ethioforum.orgethioforum.org/wp-content/uploads/2011/04/awramba_times... · 2011-04-11  ·...

23
አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 164 ቅዳሜ ሚያዚያ 15 2003 ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው በሰላም አደረሳችሁ ‹‹ዳያስፖራው ለዓለም እያሰማ ያለው እዚህ የታፈነውን ድምጽ ነው ›› ዶ/ር ያዕቆብ ኃ/ማርያም ሪፖርቱና ፖለቲካዊ አንድምታዎቹ “የጋዜጣና መጽሔት ሕትመት ዋጋ ጭማሪ ለፕሬስ ነፃነት አደጋ ነው” የጋዜጣና መጽሔቶች አሳታሚዎች አስተባባሪ ኮሚቴ በየወሩ የሚያሳቅቀን የነዳጅ ጭማሪ መጨረሻ የለውምን? የጅብ ‹‹መንደር›› በመሀል ሸገር ሁለት ወገን ፋሲካ The ECONOMIST የኢትዮጵያና ግብጽ አለመግባባት በአባይ ላይ ባለሥልጣን መ/ቤቱ ‹ሁለት አፍ›፤ አሳታሚ ድርጅቱ ‹ከሁለት የለሽ› የሚያምኑ ሁሉ እንዳይጠፉ… …ጎልማሳው በትህትና ከቀረበው በኋላ ‹‹መምሕር ሆይ›› በማለት ሰላምታ አቀረበለት፡ ትህትናውን የሚመለከት ማንኛውም ሰው ይህ ጎልማሳ በታሪክ ውስጥ እጅግ ከባዱን የክህደት ተግባር እየፈጸመ ነው ለማለት አይደፍርም፡ ሰላምታው የቀረበለት መምሕር ግን ‹‹ይሁዳ ሆይ በመሳም የሰውን ልጅ አሳልፈህ ትሰጣለህን?›› የሚል ጥያቄ በማቅረብ እየሆነ ስላለው ነገር ተከታዮቹ እንዲያውቁ አደረገ፡፡ ስፍር ቁጥር የሌላቸው ተከታዮችና እስከዚያች ቅጽበት ድረስ ከጎኑ ያልተለዩ ደርዘን ያህል ደቀመዛሙርት ነበሩት፡፡ ገፅ 16 4 “የማልወደው የጋዜጠኝነት ሥራዬን ነው” የዋጋ ግሽበት እየተባባሰ ነው ገፅ 19 12 3 19 11 17

Upload: others

Post on 22-Apr-2020

28 views

Category:

Documents


1 download

TRANSCRIPT

Page 1: ethioforum.orgethioforum.org/wp-content/uploads/2011/04/Awramba_Times... · 2011-04-11  · ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ 4 ፊ ቸ ር አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 164 ቅዳሜ ሚያዚያ 15 2003

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

እ ን ኳ ን ለ ብ ር ሃ ነ ት ን ሳ ኤ ው በ ሰ ላ ም አ ደ ረ ሳ ች ሁ

‹‹ዳያስፖራው ለዓለም እያሰማ ያለው እዚህ የታፈነውን ድምጽ ነው››ዶ/ር ያዕቆብ ኃ/ማርያም

ሪፖርቱና ፖለቲካዊ አንድምታዎቹ

“የጋዜጣና መጽሔት ሕትመት ዋጋ ጭማሪ ለፕሬስ ነፃነት አደጋ ነው”የጋዜጣና መጽሔቶች አሳታሚዎች አስተባባሪ ኮሚቴ

በየወሩ የሚያሳቅቀን የነዳጅ ጭማሪ መጨረሻ የለውምን?

የጅብ ‹‹መንደር›› በመሀል ሸገር

ሁለትወገን ፋሲካ

The ECONOMISTየኢትዮጵያና ግብጽ አለመግባባት በአባይ ላይ

ባለሥልጣን መ/ቤቱ ‹ሁለት አፍ›፤ አሳታሚ ድርጅቱ ‹ከሁለት የለሽ›

የሚያምኑ ሁሉ እንዳይጠፉ…

… ጎ ል ማ ሳ ው በትህትና ከቀረበው በኋላ ‹‹መምሕር ሆይ›› በማለት ሰላምታ አቀረበለት፡፡ ትህትናውን የሚመለከት ማንኛውም ሰው ይህ ጎልማሳ በታሪክ ውስጥ እጅግ ከባዱን የክህደት ተግባር እየፈጸመ ነው ለማለት አይደፍርም፡፡ ሰላምታው የቀረበለት መምሕር ግን ‹‹ይሁዳ ሆይ በመሳም የሰውን ልጅ አሳልፈህ ትሰጣለህን?›› የሚል ጥያቄ በማቅረብ እየሆነ ስላለው ነገር ተከታዮቹ እንዲያውቁ አደረገ፡፡ ስፍር ቁጥር የሌላቸው ተከታዮችና እስከዚያች ቅጽበት ድረስ ከጎኑ ያልተለዩ ደርዘን ያህል ደቀመዛሙርት ነበሩት፡፡

ገፅ 16 4

“የማልወደው የጋዜጠኝነት ሥራዬን ነው”

የዋጋ ግሽበት እየተባባሰ ነው

ገፅ 19

12

3 19 11

17

Page 2: ethioforum.orgethioforum.org/wp-content/uploads/2011/04/Awramba_Times... · 2011-04-11  · ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ 4 ፊ ቸ ር አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 164 ቅዳሜ ሚያዚያ 15 2003

T’@Í=”Ó ›?Ç=}` Ç©ƒ ŸuÅ

ª“ ›²ÒÏõì<U TV

(›É^h ¾” ¡/Ÿ kuK? 03/04 ¾u?.l 1540)

U/ª“ ›²ÒЋ Ó³¨< KÑW¨<wgƒ �Â

Ÿõ}— ›²ÒÏ ›u?M ¯KT¾G<

›²ÒϨc”cÑÉ Ñ/Ÿ=Ç”

Ÿõ}— ]þ`}a‹

›?MÁe Ñw\c<^õ›?M Ó`T

¯UÅ™‹ ›uu „L

cKV” VÑeƒ°Óeƒ ¨”ÉS<

iÁß“ Te�¨mÁ }hK cÃñ}hK ¨ÇÏ

¢Uú¨<}` îG<õ SpÅe õeN

Ó^ò¡e ›?Ç=}` ’w¿ Seõ”

(0911 18 09 33)E-Mail:[email protected]

¾´Óσ ¡õK< eM¡eM¡:- ®911 62 92 78 ®911 62 92 82 0911 15 62 48

þ.X.l [email protected]://www.awramba.com

›d�T>¨<ብሉ ኤርዝ ጀነራል ቢዝነስ

ኃላ/የተ/የግል/ማህበር

ር ዕ ሰ አ ንቀፅ

ማን ምን አ ለ

2

ከትናንትና እና ከዛሬ ጋር ከተጣላን፣ ነገን ወደ ማጣት እንደርሳለን፡፡›› ይህንን የተናገሩት ከዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ ፕሬዝዳንቶች አንዱ ናቸው፡፡ ይህ አባባል፣ ፕሬዝዳንቱ በምርጫ መንበረ ሥልጣንን ሲረከቡ ካደረጉት ንግግር እየተነቀሰ ዘወትር የሚጠቀስላቸውና ዘመን የማይሽረው ቁም ነገር ያዘለ መልዕክት ያለው ነው፡፡

በእርግጥም አባባሉ ጊዜና ቦታ የማይገድበው ነው፡፡ ምክንያቱም ትናንትና ዛሬ አይደለም፡፡ ዛሬ ሌላ ቀን ነው፡፡ ዛሬ ከትናንትና ሁለንተናዊ ሕይወታችን ተነስተን፣ ስህተታችንን አርመን፣ ጉድለታችንን ሞልተን፣ ጥንካሬአችንን አጎልብተን፣ የነገዋን ቀን በተስፋ የምንቃኝበት ዕለት ነው፡፡ ነገን ግን ዛሬ ላይ ቆመን በትናንትና ሕይወት ብቻ የምንቆዝም ከሆነ፣ ነገ ማድረግ የሚገባንን ማድረግ አንችልም፡፡ ነገ መሆን ያለብንን አንሆንም፡፡ ነገ መድረስ ያለብን ቦታ ላይ መድረስ አንችልም፡፡ በአጭሩ ነገን ወደማጣት እንደርሳለን፡፡ ነገን ላለማጣት ደግሞ ዛሬ ማድረግ የሚገባንን፣ ማድረግ እንዳለብን ማናችንም ነጋሪ አያስፈልገንም ብለን እናምናለን፡፡

ይህንን የምንለው ካለ ምክንያት አይደለም፡፡ ባለፈው ሳምንት የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መ/ቤት

(State Department) የ2010 ዓ.ምን ሪፖርት ይፋ አድርጓል፡፡ የ180 ሀገራትን የሰብዓዊ መብት ሪፖርት በየዓመቱ ይፋ በማድረግ የሚታወቀው የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መ/ቤት፣ በዚህ ዓመትም የኢትዮጵያን የሰብዓዊ መብት አያያዝ በተመለከተ ወደ 56 ገጽ የሚጠጋ ሪፖርት አውጥቷል፡፡ ዲፓርትመንቱ በዚህ ሪፖርቱ የ2002 ዓ.ምን ሀገር አቀፍ ምርጫን፣ የዜጎች የሰብዓዊ መብት ጥሰትን፣ ወከባን፣ አፈናን፣ የእስረኞች አያያዝን ወዘተ በተመለከተ ነቀፋ ሰንዝሯል፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት በፌዴራል እና በክልል ደረጃ ወደ 10 ሺህ የሚጠጉ ታራሚዎችን በይቅርታ ወይም በምህረት መፍታቱን ‹‹አበረታች እርምጃ ነው›› ሲል በሪፖርቱ ውስጥ አስፍሯል፡፡

ይሁን እንጂ፣ የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሪፖርቱን ከማጣጣል ባሻገር፣ መረርና ከረር ያለ ምላሽ ለመስጠት ጊዜ አልወሰደበትም፡፡ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚያዝያ 7 ቀን 2003 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ፣ የስቴት ዲፓርትመንቱ ሪፖርት 80 በመቶው ካለፈው ዓመት የተገለበጠ፣ መረጃ የለሽና ያልተጣሩ፣ ፖለቲካዊ ይዘት ያላቸው፣ ከነውጥ ቀስቃሾችና ከተቃዋሚ ምንጮች የተገኙ፣ የፈጠራ ክምር ታሪኮችና የተምታቱ ብያኔዎች ወዘተ ናቸው ሲል አጣጥሏቸዋል፡፡ ስቴት ዲፓርትመንቱ ሪፖርት ‹‹የሀሰት ዘገባዎችን አሰባስቦ ማተም፣ የሀገሪቱን ገፅታ ጥላሸት

ለመቀባት ካልሆነ በቀር፣ በጎ አስተዋስኦ የለውም›› ሲልም በብርቱ ነቅፏል፡፡

እንዲያም ተባለ እንዲህ፣ የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ መ/ቤት ለአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንት የሰጠው ከረር ያለ ምላሽ በእጅጉ አስተዛዛቢ ነው፡፡ ምነው? ቢሉ፣ ይብዛም ይነስም በምድረ ኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት መፈፀሙ የሚያነጋግር አይደለም፡፡ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቱ መጠንና ዓይነት ይለያይ እንደሆን እንጂ፣ ጥሰት ስለመኖሩ ማንም ሊክድ አይችልም፡፡ ልካድም ቢባል የሚካድ አይደለምና፡፡

ሌላው ሌላውን ሁሉ ትተን፣ በቅርቡ በጋዜጦች የሕትመት ዋጋ ላይ የተደረገውን ጭማሪ መጥቀስ በቂ ነው፡፡ ይህ ያልተገመተና ያልተጠበቀ የዋጋ ጭማሪ፣ የዜጎችን መረጃ የመቀበልና የመስጠት መብት የሚጋፋ ስለመሆኑ ምንም ጥርጥር የለውም፡፡ አማራጭ መረጃ የማግኘት ዕድል የሌለው፣ ወይም ሊኖረው ያልቻለ ሕዝብ ‹‹አፈና›› አልተደረገበትም ማለት አይቻልም፡፡

ዛሬ የሀገሪቷን መንበረ ሥልጣን የተቆናጠጡ ወገኖች፣ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ መብቶችን አጎናፅፈናል ብለው በኩራት በመመፃደቅ ከሚናገሩለት መብቶች አንዱ፣ የመናገርና የመፃፍ መብት አንዱ ስለመሆኑ፣ እነሱም እኛም የምንዘነጋው አይደለም፡፡ ይህ መብት ከወር ወር፣ ከዓመት ዓመት እየተሸረሸረ ሄዶ፣ ተወለደ የተባለው የመፃፍና የመናገር፣

ብሎም መረጃ የመስጠትና የመቀበል መብት ዛሬ ዛሬ ጭራሹን የሚጨነግፍበት ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡ በግልጽና በይፋ የተደነገገው ሕገመንግስታዊና ዴሞክራሲያዊ መብት ‹‹ፍጹም ወደተጨናበሰ›› ሁኔታ ሲያመራ እያየ፣ የማስተካከያ እርምጃ የማይወስድ ወይም የመብት ጥበቃ የማያደርግ መንግስት፣ በዚህች ሀገር የመብት ጥሰት አልተፈፀመም ቢል ‹‹ለቀባሪው አረዱት›› ዓይነት ነው የሚሆነው፡፡ ሌላም፣ ሌላም፣ ሌላም ... ማለት ይቻላል፡፡

የሆኖ ሆኖ፣ ለኢትዮጵያ መንግስት የሚበጀው፣ ባህር ተሻግሮ ለአሜሪካ መንግስት መግለጫ ‹‹ቦምብ›› ምላሽ መስጠት አይደለም፡፡ ትናንትና የተፈፀሙትን፣ ወይም ተፈፅመዋል የተባሉትን የዜጎቹን መብቶች ማክበርና እንዲከበሩ ማድረግ እንጂ፡፡

ትናትና ታግለንለታል፣ የሕይወት መስዋዕትነት ጭምር ከፍለንለታል የሚሉለት የዜጎች መብት አለመከበር፣ ዛሬ በእነሱ አመራር ጥሰት ከተፈፀመ፣ ወይም እየተፈፀመ ከሆነ፣ ፀቡ ያለው ከዛሬ ጋር ብቻ ሳይሆን፣ ከትናንትናውም መስዋዕትነት ጋር ጭምር ነው፡፡ ከዛሬና ከትናንትና ጋር የተጣላ ደግሞ፣ የሚያጣው ነገንም ነው የተባለው ለዚህ ነው፡፡

የተሻለ የሰብዓዊ መብት ክብር ለኢትዮጵያ ሕዝብ ሁሉ!!

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!

የካቲት 2000 ዓ.ም ተመሠረተ

አውራምባ ታይምስ፡- በብሉ ኤርዝ ጀነራል ቢዝነስ ኃላ/የተ/የግል/ማህበር ስር የሚታተም፤ በፖለቲካዊና ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩር፤ በንግድ ሚኒስቴር በቁጥር 020/2/6572/2001 የተመዘገበ ሳምንታዊ ጋዜጣ ነው፡፡

አድራሻ አራዳ ክ/ከተማ ቀበሌ 09

የቤት ቁጥር 191

ከአራት ኪሎ ወደ ፒያሳ በሚወስደው መንገድ ፣ ከራስ መኮንን ድልድይ አለፍ ብሎ ወደ ሀገር ፍቅር ቲያትር መገንጠያ አስፋልት ላይ በሚገኘው ባህረ ነጋሽ ሕንፃ ግቢ ውስጥ፡፡

አታሚ፡-

ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ክ/ከተማ፡- አራዳቀበሌ፡- 17የቤት ቁጥር፡- 984

‹‹80 ሚሊዮን ሕዝብ ይዘን ከዚህ መካከል ሰባት ሚሊዮን የተቀቀለ ስንዴ የሚረዳ ነው፡፡ ከዚህ

የበለጠ ውርደት ምን አለ?›› አቶ ታደለ ደርሰህ /የቪዥን ኢትዮጵያ ኮንግረስ

ፎር ዴሞክራሲ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተርና የሰላም አምባሳደር/

መሰናዘሪያ ጋዜጣ ባለፈው ዓመት በወጣው የ‹መያድ› ሕግ ዙሪያ ላቀረበላቸው ጥያቄ

ከሰጡት ማብራሪያ፡፡

‹‹መጀመሪያ ግብጽ፣ በኋላም ግብጽ፣ መጨረሻም ግብጽ የሚል አስተሳሰብ

በህዝቦቻቸው ላይ ለመቅረጽ ያላሰለሰ ጥረት ስላደረጉ ነው››

ጋዜጠኛና ደራሲ ጌታቸው ወልዩ

ግብጽና ሱዳን በአባይ ተፋሰስ አገራት ስምምነት ለምን መገዛት እንዳልፈለጉ ከአዲስ ወሬ ጋዜጣ

ለቀረበላቸው ጥያቄ የሰጡት አስተያየት፡፡

‹‹ሰዎቹ በራሳቸው መግለጫ ራሳቸውን እያጋለጡ ነው››አቶ ኃ/ማርያም ደሳለኝ

ም/ጠ/ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር

ከትላንት በስቲያ በጽ/ቤታቸው በሰጡት መግለጫ ወቅት የተቃዋሚ ፓርቲዎች ስብሰብ የሆነው መድረክ ከሚሊኒየም

ግድብ ግንባታ በፊት ቅድሚያ ሊሰጣቸው የሚገቡ ጉዳዮች መኖራቸውን አስመልክቶ በሰጠው መግለጫ ላይ

አስተያየታቸውን ሲሰጡ

ከትናትና እና ከዛሬ - ለነገ‹‹

Page 3: ethioforum.orgethioforum.org/wp-content/uploads/2011/04/Awramba_Times... · 2011-04-11  · ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ 4 ፊ ቸ ር አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 164 ቅዳሜ ሚያዚያ 15 2003

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

ኮሜንተሪ 3

በአንድነት ተጣምረዋል፡፡

ሀገራቱ ሊሳካላቸው ይችላል፡፡ ከአስርት ዓመታት ከፍተኛ የሕዝብ ዕድገት በኋላ፣ በሕዝብ ቁጥር ብዛት በአፍሪካ ሁለተኛ ደረጃን ይዛ ከነበረችው ግብፅ፣ ደረጃውን ኢትዮጵያ ተረክባለች፡፡ የላይኛው ተፋሰስ ሀገራት ድምር የሕዝብ ብዛት 240 ሚሊየን ሲሆን፣ የሁለቱ የታችኛው ተፋሰስ ሀገራት ድምር የሕዝብ ቁጥር ብዛት 130 ሚሊየን ነው - ግብፅ 85 ሚሊዮን፣ ሱዳን ደግሞ 45 ሚሊየን፤ ሱዳን ሁለቱም ወገኖች እየተደራደሩባቸው የሚገኙና በቅርብ ራሷን የቻለች ሀገር የሚፈጥሩ 14 ሚሊየን ደቡብ ሱዳንያውያንን ያካተተች መሆኗን ልብ ይሏል፡፡

የአባይ ድርሻቸውን ለመገደብ የቆረጡት የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ፣ በመጋቢት 29/2003 ላይ የታላቁን ሚሊንየም ግድብ መሰረተ ድንጋይ ጥለዋል፡

The ECONOMISTሰመጉ

የስብሰባ ጥሪ የሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ (ሰመጉ) 20ኛ ዓመት 1ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን

ሚያዚያ 22 ቀን 2003 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት ጀምሮ ስታዲየም ሳህለሥላሴ

ህንፃ በሚገኘው በዋናው ጽ/ቤት ያካሂዳል፡፡ በመሆኑም የሰመጉ አባል የሆናችሁ ሁሉ በስብሰባው

ላይ እንድትገኙ ተጋብዛችኋል፡፡

ማሳሰቢያበመተዳደሪያ ደንባችን መሠረት መደበኛ አባላት የሆናችሁ ስብሰባውን

ለመካፈል የአባልነት መዋጮአችሁን ማጠናቀቅ ያለባችሁ ስለሆነ ክፍያችሁን ከስብሰባው እለት በፊት ወይም ከስብሰባው ሰዓት ቀደም

ብላችሁ በመገኘት እንድታጠናቅቁ እናሳስባለን፡፡

የሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ

ለበለጠ መረጃ፡ 011-5-517704/ 011-5-514489

፡ 5.25 ጊጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ለማመንጨት የታቀደው ይህ ግድብ ሲጠናቀቅ የሚይዘው የውሃ መጠን በሀገሪቱ ትልቁ ከሆነው ጣና ሐይቅ ሁለት እጥፍ እንደሚሆን ነው የተገለፀው፤ ዋነኛ ግቡም እኤአ በ2020 የሀገሪቱን የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት መጨመር ነው፡፡

ርካሽ የኤሌክትሪክ ኃይል አማራጭ እንደቀረበላት በመግለፅ፣ ወደፊት ግብፅም ከግድቡ ተጠቃሚ እንደምትሆን አቶ መለስ ያስረግጣሉ፡፡ ሆኖም ግን ግድቡን ለመገንባት የሚያስፈልለውን ገንዘብ ኢትዮጵያ እንዳታገኝ በማሴር ግብፃውያንን በመወንጀል፣ እምብዛም መልካም ፍቃደኝነት አይታይባቸውም፡፡ ያም ሆነ ይህ ‹‹እቅዳችንን ከግብ ለማድረስ፣ ያለችንን እያንዳንዷ አቅም፣ ማጠራቀም የምንችለውን እያንዳንዷን ሳንቲም›› በመጠቀም፣ ኢትዮጵያ እቅዷን ለማሳካት ትገፋበታለች፡፡

የኢትዮ-ላይፍ ኢንሹራንስ አክሲዮን ማህበርበሥራ ላይ ያለው ኢትዮ-ላይፍ ኢንሹራንስ አ.ማ ውስን

የመስራች አክሲዮኖችን በመሸጥ ላይ ይገኛል!!!

ሽያጭ የሚከናወንበት ቦታ 1. ቦሌ ፍሬንድሽፕ ሕንፃ 7ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 705/1 ስልክ 0116621561 /09137028162. ዝቋላ ኮምፕሌክስ ህንፃ ከእስጢፋኖስ ወደ ባምቢስ ሱፐርማርኬት በሚወስደው መንገድ ኖክ ነዳጅ ማደያ ፊት ለፊት 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 1 ስልክ ቁጥር 0115549650

ትርፋማነቱ አስተማማኝነት ያለው በመሆኑ አክሲዮን

በመግዛት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ተጋብዘዋል፡፡

ፈጥነው የዚህ ታላቅ ኩባንያ ባለቤት ይሁኑ!!

የኩባንያው የቦርድ አማካሪዎች 1. አቶ ዮሴፍ ቡርቃ 09112553622. ዶ/ር ወልዳይ አምሀ 09112140013. አቶ ብስራት ንጋቱ

የኩባንያው መስራችና የቦርድ አባላት1. አቶ ተሾመ በየነ 0912111781 የኢትዮ-ላይፍ ኢንሹራንስ ቦርድ ሰብሳቢ

2. አቶ ኤርምያስ ንጉሴ 0911229495 የኢትዮ-ላይፍ ኢንሹራንስ ኩባንያ መስራችና የቦርድ አባል

3. አቶ ዝክረ ንጋቱ 0911231201 የኢትዮ-ላይፍ ኢንሹራንስ ኩባንያ መስራችና የቦርድ አባል

4. አቶ ኪዳነ ማርያም አብርሃ 0911678147 የኢትዮ-ላይፍ ኢንሹራንስ ኩባንያ መስራችና የቦርድ አባል

5. አቶ ሽመልስ ገ/ጊዮርጊስ 0913830947 የኢትዮ-ላይፍ ኢንሹራንስ ዋና ሥራ አስኪያጅ

የሚያስገኘው ጥቅም፡- • ፈራሚዎች ከተመዘገቡበት ከአንድ ወር ጀምሮ ትርፍ ታሳቢ ይሆናል፡፡ • ዳጎስ ያለ አመታዊ ትርፍ ተካፋይ ይሆናሉ፡፡ 5% የመሥራች ጥቅም ያስገኛል፡፡ • የአንድ አክሲዮን መደበኛ ዋጋ ብር 1000.00 (አንድ ሺ)• ለአንድ አክሲዮን የሚከፈል የአገልግሎት ዋጋ ብር 70.00 (ሰባት በመቶ)• ዝቅተኛ የአክሲዮን መጠን 5 አክሲዮኖች (ብር 5350.00) የአገልግሎት ዋጋን ጨምሮ • ከፍተኛ የአክሲዮን መጠን (ብር 4,280,000.00) የአገልግሎት ዋጋን ጨምሮ

የአከፋፈል ሁኔታ 35 % በምዝገባ ወቅት 35 % 01/01/2004 እስከ 30/10/200430% 01/11/2004 እስከ 30/08/2005 እን

ኳን ለ

ፋሲካ

በዓል

አደረሳ

ችሁ

የኢትዮጵያና ግብጽ አለመግባባት በአባይ ላይ

ወደ ዝቅተኛ መዳረሻዎቹ እ የ ተ ም ዘ ገ ዘ ገ የሚነጉደውና በዓለም በርዝመቱ አንደኛ

የሆነው የአባይ ወንዝ፣ አብዛኛው ውሃ መነሻው ከኢትዮጵያ ተራራማ መሬቶች ነው፤ ይህም መቀመጫቸውን በሀገሪቱ ዋና መዲና - አዲስ አበባ ያደረገውን መንግስት አመራሮች ወንዙን ግልጋሎት ላይ ለማዋል እምብዛም ያልነበራቸውን ያልተለመደ ብርታት ሰጥቷቸዋል፡፡ ሆኖም የአባይ ወንዝ ዋነኛ ተጠቃሚና ጠንካራ ተፅዕኖ አሳዳሪ ግብፅ፣ ባጋጠማት ውስጣዊ አብዮታዊ ምስቅልቅል ምክንያት ትኩረቷ የተከፋፈለ በመሆኑ ይህ እየተለወጠ ሊሆን ይችላል፡፡ ኢትዮጵያ እና ሌሎቹ የአባይ የላይኛው ተፋሰስ ሀገራት - ቡሩንዲ፣ ኮንጎ፣ ኬንያ፣ ሩዋንዳ፣ ታንዛንያ እና ዩጋንዳ - ግብፅን በይበልጥ ተጠቃሚ የሚያደርጋትን የ1959 (እ.አ.አ) ሥምምነት ከእንደገና ለመፃፍ

Page 4: ethioforum.orgethioforum.org/wp-content/uploads/2011/04/Awramba_Times... · 2011-04-11  · ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ 4 ፊ ቸ ር አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 164 ቅዳሜ ሚያዚያ 15 2003ፊ ቸ ር4

በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት፤ በዓለም አቀፍ ጉዳዮች ምክትል ሴክሬታሪ ስር የሚተዳደሩ ሦስት ቢሮዎች አሉ፡፡ ከእነዚህ ቢሮዎች አንዱ የዴሞክራሲ፣ የሥራና የሰብአዊ መብት ጉዳዮች ቢሮ ነው፡፡ በታዋቂው አሜሪካዊ የሕግ ባለሙያ በማይክል ኤች ፓዝነር የሚመራው ይህ ቢሮ ዋነኛ ኃላፊነቱ ‹‹አሜሪካ ትሟገትለታለች›› የሚባለውን ዴሞክራሲ በመላው ዓለም እንዲሰፍን የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን ማድረግ፣ የአሜሪካ የሰብአዊ መብት ፖሊሲዎችን በመቀመር ከሥራና ሰብአዊ መብት ጋር ግንኙነት አላቸው የሚባሉ ዓለም አቀፍ ጉዳዮችን ማስተባበር፣ እንዲሁም ከሰብአዊ መብት አያያዝ ጋር በተያያዘ አሜሪካ የምትሰጠውን ድጋፍ ማስተዳደር ይገኝበታል፡፡

የማይክል ፓዝነር ቢሮ ከዚህ በተጨማሪ በየዓመቱ ይፋ የሚደረገውና (ከአሜሪካ ውጪ ያሉ) የዓለም አገራት የሰብአዊ መብት አያያዝን የሚተነትነው ሪፖርት በየዓመቱ ይፋ ያደርጋል፡፡ በሚስተር ፓዝነር ቢሮ ቀጥተኛ ትዕዛዝ ለሪፖርቱ ግብአት የሚሆኑ መረጃዎችን ከማሰባሰብ ጀምሮ ሪፖርቱን የማዘጋጀቱ ተግባር በየአገራቱ ባሉ ኤምባሲዎች አማካኝነት ይከናወናል፡፡ የየአገራቱን ሪፖርት በተመለከተ ኃላፊነቱን የሚወስዱት በየአገራቱ ኢምባሲዎች የሚገኙና ይህንኑ ተግባር የሚወጡ ዲፕሎማቶች ናቸው፡፡ ይህ ሪፖርት በየዓመቱ ለአሜሪካ እንደራሴዎች ምክር ቤትም (ኮንግረስ) እንደሚቀርብ ይታወቃል፡፡

ሪፖርቱና የአገራቱ ምላሽእ.ኤ.አ ከ1977 ጀምሮ ይፋ መደረግ

የጀመረው ይህ ሪፖርት በርካታ የዓለም አገራት መሪዎችን በማስቆጣት ይታወቃል፡፡ ከእነዚህ አገሮች አንዷ የሆነችው ቻይና በየዓመቱ ‹‹የአሜሪካን የሰብአዊ መብት አያያዝ ብቻ የሚዳስስ የራሷን አጸፋዊ ሪፖርት በማዘጋጀት ምላሽ ትሰጣለች፡፡ ሩስያ በበኩሏ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ በኩል እንደገለጸችው ‹‹አሜሪካውያን የሌላውን እንጂ የራሳቸውን ችግር መመልከት አይፈልጉም›› ያለው መግለጫው ‹‹በኢራቅና አፍጋኒስታን ላይ በወሰዱት ጅምላ የኃይል እርምጃ በመቶዎች የሚቆጠሩ ንጹሐን ለህልፈት ሲዳረጉ፤ በጸረ ሽብርተኝነት ትግል ስም ስልክ መጥለፍን የመሳሰሉ የግለሰብ ነጻነትን የሚጋፉ ድርጊቶች በግልጽ ይፈጽማሉ›› ያለው የሩስያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሜሪካ የዓለማችን የዴሞክራሲ ፊታውራሪ መሆን የምትችለው ዴሞክራሲን ለማክበር ቆራጥ ወኔ ሲኖራት ነው ብሏል፡፡ የኩባ ኮሚኒስት ፓርቲ በበኩሉ ‹‹ሂላሪ በአገራቸው ያለውን ሁኔታ ችላ በማለት ሌሎችን መተቸት ይቀናቸዋል›› ካለ በኋላ ‹‹በአሜሪካ 20 ሚሊዮን ሴቶች ጾታዊ ጥቃትን ጨምሮ የተለያዩ በደሎች እንደሚፈጸምባቸው የሚያሳዩ መረጃዎች እያሉ፤ በህዝብ ትምህርት ቤቶች ሳይቀር ግድያዎች እንደሚፈጸሙ እየታወቀ ሪፖርቱ በሌሎች ላይ ብቻ ጣቱን መቀሰሩ አሳዛኝ ነው›› ሲል ገልጾአል፡፡

መንግስት የሚለካው …

ቀዳሚዋ ኃያል ሀገር - አሜሪካ፤ ጥቅሟን ለማስጠበቅ እና ኃይሏን የበለጠ ለማጎልበት በተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች በምታደርገው እንቅስቃሴ የተነሳ ብዙ ሕገ-ወጥ እና ኢ-ሞራላዊ ድርጊቶችን ከመፈጸም ነጻ አለመሆኗን የሚገልጸው የፖለቲካል ሳይንስ ተመራማሪና ተንታኝ ጃዋር ሲራጅ መሐመድ ‹‹በተለይ በ”ቀዝቃዛው ጦርነት” እና በ”ጸረ ሽብር” ዘመቻው ሂደት የጸጥታና የስለላ ተቋማቶቿ አማካኝነት

ብዙ ኩነኔዎችን መፈጸሟ፣ ማስፈጸሟን አሊያም አይታ እንዳላየች ፊቷን ከማዞሯ አንጻር ስናየው ሌሎች መንግስታት የሚፈጽሙትን በደል ለማውገዝ ሞራላዊ ብቃት ያንሳታል ሊባል ይችል ይሆናል፡፡ ነገር ግን ሊሰመርበት የሚገባው ወሳኙ ነገር እሱ አይደለም፡፡›› ሲል ወጣቱ የፖለቲካ ተንታኝ ይከራከራል፡፡ ‹‹የአንድ መንግስት ተጠሪነት እና ኃላፊነት ዋናው መለኪያ የራሱ ዜጎች አያይዝ ነው። ከዚህ አንጻር ስናየው የአሜሪካ መንግስት የራሱን ዜጎች መብት እና ጥቅም በማክበር እና ማስከበር ረገድ አይታማም›› በማለት ስካንዴኒቪያንና ካናዳን ከመሳሰሉ ሀገራት ጋር ባትወዳደርም ከብዙዎቹ የዓለም መንግስታት በተሻለ ሁኔታ ሕግና ስርዓት የሰፈነባት ሀገር ናት›› ሲል ምስክርነቱን ይሰጣል፡፡ ከሰላሳ ሀገራት በላይ የመጎብኘት እድል ያገኘው ጃዋር - እንደ አሜሪካ የተረጋጋ እና የዜጎች ሙሉ ነጻነት የተከበረበት ሀገር እንዳላጋጠመው ገልጾ ‹‹ከዚህ አንጻር እንደ ቻይና፣ ሩሲያ እና ኢትዮጵያን የመሳሰሉ ዜጎቻቸውን በመጨቆን የሚታወቁ መንግስታት አሜሪካን የመተቸት የሞራል ብቃቱ የላቸውም። አሜሪካ ለባዕድ ክፉ በትሆንም፣ ዜጎቿን ግን ተንከባክባ፣ አክብራ እና አዳምጣ ነው የምትኖረው።››

በኢትዮጵያ ላይ የቀረበው ሪፖርት

በ43 ገፅ የተዘጋጀውና የኢትዮጵያን ሰብአዊ መብት አያያዝ የሚተነትነው ይህ ሪፖርት በመጀመሪያው ክፍል ምርጫውን አስመልክቶ ከጠቀሳቸው ነጥቦች መካከል 82 ሚሊዮን ሕዝብ በሚኖርባት ኢትዮጵያ ባለፈው ግንቦት የተደረገው ምርጫ ከ547 የፓርላማ መቀመጫ ውስጥ ኢህአዴግና አጋሮቹ 545 ያህሉን አሸንፈዋል ካለ በኋላ ‹‹ምንም እንኳን በአገሪቱ ከ90 በላይ የሚሆኑ የፖለቲካ ፓርቲዎች ቢኖሩም

ከ99% በላይ የሚሆኑ መቀመጫዎችን ገዥው ፓርቲ ብቻውን ሊቆጣጠር ችሏል›› ብሏል፡፡ አያይዞም ጥቂት ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ብቻ ምርጫውን እንዲታዘቡ ቢፈቀድላቸውም የምርጫው ዕለት እየተቃረበ በመጣ ቁጥር ግን ነፃና ፍትሃዊ እንዳልነበረ አንዳንዶቹ ታዛቢዎች መግለፃቸውን ሪፖርቱ አብራርቷል፡፡ ከ1997 ወዲህ ስራ ላይ የዋሉ በርካታ ሕጎች፣ አዋጆች እና ደንቦች ኢህአዴግ በምርጫው ሂደት ላይ የበላይነት ይኖረው ዘንድ አመቺ ዕድል ፈጥረውለታል ሲል ገልጻEል፡፡

የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ዓመቱ ጥቂት የማይባሉ የሰብአዊ

መብት ጥሰቶች የተፈፀመበት ነበር ያለው ሪፖርቱ ከእነዚህም ውስጥ ሕገ-ወጥ ግድያ፣ ሰቆቃ ግርፋት እንዲሁም ተገቢ ያልሆነ የእስረኞች አያያዝ በተለይም ተቃዋሚዎችን በሚደግፉ ዜጎች ላይ በፀጥታ ኃይሎች፣ በልዩ የፖሊስ አባላትና በአካባቢ ሚሊሺያዎች አማካኝነት የመብት ጥሰት ስለመፈፀሙ መረጃዎች አሉ ሲል ጠቅሷል፡፡ በጥር ወር በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ አርሲ ዞን አርዳይታ ኮሌጅ የኦሮሚያ ፖሊስ በሁለት ሲቪል ተማሪዎች ላይ ተኩስ መክፈቱንና አንዱ ከጥቃቱ በኋላ ህይወቱ እንዳለፈ የገለፀው ሪፖርቱ ሁለት ከፍተኛ መኮንኖች በዚህ ምክንያት (ተገቢ ያልሆነ ትዕዛዝ በመስጠታቸው) ከስራቸው እንደተባረሩና አንዱ የፖሊስ አባል ደግሞ ክስ ተመስሮቶበት ወህኒ መውረዱን አትቷል፡፡

በሰኔ ወር በአዲስ አበባ የ17 ዓመቱ በሱፍቃድ ታመነ ፖሊስ ባደረሰበት ድብደባ ህይወቱ እንዳለፈና ይህንን ሕገ-ወጥ ድርጊት የፈፀሙ የፖሊስ አባላትም እንደታሰሩና ክስ እንደተመሰረተባቸው ሪፖርቱ ዘርዝሯል፡፡

ስለ ፖለቲካ እስረኞችበማዕከላዊ የምርመራ ጣቢያ ከግንቦት

7 ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር የዋሉ ታሳሪዎች ፍርድ ቤት ከመቅረባቸው በፊት ሰቆቃና አካላዊ ጥቃት እንደተፈፀመባቸው (በወቅቱ እስረኞቹ ለፍ/ቤት ያቀረቡትን አቤታቱ መነሻ በማድረግ) የጠቀሰው ሪፖርቱ ምንም እንኳን የኢትዮጵያ መንግስት ቃል አቀባይ በወቅቱ አቤቱታውን ውድቅ እንዳደረጉት በማስታወስ መንግስትን በሚቃወሙ የዳያስፖራ አባላት የተቋቋመው Global Alliance Against Torture in Ethiopia የተሰኘ ሲቪክ ተቋም ያወጣውን መግለጫ በሪፖርቱ አካቷል፡፡

የአሜሪካ መንግስት የሰብአዊ መብት ሪፖርት ከዚህ በተጨማሪ የአገር ውስጥና የውጭ ሲቪክ ድርጅቶች ያወጧቸውን መግለጫዎች መነሻ በማድረግ ከ200 እስከ 300 የሚሆኑ የፖለቲካ እስረኞች ኢትዮጵያ ውስጥ እንደሚገኙ ገልጿል፡፡ በነሐሴ ወር በርካታ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎችና ደጋፊዎቻቸው በኦሮሚያ፣ በአማራና በትግራይ መታሰራቸውን ገልፀዋል ብሏል፡፡

ወ/ሪት ብርቱካንን አስመልክቶ ሪፖርቱ እንደሚገልፀው የተሰጣት ይቅርታ ተነስቶና የዕድሜ ልክ እስራቱን ፀንቶባት በህዳር ወር 2001 ዓ.ም ለእስር ከተዳረገች በኋላ በጥቅምት ወር 2003 ዓ.ም ከእስር ብትፈታም በርከት ላሉ ጊዜያት በአንድ ከፍል ውስጥ ለብቻዋ እንድትታሰር መደረጉን ጠቅሷል፡፡ በተቃዋሚ ፓርቲ መሪዋ ላይ ይህ የተፈጸመው ‹‹ሕገ መንግስታዊ መብቷን የሚጥስ ድርጊት ነው›› ብሎ ፍርድ ቤት ያረጋገጠላትን መብት ሳይቀር ተጥሶ ነው ብሏል ሪፖርቱ፡፡

በየካቲት ወር የኢትዮጵያ መንግስት 182 የሚሆኑ የመኢአድ አባላትን በይቅርታ

ይግባኝ የሌለው ቅጣት

ሪፖርቱና ፖለቲካዊ አንድምታዎቹ

መፍታቱን የገለፀው ሪፖርቱ ሰዎች በ1997 ዓ.ም ሕገ መንግስታዊ ስርዓቱን በኃይል ለማፍረስ በመሞከር ተከሰው ፍርድ የተላለፈባቸውና በመኢአድና በኢህአዴግ መካከል የተፈረመው የምርጫ ስነ ምግባር ደንብ ተከትሎ መፈታታቸውን ሪፖርቱ ይተነትናል፡፡

የፕሬስ ነፃነትየአገሪቱ ሕገ-መንግስት ለንግግርና

የፕሬስ ነፃነት ዋስትና ቢሰጥም መንግስት ግን እነዚህን መብቶች በተግባር አያከብራቸውም ያለው የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ሪፖርት፣ አሁንም በጋዜጠኞችና አሳታሚዎች ላይ እስራት፣ ክስና ወከባው እንዳልቆመ፤ መንግስት የኤሌክትሮኒክስ ሚዲያውን ሙሉ ለሙሉ ሊባል በሚችል አኳኋን መቆጣጠሩን፤ በግሉ ዘርፍም ሆነ በመንግስት ሚዲያ ላይ የሚሰሩ ጋዜጠኞችም ራሳቸውን በቅድመ ምርመራ (censorship) እንደሚገድቡ ሪፖርቱ አመልክቷል፡፡ የግንቦቱ ብሄራዊ ምርጫ ሊከናወን ሁለት ቀን ሲቀረው በወቅቱ የአውራምባ ታይምስ ዋና አዘጋጅ የነበረው ውብሸት ታዬ ወደ ኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን ተጠርቶ ‹‹በዘገባዎቻችሁ መድረክ ለተባለው የተቃዋሚዎች ስብስብ ወገንተኛ መሆናችሁን አረጋግጠናል›› መባሉን የዘረዘረው የአሜሪካ መንግስት ዓመታዊ ሪፖርት ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ለዚህ መነሻ ያደረገው ምርጫው ከመከናወኑ ከአንድ ሳምንት በፊት የወጣው የፊቸር ዘገባ እንደሆነ አመልክቷል፡፡

‹‹ይህ ሕዝብ የት ገባ?›› በሚል ርዕስ የቀረበው የፊቸር ዘገባ በ1997 ዓ.ም ምርጫ ወቅት ዴሞክራሲያዊ መብቱን ተጠቅሞ በመስቀል አደባባይ የተሰበሰበው ሕዝብ ከአምስት ዓመት በኋላ የት እንደገባ በመጠየቅ የአገሪቱን ዴሞክራታይዜሽን ወዴት እያመራ ነው? በሚል በንፅፅር የቀረበ ትንታኔ ነበር፡፡ ፊቸሩ ከአምስት ዓመት በፊትና በኋላ በተመሳሳይ ዕለት የተነሱ ፎቶግራፎችን በንጽጽር ያቀረበ ነው፡፡ ሆኖም ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከምርጫው ጋር ተያይዞ አንዳች ነገር ቢከሰት ጋዜጣው ኃላፊነቱን እንደሚወስድ ከገለፀ በኋላ ጋዜጠኛ ውብሸት ከዋና አጋጅነት ኃላፊነቱ ለመልቀቅ እንደተገደደ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ሪፖርት አመልክቷል፡፡

ሪፖርቱ ከዚህ በተጨማሪ የሲፒጄን ሪፖርት በመጥቀስ በአውራምባ ታይምስ የመልዕክት ሳጥን ቁጥር አማካኝነት ወደ ዝግጅት ክፍሉ የሚላኩ ፖስታዎች በተደጋጋሚ የመከፈትና የመቀደድ አደጋ እንደሚያጋጥማቸው፣ ይህንኑ አስመልክቶ ጋዜጣው ለድርጅቱ ቢያሳውቅም ‹‹ለፓስታዎቹ መቀደድ ዋናው ምክንያት የፖስታዎቹ የጥራት ደረጃ ሊሆን ይችላል›› የሚል አስገራሚ ምላሽ ኃላፊዎቹ መስጠታቸውንም ሪፖርቱ ጠቅሷል፡፡ ሪፖርተር ጋዜጣን አስመልክቶ ሪፖርቱ እንደገለፀው የጋዜጣው አሳታሚ በዱከም ከተማ ማተሚያ ቤት ለመክፈት መከልከሉንና የድርጅቱ ቢሮም በኪራይ ቤቶች ኤጀንሲ መነጠቁን ጠቅሷል፡፡

ሪፖርቱ የመገናኛ ብዙሐን ነፃነት በሚተነትነው ንዑስ ርዕስ ስር በነሐሴ ወር የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር የመረጃና የዜና ምንጫዎቻችሁን አሳውቁን ሲሉ ለአውራምባ ታይምስ ጋዜጣ ዝግጅት ክፍል ደብዳቤ መላካቸውን ካብራራ በኋላ ለፍርድ ቤት ሳይቀር አንድ ጋዜጠኛ የመረጃ ምንጩን ለማሳወቅ እንደማይገደድ በሕገ-መንግስቱ የተደነገገ ቢሆንም ብሮድካስት ባለስልጣን ይህንን መጠየቁ አግባብ አለመሆኑን አመልክቷል፡፡

በጥር ወር 2002 የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት መኮንኖች የመኖሪያ

በዳዊት ከበደ

የአሜሪካ ፖሊሲ አውጪዎች ቅድሚያ የሚሰጡት አቶ መለስ ለአሜሪካ ብሄራዊ ጥቅም የሚያግዝ

ምን ውለታ ሰሩ፣ የሚለውን እንጂ በዜጎቻቸው ምን በደል ፈጸሙ የሚለው ብዙም አያሳስባቸውም፡

፡ በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ ቁጥራቸው ቀላል የማይባል የአሜሪካ ፖሊሲ አውጪዎች ፣ ኢትዮጵያን

በመሳሰሉ አገሮች ያሉ ህዝቦች ነጻነት የሚፈልጉ ወይም የሚገባቸው መስሎ ስለማይታያቸው በዚህ

ምክንያት ከእነደዚህ አይነት መንግስታት ጋር ያላቸው ሽርክና ጥያቄ ውስጥ እንዲገባ አይፈልጉም››

Page 5: ethioforum.orgethioforum.org/wp-content/uploads/2011/04/Awramba_Times... · 2011-04-11  · ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ 4 ፊ ቸ ር አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 164 ቅዳሜ ሚያዚያ 15 2003

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

5ማስታወቂያ

ሸሪክ በሆኑ ሀገራት መካከል በሚደረገው ምርመራና ጥናት መካከል ሰፊ ልዩነት አለ። እንደ ኢትዮጵያ በመሳሰሉ ሀገራት ውስጥ የይሥሙላ ስራ ነው የሚሰራው›› በማለት ለሪፖርቱ የሚጠቀምበትን መረጃ እራሱ ከመሰብሰብና ከመመርመር ይልቅ ከሶስተኛ አካል መቀበልን እንደሚመርጥ ገልጾ ‹‹የተሟላ የሰብአዊ መብት ሪፖርት በማቅረብ ረገድ እንደ ሀዩማን ራይትስ ዎች፣አምነስቲ ኢንተርናሽናልና ሲፒጄ የመሳሰሉ ገለልተኛ የመብት ተሟጋች ድርጅትቶች የተሸሉ መሆናቸውን ይገልጻል።

ሪፖርቱ በኢትዮ-አሜሪካ ግንኙነት ላይ ያለው ተጽዕኖአሜሪካ ቅድሚያ የምትሰጠው

ለራሷ ብሄራዊ ጥቅም ነው። ጥቅሟን ለማስክከበር እስካስቻለት ድረስ አጋር መንግስታት በአገሮቻቸው ሰብዓዊ መብት ቢጨፈልቁም በቃል ከማውገዝ ያለፈ ግንኙነቷን የሚያሻክር ተጫባጭ እርምጃ ትወስዳለች ማለት የዋህነት ነው የሚለው የፖለቲካ ተንታኝ ጃዋር መሀመድ ‹‹አንደኛ የአሜሪካ ፖሊሲ አውጪዎች ቅድሚያ የሚሰጡት አቶ መለስ ለአሜሪካ ብሄራዊ ጥቅም የሚያግዝ ምን ውለታ ሰሩ፣ የሚለውን እንጂ በዜጎቻቸው ምን በደል ፈጸሙ የሚለው ብዙም አያሳስባቸውም፡፡ በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ ቁጥራቸው ቀላል የማይባል የአሜሪካ ፖሊሲ አውጪዎች ፣ ኢትዮጵያን በመሳሰሉ አገሮች ያሉ ህዝቦች ነጻነት የሚፈልጉ ወይም የሚገባቸው መስሎ ስለማይታያቸው በዚህ ምክንያት ከእነደዚህ አይነት መንግስታት ጋር ያላቸው ሽርክና ጥያቄ ውስጥ እንዲገባ አይፈልጉም›› ይላል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝም ባለፈው ሐሙስ በገደምዳሜ የገለጹት የጃዋርን ሐሳብ የሚያጠናክር ነው፡፡ ‹‹እኛ ውድቅ ያደረግነው ሪፖርቱን ብቻ ነው፤ የኢትዮ-አሜሪካ ዴፕሎማሲያዊ ግንኙነትማ ይቀጥላል›› በማለት ሪፖርቱ በዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቱ ላይ ይህ ነው የሚባል ጫና እንደማይፈጥር አረጋግጠዋል፡፡

በጃዋር እምነት የኢትዮጵያ ልሂቃን ለሰብዓዊ መብት፣ ዲሞክራሲ እና ነጻነት ያላቸው ቁርጠኝነት እምብዛም በመሆኑ አሜሪካዊያን ከአቶ መለስ ውጪ ሌላ

አማራጭ አለ ብለው እንዳያስቡ ምክንያት መሆኑን ይገልጻል፡፡ ከፕሬዚዳንት ኦባማ አማካሪዎች መካከል በስብዓዊ መብት ተሟጋችነት የሚታወቁ፣ አንደ ሳማንታ ፖወር እና ማክል ማክፎል የመሳሰሉ ምሁራን መኖራቸው፣ የከፋ የስብዓዊ መብት ረገጣ በሚፈጽሙ መንግስታት ላይ ጫና በማድረግ ረገድ ከቡሽ ይልቅ የኦባማ አስተዳደር የተሻለ መሆኑን ጃዋር ይስማማበታል።

የአምባሳደር ቡዝ አቋም እና ሪፖርቱ

በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር የሆኑት ዶናልድ ቡዝ መጋቢት 22 ቀን

2003 ዓ.ም በሰጡት መግለጫ፤ ከሰብአዊ መብት ጋር በተገናኘ ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽ ሲሰጡ ‹‹…ከልማት ጋር የተያያዙ፣ የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ሊያሳድጉ በሚችሉ ጉዳዮች ላይ እንስማማለን፡፡ በፀጥታና ተያያዥ ጉዳዮችም ላይ ተመሳሳይ አቋም አለን፡፡ ተስማምተንም አብረን እየሰራን ነው፡፡ ስለዚህ ብዙ የሚያስማሙን ነገሮች የመኖራቸውን ያህል ተጨማሪ ውይይት የሚጠይቁ ጉዳዮች እንዳሉ ይታወቃል፡፡ ከእነዚህ ጉዳዮች አንዱ ሰብአዊ መብትን የሚመለከቱ ነጥቦች ናቸው፡፡ እነሱም ቢሆኑ እየተሻሻሉ ነው…›› ሲሉ ነበር ምላሽ የሰጡት፡፡

‹‹በ2002ቱ ምርጫ ኢሕአዴግ 99.6% ማሸነፉ በቀጣይነት በኢትዮጵያ ሊኖር ከሚገባው የዴሞክራሲ ግንባታ አንፃር ውጤቱን እንዴት አገኙት?›› ሲል አውራምባ ታይምስ ላቀረበላቸው ጥያቄ መንግስታቸው በወቅቱ በጉዳዩ ላይ መግለጫ ማውጣቱን አስታውሰው ‹‹የኢትዮጵያ ሕዝብ የምርጫውን ውጤት ተቀብሏል›› በማለት ነበር ሰሞኑን ከወጣው ሪፖርት ጋር የማይጣጣም አስተያየት የሰጡት፡፡ ጃዋር ግን የሰብዓዊ መብት ሪፖርቱ የአሜሪካን የፖሊሲ አቋም እምዛም ያንጸባርቃል ተብሎ ስለማይታሰብ የአሜሪካን ብሔራዊ ጥቅም ለማስከበር አዲስ አበባ የተላኩት አምባሳደር ከሪፖርቱ ጋር የሚጋጭ ነገር መናገራቸው ብዙም እንደማያስገርም በመግለጽ አምባሳደሩ የተጠቀሙባቸው ቃላት የአሜሪካን መንግስት አቋም ያንጸባርቃሉ ብሎ እንደማያምን ይገልጻል።

‹‹አምባሳደሩ “የኢትዮጵያ ህዝብ የምርጫውን ውጤት ተቀብሎታል” ማለታቸው ከእውነት የራቀ ከመሆኑም በላይ፣ በምርጫው ማግስት፣ የሀገራቸው ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር የፕሬዝዳንቱ ቃል አቀባይ ፣ እንዲሁም በርካታ የኮንግረስ እና ሴነት አባላት “የተደርገው ምርጫ ዓለም አቀፍ መስፈርት ያላሟላ ነው” በማለት አጣጥለው ከሰጡት መግለጫ ጋር የሚጋጭ ነው›› በማለት መግለጫው የመንግስታቸውን ሳይሆን በአብዛኛው የግላቸውን ሃሳብ የሚያንጸባርቅ እንደሆነ አስምሮበታል፡፡

ሪፖርቱና ፖለቲካዊ አንድምታዎቹፍቃድ የነበረውን የውጭ ጋዜጠኛ ለ48 ሰአታት ማሰራቸውን ሪፖርቱ ገልጾ ጋዜጠኛው ከምግብ እርዳታ በስተጀርባ የሚደረገውን ፓለቲካ አስመልክቶ ምርመራ ዘገባ ለመስራት ከተጓዘበት ትግራይ ክልል በፀጥታ ሀይሎች ታግቶ ሌሊቱን ሙሉ ምርምር እንደተደረገለት ከዛ በኋላ በሁለት ቀናት ውስጥ ኢትዮጵያን ለቆ እንዲወጣ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እንደተነገረውና ትንሽ ቆይቶም የስራ ፈቃድ ተመልሶለት ስራውን መቀጠል እንደሚችል ተነግሮታል ይላል ሪፖርቱ፡፡

ይኸው አመታዊ ሪፖርት እንደዘረዘረው የአሜሪካ ድምፅ ሬዲዮ የአማርኛው አገልግሎት የመሸበብ አደጋ እንደገጠመው፤ በአምስተርዳም የሚገኘው የኢትዮጵያ የሳተላይት ቴሌቪዥን በተደጋጋሚ ጃም የመደረግ አደጋ እንደሚገጥመው ሪፖርቱ ዘርዝሯል፡፡ (የቴሌቭዥን ጣቢያው በግንቦት 7 እንደሚደገፍ ሪፖርቱ ቢገልጽም የጣቢያው ቃል አቀባይ ከወራት በፊት ለአውራምባ ታይምስ በሰጡት ቃለምልልስ ግን ለየትኛውም የፖለቲካ ድርጅት እንደማይወግን መግለጻቸው ይታወሳል)

የኢንተርኔት ነፃነትመቀመጫቸው ከኢትዮጵያ ውጪ

ባደረጉ ድረ-ገጾችና ብሎጎች ኢትዮጵያ ውስጥ እንደማይጎበኙ የገለፀው ይኸው ሪፖርት የቪኦኤ ድረ-ገጽም ከመጋቢት እስከታህሳስ ድረስ ተመሳሳይ ዕጣ እንደገጠመው ገልጾ አለም አቀፉ የፕሬስ ነፃነት ተሟጋቹ ሲፒጄ ሳይቀር ድረገፁ ኢትዮጵያ ውስጥ እንደማይከፈት አስታውቋል፡፡

ካለፈው አመት መጋቢት ወር አንስቶ ኢትዮጵያ ውስጥ 42,707 የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች እንዳሉ የቴሌኮሙኒኬሽን መረጃ ዋቢ በማድረግ ያቀረበው ሪፖርቱ በአለም አቀፍ የቴሌኮሙኒኬሽን ሕብረት መረጃ መሠሠት ከአገሪቱ ዜጎች 0.45% ብቻ የኢንተርኔት አልግሎት ተጠቃሚ መሆናቸውን አስታውቋል፡፡

ሪፖርቱ ምን አዲስ ነገር ይዞ መጣ?በአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት

ይፋ የተደረገው የ2010 ሪፖርት ‹‹የፈጠራ ሪፖርት›› ሲል ሚያዝያ 7 ቀን ባወጣው መግለጫ ያጣጣለው የኢትዮጵይ መንግስት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ‹‹የሪፖርቱ 80% ቀደም ባሉ ዓመታት ካቀረበው ውስጥ ቃል በቃል ገልብጦ በድጋሚ ያቀረበው ነው›› ብሏል፡፡ ይህ ሪፖርት ብሏል ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ‹‹ይህ ሪፖርት ካልታመኑ ምንጮች የቀረቡና ፖለቲካዊ ይዘት ያላቸው በተለይ ‹ሁከት ቀስቃሽ› የሆኑ የተቃዋሚ ኃይሎች ያቀረቧቸውን መረጃዎች መነሻ አድርጎ የቀረበ የፈጠራ ክምር›› በማለት ‹‹ኢትዮጵያ ያለችበትን ነባራዊ ሁኔታ ያላገናዘበ ነጭ ውሸት›› ያለው ሚኒስትር መስሪያ ቤቱ ‹‹ተቃዋሚዎች የመንግስትንና የአገሪቱን ገፅታ ለማበላሸት እንዲጠቀሙበት የቀረበ ካልሆነ በስተቀር ዓላማው ግልፅ አይደለም›› ብሎታል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ ጉዳዩን አስመልክተው ከትናንት በስቲያ ለጋዜጠኞች በሰጡት አስተያየት ‹‹እኛ ሁሌም አገራችንን የሚጠቅም ጉዳይ ላይ ከአሜሪካ መንግስት ጋር አብሮ ለመስራት ዝግጁ ነን፤ሪፖርቱ ግን በመረጃ ሳይሆን በወሬ ላይ ብቻ የተመሰረተ በመሆኑ አንቀበለውም›› ብለዋል፡፡

ሪፖርቱ ከዚህ በፊት በስፋት የተዘገቡ ጉዳዮችን አሰባስቦ ከማቅረብ የዘለለ ብዙም አዲስ ነገር የለውም። የሚለው የፖለቲካ ተንታኝ ጃዋር መሀመድ ብዙዎቹ ጉዳዮች ሁላችንም የምናውቃቸውና በሚዲያም የተዘገቡ በመሆናቸው የሪፖርቱ እውነታነት እንደማይጠራጠር ይገልጻል። ዋናው ቁምነገር ይህ ሪፖርት ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የሰብዓው መብት ሁኔታ ሙሉ ገጽታ ያሳያል ወይ የሚለው ነው። የሚለው ጃዋር ‹‹ይህን መረጃ የሚሰበስበው አካል (Bureau of Democracy, Human Rights, and Labor) የሚሰራው ስራ ጥራት እና ጥልቀት ከሀገር ሀገር እንደሚለያይ ገልጾ። ‹‹በአሜሪካ መንግስት ብዙም በማይወድዱ ሀገራት እና የአሜሪካ

የዴሞክራሲ፣ የስራና የሰብአዊ መብት ጉዳዮች ቢሮ ረዳት ሴክሬታሪ የሆኑት ማይክል ኤች ፓዝነር፤አመታዊ የሰብአዊ መብት ሪፖርቱን አስመልክተው ለጋዜጠኞች መግለጫ ሲሰጡ

Page 6: ethioforum.orgethioforum.org/wp-content/uploads/2011/04/Awramba_Times... · 2011-04-11  · ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ 4 ፊ ቸ ር አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 164 ቅዳሜ ሚያዚያ 15 20036

(ባለፈው ሳምንት ሁሉም የሰው ልጆች እንቅስቃሴ ከኃይል ፍላጎት (the will to power) ጋር የተቆራኘ መሆኑ የኒቼ መሠረታዊ እሳቤ እንደሆነ አንስተናል፡፡ ኃይልን መፈለግ ክፉ ነገር እንዳልሆነ የሚጠቁመው ኒቼ ለጥፋት ተጠያቂው እርሱ (የኃይል ፍላጎት) ቢሆንም፣ ባህል እና ፍልስፍናን ጨምሮ ሰብዓዊ ፍጡራን ለሚጣጣሩላቸው ለሁሉም ነገሮችም ምክንያትም እንደሆነ ይጠቁማል፡፡ እናም አዛኝነት፣ ሽቁጥቁጥነት እና መስዋዕት ከፋይነት የመሳሰሉ የሰው ልጅ ስሜቶችን ኃይል ከማካበቺያ (ከመጨመሪያ) እቅዶች አንፃር በጥንቃቄ ተርጉሟቸዋል፡፡ ኒቼ ሁሉንም ሃይማኖቶች እና የሞራላዊነት ሥርዓቶች በተመሳሳይ መንገድ እንደተረጎማቸው ገልፀን ነበር ያቆምነው፤ ካቆምንበት ቀጠልን፡፡)ዋነኛው የምዕራባዊ እሴቶች ምንጭ ክርስትና እንደነበር የሚያስረግጠው ኒቼ ክርስትና ላይ ከሁለት አቅጣጫዎች ትችቱን ሰንዝሮበታል፡- ከሞራላዊነቱ እና ከዲበ አካል (metaphysics)፡፡ [የማርክሲዝም ሌኒኒዝም መዝገበ ቃላት ‹metaphysics› ወይም ዲበ አካልን እንዲህ ይተረጉመዋል፡- ዲበ በላይ ወይም ባሻገር ማለት ሲሆን አካል ደግሞ የሚዳሰስ የሚጨበጥ ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ዲበ አካል ማለት ከቁሳዊ ነገሮች ባሻገር የሚገኙ የረቂቅ ነገሮች ጥናት ማለት ነው፡፡] የሞራል ሥርዓቶችን በሁለት ምድብ ይከፍላቸዋል፡- የገዥዎች ወይም የጌቶች ሞራሊቲ (master morality) እና የባሪያ ሞራሊቲ (slave morality)፡፡ ክርስትና የክላሲካል ዘመኑን አሪስቶክራቲክ የጌቶች ሞራሊቲ አስወግዷል፡፡ የጌቶች ሞራሊቲ በየበላይነት ላይ በማተኮር የበታች ነው ያለውን ሲጫነው፣ የክርስትና ሞራሊቲ በብሶት ላይ የተመርኩዘ ነበር፡፡ እርሱም (የክርስትና ሞራሊቲም) ቢሆን የመጫን ህልም ሰንቋል፤ ነገር ግን የበላዩን በመገደብና ሁሉም እኩል ዋጋ እንዳለው አፅንዖት በመስጠት ይበልጥ በማያስታውቅ መንገድ ነበር፡፡ ለጭምትነት እና ለጥሩነት እንደሚሰጠው ትኩረት ሁሉ በዚያው ልክም እንደተቀናቃኙ አሪስቶክራቲክ የኃይል ፍላጎት መገለጫ ነበር፡፡ የዝቅተኛ ሥርዓቶችን እሴቶች - ጭምትነት፣ ተገዢነት እና ምስኪንነት - ያስፋፋል፤ እንዲሁም የአሪስቶክራቲክ መኩራራትን እንደመሠረታዊ ሀጥያት ያወግዛል፡፡ ሊበራዝም እና ሶሻሊዝምን ጨምሮ ከክርስትና የመነጩ ርዕዮተ ዓለሞችም በእኩልነት እና በጭምተኝነት ላይ የተመሠረቱ ሲሆኑ፣ በእኩል መጠን ጥቅም የለሽ ናቸው፡፡ ብዙሃኑ ለገዢዎቹ ወይም ለበላዮቹ

ባለው ምሬት ላይ መሠረት ያደረጉ መንጋ ሞራሊቲዎች ናቸው፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ኒቼ ክርስትናን ህይወትን የሚያረጋግጥ (እንደ ጥንታዊት ግሪክ ሃይማኖት) ከመሆን ይልቅ ህይወትን እንደማይቀበል ወይም እንደሚቃወም አድርጎ ያወግዘዋል፡፡ ሆኖም ከክርስትና አሉታዊ ተፅዕኖዎች አንዱ በምዕራቡ ህሊና ውስጥ የእውነትን ፍቅር ማስረፁ ነው፤ የዚህ አንዱ ውጤትም የሳይንስ እድገት ሆኖ ቆይቷል፤ ሳይንስም በምትኩ የእግዚአብሔርን ንድፈ-ሀሳብ ሲንድ ቆየ፤ ኒቼም ስለመኖሩ መከራከር የማይቻልበት ቦታ ላይ መደረሱን አሰመረበት፡፡ ይህም የክርስትናን መሠረታዊ ዲበ አካል ብቻ ሳይሆን ሁሉንም ዲበ አካል እና ሁሉንም ትርጓሜ ነጠቀ፡፡ ከሌሎች ነገሮች ጋር በመሆን፣ የእግዚአብሔር ንድፈ-ሀሳብ በመጨረሻ ትንታኔው አንድ ወጥ የሆኑ ሁል-አቀፍ አመለካከቶች ስለመኖራቸው ዋስትና የሚሰጥ ይመስላልና ለነባራዊነት (objectivisim) እና ለእውነት እሳቤዎች መሠረት ሆኗል፡፡ ከእግዚአብሔር ውጪ አንደኛው ከሌላኛው የማይበልጥ ወይም የማይሻል አያሌ የአመለካከት አቅጣጫዎች መኖራቸውን ልናውቅ ግድ ነው፡፡ ይህ ‹እይታዊነት› ወይም ‹perspectivism› የአንፃራዊነት (relativism) ሌላ መልክ ሲሆን እራሱን መነሻ የሚያደርጉ ተመሳሳይ ጉድለቶች አሉት (ሁሉም እውነት አንፃራዊ ነው የሚለው አባባል እራሱ ብቻ እውነትነቱ አንፃራዊ ለምን አልሆነም?)፤ ኒቼ እስከመጨረሻው መፍትሔ አልሰጠበትም፡፡ ያም ሆነ ይህ፣ ኒቼ የእውቀት እና ሞራላዊነት መሠረቶችን ጠራርጓቸዋል፡፡ ኒቼ በምዕራቡ ዲበ አካል አጠቃላይ ባህል ላይ ትችቱን ሰንዝሯል፤ ይህንንም ያደረገው የቃላት ስህተቶች ላይ መሠረት በማድረግ ነው፤ የቋንቋ ተፈጥሮ ያልተረጋገጠ የዲበ አካል ቅድመ ግምቶችን እንድንወስድ ያማልለናልና፡፡ ከስሜት ህዋሳት ቁጥጥር ውጪ ለሆነ ለማንኛውም የዲበ አካል ሁኔታ ምንም ማረጋገጫ ወይም ማስረጃ እንደሌለ ያስረግጣል፡፡ በተመሳሳይም የምዕራቡ ሳይንስን እንደ የእውነት መንገድ የማየት እምነት ቦታውን አጥቷል፡፡ ፍፁም ነባራዊ እውነት የሚባል ነገር የለም፤ አተረጓጎሞች ብቻ ናቸው ያሉት፡፡ እውነት የሆነው ነገር ጠቃሚ የሆነው ነገር ብቻ ነው፤ ማለትም፣ ኒቼ ለእውነት ያለው አመለካከት ተግባር ተኮር (pragmatic) ነው፡፡ ሳይንስ በየትኛውም ፍፁማዊ አግባብ እውነት መሆን ሳያስፈልገው ጠቃሚ የሆነ የሰው ልጅ እሳቤ ነው፡፡ ኒቼ በራሱ አስተምህሮዎች

የፖ ለቲካ ፈ ላ ስፎችበግዛው ለገሠ

ኢያን አዳምስ እና አር. ደብሊው. ዴይሰን በጋራ ባሰናዱት “FIFTY MAJOR POLITICAL THINKERS” መፅሐፋቸው

ከቀደምት አንስቶ እስከ ቅርብ ጊዜ ካሉት ውስጥ አምሳ የፖለቲካ ፈላስፎችን በመምረጥ ለዓለም አስረክበው ያለፏቸውን

ፖለቲካዊ እሳቤዎች በዝርዝር አዋቅረው አቅርበዋቸዋል፡፡ እኛም ለአንባቢ በሚያመች መልኩ እንዲህ አቅርበናቸዋል፡፡

ይህንን ለማለት ተዘጋጅቷል፤ በዚህ ጉዳይ በወጥነት የቀጠለ ባይሆንም፡፡ እንደ ኒቼ እምነት፣ ከእግዚአብሔር ሞት በኋላ ሥልጣኔ ቀውስ ውስጥ የገባ ሲሆን በአዲስ መሠረት ላይ ሊገነባ የግድ ነበር፡፡ ደካሞች እና እራሳችንን የምናታልል ካልሆንን በቀር (ብዙዎቻችን ነን) በዲዮናይሲያን የህይወት አሰቃቂነት እና ትርጉም የለሽነት ላይ በድጋሚ ማተኮርን መማርና ልክ እንደ ግሪኮቹ ምንም ሆነ ምን በሙሉ ኃይል የመኖር ወኔ ይኖረናል፡፡ እናም ይበልጥ በሚታወቅለት ግን ደግሞ ከሥራዎቹ ሁሉ ምርጡ ባልሆነው “Thus Spake Zarathustra” በተሰኘው መፅሐፉ ይህንን ማድረግ የቻሉ ሁሉ የወደፊቱ ወይም የመጪው ዘመን ሰዎች እንደሆኑ ኒቼ አፅንዖት ይሰጥበታል፡፡ እነዚህ ኒቼ “Übermensch” የሚላቸውን፣ በተለምዷዊ ትርጓሜው “supermen” ወይም “ልዕለ-ሰብ” የሚላቸውን ሰዎች ያካተቱ ጥቂቶች ናቸው፡፡ እነዚህ የሰዎች የበላይ የሆኑት አብላጫው በተስማማበት ሞራላዊነት ሳይገደቡ ብቻቸውን የራሳቸውን እሴቶች የመፍጠር እና የማመንጨት አቅም አላቸው፡፡ ይህ ማለት ሌላውን ሰው በማስጨነቅ ተግባር ላይ ይሰማራሉ ማለት አይደለም፡- ይልቁንም የእነሱ ከፍተኛው ስኬት ወረራ ሳይሆን ባህል ይሆናል፡፡ ያም ሆነ ይህ አሁን የሚገኘው የሰው ዘር ከእንሰሳት ጋር የሚራራቀውን ያህል እነዚህ ‹ልዕለ-ሰቦች› ደግሞ አሁን ከሚገኘው የሰው ዘር የራቁ ወይም ልዩነታቸው የሰፋ እንደሆኑ ኒቼ ያምናል፤ ይህም በተወሰነ መልኩ አሳማኝ አይደለም፡፡ ከዛራቱስትራ መፅሐፉ በኋላ ‹ልዕለ-ሰብ› በድጋሚ አልተጠቀሰም፡፡ ይሁንና ግን አሁንም ኒቼ በአምሳልነት የሚጠቅሰው የሆነ ዓይነት ላዕላይ ፍጡር አለ፤ ብቸኛዎቹ ተደርገው ባይሆንም በምሳሌነት እንደ ናፖሊዮን ወይም ጎቴ ያሉ ትክክለኛ ሰብዓዊ ፍጡራን ተጠቅሰዋል፡፡ ሆኖም ህብረተሰብ እንዴት መደራጀት እንዳለበት ኒቼ የሚጠቁመን መንገድ ጠባብ እንደመሆኑ፣ የእነዚህ ላዕላይ ፍጡራን ሚና ምን እንደሆን ለመረዳት ከባድ ነው፡፡ ማለት የምንችለው ነገር ቢኖር፣ በሕጎች እና በልማዶች እንደማይገደቡና እሴቶችን በተለየ መልኩ ተመልክተው የተሻሉ እንደሚያደርጉ፣ በዚህም ለአዲስ ዘመን አዲስ ሞራላዊነትን እንደሚፈጥሩ ማመኑን ነው፡፡ ነገር ግን ከሰው ዘር የበላይ የሆኑት ዝርያዎች ህይወት ወይም አኗኗር ያን ያህል ግልፅ ባይሆንም፣ እነሱ ተነስተው ካልጎለበቱ ወይም ካልተንሰራፉ በቀር የሰው ዘር

ማስታወቂያ

ፍፃሜ ስለመሆኑ ኒቼ ከምንም በላይ ግልፅ ነው፡፡ ሆኖም ፍፃሜው ወዴት የሚያመራ ነው? ምናልባትም በዚህ ጉዳይ የኒቼ ምልከታ በዛራቱስትራ መፅሐፉ ‹Last Man› ወይም ‹የመጨረሻ ሰው› ተብሎ የተጨቀሰው ላይ ይበልጥ የሚታይ ነው፡፡ የመጨረሻው ሰው እንደተቀረው ሰው መሆንን፣ የተመቸው እና ደስተኛ መሆንን ብቻ የሚፈልግ መንጋ-ሰው ነው፡፡ የበላይነትን ሊቆናጠጥ የሚችል ነገር ግን ወደ ተራነት እና ሞራል የለሽነት፣ እንዲሁም በሰው ልጅ እምቅ ኃይል ውስጥ ያለውን ምርጥ ነገር ሁሉ ወደመካድ ብቻ ሊመራ የሚችል አመለካከት እንደሆነ ኒቼ በግልፅ ተሰምቶታል፡፡ ታዲያ በፖሊሲዎች እና በፖለቲካዊ አደረጃጀት ውስን አግባብ አንፃር ስለ ፖለቲካስ ምን ይላል? የአእምሮ ጤናው ከመቃወሱ ጥቂት ጊዜ አስቀድሞ ኒቼ ፖለቲካን ባልተገባ መልኩ ችላ ብሎት መቆየቱን አምኗል፤ ይክሰው ዘንድ እድሉ ያልነበረው ቸልታ፡፡ ሆኖም ከፅሁፎቹ ሊመነዘር የሚችል አያሌ አሉታዊም ሆነ አዎንታዊ ሀሳብ አለ፡፡ በግልፅ በሚታይ መልኩ፣ ፖለቲካ ለኒቼ ስለእድገት ወይም ስለ ማህበራዊ ፍትሕ፣ አልያም ነፃነትን ስለማምጣት ወይም እኩልነትን ስለማስፈን ወይም ሰብዓዊ መብቶችን ስለማስከበር አይደለም፤ እነዚህ የተሳሳተ እምነትን በራስ ላይ የሚያስጭኑ ዴሞክራቲክ የባሪያ ሞራሊቲዎች እሳቤዎች ናቸው፡፡ የእርሱ አምሳሎች (ideals) አሪስቶክራቲክ ናቸው፡፡ ፖለቲካ ለሰው ልጅ ታላቅነት የሚያግዙ ሁኔታዎችን ስለመፍጠር ነው፡፡ ያ ታላቅነት ብቻ ነው አስቀያሚውን አኗኗራችን ሊያረጋግጥ የሚችለው፡፡ የብዙሃኑ የሰው ዘር መኖር (እንደ ግሪክ ራስ-ገዞች) እነዚህን ላዕላይ ፍጡራን ለማገልገል ይመስላል፡፡ ይሁን ግን ስለ ሕጎች እና ስለ ተቋማዊ አወቃቀሮች ኒቼ የሚያነሳው ነገር የለም፡፡ ይህ ሁሉ ነገር ትርጉም የለሽ ሊመስል ይችላል፤ ነገር ግን ኒቼ ያለው ዋጋ ተለይተው በሚጠቀሱ ፅሁፎቹ ላይ የሚመረኮዝ አይደለም፡፡ ይልቁንም ሁላችንም ስምምነት ላይ ለደረስንባቸው ወይም ለተለመዱ የአስተሳሰብ አቅጣጫዎቻቸን ባቀረባቸው ፈታኝ መከራከሪያዎቹ፣ እንዲሁም ለተወሰኑ ጥልቅ ችግሮቻችን ባቀረባቸው ፍንጮች እና ግንዛቤዎቹ ላይ የሚመረኮዝ ነው፡፡ በትክክልም በሁሉም ዓይነት ፈላስፎች እና ፀሐፍት ዘንድ፣ እንዲሁም በፖለቲካው ዘርፍ ከሶሻሊስቶች እስከ ፋሺስቶች እስከ ሊበራሎች እስከ አናርኪስቶች እና (ለሴቶች ጥላቻ ቢኖረውም) እስከ ፌሚኒስቶች ጭምር ተፅዕኖውን በስፋት ሲያሳድር ቆይቷል፡፡ በተጨማሪም ብዙዎቹን ጭብጦቻቸውን በማመንጨት የመጀመሪያው በመሆን በቅርብ አስርት ዓመታት ውስጥ በተለይ በፖስት-ስትራክቸራሊስቶ እና በፖስትሞደርኒስቶች ላይ ተፅዕኖ አሳድሮ ታይቷል፡፡ ምናልባትም ከነዚህ ተፅዕኖዎቹ ውስጥ ይበልጥ መሠረታዊው እና ከፍተኛው የእውቀታችንን፣ የእምነቶቻችንን እና የእሴቶቻችንን ማንኛውንም ዲበ አካላዊ መሠረቶች ያለመቀበል ድምዳሜውን የሚመለከት ነው፡፡ እንዲህ ያሉ መሠረቶች ሳይኖሩ እንዴት ማወቅ፣ መኖር፣ መንቀሳቀስ እና መፍጠር እንችላለን የሚለው ብዙዎች ዛሬም የሚታገሉት ጥያቄ ነው፡፡

የኃይል ፍላጎት እና የኒቼ ልዕለ-ሰቦችፍሬድሪሽ ቪልሄልም ኒቼ /1844-1900/

በኤድና ሞል ማቲ ሲኒማከሰኞ እስከ

እሁድ በ10፡00 ፣

በ12፡00 እና ከምሽቱ በ3፡00 ሰዓት

Page 7: ethioforum.orgethioforum.org/wp-content/uploads/2011/04/Awramba_Times... · 2011-04-11  · ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ 4 ፊ ቸ ር አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 164 ቅዳሜ ሚያዚያ 15 2003

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

ማስታወቂያ

7

የ አቤቶ ወግ

አቤ ቶክቻው[email protected]

Training Courses include: -Report Writing - Advanced Writing Skills - Proposal Writing -Academic Writing -Business Writing -Presentation Skills -Facilitation Skills -Speak Easy -Train the Trainer -Pedagogic Training Unique Features of Our Trainings•Highly interactive (hands on activities) , customized, and definitely up-grading your skills•Supported by cutting edge technology•Full pack of materials: Instructor’s and participant’s manual, pre and post tests, quick-reference guide

Specialized Trainings for ProfessionalsFrom

IMPACT Research & Capacity Building

www.impactsole.comIMPACT Born to fill the gap!

Registration begins on 11 April 2011

Bole RD, DH GEDA Tower, Rm No 3-12 Call 0116 63 41 12 or 0921 78 49 33

Ñ”²w ” ¾T>Á¨<K<uƒ” x uØ”no SU[Ø wMI’ƒ ’¨<!uÑuÁ ¨<eØ }ðƒ• ÁKð-

KvK ›¡c=Ä•‹ Ñ”²w - እÏÑ<” ¾T>Ö’kp

²S’< ¾T>ÖÃk¨<” ‚¡•KAÍ= ¾}ÖkS ²¨ƒ` uK¨<Ø Là ÁK }sU - ÁeðMÓዎ M::

w`H” ›=”}`“i“M v”¡ }ÚT] ›¡c=Ä•‹” uSgØ LÃ ’¨<

w`H” ›=”}`“i“M v”¡ ›.T. SMካU ¾ƒ”X›? u¯M እ”Ç=J”Mዎ ÃS—M

SWIFT: BERHETAA Tel. +251 11 618 5732 +251 11 662 3421 Fax. +251 11 662 3431 P.O.Box 387 Code 1110 Addis Ababa, Ethiopia e-mail: [email protected] www.berhan-bank.com

Page 8: ethioforum.orgethioforum.org/wp-content/uploads/2011/04/Awramba_Times... · 2011-04-11  · ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ 4 ፊ ቸ ር አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 164 ቅዳሜ ሚያዚያ 15 20038

“...መቶ ሺህ ብር ይውጣ ሰው ጠግቦ እንዲጠጣ እየበላህ ብላ እየጠጣህ ጠጣ ለሒሳቡ አታስብ ካንተ ኪስ

አይወጣ...”

በገደምዳሜ ለመነካካት ያሰብኩት የሞገስ ሀብቱን ግጥም ነው፡፡ “መንግስት ሲጋብዝ” ብሎ በእፍታ ላይ ካሳተመው ለኔ ሃሳብ እንደመግቢያነት እንዲመቸኝ አድርጌ የወሰድኩት፡፡

በዓል ነው፡፡ ፋሲካ፡፡ ትልቅ በዓል፡፡ ይህ ደግሞ አንድ ቀን ብቻ ተከብሮ የሚያበቃ ሳይሆን፣ እየደገመ የሚከበር፡፡ እና ሁለት መልክ አለው ወይም ሊኖረው ግድ ሆነብን፡፡

ከሰሞኑ መንገድ ላይ በእግሬ እጓዛለሁ፡፡ አንድ የኔ ብጤ አንድ ትልቅ የቤት ግቢን በር ያንኳኳል፡፡ አንድ ፍሪዝ ወጣት በሩን ከፍቶ ወጣና አፍጥጦ ተመለከተው፡፡

‹‹ምን ፈለግህ?›› በድምፁ ውስጥ ንቀት ለመኖሩ ሳይኮሎጂስት መሆን አይጠበቅብኝም ነበር፡፡ (ለነገሩ ሰበር ሰካ የምትል የመኝታ አጋሩን እየጠበቀ እያለ ሊሆን ይችላል፤ በጉጉት የከፈተው በር ድሪቶ የለበሰ ደሀን ሲያጋፍጠው የተበሳጨው) ይህ ወጣት ሰውየውን በቶሎ ከፊቱ ማባረር ፈልጓል፡፡ ባይፈልግማ ኖሮ የኔ ቢጤ በበሩ ቆሞ ‹‹ምን ፈለግህ?›› ብሎ ባላንጓጠጠ ነበር፡፡ ድሃ ምን ይፈልጋል? ያው ትንሽ ጉርሻ!

ቀጥሎ ለመስማት እንኳ ወኔን በሚያስከዳ አሳዛኝ ድምፅ የኔ ቢጢው ተናገረ፡፡ ‹‹እዚያ ጋር ያለውን ምግብ ልብላው?›› በእጁ ወደ ግቢው አጥር (አስፓልቱ ዳር) በፌስታል ተጠቅሎ ወደ ተጣለ ነገር ያመለክታል፡፡

ወጣቱ ወደ ፌስታሉ አመራ፡፡ (ወርቅ እንደሆነ ተጠራጥሮ ይሆን?)

መርከቢቱ እንደ መርከብ ሆና መኖር ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ ብዙ ማዕበሎችና ወጀቦች ሲያናውጧት ከርመዋል፡፡ የተፈጥሮም ሆነ ሰው ሰራሽ ማዕበሎች በየዘመናቱ እንደ ዱብ ዕዳ እየወረዱ ጉዞዋን ሊያሰናክሉ ሞክረዋል፡፡

አንዳንደ ልምድ የሌላቸው ካፒቴኖች የዘወሯት ይቺ መርከብ በ1928ቱና በመሰል የእገታ መረቦች ውስጥ ብትገባም፣ በመንገደኞቿ ብርታት እንዲሁም ባልተንበረከኩት ካፒቴኖቿ አማካይነት ነፃ ወጥታለች፡፡ የነገውንና ከነገ በስቲያ ያለውን የመርከቢቱን ጉዞ አፍረጥርጦ ለመናገር የለበስነው ሥጋ አግዶናል፡፡

ታሪክ ይመለከተናል የሚሉ ሰዎች የመርከቢቱ ዕድሜ ይሄ ነው አይደለም በሚል ክርክር ተጨቃጭቀዋል፤ ተነታርከዋል፡፡ የዕድሜዋ ማነስ ወይም መርዘም የዚህን ጽሑፍ ሙሉዕነት አያጎድለውም፡፡ የታሪክ ሰዎች በሚያስቀምጡት የመርከቢቱ ዕድሜ ውስጥ ብዙ ብርሃኖች እየተፈጠሩ አብርተዋል፤ ብርሃኖቹ የቀን ጎዶሎ ሲገጥማቸው የተወሰነ ገፅታቸው ያደቀድቃል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ እስከ ዛሬ ድረስ ቆይተው ትውልድ ያልተገረመባቸው ብዙ ብርሃኖች በተለያዩ ወቅቶች በተነሱ አጋቾች ወድመው ጠፍተዋል፡፡ ግን ደግሞ የፈለገውን ያህል ብርሃን ቢጠፋና ቢወደድም፣ መርከቢቱ በብርሃን ቀፎ ኖራ ከብርሃን ቅርፊት ውስጥ የተፈለፈለች መሆኗን የሚያውጁ ብርሃኖች ዛሬም ድረስ በመኖራቸው ላለፈው ትውልድ በእንቅብ የሞላ ምስጋና ማቅረብ ግድ ነው፡፡

መርከቢቱ ከተሰራችበት ጊዜ ጀምሮ ይብዛም ይነስ

ኮሜንተሪ

መንገደኞችን ያላሳፈረችበት ጊዜ የለም፤ አልነበረምም፡፡ መርከቢቱ ኢትዮጵያ ተጓዣቹ ኢትዮጵያውያን ሁሌ እንደተጓዙ ነው፡፡ መርከቢቱ በሚፈለገው የዕድገት መጠን ተጓዘችም አልተጓዘችም፣ መንገደኞቹ መሳፈራቸውን አያቆሙም፡፡

ኖህ የሚባለው ሰውዬ መርከብ እንደነበረው ብዙ ሰዎች ይናገራሉ፡፡ ሰዎቹ ሰውዬው መርከብ እንዳለው ብቻ አይደለም የሚናገሩት፡፡ መርከቡ በጣም ጠንካራና የተለያዩ ሞገዶችንና ወጀቦችን መካች እንደነበረ አብረው ያወራሉ፡፡ የሰውዬው መርከብ ዓላማው ‹‹ማጥፋት›› የሆነውን ውሃ በሚገርም ሁኔታ ተቋቁሞ በውስጡ ያሉትን ነፍሳት አንዳች ጠብታ ውሃ ሳያስነካቸው፣ ውሃው በጥፋት መልክ መውረዱን አቆመ፡፡

በቃ! የኛም መርከብ እንደ ሰውዬው ያለ ዲዛይነር ያስፈልጋታል፡፡ ... ሶዶማውያን ‹‹አጥፍታችኋል›› ተብለው የእሳት ፍርድ ሲበየንባቸው፣ ሎጥ ከነቤተሰቡ ሽሽት ነው የመረጠው፡፡ ስደትን ነው አማራጩ ያደረገው፡፡ ሎጥ እንደኖህ ቆም ብሎ አላሰበም፤ ‹‹ሀገሬ›› ቅብርጥሴ ሳይል ስደት ጀመረ፡፡

የዛሬይቱ የኢትዮጵያ ልጆች (ማጠቃለል ይከብዳል) እንደሎጥ ያሉ ናቸው፡፡ መሸሽ ነው ሥራቸው፡፡ አንደ ኖህ ችግርን መጋፈጥ የማያውቁ ደካሞች ናቸው፡፡ መርከባቸውን ጠጋግነው፣ መርከቢቱ ከመጣባት ማዕበል አሊያም ፍርድ ከማስመለጥ ይልቅ፣ እንደሎጥ መሸሽን የመረጡ ሰነፎች ናቸው፡፡

መብረቅ በባረቀ ቁጥር የሚደነብር ትውልድ መርከቢቱ ልታሳፍርና ከዚህኛው ዘመን ወደዚያኛው ልታሻግር አይገባም፡፡ የአንዳንዶቹ ኢትዮጵያውያን ሎጦች አቋም ትንሽ ባስ ያለ ነው፡፡ መርከቢቱ ላይ ኮሽ ካለ መደንበር፤ መበርገግ፤ አሜሪካ ኤምባሲ መሯሯጥ (ለቪዛ)፤ መጋፈጥ የማይችል ተብረክራኪ ትውልድ ከየትኛው የመርከቢቱ ክፍል የተገኘ ይሆን? ያኔማ መርከቢቱ የመስዋዕት ሜዳ ነበረች፡፡ በሜዳው ላይ የደም ጎርፍ ይታያል እንጂ ለማዕበል መንበርከክ የት ታውቅና መርከቤ፡፡

... አዎ! መርከቢቱ ጉዞ ያቋረጠችበት ወቅት የለም፡፡ ወደኋላ ሄደን፣ ያለፉ የመርከቢቱን ካፒቴኖች ዘመን ስንጎበኝ ይብዛም ይነስ ትጓዝ ነበር - መርከቢቱ፡

፡ በሁሉም ካፒቴኖች ዘመን እንደተዘወረች ነው፡፡ ዘመነ መሳፍንትን ጨምሮ፣ በተለያዩ አስተዳደራዊ ጊዜያት የመርከቢቱ ጉዞ እንደ ካፒቴኖቹ (መሪዎቹ) ይለያያል፡፡ የራሱን ሃሳብ እየገበረ የመርከቢቱን ጉዞ ወደኋላ ያንቀራፈፈ ካፒቴን ታሪክና ትውልድ ፈርዶበት ከመሪነቱ ተፈናቅሏል፡፡

አንድ የመኪና ሾፌር ‹‹ዋናው መሾፈር ነው›› ብሎ ሄዶ መርከብ ሊዘውር አይችልም፡፡ ዕድልና አጋጣሚ ፈቅዶለት እንኳን መርከቢቱን ቢዘውር፣ ማዕበል በተቀሰቀሰ ጊዜ ተጓዦቹን በጥበብ የማትረፍ ብቃቱ ያሽቆለቁላል፡፡

አንድ ሰው የመኪና ሾፌር ከሆነ መኪናውን ነው ማሳደድ ያለበት እንጂ፣ በ‹‹መሪ›› ስም ያገኘውን ነገር በካፒቴንነት ማሳደድ የለበትም፡፡ አንድ የቀበሌ ሊቀ-መንበር የአንድ ቀበሌ ነዎሪዎችን በመሪነት አስተዳድሯልና ሀገሪቱን ይዘውር አይባልም፡፡ በላዳና በመርከብ መሀል የተንቦረቀቀ ሰፊ ልዩነት አለ፡፡

... አጤ ምኒሊክ ወደ መሬት መቅረባቸውን ቀልባቸው በነገራቸው ሰዓት ‹‹አልጋ ወራሼ ኢያሱ ነው›› ብለው ለመኳንንቱና ለሕዝቡ አስታወቁ፤ ሕዝቡም አጤውን ይወድ ስለነበር ‹‹ለልጅ ኢያሱ እንገዛለን›› በማለት የልጅ ኢያሱን አልጋ ወራሽነት ተቀበለ፡፡ በወቅቱ ሕዝቡ የወደደው ልጅ ኢያሱን ሳይሆን አጤውን ነበር፡፡ ሕዝቡ አጤውን ስለሚወዳቸው ብቻ የማያውቀውን መሪ መርከቢቱን እንዲዘውር ሥልጣን ሰጠው፡፡

ካፒቴን ኢያሱ ለመርከቢቱ ያልተገባ መሪ መሆኑ እያደር ታወቀ፡፡ አስቀድሞ የነበሩ ካፒቴኖች

ይፈፅሟቸው የነበሩትን ሕጎች ወደ ጎን በማሽቀንጠር፣ የፈረሰ ጉግስ መጫወትና ሴት ማሳደዱን ተያያዘው፡፡ አሁን ይህ ሰው ትክክለኛ ካፒቴን ሆኖ ሳይሆን፣ በአጋጣሚ የመሪነት ሥልጣን ስላገኘ መርከቢቱን እንደፈለገው ነዳት፡፡ አንዲት ሕዝብን ያሳፈረች መርከብ ካፒቴኑ እንደ ፈለገ ሊዘውራት አይችልም፡፡

መርከቢቱ አሁን ያለችበትን ጉዞ ከአንድ ንጉስ ጋር ስናነፃፅረው ጥያቄ ውስጥ ይከተናል፡፡

ላሊበላ የተባለው ካፒቴን ዛሬ መመኪያ የሆኑ ቅርሶችን (ብርሃኖችን) ሰርቶ ለመጨረስ የወሰደበት ጊዜ 23 ዓመት ነው፡፡ የአፄ ኃ/ሥላሴን፣ የደርግን እና የኢሕአዴግን የካፒቴንነታቸውን ዘመን እናስላው፡፡ ኃ/ሥላሴ 44 ዓመት ነገሱ፤ ደርግ 17 ዓመት ገዛ፤ ኢሕአዴግ ደግሞ መርከቢቱን መዘወር ከጀመረ 20 ዓመት ሊደፍን ሁለት ወር ቢቀረው ነው፡፡ የሶስቱን መንግስታት አስተዳደራዊ ዘመን ስንደምረው 81 ዓመት ይሆናል፡፡ የላሊበላ የካፒቴንነት ዘመን 40 ዓመት ቢሆንም፣ ውቅር አብያተ-ክርስቲያናቱን በ23 ዓመት ሰርቶ አጠናቋል፡፡ በሶስቱ መንግስታት 81 ዓመታት ውሰጥ እንደ ካፒቴን ላሊበላ ፈረንጆችን ያስኮበለለ ሥራ አልተሰራም፡፡

ይቺ መርከብ ፀሃይና ጨረቃ በተፈራረቁ ቁጥር ብዙ የእገታ መረብ ውስጥ የገባች ናት፡፡ የእገታዎቹ ትርጉም ግን ይለያያል፡፡ በየትኛው ክ/ዘመን መርከቢቱ በቀላሉ የእገታ መረብ ውስጥ ልትገባ አልወደደችም፡፡ መርከቢቱ ውስጥ ያሉት ተጓዦች (ሃበሾቹ) ቀላል መንገደኛ አልነበሩም፡

ሲደርሰ ግን ፌስታሉን በእጁ ለመንካት አልደፈረም፡፡ ምግብ የተባለው የትርፍራፊ እና የሻጋታ ግብስብስ እንዳስጠላው ፊቱ ላይ ይነበባል፡፡

‹‹ብላው!›› የሚል ጩኸቱን ወደ የኔ ቢጤው ሰንዝሮ ቁሞ መመልከት ጀመረ፡፡

የኔ ቢጤውም በመስገብገብ መልክ በምግቡ (በፌስታሉ) ዙሪያ ተስፋፍቶ ተቀመጠ፡፡ የየኔ ቢጤውን ጥድፊያ እየተመለከተ ወጣቱ የስደብ ናዳውን አወረደ፡ ‹‹ውሻ! ቦርኮ!››

ለመሆኑ ምን አይነት ትውልድ እየመጣ ነው? ሥነ-ሥርዓት ይሉት ነገር የጠፋብን ስለምንድን ነው? ስግብግቦችና አረመኔዎች መሆናችን ለምንድን ነው? (መቼስ የአስተዳደግ በደል ብቻ ብለን ሁሉን በወላጅ እናላክክ ወይ የትምህርት በደል ብለን ኹሉን በመንግስት አናሳብብ) እንደው ህሊና የምንለውን ነገር በወዴት ጣልነው?

የራበው አንድ ኢትዮጵያዊ ስለምን ሊያሳዝነን አልቻለም? አለማዘናችን እንዳለ ሆኖስ ለምን ጨከንን? ብንጨክንስ ስለምን እንሳደብ?

ይህ ወጣት ኢትዮጵያዊ ነው ለማለት ፍላጎቱም ፈቃኝነቱም የለኝም፡፡ (ብቻ ኢትዮጵያ ላይ

በጥጋበኝነት የሚኖሩት የሱ ዓይነት ሆድ-ረሶች መሆናቸው ይቆጫል እንጂ)

እንግዲህ እኒህ ሁለት ወገኖች ፋሲካ መጣላቸው ማለት አይደል? ወጣቱ (ከተወሰነ ግዜ በፊት በአንድ የግል ጋዜጣ እንዳነበብኩት) የፆምን መግባትና መውጣት ምክንያት በማድረግ ታላቅ የስካርና የዝሙት ፌስቲቫል ላይ ተካፋይ ይሆናል፡፡ እንደ እኩዮቹ፡፡ እንደ መሰሎቹ... ህሊናው ከዚህ በላይ ሊያስብ አልቻለምና!

ባልተራበ ሆዳቸው ላይ የምግብ ናዳ እየከመሩ፣ ባልተጠማ ጉሮሮአቸው ላይ የመጠጥ ዓይነት እያዘነቡ፣ የአልጋ ወረፋ በጠፋበት የነውር አዳራሻቸው ኮሪደር ላይ ስልጣናዊ ዝሙትን እየፈፀሙ... ይዝናናሉ፡፡

አስፓልት መኻል ላይ መኪናቸውን አቁመው በሰው ላይ ይታያሉ፡፡ ሲልላቸው ግብረ-ወጥ ስድባቸውን፣ ሲያሻቸው ሲያጠራቅሙት የዋሉትን ቃርሚያቸውን፡፡ ይኼው ነው፡፡ ይህች ሀገር የእነሱ ብቻ፤ ሁሉም ነገር በእጃቸው ሁሉም ጉዳይ በገንዘባቸው የሆነላቸው፡፡

ትንሽ ጊዜው ሳይቆይ አልቀረም፡፡ አንድ ጓደኛዬ ዓይኖቹ እሳት እየተፉ ከፍ ባለ መናደድ ውስጥ ሆኖ ተገናኘን፡፡ እና ምን እንደነካው

ስጠይቀው የሚከተለውን ነገር ነገረኝ፡፡

‹‹ሁለት የስምንተኛ ክፍል ተማሪዎች (በተለያየ ት/ቤት የሚማሩ የአንድ ሰፈር ልጆች) አንደኛው በሀብታሞች የግል ት/ቤት አንደኛው በመንግስት ት/ቤት ይማራሉ፡፡

እና የመንግስት ት/ቤት ተማሪው አልጋ ላይ ላለች ታማሚ እናቱ ደረቅ እንጀራ መግዣ ጓደኛውን ይለምናል፡፡ የሀብታም ልጅ ጓደኛውም ከኪሱ ብዙ የሚያጓጉ ብሮችን አውጥቶ እያስጎመዠ ‹‹ጫማዬን ሳምና›› አለው፡፡

ይህንን ስሰማ እንደጓደኛዬ በንዴት ሳይሆን በሀዘን አረርኩ፡፡ እንዲህ ያለ በፀጉር የተሸፈነ ባዶ አዳራሽ አንገቱ ላይ አስቀምጦ የሚጓዝ ዜጋ ለዚህች ሀገር ምን ይረባታል? (ለዚያውም ቀን ከሌት መሳደድ እቅዱ የሆነ ባንዳ!)

የደረቅ እንጀራ መግዣ ሦስት ብር ለመስጠት ጫማውን ማስሳም ፈለገ፡፡ አልጋ ላይ እያጣጣረች ያለች ነፍስ ለእሱ ምኑም አይደለችም! የእድሜ አቻው የነፍስ ጭንቀትና ስቃይ ብቸኝነት እና ችግር ለሱ ምኑም አይደለም፡፡

መራብ ምን እንደሆነ መቸገር እስከምን እንደሆነ፣ ፍቅር ምን ማለት እንደሆነ፣ ረህራሔ ትርጉሙ፣ ሀበሻነት፣ ኢትዮጰያዊነት፣ ጎረቤትነት፣ ጓደኝነት፣ መረዳዳት፣ መበዳደር የሚሏቸው ቃላት በእሱ ህሊና ውስጥ በስህተትም አልተመዘገቡም፡፡

ይኼ ቢያድግ ምን ይረባል? ትልቅ ጅብ ከመሆን ያለፈ ምን ችሎታ አለው? ሀገርንና ህዝቡን በዝብዞና ሽጦ፣ ረግጦና ግጦ ቦርጭ ከማውጣት ባለፈ ይኼ የትኛውን ጠበብ ይፈልጋል? የትኛውን ሀገራዊነት ያንፀባርቃል? ሰንደቅዓላማን እንደምን ይረከባል?

በተቻለው ሁሉ ሻሽጦ ከድቶ ይጠፋል እንጂ!

በነገራችን ላይ እንደዚህ በድፍረት የምተነብየው አንድም ወላጆቹ ሲያደርጉት ያየውን፣ አንድም አድርግ ያሉትን እንደሚያደርግ ስለምገምት ነው፡፡

‹‹ከማንም ልቅምቃሚ፣ ቡትቷም፣ ጨርቃም ደሀ ጋር አብረህ እንዳትቆም›› ብላ ትዕዛዝ ለልጇ የምትሰጥ እናት የለችም ብሎ ማሰብ የዋህነት ነው፡፡

‹‹ውሀ ለጥፍሬ እንጂ ለጉሮሮዬ አላሳየውም! ልጄ ቀብረር ብለህ ኑር! ከማንም ኩሊ ጋር አብረህ አትቁም! እኔ ልኑርልህ›› የሚል አባት እኒህን የመሰሉ ልጆችን እያፈራ አይደል!?፡፡

የሚገርመኝም የማዝነውም እኒህ ህሊና ቢስ ግለሰቦች ድሆችን በመበዝበዝና በማስጨነቅ እንጂ ከአእምሯቸው አፍልቀው አዲስ ሳይንሳዊ ግኝት አስመዝግበው ሀብታም እንደልሆኑ እናውቃለን፡፡ ይህ ድሀን የመጋጥ አባዜ እንዴት እንደተጠናወታቸው ለማየት ዘይት በተመን አንሸጥም ማለታቸውን ብቻ ማስታወስ በቂ ነው፡፡

ከምግብ ቤት በር ላይ ትርፍራፊ ለመብላት የተሰባሰቡ የተራቡ ታዳጊዎችን አፍ አውጥቶ ቃል መርጦ ቅስም ሰባሪ ስደብ የሚሳደብ ሆዳም ወጣት አየሁ፡፡ ታዝቤው እመለከተዋለሁ፡፡ ለአንድ ሰው የማይመስል (በተለይ በዋጋው) የምግብ ዓይነት መርጦ አዘዘ፡፡ በረንዳ ላይ ተቀምጦ፡፡

መኪና አቁማ ምሳ ልትበላ የመጣችን ግለሰብ ካልጋበዝኩሽ ብሎ እምቧ ከረዮ ማለት ጀመረ፡፡ ሳትፈልግ ከፈለላት፡፡ ቀጥሎ ስልክ ሊጠይቃት፡፡ ያልመጣውን ሳቅ ይገለፍጣል፡፡ ያልተጠየቀውን ስለቁንጅናዋ ይቀባጥራል፡፡

የሚገርመኝ ሰውን እንዲህ

በታዲዎስ ጌታሁን

ሞገድ ተለይቷት የማታውቀው መርከብ እና ካፒቴኖቿ

ወደ ገፅ 23 ዞሯል

ሁለት ወገን ፋሲካደሳለኝ ሥዩም

[email protected]

ኃ/ሥላሴ 44 ዓመት ነገሱ፤ ደርግ 17 ዓመት ገዛ፤

ኢሕአዴግ ደግሞ መርከቢቱን መዘወር ከጀመረ 20 ዓመት

ሊደፍን ሁለት ወር ቢቀረው ነው፡፡ የሶስቱን መንግስታት

አስተዳደራዊ ዘመን ስንደምረው 81 ዓመት ይሆናል፡

፡ የላሊበላ የካፒቴንነት ዘመን 40 ዓመት ቢሆንም፣ ውቅር

አብያተ-ክርስቲያናቱን በ23 ዓመት ሰርቶ አጠናቋል፡፡

ወደ ገፅ 23 ዞሯል

ለመሆኑ ምን አይነት ትውልድ እየመጣ ነው? ሥነ-ሥርዓት ይሉት ነገር የጠፋብን ስለምንድን ነው? ስግብግቦችና አረመኔዎች መሆናችን ለምንድን ነው? (መቼስ የአስተዳደግ በደል ብቻ ብለን ሁሉን በወላጅ እናላክክ ወይ የትምህርት በደል ብለን ኹሉን በመንግስት አናሳብብ) እንደው ህሊና

የምንለውን ነገር በወዴት ጣልነው?

Page 9: ethioforum.orgethioforum.org/wp-content/uploads/2011/04/Awramba_Times... · 2011-04-11  · ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ 4 ፊ ቸ ር አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 164 ቅዳሜ ሚያዚያ 15 2003

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

በየወሩ የሚያሳቅቀን የነዳጅ ጭማሪ መጨረሻ የለውምን?

9ኮሜንተሪ

የታክሲ ረዳቱ የጎደለውን ሰው ሲጣራ የእጅ ምልክት አሳየሁት፡፡ ዓይኖቹን ወደ እኔ ጥሎ ‹‹አፍጥነው ጀለሴ አፍጥነው!›› አለኝ፡፡ ምን ይሉት

አማርኛ ነው ጃል? ‹‹ፍጠን›› ለማለት ነው ‹‹አፍጥነው›› የሚለኝ? ስል እያሰብኩ ወደታክሲው ዘለቅሁ፡፡ አሁን ሁላችንም በታክሲው ሆድ ውስጥ ታጉረናል፡፡ የተከፈተው ሬዲዮ የሰዓቱን ዜና ያንበለብለዋል፡፡ ለታላቁ ሚሊኒየም ግድብ ሕብረተሰቡ ያለውን ተነሳሽነትና የሰጠውን ድጋፍ ይተነትናል፡፡ ‹‹የእከሌ መ/ቤት ሠራተኞች የአንድ ወር ሙሉ ደመወዛቸውን ለገሱ፤ እንዲህ የተባለው ድርጅት የዚያን ያህል ሺህ ብር ቦንድ ገዛ፤ የዚህ አካባቢ ነዋሪዎች በአዲሱ ሚሊኒየም ግድብ ደስታቸውን ገለፁ…›› የሚሉ የወቅቱን ዜናዎች እያሰማን ነው፡፡

ረዳቱ ፍራንካውን ይሰበስባል፡፡ ወዲያው በሂሳብ ምክንያት ከአንድ አዛውንት ጋር አተካሮ ገጠመ፡፡ ተሳፋሪዎች በሙሉ ረዳቱን ወግነው ቆሙ፡፡ በነዳጅ ጭማሪው ምክንያት የትራንስፖርት ዋጋው 0.25 ሳንቲም መጨመሩን ሁሉም ሰው ገለፀላቸው፡፡ አዛውንቱ ጭማሪውን ያወቁ አይመስሉም፡፡ ወዲያው ሞባይላቸውን መዘዙና የሆኑ ቁጥሮች ነካኩ፡፡ ምን ሊያደርጉ ይሆን? ብለን አየናቸው፡፡ ከጥቂት አፍታ በኋላ የስልክ ንግግራቸውን ቀጠሉ፡- ‹‹ስሚ አልማዝ ትላንት ነዳጅ ጨምሯል እያሉ ነው፡፡ በይ አንቺም ያንን ነገር የ500 ብር ጨምረሽ ግዥ፡፡ ምናልሽ? ተይ እንጂ? በቃ ተይው›› ሞባይላቸውን ዘግተው ወደ ኪሳቸው መለሱ፡

፡ አጠገባቸው ወዳለው ተሳፋሪ ዞር አሉናም፣ ‹‹ይገርማልኮ ባለቤቴ ጤፍ ልትገዛ ወጥታ ነበር፤ ነዳጅ ከቀጠለ ጤፍም ይቀጥላል ብዬ ጨምረሽ ግዥ ልላት ብደውል ከትላንት ዋጋው በኩንታል መቶ ብር ጨምሯል አሏት፡፡›› አዛንውቱ ትክዝ አሉ፡፡ ከዚህ በኋላ የነበርንበት ታክሲ የኑሮ ሁኔታ የሚሰለቅበት የውይይት መድረክ መሰለ፡፡

ቀኑን ከዋልኩበት አመሻሽ ወደቤቴ ስመለስ ደግሞ ብዙዎቹ የመንደር ሱቆች መታሸጋቸውን አስተዋልኩ፡፡ በመንገዴ ላይ የነበሩት አብዛኞቹ ሱቆች የእሸጋ ወረቀት ተለጥፎባቸዋል፡፡ አንድ የማውቀው ሰው አይቼ የሸቀጥ ሱቆቹ ለምን ተዘጉ? ብለው ከተመን ውጪ ሽያጭ በማካሄዳቸው በቀበሌው የደንብ አስከባሪዎች መታሸጋቸውን ነገረኝ፡፡ በእርግጥም ሱቆቹ መንግስት ያወጣውን ተመን ተግባራዊ እንዳላደረጉት አውቃለሁ፡፡ ለምሳሌ 40 ብር ይሸጡት የነበረውን ‹ሀቱን› ዘይት በአንድ ቀን ለውጥ 47 ብር አስገብተውታል፡፡ ስኳርማ ሜርኩሪ ሆኗል፡፡ በአንዳንድ ቦታዎችም በጥቁር ገበያ እንደሚሸጥ ይነገራል፡፡ ተፈላጊ ሸቀጦች አይገኙም፡፡ ያሉትም ዋጋቸው አይቀመስም፡፡ አልፎ አልፎም በድርድር ይሸጣሉ፡፡ በዚህም ሆነ በዚያ የኑሮ ውድነቱ ይበልጥ አሳሳቢና አንገብጋቢ እየሆነ ይገኛል፡፡

መንግስት ኢኮኖሚውን ለማሻሻልና የዋጋ ንረቱን ለማረጋገጥ የወሰዳቸውን ተከታታይ እርምጃዎች እንደገና ቆም ብሎ ሊፈትሻቸው የሚገባ ይመስለኛል፡፡ እርምጃዎቹ ምን አበረታች ለውጥ አመጡ? ምን የተሻለ ነገር ተገኘ? ምን የከፋ ሁኔታንስ አስከተለ? የሚለውን በጥንቃቄ መመርመርና ለኢኮኖሚ ችግሮቹ ፍቱን መፍትሔ ለመስጠት መዘጋጀት ይኖርበታል፡

፡ ብዙ ጊዜ የመንግስት የፖለቲካ ውሳኔዎች ኢኮኖሚውን ሊያሻሽሉት አይችሉም፡፡ ለኢኮኖሚው ችግሮች ፖለቲካዊ እና አስተዳደራዊ ብቻ ሳይሆን ኢኮኖሚያዊ መፍትሔዎችም ይሰጡ፡፡ በአመዛኙ የተሳሳቱ የፖለቲካ ውሳኔዎች የኢኮኖሚ ችግሩን ይበልጥ ሲያወሳስቡትና ይበልጥ ሲያቆላልፉት እንጂ ሲያቃልሉት አላየንም፡፡ አሰራሮች ብቻ ሳይሆኑ ፖሊሲዎችም ይፈተሹ፡፡

መንግስት ከሸማቹ ጋር ተቀያይሞ፣ ከአምራችና ከአስመጪው ጋር ተኮራርፎ፣ ከቸርቻሪዎች ጋር ተጣልቶና ተጠማምዶ እንዴት ይዘልቀዋል? እነዚህን ወገኖች ተራ በተራ በየፊናው ከመወንጀል የመፍትሔው አካላት እንዲሆኑ ሁኔታዎችን ማመቻቸት መቻል አለበት፡፡ የሀገራችን ነጋዴና አስመጪዎች አንዳንድ ችግሮች ቢኖርባቸውም ያን ያህል ስግብግብና ለወገናቸው ደንታ ቢስ ናቸው ብዬ አላምንም፡፡ መንግስት ነጋዴዎቹን ከማስጨነቅ፣ ከማስፈራራትና ከማሳቀቅ ይልቅ ኢኮኖሚው እንዲረጋጋ የበኩላቸውን ገንቢ አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ማማከርና ማበረታታት ይኖርበታል፡፡ ከማሰር፣ ከማስፈራራትና ከማስገደድ የተሻለ መፍትሔ ለምን ጠፋን? የሰውን ልጅ ከእዝ ይልቅ ፍቅር ይገዛዋል፡፡ ፍቅርና በጎ ፍቃድ ሰዎችን ሁሉ የበለጠ ምርታማ ያደርጋቸዋል፡፡ ቁጥጥርና ኃይል ምርታማነትን ይቀንሳል፣ የባሰውንም ችግር ይወልዳል፡፡

በቅርብ የማውቀው አንድ ሰው ‹‹ወር በመጣ ቁጥር እጨነቃለሁ›› አለኝ፡፡ ለምን ብለው፣ ‹‹በየጊዜው የነዳጅ ጭማሪ ስለሚደረግ በነዳጁ ላይ የምትጨመረው እያንዳንዷ ሳንቲም ሕይወቴን እየነካች ነው›› አለኝ፡፡ በእርግጥም ይህ ጭንቀት የዚህ ሰው

ብቻ ሳይሆን የብዙዎቻችን ይመስለኛል፡፡ ከቶ የነዳጅ ጭማሪው ማብቂያ የት ላይ ነው? ዛሬ ከአንዱ የከተማው ክፍል ወደሌላው የከተማ ክፍል በታክሲ ስንጓዝ የምንጠየቀው ሂሳብ ቀደም ሲል ከአዲስ አበባ ወጣ ብለን ወዳጅ ዘመድ ጠይቀን ከምንመለስበት ዋጋ ያላነሰ ሆኗል፡፡ የነዳጅ ዋጋው በየወሩ ሲንር ሰውነታችን ከሚያልቅ እንደጥንቱ አባቶቻችን በመሀል ከተማው በፈረስና በበቅሎ ብንጠቀም ይሻለን ይሆን? ኑሯችን የፊቱን ሳይሆን የኋላውን ያስመኛል፡፡

መንግስት የሕዝቡን ጩኸት ሊያዳምጥ ይገባዋል፡፡ በፈቃዱ መስማት ከልቻለ ተገዶ የሚሰማበትን ቀን እያቀረበ መሆኑን ይወቀው፡፡ ላለፉት 20 ዓመታት በዴሞክራሲውም ሆነ በልማቱ ያገኘው ውጤት እጅጉን አናሳ ነው፡፡ ጥሩ ሪከርድ አስመዝግቤያለሁ ብሎ መኩራራት ራስን ማታለል ይሆናል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለተቃዋሚዎቻቸው ሲናገሩ፣ ‹‹መንግስት መስማትና ማየት የተሳነው አይደለም›› ብለው ነበር፡፡ ሕዝብም ቢሆን መስማትና ማየት የተሳነው አይደለም፡፡ ያሉትን የኢኮኖሚ ችግሮች መሸፋፈን ሳይሆን ችግሮቹን አምኖ መቀበል አንድ የመፍትሔው አካል ነው፡፡ ኢህአዴግ ቀለበት መንገድ መስራቱን እናውቃለን፡፡ ኢህአዴግ ኮንዶሚኒየም መገንባቱንም እናውቃለን፡፡ በከተሞች ውስጥ ፎቅ መስራቱን አናውቃለን፡፡ በገጠሩም ረጃጅምና ያማሩ መንገዶችን ሰርቷል፡፡ እነዚህን አልሰራም ብንል ዋሾዎች ነን፡፡ ኢህአዴግም ሳይሆን ሥራዎቹ ይመሰክሩብናል፡፡ ነጋ ጠባ ግን እነዚህን በሚዲያ እያቀረቡ ከራስ የእጅ ሥራ ጋር ፍቅር መውደቅ የሚበጀ አይሆንም፡፡ ኢህአዴግ በበቂ አልሰራልንም የሚለው አንደበታችን

ብቻ አይደለም፡፡ የሆዳችን ጩኸት፣ ኑሮና ገፅታችን ጭምር ይናገራል፡፡ ጥቂቶችና ከሥርዓቱ ጋር ‹ተሞዳሙደው› በመዲናችን ውስጥ የቅንጦት ኑሮ የሚኖሩትን ከማየት የብዙሃኑን ሕይወት ማስተዋል የተገባ ነው፡፡ የህወሓት/ኢህአዴግ ወጣቶች የታገሉት፣ ደማቸውን ያፈሰሱት፣ ሕይወታቸውን የሰዉት ይህን የጥቂቶች ድሎት ለማመቻቸት ነበር እንዴ? እራሳቸውን ይፈትሹ፡፡ ባለቅኔ ፀጋዬ ገ/መድህን በብዕሩ አፄ ቴዎድሮስ አሉ እንደሚለን፡-

‹‹ያለፈ ጥረታችንን ሳስታምመው ትዝ ሲለኝ

ከሞከርነው ይልቅ ያልሞከርነው ነው የሚቆጨኝ›› ማለቱ የሚጠቅም ነው፡፡

ባለፈው ሳምንት አንድ የማላውቃቸው ሰው መንገድ ላይ አስቆሙኝ፡፡ ፎቶዬን እዚህችው ጋዜጣ ላይ አይተው ይመስለኛል፡፡ ክንዴን ለቀም አድርገው ወደጥግ እየወሰዱኝ ‹‹ጋዜጠኞች እባካችሁ ሌላ ሌላውን ወሬ ትታችሁ ስለኑሮ ውድነቱ አቤት በሉልን፤ ኑሮ ከበደ፣ እባካችሁ ለመንግስት አቤት በሉልን!›› ሲሉ ደጋግመው አሳሰቡኝ፡፡ ይኸው ‹‹አቤት!›› ብያለሁ አባቴ፡፡ ነገር ቢበዛ በአህያ አይጫንም፡፡ በአጭሩ የምንለው መንግስት ኢኮኖሚውን ያሻሽል ነው፡፡ የዜጎች ምሬት ከፍቷል፤ እንባና ሀዘናችን በዝቷል፡፡ የነዳጅ ዋጋን በሚችለው አቅም ይደጉም፤ አልያም ከምግብ ምርቶች ላይ የሚሰበስበውን የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ያንሳ፡፡ ኢህአዴግ እንደሚለው ኳሷ ያለችው በራሱ እጅ ላይ ነው፡፡ እኛ የምንለው ደግሞ ‹‹ጨው ለራስህ ስትል ጣፍጥ...›› ነው፡፡

መልካም ትንሳኤ!

ኢህአዴግ ቀለበት መንገድ መስራቱን

እናውቃለን፡፡ ኢህአዴግ ኮንዶሚኒየም

መገንባቱንም እናውቃለን፡፡ በከተሞች ውስጥ ፎቅ መስራቱን አናውቃለን፡፡ በገጠሩም ረጃጅምና

ያማሩ መንገዶችን ሰርቷል፡፡ እነዚህን አልሰራም ብንል ዋሾዎች ነን፡፡ ኢህአዴግም

ሳይሆን ሥራዎቹ ይመሰክሩብናል፡፡ ነጋ ጠባ

ግን እነዚህን በሚዲያ እያቀረቡ ከራስ የእጅ

ሥራ ጋር ፍቅር መውደቅ የሚበጀ አይሆንም፡፡

በሰሎሞን ሞገስ (ፋሲል)[email protected]

በመገንባት ላይ ያለ የወተት ማቀነባበሪያ ፋብሪካ

ሰንዳፋ አካባቢ የተጀመረው የወተት ማምረት ሥራ

Page 10: ethioforum.orgethioforum.org/wp-content/uploads/2011/04/Awramba_Times... · 2011-04-11  · ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ 4 ፊ ቸ ር አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 164 ቅዳሜ ሚያዚያ 15 2003

የኑሮ MAP

የስኬት ጉዞ

10

p Ç T@ S ´ “ —

በንፍታሌም

መፅሐፏ በውስጧ አምቃ የያዘቻቸው በርካታ ጉዳዮች በ ማ ን ኛ ው ም ሰው የዕለት ተዕለት ህይወት

ዙሪያ ያጠነጠኑ በመሆናቸው የመደነቅ ስሜትን ይፈጥራሉ፡፡ የመፅሐፉ አንባቢ በእያንዳንዷ ገፅ ውስጥ የራሱን ግለ-ህይወት እንዲፈትሽ ይገደዳል፡፡ የራሱን ግለ-ህይወት ከአካባቢው እና ከማህበረሰቡ መስተጋብር ጋር እያወሳሰበ ይመለከታል፡፡

ከዚያም ባሻገር ከሀገራዊ ህይወቱ ጋር እያስተያየ ድክመትና ብርታቱን፣ ችግሩንና ስኬቱን ይመዝን ዘንድ ግድ የሚለው ዕውነት ያገኛል፡፡ እናም “ይህም አለ ለካ” እያለ፣ ያላስተዋለውን እያስተዋለ፣ በአዲስ መንፈስና መነቃቃት እስከመጨረሻዋ ገፅ ድረስ ይጓዛል፡፡ ምክንያቱም የዚህች መፅሐፍ ዋንኛ አስኳል ወይም ጭብጥ “ኑሮ” ነው፡፡ ደራሲው ለመፅሐፉ “የኑሮ MAP” የተሰኘ ርዕስ ነው የሰጧት፡፡

ደራሲው ዶ/ር ኤርሲዶ ለንደቦ ይባላሉ፡፡ ከመፅሐፉ ዋንኛ ርዕስ ስር (በውጪው ሽፋን) “እያንዳንዱ ሰው የራሱ ህይወት ቀራፂ” መሆኑንም ይነግሩናል፡፡ በሌላ አገላለፅ እያንዳንዱ ሰው፣ ግለ-ህይወቱን አስደሳችና የበለፀገ በማድረግ ከስኬት ወደ ስኬት መሸጋገር ይችላል ይሉናል፡፡ እያንዳንዱ ሰው ህይወቱን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር፣ አዲስ እና የታመነበት ውጤታማ ሳይንስ የተገኘ መሆኑንም ያስተዋውቁናል፡፡ ይህ አዲስ ሳይንስ “system thinking” መሆኑንም ይነግሩናል፡፡ ደራሲው ይህንን አዲስ ሳይንስ “ቅንብራዊ አስተሳሰብ” ሲሉ ይተረጉሙታል፡፡

ደራሲው ዶ/ር ኤርሲዶ ለንደቦ “ኑሮ

MAP” ሲሉ የሰየሙትን መፅሐፍ ዓላማ በዚህ መልኩ ይገልፁታል፡፡ “አስደሳችና የበለፀገ ህይወት እንዲያው በዘፈቀደ እውን አይሆንም፡፡ በትምህርት ሆነ በሥራ ዓለም በቢዝነስም ሆነ በፍቅር ግንኙነት፣ በቤተሰብም ሆነ በተቋም፣ በማህበርም ሆነ በሀገር ደረጃ፤ በሁሉም መስክ የስኬት ጉዞአችንን ለመጀመርና ለማፋጠን የምንችልበትን መንገድ ማወቅ አለብን፡፡ ስኬትን ለመጎናፀፍ ከተፈጥሮ ጋር ተጣጥሞ የተቀናበረ እንዲሁም በተጨባጭ ሥራ ላይ ሊውል የሚችል ትክክለኛ አስተሳሰብና አስተማማኝ መሣሪያዎች ያስፈልጉናል፡፡...” (ገፅ 11)

የዚህ “ኑሮ MAP” መፅሐፍ ደራሲ እያንዳንዱ ሰው የራሱን ህይወት መቅረፅ ያስችለዋል ያሉትን እና “ጥንቅራዊ አስተሳሰብ” ሲሉ ትርጉም የሰጡትን አዲስ ሳይንስ ጥልቅ በሆነ መንገድ ለመተንተን የሚንደረደሩት አንድ ተረትና ምሳሌ በማስቀደም ነው፡፡ መፅሐፉን በአምስት ዋና ዋና ክፍሎች (ምዕራፎች) ነው የሰደሩት፡፡ በክፍል አንድ “የአሳዎቹ ታሪክ” በሚል ርዕስ በ30 ገጾች (ከገፅ 17-47) የተረኩት የመፅሐፏን ሁለንተናዊ ይዘት ጠቅልሎ የያዘ ነው ማለት ይቻላል፡፡

ደራሲው የአሳዎቹን ታሪክ ተረት የከሸኑበት ስልት እጅግ መሳጭ ነው፡፡ የቃላት አጠቃቀማቸው የተመረጠ፣ የዓረፍተ ነገር አሰዳደራቸው የተመጠነና ቅልብጭ ያለ መሆኑ፣ እያንዳንዱ አንባቢ የየራሱን ግለ-ህይወት፣ እንዲሁም ግለ-ህይወቱ ከማህበረሰቡ ጋር ያለውን መስተጋብር በዓይነ ህሊናው ቁልጭ አድርጎ እንዲመለከት ግድ የሚል ነው፡፡ ይህ ብቻ አይደለም፤ ማንኛውም አንባቢ ከግላዊ ህይወቱና ከማህበራዊ መስተጋብሩ ባሻገር ሀገራዊና ዓለማቀፋዊ የተወሳሰቡ ችግሮችን፣ እንዲሁም መፍትሔዎችን አሰባጥረው ያቀናበሩበት ስልት የአስተውሎት ችሎታችንና ብቃታችንን

እንድንለካ የሚያደርግ፣ ህሊናዊ መነቃቃትን የሚፈጥርና ወደስኬት የማምራትን ሰዋዊ ፍላጎት የመቀስቀስ ኃይል ያለው ነው፡፡

እንደው በጥቅሉ የአሳዎቹን ተረት የተረኩበት ስልት እንደ ዕድሜ ጠገብ አዛውንት በአክብሮት እንድንከታተላቸው አድርገው ህሊናችንን ሰቅዘው ይይዛሉ፤ በሃይማኖታዊ ትምህርት እንደሚመስጥ ሰባኪ ናቸው፤ ተማሪዎቹን በፍቅር እንደሚያንፅ ድንቅ መምህር እንድናያቸው ማድረግም ችለዋል፡፡ በዚህም የተነሳ ወደሚቀጥሉት ገጾች አምርተን አንዳች ዕውቀት ለመቅሰም ጉጉት ያሳድሩብናል፡፡ ይህም የመፅሐፏን ቱባ ቱባ መልዕክቶች ወደ አንባቢያን ዘንድ በማድረስ ረገድ የተዋጣላቸው እንዲሆኑ አስችሏቸዋል ቢባል ግነት አይደለም፡፡

የሥነ-ፅሁፍ ባለሙያዎች ተረትን የሚመድቡት ከሥነ-ቃል ዓይነቶች መሀል በማዳበል ነው፡፡ የሥነ-ቃል ዓይነቶች እንደየሀገሩ እና እንደየባህሉ የተለያዩ ቢሆንም፣ በሁለት ዓበይት ቅርጾች ሊከሰቱ እንደሚችሉ የዘርፉ ባለሙያዎች ያሰምሩበታል፡፡ የመጀመሪያው በዝርዝርና በትረካ መልክ የሚቀርብ ሲሆን፣ ሀለተኛው በግጥም ቅርፅ የሚከሸኑና የሚዜሙ ናቸው ይሏቸዋል፡፡

በዝርውና በትረካ መልክ የሚቀርበው ተረት የማህበረሰብን ወግ፣ ልማድና ሥነ-ምግባር፣ ብሎም አጠቃላይ አመለካከትን ማስተላለፊያ ዓይነተኛ መሣሪያ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡ ተረት አንድ ማህበረሰብ ሰናይ እና እኩይ ብሎ የመደባቸውን የሥነ-ምግባር መልኮች ያንፀባርቃል፡፡ ሰናይን የማመስገንና የማወደስ፣ እኩዩን ደግሞ በማውገዝ ማህበረሰቡን፣ በተለይም ታዳጊ ወጣቶችንና ልጆችን በተወሰነ አቅጣጫ ለመምራት ጠቃሚ መሆኑ በፅኑ ይታመንበታል፡፡

ተረት በሰውና በእንሰሳት ገፀ-ባህሪይ

ወኪልነት የሚነገር ቢሆንም፣ ዋንኛ ዓላማው የሰው ልጆችን ሁለንተናዊ ህይወት የተለያዩ ገፆች በማሳየት ረገድ የሚኖረው ለዛ ማንኛውንም መልዕክት በማስተላለፍ፣ ቅቡልነት የተጎናፀፈ ነው፡፡

የዶ/ር ኤርሲዶ፣ የአሳዎቹ ተረት ትረካ በዚህ ስልት የተዋዛ በመሆኑ ማንኛውም አንባቢ በአሳዎቹ ህይወት ፈንታ ራሱን እየተካ፣ የኑሮን ስኬትና ውድቀት እያስተዋለና እያመዛዘነ፣ እየተገረመና እየተመመ፣ እየፈገገና እየሳቀ፣ እየተማረረና እየተከፋ … ወዘተ ንባቡን እንዲያጣጥም (እንዲቀጥል) የማድረግ ኃይል ያለው ነው፡፡

ለዚህም ይመስለኛል ደራሲው በመፅሐፋቸው መግቢያ “ወደ ሌሎቹ ክፍሎች ከመሸጋገራችሁ በፊት፣ ክፍል አንድን (የአሳዎቹ ታሪክ) ከተቻለ ሁለት ጊዜ፣ ካልሆነም አንዴ ማንበብ ቀጣዮቹን ክፍሎች በጥልቀት ለመረዳት ያግዛል›› ሲሉ (ገፅ 15) በአጽንኦት የሚያሳስቡት፡፡

በእርግጥም ይህ ክፍል የመፅሐፏን ቁልፍ ቁልፎ ሁነቶች ሁሉ በአንድነት ጠቅልሎ የያዘ ነው፡፡ ቀጣዮቹ ክፍሎች የተረቱን ዋና ዋና መልዕክቶች በተለያየ መልኩ በተጠና ሳይንሳዊ ስሌት የሚተነትኑ ናቸው፡፡ በሌላ አባባል ክፍል ሁለት ስለ ስኬት መንገድ፣ ክፍል ሶስት ስለ ስኬት መሣሪያዎች፣ ክፍል አራት ስለ ህይወት ክህሎት፣ ክፍል አምስት ስለ ስኬታዊ የህይወት ካርታ ምንነት፣ ግልፅ በሆነና ቀለል ባለ ቋንቋ ትንታኔ የተሰጠበት ነው፡፡

ደራሲው ማንኛውም ሰው ወደስኬት ጎዳና ሊሸጋገርበት ያስችለዋል ያሉትን አዲሱንና ሳይንሳዊውን ቅንብራዊ አስተሳሰብ በአምስት ክፍሎች ሸንሽነው፣ ደረጃ በደረጃና ቅደም ተከተላዊነት ባለው መልኩ ያደራጁበት ስልት የየራሳችንን ህይወት ፈትሸንና ችግሮቻችንን ለይተን፣ ወደ መፍትሔ ብሎም ወደ ስኬት እንድንጓዝ ማድረግ የሚያስችሉን ሆነው ነው የምናገኛቸው፡፡

ለዚህ አባባላችን አብነት ይሆነን ዘንድ በክፍል (ምዕራፍ) ሁለት “ስኬታማ መንገድ” በተሰኘው አቢይ ርዕስ ስር “መንስኤና ውጤት ተቀራራቢ ላይሆኑ ይችላሉ” በሚል ንዑስ ርዕስ ሰጥተው በሁለት ገጾች ብቻ (ገፅ 57-58) ያሰፈሩትን ሀሳብ መንቀስ ይበቃል፡፡

ደራሲው በዚህ ርዕስ ስር መንስኤና ውጤት፣ ሰበብና መዘዝ እንደ ሁኔታ፣ በጊዜና በቦታ ተቀራራቢ ሆነው ሊገኙ እንማይችሉ ይጠቁማሉ፡፡ በአንፃሩ ቀላል ችግሮችና አነስተኛ ስኬቶች በአብዛኛው መንስኤና ውጤታቸው አጠገብ ለአጠገብ ሆነው ሊገኙ እንደሚችሉ ይዘክራሉ፡፡ ሆኖም ግን ብዙዎቹ የዓለማችን ውስብስብ ችግሮች መንስኤያቸው አጠገባቸው የማይገኝ እንደሆነም በአፅንኦት ይገልፃሉ፡፡ የእነዚህን ውስብስብ ችግሮች መንስኤ ተረድቶ መፍትሔ ለማበጀት በጊዜና በቦታ፣ ሰፋ አድርጎ መመልከት እንደሚገባም ያትታሉ፡፡

የዚህ መፅሐፍ ዳሰሳ አቅራቢ፣ ይህንን

ክፍል ባነበበ ጊዜ ቀድሞ ወደ ህሊናው የመጣው የቀድሞው የተ.መ.ድ ዋና ፀሐፊ የነበሩት ጋናዊው ኮፊ አናን፣ በአንድ ወቅት ለታይም መፅሔት የሰጡት ቃለ-ምልልስ ነው፡፡

ኮፊ አናን፣ ይህንን ዓለም አቀፍ ድርጅት ለመምራት የሚያስችል ብቃትና ክህሎት ይኖርዎ ዘንድ የረዳዎት አጋጣሚ ካለ ቢነግሩን? በሚል ከታይም መፅሔት ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ፣ የ7ኛ እና የ8ኛ ክፍል ተማሪ በነበሩበት ወቅት አንድ መምህራቸው እንዴት ማሰብ እንደሚገባቸው የነገሯቸውን ነው በዋቢነት የጠቀሱት፡፡

“አንድ ቀን መምህራችን ወደ ክፍል እንደገባ፣ ነጩና ሰፊው ሰሌዳ ላይ በጥቁር ፓርከር አንዲት ነጥብ ብቻ አስቀመጠ፡፡ እና ‹ተማሪዎች ምን ይታያችኋል?› ብሎ ጠየቀ፡፡ ሁላችንም የክፍሉ ተማሪዎች በአንድ ድምፅ ‹ጥቁር ነጥብ› ብለን መልስ ሰጠን፡፡ ‹በጣም ትገርማላችሁ፡፡ ሰፊውንና ነጩን ሰሌዳ ሳታስተውሉ እንዴት ጥቁሯን ነጥብ ብቻ ነጥላችሁ ታያላችሁ?› አለንና መከረን፡፡ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ነገሮችን ሰፋ አድርጌ መመልከት እንዳለብኝ ተረዳሁ፡፡ ያቺ አጋጣሚ በህይወቴ ልዩ ቦታ የምሰጣት ናት...” የሚል ምላሽ ነው የሰጡት፡፡

የ“ኑሮ MAP” መፅሐፍም እንዲህ ባለ መልኩ ችግሮቻችንን እንድንመለከት፣ ተመልክተንም መፍትሔ እንድንሰጥና ወደ ስኬት እንድናመራ የሚያደርጉ፣ እንዲሁም ወደ ተጨባጭ ህይወት ለውጥ የሚያስጉዙ በርካታ ስንቆችን የያዘ (ሳይንሳዊ) ነው፡፡ በዚህም የተነሳ መፅሐፉን አንዴ ብቻ አንብበን የምናስቀምጠው ወይም የምንጥለው ሳይሆን፣ በየጊዜው እንደመሣሪያ እያነሳን ልንጠቀምበት የሚገባን የህይወት መመሪያ ነው ብንል ስህተት አይሆንም፡፡

በጥቅሉ ተማሪው በትምህርቱ፣ ሠራተኛው በሥራው፣ ነጋዴው በንግዱ፣ ሌላውም ሰው እንደየሙያውና እንደየፍላጎቱ … ወዘተ ስኬትን የሚጎናፀፍበት ስልትን ቀምሮና አጭቆ የያዘ መፅሐፍ ነው፡፡

ደራሲው ቱባ ቱባ ቁም ነገሮችን በማስተላለፍ ረገድ የተዋጣላቸው እንዲሆኑ ያስቻላቸው በሙያቸውና በሥራ ልምዳቸው ያዳበሩት ክህሎት ጭምር ነው፡፡ ደራሲው በህክምና የዶክትሬት ዲግሪ ያገኙ፣ ለአምስት ዓመት ያህል በሐኪምነት ያገለገሉ ከመሆናቸው ባሻገር፣ የደቡብ ብሔር/ብ/ሕ/ክ የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ጽ/ቤትን በኃላፊነትም ለስምንት ዓመታት የመሩ ናቸው፡፡

ከዚያም በዩ.ኤን.ዲ.ፒ የሚካሄደውንና በቅንብራዊ አስተሳሰብ ላይ ያተኮረ የሜይን ስትሪሚንግ ሥልጠና በመውሰድ ከአዲሱ ሳይንስ ጋር የተዋወቁ ናቸው፡፡ ለ4ኛ ጊዜ ያህል ወደ ደቡብ አፍሪካ ተጉዘውም የአሰልጣኞች ሥልጠና ወስደዋል፡፡ ወደ አገራቸው ተመልሰውም ከ10 ሺህ በላይ የሥራ ኃላፊዎችን፣ ወጣቶችን፣ መምህራኖችንና ሌሎችን አሰልጥነዋል፡፡ በዚህም ተግባራቸው ልዩነት መፍጠራቸውንና ውጤታማ መሆናቸውን በመፅሐፋቸው የመጨረሻ ገፅ (ቅጠል) ላይ አስፍረዋል፡፡

ይህን አዲስ ሳይንሳዊ ፅንሰ-ሀሳብ እና የተግባር መሣሪያ ሊሆን የሚችል መፅሐፍ ለማዘጋጀት ከ200 በላይ ሥልጠናዎችን በሚሰጡበት ጊዜ ኢትዮጵያዊ ሀሳቦችን በመሰብሰብና በማጠናከር፣ እንዲሁም ሌሎች ጥረቶችን በማድረግ ሰባት ዓመት ያህል እንደፈጀባቸውም ገልፀዋል፡፡ “ይህንን ጥልቅ ግን ቀላል ሳይንስ ምቹ በሆነ መንገድ ለሚሊዮኖች ማሳወቅ እንደሚቻል በማሰብ” መፅሐፉን ለህትመት እንዳበቁት፣ የአሳዎቹን ተረት ሶስት የሲንጋፖር ዩኒቨርስቲ ፕሮፌሰሮች ከፃፉት “Big Fish Eat Small Fish” የሚል ርዕስ ካላት ትንሽ መፅሐፍ ተውሰውና አሻሽለው እንዳቀረቡትም አትተዋል፡፡

በማጠቃለያቸው መፅሐፉን በኦሮምኛ፣ በትግርኛና በሌሎች ቋንቋ ለመተርጎምና አብሮአቸው ማሳተም ለሚፈልግ፤ ለሕፃናት በሚሆን መልኩ ማዘጋጀት ለሚሻ ባለሙያ፣ በኑሮ MAP ፍልስፍና ላይ የተመሰረተ ልብ ወለድና ሌላም የሥነ-ጥበብ ሥራ ለመስራት ዕቅድ ላለው ግብዣ አቅርበዋል፡፡

መፅሐፉን አንብበው በሚያገኙት ውጤት የህይወት ልምዳቸውን ለሚፅፉላቸው ታሪካቸውን ለህትመት እንደሚያበቁላቸው እና የሽልማትም ተቋዳሽ እንደሚያደርጓቸው ገልፀዋል፡፡ እኛም አንባቢያንን ወደስኬት ሊያመራ የሚያስችለውን ይህን መፅሐፍ በመጋበዝ ነው ዳሰሳችንን የምንቋጨው፡፡

ዳ ሰ ሳ

ዓባይን እንጠጣው ቢደፈርስም1. እስከ መቼ ድረስ እንሙት በውሃ ጥም

እስከ መቼ ድረስ ይኑር 2. አቅሉን ጥሎ

መንገደኛው ዓባይ ይሂድ አረፍ ብሎ

እገዛለሁ እንጂ ካንድም ሁለት 3. ቦንድ

አንዱ ለጥበቃ አንዱ ለግድብ

የሌለኝን ገንዘብ አስወጥተኸኝ4. ዓባይ አደራህን እንዳትሸውደኝ

በዚህ አጉል ጊዜ በዚህ አጉል 5. ስዓት፣

በሌለው ተገንዓባይ እሳት ጭሮ እንዳያስፈጀን

ከራስጌ ከግርጌ የሚንከባከበው6. ዓባይ መች ሰው አጣ ቢተኛ እንደወትሮው

ዓባይ ሽብርተኛ አይባልም 7. ወይ

እንቅልፍ ሲነሳ ከታች እስከላይ

የጣና ልጅ ዓባይ ያበሻው 8. ፈረንጅ

ቢቆጡት አይሰማ አያውቅ አኮርባጅእንዴት ተመልሶ ይሁን የኛ ልጅ

ዓባይ በስተርጅና ተምሮ 9. ቢዝነስ

ቦንድ ያስገዛ ጀመር ዲያቆን ከቀሲስ

በስምንተኛው ሺ እጅ በበዛበት10. ገንዘብ አለኝ ባይል ዓባይ ምናለበት

ከተዛዘኑበት ሀብታምና ድሀ11. ግንፍሌም በቂ ናት እንኳን የዓባይ ውሀ

ጭልፊትና አሞራ ሰማይ 12. ጠበባቸው

ዓባይ ላይ ፍሪዳ ተጣለ ቢሏቸው

ዓባይ ምነው እንዲህ 13. ባይንቀባረር

አዋሽና ጊቤ ባቀኑት አገር

ዛሬስ ወንድ ወጥቶታል 14. ጎብዟል ዓባይ

አሰልፎ አቆመው ሁሉን ባንድ ላይ

ዓባይ ሰው ይወቅህ ውጣ 15. ከማጀት

አላዋጣምና ዓይን አፋርነት

ዓባይ ሰለቸኸን አንገፈገፍከን16. ሁሌ መውሰድ እንጂ አታውቅ ሰጥተኸን

ለኤሌክትሪኩስ ዓባይ ጊቤ 17. አለን

የቤንዚን ግድብ ነው አሁን የቀረን

‹‹ምናችሁ ነኝ›› ላይል ሰው 18. ላያስቀደም

የሁሉም መሆኑን ዓባይ ይፈጠም

አይዟችሁ ሱዳኖች ግበፆች 19. አይዟችሁ

አያመልጥም ዓባይ ነን ከጎናችሁ

ተው አትሸልል ዓባይ 20. አትፎክር እንዲህ

ገና ሳይታወቅ ማለፍ መውደቅህ

ዓባይን በጭልፋከዘመን ዘመን ስለ ዓባይ ተዚሟል፡፡ ላዕከ ተ/ማርያም ወቅታዊውን ጉዳይ መሰረት

በማድረግ እንዲህ መቀኘቱን ያስነብበናል፡፡

እናየመፅሐፉ ርዕስ፡- የኑሮ MAP

የመፅሐፉ ዓይነት፡- ኢ-ልብ ወለድ

የመፅሐፉ ደራሲ፡- ዶ/ር ኤርሲዶ ለንደቦ

የገፅ ብዛት፡- 200 ገፅ

የታተመበት ዘመን፡- መጋቢት 2003 ዓ.ም

የመፅሐፉ ዋጋ፡- 40 ብር

Page 11: ethioforum.orgethioforum.org/wp-content/uploads/2011/04/Awramba_Times... · 2011-04-11  · ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ 4 ፊ ቸ ር አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 164 ቅዳሜ ሚያዚያ 15 2003

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

11

p Ç T@ S ´ “ —

አ ፍታ1

ያስፈልጋል፡፡ እኛ ደግሞ አሳዋቂ ተብለው ከሚመደቡ ሰዎች የምንቆጠር ስለሆንን፣ የሥራችንም አካል ነውና፣ ህጉን አክብረን ሥነ-ሥርዓት ባለው መንገድ ህዝቡ የተደበቁ ችግሮችን በአደባባይ እንዲያወራ መታገል መቻል አለብን፡፡ እኔ እንደሚመስለኝ፣ ይኼን የሚሉት ሰዎች “መኃልየ መኃልየ ዘ-ካሳንቺስ” በሚለው መፅሐፍ ነው፡፡አዎ!... ለትንሽ ነው የቀደምሽኝ...ይገርማል!... ያ የጨለማ ህይወት አይነገረን ነው የሚሉት? የኖሩትስ ሰዎች? እኛ ስላሳተምነው ነው እንዴ ሰው የሚጨነቀው!?...፡፡ እዛ መፅሐፍ ውስጥ እንዲህ ኖርን የሚሉ ሴቶች ህይወቱን አልፈውበታል እኮ፡፡ በመሠረቱ አንድ ሴት፣ ሴተኛ አዳሪ በመሆኗ ብቻ ይህ ሁሉ በደል ሊደርስባት ይገባል ወይ? መነጋገር ካለብን በትክክል መነጋገር ነው ያለብን፡፡ ተደባብቀን የትም አንደርስም፡፡ ደግሞ ዘመኑ የመነጋገር ነው፡፡ ነገር ግን መፅሐፉ የያዛቸው ታሪኮች በተለይ ታዳጊ ወጣቶችን ወደዚያ ህይወት እንዲገቡ የሚገፋፋ ወይም የሚያነሳሳ ነው ብለው የሚሞግቱ አሉ፡፡ ምን ማለት ነው ይኼ? አውቀህ መሄድና ሳታውቅ መሄድ የተለያዩ ነገር ናቸው፡፡ እዚያ ቦታ እንዲህ አይነት ነገር አለ ብሎ አውቆ መሄድና ሳያውቁ መሄድ ውጤታቸው የትየለሌ መሆኑን መናገር ያለብኝ አይመስለኝም፡፡ እና... ገና ለገና ይሄዳሉ ተብሎ፣ እዚያ ሰው እያለቀ ዝም በሉ ነው የሚባለው? ደግሞ እንደዚህ ብለው የሚሟገቱ ሰዎች አንዳንድ ናቸው፡፡ በጣም ጥቂት ናቸው፡፡ እኔ መፅሐፉን ከማሳተሜ በፊት በረቂቅ ደረጃ ሳነበው ለሴቶቻችን በጣም ነው ያዘንኩት፡፡ እና ደግሞ፣ ወንዶቻችን ምን ሆኑ? ነው ያልኩት፡፡ ገንዘብስ ቢኖራቸው እንዲህ ማድረግ ጤነኝነት ነው ወይ? አይደለም፡፡ ይኼ እኮ ማህበራዊ መበስበስን

ስንዱ ራሷን እንዴት ትገልፀዋለች ቢባል ምን ትያለሽ?ጠይም፣ አጭር እና ሳቂታ፡፡ በቃ?(ሳቅ) በቃ ስለ እብደት አስበሽ ታውቂያለሽ?እንዴት? እንዴት አላስብም? ሰው አይደለሁ እንዴ!? ምን ማለት ነው ግን ስለ እብደት አስበሽ ታውቂያለሽ ማለት? ብዙ ሰዎች ስለአንቺ ሲናገሩ፣ የምትሰሪው የምታደርገው ሁሉ የእብደት ነው ይላሉ፡፡ (አቋረጠችኝ) እንጃ እንግዲህ፡፡ ሰዎቹ ናቸው እንዲህ የሚሉት፡፡ እንጂ እኔ የምሰራውን ሥራ ሁሉ በአግባቡ እንደምሰራ ነው የማውቀው፡፡ ለሰዎች ክብር የላትም፤ የመሰላትን ከመናገር ወደ ኋላ አትልም... ወዘተ ባይ ብዙ ናቸው፡፡... እኔ ሰዎችን በጣም ነው የማከብረው፡፡ በተለይ ሥራን በተመለከተ ምንም ነገር ብትጠይቀኝ፣ የሚመለከተኝን ጉዳይ ከሆነ ፊት ለፊት እናገራለሁ፡፡ ሰውን በማክበር ደረጃ፣ እንደ እኔ ሰው የሚያከብር ያለ አይመስለኝም፡፡ ከማህበረሰቡ አስተሳሰብ ያፈነገጠች ናት የሚባለውስ? ምን ማለት ነው የማህበረሰብ አስተሳሰብ? የተቀመጠ፣ የማህበረሰብ አስተሳሰብ የሚባል እኮ የለም፡፡ ነገር ግን... አብዛኛው ሰው ይኼ ነገር በማህበረሰቡ የማይደገፍ ወይም የተከለከለ ነው የሚለው ነገር አለ፡፡እንዴ!? እስከመቼ ነው በዚህ ጨለማ ውስጥ የምንኖረው? የተከለከለ ነው እያልን እኮ እያለቅን ነው፡፡ ስለዚህ መነጋገር አለብን፡፡ እኔ የማምነው በመነጋገር ነው፡፡ እውቀት ያድናል፡፡ ስለዚህ ማወቅ አለብን፡፡ ማወቅ ያለብንን ነገር ደግሞ ለማወቅ መትጋት

ነው የሚያሣየው፡፡ የማህበረሰቡን መበላሸት ነው የሚያሳየው፡፡ እና ችግሩን ለመፍታት የችግሩን ምንጭ ማወቅ ያስፈልጋል በሚል ዕምነት ነው “መኃልየ መኃልየ ዘ ካዛንቺስ” ያሳተምኩት፡፡ በአጭሩ የሴተኛ አዳሪ እህቶቻችን ችግር ወይም ህይወት ይመለከተናል የሚል ማንኛውም ወገን፣ ደግሞም ይመለከተናልና፣ ዜጋ ናቸውና፣ ወገንም ናቸውና ሁላችንም ጉዳዩን አውቀን እርምጃ መውሰድ ይገባናል፡፡ በመሠረቱ ፀሐፊም ሆነ አሳታሚ “ጠቋሚ” ማለት ነው፡፡ እኛም ያለውን ችግር አሳይተናል፡፡ እኔም ሆንኩ ደራሲው ችግሩ በይፋ እንዲታይ “ኡ! ኡ!” ብለናል፡፡ በሕግ የሚያስጠይቀን ቢሆን ኖሮ እስካሁን እንጠየቅ ነበር፡፡ ስለተወደደና ስለተጠላ አይደለም፡፡ እሱም ቢሆን የማጣጣም ጉዳይ ነው፡፡ እኔም ጠቃሚ ስለሆነ ነው ያሳተምኩት፡፡ አንቺ እንዲህ ብትይም በ”በመኃልየ መኃልየ ዘ-ካዛንቺስ” መፅሐፍ ላይ ቅዋሜ ያላቸው ሰዎች አሉ፡፡ ችግሩ ምኑ ላይ ይመስልሻል?ብዙ ሰው!... እጅግ በጣም ብዙ ሰው መፅሐፉን ወዶታል፡፡ በተቃራኒው ግን!... በተለይ የህትመት ሚዲያ ጋዜጠኞች መፅሐፉ ሳይነበብ ህዝቡ ባልሆነ መንገድ እንዲያየው አድርገውታል፡፡ የጋዜጠኞች ችግር ነው እንጂ ህዝቡማ ወዶት እናመሰግናለን ብሎኛል፡፡ መንግስትም እናመሰግናለን ብሎኛል፡፡ መልካም፡፡ ስንዱ አሁን አንቺ በየትኛው ሙያ ነው የምትመደቢው? ቲያትረኛ፣ ፀሐፊ፣ ጋዜጠኛ ወይስ አሳታሚ?ወደየትኛው እንደምመደብ አላውቅም፡፡ ድሮ ተዋናይ ነበርኩ፡፡ ጋዜጠኛም ነበርኩ፡፡ አሁን በህይወት መንገድ ተጉዤ አሳታሚ ሆኛለሁ፡፡ ከእነዚህ ሙያዎች

ወደ ገፅ 23 ዞሯል

የቲያትር ጥበብን ሞካክራለች፡፡ ከዚያም ወደ ጋዜጠኝነቱ ዓለም ገባች፡፡ ለ11

ዓመታት ያህል በጋዜጠኝነት ካገለገለች በኋላ ራሷን ከሙያው አገለለች፡

፡ ከዚያም ወደ መፅሐፍ አሳታሚነት ተሸጋገረች፡፡ በቅርቡ የፈንሳዊውን

አርተር ራምቦ ግለ-ታሪክ ተርጉማ 8ኛ መፅሐፍ ለህትመት አብቅታለች፡፡ “ በጋዜጠኝነት ያሳለፍኩትን ዘመን ነው

የምጠላው” ከምትለው ፀሐፊና አሳታሚ ስንዱ አበበ ጋር ወሰንሰገድ ገ/ኪዳን

የ”አንዳፍታ” ቆይታ አድርጓል፡፡

“የማልወደው

ሥራዬን ነው”የጋዜጠኝነት

ደራሲና አሳታሚ- ስንዱ አበበ

‹‹ተዓምራዊ ኃይል›› መፅሐፍ ገበያ ላይ ዋለ

በዕውቋ አውስትራሊያዊት ደሪሲ ርሆንዳ ባይርኔ የተፃፈው እና በዓለም ዙሪያ ከፍተኛ ተወዳጅነትን ያተረፈው ‹‹The Power›› በአማርኛ ቋንቋ ተተርጉሞ ለአንባቢያን ቀረበ፡፡

አውስትራሊያዊቷ ደራሲ ከዚህ በፊት ‹‹The Secrete›› በሚል ርዕሥ ለህትመት ያበቃችው መፅሐፍ በመላው ዓለም ተሰራጭቶ 19 ሚሊዮን ኮፒ የተቸበቸበላት ሲሆን፣ በቅርቡ ለአንባቢያን ያበረከተችው እና አሁን ወደ አማርኛ ቋንቋ የተተረጎመው መፅሐፍም ከፍተኛ ሽያጭ ማስመዝገቡ ታውቋል፡፡

‹‹The Power›› የተሰኘውን የዚህችን ዕውቅ ደራሲ መፅሐፍ ወደ አማርኛ ቋንቋ ተርጉመው ያቀረቡት የአዲስ አድማስ ጋዜጣ ም/ዋና አዘጋጅ ኢዮብ ካሳ እና የአዲስ አድማስ ጋዜጣ አምደኛ ሰለሞን ከበደ ናቸው፡፡

መፅሐፉ በገንዘብ ለመበልፀግ፣ የተሟላ ጤንነት ለመቀዳጀት፣ የሰመረ ትዳር ለመመስረት፣ እንከን የለሽ ግንኙነት ለመፍጠርና፣ ሰኬት በስኬት ለመሆን የሚያስፈልገውን ‹‹ተዓምራዊ ኃይል›› ያስተዋውቃል ትላለች፡- ደራሲዋ፡፡

ኢዮብ ካሣ እና ሰለሞን ከበደ ‹‹ተዓምራዊ ኃይል›› በሚል ርዕሥ የተረጎሙት ይህ መፅሐፍ ባለ 160 ገፅ ሲሆን፣ ለአንባቢያን የቀረበው በ20 ብር ዋጋ ነው፡፡

ወላጆቻቸውን ላጡ ተማሪዎች የምሳ ፕሮግራም ተዘጋጀመቅደላ የልማት ማህበር ለፋሲካ ከኪነጥበብ ባለሙያዎች፣

ከኤፍ ኤም ሬዲዮ ጣቢያ አዘጋጆች እና ከአትሌቶች ጋር በመተባበር ወላጆቻቸውን ላጡ 1000 /አንድ ሺህ/ ለሚሆኑ ተማሪዎች የምሳና የመዝናኛ ፕሮግራም በትንሿ ሁለገብ ስታዲየም አዘጋጀ፡፡

ዕለቱን የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎቹ ለሕፃናቱ የሙዚቃ ዝግጅት፣ ድራማ፣ እና የኮሜዲ ሥራዎች በማቅረብ ሕፃናቱ ቀኑን በደስታ እዲያሳልፉ እና በትምህርታቸው ጠንካራ ዜጋ እንዲሆኑ ለማድረግ መታሰቡን መቅደላ የልማት ማህበር ገልጿል፡፡

Page 12: ethioforum.orgethioforum.org/wp-content/uploads/2011/04/Awramba_Times... · 2011-04-11  · ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ 4 ፊ ቸ ር አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 164 ቅዳሜ ሚያዚያ 15 200312 እ ን ግ ዳ

ማስታወቂያ

በዓውዳመት ዋዜማ ላይ በመሆናችን፣ በተዘዋዋሪም ቢሆን ግንኙነት ካለው የገበያ ሁኔታ እንነሳ፡፡ በንግዱ ማሕበረሰብ ላይ ስለወጣው የቁርጥ ዋጋ ተመንና መመሪያውን ተከትሎ በነጋዴውና ሸማቹ መካከል እያጋጠሙ ስላሉ ግብይቶች ምን ታዝበዋል?

በእውነቱ ምስቅልቅል ያሉ ነገሮች ናቸው ያሉት፡፡ ወደረቀቁ የገበያ ፖሊሲ ሥርዓቶች መሄድ ሳያስፈልገን፣ በማዕከላዊነት ታሳቢ ልናደርጋቸው የምንችላቸው የግብይት ዕሳቤዎች አሉ፡፡ ፍላጎትና አቅርቦትን ለማጣጠም፣ ወይም በነጋዴውና በሸማቹ መካከል ሚዛናዊ ግብይት እንዲፈጠር፣ እንደመንግሥት የሚኬድባቸው መንገዶች አሉ፡፡ ቁጥጥር የሚደረግበት አግባብም አለ፡፡ በመንግሥት በኩል የቁጥጥር መመርያ ሲወጣ ይህን የግብይት ሥርዓት የተሻለ ለማድረግና ለማገዝ መሆን አለበት እንጂ አሁን እንደምናየው በሕዝቡም በነጋዴውም ላይ የተዛባ ተፅዕኖ ማሳረፍ አይደለም፡፡ ...

በግልዎ በንግዱ ላይ የተሰማሩ ወገኖችን ያነጋገሩበት አጋጣሚ ይኖር ይሆን?

በተለያየ አጋጣሚ ያገኘኋቸው፣ እንደሁም በዘርፉ

የተሰማሩ አንዳንድ ወዳጆቼ አሉ፡፡ አሁን የተከሰተው ሁኔታ እጅግ ፈታኝ እንደሆነባቸው ነው የሚገልፁት፡፡ የንግድ ፈቃዳቸውን ለመመለስም፣ ለመስራትም ተቸግረዋል፡፡ ሌላው፣ አነስተኛ የንግድ ካፒታል እንዳላቸው የሚታወቁ ወገኖችን ሳይቀር የሰባትና የስምንት ሺህ ብር ካሽ ሬጂስተር [ዕለታዊ የገቢ መመዝገቢያ ማሽን] ካልገዛችሁ የሚባልበት አስቸጋሪ ሁኔታ ነው፡፡

ጠ/ሚኒስትር መለስ በቅርቡ የመንግሥታቸውን የስምንት ወር የሥራ አፈጻም ሪፖርት ለፓርላማው ባቀረቡበት ወቅት ይህ ጉዳይ ተነስቶላቸው፣ ‹‹ይህን የሚያደርጉ ካሉ ይታሰራሉ፡፡ ... ማሕበረሰቡ ይጠቁም፣ ያጋልጥ ... ›› ብለው ነበር፡፡ እንዴት አገኙት?እንደዚህ ዓይነት ነገር እኮ ሁልጊዜ ይባላል፡፡ ... [ሁኔታው ምንም ስሜት እንዳልሰጣቸው በሚያስታውቅ ሁኔታ ለአፍታ በቅሬታ ዝም ካሉ በኋላ፣ ምላሻቸውን የራሳቸውን ጥያቄ በማስከተል አቀረቡ] ... ይህንኑ ሪፖርት ባቀረቡበት ማብራሪያቸው ላይ አስተውለህ እንደሆነ መንግሥታቸው ‹‹አይንና ጆሮ›› እንዳለው ከመግለፅ አልፈው፣ በምስጢር አመፅ ቀሰቀሱ ሲሉ የከሰሷቸውን ሳይቀር ለማስጠንቀቅ ሞክረዋል፡፡ ታዲያ ለቀናት በጠራራ ፀሐይ የተፈፀሙ እርምጃችን

‹‹ዳያስፖራው እዚህ የታፈነውንድምጽ ነው ለዓለም እያሰማ ያለው››

ዶ/ር ያዕቆብ ኃ/ማርያም

ያለፉትን ስድስት ወራት ተከታታይ ፖለቲካዊ ሁነቶች በቅርብ የሚከታተሉ የሥነ-መንግስት አጥኚዎች፣ አገራችንን ጨምሮ አብዛኞቹ የአፍሪካ አገራት ሕዝቦች አዲስ ዓይነት የፖለቲካ አስተሳሰብ ባሕል እያዳበሩ እንደመጡ ይናገራሉ፡፡ ይህ አስተሳሰብ ደግሞ (የየአገራቱ) መሪዎቹ ቀደም ሲል ይከተሉት በነበረው የአገዛዝ ሥልት ሊቀጥሉ እንደማይችሉ ስላረጋገጠላቸው፣ ፈጣንና ተከታታይ የትኩረት ማስቀየሻ ግብረ- ተምኔቶችን በመገናኛ ብዙሃን እንዲያሰራጩ አስገድዷቸዋል የሚል ዕምነት ፈጥሯል፡፡ ወደ አገራችን ስንመለስ፣ በንግዱ ማሕበረሰብ ላይ የተደረገውና የታሰበውን ግብ አልመታም የሚባለው የቁርጥ ዋጋ ተመን፤ የአገር ሽማግሌዎችና የሃይማኖት አባቶች ይዘውት ቢቆዩም፣ መጨረሻው ሳይታወቅ ተድበስብሶ የቀረው የደርግ ከፍተኛ ባለሥልጣናት የይቅርታ ጥያቄ፤ ግልፅነት የጎደለው ነው የሚባለውና የኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት በኤርትራ ላይ አድርገናል ያሉት፣ የሀገሪቱን መንግስት ከሥልጣን እስከማስወገድ የሚዘልቅ፣ የአቋምና የሥትራቴጂ ለውጥ፤ እንዲሁም ፈፅሞ ባልተጠበቀ ሁኔታ የጣና ኃይቅን ሁለት ያህል መጠን ያለው የውሃ ክምችት እንደሚይዝ የተገለፀው የአባይ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብ፣ ወይም ሚሌኒየም ግድብ፤ ወዘተ የዚህ ፈጣንና ተከታታይ የትኩረት ማስቀየሻ ግብረ-ሥልት አካል ሊሆኑ ይችላሉ የሚሉ ኃሳቦች በመንሸራሸር ላይ ይገኛሉ፡ በመላው የክርስትና ዕምነት ተከታዮች ዘንድ በድምቀት ተከብሮ በሚውለው የትንሳኤ በዓል ዋዜማ፣ ዓለም አቀፍ የሕግ ባለሙያ ወደ ሆኑት ዶ/ር ያዕቆብ ኃ/ማርያም ቢሮ ያቀናው ባልደረባችን ውብሸት ታዬ፣ ከላይ በተጠቃቀሱትና በሌሎችም ጉዳዮች ዙሪያ ‹‹እኛ ኢትዮጵያውያን ከልባችን ቆርጠን ከተነሳንና አንድ ከሆንን፣ የምስጢሮች ሁሉ ቁልፍ በእጃችን ማሕል ነው›› ከሚሉት አንጋፋ ባለሙያ ጋር ቀጣዩን ቆይታ አድርጓል፡፡

Page 13: ethioforum.orgethioforum.org/wp-content/uploads/2011/04/Awramba_Times... · 2011-04-11  · ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ 4 ፊ ቸ ር አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 164 ቅዳሜ ሚያዚያ 15 2003

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

13

እ ን ግ ዳ

ማስታወቂያ

እንዴት ፈፅሞ ሳያውቁ ቀሩ?

እንደሚያስታውሱት በቅርቡ የኢህአዴግ መንግሥት በኤርትራ ላይ ሥርዓቱን ከሥልጣን እስከማስወገድ የሚደርስ የአቋምና የሥትራቴጂ ለውጥ ማድረጉን አውጇል፡፡ ይህ አቀራረብ ከዓለም አቀፍ ሕግና ከፖለቲካ አንድምታ አንፃር እንዴት ይታያል?ከሕግ አንፃር ምንም የሚያወላዳ ነገር የለም፡፡ የአፍሪካ ሕብረትም ሆነ የተባበሩት መንግሥታት ቻርተር በሌሎች አገራት የውስጥ ጉዳይ መግባት እንደማይቻል በግልፅ ያስቀመጧቸው አንቀጾች አሉ፡፡ ማንም አገር ራሱን የመከላከል መብት አለው፡፡ በሌላ በኩል ግን የኤርትራን መንግሥት የመቀየር ጉዳይ የኤርትራውያኑ ጉዳይ ብቻ ነው፡፡

ፖለቲካዊ አንድምታውን በተመለከተ ግን በጣም አሳሳቢ ነው የሚሆነው፡፡ ጠ/ሚኒስትሩ ባለፈው ‹‹ግብፅ ብትወረን በጦርነት ልታሸንፈን አትችልም›› የሚል ይዘት ያለው ንግግር አድርገው ነበር፡፡ የሶማሊያው ዘመቻ ጉዳይ አለ፡፡ አሁን ደግሞ የኤርትራን መንግሥት ስለማስወገድ እየተባለ ያለው አለ፡፡ እነዚህ መገለጫዎች ተጠቃለው ሲታዩ አገራችንን ጠብ-አጫሪ ያስመስሏታል፡፡ ...

... ቀደም ሲል እኮ በአፍሪካ ውስጥ የምንታወቀው በአስታራቂነት ባሕላችን ነው፡፡ በንጉሱ [ኃ/ስላሴ] ጊዜ እንደ ደቡብ ሱዳንና ሰሜን ሱዳን በግጭት ውስጥ የቆዩ ሕዝቦችን ያስታረቅንባቸው ተሞክሮዎችንና ሌሎችንም በርካታ ምሳሌዎችን እዚህ መዘርዘር ይቻላል፡፡ጠ/ሚኒስትር መለስ ያንን አቋም ሲገልፁ የኤርትራ ሕዝብ ይደርስበታል ከሚባለው የሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ረገጣ አኳያ ድጋፉን ይሰጠናል ብለው ያሰቡ ይመስልዎታል?

በእውነቱ እንደዚያ አስበው ከሆነ አስገራሚ ነው የሚሆነው፡፡ የትኛውም ሕዝብ ቢሆን እኮ አምባገነን መሪዎቹን በራሱ መንገድ መታገል ይፈልጋል እንጂ በዚህ መንገድ አስወግደውለት የሚፈልጉትን እንዲያስቀምጡበት አይፈልግም፡፡ የኤርትራ ሕዝብ ደግሞ በጣም ብሔርተኛ ነው፡፡ በዚህ መንገድ መገለፁ እንዲያውም የብሔርተኝነት ስሜቱን ያነቃቀዋል እንጂ ጮቤ አያስረግጠውም፡፡ በነገራችን ላይ ያለነውም እኮ በ21ኛው መቶ ክ/ዘመን ላይ መሆኑን ያለመዘንጋት ያስፈልጋል፡፡ ግጭቶች እየተፈቱ ያሉት በድርድርና በውይይት፣ ከዚያም ሲያልፍ ወደ ዓለም አቀፍ ፍ/ቤቶች በመሄድ ነው፡፡ እንዲያውም ሁሉም ወደዚያ እየሄደ በመሆኑ የዓለም አቀፉ ፍ/ቤት ሥራ እየበዛበት ነው፡፡ እነዚህ አማራጮች ሳይሳኩ ሲቀሩ ደግሞ እንደ መንግሥት ጉዳን ወደ ሕዝብ አውርዶ በማወያየት፣ ለፓርላማ በማቅረብ፣ ወይም ከብራ ደህንነት ጋር የሚያያዝ ሲሆን ደግሞ በምስጢራዊ መንገድ የሚሰሩ ሥራዎች ይኖራሉ፡፡

በነገራችን ላይ፣ በቅርቡ በዚህ ጉዳይ ላይ የጀርመን ድምፅ የአማርኛው ዝግጅት ክፍል የተለያዩ ምሁራንን አወያይቶ ነበር፡፡ ምሁራኑን በሶስት ከፍለን እንመልከታቸው ያልን እንደሆነ የሁለቱን አገራት ግጭት ከድንበር ውዝግቡ ጋር ብቻ አያይዘው በማንሳት የሔግ ውሳኔ በአስቸኳይ ተግባራዊ ይሁን የሚሉ (ኤርትራዊው ፕ/ር አስመሮም ለገሰ)፣ የአሰብና የቀይ ባሕር ጉዳይ የኢትዮጵያ የብሔራዊ ጥቅም አጀንዳነት ቁልፍ ጉዳይ ነው ሲሉ የሚከራከሩ (የፖለቲካ ተንታኙ ጃዋር ሲራጅ መሐመድ ይጠቀሳል)፣ እና እንዲሁም መፍትሄው የኢትዮ-ኤርትራ ወዳጅነት መፈጠር ብቻ ነው የሚሉ (የኢትዮ-ኤርትራ ወዳጅነት መድረክ አስተባባሪ የሆኑት ዶ/ር ወርቁ ነጋሽ) ይገኙበታል፡፡ እርስዎ ካለዎት ልምድ በመነሳት ሶስቱን አማራጮች እንዴት ይገመግሟቸዋል? ... የሔግ ውሳኔ ተፈፃሚ ይሁን ከሚሉት ይጀምሩልኝ?

በነገራችን ላይ፣ የሔግ ውሳኔ ተፈፃሚ ሊሆን የሚችልበት ምንም መንገድ የለም፡፡ የአልጀርሱን ስምምነት [የኤርትራ መንግስት] በተደጋጋሚ ጥሶታል፡፡ ውሳኔው ሕጋዊ የሚሆነው በሥምምነቱ ማዕቀፍ ውስጥ ያሉት ጉዳዮች እስከተጠበቁ ድረስ ብቻ ነው፡፡ በእርግጥ በመንግሥት በኩል እስካሁን ‹‹ሥምምነቱ በዚያኛው በኩል ስለተጣሰ አንገዛበትም›› የሚል ደብዳቤ ለተባበሩት መንግስታት አልተፃፈም፡፡ ይሁን እንጂ ነገሮቹ እንደሚታሰቡት ቀላል ስላልሆኑ በዚህ እውነታ ውስጥ ማንም ባድመን አስረክቡ ሊለን አይችልም፤ እና ... ሊተውት ይገባል፡፡ሁለቱ ወገኖች ለዳኝነት ሲስማሙ፣ ‹‹ውሳኔው ምንም ይሁን ምን፣ ይግባኝ የማይጠየቅበት›› እንደሚሆን ተስማምተዋል፡፡ አገራዊ አጀንዳን የሚያህል ነገር ‹‹ይግባኝ የማልጠይቅበት ፍርድ ስጡኝ›› የሚባልበት ‹‹አሳሪ ውል›› ውስጥ ራስን ማስገባት መሰረቱ ምንድነው? ከሕግ አንፃርስ እንዴት ይታያል?

በእውነቱ የአልጀርስ ስምምነት የኢትዮጵያን ጥቅም ሙሉ ለሙሉ ያስረከበ ነው፡፡ ‹‹ይግባኝ የማይጠየቅበት›› የሚለውም ኃላፊነት የጎደለው ድርድር ነው፡፡ መጀመሪያውኑ ወደ አልጀርስ መሄድ አያስፈልግም ነበር፡፡ ወደ ዓለም አቀፉ ፍ/ቤት [International Court of Justice] መሄድ እየተቻለ የተሄደው ግን ወደ ግለሰቦች ነው፡፡ ...ወደ ግለሰቦች ማለት?

ሁለቱም ወገኖች አሸማግሉን ብለው በሥምምነት የመረጧቸውን ዳኞች ነው የሰየሙት፡፡ የዚህ ዓይነቱ አካሄድ ወደፊት በስፋት በሚገለጽ ሁኔታ በአደጋ የተከበበ ነበር፡፡ ለምሳሌ አብዱል አዚዝ የተባለው አንደኛው አደራዳሪ ሻዕቢያን በግልፅ ይደግፍ የነበረ ነው፡፡ በዳኝነቱ ላይ ከነበሩት አንዱ ደግሞ በዚሁ የወገንተኝነት አመለካከቱ ከዳኝነቱ እንዲነሳ ሁሉ ተደርጓል፡፡ ሌላው ደግሞ ብዙዎቹ የአውሮፓ አገራት ኤርትራ በኢትዮጵያ ስትበደል እንደኖረች አድርገው ስለሚያስቡ፣ ከትግሉ ወቅት ጀምሮ እንደሚደግፏት ይታወቃል፡፡በተወካዮቹ አመራረጥ ላይ የሚቀርቡት የተለያዩ ቅሬታዎችስ?

ትክክለኛ ቅሬታዎች ናቸው፡፡ ኢትዮጵያን ወክለው ወደ ድርድሩ ከሄዱት ተወካዮች፣ ከ14ቱ ኢትዮጵያውያን የነበሩት ሶስት ብቻ ሲሆኑ፣ በክርክሩ ዘርፍ ከነበሩት ከሰባቱ ደግሞ አንድም ኢትዮጵያዊ አልነበረም፡፡ ሌሎች ነገሮችን ጠልቅና ዘርዘር አድርገን እንያቸው ብንል ሙሉ ለሙሉ ለምን እንደተጎዳን ማወቅ ይቻላል፡፡በሁለቱ አገራት መካከል ያለው ግጭት በአስተማማኝ ሁኔታ እንዲወገድ ከተፈለገ የኢትዮጵያ ታሪካዊ መብትና የብሔራዊ ጥቅም አጀንዳ የሆኑት አሰብና ቀይ ባሕር ወደጎን ሊደረጉ አይገባም ሲሉ የሚከራከሩት ወገኖችስ?

ሁልጊዜ አንድ ወገን አንድ ነገር ሲጠይቅ የሌላውን ወገን ጥያቄዎችም ታሳቢ ማድረግ አለበት፡፡ ኢትዮጵያን አስመልክቶ የአሰብ ጉዳይ በፍፁም የተዘጋ ፋይል አይደለም፡፡ ህልውናችንን ማስጠበት አለብን፤ አሰብን ማግኘት አለብን፡፡ በመሰረቱ ይህ ኃሳብ ኤርትራ በምትገነጠልበት ወቅት መነሳት ነበረበት፡፡ ሕወሓት በወቅቱ ስለተወው የኢትዮጵያ ሕዝብ ይተወዋል ማለት አይደለም፡፡ አሰብ የኢትዮጵያ ስለመሆኗ በርካታ ማስረጃዎች አሉ፡፡ ቀደም ሲል እንዳነሳነው ዳኝነት ለመጠየቅ የተሄደው ወደ ዓለም አቀፉ ፍ/ቤት ቢሆን ኖሮ፣ ፍ/ቤቱ በእርግጠኝነት የ80 ሚሊዮን ሕዝብ የህልውና ጉዳይ የሆነውን የአሰብን ጉዳይ ያነሳው ነበር፡፡ በተረፈ፣ በሁለቱ ሕዝቦች መካከል የወዳጅነት መድረክ በማዘጋጀት ላይ ያሉት ወገኖች ተግባር ይበል ያሰኛል፡፡ መፃኢ ዕድላችን የተሳሰረ ነው፡፡ በዓለም ላይ እንደ ሁለቱ ዓይነት በጣም የተሳሰረ ሕዝብ የትም አላየሁም፡፡ አንዳችን ብንጎዳ ሁላችንም እንጎዳለን፡፡

በእውነቱ የአልጀርስ ስምምነት የኢትዮጵያን ጥቅም ሙሉ ለሙሉ

ያስረከበ ነው፡፡ ‹‹ይግባኝ የማይጠየቅበት›› የሚለውም ኃላፊነት

የጎደለው ድርድር ነው፡፡ መጀመሪያውኑ ወደ አልጀርስ መሄድ

አያስፈልግም ነበር፡፡ ወደ ዓለም አቀፉ ፍ/ቤት [International Court of

Justice] መሄድ እየተቻለ የተሄደው ግን ወደ ግለሰቦች ነው፡፡ ...

ወደ ገፅ 23 ዞሯል

Page 14: ethioforum.orgethioforum.org/wp-content/uploads/2011/04/Awramba_Times... · 2011-04-11  · ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ 4 ፊ ቸ ር አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 164 ቅዳሜ ሚያዚያ 15 2003

ባለሥልጣን መ/ቤቱ ‹ሁለት አፍ›፤ አሳታሚ ድርጅቱ ‹ከሁለት የለሽ›

14 ተጠየቅ

በሱራፍኤል ግርማ

‹‹ማንኛውም ሰው ያለማንም ጣልቃ ገብነት ሀሳቡን የመግለጽ ነፃነት አለው፡፡ ይህ ነፃነት በአገር ውስጥም ሆነ ከአገር ውጭ ወሰን ሳይደረግበት በቃልም ሆነ በፅሁፍ ወይም በህትመት፣ በሥነ-ጥበብ መልክ ወይም በመረጠው በማንኛውም የማሰራጫ ዘዴ ማንኛውንም ዓይነት መረጃና ሀሳብ የመሰብሰብ የመቀበል እና የማሰራጨት ነፃነቶች አሉት፡፡›› የሚለው የኢፌዴሪ ሕገመንግሥት አንቀጽ 29 ንዑስ አንቀጽ 2 ነው፡፡ ነገር ግን የአገሪቱ የሕጎች ሁሉ የበላይ በሆነው ሕገመንግሥት የተደነገገው ሀሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት በመንግሥት አስፈፃሚ አካላት እና ኃላፊዎች በተደጋጋሚ ሲጣስ እየተስተዋለ ነው፡፡

ሰሞኑን ደግሞ ‹‹ሐምራዊ ጀነራል ቢዝነስ ኃ/የተ/የግ/ማህበር›› የተባለ አሳታሚ ድርጅት ጋዜጣ የማሳተም ፈቃድ ተሰጥቶኝ ሳለ ወደህትመት እዳልሰማራ ታግጃላሁ በማለት የፀረ-ፕሬስ እርምጃ ሰለባ መሆኑን አስታውቋል፡፡

ከመስከረም 1999 ዓ.ም ጀምሮ ‹‹ሐምራዊ›› መፅሔትን ሲያሳትም የቆየው ይህ ድርጅት ተሰማርቶበት ከነበረው መፅሔት የማሳተም ሥራ ጋዜጣ ወደማሳተም ለመሸጋገር ፈልጎ በተገቢው ሕጋዊ መንገድ ከኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን የምዝገባ ሰርተፊኬት ጠይቆ ቢሰጠውም ከቀናት በኋላ ግልፅ ባልሆነ ምክንያት እንደታገደበት ይገልፃል፡፡

ድርጅቱ በ28 የካቲት 2003 ዓ.ም ‹‹...ከአንባቢያን በሰበሰብነው መረጃና አሳታሚ ድርጅቱ ባካሄደው ቅኝትና ጥናት በወር የጊዜ ገደብ ውስጥ ከመውጣት ይልቅ በየሳምንቱ ለሕትመት በሚበቃ ጋዜጣ ከአንባቢያን ጋር መገናኘት የተሻለ መሆኑን አምነንበታል፡፡ ስለዚህም በኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና ማኅበራዊ ጉዳዮች ላይ በማተኮር በየሳምንቱ ለሕትመት የሚበቃ ‹ሐበሻ ሪቪው› ጋዜጣ ለማሰናዳት ተዘጋጅተናል›› ሲል ፈቃድ እንዲሰጠው የብሮድካስት ባለሥልጣንን ጠይቆ ነበር፡፡

ጥያቄው የቀረበለት ባለሥልጣን መ/ቤትም፣ ‹‹...የህትመቱን ዓይነትና ስያሜ ለመቀየር ህትመቱ ጋዜጣ እንዲሆንና ስሙም ‹ሀበሻ ሪቪው› በሚል እንዲቀየርላቸው የካቲት 28 ቀን 2003 ዓ.ም በተፃፈ ደብዳቤ ባመለከቱት መሠረት የህትመቱ ስም ‹ሀበሻ ሪቪው› በሚል መጠሪያ፤ ዓይነቱም ጋዜጣ ሆኖ የተመዘገበላቸው መሆኑን እናስታውቃለን›› ሲል ለንግድ ሚኒስቴር በፃፈው ደብዳቤ አረጋግጧል፡፡

ነገር ግን ባለሥልጣን መ/ቤቱ ለድርጅቱ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ከሰጠ ከስምንት ቀናት በኋላ ጋዜጣው እንዳይታተም ማገዱ ጥያቄ አስነስቷል፡፡

እኛም ስሙ ከፍ ብሎ በተጠቀሰው አሳታሚ ድርጅት የቀረቡትን ቅሬታዎች በመንተራስ ለኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን ጥያቄ አቅርበን ነበር፡፡ በባለሥልጣን መ/ቤቱ የኢንፎርሜሽንና የሕዝብ ግንኙነት የሥራ ሂደት ዳይሬክተር ለሆኑት አቶ ልዑል ገብሩ የሰነዘርነው የመጀመሪያ ጥያቄ፣ ‹‹ለሀበሻ ሪቪው ጋዜጣ እግድ ምክንያት ምንድን ነው?›› የሚል ነበር፡፡ እሳቸውም ለጋዜጣው መታገድ ምክንያቶቹ፣ አሳታሚው ድርጅት ከመፅሔት ማሳተም ወደ ጋዜጣ ማሳተም ሥራ ሲሸጋገር የቀድሞውን የምስክር ወረቀት መልሶና ተሰርዞ እንደ አዲስ ማመልከቻ ባለማስገባቱ እና የአሳታሚ ማኅበሩ አባላት በሌሎች የሚዲያ ተቋማት ላይ ውጤታማ ቁጥጥር እንዳላቸውና እንደሌላቸው ማጣራት ባለመደረጉ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

የአውራምባ ታይምስ የዝግጅት ክፍልም ‹‹የሀበሻ ሪቪው ጋዜጣን ፈቃድ ከመስጠታችሁ በፊት የሐምራዊ መፅሔትን ፈቃድ ለምን አልተቀበላችሁም? የማጣራት ሥራውንስ ፈቃድ ከመስጠታችሁ በፊት ማከናወን አትችሉም ነበር?›› የሚሉ ተያያዥ ጥያቄዎችን ለአቶ ልዑል አቅርቧል፡፡ የባለሥልጣን መ/ቤቱ የኢንፎርሜሽንና የሕዝብ ግንኙነት የሥራ ሂደት ዳይሬክተርም በዚህ ረገድ መ/ቤታቸው ጥፋት መስራቱን አምነዋል፡፡

የዴሞክራሲ ግንባታ አካልነታቸውን በመተማመንና የዜጎች የመናገርና የመፃፍ መብት በሕገመንግሥቱ የተደነገገ መሆኑን በመገንዘብ የተጣለባቸው እገዳ ማጣራት ተደርጎበት ቢበዛ በ24 ሰዓታት ውስጥ ሊነሳ እንደሚችል ገምተው እንደነበር የሚገልፁት የአሳታሚው የሥራ ኃላፊዎች ያሰቡት ሳይሆን ቀርቶ ጉዳያቸው በእንጥልጥል እንዳለ ከአንድ ወር በላይ መሆኑን ይናገራሉ፡፡

በአካል እየተመላለሱም የሚመለከታቸውን የባለሥልጣኑን ኃላፊዎች ለማነጋገር ቢጥሩም ከባለሥልጣን መ/ቤቱ ያገኙት መልስ ፍፁም ምክንያታዊ ያልሆነ፣ በግምት ላይ የተንተራሰና የመስራት ሞራልን በከፍተኛ ደረጃ የሚፈታተን እንደሆነባቸው ይገልፃሉ፡፡

ጋዜጣ እንዳያሳትም የታገደው ድርጀት ሥራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ፍቃዱ ማ/ወርቅ ጉዳዩን አስመልክቶ ለአውራምባ ታይምስ እንደተናገሩት፣ በባለሥልጣን መ/ቤቱ ዋና ኃላፊ አቶ ደስታ ተስፋው ‹‹...በዚህ ሰዓትና ወቅት የፖለቲካ ጋዜጣ ለመስራት ለምን ፈለጋችሁ?›› ተብለው መጠየቃቸውንና ‹‹ጀርባችሁ እነማን እንዳሉ እናውቃለን!›› የሚል በማስረጃ ያልተደገፈ ማስፈራሪያ እንደተሰነዘረባቸው፤ ይህም ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታው አደገኛ መሰናክል መሆኑን በአፅንዖት ይገልፃሉ፡፡

የሐምራዊ ጀነራል ቢዝነስ ኃ/የተ/የግ/ማ የሥራ ኃላፊዎች የባለሥልጣኑ ዋና ኃላፊ ‹‹ሰነዘሩብን›› ያሉትን ማስፈራሪያ ለአቶ ልዑል በማስታወስ ከተጠቀሱት ሁለት ምክንያቶች ውጪ ባለሥልጣን መ/ቤቱ ጋዜጣውን ለማገድ ሌላ ምክንያት ይኖረው እንደሆን ጠይቀናቸው ነበር፡፡ ‹‹አቶ ደስታ ‹አሉ› የተባለው በማስረጃ ያልተደገፈ ነው›› የሚሉት የኢንፎርሜሽንና ሕዝብ ግንኙነት የሥራ ሂደት ዳይሬክተሩ፣ ‹‹ለሀበሻ ሪቪው ፈቃድ ከሰጠን በኋላኮ ለበርካታ የፖለቲካ ጋዜጦች ፈቃድ ሰጥተናል፡፡ እነሱን የምንከለክልበት ምንም ምክንያት የለንም›› ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

አቶ ልዑል ለዝግጅት ክፍላችን የገለፁት እንዳለ ሆኖ፣ የብሮድካስት ባለሥልጣን የሀበሻ ሪቪውን ፈቃድ አስመልክቶ ለንግድ ሚኒስቴር የፃፈው ደብዳቤ መሻሩን የሚገልፅና ለጋዜጣው እግድ የተጠቀሱትን ምክንያቶች የያዘ ደብዳቤ ለአሳታሚ ድርጅቱ በ12 ሚያዚያ 2003 ዓ.ም ፅፏል፡፡ የዚህ ደብዳቤ ግልባጭ ለንግድ ሚኒስቴር መሰጠቱንም የደብዳቤው ግርጌ ይገልፃል፡፡

በመገናኛ ብዙሃንና መረጃ ነፃነት አዋጅ ቁጥር 590/2000 አንቀፅ 7 መሠረት አንድ አሳታሚ በተመሳሳይ ቋንቋ በሚታተም ህትመት በተመሳሳይ ወይም በተደራራቢ ገበያ የሚሰራጭ ባለቤት መሆን እንደማይችል መደንገጉን የሚያስታውሰው ይህ ደብዳቤ፣ ‹‹በድርጅታችሁ ለመ/ቤቱ ሞልታችሁ ያቀረባችሁት ቅፅ የስያሜ ለውጥና የይዘት ለውጥ እንጂ የአዲስ ህትመት ጥያቄ አለመሆኑን አረጋግጠናል›› ይላል፡፡

ምንም እንኳን ደብዳቤው ይህን ቢልም የሐምራዊ ጀነራል ቢዝነስ ኃ/የተ/የግ/ማኅበር ሥራ አስኪያጅ አቶ ፍቃዱ ማ/ወርቅ በዚህ አይስማሙም፡፡ ከአንድ በላይ የህትመት ውጤት ላይ መሰማራት ክልክል መሆኑን ድርጅታቸው በደንብ እንደሚገነዘብ ያስታወሱት አቶ ፍቃዱ ‹‹መጀመሪያ ማመልከቻ ስናስገባ የጠየቅናቸው መፅሔቱ ቆሞ ጋዜጣ መሥራት እንድንጀምር ነበር›› ይላሉ፡፡

የዚህ ደብዳቤ የመጨረሻ ክፍል አግራሞት ከማጫሩ በላይ ወንጀለኛ እንደሚያደርግ አቶ ፍቃዱ ሳይገልፁ አላለፉም፡፡ ‹‹... የቀድሞው ህትመት ያልተቋረጠና የምስክር ወረቀቱም በእጃችሁ የሚገኝ በመሆኑ የቀድሞው ህትመት ተሰርዟል ማለት ስለማይቻል በቀድሞው ህትመት ሥራችሁን መቀጠል ትችላላችሁ›› የሚል መልዕክት በደብዳበቤው መገለፁ ለአቶ ፍቃዱ ግራ አጋቢ ሆኗል፡፡

የሐምራዊ መፅሔት ፈቃድ ተዘርዞ እጃቸው ላይ የሚገኘው የሐበሻ ሪቪው ጋዜጣ ፈቃድ እንደሆነ የሚያስገነዝቡት የማኅበሩ ሥራ አስኪያጅ ‹‹እኛ እየጠየቅናቸው ያለው የሀበሻ ሪቪው እግድ እንዲነሳ እንጂ የሐምራዊ ፈቃድ እንዲመለስልን

አይደለም፤ ያልጠየቅናቸውን ነው እየመለሱ ያሉት፡፡ ደግሞስ በፕሬስ ሕጉ መሠረት ሁለት የህትመት ውጤቶችን ማሳተም እንደማይቻል ተደንግጐ ባለበት ሁኔታ ፈቃዱ የተሰረዘውን ሐምራዊ መፅሔት ‹ስሩ› ማለት እኛን ወደ ወንጀል መገፋፋት አይሆንም?›› ሲሉ ይጠይቃሉ፡፡ የአቶ ፍቃዱ ጥያቄ ባለሥልጣን መ/ቤቱ ሀበሻ ሪቪው ጋዜጣ በጊዜያዊ መልኩ መታገዱን ወደገለፀበት ደብዳቤ ይመራናል፡፡ ጉዳዩን አስመልክቶ አውራምባ ታይምስ ያነጋገራቸው የሕግ ባለሙያ ደብዳቤዎቹን በማጠቀስ የሚከተለውን ማብራሪያ ይሰጣሉ፡፡

‹‹ይህ መጋቢት 6 ቀን 2003 ዓ.ም የተፃፈ ደብዳቤ ‹ጉዳዩ› በማለት የተፃፈበትን ዓላማ እንዲህ ይገልፀዋል፡- “በየጊዜው ለሚወጣ ህትመት የተሰጠ የምዝገባ ሰርተፊኬት ለጊዜው የታገደ መሆኑን ስለመግለፅ”፡፡ በዚህም የሀበሻ ሪቪው ጋዜጣ ህትመት ፈቃድ ከነጭራሹ አለመታገዱን ብቻ ሳይሆን እግዱም ጊዜያዊ መሆኑንም ያስገነዝባል፡፡ ይህ ባለበት ሁኔታ የቀድሞውን [ሐምራዊ] መፅሔት በማሳተም መቀጠል ትችላላችሁ መባሉ ሁለት የህትመት ውጤቶችን የማሳተም ፈቃድ እንደመያዝ ይቆጠራልና የአቶ ፍቃዱን መከራከሪያ ያጠናክረዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ደብዳቤው ለጊዜያዊ እግዱ ምክንያቶችን ሲያብራራ፣ “… ስያሜው ከተቀየረና የቀድሞው ‹ሐምራዊ› ከተሰረዘ በኋላ ማህበሩ በመጋቢት ወር 2003 ዓ.ም በተሰረዘ ስያሜ መፅሔት አሳትሞ ማሰራጨቱ ተረጋግጧል” ማለቱ ሐምራዊ መፅሔትን ማሳተም እንደማይችሉ እያመለከተ ነበር፤ ምክንያቱም ተሰርዟልና፡፡››

ይሁንና መ/ቤቱ ሚያዚያ 12 በፃፈላቸው ደብዳቤ ግን የቀድሞውን ህትመት መቀጠል ትችላላችሁ ማለቱ ባለሥልጣን መ/ቤቱን ‹ሁለት አፍ› ያደርገዋል፤ አሳታሚ ድርጅቱን ደግሞ ‹ከሁለት የለሽ›፡፡

ሀበሻ ሪቪው ለጊዜው እንደታገደ የተገለፀበት ደብዳቤ ሌላ ተጨማሪ ምክንያት አስቀምጧል፡፡ ይኸውም የመገናኛ ብዙሃንና መረጃ ነፃነት አዋጅን በተቃረነ መልኩ ‹‹ማህበሩም [አሳታሚ ድርጅቱም] ሆነ የማህበሩ አባላት በሌሎች የህትመት ሥራዎች ውስጥ ውጤታማ ቁጥጥር [ከ15 በመቶ የባለቤትነት ድርሻ በላይ] ያላቸው ስለመሆኑ›› ለባለሥልጣን መ/ቤቱ ‹መረጃ› እንደደረሰው የሚጠቁም ነበር፡፡ በቀድሞው ህትመት መቀጠል እንደሚችሉ የሚገልፀው የመጨረሻው የባለስልጣን መ/ቤቱ የሚያዚያ 12 ደብዳቤም እንዲሁ፣ ‹‹… ከባለቤትነት ጋር ተያይዞ ለመ/ቤታችን የቀረበውን ጥቆማ በተመለከተ መረጃዎችን እያጣራን ስለምንገኝ ወደፊት የምናሳውቃችሁ መሆኑን እንገልፃን›› ይላል፡፡ እዚህ ላይ ከአንድ ወር በላይ ጊዜ አልፎም ባለሥልጣን መ/ቤቱ ‹መረጃን› ወደ ማስረጃነት አጠናክሮ ውሳኔ ማሳለፍ እንደምን ተሳነው የሚል ጥያቄ ያስነሳል፡፡ በተለይ ደግሞ ይህ መ/ቤት ከተጣለበት ሥልጣን እና ኃላፊነት አንፃር ለተመለከተው ሊያስገርም ይችላል፡፡

ከዚህ ጋር በተያያዘም ያነጋገርናቸው የሕግ ባለሙያ፣ ‹‹አዲሱ የፕሬስ አዋጅ ሥራ ላይ ከዋለ በኋላ የቀድሞውን የማስታወቂያ ሚኒስቴር ኃላፊነት የተረከበው መ/ቤት አዋጁን ያስፈፅም ዘንድ በሥራ ላይ የሚገኙትን የህትመት ውጤቶች እንዲሁም አዲስ የሚመሰረቱትን መመዝገብ እና ፈቃድ መስጠት ነበረበት›› ይላሉ፡፡ አያይዘውም፣ ‹‹ይህንንም ሲያደርግ የመመዝገቢያ ቅፅ አዘጋጅቶ የነበረ ሲሆን የሁሉም የህትመት ውጤቶች ባለቤቶች ማንነታቸውን እና በየካምፓኒያቸው ላይ ያላቸውን የባለቤትነት ድርሻ መጠን ጠይቆና አስሞልቶ ተረክቧል›› በማለት ይገልፃሉ፡፡ ስለዚህም ማን በየትኛው አሳታሚ ድርጅት ውስጥ ምን ያህል የባለቤትነት ድርሻ አለው የሚለውን ለማወቅ ከመረጃም በላይ አረጋጋጭ ማስረጃ በእጁ ይገኛል፡፡ ወይም በእጁ ይገኛል ተብሎ ይገመታል፤ እዚያ ላይም ስህተት ተሰርቶ ካልሆነ በቀር፡፡ እናም ይህንን የባለቤትነት ጉዳይ ለማጣራት ስንት ቀን ይፈጃል? ጉዳዩ ከተጀመረ ከ45 ቀናት በላይ አልፎታል፡፡

አውራምባ ታይምስ ያነጋገራቸው የሕግ ባለሙያ ጉዳዩ ወሰብሰብ እንዳለባቸው ይጠቁማሉ፡፡ ‹‹ነገሩ የተወሳሰበ ነው፡፡ ባለሥልጣን መ/ቤቱ ከመነሻው የተጠየኩት የስያሜ እና የይዘት ለውጥ እንጂ የአዲስ ህትመት ጥያቄ አይደለም ይላል፡፡ እዚህ ላይ ብቻ ብንቆም ዋናው መፍትሔ የማመልከቻ ጥያቄህን አስተካክለህ ና ማለት ይሆን ነበር፡፡ በሌላ በኩል ግን የአዲስ ህትመት ጥያቄ እንደቀረበለት አድርጎ የባለቤትነት ቁጥጥር መጠንን እያጣራሁኝ ነው ይላል፡፡ ይኼ ማለት ደግሞ ወይ መጀመሪያ የቀረበለት ጥያቄ የአዲስ ህትመት ጥያቄ ነው፣ አልያም ጥያቄውን በራሱ አስተካክሎ ጉዳዩን እየተመለከተው ነው፡፡ በዚህ የምንረጋ ከሆነ ደግሞ፤ ጉዳዩ የሚያጣላም፣ ጊዜ የሚፈጅም አይመስልም፡፡››

ጉዳዩ በእንጥልጥል ቀርቶ ድርጅታቸው ከሁለት ያጣ በመሆን ያለምንም ሥራና ለቀጠራቸው ሠራተኞች ደመወዝ እየከፈለ ከ45 ቀናት በላይ መቁጠሩ እንዳሳሰባቸው የሚገልፁት የሐምራዊ ጀነራል ቢዝነስ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ሥራ አስኪያጅ፣ አቶ ፍቃዱ ማ/ወርቅ ሀሳባቸውን ያጠቃለሉት፣ ከዚህ በኋላ ብሮድካስት ባለስልጣን አሟሉ ያላቸውን ሁሉ በማሟላት መፍትሔ ለማግኘት ጥረታቸውን እንደሚቀጥሉ በመግለፅ ነው፡፡

ባለሥልጣን መ/ቤቱ ከመነሻው

የተጠየኩት የስያሜ እና የይዘት

ለውጥ እንጂ የአዲስ ህትመት

ጥያቄ አይደለም ይላል፡፡ እዚህ

ላይ ብቻ ብንቆም ዋናው መፍትሔ

የማመልከቻ ጥያቄህን አስተካክለህ

ና ማለት ይሆን ነበር፡፡ በሌላ

በኩል ግን የአዲስ ህትመት ጥያቄ

እንደቀረበለት አድርጎ የባለቤትነት

ቁጥጥር መጠንን እያጣራሁኝ ነው

ይላል፡፡ ይኼ ማለት ደግሞ ወይ

መጀመሪያ የቀረበለት ጥያቄ የአዲስ

ህትመት ጥያቄ ነው፣ አልያም

ጥያቄውን በራሱ አስተካክሎ ጉዳዩን

እየተመለከተው ነው፡፡

Page 15: ethioforum.orgethioforum.org/wp-content/uploads/2011/04/Awramba_Times... · 2011-04-11  · ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ 4 ፊ ቸ ር አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 164 ቅዳሜ ሚያዚያ 15 2003

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

ባለሥልጣን መ/ቤቱ ‹ሁለት አፍ›፤ አሳታሚ ድርጅቱ ‹ከሁለት የለሽ›

15

ሕብር ስኳር አክሲዮን ማህበር Hiber Sugar Share Company

ሕብር ስኳር አ.ማ ከ5,280 በላይ የሚሆኑ አባላቱን በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ጽ/ቤት ማስፈረም ጀምሯል፡፡ ቀዳሚዎቹ ፈራሚዎች የቦርድ አባላትና 32ቱ ዋና መስራቾች ሆነዋል፡፡

ስለሆነም እስከ ጥር 25/2003 ዓ.ም አክሲዮን የገዛችሁ የተከበራችሁ የሕብር ስኳር አ.ማ ቀሪ መሥራች አባላትና ባለአክሲዮኖች በሚከተለው ሠንጠረዥ መሠረት በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ቢሮ ቀርባችሁ እስከ ሚያዚያ 30 ቀን 2003

ቀን ድረስ እንድትፈርሙ የአክብሮት ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡

ወደ ሰነዶች ምዝገባና ጽ/ቤት ለፊርማ በምትመጡበት ጊዜ

የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ ወይም መንጃ ፍቃድ ወይንም ፓስፖርት 1. አክሲዮን የገዛችሁበትን የምዝገባ ቅጽ2. ገንዘብ የከፈላችሁበትን የባንክ ደረሰኝ3. ሕጋዊ ውክልና ማስረጃ4. ለሕፃናት የገዛችሁ (የልደት ሰርተፍኬት)5. በጋራ የገዙ ባለትዳሮች የጋብቻ ሰርተፍኬት (አንዳቸው እንዲፈርሙ)6. በማህበር የገዛችሁ (የተወከላችሁበትን ቃለ-ጉባዔ፣ መተዳደሪያና መመስረቻ ጽሁፎች ወይም የምዝገባ ሰርተፍኬት)

ይዛችሁ እንድትቀርቡ እያሳሰብን ሰነድ ላይ ፊርማችሁን ያላኖራችሁ አባላት የሕብር ስኳርን የአክሲዮን ባለቤትነት ሰርተፍኬት ማግኘት የማትችሉ መሆናችሁን ከወዲሁ እናስታውቃለን፡፡

ለስራ ቅልጥፍና ሲባል የምዝገባ ተራ ቁጥራችሁን በስልክም ሆነ ዋናው መ/ቤት በመምጣት ለማወቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ የሕብር ስኳር አክሲዮን ሽያጭ በሰነዶች ማረጋገጫ እና ምዛገባ ፅ/ቤት ፊርማው እስኪጠናቀቅ ድረስ ስለሚቀጥል አክሲዮናችሁን እንድታሳድጉና ሌሎች ፍላጎት ያላችሁ ሁሉ አክሲዮን በመግዛት የመጨረሻው ዕድል ተጠቃሚ እንድትሆኑ ጥሪ እናቀርባለን፡፡

የአንድ አክስዮን ዋጋ • = 1000ዝቅተኛው የአክሲዮን መጠን 1ዐ አክሲዮኖች • = 10,000የአገልግሎት ክፍያ 7• %

አክስዮን መግዛት የምትፈልጉ ሁሉ በኢትዮጵያ ፖስታ ድርጅት መላው ቅርንጫፎች እና በዋናው መስሪያ ቤት እንዲሁም በሽያጭ ወኪሎች አማካይነት መጠቀም የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

አድራሻ፡- ሕብር ስኳር አ.ማ ሜክሲኮ ከዲ’አፍሪክ ሆቴል ፊት ለፊት ታደሰ ተፈራ ሕንፃ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁ. 105ስልክ ቢሮ 0118501357/58 E-mail - [email protected] web - www.hibirsugarethiopia.com

ስማችሁ የሚጀምርበት ፊደልና ተራ ቁ. የመፈረሚያ ቦታ

(A)የ አ ዝርያ(ከተራ ቁ. 1-913)

ዋናው መስሪያ ቤትሜክሲኮ አደባባይ አጠገብ ጨለለቅ አልሣም ታወር 2ኛ እና 3ኛ ፎቅ

(B, C, D, E)በ፣ ቸ፣ ጨ፣ ደ፣ ኢ፣ ኤ፣ እ ዝርያ(ከተራ ቁ. 914-1789)

ቅርንጫፍ 4 ጽ/ቤትአምስት ኪሎ አ.አ.ዩ ቴክኖሎጂ ፋኩልቲ ፊት ለፊት

(F, G, H, I, J, K) ፈ፣ ገ፣ ሀ፣ ሐ፣ኀ፣ ኸ፣ ጀ፣ከ፣ቀ ዝርያ(ከተራ ቁ. 1790-2731)

ቅርንጫፍ 1 ጽ/ቤትደብረ ዘይት መንገድ ተሻለ ገራዥ አጎና ሲኒማ ቤት አጠገብ ባለኬር ሕንፃ 1ኛ ፎቅ

(L, M, N, O, P, Q, R) ለ፣ መ፣ ነ፣ ኦ፣ ጰ፣ ረ ዝርያ(ከተራ ቁ. 2732-3613)

ቅርንጫፍ 3 ጽ/ቤት መገናኛ መንገድ ትራንስፖርት ሕንፃ ጀርባ ራሒም ሕንፃ 1ኛ ፎቅ

(S, T) ሰ፣ ሠ፣ ሸ፣ ተ፣ ጠ፣ ፀ፣ ጸ ዝርያ(ከተራ ቁ. 3614-4656)

ቅርንጫፍ 5 ጽ/ቤትሰሜን ማዘጋጃ ሸገር መናፈሻ አካባቢ ብርሃን ሕንፃ 1ኛ ፎቅ

(U, V, W, Y, Z)ኡ፣ ቪ፣ ወ፣ የ፣ ዘ፣ ዝርያ (ከተራ ቁ. 4657-5280)

ቅርንጫፍ 2 ጽ/ቤትመርካቶ ክፈለ ሀገር አውቶቢስ ተራን አለፍ ብሎ ሸዋ ፀጋ ሕንፃ 2ኛ ፎቅ

መልካም የፋሲካ በዓል ይሁንላችሁ!!!

ማ ስ ታ ወ ቂ ያ

Page 16: ethioforum.orgethioforum.org/wp-content/uploads/2011/04/Awramba_Times... · 2011-04-11  · ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ 4 ፊ ቸ ር አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 164 ቅዳሜ ሚያዚያ 15 200316

በውብሸት ታዬ

…ጎልማሳው በትህትና ከቀረበው በኋላ ‹‹መምሕር ሆይ›› በማለት ሰላምታ አቀረበለት፡፡ ትህትናውን የሚመለከት ማንኛውም ሰው ይህ ጎልማሳ በታሪክ ውስጥ እጅግ ከባዱን የክህደት ተግባር እየፈጸመ ነው ለማለት አይደፍርም፡፡ ሰላምታው የቀረበለት መምሕር ግን ‹‹ይሁዳ ሆይ በመሳም የሰውን ልጅ አሳልፈህ ትሰጣለህን?›› የሚል ጥያቄ በማቅረብ እየሆነ ስላለው ነገር ተከታዮቹ እንዲያውቁ አደረገ፡፡ ስፍር ቁጥር የሌላቸው ተከታዮችና እስከዚያች ቅጽበት ድረስ ከጎኑ ያልተለዩ ደርዘን ያህል ደቀመዛሙርት ነበሩት፡፡

እንዲያውም ጴጥሮስ የተባለው ደቀ መዝሙሩ ሁሉ ቢሰናከሉ እኔ ግን ሕይወቴን እስከመስጠት ቢሆን እንኳ አልለይህም ሲል የትምክህት ንግግር አድርጎ ነበር፡፡ በዚያች የመጨረሻ ፈታኝ ወቅት የሆነው ግን ከአእምሮ የማይፋቅ ክስተት ነው፡፡ ይህ የእውራንን ዓይን ያበራ፣ አንካሶችን ያዘለለ ሌላ ቀርቶ ሙታንን ያስነሳ ታላቅ መምሕር በመጨረሻ ብቻውን ቀረ፡፡

ወንጌላዊውና ደቀመዝሙሩ የነበረው ማርቆስ በቅዱስ መጽሐፍ ስለሁኔታው ሲገልጽ ‹‹ሁሉም ትተውት ሸሹ›› ብሏል፡፡/ማር፤13፤ 50/፡፡ በመላው የክርስትና ዕምነት ተከታዮች ዘንድ በታላቅ ድምቀት ተከብሮ በሚውለው የትንሳኤ በዓል ዋዜማ ላይ ሆነን እያወሳን ያለነው ስለክርስቶስ ኢየሱስ መሆኑ አይጠረጠርም፡፡

አሁን የሚነሳው ጥያቄ ከላይ ለመመልከት እንደሞከርነው ብዙዎችን በበረከቱ የዳሰሰ መሲህ ለምን በዚህ መንገድ የክህደት ድርጊት ሊፈጸምበት ቻለ? አይሁዳውያን በተስፋ ሲጠበቁት የነበረውና ነቢዩ ሚክያስ ‹‹አንቺ ቤተልሔም ኤፍራታ ሆይ፤ አንቺ በይሁዳ አእላፋት መካከል ትሆኚ ዘንድ ታናሽ ነሽ፡፡ ከአንቺ ግን አወጣጡ ከቀድሞ ጀምሮ ከዘላለም የሆነ በእስራኤልም ላይ ገዥ የሚሆን ይወጣልኛል፡፡…››/ሚክ፤- 5፤2-5/ የተባለለትን መሲህ የጠበቁበት መንገድ ምን ቢሆን ነው? የሕማማቱና ቤዛዊ መስዋዕትነቱ ዋጋ ለአማኞቹ ምን ትርጉም ይኖረዋል? ወዘተ…የሚሉት ናቸው፡፡

ለምን መጣ? የመጽሐፍ ቅዱስ የመጀመርያው

ክፍል የሆነው ኦሪት ዘፍጥረት[ዘፍረት] በምዕራፍ ሶስት ላይ የመጀመርያዎቹ ሰብአዊ ፍጡራን የነበሩት አዳምና ሔዋን በሚኖሩባት የኤደን ገነት ውስጥ በፈጣሪ ተሰጥቷቸው የነበረውን ሕግ እንደጣሱ ይገልጻል፡፡ ሕጉ የራሱ የሆነ መንፈሳዊ ዕሳቤ ቢኖረውም በገነት መካከል ያለውን የዛፍ ፍሬ መብላት ሞትን እንደሚያስከትል ከፈጣሪ የተሰጠ ሕግ ነበር፡፡ አዳምና ሔዋን ይህን ሕግ ጥሰው በመገኘታቸው ከኤደን ገነት የተባረሩ ሲሆን ለልጆቻቸውና ለልጅ ልጆቻቸው ኃጢያትን አወረሱ፡፡ ይህም በመላው የሰው ዘር ላይ መንፈሳዊ ሞትን ያሰፈነ ነበር፡፡

ስለዚህ ፈጣሪ መላውን የሰው ዘር ለመታደግ ልዩ ቤዛ አዘጋጀ፡፡ ወንጌላዊው ዮሐንስ ‹‹በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና››/ዮሐ፤- 3፤16/ ሲል የክርስቶስን መምጣት ዓላማ ገልጾታል፡፡

ፋሲካ እና ትንሳኤእነዚህን ሁለት ቃላት አንድና ተመሳሳይ

አድርጎ መጠቀም የተለመደ ነው፡፡ይሁንና የፋሲካ በዓል የተመሰረተው ከክርስቶስ መወለድ ቀደም ብሎ /እስራኤላውያን በግብጽ ባርነት ላይ በነበሩበት ወቅት/ እንደሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ይገልጻል፡፡ ‹‹ፋሲካ›› የሚለው የእብራይስጥ ቃል ‹‹ማለፍ›› የሚል አቻ ትርጉም ያለው ሲሆን በሙሴ አማካይነት ለግብጹ ፈርኦን ይተላለፉ የነበሩ የ‹‹ሕዝቤን ልቀቅ›› ትዕዛዞች ባለመፈጸማቸው በግብጻያን ላይ ከደረሱት ተአምራዊ ቅጣቶች ጋር የተያያዘ ነው፡፡

‹‹ሕዝቤን ልቀቅ›› ለሚለው መልዕክት ፈርኦን ‹‹እምቢ ከቶ እ/ር ማነው?›› በማለቱ በግብጽ ምድር የነበሩ ግብጻውያንና እነርሱን መስለው የሚኖሩ ዜጎች የበኩር ልጆች (እንስሳትም ጭምር) በሙሉ ህይወታቸውን ያጡበት መንፈሳዊ ቅጣት የተፈፀመበት ሁነት ነው፡፡

ሙሴ በነገራቸው መሰረት የእስራኤል ልጆች ከቅጣቱ ለማምለጥ የዓመቱ የመጀርያ ወር አጋማሽ ላይ ጠቦት በማረድ ደሙን በበራቸው መቃን ላይ ቀቡት፡፡ ስጋውንም ጠብሰው በሉ፡፡ በግብጽ ምድር ያሉ በኩሮችን ለመግደል የሚንቀሳቀሰው መልአክም የደሙን ምልክት ከመቃኑ ላይ ሲመለከት እያለፈ ይሄዳል፡፡ ይህን ያላደረጉ ቤተሰቦች የበኩር ልጆች በሙሉ አለቁ፡፡

ክርስቶስም ከልጅነት ዕድሜው ጀምሮ የፋካን በዓል ከስጋዊ ቤተሰቦቹ ጋር በመሆን በኢየሩሳሌም ያከብር ነበር፡፡/ሉቃ፤2፤41,42/ በዚያ የመጨረሻ የፋሲካ ተአምር ከግብጽ ባርነት ነጻ የወጡት እስራኤላውያን ግን ከዚ ቀጥሎ ያጋጠሟቸው ነገሮች አልጋ በአልጋ እንዳልሆኑ የሚጠቁም ነበር፡፡ 40 ቀን ብቻ ይፈጅ የነበረው የእስራኤላያኑ ጉዞ 40 ዓመታት የፈጀ ሲሆን ከዚያ በኋላም ቢሆን የተስፋይቱ ምድር በነጻነት የሚኖሩባት አልሆነችም፡፡ የተለያዩ መንግስታት እየቀጠቀጡ ይገዟቸው ስለነበር ከዚ የግፍ አገዛዛ ነጻ ያወጣናል በማለት መሲሁን ይባበቁ ጀመር፡፡ የመሲሁን ነፃ አውጭነት በጉጉት ካስጠበቁት አገዛዞች የተወሰኑትን እንመልከት፡፡

ከዓለማዊ ጭቆና ነፃ አውጪ?ከግብጽ ባርነት ከወጡ በኋላ ባሳዩት

ውለታ ቢስነት የ40 ቀን መንገድ 40 ዓመታት የፈጀባቸው ሲሆን ያም ቢሆን በከባድ መከራች የተሞላ ነበር፡፡ እስራኤላያኑን ይመራቸው የነበረው ሙሴ ወደ ተስፋይቱ ምድር ያልገባ

ሲሆን ተራፊዎቹ ከነአን ገብተው ገና መንግስታቸውን በማቋቋም ላይ እንዳሉ በአሶራውያን አገዛዝ ስር ወደቁ፡፡ የአሶራውያን ጨካነ የተሞላበት ቅኝ ግዛት የጀመረው ቅድመ ልደት በ800 ዓ.ዓ ሲሆን ለ200 ዓመታት በባርነት ገዟቸው፡፡

ከአሶራውያን ላይ የአገዛዝ ቀንበሩን የተቀበሏው በ600 ዓ.ዓ የተጠናከረ ወታደራዊ ኃይል የነበራቸው ባቢሎናውያን ናቸው፡፡ የባቢሎናውያኑ አገዛዛ ከአምሳ ዓመት በኋላ በፐርሺያውያን ተተካካ፡፡ የፐርሺያውን ንጉስ ቂርቆስ ቀደም ሲል በባቢሎናውያን አዋጅ መሰረት ከአከባቢያቸው እንዲወጡ የተደረጉ አይሁዳውያን መመለስ እንዲችሉ የፈቀደ ቢሆንም የነጻታቸው ዘመን ግን እውን ሊሆንላቸው አልቻለም፡፡ ታሪክ በስፋት የሚተርክለት ታላቁ እስክንድር ዓለምን እያስገበረ መጥቶ እነሱንም ጠቀለላቸው፡፡

የዚህ ዓይነቶቹ ማለቂያ የለሽ ባርነቶች ቅዱሳን መጻፍት በአንጸባራ ሁኔታ የገለጹትን መሲህ እንዲብቁ አድርጓቸዋል፡፡ ቀደም ሲል የተመለከትነውን የነቢዩ ሚክያስን የትንቢት ቃላት የተረጎሟቸው በዚህ መንገድ ነበር፡፡ ‹‹አንቺ ቤተልሔም ኤፍራታ ሆይ! አንቺ በይሁዳ አእላፋት

መካከል ትሆኚ ዘንድ ታናሽ ነሽ፡፡ ከአንቺ ግን አወጣጡ ከቀድሞ ጀምሮ ከዘላለም የሆነ በእስራኤልም ላይ ገዥ የሚሆን ይወጣልኛል፡፡... መንጋውን ይጠብቃል፡፡... እስከ ዓለም ዳርቻ ድረስ ታላቅ ይሆናልና፡፡›› (ሚክ 5፡2-5)

ወጣቱ የጦር ጄኔራልና ንጉስ ታላቁ አስክንድር በግዛቱ ስር የሚያደርጋቸው ‹‹ተሸናፊዎች›› እስከታዘዙ፣ ግብር እስከከፈሉና እስካላመጹበት ድረስ እንክብካቤ አስተዳደራዊ አያያዙ የተሻለ የሚባል አይነት ነበርር፡፡ ከስምንት ዓመት ግዛቱ በኋ ግን በ32 ዓመት ዕድሜው ሕይወቱ ሲልያፍ ያለእረፍት የገሰገሰበት ግዛቱ በአራቱ የጦር ጄኔራሎቹ የመከፋፈል ዕጣ ደረሰበት፡፡ ይህ ደግሞ በማለቂያ የለሽ ጭቆና ለሚማቅቁት ወገኖች የባሰ አስከፊ ነበር፡፡ እንደገና ለ400 ዓመታት በአስከፊ ጭቆና ስር ወደቁ፡፡

መሲሁን ከዓለማዊ ጭቆና ነፃ የሚያወጣ አድርጎ ለማሰብ ሰበብ የሆኑ በደሎቻቸው ተቆጥረው አያልቁም፡፡ ክርስቶስ በተወለደበት ወቅት እንኳ ሮማውያን ከአባት ወደልጅ እየተወራረሰ በመጣ ሥርወ መንግስት እየገዟው ነበር፡፡

‹‹ስጋ የለበሰ ሁሉ የእግዚአብሔርን

ማዳን ይይ››እነዚህ የትንቢት ቃላት በነቢዩ

ኢሳያስ የጌታን መንገድ ጠራጊ ለተሰኘው መጥምቁ ዮሐንስ የተነገሩ ነበሩ፡፡ ዮሐንስ የንስሐ ጥምቀጥ እየሰጠ በሚያስተምርበት ወቅት ክርስቶስ እንደሆነ አድርገው ያሰቡት ወገኖች ስላጋሙት ከእሱ በኋላ የሚመጣውን/ኢየሱስ ክርስቶስን/ የጫማን ጠፍር መፍታት እንኳ የማይገባኝ በማለት ስለመሲሁ ታላቅነት እንዲገነዘቡ አድርጓቸዋል፡፡ የእግዚአብሔር ማዳን በክርስቶስ መስዋዕትነት እውን ይሆን ዘንድ የሚያመለክት ነበር፡፡

የትንሳኤ በዓል በተለያየ የክርስትና ዕምነት/ተቋማት/ ተከታዮች ዘንድ በተለያ ስርዓት ይከበራል፡፡ ‹‹በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና››/ዮሐ፤- 3፤16/ የሚሉት የወንጌላዊው ዮሐንስ ቃላት ግን ሁሉንም አንድ ያደርጓቸዋል፡፡ በነገራችን ላይ በክርስቶስ ስቅለት ወቅት የተፈጥሮ ስርዓት በእጅጉ በመዛባት ለማንነቱ ምስክርነት ሰጥታለች፡፡ ከዋክብት ረግፈዋል፣ ፀሐይ ብርሃኗ ነፍጋለች፣ ጨረቃ ደም ለብሳለች፣ መቃብራት ተከፍተዋል…፡፡

ሕያውን ስለምን ከሙታን መካከል?ዕሁድ ማለዳ ላይ የጌታ ስጋዊ አካል

ወደነበረበት የመቃብር ስፍራ ሔደው የነበሩት ወገኖች የመቃብሩ መዝጊያ የነበረው ድንጋይ ተንከባሎ ሲያገኙት በእጅጉ ተረበሹ፡፡ በዚህ ወቅት መላዕክት ‹‹ሕያውን ከሙታን መካከል ስለምን ትፈልጉታላችሁ? ተነስቶአል እንጂ ከዚህ የለም፡፡››/ሉቃ፤24፤5/ የሚለውን የምስራች አበሰሯው፡፡ ዓለም ሁሉ እንዲድን እንጂ እንዳይጠፋ!

እንኳን አደረሰዎ!!

የሚያምኑ ሁሉ እንዳይጠፉ…

‹‹ሕዝቤን ልቀቅ›› ለሚለው መልዕክት ፈርኦን ‹‹እምቢ ከቶ እ/ር ማነው?›› በማለቱ በግብጽ ምድር የነበሩ ግብጻውያንና እነርሱን መስለው

የሚኖሩ ዜጎች የበኩር ልጆች (እንስሳትም ጭምር) በሙሉ ህይወታቸውን ያጡበት መንፈሳዊ ቅጣት

የተፈፀመበት ሁነት ነው፡፡

አረቦችና ሌሎች ሕዝቦች እኮ ሁኔታችንንም ‹ሀበሾች› ነው የሚሉን፡፡ ...

... የኢትዮ-ኤርትራ ሕዝብ የተለያየው ከአፍንጫቸው በላይ በማያስቡ መሪዎች ነው፡፡ ኤርትራውያን በ1990ው ጦርነት ከዚህ ሲሄዱ እምባ ተራጭተን ነው የሸኘናቸው፡፡ ሻዕቢያ ኤርትራን እንደ ተቆጣጠረ በኢትዮጵያውያን ላይ ያደረሰውን ግፍ የኤርትራ ሕዝብ ተቃውሞታል፡፡ በ1983 ዓ.ም ሲገነጠሉ የፌዴሬሽን ወይም የኮንፌዴሬሽን አማራጭ አልቀረበላቸውም፡፡ የሁለቱም ወገን መሪዎች ኢትዮጵያን ቅኝ የገዛች ሲሏት ስለከረሙ የተፈለገው መገንጠል ብቻ ነበር፡፡ ወደፊት በሁለቱም አገራት ውስጥ ዴሞክራሲያዊ መንግሥት ቢፈጠር፣ በእርግጠኝነት በምስራቅ አፍሪካም ሆነ በመላው አፍሪካ ትልቅ አገር መፍጠር እንችላለን፡፡ከዚሁ ጋር በተያያዘ፣ አንዳንድ የኢትዮጵያን መንግሥት የሚቃወሙ ድርጅቶች ወደ ኤርትራ መሄዳቸውን አምርረው የሚቃወሙ ወገኖች አሉ፡፡ ከእነዚህ ወገኖች አንዳንዶቹ በአገር ውስጥ ያሉ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች ናቸው፡፡ ምንድነው አስተያየትዎ?

መቼም እያንዳንዱን ነገር ከተለያየ አቅጣጫ መመልከቱ ተገቢ ይሆናል፡፡ የኢትዮጵያ ተቃዋሚዎች ለምን በአገር ውስጥ ሆነው አይታገሉም ስንል የፖለቲካ ሥነ-ምህዳሩ ምን ያህል እየጠበበ

እንደሄደ እንረዳለን፡፡ በተቃዋሚ ፖለቲካ ድርጅቶችና አባሎቻቸው ላይ እየደረሰ ስላለው እንግልት በየጊዜው እየገለጹ ነው፡፡ ሕዝቡስ ዴሞክራሲያዊ መብቶቹ ተከብሮለታል ወይ? የመሰብሰብ፣ የመደራጀትና ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ መብቶች በተግባር እየተተረጎሙ ናቸው ወይ? ሁሉን አሳታፊ የፖለቲካ መድረክ እንዲፈጠር ቢፈቀድ ኖሮ እውን ተቃዋሚ ድርጅቶች ይህን አማራጭ ይከተሉ ነበር ወይ? የሚለውን መፈተሽና እውነተኛው ነጥብ ላይ መድረስ ያስፈልጋል፡፡ መንግሥት የኤርትራን መንግሥት የማስወገድ ቁርጠኝነቱን በአገር ውስጥ ዴሞክራሲን ለማስፈን ቢጠቀምበት ኖሮ ይህ ጥያቄ ራሱ ባልተነሳ ነበር ብዬ አምናለሁ፡፡ሌላው የሕዝቡን የትኩረት አቅጣጫ ለማስቀየር ሲባል መክኖ የቀረ፣ ወይም በእንጥልጥል የተተወ ነው የሚባለው በሃይማኖት መሪዎች ተይዞ የነበረው የደርግ ከፍተኛ ባለሥልጣናት የይቅርታ መጠይቅ ሂደት ነው፡፡ የዚህ ዓይነቶቹ ትልልቅ አጀንዳዎች ተጨባጭ መደምደሚያ ላይ ከመድረሳቸው በፊት ብዙ ተነግሮላቸው ተድበስብሰው ሲቀሩ የሚፈጥረውን ተፅዕኖ እንዴት ያዩታል?

እንዳልከው ጉዳዩን ይዘውት የነበሩት የሃይማኖት መሪዎችና ዕውቅ ግለሰቦች ነበሩ፡፡ ተሳካም አልተሳካም ለሕዝቡ ስለደረሱበት የመጨረሻ ውጤት

አልገለፁም፡፡ በአገራችን የሽምግልና ታሪክ ደግሞ የአገር ሽማግሌ የማይሸመግለው ነገር የለም፡፡ በዚህ መንገድ መቋጨቱ ግን እንኳን ከሃይማኖት መሪዎች፣ ከአንድ ግለሰብ እንኳ አይጠበቅም፡፡ ኢሕአዴግ ያልደገፈው ነገር ከመሬት የማይነሳ ስለሆነ ተብሎ ከሆነም አሳፋሪና የሽግሌዎቹን ክብር የሚነካ ነው፡፡ በአጠቃላይ ግን እንደ ሕዝብ ብሔራዊ ዕርቅ ነው የሚያስፈለገን፡፡ አንድ ቀንም በተግባር ይተረጎማል፡፡ከሳምንት በፊት የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚ/ዴኤታንና ሌሎች ሚኒስትሮችን እንዲሁም የክልል ከፍተኛ ባለስልጣናትን ያካተተ ከ50 በላይ አባላት ያሉት የልዑካን ቡድን በአሜሪካ የተለያዩ ከተሞች /ግዛቶች/ በመንቀሳቀስ በዚያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያንን ለማነጋገር ያደረገው ሙከራ ተቃውሞ አስተናግዶ እንደነበር ይታወሳል፡፡ በውጭ አገር ለረዥም ጊዜ ከመቆየትዎ አንፃር መንስኤው ምንድን ነው ይላሉ? ስለ አምስት ዓመት የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ስለሚባለውና በተጨባጭ እየሆነ ስላለው በማነጻጸር ቢመልሱልኝ?

ስለትራንስፎርሜሽኑ በጣም ብዙ እየተወራ ነው፡፡ በተጨባጭ እየሆነ ያለው ግን ሌላ ነው፡፡ ቅድም እንደጠቀስኩልህ ነጋዴው፣ ሰራተኛው፣ ተማሪው በከፍተኛ ችግር ውስጥ ነው ያሉት፡፡ ዕድገት የሚታየው እኮ በአጠቃላይ በሕዝቡ ዕሴቶች መበልጸግና

በግለሰብ ደረጃ በዜጎች ኑሮ ላይ አዎንታዊ ለውጥ ሲኖር ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት ዜጎች በከፍተኛ የኑሮ ውድነትና ስር በሰደደ ድህነት እየማቀቁ ይገኛሉ፡፡ የነፍስ ወከፍ ገቢያችን በመካከለኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ካሉ አገራት ጋር ሲነፃፀር እጅግ በጣም ዝቅተኛ ነው፡፡ በተረፈ ዳያስፖራውን ማወያየቱ ለምን አልተሳካም? ለሚለው፣ መጀመሪያ ነገርኮ ልዑካኑ ስንትም ሆነው ይሂዱ የአንድ ፓርቲ አስተሳሰብና አማራጭ ይዘው ነው የሄዱት፡፡ የኢህአዴግ ችግር ሁልጊዜ አንድ ፓርቲነት ነው፡፡ የሌላው ድምፅ መቼ ተደመጠ? ሌላው መታወቅ ያለበት ደግሞ እዚያ የሚሆነው ሁሉ እዚህ ለሚሆነው ነፀብራቅ ነው፡፡ እዚህ ጠንካራ እንቅስቃሴ ሲኖር ዳያስፖራውም ለዴሞክራሲው መበልፀግ በጣም የሚያግዝ እንቅስቃሴ ያደርጋል፡፡ በምርጫ 97 ወቅት የሆነው ለዚህ ማስረጃ ነው፡፡ ዳያስፖራው እዚህ የታፈነውን ድምጽ ነው ለዓለም እያሰማ ያለው፡፡በመጨረሻ ማስተላለፍ የሚፈልጉት መልዕክት ካለ?

ለክርስትና ዕምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለትንሳኤ በዓል አደረሳችሁ እላለሁ፡፡ በዓሉን የደስታና የሰላም ይሁን፤ እግዚአብሔር የቀጣዩን ዓመት በዓል በተሻለ የኑሮ ሁኔታ ላይ ሆነን እንድናሳልፈው ያድርገን፡፡ አንድ እንሁን፣ እንተሳሰብ፡፡ እኛ ኢትዮጵያውያን ከልባችን ቆርጠን ከተነሳንና አንድ ከሆንን የምስጢሮች ሁሉ ቁልፍ በእጃችን ማሕል ነው፡፡

‹‹ዳያስፖራው እዚህ...

Page 17: ethioforum.orgethioforum.org/wp-content/uploads/2011/04/Awramba_Times... · 2011-04-11  · ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ 4 ፊ ቸ ር አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 164 ቅዳሜ ሚያዚያ 15 2003

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

ል ዩ ቅ ኝ ት 17

ከአያ ጅቦ ጋር ድንገት ቢፋጠጡ እርስዎ ይደነግጡ ይሆናል እንጂ ወ/ሮ አበበች ከበደ ለ25 ዓመታት የለመዱት ይሄ እውነት ግድ አይሰጣቸውም፤ ከጅቦች ጋር በጠራራ ፀሐይ አጠገብ ለአጠገብ እየተላለፉ፣ ‹‹እያወሩ›› መኖር የቀን ተቀን ህይወታቸው አካል ነው፡፡

ኦሎምፒያ- ጌቱ ኮሜርሻል ህንፃ እና በፒኮክ መናፈሻ መሀከል በሚገኘው ቡልቡላ ችግኝ ጣቢያ ስራ የጀመረው በ1973 ዓ.ም. ሲሆን ወ/ሮ አበበች ደግሞ ችግኝ ጣቢያን የተቀላቀሉት ከሁለት ዓመት በኋላ ነው፡፡ በወቅቱ ይህ ጊቢ ጥቅጥቅ ያለ ደን እንደነበር የሚገልፁት ወይዘሮዋ በውስጡ የሚታዩት የጅቦች ቁጥር ከአምስት እስከ ሰባት የሚገመት ነበር፡፡ አሁን ይህ አሀዝ በግምት ከሃያ መብለጡን የሚያወሩ፣ ‹‹ኧረ ከአርባ ተሻግሯል›› ብለው የሚከራከሩ አሉ፡፡

ሀገር አባተ አምስት ነጥብ አምስት (5.5) ሄክታር ግምታዊ የመሬት ስፋት ባለው ስፍራ ላይ የሚገኘው የቡልቡላ ችግኝ ጣቢያ አስተባባሪ ናት፡፡ ለህብረተሰቡ በርካሽ ዋጋ ችግኝ አምርቶ ማቅረብ እንዲሁም አዲስ አበባ ተፈጥሮ ሚዛኗን የጠበቀች አገር እንድትሆን ለትምህርት ቤቶች፣ ቀበሌዎች እና ለሌሎች ከተማና አካባቢን ለማስዋብ ለሚረዱ የመንግስት ተቋማት በነፃ ችግኞችን ማቅረብ ዋና ተግባራቸው መሆኑን የምትገልፀው ሀገር አምና 89 ሺህ ብር ያስገባው ዘንድሮ 100 ሺህ ብር ለማስገባት ወዳሰበው መስሪያ ቤቷ አባል ከሆነች ዓመት አልሞላትም፡፡

ለመጀመሪያ ሰሞን ሰውነቷ እስኪርድ ድረስ ጅቦቹን ስታይ ትደነግጥ ስለነበር ቢሮዋን ስትቀመጥ ቆልፋ፣ ስትወጣም እነ ‹‹ገንዶ›› በአካባቢው እንደሌሉ አጠያይቃ ካረጋገጠች በኋላ ነበር፡፡ አሁንም ስታያቸው የመረጋጋት ስሜት አይሰማትም ግን በድንገት በጊቢ ውስጥ ስትዟዟር በአጠገቧ ‹‹እልፍ›› ይላሉ፡፡ ‹‹ጠዋት ስልክ እያወራሁ በአጠገቤ አልፈዋል፡፡››

ጅቦቹ ጊቢው ውስጥ ካለው ጫካ የሚወጡበት ሰዓት ምሽት ብቻ አይደለም፡፡ በቀን ሲንጎማለሉ ይውላሉ፡፡ ከእኔም ጋር ተፋጠዋል፡፡ ጅቦቹን የሚፈሯቸው፣ ሲያይዋቸው ሰውነታቸው የሚርድ፣ ምንም የፍርሃት ስሜት የሌለባቸው፣ በቅርብ ርቀት ምግብ የሚያቀብሏቸው የችግኝ ጣቢያው ሰራተኞች በጊቢው ውስጥ አሉ፡፡

ቆፍጣኒት፣ ገንዶ፣ አለሚቱ...ቆፍጣኒት፣ ገንዶ፣ ቆንጆ፣ አለሚቱ፣ በጣቢያው ውስጥ የሚርመሰመሱት ጅቦች

ከሰራተኞች የሰጣቸው መጠሪያ ነው፡፡ ምንም ቢሆን ጅብ ‹‹ለማዳ›› ነው ብሎ መተማመኛ ማግኘት አይቻልምና ሲቀርቧቸው በተጠቀሱት ስሞች ‹‹እየጠሩ›› ያባብሏቸዋል፡፡ ጾታቸውን ባይለያቸም በአንስታይ ጾታ መጥራት ይቀላቸዋል፡፡ ‹‹እናቱ›› እና ‹‹አባቱ›› ሲሉ በክፉ አይን እንዳያይዋቸው ይለማመኗቸዋል፡፡ መጠሪያ ሸለሟቸው እንጂ በመልክ አይለይዋቸውም፡፡ ቆፍጣኒትን ገንዶ ብለው ሊጠሯት ይችላሉ፡፡

እንደ ወ/ሮ አበበች እና ሌሎች ባልደረቦቻቸው እምነት ጅቦቹ የውስጥ እና የውጪ ሰው ይለያሉ፡፡ ‹‹የውጪ ሰው ሲመጣ የመሸሽ ባህሪ አላቸው፡፡ እኛን ግን ቀና ብለው አይተው በአጠገባችን ያልፋሉ›› ይላሉ፡፡

እነ ‹‹ቆንጆ›› ጠዋት እስከ ሁለት ዓመት ድረስ፣ ከሰዓት ከአስር ሰዓት በኋላ ቢያገኙም፣ ባያገኙም ‹‹ለመለቃቀም››፣ ፀሐይ ለመሞቅና ‹‹›ዎክ›› ለማድረግ ጊቢ ውስጥ ካለው ጫካ ይወጣሉ፡፡ አንዳንድ ቀን ሙሉ ቀን ልታዩዋቸው ትችላላችሁ፡፡ ‹‹ሰው ሊያያቸው ሲመጣ ያውቃሉ መሰለኝ ብዙ ጊዜ አይሳካላንም፡፡ ዝናብ ባለ ጊዜ ግን መጠለያ ውስጥ በብዛት ይገኛሉ›› ትላለች ሀገር፡፡

በተለይ ለችግኞቹ እንክብካቤ የሚረዳ መስኖ ሲለቀቅ ለመጠጣት በሚደረገው እሽቅድድም ፀብ ይፈጥራሉ፡፡ ወላድ ጅቦች ልጆቻቸውን የሚገላገሉበትና የሚያስቀምጡበት ትቦም ታያላችሁ፡፡ ግልገሏ ጅብ የእንኳን ደህና መጣህ አቀባበል በአይኗ አድረጋልኛለች፡፡ ከትቦው ውስጥ ሆና ‹‹ፍጥጥ›› ብላ በማየት፡፡

ከ1985 ዓ.ም. ጀምሮ በቡልቡላ ችግኝ ጣቢያ በጥበቃ ባለሙያነት እና በዕፅዋት ተንከባካቢነት በመስራት ላይ የሚገኙት አቶ ተስፋዬ ብርሃኑ በጊቢው ውስጥ ካሉት ጅቦች ጋር አብረው ስለኖሩ ጅብ የዱር አራዊት መስሎ አይታያቸውም፡፡ ‹‹በፊት በጥበቃነት ስሰራ ሌሊትም ጎን ለጎን እንተላለፋለን፡፡ እኛ እነሱን፤ እነሱም ወደ እኛን

ለመንካት (ለማባረር) አንሞክርም›› በማለት ‹‹ተከባብረው›› እንደኖሩ ይገልፃሉ፡፡ ጅቦቹ እንቅስቃሴያቸውን ገትተው ቆም ካሉ ሰራተኞች ይሸሻሉ፡፡ ‹‹ጨክነን ከሄድን ግን ጅቦቹ ይለቃሉ›› ሲሉ ያስረዳሉ፤ አቶ ተስፋዬ፡፡

እዚያው ተራብተው ቁጥራቸው የጨመረው እነ አያ ጅቦ የማንም አይደሉም፡፡ አዋጅ ቁጥር 541/1999 ቅጣት በሚለው ርዕስ 16ኛ ተራ ቁጥር ንዑስ ቁጥር ሶስት ላይ ‹‹የዱር እንስሳት ወይ የዱር እንስሳት ውጤቶችን ያለ ፈቃድ ይዞ መገኘት ከብር አምስት ሺህ በማያንስና ከብር 30 ሺህ በማይበልጥ መቀጫ ወይም ከአንድ ዓመት በማያንስ በአምስት ዓመት በማይበልጥ እስር ይዳርጋል፡፡ ህገ ወጥ የዱር እንስሳት አደን ወይም የንግድ ድርጊት መፈፀም፣ በዱር እንስሳት ጥበቃ ቦታዎች ውስጥ ያልተፈቀዱ ተግባሮችን ማከናወን ወይም ጉዳት ማድረግ በተመሳሳይ የተጠቀሰውን ቅጣት ያስወስናል፡፡ ቡልቡላ ችግኝ ማፍያም የዱር እንስሳት መጠለያ፣ ፓርክ ወይም የዱር እንስሳት ጥብቅ ክልል ባይሆንም ጉዳት ማድረስ ከተጠያቂነት አያድንም፤ ጉዳት ሊያደርሱባቸው እስካልተጠጓቸው ድረስ፡፡

ጅብ፤ ጅብ ነውበጠራራ ፀሐይ ስሪያ ይፈፅማሉ፡፡ በዚህ ጊዜ የጊቢው ሰራተኞች ‹‹ለምደውናል›

ብለው አይዘናጉም፡፡ ጅብ- ጅብ መሆኑ ትዝ ይላቸዋል፡፡ በተለይ ሴቷ በስሪያ ወቅት ባዕድ ነገር ስታይ ቁጡ ስለሆነች በጣም ይጠነቀቋታል፡፡

‹‹ጅብ ለማዳ አይደለም›› የሚሉት የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ልማትና ጥበቃ ባለስልጣን የእንስሳት ልማትና ጥበቃ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ የኔነህ ተካ ከዱር እንስሳት ውስጥ የሚመደበው ይህ አጥቢ እና ስጋ በሊታ እንስሳ በማንኛውም መልኩ ለማዳ ነው ብሎ ማሰብ እንደማይቻል ያሰምሩበታል፡፡ ‹‹በአገራችን በተለያየ ስፍራ ጅብን የሚያለምዱ አሉ፡፡ ሀረር ውስጥ ጅብ ራት የማብላት ስርዓት፣ [ጅቦቹን በአፍ ስጋ ማጉረስ] በጥሪ መምጣት እና መሄድ የጎብኚዎችን ቀልብ የሚስብ ድርጊት ነው፡፡ ይህ ማለት ግን ጅብ ይለምዳል ማለት አይደለም፡፡ ያስለመድነውን ነገር ቢያጣ ወደ ተፈጥሯዊ ባህሪው ተመልሶ ጉዳት የማድረስ አጋጣሚው ከፍተኛ ነው›› ሲሉ ጥንቃቄ እንደሚያሻ ያሳስባሉ፡፡

አቶ ተስፋዬም መለመዳቸው ቢበረታም ጅብን ‹‹አውሬ›› መሆኑን እንደመርሳት እንደማያደርስ ይጠቁማሉ፡፡ ወ/ሮ አበበችም ከጅቦች አቅራቢያ ዕቃ ለማንሳት፣ ለስራ ለመንቀሳቀስ ‹‹አንቺን ለምደውሻል›› እየተባለ ለመድፈር ብርቱ ቢሆኑም የመላዕክት ስም እየጠሩ እንዳይተናኮሉ የሚያባብሏቸው ጅቦች ነገ ተፈጥራዊ ባህሪያቸው ፈጦ እንደማይወጣ መተማመኛ የላቸውም፡፡

እንደ አቶ የኔነህ ገለፃ የዱር እንስሳት በባህሪያቸው በአብዛኛው የቤት እንስሳትን ወይም ሰውን ሊያጠቁ የሚችሉት ወደ መኖሪያቸው ተጠግቶ ጉዳት ሊያደርሱባቸው ሲሞክሩ ወይም እንስሳው ከፍተኛ የምግብ ችግር ሲኖርበት ነው፡፡ የባላንጣነት ስሜት የሚፈጥር ሁኔታ ሳይፈጠር አብሮ መኖር መቻል ‹‹ነገ ሰላም እኖራለሁ›› ለማለት ማረጋገጫ አይሆንም ባይ ናቸው፡፡

የባለሙያው ስጋት የሰራተኞቹም ስጋት ነው፡፡ በጠረኑ ሳቢያ ‹‹ጉንፋን›› ሲሸልማቸው የኖረው አያ ጅቦ ነገ ቢተናኮለንና አካላዊ ጉዳት ቢያደርስ ወይ ህይወታችን ቢያልፍ የሚል ስጋታቸውን ይዘው ከቀበሌ አስተዳደር አንስቶ እስከ ከተማው አስተዳዳር ከፍተኛ ሹማምንት ጋር ቢኳትኑም አዳምጦ ከመፍትሄ የሚያገናኛቸው አለመኖሩ ተስፋ አስቆርጧቸዋል፡፡

የችግኝ ጣቢያ የበላይ አካል የሆነው የአዲስ አበባ አስተዳዳር የውበት፣ መናፈሻና ዘላቂ ማረፊያ ልማትና አስተዳዳር ኤጀንሲ ዋና ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ፀጋዬ ገ/ማርያም ጉዳዩ አሳሳቢ መሆኑን አልሸሸጉም፡፡ ‹‹ጅቦቹ ከሰራተኞቻችን ጋር ለማዳ ሆነዋል፡፡ ጅቦቹ ወደ ተፈጥሯዊ ባህሪያቸው ሊመለሱ ስለሚችሉ ይሄ (ሰላማዊ ግንኙነታቸው) ለሁልጊዜ ይቀጥላል ማለት አይቻልም›› የሚሉት ስራ አስኪያጁ የጊዜያዊ እና ዘላቂ መፍትሄን መስሪያ ቤታቸው እየዘየደ እንደሆነ ይገልፃሉ፡፡ ‹‹ጊቢ ውስጥ እንዳየኸው ጫካ አለ፡፡

የጅብ ‹‹መንደር›› በመሀል ሸገርበመሀል አዲስ አበባ ቦሌ-ኦሎምፒያ አካባቢ በሚገኝ አንድ ጊቢ ውስጥ ሰው ‹‹የማይተናኮሉ›› ጅቦች ቀን፣ ማታ ሳይሉ በኩራት ይንጎማለላሉ፡፡ ከጅቦቹ ጋር የተፋጠጠው

አቤል ዓለማየሁ ጅብ ተፈጥሯዊ ባህሪውን ሊረሳ ይችላል ብሎ እርግጠኛ መሆን አይቻልምና ‹‹ለማዳ›› ነው ብሎ አብሮ መኖር እንደምን ይቻላል? ሲል ጉዳዩ ትኩረት እንዲሰጥበት በልዩ ቅኝቱ ያሳስባል- መልካም በዓል፡፡ጅብን ለማዳ ነው ብሎ ማመን ይቻላል?

አቶ ተስፋዬም መለመዳቸው

ቢበረታም ጅብን ‹‹አውሬ››

መሆኑን እንደመርሳት

እንደማያደርስ ይጠቁማሉ፡፡ ወ/ሮ

አበበችም ከጅቦች አቅራቢያ ዕቃ

ለማንሳት፣ ለስራ ለመንቀሳቀስ

‹‹አንቺን ለምደውሻል›› እየተባለ

ለመድፈር ብርቱ ቢሆኑም

የመላዕክት ስም እየጠሩ

እንዳይተናኮሉ የሚያባብሏቸው

ጅቦች ነገ ተፈጥራዊ ባህሪያቸው

ፈጦ እንደማይወጣ መተማመኛ

የላቸውም፡፡

ፎቶ፡- ሲሳይ ጉዛይ

ወደ ገጽ 19 ዞሯል

Page 18: ethioforum.orgethioforum.org/wp-content/uploads/2011/04/Awramba_Times... · 2011-04-11  · ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ 4 ፊ ቸ ር አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 164 ቅዳሜ ሚያዚያ 15 200318

ሴት

ዓውድ ዓመት በመጣ ቁጥር ከግንዛቤ ውስጥ ከሚገቡ ነገሮች ዋንኛው በዓሉን ለማድመቅ በሚል ለሚሸመቱት የሸመት ዕቃዎች የሚወጣው ገንዘብ ነው፡፡ አንዳንድ ጊዜ ወጪው ቀጣዮቹን ጊዜያት በተቸጋገረ ሁኔታ ውስጥ እንድናሳልፍ ሁሉ ተጽዕኖ ያሳርፉብናል፡፡ ለሁሉም ጊዜ አለው ቢባልም ከእቅድ በላይ ለማውጣትም ጊዜ አለው ማለት እንዳልሆነ ለማሳሰብ/ ሃሳቤን ለማጋራት እወዳለሁ፡፡ ይህን በመንደርደርያችን ላይ ያነሳነው ግን በበዓላት

ወቅት ስለሚወጣው ወጪ ለማስላት ሳይሆን ከዚያ የላቀ ሆኖም ብዙም ከግንዛቤ ገብቶ ስለማያውቅ ጉዳይ ለመወያየት ነው፡፡

ጉዳዩ… እሷ ናት! ዓውድ ዓመትኮ ይዞ የሚመጣው ያልታሰበ ከፍተኛ ወጪ ብቻ አይደለም፡፡ በእሷ ላይ ተሰፍሮ የማያልቅ የሥራ ጫና ጭምር እንጂ፡፡ እና ዋናው ነገር መሆን ያለበት እሱ ነበር፡፡ ለምንድነው ስለወጪው ብቻ የምንነጋገረው? …

በተለይ እንደ ትንሳኤ ባሉ በዓላት ወቅት የሴቶች የሥራ ድርሻ በእጅጉ ይጨምራል፡፡ ዓላማችን ክብረ በዓሉን ለማድመቅ ለምን አስተዋጽኦ አደረጉ ማለት አይደለም፡፡ ሁሉም እንደየዕምነት ስርዓቱ ለሚያበረክታቸው ተግባራት መንፈሳዊ በረከት እንደሚያገኝ ይታመናል፡፡ በረከቱን ሁለቱም ምናለ ቢጋሩት ለማለት ነው፡፡ በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ እንደሚባለው ማለት ነው፡፡ የሆነ ሆኖ ሴቶች ባይኖሩ በዓላትን እንዴት እናሳልፋቸው ነበር?

ድካሙን፣ የሥራ ጫናውን፣ ወዘተ ለበረከት ያድርገው በሚለው ተስማምተንና ይህንኑ መንፈሳዊ ትሩፋት ብታውቁበት ወንዶችም ባፈሳችሁት ነበር ብለን ወደተያያዥ ወጋችን እንግባ፡፡ ያለ እሷ

አይደምቅም፡፡ በዓል እና ሴት - ሴት እና በዓል፣ ምን አንድ ያደርጋቸዋል እንዳይሉኝ፡፡ `በዓሉ ያለእሷ አይደምቅም` ለማለት የሚያስደፍሩ ብዙ ነገር አለና፡፡

በዓል ለእያንዳንዳችን የሚፈጥረው ልዩ ስሜት አለ፡፡ ለምሳሌ ሁሉም የኃይማኖት ተቋማት በጋራ የሚያከብሩት የአዲስ ዓመት ዋዜማ ምሽት፣ ለአይን በሚስብ መልኩ የሚቀራረበው ቡና /በክርስትና ዕምነት ተከታዮች ከሆነ ችቦ ከመለኮሱ በፊት መጠጣት አለበት/ እሷ በዚያን ሰዓት ለቤቱ ድባብ መቀየር ትልቅ አስተዋጽኦ አላት፡፡ እንደዓይን ኩልል ያለ ፈንዲሻ ላይ በስኳር የተለወሰ ኑግ ጣል ጣል ብሎበት ማየት የተለመደ ነው፡፡ አንዳንዴ ይህ ቀን ለሚፈጥርብን የደስታ ድባብ ስንል ብቻ በዓሉን የምንናፍቅበት ሁኔታ የለም ይሆን? አዲስ አመት ይደገም እንዴ?

ወደ ትንሳኤ በዓል መለስ ስንል የፋሲካ በዓልን ከሌሎች በዓል በተወሰነ መልኩ ለየት የሚያደርገው ነገር አለ፡፡ በተለምዶው የፋሲካ በዓል ፍስክ በለሊት ነው፡፡ በፋሲካው ዋዜማ ምሽት (ለሊት) ምን አልባትም እርስዎ ተኝተው ይሆናል፡፡ ልጆችዎም እንደዚያው፡፡ አንዳንዴ የማይተኙበት አጋጣሚም ይኖራል፡፡ ምክንያቱም እሷ የምትሰራውን ነገር በአይነቁራኛ መከታተል የሚሰጠው ደስታ አለውና ነው፡፡ ‹ኧረ ተኙ› ብትለን እንኳ አንተኛም፡፡ የተኛን መስለን ጆሮአችን የእሷን ጥሪ ይጠብቃል፤ ይናፍቃል፡፡ የማክፈያ ሰዓት (9፡00) ሰዓት ከመሆኑ በፊት እርሷ ከእምነት ተቋማቱ የብስራት ደወል ቀድማ ትዘጋጃለች፡፡ ከዚያም የማክፈሉ ብስራት የእሷ ስራ ነው፡፡

ኢየሱስ ክርስቶስ ስጋዊ አካሉ ካረፈበት ቦታ ማልደው የጌታቸውን አካል ሽቶ ሊቀቡ

ሄደው የነበሩት ሴቶች መሆናቸውን እንዲሁም የእርሱን መነሳት ለመጀመሪያ ጊዜ ለደቀ መዛሙርቱ ያበሰሩት ሴቶች እንደሆኑስ ልብ ብለዋል? ልጆችንና ባልን መቀስቀስ እና ያዘጋጀችውን እያንዳንዱን ነገር ማስቀመስ የእሷ ኃላፊነት ነው፡፡ ያኔ፣ ምንም እንኳን ለመጾም ያልደረስን ልጆች ብንሆንም… እሷ ያዘጋጀችውን ስንቀምስ ውስጣችን እንዴት እንደሚረካ የሚረሳ ያለ አይመስለኝም፡፡

ለዚህ ሁሉ ነገር መሳካት ምን አልባትም የትዳር አጋርህ የቤት እመቤት ከሆነች ኪስህ ሊሰጥ የፈቀደውን ብቻ ሊሆን ይችላል የሰጠሃት፡፡ በበዓል ቀን አታስጨንቅህ ይሆናል፡፡ ያ በቂ ሆኖ ባይታያት እንኳ እንደሚበቃ አድርጋ አዘጋጅታው ‹‹ከማንም እንዳናንስኮ ነው›› ትልሃለች፡፡ ያቺን እራፊ ብር ምሉዕ ታደርጋታለች፡፡ ዛሬ ደግሞ የገንዘብ አቅም የት እንደደረሰ ይታወቃል፡፡

በተለምዶው ለበዓል ዋዜማ የመዝናናት ኃላፊነት የወንዶች ብቻ ነው ተብሎ ይታሰባል - ‹ኢቭ› ይሉታል፡፡ አንተ ያለኸው ከጓደኞችህ ጋር እየተዝናናህ ሊሆን ይችላል፡፡ ያ ግን ብዙውን ጊዜ እሷን ያካተተ ሲሆን አናየውም፡፡ የእርሷ ድርሻ በቤት ውስጥ ደስታን መፍጠር እስኪመስላት ድረስ ትደክማለች፡፡ ደስታን የሚፈጥር ሰው የእሱ ደስታ የሌላው ደስታ ማየት ነውና እሷ ያን ታደርጋለች፡፡

በበዓል ቀን የእርሷ በቦታው መኖር ለቤቱ ትልቅ ውበትና ድምቀትን ሲሰጠውስ አላስተዋሉም? የገዛ ቤታችን አይተነው በማናውቀው ነገሮች እስኪገርመን ድረስ ይሞላል፤ ያሸበርቃል፡፡ ቡናው፣ ዳቦው፣ ዶሮው ጠላው... ይህ ሁሉ በእርሷ ነው የሚከወነው፡፡ መቼም ስለ ‹‹እኩልነት›› ብዙ ሲባል እንሰማለን፡፡ እባክዎ የእኩልነትን ዕሳቤ ኃላፊነቶቻችንንና የቤት ውስጥ የሥራ ጫናዎችን በመጋራት እንግለጸው፡፡ - ማለቴ ተጨባጭ እውነታ እናድርገው፡፡ እንደዚህ ከሆነ እንኳን አደረሰዎ!!

መልካም በዓል!

ምክር ቤቱ

ሸክሙን በመጋራት በረከቱን መጋራት!

በመቅደስ ፍስሐ [email protected]

የተኛን መስለን

ጆሮአችን የእሷን ጥሪ

ይጠብቃል፤ ይናፍቃል፡፡

የማክፈያ ሰዓት (9፡00)

ሰዓት ከመሆኑ በፊት

እርሷ ከእምነት ተቋማቱ

የብስራት ደወል ቀድማ

ትዘጋጃለች፡፡ ከዚያም

የማክፈሉ ብስራት

የእሷ ስራ ነው፡፡

በሱራፍኤል ግርማ

ባሳለፍነው ማክሰኞ የ1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 21ኛ መደበኛ ስብሰባውን ያከናወነው የኢፌዴሪ 4ኛው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት በአጀንዳነት ይዞት የተሰየመው የሴቶች፣ ሕፃናት እና ወጣች ጉዳይ ሚኒስቴርን የ2003 ባጀት ዓመት የ9 ወር ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርትን ማዳመጥ ነበር፡፡

የሴቶች፣ ሕፃናት እና ወጣቶች ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ወ/ሮ ዘነቡ ታደሰ የመ/ቤታቸውን ሪፖርት በንባብ ባሰሙበት ጉባዔ የተመዘገበው የቀሪዎች ቁጥር 246 ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

ሚኒስትሯ ያቀረቡት ባለ 21 ገጽ ሪፖርት፣ ባመዛኙ በሚኒስቴሩ አማካኝነት ስለተሰጡ ሥልጠናዎች እና ሴሚናሮች፣ ስለተከናወኑ የጋራ ምክክርች እና ውይይቶች፣ እንዲሁም ስለተከበሩ ‹‹ዓለም አቀፍ ቀናት›› የሚያትት ነበር፡፡

የመ/ቤቱ የአሰራር ሥርዓት በዘመናዊ ቴክኖሎጂ (IT) እንዲታገዝ ከማድረግ ጋር ተያይዞ፣ በሀገሪቱ የጉዲፈቻ አገልግሎት ተጠቃሚ ሆነው ከኢትዮጵያ ውጭ ለሚሄዱ ሕፃናት አጠቃላይ መረጃን በተመለከተ ለሕፃናቱ ቅርብ እንዲሆን፣ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ያሉትን ‹‹ምርጥ ተሞክሮዎች በመፈተሽ››፣ በጣት አሻራና በይለፍ ቁልፍ በመታገዝ፣ የሕፃናትን የግል መረጃዎች ደህንነትና ዋስትና የሚያረጋግጥ የዲዛይን ጥናት መጠናቀቁን ሪፖርቱ ያሳያል፡፡

የሕፃናት ማሳደጊያዎችን በተመለከተ ደግሞ፣ ከበጎ አድራጎት ድርጅቶች እና ከሲቪል ማህበራት ምዝገባ ኤጀንሲ ጋር በመተባበር በአማራ፣ ደቡብ፣ ድሬዳዋ እና ሀረሪ ክልሎች ውስጥ በሚገኙ 108 የሕፃናት ማሳደጊያዎች ላይ ግምገማ ተካሂዶ፣ ከፍተኛ ግድፈት የታየባቸው 46 ማሳደጊያዎች እንዲዘጉ፣ እና ለ48 ማሳደጊያዎች ደግሞ ማስጠንቀቂያ መሰጠቱ በሰነዱ ላይ ሰፍሯል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ፣ ከፍርድ ቤት ለሚላኩ የጉዲፈቻ አሳድጊ ቤተሰቦች እና የጉዲፈቻ ተደራጊ ሕፃናትን ማስረጃዎች በመፈተሽ እና አስተያየት በመስጠት፣ በፍ/ቤት ውሳኔ ላገኙ ጉዳዮች ምላሽ ለመስጠት በታቀደው መሰረት፣ 1749 ሕፃናት የጉዲፈቻ አገልግሎት አግኝተው ወደ ተለያዩ ሀገራት መጓዛቸው ሪፖርት ተደርጓል፡፡

የመ/ቤቱን ጠንካራና ደካማ ጎኖች ‹‹የተዘረዘሩበት››፣ የመጨረሻው የሪፖርቱ ክፍል ነበር፡፡ ተቀናጅቶ የመስራት ባህል አለመዳበር፣ የለውጥ ሥራውን በሚፈለገው ፍጥነትና ደረጃ ያለመስራት እና የማስፈፀም አቅም ማነስ ‹‹ደካማ ጎኖቼ›› ሲል የሴቶች፣ ሕፃናት እና ወጣቶች ጉዳይ ሚኒስቴር ሪፖረት አድርጓል፡፡ ነገር ግን የቀረበው ሪፖርት ጉልበታቸው እየተበዘበዘ ስለሚገኙ ሕፃናት፣ በጉዲፈቻ ስም ወደ ውጭ ሀገራት ሄደው ስቃይ ስለሚደርስባቸው ሕፃናት ወዘተ ምንም አለማለቱ ከተወሰኑ የም/ቤቱ አባላት ዘንድ ‹‹ለምን?›› የሚል ጥያቄን ማስነሳቱ አልቀረም፡፡

የመጀመሪያው ጠያቂ፣ ‹‹ኢትዮጵያ ከሌሎች ሀገራት ሁሉ ልጆቿን ወደ ውጭ ለመላክ በጣም ዝግጁ፤ [እና ግን] ከሄዱ በኋላ ደግሞ ስለሁኔታቸው ለመከታተል በጣም ዝንጉ›› መሆኗን በማስታወስ፣ ‹‹ዘንድሮም 1749 ሕፃናት ወደ ውጭ ሀገራት መላካቸው በጣም ብዙ ነው፤ ይሄን ለመቀነስ ምን እየተሰራ ነው?›› ሲሉ ጥያቄ አቅርበዋል፡፡ ለጥያቄውም ምላሽ የሰጡት የመ/ቤቱ የሥራ ኃላፊ፣ የተጠቀሰው ቁጥር

በእርግጥም ብዙ መሆኑን አምነው፣ ‹‹ነገር ግን ይህ ቁጥር ካለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር ቀንሷል፤ ከመጋቢት 1/2003 በፊት፣ በቀን ከ30 እስከ 40 የጉዲፈቻ ፋይሎችን እናይ ነበር፡፡ አሁን ግን በቀን 5 ፋይሎችን ብቻ ነው እያየን ያለነው›› ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

የማህበራዊ ጉዳዮችና የሕግ፣ የፍትህ እና የአስተዳዳር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴዎች የግል ድርጅቶች ሰራተኞች ጡረታ ረቂቅ አዋጅ ላይ ከማህበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ እና ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ተወካዮች ጋር ያደረጉት ስብሰባ፣ ባገባደድነው ሳምንት ም/ቤቱ ያደረገው ሌላኛው ስብሰባ ነበር፡፡ ረቡዕ በተከናወነው ስብሰባ ላይ የተገኙ የማህበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ የሥራ ኃላፊዎች፣ የግል ድርጅቶች ውስጥ ተቀጥረው የሚያገለግሉ ሰራተኞች ጡረታ እንዲኖራቸው ማድረግ በጣም አስፈላጊ እንደሆነ በማስመር፣ ጡረታ የማግኘት መብት ሰብዓዊ መብት መሆኑንም ጭምር አስገንዝበዋል፡፡

ይሁንና፣ በደፈናው መልካምነቱ የተነገረለት የግል

ድርጅቶች ሰራተኞች ጡረታ ረቂቅ አዋጅ፣ ባካተታቸው የተወሰኑ አንቀጾች ምክንያት፣ ጉዳዩ በቀጥታ ከሚመለከታቸው የግል ድርጅቶች ሰርተኞች እና ከአንዳንድ የም/ቤቱ አባላት ጥያቄ ሳይነሳበት አልታለፈም፡፡ በተለይም ስለጡረታ መዋጮ ተመላሽነት የሚደነግገው አንቀጽ 26 አነጋጋሪነቱ ጉልህ ሆኖ ተስተውሏሏ፡፡ በአንቀፁ መሰረት፣ አንድ የግል ድርጅት ሰራተኛ፣ ከ10 ዓመት ያላነሰና 20 ዓመት ያልሞላ አገልግሎት ፈጽሞ በራሱ ፈቃድ ሥራውን ከለቀቀ፣ ወይም ከ20 ዓመት ያነሰ አገልግሎት ፈፅሞ በአዋጁ ከተጠቀሱት ውጪ በሆነ ምክንያት ከሥራ ከተሰናበተ፣ የአሰሪውን ድርሻ ሳይጨምር ሰራተኛው ራሱ ባዋጣው መጠን ብቻ የጡረታ መዋጮ ይመለስለታል፡፡ ከ10 ዓመት ያነሰ አገልግሎት ፈፅሞ በራሱ ፈቃድ ሥራውን ከለቀቀ ደግሞ፣ ምንም ዓይነት ክፍያ አያገኝም፡፡

በረቡዕ ስብሰባ ላይ ለአስፈፃሚ አካላቱ ለቀረቡት ጥያቄዎች መካከል ረቂቁ ለመጀመሪያ ጊዜ ለም/ቤት ቀርቦ ውይይት በተደረገበት ወቅት፣ ከም/ቤት አባላት ተነስተው የነበሩ ጥያቄዎች ይገኙበታል፡፡ የአዋጁ አንቀጽ 26 ንዑስ አንቀጽ 2፣ አንድ የግል ድርጅት ሰራተኛ ከአስር ዓመት ያነሰ አገልግሎት ፈፅሞ በራሱ ፈቃድ ሥራውን ከለቀቀ ምንም ዓይነተ ክፍያ እንዳያገኝ መደንገጉ፣ ‹‹ይሄማ የሰራተኞችን፣ የላባቸውን ፍሬ ከመውረስ አይተናነስም›› የሚል አስተያየት ያዘለው ጥያቄ ተጠቃሽ ነው፡፡

‹‹አስር ዓመት አላገለገላችሁም በሚል ስምንና ዘጠኝ ዓመት ያገለገሉ ሰራተኞች ሁሉ ከሥራ በሚወጡበት ጊዜ ያጠራቀሙትን ገንዘብ ሊከለከሉ አይገባም፤ ፍትሀዊም አይደለም፡፡ ስለዚህ ገንዘባቸውን ከነወለዱ የሚያገኙበት ሥርዓት ለምን አይዘጋጅም?›› ለሚለው ጥያቄ የተሰጠው ምላሽ ቁርጥ ያለ ነበር፡፡ ከጠ/ሚኒስትሩ ጽ/ቤት የመጡት የሥራ ኃላፊ፣ ‹‹ወደ ጡረታ ፈንድ ገንዘቡ ከገባ በኋላ፣ ገንዘቡ የግለሰቡ አይደለም፡፡ ስለዚህ መመለስ በመርህ ደረጃ የሚቻል አይደለም›› የሚል መልስ ሰጥተዋል፡፡ ምላሹም፣ ‹‹ረቂቁ አዋጅ ሆኖ ሲወጣ ይህን ያህል የይዘት ለውጥ አይኖረውም›› የሚል ግምት እንዲሰነዘር ምክንያት ሆኗል፡፡

ረቂቅ አዋጁ ሳይሻሻል ይጸድቅ ይሆን?

የመ/ቤቱ የአሰራር ሥርዓት በዘመናዊ ቴክኖሎጂ (IT)

እንዲታገዝ ከማድረግ ጋር ተያይዞ፣ በሀገሪቱ የጉዲፈቻ

አገልግሎት ተጠቃሚ ሆነው ከኢትዮጵያ ውጭ ለሚሄዱ ሕፃናት

አጠቃላይ መረጃን በተመለከተ ለሕፃናቱ ቅርብ እንዲሆን፣ እና

በዓለም አቀፍ ደረጃ ያሉትን ‹‹ምርጥ ተሞክሮዎች በመፈተሽ››፣

በጣት አሻራና በይለፍ ቁልፍ በመታገዝ፣ የሕፃናትን የግል

መረጃዎች ደህንነትና ዋስትና የሚያረጋግጥ የዲዛይን ጥናት

መጠናቀቁን ሪፖርቱ ያሳያል

የጅብ ‹‹መንደር››...

Page 19: ethioforum.orgethioforum.org/wp-content/uploads/2011/04/Awramba_Times... · 2011-04-11  · ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ 4 ፊ ቸ ር አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 164 ቅዳሜ ሚያዚያ 15 2003

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

በሱራፍኤል ግርማ

የመጋቢት ወር 2003 ዓ.ም አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት ካለፈው ዓመት መጋቢት ወር ጋር ሲነፃፀር በ25 በመቶ መጨመሩን ማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ ያወጣው መረጃ አመለከተ፡፡ ለአጠቃላይ ግሽበቱ መጨመር ዋንኛው ምክንያት በ5.4 በመቶ ጭማሪ ያሳየው የእህል ዋጋ ነው፡፡ ከሥጋና ከተወሰኑ እህሎች በስተቀር፣ በተለይ ስንዴ በቆሎ፣ ገብስ፣ ጥራጥሬ፣ ቡና እና በርበሬ በመሳሰሉት ላይ በመጋቢት ወር 2003 ዓ.ም ዋጋ ጭማሪ መታየቱንና ምግብ ነክ ባልሆኑት ላይ የዋጋ ግሽበቱ 24.3 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱን ኤጀንሲው ያዘጋጀው ሰነድ ይገልፃል፡፡

በማዕከላዊ ስታትስቲክስ ሪፖርት መሠረት በመጋቢት ወር የታየው የአትክልትና ፍራፍሬዎች ዋጋ 80.8 በመቶ ጭማሪ በማሳየት ከፍተኛው ሆኖ የተመዘገበ ሲሆን፣ ሌሎች በርካታ ነገሮችም ጭማሪ አሳይተዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ በመጋቢት ወር የተስተዋለው የምግብ ዋጋ ግሽበት 25.5 በመቶ ሲሆን፣ በዚህ ዓመት ከተመዘገቡት የዋጋ ግሽበቶች ሁሉ ከፍተኛው ነው፡፡ በመስከረም ወር 2003 ዓ.ም የነበረው አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት 7.5 በመቶ፣ የምግብ ዋጋ ግሽበት 1.4 በመቶ፣ ምግብ ነክ ያልሆኑ ነገሮች ላይ ደግሞ የ17.2 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል፡፡

ከእነዚህም ውስጥ፤ ጥራጥሬ በ29.7 ከመቶ፣ ዘይትና ቅባቶች በ54.9 ከመቶ፣ ቅመማ ቅመም በ50.9 ከመቶ፣ ድንችና ሌሎች ሥራ ሥሮች በ27.4 ከመቶ፣ እንዲሁም ያልተቆላ ቡና እና ሻይ ቅጠል በ112.2 ከመቶ ጭማሪ አሳይተዋል፡፡ በሌላ በኩል ሥጋ የ7.2

ከመቶ ቅናሽ አሳይቷል፡፡ መስከረም ወር ላይ 7.5 ከመቶ

የነበረው አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት በተከታዩ ጥቅምት ወር ላይ 10.6 ሲደርስ፣ የምግብ የዋጋ ግሽበት ከ1.4 በመቶ ወደ 5.4 በመቶ ከፍ ብሏል፡፡ ምግብ ነክ ያልሆኑ ሸቀጦች የዋጋ ግሽበት ደግሞ ከ17.2 በመቶ ወደ 18.7 በመቶ ተሸጋግሯል፡፡

የህዳር ወር አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት ካለፈው ዓመት ህዳር ወር ጋር ሲነፃፀር በ10.2 በመቶ ከፍ ብሎ ነበር፡፡ የምግብ ዋጋ ግሽበት ካለፈው ዓመት ህዳር ወር ጋር ሲነፃፀር የ5.8 በመቶ እና ምግብ ነክ ያልሆኑ የዋጋ ግሽበት የ16.7 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል፡፡

በታህሳስ ወር በአገሪቱ የነበረው አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት ወደ 14.5 በመቶ አሻቅቧል፡፡ የወሩ ምግብ ዋጋ ግሽበትም በ8.9 ከመቶ ጭማሪ አሳይቷል፡፡ ምግብ ነክ ያልሆኑ ነገሮች ደግሞ ካለፈው ዓመት ታህሳስ ወር ጋር ሲነፃፀር የ22.9 በመቶ ጉልህ ጭማሪ ማሳየቱን የማዕከላዊ ሰታትስቲክስ ኤጀንሲ መረጃ ይጠቁማል፡፡

የ17.7 በመቶ አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት በታየበት ጥር ወር ላይ የምግብ ዋጋ ግሽበትም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወር ጋር ሲነፃፀር የ13.6 በመቶ ጭማሪ እንደተስተዋለበት በወቅቱ ከተዘጋጀው መረጃ መረዳት ይቻላል፡፡ ምግብ ነክ ያልሆኑ የዋጋ ግሽበት ከጥር ወር 2002 ዓ.ም ጋር ሲነፃፀር የ23.7 በመቶ ጭማሪ ተመዝግቧል፡፡

የያዝነው በጀት ዓመት የካቲት ወርም ቢሆን ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወር በ16.5 በመቶ የጨመረ አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት አስመዝግቧል፡፡ የምግብ ዋጋ ግሽበቱ የ12.8 በመቶ ጭማሪ ያሳየ ሲሆን፣ ምግብ ነክ ያልሆኑ ነገሮችም የዋጋ ግሽበት በ22 በመቶ ጨምሯል፡፡

ዜ ና ዎ ች 19

የጋዜጣና መጽሔት ሕትመት ዋጋ ጭማሪ ለፕሬስ ነፃነት አደጋ ነው

የጋዜጣና መጽሔቶች አሳታሚዎች አስተባባሪ ኮሚቴ

በሕገመንግስቱም ሆነ ሕገመንግስቱን መሠረት አድርገው በወጡ የፕሬስ ነፃነት ነክ ሕጎች መሠረት፣ በርካታ ጋዜጦችና መፅሔቶች ተፈጥረዋል፡፡ ለሕብረተሰቡ መረጃ በመስጠትም የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እያደረጉ ይገኛሉ፡፡ አማራጭ የሆነ መረጃ ለሕብረተሰቡ በመስጠት እየተጫወቱት ያለው ሚና በቀላሉ የሚገመት አይደለም፡፡

የገንዘብ አቅማቸው ደካማ በመሆኑ ሁሉም ሕልውናቸው አደጋ ላይ ነው፡፡ ይህ ማለት እነሱም አማራጭ መረጃ የመስጠት ግዴታ፣ ሕዝብም አማራጭ መረጃ የማግኘት መብቱ ሁልጊዜ አደጋ ላይ ነው ማለት ነው፡፡

በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የጋዜጣና መጽሔቶች ማተሚያ ዋጋ በመጨመሩ ምክንያት የሕልውናቸው ጥያቄ ወሳኝ ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡ ማተሚያ ቤቶች የወረቀት ዋጋ ጨምሮብናል በሚል ምክንያት ዋጋ ላይ ጭማሪ ስላደረጉ ጋዜጣና መጽሔት አሳታሚዎች ሊሸከሙት የማይችሉት ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡

ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት 45% የሚያክል ዋጋ ሲጨምር ሌሎች ማተሚያ ቤቶችም ተመሳሳይ ጭማሪ እያደረጉ ስለሆነ በሁሉም ማተሚያ ቤቶች የሚታተሙ ጋዜጦችና መጽሔቶች ‹‹መኖር ወይስ አለመኖር!›› የሚል ጥያቄ አንዣቦባቸዋል፡፡

በተለይ ደግሞ በግል ድርጅቶች ባለቤትነት ስር ያሉ ጋዜጦችና መጽሔቶች ለተለያዩ ማተሚያ ቤቶች በዓመት ከ30 ሚሊዮን ብር በላይ ይከፍላሉ፡፡ የደንበኝነት ዕድሜያቸው የአንዳንዶቹ ከ15 ዓመት በላይ ነው፡፡

ካለው የጭማሪ መጠን ከፍተኛነት፣ ካለው የደንበኝነት ዕድሜ፣ ካሉት የደንበኞች ብዛት እና ከሚከፈለው ገንዘብ መጠን ጋር ሲገናዘብ ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ከፍተኛውን ደረጃ ስለሚይዝ የጋዜጣና የመጽሔት አሳታሚዎች በጋራ ለብርሃንና ሰላም ደብዳቤ ጽፈው ነበር፡፡ በግልባጭም ለማተሚያ ድርጅቱ ቦርድና ተቆጣጣሪ ባለሥልጣን ኃላፊዎች ጽፈዋል፡፡ የአሳታሚዎች ጥያቄም በገንዘብ ዓይን ሲታይም ሆነ የሕዝብ አማራጭ መብት የሚያስከትለው ጉዳት ከፍተኛ ስለሆነ፣ ሁኔታውን ለማጥናትና አቋም ለመውሰድ የጭማሪው ተግባራዊነት ለሶስት ወራት ያህል እንዲቆይና ውይይቱ እንዲቀጥል የሚጠይቅ ነበር፡፡

በዓለም ላይ የምርቶች ዋጋ እየጨመረ በመሄድ ላይ ስለሚገኝ በወረቀት ላይም ዋጋ ጨምሯል ቢባል አሳታሚዎች የምንጠብቀው ነው፡፡ የጭማሪው ዋጋ በእያንዳንዱ ጋዜጣና መጽሔት አሳታሚ ድርጅት ላይ ያሳረፈውን ጫና ግን ልንቀበለው ያስቸገረን መጠን ሆኗል፡፡

ማተሚያ ቤቶች ሳይከስሩ፣ ጋዜጦችና መጽሔቶች ሳይዘጉ መኖርም መቀጠልም ይችላሉ ብለን እናምናለን፡፡ ለመፍትሄው በሁሉም በኩል ቅን የሆነ አመለካከት ካለ የጋዜጣና የመትሔት አሳታሚዎች ስለ ዋጋ ጭማሪ እያሳሰበን ያለው ‹‹የዚህ ጋዜጣ ትርፍ ይቀንሳል፣ የዚህ መጽሔት ገቢ ይጓደላል፣ ወይም ደግሞ ጋዜጦችና መጽሔቶች አቅም አጥተው ሕልውናቸውን ያጣሉ›› ከሚል መመዘኛ ብቻ አይደለም፡፡ ዋነኛው አሳሳቢ ጉዳይ በሕገመንግስቱና በሌሎች የሚዲያ ሕጎች፣ ፕሬስ የተለያየ መረጃ የመስጠት መብትና ግዴታ አለበት፤ ሕዝብም መረጃ የማግኘት መብት አለው፤ ቢባልም ጋዜጦችና መጽሔቶች አቅም አጥተው ከተዘጉ በሕገመንግስቱ የተደነገገው መብት ተግባራዊ ሳይሆን ይቀራል፡፡ አማራጭ መረጃዎችና የተለያዩ አስተሳሰቦች በሕብረተሰብ የማንሸራሸር ሁኔታ አይኖርም፡፡

ስለሆነም፣ የወረቀት ዋጋ ጨምሯል ተብሎ የጋዜጦችና መጽሔቶች አሳታሚዎች ላይ የማይችሉትን የዋጋ ጭማሪ መጫን የሚያስከትለው ችግር የአገር ችግር፣ መረጃ የማሰራጨትና የማግኘት ችግር እንደሚሆን በመገንዘብ ሕዝብም፣ መንግስትም፣ የሚመለከታቸው መሥሪያ ቤቶችም ለችግሩ ልዩ ትኩረት ሰጥተው መፍትሄ ለማግኘት የበኩላቸውን እንዲወጡ እንጠይቃለን፡፡

በሽቦ አጥር አበጅተንለት እዚያ አስገብተን ልናኖራቸው እቅድ አለን፡፡ በዘላቂነት ከኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ልማትና ጥበቃ ባለስልጣን ጋር ይፋዊ ግንኙነት አድርገን የመጨረሻ ውሳኔ ላይ ለመድረስ እናስባለን›› ይላሉ፡፡ የዘላቂ መፍትሄው- መጨረሻ ጅቦቹን ከጣቢያው ማስለቀቅ ነው፡፡ በአጥር ከለላ በዚያው ለማኖር በቀጣዩ ዓመት የበጀት ዓመት እቅድ ውስጥ የተካተተ ነው፡፡ ጅቦቹን እየቀለቡ ማኖር የሚያስችል በጀት ሊኖራቸው ስለማይችል በበለጠ ዘላቂውን የመፍትሄ ሀሳብ ቁልፍ መጫኑ ላይ ሀሳቡ እንዳላቸው አቶ ፀጋዬ ለአውራምባ ታይምስ ገልፀዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ልማትና ጥበቃ ባለስልጣን የስሙ ስያሜ እንደሚያመለክተው የአያ ጅቦ ጉዳይ ይነካቸዋል፡፡ ‹‹የችግኝ ጣቢያው ሰራተኞች ከጅቦቹ ጋር ያለን ፍቅር አልቋል ብለው ችግር እንደሚያስከትሉባቸው ገልፀው ከአዲስ አበባ መስተዳዳር አቅም በላይ ከሆነ የተለያየ ዘዴ በመጠቀም ቅራኔውን እንፈታለን፡፡ ዱር ባለመሆኑ ጅቦቹ እዚያ

ቦታ መኖር የለባቸውምና ከዚያ እንዲወጡ እናደርጋለን፡፡ አሻፈረኝ ካሉ (የማይወጡ ከሆነ) እንዲወገዱ እናደርጋን ምክንያቱም ከሁለም የሰው ህይወት ይበልጣልና›› በማለት የገለፁት አቶ የኔነህ ተካ እስካሁን ድረስ ከችግኝ ጣቢያውም ሆነ የውበት፣ መናፈሻና ዘላቂ ማረፊያ ልማትና አስተዳዳር ኤጀንሲ የተሰደደላቸው መልዕክት የለም፡፡ ‹‹ከእኛ አቅም በላይ ነው ችግሩን ፍቱልን ካሉን መፍትሄ ለመስጠት እንሞክራለን›› ብለዋል፡፡ ይህ የእነ አቶ ፀጋዬን ብርታት የሚጠይቅ ነው፡፡

ጠቃጠቆዎቹበዓለም ላይ ሦስት አይነት የጅብ

ዝርያዎች አሉ፡፡ ጠቃጠቆ ጅብ (spotted hyena) እና ባለመስመሩ ጅብ (stripe hyena) በኢትዮጵያ የሚገኙ ሲሆን ሦስተኛው ቡናማ ጅብ (Brown hyena) ደቡብ አፍሪካ ውስጥ ብቻ ይገኛል፡፡

በቡልቡላ ችግኝ ጣቢያ ውስጥ ያለው ነጠብጣብ ያረፈበት ‹‹ጠቃጠቆ ጅብ›› ነው፡፡ እነ ወ/ሮ አበበች ለጠቃጠቆዎቹ ጅቦች

ከሚያውቋቸው ሰዎች መልዕክት ሳይዙ ወደ ጊቢው አይገቡም፡፡ ‹‹ጅቦችሽ ደህና ናቸው?›› የሚላቸውን ‹‹ቆፍጣኒት ወለደች እኮ የአራስ ጥሪ እጃችሁ ከምን?›› ሲሉ ያስፈግጓቸዋል፡፡

ለእዚህ ፅሁፍ ማዳበሪያ እንዲሆን በጫካ ውስጥ ከትሁቱ ምስል አስቀሪ ባለሙያ ሲሳይ ጉዛይ ምስል ማስቀሪያ ላይ ጠቃጠቆ ጅብን ለማኖር ረቡዕ ማምሻውን ከሁለት ሰዓት በላይ በጫካ ውስጥ ተሯሩጠናል፡፡ ቅጠል ሲወድቅ ነፍሳችን ‹‹በራ›› ልትወጣ ምንም አልቀራት፡፡ በድምሩ አምስት ጅቦችን ከጫካ ውስጥ ለመመልከት ምስሉን ለማስቀረት በዛፍና በቅጠላ ቅጠል በመከለላቸው ያሰብነውን ያህል አልተሳካልንም፡፡ በሳምንቱ ሁለት ቀናት (ሰኞ ጠዋትና ረቡዕ ማምሻውን) በጊቢ ባደረጉት ቆይታ ይንጎማለሉበታል፣ ይተኙበታል፣ ወጥተው ይጫወቱበታል ከሚባለው የችግኝ ጣቢያ አረንጓዴ ቤት አቅራቢያ በህብረት ምስላቸውን ለማግኘት ባንችልም ሲተረማመሱ ተመልክተናል፡፡

ከግልገል ጅብ ጋር በሦስት እርምጃ

ርቀት ተደፋፍረናል፡፡ በጊቢው ተኝተው የነበሩት የመንደር ውሾች ደግሞ በድንገት ከፒኮክ መናፈሻ አካባቢ ከሚወርደው ወንዝ አቋርጦ ወደ ጓደኞቹ ለመቀላቀል የሚሄደውን ጅብ አላሳልፍ ብለው ሲጮሁበት ተመልክተን (ፎቶ) ይህንን አስቀርተናል፡፡ የጥበቃ ባለሙያው እሸቱ ረዳ ‹‹ውሾቹ እና “ለማዳ” ጅቦቹ ተናንቀዋል›› ሲል ውሾቹ እንደማይፈሯቸው የነገረንን በአይናችን አረጋግጠናል፡፡ [አንገቱ ረዥም ስለሆነ ወንድ ጅብ እንደሆነ እሸቱ ነግሮናል፡፡] ራሱን ለመከላከል ብቻ ዞር ብሎ አስፈራርቶ መንገድ ሲያስለቅቅ ተመልክተናል፡፡ ማስጠንቀቂያውንም አልረሳሁም፤ አንድ የጥበቃ ባለሙያ መረጃ ስሰበስብ እየተከተለችኝ ‹‹የጅብ አስወጋጅ ዋና የስራ ሂደት ባለቤት›› ያህል ቆጥራኝ ማስጠንቀቂያ ታቀብለኝ ነበር፡፡ ‹‹ጅቦቻችንን እንፈልጋቸዋለን እንዳትነኩብን›› በማለት፡፡

የጅብ ‹‹መንደር››...

በኤልያስ ገብሩ

የፌዴራል የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን በያዝነው ዓመት ከህዳር ወር መጨረሻ የጀመረው በሦስቱ የመንግስት ስልጣን መዋቅር ስር የሚገኙ ባለስልጣናትን ሀብት ምዝገባ የዘጠኝ ሺ የመንግስት ባለስልጣናትና ተሿሚዎችን ሀብት እንደተመዘገበ ተገለፀ፡፡

በኮሚሽኑ የሀብት ማሳወቅና ማስመዝገብ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ግርማ ወርቁ ለአውራምባ ታይምስ ጋዜጣ እንደገለፁት ከሆነ ላለፉት አራት ወራት ያህል የሚመለከታቸውን የመንግስት ከፍተኛ ሹመኞች ጨምሮ የፌዴራል መ/ቤት ሰራተኞችን ያካተተ የሀብት ምዝገባ ተካሂዷል፡፡ የመንግስት ሠራተኞችን የሀብት ምዝገባ በያዝነው ወር ኮሚሽኑ መዝግቦ እንደሚያጠናቅቅ፣ በቀጣይ ሁለት ወር ደግሞ በመንግስት የልማት ድርጅቶች ላይ ትኩረት አድርገው እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡

በማያያዝም “ምዝገባው በዕቅዱ መሠረት በዚህ በጀት ዓመት የሚጠናቀቅ ቢሆንም፣ መቼም የማይቋረጥ ሂደት ነው፡፡ ዛሬ ሀብታቸውን ያስመዘገቡ የመንግስት ሹመኞችና ሰራተኞች በተለያየ ምክንያት ከቦታቸው በሚነሱበት ጊዜ ለውጣቸውን ያስመዘግባሉ፡፡ በእነሱ የሚተኩ ሰዎች ምዝገባም ይቀጥላል” ብለዋል፡፡

የምዝገባው ሂደት በየሁለት ዓመቱ ማደስን የሚጠይቅ እንደሆነም ገልፀዋል፡፡ እስከ 2005 ዓ.ም ድረስ ዕደሳው ቀጥሎ አሁን የተመዘገበውና በምዝገባ ስርዓት ውስጥ የቆየው ሀብት ላይ የታዩ ለውጦችን መሠረት በማድረግ እንደገና ምዝገባ እንደሚካሄድም አመልክተዋል፡፡

የተመዘገቡ ሀብቶችን በተመለከተ መረጃ የሚፈልግ አካል መቼ ማግኘት እንደሚችል ከአውራምባ ታይምስ ጋዜጣ ለቀረበላቸው ጥያቄ አቶ ግርማ ምላሽ አሁን እየተመዘገበ ያለው ሀብትና ንብረት ምን ያህል ትክክል ነው? የሚለው ከተጣራ በኋላ በቀጣዩ ዓመት ለመረጃ ፈላጊ አካል ግልፅ እንደሚደረግ አብራርተዋል፡፡

“በአፍሪካ አገሮች ያሉ ብዙ የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናቶች ከሙስና ጋር በተያያዘ ክስ የሚቀርብባቸው ከስልጣናቸው ከወረዱ በኋላ ነው፡፡ ኮሚሽኑም ከፍተኛ የመንግስት ሹማምንቶችን አይነካም የሚሉ ወገኖች አሉ፡፡ በከፍተኛ የመንግስት ሹመኞች ላይ ጠንክራችሁ ሙስናን የማጋለጥ አቅማችሁ ምን ያህል ነው? በማለት አውራምባ ታይምስ ላቀረበላቸው ጥያቄ፣ አቶ ግርማ የኢትዮጵያ ሁኔታ ከሌሎች አፍሪካ አገሮች የተለየ እንደሆነ ገልፀዋል፡

በኤልያስ ገብሩ

ኤልሻዳይ ሪሊፍ ኤንድ ዴቨሎፕመንት አሶሴሽን በመላ አገሪቱ ተግባራዊ የሚሆነውን ፕሮጀክት ለማሳካት የሚያስፈልገውን በጀት ለማሰባሰብ የተለያዩ የገቢ ማሰባሰቢያ ስልቶችን ነድፎ እየተንቀሳቀሰ ላይ እንደሚገኝ ጠቅሶ፣ እስከአሁን ደረስ ልመናን ለማስወገድ ባደረገው እንቅስቃሴ ላይ አስተዋጽኦ ያበረከቱ ወገኖችን ለማመስገንና ህብረተሰቡንም በእንቅስቃሴው ላይ ተሳታፊ እንዲሆን ለማነሳሳት ሚያዚያ 23/2003 ዓ.ም በሚሊኒየም አዳራሽ

‹‹የምስጋና ቀን›› የሚል ክብረ በዓል ማዘጋጀቱን ገለፀ፡፡

በክብረ በዓሉም ላይ ሚኒስትሮችና የክልል ርዕስ መስተዳድሮች፣ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት፣ ታዋቂ ሰዎችና የኃይማኖት አባቶች በአጠቃላይ ከ8000 በላይ እንግዶች እንደሚገኙም አመልክቷል፡፡ በዝግጅቱ ላይ ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደ ጊዮርጊስና ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ይገኛሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም አትቷል፡፡ ሚያዚያ 22/2003 ዓ.ም ከቀኑ 10፡00 እስከ 12፡00 ሰዓት ድረስ ከ10 ሺህ በላይ የሚሆኑ ወጣቶች የሚሳተፉበት

የሻማ ማብራትና የቃል ኪዳን ፕሮግራም በመስቀል አደባባይ እንደሚካሄድ አሶሴሽኑ ለአውራምባ ታይምስ ከላከው ደበዳቤ ለማወቅ ተችሏል፡፡

እንዲሁም የክብረ በዓሉን ዓላማና ዝግጅት እንዲሁም ልመናን ለማስወገድ በተደረገው እንቅስቃሴ የተገኙ ውጤቶችን አስመልክቶ ሚያዝያ 19/2003 ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ላይ የሰራተኛና ማሕበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትርና ባለድርሻ አካላት በሚገኙበት ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣል፡፡

‹‹የምስጋና ቀን›› የሚል ክብረ በዓል ይዘጋጃል

፡ በሕብረተሰቡ ውስጥ የሙስና ችግር መኖሩን አውቆ መንግስት በራሱ ግምገማ በመነሳት ተቋም በማደራጀት ሙስናን ለመዋጋት እየሰራ እንደሚገኝ፣ ተቋማቸው የሙስና ወንጀል ከተፈፀመ ትንሽ ትልቅ ባለስልጣን ሳይል በራሱ የምርመራ ዘዴ በመጠቀምና በሌሎች ጥቆማዎችን መሠረት ከክስ ሂደት ተነስቶ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ላይ አስፈርዶ ማሳስሩን ዳይሬክተሩ አብራርተዋል፡፡

የ9 ሺ የመንግስት ባለሥልጣናትና ሹመኞች ሀብት ተመዘገበ

የዋጋ ግሽበት እየተባባሰ ነው

Page 20: ethioforum.orgethioforum.org/wp-content/uploads/2011/04/Awramba_Times... · 2011-04-11  · ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ 4 ፊ ቸ ር አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 164 ቅዳሜ ሚያዚያ 15 2003ጤ ና20

በኤልያስ ገብሩ

አልኮል መጠጥን በጭራሽ ከማይጠጡና በጣም አብዝተው ከሚጠጡ ሰዎች ይልቅ፣ በመጠኑ የሚቀማምሱ የተሻለ ጤናና ረዥም ዕድሜን እንደሚኖሩ የድረ-ገፅ መረጃዎች ያስረዳሉ፡፡ እንደ ቢራ፣ ወይን፣ ውስኪ፣ ቮዳካ፣ እና ሌሎች የመጠጥ አይነቶችን መጥነው የሚጠጡ ግለሰቦች በልብ፣ በድንገተኛ የደም ዝውውር መቆም (ስትሮክ)፣ በስኳር፣ በመገጣጠሚያ አጥንቶች ዕብጠት/የጤና ዕክል፣ በሚያድግ የወንድ የዘር ፍሬ ዕጢ፣ አልዛይመርን ጨምሮ በአዕምሮ ሕመምና ጉዳት ምክንያት የሚደርስ የአዕምሮና የአስተሳሰብ መዛባት (ዲሜንሽያ) እና በሌሎች ዋና ዋና የካንሰር ሕመሞችና በሽታዎች የመጠቃት ዕድላቸው አነስተኛ መሆኑ ይገለፃል፡፡

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን የሕፃናትና ቤተሰብ ጉዳዮች የምግባረ ሰናይ ጠቅላላ ሆስፒታል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊ፣ የውስጥ ደዌ ስፔሻሊስትና በሙያቸው 22 ዓመታት ያገለገሉት ዶ/ር ኪዳኔ መለስ፣ አልኮል መጠጥን አስመልክቶ ለአውራምባ ታይምስ ሙያዊ አስተያየትና ምክራቸውን ለግሰዋል፡፡

‹‹ማንኛውም ነገር መጠኑ ከበዛ ይጎዳል›› የሚሉት ዶ/ር ኪዳኔ፣ መርዝም በጠብታ መድኃኒት

እንደሚሆን ጠቅሰው፣ መጠጥ ውግዝና ‹‹መጠጣት የለበትም ወይም አያስፈልግም›› የሚባል ነገር አለመሆኑንና ሰዎች መጠጥን እንደ መጥፎ ነገር አድርገው መናገር እንደማይችሉ ገልፀዋል፡፡ ነገር ግን፣ አልኮል መጠጥ ከበዛና በተደጋጋሚ ከተወሰደ፣ የሱስ ዓይነት ፀባይ ካለውና ሱስ ከሆነ በጤና፣ በኢኮኖሚ፣ በማሕበራዊ ኑሮና በሥራ ጉዳይ ላይ ተፅዕኖ እንዳለው ያስረዳሉ፡፡

በአሜሪካን አገር ‘ናሽናል ኢንስቲትዩት ኦን አልኮል አቢውዝ እና አልኮሊዝም’ (NIAAA) የተባለ ተቋም በጥናቱ፣ መጠነኛ የአልኮል መጠጥ አወሳሰድ ከልብ ጋር ተያያዥ የሆኑ አጠቃላይ በሽታዎችና በተለየ ሁኔታ ለልብ ደም ከሚያቀብለው የደም ማዘዋወሪያ ቱቦ (ኮሮናሪ አርተሪ) ጋር ጠንካራና ያልተቋረጠ ግንኙነት ያለው መሆኑን አስታውቋ፡፡ ተቋሙ በመጠን መጠጣት ለልብ ጤና ጥቅም ለማግኘትና የተሻለ ዕድሜን ለመኖር እንደሚረዳ ከመጠቆም ባሻገር፣ ለልብ በሽታ ተጋላጭነትን ከ40-60 በመቶ ያህል መቀነስ እንደሚቻል ያስገነዝባል፡፡

በአሜሪካን ከልብ ጋር ተያያዥ የሆኑ በሽታዎች ለሞት መንስዔነት ቁጥር አንድ እንደሆኑና፣ በልብ በሽታም በየዓመቱ አንድ ሚሊዮን

አሜሪካውያን ለህልፈተ ሕይወት የሚዳረጉ መሆናቸው ጉዳዩ ትኩረት የሚያሻው ወሳኝ መሆኑን መረጃዎች ያስረዳሉ፡፡ የአሜሪካን የልብ ማሕበር የምግብ ስርዓት ኮሚቴ በበኩሉ እንደ መጠጡ ዓይነትና ይዘት ዘወትር አንድ ወይም ሁለት ብርጭቆ የሚጎነጩ ሰዎች ለሞት ያላቸው ተጋላጭነት ዝቅተኛ እንደሆነ አስረድቷል፡፡

‹‹መጠጥ ከሰዎች ጋር ተግባብቶ ለመነጋገርና ራስን ለማዝናናት አልፎ አልፎ ቢወሰድ መጥፎ ነገር ነው የሚባል አይደለም›› የሚሉት ዶ/ር ኪዳኔ፣ ከበዛና በተደጋጋሚ ከተወሰደ ሱስ ሆኖ አደገኛ እንደሚሆን በድጋሚ ገልፀው፣ ‹‹መጠጡ ሱስም ባይሆን እንኳን በተደጋጋሚ በየቀኑ በሚወስዱ ሰዎች የተወሰነ የሰውነት ክፍሎቻቸው ላይ ጉዳት የማድረስ አቅም አለው›› ሲሉ ሙያዊ ሀሳባቸውን ይለግፃሉ፡፡ አያይዘውም፣ ‹‹በተለይ በአገራችን፣ አብዝተው የሚጠጡ ሰዎች ለጉበት በሽታ በጣም በጣም የተጋለጡ›› እንደሚሆኑና በሽታውም በአገሪቱ በጣም እየተስፋፋ እንደሚገኝ አስረድተዋል፡፡ በመሰል በሽታ የተያዙ ሰዎች ፊት ላይ የተለያዩ የበሽታው ምልክቶች እንደሚታዩ፣ አልኮሊክ ሂፒታይተስ ቢ ለሚባል የታወቀ በሽታ እንደሚጋለጡ፣ እንዲሁም ድካም፣ የልብና የነርቭ ሕመሞች ሊከሰቱባቸው እንደሚችሉ ያስረዳሉ፡፡

መጠጥን መመጠንየሕክምና ዘርፍ ተመራማሪዎች

የተመጠነ የመጠጥ አጠጣጥን በቀን ከአንድ እስከ ሦስት ብርጭቆ ወይም ጠርሙስ ያህል (እንደመጠጡ ዓይነትና ይዘት) መውሰድ አድርገው ይገልፁታል፡፡ በቀን ውስጥ የአንድ ብርጭቆ ወይም ጠርሙስ መጠጥ ግማሹን ብቻ መውሰድ በጣም አነስተኛ የጤና ጠቀሜታ ብቻ እንደሚሰጥ፣ ቁጥራቸው በዛ ላሉ ግለሰቦች አራት ወይም አምስት ብርጭቆ/ጠርሙስ አልኮል መጠጣት መጠነኛ ሊሆን ቢችልም፣ በዕድሜ አነስተኛና ደከም ላሉ ሰዎች እንደሚበዛባቸው መረጃዎች ይጠቅሳሉ፡፡ በአጠቃላይ ሴቶች ባላቸው አነስተኛ አካላዊ መጠንና ሥነ-ሕይወታዊ ልዩነት ምክንያት፣ አማካኙ ወንድ ከሚወስደው የአልኮል መጠን ከ25-30 በመቶ ያህል ያነሰ እንደሚጠጡ ይገለፃል፡፡

በአልኮል መጠጥ መደበኛ ደረጃ መሠረት 12 ኦውንስ የተለመደው የቢራ ጠርሙስና አምስት ኦውንስ ደግሞ የአንድ ወይን መጠጫ

ከመዲናችን ጉልላት፤ከሀገራችን ውበት፤

ከአዋሽ ታወርስ፣ ከማማው፤የዋስትናው ባላባት መልዕክት እነሆ!

እንኳን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስየትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ

ታማኝና ቅን አገልጋይዎ አዋሽ ኢንሹራንስ በዓሉ የሠላምና የደስታእንዲሆንልዎ ምኞቱን ሲገልፅ በታላቅ አክብሮት ነው፡፡

አዋሽ ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ.አድራሻ አዋሽ ታወርስ በድሉ ሕንፃ አጠገብ ስልክ 011 557 00 01ፋክስ 011 557 02 08ፖ.ሣ.ቁ. 12637 ኢ-ሜይል - [email protected]

መጥነው ይጎንጩአልኮልን

ብርጭቆ መጠን ጋር እኩል ነው፡፡ እንዲሁም በአንድ ተንፋሽ መጎንጨት (ሻት) መጠኑ አንድና አንድ ከግማሽ ኦውንስ ሲሆን፣ በምሳሌነትም በዚህ በአልኮል መጠጥነታቸው የተረጋገጡት እንደ ቮድካ፣ ተኪላ ወይም ራም የተባሉት ይጠቀሳሉ፡፡

‘ናሽናል ኢንስቲትዩት ኦን አልኮል አቢውዝ ኤንድ አልኮሊዝም’ የተመጠነ የአልኮል አወሳሰድ ደረጃን በማውጣት ሴቶች በቀን ከ1-2፣ ወንዶች ደግሞ ከ2-4 ብርጭቆ/ጠርሙስ ያህል አልኮል መጠት መውሰዳቸው ለሞት ያላቸውን ተጋላጭነት ይበልጥ እንደሚቀንሰው በዓለም ዙሪያ በሚገኙ 1,105,834 ወንዶችና ሴቶች ላይ 34 ጥናቶች በማድረግ ማረጋገጡን ይገልፃል፡፡ በሌላ ጥናት መሠረት በየቀኑ መጠነኛ የሆነ መጠጥ የሚወስዱ ሰዎች ወደ ሆስፒታል የማምራታቸው ነገር ዝቅተኛ መሆኑን ነው፡፡ ‹‹አልኮል መጠጥን ሙሉ በሙሉ ከማይጠጡት ሰዎች በተሻለ፣ መጠነኛ ጠጪዎች ድብርትና አካላዊ ውጥረታቸው እንደሚቀንስና አልዛይመር በሚባል የአዕምሮ ሕመም የመጠቃት ዕድላቸው አነስተኛ ነው፡፡›› ሲል ይኼው ጥናት አመላክቷል፡፡

መጠነኛ የአልኮል መጠጥ መጠጣት ዘወትር ከሚደረግ አካላዊ እንቅስቃሴ ጋር ከታገዘ በዕድሜ መግፋት ምክንያት የሚከሰተውን የጤና ብቃት ማነስ ችግርን እንደሚያሻሽል ዕድሜያቸው 65 እና ከዚያ በላይ በሆኑ 2500 ሰዎች ላይ ለስምንት ዓመታት ያህል የተደረገ ጥናት ማሳየቱን መረጃዎች ያሳያሉ፡፡

አልኮል በሰውነታችን ውስጥ ያለ የኮሌስትሮል መጠን እንዲስተካከል፣ የደም መርጋት እንዲቀንስ፣ ደም እንዲረጋ የሚያደርጉ ፋይብሪኖጅንስ እንዲቀንሱና የረጋው ደም እንዲሟሟ የሚያደርገው ሂደት (ፋይብሪኖሊስስ) እንዲጨምር የማድረግ አቅም ያለው ሲሆን፣ ደምን ወደ ልብ የሚወስዱ ደም ቅዳዎች ኮሮኖሪ አርተሪስ ጫናን እንዲቋቋሙ፣ የደም ፍሰቱ እንዲጨምር፣ የደም ግፊትና በደም ውስጥ የሚገኝ የስኳር መጠን እንዲቀንስ ያደርጋል፡፡ የተለያዩ የካንሰር ሕመም ችግሮችንና የጉንፋን ቫይረሶችን ለመቋቋም እንደሚረዳ በአሜሪካን የተደረጉ የምርምር ውጤቶች ይገልፃሉ፡፡

አልኮል መጠጥን በተደጋጋሚ መወሰዱ በጤና ላይ ከሚያስከትለው ጉዳት በተጨማሪ፣ አልፎ አልፎ በብዛት ሲጠጣ ለንዴት ዳርገው ለጠብ፣ ለግጭትና ለድብድብ፣ እንዲሁም ለመኪና አደጋ እንደሚያጋልጥ የሚናገሩት የአገራችን የውስጥ ደዌ ስፔሻሊስት ዶ/ር ኪዳኔ ናቸው፡፡ ‹‹ሰዎች በተቻለ መጠን አልኮል ባያዘወትሩ ይመረጣል፡፡ ሰዎች መጠጥ ባዘወተሩ ቁጥር ሰውነታቸው እየለመደና የመልመድ አቅማቸውም እየዳበረ ይሄዳል፡፡ ልምዱ የሌለው ሰው ደግሞ በቀላሉ ለስካር ይጋለጣል፡፡ በመጀመሪያ በሶስት ቢራ የሚሰክር ሰው፣ እየለመደው ሲሄድ ይበልጥ ጠጪ ይሆናል›› ሲሉ ዶክተሩ ይመክራሉ፡፡

ሰውነታችን መጠጥን በምግብ መልክ የሚቀበልበት መንገድ እንዳለና የሚሰጠው የራሱ ጥቅም እንዳለው በመጥቀስ ለሰውነት ጠቃሚ የሆኑ ምግቦችን ከሌሎች ነገሮች ማግኘት ከተቻለ የግድ መጠጥ መጠጣት ባያስፈልግም ሳይበዛ መውሰዱ ችግር እንደሌለው ዶ/ሩ ይናገራሉ፡፡ በተጨማሪም፣ በዕድሜ የገፉ ሰዎች መጠነኛ የአልኮል መጠጥ የሚወስዱ ከሆነ፣ የተወሰነ ኃይል እንደሚሰጣቸውና ጥሩ እንቅልፍ እንዲያገኙ እንደሚያደርጋቸው አልሸሸጉም፡፡ ‹‹ሰዎች ካሉባቸው የጤና ችግሮች አኳያ መጠጥን ለይተው መጠቀም አለባቸው፡፡ የሰውየው አቋምና ዘረ-መል (ጄኔቲክ) ሁኔታ፣ እያንዳንዱ ሰው ስሪቱ እንዴት ነው የሚለው በደንብ መጠናት አለበት፡፡ ለሁሉም ሰው መጠጥ ጥሩ ነው ለማለት አስቸጋሪ ነው›› ሲሉ ሙያዊ አስተያየታቸውን የሚሰጡት ዶ/ር ኪዳኔ፣ ብዙ ክርስቲያኖች በአብይ ጾም ወቅት ከብዙ ነገር ተለይተው በመቆየታቸው፣ በአንዴ ብዙ ወደ መብላትና መጠጣት ማምራት እንደማያስፈልጋቸውና ያንንም እንደማያደርጉት ያላቸውን እምነት ይገልፃሉ፡፡

በመጨረሻም ምግብ ከተበላ በኋላ መጠጥ መጠጣት የተበላውን ለማንሸራሸር ስለሚጠቅም፣ ከምግብ በኋላ ቢወሰድ አልኮሉ ወዲያው ወደ ደም ውስጥ እንዳይገባ እንደሚከላከል በመጠቆም፣ ‹‹በባዶ ሆድ መጠጣት ለጨጓራና ለሌላ ችግር ያጋልጣል፡፡ ከምግብ በኋላ ቢጠጣ የተሻለ በመሆኑ፣ አመጋብና አጠጣጥን ማመጣጠን ይገባል፡፡ መጠጥ አብዝቶ መጠጣት ጉዳት ሊያደርስብን ይችላል ብሎ ማሰብ አለብን፡፡ ለምሳሌ፣ በጀርመን አገር አንድ ሰው ቢራን በቀን ምን ያህል መውሰድ እንዳለበት ስለሚታወቅ በዚያ መሠረት ይወስዳል›› ሲሉ በምሳሌ አስደግፈው ጠንካራ ምክራቸውን ለግሰዋል፡፡

‹‹ሰዎች በተቻለ

መጠን አልኮል

ባያዘወትሩ ይመረጣል፡

፡ ሰዎች መጠጥ

ባዘወተሩ ቁጥር

ሰውነታቸው

እየለመደና የመልመድ

አቅማቸውም

እየዳበረ ይሄዳል፡

፡ ልምዱ የሌለው

ሰው ደግሞ በቀላሉ

ለስካር ይጋለጣል፡

፡ በመጀመሪያ በሶስት

ቢራ የሚሰክር ሰው፣

እየለመደው ሲሄድ

ይበልጥ ጠጪ

ይሆናል››

Page 21: ethioforum.orgethioforum.org/wp-content/uploads/2011/04/Awramba_Times... · 2011-04-11  · ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ 4 ፊ ቸ ር አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 164 ቅዳሜ ሚያዚያ 15 2003ስ ፖ ር ት22በአቤል ዓለማየሁ

ከ1993 - 2003አቶ ታምራት ግርማ እና ወ/ሮ ዘነበች ዓለማየሁ ለ10ኛ ዓመት የጋብቻ በዓላችሁ እንኳን አደረሳችሁ!!! ወንድማችሁ ቴዎድሮስ ወ/ገብርኤል

እንኳን አደረሳችሁ!

1993

2003

ከእናንተ አንባቢያን ጋር ለመገናኘት የሳምንታዊ ድግሳችን የምናጠናቅቅበት ቀን በመሆኑ በእለተ አርብ ወደ ቢሯችን ብትመጡ የውክቢያው ወላፈን ገረፍ ሳያደርጋችሁ

አይቀርም፡፡ ባለፈው ሳምንት አርብ ይህን ሳምንታዊ ሁነት አጠናቀን ከባልደረባዬ ኤሊያስ ገብሩ ጋር ‹‹ሻይ፣ቡና›› ለማለት ከደረስንበት የካዛንቺሱ ትሪዮ ካፌ ከታደመን በግምት 25 ደቂቃ ቢሆነን ነው፡፡ ከምሽቱ ሁለት ሰዓት ከ18 ደቂቃ ላይ ወደ እጅ ስልኬ የተንደረደረው ጥሪ በጭምጭምታ ከምሰማው አንፃር ሊሆን እንደሚችል የገመትኩት ቢሆንም ‹ኧረ ባክህ?›› ብዬ በመገረም ስጠይቅ አይኖች ትኩረታቸውን ወደ እኔ ከማድረግ ለማምለጥ እድል አልነበራቸውም፡፡

የደወለልኝ ወዳጄ የተሰናባቹ የኢትዮጵያ ብሕራዊ ቡድን አሰልጣኝ ኢፌ ኦኑራ የቅርብ የሚባል ሰው ነው፡፡ ‹‹ኢፊ አሁን ደውሎ ነገረኝ፤ አሰናበቱት፡፡ ጉዳዩ ገና ይፋ ስላልሆነ ለማንም አትናገር፡፡ ለእሱም አትደውልለት›› ሲል ‹‹ለማንም እንዳትናገር›› ተብሎ የተነገረውን መረጃ ‹‹ለማንም አትንገር›› ብሎ አቀበለኝ፡፡ በወቅቱ ማተሚያ ቤት መግባታችን በጀ እንጂ ይህን የመሰለ ‹‹ጮማ›› ዜና ከግራ ከቀኝ መረጃ በመጠናቀር እምረው ነበርን? ስል ጠየቅኩ፡፡ ‹‹አልምረውም ነበር፡፡›› ግን ለምን ተባረሩ?

ቁጡው ሰውኢፊ ኦኑራን በአንድ ቃል አማርኛ

መግለፅ ከባድ ይመስለኛል፡፡ በጣም ሳቂታና ተጨዋች ናቸው፡፡ ይህን የሚያደርጉት ከሚያዙባቸው ተጨዋቾች ጋር ብቻ እንዳይመስላችሁ ከፌዴሬሽኑ ቅጥር ግቢ የውጪ በር ጀምሮ ከሚያገኝዋቸው የጥበቃ ባለሙያዎች ትጥቅና ኳስ ከሚሰበስቡ ልጆች ጋር ሲቀልዱ ትመለከቷቸዋላችሁ፡፡ በድንገት

እንደሚፈጥሩት ቀልድ ሁሉ በድንገት ይቆጣሉ፡፡ ከሦስት ሳምንት በፊት ለቃለ ምልልስ ባገኘኋቸው ወቅት ‹‹የኢትዮጵያ እግር ኳስ ያጣውን ስኬት ማስገኘት የሚችል የአሰልጣኝነት ልምድ እንደሌለዎት የሚናገሩ አሉ...›› ብዬ ጥያቄዬን ሳልጨርስ አይናቸውን አጉረጥርጠው ሀሳቡን እንደማይቀበሉት የገለፁበትን የቁጣ መንፈስ ብታዩ በቶሎ ሳቃቸው ይመለሳል ብላችሁ አትገምቱም፡፡ ቀጣዩ ጥያቄዬ ላይ ግን ወዲያው ወደ ሳቃቸው ተመለሱ፡፡

በልምምድ ሜዳ ላይ ተጨዋቾቻቸውን የሚያስተምሩት ‹‹ዘና›› እያደረጉ ቢሆንም ተደጋጋሚ የሆኑ ስህተቶችን ሲመለከቱ በቁጣቸው ያርቃሉ፡፡ በእሳቸው ዙሪያ የመገናኛ ብዙሐን አቋም ምን እንደሆነ ጠንቅቀው ያውቃሉ፡፡ የተከፈተባቸውን ዘመቻ እንኳን ምንጭ ከየት እንደሆነ እርስዎ ከሚጠረጥሩት በላይ እሳቸው ያውቃሉ፡፡ ሁኔታው ግን ቁጡ አላደረጋቸውም፡፡ በሁለት ክፍልፋይ ብቻ መገናኛ ብዙሐን ለዩ ጥሩዎቹ እና መጥፎዎቹ በማለት፡፡

በፍቅር እንደመጡ በፍቅር መለየትን መርጠዋል፡፡ በመጨረሻው ሰዓት ቁጡነታቸው በማንም እና በምንም ላይ አልተንፀባረቀም፡፡ ‹‹በድጋሚ አንድ ቀን እንደምመለስ አስባለሁ፡፡ ሁሌም በምሄድበት ስለ ኢትዮጵያ ጥሩ እንጂ መጥፎ ነገር አላወራም›› ሲሉ ስለነበራቸው ቆይታ አመስግነው በሳቅ ታጅበው ‹‹ቻው›› ማለትን ብቻ መርጠዋል፡፡ ብዕራቸው ሰይፍ አለመምዘዙ የሚታየው ግን በሂደት ይሆናል፡፡

ኢ.እ.ፌ - ስህተት የማያጣው ቤት

የኢትዮጵያ እግር ኳስ የሰከነ እና ጠቃሚ ውሳኔ የሚያሳልፍ አመራር ለማግኘት ማሰነ እንጂ ‹‹እፎይ›› የሚያስብለው የቁርጥ ቀን ልጅ ማግኘት አልቻለም፡፡ ዛሬም በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ውስጥ ታሪካዊ ስህተቶች እየተፈፀሙ ነው፡፡ በእኔ አስተያየት የኢፊ ኦኑራ ድንገተኛ ስንብትም እዚሁ ውስጥ የሚደመር ነው፡፡ ስኮትላንዳዊው አሰልጣኝ ከ82 ሚሊየን በላይ ህዝብ የሚወክለውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለማሰልጠን ፊርማቸውን ያኖሩት ማንነታቸው ተጠንቶ አሊያም በሚመለከተው ባለሙያ ተጠቁመው እና

ተገምግመው አለመሆኑ የትልቁ ታሪካዊ ስህተት የመጀመሪያው መጀመሪያ ነው፡፡ በርግጥ ኦኑራ የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር የማሰልጠን ፍቃድ ስላላቸው እንኳን በኢትዮጵያ ይቅርና በምድረ እንግሊዝም የትልልቅ ቡድኖች አሰልጣኝ መሆን ይችላሉ፡፡ [የያዙት ሰርተፍኬት ግዙፍነት ብቻ ግን ለአገሬ እግር ኳስ ተመራጭ ያደርጋቸዋል ብዬ አላስብም፡፡] ለዚህ ነው ከብት ባለበት የልምምድ ሜዳ ሲወሰዱ፣ ምቹ የመጫወቻ ሜዳ ሲያጡ፣ ጉዳይ አስፈፃሚ ሲሆኑ ‹‹ግር›› ያላቸው፡፡ ከትውልድ አህጉሩ አፍሪካ ርቆ በእግር ኳስ መሠረት ልማት ጫፍጋ በምትገኝ አገር (እንግሊዝ) ለተገኘ ሰው ይህ ሁሉ ቢያስደንቀው አያስገርምም፡፡ [ልዩነት ይኖራል ብሎ ቢያስብ እንኳን ይህን ያህል የተንቦራቀቀ ይሆናል ብሎ ማሰብ አስቸጋሪ ነው፡፡] አስገራሚው በእግር ኳስ መሰረት ልማት ችግር ጎርፍ እየተወሰደ ስላለ አገር እግር ኳስ ምንም ግንዛቤ የሌለውን ሰው አምጥቶ የሾመው ነው፡፡

እናም ምንም ትርፍ ባላስገኘው የኢፊ ኦኑራ መምጣትና መሄድ የአቶ ሳህሉ ገ/ወልድ ካቢኔ ኃላፊነት ሊወስድ ግድ ይለዋል፡፡ ከኦኑራ የፊርማ ማኖር ይበልጥ የፊርማ መቅደድ (ስንብቱ) ሁኔታ መነጋገሪያነቱ ያመዝናል፡፡ አርብ ምሽት የስንብት ደብዳቤ ሰጥቶ ሰኞ ከአገር እንዲወጣ ከማለት ቀድሞ በጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ ለመገናኛ ብዙሐን ለመስጠት ፌዴሬሽን ቁርጠኛ መሆን ይገባው ነበር፡፡ ከሁሉ በላይ አሳዛኙ ነገር አገር ለቀው እስከሚሄዱ ለሁለት ቀን መታገስ አቅቶ መኪናቸውን መቀማት፣ የምግብና የመኝታ አገልገሎታቸውን ማቋረጥ የእንግዳ ተቀባይነት መልካም ገፅታን እንደሚያጎድፍ የ‹‹መልካም ገፅታ›› ተቆርቋሪዎቹ ሊያስቡበት በተገባ ነበር፡፡

መልዕክቴ!!!በኦኑራ ዙሪያ የሚወሩ ወሬዎች

ውስጥ ብዙዎቹ የዓለም አቀፍ የእግር ኳስ እውነታ ላይ መሰረት ያደረጉ አልነበሩም፡፡ የሚከፈላቸው 13 ሺህ ዶላር [ከ220 ሺህ ብር በላይ] ወርሐዊ ደሞዝ የሚያንጨረጨራቸው ሀሳባቸን ሲገልፁ ይሰማል፡፡ [አሀዙ ከምክትል አሰልጣኛቸው 73 እጥፍ በላይ ነው] በርግጥ ይሄ ገንዘብ ለብዙሐኑ ኢትዮጵያውያን ቀላል

ገንዘብ አይደለም፡፡ በዓለም አቀፍ የእግር ኳስ የገበያ ልውውጥ ላይ ስናየው ብዙ አስገራሚ አይሆንም፡፡

ኢትዮጵያ ላይ አራት ጎል ያዘነበችው ናይጄሪያ አሰልጣኝ ሳምሶን ሱያሲያ ከበተጨማሪ ጥቅማጥቅም ጋር የኦኑራን ሦስት እጥፍ ወርሃዊ ገንዘብ ኪሳቸው ይከታሉ፡፡ እናም በብዙሐኑ ኢትዮጵያዊ ገቢ ጋር እያነፃፀሩ ስሌት ውስጥ መግባት ዓለም አቀፉን እግር ኳሱ ገበያ ካለማወቅ የሚመጣ ነው፡፡

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የመክፈል አቅም የለኝም ብሎ ደጅ የጠናቸው ሼህ መሀመድ አላሙዲ የአሰልጣኙን ወርሃዊ ደሞዝ ብቻ ሳይሆን አስፈላጊ ነገሮችን ሁሉ እንዲሟላ በመፍቀድ ቅጥሩ አውን ሆነ፡፡ የሚገርመው ግን ሼሁ ለከፈሉት እና ለሚከፍሉት ብር ሌሎችን ለምን እንዳሳከካቸው ነው፡፡

ለማንኛው ኦኑራ ወጡ፤ ኦኑራ ሄዱ፡፡ ላለፈው እሁድ በራስ ሆቴል የተሰናበታቸው ተጨዋቾች አይናቸው እንባ አቀረረ፡፡ (በመባረራቸው የሚያተርፉ (በተለየ መልክ) ሳይደሰቱ አይቀርም) የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ታሪካዊ ስህተት መስራቱን ቀጥሏል፡፡ በቅጥራቸው ላይ የተሰራው ስህተት በስንብታቸውም ላይ ተደገመ፡፡ በቅጥራቸው ታላቅነታቸው ተመስክሮለት የተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ለስንብታቸው ሳይደረግ ቀርቷል፡፡ ኢትዮጵያውያን ጋዜጠኞች በተገኙበት አልሆነም እንጂ ‹‹ብዕር ከሰይፍ ይሰላል›› እንደሚባለው እጃቸው ላይ ባለው ብዕር በመደበኛነት በሚፅፉበት ፎር ፎርቱ እና በሌሎች ላይ ሊገልፁ እንደሚችሉ አይረሳ፡፡

አሁንም የቁልቁለት ጉዞው ቀጥሏል፡፡ ሁለት ቢጫ ያየን ተጨዋች ዓመት አግዶ ግማሽ ዓመት ካለፈ በኋላ ስህተትን ማመን፣ መሠረታዊ ነገሮች ወይም ሊመቻቹለት ቃል የተገባላቸው ነገር እውን ባለመሆኑ የመልቀቅ ጥያቄ ያቀረበ ቴክኒካል ዳይሬክተር ቀርቦ ምክንያቱን ሳይጠይቁ ‹‹ተቀብለናል›› ብሎ ግልግል ማለት ፌዴሬሽኑን የስህተት ቤት አስመስሎታል፡፡ ከ82 ሚሊየን በላይ ህዝብን የሚወክል ፌዴሬሽን በግለሰቦች ፍላጎት ላይ ብቻ መሠረት ባደረገ ውሳኔ ሲተራመስ የሚመለከተው አካል በዝምታ ሊያልፈው አይገባም፤ ‹‹ኧረ ስህተት በዛ!›› በሏቸው፡፡

በአቤል ዓለማየሁ

የኢፊ ኦኑራ ስንብት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ሌላው ታሪካዊ ስህተት

Page 22: ethioforum.orgethioforum.org/wp-content/uploads/2011/04/Awramba_Times... · 2011-04-11  · ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ 4 ፊ ቸ ር አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 164 ቅዳሜ ሚያዚያ 15 2003

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

23

}SdeK¨< Ÿ}c\ ð×” ¾h¨` ¨<H TVmÁ U`„‹ ÃÖ”kl ƒ¡¡K—¨<” ¾w^²=M

¾h¨` ¨<H TVmÁ ÃÖkS<

Brazmart International General Trading Plc. Address!- •Urail Alem Brehan Plaza 1st Floor #106 1. ›<^›?M u?} ¡`e+Á” ›”vu= ¯KU w`H” ýL³ 1— öp u=a lØ` 1062. Ku< ›Åvvà òƒ Kòƒ dS<›?M I”íuT”—¨<U ¾vD”vD“ ¾h¨` u?ƒ n ‹ SgÝ“ ”Ç=G<U u¾I”í SX]Á SÅwa‹ ÁÑ–< M::

c=Ѳ< ƒ¡¡K— ¾w^²=M U`ƒ SJ’<” Á[ÒÓÖ<! Tel. 251-11 552 -6011 /12 Fax 251-11-5526012

ውስጥ የማልወደው የጋዜጠኝነት ሥራዬን ነው፡፡ ለምን?ምክንያቱም ጋዜጠኝነት ማለት ምስክርነት ማለት ነው፡፡ ምስክርነት ደግሞ ብዙ ሥነ-ምግባር ይጠይቃል፡፡ ከዚያም ውጭ ደግሞ ብዙ ማወቅ የማይገቡኝን ሚስጢሮች አወቅኩ፡፡ አየሁ፡፡ ሰማሁ፡፡ እነዚህ ምስጢሮች ፈታኞች ናቸው፡፡ልናገራቸውም ይከብደኛል፡- ሙያዬ ሆኖ ማለት ነው፡፡ በቃ! ከዚያ በኋላ አበቃ፡፡ ትዕዛዝ ምናምን የሌለበት ሥራ አሰብኩና ራሴን ወደ አሳታሚነት ወሰድኩት፡፡ ምናልባት የጋዜጠኝነቱን ህይወት ለመጥላት ምክንያት የሆነሽ?(አቋረጠችኝ) አይ!.. ብዙ ነገሩ ምቹ አይደለም፡፡ እንደገና ደግሞ አደጋ ይበዛበታል፡፡ እኔ ደግሞ መኖር የምወድ ሰው ስለሆንኩ አደጋ እጠላለሁ፡፡ እጣላለሁ፣ እጮሃለሁ ምናምን በቃ!!፡፡ እኔ ይህንን የማደርገው ግፍ ስለማልወድ እንጂ በጣም ሰላማዊ ህይወትን የምመርጥ ሰው ነኝ፡፡ በጋዜጠኝነት ስሰራ አንድ ቀን ተከስሼ አላውቅም፡፡ የሙያውን ሕግጋት በጣም ነው የማከብረው፡፡ ስንዱ፣ በቅርቡ ያሳተምሽው ‹‹አርተር ራምቦ›› መፅሐፍ ስንተኛ መፅሐፍ ነው? ስምንተኛ!የእሱን ታሪክ ለመተርጎምና ለማሣተም ያነሳሳሽ ነገር ምንድነው?ፈረንሳውያን ጓደኞቼ በጣም ያመልኩታል፡፡ እሱ ምን ስለሆነ ነው ይኼን ያህል የሚያመልኩት? አልኩ፡፡ ማለት በስም አውቀዋለሁ፡፡ ሐረር ውስጥ ሙዚየም እንዳለው አውቃለሁ፡፡ ግን ይኼን ያህል ድንቅና የሚመለክ ሰው ነው ብዬ አላስብም ነበር፡፡ እና... ስለ እሱ ስራዬ ብዬ አነበብኩ፡፡ በጣም ድንቅ ሆኖ አገኘሁት፡፡ ራምቦ የዓለማችን ድንቅ ሰው ነው፡፡ በህይወት ታሪኩ ዙሪያ ከ400 በላይ መፅሐፍ የተፃፈለት፣ በሆሊውድ ፊልም የተሰራለት ለዚያውም ራምቦን የወከለው ዲካፕሪዮ ነው፡፡ የሚገርም ህይወት የኖረ ሰው ነው፡፡ በቃ! በፍቅር የሰራሁት ሥራ የአርተር ራምቦን መፅሐፍ ነው፡፡ አሳታሚነት ገንዘብ ይጠይቃል፡፡ አንቺ ደግሞ 8ኛውን መፅሐፍ ለህትመት አብቅተሻል፡፡ አሳታሚ ማድረግ የሚችል ገንዘብ ከየት አመጣሽ?መጀመሪያ የ”መኃልየ መኃልየ ዘ-ካዛንቺስ”› ዕትም ከቤተሰብ ተበድሬ ነው፡፡ ያውም ለሌላ ስራ ብዬ፡፡ እና... አሰራሩ ከባድ ስለሆነ ገቢውን በትክክል ባላውቅም ጥሩ ፍራንክ ካገኘሁበት መፅሐፍ አንዱ እሱ ነው፡፡ በእሱ ትርፍ ወዲያው የራሴን “ከርቸሌ” እና የባሴ ሀብቴን “ወንድም ጌታ” አተምኩ፡፡ ያኔ ታነቅሁ፤ ማለት ገንዘብ አጠረኝ፡

፡ እገታው ምንም ዓይነት ጥንካሬ ቢኖረውም፣ የፈለገውን ዓይነት ትጥቅ ቢታጠቅም መንገደኞቹ አንገታቸውን ደፍተው የሚንሸራሸሩ አልነበሩም፡፡

የተሳፈሩበትንና ያለሙትን ሃሳባቸውን የሚያሳኩበት መርከባቸውን ሊነጥቅ አሊያም በአፍጢሟ ሊተክላት የመጣውን አጋች በመግደርደር አላዩትም፡፡ የመታገት ትርጉም በብዙ መልኩ ይተረተራል፤ የመርከቢቱ አንድ ተጓዥ ‹‹ታገተ›› ማለት የመርከቢቱ ወደ ፊት የመፍጠኗ ሂደት በአንድ ሰው መጠን ወደኋላ ይጎተታል፡፡ ጣሊያን መርከቢቱን ለማገት የተመኘችው ከዳር እስከ ዳር ነበር፡፡ በ1928 የተጀመረው የእገታ ጦርነት የመርከቢቱን ሙሉ ክፍል በመቆጣጠር፣ መርከቢቱ በማታውቀው ካፒቴን እንድትነዳ ማድረግ ዋነኛ ዓላማው ነበር፡፡

መንጋዎች እረኛቸውን በሚገባ ያውቁታል፤ አዲስ እረኛ ሊያሰማራቸው የወደደ እንደሆነ በመደንበር ይበታተናሉ፡፡ አዲሱን እረኛም በቀንዳቸው ሊወጉት ይዳዳቸዋል፡፡ የመርከቢቱ ተጓዦችም ከዚህ በፊት የማያውቁት አዲስ ካፒቴን (ፋሺስት)

መርከባቸውን ሊነዳባቸው ሲል ቀንዳቸውን ባይሆንም ጦራቸውን አሹለው ወጡ፡፡ ‹‹አግታችኋለሁ›› ብሎ የመጣውን ወፍ-ዘራሽ ካፒቴን ተፋልመው መርከቢቱን ነፃ አወጧት፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ ግለሰባዊ እገታ አለ፡፡ ግለሰቦች ሰነድ አውጥተው በመሸጥ፣ ‹‹ይገደል›› የሚል ጽሑፍ ያለበት ወረቀት ላይ በመፈረም ... እና በሌሎች መረቦች ይታገታሉ፡፡ የግለሰቦች እገታ እየተጠራቀመ ለመርከቢቱ ጉዞ ፈታኝ ይሆንባታል፡፡

አፄ ዮሐንስ ኢትዮጵያን በሚዘውሩበት ሰዓት በተመሳሳይ ኢስማኤል የተባለው ካፒቴን ግብፅን ይነዳት ነበር፡፡

ይህ የግብፅ መሪ ከሜዲትራንያን አጠገብ ከሚገኘው ከራሱ ግዛት ከግብፅ አንስቶ ከሱዳን ጋር ኢትዮጵያን ጨምሮ ግዛቱን እስከ ሕንድ ውቂያኖስ ለማድረስ ያስብ ነበር፡፡ እስማኤል መርከቢቱን ለማገት ያደረገው ጥረት በሽንፈት ተጠናቀቀ፡፡ መርከቢቱ መታገት የማይፈልግ ተጓዥ በማሳፈሯ ነው ይሄ የሆነው፡፡

... የዛሬዎቹ ግብጾች ቢመቻቸው በናይል (አባይ) ወንዝ አሳበው

ኢትዮጵያን ለማገት ይመኛሉ፡፡ ኢትዮጵያም የእገታውን መረብ እንደ አፄ ዮሐንስ በጣጥሳ መጣል አለባት፡፡

... ብዙ ሰዎችን ያሳፈረች መርከብ በጉዞዋ ላይ እንቅፋት ከገጠማት መናወጧ የማይቀር ነው፡፡ ሀበሾቹ መርከብ በሆነችው ኢትዮጵያ ላይ ተሳፍረዋል፡፡ የሁሉም መንገደኞች ተስፋና ህልም ለየብቻ ነው፡፡ መርከባቸው ግን አንዷ ኢትዮጵያ ናት፡፡

መርከቢቱ በጉዞዋ ላይ ማዕበል ተቀሰቀሰባት፤ ሁሉም መንገደኞች በመርከባቸው መናወጥ ተጨንቀዋል፡፡ ብዙዎቹ መንገደኞች መርከቢቱን ወደሚዘውራት ካፒቴን ጮሁ፡፡

የትራንስፖርት ችግሩ፣ የመብላት ዋስትና አጣብቂኝ ውስጥ መግባቱ፣ ስኳርና ዘይት ለመግዛት ትልቅ እንቅፋት የሆኑ አቅለሽላሽ ሰልፎች በየቦታው መከሰታቸው፣ ጋዜጣና መጽሔቶች የገቡበት የዋጋ ንረት ገደል፣ የመንግስት ሚዲያዎች የሚያወሩት ከበርቻቻ ዜናና ስማቸው ያልተጠቀሱ ሞገዶች (ማዕበሎች) መርከቢቱን (ሀገሪቱን) ሳያሰምጧት በፊት ካፒቴን ኢሕአዴግ፣ በመርከቢቱ ውስጥ ለሚሰማው የነፍስ አድን ጥሪ መላ ያበጅላት፡፡ ‹‹በላዳና በመርከብ መሀል ሰፊ የመሪነት ልዩነት አለ››፡፡

ሞገድ ተለይቷት...

፡ ከዚያዛ ፈረንሳይ ኤምባሲ የባሴ ሀብቴን ሥራ “ሲራኖ”ን ስፖንሰር አደረገኝ፡፡ እሱ ደግሞ “እብዱ”ን ወለደ፡፡ አሁን ደግሞ የ”አርተር ራምቦ”ን ታሪክ ለህትመት አበቃሁ፡፡ እንዲህ እያደረግኩ ነው ያለሁት፡፡ መፅሐፍ በጣም ፍራንክ የሚበላ ስራ ነው፡፡ የሀብታም ሥራ ነው፡፡ ለእንደኔ ዓይነቷ ደሃ የሚሆን ሥራ አይደለም፡፡ ግን... ከተማው ላይ ያለ ፀሐፊን የሚያኮራ አንድ ድርጅት እንዴት አይኖርም? በሚል፣ በእልክ ነው የምሠራው፡፡ የዱሮው ኩራዝ ይሻላል፤ ሳንሱር አድርጎም ቢሆን፣ የሶስትም ይሁን የአምስት ደራሲ ሥራ ለህትመት ያበቃ ነበር፡፡ አሁን የደራሲዎች ዓለም እኮ ጨለማ ነው፡፡ ብቻ ... የቻልኩትን ያህል በማድረግ እየተጋሁ ነው፡፡ የምታሳትሚያቸው መፅሐፎች ይዘት ወጣ ያለ ነው፡፡ ለምሣሌ ‹‹እብዱ››ን መጥቀስ ይቻላል፡፡ ምንድነው ‹‹እብዱ››ን ለማሣተም ያነሣሣሽ? ሰው አብዶ ከመፃፍ በላይ ደግነት አለው!?..ማን ከዚህ በላይ ደግ ሊሆን ይችላል!? እንደ ህሩይ [ደራሲው ነው] ደግ ሰው አይቼ አላውቅም፡፡ ምናልባት ከደራሲዎቹ ጋር ቅርበት ስላለሽ ይሆን? አይደለም፡፡ “እብዱ” እኮ 23 ዓመት እኔ ቁምሳጥን ውስጥ ተቆልፎበት ነው የኖረው፡፡ አውግቸው (ህሩይ) ከዛ በኋላ ሲታመም የነበሩትን ፋይሎች በሙሉ ነው ሰብስቦ ያቃጠላቸው፡፡ ከ23 ዓመት በኋላ ይህቺም መረጃ የተገኘችው እኔ ጋ ነው፡፡ ቅርበት ስላለኝ ብቻ ሳይሆን፣ ድሮም ልጅ ሆኜ የሆነ ነገር አንብቤ ደስ ካለኝ ወይም ከመሰጠኝ ኮፒ ማድረግ እወዳለሁ፡፡ ዓይንሽ እምባ እያቀረረ ነው!... ስሜተ-ስስ ነሽ ልበል?[ዕንባዋን እየጠረገች] ኖ!..ኖ!.. የአውግቸው ነገር ሲነሣ በጣም ነው የሚያመኝ፡፡ አስራ ምናምን መፅሐፍ ያለው ሰው የሚኖረውን ህይወት፣ በዚያ ላይ የአዕምሮ ህመም ሲያሰቃየው ማየት ... ልብ ይነካል፡፡ እንደጓደኛ ስታየው መፅሐፉን ከማተም ይልቅ የማሳተሚያውን ፍራንክ መስጠት ነው ትክክለኛው፡፡ እውነታው ይኼ ቢሆንም፣ እሱም እኔም ተጠቃሚ አንሆንም፡፡ ግን መፅሐፉ ቢታተም አንተም ችፍቻፊው ይደርስሃል፡፡ እሱም ህይወቱን ለማስቀጠል የሚያሰችለው ጥሬ መቆርጠሚያ ያገኛል በሚል ነው ያተምኩት፡፡ ስንዱ ሁሉን ነገር የመነካካት ባህርይ ያለሽ ይመስለኛል?እንዴት ማለት ነው እሱ?ፖለቲከኛ የመሆን ዝንባሌ ነበረሽ፡፡ በምርጫ 97 የግል ተወዳዳሪ ሆነሽ ቀርበሽ ነበር፡፡ እስቲ ስለ እሱ ነገር እንጨዋወት?ህይወት እኮ ነው የሚመራህ፡

፡ በመኖር ውስጥ እያለህ ያጋጠመህን እየመረመርክ፣ እየፈታህ፣ እየወደቅክ፣ እየተነሳህ ነው የምትቀጥለው፡፡ እና በህይወት ውስጥ የሚገጥመኝን ለማሳካት እሞክራለሁ፡፡ እና የምርጫው ጉዳይ፣ አንደኛ በህገ መንግስቱ የተፈቀደልኝ መብቴ ነው፡፡ ከ18 ዓመት በላይ መወዳደር ይችላል፡፡ ሁለተኛ ጋዜጠኛ ነበርኩ፡፡ ብዙ የሚያበሳጩኝ ጉዳዮች ገጥመውኛል፡፡ እንደው እድሉን ባገኝ ልመረምራቸው የምፈልጋቸው ጉዳዮች አሉ፡፡ በነገራችን ላይ እኔ ክስ አልወድም፡፡ የተወካዮች ም/ቤት ክስ ስለሚበዛበት አልወደውም፡፡ አልወደውም ብሎ ከመናገር ገብቶ መሞከር ያስፈልጋል ብዬ ወደ ምርጫ ገባሁ፡፡ ስለዚህ፣ በደንብ ራሴን ከገለፅኩ፣ ሃሳቤን ማስተላለፍ ከቻልኩ፣ ለምን አልወዳደርም ብዬ ነው የሞከርኩት፡፡ውጤቱን እንዴት አገኘሽው ታዲያ?(ሳቅ) ተጭበረበርኩ!... እንደተባለው ነው፡፡ በማን? ብትለኝ በሁሉም!... የሁላችንም ጭንቅላት ነው የተጭበረበረው እኮ (ሳቅ)ስንዱ፣ ብዙ ሰዎች የአነጋገር ዘይቤሽን ከስብሐት ገ/እግዚአብሔር ጋር ያመሳስሉታል፡፡ ትስማሚበታለሽ?አዎ! የሚያመሳስለን ነገር ይኖራል፡፡ ለምን አይኖርም? ከሃያ አመት በላይ ጓደኛዬ ናቸው፡፡ ዩኒቨርስቲዬ ናቸው ልትል ትችላለህ፡፡ ስብሃትን የሚመስል ዕውቀት ያለው ሰው አግኝቼ ነው!?፡፡ እሳቸውን ትመስያለሽ ብትለኝ አይደንቀኝም፡፡ በህይወትሽ በጣም የተደሰትሽበት ቀን?የተደሰትኩበት ቀን ሳይሆን፣ ገና የምደሰትበትን ቀን ነው የማስበው፡፡ የሙሉጌታ ተስፋዬን ግጥሞች አትሜ ያቀረብኩ ቀን በጣም! በጣም! የምደሰት ይመስለኛል፡፡ ስማ፣ አሁን የፃፍኩትና ያሣተምኩት የ”አርተር ራምቦ” ታሪክ በጣም ነው የተወደደው፡፡ ራምቦን ለመፃፍ የቀለለኝና እንዲዋጣልኝ ያደረገኝ የሙሉጌታን ህይወት ማወቄ ነው፡፡ ሙሉጌታን ባላውቀው ራምቦን እንኳን ልፅፈው ሊገባኝ አይችልም፡፡ እና የሙሉጌታ ግጥም እስኪታተም እኛ አገር ግጥም አልታተመም ነው የምለው፡፡ የእሱ ግጥም ሲታተም ነው የምደሰተው፡፡ ስንዱ የህይወት ግብሽ ምንድነው?መኖር!... በአጭር ቋንቋ መኖር!ነገ ፋሲካ ነው፡፡ ዓመት በዓልን እንዴት ነው የምታሳልፊው?በመጀመሪያ ደረጃ፣ እኔ ለዓመት በዓል ግድ የለኝም፡፡ እንደው በአጭሩ፣ ዓመት በዓልን በመቀላወጥ ነው የማሳልፈው፡፡

“የማልወደው...

መንከባከብ ከቻለ ስለምን የተራቡትን ይሳደባል? ሳይጠይቁት፣ አብላን ሳይሉት፣ ትርፍራፊ ጠብቀው ለሚኖሩ ስለ ምን ይሰድባቸዋል? የዚህ ነገር ትዕምርት ምንድን ነው? ሀገሪቱን እኛ ብቻ እንኑርበት ደሀ የሚባል በዓይናችን እንዳናይ፣ እኛ እንኑር፣ እኛ እንጠጣ፣ እንገባበዝ ማለት አይደለም?

ጫማውን አስተካክሎ ማሰር ሳይችል የባለ ገንዘብ ልጅ ጠግቦ ሲተፋ ስላደረ ጫማ ጠራጊን መርገጥ፣ ጫማ ሰሪን መሳደብ፣ ጫማ ሻጭን ማንቋሸሽ ይፈልጋል፡፡

ሲገላበጥበት ያደረውን አልጋ አስተካክሎ ማንጠፍ የማይችል፣ ተኝቶ በወላጆቹ እጅ ስለተቀለበ ብቻ የቤት ስራተኝ መደባደብና የጉልበት ሰራተኛን መሳደብ ይቀናዋል፡፡

አስራ ሁለት አመት ተምሮ ስሙን እንኳ አስተካክሎ መፃፍ የማይችል ከዚህ ክፍል ወደ ቀጣዩ ክፍል ካለፍክ መኪና፣ ከዚያ ወደ ቀጣዩ ካለፍክ ቤት እገዛልሀለሁ እየተባለ፣ በመቶ አርባ አራት ጉዞ እየተደለለ ስለተማረ ብቻ ተማሪን መደባደብ፣ አስተማሪን መዝለፍ፣ ሀገርን ማንቋሸሽ ይፈልጋል፡፡

እና እንዲህ ላለ ጥጋበኛ የመጣው ፋሲካ በሌላም መልኩ ፋሲካ ሆኖ ይመጣል፡፡

ከሁለት አመት በፊት አንድ ወዳጄ ይህንን ታሪክ ነገረኝ- እኔ እያለ፡፡

‹‹አንዲት ጎረቤት ነበሩኝ፡፡ አንድ የልጅ ልጃቸውን እያሳደጉ በብቸኝነት ይኖራሉ፡፡ ደሀ ናቸው፡፡ ለፋሲካ ለምሳ እቤታቸው ጋበዙኝ፡፡ ደሳሳዋ እና የተጣመመችዋ ቤት ነፍስ ዘርቶባት ዓውደ አመት፤ ዓውደ ዓመት ትሸታለች፡፡ ሁለም

ነገር ዓመት በዓል መሆኑን ይናገራል፡፡ በተለይ የሴትዮዋ ፈገግታ፡፡

ደስ የሚል ምሳ በላሁ፡፡ (በነገራችን ላይ ጓደኛዬ ለበዓል ግድ የለሽ ስለሆነ ለራሱ ሳያጣ ተኝቶ መዋልን ይመርጣል) በዚህ ቀን ግን ደስ፣ በጣም ደስ ብሎኝ አለፈ፡፡

በወሬአችን መካከል ሴትየዋ ለምሳ የተሰራውን ስጋ ከየት እንዳገኙት እንዲህ ብለው ነገሩኝ፡፡

‹‹እዚህ ትልቁ ቤት ብዙ ስጋ ገዝተው መዘልዘል አቃታቸው፤ ቀኑን ሙሉ ስዘለዝል ውዬ የተቀነጣጠበውን ይዘሽ ሂጅ አሉኝ››

ትልቁ ቤት የተባለው ለእኔም ለእሳቸውም ጎረቤት ነው፡፡ እሳቸውም እኔም ግን ወደ ትልቁ ቤት ለበዓሉ አልተጠራንም፡፡

ጓደኛዬ ይህንን ነገር ሲነግረኝ በልቤ ስለ እኒያ ኢትዮጵያዊ ጎረቤቱ አስብ ነበር፡፡ ሳላያቸው እየወደድኳቸው፡፡ ሳላውቃቸው እየናፈቅኋቸው፡፡ አብሮ መኖር ስለመውደዳቸው፤ ስለፍቅር በማወቃቸው እያመሰገንኳቸው፡፡

ጓደኛዬ ቀጥሎ ያነበበው ሐሳብ ስለገዛኝ እንዳለ እነግራችኋለሁ፡-

“እኛን ያኖረን፣ የሚያኖረንም ይኼው መዋደዳችን ነው፡፡ መተሳሰባችን ነው፡፡ በዓላችንን በዓል የሚያደግልን፣ ደስታችንን ደስታ የሚያደርግልን ይኼው ነው፡፡ ምንም ባይኖረን ተሳስበን ማደራችን፣ ምንም ባንይዝ ተጠራርተን መዋላችን፡፡ ምንም ባንደግስ ፈንዲሻ አፍክተን፣ ቡና አጫጪሰን ስንሳሳቅና ስንጫወት መዋላችን፡፡ ይኸው ነው እኛንና ሀገራችንን አንድ አድርጎን ያለው፡፡

እኛ ፍቅር እናውቃለን፡፡ ስናፈቅር ከምንም ተነስተን፣ ስንወድ ምንም ሳናይ፣ መስጠትን እንጂ መቀበልን እንደመስፈርት ሳናስቀምጥ፡፡ እንጂማ ራበኝ ብሎ ከሚሰደደው፣ ጠግቦ የሚሰደደው ባልበዛ ነበር፡፡ የጠገቡ ፍቅር አያውቁማ!! ኢትዮጵያዊነትን፣ ተሳስቦና ተዛዝኖ መኖርን አያውቁምና ‹እንሰደድ እንሂድ› ከሚሉት ብዙውን እጅ ያዙት፡፡

እኛ ፍቅር ባናውቅማ ኖሮ ሀገር ለጉልበት ሥራ ሆነ ለጠላት መካችነት ጥሪ በጠራች ቁጥር ሀብታሙ በተካለፈ፡፡ ግና ሀገር ስትጠራው ቀድሞ የሚደርሰው ደሀው ነው፡፡ ለምን? ፍቅር ያውቃላ!

የአንድ ሰው ነፍስ፣ የአንድ ሰው ጭንቀት፣ የአንድ ሰው ስቃይ ምን ማለት እንደሆነ ያውቃልና እያንዳንዱ ይረዳዳል፡፡ ለታክሲ የያዛት አንድ ብር መሆን ያለበት ለየኔ ቢጤው ዳቦ መግዣ ነው ብሎ ያምናል፡፡ ሀብታሙ ግን የሁለት ብር ኪኒን አጥቶ መንገድ ዳር ወባ ከሚያንደፋድፈው የደሀ ነፍስ ይልቅ ውስኪ የጠማት ጓደኛው ቀድማ መርካት እንዳለባት ያምናል፡፡ ይኼው ነው ልዩነታችን፡፡ ለእነሱ የሚመጣ ፋሲካ ለእኛም ይመጣል፡፡ እኛ እንደተማርነው በፍቅር፣ እነሱ እንዳወጁት በጥጋብ ያልፋል!”

እንደመውጫአሻግሯቸውና ከብቶቻችን

ይብሉያ ሳር አይደለም ወይ የምናየው

ሁሉ(ይድነቃቸው ተሰማ)

ሁለት ወገን ...

Page 23: ethioforum.orgethioforum.org/wp-content/uploads/2011/04/Awramba_Times... · 2011-04-11  · ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ 4 ፊ ቸ ር አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 164 ቅዳሜ ሚያዚያ 15 200324 ማ ስ ታ ወ ቂ ያብርሃ

ንና ሰ

ላም ማ

ተሚያ ድ

ርጅት