ንደ3 - ethioforum.orgethioforum.org/wp-content/uploads/2014/01/sendek435.pdfሰንደቅ 9ኛ...

24
ወደ ገፅ 5 ዞሯል ኢኮኖሚ...8 ፖለቲካ...6 መዝናኛ...10 የኔ ሃሳብ...20 የዶ/ር ነጋሶ ስንብት፣ የአንድነት ብሔራዊ ምክር ቤት ግምገማ፤ የኢንጅነር ግዛቸው አዲስ የቀያጭነት ጥሪ እና የመድረክ አንደምታዎች የፌዴሬሽን ምክርቤትን የከፈለው የአቶ መላኩ ፈንታ ጥያቄ ሰንደቅ 9ኛ ዓመት ቁጥር 435 ታህሳስ 30 2006 ዋጋ 6 ብር ቴዲ አፍሮ ሰጥቶታል በተባለው ቃለመጠይቅ ውዝግብ 10 ሚሊዮን ብር አጣ ወደ ገፅ 7 ዞሯል ወደ ገፅ 21 ዞሯል የመንግስት ሠራተኛው በመንግስት ላይ የኑሮ ውድነት ማሻሻያ ድጎማ ጥያቄ አነሳ “ኬኩ አላደገም” አቶ ሶፊያን አህመድ ከኦነግ ጋር በተያያዘ ክስ ከተመሰረተባቸው መካከል 45ቱ በእስራት ተቀጡ እንኳን ለገና በዓል አደረሳችሁ

Upload: others

Post on 15-Apr-2020

23 views

Category:

Documents


1 download

TRANSCRIPT

Page 1: ንደ3 - ethioforum.orgethioforum.org/wp-content/uploads/2014/01/sendek435.pdfሰንደቅ 9ኛ ዓመት ቁጥር 435 ረቡዕ ታህሳስ 30 2006 አታሚ፤ ብርሃንና

ወደ ገፅ 5 ዞሯል

3

ኢኮኖሚ

...8

ፖለቲ

ካ...6

መዝናኛ

...10

የኔ ሃ

ሳብ...20

ሰንደቅ

የዶ/ር ነጋሶ ስንብት፣ የአንድነት ብሔራዊ ምክር ቤት ግምገማ፤ የኢንጅነር ግዛቸው አዲስ የቀያጭነት ጥሪ እና የመድረክ አንደምታዎች

የፌዴሬሽን ምክርቤትን የከፈለው የአቶ መላኩ ፈንታ ጥያቄ

ሰንደቅ 9ኛ ዓመት ቁጥር 435 ታህሳስ 30 2006 ዋጋ 6 ብር

ቴዲ አፍሮ ሰጥቶታል በተባለው ቃለመጠይቅ ውዝግብ

10 ሚሊዮን ብር አጣ

ወደ ገፅ 7 ዞሯል

ወደ ገፅ 21 ዞሯል

የመንግስት ሠራተኛው በመንግስት ላይ የኑሮ ውድነት ማሻሻያ ድጎማ ጥያቄ አነሳ

•“ኬኩ አላደገም” አቶ ሶፊያን አህመድ

ከኦነግ ጋር በተያያዘ ክስ ከተመሰረተባቸው መካከል 45ቱ በእስራት ተቀጡ

እንኳን ለገና በዓል አደረሳችሁ

Page 2: ንደ3 - ethioforum.orgethioforum.org/wp-content/uploads/2014/01/sendek435.pdfሰንደቅ 9ኛ ዓመት ቁጥር 435 ረቡዕ ታህሳስ 30 2006 አታሚ፤ ብርሃንና

ሰንደቅ 9ኛ ዓመት ቁጥር 435 ረቡዕ ታህሳስ 30 2006

አታሚ፤ ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት አድራሻ፤ አራዳ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 07 የቤት ቁጥር 984

የአሳታሚው አድራሻ:- ቦሌ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 05/03 የቤት ቁጥር 027 ከአትላስ ሆቴል በስተጀርባ 011-6-62 81 90/ 011-6-18 40 34/ 0911 73 59 18 / 0911 95 58 16 ፖ.ሣ.ቁ. 80964

“ሰንደቅ” ጋዜጣ በሰንደቅ የሕትመትና የማስታወቂያ አገልግሎት ኃ/የተ/የግ/ማኅበር በንግድ ሚኒስቴር በንግድ ሥራ ፈቃድ ቁጥር 14/673/7498/2004፣ በብሮድካስት ባለሥልጣን የምዝገባ ቁጥር 38/2001 የተመዘገበ ሳምንታዊ ጋዜጣ ነው

የገበያ ጥናት፤የማስታወቂያ እና ስርጭት

ባይለየኝ ወርቁ 0921 56 95 030912 95 67 95

ዋና አዘጋጅ ፍሬው አበበቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 የቤት ቁጥር 12/201

0911 61 79 [email protected]

ም/ዋና አዘጋጅፋኑኤል ክንፉ 0911 [email protected]

ከፍተኛ አዘጋጅ ዘሪሁን ሙሉጌታ [email protected]

አዘጋጅ ፀጋው መላኩ

ከፍተኛ ሪፖርተሮች አሸናፊ ደምሴ መስከረም አያሌው

ግራፊክ ኤዲተርነብዩ መሥፍን 0911 18 09 [email protected]

ኮምፒዩተር ጽሁፍ አለምነሽ ታከለሰብለወንጌል ንጉሴ ምናለሸዋ ተ/አረጋይ

ርዕሰ አንቀጽ

ቁጥሮች16489621487965214569856154685548565541857985648985654+689554465418956898+548655544 16489621487965214569856154685548565541857985648985654+689554465418956898+548655544 16489621487965214569856154685548565541857985648985654+689554465418956898+548655544251845586854178854818565

2

መ ል ዕ ክ ቶ ች

ህትመት ክትትልና ስርጭት በዛብህ ተክሉ 0911 41 68 00

የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ

7ሺበፕሮጀክቱ ውስጥ የሚገኙ ጠቅላላ ሠራተኞች ቁጥር

600ከጠቅላላ ሠራተኞች የውጪ

ዜጎች ብዛት

13ሺበቅርቡ ይደርሳል ተብሎ የሚጠበቀው የጠቅላላ ሠራተኞች ቁጥር

ምንጭ - የውሃ፣ መስኖ ልማትና ኢነርጂ

ሚኒስቴርn

ከሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር የተገኘ መረጃ እንደሚጠቁመው ኢትዮጽያ ውስጥ ከአንድ ሚሊየን በላይ የመንግስት ሰራተኞች ይገኛሉ። የግሉ ዘርፍ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ሲጨመሩ ቁጥሩ የትየለሌ ይሆናል። በአገራችን የድህነት ነገር ሆኖ ኑሮ ሽቅብ በወጣ ቁጥር ለሠራተኞች ደመወዝ ጎን ለጎን ማሻሻያ የሚደረግበት ቋሚ አሰራር ባለመኖሩ ተቀጣሪ ሠራተኞች በከፋ የኑሮ ድቀት ውስጥ

ለመዳከር ተገደዋል። እርግጥ ነው፤ በአንድ ወቅት ለመንግስት ሠራተኞች 320 ብር የነበረውን ደመወዝ 420፤ 3‚152 የነበረውን የመምሪያ ኃላፊ ደመወዝ 4‚343 ያስገባ ጭማሪ ተከናውኗል። ይህም ጭማሪ ቢሆን ግን የኑሮ ውድነቱ ጋር የሚስተካከል ባለመሆኑ በተጨባጭ የሠራተኛውን የገቢ ማነስ ችግር ለመቅረፍ አቅም ሳያገኝ ቀርቷል። በዚህም ምክንያት ይመስላል፤ በተለይ በመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ከትንሽ እስከትልቅ እርከኖች ውስጥ በሥራቸው፣በኑሮአቸው ደስተኛ ያልሆኑ ሠራተኞችን ማግኘት ከባድ ያልሆነው። በሥራው እርካታ የሌለው ሠራተኛ ደግሞ ለሙስናና ብልሹ አሰራር የመጋለጡ ዕድሉ ሰፊ መሆኑ አያከራክርም።

የመንግስት ሠራተኞችን የኀሳብና የጥቅም ተካፋይ ማድረግ፣ በየጊዜው ተለዋዋጭ ከሆነው የኑሮ ውድነት ጋር አብሮ ሊሄድ የሚችል የክፍያ ሥርዓት መዘርጋት በተለይ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን፣ ሙስናና ብልሹ አሰራሮችን ለመቀነስ ትልቅ አስተዋጽኦ ሊኖራቸው እንደሚችል ይታመናል። የአገልግሎት አሰጣጡ መሻሻል ደግሞ ዜጎች ጉዳያቸውን በፍጥነትና በጥራት ለመፈጸም የሚያስላቸው ከመሆኑም በላይ በመንግስት ላይ ያላቸውም እምነት እንዲጨምሮ ትልቅ አስተዋጽኦ ይኖረዋል። ይህ የሠራተኛው ፍላጎት ከአገሪቱ አቅም ጋር እንዴት ሊታይ ይችላል የሚለው ራሱን የቻለ ጥናት የሚፈልግ ቢሆንም የጥያቄው ፍትሃዊነት ግን የሚያወዛግብ አይሆንም።

ባለፈው ሳምንት በጠ/ሚኒስትር ጽ/ቤት የሠራተኞች ማኀበር መሪዎች፣ ጠ/ሚኒስትሩን ጨምሮ ከመንግስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ጋር ያደረጉት ውይይት መድረክ ላይ በሠራተኞች በኩል የተነሳው የኑሮ ውድነት ማስተካከያ ጥያቄ የሚያመለክተውም ይህንኑ ሐቅ ነው። ሠራተኞች አሁን ባላቸው ከእጅ ወደአፍ በሆነ ወርሃዊ ደመወዝ (ክፍያ) ከመኖር ወደአለመኖር እያዘቀዘቁ የመምጣታቸው ጉዳይ አገር ያወቀው፣ ጸሐይ የሞቀው ከሆነ ሰንብቷል። መንግስት ይህን ወቅታዊ ጥያቄ የተስፋ ዳቦ በመጣል ለማለፍ የማይችልበት ነባራዊ ሁኔታም ከፊቱ ተጋርጧል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ ከሠራተኞች ወርሃዊ ደመወዝ የሚቆረጠው

የደመወዝ ግብር ከፍተኛ መሆንም እንዲሁ አነጋጋሪ ሆኖ የኖረ ጉዳይ ነው። የሠራተኞች የደመወዝ ግብር ስሌት ከ10 እስከ 35 በመቶ የሚዘልቅ ሲሆን ሠራተኞች ከፔሮላቸው ላይ በቀጥታ ግብሩ የሚቆረጥባቸው በመሆኑ ያለአንዳች ችግር መንግስት ግብሩን መሰብሰብ የሚችል ሲሆን በአንጻሩ ከፍተኛ ዓመታዊ ገቢ ያላቸው የንግድ ተቋማት የተለያዩ ዘዴዎችን በመፍጠር ከታክስ መረቡ የሚያመልጡበት ወይም እጅግ አነስተኛ ክፍያን የሚከፍሉበት ሁኔታ መኖሩ የሚታወቅ እውነታ ነው። ይህ በራሱ የፍትሃዊነት ጥያቄን የሚያስነሳ ነው።

በሌላ በኩል ደግሞ ሠራተኛው የግብር ግዴታውን በአግባቡ በመወጣቱ ከመንግስት በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የሚያገኘው አንዳችም ጥቅማጥቅም ለምሳሌ አንዳንድ ዕቃዎችን ሲሸምት ከግብርና ታክስ ነጻ ማድረግ ወይንም ቅናሽ እንዲያገኝ አለመደረጉም በርካታ ሠራተኞችን የሚያሳዝን ነው።ሌላው ቀርቶ እንደታክስ ከፋይም ሠራተኛው ተገቢውን ክብር እንኳን የሚያገኝ አለመሆኑ በጣም አሳሳቢ ነው። በተጨማሪም በደመወዝ ግብር ላይ የተቆለለውን ግብር በመቀነስ በተዘዋዋሪ ለሠራተኞቻቸው ጥቅማጥቅም የሚሰጡ የግልም ሆኑ የመንግስት ተቋማትን የታክስ ቅነሳ ማበረታቻ ተጠቃሚ የሚሆኑበት ሥርዓትን መዘርጋት የሠራተኞችን ውጤታማነት ለማሳደግ ይረዳል።

በአሁኑ ወቅት በወር 1500 ብር ደመወዝ የሚያገኝ ሠራተኛ 182 ብር ከ50 ሳንቲም ወርሃዊ ግብር ይከፍላል። 3ሺ ብር የሚያገኘው 515 ብር፣ 4ሺ500 ብር የሚያገኘው 937ብር ከ50 ሳንቲም፣ 6000 ብር የሚገኘው 1ሺ437 ብር ከ 50 ሳንቲም የደመወዝ ግብር ይከፍላሉ። ለምሳሌ 937 ብር ከ50 ሣንቲም ግብር የሚከፍለው ሠራተኛ በዓመት 11ሺ250 ብር ሲከፍል፣ 1ሺ437 ብር ከ50 ሣንቲም ግብር የሚከፍለው ሠራተኛ ደግሞ በዓመት 17ሺ244 ብር ግብር ይከፍላሉ ማለት ነው። ይህ ገንዘብ አንድ ቦቴ ተሸከርካሪ ያለው ግለሰብ ነጋዴ በዓመት ከሚከፍለው ግብር ጋር ሲነጻጸር ሠራተኞቹ የሚከፍሉት እጅግ የበዛ መሆኑን በአንድ ወቅት በዘርፉ ጥናት ያደረጉ ምሁራን አስረድተዋል።

አንዳንድ የመንግሥትም ሆኑ የግል ተቋማት ይህን የተጋነነውን የሠራተኞች የደመወዝ ግብር ምጣኔ ለማካካስ ወይንም ብቁ ባለሙያዎችን ከገበያ ውስጥ ለማግኘት ሲሉ በሚል አንዳንድ ክፍያዎችን ግብር በማይጣልባቸው እንደአበል ያሉ (የኃላፊነት፣ የነዳጅ፣ የትራንስፖርት፣ የቤት….) የጥቅማጥቅም ክፍያዎች ላይ ለማሳረፍ ተገደዋል። እናም መንግስት የደመወዝ ግብር ላይ ማሻሻያ ማድረጉ ለሠራተኛው ተጨማሪ ገንዘብን ከማስገኘት ባለፈ ፍትሃዊ የታክስ አስተዳደር ሥርዓትን ለመዘርጋት ለሚደረገው አገራዊ ጥረትም ትልቅ ማሳያ ይሆናል።¾

መንግሥት ለሠራተኞች ደመወዝና ጥቅማጥቅም ማደግ ልዩ ትኩረት ይስጥ

ሌሎች ተማሪዎችስ ምን ዋስትና አላቸው?

ባለፈው ሳምንት እትማችሁ በደ/ማርቆስ ዩኒቨርስቲ በጤና መኮንንነት ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የነበሩ 175 ተማሪዎች ለአንድ ዓመት ያህል ከትምህርት ገበታቸው መታገዳቸውን አንብበን በጣም አዝነናል። ወላጅ ያለውን ነገር ሰጥቶ ልጁን ወደ ትምህርት ቤት የሚልከው ነገ ያሳልፍልኛል ብሎ እንጂ በአንድ ሰው ውሳኔ ብቻ ተሰተጓጉሎ እንዲቀር አይደለም። እነዚህ ተማሪዎች ከዩኒቨርስቲው እንዲወጡ ከተደረጉ በምን ሁኔታ ላይ ሊገኙ እንደሚችሉ መገመት አያዳግትም። መንግስት ልጆቻችንን ለማስተማር ኃላፊነቱን ከወሰደ በኋላ እኔ ባልኳችሁ ካልተሰማማችሁ ግቢውን ለቃችሁ ውጡ በሚል ፈላጭ ቆራጭ ውሳኔ እንዲንገላቱ የሚያደርግ ከሆነ ሌሎቹ ተማሪዎችስ ይህ እጣ ፈንታ እንደማይደርስባቸው በምን ማረጋገጥ ይቻላል?

መምህርት ሶስና -ከሾላn

በስንቱ እንዋረድ?ከሰሞኑ የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን በሀገራችን በጉዲፈቻ ሰበብ እየተሰሩ ያሉትን ደባዎች

በወላጆች ፀፀትና በልጆች እንባ እያጀበ ሲያቀርብልን ነበር። በዚህ ፕሮግራም ላይ በተላለፈው መልዕክት የሁላችንም አንጀት ነው የተላወሰው። የእናንተ ጋዜጣ ይዛው የወጣችው እውነታ ደግሞ አስደንጋጭ ነው። የሴቶች፤ ህፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ሚኒስተርም የስራ ኃላፊነቱን የዘነጋ ይመስላል። ቢያንስ ያለውን እውነታ ለህዝቡ አሳውቆ ሁሉም ተረባርቦ መፍትሄ እንዲያፈላልግ ማድረግ ሲቻል እውነታን መደበቅ እና ቁጥሮችን ማዛባትን እንደመፍትሄ የወሰደው ለምን ይሆን? እኛ አድገው ራሳቸውን የቻሉት ወጣቶች ለምን በሰው ሀገር ይንከራተታሉ? ለምን ይንገላታሉ እያልን ስናዝን፤ ገና ምኑንም የማያውቁት ጨቅላ ህጻናት ማንነታቸውን እንኳን ሳያውቁ እንዲቀሩ የሚደረገው ለምንድን ነው? ችግሩን ከስሩ መቅረፍ ካልተቻለ ልክ ዛሬ ሳዑዲ አረቢያ እያደገችው እንዳለው ሁሉ ነገር ደግሞ እነዚህ ወደ ሰው ሀገር የተሸጡ ህፃናት ወደየመጣችሁበት ተመለሱ መባላቸው አይቀርም። እነዚህኞቹስ ማንነታቸውን ስለሚያውቁ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ። እነዚያ ህጻናት ግን የኔ የሚሉት ነገር ስለሌላቸው እድሜ ልካቸውን ሲያዝኑ መኖራቸው አይቀርም። አንዱን ስንለው ሌላው እየቀጠለ በስንቱ ተዋርደን ሀገራችንንስ እናዋርዳት?

በስልክ የተሰጠ አስተያየትn

Page 3: ንደ3 - ethioforum.orgethioforum.org/wp-content/uploads/2014/01/sendek435.pdfሰንደቅ 9ኛ ዓመት ቁጥር 435 ረቡዕ ታህሳስ 30 2006 አታሚ፤ ብርሃንና

ሰንደቅ 9ኛ ዓመት ቁጥር 435 ረቡዕ ታህሳስ 30 2006 3ዜና

በዘሪሁን ሙሉጌታ

ቅዳሜ ታህሳስ 26 ቀን 2006 ዓ.ም በጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽ/ቤት በተካሄደ ውይይት ላይ በመንግስትና

በመንግስት የልማት ድርጅቶች እንዲሁም በግል ተቋማት የሚሰሩ ሰራተኞችን የሚወክሉ ከልዩ ልዩ የስራ ዘርፎች የተውጣጡ የሰራተኛ ማህበራት ወኪሎች በአሁኑ ወቅት ያለውን የኑሮ ውድነት መቋቋም ባለመቻሉ የኑሮ ውድነት ማሻሻያ ድጎማ ጥያቄ አቀረቡ።

በዕለቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝን ጨምሮ የሀገሪቱ ባለስልጣናት የተገኙ ሲሆን የሰራተኛው ጥያቄ በመሰረታዊነት ለመመለስ የሚቻለው የሀገሪቱ የኢኮኖሚ እድገት (ኬኩ) ሲያድግ ነው የሚል ምላሽ የተሰጠ ሲሆን የደመወዝ ገቢ ግብር ማሻሻያ እንደሚደረግ ግን ፍንጭ ተሰጥቷል።

ከጠዋቱ ሁለት ሰዓት ተኩል እስከ ስምንት ሰዓት በተካሄደው ውይይት ላይ የሰራተኞቹ ተወካዮች በርካታ ጥያቄዎችን አንስተዋል። ከተነሱ ጥያቄዎች መካከል በአሁኑ ወቅት በሰራተኛው የተጫነው የኑሮ ውድነት ከእነቤተሰቡ ለረሀብ

እንዲጋለጥ እያደረገው መሆኑን ገልጸዋል። ሰራተኛው አሁን በሚከፈለው ደመወዝ እየኖረ አይደለም። በምርታማነትም ላይ ከፍተኛ አደጋ በማንዣበቡ ከአቅሙ በላይ መሆኑ በስፋት ተነስቷል። በመሆኑም ከደመወዝ ጭማሪ ባሻገር የደመወዝ ገቢ ግብር እንዲሻሻልና ሌሎች የማኅበራዊ ድጎማዎች እንዲደረግ ጥያቄ ቀርቧል።

በአሁኑ ወቅት በንግድ ድርጅቶች ተጥሎ የነበረው 45 ፐርሰንት የገቢ ታክስ ወደ 30 ፐርሰንት ዝቅ ቢልም በሰራተኛው ላይ ከፍተኛ ደመወዝ ተከፋይ 35 በመሆኑ ወደ 30 ፐርሰንት ዝቅ እንዲልና የዝቅተኛው የደመወዝ እርከን ላይ የተጣለውም የደመወዝ ገቢ ግብር እንዲስተካከል ሲሉ ጠይቀዋል።

በዕለቱ ውይይት ላይ ተገኝተው ከነበሩ ከፍተኛ የሀገሪቱ ባለስልጣናት አንዱ የነበሩት የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ ሶፊያን አህመድ በሰራተኞቹ በኩል የተነሳው የኑሮ ውድነት ማሻሻያ ድጎማ ጥያቄ ግልፅነት ቢጎድለውም፤ መንግስት ከዚህ ቀደም የኑሮ ውድነትን ለማረጋጋት በመሰረታዊ የፍጆታ እቃዎች ላይ ድጎማ እያደረገ መሆኑን

ተናግረዋል። ስኳር፣ የስንዴ ዱቄት፣

የምግብ ዘይትና ዳቦን የመሳሰሉ መሰረታዊ ፍጆታዎች ላይ አሁንም መንግስት ከፍተኛ ድጎማ እያደረገ በመሆኑ መንግስት ከዚህ በላይ አቅም እንደሌለው አስረግጠው ተናግረዋል።

“በዋናነት የኑሮ ውድነቱ ሊፈታ የሚችለው ኬኩ ሲያድግ ነው” ያሉት አቶ ሶፊያ ኢኮኖሚው እያደገና እየሰፋ ሲሄድ መንግስትም ባለሀብትም ለሰራተኛው ጥሩ ክፍያ ይከፍላል። ሰራተኛውም ከኬኩ ማጋራት ይችላል። ስለሆነም ኬኩ እንዲያድግ ጠንክሮ ከመስራት ውጪ ሌላ አማራጭ እንደሌለም ቁርጥ ያለ መልስ ሰጥተዋል።

የደመወዝ ገቢ ግብርን በተመለከተ መንግስት አዋጁን እያስጠና መሆኑን የጠቀሱት ሚኒስትሩ ጥናቱ ሲጠናቀቅ አዋጁ ሊሻሻል እንደሚችል ፍንጭ ሰጥተዋል። አዋጁ በሚሻሻልበትም ወቅት በዋናነት ዝቅተኛ የደመወዝ እርከን ላይ ለሚገኙ ሰራተኞች የታክስ ማሻሻያው ተጠቃሚ ሊሆኑ እንደሚችሉም ተናግረዋል።

ከዚህ ጋር በተያያዘ የተጠናከረውን ዘገባ በገፅ 6 ይመልከቱn

የኢትዮጵያ ብሄራዊ የጋዜጠኞች ህብረት የጋዜጠኛ አስፋው ብርሃኑን እስር ተቃወመ

በጋዜጣው ሪፖርተር

የደቡብ ክልል የሪፖርተር ጋዜጣ ዘጋቢ የሆነው ጋዜጠኛ አስፋው ብርሃኑ በሪፖርተር ጋዜጣ ነሐሴ 29 ቀን 2005 ዓ.ም በሰራው የዜና ዘገባ ምክንያት ተከስሶ በእስራት እንዲቀጣ መደረጉ አግባብ አለመሆኑን በመጥቀስ ጋዜጠኛው ያለምንም ቅድመሁኔታ እንዲፈታ ሲል የኢትዮጵያ ብሄራዊ የጋዜጠኞች ህብረት ጠየቀ።

ኀብረቱ ታህሳስ 25 ቀን 2006 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ እንደጠቀሰው ጋዜጣውም ሆነ ዘጋቢው ስህተታቸውን በማመን እርማት አውጥተውና ይቅርታ ጠይቀው ሲያበቁ የክልሉ መንግስት ጋዜጠኛውን በሰራው የሙያ ስራ ምክንያት ሊያስርና ክሱንም የመመርመርና የመዳኘት ህጋዊ ስልጣን ሳይኖረው ከህግ ውጭ አስሮ አንገላቷል። የክልሉ ፖሊስም በህግ ከተደነገገው ውጭ በስልጣኑ አለአግባብ በመጠቀም ህገወጥ የፍርድ ቤት መጥሪያ በማውጣት ከአዲስ አበባ ጋዜጠኛ አስሮ ወስዶ እንዲመሰክር አስገድዷል ብሏል።

በአዲስ አበባ በታተመ የሪፖርተር ጋዜጣ ላይ ታትሞ በተሰራጨው የዜና ዘገባ የደቡብ ለክልል ፍርድ ቤት ምንም አይነት ስልጣን ሳይኖረው የቀረበለትን መዝገብ መርምሬያለሁ በሚል ምንም አይነት የህግ ጥሰት ያልፈጠረውን ጋዜጠኛ አስፋውን በሁለት ዓመት ከስድስት ወር እስራት መቅጣቱ ተገቢ አይደለም ሲል የፍ/ቤቱን ውሳኔ ተቃውሟል።

በጋዜጣ ታትሞ በወጣ ዘገባ የመጀመሪያው ተጠያቂ ዋና አዘጋጁ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን የደቡብ ክልል ፍርድ ቤት ሪፖርተሩን በእስር የቀጣው በየትኛው የህግ አንቀጽ እንደሆነ እንኳን ብሄራዊ የጋዜጠኞች ህብረት ለማወቅ አለመቻሉን ገልጾአል።

የክልሉ መንግስት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ የታሰረውን ጋዜጠኛ ፈትቶ እንዲለቅ የጠየቀው ማኀበሩ በቀጣይ ማህበራችን ከሚመለከታቸው አካላት ሁሉ ጋር በመተባበር በደቡብ ክልል እየተከናወኑ የሚገኙ የሙስናና የብልሹ አሰራር ሁኔታዎችን ጋዜጠኞች ያለምንም መሸማቀቅ የሚዘግቡበትንና የሚያጋልጡበትን የአሰራር ስርዓት ለማበጀት ጥረት እንደሚያደርግ እናረጋግጣለን ብሏል።

ጋዜጠኞች በየትኛውም አካባቢ የሚሰራውን ህገወጥ ስራ ያለምንም መሸማቀቅና ጣልቃ ገብነት የማጋለጥ ህገመንግስታዊ መብታቸውን እንዳይጠቀሙበት የሚያደርጉ ሁሉ ህገ ወጦች በመሆናቸው እንቃወማቸዋለን ሲልም አክሏል።

የፌዴራሉ መንግስት የደቡብ ክልል እየተከተለ የሚገኘውን ስርአት አልበኝነት ጣልቃ ገብቶ እንዲያርምና ጋዜጠኛውን በአስቸኳይ እንዲያስፈታ ህብረቱ በመላው ጋዜጠኛ ስም ጥሪውን አቅርቧል።

የኀብረቱን መግለጫ ተከትሎም ዓለም አቀፉ የጋዜጠኞች ፌዴሬሽን ታህሳስ 25 ቀን 2006 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ በተመሳሳይ መንገድ የጋዜጠኛ አስፋው ብርሃኑን መታሰር በጥብቅ አውግዟል።n

ከኦነግ ጋር በተያያዘ ክስ ከተመሰረተባቸው መካከል 45ቱ

በእስራት ተቀጡበአሸናፊ ደምሴ

በትምህርት ተቋማት ላይ ቦምብ በማፈንዳት፤ በፊንጫ ስኳር ፋብሪካ ላይ በደረሰው የ2 ሚሊዮን ብር ዝርፊያ በመሳተፍ፣ አብያተ-ክርስቲያናትን በማቃጠል፣ አባላትን በመመልመልና አመፅ በማነሳሳት የኦሮሚያ ፌዴሬሽንን ከህገ-መንግስቱ ተቃራኒ በሆነ መንገድ ከኢትዮጵያ ግዛት ለመገንጠል ሲንቀሳቀሱ ይዣቸዋለሁ ሲል የፌዴራሉ ዐቃቤ ሕግ ክስ ከመሰረተባቸው 69 ተከሳሾች መካከል 45ቱ ጥፋተኛ ሆነው በመገኘታቸው ከ3 እስከ 12 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት ሲቀጡ 18 በነፃ ተሰናበቱ።

የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 4ኛ ወንጀል ችሎት ከትናንት በስቲያ (ሰኞ) ባስቻለው ችሎት፤ የፈፀሙት ድርጊት በንባብ ሲቀርብ እንደተሰማ ነው ተከሳሾቹ በኬኒያ፣ በሶማሊያና በኤርትራ በመዘዋወር የጦር ስልጠናን በመውሰድና የአባላትን ቁጥር ለመጨመር ከመስራት በተጨማሪ በሀገር ውስጥና በውጪ ከሚገኙ ሰዎች የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ወይም ኦነግ ለተሰኘውና መንግስት አሸባሪ ብሎ በሰየመው ቡድን ስም የገንዘብ ዝውውር ሲያደርጉ እንደነበር ተዘርዝሯል።

በተለይም 1ኛ ተከሳሽ ተሻለ በከሺ፤ በ1998 ዓ.ም በፊንጫ ስኳር ፋብሪካ ላይ በተካሄደው ዝርፊያ ከግብረአበሮቹ ጋረ በመሳተፍ መንግስት 2 ሚሊዮን ብር እንዲያጣ ከማድረጉም በተጨማሪ በአንድ ትምህርት ቤት ላይ ቦምብ በመወርወር ወንጀል ጥፋተኛ ተብሏል። ሌላኛው ተከሳሽም በኦሮሚያ ቆሬ መንደራደዩ በሚባል አካባቢ ከኦነግ አባል በተሰጠ ትዕዛዝ በ1996 ዓ.ም አብያተ ክርስትያናትን አቃጥለው ሰው ገድለዋል ሲል ዐቃቤ ሕግ የክስ ዝርዝሩን ያስረዳል። ተከሳሾቹ መንግስትን በኃይል ለመገልበጥ በማሴር፤ ገንዘብ በማሰባሰብና መሳሪያ በመግዛት፤ አባላትን በመመልመልና በራሪ ወረቀቶችን በማዘጋጀት የሽብር ቡድኑን አላማ በመደገፍ ሲንቀሳቀሱ ነበር ሲል ዐቃቤ ሕግ ያስረዱልኛል ያላቸውን ከሃምሳ በላይ የሰውና የሰንድ ማስረጃዎችን ለፍርድ ቤት አቅርቧል።

የግራ ቀኙን ሀሳብ ሲመረምር የቆየው ፍርድ ቤቱ፤ ተከሳሾቹ የፈፀሙትን ወንጀል ያብራራው የዐቃቤ ሕግ የክስ መዝገብ የደረሰውን ውድመት በዝርዝር የሚያሳይ ካለመሆኑ መነሻነት የወንጀሉን ደረጃ መካከለኛ ነው ሲል ያስቀመጠው ሲሆን፤ ይህም ቢያንስ እስከ 15 ዓመት ፅኑ እስራት ያስቀጣ እንደነበር በማስታወስ ተከሳሾቹ ያቀረባቸውን በርካታ የቅጣት ማቅለያዎች ከግምት ውስጥ በማስገባት የቅጣት ውሳኔው መዘጋጀቱን አትቷል።

ሰኞ ዕለት የቅጣት ውሳኔውን ያስተላለፈው የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 4ኛ ወንጀል ችሎትም ዐቃቤ ሕግ ያቀረባቸውን የሰውና የሰነድ ማስረጃዎች በአግባቡ ካየ እና የተከሳሾቹንም የመከላከያ ማስረጃዎችና የቅጣት ማቅለያዎችን ከመረመረ በኋላ ቀደም ላለው ጊዜ 18 የሚሆኑትን ተጠርጣሪዎች ነፃ ናችሁ ሲል በብይን ያሰናበታቸው ሲሆን፤ የሁለት ተከሳሾች ጉዳይ ደግሞ ለብቻው ተነጥሎ በመታየት ላይ ነው ሲል አስረድቷል። በተቀሩት 45 ተከሳሾች ላይም የጥፋተኝነት ውሳኔ ካስተላለፈ በኋላ ከ3 እስከ 12 ዓመታት በሚደርስ ፅኑ እስራትና 40 በሚደርሱት ላይም ከ2 እስከ 3ዓመት የሚደርስ የህዝባዊ መብት እገዳ ጥሎባቸዋል። n

የመንግስት ሠራተኛው በመንግስት ላይ የኑሮ ውድነት ማሻሻያ ድጎማ ጥያቄ አነሳ

•“ኬኩ አላደገም” አቶ ሶፊያን አህመድ

በዘሪሁን ሙሉጌታ

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) ሦስተኛ መደበኛ ጉባኤውን ካካሄደ በኋላ ኢንጂነር ግዛቸው ሽፈራውን በፕሬዝደንትነት ቢመርጥም በቀረው የፓርቲው አመራር ቦታ ላይ አዳዲስና ወጣት አመራሮችን በነባሮቹ ተክቷል።

ባለፈው ቅዳሜ በአዲስ ቪው ሆቴል በተካሄደ ሥነስርዓት ላይ በፓርቲው ሕገ-ደንብ መሠረት በጠቅላላ ጉባኤው የተመረጡት ኢንጂነር ግዛቸው ሽፈራው ለ13ቱን ቋሚ ኮሚቴዎች የሚመሩ 13 የካቢኔ አባላትን ለብሔራዊ ም/ቤቱ አቅርበው አፅድቀዋል። ሁለት ቀሪ የካቤኔ አባላትን በይደር ለሌላ ጊዜ አስተላልፈዋል።

በቀጣዮቹ ሦስት ዓመታት ፓርቲውን በስራ አስፈፃሚነት (ካቢኔ አባልነት) የሚመሩ ተቀዳሚ ም/ቤት ፕሬዝዳንት አቶ ተክሌ በቀለ፣ አቶ በላይ ፈቃዱ ም/ል ሊቀመንበር፣ አቶ ስዩም መንገሻ ዋና ፀሐፊ፣ አቶ ዳንኤል ተፈራ የድርጅት ጉዳይ፣ አቶ ሃብታሙ አያሌው ህዝብ ግንኙነት፣ አቶ ሰሎሞን ስዩም የፖለቲካ ዘርፍ አላፊ፣ ኢንጂነር ዘለቀ ረዲ የውጪ ግንኙነት ኃላፊ፣ አቶ ዳዊት አስራደ የኢኮኖሚ ጉዳይ ኃላፊ። አቶ አለነ ማዕጠንቱ የማኅበራዊ ጉዳይ ኃላፊ፣ አቶ አስቻለው ከተማ የፋይናንስ ጉደይ ኃላፊ፣ ወ/ሮ የትናየት ቱጂ የሕግና ሰብአዊ መብት ኃላፊ፣ አቶ ትዕግስቱ አወሉ የአዲስ አበባ ሰብሳቢ በመሆን የስራ አስፈፃሚ አባል ሆነው ተመርጠዋል። በቀጣይም የወጣቶችና የሴቶች ጉዳይ ኃላፊዎች የሚመረጡ ይሆናል።

አዲሱ ካቢኔው በዕድሜ ከ28 እስከ 35 የሚሆኑት ከአጠቃላይ

የስራ አስፈፃሚ አባላት 60 በመቶ ሲሆኑ፤ ዕድሜአቸው ከ40 እስከ 45 የሚሆኑ 26 ናቸው የተቀሩት ከ50 እስከ 65 የሚሆኑ ደግሞ 13.3 በመቶ እንደሆኑ ተገልጿል። በትምህርት ዝግጅት ረገድ ከአጠቃላይ የስራ አስፈፃሚ አባላቱ 7ቱ የማስተርስ ዲግሪ ያላቸው ሲሆን፤ 4ቱ የመጀመሪያና ሁለቱ ዲፕሎማ መሆናቸውም ተገልጿል። የሥራ አስፈፃሚ አባላቱ የተመረጡት ከ44 የብሔራዊ ም/ቤት አባላት የ39ኙን ድጋፍ ሲያገኙ የአንድ ተቃውሞና በሦስት ድምፀ-ተአቅቦ ነው የተመረጡት።

በአሁኑ የሥራ አስፈኀሚ አባላት ምርጫ የብሔር ተዋፅኦ ትኩረት እንዳልተሰጠው ተገልጿል። በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ የሰጡት የፓርቲው የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሃብታሙ አያሌው ፓርቲው በብሔረሰብ እኩልነት እንጂ ስልጣንን በብሔር በማከፋፈል አያምንም፣ ነገር ግን ፓርቲው ሥልጣን በብቃትና ችሎታ ስለሚያምን ለብሔር ተዋፅኦ ትኩረት አለማድረጉን አስረድተዋል። በሀገሪቱ ከ80 በላይ ብሔረሰቦች ቢኖሩም በ13 ሥራ አስፈፃሚዎች ውስጥ ሁሉንም ብሔረሰብ መወከል አይቻልም ብለዋል። ያም ሆኖ እንደ አጋጣሚ ቢሆን በሀገሪቱ ያሉ አብዛኛዎቹ ብሔረሰቦች የተካተቱበት ሥራ አስፈኀሚ መመስረቱ ተገልጿል። በሴቶች ተሳትፎ ረገድ ቀደም ሲል የነበረው የሥራ አስፈፃሚ አንድም ሴት ባይኖረውም በአሁኑ ግን አንድ ሴት ማሳተፉን አቶ ሐብታሙ በጥሩ ጎኑ ሊታይ እንደሚችል ተናግረዋል። የሴቶች ተሳትፎ ችግር የአንድነት ፓርቲ ብቻ ሳይሆን የሀገሪቱም ችግር እንደሆነ ጠቅሰው ገዢው ፓርቲ እንኳ ከ60 በላይ ሚኒስትሮችና ሚኒስትር ዴኤታዎች

ቢኖሩትም የሴቶች ተሳትፎ በቁጥር ከስድስት አይበልጥም ብለዋል።

በቀጣይ አዲሱ የሥራ አስፈፃሚ በርካታ ተግዳሮቶች ከፊቱ መቆማቸው እየተገለፀ ነው። በተለይ የ2007 ምርጫ መቃረብና የፓርቲዎች የውህደት ጥያቄ ቀዳሚ ጉዳይ ነው። አዲሱ የስራ አስፈፃሚ ከፓርቲዎች ጋር መዋሃድን ቀዳሚ አድርጎ እንደሚሰራና ከማይዋሃዳቸው ፓርቲዎች ጋር መዋቅራዊ ባልሆነ ሁኔታ በትብብር ለመስራት መዘጋጀቱን ከአቶ ሀብታሙ ገለፃ መረዳት ተችሏል። በተጨማሪም ኢህአዴግ ከያዘው አምባገነናዊ አውራ ፓርቲ ግትር አቋም ሀገሪቷን ወደ ቀውስ እያመራ በመሆኑ ወደ ድርድር እንዲመጣ ሥራ አስፈፃሚው የበኩልን ጥረት ያደርጋል ያሉት አቶ ሐብታሙ፤ ድርድር ሲባል ስልጣን መከፋፈል አለመሆኑ ታውቆ በምትኩ በሀገሪቱ ነፃ የዴሞክራሲ ተቋማት ለማረጋገጥ፣ ከሕግ የበላይነት ጋር በተያያዙ ጥያቄዎች ላይ፣ የታሰሩ ፖለቲከኞች ጋዜጠኞችና የመብት ተሟጓቾች ጉዳይ ለመወያየትና ብሔራዊ መግባባት እንዲፈጠርም ጥረት ያደርጋል ብለዋል።

ከመድረክ ጋር ስላለው ግንኙነት በተመለከተ በጉባኤው በተሰጠው አቅጣጫ መሠረት በሦስት ወር እልባት እንደሚሰጠው የጠቀሱት ህዝብ ግንኙነቱ ከመድረክ ጋር የሚኖረው ግንኙነት በውህደት ሊፈታ እንደሚችል ያላቸውን እምነት ገልፀዋል። በአሁኑ ወቅትም የመድረክ አባል የውህደት ድርድሮችን እያደረጉ መሆኑንም አስረድተዋል። ከመድረክ ውጪ ያሉ ፓርቲዎችም ቢሆኑ አንድ ግዙፍ ዴሞክራሲያዊ ኃይል ለመፍጠር በሚደረገው ጥረት ውስጥ አንድነት ግፊት ማድረጉን ይቀጥላል ብለዋል።¾

አንድነት ነባር አመራሩን በወጣቶች ተካ

Page 4: ንደ3 - ethioforum.orgethioforum.org/wp-content/uploads/2014/01/sendek435.pdfሰንደቅ 9ኛ ዓመት ቁጥር 435 ረቡዕ ታህሳስ 30 2006 አታሚ፤ ብርሃንና

ሰንደቅ 9ኛ ዓመት ቁጥር 435 ረቡዕ ታህሳስ 30 20064 ማስታወቂያ

Page 5: ንደ3 - ethioforum.orgethioforum.org/wp-content/uploads/2014/01/sendek435.pdfሰንደቅ 9ኛ ዓመት ቁጥር 435 ረቡዕ ታህሳስ 30 2006 አታሚ፤ ብርሃንና

ሰንደቅ 9ኛ ዓመት ቁጥር 435 ረቡዕ ታህሳስ 30 2006 5ፖለቲካ

ወደ ገፅ 16 ዞሯል

በጋዜጣው ሪፖርተር

የዛሬን አያድርገውና ታህሳስ 2001 ዓ.ም በኢምፔሪያል ሆቴል ውስጥ መድረክ ሲፀነስ፤ የቀድሞ የኢትዮጵያ መንግስት መከላከያ ሚኒስትር የነበሩት አቶ ስዬ አብርሃ ባቀረቡት የመነሻ ጥናት ወረቀት “የሰላማዊ የትግል አማራጭ፤ የሰላማዊ ፖለቲካ የሽግግር ጥያቄ

እና የሰላማዊ ትግል መልኮችና ተግባራዊነታቸው በኢትዮጵያ” በሚለው ላይ እንዳሰፈሩት፤ “በዓላማ በስትራቴጂ እና በስልት መካከል ያለው ግንኙነት የተዋረድ ነው። ስትራቴጂ ለመንደፍ የትግሉ ዓላማ እንደግብዓት መነሻ ይወሰዳል፤ ስልቶችን ለመምረጥ እና ለመቀመር ዓላማው እና ስትራቴጂው እንደግብዓት ይወሰዳሉ። አንድን የተመረጠ የትግል ዓላማ ለማሳካት በመንገድ ላይ የተገኘን ስትራቴጂ አንስቶ ተግባራዊ አደርጋለሁ ቢሉ ውጤቱ ዓላማው ዘንድ ላይደርስ ይችላል። ስልት እና ስትራቴጂ እንደዚሁ ለየቅል ከሆኑ ብዙ ተለፍቶም ውጤት ላይ ላይደርስ ይችላል። “ከየትም ፍጪው ዱቄቱን አምጪው” የሚል መርህ አይሰራም” ብለው ነበር።

አቶ ስዬ ይህን መሠረታዊ ሃሳብ በፅንሰቱ ጊዜ ቢያሰፍሩትም መድረክ በአዲስ አበባ ስድስት ኪሎ በሚገኘው ጽ/ቤቱ ውስጥ ሐምሌ 14 ቀን 2004 ዓ.ም. ባካሄደው የጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ “መድረክ ለዴሞክራሲ ትብብር በኢትዮጵያ” በሚል በ2001 ዓ.ም. የመሠረተውን ጊዚያዊ የፖለቲካ ቅንጅትን በማፍረስ ወደ ፖለቲካ ግንባር መለወጡን ይፋ ማድረጉ ይታወሳል።

በዚህ የፖለቲካ ግንባር ምስረታው ላይ የተሳተፉት ፓርቲዎች፤ የኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራቲክ ፓርቲ፣ የኦሮሞ ሕዝብ ኮንግረስ፣ የኦሮሞ ፌደራሊስት ዴሞክራሲ ንቅናቄ፣ አረና ትግራይ ለሉአላዊነትና ለአንድነት ፓርቲ እና አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ናቸው። እነዚህ አምስት ፓርቲዎች ወደ ፖለቲካ ግንባር ምስረታ ከመምጣታቸው በፊት የየራሳቸውን ጠቅላላ ጉባኤ አድርገዋል። የፖርቲዎቻቸውን የጠቅላላ ጉባኤ ውሳኔ ለጉባኤው በማቅረብ የፓርቲ ሕልውናቸውን እንደተጠበቀ ሆኖ፤ “የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲ አንድነት ግንባር /መድረክ/” በሚል ስያሜ ወደ አንድ የፖለቲካ ግንባር መሸጋገራቸውን ይፋ ማድረጋቸው ይታወሳል።

ከእነዚህ መስራች የፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ በብሔራዊ ም/ቤቱ መጋቢት 14 ቀን 2005 ዓ.ም. ባሳለፈው ውሳኔ መነሻነት የመድረክን ሙሉ እንቅስቃሴ እንዲገመገም አቅጣጫ አስቀመጠ። በውሳኔው መሰረት ለአንድ ወር የተቋቋመው ኮሚቴ ሚያዝያ 19 ቀን ዓ.ም. ሪፖርቱን ለምክር ቤቱ አቀረበ። ከገምጋሚዎቹ መካከል አቶ ሃብታሙ አያሌው ለሰንደቅ የሪፖርቱን ይዘት በስፋት ተንትነው መስጠታቸው ይታወሳል።

አቶ ሐብታሙ አያሌው እንደተናገሩት፤ “የመድረክ መተዳደሪያ ደንብ ሙሉ በሙሉ ዴሞክራሲያዊ አይደለም። አንድ ጥሩ ምሳሌ የሚሆነው አቶ ግርማ ሰይፉ (ብቸኛው የፓርላማ የተቃዋሚ ፓርቲ ተወካይ) በማንኛው መመዘኛ መድረክን መወከል አይችልም በማለት ፕሮፌሰር በየነ አቋም ይዟል። ይሄንን አቋም የያዙት በመድረክ ሕገ-ደንብ መሠረት ማንኛውም ውሳኔ በመቶ ፐርሰንት ይወሰናል በሚለው ደንብ መሠረት ነው። ስለዚህ ግርማ ሰይፉ መድረክን አይወክልም ብለው አጀንዳ ሲያቀርቡ፤ አንድነት ብቻውን ቢቃወም እንኳ ተቀባይነት ሊያገኝ አይችልም።

አባል ፓርቲዎች ለመግባትም ሆነ ለመውጣት ቢፈልጉ ደንቡ ላይ ዴሞክራሲያዊ ባህሪ የለውም። መድረክ ወደ ግንባር የመጣበት ፕሮግራም የአንድን ግንባር ፎርማሊቲ በማያሟላ ደረጃ ላይ መሆኑን ተረድተናል። አንደኛው በፖለቲካ መርህ ደረጃ ወሳኝ በሆነ ሁኔታ ጫፍ በረገጡ ፓርቲዎች ነው ግንባር የፈጠሩት። በግንባሩ ውስጥ የሊብራሊዝም አስተሳሰብን የሚያራምዱና የቡድን መብትን የሚያራምዱ በመሆኑ ይሄንን ልዩነት ሳያጠቡ ወደ ግንባር የመጡት። ስለዚህ በፕሮግራም ደረጃ መድረክ ከፍተኛ ችግር አለበት።

እንዲያውም አንዳንዶቹ ፕሮግራሞች የተድበሰበሱና ግልፅ ያልሆኑ ናቸው። በተለይ የመሬት እና የፌዴራሊዝም ጉዳይ ወሳኝና አንገብጋቢ የፖለቲካ ጉዳዮች ቢሆኑም እንዲሁም በቡድን እና ግለሰብ መብቶች ቅደም ተከተል ላይ ግልፅ የሆነ የፖለቲካ አስተሳሰብ ሳይያዝ ነው ግንባር ለመፍጠር የተሞከረው። እዚው ግንባር ውስጥ የቡድን መብትን ማስከበርን አስቀድመው የጋራ ዓላማ በማለት የሊብራሊዝምን አስተሳሰብ አስቀምጠዋል። ጫፍ የረገጠ የርዕዮተ ዓለም ፍልስፍና እየተከተሉ በጋራ ግንባር ማቋቋም ፈፅሞ አይቻልም።

ስለዚህ የርዕዮተ ዓለም ልዩነቱ ሳይጠብ ወይም ሳይጠፋ ወደ ግንባር መመጣቱ በፕሮግራሙ ላይ ከፍተኛ ችግር እንዳለበት የሚያሳይ ነው።

በተፈረካከሰ ርዕዮተ ዓለም ግንባር ለመፍጠር የተሄደበት እርቀት የሁኔታውን አስገራሚነት ይበልጥ የሚያጎላው ነው። ለምሳሌ መሬት የሀገሪቱ ኢኮኖሚ መሠረት መሆኑ እየታወቀ፣ በዚህ ላይ ጥርት ያለ ወሳኝ አቋም ሳይያያዝ እንዴት አድርገህ “ግንባር” ብለህ ትመጣለህ? ፌዴራሊዝም በተመለከተም ግልፅነት የለም።

በአሁኑ ወቅት ስብስቡ የግንባርነት ደረጃውን ሳይጨርስ ወደ ግንባር ማደጉ ትክክል አይደለም። የ“ግንባርን” ፎርማሊቲ ሳያሟሉ ወደ “ውህደት” መሄድ አስቸጋሪ ስለሆነ አሁን መድረክ እንደ መድረክ እንዲሁም እንደ አባል ፓርቲ ቆም ብለን የምናይበት ጊዜ መሆኑን አስረድተናል። ወደ ሌሎች ጣት ከመጠቆም በፊት እራስን ማየት ተገቢ ነው ብለን አይተናል። አንድነት እንደ ፓርቲ በብሔር መደራጀትን ዴሞክራሲያዊ መብት ነው ብሎ ያመናል። ነገር ግን በብሔር መደራጀት ለኢትዮጵያ ፖለቲካ ይጠቅማል ብሎ አያምንም። በብሔር ከተደራጁ ፓርቲዎች ጋር ዴሞክራሲያዊ መብታቸው ነው ብሎ ሲያበቃ ከዚህ አስተሳሰባቸው እንዲላቀቁ በዴሞክራሲያዊ መንገድ አብሮ መስራቱ ጠቀሜታ አለው ብሎ ያምናል። ስለዚህ ከኢህአዴግ የሚለየውን ግልፅ አቋምና አስተሳሰብ ይዘህ ሕዝቡን “የያዝኩት አስተሳሰብ ይህ ነው ከጠቀመህ ምረጠኝ” ነው የምትለው። አለበለዚያ በተድበሰበሰ ወይም በጨበጣ ስልጣን ላይ መውጣት ነው የሚሆነው።

መድረክ ሊያድግ ከተፈለገ ብትንትን አድርጎ በመወያየት ወደ ለውጥ ማምራት አለበት። ለለውጥ ዝግጁ ካልሆነ ግን በምንም ተአምር በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ዕድል እንደሌለው ግልፅ አድርጎ ማሳየት ይገባል” ብለው ነበር።

አቶ ሃብታሙ ይህን የግምገማ ውጤት ይፋ ቢያርጉም መድረክ ሲመሰረት ለሰንደቅ አስተያየታቸውን የሰጡትን ሙህራንም አስተያየት መመልከቱ ተገቢ ሆኖ አግኝተነዋል።

በወቅቱ ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ መምህር አሁን በወቅቱ የተፈጠረውን የመድረክ ግንባርን የገለፁት በአንፃራዊነት፤ “በቅርፃዊ ሥነ አመክንዮት (Formal Logic) ነው።” ይህም ሲባል አሉ መምህሩ፤ “ቅርፃዊ ሥነ አመክንዮት የአስተሳስብ አወቃቀር ወይም ቅርፅ የሚያጠና ሳይንስ ሲሆን፤ የአስተሳሰብን ተጨባጭ ይዘት አንጥሮ በመተው የቅርጽን ክፍሎች የሚያቆራኙትን አጠቃላይ ሁኔታዎች መርጦ የሚያቀናጅ ነው። ቅርፃዊ ስነ አመክኒዮ ለቅርጽ ከፍተኛ ትኩረት የሚሠጥ በመሆኑ በተጨማሪም፤ ነገሮችን ወይም ክስተቶችን በተናጠል የሚያይ በመሆኑ ትክክለኛውን ጣምራ ህልውናቸውንና ግንኙነታቸውን በጥልቅ ሊገነዘብ አይችልም” የሚል ነው። ይህም ማለት የመድረክ አባል ፓርቲዎች ያላስማማቸውን ጉዳዮች በመያዝ ወደ ግንባር ማደጋቸውን ያሳያል። አንድ ግንባር ወጥ ፕሮግራም ይዞ ወደ ሕዝብ ለመቅረብ በቅድሚያ አባላቱ በውስጠ ፓርቲ ትግል ተፋጭተው የሚበጀው ይሄ ነው ብለው መምጣት አለባቸው። ስለዚህም፤ መዋቅራዊ አደረጃጀት ብቻውን ከይዘት ተነጥሎ ብዙ ርቀት አይጓዝም። በአንፃሩ የመድረክ ግንባርነት የይዘት ሳይሆን የቅርፅ ነው ያስባለው መከራከሪያ ይኼው ነው” ማለታቸው ልብ ይሏል።

አያይዘውም ከቅርፃዊ ሥነ አመክንዮት አንፃር ግንባር የሆነውን መድረክ ስንመለከተው፤ “በስብስብ ውስጥ ያለውን የተለያየ የፖለቲካ

መርህ እና አስተሳስብን በተናጠል ለመመልከት በመሞከራቸው በውስጣቸው ያለውን የቅራኔ ልዩነቶች እንዳይመለከቱና ወደ አንድነት መርህ ሊያመራ የሚችል አስተሳሰብ ብቻ ላይ አትኩሮት እንዲያደርጉ ተገደዋል። ይህ አይነት ስሜት ቅርፃዊ አመክንዮን የሚያሳድረው ጫና ስለሆነ “ግንባርን በግንባር” መዋጋት ነው የሚለውን ነው አሁን እየሰማን ያለነው። የዚህ መሰረታዊ እሳቤም በቅርጽ ላይ የተንጠለጠለ የፖለቲካ ጨዋታ ከመፍጠር ውጪ በይዘት ደረጃ ወደ ፖለቲካ ጨዋታው ሜዳ የተገባበት ሁኔታ ባለመኖሩ ፋይዳው ብዙም አይደለም። ምክንያቱም፤ በስብስቡ ውስጥ ሁሉንም ፓርቲዎች መግዛት የሚችል የታሸ እና ነጥሮ የወጣ ገዢ ፖለቲካዊ አስተሳሰብ ባለመኖሩ አደረጃጀቱ ስንጥቅ አለው” ብለው ነበር።

ሌላው በወቅቱ አዲሱ “ግንባር” ድፍረት

ያነሰው “ግንባር” ነው ያሉት በዓለም ዓቀፍ ግንኙነት እና የፖለቲካ ሳይንስ ባለሙያ የሆኑት አቶ ሰለሞን አሰፋ (ስማቸው የተቀየረ)፤ “በፖለቲካ ሳይንስ ይህን መሰል ግንባር አፈጣጠር የሚገለፀው በቀያጭነት ነው። ይህም ሲባል ቀያጭነት (Eclecticism) ሊዛመዱ የማይችሉ ልዩ ልዩ ፍልስፍናዎች ርዕዮተዓለሞችን አስተሳሰቦችና የፓርቲ መመሪያዎች መራርጦ ለማስታረቅ የሚሞክር አመለካከት በመሆኑ ነው።

“ለምሳሌ በአዲሱ ግንባር ውስጥ ያለውን የፖለቲካ ሰልፍ ብትወስድ፤ የሚቃረኑ ንድፈ ኀሳቦችን ለማስታረቅ እየተሞከረ ያለበት ሁኔታ ነው ያለው። የዘውግ አሰላለፍን ከዘውግ ዘለል አሰላለፍ ጋር፣ የግለሰብን መብት ከብዙሃን መብት ጋር፣ ሶሻል ዴሞክራሲን ከሊብራል ዴሞክራሲ ጋር ለማዛመድ የሚሞክር ነገር ግን መሠረታዊ ልዩነቶችን መፍታት የማይቻልበት ሁኔታ መኖሩን የዓለም ፖለቲካ ምስክርነት ባለበት በአማራጭነት የተወሰደ አካሄድ ነው”

አያይዘውም፤ “የዚህ አይነት የፖለቲካ መስመር ላይ የሚገኙ ፖለቲከኞች መሠረታዊ ዕሳቤ ስህተት በአንድ ኅብረተሰብ ውስጥ ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ ከከባቢያዊ ፖለቲካው ጋር ያለውን መሠረታዊ ግንኙነት ለይቶ ለማወቅ አለመቻላቸው ሲሆን፤ ከዚህም የተነሳ የሚከተሉት ፖለቲካዊ መስመር ከተጨባጭ ሁኔታዎች ጋር ያለውን ሰንሰለታዊ ግንኙነትን ስለሚክድ ኅብረተሰቡ ሊቀረፍለት የሚፈልገውን ችግር በተገቢው ሁኔታ መመለስ አይችሉም። የኅብረተሰቡን ፖለቲካ ተሳትፎ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ሊያከስመው ይችላል” ብለው ነበር።

“ምክንያቱም፤ የአንድ የፖለቲካ ፓርቲ ወይም የፖለቲካ ፓርቲዎች ስብስብ በፖለቲካ ውስጥ ያላቸው ዋነኛ ግብ ስልጣን መጨበጥ ነው። ወደ ስልጣን የሚደረግ ማንኛውም እንቅስቃሴ ለልዩነት የሚዳርጉ ማናቸውም የፖለቲካ በሮች ተዘግተው የሚደረግ የፖለቲካ ጨዋታ እንጂ፤ ለተቃራኒ ፖለቲካ ፓርቲ በቀላሉ ለፕሮፖጋንዳና ቅስቀሳ በሚያመች መልኩ ራስን አጋልጦ የፖለቲካ ጨዋታ አይኖርም። ስለዚህም፤ አሁን ተፈጠረ የተባለው አዲስ ግንባር በተቃራኒ ፖለቲካ ፓርቲ በቀላሉ የሚተረተርበት ከፍተኛ ክፍተቶች አሉ። በተለይ ውቅሩ ቀያጭ ከመሆኑ አንፃር ስንወስደው አደጋው የከፋ ሊሆን ይችላል” ሲሉ ስጋታቸውን ማስቀመጣቸው ይታወሳል።

ከላይ ከሰፈሩት የግምገማ ውጤት እና የሙህራን አስተያየት በተለየ ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ የራሳቸውን ሃሳብ ይዘው ብቅ አሉ። ዶክተሩ እንደሚሉት፤ “የግንባር መሠረተ ሃሳብ የጋራ አጀንዳ ያላቸው፣ ግን የተለያዩ ፍላጎት ሊኖራቸው የሚችሉ የፖለቲካ ድርጅቶችና ቡድኖች (የግራ ዘመም፣ የመሀልና የሊብራል ቡድኖች ሊሆኑ ይችላሉ) የጋራን አጀንዳ ለማራመድና ውጤታማ እንዲሆን ለማድረግ ተመሳሳይ ርዕዮተ ዓለም ያላቸው ድርጅቶች፣ ወይም የተለያዩ ርዕዮተ ዓለም ያላቸው ድርጅቶች ሰፋ ያለ (Broad) አንድነት የሚፈጥሩበት አደረጃጀት ነው።

በርዕዮተ ዓለም ባይስማሙም የጋራ አጀንዳ ያላቸው፣ የጋራ ጠላት፣ ተቃዋሚ ወይም ተፃራሪ አቋም ያላቸው ኃይሎች በፈቃደኝነት ተስማምተው ገብተው አንድ የጋራ ፕሮግራም ነድፈው ለረጅም

የዶ/ር ነጋሶ ስንብት፣ የአንድነት ብሔራዊ ምክር ቤት ግምገማ፤ የኢንጅነር ግዛቸው አዲስ የቀያጭነት ጥሪ እና የመድረክ አንደምታዎች

አቶ ሃብታሙ አያሌው

ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ

ኢ/ር ግዛቸው ሽፈራው

ቀያጭነት (Eclecticism)

ሊዛመዱ የማይችሉ

ልዩ ልዩ ፍልስፍናዎች

ርዕዮተዓለሞችን

አስተሳሰቦችና የፓርቲ

መመሪያዎች መራርጦ

ለማስታረቅ የሚሞክር

አመለካከት በመሆኑ ነው

Page 6: ንደ3 - ethioforum.orgethioforum.org/wp-content/uploads/2014/01/sendek435.pdfሰንደቅ 9ኛ ዓመት ቁጥር 435 ረቡዕ ታህሳስ 30 2006 አታሚ፤ ብርሃንና

ሰንደቅ 9ኛ ዓመት ቁጥር 435 ረቡዕ ታህሳስ 30 20066 ፖለቲካ

ወደ ገፅ 13 ዞሯል

በዘሪሁን ሙሉጌታ

ባለፈው ቅዳሜ (ታህሳስ 26 ቀን 2006 ዓ.ም) በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት አንድ ስብሰባ ተካሂዶ ነበር። ስብሰባው በሀገሪቱ ሰራተኞች፣ አሰሪዎችና መንግስት መካከል ስላለው ግንኙነት ትኩረት ያደረገ ሲሆን፤ በዋናነትም የስብሰባው አዘጋጅ የኢትዮጵያ ሰራተኛ ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) ነበር።

በስብሰባው ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ጨምሮ ሚኒስትሮች፣ ኮሚሽነሮችና ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ጭምር የተገኙበት ነበር። በሰራተኛው በኩል ሰራተኛውን ይወክላሉ የተባሉ በየሴክተሩ የተቋቋሙ የሰራተኛ ማኅበራትና በመጠኑም ቢሆን የአሰሪዎች ተወካዮች ተገኝተው ነበር።

የመደራጀት መብት አለመከበር፣ የኑሮ ውድነትና

የታክስ መደራረብየዕለቱ ስብሰባ ተጀምሮ

የነበረው ሰራተኛውን የሚወክሉ የማኅበራት መሪዎች በዘርፍ በዘርፉ ተከፋፍለው በሰራተኛው የሚነሱ አሉ የተባሉ ጥያቄዎችን አንስተው ነበር። ጥያቄዎቹ በርካታ ቢሆኑም በዋናነት የሰራተኛው የመደራጀት መብት አለመከበር፣ የኑሮ ውድነት፣ በአሰሪና ሰራተኛ ወቅት የተፈጠሩ አለመግባባቶችን ለመፍታት አግባብ ያለው ፍርድ አለማግኘት፣ ሙስና የሚያጋልጡ ጠቋሚ ሰራተኞች ጥበቃ አለማድረግ ተደራራቢ የደመወዝ ገቢ ግብር ታክስና ሌሎች ጥያቄዎች ናቸው።

በሰራተኞቹ ተወካዮች በኩል በመረረ መንገድ ተደጋግሞ የተነሳው የሰራተኛው የመደራጀት መብት አለመከበሩ ብቻ ሳይሆን በአደባባይ ሕገ-መንግስታዊ መብታቸው መጣሱን ነው። ይህ የሰራተኛው የመደራጀት መብት ሲጣስም በመንግስት በኩል አርኪ ምላሽ አለመገኘቱ በስፋት አወያይቷል። ከዚሁ የመደራጀት መብት መጣስ ጎን ለጎን የኑሮ ውድነት ጥያቄውም የዕለቱን መድረክ የተቆጣጠረ ጉዳይ ነበር። “ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር” በሚል ተማፅኖ በተደጋጋሚ ጊዜአት ለጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ማስገንዘቢያ የሚመስሉ ጥያቄዎች ከሰራተኛው ተወካዮች ተወርውረዋል።

የሰራተኛው ተወካዮቹ በአሁኑ ወቅት በወር በሚከፈለው ደመወዝ እየኖረ አለመሆኑን አፅንኦት ሰጥተው ተናግረዋል። ኑሮ ከአቅም በላይ መሆኑንና ሰራተኛው የኑሮ ውድነቱን መሸከም እንዳልቻለ ገልፀዋል። ስለሆነም የኑሮ ውድነት ማሻሻያ ድጎማ እንዲደረግ ሲሉ ጠይቀዋል። በተመሳሳይ ሰራተኛው ላይ ተደራራቢ ታክስ መበራከቱ የሰራተኛውን ኑሮ ከድጡ ወደ ማጡ እየከተተው በመሆኑ የገቢ ግብርና የቫት ታክስ ማሻሻያ ጥያቄ አቅርበዋል።

በአሁኑ ወቅት ታማኝ ታክስ ከፋይ ሰራተኛው ቢሆንም በሰራተኛው ላይ የተጫነው ተደራራቢ ታክስ እንዲሻሻል በተደጋጋሚ ተጠይቋል። በተለይ በአንዳንድ የግል ድርጅቶችና በመንግስት የልማት ድርጅቶች አካባቢ “እጅግ በጣም አሳዛኝ” በሚል አገላለፅ የመደራጀት መብት መምከኑን የገለፁ የሰራተኛ ወኪሎች ነበሩ። ግዙፉ የብረታ ብረት ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽንን ጨምሮ በርካታ የልማት ድርጅቶች የሰራተኛው ሕገ-መንግስታዊ የመደራጀት መብት መጣሳቸውን ተናግረዋል። በእነዚህ በተጠቀሱ ተቋማት አዳዲስ የሰራተኛ ማኅበርን ለማቋቋም የሚጥሩ ሰራተኞችን ከስራ ማባረር የዕለት ተዕለት ተግባር መሆኑን ገልፀዋል። የሕገ-መንግስቱ አንቀጽ 31 እና 42 በአደባባይ መጣሳቸውን በይፋ ተናግረዋል። ከሀገሪቱ ሕገ-

መንግስት ባሻገር ሀገሪቱ ከየትኛውም የአፍሪካ ሀገር በፊት ግንባር ቀደም ሆና የፈረመቻቸው የዓለም የስራ ድርጅት (ILO) ድንጋጌዎች ጭምር እየተጣሱ፣ ሰራተኞች እንዳይደራጁ ከተደራጁም በኋላ ምክንያት እየተፈለገ ሥራ ፈት እንዲሆኑ፣ ሰራተኞቹና ቤተሰቦቻቸው ለረሃብ እንዲጋለጡ መደረጉን አስረድተዋል።

አንዳንድ የግል አሰሪዎችና የመንግስት ኃላፊዎች የሀገሪቱን ሕገ-መንግስት እየጣሱ ነው በማለት “ማን ሃይ ይበላቸው” ሲሉ የተማፀኑት የማኅበራት መሪዎቹ “በነፃ መደራጀት አቅቶናል” ሲሉ አምርረው ገልፀዋል። “ሕገ-መንግስቱን የሚያስከብረው ማነው?” ሲሉ መሰረታዊ ጥያቄ አንስተዋል።

ከመደራጀት መብት እና ከሙያ ደህንነት ጋር በተያያዘ ተገቢ ጥንቃቄ ባለመወሰዱ በኮንስትራክሽን አካባቢ በኬሚካል መመረዝን ጨምሮ በርካታ ጉዳቶች ስለሚደርሱ ሰራተኛው ለጊዜያዊና ዘላቂ ችግሮች እየተጋለጠ

እንደሆነም ተናግረዋል። ለሰው ልጅ ጤንነት አደገኛ የሆኑ መራዥ ኬሚካሎች የሰራተኛውን ዓይን እንዲያጣ፣ በቆዳው እና በመራቢያ አካላቱ ላይ ችግር እየተፈጠረ መሆኑን አብራርተዋል።

ከመብት ማስከበር አንፃር የሰራተኛ ማኅበር መሪዎች አለአግባብ ከስራ እንደሚሰናበቱና በፍርድ ቤት ተከራክረው ሲመለሱ የፍርድ ቤት ውሳኔ በመጣስ ለኢንዱስትሪ ሰላም ሲባል ካሳ ተከፍሎአቸው እንዲባረሩ ይደረጋል ብለዋል። በሁለት ወር ማለቅ ይገባው የነበረው የአሰሪና ሰራተኛ ክርክር እስከ አንድ ዓመት ተኩል ስለሚራዘም ፍትህ እየተዛባ መሆኑን ተናግረዋል። የመንግስት ሰራተኞችም እንደሌሎቹ ሰራተኞች የመደራጀት መብታቸው በሕገመንግስቱ መሠረት እንዲከበር ጠይቀዋል። በዚህ በኩል በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 377/96 የተቀመጠው ገደብ እንዲነሳም አሳስበዋል።

ሌላው ሀገሪቱ የአስተዳደር ሕግ (administrative law) የሌላት በመሆኑ በኃላፊዎችና በባለስልጣናት በርካታ ችግሮች መፈጠሩን የሰራተኞቹ ተወካዮች ሳይገልፁ አላለፉም። አንዳንድ የመንግስት የልማት ድርጅት ሰራተኞችን በሕገ-ወጥ መንገድ ከስራ ካሰናበቱ በኋላ ወደ ስራ ሲመለሱ ወጪውን የሚሸፍነው የልማት ድርጅቱ በመሆኑ ኃላፊዎች እንዳሻቸው ሰራተኛውን እያጉላሉ እንደሆነም ጠቅሰዋል።

አንዳንድ አሰሪዎች ሰራተኛውን የሚያስሩበት የራሳቸው እስር ቤት ያላቸው መሆኑን በምሬት የገለፁት የሰራተኛ ማኅበራት ወኪሎቹ፤ ከስራና ሰራተኛ አገናኝ ጋር በተያያዘ ከአረብ አገር በባሰ መልኩ በሰራተኞች እየተነገደ መሆኑንም አስረድተዋል። በዚህ ረገድ በአንዳንድ የውጪ ድርጅቶችና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ውስጥ የጉልበት ብዝበዛ እየተፈፀመ ነው ብለዋል። ከአንድ ሰራተኛ በነፍስ ወከፍ እስከ 4ሺህ ብር እየተቀበሉ በተጨባጭ ለሰራተኛው ጥቂት መቶ ብሮች በመክፈል ኢ-ሰብአዊ ድርጊት የሚፈፅሙ ደላላዎች ቢኖሩም መንግስት በቸልታ እየተመለከታቸው ነው ብለዋል። በጥቅሉ ከአሰሪና ሰራተኛ አገናኝ ጋር በተያያዘ ከአረብ አገር የባሰ የጉልበት ብዝበዛ እየተካሄደ እንደሆነ ነው ያስረዱት።

ሰራተኛውና መንግስት የተፋጠጡበት መድረክ

የጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዝዳንቱ አቶ ተገኔ ጌታነህ

በበኩላቸው በፍ/ቤቶች በኩል በአሰሪና ሰራተኛ መካከል

ስላለው የፍትህ መጓደል ምላሽ ሰጥተው ነበር። ችግሩን

ለመፍታት የፍርድ ቤቶችን ቁጥርና የዳኞችን ቁጥር

ለመጨመር እንደሚሰሩ ተናግረዋል

Page 7: ንደ3 - ethioforum.orgethioforum.org/wp-content/uploads/2014/01/sendek435.pdfሰንደቅ 9ኛ ዓመት ቁጥር 435 ረቡዕ ታህሳስ 30 2006 አታሚ፤ ብርሃንና

ሰንደቅ 9ኛ ዓመት ቁጥር 435 ረቡዕ ታህሳስ 30 2006 7

ምልከታ

ወቅታዊ

የጸደቀው የሕገመንግሥት አጣሪ ጉባዔ

የውሳኔ ኀሳብኅዳር 23 ቀን 2006 ዓ.ም

የአጣሪ ጉባዔው አባላት፤ አቶ ተገኔ ጌታነህ ሰብሳቢ አቶ መድሕን ኪሮስ ም/ሰብሳቢአቶ ጌታቸው አምባዬ አባል ወ/ሮ ደሚቱ ሐምቢሳ አባል አቶ መለሰ ዓለሙ አባል ዶ/ር ፋሲል ናሆም አባል ዶ/ር ሀሺም ተውፊቅ አባል አቶ ክፍለጽዮን ማሞ አባል

ያልተገኙ አባላት አቶ ሚሊዮን አሰፋ አቶ እሸቱ ወ/ሰማያት ወ/ሮ አይሮሪት መሐመድ

የሕገ መንግስት ትርጉም ጥያቄ አቅራቢ፤ ፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 15ኛ ወንጀል ችሎት፤

ይህ ጉዳይ ለሕገ መንግስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ ሊቀርብ የቻለው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በሙስና ወንጀል የተከሰሱት አቶ መላኩ ፋንታ ቻይ የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር በነበሩበት ጊዜ በሚኒስትር ማዕረግ ሆነው ሲሰሩ ስለቆዩ የተከሰሱበት ጉዳይ መታየት ያለበት በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ወይስ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በሚለው ጭብጥ ላይ የግራ ቀኙን ክርክር ካዳመጠ በኋላ ለጉዳዩ አግባብነት ያላቸው የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 25/88 አንቀጽ 8/1 እና የተሻሻለው የፀረ-ሙስና ልዩ የሥነ ሥርዓትና የማስረጃ ሕግ አዋጅ ቁጥር 434/97 አንቀጽ 7/1 የሕገ መንግስቱን አንቀጽ 20(6) እና አንቀጽ 25 ይጥሳሉ ወይስ አይጥሱም የሚለው ነጥብ ሕገ መንግስታዊ ትርጉም የሚያስፈልገው ነው በማለት በመዝገብ ቁጥር 141356 በ11/3/2006 በዋለው ችሎት ለጉባኤው ስለመራው ነው።

ለሕገ መንግስት ትርጉም ጥያቄ መነሻ ሆኖ ለቀረበው ጉዳይ የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 25/88 አንቀጽ 8/1 እንዲሁም የተሻሻለው የፀረ ሙስና ልዩ የሥነ ሥርዓትና የማስረጃ ሕግ አዋጅ ቁጥር 437/97 አንቀጽ 7/1 ከሕገ መንግስቱ አንቀጽ 20(6) እና አንቀጽ 25 አንፃር ማየቱ ተገቢ ይሆናል።

በኢፌዲሪ ሕገ መንግስት መሰረታዊ መብቶችና ነፃነቶችን በሚደነግገው ምዕራፍ ሦስት ስር በአንቀጽ 20 የተከሰሱ ሰዎችን መብት በተመለከተ በንዑስ ቁጥር 6 ሥር ክርክሩ በሚታይበት ፍርድ ቤት በተሰጠ ትዕዛዝ ወይም ፍርድ ላይ ሥልጣን ላለው ፍርድ ቤት ይግባኝ የማቅረብ መብት አላቸው ይላል።

በተመሳሳይ መልኩ ኢትዮጵያ በተቀበለቻቸው የዓለም አቀፍ የሲቪልና የፖለቲካ መብቶች ኮቬናንት እና የአፍሪካ የሰዎችና የህዝቦች መብቶች ቻርተር እንደ ቅደም ተከተላቸው በአንቀጽ 14(5) እና 7 ሥር ተከሰሰው የተፈረደባቸው ሰዎች ይግባኝ የማቅረብ መብት እንዳላቸው ደንግገዋል። የተከሰሱ ሰዎች ቢፈረድባቸው የይግባኝ መብት ያላቸው መሆኑ በሕገ መንግስት ምዕራፍ ሦስት ሥር ሲደነግግ መብቱ ከ1950ዎቹ መጀመሪያ ጀምሮ በአዋጅ ደረጃ ከነበረበት ከፍ ብሎ ሕገመንግስታዊ ዋስትና እንዲኖረው መደረጉን ስለሚያሳይ በሕገ መንግስቱ ከተቀመጠው ውጭ መብቱን በማስፈፀም ሂደት በማንኛውም አሰራር ሊጣስ ወይም ሊገፈፍ አይችልም።

የይግባኝ መብት እንደ መብት ሕገ መንግስታዊ ዕውቅና ማግኘቱ በራሱ የመብቱ አስፈላጊነት ምን እንደሆነ እንዲሁም መብቱን ለማስፈፀም የሚዘረጉ አሰራሮች የሚከተሉት አቅጣጫ ምን እንደሚመስል ያመላክታል። ጊዜያዊ አገልግሎት ያለው ትዕዛዝ ካልሆነ በቀር በአንድ ጉዳይ ላይ የመጀመሪያ ደረጃ ስልጣን ባለው ፍርድ ቤት በሚሰጥ ውሳኔ የመጨረሻ

የመጨረሻ ክፍል

በነብዩ ግርማ(ዳካር)

ባለፉት ሁለት ሳምንታት አፍሪካን ከዴሞክራሲ፣ ከመልካም አስተዳደር፣ ከሕግ የበላይነት እና ከመሳሰሉት ጋር አያይዘን ምጥን ቅኝት አደረግን። መነሻችን ባለፈው ህዳር ወር በሴኔጋል ዋና ከተማ በዳካር የተካሄደው አፍሪካዊ ምክክር ነበር። በአፍሪካ ህብረት የፖለቲካ ጉዳዮች ኮሚሽን ለሁለተኛ ጊዜ የተካሄደው ትልቅ መድረክ ከተወያየባቸው የተለዩ ሀሳቦች አንዱ ደግሞ “አጀንዳ 2063 (Agenda 2063)” ነበር። በዚህ ጽሁፍ የዚህን አጀንዳ ምንነት፣ ለምን እንዳስፈለገ እና በዚህ ወቅት ለምን እንደተነሳ እንቃኛለን።

“አጀንዳ - 2063” እንደ ርዕይም እንደ ድርጊት መርሀ-ግብርም የተቀመጠ አጀንዳ ነው። አፍሪካና አፍሪካውያን የጋራ እሴቶቻቸውን ለይተው በማውጣት፣ የመጪው ዘመን ዕጣ ፈንታቸውን በቅጡ በመገንዘብ የበለፀገች፣ የተባበረች አንዲት አፍሪካን ለመመስረት በጋራ መሥራት እንዲችሉ የተዘጋጀ የድርጊት መርሃ-ግብር ወይም አፍሪካዊ የተግባር ጥሪ ተደርጎ ተወስዷል። “አጀንዳ-2063”ን ዕቅድ አድርጐ ያስቀመጠው የአፍሪካ ኅብረት የፖለቲካ ጉዳዮች ኮሚሽን ነው።

የአፍሪካ አንድነት ድርጅት እና የአፍሪካ

ኅብረት ሃምሳኛ ዓመት የወርቅ ኢዮ ቤልዩ በዓል በተከበረበት ወቅት የአፍሪካ መሪዎች እና መንግሥታት ቃል የገቡባቸው የተለያዩ ጉዳዮች ነበሩ። የአፍሪካ ያለፉት ሃምሳ ዓመታት ስኬቶች፣ ተግዳሮቶችና ሌሎችም በአፍሪካዊው ክብረ-በዓል ወቅት በዝርዝር መታየታቸው አይዘነጋም። ከእስከዛሬው በመነሳትም መሪዎቹ በአፍሪካ ከመቼውም የበለጠ ልማት እና የቴክኖሎጂ ዕድገትን በአፍሪካ እውን ለማድረግ ቃል ገብተዋል። አፍሪካውያኑ መሪዎች የገቡትን ቃል መነሻ በማድረግም የአፍሪካ መጪ ዘመን በብርሃን የተንቆጠቆጠ እንዲሆን ያስችለናል ያሉትን ርዕይ እና ብንሰራባቸው ይጠቅሙናል፣ ለአፍሪካ ህዳሴም ዋልታና ማገር ሆነው ያገለግሉናል ያሏቸውን ስምንት ያህል ነጥቦች ዘርዝረው አስቀምጠው ነበር። “አጀንዳ-2063” አፍሪካ በመጪዎቹ ዘመናት ቀና በሆነ መንገድ ለመሄድ የሚያስችላትን የተጠና ስሌት አጥብቃ እንድትይዝ፤ እጅግ ፈጣን በሆነ የዓለም አውድ ውስጥ እንደመገኘቷም ለዕቅዶቿ ታማኝ፣ መስዋዕትነት ከፋይ በመሆን ለህዳሴዋ እንድትተጋ የሚያበቃት አጀንዳ ተደርጐ ነው በዳካሩ ምክክር ላይ የተሳለው።

“አጀንዳ-2063”ን በተመለከተ ጥያቄ የሚያስነሱ (የተነሳባቸውም) የተለያዩ ጉዳዮች አሉ። ከእነዚህ ጉዳዮች አንዱ “የሃምሳ ዓመት አጀንዳ ለምን አስፈለገ” የሚለው ይገኝበታል። የአፍሪካ ኅብረት የፖለቲካ ጉዳዮች ኮሚሽን ለዚህ ጥያቄ ምላሽ አለው።

1. አፍሪካ የሃምሳ ዓመት አጀንዳ ለምን ያስፈልጋታል?

በየትኛውም የልማት እና የብልፅግና የዕቅድ አድማስ ሃምሳ ዓመታት ረጅም ስለመሆናቸው ጥያቄ አያስነሳም። የቱንም ያህል ስትራቴጂክ ነን ብለን ብናስብ ሃምሳ ዓመታት ብዙ ናቸው። በርግጥ ይህን ዓይነቱን አማራጭ ከልብ እና ከቀልብ የታሰበበት ለአፍሪካ አስፈላጊ የሆነ አማራጭ ይሆን? በዓለምም ይሁን በአፍሪካ ደረጃ የሚስተዋለውን እጅግ ፈጣን፣ ትንፋሽ የማይሰጥ የለውጥ ሁነት ለተገነዘበ እንዲህ ያለ የረጅም ዘመን አጀንዳ መወጠን የቱን ያህል ተጨባጭ ነው? ከእንዲህ ዓይነቱ የረጅም ዘመን ዕቅድ አፍሪካ ምን ያህል እንደምትጠቀም እንዴት እርግጠኛ መሆን ይቻላል? እነዚህና ሌሎችም ጥያቄዎች ከሃምሳ ዓመታቱ ውጥን መመዘዛቸው አይቀርም (አልቀረምም)። የአፍሪካ ኅብረት ለእነዚህ ጥያቄዎች የሚያስቀምጧቸው ምላሾች አሉ።

በመጀመሪያ ደረጃ ኅብረቱ ሃምሳ ዓመታትን እንዲመርጥ መነሻ የሆነው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ነው። የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ከተመሠረተ ሃምሳ ዓመታትን ደፍኖ ሃምሳ አንደኛውን አሃዱ ብሏል። አፍሪካ ሰፊ የሆነ ልምድን፤ ስኬትንም ውድቀትንም ከተለያየ አንፃር ያስተናገደችባቸው ዓመታት ናቸው - ያለፉት ሃምሳ ዓመታት። እነዚህን ሃምሳ ዓመታት በአግባቡ መገምገም እና መረዳት ከተቻለ ቀጣዮቹን ሃምሳ ዓመታት በጥንቃቄ በመሸንሸን የሃምሳ ዓመታት ዕቅድን እና የድርጊት መርሃ-ግብርን

በማስቀመጥ ለመሥራት መነሳት ጠቃሚ እንደሆነ የአፍሪካ ኅብረት ያምናል። ለረጅም ዘመን የሚኖር ርዕይ ባለቤት መሆን፣ በዚህ ርዕይ መነሻነት የረጅም ጊዜ ዓላማ እና ግብን በመንደፍ ለመትጋት መነሳሳት ለአፍሪካ የሚጠቅማት እንጂ የሚያጥበረብራት እንደማይሆንም ኅብረቱ ያስረዳል።

“አጀንዳ-2063” ልክ ነው፤ የረጅም ዘመን አጀንዳ ነው። በረጅምነቱ ነው፤ “አጀንዳ-2063”ን የሚሰጠን። በረጅሙ ዕቅድ ውስጥ የ25 ዓመታት፣ የ10 ዓመታት፣ የ5 ዓመታት እና ሌሎችም አጫጭር የድርጊት መርሃ-ግብሮች ተዘርዝረው ስለተቀመጡ ጥቅል የሚመስለው “አጀንዳ-2063” ያን ያህል ውስብስብ እንዳልሆነ በመግለፅ የአፍሪካ ኅብረት “ሃሳብ አይግባችሁ!” በማለት ነው፤ አፍሪካ የሃምሳ ዓመታት አጀንዳ ለምን እንደሚያስፈልጋት የሚነሳውን ጥያቄ የሚመልሰው።

2. “አጀንዳ-2063” ለአፍሪካ በዚህ ሰዓት ለምን ያስፈልጋታል?

አፍሪካን የረጅም ዘመን የልማት እና የዕድገት ርዕይ፣ ዕቅድ፣ ዓላማና ግብ ባለቤት እንድትሆን የተጀመረው ይህ አዲስ ጥረት በተለያዩ ምክንያቶች ወቅታዊ እንደሆነ የአፍሪካ ኅብረት ያምናል። የተወሰኑትን ምክንያቶች እንመልከት፡-

የዓለማችን ዛሬያዊ ሁኔታ አንዱ ነው። የዓለማችን የለውጥ ሂደት እና ፍጥነት ከተዓምር በላይ መርቀቁ የረቀቀ ትጋትን ጠይቋል። ለዓለም

የአፍሪካ ዴሞክራሲና መልካም አስተደደር የዳካር ጉባዔ ቅኝት

ወደ ገፅ 20 ዞሯል

ወደ ገፅ 20 ዞሯል

ወደ ገፅ 20 ዞሯል

የፌዴሬሽን ምክርቤትን የከፈለው የአቶ መላኩ ፈንታ ጥያቄ

በፍሬው አበበ

የቀድሞ የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ መላኩ ፈንታ ከተከሰሱበት የሙስና ወንጀል ጋር በተያያዘ የተነሳው “በየትኛው ፍርድ ቤት ይዳኙ ጥያቄ” አከራካሪ ርዕሰ ጉዳዮችን ቆስቁሷል።

አቶ መላኩ ፈንታ ክሳቸው በፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 15ኛ ወንጀል ችሎት በመታየት ላይ ሲሆን የተነሳው ክርክር በአጭሩ ሚኒስትር በመሆኔ ጉዳዬ ሊታይ የሚገባው በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ነው እንጂ በከፍተኛው ፍርድ ቤት አይደለም የሚል ጭብጥን የያዘ ነው። ለዚህም ክርክራቸው የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 25/88 አንቀጽ 8(1) እና የተሻሻለው የጸረ ሙስና ልዩ የስነስርዓትና ማስረጃ አዋጅ ቁጥር 434/97 አንቀጽ 7(1) ድንጋጌዎችን ጠቅሰዋል። ጉዳዩ የቀረበለት ፍርድ ቤት በአዋጅ ቁጥር 25/88 እና በአዋጅ ቁጥር 434/97 መሰረት ሚኒስትሮችን ጨምሮ የፌዴራል መንግስቱ ባለስልጣናት በሥራ ኃላፊነታቸው ምክንያት ተጠያቂ በሚሆኑባቸው ወንጀሎች(ሙስናን ጨምሮ) በማናቸውም የወንጀል ጉዳዮች የፌዴራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የመጀመሪያ ደረጃ የሥረ ነገር ክርክር ማስኬጃ እንዲሆን ስልጣን የተሰጠው መሆኑ በግልጽ መደንገጉን አረጋግጧል። ሆኖም የእነዚህ አዋጆች አንቀጾች ሕገመንግስታዊ ናቸው ወይስ አይደሉም የሚለው የተጣራ ትርጉም ያስፈልገዋል በሚል ጉዳዩን ለፌዴሬሽን ምክርቤት መርቶታል።

በምክርቤቱ ሥር የሚገኘውና የተለያዩ ከፍተኛ የሕግ ዕውቀት አላቸው ተብሎ የሚገመቱ የህግ ባለሙያዎች፣የጠ/ፍርድ ቤት ከፍተኛ አመራሮችና ታዋቂ

ለዚህ ጉዳይ ሲባል

ያነጋገርናቸው አንድ የሕግ

ባለሙያ እንዳሉት እንዲህ

ዓይነቱ ውሳኔ ዜጎች በሕግና

በስርዓት ላይ ያላቸውን

መተማመን በእጅጉ የሚጎዳ

ነው። በኳስ ጨዋታ ሕግ ፍጹም

ቅጣት ክልል ውስጥ መጠለፍ

የፍጹም ቅጣት ምት ቅጣት

እንደሚያስከትል ይታወቃልአቶ መላኩ ፈንታ

Page 8: ንደ3 - ethioforum.orgethioforum.org/wp-content/uploads/2014/01/sendek435.pdfሰንደቅ 9ኛ ዓመት ቁጥር 435 ረቡዕ ታህሳስ 30 2006 አታሚ፤ ብርሃንና

ሰንደቅ 9ኛ ዓመት ቁጥር 435 ረቡዕ ታህሳስ 30 20068

በፀጋው መላኩ

የኢትዮጵያ ተስማሚነትና ምዘና ድርጅት ያለውን አሰራር በተመለከተ ለተለያዩ መገናኛ ብዙኃንና ለማስታወቂያ ድርጅት ኃላፊዎች ማብራሪያ ሰጥቷል። ያለውንም አጠቃላይ

አሰራር በተመለከተ ድርጅቱ የሚሰራባቸውን ላብራቶሪዎች በማስጎብኘት በባለሙያ የተደገፈ ገለፃም ተደርጓል። የኢትዮጵያ ተስማሚነትና ምዘና ድርጅት ቀደም ባለው አሰራር መሠረት በኢትዮጵያ ጥራትና ደረጃዎች ባለሥልጣን በአንድ ላይ ተጠቃሎ ስራው ሲከናወንበት የቆየበት ሁኔታ ነበር። ሆኖም አሰራሩን ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያለው አሰራር ከማድረግ አንጻር የቀድሞው ባለሥልጣን መስሪያ ቤት ህልውና አክትሞ የተለያዩ ድርጅቶች በሕግ ተቋቁመው ወደ ስራ እንዲገቡ ተደርጓል። የባለሥልጣንን መስሪያቤቱ ህልውና ማክተም ተከትሎ የተቋቋሙት ድርጅቶች የሥራ ድርሻቸውም ሆነ ኃላፊነታቸው ይለያይ እንጂ ከውጤት አንጻር ሲታይ የምርት ወይም የአገልግሎት ጥራት እንዲጠበቅ የሚሰሩ ናቸው። ለምሳሌ የኢትዮጵያ ደረጃዎች ኤጀንሲ ከተለያዩ የሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር የተለያዩ ምርቶችን ደረጃ በማውጣት በብሔራዊ የደረጃዎች ምክር ቤት አቅርቦ ያፀድቃል። የሚወጡት ደረጃዎች አስገዳጅ የሆኑ ወይም ያልሆኑ ተብለው የሚከፈሉ ናቸው። ኤጀንሲው የምርትና አገልግሎቶችን ደረጃ ከማፅደቅና ይፋ ከማድረግ ውጪ የትኛውም አካል የወጣውን ደረጃ በአስገዳጅነት እንዲከተል የማድረግ ስልጣን የለውም። በአዲሱ አሰራር መሰረት አስገዳጅ በሆኑ ምርቶች ላይ የማስፈፀሙን ስራ በዋነኝነት የሚያከናውነው ንግድ ሚኒስቴር ነው።

አንድ ምርት ወይም አገልግሎት ደረጃ ከወጣለት በኋላ ቀደም ሲል ደረጃዎች ኤጀንሲ ባወጣው የኢትዮጵያ ደረጃዎች መሰረት ተስማሚነቱ ተፈትሾ የሚረጋገጥበት ሁኔታ ይኖራል። ምርቶቹ፣ አገልግሎቶቹ፣ ቁሶቹ እንዲሁም የአሰራር ስርዓቶቹ ተፈትሸው የሚረጋገጡት ደግሞ በኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት ላብራቶሪዎች አማካኝነት ነው። በዕለቱ ከተደረገው ገለፃ መረዳት እንደተቻለው በአሁኑ ሰዓት ድርጅቱ የሚሰጣቸው አገልግሎቶች የላብራቶሪ ፍተሻ አገልግሎት፣ የኢንስፔክሽን አገልግሎት እንዲሁም የሰርተፊኬሽን አገልግሎት በመባል የሚታወቁ ናቸው። በላብራቶሪ የፍተሻ አገልግሎቶች በአሁኑ ሰዓት በዋናው የፍተሻ ስራዎቹን እያከናወነ ያለው ለኬሚካል፣ ለኤሌክትሪካል፣ ለማይክሮባዮሎጂ፣ ለመካኒካል፣ ለጨርቃጨርቅና ቆዳ እንደዚሁም ለጨረራ ነው። አብዛኞቹ ላብራቶሪዎች የጉብኝቱ አካል የነበሩ ሲሆን በእለቱም ላብራቶሪዎቹ በምን መልኩ ፍተሻቸውን እንደሚያከናውኑ ከባለሙያዎቹ ገለፃ ጋር መመልከት ችለናል። ከላብራቶሪዎቹ መካከል አንዱ የሆነው ኤሌክትሪካል ላብራቶሪ በተለያዩ ከውጪ በሚመጡና ሀገር ውስጥ በሚገቡ ምርቶች ላይ ፍተሻ በማድረግ ከኢትዮጵያ ደረጃዎች ጋር ተስማሚ መሆኑን ያረጋግጣል። ለምሳሌ የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ ሽቦዎች (cables) ከሚደረጉባቸው ፍተሻዎች መካከል አንደኛው የሽቦው የስሪት ግብዓት የጥራት ደረጃን የሚመለከተው ይገኝበታል። ከላብራቶሪ ባለሙያዎቹ ገለፃ መረዳት እንደቻልነው አንድ የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ ሽቦ ከመዳብ (Copper) የሚሰራ ሲሆን በመዳቡ ውስጥ ብረት (Iron) እየተቀላቀለ የሚመረትበት ሁኔታ አለ። መዳቡ ኤሌክትሪክን በቀላሉ የሚያስተላልፍ ሲሆን በአንፃሩ ከብረት ጋር በሚቀላቀልበት ወቅት ደግሞ ኤሌክትሪክ የመቋቋም አቅሙ (Resistance) መጠን ከፍ ስለሚል ሽቦው ኤሌክትሪክ በሚያስተላልፍበት ወቅት በቀላሉ የመጋል ሁኔታ የሚታይበት መሆኑን ከገለፃው መረዳት ችለናል። ከዚሁ ጋር በተያያዘም በአጠቃቀም ችግር የሚፈጠረው የኤሌክትሪክ እቃዎች መቃጠልና መጎዳት እንደተጠበቀ ሆኖ በተለይ የማከፋፈያ ቁሶችና የመሳሰሉት እቃዎች ደረጃውን ባልጠበቁ

ግብዓቶች በሚሰሩበት ወቅት ከፍተኛ ግለትን በመፍጠር ኤሌክትሪክን የሚያባክኑ ብሎም የአገልግሎት ጊዜያቸውም አጭር እንደሚሆን ባለሙያዎቹ ገልጸዋል።

ይህም በመሆኑ ድርጅቱ በላብራቶሪው አማካኝነት በሀገር ውስጥ የሚመረቱትንም ሆነ ከውጪ የሚመጡትን የኤሌክትሪክ ሽቦዎች በተቀመጠላቸው መስፈርት መሰረት ፈትሾ የኢትዮጵያ ደረጃዎችን መሟላት አለመሟላታቸውን ያረጋግጣል። በሽቦ ምርመራው ወቅት የኤሌክትሪክ ሽቦው የጥራት ደረጃ (purity) ብቻ ሳይሆን የውፍረቱ መጠንም የሚለካበት ሁኔታ አለ። የሽቦው የውፍረት መጠን በደረጃ የተቀመጠለት ሲሆን በፍተሻ ወቅትም የውፍረቱ መጠን ከደረጃ በታች ሆኖ የሚገኝበት ሁኔታም መኖሩ ታውቋል። ይህ ብቻ ሳይሆን የሽቦ መሸፈኛ ፕላስቲኮች የውፍረት ደረጃም አንዱ የፍተሻው አካል ነው። የኤሌክትሪክ ገመዶች አስገዳጅ ደረጃ ከወጣላቸው ምርቶች ውስጥ የሚመደብ በመሆኑ ደረጃውን በላብራቶሪ ፍተሻው ማሟላት አለመቻል ምርቱ ወደገበያ እንዳይገባ የሚያደርግ ይሆናል። ቀደም ሲል በርካታ የኤሌክትሪክ ሽቦዎች (cables) ከውጪ ይገቡ የነበረ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት ግን እንደ ኤልሲዊዲ እና ዩሮ ኬብልን የመሰሉ የኤሌክትሪክ ገመዶች በሀገር በስፋት እየተመረቱ ነው።

የተስማሚነትና ምዘና ድርጅት የቀረቡለትን ምርቶች ከፈተሸ በኋላ የፍተሻ ውጤት ሪፖርቱን እንዲፈተሽ ላቀረበው አካል መልሶ ያስረክባል። እንደባለሙያዎቹ ገለፃ በፍተሻው ሂደት የፍተሻውን ውጤት ብቻ የሚፈልጉ አሉ። እንደዚሁም ሰርተፍኬት የሚፈልጉም አሉ። የጥራት መመዘኛ ውጤቶችን ብቻ ለሚፈልጉ ከፍተሻ በኋላ ውጤቱ የሚሰጣቸው ሲሆን ሰርተፍኬት ለሚፈልጉ ደግሞ ሰርተፍኬቱ ድርጅቱ በቀጣይነት ጥራት ያለው ማምረት ይችላል በሚል ለጠያቂው ድርጅት ወይንም ኩባንያ የሚሰጥ በመሆኑ ከምርት ፍተሻው በተጨማሪ ፍተሻው በየሶስት ወሩ መደበኛ የጥራት የኦዲት ስራም ይካሄድበታል። የፍተሻ ስራው ድንገተኛ ፍተሻና (Surprise visit) ጭምር የሚያካትት መሆኑን ከባለሙያዎች ገለፃ

መረዳት ችለናል።የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት

በላብራቶሪ ፍተሻው ከግንባታ ግብዓቶች ጋር በተያያዘ የኤሌክትሪክ ገመዶችን ብቻ ሳይሆን ሲሚኒቶና ሲሚንቶ ነክ ምርቶችን፣ ብሎኬቶችን፣ የጣራ ንጣፎችን፣ ጡቦችን እንደዚሁም የሸክላ ብሎኬቶችንና የመሳሰሉትንም ግብዓቶችም ከተቀመጠላቸው የጥራት ደረጃ አንፃር ይፈትሻል። በአሁኑ ሰዓት መንግስት በስፋት የቤቶችና ግንባታ እያከናወነ ሲሆን ከቤቶቹ የግንባታ ግብዓት የጥራት ደረጃ ጋር በተያያዘ ከፍተኛ ወቀሳዎች ይደመጣሉ። ለችግሩም መፍትሄ ለማፈላለግ የቤቶች ልማት ኤጀንሲ የቤቶቹን ግብዓት የጥራት ደረጃ አስፈትሾ ለማረጋገጥ ሙሉ ኃላፊነቱ ለኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ያስረከበ መሆኑን ባለሙያዎቹ ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት ተጠሪነቱ ለሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሆኖ በመንግስት የልማት ድርጅትነት የተቋቋመ በመሆኑ ገቢው በሚሰጠው የሰርተፍኬሽን፣ የኢንስፔክሽንና የላብራቶሪ ፍተሻ አገልግሎት ላይ የተመሰረተ ነው። ሀገራት በተለይም ያደጉት ሀገራት ምርቶች ከጤንነት፣ ከአካባቢ ደህንነት ተስማሚነት አንጻር ስለሚመለከቱ በየጊዜው በምርቶች የጥራት ሁኔታ ላይ ከባድ ቁጥጥር ያደርጋሉ። ላኪዎች ምርቶቻቸውን ወደተለያዩ ሀገራት ሲልኩ ከሁሉም በፊት የጥራት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ማግኘት ይጠበቅባቸዋል። ይህንንም የጥራት ማረጋገጫ የግድ ገለልተኛ የሆነ አካል መሰጠት ይኖርበታል። የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት የምርት ጥራቶቹን ደረጃ ከመስጠበቅ አንጻር ፋብሪካዎቹን ከመገምገም ባለፈ ምርቶቹን በማምረት ሂደት ውስጥ የሚያልፉ ጥሬ እቃዎንና ግብዓቶችን ናሙና በመውሰድ የኢንስፔክሽን ስራን ያካሂዳል።

ፍተሻ ከሚደረግባቸው የተለያዩ ምርቶች መካከል የቢራና ልዩ ልዩ የአልኮል ምርቶች የምግብ ዓይነቶችና ማርም ይገኝበታል። የቢራና ልዩ ልዩ የአልኮል ምርቶችን በተመለከተ ፋብረካው ካመረተ በኋላ በጠርሙስ ላይ የሚለጥፈው የአልኮል መጠን አልኮሉ በውስጡ ከያዘው መጠን ጋር በንፅፅር ይታያል።n

በኢትዮጵያ የምርት ጥራት መፈተሻ የላብራቶሪ ሁኔታ

Page 9: ንደ3 - ethioforum.orgethioforum.org/wp-content/uploads/2014/01/sendek435.pdfሰንደቅ 9ኛ ዓመት ቁጥር 435 ረቡዕ ታህሳስ 30 2006 አታሚ፤ ብርሃንና

ሰንደቅ 9ኛ ዓመት ቁጥር 435 ረቡዕ ታህሳስ 30 2006 9

በበርካታ የአፍሪካ ሀገራት የመረጃ መረቦች ላይ ተከታታይ ጥቃቶች እየደረሱ ሲሆን በዚህም በርካታ ሀገራት የደህንነትና የኢኮኖሚ ሁኔታ አደጋ ላይ እየወደቀ መሆኑን ከሰሞኑ የወጡ ዘገባዎች ያመለክታሉ። በተለይ ከገንዘብ ተቋማት ጋር በተያያዘ እንደ ኬኒያና ታዛኒያ ያሉ ሀገራት የፋይናንስ ተቋማት ካልታወቁ አካባቢዎች በደረሰባቸው ጥቃት ከፍተኛ ገንዘብ የተዘረፉ ሲሆን ኬኒያ የደረሰባትን ጥቃት ተከትሎ ችግሩን ለመቋቋም በ2013 እስከ 2 ቢሊዮን ሸልንግ የሚጠጋ ገንዘብ ጥቅም ላይ አውላለች። ታንዛንያም የገጠማትን የሳይበር ጥቃት ለመቋቋም ከዚህ ቀደም በጥፋቱ ውስጥ የተገኙ አካላትን የሚቀጣ ጠበቅ ያለ ህግን

ብትተገብርም ውጤቱ ግን የተፈለገው ያህል አልሆነም። እንደታዛንያ ባለሥልጣናት ከሆነ ችግሩ ድንበር ዘለል በመሆኑ አንድ ሀገር በግሉ የሚያወጣቸው ህጎችም ሆኑ የሚያካሄደው ዘመቻ ብቻውን የተፈለገውን ውጤት ሊያመጣ አይችልም።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ የአፍሪካ ሀገራት በቀጣይ በሳይበር ጥቃት ደህንታቸው እንዳይወድቅ ብሎም የፋይናንስ ዝርፊያ እንዳይካሄድባቸው በጋራ መስራት ያለባቸው መሆኑ ተመልክቷል። በቅርቡ በጥር ወር በሚካሄደው የአፍሪካ ህብረት አባል ሀገራት ስብሰባ ላይ የሳይበር ጥቃትን በተመለከተ ሰፊ ውይይት ይካሄድበታል ተብሎ ይጠበቃል።n

ሰንደቅ፡- ይህ ዘመቻ ለምን ያህል ጊዜ ነው የሚቆየው?ሚስተር ፍራንሲስ፡- ይህ የረዥሙ ጉዞ መጀመሪያ እና አንድ አካል ነው። ይህ ዘመቻ እኛ ኢትዮጵያ ውስጥ እስካለን ድረስ በሀገሪቱ ያለው የመኪና አደጋ እንዲቀንስ የምንሰራው ቀጣይ ስራ ነው። የስራችን አንዱ አካል አድርገን እናየዋለን።

ሰንደቅ፡- በሌሎች የእናተ ኤንቨስትመንቶች ባሉባቸው ሀገሮች ዜጎች ከአልኮል መጠጥ ጋር በተገናኘ ጠጥተው በማሽከርከር ለጉዳትና ለሞት እንዳይዳረጉ የሰራችሁት ተመሳሳይ ስራ አለ?ሚስተር ፍራንሲስ፡- ይሄንን አይነት ስራና ዘመቻ በተመለከተ በዓለም አቀፍ ደረጃ ወደ አንድ መቶ ሰማኒያ በሚጠጉ ሀገራት መሰል ስራን ያከናወንን ሲሆን በአፍሪካ ደግሞ ከአርባ በሚበልጡ ሀገራት ተመሳሳይ ልምድ አለን። ይህንን ስራ የምናከናውነው ብቻችንን ሳይሆን ከቢዝነስ አካላት ጋር እንደዚሁም ከመንግስታት ጋር በመተባበር ነው።

ሰንደቅ፡- አሁን በኢትዮጵያ እንደጀመራችሁት አይነት ሰዎች አልኮል ጠጥተው እንዳያሽከረክሩ የሚያደርገው የግንዛቤ መፍጠሪያ ዘመቻ በሌሎች መሰል ሀገራት የነበረው ስኬታማነት ምን ይመስላል?ሚስተር ፍራንሲስ፡- በሌሎች ሀገራት ይሄንን ሥራ በመስራቱ ረገድ ውጤታማ ነን ማለት እችላለሁ። እንደውም በአንዳንድ ሀገራት በነበሩን የግንዛቤ ማስጨበጫ ዘመቻዎች እኛም ሆነ አብረውን የሚሰሩት አገሮቻችን በነበረን ቁርጠኝነት በዚህ ዙሪያ የነበሩ የህግና የደንብ ክፍተቶቹን መንግስታት እንዳያስተካክሉ ማድረግ ችለናል። ጠጥቶ ማሽከርከርንም በተመለከተ ሊያስከትለው የሚችለው ጉዳት ሰዎች አስተሳሰብ ውስጥ መሰረታዊ ለውጥ እንዲመጣ አድርገናል።

ሰንደቅ፡- በኢትዮጵያ ውስጥ ይሄንን የግንዛቤ ማስጨበጫ ፕሮግራም ለማስጀመር ለምን ያህል ጊዜ

ሜታ እና “ሹምሹፌር”ሜታ አቦ ቢራ እና ዲያጆ ከኢትዮጵያ መንገድ ትራንስፖርት ባለስልጣንና ከሌሎች አጋሮች ጋር በመተባበር በኢትዮጵያ ያለውን አስከፊ የመኪና አደጋ ለመቀነስ ዘመቻ የጀመሩ መሆናቸውን ከሰሞኑ አስታውቀዋል። ዘመቻው ሰዎች ጠጥተው እንዳይነዱና ለአደጋ ብሎም ለሞት እንዳይዳረጉ ግንዛቤን ለመፍጠር የሚያስችል ነው። “ሹሙ ሹፌር” የሚል ስያሜ የተሰጠው ይሄው የግንዛቤ ማስጨበጫ ዘመቻ አሽከርካሪዎች ከመጠጣታቸው በፊት ምንም አይነት አልኮል መጠጥ ሳይጠጣ ሊያሽከርክርላቸው የሚችል ሰው እንዲያዘጋጁ ማድረግ አላማን የሰነቀ ነው። ይሄው ፕሮግራም ባለፈው አርብ በሂልተን ሆቴል ይፋ በሆነበት ወቅት በርካታ ታዋቂ ሰዎች በአካል በመገኘት በተዘጋጀው የቃል መግቢያና ቢልቦርድ ላይ ፊርማቸውን አኑረዋል። ፊርማቸውን ካኖሩት ታዋቂ ሰዎች መካከል አርቲስት ስለሺ ደምሴ(ጋሼ አበራ ሞላ)፣ ድምጻዊ ዮሴፍ ገብሬ (ጆሲ)፣ የጃኖ ባንድ አባላት፣ አትሌት ኃይሌ ገብረስላሴ፣ እንዲሁም የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ወይዘሮ ሙሉ ሰለሞን ይገኙበታል። በእለቱ የመንግስት ባለስልጣናትና ሚኒስትሮችም ተገኝተው ነበር። የግንዛቤ መፍጠር ዘመቻውን አጠቃላይ ይዘት በተመለከተ አጠር ያለ ማብራሪያ እንዲሰጡን ከሜታ አቦ አክስዮን ማኅበር ማኔጂግ ዳይሬክተር ከሚስተር ፍራሲስ አግቦንላሆሮ ጋር ያደረግነውን የደቂቃዎች ቆይታ እንደሚከተለው አዘጋጅተን አቅርበነዋል።

አፍሪካ በሳይበር ጥቃት ከፍተኛ ጉዳት እየደረሰባት ነው

ራሳችሁን ስታዘጋጁ ቆይታችኋል?ሚስተር ፍራንሲስ፡- ይህ ፕሮግራም የዋናው ስራችን አንድ አካል ነው። በኃላፊነት ስሜት መጠጣት የሚለው እንቅስቃሴ ከሁለት ዓመት በፊት ነው የተጀመረው። አሁን በቀጣይም ስራውን እያሰፋነው እንሄዳለን የሚል እምነት አለኝ።

ሰንደቅ፡- በዚህ ዘመቻችሁ “ሹም ሹፌር” የሚለውን መሪ ቃል ስትጠቀሙ ምን ለማለት ፈልጋችሁ ነው?ሚስተር ፍራንሲስ፡- “ሹም ሹፌር” ስንል ሰዎች በማንኛውም አጋጣሚ ከጓደኛቸው እንዲሁም ከቤተሰቦቻቸው ጋር በመኪና ለመዝናናት የሚወጡባቸው አጋጣሚዎች ይኖራሉ። በዚህ ወቅት ለመዝናናት የተለያዩ አልኮሎችን ሊጎነጩ ይችላሉ። ይህ ከመሆኑ በፊት ግን አንድ የመጠጡ አካል ያልሆነ የመኪና አሽከርካሪ መኖር አለበት። ይህንን ነው “ሹም ሹፌር” የምንለው። ይህ በሚሆንበት ወቅት በመጠጥ ሊከተል የሚችለውን የመኪና አደጋ በከፍተኛ ደረጃ መቀነስ ይቻላል። አልኮል ሰዎች ሊዝናኑበት የሚገባ እንጂ ከመኪና አደጋ ጋር በተያያዘ ለአካል ጉዳት ብሎም ለሞት

እኛ በአልኮል መጠጥ ማምረት ሂደት ውስጥ

ረዥም እድሜን ያስቆጠርንና በበርካታ

የአለማችን ሀገራት ብሎም በአፍሪካ ምድር

በሰፊ ኢንቬስትመንት የተሰማራን ነን። እኛ

ዋናው ዓላማችን ሰዎች የትም ሆነው፤ መቼም

ቢሆን በህይወት ዘና እንዲሉ ነው

የሚዳርጉበት መዝናኛ መሆን አይገባውም።

ሰንደቅ፡- አንድ አልኮል መጠጥ አምራች ኩባንያ እንደዚህ አይነት ዘመቻ ሲጀምር ለብዙዎች ግራ መጋባትን የሚፈጥር ነውና ይህንን በምን መልኩ ማስረዳት ይቻላል?ሚስተር ፍራንሲስ፡- እኛ በአልኮል መጠጥ ማምረት ሂደት ውስጥ ረዥም እድሜን ያስቆጠርንና በበርካታ የአለማችን ሀገራት ብሎም በአፍሪካ ምድር በሰፊ ኢንቬስትመንት የተሰማራን ነን። እኛ ዋናው ዓላማችን ሰዎች የትም ሆነው፤ መቼም ቢሆን በህይወት ዘና እንዲሉ ነው። ይህንን ስንል ግን በኃላፊነት መሆን አለበት። አልኮል ሰዎች ሊዝናኑበት የሚገባ ምርት ነው። ነገር ግን ፈፅሞ አግባብነት በሌለው ሁኔታ ጥቅም ላይ መዋል የለበትም። እኛ ሰዎች በኃላፊነት ስሜት ይጠጡ ስንል የቢዝነሳችን አንዱና ዋኛው ስትራቴጂ እንደሆነ መታወቅ አለበት። ቢዝነሱም የሚኖረው እኮ በመጀመሪያ ሰዎች ሲኖሩ ነው። ምንም ነገር ሲበዛና ከአግባቡ ውጪ ጥቅም ላይ ሲውል ጉዳት ያስከትላል ምግብ እንኳን ቢሆን ማለቴ ነው።n

Page 10: ንደ3 - ethioforum.orgethioforum.org/wp-content/uploads/2014/01/sendek435.pdfሰንደቅ 9ኛ ዓመት ቁጥር 435 ረቡዕ ታህሳስ 30 2006 አታሚ፤ ብርሃንና

ሰንደቅ 9ኛ ዓመት ቁጥር 435 ረቡዕ ታህሳስ 30 200610

በአሸናፊ ደምሴ

“ላፎንቴን” በሚል የጋራ ስያሜያቸው ከሚታወቁት ዝነኛ ድምጻዊያን አንዱ ነው፤ ታደለ ሮባ። ትውልዱ ሀገረ ማርያም የሆነው ታደለ ሮባ ወጣትነቱን በአዲስ አበባ አሳልፏል። በዘመኑም ከቅርብ ጓደኛው ብርሃኑ ተዘራ ጋር በጋራ በመሆን ላፎንቴን የተሰኘ ህብረት ፈጥረው የሌሎችን ሰዎች ዘፈኖች በመጫወት ጀምረዋል።

በዚህም መነሻነት “ተው አምላኬ” የተሰኘ የመጀመሪያ አልበማቸውን ለአድማጭ ጆሮ ካደረሱ በኋላ የታዋቂ ድምፃውያንን ዘፈኖች በራሳቸው ስልት ይዘው በመቅረባቸው ይሁንታን ሲያገኙ፤ በተከታታይ “እንዲች- እንዲች” ከዚያም “እጅ አንሰጥም” የተሰኙ አልበሞቻቸውን አበርክተዋል። በቅርቡም የመጨረሻ የጋራ ስራቸው የሆነው “ጓደኛ (ባቡሬ)” የተሰኘውን አልበም ካወጡ በኋላ ጆሮ ገብ የሆኑ ነጠላ ዜማዎችን በተናጠልና በጋራ እንካችሁ ማለታቸው ይታወሳል።

እነሆ በገና በዓል ዋዜማ ደግሞ ድምፃዊ ታደለ ሮባ ከአምስት ዓመታት ላላነሰ ጊዜ ደክሜበታለሁ ያለውን አዲስ አልበም “ምስጋና” ሲል ሳይሞት አስደምጦናል። “አስቤው አይደለም ለገና ያወጣሁት” የሚለው ድምጻዊ ታደለ ሮባ ከዛሬ ነገ ሲባል ድንገት የሆነ ነገር መሆኑን ባሳለፍነው አርብ አልበሙን አስመልክቶ በቤልቪው ሆቴል በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ወቅት ተናግሯል። የአልበሙን መጠሪያ “ምስጋና” ያለው ለአምላኩ ስለመሆኑ የገለፀው ድምጻዊው፤ ሁሉም በሃይማኖቱ የሚያመሰግነው አምላኩን እንደሆነ እያሰበ ያደምጥልኛል ሲል ጋብዟል። ይህን አልበም ዳሸን ቢራ በ1.3 ሚሊዮን ብር በቀዳሚነት ስፖንሰር ማድረጉንም ለማወቅ ተችሏል። ከዚህም ሌላ የህገ-ወጥ ቅጂውን ለመከላከል እንዲረዳ ሰልፍ ሚዲያ “ኢንሀንስ ሲዲ” የተሰኘ ቴክኖሎጂን ተጠቅሞበታል። አልበሙን ላላ ፕሮዳክሽን ሲያጠናቅቀው የውጪ ሀገር ስርጭቱን ደግሞ “ቢግ-ዲ” እንደሚሰራው ታውቋል።

በ“ምስጋና” አልበም ላይ እነማን ተሳተፉ?

በበርካቶች ዘንድ ተወዳጅነትን አትርፎ ከመድረክ ተሰውሮ የቆየው ኤሊያስ መልካ በ“ምስጋና” አልበም ተመልሷል፡፤ ከእርሱ በተጨማሪም ቅንብሩን ካሙዙ ካሳ ሰርቶታል። በግጥምና ዜማ በኩል አንድ ዘፈንም ቢሆን ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ)ን ጨምሮ በርካታ ወጣት ባለሙያዎች ተሳትፈውበታል። አበጋዝ ክብረወርቅ ሺዎታ የመጨረሻዋን ዘፈን ቅንብር ከመስራቱም በተጨማሪ የአልበሙን ሙሉ ማስተር የሰራው እርሱ እንደሆነ ታውቋል።

በ“ምስጋና” አልበም ላይ አብዛኞቹ የሞያ አጋሮቹ ሀሳባቸውን ሰጥተውበታል። የታደለ ሮባን ለየት ያለ የሙዚቃ አቀራረብና ለዘመናዊ የሙዚቃ ስራ ያበረከተውን አስተዋፅኦ አስመልክቶ በርካታ ድምጻዊያን አስተያየታቸውን ሲሰጡ የሚያሳይ ፊልም ተካቶ ከኦርጂናል ስራው ጋር መቅረቡ ለስራው ምን ያህል ትኩረት እንደተሰጠ ያመለከተ ነው ማለት ይቻላል። በ“ምስጋና” አልበም ዙሪያ የግል አስተያየታቸውና አድናቆታቸውን ከገለፁት እውቆች መካከል፤ ስለሺ ደምሴ (ጋሽ አበራ ሞላ) ፣ ጆኒ ራጋ፣ ጆሲ ኢን ዘ ሀውስ፣ ታደለ ገመቹና ማዲንጎ አፈወርቅ ይጠቀሳሉ።

በአልበሙ ምን የተለየ ነገር ተሰርቷል?

በእርግጥም እንደዚህኛው ይፋ ባይሆንም “ሰልፍ ሚዲያ” በተሰኘ ድርጅት ስር የኮፒ ራይትን

ስርቆት በመጠኑም ቢሆን ሊገታ የሚችል “ኢንሀንስ ሲዲ” ቴክኖሎጂ መተዋወቁን ሰምተናል። ከዚያ ቀደም ድምፃዊ ፀሃዬ ዮሃንስ እና ጂሲ ኢን ዘ-ሀውስ ይህን ቴክኖሎጂ የተጠቀሙ ሲሆን ድምጻዊ ታደለ ሮባ ሶስተኛውን ተክኖሎጂውን በይፋ ያስተዋወቀ ስለመሆኑ ተነግሯል።

የሙዚቃ አፍቃሪያን ኦሪጂናል የሆነውን ሲዲ በመግዛት እንዲያደምጡ ለማበረታታት በሚል የተለያዩ ማበረታቻዎች ተካተውበት የቀረበ አልበም ነው። ስራው “ኢን-ሀንስ” የተሰኘንና በቀላሉ ለመገልበጥ ወይም ለመቅዳት የማያስችልን ቴክኖሎጂ የያዘ ከመሆኑም ባሻገር የድምፃዊ ታደለ ሮባን አጭር የህይወት ታሪክ የሚያሳይ ዘጋቢ ፊልም፤ በሙዚቃው ላይ የተሳተፉትን ባለሙያዎች ዝርዝር፤ ቀድሞ የተሰራ ክሊፕ እና በሙዚቃ መሳሪያ ብቻ የታገዘ የሙዚቃውን ግጥሞች በቲቪ ስክሪን ማንበብ የሚያስችል “ካራጎራ” እንዲሁም 30 ሰከንድ የሚወስድ የስፖንሰር ማስታወቂያዎችን አካቶ ይዟል። ከዚህም በተጨማሪ የድምፃዊው ከወጣትነት እስከቅርብ ጊዜ

ድረስ የተነሳቸውን ፎቶዎቹን “በፎቶ ጋለሪው” አካቶ በመያዙ የመጀመሪያ ደረጃ መረጃን ለማግኘት እንደምንጭ ሊያገለግል ይቻላል ተብሎለታል።

አልበሙ ለምን ዘገየ?ከአምስት ዓመታት ላላነሰ ጊዜ ሲሰራ የቆየው

ይህ “ምስጋና” የተሰኘ አልበም ለምን ዘገየ የሚል ጥያቄም ከበርካታ ጋዜጠኞች ተነስቶ ነበር። የኮፒ ራይት ጥሰት እየተባባሰ መምጣቱ ዋናው ስጋቱ እንደነበር ተጠቅሷል። “ሁሉም አርቲስት ማስተሩን ይዟል”፤ ነገር ግን ይህ ማስተር የካራቴ ቢሆን ሳይሻል አይቀርም” ሲል ታዳሚውን ፈገግ ያሰኘው ድምፃዊ ታደለ ሮባ፤ አሁንም ቢሆን የኮፒ ራይትን ነገር መቀነስ እንጂ ፈፅሞ ማጥፋት እንደማይቻል ታምኖ ዳሽን ቢራን የመሳሰሉ ከሙዚቃው ኢንዱስትሪ ደጋፊዎች እና ስፖንሰር አድራጊዎች ሊበረከቱ ይገባል ብሏል።

እዚህ’ጋ አርቲስቱ ለኮፒ ራይት ጉዳይ ላይ የመረረ አስተያየቱንም አስደምጧል፤ “መንግስት ባለበት ሀገር መንግስት እንደሌለ የሚያስመስል ተግባራት ታዝቤያለሁ። ምክንያቱም አንድ ሰው በህጋዊ መንገድ መስራት እየቻለ በአደባባይ በሚለጠፍ ታፔላ ላይ “በሚሞሪ ካርድ ሙዚቃ እንጭናለን” ተብሎ እየተፃፈ ሲሰራ ማየት በጣም ያሳዝናል። ለሙዚቃችን ውድቀት ምክንያት እነዚህ ናቸው” ሲል ገልጿል።

ስለላፎንቴኖች መለያየትእስከቅርብ ዓመታት ድረስ ድምፃዊያኑ የአንድ

ሳንቲም ሁለት ገፅታዎች ናቸው። ስያሜያቸውን “ላፎንቴን” ብለውም አብረው ሰርተዋል፤ ድምጻዊ ታደለ ሮባ እና ድምፃዊ ብርሃኑ ተዘራ። ድምጻዊ ብርሃኑ ተዘራ “ተለቺሳ” የተሰኘ አልበሙን ብቻውን ማውጣቱም የሚታወስ ነው። ያም ሆኖ ለመለያየታቸው ምክንያት ሆኖ በበርካቶች ዘንድ ለጭምጭምታ የተነገረው ነገር እውነት አለመሆኑን ድምጻዊ ታደለ ሮባ ለጋዜጠኞች በይፋ ተናግሯል፡፤ ከጋዜጠኞች፤ “አንተና ብርሃኑ የተለያያችሁት ብርሃኑ በታደለ ተከልሎ እየሰራ ነው በሚል መነሻ እንደሆነ ይወራል፤ ይሄ ምን ያህል እውነት ነው? የሚል ጥያቄ የቀረበለት ድምፃዊ ታደለ ሮባ ሲመልስ፤ “እኔና ብርሃኑ በኑሮ ምክንያት ተራርቀናል እንጂ አሁንም ድረስ አብረን ነው የምንሰራው። ብሬ የሚኖረው አሜሪካ እኔ የምኖረው ደግሞ እዚህ በመሆኑ አብረን መስራት አልቻልንም። ያም ሆኖ የሙዚቃ ኮንሰርት ሲኖር ግን አዘጋጆቹ ሲጋብዙን አብረን ነው የምንሰራው። በኔና በእርሱ መካከል ምንም ክፍተት የለም። ያውም እርሱም የኔን ልጅ፤ እኔም የእርሱን ልጅ የአይን አባት በመሆን ዘመዳማቾች ሆነናል። ምናልባትም የእኛ ተለያይቶ መስራት በእኛ ሀገር እንግዳ ሆኖ እንጂ ውጪ ሀገር የተለመደ ነው” ሲል አስረድቷል።

የ“ምስጋና” አልበም የሙዚቃ ስልቶች

የተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮን እንዳካተተ የተነገረለት “ምስጋና” የተሰኘው የሙዚቃ አልበም በውስጡ የተለያዩ የሙዚቃ ስልቶችን አካቶ ይዟል። ከነዚህም ውስጥ ኦሮምኛ “ሀረርጌ ሆማ” (ይህ የሻለቃ ወጋየሁ ደግነቱ ስራ ሲሆን በ1951 ዓ.ም የተሰራና በቤተሰቦቻቸው መልካም ፈቃድ በድጋሚ የሰራው ነው) ቀጥሎም “ገና ለጋ ናት” የተሰኘ ዘፈን በሱማሊኛ ስልት፤ የተጫወተ ሲሆን በሀደሪኛ፣ በሬጌ፣ በዳንሶል፣ በቴክኖና በቺለቺካ ስልቶችም በመጫወት ለእርሱ አዳዲስ ስልቶች የሆኑትን ሙዚቃዎች ጭምር ስለመስራቱ ድምፃዊ ታደለ ሮባ ተናግሯል።n

የአርቲስት ታደለ ሮባ “ምስጋና” እና አንዳንድ ነገሮች

ዳሸን ቢራ በ1.3 ሚሊዮን ብር ተቀዳሚ ስፖንሰር ሆኖታል

Page 11: ንደ3 - ethioforum.orgethioforum.org/wp-content/uploads/2014/01/sendek435.pdfሰንደቅ 9ኛ ዓመት ቁጥር 435 ረቡዕ ታህሳስ 30 2006 አታሚ፤ ብርሃንና

ሰንደቅ 9ኛ ዓመት ቁጥር 435 ረቡዕ ታህሳስ 30 2006

አንዳንድ

11

በመስከረም አያሌው

በድሮ ጊዜ አንድ ሀብታምና አዋቂ ገበሬ ይኖር ነበር። ይህም ገበሬ በርካታ ልጆች ነበሩት። ገበሬው ልጆቹ ጊዜያቸውን በማይገባ ነገር ከሚያባክኑ ይልቅ ሥራ እንዲወዱና

እንዲያከብሩ ያለመታከት ይነገራቸው ነበር። እነሱ ግን “እኛ ለምን እንሰራለን። ብዙ አሽከሮች አሉ። እነሱ አይሠሩትምን?” እያሉ ይመልሱለታል።

ለብዙ ጊዜያትም “ከቶ እነዚህን ልጆች ምን ባደርጋቸው ሥራ ይለምዱ ይሆን? እኔ ከሞትኩ በኋላስ እራሳቸውን መርዳት የሚችሉት እንዴት ነው?” እያለ ያስብ ነበር።

በመጨረሻም እለተ ሞቱ መቃረቡንና ከልጆቹ የሚለይበት ቀን መድረሱን ተረዳ። ስለዚህም ሁሉንም ልጆች ጠራና “ሰማችሁ ልጆቼ፤ እስካሁን ድረስ አስፈላጊውን ነገር ሁሉ እያደረግሁ አሳድጌአችኋለሁ። ሥራ ወዳዶች እንድትሆኑና ጊዜያችሁን ባልባሌ ቦታ እንዳታሳልፉም መክሬያችኋለሁ። ከእንግዲህ ሕይወታችሁን መምራት ያለባችሁ እናንተ ናችሁ”

አለና ለጥቂት ጊዜ ፀጥ አለ። ቆይቶም “እነሆ ዕድሜዬ ገፍቷል። ጤንነትም አይሰማኝም። በአጭር ቀናት ውስጥ እንደምሞትም ይሰማኛል። ዛሬ የሰበሰብኳችሁም ሀብቴን የቀበርኩበትን ቦታ ልነግራችሁ ነው” አላቸው።

ልጆቹም ገንዘቡን ለማግኘት በነበራቸው ጉጉት “የት ነው? የት ነው?” በማለት ጠየቁት።

አባታቸው ጉጉታቸውን በደንብ ተገነዘበና “የትኛው ቦታ እንደሆነ በትክክል ልነግራችሁ አልፈልግም። ነገር ግን በእርሻዎቻችን ውስጥ መሆኑን ልጠቁማችሁ እወዳለሁ። ስለዚህ ሌላ ማንንም ሳትጨምሩ እራሳችሁ ያረሳችሁት እንደሆነ ወርቁን ታገኙታላችሁ። ስለዚህ እንደሞትኩ በሶስተኛው ቀን ወርቁን ፈልጉት” ብሎ መከራቸው።

ይህንን እንደተናገረም ሕይወቱ አለፈች። በሶስተኛው ቀንም ሁሉም ልጆች በሁሉም እርሻዎች ተሰማርተው በዶማ በመቆፈሪያ በተጠመዱ በሬዎች መሬቱን ገለባብጠው አረሱት። ዳሩ ግን አባታቸው

ከመሬት ላይ ቀብሬዋለሁ ያለውን ወርቅ ከቶ ሊያገኙ አልቻሉም።

ተስፋ ቆርጠው ከመሰናበታቸው በፊትም “አባታችን ወርቁን እርሻው ውስጥ ቀብሬዋለሁ ብሎን ነበር። ይሁንና ልናገኘው አልቻልንም። ምናልባት ሲቀብር ያየ ሰው በስዶት ይሆናል። ስለዚህ ምን ብናደርግ ይሻላል?” ሲሉ ተወያዩ።

በመጨረሻም “አባታችን ለምን ይህን እንዳለን ምስጢሩን የሚፈታልን አዋቂ እስክናገኝ ድረስ ወይን እንትከልበት” አሉና ተከሉበት። ለረጅም ሠዓታት ያለመታከት በመሥራትና ይንከባከቡት ጀመር፤ ከዱር እንስሳትም ጠበቁት።

የወይን ተክሉም ታይቶና ተለምቶ በማይታወቅ ሁኔታ አፈራ። ወደገበያ ወስደው ሲሸጡትም ከፍተኛ ወርቅ አወጣላቸው። “እንዴ! ይህን ያህል ማግኘት ከቻልን ለምን እርሻውን እንደገና አናለማውም” ተባብለው ካለፈው ዓመት በተሻለ ሁኔታ ገለባብጠው አረሱት፤ መሬቱ እንዲዳብርም ፍግ ጨመሩበት።

የወይን ተክልም ተከሉበት። የበለጠ ምርት አመረቱና በከፍተኛ ዋጋ ሸጡት።

በነሱ አካባቢ የወይን ምርቱን በከፍተኛ ዋጋ የሸጡ እነሱ እንደሆኑም ይነገር ጀመር። በሁለት ዓመታት ውስጥ ከአባታቸው የበለጡ ሀብታሞች ሆኑ። ከፍተኛ ሀብት በማሰብሰባቸውና ሥራ በመውደዳቸውም ሁሉም አከበራቸው። አደነቃቸው።

ከዕለታት አንድ ቀን ተሰባስበው ሲጨዋወቱ አንደኛው ልጅ “አባታችን ደጋግሞ ሥራ እንድንወድና ጊዜያችንን በአልባሌ ስፍራ እንዳናጠፋ አዘውትሮ ይነግረን ነበር። ጠንክራችሁ መሬቱን ካረሳችሁለትና ወይንም ከተከላችሁበት ብዙ ሀብት ታገኙበታችሁ ማለቱ ይሆን እንዴ? በማለት ጠየቀ። ሁሉም “አዎን! ጠንክሮ መሥራትና ጊዜን በከንቱ አለማሳለፍ ያስከብራል” አሉ።n

የኤዞፕ ተረቶች -በተሾመ ብርሃኑ

አትመርቁንበሚገርም ፍቅር ተሳስረንበንጹህ ልብ ተዋደንሲነጋ በደስታ ተገናኝተንሲመሽ በእንባ ተለያይተንተነፋፍቀን ይኽው አለን። እናንተ ትልቅ የሆናችሁልጅነትን ያለፋችሁምነው እናይ ተፋቅራችሁ? ማደግ ፍቅርን ከቀነሰቂም ጥላቻን ካነገሰክፋት ብቻ ካስተማረተንኮል ልብ ውስጥ ካሳደረ አትመርቁን እባካችሁ “ እ ደ ጉ ል ን ” እያላችሁ።

ምልክት - በሳምሶን ይርሳውnn

ልዑል ዓለምአየሁልዑል አለማየሁ ቴዎድሮስ

የተወለደው እ.ኤ.አ. በ23 ቀን 1869 ነው። የእንግሊዝ ሠራዊት በመቅደላ ምሽግ ላይ እሳት ለቆበት የልዑሉ አለማየሁ መኖሪያ ቤትን ጨምሮ 3ሺ ቤቶች ሲቃጠሉ እናቱ ወይዘሮ ጥሩወርቅ ልጃቸው ኢትዮጵያ ውስጥ በህይወት መቆየቱ አስተማማኝ አልመሰላቸውም። እናም ልዑል እና እቴጌ ጥሩወርቅ ከአጃቢዎቻቸው ጋር ወደ ቀይ ባህል ወደብ ጉዞ ጀመሩ። በወቅቱ አብሯቸው የነበረው እንግሊዛዊው ሰዓሊ ሲምፕሳን ልዑል አለማየሁ በዚያ ጉዞ ወቅት ምን ይመስል እንደነበረ እንዲህ ገልጾታል።

“የሰባት ዓመቱ ልጅ፤ የአቢሲኒያ ባህላዊ ልብስ፣ ሸማ ለብሷል። ሸማው ከጥጥ የተሰራ ባለ ቀይ ሰፊ ጥለት (ጃኖ) ነው። የተለያዩ የአንገት ጌጦችን ማርዳ፣ ክርስትና መነሳቱን የሚገልፅ ሰማያዊ የሀር ክር አንገቱ ላይ አስሯል። በአቢሲኒያ ባህላዊ ልማድ መሰረት አናቱ ላይ ቅቤ ተቀብቷል። ቅቤው እየቀለጠ በፊቱ ግራና ቀኝ ኮለል ብሎ ሲወርድ ይታያል”

አፄ ቴዎድሮስ- የሺህ አመቱ ጀግና በማርቆስ የሻነውn

አባትና ልጆቹ

Page 12: ንደ3 - ethioforum.orgethioforum.org/wp-content/uploads/2014/01/sendek435.pdfሰንደቅ 9ኛ ዓመት ቁጥር 435 ረቡዕ ታህሳስ 30 2006 አታሚ፤ ብርሃንና

ሰንደቅ 9ኛ ዓመት ቁጥር 435 ረቡዕ ታህሳስ 30 200612 ህይወት

ጥቃቅን ኤግዚቢሽኖች -

ለአብዛኛው የህብረተሰብ የቀረቡ አማራጮች

በመስከረም አያሌው

የተለያዩ ክብረ በዓሎችን መቃረብ አስመልክቶ ከተማዎች አስቀድመው ከሚደምቁባቸው ነገር ኤግዚቢሽን እና ባዛር አንዱ ነው። በመዲናችን አዲስ አበባም በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች ገና በዓል አንድ ሳምንት ሲቀረው ጀምሮ በኤግዚቢሽን እና ባዛር ማሸብረቅን ልማድ አድርገውታል። በዋነኝነት ትላልቅ ምርቶችን በማቅረብ ከሚታወቀው የአዲስ አበባ ኤግዚብሽን ማእከል በተጨማሪም በየቦታው ደመቅመቅ የሚሉት ጥቃቅን ኤግዚቢሽን እና ባዛሮች የብዙዎችን ቀልብ እየገዙት ይገኛሉ።

ወቅቱ የገና በዓል መዳረሻ እንደመሆኑም ከባለፈው ሰኞ ጀምሮ ከተማችን በየቦታው በተከፈቱ ባዛሮች ደመቅመች ብላለች። በሜክሲኮ፣ በፒያሳ፣ በአዲሱ ገበያ፣ በአራት ኪሎ፣ በቀበና እና በመሳሰሉት አካባቢዎች ሞቅ ባለ ሙዚቃ እየታጀቡ ምርቶቻቸውን ለተጠቃሚ በማቅረብ ላይ ያሉ አምራቶችም ሰሞኑን ፋታ የላቸውም። ሸማቹም ቢሆን በሆደ ሰፊው መርካቶ ገብቶ ከመጋፋት ይልቅ በግልፅ ከተደረደሩት ለኤግዚቢሽን ከቀረቡ ምርቶች አማርጦ መግባትን ይመርጣል።

በካዛንችስ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አካባቢ በተከፈተ ኤግዚቢሽን የቤት እቃ በመግዛት ላይ ሳሉ ያገኘናቸው አንዲት እናት እንደገለፁልን ከሆነ፤ እነዚህ በኤግዚብሽን እቃ የሚሸጡ አምራቾች የተሻለ አማራጭ ይዘው መጥተዋል። በአሁኑ ጊዜ ሰው ጊዜ እያጠረው ነው። መርካቶ ሄዶ የሚፈልገውን ነገር ለመግዛት ጊዜ አይኖርም። ቦታው የሚርቀውም አለ። እንደዚህ በየአካባቢያችን ሲከፈትልን ግን በፈለግነው ጊዜ አማርጠን መግዛት እንችላለን። መርካቶ ሄዶ ከሚያጋጥመው ግፊያ እና ግርግርም ይሄ ይሻላል። እቃውን አይተን እና አማርጠን መግዛት እንችላለን” የሚሉት እኚህ እናት፣ ከዚህ በተጨማሪም በእቃው ዋጋ ላይ እርግጠኛ ለመሆን ያግዛል ይላሉ።

በአራት ኮሎ በተከፈተው ኤግዚብሽን ላይ ምርቶቻቸውን ካቀረቡ ባለሞያዎች መካከል የ“ሀሊማ የባልትና ውጤቶችን” ለገበያ ያቀረቡ ወይዘሮ ሳቢያ በበኩላቸው፣ እነዚህ ጥቃቅን የኤግዚቢሽን ገበያዎች በዋናው ኤግቢሽን ማዕከል ምርት ያልተናነሰ ጥራት ያለው ምርት ቢያቀርቡም የአብዛኛውን ህብረተሰብ ትኩረት መሳብ መቻላቸውን ይናገራሉ። “ኤግዚብሽን ማእከል ብትገባም የምናገኘው እኛ የያዝነውን አይነት ምርት ነው። በተለይ የባልትና ውጤቶቹ ተመሳሳይ ናቸው። ሆኖም ሰው ከኤግዚብሽን ማእከል ይልቅ እነዚህን ኤግዚቢሽኖች የበለጠ እየመረጠ ይመጣል። በዚህ የሚያልፈው አብዛኛው ሰው ይጠይቀናል። የሚገዛ ገዝቶ፣ የማይገዛው ደግሞ መኖራችንን አውቆ ስለሚሄድ በሌላ ጊዜ መጥቶ ሊገዛን ይችላል። አንዳንዶቹ ቢዝነስ ካርዳችንን ተቀብለው ከሄዱ በኋላ እየመጡ ከሱቃችን ይገዙናል” ይላሉ።

ከላይ የጠቀስናቸው እናትም ቢሆኑ እርሳቸው እና መሰሎቻቸው እነዚህን ቦታዎች የሚመርጡበትን ምክንያት አጫውተውናል። “እዚያ (ኤግዚቢሽን ማዕከል) ስንሄድ በነፃ አይደለም የሚገባው። በር ላይ ብር ይከፈላል። ውስጥ ሲገባም ገዢውም ሀብታም ስለሚሆን ዋጋውን እንፈራለን። ደሃ እንደ አቅሙ የሚያገኘው እነዚህ ኤግዚቢሽኖች ጋር

ሲሆን ብቻ ነው” ያላሉ።እኛም ይሄንን የህዝብ

አመለካከት ይዘን እውን የዋጋ ልዩነቱ ከፍተኛ በማለት ለማጣራት ሞከርን። የመጀመሪያ ቅኝታችን በባልትና ውጤቶች ላይ ነው። በኤግዚቢሽን ማእከል ለሽያጭ የቀረበ የአንድ ኪሎ በርበሬ ዋጋ ከ75 ብር ጀምሮ እስከ 85 ብር ዋጋ አለው። አንድ ኪሎ ሚጥሚጣ ከ45 ብር እስከ 50 ብር ይሸጣል። አንድ ኪሎ የተፈጨ በሶም ከ32 ብር እስከ 35 ብር ዋጋ አለው። አንድ ኪሎ ምጥን ሽሮ ከ35 ብር እስከ 40 ብር ዋጋ ያለው ሲሆን፣ አንድ ኪሎ ነጭ ሽሮ ደግሞ ከ28 እስከ 30 ብር ዋጋ ያወጣል።

የእነዚህ የባልትና ውጤቶች ዋጋ በጥቃቅኖቹ የኤግዚቢሽን ቦታዎች ያላቸውን ዋጋ ስንመለከትም ሸማቾች እንደሚሉት መጠነኛ የሆነ የዋጋ ልዩነት ይስተዋልባቸዋል። በመሆኑም በርበሬ በኪሎ ከ72 እስከ 75 ብር ዋጋ ሲኖረው፤ ሚጥሚጣ ደግሞ በ40 ብር

በመሸጥ ላይ ይገኛል። አንድ ኪሎ በሶ በ34 ብር፣ አንድ ኪሎ ምጥን ሽሮ በ32 ብር እና ነጭ ሽሮ ደግሞ በ28 ብር በመሸጥ ላይ ናቸው። በሁለቱም ቦታዎች ተመሳሳይ ዋጋ ያላቸው እንቁላል የሀበሻው በ2.75 ሳንቲም፣ የፈረንጁ 2.80 ሳንቲም ዋጋ አላቸው።

በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል የሚገኙ ነገር ግን በእነዚህ ጥቃቅን የኤግዚቢሽን ቦታዎች ሊገኙ የማይችሉ የባልትና ውጤቶችንም ለማየት ችለናል። በኤግዚቢሽን ማዕከል ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየተለመደ የመጣ የተበለተ ዶሮ እና ቁሌት ሽያጭም በመካሄድ ላይ ይገኛል። አንድ ተበልቶ እና ታጥቦ የታሸገ ሙሉ ዶሮ በ160 ብር ይሸጣል። ይህ ዶሮ ሁሉ ነገሩ ተጠናቆ ጣጣውን የጨረሰ በመሆኑ ቀጥታ ወስዶ ቁሌት ውስጥ ጨምሮ ማብሰል ብቻ እንደሆነ ነው ባለቤቶቹ በተደጋጋሚ የሚገልጹት።

ሌላው በኤግዚቢሽን ማእከል ለገበያ የቀረበው ቁሌት ነው። ይህ ቁሌት በሩብ ኪሎ፣ በግማሽ ኪሎ፣ በአንድ ኪሎ፣ በሁለት እና በአምስት ኪሎ ተከፋፍሎ ታሽጎ የሚሸጥ ነው። ዋጋውን ስንመለከትም አንዱ ኪሎ ከ25 እስከ 30 ብር ዋጋ አለው። ግማሹ ከ15 እስከ 20 ብር እንዲሁም ሩቡ በ10 ብር ይሸጣል።

በጥቃቅን ኤግዚቢሽን ምርታቸውን የሚያቀርቡ አምራቾችም ቢሆኑ በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማእከል ካለው ዋጋ ቀንሰው እንደሚሸጡ ይገልፃሉ። ምክንያታቸው ደግሞ ይሄን አይነቱ አጋጣሚ ምርታቸውን የሚያስተዋውቁበት ወቅትም ጭምር በመሆኑ ነው። በፒያሳ አካባቢ ለኤግዚቢሽን የጠጅ ምርት ይዛ ያቀረበችው እቴነሽም ይሄንን ነው የገለፀችው። “እኛ ጠጅ ማቅረብ የጀመርነው ተደራጅተን በመጣል ነው። ጠጃችንን ለገበያ ስናቀርብ ይሄ ሁለተኛችን ነው። ኤግዚቢሽን ማዕከል የሚገቡት ብዙ ሰው የሚያውቃቸው እና ስም ያላቸው ናቸው። እኛ ደግሞ እዚያ ደረጃ ላይ ለመድረስ ህዝቡ ሊያውቀን ይገባል። እዚህ አንድ ጠርሙስ ጠጅ በ20 ብር ነው የምንሸጠው። ኤግዚቢሽን ማእከል እስከ 50 ብር እንደሚሸጥ እናውቃለን። ግን እኛ ዋናው አላማችን ምርታችንን ማሳወቁ ነው” ትላለች።

በእነዚህ ጥቃቅን ኤግዚቢሽኖች ምርቶቻቸውን የሚያቀርቡት በአብዛኛው ተደራጅተው የሚሰሩ ወጣቶች እንደመሆናቸው ዋናው አላማቸውም ምርታቸውን ማስተዋወቅ

እንደሆነ ነው የሚናገሩት። እንደ ትልልቆቹ አዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል ገብተው በከፍተኛ ዋጋ ለመሸጥ እስከሚደርሱ ድረስ የተጋነነ ትርፍ ማግኘት ሳይሆን አላማቸው ገበያውን ሰብረው ሊገቡ የሚችሉበትን መንገድ ማመቻቸት ነው። በዚህም ሳቢያ እንደ ኩኪስ፣ ቆሎ እና የመሳሰሉት የባልትና ምርቶች በሌላው ቦታ ካለው ዋጋ በቅናሽ ይሸጣል። በዚህም ሳቢያ በዝቅተኛና መካለኛ ገቢ የሚተዳደረውን የህብረተሰብ ክፍል በብዛት መሳብ ላይ ይገኛሉ።

ለአመት በዓል የሚያስፈልጉ ነገሮችን ዋጋ ማንሳታችን ካልቀረ የአውዳመት ገበያው በሌሎች ምርቶች ላይ ያለውን ዋጋም መቃኘታችን አልቀረም። በፒያሳ አትክልት ተራ አንድ ኪሎ የሀበሻ ሽንኩርት ከ15 እስከ 18 ብር ዋጋ ያለው ሲሆን የፈረንጅ አንድ ኪሎ ሽንኩርት ከ8 ብር እስከ 12 ብር ዋጋ አለው። አንድ ኪሎ ነጭ ሽንኩርት ከ18 እስከ 20 ብር ዋጋ ያለው ሲሆን ዛላ በርበሬ በመሳለሚያ አንደኛ ደረጃ ማረቆ በኪሎ በ33 ብር እየተሸጠ ያለ ሲሆን፣ ሌሎቹ እንደየደረጃቸው ከ28 እስከ 30 ብር ዋጋ አላቸው። አንድ ወንድ ዶሮ ከ140 ብር ጀምሮ የሚሸጥ ሲሆን፤ ሴት ዶሮ ከ80 ብር ጀምሮ ባለው ዋጋ ማግኘት ይቻላል።

አንዳንድ ያነጋገርናቸው ሸማቾች እንደገለፁትም በዚህኛው በዓልም ያለው የአውዳመት ዋጋ ከሌሎች የአውደዓመት ዋጋ ብዙም ጭማሪ የለውም። ይልቁንም በከተማዋ ውስጥ በመካሄድ ላይ ባለው ግንባታ ምክንያት እንደልብ ተንቀሳቅሶ መሸማመት አለመቻሉ እንደ ችግር ተገልጿል። ይሄንን ችግር ለመቅረፍ ከሚያግዙ ዘዴዎችም አንዱ እነዚህን ጥቃቅን ኤግዚቢሽኖች ማስፋፋቱ ነው ይላሉ ብዙዎች። ከዚህ በተጨማሪም ለኤግዚቢሽን የሚቀርቡት ምርቶች ሁሉን አቀፍ መሆን እንዳለባቸው አቅራቢዎች ይገልፃሉ።

እንደ ወይዘሮ ሳቢያ አገላለጽ በኤግዚቢሽን የሚቀርቡ እቃዎች ገደብ ሊኖራቸው አይገባም። ገዢ የሚፈልገውን ነገር ሁሉ በአንድ ቦታ ማግኘት መቻል አለበት። ለምን ሽንኩርትስ በኤግዚቢሽን አይቀርብም? የማይበላሹ አትክልትና ፍራፍሬዎች ቢቀርቡ ሰው የማይገዛበት ምክንያት የለም። እንደዚያ ሲሆን እኛም በስፋት መስራት እንችላለን። ገዢውም ሳይንከራተት በአንድ ቦታ ገዛዝቶ ይሄዳል” ይላሉ።n

አንዳንድ ያነጋገርናቸው

ሸማቾች እንደገለፁትም

በዚህኛው በዓልም

ያለው የአውዳመት ዋጋ

ከሌሎች የአውደዓመት

ዋጋ ብዙም ጭማሪ

የለውም

Page 13: ንደ3 - ethioforum.orgethioforum.org/wp-content/uploads/2014/01/sendek435.pdfሰንደቅ 9ኛ ዓመት ቁጥር 435 ረቡዕ ታህሳስ 30 2006 አታሚ፤ ብርሃንና

ሰንደቅ 9ኛ ዓመት ቁጥር 435 ረቡዕ ታህሳስ 30 2006 13

www.sendeknewspaper.comwww.sendeknewspaper.comwww.sendeknewspaper.comwww.sendeknewspaper.com www.sendeknewspaper.comwww.sendeknewspaper.com www.sendeknewspaper.comwww.sendeknewspaper.com

www.sendeknewspaper.comwww.sendeknewspaper.comwww.sendeknewspaper.comwww.sendeknewspaper.com www.sendeknewspaper.comwww.sendeknewspaper.com www.sendeknewspaper.comwww.sendeknewspaper.com

www.sendeknewspaper.comwww.sendeknewspaper.comwww.sendeknewspaper.comwww.sendeknewspaper.com www.sendeknewspaper.comwww.sendeknewspaper.com www.sendeknewspaper.comwww.sendeknewspaper.com

www.sendeknewspaper.comwww.sendeknewspaper.comwww.sendeknewspaper.comwww.sendeknewspaper.com www.sendeknewspaper.comwww.sendeknewspaper.com www.sendeknewspaper.comwww.sendeknewspaper.comww

w.se

ndek

news

pape

r.com

ሰራተኛውና...“ሰራተኛው አንድ ጫማ ከቀየረ

ይበቃዋል። በዚያው መጠን አምስትና ስድስት መኪና የሚቀያይሩ ቀጫጭን ባለሀብቶች ተፈጥረዋል” ሲሉ ቅሬታ ያቀረቡት የሰራተኞቹ ተወካዮች፤ “በአሰሪውና በሰራተኛው የጨቋኝና ተጨቋኝ መደባዊ ግንኙነት እየተፈጠረ ነው” ሲሉ ስጋታቸውን ገልፀዋል። “ድሮ የምናውቀው ወፍራም ባለሀብት ነበር፤ የዛሬ ባለሀብቶች ግን ቀጫጭን ናቸው። የጋራ ሀገራችን በጋራ ማልማት አለብን። ሕገ-መንግስቱ ለድርድር መቅረብ የለበትም። አሁን ያለው ሰራተኛ ከሁለት ሚሊዮን ላይበልጥ ይችላል። በቀጣይ ዓመታት ሃያና ሰላሳ ሚሊዮን ሰራተኛ ሲፈጠር በዚህ መንገድ መቆጣጠር አይቻልም” ሲሉ ስጋታቸውን ገልፀዋል።

አንዳንድ አሰሪዎች የሰራተኛ መደራጀትን የኮሚኒዝምና የሶሻሊዝም ፍልስፍና ርዕዮተ ዓለም አድርገው የሚያስቡ አሉ በማለት የመደራጀት መብትን ከሕገ-መንግስቱ የተገኘ አድርጎ ያለማሰብ ሁኔታ መኖሩን ገልፀዋል። በዚህ አስተሳሰብ ውስጥ የመንግስት ኃላፊዎችም ሳይቀሩ እንዳሉበት አስረድተዋል። ከዚያ ባለፈ የውጪ ባለሃብቶች በሀገራቸው የሰራተኛ ማኅበርን እያከበሩ ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ የሰራተኛውን መብት እንደሚጥሱ ገልፀዋል። አንዳንድ የውጩ ሰራተኞች የቀን ሰራተኛ ከመሆን ጀምሮ ኢትዮጵያውያን መሰማራት በሚገባቸው የስራ ዘርፍ ሕገ-ወጥ በሆነ መንገድ ተሰማርተው እንደሚገኙም ተናግረዋል።

የመንግስት ባለስልጣናቱ ምላሽበሰራተኞች ማኅበራት

ተወካዮች ለተነሱ በርካታ ጥያቄዎች ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያምን ጨምሮ የመንግስት ኃላፊዎች ምላሽ ሰጥተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም፤ ሀገሪቱ የኢኮኖሚ መዋቅር ከግብርና ወደ ኢንዱስትሪ ሽግግር ላይ በመሆኑ የሰራተኛው ሚና ጉልህ መሆኑን ደጋግመው ገልፀዋል። ለዚህ ደግሞ የሰራተኛው የመደራጀት መብት ለድርድር መቅረብ እንደሌለበት አስምረውበታል። ሰራተኞች በማኅበር የሚደራጁት ለውዝግብ ሳይሆን የጋራ ሀገራዊ ራዕይን ለማሳካት፣ ለምርታማነት መሆን እንዳለበት ገልፀዋል። በመሆኑም መንግስት፣ አሰሪና ሰራተኛ በጋራ በመሆን ለምርታማነት እድገት መስራት እንዳለባቸው አሳስበዋል። አንዳንድ ኃላፊነት የጎደላቸው አሰሪዎች የሚፈፅሙትን ችግር የሁሉም አሰሪ አድርጎ ማቅረብ ግን ተገቢ አለመሆኑንም ተናግረዋል።

ከጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ባለፈ በሕግና በመደራጀት በኩል ስላሉ ችግሮች የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩና የሰራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትሩ ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል። በመንግስት በኩል ያሉ ክፍተቶችን በመዝጋት በኩል የሚቀሩ ነገሮች እንዳሉ አምነው የፖሊሲና የሕግ አፈፃፀሞች ላይ እንደሚሰሩም ተናግረዋል።

የታክስና የኑሮ ውድነትን በተመለከተም የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ ሶፊያን አህመድ ምላሽ ሰጥተው ነበር። ለታክስ መሻሻሉም ሆነ ለደመወዝ ጭማሪ የሀገሪቱ ኢንዱስትሪ ማደግን በቅድመ ሁኔታነት አስቀምጠዋል። በአጭር አገላለፅ “ኬኩ ካላደገ” የታክስ ማሻሻያውም ሆነ ድጎማና የደመወዝ ጭማሪ ማድረግ እንደሚያስቸግር ነው የገለፁት። “ትልቁን ስዕል ማየት አለብን” ያሉት አቶ ሶፊያን የደመወዝ ጭማሪም ሆነ ሌሎች ድጎማዎች ከሀገሪቱ እድገት ጋር የሚያያዝ ነው ብለዋል። ከደመወዝ ገቢ ግብር ጋር በተያያዘም የገቢ ግብር ታክሱን ለማሻሻል ጥናት እየተከናወነ መሆኑን በመጥቀስ በገቢ ግብር አዋጁ ሲሻሻል ዝቅተኛ ደመወዝ ላይ የገቢ

ታክስ ማሻሻያ እንደሚኖር ፍንጭ ሰጥተዋል። በተለይ የገቢ ግብር አዋጁ ሲሻሻል የተወሰኑ አሰሪዎች ለሰራተኞች ምግብ የሚመግቡ ከሆነ ከገቢ ግብር ነፃ እንደሚደረጉም ከወዲሁ አብስረዋል። የመኖሪያ ቤት ሰርተው የሚሰጡ አሰሪዎች ካሉም በዚሁ ማሻሻያ የሚታዩ እንደሆነም አስረድተዋል።

ምግብ ላይ የተጣለው ተደራራቢ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት)ን በተመለከተ መንግስት አሁንም በመሰረታዊ የምግብ ሸቀጦችን ከቫት ነፃ ማድረጉን የገለፁት አቶ ሶፊያን፤ ነገር ግን በምግብ ስም በሆቴሎችና ሬስቶራንቶች የሚቀርቡ ምግብ ላይ ታክስ ማንሳት ጥንቃቄ የሚያስፈልገው ጉዳይ ነው በማለት ለጊዜው ቫት የሚነሳበት ዕድል እንደሌለ ነው የጠቀሱት።

የኑሮ ወድነትን በተመለከተ መንግሰት ደመወዝ ከመጨመር አንስቶ ስንዴ፣ ስኳር፣ ዘይትና ዳቦ በከፍተኛ ድጎማ እያከፋፈለ መሆኑን። በዋናነት የኑሮ ውድነቱ ችግር ሊፈታ የሚችለው ኬኩ ሲያድግ ነው ብለዋል። ኢኮኖሚው እያደገ ሲሄድ መንግስትም፣ ባለሃብቱም ጥሩ ደመወዝ የሚከፍሉት ኬኩ ሲያድግ ነው ሲሉ አስረግጠው ተናግረዋል።

የጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዝዳንቱ አቶ ተገኔ ጌታነህ በበኩላቸው በፍ/ቤቶች በኩል በአሰሪና ሰራተኛ መካከል ስላለው የፍትህ መጓደል ምላሽ ሰጥተው ነበር። ችግሩን ለመፍታት የፍርድ ቤቶችን ቁጥርና የዳኞችን ቁጥር ለመጨመር እንደሚሰሩ ተናግረዋል። በሕጉ በተቀመጠው የአሰሪና ሰራተኛ ክርክር ችሎቶች በሁለት ወር ማለቅ ሚኖርበትም ከ2000 የስራ ክርክር መዝገቦች ወደ መቶ የሚሆኑ መዝገቦች በሕግ ከተቀመጠው ጊዜ መዘግየታቸውን አምነዋል። አንዳንዶቹ መዝገቦች ሰራተኞች ጉዳያቸውን በድርድርና በፍርድ አፈፃፀም የሚዘገዩ ናቸው ብለዋል።

ሙስና በማጋለጥ ረገድ ለሰራተኞች ተገቢውን ከለላ አይደረግም ለሚለው የሰራተኞቹ አቤቱታ የስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽነሩ አቶ ዓሊ ሱሌይማን ምላሽ ሰጥተው ነበር። ኮሚሽነሩ፤ “ከለላ የጠየቀን ሰራተኛ የለም” ቢሉም በሰራተኞቹ በኩል ሙስናን በማጋለጥ ረገድ በሰራተኞች ላይ በርካታ በደል እየደረሰ መሆኑን ተናግረዋል። ከበደሉ የተነሳ “ሰራተኛውን ሙስናን ከመታገል ውጪ አድርጉት ወይም ጥበቃ አድርጉለት” እስከማለት ደርሰው ነበር። የፌዴራል የሥነምግባርና ፀረሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ዓሊ ሱሌይማን ግን በዚህ ረገድ የቀረበውን አቤቱታ ቀዝቀዝ ያለ መልስ ነበር የሰጡት። ኮሚሽኑ ከሰራተኛው ጋር በንቃት እየሰራ ከመሆን ባለፈ ቅሬታው የጎላ አለመሆኑን ጠቅሰው አልፈውታል። በተለይ የስነ-ምግባር መኮንኖች ተጠሪነት ለስራ አስኪያጁ መሆናቸው ጋር በተያያዘ ለተነሳው ቅሬታ “የስነ-ምግባር መኮንኖቹ ስራ አስኪያጅን ለመሰለል የተቀመጡ አይደሉም” ብለዋል። በአንፃሩ የስነ-ምግባር መኮንኖቹ ግን በቀጥታ ከኮሚሽኑ ጋር የሚገናኙበት መስመር መኖሩን ጠቅሰዋል።

ሌላው በሰራተኞች ቀርቦ የነበረው ከ10 ሺህ በላይ ሰራተኞች የነበሩት የቀድሞው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሸን ለሁለት መከፈሉን ተከትሎ ሰራተኞች እንዳይቀነሱ የሚለውን ስጋት በተመለከተም ዶ/ር ደብረፂዮን ገ/ሚካኤል በኮርፖሬሽኑ ለሁለት መከፈል የሚቀነስ ሰራተኛ እንደሌለና ይልቁንም ተጨማሪ 4 ሺህ ሰራተኛ ይቀጠራል ብለዋል። የመስሪያ ቤቱ

ለውጥ ሰራተኛ ለመቀነስ ሳይሆን የሀገሪቱን ኢንዱስትሪ ልማት ለማሳደግ ነው ብለዋል። ለውጡም ከሰራተኛው ጋር በሚደረግ ውይይትና ምክክር መሆኑንም አስረድተዋል።

በሚኒስትር ማዕረግ የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ አቶ በረከት ስሞኦን በበኩላቸው ሰራተኛው በሀገሪቱ ፈጣን የእድገት ሂደት ውስጥ ዋና ተዋናይና ተጠቃሚ መሆን እንዳለበት ገልፀዋል። የሰራተኛ የመደራጀት መብት በተመለከተ ያለው ችግር የቆየ መሆኑን፣ እንቅፋቶቹም ትንሽ አለመሆኑን ጠቅሰዋል። የሀገሪቱን የኢኮኖሚ እድገት በእድገት ላይ በመሆኑና ብዙ ስራ አጥ በመኖሩ ባለሃብቱ ሰራተኛውን እንደፈለገው ሊያደርግ ይችላል ብለዋል። መሠረታዊ መፍትሄው የኢኮኖሚ እድገቱን ማፋጠንና ሰራተኛውን ተጠቃሚ እንዲሆን እና የመደራጀት መብት የሕግ ከለላ መስጠት እንደሚገባም ገልፀዋል። በዋናነት መንግስት በሰራተኛው ብቃትና የግዜ አጠቃቀም ላይ የራሱ ስጋቶች ቢኖሩም፤ በሰራተኛው መብትና ጥቅም ክልል ውስጥ ሆኖ በነፃ የሚገኝ የመደራጀት መብት አለመኖሩን አውቆ ሰራተኛው ትግሉን እንዲቀጥል ብለዋል።

የብረታ ብረት ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ላይ ለተነሳው ቅሬታ ብርጋዴል ጀነራል ክንፈ ዳኘው ሰፋ ያለ ማብራሪያ ሰጥተው ነበር። ኮርፖሬሽኑ ቀደም ሲል በልማት ድርጅትነት ተቋቁመው በሚሰሩ ድርጅቶች የቆመ ድርጅት መሆኑን በማስታወስ የሰራተኛ ማኅበራት መፍረሳቸውን ገልፀዋል። ሆኖም ግን እንደ ኮርፖሬሽን የራሱ ሰራተኛ ማኅበር መቋቋም እንዳለበት ኮርፖሬሽኑ ያምናል ብለዋል። በጀነራሉ አገላለፅ ተቋሙ ዴሞክራሲያዊ ህይወት እንዲኖረው ይፈልጋል። ዴሞክራሲያዊ ህይወት የሌለው ድርጅት ምርታማ አይሆንም ብለዋል። ስለሆነም ማደራጀት ላይ ችግር የለውም። ነገር ግን 15 ሺህ ሰራተኛ እንዴት ይደራጅ የሚለው ላይ መዘግየት መኖሩን ጠቅሰዋል። ለመዘግየቱም የኮርፖሬሽኑ በአዋጅ ለመከላከያ የተሰጡት ስልጣኖች አሉት። የልማት ድርጅት ቢሆንም፤ የጦር መሳሪያ የሚያመርት ተቋም ነው። የመከላከያ ሰራዊት አባላትም የኮርፖሬሽኑ ሰራተኞች ናቸው። ተቋሙ በተወሰነ ደረጃ ዴሞክራሲያዊ መብት ገደብ የሚጣልበት በመሆኑ ጦር መሳሪያ የሚያመርት ተቋም የተደራጀ ሰራተኛ እንዴት እንደሚኖረው ተጠንቶ ተግባራዊ መደረግ አለበት የሚለው ተጠንቷል። ከብሔራዊ ጥቅም ጋር ታይቶ በሚመለከተው አካል ሲፀድቅ ተግባራዊ ይሆናል ብለዋል። ጀነራሉ እግረ መንገዳቸውንም ኢሰማኮ ኮርፖሬሽኑን ቀርቦ በማየት በኩል ድክመት ያለበት ኮንፌዴሬሽን መሆኑን በመግለፅ “የተንሳፈፈ” ሲሉ ወቅሰዋል።

አሰሪዎችን በመወከል አቶ ታደለ ይመርም በጉዳዩ ላይ ሰፋ ያለ ማብራሪያ ሰጥተዋል። የሰራተኛ ማኅበራት ከድርድር ባለፈ ለጋራ እድገትና ተጠቃሚነት መስራት እንዳለባቸው ጠቅሰዋል። አሰሪዎችና ሰራተኞች ከተጠራጣሪነት መንፈስ እንዲላቀቁ መፍትሄ ነው ያሉትን ጉዳይ ዘርዝረዋል።

በአጠቃላይ መድረኩ ሰራተኞችም አለብን ያሉዋቸውን ችግሮች ያቀረቡበት መንግስም ለሰራተኞቹ ጥያቄ ከገቢ ግብር የማሻሻያ ተስፋ ውጪ ሌሎች ጥያቄዎች በአመዛኙ አርኪ ምላሽ ያላገኙባቸው መድረክ ሆኖ ተጠናቋል።¾

Page 14: ንደ3 - ethioforum.orgethioforum.org/wp-content/uploads/2014/01/sendek435.pdfሰንደቅ 9ኛ ዓመት ቁጥር 435 ረቡዕ ታህሳስ 30 2006 አታሚ፤ ብርሃንና

ሰንደቅ 9ኛ ዓመት ቁጥር 435 ረቡዕ ታህሳስ 30 200614 ምልከታ

ከግዛቸው ሙሉጌታberygiz!yahoo.com.

አገሩን የሚወድ፣ በትምህርቱ የበረታ አንድ ኢትዮጵያዊ ትውልድ (ጀነሬሽን) የማነፅና የመፍጠር ተግባር ከፍተኛ ጥረት፣ ቁርጠኝነትና መነሳሳትን ይጠይቃል። ትውልድ በማነፅ ረገድ የስምንቱ ኢትዮጵያውያን ጥረትና ለውጤት መብቃት

ዛሬ ላይ እንዲህ ሲገለፅ ቀላል ሊመስል ይችላል። ገና በሀሳብ ደረጃ ውጥኑ ሲተገበር የመጣበት ሂደትና መነሻውን ወደ ኋላ ተጉዞው ሲቃኙት “ለካ እንዲህ ሩቅ ነበር!” ቢያሰኝም። “ነበር” የተባለው ይህ ጉዳይ ለውጤት እንዲበቃ በማድረግ ትውልድ በማነፅ ሂደት የተደረገውን እንቅስቃሴ ከመነሻው መቃኘት ግድ ይላል።

አሜሪካ ለስራ ጉዳይ በሄድኩበት ወቅት በነበረኝ ቆይታ የቃኘሁት ይህ ትውልድ የማነፅ ጉዳይ ኢትዮጵያውያኑና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የራሳቸውን ሚና በመጫወት ታላቅ ተግባር በማከናወን ላይ እንደሚገኙና የድርሻቸውን እየተወጡ መሆናቸውን ተገንዝቤያለሁ።

በተለያዩ አጋጣሚዎች ወደ ተለያዩ አገራት በተለይም አሜሪካ ዘልቀው ሕይወታቸውን የሚመሩ ለዘለቄታውም እዚያው የሚኖሩ አሁን አሁን ደግሞ እዚህ አገር ቤት በመምጣትና በመመለስ “በኢትዮጵያውያን ጉዳይ፣ በአገር ማንነት ዙሪያ፣ የሚጨነቁ፣ ተፅዕኖና ጫናውን ቢቋቋሙትም የሚያሳስባቸው በርካታ ችግሮች መኖራቸው አይካድም። በተለይም የልጆቻቸው ዕጣ ፈንታ ምን መሆን እንዳለበት? አስተዳደጋቸው ጭምር ጥያቄ እየጫረ መፍትሄ መፈለግ የግድ የሚልበት ደረጃ መድረሱን ተገንዝበው መሆን ባለበት ጉዳይ መጠያየቅና መመካከር አስፈላጊ ነው። በዚህ መሰረት ስምንት ኢትዮጵያውያን በአንድ ግለሰብ ተነሳስተው በመሰባሰብና እርስ በእርስ በመመካከር በልጆቻቸው ጉዳይ የወሰዱት የመፍትሄ አማራጭ ትውልድ በማነፅ ጥረት አርአያነት ያለው ተግባር መፈፀም ችለዋል።”

“ዕድሜ ለአሜሪካ መንግስት!” አሜሪካ የሚገኙ ልጆች በተሻለ የትምህርት አሰጣጥ ተምረው፣ በነፃነት ወይም በልቅ ገደብ የለሽ አስተዳደር በአሜሪካዊ ማንነት ተኮፍሰው የሚያድጉበት ሁኔታ ቢኖርም “ጨዋ” የምንለውን ኢትዮጵያዊ ማንነት ተላብሰው በጥሩ ስነምግባር ታንፀው የሚያድጉም በርካቶች ናቸው። ይህን ኢትዮጵያዊ ማንነት ጠብቀው ልጆቻቸው በጥሩ ስነምግባር ታንፀው እንዲያድጉና የመጡበትን ኢትዮጵያዊ ባህል እንዲያውቁና የተሻለ ትውልድ እንዲፈጠር ለማድረግ የሚደረገው ጥረት በሁሉም ዘንድ ቢተገበር ጠቀሜታው ቀላል የሚባል አይደለም።

አሜሪካ ውስጥ ልጆች ማሳደግ ብዙ ውጣ ውረድና ፈተና ባይኖረውም በልጆቹ ቀጣይ ሕይወት ዘላቂ ማንነትና ብቁ ሆነው እንዲያድጉ ለማድረግ የሚያጋጥሙ ወጣ ያሉ ተግዳሮቶች የየራሳውን ጥላ በማጥላት የሚኖራቸው ተፅዕኖ ቀላል አይባልም። በዚህ ምክንያት የወላጅና የአሳዳጊ ሚና ችግሩን ከመቅረፍ ባለፈ በልጆቻቸው ጉዳይ ትኩረት ሰጥተው በተሻለ ሁኔታ እንዲገነባ ለማድረግ በኃላፊነት መንቀሳቀስን ይጠይቃል። ለዚህም በተናጠል ሳይሆን በአገር ልጅ በወንዝ ልጅ ተሰባስቦ በልጆች ጉዳይ የተደረገው ምክክር ተስፋ በመጫሩ የተጠናከረ ስራ መስራት እንደተቻለ ማየት ይቻላል። ከዚህ በተጨማሪ በአሜሪካ “ከነፃነትና ዴሞክራሲ” ጋር ተያይዞ የሚያገኘው መሰናክሎችና ተግዳሮቶች መኖራቸው ወላጆችን ያሳስባቸዋል።

ሕግ ከፈቀደው ግብረሰዶም ጀምሮ ተገቢ ያልሆነ አደንዛዥ ዕፆችን (Drugs) የመጠቀም ምቹ ሁኔታ መኖሩ፣ መጠጥ መጠጣትና መስከር ከዚያም ባለፈ ወንጀሎችን መፈጸም ምንም ማንም ከልካይ ስለሌለው በአሜሪካ የልጆች አስተዳደግ አሳሳቢ መሆኑ እውነት ነው። ምክንያቱም ዜግነትን ያጎናፀፈው አሜሪካዊነት የሕይወት ሜዳውን ልቅና የተደላደለ በማድረጉ ነው። ታዲያ ኢትዮጵያውያኑ በምን ዕዳቸው ልጆቻቸውን በዚህ ዓይነቱ ልቅ የሕይወት ሜዳ እንዲፈነጩ ይፈቅዳሉ? በትንሽ ጉዳይ ለምን ተቆጡኝ ብሎ 991 ደውሎ ፖሊስ በሚጠራበት አገር ልጅን በኢትዮጵያዊ ባህል እንዴት ማሳደግ ይቻላል? የትውልድ ሀገር ሲመዘዝ ከኢትዮጵያዊ ዘር የተገኘን ልጅ በኢትዮጵያዊ ባህል ኮትኩቶ የተሻለ ሆኖ እንዲታነፅ ምን መደረግ አለበት? እነዚህ ጥያቄዎች ከኢትዮጵያዊ ወላጅ አንጻር እጅግ አሳሳቢ በመሆናቸው መላ መዘየድ ግድ ይላል። ቋንቋን ከመጠቀም ጀምሮ በስራ ምክንያት ጠዋት ወጥቶ ማታ በሚመለሱበት

አገር ባለው የሕይወት ሂደት ልጆችን ገና ከሕጻናት ጀምሮ በመንከባከብ፣ በመከታተል በስርዓት ለማሳደግ የመንግስት ጣልቃ ገብነት መኖሩ በራሱ ችግር መሆኑ አይካድም። ልጅ ሲያልቅስ መቆጣትና መቅጣት በተከለከለበትና፣ ጎረቤት እንዳይረበሽ በጥንቃቄ መኖር ግድ በሆነበት አሜሪካ በልጆች አስተዳደግ ላይ ኢትዮጵያውያኑን በመሰባሰብ፣ በመመካከር መፍትሄ መፈለግ ነበረባቸው። አሜሪካዊ ሆኖ የሚያድግን ልጅ ለማሳደግ የመጀመሪያው ምዕራፍ “ቆንጥጦ ማሳደግ” የሚባልበት ባለመሆኑ ልጅ ወልዶ በማሳደግ ጥሩ ትውልድ ለማነፅ የወላጅ ወይም የቤተሰብ ሚና ወሳኝ በመሆኑ በዚህ ጉዳይ በመመካከር ትኩረት ሰጥተው የተንቀሳቀሱት ስምንት ኢትዮጵያውያን እንቅስቃሴያቸው ለሌላውም በአስተማሪነት ጠቀሜታ ያለው ነው።

ስምንቱ ኢትዮጵያውያን በአለፍገደም /informal/ ግንኙነታቸው ቡና ሲጠጡ፣ ከአገር ቤት መርዶ ሲመጣ ለቅሶ ለመድረስ፣ በአንዳንድ ባህላዊ ክንዋኔዎች እየተገናኙ፣ በመጠያየቅ ግንኙነት ያደርጋሉ። የነበራቸው ግንኙነት የእለት እለት ወይም የአንድ ወቅት መሰባሰብ በመሆኑ ይህንን መልክ በማስያዝ /informal/ ዘልቆ በልጆቻቸው ጉዳይም መመካር ግድ አላቸው። ዓላማው አገሩን የሚወድ በትምህርቱ የበረታ አንድ ኢትዮጵያዊ ትውልድ /ጄኔሬሽን/ የማነፅ፣ የመፍጠር እንቅስቃሴ ሲሆን ጉዳዩ ለነገ የሚባል አልነበረም። በአንድ ዘመን እዚህ አገር ቤት በትምህርት ቤትም፣ በኮሌጅም፣ በዩኒቨርስቲም የሚተዋወቁ እነዚህ ስምንት ኢትዮጵያውያን የጀመሩትን የአለፍገደም /informal/ ግንኙነት እንዲጠናከር ጎልብቶም በትውልዱ ላይ ውጤት በመምጣት የራሳቸውን አሻራ ለማስቀመጥ ተመካከሩ። እነኚህ ስምንት ኢትዮጵያውያን አሜሪካ ሜትሮፖሊታንት ዋሽንግተን አካባቢ ከአስር ዓመታት ባላነሰ በመኖር የተሻለ ህይወት ይመራል። የልጆቻቸው ጉዳይ ግን አሳስቦአቸው መከሩ፤ ተነጋገሩ። አወጡ አወረዱና “አብረን እንሁን መረዳጃ ማህበር!” እ.ኤ.አ. በ2006 ዓ.ም መሰረቱ። ቀደም ሲል የጀመሩትን የመጠያየቅ የአብሮነት ግንኙነት በተሻለ ሁኔታ እንዲቀጥል፣ በልጆቻቸው ጉዳይ በማተኮር፣ ልጆች ኢትዮጵያዊነትን እንዲላበሱ፣ በኢትዮጵያ ባህል እንዲታነፁ፣ የአገራቸውን ባህል፣ ታሪክ፣ ቋንቋ እንዳይዘነጉ የማድረግ በአጠቃላይ በልጆቻቸው አዎንታዊ አስተዳደግ ዙሪያ፣ በመረጃ ልውውጥ፣ በስኮላርሽፕና፣ በተሻለ የትምህርት ተሳትፎ ትኩረት ሰጥተው በመንቀሳቀስ ተሳፎአቸውን አጠናክረው ቀጠሉ። አሜሪካ ባለው ገደብየለሽ ነፃነት፣ ልቅ የሆነ አኗኗር ዘዴ ልጆችን እንዴት በተሻለ ሁኔታ ማሳደግ እንደሚቻል ማሳሰቡ ብቻ ሳይሆን ከመጥፎ ልማዶች ርቀው፣ ከአባታዊ ክትትልና ከባህልና ምክር ባለፈ በዕለት ተዕለት ክትትል በጥሩ ሁኔታ ለመቅረፅና ለማስተካከል፣ በተለይም ችግሩ ከመከሰቱ በፊት ለማስተካከል የማህበሩ አባላት ትልቅ እንቅስቃሴ አድርገዋል። የማህበሩ ዓላማን በማሳካት ስምንቱ ኢትዮጵያውያን ዛሬ ቁጥራቸው ጨምሮ በሰሩት ሥራ በአርአያነት ሲጠቀሱ በውጤቱ አድናቆት አግኝተዋል።

በዚህ መሠረት ስምንቱ ኢትዮጵያውያን ትውልድ ለማነፅ መነሻው የየራሳቸው ልጆች በመሆናቸው የመነሻ ሀሳቡን ከወጠኑት ግለሰብ ጋር በመሆን ምን እናድርግ? በማለት ተነጋገሩ። የእነዚህ ስምንት ኢትዮጵያውያን ትውልድ የማነፅ ጥረት የሀሳቡ ጠንሳሽ አቶ ዘለቀ ደለሳ ዳዲ (ዘለቀ ዳዲ) ይባላሉ። ማህበሩን ከመመስረት ጀምሮ ያከናወኗቸው ተግባራት ለኢትዮጵያውያንም ኩራት በመሆናቸው ከማድነቅ ባለፈ ለሌሎችም ተሞክሮ ስለሚሆን እንደሚከተለው አቅርቤዋለሁ።

“አብረን እንሁን መረዳጃ ማህበር” ባለፈው ዓመት (2005 ዓ.ም) ማህበሩ የተማሪዎች ማበረታቻ ቀን ባከበረበት ወቅት አባላቱ ሰፊ ተሳትፎ ማድረጋቸውን የአሜሪካ ድምፅ ሬዲዮ የአማርኛ ክፍል ባልደረባ አቶ አዲሱ አበበ ማህበሩን አስመልክቶ ከመስራች አባላት መካከል አቶ ቴሶ ቆሳን እና አቶ ደመቀ ስዩምን ስለማህበሩ አነጋግሮአቸው ነበር። ለመሰበሰባቸው ምክንያትና በማህበር ለመደራጀት ግፊት ያደረጉት አቶ ዘለቀ ዲዳ ትኩረት በመስጠት እንደተንቀሳቀሱ ማህበሩ በማንነት የሀገር ሀብትና ባህላዊ እሴቶችን በማበልፀግ ውጤታማ በመሆን ላይ እንደሚገኝ አስረድተዋል።

ማህበሩ ከተቋቋመበት ዋንኛ ዓላማ መካከል ልጆች መገኛ የአገራቸውን ባህልና ቋንቋ እንዳይረሱና የሁለትና ከዚያ በላይ ቋንቋ ተናጋሪ መሆን ለትምህርታቸውና ለህይወታቸው ተወዳዳሪ ስለሚያደርጋቸው፤ ለዚህ ስኬት የአባላት ልጆች ተከታታይነትና ቀጣይነት ያለው የአማርኛ ቋንቋ መናገር፣ መፃፍ፣ ማንበብና መስማት እንዲችሉ ማብቃት፣ የመገናኛ አገራቸውን ጂኦግራፊ ታሪክ መለያ የሆኑ ባህላዊ ክዋኔን የሚመለከቱ ትምህርቶችን

መስጠት ነው። በዚህ ዓላማ መሠረት የአባላት ልጆች የአማርኛ ቋንቋ መናገር መፃፍ ማንበብና መስማት እንዲችሉ ደረጃውን የጠበቀ ትምህርት መስጠት የተቻለ ሲሆን ለአባላት ልጆች የኢትዮጵያን ልዩ ገፅታ፣ መለዮ ባልና ታሪክ እንዲያውቁ በመረጃ ላይ የተደገፈ ትምህርት ተሰጥቷል። ከዚህ በተጨማሪ በአባላት ልጆች በትምህርት፣ በባህሪና በድርጊት መበልፀግና ለከፍተኛ ስኬት መብቃት የእናቶች ሚና ወሳኝ አስተዋፅኦ ያለው መሆኑን በመረዳት ይህንኑ ተግባር በአባላት መካከል ለማስረፅና ለሌሎች ወገኖችም በትምህርትነቱ ለማስተላለፍ የሚረዳ ዝግጅት እየተካሄደ ይገኛል። ማህበሩ የአባላት ልጆች በትምህርታቸው ተግተው በባህሪያቸው የታረሙ እንዲሆኑ በቤተሰብም ሆነ በማህበረሰብ ደረጃ ሁለገብ ድጋፍ ያደርጋል።

በማህበሩ ዓላማ እንደተገለፀው ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ልጆቻቸው በትምህርት እንዲታነፁ፣ እንዲጎለብቱ፣ ልጆች የአገራቸውን ባህል፣ ታሪክ፣ ቋንቋ እንዳይዘነጉ ማድረግ የአማርኛ ፊደል መፃፍና ማንበብ እንዲችሉ ማስተማርና ስልጠና በመስጠት ማብቃት (ብቁ ማድረግ ነው)። በዚህም የተሻለ አንድ ኢትዮጵያዊ ትውልድ /ጄኔሬሽን/ የማነፅ ትልቅ ስራ መስራትና ይህንን ዓላማ ማሳካት ዋናው ጉዳይ ነው። በዓመት አንድ ጊዜ በሚካሄድ ዝግጅትና ስነሥርዓት ለአንድ ወር የሰለጠኑ ልጆች የምስክር ወረቀት ተሰጥቷቸዋል። ይህ የምስክር ወረቀት በሀገሪቱ የትምህርት ስርዓት ተቀባይነት ያለው ሲሆን በዚህ ከመቶ ኢትዮጵያዊ ቤተሰብ ያላነሰ ተጠቃሚ ሆኗል። ማህበሩ አባላትና ልጆቻቸው ለኮሚኒቲ የገንዘብ፣ የማቴሪያል የዕውቀትና የጎልበት ነፃ አስተዋፅኦ በማድረግ የዜግነት ሚና መጫወት ላይ ይገኛሉ።

ከስምንት መስራቾች ወደ አስራ አምስት አባላት ያደገው ይህ የኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ማህበር የቤት ለቤት ክትትልና እገዛ በማድረግ በየወሩ አንድ ቀን በአባላት ቤት በመዘዋወር ቆሎና ለስላሳ ተይዞ በልጆች አስተዳደግ ላይ ምክክር ይደረጋል። በየቤቱ ያለውን የልጆች አስተዳደግ በመመልከት ውይይት ይካሄዳል። ከዚህ ጋር በዕድር እርስ በእርስ በመተጋገዝ፣ በመጥፎ ጊዜ፣ በሞት

ትውልድን የማነፅ ጥረት

በአሜሪካ!ወቅት አስክሬን ወደ አገር ቤት የመላክ፣ በቅርብ ተገኝቶ ማስተዛዘንና ተጎጂውን ግለሰብ የማገዝ ተግባር በማህበሩ ይከናወናል።

ከዚህ በተጨማሪ ኢትዮጵያውያን ተቀባይ ብቻ አለመሆናቸውን ለማሳየት ከሞንትጎመሪ ካውንቲ ሆምለስ መ/ቤት ጋር በመተባበር ካሁን ቀደም ሲደረግ የቆየውን ከድርጅቱ ተጠቃሚ በመሆን ለሚገኙ ቤት የለሽ ግለሰቦች ወደ ማህበረሰቡ ዘልቀው Community out reach በሚል ወደ 200 የሚጠጉ ቤት አልባዎችን ዘንድ በመሄድ የቁርስ ግብዣ በማዘጋጀት፣፣ ቁርስ አብሮ የመብላት ስነስርዓት አካሂደዋል። ይህ ተግባር ኢትዮጵያውያን ተቀባዮች ብቻ ሳይሆኑ ይሰጣሉ፣ መስጠት ይችላሉ አስብሏቸዋል። ከዚህ ጋር /NIN (National institution of Health) ጋር በመተባበር በተለያዩ ህመም ተጠቅተው የህክምና ክትትል በማድረግ ላይ ለሚገኙ ህፃናት በቀጥታ በመገናኘት በተቋሙ ለሚገኙ ልጆች የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ስራ ተሰርቷል።

የማህበሩ አባላት በትምህርት ጉዳይ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመገናኘትና፣ በመነጋገር የልጆቻቸውን የትምህርት ይዞታ ይከታተላሉ፣ ትኩረት ይሰጣሉ። በክትትሉ ትውልድ የማነፅ ተግባር ተከናውኗል። በአካባቢው አካል (locals) ፖሊስ ጽ/ቤት ጋር በልጆቻቸው ጉዳይ በቅርብ ውይይት ያደርጋሉ። የማህበሩ አባላት “በራስ ገንዘብ ልጆቻችንን የማዳን ስራ ነው የምንሰራው፤ ማህበሩ ከሌሎች ማህበራት የሚለየው በልጆችና ልጆች ላይ ብቻ ማተኮሩ ነው።” ይላሉ በእርግጥም የልጆቹን ስኬት የማይፈልግ ወላጅ ስለሌለ የተነሱበት ጉዳይ ትልቅ ተልዕኮ የያዘ በመሆኑ ሊበረታቱ ይገባል። የአብረን እንሁን አባላትና ልጆቻቸው ከአሜሪካውያን ጋር አብሮ መኖርና የመስራት፣ የችግር አፈታት በጥልቅ እንዲገነዘቡና በሂደትም ሰላማዊ ውህደት እንዲያደርጉ የመርዳት እንዲሁም የአብረን እንሁን ራዕይና አስተዋፅኦ ለኮሚኒቲው በማስተዋወቅ ሰፊስራ ተሰርቷል።

የማህበሩ አባላት በየወሩ እየተገናኙ በልጆቻቸው ዙሪያ መምከራቸው መወያየታቸው ልጅ የአባቱን ፈለግ እንዲከተል እንዲሆን አባትም ለልጆቹ ጥሩ አርአያ እንዲሆን የማስቻል ስራ በመስራት በመሆኑ የመሰባሰባቸው ምክንያት ለሌላውም ኢትዮጵያውያንም ተሞክሮአቸውን በመጋራት መተግበር ያስፈልጋል።

ማህበሩ በልጆች ዙሪያ ቢያተኩርም እናቶችንም አልዘነጋም። የእናቶች ሚናም የላቀ በመሆኑ በልጆች አስተዳደግ ድርሻቸው እንዲጎለብት ተሳትፎ ይደረጋል። በዓመት አንድ ቀን በሚከበር የእናቶች ቀን ምስጋና እና ስጦታም ይደረጋል። እናቶች በልጆች አስተዳደግ የበለጠ አስተዋፅኦ እንዲኖራቸው ምቹ ሁኔታም ተፈጥሯል።

የማህበሩ አባላት ልጆችም ሆኑ ኢትዮጵያውያን ልጆች በተለይም ትልልቆቹ አሁን በደረሱበት ዕድሜ ሁለተኛ ዲግሪ /MA/ እያገኙ በመሆኑ በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በአፍሪካ ጭምር የበጎ አገልግሎት ስራ እንዲሰሩ የማድረግ እቅድ ተይዟል። ይህም በቀጣይነት ለመተግበር ትኩረት ተሰጥቷል። በአሜሪካ ህግ ከትምህርት በኋላ በወጣትነት የሚሰጠውን የነፃ አገልግሎት ኢትዮጵያ ውስጥ ለመስጠት የተያዘው ዕቅድ ተስፋ ሰጪ ነው። ልጆቹ ለሚሰለጥኑበትና በተለያዩ ቦታዎች ለሚያበረክቱት አገልግሎት በማህበሩ የሚሰጣቸው ስልጠናን ጨምሮ የድጋፍ ደብዳቤ ስለሚሰጣቸው በየዩኒቨርስቲውና ለሌላ የስራ ዕድል ተቀባይነት በማግኘት የተሻለ ጥቅምና ዕድል እንዲያገኙ ተደርጓል። አሜሪካ ሰፊ አገር ናት። በዋሽንግተን ዲሲ የሚኖረው ኢትዮጵያዊ ቁጥሩ ቀላል ባለመሆኑ አማርኛ በብሔራዊ ቋንቋነት አገልግሎት ላይ ውሏል። በየግዛቶቹ ያለው ኢትዮጵያዊ በፖለቲካ አመለካከት ያለው ልዩነት እጅግ አነጋጋሪ ቢሆንም ስጋት አይደለምና ይህን አቻችሎ በኢትዮጰያዊነት መሰብሰብ ጥሩ ነው እላለሁ። በማህበር ደረጃ የበለፀገ ዕድሜ ወይም የበረከተ ጊዜ የተቆጠረለት ማህበር አለ ባይባልም በልጆች ጉዳይ ያተኮረው ሜትሮፖሊታን ዋሽንግተን አካባቢ ነዋሪ ኢትዮጵያዊያን የተመሰረተው ማህበር ግን ይደግ ይመንደግ ያስብላል። የነጠረ ዓላማ ሳይኖር በፖለቲካ ጉዳይ በመሰባሰብ የሚገነባ ማህበር ወዲያው ሲፈርስ በሚስተዋልባት አሜሪካ በልጆች ጉዳይ የተንቀሳቀሰው ይህ ማህበር ግን ከስድስት ዓመታት በላይ ዘልቆ ለውጤት መብቃቱ ሊበረታታም ይገባል።

በመጨረሻ ትውልድ በማነፁ የስምንቱ ኢትዮጵያውያን ጥረት በጎ ጅምር በመሆኑ ድጋፍና እገዛ እንደሚፈልግ ኤምባሲያችንም ቢሆን ጥረቱን ቢያንስ ቢያደንቅ። ይህ ትውልድ የማነፅና ኢትዮጵያዊነትን የማስረፅ በጎ ጅምር ተጠናክሮ እንዲቀጥል ሌሎቹም ቢተገብሩት መልካም ነው እላለሁ።n

Page 15: ንደ3 - ethioforum.orgethioforum.org/wp-content/uploads/2014/01/sendek435.pdfሰንደቅ 9ኛ ዓመት ቁጥር 435 ረቡዕ ታህሳስ 30 2006 አታሚ፤ ብርሃንና

ሰንደቅ 9ኛ ዓመት ቁጥር 435 ረቡዕ ታህሳስ 30 2006 15

ኪነጥበብ-ዜና በአሸናፊ ደምሴ

በአሸናፊ ደምሴ ......... [email protected]

ያዛት። (ያኔ ይሆን እንዴ የአበራሽን ጠባሳ ያየ በእሳት አይጫወትም የተባለው?) ታዲያ ይሄኔም ሴትየዋ ቅኔ አላጠራትም፤

አይሰማም ብዬ እንዴት በጉድ ወጣሁመንጠልጠያ ባገኝ ከሰማይ በወጣሁመውረጃ ባገኝ ከምድር በገባሁ። በማለት አለቀሰች ይባላል። የሴትየዋን ሐዘን እና ጭንቀት

ያስተዋሉት አፄ ቴዎድሮስም ምህረት አድርገው ብርና አሽከር ሰጥተው አሰናበቷት ይባላል።

ጐበዝ አስተዋይ መሪ እና ብርቱ ምርኩዝ አያሳጣን። አዲስ መንገድ የሚያሳየንን መሪ ማማረር፣ አዲስ ዕውቀት የሚጨምርልንን መምህር ማንጓጠጥ፣ አዲስ ጤና የሚለግሰንን ዶክተር መሸወድ ግን መዘዙ ብዙ ነው። “…. ምን ቢሸፍት፣ እጓሮ ድረስ ነው” እንዲሉ ከዕውቀትም፣ ከስልጣንም፣ ከሀብትም ምንም ሳይኖረን የሚመራንን ማማረር በራሳችን ላይ መዘዝ እንደመምዘዝ ይቆጠራል።

መጋቢ አእላፍ መክብብ አጥናው “የአባቶች ጨዋታ” በሚል በሰየሙት መፅሐፍ ውስጥ የምትከተለዋን ታሪክ አስፍረው እናገኛለን።

በኢትዮጵያ ወሎ ክፍለ ሀገር ውስጥ ጃማ-ወረይሉ በሚባል አውራጃ ጅባት ተብሎ የሚጠራ ሰፊ ሜዳ የሰው ዘር የማይታየበት ገና ያልቀና አካባቢ ነበር። ዛሬ በካሪቢያን አገር ጀማይካ ተብሎ የተሰየመው ታላቅ ደሴት ከዚህ ስም የተወረሰ ነው። ታዲያ ያን ሜዳ አቋርጦ ለመሄድ ብዙ ሰዓት መጓዝን ይጠይቃል። የማየት ችግር የነበረበት አንድ ሰው በዚያ ቦታ ጉዞ ላይ ሳለ መሪውን ተጣልቶት እስስቱን /ጉረሮውን አንቄ ልግደል አለ። መሪውም አዝኖለት “እረ እባክህ በረሃውን አቋርጠን እስክናልፍ ድረስ እንኳ ታገሰኝ” ብሎ ቢለምነው የማይበገር ሆኖ “ካንተ ጋር አልሄድም፤ ፈጽሞ አትንካኝ” አለው። መሪውም ግራ ገብቶት “የስካር ጉዳይ ይሆናልና እስኪያልፍለት ልጠብቅ” ብሎ በርቀት ሲጠብቀው ቆየ። የማየት ችግር ያለበትም ያ ሰው ወዲያና ወዲህ እየተወራጨ ብዙ ጊዜ ሲንገላታ ቆይቶ፣ ግራ ሲገባው መሪው ተመልሶ ቢመጣለት ይቅርታ ሊጠይቀው ተመኘ። መሪውም ራርቶለት፤ ተመልሶ መጣለትና ታርቀው እንደ ገና ጉዞ ጀመሩ ይሉናል። አልፎ-አልፎም ቢሆን እንዲሁ ለመሪው አስቸጋሪ የሆነ ተመሪ ወይም ለተመሪው አስቸጋሪ የሆነ መሪ በየዘርፉ ሊያጋጥም ይችላል። አንድዬ ብቻ መሪ የሌለው ጨንባሳ፣ ምርኩዝ የሌለው አንካሳ ከመሆን ይሰውረን፤ ቸር እንሰንብት።¾

መሪ እና ምርኩዝ የሌለውመሪውን

የሚያስቸግር ሕዝብ፣

የሚመራውን

ህዝብ የሚያስለቅስ

መንግስት፣

መምህሩን

የሚያስቸግር ተማሪና

ዶክተሩን የሚሸውድ

በሽተኛ ሁሉም

አንድ ናቸው፤

ዳፋው ለራሳቸው

የሚደርሳቸው

ይሆናልና

2000 ሀበሻ የተሰኘው የባህል ምግብ ቤት በ59 ሚሊዮን

ብር ባለስድስት ፎቅ ህንጻ ሊያስገነባ መሆኑን አስታወቀ። በ370 ካሬ ሜትር ላይ የሚገነባው ይህ ህንፃ የኢትዮጵያን ባህል ከሚስተዋወቁም በተጨማሪ ለበረካታ እንግዶች አማራጭ ማረፊያ ይሆናል ሲሉ የ2000 ሀበሻ ባህላዊ ሬስቶራንት ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ነጋሲ ገ/ማርያም ተናግረዋል።

ካሳና ልጆቹ ከተሰኘ የህንጻ ተቋራጭ

ጋር ባሳለፍነው ሐሙስ የፊርማ ስነሥርዓቱን ያደረገው 2000 ሀበሻ የባህል ምግብ አዳራሽ፤ ህንጻው ተገንብቶ ሲጠናቀቅ 40 የመኝታ ክፍሎች፣ 26 መኪናዎችን በአንድ ጊዜ ማስተናገድ የሚችል ፓርክ እና ከ120 ያላነሱ ተሰብሳቢዎችን ማስተናገድ የሚችል የስብሰባ አዳራሽንም እንደሚያካትት ተናግሯል።ሆቴሉ አዲስ በሚወጣው የሆቴሎች ደረጃ ልኬት ላይ ሲቀመጥም ባለ ሶስት ኮከብ ይሆናል ተብሎ እንደሚጠበቅ ለማወቅ ተችሏል።n

ስላለፈውም ሆነ ስለመጪው በዓል እንኳን አደረሰን ብንባባል ትዝብት ላይ እንደማይጥለን ተስፋ እናደርጋለን። እንደምን ሰነበታችሁ ወዳጆቼ?!... የበዓል ግርግር እንዴት ይዟችኋል? እኔ የምለው ሰው ግን ያለ ዓመት በዓል ሰሞን ግብይትን አያውቅም እንዴ?... ምን ይደረግ ለሁሉም ነገር ምክንያት ፈላጊዎች

ሆነናል። ሥጋ ለመብላት ምክንያት፣ ዶሮ ለማረድ ምክንያት፣ በሬ ለመጣል ምክንያት ይኸውና ደግሞ አሁን-አሁን ቡና ለማፍላት እራሱ ምክንያት ያስፈልገናል ብለናል። ዳሩ ምን ያደርጋል ኑሮ ለሚመራው ሕዝብ የሥጋ ነገር ስጋትን እንጂ አምሮትን የሚፈጥር አልሆነም። (እዚህች’ጋ የምንናገረው ነገር አለ፤ የባንኮቹ ማስታወቂያ ሁሉ “መቼም ሀበሻ መደጋገፍ ልማዱ ነው፤ ከወዳጅ ዘመድዎ ብር እየተላከልዎ ስለሆነ በባንካችን በኩል ይቀበሉ” አይነት የዕርዳታ ድምፅ እየበዛ ነው ያልከው ወዳጄ? እኛ የምንልከው ሚጥሚጣና በርበሬ አልታየም ለማለት እንደሆነ ገብቶኛል።)

እስቲ ደግሞ ወደዛሬው ትዝብታዊ ወጋችን እንመለስ፤ ለመምራትም ለማስረዳትም የቸገረ ነገር ገጥሟችሁ ያውቃል? አሁን ዕለት “ይሄን ሕዝብ ከማስተዳደር እኮ ጉንዳን ማሰለፍ ይቀላል” ሲሉ የእኛ ሰፈር ዕድር ሊቀ-መንበርን ምሬት ሰምቼ ገረመኝ። ለካ እድርም ለአመራር ያስቸግራል ጐበዝ? መምህሩን የሚያደናብር እና የሚያስቸግር ተማሪ ገጥሟችሁ ያውቃል? ይህን ሲያስተውል ወዳጄ “ከዕውቀት ነፃ የሆነ ትውልድ” ይል ነበር። ዶክተሩን የሚያጭበረብር ታካሚ ቢገጥማችሁስ ምን ትሉታላችሁ?...

መሪውን የሚያስቸግር ሕዝብ፣ የሚመራውን ህዝብ የሚያስለቅስ መንግስት፣ መምህሩን የሚያስቸግር ተማሪና ዶክተሩን የሚሸውድ በሽተኛ ሁሉም አንድ ናቸው፤ ዳፋው ለራሳቸው የሚደርሳቸው ይሆናልና። እዚህች’ጋ አንዲት ጨዋታ ትዝ አለችኝ።

ሰውዬው በአተነፋፈስ ችግር ምክንያት ሆስፒታል ገብቶ እያገገመ ነበር። ሲጋራ ያጨስም ስለነበረ ዶክተሩ ደጋግሞ ማጨሱን እንዲያቆም ይመክረዋል። ታካሚውም ዶክተሩን “እሺ” ይበለው እንጂ በድብቅ ወጣ እያለ ያጨሳል። ታዲያ አንድ ቀን እንደለመደው ሰው አየኝ አላየኝ ብሎ ሲጃራውን ቡንንን ሲያደርግ ሐኪሙ ከች ይልበታል። ዶ/ር - “ምነው? በሽታህን እያወከው እንዴት ሲጋራ ታጨሳለህ?”ታካሚ - “ምን ላድርግ ዶክተርዬ”ዶ/ር - “እንዴት ምን ላድርግ ትላለህ አታጭስ ብዬህ አልነበረ?”ታካሚ - “ዶክተርዬ እርስዎ ሲያጨሱ አስቀኑኝ እኮ”(ታማሚው ይህን ያለው ዶክተሩ ሲያጨሱ ደጋግሞ ይመለከታቸው ስለነበረ ነው)ዶ/ር - “ታዲያ እኔ ባጨስ በአንተ ሳንባ መሰለህ እንዴ?” ብለውት እርፍ። (ጨው ለራስህ ስትል ጣፍጥ ማለት እንግዲህ እንዲህ ነው)

እናላችሁ በእኛ ስር ሆነው ለእኛ የማይመቹ ስንቶች መሰሏችሁ። እዚህ’ጋ ተመሪዎች ብቻ ሳይሆኑ መሪዎችም በእኛ ስር ናቸውና ለሚመሩት ሕዝብ አይመቹም ብለን ልንታዘባቸውና ልንቦጭቃቸው እንደምንችል ማስታወስ ግድ ይላል።

ትዝብታችንን በጨዋታ ለማጣፈጥ ያክል አንዲት ወግ እናንሳ፤ በታሪክ ተመዝግቦ እንደምናገኘውና ጋዜጠኛ ጳውሎስ ኞኞ እንዳስነበበን ይታወቅልኝ። አፄ ቴዎድሮስ እናቷን፣ አባቷን፣ እህቷንና ወንድሟን በእሳት አቃጥለው የፈጁባት አበራሽ የምትባል የሸዋ ሴት በንጉሱ ስራ እርር ድብን በማለቷ የሚከተለውን ተቀኝታ ነበር፤

ሺ ፈረስ ከኋላ ሺ ፈረስ ከፊቱሺ ነፍጥ በኋላ ሺ ነፍጥ በፊቱይህን ሳታይ ሞተች ኮሶ ሻጭ እናቱ።በሸዋ በትግሬ የተቀመጣችሁ በጎጃም በላስታ የተቀመጣችሁአንድ ዛላ በርበሬ መንቀል ተስኗችሁበሉ እንዲህ ቆጥቁጦ ለብልቦ ይፍጃችሁ። (እውነቱን ለመናገር ይህቺ ሴት በአፄው የተናደደችው

ንዴት ቦአዚዝ በቱኒዚያው መሪ ላይ ከተናደደው ቢልቅ እንጂ አይቀልም።)

ታዲያ ይህን በደሀ አደግነታቸው ላይ የሚዘባበት ግጥም የሰሙት አፄ ቴዎድሮስ፤ “ካሳ አንድ ለእናቱ! የአበሻ ባል! የእየሩሳሌም ውሽማ!” በማለት ፎከሩ። ሴትየዋንም ወታደሮች ልከው ካለችበት አስመጧት። የአፄውን ፊት ስታይ አበራሽ ብርክ

“2000 ሀበሻ”ባህልን ማስተዋወቅ የሚያስችል ባለ3

ኮከብ ሆቴል ሊገነባ ነው

26 መኪናዎችን

በአንድ ጊዜ ማስተናገድ

የሚችል ፓርክ

እና ከ120 ያላነሱ

ተሰብሳቢዎችን

ማስተናገድ የሚችል

የስብሰባ አዳራሽንም

እንደሚያካትት

ተናግሯል

Page 16: ንደ3 - ethioforum.orgethioforum.org/wp-content/uploads/2014/01/sendek435.pdfሰንደቅ 9ኛ ዓመት ቁጥር 435 ረቡዕ ታህሳስ 30 2006 አታሚ፤ ብርሃንና

ሰንደቅ 9ኛ ዓመት ቁጥር 435 ረቡዕ ታህሳስ 30 200616 5

ኪነ-ጥበብ እና ባህል

በጥበቡ በለጠ

ታላቁ ባለቅኔ ከበደ ሚካኤል ‘ስልጣኔ ምንድን ነች?’ የሚል መፅሀፍ ከብዙ ዓመታት በፊት አሳትመዋል። ቀዳማዊ ኃይለስላሴ በደርግ እስር ቤት ውስጥ ይህችን መፅሀፍ ደጋግመው ሲያነቡ በወቅቱ የተቀረፀው ምስላቸው እማኝ ነው። እናም ስልጣኔ ናፋቂ ህዝቦች መሆን አለብን። የሠለጠኑ ህዝቦችንም ማክበርና ምሳሌነታቻቸውን መቀበል ያስፈልጋል። ታዲያ ስልጣኔ ምንድን ነው የሚለው መመለስ ያለበት ጉዳይ ነው።

ዛሬ አጠገባችን መጥተው የተዋለዱን ያህል አብረውን ያሉት ቻይናውያን ማንነታቸውን፣ ባህላቸውን ጠብቀው የስልጣኔን ጎዳና ከያዙት ቆይተዋል። ሰፍር ቁጥር የሌላቸው ችግሮችን እየተጋፈጡ መፍትሄም እየሠጡ ዛሬ የደረሡበት ደረጃ ላይ ለመብቃት የታደሉት እነዚህ ህዝቦች ለኛ ምሣሌ ሊሆኑ ይችላሉ።

እኛ ኢትዮጵያውያን ደግሞ ስልጣኔዎች በወቅቱ እየመጡልን አለመታደል ሆኖ ደግሞ እንደገና ይከስማሉ። አክሱም ላይ የታየው የስልጣኔ ማማ የት ገባ? ዛጉዌዎች ያሳዩን ስልጣኔስ የት ገባ? ጎንደር ላይ የታየው ፍፁም ዘመናዊነት እንዴት በነነ? እያልን ከነዚህ ተመክሮዎች በመነሣት ራራሣችንን መፈተሸ አለብን።

ዛሬ ምዕራብ አውሮፓ የሚባለው፣ በስልጣኔውም የሚጠቀመው ክፍለ አህጉር ለምን እዚህ ደረጃ ደረሠ? የትኛው ዘመን ነው እንዲያፈተልክ ያደረገው? እኛ ደሃ እነሡ ባለፀጋ ያደረጋቸው ሀይል ምንድን ነው? እንዲህ በምንም መለኪያ ሊወዳደር የማይችል የኢኮኖሚ ወይም ሰው የመሆን ሁኔታን ልዩነት ያመጣው ምንድን ነው? ሁልጊዜ ማጥናት መመራመር ያለብን ርዕሰ ጉዳይ ነው ነገሩ።

ታህሣስ ወር 1991 ዓ.ም እኔና የዛሬው የደራሲያን ማህበር የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባሉ ደራሲ አፈወርቅ በቀለ አንድ ጥናት አቅርበን ነበር። ርዕሱ “የዘመን ‘ባሮክ’ /ኒዮ ክላሲካል/ ሥነ-ጥበብ፣ ኪነ-ጥበብ /Art/፣ ሙዚቃ እና ሥነ ፅሁፍ” የሚል ሲሆን ርዕሠ ጉዳያችንን ወደ አውሮፓ ወስዶ ቆይታችንንም እዚያው ያደርጋል ጥናቱ።

ባሮክ የሚባለው ዘመን በተለይ ምዕራብ አውሮፓ ተሸቀንጥራ ወደ ስልጣኔው ጎራ የተቀላቀለችበት ወይም እመርታ ያሳየችበት ነው። እናም ዘመኑ ለኛም ትምህርት ሰጭ ስለሆነ በጥቂቱ ልቃኛው ፈለኩኝ። የስልጣኔውን ደርዝ ያመላክተናል የሚልም እምነት ስላለኝ ነው።

ከመካከለኛው ክ/ዘመን ጀምሮ እስከ 17ኛው መቶ ክ/ዘመን መዳረሻ በአውሮፓ ማህበረሰቡ በአደረጃጀቱና ከነበረበት መስመር ውጭ ብሎም በአለም አቀፍ ሁከቶች የተሞላ ነበር።

በሌላ መልኩ ግን አዳዲስ ፍልስናዎች ማለትም ህልውናት /Existentialism/፣ ፅንፋዊነት Extremism/፣ ሥነውበት /Aesthetic/፣ ዳሣሽነት /Empiricism/፣ ሁለንተናዊነት /universality/፣ አብርሆ /Enlighten/፣ ምኩናዊነት /Rationalism/፣ ፈንጋጣ /Deviation/፣ ደብተራዊነት /Clericalism/፣ ህውስታዊነት /Sensationalism/ ወዘተ ...

በየአቅጣጫው ብቅ ያሉበትን ለስርፀታቸውም ትግል የተደረገበት ወቅት እንደነበር ከታሪክ መረዳት ይቻላል።

ይህ በእንዲህ እያለ የዘመኑ ታላላቅ ክህሎት ያላቸው ሠዎች የማህበረሰቡን መጣጣም አቅጣጫ እያስያዙ ተምህሮትን /Scholasticism/ መሰረት በመጣልና ከፍ በማድረግ አለምን በሁለንተናዊ መልኩ ለሠው ልጆች ጥቅምና ደህንነት ለማዋል የሚያስችሉ ህግጋትን በመቀመር በኪነ-ጥበብ፣ በሥነ- ፅሁፍና በሙዚቃ ድንቅ የተባሉ ውጤቶችን ለማምጣትና ከፍተኛ ደረጃ ላይም ለመድረስ ችለዋል።

ሥነ-ጥበብ በጥቅሉና ኪነ-ጥበብ፣ ሥነ ፅሁፍ እንዲሁም ሙዚቃ በዝርዝር፣ የሰው ልጆች አበይት ክንውኖች ናቸው። እነዚህን ክንውኖች ደግሞ የሠው ልጅ በቅደም ተከተል በታሪኩ ይመዘግባቸዋል። ለተተኪው ትውልድም ያስተላልፏቸዋል። ተተኪው ትውልድም በዚሁ ላይ በመመስረት የፈጠራ ክህሎቱን ከፍ አድርጎታል።

የኪነ-ጥበብ ፈለጎችን፣ ንቅናቄዎችን፣ መንገዶችንና ፍሰቶችን፣ የተነሡበትን ዘመን፣ ጊዜና ወቅት፣ እንደተከሰቱትና እንዳስከተሉት ለውጥ ያስቀምጣቸዋል። ለዚህም በመነሻነትና በምንጭነት በሚያጣቅስበት ልዩ ልዩ ዘዴ ይፈጥራል። ለምሣሌ ጊዜው በዘመኑ ታላቅ የፈጠራ ክህሎት ባለው ሠው እንዲጠቀስ ከተፈለገ ግለሠቦችን መሠረት በማድረግ በሆመርና፣ የሞዛርት ጊዜ ወይም ዘመን ይለዋል። ሊያጣቅሠው የፈለገው በዘመኑ ርዕስ ከሆነ የመካከለኛው፣ የሬናይሠንስ እያለ፣ ክስተቱን ከሰው ልጆች አበይት ጉዳይ ጋር ማያያዝ ሲፈልግ ደግሞ ፍልስፍናዊ፣ አሳዛኝ፣ ታሪካዊ፣ ጂኦግራፊያዊ ሁኔታ ለማመልከት ደግሞ የግሪክ፣ የፈረንሳይ እያለ በሌላ በኩል ደግሞ ታዳሚ የነበረውን ህብረተሠብ ለመዘከር ሲፈልግ የከፍተኛውን፣ የመካከለኛውን ማህበረሰብ በማለት እየለየ ያስቀምጣቸዋል።

ከዚህ በመነሣት የዘመነ ባሮክ ስነ-ጥበብ፣ ኪነ-ጥበብ ሥነ-ፅሁፍ ሙዚቃ በአጭሩ ለመመልከት ጥረት ያደርጋል። የዚህም የመንደርደሪያ ፅሁፍ አላማ በአውሮፓ ከስነ-ጥበብ ደግሞ ልደትን እያሣየ ዘመነ ባሮክን ወይም የ17ኛው መቶ ክ/ዘመንን ጥበባቸውን ያሣየናል። በዚሁ ዘመን የኛንም ሀገር ሁኔታ በአዕምሮችን እናስብ።

በዚሁ በዘመነ ባሮክ Louis XII እና Louis XV ይጠቀሣሉ። አውሮፓም በተለይ በ16ኛው መቶ ክ/ዘመን ማለቂያ እጅግ ቀዝቃዛ አየር አኮራምቷት ነበር። እስከ 18ኛው መቶ ክ/ዘመን አጋማሽ ድረስ ደግሞ የበረዶ ግግርም ሌላው ሳንካ ነበር። ለበርካታ ጊዜያት ቅዝቃዜው በመቀጠሉ የባህር አሣዎች ሁሉ አደገኛ ችግር ውስጥ ገቡ። ይህም ተዳምሮ የምግብ አቅርቦት ችግር እንደተከሠተ ተፅፏል። የሸቀጦች ዋጋ መናር የምግብ አቅርቦትና የሌሎች አላቂ መገልገያዎች ፍላጎቶችን አናሣ እንዲሆን አድርጓል።

በህዝብ ብዛትም በኩል የነበረው ሁኔታ ለመገመት እንዲያስችል በአውሮፓ ቆጠራ የተጀመረበት ዘመን ነበር። በሩሲያ፣ በሲዊዲን፣ በፈረንሳይና በኢንግላንድ የህዝቦችን መጠን መቁጠርና መመዝገብ አዲስ ጥበብ የያዘበት ወቅት ነበር። ፈረንሳይ በህዝብ ብዛቷ በወቅቱ የተመዘገበው

ከሌላው የአውሮፓ ክፍል ይበልጣል። ሃያ ሚሊዮን ህዝብ ነበራት። በሌሎችም አከባቢዎች እስከ 1750 ድረስ የህዝብ ቁጥር እያደገ መጥቷል። ይሁን እንጂ በ1661 ቱርክን፣ በ1665 ሎንደንን ወረርሽኝ መቷቸዋል። በ1690ዎቹ ፈረንሳይና ስፔይን እንዲሁ በወረርሽኝ ተጠቅተው ነበር። በ1708 እና በ1713 ባለው መካከል ፖላንድና ጀርመን ክፉኛ ተጠቁ። በዚህም የተነሣ የበሽታ አምጪ ህዋሶች እንዳይራቡ ሲባል የከተሞች ፅዳት ትኩረት ይሰጥበት ገባ። የቤት አሠራር ከእንጨት ወደ ሸክላና ድንጋይ በመቀየሩ ልዩ ልዩ ውበት ያላቸው ህንፃዎች መገንባትና መታየት ጀመሩ።

በሌላ መልኩ ደግሞ ሰዎች ከተፈጥሮ ጋር በሚያደርጉት ግብ ግብ እርሻቻቸውንም ማስፋፋት ጀመሩ። ለመሬት የሚሰማሙ ምርጥ ምርጥ ዘሮች በመፈለግ በጥራጥሬ ምርት እምርታ አሣዩ። ንግዱም እንዲሁ እየጎለበተ የመጣ የስራ ዘርፍ ሆነ። በአውሮፓ ኢኮኖሚው በሁለት እግሩ መቆም ሲጀመር ወታደራዊ ማሠልጠኛዎች ተቋሞችና የኢንዱስትሪዎችም ማደግ ሌላው ገፅታ ሆነ። ምዕራብ አውሮፓ ከግብርናው ወደ ኢንዱስትሪው ዓለም ተሸጋገረ።

በዚህ ወቅት ለበርካታ ጊዜያት ሲሞከሩ የነበሩት ኢንዱስትሪዎች ማቆጥቆጥና ማሰብ ጀመሩ። ማዕድናትንም ከከርሰ መሬት ስር ሰርስሮ ማወጣት የኢኮኖሚ መዳበር አስከተለ። ከዚሁ ጋር ተያይዞ የሠራተኛው ቁጥር ማደግ ጀመረ። የወዛደሮች ከአንዱ ከተማ ወደ ሌላው ከተማ ሥራ ፍለጋ መንጐዱ አንዱ ትዕይንት ነበር። ይህን ጉዳይ በተመለከተ የዚሁ ዘመን ደራሲና ጋዜጠኛ የነበረው ዳንኤል ዲፎ እንደገለጸው

የስራ አጥነት ሁኔታ እንደማይታይ፣ ሁሉም ሰርቶ እንደሚበላ ነበር። ሆኖም ግን አንዳንድ አጥኚዎች በዘመኑ ስራ አጦችም እንደነበሩበት ይናገራሉ። ልመናና የወንጀል ድርጊቶች ተስፋፍተው እንደነበርም ያስረዳሉ። ከከተሞች እድገት ጋርም እንዲሁ ዝርፊያ ማጅራት መቺነት አድገውም እንደነበር ይገልፃሉ። ከዚህ ሌላ ጥቂቶች የበለፀጉበት አብዛኛው ህዝብ የደኸየበትም ነበር ይባላል። ድህነት አንዱ አስቸጋሪ ሁኔታ ነበር። ድሃ የሆኑ ሰዎች አንዳንዶች ወደ ወንጀል ተግባር ሲያመሩ ሌሎቹ ደግሞ ወደ ልመና ገቡ።

በዚህም የተነሣ የረድኤት ድርጅቶች መቋቋም የጀመሩበት ዘመን ነው ባሮክ። እጓለማውታን ለሆኑ ልጆች /Orphans/ ለድሆች እና ለአካል ጉዳተኞች ጭምር በተለይ የካቶሊክ ቤተ-ክርስቲያን ሕገ-ደንብ በእርዳታ ላይ እንዲመሠረትም የተደረገበት ይህ ዘመን ነበር።

ይህ በእንዲህ እያለም የንግድ እንቅስቃሴዎች አድማሳቸውን እያሠፉ የመጡበት ወቅት ሆነ። የመንግስት የመተዳደሪያ ከንግድ በሚገኘው ቀረጥና ግብር ነበር። በዚህም የተነሣ ወደቦችን መጠገን፣ የገበያ ስፍራዎችን መገንባት ሌሎችም ክንውኖች ጥናቶች ያሣያሉ። የባርያ ንግድም አንዱ ስር የሠደደ የዘመኑ እንቅስቃሴ ነበር። ከምዕራብ አፍሪካ የሚፈነግሏቸውን ሰዎች በባርነት መልክ በአውሮፓና በአሜሪካ ክፍለ ከተሞች ይሽጧቸዋል። የደለበ አዱኛ ማፈሻም ነበር ሲሉ ስለዚሁ እንቅስቃሴ የታሪክ አጥኚዎች ይናገራሉ።

የባንክ አገልግሎት መጀመር የዚሁ ዘመን አንዱ ገፅታ ነው። ባንክ ቤት ወርቅን፣ አልማዝን ሌሎች የከበሩ ማዕድናትንና ገንዘብን በማስቀመጥ ለንብረት ብክነት እንዳይጋለጡ ሆነዋል። በተጨማሪም የወለድ አገልግሎት በመኖሩ ተጠቃሚው እየበዛ መጣ ሆኖም ግን በዚሁ ዘመን ሌላ ችግር መከሰቱ አልቀረም። የሀይማኖት መሪዎች ተቃውሞ ማስነሣታቸውም ይጠቀሣል። ወለድ መቀበል ማለት ከሌብነት ቀጥሎ የሚታይ አይደለም በማለት ቁጣቸውን አሰምተው እንደነበር የዘመኑ ታሪክ ይዘክራል።

ይህ የባሮክ ዘመን በተለይ በቅርፃ ቅርፅ፣ በኪነ-ህንፃ /Architecture/ በስዕል ወይም በቀለም ቅብ /Painting/ እጅግ ገናና ስም የያዘበት ዝናንም ያተረፈበት ነበር። እስከ አለንበት ዘመን ድረስም ቢሆን በአለማችን ላይ ውብ የተሠኙ ከተሞች ግርማ ሞገሣቸውን የተላበሱበትና ንግግር የማድረግ ያህል ነበርን፣ አለን እንደማለት ደረታቸውን ገልብጠው ሊታዩ የበቁበት ዘመን ባሮክ ነው።

የህንፃዎቹ አመሠራረት፣ አወቃቀር፣ አወጣጥና ጉልላታዊ ቅርፅ እንዲሁም ውጪያዊና ውስጣዊ ይዞታቸው የሚያመለክቱት የቅርብ ሥራዎቻቸው እጅግ የሚገርሙ ናቸው። ሁለንተናዊ የሥፍራና ድባብ አመራረጣቸው ብሎም ጥበባዊ ውጤቶቻቸው ጉድ እንደሚያሰኙ በዚሁ ዘርፍ ጥናት ያደረጉ በርካታ ተመራማሪዎችና ታሪክ ዘጋቢዎች መስክረውላቸዋል።

በዘመነ ባሮክ በአውሮፓ የተገነቡት ቤተ መንግስቶች ውቅሮቻቸውና ውስጣዊ ገፅታቸው የዘመኑን የኪነ-ጥበብ ሰዎችን ምናባዊ ምጥቀት

ጊዜ አብሮ ለመስራት የሚቋቋሙ የግንባር አደረጃጀቶችም ሊፈጠሩ ችለዋል። ይችላሉም ከዚህ አኳያና የአገሪቱ ሕግ በደነገገው መሠረት መድረክ ግንባር ሆኖ ተመዝግቧል።

የመድረክ ግንባርነት ባህሪይን ስንመለከት ግንባርነቱ የተመሠረተው በሰፊ (Broad) አንድነት ላይ ነው እንጂ በርዕዮተ ዓለም አንድነት ላይ የተመሠረተ አይደለም።

የመድረክ ግንባርነት ባህሪይና የትግል ስልት አንፃር ሲታይ መድረክ ወይ የመድረክ አባል ድርጅቶች በርዕዮተ ዓለም አንድነት ላይ የተመሠረተ ውህድ ፓርቲ መሆን አለበት፣ ያለበለዚያ በቅንጅትነት (ጥምረትነት) ደረጃ መንቀሳቀስ አለበት የሚሉ ሰዎች ምክንያታቸውን የበለጠ ቢያብራሩ አስተማሪነቱ የሚናቅ አይደለም።

ወደ አሁኑ ሁኔታ ስንመለስ

መድረክ ሰፊ (Broad) ግንባር ነው። ሆኖም ግን በምርጫ ኢህአዴግ ከተሸነፈ በኋላ ኢህአዴግን ጨምሮ (ኢህአዴግ በፓርላማ ወንበር ካገኘ) ከሌሎች የፓርላሜንታዊ ፓርቲዎች ጋር የብሔራዊ አንድነት መንግሥት ለማቋቋም ይፈልጋል። በዚያን ወቅት ሆነ ከዚያም በኋላ አንድነትዋ፣ ነፃነትዋና ሉዓላዊነትዋ የተጠበቀች፣ ሁሉም የግለሰቦችና የቡድኖች መብቶች እኩል የተከበሩባት፣ የብሔር ብሔረሰቦች እኩልነት የተረጋገጠባት ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን ለመገንባት ይታገላል ብሎ የመድረክ ግንባር ቃል ገብቷል። ስለሆነም የመድረክ ግንባርነት፣ ከርዕዮተ ዓለም አንድነት በመለስ ከኢህአዴግ ሰፊ ግንባርነት (Broad Front) ከፍ ያለ ነው። ስለሆነም መድረክ በዚያው ደረጃ ቢቆይ ይሻላል እንጂ ወደ ጥምረት /ቅንጅት ደረጃ እንዲወርድ መፈለጉም ሆነ ወደ ውህድ ፓርቲ መግፋት መፈለጉ በአሁኑ ወቅት

ጠቀሜታው አልታየኝም። ያም ሆነ ይህ ዋናው ቁም ነገር ለአንድ ዓይነት ዓላማ በጋራ መስራት ጠቃሚ የመሆኑ ጉዳይ ነው” ሲሉ ልዩነታውን አስቀምጠው ነበር።

ከላይ የሰፈሩት ልዩነቶች እንደተጠበቁ ሆነው አዲሱ የአንድነት ሊቀመንር የሆኑት ኢንጅነር ግዛቸው ለበርካታ የፖለቲካ ፓርቲዎች ለውህደት ጥሪ አቅርበዋል። ይህን መሰል ጥሪ ከሙህራኑ እንደሰፈረው በቀያጭነት የሚፈረጅ ነው። ይህም ሲባል ቀያጭነት (Eclecticism) ሊዛመዱ የማይችሉ ልዩ ልዩ ፍልስፍናዎች ርዕዮተዓለሞችን አስተሳሰቦችና የፓርቲ መመሪያዎች መራርጦ ለማስታረቅ የሚሞክር አመለካከት በመሆኑ ነው።

የሊቀመንበሩ ጥሪ አንድም ሌሎችን ፓርቲዎች ከአንድነት ጋር እንዲሆኑ ወይም አንድነት ብቻውን ተገንጥሎ ለመውጣት የፈለገበት

ስልታዊ አካሄድ ተደርጎ ተወስዷል። ዶክተር ነጋሶ በእነሃብታሙ የፖለቲካ አስተሳሰብ መበለጣቸውን ያሳያል። ኢንጅነር ግዛቸውም የውህደት ጥያቄውን በግልፅ ማስቀመጥ ካልቻሉ የወጣቶቹ ትግል እሳቸውንም ከጨዋታ ውጪ ሊያደርጋቸው የሚችልበት እድል ሰፊ ነው።

ምክንያቱም ግልፅ የሆነ የፖለቲካ መስመር ልዩነት በመካከላቸው መፈጠሩ አይቀሬ በመሆኑ ነው። የፖለቲካ መስመር አንድ ዓይነት ርዕዮተዓለም ያላቸው የፖለቲካ ድርጅቶች አንግበው የተነሡትን ዓላማ ከግብ ለማድረስ የሚከተሉት የትግል ፈር ወይም የሚወስዱት አቋም ነው። ይህ የፖለቲካ መስመር ከተራ ፕሮፖጋንዳ ባለፈ በዕለት ተዕለት የፖለቲካ ፓርቲዎቹ እንቅስቃሴ ላይ የሚታይ መናበብ እና መቀናጀት የሚስተዋልበት የትግል መስመር በመሆኑ መናበብ ከማይችሉ

ፓርቲዎች ጋር ለመቀጠል ያለው እድል አሁን ባለው የአንድነት የፖለቲካ ድባብ ውስጥ አስቸጋሪ ስለሚያደርገው ኢንጅነሩ ያቀረቡትን የውህደት ጥሪ በግልፅ ሊያሰፍሩት የሚገደዱበት ሁኔታ በጣም ሰፊ ነው።

በተለይ የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ አሁን ግንባር ከፈጠራቸው ፓርቲዎች እና ከገዢው ፓርቲም ጭምር ፍፁም የተለየ በዘውግ ያልተደራጀ ፓርቲ መሆኑ ይታወቃል። አሁን ልዩነቱን መፍታት ካልቻለ በምርጫ ወቅት በብሔር ከተደራጁ ኃይሎች ከፍተኛ ፈተና ይጠብቀዋል። ስለዚህም አንድነት ብቻውን ነጥሮ የመውጣትን አቅጣጫ አጠንክሮ እንደሚሄድ የብዙ ባለድርሻው አመለካከት እየሆነ መምጣቱን የሰንደቅ ምንጮች ገልጸዋል። ኢንጂነሩ ግን ቀያጭ ሆነዋል እየተባለ ነው።¾

የዶ/ር ነጋሶ ስንብት...

የስልጣኔው ዘመን የቱ ይሆን?

በዚህ ዘመን ሀገራችን ኢትዮጵያ ምን

ነበረች? ይህ ዘመን ላይ ኢትዮጵያም

በኪነጥበብ የተንደላቀቀችበት ነበር።

የጐንደሩ ጉዛራ ቤተ-መንግሥት፣

የጐርጐራው የአፄ ሱስንዮስ ቤተ-

መንግሥት፣ የካቶሊኮች ቤተ-ክርስቲያን

ወዘተ. ተጠቃሽ ናቸው

Page 17: ንደ3 - ethioforum.orgethioforum.org/wp-content/uploads/2014/01/sendek435.pdfሰንደቅ 9ኛ ዓመት ቁጥር 435 ረቡዕ ታህሳስ 30 2006 አታሚ፤ ብርሃንና

ሰንደቅ 9ኛ ዓመት ቁጥር 435 ረቡዕ ታህሳስ 30 2006 17ኢንቫይሮመንት

በአይቸው ደስአለኝ

በአዲስ አአባና በሌሎች ከተሞች ነዋሪዎች ውስጥ አብዛኛው ለየዕለት ህይወቱ የሚያስፈልገውን ምግብ ለማዘጋጀት የሚጠቀመው የኢነርጂ ምንጭ የተፈጥሮ ውጤት የሆኑ ማገዶዎችንና ከሰልን ነው። ይህም በአካባቢ ጥበቃ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እያስከተለ የሚገኝ ሲሆን ይህን ጥፋት ለማስቀረትም አሁን ያለው ትውልድ ብዙ መስራት ይጠበቅበታል። ይህን ችግር ደረጃ በደረጃ ለመቅረፍ የሚቻለው አንደ መንገድ ህብረተሰቡ እንደገቢው መጠንና አቅም ለቤት ውስጥ የሚያስፈልገውን የሃይል ምንጭ ታዳሽ በሆነው የኤሌትሪክ ኃይል መቀየር ሲችል ሲሆን ሌላኛው ዘዴ ደግሞ እንጨትና ከሰልን የሚጠቀመው ህብረተሰብ ቆጣቢ በሆነ ምዳጃዎች መገልገል ሲችል ነው። በኃይል ቆጣቢ ምድጃዎች መጠቀም ኃይል እንዳይባክን ስለሚያደርግ በጥቂት ኃይል ብዙ ስራ መስራት ያስችላል። ይህ ሆነ ማለት ደግሞ ቶሎ ቶሎ ወደ ማገዶ ሸመታ አይሄድም ማለት ነው። ይህም ሁኔታ የማገዶ ደን ቶሎ ቶሎ እንዳይቆረጥ ስለሚያደርግ አካባቢን መጠበቅ ያስችላል። ከዚሁ ከቆጣቢ ምድጃም ጋር ተያይዞ ሌላ የማገዶና የከሰል ምርቶችን አምርቶ ወደ ገበያ የማቅረብ ስርዓትም እየተገባ ነው። የቡና ተረፈ ምርት ወይም ገለባው አለጥቅም የትም እንዳይጣል በማሽን ተፈጭቶና ቅርፅ ወጥቶለት ጭሱ ከውስጡ ወጥቶ ወደከሰልነት እየተቀየረ በቆጣቢ ምድጃ አመካኝነት ጥቅም ላይ እየዋሉ ይገኛሉ። ይህ ሁኔታም ከላይ እንደተጠቀሰው ለአከባቢ ጥበቃ የበኩሉን እገዛ እያደረገ ይገኛል።

ይህ የአርቴፊሻል ከሰልና የኃይል ቆጣቢ ምድጃ ምርትና ስርጭት ለብዙ ወገኖችም የስራ ዕድል እየፈጠረና ህብረተሰቡም ምርቱን እየለመደው የሚገኝ ሲሆን ከሰሉ ከጭስ ነፃ በመሆኑም ተጠቃሚውን ከጤና ጉዳት መታደግ ችሏል። በዚህ ስራ ከተሰማሩ በርካታ ማህበራት ውስጥም በአዲስ አበባ በሶስት ወጣቶች ትብብር የተቋቋመውና በአሁኑ ወቅት እውቅናን እያተረፈ የመጣው የጎግል ማገዶ ቆጣቢ ምድጃ አምራች ነው። አቶ ተራማጅ ከበደ የማህበሩ አመራር አባል ሲሆን ቀደም ሲል እርሱና ጓደኞቹ በማዕድንና ኢነርጂ ሚኒስትር በቴክኒሽያንነት ሰርተዋል። በዚያን ወቅት በነበራቸው አካዳሚያዊና ቴክኒካዊ እውቀትና ልምድ ተጠቅመው ለአንድ ዓመት ያህል ጥናትና ምርምር በማድረግ የቡና ገለባን ፈጭቶና ውስጡ ያለውን ኬሚካላዊ ንጥረ ነገር በማስወገድ ማገዶ ቆጣቢ ምድጃዎችን በማምረት ሰፊ የገበያ ትስስር ከመፍጠር አልፈው ለበርካታ ወገኖች የስራ እድል ለመፍጠር ችለዋል። እንደ አቶ ተራማጅ ገለፃ ማህበሩ የተመሰረተው ከአምስት ዓመታት በፊት ነው። በሀገራችን የቡና ገለባ በተትረፈረፈ ሁኔታ በቀላሉ የሚገኝ ነው። ይህ ሁኔታም ለአባላቱ እንደመልካም አጋጣሚ ስለሆነላቸው የብዙ ጊዜ ሙከራ ካደረጉ በኋላ ወደ ምርት ስራው ለመግባት ችለዋል። በመሰረቱ የቡና ምርት ሲዘጋጅ ብዙ ሂደትን ስለሚያልፍ በተለይ በገለባው ላይ ኬሚካላዊ ንጥረ ነገር በእጥበት ወቅት በአብዛኛው ይወጣል ከዚያም ቀሪው መርዛማ ንጥረ ነገር በከሰል ማመረቻው ማሽን አማካኝነት ስለሚወገድ ከሰሉ ከጭስ ነፃ ይሆናል።

ከሰሉ የመድቦልቦል ቅርፅ እንዳይዝ የሚያደርገውም ማሽኑ ሲሆን ይህም ከሰሉ በቁጠባ መልኩ እንዲቀጣጠል ያደርገዋል። ይህም የፈጠራ ባለቤቶቹ የሆኑት የአቶ ተራማጅና ጓደኞቹ የምርምር ውጤት ነው። በከተማችን ሌሎች እንዲሁ በኃይል ቆጣቢና በአርቴፊሻል ከሰል ምርት ማምረት ስራ የተሰማሩ ደርጅቶችም ከሰልን ከቡና ገለባ ብቻ ሳይሆን ከጫት ገራባና ከሌሎች ውድቅዳቂ እንጨቶችን በማሽን አማካኝነት ወደ ከሰል ቀይረው ወደ ገበያ እየቀረቡ እንደሚገኝ የሚታወቅ ነው። ከዚህ አኳያ ሌሎች ተረፈ ምርቶችም ከተማን ከማቆሸሽ አልፈው ለብክለት መንስኤ እንደሆኑ ይታወቃል። ከዚህ አንፃር በዘርፉ በርካቶችን ወደ ስራ ማሰማራት እንደሚቻል የከሰል ፍላጎትን በማሟላት ከተማዋም ጽዱ ማድረግ ይቻላል።

እንደ አቶ ተራማጅ ገለፃ በአሁኑ ወቅት የከሰልና የቆጣቢ ምድጃው ተፈላጊነት በህብረተሰቡ ዘንድ እየጨመረ ነው። ዋጋውም ተመጣጣኝ ሲሆን የአንድ የተድበለበለ 1 ኪሎ ከሰል ዋጋም አራት ብር ብቻ ነው። ይህ ከሰል በአምራቾቹ “ምርጫዬ” የሚባል ስያሜ ተሰጥቶታል። ይህም የሆነው ህብረተሰቡ በዋጋም ተመጣጣኝ እንዲሁም ጭስ አልባበመሆኑ መርጦ እንዲሸምተው ለማድረግ ነው። ቆጣቢ ምድጃውም ከከሰሉ ጋር አብሮ እንዲሄድ ተደርጎ የተሰራ ሲሆን በላቦራቶሪ ፍተሻ ተደርጎለት ኃይልን በመቆጠብ ረገድ ከነባሮቹ ምድጃዎች ጋር ሲነፃፀር 40 በመቶ እንደሚቀንስ ተረጋግጧል። ከሰሉ ለራሱ ምድጃ ያስፈለገበትን ምክንያት አቶ ተራማጅ ሲገልፅ አርቴፊሻል ከሰሎች በተፈጥሮአቸው ጠንካሮች ባለመሆናቸው እነርሱን ሊያስተናግድ እንዲችል ተደርጎ ነው ምድጃው የተሰራው እንደዛም ሆኖ ምድጃው ለሌሎች ከሰሎችም መሆን ይችላል። በአሁኑ ወቅትም ምድጃው በአዲስ አበባና በሌሎች ከተሞች በስፋት ገበያ ላይ እየተሰራጨ ይገኛል።

እንደሚታወቀው በባህላዊው የከሰል አሰራር ዘዴ የሚመረት ከሰል ብዙ ክህሎትን አይጠይቅም። እሳቱን አንድዶ በደምብ ከተፋፋመ በኋላ አዳፍኖ በአፈርና በሌላም ነገር ማጥፋትና ማክሰል ነው። ብዙም አያስቸግርም አንዳንድም ጥንቃቄ ስለማይደረግበት ጭሱን ያልጨረሰ ከሰል ወደ ገበያ በመቅረብ ጥቅም ላይ ሲውል ከውስጥ በሚወጣው ካርበን ሞኖክሳይድ አማካኝነት የበርካቶችን ህይወት ሲቀጥፍ ይስተዋላል። ከዚህ አኳያ ይህን ችግር ለመቅረፍ የጎግል ምድጃ ቆጣቢ ድርጅት ከፍተኛ ጥንቃቄ አድርጓል። የከሰል ማምረቻ ማሽኑን ለማምረት አንድ ዓመት ያህል ጊዜ ወስዶበታል። እንደ አቶ ተራማጅ ገለፃ በመጀመሪያው ሂደት ማሽኑን ቅርፅ የማስየዝ ስራ ነበር ትኩረት የተሰጠው። ይህን ለማጠናቀቅም አንድ ዓመት ያህል ጊዜ ጠይቋል። ይህ ተጠናቆ ወደ ስራ ሲገባም ከሰሉ ለስላሳ ስለነበር የመሰባበር ሁኔታ ያጋጥም ነበር። ከሰሉ በአየርና በፀሐይ እንዲደርቅ ስለሚደረግ ከቦታ ቦታ ሲንቀሳቀስ የመሰንጠቅ ችግር ያጋጥም ነበር። ከዚያም ቀስ በቀስ ምርምር በማካሄድ ማሽኑ ላይ ከሰሉን የሚያጠነክር መሳሪያ ተገጠመለት። በዚህ አካሄድም ችግሩ ሊወገድ ቻለ። ከዚህ መረዳት እንደሚቻለው ማሽኑን ያመረቱት አምራቾች ከፍተኛ የምርምርና የፈጠራ ክህሎታቸው መጠቀም ባይችሉ ኖሮ ምርቱ እውን መሆን ሳይችል ይቀር እንደነበር ነው። ይህም ብቻ ሳይሆን እንደ ማህበሩ መሪ አገላለፅ ከሰሉ ገበያ ላይ ከዋለ በኋላ ከሰሉ ስላለበት ጉድለት ከሸማቹ ሃሳብ እየተቀበሉ የተለያዩ የማሻሻያ ስራ ሰርተዋል።

አቶ ተራማጅና ሁለት የስራ ባልደረቦቹ አሁንም አብረው እየሰሩ ነው። ድርጅታቸውም ከአነስተኛ ጥቃቅን ኢንተርፕራይዝ ወደ መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ያደገ ሲሆን የድርጅታቸው መጠሪያም ጎግል ኃይል ቆጣቢ ምድጃና ኢንጂነሪንገ የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል። ድርጅታቸው ከከሰል ማምረት ስራ ባሻገር ለህብረተሰቡ የከሰል አመራረት ስልጠና በመስጠት በስራ አጥ ወገኖች የስራ እድል እንዲፈጠርላቸው አድርጓል። በተጓዳኝም ምድጃዎችን በመስራት ለገበያ ያቀርባሉ። በአጠቃላይ ኢንተርፕራይዝ በአሁኑ ወቅት በቀን 2500 ከሰሎችን በማምረት ለገበያ ያቀርባል። ተፈላጊነትም በየጊዜ እየጨመረ ስለሚሄድ በድርጅቱ ስር ሆነው ከሰል የሚያመርቱ ሠራተኞችን ለማሰባሰብ ችለዋል።

ከዚህ አኳያ የዚህ መሰል ድርጅቶች የኃይል አቅርቦትን ከማስገኘትና የአካባቢ ጥበቃ ስራ እንዲጠናከር ከማድረግ በተጨማሪ ለስራ አጥ ወገኖች ስራ የመፍጠር እድል እንደ ትልቅ አጋጣሚ የሚቆጠር ነው። በተለይ እንደ አዲስ አበባ ባሉ ትላልቅ ከተሞች የስራ አጡ ቁጥር ጣራ በነካበት ሁኔታ በጣም ብዙ ካፒታል ሳያስፈልግ ነገር ግን ብዙ ጉልበትን ወደ ስራ ማሰማራት የሚችሉ ኢንተርፕራይዞች እንዲጠናከሩ እገዛ ሊደረግ ግድ ይላል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአካባቢ ጥበቃ

ቢሮም እስከዛሬ እንደሚያደርገው ለእንደዚህ መሰል ስራ ፈጠራ ድርጅቶች እውቅና ከመስጠት በተጨማሪ በሞራልና በማቴሪያል ሊያገዝ ይገባል። የቢሮው አንዱ አላማ በኢነርጂ ዙሪያ የፈጠራ ስራዎችን ማበረታታትና በየትምህርት ተቋማትና ማምረቻ ድርጅቶች የኢነርጂ ውጤቶች ጥቅም ላይ እንዲውሉ የገበያ ትስስር መፍጠር እንደመሆኑ እገዛውና ድጋፉ ሌሎች እጃቸውን አጣጥፈው የተቀመጡ ስራ አጦችም በዘርፉ እንዲሰማሩ የሚያበረታታ ነው።

የጎግል ኢንተርፕራይዝ አስተባባሪ የሆነው አቶ ተራማጅ ይህን የፈጠራ ስራ አስቦ ወደ ተግባር እንደገባ ምን መልካም አጋጣሚዎች እንደነበሩ ተጠይቆ ሲመልስ በመጀመሪያ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኘውን ራስ አገዝ ማህበርን ለማመስገን እንደሚፈልግ ጠቅሶ ማህበሩ ከ10ሺህ በላይ እናቶችን ያደረጃ እንደመሆኑ የማህበሩ አባላት ከከሰል ምርት ጋር እንዲተዋወቁ መቻላቸው እርካታን እንደፈጠርለት አመልክቷል። በተለይ የማህበሩ መሪ ወ/ሮ ፀደይ በርሄ የማሸኑን መስሪያ ቁሳቁሶች ገዝተው ለጎግል አምራቶች ማበርከታቸው ለስራቸው መቃናት ለነርሱም ሞራል መነቃቃት ከፍተኛ እገዛ እንዳደረገ አስረድቷል። ሴቶቹ ከሰሉን በማምረት መጠነኛ ገቢ ከማግኘታቸው በተጨማሪ ምርቱን ቤታቸው ወስደው በመጠቀማቸው ህብረተሰቡ ከምርቱ ጋር እንዲተዋወቅ አድርገዋል። በዚህ በመበረታታቸውና ምርታቸው በመታወቁ ምድጃውንም በስፋት ማስተዋወቅ ተያያዙ። ከዚያም በሀገር አቀፍ ደረጃ ያለው የአነስተኛና ጥቃቅን ኢንተርፕራይዝ የጎግልን ጥረት ተገንዝቦ አስፈላጊውን የማምረቻ ቦታ በመስጠት የምርቱ መጠን እንዲስፋፋ አድርጓል። የገበያ ትስስር እንዲፈጠርም ምርቶቻቸው በኤግዚቪሽንና በባዛር ላይ አንዳንዴ በመጠነኛ ገንዘብ አንዳንድ በነፃ በማቅረብ ከህብረተሰቡ ጋር ትውውቅ እንዲያደርጉ እገዛ አድርጎላቸዋል።

ይሄ ብቻ ሳይሆን ስለ አመራረቱ ለገበያ ትስስሩና በተለያዩ ድርጅቶች ከሰሉ ጥቅም ላይ ስለማዋሉ በተመለከተ ሀገር አቀፍ የአነስተኛና ጥቃቅን ተቋም ዶክሜንተሪ ፊልም በማዘጋጀት በህብረተሰቡ ዘንድ እንዲሰራጭና እንዲታይ አድርጓል። ይህ በተለይ ማሽን የማምረት ስራ የፈጠራ ሙያ ባለቤትነት መብትን የሚያስገኝ እንደመሆኑ እውቅና ማግኘቱ ከገንዘበ በላይ ዋጋ ያለው ነው። ነገር ግን በከተማችን አንዳንድ ወጣቶች የፈጠራ ባለቤትነት መብት ከአእምሮአዊ ንብረት ጽህፈት ቤት ሰርተፊኬት አግኝተው ወደስራ ሳይሰማሩ በየአመቱ የስራ ፈቃድን በማስደስ ብቻ ምንም ምርት ሳያመርቱ እንደሚገኙ የጠቆመው አቶ ተራማጅ የዚህ ዓይነቱ አካሄድ እውቀትና ችሎታ የጋን ውስጥ መብራት እንዲሆን ስለሚያደርግ የዚህ መሰሉ ልምድ መሰበር አለበት ብሏል። እንደ እርሱ ተሞክሮች ልምድ የፈጠራ ባለቤቶች ወደ ስራ ለመግባት የሚያስችለውን አስፈላጊውን ምክር ከአእምሮአዊ ንብረት ጽ/ቤት ማግኘት ስለሚችሉ ሃሳቦችን በመውሰድ በአእምሮአቸው ያለውን እውቀት ወደ ፈጠራና ምርት መለወጥ ይችላሉ። ጽህፈት ቤቱ ድርጅቶችን ከድርጅቶች፣ ባለእውቀትን ከባለገንዘብ ጋር ያገናኛል። እንዲሁም የገበያ እድል የሚገኝበትን ዘዴ ይቀይሳል። ስለዚህ ይህን በመጠቀም ሰዎች ከእውቀት ባለቤትነት ወደ ባለሀብትነት መቀየር ይችላሉ። ስለሆነም አንዳድ ሰዎች “ፓተንት አለኝ” ብለው ብቻ ቢቀመጡ ዋጋ የለውም ሲል ይገልጻል።

ይህ የጎግል ኃይል ቆጣቢ ምድጃና ኢንጂነሪንግ ድርጅት ባላቸው የፈጠራ ክህሎትና ተግባር የ2013 የሲዲኤን ሲ ዓለም አቀፍ ተሸላም እንዲሆን አስችሎታል። ይህ ሽልማት ለድርጅቱም ሆነ ለሀገራችን ትልቅ ኩራት ነው። መቀመጫውን ደቡብ አፍሪካ ያደረገው በታዳሽ ኃይል ላይ ለሚሰሩ ሽልማት የሚጠው ድርጅት ውድድሩን ያዘጋጀው በዓለም አቀፍ ደረጃ ሲሆን ከተለያዩ የዓለም አካባቢ የሚገኙ ተቋማት በውድድሩ ተካፍለው ነው። ጎግል በማሸነፍ አንደኛ የሆነው እንደ አስተባባሪው አቶ ተራማጅ ገለፃ ውድድሩ በጣም ፈታኝና ከአንድ ዓመት በላይ ጊዜ የወሰደ ነበር። ሳምፕል መውሰድ ከዚህ በፊት የተሰሩ ስራዎችን ወስዶ መመልከት እንዲሁም ከተለያዩ ተቋማት የተገኙ የእውቅና ማረጋገጫዎችን ወስዶ መፈተሸና ማጣራት ረጅም ጊዜ ወስዷል። ከዚህ ቀደም ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሳይንስ ፋኩልቲ ጋር አንዳንድ የምርምር ስራ መስራታቸው ለእወቅናው ተጨማሪ ግብአት ሆኖላቸዋል። ከዚህ በተጨማሪ ህንድ ሀገር የሚኝ ቲያሪ የሚባል በታዳሽ ኃይል ላይ የሚሰራ ተቋም አንድ አባላቸውን ወስዶ ህንድ ሀገር ማሰልጠኑ የመወዳደሪያ አቅማቸውን አጎልብቷል። አንድ ከአወዳዳሪው ተቋም የመጣ ሙያተኛም እዚህ አዲስ አበባ መጥቶ ስራቸውን ተመልክቶ አስፈላጊውን መስፈርት ማሟላቱን በሰጠው ማረጋገጫ ለመሸለም በቅተዋል።፡ በአጠቃላይ የጎግልን የመሰል ተቋማት ኃይል ቆጣቢ ምድጃዎችንና ከሰልን ለህብረተሰቡ በማቅረብ የአካባቢ ጥበቃ እንዲጠበቅ ከማድረግ ባሻገር የፈጠራ ክህሎት እንዲዳብርና የስራ እድል እንዲፈጠር ማስቻላቸው ይበል የሚያሰኝ ስለሆነ የባለ ድርሻ አካላት እገዛ ያስፈልጋቸዋል።n

ኃይል ቆጣቢ ምድጃዎች ለአካባቢ ጥበቃና ለስራ እድል ፈጠራ

- ጎግል ማገዶ ቆጣቢ ምድጃ እንደማሳያ

ስለ አመራረቱ

ለገበያ ትስስሩና

በተለያዩ ድርጅቶች

ከሰሉ ጥቅም ላይ

ስለማዋሉ በተመለከተ

ሀገር አቀፍ

የአነስተኛና ጥቃቅን

ተቋም ዶክሜንተሪ

ፊልም በማዘጋጀት

በህብረተሰቡ ዘንድ

እንዲሰራጭና

እንዲታይ አድርጓል

እጅጉን እንድንገረምባቸው ያደርጉናል። በፀሎት ቤቶችና በቤተ-ክርስቲያኖች አፀድ ውስጥ የሚገኙት ሁሉ ከግንባታቸው እስከ ቅብ ሥራዎቻቸው ድረስ ምትሃታዊ አመለካከትን የሚጭሩ በዚህም መነሻነት ወደ ከፍተኛ ምናብ የሚያደርሱ ናቸው። በውስጣቸው ግድግዳና ጣሪያ ዙሪያ ገብ የፈጣሪ ምስል፣ የቅዱሳንና የመላዕክት፣ የሲኦልና የገነት ስዕል ስራዎች ሀውልቶችና ቅርፃ ቅርፆች የዛን ዘመን አዲሡን ባሮክ ፈጥረዋል። ከከተማው ወጣ ብሎ ከከበርቴዎች በዘመኑ የኪነ-ጥበብ ሠዎች የሠሯቸው የነበሩ የገጠር መኖሪያ ቤቶች /ቪላዎች/ ዛሬም በታሪክ መዘርክነት አሉ።

ለዚህ መልኩ እምርታና እድገት ግስጋሴ በቅድሚያ ተጠሪዋ ሀገር ጣሊያን ናት። በተለይ የሮማ ከተማ ከሙሉው አውሮፓ ልዩ በሆነ መልኩ የምትታይ የምትወደስና የምንታንፀባርቅ ነበረች። እ.ኤ.አ በ1600 የነበራትን የቆዳ ስፋት ከ1500 ከነበራት በእጥፉ ለጥጣዋለች። 1700 ደግሞ ይህንኑ በግማሽ ጨምራለች። ይህ ሁሉ እንዲህ የተፈጠረውና የተከወነው በዘመን ባሮክ ልዩ አለም ነበር። በዚህም የተነሣ ዘመነ ባሮክ ውብ ሮማን ለመጐብኘት ትምህርት ለመቅሰምም ሆነ ለመኖር ከመላው አውሮፓ የሚፈለሡባት ህዝቦች ቁጥር እየጎለበተ መጣ።

ስለዚህ ጉዳይ አንድ አጥኚ እንደተናገሩት ብዙ የአለም ህዝቦች ሮማን የገነት ከተማ ይሏት እንደነበር ገልፆአል። እነዚህ የኪነ-ጥበብ ሠዎች የቀለም ቅብና የሥዕል ስራ አርቲስቶች ዘመኑ የፈጠረው የኪነ-ጥበብ ዕድል ፋና ወጊ ሆነው በቀደዱት ፈር በመጠቀም ወደ ሌሎች አውሮፓ አህጉራትና ከተሞች በሙያቸው እየተፈለጉና እየተቀጠሩ ይሄዱ እንደነበርም ይነገራል። ፈላጊዎቻቸውም እየተበራከቱ መጡ። የሀገር መሪዎች፣ ነገሥታት፣ የሃይማኖት አባቶችና ሀብታም ነጋዴዎች በባትሪ ይፈልጓቸው ገቡ። በተለይ ፈረንሣይ ለእነዚህ የጥበብ ሰዎች አያሌ ሁኔታዎችን በማመቻቸት ትስባቸው ገባች። በዘመኑ ከህንፃ፣ ከቅርፃ ቅርፅ፣ ከቀለም ቅብ ባሻገር የቤት ቁሳቁስ እና መገልገያዎች ከብርና ከወርቅ ከእንቁ የሚሰሩ ጌጣጌጦች የዘመኑ አልባሳቶች ሳይቀሩ የባሮክን ፋሽን አጐልብተው ያሳዩ ነበር።

ቫልስኩየን፣ ጆርጅ ሊላቶር እና ሌሎችም በተለይ በ17ኛው ክ/ዘመን የሮማን ከተማ በአራቱ ማዕዘናት በኩል በርካታ የአውሮፓ ሀገሮች የነዚህን የጥበብ ሰዎች ፈለግ በመከተል የከተማ ህንፃዎቻቸውን አሠራርና የስዕል ጥበባቸውን ማሳደግ እንደቻሉ ታሪክ ይመሰክራል። በተለይ በቅብ ጥበብ ፔየትሮ ዳ ኮርታና ፑዞ ግንባር ቀደሞቹ ናቸው። በአብያተ ክርስትያናት ውስጣዊ ጣሪያ ላይ የሚስሏቸው መላዕክት በአየር ላይ ሲበሩ የእውን የሚታዩ ስለሚመስሉ ልዩ የሆነ ውበትና አግራሞትን ያስከትላሉ። ቀልብን በእጅጉ የሚስቡት እነዚህ የጣሪያና የግድግዳ ምስሎች እስከ አሁንም ድረስ ለዋቢነት ውበታቸውን ጠብቀው ይገኛሉ።

በመቀጠልም ፓሲና ክላውዲ ሎሬን ተጠቃሾች ናቸው። ለሮማ ከተማ የጥበብ መስዕብነት ጉልህ ሚና እንደነበራቸው ታሪክ ይመሰክርላቸዋል። የነዚህ የኪነ-ጥበብ ሰዎች ድንቅ ስራ ዛሬም ቢሆን በሮማ ከተማ የበርካታ ቱሪስቶችን ቀልብ እንደሳበ ሲያነሆልላቸው ይታያል። የቅዱስ ጴጥሮስ ቤተ-ክርስቲያን ውስጣዊ ቅቦችን ማስተዋል እንችላለን።

በጣሊያን በዘመነ ባሮክ የካርሎ ማደሮን 1556-1629 በሮማ የሚገኘው ስራዎች በ17ኛው ክ/ዘመን በምዕራቡ ዓለም የሚገኙ ለአብዛኛዎቹ ውብ ህንፃዎች መሠረትና ማገናዘቢያ ሆነው እንደነበር በታሪክ ይጠቀሳል። ይህ ሰው ህይወቱን በከፊል በኪነ-ጥበብ ስራ ውስጥ ሲያሳልፍ በ1597 ስር ነቀል የሆነውን ስራውን እሱ ነበር ያበረከተው። ይህ በእንዲህ እያለ በዚህ የኪነ-ጥበበ ዘርፍ በዘመኑ የነበሩ የጣሊያን ፊት አውራሪዎች ሶቫኒ ሌውሬንዞ በርኒኒ 1598-1680፣ ፍራንሲስኮ በርሚኒ 1599-1667፣ ፔትሮ ዳኮታና 1596-1669 እና ጐሬኖ ጉራኒ 1674-1683 ይጠቀሳሉ። በርኑኒ በ1656 በሮም የሚገኘውን የቅዱስ ጴጥሮስ ቤተ-ክርስቲያን ፊት ለፊት አሁንም ድረስ ጐልቶ የሚታየውን አደባባይ ዲዛይን በማድረግና በመገንባት በመቅረፅና በማሳመር የሚታወቅ ሲሆን በሌሎቹም ድንቅ ስራዎች የሚታወቅ ነው።

በስፔንም በዘመነ ባሮክ ኪነ-ጥበብ የጣሊያኑን ፈለግ እየተከተለች ነበር። ተጠቃሽ የኪነ-ጥበብ ተጠሪዎች እንደ አለንሶ ካኖ 1601-67 ዩፍራሶ ሎፔዝ ዲሮዥ 1684 ወዘተ. ስራዎቻቸው ከጣሊያኑ ባሮክ የተፀነሱ ናቸው።

በቤልጂየም፣ በሆላንድ፣ በመካከለኛው አውሮፓ እንዲሁም ዝናን ያተረፉ የኪነ-ጥበብ ተጠሪዎች በብዛት በዘመኑ የወጡበት ሲሆን በእንግሊዝም ኢንጐ ጆንስ 1573-1652 የእንግሊዝ ስነ-ህንፃ ዕጣ ፈንታ ወደ ባሮክ እንደቀላቀለው ይነጋራል።

በፈረንሣይም ሳልምን ዲብሮሲ በዘመነ ባሮክ ስነ-ህፃን ውልደት የተጫወተው ሚና ቀላል እንዳልሆነ ታሪክ የሚመሰክርለት ሲሆን እንዲሁም ሌሎች ስመጥር የኪነ-ጥበብ ሰዎች በዘመኑ በምዕራብ አውሮፓ ተከስተዋል።

በዚህ ዘመን ሀገራችን ኢትዮጵያ ምን ነበረች? ይህ ዘመን ላይ ኢትዮጵያም በኪነጥበብ የተንደላቀቀችበት ነበር። የጐንደሩ ጉዛራ ቤተ-መንግሥት፣ የጐርጐራው የአፄ ሱስንዮስ ቤተ-መንግሥት፣ የካቶሊኮች ቤተ-ክርስቲያን ወዘተ. ተጠቃሽ ናቸው። የዓለምን ቱሪስቶች ቀልብ የሚስቡትን የአፄ ፋሲልን ቤተ-መንግሥት ያነፀውን ኢትዮጵያዊ አርቴክት አባ ገብረክርስቶስን ስንቶቻችን እናውቀው ይሆን? የፃዲቁ ዮሐንስን ቻንስለሪ ጽ/ቤት የገነባውን አርክቴክ ወልደጊዮርጊስን በቅጡ ታሪካቸው አልተፃፉም። በቅርቡ ስለነዚህ ሰዎች አጭር መጣጥፍ አቀርባለሁ።¾

Page 18: ንደ3 - ethioforum.orgethioforum.org/wp-content/uploads/2014/01/sendek435.pdfሰንደቅ 9ኛ ዓመት ቁጥር 435 ረቡዕ ታህሳስ 30 2006 አታሚ፤ ብርሃንና

ሰንደቅ 9ኛ ዓመት ቁጥር 435 ረቡዕ ታህሳስ 30 200618 ሕግበኪዳኔ መካሻ

[email protected]

ፍልስፍና/ስነልቦና

- በሕጎቻችን መወለድ ማለት ምን ማለት ነው?

- መውለድንስ በምን መልኩ ማስረዳት ይቻላል?

- ከልደትና ከልደት ምዝገባ ጋር ሕጎቻችን ያስቀመጧቸው ግዴታዎች

የገና በዓል እንዴት ነበር? ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል አደረሳችሁ ብያለሁ። ዛሬ የተገናኘነው በልደት በዓል ማግስት እንደመሆኑ ከበዓሉ ስሜት ውስጥ ሆነን ስለመውለድ እና ተያያዥ ጉዳዮች ሕጎቻችን ምን እንደሚሉን እናወጋለን።

መውለድ መቼ ነው?የሰው ልጅ ወደዚህች ዓለም

መጣ የሚባው ከእናቱ ማህጸን ወጥቶ ሲወለድ ነው። ስለ ሰዎች ፍትሕ ብሔራዊ ግንኙነቶችን የሚደነግገው የፍትሐብሔር ሕጋችንም የመጀመሪያው አንቀፁ የጀመረው ሰው ከተወለደበት ቀን አንስቶ እስከሞተበት ቀን ድረስ የሕግ መብት አለው የሚለውን አብሳሪ ድንጋጌ በማስቀመጥ ነው። ስለዚህ እንደ ሰው ያሉን መብቶች ከውልደት ጀምረው እስከ ሞት የሚቀጥሉት ነው።

በርግጥ በተወሰኑ ሁኔታዎች በህፃኑ ጥቅም ግድ ሲል ለቅድመ ውልደትም መብት ይጀምራል። ከሞት በኋላም የተወሰኑ መብቶች ይቀጥላሉ። ሟች ተነስቶ ባያስከብረውም አስክሬኑ ተገቢውን የቀብር ስርዓት እንዲያገኝ ስሙ እንዳይጠፋና ምስሉ አላግባብ ጥቅም ላይ እንዳይውል ሕግ ጥበቃ አድርጎለታል።

መወለድ ምንድን ነው ለሚለው ሕጋችን ያስቀመጠው ትርጓሜ የለም። ሆኖም አንድ ሰው ተወለደ የሚባለው ከእናቱ ማህፀን ሙሉ በሙሉ ተላቆ ከነሕይወቱ ሲወጣና እትብቱ ተቆርጦ ሲለያይ ነው። ለመወለድ ከእናቱ ማህፀን መውጣት ብቻ ካልሆነ ይህ ከእናትየው አካል ጋር የሚያቆራኘው እትብት መቆረጥ አለበት። ያለጊዜ መወለድ ሆኖ ከተለመደው የእርግዝና ጊዜ ቆይታ መወለድ ቢኖርም የውልደት ቀን የሚባለው ልጁ ከእናቱ ማህጻን ሙሉ በሙሉ ወጥቶ የተለያየበት ቀን ነው።

ሆኖም ግን በፍ/ብሔር ሕጋችን በሕይወት የተወለደ ልጅ ሁሉ ተወልዶአል መብቶችንም አግኝቷል ብሎ ለመቀበልና ተወልዶ በህይወት ኖሮአል ለመባል አንድ ቅድመ ሁኔታ አስቀምጧል። በቁ 4 ላይ ህጻኑ ለ48 ሰዓታት በሕይወት የመቆየት ግዴታ አለበት። በህይወት የቆየው ከ48 ሰዓት በታች ከሆነ ግን ወደዚህች አለም ብቅ ማለቱ እርግጥ ቢሆንም ሕጋችን እንዳልኖረ ነው የሚቆጥረው። ስለዚህ በሌላ አነጋገር በዚህች አለም ላይ ተወልዶ በሕይወት ኖሯል ለመባል በህይወት መወለድ ብቻ አይበቃም። ቢያንስ ለአርባ ስምንት ሰዓታት በሕይወት መቆየት የፍታብሔር ሕጋችን ይጠይቃል።

ይሁን እንጂ ህጻኑ ከ48 ሰዓታት በታች በህይወት ቢቆይም ለሞት ያበቃው በተፈጥሮ ጉድለት ምክንያት ያልሆነ ሌላ ሁኔታ መሆኑን ማስረዳት ከተቻለ ህጻኑ የ48 ሰዓቱን በሕይወት የመቆየት ግዴታ ባያሟላም እንደኖረ ሊቆጠር ይችላል። ምክንያቱም ህጻኑ ወደዚህች ዓለም የመጣው በሕይወት ለመቆየት በሚችልበት ተፈጥሮ አቋም ላይ ሆኖ ሳለ ለሞት ያበቃው ግን ተፈጥሮአዊ ያልሆነ ምክንያት ከሆነ ለምሳሌ አደጋ፣ ተገቢው ጥበቃና አያያዝ በማጣት፣ ሆን ተብሎ በሰዎች በደረሰበት ጉዳት እና በሌሎች

ምክንያቶች መሆኑ ከተረጋገጠ ሕጉ እነዚህ ከህጻኑ ተፈጥሮ ጋር ያልተያያዙ ክስተቶች ባያጋጥሙት ኖሮ መኖር እንደሚችል ስለሚገመት ነው።

እዚህ ጋር አሁን ገና ጡት ለጎረሰ አራስ ልጅ በሕይወት ኖሯል መብት ነበረው ብሎ ማለት ምን ይጠቅማል የሚል ሰው ካለ በየዋህነት አስቦት ነው። ህጻናት እራቁታቸውን ወደዚህ አለም ቢመጡም ገንዘብ ካላቸው ወላጆች ከተወለዱ ወላጆቻቸው ሲሞቱ የመጀመሪያ ደረጃ ወራሽ ናቸው። ለነገሩ ካጣ ከነጣ ቤተሰብ የተወለደ ህፃንም ወላጆቹ ለመውረስ የሕግ መብት አለው። ጥያቄው ምንም ከሌላቸው ምናቸውን ይወርሳል ነው። ይህ የውርስ መብት በህፃኑ ብቻ አያበቃም ህጻኑ የመውረስ መብቱን አግኝቶ ከሞተ በህይወት ያሉት ወላጆቹ የመውረስ መብት አላቸው። ወላጆቹ በህይወት ከሌሉ በእነሱ በመተካት እህት ወንድሞች ይወርሱታል። ይህንንም ሆነ ሌሎች መብቶችን ለማግኘት ተወልዶ ተፈጥሮአዊ በሆነ ምክንያት ሳይሞት ለ48 ሰዓታት መቆየት አለበት።

አንደ ሕግ ት/ቤት መጀመሪያ ዓመት ስለሰዎች ሕግ ስንማር የማስታውሳትን ምሳሌ ላንሳ፡- አቶ ከበደ ሚሊየነር ናቸው። ግን ልጅ አልነበራቸውም። ይሄን ሁሉ ብር ማን ይወርሰው ይሆን ተብሎ ሲጠበቅ ከአንዲት በምን አጋጣሚ እንደተገናኟት ከማይታወቅ አማረች ከምትባል ምስኪን ወጣት ልጅ ማስረገዛቸው ተሰማ። እሳቸውም አባትነታቸውን አምነው ልጃቸውን ሲንከባከቡ ቆዩ። ሆኖም ግን አይንህን በአይንህ አትይ ሲላቸው ህፃኑ በተፀነሰ 6ኛው ወሩ ላይ በድንገተኛ ህመም ሞቱ። ይሄን የአቶ ከበደ ወንድምና እህቶች የወንድማቸውንሀብት ለመውረስ ክስ ከፈቱ። ጊዜው ደርሶ የአቶ ከበደ ልጅ ተወለደ ሆኖም ህጻኑ በተወለደ በአንድ ቀኑ ከሆስፒታል ወደ ቤት ሲጓዝ በደረሰ የመኪና አደጋ ህጻኑ ወዲያውኑ ሲሞት እናቱ ደግሞ ህፃኑ ከመቶ ከግማሽ ሰዓት በኋላ ሞተች። የህፃኑም የእናቱም ሞት የመኪና አደጋው መሆኑ በሃኪሞች ተረጋግጠ። ሁኔታው አሳዛኝ ቢሆንም የአቶ ከበደ አህትና ወንድሞች ግን የወንድማቸው ሀብት ወራሽነታቸው የተረጋገጠ መሰላቸው።

በፍ/ቤት ክርክር ከተደረገ በኋላ ግን የአቶ ከበደ ሙሉ ሀብት ወራሽ መሆናቸው የተረጋገጠው ወንድም እህቶቻቸው ሳይሆኑ አቶ ከበደን በስም እንኳን የማያውቋቸው ለልጃቸው ለአማረች ቀብር ከገጠር የመጡትና ሕግ አዋቂ አማክረው የልጄ ልጅ ምትክ ወራሽነኝና የአቶ ከበደ ሀብት ይገባኛል ሲሉ ፋይል የከፈቱት አይደለም በሚሊዮኖች የሚቆ;ጠር ብር ሚሊዮን የሚባል ቁጥር መኖሩን እንኳን ማያውቁት ወ/ሮ አየለች ነበሩ። ነገሩ እንዴት መሰላችሁ አቶ ከበደ ልጃቸው ሳይወለድ ቢሞቱም በፍ/ብ/ሕ/ቁ 2 መሰረት የተፀነሰ ልጅ በህይወት ከተወለደና የሚኖር ከሆነ ለህጻኑ ጥቅም ሲባል እንደተወለደ ይቆጠራል። በመሆኑም አቶ ከበደ በመሞታቸው ሕጻኑ ሀብታቸውን በሙሉ በፍ/ብ/ሕ/ቁ 842(1) መሰረት በሕግ የመድረስ መብት አግኝቷል።

ሕፃኑ በተወለደ በአንድ ቀኑ 48 ሰዓት በሕይወት ላይ ቢቆይም የሞተው ክሰ አፈጣተር ውጭ በሆነው የመኪና አደጋ በመሆኑ በህክምና ማስረጃ በመረጋገጡ በፍ/ብ/ሕ/ቁ 4(3) መሰረት ከ48 ሰዓት በላይ በህይወት እንደኖረ ስለሚቆጠር በፍ/ብ/ሕ/ቁ 834 መሰረት የመውረስ መብቱን አግኝቷል። በመሆኑም አቶ ከበደ ልጅ ወልደው ስለሞቱ በፍ/ብ/ሕ/ቁ 842(1) መሰረት ስሙ ያልታወቀው ልጃቸው ይወርሳቸዋል።

አማረች ልጇ ከመቶ ከግማሽ ሰዓት በኋላ በመሞቷ ልጇ ሲሞት በሕይወት ስለነበረች በፍ/ብ/ሕ/ቁ 830 መሰረት እና በ843 ድንጋጌ ልጅ ያልወለደ ሟች እናትና አባቱ በሁለተኛ ደረጃ በሕግ የመውረስ መብት ስላላቸው አማረች ልጇ ከአባቱ ከአቶ ከበደ የወረሰውን ሀብት ወርሳ ነው የሞተችው። እርሷ ስትሞት ደግሞ ከሞተው ህጻን ሌላ ልጅ ስለሌላት የመውረስ መብቱን የሚያገኙት እናትና አባቷ ናቸው። አባቷም ሆኑ ሌሎች ምትክ ወራሾች ስለሌሉ ብቸኛው የአቶ ከበደ

ሀብት ወራሽ የአማረች እናት ወ/ሮ አየለች ናቸው። አይገርምም ህጻኑ በህይወት ከአንድ ቀን በላይ ለመቆየት ባይታደልም ተወልዶ ሕጉ እንደሚለው ኖሮ በመሞቱ የአቶ ከበደን ሀብት ከወንድም እህቶቻቸው ወደ ማያውቁት ወደማያውቃቸው አያቱ ወ/ሮ አየለች አዞረው።

መወለድና ወላጅነትስለመወለድ አንስተናል አይደል?

ከመወለደ ጀርባ እናትና አባት አሉ። የእነሱስ ገዳይ የሚለውን ለመመለስ የተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ ድንጋጌዎችን እንመልከት። እናትነትን በተመለከተ ልጁን የወለደችው በመሆኑም ብቻ እናትነቷ እንደሚታወቅ በአንቀፅ 124 ላይ ተደንግጓል። እዚህ ጋር በሕንድና በሌሎች ሀገሮች ሲደረግ እንደምንሰማው በማህጸን ኪራይ የሌላ ሴት እንቁላልና የወንድ የዘር ፍሬ ተቀላቅለው የፈጠሩትን ፅንስ በህክምና ዘዴ ማህፀናቸውን አከራይተው አርግዘው ፅንሱ ተገቢው የእድገት ደረጃ ላይ ደርሶ የሚወለዱ እናቶች ናቸው የልጁ እናት የሚለውን ትርጓሜ ያመጣል። ህጋችን ምክንያቱም እናትነት የሚታወቀው ልጁን በመውለድ ነው ስለሚል የአንድ ልጅ አባትነትን በተመለከተ በሶስት መንገዶች እንደሚረጋገጥ የቤተሰብ ሕጉ ይደነግጋል።

1. የአባትነት የሕግ ግምት፡- በ/የቤ/ሕ/አ 125(1) ልጁ በሚፀነስበት ወይም በሚለወድበት ጊዜ በእናትየዋና በአንድ ወንድ መካከል በሕግ የታወቀ ግንኙነት በመኖሩ አባትነት እንደሚታወቅ ይደነግጋል።

በፍ/ብ/ሕ/ቁ 3 መሰረት የልጁ መፀነስ የሚቆጠረው ከተወለደበት በፊት ካለው ከሶስት መቶኛው ቀን ወዲህ ነው። በዚህ ድንጋጌ መሰረት ልጅ በጋብቻ ውስጥ የተፀነሰ ወይም የተወለደ ከሆነ አባቱ ባልየው ነው። ህጻኑ በጋብቻ ውስጥ እንደተፀነሰ የሚቆጠረው። ጋብቻው ከተፈፀመ ወይም ጋብቻ ባይፈፀሙም እንደ ባልና ሚስት መኖር ከጀመሩበት ከ180 ቀናት በኋላ የተወለደ ከሆነ ነው። ጋብቻው ቢፈርስ ወይም እንደ ባልና ሚስት አብሮ የመኖሩ ሁኔታ ሲቋረጥ ደግሞ ህጻኑ ጋብቻው ቢፈረስ ወይም እንደ ባልና ሚስት አብሮ መኖሩ በተቋረጠ በ300 ቀናት ውስጥ ከተወለደ አባትየው ነው ብሎ ሕግ የሚገምተው ባልየውን ወይም ጋብቻ ሳይፈፅም እንደ ባል አብሮ ሲኖር የነበረውን ሰው ነው።

2 ልጅነትን መቀበል፡- አባትነትን በሕግ ግምት ማረጋገጥ ካልተቻለ ደግሞ በተ/የቤ/ሕ/አ 131 መሰረት የተወለደውን ወይም የተፀነሰውን ልጅ አምኖ ልጄ ነው ብሎ በመቀበል አባት መሆን ይቻላል። አባትነትን መቀበል በክብር መዝገብ ሹም ፊት (ልደት ሞትን ጋብቻን የሚመዘግብ ሹም) ቀርቦ ቃልን በመስጠት በፅሁፍ በሚደረግ ኑዛዜ ወይም ስልጣን በተሰጠው አካል በተረጋገጠ ሰነድ አባት መሆንን በመግለፅ አባትነትን መቀበል እንደሚቻል የቤ/ሕ/አ133 ይደነግጋል። ሆኖም ግን በአንቀፅ 136 መሰረት እናት የአባት ነኝ ባዩን ቃል እውነትነት ካላረጋገጠች በሕግ ፊት እውቅና አይሰጠውም። አንድን ልጅ ብዙ አባቶች ልጃችን ነው በሚል ሊቀበሉት ግን አይችሉም። አንድ አባት ልጄ ነው ብሎ ከተቀበለ በኋላ ሌላ አባት ልጁን ለመቀበል የቀድሞው አባት የሰጠው ቃል መሻር እንዳለበት በቤተሰብ ሕግ በአንቀፅ 142 ላይ ተደንግጓል።

3 በፍ/ቤት የሚወሰን አባትነት፡- ከላይ በተጠቀሱት መንገዶች የልጁን አባት መወሰን ካልተቻለ ፍ/ቤት በተሸሻለው የቤ/ሕአ 143 በተለያዩ ሁኔታዎች አባት ነው የሚባለውን ሰው ሊወሰን ይችላል። ልጁ ሲፀነስ በእናቲቱ ላይ አስገድዶ መድፈር ወይም በተስፋ ቃል የማሳት ተግባር ከተፈፀመ ልጅነትን የማያረጋግጡ ደብዳቤዎችና ሌሎች ፅሁፎች ሲገኙ፣ በሕግ ከታወቁት ግንኙነቶች ውጭ እናትና አባት በቀጣይነት በግብረ ስጋ ግንኙነት አብረው ከቆዩ፣ አባት የሚባለው ሰው ልጁን በመንከባከብ ወይም በማሳደግ ሂደት እንደአባቱ ከተሳተፈ አባትነትን በፍ/ቤት ውሳኔ ይረጋገጣል።ሆኖም የአባትነት የህግ ግምት የሚሰጠው ሰው ካለ ልጅ መወለድ

አለመቻሉ በአስተማማኝ የሕክምና ዘዴ ካልተረጋገጠ፣ በመጥፋቱ ወይም በአደጋ አባት መሆን የማይችልበት፣ ወይም በደም ምርመራ ወይም እንደዲኤንኤ ምርመራ ካሉት የህክምና ምርመራዎች አባት ነው የተባው ሰው አባት ሊሆን እንደማይችል ከተረጋገጠ ነው ሌላ ሰው ላይ በፍ/ቤት የአባትነት ውሳኔ እንዲወሰን የተ/ቤ/ሕ/አ 135 መሰረት ክስ የሚቀርበው።

ልደትወሳኝ ኩነቶች የሚባሉት

በሰው ልጅ የህይወት ጉዞ ውስጥ ሁነኛ ስፍራ ያላቸው የመወለድ የጋብቻ እና የመሞት ኩነቶች ናቸው። እነኚህ ኩነቶች እንዲመዘገቡ በፍ/ብ/ሕጉ ውስት የተደነገጉ ቢሆንም በተግባር ግን ብዙም ሳይሰራባቸው ለ52 ዓመታት ቆይተዋል። በ2004 ዓ.ም የወጣው የወሳኝ ኩነት ምዝገባ እና የብሔራዊ መታወቂያ አዋጅ ቁጥር 760/2004 እነዚህ ኩነቶች በዘመናዊ መልክ እንዲመዘገቡ ያዛል።

ልደትን በተመለከተ በአዋጁ አንቀፅ 18(2) መሰረት ሊያዘገይ የሚያስችል በቂ ምክንያት ከሌለ በስተቀር በ90 ቀናት ውስጥ መመዝገብ አለበት።መዝጋቢው ኃላፊነቱ የተሰጠው የክብር መዝገብ ሹም ነው። የልደት መዝገብ በአዋጅ አንቀጽ 24 መሰረት የህፃኑን ሙሉ ስም፣ ጾታ፣ የትውልድ ቀን የትውልድ ቦታ የልደቱን አይነት ነጠላ ወይም የአንድ በላይ እና በውልደት ጊዜ የተደረገ እርዳታ መጥቀስ አለበት።

በተጨማሪም የወላጆቹን መረጃዎቹ ሙሉ ስም የትውልድ ቀንና ቦታ መደበኛ መኖሪያ ቦታ የጋብቻ ሁኔታ ዜግነት ኃይማኖት፣ ብሔር እና በሕይወት ካሉ ፊርማቸውን መያዝ አለበት። አስመዝጋቢው፣ ወላጅ ካልሆነም ሙሉ መረጃውን ለህጻኑ ያለውን ዝምድና እና ፊርማውን የሚያካትት ሲሆን የመዝጋቢው አካል ስም ፊርማ ማህተምና የምዝገባን ቀን መስፈርም አለበት።

ተጥሎ የተገኘ ሕፃን፡- ህጻኑ ተጥሎ የተገኘ ከሆነ በአዋጁ አንቀጽ 24 መሰረት ለህፃኑ የተሰጠውን ስም ፆታ የሚገመተውን እድሜ የተገኘበት ቀንና ቦታ የሚያመለክቱ ዝርዝር መረጃዎችን እና በቅፁ ጀርባ ላይ ተጥሎ የተገኘ የሚል መግለጫ መስፈር አለበት።

ልደትን የማስመዝገብ ግዴታ በአንቀጽ 26 ላይ ተጥሏል። ግዴታው የተጣለባቸው የህፃኑ እናት ወይም አባት ወላጆቹ ከሌሉ የህፃኑ አሳዳሪ ለሌላው ህጻኑን በመንከባከብ ላይ ያለው ሰው ነው። ህጻኑ ተጥሎ ከተገኘ ወይም ወላጆቹ የማይታወቁ ከሆኑ ይህን ሁኔታ የሚያውቅ ማንኛውም ሰው በአቅራቢያው ለሚገኝ ፖሊስ ወይም አግባብ ላለው ሌላ የመንግስት አካል ሪፖት ማድረግ አለት። ይህ ሪፖትር የደረሰው አካል ደግሞ በሶስት ቀን ጊዜ ውስጥ በአቅራቢያው በሚገኘው የክብር መዝገብ ሹም ፊት ለመቅረብ የማስመዝገብ ግዴታ ተጥሎበታል።

ህጻኑ መወለድ የሚመዘግብ ሸም ለህጻን የተሰጠውን ወይም ሊሰጠው ያሰበውን ስም ከአስመዝጋቢው መጠየቅ አለበት። ሹሙ ካልተነገረ ወይም ስሙ ህግን ወይም ልማድን የሚቃረን ከሆነ ደግሞ በአዋጁ አንቀጽ 27 የክብር መዝገቡ ሹሙ ለህጻኑ የግል ስም እንዲያወጣለት ይደነግጋል።

የልደት ምዝገባ ቦታ የህፃኑ ወላጆች መደበኛ መኖሪያ ቦታ አቅራቢያ የሚገኝ የአስተዳደር ጽ/ቤት ሲሆን ልጁ ተጥሎ ከተገኘ ወይም ወላጆቹ ካልታወቁ ደግሞ በተገኘበት ቦታ አቅራቢያ የሚገኝ የአስተዳደር ጽ/ቤት ነው። ህፃኑ የተወለደው በጤና ተቋም ውስጥ ከሆነ ደግሞ የተቋሙ ኃላፊ አስፈላጊዎቹን መረጃዎች የያዘ የምስክር ወረቀት ወዲያውኑ አዘጋጅቶ ልደቱን የማስመዝገብ ግዴታ ላለበት ሰው መስጠት አለበት።

መወሰለድን የማሳወቅ ግዴታን አለመወጣት

በአዋጁ አንቀጽ 66 ላይ ወሳኝ ኩነትን የማስምዝገብ ግዴታን አለማክበር ከስድስት ወር በማይበልጥ ቀላል እስራት ወይም እስከ ብር አምስት ሺህ በሚደርስ የገንዘብ መቀጮ እንደሚያስቀጣ ደንግጓል። የወንጀል ሕጋችን በአንቀጽ 656 ላይ ሕግ በሚያዘው መሰረት የአንድ ህጻንን መወለድ ለክብር መዝገብ ሹም ያላሳወቀ ማንኛውም ሰው ከአምስት መቶ ብር በማይበልጥ መቀጮ ወይም በአንድ ወር እስራት እንደሚቀጣ ይደነግጋል። የተጣለን ህጻን አግኝቶ ለሚመለከተው አካል አለማሳወቅም ቅጣቱ ተመሳሳይ ነው።

በተጨማሪ በክብር መዝገብ ሊመዘገብ የሚገባውን ማንኛውንም ፍሬ ነገር የደበቀ ወይም ወደ ሀሰት የቀየረ በተለይም የአንድን ህጻን ማንነት ወይም ልደት በሚመለከት አስቦ ሀሰተኛ መግለጫ የመዘገበ ወይም ያስመዘገበ ሰው በቀላል እስራት ይቀጣል። ጥፋቱ አስቀድሞ ሊታወቅ የሚችል ከባድ ውጤት ያስከተለ ወይም ሊያስከትለ የሚችል ሆኖ በተለይም ህጻንን አለዋወጦ የማስመዝገብ ድርጊት የሚያስከትለውን ውጤት የሚመለከት ከሆነ ቅጣቱ ከአምስት ዓመት የማይበልጥ ጽኑ እስራት እንደሆነ የወ/ሕ/አ 657 ይደነግጋል።n

በልደት ማግስት ስለውልደት

መዝጋቢው ኃላፊነቱ የተሰጠው የክብር መዝገብ ሹም ነው።

የልደት መዝገብ በአዋጅ አንቀጽ 24 መሰረት የህፃኑን ሙሉ ስም፣ ጾታ፣ የትውልድ ቀን የትውልድ ቦታ የልደቱን አይነት ነጠላ ወይም

የአንድ በላይ እና በውልደት ጊዜ የተደረገ እርዳታ መጥቀስ አለበት።

Page 19: ንደ3 - ethioforum.orgethioforum.org/wp-content/uploads/2014/01/sendek435.pdfሰንደቅ 9ኛ ዓመት ቁጥር 435 ረቡዕ ታህሳስ 30 2006 አታሚ፤ ብርሃንና

ሰንደቅ 9ኛ ዓመት ቁጥር 435 ረቡዕ ታህሳስ 30 2006 የኔ ሃሳብበዚህ ዓምድ ስር የሚወጡ ጽሁፎች የፀሐፊውን እንጂ የኤዲቶሪያሉን አቋም አያንፀባርቁም

19

(ክፍል አንድ)

በ1997 ዓ.ም በተካሄደው አገር አቀፍ ምርጫ የያኔውን ኢዴአፓ-መድህን/ቅንጅት ፓርቲን ወክለው፣ በአዲስ አበባ ከተማ በወረዳ 5 የምርጫ ክልል ተወዳድረው በማሸነፋቸው የ3ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የነበሩትን የተከበሩ አቶ ተመስገን ዘውዴን የሕይወት “ታሪክ” እና የፖለቲካ “ቁጭት” የያዘ መጽሐፍ “ከፓርላማው በስተጀርባ” በሚል ርዕስ ታትሞ በቅርቡ በገበያ ላይ ውሏል።

ይህ መጽሐፍ የተሰናዳው ዳንኤል ተፈራ በተባለ (አንተ ያልኩት ያው በተለምዶ ጋዜጠኛና ደራሲ ‘አንተ’ ስለሚባል ነው) ግለሰብ ነው። ካልተሳሳትኩ አቶ ዳንኤል ከዚህ ቀደም የዶ/ር ነጋሦ ጊዳዳን የሕይወት ታሪክ የያዘ መጽሐፍ “የነጋሦ መንገድ” በሚል ርዕስ አሰናድቶ ማሳተሙ ይታወሳል። ይህ ሁለተኛ መጽሐፉ መሆኑ ነው። በነካ እጁ ሦስት፣ አራት፣… እያለ እንደሚቀጥል ተስፋ አደርጋለሁ።

“ጋዜጠኛ” ዳንኤል (አሁን ፖለቲከኛም ሆኗል ሲባል ሰምቻለሁ) የጀመረው የታዋቂ ግለሰቦችን የሕይወት ታሪክ (ባዮግራፊ) ቃለ ምልልስ አድርጎ የማቀነባበር ዘዴ ሌሎችም እየተከተሉት ያለ የሚበረታታ አሰራር ነው። ይሁን እንጂ፣ አቶ ዳንኤል “በፖለቲከኛነት” እና “በጋዜጠኛነት” መሀል ላይ ቆሞ ከሚመናተል አንዱን አቅጣጫ ቢመርጥ የተሻለ መስሎ ታይቶኛል። ምክንያቱም ጋዜጠኛነት ገለልተኛነትን ይጠይቃል። ፖለቲካው ደግሞ ወገንተኛነትን ይጠይቃልና ነው።

አቶ ዳንኤል የአቶ ተመስገን ዘውዴን ታሪክ ባቀነባበረበት በዚሁ መጽሐፉ በገጽ 92 ላይ እንዲህ የሚል ሃሳብ አስፍሯል፤ “የየትውልዱን ሀቀኛ ታሪክ ሳይበረዝ ልናስተላልፍ የምንችለው ከባለታሪኮች አፍ በመስማት ይመስለኛል” ይላል። በዚህ አባባል መስማማት ይቻላል። ይሁን እንጂ፣ ከባለ ታሪክ አፍ የተነገረ ሁሉ “ሀቀኛ” ታሪክ ሊሆን አይችልም። አንድ ታሪክ “ሀቀኛ ታሪክ” ሊሆን የሚችለው ባለታሪኮቹ ለነፍሳቸውም ለስጋቸውም አድረው፤ ያዩትን፣ የሰሙትንና የሆነውን ሳይቀንሱ፣ ሳይጨምሩና ሳይበርዙ የተናገሩት እንደሆነ ብቻ ነው። ያ ካልሆነ ታሪኩ “የውሸት ታሪክ” ነው የሚሆን!

ታሪክን የሰሚሩትም ሆኑ የሚተርኩት ሰዎች ናቸው። ከሰዎች ውስጥ ደግሞ አንዳንዶቹ ሰው በመሆናቸው የሰው ባህሪ የሆነው ከሀቅ የመሸሽ እና ከእውነት የመራቅ ዝንባሌ ይታይባቸዋል። ይህንን ዝንባሌ በማረቅ ማስተካከል የሚቻለው ደግሞ ከፖለቲካ ወገንተኛነት በራቀ መንፈስ ድርሳናትን የሚያትቱ ሀቀኛ ጸሐፊዎች ናቸው። ዛሬ በየስፍራው ያሉ ዕድሜ ጠገብ የታሪክ ሰነዶቻችን ተዓማኒነት አጥተው በታሪክ ምሁራን ዘንድ “የደብተራ ታሪክ” የሚል ስም የተሰጣቸው፤ በማሞገስና በማወደስ የተሞሸሩ፣ በውሸትና በማጋነን ላይ የተመሰረቱ፣ የአንድ ወገን የትረካ ውጤት በመሆናቸው ይመስለኛል።

አቶ ዳንኤል የአቶ ተመስገንን የሕይወት ታሪክ ሲያዘጋጅ እሳቸው ያሉትን ነገር ሁሉ እንደ ወረደ በመጻፉ፤ ጊዜና ጉልበት ያባከነበትን መጽሐፍ በሕጸጽ የተሞላ እንዲሆን አድርጎታል። አቶ ዳንኤል የሚያዘጋጀው የታሪክ መጽሐፍ መሆኑን ነግሮናል። ይሁን እንጂ፣ አቶ ተመስገን ስለሚናገሩት ነገር እውነት መሆን ወይም አለመሆን ጭራሽ ያሰበው አልመሰለኝም። ከዚህ በፊት አቶ ዳንኤል ባሳተመው መጽሐፍ ዶ/ር ነጋሦ ስለማያውቁት ነገር መናገራቸውን ያዩ አንዳንድ ሰዎች በጋዜጦች ላይ አስተያየት ማቅረባቸውን አስታውሳለሁ።

አቶ ዳንኤል፤ አቶ ተመስገን ስማቸውን እያነሱ አስተያየት የሰጡባቸውን ሰዎች (ሁሉንም ባይሆንም) የተወሰኑትን አግኝቶ “እከሌ እንዲህ የሚል ሃሳብ ተናግሯል፣ ይህ

ከፓርላማው በስተጀርባ የነበረው የአቶ ተመስገን ዘውዴ ገመና

ነገር እውነት ነው ወይ?” የሚል ጥያቄ በማቅረብ የተሟላ ሰነድ ቢያዘጋጅ የተሻለ ይሆን ነበር የሚል እምነት አለኝ። ያን ቢያደርግ ኖሮ፤ እኔንም ይህቺን ማስታወሻ ከማዘጋጀት ያድነኝ ነበር። ለዛሬው ለመጽሐፉ አዘጋጅ ሳይሆን የውሸት ታሪክ በመናገር የመጽሐፉን አዘጋጅና አንባብያንን ላሳሳቱት ለአቶ ተመስገን ዘውዴ የሚከተለውን መልስ አቀርባለሁ።

የተከበሩ አቶ ተመስገን ዘወዴ “የሕይወት ታሪኬ ነው” ብለው የተረኩትን መጽሐፍ ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ አንብቤዋለሁ። በገጽ 150 ላይ አቶ ተመስገን እንዲህ ይላሉ “በእውነት ፊት ቆሜ ለትውልዱ ማስተላለፍ በምፈልገው በዚህ መጽሐፍ ውስጥ መዋሸት አልፈልግም” ይላሉ። ውድ አቶ ተመስገን! “መዋሸት አልፈልግም” ማለትን ምን አመጣው? ነገሩ “የገብርኤልን መገበሪያ የበላ…” መሆኑ ነው። ቃልና ተግባራቸው ለየቅል የሆነው አቶ ተመስገን እንዲህ ያለ መሀላ ቢደረድሩም በተለይ እኔን በተመለከተ ስሜን ጠቅሰው ነጭ ውሸት መተረካቸውን አንብቤአለሁ። በሌሎች እኔም በማውቃቸው ጉዳዮች ላይም እንዲሁ የተሳሳተ፣ ከመጠን በላይ የተጋነነ እና “ሳይሆን አይቀርም” በሚል ጥርጣሬ ላይ ተመስርተው ሃሳብ መሰንዘራቸውን አስተውያለሁ። ሊታረሙ ይገባቸዋል የምላቸው ጉዳዮች በርካታ ቢሆኑም የጋዜጣውን ዓምድ ላለማጣበብ

ዋና ዋና በምላቸው ላይ ብቻ ማተኮርን መርጫለሁ።

ቅድሚያ ሰጥቼ የማነሳው የእኔና የአቶ ተመስገንን ፀብ በተመለከተ ነው። በዚህ ጉዳይ ላይ አቶ ተመስገን ትንሽ እውነት ይዘው በርካታ ውሸትና ተረት ነው የተናገሩት። መጣላታችን፣ ከአንዴም ሁለት ጊዜ ሊደበድቡኝ መወራጨታቸው፣ በዚህም ምክንያት እኔ ክስ ማቅረቤና ሽማግሌ ልከው መታረቃችን እውነት ነው። ከዚያ ውጪ ያለው የፈጠራ ተረት ነው። የእርሳቸውን ሃሳብ እየጠቀስኩ ላብራራ።

የጠቡን መነሻና ሂደት በተመለከተ እንዲህ ይላሉ አቶ ተመስገን፤ “…አንድ ቀን የአማካሪ ምክር ቤት ስብሰባ ላይ ከመሬት ተነስቶ ‘አቶ ተመስገን እኛ እኮ ነን ፖለቲካ ያስተማርንህ’ አለኝ… ስንወጣ ተከተልኩና ‘አንተ! እንዴት ነው እኔን ፖለቲካ ልታስተምረኝ የምትችለው?’ አልኩት… ፈጠን እያለ ሰምቶ ያልሰማ በመምሰል ከእኔ እየራቀ ሄደ። በሌላ ቀን እኔ ወደ ፓርላማ ስገባ እሱ ደግሞ ሲወጣ ተገጣጠምን። እኔ መጣላታችንን ረስቼው ሰላም ልለው ሲቃጣኝ ‘በህግ አምላክ! እንዳትጠጋኝ! ሊደበድበኝ ነው’ ብሎ ጮኸ። … ሚጢጢ ሴራ እንደሆነች ለመገመት ብዙ አልፈጀብኝም…” (ገጽ 207-208)

ወንድሜ አቶ ተመስገን ሆይ! አሁን ሁሉም ነገር አልፏል። እኔና እርስዎም ታርቀን ከዚያ በኋላ በሰላም ብዙ አሳልፈናል። ፓርላማውንም ለቀናል። እኔማ ፖለቲካውንም ለቅቄ የእፎይታ ኑሮ መኖር ከጀመርኩ እነሆ አራት ዓመት መሆኑ ነው። ታዲያ አሁን እንዲህ ያለውን ተራና የማይረባ ጉዳይ እንደ ትልቅ ነገር በመጽሐፍ እንዲታተም ማድረግ ምን ፋይዳ አለው? ለአንባቢውስ ምን ያስተምራል? ምን ዓይነት የፖለቲካ ትርፍስ ያስገኛል?

ውድ አቶ ተመስገን! እዚያ ቅንጅት የሚባል ስብስብ ውስጥ የነበራችሁ ሰዎች አንዲት ተራ የብልጠት መንገድ አለቻችሁ። ከሰረቀ በኋላ “ሌባ! ሌባ!” እያለ እንደሚሮጠው የመርካቶ ጮሌ፤ አንድ መሆን የማይገባው ስህተት ራሳችሁ ትሳሳቱና በነገሩ በሌለበት የዋህ ላይ ሀጢያቱን ለማላከክ “ያዘው!... እሱ ነው!... ከእነከሌ ጋር ሆኖ እያሴረ ነው!” ወዘተ. እያላችሁ በማዋከብ የየዋሃንን ቀልብ ለመሳብ የማትወጡት ተራራ የማትወርዱት ቁልቁለት የለም። እንዲህ ያለው የተባነነበት የብልጣብልጥ መንገድ ጊዜአዊ እርካታን ያስገኝ እንደሆነ እንጂ ዘላቂ ውጤት አያመጣም። ሐቁ ገሃድ ሲወጣ እርቃናችሁን መቅረታችሁ ተደጋግሞ ታይቷል። ይህ የተነቃበት ታክቲክ ለጊዜው ለመጽሐፍ ማሻሻጫ ይሆን ይሆናል። አቶ ተመስገን በዚህ መልኩ ውሸት ያቀረቡት እኔ ከፖለቲካው መድረክ ስጠፋ ከምድረ-ገጽ የጠፋሁ መስሎአቸው ከሆነ አሁንም የባሰ ስህተት ነው የሚሆን።

ነገሩ ከተነሳ አይቀር የተሳሳተውን ለማረቅ ይቻል ዘንድ በዚያ እለት የሆነው እንዲህ ነው። በስብሰባው ላይ “አቶ ተመስገን እኛ እኮ ነን ፖለቲካ ያስተማርንህ” ያልኩት ከመሬት ተነስቼ አልነበረም። አቶ ተመስገን “ኢዴፓ የሚባል ፓርቲ የለም። በውህደት ከስሟል” በማለት የመጀመሪያዋን ጠጠር ወረወሩ። እኔ የመናገር እድል ሲሰጠኝ ደግሞ “የለም አቶ ተመስገን ኢዴፓ አልከሰመም። እርስዎ ራስዎ እዚህ የተገኙት በኢዴፓ ነው። እርስዎ የግል እጩ ተወዳዳሪ ነበሩ። እኛ ወደ ኢዴፓ አምጥተን፣ የፖለቲካ ርዕዮተ ዓለማችንን አስተምረን፣ በኢዴፓ ስም አወዳድረን፣ አባሎቻችንና ደጋፊዎቻችን በቅስቀሳና በታዛቢነት እንዲያግዙዎት ባናደርግ ኖሮ እንደ ሌሎቹ የግል ተወዳዳሪዎች እርስዎም አይመረጡም ነበር። እዚህ ቦታም ላይ አይገኙም ነበር…” የሚል መንፈስ ያለው ሃሳብ ነበር የተናገርኩት። ኢዴፓን ወክዬ እዚያ ቦታ ላይ እስካለሁ ድረስ ይህንን የመናገር ግዴታ ነበረብኝ። ደግሞም የተናገርኩት አንድም ስህተት

አልነበረውም። አቶ ተመስገን ፖለቲካ ቢያውቁ

ኖሮ፣ አቶ ተመስገን ስለዴሞክራሲ የጠራ ግንዛቤ ቢኖራቸው ኖሮ፣ አቶ ተመስገን የሊበራል ዴሞክራሲ አስተሳሰብ ቢገባቸው ኖሮ፣… እኔ “ፖለቲካ አስተማርኩህ” ብላቸው እንኳ ሃሳቤን በሃሳብ ለማሸነፍ እዚያው መድረክ ላይ ይከራከሩ ነበር እንጂ በቡጢ ካልነረትኩህ ብለው በተደጋጋሚ ለድብድብ አይጋበዙም ነበር። እንዲያው ለነገሩ “ፖለቲካ ያስተማርንህ እኛ ነን” ማለትስ ያን ያህን ደምን የሚያፈላ ሆኖ ለዱላና ለድብድብ የሚጋብዝ ነገር ነው? ይሄ ነው እንግዲህ የአቶ ተመስገን የፖለቲካ ብስለት!

አቶ ተመስገን በመጀመሪያው ቀን እየተሳደቡ ሲከተሉኝ ሸሸሁ። በወቅቱ ግን አቶ አብዱረሂም ያሲን የተባሉ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመጡ የኮሚቴአችን አባል አብረውን ስለነበሩ “ይሄን ሁኔታ ልብ አድርጉልኝ” አልኩና አለፍኩት። ….እኔ ነገሩ እለታዊ ግጭት መስሎኝ ትቼው ነበር። በሃሳብ መሸነፉ ያንገበገባቸው አቶ ተመስገን ግን ሳምንት ባልሞላ ጊዜ አሁንም ቡጢያቸውን አሳምረው ሊነርቱኝ ከእሳቸው በማይጠበቅ ሁኔታ እየተሳደቡ ሲከተሉኝ በወቅቱ በጥበቃ ላይ ወደነበሩት ፖሊሶች እያመለከትኩ “በህግ አምላክ” እያልኩ ሸሸሁ። ፖሊሶቹም እዚያ የተቀመጡት የእኛኑ ደህንነት ለመጠበቅ በመሆኑ አቶ ተመስገንን ‘ተው’ ብለው እንዳይመቱኝ ሲከላከሉ አቶ ተመስገን እነሱን ጭምር ይሰድቧቸውና ይዘልፏቸው ጀመር።

ከዚያ በላይ መታገስ ሕይወቴን አደጋ ላይ እንደሚጥል ስለገመትኩ በምክር ቤቱ ደንብ መሰረት ከሰስኩ። ታዲያ ይሄ ምነድነው ጥፋቱ? አቶ ተመስገን ራሱ ተማቶ ራሱ እንደሚጮኸው ጅራፍ፤ ምንም ሳልደርስባቸው ካልተማታሁ አሉ፣ ስከስ ደግሞ ከኢህአዴግ ጋር ተመሳጥሮ ከሰሰኝ ይላሉ። አሁን ይሄ አባባል የጤና ነው? ወይስ ‘እኔ ብፈልግ ልስደብህ፣ ላዋርድህ፣ አለፍ ሲልም በቡጢ ላደባይህ፣ አንተ አንገትህን ደፍተህ ሁሉንም ነገር አንገትህን ደፍተህ መቀበል ነበረብህ’ ነው የሚሉት አቶ ተመስገን? ሽማግሌ ልከው የታረቅነው እኮ እኔ ጥፋተኛ ስለሆንኩ አይደለም። ከዚህ በላይ የምለው የለም። ሁሉንም ነገር አንባቢ ይፍረደው!!!

ከዚህ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ሦስት ነገሮችን በታሪክ ፊት መናገር እፈልጋለሁ። (1ኛ) እንኳን ከእኔ ጋር ሴራ ሊያቀነባብር አቶ ተመስገንን በእኔ ክስ ምክንያት ከም/ቤት እንዳይባረሩ ያደረገው ኢህአዴግ ነው። መጽሐፉ ላይ እንደተጠቀሰው አቶ ተመስገን እኔን ይቅርታ እንዲጠይቁ አቅጣጫውን ያመላከቷቸው፣ መላውን የነገሯቸው የኢህአዴግ አባል ናቸው። እኔን ደግሞ አንድ የኢህአዴግ ከፍተኛ ሰው ጠሩኝና በክሱ ላይ አክርሬ ብሄድ ለምክር ቤቱ፣ ለአቶ ተመስገን፣ ለተቃዋሚው ጎራም ሆነ ለመረጠን ሕዝብ ጭምር ጥሩ እንዳልሆነ በመግለጽ ነገሩን ረጋ ብዬ እንዳየው መከሩኝ። የእኔም ፍላጎት አቶ ተመስገን ከፓርላማ እንዲባረሩ ለማድረግ ባለመሆኑ ክሴንም ሳላነሳ፣ እርቁንም እምቢ ሳልል በእንጥልጥል ተውኩት። ክሱን ያላነሳሁት የአቶ ተመስገን ባህሪ አስቸጋሪ በመሆኑ ሌላ ጊዜ እቀብጣለሁ ቢሉ የመጨረሻዋን ካርድ ለመምዘዝ እንዲያመቸኝ በማሰብ ነው።

(2ኛ) አቶ ተመስገን ተደጋጋሚ የድብድብ “ግብዣ” ሲያቀርቡልኝ መሸሽን የመረጥኩት ደካማና አቅመቢስ ስለሆንኩ አልነበረም። እንኳን ከአቶ ተመስገን ጋር ቀርቶ ከዕድሜ እኩዮቼም ጋር ቢሆን እራሴን ከጥቃት ለመከላከል የሚያስችል አፍላ የወጣትነት ጉልበት እንዳለኝ አምናለሁ። ይሁን እንጂ፣ አንደኛ፡- እኔ የወጣሁበት ማህበረሰብም ሆነ በመልካም ስነ-ምግባር ኮትኩቶ ያሳደገኝ ቤተሰቤ እንኳን በእድሜ ከሚበልጠኝ አዛውንት ከእድሜ እኩዮቼም ጋር ቢሆን ግጭትን በድብድብ እንድፈታ ስላላስተማረኝ፣ ሁለተኛ፡- በነበረኝ የፖለቲካ ሕይወትም እከተለው የነበረው መርህ ግጭትን

በውይይት በመፍታት ላይ የተመሰረተ ስለነበር፣ ሦስተኛ፡- አቶ ተመስገን ጋር መደባደብ አቶ ተመስገንን ጀግና (Hero) ማድረግ መሆኑን ከግንዛቤ በማስገባት፣ አራተኛ፡- በግለሰባዊ ሕይወቴም በሕግ የበላይነት የማምንና ለሰላማዊ አማራጭ የቅድሚያ ቅድሚያ የምሰጥ በመሆኑ፣ የአቶ ተመስገንን የድብድብ ትንኮሳዎች በመሸሽ ማሳለፍን እንድመርጥ አስገድዶኛል።

(3ኛ) አቶ ተመስገን ስማቸውን እያነሱ ከወቀሷቸው ሰዎች አንዱ የምክር ቤቱ አፈ-ጉባዔ የነበሩት አምባሳደር ተሾመ ቶጋ ናቸው። አቶ ተመስገን አላወቁትም እንጂ አምስት ዓመት ሙሉ መድረክ ሰጥተው እንዲናገሩ ያደረጓቸው አምባሳደር ተሾመ ናቸው። ሰው መመስገን ያለበት ሲሞት ብቻ መሆን የለበትም። አምባሳደር ተሾመ የሰለጠነ አስተሳሰብ ያላቸው፣ የዲፕሎማሲ ጥበብን የተካኑ፣ ስለፓርላማ ምንነት ብቻ ሳይሆን ስለአሰራሩም የጠለቀ ግንዛቤ ያላቸው፣ እያንዳንዷን ሰነድ አንብበው ወደ ስብሰባ የሚመጡ ጥንቁቅ ፖለቲከኛ መሆናቸውን በአምስት ዓመት ቆይታዬ አስተውያለሁ። አምባሳደር ተሾመ 547 ባህሪ፣ 547 ፍላጎት፣ 547 አመለካከት፣… ያላቸውን የምክር ቤት አባላት አቻችለው በመምራት ለመድብለ ፓርቲ አሰራር ባዶ የነበረውን ፓርላማ በሰነድ የተደገፈ የአሰራር ስርዓት እንዲኖረው ያደረጉ ሰው ናቸው።

በአንድ ፓርቲ ስም ተወዳድረው የተመረጡ የምክር ቤት አባላት ምክር ቤት ከገቡ በኋላ ፓርያቸውን ቢለቁም መቀመጫቸው ባስመረጣቸው ፓርቲ ስም እንዲሆን በምክር ቤቱ ደንብ ላይ የተደነገገ በመሆኑ የኢዴአፓ-መድህን አባል የነበሩት እነ አቶ ተመስገን ዘውዴ መቀመጫ አልነበራቸውም። እናም አምባሳደር ተሾመ በሕግ መሰረት መብትና ጥቅሙ ሊከበርለት የሚገባውን እያከበሩ፣ ለሌሎች ደግሞ ከተጨባጭ ሁኔታው በመነሳት መፍትሄ (Pragmatic Solution) እንዲኖር ባያደርጉ ኖሮ እነ አቶ ተመስገን የምክር ቤቱን መቀመጫ አሙቆ ከመሄድ የዘለለ ሚና አይኖራቸውም ነበር።

ተቃዋሚዎች በተትረፈረፈ ሰዓት አንድ ደቂቃ፣ ሁለት ደቂቃ ተሰጠን የሚል አቤቱታ እንደሚያሰሙት ሁሉ፤ የኢህአዴግ አባላት ደግሞ ‘አፈ-ጉባዔው የኢህአዴግን ሰዓት ለተቃዋሚዎች እየሰጠ ምክር ቤቱን ፋይዳ ያለው ሃሳብ ማቅረብ የማይችሉ ጥራዝ ነጠቅ ተቃዋሚዎች መፈንጫ አደረገው፣ በራሳችን ሰዓት አሰደበን’ ወዘተ. ይሏቸው እንደነበር አስታውሳለሁ።

ከዚህ ሌላ ስለ አምባሳደር ተሾመ መናገር የሚገባኝ ነገር አለ። በምክር ቤቱ ደንብ መሰረት አፈ-ጉባዔው ገለልተኛ መሆን የሚጠበቅበት ስብሰባዎችን በሚመራበት ወቅት መሆኑ ተደንግጓል። አምባሳደር ተሾመ ግን ይህንን ቢያውቁም በብዙ አጋጣሚዎች የሁሉም የምክር ቤት አባላት አፈ-ጉባዔ መሆናቸውን ለማሳየት ሲጥሩ አስተውያለሁ። ለምሣሌ፤ አቶ ተመስገን ዘውዴ እና አቶ ገብሩ ገ/ማሪያም ታመው በውጪ ሀገር እንዲታከሙ የገንዘብ መዋጮ ማሰባሰብ ባስፈለገበት ወቅት አምባሳደር ተሾመ በምክር ቤት ጉዳዮች አማካሪ ኮሚቴ ስብሰባ ላይ የመጀመሪያውን ፊርማ ከማኖራቸውም በላይ ሌሎች የኮሚቴው አባላትም እንዲያዋጡ አርአያነት ያለው ተግባር መፈጸማቸውን አይቻለሁ።

እናም፣ አምባሳደር ተሾመ ሁሉንም አቻችለው ምክር ቤቱን መምራታቸውን በበኩሌ በአድናቆት ነው የማየው። ስለሆነም፣ አምባሳደር ተሾመ የእነ አቶ ተመስገን ባለውለታ ናቸው እንጂ በክፋት መንፈስ ስማቸው መነሳት የሚገባቸው ሰው አይመስሉኝም። በሌላ በኩል፣ በአምባሳደር ተሾመ ቦታ አቶ ተመስገን ቢሆኑ ኖሮ የስንት የምክር ቤት አባላት አፍንጫ በቦክስ ሊሰበር እንደሚችል የአቶ ተመስገንን መጽሐፍ ያነበበ ሁሉ ሊረዳው የሚችል ይመስለኛል።

ይቀጥላል …..¾

(ከአብዱራህማን አህመዲን፤ የቀድሞ የፓርላማ አባል)

Email: [email protected]

ውድ አቶ ተመስገን!

እዚያ ቅንጅት የሚባል

ስብስብ ውስጥ

የነበራችሁ ሰዎች

አንዲት ተራ የብልጠት

መንገድ አለቻችሁ።

ከሰረቀ በኋላ “ሌባ! ሌባ!”

እያለ እንደሚሮጠው

የመርካቶ ጮሌ

Page 20: ንደ3 - ethioforum.orgethioforum.org/wp-content/uploads/2014/01/sendek435.pdfሰንደቅ 9ኛ ዓመት ቁጥር 435 ረቡዕ ታህሳስ 30 2006 አታሚ፤ ብርሃንና

ሰንደቅ 9ኛ ዓመት ቁጥር 435 ረቡዕ ታህሳስ 30 200620

አቀፉ (Globalization)፣ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂው በድሮ በሬ ማረስ እንደማይቻል የሚያሳስቡ የማንቂያ ደውሎች ሆነዋል። በዚህ ዐውድ ውስጥ ተግባቢ፣ ተስማሚ እና ተገቢ ፖሊሲዎችን ቀርፀው የሰሩና እየሰሩ ያሉ የዓለማችን ክፍሎች ከዚህ ዘመን ማግኘት የሚገባቸውን በመውሰድ እየተጠቀሙ ነው። በሚገባቸው ፍጥነት መራመድም ችለዋል። ህዝቦቻቸውን ከድህነት ነፃ አውጥተዋል። የወገኖቻቸውን ገቢ አሻሽለዋል፣ ህይወታቸውን ለውጠዋል። በአጠቃላይ ኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ ለውጦችን ለማስመዝገብ በቅተዋል። ከዚህ አንፃር ስንመለከት በአፍሪካም አመርቂ የሚባሉ ስኬቶች አሉ። አብዛኛው የአፍሪካ ኢኮኖሚ አግባብ ያለው ሊባል የሚችል የማክሮ ኢኮኖሚ እና ገበያ-መር የሆነ ኢኮኖሚ መመሥረት በመቻሉ ትርጉም ያለው ዕድገት፣ የተስፋፋ የገበያ እና የኢንቨስትመንት አማራጮችን እውን ማድረግ ተችሏል። ስለዚህ አፍሪካ ከዓለማችን ወቅታዊ ሁኔታዎች ጋር ተጣጥማ ለመዝለቅ “አጀንዳ-2063”ን የመሰለ የረጅም ጊዜ ዕቅድ ያስፈልጋታል። ለዚህ ደግሞ ትክክለኛው ጊዜ ዛሬ ነው። “አጀንዳ-2063” ለአፍሪካ ወቅታዊ የሚሆንበት አንዱና ወነኛ ምክንያትም ይሄው ነው።

ሁለተኛው ምክንያት የኔፓድ (ለአፍሪካ ልማት አዲስ አጋርነት) ልምድና ውጤት ነው። የኔፓድን ሀሳብ ተግባራዊ ለማድረግ በሀገራት፣ በክፍለ-አህጉር እና በዓለም አቀፍ ደረጃ የተደረጉ ጥረቶች አፍሪካ ኅብረት እንደ አህጉሪዊ ተቋም የተለያዩ ተቋማትን በሥሩ እንዲያደራጅ ምክንያት ሆነዋል። አፍሪካዊ በሆኑ የጋራ አጀንዳዎች ላይ በቁርጠኝነት ለመሥራትም ፈር ቀዷል። “አጀንዳ-2063”ም የኔፓድን ተልዕኮ ከሌሎች ጋር በማቀናጀት የሚዘጋጅ አህጉራዊ ሰነድ ይሆናል።

ከመቼውም ጊዜ በተሻለ እጅጉን የተባበረች እና የጠነከረች አፍሪካ እየታየች ያለንበት ወቅት ላይ መሆናችን ሌላኛው ምክንያት ነው። የዛሬዋ አፍሪካ ከቀደመችዋ አፍሪካ የምትለይበት ብዙ ገፅታዎች አሏት። የዚህ ዘመኗ አፍሪካ ከእስከዛሬዋ የበለጠ ትብብር እና ኅብረት የሚታይባት አህጉር ሆናለች። በዓለም አቀፍ ደረጃ ያላት ተሰሚነትና ጉልበትም እያደገ ነው። አሁን ላለችበት ሁኔታም ይሁን ለመጪው ዘመን ጉዞዋ ደግሞ የተቀናጀ እና እንደ አንድ የተዋሃደ አጀንዳ ያስፈልጋታል። አፍሪካ እንደ አንድ አካል አንድ ድምፅ የምታሰማ፤ በዚህም በፈረጠመ አቅም የመደራደር ብቃቷን የምታጠናክር ብሎም አንዲት አፍሪካን ሳይሆን የተከፋፈለችና የተበታተነች አፍሪካን ለማየት ሁልጊዜ የሚጓጉ እና ለዚህም ተግተው የሚሰሩ ወገኖችን የምትቋቋም መሆን ይጠበቅባታል። ለዚህ ደግሞ አንድ ወጥ ርዕይ፣ በረጅሙ ተሰልቶ የተወጠነ አፍሪካዊ ዕቅድ ዓላማ እና ግብ ያስፈልጋታል። “አጀንዳ-2063” የዚህ ፍላጐት መልስ ይሆናል። በዚህም “አጀንዳ-2063” ከምንም በላይ ወቅታዊ ነው።

በአፍሪካ ጠንካራ እና ስራቸውን በአግባቡ እያከናወኑ የሚገኙ ስምንት ክፍለ-አህጉራዊ ተቋማት አሉ። እነዚህ ተቋማት በአፍሪካ ኅብረት ከፍ ያለ ይሁንታ እና ዕውቅና ያላቸው ክፍለ-አህጉራዊ የኢኮኖሚ ማኅበረሰብ ተቋማት ናቸው። ኢጋድን ጨምሮ በየክፍለ-አህጉሩ የተዋቀሩት እኒህ ስምንት ተቋማት አፍሪካውያን የሚመኩባቸው የልማት እና የፖለቲካ ተቋማት መሆን ችለዋል። “አጀንዳ-2063” በእነዚህ ተቋማት ጠንካራ ስብዕና ላይ የተመሠረተ (የሚመሠረት) በመሆኑ “አጀንዳ-2063” ለአፍሪካ ወቅታዊ እና አስፈላጊም ነው።

አፍሪካ አዳዲስ የልማት እና የኢንቨስትመንት ዕድሎችን እና አማራጮችን ማስፋት ስለሚያስፈልጋትም “አጀንዳ-2063” በዚህ በኩልም ወቅታዊ ነው። አፍሪካ ከምንም በላይ ከግምት እና ከጦርነት የፀዳች አህጉር መሆን ይጠበቅባታል። አፍሪካ ከመቼውም ጊዜ የተሻለ ሰላምን፣ የተሻለ መረጋጋትን የምትሻ፤ በዴሞክራሲ እና በመልካም አስተዳደር በኩልም ከፍተኛ እመርታ ማሳየት የሚያስፈልጋት አህጉር ናት። ይህ እንዲሆንም አፍሪካ አንድ ወጥ ርዕይ፣ ዓላማና ግብ ያስፈልጋታል። “አጀንዳ-2063” ይህንን ጥያቄ ይመልሳል የሚል ተስፋ ተጥሎበታለ። የተስፋው መሠረት መጣል ካለበት ደግሞ ጊዜው ዛሬ ነው። ስለዚህ “አጀንዳ-2063” ለአፍሪካ፤ ወቅታዊ የተግባር ዕቅድ ይሆናል።

በአጠቃላይ ቀደም ብለን የዘረዘርናቸው ሃሳቦች አፍሪካ ቅድሚያ ሰጥታ ልታተኩርባቸው የሚገቡ ተደርገው ይወሰዳሉ። “አጀንዳ-2063” እነዚህን ነጥቦች እና ዕድሎች እንደዋና ግብዓት ይጠቀማቸዋል። ከሁሉ ከሁሉ ደግሞ ለአፍሪካ ስኬት መሠረት ናቸው ያላቸውን ትልልቅ ቅድመ-ሁኔታዎች በዝርዝር አስቀምጧቸዋል። የዓላማ አንድነት፣ ግልፅነት፣ ከምንም በላይ የዜጐችን ህልውና፣ ፍላጐት እና ጥቅም ማስቀደም፣ አግባብ ያለው የመልካም አስተዳደር ሥርዓትን ማስፈን እንዲሁም ምንም ዓይነት ተግባርን በጊዜ እና በቦታው ለመፈተሽ ወይም ለመገምገም የሚያስችል አቅምን በማጐልበት ለዚህም ፍፁም ፍቃደኛ በመሆን የሚያጋጥሙ እንከኖችን ውለው ሳያድሩ ለማስተካከል ቁርጠኛ መሆን፤ የበለፀገች፣ የፈረጠመች፣ ሰላማዊ፤ በአጠቃላይ የተባበረች አንዲት አፍሪካን ተመሥርታ እንድናይ ያስችለናል። “አጀንዳ-2063” አፍሪካ ኅብረት እንደሚለው የዚህ ቅኝት ውልድ የሆነ አፍሪካዊ ርዕይ፤ በዚህ ርዕይ ላይ ተመሥርቶ በተለያዩ አንጓዎች የተከፋፈለ አፍሪካዊ የሃምሳ ዓመት ዓዙፍ ሰነድ ይሆናል።

“አጀንዳ-2063” በአፍሪካ እየተመዘገበ ያለውን መልካም የሚባል ዕድገት የሚያድስ፣ ይህንኑ ጥረትም የበለጠ የማጠናከር ግብ ያለው፣ አፍሪካዊ ትብብር ኅብረትና አንድነትን እንዲቀላጠፍ የሚያስችል ቀና ቀናውን በምክንያት የሚያስቀጥል ማቀጣጠያ እንደሚሆን አፍሪካ ኅብረት ያምናል። “አጀንዳ-2063” የአፍሪካን ትናንት ከዛሬ፣ የዛሬውንም ከነገ በማቆራኘት አዲስ አፍሪካዊ ትውልድ የመፍጠር ግብንም ይዟል። የአፍሪካን ተስፋ በማለምለም አፍሪካውያን አባቶች የነበራቸውን ተስፋ እና ቃል ኪዳን እንደሚያድስም ይጠበቃል። በዚህ ሁሉ በማቆራረጥም በቃል የሚፎከረውን ብቻ ሳይሆን እውነት እና ህያው የሆነውን የአፍሪካ ህዳሴ ለማብሰር የሚሰናዳ የአፍሪካ እና የአፍሪካውያን የቃል ኪዳን ሰነድ ይሆናል፤ “አጀንዳ-2063”።¾

ሆኖ በዚያው እንዲያበቃ ያልተደረገበት እና ይግባኝ የሚባልበት እንዲሆን የተደረገበት ምክንያት በዋናነት በውሳኔ አሰጣጥ ላይ ከሕግ ወይም ከማስረጃ ጋር ተያይዘው ሊፈፀሙ የሚችሉ ስህተቶች ሊታረሙ የሚችሉበት እድል ካልተመቻቸ የስርዓቱ ፍትሐዊነት /Fairness/ ስለሚጓደል እንዲሁም በሕገ መንግስቱ የተረጋገጡ ሌሎች መብቶች ተፈፃሚነት ላይ አደጋ ሊወድቅ የሚችል በመሆኑ ነው። ከዚህ በተጨማሪ የይግባኝ ስርዓት የውሳኔ ወጥነትንና ተገማችነትን እንዲሁም የዳኞችን ተጠያቂነት ለማረጋገጥ የሚያስችል መሳሪያ ስለሆነም ነው።

የይግባኝ መብት ትዕዛዝ ወይም ፍርድ ለተሰጠባቸው ሰዎች ልዩነት ሳይደረግባቸው የተረጋገጠ መብት እንደሆነ የሕገ መንግስቱ አንቀጽ 20(6) እና 25 ጣምራ ንባብ ያስገነዝበናል። የይግባኝ መብት በሕገ መንግስቱ ከተረጋገጠው የእኩልነት መብት እንዲሁም ተከሰው የተቀጡ ሰዎች በሃይማኖት፣ በፖለቲካ ዕውቀት ምክንያት የተለያየ አቋም ላይ መገኘታቸው በመብቱ አተገባበርና አጠቃቀም ላይ ልዩነት ለመፍጠር ምክንያት ሊሆን እንደማይችል ከአንቀጽ 25 ድንጋጌ ማየት ይቻላል።

በሕገ መንግሥቱም ሆነ ኢትዮጵያ ከተቀበለቻቸው ዓለም አቀፍ ሕግጋት

አንፃር የይግባኝ መብትን በሚመለከት ከላይ በአጭሩ የተገለፀ ሲሆን ለቀረበው የሕገ መንግስት ትርጉም ጥያቄ ምክንያት ሆነው የተጠቀሱትን ሕጎች ቀጥለን እናያለን።

አዋጅ ቁጥር 25/88 ስለፌዴራል ፍርድ ቤቶች የዳኝነት ስልጣን በአንቀጽ 8(1) ሲወስን

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የፌዴራል መንግሥቱ ባለሥልጣኖች በስራ ኃላፊነታቸው ምክንያት ተጠያቂ በሚሆኑባቸው የወንጀል ጉዳዮች ላይ የመጀመሪያ ደረጃ ብቸኛ የዳኝነት ሥልጣን ይኖረዋል በሚል ደንግጎ እናገኛለን። የፌዴራል ፍርድ ቤቶች በሙስና ወንጀል ጉዳዮች ላይ ያላቸውን የመጀመሪያ ደረጃ የዳኝነት ስልጣን ከመወሰን አንፃር የተሻሻለው የፀረ ሙስና ልዩ የሥነ ሥርዓትና የማስረጃ ሕግ አዋጅ ቁጥር 434/97 ይህንኑ ነጥብ በማጠናከር አግባብ ባለው ሕግ መሰረት በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የመጀመሪያ የዳኝነት ሥልጣን እንዲታዩ የተደነገጉት እንደተጠበቁ ሆነው ሌሎች በፌዴራል መንግስት ሥር የሚወድቁ የሙስና ወንጀሎችን በሚመለከት የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የመጀመሪያ ደረጃ የዳኝነት ስልጣን ይኖረዋል ሲል በአንቀጽ 7/1 ላይ

አስቀምጧል። የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የወንጀል

ይግባኝ ዳኝነት ስልጣንን አስመልክቶ አዋጅ ቁጥር 25/88 በአንቀጽ 9 ላይ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመጀመሪያ ደረጃ የዳኝነት ስልጣኑ በሰጠው ውሳኔ ላይ የይግባኝ ስልጣን እንዳለው ደንግጓል።

ከላይ ከተጠቀሱት የአዋጅ ቁጥር 25/88 እና የአዋጅ ቁጥር 434/97 ድንጋጌዎች መረዳት የሚቻለው ከኃላፊነታቸው ወይም ከሰራቸው ጋር በተያያዘ ወንጀል ፈጽመው የተቀጡ የፌዴራል መንግስቱ ባለስልጣናት በውሳኔው ቅር ቢሰኙ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞ ሲገኝ በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ሊታይ የሚችልበት ሁኔታ ከመኖሩ በቀር በመደበኛ ይግባኝ ሊታይ የሚችልበት ሥርዓት ያልተዘረጋ ወይም የተገደበ መሆኑን እንዲሁም በመንግስት መሥሪያ ቤቶች ከኃላፊነታቸውና ከስራቸው ጋር በተያያዘ ለሚፈጽሙት ወንጀል በመስሪያ ቤቱ ያላቸውን የስራ ኃላፊነት መነሻ በማድረግ ጉዳያቸው በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት እና በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እንዲታይ መደረጉን ነው።

ከስራና ኃላፊነታቸው ጋር ተያይዞ

ወንጀል ፈጽመዋል የተባሉ የመንግስት ባለስልጣናት ጥፋተኞች ሆነው ቢቀጡ ተመሳሳይ ወንጀል ፈጽመው ከሚቀጡ የመንግስት ሰራተኞች በተለየ ሁኔታ የይግባኝ መብት እንዳይኖራቸው መደረጉ በሕገ መንግስቱ አንቀጽ 20(6) የተረጋገጠውን ፍርድ ለተሰጠባቸው ሰዎች የተፈቀደውን ይግባኝ የማቅረብ መብት የሚጥስ ሲሆን በመንግስት መስሪያ ቤት የሚሰሩ ሰዎች ከስራ እና ከኃላፊነታቸው ጋር ተያይዞ ለሚፈጽሟቸው ወንጀሎች ባለስልጣናቱ በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ ቀሪዎቹ ሰራተኞች ደግሞ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት እንዲዳኙ መደረጉ በሕገ መንግስቱ አንቀጽ 25 ላይ የተረጋገጠውን በሕግ ፊት እኩል የመሆን መብትን የሚቃረን ነው። በመሆኑም የአዋጅ ቁጥር 25/88 አንቀጽ 8(1) እና ከአዋጅ ቁጥር 434/97 አንቀጽ 7(1) ውስጥ አግባብ ባለው ሕግ መሰረት በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የመጀመሪያ ደረጃ የዳኝነት ሥልጣን እንዲታዩ የተደነገጉት እንደተጠበቁ ሆነው የሚለው ሐረግ ከሕገ መንግስቱ አንቀጽ 20(6) እና አንቀጽ 25 ጋር የሚቃረኑ በመሆናቸው በሕገ መንግስቱ አንቀጽ 9(1) መሰረት ተፈፃሚነት እንዳይኖራቸው ሊደረግ ይገባል።

በዚህ መሰረት የፌዴራል ጠቅላይ

ፍርድ ቤት የመንግስት ባለስልጣናት ከስራቸውና ኃላፊነታቸው ጋር በተያያዘ ተጠያቂ የሚሆኑባቸውን ጉዳዮች ለማየት የነበረው የመጀመሪያ ደረጃ የዳኝነት ሥልጣን ከፍ ሲል በተገለፀው ምክንያት በሕገ መንግስቱ አንቀጽ 9/1 መሰረት ሲሰረዝ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሙስና ጉዳዮችን ለመዳኘት አስቀድሞ ባለው የመጀመሪያ ደረጃ የዳኝነት ስልጣን መሰረት የመንግስት ባለስልጣናት ከስራና ኃላፊነታቸው ጋር በተያያዘ ተጠያቂ በሚሆኑበት የሙስና የወንጀል ጉዳይ ላይ የመጀመሪያ ደረጃ የዳኝነት ስልጣን ይኖረዋል ማለት ነው።

ለማጠቃለልም አቶ መላኩ ፋንታ ቻይ የመንግስት ባለሥልጣን በመሆናቸው ብቻ ይግባኝ በሌለው ፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ክሳቸው እንዲታይ ማድረግ የሕገ መንግስቱን አንቀጽ 20(6) እና 25 መጣስ ስለሚሆን የአዋጅ ቁጥር 25/88 አንቀጽ 8(1) እና ከላይ የተጠቀሰው የአዋጅ ቁጥር 434/97 አንቀጽ 7(1) ሐረግ በሕገመንግስቱ አንቀጽ 9(1) መሰረት ተፈፃሚ እንዳይሆኑ ሊደረግ ይገባል በማለት ይህ የውሳኔ ኀሳብ ቀርቧል።n

የጸደቀው የሕገመንግሥት...

የአፍሪካ ዴሞክራሲና...ግለሰቦች የተካተቱበት የሕገመንግስት አጣሪ ጉባዔ የተመራለትን አከራካሪ ጉዳይ ተመልክቶ በእርግጥም አንቀጾቹ የሕገመንግስት ትርጉም ያስፈልጋቸዋል በሚል ወሰነ። ቀጠለናም ጉዳዩን መርምሮ እነዚህ አንቀጾች ሰዎች ባለስልጣን በመሆናቸው ብቻ የተለየ ጥቅም እንዲገያገኙ የሚደግፍ፣ ሰዎች በሕግ ፊት እኩል ናቸው የሚለውን የሕገመንግስት ድንጋጌ የሚጥስ፣ በጠ/ፍርድ ቤት ጉዳያቸው የሚታይ ባለሰልጣናት ይግባኝ የማለት ሕገመንግስታዊ መብታቸውን የሚያጠብ ነው በሚል አንቀጾቹ ከሕገመንግስቱ ድንጋጌዎች ጋር በግልጽ ይጋጫሉ ሲል የውሳኔ ሃሳብ አቀረበ። ይኸው ጉዳይ 17 አባላት ላሉት የፌዴሬሽን ምክርቤት የሕገመንግስትና የክልሎች ጉዳይ ቋሚ ኮምቴ ቀርቦ በአብላጫ ድምጽ አጣሪ ጉባዔው ያቀረበው የውሳኔ ኀሳብ ተቀባይነትን አግኝቷል።የቋሚ ኮምቴው የውሳኔ ኀሳብ ሐሙስ ታህሳስ 24 ቀን 2006 ዓ.ም በፌዴሬሽን ምክርቤት አፈጉባዔ በአቶ ካሳ ተክለብርሃን በአስቸኳይ ለተጠራው የምክርቤቱ ስብሰባ በቀረበበት ወቅት በርዕሰ ጉዳዩ ላይ የአጣሪ ጉባዔው አባላት መጥተው እንዲያስረዱ መደረጋቸውንና ጥልቅ ውይይት መደረጉን በቋሚ ኮሚቴው በኩል ማብራሪያ ተሰጥቶበታል። ሆኖም በአናሳ ድምጽ የተሸነፉ ወገኖች የልዩነት ኀሳባቸው ምን እንደሆነ ለጋዜጠኞች በታደለው ማብራሪያ ላይ ያልተጠቀሰ ቢሆንም አንዳንድ የምክርቤቱና የቋሚ ኮምቴው አባላት የልዩነት ኀሳባቸውን በምክርቤቱ ስብሰባ ወቅት በድጋሚ በማንሳት በምክርቤቱ ታሪክ የመጀመሪያ ሊባል የሚችል የሞቀ ክርክርን አካሂደዋል።

- አንቀጾቹ ከህገመንግስቱ ጋር አይጋጩም፣

በአናሳ ድምጽ የተሸነፉት ወገኖች የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 25/88 አንቀጽ 8(1) እና የተሻሻለው የጸረ ሙስና ልዩ የስነስርዓትና ማስረጃ አዋጅ ቁጥር 434/97 አንቀጽ 7(1) ድንጋጌዎች ከሕገመንግስቱ ጋር ምንም የሚያጋጫቸው ነገር እንደሌለ ለማሳየት ሕጎቹን የሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት ሲያወጣቸው የነበረውን ፍላጎት (Intention) በጥንቃቄ ማየት እንደሚገባ አንስተዋል። የፓርላማው ፍላጎት ከፍተኛ ባለስልጣናት ከስራቸው ጋር በተያያዘ ወንጀል ፈጽመው ሲገኙ በሕገመንግስቱ የተቀመጠውን የኢትዮጽያ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ጥቅም ለማስከበር ሲባል የተፋጠነ ፍትህ በጥራት አግኝተው

ሕገመንግስቱ የቆመለትን የሕዝብ ዘላቂ ጥቅም ማስከበርን ታሳቢ ያደረገ ነው ሲሉ ተከራክረዋል። ፍ/ቤቶች ጉዳዮችን ከፋፍለው በየደረጃው የሚያዩበት አሰራር የቆየና የተለመደ መሆኑን በማስታወስ ባለስልጣናትም አጥፍተው ሲገኙ በጥንቃቄ፣ አስተማሪ የሆነ ቅጣት እንዲጣልባቸው ታስቦ የተዘጋጀ ሕግ መሆኑን፣ በዚህ ሕግ የቀድሞ ጠ/ሚኒስትር አቶ ታምራት ላይኔ እና ሌሎች ባለስልጣናት ጉዳይ መታየቱንም አስታውሰዋል። በመሆኑም ሕጉ ከሕገመንግስቱ ጋር የሚጋጭበት ምንም ዓይነት ምክንያት የለም ሲሉም ተከራክረዋል።

የጉዳዩ አመጣጥ በየትኛው ፍርድ ቤት እንዳኝ የሚል እንጂ ሕገመንግስት ጥሰት አለ ወይስ የለም የሚል አለመሆኑን በማንሳት ሕገመንግስቱን ይጥሳል ወይስ አይጥስም የሚለው ጭብጥ ባልቀረበ ጥያቄ ላይ የተመሰረተ ነው ያሉም የምክርቤት አባላት ነበሩ።

የይግባኝ ጥያቄ የግለሰብ መብት መሆኑን፣ከፈለገ መጠየቅ ካልፈለገም አለመጠየቅ እንደሚችል የጠቀሱ አንድ የምክርቤት አባል ግለሰቡ በጠቅላይ ፍርድ ቤት ልዳኝ፣ህግ ይፈቅድልኛል ሲሉ፤ የለም የየይግባኝ መብትህን ያሳጣሃል በሚል መንግስት እንዴት ይከራከራል፤ ይህ የመንግስት ጉዳይ ነው ወይ ሲሉም በአግራሞት ጠይቀዋል።

- አንቀጾቹ ሕገመንግስቱን ይጥሳል ባይ ወገኖች፣

አብላጫ ድምጽ ያላቸው ወገኖች

አንቀጾቹ አድልኦ የሚታይባቸው ብቻም ሳይሆን የፊውዳል ባህርይ የሚታይባቸው አንቀጾች ናቸው በማለት በምሳሌ የተደገፈ ማብራሪያ ሰጥተዋል። በተከሰሱ ሰዎች መካከል አንዱ ይግባኝ መብት እንዲያገኝ ሌላው እንዳያገኝ ያደርጋል በሚል አንቀጾቹ ከሕገመንግስቱ ጋር ስለሚጋጩ ተፈጻሚ እንዳይሆኑ ጠይቀዋል።

ሌላው የአጣሪ ጉባዔ አባልም የአቶ ታምራት ላይኔ ቀደም ሲል በዚህ ሕግ መዳኘታቸውን አስመልክተው በሰጡት ምላሽ አቶ ታምራት በተዳኙበት ወቅት የዚህ ዓይነት ጥያቄ ባለመቅረቡ እንዳልታየ፣ አሁን ደግሞ በመጠየቁ እየታየ መሆኑን ለማሳየት ሞክረዋል።

አንዳንዶቹም በሕግ አወጣጥ ወቅት አልፎ አልፎ ስህተት ማጋጠሙ የተለመደ ክስተት መሆኑን በማስታወስ በታወቀ ጊዜ መታረሙ አግባብ ነው ሲሉ ተከራክረዋል።

ምክርቤቱ በግራና ቀኝ

የተደረገውን ክርክር ካዳመጠ በኋላ ጉዳዩ በይደር በድጋሚ ይታይ ወይስ ይህ ውይይት በቂ ሆኖ ውሳኔ ይሰጥ በሚለው ላይ ድምጽ እንዲሰጥ ተደርጎ በዚሁ ይወሰን የሚለው አብላጫ ድምጽ በማግኘቱ ወደድምጽ መስጠት ተሸጋግሮአል። በዚሁ መሰረት አጣሪ ጉባዔው ያቀረበውና በቋሚ ኮምቴ ታይቶ በአብላጫ ድምጽ የጸደቀው ኀሳብ አሁንም በአብላጫ ደምጽ ተወስኗል። በዚሁ መሰረት አቶ መላኩ ፈንታ ያቀረቡት በጠቅላይ ፍርድቤት ለመዳኘት ሕግ ይፈቅድልኛል የሚለው ክርክር ውድቅ ሆኗል። (የሕገመንግሥት አጣሪ ጉባኤ የውሳኔ ኀሳብ ከዚህ ጹሑፍ ጋር ተያይዞ ቀርቧል)

ለዚህ ጉዳይ ሲባል ያነጋገርናቸው አንድ የሕግ ባለሙያ እንዳሉት እንዲህ ዓይነቱ ውሳኔ ዜጎች በሕግና በስርዓት ላይ ያላቸውን መተማመን በእጅጉ የሚጎዳ ነው። በኳስ ጨዋታ ሕግ ፍጹም ቅጣት ክልል ውስጥ መጠለፍ የፍጹም ቅጣት ምት ቅጣት እንደሚያስከትል ይታወቃል። ስለሆነም ተጨዋቾች ጥፋት ላለመስራት የጨዋታውን ሕግ አክብረው ይንቀሳቀሳሉ። ነገር ግን አንድ ወገን ጥፋት ሲሰራ ተጠብቆ ፍጹም ቅጣት ምት መስጠት ሕጉ ቢፈቅድም ይህ ሕግ ከፊፋ ሕግ ጋር አለመጣረሱ ይመርመርልኝ በሚል ዳኛው ጉዳዩን ወደፊፋ ቢመራና ፊፋም ጉዳዩ ሌሎች ሕጎችን ይጥሳል ብሎ ቅጣቱን ቢሽረው የጨዋታውን ሕግ ይጎዳል። ከዚያ በኋላ ተጨዋቾች ፊፋ ካልሻረው እናሸንፍ ይሆናል በሚል ሜዳ የሚገቡ ካልሆነ በስተቀር በሕጉ ላይ ያላቸው መተማመን መሸርሸሩ የማይቀር ይሆናል። ይህ ክስተት ለፊፋም ቢሆን ሕግና ስርዓትን በቀጣይ ለማስከበር የሚጠቅመው አይሆንም። በእነአቶ መላኩም የሆነው በአጭሩ ከዚህ አብነት ጋር የሚመሳሰል ነው። በሕግ ተማምነው አቤቱታ ሲያቀርቡ ከሕገመንግስት ጋር ይጋጫል ተብሎ የጠቀሱትን ምናልባትም ሊጠቅማቸው የሚችለው ሕግ እንዲሻር ተደረገ። ምናልባትም ነገና ከነገወዲያ በተመሳሳይ ሁኔታ ሌሎች በርካታ ህጎች ይሻሩ ይሆናል። ይህም ዜጎች በፍትህ ስርዓቱ ላይ ያላቸውን ፍጹም መተማመን የሚሸረሽር መሆኑ ግልጽ ነው ብለዋል።

ይህ አንቀጽ ከ18 ዓመታት ቆይታ በኋላ ከሕገመንግስቱ ጋር ይጋጫል ተብሎ ሲሻር ቀደም ሲል በዚህ አንቀጽ የተዳኙ ባለስልጣናት ኢ-ሕገመንግስታዊ በሆነ ሕግ ተዳኝተዋል በሚል በአደባባይ እማኝነት እየተሰጠ መሆኑን ማስተዋል አለመቻሉ ያስገርማል ብለዋል፤ ባለሙያው።

የፌዴሬሽን ምክርቤትን...

Page 21: ንደ3 - ethioforum.orgethioforum.org/wp-content/uploads/2014/01/sendek435.pdfሰንደቅ 9ኛ ዓመት ቁጥር 435 ረቡዕ ታህሳስ 30 2006 አታሚ፤ ብርሃንና

ሰንደቅ 9ኛ ዓመት ቁጥር 435 ረቡዕ ታህሳስ 30 2006 21ዜና

ቴዲ አፍሮ ሰጥቶታል በተባለው ቃለመጠይቅ ውዝግብ 10 ሚሊዮን ብር አጣ

በፍሬው አበበ

ድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) በቅርቡ “የፍቅር ጉዞ” በሚል ለአንድ ዓመት የሚቆይ የሙዚቃ ኮንሰርት ለማቅረብ በደሌ ቢራ ፋብሪካን ከገዛው ሄኒከን ኩባንያ ጋር ውል ቢፈራረምም አፄ ሚኒሊክን በተመለከተ በዕንቁ መጽሔት ሰጥቶታል ከተባለው ቃለምልልስ ጋር በተያያዘ በተነሳ ውዝግብ ሄኒከን ውል ለማቋረጥ መገደዱን አስታውቋል። ቴዲ ለዚህ ኮንሰርት የተፈራረመውን ገንዘብ በይፋ ለመግለፅ ፈቃደኛ ባይሆንም፤ ለጉዳዩ ቅርበት ካላቸው ወገኖች ባገኘነው መረጃ መሠረት 10 ሚሊየን ብር እንደነበረ ታውቋል።

ቴዲ አፍሮ ከሄኒከን ጋር ቀደም ብሎ ገብቶት በነበረው ውል መሠረት ጥር 3 ቀን 2006 ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ የኮንሰርት ዝግጅቱን የሚጀምር የነበረ ሲሆን በቀጣይም በአዳማ፣ በጅማ እና በአዲስ አበባ ለማካሄድ ታቅዶ ነበር። ዓላማውም በፍቅር አንድነትን ለማምጣት የታሰበ እንደነበር በቅርቡ በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ መገለፁ አይዘነጋም።

ቴዲ አፍሮ ለዕንቁ መፅሔት አፄ ሚኒሊክ ኢትዮጵያን አንድ ለማድረግ ያካሄዱት ጦርነት “ቅዱስ ጦርነት” ነው በሚል ቃለ ምልልስ ሰጥቷል ከተባለ በኋላ በተለይ እንደፌስቡክና ቲዊተር ባሉ ማኅበራዊ ድረገጾች በርካታ ወገኖች ተቃውሞ ከማስማት አልፈው ፒቲሽን በመፈራረም ጫና ለማሳደር ሞክረዋል። ቴዲ አፍሮ ቃለምልልሱን እንዳላደረገ ቢያስተባብልም ሁኔታው ከመርገብ ይልቅ ተባብሶ “በደሌ ቢራን አትጠጡ” የሚል ዘመቻ ሊከፈት ችሏል።

ጉዳዩ ያሳሰበው ሄኒከን ኩባንያ ከቴዲ ጋር የገባውን ውል ለማፍረስ መገደዱ የታወቀ ሲሆን፤ የሄኒከን ውሣኔ በማኅበራዊ ድረገጾች ከተከፈተው ዘመቻ ጋር በቀጥታ ይያያዝ፣ አይያያዝ ግን ለጊዜው የታወቀ ነገር የለም።¾

በአሸናፊ ደምሴ

የአየር ኃይል ቬተራንስ አሶሴዬሽን በቢሾፍቱ ከተማ ግንባታውን ላስጀመረው ባለአራት ፎቅ ህንፃ ማስፈፀሚያና የኢትዮጵያ አየር ኃይል ታሪክን ከ1936 እስከ 1983 ዓ.ም ድረስ አጠናቅሮ የያዘውን መፅሐፍ ለማሳተም እንዲረዳው ባሳለፍነው ሐሙስ ታህሳስ 24 ቀን 2006 ዓ.ም በሸራተን አዲስ ላሊበላ አዳራሽ በተካሄደው የገቢ ማሰባሰቢያ የእራት ግብዣ ላይ 600 እንግዶች የታደሙ ሲሆን፤ የ1.5 ሚሊዮን ብር ተገኝቷል።

አሶሴሽኑ አባላቱን በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ የልማት ዘርፎች ተጠቃሚ ለማድረግ ከመነሳቱም በተጨማሪ ለትውልድ ሊቀር የሚችልን ታሪክ በመፀሀፍ መልክ ጠርዞ ማዘጋጀቱንና በማዕከሉም የቀደምት አየር ኃይሉን ታሪክ ሊያሳዩ የሚችሉ ቁሳቁሶችን ለዕይታ የማቅረብ ዓላማ እንዳለው

ለማወቅ ተችሏል። በምሽቱ በተካሄደው ፕሮግራም ላይ የቀድሞ የኢፊዲሪ ፕሬዝዳንትን የ10 አለቃ ግርማ ወ/ጊዮርጊስን ጨምሮ በርካታ ታላላቅ እንግዶች በስፍራው ተገኝተው ነበር።

በፕሮግራሙ ላይ የአየር ኃይሉን አጀማመርና ታሪክ በየመንግስታቱ የሚያሳይ ዘጋቢ ፊልም ከመቅረቡም ባሻገር ሻምበል ለማ ጉያ እንደሰሯት የተነገረላት አውሮፕላን ለጨረታ ቀርባ ገቢ አስገኝታለች።

የአየር ኃይል ቬተራንስ አሶሴዬሽን በቀጣይም የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም የማካሄድ እቅድ እንዳለው የተገለፀ ሲሆን፤ የሸራተን አዲሱን የእራት ግብዣ በነፃ እንዲደረግ የፈቀዱትን ክቡር ዶክተር ሼህ መሀመድ ሁሴን አሊ አላሙዲንን ጨምሮ ድጋፍ ያደረጉላቸውን ወገኖች በመላ የአሶሲየሽኑ ሊቀመንበር ብርጋዴል ጄኔራል ተጫኔ መስፍን አመስግነዋል።n

በፀጋው መላኩ

የእስራኤል መንግስት በህገወጥ መንገድ የገቡትን አፍሪካውያን ስደተኞች ለማባረር ዝግጅት እያደረገ ሲሆን ባለፈው እሁድ በቴላቪቭ ከባድ ተቃውሞ ገጥሞታል። ከአፍሪካውን ስደተኞች መካከል የሚበዛውን ቁጥር የሚይዙት ኤርትራውያን፣ ሱዳናውያንና ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን የኤ ኤፍ ፒ ዘገባ ያመለክታል።

የእስራኤል መንግስት ስደተኞቹን ወደ ሀገራቸው ለመመለስ ዝግጅት ማድረግ ከጀመረ ወራት የተቆጠረ ሲሆን ከምንም በላይ ከፍተኛ ቁጣን የቀሰቀሰው የሀገሪቱ ፓርላማ ባስተላለፈው ውሳኔ መሰረት በህገወጥ የገባ ማንኛውም ስደተኛ ፍርድቤት ሳይቀርብ ያለምንም ጥያቄ አንድ ዓመት የሚታሰር መሆኑ ነው። ፓርላማው ይሄንን ውሳኔ ያስተላለፈው ባለፈው ህዳር ወር ሲሆን የትግበራ

ጊዜው ግን እውን የሚሆንበት ደረጃ ላይ እየደረሰ ነው።ከሁሉም በፊት የሀገሪቱ መንግስት ህገወጥ

ስደተኞቹ የተወሰነ የኪስ ገንዘብ እየተሰጣቸው በፈቃደኝነት ወደየሀገሮቻቸው እንዲመለሱ የማግባባቱን ስራ ሲሰራ ቢቆይም ይህ ነው የሚባል ውጤትን ግን ሊያመጣ አልቻለም። አብዛኞቹ ስደተኞች በሱዳን በኩል በግብፅ አቋርጠው ወደ እስራኤል የገቡ ናቸው። በእሁድ እለቱ ተቃውሞ እስከ 30ሺ የሚሆኑ ስደተኞች በቴላቪቭ በመሰብሰብ መንግስት በእነሱ ላይ የያዘውን አቋም እንዲቀየር ጥሪ አቅርበዋል። በተለይ አብዛኞቹ የኤርትራ ስደተኞች “የፖለቲካ ጥገኝነት ጠያቂዎች ነን” በማለት በማናቸውም ሁኔታ ወደ ሀገራቸው የማይመለሱ መሆናቸውን ገልፀዋል። እሁድ እለት የተደረገው ሰላማዊ ሰልፍ በሀገሪቱ ታሪክ በስደተኞች የተደረገ ትልቅ ሰልፍ መሆኑን የኤ ኤፍ ፒ ዘገባ ያመለክታል።n

የአየር ኃይል ቬተራያስ ባዘጋጀው የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም

1.5 ሚሊዮን ብር ተገኘ

በፕሮግራሙ ላይ የአየር

ኃይሉን አጀማመርና ታሪክ

በየመንግስታቱ የሚያሳይ

ዘጋቢ ፊልም ከመቅረቡም

ባሻገር ሻምበል ለማ ጉያ

እንደሰሯት የተነገረላት

አውሮፕላን ለጨረታ ቀርባ

ገቢ አስገኝታለች

ኢትዮጵያኖችን ጨምሮ በእስራኤል የሚገኙ አፍሪካውያን ወደ ሀገራቸው ላለመመለስ እየታገሉ ነው

Page 22: ንደ3 - ethioforum.orgethioforum.org/wp-content/uploads/2014/01/sendek435.pdfሰንደቅ 9ኛ ዓመት ቁጥር 435 ረቡዕ ታህሳስ 30 2006 አታሚ፤ ብርሃንና

ሰንደቅ 9ኛ ዓመት ቁጥር 435 ረቡዕ ታህሳስ 30 200622ስፖርት

በቆንጂት ተሾመ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከሳምንት በኋላ በሚጀመረው የአፍሪካ ሀገሮች የእግር ኳስ ዋንጫ (ቻን) ተሳትፎ ይረዳው ዘንድ ቅዳሜ እለት ከናይጄሪያ ሁለተኛ ቡድን ጋር በአደረገው የወዳጅነት ጨዋታ የ2ለ1 ሽንፈት ገጥሞታል። ውጤቱ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን እንደ ናይጄሪያ ካሉ የምዕራብ አፍሪካ ቡድኖች ሲጫወት ከደረሰበት ተደጋጋሚ ሽንፈት መማር አለመቻሉን ያረጋገጠ ሆኗል።

ባለፈው ቅዳሜ በአቡጃ ብሔራዊ ስታዲየም ቡድን በአንድ አመት ውስጥ ለአራተኛ ጊዜ የስቴፈን ኬሺን ቡድን የገጠመው የኢትዮጵያ ብሔራዊ በታዳጊዎች በተዋቀረው የናይጄሪያ ሁለተኛ ቡድን ሽንፈት ደርሶበታል። የኢትዮጵያ ቡድን ልምድ በሌለው በተጋጣሚው ቡድን በጨዋታ እንቅስቃሴም ተበልጦ መሸነፉ የወደፊት ጉዞውን አሳሳቢ አድርጎታል። ቡድኑ ላለፉት በርካታ አመታት በናይጄሪያ ቡድን ከደረሰበት ተደጋጋሚ ሽንፈት ትምህርት ወስዶ አለመዘጋጀቱ ብቻ ሳይሆን ለወደፊትም ተሰፋ ሰጪ ነገር አለማሳየቱ በተለይ አሰልጣኞቹን ለትችት የሚዳርግ ነው።

የወቅቱ የዋልያው ቡድን ዋና አሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው ከየትኛውም አሰልጣኝ በበለጠ ሁኔታ የናይጄሪያ ቡድን በብዛት ከመግጠማቸው አንጻር ናይጄሪያን ለማሸነፍ የሚያስችል ስትራቴጂን ጠንቅቀው ማወቅና መተግበር እንደነበረባቸው ብዙ አስተያየት ሰጪዎች ይናገራሉ። በጥቂት ወራት ውስጥ

በኢትዮጵያ ቡድን ላይ ሶስት ተከታታይ ድሎችን ያስመዘገበው አሰልጣኝ ስቴን ኬሺን ስልጠናና የጨዋታ ታክቲክ በመረዳት እሱን ለመርታት የሚያስችላቸው ልዩ ዝግጅት ማድረግ እንደነበረባቸውም የሚገልጹ አሉ።

ኢትዮጵያና ናይጄሪያ ባሳለፍነው የፈረንጆቹ የ2013 የውድድር አመት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ የተገናኙት በደቡብ አፍሪካው የአፍሪካ ዋንጫ በምድብ ማጣሪያ ጨዋታ ነበር። በወቅቱም የስቴን ኬሺ ቡድን በቪክቶር ሞሰስ ሁለት የፍጹም ቅጣት ምቶች 2ለ0 ማሸነፉ ይታወሳል። በዚያው አመት መጨረሻ ላይ ለብራዚሉ የአለም ዋንጫ የመጨረሻው ምዕራፍ ማጣሪያ በደርሶ መልስ ጨዋታዎች ተገናኝተው ነበር። በአዲስ አበባው ጨዋታ ንስሮቹ የ2ለ1 ድል ሲያስመዘግቡ በሜዳቸው በአደረጉት የመልስ ጨዋታ ደግሞ 2ለ0 ማሸነፋቸው ይታወሳል።

ባለፈው ቅዳሜ ለአራተኛ ጊዜ አቡጃ ላይ በወዳጅነት ጨዋታ ሲገናኙ የኢትዮጵያ ቡድን የማሸነፍ እድሉ ከተጋጣሚው የበለጠ እንደሆነ ተገምቶ ነበር። የናይጄሪያን የበላይነት የሚገታበት መልካም አጋጣሚ እንዳገኘም ታስቦ ነበር። ለዚህም ዋነኛው ምክንያት አሰልጣኝ ስቴፈን ኬሺ ይዞ የቀረበው ቡድን ዋናውን ሳይሆን ሁለተኛውን ቡድን በመሆኑ ነበር። የኢትዮጵያ ቡድን ደግሞ ዋናው ቡድን ይዞ በመቅረቡና ተጫዋቾቹም ለሁለት አመት አብረው የዘለቁ በመሆናቸውም ጭምር እንደሚያሸንፉ ነበር የተገመተው። ዋልያው በንስሮቹ የደረሰበት ተደጋሚ ሽንፈት የሚበቀልበት ውጤት እንደሚያስመዘግብም የብዙዎች እምነት ነበር። ይሁንና የአሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው ቡድን በአስገራሚ ሁኔታ ታዳጊዎችን በአሰባሰበው በናይጄሪያ ሁለተኛ ቡድን የጨዋታ ብልጫ ተወስዶበት የ2ለ1 ሽንፈትን አስተናግዷል።

የናይጄሪያ ቡድን ከእረፍት በፊት ኢፊአኒይ ኢዴ እና ኡጎና ኡዞቹክው

የተባሉ ተጫዋቾች በ3ኛውና 30ኛው ደቂቃ ባስቆጠሯቸው ግቦች 2ለ0 ሲመራ ቆይቶ፣ ከእረፍት መልስ የታዳጊዎቹ ንስሮች ግብ ጠባቂ ቺኮዚ ኤግቢ የኢትዮጵያ ቡድን በዜሮ ከመውጣት እንዲተርፍ ያደረገችውን ግብ በራሱ ላይ እንዳስቆጠረ መረጃዎች ያመለክታሉ። በእለቱ በጨዋታ እንቅስቃሴም የስቴፈን ኬሺ ታዳጊ ተጫዋቾች ብልጫ እንደነበራቸው ከወደ ናይጄሪያ የወጡ ዘገባዎች ያስረዳሉ። ዋልያዎቹ የተጋጣሚያቸውን የተከላካይ መስመር ሰብረው ለማለፍና የግብ ሙከራዎችን ለማድረግ ተቸግረው መቆየታቸውንም ነው ዘገባዎቹ ያመለከቱት።

የወዳጅነት ጨዋታው ኢንተርናሽናል ጨዋታዎች ልምድ ለሌለው ለናይጄሪያ የሚጠቅም ቢሆንም፣ ከውጤቱም ሆነ የጨዋታው እንቅስቃሴ በመነሳት የኢትዮጵያ ቡድንም ከቀድሞ ሽንፈቱ አለመማሩን የተረጋገጠበት እንደሆነ መናገር ይቻላል። በአንድ አመት ውስጥ በተደጋጋሚ ከናይጄሪያ ቡድን ጋር ተጫውቶ ሽንፈት የገጠመው የአሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው ቡድን ከቀደመው ዋልያ በተሻለ መልኩ ከስህተቶቹ ተምሮ በመገኘት ናይጄሪያን ማሸነፍ እንደነበረበት የብዙዎች እምነት ነበር።

ይሁንና የዋልያው ዋና አሰልጣኝ እምነትና አስተሳሰብ የተለየ እንደነበር ከጨዋታው በፊት ከሰጡት አስተያየት በመነሳት መናገር ይቻላል። ለቅዳሜው የወዳጅነት ጨዋታ ወደ ናይጄሪያ ከመሄዳቸው በፊት በግዮን ሆቴል በተካሄደው የብሔራዊ ቡድኑ የሁለት አመት የወፍ በረር ግምገማና ውይይት ላይ በሰጡት አስተያየት ናይጄሪያን ማሸነፍ እንደማይቻል ተናግረው ነበር። ለዚህም ደግሞ “ጡንቻው የፈረጠመና በጭንቅላት መግጨት የሚችል ተጫዋች እስካልተፈጠረ ድረስ ናይጄሪያን አናሸንፍም” በማለት ነበር ምክንያታቸውን ያስረዱት።

አሰልጣኝ ሰውነት ናይጄሪያንም

የኢትዮጵያ ቡድን

የናይጄሪያን የበላይነት መግታት አልቻለም

Page 23: ንደ3 - ethioforum.orgethioforum.org/wp-content/uploads/2014/01/sendek435.pdfሰንደቅ 9ኛ ዓመት ቁጥር 435 ረቡዕ ታህሳስ 30 2006 አታሚ፤ ብርሃንና

ሰንደቅ 9ኛ ዓመት ቁጥር 435 ረቡዕ ታህሳስ 30 2006

ለኪንታሮትለወሲብ ድክመት /ለመንስኤ እስኬት/ለአሜባበቆዳ ላይ ለሚከሰቱ ቁስሎችለአልማዝ ባለጭራለነቀርሣለጃርዲያለታይፎይድለጨጓራ ሕመምለራስ ምታትለወባለጥርስ ሕመምለሆድ ትል

ለአዕምሮ ጭንቀትለጆሮ ሕመም /ለሚመግል/ለደም ብዛትለጡት ሕመምለኩላሊትለማኅፀን ኢንፌክሽንለጉበትለእጀሰብለአፍና ለአፍንጫ ጠረንለወር አበባ ብዛትለተቅማጥለሪህ

አብይ ደስታበተለያዩ ሕመምና ደዌ ለምትሰቃዩ ሁሉ ሐኪም ፍቅረሰብ መኮንን የባሕላዊ ሕክምናን መነሻ በማድረግ በዕፅዋት ቅመማ ሕክምና አገልግሎት ብቃትና ችሎታቸውን ይዘው ይበልጥ ብዙሀኑን ህዝብ በእግዚአብሔር እርዳታ ለማገልገል በተለያዩ በሽታ ደዌ ለሚሰቃዩ ሁሉ የአልጋ ቁራኛ የሆኑትን ፈውስ ለመስጠት ጠበብት ሙያቸውን ይዘው ይገኛሉ። ይህንን ሙያቸውን ይበልጥ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ የባሕላዊ መድኃኒት ቅመማ ሕክምና ጥናት ማኅበር ብቃታቸውን በማሳወቅ የአባልነት መታወቂያና የሙያ ማስረጃ ተሰጥቷቸዋል። ማየት ማመን ነው ሐኪም ፍቅረሰብ መኮንን ፈውስ ከሚያስገኙባቸው በሽታዎች መካከል እንደሚከተለው ቀርበዋል።

እንዲሁም ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥራችን ወይም በአካል በሕክምና ቦታችን መጥተው ማነጋገር ይችላሉ። አድራሻችን ቁጥር 1፡- አዲስ አበባ የካ ክፍለ ከተማ 22 ከትራፊክ ጽ/ቤት ጀርባ

ለበለጠ መረጃ ሞባይል 0911-43 71 87 የመሥሪያ ቤት ስልክ 011-6-51 84 35ስለምንገኝ ደውለው ይጠይቁን

ፖ.ሳ.ቁ 1790 ኮድ 1250 አዲስ አበባ ኢትዮጵያWeb:- www.fikreseb.com E-mail: [email protected]

23ስፖርትበቆንጂት ተሾመ

በኢትዮጵያ እግር ኳስ ታሪክ ውስጥ የራሳቸውን አሻራ በማኖር ያለፉ ኢትዮያውያን የቀድሞ እግር ኳስ ተጫዋቾች ለበጎ አድራት ተግባር በቅርቡ ወደ ሀገር ቤት ይመጣሉ። ከስመ ጥር የቀድሞ ተጫዋቾች መካከልም ሙሉጌታ ወልደየስ፣ ካሳዬ አራጌና ለማ ክብረት እንደሚገኙበት ታውቋል።

የቀድሞ ተጫዋቾቹ ወደ ሀገር ቤት የሚመጡበት ምክንያት ኢትዮጵያውያን ተጫዋቾችን ለመርዳት በሚካሄደው የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ላይ ለመካፈል መሆኑ ታውቋል። የዝግጅቱ ዋና አስተባባሪ ደግሞ በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያውያን እግር ኳስ ተጫዋቾችና ደጋፊዎች ማህበር ነው። ማህበሩ በተለይ ለሰንደቅ እንደገለጸው በሰሜን አሜሪካ፣ ካናዳ፣ አውሮፓና አውስትራሊያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የቀድሞ ስመጥር ተጫዋቾች ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ችግር ላይ የሚገኙ ተጫዋቾችን ለመርዳት በሚካሄደው ዝግጅት ላይ ይሳተፋሉ። በውጭ ሀገራት የሚገኙት ተጫዋቾቹ ቀደም ሲል ገንዘብ አሰባስበው በመላክ የገንዘብም ሆነ የህክምና ድጋፍ የሚሹ እግር ኳስ ተጫዋቾችን በመደገፍ የቆዩ ሲሆን፣ በቅርቡ አዲስ አበባ ስታዲየም በሚካሄድ የገቢ ማሰባሰቢያ የወዳጅነት ጨዋታ ላይ ለመካፈል

ወደ ሀገር ቤት ይመጣሉ። አምስት አመታትን ያስቆጠረው

በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያውያን እግር ኳስ ተጫዋቾችና ደጋፊዎች ማህበር በእግር ኳስ ህይወታቸው የተጎዱና ድጋፍ የሚያስፈልጋቸውን የመርዳት አላማ ሲኖረው፣ እስከ አሁንም ለ11 ተጫዋቾች 400ሺ ብር በሚደርስ ወጪ የገንዘብና ህክምና እርዳታ እንዲያገኙ ማድረጉን አስታውቋል። በቀጣይም ድጋፉን አጠናክሮ ለመስጠት የተለያዩ እቅዶችን ዘርግቶ በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኝ ሲሆን፣ በቅርቡም ልዩ የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅቶችን ለማካሄድ እየተሰናዳ ነው።

ከገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅቶቹ መካከልም በሰሜን አሜሪካና በተለያዩ የአውሮፓ ሀገሮች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የቀድሞ ተጫዋቾችን ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ሀገር ቤት ካሉ አቻዎቻቸው ጋር ጥር 11 ቀን 2006ዓ.ም. የሚያደርጉት የወዳጅነት ጨዋታ ዋነኛው ነው። የእግር ኳስ ጨዋታው በመንግስቱ ወርቁ መታሰቢያነት የሚሰየም መሆኑን ማህበሩ በተለይ ለሰንደቅ በሰጠው መረጃ አስታውቋል። በእለቱ በአዲስ አበባ ስታዲየም በርካታ ደጋፊዎች ያሏቸው በፕሪሚየር ሊጉ የሚገኙ ሁለት ክለቦችንም የወዳጅነት ጨዋታ

የሚያደርጉበት ሁኔታንም እያመቻቸ መሆኑን ገልጿል። ከእግር ኳስ ግጥሚያው አስቀድሞ ጥር8 ቀን 2006ዓ.ም. ታዋቂ የሙዚቃ ባለሞያዎች የሚሳተፉበት የሙዚቃ ኮንሰርት እንደሚካሄድ ማህበሩ ጨምሮ አስታውቋል።

ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመጡ ከሚጠበቁት ከ80 በላይ የቀድሞ ተጫዋቾች መካከልም በኢትዮጵያ እግር ኳስ ታሪክ ውስጥ አይረሴ ያደረጋቸውን ታሪክ የሰሩ ይገኙበታል። በተለይም ደግሞ በክለባቸውና በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ውስጥ የላቀ ሚና በማበርከት ያለፉት እንደ ሙሉጌታ ወልደየስ፣ ካሳዬ አራጌና ለማ ክብረት የመሳሰሉት የቀድሞ ተጫዋቾች ከብዙ አመታት በሃላ ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመጡ ተገረጋግጧል።

ከዚህ በተጨማሪም ፍሰሀ ወልደአማኤል፣ መንግስቱ ሁሴን፣ ብሩክ እስጢፋኖስ (ካንቶና)፣ አፈወርቅ ጠናጋሻው፣ አቦነህ ማሞ፣ አፈወርቅ ኪሮስ፣ አየለ መንጀታ፣ እሱባለው ኦሜጋና ክፍሉ መብራቱ የመሳሰሉ የቀድሞ ስመጥር ተጫዋቾች ለጥር 11 ቀኑ የወዳጅነት ጨዋታ ወደ ኢትዮጵያ ከሚመጡ ከ80 በላይ ተጫዋቾች መካከል ጥቂቶቹ ናቸው።¾

በቅርቡ በስነ ምግባር ጉድለት ጋር በተያያዘ ከኢትዮያ ብሔራዊ ቡድን እስከመታገድ ያደረሰ ቅጣት ተላልፎባቸው የነበሩት የቅዱስ ጊዮርጊሱ ተከላካይ አበባው ቡታኮና የደደቢቱ ግብ ጠባቂ ሲሳይ ባንጫ አሁን ደግሞ በበጎ አድራጎት ምግባራቸው የሚጠሩ ሆነዋል። ተጫዋቾቹ በሜሪ ጆይ የህጻናትና አረጋውያውያን መርጃ ማዕከል እስከ 20ሺ ብር የሚደርስ እርዳታ በመለገስ ለሌሎችም ስፖርተኞች አርአያነት ሊከተሉት የሚገባ ተግባር ፈጽመዋል። በዚህም በመካከላቸው ተፈጥሮ የነበረው ጸብ ጊዜያዊና ለቅጣት የሚያደርስ እንዳልነበረ ለማስረዳት ችለዋል።

ሁለቱ የዋልያ ቡድን አባላት በአለም ዋንጫ ማጣሪያ ኢትዮጵያ በናይጄሪያ ከተሸነፈች በኋላ እዚያው ካላባር በመደባደብ በአሳዩት ያልተገባ ምግባር ሲተቹ ቆይተዋል። ተጫዋቾቹ በብሔራዊ ቡድን ብቻ ሳይሆን በክለባቸውም ውስጥ ፈጽመዋል በተባሉበት ተደጋጋሚ የስነ ምግባር ጉድለት ተወቃሽ ሆነዋል። በዚህም ከኢትዮጵያ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድን እንዲታገዱና የገንዘብ ቅጣት እንዲጣልባቸው መደረጉ ይታወሳል። ሲሳይ

ባንጫ 10ሺ ብር፣ አበባው ደግሞ የ5ሺ ብር የገንዘብ ቅጣት እንዲከፍሉ ነው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የወሰነባቸው።

ተጫዋቾቹ የቀረበባቸውን ክስ በመቀበላቸውና በብሔራዊ ቡድን አሰልጣኙ በመፈለጋቸው የገንዘብ ቅጣቱ ብቻ ጸንቶ ዋልያውን እንዲቀላቀሉ ተደርጓል። የአሰልጣኝ ሰውነት ቢሻውን ቡድን የተቀላቀለው ግን አበባው ቡጣኮ ብቻ መሆኑ ታውቋል። ቡድኑን እንዲቀላቀል ሰኞ እለት ለክለቡ ደብዳቤ የተጻፈለት ሲሳይ ባንጫ ማክሰኞ እለት ግን ለልምምድ ሲሄድ ዘግይተሀል ተብሎ ናይጄሪያ ከተጓዘው ዋልያ ቡድን ውስጥ መካተት አልቻለም። የደደቢቱ ግብ ጠባቂ ሲሳይ ባንጫ ለክለቡም ሆነ ለብሔራዊ ቡድን የጎላ አስተዋጽኦ በማድረግ ከሚጠቀሱ ተጫዋቾች መካከል አንዱ ነው። በተለይም ዋልያው ለደቡብ አፍሪካው የቻን ውድድር ማለፉን ባረጋገጠበትና ሩዋንዳን በመለያ ምት ባሸነፈበት በወሳኙ የማጣሪያ ጨዋታ ሁለት የመለያ ምቶችን በማዳን የላቀ አስተዋጽኦ ማበርከቱ አይዘነጋም።

አበባውና ሲሳይ ከፈጸሙት ያልተገባ ምግባርና ከተጣለባቸው ቅጣት ጋር በተያያዘ

በስፖርት ቤተሰቡ ዘንድ መነጋገሪያ ሆነው ሰንብተዋል። ተጫዋቾቹ ለሌሎች አርአያ ያልሆነ ምግባር መፈጸማቸው በብዙዎች አስወቅሷቸዋል። በብሔራዊ ቡድን ውስጥ ከሰጡት መልካም ነገር ይበልጥ ጥፋታቸው ጎልቶ ታይቷል። በመጥፎ ምግባራቸውም የተለዩ የዋልያው አባላት ሆነዋል። ይህ ያስከፋቸው የሚመስሉት ሁለቱ ተጫዋቾች ግን ባለፈው ሳምንት መጨረሻ የበጎ አድራት ተግባር በመፈጸም ለተቺዎቻቸውና ወቃሾቻቸው መልስ ሰጥተዋል። በሜሪ ጆይ የህጻናትና አረጋውያን መርጃ ማዕከል በመገኘት አሳዳጊ ላጡና በማዕከሉ ለሚገኙ ህጻናት 20 ሺ ብር የሚሆን ልገሳ ማድረጋቸው ታውቋል።

የተጫዋቾቹ የበጎ አድራጎት ተግባር ሌሎችም ስፖርተኞች በአርአያነት ሊከተሉት የሚገባ ከመሆኑም በላይ ለእግር ኳስ ፌዴሬሽንና ለተቺዎቻቸው “እኛስ ሆነናል ፍቅር በፍቅር…” የሚል መልዕክት ያስተላለፈ ነበር። ጸባቸውም ጊዜያዊና የመረረ ሆኖ ለቅጣት የሚዳርግ እንዳልሆነ ለሚመለከተው ሁሉ ለማሳወቅም የፈለጉ ይመስላል።¾

ሆነ ሌሎች ጠንካራ ቡድኖችን ለማሸነፍ የሚቻልበትን ስትራቴጂና ስልጠና ላይ ትኩረት ሰጥተው አለመስራታቸው የሰጡት ተስፋ አስቆራጭ አስታያየት ያስረዳል። እርሳቸው ለሁለት አመት ያህል ብሔራዊ ቡድኑንን በማሰልጠን በነበራቸው ቆይታ ናይጄሪያንም ሆነ መሰል የምዕራብ አፍሪካ ጠንካራ ቡድኖችን ለማሸነፍ የሚያስችል ስልጠና ላለመተግበራቸውና ለወደፊቱም መልካም መሰረት የሚሆንም ነገር ላለመጣላቸው ምክንያት ሲጠየቁ የእሳቸው ችግር እንዳልሆነ ነው የሚገልጹት። በተጫዋቾች ክህሎት ላይ ሳይሆን በዳበረ ተክለሰውነት ላይ ያመዘነ የጨዋታ ፍልስፍናቸውን መፈተሽ ግን የሚፈልጉ አይመስሉም።

የወቅቱ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በደቡብ አፍሪካው የቻን ውድድር ላይ የሚገጥማቸው ቡድኖችን ለማሸነፍ ያለው አቅምና ብቃትም ምን ያህል እንደሆነና የት ድረስ ሊጓዝ እንደሚችል ከወዲሁ መገመት የሚያዳግት ሆኗል። ቡድኑ ከሌሎች ተሳታፊ አገሮች በተሻለ ሁኔታ ለረጅም ጊዜ አብረው የቆዩ ተጫዋቾችን ያሰባሰበ፣ በአፍሪካ ዋንጫ ውድድርና በአለም ዋንጫ ማጣሪያ በመሳተፍ የኢንተርናሽናል ውድድሮች ልምድን ያካበተ በመሆኑ እስከ ዋንጫ ድረስም የመጓዝ እድሉ አለው። ነገር ግን አሁንም አሰልጣኙ “ጡንቻው የዳበረና ኳስን በጭንቅላት መግጨት የሚችል ተጫዋች ካልተገኘ ውጤት አይኖርም” በሚል አስተሳሰባቸው የሚጓዙ ከሆነ ቡድኑ ከምድቡ የማለፉም ነገር የሚሳካ አይመስልም።

በደቡብ አፍሪካው ሶስተኛው የቻን ውድድር ኢትዮጵያ በምድብ ሶስስት ከሊቢያ፣ ኮንጎና ጋና ጋር መመደቧ ይታወቃል።¾

የኢትዮጵያ ቡድን

የናይጄሪያን የበላይነት መግታት አልቻለም

የሲሳይ ባንጫና አበባው ቡታኮ የበጎ አድራጎት ምላሽ

የቀድሞ ተጫዋቾች ወደ ኢትዮጵያ ይመጣሉ

Page 24: ንደ3 - ethioforum.orgethioforum.org/wp-content/uploads/2014/01/sendek435.pdfሰንደቅ 9ኛ ዓመት ቁጥር 435 ረቡዕ ታህሳስ 30 2006 አታሚ፤ ብርሃንና

ሰንደቅ 9ኛ ዓመት ቁጥር 435 ረቡዕ ታህሳስ 30 200624ማስታወቂያ