18. የእምነት ዶክትሪን

6
የአንበሳው ጥሪ ለሰው ልጆች ሁሉ አለም አቀፍ አገልግሎት እምነት “ጨውና ብርሃን ናችሁ።” ማቴዎስ.5፥13-16 በመጋቢ ሊዮን ኢማኒኤል

Upload: the-lions-call-for-all-nation-international-ministry

Post on 18-Jul-2015

82 views

Category:

Spiritual


5 download

TRANSCRIPT

Page 1: 18. የእምነት ዶክትሪን

የአንበሳው ጥሪ ለሰው ልጆች ሁሉ አለም አቀፍ አገልግሎት

እምነት

“ጨውና ብርሃን ናችሁ።” ማቴዎስ.5፥13-16 በመጋቢ ሊዮን ኢማኒኤል

Page 2: 18. የእምነት ዶክትሪን

እምነት

1. እምነት ማለት ተስፋ ስለምናደርገው ነገር የሚያስረግጥ የማናየውን ነገርየሚያስረዳ ነው። (ዕብ.11፥1-3)

2. ዘመኖች፣ የሚታየው ሁሉ ነገር ከማይታየው አለምና ከእግዚአብሔር እንደ ሆነእንዲሁም እግዚአብሔር እንዳለ የምንረዳው በእምነት ነው። (ዕብ.11፥1-3)

3. በመንፈሳዊው እውነት ለሸመገሉ አማኞችና አባቶች የተመሰከረላቸው በሥራቸውናበቅድስናቸው ሳይሆን በእምነታቸው ነው። (ዕብ.11፥1-3)

4. ያለ እምነት እግዚአብሔር ፈጽሞ ደስ ማስኘት አይቻልም። (ዕብ.11፥6)

“ጨውና ብርሃን ናችሁ።” ማቴዎስ.5፥13-16 በመጋቢ ሊዮን ኢማኒኤል

Page 3: 18. የእምነት ዶክትሪን

እምነት

5. እምነት የሚመጣው የእግዚአብሔር ቃል ከመስማት ነው። ይህ መስማት ግንበትክክል መሰማቱ የሚታወቀው የተፈጠረብን ወይም የመጣልን እምነትበሕይወታችን ስርቶ ሲታይ ወይም የሰማነውን ሆነን ስንገኝ፣ ስንታዘዝናሕይወታችን ላይ ሲንጸባረቅ እምነት እንደተቀበልን በሥራችን እናስርግጣለንእናጸናለን። (ሮሜ.4, 10፥17, ያቆ.2፥14-6)

6. እምነት ጅማሬና ፍጻሜ፣ ጀማሪና ፈጻሚ አለው። (ዕብ.12፥2, 1.ጴጥ.1፥9)

7. የመጀመሪያው እግዚአብሔር ያተመው ሥራና ለሰው ልጆች ሁሉ የተሰጠው ስራማመን ነው። እግዚአብሔር ከሰው ልጆች በመጀመሪያ እንዲስሩ የሚጠብቀው ስራማመን ነው። (ዮሐ.6፥27-29)

“ጨውና ብርሃን ናችሁ።” ማቴዎስ.5፥13-16 በመጋቢ ሊዮን ኢማኒኤል

Page 4: 18. የእምነት ዶክትሪን

እምነት

8. በእግዚአብሔር የሚያምን፦

I. ከሞት ወደ ሕይወት ይሻገራል፦ (ዮሐ.5፥24)II. ፈውስን ጤንነትን ይቀበላል፦ (ዮሐ.8፥43-48)III. ጸሎቱ ይሰማል የመለስለታል፦ (ያቆ.5፥13-15)IV. በመንፈስ ይታተማል፦ (ኤፌ.1፥13)V. ከብዙ ነገር ይድናል፦ (ሐዋ.16፥29-34)VI. ድፍረትን ያገኛል፦ (ኤፌ.3፥12)VII. ጽድቅን ይቀበላል፦ (ሮሜ.3፥22, 4)VIII. ትንሳኤን ይቀበላል፦ (ቆላ.2፥12)IX. ታላቅ ነገሮች ያደርጋል፦ (ዕብ.11) …ወዘተ

9. ጸጋውን ለመጠቀም እምነት ያስፈልጋል። ጸጋው ያለ እምነት ፈጽሞ አይሰራም።(ኤፌ.2፥8)

10. የሰው እምነቱ በእግዚአብሔር ይፈተናል። (ማቴ.4፥1-10, ዘፍ.22፥1-19, ዕብ.11፥17-19,1.ጴጥ.1፥6-9)

“ጨውና ብርሃን ናችሁ።” ማቴዎስ.5፥13-16 በመጋቢ ሊዮን ኢማኒኤል

Page 5: 18. የእምነት ዶክትሪን

እምነት

11. እምነት ያድጋል ይህም የእምነት ዕድገት የሚወሰነው በሰማነው የእግዚአብሔርቃል መሰረትና መጠን ነው። (ቆላ.1፥5-6)

12. ጻድቅ በእምነት እንጂ በማየት አይመላለስም። ይህም ሕይወት ጻድቅን በጽድቅናበቅድስና ያኖረዋል። (2.ቆሮ.5፥6, ዕብ.10፥38, እንባ.2፥3-4)

13. እምነት ወደ ተስፋ ያሳድገናል። የእምነት መጨረሻው ግን ፍቅር ነው። ያን ጊዜየእምነት ተቃራኒ የሆነው ፍርሃት ፈጽሞ ከሰው ይጠፋል። (1.ቆሮ.13፥1-2,13,ገላ.5፥6)

14. እግዚአብሔር ባናምነው እርሱ ራሱ የታመነ ሆኖ ይኖራል። ራሱን አይክድምናነው። (2.ጢሞ.2፥13, ገላ.2፥16)

15. በእግዚአብሔር ላይ እምነትን ማድረግ የሁሉ መሰረት ነው። (2.ጴጥ.1፥5-8)

“ጨውና ብርሃን ናችሁ።” ማቴዎስ.5፥13-16 በመጋቢ ሊዮን ኢማኒኤል

Page 6: 18. የእምነት ዶክትሪን

እምነት

16. እግዚአብሔር የሚወደው መታዘን ከእምነት የሚወጣን መታዝዝ ነው። (ሮሜ.1፥5,2.ቆሮ.10፥1-6)

17. እምነት የመንፈስ ቅዱስ ስጦታም ሆኖ ይሰጣል። ይህ ሲሆን ግን በእግዚአብሔርመለኮታዊ ሃይል እንጂ ቃሉን በመስማት አይደለም። (1.ቆሮ.12፥8)

18. እግዚአብሔር ለእያንዳንዱ ሰው የተወስነ የእምነት መጠንን አስቀድሞ ይሰጣል።(ሮሜ.12፥3, ይሁ.3, ፊልሞ.6)

19. እምነትን ያናቀ የእግዚአብሔር ቃል ይንቃልና ይፈረድበታል። (1.ጢሞ.5፥12, 6፥11)

20. ያለ እምነት የሆነ ነገር ሁሉ በእግዚአብሔር እይታ ሃጢያት ነው። ምክንያቱምከእግዚአብሔር ቃል ውጭ ስለሚሆን ነው። (ሮሜ.14፥23)

21. ትልቁ የእምነት ምሳሌ የሆነው የእምነት አባት ተብሎ የሚታወቀው አብርሃም ነው።ይሁንና ከእርሱም በፊት ሆነ ከእርሱም በኃላ ያመኑ ታላላቅ መንፈሳዊ አባቶች አሉ።(ዘፍ.12፥25, ሮሜ.4, ዕብ.6፥13-20, 7፥1-10, 11፥8-19)

“ጨውና ብርሃን ናችሁ።” ማቴዎስ.5፥13-16 በመጋቢ ሊዮን ኢማኒኤል