቻ አይደለም” እሱን የማይመርጡትን ለይቶ በማወቅ ቢቻል ውሳኔያቸውን ማስለወጥ ካልተቻለም ብዛታቸውን ማወቅ በጣም ጠቃሚ ነው፡፡

ከላይ የተገለጸው ሁሉ ተሰርቶ ታዛቢ ከሌለ አጭዶ መበተን ነው፡፡ ስለሆነም በእያንዳንዱ ፓርቲው በሚወዳደርበት የድምጽ መስጫም ሆነ የምርጫ ጣቢያ መመሪያው በሚፈቅደው መጠን ታዛቢ ለማስቀመጥ ተግቶ መስራት አለበት፡፡ ታዛቢ ሲባል ምርጫው ወራት ሲቀሩት ተመልምሎ አበል ይከፈልሃል ተብሎ የሚሰማራ ታዛቢ አይደለም፡፡

Page 27: Semayawi1/Newly formed political party the blue (Semayawi)  founder, Professor Mesfin Wolde Mariam

ሰዎች በላይ ጥልቅ በሆነ ፍላጎትና መጠኑ በማይለካ ስሜት አሜሪካንን ያፈቅራሉ፡፡ ሃገር ወዳድነታችንና አርበኝነታችን ሚስቱን በግልፅነት እንደሚያፈቅር ወንድ መሆን አለበት የሚል እምነት አለኝ፡፡ ሚስቱን በትክክል የሚያፈቅር ባል በሚስቱ ውበት ይማረካል፤ ስህተቶቿንም ያውቃል፡፡ እኛም ሃገራችንን ስንወድ እንዲሁ ነው፡፡ አሜሪካንን የምናውቅ የአሜሪካንን ውበት፣ ሃብታምነት፣ ለማደግና ለመለወጥ የምትሰጠውን ታላቅ እድል እናፈቅራለን፤ አሜሪካንን የምናውቅ የአሜሪካን ተራራዎቿን፣ ሸለቆዎቿን፣ ጫካዎቿን፣ በርሃዎቿን፣ ወንዞቿን ከሁሉ በላይ ደግሞ ታላላቅ ሃብትን፤ ባለድንቅ ውበት የስነጥበብ ውጤቶችን የፈጠረውን ህዝቧን፣ ለነፃነት መሰረትነቷ ያለሙና የሰሩ ታላላቅ መስራቾቿን እናፈቅራለን፡፡ ነገር ግን አሜሪካንን የምናውቅ በተመሳሳይ ጥልቅ ስሜት የአሜሪካን አርቲፊሻልነትን፣ አስመሳይነትን፣ ስግብግብነትን፣ ንቅዘትን፣ እብደትን፣ መነሻውና መድረሻው የማይታወቅ በወርቅ ቅብ በተቀባ የተቀረፀ ጥጃ የማምለክ ባህሏን እንጠላለን፡፡አሜሪካ ወደ ዓለም ጦርነት የምትገባው ዲሞክራሲን በአለም ሁሉ አስከብራለሁ ብላ ከሆነ አሜሪካን በመጀመሪያ ዲሞክራሲን አዚህ ማስፈን ይጠበቅባታል፡፡ ዛሬ በእያንዳንዷ ቀን እዚህ በሃገር ቤት ዲሞክራሲ እየተረገጠ፣ ሃሳብን የመግለፅ መብት እየተጨፈለቀ፣ ሰላማዊ ስብሰባዎች እስከ አፍንጫቸው በታጠቁ ባለ ዩኒፎርም ጋጥወጦች እየተሰበሩ፣ የነፃ ፕሬስ አንገት ሸምቆቆ ውስጥ እየገባና እያንዳንዱ ገለልተኛ አስተሳሰብ ሲጥ እየተደረገ ወደ “ጦርነቱ የገባሁት በሌላው ዓለምም ዲሞክራሲ ለማምጣት ነው” የሚለውን የአሜሪካን ጩኸት ቀሪው ዓለም እንዴት ትክክል ነው ብሎ መቀበል ይችላል? እኛ የሌለንን ዲሞክራሲ እንዴት ለሌሎች ልንሰጥ እንችላለለን? ከወታደር ጡንቻ ውስጥ የሚፀነስ፣ ብዙሃንን የኢኮኖሚ ባሪያ በማድረግ የድሆችን ደምና እንባ በመምጠጥ የተገነባ ዲሞክራሲ ፈፅሞ ዲሞክራሲ ሊሆን እንደማይችል በእርግጠኝነት እናገራለሁ፡፡ እንደዚህ ዓይነቱ ድርጊት ዲሞክራሲ ሳይሆን የተጠራቀመ የግፍ ሰንሰለት ውጤትና የለየለት አምባገነንነት ስለሆነ እናንተ የምትኮሩባቸው አባቶቻችሁ ባወጡት አደገኛ ሰነድ ውስጥ እንደተገለፀው ህዝብ እንዲህ ዓይነቱን ግፍ የመቃወምና የማስወገድ መብት አለው፡፡የከሳሻችን ጠበቃ ከእኛ ማንፌስቶ ውስጥ የወሰዳትን “ዘመቻውን ተቃወሙ” የምትለዋን ሃረግ በመምዘዝ የእኛን ህገ ወጥነት ለማሳየት እየደጋገመ ሲያቀርባት እናያለን፡፡ የተከበራችሁ ዳኞች ሆይ! በአክብሮት እንድታስታውሱልን የምንፈልገው እንዲህ አይነት ነገር በክሳችን ላይ ያልተጠቀሰ መሆኑን ነው፡፡ ጥያቄም ማቅረብ የሚፈቀድልኝ ከሆነ ግን እኛ የምናምነውና በማንፌስቶአችን የተገለፀው “ዘመቻውን ተቃወሙ” የሚለው አገላለፅ በእውነቱ አንድ ብቻ መልዕክት አለውን? መቃወም ማለት የተቃወሙትን በጥይት መግደል ማለት ብቻ ነውን? መቃወም ማለት ላለመታዘዝ መጥፋት ብቻ ማለት ነውን? መቃወም ማለት የሚወነጨፉ መሳሪያወችንና ፈንጅዎችን መወርወር ማለት ብቻ ነውን? ከእነዚህ የተለየ ተቃውሞ የለም ብላች ታስባላችሁ?

አስፈላጊነቱን በማናምንበት ጦርነት ውስጥ መዋጋት አንፈልግም በማለት ሰዎች እጃቸውን አጣጥፈው ቢቀመጡ በእውነቱ ይህ መቃወም ማለት አይደለምን? ህገ መንግስቱን የሚፃረሩ አዋጆችና ደንቦች በወጡ ጊዜስ ሰዎች ቅሬታቸውን በፅሁፍ፣ በንግግር ወይም በሌላ በህገ መንግስቱ በተፈቀደ በማንኛውም የማድረግ መብት ሃሳባቸውን መግለፅ መቃወም ማለት አይደለምን? የሰዎችን ሃሳብ ለእሱ ፍላጎት እንዲስማማው እያደረገ የመተርጎም ሥልጣንን ለአንድ የወረዳ ጠበቃ የሰጠው ማን ነው? የተከበራችሁ ዳኞች ሆይ! ከሁሉ በላይ ክሳችን ከዘመቻ ህጉ ጋር የሚያገናኘው አንዳችም ነገር የሌለው መሆኑን በአፅንኦት መናገር እፈልጋለሁ፡፡ ከሳሻችን “በወታደራዊ ዘመቻው ላይ ሴራ አድርጋችኋል” የሚል ክስ ከማቅረቡ ውጭ የተከሰስንበትን ሴራ በምንም መንገድ በምንም ሁኔታ ካለማሳየቱ በተጨማሪ ህግ መተላለፋችንንም ሆነ ጥፋተኛ መሆናችንን የሚያሳይ አንዲት ነገር ማቅረብ አልቻለም፡፡የተከበራችሁ ዳኞች ሆይ! የእኔን እይታ በግድ እንድትጋሩኝ፣ እንድትቀበሉኝ ወይም በምክንያት እንድትዘረዝሩልኝ አልፈልግም፡፡ ወይም “አስተሳሰባችሁ በህግ ውስጥ ነው ወይም ከህግ ውጭ ነው” በማለት እንድትወስኑም አንፈልግም፡፡ በዚህ የህግ ወንበር የተቀመጣችሁት ኢማ ጎልድማንና አሌክሳንደር በርክማን የተባሉ ሁለት ግለሰቦች “ሰዎች የወታደራዊ ዘመቻውን ህግ እንዲቃወሙና እንዳይመዘገቡ በንግግርና በፅሁፍ ቀስቅሰዋል” በማለት ክስ የመሰረተብን የከሳሽ ጠበቃ ይህንን በማስረጃ ማረጋገጡንና አደረጉ የተባልነውም ፅሁፍና ንግግር የሞራል ህግን የሚፃረሩ መሆን ወይም አለመሆናቸውን እንድትወስኑ ብቻ ነው፡፡የተከበራችሁ ዳኞች ሆይ! ውሳኔአችሁ ምንም ይሁን ምን ግን እያደገና እየጠነከረ በመጣው የዚህች ሃገር ሰዎች የጦርነት ተቃውሞ ላይ ምንም ተፅዕኖ እንደማይኖረው፣ ምንም እንኳን በጠነከረ ፕሮፓጋንዳ ወደ ጦርነት መግባትን ምክንያታዊ ለማድረግ ቢሞከርም ጦርነቱ ለወታደራዊ የበላይነትና በሌሎች ላይ የተፈፀመ ወረራ መሆኑን፣ የዘመቻ ህጉ የአሜሪካንን የወታደረዊና የኢንዱስትሪ ጡንቻ ለማሰየት በአሜሪካን ህዝብ ጉሮሮ ላይ የተነጣጠረ መሆኑን፣ የሰው ልጅ ህይወት ለአረመኔ ደም መጣጭ አምባገነኖች ፌሽታ ድግስ ሆኖ የማይቀርብ እጅግ የተቀደሰ ነገር በመሆኑ የእናንተ ውሳኔ ቅንጣት ታክል እንኳን ተፅዕኖ እንደማይኖረው እንድታውቁ ነው፡፡ የእናንተ ውሳኔ ምንም ይሁን ምን ይልቅስ በዚህች አገር በእውነት ፍትህና ነፃነት አሉ ወይስ የባለፉት ዘመናት ጥላ ብቻ ናቸው በሚል እያነጋገረ ለመጣው የህዝብ የመከራከሪያ ሃሳብ የትኛው አስተያየት እውነት እንደሆነ ማረጋገጫ ይሆናል፡፡ ውሳኔአችሁ ምንአልባትም፤ እንዲያውም በእርግጥም በእኛ ላይ ጊዚያዊና አካላዊ የጉዳት ስሜት ሊያደርስ ይችል ይሆናል፡፡ በአላማችንና በመንፈሳችን ላይ ግን ፈፅሞ ቅንጣት ተፅዕኖ ሊፈጥር አይችልም፡፡ በዚህ የፍርድ ሂደት ጥፋተኛ ተብለን ግድግዳ ተደግፈን እንድንረሸን ቢፈረድ እንኳን ለመቀበል ዝግጁ መሆናችንንና ታላቁ ሉተር “የቆምኩት እዚሁ ነው እምነቴም ይኸው ነው ከዚህ ሌላም የማደርገው ነገር

የለም” እንዳለው እኛም ከዚህ ውጭ አንዳችም ነገር ለማድረግ እንደማንፈልግ እነግራችኋለሁ፡፡እናም የተከበራችሁ ዳኞች ሆይ! ሃሳቤን ለማጠቀላል ከተፈቀደለኝ ተከሳሽ ጓደኛዬ ሚስተር በርክማን እንዲህ እያለ የሚናገረው ነገር ትክክል ነው፡፡ “ዛሬ የአሜሪካን ህዝብ ዓይኖች እናንተ ላይ አርፈዋል፡፡ የእናንተን ፍትሃዊነት የሚጠብቁት ለእኛ እንድትራሩልንና እኛ የምናራምደውን አናርኪዝም እንድትደግፉ አይደለም፡፡ ይልቅስ የአሜሪካን ህዝብ ዓይኖች በእናንተ ላይ የሆነው ዛሬ በዚህ በምንኖርባት አሜሪካ ዲሞክራሲ ሳናሰፍን በአውሮፓና በሌላው ዓለም ላሉ ሰዎች ዲሞክራሲ እናወርዳለን እያልን ለህዝብ የምናወራው ነገር ትክክል ነው?፣ ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት እንዲጠፋና እንዲጨፈለቅ እንፍቀድ?፣ የማንስማማበትን ሃሳበ የመንቀፍ፤ በስለላ አዋጅ እንኳ ለመንቀፍ ያልተከለከልነው መብት ይገፈፍ?፣ ፍትህ የአባቶቻችን፤ ያውም የታላላቅ አባቶቻችን ትግል ጥላ ብቻ ሆኖ እንዲቀር እንፍቀድ? ፍትህ በማንም መርማሪ ነኝ ባይ ወይም ፖሊስ ጫማ ስር ስትረገጥ ዝም እንበል? ወይስ ሃሳብን የመግለፅ መብት፣ በነፃነት የመሰብሰብ መብትና የብዙሃን መገናኛ በነፃነት የመዘገብ መብትን በማስከበር የአሜሪካን ህዝብ ውርስና ቅርስ ሆነው እንዲቀጥሉ እንታገል?” የሚሉ አከራካሪ ሃሳቦች ላይ ይፍጠንም ይዘግይም መወሰን ስላለበት የአሜሪካን ህዝብ ዛሬ የእናንተን ውሳኔ በጉጉት በመጠበቅ ላይ ነው፡፡የተከበራችሁ ዳኞች ሆይ! የፍርድ ቤቱ ውሳኔ ምንም ይሁን ምን በእኛ በኩል ምንም የሚለወጥ ነገር የለም፡፡ እኔ በእስካሁኑ ሕይወቴ ለማምንበት ሃሳብ ኖሬአለሁ፡፡ የማምንበትንም ሃሳብ በአደባባይ ለህዝብ አያሳወቅኩ ያለፉትን 25 ዓመታት የሕይወት ዘመኔን አሳልፌአለሁ፡፡ በዚህች ምድር ላይ ምንም ነገር ይህንን እምነቴን የሚያስቀይረኝ የለም፡፡ የእኔን እምነት የሚያስቀይረኝ አንድ ነገር ብቻ ሲሆን እሱም እኔና ጓደኛዬ የቆምንበት እምነት ስህተት፣ ደካማ ወይም ታሪካዊ ሃቅ የሚያንሰው መሆኑን ማረጋገጥ ስትችሉ ብቻ ነው፡፡ ነገር ግን እናንተ ጥፋተኛ ነሽ ስላላችሁኝ ብቻ የቆምኩለትን እውነት አልለውጠውም፡፡ ክቡራን ዳኞች! በእርግጠኝነት እናንተ የማታውቋቸው ሁለት ታላላቅ አሜሪካዊያንን ላስታውሳችሁ!! ራልፍ ዋልዶ ኤመርሰን እና ሄንሪ ዴቪድ ቶሪው ይባላሉ፡፡ ቶሪው “ታክስ ለመክፈል ፈቃደኛ አልሆንክም” ተብሎ ታስሮ በነበረበት ጊዜ ጓደኛው ኤመርሰን እስር ቤት ሄዶ “ዴቪድ እዚህ እስር ቤት ምን ታደርጋለህ?” ሲለው “ኤመርሰን እውነተኛ ሰዎች ላመኑበትና ትክክል ለሆነ ነገር በየእስር ቤቱ ሲወረወሩ አንተ ከእስር ቤት ውጭ ምን ታደርጋለህ?” በማለት መልሶለት ነበር፡፡ የተከበራችሁ ዳኞች ሆይ! በውሳኔያችሁ ላይ ተፅዕኖ የመፍጠር ዓላማ የለኝም፡፡ ለሰው ልጅ ያላችሁን ጥልቅ ፍቅር በመቀስቀስ አቤቱታዬን ለማሰማትም አልፈልግም፡፡ ሴትነቴንም በማዬት እንድታዝኑልኝና በውሳኔያችሁ ላይ እንድትወላውሉም አልፈልግም፡፡ በህይወቴ ሙሉ እንደዚህ ያለ ፍላጎትም ሆነ ዘዴ ኖሮኝ አያውቅም፡፡ ይልቅስ ይህንን

ቅጽ 1 ቁጥር 1 ጥቅምት 2005 ዓ.ም

ኢማ ጎልድማ...

27ወደ ገጽ 15 ዞሯል

Page 28: Semayawi1/Newly formed political party the blue (Semayawi)  founder, Professor Mesfin Wolde Mariam

ቅጽ 1 ቁጥር 1 ጥቅምት 2005 ዓ.ም

ወንጀለኞች ነን፡፡ ከእነዚህ ታላላቅ ሰዎች ጎራ በመመደባችን ግን ታላቅ ኩራት ይሰማናል፡፡ ታላቁ ሳይኮሎጅስት ሃቬሎክ ኤሊስ እንደገለፀው ለሰብአዊ ፍጡር ባላቸው ጥልቅ ፍቅር፣ ለነፃነታቸው በሚሰጡት ያልተገደበ ዋጋ፣ በነፃነት ለማሰብና ለእምነታቸው ክብር የደም ዋጋ ሳይቀር ለመክፍል ዝግጁ በመሆናቸው ብቻ ዛሬ ሰዎች በዓለም ዙሪያ የፖለቲካ ወንጀለኞች ተብለው ስቃይና መከራ እንደሚፈፀምባቸው ከአሜሪካን በስተቀር በሰለጠነው ዓለም የሚኖሩ የሰው ልጆች ሁሉ የተረዱት ሃቅ ሆኗል፡፡ እኛም ከእነዚህ የፖለቲካ ወንጀለኞች ጎራ በመዋላችን ደስታ ይሰማናል፡፡ እኔና ጓደኛዬ ለራሳችን እውነተኞች መሆን ከፈለግን ከዚህ ሌላ የምናደርገው ነገር የለም፡፡ ምክንያቱም የፖለቲካ ወንጀለኛ መሆን ማለት ለሰው ልጅ እድገትና የተሻለ ነፃነት ፈር ቀዳጅነት መሆኑን እኔና ጓደኛዬ በደንብ እናውቃለን፡፡ እኛ የዛሬ የፖለቲካ ወንጀለኞች የቀጣዩ ትውልድ ጀግኖች፣ ሰማዕትና ቅዱሶች እንደምንሆን ታሪካ አስተምሮናል፡፡“ሊታሰብ የማይችለውን ሃሳብ በፅሁፍ ለሌሎች ከማስተላለፋችሁ በተጨማሪ አሁን ባለው ህግ መሰረትና በዚህ ሰዓት የአርበኝነት ስሜት የጎደለው አደገኛ መመሪያ አሰራጭታችኋል፤ በየቦታው ለተደረጉት የሃሳብና የድርጊት ተቃውሞዎች ምክንያት ናችሁ” በማለት የከሳሻችን ጠበቃ እኛን ወንጅሎናል፡፡ ነገሩ ያለጥርጥር እውነት ነው፡፡ ነገር ግን በሰማይ ላይ ለዘለዓለም ተንጠልጥለው እንደሚኖሩ ከዋክብት እኛ ልናንቀሳቅሳቸውና ልንለውጣቸው ወይም ልንለያያቸው ለማንችላቸው ነገሮች እኔና ጓደኛዩን ተጠያቂ ማድረግ ይቻላል?የተከበራችሁ ዳኞች ሆይ! የአርበኝነት ስሜታችሁን እናከብራለን፡፡ ስለአርበኝነት ያላችሁን ትርጉምም መለወጥ ብንችል እንኳን መለወጥ አንፈልግም፡፡ ነገር ግን የተለያየ አይነት ነፃነት እንዳለ ሁሉ የተለያየ ዓይነት ሃገር ወዳድነት እንዳለ ታውቁ ይሆን? እኔ በበኩሌ አንድ ሰው ለሃገሩ ያለውን ፍቅር ለማሳየት ማህበረሰቡ የሚፈፅማቸውን ስህተቶች አለማየት ከሆነ፣ ለማህበረሰብ ግጭቶች መሸፈኛ ማድረግ ከሆነ፣ ወይም ያ ማህበረሰብ ለሚያራምዳቸው የተሳሳቱ እምነቶች ማሳመሪያ ከሆነ፤ ይህ ዓይነቱ ሃገር ወዳድነት የተበላሸ አርበኝነት ነው የሚል እምነት አለኝ፡፡ በሌላም በኩል በዚህች ሃገር መወለድ ብቻ ሃገር ወዳድ መሆንን ወይም የዚህችን ሃገር የዜግነት ወረቀት መነጠቅ ብቻ ሃገር መጥላትን ይፈጥራል የሚል እምነት የለኝም፡፡በዚህች ሃገር ያልተወለዱና የዜግነት የምስክር ወረቀትም ለማግኘት አመልክተው የማያውቁ ብዙ ሰዎችን አውቃለሁ፡፡ እኔ ራሴ ከእነዚህ ሰዎች አንዷ ነኝ፡፡ አነዚህ ሰዎች የአሜሪካን ብሔራዊ መዝሙር ሲዘመር ከመቀመጫቸው ያልተነሱ ሰዎችን በመገፍተር፣ በመማታትና በመሳደብ ለሃገራቸው ያላቸውን ፍቅር ከሚገልፁ የአሜሪካን ዜግነት ካላቸው

ከፈረንሳይ መንግስት ጋር ህብረት እንደፈጠረ የምታውቁ ይመስለኛል፡፡ እንዳስታውሳችሁ የምትፈልጉ ከሆነ ልንገራችሁ፡፡ በፈረንሳይ ውስጥ ተፈጥሮ የነበረውን የህዝብ አመፅ ለማረጋጋትና የህዝብን ጥያቄ ለመመለስ ህግ ከሚባለው በላይ የመፍትሄ ሃሳብ መቅረቡን አታውቁ ይሆን? በታዋቂዎቹ በእነ ዳንትስ፣ በእነ ሮበስፔይረስ፣ በእነ ማራትስ፣ በእነ ሄርበርትስ፣ አለፍም ሲል የሕዝብን የትግል መንፈስ ያብላላው የአብዮታዊው ሙዚቃ ባለቤት ማርሴላይስ ሳይቀር (ምንም እንኳን ሙዚቃው በኋላ ወዳልተፈለገ የጦርነት ቅኝት ቢወርድም)፣ ከዚህም በጣም አለፍ ሲል ካሚሌ ዴስሚዩሊንስን ጨምሮ ያቀነቀኑት ሃሳብ በሙሉ በፈረንሳይ ህግ ማዕቀፍ ውስጥ አልነበረም፡፡ እነዚህ ታላላቅ የፈረንሳይ ነፃነት ፈር ቀዳጆችና አርበኞች በፈረንሳይ ህግ ብቻ ታጥረው ቢቀመጡ ኖሮ የፈረንሳይ ህዝብ ነፃነት ከፈረንሳይ ህዝብ እጣ ፈንታ ይልቅ ጥንቸልን የማደን ስፖርት የበለጠ በሚያስጨንቀው ስራ ፈቱ ሉዊስ 16ኛ የአገዛዝ አስኳል ስር ለዘለዓለም ተቀፍድዶ እንደሚቀር ያውቁ ነበር፡፡አዲስ አስተሳሰብ በህግ ውስጥ ፈፅሞ ሊንቀሳቀስ አይችልም፡፡ አንድ ፖለቲካዊም ይሁን ማሕራዊ ወይም ሌላ ማንኛውም የሰው ልጅ ሃሳብ ወይም ማንኛውም ሳይንስ፣ ስነ ጥበብ፣ ሙዚቃ ሌላም ማንኛውም ለነፃነት፣ ለደስታና ለውበት መግለጫ የሚሰራ ነገር በህግ ውስጥ መንቀሳቀስን መቃወም አለበት፡፡ አለበለዚያ እነዚህን አዳዲስ ሃሳቦች ማራመድ የማይታሰብና የማይሆን ነገር ነው፡፡ ምክንያቱም ህግ ሁልጊዜ የደነዘዘ፣ ግትር ያለ፣ መካኒካል፣ የቦታንና የሁኔታን መለያየት ግምት ውስጥ የማያስገባ፣ እንደ ማሽን ሁሉንም በእንድ ላይ የሚያደቅ ወፍጮ ነው፡፡ ህግ ነገሮች የሆኑበትን መነሻ ምክንያትና መድረሻ ውጤት የማያይ፣ የሰውን ልጅ ውስብስብ አስተሳሰብ ግምት ውስጥ ሳያስገባ ለማሰርና ለመገደብ ብቻ የተፈጠረ ማሰሪያ ነው፡፡ በአንፃሩ የለውጥ ሃሳብ ድርቅ ብሎ ከመቆም ጋር ምንም ዝምድናና ግንኙነት የለውም፡፡ ለውጥ በአንድ በታወቀ ቅርፅ ውስጥም ተጨፍልቆ ሊቀመጥ አይችልም፡፡ ለውጥና መሻሻል የሚፈልግ አስተሳሰብ ለአምባገነን አስተሳሰብ ማጎብደድን አይቀበልም፡፡ እኔ እንዲያውም ህግ መሆን ያለበት ይህ ነው እላለሁ፡፡ እግዚአብሔርም ህግ እንዲሆን የፈለገው ይህ በእኔ ውስጥ ያለው ሃሳብ ነው ብዬ አምናለሁ፡፡ ደጋግሜ የምለውም ይህንኑ ነው፤ ዕድገት ሁልጊዜ የሚታደስ፣ ሁልጊዜ የሚመጣ ሁሉጊዜ የሚለወጥ በፍፁም በህግ ውስጥ ያልታሰረ ነው፡፡ እንግዲህ አዲስ ሃሳብ ማምጣትና ለውጥ መፈለግ ወንጀል ከሆነ፣ አዎ እኔና ጓደኛየ ወንጀለኞች ነን፡፡ አዎ ልክ እንደ ክርስቶስ፣ እንደ ሶቅራጥስ፣ እንደ ጋሊሊዮ፣ ብርኖ፣ ጆን ብራውንና ሌሎች ስፍር ቁጥር የሌላቸው የለውጥና የእውነት አራማጆች እኛም

አዘጋጅ፡- ኢማ ጎልድማንትርጉም፡- ወረታው ዋሴ[email protected]

ለውጥና መሻሻል በህግ ውስጥ ሆኖ አያውቅም!!!

ክቡራን ሆይ!! የተከሰስንበትን ህግን የመጣስና ሴራ የመጠንሰስ ወንጀል የተከበረው ፍርድ ቤት ያምንበት እንደሆነ በተደጋጋሚ በጠየቅን ጊዜ “የተከሰሳችሁበት ጉዳይ በአብዛኛው ሰው ተቀባይነት ያለውን ህግ የሚፃረር ሃሳብ መሆኑ በህጉ መሰረት ከተረጋገጠ ወይም የክሱ መነሻ በህጉ ውስጥ እስካለ ድረስ ፍርድ ቤቱ ክሱን ይቀበለዋል” የሚለውን መልስ ከዳኞች በተደጋጋሚ ሰምተነዋል፡፡ ነገር ግን የተከበረው ፍርድ ቤት መናገር የማይፈልገው አንድ ነገር አለ፡፡ ሁልጊዜም ቢሆን አዲስ አስተሳሰብ ምንም እንኳን እጅግ ሰላማዊና ሰብአዊነት የተሞላዉ ቢሆንም በስልጣን ላይ የተፈናጠጡ አምባገነኖች ሊቀበሉት ቀርቶ በህግ ውስጥ ሊካተት እንደሚችል እንኳ ማሰብ እንደማይፈልጉ በጭራሽ መናገር የማትፈልጉት ሃቅ ነው፡፡ የሰው ልጅ የዕድገትና የብልፅግና ታሪክ ስንል የብሩህ ዘመን መቃረብን የሚያበስሩ የእያንዳንዱ አዳዲስ ሃሳብና አመለካከት ታሪክ ማለታችን ቢሆንም እነዚህ የለውጥና የብሩህ ተስፋ አብሳሪ ሃሳቦች ሁልጊዜም ቢሆን “የጋጥ ወጦች ሃሳብ፣ ህግን የሚያፈርሱና ተቀባይነት የሌላቸው” እየተባሉ ሲወገዙ መኖራቸው የታወቀ ነው፡፡ የተከበራችሁ ዳኞች ሆይ!! መቼም አብዛኛዎቻችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ አስተምህሮት እንደምታምኑ በእርግጠኝነት መናገር እችላለሁ፡፡ አስታውሱ! ክርስቶስን ለሞት ያደረሰው “አመለካከትህ ህግን የሚፃረር ነው” ተብሎ እንደሆነ ታውቃላችሁ፡፡ ከእናንተም አብዛኛዎቻችሁ በአሜሪካዊነታችሁ እንደምትኮሩ በእርግጠኝነት መናገር እችላለሁ፡፡ አሁንም ግን አስታውሱ!! እነዚያ ለእናንተ ነፃነት የተዋደቁና የደሙ ወገኖቻችሁ “ህግ አፍራሽና ወንጀለኞች፣ አደገኛ በጥባጮችና ችግር ፈጣሪዎች” ተብለው ተወንጅለው እንደነበረም ታውቃላችሁ፡፡ የነፃነት አባቶቻችሁ ያስተማሩን ነፃነትን ለማግኘት የተቃውሞ ሃሳብን መግለፅ ብቻ ሳይሆን በቦስተን ወደብ የሻይ ምርቶችን በመድፋት በድርጊትም ጭምር በመግለፅ ነበር፡፡ “አምባገነኖችን መታገልም ለእግዚአብሔር መታዘዝ” ነው በማለትም አስተምረዋል፡፡ ገዥዎቻቸው እጅግ የሚጠሉት “የነፃነት አዋጅ” የተሰኘ አደገኛ ሰነድም አውጥተዋል፡፡ እንዲህ ዓይነቱ ሰነድ አስካሁንም ድረስ አደገኛ እንደሆነ ነው፡፡ በዚያን ወቅት ይህንን አደገኛ ሰነድ ለህዝብ ያሰራጨ ወጣት በኒው ዮርክ ፍርድ ቤት ቀርቦ በ19 ቀን እስራት እንዲቀጣ ተፈርዶበታል፡፡ ምክንያቱም የዚህ ሰነድ አዘጋጆችም ሆኑ አሰራጮች በወቅቱ አናርኪስት ነበሩ፤ በገዥዎቻቸው ህግ ውስጥ አልነበሩምና፡፡የተከበራችሁ ዳኞች ሆይ!! መንግስታችሁ

ኢማ ጎልድማንና አሌክሳንደር በርክማን የአሜሪካን አናርኪስት እንቅስቃሴ መስራችና የድርጅታቸው ልሳን የሆነው የወርሃዊ ዕትም ማዘር እርዝ የተሰኘው መፅሔት አዘጋጆች ነበሩ፡፡ ኢማ እና ጓደኛዋ በአንደኛው የዓለም ጦርነት በአሜሪካን የወጣውን የወታደራዊ ግዴታ ረቂቅ አዋጅ ወጣት ወንዶች እንዲቃወሙ የሚቀሰቅስ ማንፌስቶ በማሰራጨታቸው የአሜሪካንን የዘመቻ ህግ በመጣስ ሴራ ተከሰው ፍርድ ቤት ቀርበዋል፡፡ ሃሳብን በነፃነት የመግለፅና አምባገነኖችን የመቃወም መብቶች እንዲከበሩ እ.ኤ.አ በሰኔ 1917 ኢማ በችሎቱ ፊት ቀርባ ያደረገችውን ንግግር ለዛሬው ትውልድና ለሰላማዊ ታጋዮች የሚያስተምን ነገር አለ ብዬ ስላመንኩ ትርጉሙን እንደሚከተለው አቅርቤዋለሁ፡

፡ መልካም ንባብ!!!

ወደ ገጽ 27 ዞሯል 28